#ማስታወቂያ
ገንዘብ መስራት ይፈልጋሉ
➯ እንጊዲያውስ ከTelegram ሳይወጡ በኢትዮጵያውያን በቀረበው በhulepay bot Start ብለው ገንዘብ ይስሩ።
👫 ይጋብዙ እና ገንዘብ ይስሩ !
🎁 አንድ ሰው ሲጋብዙ 1 ብር ይሰራሉ።
➯ ማውጣት የምትችሉት ገንዘብ ከ10 ብር ጀምሮ ነው።
➯ ገንዘቡን ስልክ ቁጥራችሁን በማስገባት በቴሌብር ማውጣት ትችላላችሁ።
huleypay bot Link👇👇👇
/channel/hulepay_official_bot?start=r09032832040
✅ ዛሬውኑ ጀምሮ ገንዘብ ያካማቹ እና በቴሌብር ይቀበሉ።
#ማሳሰቢያ በፍፁም ሐሰት ነው ብላችሁ እንዳታስቡ እውነተኛ በኢትዮጵያዊያን የተሰራ የገንዘብ ማግኛ የTelegram bot ነው።
#ሐምሌ_27
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሐምሌ ሃያ ሰባት በዚህች ቀን #ቅዱስ_አሞን በሰማዕትነት ዐረፈ፣ ኢትዮጵያዊቷ #ቅድስት_መስቀል ክብራ ዕረፍቷ ነው፣ የአዳም ልጅ #ቅዱስ_ሴት ዕረፍቱ ነው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ሰማዕቱ_ቅዱስ_አሞን
ሐምሌ ሃያ ሰባት በዚህች ቀን ቅዱስ አሞን በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ ይኸውም ቅዱስ ተርኑጥ ከሚባል አገር የተገኘ ሰማዕት ነው፡፡ ወደ ላይኛው ግብጽ በሄደ ጊዜ የእንዴናው ገዥ ሰማዕታትን ይዞ በጽኑ ሲያሠቃያቸው ተመለከተ፡፡ እርሱም በመኮንኑ ፊት ቀርቦ የጌታችንን አምላክነት መሰከረ፡፡ መኮንኑም ይዞ ታላቅ ሥቃይን አሠቃየው፡፡ ሥጋውን ሁሉ ሰነጣጥቆ ከጣለው በኋላ ዳግመኛ በትላልቅ ችንካሮች ቸነከረው፡፡ ነገር ግን ጌታችን አጽናንቶ ከቁስሉ ፈውሶ ጤነኛ አደርጎ አስነሣው፡፡
መኮንኑም ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ ቅዱስ አሞንን ወደ እስክንድርያ ከተማ ላከው፡፡ በዚያም ሳለ ጌታችን ተገለጠለትና ስሙን ለሚጠራና ገድሉን ለሚጽፍ በሕይወት መጽሐፍ እንደሚጽፍ ቃልከዳን ከገባለት በኋላ ሰማዕትነቱን በድል እንዲፈጽም ነገረው፡፡
ወዲያውም ይዘው ጽኑ በሆኑ ልዩ ልዩ ሥቃዮች አሠቃዩት፡፡ ጌታችንም ከመከራው እያዳነው ልዩ ልዩ ተአምራትን ስላደረገለት ይህንን ያዩ ብዙዎች ‹‹በቅዱስ አሞን አምላክ አምነናል›› እያሉ በመመስከር ሰማዕትነትን ተቀበሉ፡፡ እነርሱም ውስጥ ቲዮጲላ የምትባል ድንግል ነበረች፡፡ እርሷም ወደ መኮንኑ ዘንድ በመሄድ በጌታችን ታመነች፡፡ መኮንኑም እቶን እሳት ውስጥ ከተታት ነገር ግን እሳቱ አላቃጠላትም፡፡ በመጨረሻም ራሷን በሰይፍ ቆረጡትና የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀች፡፡
ከዚህም በኋላ አባለ ዘሩንና አካሉን ሁሉ በሰይፍ እየቆረጡ ቅዱስ አሞንን እጅግ ካሠቃዩት በኋላ አንገቱን በሰይፍ ቆረጡትና የሰማዕትነቱ ፍጻሜ ሆነ፡፡ በመንግሥተ ሰማያትም የክብር አክሊልን ተቀዳጀ፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_መስቀል_ክብራ
በዚህችም ቀን ኢትዮጵያዊቷ ቅድስት መስቀል ክብራ ዕረፍቷ ነው፡፡ ይኽችም ቅድስት የቅዱስ ላሊበላ ባለቤት ስትሆን የትውልድ ሀገሯ ወሎ ላስታ ቡግና ነው፡፡ የታላቁ ጻድቅ ንጉሥ የቅዱስ ላሊበላ ሚስት ናት፡፡ ከእርሱም ደገኛውን ይትባረክን ወልዳለች፡፡ ቅዱስ ላሊበላን እና ቅድስት መስቀል ክብራን ሁለቱ እንዲጋቡ ያዘዛቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማይ ነጥቆ ወስዶ የሚያንጻቸውውን የሕንጻ ዲዛኖችና ሌሎችንም ብዙ ምሥጢራትን ካሳየውና ወደ ምድር ከመለሰው በኃላ ድጋሚ ተገልጦለት "እንዳንተ የተመረጠች ናት እንደ ልብህም ትሆናለች፣ ሥራዋም ከሥራህ አያንስም እርሷ የተመረጠች የእግዚአብሔር አገልጋይ ናትና" በማለት መልአኩ የቅድስት መስቀል ክብራን ንጽሕናና ቅድስና መስክሮላታል፡፡
ቅዱስ ላሊበላ 11 እጅግ አስደናቂ የሆኑ ፍልፍል ቤተ መቅደሶቹን ከመላእክት ጋር ሲያንጽ ብታየው ልቧ በመንፈሳዊ ተመስጦ ተመልቶ እርሷም እግዚአብሔር ፈቅዶላት አስደናቂውን የአባ ሊባኖስን ቤተመቅደስ ራሷ እንዳነጸችው መጽሐፈ ገድሏና ገድለ ቅዱስ ላሊበላ ያስረዳል፡፡
ቅድስት መስቀል ክብራን ወደ ትግራይ እየመራ የወሰዳት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ እርሷን በትግራይ ቅዱስ ሚካኤል እንዲጠብቃት ከተዋት በኃላ ቅዱስ ላሊበላን ደግሞ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ መንግሥተ ሰማያት አውጥቶታል፡፡
ቅድስት መስቀል ክብራም በትግራይ ሆና መልአኩ እየጠበቃት ከሰው ተለይታ በታላቅ ተጋድሎ ኖረች፡፡ በቀን እልፍ እልፍ እየሰገደች በታላቅ ተጋድሎ ስትኖር ጌታችን ተገልጦ ክብሯ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ጋር እኩል መሆኑን ነግሯታል፡፡
ይኽችም ቅድስት ብዙ ሐዋርያዊ አገልግሎት ፈጽማለች፡፡ ለምሳሌ በመስቀል ጦርነት ጊዜ እስላሞች ከባሕር ማዶ እየፈለሱ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ በፍቅር እየተቀበለችና እያስተናገደች ሃይማኖትንና ሕገ እግዚአብሔርን እያስተማረች ወደ ክርስትና እንደገቡና እንዱጠመቁ አድርጋለች፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ሴት_ነቢይ
ዳግመኛም በዚህች ቀን የአዳም ልጅ ሴት ዕረፍቱ ነው፡፡ እርሱም ሁለት መቶ አምስት ዓመት ኖረ፡፡ ሔኖስንም ወለደው፡፡ ሔኖስንም ከወለደ በኋላ ሰባት መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፡፡ ወንዶችንና ሴቶች ልጆችንም ወለደ፡፡ መላ ዕድሜውም ዘጠኝ መቶ ዐሥራ ሁለት በሆነ ጊዜ በሰላም ዐረፈ፡፡
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ እና #ከገድላት_አንደበት)
ከብዙ ተአምራቱም አንዱ የቂሳርያውን ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስን እረድቶ ከሃዲውን ዑልያኖስን የገደለበት ነው፡፡ ዑልያኖስ ነግሦ የክብር ባለቤት ጌታችንን ክዶ ጣዖታትን ማምለክና ክርስቲያኖችን ማሠቃየት ጀመረ፡፡ የቂሳርያው ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስም አስተምሮ ሊመልሰው ወደ ንጉሡ ቢመጣ ክብር ይግባውና ዑልያኖስ ጌታችንን ሰድቦ ባስልዮስንም አሰረው፡፡ ባስልዮስም በእሥር ቤት ሳለ በቅዱስ መርቆሬዎስ ሥዕል ፊት ጸለየ፡፡ ሥዕሉም ወዲያው ተሰወረው፡፡ ያንጊዜም ወደ ከሃዲው ንጉሥ ዑልያኖስ ዘንድ ሄዶ በጦር ወግቶ ገደለውና ወዲያው ወደ ቦታው ተመለሰ፡፡ ከጦሩም አንገት ደም ይንጠፋጠፍ ነበር፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ከሃዲውን ንጉሥ እንደገደለው ዐውቆ ‹‹የክርስቶስ ምስክር ጌታዬ ሆይ የእውነት ፀር የሆነ ዑልያኖስን ገደልከውን?›› አለው፡፡ ሥዕሉም ያን ጊዜ አዎን እንደሚል ራሱን ዘንበል አደረገ፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ደስ ብሎት እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡
ሌላው ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ በተአምሩ ከእስልምና እምነት መልሶ ክርስቲያን ያደረገው አንድ እስላም ሰው አለ፡፡ ይኸውም የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያኑ በተሠራችበት በምስር አገር የሚኖር ከመሳፍንት ወገን የሆነ ወጣት ነበረ፡፡ ከብዙ ሰዎችም ጋር ሆኖ ወደ መሐመድ መቃብር ለመሄድ እንዳሰበ ለአባቱ ሲነግረው ስንቅ ሰንቀው በሰላም ወደ መካ መዲና ሸኙት፡፡
መካ ደርሰውም ሥራቸውንም ፈጽመው ወደቤታቸው እየተመለሱ ሰባት ቀን ተጓዙ፡፡ በሌሊትም ሲጓዙ ስለ ሥጋዊ ግዳጁ ያ እስላም ወጣት ከግመል ላይ ወርዶ ለመጸዳዳት ዘወር አለ፡፡ እነርሱም አብሯቸው የሚጓ መስላቸው ስለነበር ባልንጀሮቹም በበረሃው ውስጥ ትተውት ሄዱ፡፡ እርሱም ወዴት እንደሚሄድ ስላላወቀ አራዊትም እንዳይበሉት ፈርቶ እጅግ ደነገጠ፡፡ በዚያም ጊዜ በምስር አገር በአባቱ ቤት አቅራቢያ ያለች የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስን ቤተ ክርስቲያን አስታውሶ በልቡ ቅዱስ መርቆሬዎስን እንዲያድነው በመለመን ተሳለ፡፡ ወዲያውም ቅዱስ መርቆሬዎስ በፈረሱ ተቀምጦ ወደ እርሱ መጣና ‹‹ከወዴት ነህ? ከዚህ በረሃ ውስጥስ እንዴት ጠፋህ?›› አለው፡፡ ወጣቱ እስላምም የሆነውን ነገረው፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም ‹‹ና በኋላዬ በፈረሱ ላይ ተፈናጠጥ›› አለውና በአየር ላይ እየበረረ በምስር አገር ወዳለች የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደ ዐይን ጥቅሻ አደረሰውና እንደተዘጋች በውስጧ አስገባውና ከእርሱ ተሰወረ፡፡ ይህም ወጣት በኋላ አምኖ ተጠምቆ ብዙ ሰማዕትነት ተቀብሏል፡፡ ገዳምም ገብቶ ብዙ ከተጋደለ በኋላ እንደገና ወደ አገሩ ተመልሶ ብዙዎችን ወደ ክርስትና አምጥቷል፡፡ በቅዱስ መርቆሬዎስ ስም ቤተ ክርስቲያን አሠርቶ አበ ምኔትም ሆኖ ብዙ መነኮሳትን አፍርቷል፡፡
የሰማዕታቱ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!
ምንጭ፦በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን (ከገድላት አንደበት)
🌾🍂🌿አቡነ ሕፃን ሞዐ🌾🍂🌿
አቡነ ሕፃን ሞዐ ሰማዕትነት ከተቀበለ በኋላ በተነፈሰበት ቦታ ላይ ዛሬም ድረስ እየታየ ያለ ተኣምር አለ፤ ይኸውም በጻድቁ እስትንፋስ አምሳል ከመሬት ውስጥ የሚወጣው እስትንፋስ ለአስም በሽታ መድኃኒት ሆኖ ብዙዎችን እየፈወሰ ይገኛል።
🍂አቡነ ሕፃን ሞዐ በአባታቸው አርከሌድስ እናታቸው ትቤ ጽዮን ይባላሉ። የተወለዱት ጥር 25 ነው" ጻድቁ ከእነ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጋር የሥጋ ዝምድና አላቸው" ይኸውም አባታቸው እርከሌድስና ጸጋ ዘአብ ወንድማማቾቸ ናቸው። አርከሌድስና ጸጋ ዘአብ ሌሎች 4 ወንድሞች አሏቸው" እነርሱም እንድርያስ፡ ዘርዐ አብርሃም፤ ቀሲስ ዮናስ እና ቀሲስ ዮሐንስ ናቸው። አርከሌድስ ሕፃን ሞቦን ይወልዳል፣ ጸጋ ዘአብ ተክለ ሃይማኖትን ይወልዳል፣ እንድርያስ ሳሙኤል ዘወገግን፡ ዘርዐ አብርሃም ታላቁ አኖሬዎዮስን ተሲስ ዮናስ ገላውዲዮስንና የፈጠጋሩን ማትያስን፣ እና ቀሲስ ዮሐንስ ዜና ማርቆስን ይወልዳሉ"
እነዚህም እጅግ የከበሩ ቅዱሳን አባቶቻችን በእናታቸውም ወገን ቢሆን እንዲሁ በዝምድና የተቆራኙ ናቸው። ጻድቁ አቡነ ሕፃን ሞዐ ይህችን ከንቱ ዓለም ንቀው አባታችውን ታላቁን ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በግብር ለመመሰልና በምንኩስና ሥርዓት የቅዱሳንን አምላክ ልዑል እግዚአብሔርን በንጽሕና ለማገልገል ለምናኔ ሕይወት ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ለመሔድ ሲያስቡ የክብር ባለቤት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአካል ተገልጾላቸው ተስፋቸውን ነገራቸው" መልአኩንም ላከላቸውና ዕጣ ክፍላቸው የሆነችውን ቦታ ደብረ በግዐ ገዳምን አሳያቸው። መልአኩም እየመራ ካደረሳቸው በኋላ ጻድቁ በቦታው ላይ ገዳም ገድመው ሥርዓት ሠርተው ተከታዮቻቸውን አብዝተው በጽኑ ተጋድሎ ምድራዊ መላእክት መስለው ኖሩ።
🍂አቡነ ሕፃን ሞዐ በሌላኛው ስማቸው ሕፃን ዘደብረ በግዕ ተብለውም ይጠራሉ። ይኸውም የደብረ በግዕን ገዳም የመሠረቱት እርሳቸው ስለሆኑ ነው። ጻድቁ ከ47ቱ የሀገራችን ቀደምት ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው። በመንዝና በተጉለት የሚገኙ ታላላቅ ገዳማትን አብዛኞቹን የመሠረቷቸው አቡነ ሕፃን ሞዐ ናቸው
ጻድቁ በክፉዎች ወሬና ሴራ ምክንያት ቀኑን ሙሉ ከበሬ ጋር ተጠምደውና ተገርፈው ሰማዕትነት የተቀበሉ አባት ናቸው። ከበሬ ጋር ሲታረሱና ሲገረፉ ውለው በእጅጉ ከደከማቸው በኋላ በኃይል የተነፈሱባት ምድሪቱ ዛሬም ድረስ ልክ እንደሰው የሚሞቅ ትንፋሽ ታወጣለች። ይኸችም እስከ ዳግም ምጽዓት ድረስ እንደሰው የምትተነፍሰዋ ተአምረኛ ምድር ‹‹የእስትንፋስ ተራራ›› ተብላ ትጠራለች። ያም በጻድቁ እስትንፋስ አምሳል ከመሬት ውስጥ የሚወጣው እስትንፋስ ለአስም በሽታ መድኃኒት ነው።
🌾የአቡነ ሕፃን ሞዐ ገዳም-ደብረ በግዕ🌾
ገዳማቸው ከደብረ ብርሃን ከተማ በእግር የ2 ሰዓት መንገድ ርቀት ላይ ይገኛል። ይኸውም ከወንይዬ ተክለ ሃይማኖት ገዳም አጠገብ ነው። በሌላም በኩል ከጫጫ ከተማ ቂጣለኝ ከተባለው ቦታ በመሔድ ከዚያ ወደ ደብረ በግዕ ገዳም በእግር መጓዝ ይቻላል ።
🍂ጻድቁ ጥር 25 ልደታቸው ጥቅምት 25 ቃልኪዳን የተቀበለበትን ዕለት ሲሆን ዕረፍታቸው ደግሞ ሐምሌ25 ነው
የአቡነ ሕፃን ሞዐ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጽሎታቸው ይማረን !
ምንጭ በእንተ ኅሩይ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ የተወስደ
እግዚአብሔር ወንድማችን ገብረ ሥላሴ በዕድሜ በጤና ይጠብቅልን
✝✝††† እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ዘዮሐንስ እና ለሰማዕቱ አባ ኖብ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ †††
††† ኢትዮጵያዊው ጻድቅ የተወለዱት በ13ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ሲሆን ሃገረ ሙላዳቸው ሸዋ (መርሃ ቤቴ) ነው:: ወላጆቻቸው ዘካርያስ እና ሶፍያ እግዚአብሔርን የሚፈሩ : እመ ብርሃንን የሚወዱና ለነዳያን የሚራሩ ነበሩ::
ደጉ ዘካርያስ መስፍን ሲሆን እርሱ በሌለበት የሸዋ ገዢ ሊያገባት በመሞከሩ ቅዱስ ገብርኤል ቀስፎታል:: ሕዝቡ ገዢነቱን ለዘካርያስ ሰጥተውታል:: ከቆይታ በኋላም ድንግል ማርያም የተባረከ ፍሬ ሰጠቻቸው:: ስሙን "ዮሐንስ" አሉት:: በሒደት ግን ዘዮሐንስ (የዮሐንስ) ተብሏል::
ቅዱሱ ዘዮሐንስ እስከ ሰባት ዓመቱ ድረስ በእናቱ እቅፍ ቆይቶ ወደ ትምሕርት ገብቷል:: ጸጋ እግዚአብሔር ጠርቶታልና በአጭር ጊዜ ብሉይ ከሐዲስ ጠነቀቀ:: አደን ይወድ ነበርና ሊያድን ሲወጣ 'ብርሕት ደመና' ድንገት ነጥቃ ከኢትዮጵያ (ሽዋ) ወደ ኢየሩሳሌም (ጐልጐታ) አደረሰችው::
ደስ ብሎት ቅዱሳት መካናትን ተሳልሞ ደመናዋ ወደ ሃገሩ መለሰችው:: ከጥቂት ጊዜ በኋላም ከሰማይ ነቢዩ ኤልያስና መጥምቁ ወርደው ባረኩትና "ክፍልህ ከእኛ ጋር እንዲሆን መንን" አሉት::
ዘዮሐንስ ወላጆቹንና ቤተ ክርስቲያንን እያገለገለ (ዲቁና ነበረውና) ሃያ አምስት ዓመት ሞላው:: ያን ጊዜ ወላጆቹ "እንዳርህ" ቢሉት "የለም! አይሆንም" አላቸው:: አርጅተው ነበርና ስለእነርሱ ዕረፍት ጸለየ:: ፈጣሪም ሰምቶታልና ሁለቱም በክብር ተከታትለው ዐረፉ::
ሕዝቡ በወላጆቹ ፈንታ "እንሹምሕ" ቢሉት "እንቢ" ብሎ ወርቁን : ብሩን : ርስቱን : ቤቱን ሁሉ ለነዳያን አካፍሎ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገባ::
ጊዜው አቡነ ተክለ ሃይማኖት ባረፉ በሃምሳ ዓመት አካባቢ ሲሆን አባ ሕዝቅያስ አበ ምኔት ነበሩ::
(ከዚህ በኋላ አንቱ እያልን እንቀጥል)
አባ ዘዮሐንስ ለሰባት ዓመታት ገዳሙን ረድተው መነኮሱ:: እንደ ልማዱ ደመና ነጥቆ ወስዷቸው ከኢየሩሳሌሙ ሊቀ ጳጳሳት ቅስና ተቀብለዋልና በደብረ ሊባኖስ ለሃያ አምስት ዓመታት አገለገሉ:: ቤተ መቅደሱን በመዓልት ሰባት ጊዜ በሌሊት ሰባት ጊዜ ያጥኑ : እልፍ እልፍ ይሰግዱ : ተግተው ይጸልዩ : ይታዘዙም ነበር::
ከዚያም በፈጣሪ ትዕዛዝ በትግራይና በሌሎቹ የሃገራችን ክፍሎች ወንጌልን ሰብከዋል:: እድሜአቸው ሰባ በሆነ ጊዜ ወደ ጌታ መቃብር (ጐልጐታ) ሔደው ተሳልመው በእርሱ (በጌታ) ትዕዛዝ ወደ ደራ (ጣና ዳር) ተመለሱ::
በአካባቢውም ገብርኤልና መስቀል ክብራ የሚባሉ ደጋግ ባለ ትዳሮች ነበሩና በእንግድነት ከቤታቸው አደሩ:: ቤቱ በቅጽበት በበረከት ሞላ:: እነርሱም የጻድቁን አምላክ አመሰገኑ::
ቀጥሎም በመስቀል ክብራ መሪነት ጻድቁ ዘዮሐንስ ወደ ክብራን ገብርኤል ደሴት ገቡ:: (በነገራችን ላይ ደሴቱ ክብራን የተባለ መስቀል ክብራ በምትሰኘው ደግ ሴት ስም ነው:: እርሷና ባሏ ገብርኤል የተቀደሱ ሰዎች ነበሩና::)
ጻድቁ አቡነ ዘዮሐንስ ወደ ደሴቶቹ (ክብራንና እንጦንስ ኢየሱስ) እንደ ገቡ ደሴቶቹ በግማሹ የስውራን ቤት : እኩሉ ደግሞ የጣዖት (ዘንዶ) አምላኪዎች መኖሪያ ነበር:: ጻድቁ ክብራን ገብርኤልንና እንጦንስ ኢየሱስን የመሠረቱት በ1315 ዓ/ም አካባቢ በዐፄ ዓምደ ጽዮን ዘመን ነው:: በአካባቢው ዘንዶ ይመለክ ነበርና ያንን በጸሎታቸው አጥፍተው ሕዝቡን አጥምቀዋል::
በዚያም ገዳሙን የወንድና የሴት ብለው ከፈሉ:: የወንዶች ክብራን ሲሆን ሴት አይገባበትም:: አበ ምኔቱም ራሳቸው ጻድቁ ነበሩ::
የሴቶች እንጦንስ ኢየሱስ ከካህናት በቀር ወንድ አይገባበትም:: እመ ምኔቷም እናታችን ቅድስት ክብራ (መስቀል ክብራ) ሆነች::
ጻድቁ አቡነ ዘዮሐንስ በክብራን ለሰላሳ አምስት ዓመታት ተጋድለዋል:: ለጸሎት ከመቆማቸው ብዛት እግራቸው አብጦ : ቆሳስሎ ነበር:: የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘወትር ይገለጽላቸው : ያነጋግራቸውም ነበር::
እጅግ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን ሠርተው: ለወንጌል እንደሚገባ ኑረው: በተወለዱ በመቶ አምስት ዓመታቸው በዚህች ቀን ዐርፈዋል:: ጌታችንም በስማቸው ለተማጸነና ገዳማቸውን ለሳመ የምሕረት ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል:: ልደታቸው ደግሞ ኅዳር 13 ቀን ይከበራል:: ገዳማቸው (ክብራን ገብርኤልና እንጦንስ ኢየሱስ) ድንቅ ነውና እንድታዩት ተጋብዛቹሃል::
††† ቅዱስ አባ ኖብ ሰማዕት †††
††† በምድረ ግብጽ ከታዩ ታላላቅ ከዋክብት አንዱ ቅዱስ ኖብ በሃገረ ንሒሳ ተወልዶ ያደገ ሲሆን ዘመኑም ዘመነ ሰማዕታት (3ኛው መቶ ክ/ዘመን) ነው:: ወላጆቹ በልጅነቱ ብዙ ሃብት ትተውለት ያርፋሉ:: ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔዶ ካህኑ ስለ ምናኔና ሰማዕትነት ሲሰብክ ይሰማዋል::
ገና በአሥራ ሁለት ዓመቱ በቤቱ የነበረውን ሁሉ ለነዳያን አካፍሎ መስቀለ ክርስቶስን ሊሸከም ወደ ዐውደ ስምዕ (የምስክርነት አደባባይ -የክርስቲያኖች መገደያ ቦታ) ተጓዘ:: በዚያም በጉባዔ መካከል ክርስቶስን ሰበከ:: በዚህ ምክንያት በሰብዓዊ አካል ሊሸከሙት የማይችሉትን መከራ በልጅ ገላው ተቀብሏል::
በዚያው ልክም ብዙ ተአምራትን ሰርቷል:: በተአምራቱና በጣዕመ ስብከቱም ከመቶ ዘጠና ሺህ በላይ አሕዛብን ወደ ክርስትና መልሶ ሁሉም ተሰይፈዋል:: በእሳት: በስለት: በሰይፍ: በባሕርና በየብስ መከራን ከተቀበለ በኋላ በዚህች ቀን አክሊለ ክብርን ይቀበል ዘንድ አንገቱን ተከልሏል::
ጌታችን የገባለት ቃል ኪዳኑ ግሩም ነውና ዛሬ በግብጽ በድምቀት ይከበራል:: ምንም በእድሜ ልጅ ቢሆን ቤተ ክርስቲያን አባ (አባታችን) ኖብ ትለዋለች::
††† ቸር ጌታ መድኃኔ ዓለም በጻድቁና በሰማዕቱ ጸሎት ይማረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
††† ሐምሌ 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ዘክብራን (ኢትዮጵያዊ)
2.ቅዱስ አባ ኖብ ሰማዕት
3.መቶ ዘጠና ሺህ ሰማዕታት (የአባ ኖብ ማኅበር)
4.አባ ተክለ አዶናይ ዘደብረ ሊባኖስ
5.አቡነ ተወልደ መድኅን (ኢትዮጵያዊ)
6.አባ ስምዖን ጻድቅ ሊቀ ጳጳሳት
7.ቅድስት ክብራ (መስቀል ክብራ) ዘእንጦንስ ኢየሱስ
††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
2.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤጲስቆጶስ)
3.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
4.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
5.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
6.ሃያ አራቱ ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል)
7.ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም (ኢትዮጵያዊ)
††† "ስለዚህ እኔ ደግሞ በእናንተ ዘንድ ስለሚሆን በጌታ በኢየሱስ ስለማመንና ለቅዱሳን ሁሉ ስለሚሆን መውደድ ሰምቼ ስለ እናንተ እያመሰገንሁ ስጸልይ ስለ እናንተ ማሳሰብን አልተውም::" †††
(ኤፌ. ፩፥፲፭)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
1 ሳምንት
* ሳምንት “ሰመነ ስምንት/8/ አደረገ ከሚለው ከግዕዝ ቃል የተገኘ ነው። * በሕገ ዑደት መሠረት ዕለት ከተነሣበት ማለትም ከእሑድ እስከ እሑድ ያለው ጊዜ ሳምንት ተብሎ ይጠራል።
በዚህ ሳምንት ውስጥ ያሉት ቀናት እያንዳንዳቸው 24 ሰዓት ያላቸው ናቸው።
2 የዕለታት ስያሜ
1 እሑድ ፡ አሐደ ከሚለው ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም አንድ አደረግ * የመጀመረያ ሆነ ማለት ነው፡፡ በዚህ ቀን ፍጥረታት መፈጠር ስለጀመሩ እሑድ ተብሏል፡፡
2. ሠኑይ ያሰኞ/፡ ሠነየ ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ሁለት አደረገ ማለት ነው፡፡ ለሥነ-ፍጥረት ሁለተኛ ስለሆነ ሰኑይ/ ሰኞ/ ተብሏል።
3. ሠሉስ ማክሰኞ ፡ ሠለሰ ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን ሦስት አደረገ
ማለት ነው፡፡ ማክሰኞ የሚለው የሰኞ ማግስት ማለት ነው፡፡
4. ረቡዕ ፡ ረብዐ /አራት አደረገ/ ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን ለሥነ ፍጥረት አራተኛ ቀን ማለትነው፡፡
5. ሐሙስ፣ ሐመሰ ኣምስት አደረገ ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን ለሥነ
ፍጥረት አምስተኛ ቀን ማለት ነው።
6. ዓርብ ፡ ዓረበ ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን ተካተተ ማለት ነው። ፍጥረታት እሑድ መፈጠር ጀምረው አርብ ስለተካተቱ ተፈጥረው ስለተፈፀሙ አርብ ተብሏል።
7 ቅዳሜ፡ ቀዳሚት ማለት ሲሆን ሰንበተ ክርስቲያን ከሆነችው ከዕለተ እሑድ ቀድማ ስለምትገኝ ቀዳሚት ሰንበት ቅዳሜ ተብላለች፡፡
+ + +
ሰማዕቱ ቅዱስ መቃርስ፡- ይኽም ቅዱስ ሰማዕት የጭፍሮች አለቃ የሆነ የታላቁ ሰማዕት የቅዱስ ፋሲለደስ ልጅ ነው፡፡ አባቱ ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ፋሲለደስ የሮሙ ንጉሥ የሠራዊቱ አለቃ ነበር፡፡ ለአንጾኪያ ነገሥታትም አባታቸውና መካሪያቸው ነው፡፡ በመንግሥት ሥልጣኑ እጅግ የበዙ አገልጋዮች ነበሩት፡፡ የፋሲለደስ ሚስት ለቅዱስ ፊቅጦር እናት እኅቷ ናት፡፡ ከእርሷም አውሳብዮስንና መቃርስን ወለደ፡፡ ንጉሡና ሁሉም የመንግሥት ልጆች በጦርነት ላይ ሳሉ የንጉሡ ሴት ልጅ ከሃዲው ዲዮቅልጥያኖስን አግብታ አነገሠችው፡፡ እርሱም ከነገሠ ከጥቂት ቀን በኋላ ጣዖታትን ማምለክና ክርስቲያኖችን ማሳደድ ጀመረ፡፡ ቅዱስ ፋሲለደስም ከጦርነት ሲመለስ ይህን ሲሰማ እጅግ አዝኖ የመንግሥት አገልግሎቱን ተወ፡፡ ንጉሡ ኑማርያኖስ አስቀድሞ ወደ ጦርነት ልኳቸው የነበሩት ልጁ ዮስጦስና የፋሲለደስ ልጅ አውሳብዮስ ጠላቶቻቸውን ሁሉ ድል አድርገው ደስ ብሏቸው ሲመለሱ ዲዮቅልጥያኖስ ነግሦ ክርስቶስን ክዶ ጣዖት አቁሞ አገኙት፡፡ ሁሉም እጅግ ተቆጥተው ሰይፎቻቸውን መዘው ዲዮቅልጥያኖስን አጥፍተው የንጉሡን ልጅ ዮስጦስን ሊያነግሡ ወደው ነበር ነገር ግን ቅዱስ ፋሲለደስ ለመንግሥት ልጆች ሁሉ አባታቸው ነበርና ከዚህ ሥራ ከለከላቸው ይልቁንም ሁሉም በጌታችን ስም ሰማዕት ይሆኑ ዘንድ ተማከሩ፡፡ ቅዱስ ፋሲለደስ ልጁን አውሳብዮስንና ሌሎቹንም የመንግሥት ልጆች ሁሉ ጠርቶ ስለ ዲዮቅልጥያኖስ ክህደት ከነገራቸው በኋላ ‹‹እኔ ስለ ፈጣሪዬ ስለ ክርስቶስ ስም ደሜን አፈሳለሁ›› ሲላቸው ሁሉም በዚህ በጎ ምክር ተስማምተው እርስ በርሳቸው ተማማሉ፡፡ በዚህም ጊዜ ከሰማይ ድምጽ መጣላቸውና ጌታችን ሰማዕት ይሆኑ ዘንድ እንደመረጣቸው ነገራቸው፡፡ የሚደርስባቸውንም መከራ ሁሉ አስረዳቸው፡፡
ሁሉም የመንግሥት ልጆች ንጉሡን ‹‹ሰማዕትነታችንን ፈጽምልን፣ ካልሆነ ከመንግሥትህ እናወርድሃለን›› እያሉት በሰማዕትነት ይገድላቸው ዘንድ አዘዙት፡፡ እነርሱም እጅግ ኃያላን ነበሩና ንጉሡ ፈራቸው፡፡ እንደፈቃዳቸውም ሰማዕት ይሆኑ ዘንድ ወደተለያዩ አገራት ላካቸው፡፡ የቅዱስ ፋሲለደስን ልጅ ቅዱስ መቃርስን ዲዮቅልጥያኖስ የሚያደርገውን ቢያጣ ወደ እስክንድርያ ላከው፡፡ ወደ እስክንድርያም ሲወስዱት ጌታችን ለቅዱስ መቃርስ ተገልጦለት ካጽናናው በኋላ ሰማዕትነቱን በትዕግስት እንዲፈጽም ነገረው፡፡ እስክንድርያ ከተማ በደረሰም ጊዜ ንጉሡ ኅርማኖስ ፊት አቆሙት፡፡ መኰንኑም የቅዱስ ፋሲለደስ ልጅ እንደሆነ ባየ ጊዜ ብዙ በማባበል ለመነው፡፡ ሰማዕቱ መቃርስ ግን በሀሳቡ አልተስማማም ይልቁንም ጣዖት አምላኪነቱን ነቀፈበት፡፡ ከዚህም በኋላ ሰውነቱ እስኪቀልጥ ድረስ እጅግ አሠቃየው፡፡ ጌታችንም የቅዱሳንን ማደሪያዎች፣ የአባቱንና የወንድሙን ማደሪያ አሳይቶት ሰውነቱንም ፈወሰለት፡፡ መኰንኑም ወደ ኒቅዮስ አገር ሰደደውና በዚያም እጅግ አሠቃዩት፡፡ የብረት ችንካሮችን ሠርተው በእሳት አግለው ጎኖቹን በሱት፡፡ ምላሱን ቆርጠው ጣሉት፡፡ ክንዶቹንም በየተራ ቆረጡት ነገር ግን ጌታችን አሁንም ፈወሰው፡፡ ሰማዕቱም እጅግ አስገራሚ የሆኑ ታላላቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን በእግዚአብሔር እንዲያምኑ አደረጋቸው፡፡ የሞተንም ሰው እያስነሣ ስለ ጌታችን አምላክነት እንዲመሰክር ያደርግ ነበር፡፡ በክርስቶስ ያመኑትን አሕዛብም ንጉሡ በሰይፍ ፈጃቸው፡፡ ጌታችንም ለሰማዕቱ መቃርስ የሰማዕትነት ፍጻሜው እንደሆነ ነግሮት ሐምሌ 22 ቀን አንገቱን በሰይፍ ቆረጡትና የሰማዕትነቱ ፍጻሜ ሆኖ የክብር አክሊልን ተቀዳጀ፡፡ ጻዲቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስም ከነገሠ በኋላ ሃይማኖት ተመለሰች፡፡ አብያተ ክርስቲያናትም መታነጽ ሲጀመሩ ሰማዕቱ ቅዱስ መቃርስ ለአንዱ ደግ ክርስቲያን መኰንን ተገለጠለትና ቅዱስ ሥጋው ያለበትን ነገረው፡፡ መኰንኑም ሰማዕቱ ወዳመለከተው ቦታ ሄዶ ቅዱስ ሥጋውን ወስዶ የሚያምር ቤተ ክርስቲያን አሠርቶ በውስጡ አኖረው፡፡ በዚያም ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ይሠራ ጀመር፡፡ የሰማዕቱ የቅዱስ መቃርስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!
+ + +
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል፡- ኢዮር፣ ራማ እና ኤረር የተባሉ ሦስት የመላእክት ከተሞች አሉ፡፡ እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክት ከፈጠራቸው በኋላ በነገድ 100 በአለቃ 10 አድርጎ በሦስቱ ሰማያት አስፍሯቸዋል፡፡ ኢዮርን በ4፣ ራማን በ3፣ ኤረርንም በ3 ከፍሎ ነው በዓሥሩ ከተማ ያሰፈራቸው፡፡
በዚህም መሠረት ኢዮርን ላይና ታች አድርጎ በ4 ከተማ ከፍሏታል፡፡ በእርሷ ያሉትን መላእክትን በ40 ነገድ 4 አለቃ አድርጎ ከፈላቸው፡፡ የመጀመሪያው ነገድ ‹‹አጋእዝት›› ይባላሉ፡፡ አለቃቸው ሣጥናኤል ነበር፤ እርሱም የመላእክትን ሁሉ ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ያሳርግ ነበር፡፡ ከክብሩ ሲዋረድ ቅዱስ ሚካኤል በምትኩ ተሹሞበታል፡፡ ሁለተኛው ነገድ ‹‹ኪሩቤል›› ይባላሉ፡፡ እነርሱም መንበረ ሥላሴን ይሸከማሉ፡፡ የቀሳውስት አምሳል ናቸው፡፡ አለቆቻቸው ገጸ ሰብና ገጸ አንበሳ ናቸው፡፡ በሦስተኛው ከተማ በኢዮር ያሉት ሱራፌል ይባላሉ፡፡ የዲያቆናት አምሳል ናቸው፡፡ በትንቢተ ኢሳያስ በምዕራፍ 6 ላይ የተገለጹትና ኢሳያስን ከለምጹ እንዲፈወስ ያደረጉት ናቸው፡፡ አለቆቻቸው ገጸ ላህምና ገጸ ንስር ናቸው፡፡ (በነገራችን ላይ ‹‹ኪሩቤል›› ወይም ‹‹ሱራፌል›› የሚባሉ የግለሰብ መጠሪያ ስሞች ስህተት ናቸው፡፡ አንደኛ እነዚህ ስሞች የብዙ መላእክት መጠሪያን የሚወክሉ ናቸው፡፡ ለአንዱ ሲሆን ‹‹ኪሩብ፣ ሱራፊ›› ይባላል፡፡ ‹ኪሩቤል› ወይም ‹ሱራፌል› ማለት ግን የብዙ ቁጥራቸው መጠሪያ ነው፡፡ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ የቅዱሳን መላእክትን ስም እንዳለ በቁሙ ወስዶ ለግል መጠሪያ ስም ማዋል ተገቢ አይደለም፡፡ ‹‹ወለተ ሚካኤ፣ ክብረ ገብርኤል….›› እየተባሉ ይሰየማሉ እንጂ ቀጥታ ‹ሚካኤል›፣ ‹ገብርኤል› እያሉ ሰዎችን መሰየም ስህተት ነው፡፡ 4ኛው ከተማ በኢዮር ያሉት ኃይላት ይባላሉ፡፡ የእሳት ሰይፍ ይዘው በሥሉስ ቅዱስ ፊት የሚቆሙ ናቸው፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወት የዛሉና የደከሙ ክርስቲያኖችን የሚያበረታቱ ናቸው፡፡ አለቃቸውም ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡)
ዳግመኛም እግዚአብሔር በራማ ያሉትን መላእክት በ30 ነገድ በ3 አለቃ አድርጎ ከፈላቸው፡፡ የመጀመሪያዎቹ ‹‹አርባብ›› ይባላሉ፡፡ የሥላሴ እልፍኝ አስከልካዮች ናቸው፡፡ የእግዚአብሔርን መንበር በክንፎቻቸው ይሸፍናሉ፡፡ አለቃቸው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ሁለተኞቹ በራማ ከተማ ያሉት ‹‹መናብርት›› ይባላሉ፡፡ ለእግዚአብሔርን እጅግ ቅርብ የሆኑ ናቸው፡፡ የመብረቅ ጋሻቸውን የእሳት ጦራቸውን ይዘው የሥላሴ ጋሻ ጃግሬዎች ሆነው በተጠንቀቅ ይቆማሉ፡፡ የሰውን ችግር ለእግዚአብሔር ያቀርባሉ፡፡ መዝ 88፡6፡፡ አለቃቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ሦስተኞቹ በራማ ከተማ ያሉት ‹‹ሥልጣናት›› ይባላሉ፡፡ መላውን ፍጥረት ለመጠበቅ ሥልጣን የተሰጣቸውና የምጽአት ዕለት አዋጅ ነጋሪዎች ናቸው፡፡ ዳን 12፡1፡፡ አለቃቸው ቅዱስ ሱርያል ነው፡፡
"ቋንቋ መግባቢያዬ" በዘማሪ ዲ/ን መዝገቡ ሀይሌ New Ethiopian Orthodox mezmur #maryam #or...
https://youtube.com/watch?v=4TC8xuuuz38&feature=share
✳#አቡነ ቀውስጦስ ማለት⁉
🌹☞•••ወር በገባ በ21 የሚታሰቡ በእመቤታችን ልደት ግንቦት 1የተወለዱ በእመቤታችን የዕረፍት ቀን ጥር 21 ያረፉ የእመቤታችን ወዳጅ የአቡነ ቀውስጦስ ወርሐዊ መታሰቢያቸው ነው፡፡
♨☞ጻዱቁ አባታችን አቡነ ቀውስጦስ የተወለዱት በሸዋ ክፍለ ሀገር በውግዳና ቡልጋ ውስጥ ሲሆን አባታቸው ገላውዴዎስ እናታቸው እምነጽዮን ይባላሉ፡፡
♨☞የጻድቁ የአቡነ ተክለሃይማኖት እናት እግዚኃሪያ አምነጽን ታናሽና ታላቅ
እህትማማቾች ናቸው፡፡
♨☞ገላውዴዎስ እና አምነጽዮን እግዚአብሔር የተባረከ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ለዓመታት በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሰዕል ፊት ሲጸልዮና ሲለምኑ እመቤታችንም በስዕሏ ላይ አድራ አናገረቻቸው እንዲህም አለቻቸው፡
☞አንድ ልጅም ትወልዳላችሁ የሚወለደውም እኔ በተወለድኩበት ግንቦት 1 ቀን ሲሆኖ እረፍቱም በእኔ የዕረፍት ቀን ጥር 21 ቀን ነው እሱም የሰማያዊ ንጉሥ ጭፍራ ይሆናል አለቻቸው፡፡ በቃሉ መሠረትም ግንቦት 1 ቀን ጻድቁ አቡነ
ቀውስጦስ ተወለዱ፡፡
☞ጻድቁ አባታችን አቡነ ቀውስጦስ የዚህን ዓለም ተድላ፤ደስታና ጣዕም ንቀው
ፈለገ ሐዋርያትን ተከትለው በሸዋ በከፋና በጅማ ዞረው የጌታችን መድኃኒታችን
የእየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በማስተማር በአረማውያን ነገስታት የሚደርስባቸውን መከራ በመታገስ በተጋድሎ ጸንተው ብዙ ሕዝብ ከአምልኮ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር፤ ከኃጥያት ወደ ጽድቅ መልሰዋል፡፡
☞በተለይም በሸዋ ክፍለ ሀገር ፈንታሌ ላይ ሠሪቲ ለምትባል ጠንቋይ እየተላላኩ ሕዝቡን የሚያስቱና የሚያስቃዩ(አራት መቶ ሰባ ሦስት መቶ) አጋንንትን እንደ ነብዩ ኤልያስ በጸሎታቸው ከሰማይ እሳት አውርደው ተራራውን ደምሰስው አጋንንቱን አቃጥለዋል፡፡ ሕዝቡንም ለጣዖት ለጠንቋይ ከመገዛት አድነውታል፡፡
☞ጻድቁ አባታችን አቡነ ቀውስጦስ በብዙ ተጋድሎ ሲኖሩ በሰማዕትነት ያርፋ
ዘንድ ሰለ እግዚአብሔር መንግሥትና ዘላላማዊ ሕይወት የሚተጉ እንጂ የዚህ
ዓለም መንግሥት ሀብትና ሥልጣን የማይሹ እውነተኛ መናኝ ነበሩ፡፡
☞የታናሽ ወንድማቸው የአፄ ይኩኖ አምላክ ልጅ አፄ አምደ ጽዮን የአባቱን
እቁባት በማግባቱ ይህንን ልታደርግ አይገባህም ብለው እንደ መጥምቀ መለኮት ዮሐንስ ቢገስጹት 11አሸከሮቹን በሌሊቱ ልኮ ከበዩ ወደ አንሣሮ ሀገር
ከወሰዳቸው በኃላ ኮሶ አረህ ከሚባል አፋፍ ላይ በእኩለ ሌሊት በጦር ጎናቸውን አሰወግቶ ደማቸውን አስፈሰሰ፡፡
☞ደማቸውም አስከታላቁ ወንዝ ጀማ ድረስ ሆነ፡፡
☞የፈሰሰው ደማቸውም ቀይ ብርሃን ሲሆን የሌሊቱ ጨለማ ከፀሐይ ሰባት እጅ የሚበልጥ ብርሃን በአውራጆቹ ሁሉ ታየ፡፡ በዘህ የተነሣ እሰከ ዛሬ ድረስ ሀገሩ ቀን ተብሎ ይጠራል፡፡
☞ነፍሳቸው ከስጋቸው ስትለይ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ
ከቅዱስ ድንግል ማርያም ጋር መጣና እንዲህ አላቸው፡፡
☞በዘመንህ ሰላሰለፍከው ክርስቲያናዊ ፍፁም ተጋድሎህ (7) የብርሃን አክሊል (ዘውጆች)ያዘጋጀውልህ ሲሆን
☞2 ለቱ እንደ ነብዩ ኤልያስና ነብዩ ሳሙኤል ለሆነው ንፅህናህ፡፡
☞2ለቱ እን አነ ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ ለሆነ የወንጌል ሰብከትህ፡፡
☞2ለቱ እንደ አነ ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅዱስ ፊቅጦር በትዕግሥት ሰለተጋደልክ፡፡
☞አንዱ(1) ሰለ ልብህ ርህራሄ ናት ብሎ አጎናጽፈኩህ፡፡
☞እንዲሁም ሰለ እኔ ምስክርነት የሞትከባት ምድር እንደ ዳዊት ሀገር እንደ
እየሩሳሌም ትሁንልህ፡፡ ወደ እርሷ የሆደውም ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ
መቃብሬ ጎለጎታ እንደሄደ እቆጥርለታለሁ፡፡
☞ቡዙ ኃጢያት የሠራ ሰው ንሰሐ ገብቶ በዚያች ሀገር በስምህ ጥቂት ምጽዋት ቢሰጥ እኔ ኃጥአቱን አደመሰሰለታለሁ፡፡ ጠበልህንም ቢጠመቅ በደሉን አጠፋለታለሁ፡፡
☞በእረፍትህ ዕለት ለቤተክርስቲያን ለቅዱስ ቁርባን ሰንዴ፤ ወይንና ዕጣን
ያቀረበ ሰለ ኃጢአቱ ንሰሀ የገባ ሰው ቅዱስ ሥጋውንና ከቡር ደሙን ደሙን
እንደተቀበለ ንጹህ ሰው አደርገዋለሁ፡፡
☞ለስምህ መታሰቢያ በታነጸው ቤተ መቅደስ በንጽህና ቅዱስ ሰጋውንና ከብር
ደሙን የሚቀበል ሰው ራሱን ቤተሰቡን ባልንጀሮቹን ያድናል፡፡
☞ጌታችን ለጻድቁ አቡነ ቀውስጦስ ይህንን ቃል ኪዳን ሰጥቷቸው አረገ፡ ቅዱሳን መላእክትም ነፍሳቸውን ከስጋቸው በክብር ለዩ፡፡
☞እመቤታችን ቅድስት ድንገል ማርያምም በሰማይ መካከል ነፍሳቸውን
በፈገግታ ተቀበለች፡፡
☞የእረፍታቸውም ዕለት እመቤታችን ድንግል ማርያም ባረፈችበት ጥር 21
በመሆኑ እመቤታችንም መታሰቢያህን ለሚያደርጉ ሁሉ በልጄ በረከት
እባርካቸዋለሁ ብላ ቃል ኪዳን ገባችላቸው፡፡
☞የጽሁፍ ምንጭ ☞(ገድለ አቡነ ቀውስጦስ)
☞የጻድቁ አቡነ ቀውስጦስ በረከታቸው አማላጅነታቸው አይለየን፡፡
የቃልኪዳናቸው ተካፋ ያድርገን፡፡
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህ ልጅ
✝✝††† እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም : ቅዱስ ዑራኤል እና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ድንግል እመቤታችን እና ቅዱስ ዑራኤል †††
††† በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት በዚህች ቀን ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ የሆነው ቅዱስ ዑራኤል:-
1.ድንግል ማርያም በአካለ ሥጋ እያለች ወደ ሰማይ አሳርጓታል:: በሠረገላ ብርሃን ጭኖ: በክንፎቹም ተሸክሞ: አስቀድሞ ገነትን ቀጥሎም ሲዖልን አስጐብኝቷታል:: በዚህም ምክንያት እመ ብርሃን ስለ ኃጥአን የምታለቅስ: የምትለምንና የምትማልድ ሆናለች:: ለምናም አልቀረች የምሕረት ቃል ኪዳን ተቀብላለች::
2.ቅዱሱ መልአክ እመ ብርሃንን በስደቷ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መርቶ አምጥቷታል:: በክንፉ ተሸክሞ: በአራቱም አቅጣጫ አዙሮ አሳይቶ አሥራት እንድትቀበል አድርጓል::
3.ጌታችን በተሰቀለ ጊዜ ደሙን በጽዋዕ አድርጐ በኢትዮጵያ ወንዞች ላይ አፍስሷል::
4.ለብዙ ቅዱሳን (አባ ጊዮርጊስን ጨምሮ) ጽዋዐ ልቡናን አጠጥቷል::
††† አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ኢትዮጵያዊ †††
††† ወላጆቻቸው ማርቆስ እና እግዚእ ክብራ ይባላሉ:: ተአምራትን ገና ከእናታቸው ማኅጸን ጀምሮ ይሠሩ የነበሩት ጻድቁ በልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው መንነዋል:: በስብከተ ወንጌልም ትግራይና አካባቢውን አድርሰዋል:: በነዚህም ጊዜያት ብዙ አርድእትን አፍርተዋል::
በጋስጫ ገዳም መስርተው የወንድና የሴት ብለውም ለይተዋል:: ሲጸልዩም ሆነ ሲያስተምሩ ተደሞ ይመጣባቸው የነበረ ሲሆን አንድ ቀን እባቡን ዓሣ አድርገው ደቀ መዛሙርትን አስደንቀዋል::
ከጾም: ከጸሎትና ከስግደት ባሻገር ከወቅቱ ንጉሥ ዓምደ ጽዮን መከራ በመቀበላቸው እንደ ሰማዕትም ይቆጠራሉ:: ከብዙ የገድል ዓመታት በኋላም በ1330 ዓ/ም በዚህች ቀን ትግራይ ውስጥ ዐርፈዋል:: በቆይታ ግን ወደ ጋስጫ ዐጽማቸው ፈልሷል::
††† ቅዱስ ላዕከ ማርያም ኢትዮጵያዊ †††
††† ቅዱሱ የአፄ ናዖድ የልጅ ልጅ : የቅድስት ሮማነ ወርቅ ልጅ : የልብነ ድንግል የእህት ልጅና የገላውዴዎስ አጐት ነው:: በግራኝ አህመድ ዘመን ተማርኮ ወደ የመን : ከዛም ቱርክ ተወስዷል::
ሃይማኖቴን አልክድም ስላለ ብዙ አሰቃይተው : አባለ ዘሩን ቆርጠው ጃንደረባ አደረጉት:: በድንቅ ተአምር ግን ወደ ሃገሩ ተመለሰ:: እስከ ዕለተ ሞቱም ነዳያንን ሲያበላ ኑሮ ዛሬ ዐርፏል::
††† ቅዱስ ሱስንዮስ †††
በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ የኤፌሶን ሰው ሲሆን ጃንደረባም ነበር:: በ431 ዓ/ም ሁለት መቶውን የጉባዔ ኤፌሶን ሊቃውንት አገልግሎ በዛው ዓመት አርፏል:: ቅዱስ ቄርሎስ ገንዞ ቀብሮታል::
††† ብጹዕ አወ ክርስቶስ †††
ከተባረከች ሚስቱ ጋር በአንድ ቤት ውስጥ : ግን ደግሞ በድንግልና ኑረዋል:: ቀን ቀን እንግዳ ሲቀበሉ: ነዳያንን ሲያበሉ ውለው ሌሊት ሲገሰግዱና ሲጸልዩ ያድሩ ነበር:: ጌታችን ከሰማይ መስክሮላቸው ዛሬ ዐርፈዋል::
††† ቅዱስ ዮራኖስ †††
በሉቃስ ወንጌል ላይ (ሉቃ. 23:47) የምናገኘው የመቶ አለቃው ሲሆን በጌታችን ትንሣኤ ቀን የጠፋች ዓይኑ በርታለት በክርስቶስ አምኖ ለሰማዕትነት በቅቷል::
††† ከእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟን ፍቅሯን : ከቅዱሳኑ ሁሉ ጸጋ በረከትን እግዚአብሔር ያድለን::
††† ሐምሌ 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት ድንግል እግዝእትነ ማርያም ወላዲተ አምላክ
2.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
3.አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ጻድቅ (ኢትዮጵያዊ)
4.ቅዱስ ላዕከ ማርያም ሔር (ኢትዮጵያዊ)
5.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ (ኢትዮጵያዊ) ልደታቸው
6.ብጹዕ አወ ክርስቶስና ሚስቱ (ጻድቃን)
7.ቅዱስ ሱስንዮስ ጻድቅ
8.ቅዱስ ዮራኖስ መኮንን (የመቶ አለቃው)
††† ወርኀዊ በዓላት
1.አበው ጎርጎርዮሳት
2.አቡነ ምዕመነ ድንግል
3.አቡነ አምደ ሥላሴ
4.አባ አሮን ሶርያዊ
5.አባ መርትያኖስ ጻድቅ
††† "እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ: ስለ ሶምሶንም: ስለ ዮፍታሔም: ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም: ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና:: እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ:: ጽድቅንም አደረጉ:: . . ." †††
(ዕብ. ፲፩፥፴፪)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
✝††† እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና ለታላቁ ሰማዕት ማር ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ✝በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም✝ †††
††† ለስም አጠራሯ ክብር ይሁንና እመ ብርሃን ድንግል ማርያም በዚህች ቀን ወደ ቤተ መቅደስ ገብታለች:: በዓሉ ከሰላሳ ሦስቱ የእመቤታችን በዓላት እንደ አንዱ አይቆጠርም:: ምክንያቱም ቅዱሳን ሊቃውንት በዓታ ከበዓታ ጋር ይስማማል ብለው የታኅሣሥ ሦስትን በዓል ከሰላሳ ሦስቱ ደምረውታል::
እመቤታችን ወደ ቤተ መቅደስ የገባችው ሁለት ጊዜ ሲሆን:-
1.ዛሬ የምናከብረውና በተወለደች በሰማንያ ቀኗ የገባችበት ነው:: (ከግንቦት 1 ጀምረን እናስላው: 80 ቀን ይመጣል::)
ኦሪት እንዳዘዘው ቅዱሳን ኢያቄምና ሐና ንጽሕት ሕፃን ድንግል ማርያምን ታቅፈው: የርግብ ልጆች (ግልገሎች): ዋኖስም ይዘው ወደ ቤተ መቅደስ ሒደዋል::
ካህናቱ ዘካርያስና ስምዖን ወጥተው በደስታ ተቀብለዋቸዋል:: እመቤታችን ለወላጆቿ ማኅጸን የከፈተች በኩር ናትና በእግዚአብሔር ፊት አቅርበዋታል::
2.ከሦስት ዓመታት በኋላ እንደ ስዕለታቸው ወደ ቤተ መቅደስ ወስደው ለእግዚአብሔር ሰጥተዋት ተመልሰዋል::
እግዚአብሔር ዛሬ ያልቃል: ነገ ይደቃል የማይባለውን የድንግል እናቱን ፍቅር አብዝቶ ያድለን:: በረከቷም በእኛ ላይ ጸንቶ ይኑር::
†††✝ ቅዱስ ቴዎድሮስ ሰማዕት✝ †††
††† በቤተ ክርስቲያን የሰማዕታት አለቅነት ከተሰጣቸው ሰማዕታት አንዱ የሆነው ማር ቴዎድሮስ የተወለደው በምድረ አንጾኪያ (ሶርያ) በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: አባቱ ዮሐንስ በትውልድ ግብጻዊ የሆነ ክርስቲያን ነው:: እናቱ ግን አስቸጋሪና ጣዖት አምላኪ ሶርያዊት ነበረች::
ባልና ሚስት አብረው ሲኖሩ ሚስት ባሏ ክርስቲያን መሆኑን አታውቅም ነበር:: ቴዎድሮስ (የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው) በተወለደ ጊዜ ግን ጠብ ተነሳ:: እሱ ክርስትና ለማስነሳት: ሚስት ደግሞ ወደ ጣዖት ቤት ለመውሰድ ተጋጩ:: ሚስት ወገኖቿ ባለስልጣኖች ናቸውና ልጁን ቀምታ ባሏን ዮሐንስን ወደ ግብጽ አሳደደችው::
ዮሐንስ በስደት ባለበት ሃገር ስለ ልጁ ፈጽሞ ይጸልይ: ያለቅስም ገባ:: እግዚአብሔር ደግሞ ልመናውን ሰማ:: ማር ቴዎድሮስ ወጣት በሆነ ጊዜ ማንም ሳይጠራው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔዶ ተማረ: ተጠመቀ:: ዕለት ዕለትም ጾምና ጸሎትን ከምጽዋት ጋር ያበዛ: ድንግልናውን ለመጠበቅ ይተጋ ነበር::
በዛው ልክ ደግሞ ገና በሃያ ዓመቱ በጉልበቱ ኃያል: በውበቱም ደመ ግቡ: በጠባዩም ገራገር ነበርና ተወዳጅ ነበር:: ነገሥታቱም የአንጾኪያ የጦር ሠራዊት አለቃ አድርገው ሾሙት:: እነሆ እስከ ዛሬ "የሠራዊት አለቃ" ተብሎ ይጠራል::
ማር ቴዎድሮስ በተሳተፈባቸው ጦርነቶች ሁሉ ተሸንፎ አያውቅም:: ይልቁኑ የነገሥታቱን (የጠላት) ልጆች በመማረክ ነው የሚታወቀው:: እንዲያውም አንድ ጊዜ ከአሕዛብ ጋር በተደረገ ጦርነት ብቻውን አሸንፏቸዋል::
የፋርስ ሰዎች ሊዋጉ ሲመጡ መልአክ ከሰማይ ወርዶ ሰይፍ ሰጠው:: ፋርሶችን "በከንቱ ከምትጠፉ ወደ ሃገራችሁ ተመለሱ" አላቸው:: እነርሱ ግን ተሳለቁበት:: ከፈረሱ ወርዶ ወደ ምስራቅ ዙሮ ጸልዮ በመስቀል አማተበ:: በመካከላቸው ገብቶም በመልአኩ ሰይፍ ለወሬ ነጋሪ ሳያስቀር አጠፋቸው::
አንድ ቀን ወደ አንድ ከተማ ቢገባ ዘንዶ ሲመለክ አገኘ:: ይባስ ብሎ የአንዲት ክርስቲያን ልጆችን ለመስዋዕትነት ሲያቀርቧቸው ተመለከተ:: በስመ ሥላሴ አማትቦ: በፈረሱ ላይም ተቀምጦ ዘንዶውን በጦር ገደለው:: የዘንዶውም ርዝመት ሃያ አራት ክንድ ነበር::
ከነገር ሁሉ በኋላ ቅዱስ ቴዎድሮስ ስለ አባቱ ወሬ ሰምቶ: ካለበት ሥፍራ አፈላልጎ አግኝቶ ደስ አሰኘው:: እስኪያርፍ አብሮት ቆይቶ: ቀብሮት ወደ አንጾኪያ ሲመለስ ግን የሚያሳዝን ነገር ጠበቀው::
ክርስቶስ ተክዶ:
ጣዖት ቁሞ:
አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለው:
የክርስቲያኖች ደም ፈሶ:
ከተማዋ በግፍ ተሞልታ ተመለከተ:: እርሱም በዚያች ሰዓት መወሰን ነበረበትና አደረገው:: የሁሉ ሠራዊት አለቃ ቢሆንም የክብር ልብሱን አውልቆ: ባጭር ታጥቆ በንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ ፊት ቆመ::
††† ማር ቴዎድሮስ በአደባባይ እንዲህ ተናገረ:- "አንሰ አመልኮ ለክርስቶስ ንጉሠ ስብሐት በኩሉ ልብየ: ወእሠውዕ ሎቱ - እኔስ የክብር ባለቤት ክርስቶስን በፍጹም ልቤ አመልከዋለሁ: ለእርሱም ብቻ እሠዋለሁ::" ንጉሡ በቁጣ መሬት ላይ ጥለው እንዲደበድቡት አዘዘ:: ወታደሮቹ ደሙ እስኪንጠፈጠፍ ገረፉት::
በብዙ መክፈልተ ኩነኔ አሰቃይተው በእሳት አቃጠሉት:: እርሱ ግን በጸሎቱ እሳቱን ውኃ አደረገው:: ወታደሮቹ እርሱን በብዙ አሰቃዩ:: እርሱ ግን በእግዚአብሔር ኃይል ጸና: ታገሠ::
በመጨረሻም ጌታችን በግርማ ወርዶ "ወዳጄ ቴዎድሮስ ስምህን የጠራ: መታሠቢያህን ያደረገ: ገድልህን (ዜናህን) የጻፈ: ያጻፈ: ያነበበ: ገዝቶ በቤቱ ውስጥ ያኖረውን ሁሉ እምርልሃለሁ" አለው::
በስሙም ረድኤት እንደሚደረግ ነግሮት ዐረገ:: ወታደሮቹም በዚህ ቀን አንገቱን ሰይፈው የክብር አክሊልን ተቀብሏል:: እጅግ ብዙ ሺህ ሰዎችም አብረውት ተሰይፈዋል::
††† ቸሩ ፈጣሪ ከሰማዕቱ በረከት ይክፈለን::
††† ሐምሌ 20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም (በሰማንያ ዕለት)
2.ቅዱስ ወክቡር ማር ቴዎድሮስ ሰማዕት (የሠራዊት አለቃ)
3.ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘእስክንድርያ
4.አራት መቶ አራት ሰማዕታት (የቅዱስ ቂርቆስ ማኅበር)
5.ቅድስት አውስያ (የማር ቴዎድሮስ እናት - በልጇ ምክንያት ያመነች እናት ናት)
††† ወርኀዊ በዓላት
1..ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
2.ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
3.ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮጵያ)
4.አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና
5.ቅድስት ሳድዥ የዋሒት
††† "እግዚአብሔር ለኛ የሰማዕትነትን ሥራ ይሰጠን ዘንድ ቅዱሳን ስለሚሆኑ ሰማዕታት እንማልዳለን::" †††
(ሥርዓተ ቅዳሴ ቁ. ፸፫)
††† "በጐንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማን ነው? ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኳ መከራን ብትቀበሉ ብጹዓን ናችሁ:: ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ:: አትናወጡም:: ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስን በልባችሁ ቀድሱት:: በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ:: ነገር ግን በየውሃነትና በፍርሃት ይሁን::" †††
(፩ጴጥ. ፫፥፲፫-፲፮)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
ዠመርጌታ የባህል ህክምና
የምንሰጣቸዉ የጥበብ አገልግሎት ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል ለበለፀ መረጃ ይደዉሉ 📲0913179074
1 ,ለባል እና ሌሎች ማህበረሰብ የሚያዋድድ
2 ,ለህመም
3, ለሀብት
4, ለገበያ
5,ለሥራ
6,ለአጋንንት
7 ,ለግርማ ሞገስ
8 ,ለብልት
9,ለበረከት
10 ,ለኤችአይቪ ፈዋሽ መድሀኒት
11 ,ለጠላት
12 ,ለጭንቀት
13 ,ለዕድል
14 ,በግብረ ስጋ ግንኙነት ጥሩ እና ያማረ ስሜት እንድኖር
15 ,ብር እንዳይባክን
16, የወር አበባ ችግር ካለ
17,በመኝታ ሽንት ለሚያመልጠው
18,ለድምፅ መታፈን
19,ከአጫሽነት ለመላቀቅ
20,ራስን ስቶ በስቃይ ለሚኖር
21,ለመስተፋቅር
22,ለአይነ ጥላ
23,ለቁብ
ማሳሰቢያ፦የሰውን ልጅ ለመጣል ለማሳበድ በ አጠቃላይ ከህይወት መስመር ለማውጣት አንሰራም
ለጥያቄወ 0913179074
ሐምሌ 19/11/2015 #ቅዱስ_ገብርኤል
👉አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ዐሥራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ሕፃኑ #ቅዱስ_ቂርቆስና እናቱ #ቅድስት_ኢየሉጣ በሰማዕትነት መከራ ተቀበሉ ይህም ሕፃን ዕድሜው ሦስት ዓመት ሲሆነው ከሮሜ አገር ወደሌላ ሀገር እናቱ ይዛው ሸሸች በዚያም የሸሸችውን መኰንን አገኘችው።
👉ሰዎችም ነገር ሠሩባት ወደርሱ አስቀረባትና ስለ አምልኮ ጠየቃት እርሷም መኰንን ሆይ ዕድሜው ሦስት ዓመት የሆነው ሕፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እርሱን ጠይቅ አለችው።
👉ሕፃኑም ወደአለበት ጭፍራውን ልኮ ወደርሱ አስመጣው ሕፃኑንም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና አንተ ደስተኛ ሕፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው። ሕፃኑም መልሶ አዎ ለእኔ ደስታ ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ኀዘንና ልቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው መጽሐፍ ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏልና አለው እግዚአብሔር ኃይልና ንግግርን ሰጥቶታልና ብዙ ተናገረ በዚያም ያሉትን እስከ አስደነገጣቸው ድረስ ንጉሡን መኳንንቱንና ጣዖታቱን ረገማቸው ከብርታቱም የተነሣ አደነቁ።
👉መኰንኑም በአፈረ ጊዜ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይ ታላላቆች የማይችሉትን ታላቅና አስጨናቂ የሆነ ሥቃይን አሠቃየው እናቱንም ከርሱ ጋር እንደ እርሱ አሠቃያት እግዚአብሔርም ያለምንም ጉዳት ያነሣቸው ነበር። ብዙዎች አሕዛብም ይህን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አምነው በሰማዕትነት ሞቱ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበሉ።
👉በሕፃኑ ላይም የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት። ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችንም አደረገ ብዙዎች በሽተኞችንም አዳናቸው።
👉ከዚህም በኋላ መኰንኑ በታላቅ የናስ ጋን ውስጥ ውኃ ጨምረው በእሳት ያፈሉት ዘንድ አዘዘ የፍላቱም ድምጽ እንደ ክረምት ነጐድጓድ ሆነ ያን ጊዜም ፍርሀትና የሃይማኖት ጉድለት በእናቱ ላይ ደረሰባት ሕፃኑም ስለ እናቱ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።
👉ያን ጊዜ ጌታችን ልቧን ወደ ሰማይ አሳርጎ ለቅዱሳን ሰማዕታት የተዘጋጁ የብርሃን ማደሪያዎችን አየች ከዚህም በኋላ ጸናች እግዚአብሔርንም አመሰገነችው ልጅዋንም ልጄ ሆይ ከእንግዲህ አንተ አባቴ ነህ እኔም ልጅህ ነኝ አለችው።
👉ያቺ ከኔ የተወለድክባትም ቀን የተባረከች ናት አለች ወደዚያ ወደ ጋኑ ውስጥ በገቡ ጊዜም የውኃው ፍልሐት እንደ ንጋት ጊዜ ውርጭ ቀዘቀዘ ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የእሳቱን ኃይል አቀዝቅዞታልና።
👉ከዚህም በኋላ መኰንኑ ሥጋቸው ተቆራርጦ እስከሚወድቅ ድረስ በመቃጥን ውስጥ አድርገው እንዲጐትቷቸው አዘዘ ከእግዚአብሔርም የታዘዘ መልአክ አዳናቸው መኰንኑም በታላቅ ሥቃይ ያሠቃያቸው ዘንድ አስቦ እስኪመክር ድረስ በወህኒ ቤት ዘጋባቸው።
👉ያን ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕፃኑ ቂርቆስ ወርዶ አጽናናው አረጋጋውም። ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጠው።
👉ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ቂርቆስና በቅድስት ኢየሉጣ ፀሎት ይማረን በረከታቸውም ትድረሰን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሀገራችንን ህዝባችንን ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅልን የመልአኩ ቅዱስ #ገብርኤል ጥበቃ ተራዳኢነት ቃል ኪዳን ለሁላችንም ይድረሰን "አሜን"
#ቅዱስ_ገብርኤል
እንኳን ለታላቁ መልአክ ለቅዱስ ገብርኤል #ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ፤አደረሰን!!!
➩ በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል ነው፡፡ ይህ ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት እየሉጣንና ልጇን ቅዱስ ቂርቆስን ከሞት አደጋ እንደታደገበት የሚታሰብበት ዕለት ነው።
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
💚 @Addis_Mezmure 💚
💛 @Addis_Mezmure 💛
❤️ @Addis_Mezmure ❤️
++ በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ ወደ እርሱ ቀርቦ፦ ጌታ ሆይ፥ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ልተውለት? እስከ ሰባት ጊዜን? አለው ።
ኢየሱስ እንዲህ አለው፦ #እስከ_ሰባ_ጊዜ_ሰባት
እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ አልልህም።
ስለዚህ መንግሥተ ሰማያት
ባሮቹን ሊቈጣጠር የወደደን ንጉሥ ትመስላለች።
መቈጣጠርም በጀመረ ጊዜ፥ #እልፍ_መክሊት_ዕዳ_ያለበትን_አንድ_ሰው_ወደ_እርሱ_አመጡ። የሚከፍለውም ቢያጣ፥ እርሱና ሚስቱ ልጆቹም ያለውም ሁሉ እንዲሸጥና ዕዳው እንዲከፈል ጌታው አዘዘ። ስለዚህ ባሪያው ወድቆ ሰገደለትና፦ ጌታ ሆይ፥ ታገሠኝ፥ ሁሉንም እከፍልሃለሁ አለው።
የዚያም ባሪያ ጌታ አዘነለትና ለቀቀው፥ ዕዳውንም ተወለት።
ነገር ግን ያ ባሪያ ወጥቶ ከባልንጀሮቹ ከባሮቹ መቶ ዲናር ዕዳ ያለበትን አንዱን አገኘና፦ ዕዳህን ክፈለኝ ብሎ ያዘና አነቀው።
ስለዚህ ባልንጀራው ባሪያ ወድቆ፦ ታገሠኝ፥ ሁሉንም እከፍልሃለሁ ብሎ ለመነው። እርሱም አልወደደም፥ ግን ሄዶ ዕዳውን እስኪከፍል ድረስ በወኅኒ አኖረው።
ባልንጀሮቹ የሆኑ ባሮችም ያደረገውን አይተው እጅግ አዘኑ፥መጥተውም የሆነውን ሁሉ ለጌታቸው ገለጡ።
ከዚያ ወዲያ ጌታው ጠርቶ፦
#አንተ_ክፉ_ባሪያ፥ ስለ ለመንኸኝ ያን ዕዳ ሁሉ ተውሁልህ፤
እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህ የሆነውን ያን ባሪያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን? አለው።ጌታውም ተቈጣና ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍለው ድረስ ለሚሣቅዩት አሳልፎ ሰጠው።
#ከእናንተ_እያንዳንዱ_ወንድሙን_ከልቡ_ይቅር_ካላለ ፥
#እንዲሁ_ደግሞ_የሰማዩ_አባቴ_ያደርግባችኋል።
______ / ማቴ 18 ፥21 - 35 /______
✝✝††† እንኳን ለአቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን : ለአረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ እና አባ ጢሞቴዎስ ዘአልቦ ጥሪት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††
†††✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††✝
†††✝ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን †††✝
††† ቅዱሱ በትውልዳቸው ግሪካዊ ቢሆኑም ሶርያ አካባቢ እንዳደጉ ይታመናል:: በቀደመ ስማቸው ፍሬምናጦስ የሚባሉት አቡነ ሰላማ ወደ ኢትዮዽያ የመጡት በአደጋ ምክንያት (በድንገት) ቢመስልም ውስጡ ግን ፈቃደ እግዚአብሔር ነበረበት::
በድንበር ጠባቂዎች (በአደጋ ጣዮች) ከባልንጀራቸው ኤዴስዮስ ጋር ተይዘው ወደ አክሱም የመጡት በንጉሥ ታዜር (አይዛና) እና በሚስቱ ሶፍያ (አሕየዋ) ዘመን ነው:: ጊዜው በውል ባይታወቅም በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው::
ፍሬምናጦስ ምንም የመጡበት ዓላማ ስብከተ ወንጌል ባይሆንም በአክሱም ቤተ መንግስት አካባቢ ይሰበኩ ነበር:: ያን ጊዜ በጃንደረባው ቅዱስ ባኮስ የተቀጣጠለው የክርስትና ችቦ ውስጥ ውስጡን በሃገሪቱ ነበረና ፍሬምናጦስ አልተቸገሩም:: በተለይ ሕጻናቱን (ኢዛናና ሳይዛናን) ገና ከልጅነት ስላስተማሯቸው ነገሮች የተሳኩ ሆኑ::
ልክ ንጉሥ ታዜር እንደ ሞተ ሁለቱ ሕጻናት በመንበሩ ተቀመጡ:: ፍሬምናጦስንም ወደ ግብፅ ዻዻስና ጥምቀት ከመጻሕፍት ጋር እንዲመጣላቸው ላኩ:: ሐዋርያዊ ቅዱስ አትናቴዎስም ፍሬምናጦስን "ሰላማ" ብሎ ሰይሞ : በዽዽስና : በንዋየ ቅድሳትና በመጻሕፍት ሸልሞ መለሳቸው::
አቡነ ሰላማ ወደ ኢትዮዽያ እንደተመለሱ ከነገሥታቱ ጀምረው ለሕዝቡ ጥምቀትን አደሉ:: ኢዛናና ሳይዛናም አብርሃ (አበራ) እና አጽብሃ (አነጋ) ተብለው ስማቸው ተደነገለ:: ከዚያ በሁዋላ ድንቅ በሚሆን አገልግሎት ነገሥታቱ : ዻዻሱ ሰላማና ሊቀ ካህናቱ እንበረም ለክርስትና መስፋፋት በጋራ ሠርተዋል::
††† ✝የአቡነ ሰላማ ትሩፋቶች:-✝
1.ዽዽስናና ክህነትን ከእውነተኛ ምንጭ አምተዋል::
2.ክርስትናና ጥምቀትን በሃገራችን አስፋፍተዋል::
3.ቅዱሳት መጻሕፍትን ከውጭ ልሳኖች ተርጉመዋል::
4.ገዳማዊ ሕይወትን ጀምረዋል::
5.አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል::
6.ግዕዝ ቋንቋን አሻሽለዋል::
ሀ.ከግራ ወደ ቀኝ እንዲፃፍ
ለ.እርባታ እንዲኖረው
ሐ.ከ"አበገደ" ወደ "ሀለሐመ" ቀይረዋል::
ባላቸው ንጹሕ የቅድስና ሕይወት ለሕዝቡ ምሳሌ ሆነዋ:: "ወበእንተዝ ተሰይመ ከሳቴ ብርሃን" እንዲል ገድላቸው በነዚህ ምክንያቶች "ከሣቴ ብርሃን" (ብርሃንን የገለጠ) ሲባሉ ይኖራሉ:: በመጨረሻም ከመልካሙ ገድል በሁዋላ በ352 ዓ/ም ዐርፈው ተቀብረዋል::
†††✝ ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ ✝†††
††† በሐዲስ ኪዳን መጀመሪያ አካባቢ ስም አጠራራቸው ከከበረ ደጋግ እሥራኤላውያን አንዱ የእመቤታችን ጠባቂ ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ ነው:: ትውልዱ ከነገደ ይሁዳ ሲሆን አባቱ ያዕቆብ ይሰኛል::
በጉብዝናው ወራት የእመቤታችንን አክስት ማርያምን አግብቶ ብዙ ልጆችን ወልዶ አርጅቷል:: ከልጆቹም ዮሳ: ያዕቆብ: ይሁዳ: ስምዖን እና ሰሎሜ በቅዱስ መጽሐፍ ተዘክረዋል:: ቅዱስ ዮሴፍ እድሜው 75 ሲሆን ሚስቱ ማርያም ሞተችበት::
ከጥቂት ወራት በሁዋላም በመንፈስ ቅዱስ ድንግል ማርያምን ሊያገለግል ተመረጠ:: "እጮኛ" የሚለውም ለዛ ነው:: (ለአገልግሎት ነው የታጨው) እመቤታችን ለአረጋዊ ዮሴፍ በ2 ወገን ልጁ (ዘመዱ) ናት::
1.የሚስቱ ማርያም የእህት (የሐና) ልጅ ናት::
2.የቅድመ አያቱ የአልዓዛር የልጅ ልጅ ናት::
ደጉ ሽማግሌ ቅዱስ ዮሴፍ ምን ቢያረጅ እመቤታችንን ለማገልገል አልደከመውም:: አብሯት ተሰደደ:: ረሃብ ጥማቷን: ጭንቅና መከራዋን: ሐዘንና ችግሯን ተካፍሏል:: ከእመ ብርሃንና አምላክ ልጇ ጋር ለ16 ዓመታት ኑሯል::
ከእነዚህ ዘመናት በሁዋላም በ16 ዓ/ም : በተወለደ በ91 ዓመቱ ሲያርፍ ጌታችን "ሥጋሕ አይፈርስም" ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶለታል::
"ኢየሱስ ክርስቶስ በከመ አሠፈዎ ኪዳነ::
ኢበልየ በመቃብር ወኢሂ ማሰነ::
እስከ ዮም በድኑ ሐለወ ድኁነ::" እንዳለ መጽሐፈ ስንክሳር::
†††✝ ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘአልቦ ጥሪት ✝†††
††† ይህ ቅዱስ አባት በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የእስክንድርያ ፓትርያርክ የነበረ አባት ነው:: ዘመነ ሲመቱም ከ377 እስከ 387 ድረስ ለ10 ዓመታት ነው:: በእነዚህ ዘመናቱ "ዘአልቦ ጥሪት" (ገንዘብ የሌለው / ነዳዩ አባት) ነበር የሚባለው:: ገንዘብንና ዓለምን የናቀ አባት ነበር::
ቅዱስ ጢሞቴዎስ የቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ደቀ መዝሙር እንደ መሆኑ ከመንፈሳዊ አባቱ መልካም ሕይወትን ወርሷል:: ምሥጢራትንም አጥንቷል:: በዘመኑ የአርዮስ ውላጆች ቤተ ክርስቲያንን ያስቸግሩ ነበርና ከእነርሱ ጋር ተዋግቷል:: ምዕመኑንም ከተኩላዎች ይጠብቅ ዘንድ ተግቷል::
በ381 ዓ/ም በቁስጥንጥንያ ጉባዔ በተደረገ ጊዜ ማሕበሩን በሊቀ መንበርነት መርቷል:: ለመቅዶንዮስ : ለሰባልዮስና ለአቡሊናርዮስ ኑፋቄዎችም ተገቢውን ምላሽ ሰጥቶ አውግዟል:: ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘአልቦ ጥሪት በቅድስና ተመላልሶ በ387 ዓ/ም በዚህች ቀን ዐርፏል::
††† ፈጣሪ ከአቡነ ሰላማ : ከአረጋዊ ዮሴፍና ከቅዱስ ጢሞቴዎስ በረከትን ያሳትፈን::
††† ሐምሌ 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
2.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ (የድንግል ማርያም ጠባቂ)
3.ቅዱስ አባ ጢሞቴዎስ (ዘአልቦ ጥሪት)
4.አባ ሮዲስ
††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
2.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
3.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
4.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
††† "እናንተ የምድር ጨው ናችሁ . . . እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ:: በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትም:: መብራትንም አብርተው በዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያናሩታል:: በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል:: መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ::" †††
(ማቴ. 5:13-16)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ሐምሌ 25-ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ ድንቅ ተአምር ያደረገበትና ቅዳሴ ቤቱ የከበረበት ዕለት ነው፡፡ ልደቱም በዚሁ ዕለት ነው፡፡
+ ከበሬ ጋር ተጠምደው ሰማዕትነትን የተቀበሉት ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ሕፃን ሞዐ ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ ነቢዩ ሄኖክ ዕርገቱ ነው፡፡
+ የቅዱስ ጳውሎስ ረዳት የሆነችው ሰማዕቷ ቅድስት ቴክላ ዕረፍቷ ነው፡፡
+ ሰማዕቱ ቅዱስ ዱማድዮስ ዕረፍቱና ፍልሰተ ሥጋው ነው፡፡
+ ሰማዕቱ ቅዱስ አበከረዙን ዕረፍቱ ነው፡፡
+ ሰማዕቷ ቅድስት ኢላርያ ዕረፍቷ ነው፡፡
+ ሰማዕታቱ ቅድስት ቴክላ እና ቅድስት ሙጊ ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ ሰማዕቱ ቅዱስ እንዲኒና ዕረፍቱ ነው፡፡
+ ሰማዕቱ አቡነ ይስሐቅ ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ የ600 ሰማዕታት መታሰቢያቸው በዓላቸው ነው፡፡
+ ዳግመኛም በዚህች ዕለት የ25 ሺህ የአትሪብ ሰማዕታት መታሰቢያቸው ሆነ።
+++
አቡነ ሕፃን ሞዐ፡- በአባታቸው አርከሌድስ እናታቸው ትቤ ጽዮን ይባላሉ፡፡ የተወለዱት ጥር 25 ነው፡፡ አቡነ ሕፃን ሞዐ ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ጋር የሥጋ ዝምድና አላቸው፡፡ ይኸውም አባታቸው አርከሌድስና ጸጋ ዘአብ ወንድማማቾቸ ናቸው፡፡ አርከሌድስና ጸጋ ዘአብ ሌሎች 4 ወንድሞች አሏቸው፡፡
እነርሱም እንድርያስ፣ ዘርዐ አብርሃም፣ ቀሲስ ዮናስ እና ቀሲስ ዮሐንስ ናቸው፡፡ አርከሌድስ ሕፃን ሞዐን ይወልዳል፣ ጸጋ ዘአብ ተክለ ሃይማኖትን ይወልዳል፣ እንድርያስ ሳሙኤል ዘወገግን፣ ዘርዐ አብርሃም ታላቁ አኖሬዎዮስን፣ ቀሲስ ዮናስ ገላውዲዮስንና የፈጠጋሩን ማትያስን፣ እና ቀሲስ ዮሐንስ ዜናማርቆስን ይወልዳሉ፡፡ እነዚህ የከበሩ ቅዱሳን አባቶቻችን በእናታቸውም ወገን ቢሆን እንዲሁ በዝምድና የተቆራኙ ናቸው፡፡ አቡነ ሕፃን ሞዐ በሌላኛው ስማቸው ሕፃን ዘደብረ በግዕ ተብለውም ይጠራሉ፡፡ ይኸውም የደብረ በግዕን ገዳም የመሠረቱት እርሳቸው ስለሆኑ ነው፡፡ ከ47ቱ የሀገራችን ቀደምት ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ በመንዝና በተጉለት የሚገኙ ታላላቅ ገዳማትን አብዛኞቹን የመሠረቷቸው አቡነ ሕፃን ሞዐ ናቸው፡፡ ጻድቁ በክፉዎች ወሬና ሴራ ምክንያት ከበሬ ጋር ተጠምደው ሰማዕትነት የተቀበሉ አባት ናቸው፡፡ ከበሬ ጋር ሲታረሱ ውለው በእጅጉ ከደከማቸው በኋላ በኃይል የተነፈሱባት ምድሪቱ ዛሬም ድረስ ልክ እንደሰው የሚሞቅ ትንፋሽ ታወጣለች፡፡ ያም በጻድቁ እስትንፋስ አምሳል ከመሬት ውስጥ የሚወጣው እስትንፋስ ለአስም በሽታ መድኃኒት ሆኖ ብዙዎችን እየፈወ ነው፡፡ ገዳማቸው ከደብረ ብርሃን ከተማ በእግር የ2 ሰዓት መንገድ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ይኸውም ከወንይዬ ተክለ ሃይማኖት ገዳም አጠገብ ነው፡፡ ጻድቁ ጥር 25 ቀን ልደታቸው፣ ጥቅምት 25 ቃል ኪዳን የተቀበሉበት ዕለት ሲሆን ሐምሌ 25 ደግሞ ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ ++
ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ
‹‹መርቆሬዎስ›› ማለት የአብ ወዳጅ ማለት ነው፡፡ ዳግመኛም የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ወላጆቹ አስሊጥ ከምትባል ሀገር ቢሆኑም እርሱ ግን ተወልዶ ያደገው በሮሜ ከተማ ነው፡፡ አያቱና አባቱ ሥራቸው አውሬ ማደን ስለነበር አንድ ቀን እንደልማዳቸው አውሬ ሲያድኑ ከገጸ ከለባት ወገን የሆኑ ሁለት ወንዶች አግኝተዋቸው የመርቆሬዎስን አያት በሉት፡፡ አባቱንም ሊበሉት ሲሉ የታዘዘ መልአክ ከለከላቸው፡፡ ዙሪያቸውንም በእሳት አጥሮ ከበባቸው፡፡ እነርሱም በተቸገሩ ጊዜ ለመርቆሬዎስ አባት ሰገዱለት፡፡ በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር ፍጥረታቸውን ወደገራምነት ለወጠውና እንደበጎች የዋሆች ሆነው አብረውት ወደ መንደር ገቡ፡፡
ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዎስ ተወለደና ስሙ ፒሉፓዴር ተባለ፡፡ የውሻ መልክ ያላቸውም በእርሱ ዘንድ ብዙ ዘመናት ኖሩ፡፡ ከዚህም በኋላ ክርስቲያኖች ሆኑ፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስም ወላጆች አስቀድመው አረማውያን ነበሩና የክርስትና ጥምቀትን በጸጋ ተቀበሉ፡፡ አባቱን ኖህ እናቱንም ታቦት ብለው ሰየሟቸው፡፡ ቀድሞ ፒሉፓዴር የነበረውም ስሙ ተለውጦ መርቆሬዎስ ተባለ፡፡ የውሻ መልክ ያላቸው ግን መልአኩ በተገለጠላቸው ጊዜ እንደነገራቸው ለቅዱስ መርቆሬዎስ አባት የሚታዘዙና የሚያገለግሉ ሆኑ፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባትና የውሻ መልክ ያላቸውን ዜናቸውን ሲሰማ ወታደሮቹን ልኮ በፊቱ አቆማቸው፡፡ እግዚአብሔርም የቀድሞ ፍጥረታቸውን መልሶላቸው አራዊት አደረጋቸውና ንጉሡን እጅግ አስፈሩት፡፡ ንጉሡም የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት የአራዊት ተፈጥሮአቸውን ያርቅለት ዘንድ ለመነው፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስም አባት በለመነ ጊዜ ተፈጥሮአቸውን መልሶላቸው ገራሞች ሆኑ፡፡
ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ገዥና የሠራዊቱ አለቃ አድርጎ ሾመው፡፡ የውሻ ፊት ያላቸውም አብረው ያገለግሉት ስለነበር ሁሉም ይፈራው ነበር፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ወደ ጦርነት ከላከው በኋላ ሳይመለስ ስለቀረ ሚስቱን ሊያገባት አሰበ፡፡ የመርቆሬዎስ አባትም የመርዶሳውያን አገሮች ሁሉ ገዢ በነበረው ንጉሥ ተይዞ ቢማረክም ገዥው ክርስቲያን መሆኑን አይቶ አከበረው፡፡ ቆይቶም በሀገሩ ላይ ሾመው፡፡ ሚስቱም ጠፍታ ከሀገሯ ወጥታ ሄዳ ስለነበር ከባሏ ተገናኝተው በዚያው መኖር ጀመሩ፡፡ መርቆሬዎስም አባቱና እናቱ ከሞቱ በኋላ ንጉሡ በአባቱ ፈንታ በመርዶሳውያን አገር ላይ ሾመው፡፡
መርቆሬዎስ መኰንንነት በተሾመም ጊዜ ገጸ ከለባቱ አብሮት ነበር፡፡ ለመዋጋትም በወጣ ጊዜ የቀድሞው የአራዊት የሆነ ተፈጥሮውን እግዚአብሔር ይመልስለት ስለነበር ማንም አይቋቋመውም ነበር፡፡ ለቅዱስ መርቆሬዎስ ታላቅ የድል አድራጊነት ኃይል ተሰጠውና ዜናው በሁሉም አገሮች ተሰማ፡፡ በሮሜ ሀገር ጣዖትን የሚያመልከው ዳኬዎስ የተባለውም ንጉሥ የበርበር ሰዎች ጋር ጦርነት ሊገጥም በወጣ ጊዜ እጅግ ሲበዙበት ፈራ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም በጦሩ መሀል የተሳለ ሰይፍ የያዘ የእግዚአብሔርን መልአክ ስላየ ንጉሡን እግዚአብሔር ያጠፋቸዋልና አትፍራ›› አለው፡፡ መልአኩም ሰይፉን ለቅዱስ መርቆሬዎስ ሰጠውና ‹‹ጦርነቱን ድል ባደረግህ ጊዜ እግዚአብሔርን አስበው›› አለው፡፡
ጦርነቱን ድል አድርጎ ሲጨርስም መልአኩ ድጋሚ ተገልጦለት ‹‹ለምን የፈጣሪህን ስም መጥራት እረሳህ?›› አለው፡፡ ከጦርነቱም በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረግ በዓልን አደረገ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም በዚያ ስላልተገኘ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረጉ እንዳልተባበረ ንጉሡ ሲያውቅ መልእክተኞችን ልኮ አስመጣው፡፡ ንጉሡም ‹‹ከእኔ ጋር ለምን አታጥንም?›› ባለው ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ ትጥቁንና ልብሱን አውልቆ ከወረወረለት በኋላ ‹‹ክብር ይግባውና አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን ፈጽሞ አልክደውም፣ ለረከሱ ጣዖቶችህም አልሰግድም›› አለው፡፡ ንጉሡም ተናዶ ልዩ ልዩ በሆኑ ሥቃዮችም እጅግ አሠቃየው፡፡
ንጉሡም ስለ መርቆሬዎስ ብለው የአገሩ ሰዎች እንዳይነሱበት ፈርቶ በብረት ችንካር ቸንክሮ የቀጵዶቅያና የእስያ ክፍል ወደሆነች ወደ ቂሳርያ ከደብዳቤ ጋር ላከው፡፡ በዚያም እጅግ ካሠቃዩት በኋላ ንጉሡ ዳኬዎስ እንዳዘዘ ኅዳር 25 ቀን አንገቱን በሰይፍ ቆረጡትና የሰማዕትነት ተጋድሎውን ፈጸመ፡፡ የሕይወትንም አክሊል ተቀዳጀ፡፡ በዓለሙ ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ታነጹለት፡፡ እግዚአብሔርም ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን በቅዱስ መርቆሬዎስ ስም አደረገ፡፡
#መረጃ (ቋሚ ሲኖዶስ ትግራይ ክልል በተፈጸመው ሕገ ወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት ጉዳይ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ እንዲካሄድ ወሰነ።)
➯በትግራይ ክልል በማእከላዊ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሐምሌ 16 ቀን 2015 ዓ.ም ሕገ ወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት ተፈጽሞ በመገኘቱ አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንዲጠራ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ለኢኦተቤ ቴቪ የተላከው መግለጫ ያስረዳል፡፡
👉 በመሆኑም ፦
1ኛ. ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓም ለሁሉም የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጥሪ እንዲተላለፍ፣
2ኛ. የመክፈቻ ጸሎቱ ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በ10፡00 ሰዓት እንዲከናወን
3ኛ. ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ እንዲካሄድ በማለት ቋሚ ሲኖዶስ መወሰኑን የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ለመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡
#መረጃው፦ የEOTC TV በመ/ር አቤል አሰፋ
ውድ ጓደኞቼ እንደምን ከረማቹ ሁሉም መልካም ነው ስሜ ታሪኩ ታምራት
ነገ 23/11/2015 ከ4:00-8:00 በኢቲቪ መዝናኛ ቻናል በሚተላለፈው የኢትዮጵያ አይዶል የትወና ተወዳዳሪ ስለሆንኩ 8600 ላይ ኮዴን በማስደገባት እንድትመርጡኝ እና ከጎኔ እንድትሆኑ ስል በትትህና ጠይቃለሁ ስለትብብራቹ አመሰግናለው
የተወዳዳሪ ሙሉ=ታሪኩ ታምራት
የምወዳደርበት መደብ = የትወና ተወዳዳሪ
በቴክስ ጥቅል ፓኬጅ የማይሰራ(የማይቆጠር) መሆኑን ከወዲሁ ላስታውስ እወዳለሁ 🙏🙏
ዳግመኛም እግዚአብሔር በኤረር ያሉትን መላእክት በ30 ነገድ በ3 አለቃ አድርጎ ከፈላቸው፡፡ የመጀመሪያዎቹ ‹‹መኳንንት›› ይባላሉ፡፡ የስላሴ የእሳት ባለ ቀስት ናቸው፡፡ የሰው ልጅ ልዩ ጠባቂዎች ናቸው፤ በተለይ በአደጋ ጊዜ ሎጥን እንዳዳኑት ፈጥነው ይደርሳሉ፡፡ በዕለተ ምጽዓት የሰውን ሁሉ ዐፅም ሰብስበው ለትንሣኤ ዘጉባኤ ያበቃሉ፡፡ አለቃቸው ቅዱስ ሰዳካኤል ነው፡፡ ሁለተኛዎቹ ‹‹ሊቃናት›› ይላሉ፡፡ የሥላሴ የእሳት ፈረሶች ናቸው፡፡ በእሳት ፈረስ ይመላለሳሉ፡፡ እነዚህም 24ቱ ካህናተ ሰማይ ሲሆኑ አለቃቸው ቅዱስ ሰላታኤል ነው፡፡ በኤረር ከተማ የሰፈሩት ሦስተኛዎቹ ‹‹መላእክት›› ይባላሉ፡፡ ፍጥረትን ሁሉ የሚጠብቁ ናቸው፡፡ አለቃቸው ቅዱስ አናንኤል ነው፡፡ በእነዚህ የማይጠበቅ ፍጥረት የለም፡፡ ከአዝርእት ጀምሮ ሁሉን ይጠብቃሉ፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ ‹‹በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙ 7 መላእክትን አየሁ›› (ራዕ 8፡2) እንዳለ ሊቃነ መላእክት በቁጥር 7 ናቸው፡፡ እነርሱም፡- ቅዱስ ሚካኤል፣ ቅዱስ ገብርኤል፣ ቅዱስ ሩፋኤል፣ ቅዱስ ራጉኤል፣ ቅዱስ ዑራኤል፣ ቅዱስ ፋኑኤል እና ቅዱስ አፍኒን ናቸው፡፡
‹‹ዑራኤል›› የሚለው ስም ‹ዑር› እና ‹ኤል› ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው፡፡ ‹‹ዑራኤል›› ማለት ትርጉሙ ‹‹የብርሃን ጌታ፣ የአምላክ ብርሃን›› ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ዑራኤል ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ ነው፡፡ በመሆኑም መጽሐፈ ሄኖክ እንደሚገልጸው መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል፡፡ ምሥጢረ ሰማይንና ሰማያዊውን ዕውቀት ሁሉ ለሄኖክ የገለጸለት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ የፀሐይን፣ የጨረቃን፣ የከዋክብትንና የሰማይ ሠራዊትን ብርሃንን የሚመራው ይኸው ገናና መልአክ ነው፡፡ መጽሐፈ ሄኖክ 28፡13፡፡
መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ ሆኖ በተሰቀለ ጊዜ ክቡር ደሙን በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ በብርሃነ መነሳንስ በዓለም ላይ የረጨው ይኸው ገናና መልአክ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡
ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋ ጥበብን አጠጥቶ ሰማያዊውን ምሥጢር የገለጠለት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ ዕውቀት ተሠውሮበት ለነበረው ለኢትዮጵያዊው ሊቅ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም በእመቤታችን ትእዛዝ ጽዋ ጥበብን አጠጥቶ ሰማያዊውን ምሥጢር የገለጠለት ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ ‹‹ዑራኤል የተባለ መልአክ ሊረዳኝ መጣ፡፡›› መጽሐፈ ዕዝራ 2፡1፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር የሕይወትና የይቅርታ ዝናም በምድራችን ላይ ያዘንብ ዘንድ እንዲሁም የእርሻችንን አዝመራ በዝናም አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ ለምግብነት እንዲበቃ ከፈጣሪ ዘንድ ምሕረትን የሚለምን መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡
ሊቁ አባ ጊዮርጊስም በመልአኩ አማላጂነት እጅግ ብዙ ድርሰቶችን የደረሱት መልአኩ ጽዋ ሕይወትን ካጠጣቸው በኋላ ነው፡፡ በመጀመሪያም አባ ጊዮርጊስ የተወለዱት በቅዱስ ዑራኤል አብሳሪነት ነው፡፡ በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ የተመሠረቱ አብዛኞቹ ቅዱሳት ገዳማት በቅዱስ ዑራኤል መሪነት ነው፡፡ ድርሳኑ ላይ የማይጠቅሳቸው የሀገራችን የከበሩ ቅዱሳት ገዳማትና ቅዱሳን ነገሥታት የሉም፡፡
የብርሃን እናቱ ድንግል ወላዲተ አምላክን ከልጇ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ስትሰደድ መንገድ እየመራ ወደ ግብጽ እና ወደ አገራችን ኢትዮጵያ ያመጣቸው ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ እመቤታችንን ከተወደደ ልጇ ጋር በደመና ጭኖ መላ ኢትዮጵያን ካስጎበኛት በኋላ ቅድስት አገራችንን ለእመቤታችን የዓሥራት አገር እንድትሆን ያደረገው መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡
መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል በዓመት 3 ዓበይት በዓላት አሉት፡፡ ጥር 22 በዓለ ሲመቱ ነው፡፡ መጋቢት 27 የጌታችንን ክቡር የሆነ ወርቀ ደሙን ለዓለም የረጨበት ነው፡፡ ሐምሌ 22 ቀን ቅዳሴ ቤቱ የሚከበርበትና ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል የዕውቀትን ጽዋ ያጠጣበት ዕለት ነው፡፡
የሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል ጥበቃ አይለየን!
(ከገድላት አንደበት)
✞ ✞ ✞
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ሐምሌ 22-ሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበትና ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል የዕውቀትን ጽዋ ያጠጣበት ዕለት ነው፡፡
+ የታላቁ ሰማዕት የቅዱስ ፋሲለደስ ልጅ የሆነውና ምስክርነቱን በብዙ ሥቃይ የፈጸመው ሰማዕቱ ቅዱስ መቃርስ ዕረፍቱ ነው፡፡
+ ከዕረፍቱ በኋላ ተገልጦ ብዙ ተአምራትን ያደረገው ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ለውንትዮስ ዕረፍቱ ነው፡፡
ሰማዕቱ ቅዱስ ለውንትዮስ፡- ሀገሩ ሶርያ ጠራብሎስ ሲሆን ሃይማኖቱ የቀና ደግ ክርስቲያን ነው፡፡ በሥጋዊ ሥራውም የከጋዲው ንጉሥ ሠራዊቶች ጋር ነበር፡፡ ቅዱሳት መጸሕፍትን እያነበበ ሁልጊዜ በጾም በጸሎት ይተጋ ነበር፡፡ ባልንጀሮቹ የሆኑ ወታደሮቹንም ጣዖታን ማምለካቸውን ትተው እውነተኛውን አምላክ እንዲያምኑ ያስተምራቸዋል፡፡ ወደ ቀናች ሃይማኖትም የመለሳቸውና በጌታችን ያመኑ ብዙ አሉ፡፡ ከዚህም በኋላ ክፉዎች ወደ ገዥው መኮንን ሄደው ‹‹ለውንትዮስ አማልክትህን አቃለላቸው፤ ‹ሰማይና ምድርን በውስጣቸውም ያለውን ሁሉ የፈጠረ ክርስቶስ ነው› እያለ ያስተምራል›› ብለው ከሰሱት፡፡
መኮንኑም በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ አስቀርቦ ጠየቀው፡፡ ቅዱስ ለውንትዮስም ከልጅነቱ ጀምሮ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደሚያመልከውና ለእርሱም እንደሚሰግድ በከሃዲው መኮንን ፊት መሰከረ፡፡ መኮንኑም አስሮ ካሠቃየው በኋላ በማግሥቱ ‹‹የንጉሡን ትእዛዝ ለምን ትተላለፋለህ? አማልክቶቹን ለምን አታመልክም?›› አለው፡፡ ቅዱስ ለውንትዮስም መኮንኑን ‹‹አንተም የረከሱ ጣዖታትን ማምለክህን ትተህ የክብርን ባለቤት ጌታችንን ብታመልከው የዘለዓለም መንግሥትን ባወረስህ ነበር›› አለው፡፡ መኮንኑም ይህንን በሰማ ጊዜ ቅዱስ ለውንትዮስን ደሙ እንደ ውኃ እስኪፈስ ሥጋውም እስኪቆራረጥ ድረስ ጽኑ ግርፋትን አስገረፈው፡፡ እግሩን እየጎተቱና ውኃ ውስጥም እየዘፈቁት ብዙ ካሠቃዩት በኋላ ሰማዕትነቱን ፈጸመና ጌታችን ቅድስት ነፍሱን ተቀበላት፡፡ ከታላላቅ መኳንንት ውስጥ የአንዱ ሚስት የሆነች አንድ አማኝ ደግ ክርስቲያን ሴትም መጥታ ለወታደሮቹ ገንዘብ ከፍላ የቅዱስ ለውንትዮስን ሥጋ ወስዳ በወርቅ ሣጥን ውስጥ አድርጋ በቤቷ ውስጥ በክብር አስቀመጠችው፡፡ ሥዕሉንም አሠርታ በወርቅ ሣጥኑ ላይ አስቀምጣ ሁልጊዜ በፊቱም የሚበራ መብራት አኖረች፡፡
ሰማዕቱም የፍቅሯንና የድካምዋን ዋጋ ቆጥሮ ብዙ አስደናቂ ተአምራትን አድጎላታል፡፡ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ በመኮንኑ ባሏ ላይ በሆነ ሥራ ምክንያት ተቆጣና በአንጾኪያ ከተማ በወህኒ ቤት አሠረው፡፡ ቅዱስ ለውንትዮስም ለሥጋው መልካም ለሠራችለት ለመስፍኑ ሚስት መልካም የሆነ ዋጋዋን ሊከፍላት ሽቶ በዚያች ሌሊት በወህኒ ቤት ላለው ባሏ ተገለጠለት፡፡ ከወህኒ ቤቱም ታላቅ ብርሃን ወጣ፡፡ ለመኮንኑ ባሏም የተገለጠለት የራሱ የሆነውን ቤቱ ያስቀመጠውንና የሚያውቀውን የወርቅ ልብስ ለብሶ በጎልማሳ ፈረሰኛ አምሳል ነበር፡፡ ለመስፍኑም እንዲህ አለው፡- ‹‹አትዘን አታልቅስም፣ ዛሬ ከዚህ ወህኒ ቤት ወጥተህ ከንጉሥ ጋር በማዕዱ ትቀመጣለህና ከዚያም ወደቤትህ ወጥተህ በሰላም ትሄዳለህ፡፡››
የታሠረው መስፍንም ይህን ጎልማሳ ፈረሰኛ ስላየው፣ በላዩም ስለወጣው ታላቅ ብርሃን፣ የወህኒ ቤቱም ደጅ እንደተዘጋና እንደተቆለፈ ወደ እርሱ ስለመግባቱ፣ ደግሞም የራሱ የሆነውንና በቤቱ ውስጥ የተወውን የወርቅ ልብስ ለብሶ ስለማየቱ በእጅጉ ተደነቀ፡፡ ቅዱስ ለውንትዮስም በዚያች ሰዓት ወደ ንጉሡ ሄዶ በመኝታው ተኝቶ ሳለ ረገጠው፡፡ ንጉሡም እጅግ ደነገጠ፡፡ ቅዱስ ለውንትዮስም ‹‹ንጋት በሆነ ጊዜ መስፍን እገሌን ከወህኒ ቤት አውጣው አክብረውም፣ በክፉ አሟሟትም ሞተህ እንዳትጠፋ ወደቤቱ ይሄድ ዘንድ በሰላም አሰናብተው›› አለው፡፡ ንጉሡም ከቅዱስ ለውንትዮስ ግርማ የተነሣ እጅግ ፈርቶ እየተንቀጠቀጠ ‹‹እሺ ጌታዬ እንዳዘዝከኝ አደርጋለሁ›› ብሎ መለሰለት፡፡ በነጋም ጊዜ ንጉሡ ወደ ወህኒ ቤት ሄዶ መስፍኑን አወጣውና በክብር ልብሶች አስውቦ ከእርሱ ጋር በማዕዱ አስቀመጠው፡፡ ንጉሡም ግርማው እጅግ የሚያስፈራ ፈረሰኛ ተገልጦለት መስፍኑን ይፈታው ዘንድ እንዳዘዘው ሲነግረው መስፍኑ ተደነቀ፡፡ ንጉሡም የሥራይ ሥራ እንደሆነ ሲናገር መስፍኑም ‹‹እኔ የሥራይ ሥራ ፈጽሞ አላውቅም፣ የተገለጠልህም ማን እንደሆነ አላውቅም›› አለው፡፡ ከግርማው የተነሣ ፈርቷልና ከማዕዱ በኋላ ንጉሡ በሰላም አሰናበተውና መስፍኑ ወደ ሀገሩ ጠራብሎስ ሲጓዝ ቅዱስ ለውንትዮስ በመልአክ አምሳል ተገለጠለትና እቤቱ እስኪደርስ ድረስ እንደ ጓደኛ እያወራው ሲደርስ ተሰወረው፡፡
መስፍኑም ወደቤቱ በገባ ጊዜ የሆነውን ሁሉ ለቤተሰቦቹ ነገራቸው፡፡ ሚስቱም ያዳነው ቅዱስ ለውንትዮስ መሆኑን ዐውቃ ‹‹ብታየው ታውቀዋልህን?›› አለችው፡፡ እርሱም ‹‹አዎን ባየው ዐውቃዋለሁ›› ሲላት የቅዱስ ለውንትዮስ ሥዕል ወዳለበት ቤት ይዛው ገባች፡፡ መስፍኑም አይቶ ‹‹በእውነት የተገለጠልኝ ይህ ነው›› አለ፡፡ ሁለተኛም የቅዱስ ለውንትዮስ ሥጋ ያለበትን የወርቅ ሣጥን ከፈተችውና ያንጊዜ የመስፍኑን የወርቅ ልብስ እንደለበሰ አየው፡፡ የፊቱንም መሸፈኛ ገልጦ የተገለጠለትና ያዳነው እርሱ መሆኑን ከተረዳ በኋላ ማን እንደሆነ ሚስቱን ጠየቃት፡፡ እርሷም የቅዱስ ለውንትዮስን ገድል አንድ በአንድ ነገረችው፡፡ መስፍኑም ይህን መልካም ሥራ በመሥራቷ ሚስቱን እጅግ አድርጎ አመሰገናት፡፡ በቅዱሳኑ ላይ አድሮ ድንቅ ድንቅ ነገርን የሚሠራ እግዚአብሔርን ካመሰገነ በኋላ መብራትና ማዕጠንት እንዳይለየው ሚስቱን አዘዛት፡፡ ከሃዲውን ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስን ጌታችን እስካጠፋው ድረስ እንዲሁ እያደረጉ ቆዩ፡፡ ከዚህም በኋላ ያማረች መልካም ቤተ ክርስቲያን አንጸውለት ቅዱስ ሥጋውን ሰኔ አንድ ቀን በውስጧ አኖሩት፡፡ ዕለቷንም አከበሯት፡፡ ከቅዱስ ለውንትዮስም ሥጋ ብዙ አስደናቂ የሆኑ እጅግ የበዙ ተአምራት ተደርገው ታዩ፡፡ የሰማዕቱ የቅዱስ ለውንትዮስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!
† ቅድሥት ሆይ ለምኝልን †
★ ሁላችንም ከልብ እንጸልየው ★
ንግሥተ ሰማይ ወምድር፣የአዳም ተስፋ የሔዋን መመኪያ፣እናትነትን ከድንግል ጋር አስተባብረሽ የያዝሽ የጌታዬ እናት እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ እግዚአብሔር በአንቺ የሰራው ታላቅ መለኮታዊ መገለጥ ለአዕምሮ የረቀቀ ከልብ ማስተዋል በላይም እጅግ የመጠቀ ነውና አንቺን ለመረጠ ጌታ ጸባዖት ምሥጋና ይገባል።
ድንግል ሆይ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጀውን ጌታ በክንድሽ ታቀፍሽው፣ኪሩቤል በመራድና በመንቀጥቀጥ በፊቱ የሚቆሙለትን ቅዱስ በጀርባሽ አዘልሽው፣መላዕክት በፊቱ የሚሰግዱለትን ኃያል አምላክ በደረትሽ ታቀፍሽው።አንቺ ታናሽ ብላቴና ሳለሽ እግዚአብሔር የክብሩ ነጸብራቅ ባንቺ እንዲገለጥ የፍጥረት ሁሉ መድኃኒት ከአንቺ እንዲወለድ ጌታ ጸባዖት መርጦሻልና ለእናትነትሽ ክብርና ውዳሴ ይገባል።
ድንግል ሆይ አንቺ በምድር የተገኘሽ ሁለተኛ ሰማይ ነሽ፣ማኅፀንሽን ዙፋን አድርጎ ንጉሥ የከተመብሽ የልዑል ማደሪያ ነሽ። የአርያሙ ንጉሥ ለማደሪያነት አስቀድሞ የመረጠሽ፣ መንፈስ ቅዱስ ከነውርና ከኃጢአት የከለለሽ፣እንደ ነጭ ዕንቁ እያበራሽ በቅዱሳን የዘር ሐረግ ውስጥ ያለፍሽ ለአብ አንድያ ልጅ በምድር እናት የሆንሽ፣ከሔዋን ዘር ሁሉ ለይቶ ቃል ለተዋሕዶ የመረጠሽ ብፅዕትና ቅድሥት የመለኮት አዳራሽ ነሽ።
ድንግል ሆይ የፍጥረቱን ስቃይና ሰቆቃ ተመልክቶ ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነስቶ ዓለምን ያዳነ ጌታ ዛሬም የዓለምን ሰቆቃና ጭንቀት ተመልክቶ ክንዱን ከአርያም ይዘረጋ ዘንድ በእናትነትሽ ፍቅር ለምኝልን።ዓለም በጭንቅ ተይዛለች፣በሽታ ትውልዱን እንደዋዛ እየቀጠፈ ነው፣መውጣት መግባታችን ሁሉ የሰቀቀን ነው ምንም እንኳ ኃጢአትና በደላችን የእግዚአብሔርን ምህረት ከምድራችን ቢያርቀውም አንቺን የመማጸኛ ከተማ ሰጥቶናልና አማልጅን ብለን እኛ ደካማ ልጆችሽ እንማጸናለን።
ድንግል ሆይ በመስቀል ሥር እናት ሆነሽ የተሰጠሽን የመከራ ቀን ስጦታችን ነሽና በሐዘናችን ራሪልን፣እናት በልጇ ስቃይና ሰቆቃ አትጨክንምና ለእኛ ለልጆችሽ ምልጃሽ ፈጥኖ ያግዘን፣በምድራችን ላይ የወረደውን የሞት መንፈስ የጌታ ክንድ ወደ ጥልቁ ይጣለው ፣ሠራዊተ አጋንንት በሰው ዘር ላይ የበተኑት የበሽታ ተውሳክ ሁሉ በልጅሽ በኢየሱስ ክርስቶስ ክንድ ከምድራችን ላይ ይንቀል።ሞት ይደንግጥ፣አለማመን ይራቅ፣የጨለማ አበጋዝ ይጨነቅ፣የጥፋት ሠራዊት ይበተን።ምድራችን በልጅሽ መለኮታዊ ክብር ትከደን።ፍጹም እረፍትና ፈውስ ለሰው ልጆች ሁሉ ይሁን ።ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን።
ቅድሥት ሆይ ምድራችንን የልጅሽ ደም ይፈውሳት ዘንድ ምልጃሽ ያግዘን።ጭንገፋ ከምድራችን ይራቅ፣የእስራኤልን በኩር የነጠቀ ሞት በደጃችን አይለፍ፣ መልአከ ሞት የደሙን ማኅተብ ከግንባራችን አይቶ ይሽሽ።ዋይታና ለቅሶ ሳይሆን ዝማሬ ምድራችንን ይክደናት።በአራቱም አቅጣጫ የሰላም አየር ይንፈስ። ህጻናቱ በጤና ይደጉ፣አረጋውያን በደስታ ይጦሩ።ሕዝብ ፍቅርን እንደ ሸማ ለብሶ የምድርን በረከት ይውረስ ።የየዕለት ዜናችን የእግዚአብሔር ማዳን ብቻ ይሁን።ጭንቀትና መርዶ ከምድራችን እንደ ጉም ይበተኑ። ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን።
እባካችሁ ሌሎችም እንዲጸልዩ ሼር አድርጉት።
መ/ር ታሪኩ አበራ
ዝ ውእቱ እድሜ ሣህልኪ ወዘተአምርኪ ጊዜ፣
ማርያም ድንግል ምልዕተ ምሕረት ከመ ተከዜ፣
እስከ ማእዜኑ እሄሉ ማዕከለ ብካይ ወእንባዜ፣
ኦ ናዛዚት እንተ ወለድኪ ናዛዜ፣
ኦ ንግሥት በቋዒት ብቊዕኒ ይእዜ።
በጽሎታችን
ውስጥ እችን እንጨምር አባታችንን እንለምነው 7ጊዜ
ቃል ኪዳን አለው
ቅዱስ ማር ቴዎድሮስ ተራድአነ
ቅዱስ ማር ቴዎድሮስ ተራድአነ
ቅዱስ ማር ቴዎድሮስ ተራድአነ
ቅዱስ ማር ቴዎድሮስ ተራድአነ
ቅዱስ ማር ቴዎድሮስ ተራድአነ
ቅዱስ ማር ቴዎድሮስ ተራድአነ
ቅዱስ ማር ቴዎድሮስ ተራድአነ
አዲስ መዝሙር|ዘማሪ አይደፈር ጋሻው||ገብርኤል መልአከ||
https://youtube.com/watch?v=L-oQMsJqEW4&feature=share
ከዚህም በኋላ አርያኖስ ከክርስቲያን ወገን ያገኙትን ሁሉ እንዲገድሉ ጭፍሮቹን አዘዘ፡፡ የከበረ ባሕታዊ ይስሐቅም ክርስቲያኖቹን ሰማዕትነትታቸውን በትዕግሥት አንዲፈጽሙ ያበረታቸው ነበር፡፡ ወደ ሥቃይ ቦታም ሲወስዷቸው መኮንን ባዩት ጊዜ ሁሉ በአንድ ቃል ‹‹በአምላካችን በክርስቶስ የታመንን ክርስቲያን ነን›› ብለው ጮኹ፡፡ መኮንኑም ሐምሌ 19 ቀን የእስናን ከተማ ክርስቲያኖችን ከታላላቆች እስከ ታናናሾች ያሉትን ሴቶችንም ወንዶችንም ሁሉንም እንደበግ አሳረዳቸው፡፡ ሁሉም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጁ፡፡ መኮንኑም ወደ እስዋን ከተማ ከሄደ በኋላ ተመልሶ ወደ እስና ከተማ በመጣ ጊዜ ሦስት ገበሬዎችን አገኙ፡፡ እነርሱም ያደረገውን ዐውቀው ‹‹እኛም ክርስቲያን ነንና በሰማዕትነት ግደለን›› አሉት፡፡ እርሱም በሚያርሱበት ቦታ በያዙት የእርሻ መሣሪያ መስከረም 11 ቀን ገደላቸው፡፡ ስማቸውም ሱሩፋስ፣ አንጣኪዮስ፣ ስሐድራ ይባላል፡፡ ኤጲስቆጶስ ቅዱስ ይስሐቅንም መኮንኑ አሥሮ ለጣዖት እንዲሠዋ አስገደደው፡፡ ቅዱስ ይስሐቅም ጌታችንን በማመን መጽናቱን ባየው ጊዜ መኮንኑ ቅዱሱን ባሕታዊ እሳት ውስጥ ከተተውና ሰማዕትነቱን በዚያው ፈጽሞ የድል አክሊልን ተቀዳጀ፡፡ ይኸውም ታኅሣሥ 14 ቀን ነው፡፡ የመከራውም ዘመን ካለፈ በኋላ ምእመናን በስሙ ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ቅዱስ ሥጋውን በውስጧ አኖሩ፡፡ የሰማዕታቱ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!
+ + +
ሰማዕቱ ቅዱስ በጥላን፡- የዚኽም ቅዱስ አባቱ አውሱጢኪዮስ አረማዊ የነበረ ሲሆን እናቱ ኤልያና ግን አማኝ ክርስቲያን ነበረች፡፡ በጥላንም ባደገ ጊዜ ጥበብን ሁሉ ተምሮ እጅግ አዋቂ ሆነ፡፡ አንድ ቄስም የበጥላንን እጅግ አዋቂነትና አስተዋይነት እያደነቀ ነገር ግን ከሃዲ ስለመሆኑ እያዘነ በቤታቸው አቅራቢያ ይኖር ነበር፡፡ እርሱም መርቶ ወደ ቀናች ሃይማኖት ይመራው ዘንድ ስለ በጥላን ጌታችንን በጸሎት ይጠይቀው ነበር፡፡ ቄሱም ጸሎቱን ባበዛ ጊዜ ጌታችን በጥላን በእርሱ እጅ ያምን ዘንድ እንዳለው በራእይ ገለጠለት፡፡
ቄሱም በጥላንን ባገኘው ጊዜ ሰላምታ እየሰጠው በመካከላቸው ፍቅር ጸና፡፡ በጥላንም ወደ ቄሱ ቤት እየገባ ሁለቱ ያወሩ ጀመር፡፡ ቄሱም የጌታችንን አምላክነትና በእርሱም ላመኑ የፈውስን ጸጋን እንደሚሰጣቸው አስተማረው፡፡ ከተማረም በኋላ በጥላን በጌታችን አመነ፡፡ አንድ ቀን በጎዳና ሲሄድ እባብ ነድፎት ለሞት የተቃረበ ሰው አገኘ፡፡ እባቡም በዚያው ነበር፡፡ በዚህም ጊዜ በጥላን ‹‹መምህሬ ‹በክርስቶስ ካመንክ በስሙ ተአምራት ታደርጋለህ› ብሎኛልና እስቲ የመምህሬን ቃል ልፈትን›› ብሎ ሰውየው ይፈወስ ዘንድ እባቡም ይሞት ዘንድ ወደ ጌታችን ጸለየ፡፡ ጌታችንም ጸሎቱን ሰምቶት ሰውየው ፈጥኖ ዳነ፣ ከይሲውም ወዲያው ሞተ፡፡ የበጥላንም ሃይማኖቱ ተጨመረለት፡፡
ከዚህም በኋላ በጥላን ወደ ቄሱ ዘንድ ሄዶ ተጠመቀ፡፡ ሁልጊዜም እየሄደ ይማር ነበር፡፡ በአንዲት ዕለትም አንድ ዐይነ ሥውር ሰው ወደ ቅዱስ በጥላን ቤት ሲመጣ አባቱ ሰውየውን ከውጭ መለሰው፡፡ ቅዱስ በጥላንም አባቱን ‹‹ማነው የፈለገኝ?›› ሲለው አባቱ ‹‹ልታድነው የማትችለው ዐይነ ሥውር ሰው ነው›› አለው፡፡ ቅዱስ በጥላንም ዐይነ ሥውሩን ጠርቶት በላዩ ጸሎትን ጸልዩ ፈወሰው፡፡ የዐይነ ሥውሩን ዐይኖች ተገልጠው ማየት ቻሉ፡፡ ዐይነ ሥውር የነበረው ሰውና አባቱም ይህን ባዩ ጊዜ በጌታችን አመኑ፡፡ በጥላንም ወደ ቄሱ ዘንድ ወሰዳቸውና ተጠመቁ፡፡ ቅዱስ በጥላን ጥበብን እያደረገ ድውያንን ያለ ዋጋ ይፈውሳቸው ነበር፡፡ ነገር ግን በጌታችን እንዲያምኑ ያደርጋቸዋል፡፡ የሀገሪቱ ጥበበኞች ሰዎችን በክፋት ተነሡበትና ካሳመናቸው ክርስቲያኖች ጋር ለንጉሡ ከሰሱት፡፡ ንጉሡም ያመኑትን ሰዎች ለአማልክቱ እንዲሠው ቢያዛቸው ሳይታዘዙለት ስለቀሩና በጌታችን ስም ስለታመኑ ራስ ራሶቻቸውን በሰይፍ አስቆረጣቸው፡፡ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀዳጁ፡፡
ቅዱስ በጥላንን ግን ንጉሡ በብዙ ማሠቃያዎች አሠቃየው፡፡ ቅዱሱም በተአምራቱ ብዙዎችን ጌታችንን ወደ ማመን እያመጣቸው በሰማዕተነት ዐረፉ፡፡ ንጉሡም ቅዱስ በጥላንን ለተራበ አንበሳ ቢሰጠው አንበሳው ከእግሩ ሥር ወድቆ እግሩን ላሰለት እንጂ አልነካውም፡፡ ንጉሡም በዚህ ተናዶ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡት ዘንድ አዘዘ፡፡ እንደትእዛዙም አደረጉበትና ቅዱስ በጥላን ሰማዕትነቱን በድል ፈጽሞ የክብርን አክሊል ተቀዳጀ፡፡ የቅዱስ በጥላን ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!
ከገድላት አንደበት
✞ ✞ ✞