የቤተ ክርስቲያን ደጃፉን ለምን እንደሚሳለሙ ያውቃሉ?
በትእምርተ መስቀል ካማተብን በኋላ የቤተ መቅደሱን ደጃፍ በእምነት ስንሳለም ተመልክተው የሚገርማቸው አይጠፉም::
እንዲህ ያሉ :ሰዎች ዐጸዱን፣ደጃፉን ፣በሩን ፣ መስኮቱን መሳለማችን እነርሱ እንደሚያስቡት በልማድ እና ያለምክንያት አይደለም፡፡
ደጃፉን የምንሳለምበት የተለያየ ምክንያት አለን፡፡
☞☞☞ ፩(1) -ቤተ መቅደሱን እንዲሁ በውስጡና በዙሪያው ያለውን የነካ ስለሚቀደስበት
“የቅብዐት ዘይትን ወስደህ ማደሪያውን በእርሱም ያለውን ሁሉ ትቀድሳለህ ቅዱስም ይሆናል” ሲል ለሙሴ አዞታል ኦሪ ዘፀ ፵፥፱ /40፥9/
እግዚአብሔር ቤተ መቅደሱና በዙሪያው ያሉ ሁሉ እንዲቀደሱ አዟል፡፡ደብተራ ኦሪት ሲተከል የሰሎሞን ቤተ መቅደስ ሲሰራ ዙሪያው በቅብዓ ቅዱስ ተቀድሷል የቤተ መቅደሱ ደጃፍ መሳለም መሳም የሚያስፈልገው ለዚህ
ነው፡፡
ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ ደጃፉ በቅብዓ ሜሮን የከበረ የተቀደሰ ስለሆነ የሚሳለመው የሚስመው የሚተባበሰው ሁሉ ይቀደሳል፡፡
☞☞☞ ፪(2)- ቤተ መቅደስ የክርስቶስ ማደሪያ ስለሆነ
በሌላ በኩል ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ አካል ዘርፉ ልብሱ መቅደሱ ናት፡፡ ኤፌ ፭፥፳፫/5፥23/፡፡ አካል ከራስ ጠጉር እስከ እግር ጥፍር ያለውን ሁሉ እንደሚይዝ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ አካል ናት ሲባል የቤተ ክርስቲያኑ አካል ሁሉያጠቃልላል፡፡ ስለዚህ አካሉ የሆነችው ይህች ቤተ ክርስቲያን/ቤተ መቅደስ/
መሳለም መተባበስ የጌታችንን የልብሱን ዘርፍ በመንካቷ አስራ ሁለት ዓመት ሙሉ ደም ሲፈሳት ኖራ እንደተፈወሰችው ሴት የእምነት ጥንካሬ ምልክት ነው ሉቃ ፰፥፵፫- ፵፰ /8፥43-48/ ፡፡
በእምነት ለሚሳለም በእምነት ለሚኖር ሰው የቤተ ክርስቲያን ደጃፎቿ ዐጸዱ በቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ያለው
ጠበል አጥሩ ቅጥሩ ውስጡ ውጪው ሁሉ ፈውስና መድኃኒት ይሆነዋል፡፡
☞☞☞ ፫(3)- ቤተ መቅደሱ የመለኮት ማደሪያ ስለሆነ
ቤተ ክርስቲያን/ቤተ መቅደሱ/ የመለኮት ማደሪያ ነው፡፡በሰማይ በክብር የሚኖር እግዚአብሔር በቤተ መቅደሱን በረድኤት ያድራል፡፡
ቤተ መቅደሱን የክብሩ መገለጫ አድርጎታልና፡፡ “አሁንም ስሜ ለዘለዓለም በዚያ ይኖር ዘንድ ይህን ቤት መርጫለው ቀድሻለውም ዐይኖቼና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ” ፪/2/
ዜና፯፥፲፮ /7፥16/ “ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን” መዝ ፻፴፩፥፯/131፥7/ እንዲል ቤተ መቅደሱ የእግዚአብሔር ማደሪያ ስለሆነ ደጃፉ አጥሩ ቅጥሩ ሁሉ የተቀደሰ በበረከት የተሞላ ነው፡፡
ስለዚህ ወደ ቤተ መቅደስ የሚቀርብ ሰው ይህን እያሰበ ይሳለማል፡፡
ስለዚህ ሰው ሁሉ የቤተ ክርስቲያን ደጃፏን / ደጀ ሠላሟን/ “ሠላም ለኪ ቤተ ክርስቲያን አምሳለ ኢየሩሳሌም ቅድስት” /ቅድስት የምትሆን የሰማያዊ ኢየሩሳሌም አምሳል የሆንሽ ቤተ ክርስቲያን ሆይ ሠላምታ ይገባሻል/ እያልን ደጃፏን አጥሯን እንሳለም::
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ወለወላዲቱ ድንግል!
ወለመስቀሉ ክቡር!
3.ቅዱስ ባስሊቆስ (ኃያል ሰማዕት)
4.ቅዱስ ድምጥያና ደቀ መዛሙርቱ (ሰማዕታት)
✞✞✞ ወርኀዊ በዓላት
1.አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል)
2.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ
3.ቅዱስ ፊልጶስ ሐዋርያ
4.ቅዱስ ሙሴ (የእግዚአብሔር ሰው)
5.አባ ዮሐንስ ጻድቅ
6.እናታችን ቅድስት ነሣሒት
✞✞✞ "የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና . . . መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ:: የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ:: እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን::" ✞✞✞
(፩ቆሮ. ፩፥፲፰-፳፫)
✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞
ከፆሙ በረከት መሳተፍ ለምትፈልጉ 😍
ማስቀደሻ ( ጧፍ፣ እጣን ፣ዘቢብ ) እጥረት ላለባቸው ለ 100 ቤተ ክርስቲያኖች በረከት መሳተፍ ለምትፈልጉ በውስጥ መስመር አናግሩን 😍🙏
ጻድቁ የዲቁናና የቅስና ማዕረግ የተቀበሉት ወደ ሸዋ ምድር በመምጣት ነው በዘመኑም የነበረው የኢትዮጵያ ንጉሥ ዐፄ ዳዊት ነበረ አቡነ ቡሩከ አምላክ በመንፈቀ ሌሊት ቆሞ እየጸለየ ሳለ እግዚአብሔር በሦስትነቱ ተገልጦለት የኤፍራጥስና የጤግሮስ፣ የኤፌሶንና የግዮን አምሳል ደጋግ መነኰሳት የሚኖሩባት፣ ከጎንህ ውኃ የሚፈስባት የምትኖርባትና በሞት ዐርፈህ የምትቀበርባት ቦታ ደብረ ኮል ናት፣ አጋንንት ከእርሷ ይርቃሉ፤ በእርሷ ዘንድ በጸሎት ውኃዋ ሕሙማን ይፈወሳሉ፣ መላእክትም በውስጧ ይወርዳሉ ይወጣሉ፣ ገዳምህ ደብረ ኮል እንደ ተወለድኩባት እንደ ቤተልሔም፣ እንደ ተሰቀልኩባት ቀራንዮ የከበረች ትሆናለች…›› በማለት ጌታችን ስለ ገዳሙ ደብረ ኮል ነገረው።
✝አቡነ ቡሩከ አምላክ የአቡነ አብሳዲ ልጅ ሆነው በደብረ ማርያም ገዳም በታላቅ ተጋድሎ ኖረው በኋላም ለዘለዓለም ማረፊያቸው ወደሆነችው ወደ መራጉዝ መጥተው ገዳማቸውን ደብረ ኮልን መሠረቱ።
✝የአቡነ ቡሩከ አምላክ ትውልዱ ከያፌት ወገን ነው፤ ሀገሩ ከዘጠኙ ቅዱሳን ሀገር ከሮም ነው፤ ጥንተ ሙላዱም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ከሚከተሉ ከሮም ነገሥታት ወገን ነው፤ አባቱም የሮም ንጉሥ ነበረ፤ ዘውድ ደፍቶ ሃይማኖታቸው በቀና ሰዎች ላይ ነግሦ ነበረ። ተላላኪው አባ ጌርሎስም ያዘዘውን ኹሉ ይላላከው ነበረ። አቡነ ቡሩከ አምላክንም የቀናች ቅድስት ሥላሴን ማመንን በምትናገር በቀናች የተዋሕዶ ሃይማኖት ያጠመቀው አባ ጌርሎስ ነበረ አቡነ አብሳዲ ጾሙንና ጸሎቱን፣ ትሕትናውን፣ መላላኩንና ክህነቱን ተመልክቶ ‹‹እንግዲህስ አዳምን ለማዳን ሰው የሆነ የጌታህን የኢየሱስ ክርስቶስን ትእዛዝና የእኔን ትእዛዝ ፈጽመሃል›› አለው። ዳግመኛም ‹‹በቅድስት ሥላሴ ስም በመንፈስ ቅዱስና በወንጌል ትምህርት ከአንተ የሚወለዱ ብዙ ሕፃናት እንዲሁም ብዙዎች በምንኵስና ቀንበር ከአንተ ይወለዳሉ። ስብከትህና ወንጌል ማስተማርህ በዓለሙ ሁሉ ይሰማል። የመንፈስ ልጅህ የልጅ ልጅህ ለዘላለም ይኖራል። ትንቢታቸውና ትምህርታቸው እስከ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ድረስ አይጠፋም፤ እነርሱም እንዲሁ አይጠፉም። እኔ የአምላኬን ፈቃድ ፈጽሜአለሁና ዛሬም የእኔ ፈቃድ አይደለም፤ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው እንጂ። አንተም የፈጣሪህን ትእዛዝ ፈጽም። ይህ ነገር ከእኔ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ነውና ስለተናገረኝ እንዲህ እልሃለሁ። አቡነ ቡሩከ አምላክም ራሱን ዝቅ አድርጎና ከእግሩ በታች ሰግዶ እሺ በጄ አለው። አቡነ አብሳዲም ከእንባ ጋር ከምድር አንሥቶ ሳመው፤ እግዚአብሔር ወደፈቀደልህ ሂድ፤ እኔን ያሳየኝ እሸኝህ ዘንድ ነው›› አለው። አቡነ አብሳዲ ይኽንም ያየው በደብረ ማርያም አበ ምኔት ሆኖ ሳለ ነበረ።
✝በንጉሥ ዐምደ ጽዮን ዘመነ መንግሥት አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ከኢትዮጵያ ተነሥቶ ወደ አርማንያ ሔደ። ዕዝራ ቅድስት ሀገርን በምታለቅስ ሴት አምሳል እንዳያት አባ ኤዎስጣቴዎስ በአርማንያ ሆኖ ሲጸልይ ሳለ አቡነ ቡሩከ አምላክ በኢትዮጵያ ሆኖ በጸሎት ሲተጋ ሲሰግድና የብርሃን ምሰሶ ከሚጸልይበት በኣት ተተክሎ ያይ ነበረ። እግሩ ከረገጠበት ቦታም ኤፍራጥስና ጤግሮስ ኤፌሶንና ግዮን ይመላለሱ ነበሩ። አቡነ ኤዎስጣቴዎስም ይኽን ባየ ጊዜ ‹‹ወንጌል የሚያንሰው ይበልጠዋል እንዳለ ይኽም ሕፃን እንደ መልከ ጼዴቅ ክህነትና እንደ አቤል መሥዋዕት ከእኔ ይበልጣል›› አለ። ከዚኽም በኋላ ጻድቁ ወግረ ስኂን ተብሎ ከሚጠራው ከደብረ ማርያም በወረደ ጊዜ የዱር አራዊት ሁሉ ተቀበሉት። እነርሱም አንበሶችና ነብሮች፣ ዝሆኖችና ቀይ ቀበሮዎች፣ ሽኮኮዎች፣ አሳማዎች፣ አውራሪስ፣ ጦጦዎችና ዝንጀሮዎች ናቸው። ኹሉም በስምምነት ‹‹አባ ክቡር ሆይ! የት ትሔዳለህ?›› እያሉ ሰገዱለት። እግዚአብሔር የአቡነ ቡሩከ አምላክን ሥራ ይገልጥ ዘንድ የሰውን ቋንቋ ገልጦላቸዋልና። አባታችን ወደ ደብረ ኮል ከገቡ በኋላ እያስተማሩ ያመነኰሷቸው መነኰሳት ቊጥራቸው እጅግ ብዙ ሆነ። አባታቸው አቡነ አብሳዲም ጌታችን በቃሉ አዝዟቸው በደመና ተጭነው መጥተው ጎብኝተዋቸው ሹመትንም ሰጥተዋቸዋል። አባታችን ቡሩከ አምላክ ያመነኰሷቸውን ቊጥራቸው መቶ የሚሆኑ ሴቶች መነኮሳይያትን በአንድ ጸንተው እንዲኖሩ ካስተማሯቸው በኋላ ታላቋንና መጻሕፍትን የምታውቀውን ጸበለ ማርያም እመ ምኔት አድርው ሾሙላቸው።
✝ጻድቁ ሃይማኖቱ በቀና በኢትዮጵያው ንጉሥ በዐፄ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ኹለት ሕንጻ አብያተ ክርስቲያናትን አምላክን በወለደች በክብርት እመቤታችን ስም ጋርፋ በምትባል ሀገር እንዲሁም በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ስም ቤተ ክርስቲያን አነጹ፤ ነገር ግን የቅዱስ ሚካኤልን ሕንጻ ቤተ መቅደስ ኹለተኛው ሄሮድስ የተባለ ግራኝ አህመድ አቃጠላት። የእመቤታችን ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ግን ተሰወረችው። አባታችን ገዳማትን መጎብኘት በፈለገ ጊዜ ደመና ጠርቶ በደመና ተጭኖ ይሔድ ነበረ። ታኅሣሥ ሃያ ዘጠኝ ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደተወለደባት ወደ ቤተልሔም ይሔድ ነበረ፤ መጋቢት ሃያ ሰባት ቀንም ጌታ ወደተሰቀለበትና ወደተቀበረበት ወደ ጎልጎታ፤ ወደ እናቱ መቃብር ወደ ጌቴሴማኒ እንዲሁም ጌታችን ከእናቱ ጋር ወደ አደረባት ወደ ደብረ ቊስቋም በደመና ተጭኖ ይሔድ ነበረ። ይኽንንም ሲያደርግ ከፈጣሪው በቀር ሰው አያውቅበትም ነበረ። ለመነኰሳትም ቤቱ ውስጥ ጸሎት የሚያደርግ ይመስላቸው ነበረ። ከትሕትናውም የተነሣ በቤተ ክርስቲያን በአገልግሎት ጊዜ ‹‹መጻሕፍትን አንብብ›› በሚሉት ጊዜ ‹‹አላነብም አትሮንስ አቀርባለሁ፣ ጥላና መጽሐፍን እይዛለሁ እንጂ›› ይላቸው ነበረ። ‹‹ዋና ሠራኢ ካህን ሆነህ ቀድስ›› በሚሉት ጊዜ ‹‹አልችልም›› ይል ነበረ። አንድ ቀን ሠራዒ ሆኖ የሚቀድስ ሰው ጠፋ። እነርሱም ‹‹እባክህ ዛሬ በሠራዒ ቀድስ›› አሉት፤ እርሱም ‹‹እሺ በጄ›› ብሎ በቀደሰ ጊዜ ከመሬት በአንድ ክንድ ከፍ አለ። ቊጥር የሌላቸው መላእክትም መቅደሷን ከበቧት። ‹‹አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ›› ባለ ጊዜ እና ‹‹ሀበነ ንኅበር›› ባለ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በነጭ ርግብ አምሳል በአቡነ ቡሩከ አምላክ ላይ ረበበ። ቀሳውስቱም ይኽንን ተመልተው ገረማቸው፤ ‹‹በእውነት ይኽ መነኵሴ ከእኛ ይበልጣል›› አሉ። እንዲሁም የካቲት ዐሥራ ስድስት ቀን አባታችን ሠራዒ ሆኖ በቅዳሴ ማርያም ላይ ‹‹አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም›› ባለ ጊዜ አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችን ወረደች። እንዲሁ ግንቦት አንድ ቀን ‹‹ኦ ማርያም በእንተ ዝ ነዐብየኪ ወናፈቅረኪ›› ባለ ጊዜ ቃል በቃል አነጋገረችው፤ ‹‹ወዳጄና የልጄ ወዳጅ ቡሩከ አምላክ ሆይ!
#ደብረ_ታቦር
ደብረ ታቦር ከገሊላ ባሕር በምዕራባዊ በኩል 10 ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኝ ተራራ ሲሆን፤ ከፍታው ከባሕር ወለል በላይ 572 ሜትር ይሆናል፡፡ በዚህ ተራራ ላይ ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን እንደሚገልጽ ምሳሌና ትንቢት ተነግሯል፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በትንቢቱ “#ታቦርና #አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል” ብሎ የተናገረው ትንቢት እንዲፈጸም ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተአምራቱን በዚህ ተራራ ላይ ገልጧል /መዝ. 88፥12/፡፡ በዘመነ መሳፍንት ባርቅ ሲሣራን ከነሠራዊቱ ድል ያደረገው በደብረ ታቦር ተራራ ላይ ነው፡፡ ምሳሌነቱም ባርቅ የጌታችን ሲሣራ ደግሞ የአጋንንት ነው፡፡ ጌታችን በደብረ ታቦር ክብሩን በመግለጥ በአይሁድ እያደረ አምላክነቱን እንዲጠራጠሩ ያደረጋቸውን አጋንንት ድል የማድረጉ ምሳሌ ነው /መሳ. 4፥6/፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን በቂሳርያ “የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?” ብሎ ከጠየቃቸው ከስድስት ቀን በኋላ #አዕማድ ተብለው የሚጠሩ ሦስቱን ሐዋርያት ይዞ ወደ ረጅም ታቦር ተራራ ወጣ፡፡ በፊታቸውም ተለወጠ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ፡፡ እነሆም #ሙሴና #ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው፡፡ ቅዱስ #ጴጥሮስ መልሶ ጌታችን ኢየሱስን ጌታ ሆይ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፡፡ ብትወድስ በዚህ #ሦስት ዳስ እንስራ አንዱን ለአንተ አንዱን #ለሙሴ አንዱን #ለኤልያስ አለ፡፡ በዚህ ጊዜ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፡፡ ከደመናውም በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት የሚል ድምፅም ተሰማ፡፡ ሐዋርያት ይህንን ሰምተው የጌታችንን መለኮታዊ ክብር አይተው በፊታቸው ወደቁ እጅግ ፈርተው ነበር፡፡ ጌታችንንም ተነሡ አትፍሩም አላቸው፡፡ በዚህ መልኩ አምላክነቱን ገለጠላቸው /ማቴ. 17፥1-10/፡፡
፠፠፠
#አዕማደ_ሐዋርያት_(#ጴጥሮስ፣ #ያዕቆብና #ዮሐንስ )#ለምን_ተመረጡ
አዕማደ ሐዋርያት
"አዕማደ ሐዋርያት ተብለው የተጠሩት #ጴጥሮስ፣ #ያዕቆብና #ዮሐንስ ናቸው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ጴጥሮስ፣ ዮሐንስና ያዕቆብን “አዕማድ ሐዋርያት” እያለ ጠርቷቸዋል /ገላ. 2፥9/፡፡ ስያሜውን ያገኙበት ዋናው ምክንያት የኢየሩሳሌምን ቤተ ክርስቲያን በሓላፊነት ያስተባብሩ ስለነበረ ነው፡፡ ከዚህን በተጨማሪ ጌታችን በኢያኢሮስ ቤት ልጁን ሲፈውስ፣ በጌቴ ሴማኒ ሲጸልይና በደብረ ታቦር ምስጢረ መለኮቱን ሲገልጥ ከእሱ ስላልተለዩና ይዟቸው ስለሔደ ነው /ማር.5፥37-43/፡፡
ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሦስቱ ደቀ መዛሙርት የተመረጡበትን ምክንያት ሲያትቱ እንዲህ ብለዋል፡፡ ሦስቱ ደቀ መዛሙርት ሹመት፣ ሽልማትና ክብር ፈላጊዎች ነበሩ፡፡ ከዚህ ሃሳብ እንዲወጡ ከብልየታቸው እንዲታደሱ ለይቶ አውጥቷቸዋል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ለድኅነተ ዓለም የመጣው በሕማማቱ በሞቱ ቤዛ የሚሆነን አምላክ “ልሰቀል ነው” ባላቸው ጊዜ “አይሁንብህ” ብሎት ነበር፡፡ እንዲህ ያለው ሃሳብ የጠላት እንጂ የሰው ልጆች ሊሆን አይችልም ከሞቱ በቀር ድኀነት ሊያስገኝልን የሚችል የለምና፡፡ ደቀ መዝሙሩ ግን ከሞተ ክብሬ ምንድን ነው ብሏልና “አይሁንብህ” አለ፡፡ /ማቴ. 16/ በሌላም ስፍራ እንዲሁ “ሁሉን ትተን ተከተልንህ እንግዲያስ ምን እናገኝ ይሆን?” በማለት ይጠይቃል፡፡ /ማቴ.19/፡፡ ጌታ ግን ዋጋችሁ #ሰማያዊ #ክብራችሁ ዘላለማዊ ነው ሲል እስከ ፍጹማን መዓርግ /ነጽሮተ #ሥሉስ ቅዱስ/ አድርሶ ብርሃነ መለኮትን ገልጦ ተስፋውን ነገራቸው፡፡
ሁለቱ ወንድማማች ደቀ መዛሙርትም እናታቸውን ልከው ሹመት ሽልማት መዓርግ ለምነዋል፡፡ ስለዚህም ጌታችን በደብረ ታቦር “በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው ነገር” ስለሞቱ እንዲነጋገሩ አደረገ፡፡ ሞቱ እርግጥ ሆነ ማለት ነው፡፡ አባቱም “ኦሆ በልዎ ለክርስቶስ”፤ እሺ በሉት እርሱን ስሙት ሲል፡፡ ሞቱ እርግጥ በመሆኑ ከልባቸው እንዲጠፋ መርጦ ወደ ቅዱስ ተራራ ይዟቸው ወጥቷል፡፡
“እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም” እንዲል /ሚል 3፥6/ በእርሱ ዘንድ ወረት የለም፡፡ አስቀድሞ ከተዓምራቱ ከምሥጢሩ አይለያቸውም ነበርና ብርሃነ መለኮትን ለማየት አበቃቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ለማወቅ፣ ለመማር፣ ለመጠየቅ ያሳዩት ትጋት ምስጢር ተገልጦላቸዋል፡፡ ይህ ምስጢር ለሦስቱ ደቀ መዛሙርት ተገልጦ የሚቀር አይደለም፡፡ እስከ ዓለም ፍፃሜ እግዚአብሔር ለመረጣቸው ሲገለጥ፣ በመረጣቸውም ሲነገር የሚኖር ነው፡፡ደቀ መዝሙሩ ጴጥሮስ “አልክድህም አልተውህም” የሚለው /ማቴ. 26፥35/ ቢወድደው አይደለምን? ፍቅሩን መግለጡ ለክብር አብቅቶታል፡፡ ሁለቱ ደቀ መዛሙርትም “ጽዋዬን ልትጠጡ አትችሉም” ቢላቸውም /ማቴ. 20፥22/ አንዳችን በቀኝ ሌላችን በግራ ሆነን አብረንህ እንሞታለን ሲሉ በምስጢር ለምነዋል፡፡ ሞታቸውን ከሞቱ ጋር መደመራቸው ፍቅራቸውን መግለጣቸው ነው፡፡
፠፠፠
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤ / የተዘጋጀ :: ꔰ
#ነሐሴ_12
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ዐሥራ ሁለት በዚች ቀን የመላእክት አለቃ የከበረ #ቅዱስ_ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው፣ #ቅዱስ_ቈስጠንጢኖስ ወደ ሮሜ ከተማ ገባ በሮሜ አገሮችም ሁሉ ላይ ነገሠ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ሚካኤል_ሊቀ_መላእክት
ነሐሴ ዐሥራ ሁለት በዚች ቀን የመላእክት አለቃ የከበረ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።
በዚች ቀን እግዚአብሔር ወደ ዕሌኒ ልጅ ወደ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ልኮታልና ለእርሱም ጠላቶቹን እስከ አሸነፋቸው መንግሥቱም እስከ ጸናች ድረስ ኃይልን ሰጠው የጣዖታትንም ቤት አፍርሶ አብያተ ክርስቲያናትን ሠራ። በጌጥም ሁሉ አስጌጣቸው።
ስለዚህም አባቶቻችን የቤተክርስቲያን መምህራን የከበረ የመላእክት አለቃ የሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ በየወሩ በዐሥራ ሁለተኛው ቀን እናደርግ ዘንድ አዘዙን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ታላቁ_ንጉሥ_ቅዱስ_ቆስጠንጢኖስ
በዚህችም ቀን ቈስጠንጢኖስ ወደ ሮሜ ከተማ ገባ በሮሜ አገሮችም ሁሉ ላይ ነገሠ።
(ዜናውም መጋቢት ሃያ ስምንት ቀን ላይ ተጽፏል።)
የዚህ ቅዱስ የአባቱ ስም ቍንስጣ የእናቱ ስም ዕሌኒ ነው ቊንስጣም በራንጥያ ለሚባል አገር ንጉሥ ነው መክስምያኖስም በሮሜ በአንጾኪያና በግብጽ ላይ ነግሦ ነበር።
ይህም ቍስጣ አረማዊ ነበር ግን በጎ ሥራ ያለው እውነትን የሚወድ በልቡናውም ይቅርታና ርኃራኄን የተመላ ክፋት የሌለበት ነው። ወደሮሐ ከተማ በሔደ ጊዜ ዕሌኒን አይቶ ሚስት ልትሆነው አገባት እርሷም ክርስቲያናዊት ናት። ንጉሥ ቈስጠንጢኖስንም ፀንሳ ወለደችው ስሙንም ቈስጠንጢኖስ ብላ ጠራቸው ይህም ዝንጉርጒር ማለት ነው።
ከዚህም በኋላ ንጉሥ ቊንስጣ ዕሌኒን በዚያው ትቷት ወደ በራንጥያ ከተማ ተመለሰ። እርሷም ልጇን እያሳደገች በዚያው ኖረች የክርስትናን ትምህርት አስተማረችው ይቅርታንና ርኅራኄን በክርስቲያን ወገኖች ላይ እንዲያደርግ በልቡናው ትዘራበት ነበር። እርሷ ክርስቲያን ስትሆን የክርስትና ጥምቀትን ታጠምቀው ዘንድ አልደፈረችም መንፈሳዊ ዕውቀትን ሁሉ በማስተማር አሳደገችው ዳግመኛም ለመንግሥት ልጆች የሚገባውንም ሁሉ።
ከዚያም በኋላ ወደ አባቱ ሰደደችው አባቱም በአየው ጊዜ ደስ ተሰኘበት ዕውቀትን የተመላ ሁኖ ፈረስ በመጋለብም ብርቱና የጸና ሆኖ አግኝቶታልና በበታቹም መስፍን አድርጎ ሹሞ በመንግሥቱ ሥራ ላይ ሁሉ ሥልጣን ሰጠው።
ከሁለት ዓመትም በኋላ አባቱ አረፈ ቈስጠንጢኖስም መንግሥቱን ሁሉ ተረከበ የቀና ፍርድንም የሚፈርድ ሆነ ከእርሱ በፊት የነበሩ ነገሥታት የጫኑባቸውን ጽኑ አገዛዝ ከሰዎች ላይ አስወገደ። አሕዛብም ሁሉ ታዘዙለት ወደዱትም የአገዛዙ ቅንነትና የፍርዱ ትክክለኛነት በአገሮች ሁሉ እስቲሰማ ተገዙለት።
የሮሜ ሰዎች ታላላቆች መልእክትን ወደርሱ ላኩ ከከሀዲ መክስምያኖስ ጽኑ አገዛዝ እንዲያድናቸው እየለመኑ እርሱ አሠቃይቷቸው ነበርና። ነመልእክታቸውንም በአነበቡ ጊዜ ስለ ደረሰባቸው መከራ እጅግ አዘነ ያድናቸውም ዘንድ ምን እደሚያደርግ በዐደባባይ ተቀምጦ እያሰበ ሲያዝን እነሆ ከቀኑ በስድስት ሰዓት በቀትር ጊዜ ኅብሩ እንደ ከዋክብት የሆነ መስቀል ታየው በላዩም በዮናኒ ቋንቋ ኒኮስጣጣን የሚል ጹሑፍ አለ ትርጓሜውም በዚህ ጠላትህን ድል ታደርጋለህ ማለት ነው።
የመስቀሉም ብርሃን የፀሐይን ብርሃን ሲሸፍነው በአየ ጊዜ አደነቀ። በላዩ ስለተጻፈውም አስቦ ለጭፍሮቹ አለቆችና ለመንግሥቱ ታላላቅ ባለሥልጣኖች አሳያቸው። እነርሱም ቢሆኑ ይህ መስቀል ስለምን እንደተገለጠ አላወቁም።
በዚያችም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ለቈስጠንጢኖስ በራእይ ተገልጦ እንዲህ አለው በቀኑ እኩሌታ በቀትር በአየኸው በዚያ መስቀል አምሳል ላንተ ምልክት አድርግ በርሱም ጠላትህን ድል ታደርጋለህ አለው። ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ ልቡ ጸና የወርቅ መስቀልም አሠርቶ በነገሠበት ዘውድ ላይ አደረገው መኳንንቱንና ወታደሮቹን ጭፍሮቹን ሁሉ መስቀል ሠርተው በጦር መሣሪያቸው ላይ ያደርጉ ዘንድ አዘዛቸው እነርሱም እንዳዘዛቸው አደረጉ።
ይህም የሆነው በበራንጥያ በነገሠ በሰባተኛ ዓመቱ ነው። የሮሜን ሰዎች ከሥቃያቸው ሊያድናቸው ሠራዊቱን ሰብስቦ ተነሥቶ ወጣ። መክስምያኖስም ሰምቶ በታላቅ ወንዝ ላይም ታላቅ ድልድይ ሠርቶ ወደ ቈስጠንጢኖስም ተሻግሮ ከእርሱ ጋራ ተዋጋ።
የመስቀሉም ምልክት ቀድሞ በታየ ጊዜ የመክስምያኖስ ሠራዊት ድል ይሆኑ ነበር የቈስጠንጢኖስም ሠራዊት ከመክስምያኖስ ሰራዊት ብዙ ሰው ገደሉ። የቀሩትም ሸሽተው ሲሔዱ ከመክስምያኖስ ጋር ሊሻገሩና ወደ ሮሜ ሊገቡ ድልድይ ላይ ወጡ ድልድዩም ፈርሶ ፈርዖን ከሠራዊቱ ጋራ እንደ ሠጠመ እንዲሁ መክስምያኖስ ከሠራዊቱ ጋራ ሠጠመ።
ቈስጠንጢኖስም ወደ ሮሜ ከተማ ሲገባ የሮሜ ሰዎች ከካህናት ጋራ መብራቶች ይዘው በእንቍ የተሸለሙ አክሊሎችን ደፍተው እምቢልታ እየነፉ ተቀበሉት የተማሩ ሊቃውንትም የከበረ መስቀልን ሲያመሰግኑት የሀገራችን መዳኛ ይሉት ነበር ለከበረ መስቀልም ሰባት ቀን በዓል አደረጉ።
ቈስጠንጢኖስም ዳግመኛ በሮሜ ነገሠ ከሀዲዎች የሆኑ መክስምያኖስና ዲዮቅልጥያኖስ ስለ ክብር ባለቤት ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት ያሠሩአቸውን እሥረኞች ሁሉንም ፈታቸው ደግሞ የጣዖታት ቤቶች ይዘጉ አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ ብሎ ዓዋጅ አስነገረ።
ዳግመኛም ክርስቲያኖችን እንዲአከብሩአቸው እንጂ እንዳያዋርዱአቸው የጣዖታቱንም ገንዘብና ምድራቸውን ለካህናት እንዲሰጧቸው አዘዘ ክርስቲያኖች በአረማውያን ላይ እንዲሾሙ አደረገ። ዳግመኛም አባቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙ ማንም ሰው በሰሙነ ሕማማት ሥራ እንዳይሠራ አዘዘ።
በነገሠ በሥስራ አንድ ዓመት በሮሜ ሊቀ ጳጳሳት በሶል ጴጥሮስ እጅ የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቀ። ሠራዊቱም ሁሉ። ይህም የከበረ መስቀል ከተገለጠለት በኋላ በአራት ዓመት ነው።
ከዚህ በኋላም በእርሱ ርዳታና ድል ያገኘበትን የሚያድን ስለ ሆነ ስለ ጌታችን መስቀል ትመረምር ዘንድ እናቱ ዕሌኒን ወደ ኢየሩሳሌም ላካት። እርሷም ዐመፀኞች አይሁድ ቀብረው ከደፈኑት ቦታ አወጣችው።
በዘመኑ ሃይማኖታቸው የቀና የሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ጳጳሳት የአንድነት ስብሰባ በኒቅያ ስለ አርዮስ ተደረገ። ለክርስቲያኖች መመሪያ በበጎ አሠራር ክርስቲያናዊት ሥርዓት ተሰራች።
ከዚህም በኋላ በበራንጥያ ታላቅ ከተማ ሊሠራ አሰበ እንደ አሰበውም ታላቅ ከተማ ሠርቶ በስሙ ቍስጥንጥንያ ብሎ ጠራት። በውስጧም አምላክን በወለደች በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በአግያና በሶፍያም ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ሠራ መንፈሳዊ በሆነ በመልካም ጌጥ ሁሉ አስጌጣት። በውስጥዋ ከሐዋርያት የብዙዎቹን ዓፅም ከሰማዕታትና ከቅዱሳን ጻድቃን ሥጋቸውን ስለሚሰበስብ።
የክብር ባለቤት ጌታችንን ደስ አሰኝቶ መልካም ተጋድሎውን ከፈጸመ በኋላ በኒቆምድያ ከተማ ጥቂት ታሞ መጋቢት ሃያ ስምንት አረፈ።
ገንዘውም በወርቅ ሣጥን አድርገው ተሸክመው ወደ ቊስጥንጥንያ አደረሱት የጳጳሳት አለቆችና ካህናቱ ከሁሉ ሕዝብ ጋር ወጥተው ተቀበሉት በብዙ ጸሎት በመዘመርና በማኅሌት በምስጋና ወደ ከበሩ ሐዋርያት ቤተ መቅደስ አስገብተው በክብር አኖሩት።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ_እና_መጋቢት)
ነሐሴ 12/2015 #ቅዱስ_ሚካኤል
#ፆመ_ማርያም
👉አንድ አምላክ በሆነ #በአብ_በወልድ_በመንፈስ_ቅዱስ ስም ለመልአኩ #ቅዱስ_ሚካኤል ወርሐዊ መታሰቢያ በአል እንኳን አደረሰን የእናታችን #ማርያም ምልጃና ፀሎት ክቡር የሆነዉ ቃል ኪዳኗ ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን"
👉ሚካኤል ማለት ‹‹መኑ ከመ አምላክ (እግዚአብሔር)፤ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው›› ማለት ነው፡፡ ይህም የእግዚአብሔርን ገናንነትና እርሱን የሚመስል አምላክ እንደሌለ፣ እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ፣ ርኀሩኅ፣ ኃያልና ረቂቅ ማንም እንደሌለ የሚያመለክት ነው፡፡
👉ቅዱስ ሚካኤል ሌሎች መጠሪያዎች አሉት፤ እነዚህም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠውን የባለሟልነት ክብር የሚገልጹ ናቸው፡፡ እነርሱም ‹‹መልአከ ኃይል፣ መጋቤ ብሉይ፣ መልአከ ምክሩ፣…›› ናቸው፡፡ መልአከ ኃይል የተባለው እግዚአብሔር በእርሱ አማካይነት ታላላቅ ሥራዎችን በመሥራት ኃይሉን ስለገለጸና ዲያብሎስን ከነሠራዊቱ ስላሸነፈ ነው፡፡
👉መጋቤ ብሉይ የተባለበት ምክንያት በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከእግዚአብሔር እየተላከ ብዙ ታላላቅ ሥራዎችን የሠራ በመሆኑ ነው፡፡ መልአከ ምክር ወይም የእግዚአብሔር የምክሩ አበጋዝ የተባለበት ምክንያት እግዚአብሔርን በምክሩ ይረዳዋል ለማለት ሳይሆን እግዚአብሔር የሚሠራውን ሥራ ለወዳጁ ለቅዱስ ሚካኤል ይገልጽለታልና በእርሱ አማካኝነት ይሠራል ለማለት ነው፡፡
👉ቅዱስ ሚካኤል በዚህ ሁሉ ልዕልና ላይ ትሕትናን ደርቦ የያዘ፣ በጸሎቱ ተማጽኖና በተራዳኢነት አምኖ ለሚለምነው ሁሉ ፈጥኖ በመድረስ ከሠራዊተ አጋንንት ተንኰል የሚያድን መልአክ እንደሆነ በቅዱስ መጽሐፍ ተጠቅሶ እናገኛለን፡፡
👉ለምሳሌ ሙሴንና እስራኤልን በሲና በረሃ (ዘፀ.፳፫÷፳-፳፪)፤ (ዘፀ.፲፬÷፲፭-፳) ኢያሱን በኢያሪኮ (ኢያ.፭÷፲፫-፲፭)፤ ከአሞራውያንም እጅ ሕዝቅያስን እንደረዳቸው ተጽፏል፡፡ (ኢሳ.፴፯÷፴፮) በትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ፲ ቁጥር ፲፫ ላይ ‹‹የፋርስ መንግሥት አለቃ ግን ሃያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ፤ እነሆም ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ›› በማለት የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት ተገልጿል፡፡
👉በዚሁ የመጽሐፍ ክፍል ምዕራፍ ፲፪ ቁጥር ፩ ላይ ‹‹በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል›› በማለት ታላቅነቱን፣ ለሰው ልጆች ሁሉ በአማላጅነቱና በተራዳኢነት የሚቆም እንደሆነ በማያሻማ ቃል ተገልጿል፡፡
👉በአጠቃላይ በኦሪት የእግዚአብሔር መልአክ እየተባለ የሚጠራው አብዛኛውን ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ያስተምራሉ፤ በድርሳነ ሚካኤልም ተጽፎ ይገኛል፡፡ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ያልረዳው ቅዱስ የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ በዘመነ ሰማዕታት በተጋድሎ ያጸናቸው ይህ ሩኅሩኅ መላክ እንደሆነ በእነ ቅዱስ ፋሲለደስ እንዲሁም በእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገድላት ላይ በሰፊው ተገልጿል፡፡
👉የቤተክርስቲያን አባቶች በየወሩ በ፲፪ ቀን መታሰቢያውን እንድናደርግ አዘውናል ይህንንም ያልቻለ በዓመት አራት ዓበይት በዓላትን ከቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ጀምሮ እንደተቻለ ማዝከር ይገባል፡ እነዚህም ኅዳር ፲፪ ቀን ቀጥሎ ሰኔ ፲፪ ቀን ከዚያም ነሐሴ ፲፪ ቀንና ታኅሣሥ ፲፪ ቀን ናቸው፡፡
👉ሰኔ ፲፪ በቅዳሴያችን ‹‹ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል፤ ለሚካኤል ምሕረት (ይቅርታ ርኀራኄ) ተሰጠው እንላለን፤ ነቢዩ ሄኖክም ምሕረት ለሚካኤል መሰጠቱን ገልጿል፤ ትሕትናውን ታዛዥነቱን አስረድቷል፡፡ (ሄኖ.፮÷፭፣፲÷፲፪)
👉የሰማያውያን ሠራዊት አለቃ፣ ለሰው ሁሉ የሚራራና ስለ ሰው ልጆች ሳያቋርጥ ወደ ፈጣሪው የሚለምን፣ ርኀሩኀና ትሑት የሆነው ኃያሉ ቅዱስ ሚካኤል የሠራውን ሥራ፣ የክብሩንና ገናንነቱን ጽፈን ለመጨረስ የሚቻለን አይደለም እንዲሁ በጥቅሉ ጸሎቱ እና በረከቱ፣ ተራዳኢነቱም ሀገራችንና ሕዝባችንን ይጠብቅልን ከማለት በስተቀር "አሜን"
ሰላማችሁ በክርስቶስ ይብዛ
የጾም ወቅት ውስጥ እንደመሆናችን መጠን አንድ የበረከት ስራ እንስራ ስር በልዑል እግዚአብሔር ስም እጠይቃችዋለው
ለ100 ቤተክርስቲያናት ጧፍ ፤ እጣን ፤ ዘቢብን ጨምሮ ገቢ ማድረግ ነው የዚህ የበረከት ስራ አላማ ስለሆነም ሁላችሁም የአቅማችሁን ያህል ተሳተፉ በዋነኝነት አንድ ሰው 1800ብር አዋጣ ማለት አንድ ቤተክርስቲያንን አገዘ ማለት ነው።እስካሁን ባለው 80%ያህል ተሸፍኗል አሁን ላይ ተባብረን ይሄንን የበረከት ስራ ማስፈጸም አለብን።ከ100 ብር መጀመር ትችላላችሁ ለነፍሳችን ድህነት 100ብር ምንም አይደለም እህት ወንድሞቼ ከላይ ባለው የባንክ አካውንት የዚህ የበረከት ስራ ውስጥ መሳተፍ ትችላላችሁ።አስገብታችሁ ስትጨርሱ ደረሰኙን @Joseph2716 በዚህ አካውንት ለወንድማችን ላኩለት።
ሰላመ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን!!!
††† እንኳን ለቅዱስ አባ ሞይስስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ቅዱስ አባ ሞይስስ ጻድቅ †††
††† ቅዱሱ በኋላ ዘመን ከተነሱ አበው አንዱ ሲሆን ትውልዱ: ነገዱ ከግብፅ ነው:: ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ ቢሆንም ክርስቲያኖች ጠንካሮች ነበሩ:: አባ ሞይስስ ከክርስቲያን ወላጆቹ ተወልዶ: ገና በልጅነት ወደ ትምህርት ቤት ገብቷል::
††† የዘመኑ ትምሕርት ሁለት ወገን ሲሆን
1ኛው የሃይማኖት ትምሕርት:
2ኛው ደግሞ ፍልስፍና ነበር::
የጻድቁ ምርጫው የቤተ ክርስቲያን ትምሕርት ነበርና ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምሯል:: እንደሚገባ ተምሮ ስለ ነበርም ዲቁናን ሹመውት ተግቶ አገልግሏል::
ከጥቂት ዘመናት በኋላም በተሻለው ጐዳና እግዚአብሔርን ሊያገለግል ተመኘ:: ይህቺን ዓለምም ይንቃት ዘንድ ወደደ:: መልካም ምኞትን መፈጸም ለእግዚአብሔር ልማዱ ነውና የልቡናውን ተምኔት ፈጸመለት:: ከከተማ ወጥቶ: ቁራጭ ጨርቅ ለብሶ ገዳም ገባ::
በዚያም በረድእነት ያገለግል ገባ:: በፍጹም ልቡ በትሕትና እግዚአብሔርን ደስ አሰኘ:: በጉብዝናው ወራት ይህንን መርጧልና:: ገዳሙንም ሲያገለግል ዕረፍትም አልነበረውምና በመነኮሳት ዘንድ እጅግ ተወዳጅ ነው::
ከጊዜም በኋላ "በቅተሃል" ብለው አበው ከአሞክሮ ወደ ምንኩስና: ከምንኩስና ወደ አስኬማ አሸጋግረውታል:: እርሱም ለአሥራ ስምንት ዓመታት አገልግሎቱን ሳያስታጉል: ወጥቶ ወርዶ ገዳሙን ረድቷል:: በእነዚህ ጊዜያት በጸሎት: በጾምና በስግደት ይጋደል ነበር::
በጠባዩም ትእግስትን: ትሕትናን: ተፋቅሮን የሚያዘወትር ነበር:: ጐን ለጐንም ለቤተ መቅደስ አገልግሎት ይፋጠን ነበር:: በዘመኑ የግብፅ ፓትርያርክ አባ ሚካኤል ይባሉ ነበር::
አውሲም በምትባል አውራጃ ኤጲስ ቆጶስ ዐርፎባቸው "ማንን ልሹም" እያሉ ይጨነቁ ነበርና እግዚአብሔር ስለ አባ ሞይስስ ገለጠላቸው::
አባ ሚካኤልም "ለሕዝቤ የሚጠቅም መልካም እረኛ አገኘሁ" ብሎ ደስ አለው:: ጊዜ ሳጠፋም እርሱን አስጠርቶ "ተሾም" አለው:: አበው ትሕትና ሙያቸው ነውና "አይቻለኝም: ተወኝ ይቅርብኝ" ሲል መለሰ::
አባ ሚካኤል ግን "የምሾምህ መቼ በሰው ፈቃድ ሆነና: በእግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ" ብሎ ዕለቱኑ ሹመውታል:: እርሱም የአውሲም ጳጳስ ሆኗል:: ቅዱሱ አባ ሞይስስም ወደ ሃገረ ስብከቱ ሔዶ አገልግሎቱን ጀመረ::
በጵጵስና ዘመኑ እንደ ከተማ ሰው መኖርን: የሥጋ ምቾትን አልፈለገምና ጠባቡን መንገድ መርጧል:: በገዳም ሲሰራው ከነበረው ተግባር መካከል ያቋረጠው አልነበረም:: ከብቃቱ የተነሳ ለወደፊት የሚደረገውን ያውቅ ነበር:: እርሱ የተነበየው ሁሉ ተፈጽሟልና::
ሕዝቡን ይመራቸው ዘንድም ተግቶ ያስምራቸው ነበር:: ዘወትርም ከክፋት: ከኃጢአት ይጠብቃቸው ዘንድ ይጸልይላቸው ነበር:: ያዘኑትን ሲያጽናና: በደለኞችን ሲገስጽ ዘመናት አለፉ:: አንድ ወቅት ላይም ስለ ሃይማኖቱ ታሥሮ በረሃብ ተቀጥቷል: ግርፋትንም ታግሷል::
ጻድቁ ጳጳስ አባ ሞይስስ እንዲህ ተመላልሶ የሚያርፍበት ቀን ቢደርስ ሕዝቡን ሰበሰባቸው:: "እኔ ወደ ፈጣሪዬ እሔዳለሁና ሃይማኖታችሁንና ቤተ ክርስቲያንን ጠብቁ" ብሏቸው በትእምርተ መስቀል አማትቦ ዐረፈ:: ምዕመናንም በብዙ እንባና ምስጋና ቀብረውታል:: ከተቀደሰ ሥጋውና ከመቃብሩም ብዙ ተአምራት ታይተዋል::
††† አምላከ ቅዱሳን ከቅዱሱ አባት በረከት ይክፈለን::
††† ነሐሴ 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አባ ሞይስስ
2.ቅዱስ አብጥልማዎስ
3.ሦስት መቶ ሰማዕታት (የቅዱስ ፋሲለደስ ማኅበር)
††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ያሬድ ካህን
2.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
3.ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና
4.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
5.ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት
††† "ስለዚህ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያንን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት: ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ:: ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ እኔ አውቃለሁ:: ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሰጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ::" †††
(ሐዋ. ፳፥፳፰)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
✞✞✞ እንኳን ለጌታችን ቅዱስ ዕፀ መስቀል ዓመታዊ የተአምር በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ✞✞✞
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ✞✞✞
✞✞✞ ቅዱስ ዕፀ መስቀል ✞✞✞
✞✞✞ የዕፀዋት ሁሉ ንጉሣቸው የሚሆን ቅዱስ ዕፀ መስቀል ለእኛም ኃይላችን: ቤዛችን: መዳኛችን: የድል ምልክታችን ነው:: መስቀል በደመ ክርስቶስ ተቀድሷልና አንክሮ: ስግደት ክብርና ምስጋና በጸጋ ይገባዋል::
ቅዱስ መስቀለ ክርስቶስ ላለፉት ሁለት ሺ ዓመታት ብዙ ተአምራትን ሠርቷል:: ከእነዚህ መካከልም አንዱን በዚህ ዕለት እናዘክራለን::
ታሪኩ: ምሥጢሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
በ400 ዓ/ም አካባቢ በግብፅ አባ ቴዎፍሎስ ፓትርያርክ ሳለ: ቅዱስ ቄርሎስም በሊቀ ዲቁና ሲያገለግል ሳለ በእስክንድርያ ከተማ ሁለት ደሃ ክርስቲያኖች ይኖሩ ነበር:: የቀን ሠራተኞች በመሆናቸው ከዕለት ምግብ አይተርፋቸውም ነበር::
ከሁለቱ አንዱ ፍጹም አማኝ ሲሆን ሌላኛው ግን ተጠራጣሪ ነበር:: ስለ ምን ነው ቢሉ:- በከተማዋ ብዙ ሃብታም አይሁድ ነበሩና እነሱን እየተመለከተ ነው:: ለእርሱ ክርስትና ማለት ገንዘብ መስሎታልና ዘወትር "ለምን ክርስቶስን እያመለክን ድሃ እንሆናለን?" እያለ ያማርር ነበር::
"ያዛቆነ ሰይጣን . . . " እንደሚባለው አንድ ቀን ባልጀራውን "ለምን ክርስቶስን አንክደውም? (ሎቱ ስብሐት!) እርሱን ከማምለክ የተረፈን ድህነት ብቻ ነው" አለው:: ባልንጀራው ሊመክረው ሞከረ:: "እግዚአብሔር አምላከ-ነዳያን ነው:: ቅዱሳን ነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃን: ሰማዕታትም በሥጋዊ ሃብት ነዳያን ነበሩ::" ብሎ ቢለውም ሰይጣን ሠልጥኖበታልና አልሰማውም::
ያ ስሑት ደሃ ወዲያው ወጥቶ ወደ ማኅበረ አይሁድ ሔደ:: እነርሱ በቁጥር ብዙ ሁነው በአንድነት ይኖሩ ነበር:: "ሥራ ቅጠሩኝ" አላቸው:: "በእምነት አትመስለንምና አይሆንም" አሉት:: ያን ጊዜ ለአለቃቸው (ፈለስኪኖስ) "አንተ ሥራ ቅጠረኝ እንጂ እኔ ክርስቶስን እክዳለሁ::" (ሎቱ ስብሐት!) አለው::
ወዲያው የከተማው ሕዝብ ተጠርቶ: በጉባኤ መካከል ሊያስክዱት ተዘጋጁ:: በፍጥነትም መስቀል: ጦር: ሐሞት አዘጋጁ:: ሥዕለ ስቅለቱንም አመጡ:: ያን ደሃ ከሃዲም "በል-ክርስቶስ ሆይ! ካድኩህ ብለህ ምራቅህን ትፋበት: ሐሞቱን አፍስበት: በጦርም ውጋው::" (ሎቱ ስብሐት!) አሉት::
ያ ልቡ የደነቆረ መስቀለ ክርስቶስ ላይ ተፋ:: ሐሞትም አፈሰሰበት:: በመጨረሻ በጦር ሲወጋው ግን ድንቅ ተአምር ተገለጠ:: በጦር ከተወጋው ከመስቀሉ ጐን ብዙ ደም ፈሰሰ:: ለረዥም ሰዓትም አላቋረጠም:: በዚህች ሰዓት በአካባቢው የነበሩ ሁሉም አይሁድ በግንባራቸው ተደፍተው ለክርስቶስና ቅዱስ መስቀሉ ሰገዱ::
ሁሉም በአንድነት "ክርስቶስ የአብርሃም አምላክ ነው:: መድኃኒትም ነው::" ሲሉ እየጮሁ ተናገሩ:: ባለማወቅ ስላደረጉት እነርሱ ምሕረትን ሲያገኙ ያ አዕምሮ የጐደለውን ደሃ ግን ዘወር ብለው ሲያዩት ወደ ድንጋይነት ተቀይሮ ነበር:: ነፍሱንም: ሥጋውንም በፈቃዱ አጠፋ::
የአይሁድ አለቃም ዓይነ ሥውር ዘመድ ነበረውና ወዲያው አምጥቶ ከደሙ ቢቀባው ዐይኑ በራ:: ታላቅ ደስታም በዚያ ሥፍራ ተደረገ:: ነገሩን የሰሙት ቅዱሳን ቴዎፍሎስ እና ቄርሎስ ሲመጡ ደሙ ከመፍሰስ አላቆመም ነበር::
በተአምሩ ደስ ተሰኝተው: ከደመ ክርስቶስ ለበረከት ተቀቡ:: የፈሰሰውን ቅዱስ ደም ከነአፈሩ አንስተው: መስቀሉን በትከሻ ተሸክመው: በፍፁም እልልታና ዝማሬ ወስደው በቤተ መቅደስ አኑረውታል:: የከተማዋ ሁሉም አይሁድም በክርስቶስ አምነው ተጠምቀዋል::
✞✞✞ ቅዱሳን ስምዖንና ዮሐንስ ✞✞✞
✞✞✞ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ አስደናቂ ታሪክ ካላቸው ጻድቃን እነዚህ ሁለቱ ቅድሚያውን ይይዛሉ::
እርሱስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
ቅዱሳኑ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ሶርያ አካባቢ ተወልደው ያደጉ ክርስቲያኖች ናቸው::
ዘመዳሞች ከመሆናቸው ባሻገር አብረው ስላደጉ እጅጉን ይፋቀሩ ነበር:: የዋሃንም ነበሩ:: ወጣት በሆኑ ጊዜ ትልቁ ዮሐንስ ሚስት አገባ:: ታዲያ አንድ ቀን ከጌታችን መቃብር ኢየሩሳሌም ደርሰው ሲመለሱ ገዳመ ዮርዳኖስ አካባቢ ደረሱ:: እርስ በእርሳቸውም "ይህ ገዳምኮ የመላእክት ማደሪያ ነው::" ተባባሉ::
በዚያውም መንነው ለመቅረት አሰቡ:: ፈረስና ንብረታቸውን ለዘመዶቻቸው ልከው ጸሎት አደረሱ:: ፈቃደ እግዚአብሔርን ሊረዱም ዕጣ ተጣጣሉ:: ዕጣውም "ወደ ገዳም ሒዱ" የሚል ስለሆነ ተቃቅፈው ደስ አላቸው::
ወደ ገዳሙ ሲደርሱም አበ ምኔቱ አባ ኒቅዮስ ፈጣሪ አዞት የገዳሙን በር ከፍቶ ጠበቃቸው:: ተቀብሎ ሲያስገባቸውም አንድ ደግ መነኮስ ሲያልፍ: ቆቡ ቦግ ቦግ እያለ እንደ ፋና ሲያበራ እና መላእክት ከበውት አዩ:: ወዲያውም አበ ምኔቱን "እባክህ አመንኩሰን" አሉት::
እርሱም የአምላክ ፈቃድ ነውና በማግስቱ አመነኮሳቸው:: ፍቅረ ክርስቶስ ገዝቷቸዋልና በጥቂት ዓመታት ተጋድሎ ከብቃት (ከጸጋ) ደረሱ:: ሁለቱም ቆመው በፍቅር ሲጸልዩ የብርሃን አክሊል በራሳቸው ላይ ይወርድ ነበር:: አካላቸውም በሌሊት ያበራ ነበር::
እንዲህ ባለ ቅድስና ለዓመታት ቆይተው ከገዳሙ ወደ ጽኑ በርሃ ሊሔዱ ስለ ፈለጉ የገዳሙ በር በራሱ ተከፈተ:: አበ ምኔቱ አባ ኒቆን (ኒቅዮስ) እያነባ በጸሎት ሸኛቸው:: በበርሃም በጠባቡ መንገድ: በቅድስና ተጠምደው ለሃያ ዘጠኝ ዓመታት ተጋደሉ:: በዚህ ሰዓት ግን ሁለቱን የሚለያይ ምክንያት ተፈጠረ::
እግዚአብሔር ቅዱስ ስምዖን ወደ ከተማ እንዲገባ: ቅዱስ ዮሐንስ ግን በዚያው እንዲቆይ አዘዘ:: ሁለቱ ለረዥም ሰዓት ተቃቅፈው ተላቅሰው ተለያዩ:: ከሃምሳ ዓመታት በላይ ተለያይተው አያውቁም ነበርና::
ቅዱስ ስምዖን ወደ ከተማ ሲገባ ክብሩን ይደብቅ ዘንድ እንደ እብድ ሆነ:: በዚህ ምክንያትም የወቅቱ ከተሜዎች ይንቁት: በጥፊም ይመቱት ነበር:: (እባካችሁ ብዙ በየመንገዱ የወደቁ አባቶች አሉና እንጠንቀቅ!) ቅዱሱ ግን ስለ እነርሱ ይጸልይ ነበር::
በከተማዋ የነበሩ እብዶችን ሁሉንም በተአምራት ፈወሳቸው:: አንድ ቀን ግን ክርስቲያን ነን የሚሉ ሰዎች ደብድበውት ደከመ:: የእግዚእብሔር መልአክ ወርዶ "ና ልውሰድህ" ብሎ ዮሐንስን ከበርሃ: ስምዖንን ከከተማ በዚህች ቀን ወሰዳቸው:: እነሆ ብርሃናቸው ዛሬም ድረስ ለሚያምንበት ሁሉ ያበራል::
✞✞✞ ቅዱስ ባስሊቆስ ሰማዕት ✞✞✞
✞✞✞ በመጀመሪያው ምዕተ ዓመት ከነበሩ ስመ ጥር ሰማዕታት አንዱ ቅዱስ ባስሊቆስ ነው:: ብዙ ጊዜ "ኃያሉ ሰማዕት" በመባልም ይጠራል:: ስለ ፍቅረ ክርስቶስ በመከራ በቆየባቸው ዘመናት ሁሉ ከማመስገን በቀር ምግብ አይቀምስም ነበር::
"ለምን አትበላም?" ሲሉት "እኔ የአምላኬ ስሙና ፍቅሩ አጥግቦኛል::" ይላቸውም ነበር:: አሥረው በግድ ለጣዖት ሊያሰግዱት ወደ ቤተ ጣዖት ቢያስገቡት በጸሎቱ እሳት ከሰማይ ወርዳ አማልክቶቻቸውን በልታለች:: ተበሳጭተው ለቀናት የደረቀ ባላ ላይ አንጠልጥለው ቢገርፉት ደሙ ፈሰሰ::
የታሠረባት ደረቅ እንጨት ግን ለምልማ: አብባ: አፍርታ በርካቶች ተደንቀዋል:: ከበረከቱም ተሳትፈዋል:: ኃያል ሰማዕት ቅዱስ ባስሊቆስ በዚህች ቀን ተከልሎ ጌታችንና መላእክቱ ወርደው ሲያሳርጉት ብዙ ሰው አይቶ አምኗል::
✞✞✞ አምላከ ቅዱሳን ከፍቅረ መስቀሉ አድሎ: በኃይለ መስቀሉ ይጠብቀን:: የወዳጆቹን ጸጋ ክብርም ያድለን::✞✞✞ ነሐሴ 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ መስቀለ ክርስቶስ
2.ጻድቃን ቅዱሳን (አባ ስምዖንና አባ ዮሐንስ)
የአዳምና የሔዋን ብቻ አለኝታ አይደለሁም፣ ለእናትህና ለአባትህ በልጄ ዘንድ አለኝታቸው እኔ ነኝ፤ አንተንም ያገኙህ በእኔ በኩል ነው›› አለችው። ዳግመኛም ‹‹በጸጋ በጸጋ ሰጠሁህ፤ በሚያምረው ዜማህ ተደስቻለሁና። መኖሪያህንም ከሶርያው ኤፍሬምና ከብህንሳው ከአባ ሕርያቆስ ጋር አደርጋለሁ። አስቀድሜ ከአንተ አልተለየሁም፣ ከእንግዲህም ወዲያ ከአንተ አልለይም›› አለችውእመቤታችን ይኽን ብላ በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገች። አቡነ ቡሩከ አምላክ በዚህ ገዳም በብሕትውና ተጋድሎ ለ63 ዓመታት ኖረዋል። ጻድቁ በገዳመ ደብረ ኮል ያደረጓቸው ታላላቅ ተኣምራት ተቆጥረው የሚያልቁ አይደሉም። እግዚአብሔር በሰጣቸው ጸጋ እንደሙሴ ከዐለት ላይ ያፈለቁት ጠበል ብዙ በደዌ የተያያዙ ምእመናንን እየፈወሰ ይገኛል። ለአቡነ ቡሩከ አምላክ አባታቸው አቡነ አብሳዲ የሰጧቸው ኹለት ማቆሚያዎች ነበሯቸው። አንደኛዋ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚደገፉባት ስትሆን ሁለተኛዋ ደግሞ
ለአገልግሎት በየቦታው ሲዘዋወሩ ሕሙማንን የሚፈውሱባት ናት።
✝ ከዕለታት በአንደኛው ቀን ወደ ሀገረ እምብርት (ዓዲ ሕምብርቲ) ሔደው ሕዝቡን ወንጌል አስተምረው ጨርሰው ሊሔዱ ሲሉ ማቋሚያቸው ያስተምሩበት በነበረው ቦታ ላይ በተኣምር ተተክላ ሥር ሰዳ ተገኘች፤ እርሳቸውም ሊያንቀሳቅሷት ስላልቻሉ ተጨንቀው ‹‹አቤቱ ጌታ ሆይ! ምንድነው ያጠፋሁት?›› ብለው እግዚአብሔርን በጸሎት ሲጠይቁት የታዘዘ መልአክ መጥቶ ‹‹…መቋሚያህ ለሀገሪቱ በረከት ትሆን ዘንድ ከዚሁ ትቀመጥ›› አላቸው። መቋሚያዋም ለምልማ ቅጠል አውጥታ ትልቅ ዛፍ ሁና ከሥሯ ጠበል ፈልቆ ጠበሉ እስከአሁን ሕሙማንን እየፈወሰ ይገኛል። ✝የክብር ባለቤት ለአቡነ ቡሩከ አምላክ የገባላቸው ቃልኪዳን፡- ‹‹በእጅህ የባረክኸው በእግርህም የረገጥከው ዓለም ከመፈጠሩ በፊት በመንፈስ ለአንተና ለልጆችህ ያዘጋጀሁት ይሁንህ›› አለው። ዳግመኛም ‹‹በገዳምህ ለሚያገለግለውና መታሰቢያህን ለሚያደርገው እምርልሃለሁ ብየ ቃል እንደገባሁልህ በራሴ ማልሁልህ፤ ለባሪያዬ ለኖኅ፣ ለወዳጄ አብርሃም፣ ለታማኜም ለዳዊት ቃል ኪዳን የገባሁ እኔ ነኝ፤ እኔ ሲኦልን በዕለተ ዓርብ እንደበዘበዝኳት ለአንተም የእሳት ፈረስ ሰጠሁህ፤ አንተም ዳግመኛ ሲኦልን ትበዘብዛታለህ፤ መባርቅታና ነጎድጓድ ይከተሉሃል፤ መላእክትም በየወገናቸው ይሸኙሃል፤ ስለገባሁልህ ቃል ኪዳን ሲኦልን ለመማረክ ከአንተ ጋር አንድ ይሆናሉ፤ በሞት ከማረፍህ በፊት በሕይወት ሳለህ ሲኦልን ትበረብራት ዘንድ ፈቀድሁልህ፤ አንተ ከሲኦል የምታወጣቸው ነፍሳት በቊጥራቸው ከሰማይ ከዋክብትና ከምድር አሸዋ ይበዛሉ፤ እንደ ጻድቃንና እንደ ሰማዕት እንደ ሐዋርያትና እንደ ነቢያት ይኽን ሁሉ ፈጸምህ፤ ዳዊት ‹የድካምህን ዋጋ ተመገብ› እንዳለ። ይኽን ሁሉ የኦሪትና የነቢያትን የወንጌልንና የሐዋርያትን ሥራ የብሉይንና የሐዲስ ትእዛዛትን ፈጸምህ። እኔ የአምስት ገበያ የሚያህሉ ሰዎችን እንዳስተማርኩ አንተም እንዲሁ ስላስተማርህ ቃል ኪዳኔን ሰጠሁህ፤ ዐራቱ ወንዞች ገነትን እንደሚያጠጧት በአራቱ የምድር ማዕዘኖች ወንጌልን አስተማርህ፤ ያልተጠመቁትን ይድኑ ዘንድ ያጠመቅህ፤ ያላመኑትንም ያሳመንህ አንተ ቡሩከ አምላክ ነህ፤ የተጣሉትንም አስታረቅህ፤ በጾምና በጸሎትም አስደሰትከኝ፤ የሰማዕታቱን የጊዮርጊስን የፋሲለደስንና የገላውዴዎስን ተጋድሎ ትፈጽም ዘንድ ገድል ተዘጋጅቶልሃል፤ አንገትህ በሰይፍ ይቆረጣል፤ ጎንህም በጦር ይወጋል።›› አባታችን የሀገረ ገዥ ልጅ ሆነው ሳለ እርሳቸው ግን ለሰማያዊ ንግሥና ራሳቸውን አጭተው ገና በሕፃንነት ዕድሜያቸው ወደ ሀገራችን በመምጣት በብዙ ተጋድሎ ቢኖሩም በዐፄ ዳዊት ዘመን የነበሩ ክፉዎች ወደ አቡነ ቡሩክ ገዳም ወደ ደብረ ኮል መጥተው ስለሃይማኖታቸው ጽናት በሰማዕትነት ገድለዋቸዋል። አቡነ ቡሩከ አምላክም ይህ እንደሚሆን አስቀድመው በራእይ ታይቷቸው ነበርና ገዳዮቻቸውን ተዘጋጅተው ይጠብቋቸው ነበር። የሰማዕትነት አክሊል እየታያቸው ከእርሳቸው ጋር የነበሩ መነኰሳትም ‹‹እኔ ነኝ የምቀድመው፣ እኔ ነኝ መጀመሪያ የምሞተው…›› ብለው እየተሽቀዳደሙ ነሐሴ 14 ቀን በሰማዕትነት ዐረፉ። አባታችን በሰማዕትነት የሚያርፉበትን ዕለት አስቀድመው በመንፈስ ቅዱስ ያውቁት ስለነበር ለተከታዮቻቸው እንዲህ አሏቸው፡- ‹‹ከእንግዲህስ ከዚኽ ዓለም የምለይበት ኹለት ሳምንት ብቻ ቀረኝ። ከእናንተ መካከልም በሱባዔው ፍጻሜ ነሐሴ ዐሥራ ዐራት ቀን ሕይወቴን አታዩም፤ ሞቴን ግን ታያላችሁ። ያልኳችሁንም በልባችሁ አኑሩት። ከእንግዲህ ከእናንተ ጋር አልኖርም። በእግዚአብሔር ፊት በደና እንገናኝ።›› ይኽን ካላቸው በኋላ ከእነርሱ ተለይቶ ወደ ጸሎቱ ሥፍራ ሔደ። አቡነ ቡሩከ አምላክ ሲጸልይ በነበረበት ቦታ ጌታችን መጥቶ ‹‹ወዳጄ!
የሰማዕትነትህ ቀን ደረሰ›› አለው። በዚያች ዕለትም እግዚአብሔርን የማይፈራው አንድ ሽፍታ መጥቶ ቀኝ ጎኑን በጦር ወጋው፤ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ።
✝አቡነ ቡሩከ አምላክን ገዳዮቹ ጐናቸውን ከወጓቸው ቦታ ላይ ንጹሕ ጠበል ፈልቆ አሁንም ድረስ በርካታ ሕሙማንን እየፈወሰ ድንቅ ድንቅ ተኣምራት እያደረገ ይገኛል። መጠኑም በክረምት አይጨምርም በበጋም አይቀንስም፤ ይኽም እስከ ምጽአተ ክርስቶስ ድረስ እንዲሁ እንደሚቆይ ገድላቸው ይናገራል። ጻድቁ በሕይወት ሣሉ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነጭ ፈረስ ሰጥቷቸው ስለነበር በሰማዕትነት ከማረፋቸውም በፊት ‹‹ስምህን የጠራ፣ ዝክርህን የዘከረ፣ ገድልህ የጻፈና ያጻፈ፣ በስምህ ለተራበ ያበላ፣ ለተጠማ ያጠጣ፣ ለታረዘ ያለበሰ፣ ለገዳምህ ምብዓ ዕጣ ሻማ ስንዴ ወይን የሚሰጥ፣ ቤተ ክርስቲያንህን በትጋት የሚያገለግል፣ የሚሳለም፣ በጠበልህ በእምነት የሚታጠብ፣ በሰጠሁህ በዚህ ነጭ ፈረስ በእሳት መካከል እኔ አሻግረዋለሁ›› የሚል ድንቅ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል። አባታችን አዳም ‹‹አዳም ሆይ! መሬት ነበርክና ወደ መሬት ትመለሳለህ›› እንደተባለ አቡነ ቡሩከ አምላክም 63 ዓመት በገዳማቸው 🌹በደብረ ኮል፣ 62 ዓመት 🌹በደብረ ማርያምና አስቀድመው በቤተሰባቸው ዘንድ በጠቅላላ🌻 በ125 🌻ዓመታቸው 🌹🌹ነሐሴ 14 ቀን 1415 ዓ.ም 🌹በክፉዎች ሰዎች እጅ በሰማዕትነት ዐርፈው ከዚህች መከራና ኀጢአት ከበዛባት ዓለም ወደማታልፈው መንግሥተ ሰማያት ተሸጋገሩ። በተቀበሩበት ቦታ በስማቸው ቤተ ክርስቲያን የታነጸ ሲሆን ከመቃብራቸው ውስጥም ፈዋሽ ጠበል ፈልቆ ብዙ ተኣምራት እያደረገ ይገኛል። ሕሙማንም ከጥንት ጀምሮ እስከአሁን ድረስ ከተለያዩ ዓለማት እየመጡ የጻድቁን መካነ መቃብር ተሳልመው ጠበሉን ጠጥተው እየተፈወሱ ይሔዳሉ።የአቡነ ቡሩከ አምላክ የከበረች በረከታቸው ከኹላችን ጋር ይሁን፣ በጸሎታቸው ሀገራችንን ይጠብቁልን።
(ምንጭ በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን መጽሐፍ ገጽ 125-133)
ነሐሴ 13/12/2015ዓ.ም
Kuwait
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ገና በእናታቸው ማሕፀን ሳሉም ድዉይ ይፈውሱ የነበሩት አቡነ ቡሩክ አምላክ የዕረፍት በዓል አደረሳችሁ አደረስን
በእርጋታ አንብቦት.
✝የአቡነ ቡሩከ አምላክ ገዳም ከአስመራ በደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ 73 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከመንደፈራ ወደ እምኒ ሓይሊ-ዓዲ ሓውያ በሚባል ቦታ ልዩ ስሙ መራጉዝ በሚባል ቦታ ይገኛል።
✝ገዳሙ ‹‹ሙራደ ቃል ደብረ ኮል አቡነ ቡሩከ አምላክ ገዳም›› ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በዱር የተሸፈነ በተፈጥሮአዊ አቀማመጡ አስደናቂ ነው። በእግር አንድ ሰዓት ተኩል የሚፈጅ የእግር መንገድ አለው። ገዳሙን የመሠረቱት አቡነ ቡሩከ አምላክ ሲሆኑ እርሳቸውም ከታላቁ ጻድቅ ከአቡነ አብሳዲ ዘደብረ ማርያም ተምረው በዚያም ሲያገለግሉ ከኖሩ በኋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ ወደ መራጉዝ ሔደው ገዳማቸውን ገድመዋል። ገዳሙ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተኣምራት የሚደረጉበት፣ በርካታ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትንና መምህራንን ያፈራ፣ የበቁ ባሕታውያንም መናኸሪያ ነበር። አቡነ ቡሩከ አምላክ ከሴም ወገን ሲሆኑ የትውልድ ሀገራቸው ሮም ነው። አባታቸው ቴዎቅሪጦስ እናታቸው ሚሊዳማ የሚባሉ ከነገሥታት ወገን ሲሆኑ ኹለቱም እንደ አብርሃምና ሣራ በቃል ኪዳን የጸኑ ነበሩ። እነርሱም ብዙ ሀብትና ንብረት ቢኖራቸውም ልጅ ስለሌላቸው ሁልጊዜ እያዘኑ ወደ እግዚአብሔር ይጸልዩ ይለምኑ ነበር። ልዑል እግዚአብሔርም ጸሎታቸውን ሰምቶ ቅዱስ ሚካኤልን ወደ ሚሊዳማ በመላክ እንዲያበሥራት አዘዘው። ሚሊዳማ ዕድሜዋ እንደ ሣራ ገፍቶ ስለነበር ብሥራቱን ስትሰማ መልአኩን ‹‹…በዚኽ ዕድሜዬ እንዴት ይሆንልኛል?›› አለችው። ቅዱስ ሚካኤልም ‹‹ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም›› አላት፤ እርሷም እመቤታችንን አብነት አድርጋ ‹‹…እሺ እንደ ፍቃዱ ይሁንልኝ›› አለች። አባታችን አቡነ ቡሩክም በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም በዕለተ ጽንሰቷ ነሐሴ 7 ቀን ተፀንሰው በዕለተ ልደቷም ግንቦት 1 ቀን 1290 ዓ.ም ተወለዱ።ጻድቁ ገና በእናታቸው ማሕፀን ሳሉም ድዉይ እንደፈወሱ በገድላቸው ላይ ተጽፏል። ከእናቷ ማሕፀን ጀምሯ የታመመች አንዲት ሴት ነበረች።
✝አቡነ ቡሩከ አምላክ በእናታቸው ማሕፀን ሳሉ የሮሙ ንጉሥ አባታቸውና ንግሥቲቱ እናታቸው ግብዣ አድርገው ሳለ ከተወለደች ጀምሮ እስከ ሠላሳ አምስት ዓመቷ ድዉይ የነበረችው ያቺ የታመመች ሴት ወደ ግብዣው መጥታ ሳለ የአቡነ ቡሩከ አምላክ እናት የሚሊዳማ ጥላዋ ቢያርፍባት ከነበረባት ሕመም ፈጥና ዳነች። አምላክን የወለደች ቅድስት ድንግል ማርያም በእናቷ በቅድስት ሐና ማሕፀን ሳለች ብዙ ሕሙማንን እንደፈወሰች ኹሉ አቡነ ቡሩከ አምላክም እንዲሁ በእናታቸው ማሕፀን ሳሉ ድዉይ ፈወሱ። ሴቲቱም ፈጽማ ድና እግዚአብሔርን እያመሰገነች በእግሮቿ ቀጥ ብላ ቆማ ወደ ሀገሯ ሔደች። ባልም አግብታ ልጆችን የወለደች ሲሆን ልጆቿ በኋላ የአቡነ ቡሩከ አምላክ ተከታዮችና አገልጋዮች ሆነዋል። አቡነ ቡሩከ አምላክ ገና በተወለዱ በ5ኛ ቀናቸው ‹‹አንድ አምላክ ለሚሆን ለአብ ምስጋና ለወልድ ምስጋና ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን›› ብለው ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል። ዳግመኛም ‹‹ለድንግል ማርያም ምስጋና፤ ለኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ምስጋና ይሁን›› እያሉ ከእናታቸው ማሕፀን ጀምሮ የጠበቃቸውን አምላካቸውን አመሰገኑ። በ40ኛ ቀናቸውም ሥርዓተ ጥምቀት ሲፈጸምላቸው እስከመጨረሻ ድረስ ‹‹…አሜን ይሁን›› እያሉ ይቀበሉ ነበር። ስመ ጥምቀታቸውም ዓምደ ሚካኤል ይባላል። ከጥምቀታቸውም በኋላ ዘወትር ረቡዕና ዐርብ የእናታቸውን ጡት አይጠቡም ነበር፣ ሁልጊዜም የእግዚአብሔርን ምስጋና ከአፋቸው አይለይም ነበር። ሦስት ዓመት ሲሆናቸው የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እንዲማሩ ወላጆቻቸው ለመምህር ቢሰጧቸውም እርሳቸው ግን እግዚአብሔር የመጻሕፍትን ምሥጢር ስለገለጠላቸው ቅዱሳን መጻሕፍትን በፍጥነት አጥንተው ዐወቁ። አባታችን ከልጅነታቸው ጀምረው ምግባቸውንና ልብሳቸውን ለነዳያን ይመጸውቱ ነበር፤ እርሳቸው ግን ከመምህራቸው ሳይለዩ በጾም በጸሎት ተግተው ይኖሩ ነበር።
✝ ከዚኽም በኋላ ዕድሜያቸው እንደደረሰ ወላጆቻቸው ሚስት እንዲያገቡ ወሰኑላቸው ነገር ግን አባታችን ከዚኽ ሀሳብ ይድኑ ዘንድ በጸሎት እንዲያግዟቸው ለመምህራቸው በመንገር እርሳቸውም በጸሎት ተግተው እየጸለዩ ሳለ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ መጥቶ ከዚያ ሀገር ተነሥተው ወደ ምድረ አግዓዚ እነ አቡነ አብሳዲና እነ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ዘንድ እንዲሔዱ ነገራቸው። በዚያም የብዙዎች አባት እንደሚሆኑና በእርሳቸው አማካኝነት ብዙዎች እንደሚድኑ ነገራቸው። አቡነ ቡሩክም ማንም ሳያያቸው በመንፈቀ ሌሊት ተነሥተው በመልአኩ መሪነት ቀድሞ ወደነገራቸው ቦታ ወደ ደብረ ማርያም መጡ።
✝አቡነ ቡሩከ አምላክን እግዚአብሔር እንደነ ነቢዩ ኤርምያስ ገና በእናታቸው ማሕፀን ሳሉ ስለመረጣቸው በ7 ዓመታቸው ዲቁና ከተቀበሉ ከ5 ዓመት በኋላ መመንኰስ እንደሚፈልጉ ለአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ነገሯቸው። አቡነ ኤዎስጣቴዎስም ‹‹ቅዱስ ሚካኤል እንዳዘዘህ ምንኵስና የምሰጥህ እኔ አይደለሁም፣ ወደ ልጄ አብሳዲ ሒድ›› ብለዋቸው ወደ ዓረዛ ቆላ ሰራየ ሔዱ። በዚያም በ12 ዓመታቸው በአቡነ አብሳዲ እጅ መነኰሱ፤ ስማቸውንም ብሩከ አምላክ አሏቸው። አቡነ ቡሩከ አምላክ ከመነኰሱ በኋላ የክብር ባለቤታችን ጌታችን ‹‹እኔን ሊያገለግለኝ የሚወድድ ሰው ቢኖር ነፍሱን ይጥላት፣ ጨክኖ የሞቱን መስቀል ተሸክሞ ይከተለኝ፣ ነፍሱን ሊያድናት የሚወድድ ሁሉ ይጣላት፤ ነፍሱን ስለ እኔ ብሎ የጣላት ያገኛታል፤ ዳግመኛም ‹ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢገዛ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጠፋ ምን ይጠቅመዋል? ለነፍሱ ቤዛስ ምን ይሰጣል?›› በማለት የተናገረውን አስበው የምኵስናን ሥራ ይሠሩ ዘንድ ገባ የተባለ እሾህ አምጥተው ወንድማቸውን ‹‹እኔ መንኵሴ ልባል የማይገባኝ ኀጢአተኛ ነኝና የኀጢአት ማስተሠረያ ይሆነኝ ዘንድ በዚኽ ግረፈኝ›› አሉት። በእሾሁም በተገረፉ ጊዜ ደማቸው እንደ ውኃ ፈሰሰ። አቡነ ቡሩከ አምላክ የተገረፈባት ሀገር እስከዛሬ ድረስ🌹 ዓዲ-ጋርፋ 🌹እየተባለች ትጠራለች። ትርጕሙም🌻 የመገረፍ ሀገር 🌻ማለት ነው። ምልክቷም ብዙ መነኰሳይያት ይኖሩባታል። ይኽም ገባ በሚባል እሾህ የተገረፈባት ማለት ነው። በሌላም ጊዜ ቆዳው እስኪሰነጣጠቅና ቊስል እስኪሆን ድረስ በሸንበቆ የሚገረፍበት ጊዜ ነበረ፣ ከዚኽም በተጨማሪ መላ አካሉ ቈስሎ ሳለ በላዩ ላይ ግርፋቶችን ይጨምርበታል። በዚኽ ዓለም በመስቀል ላይ እንደተሰቀለ በብረት ችንካሮች እጆቹንና እግሮቹን እንደተቸነከረ የጌታችንን ሕማማቱን እያሰበ ሥጋውን አያሳርፋትም ነበረ። ከታናሽነቱ ጀምሮ የንጉሥ ልጅ ሲሆን ምድራዊ መንግሥትን ትቶ እግዚአብሔርን አገለገለ። ጌታችን በወንጌሉ ‹‹ማንም ቢሆን ስለ ስሜ ብሎ ርስትንና ልጆችን፣ ወንድሞችንና እኅቶችን፣ እናትንና አባትን ያልተወ መንግሥተ ሰማያትን ሊወርስ አይችልም›› ብሎ የተናገረውን አስቦ ከታናሽነቱ ጀምሮ ጌታውን አገለገለ።
✝ ከዕለታትም በአንዲቱ እህልና ውኃ ወደማይገኝበት ምድረ በዳ ሔደ። ዐርባ ቀንና ዐርባ ሌሊት ሥጋውን በረኀብና በውኃ ጥም ቀጣ፤ ከሰንበቶች በስተቀር ምንም አልቀመሰም። እንደ መላእክት ንጹሕ፣ ለጸሎት ትጉ፣ እውነተኛ መነኵሴ፣ ችግርን ወዳጅ፣ መንግሥትን መናኝና መስቀል ተሸካሚ የሆነ አቡነ ቡሩከ አምላክ ከዚኽ ዓለም አንዳች ነገርን የራሱ አላደረግም።
ነሐሴ 13/2015 #ደብረ_ታቦር
#ፆመ_ማርያም
👉አንድ አምላክ በሆነ #በአብ_በወልድ_በመንፈስ_ቅዱስ ስም ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ አመታዊ #የደብረ_ታቦር በአል እንኳን አደረሰን የእናታችንና የእመቤታችን ወላዲተ አምላክ ምልጃና ፀሎት ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን"
👉ይህ በአል ከጌታችን ዘጠኙ በዐላት መካከል አንዱ ነው በአሉ በየአመቱ ነሐሴ 13 ላይ ይከበራል
👉"ቡሔ" ማለት በደብረ ታቦር የተገለጠወ የጌታችን የፊቱ ብርሐን ጰዳል የልብሱን እንደ በረዶ ነጭ መሆን ያስረዳል ስለዚህ የብርሐን ብርሐናዊ ማለት ነው
👉ታሪኩም በሶስቱ ወንጌላት ላይ የተፃፈ ሲሆን ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ስምንቱ ሐዋርያትን ከእግር ደብረ "ከተራራው" ሶስቱን
✔ጴጥሮስ
✔ያዕቆብ
✔ዮሐንስን ይዙአቸው ወደ ደብረ ታቦር ተራራ በመውጣት የሞተውን ሙሴ አስነሰቶ የተሰወረውን ኤሊያስንም ከብሔረ ሕያዋን አምጥቶ የሕያውን አምላክ እና ሙታንን አንሺው እርሱ መሆኑን ብርሀኑ የገለፀበት ማቴ 17:1-9
👉ብዙ ተራራ እያለ ደብረ ታቦር ተራራ የመረጠበት አስቀድሞ የጌትነት ክብሩ በዚያ ተራራ ላይ እንደሚገለፅ በነበዩ ዳዊት
"ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ይደሰታሉ" (መዝ 88:12)
👉በማለት ጌታ በዚያ ተራራ ላይ ብርሀኑን ሲገለፅ የብርሐኑ ነፀብራቅ እስከ አርሞንኤም ተራራ ድረሰ እንደሚታይ የተነገረው ትንቢት ለመፈፀም ነው
👉ለምን ሙሴ እና ኤሊያስን መረጠ ሐዋርያትን ስለማንነቱ እንደጠየቃቸው እንደመለሱለት ሁሉ በእውነት የሙሴ እና የኤሊያስ ጌታ እና አምላካቸው እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን በተራራው ላይ መስክረዋል ማቴ16:13
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከበዐሉ ረድኤትና በረከት ያሣትፈን "አሜን"
👉በዚህ እለት የሊቀ ነብያት #ቅዱስ_ሙሴ የልደቱ መታሠቢያ በአል ነዉ ረድኤት በረከቱ አይለየን "አሜን"
✞✞✞ ✝እንኩዋን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ደብረ ታቦር በሰላም አደረሳችሁ ✝✞✞✞
✞✞✞ ✝ደብረ ታቦር✝ ✞✞✞
=>ደብረ ታቦር በቁሙ እሥራኤል ውስጥ ከሚገኙ ተራሮች አንዱ ነው:: ተራራው ብዙ ታሪካዊ ዳራዎች ቢኖሩትም ክብሩ ከፍ ከፍ ያለው ግን ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን ስለ ገለጸበት ነው:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
+አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋችንን በተዋሐደባት በዚያች በተወደደች ጊዜ: ደቀ መዛሙርቱ ስለ እግዚአብሔር መንግስት ምሥጢርን ይማሩ ነበር:: በጊዜው ግን አበው ሐዋርያት ምሥጢር ባይገባቸው: አንድም ገና መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ አልወረደም ነበርና እምነታቸው ሙሉ አልነበረም::
+ጌታም አምላክነቱን በየጊዜው በቃልም: በተግባርም ይገልጥላቸው ነበር:: በርግጥ ያንን ነደ እሳት: ሰማያት የማይቸሉትን ግሩማዊ አምላክ በትሑት ሰብዕና መመልከቱ ሊከብድ እንደሚችል መገመት አያዳግትም::
+ጌታችን ብዙ ተአምራትን በአምላካዊ ጥበቡ ሠርቷል:: እጅግ ድንቅ ከሆኑት መካከል ደግሞ ቅድሚያውን ደብረ ታቦር ይይዛል:: ጌታ ስለ ምን መለኮታዊ ክብሩን በደብረ ታቦር ገለጸ ቢሉ:-
1.ትንቢቱ ሊፈጸም (መዝ. 88:12)
2.ምሳሌው ሊፈጸም (ባርቅና ዲቦራ በሢሣራ ላይ ድልን ተቀዳጅተዋልና)
3.ሊቀ ነቢያት ሙሴ "ልይህ" ብሎ ከ1,500 ዓመታት በፊት ጠይቆ ነበርና እርሱን ለመፈጸም
4.አንድነቱን: ሦስትነቱን ለመግለጽ
5.ቤተ ክርስቲያንን በምሳሌ ለማሳየት
6.ተራራውን ለመቀደስ
7.የሐዋርያቱን ልብ ለማጽናት . . . ወዘተ ነው::
+ነሐሴ 7 ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ቂሣርያ ፊልዾስ ወስዶ "የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?" ብሎ ጠይቁዋቸው ነበር:: እነርሱም የራሳቸውን ሐሳብ የሌላ እያስመሰሉ "አንዳንዶቹ ኤልያስ: አንዳንዶቹም ሙሴ: ሌሎቹም ከነቢያት አንዱ ነው ይሉሃል" አሉት::
+ኩላሊትን የሚመረምር ፈጣሪ ነውና "እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?" ቢላቸው ደንግጠው ዝም አሉ:: የሃይማኖት አባት: ባለ በጐ ሽምግልና ቅዱስ ዼጥሮስ ግን በመካከላቸው ቆሞ "አንተ ውዕቱ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው - የሕያው እግዚአብሔር አንድያ የባሕርይ ልጁ ክርስቶስ አንተ ነህ" አለው:: በዚያን ጊዜ ቃለ-ብጽዓን እና የመንግስተ ሰማያት መክፈቻ ተሰጠው:: (ማቴ. 16:13)
+መጽሐፍ እንደሚል ደግሞ እንዲህ ከሆነ ከ6ኛው ቀን በሁዋላ ጌታችን 12ቱን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ደብረ ታቦር ወሰዳቸው:: ዘጠኙን በእግረ ደብር (ከተራራው ሥር) ትቶ 3ቱን (ዼጥሮስን: ዮሐንስንና ያዕቆብን) ይዟቸው ወጣ:: እኒሕ ሐዋርያት "አዕማድ: አርዕስት: ሐዋርያተ ምሥጢርም" ይባላሉ::
+በተራራው ላይ ሳሉም ድንገት የጌታችን መልኩ ከፀሐይ 7 እጅ አበራ: ከመብረቅም 7 እጅ አበረቀ:: "ወኮነ ልብሱ ጸዐዳ ከመ በረድ" እንዲል ከታቦር የተነሳው ብርሃነ ገጹ አርሞንኤም ደርሷል:: ያንን ተመልክተው መቆም ያልቻሉት ሐዋርያቱ ፈጥነው መሬት ላይ እንደ ሻሽ ተነጠፉ::
+በዚያች ሰዓት ሙሴ ከመቃብር: ኤልያስም ከብሔረ ሕያዋን መጡ:: አንዳንዶቹ ጌታን 'ነቢይ' (ሎቱ ስብሐት) ብለውታልና ሙሴና ኤልያስ ተናገሩ:- "ስለ ምን አንተን ነቢይ ይሉሃል: እግዚአ ነቢያት - የነቢያት ፈጣሪ ነህ እንጂ" እያሉ ተገዙለት: አመሰገኑት::
+ነገር ግን በቦታው ጸንተው መቆየት አልቻሉም:: መለኮታዊ ብርሃኑ ቢበዘብዛቸው ቅዱስ ሙሴም ወደ መቃብሩ: ቅዱስ ኤልያስም ወደ ማደሪያው በድንጋጤ ሩጠዋል::
+በዚያች ሰዓት ሊቀ ሐዋርያት ጌታን "ሠናይ ለነ ኀልዎ ዝየ: ንግበር ሠለስተ ማሕደረ: አሐደ ለከ: ወአሐደ ለሙሴ: ወአሐደ ለኤልያስ - ጌታ ሆይ! በዚህ መኖር ለኛ መልካም ነው:: በዚህም 3 ዳስ እንሥራ:: አንዱን ላንተ: አንዱንም ለሙሴ: አንዱን ለኤልያስ" ብሎታል::
+ቅዱስ ዼጥሮስ ለራሱ ሳያስብ ለጌታና ለቅዱሳን ነቢያቱ "ቤት እንሥራ" በማለቱ ሲመሰገን ጌታን የመጣበትን የማዳን ሥራ የሚያስተው ጥያቄ በማቅረቡ ከድካም ተቆጥሮበታል:: ለሁሉም ግን ሐሳቡ ድንቅና መንፈሳዊ ነው::
+እርሱ ይሕንን ሲናገር መንፈስ ቅዱስ በደመና አምሳል ወረደና ከበባቸው:: አብ ከሰማይ ሆኖ "ዝንቱ ውዕቱ ወልድየ ዘአፈቅር: ወሎቱ ስምዕዎ - የምወደው: የምወልደው: ሕልው ሆኘ የምመለክበት የባሕርይ ልጄ እርሱ ነውና ስሙት" ሲል ተናገረ::
+ደቀ መዛሙርቱም ከፍርሃት የተነሳ በዚያች ሰዓት እንደ በድን ሁነው ነበርና ጌታችን ቀርቦ ቀሰቀሳቸው:: በተነሱ ጊዜ ግን ሁሉም ነገር ወደ ነበረበት ተመልሶ ነበር:: (ማቴ. ማር. ሉቃ. )
+በደብረ ታቦር የጌታችን ብርሃነ መለኮት ያዩ 3ቱ ሐዋርያት ብቻ አይደሉም:: እመ ብርሃን ካለችበት ሆና ስትመለከት 12ቱ ሐዋርያት ደግሞ በተራራው ሥር ሆነው በተደሞ ተመልክተዋል::
+ይሕንን ድንቅ ብርሃነ መለኮት ያላየ ይሁዳ ብቻ ሲሆን እርሱም ስለ ክፋቱ የኢሳይያስ ትንቢት ተፈጽሞበታል:: ኃጢአተኛው የእግዚአብሔርን ክብር እንደማያይ ተነግሮበታልና:: "ያአትትዎ ለኃጥእ ከመ ኢይርዐይ ስብሐተ እግዚአብሔር" እንዲል:: (ኢሳ.)
ሊቁም የደብረ ታቦርን ምሥጢር ሲያደንቅ እንዲህ ብሏል:-
"ጸርሐ አብ ኪያከ በውዳሴ:
ወበርእስከ ጸለለ መንፈሰ ቅዳሴ:
አመ ገበርከ እግዚኦ በታቦር ምስለ ሐዋርያት ክናሴ:
መንገለ ሀሎ ኤልያስ ወኀበ ሐለወ ሙሴ:
ዘመለኮትከ ወልድ ከሠትከ ሥላሴ::"
=>ለወዳጆቹ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠ ጌታ የእኛንም ዐይነ ልቡናችንን ያብራልን:: ከበዓሉ በረከትም ያሳትፈን::
=>ነሐሴ 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ደብረ ታቦር / ደብረ ምሥጢር / ደብረ በረከት
2.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት (ልደቱ)
3.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
4.ቅዱሳን አበው ሐዋርያት
5.አባ ጋልዮን መስተጋድል
6.አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ (ልደታቸው)
7.ቅድስት ኦፍራ ሰማዕት
=>ወርኀዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
3."99ኙ" ነገደ መላዕክት
4.ቅዱስ አስከናፍር
5."13ቱ" ግኁሳን አባቶች
6.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
7.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ
=>+"+ ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል::
ክንድህ ከኃይልህ ጋር ነው::
እጅህ በረታች: ቀኝህም ከፍ ከፍ አለች:: +"+ (መዝ. 88:12)
=>+"+ ከስድስት ቀንም በሁዋላ ጌታ ኢየሱስ ዼጥሮስን: ያዕቆብንና ወንድሙን ዮሐንስን ይዞ ወደ ረዥም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው:: በፊታቸውም ተለወጠ:: ፊቱም እንደ ፀሐይ አበራ:: ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ:: እነሆም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው:: ዼጥሮስም መልሶ ጌታ ኢየሱስን:- "ጌታ ሆይ! በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው:: ብትወድስ በዚህ ሦስት ዳስ: አንዱን ለአንተ: አንዱንም ለሙሴ: አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ" አለ:: እርሱም ገና ሲናገር እነሆ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው:: እነሆም ከደመናው:- "በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው: እርሱን ስሙት" የሚል ድምጽ መጣ:: ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ:: +"+ (ማቴ. 17:1)
✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞
የአህያ ስጋ ለምግብነት እየሸጠ የተያዘው ጉድ //#donkeytube #viral
https://youtube.com/watch?v=biZL8MOYtIQ&feature=share
"ቤተክርስቲያን ደብረ ብዙኃን
ምነው እንደ ዳዊት ዘመን ዛሬም በሆንሽ በድንኳን
ምቀኛ ሲገፋሽ ጠቅልዬሽ እንዳሸሽ
ምቀኛ ሲተውሽ መልሼ እንድተክልሽ"
ዲ/ን ሄኖክ ሃይሌ
/channel/dnglemaryamenate
የንጉስ ጭካኔ ፥ ክንዱ ቢበረታ፤
ለጣዖት ሳንሰግድ፥ እኛ ሳንረታ፡፡
የምናምነው አምላክ፥ ሊያድነን ወደደ፤
ገብርኤል መጣና፥ እሳቱ በረደ፡፡
፤
ፍላፃና ሠይፉን፥ አጠፋው መላኩ፤
ሰላም ይዞ መጣ፥ ባለም ለታወኩ፡፡
አትጠራጠሩ፥ ምልጃው ያስምረናል፤
የሚነደው እሳት፥ ሳይነካን ወተናል፡፡
፤
የሰልስቱ ደቂቅ፥ የእየሉጣ ብርታት፤
የድንግል አብሳሪ፥ የቂርቆስ ረዳት፡፡
በሚመጣው አለም፥ እንዳይበላኝ እሳት፤
አማልደኝ ከጌታ፥ ነፍሴን እንዲምራት፡፡
፤
የነገርኩህ ሁሉ፥ በቀኑ ደረሰ ፤
በዘብር ገብርኤል፥ እንባዬ ታበሰ፡፡
ና ልጄ ስትለኝ፥ አልልህም እንቢ፤
ስለቴን ተቀበል፥ አባቴ ቁልቢ፡፡
፤
የልቤን ነግሬህ፥ የግቢው ገብርኤል፤
ሳትረሳ ፈፀምከው፥ ስለቴን ተቀበል፡፡
ለንግስ እንመጣለን፥ አንተ አትረሳምና፤
ደሞ የዛሬ አመት፥ አድርሰን በደህና፡፡
/channel/dnglemaryamenate
ነሐሴ 9/2015 #ፆመ_ማርያም
#አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ
👉አንድ አምላክ በሆነ #በአብ_በወልድ_በመንፈስ_ቅዱስ ስም ለፃድቁ አባታችን #አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን የፃድቁ ምልጃና ፀሎት ቃል ኪዳን ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን"
👉ሰዎች በከበረ ሰው ለመክበር ዘር ሲቆጥሩ ይደክማሉ ባዕለ ጸጋው ዘመዴ ነው ሳይል የባለሥልጣን ወገን ነኝ ለማለት ይደክማል የሚደክሙም ይኖራሉ
👉አምላካችን #እግዚአብሔር ግን የእኔ ወገን ወንድሞቼ ናችሁ በማለት ክብርን ሰጥቷል የእመቤታችን #ድንግል_ማርያም ልጆች ለመባል መብቃት ምንኛ ያኮራል
👉መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ አምላክ፣ፈጣሪ፣አዳኝ ሲሆን ወንድማችን መሆኑ፤እናቱ እናታችን መሆኗ፣ክርስቶስ በመስቀል ላይ እያለ ከተረጋገጠልን፣ከዚህ በላይ የሚያኮራ ምን ደስታ አለ
👉የምድሩ እዚሁ የሚቀር ነው፤የማይቀር ልጅነት የማያልፍ ስጦታ፣የጌታ ወንድሞች መባል፣አብሮ መንግስቱን መውረስ ሲሰጥ ምንኛ ደስ ሊለን ይገባል
👉የእናታችን #ማርያም ስም ሲጠራ ሰማይም ምድርም ደስ ይላቸዋል ነቢያት ትመጣለች፣አምላክን ትወልዳለች ብለው ተስፋ ያደርጉ ነበር፤ሐዋርያትም እርሷን ይሰብኳት ነበር አኛም የመስቀል ስር የስጦታ ልጆቿ ምእመናን ደግሞ የምንፅናናባት እርሷ ናት አሜን ታፅናናን
👉እናታችን ማርያም በምልጃ ፀሎትሽ አስቢን የከበረዉ ቃል ኪዳንሽ ሀገራችንን እኛን ልጆችሽን ለዘለዓለም ይጠብቀን "አሜን"