kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ጳጒሜን_4

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጳጒሜን አራት በዚህች ቀን #የአባ_ባሞይን (#አባ_ጴሜን)ና #የ6ቱ_ወንድሞቹ እንዲሁም #የሮሜ_ሊቀ_ጳጳሳት_አባ_ሊባርዮስ የእረፍታቸው መታሰቢያ ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_ባይሞን (#አባ_ጴሜን)

ጳጒሜን አራት በዚህች ቀን ተጋዳይ አባ ባይሞን አረፈ። ይህም ቅዱስ ከምስር ሀገር ነው ስማቸው ዮሐንስ፣ ኢዮብ፣ ዮሴፍ፣ ላስልዮስ፣ ያዕቆብ፣ አብርሃም የሚባል ስድስት ወንድሞች አሉት ሁሉም መነኰሳት ሁነዋል። ከእሳቸውም ዮሐንስ ይልቃል ነገር ግን በእውቀትና በጥበብ ባይሞን ይበልጣል።

ሁሉም ተስማምተው ከዓለም ወጡ ከሰውም ሩቅ በሆነ ቦታ የሚኖሩ ሆኑ የክብር ባለቤት የሆነ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም ቀንበር ተሸክመው ከዘመድም ተለይተው በጠባብ መንገድ ተጓዙ።

እናታቸውም ልታያቸው ወዳ ወደ በዓታቸውም ደርሳ በውጭ ቆመች ወደርሷም መጥተው እንድታያቸው ላከችባቸው እነርሱም ወደርሷ እንዲህ ሲሉ ላኩ በዚህ በኃላፊው ዓለም ልታይን ከወደድሽ በወዲያኛው ልታይን አትችይም እርሷም አስተዋለች አልመለሰችላቸውም መንገዷን ተጓዘች።

ይህም አባት ባይሞን በአስቄጥስ ገዳም ለሽማግሌዎችም ለጐልማሶችም አረጋጊ ወደብ ሆነ። ከጠላት ሰይጣን ፈተና የሃይማኖት ጥርጥር ወይም ደዌ ያገኘው ሁሉ ወደርሱ ይመጣል ወዲያውኑ ያረጋጋዋል ከደዌውም ይፈውሰዋል። ይህም አባት በምንኲስና ሕግ ስለ መጋደል ስለ አምልኮም ብዙ ድርሳናትንና ተግሣጻትን ደረሰ።

በትምህርቱም እንዲህ አለ የተሰነካከለ ወንድምን ብታይ ስለርሱ ተስፋ አትቁረጥ ልቡን አንቃለት እንጂ ከወደቀበትም እንዲነሣ አጽናንተህ ሸክሙን አቃልለት። አፍህ የተናገረውን ይሠራ ዘንድ ልብህን አስተምረው አለ።

አንድ ወንድም እንዲህ አለው ሥራው መልካም የሆነ ወንድም ያየሁ እንደሆነ ደስ ይለኛል ወደቤቴም አስገብቼ ባለኝ ነገር ደስ አሰኘዋለሁ። ግን ሥራው ብልሹ የሆነ ወንድም ያየሁ እንደሆነ አልፈቅደውም ወደ ቤቴም አላስገባውም። አባ ባይሞንም እንዲህ ብሎ መለሰለት ሥራው በጎ ለሆነው እንዳረግኸው ለዚህም ሥራው ብልሹ ለሆነው ዕጥፍ አድርገህ በመሥራት ደስ አሰኘው ለታመመ መድኃኒት ያደርጉለት ዘንድ ይገባልና።

ከዚህም በኋላ ለዚያ ከርሱ ጋር ለሚነጋገር ወንድም እንዲህ ብሎ ነገረው በመነኰሳት ገዳም ስሙ ጢሞቴዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ በኃጢአትም ወድቆ አቤቱ ይቅር በለኝ እያለ የሚጮህና የሚያለቅስ ሆነ። ከሰማይም እንዲህ የሚል ቃል መጣ አንተ ወንድምህን በመከራው ጊዜ ቸለል ያልከው ባትሆን እኔ ባልጣልኩህም ነበር።

ይህ አባት ደግሞ እንዲህ አለ እኛ የወንድማችን በደል ብንሰውር እግዚአብሔርም በደላችንን ይሠውርልናል። ይህም አባት ዕድሜውን በተጋድሎና በትሩፋት ሥራ ከፈጸመ በኋላ ወደ መልካም ዕርግና ደርሶ እግዚአብሔርን አገልግሎ በሰላም አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ሊቀ_ጳጳሳት_አባ_ሊባርዮስ_አረፈ

ዳግመኛም በዚችም ቀን የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሊባርዮስ አረፈ። ይህም አባት አርዮሳዊ በሆነ በሁለተኛው ቈስጠንጢኖስ ዘመን ተሾመ። የቈስጠንጢኖስም ወንድሙ ቊንስጣ በሮሜ ነግሦ ነበር።

ሐዋርያዊ አትናቴዎስንና ጳውሎስን ከመንበረ ሢመታቸው በአሳደዳቸው ጊዜ እነርሱም ወደዚህ አባት ሊባርዮስ መጡ። ይረዳቸውም ዘንድ ለመኑት እርሱም ተቀበላቸው ከደብዳቤ ጋርም ወደ ንጉሥ ቊንስጣ ላካቸው ንጉሡም ደብዳቤያቸውን ተቀብሎ በጎ ነገር እንዲያደርግላቸው ወደ መንበረ ሢመታቸውም እንዲመልሳቸው ወደ ወንድሙ ቈስጠንጢኖስ ደብዳቤ ጻፈላቸው።

እርሱም የወንድሙን ደብዳቤ በአነበበ ጊዜ አትናቴዎስን ወደ መንበረ ሢመቱ እስክንድርያ፣ ጳውሎስንም ወደ መንበረ ሢመቱ ቊስጥንጥንያ መለሳቸው።

ከዚህም በኋላ ቊንስጣ ንጉሥ በዓመፀኞች በተገደለ ጊዜ ቈስጠንጢኖስ ወደዚህ አባት ሊባርዮስ መልእክት ላከ ሐዋርያዊ አትናቴዎስን ያሳድደው ዘንድ የአርዮስንም ወገን እንዲቀበላቸው ብዙ ቃል ኪዳናትንም ገባለት እርሱ ግን አልተቀበለውም በምክሩም ከእርሱ አልተስማማም።

ስለዚህም ይህን አባት ሊባርዮስን ሩቅ አገር አጋዘው። ከዚህም በኋላ ወንዱሙ ቈንስጣን የገደለውን ጭፍራ ልኮ ገደለው። ከዚህም በኋላ ቈስጠንጢኖስ ወደ ሮሜ ከተማ ሔደ ስለዚህ አባት ሊባርዮስም የገዳማትና የአድባራት ሊቃውንት ካህናቱም ሁሉ ወደ መንበረ ሢመቱ ይመልሰው ዘንድ ንጉሡን ለመኑት እርሱም ምልጃቸውን ተቀብሎ ወደ መንበረ ሢመቱ መለሰው።

ይህ አባት ወደ መንበሩ በተመለሰ ጊዜ በቀናች ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ ሁልጊዜ መንጋዎቹን ማስተማር ጀመረ ብዙ ድርሳናትንና ተግሣጻትንም ደረሰ የአርዮስ ወገኖችንም እየተቃረናቸው ኖረ ያወግዛቸውና ያሳድዳቸውም ነበር። ከስደት ከተመለሰ በኋላ በሰባት ዓመት በሰላም አረፈ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጳጉሜን)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ጳጉሜ 3/2015 #ቅዱስ_ሩፋኤል

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱስ #ሩፋኤል ስም ለምናመሰግንበት መልአኩ #ቅዱስ_ሩፋኤል በጥበቃዉ በምልጃዉ እንዳይለየን ለምንማፀንበት አመታዊ የንግስ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉ቅዱስ ሩፋኤል ቊጥሩ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሲኾን፤ ሩፋ ማለት ሐኪም፤ ኤል ማለት እግዚአብሔር ማለት ሲኾን ሩፋኤል ማለት “እግዚአብሔር ሐኪሜ ነው” ማለት ነው፤ ሄኖክም “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” ይለዋል (መጽሐፈ ሄኖክ 6፥3)::

👉ይኽ መልአክ በራማ ሰማይ ያሉ ነገደ መናብርትን የሚመራቸው ነው ነገደ መናብርት ያላቸው ቅዱስ ሩፋኤል የሚመራቸው በራማ ሰማይ የሚኖሩ ነገደ መላእክት ናቸው፡፡

👉ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በሥነ ፍጥረት መጽሐፉ ላይ “ወለዳግም ጾታ ዐሠርቱ ስሞሙ መናብርት ወሊቆሙ ሩፋኤል እሉ እሙንቱ እለ ይቀልል ሩጸቶሙ እምነፋስ ወእለ ይጸውሩ ወላትወ መብረቅ ወኲናተ እሳት ዘይነድድ ወአንበሮሙ በዳግሚት ሰማይ” ይላል በራማ ሰማይ የሚገኘውን ኹለተኛውን ዐሥሩን ነገድ መናብርት ሲላቸው አለቃቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፤ እነዚኽም ረቂቅ የኾነ የመብረቅ ጋሻ የእሳት ጦር ይዘው ከነፋስ ይልቅ የፈጠኑ ሲኾኑ በራማ በኹለተኛው ክፍል ላይ አስፍሯቸዋል፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል ከሚመራው ከዚኽ ነገድ 24ቱ ካህናተ ሰማይ ወጥተዋል፡፡

👉አባ ጊዮርጊስም በሰዓታቱ ላይ ስለነዚኽ መላእክት ፡-

“ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ጽርሐ አርያም ማኅፈዱ
መካነ ትጉሃን ዐጸዱ ካህናተ ሰማይ ቅዉማን በዐውዱ አክሊላቲሆሙ ያወርዱ ቅድመ መንበሩ እንዘ ይሰግዱ ይርዕዱ ወኢይዝብጦሙ ሶበ ይበርቅ ነዱ”

👉ጽርሐ አርያም አዳራሹ፤ የትጉሃን መኖሪያ ቦታው የሚኾን እግዚአብሔር ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ተብሎ በአንድነት በሦስትነት ይመሰገናል፤ ካህናተ ሰማይ በዙሪያው ይቆማሉ፤ በዙፋኑ ፊት እየሰገዱ አክሊሎቻቸውን ያወርዳሉ፤ እሳትነቱ ባሕርዩ በሚበርቅ፣ ወገግ በሚል ጊዜ እንዳይመታቸው ይንቀጠቀጣሉ ይላል

👉ሊቁ እንደጠቀሰው በዕለተ እሑድ ሥሉስ ቅዱስ ሰባቱን ሰማያት ፈጥረዋል፤ ከዚያም ልዑል እግዚአብሔር በዕለተ እሑድ ሰባቱን ሰማያት ከፈጠረ በኋላ ሊቁ በአክሲማሮስ እንደገለጸው ከቅዱሳን መላእክት መኻከል፡-

“ወእምዝ ነሥአ እግዚአብሔር እምሰራዊተ ሩፋኤል ፳ወ፬ተ ሊቃናተ ወአቀሞሙ ዐውደ መንበሩ፤ ወሰመዮሙ ለእሙንቱ ካህናተ ሰማይ ወወሀቦሙ ማዕጠንታተ ዘእምወርቀ እሳት ወአክሊላተ ብርሃን ዘእምጳዝዮን ወአብትረ ዘከተማሆን መስቀል ወአልበሶሙ አልባሰ ክህነት” እንዲል ከሰራዊተ ሩፋኤል ፳፬ት ሊቃናትን መርጦ በመንበረ ስብሐት በመጋረጃዋ ውስጥ ዙሪያዋን ክንፍ ለክንፍ ገጥሞ አቁሟቸዋል (ሕዝ ፩፥፲፩-፲፪)።

👉ቊጥራቸውን ኻያ አራት ማድረጉ በኻያ አራቱ ጊዜያት ጸልየው ሌላውንም ራሳቸውንም ጠብቀው ዋጋቸውን ተቀብለው የሚኖሩ በመኾናቸው ሲኾን እነዚኽንም መላእክት “ካህናተ ሰማይ” ሲላቸው የእሳት የወርቅ ጽና ሲያሲዛቸው የብርሃን አክሊል ጳዝዮን የሚባል የብርሃን ዘውድ ደፍቶላቸዋል፤ የብርሃን ዘንግ ማኅተሙ መስቀል የኾነ ሲያሲዛቸው የብርሃን ካባ ላንቃ ሕብሩ መብረቅ የመሰለ አልብሷቸዋል ( ራእ ፬፥፬-፭፤፲-፲፩)።

👉እነዚኽ ከሰራዊተ ሩፋኤል የወጡ ሰማያውያን ካህናት በአንድ ላይ ባጠኑ ጊዜ ዛሬ በክረምት ጊዜ ጉም ተራራውን እንደሚሸፍነው ከማዕጠንታቸው የሚወጣው ጢስ መልኩ መብረቅ፣ ድምፁ ነጐድጓድ፣ መዐዛው መልካም የኾነና ጽርሐ አርያም፣ መንበረ መንግሥት የተባሉትን የብርሃን ሰማያት የሚሸፍንና የሚጋርድና ከጢሱ ጋር የቅዱሳን ጸሎት ዐብሮ ወደ እግዚአብሔር ፊት ይወጣል።

👉ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሠዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሠዊያ ላይ ለቅዱሳን ኹሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ እንዳለ ዮሐንስ በራእዩ (ራእ ፰፥፫-፭)፡፡

👉ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በአክሲማሮስ ላይ “ወቦ ኪሩቤል ይቀውሙ በየማን በአምሳለ ቀሳውስት ወሱራፌል ይቀውሙ በአምሳለ ዲያቆናት ወድኅሬሆሙ ካህናተ ሰማይ ወቦ እልፍ አእላፋት ወትእልፊተ አእላፋት መብረቅ ወነጐድጓድ ወሠረገላሆሙኒ ምሉኣነ አዕይንት” እንዳለ

👉ኪሩቤል በቀኝ ሱራፌል በግራ ከፍ ብለው የሩፋኤል ሰራዊት ካህናተ ሰማይ ክንፍ ለክንፍ ገጥመው በስተኋላቸው ሲታዩ በሰማይ ውዱድ ዙሪያ እልፍ አእላፋት መብረቅ፣ ነጐድጓድ፣ ሠረገላ፣ እንደ መስታየት ብሩህ የኾነ ሲኖርበት እነዚኽ ቅዱሳን መላእክትም ሳያቋርጡ “ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ እግዚአብሔር” እያሉ ፈጣሪያቸውን በአንድነቱ በሦስትነቱ ያመሰግኑታል (ራእ ፬፥፰)

👉በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሠ

👉#የእግዚአብሔር አምላክ ቸርነት የመልአኩ #ቅዱስ_ሩፋኤል ጥበቃና ተራዳኢነት አይለየን "አሜን"

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ለ 6ቀን መጾም ጸሎት የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው 🙏⛪️⛪️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ጳጒሜን_1

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጳጉሜን አንድ በዚህች ቀን እና #ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ የታሰረበት፣ #የዑቲኮስ_ሐዋርያና #ቀሲስ_አባ_ብሶይ የእረፍታቸው መታሰቢያ ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ

ጳጒሜን አንድ ቀን በዚህች ዕለት ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ወደ እሥር ቤት ገብቷል። ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ፦ ንጉሡ ሔሮድስ የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሔሮድያዳን በማግባቱና በመሰል ክፋቶቹ ቅዱስ ዮሐንስ ይገስጸው ነበር። ቅዱስ ዮሐንስ "መምሕር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ" "ፊት አይቶ የማያዳላ" ነውና ገሰጸው።

ሔሮድስ ቅዱሱን ይፈራው ያከብረውም ነበር። በኋላ ግን ፈቃደ ሥጋው ስላየለበት በተለይ ደግሞ ከሰባት ቀናት በኋላ ልደቱን ሲያከብር እንዳይረብሸው በመስጋት በዚህች ቀን በወታደሮቹ አስይዞ እሥር ቤት ውስጥ
ጥሎታል። ለሰባት ቀናት በጨለማ ውስጥ አሥሮ መስከረም 2 ቀን አስቆርጦታል።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዑቲኮስ_ሐዋርያ

በዚህች ቀን የወንጌላዊ ዮሐንስ ረድእ ሐዋርያና ሰማዕት የከበረ ዑቲኮስ አረፈ ።

ይህም ቅዱስ ወንጌላዊ ዮሐንስን ሲያገለግለውና ሲታዘዘው ኖረ። ከዚያም ከሐዋርያ ጳውሎስ ጋራ ሔደ እርሱም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰም እንዲሰብክ አዘዘው በአረማውያንና በዮናናውያንም መካከል ሰበከ። የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም ወደማወቅ ብዙዎችን መለሳቸው የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው።

የጣዖታት ቤቶችን አፍርሶ አብያተ ክርስቲያናትን ሠራ። ከከሀድያንም ብዙ መከራ ደረሰበት መታሠርና ብዙ ቀኖች ግርፋቶችን በመቀበል፤ የእግዚአብሔርም መልአክ ወደ እሥር ቤት ከምግብ ጋር መጥቶ ይመግበዋል።

ከዚህም በኋላ ከእሳት ውስጥ ጣሉት እሳቱም ከቶ አልነካውም ሁለተኛም ለአንበሶች ጣሉት እነርሱም እንደ በጎች ሆኑለት። ከዚህም በኋላ ወደቍስጥንጥንያ ሀገር ሔደ። ሲሔድም የእግዚአብሔር መልአክ ይመራውና ያጸናናው ነበር ተጋድሎውንም ፈጽሞ በበጎ ሽምግልና ወደ እግዚአብሔር ሔደ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቀሲስ_ብሶይ_ሰማዕት

በዚችም ቀን የአባ ሖር ወንድም ቀሲስ ብሶይ በሰማዕትነት ሞተ። ይህም ቅዱስ ከአንፆኪያ አገር ክብር ካላቸው ወገኖች ውስጥ ነው ስለ ዕውቀቱና ስለ ሃይማኖቱ ጽናት ቅስና ተሾመ።

ወንድሙ አባ ሖርና እናቱ ወደ ግብጽ አገር ሔደው በሰማዕትነት ከሞቱ በኋላ እርሱም ተነሥቶ ወደ እስክንድርያ ሥጋቸውን ያይ ዘንድ ሔደ። ገንዘቡን ሁሉ ለድኆች ሰጠ ከሦስት እንጀራና ከሚመረጐዛት ከአንዲት የሰኔል በትር በቀር ምንም አልያዘም ነበር።

ወደ እስክንድርያ አገርም በደረሰ ጊዜ የዘመዶቹ በድን ወዳለበት ሰዎች መርተው አደረሱት የእናቱንና የወንድሙንም ሥጋ በአየ ጊዜ ከእርሳቸው ስለ መለየቱ መሪር ልቅሶን አለቀሰ። ከዚህም በኋላ ወደ መኰንኑ ሒዶ በፊቱ ቁሞ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ።

ለመኰንኑም የአባ ሖር ወንድም እንደሆነ ነገሩት መኰንኑም ታላቅ የደንጊያ ምሰሶ በሆዱ ላይ እንዲአቆሙበት አዘዘ ይህንንም በአደረጉበት ጊዜ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ሰጠ።

ከዚህም በኋላ ደግሞ ሥጋውን ከወንድሙና ከእናቱ ሥጋ ደግሞ ቍጥራቸው ሰማንያ ስምንት ከሆነ ከሌሎች ሰማዕታት ሥጋ ጋር በአንድነት ያቃጥሉ ዘንድ መኰንኑ አዘዘ ወደ እሳት በጨመሩአቸውም ጊዜ ከቶ እሳቱ አልነካቸውም።

ምዕመናን ሰዎችም መጥተው የከበሩ የአባ ሖርንና የወንድሙ የአባ ብሶይን የእናታቸውንም ሥጋ ወሰዱ። ሀገሯ ዲብቅያ የሚባል የቅድስት ዳሞንንም ሥጋ፣ ሀገሩ በረሞን የሚባል የቅዱስ ቢማኮስንም ሥጋ፣ ጡልያ ከሚባል አገር የመጣ የውርሱኑፋን ሥጋም፣ አብስላሲ ወደሚባል አገር እስከሚያደርሷቸው በመርከብ ጫኗቸው። የስደቱ ወራት እስከሚፈጸም አክብረው ወስደው በመልካም ቦታ አኖሩዋቸው።

ከዚህም በኋላ አብያተ ክርስቲያን ተሠርቶላቸው ሥጋቸውን በውስጣቸው አኖሩ ከእርሳቸውም ተአምራት ተገለጡ ለሕሙማንም ፈውስ ሆኑ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእኒህ ቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጳጉሜንና #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ወርኀ_ጳጉሜ "ጳጉሜን"

#ጳጉሜ_ማለት ጭማሪ ማለት ነው፡፡ ይህም በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን የምትመጣ ናት፡፡ በአራት ዓመት አንዴ ማለትም በዘመነ ዮሐንስ ጳጉሜ ስድስት ቀን ይሆናል፡፡ በዚህም ሐገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ በመባል ትታወቃች ፡፡ ጳጉሜ በዘመነ ዮሐንስ ስድስት በምትሆንበት ጊዜ ጾመ ነቢያት / የገና ጾም/ ህዳር 14 ቀን ይገባና ታህሳስ 28 ቀን ጾሙ ተፈቶ የልደት በዓል ይከበራል፡፡ በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜ ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው፡፡

ይህም ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ግን እንደ አንደኛው የፈቃድ ጾም /ጽጌ ጾም/ በብዙዋኑ ዘንድ የታወቀ አይደለም፡፡ የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡ እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋርስ ንጉስ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ ድንበር አስፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ዮዲት 2፥2-7፡፡ እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመኑ 12ሺህ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡ 12ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሔድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ በዚህም ብዙ ጥፋ በመድረሱ የእስራኤል ልጆች አለቀሱ፡፡ ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ ርቃ ንጽሕናዋን ጠብቃ በጾም በቀኖና በሀዘን ተወስና ትኖራለች በተፈጠረው ጥፋት ህዝቡ ላይ ለመጣው መከራ ማቅ ለብሳ በራስዋ ላይ ትብያ ነስንሳ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች፡፡ የፍጥረቱን ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር አምላክም ሕዝቡን የሚያድኑበትን መንገድ ለመጠየቅ ሱባኤ በገባች በሦስተኛው ቀን ገለፀላት፡፡ ዮዲት8፥2 ፡፡ ከዚህ በኋላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል፡፡ ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾምና በጸሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ኃይል አግኝታ ነው፡፡ ስለዚህ ምዕመናን ጥንተ ጠላታችን ሰይጣንን ፈቃደ ሥጋን ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መጎናጸፍ አለብን ብለው ጳጉሜን በፈቃድ ይጾማሉ፡፡

_ብዙዎቻችን የጳጉሜ ወር ዝም ብለን እንደዋዛ ፣ ጎደሎዋ ወር፣
አሮጌዋ ወር ፣ ሌላም ሥም እየሰጠናት እናሳልፋታለን። ግን አይደለም
ክርስቲያን_ሆይ የዘመናት ባለቤት እግዚአብሔር ቀናቶቹን ሁሉ
ውብ አድርጎ ሰጦናል የንስሐ ጊዜ ናት እንጂ ትርፍ ጊዜ አይደለችም ።

_ የጳጉሜ ወር መብላቸው ፣ መጠጣቸውንና መኝታቸውን
ስለ እግዚአብሔር "ክብር ሲሆንእንደሚገባቸው ተረድተው ህይወታቸውን ሙሉ ሲያለቅሱ፣ ሲፀልዩ የነበሩ ቅዱሳን አባቶቻችን
እነ ቅዱስ ዮሐንስን "የምንዘክርበት ሳምንት ነው።
የጳጉሜ ወር ለንስሀ የተጨመረችልን ዕድሜ ትመስላለች
ተረፍ አመት ናትና።
እግዚአብሔር የፈቀደላቸው የተዋህዶ ቤተሠቦች ፀበል በመጠመቅ
እንዲሁንም "ፆምና ፀሎት ሱባኤም በመያዝ በቅድስት ቤተክርስቲያን
አካባቢ ይሠነብታሉ ለፍርድ ለምትመጣበት ለዚያች አስፈሪ ቀን
በክብር "ለመቆም አብቃን እያሉ ይማፀናሉም። የጳጉሜ"ወር የጌታ
ምፅአትናት ተብሎ ይጠበቃልና።
ጳጉሜን በገባ በሦስተኛው ቀን (ጳጉሜ 3) "የማቴዎስ ወንጌል
ምራ.24" ሙሉውን ይነበባል የነገር ምፅአት ታሪክን የሚያስረዳ
ነውና ይሠበካል።
ምፅአት ማለት የጌታን መምጣት የሚያረዳ
በመሆኑ ቤተክርስቲያን የጌታን ምፅአት በአመት ሁለት ጊዜ
ታስታውሳለች ይህውም በጳጉሜ ወርና በጌታ ፆሙ እኩሌታ
(ለደብረ ዘይት)ነው።
መዝሙረ ዳዊት49፣2-4 ስለነገር ምፅአት ይነገራል።

አንድም የጳጉሜ ወር በእለተ ምፅአት የሚመሰልበት ምክኒያት ጳጉሜ የዓመታት መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት ወቅት ወደ ማብቂያው የምናልፍባት እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነውና ነው፡፡ ክርስቲያኖች ሁሉ በየዓመቱ በጳጉሜ ወር ሁሉም ተሰብስበው ከሌሊት ጀምረው በቤተክርስቲያን ተገኝተው ጸበል ይጠመቃሉ፡፡ ይህንን የምናደገውም እግዚአብሔር የተባረከ ዓመት እንዲሰጠን፣ ባሳለፍነው ዓመት የሰራነውን ኃጢአት ይቅር እንዲለን ነው፡፡ የምንጠመቀውም ንስሐ ገብተን ነው፡፡ በእግዚአብሔር ስም የተቀደሰው ጸበል ደግሞ ከበሽታችን ያድነናል፣ የተቀደስንም ያደርገናል፣ መጪውንም ህይወታችን የተባረከ ያደርግልናል፡፡
የጌታ አመጣጥ እንደ ሌባ ነውና በተሠጠን ፀጋ ቅዱስ አምላካችንን እያመሰገን ተዘጋጅተን እንድንጠብቀው የእመቤታችን ምልጃ ይርዳን ቀጣዩ ዘመን ቃሉን ፈጽመን ፍሬ የምናፈራበት ይሁንልን።

መልካም የአዲስ ዓመት ዋዜማ (ጳጉሜን) ይሁንላችሁ፡፡

ምንጭ፦ የ ደ/ብ/ሥላሴ ሰንበት ት/ቤት ጎንደር

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

።።።።። † ልደቱ ለአቡነ ዘርዓ ብሩክ † ።።።።።።

ቀደም ግዮን ሲባል የሚጠራውን ወንዝ ፤ ግሺ አባይ በማለት ለሰዮሙት ለታለቁ አባት አቡነ ዘርዓ ብሩክ የልደት በዓል አደረሳቹ፡፡

የጻድቁ አባታችን #የአቡነ_ዘርዓ_ብሩክ አባት እና እናት የተባረኩ ከቅዱሳን ወገን የሚሆኑ ነበሩ። የአባታቸው ስምም ቅዱስ ደመ ክርስቶስ ሲባል እናታቸው ደግሞ ቅድስት ማርያም ሞገሳ ትባላለች። ጻድቁ አባታችን ገና በእናታቸው ማህጸን እያሉ ነበር ብዙ ተአምራት የሚያደርጉት እግዚአብሔር መርጧቸዋልና።
በኋላም ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ8ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ ላይ በነሐሴ 27 ጻድቁ አባታችን ተወለዱ። በ40ኛ ቀናቸውም ተጠምቀው በካህናት አፍ "ጸጋ ክርስቶስ" ተባሉ ከዛም ቤተሰቦቻቸው በጥሩ እድገት አሳደጉአቸው። 7 አመትም በሞላቸው ግዜ "በልጅነቴ የዚን ዓለም ክፋቱን እንዳላይ" ብለው ቢጸልዩ ዓይናቸው ታውሯል።

ቤተሰቦቻቸውም ጠቢቡ ሰሎሞን "የእግዚአብሔር ቃል ነውርን ይሸፍናል" እዳለው ትምህርት ሊያስተምሩአቸው አስተማሪ ጋር ቢወስዱአቸው ታመው ተመልሰዋል የእግዚአብሔር ፈቃድ አይደለምና። ነገር ግን የሚያስፈልጋቸውን እውቀት ፈጣሪ አምላክ ራሱ ገልጾላቸዋል:: ክህነትን እስከ ጵጵስና እራሱ መድሃኔ ዓለም ክርስቶስ ሰጥቷቸዋል። 12 አመትም በሞላቸው ግዜ በእግዚአብሔር ፈቃድ አይናቸው በርቶላቸው ታላላቅ ተጋድሎን ማድረግ ጀመሩ።

በእግዚአብሔር ዘንድ ጵጵስና እንደተሾሙ የኃጥያት ማሰርያን ያስሩና ይፈቱ ዘንድ ጵጵስናን በሾማቸው ግዜ እግዚአብሔር ያወጣላቸው ሁለተኛ ስም "ዘርዓ ብሩክ" ይባል ነበር። 3ኛውም ስማቸው ደግሞ "ጸጋ እየሱስ" ይባላል:: ጻድቁ አባታችን በዚህ አለም በህይወተ ሥጋ ሳሉ አቡቀለምሲስ እንደሚባል እንደ ሐዋርያው ዮሃንስ .. እግዚአብሔር እሱ ወዳለበት ወደ ሰማይ አውጥቶ በገነት መካከል ያኖራቸው ነበር:: እግዚአብሔር አምላክ ለወዳጁ ለብጹዕ አባታችን ዘርዓ ብሩክ በጎ ነገር እንዳደረገለትና ያለ ድምጽ የሰማይ ደጆችን አልፎ የእሳት ባህርን ተሻግሮ ፈራሽ በስባሽ ሲሆን እንደ ህያዋን መላእክት በፍጥነት ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ከአድማስ እስከ አድማስ ይደርስ ዘንድ 12 ክንፍን ሰጣቸው። መላእክትም ለሌሎች ቅዱሳን ያልተሰጠ ይህንን ስልጣን አይተው ለምድራዊ ሰው ይህ ነገር እንዴት ይቻላል? እያሉ አደነቁ።ከዛም በኋላ ጻድቁ አባታችን ከፈጣሪ ዘንድ የመላእክትን አስኬማ፣ የሾህ አክሊል አምሳያ የሆነውን መንፈሳዊ ቆብን,ሰማያዊ ቅናትን እና የደረት ልብስን(ስጋ ማርያም) ተቀብሎ በጾም እና በጸሎት በልመና እና በስግደት እግዚአብሄርን ሲያገለግል ኖረ። ከዛም በላይ ወንጌልን እጅግ ብዙ በማስተማር ደከመ።

ከኢትዮጵያም አልፎ ግብጽ ድረስ ገባ የእስክንድርያውን ሊቀ ጳጳስ አባ ዮሐንስን አገኘውና እርስ በርስ ሰላምታን ተለዋውጠው እጅ ተነሳሱ ከዛም ተመልሶ ወደ ሃገሩ መጣ ከዛም ኢትዮጵያ ውስጥ እየተመላለሰ ወንጌልን አስተማረ እጅግ ስጋን በሚያስጨንቅ ትጋትም #የኢትዮጵያን ህዝብ ማርልኝ እያለ እያለቀሰ ይጸልይ ነበር።
#አቡነ_ዘርዓ_ብሩክ "#ዓባይ" እና "ግሽ ዓባይ" የሚሉ ስሞች እንዳወጡ አንድ ቀን አባታችንን የንጉስ ጭፍሮች ሲያሳድዷቸው ግዮን ደረሱ። እንደደረሱባቸው ሲያውቁ ዳዊታቸውንና ለወንጌል ስብከት ሲጠቀሙባቸው የነበሩ 7 መጻሕፍት ሁሉ #ለግዮን ወንዝ አደራ ሰጡዋት። ከ5 አመት በኋላ ሲመለሱ" #ኦ_ግዮን_ግሥኢ መፃሕፍትየ -- #ግዮን_ሆይ_መጻሕፍቴን_ግሺ_መልሺልኝ " (#ግሽ_ዓባይ የተባለውም ከዚሁ በመነሳት ነው ።) _ቢሉአት አንድም የውሃ ጠብታ ሳይኖርባት ዳዊታቸውን ብትመልስላቸው ለደቀ መዝሙራቸው #ዘሩፋኤል አሳዩት ሁለቱም የእግዚአብሔርን ሥራ አደነቁ። ከዛም በኋላ ግዮንን #ባረክዋትና "ይኩን ፈውስ ዓብይ በውስቴትኪ .. .በውስጥሽ ታላቅ ድኅነት ይደረግብሽ" አሉ። ከዛ ጊዜ ጀምሮ መካኖች ይወልዱ፣ ድዉዮች ይድኑ ጀመር "ወእም አሜሃ ተሰምየት ዓባይ ይእቲ ፈለግ ::ከዛ ጊዜ ጀምሮ ይህች ዓባይ ተብላ ተጠራች።" እስካሁንም በዚሁ ስም የሚጠራው ከዚ በመነሳት ነው:: ከዚህም ሌላ ጻድቁ አባታችን በዚሁ ወንዝ አካባቢ ለ 30 አመት ሲጸልዩ ፈጣሪ አምላክ ጸሎታቸውን ሰምቶ እጅግ ልዩ የሆነ ቃል ኪዳን ሰቶአቸዋል።

በስተመጨረሻም የሚያርፉበት እለት በደረሰ ሰአት መልአከ ሞት መቶ እስኪደነግጥ እና ወደ ኋላው እስኪያፈገፍግ ድረስ ነው እግዚአብሔር ጸጋውንና ክብሩን ያበዛላቸው: በስተመጨረሻም ጥር በገባ በ13ኛው ቀን በ482 አመታቸው ስጋቸው ከነፍሳቸው ተለይታ ገነትን ወርሰዋል:: በረከታቸው ይደርብን ፣ ምልጃቸው አይለየን ፡፡

።።። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ።።።።።

። ። ። ቅዱስ ሥዕል በሠዓሊ ዘሪሁን ገብረወልድ ። ።

ጽሑፍ ከ

ርእሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ገፅ የተወሰደ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ እንድርያስ እና ለቅዱስ ሚልክያስ ነቢይ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† መሐሪ እግዚአብሔር ኃጢአታችሁ በዛ: ሰውነታችሁ ከፋ ሳይል በአባታዊ ርሕራሔው ጠብቆ ይሔው ወርኀ ነሐሴን በሰላም አስፈጸመን:: አይመስለንም እንጂ በእነዚህ ሰላሳ ቀናት ሚሊየኖች አንቀላፍተዋል: ሚሊየኖች በደዌ ዳኝነት ተይዘዋል: በርካቶቹም ከሃይማኖታቸው ወጥተዋል::

እኛ ይህ ሁሉ ያልደረሰብን በጐ ስለሆንን አይደለም:: ይልቁኑ ቸርነቱ በእኛ ላይ ስለበዛ ብቻ ነው እንጂ:: አሁንም በሰላም ከአዲሱ ዘመን እንዲያደርሰን ልንማጸነው ይገባል::
በዚህች ዕለት ደግሞ እነዚህን ቅዱሳን እናከብራለን::

††† ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ †††

††† ቅዱሱ ሐዋርያ ተወልዶ ያደገው በቤተ ሳይዳ አካባቢ ሲሆን የሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ትንሽ ወንድም ነው:: አባቱም ዮና ይባላል:: ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ዓሣ ማጥመድን ከትልቅ ወንድሙ ተምሯል:: እድሜው ከፍ ባለ ጊዜ ኦሪትን ተምሮ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሆኗል::

ከእርሱም እያገለገለ ለስድስት ወራት ተምሯል:: በወቅቱ ከወንጌላዊው (ወልደ ዘብዴዎስ) ዮሐንስ ጋር ቅርብ ባልንጀራም ነበር:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተጠመቀ ጊዜ ያን ድንቅ ምሥጢረ ሥላሴ ከተመለከቱትም አንዱ ነው::

ጌታ ከጾም (ከገዳመ ቆረንቶስ) በተመለሰ ጊዜ እንድርያስ መንፈስ ቅዱስ አነሳስቶት ተከትሎታል:: መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ "ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ዘያዐትት ኃጢአተ ዓለም - የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ እነሆ::" ማለቱን ሰምቶ ቅዱስ እንድርያስ ጌታን ተከተለ::

በዚህም የመጀመሪያው የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ለመባል በቃ:: (ዮሐ. 1:47) ሊቁ ማር ገላውዴዎስም እመቤታችንን ሲያመሰግናት
"ለሐዋርያ እንድርያስ ቀዳማዊ ማርያም ሃይማኖቱ ( ለመጀመሪያው ሐዋርያ ለእንድርያስ ሃይማኖቱ ማርያም አንቺ ነሽ::)" ብሏል::
(መልክዐ ስዕል)

ቅዱሱ ሐዋርያ ስሉጥ (ፈጣን) አገልጋይ እንደ ነበርም ወንጌል ይነግረናል:: (ዮሐ. 6:9, 12:22) ለሦስት ዓመታት ከሦስት ወር ከጌታ እግር ሥር ተምሮ: በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀበሎ: ምን ሃገረ ስብከቱ ልዳ ብትሆን ብዙ አሕጉረ ዓለምን ሰብኳል::

ይህች ቀን ሐዋርያው ከጌታ ጋር በመርከብ ውስጥ የተነጋገረባትና ቅዱስ ማትያስን ሰውን ከሚበሉ ሰዎች እጅ ያዳነባት ናት::
ቅዱስ እንድርያስ ሰላሳ ቀናት የሚፈጅ የባሕር ላይ ጉዞ ለማድረግ ከአርድእቱ ጋር ወደ ወደብ ቢሔድም መርከበኞች ሁሉ አናሳፍርም በማለታቸው የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወጣት መርከበኛ መስሎ ሐዋርያውንና አርድእቱን የሰላሳውን ቀን መንገድ በሰዓታት ልዩነት እንዲጨርሱ አድርጓል::

ቅዱስ እንድርያስም ፍጡር (እንዲሁ ሰው) መስሎት ለጌታችን ስለ ጌታችን ሰብኮለታል: መርቆታልም:: መርከበኛው ጌታችን መሆኑን ሲያውቅም ደንግጦ አልቅሷል::

"ሶበ አእመረ ኪያሁ ወጠየቀ አምሳሎ:
ዘተናገርኩ በድፍረት ምስሌከ ኩሎ:
ሥረይ ሊተ ጌጋይየ ወኅድግ ይቤሎ::" እንዲል "ማረኝ?" ብሎታል:: ጌታችንም "አይዞህ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ::" ብሎታል:: ቅዱሱ ሐዋርያ ለወንጌል አገልግሎት ተግቶ ያረፈው ታኅሣሥ 4 ቀን ነው::

††† ቅዱስ ሚልክያስ ነቢይ †††

††† ሚልክያስ ከአሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ሲሆን "የመጨረሻው ነቢይ" እየተባለ ይጠራል:: ለዚህ ምክንያቶቹ ሁለት ናቸው::
1ኛ. ከእርሱ በኋላ የተጻፈ ጥሬ የትንቢት መጽሐፍ የለም::
2ኛ.እርሱ ካረፈ በኋላ ያለው ዘመን "ዘመነ ካህናት" በመሆኑ ምንም ነቢያት በየጊዜው ባይጠፉ ጐልተው የተነገረላቸው ጥቂቶቹ ናቸው::

ቅዱሱ የተወለደው ቅ/ል/ክርስቶስ ስድስት መቶ ዓመት አካባቢ ሲሆን ከሚጠት (ከባቢሎን ምርኮ መልስ) ሕዝቡን ገስጿል:: ሕዝቡ ከሰባ ዓመት መከራ እንኳን ተመልሶ ኃጢአትን መሥራትን ቸል አላለም ነበር::

በተለይ የልጅነት ሚስታቸውን የሚያታልሉትን ገስጿል:: (ሚል. 2:14) ስለ አሥራትና በኩራትም ተናግሯል:: (ሚል. 3:8) እመቤታችን ድንግል ማርያምንም በንጽሕት አዳራሽ መስሎ ተናግሯል::
"ጽርሕ ንጽሕት ዘሚልክያስ" እንዳሉ አባ ሕርያቆስ::
(ቅዳሴ ማርያም)

ነቢዩ ቅዱስ ሚልክያስ ፈጣሪውን አገልግሎ: ሕዝቡን መክሮ ዐርፏል:: ሚልክያስ ማለት "መልአክ: አንድም የተላከ" ማለት ነው:: ነገዱ ከነገደ ይሳኮር ነው::

††† አምላከ ቅዱሳን አሥራ ሁለቱን ወራት እንደ ባረከልን አሥራ ሦስተኛዋንም ለንስሐ ቀድሶ ይስጠን:: ከቅዱሳኑም በረከትን ያካፍለን::

††† ነሐሴ 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ ሚልክያስ ነቢይ
3.አባ ሙሴ ዘሃገረ ፈርማ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ (ሐዋርያ)
2.አባ ሣሉሲ ክቡር
3.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
4.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
5.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት

††† "ስለዚህ መንፈሳችሁን ጠብቁ:: ማንም የልጅነት ሚስቱን አያታልል:: 'መፋታትን እጠላለሁ' ይላል የእሥራኤል አምላክ: የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር::" †††
(ሚል. ፪፥፲፭)

††† "ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃቹሃል:: እናንተም 'የሰረቅንህ በምንድን ነው?' ብላቹሃል:: በአሥራትና በበኩራት ነው:: እናንተ: ይህ ሕዝብ ሁሉ እኔን ሰርቃቹሃልና በእርግማን ርጉሞች ናችሁ::" †††
(ሚል. ፫፥፰)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ከኃጢአት መታጠቢያ ወቅት ነው
ዓመታትን የሚያፈራርቅ እየጠበቀን ነው https://youtu.be/eoPLg5CwwAs?si=cakNJarfvUv2Aw8y

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/CKxl6Gr22kc?si=3mv5IRLKGWrB6lhI

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝✞✝ በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን:: ✝✞✝

""" ነሐሴ 27ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት """

+" 12ቱ አበው ደቂቀ እሥራኤል "+

=>እነዚህ አበው የአብርሃምና የይስሐቅ የልጅ ልጆች የያዕቆብ ደግሞ ልጆች ናቸው:: ትውልድ ከአዳም እስከ ቅዱስ ያዕቆብ አንድ ሐረግ ይዞ መጥቶ እዚህ ላይ ሲደርስ ይበተናል:: አባታችን ያዕቆብን እግዚአብሔር ሲባርከው እሥራኤል አለው:: ትርጉሙም "ሕዝበ እግዚአብሔር: ወልድ ዘበኩር (የበኩር ልጅ): ከሃሊ: ነጻሪ (አስተዋይ) እንደ ማለት ነው::

+ይህ ቅዱስ አባት ለድንግል ማርያም ቅድመ አያት ከመሆኑ ባሻገር ነቢያትን: ካህናትን: ነገሥታትንና መሣፍንትን ወልዷል:: ከወንድሙ ኤሳው ጋር ተጣልቶ ወደ ሶርያ በሔደ ጊዜ ከ2ቱ ሚስቶቹ (ልያና ራሔል) 8 ልጆችን: ከ2ቱ የሚስቶቹ ደንገ ጥሮች (ዘለፋና ባላ) 4 ልጆችን: በድምሩ 12 ልጆችን ወልዷል::

#‎ልያ የወለደቻቸው:-
1.ሮቤል
2.ስምዖን
3.ሌዊ
4.ይሁዳ
5.ይሳኮር እና
6.ዛብሎን ይባላሉ::

#‎ራሔል የወለደቻቸው:-
7.ዮሴፍና
8.ብንያም ይባላሉ::

#‎ባላ :- 9.ዳን እና
10.ንፍታሌምን ስትወልድ

#‎ዘለፋ :- ደግሞ 11.ጋድና 12.አሴርን ወልዳለች::

#‎12ቱ ደቂቀ እሥራኤል (ያዕቆብ) ማለት እኒህ ናቸው::

+ከ12ቱ በቅድስና ዮሴፍ ከፍ ቢልም እግዚአብሔር ለክህነት ሌዊን: ለመንግስት ደግሞ ይሁዳን መርጧል:: ከእነሱ ዘርም ዓለምን ለማዳን ተወልዷል:: 10ሩ አበው በተለይ በዮሴፍ ላይ ግፍ ሠርተው የነበረ ቢሆንም በኋላተጸጽተዋል:: እነሆ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ታስባቸዋለች:: (ዘፍ. ከ28-31)

+" ነቢዩ ቅዱስ ሳሙኤል "+

+እሥራኤል ከግብፅ ባርነት ወጥተው ከነዓንን ከወረሱበት ዘመን ጀምረው መሳፍንትና ካህናት ያስተዳድሯቸው ነበር:: በወቅቱ ታዲያ ክህነት ከምስፍና ተስማምቶለት ኤሊ የተባለ ሊቀ ካህናትና ልጆቹ (አፍኒና ፊንሐስ) ያስተዳድሩ ጀመር::

+በዘመኑ ደግሞ ማሕጸኗ ተዘግቶባት ዘወትር የምታለቅስ ሐና የሚሏት ደግ ሴት ነበረች:: እግዚአብሔር የእርሷን ጸሎትና የሊቀ ካህናቱን ምርቃት ሰምቷልና ቅዱስ ልጅን ሰጣት:: "ሳሙኤል" አለችው:: "ልመናየን አምላክ ሰማኝ" ማለት ነውና::

+ሐና ስዕለቷን ትፈጽም ዘንድ ሳሙኤልን በ3 ዓመቱ ለቤተ እግዚአብሔር ሰጠችው:: በዚያም ስብሐተ እግዚአብሔርን እየሰማ: ማዕጠንቱን እያሸተተ: ከደብተራ ኦሪቱ ሳይለይ በሞገስ አደገ:: የኤሊ ልጆች (አፍኒና ፊንሐስ) በበደል ላይ በደልን አበዙ::

+ወቅቱ የአሁኑን ዘመን ይመስል ነበር:: ሁሉም ሰው ክፋተኛ የሆነበት በመሆኑ እግዚአብሔር ርቆ ስለ ነበር ትንቢትና ራዕይ ብርቅ ነበር:: አምላክ ተቆጥቷልና ሳሙኤልን በሌሊት 3 ጊዜ ጠራው:: ነቢዩም ታጥቆ የፈጣሪውን ቃል ሰማ:: በዚሕም የተነሳ ታቦተ ጽዮን ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ ተማረከች:: ከ34ሺ በላይ ሕዝብ በኢሎፍላውያን አለቀ:: አፍኒና ፊንሐስም ተገደሉ:: ኤሊም ወድቆ ሞተ::

+ከዚህች ቀን በኋላ ቅዱስ ሳሙኤል በእሥራኤል ላይ ነቢይና መስፍን ሆኖ ተሾመ:: በዘመኑ ሁሉ እንደሚገባው እየኖረ: የእግዚአብሔርን ለእሥራኤል: የእሥራኤልን ለእግዚአብሔር ሲያደርስ ኑሯል:: ሕዝቡ ንጉሥ በፈለጉ ጊዜ ሳዖልን ቀብቶ አነገሠላቸው:: እርሱ (ሳዖል) እንደ ሕጉ አልሔደምና ፈጣሪ ናቀው::

+ሳሙኤል ግን ደግ አባት ነውና ክፋተኛውን (ሳዖልን) ከጌታው ጋር ያስታርቅ ዘንድ ብዙ ደከመ: አለቀሰም:: እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን:- "አትዘን! እንደ ልቤ የሆነ: ፈቃዴን የሚፈጽም ዳዊትን አግኝቸዋለሁና እርሱን በእሥራኤል ላይ አንግሠው" አለው::
ቅዱስ ሳሙኤልም ወደ ቤተ ልሔም ሔዶ: ከእሴይ ልጆችም መርጦ ልበ አምላክ ዳዊትን ቀባው: አነገሠውም::

+ቅዱስ ሳሙኤል በተረፈው ዘመኑ ለፈጣሪው እየተገዛ ኑሯል:: ነቢዩ ዘወትር ከእጁ የሽቱ ሙዳይና የቅብዐት እቃ (ቀንድ) አይለይም ነበረ:: እነዚህም የድንግል ማርያም ምሳሌዎች ናቸውና አባ ሕርያቆስ:-
"ሙዳየ ዕፍረት ወቀርነ ቅብዕ ዘሳሙኤል" ብሎ አመስግኗታል::

+ነቢዩም በወገኖቹ መካከል በዚሕች ቀን አርፏል:: እሥራኤልም አልቅሰውለታል:: ዛሬ ቅዱሱ ነቢይ ለአገልግሎት የተጠራበት ቀን ነው::

+" ቅዱስ ሱርያል ሊቀ መላዕክት "+

+ከታላላቅ ሊቃናት አንዱ የሆነው ቅዱስ ሱርያል ክብሩ ብዙ ቢሆንም ብዙ ምዕመናን አያውቁትም:: የመላእክት መዓርግ ሲነገር ሚካኤል: ገብርኤል: ሩፋኤል ብሎ ቀጥሎ የሚመጣው ሱርያል ነው::

+በ3ቱ ሰማያት ካሉት 9ኙ ዓለመ መላእክት የአንዱ (የሥልጣናት) መሪ (አለቃ) ነው:: መልአኩ እጅግ ርሕሩሕ እና ተራዳኢ ነውና አንዘንጋው:: ለኖኅ መርከብርን ያሳራው: ከጥፋት ውሃም ያዳነው ይህ ቅዱስ መልአክ ነው::

+በገድለ ሰማዕታትም ላይ እንደተጠቀሰው የሰማዕታት ረዳትና አዳኝም ነው:: ቅዱስ ሱርያል በሌላ ስሙ "እሥራልዩ" ይባላል:: "የእሥራኤል ረዳት" እንደ ማለት::

=>ቸሩ አምላከ ቅዱሳን ስለ አባቶቻችን ብሎ ይማረን:: ከበረከታቸውም ያድለን::

=>ነሐሴ 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1."12ቱ" ደቂቀ ያዕቆብ (እሥራኤል)
2.ቅዱስ ሳሙኤል ነቢይ (የተጠራበት)
3.ቅዱስ ሱርያል ሊቀ መላእክት
4.ቅዱስ ብንያሚንና እህቱ አውዶከስያ (ሰማዕታት)
5.ቅዱስ ፊቅጦርና እናቱ ሣራ
6.አባ ባስልዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮዽያ (የተሾሙበት)

በ 27 የሚከበሩ ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት
1.የጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በዓለ ስቅለት
2.አቡነ መብዐ ፅዮን ጻድቅ
3.ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ)
4.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
5.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
6.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት
7.ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት

=>+"+ እነዚህም ሁሉ አሥራ ሁለቱ የእሥራኤል ነገዶች ናቸው:: አባታቸው የነገራቸው ይህ ነው:: ባረካቸውም:: እያንዳንዳቸውን እንደ በረከታቸው ባረካቸው:: +"+ (ዘፍ. 49:28)
=>+"+ በመንፈስም ወደ ታላቅና ወደ ረዥም ተራራ ወሰደኝ:: የእግዚአብሔርም ክብር ያለባትን ቅድስቲቱን ከተማ ኢየሩሳሌምን ከሰማይ: ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አሳየኝ . . . አሥራ ሁለት ደጆችም ነበሯት:: በደጆቹም አሥራ ሁለት መላእክት ቆሙ:: የአሥራ ሁለቱም የእሥራኤል ልጆች ነገዶች ስሞች ተጽፈውባቸው ነበር:: +"+ (ራዕይ. 21:11)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የትብብር ጥሪ!

እኚህ በፎቶው ላይ የምትመለከቷቸው አባት አቶ ገብረመድህን ተስፋዬ መሀሪ ይባላሉ። በትናንትናው እለት ከሽሬ ወደ አዲስ አበባ በአውሮፕላን መጥተው ነበር፣ ከዛ በሗላ ቦሌ ብራስ አካባቢ እንደታዩ ብንሰማም ጠፍተውብናል። እድሜያቸው 75 ሲሆን ቀይ ኮፍያ እና ካፖርት አርገው ነበር።

አቶ ገብረመድህንን ያያችሁ እንድትጠቁሙን እንማፀናለን:

አድሀኖም: 0912648085
ትርሀስ: 0912174538

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለቅዱስ እንድርያኖስ ሰማዕት እና ለታላቁ አባ ቢጻርዮን ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ እንድርያኖስ ሰማዕት †††

††† ቅዱሱ በ3ኛው መቶ ክ/ዘ የነበረ አረማዊ ሰው ሲሆን ከከሃዲው መክስምያኖስ ወታደሮችም አንዱ ነበር:: "ሊቀ መሓዛት" ይሉታል: የጐበዛዝቱ አለቃም ነበር:: ይህ ሰው ምንም ክርስቲያን አይሁን እንጂ በልቡ ቅንነት ተገኝቶበታል:: እንደ አሕዛብ ልበ ድንጋይ አልነበረም::

በወጣትነቱም አንዲት ደመ ግቡ ሴት አግብቷል:: ይህች ሴት ' #ኤልያና' ስትባል የተባረከች ክርስቲያን ናት:: እርሱ ግን አያውቅም:: ከተጋቡ ከዓመታት በሁዋላ ጌታ እግዚአብሔር ስለ ሚስቱ ጸሎት በጐ ጐዳና ሊመራው ፈለገ::

እንድርያኖስ ሁሌም በየቀኑ ክርስቲያኖች ደማቸውን ሲያፈሱ ይመለከታል:: የትእግስታቸው መጠንም ይገርመው ነበር:: በተለይ አብዛኞቹ በመከራው ደስተኞች ነበሩ:: ነገሩ ግራ ቢያጋባው 24 ባለንጀሮች ሊገደሉ ወደ ታሠሩበት ቦታ ሒዶ ጠየቃቸው::

"ምን ልታገኙ ነው ግን ይሕንን ሁሉ ስቃይ በአኮቴት (በምስጋና) የምትቀበሉት?" ቢላቸው "በሰማይ በክርስቶስ ዘንድ የሚጠብቀንን የክብር ሕይወት ሥጋዊ አንደበት አከናውኖ መናገር አይቻለውም:: ዝም ብሎ 'ዕጹብ: ዕጹብ' እያሉ የሚያደንቁት ነው እንጂ" አሉት::

እርሱም ተደላድሎ ተቀምጦ "እስኪ በደንብ አስረዱኝ" አላቸው:: ከዓለም መፈጠር እስከ ጌታችን የማዳን ሥራ: አልፎም ስለ ፍርድ ቀን በጥዑም አንደበታቸው አስተማሩት:: ቅዱስ እንድርያኖስ በቅጽበት ልቡ ወደ ክርስቶስ ፍቅር ሸፈተ::

በፍጥነት ተነስቶ የራሱን ስም ከሰማዕታቱ 25ኛ አድርጐ አጻፈ:: ንጉሡ ይሕንን ሲሰማ "አብደሃል" ቢለው ቅዱሱ መልሶ "የለም! ዛሬ ገና ከእብደቴ ተመለስኩ" በማለቱ ከ25ቱ ቅዱሳን ጋር ታሠረ:: ቅድስት ኤልያና (ሚስቱ) ነገሩን ስትሰማ ፈጽሞ ደስ አላት::

ወደ እስር ቤት ሒዳ "አይዞህ በርታ! ስለ ክርስቶስ የሞትክ ቀን ብቻ እኮራብሃለሁ" ብላ: እግራቸውን አጥባቸው ተመለሰች:: በሚገደሉበት ቀንም ልሰናበታት ብሎ ቅዱስ እንድርያኖስ ቢመጣ ቅድስት ኤልያና ቤቷን ዘግታ ገሠጸችው:: እርሷ ክዶ የመጣ መስሏት ነበር::

እርሱ ግን የሚስቱን የእምነት ጥንካሬ ተረዳ:: ቅዱሱና 24ቱ ቅዱሳን ለቀናት ብዙ መከራን እየተቀበሉ ሰነበቱ:: አካላቸውን እየቆራረጡ: ደማቸውን እያፈሰሱ ሆዳቸውንም እየቀደዱ መከራን አጸኑባቸው:: በመጨረሻው በዚህች ቀን ሲገደሉ ቅድስት ኤልያና "የእኔን ባል አስቀድሙት" አለች:: (የሌሎቹን አይቶ እንዳይደነግጥ ነው)

እንዳለችውም የእርሱንና የባልንጀሮቹን ጭን ጭናቸውን እየሰበሩ ገድለዋቸዋል:: ቅድስት ኤልያናንም መሣፍንቱ "ካላገባንሽ" እያሉ ሲያስቸግሯት ተሰዳ ሒዳ ከሰማዕታቱ መቃብር ላይ አለቀሰች:: ጌታም ጠርቷት እዚያው ዐረፈች::

††† ታላቁ አባ ቢጻርዮን †††

ታላቁ ገዳማዊ ሰው የመጀመሪያ መነኮሳት ከሚባሉ አባቶች አንዱ ሲሆን ዓለምን ንቆ ከመነነ በሁዋላ ከአባ #እንጦንስ ዘንድ መንኩሷል:: ከእርሳቸው ዘንድ በረድእነት ለብዙ ዓመታት አገልግሏል:: አገልግሎቱን በፈጸመ ጊዜም አስኬማን ተቀብሎ ወደ በርሃ ወጥቷል::

ምንም የራሱን ገዳም ባይመሠርትም በ4ኛው መቶ ክ/ዘ የምናኔ ሕይወት እንዲስፋፋ ካደረጉ አበው እርሱ ዋነኛው ነው:: በተጋድሎ ዘመኑም የሚታወቅባቸው ነገሮች አሉ:: ከእነሱም ጥቂት እንጠቅሳለን:: አባ ቢጻርዮን:-
1.ጾሙም ሆነ ጸሎቱ በ40 ቀናት የተወሰነ ነበር:: ጾምን ከጀመረ ያለ 40 ቀን እህል አይቀምስም:: ለጸሎት ከቆመም የሚቀመጠው ከ40 ቀናት በሁዋላ ነው::
2.ሁሌም በየበርሃው እየዞረ ያለቅሳል:: "ምነው" ሲሉት "ወገኖቼ አለቁብኝ: ደሃም ሆንኩ" ይላቸው ነበር:: እንዲህ የሚለው አጋንንት ብዙ ነፍሳትን እየነጠቁ ሲወስዱ ስለሚመለከት ነው::
3.በየገዳማቱ እየለመነ ለነዳያን ያከፋፍል ነበር::
4.ሐፍረቱን ከሚሸፍን ጨርቅ በቀር ምንም ልብስ አይለብስም ነበር::
5.ውዳሴ ከንቱን አምርሮ ይጠላ ነበር::
6.በባሕር ላይ ተራምዶ ሲሔድና እግሮቹ ሳይርሱ ሲቀሩ አበው ተመልክተዋል::
7.መርዝነት ያለውን ውሃም ጣፋጭ አድርጐታል::

††† ቅዱሱ ድውያንን ፈውሶ: አጋንንትን ከአካባቢው አሳዶ: ብዙ ፍሬ አፍርቶ: ገዳም ውስጥ በገባ በ57 ዓመቱ በመልካም ሽምግልና ዐርፏል::

††† ቸር አምላክ በክብረ ቅዱሳን ይከልለን:: ከበረከታቸውም ያብዛልን::

††† ነሐሴ 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ እንድርያኖስ ሰማዕት
2."24ቱ" ሰማዕታት (ማሕበሩ)
3.ቅድስት ኤልያና (ሚስቱ)
4.ታላቁ አባ ቢጻርዮን ገዳማዊ
5.ቅዱስ ኤልያኖስና እህቱ አውዶክስያ (ሰማዕታት)

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
2.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
3.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
4.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
5.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)
6.ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ

††† "ነገር ግን የሆነው ሁሉ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን: የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን ከእግዚአብሔር ነው:: #እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከእርሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና: በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር:: በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ:: እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማለድ ስለ ክርስቶስ መልእክተኞች ነን:: ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን::" †††
(2ቆሮ. 5:18)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በኋላ ግን ቆይቶ ቀይ ነጭ ሰማያዊ ፈትሎች በአንድ ላይ ተገምደው በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሕፃናት ክርስትና ሲነሱ ኢ-አማንያን አምነው ሲጠመቁ መታሰር ጀመረ፡፡ ትርጓሜውም የሶስቱ አንድ ላይ መገመድ ሥላሴን አንድነት ሶስትነት የሚያመለክት ምሳሌ ሲሆን ቀለሞቹ ደግሞ ቀይ ክርስቶስ ደሙን አፍሶ አድኖናል ስለስሙ በሰማዕትነት ደማችንን ማፍሰስ ይገባናል የማለት ሲሆን ነጩ የጥምቀት በጥምቀትም የሚገኝ ሥርየተ ኃጢያት (ከኃጢአት ምንጻት) ሰማያዊ አባት አለኝ (በፀጋ ልጅነት አግኝቻለሁ) ሰማያዊ ርስት መንግስተ ሰማይ ይቆየኛል ስለዚህም በሰማያዊ ግብር ጸንቼ መኖር በሰማያዊ ሕግ ሕገ ክርስቶስ ወንጌል ተመርቼ መኖር ይገባኛል እንደ ማለት ነው፡፡

ይኸንንም ጠቅለል ባለ መልኩ ኢትዮጵያዊው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሲያስረዱ ሥላሴ ማዕተበ ብርሃን ኃይል ሃይማኖቶሙ ለክርስቲያን÷ ሥላሴ ለክርስቲያን ሁሉ የሃይማኖታቸው ጉልበት መታወቂያ የብርሃን ማዕተብ (ምልክት) ናቸው ብለዋል፡፡
 


 

 
 

ማዕተብ ያላሠረ ኦርቶዶክሳዊ በውግዘት ከቤተክርስቲያኒቱ እንደ መናፍቅ ተቆጥሮ ባይለይም ማዕተብ አለማሠሩ ግን የአባቶቹ ትውፊት እንዳልተቀበለ ያስቆጥረዋል፡፡ በምሳሌያዊ አነጋገርም ሃይማኖት አልባውን ማለትም ክርስቲያን ያልሆነውን ማተብ የለሽ ያልተጠመቀ አረሚ ይሉታል ክርስቲያን በማተቡ መነኩሴ በቆቡ እንዲታወቅ ማተብ አልባ መሆን ደግሞ ክርስቲያን ይሁን ያልተጠመቀ መሆኑ ለማወቅ ያስቸግራል፡፡ በመለዮዋቸው ሌሎች እንዲታወቁ ክርስቲያን በማተቡ ክርስትናውን ሲያሳውቅ ኖሯል፡፡

በተለመደው አነጋገር እገሌ ማተብ አለው ባለማተብ ነው ሲባል እገሌ ታማኝ ክርስቲያን ነው እውነተኛ ሐቀኛ ነው የማለት ትርጉምን ይሰጣል "ባለማተቢቱ" ሲባል ከአሚን ባሏ የረጋች ከባሏ ሌላ የማታውቅ እውነተኛ ታማኝ ክርስቲያን የማለት ፍች አለው፡፡

በዚህ ምክንያት በክርስቲያኑ ኅብረተሰብ የማተብ ትርጉም ከፍተኛ ቁም ነገርን አዝሎ ይገኛል፡፡ አንዲት ሀገር ነፃ መሆኗ የሚታወቀው ወይም ራሷን የቻለች የራሷ መንግስት ያላት ከባዕድ ቀንበር ቅኝ ግዛት ነፃ የወጣች መሆኗ የሚታወቀው በባንዲራዋ ምልክትነት እንደሆነ እንደዚሁም አንድ ክርስቲያን በክርስቶስ አምኖ በጥምቀት ከዲያብሎስ ቁራኝነት ነፃ መውጣቱ ነፃነት ያለው አማኝ መሆኑ የሚታወቀው በማተቡ ምልክት ነው፡፡ ለደብዳቤ ለጽሑፍ ዓርማ ማኅተም ፊርማ እንደሚያስፈልገው ያም ለመተማመኛ እንደሚያገለግል ጥቅሙ ታውቆ ይሠራበታል፡፡

የክርስቲያን ማዕተብም በዚሁ አንፃር ብዙ ኃይማኖታዊ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ መጀመሪያ በልቡ የሚያምነው ሃይማኖት ክርስትናን ሳያፍርበት በአንገቱ ባለው ማተብ መግለጹ በክርስትናው አለማፈሩን ክርስትናህን ካድ ማተብህን በጥስ የሚል ዐላዊ ቢመጣና ያንን ምልክት ዓይቶ ቢሰዋው የሰማዕትነትን ክብር ያገኝበታል፡፡ ያም ባይሆን በማተቡ ምልክትነት በመናፍቃንና በኢአማንያን የሚቀበለው ዘለፋ ስለ ክርስቶስ መስቀል እንደተሸከመ ያስቆጥረዋል፡፡

ሁለተኛው ከክርስቲያን ወገኖች ጋር ያለ ጥርጥር ማለትም ክርስቲያን መሆኑ ታውቆለት በቀላሉ ክርስቲያናዊ ተሳትፎውን ማከናወን ይችላል፡፡ ማተብ ከሌለው ግን ክርስቲያን ይሁን ያልተጠመቀ ስለማይታወቅ በሃይማኖት ዜጎች ዘንድ በቀላሉ ተቀባይነት ማግኘት አይችልም ሶስተኛ ከማይታወቅበት አገር በአደጋም ይሁን በበሽታ እንደወጣ ሞት ቢደርስበት በማተቡ መታወቂያነት የክርስቲያን ሥርዓት ተፈጽሞለት አስክሬኑ ተፈርቶ በቤተክርስቲያን ሊቀበር ይችላል፡፡ ማተብ ከሌለው ግን ለክርስቲያንነቱ ማረጋገጫ የሰው ምስከር በአካባቢው ያውም በሰበካው ቤተክርስቲያን የሚታመን ክርስቲያን ከሌለ እንደ አልተጠመቀ ተቆጥሮ እንደ አሕዛብ ሥጋው ዱር ከበረሐ ወድቆ ይቀራል፡፡

አራተኛ ማተብና መስቀል ያለው ክርስቲያን በውሃ ዋና ወይም በበረሐ ጎዳና በውሃ የሚኖሩ ወይም በበረያ ያሉ አጋንንት በቀላሉ ሊለክፉት አይችሉም፡፡ ይህም በየጠበሉ ሥፍራ በተአምራት ተረጋግጧል፡፡ አጋንንት የለከፋቸው ሰዎች ማተብና መስቀል አይወዱም፡፡ የሠፈረባቸው ርኩስ መንፈስ ማተብ እንዲበጥሱ መስቀል እንዲጥሉ ያደርጋቸዋል፡፡ ማተብ በሰይጣን ዘንድ ከተጠላ በአጋንንት ላለመለከፍ የማተቡ መኖር ይጠቅማል ማለት ነው፡፡

አንዳንድ ሰዎች የማዕተብ ሥርዓትን ለመቃወምና ዘመናውያን መስለው ለመታየት "ሃይማኖት በልብ ነው" ይላሉ ተሳስተዋል፡፡ ሃይማኖት የልብ ብቻ አይደለም የጠቅላላው ሕዋሳት ሁሉ ናት እግዚአብሔርን ስንወደውና ስናመልከው በልባችን ብቻ ሳይሆን በአፋችንም በአንገታችንም በጠቅላላው ሰብአዊ ተፈጥሮአችን ሁሉ መሆን ይገባዋል፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር የጠቅላላው ሰውነታችን አምላክና ፈጣሪ ስለሆነ ነው፡፡ "ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ፡፡" ማቴ ፲፤ ፴፪-፴፫

በዚህ ቃል መሠረት በኢአማንያን ዘንድ ክርስቲያን መሆናችንን የምንገልፀው በልባችን ብቻ ሳይሆን በቃላችንና በሥራችንም ጭምር ነው፡፡ በአንገታችንስ እንዳንመሰክርለት ማን ያግደናል? በአንገታችን ባለው ማዕተብም ለእግዚአብሔር እንመሰክራለን የስሙን ምልክት በአንገታችን እናኖራለን አናፍርበትም፡፡ የክርስቶስን ሞትና ትንሣኤ በጥምቀታችን እንደምንመሰክር የጥምቀታችንንም አርማ በማተባችን እናረጋግጣለን፡፡ /ሮሜ ፲፤፮-፲፫፡፡ ኢዮኤ ፪፤፴፪፡፡ ሮሜ ፮÷፩-፭ ፣ ማቴ ፭÷፲፩-፲፪፡፡ ፩ጴጥ ፫÷፳፩-፳፪ ፩ጴጥ ፬÷፲፪-፲፮/ ተመልከት፡፡

ሌሎችም ማተብ መሠርን ብቻ ሳይሆን ጥምቀተ ክርስትናንም ለመቃወም ከሚሰነዝሯቸው ትችቶች አንዱ ሰው ሁሉ ሲወለድ ክርስቲያን ሳይሆን ይወለዳል፡፡ እናንተ ክርስቲያኖች ግን በውሃ ነክራችሁ እንደ ውሻ በአንገቱ ላይ ክር ታሥሩለታላችሁ ስለዚህም ማተብ አልባነት ከማኅፀን ጀምሮ የተፈጥሮ ሲሆን ክርስትና ግን ሰው ሠራሽ በኋላ የመጣ ነው ይላሉ፡፡ ከአምላክ ሕግ ከወንጌል ይልቅ በሌላ ሥርዓት የሚሄዱ ከክርስትና በኋላ የመጡ ስለሆነ ባለማወቃቸው ቢተቹ አንደነቅም፡፡

ከወንጌል የተለየች ትምህርት እንዳንቀበል ሐዋርያት አስጠንቅቀውናል፡፡ መላእክት በራእይ ገልጸውልናል ከእግዚአብሔር አግኝቻለሁ እያሉ የሚመጡትን መናፍስት እንድንበረምራቸው ከወንገል ትምህርት የሚቃረን ትምህርት ካላቸው እንዳንቀበል ቅዱሳት መጻህፍት ያስጠንቅቁናል ቅዱ ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ እንዲህ ይላል "ወዳጆች ሆይ መንፈስን ሁሉ አትመኑ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደሆነ መርምሩ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፡፡

 


ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ እንደመጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፡፡ ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፡፡ ይህም እንዲመጣ ሰምታችኋል አሁንም እንኳ በዓለም አለ፡፡" ፩ኛ ዮሐ ፬÷፩-፫/

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Selam yetewahdo lijoch endet aderachu 1 tyake nebrgn መስቀል አንገታችን ላይ የምናስርበት ምክንያት ምንድነው እና በእጃችን ማሰር ይገባናል ወይስ አይገባም ከነ ምክንያቱ በትነግሩኝ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ከዚህም በኋላ ከዕለታት ባንደኛው ቀን እናታችን ክርስቶስ ሠምራ አገልጋዮቿን ወደ ቤተ ክርስቲያን እንሄድ ዘንድ ተዘጋጁ አለቻቸውና እነሱም አሺ በጎ ብለው አጅበዋት ወደቤተ ክርስቲያን ሄዱ። ከዚያም እንደደረሱ "በሉ እንዲህ እኔ ከዚህ ጥቂት እቆያለሁና እናንተ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ ለኔ ይህች አንድዲት አገልጋይና ይህ ሕፃን ልጅ ብቻ ይበቁኛል አለቻቸው። በዚያኑ ጊዜ አገልጋዮቿ እጅ እየሱ ወይም እየተሰናበቱ ወደቤታቸው ተመለሱ። ከዚያም ከዳዊት መዝሙር "ልቤ ጽኑ ነው አቤቱ ልቤ ጽኑ ነው እግዚአብሔርን ፈጽሜ አመሰግነዋለሁ እግዚአብሔር የደህንነቴ መብራት ስለሆነ ምን ያስደነግጠኛል እግዚአብሔር የሕይወቴ መተማመኛ ነው ምንስ ያስፈራኛል የሚለውን እየጸለየች የሚያልፈን ዓለም በማያልፈው ዓለም ለመተካት ወይም ለመለወጥ አውጭኝ እግሬ ብላ ገሠገሠች። ያ በልስላሴና በእንክብካቤ የኖረ እግር ከመንገዱ ብዛት እንደዚሁም ከቅርቅፍቱና ከእንቅፋቱ የተነሣ ፈለግ ሲያወጣ ሥጋውን እየቆረጠች ስትጥለው ደሙ እንደጒርፍ ውሃ ይወርድ ነበር። ያች የተከተለቻት አገልጋይ ግን ከእመቤቷ እግር እየተቆረጠ የሚወድቀውን የአካል ቊራጭ እያነሳች በልብሷ ትቋጥረው ነበር። በዚህ ዓይነት ችግርና ፀሐይ ሐሩር የብዙ ጐዳና ጉዞ ተጉዛ ከአሰበችበት አገር ደረሰች። በደብረ ሊባኖስ አቅራቢያ ወይም አካባቢ ስትደርስ የራስ ፀጒራን ይዛው በነበረ ምላጭ ላጨች ልብሷንም አውልቃ ለነዳያን አከፋፈለች የያዘችውንም ገንዘብ በመንገድ ላይ ላገኘችው ሁሉ መፅውታ ጨረሰች። ከዚያም አስቀድማ ያዘጋጀችውን ልብስ ምንኵስና ማለት ቀሚስዋን አጥልቃ አጽፋን ተጐናጽፋ ቆቧን ደፍታ ደብረ ሊባኖስ ከሴቶች ገዳም ደረሰች። የገዳሙ መነኰሳትም በታላቅ ክብር ተቀብለው ወደበዓታቸው አስገቧት ...

እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ለሳጥናኤል ምሕረት እንደለመነች፦ ከዕለታት በአንድኛው ቀን እናታችን ክርስቶስ ሠምራ ጓንጉት በምትባል ደሴት ውስጥ ዓርብ ዕለት ከቀኑ በስድስት ሰዓት ላይ ስለሰው ልጆች ስትጸልይ ሣለ። ዓለሙ ሁሉ ከንቱ እንደሆነና የሰውም ልጅ ሕይወት እንደጥላ ኃላፊ ጠፊ መሆኑን ፈጽማ ተመለከተች። ነቢዩ ዳዊት "ሰው ከንቱ ነገርን ይመስላል ዘመኑ ወይም ሕይወቱ እንደጥላ ያልፋል" ሲል ተናግሯልና። ዳግመኛም "ሰው ክብር እንኳ ቢሆን ሊኖር አይችልም እንደሚጠፋ ወይም ማስተዋል እንደሌለው እንስሶች መሰለ... አለ ክቡር ዳዊት። ስለዚህም ሁሉ ነገር አቤቱ ማራቸው ይቅርም በላቸው መፃተኛዋ ባሪያህንም ኃጢአቷን አታስብባት እያለች ወደፈጣሪዋ መሪር ዕንባን አለቀሰች። ያን ጊዜ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በታላቅ ግርማ ወደስዋ መጣ። በታላቅ ግርማ ሆኖ ባየችውም ጊዜ ደነገፀች ከእግሩ ሥርም ወደቀች። ከዚህ በኋላ ነውር በሌለባቸው ንዑዳት ክቡራንና ንጹሐን በሆነ እጆቹ አነሣት። ቀጥሎም "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ አትደንግጭ ነገር ግን የልብሽን ሃሳብ ንገሪኝ" አላት። እስዋም "አቤቱ ባሪያህንስ በባለሟልነት ካሠለጠንካት አባታችን አዳምን በአርአያህና በአምሣልህ ስለምን ፈጠርከርው። በእንጨት መስቀልስ ላይ ለምን ተሰቀልክ ስለአዳምና ስለልጆቹ አይደለምን?" አለችው። "አዋን ስለነሱ ስል ተሰቅያለሁ" አላት። "እግዲያውስ መሰቀልህ ወይም የተሰቀልከው ስለነሱ ከሆነ ከአቤል ጀምሮ እስከ ዛሬ የሞቱን ከዛሬም በኋላ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ የሚሞቱትን አቤቱ ማራቸው ይቅርም በላቸው" አለችው። "አንተ ቸር ይቅር ባይ መዓትህ የራቀ ምሕረትህ የበዛ ነህና ከአንተ ሌላ አምላክ የሌለ እውነተኛ አምላክ ነህ ሁሉ ይቻልሃልና የሚሣንህ ነገር ከቶ የለምና ዓለም በጠቅላላዋ በእፍኝህ አትሞላም" በማለት እያለቀሰች ለመነችው። በዚያ ጊዜ ጌታ መልሶ "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ እስኪ አንቺ ራስሽ ፍረጅ አዳም ከነልጆቹ ከሠራው ኃጢአት እና እኔ በጰንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን በቀያፋና በሐና አደባባይ በዕለተ ዓርብ ከተቀበልኩት ሕማማተ መስቀል ቢመዘን የትኛው ይመዝን ይመስልሻል?" አላት። ይህንም ባላት ጊዜ ደነገጠችና ከመሬት ላይ ወደቀች። በዚህ ጊዜ ቅዱሳት በሆኑ እጆቹ ከወደቀችበት አነሣትና "እንግዲህ ይህን ሁሉ መከራ የተቀበልኩ ለማን ወይም በማን ምክንያት ይመስልሻል" አላት።

ጌታም "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ እስኪ የልብሽን ሃሳብ ወይም ፍላጐትሽን ንገሪኝ" አላት። በዚህን ጊዜ "አቤቱ ፈጣሪየ ፈቃድህስ ቢሆን የአዳም ልጆች ከሥቃይ ከኵነኔ ይድኑ ዘንድ ዲያብሎስን ይቅር ትለው ወይም ትምረው ዘንድ እለምንሃለሁ። የኃጥእን መመለሱን እንጂ ጥፋቱን አትወድምና" አለችው። "የምለምንህ ወይም ማረው የምልህ ዲያብሎስን ወድጄው አይደለም ነገር ግን እርሱ ከተማረ በአዳም ልጆች ላይ ሥቃይና ኵነኔ ሊኖር አይችልም ብየ በመገመት እንጂ። የነሱ ሥጋ ሥጋየ እንደሆመኑ መጠን የኔም ሥጋ ሥጋህ ነውና" አለችው። ይህንም ባለችው ጊዜ ጌታ ፍግግ ብሎ "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ ሌሎች ካንቺ በፊት የነበሩ ካንቺም በኋላ የሚነሱ የማያስቡትን እጅግ የሚያስደንቅ ልመና አቀረብሽ" አላት። ይህንም ካለ በኋላ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ጠርቶ "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ዲያብሎስን ማርልኝ ስትል ልመና አቅርባለችና እሺ ካላት ታወጣው በንድ ወደሲዖል ይዘሃት ሂድ" ብሎ አዘዘው። በዚህ ጊዜ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እሺ ብሎ ሰግዶ እጅ ነሥቶ ወደሲዖል ይዞአት ሄደ። አብረው በሚጓዙበትም ጊዜ "እንግዲህ ዲያብሎስ ከታረቀ ወይም ከተማረ የሰው ልጆች ሁሉ ያርፋሉ" እያለች ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል ታሳስበው ነበር። ይህን አምላክነትን ሲሻ ከክብሩ የተዋረደ ዲያብሎስ ምሕረት ለማግኘት ይሻ መስሏት ነበርና።

ከሲዖል አፋፍ በደረሱም ጊዜ የተመለከተችው ሥቃይ ተነግሮ የማያልቅ ነው ሰዎች ከሰዎች ጋር እንደውሻ ይናከሱ ነበር። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል "ምሕረት የሚፈልግ ከሆነ እስኪ በይ ዲያብሎስ ብለሽ ጥሪው" አላት። በዚህ ጊዜ በመላእክት ቋንቋ ሦስት ጊዜ "ሣጥናኤል ሣጥናኤል ሣጥናኤል" በማለት ጠራችው። ዲያብሎስም "ከዚህ በብዙ ሠራዊት ላይ ነግሼ ከምኖርበት አገር ማን ነው እሱ የሚጠራኝ" እያለ በታላቅ ቃል አሰምቶ ተናገረ። ከዚህም በኋላ "ለብዙ ዘመን ስፈልግሽ ወይም ሳድንሽ ቆይቼ ነበር ዛሬ ግን ከምኖርበት ቤቴ ድረስ መጣሽን" አላት። እርሷም "ጌታ ይቅርታ አድርጓልሃልና ከዚህ ከሥቃይና ከመከራ ቦታ ከወገኖችህ ጋራ ና ፈጥነህ ውጣ" አለችው። ይህንም በለችው ጊዜ ልቡ እንደ እሳት ነደደ አፈፍ ብሎ ተረማምዶ በግራ እጁዋን ይዞ ከሲዖል ረግረግ ውስጥ ወረወራት። በዚያን ጊዜ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል የእሳት ሰይፍ ይዞ ከኋላ ከኋላዋ ይከተላት ነበርና ይህን ምሕረት የሌለው ዕቡይ ዲያብሎስ በያዘው ሰይፍ ቢቀጣው የሲዖል ደጃፍ ተከፈተች። በዚህ ሰዓት ታላቅ ጨኸትና ውካታ ወይም መደበላለቅ ሆነ በሲዖል ያሉ የሰዎች ነፍሳት እንደንብ ከበቧት ወይም ሠፈሩባት። በዚያን ጊዜ በቅዱስ ሚካኤል ክንፍና በስዋም በተሰጣት ክንፈ ረድኤት ከሲዖል የወጡት ነፍሳት ቁጥር ዓሥር ሺህ ያህል ነበር። እነዚህ ከመከራ ያመለጡ ከሥቃይ የወጡ ነፍሳትን ባየች ጊዜ እጅግ አድርጋ ተደሰተች ከደስታዋም ብዛት የተነሣ የእናቱን ጡት እየጠባ እንደሚዘል እምቦሳ ጥጃ በመካከላቸው ትዘል ነበር።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሩፋኤል ተቀበል ፀሎቴን | ዘማሪ ብርሃኑ ተረፈ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለቅዱስ ቲቶ ሐዋርያ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ቲቶ ሐዋርያ †††

††† የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ቅዱስ ቲቶ ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ሲሆን በተወሰነ መንገድም ቢሆን የተዘነጋ ሐዋርያ አይደለም:: በተለይ ደግሞ ቅዱስ ጳውሎስ ከጻፋቸው አሥራ አራት መልእክታት መካከል አንዷ የተላከችው ለዚህ ቅዱስ በመሆኗ ታሪኩ እንኳ ባይነገር ስሙ አይረሳም:: ቅዱስ ጳውሎስም በመልዕክታቱ በጐ ስሙን እየደጋገመ ያነሳዋል::

ለመሆኑ ሐዋርያው ቅዱስ ቲቶ ማን ነው?
ቅዱስ ቲቶ የተወለደው በ1ኛው መቶ ክ/ዘመን እስያ ውስጥ: ቀርጤስ በምትባል ከተማ ነው:: የዘር ሐረጉ ከእሥራኤልም: ከጽርእም (ግሪክ ለማለት ነው::) ይወለዳል:: አካባቢው አምልኮተ እግዚአብሔር የጠፋበት ስለሆነ እሱም: ቤተሰቦቹም የሚያመልኩት ከዋክብትን ነበር::

መዳን በእውቀት ይመስላቸው ስለ ነበር የአካባቢው ሰዎች የግሪክን ፍልስፍና ጠንክረው ይማሩ ነበር:: ቅዱስ ቲቶም በወጣትነቱ ወደ ት/ቤት ገብቶ የግሪክን ፍልሥፍናና የዮናናውያንን ጥበበ ሥጋ ተማረ:: በጥቂት ጊዜም የሁሉ የበላይ ሆነ::

ቅዱሱ በወቅቱ ምንም እውነተኛውን ፈጣሪ አያምልክ እንጂ በጠባዩ እጅግ ቅንና ደግ ነበር:: ምክንያቱን ሳያውቀው ለእኔ ቢጤዎች ያበላ: ያጠጣ: ይንከባከባቸውም ነበር:: እግዚአብሔር ግን የዚህ ቅን ሰው በጐነቱ እንዲሁ እንዲቀር አልወደደምና አንድ ቀን በራዕይ ተገለጠለት::

በራዕይም አንድ ምንነቱን ያልተረዳው ነገር "ቲቶ ሆይ! ስለ ነፍስህ ድኅነት ተጋደል:: ይህ ዓለም ኃላፊ ነው::" ሲለው ሰማ:: ከእንቅልፉ ነቅቶ በእጅጉ ደነገጠ:: የሚያደርገውንም አጣ:: ያናገራቸው ሁሉ ምንም ሊገባቸው አልቻለም::

ለተወሰነ ጊዜም ለጉዳዩ ምላሽ ሳያገኝለት በልቡ እየተመላለሰ ኖረ:: ድንገት ግን በዚያ ሰሞን ከወደ ኢየሩሳሌም አዲስ ዜና ተሰማ:: "ክርስቶስ የሚሉት ኢየሱስ: እርሱም የባሕርይ አምላክ የሆነ ወደ ምድር ወርዶ: ስለ እግዚአብሔር መንግስትም እየሰበከ ነው::" ሲሉ ለቲቶ ነገሩት::

"ሌላስ ምን አያችሁ?" አላቸው:: "በእጆቹ ድውያን ይፈወሳሉ:: ሙታን ይነሳሉ:: እውራን ያያሉ:: ለምጻሞች ይነጻሉ:: ሌሎች ብዙ ተአምራትም እየተደረጉ ነው::" አሉት:: የወቅቱ የሃገረ አክራጥስ መኮንን ፈላስፋ ነበርና ስለ ክርስቶስ ሲሰማ ሊመራመር ወደደ::

እርሱ መሔድ ስላልተቻለው "ብልህ ጥበበኛ ሰው ፈልጉልኝ::" ብሎ ተከታዮችን ቢልካቸው ከቲቶ የተሻለ በአካባቢው አልነበረምና እርሱኑ አመጡት:: መኮንኑ ቲቶን "ነገሩ ትክክል ወይም ስሕተት መሆኑን በጥልቅ መርምረህ ምላሽ አምጣልኝ::" ብሎ ላከው::

ቅዱስ ቲቶም ፈጥኖ ተነስቶ ወደ ኢየሩሳሌም ገሰገሰ:: ወደ ከተማዋ እንደገባም ጌታችንን አፈላልጐ አገኘው::
1.ጌታችን ክርስቶስ በሥልጣነ ቃሉ ደዌያትን ሲያርቅ: አጋንንትን ሲያሳድዳቸው ተመልክቶ ይህ ሥራ የፍጡር እንዳልሆነ ተረዳ::
2.ጌታችን የሚያስተምረው ትምሕርት ከግሪክ ፍልሥፍና እጅግ ርቆና መጥቆ አገኘው:: የግሪክ ፍልሥፍና መነሻውም ሆነ መድረሻው ሥጋዊ ነው:: ጌታ ግን በጣዕመ ቃሉ የሚያስተምረው ሰማያዊ: በዚያ ላይ ዘላለማዊ የሆነ ትምሕርት ነው:: በራዕይ "ስለ ነፍስህ ተጋደል::" ያለው ምሥጢር አሁን ተተረጐመለት::

በዚህ ምክንያትም ጊዜ አላጠፋም:: ወዲያውኑ አምኖ ተከታዩ ሆነ:: ጌታም ከሰባ ሁለቱ አርድእት ደመረው:: የአክራጥስ መኮንን "ምነው ዘገየህ?" ቢለው ያየውን ሁሉ ጽፎ: እንደማይመለስም አክሎ ደብዳቤ ላከለት::

ከዚህ በኋላ ቅዱስ ቲቶ ከጌታችን እግር ለሦስት ዓመታት ተምሮ: በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ: በመላው እስያ ለስምንት ዓመታት ወንጌልን ሰብኳል:: ቅዱስ ጳውሎስ ባመነ ጊዜ ደግሞ የእርሱ ደቀ መዝሙር ሆኖ ለሃያ አምስት ዓመታት አስተምሯል::

ቅዱስ ጳውሎስ ሰማዕት ከሆነ በኋላ ደግሞ ወደ አክራጥስ ተመልሶ: ሕዝቡን አሳምኖና አጥምቆ: ቤተ ክርስቲያንን አንጿል:: ዕድሜው በደረሰ ጊዜም መምሕራንን: ካህናትን ሹሞላቸው: ባርኳቸውም በዚህች ቀን ዐርፏል::

††† አምላከ ቅዱስ ቲቶ መልካሙን የሕይወት ምሥጢር ይግለጽልን:: ከሐዋርያውም በረከቱን ያድለን::

††† ጳጉሜን 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ቲቶ ሐዋርያ (ከሰባ ሁለቱ አርድእት)

††† ወርኀዊ በዓላት
(የለም)

††† "የእግዚአብሔር ባሪያና የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ. . . መድኃኒታችን እግዚአብሔር እንዳዘዘ: ለእኔ አደራ በተሰጠኝ ስብከት ቃሉን ገለጠ: በሃይማኖት ኅብረት እውነተኛ ለሚሆን ልጄ ቲቶ::
ከእግዚአብሔርም አብ: ከመድኃኒታችንም ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት: ሰላምም ይሁን::" †††
(ቲቶ. ፩፥፩)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/W422JDUgHwo?feature=share

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝✞✝ 12ቱን ወራት (360ውን ቀናት) በእድሜና በጤና ያቆየ::
ይልቁኑ በሃይማኖታችን ያሰነበተን የቅዱሳን አምላክ #መድኃኒታችን #እግዚአብሔር . . . ቸርነቱ ምን ይረቅ!!! ምንስ ይጠልቅ!!! ✝✞✝

<< #የእመ_ብርሃን ምልጃና #የቅዱሳኑ ረድኤትም ድንቅ ነው:: >>

☞የነደደው ኃጢአት፡ መከራ፡ ስጋትና ፍርሐት ይወገድ ዘንድም ንስሃ እንግባ!

✝✞✝ እስኪ ደግሞ ቀሪውን ጊዜ ለበረከት ሰጥቶ ከዘመነ ቅዱስ #ሉቃስ ይደምረን!!! ✝✞✝ አሜን።

✝ ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር✝

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ጳጉሜ_ወይም_ጾመ_ዮዲት"

➯#ጳጉሜ ማለት ጭማሪ ማለት ነው፡፡ ይህም በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን የምትመጣ ናት፡፡ በአራት ዓመት አንዴ ማለትም በዘመነ ዮሐንስ ጳጉሜ ስድስት ቀን ይሆናል፡፡ በዚህም ሐገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ / Thirty months of sunshine / በመባል ትታወቃች ፡፡

➯ጳጉሜ በዘመነ ዮሐንስ ስድስት በምትሆንበት ጊዜ ጾመ ነቢያት /የገና ጾም/ ህዳር 14 ቀን ይገባና ታህሳስ 28 ቀን ጾሙ ተፈቶ የልደት በዓል ይከበራል፡፡ በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜ ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው፡፡ ይህም ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ግን እንደ አንደኛው የፈቃድ ጾም /ጽጌ ጾም/ በብዙዋኑ ዘንድ የታወቀ አይደለም፡፡ የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡

➯እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋርስ ንጉስ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ ድንበር አስፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ (ዮዲ.፪፥፯)፡፡ እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመኑ 12ሺህ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡ 12ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሔድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ በዚህም ብዙ ጥፋ በመድረሱ የእስራኤል ልጆች አለቀሱ፡፡

➯ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ ርቃ ንጽሕናዋን ጠብቃ በጾም በቀኖና በሀዘን ተወስና ትኖራለች በተፈጠረው ጥፋት ህዝቡ ላይ ለመጣው መከራ ማቅ ለብሳ በራስዋ ላይ ትብያ ነስንሳ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች፡፡ የፍጥረቱን ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር አምላክም ሕዝቡን የሚያድኑበትን መንገድ ለመጠየቅ ሱባኤ በገባች በሦስተኛው ቀን ገለፀላት፡፡ ዮዲ.፰፥፪፡፡ ከዚህ በኋላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል፡፡ ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾምና በጸሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ኃይል አግኝታ ነው፡፡ ስለዚህ ምዕመናን ጥንተ ጠላታችን ሰይጣንን ፈቃደ ሥጋን ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መጎናጸፍ አለብን ብለው ጳጉሜን በፈቃድ ይጾማሉ፡፡

➯የጳጉሜ ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበትም ወር ነው፡፡ ይህም ጳጉሜ የዓመታት መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት ወቅት ወደ ማብቂያው የምናልፍባት እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነውና ነው፡፡

➯ክርስቲያኖች ሁሉ በየዓመቱ በጳጉሜ ወር ሁሉም ተሰብስበው ከሌሊት ጀምረው በቤተክርስቲያን ተገኝተው ጸበል ይጠመቃሉ፡፡ ይህንን የምናደገውም እግዚአብሔር የተባረከ ዓመት እንዲሰጠን፣ ባሳለፍነው ዓመት የሰራነውን ኃጢአት ይቅር እንዲለን ነው የምንጠመቀውም ንስሐ ገብተን ነው፡፡ በእግዚአብሔር ስም የተቀደሰው ጸበል ደግሞ ከበሽታችን ያድነናል፣ የተቀደስንም ያደርገናል፣ መጪውንም ህይወታችን የተባረከ ያደርግልናል፡፡


መልካም ጾም

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ቃለ ሕይወት ያሠማልን በድሜ በጤና ይጠብቅልን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Ybat foto nw ebat ytnsa😍👄

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Watch "🔴መደመጥ ያለበት አንጀት የሚያርሡ የፍልሠታ መዝሙሮች ልብ የሚነኩ በፆም መደመጥ ያለባቸው መዝሙሮች#viral #orthodox #orthodoxmezmur" on YouTube
https://youtu.be/FjiRfNWN1HM

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

@kedusgebreal
@kedusgebreal
@kedusgebreal

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝✞✝ በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን:: ✝✞✝

""" ነሐሴ 27ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት """

+" 12ቱ አበው ደቂቀ እሥራኤል "+

=>እነዚህ አበው የአብርሃምና የይስሐቅ የልጅ ልጆች የያዕቆብ ደግሞ ልጆች ናቸው:: ትውልድ ከአዳም እስከ ቅዱስ ያዕቆብ አንድ ሐረግ ይዞ መጥቶ እዚህ ላይ ሲደርስ ይበተናል:: አባታችን ያዕቆብን እግዚአብሔር ሲባርከው እሥራኤል አለው:: ትርጉሙም "ሕዝበ እግዚአብሔር: ወልድ ዘበኩር (የበኩር ልጅ): ከሃሊ: ነጻሪ (አስተዋይ) እንደ ማለት ነው::

+ይህ ቅዱስ አባት ለድንግል ማርያም ቅድመ አያት ከመሆኑ ባሻገር ነቢያትን: ካህናትን: ነገሥታትንና መሣፍንትን ወልዷል:: ከወንድሙ ኤሳው ጋር ተጣልቶ ወደ ሶርያ በሔደ ጊዜ ከ2ቱ ሚስቶቹ (ልያና ራሔል) 8 ልጆችን: ከ2ቱ የሚስቶቹ ደንገ ጥሮች (ዘለፋና ባላ) 4 ልጆችን: በድምሩ 12 ልጆችን ወልዷል::

#‎ልያ የወለደቻቸው:-
1.ሮቤል
2.ስምዖን
3.ሌዊ
4.ይሁዳ
5.ይሳኮር እና
6.ዛብሎን ይባላሉ::

#‎ራሔል የወለደቻቸው:-
7.ዮሴፍና
8.ብንያም ይባላሉ::

#‎ባላ :- 9.ዳን እና
10.ንፍታሌምን ስትወልድ

#‎ዘለፋ :- ደግሞ 11.ጋድና 12.አሴርን ወልዳለች::

#‎12ቱ ደቂቀ እሥራኤል (ያዕቆብ) ማለት እኒህ ናቸው::

+ከ12ቱ በቅድስና ዮሴፍ ከፍ ቢልም እግዚአብሔር ለክህነት ሌዊን: ለመንግስት ደግሞ ይሁዳን መርጧል:: ከእነሱ ዘርም ዓለምን ለማዳን ተወልዷል:: 10ሩ አበው በተለይ በዮሴፍ ላይ ግፍ ሠርተው የነበረ ቢሆንም በኋላተጸጽተዋል:: እነሆ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ታስባቸዋለች:: (ዘፍ. ከ28-31)

+" ነቢዩ ቅዱስ ሳሙኤል "+

+እሥራኤል ከግብፅ ባርነት ወጥተው ከነዓንን ከወረሱበት ዘመን ጀምረው መሳፍንትና ካህናት ያስተዳድሯቸው ነበር:: በወቅቱ ታዲያ ክህነት ከምስፍና ተስማምቶለት ኤሊ የተባለ ሊቀ ካህናትና ልጆቹ (አፍኒና ፊንሐስ) ያስተዳድሩ ጀመር::

+በዘመኑ ደግሞ ማሕጸኗ ተዘግቶባት ዘወትር የምታለቅስ ሐና የሚሏት ደግ ሴት ነበረች:: እግዚአብሔር የእርሷን ጸሎትና የሊቀ ካህናቱን ምርቃት ሰምቷልና ቅዱስ ልጅን ሰጣት:: "ሳሙኤል" አለችው:: "ልመናየን አምላክ ሰማኝ" ማለት ነውና::

+ሐና ስዕለቷን ትፈጽም ዘንድ ሳሙኤልን በ3 ዓመቱ ለቤተ እግዚአብሔር ሰጠችው:: በዚያም ስብሐተ እግዚአብሔርን እየሰማ: ማዕጠንቱን እያሸተተ: ከደብተራ ኦሪቱ ሳይለይ በሞገስ አደገ:: የኤሊ ልጆች (አፍኒና ፊንሐስ) በበደል ላይ በደልን አበዙ::

+ወቅቱ የአሁኑን ዘመን ይመስል ነበር:: ሁሉም ሰው ክፋተኛ የሆነበት በመሆኑ እግዚአብሔር ርቆ ስለ ነበር ትንቢትና ራዕይ ብርቅ ነበር:: አምላክ ተቆጥቷልና ሳሙኤልን በሌሊት 3 ጊዜ ጠራው:: ነቢዩም ታጥቆ የፈጣሪውን ቃል ሰማ:: በዚሕም የተነሳ ታቦተ ጽዮን ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ ተማረከች:: ከ34ሺ በላይ ሕዝብ በኢሎፍላውያን አለቀ:: አፍኒና ፊንሐስም ተገደሉ:: ኤሊም ወድቆ ሞተ::

+ከዚህች ቀን በኋላ ቅዱስ ሳሙኤል በእሥራኤል ላይ ነቢይና መስፍን ሆኖ ተሾመ:: በዘመኑ ሁሉ እንደሚገባው እየኖረ: የእግዚአብሔርን ለእሥራኤል: የእሥራኤልን ለእግዚአብሔር ሲያደርስ ኑሯል:: ሕዝቡ ንጉሥ በፈለጉ ጊዜ ሳዖልን ቀብቶ አነገሠላቸው:: እርሱ (ሳዖል) እንደ ሕጉ አልሔደምና ፈጣሪ ናቀው::

+ሳሙኤል ግን ደግ አባት ነውና ክፋተኛውን (ሳዖልን) ከጌታው ጋር ያስታርቅ ዘንድ ብዙ ደከመ: አለቀሰም:: እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን:- "አትዘን! እንደ ልቤ የሆነ: ፈቃዴን የሚፈጽም ዳዊትን አግኝቸዋለሁና እርሱን በእሥራኤል ላይ አንግሠው" አለው::
ቅዱስ ሳሙኤልም ወደ ቤተ ልሔም ሔዶ: ከእሴይ ልጆችም መርጦ ልበ አምላክ ዳዊትን ቀባው: አነገሠውም::

+ቅዱስ ሳሙኤል በተረፈው ዘመኑ ለፈጣሪው እየተገዛ ኑሯል:: ነቢዩ ዘወትር ከእጁ የሽቱ ሙዳይና የቅብዐት እቃ (ቀንድ) አይለይም ነበረ:: እነዚህም የድንግል ማርያም ምሳሌዎች ናቸውና አባ ሕርያቆስ:-
"ሙዳየ ዕፍረት ወቀርነ ቅብዕ ዘሳሙኤል" ብሎ አመስግኗታል::

+ነቢዩም በወገኖቹ መካከል በዚሕች ቀን አርፏል:: እሥራኤልም አልቅሰውለታል:: ዛሬ ቅዱሱ ነቢይ ለአገልግሎት የተጠራበት ቀን ነው::

+" ቅዱስ ሱርያል ሊቀ መላዕክት "+

+ከታላላቅ ሊቃናት አንዱ የሆነው ቅዱስ ሱርያል ክብሩ ብዙ ቢሆንም ብዙ ምዕመናን አያውቁትም:: የመላእክት መዓርግ ሲነገር ሚካኤል: ገብርኤል: ሩፋኤል ብሎ ቀጥሎ የሚመጣው ሱርያል ነው::

+በ3ቱ ሰማያት ካሉት 9ኙ ዓለመ መላእክት የአንዱ (የሥልጣናት) መሪ (አለቃ) ነው:: መልአኩ እጅግ ርሕሩሕ እና ተራዳኢ ነውና አንዘንጋው:: ለኖኅ መርከብርን ያሳራው: ከጥፋት ውሃም ያዳነው ይህ ቅዱስ መልአክ ነው::

+በገድለ ሰማዕታትም ላይ እንደተጠቀሰው የሰማዕታት ረዳትና አዳኝም ነው:: ቅዱስ ሱርያል በሌላ ስሙ "እሥራልዩ" ይባላል:: "የእሥራኤል ረዳት" እንደ ማለት::

=>ቸሩ አምላከ ቅዱሳን ስለ አባቶቻችን ብሎ ይማረን:: ከበረከታቸውም ያድለን::

=>ነሐሴ 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1."12ቱ" ደቂቀ ያዕቆብ (እሥራኤል)
2.ቅዱስ ሳሙኤል ነቢይ (የተጠራበት)
3.ቅዱስ ሱርያል ሊቀ መላእክት
4.ቅዱስ ብንያሚንና እህቱ አውዶከስያ (ሰማዕታት)
5.ቅዱስ ፊቅጦርና እናቱ ሣራ
6.አባ ባስልዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮዽያ (የተሾሙበት)

በ 27 የሚከበሩ ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት
1.የጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በዓለ ስቅለት
2.አቡነ መብዐ ፅዮን ጻድቅ
3.ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ)
4.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
5.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
6.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት
7.ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት

=>+"+ እነዚህም ሁሉ አሥራ ሁለቱ የእሥራኤል ነገዶች ናቸው:: አባታቸው የነገራቸው ይህ ነው:: ባረካቸውም:: እያንዳንዳቸውን እንደ በረከታቸው ባረካቸው:: +"+ (ዘፍ. 49:28)
=>+"+ በመንፈስም ወደ ታላቅና ወደ ረዥም ተራራ ወሰደኝ:: የእግዚአብሔርም ክብር ያለባትን ቅድስቲቱን ከተማ ኢየሩሳሌምን ከሰማይ: ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አሳየኝ . . . አሥራ ሁለት ደጆችም ነበሯት:: በደጆቹም አሥራ ሁለት መላእክት ቆሙ:: የአሥራ ሁለቱም የእሥራኤል ልጆች ነገዶች ስሞች ተጽፈውባቸው ነበር:: +"+ (ራዕይ. 21:11)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለቅዱስ እንድርያኖስ ሰማዕት እና ለታላቁ አባ ቢጻርዮን ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ እንድርያኖስ ሰማዕት †††

††† ቅዱሱ በ3ኛው መቶ ክ/ዘ የነበረ አረማዊ ሰው ሲሆን ከከሃዲው መክስምያኖስ ወታደሮችም አንዱ ነበር:: "ሊቀ መሓዛት" ይሉታል: የጐበዛዝቱ አለቃም ነበር:: ይህ ሰው ምንም ክርስቲያን አይሁን እንጂ በልቡ ቅንነት ተገኝቶበታል:: እንደ አሕዛብ ልበ ድንጋይ አልነበረም::

በወጣትነቱም አንዲት ደመ ግቡ ሴት አግብቷል:: ይህች ሴት ' #ኤልያና' ስትባል የተባረከች ክርስቲያን ናት:: እርሱ ግን አያውቅም:: ከተጋቡ ከዓመታት በሁዋላ ጌታ እግዚአብሔር ስለ ሚስቱ ጸሎት በጐ ጐዳና ሊመራው ፈለገ::

እንድርያኖስ ሁሌም በየቀኑ ክርስቲያኖች ደማቸውን ሲያፈሱ ይመለከታል:: የትእግስታቸው መጠንም ይገርመው ነበር:: በተለይ አብዛኞቹ በመከራው ደስተኞች ነበሩ:: ነገሩ ግራ ቢያጋባው 24 ባለንጀሮች ሊገደሉ ወደ ታሠሩበት ቦታ ሒዶ ጠየቃቸው::

"ምን ልታገኙ ነው ግን ይሕንን ሁሉ ስቃይ በአኮቴት (በምስጋና) የምትቀበሉት?" ቢላቸው "በሰማይ በክርስቶስ ዘንድ የሚጠብቀንን የክብር ሕይወት ሥጋዊ አንደበት አከናውኖ መናገር አይቻለውም:: ዝም ብሎ 'ዕጹብ: ዕጹብ' እያሉ የሚያደንቁት ነው እንጂ" አሉት::

እርሱም ተደላድሎ ተቀምጦ "እስኪ በደንብ አስረዱኝ" አላቸው:: ከዓለም መፈጠር እስከ ጌታችን የማዳን ሥራ: አልፎም ስለ ፍርድ ቀን በጥዑም አንደበታቸው አስተማሩት:: ቅዱስ እንድርያኖስ በቅጽበት ልቡ ወደ ክርስቶስ ፍቅር ሸፈተ::

በፍጥነት ተነስቶ የራሱን ስም ከሰማዕታቱ 25ኛ አድርጐ አጻፈ:: ንጉሡ ይሕንን ሲሰማ "አብደሃል" ቢለው ቅዱሱ መልሶ "የለም! ዛሬ ገና ከእብደቴ ተመለስኩ" በማለቱ ከ25ቱ ቅዱሳን ጋር ታሠረ:: ቅድስት ኤልያና (ሚስቱ) ነገሩን ስትሰማ ፈጽሞ ደስ አላት::

ወደ እስር ቤት ሒዳ "አይዞህ በርታ! ስለ ክርስቶስ የሞትክ ቀን ብቻ እኮራብሃለሁ" ብላ: እግራቸውን አጥባቸው ተመለሰች:: በሚገደሉበት ቀንም ልሰናበታት ብሎ ቅዱስ እንድርያኖስ ቢመጣ ቅድስት ኤልያና ቤቷን ዘግታ ገሠጸችው:: እርሷ ክዶ የመጣ መስሏት ነበር::

እርሱ ግን የሚስቱን የእምነት ጥንካሬ ተረዳ:: ቅዱሱና 24ቱ ቅዱሳን ለቀናት ብዙ መከራን እየተቀበሉ ሰነበቱ:: አካላቸውን እየቆራረጡ: ደማቸውን እያፈሰሱ ሆዳቸውንም እየቀደዱ መከራን አጸኑባቸው:: በመጨረሻው በዚህች ቀን ሲገደሉ ቅድስት ኤልያና "የእኔን ባል አስቀድሙት" አለች:: (የሌሎቹን አይቶ እንዳይደነግጥ ነው)

እንዳለችውም የእርሱንና የባልንጀሮቹን ጭን ጭናቸውን እየሰበሩ ገድለዋቸዋል:: ቅድስት ኤልያናንም መሣፍንቱ "ካላገባንሽ" እያሉ ሲያስቸግሯት ተሰዳ ሒዳ ከሰማዕታቱ መቃብር ላይ አለቀሰች:: ጌታም ጠርቷት እዚያው ዐረፈች::

††† ታላቁ አባ ቢጻርዮን †††

ታላቁ ገዳማዊ ሰው የመጀመሪያ መነኮሳት ከሚባሉ አባቶች አንዱ ሲሆን ዓለምን ንቆ ከመነነ በሁዋላ ከአባ #እንጦንስ ዘንድ መንኩሷል:: ከእርሳቸው ዘንድ በረድእነት ለብዙ ዓመታት አገልግሏል:: አገልግሎቱን በፈጸመ ጊዜም አስኬማን ተቀብሎ ወደ በርሃ ወጥቷል::

ምንም የራሱን ገዳም ባይመሠርትም በ4ኛው መቶ ክ/ዘ የምናኔ ሕይወት እንዲስፋፋ ካደረጉ አበው እርሱ ዋነኛው ነው:: በተጋድሎ ዘመኑም የሚታወቅባቸው ነገሮች አሉ:: ከእነሱም ጥቂት እንጠቅሳለን:: አባ ቢጻርዮን:-
1.ጾሙም ሆነ ጸሎቱ በ40 ቀናት የተወሰነ ነበር:: ጾምን ከጀመረ ያለ 40 ቀን እህል አይቀምስም:: ለጸሎት ከቆመም የሚቀመጠው ከ40 ቀናት በሁዋላ ነው::
2.ሁሌም በየበርሃው እየዞረ ያለቅሳል:: "ምነው" ሲሉት "ወገኖቼ አለቁብኝ: ደሃም ሆንኩ" ይላቸው ነበር:: እንዲህ የሚለው አጋንንት ብዙ ነፍሳትን እየነጠቁ ሲወስዱ ስለሚመለከት ነው::
3.በየገዳማቱ እየለመነ ለነዳያን ያከፋፍል ነበር::
4.ሐፍረቱን ከሚሸፍን ጨርቅ በቀር ምንም ልብስ አይለብስም ነበር::
5.ውዳሴ ከንቱን አምርሮ ይጠላ ነበር::
6.በባሕር ላይ ተራምዶ ሲሔድና እግሮቹ ሳይርሱ ሲቀሩ አበው ተመልክተዋል::
7.መርዝነት ያለውን ውሃም ጣፋጭ አድርጐታል::

††† ቅዱሱ ድውያንን ፈውሶ: አጋንንትን ከአካባቢው አሳዶ: ብዙ ፍሬ አፍርቶ: ገዳም ውስጥ በገባ በ57 ዓመቱ በመልካም ሽምግልና ዐርፏል::

††† ቸር አምላክ በክብረ ቅዱሳን ይከልለን:: ከበረከታቸውም ያብዛልን::

††† ነሐሴ 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ እንድርያኖስ ሰማዕት
2."24ቱ" ሰማዕታት (ማሕበሩ)
3.ቅድስት ኤልያና (ሚስቱ)
4.ታላቁ አባ ቢጻርዮን ገዳማዊ
5.ቅዱስ ኤልያኖስና እህቱ አውዶክስያ (ሰማዕታት)

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
2.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
3.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
4.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
5.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)
6.ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ

††† "ነገር ግን የሆነው ሁሉ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን: የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን ከእግዚአብሔር ነው:: #እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከእርሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና: በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር:: በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ:: እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማለድ ስለ ክርስቶስ መልእክተኞች ነን:: ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን::" †††
(2ቆሮ. 5:18)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ቅዱስ ጳውሎም "ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን … ይህም ድንቅ አይደለም ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና እንዲህ አገልጋዮቹ ደግሞ የጽድቅን አገልጋዮች እንዲመስሉ ራሳቸውን ቢልጡ ታላቅ ነገር አይደለም፡፡ ፍጻሜአቸውም እንደ ሥራቸው ይሆናል፡፡" /ገላ ፩÷፰-፱ ፪ቆሮ ፲፩÷፩፬-፲፭፡፡/

አንዳንድ ተቃዋሚዎች የክርስቲያን ማተብ ማሰር ልምድ ከአረማውያን የተሰወረ ነው ይላሉ፡፡ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ የማያምኑ የተረፈ አይሁድ አባባል ስለሆነ ተቃውሞውን ዋጋ ሳንሰጠው በትዕግስት እናልፈዋለን፡፡ ስለ እኛ ሞቶ የተነሳውን ጌታ ባለማመናቸው የሚናገሩት ስለሆነ ቅዱስ ጳውሎስ የነገረንን ምክር በማስታወስ ማተባችንን እናጠብቃለን፤ "ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል መከራ ወይስ ጭንቀት፤ ወይስ ስደት ወይስ ረሃብ ወይስ ራቁትነት ወይስ ፍርሃት ወይስ ሰይፍ ነውን? ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደተጻፈ ነው፡፡ በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን፡፡

ከዚህችም ዓለም ገዦች አንዱ እንኳ ይህን አላወቁም አውቀውስ ቢሆን የክብርን ጌታ ባልሰቀሉት ነበር፡፡ ይህ የክብር ንጉስ ማነው? የጭፍሮች አምላክ እግዚአብሔር እርሱ የክብር ንጉሥ ነው፡፡" ሮሜ ፰÷፴፭-፴፯ ፤ ፩ቆሮ ፪÷፰ ፤ መዝ ፳፫÷፲

እንደ ውሻ በአንገታችሁ ማዕተብ ማሰራችሁ ተብለን በመነቀፋችንም እንደሰትበታለን እንጂ አንከፋም፡፡ ምክንያቱም ውሻ ለጌታው ታማኝ ነው፡፡ ሌሎች የተለከፉ ያበዱ ዘላን ውሾች እንዳይለክፉትና ከሞት እንዳያደርሱት ወይም ወንበዴዎች በሥጋ መርዝ ቀብተው ለሥጋው ሲሳሳ እንዳይገድሉት ትንሽ ጎጆ ሠርቶለት ቢያስረው ለውሻው ሕይወት አስፈላጊ እንደሆነ በሁሉም ያታወቀ ነው፡፡ ቀበሮ ወይም ተኩላ ከሆነ ግን አውሬ ስለሆነ ለማዳ ካልሆነ በስተቀር ማንም አያስረውም ለበጎችም ፀር ስለሆነ ከተገኘ የሚምረው የለም፡፡

በዚሁ አንፃር ክርስቲያን ለክርስቶስ ታማኝ በመሆኑ በነፍሱ ሞግዚት፣ በቄሱ እጅ ከሕፃንነቱ ጀምሮ የድኅነቱ ምልክት በሚሆን አንገቱ በማዕተብ ክርስትና ይታሠራል፡፡ ጌታ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ በብረት ሐብል በብረት ገመድ ስለ እኛ ቤዛ ለመሆን አይሁድ በአንገቱ ታሥሮ መጎተቱን ስለሚያስታውሰን ለታማኝነታችንና ለክርስቲያንነታችን ምልክትነቱ ማረጋገጫ ስለሆነ አናፍርበትም፡፡ በድርሳነ ሰንበት ቅዱስ ያዕቆብ ዘሰሩግ ስለውሻ ታማኝነት ለክርስቲያን ታማኝነት ምሳሌ አድርጎ ገልጾታል "ከልብሰ የአምር እግዚኡ" ውሻ ጌታውን ያውቃል ጌታችንም በቅዱስ ወንጌል ያችን ከነናዊት በውሻ የተመሰለችውን ሴት ስለታማኝነቷ አድንቋታል ልጅዋንም ፈውሶላታል /ማቴ ፲፭÷፳፩-፳፰/

ማዕተብን የሚቃወሙ ሌሎች ጽዳት ያጎድላል በማለት ያመካኛሉ፡፡ የጠንቋይ ክታብ የቃልቻ ግሥንግሥ መሰብሰቢያ ካደረጉት የሥጋ ንጽሕናን ብቻ ሳይሆን የሚያጎድለው የነፍስንም ጽዳት የሚያጎድል መሆኑ እውቅ ነው፡፡ ማተብና መስቀሉ ግን ጽዳት ያጎደለበት ጊዜ ስለሌለ ሰበብ አያዋጣም፤ ስለዚህ የክርስትናችንን ዓርማ የነፍሳችንን ሰንደቅ ዓላማ በነፃነት ስናውለበልብ ለመኖር ያብቃን አሜን፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ማህተብህን በአንገትህ እሰረው ስትሔድ ይመራሃል

ስትተኛ ይጠብቅሃል" ምሳ 6÷21

 

 

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች በአንገታቸው ላይ ክር ያስራሉ ለሕፃናቶቻቸውም ክርስትና ሲነሱ ክር ያስሩላቸዋል በሕፃናቱም ሆነ በአዋቂዎቹ ክርስቲያኖች የሚታሰረው ክር በግዕዝ ማዕተብ በአማርኛ ማተብ ይባላል፡፡ ቃሉ የወጣው ዐተበ ካለው ግዕዛዊ ግሥ ሲሆን ዐተበ ፍቺው አመለከተ ባረከ ማለት ነው፣ ማዕተብ ከዚህ ይወጣል ምልክት ማለት ነው፡፡ ለተጠመቁ ክርስቲያኖች የክር ማዕተብ ለሃይማኖት ምልክትነት ወይም መታወቂያ ከመሆኑ በፊት በብሉይ ኪዳን ዘመን የሃይማኖት አባቶች ከጣዖት አምላኪዎች ተለይተው የሚታወቁበት ምልክት ነበራቸው፡፡




ስለ ታላቁ የሃይማኖት አባት ስለ ፃድቁ አብርሃም የሃይማኖት ማኅተም (ምልክት) ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይላል ሳይገረዝም በነበረው እምነት ያገኘው የፃድቅ ማኅተም የሆነ የመገረዝን ምልክት ተቀበለ" (ሮሜ ፬÷11 ፣ ዘፍ ፲፯÷፱-፲፬)

በሥርዓተ ኦሪት ብኩርና ከጥንት ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ገንዘብ ሆኖ ስለሚቆጠር ብኩርና ላለው ሁሉ የአባት በረከት ከሌሎች ይልቅ በይበልጥና ምርቃት ዕጥፍ ድርብ ሆኖ ስለሚሰጠው ብኩርና ይወደዳል ይፈቀራል ብኩርናን ማቃለል ዋጋ የሌለው ፀፀትን ያስከትል ነበር፡፡ ብኩርና ለዘመነ ሐዲስ ክርስትና ምሳሌ እንደሆነ ይታመናል፡፡

ክርስትናውን ንቆ አቃሎ አለምን መስሎ የሚኖር ሰው በኩርነቱን ለሆዱ ጊዜያዊ ፍላጎት በሸጠው በያዕቆብ ወንድም በኤሳው ተመስሏል፡፡ "ስለ አንድ መብል በኩርነቱን እንደሸጠው እንደ፣ ኤሳው ለዚህ ዓለም የሚመች ሰው እንዳይሆን ተጠንቀቁ ከዚህ በኋላ እንኳ በረከቱን ሊወርስ በወደደ ጊዜ እንደ ተጣለ ታውቃላችሁና በእንባ ተግቶ ምንም ቢፈልገው ለንስሐ ሥፍራ አላገኘምና" (ዕብ ፲፪÷፲፮-፲፯ ዘፍ ፳፭÷፴፬ ፣ ዘፍ ፳÷፵) ብኩርና ለክርስትና ምሳሌ መሆኑ ከላይ ተገልጿል፡፡

ከይሁዳ ትዕማር መንትያ ልጆችን ፀንሳ በምትወልድበት ጊዜ በኩር እጆቹን ሲያወጣ አዋላጅቱ ቀይ ፈትል ለምልክት አስራበታለች፡፡ ይህ ምሳሌያዊ ድርጊት በሐዲስ ኪዳን ሲተረጎም ከትዕማር የተወለደው በኩሩ ዛራ ለክርስቲያን ምሳሌ ሲሆን ቀዩ ፈትል ለክርስትናው ምልክት ለማዕተብ ምሳሌ ሆኗል፡፡

አዋላጂቱ ለአጥማቂው ቄስ ምሳሌ ናት ትዕማር የቤተክርስቲያን ምሳሌ ስትሆን በኋላ የወጣው ፍሬስ በኩሩን ጥሶ ቀድሞ መወለዱና ከቀይ ፈትል አልባ መሆኑ በምሳሌያዊ ትንቢትነት ከቤተክርስቲያን ከጥምቀት የፀጋ ልጅነትን አግኝተው ከተወለዱ በኋላ ክርስትናቸውንና ጥምቀታቸውን ክደው የእውነተኞቹ ክርስቲያኖች ተቃዋሚዎች በመሆን ፊት ከተፈጠረ ጆሮ እንደ ቀንድ ብቅ ያሉ የመናፍቃን ወይም የኢጥሙቃን ኢ-አማንያን ምሳሌ እንደሆኑ ሊቃውንት በትርጓሜ ያስተምራሉ፡፡ (ማቴ ፩÷፫ ዘፍ ፴፭÷፳፮-፴) በዛራ ልማድ ጌታችን ከድንግል ማርያም በተወለደ ጊዜ እመቤታችን አውራ ጣቱን በክር አስራዋለች፡፡ ቅ/ገብርኤል ለእረኞች ተገልጦ ምልክቱን እንዲህ ሲል ነግሯቸዋል "ወከመዝ ትእምርቱ ለክሙ ትረክቡ ሕፃነ እሱረ መንኮብያቲሁ…" ምልክቱ ይህ ነው ሕፃኑ አውራ ጣቱ ታስኖ ታገኙታላችሁ፡፡" ሉቃ ፪÷፲፪ ማስረጃው "ወወለደት ወልደ ዘበኩራ ወአሠርቶ መንኮብያቲሁ የበኩር ልጅዋን ወለደች አውራ ጣቱን አሰረችው ሉቃ ፪÷፯

በመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር የታተመው የአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ የተወሰነውን ገድፎታል፡፡ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የታተመውን ግዕዝና አማርኛ ነጠላ ትርጉም ሐዲስ ኪዳን ብንመለከት እናገኘዋለን፡፡ ድንግል ማርያም አውራ ጣት ማሰሯ ለክርስቲያኖ ማዕተብ ማሠር አብነት ሆኗል፡፡ ጣቱን ማሠሯ ያለምክንያት አልነበረም፡፡ ፩ኛ/ ሕፃን ስለሆነ እንዲያፀናው ፪ኛ/ ጣቱ ባይታሠር ምትሐት ነው ሰው አልሆነም ለሚሉ መናፍቃን ለክህደታቸው ምክንያት ባገኙ ነበርና ምክንያት ለማሳጣት ፫ኛ/ ቀደም ብለን እንደገለጽነው ልማዳችንን አስቀረብን እንዳይሉ በዛራ ልማድ ፬ኛ/ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ በዕለተ ዓርብ ከመስቀል አውርደው እንዲህ አድርገው ይገንዙሃል ለሰው ቤዛ ለመሆን ልትታሠር መጣህን? ስትል ነው፡፡ በማለት መምህራነ ቤተክርስቲያን (ሊቃውንት) በአንድምታ ትርጓሜያቸው ያትታሉ፡፡

በኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ዘንድ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ማተብ የማሠር ልምድ የጀመረው በሃይማኖት አበው በድርሳነ ያዕቆብ መረጃው እንደሚያስረዳው ከልደተ ክርስቶስ በኋላ በእስክንድርያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በአምስተኛው ምዕተ ዓመት ያስተምር በነበረው በሊቀ ጳጳሱ በያዕቆብ ዘእልበረዳኢ ዘመነ ስብከት ነበር፡፡

በኢትዮጵያ ክርስትና የገባው በዘመነ ሐዋርያት መሆኑ ቢታወቅም የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በመንበረ ጵጵስና ከሌሎች ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት ጋር የእኩልነት ማዕረግ ያገኘችው በ፬ኛው ምዕተ ዓመት በቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡ በዚህ ዘመን አቡነ ሰላማ በሰሜን ያሉትን አጥምቀው ወደ ክርስትና ሲያስገቡ ለክርስትናቸው ምልክት ከግንባራቸው ላይ እየበጡ መስቀለኛ ምልክት ያደርጉላቸው እንደነበር ይተርካል እስከአሁንም አልፎ አልፎ በሰሜናውያን ዘንድ በመብጣትም ሆን በንቅሳት ለክርስትናቸው ምልክት መስቀል ከግንባራቸው ይታያል፡፡ የማዕተብ ማሠር ልምድ ከግብጽ ቤተክርስቲያን ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ ይሠራበት ጀመር በ፱ኙ ቅዱሳን ዘመንም እየተስፋፋ ሔዶ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በቤተክርስቲያን ክርስትና ለሚነሱ ሁሉ ማዕተብ ማሠር ትውፊት ሥርዓት ሆኖ ቆይቷል፡፡

ቀደም ብለን እንደገለጽነት የማዕተብ ማሰር ልምድ በግብጽ ቤተክርስቲያን ያዕቆብ ዘእልበረዳኢ ሲያስተምር እንደጀመረው ጠቅሰናል ያዕቆብ ዘእልበረዳኢ የሶርያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባት ነው፡፡ መምህሩ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ የእስክንድርያው ሊቀጳጳሳት ስለ ተዋሕዶ ሃይማኖት ሲመሰክር በግድ በቁስጥንጥንያው ንጉስ በመርቅያን ተፅዕኖ በንግስት ብርክልያ በመለካውያን (ልዮናውያንና ንስጥሮሳውያን) ግፊትና ተቃውሞ መከራ ሲቀበል ሳለ በብርክልያ ደንገጡሮች ጽሕሙ ተነጭቶ ጥርሶቹ ረግፈው ስለነበር የተነጨ ጽሕሙን የረገፉ ጥርሶቹን በመሐረም ቋጥሮ "ዝንቱ ፍሬ ሃይማኖቱ ለእግዚአብሔር ለእግዚአብሔር የማናቀርብለት የሃይማኖት ፍሬ ይህ ነው" በማለት ለእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን በያዕቆብ ዘእንበረዳኢ እጅ ልኮለታል፡፡ እሱም ስለ ሃይማኖት በደሴተ ጋግራ ታሥሮ ሙቷል፡፡

ደቀመዝሙሩ ቅዱስ ያዕቆብ አልባሌ መስሎ በሶርያ ብቻ ሳይሆን በእስክንድርያም የሴት ቀሚስ ሳይቀር ለብሶ ሲያስተምር ንስጥሮሳውያን ከጉባኤው እየገቡ ስላስቸገሩት ኦርቶዶክሳውያንን ከመናፍቃን ለመለየት ከእግዚአብሔር ባገኘው ምልክት ጥቁር ቀይ ብጫ ክሮች አንድ ላይ ፈትሎ በአንገታቸው ላይ ያስርላቸው ጀመር ሌሊት ሌሊት ሲያስተምርና ሲፀልይ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ጥርሶቹ እንደ ፋና ያበሩለት ነበር፡፡ ይህም በተአምራት የተፈፀመ ነው ሶስት ቀለማት ያላቸው ክሮች የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ሲሆኑ አንድ ላይ መፈተላቸው ወይም አንድ መሆናቸው ቅድስት ሥላሴ ማለት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በመለኮት በህልውና አንድ አምላክ መሆናቸውን ያመለክታል፡፡ ጥቁሩ ክርስቲያን ስለሃይማኖት የሚቀበለው መከራ የሚሸከመው መስቀል ሲሆን ቀጡ በሰማዕትነት ደም የማፍሰስ ብጫው የክርስቲያን ተስፋ የሃይማኖት ምልክት ነው፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ከዚህም በኋላ ወደ ፈጣሪዋ ሄዳ "አቤቱ ፍርድህ ከቶ እንደዚህ ነውን?" እያለች አደነቀች። ጌታም "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ ዲያብሎስን ድል አድርገሽ ጥቂት ምርኮን አገኘሽን" አላት። እስዋም "አዋ ጌታዬ በኃይልህና በቸርነትህ አገኘሁ" አለችው። ከዚህ በኋላ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሚካኤል ጠርቶ "እሊህን ነፍሳት ዓለም ሳይፈጠር ወደ አዘጋጀሁላት ወደ ክርስቶስ ሠምራ መኖሪያ ቦታ ውሰዳቸው" አለው። በዚህ ጊዜ "አቤቱ ፈጣሪየ የእኔ መኖሪያየ ወዴት ነው?" አለችው። ጌታም "መኖሪያሽ ከእናቴ ከድንግል ማርያም ጋራ ነው እነሆ በትረ ማርያም ብየ ሰየምኩሽ መቀመጫሽን ወይም ደረጃሽን ከእርስዋ ቀጥሎ ሁለተኛ አደረግሁልሽ የባለሟልነት ግርማ አጐናጸፍኩሽ አንቺን የሚወዱ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው" አላት። ይህንም ባላት ጊዜ ፈጽማ ደስ ተሰኘች ወደ ኋላዋም መለስ ብላ ብትመለከት ለዓይን የሚያንፀባርቁ ዓሥር አክሊላት አየች። በየአንዳንዳቸው አክሉል ላይ ዐራት ከዋክብት አሉባቸው የእሊህ ከዋክብት ቊጥራቸው ሲደመር አርባ ይሆናል። በዚህ ጊዜ ከስዋ ጋራ የነበረውን መልአክ "እሊህ በላያቸው ብርሃናውያን ከዋክብት ያሉባቸው አክሊላት ለማን የተዘጋጁ ናቸው ሰውነቴ እጅግ አድርጋ ወዳቸዋለችና" አለችው። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም "ላንቺ ቢሆን ደስ አይልሽምን?" አላት። እርስዋም "አዎን ጌታየ ለኔ ቢሆን እወዳለሁ" አለችው። "እንግዲያስ ላንቺ የተዘጋጁ ናቸው" አላት። "በምን ሥራዬ ለኔ ተሰጡኝ" አለችው። "ዐሠርቱ ቃላት ኦሪትን ስድስቱን ቃላተ ወንጌል ጠብቀሽ ቤትሽን ጥለሽ ይህን ዓለም ንቀሽ አጥቅተሽ የክርስቶስን ቀምበር ተሸክመሽ ፈጣሪሽን ስለተከተልሽው ነው" አላት። ይህንንም በአላት ጊዜ እጅግ አድርጋ ተደሰተች ሁሉን ማድረግ የሚችል እግዚአብሔርንም ፈጽማ አመሰገነች።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን። በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኅ_ነሐሴ እና #ገድለ_ቅድስት_ክርስቶስ_ሠምራ)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርቶስ ወደርሱ መጣ ከእርሱም ጋራ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ደግሞ የከበሩ ነቢያትና ሐዋርያት ሁሉም ሰማዕታትና ጻድቃን የጳጳሳት አለቆች የመላእክት አለቆችም ከሠራዊቶቻቸው ጋራ አሉ።

መድኃኒታችንም እንዲህ አለው ወዳጄ ሆይ አንተ በመከራዬ መሰልከኝ እኔም በመንግሥቴ ከእኔ ጋራ እንድትመስለኝ አደርግሃለሁ። እነሆ የዚህ ዓለም ድካምህ ተፈጸመልህ በእኔ ዘንድም የምቀበለው ሆነ ከእንግዲህስ መንግሥተ ሰማያትን ትወርስ ዘንድ ና። እነሆ ስምህን ለሚጠራ መታሰቢያህን ለሚያደርግ ገድልህን ለሚጽፍ ለሚያነበውና ለሚሰማውም ቤተ ክርስቲያንህን ለሚሠራ በስምህ መባ ለሚሠጥ ለድኆችም በስምህ ለሚመጸውት በመታሰቢያህም ቀን ለሚቆርብ ስለ አንተ በጎ ሥራ ለሚሠራ ሁሉ እኔ እስከ ዐሥር ትውልድ እምርልሃለሁ።

አባታችንም እጅግ ደስ አለው ለጌታችንም ሰገደ ጌታችንም ከእርሱ ዘንድ በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ። ከዚህም በኋላ አባታችን በንዳድ በሽታ ታመመ ዕድሜውም ዘጠና ዘጠኝ ዓመት ከስምንት ወር ከአንድ ቀን ሆኖት በለመለመ ዕርጅና አረፈ። በመዘመርና በማመስገን አክብረው ገንዘው በዋሻው ውስጥ ቀበሩት።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስት_ክርስቶስ_ሠምራ

በዚህች ቀን ደግሞ ኢትዮጵያዊት የሆነች ተጋዳይ የከበረች ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው፡፡ በሸዋ ከፍለ አገር በቡልጋ አውራጃ ልዩ ስሟ ቅዱስ ጌዬ የተባለች አገር ነበረች ይህችም የእናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የትውልድ አገሯ ናት። በዚህም አገር በወርቅና በብር በሐር እና በልዩ ልዩ ልብስ በወንድና በሴት አገልጋዮች በፈረስና በበቅሎ የከበረ አንድ ስሙ የታወቀ ሰው ነበር። የዚህ ሰው ስሙ ቅዱስ ደረሳኒ ሲሆን የሚስቱም ስም ቅድስት ዕሌኒ ይባላል ሁለቱም ባልና ሚስቱ እግዚአብሔር የሚፈሩ ደጋግ ሰዎች ስለነበሩ በጎ ሥራቸው በዓለም ሁሉ የታወቀ ነበር። እሊህም ሰዎች በእግዚአብሔር ዘንድ የተመረጠችና የከበረችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን ወልደው በደም ግባቷና በጠባይዋ እየተደሰቱ አሳደጓት ከዚያም የእግዚአብሔርን ሕግጋትና ሥርዓቶችንም ሁሉ አስተማሯት። ባደገችና ለአቅመ ሔዋን በደረሰች ጊዜ የንጉሥ ባለሟል የሆነ ትውልዱ፤ ነገዱ ከአባ ፃሠርጓ ወገን የሆነ ለኢየሱስ ሞዓ ልጅ ለሠምረ ጊዮርጊስ በሕግ አጋቧት። እሱም በዚህ ዓለም ገንዘብ በጣም የከበረ ከመሆኑም በላይ በይበልጥ መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ሰው ነበረ። ከደም ግባቷ የተነሣ ሙሽራይቱ ማለት እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን እጅግ አድርጎ ወደዳት። አሟቷ ኢየሱስ ሞዐም ይህች ብላቴና "በታላቅ ቁም ነገር የተመረጠች ነች" በማለት ትንቢት ይናገርላታል ስለዚህ እንደ እመቤቱ አድርጐ ያከብራት ነበር። ከዚህም በኋላም ለሕጋዊ ባሏ ለሠምረ ጊዮርጊስ ዓሥራ አንድ ልጆች ወለደችለት ከነዚህም መካከል ዘጠኙ ወንዶች ሁለቱ ሴቶች ነበሩ። ልጆችዋንም ሕገ እግዚአብሔርን እያስተማረች በክብር በሥርዓት አሳደገቻቸው።

በዚያን ዘመን የእግዚአብሔር ባለሟል የሚሆን ዓፄ ገብረ መስቀል የሚባል የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበር። እርሱም ዝናዋን ሰምቶ ሥነ ምግባሯን ተመልክቶ ይልቁንም በሷ ላይ ያደረውን ኃይለ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ስለገለጸለት እጅግ አድርጐ ይወዳትና ያከብራት ነበር። ከዕለታት ባንድ ቀን በጸሎትሽ አስቢኝ በማለት በራሱ በንጉሡ ቤተ መንግሥት ከሚያገለግሉ አገልጋዮች ወይም ሠራተኞች መካከል እንዲያገለግሏት 174 አገልጋዮች ላካላት። ዳግመኛም ፈረስና በቅሎ ከነሥራታቸው እንደዚሁም ለነሥታት ሚስቶች የሚገባ ከሐርና ከወርቅ የተሠራ ልብስና የወርቅ ጫማ ላከላት። ነገር ግን እሷ ይህን ሁሉ ክብር አልፈለገችም ይልቁንም ለዓላማየ ዕንቅፋት ወይም ከንቱ ውዳሴ ይሆንብኛል በዚያውስ ወርቁ ጌጡ ልብሱ ተሸጦ ለነዳያን ይመጸወታል ለቤተ ክርስቲያን መባዕ ይሰጣል እኒህን አገልጋዮች ግን ምን አደርጋቸዋለሁ በማለት ወደ እግዚአብሔር እያመለከተች ቆየች።

ከአገልጋዮችዋ መካከል ምግባሯ የከፋ የምታናድዳትና የምታበሳጫት አገልጋይ ነበረች። ከዕለታት በአንድኛው ቀን እናታችን ክርስቶስ ሠምራ በጣም ተበሳጨችና በዚያች አገልጋይ አፍ ውስጥ የእሳት ትንታግ ጨመረችባት። ያም እሳት ትንታግ በአገልጋይዋ ጉረሮ ድረስ ዘለቀና ገደላት። በዚህን ጊዜ ቤተሰቦችዋ መጥተው የአገልጋይቱን አስከሬን ወደሌላ ክፍል ወሰዱት። ብፅዕት ክርስቶስ ሠምራም ደንግጣ ካለችበት ቤት ውስጥ ወደ ሌላው ክፍል ገባችና ወደ ሰማይ አቅንታ "ወይኔ ወዮልኝ ወዮታ አለብኝ የካህን ሚስት ስሆን ነፍስ ገዳይ ሆኛለሁና። ሰውስ ምን ይለኛል ለነፍሴስ ምን እመልስላታለሁ ከእግዲህ ከክርስቲያን ወገን ልቆጠር አይገባኝም በደሌንስ እንደምን አድርጌ ልሸሸሽጋት እችላለሁ" እያለች አለቀሰች።

ከዚህ በኋላ እንዲህ ስትል ለእግዚአብሔር ብፅዓት አደረገች "አቤቱ ይህችን በእኔ እጅ የሞተችውን አገልጋይ ነፍስዋን ከሥጋዋ አዋህደህ ብታሥነሣልኝ ልጆቼን ቤቴን ንብረቴን ትቼ ባለ ዘመኔ ሁሉ አንተን እከተላለሁ። አንተን ከመከተል ከቶ ወደኋላ አልልም። ለሰውነቴ ጌጥ ወይም ግርማ ሞገስ የሚሆናት ወይም የሚሞቃት ልብስ ከቶ አልለብስም ሥጋዬን የሚያረካ ምግብም አልመገብም። አቤቱ ጌታዬ ሆይ ጸሎቴን ስማኝ ልመናዬም በፊትህ ፈጥኖ ይድረስ አቤቱ ፊትህን ከኔ ከባሪያህ አትመልስ"። እንዲህ እንዲህ እያለች በልቅሶና በኀዘን ለብዙ ሰዓት ከጸለየች በኋላ ድካም ተሰማትና ዕረፍት አደረገች። ከዚህ በኋላ ቤተሰቦችዋ እስዋ ወዳለችበት ክፍል መጥተው "እመቤታችን ሆይ ሙታ የነበረችው አገልጋይሽ በእግዚአብሔር ኃይልና በአንቺ ጸሎት ተነሥታለችና ደስ ይበልሽ" አሏት። በዚህ ጊዜ ፈጥና ተነሥታ ደስ እያላት ሙታ የነበረችው አገልጋይ ካለችበት ቦታ ደረሰችና ሕይወት አገኘቻት ከዚያም ቃሏን ከፍ አድርጋ "ልመናዬን ቸል ያላለ ቸርነቱንም ከኔ ከባሪያው ያላራቀ ፈጣሪ ይክበር ይመስገን" ብላ በታላቅ ምስጋና እግዚአብሔር አመሰገነች።

ከዚህ በኋላ አስቀድሞ ከአፏ የወጣውን ከአንደበቷ የተነገረውን ቃል አስባ ልብሰ ምንኵስናዋን ማለት ቆቧን ቀሚሷን አጽፏን መታጠቂያዋን አዘጋጀች። ቤተሰቦቿና አገልጋዮቿም "እመቤታችን ሆይ ይህ የምታዘጋጂው የምናኔ ልብስ ለምንሽ ነው ወይስ ለማን ነው የምታዘጋጂው" አሏት። እርሷም " ሃይማኖት ያስተማሩኝ አባቴ ልብስ አልቆባቸዋል ሲሉ ሰምቼ ለሳቸው ነው የማዘጋጀው" አለቻቸው።

Читать полностью…
Subscribe to a channel