kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#መስከረም_9

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
መስከረም ዘጠኝ በዚህች የመላእክት አለቃ #ቅዱስ_ሚካኤል በሮም አገር ፍሩምያ በምትባል ከተማ ላደረገው ተአምር መታሰቢያ ነው፣ #ቅዱስ_አባት_አባ_ቢሶራ በሰማዕትነት አረፈ፣ #ቅዱስ_ያሳይ_ንጉሥ እረፍቱ ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ሚካኤል

መስከረም ዘጠኝ በዚህች ቀን በሮም አገር ፍሩምያ በምትባል ከተማ ለሆነው ተአምር መታሰቢያ ሆነ። ይህም እንዲህ ነው የሰማይ ሠራዊት አለቃ በሆነ በከበረ መልአክ በሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚታዩ ድንቆችና ተአምራቶች ምክንያት ዮናናውያን ሰዎች ሰይጣናዊ ቅናትን እንደ ቀኑ ከመቅናታቸውም ብዛት የተነሣ በዚያ አካባቢ የሚወርደውን የወንዝ ውኃ በዚያች ቤተ ክርስቲያን ላይ ሊመልሱትና ከሚጠብቃት መጋቢዋ ጋር በውኃ ስጥመት ሊአጠፉአት ፈልገው መለሱት።

የሰማያውያን ሠራዊት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለቤተ ክርስቲያኑ መጋቢ ለናርጢኖስ ተገለጠለት ወደርሱም ቀርቦ ጽና አትፍራ አለው ይህንን ብሎ በእጁ ውስጥ ባለ በትር አለቱን መታው አለቱም ተደንጥቆ እንደ በር ሆነ የዚያ ወንዝ ውኃም በውስጡ አልፎ ሔደ።

ይህንንም ያዩ ምስጉን እግዚአብሔርን አመሰገኑት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልንም አከበሩት። ከዚያች ቀን እስከ ዛሬ የወንዙን ውኃ በዚያች በተሠነጠቀች አለት ውስጥ አልፎ ሲሔድ ያዩታል ወደ መላእክት አለቃ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከቶ አይቀርብም።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አባት_አባ_ቢሶራ

በዚህችም ቀን መጺል የምትባል አገር ኤጲስቆጶስ ቅዱስ አባት አባ ቢሶራ በሰማዕትነት አረፈ።

ይህም ቅዱስ በግብጽ አገር እግዚአብሔርን በምትወድ መጺል በምትባል ከተማ ኤጲስቆጶስ ሆነ። ዲዮቅልጥያኖስም ነግሦ ክርስቲያኖችን በሚያሠቃያቸው ጊዜ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ስም ደሙን ያፈስ ዘንድ ይህ አባት ወደደ።

ሕዝቡንም ሀሉ ሰብስቦ በቤተ መቅደሱ ፊት በዐውደ ምሕረቱ አቆማቸው ሊጠብቁት የሚገባውን ለጽድቅ የሚያበቃቸውን ትእዛዝ ሁሉ አዘዛቸው። ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ስም ደሙን ማፍሰስ እንደሚሻ ነገራቸው ይህንንም በሰሙ ጊዜ ታላቆችም ታናሾችም በላዩ አለቀሱ።

የሙት ልጆች እንሆን ዘንድ የምትተወን ምን ያደርግልሃል እኛስ እንድትሔድ አንለቅህም አሉት ሊይዙትም ቃጡ ግን አልተቻላቸውም ተውትም እርሱም ወደ ክብር ባለቤት ክርስቶስ አደራ አስጠበቃቸውና ሰላምታ ሰጥቷቸው ከእነርሱ ዘንድ ወጥቶ ተጓዘ። እነርሱም መሪር ልቅሶን እያለቀሱ ሸኙት።

ስማቸው ቢስኮስ ፊናቢክስ ቴዎድሮስ የሚባሉ ኤጲስቆጶሳት አብረውት ሔድ መኰንኑ ወደ አለበት አገርም ደርሰው የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ። እርሱም መኰንኑ አሠቃያቸው ኤጲስቆጶሳትም እንደሆኑ አውቆ ሥቃያቸውን አበዛ እሊህ አባቶች ግን በታላቅ ትዕግሥት የጸኑ ናቸው። ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስ ያጸናቸዋልና።

ከዚህም በኋላ መኰንኑ ራሶቻቸውን በሰይፍ ይቆርጧቸው ዘንድ አዘዘ የሕይወት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። የቅዱስ ቢሶራ ሥጋው ግን ንሲል በሚባል አገር እስከ ዛሬ ይኖራል።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ያሳይ_ንጉሥ

በዚችም ቀን ተጋድሎውን በዛፍ ላይ ሆኖ የፈጸመ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘ ንጉሥ ያሳይ አረፈ።

በቀደመው ዘመን መንግስታቸውን ትተው ከመነኑ ነገሥታት አንዱ ቅዱስ ያሳይ ነው። ምናኔ በቁሙ ከባድ ነው። መንግስትን፣ ዙፋንን፣ ክብርን ትቶ መመነንን ደግሞ ከማድነቅ በቀር እንዲህ ብለው ሊገልጹት ይከብዳል።

ቅዱስ ያሳይም መንግስቱን ትቶ ልምላሜ ወደሌለበት ደረቅ በርሃ ሔደ። በዚያም ከአንዲት ዛፍ በቀር ምንም ነገር አላገኘም። በዚያች ደረቅ ዛፍ ላይ ወጥቶ ለዓመታት በጾምና በጸሎት ተጋደለ።

በዘመነ ተጋድሎው ከዛፏ አልወረደም ሰውም አይቶ አያውቅም። በመጨረሻም ስለ ቅድስናው ዛፏ ለምልማለች። እርሱም በዚህች ቀን ዐርፏል።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም ቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መስከረምና_ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/WmHUEkshTP0?si=lvHvb3oZi4LFUeSo

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

‹‹‹‹ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፤፤››››

መስከረም 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

+"* ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት *"+

+ቅዱሳን ነቢያት እጅግ ብዙ ናቸው:: ከፈጣሪያቸው የተቀበሉት ጸጋም ብዙና ልዩ ልዩ ነው:: ያም ሆኖ ከሁሉም ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ይበልጣል:: መጽሐፍ እንደሚል ከእርሱም በፊት ቢሆን ከእርሱ በሁዋላ እንደ እርሱ ያለ ነቢይ አልተነሳምና:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

*ዓለም በተፈጠረ በ3,600 ዓመት እሥራኤል በረሃብ ምክንያት 75 ራሱን ወደ ምድረ ግብፅ ወረደ:: በዚያም ልጆቹና የልጅ ልጆቹ ለ215 ዓመታት ተከብረው: ለ215 ዓመታት ደግሞ በባርነት: በድምሩ ለ430 ዓመታት በምድረ ግብፅ ኑረዋል::

*በባርነት ዘመናቸውም 'ራምሴና ጋምሴ' የሚባሉ 2 ከተሞችን (ዛሬ ፒራሚዶች የምንላቸውን) ገንብተዋል:: ግፋቸው እየበዛ ሲሔድ ግን ጩኸታቸው ቅድመ እግዚአብሔር ደረሰ:: ያድናቸውም ዘንድ አንድ ቅዱስ ሰው እንዲወለድ አደረገ:: ይኽም ሰው ሙሴ ይባላል::

*ወላጆቹ መታመናቸውን በፈጣሪያቸው ያደረጉ 'እንበረም'ና 'ዮካብድ' ሲሆኑ ከሌዊ ነገድ ናቸው:: ከሙሴ ውጪም አሮንና ማርያምን ወልደዋል:: ቅዱስ ሙሴ በተወለደበት ወራት ወንድ የእሥራኤል ሕጻናት ይፈጁ ነበር:: ጌታ ግን በገዳዮቹ ልቡና ርሕራሔን አምጥቶ አትርፎታል::

*በኋላም በ3 ወሩ ዓባይ ወንዝ ላይ ጥለውት ተርሙት (የፈርኦን ልጅ ናት) ወስዳ በቤተ መንግስት አሳድጋዋለች:: 'ሙሴ' ያለችውም እርሷ ናት:: 'ዕጉዋለ ማይ / እማይ ዘረከብክዎ' (ከውሃ የተገኘ) ለማለት ነው:: ወላጆቹ ያወጡለት ስም ግን 'ምልክአም' ይባላል:: ገና ሲወለድ ፊቱ እንደ መልአክ ያበራ ነበርና::

*ቅዱስ ሙሴ 5 ዓመት በሆነው ጊዜ ፈርኦንን በጥፊ በመማታቱ ለፍርድ ቀርቦ እሳትን በመብላቱ አንደበቱ ኮልታፋ ሆኖ ቀርቷል:: እናቱ ዮካብድ ሞግዚት ሆና ስላሳደገችው 40 ዓመት በሆነው ጊዜ የፈርኦንን ቤት ምቾትና የንጉሥ ልጅ መባልን ናቀ:: ቅዱስ ዻውሎስ እንደሚለው በአሕዛብ ቤት ካለ ምቾት ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራን ሊቀበል ወዷልና:: (ዕብ. 11:24)

*አንድ ቀንም ለዕብራዊ ወገኑ ተበቅሎ ግብጻዊውን ገድሎት ወደ ምድያም ሸሸ:: በዚያም ለ40 ዓመታት የካህኑን ዮቶርን በጐች እየጠበቀ: ኢትዮዽያዊቱን ሲፓራን አግብቶ ኖረ:: ልጆንም አፈራ:: 80 ዓመት በሞላው ጊዜ እግዚአብሔር በደብረ ሲና ተናገረው:: ሕዝቡንም ከባርነት ቀንበር እንዲታደግ ላከው::

*ቅዱስ ሙሴም ከወንድሙ አሮንና ከአውሴ (ኢያሱ) ጋር ግብጻውያንን በ9 መቅሰፍት: በ10ኛ ሞተ በኩር መታ:: እሥራኤልንም ነጻ አወጣ:: ሊቀ ነቢያት የሠራቸው ሥራዎች ተዘርዝረው የሚያልቁ አይደሉም::

>እርሱ ባሕረ ኤርትራን ከፍሎ ሕዝቡን በደረቅ አሻግሯል::
>ግብጻውያንን ከነሠረገሎቻቸው በባሕር ውስጥ አስጥሟል::
>ለሕዝቡ መና ከደመና አውርዷል::
>ውሃን ከጨንጫ (ከዓለት) ላይ አፍልቁዋል::
>በብርሃን ምሰሶ መርቷቸዋል::
>በ7 ደመና ጋርዷቸዋል::
>ጠላቶቻቸውን ሁሉ ድል ነስቶላቸዋል::

*ስለዚህ ፈንታ ግን ወገኖቹ ብዙ አሰቃይተውታል:: እርሱ ግን ደግ: ቅንና የዋህ ሰው ነውና ብዙ ጊዜ ራሱን ለእነሱ አሳልፎ ሰጥቷል:: "ሙሴሰ የዋህ እምኩሎሙ ደቂቀ እሥራኤል" እንዲል:: (ዘኁ. 12:3) ቅዱስ ሙሴ ለ40 ዓመታት ሕዝቡን ሲመራ ከእግዚአብሔር ጋር ለ570 ጊዜ ተነጋግሯል::

*ከጸጋው ብዛትም ፊቱ ብርሃን ስለ ነበር ሰዎች እርሱን ማየት አይችሉም ነበር:: ታቦተ ጽዮንንና 10ሩ ቃላትን ተቀብሎ ጽላቱ ቢሰበሩ ራሱ ሠርቶ በጌታ እጅ ቃላቱ ተጽፈውለታል:: "የቀረው የቅዱሱ ሕይወት በመጻሕፍተ ኦሪት (በብሔረ ኦሪት) ውስጥ የተጻፉ አይደሉምን?"

*እኔ ግን ደካማ ነኝና ይህቺ ትብቃኝ:: ቅዱስ: ክቡር: ታላቅ: ጻድቅ: ነቢይና ደግ ሰው ቅዱስ ሙሴ በ120 ዓመቱ ዐርፎ በደብረ ናባው ሊቃነ መላእክት ቅዱሳን ሚካኤል: ገብርኤልና ሳቁኤል ቀብረውታል:: መቃብሩንም ሠውረዋል:: (ይሁዳ. 1:9)

+" ቅዱስ ዘካርያስ ካህን "+

+ስም አጠራሩ የከበረ: ሽምግልናውም ያማረ ቅዱስ ዘካርያስ የቅድስት ኤልሳቤጥ ባል: የመጥምቁ ዮሐንስም አባት ነው:: በእሥራኤል ታሪክ የመጨረሻው ደግ ሊቀ ካህናት ነው:: ይህ ቅዱስ ሰው ከአሮን ወገን ተወልዶ: በሥርዓተ ኦሪት አድጐ: በወጣትነቱ መጻሕፍተ ብሉያትን ተምሮ: ሊቀ ካህንነቱን እጅ አድርጉዋል::

*በጐልማሳነቱም ቅድስት ኤልሳቤጥን አግብቶ በደግነትና በምጽዋት አብሯት ኑሯል:: ከኢያቄምና ከሐና ጋር ቅርብ ወዳጆች ነበሩና አልተለያዩም:: ቅዱሱ ዘወትር ለማስተማር: ለመስዋዕትና ለማዕጠንት ይተጋ ነበር:: ጸሎቱና እጣኑም ወደ ቅድመ እግዚአብሔር ይደርስለት ነበር::

*እስኪያረጅ ድረስ ባይወልድም አላማረረም:: ደስ የሚለው ደግሞ እመ ብርሃን ድንግል ማርያምን ከወላጆቿ ተቀብሎ ለ12 ዓመታት ያሳደጋት እርሱ ነው:: ዘወትር መላእክት ከበው ሲያገለግሏት እየተመለከተ ይመሰጥ ነበረ::

*የልጅ አምሮቱን የሚረሳው ከእርሷ ጋር ሲሆን ነው:: እንደ አባት አሳደጋት: እንደ እመቤትም ጸጋ ክብር አሰጥታዋለች:: እድሜው መቶ ዓመት በሆነ ጊዜ በቅዱስ ገብርኤል ተበስሮ ዮሐንስን አገኘ:: ለ9 ወራት የተዘጋ አንደበቱ ሲከፈት "ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ እሥራኤል" ብሎ ትንቢትን ተናገረ::

*ሔሮድስ ሕጻኑን ሊገድለው በፈለገ ጊዜም ሕጻኑን ቅዱስ ዮሐንስን ወስዶ በክንፈ ኪሩብ ላይ አስቀመጠውና መልአክ ወደ በርሃ ወሰደው:: ቅዱስ ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደሱ መካከል 70: 80 ዓመት በንጽሕና ባገለገለበት ቦታ ላይ ገደሉት::

*ሥጋውን አምላክ ሰውሮት የፈሰሰ ደሙ እንደ ድንጋይ ረግቶ ሲጮህ ተገኝቷል:: ለ68 ዓመታትም ደሙ ሲፈላ ኑሯል:: በ70 ዘመን ጥጦስ ቄሣር አይሁድን ሲያጠፋቸው ደሙ ዝም ብሏል:: ይህ ቅዱስ: ጻድቅ: ነቢይና ካህን ስሙ በተጠራ ጊዜ ሲዖል ደንግጣ ነፍሳትን እንደምትሰጥ ሊቃውንት ነግረውናል:: (ማቴ. 23:35)

+" ቅዱስ አሮን ካህን "+

+በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት የቅዱሱ ካህን የአሮን በትር ሳይተክሏትና ውሃ ሳያጠጧት ለምልማ: አብባ: አፍርታ የተገኘችው በዚህ ቀን ነው:: ዳታን: አቤሮንና ቆሬ ከተከታዮቻቸው ጋር በፈጠሩት ሁከት ምድር ተከፍታ ከዋጠቻቸው በሁዋላ እግዚአብሔር የ12ቱን ነገደ እሥራኤል በትር ሰብስቦ ሲጸልይበት እንዲያድር ሙሴን አዞት: እንዲሁ ሆነ::

+በነጋም ጊዜ ይህቺ ደረቅ የነበረች በትረ አሮን 12 ፍሬ (ለውዝ: ገውዝ: በኩረ ሎሚ) አፍርታ ተገኘች:: (ዘኁ. 17:1-11) ለጊዜው ክህነት ከቤተ አሮን እንዳይወጣ ምልክት ሆናለች:: ለፍጻሜው ግን ምሳሌነቷ ለድንግል ማርያም ነው:: እመ ብርሃን የወንድ ዘር ምክንያት ሳይሆናት አምላክን ወልዳ ተገኝታለችና::

"ጸናጽል ዘውስተ ልብሱ ለአሮን ካህን: ወዓዲ በትር እንተ ሠረጸት: ወጸገየት: ወፈረየት" እንዳለ አባ ሕርያቆስ:: (ቅዳሴ ማርያም)

+የእነዚህ ቅዱሳን ነቢያትና ካህናት አምላክ ደግነታቸውን አስቦ: ከግራ ቁመት: ከገሃነመ እሳትም ይሰውረን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::

+መስከረም 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2.ቅዱስ ዘካርያስ ካህን (ጻድቅ ነቢይ)
3.ቅዱስ አሮን ካህን
4.ቅዱስ ዲማድዮስ ሰማዕት

ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ)
3.አባ ብሶይ (ቢሾይ)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እንዲህም ከሆነ የጦር መሣርያ የጦር ሠራዊትም አንሻም…››ብለው ደብዳቤ ጽፈው እንደላኩ ነገሥታቱ ያለ ምንም ጦርነት የፋርስን ሀገር ሰዎች አሸንፈው ወደ ሀገራቸው መልሰዋቸዋል፡፡አቡነ ሳዊርያኖስ በገብላ አገር ኤጲስቆጶስነት ከተሾሙ በኋላ የሙሴን ሕግ በማወቁ የሚመካ አንድ ስሙ ስቅጣር የሚባል አይሁዳዊ ወደ እርሳቸው መጥቶ ተከራከራቸው፡፡የጻድቁንም ቃላቸውን ሊሰማቸው አልቻለም ነበር፡፡በዚህም ጊዜ ጌታችን ለአቡነ ሳዊርያኖስ ተለጠላቸውና ‹‹እኔ ካከበርኳቸው ወገኖች ይሆናል›› በማለት እንደሚያምን ነገራቸው፡፡ያም አይሁዳዊ ወደቤቱ በገባ ጊዜ ወገኖቹ አይሁድ ሲኦል ውስጥ ሆነው ሲሠቃዩ በራእይ ተመለከተ፡፡‹‹ከሃዲዎች ዘመዶችህን እነሆ እይ›› የሚል ድምንም ሰማ፡፡በማግሥቱም ይህ አይሁዳዊ ወደ አቡነ ሳዊርያኖስ መጥቶ ከእግራቸው ሥር ወድቆ እንዲያስተምሩትና የክርስቶስ ወገን እንዲያደርጉት ለመናቸው፡፡እርሳቸውም አስተምረው ከሀገሩ ሰዎች ጋር አንድ ላይ አጠመቋቸው፡፡የቀሩት ብዙ አይሁድም በጌታችን አምነው ተጠመቁ፡፡አቡነ ሳዊርያኖስ ሥራየኛ ጠንቋዮችን ሁሉ እያሳመኑ አስተምረው አስጠምቀዋቸዋል፡፡አቡነ ሳዊርያኖስ ስለ ዮሐንስ አፈወርቅ ስደትና እንግልት ያለችበት ድረስ ሄደው ንግሥት አውዶክስያን ቢመክሯትና ቢገሥጹዋትም በክፋቷ ጸንታ አልሰማቸው ብትል ተመልሰው ወደ አገራቸው ሄደዋል፡፡አቡነ ሳዊርያኖስ ተአምራታቸው

ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም፡፡በጣም ብዙ ድርሳናትን ደርሰዋል፡፡100 ዓመት በሆናቸው ጊዜ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ከ10 ቀን በኋላ በሞት እንደሚያርፉ ነገራቸው፡፡ ሕዝቡንም ጠርተው በሃይማኖት እንዲጸኑ ከመከሯቸውና
ከተሰናበቷቸው በኋላ መስከረም 7 ቀን በሰላም ዐርፈዋል፡፡ይኸውም ዕረፍታቸው የተከናወነው ኤጲፋንዮስ ባረፈ በ2ኛ ዓመቱ ዮሐንስ አፈወርቅ ባረፈ በዓመቱ ነው፡፡ጌታችን የብርሃን ሰረገላ ሰጥቷቸዋል፡፡ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣በጸሎታቸው ይማረን፡፡
+ + + + + + + + + + + + + + +
ሰማዕታቱ ቅድስት ራፊቃ እና አራት ልጆቿ፡- ለቅድስት ራፊቃ እና ለአራት ልጆቿ ማለትም ለአጋቶን፣ ለጴጥሮስ፣ ለዮሐንስና ለአሞን ጌታችን ለሁሉም በራእይ ተገልጦላቸው በስሙ መስክረው ሰማዕት እንሚሆኑ ነገራቸው፡፡አስቀድሞም
ታላቁ አጋቶን በአገሩ ተሹሞ በሥልጣን ሆኖ ነበር። የጌታችንንም የሰማዕትነት ጥሪ ተቀብለው ከላይኛው ግብጽ ከቁስ አውራጃ ተነሥተው በከሃዲው መኮንን በዲዮናስዮስ ፊት ስለ ጌታችን አምላክነት መሰከሩ፡፡መኮንኑም ብዙ ሥቃዮችን አደረሰባቸው፡፡ጌታችንም በተአምራት ከመከራቸው ሲያድናቸው ያየ ብዙ ሰዎች ሲያምኑ መኮንኑ እጅግ ተቆጥቶ ጽኑ ሥቃይ አደረሰባቸው፡፡ማሠቃየትም
በሰለቸው ጊዜ ወደ እስክንድርያው ገዥ አርማንዮስ ዘንድ ላካቸው፡፡ከሃዲው አርማንዮስም ሥጋቸውን ቆራርጦ በመንኮራኩር ውስጥ ጨመራቸው፡፡ነገር ግን ጌታችን ጤነኛ አድርጎ ፈወሳቸው፡፡ዳግመኛም ዘቅዝቀውም ሰቀሏቸው፡፡
አሁንም ጌታችን አዳናቸው፡፡በተአምራተቸውም ብዙዎች በጌታችን አመኑ፡፡በመጨረሻም ራሶቻቸውንም በሰይፍ ቆርጠው ሥጋቸውን ወደ ባሕር ጣሉት፡፡ቅድስት ራፊቃና
አራት ልጆቿም ሰማዕትነታቸውን በዚሁ ፈጸሙ፡፡የታዘዘ መልአክም መጥቶ ለአንዱ ባለጸጋ የቅዱሳኑን ሥጋ ያለበትን ነግሮት እንዲያወጣውና በክብር እንዲያስቀምጠው አዘዘው፡፡ባለጸጋውም የቅዱሳኑን ሥጋቸውን ከባሕሩ
አወጥቶ የመከራ ዘመን እስኪያልፍ በክብር አኖረው፡፡ ከሥጋቸውም ብዙ ተአምራት ተገልጠው ታዩ፡፡ የሰማዕታቱ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣በጸሎታቸው ይማረን፡፡
+ + + + + + + + + + + + + + +
+ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት እመቤታችን ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክን የወለደቻት ቅድስት ሐና ልደቷ ነው፡፡ሐና ማለት ‹‹ጸጋ›› ማለት ነው፡፡አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም እናት ናት፡፡እርሷም ከኢየሩሳሌም አገር ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ትውልድ የሌዊ የሜልኪ ልጅ
ለሆነ ለማጣት ልጁ ናት፡፡የቅድስት ሐና አባት ማጣትና እናቷ ሄርሜላ ከእርሷ በተጨማሪ ሶፍያና ማርያም የሚባሉ ሌሎች ሁለት ሴት ልጆችን ወልደዋል፡፡ቅድስት ሐና ከይሁዳ ነገድ የሆነውን ጻድቅ ኢያቄምን አግብታ ቅድስት ድንግል ማርያምን ወለደች፣ ድንግል ማርያምም መድኃኔዓለም ክርስቶስን ወለደች፡፡ሶፍያ ኤልሳቤጥን ወለደች፣ ኤልሳቤጥም መጥምቁ ዮሐንስን ወለደች፡፡ከሦስቱም ታናሽ የሆነችው ‹‹ማርያም›› የተባለችው የማጣትና የሄርሜላ ልጅ
ደግሞ ሰሎሜን ወለደቻት፡፡ይኽችም ታላቅ እናት ቅድስት ሐና አምላክን በድንግልና ሆና በሥጋ ለወለደችው ለቅድስት ድንግል ማርያም ወላጇ ትሆን ዘንድ የተገባት ሆናለችና ከሴቶች ሁሉ እንደምትበልጥና እንደምትከብር እንረዳ፡፡ ለዓለም ሁሉ ድኅነት የተደረገባትን ልዩ ስጦታ የሆነች ድንግል ማርያምን እርሷ አስገኘቻት፡፡ለክብር ባለቤት ለጌታችን ለአምላችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ አያቱ ሆናለችና ምን ያህል ክብርት እንደሆነችና እግዚአብሔር የመረጣት ንጽሕት ቅድስት እንደሆነች በዚህ ይታወቃል፡፡
ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ ይማረን፡፡
ከገድላት አንደበት
✞ ✞ ✞

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

‹‹‹‹ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፤፤››››

መስከረም 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

+" ቅዱስ ኢሳይያስ ነቢይ "+

+በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የኢሳይያስን ያህል ትንቢት የተናገረ ነቢይ አይገኝም:: ከትንቢቱ ብዛትና ከምስጢሩ ጉልህነት የተነሳ: አንድም ደፋር ስለ ነበር 'ልዑለ ቃል' ተብሎ ተጠርቷል:: ቅዱስ ኢሳይያስ የተወለደው ከክርስቶስ ልደት 800 ዓመታት በፊት ሲሆን ለነቢይነት የተመረጠው ገና በወጣትነቱ ነበር::

+ወላጆቹ 'ኢሳይያስ' (መድኃኒት) ያሉት በትምሕርቱ: በትንቢቱ የጸጋ መድኃኒትነት ስላለው ነው:: እርሱ በነቢይነት በተሾመበት ወራት ሊቀ ካህናቱ አዛርያስ: ንጉሡ ደግሞ ዖዝያን ይባሉ ነበር:: በሊቀ ካህናቱና በንጉሡ መካከል በተነሳ ጠብ ንጉሡ የበላይነቱን ለማሳየት ሃብተ ክህነት ሳይኖረው ሊያጥን ወደ ቤተ መቅደስ ገባ::

+ይህንን የተመለከተው ኢሳይያስ ሊገስጸው ሲገባ 'ወዳጄ ነው' በሚል ዝም አለው:: ፈታሒ እግዚአብሔር ግን ዖዝያንን በለምጽ መታው:: የግንባሩን ለምጽ በሻሽ ቢሸፍነው ከሻሹ ላይ ወጣበት:: በእሥራኤል ለምጽ ያለበት እንኩዋን በዙፋን ከተማ ውስጥም መቀመጥ አይችልምና አስወጡት:: በእርሱ ፈንታም ኢዮአታም ነግሷል::

+ኢሳይያስ ደግሞ እግዚአብሔር በሰጠው አንደበት ሙያ አልሠራበትምና ከንፈሩ ላይ ለምጽ ወጣበት:: እርሱንም ወስደው ጨለማ ቤት ዘጉበት:: ሃብተ ትንቢቱንም ተቀማ:: ቅዱሳን ትልቁ ሃብታቸው ንስሃቸው ነውና በዚያው ሆኖ ንስሃ ገባ: ተማለለ: ጾመ: ጸለየ::

+እግዚአብሔርም ንስሃውን ተመለከተለት:: ከዚያም ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት ኢሳይያስ እግዚአብሔርን በረዥም (ልዑል) ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ: ኪሩቤል ተሸክመውት: ሱራፌል (24ቱ ካህናተ ሰማይ) "ቅዱስ: ቅዱስ: ቅዱስ" እያሉ ሲያመሰግኑት ተመለከተ:: (ኢሳ. 6:1)

+አበው ሲተረጉሙ "አንተ ያፈርከው ዖዝያን እነሆ ሞተ:: እኔ ግን መንግስቴ የዘለዓለም ነው" ሲለው ነው ይላሉ:: ያን ጊዜ እግዚአብሔር "ወደ ሕዝቤ ማንን እልካለሁ?" አለ:: ኢሳይያስም "ጌታየ! እኔ ከንፈሮቼ የረከሱ አለሁ" አለው:: እግዚአብሔርም ሱራፊን ላከለት:: መልአኩም ፍሕም (እሳት) በጉጠት አምጥቶ ከንፈሩን ቢዳስሰው ነጻ:: ሃብተ ትንቢቱም ተመለሰለት:: ይኸውም የሥጋ ወደሙ ምሳሌ ነው::

+ከዚህች ቀን በኋላ ግን ኢሳይያስ የተለየ ሰው ሆነ:: ማንንም የማይፈራ እውነተኛ የልዑል ወታደር ሆነ:: ከኦዝያን በሁዋላ በየዘመናቸው 4ቱንም ነገሥታት ገሰጸ:: እነዚህም ኢዮአታም: አካዝ: ሕዝቅያስና ምናሴ ናቸው::

+ቅዱስ ሕዝቅያስ በነገሠ በ14ኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም በጠላትነት ተነሳበት:: ወደ አካባቢውም መጥቶ: ከቦ አስጨነቀው:: ሰናክሬም በጦር እጅግ ኃይለኛ ነበር:: በዚያውም ላይ ጦር የሚመዙ ከ185,000 በላይ ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩትና ሕዝቅያስ እንደማይችለው ተረድቶ መልእክተኛ ላከበት::

+ሰናክሬም ግን ሰይጣን ያደረበት ነውና የሕዝቅያስን ልመና ወደ ጐን ብሎ የእሥራኤልን አምላክ: ቅዱስ ስሙንም ተገዳደረ:: ቅዱስ ሕዝቅያስ በዚህ ጊዜ የፈጣሪው ስም ሲቃለል ሰምቷልና ፈጽሞ አዘነ::

+መልእክተኞችን ወደ ነቢዩ ቅዱስ ኢሳይያስ ልኮ እርሱ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ:: በእግዚአብሔር ፊት ልብሱን ቀድዶ ማቅ ለበሰ:: ስለ ኢየሩሳሌምና ሕዝቡም ፈጽሞ አለቀሰ:: በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር በኢሳይያስ አንደበት እንዲሕ አለ:- "ስለ ባሪያየ ስለ ዳዊት ከተማዋን አድናታለሁ::"

+በዚያች ሌሊትም ድንቅ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ከሰማያት በግርማ ወረደ:: ወደ ሰናክሬም የጦር ሠፈር ደርሶ አንድ ጊዜ የእሳት ሰይፉን መዝዞ ቢያሳያቸው ከአሕዛብ ሠራዊት 185 ሺ ኃያላን እንደ ቅጠል ረገፉ:: (1ነገ. 18:13, 19:1)

+ታላቁ ነቢይ ልዑለ ቃል ኢሳይያስ ሐረገ ትንቢትን ያፈስ ነበርና ከተናገራቸው ትንቢቶችም አንዱ "ድንግል ትጸንሳለች: ወንድ ልጅም ትወልዳለች" የሚል ነበር:: (ኢሳ. 7:14)

+በወቅቱ የነበሩ አንዳንድ ክፉ መካሪዎች ቀርበው ንጉሡን በውዳሴ ከንቱ ጠለፉት:: "ንጉሥ ሆይ! ሺህ ዓመት ንገሥ:: እንዳንተ ያለ ማንም የለም:: ነቢዩ የተናገረው ትንቢትም እኮ ላንተ ነው:: 'ድንግል' የተባለች ኢየሩሳሌም ስትሆን 'ወልድ-ወንድ ልጅ' የተባልክ ደግሞ አንተ ነህ" አሉት::

+ይሕንን ጠማማ ትርጉም እህ ብሎ የሰማቸው ቅዱስ ሕዝቅያስ አልወቀሳቸውም:: በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር ተቆጥቶ ኢሳይያስን ላከው:: ነቢዩም መጥቶ ንጉሡን አለው:- "ትሞታለህ እንጂ አትተርፍምና ቤትህን ሥራ::"

+ወዲያውኑ ሕዝቅያስ ታመመ: ደከመ:: ንጉሡ ወደ ፈጣሪ:- "ጌታ ሆይ! እንደ ቸርነትሕ በፊትህ በቅን መንገድ መሔዴን አስብና ይቅር በለኝ" ሲል ተማጸነ:: ይህ ሲሆን ቅዱስ ኢሳይያስ ገና ከንጉሡ አካባቢ አልራቀም ነበርና የእግዚአብሔር ቃል ወደ እርሱ መጣ::

+ሕዝቅያስን በለው:- "ጸሎትህን ሰምቼ: ስለ ባለሟሌ ስለ ዳዊት ብየ ምሬሐለሁ:: በዘመንህም ላይ 15 ዓመታትን ጨምሬልሃለሁ በለው" አለው:: ነቢዩም ወደ ንጉሡ ተመልሶ ይሕንኑ ነግሮ "እስከ 3 ቀን ድረስ ወደ ቤተ መቅደስ ድነህ ትመለሳለህ" አለው::

+ቅዱስ ሕዝቅያስ "ይሕ እንደሚደረግ በምን አውቃለሁ?" አለው:: ኢሳይያስም ፀሐይን ዓለም እያየ 10 መዓርጋትን ወደ ሁዋላ መለሳት::

+ልዑለ ቃል ቅዱስ ኢሳይያስ ለ70 ዘመናት ሕዝቡን አስተምሮ: ነገሥታቱን ገስጾ: 68 ምዕራፎች ያሉትን ሐረገ ትንቢት ጽፎ አረጀ:: በዘመኑ የነበረው ንጉሥ ምናሴ ግን ይባስ ብሎ ጣዖትን አቆመ: ለጣዖትም ሰገደ:: ቅዱሱ ይህንን ሲያደርግ ዝም አላለውም:: በአደባባይ ገሰጸው እንጂ::

+በዚህ የተበሳጨ ምናሴም ሽማግሌውን ነቢይ በእንጨት መጋዝ ለሁለት አሰነጠቀው:: ቅዱስ ኢሳይያስ በዚህ ዓይነት ሞት በጐ ሕይወቱንና ሩጫውን ፈጸመ:: የተናገራቸው ትንቢቶች ግልጽ ስለ ሆኑ 'ደረቅ ሐዲስ' በመባል ይታወቃሉ::

+ቸሩ አምላክ 'ደሃ ተበደለ: ፍርድ ተጉዋደለ' የሚሉ መምሕራን አባቶችን አይንሳን:: ከነቢዩም በረከቱን ይክፈለን::

+መስከረም 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ኢሳይያስ ነቢይ (ልዑለ ቃል)
2.ቅድስት ሰብልትንያ ሰማዕት
3.አባ ያዕቆብ ገዳማዊ
4.ቅዱስ አናቲሞስ ኤዺስ ቆዾስ


በ 06 የሚከበሩ ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም
2.አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን
3.አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል
4.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
5.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
6.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
7.ቅድስት ሰሎሜ
8.አባ አርከ ሥሉስ
9.አባ ጽጌ ድንግል
10.ቅድስት አርሴማ ድንግል

++"+ ኑ እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር:: ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች:: እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች:: እሺ ብትሉ: ለእኔም ብትታዘዙ የምድርን በረከት ትበላላችሁ:: እንቢ ብትሉ ግን: ብታምጹም ሰይፍ ይበላቹሃል:: የእግዚአብሔር አፍ ይህንን ተናግሯልና:: +"+ (ኢሳ. 1:18)

‹‹‹‹ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ››››

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🌻🌻🌻አባ ጴጥሮስም አቡነ መልክአ ክርስቶስን ካመነኰሰው በኋላ ወደ ቀደመ ቦታው ሔዶ በዚያ ያሉትን በክህነቱ እንዲያገለግላቸው እንዲያመነኩሳቸው መስቀል ሰጥቶ ሸኘው። እርሱም ተጨማሪ 12 ዓመት አገልግሏቸው በአጠቃላይ 22 ዓመት ሲሞላው የእግዚአብሔር ጸጋ የበዛላት ወለተ ጽዮን ስታርፍ ፍትሐት አድርሶ ከቀበራት በኋላ ወደ ሌላ ቦታ በመሔድ የእግዚአብሔር መልአክ እየመራው ዳውንት ደረሰ። በዳውንት አጽፍት ሚካኤል ዘጠኝ ዓመት አገልግሎ ብዙዎችን አመነኰሰ። ከዚያም ወደሌላ ቦታ እንዲሔድ እግዚአብሔር ነግሮት ለመሔድ ጉዞ ሲጀምር ድንጋዮች ዕፅዋቶች ከነበሩበት ተነሥተው ይከተሉት ጀመር፣ እርሱ ግን በሥልጣኑ በቦታቸው እንዲወሰኑ አዘዛቸው። ወደ ዋድላ በመሔድ በሰለልኩላ በየጭራ በሐዲስ አምባ እና በደብረ ዳሪት አቡነ አሮን ተመላልሶ ወንጌልን ሰበከ ድዉያንን ፈወሰ ብዙዎችንም አመነኰሰ።

ከዚኽም ዐብይ ጾምን ወደ ጎንደር ሔዶ ሱባኤውን በዚያ ከቆየ ስለ ወደ ሰለልኩላ ተመለሰ። የቅድስት ድንግል ማርያምና የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤል ታቦታት አብሮ ይዞ ስለነበር ሀገሩ እንዲባረክ በሰላልኩላ የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስትያን ሠርቶ ታቦተ ሚካኤልን አስገብቶ አከበር ዛሬ ድረስ በዋድላ ስለልኩላ ሚካኤል በሰለልኩላ ቅዳሴ መገኛነቱ በብዙዎት ዘንድ ይታወቃል። አባታችንም ጥቂት ጊዜ በስለልኩላ ሚካኤል እንደቆየ እመቤታችን ይህ ስፍራህ አይደለምና ወደ ደብረ አብ ደብረ ወለድ ደብረ መንፈስ ቅዱስ ሒድ አለችው። በተነገረው ቦታም ተወስነው የሚጸልዩ ሦስት ደገኛ መነኰሳት አባቶች በቶሎ ወደዚህ ና በዚህ አንተ የብዙዎች አባት ትሆናለህ ብለው ወደ አቡነ መልክአ ክርስቶስ መልእክት ላኩበት። አባታችንም ከዳውንት ወደ ግሽቅ መሔጃ መንገዱ ላይ መንኳክ ማርያም ደርሶ አደረ፡ ጸሎት አድርሶ ቦታዋን ቢባርካት ጠበል ፈለቀ፡ የገዳም ሥርዓትንም ሠራላት። ዛሬም ድረስ አባታችን ያፈለቀው ጠበል ብዙ ተኣምራት እያደረገ ምስክር ሆኖ በቦታው ላይ አለ።

🌻🌻🌻አቡነ መልክአ ክርስቶስ የእመቤታችንን ታቦት ይዞ በሽሎ የሚባል ወንዝ ሲደርስ እንደ ሱራፌል ቀንና ሌሊት ሳያስታጉሉ የሚያመሰግኑ ሥዉራን ቅዱስ በደብሩ እንዳሉ አስተዋለ" እመቤታችን እየመራችው በደብሩ አናት አድርሳ | ይህ ቦታህ ይሁን ስሙም ግሸቅ ይባል፡ ታቦቴንም በቀኝህ አኑር" አለችው: ዳግመኛም “ልጄ ገዳመ አስቄጥስን ገዳመ ሲሐትን እንደባረከ ይህን ገዳምን ይባርክልህ፣ ማህበረ መቃርስ ወማኅበረ ጳኩሚስ ማኅበረ ሖር ወአባ አብሎ ደብረ ኮኖብዮስ እና ሌሎችንም እንድባረከ ይባርክልህ፡ ከአንተ የሚወለዱ አንዱስ እንኳን አይጠፋም፣ በገዳምህ የተቀበረ አይጠፋም› አለችው።

🌻🌻🌻አባታችንም ገዳሙን ግሸቅ ካደረገ በኋላ ገዳማዊ አንድነቱ እየጠነከረ በመምጣቱ በደብሩ ዙሪያ የነበሩ ክፉዎች ‹ቦታችንን ሊቀሙን ነው›› ብለው በማሰብ ክፋትን ማድረግ ጀመሩ። በድንግልና ራሳቸውን ጠብቀው ከዓለም የተለዩ ደናግል መነኰሳት ሴቶቹን በማየት እንዲፈተኑ ተንኮል አስበው መነኰሳት አባቶች ውኃ ከሚቀዱበት ማይ ዘአጋም ከተባለ ምንጭ ሴቶች ልጆቻቸውን መላክ ጀመሩ።

🌻🌻🌻መነኰሳቱም በዚህ አዝነው ውኃ ሳይቀዱ በመመለስ ለአቡነ መልክአ ክርስቶስ የሆነውን ሲነግሩት «ልጆቼ ይህን ቦታ እመቤታችን ነች የሰጠችኝ፤ ‹አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የፈቀዱልህ ቦታህ ነው ለአንተና ለልጆችህ ለዘለዓለም ማደርያ ርስትህ ይሁን፣ ወገን የሌላቸው ታማሚዎች ስምህን በመዘከር ከመከራ ይዳኑ ብላ ተናግራ ሰጥታኛለች፤ እግዚአብሔር ለኛ ካለው ያድርገው ለእነርሱ ካለው ይሁን

ብሎ ሱባኤ ይዞ እናትና ልጅን ለመነ። የአካባቢው ሰዎችም እግዚአብሔርን አሳዝነዋልና ከእነርሱ ውስጥ ብዙዎች በሕማም በደዌ ተመቱ ብዙ ሰው መሞት ጀምር ቀሪዎቹ ከገዳሙ ክልል ሸሽተው ወጡ። በዚህም ጊዜ የአቡነ መልክአ ክርስቶስ ዝና በመላው ኢትዮጵያ ደረሰ።

🌻🌻🌻ዳግመኛም አባታችን ‹‹የኤርትራን ባሕር ከፍለህ ሕዝብህን ያሻገርኸ፡ 🌼እንዳይርባቸው በበረሓ መና ያወረድኸ 🌼እንዳይጠሙ ከዓለት ውኃ ያፈለቅኽአምላክ ሆይ! ዛሬም አንተ ነኽና ውኃ አፍልቅልኝ›› ብሎ ቢማጸን በግሸቅ ተራራ ላይ ውኃ ፈለቀለት በገዳሙ የነበሩ ሁሉ ከእርሷ ተጠምቀው ጠጥተው ተፈወሱ። የጎንደሩ ንጉስ አድያም ሰገድ ኢያሱ ሙያተኞችን ልኮ በግንብ አሰራት። የአጼ ኢያሱ ልጅ ልዑል ሰገድ ተክለ ሃይማኖትም ውኃ የሚቀዱበት በቅሎ ሰጥቷቸዋል።

🌻🌻🌻ማኅደረ ክርስቶስ የሚባል ክፉ ጠላት በብዙ ፈተና የሚያሠቃየው የአቡነ መልክአ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር በደብሩ ነበር። አቡነ መልክአ ክርስቶስም በጸሎቱ ክፉ ጠላትን ድል አደረገለት። ‹‹ልጄ አይዞህ አትፍራ ጽና›› ይለው ያበረታው ነበር። ከዚኽም በኋላ በጎንደር ዙሪያ ብዙ መነኰሳት ሰማዕት በሚሆኑበት ዘመን ማኅደረ ክርስቶስ ለአባታችን በራእይ ያየውን ነገረው፤ ‹‹አንተ ሰማዕት ለመሆን ሒድ፣ አቡነ መልክአ ክርስቶስ ግን አይሔድም፣ ብዙ ሥራ ከፊቱ አለ፣ ብዙዎችን ወደ መንግስተ ሰማያት ይጠራልና›› ተብያለው በማለት የተነገረውን መልእክት አስረዳው። አባታችንም ‹የነብያትን መንገድ ያቀና ሰማዕታትን በፈተና ሁሉ ያጸና አምላክ መንገድህን ያቅናልህ ያስፈጸምህ›› ብሎ ልጁን መረቀውና ሰማዕትነት ወደሚቀበልበት ቦታ ሰደደው። ማኀደረ ክርስቶስም ወደ ንጉሥ ወታደሮች ዘንድ ቀርቦ ስለ ሃይማኖቱ መስክሮ አንገቱን በሰይፍ ተቆርጦ የክብር አክሊልን ተቀዳጀ። አንገቱንም በሰይፍ ከቆረጡት በኋላ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ራስ የሰማዕቱ ማኅደረ ክርስቶስ ራስ መዝሙረ ዳዊት መኃልየ ሰሎሞን ውዳሴ ማርያም ዘመረች።

🌻🌻🌻አባታችን መልክአ ክርስቶስ ከልጆቹ ተለይቶ ከገዳሙ ወጥቶ በተራራ ሥር ወደሚገኝ ዋሻ ገብቶ ምግብ ሳይቀምስ ለንቋጣ የሚባል የዛፍ ፍሬን ብቻ እየተመገበ የሰውን ፊት ሳያይ አንድ ዓመት በታላቅ ተጋድሎ ተቀመጠ። በዚያም በበረሓ ሳለ ከዕለታት በአንደኛው ቀን አንዲት ሚዳቋ በውሾች ከበው ከሚድኗት አዳኞች ሸሽታ ሮጣ በመምጣት ከአባታችን ዘንድ ተጠጋች። መጽሐፍ ‹‹ጻድቅ ሰው ለእንስሳው ነፍስ ይራራል›› (ምሳ 12፡10) እንዲል አባታችን መልክአ ክርስቶስም ይኽችን ሚዳቋ በአጽፉ ሸፈናትና ጠቅልሎ ከሸሸጋት በኋላ እርሱ ግን ወገቡን በትንሽ ልብስ አስሮ ራቁቱን ቆመ። የሚያባርሯት አዳኞችም ወደ እርሱ ደርሰው ሚዳቋ በዚህ ስታልፍ አላየህምን? ብለው ጠየቁት፤ እርሷን በማጣታቸው እነርሱ ልብ ጠፍቷልና ሳር ለማጨድ ወይም ዕንጨት ለመቁረጥ የመጣ ሰው መስሏቸዋልና እንዲህ ብለው ጠየቁት። እርሱም እናንተ ባላችሁበት መንግድ አዎን አሁን አለፈች አላቸው. እነርሱም እውነት መስሏቸዋልና ሔዱ። ከሔዱም በኋላ እንዳያገኟት በሌላ መንገድ ሰደዳት። (ሚዳቋ ወይም ሰሳ የምትባለውን እንስሳ በገጠሩ የሀገራችን ክፍል አደን እንያደኑ አርደው ይበሏታል፣ ሥጋዋም እንደ ፍየል ሥጋ ነው።)

🌻🌻🌻ዳግመኛም አባታችን መልክእ ክርስቶስ በሌላ ቀን ከመንጋዋ የተለየች አንዲት ዝንጀሮ በእርሻ ዳር ቁማ አያት። እርሷም እህል ትበላ ዘንድ ትፈልግ ነበር ነገር ግን የምትገባበትን መንገድ አጥታ የእህሉን ጠባቂ ፈርታ ቁማለች። የገዳሙንም እህል የሚጠብቀው ረዳታቸው የሆነው አባ ስብሐት ለአብ ነበር። አባታችን መልክአ ክርስቶስም “ልጄ ስብሐት ለአብ ሆይ ና ወደ ሌላ ሥራ ልላክህ አለው። ልጁም የምጠብቀውን እህል ለማን ትቼ እሔዳለሁ? ሲለው አባታችንም እስክትመጣ ድረስ እኔ እጠብቅልሃለሁ› አለውና ወደ ሌላ ቦታ ልኮት ከሔደ በኋላ አባታችን ያችን ዝንጀሮ ዛሬ ገብተሸ ብዪ›› አላትና ከእህሉ ውስጥ ገብታ በላች የሚበቃትንም ያህል ወሰደች።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ከዚህም በኃላ ሁለተኛ ያዙት ወስደውም ከሚነድ እሳት ውስጥ ጨመሩት ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አዳነው። ዳግመኛም ተነጣጥቀው እንዲበሉት አንበሶችን በላዩ ሰደዱ በእግዚአብሔርም ኃይል በአንበሳ ላይ ተቀመጠ።

ከዚህም በኃላ ብዙ አሠቃዩት ሕዋሳቶቹ እስቲለያዩና የሆድ ዕቃው እስቲፈስ ጎተቱት ተጋድሎውንና ምስክርነቱን በዚህ ፈጽሞ የሰማዕትነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አፄ_ልብነ_ድንግል

በዚህችም ቀን እግዚአብሔርን የሚወድ ሃይማኖቱ የቀና ደግ ጻድቅ የኢትዮጵያ ንጉሥ ልብነ ድንግል አረፈ።

እኒህ ንጉሥ ኢትዮዽያን ለዓመታት (ከ1500 እስከ 1532 ዓ.ም) ቢያስተዳድሩም 15ቱ ዓመት ያለቀው በስደት ነው። ከደጋጉ አፄ ናዖድና ንግሥት ወለተ ማርያም ተወልደው በሥርዓቱ አድገው ቢነግሡም በክፉ መካሪዎች ጠንቅዋይ ወደ ቤታቸው ገብቶ ሃገሪቱን ለመከራ ዳርጓታል።

ዛሬም ድረስ ጠባሳው ያለቀቀው የግራኝ ወረራ ለ15 ዓመታት ሃገሪቱን ያለ ካህንና ቤተ ክርስቲያን አስቀርቷት ነበር። ብዙ ክርስቲያኖችም ሰልመው ቀርተዋል። አፄ ልብነ ድንግል ግን ደብረ ዳሞ ገዳም ውስጥ ገብተው ንስሃ ጀመሩ አለቀሱ ተማለሉ።

እመቤታችን ተገልጣም "ይቅርታን በነፍስህ እንጂ በሥጋህ አታገኝም" አለቻቸው። እርሳቸውም ሱባኤውን ቀጥለው ስብሐተ ፍቁርን፣ መልክአ ኤዶምን የመሰሉ መጻሕፍትን ደርሰው በዚህች ቀን ዐርፈዋል። እኛ ክርስቲያኖችም እናከብራቸዋለን።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መስከረም፣ #ከገድላት_አንደበት እና #ዝክረ_ቅዱሳን)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/+LNbJmr7thGAxNjJk

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እግዚአብሔር ከኛ ጋር ባይሆን | ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† መስከረም 3 ቀን የሚከበሩ የቅዱሳን በዓላት †††

††† እንኳን ለጻድቁ አባ ሙሴ እና አባ አንበስ ኢትዮዽያዊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† አባ ሙሴ ዘሲሐት †††

††† #ገዳመ_ሲሐት የሚባሉ ብዙ ቦታዎች አሉ:: ቅድሚያውን የሚይዘው ግን የግብጹ ነውና ዛሬ የዚህን ገዳም አንድ ቅዱስ እናስባለን:: ሕይወታቸውም በእጅጉ አስተማሪ ነው:: ቅዱሱ አባ ሙሴ ይባላሉ:: የ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ክርስቲያን ናቸው::

እኒህ ጻድቅ አንድ ነገር ከሌሎች ቅዱሳን ይለያቸዋል:: ከምግባርና ትሩፋት በቀር አንድም የእግዚአብሔር ቃል አያውቁም:: ዝም ብለው በየዋሕነት ይኖሩ ነበር እንጂ:: ተወልደው ባደጉበት በምድረ ግብጽ በቅን ሕይወት ኑረው: በወጣትነታቸው ወደ ደብረ ሲሐት ገቡ::

በዚያም በብሕትውና ዘግተው በጾምና ጸሎት ተወስነው ለ45 ዓመታት ኖሩ:: እጅግ የዋሕ ሰው ናቸውና ከጸጋ (ከብቃት) ደረሱ:: ሰው በአካባቢው አልነበረምና አብረው የሚውሉት ከግሩማን አራዊት ጋር ነበር:: አራዊቱም ጻድቁን ያጫውቷቸው: ይታዘዙላቸውም ነበር:: በፈንታው ደግሞ አባ ሙሴ በተአምራት ዝናብ ያዘንቡላቸው: ምግብም ይሰጧቸው ነበር::

አባ ሙሴ ልብስ አልነበራቸውምና በቅጠል ይሸፈኑ ነበር:: የምግባቸው ነገርማ "በመጠነ ኦፍ" ይላል . . . ትንሽ ድንቢጥ የምትበላውን ያህል ቀምሰው: ጥርኝ ውሃም ተጐንጭተው ነበር የሚኖሩት:: በሁዋላ ግን እጅግ ከመብቃታቸው የተነሳ ዐይናቸውን ሲገልጡ 'ገነት' (የአትክልት ሥፍራ) ይታያቸው ነበር:: ከዚያም ለበረከት ቆርጠው ይበሉ ነበር::

ሰይጣን እርሳቸውን ይጥል ዘንድ እጅግ ቢጥርም አልተሳካለትም:: በስተ መጨረሻ ግን የሚጥልበት መንገድ ተከሰተለት:: ምንም ባለ መማራቸው ሊፈትናቸውም ተነሳ:: አንድ ቀን ከበአታቸው በር ላይ ከአራዊት ጋር ተቀምጠው ሳለ ሰይጣን ሽማግሌ መነኩሴ መስሎ እየተንገዳገደ መጣ::

አራዊቱ ደንግጠው ሲሸሹ እርሳቸው ግን ሳያማትቡ ሮጥ ብለው ደገፉት:: ወደ በዓታቸውም አስገቡት:: ማታ ላይ ሲጨዋወቱ "ማንነትዎን ይንገሩኝ" አላቸው:: ለአባ ሙሴ ሰይጣኑ የበቃ አባት መስሏቸዋልና የ45 ዓመታት ድንግልናዊ የተባሕትዎ ሕይወታቸውን ነገሩት::

እርሱም በፈንታው ሐሰቱን ቀጠለ:: "እኔ ግፍ እየሠራሁ በዓለም እኖር የነበርኩ ሰው ነኝ:: ነገር ግን ዓለምን ትቼ ላለፉት 40 ዓመታት በበርሃ በንስሃ ኑሬአለሁ:: ያም ሆኖ አንዲት ሴት ልጅ አለችኝና 'ማን ያገባታል' ብየ ስጨነቅ አንተ እንደምታገባት ተገለጠልኝ" አላቸው::

አባ ሙሴ ደንግጠው "እንዴት ድንግልናየንና ሕይወቴን ትቼ አገባለሁ?" ሲሉም ጠየቁ:: ሰይጣን ግን ቃለ እግዚአብሔር እንደማያውቁ ተረድቷልና "አንተ ከአብርሃም: ከያዕቆብ: ከዳዊት ትበልጣለህ? እነሱ አግብተው የለ!" ብሎ ቢገስጻቸው አንዳንዴ አለ መማር ክፉ ነውና አባ ሙሴ ሸብረክ አሉ: ተረቱ::

ከዚያም ተያይዘው ጉዞ ወደ ዓለም ሆነ:: መንገድ ላይ ግን መነኩሴ ነኝ ያለው ሰይጣን ወደቀና የሞተ መሰለ:: አባ ሙሴ በእንባ ቀብረውት ሲሔዱ ተኖ ጠፋ:: አባ ሙሴ ቀና ሲሉ ሰይጣን በምትሐት የሠራውን ያማረ ግቢና ቆንጆ ሴት አዩ:: ወደ እሷ እቀርባለሁ ሲሉ አውሎ ንፋስ ማጅራታቸውን መትቶ ጣላቸው::

አባ ሙሴ ከወደቁበት ሲነሱ ያዩት ነገር ሁሉ ሰይጣናዊ ምትሐት መሆኑን አወቁ:: ወደ በአታቸው መጥተው ከገነት ፍሬ ቢቀምሱ ጸጋ እግዚአብሔር ተለይቷቸዋልና መራራ ሆነባቸው:: እያለቀሱ ከበዓታቸው ወጡ::

መንገድ ላይ ያው ሰይጣን ነጋዴ መስሎ: "መንገድ ልምራዎት" ብሎ ምንም ከሌለበት በርሃ ላይ ጥሏቸው ተሰወረ:: የሚያደርጉት ጠፋባቸው:: ረሃቡ: ጥሙ: ከፈጣሪ ጸጋ መለየቱ አቃጠላቸው:: አሁንም አንዲት ሴት መነኩሴ ድንገት መጥታ ወደ በዓቷ አስገባቻቸው::

የማይገባውን ድርጊት እናድርግ ብላ አባበለቻቸው:: ይባስ ብላ ወደ አይሁድ እምነት እንዲገቡ አሳመነቻቸው:: ወዲያውም ወደ ሌላ በርሃ ወስዳ "አወቅኸኝ?" አለቻቸው:: "የለም" አሏት:: እዚያው ላይ ተቀይራ ጋኔን መሆኗን አሳይታቸው ተሠወረች::

#አባ_ሙሴ በዚያው ሥፍራ በአንድ ጊዜ ሁሉንም አጡ:: አለቀሱ: ተንከባለሉ:: እንባቸው እንደ ዥረት ፈሰሰ:: ልቡናቸው ሊጠፋ ደረሰ:: ወደ ፊታቸው አፈር እየረጩ: "ወየው" እያሉ ሲያለቅሱ ጌታችን መልአኩን ላከላቸው::

እንደ ቀድሞውም ፊት ለፊት ታይቶ አጽናናቸው:: "አይዞህ! ፈጣሪ እንባህንና ንስሃህን ተቀብሏል" ብሎ ወደ ስውራን ከተማ ወሰዳቸው:: በዚያም ለ7 ቀናት ቆይተው በዚህች ቀን ዐርፈዋል:: #አባ_ሳሙኤልም ቀብሯቸዋል::

††† አባ አንበስ ኢትዮዽያዊ †††

††† ጻድቁ የነበሩት በ13ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን የተወለዱት ትግራይ ውስጥ ነው:: ዛሬም ድረስ የብዙ ስውራን ቤት እንደ ሆነ የሚታወቀውን #ደብረ_ሐዘሎንም እርሳቸው እንደ መሠረቱት ይነገራል:: አባ አንበስ ከገዳማዊ ትሩፋታቸው ባሻገር በአንበሶቻቸው ይታወቁ ነበር::

የትም ቦታ ሲሔዱ በአንበሳ ጀርባ ላይ ነበር:: በእርግጥ አባቶቻችን ከዚህም በላይ ብዙ ድንቆችን ማድረግ ይችላሉ:: ምክንያቱም #እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ነውና:: ጻድቁ የአቡነ #ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ: #የሳሙኤል_ዘዋልድባና #የአባ_ብንያሚን ባልንጀራ ናቸው:: ዛሬ ደግሞ ዕረፍታቸው ነው::

††† #አምላከ_ቅዱሳን የወዳጆቹን ፈተና አስቦ እኛን ከመከራ ይሰውረን:: በቃል ኪዳናቸው ይጠብቀን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::

††† መስከረም 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አባ ሙሴ ዘደብረ ሲሐት
2.አባ አንበስ ኢትዮዽያዊ
3.አበው ኤዺስ ቆዾሳት
4.አባ ዲዮናስዮስ
5.አባ ዲዮስቆሮስ ሰማዕት
6.ቅዱስ በትንከል ዲያቆን

††† ወርኀዊ በዓላት
1.በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው (ዘካርያስና ስምዖን)
4.አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
5.አቡነ ዜና ማርቆስ
6.አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል
7.ቅዱስ ቄርሎስ ሊቅ (ዓምደ ሃይማኖት)

††† "በመጠን ኑሩ: ንቁም:: ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጐ እንደሚያገሳ አንበሳ ይዞራልና:: በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት::" †††
(1ዼጥ. 5:8)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#መስከረም_2

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
መስከረም ሁለት በዚህች ቀን #ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ ሰማዕት ሆነ፣ #ቅዱስ_ዳስያ_ሰማዕት ሰማዕት ሆነ፣
#ቅዱስ_ዲዲሞስና_የቅድስት_መሪና መታሰቢያቸው ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ

መስከረም ሁለት በዚህች ቀን የካህኑ የዘካርያስ ልጅ የከበረ አጥማቂው ዮሐንስ ሕግን አፍራሽ በሆነ በንጉሥ ሄሮድስ እጅ ሰማዕት ሆነ።

ይህም እንዲህ ነው በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ነቢዩ ዮሐንስ በገሠጸው ጊዜ ፊልጶስ ወንድሙ ስለሆነ ቅዱስ ዮሐንስም የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም ይለው ነበርና።

ቅዱስ ዮሐንስም ሄሮድስን የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሄሮድያዳን ስለማግባቱና ሌላም ያደርገው ስለነበረ ክፉ ሥራ ሁሉ ይገሥጸው ነበር። ደግሞም በተግሣጽ ላይ ተግሣጽን ጨመረ። ስለዚህም ዮሐንስን ተቀየመውና በግዞት ቤት አኖረው።

ሄሮድስም ዮሐንስን ይፈራው ነበር ጻድቅ ቅዱስ ሰው እንደሆነ ያውቅ ነበርና ብዙ ይጠባበቀውም ነበር። ሄሮድስ የተወለደባትን ቀን በዓል የሚያከብርባት ዕለት ነበረች መኳንንቱን አለቆቹን መሣፍንቱን ሹሞቹን በገሊላ አገር ያሉትን ታላላቅ ሰዎች ግብር አገባ።

የሄሮድያዳ ልጅም ወደ አዳራሹ ገብታ ዘፈነች ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው ከእርሱ ጋር በማዕድ የነበሩትንም ንጉሡም ያቺን ብላቴና የምትሺውን ለምኚኝ እሰጥሻለሁ አላት። እስከ መንግሥቱ እኩሌታ ድረስም ቢሆን የለመነችውን ሊሰጣት ማለላት።

ወጥታም እናቷን ምን ልለምነው አለቻት እናቷም የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ አለቻት። ያን ጊዜም እየሮጠች ወደ ንጉሡ ገብታ የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ በወጭት አሁን እንድትሰጠኝ እሻለሁ ብላ ለመነችው። ንጉሡም ስለ መሐላው አብረውት ስለ ነበሩትም ሰዎች አዘነ እምቢ ሊላት ግን አልወደደም።

ያን ጊዜም ባለወጎችን ላከ በእሥር ቤትም ሳለ የዮሐንስን ራስ ቆረጡ ራሱንም በወጭት አምጥተው ለዚያች ብላቴና ሰጡአት እርሷም ወስዳ ለእናቷ ሰጠች። በዚያችም ቀን የቅዱስ ዮሐንስ ራስ ከሄሮድያዳ ከእጆቿ ላይ ወደ አየር ስለ በረረች ታላቅ ድንጋፄ ሆነ።

ደግሞም ሄሮድስ ሆይ የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም እያለች በመጮኽ ዘልፋዋለችና። ደቀ መዛሙርቱም በሰሙ ጊዜ መጥተው በድኑን ወስደው ቀበሩት።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዳስያ_ሰማዕት

በዚችም ቀን በግብጽ ውስጥ ታዕዳ ከሚባል አገር ዳስያ ሰማዕት ሆነ። ይህንንም ቅዱስ የእንዴናው አገረ ገዥ አርያኖስ አሠቃየው ጽኑ ሥቃይንም ከአሠቃየው በኋላ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዲዲሞስና_የቅድስት_መሪና_ሰማዕት

በዚህችም ቀን የሰማዕት ዲዲሞስና የቅድስት መሪና መታሰቢያቸው ነው።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መስከረም)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Enkuwan nadrshahhu adrsn 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🌻🌻🌻✝✝✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝✝✝

‹‹‹ እንኳን አደረሳችሁ ›››

✝ #መስከረም 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

=>ይህች ዕለት እጅግ ክብርትና ልዕልት ናት:: አዲስ ዓመት: አዲስ ሕይወት: አዲስ ተስፋ: አዲስ በረከትን እናገኝ ዘንድ እርሱ በቸርነቱ ከዚህች ዕለት አድርሶናልና:: ለእርሱ ምን ይከፈለዋል? "ተመስገን" ከማለት በቀር::

=>ይህቺ ዕለት ብዙ ስያሜዎች ቢኖሯትም እነዚህን እንጠቅሳለን:-
1.ቅዱስ ዮሐንስ (መጥምቁ ዮሐንስ ርዕሰ ቅዱሳን ስለሆነ በእርሱ ተሰይማለች)
2.ርዕሰ ዐውደ ዓመት (የዐውደ ዓመቶች ራስ)
3.እንቁጣጣሽ (ንግስተ ሳባንና ንጉሥ ሰሎሞንን አንድ ያደረገች ዕለት)
4.ዕለተ ማዕዶት (መሸጋገሪያ)
5.ጥንተ ዕለታት (የዕለታት መጀመሪያ)
6.ዕለተ ብርሃን (የአዲሱን ዓመት ብርሃን የምናይባት)

=>ከምንም በላይ ግን ይህች ዕለት የአዝማነ መንግስተ ሰማያት ምሳሌ ናት:: አሮጌው ዓመት የዚህ ዓለም ምሳሌ ሲሆን አዲሱ ደግሞ የሰማያዊው ሕይወት ምሳሌ ነው:: ዻጉሜን ደግሞ የዘመነ ምጽዓት ምሳሌ ናት:: በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች ዕለቷ ክብርት ናት::

*" ምንተ ንግበር / ምን እናድርግ? "*

+እግዚአብሔር ከእኛ ብዙና ከባድ ነገሮችን አይፈልግም:: ደግሞም አይጠብቅም:: እርሱ ቸር ነውና በአዲሱ ዓመት ከእኛ:-
1.እንፋቀር ዘንድ
2.ንስሃ እንገባ ዘንድ እና
3.የቀናውን ጐዳና እንድንመርጥ ብቻ ይፈልጋል::
*በተሠማራንበት ሥራ ሁሉ: ባለንበትም ሃገር ሁሉ እግዚአብሔርን እናክብር: ድንግል እመቤታችንን እናፍቅር: ቅዱሳንን እናስብ ዘንድ ልንተጋ ይገባል:: ለዚህም ደግሞ የሥላሴ ቸርነት: የእመ ብርሃን አማላጅነት: የቅዱሳኑ ሁሉ ጸጋ በረከት ይደርብን::

✝ ዘመኑን የፍቅር: የሰላምና የበረከት ያድርግልን:: ✝

+*" ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ "*+

✝ ወንጌል ላይ እንደ ተጠቀሰው ከ12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ ቅዱስ በርተሎሜዎስ ነው:: (ማቴ. 10:3) ነገር ግን ዜና ሕይወቱ በስፋት ሲተረክ አንሰማም:: ቅዱሱ ሐዋርያ እንደ ሌሎቹ ወንድሞቹ ዓለምን በወንጌል ትምሕርት አብርቷል:: በትውፊት ትምሕርት መሠረት 'በርተሎሜዎስ' የሚለውን ስም ያወጣለት ጌታችን ሲሆን ትርጉሙም 'ተክሎችን የሚያጠጣ' ማለት ነው::

*ከሐዋርያትም ጌታ አስቀድሞ የስም ቅያሪ ያደረገለት ለእርሱ እንደ ሆነ ይታመናል:: በርተሎሜዎስ የግብርና ሥራውን ትቶ: የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ሆኖ: ከዋለበት እየዋለ: ካደረበትም እያደረ ምሥጢረ ወንጌልን ተምሯል::

*ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበለ በኋላም ከሐዋርያት ጋር ዓለምን በዕጣ ተካፍሏል:: ሃገረ ስብከቱም 'እልዋህ' እና 'አርማንያ' ናቸው:: የአርማንያ መንበርም የእርሱ ነው:: ቅዱሱ ገድሉ እንደሚለው አሕዛብን በስብከቱና በሚያስደነግጡ ተአምራቱ አሳምኗል::

*ከቅዱስ ዼጥሮስ: ከቅዱስ እንድርያስ: ከክርስቶፎሮስና ከሌሎቹም ሰባክያን ጋር ዓለምን ዙሯል:: ሙታንን አስነስቶ: ድውያንን ፈውሶ: አጋንንትን አውጥቶ: ብዙወችን ወደ ሕይወት መልሷል:: የደረቁ እንጨቶችም በእጁ ላይ እንዳሉ ለምልመው: አብበው ያፈሩ ነበር::

*ቅዱስ በርተሎሜዎስ እያስተማረ ወደ ኢትዮዽያም ደርሶ እንደ ነበር ይነገራል:: በመጨረሻም 'ለሚስቶቻችን ንጽሕናን አስተምረሃል' በሚል ተከሶ: ንጉሥ አግሪዻ በሰቅ (ጸጉር) ጠቅልሎ: አሸዋ ሞልቶ: ባሕር ውስጥ ጥሎታል:: በዚያውም ዐርፏል::

+*" ቅዱስ ሚልኪ ቁልዝማዊ "*+

✝ይህቺ ሃገረ ቁልዝም ግብጽ ውስጥ የምትገኝ ስትሆን ብዙ ቅዱሳንን አፍርታለች:: በተለይ የአባ እንጦንስና የልጆቹ ማረፊያ ከመሆኗ ባሻገር ቅዱስ አባ ሚልኪም ወጥቶባታል:: ቅዱሱ የዘመነ ጻድቃን ፍሬ: የስለት ልጅም ነው:: ጥሩ ክርስቲያኖች የነበሩት ወላጆቹ እጅግ ባለጸጐችም ነበሩ::

*በስለት መንታ ልጆችን (ሚልኪና ስፍናን) ወልደው: በሥርዓት አሳድገዋል:: ቅዱስ ሚልኪ በሕጻንነት ወራቱ ስቆና ከሕጻናት ጋር ተጫውቶ አያውቅም:: ብሉያትና ሐዲሳትን ጠንቆቆ ካጠና በኋላ እድሜው 19 ሲደርስ ወላጆቹ "እንዳርህ" አሉት:: የልቡን እያወቀ "እሺ" አላቸው::

*ቀጥሎም "ባልንጀሮቼን ልጋብዝበት" ብሎ: 1,000 ወቄት ወርቅ ተቀብሎ: በፈረስ ተቀምጦ ሔደ:: መንገድ ላይ መቶውን ለተከተሉት: 9 መቶውን ወቄት ለነዳያን: ፈረሱን ደግሞ ለአንድ ደሃ ሰጥቶ: ጡር (ጢር) ወደ ሚባል በርሃ ገሰገሰ::

*መጥፋቱ በቤተሰብ ሲሰማ ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ ተደረገ:: እናቱም ዐይኗ ተሰወረ:: እርሱ ግን አባ አውጊን ከሚባል ባሕታዊ ሒዶ ደቀ መዝሙሩ ሆነ:: ለ3 ዓመታትም ተፈትኖ መነኮሰ::

*ከዚያም በጠባቡ ጐዳና ገብቶ በጾም: በጸሎት: በትሩፋት ከፍ ከፍ አለ:: ከቅድስናው ብዛት የተነሳ አጋንንት ገና ከርቀት ሲያዩት ይሸሹት ነበር:: የነካቸውም ሁሉ ይፈወሱለት ነበር:: በእርሱ ጸሎትም በፋርስና በሮም ሰላም ሆነ::

*አንድ ቀን የዳዊትን መዝሙር እየዘመረ ሲሔድ የአገረ ገዥውን ልጅ ዘንዶ በልቶት ሲለቀስ ደረሰ:: ጸሎት አድርጐ ዘንዶውን ጠራውና "እንደ ነበረ አድርገህ ትፋው" ሲል አዘዘው:: ዘንዶውም ተፋው: ሰይጣኑም ሸሽቶ አመለጠ::

*ሃገረ ገዥው ደስ ቢለው 300 ቤቶች ያሉት ገዳም ለማር ቅዱስ ሚልኪ አነጸለት:: በዚያም 300 መነኮሳት ተሰብስበው ትልቅ ገዳም ሆነ:: ማር ሚልኪ ሁሉን ካሰናዳ በኋላ "ከዚህ አልወጣም" ብሎ በዓቱን ዘጋ:: ሰይጣን ግን "አስወጣሃለሁ" ብሎ ፎክሮ ሒዶ በንጉሡ ልጅ አደረባትና አሳበዳት::

*"ከሚልኪ በቀር የሚያሰወጣኝ የለም" አለ:: ንጉሡ ወታደሮቹን ጠርቶ "ሒዳችሁ: አባ ሚልኪን ይዛችሁ ብትመጡ ሽልማት: ካልሆነ ግን ሞት ይጠብቃችሁአል" አላቸው:: እነርሱም በጭንቅ አግኝተው "እንሒድ" አሉት:: "በሮም ከተማ በር ላይ እንገናኝ" አላቸው::

*ልክ በዓመቱ እነርሱ ሮም ሲደርሱ ማር ሚልኪ ደመና ጠቅሶ ከተፍ አለ:: ልጅቱንም አቅርቦ ሰይጣንን "እየታየህ ውጣ" አለው:: ወደል ጐረምሳ ሆኖ ወጣ:: ወስዶም አሰረው:: ከቀናት በኋላ ሕዝቡና ንጉሡ እያዩ ማር ሚልኪ ደመና ላይ ተቀምጦ: ሰይጣኑን የድንጋይ ገንዳ አሸክሞ እየነዳ ወሰደው::

*ሕዝቡም ደስ ብሏቸው በታላቅ ዝማሬና እልልታ ሸኙት:: ሰይጣኑንም ለዘለዓለም አሰረው:: ቅዱስ ሚልኪ በገዳሙ ለዓመታት ከተጋደለ በኋላ በዚህች ቀን ቅዱሳን አባ እንጦንስ: መቃርስ: ሲኖዳና ሌሎችም መጥተው: በክብር ተቀብለውት ዐርፏል:: አበው 'ትሩፈ ምግባር' ይሉታል::

+" ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላእክት "+

✝ከዘጠኙ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን በብርሃናት ላይ ተሹሟል:: ለሃገራችን ልዩ ፍቅር ያለው መልአኩ ከሔኖክ ጀምሮ የብዙ ቅዱሳን ረዳት ነው:: ዛሬ በዓለ ሲመቱ ነው::

+" ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ "+

✝ታላቁ ጻድቅ: የትእግስትም አባቷ ቅዱስ ኢዮብ በጭንቅ ደዌ ለብዙ ዘመናት በመከራ ከኖረ በኋላ በዚህች ቀን በፈሳሽ ውሃ (በዮርዳኖስ) ታጥቦ ሰውነቱ ታድሷል:: ክብርም ተመልሶለታል:: በፈሳሽ ውሃ የምንጠመቅበት አንዱ ምክንያትም ይሔው ነው::

+የበርተሎሜዎስ አምላክ ፍቅሩን: የሚልኪ አምላክ ትሩፋቱን: የራጉኤል አምላክ ረድኤቱን: የኢዮብ አምላክ ትእግስቱን ያሳድርብን::

+መስከረም 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ርዕሰ ዓውደ ዓመት
2.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
3.ቅዱስ /ማር/ ሚልኪ (ትሩፈ ምግባር)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ወዳጄ ሆይ እስኪ ንገረኝ ለምንድነው የምታዝነው


ድሃ ስለሆንክ ነውን

ይልቁንስ በዚህ ምክንያት በማዘንህ ልታዝን ይገባሃል፤ ማዘን የሚገባኽ ድሃ ስለሆንክ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ሐሳብ ምን ያህል እንደራቅክ በማሰብ ልታዝን ይገባሃል፡፡

ሐሳብህን ከጊዜአዊው ገንዘብ አንሥተህ ሰማያዊውን አክሊል ሽልማትህን ባለማሰብህ ልታዝን ልትተክዝ ይገባሃል፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ በየቀኑ ይገደል ነበር፤ ነገር ግን አላዘነም፤ አላለቀሰም፤ ደስ ይለው ነበር እንጂ፤ ብዙ ጊዜ በረሃብ አለንጋ ይጠበስ ነበር፤ ነገር ግን አላዘነም፤ አላጉረመረመም፤ ይከብርበት ነበር እንጂ፤ ታድያ አንተ የዓመት ቀለብ የለኝም ብለህ ታዝናለህን “እኔ እኮ የቤተሰብ አባወራ ነኝ፤ ልጆችን አሳድጋለሁ፤ ሠራተኛ አለኝ፤ ሚስት አለችኝ፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ ግን ቢያስብ ለራሱ ብቻ ነው” ልትለኝ ትችላለህ፤ እኔም እንዲህ ብዬ እመልስሃለሁ ቅዱስ ጳውሎስ ያስብ የነበረው ለራሱ ብቻ አይደለም፤ ለዓለም ኹሉ እንጂ፤ አንተ አንድን ቤተሰብ ለማስተዳደር ትጨነቃለህ፤ ርሱ ግን ዓለምን ሁሉ ለማስተዳደር ይጨነቅ ነበር፤ በኢየሩሳሌም ለነበሩ ድሆች ይጨነቅላቸው የነበረው ርሱ ነው፡፡

በሜቄዶንያ ለነበሩት ያስብላቸው የነበረው እርሱ ነው፤ በየቦታው ለነበሩ ድኾች ይጨነቅላቸው የነበረው ርሱ ነው፤ ያስተዳድራቸው ከነበሩት ሰዎች ከሚሰጡት ይልቅ የሚረዱ ይበዙ ነበር፡፡

ለዓለም ሁሉ ማሰቡ በሁለት ወገን ነበር፤ በአንድ ወገን እንዲሁ የሚበሉት አጥተው እንዳይጐዱ፤ በሌላ ወገን ደግሞ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ባለጸጐች እንዲሆኑ፤ ስለዚህ አንተ ለልጆችህ ከምታስበው በላይ ቅዱስ ጳውሎስ ለዓለም ሁሉ ያስብ ነበር ብዬ እነግርሃለሁ፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ ያስብ የነበረው ለሚያምኑት ልጆቹ ብቻ እንዳይመስልህ፤ ለማያምኑትም ጭምር ይጨነቅላቸው ነበር እንጂ፤ እነርሱ ድነው እርሱ በነርሱ ፈንታ እንዲረገም ይመኝ ነበር፤ እነርሱ የዘለዓለም ሕይወት አግኝተው ርሱ ገሃነም እንዲገባ ይመኝ ነበር።
ሮሜ 9፥1-3

አንተ ግን ምንም ዓይነት ቁጣ ቢመጣም “እኔ ልራብልህ” ብለህ ስለወንድምህ አትሞትም፤ አንተ ለአንዲት ሚስትህ ብቻ ትጨነቃለህ፤ ቅዱስ ጳውሎስ ግን “ዕለት ዕለት የሚከብደኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሐሳብ ነው” እንዳለ፤ ይጨነቅ የነበረው በዓለም ሁሉ ላሉት አብያተ ክርስቲያናት ነው፡፡
2ኛ ቆሮ 11፥28

ወዳጄ ሆይ ታድያ ለምንድነው ከቅዱስ ጳውሎስ በላይ እንደምታስብ አድርገህ ራስክን የምትመለከተው❓

በምን ያህል ርቀት እንዳለህስ አታስተውልምን

ስለዚህ ማዘን፣ ማልቀስ የሚገባን በድህነት ውስጥ ስላለን አይደለም፤ ማልቀስ ማንባት የሚገባን በኃጢአት ማጥ ውስጥ ስንገባ ነው፤ የሚገባ ኀዘን ይኸው ነው፤ ከኃጢአት በቀር ለሌላ ማዘን እንዲሁ ተራ ነገር ነው ብዬ በእውነት ያለ ሐሰት እነግርሃለሁ፡፡

የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
ምሳ 1፥33

ምንጭ
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/7seSQxEODvg?si=8axJb08alKItV_V5

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፤፤ †††

††† መስከረም 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት †††

+" ✝ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት✝ "+

††† ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን የመላእክት ሁሉ አለቃቸው በፈጣሪው ኃይል ብዙ ድንቆችን ሠርቷል:: ከመጀመሪያው ሰው አዳም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ: አምነው ለሚጠሩት ረዳት ነው:: ዘወትርም ያድናቸው ዘንድ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሠፍራል:: (መዝ. 33:7)
¤እግራችን እንዳይሰናከል ዘወትር ይጠብቀናል:: (መዝ. 90:11)
¤የቅዱስ ሚካኤል ስሙ ድንቅ ነው:: (መሳ. 13:18)
¤ከእርሱ በቀርስ የሚያጸና ማን አለና! (ዳን. 10:21)
¤ለሕዝቡም የሚቆም ታዳጊ መልአክ ነው:: (ዳን. 12:1)
¤በፊቱ ሲቆምም ስለ ክብሩ ጫማ አውልቆ: ባጭር ታጥቆ ነው:: (ኢያ. 5:13)

+ይህ ድንቅ መልአክ ከሺህ ዓመታት በፊት በሮም ከተማ ይህንን ድንቅ ተአምር በዚህች ዕለት መሥራቱን ቤተ ክርስቲያን ትመሰክራለች:: በድሮው የሮም ግዛት 'ሩፍምያ' የምትባል ከተማ ነበረች:: ይህች ከተማ ክርስቲያኖችም: ኢአማንያንም ተቀላቅለው የሚኖሩባት ናት::

+በከተማዋ የክርስቲያኖች ቁጥር ትንሽ ቢሆንም በእምነት ግን ጠንካሮች ነበሩ:: በተለይ ደግሞ የቤተ ክርስቲያኗ መጋቢ ባለ ፍጹም እምነት ሰው ነበር:: በቦታው የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመኖሩም ብዙ ተአምራት ይደረጉ ነበር:: ተበለጥን የሚል ስሜት የተሰማቸው አሕዛብ (ዮናናውያን) ግን ይሕንን ቤተ ክርስቲያን ለማጥፋት ተማማሉ::

+በቀጥታ ሔደው ቢያፈርሱት ወይም ቢያቃጥሉት በሕግ እንደሚጠየቁ ያውቃሉና በሥጋዊ ጭንቅላታቸው ዘዴ ያሉትን መከሩና ወሰኑ:: በከተማዋ ዳር የሚያልፍ አንድ ትልቅ ወንዝ አለ:: በሞላ ጊዜ ያገኘውን ሁሉ ጠርጐ የሚወስድም ነበር::
+ታዲያ ክፋተኞቹ ሌሊት ሌሊት እየተነሱ የሚሔድበትን መንገድ ዘግተው: ወደ ቤተ ክርስቲያኑ አቅጣጫ መንገድ ከፈቱለት:: ከቀናት በኋላ ከባድ ዝናብ በዚህች ቀን ጣለ:: ወንዙ ትልቅ ነውና ያገኘውን ሁሉ እያገላበጠ ደረሰ::

+በወቅቱ በቅዱሱ መልአክ መቅደስ ውስጥ ከመጋቢው በቀር ሰው አልነበረምና አስፈሪ ድምጽ ሰምቶ ቢወጣ ወንዙ እየደነፋ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ እየመጣ ነው:: አሰበው: ከደቂቃዎች በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ እንዳልነበረ ሊሆን ነው::
+እርሱ አንድ ተስፋ ነበረውና ወደ ውስጥ ገብቶ ቅዱስ ሚካኤልን ተማጸነ:: ከዚያ ላለመውጣትም ወሰነ:: ትንሽ ቆይቶ በታላቅ ኃይል ወንዙ ደረሰ:: በዚህ ጊዜ ግን ቅዱስ ሚካኤል በግርማ ከሰማይ ወርዶ በወንዙ ፊት ቆመ::

+መጋቢውንም "ጽና: አትፍራ" ብሎት በያዘው የብርሃን በትረ-መስቀል መሬትን አንድ ጊዜ መታት:: በዚያች ቅጽበትም ትልቅ ሸለቆ ተፈጠረ:: ወንዙም በሸለቆው ውስጥ አልፎ ሔደ::
+የሚገርመው ሸለቆው የተፈጠረው በቤተ ክርስቲያኑ በታች ነው:: ቅዱስ ሚካኤል ግን መጋቢውን ባርኮት በክብር ዐረገ:: በማግስቱ ክርስቲያኖቹ ይህንን አይተው ደስ አላቸው:: መልአኩንም አከበሩት:: አሕዛብ ግን አፈሩ::

††† ✝ቅዱስ ቢሶራ ሰማዕት✝ †††

††† በዘመነ ሰማዕታት ክርስቲያን መሆን ብቻ የሚያስከፍለው ዋጋ ብዙ ነበር:: ከምንም በላይ መከራው የጸናባቸው ግን የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ነበሩ:: ክደው ያስክዳሉ በማለት አብዝተው ያሰቃዩአቸው ነበር:: ቶሎም አይገድሏቸውም:: መከራውን ከማራዘም በቀር::

+ከእነዚህም አንዱ አባ ቢሶራ ነው:: እርሱ በምድረ ግብፅ 'መጺል' ለምትባል ሃገር ኤዺስ ቆዾስ ነበረ:: በእድሜው አረጋዊ: በትምሕርቱ ምሑር: በምግባሩ ቅዱስና በእረኝነቱም የተመሠከረለት በመሆኑ በምዕመናን ዘንድ ተወዳጅ ነበር::

+መከራው እየገፋ ሲመጣ ግን ቅዱሱ በመፍራት ፈንታ የሰማዕትነት ፍቅር አደረበት:: ስለ ሃይማኖት መሞትን እና ቶሎ ወደ ክርስቶስ መሔድን ናፈቀ:: ነገር ግን መልካም እረኛ ነውና በጐቹን (ምዕመናንን) እንዲሁ ሊተዋቸው አልወደደም:: ሰብስቦ ምን እንዳሰበ አማከራቸው:: የሰሙት ነገር ክርስቲያኖችን አስለቀሳቸው::

+"አቡነ ለመኑ ተኀድገነ-አባታችን ለማን ትተኸን ትሔዳለህ?" ሲሉም ከእግሩ ወደቁ:: እርሱ ግን አስረድቷቸው: አጽናንቷቸውም በእንባ ተሰናበታቸው:: አንዳንዶቹ ደግሞ "አብረንህ እንሞታለን" ብለው ተከተሉት:: ቅዱስ አባ ቢሶራን ከብዙ ስቃይ በኋላ አረማውያን ከነተከታዮቹ በዚህ ቀን ገድለውታል::

††† ✝ቅዱስ ያሳይ ንጉሥ✝ †††

††† በቀደመው ዘመን መንግስታቸውን ትተው ከመነኑ ነገሥታት አንዱ ቅዱስ ያሳይ ነው:: ምናኔ በቁሙ ከባድ ነው:: መንግስትን: ዙፋንን: ክብርን ትቶ መመነንን ደግሞ ከማድነቅ በቀር እንዲህ ብለው ሊገልጹት ይከብዳል::

+ቅዱስ ያሳይም መንግስቱን ትቶ ልምላሜ ወደሌለበት ደረቅ በርሃ ሔደ:: በዚያም ከአንዲት ዛፍ በቀር ምንም ነገር አላገኘም:: በዚያች ደረቅ ዛፍ ላይ ወጥቶ ለዓመታት በጾምና በጸሎት ተጋደለ::

+በዘመነ ተጋድሎው ከዛፏ አልወረደም: ሰውም አይቶ አያውቅም:: በመጨረሻም ስለ ቅድስናው ዛፏ ለምልማለች:: እርሱም በዚህች ቀን ዐርፏል::

††† አምላከ ቅዱሳን ተራዳኢ መልአክን ይዘዝልን:: ከወዳጆቹ በረከትም አይለየን::

††† መስከረም 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ቢሶራ ሰማዕት
3.ቅዱስ ያሳይ ንጉሥ
4.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት (ልደቱ)
5."14,730" ሰማዕታት (የቅዱስ ፋሲለደስ ማሕበር)

ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት

1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት)
2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ /ኢትዮዽያዊ/
3."318ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ)
4.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን
5.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮዽያዊ)
6.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ (ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት)

††† የፋርስ መንግስት አለቃ ግን ሀያ አንድ ቀን ተቁዋቁዋመኝ:: እነሆም ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ:: እኔም ከፋርስ ነገሥታት ጋር በዚያ ተውሁት:: ††† (ዳን. 10:13)

‹‹‹‹ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ››››

/channel/zikirekdusn

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

4.አቡነ ኪሮስ
5.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
6.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)

++"+ ሙሴ ካደገ በሁዋላ የፈርኦን የልጅ ልጅ እንዳይባል በእምነት እምቢ አለ:: ከግብጽም ብዙ ገንዘብ ይልቅ ስለ ክርስቶስ መነቀፍ እጅግ የሚበልጥ ባለጠግነት እንዲሆን አስቧልና:: ለጊዜው በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ:: ብድራቱን ትኩር ብሎ ተመልክቷልና:: +"+ (ዕብ. 11:24)

‹‹‹‹ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ››››

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

♥️ ፀሐይ ብርሃን ካልሰጠች ፀሐይ አትባልም፤ ብርሃን አለመስጠት ተፈጥሮዋ አይደለምና፡፡ እንስሳት ካልተነፈሱ እንስሳት አይባሉም፤ መተንፈስ ተፈጥሮአቸው ነውና፡፡ ዓሣ ከውኃ ከወጣ ሕይወት ያለው ዓሣ መኾኑ ይቀርና ይሞታል፡፡ አንድ ክርስቲያንም እውነተኛ ክርስቲያን የሚባለው፡-

1. #ሲጸልይ ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት በወልድ ውሉድ በክርስቶስ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስም መንፈሳዊ መባል ነውና፡፡ ልጅ ከኾኑ ደግሞ አባትን ማናገር ክርስቲያናዊ ተፈጥሮ ነውና፡፡

2. #ሲያመሰግን ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት እግዚአብሔር ፈጣሬ ዓለማት ነው ብሎ ማመን ነውና፡፡ ስለዚህ ለአንድ ክርስቲያን የሰማይና የምድር ውበት እየተመለከተ እግዚአብሔርን ማመስገኑ ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነው፡፡

3.#ሲመጸውት ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት ሀብት ኹሉ ከእግዚአብሔር እንደ ኾነ መመስከር ነውና፡፡ ስለዚህ ራስን እንደ መልእክተኛ አድርጎ በመቁጠር ያለውን ለሌላው ማካፈል ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነውና፡፡

4. #ቅዱሳት #መጻሕፍትን #ሲያነብ ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት በመንፈስ ቅዱስ ሀብት ደስ የሚሰኝ ነውና፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳት መጻሕፍት በኩል ሲናገር መስማት ለአንድ ክርስቲያን ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነውና፡፡

🌹እንድናደርጋቸው እንድንሆን ይርዳን🌹

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
መስከረም 7-የብርሃን እናቱ የሆነች ድንግል ወላዲተ አምላክን የወለደቻት ቅድስት ሐና ልደቷ ነው፡፡
+ በ451 ዓ.ም በጉባዔ ኬልቄዶን ላይ ተገኝቶ ልዮንን የረታውና ያወገዘው ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ በዓለ ልደቱና ዕረፍቱ ነው፡፡
+ በአካል መሄድ ሳያስፈልጋቸው ደብዳቤ በመጻፍ ብቻ በንጉሡ ልጅ ላይ ያደረውን ሰይጣን ያስወጡትና በሀገርም ላይ የመጣውን የጠላትን ጦር በመርታት ድል ያደርጉ የነበሩት አቡነ ሳዊርያኖስ ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ ቅድስት ራፊቃ እና 4 ልጆቿ ቁልቁል ተሰቅለውና አንገታቸውን በመሰየፍ ሰማዕትነታቸውን በድል ፈጸሙ፡፡
+ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት ከቅዱስ ፋሲለደስ ጋር ማኅበርተኞቹ የሆኑ ሁለት ሺህ ሰባት ሰዎችም በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡
+ የመጥምቁ ዮሐንስ እናት የቅድስት ኤልሳቤጥም የመታሰቢያዋ በዓል ነው፡፡ ረድኤት በረከቷው ይደርብን፣
በጸሎቷ ይማረን፡፡
+ + + + + + + + + + + + + + +
ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ፡- ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት 25ኛው ነው፡፡ስለ ቀናች ሃይማኖት ታላቅ ተጋድሎን ከፈጸመ በኋላ በተሰደደበት በደሴተ ጋግራ መስክረም 7 ቀን ዐርፏል፡፡ንጉሡ መርቅያኖስ በጠራው ጉባዔ በጠሩት ጊዜ በቦታው ሲገኝ 636 ጉባኤተኞች ተሰብስበው ደረሰ፡፡‹‹ምን ጉድለት ተገኝቶ ነው ይህ ሁሉ የተጠራው?›› ሲላቸው ‹‹በንጉሡ ትእዛዝ ተጠርተን ነው››
አሉት፡፡ቅዱስ ዲዮስቆሮስም ‹‹ይህ ጉባኤ ስለ ጌታችን ክብር ቢሆን ኖሮ እኔ ተቀምጨ እግዚአብሔር በሰጠኝ በአንደበቴ እናገር ነበር ነገር ግን የጉኤው መሰብሰብ በንጉሡ ትእዛዝ ከሆነ ንጉሡ እንዳሻው ይምራው›› አላቸው፡፡ከዚህም በኋላ የክርስቶስን ባሕርይ ለሁለት የሚከፍለው የክህደትን ቃል በውስጡ የያዘውን የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ልዮን የላከውን ደብዳቤ ቀደደው፡፡ለጉባኤውም ርትእት የሆነች ሃይማኖትን ገለጸ፡፡የተዋሕዶንም ምሥጢር በነፍስና በሥጋ እንዲሁም በእሳትና ብረት እየመሰለ አስዳ፡፡ጌታችን ሰው እንደመሆኑ ወደ ሠርግ ቤት ተጠርቶ ሄደ፣ አምላክ እንደመሆኑ ውኃውን ለውጦ ወይን አደረገው›› እያለም በብዙ ምሳሌዎች ሲያስረዳቸው ከጉባኤው ሊከራከረው የደፈረ ማንም አልነበረው፡፡ነገር ግን ክፉዎች ጉባኤውን በከሃዲው በልዮን ምክር ወዳዘጋጀው ንጉሡ መርቅያንና ወደ ሚስቱ ንግሥት ብርክያል መልዕክት ልከው ከዲዮስቆሮስ በቀር እነርሱ ያዘዙትን ሃይማኖትንና ትእዛዝ የሚቃወም እንደሌለ በመናገር ነገር ሠሩበት፡፡ነገር ግን በጉባኤው ውስጥ ንስጥሮስን ያወገዙ አባቶችም ነበሩበት፡፡ንጉሡም ቅዱስ ዲዮስቆሮስን አስጠርቶት ከሌሎች ሊቃነ ጳጳሳት ጋር እስከ ማታ ድረስ ሲከራከሩ ዋሉ፡፡ቅዱስ ዲዮስቆሮስ እንዳልተመለሰላቸው ባዩ ጊዜ ንግሥቲቷና ንጉሡ በእርሱ ተቆጥተው ክፉኛ አስደበደቡት፡፡ጽሕሙን ነጭተው ጥርሱንም አስወለቁት፡፡ ቅዱስ ዲዮስቆሮስም የተነጨ ጽሕሙንና የወለቀ ጥርሱን ሰብስቦ ወደ እስክንድርያ በመላክ ‹‹እነሆ የቀናች ሃይማኖት ፍሬ ይህ ነው›› አላቸው፡፡ለጉበኤው የተሰበሰቡ ኤጲስ ቆጶሳትም በቅዱስ ዲዮስቆሮስ ላይ የደረሰውን ዐይተው ፈሩና ከከሃዲው ንጉሥ መርቅያኖስ ጋር ተስማሙ፡፡ክብር ይግባውና ‹‹ለክርስቶስ ሁለት የተለያዩ ባሕርያት አሉት›› ብለው በንጉሡ መዝገብ ላይ በእጆቻቸው ጽፈው ፈረሙ፡፡ቅዱስ ዲዮስቆሮስም እነርሱ የጻፉለትን መዝገብ እንዲልኩለት ሲጠይቃቸው ላኩለት እርሱም ጽፎ የሚፈርምበት መስሎአቸው ነበርና፡፡እርሱ ግን አባቶቻችን ሐዋርያት ካስተማሯት ከቀናች ሃይማኖት በኒቅያ የተሰበሰቡ ሃይማኖታቸው የቀና የ318 ኤጲስ ቆጶሳት አባቶቻችን ከሠሯት ሕግ የሚወጣውን ሁሉ በደብዳቤው ግርጌ ጽፎ አወገዘ፡፡መና*ፍቁ ንጉሥም ይህን ጊዜ እጅግ ተናዶ ጋግራ ወደምትባል ደሴት እንዲያግዙት አዘዘ፡፡የሀገረ ቃው ኤጲስ ቆጶስ አባ መቃርስ አብሮት ተሰደደ፡፡ሌሎቹ ግን ሸሹ። ከዚህም በኋላ እነዚያ የካዱ 636 ኤጲስ ቆጶሳት ተቀምጠው በኬልቄዶን ለራሳቸው መመሪያ የሚሆናቸውን ሥርዓት ሠሩ፡፡በጋግራ ደሴት ያለው ኤጲስ ቆጶስም ከንጉሡ ጋር የተባበረ ነበርና አቡነ ዲዮስቆሮስ ላይ ብዙ መከራ አደረሰበት፡፡የደሴቱ ሰዎች ግን በቅዱስ ዲዮስቆሮስ እጅ የሚፈጸሙ ተአምራትን
እያዩ እጅግ ያከብሩት ነበር፡፡ከዚህም በኋላ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ አባ መቃርስን ወደ እስክንድርያ ሄዶ ሰማዕት እንደሚሆን ትንቢት ነገረውና ከነጋዴዎች ጋር ላከው፡፡እንደተናገረውም አባ መቃርስ በእስክንደርያ ሰማዕት ሆኖ ዐረፈ፡፡አቡነ ዲዮስቆሮስ ግን በዚያቹ በጋግራ ደሴት ሰማዕትነቱን ፈጽሞ በክብር ዐርፏል፡፡ምእመናንም ሥጋውን በዚያው አኖሩት፡፡የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ረድኤት በረከቱ
ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡
+ + + + + + + + + + + + + + +
አቡነ ሳዊርያኖስ፡- የግሪክ አቴናን ፍልስፍናና ጥበብ ጠንቅቀው የተማሩ ናቸው፡፡ምግባር ሃይማኖታቸው የሰመረ፣ ትሩፋት ተጋድሏቸው የቀና ነው፡፡ብሉይን ከሐዲስም አጠናቀው ተምረዋል፡፡ወላጆቻቸው ያወረሷቸውን እጅግ የተትረፈረፈ ንብረት ሸጠውና ለጦም አዳሪዎች መጽውተው ለድኆች ማደሪያና ለእንግዶች ማሪፊያ ቤት ሠርተው ነዳያንን ይንከባከቡ ጀመር፡፡ይህንንም የጽድቅ ሥራቸውን የሮሜው ጻድቁ ንጉሥ አኖሬዎስ ሲሰማ እጅግ ደስ ተደስቶ አስመጥቶ ከእርሱ ጋር በቤተ መንግሥቱ አማካሪና አባቱ አድርጎ አኖራቸው፡፡ከንጉሡም ጋር አብረው ሁልጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ሌሊቱን በሙሉ ለጸሎት ቆመው ያድራሉ፡ጻድቁ የገብላው አገር ንጉሥ ሴት ልጁን ሰይጣን ይዟት ሳለ ደብዳቤ በመጻፍ ልከው በልጅቷ ላይ ያደረውን ሰይጣን በደብዳቤአቸው ብቻ አስወጥተውታል፡፡አቡነ ሳዊርያኖስ ደብዳቤ በመጻፍ ብቻ በሀገር ላይ የመጣ የጠላትንም ጦር
እያሸበሩ ድል ያደርጉ ነበር፡፡ይኸውም የቍስጥንጥንያው ንጉሥ አርቃዴዎስና አኖርዮስ በገብላ አገር ኤጲስቆጶስነት ከሾሟቸው በኋላ የፋርስ ሰዎች እነዚህን ደጋግ ነገሥታት ሊወጓቸው ሽተው በኃይል በመጡባቸው ጊዜ ወደ አባ
ሳዊርያኖስ መልአክትን ላኩ፡፡አባታችንም ለቅዱሳን ነገሥታቱ ‹‹እኛ የክርስቶስ ከሆንን መንግሥታችንም የክርስቶስ ነው፣

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🌻🌻🌻የአቡነ መልክአ ክርስቶስ የዕረፍቱ ቀን በደረሰ ጊዜ በጽኑ ደዌ ታመመ። ከመረጣቸው ጋር ቃልኪዳን ያደረገ መድኀኔዓለም ለአቡነ መልክአ ክርስቶስም እንዲሁ አደረገ። ‹‹…✝ድካምህን ተቀብያለሁ ✝በእጅህ የመነኰሱ፡✝ በመስቀልህ የተባረኩ፡✝ ከሩቅ አንተን ብለው ደጅህ የመጡ፣✝ በስምህ መታሰቢያህን የሚያደርጉትን ሁሉ የልባቸውን በጎ መሻት እፈጽምላቸዋለሁ✝፤ በደላቸውን ሳልመለከት ጸጋ በረከትን እሰጣቸዋለሁ፤✝ የወዳጆችህን ትውልድ እስከ 15 ትውልድ እምርልሃለሁ›› ብሎ ቃልኪዳን ከገባላቸው ✝በኋላ መስከረም 5 ቀን በዕለተ ቀዳሚት በ86 ዓመታቸው ነፍሳቸው ከሥጋው ተለየች። ከመቃብራቸውም ላይ ሕሙማን የሚፈወሱበት ድንቅ ድንቅ ተኣምራትን የሚያድርግ ጠበል ፈለቀ።

🌻🌻🌻አቡነ መልክአ ክርስቶስ ለአገልግሎት ሲጓዙ በመንገድ ላይ ከሞተ 900 ዓመት የሞላውን ሰው ዐፅም አግኝነተው ወደ እግዚአብሔር ጸልየው በመስቀላቸው ባርከው ከሞት አስነሥተውታል፣ ከሞት የተነሣውም ሰው ኢአማኒ ስለነበር ጻድቁ አጥምቀው ለክርስቶስ መንግሥት አብቅተውታል።

🌻🌻🌻የአቡነ መልክአ ክርስቶስ ልመናቸው ከክፉ ይጠብቀን፤ በቃልኪዳናቸው ሁላችንን ይጎብኙን።🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

✝ጥንታዊው ግሽት አቡነ መልክአ ክርስቶስ✝ ገዳም አባታችን መልክአ ክርስቶስ ገዳም የሚገኘው በደቡብ ወሎ ዞን ከደሴ ከተማ 152 ኪሜ ርቃ በምትገኘው መቅደላ ወረዳ ልዩ ስሙ ደጃ ከሚባል ቦታ ነው። ገዳሙ ፍጹም የአርምሞ ቦታ ነው፣ ጸናጽልና ከበሮ አይፈቀድም፣ ቅዳሴም ዓመት ኹለት ጊዜ ነው የሚቀደሰው፣ በበዓሉ ወቅት ታቦት ሲዞር እግዚኦታ እንጂ መዝሙር የለም ምክንያቱ ብዙ ቅዱሳን የተሠወሩበት ቅዱስ ሥፍራ ስለሆነ ነው።

በ910 ዓ.ም የተመሠረተው ጥንታዊው ግሸቅ አቡነ መልክአ ክርስቶስ ገዳም _ በውስጡ በርካታ ቅርሶች ያሉት በመሆኑ በተደጋጋሚ የዝርፊያ ወንጀሎች ተፈጽመውበታል። ታላላቆቹ ነገሥታት እነ ራስ ሚካኤል ለገዳሙ በስጦታ ያበረከቷቸው በርካታ ቅርሶችና ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት በገዳሙ የሚገኙ ሲሆን ገዳሙ በዓሥር ዓመት ውስጥ ሦስት ጊዜ ዝርፊያ ሲፈጸምበት አንደኛው ሌባ ሙክታር የሚባል በዳውንት የሚኖር ኢስላም ከግብረ አበሮቹ ጋር ወደ ገዳሙ በመግባት ስምንት 8 ጥንታዊ የብራና መጽሐፍት ዘረፈ። ሁለተኛው ዘረፋ ደግሞ የተፈጸመው አገልጋይ መነኵሴ መስሎ አንድነቱን በተቀላቀለ ሰው አማካኝነት ነበር። ነገር ግን አሁን አበ ምኔት ሆነው የሚያገለግሉት አባ ክፍለ ማርያም ጥበብ በተሞላበት ዘዴ ከሌሎች ሌቦች ጋር በጐን በመደራደር የተዘረፉትን ቅርሶች እንዲመለሱ አድርገዋል
ሥስተኛው ዝርፊያ በ2009 ዓ.ም መሣሪያ በመያዝ ስድስትሆነው ወደ ገዳሞ ለመዝረፍ የመጡት ደግሞ በጎንደርና በባህርዳር ቅርስ በመዝረፍ ልምድ ያላቸው ነበሩ ነገር ግን ዋነኛው ዘራፊ ከገዳሙ መግቢያ በር ሲደርስ በጻድቁ ተኣምር ተዝለፍልፎ ስለወደቀ አብረውት የነበሩትም ተደናግጠው የወደቀውን ደጋግፈው ተሸክመው ከተመለሱ በኋላ በመንገድ ላይ ያገኟቸውን ሦስት የገዳሙን አህዮች ይዘው ሔዱ። አሁን ላይ ገዳሙ በጠየቀው መሠረት ቀበሌው አንድ ታጣቂ ሚሊሻ መድቦላቸዋል። እርሱም የገዳሙ አባቶች ከሚመገቡት እየተመገበ ደሞዝ በየወሩ እየከፈሉት ገዳሙን ይጠብቅ ነበር። በተጨማሪም አባቶች በገዳሙ ውስጥ ውሻ ማሳደግ ጀመሩ። የገዳሙ አበ ምኔትም ስለ ቅርሶቹ ዘረፋ በተደጋጋሚ ዛቻና ማስፈራሪያ እንደሚደርስባቸው ይናገራሉ። ይኸም በሀገራችን የሚገኙት ታላላቅ ገዳማትና በውስጣቸው የያዟቸው ብርቅዬ ቅርሶች

ምን ያህል ከባድ ፈተና እንደተጋረጠባቸው አንድ ማሳያ ነው። በአሜሪካና በአውሮፓ የሚገኙ በርካታ መጻሕፍት ቤቶቻቸውና ሙዚየሞቻቸው በእኛው የብራና መጻሕፍት ታጭቀው የሚገኙትም በዚህ መንገድ በስርቆት በተወሰዱ መጻሕፍቶቻችን ነው።

የአቡነ መልክአ ክርስቶስ አምላክ ሀገራችንን ይጠብቅልን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የሚያገለግላቸውን አህያ ጅብ ቢበላባቸው በአህያቸው ፋንታ ጅቡን ለ7 አመት ውሃ እየቀዳ እንዲያገለግላቸው ያደረጉት የአቡነ መልክአ ክርስቶስ መስከረም 5 ዕረፍታቸው ነው።
🌻🌻አቡነ መልክአ ክርስቶስ🌻🌻

🌻🌻🌻ቅዱስ ገድላቸው እንደሚናገረው ታላቁን ጻድቅ አቡነ መልክአ ክርስቶስን እንደ ስዉ እየተላላከ ከበሽሎ ወንዝ ውኃ እየቀዳ ወደ ገዳማቸው የሚያመጣላቸው እንድ አህያ ነበራቸው። አህያውም ሰው ሳይጭነው ባዶ እንስራ ወደ ወንዙ ወስዶ በተአምር ውኃ በእንስራ ሲሞላለት ሳያጋድል ይዞ ሩቅ መንገድ ተጉዞ ከአባታችን ገዳም ይደርሳል። ነገር ግን በአንደኛም ቀን ይህንን አገልጋይ አህያቸውን ጅብ በላባቸው አቡነ መልክእ ክርስቶስም በአህያቸው ፈንታ ጅቡን ሰባት ዓመት ውኃ አስቀድተውታል።

🌻🌻🌻ኹለቱ ጎምቱ ታላላቅ ቅዱሳን አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስና አቡነ መልክአ ክርስቶስ በአንድ ዘመን አብረው የኖሩ ሲሆን የቅርብ ወዳጆችም ነበሩ።

🌻🌻🌻ገድላቸው እንደሚናገረው አቡነ መልክአ ክርስቶስ ከግራኝ አህመድ የ15 ዓመት ጥፋት በኋላ የቅዱስ ያሬድን የቅዳሴ ዜማ ትምህርት ጠብቆ ለትውልድ በማበርከት እጅግ የጎላ ድርሻ አላቸው።
🌻🌻🌻 ይኸውም እንዲህ ነው ቅዱስ ያሬድ ማየ ኪራህ ከሚባል ቦታ እያለ አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችን ቅዱስ ኤፍሬምን ከሶርያ አባ ሕርያቆስን ከብሕንሳ በደመና ጠቅሳ ቅዱስ ያሬድ ካለበት ማየ ኪረህ አወጣቻቸውና ‹አንተ ውዳሴዬን፣ አንተ ቅዳሴዬን ነግራችሁት እርሱ በዜማ ያድርስ በማለት ነገረቻቸው ።

🌻🌻🌻ቅዱስ ኤፍሬምና አባ ሕርያቆስም የየራሳቸውን ድርሰት እየነገሩት ቅዱስ ያሬድ ሁሉንም ድርሰታቸውን በዜማ አድርሶታል። ከዚሁም ጋር አያይዞ 13ቱንም ቅዳሴ በዜማ ደርሷል። እርሱም እነዚኽን ዜማዎቹን ለደቀ መዛሙርቶቹ _አስተምሯቸዋል። ቅዳሴ ትምህርት እንደሌሎቹ ዜማዎች ተስፋፍቶ በየገዳማቱ እየተሰጠ ቆይቷል ነገር ግን የሰይጣን መልእክተኛ የሆነ ግራኝ አህመድ በውጭ ኀይሎች እየታገዘ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን ከሀገራችን ለማጥፋት 15 ዓመት ሙሉ ሊቃውንትን ሲያርድ፣ ገዳማትን ሲያቃጥል ኖረ። በዚኸም ጊዜ የተገደለው ተገድሎ የሚሰደደው ተሰደደ፤ የቤተ ክርስቲያን ነዋየ ቅድሳትና መጻሕፍትም ተቃጠለ። በዚኸም ምክንያት በስደት ላይ የነበሩት የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ቀርበው እንዳይጠያየቁ ስደቱ ፈተና ስለሆነባቸው ዜማው እየተፋለሰ መጣ።
🌻🌻🌻የቅዳሴው የዜማ ትምህርትም ከጎንደር ተነሥቶ ወደ ዋድላ ገባ። ዋድላ ልዩ ስሙ ሰለልኩላ ይዘውት የገቡት መምህርም ዜማውን አጠናቀው ተምረው ወደምነና የተሰማሩት አቡነ መልክአ ክርስቶስ ናቸው። እርሳቸውም በምናኔ ሕይወት በተለያዩ ሀገራት እግዚአብሔርን ካገለገሉ በኋላ ወደሰለልኩላ ሀገር ገብተው የቅዱስ ሚካኤልን ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ሰለልኩላ የሚባለውን ከቅዱስ ያሬድ ሲያያዝ የመጣውን ቅዳሴ እንዳስተማሩ በጊዜው የነበሩ አባቶች ስለ ሰለልኩላ ቅዳሴ ቀደምትነት እና እንዴት ወደዚህ ሀገር እንደመጣ በጻፉት ታሪክ ላይ ተመዝግቦ በቦታው ላይ ይገኛል። ይኸም ቦታ እስከዛሬ ድረስ የሰለልኩላ ቅዳሴ ማስመስከሪያ ሆኖ ይገኛል። የደብረ ዓባይ ቅዳሴ እና የሰለልኩላ ቅዳሴ በወዝና እና በስም ነው የሚለያየው እንጂ ቅዳሴው በምልክት፣ በአገልግሎትና መንፈሳዊ በሆነ ነገሮች ሁሉ አንድ ነው፤ ይኸም በሙያው አንቱ የተባሉ የቤተ ክርስቲያኗ ጌጦች የሆኑ ሊቃውንትና ምሁራን መዝገበ ቅዳሴ ውስጥ ያሉ ቀለማትን በማንሣትና በዜማም በመጠያየቅ አንድ እንደሆነ አረጋግጠዋል በማለት ገድለ አቡነ መልክአ ክርስቶስ ይገልጻል።

🌻🌻🌻አቡነ መልክአ ክርስቶስ ዐቢይ ጾም ሲገባ ብዙ ጊዜ ብቻውን ሱባኤ ይይዛል። በዐቢይ ጾም ወቅት ከዕለታት በአንደኛው ቀን በግሽቅ ማርያም ሳለ ክፉ ጠላት በከባድ ረኀብ ፈተነው። አባታችንም በዚህ አዝኖ ሲጨነቅ ክብርት እመቤታችን ተገልጻለት ሰላም ለአንተ ይሁን ወዳጄ መልክአ ክርስቶስ›› አለችው፤ ዳግመኛም ስለምን ትተክዛለህ? አይዞህ ጽና…” ብላ በልጇ ቸርነት ሰማያዊ ኅብስት መገበችው። አባታችንም ይህን ምሥጢር ለልጁ ለአባ ሚካኤል ከነገረው በኋላ እስከምሞት ድረስ ይህን ለማንም አትንገር፣ በኋላ ግን እንደፈቃድህ›› አለው ቅዱሳን ከውዳሴ ከንቱ ለመሸሽ ሲሉ በሕይወት እያለ በጎ ሥራቸውን መደበቅ ልማዳቸው ነው።

🌻🌻🌻የአቡነ መልክአ ክርስቶስ አባት ጣዕመ ክርስቶስ፡ እናታቸው አውጋንያ ይባላሉ እነርሱም ልጅ አልነበራቸውምና የተባረከ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ዘወትር ወደ እግዚአብሔር ይማጸኑ ነበር ነገር ግን ‹‹የተባረከ ፍሬ የማትሰጠን ከሆነ ልጅ አትስጠን› እያሉም ይጸልዩ ነበር። ጣዕመ ክርስቶስና አውጋንያ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፣ ሕጉን ዘወትር የሚጠብቁ፡ ለተቸገሩ የሚራሩ ናቸው። የተራቡትን በመመገብ የታረዙትን በማልበስ የበረቱ በመሆናቸው ዘወትር ከቤታቸው ድኆች አይጠፉም ነበር። የቅዱሳኑን ልመና የተቀበለ አምላክ የእነርሱንም ልመናቸውን ሰምቶ የተባረከ ልጅ አቡነ መልክአ ክርስቶስን ሰጣቸው። አባታችን በምድረ ኢትዮጵያ ሳርካ በሚባል ቦታ ሰኔ 27 ተፀንሶ መጋቢት 27 ቀን ተወለደ። ዕድሜውም ለትምህርት ደርሶ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሲማር ከዕለታት

🌻🌻🌻አንድ ቀን ከሕፃናት ጋር ሲጫወት እመቤችን ተገልጻለት … ከእንግዲህ አንተ የምትጫወተው ከቅዱሳን መላእክት ከጻድቃንና ከሰማዕታት ጋር ይሁን አለችው እርሱም ዘወትር ጸሎትን መጸለይ ጀመረ። መንፈስ ቅዱስ ስለገለጠለት የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ወድያው አጠናቀቀ።

🌻🌻🌻ከዚኽም በኋላ አቡነ መልክአ ክርስቶስ ገና በለጋ ዕድሜው ስለ ጌታችን መስክሮ ስማዕት ይሆን ዘንድ በመመኘት በዘመነ ሰማዕታት ሰማዕትነትን ከሚቀበሉባቸው ቦታዎች ቢሔድም ሰማዕትነት ለእርሱ አልተፈቀደለትም ነበር። ወደ ወግዳ እና ምድረ ሰርማት የሚባሉ ቦታዎች ቢሔድም የተመኘውን ሳያገኝ ቀረ፣ በዚኸም ጊዜ ቃል ከሰማይ ወደ እርሱ መጣና ወዳጀ መልክእ ክርስቶስ ሆይ! ሰማዕትነት ክፍልህ አይደለም ይልቁንም እንደ አብርሃም የብዙሃን አባት የሕፃናትና የደካሞች መጠጊያ ትሆናለህ አለው።

🌻🌻🌻ከዚኽም በኋላ ጻድቁ በመንዝ በጎንደር፣ በመቄት በዳውንት፣ በላስታ፤ በዋድላና በሌሎቹም ቦታዎች ተዘዋውሮ የከበረች ወንጌልን በመስበክ ድዉያንን በመፈወስ ብዙ አገልግሏል። መንዝ ሪቅ በሚባል ቦታ አቅም የሌላቸውን በዕድሜም የግፉትን እናቶችንና አባቶችን ውኃ በመቅዳት ምግብ በማብሰል ዕንጨት በመሽከም አገለገላቸው። እንግዶች ሲመጡ እግራቸውን አጥቦ ያሳርፋቸዋል። ሥራዎችን በሚሠራ ጊዜም ከአንደበቱ ጸሎት አይቋረጥም ነበር። በእንዲህ ያለ ምግባር ዐሥር ዓመት ካገለገለ በኋላ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ደቀ መዝሙር ከሆነው ከአቡነ አኖሬዎስ ቤተ ክርስትያን ደብረ ጽጋጃ አባ ጴጥሮስ በተባለ መምህር እጅ መነኰሰ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#መስከረም_5

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
መስከረም አምስት በዚች ቀን #ቅድስት_ሶፊያ_ሰማዕት ከሁለት ልጆቿ ጋር በሰማዕትነት አረፈች፣ #አቡነ_አሮን_መንክራዊ እረፍት ነው፣ #ቅዱስ_ማማስ_ሰማዕት በሰማዕትነት አረፈ፣ ኢትዮጵያዊው ጻድቅ #አፄ_ልብነ_ድንግል እረፍቱ ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስት_ሶፊያ_ሰማዕት

መስከረም አምስት በዚች ቀን የከበረች ሶፊያ ከሁለት ልጆቿ አክሶስናና በርናባ ከሚባሉት ጋር በሰማዕትነት ሞተች ።

ዘመነ ሰማዕታት በሚል በሚታወቀው 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ብዙ ቅዱሳት እናቶቻችን ስለ ፍቅረ ክርስቶስ አንገታቸውን ሰጥተዋል:: አንዳንዶቹ ደግሞ ሕይወታቸው እጅግ የሚያምር ነበር:: ከእነዚህ ቅዱሳት እናቶቻችን አንዷ ዛሬ የምናከብራት ሐጊያ ሶፊያ ናት::

በዚህ ስም ከሚጠሩት አንዷ ስትሆን በቀደመ ሕይወቷ ክርስቶስን አታውቅም ነበር:: ጣዖትን የሚያመልኩ ወላጆቿ አሳድገው አጋቧት:: ከትዳሯም 2 ቡሩካት ሴቶች ልጆች ወልዳለች:: ስማቸውም አክሶስናና በርናባ ይባላል:: ልጆቿ ልብ እያገኙ በሔዱ ጊዜ ቅድስት ሶፍያ ስለ እውነተኛው አምላክ ትመራመር ገባች::

በወቅቱ የነበሩ ብዙ ሃይማኖቶችን መዘነች:: ከክርስትና በቀር ግን ሌሎቹ ሚዛን እንደማይመቱም አስተዋለች:: "እውነኘተኛው አምላክ ሆይ! ምራኝ እርዳኝም" ስትል ጸለየች:: መድኃኔዓለም ለጠሩት አያሳፍርምና ፈጥኖ በጐውን ጐዳና አሳያት።

ድኅነት ለልጆቿም ይሆን ዘንድ ሁለቱንም ጠርታ ስለ ክርስትና አማከረቻቸው:: ደስ ብሏቸው ተቀበሏት:: እርሷም ጊዜ ሳታጠፋ ወደ ዻዻስ ሒዳ ማሕተመ ክርስትና: ሃብተ ውልድናን ትቀበል ዘንድ ከልጆቿ ጋር ተጠመቀች:: በቅድስናና ደስ በሚያሰኝ አኗኗርም እስከ መከራ ቀን ቆየች::

የመከራ ጊዜ ሲደርስም ልጆቿን ጠርታ "ስለ ክርስቶስ ፍቅር እንሙት" አለቻቸው:: ቡሩካቱ አክሶስናና በርናባም ደስ እያላቸው "እሺ" አሏት:: ወዲያውም በመኮንኑ ፊት ቀርበው ክርስቶስን ከመካድና ከስቃይ ሞት የትኛውን እንደሚመርጡ ቢጠየቁ እነርሱ መሞትን መረጡ:: ወደ እሥር ቤትም ከተቷቸው::

ቅድስት ሶፍያ 2 ልጆቿ ይጸኑላት ዘንድ አዘውትራ ገድለ ሰማዕታትን እና ክብራቸውን ትተርክላቸው ነበር:: በተለይ የታላቁዋን አንጌቤናይት (እመቤት) ሶፍያንና የ3 ልጆቿን (ዺስጢስ: አላዺስና አጋዺስ) ተጋድሎ እየነገረች ታጸናቸው ነበር።

ከእሥር በኋላ ግርፋት ታዞባቸው እናት ራቁቷን ስትገረፍ መልአክ ወርዶ ሲጋርዳት ልጆች በማየታቸው ደስ አላቸው:: ቅድስት ሐጊያ ሶፍያና 2 ልጆቿ እጅግ የበዛ ስቃይን ስለ ቀናች እምነት ተቀበሉ:: ምላስ እስከ መቆረጥም ደረሱ:: በመጨረሻ ግን በዚህች ቀን ተገድለው አክሊለ ሰማዕታትን ገንዘብ አደረጉ

የመከራ ዘመን ካለፈ በኋላ ታላቁ ንጉሥ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ የሁሉን ቅዱሳን ቤት ሠርቶ የእርሷን በመዘንጋቱ ለራሱ ባሰራው ቤተ መንግስት ላይ ተአምር ታይቷል። ለ3 ያህል ጊዜ ስሙን ሲያስቀርጽ መልአክ እየወረደ ይፍቀው የሶፍያንም ስም ይጽፈው ነበር።

በመጨረሻም ንጉሡ ልጁን እስከ መገበር ደርሶ ቤተ መንግስቱ የቅድስት ሶፍያና የ2 ልጆቿ ቤተ ክርስቲያን ለመሆን በቅቷል:: ምንም ለ3 ጊዜያት ያህል ሙሉ እድሳት ቢደረግለትም ዛሬ አሕዛብ የያዙትን ይህንን ቅርስ ንጉሡ የሠራው ከ1700 ዓመታት በፊት ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_አሮን_መንክራዊ

በዚህች ቀን አቡነ አሮን መንክራዊ ዕረፍታቸው ነው፡፡ አቡነ አሮን ወላጅ አባታቸው የላስታው ጻድቁ ንጉሥ ዐፄ ገብረ መስቀል ናቸው፡፡ እናታቸው አመተ ማርያም ይባላሉ፡፡ የላስታ ነገሥታት የዘር ሐረጋቸው ከንጉሥ ሰሎሞን ዘር ሲያያዝ የመጣ ነው፡፡

ከ10ኛው እስከ 13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን (920-1253 ዓ.ም ገደማ) በላስታ ቡግና ምድር የነገሡ የላስታ ቡግና ተወላጅ የሆኑ የኢትዮጵያ ቅዱሳን ነገሥታት የንግሥናቸው መጠሪያ ‹‹የዛጉዌ ሥርወ መንግሥት›› ወይም ‹‹የላስታ መንግሥት›› በመባል ይታወቃል፡፡ የንጉሥ ሰሎሞን ዘር የሆነው መራ ክርስቶስ 3 ልጆችን ወለደ፡፡ እነርሱም ጠንጠውድም፣ ግርማ ስዩምና ዣን ስዩም ናቸው፡፡ ጠንጠውድም ገብረ መስቀልን ወለደ፣ ገብረ መስቀልም አቡነ አሮንን ወለደ፣ ግርማ ስዩም ይምርሐነ ክርስቶስን ወለደ፣ ዣን ስዩም ደግሞ ገብረ ማርያምንና ላሊበላን ወለደ፡፡ ገብረ ማርያምም ነዓኲቶ ለአብን ወለደ፡፡ እነዚህ ቅዱሳን ነገሥታት እንደ መልከጼዴቅ (ዘፍ14፡18) ክህነትን ከንግሥና፣ ቅድስናን ከንጽሕና ጋር አንድ አድርገው በመያዝ እግዚአብሔርንም ሕዝብንም በቅድስናና በንጽሕና አገልግለው አልፈዋል፡፡

አቡነ አሮን ግን ገና በ7 ዓመታቸው ነው ዓለምን ፍጹም ንቀው በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል እጅ የመነኮሱት፡፡ በ16 ዓመታቸውም ዋልድባ ገዳም ገብተዋል፡፡ ነሐሴ 5 ቀን ገና ሲወለዱ ሙት አስነሥተዋል፡፡ በሀገራችን እየተዘዋወሩ ወንጌልን ሲሰብኩ የሸዋው ንጉሥ አንኮበር ድረስ ጠርቷቸው ሲሔዱ አዋሽ ወንዝ ሞልቶባቸው አገኙት፡፡ ሲሻገሩም ዳዊታቸውን ወስደባቸው፡፡ ‹‹ልጆቼን አመነኮስክብኝ›› በሚል ሰበብ ንጉሡ 7 ዓመት በግዞት አስሮ አስቀመጣቸው፡፡ ነገር ግን ከ7 ዓመት በኋላ አቡነ አሮን ተመልሰው በአዋሽ ወንዝ ሲመጡ መልአክ መጣና ‹‹መቋሚያህን ወደ ወንዙ ላክ›› አላቸው፡፡ መቋሚያቸውንም ቢልኩ ከ7 ዓመት በፊት ወደ ወንዙ ገብቶባቸው የነበረውን ዳዊታቸውን ይዘው አወጡ፡፡ ዳዊቱም በውኃው አልራሰም ነበር፣ ይልቁንም አቧራውን አራግፈው ፈጣሪያቸውን አመስግነው ዳዊታቸውን ይዘው ሄደዋል፡፡ ያ ዳዊታቸው ዛሬም ድረስ በጋይንት አበርጉት ቅዱስ ሚካኤል ይገኛል፡፡

ሰሜን ወሎ መቄት ወረዳ ውስጥ የሚገኘው እጅግ አስደናቂ ገዳማቸው ፍልፍል ዋሻ ሲሆን ጣራው ክፍት ነው፣ ክፍት በሆነው ጣራ በኩል ፀሐይ ሲገጣ ስለሚያቃጥል ጥላ ይይዛሉ ነገር ግን የጻድቁ ግዝት ስላለበት ዝናብ ወደ መቅደሱ ፈጽሞ አይገባም፡፡ እጅግ አስደናቂ ነው፡፡ አቡነ አሮን በዋድላ ሜዳ አልፈው ሲሄዱ አንችም ሜዳ ላይ እንደ ኢያሱ ፀሐይን በቃላቸው ገዝተው አቁመዋታል፡፡

ከታች ጋይንት ተነሥተው መንገድ ሲሄዱ በሰንበት ቀን በሬ ጠምዶ ሲያርስ የነበረን ገበሬ ‹‹ለምን በሰንበት ታርሳለህ?›› ቢሉት ‹‹ምቀኛ መነኩሴ›› ብሎ በጅራፉ ቢገርፋቸው በሬዎቹ ግን ፈጽሞ አልንቀሳቀስ ብለው ቆመዋል፡፡ በዚህ የተናደደው ገበሬም አቡነ አሮንን መሬት ላይ ጥሎ ገረፋቸው፡፡ እሳቸውም ተነሥተው ሲሄዱ ዛፎች ተነቅለው እየተከተሏቸው፣ ቃልም አውጥተው በሰው አንደበት አመስግነዋቸዋል።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ማማስ_በሰማዕት

በዚህችም ቀን ቅዱስ ማማስ በሰማዕትነት ሞተ የአባቱ ስም ቴዎዶስዮስ የእናቱም ያኖች ናቸው። በንጉሥ ዑልያኖስ ዘመንም ስለ ሃይማኖታቸው ይዘው አሠሩአቸው በእሥር ቤትም ሳሉ አረፉ።

አንዲት ክርስቲያናዊት ሴት መጥታ ይህን ሕፃን ወስዳ እንደ ልጅዋ አድርጋ አሳደገችው። ስሙንም ማማስ ብላ ሰየመችው ትርጓሜውም። የሙት ልጅ ማለት ነው አባትና እናት የለውምና።

ዐሥራ ስምንት ዓመትም በሆነው ጊዜ ወደ ከሀዲው ገዢ ሒደው ክርስቲያን ነው ብለው ወነጀሉት ይዘውም በበትሮች ደበደቡት በአንገቱም የሚከብድ ሸክም ታላቅ የዓረር ደንጊያ አንጠልጥለው ከባሕር ውስጥ ጣሉት። ክብር ይግባውና በእግዚአብሔር ኃይል ከባሕር ስጥመት ዳነ ወጥቶም በዋሻ ውስጥ ተሠውሮ ከጎሽ ወተትን እየተመገበ ተቀመጠ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† 🌻✝️መስከረም 4 ቀን የሚከበሩ የቅዱሳን በዓላት †††🌻✝️

†††🌻✝️ እንኳን ለታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኢያሱ እና ለቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††🌻✝️

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

†††🌻✝️ ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ ወመስፍን🌻✝️ †††

††† ቅዱሱ የተወለደው በምድረ ግብፅ በባርነት ከነበሩ እሥራኤላውያን ሲሆን የቀደመ ስሙ #አውሴ ይባላል:: ዘመኑ #እግዚአብሔር ሕዝቡን ከ215 ዓመታት ባርነት ሊያወጣ የተቃረበበት ነውና #ሊቀ_ነቢያት_ሙሴ ከምድያም ሲመለስ ከመረጣቸው ተከታዮቹ ዋነኛው ኢያሱ ነበር:: እሥራኤል ከባርነት ሲወጡ ሙሴ 80 ዓመቱ: ኢያሱ ደግሞ 40 ዓመቱ ነበር::

ሕዝቡ አንገተ ደንዳና ነበርና ለ40 ቀን የታሠበላቸውን መንገድ 40 ዓመት እንዲሆን አደረጉት:: በዚህ ጊዜ ኢያሱ ከመምሕሩ ከሙሴና ከሕዝቡ አልተለየም:: አውሴን ኢያሱ ብሎ ስም የቀየረለት ሙሴ ሲሆን ይሔውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነው::

ኢያሱ ማለት " #መድኃኒት" ማለት ነው:: ለዚሕም ምክንያቶች አሉት:-
1.ለጊዜው አማሌቃውያንን ድል ነስቶ ሕዝቡን አድኗል: ምድረ ርስትን አውርሷል::
2.ለፍጻሜው ግን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ (ጥላ) እንዲሆን ነው::

ቅዱስ ኢያሱ በበርሃው ለዘመናት እግዚአብሔርን አምልኮታል:: ሊቀ ነቢያትን ታዞታል (አገልግሎታል): እሥራኤልንም የጦር አለቃ ሆኖ ከአሕዛብ እጅ አድኗቸዋል:: በዚህም በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ዘንድ ሞገስን አግኝቷል:: ቅዱስ ሙሴ #ደብረ_ናባው ላይ ባረፈ ጊዜ ሕዝቡን: ካሕናቱንና ታቦተ ጽዮንን ተረከበ:: ይህን ጊዜ ዕድሜው 80 እየሆነ ነበር::

††† እግዚአብሔርም ኢያሱን "ከአንተ ጋር ነኝ" ብሎ በሕዝቡ ላይ ነቢይና መስፍን (አስተዳዳሪ) እንዲሆን ሾመው:: ቅዱሱም ሰላዮችን ልኮ አስገምግሞ:
¤ባሕረ ዮርዳኖስን ከፍሎ:
¤ሕዝቡን አሻግሮ:
¤የኢያሪኮን ቅጥር 7 ጊዜ ዙሮ:
¤በኃይለ እግዚአብሔር አፍርሶ:
¤የኢያሪኮን ነገሥታት አጥፍቶ:
¤ለሕዝቡ ምድረ ርስትን አወረሰ::

የገባዖን ሰዎች "አድነን" ብለው በላኩበት ጊዜ ነገሥተ አሞሬዎንን ይወጋ ዘንድ ኢያሱ ወጣ:: እነዛን ግሩማን ነገሥታት በፈጣሪው ኃይል: በጦርና በተአምራት ድል ነስቶ የእግዚአብሔር ስሙ ከፍ ከፍ አለ:: በዚሕች ዕለትም ለ12ቱ ነገደ እሥራኤል ርስትን ሲያካፍል ፀሐይን በገባዖን: ጨረቃን ደግሞ በቆላተ ኤሎም (በኤሎም ሸለቆ) አቆመ::

ሰባት #አሕጉራተ_ምስካይ(የመማጸኛ ከተሞችን) ለየ:: ነቢይና መስፍን ሆኖ ሕዝቡን ለ40 ዓመታት አገለገለ:: በመጨረሻም ለሕዝቡ:- "እኔና ቤቴ እግዚአብሔርን እናመልካለን:: (ኢያ. 24) እናንተስ?" አላቸው:: እነርሱም "እኛም እንዳንተ ነን" አሉት:: ለዚህም ምልክት ይሆን ዘንድ 3 ገጽ ያላት ሐውልትን በመካከላቸው አቆመ::

ይህችውም የቅድስት #ድንግል_ማርያም ምሳሌ ናት:: ሐውልቷ 3 ገጽ እንዳላት እመቤታችንም በ3 ወገን (በነፍስ: በሥጋ: በልቡና) ድንግል ናት:: አንድም በ3 ወገን (ከኃልዮ: ከነቢብ: ከገቢር ኃጢአት) ንጽሕት ናት:: ለዚህም ነው #አባ_ሕርያቆስ
"ሐውልተ ስምዕ ዘኢያሱ" (የኢያሱ የምስክር ሐውልት አንቺ ነሽ) ሲል ያመሰገናት::

ታላቁ ነቢይ ኢያሱ ግን ከግብጽ በወጡ በ80 ዓመት: በተወለደ በ120 ዓመቱ (ጥሬው መጽሐፍ ቅዱስ በ110 ዓመቱ ይላል) በወገኖቹ መካከል ዐርፎ በያዕቆብ መቃብር ተቀበረ:: እሥራኤልም ለ30 ቀናት አለቀሱለት::

†††🌻✝️ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ🌻✝️ †††

††† አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ እንደነገረን በመንግስተ ሰማያት ታላቁ ሰው ወንጌላዊው ዮሐንስ ነው::

ቅዱሱ ሐዋርያ ከዘብዴዎስና ከማርያም ባውፍልያ ተወልዶ: በገሊላ አካባቢ አድጐ: ገና በወጣትነቱ መድኃኔ ዓለምን ተከትሎታል:: ቅዱስ ዮሐንስ ከሐዋርያት ቀድሞ ጌታን ከመከተሉ ባሻገር በምንም ምክንያት ከጐኑ አይጠፋም ነበር:: ስለ ንጽሕናውና በጐ የፍቅር ሕሊናው ሕጻን ሳለ በወንድሞቹ ሐዋርያት ዘንድ ሞገሱ ከፍ ያለ ነው::

ጌታችንን እስከ እግረ #መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ድንግል እመቤታችንን ተቀብሏል:: ከእርሷ ጋር ለ15 ዓመታት ቢቀመጥ መዝገበ ምሥጢር ሆነ:: ስንኩዋን ከሰው ልጆች ይቅርና ከልዑላኑ መላዕክትም ማዕረጉ ከፍ አለ:: ሰው ቢበቃ መላእክትን ሊያይ ይቻለዋል:: ቅዱስ ዮሐንስን ግን መላእክት ሊያዩት ይከብዳቸዋል:: ከፍጥረት ወገን ከእመ ብርሃን ቀጥሎ ክቡር እርሱ ነው::

ቅዱሱ ከጌታችን ዕርገት በሁዋላ ለ70 ዓመታት በዚህ ምድር ሲኖር አብዛኛውን ጊዜውን ያሳለፈው በኤፌሶን አካባቢ ነው:: ሕዝቡን ወደ ክርስትና ለማምጣት በአፍም በመጽሐፍም ደክሟል::

ሶስት መልዕክታት: ራዕዩንና ወንጌልን ጽፎላቸዋል:: ሕይወትን ስለ ሰበከላቸው በፈንታው ብዙ አሰቃይተውታል:: ከእሳት እስከ ስለት: እስከ መጋዝም በስተእርጅና ደርሶበታል:: እርሱ ግን በትእግስቱ ገንዘብ አድርጉዋቸዋል::

††† እናት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሐንስን ስትጠራው እንዲሕ ነው:-
¤ወንጌላዊ
¤ሐዋርያ
¤ሰማዕት ዘእንበለ ደም
¤አቡቀለምሲስ (ምሥጢራትን ያየ)
¤ታኦሎጐስ (ነባቤ መለኮት)
¤ወልደ ነጐድጉዋድ
¤ደቀ መለኮት ወምሥጢር
¤ፍቁረ እግዚእ
¤ርዕሰ ደናግል (የደናግል አለቃ)
¤ቁጹረ ገጽ
¤ዘረፈቀ ውስተ ሕጽኑ ለኢየሱስ (ከጌታ ጎን የሚቀመጥ)
¤ንስር ሠራሪ
¤ልዑለ ስብከት
¤ምድራዊው መልዐክ
¤ዓምደ ብርሃን
¤ሐዋርያ ትንቢት
¤ቀርነ ቤተ ክርስቲያን
¤ኮከበ ከዋክብት

††† በዚህች ዕለት ቅዱሱ ሐዋርያ ከእናቱ #ማርያም_ባውፍልያ: ከአባቱ #ዘብዴዎስ መወለዱን ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች::

†††🌻✝️ አባ ሙሴ ዻዻስ🌻✝️ †††

እሥራኤላዊ ሲሆኑ ከአቡነ #ሰላማ ቀጥለው የመጡ የሃገራችን ዻዻስ ናቸው:: ፍጹም ገዳማዊና ትጉህ: ባለ ረዥም ዕድሜ ጻድቅም ናቸው::

ገዳማቸው #ወሎ ውስጥ ቢገኝም አስታዋሽ ያጣ ይመስላል:: መናንያኑ ለዕለት እንኩዋ የሚቀምሱት አጥተው ሲቸገሩ መመልከቱ እጅግ ያማል::

††† በቅዱስ ዮሐንስ ላይ ያደረ የእመቤታችን ድንግል ማርያምና የአንድ ልጇ ፍቅር በእኛም ላይ ይደር:: ቸሩ ጌታ ስም አጠራራቸው ካማረና ከከበረ ወዳጆቹ በረከትን ያሳትፈን::

††† መስከረም 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ኢያሱ ወልደ ነዌ (ነቢይና መስፍን)
2.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ (ልደቱ)
3.ቅዱሳን ዘብዴዎስና ማርያም ባውፍልያ
4.አባ መቃርስ ሊቀ ዻዻሳት
5.አባ ሙሴ ዻዻስ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
2.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
3.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት)

††† "አሁንም እግዚአብሔርን ፍሩ:: በእውነተኛም ልብ አምልኩት . . . እግዚአብሔርን ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ . . . የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ: የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ:: እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን::" †††
(ኢያሱ. 24:14)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እመ አምላክ ልበልሽ | ዘማሪ ፍቃዱ አማረ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ደጅሽ ላይ ቆሜ | ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Selam yetewahdo lijoch endet aderachu enkuwan le ametawi yekidus yohenns ametawi beal nigs beselam aderesachu aderesen

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

4.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላእክት
5.ቅዱስ ኢዮብ ተአጋሲ
6. ሜልዮስ ሊቀ ዻዻሳት

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና

++"+ የነቢዩንም የኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት:: መጽሐፉንም በተረተረ ጊዜ:-
የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው:: ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና:: ለታሠሩትም መፈታትን: ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ: የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ: የተወደደቺውንም የጌታ ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል::'
ተብሎ የተጻፈበትን ሥፍራ አገኘ:: +"+ (ሉቃ. 4:17)

‹‹‹ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ›››

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

=>+"+ እንኩዋን ለዘመነ #ሉቃስ የመጨረሻ ዕለት (ጳጉሜን 6) በሰላም አደረሳችሁ +"+

"ዮም በዛቲ ዕለት ይደልወነ ንሰብሖ ለአምላክነ: እስመ አብጽሐነ እስከ ዛቲ ዕለት በዳኅና ወበሰላም: እንዘ ኢይዜከር ኃጣውኢነ"

=>ዛሬ በዚህች ዕለት አምላካችንን #እግዚአብሔርን ፈጽመን ልናመሰግነው ይገባናል:: እርሱ ያን ሁሉ ኃጢአትና በደላችንን ሳይቆጥር እነሆ አንድ ዘመንን አስፈጽሞናልና:: ቸርነቱ: ትእግስቱም በእኛ ላይ እጅግ ታላቅ ነው::

+እልፍ አዕላፍ ኃጢአትን አይቶ እንዳላየ ዝም ማለቱ ይደንቃል:: እኛን ምክንያት ፈልጐ ይወደናል እንጂ አይጠላንም:: እኛ ግን አፈርና ትቢያ ስንሆን ለክፋት እየተፋጠንን: በትዕቢት እንኖራለን:: ቸርነቱን እንኩዋ የምናስተውልበትን ዐይን ያጣን ሁሉ ይመስለኛል::

+ይቅርና ጽድቅ መሥራት ንስሃ ለመግባትም እንኩዋ አንፋጠንም:: እግዚአብሔር ከእኛ የሚፈልገው እርስ በርሳችን እንድንዋደድ: ንስሃስ እንድንገባ አይደለምን? "እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና:: ለትሑታን ግን ጸጋውን ይሰጣል" (1ጴጥ. 5:5)

+እግዚአብሔር በእኛ ላይ ቸርነቱን አብዝቶ ከዚህ ዕለት ካደረሰን እኛ ደግሞ እናመሰግነው ዘንድ ይገባል:: መጪው ዘመንም የብርሃን: የፍቅር: የሰላም: የበረከትም እንዲሆንልን ልንማጸነው ይገባል::

=>* " ቸርነቱን: ምሕረቱን በእኛ ላይ ላበዛ: በደላችንን ላልቆጠረ: ተግባራችንንም ላከናወነ: አንድ አምላክ ለሚሆን ለአብ: ለወልድ: ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን:: ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን:: " *

+*" ዘአቅረብኩ . . . "*+

=>"ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ"
(አእላፍ ቅዱሳንን አዘክሬ ምስጋናን አቀረብኩልህ)
"እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ"
(እሊህ ቅዱሳንም ዘወትር አንተን ያገለገሉህ ናቸው)
"ለእለ አነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ"
(በድኅነቴ የማነብልህን መጽሐፍ /ምስጋና/ ተቀበል)
"እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ: እም እለ አብኡ ብዑላን ዘተርፈ"
(አንተ ብዙ ባለ ጠጐች ካገቡት ይልቅ የድሃዋን መበለት ስጦታን ተቀብለሃልና)

=>"ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባክያን"
(ቅዱሳን የሆናችሁ ነቢያት: ለማስተማር የተመረጣችሁ ሐዋርያት)
"ሰማዕታት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን"
(ሰማዕታት: ጻድቃን: ትጉሃን የሆናችሁ መላእክት)
"ደናግል ዓዲ ወመነኮሳት ሔራን"
(እናንተም ደናግል: ቸር የሃናችሁ መነኮሳት)
"ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን"
(ይህችን ጉባኤ /አንድነታችንን/ መባረክን ባርኩ)
"እስከ አረጋዊ ልሒቅ እምንዑስ ሕጻን"
(ስትባርኩም ከሕጻናቱ ጀምራችሁ እስከ ሽማግሌው ድረስ ይሁን)

=>"ለዘጸሐፎ በክርስታስ"
(በብራና: በወረቀት የጻፈውን)
"ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ"
(ሊያስደርስ በገንዘቡ ዋጅቶ ያጻፈውን)
"ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ"
(አምኖ ያነበበውን: ወደ ሌላ ልሳን የተረጐመውንም)
"ወለዘሰምዐ ቃሎ በዕዝነ መንፈስ"
(በዕዝነ ልቡና አምኖ የሰማውን)
"በጸሎተ እሙ ማርያም አራቂተ ኩሉ እምባዕስ"
(ከጠብ ከክርክር: ከመከራ ከችግር በምትሰውር በእናቱ በማርያም ጸሎት)
"ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ"
(ኢየሱስ ክርስቶስ ሁላችን አንድ ላይ ይማረን)
"ወይፈኑ ለነ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ"
(ቅዱስ መንፈሱንም ይላክልን)
"እምይእዜ ወእስከ ለዓለም አሜን"
(ከዛሬ ጀምሮ ለዘለዓለሙ አሜን)

=>+"+ የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት: በመዳራትና በሥጋ ምኞትም: በስካርም: በዘፈንም: ያለ ልክም በመጠጣት: ነውርም ባለበት ጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና . . . ዳሩ ግን የነገር ሁሉ መጨረሻ ቀርቧል:: እንግዲህ አንደ ባለ አእምሮ አስቡ:: +"+ (1ጴጥ. 4:3)

<ወስብሐት ለእግዚአብሔር>

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አዲስ ዓመት መጣ | ዘማሪ ቀሲስ አሸናፊ ገብረማርያም

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

“የማነ ብርሃን ኀደረ ኀበ ማርያም”

Читать полностью…
Subscribe to a channel