††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† መስከረም 28 †††
††† ቅዱሳን አባዲርና እህቱ ኢራኢ †††
††† በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን የሮም መንግስት ዓለምን የሚያስተዳድረው በሁለት ከተሞች: ማለትም በራሷ በሮምና በአንጾኪያ ነበር:: የወቅቱ ንጉሥ ኑማርያኖስ ሲሆን የቤተ መንግስቱ ልዑላንና የጦር አለቆች ቅዱሳኑ:- ፋሲለደስ: ገላውዴዎስ: ፊቅጦር: መቃርስ: አባዲር: ቴዎድሮስ (ሦስቱም): አውሳብዮስ: ዮስጦስ: አቦሊ: ሌሎቹም ነበሩ::
ሴቶቹ ደግሞ ቅዱሳቱ:- ማርታ: ሶፍያ: ኢራኢ: ታኡክልያ: ሌሎቹም ነበሩ:: ለእነዚህ ሁሉ የበላይ ደግሞ ቅዱስ ፋሲለደስ ነበር:: ወቅቱ ከፋርስ: ከቁዝና ከበርበር ጦርነት የሚበዛበት ነበርና ባጋጣሚ ንጉሡ ኑማርያኖስ በሰልፍ መካከል ተመትቶ ወደቀ / ሞተ::
የሮም መንግስትም ባዶ ሆነች:: ዙፋኑን መያዝ ለቅዱስ ፋሲለደስም ሆነ ለሌሎቹ ቅዱሳን ቀላል ነበር:: ግን እነሱ ዝም ብለው ጠላትን ለመዋጋት ወጡ::
በዘመኑ ደግሞ በግብጽ የፍየል እረኛ የነበረና ከልጅነቱ ሰይጣን የሚያናግረው አንድ አግሪዻዳ የሚሉት ጉልበተኛ ሰው ነበር:: ንጉሡ ከወለዳቸው ልጆች ሁለቱ ሴቶች ክፉዎች ነበሩና ትንሿ አግሪዻዳን ማንም በሌለበት አንግሣ ጠበቀቻቸው:: ስሙንም ዲዮቅልጢያኖስ አለችው::
በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከሰይጣን ቀጥሎ እንደዚህ የከፋ ስም የለም:: የዓለም ክርስቲያኖችን የጨፈጨፈ ሰው ነው:: ትልቋ ደግሞ የትንሿን አይታ መክስምያኖስ የሚባል አውሬ አግብታ አነገሠችው:: ዓለምም በእነዚህ ጨካኝ ሰዎች እጅ ወደቀች::
ሠራዊቱ ሁሉ በሚሊየን ይቆጠራሉ:: የተደረገውን ሲያዩ ተበሳጩ:: ይህንን የተመለከተው ቅዱሱ ፋሲለደስ ግን ልዑላኑንና አለቆችን ሰብስቦ:- "ይህ ዓለም ከነ ክብሩ ጠፊ ነው:: ስለዚህ የተሻለውን የክርስቶስን መንግስት እንምረጥ" አላቸው:: ሁሉም እንደ አንድ ልብ መካሪ ደስ ተሰኝተው ምድራዊ ክብራቸውን ሊተው ወሰኑ::
ቀጥለውም በአንድ ቤት ተሰብስበው ይጾሙ: ይጸልዩ ገቡ:: ወደ ውጪ የሚወጡት ለምጽዋት ብቻ ነበር:: ቅዱሳኑ አባዲርና ኢራኢም ከእነዚህ መካከል በመሆናቸው ተጋድሏቸውን ቀጠሉ:: በተለይ ቅዱስ አባዲር በሌሊት በመካነ ጸሎቱ ሲጸልይ ያድርና በቀን ነዳያንን ይጐበኛል::
አመሻሽ ላይ ደግሞ ልብሱን ለውጦ ወደ እሥር ቤት ይሔዳል:: እሱ የአንጾኪያ ሠራዊት አለቃ: ኃያል የጦር መሪ ነውና ሁሉ ይወደውና ያከብረው ነበር:: በዚህም ምክንያት የእሥር ቤት ዘበኞች ምንም ከዲዮቅልጢያኖስ ከባድ ትዕዛዝ ቢኖርባቸውም ለቅዱሱ ግን ይከፍቱለት ነበር::
እርሱም ወደ እሥር ቤት ገብቶ ቁስላቸውን ጠርጐ: እግራቸውን አጥቦ: ለረሃባቸው መደገፊያ የሚሆን ማዕድም አጉርሷቸው ይወጣ ነበር:: በእንዲህ ያለ ግብር ሳለ ስለ ክርስቶስ የሚሰዋበት ጊዜ ደረሰ::
አንድ ቀን በመካነ ጸሎቱ ለምስጋና ሲተጋ ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠለት:: "ስምህን ለዘለዓለም አከብረዋለሁ:: በሰማያዊት ርስቴም አነግሥሃለሁና ከእህትህ ኢራኢ ጋር ወደ ምድረ ግብጽ ወርዳችሁ መስክሩ" ብሎት: ለእሷም በተመሳሳይ "ወንድምሽ የሚያዝሽን ሥሪ" ብሏት መድኃኒታችን ዐረገ::
ከዚያች ቀን ጀምሮ ቅዱስ አባዲርና እህቱ ኢራኢ ወደ ግብጽ የሚወርዱበትን መንገድ ይፈልጉ ነበር:: እናታቸው ግን (የቅዱስ ፋሲለደስ እህት ናት) ነገሩን ስትሰማ አለቀሰችባቸው:: "ልጆቼ አትሙቱብኝ: ዲዮቅልጢያኖስንም አትናገሩት" ስትል አማለቻቸው::
ከጥቂት ቀናት በኋላም ቅዱሱ ከእህቱ ጋር ከሶርያ ጠፍቶ ግብጽ ገቡ:: በዚያ ግን ፈተና ገጠመው:: በየመንገዱ የሚያየው ሕዝቡና ሠራዊት ሁሉ "ጌታችን አባዲር" እያለ ይሰግድለት ገባ:: ቀደም ሲል እንዳልነው እርሱ ኃያል የጦር መሪ: የሠራዊቱም አለቃ ነውና::
ቅዱሱ ግን ወደ ክርስቶስ ሊሔድ ናፍቋልና ሠራዊቱን እና ሕዝቡን:- "የሚገርማችሁ ሁሉም ሰው እንዲህ ይለኛል:: ግን'ኮ እኔ አንድ ተራ ምስኪን ክርስቲያን እንጂ የምትሉት ሰው አይደለሁም" ብሎ አታለላቸው::
ቀጥሎ በክርስትናው ተከሶ ከእህቱ ጋር ለፍርድ ቀረበና ስቃይ ታዘዘባቸው:: ለሰው ዐይን የሚከብዱ ብዙ ስቃዮችን ካሳለፉ በኋላም ሞት ተፈረደባቸው:: ነገር ግን አንገታቸው ከመሰየፉ በፊት መኮንኑ አርያኖስ ትክ ብሎ ሲያየው ተጠራጥሮ "ማንነትህን እንድትነግረኝ በአምላክህ አምየሃለሁ" አለው::
ቅዱስ አባዲርም መልሶ "አንተም ማንነቴን ካወቅክ በኋላ እኔን መግደል እንዳትተው ማልልኝ" አለው:: ማለለትም "እኔ አባዲር ነኝ" አለው:: በዚያች ቅጽበት አርያኖስ ከመደንገጡ የተነሳ መሬት ጠበበችው:: በፊቱ ተደፍቶ "ወዮልኝ! ጌታየን አባዲርን ያሰቃየሁ" እያለ አለቀሰ:: ነገር ግን ምሏልና በ300 ዓ/ም አካባቢ እያዘነ በዚህች ቀን ቅዱስ አባዲርንና እህቱን ኢራኢን አሰይፏቸዋል::
††† ቅድስት ሶስና †††
††† ይህች እናት የነበረችው ቅ.ል.ክርስቶስ በ500 ዓመት አካባቢ ነው:: እሥራኤላውያን በናቡከደነጾር ተማርከው ፋርስ ባቢሎን ወርደው ሳሉ: የኬልቅዩስ ልጅ: የደጉ ኢዮአቄም ሚስት የሆነች እናት ናት::
ቅድስት ሶስና በስደት ሃገር እግዚአብሔርን የምታመልክ: ለባሏ የምትታመን: ለቤተሰቦቿም ኩራት የሆነች ወጣት: በዚያውም ላይ እጅግ የምታምር ነበረች:: በዘመኑ ሕግን እናውቃለን የሚሉ 2 ረበናት ግን ከቅድስናዋ ሊያጐድሏት ይሹ ነበርና: አልሳካላችሁ ቢላቸው በሃሰት ከሰው በወገኖቿ ፊት ሞትን አስፈረዱባት::
በፍርድ ፊት ቁማ ሳለ እርሷ በፍጹም እንባ ወደ ፈጣሪዋ ትጸልይ ነበርና እግዚአብሔር ፍርዱን ላከ:: ሊገድሏት ሲወስዷት የኋላው ነቢዩ ቅዱስ ዳንኤል ያን ጊዜ ብላቴና ነበርና "እኔ ከዚህች የተባረከች ሴት ደም ንጹሕ ነኝ" ሲል ጮኸ::
ይህንን የሰሙ ዳኞችም የፍርድ ዙፋኑን ለቀቁለት:: ሁለቱን ረበናት ለየብቻቸው አድርጐ ዝሙትን ስትሠራ በየት ቦታ ላይ እንዳዩዋት ጠየቃቸው:: ጌታ ሲፈርድባቸው አንዱ በኮክ: ሌላኛው በሮማን ዛፍ ሥር አለ:: በዚህ ጊዜ ሕዝቡ እነዚህን ሃሰተኛ ረበናት (መምሕራን) ስለ እርሷ ፈንታ ወግረው ገደሏቸው:: ቅድስት ሶስና ግን ባለ ዘመኗ ሁሉ ፈጣሪዋን አገልግላ በዚህች ቀን ዐርፋለች::
††† አምላከ ቅዱሳን ከክፉ ሰዎች ምክር: ከአጋንንትም ሴራ በቸርነቱ ይጠብቀን:: የወዳጆቹንም ጸጋ ክብራቸውን ያድለን::
††† መስከረም 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አባዲር ሰማዕት
2.ቅድስት ኢራኢ እህቱ
3.ቅድስት ሶስና እናታችን
4.ቅዱስ ሉቃስ መነኮስ
5.ቅዱስ ዻውፍርና
ወርሐዊ በዓላት
1.አምላካችን አማኑኤል
2.አበው ቅዱሳን አብረሃም, ይስሐቅ, ያዕቆብ
3.ቅዱስ እንድራኒቆስ ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
4.ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ
5.ቅዱስ ቴዎድሮስ ዘሮሜ ሰማዕት
††† "ሶስናም ቃሏን አሰምታ ጮኸች:- 'ዘላለም ጸንተህ የምትኖር: የተሠወረውን የምታውቅ: የሚደረገውን ሁሉ ሳይደረግ የምታውቅ ፈጣሪ ሆይ! በሐሰት እንደ ጣሉኝ አንተታውቃለህ:: እነዚህ መመሕራንም ክፉ ነገርን ባደረጉብኝ ገንዘብ: የሠራሁት ኃጢአት ሳይኖር እነሆ እሞታለሁ' አለች:: እግዚአብሔርም ቃሏን ሰማት::" †††
(ሶስና. ፩፥፵፩)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
👉#ጾመ ጽጌ ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ያለው አንድ ወር ከዐሥር ቀን ወይም 40 ቀን ወርኃ ጽጌ፣ ዘመነ ጸጌ፣ ተብሎ ይጠራል፡፡
👉በነዚህም ቀናት በየቤተክርስቲያኑ የሚነበቡ ምንባቦች፣ የሚዘመሩት መዝሙሮች፣ የሚሰበከው ስብከት፣ የሚቆመው ማኅሌት በጠቅላላው የሚነገረው ስብሐት እግዚአብሔር ሁሉ ሰማይ በከዋክብት ምድር በጽጌያት አሸብርቀው የሚታዩ መሆናቸውን የሚገልጽ ነው፡፡
ወርኃ ጽጌ ለሚከናወነው መንፈሰዊ አገልግሎት መነሻው “መልአኩ ሕፃኑንና እናቱን ወደ ግብፅ ይዘሃቸው ሽሽ፣ የሕፃኑን ነፍስ ሊገድሉት ይፈልጋሉና” ሲል ለዮሴፍ በሕልሙ በነገረው መሠረተ ዮሴፍም ሕፃኑንና እናቱን ድንግል ማርያምን ይዞ ወደ ግብፅ መሰደዱና እመቤታችንና ሕፃኑ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ በስደት ከኖሩ በኋላ /ራእይ.12፣6/ ወደ አገራቸው ወደ ናዝሬት የመመለሳቸው መታሰቢያ ነው፡፡ /ማቴ. 2፣13-23፣ ት.ኢሳ.19፣1፣ እንባቆም 3፣6-7፣ መዝ.83፣3/፡፡
👉ይህንንም በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሡ አባ ጽጌ ብርሃን ፍሬ ከአበባ አበባም ከፍሬ እንደሚገኝ ሁሉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስን በአበባና በፍሬ እየመለሰ በሚያስረዳው ድርሰታቸው እንዲህ በማለት ገልጸውለታል፡፡ “ አፈወ ሮማን ማርያም ጽጌ ቀናንሞ ወአበሜ፣ እስከ ተጸምሐየየ በጾም ዘመልክዕኪ ጊዜ ድክታሜ፣ እምተመነይኩ ተሳትፎ ከመ አኅትኪ ሰሎሜ፣ ወፍሥሓኪ ዘአልቦ ፍጻሜ”፡፡ ሲተረጎምም የሮማን ሽቱ የቀናንሞ አበባ የምትሆኚ ማርያም ሆይ፣ በርሃብ በጾም አበባ የመሰለ የመልክሽ ደም ግባት እስኪጠወልግ ድረስ በስደትና በልቅሶ የደረሰብሽን ችግርና ድካም መከራሽንም ሁሉ እንደ እኅትሽ እንደ ሰሎሜ አብሬሽ ብቀበል ምኞቴ ነበር፤ በዚህ ፍጻሜ የሌለውን ደስታሽን እሳተፍ ነበር፡፡ እንዲሁም አባ አርክ ሥሉስ በስደቷ የደረሰባትን ኀዘን ፣ ልቅሶና ሰቆቃ አስመልክተው በደረሱት ‘ሰቆቃወ ድንግል” በሚለው ድርሰታቸው እንዲህ አሉ፣ ፀሐይን የምትለብሽ የብርሃን ልጅ ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ከሄሮድስ ዘንድ ልጅሽን ባሸሸሽ ጊዜ የደረሰብሽን ችግሮች ጨረቃን የሚጫሙ እግሮችሽ በመንገድ ብዛትና በአሸዋ ግለት እንደ ጎበጎቡ ሲሰማ ሰው ይቅርና ድንጋዩም ባለቀሰ ነበር”፡
👉የእመቤታችን የስደቷ መታሰቢያ ወር በቤተ ክርስቲያናችን የሚከበረው በማኅሌት፣ በቅዳሴና በዝክር ነው፡፡ በወርኃ ጽጌ ባሉት ሳምንታት ከቅዳሜ ማታ እስከ እሑድ ጠዋት አበው ካህናት የሚያቀርቡት ዝማሬ ከቅዱስ ያሬድ ድጓ፣ ከማኅሌት ጽጌና ከሰቆቃው ድንግል የተውጣጣና ሦስት ወገን ያለው ነው፡፡ ዝክሩም፣ በአሁኑ ወቅት በከተሞች አካባቢ እየተረሳ ቢመጣም፣ ዘወትር እሑድ የአንድ አካባቢ ሰዎች ማዕከላዊ በሆነ ቦታ ተሰባስበው በእመቤታችን ስም የሚዘክሩት ነው፡፡ ዐቅመ ደካሞች፣ ድሆችና መንገደኞች ተጠርተው በእመቤታችን ስም እንዲበሉና እንዲጠጡ ይደረጋል፡፡
👉ይህም ትውፊት እመቤታችን ወደ ኢትዮጵያ በመጣች ጊዜ ኢትዮጵያውያን አባቶችና እናቶች ያደረጉላትን መስተንግዶ ለማሰብ ነው፡፡ ከእመቤታችን በረከት ያሳትፈን አሜን!!!#
ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ፤ ስደትን ለመባረክ 3. በፈቃዱ የሚሞትበት ጊዜ አልደረሰምና። 4. አዳሞ ከዚህ ዓለም አፍአ ከምትሆን ከገነት ተሰዶ ነበር። 5. ሰማዕትነት በእሳት በስለት ብቻ አይደለምና እኛን ለማስተማር ተሰደደ ብለው ሊቃውንት ይተርጉማሉ። ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተሳለቁበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣና ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደተረዳው ዘመን በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን ሁለት ዓመት ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናትን ሁሉ ግደሉ አለ። ቄሣር ሕፃናትን ሰብስበሕ ልብስ ምግብ እየሰጠህ በማር በወተት አሳድገህ ለእናት ለአባታቸው ርስት ጉልት እያሰጠህ ጭፍራ ስራልኝ ብሎኛል ብሎ አዋጅ ነገረ። በዚያ ጌዜ ያላት ልጅዋን የሌላት ልብስ ምግብ ልቀበልበት ብላ እየተዋሰች ይዛ ሂደላች። በዚያን ጌዜ 144.00 (አሥራ አራት እልፍ ከአራት ሺህ )ሕፃናት ታርደዋል።
በባሕርየ መለኮቱ ስደት የማይስማማው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌል እንደ አስተማረው ሥጋዊ ስደቱ ፤
ስደትን ለተከታዮቹ ለማስተማር በአንዲቱ ከተማ መከራ ቢያደርሱባችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ (ማቴ. 10፥23 )
ሰው መሆኑን ለመግለጽ ከአዳም አካል አንድም ያልጐደለው ሙሉ ዳግማዊ አዳም መሆኑንና የለበሰው ሥጋ የሚደማ የሚቆስል በሰይፍም ሆነ በጦር ቢወጋ ጉዳት የሚደርስበት ሰብአዊ ባሕርይ ያለው መሆኑን ለማስረዳት
ዲያብሎስን ለማሰደድ የጌታ ስደት በተዛዋሪ የዲያብሎስ ስደት ሆነ፤ ጌታ የሚቀበለው መከራ ሁሉ ዲያብሎስን በርቀት የሚመታ መሣሪያ ነው። በመጨረሻም በመስቀሉ ላይ የሆነው የጌታ ሞት የዲያብሎስ ሞት ሆነ። የኢትዮጵያ ኦቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትም ይህን አጽንተው ያስተምራሉ ያምናሉ።
የጌታንና የእመቤታችን ጉዞ ከግብፅ ወደ ኢትዮጵያ
እመቤታችን ቅዱስት ድንግል ማርያምና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አረጋዊ ዮሴፍና ሰሎሜ በብሩህ ደመና ላይ ሆነው ከግብፅ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ናግራን ከተባለ ሀገር ደረሱ። በናግራን ሳሉ ጌታ እንዲህ አለ። ከቀኝ ጐኔ የሚፈሰው ደሜ በብርሃናት አለቃ በቅዱስ ዑራኤል እጅ ተቀድቶ በቅድሚያ በዚች ሀገር ይፈሳል፣ ይረጫል ። እመ ብዙኃን ቅድስት ድንግል ማርያምን እንዲህ አላት፤ አንች በድንግልና ፀንሰሽ በድንግልና እንደወለድሽኝ አምነው የሚያከብሩሽ በእኔም የሚያምኑ ብዙ የተቀደሱ ሰዎች በዚህች ሀገር ይወለዳሉ። ከናግራን ተነሥተው ለትግራይ ትዩዩ ከሚሆን ሐማሴን ከሚባለው ሀገር ሲደርሱ በምሥራቅ በኩል ከፍተኛ ተራራ ተመለከቱና ወደ ተራራው ሄዱ። ጌታም በተራራው ላይ ሳሉ እመ ብዙኃንን እንዲህ አላት። ይህች ተራራ ምስጋናሽ የሚነገርባት ቦታ ትሆናለች። የተራራዋም ስም ደብረ ሃሌ ሉያ ወይም ደብረ ዳሞ ይባላል። ትርጓሜውም የአምላክ ልጅ፣ የመስቀሉ፣ ቦታና የስሙ መገኛ ወይም አደባባይ ማለት ነው።
ከዚያም በኋላ ታቦተ ጽዮን ወደሞትኖርበት ወደ አክሱም ደረሱ። ታቦተ ጽዮን ባለቸበት ቦታ ሳሉ ባዚን የተባለው የኢትዮጵያ ንጉሥ ታቦተ ጽዮንን ለመሳለም መጣ። የካህናቱ አለቃ አኪን ለንጉሡ የኢሳይያስን መጽሐፍ ድንግል በድንግልና ጸንሳ በድንግልና ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች የሚለውን አነበበ (ኢሳ 7 ፥ 14)
ስደተኞች ግን ለንጉሡም ሆነ ለካህናቱ ሳይገለጡ የመጽሐፋን ቃል ከሰሙ በኃላ በብሩህ ደመና ላይ ሆነው ወደ ደብረ ዐባይ ሄዱ። ጌታም እናቱን እንዲህ አላት። ይህች ሀገር እንደ አክሱም ለስምሽ መጠሪያ ርስት ትሁን፣ በኋላ ዘመን በቀናች ሃይማኖት ጸንተው ሕጌን የሚያስተምሩ አንችን የሚወዱ ሰዎች ይኖሩባታል አላት።
ከዚያም ደብረ ዐባይ ተነሥተው ዋሊ ወደሚባለው ገዳም ወደ ዋልድባ ሄዱ። በዋልድባ በረሃም ሳሉ በራባቸው ጊዜ ጌታ በዮሴፍ በትር የአንድን ዕንጨት ስር ቆፈረ። 318 ስሮችን አወጣና ለእናቱ ብይ ብሎ ሰጣት። እናቱም ይህን የሚመር እንጨት አልበለም አላችው። ጌታም በኋላ ዘመን ስምሽን የሚጠሩ አንችን የሚያከብሩ ብዙ መናንያን ይህን እየበሉ በዚህ ቦታ ይኖራሉ አላት። እንጨቱም የሚጣፍጥ ይሆንላቸዋል አላት። ከዚህ በኋላ በብሩህ ደመና ላይ ሆነው ከዋልድባ ወደ ጣና የባሕር ወደብ ሄዱ። በጣና ደሴትም ደጋግ ሰዎች ተቀብለዋቸው 3 ወር ከ10 ቀን ተቀመጡ። የኢትዮጵያ ሰዎች በደስታ ተቀብለዋቸዋል። እንደ ግብፃውያን አላሰቃዮአቸውም።
በመሆኑም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙትን ተራራዎች ሁሉ ለስሞሽ መታሰቢያ ይሆኑሽ ዘንድ አሥራት አድርጌ ሰጥቼሻለህ አላት። በብሩህ ደመና ላይ ተቀምጠው በጐጃም፣ በሽዋ ፣በጐንደር፣ በበጌ ምድር፣ በወሎ፣ በሐረርጌና በአሩሲ ፣ በሲዳሞና በባሌ፣ በጉራጌ፣ በከንባታ፣ በከፋና በኢሊባቡር፣ በወለጋና በሌሎችም ክፍላተ አኀጉር እየተዘዋወሩ አስጉብኝቶ ኢትዮጵያን በሙሉ ለእመቤታችን አሥራት በኩራት አድርጎ ሰጥቷታል። ይህ ሁሉ የሆነው በቅዱስ ዑራኤል መሪነት ነው።
ከስደት መልስ
መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ግብጽ ሄደና የሄሮድስን ሞት ለእነዮሴፍ ነገራቸው።
ሄሮድስም ከሞተ በኋላ እነሆ የጌታ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ ሕፃኑንና እመ ብዙኃን እናቱን ይዘህ ወደ እስራኤል ነገር ሂድ አለው (ማቴ. 2፥19-21 )
ስለዚህ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስተ ቅዱሳን ቅድስት ድንግል ማርያም ከአረጋዊ ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ከስደት በሚመለሱ ጊዜ ወደ ደብረ ቁስቋም የገቡበት ዕለት በየዓመቱ ኀዳር 6 ቀን ይከበራል።
በዚህ መሠረት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶና እናቱ የእኛም እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሊቀበሉት የማይገባውን ሥጋዊ መከራ ለእኛ ሲሉ በመቀበላቸው ምክንያት ለእኛ እመቤታችንና አምላክን የምናመሰግንበት ክፍለ ዘመን ዘመነ ጽጌ ስለተባለ ኢትየጵያውያን ሌቃውንት አባ ጽጌ ብርሃንና አባ ገብረ ማርያም የተባሉ አበው መነኮሳት ማሕሌተ ጽጌን ደርሰውልናል
መጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ
††† እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና ለቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ተአምረ ማርያም †††
††† ተአምር ማለት "ድንቅ: ምልክት: ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪ የሆነ ክዋኔ: በሰብአዊ አቅም ሊሠራ የማይችል ተግባር (ድርጊት)" ነው:: ተአምራት ከባለቤቱ ከጌታችን ሲሆኑ የባሕርዩ ናቸው:: ከቅዱሳኑ ሲሆኑ ደግሞ የጸጋ እንላቸዋለን:: ቅዱስ መጽሐፍ ላይ በእግዚአብሔር ወዳጆች የተሠሩ ተአምራት እጅግ ብዙ ናቸው:: ነገር ግን:-
*ተአምራት ከአጋንንትም ሊሆኑ እንደሚችሉ መረዳት::
*ሁሌ ምልክትን (ተአምርን) አለመፈለግ::
*መመርመርና ማስተዋል ከአንድ ክርስቲያን ይጠበቃል::
*ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ በድርሳኑ እንደ ነገረን ተአምር መሥራት ከሲዖል እሳት አያድንም:: ጌታም በዚህ ነገር ተባብሮበታል:: (ማቴ. 7:22, 12:39)
ከጌታችን እግዚአብሔር ቀጥሎ የድንግል ማርያምን ያህል ተአምራትን የሠራ አይገኝም:: እንዲያው ሌላውን ትተን በእያንዳንዳችን ሕይወት ላይ እንኳ ብዙ ድንቅ ነገሮችን አድርጋለችና ምስክሮቹ እኛው ራሳችን ነን:: የእመቤታችን ተአምር የተጀመረው ገና ከፍጥረተ ዓለም ነው::
በእርግጥ ይህንን ለመረዳት ሠፊ አዕምሮና አስተዋይ ልቡናን ይጠይቃል:: ድንግል ማርያም ማለት የእግዚአብሔር የቸርነቱ ግምጃ ቤት: የጸጋው ደጅ ናት:: እርሱ ይህንን መርጦ ወዷልና:: እመ ብርሃን ተጸንሳ ከተወለደች በኋላ ደግሞ እጅግ ብዙ ኃይልን ታደርግ ነበር:: በዚህ ዕለት ከ2007 ዓመታት በፊት ያደረገችው ተአምር ደግሞ ድንቅ ነው::
አጐቷ /ጠባቂዋ/ አገልጋዩዋ አረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ ከቤተ መቅደስ ተቀብሎ ካመጣት በኋላ እርሱ እንጨትን ይጠርብ ነበር:: ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ (የችግር ዘመን) በመሆኑ ለሥራ ጉዳይ ወደ ሩቅ ሃገር ሒዶ የተመለሰው ከወራት በኋላ ነው::
ዮሐንስ የሚሉት ፈላስፋ ባልንጀራ ነበረውና ሽማግሌው ዮሴፍ ልብ ያላለውን ነገር ነገረው:: "ይህች ብላቴና ጸንሳለችና መርምራት" ብሎ ሔደ:: ቅዱስ ዮሴፍ ግን ደነገጠ:: "እኔ እንዲህ ያለ ነገር እንኳን በገቢር (በሥራ) በሃሳብም አላውቅባት" ብሎት ወደ ቤት ገባ::
ቀጥሎም እመቤታችንን "ልጄ ሆይ! ከማን ጸነስሽ" አላት:: "እመንፈስ ቅዱስ" አለችው:: ግራ ገባው: ምሥጢርም ተሠወረበት:: "እንዴት አንዲት ሴት ያለ ወንድ ዘር ልትጸንስ ትችላለች?" ብሎ ያወጣ: ያወርድ: ይጨነቅም ገባ:: የእኛ እመቤት ግን እንደ ጨነቀው ባወቀች ጊዜ ጠርታ ወደ ውጪ ይዛው ወጣች::
ከረዥም ጊዜ በፊት ጠርቦ የጣለውን እንጨት አንስታ ተከለችውና ጸለየችበት:: በደቂቃም የአረጋዊው ዐይን እያየ ያ ደረቅ እንጨት ለምልሞ: አብቦ አፈራ:: ቅዱስ ዮሴፍ በጣም ደነገጠ::
"አባቴ ተመልከት እስኪ! ይህንን ማን አደረገ?" አለችው:: "ልጄና እመቤቴ! እግዚአብሔር ነው" አላት:: እርሷም "በማሕጸኔ ያለውም ኢሳይያስ ትንቢትን የተናገረለት አምላክ ነውና ሁሉን ይችላል" አለችው:: አረጋዊውም ቅዱስ ኤራቅሊስ በሃይማኖተ አበው እንደ ነገረን "ሰገደ ላቲ" ወደ ምድር ወድቆ በፊቷ ሰገደ::
††† ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ †††
††† ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)
የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል! እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር::
እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ ደግሞ 100 ደርሶ ነበር:: ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::
ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::
የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በኋላ ሰኔ 30 ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::
††† የእመቤታችን ልመናዋ: ክብሯ: የልጇ የወዳጇም ቸርነት በእውነት ከሁላችን ጋር ይሁን:: የመጥምቁንም በረከት ያብዛልን::
††† መስከረም 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት ድንግል ማርያም
2.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
3.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ (ጽንሰቱ)
4.ቅዱሳን ዘካርያስና ኤልሳቤጥ
5.ቅዱስ አቦሊ ሰማዕት (ፍልሠቱ)
††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
2.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
3.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
4.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
5.ቅዱስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
††† "ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ጽንሱ በማሕጸኗ ውስጥ ዘለለ:: በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት:: በታላቅ ድምጽም ጮኻ እንዲህ አለች:-
'አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ: የማሕጸንሽም ፍሬ የተባረከ ነው:: የጌታየ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? . . . ከጌታ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብጽዕት ናት::" †††
(ሉቃ. ፩፥፵፩)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
እንባ ብቻ 😭😭😭
1- ሁሉም የአለም ሀገራት ከታላላቅ ኃያላን ጋር መልካም ግንኙነት ለመመስረት የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ (ሴት/ሴት ወይም ወንድ/ወንድ) መቀበል እንዳለባቸው አሜሪካ አረጋግጣለች። በአሁኑ ጊዜ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ሕጋዊ የሆነባቸው 34 አገሮች አሉ፡ አንዶራ፣ አርጀንቲና፣ አውስትራሊያ፣ ኦስትሪያ፣ ቤልጂየም፣ ብራዚል፣ ካናዳ፣ ቺሊ፣ ኮሎምቢያ፣ ኮስታሪካ፣ ኩባ፣ ዴንማርክ፣ ኢኳዶር፣ ፊንላንድ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ አይስላንድ፣ አየርላንድ፣ ሉክሰምበርግ፣ ማልታ፣ ሜክሲኮ፣ ኔዘርላንድስ፣ ኒውዚላንድ፣ ኖርዌይ፣ ፖርቱጋል፣ ስሎቬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ስፔን፣ ስዊድን፣ ስዊዘርላንድ፣ ታይዋን፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ አሜሪካ እና ኡራጓይ።
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
2- ጀርመን ከአሁን በኋላ የዘር ግንኙነት የለም የሚለውን ህግ ፈርማለች ማለትም ወንድም እና እህት እናት እና ወንድ ልጅ አባት እና ሴት ልጅ ወዘተ.. 😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭 😭😭😭
3-የሚያሚ ከተማ አሁን የህዝብ የወሲብ ግዢ ከተማ ተባለች። ይህም ማለት፡ በመንገድ ላይ ወደ ቤተ ክርስቲያን
በመስጊድ ፣በገበያ ፣በኳስ ሜዳ ሴክስ ከፈለጋችሁ በማንኛውም ሰአት ያለችግር መደሰት ትችላላችሁ😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
4-ካናዳ አውሬነትን ፈቀደች(ከእንስሳት ጋር ወሲብ)😭😭😭😭😭😭😭😭
5- በስፔን: የብልግና ፊልሞች
በሁለተኛ ደረጃ እና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ተፈቅዶላቸዋል. 😭😭😭😭😭😭
6- ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች ዝሙት አዳሪነት ፈቃድ ተሰጥቷል. ማርግ ሉከር በ10 ዓመቷ የጾታ ደስታ የሚሰማት ማንኛዋም ወጣት ሴት ልጅ፣
ማንም ሊከላከልላት አይገባም
ሰውነቱ እንዴት እንደሚሰራ እወቅ 😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
7- በመጨረሻም አሜሪካ የሰይጣን አብያተ ክርስቲያናት በይፋ እንዲከፈቱ ፈቅዳለች።
ውድ ወንድሞች እና እህቶች መጨረሻው ቀርቧል፣ የክብር ጉዞው እየቀረበ ነው።
ሰዎች ትኩረታቸው እየተከፋፈለ ነው እና ዲያቢሎስ ከመለኮታዊ ምህረት ለማስወገድ ከፍተኛውን የነፍስ ቁጥር ከእሱ ጋር መጎተት ይፈልጋል። እንጠንቀቅ። 😭😭😭😭😭
አንድ ደቂቃ ካሎት...ይህንን መልእክት ሼር ያድርጉ። በቤተክርስቲያን ውስጥ ለምን እንተኛለን፣ እና በመጠጥ ቤቶች ውስጥ እንነቃለን? ስለ ኢየሱስ ማውራት በጣም ከባድ የሆነው ግን ለማማት ቀላል የሆነው ለምንድነው?
የእግዚአብሔርን መልእክት ችላ ማለት ግን የቆሸሹ መልዕክቶችን መልሶ መላክ ቀላል የሆነው ለምንድነው?
ይህን መልእክት ለጓደኞችህ ልትልክ ነው ወይስ ችላ ልትለው ነው? እግዚአብሔርን የምትወዱ ከሆነ ይህንን መልእክት በ60 ሰከንድ ውስጥ ለእውነተኛ የቅርብ ጓደኞችዎ ይላኩ። 🙏🙏🙏🙏
አግዜር ይባርክህ. አሜን!!!
በአሁኑ ጊዜ የፆታ ብልግና ዓለምን እያናጋ ነው።
አምላክ እንዲህ ብሏል፡- “የሰው ልጅ አምስት ነገሮችን የሚወድበት አምስት ነገሮችን የሚረሳበት ጊዜ ይመጣል።
1. የዚችን ዓለም ተድላ ይወዳሉ የፍርዱንም ቀን ይረሳሉ።
2. ገንዘብን ይወዳሉ እና ገንዘቡን እንዴት እንዳገኙ እና እንዳወጡት የተጠያቂነት ቀን ይረሳሉ.
3. የተፈጠሩትን ይፈራሉ ፈጣሪንም ይረሳሉ።
4. ውብ መኖሪያ ቤቶችን ይወዳሉ መቃብራቸውንም ይረሳሉ.
5. ኃጢአትን ይወዳሉ እና የእግዚአብሔርን ይቅርታ መፈለግን ይረሳሉ።
እስቲ ይህን አስብበት?.......
1. የዘላለም ሕይወት = ነፃ
2. የቤተክርስቲያን መግቢያ = ነፃ
3. የክርስቶስ ማዳን = ነፃ
4. የእግዚአብሔር ፍቅር = ነፃ
5. የሕይወት እስትንፋስ = ነፃ
ሀ. ሲጋራ = ክፍያ
ለ. ዝሙት አዳሪነት = ክፍያ
ሐ. አልኮል = ክፍያ
መ. የምሽት ክለብ መግቢያ ክፍያ = ክፍያ
ሠ. ዓለምን የሚገዙ ኃይሎች = ክፍያ
ታዲያ ለምንድነው ሰዎች ገነት ነፃ እያለች ለገሃነም የሚከፍሉት?
ሁለት ጊዜ አስብ
በክርስቶስ እመኑ ትድናላችሁ።
ሁሌም የምናስበው ስለ ቫለንታይን ቀን ነው።
የልደት ቀን
የአባቶች ቀን
መልካም የእናቶች ቀን
የህፃናት ቀን
የገበሬዎች ቀን
የአስተማሪ ቀን
የገና ዕለት
የነፃነት ቀን
የቦክስ ቀን,
በዚህ ቀን፣
እዚ ቀን,
ቀን ውስጥ ቀን ውጭ.
ስለ ሞት ቀን እና ስለ ፍርድ ቀን አስበህ ታውቃለህ? የበአል ቀን ወይም የውግዘት ቀን ይሆንልሃል?
ደህና ከሆንክ ስለ ጓደኞችህ እና የምትወዳቸው ሰዎችስ? ስለ *የሞት ቀን እና የፍርድ ቀን* በመንገር ፍቅር አሳያቸው።
እባካችሁ ይህንን ለማንኛውም ቡድን አስተላልፉ ዛሬ መንግስተ ሰማያት ለናንተ ይሁን። እባኮትን በኋላ እንዳትሉ፣ አሁኑኑ ያድርጉት ምክንያቱም ነገ በጣም ዘግይቶ ሊሆን ይችላል።
እግዚአብሔር ሆይ ይህንን መልእክት የሚያሰራጩትን ይባርክ።
አመሰግናለሁ እግዚአብሔር ይባርክህ።
ታላቅ መንፈሳዊ የንግስ ጉዞ ወደ ዝቋላ አቦ ገዳም
ጥቅምት 4 - 5
➣ትራንስፖርትና መስተንግዶ ጨምሮ➣ 600 ብር
◉ለመመዝገብ በውስጥ መስመር አናግሩኝ🙏
ታላቅ መንፈሳዊ የንግስ ጉዞ ወደ ዝቋላ አቦ ገዳም
ጥቅምት 4 - 5
➣ትራንስፖርትና መስተንግዶ ጨምሮ➣ 600 ብር
◉ለመመዝገብ በውስጥ መስመር አናግሩኝ🙏
አቢ ጠቅላላ ኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ ጥገና
👉 ኦቭን
👉 ማይክሮዌቭ
👉 ምጣድ
👉 ስቶቮች
👉 የሻይ ቡና ማሽን
👉 መፍጫዎች
👉 የውሃ ማፍያዎች
👉 የውሀ ፓምፖች
👉 ጄነሬተር በአስተማማኝ ሁኔታ እንጠግናለን
ከቤትዎ ሳይወጡ ይደውሉ ያሉበት በመምጣት እንሰራለን
📞 0938152513
/channel/abi1888
/channel/electricianbolegerji
jo1888" rel="nofollow">http://www.tiktok.com/@jo1888
የገዳመ ጎረጎር ቅዱሳን በዚኽች ዕለት መስከረም 21 ቀን በዓመታዊ በዓላቸው ስታስበው ይውላሉ። እግዚአብሔር እንደ እነ ሄኖክና ኤልያስ በሞት ፈንታ የሠወራቸው ታላላቅ ቅዱሳን ናቸው፡፡ ከእነርሱም ውስጥ ከሀብታሞች ቤት የማዕድ ፍርፋሪ እየሰበሰበ የሚያመጣና በጾም በጸሎት ላሉ ባሕታውያን የሚሰጥ አለ፤ ከእነርሱም ውስጥ የውስጥና የውጭ ቅድስናውን ንጽሕናውን ሰው እንዳያውቅበት ዕብድ መስሎ የሚኖር አለ፤ መራራ የሆነ የበረሓ ቅጠልና ሣርን የሚመገብ አለ፤ ለዚህ ዓለም ሰዎች ፊቱንና መልኩን እንዳያሳይ በገዳም ውስጥ ዘግቶ የሚኖር አለ፤ ከተራራ ሥር የተሠወረ አለ፤ ችግረኛና ድኃ መስሎ የሚኖር አለ፤ ከእነርሱም ውስጥ በኋለኛው ዘመን የሚሆነውን ነገር በትንቢት የሚናገር አለ፤ በነፋስ ክንፍ ረቂቅ በሆነ በደመና ጀርባ የሚጓዝ አለ፤ ከእነርሱም ውስጥ ስለ ተሠወሩ ምሥጢራት ሁሉ ከቅዱሳን መላእክት ጋር የሚነጋገር አለ፤ በሕይወት በብሔረ ሕያዋን የሚኖሩትን ተመልክቶና በእነርሱም ተባርኮ የሚመጣ አለ፤ በሌሊት ራእይ የገነትን ቦታዎችና ውበቷን የሚያይ አለ፤ የኀጥአንን ኑሯቸውን የጩኸታቸውን ድምፅ የሚሰማ አለ፡፡
የእዚኽም እጅግ የከበሩ ቅዱሳን ስማቸው አቡነ መርዓዊ፣ አቡነ ምሰሶ፣ አቡነ ደንቆሮ፣ አቡነ ሞአብራ፣ አቡነ ሙሴ፣ አቡነ አላሽኝ ይባላሉ፡፡ በዝምታ በተደሞ የማይሰማ
በመምሰል እንደ ደንቆሮ ሆኖ መላ ዘመኑን ለዓለም ሙት ሆኖ ስለኖረ ‹‹አቡነ ደንቆሮ›› የተባለ አለ፤ መርዓዊ ማለትም መርዓዊ ዘክርስቶስ (የክርስቶስ ሙሽራ) ማለት ነው፣
እርሱም በታላቁ በዋልድባ አብረንታት ገዳም አበ ምኔት ሆኖ መነኰሳቱን የመራ ነው፤ ምሰሶ ማለትም ዐምደ ሃይማኖት (የሃይማኖት ምሰሶ) ማለት ነው፤ ሞአብራ ማለትም ሞዐ
ሐራሁ ለክርስቶስ (አሸናፊ የሆነ የክርስቶስ ሠራዊት) ማለት ነው፤ ሙሴ ማለትም በልቡ ሽንገላን የማያውቅ ሩኅሩኅ የዋህ ማለት ነው፤ አላሽኝ ማለትም በጸሎቱ ኀይል በደልን
አበሳን ይቅር የሚያስብል፣ ምሕረትን የሚያሰጥ ማለት ነው፡፡
የእነዚኽም ክቡራን ቅዱሳን የትውልዳቸው ሀገር ምድረ አግዓዚት የተባለች ኢትዮጵያ ናት፡፡ የተወለዱበት አውራጃም ላኮመልዛ ትባላለች፣ በኋላ ላይ ወሎ ተባለች፤ ዳግመኛም የደላንታ ቦታ የዋድላ ሜዳ ይሏታል፡፡ ሌሎችም መጠሪያ ስሞች አሏት፡፡ እነዚኽም ቅዱሳን በዚኽች ሀገር ሲወለዱ ከሕፃንነታቸው ጀምረው ተጋድሏቸውን አብረው የጀመሩ ናቸው፡፡ ሰባት ዓመት ሲሞላቸው ወደ ትምህርት ቤት ገብተው አውሎጊስ ወደተባለ ደገኛ መምህር ዘንድ ሔደው የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢር ተማሩ፣ መምህራቸውም በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እነርሱ ታላላቅ ቅዱሳን እንደሚሆኑና በዘመናቸውም ግራኝ አህመድ
እንደሚነሣ ትንቢት ተናገረ፡፡
ዐፄ ሱስንዮስም በ1616 ዓ.ም የካቶሊክን ሃይማኖት ካልተቀበላችሁ ብሎ ጎንደር ደንቀዝ ላይ ከ8ሺህ በላይ የሚሆኑ ክርስቲያኖችን ከሰየፋቸው በኋላ በመቅሠፍት ተመቶ ምላሱ ተጎልጉሎ ወጣ፡፡ በዚኽም ወቅት መኳንንቱ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሲያማክሩ አንዲት
ፍኖቲ የምትባል ከቤታቸው የምትኖር ደግ ባልቴት ‹‹ከጨጨሆ በላይ ያለ ጻድቅ ስሙ አቡነ መርዓዊ የሚባል ካህን ቢባርከው ምላሱ ይመለሳል፣ እርሱም ከመንግሥቱ ይፈልሳል፣ ፋሲል ይነግሣል›› በማለት መከረቻቸው፡፡ የንጉሡም ጭፍሮች አቡነ መርዓዊ ያሉበትን አፈላልገው አግኝተው ነገሯቸው፣ እርሳቸውም በሠረገላ ብርሃን ተጭነው በመሔድ በመስቀላቸው ባርከው ምላሱን መልሰውለት ፈውሰውታል፡፡ ንጉሡም ከዳነ በኋላ ዐዋጁን በዐዋጅ ሽሮ ‹‹ተዋሕዶ ሃይማኖት ትመለስ ፋሲል ይንገሥ›› ብሎ ዐርፏል፡፡
ዐፄ ሱስንዮስ የካቶሊክን እምነት ካልተቀበላችሁ ብሎ ሊቃውንቱን በአንድ ቀን ባሳረደ ጊዜ ንጉሡ ወዲያው ‹‹ኦርቶዶክስ ይርከስ ካቶሊክ ይንገሥ›› ብሎ ያወጀበት ምላሱ ተጎልጉሎ ከወጣ በኋላ በተኣምራት ተጎልጉሎ የወጣውን ምላሱን በመስቀላቸው ባርከው ወደነበረበት በመመለስ የፈወሱት ሌሎችም ቅዱሳን እንዳሉ ታሪካቸው ያስረዳል፡፡ ለምሳሌ፡- የማኅበረ ሥላሴው አቡነ ዓምደ ሥላሴ፣ የጩጊ ማርያሙ አቡነ ምእመነ ድንግል ይጠቀሳሉ፡፡
ይኽም ማለት አቡነ ዓምደ ሥላሴ፣ አቡነ ምእመነ ድንግል፣ አቡነ መርዓዊ ወይም ሌላ ጻድቅም ቢሆን እንዲሁ ዐፄ ሱስንዮስን ምላሱን ወደነበረበት መልሰው አዳኑት ተብሎ
ለሁሉም ቅዱሳን ቢነገር ታሪኩ እርስ በእርሱ የሚጋጭ አይደለም፡፡
የእነዚኽንም እጅግ የከበሩ ስድስት ቅዱሳንን ገድላቸውን ከሌሎቹ ቅዱሳን ገድል ልዩ የሚያደርገው ነገር ቢኖር በዐፄ ልብነ ድንግል ዘመን በቱርኮች አጋዥነት በሀገራችን ላይ
ተነሥቶ ለ15 ዓመት ቤተ ክርስቲያንን ሲያቃጥል ካህናትን ሲያርድ ስለኖረው ስለ ግራኝ አህመድ መነሻ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ዘርዝሮ ስለሚያስረዳ ነው፡፡
ገድለ ስድስቱ ቅዱሳን ዘገዳመ ጎረጎር እንደሚናገረው ቅዱሳኑ ጽኑ የሆነውን ተጋድሏቸውን ከፈጸሙ በኋላ ጌታችን መስከረም 21 ቀን በክብር ተገልጦላቸው እንዲህ የሚል ታላቅ የምሕረት ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡- ‹‹ስማችሁን የጠራና የዘከረ ሰው ዕድል ፈንታው ከእናንተ ጋር ይሁን፤ ወደ ገዳማችሁ የሚመጣውን ሰው እስከ ዐሥር ትውልድ ድረስ እምረዋለሁ፤ ወደዚኽች ገዳም በልቡ ሊመጣ አስቦ መምጣት ያልቻለውን ሰው መጥቶ ሰግዶ እንደተሳለመ ይቆጠርለታል፣ እርሱ ይድናል፣ ልጆቹንና ሚስቱንም ያድናል፤ ለቤተ ክርስቲያን መባዐ የሰጠ ዋጋውን በሰማያት ያገኛል፣ መባዐ መስጠት ያልቻለ ሰው ገድላቸውን ያለምንም ጥርጣሬ ያድምጥ በፍጹም ልቡናው ለተከታተለ ሰው መባዐ እንደሰጠ ይቆጠርለታል፤ ቦታችሁ እንደ ኢየሩሳሌም ትሁን፣ ይኽችን ቦታ ያየ ሰው ኢየሩሳሌምን አላየሁም አይበል ይኽች ቦታ ኢየሩሳሌም ናትና፤ ወንዞቿ እንደ ገነት ወንዝ
እንደ ግዮንና እንደ ጤግሮስ ናቸው፤ በገዳሙ ጠበል በንጹሕ ልብ አምኖ ንስሓ ገብቶ የተጠመቀ ሰው እንደ አርባና ሰማንያ ቀን ሕፃን ይሆናል የሠራው ኀጢአቱ ሁሉ ይደመሰስለታል፤ መታሰቢያችሁን ለማድረግ የሚደክመውን ሰው በቤቱ ውስጥ የእንስሳት ሞትም ቢሆን ቸነፈር አይገባም እስከ ልጅ ልጁ ድረስ የሥራው ፍሬ ይባረካል፡፡››
ጌታችን በገባላቸው ቃልኪዳን መሠረት ቅዱሳኑ የተሠወሩባትን ምድር ጎረጎር ገዳምን እንደ መሶም አንሥተው አስባርከዋታል፣ ቅዱሳኑ እንደ ሄኖክና ኤልያስ ከሞት የተሠወሩባት ናት። የእኚህ እጅግ የከበሩ ቅዱሳን ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን።
(ምንጭ፦ ገድለ ስድስቱ ቅዱሳን ዘገዳመ ጎርጎር (ጎርጎር ማርያም ገዳም፣2010 ዓ.ም)
✞ ✞ ✞
🎁Safaricom ethiopia ሽልማት🎁
በተጠቃሚዎች ዘንድ እውቅናን ለማትረፍና ደንበኞችን ለማብዛት የቴሌግራም bot ከፍተናል
በውስጡም ብዙ ሽልማቶችን አዘጋጅተናል።
🎁ለእርስዎ እና ለ2 ጓደኛዎ የ 3000 ብር ስጦታ
🎁smart phone( s21 ultra)
🎁Asus personal computer
ይህንን ለጓደኞችዎ በመላክ ተሸላሚ ይሁኑ
ማሳሰቢያ! ይህ ሊንክ የሚያገለግለው ለ One day ብቻ ነው
/channel/Safaricom_ethiopia_new_bot?start=r09283404034
ሊያመልጣችሁ የማይገባ ስለእመቤታችን ስደት በእንባ የተሰበከ ስብከት ነው
👇👇👇ተጭነው ይመልከቱ
https://youtu.be/M_GgZ7f66Ck?si=dd1ROCRqHZ2cgDP6?sub_confirmation=1
††† እንኳን ለቅዱሳኑ ኤዎስጣቴዎስ: አንጢላርዮስ: ጤቅላ እና አባ ዮሐንስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስና ቤተሰቡ †††
††† ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ በቀድሞዋ #ሮሜ ግዛት ውስጥ የጦር አለቃ: የከተማዋ መኮንን እና እጅግ ባለጸጋ የነበረ ሰው ነው:: ግን በእምነቱ አረማዊ: በስሙም ' #ቂዶስ' ተብሎ የሚጠራ ነበር:: ምክንያቱ ባይገባውም እጅግ ቅን: ደግና ለምጽዋት የሚፋጠን ነበር::
#እግዚአብሔር ታዲያ ይህን ሰው ወደ ቀናው ጐዳና (ወደ ክርስትና) ሊመራው ወደደና ተገለጠለት:: ቂዶስ ለአደን ወጥቶ #ዋሊያ ሲያድን (ያኔ ዋሊያ ከዓለም አልጠፋም ነበር:: ዛሬ ግን ያለ #ኢትዮዽያ ውስጥ ብቻ ነው) መድኃኒታችን በዋሊያው ራስ ላይ የብርሃን መስቀልን ገልጦ ተነጋገረው::
ክርስቲያን እንዲሆንና መከራንም እንዲታገሥ አዘዘው:: ቂዶስም ወደ ቤቱ ተመልሶ ለሚስቱና ለ2 ልጆቹ የሆነውን ነገራቸው:: ክርስትናን ተምረው ሲጠመቁ አበው ቂዶስን 'ኤዎስጣቴዎስ' አሉት::
ከዚህ በሁዋላ ክርስቶስን እያመለኩ ቆይተው ረሃብ በሃገሪቱ መጣ:: ቅዱሱ ምንም መኮንንና ሃብታም ቢሆንም ገንዘቡ በምጽዋት በማለቁ ባሮቹ ተበትነው ደሃ ሆነ:: የሚበላውንም አጣ:: ከሥጋዊ ሥልጣኑም ተሻረ:: እርሱ ግን ይህንን ስለ ክርስቶስ ፍቅር ታገሠ::
ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ ረሃቡ ከአቅሙ በላይ ሲሆንበት ሚስቱንና 2 ልጆቹን ይዞ ስደት ተነሳ:: ለጉዞ በተሳፈረበት መርከብ የሚከፍለው ገንዘብ ስላልነበረው ሚስቱን ቀሙት:: ልጆቹን ይዞ እያለቀሰ ከሌላ ወንዝ ደረሰ::
እንዳይሳፈር መርከበኞቹ ልጆቹን ሊቀሙት ስለሆነ ለመዋኘት ወሰነ:: አንዱን ልጁን ተሸክሞ አሻግሮት ሲመለስ ትቶት የሔደውን ልጁን አንበሳ ወስዶት አገኘው:: እያለቀሰና እየቸኮለ ወደ 2ኛው ቢመለስ ደግሞ ይህኛውንም ተኩላ ወስዶት ነበር::
ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ አንጀቱ በሃዘን ተቃጠለ:: በግንባሩ መሬት ላይ ተደፍቶ መራራ ለቅሶን አለቀሰ:: ነገር ግን ኢዮባዊ ሰው ነውና "እግዚአብሔር ሰጠ: እርሱም ነሣ" ብሎ በእንባ ተጉዋዘ:: በአንዲት ሃገርም ባርነት ተቀጥሮ ፈጣሪውን ሲያመሰግን ኖረ::
ከብዙ ዓመታት በሁዋላ የረሃቡ ዘመን አልፎ የቅዱሱ ወዳጅ የነበረ ሰው በሮም ላይ በመንገሱ ወታደሮችን "ወዳጄን ኤዎስጣቴዎስን ፈልጋችሁ አምጡ" ብሎ ላካቸው:: ከአድካሚ ፍለጋ በሁዋላ ያ ደግ ጌታቸው በባርነት ተቀጥሮ: ተጐሳቁሎ አገኙት::
ፈጥነው ወደ ሮም ከተማ ወስደው በቀደመ ክብሩ ላይ አኖሩት:: እርሱ ግን ሃዘንተኛ ነበር:: ከቀናት በሁዋላም አዳዲስ ወታደሮችን ከተለያየ ቦታ መለመለ:: ከእነዚያም መካከል መልካም የሆኑትን 2ቱን አለቆች አደረጋቸው:: ሁለቱ ደግ ወጣቶችም በጣም ይዋደዱ ነበር::
አንድ ቀን እኒህ 2 ወጣቶች ወይን ሊገዙ ሔደው ጠባቂዋን 'ስጭን' አሏት:: ሰጥታቸው እዚያው ያወራሉ:: አንደኛው "ታሪኬን ልንገርህ" ይለዋል:: "እሺ" ሲለው "እኔ ወላጆች የሉኝም:: ሕጻን እያለሁ በሃገራችን ረሃብ መጥቶ: ሃብታችን አልቆ ስንሰደድ እናታችንን መርከበኛ ወሰዳት:: አባቴ ወንድሜን ሲያሻግረው እኔን አንበሳ ወስዶ ከአንድ መንደር ጣለኝ" አለው::
ባልንጀራው ገርሞት "ታሪካችን ተመሳሳይ ነው:: እኔም እንዳንተ ሆኜ: አባቴ ሲያሻግረኝ ተኩላ ወስዶ አንድ መንደር ውስጥ ጣለኝ" አለው:: ይህንን ትሰማ የነበረችው ወይን ጠባቂ "ልጆቼ!" ብላ ጮሃ አለቀሰችና ደነገጡ:: እርሷም ቀርባ አቅፋቸው እያለቀሰች ነገሩን ሁሉ አስታወሰቻቸው::
ይህን ጊዜ ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ ሰምቶ ደረሰ:: ከረጅም ዓመታት በሁዋላ ሚስቱ አትክልት ጠባቂ ሁና ማንም ሳይነካት: 2 ልጆቹንም አገኘ:: እያለቀሱ ተቃቀፉ:: እግዚአብሔርንም ፈጽመው አመሰገኑት:: የሰማ ሁሉ "ዕጹብ! ዕጹብ!" አለ::
(እኛ የምናመልከው ጌታ እንዲህ ነው:: ክብር ለእርሱ: ለድንግል እናቱና ለወዳጆቹ)
ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስና ቤተሰቡ በቀሪ ዘመናቸው ቤተ ክርስቲያን አንጸው በምጽዋት ኑረዋል:: በመጨረሻም ዘመነ ሰማዕታት መጥቶ "ክርስቶስን አንክድም" በማለታቸው ብዙ ተሰቃይተው 4ቱም በዚህች ቀን ሰማዕት ሆነዋል::
††† ቅዱስ አንጢላርዮስ †††
††† ይህ ቅዱስ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ እጅግ የታወቀ ነው:: በቀደመ ሕይወቱ "ሊቀ መጸብሐን-የቀራጮች አለቃ" ይሉታል:: እጅግ ኃጢአተኛና ጨካኝ ሰው ነበር::
አንድ ቀን ግን አንድ የኔ ቢጤ ነዳይ ከመሰሎቹ ጋር ተወራርዶ " #በእንተ_ማርያም" ብሎ ቢለምነው በደረቅ ዳቦ ራሱን ገመሰው:: በሌሊትም ራዕይ አጋንንት ነፍሱን ሲናጠቁዋት: #መላእክት ደግሞ በዛች ደረቅ ዳቦ አመካኝተው ሊያድኑት ሲሞክሩ አየ::
በዚያች ቅጽበትም ፍጹም ተለወጠ:: መጀመሪያ ሃብት ንብረቱን በምጽዋት ጨረሰ:: ቀጥሎ የሚመጸውተው ቢያጣ ነዳያንን "ሽጣችሁ ተካፈሉኝ" አላቸውና ሸጡት:: በባርነት በተሸጠበት ሃገርም በጾምና በጸሎት ተጋደለ:: እረኛ ሲያደርጉትም በደረቅ በርሃ ላይ ውሃ እያፈለቀ: ለምለም ሳር እያበቀለ ይመግባቸው ነበር:: ዘወትርም መልአክ ያጽናናው ነበር::
በሁዋላ ግን ማን መሆኑ ሲታወቅበት ሸሸ:: በመንገድም የከተማዋ ዘበኛ መስማትና መናገር አይችልምና እፍ ቢልበት ከቅዱሱ አፍ እንደ እሳት ያለ ነገር ወጥቶ ቢነካው ዳነ:: ቅዱስ አንጢላርዮስም ቀሪ ዘመኑን በበርሃ ሲጋደል ኑሮ በዚህች ቀን ዐርፏል::
††† ቅድስት ጤቅላ ሐዋርያዊት †††
††† ይህቺ ቅድስት እናት በመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን ከነበሩ ቅዱሳት አንስት አንዷ ናት:: #ቅዱስ_ዻውሎስ በእስያ የወንጌል ጉዞ ሲያደርግ ይህችን ቅድስት #መቄዶንያ ላይ አግኝቷል:: ቅድስት ጤቅላ ምንም ወላጆቿ አረማውያን ቢሆኑ: እርሷ እስከ 3 ቀናት ድረስ ያለ ምንም ምግብ ቃለ እግዚአብሔርን ትሰማ ነበር::
የብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስ ተከታይ ሁና በእስያ ወንጌልን ሰብካለች:: በብዙ ስቃይ ውስጥ ስታልፍም በኃይለ እግዚአብሔር እሳትን አጥፍታለች:: አንበሶችም ሰግደውላታል:: #ቅድስት_ጤቅላ ፈጣሪዋን አስደስታ በዚህ ቀን ዐርፋለች::
††† አባ ዮሐንስ ዘደብረ ጽጌ †††
††† እኒህ ኢትዮዽያዊ ጻድቅ በገዳም ውስጥ ሲጋደሉ ሰውነታቸው አለቀ:: ቅዱሱ ከማረፉቸው በፊት የገዳሙ አባቶች ውሃ በጋን ሞልተው በላያቸው ላይ ቢያፈሱ አንድም ጠብታ ወደ መሬት ሳይወርድ ቀረ:: አካላቸው ከመድረቁ የተነሳ ጠጥቶት ነበርና:: ዛሬ ዕለተ ዕረፍታቸው ናት::
††† አምላከ ኤዎስጣቴዎስ ትእግስቱን:
አምላከ አንጢላርዮስ ምጽዋቱን:
አምላከ ቅድስት ጤቅላ አገልግሎቷን:
አምላከ አባ ዮሐንስ ጽናታቸውን ያሳድርብን:: የሁሉም በረከታቸው ይብዛልን::
††† መስከረም 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስና ቤተሰቡ (ሰማዕታት)
2.ቅዱስ አንጢላርዮስ ጻድቅ
3.ቅድስት ጤቅላ ሐዋርያዊት
4.አባ ዮሐንስ ዘደብረ ጽጌ
††† ወርኀዊ በዓላት
1.የጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በዓለ ስቅለት
2.አቡነ መብዐ ፅዮን ጻድቅ
3.ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ)
4.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
5.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
6.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት
7.ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
††† " #ለቅዱሳን ስለሚሆነው አገልግሎት ልጽፍላችሁ አያስፈልግምና:: በጐ ፈቃዳችሁን አውቄአለሁና:: ስለዚህም ' #አካይያ ከአምና ጀምሮ ተዘጋጅቷል' ብየ ለመቄዶንያ ሰዎች በእናንተ እመካለሁ:: ቅንዓታችሁም የሚበዙቱን አነሣሥቷል::" †††
ጽጌ አስተርአየ በውስተ ምድርነ
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አዝማናትን በአቅማራት ሰፍራና ለክታ የአዝማናት ባለቤት ልዑል እግዚአብሔርን ታመሰግናለች። ወርኃ ክረምቱን ሸኝተን ወርኃ መጸውን (የነፋሱን ወር) በተቀበልንበት በዚህ ጊዜ አባቶቻችን በወዲህ የድንግሊቱን የቅድስት ማርያምን ዜና ስደት እና መከራዋን ዳግመኛም ከልጇ ጋር የደረሰባትን እንግልት እያሰቡ በተዋበ ድርሰት ፣ ባማረ ዜማ ፣ በተቃኘ አንደበትና በትሁት ልቡና ሲያመሰግኗት ያድራሉ። ወርኁም ዘመኑን ይዞ ወርኃ ጽጌ ፣ ዘመነ ጽጌ ተብሎ ይጠራል።
የ2016 ዓ.ም ማኅሌተ ጽጌ ፣ ከመድኃኔዓለም ወርኃዊ በዓል ጋር በአንድ የዋለ ሲሆን ነገ መስከረም 27 ቀን "ጽጌ አስተርአየ" ተብሎ በሊቃውንቱ ይጀመራል። ይህ ክቡር ማኅሌት በታላላቆቹ አድባራት ማ/ስ/ቅ/ልደታ ለማርያምና ደ/መ/መድኃኔዓለም አብያተ ክርስቲያን በደመቀ ሁኔታ የሚቆም ሲሆን ፣ ነግህ በቅዳሴና በስብከተ ወንጌል አገልግሎትም ይቀጥላል። ሁላችንም በዕለቱ በመገኘት ከእመቤታችን እና ከልጇ ከመድኃኔዓለም በረከትና ረድኤትን እንቀበል ዘንድ ከወዲሁ መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
††† እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና ለቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ተአምረ ማርያም †††
††† ተአምር ማለት "ድንቅ: ምልክት: ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪ የሆነ ክዋኔ: በሰብአዊ አቅም ሊሠራ የማይችል ተግባር (ድርጊት)" ነው:: ተአምራት ከባለቤቱ ከጌታችን ሲሆኑ የባሕርዩ ናቸው:: ከቅዱሳኑ ሲሆኑ ደግሞ የጸጋ እንላቸዋለን:: ቅዱስ መጽሐፍ ላይ በእግዚአብሔር ወዳጆች የተሠሩ ተአምራት እጅግ ብዙ ናቸው:: ነገር ግን:-
*ተአምራት ከአጋንንትም ሊሆኑ እንደሚችሉ መረዳት::
*ሁሌ ምልክትን (ተአምርን) አለመፈለግ::
*መመርመርና ማስተዋል ከአንድ ክርስቲያን ይጠበቃል::
*ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ በድርሳኑ እንደ ነገረን ተአምር መሥራት ከሲዖል እሳት አያድንም:: ጌታም በዚህ ነገር ተባብሮበታል:: (ማቴ. 7:22, 12:39)
ከጌታችን እግዚአብሔር ቀጥሎ የድንግል ማርያምን ያህል ተአምራትን የሠራ አይገኝም:: እንዲያው ሌላውን ትተን በእያንዳንዳችን ሕይወት ላይ እንኳ ብዙ ድንቅ ነገሮችን አድርጋለችና ምስክሮቹ እኛው ራሳችን ነን:: የእመቤታችን ተአምር የተጀመረው ገና ከፍጥረተ ዓለም ነው::
በእርግጥ ይህንን ለመረዳት ሠፊ አዕምሮና አስተዋይ ልቡናን ይጠይቃል:: ድንግል ማርያም ማለት የእግዚአብሔር የቸርነቱ ግምጃ ቤት: የጸጋው ደጅ ናት:: እርሱ ይህንን መርጦ ወዷልና:: እመ ብርሃን ተጸንሳ ከተወለደች በኋላ ደግሞ እጅግ ብዙ ኃይልን ታደርግ ነበር:: በዚህ ዕለት ከ2007 ዓመታት በፊት ያደረገችው ተአምር ደግሞ ድንቅ ነው::
አጐቷ /ጠባቂዋ/ አገልጋዩዋ አረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ ከቤተ መቅደስ ተቀብሎ ካመጣት በኋላ እርሱ እንጨትን ይጠርብ ነበር:: ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ (የችግር ዘመን) በመሆኑ ለሥራ ጉዳይ ወደ ሩቅ ሃገር ሒዶ የተመለሰው ከወራት በኋላ ነው::
ዮሐንስ የሚሉት ፈላስፋ ባልንጀራ ነበረውና ሽማግሌው ዮሴፍ ልብ ያላለውን ነገር ነገረው:: "ይህች ብላቴና ጸንሳለችና መርምራት" ብሎ ሔደ:: ቅዱስ ዮሴፍ ግን ደነገጠ:: "እኔ እንዲህ ያለ ነገር እንኳን በገቢር (በሥራ) በሃሳብም አላውቅባት" ብሎት ወደ ቤት ገባ::
ቀጥሎም እመቤታችንን "ልጄ ሆይ! ከማን ጸነስሽ" አላት:: "እመንፈስ ቅዱስ" አለችው:: ግራ ገባው: ምሥጢርም ተሠወረበት:: "እንዴት አንዲት ሴት ያለ ወንድ ዘር ልትጸንስ ትችላለች?" ብሎ ያወጣ: ያወርድ: ይጨነቅም ገባ:: የእኛ እመቤት ግን እንደ ጨነቀው ባወቀች ጊዜ ጠርታ ወደ ውጪ ይዛው ወጣች::
ከረዥም ጊዜ በፊት ጠርቦ የጣለውን እንጨት አንስታ ተከለችውና ጸለየችበት:: በደቂቃም የአረጋዊው ዐይን እያየ ያ ደረቅ እንጨት ለምልሞ: አብቦ አፈራ:: ቅዱስ ዮሴፍ በጣም ደነገጠ::
"አባቴ ተመልከት እስኪ! ይህንን ማን አደረገ?" አለችው:: "ልጄና እመቤቴ! እግዚአብሔር ነው" አላት:: እርሷም "በማሕጸኔ ያለውም ኢሳይያስ ትንቢትን የተናገረለት አምላክ ነውና ሁሉን ይችላል" አለችው:: አረጋዊውም ቅዱስ ኤራቅሊስ በሃይማኖተ አበው እንደ ነገረን "ሰገደ ላቲ" ወደ ምድር ወድቆ በፊቷ ሰገደ::
††† ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ †††
††† ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)
የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል! እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር::
እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ ደግሞ 100 ደርሶ ነበር:: ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::
ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::
የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በኋላ ሰኔ 30 ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::
††† የእመቤታችን ልመናዋ: ክብሯ: የልጇ የወዳጇም ቸርነት በእውነት ከሁላችን ጋር ይሁን:: የመጥምቁንም በረከት ያብዛልን::
††† መስከረም 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት ድንግል ማርያም
2.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
3.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ (ጽንሰቱ)
4.ቅዱሳን ዘካርያስና ኤልሳቤጥ
5.ቅዱስ አቦሊ ሰማዕት (ፍልሠቱ)
††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
2.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
3.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
4.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
5.ቅዱስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
††† "ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ጽንሱ በማሕጸኗ ውስጥ ዘለለ:: በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት:: በታላቅ ድምጽም ጮኻ እንዲህ አለች:-
'አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ: የማሕጸንሽም ፍሬ የተባረከ ነው:: የጌታየ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? . . . ከጌታ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብጽዕት ናት::" †††
(ሉቃ. ፩፥፵፩)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
እንኳን አደረሳችሁ
ማኀሌተ ጽጌ ነገ እንደሚጀምር አውቀዋል ወይ?
#ጽጌ_challenge
#ethiopiaorthodoxtewahedochurch #ማኀሌተ_ጽጌ
ዘመነ ጽጌ (ወርኃ ጽጌ)
እንኳን ለዘመነ ጽጌ (የእመቤታችን የስደቷ መታሰቢያ ) በሰላም በጤና አደረሳችሁ:: ወርሃ ጽጌውን በፀሎት በማህሌት በምሥጋና እንድናሳልፍ የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁንልን
ዘመነ ጽጌ ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ቀን ያሉት 40 ዕለታት ሲሆኑ ትርጓሜው የአበባ ጊዜ ማለት ነው። “ወይቤሎ ለአዳም ወሀብኩከ ርስተ ገነት ትፍስሕት በፅጌ ሥርጉተ ወበፍሬ ክልልተ ዘፍ.2፥8 ” እግዚአብሔር ጠፈርን በአድማስ ደግፎና በደመና ከፍክፎ መባርቅትንና ዝናማትን በደመና ጭኖ ደመናውን በነፋስ አሽክሞ ዓለምን በፀሐይና በጨረቃ አብርቶ በፅጌያት አስጊጦ ገነትን በአዝርዕትና በአትክልት አዘጋጅቶ መንግሥተ ሰማያትን ሠርቶ የሰውን ልጅ ፈጠረው።
አምሳላተ ጽጌ (የጽጌ ምሳሌዎች )
ጽጌ የጌታ ምሳሌ ነው
“ትወፅዕ በትር እምሥርወ እሴይ ወየዐርግ ጽጌ (ኢሳ. 11፥1 ) ትርጓሜ ይእቲ በትር አምሳለ ማርያም ቅድስት ይእቲ ወፅጌ ዘወጽአ እምኔሃ አምሳሉ ለወልድ ( ዮሐ. 1፥1- 14 ድጓ ዘጽጌ)ʼʼ
ከእሴይ ሥር በትር ትወጣለች። ከእርሷም አበባ ይወጣል፤ ይህችውም በትር የማርያም አምሳል ናት። ከእርሷ የተገኘው አበባም የወልድ አምሳል ነው። በመሆኑም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን እውነተኛ መብልና እውነተኛ መጠጥ አድርጐ በመስጠቱ የፍሬ መገኛ በሆነው አበባ ተመስሏል። ቅዱስ ያሬድ ቡሩክ ዕፅ ዘሠናየ ይፈሪ ወኃጢአተ ይሰሪ ( ድጔ ዘጽጌ ) የኃጢአት ማስተሥሪያ የሚሆን መልካም ፍሬን ያፈራ የበረከት እንጨት ክርስቶስ ነው። ለሕያዋን ፍጥረታት የሕይወት ምግብነት ከሕቱም ምድር በቅሎ አብቦና አፍርቶ የተገኘው ክርስቶስ ከፍሬው የበሉትን ደቂቀ አዳም በሙሉ አድኗል።
ፅጌ የቅድስተ ቅዱሳን ቅድስት ድንግል ምሳሌ
እመቤታችን የእውነተኛው ፍሬ ክርስቶስ መገኛ በመሆኗ በአበባ ትመሰላለች፤ እመቤታችን የኃጢአታችን ክብደት ሳይሆን የግፋችን ብዛት የታየባት እውነተኛ ችሎት (ፍትሐ አምላክ) የተገኘባት ናትና። ትውልድ ሁሉ ለዘላዓለም ያመሰግኗታል። “እስመ ርእየ ሕማማ ለአመቱ ወገብረ ኃይለ በመዝራዕቱ (ሉቃ. 1፥481) መዝገቡ ለቃል ፅጌ እንተ ኢትትነገፍ መድኃኒተ ሕዝብ (ድጔ ዘጽጌ) ያገልጋዩን መዋረድ አይቷልና በክንዱ ታላቅ ሥራን አድረገ። የቃል ማደሪያ ( የፍሬ ሙዳይ ) የሆነችው አበባ ለዘለዓለም አትረግፍም። ስለዚህ በፍሬዋ የሕዝብ መድኃኒት በመዓዛዋ የቅዱሳን የሕሊና እረፍት ናት።
‹‹ ዕፀ ጳጣስ እንተ በአማን ፅጌ ደንጐላት ሐረገ ወይን ዘእምነገደ ይሁዳ እንተ ሠረጸት ለሕይወት (ዘፍ. 49፥1 ድጓ ዘጥቅምት ማርያም) እመቤታችን ከይሁዳ ነገድ ለዘለዓለም መንግሥት የወጣች የወይን ሐረግ በደብረ ሲና በጳጦስ እንጨት ላይ የታየውን ምሳሌ በእውነት ያሳያች ናት።››
ጽጌ የመስቀል ምሳሌ
በማር ሥራ ላይ የተሰማሩ ሠራተኛ ንቦች አንድ ሆነው በአበባ ላይ እንደሚሠፍሩ ሁሉ ሕዝብና አሕዛብ በአንድነት የተሰበሰቡበት አበባ የዕለተ ዐርቡ የክርስቶስ መስቀል በመሆኑ መስቀል አበባ ይባላል። በከመ ይቤ ሰሎሞን በእንተ ማርያም ንዑ ንትፈጋዕ ወኢይኅልፈነ ፅጌ ደመና መስቀል ዘዮም አብርሃ በስነ ማርያም። (ድጓ ዘጽጌ ) ሰሎሞን ስለ ማርያም ሲናገር እነሆ ክረሞቱ፣ (ውርጩ፣ ውችንፍሩ፣ ጭቃው፣ ቁሩ ) አልፎ በረከት ተተካ እንዳለ። የክርስቶ መስቀል በማርያም ባሕርይ ዛሬ አብቧልና የበረከት አበባ ሳያልፈን ኑ እንደሰት እንዲል።
በባሕርዩ መወሰን የማይስማማውን አምላክ ማርያም በባሕርይዋ ስለወሰነችው (ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ስለሆነ) በተመረጠችው የማዳን ሰዓት / ዕለተ ዐርብ / መስቀል ያለባሕርዩ በማርያም ባሕርይ ተሸከመው።
ጽጌ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ
የክርስቶስ ሥጋ የሚያፈራባት የአበባ እንጨት የሆነችው ቤተ ክርስቲያን አበባ ትባላለች። ቅዱስ ያሬድ በዝማሬው “ወልድ እኁየ ጸዓዳ ወቀይህ ፀዓዳ ትቤሎ በእንተ ሥጋሁ ለክርስቶስ” ልጅ ወንድሜ መልከ መልካም ደመ ግቡ ቀይ ነው። ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን ስለለበሰው ሥጋ ቀይ ጐልማሳ አለችው ይላል። ቤተ ክርስቲያን ምድራዊት ስትሆን ሰማያዊት ናት። ለምድራዉያን ሰዎች የምትሰጠው ልጅነት የምታድለው ሰማያዊ ፀጋና ሀብት ነው።
‹‹ ሐረገ ወይን እንተ በሞድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕጹቂሃ›› ሥሯ በምድር ቅርንጫፚ በሰማይ የሆነች የወይን ሐረግ በፈቃደ ሥላሴ ዛላዋ የምትቆረጥ ፍሬዋ የምትለቀም የበረከትም ፍሬ የምታፈራልን የወይን ሐረግ ቅዱስት ቤተ ክርስቲያን ናት።
‹‹ቅዱስ ያሬድ “ጽጌ ብሂል ቅድስት ቤተ ክርስቲያን›› ጽጌ ማለት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት ይላታል (ድጓ ዘጽጌ)
በጽጌ የተመሰሉ የጌታችንና የእመቤታችን ስደት (ማቴ. 2፥13 -ፍ)
“እምግብፅ ጸዋዕክዎ ለወልድየ ” (ሆሴዕ. 11 ፥ 1) ልጄን ከግብጽ ጠራሁት ለጊዜው የተነገረው ለያዕቆብ ሲሆን ፍጻሜው ግን ለጌታ ነው። መልከ ጼዴቅም ዘመዶቹን ማርልኝ ቢለው ልጄን በሥጋ ሰድጄ እምርልሀለሁ ብሎ ቃል ገብቶለት ነበርና ኪዳነ መልከ ጼዴቅን ለመፈጸም ጌታ ወደ ግብጽ ተሰደደ።
“መልአከ እግዚአብሔር አስተርአዮ በሕልም ለዮሴፍ” ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ነገረው። “እንዘ ይብል ተንሥእ ወንሣእ ሕፃነ ወእሞ ወጐየይ ውስተ ሞድረ ግብፅ” ተነሥተህ እናቱንና ብላቴናውን ይዘህ ወደ ግብጽ ሂድ ብሎ ነገረው። እስመ ሀለዎ ለሄሮድስ ይኅሥሦ ለሕፃን ከመ ይቅትሎ ” ሄሮድስ ብላቴናውን ሊገድለው ይሻው ዘንድ አለውና።
ወተንሥኦ ነሥአ ሕፃነ ወእሞ በሌሊት ወሖረ ውስተ ብሔረ ግብጽ” ተነሥቶ ብላቴናውን እናቱን ይዞ በሌሊት ወደ ግብጽ ሂደ። ከላይ በመግቢያው እንደተገለጸው
ከመ ይትፈጸም ዘተብህለ እም ኃበ እግዚአብሔር በነቢይ እንዘ ይብል እምግብፅ ጸዋዕክዎ ለወልድየ” እግዚብሔር በነቢይ አድሮ ነቢይ ከእግዚብሔር ተገልጾለት በነቢዩ
ቃል ልጄን ከግብጽ ጠራሁት ተብሎ የተነገረው ይደርስ ይፈጸም ዘንድ፤ ወይወርድ እግዚእነ ውስተ ምድረ ግብጽ ዲበ ደመና ቀሊል” በደመና ተላይ ሆኖ ወደ ግብጽ ይወርዳል ተብሎ የተነገረው ይፈጸም ዘንድ።
“ወነበረ ህየ እስከ አመ ሞቱ” ለሄሮድስ” የተነገረው ይፈፀም ዘንድ ሄሮድስ እስኪሞት ድረስ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ በግብጽ ኖረ።
ጌታ ለምን ተሰደደ?
††† እንኳን ከዘመነ ክረምት ወደ ዘመነ መጸው አሸጋግሮ ለቅዱስ ዮናስ ነቢይ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ስንዱ #እመቤት #ቤተ_ክርስቲያን (ሃገራችን) ሁሉ ነገሯ በሥርዓት ነውና ዓመቱን በዘመናት ከፍላ ትጠቀማለች:: እሊሕም ዘመናት #መጸው (ጽጌ): #ሐጋይ (በጋ): #ጸደይ (በልግ) ና ክረምት ናቸው:: ዘመናቱ ወቅቶችን ከመለየትና ማሳወቅ ባሻገር የእኛ ሕይወትም ምሳሌዎች ናቸውና ልብ ልንላቸው ይገባል::
#ዘመነ_መጸው / #ወርኀ_ጽጌ/ #ጥቢ እየተባለም ይጠራል:: በዚህ ወቅት ምድር በአበባ የምታጌጥበት: ክረምት የተለፋበት አዝመራ የሚደርስበት በመሆኑ ደስ ያሰኛል:: በጊዜውም:-
1.የእመቤታችን የቅድስት #ድንግል_ማርያም ስደቷ ይታሠባል:: እርሷ ስለ እኛ:-
*የሕይወት እንጀራን ተሸክማ መራቧን::
*የሕይወት መጠጥን ይዛ መጠማቷን::
*የሕይወት ልብስን አዝላ መራቆቷን::
*ሙቀተ መንፈስ ቅዱስን የሚያድለውን ተሸክማ ብርድ መመታቷን እናስባለን::
*ዘመኑ የበረከት ነው::
2.በሌላ በኩል ጊዜው ወርኀ ትፍሥሕት (የደስታ ወቅት) ነው:: በክረምት የደከመ ዋጋውን አግኝቶ: በልቶ: ጠጥቶ ደስ ይለዋልና:: ያልሠራው ግን ከማዘን በቀር ሌላ እድል የለውም:: ይኼውም ምሳሌ ነው::
ዘመነ ክረምት የዚህ ዓለም ምሳሌ: ዘመነ መጸው ደግሞ የመንግስተ ሰማያት:: በዚህ ዓለም ምግባር ትሩፋትን የሠራ በወዲያኛው ዓለም ተድላን ሲያደርግ ሰነፎች ኃጥአን ግን እድል ፈንታቸው: ጽዋ ተርታቸው ከግብዞች ጋር የመሆኑ ምሳሌ ነው::
በወርኀ ትፍስሕት እንደ ሊቃውንቱ እንዲህ ብለን ልንጸልይ ይገባል::
"ድኅረ ኀለፈ ክረምት ወገብአ ዝናም: ዘአስተርአይከ እግዚኦ ጽጌያተ ገዳም:
አፈወ ሃይማኖት ነአልድ ወፍሬ ምግባር ጥዑም:
አትግሃነ ለስብሐቲከ ከመ ትጋሆሙ አዳም:
ለጽብስት ንሕብ ወነአስ ቃሕም::"
††† የዘመናት ባለቤት ዘመነ መጸውን #ወርኀ_ትፍስሕት ያድርግልን::
††† ቅዱስ ዮናስ ነቢይ †††
††† ዮናስ ማለት 'ርግብ: የዋህ' ማለት ሲሆን ከ12ቱ #ደቂቀ_ነቢያት አንዱ ነው:: በሰራፕታ ተወልዶ ያደገው ነቢዩ በልጅነቱ ታሞ ሙቶ ነበር:: ታላቁ ነቢይ #ኤልያስ ግን 7 ጊዜ ጸሎት አድርጐ ከሞት አስነስቶታል:: (1ነገ. 17:17) እናቱ የሰራፕታዋ መበለትም ደግ ሴት ነበረች::
ቅዱስ ዮናስ በእድሜው ከፍ ሲል የቅዱስ ኤልያስ ደቀ መዝሙር ሆነ:: የነ ኤልሳዕና አብድዩም ባልንጀራ ነበረ:: ነቢየ እግዚአብሔር ኤልያስ ካረገ በሁዋላ: ቅ.ል.ክርስቶስ በ800 ዓመት አካባቢ የነነዌ ሰዎች ኃጢአት ከመሥፈርቱ በማለፉ የእግዚአብሔር ቃል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ መጣ::
"ሒድና ለነነዌ ሰዎች ንስሃን ስበክላቸው" አለው:: ከነቢያት ወገን ከሙሴና ከዳዊት ቀጥሎ የዮናስን ያህል የዋህ (ገራገር) የለምና እንቢ አለ (ሰምቶ ዝም አለ):: #እግዚአብሔር እየደጋገመ ሲናገረው ግን "እንዲህ የሚዘበዝበኝ ከፊቱ ብቀመጥ አይደል!" ብሎ ወደ #ተርሴስ ኮበለለ::
ወገኖቼ አንድ ነገርን ልብ እንበል:: እንኩዋን ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዮናስ እኛ ክፉዎችም ከጌታ ፊት መሸሸት እንደማይቻል ጠንቅቀን እናውቃለን:: ታዲያ ለምን ሸሸ ቢሉ:- ጥበበ እግዚአብሔር በውስጡ ስለ ነበረበት ነው::
ምክንያቱም ዮናስ በአሣ አንበሪ ሆድ 3 ቀን እና ሌሊት ኖሮ: ሙስና (ጥፋት) ሳያገኘው መውጣቱ ለጌታ ትንሳኤ ጥላ (ምሳሌ) ነው:: ለዚህም ምስክሩ ራሱ ጌታችን ነው::
"ወበከመ ነበረ #ዮናስ ውስተ ከርሠ አንበሪ ሠሉሰ ዕለተ ወሠሉሰ ለያልየ: ከማሁ ይነብር ወልደ እጉዋለ እመ ሕያው ውስተ ልበ ምድር ሠሉሰ ዕለተ: ወሠሉሰ ለያልየ" እንዲል:: (ማቴ. 12:39)
ቅዱስ ዮናስ በገንዘቡ ዋጅቶ ወደ መርከብ በገባ ጊዜ ታላቅ ማዕበል ሆነ:: የእምነት ሰው ነውና እንዲያ እየተናወጡ እርሱ በእርጋታ ተኝቷል:: እነርሱ ግን ቀስቅሰው ቢጠይቁት (እጣ ወድቆበታልና) "የእኔ ጥፋት ስለ ሆነ ወደ ማዕበሉ ጣሉኝ" አላቸው::
እያዘኑ ቢጥሉት ታላቅ ጸጥታ ሆነ:: እነዚያ አሕዛብም እግዚአብሔርን በመስዋዕትና በስዕለት አከበሩ:: ዮናስ ግን በማዕበልና በአሣ አንበሪ ሆድ ውስጥ ለ3 ቀናት ጸለየ:: አሣ አንበሪው በ3ኛው ቀን ወደ ነነዌ ተፋው::
ቅዱሱም "እስከ ሠሉስ ዕለት ትትገፈታእ #ነነዌ ዐባይ ሃገር" እያለ ንስሃን ሰበከ:: የነነዌ ሰዎች ኃጢአታቸውን አምነው ቢጸጸቱ ከሰማይ ወርዶ ከደመና ደርሶ የነበረው የእሳት ማዕበል ተመልሶላቸዋል::
የነቢዩ ትንቢት ግን አልቀረምና ታላቋ ነነዌ ከ300 ዓመታት በሁዋላ ጠፍታለች:: ቅዱስ ዮናስ ግን በቀሪ ዘመኑ ፈጣሪውን እያገለገለ ኑሯል:: ጠቅላላ እድሜውም 170 ዓመት ነው::
††† አምላከ ቅዱስ ዮናስ እድሜ ለንስሃ: ዘመን ለፍስሃ አይንሳን:: ከበረከቱም ይክፈለን::
††† መስከረም 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ጸአተ ክረምት (የክረምት መውጫ)
2.ቅዱስ ዮናስ ነቢይ
3.ቅዱስ እንጦንዮስ
4.ቅድስት በርባራ
5.ሐዋርያት ዼጥሮስ ወዻውሎስ
6.ቅዱስ ዕፀ መስቀል
††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
2.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
3.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
4.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
5.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)
6.ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ
7.ታላቁ አባ ቢጻርዮን ገዳማዊ
††† "ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል:: ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም:: ዮናስ በአሣ አንበሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ: እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል:: የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስተው ይፈርዱበታል:: በዮናስ ስብከት ንስሃ ገብተዋልና:: እነሆም ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ::" †††
(ማቴ. 12:39)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
✞✞✞ እንኩዋን #ለቅዱስ_ጐርጐርዮስ_መነኮስ_ለቅድስት_ክርስቶስ_ሠምራ_እና_ለቅዱስ_አድሊጦስ_ሐዋርያ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
✞✞✞ #ቅዱስ_ጐርጐርዮስ_መነኮስ ✞✞✞
=>በዚህ ስም ተጠርተው: ለምዕመናን አብርተው ያለፉ አባቶቻችን ብዙ ናቸው:: ለምሳሌም:-
*ጐርጐርዮስ ዘኑሲስ
*ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
*ጐርጐርዮስ ዘሮሜ
*ጐርጐርዮስ መንክራዊ
*ጐርጐርዮስ ዘአርማንያ
*ጐርጐርዮስ ረዓዬ ኅቡዓትን መጥቀስ እንችላለን::
+ከእነዚህ ዐበይት ጐርጐርዮሶች አንዱ ገዳማዊው ቅዱስ ዛሬ የሚከበረው ነው:: ቅዱስ ጐርጐርዮስ የተወለደው በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በላይኛው ግብጽ አካባቢ ነው:: ወላጆቹ እጅግ ባለ ጠጐች በመሆናቸው የሚፈልገውን ሁሉ አሟልተው አሳድገውታል::
+በተለይ ደግሞ ሥጋዊ (የዮናናውያንን ጥበብ) እንዲማር አድርገው ወደ #ቤተ_ክርስቲያን ሰደውታል:: በዚያም ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን ከሥርዓቱ ጋር አጥንቶ እጅግ አንባቢ ስለ ነበረ #አናጉንስጢስ (አንባቢ) ሆኖ ተሾመ::
+አንባቢ በሆነባቸው ዘመናትም ወጣ ገባ ሳይል ያገለግል ነበርና ጣዕመ #መንፈስ_ቅዱስ አደረበት:: ስለዚህም አንደበቱ ጥዑም (ለዛ ያለው) ነበር:: ትንሽ ቆይቶም አበው 'ይገባሃል' ብለው ዲቁናን ሾሙት:: አሁንም ታጥቆ ያለ ዕረፍት ማገልገሉን ቀጠለ::
+ዘመኑ ነጫጭ ርግቦች (የተባረኩ መነኮሳት) የበዙበት ነበርና ቅዱስ ጐርጐርዮስ አዘውትሮ ወደ ገዳም እየሔደ ይጐበኛቸው: በእጆቻቸውም ይባረክ ነበር:: በተለይ #ሊቀ_ምኔት ታላቁ ቅዱስ ዻኩሚስ (#አባ_ባኹም) በቅርቡ ነበርና ሁሌ እየሔደ ይጨዋወተው ነበር::
+ትንሽ ቆይቶ ግን ቅዱሱ የምናኔ ፍላጐቱ እየጨመረ ሔደ:: አንድ ቀን ከገዳም ውሎ ሲመለስ ወላጆቹ ጥያቄ ጠየቁት::
"ልናጋባህ እንፈልጋለንና ምን ትላለህ?" አሉት:: እርሱም ጭራሹኑ እንደማይፈልግ መለሰላቸው:: ሊያሳዝኑት አልፈለጉምና ድጋሚ አልጠየቁትም::
+ትንሽ ቆይተውም ተከታትለው ዐረፉ:: ቅዱስ ጐርጐርዮስ ወላጆቹን ቀብሮ: ሃብት ንብረቱን ሸጦ ጉዞ ጀመረ:: ወደ #አባ_ዻኩሚስ ደርሶም ያን ሁሉ ገንዘብ በታላቁ ቅዱስ ፊት አፈሰሰው:: "ምን ላድርገው ልጄ?" ቢለው "አባቴ! ፈጣሪህ ያዘዘውን" አለው::
+አባ ዻኩሚስም መነኮሳት በመብዛታቸው ቤት አልነበረምና ብዙ ቤቶችን አነጸበት:: የቅዱሱ ገንዘብ ገዳም ከታነጸበት በሁዋላ ምናኔን አንድ ብሎ ጀመረ::
+ቅዱሱ ባጭር ታጥቆ: በጾምና ጸሎት: ውሃ በመቅዳት: በመጥረግ: ምግብ በማዘጋጀት: እግዚአብሔርንም አበውንም አስደሰተ:: ቅዱሱ ምንም ቢናገሩት አይመልስም:: ማንንም ቀና ብሎ አያይም::
+"እሺ" ከማለት በቀር ትርፍ ቃል አልነበረውም:: በጸሎት እንባው: በስግደት ደግሞ ላቡ ይንቆረቆር ነበር:: ፍቅሩ: ትዕግስቱ: ትሕትናውና ታዛዥነቱ እጅግ ብዙ ዓለማውያንን ማረከ:: ስለ እርሱ የሰሙ ኃጥአን ሔደው ምንም ሳይናገራቸው በማየት ብቻ ይማሩ ነበር:: ፊቱ ብሩህ: ደግና ቅን በመሆኑ እርሱን ማየቱ በቂ ነበር::
+ለ13 ዓመታት በገዳመ ዻኩሚስ ከተጋደለ በሁዋላ ወደ ገዳመ #ቅዱስ_መቃርስ ከ2ኛው አባ መቃርስ ጋር ተጉዋዘ:: በዚያም በዓት ወስኖ ከሰው ጋር ሳይገናኝ 7 ዓመታትን አሳለፈ:: በጸጋ ላይ ጸጋ: በበረከት ላይ በረከት ሆኖለት በ22ኛ ዓመቱ አባቶችን ሰበሰባቸው::
+መንገድ ሊሔድ መሆኑን ነግሯቸው "በጸሎት አስቡኝ" አላቸው:: በማግስቱ በዚህ ቀን ሲመጡ ግን በፍቅር ዐርፎ አገኙት:: መነኮሳትም በክብር ገንዘው: ከበረከቱ ተሳትፈው: በታላቅ ዝማሬ ቀብረውታል::
+"+ #ቅድስት_ክርስቶስ_ሠምራ +"+
=>ኢትዮዽያዊቷ #ቅድስት_እናት_ክርስቶስ_ሠምራ ቅንነቷ: ደግነቷና ቅድስናዋ እጅግ የበዛ ነው:: አንድ ቀን ግን ገና በትዳር ውስጥ እያለች: ከአገልጋዮቿ አንዷን ትጠራትና ታዛታለች:: ያቺ አገልጋይ ግን የታዘዘችውን ጀሮ ዳባ ልበስ ብላ ሳትታዘዛት ትቀራለች::
+ደጋግማ ብትነግራትም ልትሰማት አልቻለችም:: ያን ጊዜ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ልትገስጻት ብላ ጠጠር ብትወረውርባት ያች አገልጋይ ወድቃ ሞተችባት:: ቅድስቲቱ እጅግ ደንግጣ አለቀሰች:: የምታደርገውንም አጣች::
+ወዲያው ግን ፈጠን ብላ: ወገቧን ታጥቃ ትጸልይ ጀመረች:: "ጌታየ ሆይ! ከሞት አስነሳልኝና ዓለምን ትቼ በቀሪ ዘመኔ አንተን አገልለግልሃለሁ" ብላ ፈጣሪን በብዙ እንባ ተማጸነችው:: ያን ጊዜም አገልጋዩዋ ከሞት ተነሳችላት::
+ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ጊዜን አላጠፋችም:: ልጆቿን በቤት ትታ: ሃብትን ብረቷን ንቃ: አንድ ልጇን አዝላ: ቤቷን እንደ ተከፈተ ትታው ወደ ገዳም ወጣች:: በዚህ ዕለትም (መስከረም 24 ቀን) ወደ #ደብረ_ሊባኖስ ገዳም ገባች::
+"+ #ቅዱስ_አድሊጦስ_ሐዋርያ +"+
=>ቅዱሱ ሐዋርያ ተወልዶ ያደገው በግሪክ #አቴና (ATHENS) ውስጥ ሲሆን በነገድ እሥራኤላዊ ነው:: በአደገባት አቴና ከተማ ሥርዓተ ኦሪትን ከወገኖቹ: የግሪክን ፍልስፍና ደግሞ ከአርዮስፋጐስ ተምሯል:: #መድኃኔ_ዓለም ዘመነ ስብከቱ ሲጀምር ግን አድሊጦስ ወደ #ኢየሩሳሌም ሔዶ አደመጠው: ተማረከበትም::
+ወዲያውም "ጌታ ሆይ! ልከተልህ?" ሲል ጠየቀው:: ልብን የሚመረምር ጌታም ፈቅዶለት ከ72ቱ አርድእት ደመረው:: ከዚያም ከጌታችን ዘንድ ተምሮ: መንፈስ ቅዱስንም ተቀብሎ: ለወንጌል አገልግሎት ተሠማርቶ በርካታ አሕዛብን አሳምኗል:: በመጨረሻም ተወልዶ ባደገባት አቴና በዚህች ቀን ገድለውታል::
=>አምላከ ቅዱሳን በትእግስት: በፍቅርና በትሕትና ይሸልመን:: ከበረከታቸውም ያድለን::
=>መስከረም 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ገዳማዊ
2.ቅድስ ክርስቶስ ሠምራ (ደብረ ሊባኖስ የገባችበት)
3.ቅዱስ አድሊጦስ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
4.አቡነ ሰላማ
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት (መምሕረ ትሩፋት)
2.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
3.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ዘክብራን
4.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤዺስቆዾስ)
5.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
6."24ቱ" ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል)
7.ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም (ኢትዮዽያዊ)
=>+"+ #ፍቅር ያስታግሳል:: ፍቅር ያስተዛዝናል:: ፍቅር አያቀናናም::ፍቅር አያስመካም:: ፍቅር አያስታብይም:: ብቻዬን ይድላኝ አያሰኝም:: አያበሳጭም:: ክፉ ነገርን አያሳስብም:: ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም:: ሁሉን ይታገሣል:: ሁሉን ያምናል:: ሁሉን ተስፋ ያደርጋል:: በሁሉ ይጸናል:: +"+ (1ቆሮ. 13:4)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
††† እንኩዋን ለአበው ሰማዕታት #ቅዱስ_ዮልዮስና_ቅዱስ_ኮቶሎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †††
†††
††† #ቅዱስ_ዮልዮስ_ሰማዕት †††
=>ከሁሉ አስቀደሞ ስለ ሰማዕታት ዜና ሲሰማ ለዚህ ቅዱስ አንክሮ (አድናቆት): ክብርና የጸጋ ውዳሴ ይገባዋል:: ምክንያቱም ገድለ ሰማዕታትን የጻፈልን እርሱ ነውና:: ነገር ግን መጻፍ ሲባል: ነገሮች እንዲህ እንደ እኛው ዘመን ቀላል እንዳይመስሏችሁ:: ቅዱሱ ዜና ሰማዕታትን ለማዘጋጀት ሃብቱን: ንብረቱን: ቤተሰቦቹንና ሕይወቱንም ሰውቷል::
+ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- በመጨረሻው ዘመነ ሰማዕታት (በ3ኛው መቶ ክ/ዘ) ዓለም በደመ ሰማዕታት ስትሞላ የሰማዕታቱን ዜና የሚጽፍ: ሥጋቸውን እንኩዋ የሚቀብር አልተገኘም:: "ወኃጥኡ ዘይቀብሮሙ-የሚቀብራቸውም አጡ" እንዳለ ቅዱስ ዳዊት:: (መዝ. 78:3)
+#እግዚአብሔር ግን ስለ ወዳጆቹ #ሰማዕታት ይህንን ቅዱስ አስነሳ:: ቅዱስ ዮልዮስ በዘመኑ ደግ ክርስቲያን: ትዳርና ልጆች ያሉት: እጅግ ባለ ጸጋና 300 አገልጋዮች ያሉት: ምጽዋትንም የሚወድ ሰው ነበር::
+በወቅቱ ክርስቲያኖች በየመንገዱ ወድቀው መታየታቸው ዕረፍት ቢነሳው ከቤተሰቦቹ ጋር መክሮ መልካም ግን ደግሞ ከባድ ውሳኔን አስተላለፈ:: ውሳኔውንም ታጥቆ ይተገብረው ጀመር:: ነገሩ እንዲህ ነው:-
1.የታሠሩ ክርስቲያኖችን ቁስላቸውን እያጠበ ያጐርሳቸዋል::
2.ቀን ቀን አገልጋዮቹን አስከትሎ የሰማዕታቱን ሥጋ እየሰበሰበ: ሽቱ ቀብቶ ይገንዛቸዋል:: አንዳንዶቹን ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲልክ ሌሎቹን ራሱ ይቀብራቸዋል::
3.ሌሊት ሌሊት በ300ው አገልጋዮቹ እየታገዘ የሰማዕታቱን ዜና: ቀለም በጥብጦ: ብራና ዳምጦ: ብዕር ቀርጾ: ሲጽፍና ሲጠርዝ ያድራል:: በተረፈችው ጥቂት ሰዓት ደግሞ ይጸልያል:: ቅዱስ ዮልዮስ በእውነት ድንቅ ሰው ነው:: በምን እንመስለዋለን! እርሱን የፈጠረውን ጌታ "ዕጹብ ዕጹብ" ብለን ከማድነቅ በቀር::
+ሰማዕታቱም ስለ ደግነቱ የሚመልሱለት ቢያጡ ዝም ብለው ይመርቁት ነበር:: ምርቃናቸውም "ለሰማዕትነት ያብቃህ" የሚል ነው:: በእርግጥ ይህ ለዘመኑ ሰዎች ምርቃት ላይመስለን ይችል ይሆናል:: እርሱ ግን ይህንን ሲሰማ ሐሴትን ያደርግ: እጅም ይነሳቸው ነበር:: በዘመኑ ትልቁ ምርቃት ይሔው ነበርና::
+እንዲህ: እንዲህ እያለ ዘመነ ሰማዕታት ሊፈጸም ወራት ቀሩት:: በዚህ ጊዜ ለሰማዕትነት ከመነሳሳቱ የተነሳ ጌታችንን ተማጸነ:: ጌታችንም ተገልጾለት "ሒድና ሰማዕት ሁን: ፈቅጄልሃለሁ" አለው:: እርሱም ደስ እያለው ዜና ሰማዕታቱን ለሁነኛ ሰው ሰጥቶ: ሃብት ንብረቱን ለነዳያን አካፈለ::
+ቀጥሎም ቤተሰቦቹንና አገልጋዮቹን ጨምሮ 500 ሰዎችን አስከትሎ ወደ ሃገረ #ገምኑዲ ሔደ:: በመኮንኑ ፊት የክርስቶስን አምላክነት ቢመሰክር ፈጽመው አሰቃዩት:: በማግስቱም ወታደሮቹ ለጣዖት ካልሰገድክ ሲሉት "ቆዩማ ላሳያችሁ" ብሎ በጸሎቱ ጣዖታትን ከነ ካህናቶቻቸው ምድር ተከፍታ እንድትውጣቸው አደረገ::
+በዚህ ተአምር የደነገጠው መኮንኑ #አርማንዮስ ከነ ሠራዊቱ በክርስቶስ አመነ:: ክብሩንም ትቶ ቅዱስ ዮልዮስን ተከተለው:: ቀጥሎም ጉዞ ወደ ሃገረ #አትሪብ ሆነ:: በዚያም ብዙ መከራን ተቀብሎ ጣዖታቱን አወደማቸው::
+እዚህም የአትሪብ መኮንን ደንግጦ ከነ ሠራዊቱ አምኖ ቅዱሱን ተከተለው:: በመጨረሻ ግን ሰማዕትነት እንዳይቀርበት ስለሰጋ ቅዱስ ዮልዮስ ተአምራት ማድረጉን ተወ:: በፍጻሜውም የ3ኛው ሃገር መኮንን ቅዱስ ዮልዮስ ከቤተሰቡና ከ1,500 ያህል ተከታዮቹ ጋር: 2ቱን የሃገረ ገዥዎች ጨምሮ አንገታቸውን አሰይፏቸዋል:: ቅዱሱም የክብር ክብርን አግኝቷል::
+"+ #ቅዱስ_ኮቶሎስ_ሰማዕት +"+
=>ይህ ቅዱስ በቀደመ ሕይወቱ አረማዊ ሲሆን የክርስቶስን ስም ሰምቶ አያውቅም:: በ4ኛው መቶ ክ/ዘ በፋርስ (አሁን #ኢራን) ሳቦር የሚባል ክፉ ንጉሥ ነግሦ ክርስቲያኖችን ያሰቃይ ነበር:: እርሱ የሚያመልከው ፀሐይና እሳት ነውና::
+የዚህ ንጉሥ ልጆቹ 'ልዑል ኮቶሎስና ልዕልት አክሱ' ይባላሉ:: በቤተ መንግስት ውስጥ ስላደጉ የሚያመልኩት የአባታቸውን ጣዖት ነበር:: በፋርስ መንግስት ውስጥ ከነበሩ የጦር አለቀቆችና ሃገረ ገዥዎች አንዱ #ጣጦስ ይባላል::
+ይህ ሰው እጅግ ብሩህ የሆነ ክርስቲያን ነበርና ዘወትር ከንጹሕ አገልግሎቱ ተሰነካክሎ አያውቅም:: ትንሽ ቆይቶ ግን ክርስቲያን መሆኑን ሳቦር ስለ ሰማ ሠራዊት ይልክበታል:: "ሒዱና ጣጦስን መርምሩት: ክርስቲያን ከሆነና አማልክትን እንቢ ካለ በእሳት አቃጥላችሁ ግደሉት" አላቸው::
+በአጋጣሚ የንጉሡ ልጅ ኮቶሎስና ጣጦስ በጣም የሚዋደዱ ባልንጀሮች ነበሩና ሊያስጥለው ወዶ ሔደ:: ኮቶሎስ ቅዱስ ጣጦስ ታስሮ በእሳት ሊቃጠል ሲል ደረሰ:: ወዲያውም ወደ እሳቱ ውስጥ ጨመሩት:: እነርሱ ፈጥኖ አመድ ይሆናል ብለው ጠብቀው ነበር:: ግን አልሆነም::
+ቅዱስ ጣጦስ በእሳት መካከል ቁሞ አላቃጠለውም:: እንዲያውም በትእምርተ መስቀል ቢያማትብበት እሳቱ ብትንትን ብሎ ጠፋ:: ኮቶሎስ ተገርሞ ቅዱሱን ባልንጀራውን "ወንድሜ! ሥራይ (መተት) መቼ ተማርክ ደግሞ?" ሲል ጠየቀው::
+እርሱ እስከዚያች ሰዓት ኃይለ እግዚአብሔርን አልተረዳምና:: ቅዱስ ጣጦስ ግን "ወንድሜ! አትሳሳት: እኛ ክርስቲያኖች መተትን አናውቅም:: በፈጣሪያችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ግን ሁሉን ማድረግ እንችላለን" ሲል መለሰለት::
+ኮቶሎስ ተገርሞ "አሁን እኔ በክርስቶስ ባምን እንዳንተ ማድረግ እችላለሁ?" ቢለው ቅዱሱ "አዎ ትችላለህ!" አለው:: ወዲያውም "እሳት አንድዱልኝ" አለና እጣቱን በመስቀል ምልክት አስተካክሎ ወደ እሳቱ ቢያመለክት እሳቱ 12 ክንድ ርቆ ተበትኖ ጠፋ::
+በዚያችው ሰዓት ቅዱስ ኮቶሎሰ በክርስቶስ አመነ:: ክብሩንና የአባቱን ቤተ መንግስት አቃሎ ወደ እስር ቤት ገባ:: አባቱ ሳቦር ይህን ሲሰማ ተቆጥቶ "ምከሪው" ብሎ እህቱን አክሱን ላከበት::
+ቅዱስ ኮቶሎስ ልትመክረው የመጣችውን እህቱን አሳምኖ የክርስቶስ ወታደር አደረጋት:: አስቀድሞ #ቅዱስ_ጣጦስ: አስከትሎም #ቅድስት_አክሱ ተገደሉ:: በፍጻሜው ግን ቅዱስ ኮቶሎስን እግሩን አስረው በየመንገዱ ጐተቱት:: በጐዳናም አካሉ እየተቆራረጠ አለቀ:: ክርስቲያኖች በድብቅ መጥተው የ3ቱንም ሥጋ በክብር አኑረዋል::
=>አምላከ ቅዱሳን ሰማዕታትን ባጸናበት ጽናት ሁላችንም ያጽናን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::
=>መስከረም 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት
2."1,500" ሰማዕታት (የቅዱስ ዮልዮስ ማሕበር)
3.ቅዱስ ኮቶሎስ ሰማዕት
4.ቅድስት አክሱ ሰማዕት
5.ቅዱስ ጣጦስ ሰማዕት
6.ቅዱስ ባላን ሰማዕት
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
3.ቅዱስ ደቅስዮስ (የእመቤታችን ወዳጅ)
4.አባ እንጦንስ አበ መነኮሳት
5.አባ ዻውሊ የዋህ
=>+"+ ሰውን ከአባቱ: ሴት ልጅንም ከእናቷ . . . እለያይ ዘንድ መጥቻለሁና:: ለሰውም ቤተሰዎቹ ጠላቶች ይሆኑበታል:: ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም:: ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም:: መስቀሉን የማይዝ በሁዋላየም የማይከተለኝ ለእኔ ሊሆን አይገባውም:: +"+ (ማቴ. 10:35)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
🌹♥️ #እንኳን_አደረሳችኹ_ግሽን_ደብረከርቤ_መሄድ_ያለው_ክብር_የተገባለት_ቃል_ኪዳን_ከቃል_ኪዳኑ_ተካፋይ_ያድርገን🌹♥️👇
🌷#መስከረም_ሃያ_አንድ_ቀን_የእግዚአብሔር_አብን_ቤተ_ክርስቲያን_ቅዳሴ_ቤቱን_ባከበርንበት_ቀን_እንደ_ተገለጸልን_ሁኖ_ታየን፡፡
🌹ይህች ቦታ እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ የስሜ መመስገኛ በረድኤት መገለጫየ ናት አለን፡፡
🌻የእናቴን አማላጅነቷን አምነው ከዚህች ቦታ ውስጥ የሚኖሩትም እንደ መላእክት አደርጋቸዋለሁ።
🌷በዚህችም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሥጋዬን ደሜን የተቀበሉትን
🌹በእኔ ስም ደማቸውን እንደ አፈሰሱ የቤተልሔም ሕፃናት ይሆናሉ፡፡
🌻ይህችንም ቤተ ክርስቲያን እንደ እናቴ መቃብር እንደ ጌቴሴማኒ ትሁን ብየ አክብሬአታለሁ፡፡
🌷በችግራችሁ ጊዜ ወደ መንግሥተ ሰማያት መሸጋገሪያ መርከብ እንድትሆናችሁ።
🌹ከዚህች ቤተ ክርስቲያን ሄዶ ገብቶ የተማፀነም ለዘለዓለም አያፍርም ዋጋውን አያጣም፡፡
🌷ለእናቴ የሰጠኋትን ይህን ቃል ኪዳን አስቦ አምኖ እናቴ ባረፈችበት ጥር ሃያ አንድ ቀን ባረገችበት ነሐሴ ዐሥራ ስድስት ቀን ከዚህች ቤተ ክርስቲያን መጥቶ ዕጅ የነሣውን በዓሏን ያከበረውን♥️ለእናቴ ወገን ቤተሰብ አደርገዋለሁ፡፡
🌷በእናቴ ስም ለታነጸችው ለዚህች ቤተ ክርስቲያን
ኖራ በመለወስ ዕንጨት በመጥረብ ድንጋይ በማቅረብ ለደከማችሁ ለእናንተም ፃሕሉን ጽዋውን ንዋየ ቅድሳቱን መስቀሉን በመሥራት በማሠራት ለደከማችሁ ለእናንተ በሰው አእምሮ ሊታሰብ የማይቻል ዓይን አይቶ ጆሮ ሰምቶ ሊመረምረው የማይቻለውን ዋጋችሁን እሰጣችኋለሁ♥️ስማችሁን በሕይወት መጽሐፍ እጽፍላችኋለሁ፡፡ አለ እገልጸዋለሁ ሲል ለቅድስት እናቴ ክብር ስል የሰጠኋችሁን ይህን ቃል ኪዳን የሚጠራጠር ቢኖር በከበረ ደሜ ፈሳሽነት ላከበርኩት ቅዱስ መስቀል ክብር ስል የሰጠሁትን ቃል ኪዳን ያቃለለ ቢኖር ከእኔ አንድነት የለውም
🌻በእናቴ ድንግል ማርያም አማላጅነት ከሚገኘው ክብር ልዩ ነው ይህን ቃል ኪዳን ሰጥቶን በክብር በሥልጣን ወደ ሰማይ ዓረገ፡፡
🌹ከዚህ በኋላ በዚሁ ዓመት ነሐሴ ዐሥራ ሦስት ቀን እግዚአብሔር ለአባ ሚካኤልና ለአባ ገብርኤል
ተገልጾ ተነጋገራቸው፡ እንዲህ ብሎ አስቀድሜ ከአድባራቱ ሁሉ መር።
🌻ይህችን ቦታ እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ የስሜ መመስገኛ የጌትነቴ መገለጫ አደረኳት።በዛሬው ቀን የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት ብየ የባሕርይ ልጅነቱን በደብረ ታቦር እንደ መሰከርኩለት፡፡ በዚህች ቦታ የቸርነቴንና የርኅራሄዬን ምሥጢር ገለጽኩላችሁ።
🌷እንዲህ ብየ በዛሬው ቀን በየዓመቱ ከዚህ ቦታ መጥቶ ዕጅ የሚነሣ ሁሉ አይለይም ለዘለዓለም
አይጠፋም፡፡
🌹እኔም ይህችን ቦታ በዛሬው ቀን እንደ ዛሬው በየወሩ በየዓመቱ ይህ ዓለም እስከሚያልፍ ድረስ በረድኤት አልለያትም፡ ይህን ቃል ኪዳን ከሰጣቸው በኋላ ተሠወራቸው፡፡
🌻ይህም ቃል ኪዳን እውነት እንጂ ሐሰት አለመሆኑን ጽኑዕ በሆነ መሐላ ነገሩን፡፡
🌷ይህን ቃል ኪዳን ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ስለሰሙና ስለአገኙ አባ ሚካኤል አባ ገብርኤል ኤጲስ ቆጶሱ አባ ዮሐንስ ቀራንዮን ትሁን ብለው። ጐልጎታን ትሁን ብለው፡ ደብረ ታቦርን ትሁን ብለው ይህን ሥርዓት ሠሩ፡፡
🌹ይህችን ቦታ የሚመስላት በክብር የሚተካከላት ያለነዚህ በቀር ሌላ ቦታ አላገኘንምና፡፡
🌻ይህችን የሥርዓት እና የቃል ኪዳን መጽሐፍ የተጠራጠረ የናቀ ሰው ዕድል ፈንታው ጽዋ ተርታው ወልድን ፍጡር ብሉ ክዶ በ፫፻፲፰ ሊቃውንት እንደተለየው እንደ አርዮስ ይሁን፡፡
🌷እኛም ጌታ ቀራንዮ ያላላትን ቀራንዮ ናት፡ ጐልጎታ ያላላትን ጐልጎታ ናት፣ ደብረ ታቦር ያላላትን ደብረ ታቦር ናት፣ ኢየሩሳሌም ያላላትን ኢየሩሳሌም ናት ብለን በማናቸውም ሁሉ ጌታ ያልሰጣትን ክብርና ስም እኛ ሰጥተን፣ የክብር ክብር · የሌላትን እንዳላት አድርገን በማይገባት ክብር አክብረናት እንደሆነ ዕድል ፈንታችን ጸዋዕ ተርታችን ጌታውን ሸጦ ከማኅበረ ሐዋርያት እንደ ይሁዳ ተለየው ይሁን፡፡ዕድል ፈንታችን ጽዋ ተርታችን ጌታቸውን ጸልተው ተመቅኝተው እንደ ሰቀሉት እንደ አይሁድ ይሁን፡፡
🌹ይህን ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ቃል አግኝተን የተናገርነውን ቃል ኪዳንና የሠራነውን ሥርዓት የናቀ፣ የተለየ ይሁን ብለን አውግዘን ለይተነዋል ሥጋውን ስለተቀበልን ደሙን
የክርስቶስ አካል ማኅበር ቤተሰብ ስለተባልን ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን።
🌻ለሕዝበ ክርስቲያን ነን ለሚሉ ለምእመናን ሁሉ ለጳጳሳቱ ለካህናቱ ለነገሥታቱ ለመኳንንቱ፡፡
ለወንዶቹ ለሴቶቹም ሁሉ በየዓመቱ ከዚህች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ባርኮ በደሙ ቀድሶ ካከበራት ቦታ መጥተው ይህን ዓለም ለማዳን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል ዕጅ ይነሱ ዘንድ ይገባቸዋል፡፡
🌹እመቤታችንንና የከበረ መስቀሉን የሚያከበሩ
ኃጢአታቸው ይሠረይላቸው ዘንድ፡፡ አሜን፡፡
✝️✝️ አቢ ጠቅላላ ኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ ጥገና ✝️✝️እ
ንኳን እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ እያልን
👉 ኦቭን
👉 ማይክሮዌቭ
👉 ምጣድ
👉 ስቶቮች
👉 የሻይ ቡና ማሽን
👉 መፍጫዎች
👉 የውሃ ማፍያዎች
👉 የውሀ ፓምፖች
👉 ጄነሬተር በአስተማማኝ ሁኔታ እንጠግናለን
ከቤትዎ ሳይወጡ ይደውሉ ያሉበት በመምጣት እንሰራለን
📞 0938152513
/channel/abi1888
/channel/electricianbolegerji
jo1888" rel="nofollow">http://www.tiktok.com/@jo1888
✝️✝️ መልካም የመስቀል በዓል ✝️✝️
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን!
መስከረም 20-ድንግል የሆነች ቅድስት መሊዳማ በሰማዕትነት ያረፈችበት ዓመታዊ በዓሏ መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሳታል፡፡
+ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት ቅዱስ አትናቴዎስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ይኸውም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት 28ኛው ነው፡፡ በእስክንድርያ አገር በአንዲት ቤተ ክርስቲያን መጋቢ ሆኖ በተጋድሎ ይኖር በነበረበት ወቅት ሊቀ ጳጳሳቱ አባ ጴጥሮስ ዐረፉ፡፡ በዚህም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉና መኳንንቱ ኤጲስቆጶሳቱም በአንድ ላይ መክረው ሊቀ ጵጵስና ይሾሙት ዘንድ ተስማሙ፡፡ ሁሉም ይህንን የተማከሩት ቅዱስ አትናቴዎስ በተጋደሎው ብዛት መንፈስ ቅዱስ እንዳደረበት ስላወቁ ነው፡፡ እርሱንም ወስደው ያለፈቃዱ በግድ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት፡፡
ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና የክርስቶስን መንጋዎች በመልካም ትምህርቱና በጸሎቱ የዲያብሎስ አገልጋይ ከሆኑ ተኩላዎች በመልካም አጠባበቅ ጠበቃቸው፡፡ ሃይማኖትን ከሚያስለውጡ ቀሳጢአን ምእምናንን ለመጠበቅ ብዙ ደክሟል፡፡ በዚህ አገልግሎቱም በሹመቱ ሆኖ 7 ዓመት ካገለገለ በኋላ በዚህች ዕለት በሰላም ዐርፏል፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!