kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ጥቅምት 8/2016 #አቡነ_ኪሮስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸዉ ከምታስባቸዉ ቅዱሣን አንዱ ለሆኑት ፃድቁ #አቡነ_ኪሮስ ለወርሐዊ በአላቸው እንኳን አደረሰን የአምላካችን የመድኃኒታችን #የኢየሱስ_ክርስቶስ ቸርነት የፃድቁ አማላጅነት አይለየን አሜን

👉የጻድቁን ስም የሚጠራ አፍ ንዑድ ነው ክቡር ነው በእውነት የቅዱሱን አባት ክብር ለማግኘት መፋጠን ይበጃል አቡነ ኪሮስ የተወለዱት በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን ወላጆቻቸው ነገሥታት ናቸው

👉ተወልደው ባደጉባት ሃገር ቁስጥንጥንያ ገና በልጅነት ምቾት ሳያሳሳቸው መጻሕፍትንና ትሕርምትን ተምረዋል ወንድማቸው (ታላቁ ቴዎዶስዮስ) በነገሠባቸው የመጀመሪያ ዓመታት በቤተ መንግስቱ ዙሪያ ግፍ በዝቶ ነበርና #አቡነ_ኪሮስ ከኃጢአት ለመራቅና ለጌታ ለመገዛት ከከተማው ጠፍተው አሕጉር አቁዋርጠው ወደ ግብፅ (ገዳመ አስቄጥስ) መጡ

👉እርሳቸውን ለመፈለግ የተደረገው ሙከራ አልተሳካም ይባስ ብሎ የንጉሡ ልጅ ገብረ ክርስቶስ ሙሽርነቱን ጥሎ ወደ ሌላ ሃገር መነነ "የቅኖች ትውልድ ይባረካል" እንዳለ ቅዱስ ዳዊት አቡነ ኪሮስ ለሙሽራው ገብረ ክርስቶስ አጎቱ ናቸው አቡነ ኪሮስ በገዳም ውስጥ የታላቁ አቡነ በብኑዳ ደቀ መዝሙር ሆነው ለዘመናት ቆይተዋል

👉ቅዱስ በብኑዳን አንበሳ በበላው ጊዜ በጣም አዝነው "ለምን ጌታ ሆይ?" በሚል መሬት ላይ ወድቀው አለቀሱ "ምክንያቱ ካልተነገረኝ አልነሳም" ብለው ከወደቁበት መሬት ላይ ሳይነሱ ለ40 ዓመታት አልቅሰዋል በዚህ ምክንያት ግማሹ አካላቸው አፈር ሆኖ ሣር በቅሎበታል ጌታችን ተገልጦ ምክንያቱን ነግሯቸዋል አካላቸውንም እንደነበረ መልሶላቸዋል::

👉አንድ ቀን ጻድቁ ለቅዱስ በብኑዳ ሞት ምክንያት የሆነው መነኮስ ታንቆ መሞቱን ሰምተው በጣም አዘኑ ሱባዔ ገብተው ፍጹም አልቅሰው ከጌታም አማልደው የዛን ኃጥእ ነፍስ ከሲዖል አውጥተዋል በሌላ ጊዜ ደግሞ ኃጥአን የሞሉበት አንድ ገዳም በግብፅ ነበርና መቅሰፍት ወርዶ ሁሉንም ባንድ ቀን ሲያጠፋቸው አዩ

👉ፃድቁ በዚህም ምክንያት ለ30 ዓመታት አልቅሰው ሙታኑን አስነስተው ንስሃ ሰጥተው ገዳሙን የጻድቃን ሕይወታቸውንም የፍቅር አድርገውታል ፃድቁ እመቤታችንን ከመውደዳቸው የተነሳ በስዕሏ ፊት አብዝተው ይሰግዱና ያለቅሱ ነበር እመ አምላክም ተገልጣ ትባርካቸው ነበር

👉ከዚህ በሁዋላ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ሒደው ለ57 ዓመታት ማንንም ሳያዩ ተጋደሉጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ (ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና) በየቀኑ ይጐበኛቸው ቁጭ ብሎም ያወራቸው ነበር

👉በመጨረሻም ጌታ አእላፍ መላእክትን ፃድቃን ሰማዕታትን ድንግል እመቤታችንና ቅዱስ ዳዊትን አስከትሎ ወረደ

👉ቅዱስ ዳዊት ቀርቦ እያጫወታቸው በበገናው እየደረደረላቸው ከዝማሬው ጣዕም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው በፍቅር ተለየች ጌታችንም ታቅፎ ስሞ ይዟቸው አረገ

👉ሥጋቸውን አባ ባውማ ቀበሩት የአቡነ ኪሮስ ቁመታቸው ቀጥ ያለ ፅሕማቸውም የተንዠረገገ ነበር እድሜአቸውን ግን መገመት የሚቻል አይመስለኝም

👉የፃድቁ አባታችን ምልጃና ፀሎት ይጠብቀን ረድኤት በረከታቸዉ አይለየን "አሜን" 💒 💚 💛 ❤ 💒

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞✞✞ እንኩዋን ለታላቁ ገዳማዊ "ቅዱስ አባ ባውላ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+"+ አባ ባውላ መስተጋድል +"+

=>ቅዱሱን የመሰሉ አባቶች "መስተጋድላን" ይባላሉ በግዕዙ:: ለሃይማኖታቸው እስከ ደም ጠብታና እስከ መጨረሻዋ ህቅታ ድረስ መጋደላቸውን የሚያሳይ ነው:: መጋደል ጐዳናው ብዙ ዓይነት ነው::

+ከራሱ ጋር የሚጋደል አለ:: ከዓለም ጋር የሚጋደልም አለ:: የቅዱሳኑ ተጋድሎ ግን በዋነኝነት ከ2 አካላት ጋር ነው:: በመጀመሪያ ፍትወታት እኩያትን (ኃጣውዕን) ከሚያመጡ አጋንንት ጋር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ "ሃይማኖቸታችሁን ካዱ: ለጣዖትም ስገዱ" ከሚሉ ከሃድያን ጋር የሚደረግ ትግል ነው::

+በተለይ 2ኛው እስከ ሞት የሚያደርስ ውሳኔን ይጠይቃል:: ታላቁ አባ ባውላ ገዳማዊ ጻድቅ እንደ መሆኑ ትግሉ የነበረው ከአጋንንት ጋር ነው:: የዚህን ቅዱስ ሕይወት ለመረዳት ግን አንድ ነገርን ልብ እንድትሉልኝ እፈልጋለሁ::

+ያለንበት ዘመን ክርስትና በራድ (ቀዝቃዛ) በመሆኑ የቀደሙ አባቶች የጸና ተጋድሎ አንዳንዴ ግራ ሲያጋባን ተመልክቻለሁ:: ቅዱሳኑ ሁሌም አንድ ነገርን እያሰቡ ይኖራሉ:: ይኼውም በዘመኑ በርካቶቻችን የረሳነው: ወይም ማስታወስ የማንፈልገው ነገር ይመስላል::

+ሰማያዊው አምላክ ከዙፋኑ ወርዶ በተዋሐደው ሥጋ በቃል ሊገለጽ የማይችል መከራን ስለ እኛ ተቀብሏል:: ክርስትና ማለት ቀራንዮን በልብ ውስጥ መሳል ነው:: ፍቅረ መስቀሉን: የጌታንም ውለታ የሚያስብ ማንኛውም ሰው: የትኛውም ዓይነት መከራ ቢመጣበት አይታወክም::

+ቅዱሳኑም የፍቅራቸውና የትእግስታቸው ምሥጢር ይኼው ነው:: ጌታ "የሚወደኝ ቢኖር የሞቱን መስቀል ተሸክሞ ይከተለኝ" (ማቴ. 16:24) እንዳለው: ቅዱሳኑ ይህንን ቃል በቃል ሲፈጽሙት እነሆ እንመለከታለን::

+ታላቁ አባ ባውላ የተወለደው በላይኛው ግብጽ አካባቢ ሲሆን ዘመኑም 4ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ከክርስቲያን ወላጆቹ መንፈሳዊ ነገሮችን ተምሮ በወጣትነቱ መንኗል:: ያ ዘመን እልፍ አእላፍ ቅዱሳን የነበሩበት ነውና ወደ ጠመው አካባቢ ሔዶ ምናኔን ተምሯል::

+ሥርዓተ ገዳምን ማለትም:- አገልግሎትን: ፍቅርን: ተጋድሎንና የመሳሰሉትን ከተማረ በሁዋላም ደቀ መዝሙሩን አባ ሕዝቅኤልን አስከትሎ ለዋናው የተጋድሎ ሕይወት ወደ በርሃ ወጣ:: አባ ባውላ ዘወትር በፍቅረ ክርስቶስ ይመሰጥ ነበርና የተጋድሎ ምርጫው ልዩ ሆነ::

+አንድ ቀንም እንዲህ ሲል አሰበ:- "ጌታ ሆይ! አንተ ለእኛ ለኃጥአን ኃፍረተ መስቀልን ታግሠህ: ሞትን ከሞትክልን እኛ ደግሞ ስለ ንጹሑ አምላክ ስንል እልፍ ሞትን መታገስ አለብን::"

+ይህንን ብሎ ከወትሮው በተለየ መንገድ ሊጋደል ጀመረ:: በዚህ እጅግ የጸና ተጋድሎው ምክንያትም 7 ጊዜ ሙቶ 7 ጊዜ ተነሳ::

1.እግሩን ከረዥም ዛፍ ላይ አስሮ: ወደ ታች ተዘቅዝቆ ይጸልይ ጀመረ:: እህልም: እንቅልፍም: ዕረፍትም አልነበረውምና ደሙ በአፍ: በአፍንጫው ፈሶ አለቀ:: እንዲህ በሆነ በ40ኛው ቀንም ሞተ:: መልአከ እግዚአብሔር መጥቶ ከሞት አስነሳው::

2.ጥልቅ ባሕር ውስጥ ሰጥሞ እንዳስለመደ ይጸልይ ጀመረ:: ከባሕሩ ሳይወጣ: ከቆመ ሳያርፍ: ከዘረጋም ሳያጥፍ ለ40 ቀናት ጸለየ:: በዚያው ሳለም ለ2ኛ ጊዜ ሞተ:: ቅዱስ መልአክ መጥቶ ከሞት አስነሳው::

3.እርሱ በሚኖርበት ጠመው አካባቢ ረዥም ተራራ ነበርና ወደዚያ ወጣ:: ከተራራው ጫፍ ሆኖ ወደ ታች ተመለከተ:: የተጠራረቡ ድንጋዮች በየመንገዱ ተሰልፈው ነበር:: በዚያች ቅጽበት የጌታ ኅማማት ከፊቱ ቢደቀንበት ከላይ ወደ ታች ተወርውሮ ሔደ::
በየመንገዱ ያሉት ጥርብ ድንጋዮች ቢቀበሉት አካሉ እየተነተፈና እየተቆራረጠ በየመንገዱ ቀረ:: በዚህም ሞተ:: አሁንም ፈጣሪው ከሞት አስነሳው::

4.አንድ ቀን ደግሞ (ዕለቱ ዓርብ ነበር) የጌታን ኅማማት እያሰበ የሚያደርገው ጠፋው:: ከቆመበት አካባቢ ትልቅ ዛፍ ነበርና ወደዚያ ወጥቶ ሲመለከት ከመሬት ላይ የተነጠፈ ትልቅ ድንጋይ አየ:: ከላይ ወደ ታች ሲወድቅና ድንጋዩ ላይ ሲያርፍ ለሁለት ተከፍሎ ሞተ:: አሁንም በፈጣሪ ትዕዛዝ ተነሳ::

5.በሌላ ቀን ደግሞ በዕለተ ዓርብ ጭንቅላቱን ከእግሩ ጋር አሥሮ ይጸልይ ገባ:: ያለ ምንም እህል: ውሃና እንቅልፍ ለ40 ቀናት ቆይቶ ሞተ:: እንደገናም ተነሳ::

6.እጅግ ሊመለከቱት እንኩዋ በሚከብድ የጉድጉዋድ ውሃ ውስጥ ገብቶ ለ40 ቀናት እጆቹን ዘርግቶ ቢጸልይ ከጭንቁ ብዛት ነፍሱ ከሥጋው ተለየች::

7.አንድ ቀንም እንደዚሁ የጌታን ሕማማት እያሰበ ወደ ጽኑ ቆላ ወረደ:: በአካባቢው ከአሸዋ በቀር ምንም አልነበረምና ቆሞ ሲጸልይ አሸዋው ውጦ ደፈነውና ለ7ኛ ጊዜ ሞተ:: በዚህ ጊዜ ግን ሊያስነሳው የመጣው እንደ ወትሮው ቅዱስ መልአክ ሳይሆን ራሱ የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ ነበር::

+ጌታችን አባ ባውላን ከሞተበት አስነስቶ:- "ወዳጄ ባውላ! ስለ እኔ ፍቅር እጅግ ተሰቃየህ" አለው:: ቅዱሱ ግን "ጌታየ ሆይ! የእኔ መከራ በአንተ መከራ ሲታሰብ ኢምንት ነውና እባክህ ስለ ስምህ ሌሎች መከራዎችን እንድቀበል ፍቀድልኝ? ገና ሕማምህን አስቤ አልረካሁምና" አለው::

+ጌታ ግን "የለም! መከራው ይበቃሃል:: መጥቼ እስክወስድህ ድረስ ከአባ ብሶይ ጋር ቆይ" ብሎት: ባርኮት ዐረገ:: አባ ባውላም እንደ ታዘዘው በአባ ብሶይ ገዳም ከቅዱስ ብሶይ ጋር ቆይቶ በዚህች ቀን ዐርፏል::

+ይህቺውም ዕረፍቱ ለ8ኛ ጊዜ ሆና ተቆጥራለች:: የቅዱሱን ዜና የጻፈው ደቀ መዝሙሩ አባ ሕዝቅኤል ሲሆን ያሰፈረው እንባው እንደ ዥረት እየወረደ ነው:: አባቶቻችን ሊቃውንትስ ታላቁን ጻድቅ ሲያመሰግኑት እንዲህ አይደለምን!
"ውስተ ገድል ጽኑዕ ዘአልቦ ምምዐ:
ወደቀ ስብአ: ወተንሳእከ ስብአ::"

=>አምላከ አባ ባውላ በጻድቁ ላይ ያሳደረውን ፍቅሩን ያሳድርብን:: ከበረከቱም ያድለን::

=>ጥቅምት 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አባ ባውላ መስተጋድል
2.አባ ሕዝቅኤል ጻድቅ
3.ቅዱስ ሚናስ ሰማዕት
4.ቅዱስ ሐናሲ ሰማዕት

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
5.አባ ባውላ ገዳማዊ
6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)

=>+"+ እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ:: መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ:: ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል:: ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል:: ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ: ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል? +"+ (ማቴ. 16:24)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ጥቅምት_6

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ስድስት በዚህች ቀን እመ ሳሙኤል ነቢይ #ቅድስት_ነቢይት_ሐና ያረፈችበት፣ ቅዱስ አባት #አባ_ጰንጠሌዎን ያረፈበት፣ #ዕንባቆም_ነቢይ መታሰቢያው፣ የሀገረ አቴና ኤጲስቆጶስ #ቅዱስ_ዲዮናስዮስ በሰማዕትነት ያረፈበት እና የሴት ልጅ #ቅዱስ_ሄኖስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስት_ነቢይት_ሐና

ጥቅምት ስድስት በዚህች ቀን የታላቁ ነቢይና ካህን የሳሙኤል እናት ቅድስት ነቢይት ሐና አረፈች።

ይችም ቅድስት ከሌዊ ነገድ ናት የታኅርም ልጅ ሕልቃና አገባት ፍናና የምትባልም ሌላ ሚስት አለችው እርሷም ወላድ በመሆኗ ሐና ልጅ ስለሌላት መካንም ስለሆነች ሁልጊዜ ትገዳደራት ነበር።

ሐና ግን ፈጽማ በማዘን አትበላም አትጠጣም ባሏ ሕልቃናም ያረጋጋታል ማረጋጋቱንም አልተቀበለችውም በሊቀ ካህናቱ በኤሊ ዘመንም ወደቤተ እግዚአብሔር ወጣች እያለቀሰችና እያዘነች በእግዚአብሔር ፊት ጸለየች እንዲህም ብላ ስለትን ተሳለች አቤቱ ልጅ የሰጠኸኝ እንደሆነ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ለአንተ የሚያገለግል አደርገዋለሁ።

ካህኑ ኤሊም አያትና እርሷ የወይን ጠጅ ጠጥታ እንደ ሰከረች አሰበ እርሷ በዝምታ በልቧ ትጸልይ ነበርና በቊጣና በግሣጼ የወይን ጠጅ ጠጥተሽ ወደዚህ ወደ እግዚአብሔር ቤት ለምን መጣሽ አሁን ሒጂ ስካርሺን በእንቅልፍ አስወግጂ አላት።

እርሷም እንዲህ አለችው የወይን ጠጅ ከቶ አልጠጣሁም ልጅ ያጣሁ በመሆኔ በልቤ አዝናለሁ እንጂ ካህን ኤሊም አጽናናት እንዲሁም ብሎ ባረካት የእስራኤል ፈጣሪ የለመንሽውን ይስጥሽ በሰላም ሒጂ በቃሉም አምና ወደ ቤቷ ገባች።

ከዚህም በኋላ ፀንሳ ወንድ ልጅን ወለደች ስሙንም ሳሙኤል ብላ ጠራችው። ጡትንም በአስጣለችው ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቤት ይዛው ወጣች ወደ ካህን ኤሊም አቀረበችውና እንዲህ ብላ አስረዳችው ከአሁን በፊት ልጅን ይሰጠኝ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ስጸልይና ስለምን ያየኸኝ ሴት ነኝ ልመናዬንም ሰምቶ ይህን ልጅ ሰጠኝ አሁንም በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ለእግዚአብሔር አገልጋይ ይሆን ዘንድ አመጣሁት።

ከዚህም በኋላ ሐና እግዚአብሔርን አመሰገነችው። ልቤ በእግዚአብሔር አምኖ ጸና የሚለውን ጸሎትና ትንቢት እስከ መጨረሻው ተናገረች። ይቺም በዳዊት መዝሙር መጨረሻ ከሙሴ መኀልይ ቀጥላ ተጽፋለች።

ከዚህም በኋላ እግዚአብሔርን አገልግላ በሰላም አረፈች።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አባ_ጰንጠሌዎን

ዳግመኛም በዚችም ቀን በዋሻ ውስጥ የሚኖር ቅዱስ አባት አባ ጰንጠሌዎን አረፈ። ይህም ቅዱስ በሮሜ አገር በንጉሥ ቀኝ ከሚቀመጡ ከከበሩ ሰዎች ወገን የተወለደ ነው ። በታናሽነቱም ጊዜ ወደ መነኰሳት ገዳም ወስደውት በበጎ ምክር ዕውቀትን እየተማረ በመጸለይና በመጾም በዚያ አደገ።

ከዚህም በኋላ ከቅዱሳን ከስምንቱ ባልንጀሮቹ ጋር ወደ ኢትዮጵያ በንጉሥ አልዓሜዳ ዘመን መጣ በአንድነትም ጥቂት ዘመናት ኑረው ከዚህም በኋላ እርስበርሳቸው ተለያዩ ቅዱስ ጰንጠሌዎንም ከታናሽ ተራራ ላይ ወጥቶ ርዝመቱ አምስት ክንድ አግድመቱ ሁለት ስፋቱ ሦስት ክንድ የሚሆን ዋሻ ለራሱ ሠራ ጠፈሩም አንድ ደንጊያ ነው ከጥቂት ቀዳዳ በቀር በር የለውም።

በውስጡም ሳይቀመጥ ሳይተኛ ያለመብልና ያለ መጠጥ አርባ አምስት ዓመት ኖረ ቆዳው ከዐጥንቱ እስከሚጣበቅ በዕንባ ብዛትም ቅንድቡ ተመለጠ። በሽተኞችን በማዳን የዕውሮችንም ዐይኖች በመግለጥ ብዙ ተአምራትን አደረገ።

በአንዲትም ቀን በማታ ጊዜ ዕንጨት ተከለ አሰከሚነጋ ድረስም አድጎ ትልቅ ዛፍ ሆነ ወዲያውም ደረቀና ደቀ መዝሙሩ ፈልጦ አነደደው ፍሙንም በልብሱ ቋጥሮ ለማዕጠንት ወሰደው።

የናግራንን አገር ያጠፋትን ምእመናኖችንም የገደላቸውን አይሁዳዊ ንጉሥ ሒዶ ሊወጋው ንጉሥ ካሌብ በአሰበ ጊዜ በጸሎቱ ይረዳው ዘንድ ይህን አባት ጰንጠሌዎንን ለመነው እርሱም በሥራው ሁሉ ላይ ችሎታ ያለው እግዚአብሔር በጠላቶችህ ላይ ድል አድራጊነትን ሰጥቶህ በደኀና በፍቅር አንድነት ትመለሳለህ አለው።

ንጉሥ ካሌብም ከናግራን ሀገር በደረሰ ጊዜ ከከሀዲው ንጉሥ ከፊንሐስ ጋር ተዋጋ ድል አድርጓቸውም ከሀድያንን ሁሉ እንደ ቅጠል እስቲረግፉ አጠፋቸው አባ ጰንጠሌዎንንም በጦርነቱ መካከል ጠላቶችን ሲአሳድዳቸው እንዳዩት ብዙዎች ምስክሮች ሆኑ።

ከዚህም በኋላ ንጉሥ ካሌብ ከድል አድራጊነት ጋር በተመለሰ ጊዜ መንግሥቱን ትቶ በዚህ አባት እጅ መነኰሰ ከዋሻ ውስጥም ገብቶ በጾምና በጸሎት እየተጋደለ ኖረ።

ይህም ቅዱስ አባ ጰንጠሌዎን ተጋድሎውን በፈጸመ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደርሱ መጣ ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን የሚያደርግ ገድሉንም ለሚጽፍ ቃል ኪዳን ሰጠው እንግዲህስ ድካም ይበቃሀል ዕረፍ ያን ጊዜም ዐጥንቶቹ ተነቃነቁ በፍቅር አንድነትም አረፈና በዚያ በዋሻው ውስጥ ተቀበረ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዕንባቆም_ነቢይ

በዚችም ቀን የስሙ ትርጓሜ አዋቂ የሆነ የዕንባቆም ነቢይ መታሰቢያው ነው። ይህም ቅዱስ በአንዲት ዕለት እህሉን ለሚያጭዱለት ምሳቸውን አዘጋጅቶ ተሸክሞ ሲሔድ መልአክ ተገልጾለት ይህን መብል በባቢሎን አገር በአንበሶች ጕድጓድ ውስጥ ላለ ለነቢዩ ዳንኤል ውሰድ አለው።

ዕንባቆምም ጌታዬ ሆይ ባቢሎንን አላየኋት ጉድጓዱንም አላውቀው አለው። የእግዚአብሔር መልአክም በራሱ ጠጉር ያዘው ምግቡን በእጁ እንደያዘ ወሰደውና ጉድጓዱ እንደተዘጋ አስገባው ምግቡንም ሰጥቶ መገበው ወዲያውኑ ዕንባቆምን ወደ ይሁዳ አገር መለሰው።

በአረጀና በሸመገለም ጊዜ የእስራኤል ልጆች ከተማረኩበት ተመልሰው ቤተ መቅደስን ሠሩ። ዕንባቆምም ኢየሩሳሌም ደርሶ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ በታላቅ ደስታም ተቀበሉት ትንቢቱንም ሊሰሙ ወደርሱ ተሰበሰቡ አፉንም ከፍቶ በመንፈስ ቅዱስ እንዲህ አለ።

አቤቱ ድምፅህን ሰማሁ ሰምቼም ፈራሁ ሥራህንም አይቼ አደነቅሁ አለ። ስለ መድኃኒታችንም መውረድና በይሁዳ ክፍል በሆነች በቤተ ልሔም ስለመወለዱ ሲናገር የተመሰገነ እግዚአብሔር ግን ከፋራን ተራራ ከቴማን ከይሁዳ አውራጃ ይመጣል ብሎ እስከ መጨረሻው ተናገረ ከነቢያት መጻሕፍትም ጋራ ደመርዋት።

ከዚህ በኋላ ከእስራኤል ልጆች አንዲት ሴት ወደርሱ መጣች እያለቀሰችም እንዲህ አለችው። ሁለት ልጆች ነበሩኝ ጣዖት እንዲአመልኩ ፈለጉአቸው እምቢ በአሉ ጊዜም ገድለው በጐዳና ላይ ጣሉአቸው። ተገድለው ወደ አሉበትም አብሮዋት ሔደ ነፍሳቸውንም ይመልስላቸው ዘንድ እግዚአብሔርን ለመነው ልመናውንም ተቀበሎ በሕይወት አነሣቸው።

ዕረፍቱም በቀረበ ጊዜ ዘመዶቹን ጠራቸው። እንደሚሞትም ነገራቸውና አንዲት ሰዓት ያህል ወደላይ እየተመለከተ ተቀመጠ ። እነሆ እንደ ሰው ክንድ ያለች ታላቅ ክንድ የቤቱን ጣሪያ ሠንጥቃ ወረደች ወደ አፉም ተዘርግታ ነፍሱን ወሰደች ያን ጊዜም አረፈ።

በክርስቲያናዊ ንጉሥ በአንስጣስዮስ ዘመን እንዲህ ሆነ ገድሉን በአነበበ ጊዜ አድንቆ በግብጽ ደቡብ ቀርጣስ በሚባል ቦታ በስሙ ቤተ ክርስቲያን ተሠራለት።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ኤጲስቆጶስ_ቅዱስ_ዲዮናስዮስ

በዚችም ቀን የሀገረ አቴና ኤጲስቆጶስ ቅዱስ ዲዮናስዮስ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ በአቴና አገር በእውቀቱና በመራቀቁ የከበረና ከፍ ከፍ ያለ ነው። በአቴናው ከተማ በዐዋቂዎች የመሳፍንት አንድነት ከአማካሪዎች አንዱ እርሱ ነው።

ቅዱስ ሐዋርያ ጳውሎስም ወደዚያ በደረሰ ጊዜ ሃይማኖትን አስተምሮ የክርስትና ጥምቀትን አጥምቆ በአቴና አገር ኤጲስቆጶስ አድርጎ ሾመው።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/OZcl6DHnRBs?feature=shared

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እንኳን አደረሳቹ አደረሰን የዝቋላው ኮከብ፣ የገዳም ዕንቁ፣ የመናንያን መብራት፣ በምእመናን ልቦና ተጋድሎ ያበራ፣ መፍቀሬ ፆም፣ ፀሎት፣ ስም በፈጣሪ አንደበት የከበረ .አባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ

አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሀገራቸው ንሂሳ (ግብጽ ) ነው :: አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌያስ ይባላሉ :: ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል ::

አንድ ቀን አቅለያስ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከስዕለ ስላሴ ስር ወድቃ ስትማጸን "" ንስኢ ወልደ ዘይትሌአል ቅርኑ አምኑኅ ሰማይ ... ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበልጥ ልጅ እንኪ ተቀበዪ "" የሚል ድምጽ ሰማች :: በዚህም መሰረት አባታችን መጋቢት 29 ቀን ተጸንሰው ታህሳስ 29 ቀን ተወለዱ ::

አይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ብለው ተነስተው "" ስብሐት ለአብ , ስብሐት ለወልድ , ስብሐት ለመንፈስቅዱስ ዘአውጻእከኒ እምጽልመት ውስተ ብርሐን >> ብለው በማመስገናቸውና ሀላም ምድራዊ መብል እና መጠጥ ሳይመገቡ : ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መልአክትን ይመስላሉ

ሶስት አመት ሲሆናቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእመቤታችንና በገነት ካሉ ቅዱሳን ዘንድ አስባርኮ ገዳማውያን ካሉበት ምኔት ወስዶ ከበሩ አኖራቸው :: አበመኔቱም አባ ዘመድብርሐን ምልክት ተነግሮት ቢሄድ ፍሱሐ ገጽ ሆነ አግኝተዋቸዋል :: አበመኔቱም አሳድጎ አስተምሮ ከመአረገ ምንኩስና አድርሰዋቸዋል ::

ከዚህ ቡሐላ ሐብተ ፈውስ ተሰጥቷቸውል :: በአንድ ቀን እልፍ እውራንን እና እልፍ አንካሳ ፈውሰዋል :: በዋላ ግን ኤጲስ ቆጶሳትና ካህናቱ ዝናቸውን ሰምተው እየመጡ ግብር የሚያስፈቱአቸው ቢሆን ቅዱስ ገብርኤል ነጥቆ ከጌታ ፊት አቀረባቸው ::

በገድለህ : በትሩፋትህ : ከሞት ነፍስ ክርደት ገሀነም የሚድኑ ብዙ አሉና ከሰው ተለይተህ ወደ ጫካ ግባ :: ኑሮህም ከስልሳ አናብስትና ከስልሳ አናብርት ጋር ይሁን አለው :: ጌታዬ ምን ተመግበው ይኖራሉ አሉት ? "ዘኬድከ ጸበለ - እግረከ ይልህሱ ወበ ውእቱ ይጽግቡ ... የረገጥከውን ትቢያ ልሰው ያ ምግብ ሆኗቸው ይኖራሉ :: ብሏቸው ውሳጤ ገዳም ገብተው : ከአናብስትና ከአናብርት ጋር ይኖሩ ጀመሩ :: ዳንኤል ከአናብስት ጉድጉዋድ በተጣለ ጊዜ አናብስቱ እንደ ድመት ከእግሩ በታች ሆነው እንደተገኙ : አባታችን የረገጡትን ትቢያ እየላሱ እየታዘዙዋቸው ይኖሩ ነበር :

በዚህ መልኩ 30 አመት ከቆዩ ቡሐላ ጌታ በአንድነት በሶስትነት ተገልጾ ምን ላደርግልህ ትሻለህ ? አላቸው :: መጀመሪያ ላሉበት መጸለይ ይገባልና የምድር ገቦታን ሰዎች ማርልኝ አሉት :: 3000 ሐጥአንን ከሲኦል አውጥቶ ገነት አግብቶላቸዋል :: ከዚህ ቡሐላ ሁር ምድረ ኢትዮጵያ ወበህኒ አልውከ ነፍሳት ወታወጽኦሙ .... ወደ ኢትዮጵያ ሂድ አላቸው :: ቅዱስ ገብርኤል በሰረገላ ነፍስ ጭኖ ምድረ ከብድ አድርሷቸዋል :: ዳግመኛም ወደ ዝቁዋላ (ደብረቅዱስ ) ወስዷቸው ከዚያ ሆነው በንጹሀ ልቦና የኢትዮጵያን ሕዝብ ሐጢያት ከባህሩ ውስጥ ራሳቸውን ዘቅዝቀው ለ 100 አመት ይጽልዩ ነበር :: 40 ቀን ሲሆናቸው መልአኩ መጥቶ ዘገብረ ተዝካርከ ወዘጽውአ ስምከ እምህር ለከ ብሎሀል አላቸው :: እሳቸው ግን መላ ኢትዮጵያን ካልማረልኝ ከባህሩ አልወጣም ብለው 100 አመት በባህሩ ውስጥ በጭንቅላታቸው ተዘቅዝቀው ሲጸልዩ ኖረዋል :: ከ 100 አመት ቡሐላ ጌታ ተንስእ ወጽእ መሀርኩ ለከ ኩሎ ኢትዮጵያ ... ምሬልሀለው ውጣ ብሏቸው ወጥተዋል ::

ከዚህ ቡሐላ ምድረ ከብድ ወርደው ከምድር በላይ ከሰማይ በታች ሆነው 7አመት እንደ ትኩል አምድ ሆነው አይናቸውን ሳይከድኑ 7 አመት ሙሉ አይናቸውን ሳይከድኑ ቆመው ጸልየዋል :: ሰይጣን ግን ለምቀኝነት አያርፍምና ቁራ መስሎ መጥቶ አይናቸውን አንቁሮ አሳወራቸው :: 2 ሱባኤ ሲፈጽሙ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል መጥተው እፍፍ ብለው አድነዋቸዋል :: ከዚያ ተነስተው ወደ ዝቁዋላ ሲሄዱ ስላሴን በአምሳሌ አረጋውያን ከጥላው ስር አርፈው አገኙዋቸው :: በእግዚአብሔር ዙፋን ተማጽነንሀል አዝለክ አንድ አንድ ምህራፍ ሸኘን አሉዋቸው :: አዝለው ከሸኙዋቸው ቡሐላ በአንድነት በሶስትነት ሆኖ ታያቸው :: ድንግጠው ወደቁ : እግዚአብሔር ግን አንስቷቸው ሂድ ዝቁዋላ ሄደህ ጠላቶችህን ተበቀላቸው አላቸው :: በዛበነ መብረቅ ደርሰው 7 ቱን ሊቃነ መላእክት አጋዥ አድርገው እልፍ አእላፍ አጋንንትን አጭደዋል ::

ጻድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍታቸው መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ ስለዚህም ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር የመጋቢት 27 ስቅለት ደግሞ ጥቅምት 27 ቀን እንዲከበር ተደረገ፤ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ይህ ስርዓት ሆነ፤
••••••**••••••
የጻድቁ አባታችን ምልጃ ጸሎት አይለየን
መ/ር ሚኪያስ ዳንኤል 04/02/2016 ዓ/ም
~•••••••~•••••••~•••••~
“የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው፤ የኀጥኣን ስም ግን ይጠፋል።”
ምሳሌ 10፥7
~•••••••~•••••••~•••••~
“ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤”
፩ኛ ዮሐንስ ፩፥፩!

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ምስባክ ዘካልዓይ ጽጌ
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️

ኤፌ ፮÷፩-፲
ራእ ዮሐ ፲፪÷፩-፲፫
ግብ ሐዋ ፮÷፳፫-፴
ወንጌል፦ሉቃ ፲፪÷፲፮-፴፪
ቅዳሴ፦ዘእግዝእትነ

ምስባክ፦

ተዘከር እግዚኦ ከመ መሬት ንሕነ፤
ሰብእሰ ከመ ሣዕር መዋዕሊሁ፤
ወከመ ጽጌ ገዳም ከማሁ ይፈሪ።
መዝ ፻፪÷፲፬

ትርጉም፦

አቤቱ እኛ አፈር እንደሆን አስብ፤
ሰውስ ዘመኑ እንደሣር ነው፤
እንደዱር አበባ እንዲሁ ያብባል።

🇪🇹👇👇👇👇👇🇪🇹
👉@menkir_tube 👈
👉 @menkir_tube👈
👉 @menkir_tube👈
🇪🇹☝️☝️☝️☝️☝️🇪🇹

   @menkir_tube
#Join & share

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እናቱ የተመሠከረላት ክርስቲያን ብትሆንም እንዳለመታደል አባቱ ተንባላታዊ (አሕዛብ) ነበር። ስሙንም መዛሕዝም ይሉታል። ሕጻኑ እንደተወለደ ያወጡለት ስም አሕዛባዊ ከመሆኑ ባለፈ በሰዓቱ መጠመቅ አልቻለም። የወቅቱ ሕግ ከወላጆቹ አንዱ አሕዛባዊ ከሆነና አጠምቃለሁ ቢባል የሚከተለው ሰይፍ ነበር። በዚሕ ምክንያት ሳይጠመቅ 7 ዓመት ሞላው።

እናቱ ግን ሕጻን ቢሆንም ፍቅረ ክርስትናን ታስተምረው ነበር። ባይጠመቅም ጸበሉን እመነቱን ትቀባው ነበር። ደብቃ ቅዳሴ ታሰማውም ነበር። አንድ ቀን ግን ሕጻናት ሲቆርቡ አይቶ ካልቆረብኩ ብሎ አለቀሰ። ምን ታድርገው? ወደ ውጪ አውጥታ ከአውሎግያ (የሰንበት በረከት) አበላችው። "ጌታዬ ልጄን እርዳው" አለች።

ልክ በአፉ ሲቀምሳት መዓዛ መንፈስ ቅዱስ አደረበትና ፍጹም ተደሰተ። ትንሽ ከፍ ሲል ለምን እንደማይጠመቅና እንደማይቆርብ እናቱን ጠየቃት። "ልጄ ሆይ! ይገድሉሃል" አለችው። ከዚህች ቀን ጀምሮ የሚጠመቅበትን ዘዴ ይፈልግ ጀመር።

አስቀድሞ ትምሕርተ ክርስትናን ተማረ። ለአካለ መጠን ሲደርስ አፈላልጐ ጠንካራ ክርስቲያን የሆነች ሴት አገባ። ጥቂት ጊዜ ከቆየ በኋላ ሚስቱን ስለ መጠመቅ አማከራት። "ሌላ ሃገር ሒደህ ተጠመቅ" አለችው። ከግብፅ ተነስቶ ሶርያ ገባ። አባቶችን አፈላልጎ ተጠመቀ። ቀጥሎም መንገዱን ወደ ልዳ አደረገ።

ወደ ደብሩ ተጠግቶ አባቶችን "ስም አውጡልኝ" ቢላቸው መንፈስ ቅዱስ አናግሯቸው "ጊዮርጊስ" አሉት። እሱም ደስ እያለው ባጭር ታጥቆ የልዳውን ቅዱስ ጊዮርጊስ ያገለግለው ገባ። ትንሽ ቆይቶ ሁከት መንፈሳዊ ተሰማው። ማለትም ስለ ሃይማኖቱ ደሙን ማፍሰስ ፈለገና ወደ ግብፅ ተመለሰ።

በዚያ ያሉ አሕዛብ በክርስትና ስም ልብስና ሞገስ ሲመለከቱት ተበሳጩ። ዕለቱኑ አሠሩት። ሌሊት እናቱና ሚስቱ መጥተው አሉት "አደራ! ፍቅረ ዓለም እንዳያታልልህ። ሰማዕት ብትሆን ላንተም ክብር ለእኛም ሞገስ ነው" ብለውም አጽናኑት። እንዲህ ያሉ እናትና ሚስት ማግኘትም ታላቅ እድል ነው::

ሐዲስ ጊዮርጊስም ጸና። ከዚያች ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ደበደቡት አካሉን ቆራረጡት ደሙንም መሬት ላይ አንጠፈጠፉት። በየመንገዱ እየጎተቱ ተሳለቁበት። እርሱ ግን ክርስቶስን ወዷልና ሁሉን ታገሰ። ሌሊት በሆነ ጊዜም ጌታችን ተገልጦ "ከሰማዕታት ተቆጠርህ" አለው።

በማግስቱ በአደባባይ አንገቱን በሰይፍ ቆረጡት። ክፋታቸው የጸና ነውና ሥጋውን በእሳት አቃጠሉት። ወደ ባሕርም ጣሉት። እናቱ ከባሕር ስታወጣው ግን ምንም አላገኘውም ነበር። በዚሕች ቀን እናቱና ሚስቱ በክብር ቀብረውታል።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት እና #መጽሐፈ_አርጋኖን_መግቢያ)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† ". . . ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኩአችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ::" †††
(ይሁዳ. ፩፥፫)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ ጥቅምት 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞

+"+ ቅድስት አንስጣስያ ሰማዕት +"+

=>በቀደመው ዘመን: በተለይም በሮም አካባቢ ይኸ ስም በጣም የተለመደ ነበር:: በዚህ ስም የሚጠሩ ቅዱሳትም ቁጥራቸው ቀላል የሚባል አልነበረም:: የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደሚነግረን ሃገረ ሮሜ እስከ 5ኛው መቶ ክ/ዘመን ድረስ የኹሉ መኖሪያ ነበረች::

+ደጉም ሆነ ክፉው: ኃጥኡና ጻድቁ: አረማዊና ምዕመኑ: ጨካኙና ርሕሩሁ: ወዘተ. . . በአንድ ላይ ይኖሩባት ነበር:: በዚህ ዘመንም ቦታዋ ብዙ ሐዋርያትን: ሰማዕታትን: ሊቃውንትንና ጻድቃንን አፍርታለች:: (ዛሬን አያድርገውና)

+ከእነዚህ ቅዱሳን እንዷ ደግሞ ሰማዕትነትን ከጽድቅና ድንግልና ጋር የደረበችው እናታችን አንስጣስያ ናት:: ቅድስቲቱ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ተወልዳ ያደገችው እዛው ሮም ውስጥ ነው:: ወላጆቿ ክርስቲያኖች በመሆናቸው ገና በልጅነቷ የክርስትናን ምንነት ጠንቅቃ አውቃለች::

+ወጣት በሆነች ጊዜም ይህቺ ዓለም ጠልፋ እንዳትጥላት ትጠነቀቅ ነበር:: ይህቺ ዓለም ወጥመዶቿ ብዙ ናቸውና:: በተለይ ደግሞ መልክ ስለ ነበራትና ወላጆቿም ባለጠጐች ስለ ነበሩ እርሷ ትኅርምትን ታበዛ ነበር::

+ድንግልናዋን በንጽሕና ትጠብቀው ዘንድ ጾምንና ጸሎትን ከስግደት ጋር አዘወተረች:: በሒደትም በውስጧ ፍቅረ ክርስቶስ እየተቀጣጠለ በመሔዱ ይህንን ዓለም ልትተወው አሰበች:: ነገር ግን ወላጆቿ "ልጃችን ለአካለ መጠን ደርሰሻልና እንዳርሽ" አሏት::

+እርሷም "እኔ ለሰማያዊው ሙሽርነት: ለመንፈሳዊውም ሠርግ ተጠርቻለሁና ተውኝ" ብላቸው ወደ ገዳም ሔደች:: በዘመኑ በሮም ከተማ ዙሪያ ብዙ የደናግል ገዳማት ነበሩና ከእነዚያው ከአንዱ ገባች::እንደ ገባች ለሰውነቷ ምክንያትን ልትሠጠው አልፈለገችም::

+ራሷን በጾም ትቀጣው ዘንድ በ48 ሰዓት (በ2 ቀን) አንዴ ብቻ ትበላ ነበር:: ምግቧም ቁራሽ ቂጣ በጨው ብቻ ነበር:: ዓቢይ ጾም በደረሰ ጊዜ ግን ከእሑድ በቀር እህልን አትቀምስም ነበር:: የጌታዋ ፍቅር አገብሯታልና ለሳምንት ራሷን ከምግብና ከምቾት ትከለክል ነበር::

+ይህም ሲሆን ቁጭ ብላ አይደለም:: በጸሎትና በስግደት እየተጋች: ለደናግሉ በሙሉ እየታዘዘች ነው እንጂ:: ለጥቂት ዓመታት በእንዲህ ያለ ገድል ቆይታ ከእመ ምኔቷ ጋር በዓል ለማክበር አንድ ቀን ከገዳማቸው ወጡ:: በመንገድ ላይ ሳሉ አረማዊ ንጉሥ ክርስቲያኖችን ሰብስቦ ሲያሰቃይ ደረሱ::

+በእርግጥ ዐይተው እያዘኑ ማለፍ ቢችሉም ቅድስት አንስጣስያ ግን አልቻለችም:: የወገኖቿ ስቃይ ቢያንገበግባት በድፍረት ወደ መኮንኑ ቀርባ ዘለፈችው:: "አንተ አዕምሮ የጐደለህ! እንዴት በአምላካቸው ደም የተገዙ ክርስቲያኖችን እንዲህ ያለ በደላቸው ታሰቃያቸዋለህ?" አለችው::

+በድፍረቷ የተገረመው መኮንኑም ወደ እርሱ አስቀርቦ "ማንን ታምኚያለሽ?" አላት:: እርሷም ሰማዩንና ምድሩን: ባሕሩንና የብስን የፈጠረውን: ስለ ሰው ፍቅርም የሞተውንና የተነሳውን: ዘለዓለማዊ ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስን አመልካለሁ" አለች:: +እጅግ ስለ ተበሳጨም ስቃይን አዘዘባት:: በገድል የተቀጠቀጠ ለምለም አካሏን በብዙ መክፈልተ ኩነኔ ወታደሮቹ አሰቃዩዋት:: በመጨረሻም ሞት ተፈርዶባት በዚህች ቀን ገደሏት::

+ቅድስት እናታችን አንስጣስያ የጽድቅን: የድንግልናን: የምስክርነትን አክሊል በእግዚአብሔር መንግስት አገኘች:: ይህን ሁሉ ስትጋደል ግን እድሜዋ ገና ወጣት ነበር::

+"+ ቅድስት ማርያም እንተ ዕፍረት +"+

=>በዘመነ ሐዋርያት በተመሳሳይ 'እንተ ዕፍረት-ባለ ሽቱ' ተብለው የሚጠሩ 2 እናቶች ነበሩ:: 2ቱም ስማቸው ማርያም ስለ ነበር ለመለየት እንዲያመች አንደኛዋን 'ማርያም ኃጥዕት-ከኃጢአት የተመለሰች': 2ኛዋን ደግሞ 'ማርያም እኅተ አልዓዛር-በቢታንያ የነበረችው ብለው አበው ይጠሯቸዋል::

+በሉቃስ ወንጌል ላይ የምትገኘው ከኃጢአት ሕይወት የተመለሰችው ስትሆን በዮሐንስ ወንጌል 12:1 ላይ ያለችው የአልዓዛር እህት (ድንግሊቱ) ናት:: ዛሬም የምናስባት ይህቺውን እናታችን ነው::

+ቅድስት ማርያም መድኃኒታችን ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ በሚያስተመርበት ዘመን በቢታንያ አካባቢ ትኖር የነበረች ድንግል ወጣት ናት:: ወላጆች ባልነበረበት ቤት ውስጥ ታላቆቿ አልዓዛርና ማርታ አሳድገዋታል::

+በቤተሰብ ደረጃ እንግዳን ይቀበሉ ነበርና ጌታችን ወደዳቸው:: አልዓዛርን ከ72ቱ አርድእት: ማርያምና ማርታን ደግሞ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ቆጥሯቸዋል:: ወንድማቸው አልዓዛር በታመመ ጊዜ ወደ ጌታ ተልከው ነበር::

+ያለ ጊዜው የማይሠራ ጌታ ባይመጣ አልዓዛር ሞተ:: በ4ኛው ቀን አምላክ ሲመጣ ቅድስት ማርያም በጌታ ፊት ሰግዳ "እግዚእየ ሶበሰ ኀሎከ ዝየ እምኢሞተ እኁየ-አንተ በዚህ በኖርክስ ወንድሜ ባልሞተ ነበር" ብላ አለቀሰች:: (ዮሐ. 11)

+ጌታም ስታለቅስ ባያት ጊዜ አምላክነቱ አራርቶት አለቀሰ:: ወዲያውም በስልጣነ ቃሉ አዞ አልዓዛርን አስነሳው:: ከፋሲካ (ጌታ ከመሰቀሉ 6 ቀናት) በፊትም ቅዱሳኑ ለጌታ ግብር አገቡ:: እርሱም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ታደመላቸው:: (ዮሐ. 12:1)

+በዚያም አልዓዛር ከጌታ ጐን ሲቀመጥ: ቅድስት ማርያም ከጌታ ሥር ተንበርክካ: ናርዶስ የሚሉትን የ300 ዲናር ሽቱ በጌታ ላይ አፈሰሰች:: መዓዛ መለኮቱና ሽቱው ሲገናኝ "መልዐ መዓዛሁ" እንዲል ምስጥ የሚያደርግ ሽታ ቤቱን ሞላው::

+በወቅቱ ይሁዳ ቢቃወምም ጌታ ምላሹን ሰጥቶታል:: ቅድስት ማርያምንም "ማርያምሰ ኃርየት መክፈልተ ሠናየ ዘኢየኃይድዋ" ብሎ አመስግኗታል:: ያስመሰገናት ቁጭ ብላ በተመስጦ መማሯ ብቻ እንዳልሆነ አባ ሕርያቆስ መስከሯል::

+ሲመክረንም "አርምሞንና ትዕግስትን እንደ ማርያም ገንዘብ እናድርግ" ብሎናል:: (ቅዳሴ ማርያም) ቅድስት ማርያም በጌታችን ክርስቶስ በኅማሙ ጊዜ: ሲቀብሩት ነበረች:: ትንሳኤውንም ዐይታለች::

+ከጌታ እርገት በኋላም መንፈስ ቅዱስን ተከትላ ለወንጌል አገልግሎት ተግታለች:: ቅድስት እናታችን ማርያም እንተ ዕፍረት ዛሬ እንዳረፈች እናዘክራለን:: የእናቶቻችን ቅዱሳት አምላክ ፍቅራቸውን ያድለን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::

=>ጥቅምት 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት አንስጣስያ (ድንግል: ጻድቅት: ሰማዕት)
2.ቅድስት ማርያም እንተ ዕፍረት
3.ቅድስት ሶስና ድንግል
4.ቅድስት ኅርጣን ድንግል

ወርኀዊ በዓላት

1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
4.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
5.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር

=>+"+ ሲሔዱም ወደ አንዲት መንደር ገባ:: ማርታ የተባለች አንዲት ሴትም በቤቷ ተቀበለችው:: ለእርሷም ማርያም የምትባል እኅት ነበረቻት:: እርሷም ደግሞ ቃሉን ልትሰማ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጣ ነበረች . . . ኢየሱስም መልሶ . . . 'ማርያምም መልካም እድልን መርጣለች:: ከእርሷም አይወሰድባትም' አላት:: +"+ (ሉቃ. 10:38)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

በዛሬው ዕለት(ጥቅምት 1) ታላቋ ሰማዕት የቅድስት አናስታሲያ(አንስጣስያ) ዘ ሮሜ በሰማዕትነት አረፈች።

በ Michael Misrue

በዘመነ ሰማዕታት ጊዜ ከከበሩ እና ከተቀደሱ የሰማዕትነታቸው የሕይወት ታሪክ ለምንሰማው ለእኛ ክርስትያኖች ከሚያስደንቁ በተለይም ከቅዱሳን ሰማዕታት ሴቶች መካከል አንደኛዋ ታላቋ ሰማዕት ቅድስት አናስታሲያ(አንስጣስያ) ዘ ሮሜ ናት። አናስታሲያ(አንስጣስያ) በመባል የሚታወቁ ብዙ ቅዱሳን ሴቶች አሉ። በተለይ ሶስቱ " ሰማዕት ና ድንግል ቅድስት አናስታሲያ(አንስጣስያ) ዘሮሜ(ጥቅምት 1) ፣ ቅድስት አናስታሲያ(አንስጣስያ) ዘሮሜ ወይም ከመርዝ ታዳጊዋ በመባል የምትታወቀው(ታኅሣሥ 26) ፣ ቅድስት አናስታስያ(አንስጣስያ) ዘቍስጥንጥንያ ወይም ተለይታ በምትታወቅበት ስሟ "ክብርት" (ጥር 26) ናቸው ። ቍስጥንጥንያ " ሁለተኛዋ ሮም" ተብላ ትታወቃለች።

ነገር ግን ከዚህ በፊት ቃል እንደገባነው በዛሬው ዕለት እንደጌታ ፍቃድ ልንጽፍላችሁ የወደድነው የታላቋ ሰማዕት የቅድስት ድንግል አናስታሲያ(አንስጣስያ) ዘሮሜ የተቀደሰ የሰማዕትነት የሕይወት ታሪክ ነው። በግሪክ ቋንቋ ሥሟም "Η Αγία Αναστασία η Ρωαία ኢ አጊያ አናስታሲያ ኢ ሮሜያ" ይባላል "ዘ ሮሜ " የሚለው ስሟ ከሌሎቹ በአናስታሲያ(አንስጣስያ) ስም ከሚጠሩ ቅዱሳን ሴቶች ተለይታ የምትታወቅበት ነው።

" Ανάσταση አናስታሲ" የሚለው ትርጓሜው "ትንሣኤ" ማለት ነው "። Αναστασία አናስታሲያ" ሲሆን ለሴት ። ለወንድ ሲሆን ደግሞ " Αναστάσιος አናስታሲዮስ ነው።" የታላቋ ሰማዕት የቅድስት አናስታሲያ(አንስጣስያ) የስሟ ትርጓሜ "ትንሣኤ ወይም ተነሳች" እንደማለት ነው። የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 11 ከቁጥር 25 – 26 "ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳን ሕያው ይሆናል ሕያው የሆነ የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘለዓለም አይሞትም፤…።" ተብሎ በጌታችን እንደተነገረው ታላቋ ሰማዕት ቅድስት አናስታሲያ(አንጣስያ) ዘሮሜ በሰማዕትነት ካረፈችበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በአማላጅነቷ ለሚተማመኑ እርዳታዋን ለሚለምኑ ሁሉ ፈጥና የምትደርስ ናት ይህም በጌታችን ኢየሱስ ሕያው መሆኗን ታላቅ ምስክር ነው።

+የታላቋ ሰማዕት የቅድስት አናስታሲያ(አንስጣስያ) ልደትና ዕድገት።

ታላቋ ሰማዕት ቅድስት አናስታሲያ(አንስጣስያ) ዘሮሜ የተወለደችው በሮም ነው ወላጆቿም ክርስትያኖች ናቸው በግብጽ እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተክርስትያናት የስንክሳር እንደ ተጻፈው " ጠቃሚ የሆነ ትምሕርትን በማስተማር ክብር ባለው በመልካም ሥርዓት አሳደጓት።" ተብሎ ተጽፏል። እንዲሁም " በአደገችም ጊዜ ወላጆቿ ሊያጋቧት ፈለጉ እርሷ ግን ይህን ሥራ አልፈለገችም የምንኵስናን* ልብስ መልበስ ፈለገች እንጂ ከታናሽነቷም መንፈሳዊ ገድልን መረጠች።" የሚል ተጽፋል። ነገር ግን የታላቋ ሰማዕት የቅድስት አናስታሲያ(አንስጣስያ) የልደቷ ታሪክ የምሥራቅ ኦርቶዶክስ አብያተክርስትያናት " ገዳማዊት* ሰማዕት ቅድስት አናስታሲያ ዘሮሜ በተወለደች በ ሦስት ዓመት ዕድሜዋ ወላጆቿን በሞት አጣች በዚህን ጊዜ በአቅራቢያዋ ወደ አለ በቅድስና እጅግ ከፍተኛ ደረጃ በደረሰች በቅድስት እመምኔት ሶፍያ በሚመራ የሴቶች ገዳም እድታድግ ተሰጠች። " ብለው ጽፈውታል።

+ የታላቋ ሰማዕት የቅድስት አናስታሲያ(አንስጣስያ) የምናኔ ሕይወት።+

በግብጽ እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተክርስትያናት የስንክሳር መጽሐፍ የታላቋ ሰማዕት የቅድስት አናስታሲያ(አንስጣስያ) ዘሮሜን ከጋብቻ ሸሽታ ወደ ገዳም መሔዷን እንዲሁም የምናኔን ሕይወቷን እንዲህ ተጽፏል " ስለዚህም በሥውር ሒዳ በሮሜ ካሉ ገዳማት ወደ አንዱ ገባች ታናሽ ስትሆንም የምንኵስናን ልብስ በመልበስ በጾም በጸሎት በረኃብ በጽምዕ በመጠመድ የዚህን ዓለም ሐሳብ ከልቡናዋ ቆርጣ በመተው በመጋደል ሥጋዋን አደከመች። በቀኑ ርዝመትም ሁሉ የምትጾም ሆነች በየሁለት ቀኖችም ታከፍላለች በጌታችን ጾም ግን ያለሰንበታት ቀን የምትመገበው የለም። በሰንበታትም የምትመገበው ከቀትር ጸሎት በኋላ ነው። በነዚያም በምንኵስናዋ ወራት በእሳት ያበሰሉትን ወጥ አልቀመሰችም። በመላ በምንኵስና ዘመኗ ደረቅ ዳቦ እና ጨው ምግቧ ነው" ብለው ሲጽፉ።

የምሥራቅ ኦርቶዶክስ አብያተክርስትያናት ደግሞ " ቅድስት እመምኔት ሶፍያ ሰማዕቷን ቅድስት አናስታሲያን ዘሮሜን እግዚአብሔር በመፍራት በመታዘዝ ሕይወት ጽኑ አማኝ እንዲሁም መልካም ምግባር ያላት አድርጋ አሳደገቻት። ሰማዕቷ ቅድስት አናስታሲያ ዘሮሜ መልኳ እጅግ ያማረ ነው። ከ 17 ዓመት በኋላም በገዳሙ ብቻ ሳይሆን በአካባቢው የታወቀች መናኒት ሆነች።" ብለው ጽፈዋል።

+ታላቋ ሰማዕት ቅድስት አናስታሲያ(አንስጣስያ) ዘሮሜ በመኰንኑ ፕሮቡስ ፊት እንደቀረበች።+

የምሥራቅ ኦርቶዶክስ አብያተክርስትያናት የሰማዕቷን የቅድስት አናስታሲያ(አንስጣስያ) የሰማዕትነት ጉዞዋን እንዲህ ጽፈውታል። " ንጉሰ ነገሥት ዳኬዎስ ክርስትያኖችን ማሰቃየት ጀመረ ፕሮቡስ የተባለው መኰንንም የንጉሰ ነገሥቱን ትዕዛዝ ለማስፈጸምም ሰማዕቷ ቅድስት አናስታሲያን ይዘው እንዲያመጡለት አዘዘ። ቅድስት እመምኔት ሶፍያም መንፈሳዊ ልጇን ሰማዕቷን ቅድስት አናስታሲያ ዘሮሜን ስለ ክርስቶስ ሥም ሰማዕት ትሆን ዘንድ ባረከቻት(መረቀቻት) ከዚያም ወታደሮቹ ወደ መኰንኑ ፕሮቡስ ይዘው አቀረቧት ወጣትነቷን እና ውበቷን አይቶ በሽንገላ ቃል " ከደስታ ርቀሽ ወጣትነትሽን ለምን ታባክኛለሽ? ለዚያ ለተሰቀለው ብለሽ ይህን ሁሉ ሥቃይ መታገስሽ ለምን ነው? የኛን አማልክት አምልኪ ያማረ ባል አግቢ በክብር እና በሞገስ ኑሪ።" ብሎ ተናገራት። ሰማዕቷ ቅድስት አናታስያ በገዢው ፊት ስትቆም አእምሮዋ በተመስጦ በክርስቶስ ፊት ቆሞ ነበር፣ እናም በመንፈሳዊ አይኖቿ የሙሽራዋን ውበት አየች።" ቅድስት አናስታሲያ :- “ሙሽራዬ፣ ባለጠግነቴ፣ ሕይወቴ እና ደስታዬ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፣ እናም በማታለልህ ከእርሱ ልትለየኝ አትችልም።" ብላ መለሰችለት።" ብለው ሲጽፉ … የግብጽ እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተክርስትያናት የስንክሳር መጽሐፍ ደግሞ " በገዳሟ አቅራቢያ ሌላ የደናግል ገዳም አለ የዚያ ደብር በዓልም በደረሰ ጊዜ እመምኔቷ በዓሉን ለማክበር ይቺን ቅድስት አንስጣስያን ከእህቶቿ ደናግል ጋር አስከትላ በአንድነት ተጓዙ። ሲጓዙም የንጉሥ ዳኬዎስን ወታደሮች አየቻቸው ከእርሳቸውም ጋር የታሠሩ ክርስትያኖች አሉ ወታደሮቹም አሥረው በቁጣ ይጎትቷቸው ነበር። ልቧም በሃይማኖቷ ፍቅር ነደደና ያን ጊዜ እንዲህ ብላ ዘለፈቻቸው የእውነትን ፈጣሪን የካዳችሁ ልባችሁ የደነዘዘ እግዚአብሔር በመልኩና በአምሳሉ በፈጠራቸውና ስለእነርሱም ነፍሱን ለሞት አሳልፎ በሰጠላቸው ላይ ለምን እንዲህ ትሠራላችሁ። ይህንንም በአለቻቸው ጊዜ ወታደሮች ተቆጡ ይዘውም ወደ መኰንኑ አቀረቧት እርሱም እንዲህ ብሎ ጠየቃት በእውነት አንቺ የተሰቀለውን የምታመልኪው ክርስትያን ነሽን? እርሷም ስለእኛ የተሰቀለውን ክብር ይግባውና እርሱን አመልከዋለሁ ብላ መለሰችላት።" ብለው ጽፈዋል።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/M6Q7xvOQVWQ

ላይክ ሼር ሰብስክራይብ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አቢ ቤት ለቤት ጠቅላላ ኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ ጥገና
⚡️ ኦቭን
⚡️ ማይክሮዌቭ
⚡️ ምጣድ
⚡️ ስቶቮች
⚡️ የሻይ ቡና ማሽን
⚡️ መፍጫዎች
⚡️ የውሃ ማፍያዎች (ቦይለሮች)
⚡️ የውሀ ፓምፖች
⚡️ ጄነሬተር በአስተማማኝ ሁኔታ እንጠግናለን
ከቤትዎ ሳይወጡ ይደውሉ ያሉበት በመምጣት እንሰራለን
Door to door Electrical & Electronics Repair
⚡️ Oven
⚡️ Microwave
⚡️ Injera plates
⚡️ Stoves
⚡️ Coffee Machines
⚡️ Grinders
⚡️ Boilers (Both shower & Kitchen)
⚡️ Water pump
⚡️ Genereator....
⚡️ Electrical installation & Repair services
📞 0938152513
jo1888" rel="nofollow">http://www.tiktok.com/@jo1888
/channel/abi1888
https://instagram.com/adwa_1888_?igshid=NTc4MTIwNjQ2YQ==
/channel/electricianbolegerji

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ደህና አደራችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

መስከረም 30/2016 #መጥምቁ_ዮሐንስ
#ቅዱስ_ማርቆስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሳኑ ስም ለምናመሰግንበት ቅዱሳኑ በቃል ኪዳናቸዉ እንዲያስቡን ለምንማፀንበት ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን

👉ጸሎቱና በረከቱ ለዘለዓለሙ ከኹላችን ህዝበ ክርስቲያኑ ይሁን ነብይ ሐዋርያ ሰማዕት የሆነ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ያደረገው ተአምር ይኽ ነዉ

👉የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የበዓሉ መታሰቢያ በዕለተ እሁድ ውሎ በወርሀ ታህሳስ ኹለት ቀን በደብረ አንገች በተከበረ ጊዜ ከቅዳሴ በኋላ የመጥመቀ መለኮት ዮሐንስ መጽሐፍ ገድልን በአንዱ አረጋዊ መነኮሴ አንደበት ይሰሙ ዘንድ ካህናቱና ሕዝቡ ተሰበሰቡ

👉ያንጊዜም ወደዚህ ጉባኤ አንዲት ሴት ቀረበች ድምጿንም አሰምታ እልል እያለች ጮኽች ይህ የክርስቲያን ጉባኤ እስኪታወክ ሕዝብ ኹሉ እርስ በእርሳቸው ይቺ ሴት ምንድናት ደስታዋ ምንድነው እስኪሉ ድረስ እልልታዋን አልተወችም ያ መነኩሴ ግን ልብ እንደተሳናት እንደሰከረችም ቆጠራት ዝም ትል ዘንድ ገሠፃት

👉ይኽች ሴት ግን አባቴ ካህኑ ሆይ እኔ ልቤ ያዘነበት ሴት ነበርሁ ዛሬ ግን ለምለም ፍሬ የሌላት ደረቅ ዛፍ በሚሉኝ ጎረቤቶቼ መሳቂያ ለጠላቶቼ መዘባበቻ የነበርኩ ማኀፀኔ የተዘጋ እኔ ባሪያውን በቸርነቱ በጎበኘኝ በወዳጄ በቅዱስ ዮሐንስ አምላክ በእግዚአብሄር ልቤ ጸንቷል ከብዙ እድሜዬ በኋላ ልጅ ሰጥቶኛል እኔስ ዝም አልልም አለች

👉ያም መንፈሳዊ አባት መነኩሴ ወደሱ ትቀርብ ዘንድ የምትለውን ሕዝብ ይሰሙ ዘንድ ጠራት ይቺም ሴት ወደ ቤተክርስቲያኑ አደባባይ እልል እያለች ከወለደችው ልጇ ጋር ቀርባ አባቶቼና ወንድሞቼ እኅቶቼም ሆይ አንድ ልጅ እንኳን በማጣት ብዙ ዘመን ሳዝን ስተክዝ ኖርሁ ዘመዶቼ ሳይቀሩ ጎረቤቶቼ ኹሉ የደረቀች ዛፍ ይሉኝ ነበር

👉ስለዚህ አምና እንደ ዛሬው ወደ ወዳጄ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ መጥቼ ተሳልሁ ይኸንን መልኩ ያማረ ደም ግባቱ የተወደደ ልጅ ሰጠኝ ድንቅ ተዐምር ለሚያደርግ ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እልል እላላሁ በመጥምቁ በቅዱስ ዮሐንስ አማላጅነት ይህን ልጅ ለሰጠኝ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ ስትል መሰከረች

👉ይህን የሰሙ ሕዝቡም ኹሉ አደነቁ በማግስቱ ያ መነኩሴ ከካህናቱ ጋር ሆኖ ያን ሕፃን አጠመቀው እርሷም እልል እያለች እየዘመረች ወደ ቤቷ ተመለሰች

👉የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንሰ ጸሎቱ በረከቱ አማላጅነቱ እንዲሁም የከበረዉ ቃል ኪዳኑን ለምታምኑ ሁሉ በረከት ረድኤቱ ለሁላችሁም ይድረሳችሁ በዚህ እለት በመታሠቢያ በአሉ የምናስበዉ ሐዋርያዉ ማርቆስ ምልጃ ፀሎቱ ረድኤት በረከቱ ለሁላችንም ይድረሰን "አሜን" 💒 💚 💛 ❤️ 💒

👉ገድለ ዮሐንስ መጥምቅ
👉ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#መስከረም 29 -የሰማዕት ቅድስት አርሴማ እረፍት የቅድስት #አርሴማ እናት አትናስያ ትባላለች ልጅ በማጣት ለረጅም ዘመን ታዝን ታለቅስ ነበር በኃላም እግዚያብሔር ልመናዋን ሰማት ይህችን ክብርት ቅድስት ልጅንም ሰጣት፤ቅድስት አርሴማ ጥር 6 ነው የተወለደችው፤15 ዓመት ሲሆናት ሊያጋቡአት አሰቡ እርሷ ግን ይህን አልወደደችም፤ በደናግል ገዳም ገብታ በተጋድሎ መኖር ጀመረች። ከዚህ በኃላ እንዲህ ሆነ ከሃዲው ንጉስ ዲዮቅልጥያኖስ ሊያገባት ወደደ ቅድስት አርሴማ ግን ከደናግሉ ጋር ሸሽታ ወደ አርማንያ ሄደች በዚያም በበርሃ ለጥቂት ቀናት ተቀመጠች በኃላ ላይ ድርጣድስ የሚባል አገር ገዢ በበርሃ እንደሚኖሩ ሰማ ወታደሮችንም ልኮ አስመጣቸው፤ የቅድስት አርሴማን መልክ በተመለከተ ጊዜ ፈዞ ደንዝዞ ቀረ የፊቷ ውበት እጹብ ድንቅ፤ ግርማዋ የሚያስደነግጥ ልብ የሚያርድ ነበርና፤ስለዚህም ሊያሰቃያት አልደፈረም በእንክብካቤ በሰገነት ላይ አኖራት፤ ሌሎቹን ግን ለጣአት እንዲሰግዱ ገረፋቸው፤ ቅድስት አርሴማ እኔንም አሰቃዩኝ እያለች አምርራ ታለቀስ ነበር። ድርጣድስ ብዙ ጊዜ ሊሸነግላት ሞከረ እርሷ ግን ትዘልፈው ጣኦታቱንም ትረግም ነበር፤ እርሷ ጸንታ ደናግሉን ታጸና ነበር ትመክራቸው ታረጋጋቸው ነበር፤ ድርጣድስ ሽንገላው እንደማያዋጠው በአወቀ ጊዜ ማሰቃየት ጀመረ፤ በመጨረሻም ከብዙ ስቃይ በኃላ መስከረም 29 ቀን አንገቷን ቆረጣት ከእርሷ ጋር 27 ሰማዕታት አብረው ተሰይፈዋል። የሰማዕቷ በረከት ከእኛ ጋር ይሁን፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
ስርዓተ ማሕሌት ዘሣልሳይ ጽጌ በዓለ ቅድስት ሐና
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ነግሥ (የማንኛውም ወርኃ  በዓልና ክብረ በዓል ሥርዐተ ማኅሌት መጀመሪያ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
@menkir_tube
@menkir_tube
መልክዓ ሥላሴ
ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል፡፡

ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሐረገ ወይን፤እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕፁቂሃ ሐረገ ወይን፤እንተ በሥሉስ ትትገመድ ወታፈራ ለነ አስካለ በረከተ፤ሐረገ ወይን፤ሲሳዮሙ ለቅዱሳን፤ሐረገ ወይን፤ሠርዓ ሰንበተ በቃሉ ወጸገወ ሰላመ ለኩሉ።
@menkir_tube
ማኅሌተ ጽጌ
ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ፤ዘወለደት ጽጌ ወፀሐየ ዓለም ብርህተ፤ካዕበ (ወካዕበ) ትመስል ሳብዕተ ዕለተ፤እስመ ፈረየት ኪያኪ ተአምረ ግዕዛን ሰንበተ፤ ለእለ በሰማይ ወምድር ዘኮንኪ ዕረፍተ።

ወረብ፦
ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ ትመስል እም/፪/
ዘወለደት ጽጌ ጽጌ ጽጌ ወፀሐየ ዓለም/፪/
@menkir_tube
ዚቅ
እምኲሉ ዕለት ሰንበተ አክበረ ወእምኲሎን አንስት ማርያምሃ አፍቀረ ከመ ትኩኖ ማኅደረ ለመንፈስ ቅዱስ ወምስጋድ ለኲሉ ዓለመ።

ማኅሌተ ፅጌ፦
ከመ ታቦት ሥርጉት በወርቀ ዓረብ ወተርሴስ፤በድንግልና ማርያም ሥርጉተ ሥጋ ወነፍስ፤ ተአምረ ነቢር አርአይኪ በቤተ መቅደስ፤ኢያቄም ወሐና ቀንሞስ ቀናንሞስ፤ እምዘ ጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ
@menkir_tube
@menkir_tube
ወረብ፦
እምዘ ጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ  ኢያቄም ወሐና ቀንሞስ ቀናንሞስ/፪/
ተአምረ ነቢር አርአይኪ ተአምረ ነቢር አርአይኪ በቤተ መቅደስ/፪/
@menkir_tube
ዚቅ
ሰአሉ ለነ ኢያቄም ወሐና ዘፈረይክሙ በቅድስና መሶበ ወርቅ እንተ መና
@menkir_tube
ማኅሌተ ፅጌ፦
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።

ወረብ፦
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ/፪/
ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናየትየ ምስለ ገብርኤል ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ/፪/

ዚቅ
ዕፀ ጳጦስ ይዕቲ እንተ በአማን ለእንተ ይብልዋ ቅድስተ ቅዱሳን ንዒ ርግብየ ሠናይት ወይቤላ መልአክ ተፈስሒ ፍስሕት ቡርክት አንቲ እምአንስት

ማኅሌተ ፅጌ፦
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቄ ባሕርይ ዘይኀቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኩሎ ታሰግዲ ሎቱ ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ።
@menkir_tube
ወረብ፦
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ዘየሐቱ እምዕንቄ ባሕርይ/፪/
አክሊለ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ/፪/
@menkir_tube

ዚቅ
ይእቲ ተዓቢ እምአንስት እሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላእክት መድኃኒቶሙ ለነገሥት አክሊል ንጹሕ ለካህናት ብርሃኖሙ ለከዋክብት
@menkir_tube
ሰቆቃወ ድንግል
ተንሥኢ ወንኢ ሌዋዊት ሐና፤ትጼውዓኪ ወለትኪ ከመ ትርአዪ ኃዘና፤ እምርስትኪ ወፅአት ወተሰደት በድክትምና፤ትበኪ እምዋዕየ ሐጋይ ኃጢኣ በፍና፤ ሕፍነ ማይ ዘታሰትዮ ለፅሙዕ ሕፃና
@menkir_tube
ወረብ፦
ተንሥኢ ወንኢ ሌዋዊት ሐና ተንሥኢ ወንኢ/፪/
ትጼውዓኪ ወለትኪ ኃዘና ከመ ትርአዪ /፪/
@menkir_tube
@menkir_tube
ዚቅ፦
ኢሀለዉ አሜሃ አቡኪ ወእምኪ፤ከመ ይርአዩ ድክትምናኪ፤ወይስምዑ ገዓረኪ፤እስመ ሞቱ እምንእስኪ ወኃደጉኪ ባሕቲተኪ

ዓዲ (ሌላ) ዚቅ፦
አመ ወጽአት በፍርሃት እምሀገረ ዳዊት ዘይሁዳ በብሥራተ መልአክ ዕንግዳ ኢረከበት ማየ በፍኖት ዘታስትዮ ለወልዳ

መዝሙር፦
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፣ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ምስለ ኖኅ ኪዳነ ዘዓቀምከ፤  ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ምስለ ኖኅ ኪዳነ ዘአቀምከ ለደቂቀ እስራኤል መና ዘአውረድከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ ወስነ ገዳምኒ ምስለ ቅዱሳኒከ ፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ወከመ ወሬዛ ኀይል መላትሒሁ፤ ጉርዔሁ መዓርዒር አምሳሉ ዘወይጠል፤  ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ሰማይ ወምድረ ዘአንተ ፈጠርከ ፀሐየ ወወርኃ ዘአስተዋደድከ፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ  በከዋክብት ሠማይ ዘከለልከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤  ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ቀደሳ ወአክበራ አዕበያ ለሰንበት ወአልዓላ እምኩሉ ዕለት፤ማ፦ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፥ ወኩሉ ይሴፎ ኪያከ።

አመላለስ

ወመኑ መሐሪ ዘከማከ/፪/
ወኩሉ ይሴፎ ኪያከ ወኩሉ ይሴፎ ኪያከ/፪/

🇪🇹👇👇👇👇👇👇🇪🇹
👉@menkir_tube👈                 
👉@menkir_tube👈
👉@menkir_tube👈
🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹

      @menkir_tube
    # Join & share #

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ብዙ ድርሳናትንም ደረሰ ከእርሳቸውም አንዱ ክብር ይግባውና ስለ መድኃኒታችን ስቅለት የደረሰው በዕለተ ዐርብ የሚነበብ አንዱ ነው።

የእምነቱም ምክንያት እንዲህ ነው ከዕለታት በአንዱ በፍልስፍናው ቤት ተቀምጦ ሳለ የአቴናም ፈላስፎች በእርሱ ዘንድ ተሰብስበው ነበር እርሱ ለሁሉም አለቃ ስለሆነ በዐርብ ቀንም ቀትር ሲሆን ፀሐይ ጨለመ ታላቅ ንውጽውታም ሆነ አሕዛብ ሁሉ ደንግጠው እጅግ ፈሩ ቅድስ ዲዩናስዩስንም በዓለም ውስጥ የሆነውን ጌታችን ሆይ አስረዳን ብለው ጠየቁት።

አርሱም ፀሐይን ጨረቃንና ከዋክብትን መረመረ ጸጥ ብለው አገኛቸው ደግሞ ባሕሮችን ትልቁንም በዓለም ዙሪያ ያለውን የውቅያኖስን ባህር መረመረ እሱንም ጸጥ ብሎ አገኛው።

ከዚህም በኋላ አርስጣላባ የሚባል የፍልስፍና መጽሐፍን አንስቶ ሲመረምር በውስጡ እልመክኑን የሚል አገኘ ይህም ኀቡእ አምላክ ወረደ ወገኞቹም በእርሱ ላይ ተነስተው ሰቀሉት ማለት ነው በዚያችም ጊዜ ልብሱን ቀዶ ታላቅ ሀዘንን አዘነ ከበታቹ ምሁራን ያየውን ያስርዳቸው ዘንድ ለመኑት እርሱም ሁሉን ነገራቸው እነርሱም ይህን ሰምተው ታላቅ ፍርሃት ፈሩ።

ደቀ መዝሙሩ ኡሲፎስንም የሆነውን ሁሉ የዚያችንም ቀን ስሟን ሰዐቷን ወርዋን ዘመኑንም እንዲጽፍ አዘዘው ዳግመኛም በጣዖታቱ ቤቶች በደጃፋቸው እልመክኑን እያሉ እንዲጽፉ አዘዘ።

ከዐሥራ አራት ዓመትም በኋላ ቅዱስ ሐዋርያ ጳውሎስ ወደ አቴና አገረ መጣ ክብር ይግባውና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መውረዱን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከስጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ መወለዱን መከራ መቀበሉን መሰቀሉንና መሞቱን በሶስተኛው ቀን መነሳቱን ማረጉንም በሕያዋንና በሙታን ለምፍረድ ዳግመኛ መምጣቱን አስተማረ።

የአቴና ሰዎችም የሐዋርያዉን ስብከት በሰሙ ጊዜ እጅግ አደነቁ ወደ ዲዩናስዩስም ሩጠው እንዲህ ብለው ነገሩት አንድ ሰው ዛሬ ወደ አገራችን መጥቶ እኛ የማናውቀውን ወይም ከእኛ በፊት የነበሩ አባቶቻችን የማያውቁትን በአዲስ አምላክ ስም አስተማረን።

ዲዮናስዮስም ልኮ ሐዋርያ ጳውሎስን ወደርሱ አስመጥቶ በሀገራችን ውስጥ በአዲስ አምላክ ስም የምታስተምረው ምንድን ነው አለው።

ቅዱስ ጳውሎስም በአደባባያችሁ መካከል አልፌ ስሔድ በአማልክቶቻችሁ ቤቶች በደጃፋ ላይ እልመክኑን የሚል ጽሑፍ አየሁ ይህም የማይመረመር አምላክ ወረደ ማለት ነው እኔም ለእናንተ የምሰብከው ይህንኑ ነው ብሎ መለሰ።

በዚያንም ጊዜ ከዐሥራ አራት ዓመት በፊት ያጻፈውን ያን መጽሐፍ ያመጣው ዘንድ ኡሲፎስን አዘዘው ሁለተኛም ጊዜውንና ወራቱን ሐዋርያውን ጠየቀው እርሱም በመጋቢት ወር በሃያ ሰባት ዓርብ ቀን በስድስት ሰዓት ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርሶቶስ ያን ጊዜ እንደ ተሰቀለ ፀሐይም እንደ ጨለመ ምድርም እንደተናወጠች አስረዳው።

የአቴና ሰዎችም ይህን በስሙ ጊዜ ከቅዱስ ዲዮናስዮስ ጋር ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው ዲዮናስዮስንም በእነርሱ ላይ ኤጲስቆጶስን አድርጎ ሾመው የቤተ ክርስቲያንንም ሥርዓት የተረጐመ እርሱ ነው።

ከዚህም በኋላ በባሕር አቅራቢያ ወደ አለ አገር በመሔድ በሐዋርያት ዘመን አስተማረ ብዙ ወገኖችንም ክብር ይግባውና በጌታችንም አሳመነ ድንቆች የሆኑ ብዙዎች ተአምራትን አደረገ።

ከሀዲ ንጉሥ ጠማትያኖስም ይዞ ጽኑ ሥቃይን አሰቃየው ከዚያም የከበረች ራሱን በሰይፍ ቆረጠው የተቆረጠች ራሱንም በእጁ ይዞ ሁለት ምዕራፍ ያህል ጐዳና ተጓዘ ሁለተኛም የደቀ መዛሙርቱን የኡሲፎስንና የኡርያኖስን ራሳቸውን ቆረጠ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ሄኖስ

በዚችም ቀን የሴት ልጅ የሄኖስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው የእግዚአብሔርንም ስም መጥራት የጀመረ ይህ ሄኖስ ነው። ሄኖስም መቶ ዘጠና ዓመት ኖረ ቃይናንም ወለደው ቃይናንንም ከወለደው በኋላ ሰባት መቶ አሥራ አምስት አመት ኖረ ወንዶች ልጆችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ በቅዳሜ ቀንም አረፈ። መላ ዕድሜውም ዘጠኝ መቶ አምስት ነው።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በፈተና የሚፀና ሰው የተባረከ ነው፥ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የህይወት አክሉል ይቀዳጃሉና፣"
.ያዕቆ. 1÷12
.
ፅኑ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ሆይ ምልጃሽ ፣ ረድኤትሽና በረከትሽ አይለየን።
ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ኢትዮጵያ አስባት፣ ሰላሟም ይመለስ ዘንድ እርዳን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ ጥቅምት ፭ (5) ❖

✞✞✞ እንኩዋን ለጻድቁ "አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ" እና "ቅዱስ ኪራኮስ አረጋዊ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+"+ አቡነ ገብረ ሕይወት +"+

=>ጻድቁ የተወለዱት ግብፅ (ንሒሳ አካባቢ) ሲሆን
አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ:: አባታችን
ገብረ ሕይወት የጻድቃን አለቃ: የቅዱሳን የበላይ:
ተጋድሎአቸውና ድንቅ ተአምራቸው እንደ ሰማይ
ከዋክብት የበዛ ቅዱስ ሰው ናቸው::

+የጻድቁን ክብር መናገር የሚችል ምን አነደበት
ይኖራል?
እንደ ምንስ ባለ ብራና ይጻፋል?
ዜናቸውንስ ለመስማት የታደለ እንደ ምን ዓይነት ሰው
ይሆን?

+አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ562 ዓመታት በዚህች
ዓለም ሲኖሩ እህል ያልቀመሱ (ምግባቸው ምስጋና
ነውና): ልብስ ያልለበሱ (ጠጉር አካላቸውን ይሸፍን
ነበርና): ሐዋርያዊ ሆነው ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ
ነፍሳትን ያዳኑ አባት: ሃገራችንን አስምረው: አስራት
እንድትሆናቸውም ተቀብለው ምድረ ከብድ አካባቢ
አርፈዋል::

+ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስም: ገብረ ሕይወትም
ይባላሉ:: በ562 ዓመታት ሕይወታቸው እንደ ሐዋርያት
ከምድረ ግብጸ እስከ ኢትዮዽያ ወንጌልን ሰብከዋል::
በዚህም በሚሊየን (አእላፍ) ለሚቆጠሩ ነፍሳት የድኅነት
ምክንያት ሆነዋል::

+ጻድቁ እንደ ሰማዕታትም ከከሃዲ ሰዎች ብዙ መከራን
ተቀብለዋል:: እንደ ባሕታውያን ለብዙ መቶ ዓመታት ሰው
ሳያዩ ቆይተዋል:: ለየት የሚለው ግን የጽድቅ
ሕይወታቸው ነው:: ከእልፍ አዕላፍ አጋንንት ጋር
ተዋግተው ድል ማድረግ ችለዋልና::

+የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለኢትዮዽያ ልዩ
ፍቀር አላቸው:: ስለ ሃገሪቱና ሕዝቧ ፍቅር ሲሉ ለ100
ዓመታት በደብረ ዝቁዋላ መከራን ተቀብለዋል:: ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው
ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው::

+ስለዚህም ነው በሃገሪቱ ውስጥ ከ2,000 በላይ የጻድቁ
አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳማትና አድባራት ዛሬም
ድረስ ያሉት:: በ8ኛው ክ/ዘመን አካባቢ የተወለዱት
አባታችን ያረፉት በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ነው::
ፍጥረታትን ሁሉ አዘው መጋቢት 5 ቀን ሲያርፉ ግሩማን
መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል::

+ሥላሴን የተሸከመ አካላቸው በጐልጐታ ተቀብሯል
የሚሉም አሉ::
"ሰላም ለመቃብሪከ ዘኢተከሥተ ለባዕድ:
ከመ መቃብሩ ለሙሴ ወልደ ዮካብድ:
ዜና መቃብሪከሰ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጸማድ:
ቦ ዘይቤ በኢየሩሳሌም አጸድ:
ወቦ ዘይቤ ኀለወ በከብድ::" እንዲል::

+የጻድቁ በዓል ጥቅምት 5 ቀን የሚከበረው ብዙ ጊዜ
መጋቢት 5 ዐቢይ ጾም ውስጥ ስለሚውል ተውላጥ
(ቅያሪ) ሆኖ ነው::

+"+ ቅዱስ ኪራኮስ አረጋዊ +"+

=>ይህ ቅዱስ አባት ስም አጠራሩ የከበረ:
ሽምግልናውም ያማረ ነው:: ብዙዎቻችን የምናውቀው
በበዓለ መስቀል ስሙ ተደጋግሞ ሲጠራ ነው:: ግን ይህ
ታላቅ ሰው ለቅድስት እሌኒ መካነ መስቀሉን አሳያት
ከሚል አረፍተ ነገር የዘለለ ታሪኩ ሲነገርለት ብዙ ጊዜ
አንሰማምና እስኪ በዕለተ ዕረፍቱ ስለ ቅዱሱ ጥቂት
እንበል::

+ቅዱስ ኪራኮስ የተወለደው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን
ሲሆን እናቱ ቅድስት ሐና ትባላለች:: በእጅጉ የተባረከች
ሴት ናት:: ምንም በነገዳቸው አይሁድ ቢሆኑም የዘመኑ
የአይሁድ ክፋት አልገዛቸውም:: የተባረከች እናቱ ታሪክ
እያስጠናች ከማሳደጉዋ ባለፈ አስቀድማ ኦሪቱን:
ነቢያቱን እንዲያውቅ አደረገች::

+አስከትላም ሕገ ክርስትናን እንዲረዳ አደረገችው::
የታሪክና የመጻሕፍት ምሑሩ ቅዱስ ኪራኮስ ከእናቱ ጋር
ሆኖ እግዚአብሔርን እያገለገለ: ክርስቶስን እያመለከ
ቆየ:: በዚህ ጊዜ ግን እድሜው እየገፋ ነበር::

+ሠለስቱ ምዕት (318ቱ ሊቃውንት) ጉባኤያቸውን
ከፈጸሙ በሁዋላ ቅድስት እሌኒም መስቀሉን ፍለጋ
ስትወጣ ትልቁ ፈተናዋ የተቀበረበትን ቦታ ማወቅ
አለመቻሏ ነበር:: እንዲያውም አማራጭ ስታጣ
በአካባቢው የነበሩ አይሁድን ምሥጢር እንዲያወጡ
ቀጥታቸው ነበር:: በሁዋላ ግን ኪራኮስ ስለሚባል ደግ
ታሪክ አዋቂ ሰው ሰምታ ተገናኙ::

+ቅዱስ ኪራኮስም አባቶቹ አይሁድ ናቸውና አካባቢውን
ያውቀው ነበር:: ችግሩ ቆሻሻው ተራራ በመሆኑ ከ3ቱ
የትኛው እንደ ሆነ አለመታወቁ ነበር:: ቅዱሱ ግን
ለዚህም መፍትሔ ነበረውና "ደመራ ደምረሽ: በእሳት
አቃጥለሽ: እጣን ጨምሪበትና ይገለጥልሻል" አላት::

+ቅድስት እሌኒም የተባለችውን በትክክል ፈጽማ
የመድኅን ክርስቶስን ቅዱስ ዕጸ መስቀል አገኘች::
ቅድስት እሌኒ ወደ ሃገሯ ከተመለሰች በሁዋላም ቅዱስ
ኪራኮስ በኢየሩሳሌም አካባቢ ዻዻስ ሆኖ ተሾመ::

+አረጋዊው ቅዱስ የሚገርም እረኛ ነውና የባዘኑትን
ሲፈልግ: በቤቱ ያሉትንም ሲያጸና ብዙ ደከመ:: በቅርቡ
ያሉትን በአፉ: የራቁትን ደግሞ በጦማር (በመልእክት)
አስተማረ:: በወቅቱ በአካባቢው ኤልያኖስ የሚሉት ከሃዲ
ንጉሥ ነበርና በቅዱስ ኪራኮስ ላይ ተቆጣ::

+ወደ እርሱ አስጠርቶ በአደባባይ: ቅዱስ ቃሉን ይጽፍበት
የነበረው ቀኝ እጁን አስቆረጠው:: ቅዱስ ኪራኮስ ግን
እጁ መሬት ላይ ወድቃ: ደሙ እየተንጠፈጠፈ ተናገረ:-
"አንተ ልብ የሌለህ ንጉሥ! እጄን ቆርጠህ ከክርስቶስ
ፍቅር ልትለየኝ አትችልም" አለው::

+በዚህ የተበሳጨ ንጉሡ እሳት አስነድዶ: አልጋውን
አግሎ ቅዱሱን ጠበሰው:: ኪራኮስ ግን በእሳቱ ላይ ሳለ
ወደ እሥራኤል ፈጣሪ በእብራይስጥኛ ጸለየ:: በማግስቱ
እናቱን ቅድስት ሐናን አምጥተው የነደደ እሳት ውስጥ
ጣሏት::

+ለ3 ሰዓት ያህል በእሳት ውስጥ ስትጸልይ ቆይታ በጦር
ወግተው ገደሏት:: ቅዱስ ኪራኮስንም ለአራዊት ሰጡት::
አራዊቱ ሰገዱለት:: በሌሎች ዓይነት ስቃዮችም ፈተኑት:
ግን እንቢ አላቸው:: በመጨረሻው በዚህ ቀን ገድለውት
የክብርን አክሊል ተቀዳጅቷል::

=>አምላከ ቅዱሳን በእነርሱ ላይ የበዛች ፍቅሩን ለእኛም
ያድለን:: ፍሬ ትሩፋት: ፍሬ ክብር እንድናፈራም ይርዳን::
ክብራቸውንም አያጉድልብን::

=>ጥቅምት 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጻድቅ
2.ቅዱስ ኪራኮስ አረጋዊ (ዻዻስ ወሰማዕት)
3.ቅድስት ሐና ሰማዕት (እናቱ)
4.ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
5.አባ ዻውሎስ ሰማዕት (አርዮሳውያን አንቀው የገደሉት አባት)

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2.ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም
3.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
4.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ
5.ቅድስት አውጋንያ (ሰማዕትና ጻድቅ)

=>+"+ ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት: እኔም
ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ
መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ:: በክርስቶስ
ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት መሆን ይጠቅማል እንጂ መገረዝ
ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና:: +"+ (ገላ. 6:14)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ስርአተ ዋዜማ ዘጥቅምት ገብረ መንፈስ ቅዱስ
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
በ ፩ -
ሃሌ ሉያ እንተ አጽናዕኮሙ ለአድባር በኃይልከ፤ወቅኦታን እሙንቱ በኃይል፤ዝንቱሰ ብእሲ መምህርነ፤አባ፤ጸሊ በእንቲአነ
@menkir_tube
ምልጣን፦
ዝንቱሰ ብእሲ መምህርነ፤አባ ጸሊ በእንቲአነ፤አባ ጸሊ በእንቲአነ


አመላለስ፦
አባ ጸሊ በእንቲአነ/፪/
አባ ጸሊ ጸሊ በእንቲአነ/፬/
@menkir_tube

ለእግዚአብሔር ምድር በምላህ፦
አባ ጸሊ በእንቲአነ፤ ጸሎትከ ወትረ ይብጽሐነ፤ አባ ጸሊ በእንቲአነ።
@menkir_tube

እግዚአብሔር ነግሠ፦
ጼና አልባሢሁ አባ መባእ ጽዮን ስሂን ገነት ከመ ይርአይ ዘሜላት ዘወረደ ውስተ ገነት ከመ ይርአይ ስነ ፅጌያት
@menkir_tube

ይትባረክ፦
ኪያከ መሠረት አንተ ብነ፤ አባ ጸሊ በእንቲአነ፤ እስመ ጸሎተ ጻድቅ ይሰምዕ እግዚአብሔር
@menkir_tube

ሰላም፦
ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም ዜና ምግባሩ ትሩፍ ለአረጋዊ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ኮከብ ገዳም ፤ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም ፀጉያን እሙንቱ እምፅጌ ሮማን ወቀ ይሐን እምከላ ገዳም ፤ ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም ደቂቁ ሔራን ልኡላን ክቡር ወስያ፤ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም እንዘ የአርግ መስዋዕት ሰላም ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም፤ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም

@menkir_tube
አመላለስ፦
ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም/፪/
ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም/፬/

🇪🇹👇👇👇👇👇👇🇪🇹
👉@menkir_tube👈                 
👉@menkir_tube👈
👉@menkir_tube👈
🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹

      @menkir_tube
    # Join & share

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ዘመቻውን ይቀላቀሉ ጥቅምት 1/2016ዓ.ም እስከ ጥቅምት 30/2016ዓ.ም

ውድ የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች መዓዛ ሃይማኖት በተለያዩ መንፈሳዊ ትምሕርቶች ስናስተላልፍ መቆየታችን ይታወቃል አሁንም በማሰስተላለፍ ላይ እንገኛለን ሆኖም ግን በእናንተው በመጣልን አስተያየትና በያዝነው ዕቅድ መሰረት መዓዛ ሃይማኖት ዩቲዩብ ቻናል ላይክ ሸር በማድረግ ከመዓዛ ሃይማኖት ጋር እንዲሆኑ በአክብሮት እንጠይቃለን
እግዚአብሔር ያክብርልን፡፡

https://m.youtube.com/channel/UCKGh-U7U7pnvFUIEGXPOnNw

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ጥቅምት_3

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ሦስት በዚህች ቀን የኢትዮጵያዊው ቄርሎስ #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ በዓለ ፅንሰቱ ነው፣ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት 51ኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_አባ_ስምዖን አረፈ፣ #የቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሐዲስ የምስክርነቱ መታሰቢያ ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞#✞✞✞✞✞

#አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ

ጥቅምት ሦስት በዚህች ዕለት ከመጽሐፈ ሰዓታት ውጭ እጅግ ብዙ ድርሰቶችን የደረሰ ፈላስፋም ጻዲቅም ደራሲም መናኝ ባሕታዊም የሆነ ድርሰቶቹንም ለቅዱሳን በነፋስ ጭኖ ይልክላቸው የነበረ የቤተ ክርስቲያናችን ታላቅ ኩራት ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በዓለ ፅንሰቱ ነው፡፡

አባ ጊዮርጊስ ነገረ ሃይማኖትን ጠንቅቆ የተረዳና የሚያስረዳ ስለነበር በዘመኑ የተነሡ የሃይማኖት ክርክሮች ሁሉ እርሱ ከሌለ አይሳኩም ነበር፡፡ በዚያ ጊዜ በሸዋ በይፋት ራሳቸውን ቤተ እስራኤል እያሉ የሚጠሩ አይሁድ ነበሩ፡፡ ከአቡነ ዜና ማርቆስ ጀምሮ ብዙ መምህራን ወደነዚህ ሕዝቦች እየተሠማሩ ወንጌልን አስተምረዋል፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስ ወደ ክርስትና ለተመለሱት ቤተ እስራኤላውያን በእመቤታችን፣ በቅዱስ ሚካኤል፣ በአባ ኖብና በሰማዕቱ በጊጋር ስም አራት አብያተ ክርስቲያናትን አሠርተው ነበር፡፡ ሁለቱ የመጀመሪያዎቹ አሁንም አሉ፡፡ ይህ ሁሉ ቢሆንም ቤተ እስራኤላውያኑ ሙሉ በሙሉ ወደ ክርስትና አልተመለሱም ነበር፡፡

ከእነዚህ አይሁድ መካከል አንዱ ከክርስቲያኖች ጋር በነገረ ሃይማኖት ለመከራከር ጥሪ አቀረበ፡፡ “ክርስቲያኖች ከረቱኝ ወደነርሱ ሃይማኖት እገባለሁ እኔ ከረታኋቸውም ወደኔ ሃይማኖት ይገባሉ” ሲል ነገሩን ጥብቅ አደረገው፡፡ ዐፄ ዳዊት ይህን ጉዳይ ሲሰማ በጣም ስለ ተናደደ ሊቃነ ካህናቱን፣ ንቡራነ እዱንና የመጻሕፍት ዐዋቂዎችን ሁሉ ከየሀገሩ እንዲሰባሰቡ አዘዘ፡፡ አይሁዳዊው በአንድ ወገን መምህራኑ በአንድ ወገን ሆነው ክርክሩን ጀመሩ፡፡ የመጀመርያው እድል የተሰጠው ለአይሁዳዊው በመሆኑ ቀጥሎ ያለውን ጥያቄ አቀረበ፡- “እናንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነው የምትሉት ይሄ ክርስቶስ እውነት የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነ፣ ወደ ቢታንያ በመጣ ጊዜ አልዓዛር የተቀበረበትን ቦታ ሳያውቅ ቀርቶ 'አልዓዛርን የት ቀበራችሁት?” ብሎ እንደ ጠየቀ በወንጌላችሁ ተጽፏል፡፡ ለዚህ መልስ ስጡኝ፣ እኔንም ከመጽሐፈ ኦሪቴ ጠቅሳችሁ ጠይቁኝ?” ሲል የመከራከርያ ነጥቡን አቀረበ፡፡

በዚህ ጊዜ አባ ጊዮርጊስ ታሞ አልጋ ላይ ነበር፡፡ ሊቃውንቱም “እንዲህ ያለው ነገር ያለ እርሱ አይሆንምና አባ ጊዮርጊስ ይምጣ” ሲሉ ለዐፄ ዳዊት ጥያቄ አቀረቡ፡፡ አባ ጊዮርጊስም በአልጋ ላይ እያለ እንዲመጣ ተደረገ፡፡ በአልጋ ላይ ሆኖም በጉባኤው ላይ ተገኘ፡፡ ጉባኤተኞቹ የቀረበውን ጥያቄ ነገሩት፡፡ አባ ጊዮርጊስ የሰጠውን መልስ ገድሉ በሚከተለው መንገድ ይገልጥልናል “እኔ ግን በወንጌል ሳይሆን በኦሪት እከራከርሃለሁ፡፡ የምኩራብ መጻሕፍት ሁሉ ለቤተ ክርስቲያን የታወቁ ናቸውና፡፡ ምኩራብ ዘራች ቤተ ክርስቲያንም አጨደችው፤ ምኩራብ ፈተለችው ቤተ ክርስቲያን ለበሰችው፤ አዳምን በገነት ሳለ አዳም ሆይ ወዴት ነህ? ብሎ የጠየቀው ማነው? አብርሃምንስ ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት? ብሎ የጠየቀው ማነው? እስቲ መልስልኝ? ሰይጣንንስ ከወዴት መጣህ? ብሎ የጠየቀው ማነው? እግዚአብሔር አብ አይደለምን?” በዚህ ጊዜ አይሁዳዊው መልስ አጥቶ ዝም አለ፡፡ ንጉሡ፣ ሊቃውንቱና መኳንንቱም እጅግ ተደሰቱ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ሌላው ያጋጠመው ክርክር ቢቱ ከተባለው ሰው ጋር ያደረገው ክርክር ነበር፡፡ ቢቱ “በምጽአት ጊዜ የሚመጣው ወልድ ብቻውን እንጂ አብና መንፈስ ቅዱስ አይመጡም” የሚል ኑፋ*ቄ ማስተማር ጀምሮ ነበር፡፡ ቢቱ ከዚህ ኑፋ*ቄው በተጨማሪ የጥንቆላ ሥራም ይሠራ ነበር፡፡ ቢቱ በጥንቆላ ሥራው የተነሣ በቤተ መንግሥቱ ተቀባይነት የነበረው ሰው እንደ ነበረ ገድሉ ይናገራል፡፡ ይህን መሰሉን ተግባር አጥብቆ የተዋጋው ዘርዐ ያዕቆብ እስኪመጣ ድረስ ነገሥታቱ ምንም ክርስቲያኖች ቢሆኑ በዚህ መሰሉ ስንኩል ሕፀፅ ይዋጡ ነበር፡፡

ቢቱና አባ ጊዮርጊስ ወደ ንጉሥ ዳዊት ቀርበው በጉዳዩ ላይ መነጋገር እንደሚፈልጉ ገለጡ፡፡ ዐፄ ዳዊትም ጳጳሱና ሊቃውንቱ ባሉበት እንዲነጋገሩ ስለ ወሰነ ጳጳሱ እንዲመጡ አዘዘ፡፡ በዚህ ጊዜ ተንኮለኛው ቢቱ ከአባ ጊዮርጊስ ጋር ከተከራከረ እንደሚረታ ስላወቀ “ንጉሡ የአባቶቻችንን ሃይማኖት ክዷ*ልና አትምጣ” የሚል ደብዳቤ በአባ ጊዮርጊስ ስም ጽፎ ጳጳሱን ሊጠሩ በሄዱት መልእክተኞች እጅ ላከ፡፡ ወድያውም ለዐፄ ዳዊት ይህንን ነገር አሳበቀ፡፡ ዐፄ ዳዊትም ፈጣን መልእክተኞች ልኮ የፊተኞቹ መልእክተኞች እንዲመለሱ አደረገና ደብዳቤው ተነበበ፡፡ የቢቱ ተንኮል ያልገባው ንጉሥ ዳዊት ይህን ደብዳቤ ሲመለከት አባ ጊዮርጊስን በደም አበላ እስኪነከር ድረስ እንዲደበደብ አድርጎ ወደ እስር ቤት አስገባው፡፡ ዐፄ ዳዊት እስኪሞትና ልጁ ቴዎድሮስ እስኪነግሥ ድረስም በዚያ ቆየ፡፡ ቢቱ ግን በመልአክ ተቀስፎ ሞተ፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አባ_ስምዖን

ዳግመኛም በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ኃምሣ አንደኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባ ስምዖን አረፈ።

ይህም አባት ከእስክንድርያ ከታላላቆች ተወላጅ የሆነ ወላጆቹም ሃይማኖታቸው የቀና ነው እርሱም ከታናሽነቱ የሃይማኖት ወተትን ጠጥቶ አደገ ስለዚህም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ተማረ።

የምንኵስናንም ልብስ ሊለብስ በልቡ አስቦ ወደ አስቄጥስ ገዳም በመሔድ ከእርሱ አስቀድሞ ሊቀ ጳጳሳት በሆነ በአባ ያዕቆብ ገዳም መነኰሰ በየጊዜው በሚጨመር ተጋድሎም ሥጋውን እያደከመ አብዝቶ በመጋደል በእርሱ ዘንድ ኖረ።

ዳግማዊ አባ ማርቆስም ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ ይህን አባ ስምዖንን ስለ በጎተጋድሎውና ስለ አገልግሎቱ ከአባ ያዕቆብ ዘንድ ወሰደው እያገለገለውም ከእርሱ ጋር ኖረ።

አባ ማርቆስም በአረፈ ጊዜ አባ ያዕቆብ ተሾመ ያን ጊዜም እያገለገለው ከአባ ያዕቆብ ጋር ኖረ። ከዚህም በኋላ አባ ያዕቆብ በአረፈ ጊዜ ብዙዎች ካህናትና ኤጲስቆጶሳት የሀገር ታላላቆች ሁሉም ይህን አባት አባ ስምዖንን መረጡት። ትሩፋቱንና የአማረ ሥራውን በእነዚህ በሁለቱ ሊቃነ ጳጳሳት ዘንድ በነበረበት ጊዜ ስለተመለከቱ አምላካዊ ፍቅር አነሣሥቷቸዋልና በወንጌላዊ ማርቆስ መንበር ላይ ይዘው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት።

ከዚህም በኋላ በሹመቱ ጸንቶ መልካምን ጉዞ ተጓዘ እግዚአብሔርንም አገለገለው የሃይማኖትንም ሕግ በማስጠበቅ የክርስቶስን መንጋዎች ጠበቀ።

በሹመቱ ወራትም ቤተ ክርስቲያን በጸጥታና በሰላም ኖረች። ከዚህም በኋላ እግሮቹን በጽኑዕ ደዌ ታመመ ፈጣሪ እግዚአብሔርንም ከዚህ ደዌ ያሳርፈው ዘንድ ለመነው። ክብር ይግባውና ጌታችንም ልመናውን ተቀብሎ በሰላም በፍቅር አንድነት አሳረፈው የሹመቱ ወራትም አምስት ወር ከዐሥራ አምስት ቀን ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሐዲስ (ሰማዕት)

ሰማዕቱ የተወለደው በምድረ ግብጽ አሕዛብ (ተንባላት) በሰለጠኑበት የመጀመሪያው ዘመን ነበር። በተለይ ተንባላቱ ግብፅና ሶርያን ከያዙ በኋላ ባልተጠበቀ ፍጥነት በኃይልም በሰውም ተደራጅተው ነበር። ቅዱስ ጊዮርጊስ (ሊቀ ሰማዕታት አይደለም) የተወለደው በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ነበር።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለቅዱሳን ሊቃውንት አባ ሕርያቆስ እና አባ ሳዊሮስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ሊቁ አባ ሕርያቆስ †††

††† ክርስቲያን ሆኖ እመቤታችንን የሚወድ ሰው ሁሉ ይህንን አባት ያውቀዋል:: አባ ሕርያቆስ ተወልዶ ያደገው በምድረ ግብጽ ሲሆን አካባቢው ብህንሳ (ንሒሳ) ይባላል:: ይህቺ ቦታ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ጨምሮ በርካታ ቅዱሳንን ያፈራች ናት::

አባ ሕርያቆስን በዚህ ዘመን ነበረ ብየ ትክክለኛውን ዓ/ም ለመናገር ይከብደኛል:: ከቤተ ክርስቲያን ትውፊት መረዳት እንደሚቻለው ግን የነበረበት ዘመን 4ኛው: ወይ 5ኛው መቶ ክ/ዘመን እንደ ሆነ መገመት ይቻላል::

ቅዱሱ በዘመኑ የተለየ ማንነት የነበረው ሰው ነው:: ገና ከልጅነቱ እመ ብርሃንን የሚወዳት በመሆኑ ቅን: የዋህና ገራገር ነበረ:: መቼም እመቤታችንን ይወዳል ሲባል እንደ ዘመኑ በአፍ ብቻ እንዳይመስለን:: ቀንና ሌሊት ለፍቅሯ የሚተጋ: ማዕበለ ፍቅሯ የሚያማታው ሰው ነበር እንጂ::

የእመቤታችን ድንግል ማርያምን ስም ሲጠራ ምስጥ ብሎ ልቡናው ይሰወርበት ነበር:: ዘወትር የእርሷን ፍቅር ከማሰብ በቀር ሌላ ሥራ አልነበረውም:: የልጅነት ጊዜው ሲያልፍም ድንግልንና ቸር ልጇን ያገለግል ዘንድ መነነ::

ዘመኑ ዘመነ ሊቃውንት እንደ መሆኑ ሁሉም ለትምሕርት ሲተጉ እርሱ ግን ለጸሎትና ለደግነት ብቻ ነበር የሚተጋው:: ከትምሕርት ወገንም የሰሞን ጉዋዞችን: አንዳንድ ቅዳሴያትንና የዳዊትን መዝሙር ተምሮ ነበር::

በተለይ ግን የዳዊትን መዝሙር እየጣፈጠው መላልሶ: መላልሶ ያመሰግንበት ነበር:: ከዳዊት መካከል ደግሞ መዝ. 44ን ፈጽሞ ይወዳት ነበር:: ይህቺ ጥቅስ የምትጀምረው "ጐስዐ ልብየ ቃለ ሠናየ" ብላ ነው:: የውስጧ ምሥጢርም ስለ ድንግል ማርያምና ስለ ክርስቶስ ነው::

አባ ሕርያቆስ ይህቺን መዝሙር በቃሉ አጥንቶ: ቁሞም ተቀምጦም: ተኝቶም ተነስቶም ያለ ማቋረጥ ይላት ነበር:: እየጣፈጠችው "ልቡናየ በጐ ነገርን አወጣ" እያለ ይዘምር ነበር:: በወቅቱ ታዲያ የብህንሳ ኤዺስ ቆዾስ በማረፉ ምትክ ሲያፈላልጉ መንፈስ ቅዱስ አባ ሕርያቆስን መረጠ::

ምንም አለመማሩ ቢያሰጋቸውም "በጸሎቱ: በደግነቱ ሃገር ይጠብቃል" ብለው ሾሙት:: ነገር ግን ምንም በሥልጣን የበላያቸው ቢሆን ተማርን የሚሉ ሰዎች ይጠሉት: ይንቁትም ነበር:: እርሱ ግን እንደ ጠሉኝ ልጥላቸው: እንደ ናቁኝ ልናቃቸው ሳይል በፍቅር ያገለግል ነበር::

አንድ ቀን ታዲያ መንገድ ይወጣል:: በበርሃ ብቻውን እየተራመደ: "ጐሥዐ ልብየ ቃለ ሠናየ" እያለ እየዘመረ: ተመሥጦ ቢመጣበት መንገድ ሳተ:: እርሱ በምስጋናው ሲደሰት እግሩ ግን ከገደል ጫፍ ደርሶ ነበር:: ገደሉን ልብ አላለውም ነበርና ሳይታወቀው ወደ ገደሉ ውስጥ ተወረወረ::

በዚህ ጊዜ ደንግጦ ቢመለከት እጅግ ጥልቅ በሆነ ገደል ውስጥ ራሱን አገኘው:: ነገር ግን አንድም አካሉ አልተነካም:: ልብሱም አልቆሸሸም:: ለራሱ ተገርሞ ዙሪያ ገባውን ሲመለከት እርሱ ቁጭ ያለበት ብርሃንን የተሞላ የልብስ ዘርፍ ነበር::

"እመ ብርሃን!" ብሎ ሲጮህ የሰማይና የምድር ንግሥት የሆነች እመቤታችን ከፊቱ ቁማ ታየችው:: እመ አምላክን በገሃድ ቢያያት እንደ እንቦሳ ዘለለ::

የሚገርመው ደግሞ የተቀመጠበት የድንግል ማርያም የቀሚሷ ዘርፍ ነበር:: እመቤታችን አነጋገረችው: ባረከችው:: ፍቅሯ ቢመስጠው ከሰው ሳይገናኝ: ምግብም ሳይበላ: እዚያው ገደሉ ውስጥ ለ1 ዓመት ያህል በተመስጦ ቆይቷል::

በኋላ እመ ብርሃን መጥታ ከገደሉ አውጥታ ወደ ሐገሩ መለሰችው:: ከጥቂት ጊዜ በኋላም አንድ ፈተና ገጠመው:: አንድ ቀን እመቤታችን በተወለደችበት ግንቦት 1 ቀን ቅዳሴ "ማን ይቀድስ" ሲባል ሰዎቹ "አባ ሕርያቆስ ይሁን" አሉ::

እርሱ ግን "እኔ አይቻለኝም: እናንተ ሊቃውንት ቀድሱ" አላቸው:: "አይሆንም" ብለው እርሱኑ አስገቡት:: ይህንን ያደረጉት ለተንኮል ነበር:: ልክ ወንጌል ተነቦ ፍሬ ቅዳሴ ሲመረጥ እርሱ "እግዚእን (የጌታ ቅዳሴን) ልቀድስ" ቢል እነርሱ "የሚቀደሰው የሊቅ ቅዳሴ ነው" አሉት::

ይህንን ያሉት እርሱ የሊቃውንቱን ቅዳሴ አያውቅምና በሰው ፊት እንዲዋረድ ነው:: እንዲህም ብለው ባለመማሩ ተሳለቁበት:: አባ ሕርያቆስ ግን እያዘነ ወደ መንበሩ ዞረ:: ድንግልንም "እመቤቴ መናቄን: መገፋቴን ተመልከች" አላት::

ወዲያው ግን ድንግል ማርያም ወርዳ ቀጸበችው (ጠራችው):: በዘርፋፋው ቀሚሷ ላይም ረቂቅ የሆነ ቅዳሴን አሳየችው:: ደጉ ሰው ደስ ብሎት "ጐሥዐ ልብየ" ሲል ሁለቱ እግሮቹ ከመሬት ከፍ አሉ:: እርሱም "ወአነ አየድእ ቅዳሴሃ ለማርያም" ብሎ እስከ ኃዳፌ ነፍሱ ድረስ አደረሰው::

ሕዝቡና ካህናቱ በሆነው ነገር ሲደነቁ: አንዳንዶቹ "ዝም ብሎ ነው የቀባጠረ" አሉ:: ቅዱሱ ግን ቅዳሴ ማርያምን በብራና ጠርዞ በሕዝቡ መካከል ድውይ ፈወሰበት:: እሳት ሳያቃጥለው: ውሃ ሳይደመስሰው ቀረ::

መጽሐፈ ቅዳሴው ሙትንም አስነስቷል:: ከዚህች ሰዓት ጀምሮ በዘመኑ ቁጥር 1 ሊቅ ሆነ:: ብዙ መጻሕፍትን ሲተረጉም አጠቃላይ ድርሰቶቹም እልፍ (10,000) ናቸው:: ሊቁ እንዲህ በንጹሕ ተመላልሶ ዐርፏል:: ይህቺ ቀን ለቅዱሱ የልደቱና ዕረፍቱ መታሰቢያ ናት::

††† ታላቁ ቅዱስ ሳዊሮስ †††

††† ቅዱስ ሳዊሮስ በ6ኛው መቶ ክ/ዘመን መጀመሪያ አካባቢ በሶርያ አንጾኪያ የተነሳ አባት ነው:: ወቅቱ መለካውያን (2 ባሕርይ ባዮች) የሰለጠኑበት እንደ መሆኑ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን ያነሱበትና የሚሰደዱበት ጊዜ ነበር:: በዚህ ጊዜ ነበር ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ሳዊሮስ በሥላሴ ፈቃድ ለቤተ ክርስቲያን የተነሳው:: ሊቃውንት "አንበሳ" ሲሉ ይጠሩታል::

ቅዱሱ ለተዋሕዶ ሃይማኖት ብዙ ሆኖላታል:: የመናፍቃን ጸር በመሆኑ ብዙ ድርሰቶችን ደርሷል:: ንጉሡን ዮስጢያኖስን (Justinian) ሳይቀር በይፋ ይገስጸው ነበርና ንጉሡ ሊገድለው ቆረጠ::

ሃይማኖቷ የቀና ንግሥቲቱ ታኦድራ ግን ይህንን ስትሰማ በሌሊት ወደ ሊቁ ሒዳ "እባክህን ሽሽ" አለችው:: እርሱ ግን "ሞት ለእኔ ክብር ነውና አልሔድም" ሲል መለሰላት:: አባቶችን ሰብስባ "ስለ ቤተ ክርስቲያን ስትል" ብለው ለምነው ወደ ግብጽ ሸኙት::

እርሱ እየሔደ ገዳዮቹ ያሳድዱት ገቡ:: መንገድ ላይ ቢደርሱበትም ተሰወረባቸው:: ለብዙ ቀናትም አብሯቸው ተጓዘ:: እነርሱ ተስፋ ቆርጠው ሲመለሱ እርሱ ግን ምድረ ግብጽ ደረሰ::

በምድረ ግብጽም የዽዽስና ልብሱን ትቶ የመነኮሳትን አሮጌ ልብስ ለብሶ ሕዝቡንና መነኮሳቱን አስተማረ: አጸና:: በየቦታውም ብዙ ተአምራትን ሠራ::

አባቶች መነኮሳትም ማንነቱን ባወቁ ጊዜ ሰገዱለት:: ዶርታኦስ (ዱራታኦስ) በሚባል አንድ ደግ ሰው ቤትም በ6ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ አካባቢ የካቲት 14 ቀን ዐርፏል:: ይህቺ ቀን ዕለተ ስደቱ ናት::

††† አምላከ ቅዱሳን ሊቃውንት የድንግል እመቤታችንን ጣዕሟን ፍቅሯን ያሳድርብን:: የአበውን ሃብትና በረከትም አይንሳን::

††† ጥቅምት 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ሊቁ አባ ሕርያቆስ
2.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
3.ቅድስት ቴክላ ሰማዕት
4.አቡነ ማቲያስ ዘፈጠጋር (የአቡነ ተክለሐይማኖት የመንፈስልጅ)

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
2.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
3.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
4.ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ)
5.ቅዱስ ዮሐንስ ነቢይ (መጥምቀ መለኮት)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

+ የታላቋ ሰማዕት የቅድስት አናስታሲያ(አንስጣስያ) ስለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥም ስትል የተቀበለቻቸው ሥቃዯች።+

የምሥራቅ ኦርቶዶክስ አብያተክርስትያናት የሰማዕቷን የቅድስት አናስታሲያ(አንስጣስያ) የተቀበለቻቸውን መከራዎች " መኰንኑ ፕሮቡስ ይህን መልሷን በሰማ ጊዜ ያሸማቅቃት ዘንድ ያለ ልብስ እርቃኗን አቆማት በዚህ ጊዜ ሰማዕቷ ቅድስት አናስታሲያ " ምታኝ ግረፈኝ ቆራርጠኝም በቁስሎቼ እርቃኔ ይሸፈናልና በደሜ ኃፍረቴ ይከደናልና።" አለችው በዚህ ጊዜ መኰንኑ ፕሮቡስ ዘግናኝ በሆነ ሥቃይ አሰቃያት ነገር ግን ታላቋ ሰማዕት ቅድስት አናስታሲያ እግዚአብሔርን እያመሰገነች ሥቃዩን ተቋቋመችው ውሐ በተጠማች ጊዜ ውሐ ይሰጧት ዘንድ ለመነች በዚህ ጊዜ ቄርሎስ የሚባል ክርስትያን ወጣት ውሐ አምጥቶ ሰጣት እርሷም አመሰገነችው ነገር ግን መኰንኑ ፕሮቡት ወጣቱ ቄርሎስ ለሰማዕቷ ለቅድስት አናስታሲያ ውሐ ስለሰጣት አንቱን በሰይፍ አስቆረጠው። የሚያሰቃዯትም በዚህም አላቆሙም ሁለቱን ደረቶቿን* ቆረጡ ( *ደረት ሥል በሴት ልጅ ደረት ላይ ስለሚገኙት ማለቴ ነው።) ምላሷንም ጎልጉለው አወጡ የእግዚአብሔር መልአክ እየተገለጠ ይፈውሳት ነበር ይህን የሰማዕቷን ስቃይ ለማየት የተሰበሰበው ሕዝብም ኢሰብዓዊ የሆነ እና ጭካኔ የተመላበትን ድርጊት በሰማዕቷ በቅድስት አናስታሲያ ላይ ሲመለከቱ እጅግ አዘኑ መኰንኑ ፕሮቡስንም ተቃወሙት የሕዝቡን ተቃውሞ የተመለከተው ፕሮቡስም ሁሉም ሕዝብ አንገታቸውን እንዲሰየፉ ለወታደሮቹ ትዕዛዝ ሰጠ ወታደሮቹም የሕዝቡን ሁሉ አንገታቸውን ሰየፉ። " ብለው ሲጽፉ… የግብጽ እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተክርስትያናት የስንክሳር መጽሐፍ ደግሞ በዚያን ጊዜ ጽኑ ሥቃይን አሠቃያት በሥጋዋም እሳትን ጨመረ ከዚህም በኋላ ዘቅዝቆ ሰቀላት ከበታቿም [እሳት] አጤሱባት።" ብለው ጽፈዋል።

+የታላቋ ሰማዕት የቅድስት አናስታስያ(አንስጣስያ) ሰማዕትነት።+

ከዚህ በኋላ ታላቋ ሰማዕት ቅድስት አናስታሲያ(አንስጣስያ) ዘሮሜ ከሃይማኖቷ ባልተናወጸች ጊዜ ራሷን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ በዚህ በታላቅ ሥቃይም ውስጥ ሳለች ራሷን በሰይፍ ቆረጧት። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለች። በምሥራቅ ኦርቶዶክስ አብያተክርስትያናት እንደተጻፈው መኰንኑ ፕሮቦስ ሰማዕቷን ቅድስት አናስታሲያ(አንስጣስያን) ካሰየፈ በኋላ አራዊት እንዲበሉት ወደ ውጪ እንዲጣል አዘዘ ነገር ግን እግዚአብሔር የወዳጁን የታላቋ ሰማዕት የቅድስት አናስታሲያን(አንስጣስያ) ሥጋን ከክፉ ሁሉ ጠበቀው የእግዚአብሔር መልአክ ለቅድስት እመምኔት ሶፍያ ተገልጦላት የሰማዕቷ የቅድስት አናስታሲያ(አንስታስያ) ዘሮሜ የተቀደሰ ሥጋ ያለበትን ነገራት ቅድስት እመምኔት ሶፍያም ወደ ተባለችበት ቦታ ሄዳ የታላቋን ሰማዕት የቅድስት አንስታሲያ(አንስጣስያ) ዘሮሜን ሥጋዋን አግኝታ ከሁለት ክርስትያን ሰዎች ጋር በመተጋገዝ በክብር ቀበረችው።

በአሁኑ ሰዓት የታላቋ ሰማዕት የቅድስት አናስታሲያ(አንስጣስያ) ቅዱስ አካል የቀኝ እግሯ በግሪክ አገር በአቶስ ገዳም በግሪጎርዩ ክፍለ ገዳም የሚገኝ ሲሆን ቆዳዋ ሳይፈርስ ሳይበሰብስ ይታያል። ከቅዱስ አካሏ የተወሰነው ክፍል ደግሞ በሩሲያ በቅዱስ አሌክሳንደር ናቪስኪ ገዳም ይገኛል። ታላቋ ሰማዕት ቅድስት አናስታሲያ(አንስጣስያ) የምታደርጋቸው ታላላቅ ተአምራት እጅግ አስደናቂዎች ናቸው በእውነት ከቃላት በላይ ናቸው ልንላችሁ የምንችለው በአማላጅነቷ ታምናችሁ እዩት ነው።

የግብጽ እና የኢትዮጵያ አብያተክርስትያናት የታላቋ ሰማዕት የቅድስት አናስታሲያን(አንስጣስያ) በዓል ጥቅምት አንድ ቀን ያከብራሉ። ከምሥራቃውያን ደግሞ የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ጥቅምት 18 ቀን ታከብራለች።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የስንክሳር መጽሐፍ የአርኬ ምስጋና ለሰማዕቷ ለቅድስት አናስታሲያ(አንስጣስያ) የቀረበው ምስጋና እንዲህ ተጽፏል።

የአርኬው ምስጋና ይህ ነው።

በግዕዝ
"ሰላም ለአንስጣስያ አዘጥብዓት ኵሎ መዋዕለ። ከመ ኢትብላዕ ምንተኒ በእሳት ብሱለ። እምድኅረ ፈጸመት ዘንተ ዘመናንያን ገድለ። ወሰላም እብል ለምትረተ ርእሳ ከዋለ። ወለሶስና እኤምኅ ድንግለ።"

በአማርኛ
" በእሳት የበሰለ በዘመኗ ሁሉ እንዳትበላ ለጠነከረች (ለጨከነች) ለአንስጣስያ ሰላምታ ይገባል። ይህንን የመናንያን ገድልን ከፈጸመች በኋላ ከጀርባ በኩል ለራሷ መቆረጥ ሰላም እላለሁ። ድንግል ሶስናን ሰላም እላለሁ።"
*የአማርኛ ትርጉም በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ።*

ከታች የምትመለከቱት የታላቋ ሰማዕት የቅድስት አናስታሲያ(አንስጣሲያ) ትክክለኛ ቅዱሳን ሥዕላት ናቸው መለያዋም በምንኵስና ልብስ ተሸፋፍና መስቀልና የጸሎት መቍጠርያ እንደያዘች እንዲሁም የተጠቀለለ ጽሑፍ ይዛ እጆቿ እንደተዘረጉ ነው። በዋናነት ተለይታ በምትታወቅበት በግሪክ ቋንቋ "Η Αγία Αναστασία η Ρωαία ኢ አጊያ አናስታሲያ ኢ ሮሜያ" ቅድስት አናስታሲያ "ዘ ሮሜ " ተብሎ ተጽፎበታል። በሥም መመሳሰል ነገር ግን የተቀደሰ የሕይወት ታሪካቸው ሆነ ቅዱሳን ሥዕላቸው አንድ ያልሆኑ ብዙ ቅዱሳን አሉ ስለሆነም የተቀደሰ ታሪካቸውን በደንብ ማጥናትና ደጋግሞ ማንበብ የተቀደሰውን ሥዕላቸውን ረጅም ጊዜ ወስዶ ፈልጎ ማግኘት ይገባል።

በዚህ ጊዜ ክርስትያኖች በተለይም ኦርቶዶክሳውያን ለሚያጋጥመን ፈተና ብርታት እንድናገኝ እንደነዚህ ያሉ ቅዱሳን ሰማዕታት እናቶችን የተቀደሰ የሰማዕትነት ታሪክ ከማንበብ አንራቅ። ጊዜው የሰማዕትነት ነውና።

በታላቋ ሰማዕት በቅድስት አናስታሲያ(አንስጣስያ) ዘሮሜ ጸሎት እና አማላጅነት ለኢትዮጵያ እና ለዓለም ሰላምን ምሕረትን እንዲሰጥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በታላቋ ሰማዕት በቅድስት አናስታሲያ(አንስጣሲያ) ጸሎት ይማረን በረከቷም ለዘለዓለሙ ከእኛ ጋር ጸንቶ ይኑር አሜን አሜን አሜን።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የገነት አበባ መዓዛሽ ሠናይ
እንደ እርግብ ወረደ ፍቅርሽ ከሰማይ
የምስራቅ ውበት ነሽ የፅዮን ሙሽራ
ፊትሽ እንደ ፀኃይ ከሩቅ የሚያበራ
ሚስጥሩ ጥልቅ ነው እፁብ ያንቺ ስራ
እናቴ እመቤቴ ማርያም ሆይ የነገርኩሽን አደራ አደራ!!!

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/VeLOGu13QaQ?si=mp6PSgYzBJTksowk

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሴቶች ከወለዷቸው መካከል እንደ ዮሐንስ መጥምቅ ያለ አልተነሳም

****ዮሐንስ መጥምቅ በ7 ነገሮች ከሰው ልጇች ይለያል****

1 ) ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ ሲወለድ የአባቱን አንደበት የከፈተ ብቸኛው ልጅ ዮሐንስ መጥምቅ ነው

2) አባቱ ዘካርያስ በግፍ ተገድሎ እናቱ ኤልሳቤጥ ወደበረሃ ይዘው ተሰዳ ሳለ ትታው ሙታ በበርሃ ያለ ሰው ከአጋዘን ጋር የኖረ ያደገ ብቸኛ ልጅ ዮሐንስ መጥምቅ ነው

3 ) ሰዎች የሚለብሱትን ልብስ ሳይለብስ የግመል ጠጉር የለበሰ መጥምቁ ዮሐንስ ነው በበርሃ ሲኖር እናቱ ከግመል ጠጉር እና ገመሎ ከተባለ እንጨት ጪረቱን ታታ ጠጉሩን ፈትላ አልብሰዋለች።

4 )ሠዎች የሚመገቡትን ያልተመገበ ምግቡ አንበጣ (የጋጃ መዓር )ነበር ።

5,የሰማይና የምድርን አምላክ ያጠመቀ መጥምቀ መለኮት የተባለ ብቸኛው የሰው ልጅ ዮሐንስ ነው

6) አንገቱን ተቆርጦ በሰማእትነት ካረፈ በኋላ ራሱ ክንፍ አውጥታ ለ15 ዓመታት ከሞት በኋላ ዓለምን ዙሮ ያስተማረ ዮሐንስ መጥምቅ ነው።

7) የአዲስ ዓመት መጀመሪያ ሁኖ በስሙ ቅዱስ ዮሐንስ ተብሎ የተሰየመለት ብቸኛው የሰው ልጅ ዮሐንስ ወልደ ዘካርያስ ነው ስለዚህ ሴቶች ከወለዷቸው መካከል እንደ ዮሐንስ መጥምቅ ያለ አልተነሳም ብሎ ወንጌላዊ ማቴዎስ ጽፏል ማቴ 11፤11
መስከረም 2 ቅዱስ ዮሐንስ በሰማእትነት ያረፈበት ነው
የመጥምቀ መለኮት ዮሐንስ አማላጅነት አይለየን

መጋቤ ሐዳስ ሄኖክ ፈንቴ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለታላቁ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ሊቀ ዻዻሳት እና ለአባ ሣሉሲ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ †††

††† በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከሐዋርያት ቀጥሎ የቅዱስ አትናቴዎስን ያሕል ስለ ሃይማኖት የተዋጋ ቅዱስ ፈልጐ ማግኘት አይቻልም::

††† ቅዱስ አትናቴዎስ ማን ነው?

††† ቅዱስ አትናቴዎስ በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት በዘመነ ሰማዕታት መጠናቀቂያ (በ300 አካባቢ) እስክንድርያ ግብፅ ውስጥ ነው የተወለደው:: ወላጆቹ አረማውያን በመሆናቸው ክርስትናን አልተማረም ነበር::

ሕጻን እያለ ለጭዋታ ከቤቱ ሲወጣ የክርስቲያን ልጆች ሃይማኖታዊ ጨዋታ ሲጫወቱ ተመለከተ:: ሊቀላቀላቸው ቢፈልግም ክርስቲያን ባለመሆኑ ከለከሉት:: አትናቴዎስም ክርስቲያን ልሁንና አጫውቱኝ ብሏቸው እሺ ስላሉት ሕጻናቱ ዕጣ ተጣጣሉ::

ላንዱ ቄስ: ላንዱም ዲያቆን መሆን ሲደርሳቸው ለአትናቴዎስ ፓትርያርክ መሆን ስለ ደረሰው ሌሎቹ ሕጻናት ይሰግዱለት ጀመር:: በአጋጣሚ ሕጻናቱ ይሕንን ሁሉ ሲያደርጉ የወቅቱ ፓትርያርክ ቅዱስ እለእስክንድሮስ በመገረም ያያቸው ነበርና ለሕጻኑ አትናቴዎስ ትንቢት ተናገረለት::

ከዚያም የአትናቴዎስ አባቱ ሲሞት ሊቀ ዻዻሳቱ ከእናቱ ወስዶ አጥምቆ: የሚገባውን መንፈሳዊ ትምሕርት ሁሉ በልቡናው ላይ ቀረጸበት:: ከዚሕ በኋላ ዲቁናን ሹሞ አስተምር አለው:: ምንም ሕጻን ቢሆንም ከሊቅነቱ: ከአመላለሱና ከአንደበቱ ጣፋጭነት የተነሳ የሰማው ሁሉ ይደነቅ ነበር:: ጸጋ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ አድራለችና::

ቅዱስ አትናቴዎስ ሊቀ ዲቁና በተሾመ ወራት አርዮስ ቤተ ክርስቲያንን በመረበሹ ኒቅያ ላይ 318ቱ ሊቃውንት ሲሰበሰቡ ጸሐፊ አድርገው ሾሙት:: በጊዜውም በዕድሜ የስንት ጊዜ ትልቁ የሚሆነውን አርዮስን ተከራክሮ ምላሽ አሳጣው:: ቅዱስ አትናቴዎስ ከሊቃውንቱ ጋር ሆኖ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ: እግዚአብሔር መሆኑን በአደባባይ መሠከረ:: ጸሎተ ሃይማኖትንም ያረቀቀው እርሱ ነው::

ከዚሕ በኋላ የእስክንድርያ (የግብፅ) 20ኛ ፓትርያርክ ሆኖ ተሾመ:: ቤተ ክርስቲያንን በመልካም እረኝነት ለ48 ዓመታት ሲመግብ ብዙ መከራዎችን ተቀበለ:: ለ5 ጊዜ ከመንበሩ አፈናቅለው ወደ በርሃ ሲያግዙት በስደት ከ15 ዓመታት በላይ አሳልፏል::

በተሰደደባቸው ቦታዎች መከራን እየተቀበለ ያላመኑትን አሳምኗል:: በጎቹ እንዳይባዝኑበት ደግሞ በጦማር (በደብዳቤ) ይጠብቃቸው ነበር:: ዛሬ በሃይማኖተ አበው የምናገኘው ቃለ ሃይማኖት በዚሕ ዘመን የተጻፈ ነው:: ሐዋርያዊው ቅዱስ ስለ ኦርቶዶክስ ተዋግቶ: ብዙ ስቃይንም ተቀብሎ በ370ዎቹ ዓ/ም አካባቢ አርፏል::

††† ቤተ ክርስቲያን
¤ሊቀ ሊቃውንት:
¤ርዕሰ ሊቃውንት:
¤የቤተ ክርስቲያን /የምዕመናን/ ሐኪም (Doctor of the Church):
¤ሐዋርያዊ ብላ ታከብረዋለች::

††† ይህች ዕለት ለታላቁ ሊቅ የስደቱ መታሠቢያ: ከስደቱም የተመለሰባት ቀን ናት::
ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
በወቅቱ የነበረው ንጉሥ (ትንሹ ቆስጠንጢኖስ) የአባቱን (ታላቁ ቆስጠንጢኖስን) ዕረፍት ተከትሎ ነገሠ::

ወዲያውም አርዮሳዊ መ******ና********ፍ**********ቅ ሆነ:: ሃይማኖታቸው የቀና አባቶችንም ያሳድድ ገባ:: ከአበው ቅዱሳን መካከል ግን የዚህ መከራ ቀዳሚው ገፈት ቀማሽ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ አትናቴዎስ ነበር::

በተለይ አንድ ጊዜ ንጉሡ ቅዱሱን ወደ በርሃ አግዞ: መ**********ና********"ፍ*********ቅ ዻዻስ በግብጽ ሹሞ: ብዙ ክርስቲያኖችን በግፍ ሲያስገድል: ቅዱሱን ለ6 ዓመታት አሰቃየው:: የወገኖቹ (የልጆቹን) ስቃይ የሰማው ቅዱስ አትናቴዎስ ግን በድፍረት ወደ ቤተ መንግስት ገብቶ ተናገረው::

ሁለት አማራጭን አቅርቦ "ወይ ግደለኝና እንደ አባቶቼ ሰማዕት ልሁን: ካልሆነ ግን ወደ መንጐቼ (ምዕመናን) መልሰኝ" አለው:: መ*******ና*********ፍ*********ቁ ንጉሥም ቢገድለው ብጥብጥ እንደሚነሳ ስለሚያውቅ በስልት ሊያጠፋው ወሰነ::

ቀዛፊ: መቅዘፊያ: ምግብና ውሃ በሌላት ጀልባ ውስጥ ከቶም ሜዲትራኒያን ባሕር ውስጥ ጣለው:: ድንገት ግን ከሰማይ ጌታችን መላእክቱን አስከትሎ ወረደ::

ሚካኤልና ገብርኤል ባሕሩን እየቀዘፍ: ሌሎች መላእክት እየመገቡት በዚህች ቀን እስክንድርያ(ግብጽ) አድርሰውት ተሠውረዋል:: ሕዝቡም በታላቅ ሐሴት እየዘመሩ አባታቸውን ተቀብለውታል::

††† አባ ሣሉሲ ክቡር †††

††† የእኒህ አባት ዜና ሕይወትን ሳስበው እጅግ ይገርመኛል:: የአባቶቻችን የሕይወት ፈሊጥ ምን እንደ ሆነ እንድረዳ ስላደረጉኝ በእውነቱ አመሰግናቸዋለሁ:: ጻድቁ የዘመነ ከዋክብት አንድ ፍሬ ናቸው::

በነበሩበት ገዳም የሚታወቁት ግን 'የማይጾመው: የማይጸልየው: ሥራ ፈቱ መነኩሴ' በሚል ነበር:: ገዳሙ ውስጥ ከሚኖሩ መነኮሳት መካከል አንድም ቀን ቢሆን ሲጸልዩና ሲሰግዱ ያያቸው የለም:: ሁሌ ብቻ እንደ ሞኝ ቁጭ ብለው ያኝካሉ::

በዚህ ምክንያትም ሥጋ ወደሙን ወስደው አያውቁም:: አንድ ቀን ግን በገዳሙ በዓል ላይ አበምኔቱና መነኮሳቱ መከሩ:: 'አባ ሣሉሲን አሥረን አውለን ለቁርባን ቢያንስ እናብቃቸው' ሲሉ ወሰኑ:: በውሳኔው መሠረትም በጧት ሒደው ጻድቁን አሠሯቸው::

አባ ሣሉሲም "ፍቱኝ ቁርሴን ልብላበት" ሲሉ ተቆጡ:: መነኮሳቱ ግን "ሳትቆርብ አንለቅህም" አሏቸው:: በዚህ ጊዜ ጻድቁ ቆባቸውን አውልቀው " እመቤቴ የሰው ልጅስ ጨካኝ ነው:: አንቺ ግን ርሕርሕት ነሽ" ብለው በቆባቸው ግድግዳውን ቢመቱት ለ2 ተሰነጠቀ::

እርሳቸውም 2 ክንፍ አውጥተው በረው ተሰወሩ:: ባዩት ነገር የደነገጡ መነኮሳት እያለቀሱ 300 ጊዜ "እግዚኦ . . ." አሉ:: በዚህ ጊዜ የጻድቁን ቆብ አገኙ:: በዚህች ቆብም አጋንንትን አሳደዱ ተአምራትንም ሠሩ::

††† ምሥጢሩስ ምንድን ነው ቢሉ: አባ ሣሉሲ:-
1. 24 ሰዓት ሙሉ በተመስጦ (በልባቸው) ስለሚጸልዩ::
2. በጧት ተነስተው የሚያኝኩት ደረቅ ሣር እንጂ ምግብ አልነበረምና ነው:: ከውዳሴ ከንቱ መራቅ ማለት ይሔው ነው:: ጻድቁ በዚህች ቀን ዐርፈው ተቀብረዋል::

††† አምላከ አበው ምሥጢራቸውን አይሰውርብን:: ከበረከታቸውም ያድለን::

††† መስከረም 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
2.አባ ሣሉሲ ክቡር ጻድቅ
3.ቅዱሳን ያዕቆብና ዮሐንስ ሐዋርያት (ለወንጌል የተጠሩበት /ማር. 1:19/)
4.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘአርማንያ
5.አባ አብሳዲ ዘደብረ ማርያም
6.አባ አሮን ዘገሊላ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ (ሐዋርያ)
2.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
4.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት

††† "ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብጹዓን ናቸው:: መንግስተ ሰማያት የእነርሱ ናትና:: ሲነቅፏችሁና ሲያሳድዷችሁ: በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብጹዓን ናችሁ:: ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ:: ሐሴትንም አድርጉ:: ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳደዋቸዋልና::" †††
(ማቴ. ፭፥፲)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1. ሰባቱ አባቶች

ሀ. ሰማያዊ አባት እግዚአብሔር
ለ. የነብስ አባት
ሐ. ወላጅ አባት
መ. የክርስትና አባት
ሠ. የጡት አባት
ረ. የቆብ አባት
ሰ. የቀለም አባት

2. ሰባቱ ዲያቆናት

ሀ. ቅዱስ እስጢፋኖስ
ለ. ቅዱስ ፊልጶስ
ሐ. ቅዱስ ጵሮክሮስ
መ. ቅዱስ ጢምና
ሠ. ቅዱስ ኒቃሮና
ረ. ቅዱስ ጳርሜና
ሰ. ቅዱስ ኒቆላዎስ

3. ሰባቱ የጌታ ቃላት(እኔ ነኝ)

ሀ. የህይወት እንጀራ እኔ ነኝ
ለ. የአለም ብርሃን እኔ ነኝ
ሐ. እኔ የበጎች በር ነኝ
መ. መልካም እረኛ እኔ ነኝ
ሠ. ትንሳኤና ህይወት እኔ ነኝ
ረ. እኔ መንገድ እና ህይወት ነኝ
ሰ. እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ

4. ሰባቱ ሰማያት

ሀ. ጽርሐ አርያም
ለ. መንበረ መንግስት
ሐ. ሰማይ ውዱድ
መ. እየሩሳሌም ሰማያዊት
ሠ. ኢዮር
ረ. ራማ
ሰ. ኤረር

5.ሰባቱ ሊቃነ መላዕክት

ሀ. ቅዱስ ሚካኤል
ለ. ቅዱስ ገብርኤል
ሐ. ቅዱስ ሩፋኤል
መ. ቅዱስ ራጉኤል
ሠ. ቅዱስ ዑራኤል
ረ. ቅዱስ ፋኑኤል
ሰ. ቅዱስ ሰቂኤል

6. ሰባቱ አቢያተ ክርስቲያናት

ሀ. የኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን
ለ. የሰርምኔስ ቤተ ክርስቲያን
ሐ. የጴርጋሞን ቤተ ክርስቲያን
መ. የትያጥሮስ ቤተ ክርስቲያን
ሠ. የሴርዴስ ቤተ ክርስቲያን
ረ. የፊልድ ልፍልያ ቤተ ክርስቲያን
ሰ. የሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያን

7. ሰባቱ ተዓምራት
ጌታ እየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈፀሙ ተዓምራት

ሀ. ፀሐይ ጨልሟል
ለ. ጨረቃ ደም ሆነ
ሐ. ከዋክብት ረገፉ
መ. አለቶች ተሰነጣጠቁ
ሠ. መቃብራት ተከፈቱ
ረ. ሙታን ተነሱ
ሰ. የቤተ መቅደስ መጋረጃ

8. ሰባቱ የመስቀሉ ቃላት

ሀ. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ
ለ. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው
ሐ. ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ
መ. እነሆ ልጅሽ እናትህ እነሆት
ሠ. ተጠማሁ
ረ. ተፈፀመ
ሰ. አባት ሆይ ነብሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ

9. ሰባቱ ሚስጥራተ ቤተ ክርስቲያን

ሀ. ሚስጥረ ጥምቀት
ለ. ሚስጥረ ቁርባን
ሐ. ሚስጥረ ክህነት
መ. ሚስጥረ ሜሮን
ሠ. ሚስጥረ ተክሊል
ረ. ሚስጥረ ንሰሃ
ሰ. ሚስጥረ ቀንዲል

10. ሰባቱ አፅዋማት

ሀ. አብይ ፆም
ለ. የሐዋርያት ፆም
ሐ. የፍልሰታ ፆም
መ. ፆመ ነቢያት
ሠ. ፆመ ገሀድ
ረ. ፆመ ነነዌ
ሰ. ፆመ ድህነት

11. ሰባቱ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠሉ ነገሮች

ሀ. ትዕቢተኛ አይን
ለ. ሐሰተኛ ምላስ
ሐ. ንፁህ ደምን የምታፈስ እጅ
መ. ክፉ ሐሳብ የምታፈልቅ ልብ
ሠ. ለክፋት የምትፈጥን እጅ
ረ. የሐሰት ምስክርነት
ሰ. በወንድማማቾች መካከል ፀብን የምታፈራ ምላስ

12.ሰባቱ ፀሎተ ጊዜያት

ሀ. ነግህ (የጠዋት ፀሎት)
ለ. ሰለስት (የ 3 ሰዓት ፀሎት)
ሐ. ቀትር (የ 6 ሰዓት ፀሎት)
መ. ተሰዓቱ (የ 9 ሰዓት ፀሎት)
ሠ. ስርክ (የ 11 ሰዓት ፀሎት)
ረ. ነዋም (የመኝታ ፀሎት)
ሰ. መንፈቀ ሌሊት (የሌሊት ፀሎት)
ሼር ሼር ይደረግ ለሌሎችም አድርሱ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ነገ እኮ መስከረም 29 #ቅድስት_አርሴማ

✝️እዉነተኛዋ የአምላካችን #የክርስቶስ ምስክር ለሆነችው ለሰማእቷ #ለቅድስት_አርሴማ ሰማእት ለሆነችበት አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

✝️በዚችም ቀን ከቅድስት አርሴማና ከእመምኔቷ ከአጋታ ጋር ደናግል በሰማዕትነት አረፉ ይህም እንዲህ ነው በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን እርሱ መልኳ ውብ የሆነ ብላቴና ድንግል ሊአገባ ሽቶ በየሀገሩ ሁሉ ሒደው መርጠው ያመጡለት ዘንድ አሽከሮቹን አዘዘ

✝️ይችንም የሚመስላት የሌለ ቅድስት አርሴማን በሮሜ አገር በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ አገኙዋት ሥዕሏንም ሥለው ለንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ላኩለት ንጉሡም ሥዕሏን በአየ ጊዜ እጅግ ደስ አለውና ለሠርግ እንዲመጡ ወደ መኳንንቱ ላከ

✝️እሊያ ደናግልም ይህን ነገር በአወቁ ጊዜ ይረዳቸው ዘንድ ድንግልናቸውንም ይጠብቅ ዘንድ አልቅሰው ወደ እግዚአብሔር ለመኑ ከዚህም በኋላ ተነሥተው በሥውር ሸሹ የንጉሥ ድርጣድስ ግዛት ወደ ሆነ ወደ አርማንያ ሀገርም ደርሰው በአንድ ቦታ ተቀመጡ ከእርሳቸውም ጋር የተሰደዱ ቁጥራቸው ሰባ አምስት የሆነ ወንዶች ሴቶችም ሠላሳ ዘጠኝ የሆኑ ከእርሳቸው ጋራ አሉ ምግባቸውን አያገኙም ነበርና በታላቅ ችግር ውስጥ ኖሩ ከእነርሱም መብራት የምትሠራ አንዲት ሴት ነበረች ከእርሷም የእጅ ሥራ ከሚገኘው በየጥቂቱ ይመገባሉ

✝️ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም የከበረች አርሴማን በፈለጋት ጊዜ አላገኛትም ግን በአርማንያ አገር እንዳለች ስለርሷ ሰማ ደግሞ ለአርማንያ ንጉሥ ለድርጣድስ ስለርሷ ከዲዮቅልጥያኖስ ሸሽታ እንደ መጣች #የአርሴማን ሥራ ነገሩት እርሱም አንዱን የአርማንያ መኰንን ለእኔ ጠብቃት ወደ እኔም ላካት ብሎ አዘዘው

✝️ደናግሉም ይህን በሰሙ ጊዜ ወደ ሌላ ቦታ ተሠወሩ ወደ ንጉሥም ወነጀሉአቸው ንጉሡም #ቅድስት_አርሴማን በክብር አድርገው ያመጧት ዘንድ አዘዘ እርሷም ወደ እርሱ መምጣትን እምቢ በአለች ጊዜ እየጎተቱ ወስደው ወደርሱ አደረሷት

✝️የቅድስት #አርሴማንም ላህይና ደም ግባቷን በአየ ጊዜ ድንግልናዋን ሊያረክስ ሽቶ እናቷ አጋታን አባብላ እሺ ታሰኝለት ዘንድ አዘዛት አጋታም ወደርሷ ሒዳ ልቧን አስጨከነች እንዲህም አለቻት ዕወቂ ይህ ርኲስ አረማዊ እንዳያረክስሽና ሰማያዊ ሙሽራሽን እንዳትተዪ እርሱም ክብር ይግባውና የእግዚአብሔር ልጅ ሕያው #ክርስቶስ ነው

✝️ንጉሡም ይዞ ወደ እልፍኙ ሊአስገባት ከአደባባይ መካከል ተነሥቶ ድንግል አርሴማን ያዛት በዚያንም ጊዜ በቅድስት አርሴማ ላይ #የእግዚአብሔር ኃይል አደረባትና በምድር ላይ ጣለችው እርሱ ግን በጦርነት እጅግ የጸና አርበኛ ስለ ነበር በታናሽ ሴት ብላቴና ስለተሸነፈ ያን ጊዜ አፈረ ራሷንም በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና ቆረጧት ከዚህም በኋላ ደናግሉን ሁሉ ከእናታቸው አጋታ ጋር ይገድሏቸው ዘንድ አዘዘ

✝️አንዲት የታመመች ድንግል ነበረች በዐልጋዋ ላይም እንደተኛች ወደ ወታደሮች ጮኸች መጥተውም እንደ እኅቶቿ ራሷን ቆረጡ ሁሉም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ እነዚያንም ከሮሜ አገር አብረው የመጡ ወንዶችን ገደሏቸው ቁጥራቸውም ሰባ አምስት ናቸው ሥጋቸውም በተራራ ላይ የተጣለ ሁኖ ቀረ

✝️ሰማዕታትም ከተገደሉ በኋላ በንጉሡ ላይ ጋኔን ተጫነበት መልኩም ተለውጦ እንደ እርያ ሆነ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ወደርሱ መጥቶ በላዩ ጸልዮ እስከ አዳነው ድረስ ስለዚህም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ የቅዱሳን ሰማዕታትንም ሥጋቸውን ከተጣለበት ሰብስበው በአማረ ቦታ አኖሩአቸው ያማረች ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንም ተሠራችላቸው ከእነርሱም ታላላቅ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ

✝️✝️✝️ #ስንክሳር_ዘተዋህዶ

✝️በምልጃ በፀሎትሽ እንዲሁም በቃል ኪዳንሽ ለሚያምኑ ፈዉስና መድኃኒት የሆንሽ ፀሎትና ልመናን ከአይን ጥቅሻ ፈጥነሽ የምትሰሚ እናታችን #ቅድስት_አርሴማ ሀገራችንን ከጥፋት ህዝባችንን ከዲያብሎስ ፈተና አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ያድን ይጠብቅ ዘንድ ለምኝልን "አሜን"

✝️✝️✝️ 💚 💛 ❤ ✝️✝️✝️

Читать полностью…
Subscribe to a channel