ጥቅምት 17/2016 #ቅዱስ_እስጢፋኖስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በሰማእቱ ስም ለምናመሰግንበት ሰማእቱ #ቅዱስ_እስጢፋኖስን በፀሎቱ እንዲያስበን ለምንማፀንበት አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉ሰማእቱ #ቅዱስ_እስጢፋኖስ በዚህ እለት የተሾመበት እለት ነዉ የተዋህዶ ልጆች ስለምን ቀዳሜ ሰማዕት ተሰኘ ቅዱስ እስጢፋኖስ ካልን ከኢየሱስ በኋላ እራሱን የሰጠ የመጀመሪያው ሰው ስለሆነ ነው።
👉ቀዳሜ ሰማእት #ቅዱስ_እስጢፋኖስ የዲያቆናት አለቃ የሆነ እየወገሩት እንደ ሀጢአት አትቁጠርባቸው ያለ ደሙ እየተንፀፈፀፈ ምህረትን የለመነ ለሐዋርያት ይታዘዝና ያገለግላቸው የነበረ ፊቱ እንደ መልአክ ያበራ የነበረ የሐዋ ስራ ምዕ፣6 ከ 8-15 ብዙዎችን ወደ ሀይማኖት የመለሰ ወንጌላዊ ቅዱስ እስጢፋኖስ አባቱ ስምዖን እናቱ ሐና ይሰኛሉ
👉ቅዱስ እስጢፋኖስ የተወለደው ጥር 1 እረፍቱም ጥር 1 ሹመቱ ጥቅምት 17 መስከረም 15 ሥጋው የፈለሰበት ቀን ነው በረከቱ ይደርብን እንኳን አደረሰን አደረሳቹህ የተባረከ የተቀደሰ #ቀዳሚት_ሰንበት ይሁንልን "አሜን" 💒 💚 💛 ❤ 💒
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ስርዓተ ማህሌት ዘጥቅምት ፲ወ፯ በዓለ እስጢፋኖስ
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
ስርዓተ ነግሥ፦
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
@menkir_tube
@menkir_tube
መልክዓ ስላሴ
ሰላም ለአቊያጺክሙ እለ ተኀብዓ እም ዐይን፤አናምያኒሁ ሥላሴ ለሜላተ ሰማይ ብርሃን፤ልብሰ ሰማዕትና ይኩነኒ ምህረትክሙ ኪዳን፤ላእሌየ እስመ ኢሀሎ ልብሰ እስጢፋኖስ እብን፤ወስርጋዌሁ እሣት ለቂርቆስ ህፃን
@menkir_tube
ዚቅ
ሃሌ ሉያ ለአብ ንሴብሕ፤አሠረ እግዚኡ በጽድቅ ዴገነ ሃሌ ሉያ ለወልድ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ወዓፀዱኑ ጸገየ ለነ፤ ማቴዎስ በሃይማኖቱ ተአጽፈ ሰንዱነ፣ድርገተ ምስለ መላእክት ኮነ
@menkir_tube
ዘጣዕሙ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።
@menkir_tube
ዚቅ
እስመ ርእየ ሕማማ ለዓመቱ፤ ወገብረ ኃይለ በመዝራዕቱ፤ መዝገቡ ለቃል ጽጌ እንተ ኢትትነገፍ መድኃኒተ ሕዝብ፤ መዓዛሆሙ ለቅዱሳን።
@menkir_tube
@menkir_tube
መልክአ እስጢፋኖስ
ሰላም ለዝክረ ስምከ እንተ ጸሐፎ በአክናፉ፤እግዚእ መናፍስት ሕያው ዘኢይመውት ለዝላፉ፤ስሙዓ ዜና እስጢፋኖስ ለዓለም እስከ አጽናፉ፤ ምስለ ማህበረ በኵር አኃዊከ እለ በሃይማኖት አዕረፉ፤ስመ ዚአየ አዘክር መላእክት ይጽሐፉ
ዚቅ፦
ፃማ ቅዱሳን ዲቤሁ አዕረፈ፤ አፈዋተ ወንጌል ጸገየ ዘልፈ፤ እስጢፋኖስ ሃይማኖተ ተአጽፈ፤ ኀበ ዓምደ ወርቅ ስሙ ተጽሕፈ።
@menkir_tube
ሰቆቃወ ድንግል
እስከ ማእዜኑ እግዝእትየ ማርያም ውስተ ምድረ ነኪር ትሔልዊ፤ሀገረኪ ናሁ ገሊላ እትዊ፤ለወልድኪ ሕፃን ዘስሙ ናዝራዊ፤ለክብረ ቅዱሳን በከመይቤ ኦዝያን ዜናዊ፤እምግብጽ ይጼውዖ አቡሁ ራማዊ።
@menkir_tube
ወረብ
በከመ ይቤ ኦዝያን ኦዝያን ክብረ ቅዱሳን/፪/
እምግብጽ ይጼውዖ ለወልድኪ አቡሁ ራማዊ አቡ/፪/
@menkir_tube
ዚቅ
ትንቢተ ኢሳይያስ ዘተብህለ እምግብፅ ጸዋዕክዎ ለወልድየ ለክብረ ቅዱሳን ጸዋዕክዎ
@menkir_tube
ማሕሌተ ጽጌ
ተአምረ ፍቅርኪ ይገብር መንክረ፤እንዘ ጻእረ ሞት ያረስዕ ወያሰተጥዕም መሪረ፤በመአዛ ጽጌኪሰ ለዘበአውደ ስምዕ ሰክረ፤ውግረተ አዕባን ይመስሎ ኀሠረ፤እሳትኒ ማየ ባሕር ቆሪረ።
@menkir_tube
ወረብ፦
ውግረተ አዕባን ውግረተ አዕባን ኀሠረ ይመስሎ ይመስሎ ኀሠረ/፪/
ለዘበአውደ ስምዕ ሰክረ በመአዛ ጽጌኪ እሳትኒ ማየ ባሕር ቆሪረ/፪/
ዚቅ
ሐሙ ርኀቡ ጸምዑ ወተመንደቡ፤ ዘኢይደልዎ ለዓለም ረከቡ፤ ቦ እለ በእሳት ወቦ እለ በኵናት፤ ቦ እለ በውግረተ ዕብን ወቦ እለ በመጥባሕት ፤ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ አስበ ፃማሆሙ ነሥኡ ሰማዕት
@menkir_tube
አንገርጋሪ
እንዘ ይነብር ለአብ በየማኑ
ወይረፍቅ ውስተ ሕጽኑ
ርዕየ ወልደ እስጢፋኖስ በዓይኑ
ኩሉ ትውልድ ያስተበጽእ በበዘመኑ
አማን ምዑዝ ጽጌ ልሳኑ
@menkir_tube
አመላለስ፦
አማን በአማን አማን በአማን ምዑዝ አማን በአማን/፪/
ምዑዝ ጽጌ ልሳኑ ምዑዝ ጽጌ ልሳኑ/፪/
@menkir_tube
ቅንዋት፦
ሰማዕት በገድሎሙ አረቦነ ዘመዊዕ ነሥኡ፤እንዘ ያኄይሎሙ አምላኮሙ በመስቀሉ በውስተ ስምዕ፤ወረከቡ ዘአፍቀሩ ተሣየጡ ምድረ በደሞሙ፤ማ፦ ወነሥኡ ዕሤቶሙ፤ፍጹመ እለ መነኑ ዓለመ
🇪🇹👇👇👇👇👇👇🇪🇹
👉@menkir_tube👈
👉@menkir_tube👈
👉@menkir_tube👈
🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹
@menkir_tube
# Join & share #
አቡነ ኢያሱ ዘጀር ሥላሴ:-አቡነ ኢያሱ በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በሰሜን ሸዋ የተነሡ ሲሆን ምንኵስናቸውን ከደብረ ሊባኖሱ ከዕጨጌ አቡነ መርሐ ክርስቶስ እንደተቀበሉ ታሪካቸው ያስረዳል። ትውልዳቸው አምሐራ ሳይንት ሲሆን መካነ ሱባኤ ወተመስጦ ጀር ቅድስት ሥላሴ ገዳምን የመሠረቱ ታላቅ ጻድቅ ናቸው።
እርሳቸው የመሠረቱት ጀር ቅድስት ሥላሴ ገዳም በግራኝ ወረራ ሳይወድም ስለቀረ ጥንታዊነቱን እንደጠበቀ ስለሚገኝና ታላቅ የበረከት ቦታ የቅዱሳን መናኸሪያ ስለሆነ ብዙዎች ነገሥታት ገዳሙን እየሔዱ ተሳልመው በረከት አግኝተውበታል። የአቡነ ኢያሱን ገድላቸውን ከአቡነ ሀብተ ማርያም ገድል ጋር ጣልያናዊው ራይኔሪ በሀገሩ ሮም እንዳተመው ቀሲስ ዶ/ር አምሳሉ ተፈራ ጽፈዋል። (0s valdo Raineri, Atti di Habta Māryam (†1497) e.di Iyasu (†1508), Santi Monaci Etiopici, Roma 1990 (Or ChrA 235), 165-265.)
የጻድቁ በዓለ ዕረፍታቸው ጥቅምት 16 በገዳሙ በታላቅ ድምቀት የሚከበር ሲሆን ስለ ጻድቁ ገድል በዝርዝር ተጽፎ አላገኘንም፣ ይልቁንም አቡነ ኢያሱ ስለገደሙት ታላቁ ጀር ቅድስት ሥላሴ ገዳም ነው በብዛት የሚነገረው።
አቡነ ኢያሱ ጀር ስላሴ ከመምጣታቸውም በፊት አስቀድመው በአቡነ ዜና ማርቆስ ገዳም፣ በደብረ ሊባኖስ እና በሌሎችም ገዳማት እየተዘዋወሩ በተጋድሎ ሲቀመጡ ‹‹ቦታህ ይኸ አይደለም›› ተብለው በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል መሪነት ነው ወደ ጀር ሥላሴ የመጡት። ወደ ቦታው ከመምጣታቸው በፊት አካባቢው ባእድ አምልኮ የተስፋፋበት ነበር፣ ነገር ግን ጻድቁ ሕዝቡን ክርስትናን አስተምረው ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር መልሰውታል። የምንኵስናን መሠረት ጥለውበታል። የአቡነ ኢያሱ የዕረፍታቸው ቦታ ደብረ ሊባኖስ ቢሆንም መታሰቢያቸው በመራቤቴ በሚገኘው አስደናቂ ገዳማቸው ይታሰባል። በገዳሙ በክብረ በዓሉ ወቅት ታቦት አይወጣም፣ ከበሮ አይመታም። ምክያቱም ፍጹም የጸሎት የጽሞና ቦታ ስለሆነ ነው።
መካነ ሱባኤ ወተመስጦ ጀር ቅድስት ሥላሴ አቡነ ኢያሱ ገዳም በተፈጥሮአዊ አቀማመጡ እጅግ አስደናቂ ሲሆን በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ በደንቢ ግራርጌ ቀበሌ ጀር በሚባል ስፍራ የሚገኝ ታላቅ ገዳም ነው። ገዳሙ ከአዲስ አበባ 137 ኪ.ሜ ከደብረ ብርሃን 91 ኪ.ሜ ከለሚ ከተማ 4 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ከጥንት ጀምሮ ስዉር ገዳም ሆኖ የቆየ ነው። ገዳሙ በ1495 ዓ.ም በዐፄ ናኦድ ዘመነ መንግሥት በቅዱስ ሚካኤል መሪነት ጻዲቁ አቡነ ኢያሱ ወደዚህ ቦታ መጥተው መሥርተውታል። በጅረት ታጂቦ ስለሚገኝ ነው ጀር ሥላሴ የተባለው። የክብር ባለቤት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በራእይ አስመልክቶ ከመሠረታቸው ገዳማት አንዱ ነው። አቡነ ኢያሱም በገዳሙ በሚገኘው አንድ ትልቅ ዋርካ ሥር ቆመው ይጸልዩእንደነበር አባቶች ያስረዳሉ። አሁንም ድረስ ዋርካው በሥፍራው ላይ ሕያው ማስረጃ ሆኖ ይገኛል።
ገዳሙ ከአቡነ ኢያሱ ዕረፍት ከዘመናት በኋላ በግራኝ አህመድ ወረራ ጥቃት ደርሶበት መነኰሳቱም ተበታትነው ለ247 ዓመት ጠፍ ሆኖ ከቆየ በኋላ በ1747 ዓ.ም አቡነ ዮሴፍ የተባሉት ጻድቅ በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል መሪነት ከአምባሰል ተነሥተው መጥተው ገደሉን ቦርቡረው ቅኔ ማሕሌት፣ ቅድስትና ቅዱሳንን ያሟላ ቤተ መቅደስ በማነጽ ዳግም ገዳሙን በማቅናት የቀደመውን የአባቶችን ታሪክ ማስቀጠል ችለዋል። በግራኝ አህመድ ወረራ ወቅት ቅርሶቹና ነዋየ ቅዱሳቱ አደጋ እንዳይደርስባቸው አባቶች ሰብስበው በስውር ከተቀበሩ ከረጅም ጊዜ በኋላ የቀበሩበት ቦታ ጠፍቶባቸው ነበር ነገር ግን የወንዙ ውኃ አቅጣጫውን ቀይሮ ሽቅብ ፈስሶ ቅርሶቹ ያሉበትን ቦታ አመላክቷል።
መካነ ሱባኤ ወተመስጦ ጀር ቅድስት ሥላሴ አቡነ ኢያሱ ገዳም የበርካታ መናንያን አበው በኣት ከመሆኑም ባሻገር የወንዶች ብቻ ገዳም ሲሆን መናንያኑ ከአራዊት ጋር ተስማምተው የሚኖሩበት ነው። ዙሪያው በገደል የተከበበ ሲሆን ወደ ገዳሙ ለመውረድ የዕንጨት
💒💚💛❤ሐመረ ኖህ ነሽ💒💚💛❤
ሐመረ ኖህ ነሽ
የምህረት ቃል ኪዳን የተገባልሽ
ትውልድ ይህን አምኖ
ያከብርሻል አልቆ እና አግኖ
በእግዚአብሔር ሀሳብ ነበርሽ በህሊና
ዓለምን ሳይፈጥር አዳምን ሳይሠራ
ሁሉን የናፈቀሽ የወጣብሽ ፀሀይ
ንግሥት ነሽ ድንግል እሙ ለአዶናይ
#አዝ----------------
ያንን የጭንቅ ቀን የጥፋቱን ዘመን
አልፈነዋል ባንቺ በአማናዊት ፅዮን
ምንጭ ነሽ የእርካታ የድህነት መፍለቂያ
የዘለዓለም እረፍት አንባ እና ማረፊያ
#አዝ----------------
የነቢያት ትንቢት ተፈጽሞ አየን
አንቺ ምክንያት ሆነሽ ለመዳናችን
ድምፅሽንሲሰማ ጠላት ይሸበራል
እኛ ግን ሰምተነው በሀሴት ዘለናል
#አዝ----------------
አንዴ በገባልሽ ቃል ኪዳን መሠረት
ትውልዱን ይምራል ይኸው በቸርነት
ስምሽ ወለላ ነው ጣፋጭ ለአፋችን
ማርያም ማርያም ብለን ታብሷል እንባችን
💒መዝሙር💚
💛ዘማሪት ፋሲካ ፍሰሀ❤
አንድ አምላክ በሆኑ በአብ ፣ በወልድ ፣ በመንፈስ ቅዱስ ስም ንጹሕ ፣ ልዩ ፣ ክቡር ፣ ጽሩይ በሆኑ በሥላሴ እያመንን እና እየተማጸንን የድንግል ማርያምን ምሥጋና እንናገራለን።
ድንግል ያንቺ ልቅሶ በእጅጉ ይበቃኛል ። ሁለተኛ እንዳላለቅስ በታምርሽ አድኚኝ ። አንች ሁልጊዜም የአዳምና የልጆቹ መድኃኒት ነሽና ፤ ኃጥአንን በቸርነቱ እስከአዳነ ድረስ ንጉሥ ልጅሽ ራቁቱን እንደተሰቀለ አስቢ፡፡
#አሜን_በእውነት
#አባ_ጽጌ_ድንግል
ጥቅምት 15/2016
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን ከቅዱሳኑ #ቂርቆስ_እና_ኢየሉጣ ረድኤትና በረከት ያሣትፈን ለወርሐዊ በአላቸዉ እንኳን አደረሰን
👉ቅዱስ ቂርቆስ ዕድሜው የሦስት ዓመት ሳለ እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ ከሮሜ ወደ ሌላ ሃገር ሸሽታ ይዛው ሄደች በዚያም የሸሸችውን መኮንኑን አገኘችው የሚያውቋትም ሰዎች ሸሽታ እንደመጣች ስለተረዱ ለመኮንኑ ነገር ሰሩባት መኮንኑም ቅድስት አየሉጣን አስጠራትና ስለ አምልኮ ጠየቃት ቅድስት ኢየሉጣም መኮንን ሆይ ዕድሜው ሦስት አመት የሆነው ሕፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እርሱን ጠይቅ አለችው
👉 ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስም ወደ አለበት ጭፍራውን ልኮ ወደ እርሱ አስመጣው ሕፃኑንም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና “አንተ ደስተኛ ሕፃን ሆይ እንዴት ነህ?” አለው። ሕፃን ቅዱስ ቂርቆስም መለሰለት እንዲህም አለው “አዎ እኔ በጣም ደስተኛ ነኝ ደስታዬም ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ሐዘንና ለቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስም ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏልና” አለው። እግዚአብሔር አምላክ ኃይልንና ንግግርን ሰጥቶታልና በዚያ ለተሰበሰቡት ሰዎች እስኪደነግጡ ድረስ ብዙ ተናገረ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስም ንጉሱን መኳንንቱንና ጣዖታቱን ረገማቸው ከብርታቱም የተነሳ አደነቁ።
👉መኮንኑም በአፈረ ጊዜ በየዓይነቱ በሆነ ስቃይ፡ ታላላቆች እንኳ የማይችሉትን ታላቅ አስጨናቂ የሆነ ስቃይን አሰቃየው እናቱ ቅድስት ኢየሉጣንም ከእርሱ ጋር እንደ እርሱ በጣሙን አሰቃያት እግዚአሔብሔር ግን ያለ ምንም ጉዳት ያነሳቸው ነበር ብዙዎች አህዛብም ይህን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን በመድሃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት አምነው በሰማእትነት ሞቱ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበሉ።
👉በሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ላይም የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት ታላላቅ ድንቅ ተአምራቶችንም ያደርግ ነበር ብዙዎች በሽተኞችንም ያድናቸው ይፈውሳቸው ነበር ይህንን ያየ መኮንን በታላቅ የናስ ጋን ውስጥ ውሃ ጨምረው በእሳት ያፈሉት ዘንድ አዘዘ የፍላቱም ድምጽ እንደ ክረምት ነጎድጓድ ሆነ ድምጹም በጣም ያስተጋባ ነበር ይህን ያየችና የሰማች እናት ቅድስት ኢየሉጣም ፍርሃትና የሃይማኖት ጉድለት ታየባት ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ሁኔታዋን አይቶ ወደ አምላኩ እግዚአብሔር ጸለየ ያን ጊዜ ልዑል እግዚአብሔር ልቧን ወደ ሰማይ አሳርጎ ለቅዱሳን ሰማዕታት የተዘጋጁ የብርሃን ማደሪያዎችን አሳያት ቅድስት ኢየሉጣም እንደገና በሃይማኖቷ ጸናች እግዚአብሔር አምላኳንም አመሰገነችው ልጇን ሕፃኑን ቅዱስ ቂርቆስንም “ልጄ ሆይ አንተ ከእንግዲህ አባቴ ነህ እኔም ልጅህ ነኝ” አለችው።
👉ቅድስት እየሉጣም ለልጇ “ያች የተወለድክባት ዕለት ቀኗ የተባረከችና የተቀደሰች ናት” አለችው የመኳንንቱ ጭፍሮችም እሳት ወደ አለበት ጋኖች ውስጥ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣን በጨመሯቸው ጊዜ የውሃው ፍላት ወድያዉኑ ቀዘቀዘ ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የእሳቱን ኃይል አቀዝቅዞታልና ይህን ያየ መኮንን ሥጋቸው ተቆራርጦ እስከሚወድቅ ድረስ በመቃጥን ውስጥ አድርገው አንዲጎትቷቸው አዘዘ ከእግዚአብሔርም የታዘዘ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል አዳናቸው መኮንኑም በታላቅ ስቃይ ያሰቃያቸው ዘንድ አስቦ እስኪመክር ድረስ በወህኒ ቤት ዘጋባቸው በዚህን ጊዜ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስን አረጋጋው አጽናናው ስሙን ጠርተው መታሰቢያ ለሚያደርጉለትም በረከትን እንደሚያገኝና ሌላ ብዙ ቃል ኪዳን ሰጠው።
👉ሲነጋ መኮንኑ ከመካነ ምኩናኑ ተቀምጦ ካለበት አስጠርቶ “የተመለስከው መመለስ አለን?” አለው ቅዱስ ቂርቆስም “አይሆንም አልመለስም” አለው ሰይፍ ጃግሬውን ጠርቶ “ንሳ ውደቅበት” አለው በሰይፍ መታው ጌታም ነፍሱን ከመካነ ዕረፍት ሥጋውንም ነጥቆ በሰረገላ ኤልያስ አኑሮለታል እናቱ ቅድስት ኢየሉጣንም በማግስቱ (ጥር 16) በሰይፍ አስመትቷት በሰማዕትነት ዓርፋለች
👉እግዚአብሔር አምላካችን የሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስና የእናቱ የቅድስት እየሉጣን በረከታቸውንና ረድኤታቸውን ያድለን "አሜን"
👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአሉ የምናስበዉ ሰማእቱ ቅዱስ #ሚናስ ፀሎቱ አይለየን "አሜን" 💒 💚 💛 ❤ 💒
ወርሃዊ በዓል
1.አባ ዮሐንስ ጻድቅ
2.እናታችን ቅድስት ነሣሒት
++"+ ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል:: ጻድቅን በጻድቅስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል:: ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላቹሃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም:: +"+ (ማቴ. 10:41)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
+በነዚህ ዓመታት ሁሉ ይህ አካሉ የተለወጠ ሕጻን ቅዱስ
ዘካርያስ መሆኑን ያወቀ የለም:: እንዲህ የቆሰለውም
አሲድነት ካለው የጉድጉዋድ ውሃ ውስጥ ሰጥሞ ለ40
ቀናት በመጸለዩ ነው::
+በመጨረሻ ግን አባቱ በምልክት ለይቶት አለቀሰ::
"ልጄ! አንተ ለእኔ አባቴ ነህ" ብሎታል:: አበው
መነኮሳትም ተሰብስበው እጅ ነስተውታል:: በ7 ዓመቱ
የመነነው አባ ዘካርያስ በ52 ዓመቱ በዚህች ቀን ዐርፎ
በክብር ተቀብሯል::
=>አምላከ አፈ ወርቅ ዮሐንስ የድንግል እመ ብርሃንን
ፍቅሯንና ውዳሴዋን ይግለጽልን:: ከአባቶቻችን ክብርና
በረከትንም ያሳትፈን::
=>ጥቅምት 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን
በዓላት=
1.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
2.አባ ዘካርያስ ገዳማዊ
3.አባ ማርዳሪ ጻድቅ
4.ቅዱስ አብጥማዎስ ሰማዕት
=>ወርኀዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
3."99ኙ" ነገደ መላዕክት
4.ቅዱስ አስከናፍር
5."13ቱ" ግኁሳን አባቶች
6.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
7.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ
=>+"+ እናንተ የምድር ጨው ናችሁ . . . እናንተ
የዓለም ብርሃን ናችሁ:: በተራራ ላይ ያለች ከተማ
ልትሠወር አይቻላትም:: መብራትንም አብርተው በዕንቅብ
በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያናሩታል:: በቤት
ላሉት ሁሉም ያበራል:: መልካሙን ሥራችሁን አይተው
በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ
እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ:: +"+ (ማቴ. 5:13-16)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
https://youtu.be/NFR_-JF3V64?si=TKATo8-r7tPJyw6o
=>አምላከ ዳዊት ፍቅሩን: አምላከ ማቴዎስ
አገልግሎቱን: አምላከ ድሜጥሮስ ንጽሕናውን
ያሳድርብን:: ጸጋ በረከታቸውን ደግሞ ያትረፍርፍልን::=>ጥቅምት 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን
በዓላት=
1.ቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ (የነገሠበት)
2.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
3.ቅዱስ ድሜጥሮስ ሊቅ
4.ቅድስት ልዕልተ ወይን
5.ቅዱስ ሳሙኤል ነቢይ
6.ጻድቃን ዼጥሮስ ወዻውሎስ
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
3.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት)
5.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
6.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
=>+"+ ከሕዝቤም የተመረጠውን ከፍ ከፍ አደረግሁ::
ባሪያየን ዳዊትን አገኘሁት::
ቅዱስ ዘይትም ቀባሁት::
እጄም ትረዳዋለች::
ክንዴም ታጸናዋለች::
ጠላት በእርሱ ላይ አይጠቀምም::
የዓመጻ ልጅም መከራ አይጨምርበትም::
ጠላቶቹን ከፊቱ አጠፋለሁ::
የሚጠሉትንም አዋርዳቸዋለሁ:: +"+ (መዝ. 88:20)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
🌹#እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን📌
✅ቅዱስ ማለት ልዩ፥ ክቡር ማለት ነው፤ ሚካኤል ማለት ደግሞ «መኑ ከመ አምላክ፥ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው?» ማለት ነው። ሚካኤል የሚለው ስም ቃሉ የዕብራይስጥ ነው፤ ሚ - የሚለው «መኑ» ማለት ነው፥ ካ - የሚለው «ከመ» ማለት ሲሆን፥ ኤል - ማለት ደግሞ «አምላክ» ማለት ነው። ይህን ማለትም የቅዱስ ሚካኤልን ስም በጠራን ቊጥር የምንመሰክረው ስለ እግዚአብሔር ነው፤ በመሆኑም እግዚአብሔርን በባሕርይ የሚመስለው፥ በሥልጣንም የሚተካከለው፥ በምድርም በሰማይም እንደሌለ የሚናገር ልዩ፥ ክቡር ስም ነው። የነቢያት አለቃ ሙሴ ባሕረ ኤርትራን ለሁለት ከፍሎ ሕዝቡን ያሻገረለትንና ፈርዖንን ከነሠራዊቱ ያሰጠመለትን አምላክ እግዚአብሔርን በመዝሙር ሲያመሰግን፥ «አቤቱ በአማልክት መካከል (በስም አማልክት ከሚባሉ፥ በስመ አማልክት ከሚጠሩ፥ አንድም አማልክት ዘበጸጋ ከተባሉ ከነቢያት ከካህናት መካከል) አንተን የሚመስል ማነው? በቅዱሳንም ዘንድ እንደ አንተ የከበረ ማነው?» ብሏል። ዘጸ ፲፭፥፲፩። ቅዱስ ዳዊትም፦ «አቤቱ፥ ከአማልክት የሚመስልህ የለም፤» ብሏል። መዝ ፹፭፥፰።
የትምህርት ዕድል ያመለጠህ መስሎህ ነው? ገና ሺህ የትምህርት ዕድሎች አሉህ:: ዕድሜህ ያመለጠህ መስሎህ ነው? ነገ የሚጠብቁህ ብሩሕ ዘመናት እኮ ቁጭ ብለው አሉ? የሚረዳኝ ሰው የሚያስብልኝ ሰው አጥቼያለሁ? ብለህ ከሆነም ካልሰሙህ ጥቂቶች በላይ ልንሰማህ የምንሻ "ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ"
መከራ ጸናብኝ ኑሮ ጨለመብኝ የሀገሪቱ ሁኔታ ተስፋ አሳጣኝ ብለህ ይሆን? እኛስ አብረንህ አይደልንም? አብረን ከገባንበት ችግር አብረን ብንወጣ አይሻልም? ከአንተ በባሰ ሁኔታ የታሰርንና የተገረፍን ጳውሎሶችና ሲላሶች "ሁላችን በዚህ አለንና በራስህ ክፉ አታድርግ" ስንልህ ስማን::
ይልቅ አንተም እንደ ወኅኒው ጠባቂ "እድን ዘንድ ምን ላድርግ ብለህ?"ነፍስህን የምታድንበትን መንገድ ወደ መቅደሱ ቀርበህ ጠይቅ::
ወዳጄ ይህንን ጽሑፍ ያነበብኸውም በሕይወት ስላለህ ነው:: የአንተን ዓይን የሚጠብቁ ብዙ ጽሑፎች ፣ የአንተን ጆሮ የሚፈልጉ ብዙ ድምፆች ፣ የአንተን መሐረብ የሚፈልጉ ብዙ ዕንባዎች ፣ የአንተን ሳቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀልዶች ... ገና ብዙ ብዙ አሉ::
ስለዚህ ሰይጣንን አሳፍረው:: እንዲህ በለው :-
"ጠላቴ ሆይ፥ ብወድቅ እነሣለሁና፥ በጨለማም ብቀመጥ እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛልና በእኔ ላይ ደስ አይበልሽ" ሚክ. 7:8
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥቅምት 2016 ዓ.ም.
ሜልበርን አውስትራሊያ
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ [ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ] ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
ጥቅምት 9/2016 #አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ፃድቁ በምልጃ ፀሎታቸዉ እንዲያስቡን ለምንማፀንበት ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን
👉አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ አባታቸው መልአከ ምክሩ እናታቸው ወለተ ማርያም ይባላሉ የተወለዱበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ነው በተወለዱ ዕለት ተነስተው በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ በአንድነት በሶስትነት ለሚመሰገን ለሥላሴ #ስብሐት_ለአብ_ስብሐት_ለወልድ_ስብሐት_ለመንፈስ_ቅዱስ ብለው አመስግነዋል፡፡
👉የስማቸው ትርጓሜ #የአብ_የወልድ_የመንፈስ_ቅዱስ እስትንፋስ አንድም "የክርስቶስ እስትንፋስ" ማለት ነው ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸውና በመንገዳቸው ሁሉ እየመራቸው ነው ያደጉት መንፈስ ቅዱስ ልቡናቸውን ብሩህ አድርጎላቸው በ5 ዓመታቸው የቅዱሳት መጽሐፍት ቃላትን፣ ብሉያትንና ሐዲሳትን፣ ድርሳናትንም ጠንቅቀው ዐውቀዋል፡፡
👉በተወለዱ በ14 ዓመታቸው ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ደብረ ሐይቅ ገዳም ሄደው ከባሕር ዳር ቆመው የሙሴን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር በጸለዩ ጊዜ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ባህሩን አሻግሯቸው ወደ ቤተክርስቲያን ገብተዋል
👉ሦስት ዓመትም በኃይቅ ገዳም ለመነኮሳት እንጨት በመልቀምና ውሃን በመቅዳት ለአባቶች መነኮሳት ምግብ ሊሆናቸው ከባህር ውስጥ አሳን በማውጣት አገልግለዋል፡
👉አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ከፆሙ በኋላ ምንም እህል ሳይቀምሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ ለሙሴ በደብረ ሲና እንደሰጠው ለአባታችንም ወደ እርሳቸው መጥቶ ዓሥሩን ቃላተ ኦሪትና ስድስቱን ቃላተ ወንጌል በውስጣቸው የተጻፈባቸው ሁለት ጽላቶችን ሰጥቷቸዋል
👉አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሠሩ በኋላ ዕለቱን ስንዴ ዘርተው ወይን ተክለው ጽድን ወይራንና ግራርን ተክለው በአንዲት ቀን ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ዕለቱን አድርሰዋል ስንዴውን ለመስዋዕት ወይኑን ለቁርባን በታምራት አድርሰዋል
👉አባታችን በጸሎት ላይ እንዳሉ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ተልኮ መጥቶ አባታችንን በደመና ጭኖ ወስዶ ከጌታችን ከአምላካችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ፊት አቆማቸው፡፡
👉ጌታንም በቅዱሳኖቹ ሁሉ እንዲባረኩ ካደረጋቸው በኋላ መልአኩን ወደ ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ ወደ ኢየሩሳሌም አድርሰው ብሎት ኢየሩሳሌምን አሳልሞ ሀገራችን መልሶ አምጥቷቸዋል ሁሉንም የኢትዮጵያን ቅዱሳት ገዳማትንም ተሳልመዋል
👉የአባታችን #የፃድቁ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ፀሎትና ቃል ኪዳን ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን" 💒 💚 💛 ❤ 💒
🌹ቅዱስ እስጢፋኖስ🌹
🍀🌸🌷🌼🌺🌸🍀
†♥† እስጢፋኖስ የሚለው ቃል የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙም
“አክሊል” ማለት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ወደ ግእዝ በኋላም
ወደ አማርኛ የመለሱት አባቶች በቀጥታ የግሪኩን እስጢፋኖስ
የሚለውን ቃል ተጠቅመዋል፡፡
ቅዱስ እስጢፋኖስ ምንም እንኳ ስሙ የግሪክ ስም ይሁን እንጂ በትውልዱ አይሁዳዊ ነው፡፡ ወላጆቹ ይህንን ስም ሊሰጡት የቻሉት በፍልስጤም ጠረፋማ ከተሞች ይኖሩ ስለነበር የግርክ ባሕልና ቋንቋ ተጽእኖ አድሮባቸው ይሆናል ተብሎ ይገመታል፡፡
ቅዱስ እስጢፋኖስ በሐዋርያት ጥበቃ የነበረችውን ቤተ ክርስቲያን ከአምላክ ዘንድ ባገኘው የማስተማርና የፈውስ ሀብት ያገለግል ነበር፡፡ በእርሱም ታላላቅ ተኣምራት ይፈጸሙ ነበር፡፡ ስለዚህም ሕዝቡ ከፊት ይልቅ እጅግ እየበዛና በትምህርት እየጠነከረ መጣ፡፡
አይሁድም ይህን ተመልክተው በቅዱስ እስጢፋኖስ ላይ
በቅናትና በጠላትነት ተነሡበት፡፡ ነገር ግን ከመንፈስ ቅዱስ
ባገኘው ጥበብና ኃይል እነርሱን በቃልም በድርጊትም
ይቃወማቸው ነበርና ሊረቱት አልተቻላቸውም፡፡ ስለዚህም
እግዚአብርሔርን፣ ሙሴ ሲሳደብ ሰምተነዋል፣. ሙሴ የሠራልንን
ሥርዐት ይለውጣል፣ በዚህ ቤተ መቅደስና በሕጉ ላይ የስድብን
ቃል ይናገራል፣ ይህንንም ቤተ መቅደስ የናዝሬቱ ኢየሱስ አፍርሱ
ብሎአል እያለ ያስተምራል አያሉ፣ ሕዝቡን፣ ሽማግሌዎችንና
ጸሐፍትን በማናደድ ይዘው ከሸንጎ ፊት አቆሙት ቅዱስ
እስጢፋኖስን በሸንጎ ፊት ባቆሙት ጊዜም ፊቱ ልክ እንደ
መልአክ ፊት ሆኖ በርቶ ነበር፡፡
እርሱም ለተከሰሰበት ነጥብ መልስ ሰጠ፡፡ ከአብርሃም እስከ ክርስቶስ ለእነርሱ የተሰጣቸውን በረከት በመቃወማቸው ከተስፋ ቃል እርቀው እንደተወገዱ ገለጠላቸው፡፡ ክርስቶስንም ባለመቀበላቸው ወቀሳቸው፡፡
በዚህም ምክንያት በቁጣ ተነሣስተው ከከተማ
ውጭ በመውሰድ በድንጋይ ወግረው ገደሉት፡፡ ቅዱስ
እስጢፋኖስ አይሁድ በድንጋይ እየወገሩት ሳለ ሰማያት ተከፍተው
ክርስቶስን በአብ ቀኝ ቆሞ ተመለከተ፡፡ ይህንን ራእይ
የክርስቶስን ትንሣኤን ለማይቀበሉት አይሁድ አሰምቶ ተናገረ፤
እነርሱ ከፊት ይልቅ በእርሱ ጨከኑ በድንጋይም ወገሩት፡፡ ነገር
ግን ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታውን ክርስቶስን መስሎ ነበርና ልክ
እንደ መምህሩ ክርስቶስ “አቤቱ ይህን ኀጢአት
አትቁጠርባቸው” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ሰጠ፡፡
በቤተክርስቲያንም ታሪክ ስለክርስቶስ መስክሮ ሰማዕትነትን
የተቀበለ የመጀመሪያው ዲያቆን ሆኖአል፡፡ በደማስቆ መንገድ
ላይ ክርስቲያኖችን ያሳድድ የነበረ ሳውል በኋላም ቅዱስ
ጳውሎስ ተብሎ ስያሜ የተሰጠው ሐዋርያ ቅዱስ እስጢፋኖስ
በድንጋይ በሚወግሩበት ወቅት በእርሱ ሞት ተስማምቶና
ድንጋይን በእስጢፋኖስ ላይ ያነሡትን የአይሁድ ልብስ ይጠብቅ
የነበረ ብላቴና ነበር፡፡ ነገር ግን ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ ከሆነ
በኋላ የእስጢፋኖስን ቤተሰቦች አጥምቆአቸዋል፡፡ ይህ ደግሞ
ድንቅ ነው፡፡ ቅድስት ቤተክርስቲያናችንም ይህን ቅዱስ
የመታሰቢያ ቀን በመስጠት ጥቅምት 17 የድቁና ማዕረግን
በአነብሮተ ዕድ በሐዋርያት የተቀበለበትን፥ ጥር 1 ደግሞ
ዕረፍቱን ታስባለች፡፡ ከሰማእቱ እስጢፋኖስ በረከት ረድኤት
ይክፈለን!!†♥†
🔰 በቤተክርስቲያን ያሉ ነገሮች ምሳሌዎቻቸው
፩/ቤተክርስቲያን_የመንግሥተ ሰማይ ምሳሌ
፪/መቅደስ_የቀራንዮ ምሳሌ
፫/ታቦት፣ መንበር____የእመቤታችን ምሳሌ
፬/ኲስኲስት__የእመቤታችን ምሳሌ
፭/ማይ__የማይ ሕይወት ክርስቶስ
፮/መሠረቱ___ከአዳም እስከ ኖኅ ያሉ የአስሩ አበው ምሳሌ
፯/ሦስት ደጃፍ___የሥላሴ ምሳሌ
፰/ትልልቅ መስኮቶች___የዐበይት ነቢያት ምሳሌ
፱/ትንንሽ መስኮቶች___የደቂቀ ነቢያት ምሳሌ
፲/የውስጥ አዕማድ __የሐዋርያት ምሳሌ
፲፩/የውጭ አዕማድ___የ፸፪ቱ አርድእት ምሳሌ
፲፪/ማዕዘን__የአራቱ ወንጌላውያን ፣የኪሩቤል ምሳሌ
፲፫/መብራት__የሊቃውንት ምሳሌ
፲፬/በሮች___የቅዱሳን አበው ምሳሌ
፲፭/ጠርብ___የሰማእታት ምሳሌ
፲፮/ማገር___የረድኤተ እግዚአብሔር ምሳሌ
፲፯/ሣሩ__ ሄሮድስ ያስፈጃቸው ሕፃናት ምሳሌ
፲፰/መጋረጃ___የመላእክት ፣የረድኤተ እግዚአብሔር ምሳሌ
፲፱/የሰጎን እንቁላል___የተዘክሮ እግዚአብሔር ምሳሌ
፳/አፀደ ቤተክርስቲያን ፣ቅጽረ ቤተክርስቲያን___የመላእክት ምሳሌ
፳፩/ደጀ ሰላም___የገነት ምሳሌ
፳፪/ሁለት ቅጽር____አንዱ የናጌብ አንዱ የአድማስ ምሳሌ ናቸው።
ሁለት ቅጽር ማለት እንደ ጎንዴር ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን እንዴ አዲስ አበባ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ሁለት ቅርጽ ያለው ቤተክርስቲያንን ያመለክታል።
ምንጭ:- ፲፬ቱ መጽሐፈ ቅዳሴ አንድምታ ትርጓሜ
ወሰብሐት ለእግዚአብሔር
ወለ ወላዲቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክቡር ይቆዬን አሜን ፫
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
/channel/zikirekdusn
❖ ጥቅምት ፲፮ (16) ❖
✞✞✞ እንኩዋን አደረሳችሁ ✞✞✞
+"+ 7ቱ ኪዳናት ወአባ ያቃቱ ሊቀ ዻዻሳት +"+
+"+ 7ቱ ኪዳናት +"+
=>"ተካየደ" ማለት "ተስማማ: ተማማለ" እንደ ማለት
ሲሆን "ኪዳን" በቁሙ "ውል: ስምምነት" እንደ ማለት
ነው:: ይኸውም እግዚአብሔር ከሰዎች ጋር: ሰዎችም
ከሰዎች ጋር የሚያደርጉት ሊሆን ይችላል:: ልዩነቱ
የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ቅዱስና የማይለወጥ መሆኑ ነው::
+እግዚአብሔር አምላክ ከሥነ ፍጥረት ጀምሮ በየጊዜው
ከብዙ ወዳጆቹ ጋር ኪዳንን አድርጉዋል:: ቅድስት ቤተ
ክርስቲያንም እነዚህን ኪዳናት ጥቅልል አድርጋ 7 እንደ
ሆኑ ታስተምራለች:: ስለዚህም ዛሬ ፈጣሪ ቢረዳን
እነዚሁን 7 ኪዳናት በጥቂቱ እንመለከታለን::
"ኪዳነ ተካየድኩ ምስለ ኅሩያንየ"
"ከመረጥኩዋቸው ጋር ቃል ኪዳንን አደረግሁ" (መዝ. 88:3)
(1) +"+ ኪዳነ አዳም +"+
=>አዳም ማለት የእግዚአብሔር ድንቅ ፍጥረት:
የፍጡራን አስተዳዳሪ: ነቢይ: ካህንና ንጉሥ ነው::
እግዚአብሔር ከአዳም ጋር አስቀድሞ በእጸ በለስ
አማካኝነት ቃል ኪዳን ነበራቸው:: ነገር ግን አባታችን
በዲያብሎስ ሴራ በመረታቱ ኪዳኑ ፈረሰ:: (ዘፍ. 3:1)
+አዳምና ሔዋን ተጸጽተው ቢያለቅሱ ግን አዲስ የኪዳን
ተስፋ: "ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ኪዳንን
ተቀበሉ:: (ቀሌምንጦስ: ገላ. 4:4)
(2) +"+ ኪዳነ ኖኅ +"+
=>ከአዳም እስከ ኖኅ ድረስ ባሉት 10 ትውልድ ዓለም
በዓመፃ ተሞላች:: ቅዱስ ኖኅ በደግነቱ መርከብ ሠርቶ
ቤተሰቡን ሲያተርፍ ዓለም በማየ ሥራዌ ጠፋች::
ከመርከቡ ከወጣ በሁዋላ ኖኅና እግዚአብሔር በቀስተ
ደመና ምልክትነት ቃል ኪዳን ተጋቡ:: "ኢያማስና
ለምድር ዳግመ በማየ አይኅ" እንዲል:: (ዘፍ. 9:12)
(3) +"+ ኪዳነ መልከ ጼዴቅ +"+
=>መልከ ጼዴቅ የእግዚአብሔር ካህኑ: የክርስቶስም
ምሳሌው የሆነ የሳሌም ንጉሥ ነው:: በ15 ዓመቱ
መንኖ: አጽመ አዳምን ይዞ: በቀራንዮ በሕብስትና በወይን
ያስታኩት ነበር::
+እግዚአብሔር ለመልከ ጼዴቅ: በሐዲስ ኪዳን
ለምትሠራው ክህነትና ምሥጢረ ቁርባን ምሳሌ አድርጐ
በቃል ኪዳን አትሞታል:: በዚህም ተሰውሮ ይኖራል እንጂ
ሞትን እስካሁን አልቀመሰም:: ይህም ካህኑ መልከ
ጼዴቅ ከአብርሃም ጋር በተገናኙበት ጊዜ ተገልጧል:: (ዘፍ. 14:17, ዕብ. 7:1)
(4) +"+ ኪዳነ አብርሃም +"+
=>ቅዱስ አብርሃም የሕዝብና የአሕዛብ አባት: ሥርወ
ሃይማኖት: የጽድቅም አበጋዝ ነው:: ስለ ፍቅረ
እግዚአብሔር ሲል ከርስቱና ከወገኖቹ ተለይቶ በቅድስና
ኑሯልና እግዚአብሔር "በዘርሕ አሕዛብ ይባረካሉ"
አለው:: (ዘፍ. 12:1) የቃል ኪዳን ምልክትም ይሆነው
ዘንድ ግዝረትን ሰጠው:: (ዘፍ. 17:1-14)
(5) +"+ ኪዳነ ሙሴ +"+
=>ቅዱስ ሙሴ የነቢያት አለቃ: የእሥራኤል እረኛ:
የእግዚአብሔር ሰው እና ፍጹም ትሑት (የዋህ) ሰው
ነው:: በፈጣሪው ትዕዛዝ እሥራኤልን ከግብጽ ባርነት
አውጥቶ ለ40 ዘመናት በበርሃ ሲመራቸው
ከእግዚአብሔር የኪዳንን ጽላትና አሠርቱን ትዕዛዛት
ተቀብሏል:: (ዘጸ. 20:1, 31:18)
(6) +"+ ኪዳነ ዳዊት +"+
=>ቅዱስ ዳዊት ሥርወ ነገሥት: ጻድቅ: የዋህና ቡሩክ
የሆነ አባት ነው:: እግዚአብሔር ከእረኝነት ጠርቶ ንጉሥ
አድርጐ ሹሞት "ከሆድህ ፍሬ በዙፋንህ ላይ
አኖራለሁ" (መዝ. 131:11) ሲል ምሎለታል:: አክሎም
ሰፊ ቃል ኪዳን ሰጥቶ "አልዋሰሽህም" ብሎ ሲምልለት
እንመለከታለን:: (መዝ. 88:35)
(7) +"+ ኪዳነ ምሕረት +"+
=>በብሉይ ኪዳን የነበሩ 6ቱ ኪዳናት በዘመናቸው ክቡርና
ሕዝቡን ከመቅሰፍት ይታደጉ የነበሩ ቢሆንም ከሲዖል
ማዳን ግን አልቻሉም:: ስለዚህም አንድ ፍጹም ኪዳን
ያስፈልግ ነበር:: ይህን ፍጹም ኪዳን ይፈጽም ዘንድም
ከቅድስት ሥላሴ አንዱ ወልድ ከሰማያት ወርዶ በድንግል
ማርያም ማሕጸን አደረ::
+በፍጹም ተዋሕዶም በሕቱም ድንግልና ተወልዶ: አድጎ:
ተጠምቆ: አስተምሮ: ሙቶ: ተነስቶና ዐርጐ ሥጋ
ማርያምን በዘባነ ኪሩብ አስቀመጠው:: ኪዳነ ምሕረት
(የምሕረት ኪዳን) የምንለው አንዱ ታዲያ ይሔው ነው::
+የጌታችን መጸነሱ: መወለዱ: መሰደዱ: መጠመቁ:
ማስተማሩ: ሥጋውንና ደሙን መስጠቱ: መሰቀሉ:
መሞቱና መነሳቱ: ማረጉና መንፈስ ቅዱስን መላኩ
በአንድ ላይ ኪዳነ ምሕረት ይባላል:: ታዲያ ይህ ሁሉ
የተደረገው በሥጋ ማርያም ነውና የኪዳኑ ባለቤት
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት::
+የእርሷ ኪዳን የ6ቱን አበው ኪዳናት ፍጹም በማድረጉ
"የኪዳናት ማሕተም" ይባላል:: የድንግል ማርያም ኪዳኗ
ከሲዖልና ከገሃነም ሊታደገን አቅሙ አለውና::
መድኃኒታችን ክርስቶስ ለድንግል እናቱ ቃል ኪዳኑን
ያጸናላት ደግሞ ካረገ ከዓመታት በሁዋላ ጐልጐታ ላይ ነው::
+እመ ብርሃን በዚያ ቁማ ስለ ኃጥአን ስታለቅስ "እናቴ
ሆይ! በስምሽ ያመነውን: በቃል ኪዳንሽ የተማጸነውን
እምርልሻለሁ" ብሎ ደስ አሰኝቷታልና:: ይሔው በእመ
ብርሃን ምልጃና ቃል ኪዳን ምዕመናን ከመቅሰፍትና
ከገሃነመ እሳት ማምለጥ ከጀመሩ 2ሺ ዓመታት ሆኑ::
ዛሬም እኛ ኃጥአን ልጆቿ ከእሳት እንደምታድነን አምነን
በጥላዋ ሥር እንኖራለን::
*" ኢትዝክሪ ብነ አበሳነ: ኃጢአተነ: ወጌጋየነ፡፡
ማርያም እሙ ለእግዚእነ፡፡
በኪዳንኪ: ወበስደትኪ ድንግል ተማሕጸነ:: "*
"ድንግል ሆይ! ኃጢአታችን: አበሳችንና በደላችንን
አታስቢብን ዘንድ በስደትሽና በኪዳንሽ ተማጽነናል::"
=>ቸሩ ልጇ ከበረከተ ኪዳኗ አይለየን::
+"+ አባ ያቃቱ ሊቀ ዻዻሳት +"+
=>በምድረ ግብጽ ከተነሱና ለመንጋው ከራሩ አበው
ዻዻሳት አንዱ አባ ያቃቱ ናቸው:: አባ ያቃቱ መጻሕፍትን
የተማሩ: በገዳምም የኖሩ በመሆናቸው እንደ
ቀደምቶቻቸው ቤተ ክርስቲያኗን በቅን መርተዋል::
+ፓትርያርክ ሆነው ከተሾሙ በሁዋላ ብዙ ጭንቅ ያሳለፉ
ሲሆን እግዚአብሔር አቅሎላቸዋል:: ከማረፋቸው
በፊትም ከእርሳቸው ቀጥለው የሚሾሙትን በጸጋ
ተናግረዋል:: አባ ያቃቱ ለግብጽ 49ኛ ሊቀ ዻዻሳት
ናቸው::
=>በረከታቸው ይደርብን::
=>ጥቅምት 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን
በዓላት=
1.አባ ያቃቱ ሊቀ ዻዻሳት
2.ጻድቃን እለ ድርቂ
3.አባ ዻውሊ ገዳማዊ
4.አባ ማርቆስ መስተጋድል
5.አባ አሮን መስተጋድል
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ኪዳነ ምሕረት (የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም)
2.ቅድስት ኤልሳቤጥ (የመጥምቁ ዮሐንስ እናት)
3.ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ (የቅ/ላሊበላ ወንድም)
4.ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ
5.አባ አቡናፍር ገዳማዊ
6.አባ ዳንኤል ጻድቅ
7.ቅዱስ አባ ዮሐንስ ጻድቅ (ወንጌሉ ዘወርቅ)
=>+"+ የምድር ባለጠጐች አሕዛብ በፊትሽ ይማለላሉ::
ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብሯ ነው::
ልብሷ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው::
በሁዋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ . . .
በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ::
በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ::
ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ:: +"+ (መዝ.
44:12-17)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
💐💖የማትሰለች እናት💐💖
ለሰው ችግርህን ብትነግረው ከንፈሩን
ይመጥልሃል ለወዳጅህ የመከራህን ጥልቅ ብታወያየው
ለጥቂት ጊዜ ይደግፍሃል ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ግን
ይሰለችህና ለማየት እንኳ ይጸየፍሃል። ሁሌም የማትሰለች ከሰው ተፈጥራ የሰው ችግር የሚገባት ፣የችግርን አስከፊነት እስከ ጥጉ የምታውቅ ፣መገፋትና መናቅን በህይወቷ ያሳለፈች ፣ መራብና መጠማትን ፣በባዕድ ምድር መስቃየትን ለዓመታት የቀመሰች የምስኪኖች አለኝታ ድንግል ማርያም ናት።
💐💖በመከራ ያለፈ ሰው ለመከረኛ ይራራል ፣ችግርን የቀመሰ ለተቸገረ ሰው ፈጥኖ ይደርሳል። ድንግል ማርያምን አዛኝት እናት እያልን የምንጠራትን ግጥም ለማሳመር ሳይሆን ችግራችንን እንደ ችግሯ አይታ ፈጥና ስለምትረዳን ነው። ከልቡ ሰአሊ ለነ ቅድስት ብሎ ያፈረባት ማንም የለም። እናትነቷ ባይገባንም እርሷ ግን ልጅነታችንን አምና ተቀብላለችና የእናትነት ፍቅሯ ዛሬም ሕያው ነው። ስጦታው መስቀል ሥር ነውና አደራው ጽኑ ነው። በፍቅር ለተቀበላት ፍቅሯን ታበዛለች ፣ ሳይሰለች ለሚጠራት ሳትሰለች ትመልሳለች። ድንግል ማርያም ወረተኛ ወዳጅ አይደለችም የታመነች የጸጋ እናት ነች እንጂ። እናት አትሰለችም ፣ እናት አትጸየፍም ብታዝንም ውስጧ ርኅሩኅ ነውና ዛሬም ልጄ ብላ በዓይኗ ትፈልጋለች።
💐💖ክርስቲያን ወንጌል ሲገባው ለድንግል ማርያም ያለው ፍቅርና ክብር በእጥፍ ይጨምራል ፤ ወንጌል ወንጀል ሲሆንበት ግን ሲነቅፍ ይውላል። ድንግል ማርያም እንደ ጌታ ቃል መኖርን በሕይወትዋ ያስተማረች የጽድቅ ምሳሌ ነች ፤ ንግሥተ ሰማይ ወምድር ስትሆን እንደ አገልጋይ ምልዕተ ጸጋ ስትሆን እንደ ተራ ሰው ራስዋን ዝቅ አድርጋ በፍጹም ትሕትና የእግዚአብሔርን ሐሳብ ስታገለግል የነበረች ባለ ታላቅ አዕምሮ ናት። ድንግል ማርያም ማቅለል መቅለል ነው ስምዋን ጠርቶ ማክበር ግን ያከበራትን ጌታ ማክበር ነው።🙏
💐💖አማላጅነቷ ቃል ኪዳኗ ይጠብቀን
ልማደኛ ኃጢአተኛ የሚባል የለም።
| ጃንደረባው ሚዲያ | ጥቅምት 2016 ዓ.ም.|
✍🏽 ቀሲስ ታምራት ውቤ እንደጻፉት
የሰውን ልጅ ተስፋ ሁልጊዜ ከሚያለመልሙ ነገሮች አንዱ እግዚአብሔር ማንንም ልማደኛ ኃጢአተኛ በሚል አለማየቱ ነው። ፊቱ ቀርበን ጌታ ሆይ አመንዝርያለሁ ወይም ሰርቄያለሁ ስንለው "ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል ዳግመኛ አትበድል፥ አሁን በሰላም ሂድ" ይለናል። በፍጹም ደስታ እንዲህ ዓይነቱንማ ጌታ እንዴት ያስቀይሙታል? ብለን የተወሰነ ጊዜ ከኃጢአት እንርቅና ደግሞ መልሰን እንበድላለን። አሁንም ፊቱን ለመሻት እንደገና እንሄዳለን::
"ምነው የእኔ ልጅ ? "
"አሁንም ያው አመነዘርኩ ወይም ሰረቅሁ ስንለው"
"ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ኃጢአት ይቅር ብዬህ አልነበረም?!" ብሎ ያለፈውን የኃጢአት ዶሴ አይመዝም:: ምሕረቱ ለዘላለም የሆነው አባት ንስሐ የተገባበትን ኃጢአት ለሪከርድ የሚያስቀምጥበት መዝገብ ቤት የለውም።
መልሰን መላልሰን በተመሳሳይ ኃጢአት በፊቱ ይቅርታን ለማግኘት ብንቆም አሁንም መልሱ "ዳግመኛ እንዳትበድል ፥ የቀደመ ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል በሰላም ሂድ የእኔ ልጅ " የሚል እንጂ በዚህ ጉዳይ ይቅር የምልህ ለስንት ጊዜ ነው የሚል አይደለም። ወይም እንደዚህ ዓለም ፍርድ ቤት በፊት የሠራናቸው ጥፋቶች ለቅጣት ማክበጃነት እንደሚውሉ በርሱ ዘንድ እንዲህ አይደለም።
አሁንም እንመጣለን፣ ደግመንም እንመጣለን. . . ። ግን እኛም ለመመላለስ እርሱም ይቅር ለማለት አይደክመውም። በእርግጥ እውነተኛ ንስሐ አሮጌውን ሰውነት አስወግዶ አዲስ ሰው መሆን ፤ በአእምሮ መታደስ የሚሆን ለውጥ ስለሆነ ድግግሞሽ የለውም። በአንድ ኃጢአት ደጋግሞ መውደቅ የሚኖር ንስሐችን በቁርጥ ሕሊና በተሰበረ ልቡና ሳይሆን ሲቀር ነው።
እርሱስ ይቅር ማለት የባሕርይው ነው፥ የእኛ ለወጥ እንኳ ሳይል በአንድ አጀንዳ መመላለስ ነው የሚያሳዝነው :: ይህንን ይቅርታ የትም አናገኘውም እርሱ ዘንድ ብቻ ነው ያለው ፣ የእርሱ ብቻ ሀብት ነው። እርሱ ፍቅሩ የእውነት ስለሆነ በደላችንን አይቆጥርብንም። የእውነት ከልብ ይቅርታ ከጠየቅነው ትላንት በሠራነው እንጠየቅም።
ቅዱስ ኒፎን እንዲህ እንዳለ " ጌታ እግዚአብሔር ክርስቲያኖችን ኃጢአት ስለ ሠሩ አይፈርድባቸውም፤ ምክንያቱም በኃጢአት መውደቅ ከጎሰቆለ ባሕርይ የሚጠበቅ ነው። ጌታ የሚፈርድባቸው ንስሐ ስለማይገቡ ነው።"
(ራእየ ኒፎን - ገጽ 57 )
ምን ያህል እንደሚወደን በቃላት መግለጽ አይቻልም፤ ከባድ ነው! ከቋንቋ በላይ የሚያወራውን በቀራንዮ ለእኛ የተሰቀለውን ክርስቶስን አይቶ መመለስ አለመቻል እንዴት ያለ የልብ መደንደን ነው?! በዚያ መከራ ውስጥ እያለፈ እንኳ፥ ከስቃዩ ጋር እየታገለ ከዓይኖቹ የሚረጨውን ነፍስን የሚያብረከርክ ፍቅር ፣ ስስት፣ ርኀራኄ ከማየትና ከማወቅ በላይ ሌላ መግለጫ ማሳያ አይኖርምና።
እኛስ ስንት ጊዜ ተበድለን ስንት ጊዜ ይቅር ብለናል? ነው ጥያቄው። "እኔ እኮ አንድ ሺህ ጊዜ ይሆናል ይቅር ያልኩት" እንላለን፥ ሊሆን ይችላል! ግን ይቅር ስንል ያደረግነው ምንድር ነው? ይቅር ብንልም መዝገቡ አልጠፋም፤ ሲያስፈልግ አምጥቶ ባለፈው እኮ እንዲህ ሆኖ ነበር ለማለት ጊዜያዊ ማቆያ (Recycle Bin) ውስጥ ነው ያምናስቀምጠው። ይሄ የሚያሳየው ይቅርታችን የእውነት አለመሆኑን ነው። ስለዚህ ራሳችንን እንፈትሽ። "ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው ይቅር ተባባሉ፤ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ" ነው የተባልን። ቈላ. 3፥13-14
እኛ ይቅር የተባልን በምን መጠን መሆኑ ሲገባን የወንድምቻችንን በደል የእውነት ይቅር ለማለት ኃይል መንፈሳዊ እናገኛለን። ወንድሙን ይቅር የማይል በራሱ ላይ የይቅርታ በርን ይዘጋል:: ከወንድሙ ጋር ሳይታረቅ የሚገባው ንስሐም በምሕረት ጌታ ፊት ተቀባይነት አይኖረውም። ስሌቱ ግልጽና ቀላል ነው " ይቅር የሚሉ ይቅር ይባላሉ፤ ይቅር የማይሉ ይቅርታን አያዩም"። ይቅርታ ከመጠየቅ ይቅር ማለት ከባድ የሚሆን ታላቅ ጥቅም የሚገኝበት ስለሆነ ነው::
ምሕረት የተደረገላት ነፍስ ምሕረት ታደርግ ዘንድ ይጠበቃል። በአባታችን ፊት ለሚከሰንም የእኛ ይቅር መባባል መጥፎ ትዝታውን መቀስቀስ ስለሆነ ለማክሸፍ የሚያደርገው አይኖርም። ይቅር በመባባል የዚያችን ቀን ሕያውነት አብሳሪ እንሁን!!!
" የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፥ ይማራሉና።"
(ማቴ 5 ፥7)
/ልማደኛ-ኃጢአተኛ-የሚባል-የለም
#የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው።
እግዚአብሔርን መፍራት የህይወት #ምንጭ ነው።
እግዚአብሔርን #መፍራት ወደ ህይወት ይመራል።
እግዚአብሔርን የሚፈራ #ከሁሉ ይወጣል ና።
እግዚአብሔርን የሚፈራ #ፍፃሜው ያምራል።
እግዚአብሔርን የሚፈራ #መከራ አያግኘውም ።
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
✞✞✞ ጥቅምት 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞
✞✞✞ አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ ✞✞✞
✞✞✞ በሃገራችን ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ እኒህ ጻድቅ ናቸው:: ጻድቁ የተወለዱት በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ ኣካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ንጉሥ ይስሐቅና ቅድስት እድና ይባላሉ:: የተለወለዱበት አካባቢም ሮም ነው::
+ስማቸው ብዙ ዓይነት ነው:: ወላጆቻቸው ዘሚካኤል ሲሏቸው በበርሃ ገብረ አምላክ ተብለዋል:: በኢትዮዽያ ደግሞ አረጋዊ ይባላሉ:: አቡነ አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ::
+በዚያም በገዳመ ዳውናስ (ግብጽ) የታላቁ ቅዱስ ዻኩሚስ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል:: ከመነኮሱ ከዓመታት በኋላም ወደ ሃገራቸው ሮም ተመልሰው በማስተማር 7 ያህል የቤተ መንግስት ሰዎችን ወደ ምናኔ ማርከዋል::
+"የት ልሒድ" ብለው ሲያስቡም ቅዱስ መልአክ በክንፉ ጭኖ ወስዶ ኢትዮዽያን አሳያቸው:: ተመልሰውም ለ8 ባልንጀሮቻቸው "ሃገርስ ባሳየሁዋችሁ! ሐዋርያ ሳያስተምራት በሕጉ በሥርዓቱ ጸንታ የምትኖር" ብለው ከ8ቱ ጋር ወደ ኢትዮዽያ መጡ::
+በዚህ ጊዜም እናታቸው ቅድስት እድናና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ:: ወደ ሃገራችን የመጡ በ470ዎቹ አካባቢ ሲሆን አልዓሜዳ በክብር ተቀብሏቸዋል:: በቤተ ቀጢን (አክሱም) ተቀምጠውም መጻሕፍትን እየተረጐሙ: ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል::
+ለሥራ በተለያዩ ጊዜም አቡነ አረጋዊ በዓት ፍለጋ ብዙ ደክመዋል:: በመጨረሻ ግን ደብረ ዳሞን (ደብረ ሃሌ ሉያን) አይተው ወደዷት:: የሚወጡበት ቢያጡም ጅራቱ 60 ክንድ የሚያህል ዘንዶ ተሸክሞ ከላይ አድርሷቸዋል::
+እንደ ወጡም "ሃሌ ሉያ ለአብ: ሃሌ ሉያ ለወልድ: ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ" ብለው ቢያመሰግኑ ከሰማይ ሕብስት ወርዶላቸው ተመግበዋል:: በዚህም ቦታዋ "ደብረ ሃሌ ሉያ" ተብላለች:: ጻድቁ ቦታውን ከገደሙ በኋላ ከተለያየ ቦታ መጥተው 6ሺ ያህል ሰዎች በእጃቸው መንኩሰዋል::
+ምናኔን በማስፋፋታቸውና ሥርዓቱን በማስተማራቸውም "አቡሆሙ ለመነኮሳት ዘኢትዮዽያ-የኢትዮዽያ መነኮሳት አባት" ይባላሉ:: አቡነ አረጋዊ በሕይወታቸው ከተጋድሎ ባሻገር በወንጌል አገልግሎትና መጻሕፍትን በማዘጋጀትም ደክመዋል::
+ቅዱስ ያሬድና አፄ ገብረ መስቀልም ወዳጆቻቸው ነበሩ:: በተራራው ግርጌ ያለችውን ኪዳነ ምሐረትን ለሴቶች ሲገድሟት ቀዳሚዋ መነኮስ እናታቸው ንግስት እድና ሁናለች::
+ጻድቁ ንጹሕ ሕይወታቸውን ፈጽመው በተወለዱ በ99 ዓመታቸው በዚህ ቀን በገዳሙ በስተምሥራቅ አካባቢ ተሰውረው ብሔረ ሕያዋን ገብተዋል:: ጌታም 15 ትውልድን የሚያስምር የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል::
+" ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ "+
✞✞✞ በዘመነ ሐዋርያት በዚህ ስም የሚጠሩ አባቶች 2 ነበሩ:: አንደኛው ከ12ቱ ሐዋርያት ሲቆጠር ዛሬ የምናከብረው ደግሞ ከ72ቱ አርድእት ይቆጠራል:: ቅዱስ ፊልዾስ ያደገው የኖረውም በቂሣርያ አካባቢ ሲሆን ባለ ትዳር የልጆች አባት ነው::
+ጌታ ሲጠራው እንኩዋ 4 ደናግል ሴቶች ልጆች ነበሩት:: ከጌታ ሕማማት በፊት ተልኮ አስተምሯል:: ከበዓለ ሃምሳ በኋላም 7ቱ ዲያቆናት ሲመረጡ አንዱ እርሱ ነበር:: (ሐዋ. 6) በቅዱስ እስጢፋኖስ መሪነትም 8ሺውን ማሕበር አገልግሏል::
+ቅዱስ እስጢፋኖስ ተገድሎ 8ሺው ማሕበር ሲበተንም ቅዱስ ፊልዾስ 4ቱን ልጆቹን አስከትሎ ወደ ሰማርያ ወርዷል:: በዚያም መሠሪ ስምዖንን ጨምሮ የሃገሪቱን ሰዎች አሳምኖ አጥምቁዋል::
+መቼም ቢሆን እኛ ኢትዮዽያውያን የማንዘነጋው ግን ጃንደረባውን ባኮስን ማጥመቁን እና ለሃገራችን የወንጌልን ብርሃን መላኩን ነው:: ጃንደረባው ቅዱስ ባኮስ ከጉዞ መልስ ትንቢተ ኢሳይያስን (ኢሳ. 53) ሲያነብ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ቀርቦ ምሥጢረ ሥጋዌን አስረድቶታል::
+ሠረገላውም ቁሞለት ቅዱስ ባኮስን አጥምቆት ተነጥቆ ሔዷል:: (ሐዋ. 8:26) ቅዱስ ፊልዾስ በቀሪ ዘመኑ ከተባረኩ 4 ደናግል ልጆቹ ጋር ሲሰብክ ኑሮ በዚህች ቀን ዐርፏል::
+" ሙሽራው ቅዱስ ሙሴ "+
✞✞✞ የዚህ ቅዱስ ወጣት ታሪክ ደስ የሚልም: የሚገርምም ነው:: በሮም ከተማ በምጽዋት: በጾምና በጸሎት ከተቃኙ ሃብታሞች (መስፍንያኖስና አግልያስ) ተወልዶ: በሥርዓቱ አድጐ: መጻሕፍትን ተምሮ በተክሊል አጋቡት::
+በሠርጉ ማግስት ሙሽሪትን ቢያያት በጣም ታምራለች:: "ይህ ሁሉ ውበትና ምቾት ከንቱ አይደለምን!" ብሎ በሌሊት ጠፍቶ: ነዳያንን መስሎ ከሮም ሃገረ ሮሆ (ሶርያ አካባቢ) ሔደ::
+በዚያም በፍጹም ምናኔ: በ7 ቀን አንዲት ማዕድ እየበላ: በረንዳ ላይ እየተኛና እየለመነ ለዓመታት ኖረ:: ሁሌም ቀን የለመነውን ማታ ለነዳያን አካፍሎ እርሱ ሲጸልይ ያድር ነበር:: በአካባቢው ክብሩ ሲገለጽበትም የሐዋርያውን የቅዱስ ዻውሎስን በረከት ፍለጋ ወደ ጠርሴስ ሔደ::
+ነገር ግን ጥቅል ነፋስ መርከቧን ገፍቶ ሮም አደረሳት:: ቅዱስ ሙሴም "የአምላክ ፈቃድ ነው" ብሎ በወላጆቹ ደጅ ተኝቶ ለ12 ዓመታት ተጋደለ:: ወላጆቹ ፈልገው ስላጡት በበራቸው የወደቀው ነዳይ እርሱ ይሆናል ብለው አልጠረጠሩም::
+ከብዙ ተጋድሎም በኋላም ዜና ሕይወቱን ጽፎ በዚህች ቀን: በዕለተ እሑድ ዐርፏል:: ጌታችንም "መታሰቢያህን ያደረገውን ሁሉ ካልተጠራጠረ እምረዋለሁ" ብሎታል::
በዚያም ሕዝቡ: ካህናቱና ሊቀ ዻዻሳቱን ጌታ አዟቸው አግኝተውታል:: ወላጆቹ ማንነቱን በለዩ ጊዜም ታላቅ ለቅሶን አልቅሰዋል:: ሥጋውም ብዙ ተአምራትን አድርጉዋል::
+" ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ "+
✞✞✞ ሙሽራው ገብረ ክርስቶስ በሃገራቸው ልሳን 'አብደል መሲሕ' ይባላል:: ለቅዱስ ሙሴና ለሌሎችም ሙሽርነትን ትቶ መመነንን ያስተማረ እርሱ ነው:: አባቱ ታላቁ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ሲሆን እናቱ መርኬዛ ትባላለች:: የጻድቃን ትውልድ የተባረከ ነውና (መዝ. 111:1) ታላቁ አቡነ ኪሮስ አጐቱ ናቸው::
+ስለዚህ ቅዱስ ምን እነግራቹሃለሁ! ሙሉ ታሪኩ ከቅዱስ ሙሴ ጋር ተመሳሳይ ነውና:: ልዩነቱ ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ በገዛ ፍቃዱ አካሉ በመቁሰሉ ምክንያት ሰዎች ሊለዩት አልቻሉም ነበር::
+በአርማንያ: በእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን ደጅ ለ15 ዓመታት ሲጋደል ወደ ወላጆቹ ሃገር ቁስጥንጥንያ ተመልሶ ለ15 ዓመታት ተፈትኗል:: ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆንም የአባቱ ባሮች በጥፊ ይመቱት: ጽሕሙን (ጺሙን) ይነጩት: ቆሻሻ ይደፉበት: ሽንታቸውንም ይሸኑበት ነበር::
+ለእርሱ ወዳጆቹ ውሾች ነበሩ:: በአባቱ ደጅ ለ15 ዓመታት መከራን ከተቀበለ በኋላ "ጌታ ሆይ! የአባቴ አገልጋዮች በእኔ ላይ ያደረጉትን ሁሉ በደል አድርገለህ አትቁጠርባቸው" አለ:: በዚህች ቀን ሲያርፍም ጌታችን 7ቱን ሊቃነ መላእክት ከነ ሠራዊታቸው አስከትሎ ወርዶ በክብር አሳርጐታል:: አጠቃላይ የገድል ዓመታቱም 30 ናቸው::
✞✞✞ አምላከ ቅዱሳን ለእነርሱ ካደለው ፍቅራቸው ለእኛም አይንሳን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::
+ጥቅምት 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አቡነ ዘሚካኤል (አረጋዊ)
2.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
3.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ
4.ቅዱስ ሙሴ መርዓዊ
5.ቅድስት እድና (የአረጋዊ እናት)
6.አባ ማትያስ (የአረጋዊ ረድዕ)
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖ ጥቅምት ፲፫ (13) ❖
/channel/zikirekdusn
✞✞✞ እንኩዋን ለዓለም ሁሉ መምሕር "ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ" እና ለአባ "ዘካርያስ ገዳማዊ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+"+ ዮሐንስ አፈ ወርቅ +"+
=>ለቤተ ክርስቲያን የብርሃን ምሰሶ ስለሆነላት ስለ ታላቁ
ሐዋርያዊ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ምን እላለሁ?
ምንስ እናገራለሁ? እንደ እኔ ያለ ኃጥእ: ለባሴ ሥጋና
ገባሬ ንስሃ ስለሱ ሊናገር አይቻለውምና:: አባቶቻችን
እንደ ነገሩን ስለ አፈ ወርቅ ለመናገር "አፈ ወርቅ"
መሆን ያስፈልጋል:: እስኪ በቅዱሱ አባት ምልጃ ጥቂት
ልሞክር::
+ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ማን ነው?
=>ነገዱ ከሶርያ: የተወለደው በ347 ዓ/ም በእስክንድርያ
ሲሆን አባቱ አስፋኒዶስ እናቱ ደግሞ አትናስያ ይባላሉ::
እነርሱ ደግ ቢሆኑ ይህንን እንቁ ልጅ እግዚአብሔር
ሰጣቸው:: ዮሐንስ ለክርስቲያን እንደሚገባ በትምሕርትና
በጥበብ አደገ:: ገና በሕጻንነቱ ወደ ግሪክ ሔዶ የዘመኑን
ሳይንስ (ፍልስፍና) ከአፉ እስከ ገደፉ ተምሮ ተመልሷል::
+ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን ለየት ከሚያደርጉት
ነገሮችም አንዱ ይሔው ነው:: በዘመናዊም ሆነ
በመንፈሳዊ ትምሕርት ይህ ቀረህ የማይሉት ሊቅ
የሆነው ገና በ15 ዓመቱ ነበር:: በ2 ወገን የተሳለ ሰይፍ
በመሆኑ ስንኩዋን በሕይወተ ሥጋ እያለ ዛሬም ለንፉቃን
ትልቅ የራስ ምታት ነው::
+ቅዱሱ ገና በ16 ዓመቱ ሃብት: ንብረት: ውበት: ክብርና
እውቀት የሞላለት ቢሆንም ያለውን ሁሉ ለነዳያን ሰጥቶ
መጻሕፍትን ብቻ ሰብስቦ ከባልንጀራው ቅዱስ ባስልዮስ
ጋር በርሃ ገባ:: ሰውነቱን በጾምና በጸሎት እየቀጣ በበርሃ
ሲኖር ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስና ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ
ዼጥሮስ ወደ እርሱ መጡ:: ሊቀ ሐዋርያት የመንግስተ
ሰማያትን መክፈቻ ስልጣን ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ
ወንጌሉን ሰጥተው ተሰወሩት::
+ከዚህች እለት በሁዋላ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ባሕረ
ምስጢራት ሆነ:: ብሉይ ከሐዲስ: ከኦሪት ዘፍጥረት
እስከ ራዕየ ዮሐንስ ድረስ በአንድምታ ትርጉዋሜ
ተነተናቸው:: በተለይ ሐዲስ ኪዳንን እየመላለሰ
አመሰጠረው:: ቅዱስ ሕሊናው ሳይታክት: ንጹሕ እጆቹ
ሳይዝሉ የጻፋቸው ድርሳናት: መልዕክታትና ትርጉዋሜያት
ቢቆጠሩ አሥር ሺህ ሞሉ:: በእውነት ለዚህ አንክሮ
ይገባል! የሚገርመው ይህን ሁሉ ሲሰራ እድሜው ገና
ለጋ: ማዕርጉም ዲቁና ነበር::
+ከዚህ በሁዋላ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ቅስና ተሹሞ
በስብከተ ወንጌል ብዙ ቦታዎችን አዳረሰ:: በቅድስናው
ወደውታልና የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት::
አፈ ወርቅ ሲናገርም ሆነ ሲያስተምር እንኩዋን የሚያወራ
ኮሽ የሚል የለም:: ከጣዕመ ትምሕርቱ የተነሳ ሕዝቡ
በተደሞ ይሰሙት ነበር:: ሲያስተምር ምድራዊው ሰው
ይቅርና ልዑላኑ መላእክት ተሰብስበው ያደንቁት ነበር::
አንዴም እመቤታችን በሕዝብ መካከል "አፈ ወርቅ" ብላ
ጠርታዋለች:: ለዛም ነው "አፈ ወርቅ" የሚባለው::
ቅዱሱ በሥልጣነ ቃሉ መልዐከ ሞትን ገስፆ 10 ዓመት
አቁሞታል::
+ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለሰው ፊት አያደላም:: በርሱ
ዘንድ ንጉሥና ደሃ ነዳይ እኩል ነው:: ለሞት ያበቃውም
ይሔው ነበር:: ምክንያቱም የወቅቱ ንግስት አውዶክስያ
ያንዲት ድሃ መበለትን መሬት ቀምታ "አልመልስም"
በማለቷ መክሮ አወገዛት:: እርሷ ግን ከኃጥአንና
መ********ና*********ፍ*******ቃ******ን ጋር መክራ 2 ጊዜ አጋዘችው:: በተሰደደበት
ሃገር ፍሬ አፍርቶ: አስተምሮና አሳምኖ በ407 ዓ/ም
አርፏል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ሳይጠግቡት
እንደናፈቁት በ60 ዓመቱ አጡት:: በወቅቱ ታላቅ ሐዘንና
ለቅሶ ተደረገ::
=>ከዕረፍቱ አስቀድሞ አንድ ቀን የዘመኑ ደግ ንጉሥ
አርቃድዮስ ግብር አገባ:: (ግብዣ አዘጋጀ)
በዚያች ሌሊት ደግሞ ቅዱሱ ሊቅ ታጥቆ ሲጸልይ ሳለ:
አባ ማርዳሪ የሚባል ጻድቅ ደግሞ ከሰማይ 12ቱ ሊቃነ
መላእክት (እነ ቅዱስ ሚካኤል) ከሰማይ በግርማ
ሲወርዱ ተመለከተ::
+ደንግጦ "ወዴት ናችሁ ጌቶቼ" ቢላቸው "ቁስጥንጥንያ:
ወደ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንሔዳለን:: እርሱ እመቤታችንን
እንደሚያመሰግናት ጌታ ነግሮናልና" አሉት:: "እባካችሁ
እኔም የአፈ ወርቅ ምስጋናው እንገለጥልኝ መርቁኝ"
አላቸው:: ሊቃነ መላእክቱም መርቀውት ጐዳናቸውን
ቀጠሉ::
+በማግስቱ በቤተ መንግስት ውስጥ ሊቃውንቱ:
መሳፍንቱ: ዻዻሳቱ: ሕዝቡ ሁሉ ተሰብስበው ከድግሱ
በሉ:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ግን በመንበሩ ተቀምጦ
ነበር እንጂ አልበላም:: ድግሱ ሲጠናቀቅ ንጉሡ
አርቃድዮስ ሊቁን "ጥያቄ አለኝ" ብሎ በጉባኤ መካከል
ጠየቀው::
+"ምነው ወንጌላዊ ማቴዎስ 'ኢያዕመራ ዮሴፍ እስከ
አመ ወለደት ወለደ ዘበኩራ-የበኩር ልጇን እስክትወልድ
ድረስ አላወቃትም' ማለቱ (ማቴ. 1:25) ስለ ምን ነው?"
ቢለው ቅዱሱ ተነስቶ: በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ
ይተረጉምለት ጀመር::
+"ድንግል ማርያም ንጹሕ ብርሌን ትመስላለች:: ብርሌ
የተለያየ ቀለም ያለው ፈሳሽ ቢያስገቡበት ቀለሙ አብሮ
ይቀያየራል:: እመቤታችንም ጌታን ጸንሳለችና ሕብረ
መለኮቱ ሲለዋወጥ መልኩዋ አብሮ ሲለዋወጥ እያየ
ዮሴፍ ይደነግጥ ነበር::
+'እርሷ ማን ናት? በማሕጸኗ ያለውስ ማን ነው?' እያለ
ይጨነቅ ነበር:: ጌታን ከወለደች በሁዋላ ግን አንድ
ሕብረ መልክ ሆናለችና:: አስቀድሞ ማን እንደ ነበረች
አላወቀም::
+አሁን ግን ልጇ አምላክ ዘበአማን: እርሷም ወላዲተ
አምላክ መሆኗን አወቀ ማለት ነው" እያለ ሲተረጉም
ሰምተው ሁሉም ሲያደንቁ በዚያ የነበረች ስዕለ አድኅኖ
"አፈ ወርቅ! ልሳነ ወርቅ! አፈ በረከት!" ስትል ተናገረች::
+ያን ጊዜ አርቃድዮስ የወርቅ ልሳን በሊቁና በስዕሏ ላይ
አደረገ:: አፈ ወርቅ ግን ባጭር ታጥቆ "እሰግድ ለኪ!
እሰግድ ለኪ! ወእዌድሰኪ . . ." ብሎ ዛሬ በተአምረ
ማርያም የምናውቀውን ምስጋና ሰተት አድርጐ
አደረሰላት:: ይህንን ምስጋናም ሊቃነ መላእክቱ ሰምተው
እያደነቁ ወደ ሰማይ ወጥተዋል::
=>ቅዱሱ ሲጠራ እንዲሕ ነው:-
¤ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
¤አፈ በረከት
¤አፈ መዐር (ማር)
¤አፈ ሶከር (ስኩዋር)
¤አፈ አፈው (ሽቱ)
¤ልሳነ ወርቅ
¤የዓለም ሁሉ መምሕር
¤ርዕሰ ሊቃውንት
¤ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ)
¤ሐዲስ ዳንኤል
¤ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው)
¤መምሕር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ
¤ጥዑመ ቃል - - -
+"+ አባ ዘካርያስ ገዳማዊ +"+
=>ይህ ታላቅ ጻድቅ ባለ ጥዑም ዜና ነው:: ወላጆቹ
እሱንና አንዲት ሴትን ከወለዱ በሁዋላ አባቱ መንኖ
ገዳም ገባ:: ከዘመናት በሁዋላ ረሃብ በሃገሩ ሲገባ እናቱ
ወስዳ ለአባቱ ሰጠችው:: ይህን ጊዜ ዕድሜው 7 ዓመት
ነበር::
+በገዳም ከአባቱ ጋር ሲኖር ከመልኩ ማማር የተነሳ
አባቶች መነኮሳት "ይህ ልጅ ይህን መልክ ይዞ እንዴት
መናኝ መሆን ይችላል!" ሲሉ ሰማ:: በሌሊትም ተነስቶ
በሕጻን አንደበቱ "ጌታየ! መልኬ ካንተ ፍቅር ከሚለየኝ
መልኬን አጠፋዋለሁ" አለ:: ከገዳሙም ጠፋ::
+አባትም በጣም አዘነ:: ከ40 ቀናት በሁዋላ ግን ሊያዩት
የሚያሰቅቅ: አካሉ ሁሉ የቆሳሰለ አንድ ነዳይ ሕጻን
መጥቶ ወደ ገዳሙ ተጠጋ:: ይህ ሕጻን በጾም: በጸሎትና
በትሕትና ተጠምዶ ለ45 ዓመታት አገለገለ::
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
/channel/zikirekdusn
❖ ጥቅምት ፲፪ (12) ❖
✞✞✞ እንኩዋን ለልበ አምላክ "ቅዱስ ዳዊት":
ለቅዱስ "ማቴዎስ ሐዋርያ" እና ለቅዱስ "ድሜጥሮስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+*" ቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ "*+
=>ቅዱስ መጽሐፍ እንዲህ ይላል:-
"እግዚአብሔር ለዳዊት በእውነት ማለ:
አይጸጸትም::" (መዝ. 131:11) አሁን በእግዚአብሔር
መጸጸት ኑሮበት አይደለም:: ቅዱስ ዳዊት የማያጸጽት
ፍጹም ወዳጅ መሆኑን ሲገልጥ ነው እንጂ:: ጌታ ቅዱስ
ዳዊትን "እንደ ልቤ የሆነ: ፈቃዴን የሚፈጽም: ባሪያየን
ዳዊትን አገኘሁት" (መዝ. 88:19) ብሎ ሲናገር ሰምተን
እጅግ አደነቅን::
+እንደ አምላክ ልብ ሆኖ መገኘት ምን ይረቅ?! ምንስ
ይደንቅ?! ለዚህ አንክሮ ይገባል !! ጌታ ይቀጥልና ደግሞ
"ዳዊትን እንዳልዋሸው አንድ ጊዜ በቅዱስነቴ
ማልሁ" (መዝ. 88:35) ይላል:: *" አቤት አባታችን
ዳዊት!!! . . .
ክብር: የክብር ክብር: ውዳሴና ስግደትም ላንተ በጸጋ ይገባል "* እንላለን::
+ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ዳዊት 7 ሃብታት ሲኖሩት:-
1.ሃብተ ትንቢት
2.ሃብተ መንግስት
3.ሃብተ ክህነት
4.ሃብተ በገና (መዝሙር)
5.ሃብተ ፈውስ
6.ሃብተ መዊዕ (ድል መንሳት)
7.ሃብተ ኃይል ተብለው ይታወቃሉ::
+በ7ቱ ስሞቹም:-
1.ጻድቅ
2.የዋህ
3.ንጹሕ
4.ብእሴ እግዚአብሔር
5.ነቢየ ጽድቅ
6.መዘምር እና
7.ልበ አምላክ ተብሎ ይጠራል::
+ይህች ቀን ለእሥራኤል የነገሠባት ቀን ናት::
እግዚአብሔር ሳዖልን ከናቀው በሁዋላ ከእሴይ ልጆች
መካከል "እንደ ልቤ የሆነውን ቀብተህ አንግስልኝ"
ቢለው በዚህች ቀን ነቢዩ ሳሙኤል ቤተ ልሔም
ገብቷል::
+በዚያም ከኤልያብ እስከ አሚናዳብ: 7ቱን የእሴይን
ልጆች ቢፈትን አልሆነም:: በቅዱስ ሚካኤል ጠቁዋሚነት
ግን ከእረኝነቱ ዳዊት ተጠራ::
ገና ከርቀት ሲመጣ የዘይት ቀርኑ ቦግ ብሎ ተከፈተ::
+በቅዱስ ዳዊት ራስ ላይም እንደ እሳት ፈላ:: በአምላክ
ምርጫም በ12 ዓመቱ ንጉሥ ተባለ:: የቅዱሱ ዜና ብዙ
ነውና ለታሕሳስ 23 ይቆየን:: በቸር ቢያደርሰን በዚያው
ቀን ከክብሩ እንካፈላለንና::
+"+ ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ +"+
=>ቅዱሱ በቀዳሚ ስሙ "ሌዊ": በቀዳሚ ግብሩ ደግሞ "ቀራጩ" ይባል ነበር:: ወንጌል እንደሚል ጌታችን የጠራው ከሚቀርጥበት ቦታ ሲሆን (ማቴ. 9:9) ከ12ቱ ሐዋርያት ደምሮ (ማቴ. 10:1) ስሙን "ማቴዎስ" ብሎታል:: ትርጉሙም "ኅሩይ" (ምርጥ) እንደ ማለት ነው::
+ጌታችንን በዘመነ ሥጋዌው በፍጹም ምናኔ ከማገልገሉ
ባለፈ ከዋለበት እየዋለ: ካደረበት እያደረ: የእጁን
ተአምራት ተመልክቷል:: የቃሉንም ትምሕርት ሰምቷል::
በጌታ ሕማማት ጊዜ ምንም በፍርሃት ከተበተኑት አንዱ
እሱ ቢሆን አመሻሽ ላይ ወደ ማርቆስ እናት ቤት (ጽርሐ ጽዮን) ሒዶ ወንድሞቹን ሐዋርያትን ተቀላቅሏል::
+የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ከሙታን ተነስቶ ትንሳኤውን ሲገልጥም ቅዱስ ማቴዎስ
ነበረ:: ለ40 ቀናት መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓትን
ተምሮ በጌታ ዕርገት ጊዜ ሊቀ ዽዽስናን ተሹሟል::
በ50ኛው ቀን መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜም ጸጋውንና
71 ልሳናትን ተቀብሎ በኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ወንጌልን
ሰብኩዋል::
+ሐዋርያት ወንጌልን ለዓለም ለማዳረስ እጣ በተጣጣሉ
ጊዜ ለቅዱስ ማቴዎስ ምድረ ፍልስጥኤም ደረሰችው::
ሃገረ ስብከቱን ካዳረሰ በሁዋላም ወደ ሌሎች ሃገራት
ተጉዞ ሰብኩዋል::
+ለምሳሌ በገድለ ሐዋርያት ላይ በኢትዮዽያ: በፋርስና
በባቢሎን አካባቢ ማስተማሩን ይገልጻል:: የሚገርመው
ደግሞ ለዚህ ማረጋገጫ የሚሆን ነገር ሃገራችን ውስጥ
መኖሩ ነው::
+ወደ አክሱምና አካባቢዋ ቅዱሳት መካናትን ለመሳለም
በሔድንበት ወቅት በጻድቃነ ዴጌ/ዶጌ ገዳም ውስጥ
(አክሱም አካባቢ የሚገኝ የ3ሺ ስውራን ቦታ ነው)
የቅዱስ ማቴዎስን በትረ መስቀል መመልከት ችለናል::
አባቶችም ቅዱስ ማቴዎስ በዘመነ ስብከቱ አክሱም
አካባቢ መጥቶ እንደ ነበር ነግረውናል::
+ቅዱሱ ሐዋርያ በአይሁድ: በአሕዛብና በአረሚ መካከል
እየተመላለሰ አስተምሮ በርካታ ተአምራትን ሠርቷል::
የጣዖት ካህናትንና ነገሥታትን ጨምሮ እልፍ አእላፍ
ነፍሳትን ወደ ክርስትና መልሷል::
+ስለዚህ ፈንታም እጅግ ብዙ መከራዎች
ተፈራርቀውበታል:: ጌታችንም በየጊዜው እየተገለጸ
ያጽናናው ነበር:: በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የመጀመሪያውን
ወንጌል በምድረ ፍልስጥኤም ሲጽፍ: ዘመኑም ጌታ ባረገ
በ8ኛው ዓመት (ማለት በ43 ዓ/ም) አካባቢ ነው::
+ወንጌሉ 28 ምዕራፎች ሲኖሩት በጌታ የዘር ሐረግ
ጀምሮ የጌታችንን ትምሕርቱንና ተአምራቱን በሰፊው
ያትታል:: በመጨረሻም ከምሴተ ሐሙስ እስከ ትንሳኤ
ድረስ አትቶ ይጠናቀቃል::
+ቅዱስ ማቴዎስ ከ12ቱ ሐዋርያት በአንድ ነገሩ
ይለያል:: ከ5ቱ ዓለማት አንዱን (ብሔረ ብጹዓንን)
ያስተምር ዘንድ ተመርጧል:: ዘወትር እሑድ በደመና
እየተነጠቀ ኃጢአት ወደ ሌለበት ዓለም ገብቶ ብጹዓንን
ያስተምር ነበር::
"ሰላም ለማቴዎስ በደመና ሰማይ ዘተነጥቀ:
ኅሩያነ ይርዓይ ዘብሔረ ብጹዓን ደቂቀ::" እንዲል::
+በዚያም ዘወትር ጌታችንን ያየው ነበር:: ቅዱስ ማቴዎስ
እንዲህ ከተመላለሰ በሁዋላ በፍጻሜው ለጊዜው
ባልለየናት አንዲት ሃገር ውስጥ አረማውያን አስረው
አሰቃይተውታል:: በዚህች ቀንም ገድለውታል::
+"+ ቅዱስ ድሜጥሮስ +"+
=>ቅዱስ ድሜጥሮስ በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደ:
በመንፈሳዊ ለዛ ከአጐቱ ደማስቆስ ጋር ያደገ የዘመኑ
ደግ ሰው ነበር:: በዘመኑ ክርስቲያኖች በሰማዕትነት
ያለቁበት በመሆኑ ቤተሰቦቹ የአጎቱን ልጅ ልዕልተ ወይንን
እንዲያገባ ግድ አሉት::
+ቅዱስ ድሜጥሮስ የነርሱን ፈቃድ ለመፈፀም ጋብቻውን
በተክሊል ፈፀመ:: የፈጣሪውን ፈቃድ ለመፈፀም ደግሞ
ከቅድስት እናታችን ልዕልተ ወይን ጋር ተስማምተው ለ48
ዓመታት በአንድ አልጋ ላይ እየተኙ: አንድ ምንጣፍና
ልብስ እየተጋሩ በድንግልና ኑረዋል:: ቅዱስ ሚካኤልም
ስለ ክብራቸው ከመካከላቸው ሆኖ ቀኝ ክንፉን ለርሱ:
ግራ ክንፉን ለርሱዋ ያለብሳቸው ነበር::
+ከ48 ዓመታት በሁዋላ ቅ. ድሜጥሮስ የግብፅ 12ኛ
ሊቀ ዻዻስ ሆኖ ተሹሞ ምስጢር በዝቶለት ባሕረ-
ሐሳብን ጽፎ ሠርቷል:: ሰይጣን በሰዎች አድሮ ቅዱሱን
ሚስት አለው በሚል ቤተ ክርስቲያን ላይ ሁከት
በመፈጠሩ ቅዱስ ድሜጥሮስ በመልዐኩ ትእዛዝ ሕዝቡን
ሰብስቦ: እሳት አስነድዶ: ከቅድስት ልዕልተ ወይን ጋር
እሳቱ ውስጥ ገብተው ለረዥም ሰዓት ጸልየዋል::
+ሕዝቡም ይሕን ተአምር አይተው: የቅዱሳኑን ንጽሕና
ተረድተው: ማረን ብለው በፍቅር ተለያዩ:: መጋቢት 12
ቀን ድንግልናው ተገልጧል::
+ቅዱስ ድሜጥሮስና እናታችን ልዕልተ ወይን ተረፈ
ዘመናቸውን በቅድስና አሳልፈዋል:: በተለይ ሊቀ ዻዻሳቱ
ድሜጥሮስ ብዙ ድርሳናትን ደርሷል:: እነ አርጌንስ
(Origen) ና ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ (Clement of Alexandria) የመሰሉ መናፍቃንንም አውግዟል::
+ከጣዕመ ስብከቱም የተነሳ አርጅቶ እንኩዋ ምዕመናን
እየተበሰቡ ይማሩ ነበር:: በአልጋ ተሸክመውም
ይባርካቸው ነበር:: ቅዱሱ በ107 ዓመቱ ያረፈው በ3ኛው
መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ አካባቢ በዚህች ቀን ነው::
የመላዕክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሐገረ ኢትዮጵያን ይታደግልን!
"ኦ ሚካኤል ኦ መተንብል፣ ካህነ አርያም ትሰመይ ቢጸ ሱራፌል፣ ዘእምርዑሳን ርዑስ ወዘእምልዑላን ልዑል፣ ጊዜ ጸዋዕኩከ ቅረበኒ በምሕረት ወሣህል፡፡"
"አማላጃችን ሚካኤል ሆይ ፈጥኖ ደራሻችን ሚካኤል ሆይ የጌታን ዙፋን ከሚያጥኑ ሱራፌል ካህናት አንዱ ሰማያዊ ካህንአንተ ነህ ።
🥀የሰማያውያን ሊቃነ መላእክት ሁሉ አንተ አለቃቸው ነህ
ይልቁንም የልዑላንም ልዑል አንተ ነህና በጠራሁህ ጊዜ ሁሉ በይቅርታና በቸርነት ድረስልኝ አትራቀኝ አሜን።"
(መልክአ ሚካኤል)
+ በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ +
ይድረስ ለተከፋኸው ወንድሜ
መኖር ለደከመህ ፣ ሕይወት ለታከተህ ፣ የሚሰማህ ላጣኸው ፣ የሚረዳህ ሰው ላላገኘኸው መከረኛው ወዳጄ!
ከሞት ውጪ ሌላ መፍትሔ አልታይ ካለህ የአንተ ቢጤ መከረኞቹ ጳውሎስና ሲላስ እስር ቤት ውስጥ ሆነው እንዲህ ይሉሃል::
"በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ" ሐዋ. 16:28
አውቃለሁ ዙሪያው ገደል ሆኖብሃል:: ምነው ባልተፈጠርሁ እስክትል ድረስ ተጨንቀሃል::
ግን ይህ ስሜት በአንተ አልተጀመረም:: ሰው ሆኖ ተፈጥሮ ኑሮ ያልመረረው ማን አለ? መሞት ያልተመኘስ ማን አለ?
ሞት ያማረህ አንተን ብቻ መሰለህ?
" ስለ ምን ከማኅፀን አወጣኸኝ? ዓይን ሳያየኝ ምነው በሞትሁ" ያለውን ጻድቅ ኢዮብ አልሰማህም? (ኢዮ. 10:18)
"ከአባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ" ብሎ እንዲሞት የለመነውን ኤልያስን አላየኸውም? 1ነገሥ. 19:4
ዮናስንስ "አሁንም፥ አቤቱ፥ ከሕይወት ሞት ይሻለኛልና እባክህ፥ ነፍሴን ከእኔ ውሰድ፡ አለው" ሲል አልሰማኸውም? (ዮናስ 4:3)
ወንድሜ እመነኝ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን መኖር ያላስጠላው ሰው በታሪክ ፈልገህ አታገኝም::
ሞት ሞት የሸተተው ልቡ የተሰበረ ብዙ ነው:: አንተ ላይ ብቻ የደረሰ ልዩ ፈተና የለም:: "ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል" ይላል መጽሐፍ:: 1ኛ ቆሮ. 10:13
ምናልባት የልብህን መሰበር የኀዘንህን ጥልቀት አይቶ ምቹ ጊዜ አገኘሁ ብሎ ራስህን እንድትጎዳ ሰይጣን ሊገፋፋህ ይችላል:: እንዴት እንዲህ ዓይነት ሃሳብ በልቤ ሊመጣ ቻለ ብለህ አትረበሽ:: ሰይጣን ይህንን ክፉ ሃሳብ ላንተ ብቻ ሳይሆን ለክርስቶስም አቅርቦለታል::
"የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ወደ ታች ራስህን ወርውር" ብሎ ክርስቶስን እንኳን [ማንነቱን ሳያውቅ] ራሱን እንዲወረውር ሊገፋፋው የሞከረ ደፋር ነው:: የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሰው ግን ራሱን አይጎዳም:: "ጌታ አምላክህን አትፈታተነው" "ሒድ አንተ ሰይጣን" ብለህ ሰይጣንን ገሠፀው::
ሰይጣን ክርስቶስን "ከሕንፃ ጫፍ በመወርወር የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህን አሳይ" ሲለው ክርስቶስ ሰይጣንን ሒድልኝ ብሎ በመገሠጹ በክብር ወደ ሰማይ ዐርጎ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ::
ወንድሜ ሆይ አንተም ሰይጣንን አትስማው ሃሳቡ ራስህን ጎድተህ ከፈጣሪህ እንድትጣላ ሊያደርግህ ነው:: ሰይጣንን ከገሠጽከው በእግዚአብሔር ቀኝ ከበጎቹ ጋር ትቆማለህ::
አሁን ያለህበት ችግር ያልፋል:: የሚሰማህ ክፉ ስሜት መቼም የማይለወጥ አይምሰልህ:: ኀዘኑም ፣ ብቸኝነቱም ፣ ተስፋ ቢስነቱም ያልፋል:: ጨለማው ይነጋል:: የተዘጋው በር ይከፈታል:: ችግሩ ሲፈታ አንተ ከሌለህ ግን ትርጉም የለውም::
ስለዚህ ለሚፈታ ችግር የማይቀለበስ ውሳኔ አትወስን:: ራስን ማጥፋት ከጊዜያዊ ችግር ለመሸሽ ሲሉ ዘላቂ ችግር ውስጥ መግባት ነው:: ጊዜያዊ ሕመምን ለማስታገስ የዘላለም ሕመምን ለምን ትመርጣለህ? "የሞተ ተገላገለ" ሲሉ ሰምተህ እንዳትታለል ሞት ዕረፍት የሚሆነው ራሱ እግዚአብሔር ሲጠራህ ብቻ ነው::
"እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁ" ያለው ጌታ ሳይጠራህ ራስን ማጥፋት የዘላለም ስቃይ ያመጣል::
ወዳጄ "በራስህ አንዳች ክፉ አታድርግ"
የሕይወትህን ዋጋ ታውቅ ይሆን? አንተ እኮ የእግዚአብሔር ልጅ ለአንተ ሲል የሞተልህ ነህ:: ሊፈውስህ የቆሰለ ፣ ሊያከብርህ የተዋረደ ፣ ሊያረካህ የተጠማ ፣ ሊያለብስህ የተራቆተ ለአንተ እኮ ነው::
ክርስቶስ ስለ አንተ ሞቶአል:: አንተን ግን የጠየቀህ እንድትሞትለት ሳይሆን እንድትኖርለት ነው::
ለሞተልህ አምላክ እንዴት መኖር ያቅትሃል?
ወዳጄ ሆይ ሰውነትህ በአምላክ ደም የተገዛ ክቡር ሰውነት ነው:: አካልህ "አንተ" እንጂ "ያንተ" አይደለም:: "በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ" ይላል
ስለዚህ በከበረ የእግዚአብሔር ልጅ ደም የተገዛ ሰውነትህን ለሰይጣን በርካሽ አትሽጠው:: አትግደል የሚለው ሕግ ራስህንም ይጨምራል:: ቤተ መቅደስ የሆነ ሰውነትህን ለማፍረስ አታስብ::
"ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ" 1ኛ ቆሮ. 3:17
ሰዎች አስቀይመውህ ይሆን?
"አሳያቸዋለሁ ፤ ስሞት የእኔን ነገር ይገባቸዋል" ብለህ በሰዎች ተቀይመህ ራስህን አትጉዳ:: እመነኝ ብትሞት ሰዎች ከሳምንት በላይ አያስታውሱህም:: ለሕይወትህ ዋጋ ያልሠጡ ሰዎች ለሞትህ ዋጋ አይሠጡም:: ፈጥነውም ይረሱሃል:: ለሚረሱህ ሰዎች ብለህ የማይረሳህን አምላክ አታሳዝን:: ሰው ስለ አንተ ግድ የለውም እግዚአብሔር ግን የራስህን ቁጥር ሳይቀር በቁጥር ያውቀዋል :: እንኳንስ ራስህን ልትጎዳ አንዲት ጸጉር እንኳን ከአንተ እንድትወድቅ አይፈልግም::
እግዚአብሔርን በኃጢአት ብታሳዝነው እንኳን ኖረህ ንስሓ እንድትገባ እንጂ እንድትሞት አይፈልግም:: አባትህ ነውና ከእርሱ ጋር ባትሆንም እንድትኖር ይፈልጋል:: በምሳሌ ልንገርህ :-
ሁለት ሴቶች አንድን ሕፃን "የኔ ልጄ ነው" ብለው እየተከራከሩ ጠቢቡ ሰሎሞን ፊት ቀረቡ:: ጠቢቡ ሰሎሞን ሰይፍ አመጣና "ልጁን ቆርጬ ለሁለት ላካፍላችሁ" አላቸው:: አንደኛዋ ሴት "እሺ እንካፈል" ስትል እውነተኛዋ እናት ግን "ልጄ ከሚሞት እርስዋ ትውሰደው" አለች:: እናት መሆንዋም በዚህ ታወቀ::
ወዳጄ ያንተም ኑሮህ ከእግዚአብሔር ጋር ላይሆን ይችላል:: ዓለም የራስዋ አድርጋህም ይሆናል:: በሱስ ውስጥ ትዘፍቀህ ፣ እንደ ሶምሶን በደሊላ እቅፍ ፣ እንደ ዴማስ በተሰሎንቄ ውበት ተማርከህ ይሆናል:: እግዚአብሔር ግን አባትህ ነውና ሞትህን አይፈልግም::
"ልጄ ከሚሞት እርስዋ ትውሰደው" እንዳለችው እናት ፈጣሪህ ከነኃጢአትህም ቢሆን እንድትሞት አይፈልግም:: ከእርሱ ጋር ባትኖርም መኖርህን ይፈልጋል:: "የሟቹን ሞት አልፈቅድምና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ" ሕዝ. 18:32
የይሁዳ ኃጢአቱ ጌታውን መሸጡ አልነበረም:: ራሱን መግደሉ ነው:: እግዚአብሔር የሚያዝነው ከበደልህ በላይ በእርሱ ተስፋ ቆርጠህ ራስህን ስትጎዳ ነው::
ወዳጄ የአንተን መኖር የሚፈልጉ ብዙ ናቸው:: ፈጣሪ ወደዚህች ዓለም ያለ ምክንያት አላመጣህም:: በአንተ አለመኖርም የሚጎድል ነገር አለ:: አንተን የሚመስል ሌላ ሰው አልፈጠረምና ለዚህ ዓለም አንተን የሚተካ የለም:: በክብር ወደዚህ ዓለም ያመጣህ አምላክ በክብር ወደራሱ እስኪወስድህ ድረስ "በራስህ ላይ ክፉ ነገር አታድርግ"
"የወኅኒውም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ።
ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ፦ ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ፡ ብሎ ጮኸ" ሐዋ. 16:27-28
ይህ ሰው እስረኛ ያመለጠ መስሎት ራሱን ሊያጠፋ ሲል ጳውሎስ "ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ" አለው::
ወዳጄ አንተስ ተስፋ የቆረጥኸው ምን ያመለጠ መስሎህ ነው?
#ጥቅምት_10
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ዐሥር በዚህች ቀን የቅዱስ ባኮስ ባልንጀራ የሆነ #ቅዱስ_ሰርጊስ በሰማዕትነት አረፈ፣ የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_አውማንዮስ አረፈ፣ መስተጋድል የሆነ #ቀሲስ_ዮሐንስ አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ሰርጊስ_ሰማዕት
ዳግመኛም በዚችም ቀን ከከሀዲ ንጉሥ መክስምያኖስ ሠራዊት ውስጥ የቅዱስ ባኮስ ባልንጀራ የሆነ ቅዱስ ሰርጊስ በሰማዕትነት አረፈ። ንጉሥ መክስምያኖስም ወደ ሶርያ አገር ወደ አንጥያኮስ በላካቸው ጊዜ ቅዱስ ባኮስን ከውኃ በማስጠም በዚህ ወር በአራተኛ ቀን ገደሉት። ቅዱስ ሰርጊስን ግን አሥሮ በወህኒ ቤት አኖረው።
ከዚህም በኋላ በእግሮቹ ውስጥ ረጃጅም የብረት ችንካሮችን ቸንከረው ከፈረሰኞች ጋር ሩጻፋ ወደሚባል አገር እንዲወስዱት መኰንኑ አዘዘ።
ሲወስዱትም ያስሮጡት ነበር ደሙም በምድር ላይ እንደ ውኃ ይፈስ ነበር በጐዳናም አንዲት ድንግል ብላቴና አገኘ ከእርሷም ዘንድ ውኃን ጠጣ ሥጋዬን ትወስጂ ዘንድ እስከ ሩጻፋ ተከተይኝ አላት እርሷም ራራችለት ለጒልምስናውም አዘነችለትና ተከተለችው።
አንጥያኮስም እንዲህ ብሎ ጽፎአልና ሰርጊስ ትእዛዜን ተቀብሎ ለአማልክት ካልሠዋ ራሱን በሰይፍ ይቁረጡ። እርሱም ለቅዱስ ሰርጊስ ወዳጅ ነበርና ስለርሱም ይችን ሹመት አግኝቷት ነበርና በዚያንም ጊዜ ወታደሩ የቅዱስ ሰርጊስን ራስ ቆረጠው ያቺም ብላቴና ቀርባ ከእርሷ ጋር በነበረ የፀጕር ባዘቶ ከአንገቱ የፈሰሰውን ደሙን ተቀበለች። የስደቱም ወራት እስከ አለፈ ድረስ ሥጋውን ጠበቀች።
ከዚህም በኋላ ያማረች ቤተ ክርስቲያን ተሠራችለት ዐሥራ አምስት ኤጲስቆጶሳትም አከበሩዋት የቅዱስ ሰርጊስንም ሥጋ በውስጥዋ አኖሩ ከእርሱም ብዙ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ እጅግ ሽታው ጣፋጭ የሆነ በሽተኞችን የሚፈውስ የሽቱ ቅባት ከሥጋው ይፈስ ነበርና።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ሊቀ_ጳጳሳት_ቅዱስ_አውማንዮስ
ጥቅምት ዐሥር በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሰባተኛ የሆነ የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት አውማንዮስ አረፈ።
ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ ንጹሕ ትሑት የሆነ ለዕውነተኛ ሥራ ሁሉ የሚያገለግል ነበር ቅዱስ አብርምዮስም ትሩፋቱን አይቶ ዲቁና ሾመው በዲቁና አገልግሎትም ዐሥር ዓመት ኖረ።
ዮስጦስም ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ ትሩፋቱንና የሃይማኖቱን ቅንነት ተመለከተ ምእመናንንም ማስተማር እንደሚችል አውቆ ቅስና ሾመው። ከዚህም በኋላ ቅዱስ ዮስጦስ በአረፈ ጊዜ ይህን አባት አውማንዮስን መርጠው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት የአብያተ ክርስቲያናትንም ሥራ ሁሉ ተረከበ።
መናፍቃንንም ተከራክሮ የሚረታቸው ሆነ ብዙዎችንም ከስሕተታቸው መለሳቸው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመለኮቱ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል እንደሆነ ግልጽ አድርጎ አስተማራቸው። በሹመቱም ዐሥራ ሦስት ዓመት ከኖረ በኋላ በአንስጣዮስ ሰባተኛ ዘመነ መንግሥት በዚች ቀን አረፈ። በዘመኑም የሶፍያ ሦስቱ ልጆቿ በሰማዕትነት አረፉ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ዮሐንስ_ቀሲስ
ዳግመኛም በዚችም ቀን መስተጋድል የሆነ ቀሲስ ዮሐንስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ከተጋድሎው ብዛት የተነሣ ራሱን በሚላጭ ጊዜ በውኃ አያርሰውም ነበር።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይግባው እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት)
🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁
ምስባክ ዘሣልሳይ ጽጌ ወበዓለ ቅድስት ሐና
🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃
ምንባባት፦
፩ ቆሮ ፲÷፩-፲፬
ራእ፡ዮሐ ፲፬÷፩-፮
ግብ፡ሐዋ ፬÷፲፱-፴፩
ወንጌል፦ ማቴ ፲፪÷፩-፴፪
ቅዳሴ፦ ዘእግዝእትነ
ምስባክ፦
ጻድቅሰ ከመ በቀልት ይፈሪ፣
ወይበዝኅ ከመ ዘግባ ዘሊባኖስ፣
ትኩላን እሙንቱ ውስተ ቤተ እግዚአብሔር።
ትርጉም፦
ጻድቅ ግን እንደዘንባባ ያፈራል፣
እንደሊባኖስም ዝግባ ያድጋል፣
በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ተተክለዋል።
መዝ ፺፩÷፲፪
🇪🇹👇👇👇👇👇👇🇪🇹
👉 @menkir_tube 👈
👉@menkir_tube 👈
👉@menkir_tube 👈
🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹
✞✞✞ እንኩዋን ለአበው ቅዱሳን "አባ አጋቶን ወአባ መጥራ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+"+ አባ አጋቶን ባሕታዊ +"+
=>ይህንን ቅዱስ የማያውቅ የቤተ ክርስቲያን ሰው ይኖራል ብየ አልገምትም:: እርሱ ታላቅ ጻድቅ: ገዳማዊና የእግዚአብሔር ሰው ሲሆን አንደበቱን ከክፋት ይከለክል ዘንድ ለ30 ዓመታት ድንጋይ ጐርሶ ኖሯል::
+ይህንን ቅዱስ ሊቃውንት ሲገልጹት:
"ክምረ ክምር ጽድቁ እስከ አስተርአየ" ይሉታል:: ትእግስቱ: ደግነቱ: አርምሞው: ትሩፋቱ ከመነገር በላይ ነው:: በነበረበት በ4ኛው መቶ ክ/ዘመንም እንደ ኮከብ ያበራ ታላቅ አባት ነው::
+ታላቁ ገዳማዊ ሰው አባ አጋቶን የታላቁ መቃርዮስ ቅዱስ ልጅ ነው:: ገዳመ አስቄጥስ እልፍ አእላፍ ቅዱሳንን ስታፈራ ይህ አባት ቅድሚያውን ይይዛል:: ምንም በብዛት የሚታወቀው በአርምሞው (በዝምታው) ቢሆንም ባለ ብዙ ትሩፋት አባት ነው::
+የሚገርመው የቀደሙ አባቶቻችን የፈለገውን ያህል መናኝ ቢሆኑም የሰው ጥገኛ መሆንን አይፈልጉም:: "ሊሠራ የማይወድ አይብላ" የሚለውን መለኮታዊ ትዕዛዝ መሠረት አድርገው ከተጋድሎ በተረፈቻቸው ሰዓት ሥራ ይሠራሉ::
+አንዳንዶቹ እንደሚመስላቸው ምናኔ ሥራ መፍታት አይደለምና ሰሌን: ዕንቅብ: ሠፌድ የመሳሰለውን ይሠፋሉ:: ታላቁ አባ አጋቶንም በአንደበቱ ድንጋይ ጐርሶ: በእግሮቹ ቀጥ ብሎ ቆሞ እንቅቦችን ይሠፋ ነበር::
+ለነገሩስ ዛሬ ዛሬ እንኩዋን ወንዶቹ ሴቶችም ብንሆን ይህንን ሙያ እየረሳነው ነው:: ቅዱሱ ግን ይሰፋና ወደ ገበያ ይወጣል:: በጠየቁት ዋጋ ሽጦት አንዲት ቂጣ (ዻኩሲማ) ይገዛል:: የተረፈውን ገንዘብ ግን እዚያው ለነዳያን አካፍሎት ይመጣል እንጂ ወደ ገዳሙ አይመልሰውም::
+ታዲያ አንድ ቀን እንደልማዱ የሠፋቸውን 5 እንቅቦች ተሸክሞ ወደ ገበያ ሲሔድ መንገድ ላይ አንድ ነዳይ (የኔ ቢጤ) ወድቆ ያገኛል:: እንደ ደረሰም ስመ እግዚአብሔር ጠርቶ ይለምነዋል:: አባ አጋቶን ከእንቅቦቹ ውጪ ምንም ነገር አልነበረውምና "እንቅቡን እንካ" አለው::
+ነዳዩ ግን ወይ የሚበላ: ካልሆነም ገንዘብ እንደሚፈልግ ይነግረዋል:: ወዲያው ደግሞ "የምትሠጠኝ ነገር ከሌለህ ለምን ወደ ገበያ ተሸክመህ አትወስደኝም?" አለው:: የነዳዩ አካል እጅግ የቆሳሰለ በመሆኑ እንኩዋን ሊሸከሙት ሊያዩትም የሚከብድ ነበር::
+ጻድቁ ግን ደስ እያለው: ያለማመንታት አንስቶ ተሸከመው:: ከረጅም መንገድ በሁዋላም ከገበያ በመድረሳቸው አውርዶ ከጐኑ አስቀመጠው:: ያ ነዳይ አላፊ አግዳሚውን ሁሉ ቢለምንም የሚዘከረው አጣ:: አባ አጋቶን አንዷን እንቅብ ሲሸጥ "ስጠኝ?" ይለዋል:: ጻድቁም ይሠጠዋል::
+እንዲህ "ስጠኝ" እያለ የ5ቱንም እንቅቦች ዋጋ ያ ነዳይ ወሰደበት:: አባ አጋቶን ግን ምንም ቂጣ ባይገዛ: በሆነው ነገር አልተከፋምና ሊሔድ ሲነሳ ነዳዩ "ወደ ቦታየ ተሸክመህ መልሰኝ" አለው:: አባቶቻችን ትእግስታቸው ጥግ (ዳር) የለውምና ጐንበስ ብሎ በፍቅር አንስቶት አዘለውና ሔደ::
+ካነሳበት ቦታ ላይ ሲደርሱ ይወርድለት ዘንድ ጻድቁ ቆመ:: ነዳዩ ግን አልወርድም አለ:: መቼም እኛ ብንሆን ብለን እናስበውና . . . ምን እንደምናደርግ ይታወቃል:: ጻድቁ ግን ዝም ብሎ ቆመለት::
+ትንሽ ቆይቶ ግን ስለ ለቀቀው ሊያየው ዞር ቢል መሬት ላይ የለም:: ቀና ሲል ግን ያየውን ነገር ማመን አልቻለም:: ደንግጦ በግንባሩ ተደፋ:: ነዳይ መስሎ እንዲያ ሲፈትነው የነበረው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ነበር::
+ክንፎቹን ዘርግቶ: በብርሃን ተከቦ: በግርማ ታየው:: ከወደቀበትም አነሳው:: "ወዳጄ አጋቶን! ፍሬህ: ትእግስትህ: ደግነትህ ግሩም ነውና ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎት ተሰወረው:: ጻድቁም በደስታ ወደ በዓቱ ሔደ:: አባ አጋቶን ተረፈ ዘመኑን በአርምሞ ኑሮ ዐርፏል::
+"+ ቅዱስ መጥራ አረጋዊ +"+
=>ቅዱሱ የ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ክርስቲያን ሲሆን በትውልድ ግብጻዊ ነው:: ከልጅነት እስከ እውቀት: ከእውቀት እስከ ሽበት ክርስቶስን ሲያመልክ ኑሯል:: ዘመኑ ክርስቲያኖች ስለ ሃይማኖታቸው ከባዱን ዋጋ (ሕይወታቸውን) የሚከፍሉበት ነበር::
+በወቅቱ ብርቱ የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ቢበዙም ብርቱ መንፈሳዊያን ተዋጊ ክርስቲያኖች ነበሩና ውጊያው ተመጣጣኝ ነበር:: ዛሬ ደግሞ ሁሉም በዛለበት ዘመን ላይ ተገኝተናል::
+ቅዱስ መጥራ ካረጀ በሁዋላ ነገሥታቱ "ክርስቶስን ካዱ" እያሉ መጡ:: ቅዱሱ ወሬውን ሲሰማ እጅግ ተገረመ:: ምክንያቱም መድኃኔ ዓለምን መካድ ፈጽሞ የሚታሰብ ነገር አይደለምና:: ቅዱሱ አረጋዊ ስለ 2 ነገር ሰማዕትነትን ፈለገ::
+አንደኛ በክርስቶስ ስም መሞት የክብር ክብርን ያስገኛልና ከዚሁ ለመሳተፍ ነው:: ሁለተኛው ግን ለወጣቶች አብነት (ምሳሌ) ለመሆን ነበር:: መልካም መሪ ባለበት ዘንድ ብዙ ፍሬዎች አይጠፉምና:: ቅዱስ መጥራ እንዳሰበው ወደ መኮንኑ ሒዶ በአሕዛብ ፊት ክርስቶስን ሰበከ:: ስለዚህ ፈንታም ብዙ አሰቃይተው በዚህች ቀን ከተከታዮቹ ጋር ገድለውታል::
=>አምላከ ቅዱሳን ትእግስታቸውን ያሳድርብን:: ከአባቶቻችንም በረከትን ይክፈለን::
=>ጥቅምት 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አባ አጋቶን ባሕታዊ
2.ቅዱስ መጥራ አረጋዊ (ሰማዕት)
3.ቅድስት ሶስናና ልጆቿ (ሰማዕታት)
4.አባ ሖር
5.ቅድስት በላግያ ሰማዕት
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ)
3.አባ ብሶይ (ቢሾይ)
4.አቡነ ኪሮስ
5.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
6.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
=>+"+ ጸሎቴን በፊትህ እንደ እጣን ተቀበልልኝ::
እጅ መንሳቴም እንደ ሠርክ መስዋዕት ትሁን::
አቤቱ ለአፌ ጠባቂ አኑር::
የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ::
ልቤን ወደ ክፉ ነገር አትመልሰው::
ለኃጢአት ምክንያት እንዳልሠጥ::
ከምርጦቻቸውም ጋር አልተባበር::
ጻድቅ በምሕረት ይገሥጸኝ: ይዝለፈኝም:: +"+ (መዝ. 140:2)
✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞