kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

How long have you been thinking about staying silent? https://cutt.ly/VwRDR9HE

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሰላም ዋላቹ ጥያቄ ዛሬ እለተ አርብ ነው ፆሙ እስከ ስንት ሳኣት ነው ሚፆመው ማለቴ ማታ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/+LNbJmr7thGAxNjJk

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

+ሰባቱ ፡ምስጢራተ ፡ቤተ፡ ክርስቲያን+
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ምሥጢር ፡ ማለት ፡ቃሉ ፡የግሪክ፡ ቋንቋ ሆኖ ፡ቃሉ ፡ከግዕዝና ከአማርኛ፡ በቀጥታ ፡የተወረሰ ፡ሲሆን ፡ትርጉሙም፡ ድብቅ ፣ ስውር፣ ሽሽግ፣ ረቂቅ ፣ ለቅርብ ዘመድ ካልሆነ በቀር የማይገለጥ ማለት ነው፡፡ ለሁለት የሚከፈል ሲሆን ይኸውም የፍጡር ሚሥጢርና የፈጣሪ ሚስጥር በመባል ይታወቃል፡፡ የፍጡር ምስጢር ሁለት ይዘት አለው፡፡ የሰውና የመላዕክት ምስጢር ይባላል፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኘው የፈጣሪ #የእግዚአብሔር ሚስጥር ይህ የከበረ የተወደደ የሚናፈቅ የበረከት ስጦታ ነው፡፡ ብርሃነ አለም ሀዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እንዲህ ሲል በከበረ ቃሉ ገልፆታል፡፡ “እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ /በክርስቶስ/ አምናችሁ የእምነታችሁን ፍጻሜ እርሱን የነብሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ በማይናገርና ክብር በሞላበት ሀሴት ደስ ይበላችሁ”፡፡ በማለት ስውር ረቂቅ ከሆነው ጸጋ እግዚአብሔር የምንሰጠው ሀብት መሆኑን በማብራራት ገልፆታል፡፡ በዚህ መሰረት በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ከሚፈጸሙት ሚስጥራት በቁጥር 7 ተወስነው ተቀምጠዋል፡፡ ውሳኔነታቸው ለሰባቱ ሰማያት ስብዐተ እግዚአብሔር ለማይከፈልባቸው ከተሞች ገላጭ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰባት ሚስጥራት ቤተክርስቲያን የሚስጥርነታቸው ምክንያት በአይናችን ልናያቸው በእጃችን ልንዳስሳቸው የማንችል ልዩ ልዩ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች በእነዚህ ሚስጥራት አማካኝነት የሚሰጡን ስለሆነ ነው፡፡ አበው ሲናገሩ በንባብ የተሰወረ ብሂል ምስጢር ይባላል ብለው ስውርነቱን ረቂቅነቱን ይናገራሉ፡፡ ሰባቱ ሚስጥራተ ቤተክርስቲያን የሚባሉት እንደሚከተለው ይዘረዘራሉ፡፡
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++
1. ጥምቀት
~~~~~
2. ሜሮን
~~~~~
3. ቁርባን
~~~~~
4. ክህነት
~~~~~
5. ንስሀ
~~~~~
6. ቀንዲል
~~~~~
7. ተክሊል ናቸው፡፡

1. ሚስጢረ ጥምቀት 👈

ይህ ምሥጢረ ጥምቀት ከኃጢያት ነፃ የምንሆንበት ከዲያቢሎስ አገዛዝ አርነት የምንወጣበት ከእግዚአብሔር በጸጋ የምንወለድበት የምስጢር አይነት ነው፡፡ በቅሰዱሳት መጻህፍት እንደተገለጸው በነብየ እግዚአብሔር በቅዱስ ሕዝቅሌል ት.ሕዝ 36፡25 “ጥሩ ውሀንም ጥምቀትን እረጫችኋለሁ፡ እናንትም ትጠራላችሁ ከርኩስነታችሁም ሁሉ ከጣኦቶቻችሁ ሁሉ አጠራችኋለሁ አዲስ ልብ እሰጣችኋለው” በማለት የዚህን ምስጢር ክብርነት በረከትነት አምልቶ አስፍቶ ተናገሯል፡፡ በዚህ ሀሳብ ሌሎች ንፁሐን አበው ሀዋርያት ተባብረውታል፡፡ በምልአት ሰብከውታል፡፡ የሐዋ.2፡38 ፣ 1ቆሮ 6፡11 ፣ ዮሐ. 3፡5 ፣ ኤፌ 5፡26 ፣ ገላ 3፡27 ፣ ቲቶ 3፡5 ጥምቀት ዳግመኛ ተወልደን ወደ እግዚአብሔር መንግስት የምንገባበት ምስጢር ነው፡፡ ከመጸሕፍ #ቅዱስ ውስጥ ጥምቀት ብዙ ምሳሌዎች ይኖሩታል፡፡ እነሆ ከማየአይኅ የዳነበትን መርከብ ቅዱስ ጴጥሮስ የጥምቀት ምሳሌ እንደሆነ ገልጾታል፡፡ 1ኛ ጴጥሮስ 3፡21 ምዕመናን ከሐጢያት ከጥፋት የሚድኑት በጥምቀት ነውና
ቅዱስ ጳውሎስም እስራኤል ከግብጽ የባርነት ቀንበር ተላቀው የኤርትራን ባህር ተሻግረው ወደምድረ ርስት ያደረጉትን ጉዞ የጥምቀትን ምሳሌ አድርጎ አመስጥሮታል፡፡ 1ኛ ቆሮ 10፡1-2 ምዕመናን ባህረ ኃጢያትን ተሻግረው ምድረ ርስተ መንግስተ ሰማያትን የሚወርሱት በጥምቀት ነውና፡፡ ዳግመኛም ይህ ብርሃናዊ ሐዋርያ ጥምቀትን በሞትና በመቃብር ይመስለዋል፡፡ ሮሜ 6፡3-4 ቆላ 2፡12 በሞት ጊዜ ነፍስና ስጋ እንደሚለያዩ በጥምቀትም አሮጌው ሰውነት ይሞታል ይቀበራል አዲስ ሰውነት አዲስ ሕልውናን ይጀምራልና፡፡

2. ምስጢረ ሜሮን👈

#ይህ #ቃል የጽርዕ ቋንቋ #ነው ትርጉሙም መአዛ ያለው የሚያውድ ፣ የሚጣፍጥ፣ #ልብ የሚመስጥ ፣ ጣዕም ያለው መልኩ ጽርየቱ ዘይት ነው፡፡ በግዕዝ ቅብዕ፣ ቅብዐ ሜሮን ይባላል፡፡ ከብዙ እጽዋት ተቀምሞ የሚሰራ ነው፡፡ ሕዝበ እስራኤልን የሚያስተዳድሩ የእግዚያብሔር እንደራሴዎች ነገስታትን መሲሀን የሚባሉት ለዚህ ቅብ ተቀብተው ስለሚነግሱ ነው፡፡ ዘፍ 20፡23 1ኛ ሳሙ 10፡1 ዘዳ 28፡41 1ኛ ሳሙ 9፡6 1ኛ ነገስት 1፡34 ይህ ብቻ አይደለም እግዚአብሔር የሚገለገልባቸው የቤተመቅደስ ነዋያተ ቅድሳትን አስቀድሞ በዚህ መታተም አለባቸው፡፡ ከተቀቡ በኋላ ለቤተ መቅደስ እንጂ ለተራ አገልግሎት አይውሉም ስለ ቅብዐ ሜሮን ቅዱስ መጽሐፍን የፃፉ ሰዎች የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ቅብዐት ይሉታል፡፡ 2ኛ ቆሮ 1፡21 ዮሐ 2፡20 ቅብዕን በመንፈስ ቅዱስ ማህተምን ይሉታል፡፡ ኤፊ 1፡13 ፣4፡30 ይህ ቅብዓ ማህተመ ሕይወት በመሆኑ ለአገልግሎት ይውላል፡፡

3. ምሥጢረ ቁረባን👈

ይህ ቃል የሱርስት ቃል ነው፡፡ ትርጉሙም አምኃ #ስጦታ ማለት ነው፡፡ ሥጋውና ደሙ የተሰጠን በነፃ ያለ ዋጋ ሳይገባን በችሮታ ነውና፡፡ በቤተክርስቲያን ምሥጢራት ሁሉ መደምደሚ ቅዱስ ቁርባን ነው፡፡ መስዋዕት ማቅረብ የተጀመረው በአዳም ጊዜ ሲሆን ከአዳም እስከ ሙሴ የተነሱ አበው ሁሉ በህገ ልቦና ለእግዚአብሔር መስዋት ይሰው ቁርባን ያቀርቡ ነበር መስዋዕታቸው ከእንሰሳ ቁርባናቸው ከእህልና ከአትክልት ማለት ከስንዴ እህል፣ ከወይን ፍሬ የሚቀርብ ነው፡፡ ዘመነ ኦሪት በብሉይ ኪዳን በሙክራብ የተሰዋ እንሰሳት ሁሉ በአዲስ ኪዳን በቤተክርስቲያን ለሚሰዋው ሁሉ የክርስቶስ ሥጋና ደም ምሳሌ ነበር፡፡ መልከ ጼዴቅ ያበረከተው ኅብስተ አኮቴት ጽዋዐ በረከት ለአምላክ የሥጋውና የደሙ ምሳ ሆነው አልፈዋል፡፡ ከምሥጢራት አንዱ መሆኑ ሕብስቱ ተለውጦ የክርስቶስ ሥጋ ጽዋው ተለውጦ የክርስቶስ ደም ሲሆን አይታይም፡፡ ነገር ግን እምነት ያለው ሁሉ በእምነት መነጽር ይመለከተዋል፡፡ ይህ ሳይሆን ሳይታይ የሚወደድን ሕይወት ለማግኘት ከቁርባን በፊት ንስሐ መግባት ለአስራ ስምንት ሰዓት መጾም አለበት፡፡ ንጽሕናውን በጠበቅ አለበት፡፡ መምክረ ካህን ጸንቶ መገኘት ያስፈልጋል፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ጥቅምት_23

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ሃያ ሦስት በዚህች ቀን የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #አባ_ዮሴፍ አረፈ፣ የከሀዲ ዱድያኖስ ንጉሥ ሚስት #ቅድስት_እለእስክንድርያ መታሰቢያዋ ነው፣ የቆሮንቶስ አገር ኤጲስቆጶስ #ቅዱስ_ዲዮናስዮስ በሰማዕትነት አረፈ፣ በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ተተክለው በደብረ ሊባኖስ የተሾሙት #አቡነ_ኤልሳ ዕረፍታቸው ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አባ_ዮሴፍ_ሊቀ_ጳጳሳት

ጥቅምት ሃያ ሦስት በዚህች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ኀምሳ ሁለተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍ አረፈ ። ይህም አባት ከመኑፍ አገር ከታላላቆች ተወላጆች ወገን ነው ወላጆቹም ብዙ ገንዘብ ያላቸው ነበሩ ታናሽም ሁኖ ሳለ አባትና እናቱ ትተውት ሲሞቱ ድኃ አደግ ሆነ አንድ እግዚአብሔርንም የሚወድ ሰው አሳደገው።

አድጎ በጎለመሰም ጊዜ የወላጆቹን ገንዘብ ሁሉንም ወስዶ ለድኆችና ለምስኪኖች መጸወተ ከዚህም በኋላ ወደ አስቄጥስ ገዳም ወጥቶ ከአንድ ፃድቅ ሽማግሌ ሰው አባት ዘንድ መነኰሰ በበጎ ገድል ሁሉ እየተጋደለ ኖረ ።

ዳግማዊ አባ ማርቆስም ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ የዚህን አባ ዮሴፍን በጎ ጠባዩንና የትሩፋቱን ዜና ሰምቶ መልእክተኞችን ልኮ ወደርሱ አስመጣው በቤቱም አኖረው ።

ከብዙ ወራትም በኋላ አባ ዮሴፍ ሊቀ ጳጳሳቱን አባ ማርቆስን ወደ አስቄጥስ ገዳም እሔድ ዘንድ ተወኝ ብሎ ለመነው ያን ጊዜም ቅስና ሹሞ አሰናበተው ሊቀ ጳጳሳት አባ ስምዖንም እስከ አረፈ ድረስ በዚያ በእስቄጥስ ገዳም ኖረ ከዚህም በኋላ የግብጽ አገር ያለ ሊቀ ጳጳሳት ብዙ ወራት ኖረች ።

ከዚህም በኋላ ኤጲስቆጶሳቱ መማለጃ ስለተቀበሉ ከአንድ ሚስቱ ከሞተችበትና መዓስብ ከሆነ ጸሐፊ ጋር ሊቀ ጵጵስና ይሾሙት ዘንድ ተስማሙ እኩሌቶቹ ግን ተቃወሟቸው እንዲህም አሏቸው የአባቶቻችን ቀኖና መማለጃ የሚቀበለውን ሁሉ ወይም ስለ ክህነት ሹመት መማለጃ የሚሰጠውን ያወግዛል ። ይልቁንም ይህ ሰው ሚስት አግብቷል እንዴት ሊሾም ይችላል በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበር ላይ የሚሾም ንጹሕ ድንግልም ነውና።

ይህንንም በአሏቸው ጊዜ ፈሩ ተመልሰውም ተስማሙ ለዚች ለከበረች ሹመት የሚሻለውን ይገልጽላቸው ዘንድ ክብር ይግባውና ወደ ጌታችን በአንድ ምክር ሁነው ጸለዩ እግዚአብሔርም ሰምቷቸው ለዚች የከበረች ሹመት የሚሻል አባ ዮሴፍ እንደሆነ አሳሰባቸው።

ከዚህም በኋላ አባ ዮሴፍን ያመጡት ዘንድ ወደ አስቄጥስ ገዳም መልእክተኞችን ላኩ መልክተኞችም ይህን አባት ዮሴፍን የመረጥከው ከሆነ ምልክትን ትገልጥልን ዘንድ አቤቱ እንለምንሃለን የቤቱም ደጃፍ ክፍት ሁኖ ካገኘን ምልክት ይሁንልን ብለው ወደ እግዚአብሔር ለመኑ።

በደረሱም ጊዜ አንዱን መነኰስ እየሸኘ የበዓቱም ደጃፍ ክፍት ሁኖ አባ ዮሴፍን አገኙት በአያቸውም ጊዜ መንፈሳዊ ሰላምታ በመስጠት እጅ ነሣቸውና በደስታ ተቀብሎ ወደ በዓቱ አስገባቸው በዚያንም ጊዜ ለአባ ዮሴፍ ሊቀ ጵጵስና ይገባዋል ይገባዋል ይገባዋል እያሉ ይዘው አሠሩት ። እርሱ ግን እኔ ብዙ ኃጢአትን ሠርቻለሁና ይህ የከበረ ሹመት አይገባኝም እያለ ይጮህ ነበር እነርሱም ወደ እስክንድርያ ከተማ ወስደው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት እንጂ ምንም ምክንያት አልተቀበሉትም።

በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበርም በተቀመጠ ጊዜ ለአብያተ ክርስቲያን እጅግ የሚያስብ ሆነ ለርሱ የሆነውን የግብሩን ገቢ ወስዶ ምድሮችን በመግዛት ለአብያተ ክርስተያን መተዳደሪያ ሊሆኑ ጉልቶች ያደርጋቸው ነበርና።

አዘውትሮም ሕዝቡን የሚያስተምራቸው ሆነ በምንም በምን ለየአንዳንዱ ቸለል አይልም ነገር ግን ሰይጣን ስለቀናበት ያለ ኀዘን አልተወውም ። ይህም እንዲህ ነው በምስር አገር የተሾሙ ሁለት ኤጲስቆጶሳት በሕዝቡ ላይ ክፉ ነገር በማድረግ በማይገባ ሥራ አስጨነቋቸው እርሱም በርኅራኄና በፍቅር መንጎቻቸውን እንዲጠብቁ አዘዛቸው ለመናቸውም እነርሱ ግን ሰምተው ከክፋታቸው አልተመለሱም።

በሕዝቡም ላይ ችግርን በአበዙ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉም በጠቅላላ ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍ መጡ በፊቱም እንዲህ ብለው ጮኹ እሊህን ኤጲስቆጶሳት ከላያችን ካላነሣሃቸው እኛ ወደሌላ ሃይማኖት እንገባለን አባ ዮሴፍም በመካከላቸው ሰላምን ለማድረግ ብዙ ትግልን ታገለ ግን አልተቻለውም።

ከዚህም በኋላ በግብጽ አገር ያሉትን ኤጲስቆጶሳት ለጉባኤ ሰበሰባቸውና ስለ እሊህ ሁለት ኤጲስቆጶሳት ነገራቸው አሁንም ከመንጋዎቻቸው ጋር ሊአስታርቅ ሽቶ እሊህን ኤጲስቆጶሳት ወደ ጉባኤው አስቀረባቸው እነርሱ ግን የጉባኤውንም የእርሱንም ቃል አልተቀበሉም ስለዚህም ያ ጉባኤ ከሹመታቸው ሻራቸው።

እነርሱም ወደ ግብጽ ንጉሥ ሒደው በሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍ ላይ በሐሰት ነገር ሠሩበት ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍንም ያመጡት ዘንድ ንጉሡ ወንድሙን ከጭፍራ ጋር ላከው። የንጉሡም ወንድም ወደ ሊቀ ጳጳሳቱ በደረሰ ጊዜ ተበሳጨ ሊገለውም ወዶ ሰይፉን መዞ ሊቀ ጳጳሳቱን ሊመታው ሰነዘረበት ግን እጁ ወደ ሌላ አዘንብሎ ምሰሶ መትቶ ሰይፉ ተሰበረ እጅግም ተቆጥቶ ሌላ ሰይፍን መዝዞ በመላ ኃይሉ መታው ያን ጊዜም ሰይፉ ከአንገቱ ወደ ወገቡ ተመልሶ ልብሱንና ቅናቱን ብቻ ቆረጠ የንጉሡም ወንድም ከክፋት ንጹሕ እንደሆነ ስለዚህም አምላካዊት ኃይል እንደምትጠብቀው አሰበ አስተዋለም።

ወደ ንጉሡም በክብር አደረሰው ወንድሙ ለሆነ ንጉሥም በእርሱ በሊቀ ጳጳሳቱ ላይ የሆነውን ሁሉ ነገረው ንጉሡም ፈራው አከበረውም ከዚህም በኋላ ስለከሰሱት ስለ ሁለቱ ኤጲስቆጶሳት ጠየቀው እርሱም ስለ ክፉ ሥራቸው በጉባኤ እንደተሻሩ እውነቱን ለንጉሡ አስረዳው ያን ጊዜም ሐሰተኞች እንደሆኑ ንጉሥ አወቀ ይገድሏቸውም ዘንድ አዘዘ።

ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍም ንጉሡን እንዲህ ብሎ ማለደው ጌታችን በክፉ ፈንታ በጎ እንድናደርግ እኛን አዞናልና ስለ እግዚአብሔር ብለህ እሊህን ማራቸው እንጂ አትግደላቸው ንጉሡም ስለ የዋህነቱ አደነቀ ልመናውንም ተቀብሎ ማረለት።

ከዚህም በኋላ በሹማምንቱና በኤጲስቆጶሳቱ ሁሉ ላይ የፈለገውን ያደረግ ዘንድ ቢፈልግ እንዲሾም ወይም እንዲሽር የሚቃወመው እንዳይኖር ደብዳቤ በመጻፍ ሥልጣንን ሰጠው።

በዚህም አባት ዘመን የኢትዮጵያ ንጉሥ ወደዚህ አባት ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍ እንዲህ ብሎ መልእክትን ላከ ለወንጌላዊ ማርቆስ መንበርና በላዩ ለመቀመጥ ለተገባው ቅድስናህ እጅ እነሣለሁ በእኔና በመንግሥቴ ላይ በመላው ወገኖቼ በኢትዮጵያ ሰዎች ላይ ይቅርታ እንድታደርግና አባታችንን አባ ዮሐንስን እንድትልክልን እለምንሃለሁ ከሀገራችን ሰዎች ከእውነት መንገድ የወጡና የሳቱ ጳጳሳችንን አባ ዮሐንስን እኔ ሳልኖርና ሳላውቅ አባረውታልና ስለዚህም በሀገራችን ቸነፈርና ድርቅ ሁኖ ከሰዎችም ከእንስሶችም ብዙዎች አለቁ።

አሁንም አባቴ ሆይ ስንፍናችንን ይቅር በል መሐሪና ይቅር ባይ ወደ ሆነ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልድልን ዘንድ በከበረች ጸሎቱም ከዚህ መከራ እንድን ዘንድ አባታችንን አባ ዮሐንስን ላክልን።

አባቴ ሆይ የተባረረበትን ምክንያት እኔ አስረዳሃለሁ እኔ ልጅህ ከአባቴ ከጳጳስ አባ ዮሐንስ ቡራኬ ተቀብዬ እርሱ ከሠራዊቴ ጋር በፍቅር አሰናብቶኝ ወደ ጦር ሜዳ ሔድሁ ከጦር ሜዳም በተመለስኩ ጊዜ አባቴን አባ ዮሐንስ ጳጳሱን አጣሁት ስለርሱም በጠየቅሁ ጊዜ በቀድሞ ዘመን ዮሐንስ አፈ ወርቅን ንግሥት አውዶክስያ እንዳሳደደችው በክፉዎች ሰዎች ምክር ንግሥቲቱ ሚስቴ ማሳደዷን የቀኖናውንም ትእዛዝ በመተላለፍ በፈቃዳቸው ሌላ ጳጳስ እንደሾሙ ነገሩኝ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ጥቅምት_22

#ቅዱስ_ሉቃስ_ወንጌላዊ
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ሃያ ሁለት በዚህች ቀን ብልህ ጥበበኛ የሆነ ቅዱስ ወንጌላዊ ሉቃስ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ የከበረ ወንጌል ከመዘገባቸው ከሰባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ የተቆጠረ ነው።

እርሱም ወንጌልን ስለማስተማር በሥራው ሀሉ ሐዋርያት ጴጥሮስንና ጳውሎስን የሚአገለግላቸው ሆነ ለታኦፊላም ወንጌልንና የሐዋርያትን ዜና የጻፈ ሉቃስ ነው።

ቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስም ከተገደሉ በኋላ በሮሜ ሀገር የሚያስተምር ሆነ በቀናች ሃይማኖትም ይጸኑ ዘንድ ለምእመናን መልእክትን ይጽፍ ነበር። ስለዚህም ጣዖት አምላኪዎች ከአይሁድ ጋር በመስማማት አንድ ግምባር ፈጠሩ በንጉሥ ኔሮን ፊት ቁመው ስለ ሐዋርያው ሉቃስ እንዲህ ብለው ጮኹ ይህ ሉቃስ ብዙዎች ሰዎችን በሥራዩ ወደ ትምህርቱ አስገባቸው። ንጉሥ ኔሮንም ወደ ፍርድ አደባባይ ሉቃስን እንዲአቀርቡት አዘዘ።

ሐዋርያ ሉቃስም ከዚህ ዓለም መውጫው እንደ ደረሰ በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ወደ ባሕር ዳርቻ ሔደ። በዚያም ዓሣ የሚያጠምድ አንድ ሽማግሌ ሰው አገኘ። መጻሕፍቱንና ደብዳቤዎቹን ሰጠው ወደ እግዚአብሔር መንገድ መርተው ያደርሱሃልና እሊህን መጻሕፍት ጠብቃቸው አለው።

በንጉሥ ኔሮንም ፊት ቀርቦ በቆመ ጊዜ ንጉሡ በሥራይህ ሕዝቡን የምታስት እስከመቼ ነው አለው ቅዱስ ሉቃስም እኔ ለሕያው እግዚአብሔር ልጅ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያው ነኝ እንጂ ሥራየኛ አይደለሁም ብሎ መለሰለት።

ንጉሥ ኔሮንም ሁለተኛ እንዲህ አለው እየጻፈች ሰዎችን የምታስት ይቺን እጅህን እኔ እቆርጣታለሁ ይህንንም ብሎ የቀኝ እጁን እንዲቆርጡ አዘዘ በቆረጡትም ጊዜ ንጉሥ ሆይ እኛ የዚህን ዓለም ሞት እንደማንፈራ እወቅ ነገር ግን የጌታዬንና የፈጣሪዬን ኃይሉን ታውቅ ዘንድ አሳይሃለሁ። ይህንንም ብሎ የተቆረጠች የቀኝ እጁን በግራ እጁ አንሥቶ ከተቆረጠችበት ቦታዋ ላይ አገናኝቶ እንደ ቀድሞዋ ደኅነኛ አደረጋት። ከዚህም በኋላ ለያት በዚያም የነበሩ አደነቁ የሠራዊት አለቃውና ሚስቱ ብዙዎችም ሰዎች ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ቁጥራቸውም አራት መቶ ሰባ ሰባት ነፍስ ሆነ ንጉሡም ከቅዱስ ሉቃስ ጋር ራሶቻቸውን እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጡአቸው የምስክርነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።

ከዚህም በኋላ የቅዱስ ሉቃስን ሥጋ በማቅ አይበት ውስጥ አድርገው ወደ ባሕር ጣሉት በእግዚአብሔርም ፈቃድ ወደ አንድ ደሴት ደረሰ። ምእመናንም አግኝተው ወስደው ገነዙት በአማረ ቦታም አኖሩት።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

መንፈሳዊ ግጥም
🏮ርዕስ፦ የሰው ልጅ ፈራሹ

●➠ከኪነ-ጥበብ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ጥቅምት 21 አቡነ ዐሥራተ ወልድ.በዓለ እረፍታቸው ነው
እንኳን አደረሳችሁ?
🌼አቡነ ዐሥራተ ወልድ:- በዳሞት አውራጃ ልዩ ስሟ እነሴ በምትባል ቦታ በዐፄ ሠርጸ ድንግል ዘመነ መንግሥት በ1584 ዓ.ም ተወለዱ። አባታቸው ፃማ ክርስቶስ እናታቸው ፅጌ ማርያም ይባላሉ። ኹለቱም በሕገ እግዚአብሔር ጽንተው የሚኖሩ በሃይማኖት በምግባር የተመሰገኑ በተጋድሎ በትሩፋት የታወቁ ክርስቲያኖች ነበሩ" ነገር ግን ልጅ ስላልነበራቸው እንደ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ የተባረከ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ሁልጊዜ እግዚአብሔርን በጸሎት ይጠይቁ ነበር አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችንንም ይማጸኗት ነበር።

🌼ኹለቱም እግዚአብሔርን የሚፈሩ በምድራዊ ሀብትም የበለጸጉ ነበሩ፤ ለድኖችና ለምስኪኖች አብዝተው ይመጸውቱ ስለነበር ከጾማቸው በኋላ ያለ ድኖችና ምስኪኖች ብቻቸውን አይመገቡም ነበር። እግዚአብሔርም ጸሎት ልመናቸውን ተቀብሎ የተባረከ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ወደደ። ከዕለታትም በአንደኛው ቀን የእግዚአብሔር ሰው ለጽጌ ማርያም ታይቶ “ዝናው በአራቱ ማዕዘን ኹሉ የሚደርስ በሕይወተ ሥጋ እያለ የብዙ ሰዎችን ነፍስ በጸሎቱ ከኀጢአት ወደ ጽድቅ የሚያወጣ ወደ ሰማይም ወጥቶ የሥላሴን ምሥጢር የሚያይ የተባረከ ልጅን ትወልጂ ዘንድ አለሽና ደስ ይበልሽ በማለት ካበሠራት በኋላ አቡነ ዐሥራተ ወልድ ሰኔ ሃያ ቀን ተወለዱ።

🌼ጻድቁም በተወለዱ በስምንተኛ ቀናቸው ለአብ ምስጋና ይገባል ለወልድ ምስጋና ይገባል ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል›› ብለው ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል። እስከ ዐሥራ ኹለት ዓመታቸውም ድረስ ውኃ በመቅዳት ዕንጨት በመስበር ወላጆቻቸውን ካገለገሉ በኋላ ወላጆቻቸው ወደ ታላቁ ጻድቅ ወደ አቡነ ተጠምቀ መድኅን ዘንድ ወስደው እንዲያስተምሩላቸው አደራ ብለው ሰጧቸው።

🌼አቡነ ተጠምቀ መድኀንም ዐሥራተ ወልድን ተቀብለው የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢር ኹሉ አስተማሯቸው። በሚማሩበትም ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በአፋቸው ያቀብላቸው ስለነበር አስቀድመው የተማሩ ይመስሉ ነበር። በሦስት ዓመትም ውስጥ መጻሕፍተ ብሉያትን መጻሕፍተ ሐዲሳትን መጻሕፍተ መነኰሳትን፣አዋልድ መጻሕፍትንም ኹሉ ከነትርጓሜያቸው ከአቡነ ተጠምቀ መድኅን ተምረው እግዚአብሔርም ከሐሰት መጻሕፍት ከሟርት ከጥንቆላ መጻሕፍት በቀር ያልገለጠላቸው የመጻሕፍት ምሥጢር የለም። የመላእክትንና የቅዱስ ያሬድንም ዜማ ገለጠላቸው።

🌼ከዚኽም በኋላ አቡነ ዐሥራተ ወልድ ለመመንኰስ ወላጆቻቸውን አስፈቅደው ከመምህራን ጋር ወደ ታላቁ ገዳም ወደ ደብረ ዳሞ ሔደው በዚያም መነኮሳቱን እያገለገሉ ለ25 ዓመታት ያህል በተጋድሎ ከኖሩ በኋላ በዐፄ ፋሲል ዘመን መንግሥት በ40 ዓመታቸው በ1624 ዓም መንኰሱ። ከሊቀ ጳጳሱ ከአቡነ ሚካኤልም እጅ የቅስና ማዕረግ ተቀበሉ። ከዚኽም በኋላ ከመምህራቸው ከአቡነ ተጠምተ መድኅን ጋር ወደ ጋሾላና ጉሓን ገዳማት ሔደው ተጋድሏቸውን ጨምረው መጾም መጸለይን አበዙ። ወደ ተራራ ሔደው ዳዊት ሲያነቡ ያድራሉ፣ ምሥራቅም ዙረው እምስት መቶ ጊዜ ይሰግዳሉ፤ ወደ ምዕራብም ዙረው አምስት መቶ ጊዜ ይሰግዳሉ፤ ወደ ሰሜንም ዙረው አምስት መቶ ጊዜ ይሰግዳሉ ወደ ደቡብም ዙረው እምስት መቶ ጊዜ ይሰግዳሉ፤ እንዲህም እያደረጉ በየዕለቱ ኹለት ሺህ ይሰግዱ ነበር። ላባቸው እንደ ውኃ ፈስሶ ምድርን እስኪያርስ ድረስ ይሰግዳሉ፤ የቆሙበትም ምድር እንደ ጉድጓድ ይጎደጉዳል። እንደዚህ ባለ ታላቅ ተጋድሎ ጸንተው ብዙ ዘመን ኖሩ። የጌታችንንም ዐርባ ጾም ምንም ሳይቀምሱ በርባውን ቀን ይጾሙ ነበር።

🌼ከዚኸም በኋላ አቡነ ዐሥራት ወልድ ጃባ በሚባለው ቦታ ዐሥራ አንድ ዓመት በተጋድሎ ኖሩ። አባታችን ያከብሯት የነበረች ቅዱስ ሉቃስ የሣላት የክብርት እመቤታችን ሥዕል በዚያ ነበረችና እርሷም ድንቅ ድንቅ ተኣምራትን ታደርግላቸው ነበር። ጃባ በምትባል ቦታም ዘወትር ታነጋግራቸው ነበር። በአንደኛውም ሌሊት ተኝተው ሳሉ አምላክን በድንግልና የወለደች ክብርት እመቤታችን ተገልጣላቸው ልጄ ወዳጅ ዐሥራተ ወልድ ሆይ! በጸሎትና በልመናህ የጃባ ሰዎች ኹሉ ይድናሉ፣ በቃልህ ክርስቶስን አምነው በእጅህ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ይቀበላሉ አለቻቸው።

🌼ከዚኽም በኋላ የታዘዘ የእግዚአብሔር መልአክ ለኹለቱም ቅዱሳን ተገልጦላቸው አቡነ ተጠምቀ መድኅንን ወደ ጋዝጌ እና ወደ መተከል ሔደው የከበረች ወንጌልን እንዲያስተምሩ ሲያዛቸው አቡነ ዐሥራተ ወልድን ደግሞ ወደ ጫራ ምድር ሔደው በዚያ ወንጌልን ይሰብኩ ዘንድ አዘዛቸው። ኹለቱም ቅዱሳን እርስ በርሳቸው በመንፈሳዊ ሰላምታ እጅ ተነሣሥተው ለሐዋርያዊ አገልግሎት ተለያይተው ወደታዘዙባቸው ቦታዎች ሔዱ። አባታችን ዐሥራተ ወልድም እየጸለዩ ስምንት ዓመት ከስድስት ወር በርበር በምትባል በረሓ ውስጥ ሳሉ በአራቱም ማዕዝናት እየተዘዋወሩ በምሥራቅ አንድ ሽህ በምዕራብ አንድ ሺህ በሰሜን አንድ ሺህ በደቡብ አንድ ሺህ ጊዜ ይስግዱ ጀመር የክብር ባለቤት ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስም በዚህ ጊዚ ተገልጦላቸው ወዳጀ ዐሥራተ ወልድ ሆይ! ለምን ሥጋህን እንደዚህ አደከምህ አላቸው አባታችንም ጌታ ሆይ! ኀይላቸውን በስግደት ቀንና ሌሊት በመትጋት የሚያደክሙ በመንግሥትህ እይደሰቱምን በዓለም የደከመ ለዘለዓለም ይድናል ጻድቃን ዳግመኛም በብዙ ድካምና መከራ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንገባ ዘንድ ይገባናል እንዳለ በማለት መለሱ። ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ " ድካምህ በከንቱ አትቀርም በሰማያውያን መላእክት በተባረኩጻድቃን ድል በነሱ ሰማዕታት ንጹሐን በሚሆኑ ደናግል በፍጹማን መነኰሳት ፊት የድካምህን ዋጋ እሰጥሃለሁ። እንግዲህ ከዛሬ ጀምረህ ወደ ኣዘዝኩህ ቦታ ሒድ፣መንግሥተ ሰማያትም ቀርባለች እያልህ የመንግሥትን ወንጌል አስተምር፣ ኃይሌ ከአንተ ጋር ይኖራልና ብሎ አዘዛቸው። ጌታችን ይህን ሲነግራቸው አውሎ ነፋስ መጥቶ ጉርብ ወደ ምትባለው ዋሻ ወስዶ አደረሳቸው።

🌼በሥራ የሚኖሩ የሀገሩ ሰዎችም የአባታችን ዐሥራተ ወልድን መምጣት ሰምተው ተቆጥተው በአባታችን ላይ በጠላትነት ተነሡባቸው፣ ጋሻቸውንና ጦራቸውን ይዘው የመጡ ቢሆንም አባታችን ግን የከበረች የክርስቶስን ወንጌል አስተምረው አሳምነው አጠመቋቸው። የጫራንም ሕዝብ አምስት ዓመት ካስተማሯቸው በኋላ ዳግመኛ የሻሽናን ሕዝብ ያስተምሯቸው ዘንድ የእግዚአብሔር መልአክ እየመራው ሻሽና አደረሳቸው። አባታችን በዚያም የሀገሩን ሕዝብ አስተምረው አጠመቁ።

🌼የጐንደር ንጉሥ ጻድቁ ዮሐንስ የአባታችን ዐሥራተ ወልድን ቅድስናና ገድል በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ ያመጧቸው ዘንድ መልእክተኞችን ላከ፤ መልእክተኞችም አባታችንን በሻሽና አገኟቸው፤ አባታችን ግን መልእክተኞቹን ‹‹ልጆቼ እኔ ኃጢአተኛ ስሆን ከጐንደር እስከ ሻሽና ንጉሡ ምን ብሎ ላካችሁ?›› አሏቸው። ይኸንንም ተናግረው የንጉሥን ጭፍራ ወደ እናንተ እስክመለስ ድረስ ከዚኸ ጠብቁ›› ብለው ወደ ንጉሡ ዘንድ ከመሔዳቸው በፊት ወደ ጸሎት ቤት ገብተው ከዳዊት መዝሙር ጸለዩ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ጥቅምት 20 #ነቢዩ_ኤልሳዕ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በነብዩ ስም ለምናመሰግንበት ታላቁ ነብይ #ቅዱስ_ኤልሣን በምልጃ ፀሎቱ እንዲያስበን ለምንማፀንበት አመታዊ የእረፍት በአሉ መታሠቢያ እንኳን አደረሰን

👉በዚችም ቀን የስሙ ትርጓሜ ጠባቂና አዳኝ የሆነ የታላቁ ነቢይ የኤልሳዕ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው እርሱም አሜሁላ ከሚባል አገር ከይሳኮር ነገድ ነው ብዙ ትንቢትን ተናግሮአል ብዙ ተአምራትንም አድርጓል

👉የኢያሪኮም ሰዎች ኤልሳዕን ጌታችን እንደምታያት የዚች አገር ኑሮዋ ያማረ የተወደደ ነው የአገሩ ውኃ ግን ክፉ ነው ሴቶች ሲጠጡት ይመክናሉ አሉት ኤልሳዕም ጨው ጨምራችሁ አዲስ ሸክላ አምጡልኝ አላቸው እነርሱም አመጡለት።

👉ኤልሳዕም ወደ ውኃው ምንጭ ሒዶ ያንን ጨው በውስጡ ጨመረውና እግዚአብሔር እንዲህ አለ እርሱን ከመጠጣት የተነሣ የሚሞት እንዳይኖር የሚመክንም እንዳይኖር ይህን ውኃ ለውጥኩት አለ አላቸው።

👉ከዚያችም ቀን በኋላ ኤልሳዕ እንደተናገረ እስከ አሁን ድረስ ያ ውኃ ተለወጠ የዚህ የነቢይ ኤልሳዕ ተአምራቱ ብዙ ነው የሶርያውን ሰው ንዕማንን ከለምጹ ያነጻው እርሱ ነው ሁለት ሙታንን አንዱን በሕይወት ሳለ ሌላውንም ከሞተ በኋላ አስነሥቷል የትንቢቱንም ወራት ፈጽሞ በሰላም አረፈ።

👉ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢዩ ኤልሳዕ ጸሎት ይማረን በረከቱና ረድኤቱ ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ "አሜን" 💒 💚 💛 ❤💒

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በህልሜ ሚኪና ውስጥ ተቀምጬ እራሱ ስሄድ ደንግጬ ለማቆም ስታገል አደርኩኮ እስኪ ሚፈታልኝ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ"

መቆም ማለት / መፀለይ /መለመን /ማማለድ / ማለት ነው።

መቆም ማለት መፀለይ በሚል ይተረጎማል ስለዚህ ምልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በሉቃስ ወንጌል 1 : 19 "እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ" ማለቱ እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምፀልየው የምለምነው ገብርኤል ነኝ ማለቱ መሆኑን ማወቅ ተገቢ ነው።

ለዚህም ማስረጃይሆን ዘንድ በትንቢተ ኤርሚያስ 15:1 "እግዚአብሔርም እንደዚህ አለኝ። ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም፥ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አይዘነብልም" ሙሴና ኤርሚያስ በፊቴ ቢቆሙም ማለት ስለ ህዝቡ ቢፀልዩም ቢያማልዱም ቢለምኑኝም ማለቱ ነው።

ስለዚህ እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ ሲል እኔ ስለሰዎች የምፀልየው የምለምነው ሰዎችን ማራቸው ብዬ የማማልደው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነኝ ማለቱ መሆኑን መረዳት ይገባል።

መልአኩ በምልጃው አይለየን ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ይምርሃነ ክርሰቶስም ሕዝቡን ይዞ ተነሳና አሁን ከቅዱስ ላሊበላ ቤተ መቅደሶች 42 ኪ,ሜ ርቀት ላይ ወደሚገኘውና ጥቁር አለታማ ተራራ ሥር ወዳለው የውግረ ስሂን ዋሻ አመራ። ሲደርስም ቦታው የሰዎች ይዞታ ሆኖ ስላገኘው እኔ ንጉሥ ነኝ ብሎ እነርሱን በግፍ ሳያስለቅቅ ካሳ ከፍሎ ስፍራውን ተረከባቸው። ውስጡ ግን ውሀ የቆመበት ባህርና ርኩሳት መናፍስት የሞሉት ስለነበር መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል መናፍስቱን አባሮ በባሕሩ ላይ ቤተ መቅደሱን እንዴት እንደሚያንጽ ገለጠለት። እርሱም በተነገረው መሠረት ለግንባታው የሚያስፈልጉ እቃዎችን ከኢየሩሳሌም አስመጥቶ ማነጽ ጀመረ። የውሀውን ክፍል እንጨት ረብርቦ አፈር እየበተነ ደለደለው። ሰዎች በባህር ላይ መሠራቱን እንዳይጠራጠሩም አነስተኞ መስኮትነገር አበጀለት። (በዚህችም አሁን ድረስ በክንድ ርቀት ያህል ከሥር ያለው ውሀ ይነካል።) ከበላዩም ስስ ሆነው የተፈለጡ ድንጋዮችን በኖራ እያቦካ በማያያዝ በእኩል መጠን እየገነባ በመሀከላቸው እንደ መቀነት የተጠረቡ እንጨቶችን በማስገባት አሳምሮ አነፀው። ውስጡንም በሦስት ቤተ መቅደሶች ከፈለው በየመስኮትና በየበሮቹም ላይ እንደ ዐይነ እርግብ ሆነው የተፈለፈሉ ሐረጎችን አደረገበት ጣሪያውንም በሰባቱ ሰማያት ምሳሌ ምስጢር ባላቸው የተለያዩ ቅርፆች አስዋበው።ይህን አድርጎ ሥራውን ከጨረሰ በኋላም የቅዱስ ገብርኤልን የእመቤታችንንና የቅዱስ ቂርቆስን ታቦታት አስገባበት። በድጋሚም ቤተ መንግሥቱን በዛው ዋሻ ውስጥ አነጸና በአስተዳደሩ ደሀ ሳይበድል ፍርድ ሳያጓድል ሕዝቡን በክህነቱም ንፁህ ሆኖ እግዚአብሔርን እያገለገለ ኖረ።በስተመጨረሻም ፍጥረት ሆኖ ከመሞት ሰው ሆኖ በመቃብር ከመዋል የሚቀር አይኖርምና ንጉሣችንና አባታችን ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስም የእረፍት ዘመኑ ሲደርስ እግዚአብሔር አምላክ ቃል ኪዳኑን ለዘላለም እንደሚያፀናለት ነግሮት በዚህች በተባረከች #በጥቅምት_19 ቀን በክብር አሳረፈው።

መቃብሩንም አስቀድሞ እነደነገረው በዛው በተቀደሰ ዋሻ ውስጥ አደረገለት። እናም ዛሬ ድረስ ቦታው በክብር ተጠብቆ ይኖራል። ምእመናንም ቃል ኪዳኑን በማሰብ "ማረኝ ይምርሐ" እያሉ መቃብሩን ይዞራሉ። ያንን ከሰማይ የወረደለትን መስቀልም በቤተመቅደሱ የሚያገለግሉት ካህናት አባቶች ቦታውን ለመሳለም የሚመጣውን ሕዝበ ክርስቲያን በበዓል ቀን ይባርኩበታል፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_በርቶሎሜዎስና_ሚስቱ

ዳግመኛም በዚህች ቀን በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ቅዱስ በርቶሎሜዎስና ሚስቱ በሰማዕትነት አረፉ።

እሊህ ቅዱሳንም የግብጽ ምዕራብ ከሆነ ፍዩም ከሚባል አገር ናቸው ክርስቲያኖችም እንደሆኑ በመኰንኑ ዘንድ ወነጀሏቸው መኰንኑም ልኮ አስቀረባቸውና ስለ ሃይማኖት ጠየቃቸው እነርሱም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፊቱ ታመኑ።

መኰንኑም ጥልቅ ጒድጓድ እንዲቆፍሩላቸው በዚያም እንዲጨምሩአቸውና በሕይወታቸው እንዲደፍኑባቸው አዘዘ። መኰንኑም እንዳዘዘ አደረጉባቸው በዚህም ምስክርነታቸውን ፈጽመው የሰማዕትነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#የጳውሎስ_ሳምሳጢን_ውግዘት

በዚችም ቀን ስለ ጳውሎስ ሳምሳጢ በአንጾኪያ አገር የቤተ ክርስቲያን የአንድነት ስብሰባ ተደረገ። ይህ ጳውሎስም ከአንጾኪያ አገሮች በአንዲቱ አገር ኤጲስቆጶስነት በተሾመ ጊዜ ክፉ ዘርን ሰይጣን በልቡ ውስጥ ዘራበት አካላዊ ቃልን አካል እንደሌለ የክርስቶስም ጥንት መገኛው ከማርያም እንደሆነ እርሱም አለምን ያድንበት ዘንድ እግዚአብሔር የፈጠረው እንደሆነ ከመለኮትም ጋር ያልተዋሐደ በላዩ ወርዶ በእግዚአብሔር ፈቃድ አደረበት እንጂ ብሎ የሚያምን ሆነ በወልድም ቢሆን በመንፈስ ቅዱስም ቢሆን የሚያምን አልሆነም።

ስለዚህም ኤጲስቆጶሳት አንድነት ተሰበሰቡ የእስክንድርያ አባ ዲዮናስ የሮሜ አባ ዲዮናስዮስ እሊህ ሊቃነ ጳጳሳት ስለ እርጅናቸው ከዚያ ደርሰው ከእርሳቸው ጋር ሊሰበሰቡ አልቻሉም ነገር ግን መልእክትን ጻፉ።

የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዲዮናስም እንዲህ የሚል መልእክትን ጻፈ። የእግዚአብሔር ልጁም ቃሉም የሆነ ክርስቶስ በመለኮቱም ከእርሱ ጋር ትክክል የሆነ እርሱም ከሦስቱ አካላት አንዱ ወልድ ስለእኛ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለ ዘር ስጋንና ነፍስን ነሥቶ ፍጹም ሰው የሆነ በመለኮቱ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል ሲሆን እንደእኛ ፊጹም ሰው ሁኗል ከተዋሕዶውም በኋላ ያለ መለያየትና ያለ መቀላቀል ሁለቱ ባሕርያት አንድ ሁነዋል ከብሉይና ከሐዲስ መጻሕፍት ምስክሮችን ጠቅሶ እያስረዳ ጽፎ ይቺንም መልእክት ከሁለት ምሁራን ቀሳውስት ጋር ላካት።

በዚያንም ጊዜ አሥራ ሦስቱ ኤጲስቆጶሳትና እሊህ ሁለቱ ቀሳውስት ጉባኤ አድርገው ይህን ጳውሊ ሳምሳጢን አቅርበው የአባ ዲዮናስን መልእክት በፊቱ አነበቡ። ዳግመኛም ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጁም ቃሉም የሆነ የጌትነቱ ነጸብራቅ ነው የሚለውን የሐዋርያ ጳውሎስን ቃል በመጥቀስ እርሱ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በትክክልነት እንደሚኖር አስረዱት እርሱ ግን ቃላቸውን አልተቀበለም።

ከዚህም በኋላ በእርሱ ትምህርት የሚያምኑትን ሁሉ አው*ግዘው ከምእመናን ለይተው አሳደዱት። ለምእመናንም ሥርዓትን ሠሩ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዮሐንስ_ዘጸይለም

በዚችም ቀን የጸይለም አገር የከበረ አባት ዮሐንስ አረፈ። የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ከሀገሩ ታላላቆች ወገን ናቸው የአባቱም ስም አብርሃም የእናቱም ስም ሣራ ነው እነርሱም ልጆች ስለ ሌሏቸው ብዙ ዘመን ወደ እግዚአብሔር እየለመኑ ኖሩ።

በአንዲትም ዕለት ሁለት መነኰሳት ወደ እነርሱ እንግድነት መጡ እነርሱም በክብር ተቀብለው አሳደሩአቸው። እሊህ መነኰሳትም አብርሃምን ልጅ የለህምን አሉት እርሱም እንባውን እየአፈሰሰ አባቶቼ ልጅ የለኝም አሁንማ እኔ አረጀሁ የሚስቴም የልጅነቷ ወራት አለፈ ብሎ መለሰላቸው። እሊህ መነኰሳትም ስለ እርሳቸው ጸለዩላቸው ባርከዋቸውም ጎዳናቸውን ተጓዙ።

ከጥቂትም ቀን በኋላ ሳራ ፀነሰች ደስ የሚያሰኝም ልጅን ወለደች ስሙንም ዮሐንስ ብለው ሰየሙት በእርሱም ደስ አላቸው የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት እየአስተማሩ አሳደጉት።

ዐሥራ ሰባት ዓመትም በሆነው ጊዜ ወደ መምህሩ ቤት መነኰሳት መጡ ዮሐንስም ከእርሳቸው ጋር እንዲወስዱት ለመናቸው እነርሱም አባትህን እንፈራለንና እኛ አንወስድህም አሉት። መነኰሳቱም ወደቦታቸው እየሔዱ ሳሉ ወደ መረጠው ጎዳና ይመራው ዘንድ ዮሐንስ ተነሥቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ከመምህሩም ቤት ወጥቶ ሊደርስባቸው ወዶ መነኰሳቱን በኋላቸው ተከተላቸው ወደ ታላቅ ወንዝም ደረሰ ብቻውንም መሻገር ፈርቶ ቆመ ከዚያም ሳለ ዓረቦች ከግመሎቻቸው ጋር መጡ ያሻገሩትም ዘንድ ለመናቸው እነርሱም ከእርሳቸው ጋር አሻገሩት አንወስድህም ወደአሉት መነኰሳት ወደ ገዳማቸው በእግዚአብሔር ፈቃድ ደረሰ።

ከእርሳቸውም አንዱ አባ ስምዖን የሚባለው ዮሐንስን ወስዶ ደቀ መዝሙሩ አድርጎ ከሁለቱ ደቀ መዛሙርቱ ጋር አኖረው።

አባ ስምዖን የሚሞትበት ጊዜ እንደቀረበ በአወቀ ጊዜ ልጆቹን ጠርቶ ከሞትኩ በኋላ በእናንተ ላይ የሚሆነውን እግዚአብሔር ያሳየኝን እነግራችሁ ዘንድ ልጆቼ ኑ አላቸውና ከእናንተ አንዱን ጅብ ነጥቆ ይወስደዋል። ሁለተኛው ወደ ዓለም ተመልሶ ይባክናል። የሦስተኛው ግን ዜናው በዓለሙ ሁሉ ይሰማል አላቸው።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ጥቅምት 19/2016 #ቅዱስ_ገብርኤል

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በመልአኩ ስም ለምናመሰግንበት የመልአኩ #ቅዱስ_ገብርኤል ጥበቃና ተራዳኢነት እንዳይለየን ለምንማፀንበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉ገብርኤል ማለት፦ገብረ ኤል፣ የጌታ አገልጋይ፣ የእግዚአብሔር ሠራተኛ፣ ገብረ አምላክ፣ ገብረ እግዚአብሔር ማለት ነው

👉‘ገብረ’ እና ‘ኤል’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ የመልአክ ስም ነው #የእግዚአብሔር_ሰው ማለትም ነው

👉አብሳሪ መልአክ #ቅዱስ_ገብርኤል ሆይ እጅግ አፅናኝና አስደሳች የሆነውን ምስጢረ ሥጋዌን ዜና ይዘህ ከሰማይ ወደ ምድር እንደወረድክ ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ለመሆን ፈቃድዋ ሆኖ በተፈጸመ ጊዜ ደስ እንዳለህ እኛም እግዚአብሔርን በማክበርና ግዴታችንን በመፈፀም ደስ የምንልበትን ጸጋ አሰጠን

👉ጠባቂያችን ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ሦስቱን ወጣቶች ከሚያቃጥል እሳት እንዳዳንካቸው እኛንም በዚህ ዓለም ከሚወራው ከሚታየውና ከሚሰማው ክፉ ቀንና እለት ሁሉ አድነን እየነደደ የሚለበልበንን የኃጢያት እሳትም አጥፋልን

👉የኑሯችንን ቀጠሮ በክንፈ ረድኤትህ ከልለው ሰይጣን እንዳይሰለጥንብን ክፉ አድራጊዎች፣ ሟርተኞች፣ ሰላቢዎች ዘረኞችና ነፍሰ ገዳዮች እንዳያጠቁን ከልለን ያንተን የእሳት አጥር ዘሎ ጠላት ያጠቃን ዘንድ ጠላት አይችልምና ጥበቃ ከእኛ ከባርያዎችህ አይለየን

👉ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ሕፃኑ ቂርቆስና እናቱ እየሉጣን በንፍር ውኃ ከመቀቀል እንዳዳንካቸው ልጆችህን በማናውቀው ሁኔታ የተዘጋጀልንን የጥፋት ወጥመድ ሁሉ አስወግድልን በላያችን ላይም በክፉ ሰዎች ምክንያት የተነሳብንን እሳት አጥፋልን

👉ለእውነተኛ ሃይማኖት የጨከንንና የቆረጥንም አድርገን የሰይጣንን ፈተና የምናልፍበት እውነተኛውን ጥበብ እንደ ነብዩ ዳንኤል አስተምረን

👉ቅዱስ ገብርኤል ሆይ በደል በተገኘብኝ ቁጥር እያለቀስሁ እጠራሃለሁ ጎስቋላ የምሆን በጥቃትና በሀዘን ውስጥ የምገኝ ልጅህ የአንተን ማፅናናትና ረዳትነት ያሻኛልና ፈጥነህ ናልኝ

👉ቅድስት ማርያምን ያበሰርክ ለዓለም ሁሉ የምታበራ ገብርኤል ሆይ በሰራዊት አምላክ ይዤሃለሁ በዚህች ሰዓት ፀሎቴንና ልመናዬን ስማ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ቀድመህ የደስታ የምሥራች ቃልህን ልታበስር ወደ ገሊላ እንደወረድህ ዛሬም ለአዘንን ለእኛ ከሠማይ በሠረገላ ናልን የደስታንም ቃል አሰማን

👉ቅድስት ድንግል ማርያምን ያበሰርክ ተወዳጁ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ በምህረትና በይቅርታ ወደ እኛ ናልን ዓለም የጥፋት የሞት የክስረት የውድመትና የተስፋ መቁረጥ ድምፅን ያሰማናልና አንተ ግን ጉስቁልናችንን የሚያነሳ ስብራታችንን የሚጠግን እንባችንን የሚያብስ የብስራት ድምፅህን አሰማን እንድንፅናናም አድርገን

👉እውነተኛ ጠባቂያችን ቅዱስ ገብርኤል ሆይ፤ እኛን ለማዳን ሰው የሆነውን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን ማደሪያው የሆነችው ድንግል ማርያምን በጣም እንወዳታለን በዚህ ዓለም የምሥጢረ ሥጋዌ ተካፋዮች በመሆናችን በመንግስተ ሰማያትም ተካፋዮች ለመሆን ሁላችንንም በምልጃህ አብቃን ለምንልን

👉የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ጥበቃህ ተራዳኢነትህ አይለየን ለሀገራችን ሠላምን ለህዝባችን ፍቅር አንድነትን አድለን ርሃብ ጦርነትን ከምድራችን ላይ አስወግድልን በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የሚዉሉ ቅዱሣን የከበረዉ ቃል ኪዳናቸው ይጠብቀን "አሜን" 💒 💚 💛 ❤ 💒

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ጥቅምት_18

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት አሥራ ስምንት ቀን የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_ቴዎፍሎስ ያረፈበት፣ የከበረ #ቅዱስ_ሮማኖስ በሰማዕትነት ያረፈበት ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ቴዎፍሎስ

ጥቅምት አሥራ ስምንት በዚህች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃያ ሦስተኛ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት የከበረ አባት ቴዎፍሎስ አረፈ። ይህም አባት ንጉሥ ቴዎዶስዮስ በነገሠ በስድስተኛ ዓመት ተሾመ በወንጌላዊ ማርቆስም ወንበር ሃያ ስምንት ዓመት ኖረ።

በዘመኑ ብዙ መጻሕፍትን የተረጎመ ከእሳቸውም የወንጌላዊ ዮሐንስን ራእይና የሐዋርያ ጳውሎስን መልእክት የተረጎመ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ተነሣ ዳግመኛም ለደሴተ ቆጵሮስ ኤጲስቆጶስ የሆነ ኤጲፋንዮስ ነበረ።

በዘመኑም ሰባቱ ደቂቅ ሦስት መቶ ሰባ ሁለት ዓመት ከአንቀላፉ በኋላ ተነሡ። ይህም አባት የሐዋርያዊ ሊቀ ጳጳሳት አባት አትናቴዎስ ደቀ መዝሙር ነው የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍትና ሥርዓቱን ሁሉ እየተማረ በእርሱ ዘንድ አደገ። ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ ጢሞቴዎስም በአረፈ ጊዜ ይህ አባት በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ተሾመ አዋቂና አስተዋይም ስለሆነ ስለ ፍቅር ስለ ርኅራኄ ከንሰሐ በፊት ሥጋውንና ደሙን ከመቀበል መጠበቅ ስለ ሚገባ ስለ ሙታን መነሣትና ለኃጥአን ስለ ተዘጋጀ ስለዘላለማዊ ሥቃይ ሌሎችም ጠቃሚ የሆኑ ድርሳናትንና ተግሣጻትን ደረሰ።

ቅዱስ ቄርሎስም ለዚህ አባት ቴዎፍሎስ የእኅቱ ልጅ ነው እርሱም በበጎ አስተዳደግ አሳደገው የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት አስተማረው። ከዚያም በኋላ ወደ አባ ሰራብዮን ላከው አባ ሰራብዮንም መንፈሳዊ ተግባርን ሁሉ አስተማረው።

በአትናቴዎስም ዘመን አስቀድሞ እንዲህ ሆነ በጎ ዘመን ባገኝ ይህን ኮረብታ ባስጠረግሁት ነበር። ለከበሩ ለመጥምቁ ዮሐንስና ለነቢይ ኤልሳዕም ቤተ ክርስቲያን በሠራሁም ነበር ሲል ይህ አባት ቴዎፍሎስ አባ አትናቴዎስን ይሰማው ነበር። በሹመቱ ወራትም ይህን ነገር አስታውሶ የሚያዝንና ክብር ይግባውና ወደ ጌታችን የሚጸልይ ሆነ።

በዚያ ወራትም ባሏ ብዙ ገንዘብ ትቶላት የሞተ አንዲት ባለጸጋ ሴት ከሮሜ አገር መጣች ሁለት ልጆቿም ከእርሷ ጋር አሉ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስንም ሲያዝን አየችውና ክብር አባት ሆይ ምን ያሳዝንሐል አለችው። እርሱም ብዙ ወርቅ በዚህ ኮረብታ ውስጥ እያለ ድኆች ይራባሉና አላት እርሷም አንተ ስለ እኔ ጸልይ እኔም አስጠርገዋለሁ አለችው።

ይህንንም ብላ ያን ኮረብታ አስጠረገችው በውስጡም በደንጊያ ሠሌዳ እየአንዳንዱ የተከደኑ ሦስት ሣጥኖች ተገለጡ። በላያቸው ቴዳ ቴዳ ቴዳ የሚል ተጽፎባቸዋል አባ ቴዎፍሎስም በአየው ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ምሥጢራቸውን አውቆ ቴዳ ማለት የጌታ ስም ነው ይህም ለድኆች ይገባል አለ ሁለተኛውም ቴዳ የንጉሥ ቴዎዶስዮስ ነው ሦስተኛውም ቴዳ ቴዎፍሎስ ማለት ነው። የእኔ ገንዘብ ስለሆነ በዚህም አብያተ ክርስቲያናትን እሠራለሁ አለ። እሊህም ሣጥኖች በመቄዶንያዊው ፊልጶስ ልጅ በንጉሥ እስክንድር ዘመን እንደ ተቀበሩ የዘመን ቊጥር ተገኘ እርሱም ሰባት መቶ ዘመናት ነው።

ከዚህም በኋላ ያን የወርቅ ሣጥን ለንጉሥ ቴዎዶስዮስ ላከለት ስለዚያም የወርቅ መዝገብ አስረድቶ ቦታውን መጥቶ እንዲያይ አሳሰበው እርሱም በመርከብ ተጭኖ ወደ እስክንድርያ አገር መጥቶ ሁሉንም አየ የዚያንም ወርቅ እኵሌታ መለሰለት አባ ቴዎፍሎስም ብዙዎች አብያተ ክርስቲያንን ሠራ።

አስቀድሞም በቅዱሳን በመጥምቁ ዮሐንስና በነቢይ ኤልሳዕ በስማቸው ቤተ ክርስቲያን ሠራ ሥጋቸውንም ከእስራኤል አገር አፍልሶ አምጥቶ በውስጧ አኖረ እርሷም የታወቀች ናት ዴማስ በሚባል ቦታ ሁለተኛም በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በሀገሩ ምሥራቅ በኩል ሠራ ከዚህም በኋላ በሊቀ መላእክት ሩፋኤል ስም በደሴት ውስጥ ሠራ ሌሎችንም ብዙዎች አብያተ ክርስቲያን አሳነፀ።

ንጉሡም አብያተ ክርስቲያናትን ለመሥራት ያለውን የሊቀ ጳጳሳቱን ፍቅር አይቶ በግብጽ አገር ያሉትን የጣዖታት ቤቶችን ሁሉንም ሰጠው እርሱም ተቀብሎ አፈረሳቸውና በቦታቸው አብያተ ክርስተከያናትንና የእንግዶች ቤቶችን ሠራ ሁለተኛም ምድራቸውን ሁሉ ሰጠው።

ይህም አባት ቴዎፍሎስ የክርስትና ጥምቀትን በሚያጠምቅ ጊዜ የብርሃን በትረ መስቀል በሚጠመቁት ላይ በመስቀል ምልክት ሲያማትብ ያይ ነበር።

ይህ አባት ቴዎፍሎስና ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ልጆች በሆኑበት ጊዜ ሁለቱም በአንዲት ሌሊት አንዲት የሆነች ራእይን እነርሱ እንጨቶችን እንደሚለቅሙ አዩ። ከእነርሱም አንዱ ንጉሥ እንደሚሆን ሁለተኛውም ሊቀ ጳጳሳት እንደሚሆን ያቺን ራእይ ተረጎሟት እንዲሁም ሆነ።

ይህም አባት ቴዎፍሎስ ሊቀ ጵጵስና በተሾመባት በመጀመሪያዪቱ ዓመት ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ሃይማኖትን እናስተምራለን የሚሉ ሁሉ ሃይማኖታቸውን በመጽሐፍ ጽፈው ወደርሱ እንዲአቀርቡ አዘዛቸው እንዳዘዛቸውም አደረጉ።

ከዚህም በኋላ ንጉሡና ሊቀ ጳጳሳቱ ተነሥተው እነዚያን ጽሑፎች በመሠዊያው ላይ አድርገው ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ ጌታም ወልድ በመለኮቱ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል ነው ብሎ ከሚታመን በቀር ከውስጣቸው በቀናች ሃይማኖት የጸና እንደ ሌለ ገለጠላቸው። በዚያንም ጊዜ እሊህን የመና*ፍ*ቃን መጻሕፍትን እንዲአቃጥሏቸው እነዚያንም መና*ፍ*ቃን ከሚገዛው አገር እንዲአሳድዷቸው ንጉሥ አዘዘ።

ዮሐንስ አፈወርቅም መጻሕፍትን ማንበብና መመርመር ያበዛ ነበር ስለዚህም የአውጋርዮስን መጻሕፍት አወገዘ ያወግዙ ዘንድም ወደ እስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ወደዚህ አባት ወደ ቴዎፍሎስ ወደ ቆጵሮስ ኤጲስቆጶስ ወደ ኤጲፋንዮስ ወደ ኤዺስቆጶሳት ሁሉ በየሀገሩ ላከ። ከዚህም በኋላ መልካም ጒዞውን በፈጸመ ጊዜ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#መነኰስ_ቅዱስ_ሮማኖስ

ዳግመኛም በዚህች ቀን ክርስቲያኖችን በአሳደደ በመኰንን አስቅልጵያኖስ ዘመን የከበረ መነኰስ ሮማኖስ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ የክርስቲያን ወገኖችን መኰንኑ እንዳሳደዳቸው በሰማ ጊዜ ከቀሳውስትና ከዲያቆናት ጋር የክርስቲያን ወገኖችን ሁሉ በአንድነት ሰበሰባቸው ስለ ክርስቶስ ሃይማኖትም መክሮ አጸናቸው።

አስቅልጵያኖስም ይህን ሰምቶ እንዲአመጡት አዘዘ በፊቱም በቆመ ጊዜ አስቅልጵያኖስ በወገን የከበርክ ሮማኖስ አንተ ነህን አለው ቅዱሱም የወገን ክብር ምን ይጠቅመኛል ክብሬ ግን ክርስቶስ ነው ብሎ መለሰለት። መኰንኑም ሰምቶ እንዲሰቅሉትና ጉንጮቹን ይሰነጣጥቁ ዘንድ አዘዘ ጉንጮቹንም ሲሰነጣጥቁት ምንም አልተናገረምና መኰንኑ ትዕግሥቱን አደነቀ።

በዚያንም ጊዜ ሮማኖስ መኰንኑን እንዲህ አለው እነሆ ስንፍናህን እዘልፍ ዘንድ ፈጣሪዬ አፌን ከፈተ እውነት ነገርን ብታውቅ ለእግዚአብሔር እንሰግድ ዘንድ ይገባ እንደሆነ ወይም ለአማልክት እንዲነግረን ሕፃን ልጅ እንዲአመጡ እዘዝ መኰንኑም ታናሽ ሕፃንን እንዲአመጡ አዘዘ መኰንኑም ሕፃኑን ስግደት ለማን እንዲገባ ዕውነቱን ንገረን አለው። ሕፃኑም ልብ የሌለህ ደንቆሮ መኰንን በአንዲት ቃል ዓለሙን ሁሉ ለፈጠረ ለሕያው እግዚአብሔር ስግደትና አምልኮ እንዲገባ አታውቅምን አለው።

መኰንኑም ሕፃኑን ይሰቅሉት ዘንድ አዘዘ የሕፃኑም እናት ልታየው መጣች ሕፃኑም እናቱን ተጠምቻለሁና ውኃ አጠጭኝ አላት። እናቱም ልጄ ሆይ ከዚህ ውኃ የለም ነገር ግን ወደ ሕይወት ውኃ ሒድ አለችው።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://www.youtube.com/live/wc8WL_eOd_A?feature=share

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🙄🙄 አሞኝ ነበረ ወተት ልጠጣ ብየኮ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የዛሬውን የ ethio 360 ፕሮግራምን በቀጥታ ይከታተሉ!! ጥቅምት 24/2016 አ.ም።
https://www.youtube.com/live/XTDrmHJsYcI?si=O1o5jNE_z40GedaT

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

4. ምሥጢረ ክህነት👈

ይህ ቋንቋ የግዕዝ ቋንቋ ነው፡፡ ተክህነ አገልገለ ከሚለው ግስ የወጣ ነው፡፡ ክህነት የተጀመረው በአባታች አዳም ነው፡፡ ክህነት የአገልግሎት #ስም ሆኖ የቤተክርስቲያን ከፍተኛ መንፈሳዊ ማዕረግ ነው፡፡ እግዚአብሔር አዳምን ፈጥሮ በልጅነት አክብሮ ነብይና ካህን አድርጎ ሾሞ በኦሪት በወንጌል ሥርዓት እስኪወሰን ድረስ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ የነበሩ አበው በበረከት አበው ከእግዚአብሔር እየተሾሙ ትንቢትን ክህነት ከቅዱሱ መንፈስ እየተቀበሉ (እየተሾሙ) በነብይነታቸው ያለውን የሚመጣውን ሲገልጽ ሲያስተምሩ በሀብተ ክህነታቸው መስዋዕት ሲቀርቡ ነበር፡፡ ክህነት በዘመነ ኦሪት ለሌዊ ነገድ ከተሰጠ በኋላ ሲወርድ ሲወራረድ እስከ ክርስቶስ ደርሷል፡፡ ታላቁ ሊቀ ካህናት እየሱስ ክርስቶስ እንደ ብሉይ ኪዳን መስዋዕት እንሰሳ ሳሆን እራሱን መስዋዕት፣ እርሱ ሰዋዒ ሆኖ ወደ መቅደስ ገብቷል፡፡ ዮሐ 20፡22 ማሬ 18፡18 1ኘና ቆሮ 4፡1 ማሬ 28፡20

5. ምሥጢረ ንስሐ👈

ይህ ቃል የግዕዝ ቃል ነው፡፡ ትርጉሙም በሰሩት ኃጢያት መጸጸት ምነው ባልሰራሁት ባላደረኩት ብሎ ማልቀስ ወደ ኃጢያት ላለመመለስ መወሰን፣ በሕጉ ጸንቶ ለመኖር ቃል መግባት፡፡ ክርስቲያን በጥምቀት ከአለም ክፉ ስራዎች ሁሉ የተለየ ነው፡፡ ህይወቱ ለክርስቶስ የተሰጠ ነው፡፡ ሮሜ 12፡1 የመጨረሻው ግቡና ዓላማው ሥርየተ ኃጢያትን ማግኘት እና የዘላለም ሕይወት መወረስ ነው፡፡ አካሉ የመንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ 1ቆሮ 6-19

6. ምሥጢረ ቀንዲል👈

ይህ ቃል የላቲን ቋንቋ ነው ትርጉሙም ፍፁም መብራት ማለት ነው፡፡ ከሰባቱ ሚስራት አንዱ ቀንዲል ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘይት የፈውስ ምልክት ነው፡፡ በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ ተይዘው የሚሰቃዩ ህሙማን ወይም በድንገተኛ አጋጣሚ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ቁስለኞች እየተቀቡ ይፈወሱ ነበር፡፡ ኢሳ 1፡6 ሉቃ 10፡34 ራዕ 3፡18 ማር 6፡13 ይህ ቅብዓተ በሐዲስ ኪዳን ለሚጠመቁ ከሚደረግ ቅብዐ ሜሮን ጋር ግንኙነት የለውም ራሱን የቻለ ሕሙማነ ሥጋ ብቻ ሳይሆን ሕሙማነ ነፍስ ኃጥአን የሚቀቡት ፈውስ የሚያገኙበት ነው፡፡ ማር 6፡13 ያዕ 5፡13-15 ራዕ 1፡17፡፡

7. ምሥጢረ ተክሊል👈

ይህ ማለት “ተከለለ” ተቀናጀ ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ በሥርዓተ ጋብቻ ቅደም ተከተል መሰረት በመተጫጨት #እና በቃል ኪዳን የተመሰረተ ጋብቻ በተክሊል ይፈጸማል፡፡ ቤተክርስቲያን ምስክርነት የሚፈጸመው ጸጋ መንፈስ ቅዱስን የሚያሰጥ ስለሆነ ነው፡፡ ክርስቲያናዊ ጋብቻ ትክክለኛነቱም የሚታወቀው በተክሊል ሥጋወ ደሙ ሲፈጸም ነው፡፡ ክርስቲያናዊ ጋብቻ ትክክለኛነቱም የሚታወቀው በትክሊል ሥጋወ ደሙ ሲፈጸም ነው፡፡ ዘፍ 1፡27-28 ፣ 2-18 ማቴ 19-4 እነዚህን ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን አውቀን ተረድተን የእምነታችን ፍጻሜ የሆነውን አምላካችንን ለተፈጠርንለት ዓላማ በመገዛት የነፍሳችንን መዳን ልናረጋግጥ ይገባል፡፡

ለዚህም ቸሩ አምላካችን እግዚአብሔር እንዲረዳን የወላዲተ አማላክ አማላጅነት እንዳይለየን የጻድቃን ፀሎት የቅዱሳን በረከት እንዳይለየን ፈቃዱ ይሁንልን #አሜን

#share 👈 አድርጉት ያላነበበ ያንብበው

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እርሱ አባ ዮሐንስም ከኢትዮጵያ በአሳደዱት ጊዜ ወደ አስቄጥስ በመሔድ አስቀድሞ በመነኰሰባት በአባ ሙሴ ጸሊም ገዳም በዚያ ተቀመጠ። የኢትዮጵያ ንጉሥ መልእክትም ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍ በደረሰች ጊዜ አነበባት ስለ ኢትዮጵያ ንጉሥ የሃይማኖት ጽናት እጅግ ደስ አለው ፈጥኖም ወደ አስቄጥስ ገዳም መልእክተኞችን ልኮ አባ ዮሐንስን ወደርሱ አስመጥቶ አረጋጋው አጽናናው ከዚያም በኋላ ከደጋጎች ሰዎች ጋር ወደ ኢትዮጵያ አገር ላከው።

አባ ዮሐንስም ወደ ኢትዮጵያ አገር በደረሰ ጊዜ ቸነፈር ተወገደ ዝናብም ዘነበ ንጉሡና መላው የኢትዮጵያ ሰዎች ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑት። ይህም ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍ መናፍቃንን የሚገሥጻቸው ሆነ ሕዝቡንም ከአባቶቻቸው በተቀበሏት በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ አስተማራቸው ከቅዱሳት መጻሕፍትም ለእነርሱም ሥውር የሆነውን ተርጉሞ ያስረዳቸዋል ያስገነዝባቸዋልም በትምህርቱና በጸሎቱም እንዲህ ጠበቃቸው ጌታችንም በእጆቹ ብዙዎች ተአምራትን አደረገ ያማረች ገድሉንም ፈጽሞ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም በፍቅር አረፈ ። መላ የሕይወቱም ዘመን ሰባ ስምንት ነው ከምንኲስና በፊት ሃያ አመት በምንኲስና ተጋድሎ ሠላሳ ዘጠኝ ዓመት በሊቀ ጵጵስና ሹመት ዓሥራ ዘጠኝ ዓመት ኖረ ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስት_እለእስክንድርያ_ሰማዕት

ዳግመኛም በዚህች ቀን የከሀዲ ዱድያኖስ ንጉሥ ሚስት የከበረች እለእስክንድርያ መታሰቢያዋ ነው። ይኸውም ለጣዖቶቹ እንደሚሠዋ መስሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ በዘበተበት ጊዜ ዝንጉዕ ዱድያኖስም ዕውነት መስሎት ራሱን ሊስም ተነሣ። ቅዱሱ ግን ለአማልክት ከመሠዋት አስቀድሞ አይሆንም ብሎ እንዳይስመው ከለከለው።

ከዚህ በኋላም ዱድያኖስ ወደ ቤተ መንግሥቱ አዳራሽ ቅዱስ ጊዮርጊስን አስገባው በዚያም በንግሥት እለእስክንድርያ ፊት የዳዊትን መዝሙር በማንበብ ጸለየ። በሰማችም ጊዜ ይተረጒምላት ዘንድ ለመነችው ያን ጊዜም ተረጐመላት የክብር ባለቤት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ጌትነቱን ገለጠላት ትምህርቱም በልቡዋ አድሮ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመነች።

ከዚህም በኋላ ሲነጋ ለአማልክት ወደሚሠዋበት ቅዱስ ጊዮርጊስን ወሰዱት እርሱም የረከሱ አማልክትን ትውጣቸው ዘንድ ምድርን አዘዛት ምድርም ዋጠቻቸው። ንጉሥ ዱድያኖስም አፈረ እየአዘነና እየተከዘ ወደ ሚስቱ ወደ እለእስክንድርያ ዘንድ ገባ። እርሷም ክርስቲያኖችን አትጣላቸው አምላካቸው ጽኑዕና ኃያል ነው አላልኩህምን አለችው። ይህንንም ሰምቶ በእርሷ ላይ ተቆጣ ያሠቃዩዋት ዘንድ ጡቶቿንም ሠንጥቀው ይሰቅሏት ዘንድ አዘዘ። የሰማዕትነትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለች።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዲዮናስዮስ_ኤጲስቆጶስ

በዚችም ቀን የቆሮንቶስ አገር ኤጲስቆጶስ ዲዮናስዮስ በዐላውያን ነገሥታት በዲዮቅልጥያኖስና በመክስምያኖስ ዘመን በሰማዕትነት አረፈ ይህንንም ቅዱስ በያዙት ጊዜ ብዙ ሥቃይን አሠቃዩት ማሠቃየቱንም በሰልቹ ጊዜ ራሱን በሰይፍ አስቆረጡት የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ጻድቁ_አቡነ_ኤልሳ

ዳግመኛም በዚህች ቀን በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ተተክለው በደብረ ሊባኖስ የተሾሙት አቡነ ኤልሳ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ጻድቁ ሀገራቸው ሸዋ ነው፡፡ በዐፄ ይኩኖ አምላክ ዘመን የነበሩ ሲሆን ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቀጥለው በደብረ ሊባኖስ ገዳም በእጨጌነት የተሾሙ የመጀመሪያ ዕጨጌ ናቸው፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከማረፋቸው በፊት ‹‹በእኔ ወንበር ኤልሳዕ ይሾም ነገር ግን ዘመኑ ትንሽ ስለሆነ ከእርሱ ቀጥሎ ፊሊጶስን ትሾማላችሁ›› ብለው ለቅዱሳን ተከታይ ሐዋርያቶቻቸው ተናግረው ነበር፡፡

በዚህም መሠረት አቡነ ኤልሳዕ ተሹመው ብዙም ሳይቆዩ አንድ ዲያቆን ሞተና ሊቀብሩት ሲወስዱት በመንገድ ላይ ሳለ ድንገት ከሞት ተነሥቶ ‹‹አባቴ ተክለ ሃይማኖት ኤልሳዕ አሁን ወደኔ ስለሚመጣ ፊሊጶስን ሹሙት ብለህ ተናገር ብለውኝ ነው›› ብሎ ከተናገረ በኋላ ተመልሶ ዐርፎ ተቀበረ፡፡ አቡነ ኤልሳዕም ወዲያው ዐርፈው አቡነ ፊሊጶስ 3ኛ ሆነው ተሾሙ፡፡ አቡነ ኤልሳዕ ከተጋድሎአቸው ብዛት የተነሣ በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ጎናቸውን አሳርፈው ተኝተው አያውቁም ነበር፡፡ ነገር ግን ማረፍ ሲኖርባቸው በወንበር ላይ ተደግፈው ትንሽ ብቻ ያርፉ ነበር፡፡ አቡነ ኤልሳዕ በሞት ያረፉትም እንደልማዳቸው ጎናቸውን ሳያሳርፉ በወንበር ላይ እንደተደገፉ ነበር፡፡ አባታችን ስለዚህም ጉዳይ ሲናገሩ እንዲህ ይሉ ነበር፡- ‹‹ነፍስ ትጋትን ትወዳለች፣ ሥጋ ግን ይደክማል፡፡ ለመነኮሳትና ለእግዚአብሔር አገልጋዮች ሁሉ መኝታ ማብዛት አይገባቸውም፡፡ መኝታ ማብዛት ሕልምን ያመጣል፣ ነፍስን ይጎዳል፣ ሰውነትንም ያደክማል፡፡››

አቡነ ኤልሳዕ በዘመናቸው ወንጌልን በማስተማርና ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ይታወቁ ነበር፡፡ እንደ ነቢዩ ኤልሳዕ እሳቸውም ሙት አስነሥተዋል፡፡ ባሕር እየከፈሉ ቀደ መዛሙርቶቻቸውን ያሻግሩ ነበር፡፡ በጸሎታቸው የዠማን ወንዝም ለሁለት የከፈሉ ታላቅ አባት ናቸው፡፡

ለእግዚአብርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት እና #ከገድላት_አንደበት)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

💚💛❤✳#ቅዱስ #ጊዮርጊስ❤

"#ጊዮርጊስ ማለት ኮከብ ብርህ ሐረገ ወይን #ፀሐይ "ማለት ነው ሊቀ ሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ በጥር 22ቀን በ 277ዓ/ም ተወለደ ሃገሩ ፍልስጤም ሲሆን ልዩ ስሟ ልዳ ይበላል። አባቱ ዞሮንቶስ አንስጣስዮስ ይባላል። ከልዳ መኻንንት ተሽሞ ይኖር ነበር፥እናቱ ቴዎብስታ (አቅሌስያ ትባላለች።ማርታና እስያ እህቶች ነበሩት።

🌿❤️ #10አመት ሲሞላው አባቱ ስለ ሞተ ሌላ ደግ ክርስትያናዊ መስፍን ከቤቱ አሳደገው።በጦር ሃይልም አሰለጠነው።20ዓመት ሲሞላን 15 ዓመት ልጅ ሊያጋቡት ሲሉ እግዚአብሔር የመስፍኑን ነፍስ ወሰደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ቤሩት ሄደ።
በቤሩት አደራጎን ያመልኩና ሴት ልጃቸውን ይገብሩለት ነበርና በኃይለ መስቀል ድል ነስቶት ህዝቡን ወደ አምልኮት እግዚአብሔር አስገብቷቸዋል።
🌿❤️ #ወደፍርስ ቢመለ ዲድያኖስ ሰባ ነገስታት ሰብስቦ ጣኦታት ሰብስቦ ሲሰግድ ቢያገኛቸው ለሃይማኖት ቀናዒ ነውና ከቤተ መንግስቱ ገብቶ እኔ ክርስትያን ነኝ በእየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ አለው።እርሱንም መንነቱ ከተረዳ በኃላ አንተ እማ የእኛ ነህ በ10አህጉር ላይ እሾምሃለሁ የእኔን አምላክ አጵሎንን አምልክ አለው።ቅዱስ ጊዮርጊስም ሽሞት ሽልማትክ ለአንተ ይሁን እኔ አምላኬ እየሱስ ክርስቶስ አልክድም አለ"።በዚ ግዜ እጅግ ተናዶ መከራን አጸናበት እርሱግን"ይህን ከሀዲ እስካስፈራው ድረስ ነፍሴን አትውሰድ"በማለት እግዚአብሔር ለመነና እንደ ጸሎቱ ተደረገለት በእምነቱ ጽናት ለሰው ሊሸከም የማይቻለው መከራ የተቀበለ ቅዱስ አባት ነው።

#ወስብሓት ለእግዚአብሔር
#ወለወላዲቱ ድንግል
#ወለመስቀሉ ክብር አሜን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ጥቅምት ፳፪/22/ ቀን !

♥ቅዱስ #ዑራኤል ሊቀ መላእክት!

#ዑራኤል ማለት ትርጉሙ #"የብርሃን ጌታ፣ #የአምላክ ብርሃን" ማለት ነው፡፡ #ቅዱስ ዑራኤል #ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ #በመብረቅና #በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ ነው፡፡ በመሆኑም #መጽሐፈ ሄኖክ እንደሚገልጸው #መባርቅት #ለጥጋብና #ለበረከት #እንዲበርቁ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል፡፡ ምሥጢረ ሰማይንና ሰማያዊውን ዕውቀት ሁሉ ለሄኖክ የገለጸለት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ የፀሐይን፣ የጨረቃን፣ የከዋክብትንና የሰማይ ሠራዊትን ብርሃንን የሚመራው ይኸው ገናና መልአክ ነው፡፡ (መጽሐፈ ሄኖክ 28፥13)

#መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ ሆኖ በተሰቀለ ጊዜ ክቡር ደሙን በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ በብርሃነ መነሳንስ በዓለም ላይ የረጨው ይኸው ገናና መልአክ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡

#ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋ ጥበብን አጠጥቶ ሰማያዊውን ምሥጢር የገለጠለት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ (ዕዝራ 2፥1) ዕውቀት ተሠውሮበት ለነበረው ለኢትዮጵያዊው ሊቅ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም በእመቤታችን ትእዛዝ ጽዋ ጥበብን አጠጥቶ ሰማያዊውን ምሥጢር የገለጠለት ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡

#አምላካችን እግዚአብሔር የሕይወትና የይቅርታ ዝናም በምድራችን ላይ ያዘንብ ዘንድ እንዲሁም የእርሻችንን አዝመራ በዝናም አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ ለምግብነት እንዲበቃ ከፈጣሪ ዘንድ ምሕረትን የሚለምን መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡

#በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ የተመሠረቱ አብዛኞቹ ቅዱሳት ገዳማት በቅዱስ ዑራኤል መሪነት ነው፡፡ ድርሳኑ ላይ የማይጠቅሳቸው የሀገራችን የከበሩ ቅዱሳት ገዳማትና ቅዱሳን ነገሥታት የሉም፡፡

#የብርሃን እናቱ ድንግል ወላዲተ አምላክን ከልጇ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ስትሰደድ መንገድ እየመራ ወደ ግብጽ እና ወደ አገራችንን ኢትዮጵያ ያመጣቸው ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡

#መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል በዓመት 3 ዓበይት በዓላት አሉት፦
☞ጥር 22 በዓለ ሲመቱ ነው፡፡
☞ መጋቢት 27 የጌታችንን ክቡር የሆነ ደሙን
ለዓለም የረጨበት ነው፡፡
☞ ሐምሌ 22 ቀን ቅዳሴ ቤቱ የሚከበርበትና
ሐምሌ 21 ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል የዕውቀትን ጽዋ
ያጠጣበት ዕለት ነው፡፡

#የሊቀ መላእኩ #ቅዱስ #ዑራኤል #ጥበቃው #ምልጃው #አይለየን #አሜን!!#ጥቅምት ፳፪/22/ መልካም አዳር ❤️!

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🌼ጸሎታቸውንም ከፈጸሙ በኋላ አባታችን ወደ እነርሱ ተመልሰው ‹‹እኔ ሽማግሌ ሰው ነኝ ወደ ጐንደር ለመሔድ አልችልም›› አሏቸው። እነርሱም ‹አባታችን ሆይ! አንተ ከእኛ ጋር ካልሔድህ ተመልሰን አንሔድም›› አሉ። አባታችንም እጅግ አዝነው "ልጆቼ ሒዱ እኛ እርሰ በእርሳችን በንጉሡ ቤት እንገናኘለን አሏቸውና ተመልስው ሔዱ ተመልስው ከሔዱ በኋላ ወደ ንጉሡ ቤት ቢደርሱ አባታችንን ከንጉሡ ጋር ተቀምጠው አገኟቸው ።የንጉሡ መልእክተኞችም ለንጉሡ " እኛ ከሻሽና ከተነሣን እስከዚህ ዘጠኝ ቀናችን ነው ይኽ አባት የሚያስደንቅ ተኣምር እያደረገ በየት አለፈን? " ብለው እጅግ ተገረሙ ።ንጉሡም ይኽን ድንቅ ተኣምር በስማ ጊዜ ከአባታችን እግር ሥር ሰገደ አቡነ ዐሥራተ ወልድንም አባቴ ሆይ አስተምረህ ላሳመንኽውና ለአጠመቅኽው ሕዝብ ታቦትን ወስደህ ቤተክርስቲያን ሥራ ከታቦታትም የወደዱኻውን ምረጥ ።በማለት ጠየቃቸው። ብፁዕ አባታችን ዐሥራተ ወልድም በጣም የምወዳት እንደ ምግብ የምመገባት እንደ መጠጥ የምጠጣት እንደ ልብስ የምለብሳት፣ እንደ ምርጉዝ የምደገፋት በፍቅሯ የምረካባት የኪዳነ ምሕረት ታቦት ናትና እርሷን እወዳታለሁ›› ብለው መረጡ፤ ንጉሡም ቃላቸውን ሰምቶ ታላቅ ደስታ ተደሰተ ፈቀደላቸውም።

🌼ከዚኽም በኋላ አቡነ ዐሥራተ ወልድ ወደ ኢየሩሳሌም ሔደው በዚያ ጌታየ ሆይ መሰቀልህን በቅዱሳት መጻሕፍት ሰማሁ ይኽን በዐይኔ አሳየኝ›› እያሉ አንድ ዓመት ቆመው ጸለዩ። የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለአባታችን ተገለጠላቸውና መጀመሪያ አይሁድ እንዴት እንደሰቀሉት የእሾኽ አክሊልን እንደአቀዳጁት፣ ጐኑን በጦር እንደተወጋ አሳያቸው። አቡነ ዐሥራተ ወልድም የጌታችንን ስቅለት በተመለከቱ ጊዜ እጅግ ደንግጠው ወደቁ።

🌼በዚያን ጊዜም ጌታችን ወደ እርሳቸው መጥቶ ልታይ የማትችለውን ዕለተ ዐርብ ለምን ለመንከኝ? እንግዲህ ተነሣና ወደ ሀገርህ ተመለስ የሰበሰብሃቸው መንጋዎችህ አንተን በማጣታቸው ተበትነዋልና» አላቸው። ከዚኽም በኋላ ጌታችን ታላቅ የምሕረት ቃልኪዳን ገብቶላቸው በክብር ዐረገ። አባታችን ዐሥራተ ወልድም ከገዳማቸው ወጥተው ወደ ኢየሩሳሌም ሔደው አንድ ዓመት ከቆዩ በኋላ በትንሣኤ ዕለት ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተመስጠው ካህናት ጸሎተ ቅዳሴውን ሳይጨርሱ ገዳማቸው ዙርዙር ኪዳነ ምሕረት ደረሱ።

🌼ከዚኽም በኋላ አባታችን ጉርብ በምትባል ዋሻ ውስጥ በአድያም ሰገድ ኢያሱ ዘመን ቤተ ክርስቲያንን ሠርቶላቸው መቶ ዐሥር ዓመት ከኖሩና ጌታችንም ታላቅ የምሕረት ቃልኪዳን ከገባላቸው በኋላ የጥቅምት ወር በባተ በሃያ አንድ ቀን ከዚኽ ዓለም ድካም በሰላም ዐርፈዋል።

የአቡነ ዐሥራተ ወልድ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን።

ምንጭ በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን መጽሐፍ የተወስደ🌼🌼🌼
እግዚአብሔር ይጠብቅልን ወንድማችን ገብረ ሥላሴ🌼🌼
ጥቅምት 20/2/2015🌼🌼
Kuwait🌼

🌼22 ዓመት ተረግዞ ኖሮ በኃላ በጸሎታቸው ኃይል ፂምና ጥርስ ያለው ልጅ እንዲወለድ ያደረጉት፣ ታቦተ ጽዮንን 40 ዓመት ያጠኑ፣ አንበሳን 7 ዓመት ውኃ ያስቀዱት፣ ንግሥናን ንቀው የመነኑ ታላቁ ጻድቅ አቡነ አላኒቆስ ጥቅምት 21 ቀን ዕረፍታቸው ነው፡፡

አቡነ አላኒቆስ የትውልድ ቦታቸው ሸዋ አንኮበር ሲሆን አባታቸው ንጉሡ ዐፄ ይኩኖ አምላክ ነው፡፡ ንጉሡ አባታቸው ‹‹አግባና መንግሥቴን ይዘህ ተቀመጥ›› ቢላቸው እርሳቸው ግን ንግሥናን በመናቅ እምቢ ብለው ሄደው ከእመቤታችን ሥዕል ሥር ወድቀው ቢለምኗት እምቤታችን ተገልጣላቸው ‹‹ክፍልህ ምናኔ ነው፣ የአባትህ መንግሥት ያልፋል የልጄ መንግሥት ግን ዘላለማዊ ነው›› አለቻቸው፡፡ ጻድቁም ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ሄደው በዚያው መንኩሰው ገዳሙን እያገለገሉ ተቀመጡ፡፡ ከጸሎታቸው በኋላ ራሳቸውን ወደ ባሕሩ ይጥሉ ነበርና አንድ ቀን እንዲሁ ራሳቸውን ወደ ባሕሩ ሲጥሉ መላእክት አውጥተዋቸዋል፡፡ አቡነ አላኒቆስ ወደ አክሱም እንዲሄዱ ታዘው ከሄዱ በኋላ በዚያም የጽላተ ሙሴ የታቦተ ጽዮን አጣኝ ሆነው 40 ዓመት ተቀምጠዋል፡፡ እመቤታችንም ተገልጣላቸው በዓታቸውን እንዲያጸኑ ከነገረቻቸው በኋላ ከአክሱም ወጣ ብሎ የሚገኘውን ማይበራዝዮ ገዳምን መሠረቱ፡፡ በዚያም እጅግ አስገራሚ ተአምራትን እያደረጉ ወንጌልን እያስተማሩ አገልግለዋል፡፡

አንድ ቀን መኰንኑ ወደ ሩቅ ቦታ ሲሄድ ቤተሰባቸውን ለንስሓ አባታቸው አደራ ሰጥተው ሄዱ፡፡ የንስሓ አባታቸውም የአቡነ አላኒቆስ ጓደኛ ነበሩ፡፡ መኰንኑም ከሄዱበት ሲመለሱ ሚስታቸው ከአሽከሯ አርግዛ ጠበቀቻቸው፡፡ ‹‹ከማን አረገዝሽ?›› ብለው ጽኑ ግርፋት ቢገርፏት ዋሽታ ‹‹ያረገዝኩት ከንስሓ አባቴ ነው›› አለች፡፡ መኰንኑም መነኩሴውን እገላለሁ ብሎ ሲነሣ መነኩሴውም ወደ አቡነ አላኒቆስ ሄደው አለቀሱ፡፡ አቡነ አላኒቆስም የመኰንኑን ሚስት ቢጠይቋት ባሏን ፈርታ ‹‹አዎ ከመነኩሴው አባት ነው ያረገዝኩት›› አለች፡፡ እሳቸውም ‹‹የተረገዘው ከዚህ መነኩሴ ከሆነ በሰላም ይወለድ፣ ካልሆነ ግን አይወለድ›› ብለው በቃላቸው አስረውና ገዝተው ሸኟቸው፡፡
በግዝታቸው መሠረት ሴቲቱ ድፍን 22 ዓመት ሙሉ ሳትወልድ በጭንቅና በጣር ኖረች፡፡ በአልጋ ላይ ሆና ተጨንቃ ስትኖር በመጨረሻ ለቤተሰቦቿ ተናግራ ወደ አቡነ አላኒቆስ ዘንድ በቃሬዛ ወሰዷትና ይቅርታ ጠይቃ እውነቱን ተናገረች፡፡ እሳቸውም ‹‹እግዚአብሔር ይፍታሽ›› ቢሏት 22 ዓመት ሙሉ ተረግዞ የነበረው ልጅ ትልቅ ሰው ሆኖ ጥርስ አውጥቶ፣ ፂም አብቅሎ በሰላም ተወለደ፡፡ እርሱም ከተወለደ በኋላ አባቱ ማን እንደሆነ ተናገረ፡፡ ጻድቁ አባታችንም ልጁን አሳድገውት አስተምረው አመንኩሰውታል፡፡ ስሙንም ተወልደ መድኅን አሉት፡፡ በስሙ የተሠሰራ ቤተ ክርስቲያን በትግራይ ጽንብላ ወረዳ ይገኛል፡፡

ጻድቁ አቡነ አላኒቆስ ሌላም የሚታወቁበት አንድ ግብር አላቸው፡፡ የማይበራዝዮ ገዳማቸው አገልጋይ የሆነው መነኩሴ በሬ ጠምዶ ሲያርሱ አንበሳ ከጫካው ወጥቶ አንዱን በሬ በላው፡፡ መነኩሴውም መጥተው ለአቡነ አላኒቆስ ነገሯቸው፡፡ እሳቸውም ‹‹ጸሎቴን እስክጨርስ ድረስ ወደ ጫካው ሂድና አንበሳውን ‹አላኒቆስ ባለህበት ጠብቀኝ እንዳትንቀሳቀስ ብሎሃል› ብለህ ተናገር›› ብለው ለመነኩሴው ነገሯቸው፡፡

መነኩሴውም እንደታዘዙት ወደ ጫካው ሄደው ጮኸው በሉ የተባሉትን ተናገሩ፡፡ አቡነ አላኒቆስም ጸሎታቸውን ሲጨርሱ ወደ ጫካው ሄደው አንበሳውን የበላውን በሬ አስተፍተውት በሬውን ነፍስ ዘርተውበት ከሞት አስነሥተው ዕለቱን እንዲታረስ አድርገውታል፡፡ አንበሳውንም ገዝተው ወደ ገዳማቸው ወስደው ሰባት ዓመት ውኃ እያስቀዱት እንዲያገለግላቸው አድርገውታል፡፡

አቡነ አላኒቆስ አንበሳውን አስረው ያሳድሩበት የነበረው ዛፍና ውኃ ያጠጡበት የነበረው ትልቅ የድንጋይ ገበታ ዛሬም ድረስ በገዳሙ ይገኛል፡፡ ከ22 ዓመት እርግዝና በኋላ ሴቲቱ ጥርስና ፂም ያለው ልጅ እንድትወልድ ያደረጉበት ትልቅ ጠፍጣፋ ድንጋይም ከነቅርጹ በገዳሙ በግልጽ ይታያል፡፡ ጻድቁ ጥቅምት 21 ቀን ዐርፈው በዚያው በማይባራዝዮ ገዳማቸው ተቀብረዋል፡፡ ጸበላቸው እጅግ ልዩ ነው፣ ያላመነውን ሰው አስፈንጥሮና ገፍትሮ ይጥለዋል እንጂ አያስቀርበውም፡፡
የአቡነ አላኒቆስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!

(ምንጭ፡- ማይበራዝዮ ገዳም የሚገኘው ያልታተመ የአቡነ አላኒቆስ ገድል፣ የቅዱሳን ታሪክ-87)
##በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ቅዱስ - አልዓዛር
ጥቅምት 21
የማርታና የማርያም ወንድም
በዚችም ቀን ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው የቅዱስ አልዓዛር ሥጋው ከቆጵሮስ አገር የፈለሰበት ሆነ።

ከክርስቲያን ነገሥታትም አንዱ ሥጋው በቆጵሮስ እንዳለ በሰማ ጊዜ ከቆጵሮስ ደሴት ወደ ቊስጥንጥንያ አፈለሰው።

ሊአፈልሱትም በወደዱ ጊዜ በከበረ የደንጊያ ሣጥን ውስጥ ሁኖ በምድር ውስጥ ተቀብሮ አገኙት በላዩም እንዲህ የሚል ጽሑፍ ነበረ ይህ በመቃብር ውስጥ አራት ቀን ከኖረ በኋላ ከሙታን ለይቶ ላስነሣው ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወዳጁ የሆነ የቅዱስ አልዓዛር ሥጋ ነው።

ይህንንም በአዩ ጊዜ ደስ ተሰኙበት ተሸክመውም ወደ ቊስጥንጥንያ አገር ወሰዱት ካህናቱም ሁሉ ወጥተው በታላቅ ክብር በመዘመርና በማመስገን ተቀበሉት በአማረ ቦታም አኖሩት በዚችም ቀን በዓልን አደረጉለት።

የቅዱስ አልአዛር ረድኤት በረከት አይለየን!!!

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ እንኩዋን ለታላቁ ቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐጺር እና ለቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+" ቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐጺር "+

=>በቤተ ክርስቲያን ያሉ አበው ሊቃውንት እንደሚሉት ከቅዱሳን በቁመቱ የአባ አርሳኒን ያክል ረዥም አልነበረም:: እርሱ እንደ ዝግባ ቀጥ ያለ ነበር:: በዚያው ልክ ደግሞ የቅዱስ ዮሐንስን (ዛሬ የምናከብረውን) ያህል አጭር አልነበረም:: በዚህ ምክንያት ይሔው ለዘለዓለም "ዮሐንስ ሐጺር - አጭሩ አባ ዮሐንስ" ሲባል ይኖራል::

+ሊቃውንትም ቁመቱንና ቅድስናውን በንጽጽር ሲገልጡ:-
"ሰላም ሰላም ዕብሎ በሕቁ:
ለዮሐንስ ሐጺር ዘነዊኅ ሒሩተ ጽድቁ" ይላሉ:: "ቁመቱ እጅግ ያጠረ: ጽድቁ ግን ከሰማይ የደረሰ ቅዱስ ዮሐንስን ሰላም ሰላም እንለዋለን" እንደ ማለት ነው::

+ቅዱሱ የተወለደው በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብጽ ነው:: ወላጆቹ ምንም ከሥጋዊ ሃብት ድሆች ቢሆኑም ባለ መልካም ክርስትና ነበሩና በጐውን ሕይወት አስተምረውታል:: ወደ ምናኔ የገባው ገና በ18 ዓመቱ ሲሆን የታላቁ አባ ባይሞይ ደቀ መዝሙር ሆኖ ተጋድሎንና ትሕርምትን ተምሯል::

+ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር በወቅቱ ከነበሩ ቅዱሳን ከቁመቱ ባሻገር በትሕትናው: በትእግስቱና በመታዘዙ ይታወቅ ነበር:: አባ ባይሞይ ይጠራውና ያለ ምንም ምክንያት ደብድቦ ያባርረው ነበር:: እርሱ ግን "ምን አጠፋሁ?" ብሎ እንኩዋ ሳይጠይቅ "አባቴ ሆይ! ማረኝ?" እያለ ከእግሩ ሥር ይወድቅ ነበር::

+ለብዙ ጊዜ በተመሳሳይ ሲደበድበው: እርሱም እርሱው ተደብድቦ: እርሱው ይቅርታን ሲጠይቅ ኖረ:: አንድ ቀን ግን እንደ ልማዱ ሊገርፈው ሲሔድ 7ቱ ሊቃነ መላእክት ከበውት አይቶ ደንግጦ ተመልሷል::

+አባ ባይሞይ ይሕንን ሁሉ የሚያደርገው ጠልቶት ወይ ክፉ ሆኖ አይደለም:: አንድ ሰው የሌላኛውን ግፍ መቀበል ካልቻለ ሰይጣንን ድል አይነሳም የሚል ትምሕርት ስለ ነበረ ነው እንጂ::

+አንድ ቀን ቅዱስ ዮሐንስ ወደ መምሕሩ ቀርቦ "አባቴ ጅብ ካገኘሁ ምን ላድርግ?" ሲል ጠየቀው:: (የአካባቢው ጅብ መናጢ ነበር) አባ ባይሞይ ግን "ይዘህልኝ አምጣው" አለው:: ትዕዛዝ ነውና ቅዱሱ ወደ በርሃ ወርዶ: ጅብ አልምዶ ይዞለት መጥቷል::

+ሌላ ቀን ደግሞ አባ ባይሞይ ቅዱስ ዮሐንስን ጠራውና ተፈልጦ የወደቀ ደረቅ እንጨት ሠጠው:: "ምን ላድርገው አባ?" አለው:: "ትከለውና እንዲያፈራ አድርገው:: ከዚያ አምጥተህ አብላኝ" ሲል መለሰለት:: ይህ ነገር ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪ መሆኑን እያወቀ ቅዱስ ዮሐንስ "እሺ" ብሎ ወስዶ ተከለው::

+ከዚያም ለ2 ዓመታት ሳይታክት ውሃ አጠጣው:: ውሃውን የሚያመጣበት ቦታ ደግሞ 10 ኪሎ ሜትር ያህል ከገዳሙ ይርቅ ነበር:: ቅዱሱ ላቡን እያፈሰሰ አሁንም ማጠጣቱን ቀጠለ::

+በ3ኛው ዓመት ግን ለምልሞ አበበ: ደግሞም አፈራ:: ካፈራው በኩረ ሎሚም ወስዶ ለመምሕሩ "አባቴ! እንካ ብላ" ብሎ ሰጠው:: አባ ባይሞይ ግን ማመን አልቻለም:: እጅግ አደነቀ: አለቀሰም::

+ወዲያው ያን ፍሬ ታቅፎ ወስዶ ለገዳሙ መነኮሳት አላቸው- "ንሱ ብሉ: በረከትንም አግኙ:: ይህ የዛፍ ሳይሆን የመታዘዝ ፍሬ ነው:: ቅዱስ ዮሐንስ አባ ባይሞይ ቢታመም ለ12 ዓመት አስታሞታል::

+መምሕሩ ከማረፉ በፊትም መነኮሳቱን ሰብስቦ የቅዱስ ዮሐንስን እጅ አስጨበጣቸው:: "ይህ የያዛችሁት እጅ የሰው ሳይሆን የመልአክ እጅ ነው" ብሏቸው ዐርፏል:: ቅዱስ ዮሐንስም ከዓመታት ቆይታ በሁዋላ የገዳሙ አበ ምኔት ሆኖ አገልግሏል:: ብዙ ነፍሳትንም ለቅድስና ማርኩዋል::

+መላእክት ንጽሕናው ደስ ስለሚያሰኛቸው አብረውት ይውሉ ነበር:: ሲተኛም በተራ በተራ ክንፋቸውን ያለብሱት ነበር:: ምጽዋትን በጣም ስለሚወድ ሰፌድ እየሰፋ ይሸጥና ገንዘቡን ለነዳያን ያን ያካፍል ነበር::

+አንድ ቀን እንደ ልማዱ ወደ ገበያ ወጥቶ ሳለ ተደሞ (ተመስጦ) መጣበት:: ሰማያት ተከፍተው: ቅዱሳን ሊቃነ መላእክት ሚካኤልና ገብርኤል በግርማ በጌታ ፊት ቆመው ተመለከተ::

+"እጹብ: እጹብ" እያለ ሲያደንቅ አንድ ገዢ መጥቶ "ባለ እንቅብ ዋጋው ስንት ነው?" ቢለው "እኁየ ሚካኤልኑ የዓቢ ወሚመ ገብርኤል - ከሚካኤልና ከገብርኤል ማን ይበልጣል?" ብሎታል:: ገዢውም ደንግጦ "እብድ መነኩሴ" ብሎት ሔዷል::

+ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ወደ ባቢሎን (የአሁኗ ኢራቅ) ሒዶ ከተመለሰ በሁዋላ በበርበሮች ምክንያት ከአስቄጥስ ወደ ቁልዝም ተሰዷል:: በዚያም በአባ እንጦንስ በዓት ውስጥ ዐርፏል:: ለ400 ዓመታት በዚያው ቆይቷል::

+በ825 ዓ/ም ግን በአባ ዮሐንስ ፓትርያርክ ዘመን ክቡር ሥጋው ወደ ገዳመ አስቄጥስ ተመልሷል:: ቅዱሱ ያረፈው ጥቅምት 20 ቀን ሲሆን ዛሬ ሥጋው የፈለሠበት ነው:: በዚህ ዕለትም የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርና የታላቁ ቅዱስ መቃርስ ሥጋ በተገናኙ ጊዜ ግሩም ተአምር ተደርጉዋል:: ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ሲገባም ታላቅ የብርሃን ጐርፍ ሲፈስ ታይቷል::

+ሰማያዊ መዓዛም አካባቢውን ሞልቶታል:: ከዻዻሳቱ አንዱ እባረካለሁ ብሎ የቅዱስ ዮሐንስን ሥጋ ቢገልጠው አካባቢው ተናወጠ:: መባርቅትም (መብረቆች) ተብለጨለጩ:: ደንግጠው ቶሎ ቢያለብሱት ጸጥታ ሆኗል:: በዚህ ሁሉ ደስ ያላቸው አበው ቅዱሱን በዝማሬ ሲያወድሱት ውለዋል::

+" ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ "+

+ከነቢያተ እሥራኤል አንዱ
+ከእርሻ ሥራ ቅዱስ ኤልያስን የተከተለ
+መናኔ ጥሪት የተባለ
+በድንግልና ሕይወት የኖረ
+የታላቁ ነቢይ ኤልያስ መንፈስ እጥፍ የሆነለት
+እጅግ ብዙ ተአምራትን ያደረገ
+አንዴ በሕይወቱ: አንዴ በአጽሙ ሙታንን ያስነሳ ታላቅ ነቢይና አባት ነው::

+ቅዱስ ኤልሳዕ በጣም ረዥም: ራሱ ገባ ያለ (ራሰ በራ): ቀጠን ያለ: ፊቱ ቅጭም ያለ (የማይስቅ) ሽማግሌ ነበር::

=>አምላከ ቅዱሳን የሐጺር ቅዱስ ዮሐንስን መታዘዙን: ትሕትናውን: ትእግስቱንና ቅንነቱን ያድለን:: በበረከቱም ይባርከን::

=>ጥቅምት 20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐጺር
2.ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ
3.አባ ባይሞይ

=>ወርኀዊ በዓላት
1..ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
2.ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
3.ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
4.አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና
5.ቅድስት ሳድዥ የዋሒት
6.ቅዱስ ወክቡር ማር ቴዎድሮስ ሰማዕት

=>+"+ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ 'የማንጠቅም ባሪያዎች ነን: ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል' በሉ:: +"+ (ሉቃ. 17:10)

✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞ "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
/channel/zikirekdusn
https://youtu.be/vfyYtUTMC38?si=0PwdHcgnlRvhPs40

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Check out የ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች💚💛❤: /channel/+7wAsU1YGMRxmOGE0

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ከዚህም በኋላ አረጋዊው ስምዖን ወደ ዮሐንስ ተመልክቶ ልጄ ሆይ በክርስቶስ ፍቅር ጽና ለብዙዎች አባት ልትሆን እርሱ መርጦሃልና አለው። አባ ስምዖንም ከአረፈ በኋላ በሦስተኛው ቀን አንዱ ረድዕ ወደ ዓለም ተመልሶ ሚስት አገባ ሁለተኛው ወዴት እንደ ደረሰ አልታወቀም። አባ ዮሐንስም ብቻውን ቀረ ፈጽሞ አዘነ በልቡ እንዲህ አለ የጓደኞቼን ወሬ እጠይቅ ዘንድ ከገዳም ወጥቼ ልውረድ ይህንንም ብሎ ከገዳሙ ወጥቶ ሲወርድ የጸይለም ጦረኞች ተቀበሉት ደም ግባታቸው ከሚአምር ከሁለት ሴቶች ጋር አሥረው ወሰዱት በጒዞም ላይ እያሉ ለእንስሶቻቸውና ለራሳቸው የሚጠጡት ውኃ አጡ። አባ ዮሐንስም ከዚህ በረሀ ውስጥ ፈጣሪዬ ውኃን ቢአወጣላችሁ ትለቁኛላችሁን አላቸው አዎን አሉት። በዚያንም ጊዜ አባ ዮሐንስ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ብሎ በምድር ላይ አማተበ ውኃም ፈልቆላቸው ጠጥተው ረኩ።

የከበረ ዮሐንስም ቃል ኪዳን እንደ ገባችሁልኝ አሰናብቱኝ አላቸው እነርሱም እንዳንተ ያለ አናገኝምና ከቶ አንለቅህም አሉት። ይህንንም ብለው ወደ አገራቸው ወደ ጸይለም አደረሱት።

በዚያንም ወራት በጸይለም አገር ታላቅ መቅሠፍት ወረደ የአበ ዮሐንስም ጌታው ከቤተሰቦቹ ሁሉና ከልጆቹ ጋር ሞተ ሚስቱም ከአንዲት ልጅዋ ጋር ብቻዋን ቀረች። የጌታውም ሚስት ቅዱስ ዮሐንስን መሠርይ እንደ ሆነ አሰበች በማደሪያውም ውስጥ እያለ ሊአቃጥሉት እሳት ለቀቁበት እግዚአብሔርም ከእሳት ውስጥ በደኅና አወጣው የጸይለም ሰዎችም ይህን ድንቅ ተአምር አይተው ሴቶችም ወንዶችም በጌታችን አምነው በእጆቹ ተጠመቁ።

ከዚያም ተነሥቶ ወደ ሌላ አገር ሔደ። የአገር ሰዎችም ዛፎችን ሲያመልኩ አግኝቷቸው እርሱም ከክህደታቸው እንዲመለሱ አስተማራቸው ባልሰሙትም ጊዜ ምሳር ይዞ በሌሊት ወደ ዛፎቹ መካከል ገብቶ ክብር ይግባውና ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ምሳሩንም አንሥቶ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እቆርጣችኋለሁ አለ። ወዲያውኑ በአንዲት ምት ዐሥር ሽህ ዛፎች ወደቁ የሀገር ሰዎችም ይህን ድንቅ ተአምር አይተው ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ሁሉም ከሴቶችና ከልጆች ጋር ተጠመቁ።

ከዚያም ዳግመኛ ወደ ሌላ አገር ሔደ ሰዎችንም እሳትን ሲያመልኩ አገኛቸው እርሱም ይህን ደንቊርናቸውን ይተዉ ዘንድ አስተማራቸው ገሠጻቸውም እነርሱም በእርሱ ላይ ተቆጥተው ከእሳት ጨመሩት። እርሱም በደኅና ወጣ ሦስት ጊዜም ጨምረውት በደኅና ወጣ ውኃቸውንም ደም አደረገባቸው የሚጠጡትም አጥተው በተጨነቁ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ሁሉም አመኑ። አራት መቶ ሽህ ሰዎችም በእጁ ተጠመቁ ቤተክርስቲያንም ሠራላቸው አስተምሮም በቀናች ሃይማኖት አጸናቸው ቁጥር የሌላቸው ድንቆች ተአምራትንም አደረገ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም በፍቅር አረፈ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ጥቅምት_19

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት አስራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ደግ ንጉሥ #ቅዱስ_ይምርሃነ_ክርስቶስስ እረፍቱ ነው፣ #ቅዱስ_በርቶሎሜዎስና_ሚስቱ በሰማዕትነት አረፉ፣ ስለ #ጳውሎስ_ሳምሳጢ በአንጾኪያ አገር የቤተ ክርስቲያን የአንድነት ስብሰባ ተደረገ፣ የጸይለም አገር የከበረ አባት #ቅዱስ_ዮሐንስ አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ይምርሃነ_ክርስቶስ

ጥቅምት አስራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ደግ ንጉሥ፣ ፃድቅ ካህን፣ቤተ መቅደሱን በባህር ላይ ያነፀ መሀንዲስ ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስስ
እረፍቱ ነው።

ልክ እንደ አቡነ ተክለሃይማኖትና እንደነ አቡነ ዜና ማርቆስ እርሱም ሲወለድ ወደ ምሥራቅ ዞሮ አምላኩን ያመሰገነ ሲሆን ቤቱም በብርሃን ተሞልቶ ታይቶ አዋላጆቹን ሁሉ አስገርሞ ነበር፡፡ ገና በእናቱ ማህፀን ሆኖ አጎቱ ጠንጠውድም በንግሥና ላይ ሳለ "ከአንተ በኋላ የሚነግሠው ይምርሃነ ክርስቶስ የሚባል የወንድምህ ልጅ ነው" የሚል ንግርት ይሰማ ነበርና ‹‹ይምርሃነ ክርስቶስ›› መወለዱን ሲያውቅ ‹‹የወንድሜን ልጅ ዐየው ዘንድ አምጡልኝ›› ብሎ ላከ፡፡ ባየውም ጊዜ ደም ግባቱ እጅግ ያምር ስለነበር ‹‹ይህስ መንግሥቴን ይውረስ፣ በእውነት ልጄ ነው›› ብሎ ባረከው፡፡

ከእርሱ ጋር ስምንት ቀን ተቀምጦ በወለዳቸው ልጆቹ መካከል ሆኖ ሲጫወት በተመለከተው ጊዜ ግን በልቡ ሰይጣን አደረበትና በቅናት ሆኖ ‹‹እርሱ ነግሦ ልጆቼ ወታደሮቹ ሊሆኑ ነውን›› በማለት ይገድለው ዘንድ አሰበ፡፡ ሆኖም አማካሪዎቹ ‹‹ለጊዜው ምንም ስለማይረዳ ተወው ለወደፊቱም የንግሥና ምሥጢር እንዳያውቅ ወደ እናቱ ዘንድ መልሰውና በዚያ ከብት ሲያግድ ይደግ››ስላሉት ወደ እናቱ ላከው፡፡ እርሷ ግን በጥበብና በብልሃት አስተዋይ አድርጋ አሳደገችው። ይህንንም ሲሰማ ሊገድለው አሽከሮቹን ላከ፡፡ እናቱም የተላኩትን አሽከሮች ተቀብላ ምግብ አቅርባ አስተናገደቻቸው። ነገር ግን እግዚአብሔር የንጉሡን ተንኮል ስለተገለጠላት ልጇን ደበቀችው፡፡ በስውርም ወስዳ ከጳጳሱ ዘንድ ዲቁና እንዲቀበል ካደረገችው በኋላ ‹‹ልጄ ሆይ! አጎትህ ሊገድልህ ይፈልግሃልና በፊቴ ከሚገድልህ ርቀህ ብትሄድ ይሻላል፣ ያዕቆብን ከኤሳው የጠበቀ አንተንም ይጠብቅህ›› ብላ ሸኘችው፡፡ ይምርሃነ ክርስቶስም ወደ በጌምድር ተሰደደ፡፡ (ገድሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ በዚያም የሌዋውያን ወገን የምትሆን ቅድስት ሕዝባን አግብቶ ቅስናም ተቀብሏል ይላል።) ያም ሆነ ይህ ቅዱሱ በስደቱ ወቅት ሥጋዊውንና መንፈሳዊውን ጥበብ ተምሮ እንዳጠናቀቀና በኋላም ወንጌልን እየሰበከ፣ በተአምራቱም ሕመምተኞችን እየፈወሰ እግዚአብሔርንም እያገለገለ እንደኖረ ታሪኩ ያወሳል፡፡

በዚህ አይነት ሁኔታ ዓመታት ሲያልፉ እግዚአብሔር አምላክ ንጉሥ አጎቱ ጠንጠውድም መሞቱንና በዙፋኑም እርሱ እንደሚነግሥ ነገረውና በመልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል መሪነት ወደ ሀገሩ ተመልሶ መጥቶ በላስታ ወረዳ ሳይ (ዛሬ ሸጐላ ማርያም) ከምትባል ቦታ ላይ ወንጌልን እያስተማረ፣ ድውያንን እየፈወሰ እንዲቀመጥ አደረገው፡፡ ትምህርቱንና ተአምራቱን ያዩት የአካባቢው ሰዎችም ‹‹ነፃነትና ፍቅር የሚገኝብህ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! እኛ ሰላማዊ ብርሃናዊ ብለን ስም አወጣንልህ፣ ያንተ ግን ስምህ ማን ይባላል ንገረን›› አሉት፡፡ እርሱም ‹‹ስሜ ይምርሃነ ክርስቶስ ነው›› አላቸው ይህኔ ሕዝቡ ሁሉ በሹክሹክታ ‹‹ይምርሃነ ክርስቶስ የሚባል ሲነግሥ ሃይማኖት ይቀናል፣ ፍርድ ይስተካከላል›› እያሉ አባቶቻችን ሲናገሩ ሰምተናል አሉ፡፡

ከጠንጠውድምም ሞት በኋላ ማንም እንዳልነገሠ ሲያረጋግጡ የማን ልጅ እንደሆነ እንዲነግራቸው በእግዚአብሔር ስም ለመኑትና የጠንጠውድም ታናሽና የዣን ስዩም ታላቅ ወንድም የሆነው የግርማ ስዩም ልጅ እንደሆነ ነገራቸው፡፡ እነርሱም ‹‹የተነገረው ትንቢት ደርሷልና ሳንዘገይ እናንግሠው›› ብለው ሥርዓተ መንግሥቱን ፈጽመው በዙፋን ላይ አስቀመጡት፡፡

ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ በትረ መንግሥቱን ከያዘ በኋላ ሁሉም ሰው በተለያዩ እንቅስቃሴዎቹ ውስጥ እንደ ወንጌሉ ቃል እንዲኖር በግዛቱ ሁሉ አወጀ፡፡ እግዚአብሔርም የሚመሰገንበትን ቤት መሥራት አሰበና የተፈቀደለትን ቦታ እንኪያገኝ ድረስ ዛዚያ በምትባል ልዩ በሆነች ስፍራ ድንኳን ተክሎ እንደ ሙሴ አምላኩን ማገልገል ጀመረ፡፡ በዚህም ቦታ ሕዝቡን ከሰማይ በወረደለት መስቀል እየባረከና እርሱ ለቅዳሴ በሚገባበት ጊዜ ከአምላኩ የሚሰጠውን ሰማያዊ ኅብስትና ጽዋ እያቆረበ ለ22 ዓመት በድንኳኗ ውስጥ ኖረ፡፡ ከነዚህ ሁሉ ዓመታት በኋላም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር ተገለጠለትና እንዲህ አለው፡- ‹‹ወዳጄ ይምርሃነ ክርስቶስ ይህን ሥፍራ (ዛዚያን) ልቀቅ፣ ከእንግዲህ ወዲህ በዚህ ቦታ ሰማያዊ ኅብስትና ሰማያዊ ጽዋ አይወርድልህም፡፡ ወደማሳይህ ቦታ ተነሥተህ ሂድ፣ በዚያም እስከ ዕረፍትህ ቀን ድረስ ሰማያዊ ኅብስትና ሰማያዊ ጽዋ ይወርድልሀል፡፡ ይህን ዓለም ለማሳለፍ እስከምመጣበት እስከ ዕለተ ምፅዓት ድረስ የእኔ ጌትነት የአንተም የቅድስና ሕይወት የሚነገርበት፣ የሥጋህ የዕረፍት ቦታ የሚሆንበት፣ ለምትሠራው መቅደስ ክዳን የሚሆን ሣር የማትፈልግበት ሰፊ ዋሻ እሰጥሀለው ፣ በዚያ ቤተ መቅደሴን ሥራ፣ እኔ በምትሠራው ቤተ መቅደስ ከአንተ ጋር ለዘለዓለም ቃልኪዳኔን አቆማለሁ፡፡ በምታንጸው ቤተ መቅደስ ውስጥ ‹አቤቱ የይምርሃነ ክርስቶስ አምላክ ሆይ! ስለወዳጅህ ስለ ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ብለህ ይቅር በለኝ› እያለ ‹አባታችን ሆይ!› የሚለውን ጸሎት የሚጸልይ ዕለቱን እንደተጠመቀ አደርገዋለሁ፡፡ ነገ ማለዳ ተነሥተህ ወግረ ስሂን ወደሚባለው የዕረፍትህ ቦታ ወደሚሆነው ዋሻ ሕዝብህን አስከትለህ ሂድ፤ በዚያም ቤተ መቅደሴን አንጽ›› ብሎ ቃልኪዳን ሰጠው።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በዚያንም ጊዜ የሕፃኑን ራስ በሰይፍ እንዲቆርጡ የቅዱስ ሮማኖስንም ምላሱን ከግንዱ እንዲቆርጡ መኰንኑ አዘዘ። ያን ጊዜ መኰንኑን ይዘልፍ ዘንድ ለአባ ሮማኖስ ረቂቅ አንደበት ተሰጠው ሲዘልፈውም መኰንኑ ሰምቶ ምላሱ እንዳልተቆረጠ ተጠራጠረ። ወታደሩንም ጠርቶ ምላሱን ያልቆረጥክ ለምንድን ነው አለው ወታደሩም የምላሱን ቁራጭ ያመጡ ዘንድ እዘዝ አለው አምጥተውለትም አይቶ መኰንኑም ወደ ወህኒ ቤት አስገብተው በዚያ አንቀው እንዲገድሉት አዘዘ። እንዲህም ምስክርነቱን ፈጽሞ የምስክርነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ጥቅምት 18/2016 #ክቡር_ሠንበት
#አቡነ_ሠላማ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት አባታችን #አቡነ_ሠላማን በምልጃ ፀሎቱ እንዲያስበን ለምንማፀንበት #ክቡር_ሰንበት መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን

👉ወር በገባ በ18 ፃድቁ #አቡነ_ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ናቸው የጻድቁ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁንና ታላቁ ስመ ጥሩ አባታችን ጻድቁ አቡነ ሰላማ በ3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ከአባቱ ከቅዱስ ምናጦስና ከቅድስት እናቱ ማርያም ሰናይት በጢሮስ /ግሪክ/ ተወለደ

👉እድሜው ለትምህርት እንደደረሰ በአካባቢው በነበረው ትምህርት ቤት ውስጥ ሃይማኖታዊ ትምህርቱን በሚገባ ተከታትሎ የተማረ በመልካም ሥነ-ምግባርና አስተዳደግ ተኮትኩቶ ያደገ ደግ አባት ነበር

👉ሜሮጵዮስ የተባለ ነጋዴ ፈላስፋ ወደ ህንድ አገር ሊያልፍ ወዶ ከጢሮስ አገር በጀልባ ጉዞ ጀመረ ከእርሱም ጋር ከዘመዶቹ ወገን የሆኑ ሁለት ብላቴኖች ነበሩ የአንደኛው ስሙ ፍሬምናጦስ የሁለተኛው ደግሞ ኤዴስዮስ ሲድራኮስ ይባላል

👉ሜሮጵዮስ እነዚህን ሁለት ወጣቶች አስከትሎ ወደ አፍሪካ ባህር ጠረፍ በመምጣት በቀይ ባህር ወደብ ውሃ ለመጠጣት እግረ መንገዱንም አገር ለማየት ጀልባውን ጠረፍ ላይ አቆመ

👉በዚህ ጊዜ በአካባቢው ይኖሩ የነበሩ ሰዎች የአዱሊስ ነዋሪዎች በጀልባዋ ላይ አደጋ በመጣል ሜሮጵያስንና የጀልባዋን ቀዛሪዎች እዚያው ገድለው ሀብታቸውን ዘረፏቸው ሁለቱ ወጣቶች ግን ተረፉ በማያውቁትም አገር ያለ ዘመድ ያለ ሃብት ብቻቸውን በመቅረታቸው እያዘኑና እያለቀሱ ከዛፍ ሥር ተቀምጠው ሲጸልዩ የአካባቢው ነዋሪዎች ያዟቸውና በጊዜው በአክሱም ነግሶ ለነበረው ለንጉሥ ታዜር በፈረስ አንገት በጦር አንደበት የተማረኩ ሰዎች አመጣንልህ በማለት አስረከቡት ንጉሥ ታዜርም በቤተመንግስቱ ውስጥ እንዲያድጉ ፈቀደላቸው

👉ከጊዜ ወደ ጊዜ በቤተመንግስቱ ውስጥ ተወዳጅነትንና ታማኝነትን አገኙ የአብርሃ እና አጽብሃ አባት የነበረው ንጉሥ ታዜር ኤዴስዮስን ጋሻ ጃግሬ ፍሬምናጦስን በጅሮንድ አድርጎ ሾማቸው ንጉሱ ሊሞት በተቃረበበት ጊዜ ልጆቹ ገና አካለ መጠን አልደረሱም ነበርና መንግስቱን በሞግዚትነት እንድትይዝ ለእቴጌይቱ አደራ ሲል ሁለቱን ሶርያውያን ምርኮኞች ግን ነጻ ለቀቃቸው ነገር ግን በእቴጌይቱ ልመና ወደ አገራቸው መመለሳቸው ቀርቶ ልጆቿ እስኪያድጉ ድረስ በአስተዳደር በኩል ሲረዷትና ሲመክሯት ቆዩ

👉ፍሬምናጦስ በአክሱም በነበረበት ጊዜ የቤተመንግስቱ አማካሪ ብቻ ሳይሆን ቀደም ሲል የኦሪት እምነት በአንድ እግዚአብሄር ማመን እንደነበረ የሚታወቅ ሆኖ የተዋህዶ እምነት ጥምቀትና ክህነትን በሚገባ የሚመሰረትበትና የሚሰፋበት መንገድ ይፈልግ ነበር

👉ያን ጊዜ የነበሩት የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ሐይማኖት ብቻ እንጂ ክህነት ቁርባንና የመሳሰሉት የክርስትና ስርዓቶች አልነበራቸውም ልዑላኑ አብርሃና አጽብሐ አካለ መጠን ደርሰው የአባታቸውን መንግስት ሲረከቡ ኤዴስዮስ ወደ አገሩ ተመልሶ ካህን ሆነ

👉ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሦስት ጊዜ በላይ ግብፅ እስክንድሪያ ሄዶ ጵጵስና አምጥቶ በኢትዮጵያና በኤርትራ ሃዋርያ ሆኖ እንዲያስተምር እንዲያጠምቅ በእግዚአብሄር መልእክት ተነገረው በዚህ መሰረት ስለአየው ነገር ለነገስታቱ አስረዳቸው ከዚህ በኋላ ጵጵስና እንዲያመጣ መልካም ፍቃዳቸው ስለሆነ ወደ እስክንድርያ ሄደ

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን ከክቡር ሰንበት ከፃድቁ አባታችን #አቡነ_ሠላማ ረድኤት በረከት ያሣትፈን የፃድቁ ምልጃና ፀሎት ቃል ኪዳን ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን" 💒 💚 💛 ❤ 💒

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://www.youtube.com/live/gP-ZCjmi6Eg?si=HFysbqWXcx1PwPf8

Читать полностью…
Subscribe to a channel