ጥቅምት 29/2016 #ቅዱስ_በዐለ_ወልድ
#የጌታችን_ፅንሰት_እና_ትንሣኤ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን በዚህ ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የከበረ መልአክ የቅዱስ ገብርኤልን የምሥራች የሠማችበት አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ የተወለደበት ክቡር እና ድንቅ የሆነዉን ትንሣኤዉን የገለጠበት ወርሐዊ የግዝት በአል ነው
👉እንዲሁም በዚህች ቀን አለም የተፈጠረበት የጌታችንን ዳግመኛ ምፅአቱን የምንጠባበቅበት የከበረ ቀን ነዉ
👉 በዚህች ቀን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የከበረ መልአክ ገብርኤል የምሥራች የነገረበት ድኅነትን የተመላች ታላቅ በዓል ናት በዚህም የከበረ ወንጌል ምስክር ሁኗል እንዲህ ሲል ኤልሳቤጥ ከፀነሰች በኋላ በስድተኛው ወር #መልአኩ_ገብርኤል የገሊላ ክፍል የሆነች ናዝሬት ወደምትባል አገር ከዳዊት ወገን ለሆነ ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ
👉የድንግሊቱም ስም #ማርያም ነው መልአኩም ወደርሷ ገብቶ ደስተኛ የሆንሽ ደስ ይበልሽ ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው አንቺ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ አላት እርስዋም አይታ ከንግግሩ የተነሣ ደንግጣ እንዴት እንዲህ ያለ ሰላምታ ይቀበሏል ብላ አሰበች
👉መልአኩም እንዲህ አላት #ማርያም ሆይ #በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻልና አትፍሪ እነሆ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ስሙንም #ኢየሱስ ትዪዋለሽ እርሱ ታላቅ ነው የልዑል #እግዚአብሔር ልጅም ይባላል
👉እግዚአብሔር አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል ለያዕቆብ ወገንም ለዘላለም ነግሦ ይኖራል ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም
👉ማርያምም መልአኩን ወንድ ሳላውቅ ይህ እንደምን ይሆናል አለችው መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት #መንፈስ_ቅዱስ መጥቶ ያድርብሻል የልዑል ኃይልም ያጸናሻል ከአንቺ የሚወለደው ከሶስቱ አካል አንዱ የልዑል #እግዚአብሔር ልጅ ይባላል
👉እነሆ ዘመድሽ ኤልሳቤጥም እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ፀንሳለች ወንድልጅም አገኘች ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና #ማርያምም እነሆኝ #የእግዚአብሔር አገልጋይ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለችው።
👉ያን ጊዜም ድንግል ስትሆን ረቂቅ ፅንስን ተቀበለች የእግዚአብሔር አካላዊ ቃል #ወልድ_ዋህድ ለኩነተ ሥጋ ወርዶአልና ይህም አንድ ባሕርይ አንድ ህልውና ሲሆን ከሦስቱ አካላት አንዱ ነው ከዓለም መፈጠር አስቀድሞ የነበረ በማይመረመር ድንቅ በሆነ ተዋሕዶ እንዴትም እንደሆነ በማይታወቅ #በቅድስት_ድንግል_ማርያም ማሕፀን አደረ ፅንስ ሆኖ ኖረ
👉በዚያን ጊዜም የኋላ ኋላ መለየት ከቶ የሌለውን ፍጹም ሰውነት ነሥቶ ተዋሐደ መለኮቱ ከትስብእቱ ጋራ ያለ መለያየት አንድ ሆኖአልና ይቺም ዕለት የበዓላት ሁሉ #በኵር ናት በእርሷም #የዓለም_ድኅነት ተጀምሮዋልና
👉ዳግመኛ በዚህችም ዕለት ደግሞ በመድኃኒታችን በከበረችና ልዩ በሆነች #ትንሣኤው የዓለም ድኅነት ሆነ በረቀቀ ጥበቡ ሠላሳ ሦስት ዓመት ያህል በምድር ላይ ሥራውን ሠርቶ በፈጸመ ጊዜ በፈቃዱ ሕማማተ መስቀልን ተቀብሎ ሙቶ ከተቀበረ በኋላ በሦስተኛው በዚች ቀን በሃያ ዘጠኝ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቷልና።
👉በዚች ቀን አስቀድሞ ደጅ ለሚጠኑት በዓለም ላሉ ሰዎች ሰው በመሆኑ ድኅነታቸውን አበሠራቸው እንዲሁም ደግሞ በዚች ዕለት ከሲኦል በመዳን ሙታንና ሕያዋን ደስ አላቸው
👉በዚህም በጌታችንና በመድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በሥጋ መነሣት መነሣታቸውን አረጋገጡ የከበረ ጳውሎስ በመነሣቱ ክርስቶስ የሙታን በኵር ሆነ እንዳለ እርሱ ለሙታን በኵራቸዉ ነዉና
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከበአሉ በረከት ሁላችንንም ያሣትፈን በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸዉ የምናስባቸዉ ፃድቁ #አቡነ_እጨጌ_ዮሐንስ በምልጃ ፀሎታቸዉ ይጠብቁን "አሜን" 💒 💚 💛 ❤ 💒
ጥቅምት 28/2016 #ቅዱስ_አማኑኤል
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ለአምላካችን #ቅዱስ_አማኑኤል ለስደቱ መታሠቢያ አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ማለት ነው
👉 #የአብርሐም_የይስሐቅ_የያእቆብ አምላክ ቅዱስ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን በቸርነቱ ይጠብቀን
👉አማኑኤል ማለት አማኑኤል፣ የአምላክ ሰላም፣ የእግዚአብሔር እርቅ፣ የጌታ አንድነት ማለት ነው
👉አማኑኤል ማለት "አማኑ" እና "ኤል" ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከኛ ጋር ማለት ነዉ
👉"ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ ወይሰመይ ስሙ አማኑኤል ዘበትርጓሜሁ እግዚአብሔር ምስሌነ"
👉ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅንም ትወልዳለች ሰሙንም አማኑኤል ትለዋለች ትርጉሙም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው ( ኢሳ 7፥14)
👉ክብር ፣ኃይልና ምስጋና ለአምላካችን ለአማኑኤል ይሁን ለዘለዓሙ "አሜን"
👉እረኛችን #ቅዱስ_አማኑኤል ጥቂት ስምህን ማወቅ ብዙ ደስታን ታጎናጽፋለች በተሳዳቢ ዓለም ዝምታን አስተማርከን እየተገፉ መደሰትን እያጡ ማመስገንን ነገን እያሳይህ ዛሬ ማኖርን ባንተ ማረፍን በስምህ አስተማርከን
👉ቅዱስ አማኑኤል አባታችን እረኛችን የምታሳጣን የለም ያጣነዉም የለም እረኛችን ሆይ ካላንተ አባትም እረኛም ጠባቂም የለንም አሁንም ስለ ስምህ ጠብቀን "አሜን"
👉ቅዱስ #አማኑኤል አምላካችን ሀገራችንን ህዝባችንን ከክፉ መከራ ይጠብቅልን የስደት ቀን ስንቃችን እናታችን #ማርያም ምልጃ ፀሎትሽ ረድኤት በረከትሽ ለሁላችንም ይድረሰን "አሜን" 💒 💚 💛 ❤ 💒
አቡነ ዜና ማርቆስም አስተምረው ክርስትና ሲያነሷቸው
(ሲያጠምቁዋቸው) "ጽጌ ድንግል" አሏቸው::ሲመነኩሱም "ጽጌ ብርሃን" ተብለዋል:: ቀጥለውም
በጾምና በጸሎት ሲጋደሉ: እመቤታችንንም ሲለምኑ
ምሥጢር ተገለጠላቸው::+የእመ ብርሃንን ስዕለ አድኅኖ በአበባ ተከባ: በብርሃንም
ተውጣ ተመለከቱ:: በዚህ ምክንያትም ዛሬ በጣፋጭነቱ
የሚታወቀውን ማኅሌተ ጽጌን 150 ዓርኬ አድርገው
ደረሱ:: እስከ ዕለተ ዕረፍታቸውም እመቤታችንና ልጇን
በገዳማቸው (ወለቃ አካባቢ የሚገኝ) ሲያመሰግኑ
ኑረዋል:: በዚህች ቀንም ዐርፈዋል::
=>አምላከ ቅዱሳን በአማኑኤል ስሙ: በማርያም እሙ:
በፈሰሰ ደሙ: በተወጋ ጐኑ: በንጹሐን ቅዱሳኑ ይማረን::
ከመስቀሉና ከቅዱሳኑ በረከትም አይለየን::
=>ጥቅምት 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን
በዓላት=
1.ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
2.ቅዱስ መቃርስ ብጹዓዊ
3.አቡነ መብዓ ጽዮን ጻድቅ
4.አባ ጽጌ ድንግል ዘወለቃ
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ)
2.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
3.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
4.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት
5.ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
=>+"+ በእውነት ደዌአችንን ተቀበለ:: ሕማማችንንም
ተሸክሟል:: እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ
ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቆጠርነው:: እርሱ ግን ስለ
መተላለፋችን ቈሰለ:: ስለ በደላችንም ደቀቀ::
የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ:: በእርሱም
ቁስል እኛ ተፈወስን:: +"+ (ኢሳ. 53:4)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
✝️የሁላችንም አምላክ የሁላችንም ዳኛ የሁላችንም ፈራጅ ❤️❤️❤️❤️❤️
የሰማዩ ንጉስ የድንግል ልጅ መድኃኒአለም ነው 😥
ቸሩ መድኃኒአለም የእናቶቻችን እንባ የንጹሀንን ደም በከንቱ የሚፈሰውን አይተህ ዛሬም ታረቀን
ምህረትህን ላክልን 🤲
ሀገረ እግዚአብሔር የሆነችውን ኢትዮጵያን ጠብቅልን
አምላክ ሆይ ህዝብህን ታደግ ከጥፋት አውድማ አውጣን
አንተ የሠላም የፍቅር አምላክ ዛሬም ሠላሙን ላክልን ።
አምላካችን ሆይ የግፍ ጽዋ ሞልቶ ፈሷል እና ቶሎ ድረስልን
ሠላሙን ሁሉ ለ ኢትዮጵያ ያውርድልን
የንፁሀን ደም ጌታችን ፊት ይጮሀል ️ ጊዜ ለኩሉ እግዚአብሔር መልስ አለው ። ከታገሱት ሁሉም ያልፋል
ዛሬም ነገም ዘወትርም ለዘላለምም ቅድስት ቤተክርስቲያን
በክር ትኑርልን ኢትዮጵያ ትቅደም❤️❤️❤️🙏🙏🙏🙏 #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶለዘላለም_ፀንታትኑር #ኦርቶዶክስ_ለዘላለም_ትኑር🙏🙏🙏😍💚💛❤🌍💒💒💒💒💒💒💒🙏😭😪😭💚💛❤🌍💒💒💒💒🙅🙏 #ኦርቶዶክስ_የሆንኩት_መርጬ_ሳይሆን_ተመርጬ_ነው #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ለዘለዓለም_ፀንታ_ትኑር #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ
#ጥቅምት_26
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ሃያ ስድስት በዚህች ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ጢሞና በሰማዕትነት አረፈ፣ የጌታ ወንድም የተባለው #ቅዱስ_ያዕቆብ_ወልደ_ዮሴፍ መታሰቢያው ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ሐዋርያ_ጢሞና
ጥቅምት ሃያ ስድስት በዚህች ቀን ጌታችን ከመረጣቸውና በሽተኞችን ሁሉ ይፈውሱ ዘንድ አጋንንትንም ያወጡ ዘንድ ሥልጣንን ከሰጣቸው ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ቅዱስ ሐዋርያ ጢሞና በሰማዕትነት አረፈ።
ይህም ቅዱስ ጢሞና ሰማያዊ ሀብትን መለኮታዊ ኃይልን ገንዘብ አድርጎ በሽተኞችን ፈወሳቸው አጋንንትም ተገዙለት ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ በምድር ሳለ አገለገለው። ወደ ሰማይም ከዐረገ በኋላ ሐዋርያትን አገለገላቸው በሃምሳኛው ቀንም ጰራቅሊጦስ በወረደ ጊዜ የአጽናኝ መንፈስ ቅዱስን ጸጋ ከእርሳቸው ጋር ተቀበለ።
ከዚህም በኋላ ሰባት ሁነው ከተቆጠሩት ዲያቆናት ጋር ሐዋርያት ሾሙት እነርሱ መንፈስ ቅዱስን ዕውቀትንም የተመሉ እንደሆኑ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ምስክር ሁኖአል።
በዲቁና አገልግሎትም ጥቂት ከአገለገለ በኋላ ብልቃ ከሚባል አገር በስተምዕራብ በሆነ ስብራ በሚባል አገር ላይ ኤጲስ ቆጶስነት ሾሙት በውስጧም ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሃይማኖት አስተማረ ከዮናውያንና ከአይሁድም ብዙዎችን አጠመቃቸው።
የዚያች አገር ገዥም ይህን በሰማ ጊዜ ቅዱስ ጢሞናን ይዞ ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃይቶ በእሳት አቃጠለው በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ያዕቆብ_ወልደ_ዮሴፍ
ዳግመኛም በዚህች ዕለት ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ ዮሴፍ መታሰቢያ ነው፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ የጌታችን ወንድም የተባለውና የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ የነበረው ነው፡፡
እርሱም የጠራቢው የዮሴፍ ልጅ ሲሆን ከልጆቹ ሁሉ ትንሹ ነው፡፡ ድንግልና ንጹሕ ሆኖ ከጌታችን ጋር እየተጫወተ አብሮ አድጓል፡፡ የያዕቆብ ወላጅ እናቱ በልጅነቱ ስለሞተችበትና የብርሃን እናቱ የሆነች ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያምን ዮሴፍ አረጋዊ በ83 ዓመቱ ጠባቂ ይሆናት ዘንድ ወደቤቱ ሲወስዳት ድንግል ማርያም ያዕቆብን የሙት ልጅ ሆኖ አግኝታው ከወለደችው ከመድኃኔዓለም ክርስቶስ ጋር አብራ ተንከባክባ አሳድጋዋለች፡፡
ያዕቆብ ከጌታችን ጋር አብሮ እየተጫወተ እያለ አንድ ቀን ትግል ይገጥማሉ፡፡ ያዕቆብም ጌታችንን አንስቶ ጣለው፡፡ ድጋሚ ተያያዙና አሁንም ያዕቆብ ጌታችንን ጣለው፡፡ ሦስተኛ ጊዜም እንዲሁ ሆነና ያዕቆብ የልብ ልብ ተሰማው፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ ድጋሚ ትግል ሲያያዙ ግን ጌታችን ያዕቆብን ወደ ሰማይ ወርውሮ መሬት ላይ በኃይል ጣለው፡፡ ያዕቆብም እጅግ ደንግጦ "ኃይልህን ደብቀህ ቆይተህ አሁን ምነው እንዲህ ታደርገኛለህ?" ሲለው ጌታችንም "እኔኮ ካልጣሉኝ አልጥልም" አለው፡፡
ከጌታችን ዕርገት በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያት በኢየሩሳሌም ኤጲስ ቆጶስ አድርገው ሾመውታል፡፡ ብዙዎችንም አስተምሮ ወደ ቀናች ሃይማኖት መልሷቸዋል፡፡ ሕዝቡም የታመሙትን ድውያንን ሁሉ እያመጡለት ይፈውሳቸው ነበር፡፡ ከኢየሩሳሌምም ውጭ እየሄደ ያላመኑትንም አስተምሮ እያጠመቀ ቤተ ክርስቲያን ይሠራላቸው ነበር፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ በጾም በጸሎት ሆኖ በመቆም ብዛት እግሮቹ አብጠው ነበር፡፡
አንድ ቀን አይሁድ ተሰብስበው መጥተው ጌታችን የማን ልጅ እንደሆነ ይነግራቸው ዘንድ ወደ ያዕቆብ መጡ፡፡ እነርሱም ወደ ያዕቆብ የመጡት ጌታችን የዮሴፍ ልጅ እንደሆነና የእርሱም የሥጋ ወንድም እንደሆነ እንደሚነግራቸው አስበው ነበር፡፡ ነገር ግን ቅዱስ ያዕቆብ ከፍ ካለው ከሦስተኛው መደብ ላይ ወጥቶ ጌታችን የራሱ የያዕቆብና የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ መሆኑን መሰከረባቸው፡፡ ዳግመኛም ጌታችን ፍጹም አምላክ መሆኑን፣ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነና ከአብም ጋር ትክክል እንደሆነ መሰከረባቸው፡፡ ይህንንም በሰሙ ጊዜ አይሁድ እጅግ ተናደው በጽኑ ግርፋት ካሠቃዩት በኋላ ራሱን ቀጥቅጠው ገደሉት ሰማዕትነቱን ሐምሌ 18 ቀን በድል ፈጽሟል፡፡
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት)
ቅዱስ አቢብም በአረፈበት ቀን መታሰቢያውን ሲያደርጉ ይህ ቅዱስ አባ አብሎይ ወንድሞች ሆይ በአባ አቢብ ስም ዛሬ ጸሎትን የሚጸልየውን ኃጢአቱን እግዚአብሔር ያስተሰርይለታል በዕረፍትህ መታሰቢያ ቀን የአባ አቢብ ፈጣሪ ሆይ ኃጢአቴን ሁሉ ተውልኝ ብሎ አንዲት ጸሎትን የሚጸልየውን ሁሉ እኔ ኃጡአቱን እተውለታለሁ ሲል ቃል ኪዳን ሰጥቶታልና አላቸው።
በዚያችም ሰዓት ከመነኰሳት አንዱ አረፈ እነርሱም ሊገንዙት በዚያ ቁመው ሳሉ አባ እብሎይ ስለ ተናገረው ቃል ከመነኰሳት አንዱ ተጠራጠረ በዚያንም ጊዜ ያ የሞተው ተነሥቶ ይናገር ዘንድ ጀመረ አባ እብሎይ ስለተናገረው ቃል ለምን ትጠራጠራላችሁ ለአባታችን አቢብ በመታሰቢያው ቀን በዚህ ቃል ኪዳን እግዚአብሔር ሰጥቶናልና አላቸው ። ይህንንም ብሎ ተመልሶ አረፈ መነኰሳቱም አደነቁ ምስጉን እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።
ይህ አባ እብሎይም ብዙ ዘመናት ኖረ ልጆቹ መነኰሳትም በዙ ብዙ ገዳማትም ተሠሩለት። የኖረበትም ዘመኑ በታላቁ አባ መቃርስ ዘመን ነው የአባ እብሎይንም የትሩፋቱን ዜና አባ መቃርስ በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ ተሰኘበት እርሱን እያጽናና እያረጋጋ መነኰሳት ልጆቹንም እግዚአብሔር የሚወደውን በመሥራት ያጸናቸው ዘንድ መልእክትን ጻፈለት።
ይህንንም በአስቄጥስ ገዳም ሁኖ አባ መቃርስ ሲጽፍ አባ እብሎይ በላዕላይ ግብጽ ሳለ በመንፈስ ቅዱስ አውቆ በዙሪያው ያሉትን መነኰሳት እንዲህ አላቸው። እነሆ ማጽናናትን የተመላች መልእክትን አባ መቃርስ ጻፈልን። ከዚህም በኋላ ከአባ መቃርስ ዘንድ የተላኩትን መነኰሳት ሁሉ ወጥተው በደስታ ተቀብለው አስገቧቸው መልእክቱንም በመነኮሳቱ ሁሉ ፊት አነበቡ በታላቅ ደስታም ደስ አላቸው።
ይህም አባ እብሎይ ወደ አባ አሞንዮስ የሔደ ከእርሱ ዘንድም የምትኖረውን ስሟ የዋሂት የተባለችውን የተቀደሰች ሴት ያየ ነው። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከዚህ ዓለም ድካም ሊአሳርፈው ወዶ በየካቲት ወር በአምስተኛው ቀን አረፈ እኛ ግን የአባ እብሎይን ዜና ከወዳጁ ከአባ አቢብ ጋር ጻፍን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ዮልዮስ_ሰማዕት
በዚህችም ቀን ዳግመኛ አቅፋሐስ ከሚባል አገር ሰማዕት ለሆነ ለቅዱስ ዮልዮስ ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት ነው።
ይህም ቅዱስ ዮልዮስ በሀገረ ጥዋ በሰማዕትነት በአረፈ ጊዜ በገድሉ እንደተጻፈ ዲዮቅልጥያኖስ ከጠፋ በኋላ ጻድቅ ሰው ቈስጠንጢኖስ ሳይጠመቅ ነገሠላቸው በጥቂት ወራትም የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቀ የቤተ ክርስቲያንም ሥልጣን ከፍ ከፍ አለ ከሀድያን ነገሥታት ለገደሏቸው ንጹሐን ሰማዕታት በስማቸው አብያተ ክርስቲያናት ታነፁ።
ስለ ቅዱሳን ሰማዕታትም ስለ ሥጋቸው እንዲአስብ ገንዞ በመሸከም ወደ አገራቸው እንዲአደርሳቸው ከአገልጋዮቹም ጋር ገድላቸውን እንዲጽፍ እግዚአብሔር እንደአቆመውና እንደጠበቀው ከዚህም እርሱ ራሱ በሰማዕትነት እንዴት እንደ ሞተ የቅዱስ ዮልዮስን ዜና ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በሰማ ጊዜ ስለበጎ ተጋድሎው ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ቅዱስ ዮልዮስን አመሰገነው ።
ስለዚህም ለቅዱስ ዮልዮስ ያማረች ቤተ ክርስቲያን በግብጽ አገር ሠርተው ሥጋውን በውስጧ ያኖሩ ዘንድ ንጉሡ ወደ ግብጽ አገር ብዙ ገንዘብ ላከ በዚያንም ጊዜ ንጉሡ እንዳዘዘ አነፁለት ። የቅዱስ ዮልዮስንም ሥጋ አፍልሰው በውስጧ አኖሩት ሊቀ ጳጳሳት አባ እለእስክንድሮስም ከኤጲስቆጶሳቱ ጋር አከበራት እንደዛሬዪቱም ቀን በዓል አከበረባት ከሥጋውም ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ሕጻን_ሞዐ_ዘደብረ_ሊባኖስ
በዚህችም ቀን የደብረ ሊባኖሱ አባ ሕፃን ሞዐ ቃልኪዳን የተቀበሉበት ነው። በአባታቸው አርከሌድስ እናታቸው ትቤ ጽዮን ይባላሉ፡፡ የተወለዱት ጥር 25 ነው፡፡ አቡነ ሕፃን ሞዐ እና ከእነ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጋር የሥጋ ዝምድና አላቸው፡፡ ይኸውም አባታቸው አርከሌድስና ጸጋ ዘአብ ወንድማማቾቸ ናቸው፡፡ አርከሌድስና ጸጋ ዘአብ ሌሎች ሌሎች አራት ወንድሞች አሏቸው፡፡
እነርሱም እንድርያስ፣ ዘርዐ አብርሃም፣ ቀሲስ ዮናስ እና ቀሲስ ዮሐንስ ናቸው፡፡ አርከሌድስ ሕፃን ሞዐን ይወልዳል፣ ጸጋ ዘአብ ተክለ ሃይማኖትን ይወልዳል፣ እንድርያስ ሳሙኤል ዘወገግን፣ ዘርዐ አብርሃም ታላቁ አኖሬዎዮስን፣ ቀሲስ ዮናስ ገላውዲዮስንና የፈጠጋሩን ማትያስን፣ እና ቀሲስ ዮሐንስ ዜናማርቆስን ይወልዳሉ፡፡ እነዚህ የከበሩ ቅዱሳን አባቶቻችን በእናታቸውም ወገን ቢሆን እንዲሁ በዝምድና የተቆራኙ ናቸው፡፡ አቡነ ሕፃን ሞዐ በሌላኛው ስማቸው ሕፃን ዘደብረ በግዕ ተብለውም ይጠራሉ፡፡ ይኸውም የደብረ በግዕን ገዳም የመሠረቱት እርሳቸው ስለሆኑ ነው፡፡
ከ47ቱ የሀገራችን ቀደምት ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ በመንዝና በተጉለት የሚገኙ ታላላቅ ገዳማትን አብዛኞቹን የመሠረቷቸው አቡነ ሕፃን ሞዐ ናቸው፡፡ ጻድቁ በክፉዎች ወሬና ሴራ ምክንያት ከበሬ ጋር ተጠምደው ሰማዕትነት የተቀበሉ አባት ናቸው፡፡ ከበሬ ጋር ሲታረሱ ውለው በእጅጉ ከደከማቸው በኋላ በኃይል የተነፈሱባት ምድሪቱ ዛሬም ድረስ ልክ እንደሰው የሚሞቅ ትንፋሽ ታወጣለች፡፡ ያም በጻድቁ እስትንፋስ አምሳል ከመሬት ውስጥ የሚወጣው እስትንፋስ ለአስም በሽታ መድኃኒት ሆኖ ብዙዎችን እየፈወ ነው፡፡
ገዳማቸው ከደብረ ብርሃን ከተማ በእግር የ2 ሰዓት መንገድ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ይኸውም ከወንይዬ ተክለ ሃይማኖት ገዳም አጠገብ ነው፡፡ ጻድቁ ጥር 25 ቀን ልደታቸው፣ ጥቅምት 25 ቃል ኪዳን የተቀበሉበት ዕለት ሲሆን ሐምሌ 25 ደግሞ ዕረፍታቸው ነው፡፡
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት እና #ከገደላት_አንደበት)
ጥቅምት 25/2016 #ቅዱስ_መርቆሬዎስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በሰማእቱ ስም ለምናመሰግንበት ሰማእቱ #ቅዱስ_መርቆሬዎስን በምልጃ ፀሎቱ ለምንማፀንበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉ሰማዕታት የዚችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ ደማቸውንም ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ ስለ መንግስተ ሰማያት መራራ ሞትን ታገሱ እንደ ይቅርታው ብዛት ይቅር ይበለን አሜን (ውዳሴ ማርያም ዘሐሙስ ቁጥር ፯)
👉ቅዱስ መርቆሬዎስ አገሩ ሮም አስሌጥስ ነው አባት እናቱ አረማውያን ነበሩ ቅዱስ መርቆሬዎስ ከተወለደ በኋላ መልአኩ የተናገረው ቃል ሁሉ እንደተፈጸመ ሲያውቅ አባቱ ከነ ቤተሰቡ አምነው ተጠምቀዋል የመርቆሬዎስ ስመ ጥምቀቱ “ፕሉፖዴር” ነው፤ ገብረ እግዚአብሔር ማለት ነው በጥበብ በፈሪሀ እግዚአብሔር አድጎ አባቱ ሲሞት የአባቱን ሹመት ወረሰ
👉ንጉሱ ዳኬዎስ ይባላል መምለኬ ጣዖት ነበር በርበሮች በጠላትነት ተነስተውበት እንደምን ላድርግ ብሎ የምክር ቃል ሲልክበት መልአኩ በአምሳለ ወሬዛ ቀይህ በሊህ ሰይፍ ይዞ በዚህ ጠላቶችህን ድል ትነሳለህ ደስ ብሎህ በተመለስክ ጊዜ ግን ጌታህ እግዚአብሔርን አስበው ሲለው ታይቶት ነበርና
👉አትፍራ ጌታ ጠላቶቻችንን አሳልፎ ይሰጠናል ብሎት አጽናንቶት ዘመቱ መርቆሬዎስም ኃይል ተሰጥቶት ጠላቱን ድል ነስቶ ሲመለስ ከሃዲው ንጉስ ኡልያኖስ ወዲያው ኃይል ለሰጡን ለረዱን ለዓማልክቶቼ በዓል አድርጌአለሁና ፈጥነህ ና ብሎ ላከበት ሄዶ ሹመት ሽልማትህ ላንተ ይሁን
👉ላቆመው ጣኦት አልሰግድም በማለቱ የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይችለውን መከራ ተቀበለ በመጨረሻም ህዳር ፳፭ ቀን አንገቱን ቆርጠው ገደሉት ደም ውኃና ወተት ከአንገቱ ፈሰሰ መርቆሬዎስ ከዕረፍቱም በኋላ ብዙ ተአምራትን አድርጓል፤ ፈረሱ ለሰባት ዓመት ወንጌልን አስተምሯል በኋላም አንገቱን ቆርጠው ገድለውታል እንዴት ብሎ የሚገረም የበልአምን አህያ ይጠይቃት ዘኁልቁ 22፡28 ለእግዚአብሔር የሚሣነዉ ነገረ ስለሌለ
👉የቅዱስ መርቆሬዎስ ስዕልም በአዎንታ አንገቱን ዘንበል አድርጎ ምስክርነት ሰጥቷል ይህም ሊታወቅ ዛሬ በሀገራችን በምድረ ተጉለት በስሙ ከታነፀ ቤተ ክርስቲያን ካህናት ደነነ ስዕሉ እያሉ ሲዘምሩ ጎንበስ ቀና ሲሉ እንደሚታይ ይነገራል የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስ ረድኤቱ በረከቱ አማላጅነቱ ቃል ኪዳኑ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን እኔን የሚወድ ቢኖር እራሱን ይካድ መስቀሌንም ተሸክሞ ዕለት ዕለት ይከተለኝ ማቴ.፲፡፴፰-፵
👉እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና ዕብ ፲፪፡፩-፪
👉የሰማእቱ #ቅዱስ_መርቆሬዎስ ምልጃና ፀሎቱ ሀገራችንን ህዝባችንን ይጠብቅልን በዚህ እለት የሚታወሱ ቅዱሳን ቃል ኪዳናቸዉ ሁላችንንም ይጠብቀን የተባረከ የተቀደሰ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን"💒 💚 💛 ❤ 💒
ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ወንድሞቼ እና እኅቶቼ ዲያቆን ስንታየሁ በቀለ እባላለሁ ይህንን የዩቲዩብ ቻናል subscribe በማድረግ አበርቱኝ በቅንነትና በፍቅር subscribe አድርጉልኝ። ።ግእዝንም ከፊደል ጀምሮ እስከ ቅኔ ድረስ በዚህ ቻናል በቀላሉ ይማሩ።መንፈሳዊ ግዴታችንን እንወጣ።አንድ እንሁን ቤተክርስቲያናችንን ከፍ እናድርግ።ሰላመ እግዚአብሔር የሀሉ ምስሌነ።
አመሰግናለሁ።
ሊንኩን በመጠቀም ሰብስክራብ ያድርጉ
keradyon-8584" rel="nofollow">https://www.youtube.com/@keradyon-8584
✝እነርሱም ተካፍለው ተሸክመው መንገዳቸውን እየሔዱ ሳለ ከአገር ብዙ በራቱ ጊዜ ወንድሙን ‹ና አህያውን እንጫነውና እንደፈቀድነው እንሒድ የሚያየን የለምና›› አለው። በዚህም ምክራቸው መሠረት ተሸክመውት የነበረውን በኒው በአህያው ላይ ጫኑት፣ ነገረ ግን ወዲያው አህያው መንቀሳቀስን ፈጽሞ እምቢ አለ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላለም፤ እየገፉትና እየደበደቡት ብዙ ደከሙ፤ እንዲህ እያደረጉ ሳሉ አንድ አገልጋይ የንጉሥ መልእክት ይዞ መጣና እነዚህን ሰዎች አገኛቸውና ‹‹ጌቶቼ ለምን ትደክማላችሁ?›› አላቸው። እነርሱም ‹‹ይህ አሀ አልሔድም አለን›› አሉት። የንጉሡ መልእክተኛም መንፈስ ቅዱስ አነሣሣውና ከፊታቸው ቆመና የዚህ ነገር ምክንያቱ ምንድን ነው?› አላቸው። እነርሱም “ይህን አህያ ከአንድ መንፈስ ቅዱስ ካደረበት ቀሲስ አመጣነው፤ በዚህ ቀሲስ ቃል ላይ በጨመርን ጊዜ መሔድን እምቢ አለን›› በማለት የሠሩትን ነገሩት፤ እርሱም ‹‹እስኪ የጨመራችሁትን ቀንሱለት›› አላቸው፤ እነርሱም ሲቀንሱለት ወዲያው አህያው ተነሣና ወደሚፈልጉበት ቦታ ሔዱ። ይህንንም ሁለት ጊዜ ሦስት ጊዜ ደጋግመው አደረጉ እምቢም አላቸው። ይህ ሁሉ የሆነው የቅዱሱን ቃል በመተላለፋቸው እንደሆነ ዐወቁ፤ ያም የንጉሡ አገልጋይ ተደንቆ ኑ ይህ
✝ቅዱስ ካለበት አድርሱኝ› አላቸው። አባታችን ካለበት ቦታም ደርሶ ከእርሱ ዘንድ ተባረከ።
ያም አህያውን ተውሶ የወሰደው ሰው ከአቡነ ብርሃነ መስቀል ከአባ ዘግሩም) እግር ሥር ወድቆ እኔ ግን እንደ እኔ አይነት ሰው ነህ መስለኸኝ ቃልህን አፈረስሁ፤ አንተ ግን በፍቅርህ ገመድ ሳብኸኝ በፊትህ በድያለሁና ቃልህንም አሳብያለሁና አባቴ ሆይ! ይቅር በለኝ፣ አህያውም መሔድን እምቢ አለ፤ የጨመርንበትን ሽክም በቀነስንለት ጊዜ ግን ይሔዳል›› አለው። አባታችንም ለምን ሐሰት ተናገርህ? መጽሐፍ ሐሰት የኀጢአት መጀመሪያ ናት፣ ሐሰተኞችም የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም ይል የለምን?› በማለት ከመከረው በኋላ በሰላም ወደቤቱ እንዲሔድ ነገረው።
✝ሰውየውም ከአባታችን ዘንድ ወጥቶ መንገዱን ሔደ፤ የንጉሡ መልእክተኛም አብርሃም ከተባለ ከአቡነ ዘግሩም ዘንድ ተባርኮ ወጣ፣ የቤተ ክርስቲያኗንም አሠራር አይቶ የአባታችንን ተኣምር አደነቀ፣ የንጉሡን ትእዛዝ ይፈጽም ዘንድ መንገዱን ሔደ። ከብዙ ቀናት በኋላ ያ መልእክተኛ ከንጉሡ ዘንድ ደረሰ ስመ መንግሥቱ ቆስጠንጢኖስ ለተባለ የእግዚአብሔር ወዳጅ ለሆነ ለንጉሥ ዳዊት ነገሩን ነገረው። “ጻድቅ ንጹሕ የሆነ ቀሲስ አለ፣ በዚህ ዘመን በመንግሥትህ ሀገር ሁሉ እንደርሱ ያለ ሰው የለም፤ ሥራው ሁሉ እንደቀደሙት አባቶች ነውና›› አለው።
✝በዐይኑ ያየውን፤ በጆሮው የሰማውን ሁሉ ስለሠራት ቤተ ክርስቲያንም ነገረው፤ ንጉሡም ይህን ሁሉ በሰማ ጊዜ በልቡ ተደሰተ፤ በመንፈሱም ሐሴትን አደረገ፤ እግዚአብሔርንም እንዲህም እያለ አመሰገነው፡-
✝ “በዘመነ መንግሥቴ የተሰወረውን የሚያውቅ፤ ተአምራትን የሚያደርግ እንዲህ ያለ ጻድቅ ሰውን የሰጠኝ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ስሙ ይክበር።” ንጉሡም አባታችንን አባቴ ሆይ! ቤተ ክርስቲያን ማነጽ በፈለግህ ጊዜ ወደ እኔ ለምን አልላክህም›› ብሎ ላከበት፤ ዳግመኛም ‹‹…እኔ ከደቀ መዛሙርትህ እንደ አንዱ አይደለሁምን? በረከትህን በተቀበልሁ ነበር፣፣ በዚህ የመንግሥት ዙፋን ላይ ያለሁት በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው እንጂ በራሴ ፈቃድ ይመስልሃልን በእስረኞች መካከል ሳለሁ ከእስረኞች መካከልም ተኝቼ ሳለ ከዚያ አውጥቶ በአባቶቼ በሰይፈ አርዕድና በዐምደ ጽዮን ዙፋን ላይ አስቀመጠኝ። አንተ ግን በኀጢአቴ አትናቀኝ፤ ለቤተ ክርስቲያን የምትፈልገውን ይህን ገንዘብ ውሰድ›› በማለት ለአባታችን ልብስ ላከለት፤ ሚስቱም እንዲሁ ላከች። በጸሎቱ እንዳይረሳቸውም ተማጸኑት።
✝ከዚኽም በኋላ ይመነኵስ ዘንድ ወደደ፤ የመላእክትና የቅዱሳን ልብስ የምትሆን የምንኩስና ልብስን ያለብሰው ዘንድ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድእ ሆነው ወደ አባ ብሶይ ዘንድ ሔደ። ወደ እርሱ ደርሶ ሥርዐተ ምንኩስና ከፈጸመለት በኋላ አባታችን አብርሃም የቀድሞ ስሜን ተውልኝ›› አለው አባ ብሶይም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የደቀ መዛሙርቱን ስም እንደ ለወጠላቸው ስምህን እለውጣለሁ እንጂ አይሆንም አለው። ስምህንም አብርሃም፣ ጳውሎስ ዮሐንስ ከሚሉት መካከል ዕጣ በማጣጣል እሰይምሃለሁ› አለው። ሦስት ጊዜም ዕጣ ጣሉ፤ አብርሃም የሚለውም ስም ወጣ፤ ይህ ነገር ከእግዚአብሔር እንደሆና ዐወቀ። ከታናሽነቱ ጀምሮ የአብርሃም ምግባር የሆነውን እንግዳ መቀበልን እግር ማጠብንና የተራበውን ማብላት ጀመረ፤ ስለዚህ አብርሃም መባል ተገባው። ከታናሽነቴ ጀምሮ የአብርሃምን ሃይማኖት እንደወደድሁ፣ እንግዳ በመቀበል እንደ ኖርሁ ይህን ስም የሰጠኝ እግዚአብሔር ይመስገን›› አለ። መንሶ በፈቃዱ አብርሃም ተብሎ ተጠርቷልና በብዙ ገድልና በትሕርምት በዚያች ቦታ ኖረ።
✝የነዳያን ፍቅር በልቡ ውስጥ አለ፣ ሁል ጊዜ ስለ ምግባቸውና ስለ ልብሳቸው ያስብ ነበር፤ ለሚያስፈልጋቸው ነገርም ገንዘብ ይሰጣቸው ነበር። ለድኆች ልብሱን ያካፍላል፤ ለእነርሱም ሰጥቶ እርሱ ራቁቱን ይቆማል፤ ልጆቹም ይመጣሉ፣ “ልብስህ ወዴት ነው?›› ይሉት ነበር፤ እርሱም “ሌቦች በማያገኙበት ቦታ አለ›› ይላቸው ነበር። ውዳሴ ከንቱ እንዳይሆንበት ሁሉን ይሠውር ስለነበር ልጆቹ ግን ሥራውን አያውቁም ነበር። ድኃ ባየ ጊዜ አጽፉን ይሰጥ ነበር፡ ሌላም ምንም ልብስ አያስቀርም ነበር። አንድ ቀን አንድ ድኃ መጥቶ ስለ እግዚአብሔር ስም ምግብና ልብስ ለመነው። አባታችንም ያንን ድኃ ባየው ጊዜ አጽፉን ሰጠው፤ ዳግመኛ አንድ ድኃ መጣ፤ በቤቱም የሚሰጠውን አጣ፡ መጠምጠሚያውን አውርዶ እርሷንም ለድኃው ሰጠውና በቤቱ ተቀመጠ። አንድ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ መጥቶ ራቁቱን አገኘውና ተቆጣበት፤ ክቡር አባቴ ሆይ! ለምን እንዲህ ትሆናለህ? አለው። “ለምትበላውና ለምትለብሰው ሳታስቀር ያለ አቅምህ ለምን ምጽዋት ትሰጣለህ? ልብስህንና መጎናጸፊያህን ሰጥተህ አንተ ራቁትህን ትሆናለህን” አለው። አባታችንም ‹‹ልጄ ሆይ! ፈጽሞ ስለሚያረጅና ስለሚጠፋ የዚህ ዓለም ልብስ ፈንታ የብርሃን መጎናጸፊያ የሚያለብሰኝ አምላኬ አለልኝ›› አለው። ልጆቹም ሌላም ልብስ አምጥተው አለበሱትና ‹‹ይህንንም እንደ ቀደመው አታድርግ›› አሉት፤ እርሱ ግን ስለ ድኆችና ስለ ችግረኞች ፍቅር ብዙ ጊዜ ምጽዋት ያደርግ ነበር፤ ቅብዓት በሰውነት፣ ውኃ በአንጀት እንዲገባ የነዳያን ፍቅር ወደ ልቡ ገብቷልና።
†
🌼 [ የትሕርምት ሕይወት ! ] 🌼
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን !
🕊
[ በፈተና መጽናትን በተመለከተ ! ]
------------------------------------------------
አጋንንት እንደ ነጣቂ ተኩላዎች ናቸው !
" ሰዎች ከዚህ ዓለም አስተሳሰብ ወጥተው ስለ ሰማያዊው ሕይወታቸው መጨነቅ ሲጀምሩ ለመንፈሳዊው ሕይወት የምናደርገውን ተጋድሎ አጋንንት መቋቋም ሲያቅታቸው የሰውን አእምሮ በልዩ ልዩ ሐሳቦች እንዲረበሽ በማድረግ ሰውን ከመንፈሳዊው ተጠምዶው ለማውጣት አቅደው ይንቀሳቀሳሉ፡፡
ለዚህ የተዘጋጀ በእምነቱ ያልጠነከረ እና ተጠራጣሪ ሰው ካገኙ ግን ከመንገዱ ያስቱታል፡፡ ነገር ግን ከእነርሱ የመጣብንን ፈተና በጽናት ከታገልን እግዚአብሔር አምላክ እነርሱን ከእኛ አስወጥቶ ይሰዳቸዋል፡፡ እኛም እንደ አዲስ የወይን ጠጅ ሆነን በመንፈስ ቅዱስ ጣፍጠን እንገኛለን፡፡
አጋንንት እንደ ነጣቂ ተኩላዎች ናቸው፡፡ እነርሱ በትሕርምት ሕይወት ወደሚኖረው ተሐራሚ በአት ለመግባት ትንሽ ቀዳዳ እስከሚያገኙ ድረስ ያደባሉ፡፡ መግቢያ ቀዳዳን ሲያገኙ ፈጥነው በመግባትና አእምሮን በመለወጥ ነፍስን ወደ ጥፋት ይመሯታል፡፡
በዚህ ፈተና ውስጥ ያለ ተሐራሚ ግን አጋንንት ወደ እርሱ ይገቡ ዘንድ አንዳች ክፍተት ካልተወ ተስፋ በመቁረጥ ከእርሱ ይርቃሉ፡፡ ስለዚህ የአጋንንትን ውጊያ በመፍራት ከጽድቅ ሕይወት አትውጡ ፣ በኃጢአት ያሳድፉኛል ብላችሁም አትስጉ፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናንተን ይረዳችኋል ምንም ሊጎዷችሁ አይቻለውም፡፡
እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ ፦ “እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና፡፡” [፪ጢሞ.፩፥፯] ጌታችንም ለሐዋርያት ፦ “ሰይጣንን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ። እነሆ ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም፡፡ [ሉቃ.፲፥፲፰] በማለት ከእንግዲህ በእኛ ላይ ስልጣን እንደሌላቸው አስተምሮናል፡፡ "
🕊
[ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ]
† † †
🌼 🍒 🌼
👉 መንፈሳዊ_ግጥም 👈
📜ርዕስ፦ ምን_ይሉት_ትህትና
✍ገጣሚ፦ ጳውሎስ
🎙አቅራቢ፦ ፊሊሞና
🛑ለሌሎች እንዲደርስ ሼር በማድረግ ተባበሩን🙏🙏
🔔ቻናላችን ፦ኪነ-ጥበብ 🔔
††† እንኳን ለጻድቁ አቡነ ይምዓታ እና ለአበው ቅዱሳን መርትያኖስ ወመርቆሬዎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† አባ ይምዓታ ጻድቅ †††
††† ጻድቁ ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮዽያ ቢሆንም ሃገረ ሙላዳቸው የጥንቱ የሮም ግዛት የሆነችው ታናሽ እስያ ናት:: አባ ይምዓታ ከዘጠኙ (ተስዓቱ) ቅዱሳን አንዱ ናቸው:: ዘጠኙ ቅዱሳን ተወልደው ያደጉት ምንም በአንድ የሮም ግዛት ሥር ቢሆንም መነሻ ቦታቸው ግን የተለያየ ነው::
ሁሉንም አንድ ያደረጋቸው መንፈስ ቅዱስ በኪነ ጥበቡ ነው:: በምክንያት ደረጃ እንግለጸው ከተባለ ደግሞ የአንድነታቸው ምሥጢር:-
1.የቀናች ሃይማኖታቸው ተዋሕዶ::
2.ዓላማ (የእግዚአብሔር መንግስት) እና
3.ገዳማዊ ሕይወት ነው::
አባ ይምዓታን ጨምሮ ሁሉም ቅዱሳን ዘራቸው ከቤተ መንግስት ነው:: እነርሱ ግን ምድራዊውን ክብር ንቀው ሰማያዊውን ክብር ገንዘብ ማድረግን መርጠዋል:: አስቀድመው ቅዱሳት መጻሕፍትን ያጠኑት አበው በተለያየ ጊዜ እየመነኑ ከሮም ግዛት ወደ ግብጽ በርሃዎች ወርደዋል::
በምናኔ ቅድሚያውን አባ ዸንጠሌዎንና አቡነ አረጋዊ ይይዛሉ:: ዘመኑ የተዋሕዶ አማኞች የሚሰደዱበት 5ኛው መቶ ክ/ዘመን ነበርና እምነትን ላለመለወጥ ዘጠኙ ቅዱሳን ስደትን መረጡ::
በወቅቱ ደግሞ ለስደት መጠለያ የምትሆንና ከኢትዮዽያ የተሻለች ሃገር አልነበረችም:: ስለዚህም በ470ዎቹ ዓ/ም አልዓሜዳ በኢትዮዽያ ነግሦ ሳለ ቅዱሳኑ በአረጋዊ መሪነት መጡ::
ንጉሡም ሲጀመር የእግዚአብሔር እንግዳ ስለሆኑ: ሲቀጥል ደግሞ ቅድስናቸውን ተመልክቶ መልካም አቀባበልን አደረገላቸው:: ማረፊያ ትሆናቸውም ዘንድ አክሱም ውስጥ አንዲት ቦታን ወስኖ ሰጣቸው:: ይህች ቦታ "ቤተ ቀጢን" ትባላለች::
አባ ይምዓታና 8ቱ ቅዱሳን ወደ ሃገራችን እንደ ገቡ የመጀመሪያ ሥራቸው ቋንቋን መማር ነበር::
ልሳነ ግዕዝን በወጉ ተምረው እዛው አክሱም አካባቢ ሥራቸውን አንድ አሉ:: በወቅቱ በአቡነ ሰላማ: በአብርሃ ወአጽብሐና በአቡነ ሙሴ ቀዳማዊ የተቀጣጠለው ክርስትና በተወሰነ መንገድ ተቀዛቅዞ ነበርና እነ አባ ይምዓታ እንደ ገና አቀጣጠሉት::
ሕዝቡን በራሱ ልሳን ለክርስትና ይነቃቃ ዘንድ ሰበኩት:: የካደውን እየመለሱ: የቀዘቀዘውን እያሟሟቁ ለዓመታት ወንጌልን ሰበኩ:: ቀጣዩ ሥራቸው ደግሞ መጻሕፍትን መተርጐም ሆነ::
ከሃገራቸው ያመጧቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት ተከፋፍለው ወደ ግዕዝ ልሳን ተረጐሟቸው:: በዚህም ለሃገራችን ትልቁን ውለታ ዋሉ:: ይህ ሁሉ ሲሆን እነ አባ ይምዓታ የሚመገቡትም ሆነ የሚጸልዩት በማሕበር ነበር:: በመካከላቸውም ፍጹም ፍቅር ነበር:: ጸጋ እግዚአብሔር አልተለያቸውም::
የነ አባ ይምዓታ ቀጣዩ ተግባራቸው ደግሞ ገዳማዊ ሕይወትን ማስፋፋት ሆነ:: ይህንን ለማድረግ ግን የግድ መለያየት አስፈለጋቸው:: እያንዳንዱም መንፈስ ቅዱስ ወደ መራው ቦታ ሔደ::
*ዸንጠሌዎን በጾማዕት::
*ገሪማ በመደራ::
*ሊቃኖስ በቆናጽል::
*አረጋዊ በዳሞ::
*ጽሕማ በጸድያ::
*ሌሎችም በሌላ ቦታ ገዳማትን መሠረቱ::
*አባ ይምዓታ ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ምርጫቸው ገርዓልታ (እዛው ትግራይ) ሆነ::
ጻድቁ ወደ ቦታው ሲሔዱ ወንዝ (ባሕር) ተከፍሎላቸዋል:: ወደ ቦታው ደርሰውም ገዳም አንጸዋል:: በቦታውም ብዙ ተአምራትን ሠርተው በርካታ ደቀ መዛሙርትን አፍርተዋል:: የአቡነ ይምዓታ ገዳም ገርዓልታ (በፎቶው ላይ እንደምናየው) እጅግ ድንቅና ማራኪ ነው::
ነገር ግን እዛው ድረስ ሒዶ ለማየት ብርታትን ይጠይቃል:: በተራሮች መካከል ከመቀመጡ ባሻገር የአባቶቻችንን ጽናት የሚያሳይ ድንቅ ቦታ ነው:: ጻድቁ በዚሁ በፎቶው ላይ በምናየው ገዳም ለዘመናት ተጋድለው በዚህች ቀን ዐርፈዋል::
††† ቅዱሳን መርትያኖስና መርቆሬዎስ †††
††† እነዚህ ቅዱሳን የቁስጥንጥንያ ሰዎች ሲሆኑ የወቅቱ ፓትርያርክ አባ ዻውሎስም ደቀ መዛሙርት ናቸው:: በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ አካባቢ በአርዮሳውያን ምክንያት ስደት በሆነ ጊዜ አባ ዻውሎስ: ቅዱስ አትናቴዎስ: ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስና ቅዱስ ሊዋርዮስ ከመንበራቸው ተፈናቀሉ::
በስደቱ ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ ሲያርፍ ቅዱሳኑ አትናቴዎስና ሊዋርዮስ ተመለሱ:: አባ ዻውሎስን ግን በእሥር ቤት ውስጥ ሳለ በንጉሡ ትዕዛዝ አርዮሳውያን አንቀው ገደሉት:: ይህንን ያወቁት 2ቱ ደቀ መዛሙርቱ (መርቆሬዎስና መርትያኖስ) ቅዱስ አባታቸውን ቀብረው ንጉሡን ረገሙት::
አርዮሳዊው ታናሹ ቆስጠንጢኖስም ይህንን በሰማ ጊዜ 2ቱንም አስመጥቶ በአደባባይ በሰይፍ አስመታቸው:: ይህ ከተከናወነ ከ50 ዓመታት በሁዋላም ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ ሆኖ በመምጣቱ ሥጋቸውን አፈለሠ:: ቤተ ክርስቲያንንም አንጾ ቀድሶላቸዋል::
††† አምላከ አበው ቅዱሳን በምልጃቸው ይማረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
††† ጥቅምት 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አባ ይምዓታ ጻድቅ (ከተስዓቱ ቅዱሳን)
2.ቅዱሳን መርትያኖስ ወመርቆሬዎስ (ሰማዕታት)
3.አባታችን ያፌት (የኖኅ ልጅ)
††† ወርኀዊ በዓላት
1.አማኑኤል ቸር አምላካችን
2.ቅዱሳን አበው (አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ)
3.ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
4.ቅድስት ዓመተ ክክርስቶስ
5.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ (ሰማዕት)
6.ቅዱስ አባዲርና ቅድስት ኢራኢ
††† "በጐንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማን ነው? ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኩዋ መከራን ብትቀበሉ ብጹዓን ናችሁ:: ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ: አትናወጡም:: ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስን በልባችሁ ቀድሱት::" †††
(1ዼጥ.3:13)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
🖤 መድኃኔዓለም🖤
✝️መድኃኔዓለም ማለት ዓለምን ያዳነ የዓለም መድኃኒት ማለት ነው።ሰው በመበደሉ ምክንያት ከክብር ተዋርዶ ይኖር ነበር።
ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የተዋረደውን ሰው እርሱ በመስቀል ተሰቅሎ ወደ ቀደመ ክብሩ መለሰው።ምን ዓይነት ፍቅር ነው??
ወንድሜ/እህቴ አስባችሁታል ግን ስለእኛ ብሎ እኛን ለማዳን ብሎኮ ነው የተሰቀለው።ራቁትን መሰቀል ምን ያህል አሳፋሪ ነገር
እንደሆነ እናውቀዋለን።ጌታ ግን እኛን ለማዳን ብሎ ራቁትን መሰቀልን ናቀው። በፈጠራቸው ፍጥረታት ተተፋበት።እኛን ትእግስት ሊያስተምረን እነርሱን ማጥፋት እየቻለ እርሱ ግን በፍቅር እያየ የማያውቁትን እያውቁምና አባት ሆይ ይቅር በላቸው ይል ነበር። ክርስቶስ እኛን ለማዳን ሲሰድቡት አልተሳደበም ሲንቁት አልናቃቸውም ሲታበዩበት ሁሉ እርሱ ግን በትሕትና ያያቸው ነበር።ታድያ እኛ ደግሞ እራሳችንን ለማዳን ሰዎች ሲንቁን
ሲሰድቡን ሲታበዩብን በፍቅር በዝምታ ማለፍ ይጠበቅብናል። ይህን ካደረግን የክርስቶስ ደቀመዝሙር እንባላለን።በ5 ችንካር ነበር የቸነከሩት። በመስቀል የተገኙ ድንግል ማርያምና ሐዋርያው
ዮሐንስ ነበሩ።አንተም በመስቀሉ ስር ለመገኘት ከፈለግህ ትዕግስትን ፍቅርን ትሕትናን ገንዘብ አድርግ።
መድኃኔዓለም በቸርነቱ ይቅር ይበለን።🙏
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
✞ ጥቅምት ፳፯ (27) ✞
✞✞✞ እንኩዋን ለፈጣሪያችን "መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ" እና ለቅዱሳኑ "አባ መቃርስ": "አቡነ መብዓ ጽዮን" "ወአባ ጽጌ ድንግል" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+*" መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ "*+
=>ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው
የማዳን ሥራ ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ 3:00 ጌቴሴማኒ
ውስጥ ያዙት::
¤ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና: ከሐና ወደ ቀያፋ
ሲያመላልሱት: አስረው ሲደበድቡት አድረዋል::
+ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት::
¤ምራቃቸውን ተፉበት:: ዘበቱበት::
¤ራሱንም በዘንግ መቱት::
¤እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ::
¤በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት::
+በሠለስት (3:00 ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ
6,666 ገረፉት::
¤ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው
ወደ ቀራንዮ ወሰዱት::
¤6:00 ላይ በረዣዥም ብረቶች 5 ቦታ ላይ ቸንክረው
ሰቀሉት::
+7 ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ::
¤ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ 7 ቃላትን
ተናገረ::
¤ከቀኑ 9:00 አካባቢ በባሕርይ ስልጣኑ ቅድስት ነፍሱን
ከቅዱስ ሥጋው ለየ::
+በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ
ፈታ::
¤11:00 ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና
ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት::
በዚአች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ::
ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ:: ቅዱሳት
አንስት በዋይታ ዋሉ::
+ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት 27
ቀን ቢሆንም በዓሉ ወደ ጥቅምት እንዲመጣ ያደረጉት
አበው ሊቃውንት ናቸው:: ምክንያቱም ብዙ ጊዜ መጋቢት
27 የሚውለው ዓቢይ ጾም ውስጥ በመሆኑና የንግሥ
በዓላት በዓቢይ ጾም ስለማይፈቀዱ ነው::
+ምንም እንኩዋ በቅርብ ጊዜ በዓቢይ ጾም የሚያነግሡ
አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም አባቶቻችን ግን
እንዲህ ያለውን ሥርዓት አላቆዩልንም:: ከበሮና የቸብቸቦ
ዝማሬም በወቅቱ የተፈቀደ አይደለም::
+በዚህም ምክንያት የበዓለ ስቅለት ንግሡ ወደ ጥቅምት
27 ሲመጣ: የመጋቢት 5 ገብረ መንፈስ ቅዱስ ንግሥ
ወደ ጥቅምት 5: የመጋቢት 10 መስቀል ወደ መስከረም
17 መጥቶ እንዲከበር ሆኗል::
+"+ ቅዱስ መቃርስ ብጹዓዊ +"+
=>በዚህ ስም የሚጠሩ ቅዱሳን ብዙ ናቸው:: "ታላቁ
መቃርዮስ": "መቃርስ እስክንድርያዊ": "መቃርስ
ባሕታዊ"ን እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል:: ይህኛው
ቅዱስ ደግሞ "መቃርስ ኤዺስ ቆዾስ: መቃርስ ብጹዓዊ:
መቃርስ ዘሃገረ ቃው" ይባላል:: ሁሉም መጠሪያዎቹ
ናቸው::
+ቅዱሱ የ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ሰው ሲሆን የቅዱስ
ቄርሎስና የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ተከታይ ነው:: ከሕይወቱ
ማማርና ከቅድስናው መሥመር የተነሳ አበው
አመስግነውት አይይጠግቡም:: ልበ አምላክ ቅዱስ
ዳዊት "ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል" እንዳለው:: (መዝ. 91)
+ዳግመኛ "ወይከውን ከመ ዕጽ እንተ ትክልት ኀበ
ሙሐዘ ማይ" (መዝ. 1:3) እንዳለው ቅዱስ መቃርስ
እጅግ ብዙ ትሩፋቶችን አፍርቷል:: ከሁሉ አስቀድሞ
በበርሃ ኗሪ ከሆነበት ቀን ጀምሮ ስለ ጌታ ፍቅር እንባው
እንደ ዥረት እየፈሰሰ:: ራሱን በብረት ዘንግ ይመታ ነበር::
+"ቃው" በምትባል ሃገር ዻዻስ ሆኖ በተሾመ ጊዜም
ተጋድሎውን አልቀነሰም:: ዻዻስ ቢሆንም የሚለብሰው
የበርሃዋን ደበሎ ነው:: ከብቅዓቱ የተነሳ የሕዝቡ
ኃጢአት በግንባራቸው ላይ ተጽፎ እየታየው ስለ ወገኖቹ
ያለቅስ ነበረ:: በቤተ መቅደስ ውስጥ ቆሞ አንጀቱ ቅጥል
እስኪል ድረስም ያለቅስ ነበር::
+ሁልጊዜ ሲቀድስ ጌታችንን ከመላእክቱ ጋር ያየው
ነበር:: አንድ ቀንም ጌታ ቅዱስ መቃርስን "ዻዻሱ ሆይ
ሕዝቡን ገስጻቸው:: ብትገስጻቸውና ባይሰሙህ እዳው
በእነርሱ ላይ ነው" አለው:: ቅዱስ መቃርስም ሕዝቡ
ከኃጢአታቸው ይመለሱ ዘንድ ይመክራቸው:
ይለምንላቸውም ነበር::
+ከዚህ ሁሉ በሁዋላ በጉባኤ ኬልቄዶን (ጉባኤ አብዳን)
636 ዻዻሳት ንጉሡን ፈርተው ሃይማኖታቸውን ሲክዱ
ቅዱሳኑ ዲዮስቆሮስና መቃርስ "ተዋሐዶን አንክድም"
በማለታቸው ዘበቱባቸው:: ብዙ አሰቃይተውም ወደ ጋግራ
ደሴት አሳደዷቸው::
+ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ጋግራ ውስጥ ሲሞት ቅዱስ
መቃርስ ወደ እስክንድርያ ተመልሶ ሕዝቡን ሲመክር
ያዙት:: ከመሬት ላይ ጥለውም እየደጋገሙ ኩላሊቱን
ረገጡት:: ከመከራው ብዛትም በዚህች ቀን ነፍሱን
አሳልፎ ሰጠ:: ቅዱሱ ሙታንን ማስነሳትን ጨምሮ ብዙ
ተአምራትን ሠርቷል::
+አበውም ስለ ቅዱስ መቃርስ ብሎ ጌታ እንዲምራቸው
እንዲህ ይጸልዩ ነበር:-
"ሰላም ሰላም ለፈያታዊ ዘቀደሶ::
ሃገረ ጽጌ የአኀዝ ምስለ ጻድቃን በተዋርሶ::
ተዘከረኒ ክርስቶስ አመ ትመጽእ ለተዋቅሶ::
በእንተ መቃርስ ጻድቅ እንተ መጠወ ነፍሶ::
ወበበትረ መስቀል ዘይዘብጥ ርዕሶ::" (አርኬ ዘጥቅምት 27)
+*" አቡነ መብዓ ጽዮን "*+
=>ሃገራችን ኢትዮዽያ እጅግ በርካታ ቅዱሳንን ስታፈራ
አንዳንዶቹ ደግሞ የተለዩ ናቸው:: ጻድቁ አባ መባዓ ጽዮን
በ15ኛው መቶ ክ/ዘመን በሽዋ (ሻሞ) አካባቢ የተነሱ
ጻድቅ ናቸው:: ገና ከልጅነታቸው የእመቤታችንና የጌታችን
ፍቅር የሞላባቸው ነበሩ::
+በ3 ዓመታቸው ከእንግዳ የወሰዷት ስዕለ አድኅኖ
ተለይታቸው አታውቅም ነበር:: በወጣትነታቸው ጊዜም
ብሉያት ሐዲሳትን: ቅኔንም ጨምሮ ተምረው:
ከቤተሰባቸው አስፈቅደው በምናኔ ገዳም ገቡ::
ከዚያ በሁዋላ ያለውን ገድላቸውን ማን ችሎ
ይዘረዝረዋል!
+በተለይ ዐርብ ዐርብ የጌታን 13 ሕማማት ለማዘከር
ሲቀበሉት የኖሩት መከራ እጅግ ብዙ ነው:: ድንጋይ
ተሸክመው እንባና ላበታቸው እየተንጠፈጠፈ ይሰግዳሉ::
በድንጋይ ደረትና ጀርባቸውን ይደቃሉ:: ራሳቸውን
ይገርፋሉ:: በዋንጫ ሐሞት (ኮሶ) ሞልተው ይጠጣሉ::
+ከዚህ ሁሉ በሁዋላ ወር በገባ በ27 ስለ መድኃኔ
ዓለም ጠላ ጠምቀው: ንፍሮ ነክረው ወደ ገበያ ይወጡና
ይዘክሩ ነበር:: ከዝክሩ የነካ ሁሉ ይፈወስ ነበር:: ከእንባ
ብዛት ዓይናቸው ቢጠፋ ድንግል ማርያም መጥታ
ብርሃናዊ ዓይንን ሰጠቻቸው:: ስለዚህም "ተክለ ማርያም
(በትረ ማርያም)" ይባላሉ::
+ጌታችንም ስለ ፍቅራቸው በአምሳለ ሕጻን
ይገለጽላቸው: እርሳቸውም አቅፈው ይስሙት ነበር::
ጻድቁ ተናግረን የማንጨርሰውን ተጋድሎ ተጋድለው ጌታ
በዚህ ቀን ነፍሳትን ከሲዖል እንዲያወጡበት ስልጣንን
ሰጣቸው:: አባታችን ቅዱሱና ጻድቁ መብዓ ጽዮን ከብዙ
ትሩፋት በሁዋላ ዐርፈዋል::
+"+ አባ ጽጌ ድንግል ዘወለቃ +"+
=>ጻድቁ አቡነ ጽጌ ድንግል በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን
የነበሩ ሊቅና ገዳማዊ ናቸው:: የዘር ሐረጋቸው ምንም
ከቤተ እሥራኤል እንደሚመዘዝ ቢታወቅም ኢትዮዽያዊ
ናቸው:: አስቀድመው አይሁዳዊ በመሆናቸው ኢየሱስ
ክርስቶስንና ድንግል እናቱን አያምኑም ነበር::
+የተማሩትም ብሉይ ኪዳንን ብቻ ነበር:: በጊዜውም
"ክርስቶስ አልተወለደም:: ትክክለኛው እምነት ይሁዲ
ነው::" እያሉ ከክርስቲያኖች ጋር ይከራከሩ ነበሩ:: አንድ
ቀን ግን ከታላቁ ሊቅና ገዳማዊ አቡነ ዜና ማርቆስ ጋር
ተገናኙ::
+ጻድቁን ስላልቻሏቸው ተሸንፈው በክርስቶስ አመኑ::
ጥቅምት 26/2016 #አቡነ_ሐብተ_ማርያም
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ፃድቁ አባታችን በምልጃ ፀሎቱ እንዲያስበን ለምንማፀንበት ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን
👉አምስቱን መቅሰፍቶች የማስወገድ ስልጣን የተሰጠው ፃድቁ አቡነ ሀብተማርያም የነበሩበት ዘመን 1486 ዓ.ም ንጉስ እስክንድር በነገሰበት ጊዜ ነው አባታቸው ፍሬ ቡሩክ እናታቸው ዮስቲና ይባላሉ
👉ፍሬ ቡሩክና ዮስቲና በህገ እግዚአብሔር በሃይማኖት በትሩፋት በምግባር ፀንተው የሚኖሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ነበሩ አቡነ ሀብተማርያም ከተሰጣቸው ቃል ኪዳኖች ውስጥ አምስት መቅሰፍቶች የማስወገድ ስልጣን ተሰጧቸዋል እነሱም፡-
👉መብረቅ፣ቸነፈር፣ረሃብ፣ወረርሽኝ፣ የእሳት ቃጠሎ ናቸው
ከብዙ ተጋድሎ በኋላ ፃድቁ አቡነ ሀብተማርያም በፀሎት ላይ ሳለ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ የቆምክባትን ቦታ ምስራቁን፣ ምዕራቡን፣ ሰሜኑን፣ ደቡቡን ባርክ አለው ሲባርክም ሶስት አጋንንት በፀሎቱ ስልጣን ታስረው በፊቱ ታዩት።
👉እነዚህም አጋንንት ከኖህ ጀምሮ ሰውን በማሳት ከኖርን በኋላ ከአንተ ጋር ምን ፀብ አለን አሉ አባታችንም አቡነ ሀብተማርያም በትዕምርተ መስቀል ሲያማትብ ሁለቱን አጋንንት ምድር ተከፍታ ዋጠቻቸው አንዱ ጊዜዬ ስላልደረሰ አታጥፋኝ አለው ያን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አቡነ ሀብተማርያምን ይህንን ተወው ጊዜው አልደረሰም አለው።
👉የጌታ ቃል እንዲህ ብሎ በተናገረ ጊዜ ሰይጣን ከአባታችን ተለይቶ ጠፋ ማር 9፣23 ከዚህም በኋላ ዕለተ ሞቱ በደረሰ ጊዜ ለሞቱ ምክንያት የሚሆን ቸነፈር ያዘው ጌታችንም በምስጋና ወደ እርሱ መጥቶ ወዳጄ ሀብተማርያም ሆይ ዛሬ ወደ አንተ የመጣሁት ከድካም ወደ እረፍት እወስድህ ዘንድ ነው ሰባት የጽድቅ አክሊሎችን አዘጋጅልሃለሁ፡፡
1. ስለ ንፁህ ድንግልናህ
2. አለምንና በውስጡ ያለውን ንቀህ በመኖርህ
3. ስለ ፍፁም ምንኩስናህ
4. ዘወትር አራቱን ወንጌላትን በማንበብህና በመፀለይህ
5. ስለ እኔ ብለህ ስለተራብከው
6. በጾም ስለተጋደልክ
7. ቂምና፣ጥላቻን፣ትዕቢትን፣ ትምክህትን፣ በልብህ ውስጥ ባለማስቀመጥህ ስለ ንፁህ ተልዕኮ ክህነትህ፣ ስለ ንፁህ መስዋዕትህ ነው ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡
👉በተጨማሪም እኔ የሰጠሁህን ቃል ኪዳን ተስፋ አድርጎ መጽሐፈ ገድልህን ለሚፅፈው ስሙን በመንግስተ ሰማያት በእውነት መጽሐፍ እፅፈዋለሁ፣ ለቤተክርስቲያንህ ዘይትን፣ ወይንን፣ ዕጣንን፣ ህብስትን እስከ ቀዝቃዛ ውሃ ድረስ በአንተ ስም መብዓ የሰጠውን የወደደውን ሁሉ አደርግለታለሁ በመንግስተ ሰማያትም ከወዳጆቼ ከቅዱሳን ጋር በደስታ አኖረዋለሁ፡፡
👉የአቡነ ሀብተማርያም ፈጣሪ ኃጢአቴን ይቅር በለኝ ብሎ ያንተን ስም ጠርቶ ቢለምነኝ ኃጢአቱን አስተሰርይለታለሁ ብሎ ቃል ኪዳን ገባለት ይህንንም ካለው በኋላ ጌታችን ሶስት ጊዜ ሳመው፡፡
👉ያን ጊዜም ከመድኃኔዓለም ጣዕም ፍቅር የተነሳ ነፍሱ ከስጋው ተለየች መዝ 115/116፣6 በሰማያዊ መልአክት በምድራውያን ስውራን ቅዱሳን ዘንድ ታላቅ ደስታ ሆነ ህዳር 26 ቀን አረፈ፡፡
👉ካህናት በመልካም ልብስ ገንዘው በዝማሬ በማህሌት ከቅዱስ አባታችን ከአቡነ ተክለሃይማኖት አጽም ጋር በፃድቁ መቃብር ቀበሩት የአባታችን የአቡነ ሀብተ ማርያም በረከታቸው ይደርብን
👉በዚህ እለት በወርሐዊ በአሉ የሚታወሰዉ ፃድቁ አባታችን አረጋዊ #ቅዱስ_ዮሴፍ ፀሎት ልመናዉ ረድኤት በረከቱ ከሁላችንም አይለየን "አሜን" 💒 💚 💛 ❤ 💒
#ጥቅምት_25
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ሃያ አምስት በዚህች ቀን #ቅዱስ_አቡነ_አቢብ (አባ ቡላ) አረፈ፣ የመላእክት አምሳል የሆነ #አባ_እብሎይ አረፈ፣ የከበረ #ቅዱስ_ዮልዮስ_ሰማዕት ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት ነው፣ የደብረ ሊባኖሱ #አባ_ሕፃን_ሞዐ ቃልኪዳን የተቀበሉበት ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አቡነ_አቢብ (አባ ቡላ)
ጥቅምት ሃያ አምስት በዚህች ቀን ታላቅና ክብር የሆነ አቢብ የተባለ መስተጋድል አባ ቡላ አረፈ።
የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አብርሃም የእናቱም ስም ሐሪክ ነው እነርሱም ከሮሜ አገር ሉፊ ከሚባል አውራጃ ናቸው በዘመናቸውም ከሀዲው ንጉሥ መክስምያኖስ በክርስቲያን ወገኖች ላይ መከራ ስለ አመጣ ስደት ሁኖ ነበርና እነርሱም በስደት ብዙ ዘመን ኖሩ።
ልጅንም በአጡ ጊዜ የተባረከ ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ በጾም በጸሎት ተወስነው ወደ እግዚአብሔር ለመኑ የእግዚአብሔርም መልአክ በሕልም ተገለጠላቸውና ፍሬ የመላበትን ዘለላ ሰጣቸው።
ይህም ቅዱስ በተፀነሰ ጊዜ በቤታቸው አጠገብ ታላቅ ዛፍ በቀለ በቅጠሉም ላይ በሮማይስጥ ቋንቋ ቡላ የእግዚአብሔር አገልጋይ በጽዮንም አድሮ የሚኖር የያዕቆብ ፈጣሪ ያከበረው የሚል ጽሑፍ ነበረበት።
በተወለደም ጊዜ ክርስትና ሳያስነሡ ዓመት ሙሉ አኖሩት እመቤታችን ማርያምም ለሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ለሰለባስትርዮስ ተገልጣ ወደ አብርሃም ቤት ሒዶ ሕፃኑን እንዲአጠምቀው አዘዘችው እርሱም ሒዶ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቀው ስሙንም ቡላ ብሎ ሰየመው እናትና አባቱም ሳይነግሩት ቡላ ስለ ሰየመው አደነቁ ዕፁብ ዕፁብ አሉ።
ከዚህም በኋላ ሊቀ ጳጳሳቱ በጸለየ ጊዜ የቊርባን ኅብስትና ወይን የተመላ ጽዋ ከሰማይ ወረደ እርሱም ቀድሶ ሥጋውንና ደሙን ከሕፃኑ ጋር አቀበላቸው በዚያንም ጊዜ ሕፃኑ የአንድ ዓመት ልጅ ሲሆን በባሕርይ በህልውና በመለኮት ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ የሆነ አብ በግብር በአካል በሰም ልዩ ነው በባሕርይ በህልውና በመለኮት ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ የሆነ ወልድ በግብር በአካል በስም ልዩ ነው በባሕርይ በህልውና በመለኮት በአብ ከወልድ ጋር አንድ የሆነ መንፈስ ቅዱስ በግብር በአካል በስም ልዩ ነው ብሎ ተናገረ።
ከጥቂት ዘመንም በኋላ አባትና እናቱ ኅዳር ሰባት ቀን ሙተው ሕፃኑ ብቻውን ቀረ።
ሕፃኑም ዐሥር ዓመት በሆነው ጊዜ ለጣዖት መስገድን የሚያዝ ከሀዲ መኰንን መጣ ቅዱስ ቡላም በሰማ ጊዜ ወደ መኰንኑ ሒዶ የረከሱ አማልክቶቹን ረገመ መኰንኑም በአካል ታናሽነቱን አይቶ እጅግ አደነቀ በዚያንም ጊዜ በችንካር እንዲቸነክሩት ሥጋውንም እንዲሠነጣጥቁት ቆዳውንም ከዐጥንቱ እንዲገፉ እጆቹንና እግሮቹንም በመጋዝ እንዲቆርጡ ጀርባውንም እንዲገርፉ በሾተሎችና በጦሮች መካከል አድርገው ከመንኰርኵር ውስጥ እንዲጨምሩት ዳግመኛም በመንገድ ላይ እንዲጐትቱት አዘዘ የመላእክት አለቃ ሚካኤልም መጥቶ አዳነው ያለ ጉዳትም ጤነኛ አደረገው።
ከዚህም በኋላ ወደ ሌላ መኰንን ሒዶ እርሱንና የረከሱ ጣዖቶቹን ረገመ መኰንኑም ተቆጥቶ በሚያዝያ ወር ዐሥራ ስምንት ቀን ራሱን በሰይፍ ቆረጠው ቅዱስ ሚካኤልም ከሰማይ ወርዶ ከሙታን ለይቶ አስነሣው ወደ አንድ ገዳምም ወስዶ የምንኲስና ልብስንና አስኬማን በመስቀልም ምልክት አለበሰው። እንዲህም አለው ከቅዱሳን ጻድቃን አንድነት ትሆን ዘንድ እግዚአብሔር አዝዞሃል።
ያን ጊዜም ቅዱስ አባ ቡላ ከደረቅ ተራራ ላይ ወጣ ያለ ማቋረጥም በውስጧ እየተጋደለ ኖረ። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራውንና ስቅለቱን በአሰበ ጊዜ ከረጅም ዕንጨት ላይ በመውጣት ራሱን ወደታች ሁል ጊዜ ይወረውር ነበር።
በአንዲትም ቀን ከዛፍ ላይ በተወረወረ ጊዜ ሰይጣን ሊገድለው ስለ በረታበት ሞተ ያን ጊዜም ክብር ይግባውና መድኃኑታችን ከሞት አነሣውና እንዲህ አለው ከእንግዲህ ስምህ ቡላ አይሁን አቢብ ይባል እንጂ የብዙዎች አባት ትሆናለህና።
እርሱም የክርስቶስን ፍቅር እጅግ ጨመረ ፊቱንም እየጸፋ ሥጋውን በየጥቂቱ እየቆረጠ ጀርባውንም ሰባት መቶ ጊዜ እየገረፈ ኖረ ጌታችንም ይፈውሰው ነበር በየእሑድም ቀን ከቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም እንደተወለደ በሌሎች ቀኖችም እንደተያዘና ከአይሁድ መከራ እንደ ተቀበለ ሁኖ ይገለጽለት ነበር።
ስለዚህም ሳይበላ ሳይጠጣ አርባ ሁለት ዓመት ኖረ ዳግመኛም ናላው ፈስሶ እስቲአልቅ ዐሥራ ሁለት ወር በራሱ ተተክሎ ኖረ። በአንዲትም ቀን የጌታችንን መከራ በአሰበ ጊዜ ሰይፉን በአንጻሩ ተከለ ከዕንጨት ላይም ወጥቶ በላዩ ወድቆ ሞተ ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምም ከአእላፍ መላእክት ጋር መጥታ የእኔና የልጄ ወዳጅ ሰላምታ ይድረስህ አለችው ። ከበድኑም ቃል ወጥቶ የሰማይና የምድር ንግሥት እመቤቴ ሰላምታ ይገባሻል አላት እርሷም በከበሩ እጆቿ ዳሥሣ ከሞት አስነሣቸው።
ዕድሜውንም ፈጽሞ ከዚህ ዓለም የሚወጣበት ጊዜ ሲደርስ ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስ በእጁ ልዩ የሆኑ አክሊሎችን የሚያበሩ ልብሶችንም ይዞ ተገለጠለት ወዳጄ አቢብ ሆይ በማያልቅ ተድላ ደስታ ደስ አሰኝህ ዘንድ ወደእኔ ና ስምህን ለሚጠራ መታሰቢያህን ለሚያደርግ እኔ ኃጢአቱን አስተሠርይለት ዘንደ በራሴ ማልኩልህ ወይም ለተራቆተ የሚያለብሰውን ለተራበም የሚያጠግበውን ለተጠማ የሚያጠጣውን የገድልህን መጽሐፍም የሚጽፈውን ወይም የሚያነበውንና የሚሰማውን በጸሎትህም የሚታመኑትን ሁሉ እስከ ዐሥር ትውልድ እምራቸዋለሁ ይህንም ብሎ አፉን ሳመው በደረቱም ላይ አድርጎ ወደአየር አወጣው የመላእክትንም ምስጋና በሰማች ጊዜ ነፍሱ ከሥጋው ተለየች ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ገባች።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባ_እብሎይ
ዳግመኛም በዚህችም ቀን ደግሞ አክሚም ከሚባል አገር የመላእክት አምሳል የሆነ አባ እብሎይ አረፈ። የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አሞኒ የእናቱ ስም ሙስያ ነው ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን የሆኑ በሕጉ ጸንተው የሚኖሩ ድኆችንና መጻተኞችን የሚወዱ የሚረዱ ናቸው።
ነገር ግን ልጅ አልነበራቸውም ሙስያም ዕንጨት የያዘ ብርሃናዊ ሰው በቤቷ ውስጥ ሲተክለውና ወዲያውኑ ለምልሞ አብቦ ሲያፈራ ያ ብርሃናዊው ሰውም ከዚህ ፍሬ የሚበላ ሁሉ ለዘላለም ይኖራል ሲላት እርሷም ከፍሬው ወስዳ ስትበላና በአፏ ውስጥ ጣፋጭ ሲሆንላት በልቧም ፍሬ ይሆንልኝ ይሆን ስትል ራእይን አየች።
ከእንቅልፏም በነቃች ጊዜ ራእይን እንዳየች ለባሏ ነገረችው እርሱም እርሷ እንዳየችው ያለ ማየቱን ነገራት እግዚአብሔርንም አብዝተው አመሰገኑት ትሩፋትንና ተጋድሎን በመጨመር በየሁለት ቀን የሚጾሙ ሆኑ ምግባቸውም እንጀራና ጨው ነው።
ይህን ቅዱስ እብሎይን በፀነሰችው ጊዜ እናቱ በገድል ወንዶችን እስከምታሸንፍ ድረስ በየሌሊቱ ሁሉ አንድ ሽህ ስግደትን ትሰግዳለች ሕፃኑን እስከ ወለደችው ድረስ ዘጠኝ ወር ያህል እንዲህ ስትጋደል ኖረች።
በወለዱትም ጊዜ እብሎይ ብለው ሰየሙት በጐለመሰም ጊዜ የምንኩስናን ልብስ ሊለብስ ወደደ ምክንያትም እስቲያገኝ እንዲህ ኖረ አቢብ የሚባል ወዳጅ ነበረውና እርሱ በሌሊት ወሰደው ከላዕላይ ግብጽ በሚገኙ ገዳማት በአንዱ ገዳም ውስጥ መነኰሰ በገድልም በመጠመድ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ።
ከጥቂት ወራትም በኋላ በጥቅምት ወር ሃያ አምስት ቀን አባ አቢብ አረፈ ያን ጊዜ አባ እብሎይ አብሎግ ወደሚባል ገዳም ሔደ ወደርሱም ብዙ ሰዎች ተሰበሰቡ እርሱም በበጎ አምልኮ እግዚአብሔርን መፍራትን የሚያስተምራቸው ሆነ።
🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
ስርዓተ ማህሌት ዘጽጌ ዘሐምሳይ ሳምንት በዓለ አቡነ አቢብ ወቅዱስ መርቆሬዎስ
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ነግሥ (የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዐተ ማኅሌት መጀመሪያ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
@menkir_tube
ሰላም ለአብ ገባሬ ኩሉ ዓለም፤ለወልድ ሰላም ወለመንፈስ ቅዱስ ሰላም ፤ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም፤ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም፤ለሰማዕታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም።
@menkir_tube
ዚቅ
ዛቲ ይእቲ እኅተ ትጉሃን መላእክት፤ ወለተ ኄራን ነቢያት፤ እሞሙ ለሐዋርያት፤ ሞገሶሙ ለጻድቃን ወሰማዕት።
@menkir_tube
@menkir_tube
ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።
@menkir_tube
ወረብ፦
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ ንዒ ርግብየ ምስለ ሚካኤል/፪/
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ገብርኤል ፍሡሕ ሊቀ መላእክት/፪/
@menkir_tube
ዚቅ፦
ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ ቃልኪ አዳም ይጥዕመኒ እምአስካለ ወይን አርአዮ ለሙሴ ግብራ ለደብተራ ወተናግሮ በዓምደ ደመና እሞሙ ይእቲ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላእክት አርአዮ ለሙሴ ግብራ ለደብተራ።
@menkir_tube
ማኅሌተ ጽጌ፦
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቌ ባሕርይ ዘየኀቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ።
@menkir_tube
ወረብ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ዘይኀቱ እምዕንቄ ባሕርይ/፪/
አክሊለ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ/፪/
@menkir_tube
ዚቅ፦
አክሊሎሙ ለሰማዕት ተስፋ መነኮሳት ሠያሚሆሙ ለካህናት፤ነያ ጽዮን መድኃኒት
@menkir_tube
ማኅሌተ ጽጌ
አንብርኒ ማርያም ውስተ ልብኪ ከመ ኅልቀት፤ በከመ ማዕተብ ፁርኒ (ዘትእምርት) በመዝራዕትኪ ልዕልት፤በእንተ ርስሐትየሰ ኢትመንንኒ ንግሥት፤እስመ ወሀብኩ ንብረትየ ለፍቅርኪ ሞት፤ ዘአሠርገዎሙ ለሰማዕት በጽጌሁ ሕይወት
@menkir_tube
ወረብ፦
አንብርኒ ማርያም ውስተ ልብኪ ከመ ኅልቀት በከመ ማዕተብ ዘትእምርት በመዝራዕትኪ ልዕል/፪/
በእንተ ርስሐትየሰ ኢትመንንኒ ኢትመንንኒ ንግሥት በእንተ ርስሐትየሰ/፪/
@menkir_tube
በከመ ከዋክብት ያሠረግውዎ በሰማይ በስኖሙ ከማሁ ሰማዕትኒ ያሠረግውዋ ለቤተ ክርስቲያን በገድሎሙ
@menkir_tube
ዓዲ (ሌላ) ዚቅ
አሠርገዎሙ ለሰማዕት በሰማያት አሠርገዎሙ ለሰማዕት በሰማያት ሰንበተ ክርስቲያን ለዕረፍት ሠርዓ ሎሙ አሠርገዎሙ ለሰማዕት በሰማያት ከመ ወርቅ በእሳት ፈተኖሙ አሠርገዎሙ ለሰማዕት በሰማያት ወከመ ጽንሓሓ መሥዋዕት ተወክፎሙ አሠርገዎሙ ለሰማዕት በሰማያት
@menkir_tube
@menkir_tube
ማኅሌተ ፅጌ፦
ዘንተ(ዘኒ) ስብሐተ ወዘንተ(ወዘኒ) ማኅሌተ፤ተአምርኪ ጸገየ ወፈረየ ሊተ፤ከመ እሰብሕ ዳግመ እንዘ እጸውር ፀበርተ፤ምስለ እለ ሐፀቡ ኣልባሲሆሙ በደመ በግዑ ድርገተ፤ውስተ ባሕረ ማኅው ድንግል ክፍልኒ ቁመተ።
@menkir_tube
ወረብ፦
ምስለ እለ ሐጸቡ አልባሲሆሙ አልባሲሆሙ በደመ በግዑ/፪/
ክፍልኒ ቁመተ ድንግል ድንግል ውስተ ባህረ ማኅው/፪/
@menkir_tube
@menkir_tube
ዚቅ፦
አመ ይነግሥ ወልድ በደብረ ጽዮን፤ክፍልኒ ድንግል እቁም በየማን ምስለ አባግዕ ቡሩካን
@menkir_tube
ዓዲ ዚቅ፦
ገጹ ብሩህ ከመ ፀሐይ ወእምኵሉ ስነ ሠርጐ ሰማይ ለጊዮርጊስ ኅሩይ ዘተወልደ እመንፈስ ቅዱስ ወማይ አልባሲሁ በደመ በግዕ ዘሐፀበ ወእምሠረቅት መርዔቶ ዓቀበ
@menkir_tube
ሰቆቃወ ድንግል
እስከ ማእዜኑ እግዝእትየ ማርያም ውስተ ምድረ ነኪር ትሔልዊ፤ሀገረኪ ናሁ ገሊላ እትዊ፤ለወልድኪ ሕፃን ዘስሙ ናዝራዊ፤ለክብረ ቅዱሳን በከመ ይቤ ኦዝያን ዜናዊ፤እምግብጽ ይጼውዖ አቡሁ ራማዊ።
@menkir_tube
ወረብ
በከመ ይቤ ኦዝያን ኦዝያን ክብረ ቅዱሳን/፪/
እምግብጽ ይጼውዖ ለወልድኪ አቡሁ ራማዊ አቡ/፪/
@menkir_tube
ዚቅ
ትንቢተ ኢሳይያስ ዘተብህለ እምግብፅ ጸዋዕክዎ ለወልድየ ለክብረ ቅዱሳን ጸዋዕክዎ
@menkir_tube
@menkir_tube
መዝሙር በ5-
ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ጸገየ ወይን ወፈረየ ሮማን፤ወፈረዩ ኩሉ ዕጽወ ገዳም ቀንሞስ ዕቁረ ማየ ልብን፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ጸገዩ ደንጎላት፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ ኀለፈ ክረምት ቆመ በረከት ተሠርገወት ምድር በስነ ጽጌያት፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ እግዚአ ለሰንበት ወአቡሃ ምሕረት፤ማ፦ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ
@menkir_tube
አመላለስ፦
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ/፪/
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ወለመድኃኒት/፪/
@menkir_tube
🇪🇹👇👇👇👇👇👇🇪🇹
👉 @menkir_tube 👈
👉 @menkir_tube 👈
👉 @menkir_tube 👈
🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹
@menkir_tube
# Join & share
✝የነዳያንን የልመና ድምፅ በሰማ ጊዜ ከልቡ ደስታ የተነሣ ለመነሣት ይፈልጋል፡ አንድ ላይ ቢሆንም እንኳን ድምፃቸውን ከሰማ እጁን ወደ ማዕድ አያወርድም ነገር ሲሰጣቸውም ያለውን ሁሉ ይሰጣል እንጂ ምንም ነገር አያተርፍም ነበር። ዲን ግን ዘወትር ልመናን አያቋርጡም ነበር" አባታችንም ስለ ምግባቸውና ለብሳቸው እንደሚያስብ ዐውቀው ከቤቱ አይርም ነበር" ከዕለታት አንድ ጉን ወደ አንዲት ታላቅ ሀገር ሔዶ ከዚያ ደረሰ፤ በሰንበት ምሸት ለእሑድ እቢያ ከዚያ አደረ፤ ሥርዓተ ቍርባን ከተፈጸመ በኋላ ደቀ መዝሙሩን ልጄ ምንበላው ነገር አለህ ወይስ የለህም?› አለው፤ ደቀ መዝሙሩም አባቴ አዎን አለኝ አለው። በቤተ ክርስቲያን ያያቸውን ታላላቅ አራት መነኰሳትን ሰበሰበ። እነርሱም የተዘጋጀ ምግብና ጠላ ከቤታቸው አመጡ፣ ሁለት ያመጣ አለ፤ ሦስትም የመጣ አለ፤ ሁላቸውም እንደ አቅማቸው አመጡ፤ አባታችንም ጸሎት ያደርግ ዘንድ ተነሣ፤ ባረከላቸውም። ደቀ መዝሙሩንም “ጠላውን አምጣው› አለው፡ ሁለት መነኩሳትም እንሥራውን አመጡት፣ ለአባታችን ጣዕመ ደስ ባሰኘው አባታችን ከሩቅ ሀገር የመጡ የተራቡ ሰዎች ከቤቱ ደጃፍ እንዳሉ ባወቀ ጊዜ መነኰሳቱን ‹‹አባቶቼ፣ ወንድሞቼና ልጆቼ ፈቃዳችሁ ከሆነስ ለክርስቶስ እንሰጠው ዘንድ ለነዳያንና ለችግረኞች እንስጣቸው› አላቸው።
✝በቤተ ክርስቲያን የተሰበሰቡ ወንድሞች መነኰሳት፣ ክቡራን ካህናት፣ ዲያቆናትና ሕዝቡ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሆነ፣ በወንጌል ወተት ያደገ፣ የእግዚአብሔር ሰው የሆነ የአባታችንን ትሕትና፣ ትሩፋትና ቅድስና ባዩ ጊዜ አዝነውበት ምንም ቃል አልመለሱለትም፣ በቦታቸው ወይም በቤታቸው አልነበሩምና በልባቸው እኛስ ከሩቅ ሀገር የመጣን አይደለምን?›› አሉ። እነርሱ ግን ከዚያው ይኖሩ ነበር፤ አባታችን ግን ነዳያንን ሰብስቦ ያንን ምግብ ሰጣቸው።
✝ወደ ቤቱ ተጠርተው የመጡ እነዚያ መነኰሳትም ምንም አልተናገሩም፣ ነገር ግን በልባቸው ተቆጡ፤ አዘኑ። አባታችን ግን ደቀ መዛሙርቱን ሌላ ማዕድ ያቀርቡ ዘንድ አዘዘ፤ ከመንገድ ስንቅ ይመገቡ ነበርና ጥቂት አመጡ። ገና ሳይቀምሱም ከሕዝብ አንዱ ‹‹አባቴ ሆይ! ጸልይልኝ፤ ይህን ጥቂት በረከትም ተቀበል›› ብሎ ብዙ ጠላ ላከ፤ እነዚህ መነኰሳት ግን ይህን ባዩ ጊዜ ፈጽመው ተደነቁ፤ ፈሩ፤ ተንቀጠቀጡም። አባታችንም ተነሥቶ ‹ለክርስቶስ ሰጠሁት፤ ለተራቡትም አስቀደምሁ፤ ለድኆች የሚሰጥ ለእግዚአብሔር ያበድራል የሚል ተጽፏልና›› አላቸው።
✝መነኰሳቱም ‹‹አባታችን ሆይ! ይቅር በለን አንተ ብዙ ኀዘንን ታውቃለህና፤ እኛ ስለ ሆዳችንና ስለ ልብሳችን አዘንን፤ አንተ ግን እንደ ጌታህ ክርስቶስ
✝የድኆችና የችግረኞች ወዳጅ ነህና አሉት። ዳግመኛም ‹አላወቅንምና አባታችን ይቅር በለን፣ አንተ ፈቃደ እግዚአብሔርን ትፈጽማለህ፤ እርሱም ልመናህን ይሰማልና። እንዲሰጥህ አላወቅንም፤ ነገር ግን ጎተራህን ሁሉ እንደሚሞላልህ ሰምተን ነበር' የተዘጋጀ ምግብንም እንዳወረደልህ ሰምተን ረሳን፤ አሁንም አባታችን ይቅር በለን፤ ባንተ ላይ ተቆጥተን ነበር፤ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር እንደሆነ አላወቅንም፤ አንተ ግን አስቀድመህ ለተራቡት ሰጠህ፤ ቀጥሎም ከአምላክ በረከት ለእኛ ለመብላት ለተዘጋጀን ሰጠኸን አሉት። አባታችን ዘግሩምም ወንድሞቼና ልጆቼ ይህን የማደርገው ለሰው ልታይ ብዬ አይደለም ለትምክህትም አይደለም፤ እግዚአብሔር የሰጠኝ ሀብት ነው እንጂ” አላቸው። “እኔ እሰጣለሁ፡ እርሱም የሚያስፈልገኝን ነገር አላሳጣኝም›› አላቸው፤ እነርሱም ከእርሱ ተባረኩ ከዚኽም በኋላ ታላላቅ ተአምራትና ድንቅ ነገርን የሚያደርግ የእግዚአብሔርን ገናናነት ተነጋገሩ።
✝ከዕለታትም በአንደኛው ቀን አባ ዘግሩም ቆሞ እየጸለየ ሳለ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሱ መጣና በቸርነቱ ቅድስት የሆነች የጎኑን መወጋትና የችንካር ቍስሎቹን ሁሉ አሳየው። አባ ዘግሩምም ተደፍቶ ሰግዶ “ጌታየ ሆይ አንተን እዳስስህ ዘንድ ፍቀድልኝ አለው፤ ጌታችንም ይዳስስ ዘንድ ፈቀደለትና እንደ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ጎኑን ዳሰሰ፣ ቶማስስ ደቀ መዛሙርቱን ስላላመነ ነበር፤ አባታችን ዘግሩም ግን ጌታችን ‹ሳያዩኝ የሚያምኑኝ ብፁዓን ናቸው” ብሎ እንደተናገረው ሳያይ ያመነ ነው። አባታችን ግን ሳያይ አመነ። ወንድሞቼ ሆይ! ለአባታችን የተሰጠውን ጸጋ ተመልከቱ የመድኃኒታችንን ቍስሎች ዳስሷልና። ለተመረጡ ቅዱሳን የሚሰጥ ታላቅ ጸጋን አገኘ።
✝ከሀገሮች ሲመለስም ወደ ደብረ ጽዮን ለመሔድ ግባ ከተባለ ታላቅ ወንዝ ደረሰ፤ ከፈሳሹ ብዛት የተነሣ ስትበረታታ አገኛት። ብዙ ሰዎች ከእርሱ ጋር ነበሩና የሚያደርጉትን አጡ፤ ብፁዕ አባታችን ግን ከወንዙ ዳር ቆሞ በምርጉዙም በባሕሩ ላይ አማተበ፤ ያንጊዜም ወንዙ ወዲያና ወዲህ ተከፈለ። በዚያ የነበሩ ሰዎች ሁሉም ተሻገሩ። ነቢዩ ሙሴ የኤርትራን ባሕር በከፈላት ጊዜ እንደ ተሻገሩ ሁሉ እነዚህም አባታችን ዘግሩም ለሁለት በከፈላት ባሕር ተሻግረዋልና እግዚአብሔርን አመሰገኑ። አባታችንም ባሕርን እንደየብስ አድርጎ አሻገራቸው። ከዚኽም በኋላ በሰላም ወደ ቤቱ ደረሰ።
✝አባታችን ዘግሩም በጽኑ ተጋድሎ በዚኽች ምድር ላይ እንደ መላእክት ሆኖ ብዙ ዘመን ከኖረ በኋላ ከዕለታት በአንደኛው ቀን በሌሊት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ አባታችን ዘግሩም ዘንድ መጣና እንዲህም አለው፡- ‹ወዳጄ ዘግሩም ሆይ
✝ሰላም ለአንተ ይሁን፤ ፈለግኸኝ አገኘኸኝም። የለመንኸውን ሁሉ ሰጠሁህ በሬን አንኳኳህ መንግሥተ ሰማያትንም ከፈትሁልህ ለአንተም ተዘጋጀችልህ ወዳጄና አግልጋይ ሆይ! እነሆ ዕለተ ዕረፍትህ ደረሰ። ከድካም ወደ ዘለዓለም ዕረፍት ከድህነት ወደ ሀብት፣ ከረኀብ ወደ ጥጋብ ና ለዘለዓለም በማያልፍና በማይጠፋ ደስታ ውስጥ ከሐዘን ታርፍ ዘንድ ታማኝ ወዳጄ ና›› አለውና ታላቅ የምሕረት ቃልኪዳን ሰጠው።
✝ዳግመኛም ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ሥቃያትን ሁሉ ታገስህ በጠበበው በር ስለሔድህ ሕማማትን ስለተቀበልህ ማደሪያየ ትሆን ዘንድ ራስህን በምንኵስና ስላነጻህ እስከ አሥር ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ፤ ስለዚህ የለመንኸኝን ሁሉ ሰጠሁህ፤ የእኔን ቃል ምግብ አድርገህ የዚህን ዓለም ደስታዎችና የመባልዕትን (የምግቦችን) ጣዕም ሁሉ ንቀሃልና ሁሉን ፈጸምሁልህ፡ የተመረጥህ ዘግሩም ሆይ ና በመንግሥቴ ከእኔ ጋር ደስ ይበልህ፤ ማልሁልህ በሀገርህ ያለውንም ሁሉ ይቅር ብየልሃለሁ አለው። የክብር ባለቤት ጌታችንም ይህንን ብሎ በክብር በምስጋና ዐረገ።
✝በሐምሌ ስድስት ቀን አባታችን ዘግሩም ባረፈ ጊዜ ሚካኤልና ገብርኤል፣ ብርሃናውያንና መንፈሳውያን የሆኑ መላእክት ሊቀበሉት መጡ። ቀኖናቸውን የወደደ፤ ሕጋቸውን የጠበቀላቸው ነቢያትና ሐዋርያትም መጡ፤ ዳግመኛም ሰማዕታት ከአክሊሎቻቸው ጋር ከፀሐይ ሰባት እጅ እያበሩ መጡ፤ አባታችንም እንደእነርሱ ይሆን ዘንድ የወደዳቸው ደናግልና መነኰሳት ሁሉ መጡ፤ ከዚኸም በኋላ የአባታችን ዘግሩም ቅድስት ነፍስ መላእክት በምስጋናና በክብር በእልልታም አሳረጓት፣ ነፍሱም በመካከላቸው ከፀሓይና ከሚያዝያ ወር ጨረቃ ይልቅ ሰባት እጅ ታበራለች፤ ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊትም አሳረጓት።
✝የአባታችን የአባ ዘግሩም ጸሎቱና በረከቱ በቃል ኪዳኑ የምንታመን የወንጌል ልጆች ሁላችንን ሕዝበ ክርስቲያኑን ይጠብቀን ለዘለዓለሙ አሜን።✝
ምንጭ $በእንተ ኅሩይ ቅዱሳን መጽሐፍ የተወስደ ገጽ 222-229
🌾ወንድማችን ገብረ ሥላሴ እግዚአብሔር በዕድሜ በጤና ይጠብቅልን 🌾
የቃላት ድግፈት ካለ ማሩኝ ብያለሁ
ጥቅምት 23/2/2015
Kuwait
🌾🥀🌾ጥቅምት ፳፬(24)ጌታችን ተገልጦላቸው በፍቅር የተወጋ ጎኑን በእጃቸው እንዲዳስሱ የፈቀደላቸው እርሳቸውም ያላቸውን ሁሉ አውጥተው ለድኆችና ለችግረኞች፤ ለባልቴቶችና እናት አባት ለሌላቸው ምጽዋትን ከሰጡ በኋላ ሌላ የሚመጸውቱት ቢያጡ እርቃናቸውን እስኪቀሩ ድረስ የለበሱትን ልብሳቸውን እያወለቁ ለነዳያን ይሰጡ የነበሩት መፍቀሬ ነዳያን አባ ዘግሩም ዓመታዊ መታሰቢያ በዓላቸው ነው፡፡ ይኸውም በዚህች ዕለት መልአክ ከሰማይ ታቦተ መድኃኔዓለምን አምጥቶ ሰጥቷቸዋል፡ 🥀🌾
✝መፍቀሬ ነዳያን አባ ዘግሩም✝
✝ገድለ አባ ዘግሩም እንደሚናገረው ጻድቁ አባ ዘግሩም ያላቸውን ሁሉ አውጥተው ለድኆችና ለችግረኞች፣ እናት አባት ለሌላቸው ምጽዋትን ከሰጡ በኋላ ሌላ የሚመጸውቱት ቢያጡ እርቃናቸውን እስኪቀሩ ድረስ የለበሱትን እያወለቁ ለነዳያን ይሰጡ የነበሩ መፍቀሬ ነዳያን ናቸው። ጌታችንም በአካል ተገልጦላቸው በፍቅር የተወጋ ጎኑን በእጃቸው እንዲዳስሱ የፈቀደላቸው ታላቅ ጻድቅ ናቸው። አባታቸው ገርዜነ ጸጋ የተባለ ደገኛ ካህን ሲሆን እናታቸው ደግሞ ነፍስተ እግዚእ ትባላለች። እነርሱም በእግዚአብሔር ሕግ ጸንተው ብዙ ዘመን ሲኖሩ የተባረከ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ እግዚአብሔርን ይለመኑት ነበር። ልዑል እግዚአብሔርም መልአኩን ልኮ የተባረከ ልጅ እንደሚወልዱ አበሰራቸው አባ ዘግሩም በመልአኩ ብሥራት መስከረም 17 ቀን በተወለዱ ጊዜ ወላጆቻቸው ብርሃነ መስቀል አሏቸው፤ በኋላ ላይ የተጠሩበት ስመ ጥምቀታቸው ግን ማሕፀንተ ሚካኤል ነው።
✝ አባ ዘግሩምን ወላጆቹ በመንፈሳዊ አስተዳደግ ስላሳደጉት ከልጅነቱ ጀምሮ ጸጋ እግዚአብሔር አደረበት በመንፈስ ቅዱስ አደገ። እንደ ነቢዩ ሳሙኤል ከታናሽነቱ ጀምሮ በእግዚአብሔር ቤት አድጓልና ወደ ቤተ ክርስቲያንም መሔድን አላስታጎለም።
✝ዕድሜውም ለትምህርት ሲደርስ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍተ ነቢያትን መዝሙረ ዳዊትን ይማር ዘንድ አባቱ ለመምህር ሰጠው። በትምህርቱ እጅ አስተዋይ ሆኖ በመንፈስ ቅዱስም ኃይል የጸና ሆነ። ከዚኽም በኋላ ዲቁና ተሾመ።
✝እናቱና አባቱ ያለ ፈቃዱ ሚስት ያጩለት ዘንድ ወደዱ፤ እርሱ ግን ዓለምን ፍጹም ንቆ በምንኩስና በተጋድሎ መኖርን ወደደ። ይመነኩስም ዘንድ አባ ክርስቶስ ይባርከነ ወደተባለ አንድ መነኩሴ ወዳለበት ገዳም ሲሔድ በመንገድ መደራ በተባለች ቦታ በታላቅ ገዳም ውስጥ ከእንግዶች ጋር አደረ፤ በሌሊት በነቃ ጊዜ አንድ ድኃ በዚያች ቤት ውስጥ አገኘ። አባ ዘግሩም ግን የድኃውን ልብስ ወስዶ የእርሱን ልብስ ሰጥቶት በሌሊት ወጥቶ መንገዱን ሔደ። በነጋም ጊዜ ያ ድኃ ያደረገለትን ለሰዎቹ ተናገረ። በእንግዳ ማደሪያ ከእኔ ጋር አብሮ ያደረ አንድ ሰው እኔ የለበስሁትን ልብስ ወስዶ የእርሱን መልካም ልብስ ተወልኝ አላቸው። እነርሱም የእግዚአብሔር ሰው ነውና መልካም ሥራ አደረገልህ፡ አንተ ግን ሔደህ ስለ እርሱ ጸልይለት›› አሉት።
✝አባ ዘግሩምም ከአባ ክርስቶስ ይባርከነ ከቀድሞ ቤቱ በደረሰ ጊዜ በዚያም አላገኘውም፤ ውኃ ከሌለበት፤ ጸጥታ ከሰፈነበት ምድረ በዳም ሔደ። የፀሓይ ቃት ስለነበር በዚያ ሲመላለስ ውኃ ጥም ያዘው። ያን ጊዜም በገዳሙ ውስጥ ባዶ ወጭት አገኘና በፊቱ አስቀምጦ ወደ እግዚአብሔር በጸለየ ጊዜ ወዲያው ብዙ ዝናም ዘነመ፤ በወጭቷም አጠራቀመና እስኪበቃው ድረስ ከእርሷ ጠጣ። ከዚያም አባታችን ክርስቶስ ይባርከነን አገኘውና ሊያደርግ የሚፈልጋቸውን ምሥጢሩን ሁሉ ነገረው።
✝ከዚኽም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ መጥቶ አባታችንን « በደመና ተጭነህ ወደ ዳሞት አገር ሒድ›› አለው፤ አባታችንም በደመና ተጭኖ ፍራጽ ከተባለ ገዳም ደረሰ። በዚያም ምድርን ባረኮ ውኃ አፈለቀ፣ መልአኩም ወደ ቀኝህ ተመልከት አለውና ወደ ቀኙ ሲያይ ዐደልን ብርሃን ከቧት ተመለከተ፤ ዕፅዋትም ጭፍቅ ያሉ ነበሩ፤ አባ ዘግሩምም ይህች የዘለዓለም ማረፊያ ቦታየ ናት አለ። የጻሕናንን ምድር እየባረከም ሔዶ ዐደል ደረሰና ወደ ውስጧ ገባ። በዚያም ተቀመጠ ምድሪቷንም ባርኮ ውኃ አፈለቀ።
✝የገዳሙ አራዊትም ተደሰቱ። ሙሴ ጽላትን ከእግዚአብሔር እንደተቀበለ ጥቅምት ሃያ አራት ቀን የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ አመጥቶ የብርሃን መስቀልና የመድኃኔዓለምን ታቦት ለአባ ዘግሩም ሰጠው። ዳግመኛም የእግዚአብሔር መልአክ የተዘጋጀ ኅብስትና ጽዋን፤ ለመሥዋዕት የሚሆነውንም ሁሉ ሰጠው፣ አባታችንም ከካህናት ጋር በዚያች ቤተ ክርስቲያን ቀድሶ ሥጋውንና ደሙን ሰጣቸው።
✝በቤተ ክርስቲያን አጠገብ አንዲት የዋንዛ ዛፍ ነበረች፤ ሕዝቡም ይሰበሰቡባትና በሥራ ተቀምጠው ክፉ ሥራ ይሠሩ ነበር፤ አባታችንም ‹‹ለምን እንዲህ የማይገባ ሥራ ትሠራላችሁ? ሲላቸው እነርሱ ግን አልሰሙም። በዚህም ጊዜ አባታችንም ያቺን ዛፍ ከበታችሽ ካሉት ሕዝብ ጋር ተነሥተሽ ሒጂ›› ብሎ በቃሉ አዘዛት። ያን ጊዜም ያች ዛፍ ከሕዝቡ ጋር ተነሥታ የሁለት ጦር ውርወራ ያህል ሔደች። ጌታችን በቅዱስ ወንጌሉ ‹‹የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ ይህን ሾላ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተተከል ብትሉት ይታዘዝላችሁ ነበር፤ ይህን ተራራ ከዚህ ሒድ ብትሉት ይሔዳል›› እንዳለ አባታችን አባ ዘግሩምም ይህንን አደረጉ። ማቴ 17፡20፣ ሉቃ 17፡6።
✝ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ከአባታችን ዘግሩም ይባረኩና እጅ ይነሱ ዘንድ 44 ቅዱሳን በደመና ተጭነው አባታችን ካለበት ቦታ ወደ ዐደል መጡ። ሶምሶን ከአህያ መንጋጋ፤ ሙሴም ከዐለት ውኃ እንዳፈለቁ ሁሉ ለሚያስፈልጋቸው ነገር
✝ይጠቀሙበት ዘንድ አባታችንም በጸሎቱ በቍጥራቸው ልክ በአንድ ጊዜ የውኃ ምንችን አፍልቆ ሰጣቸው። እነርሱም ይህን አይተው አደነቁ ፡ ዘግሩም ይሁን አሉት፤ ስለዚህም አባታችን አባ ዘግሩም ተባለ፣ ምንጮቹ ድዉያንንና ሕሙማንን የሚፈውሱ ሆኑ።
✝እንዲሁም አባታችን የሚገለገልበት አንድ አህያ ነበረው፤ የሚጭነው ሰው ሳይከተለው ለሁለት ቀናት ሔዶ ወደ ጫነው ሰው ቤት ይመለስ ነበር፤ የህግ ሰዎችም ይህን አይተው ያላቸውን ሁሉ ይጭኑትና ብቻውን ሔዶ ወደ አባታችን ይመለስ ነበር።
✝የአባ ዘግሩምን የተአምራቱን ነገር በሰማ ጊዜ ከንጉሡ ባለሟሎች አንዱ መጣ። ሌላም በቤቱ አጠገብ የሚኖር አንድ ሰው መጣና ጨው ጭኜ ወደ ግ እወስድበት ዘንድ አህያህን ስጠኝ” ብሎ ለመነው። የተቸገሩትን ለመርዳት የሚልከው አንድ አህያ ነበረውና አባ ዘግሩምም የጨው መጠን ምን ያህል ነው?›› አለው። ያ ሰውም በሰቅል ስልሳ ይሆናል› አለው። አባታችን “ውሰደው ከተናገርኸው በላይ ግን አትጫነው› አለው። ሰውየውም አህያውን ወስዶ አባታችን እንዳለው ነው፤ ለአባታችን ያልነገረውን በቤቱ የተረፈውን ግን ሰውየውና ወንድሙ ተሸከሙት።
(መልክአ ተክለ ሃይማኖት)
ተክለ ሃይማኖት ሆይ በቁመት ብዛት እግርህ በመሠበሩ
በደም ለተነከረ ሰኮናህ ሰላም_እላለሁ።
ቅዱሱ አባት ሆይ ትዕግስትህ ፍጹም እንደ ኢዮብ
ትዕግስት ነው እኮን።
አባት ሆይኖኅ ልጆቹ ሴምንና ያፌትን እንደባረካቸው አንተም በዓለሙ ሁሉ ያሉ ልጆችህን ደቀ መዛሙርትህን ባርካቸው። '
( የአባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በረከት ይድረሰን #አሜን )