አይ ሌላ ነገር አይደለም እሽ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ስም እንደ ፈለጋቹህ በማንኛውም ነገር ለኮሚንት መስጫ አይደለም እንዴ እች ደሞ ምን ትላለች አይፈቀድም እንዴ ትላለች
Читать полностью…💠መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠
/(ማቴ ፫:፫/)
=>+"+ እንኩዋን ለቅዱሳን ጻድቃን "አቡነ መድኃኒነ እግዚእ" : "ቅዱስ ዓምደ ሚካኤል" እና "ቅዱስ ኪርያቆስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+
+*" አቡነ መድኃኒነ እግዚእ "*+
=>መዘንጋታቸው እጅግ ከሚያስቆጭ ኢትዮጽያውያን አባቶች ትልቁን ሥፍራ እኒህ አባት ይወስዳሉ:: የማር ወለላን በሚያስንቅ ጣዕመ ሕይወታቸው ሃገራችንን ያጣፈጡ: ብርሃን ሆነው ብዙ ቅዱሳንን የለኮሱ ታላቅ ጻድቅ ናቸው::
+አባ መድኃኒነ እግዚእ የተወለዱት በ13ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ትግራይ (አዲግራት) ውስጥ ነው:: ወላጆቻቸውም ቀሲስ ሰንበትና ሒሩተ ማርያም ይባላሉ:: በደግነትም እጅግ የታወቁ እንደ ነበሩ ገድላቸው ይናገራል:: "መድኃኒነ እግዚእ" ማለት "ጌታ መድኃኒታችን ነው" ማለት ነው::
+ብዙ ጊዜም "ዘደብረ በንኮል - ሙራደ ቃል" እየተባሉ ይጠራሉ:: "ደብረ በንኮል" ማለት ትግራይ ውስጥ የሚገኝና ጻድቁ በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ያነጹት ገዳም ነው:: "ሙራደ ቃል" ደግሞ "የቃል (የምሥጢር) መውረጃ" እንደ ማለት ሲሆን በቦታው ሱባኤ የያዘ ሰው ልክ እንደ ቅዱስ ያሬድ ምሥጢር እንደሚገጥለት የሚጠቁም ስም ነው::
+ጻድቁ መድኃኒነ እግዚእ በልጅነታቸው ከሊቁ ካህን አባታቸውና ከሌሎችም መምሕራን ተምረው: ምናኔን መርጠው ገዳም ገብተዋል:: በጾም: በጸሎትና በስግደት ተግተው ጸጋ እግዚአብሔር ሲሰጣቸው ወደ ደብረ በንኮል ሒደው ገዳም መሠረቱ::
+በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ መካከለኛው ዘመን (በተለይ ከ13ኛው እስከ 15ኛው መቶ ክ/ዘመን ድረስ ያለው) የብርሃን ዘመን ይባላል:: ምክንያቱም ዘመኑ
*ክርስትና ያበበበት::
*መጻሕፍት የተደረሱበት::
*ስብከተ ወንጌል የተስፋፋበት::
*ገዳማዊ ሕይወት የሠመረበት ወቅት በመሆኑ ነው::
+ለዚህ ትልቁ አስተዋጽኦ ደግሞ:-
¤አቡነ ተክለ ሃይማኖት::
¤አቡነ ኤዎስጣቴዎስ::
¤አባ ሰላማ ካልዕ::
¤አቡነ ያዕቆብ::
¤ቅዱሱ ንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብ::
¤አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ::
¤አቡነ መድኃኒነ እግዚእን የመሰሉ አበው መነሳታቸው ነው::
+በተጨማሪም:-
¤12ቱ ንቡራነ ዕድ::
¤7ቱ ከዋክብት::
¤47ቱ ከዋክብት::
¤5ቱ ከዋክብት የሚባሉ አበው አስተዋጽኦም ልዩ ነበር:: ከእነዚህ መካከልም የ7ቱ እና የ47ቱ ከዋክብት አስተማሪ: የአበው 3ቱ ሳሙኤሎች (ዘዋልድባ: ዘጣሬጣና ዘቆየጻ): የሌሎችም እልፍ አእላፍ ቅዱሳን አባት የሆኑት አባ መድኃኒነ እግዚእ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ::
+ጻድቁ ቅዱሳኑን ሰብስበው: አስተምረው: አመንኩሰው: መርቀው ሰደው: ሃገራችንን እንዲያበሩ በማድረጋቸው እንደ አባ ኢየሱስ ሞዐ እርሳቸውም "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን" ይባላሉ:: ታላቁ ጻድቅና ሰባኬ ወንጌል አባ ዓቢየ እግዚእም (ጐንደር ውስጥ እባብና ጅብ እንዳይጐዳ የገዘቱ አባት ናቸው) የእርሳቸው ደቀ መዝሙር ነበሩ ይባላል::
+ጻድቁ መድኃኒነ እግዚእ በተትረፈረፈ የቅድስና ሕይወታቸው ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል:: አራዊትን ገዝተዋል: በአንበሳ ጀርባ ላይ እቃ ጭነዋል:: ከረዥም የተጋድሎ ሕይወት በሁዋላም ኅዳር 3 ቀን ዐርፈዋል:: እድሜአቸውም 180 ነው::
¤" መድኃኒነ እግዚእ አቡነ መስተጋድል::
ምንኩስናሁ ምዑዝ ከመ ኮል::
በመንፈሰ ጸጋ ክሉል::" (መጽሐፈ ሰዓታት)
¤" ተአምረ ኃይልከ አባ መድኃኒነ እግዚእ አቡነ::
እም አፈ ዜናዊ ሰማዕነ:: ወበዓይነ ሥጋ ርኢነ::
መንክርኬ አእላፈ ቤትከ ንሕነ::
ባሕቱ በዝ ተአምሪከ ርድአነ::
ለሰይፈ አርዕድ ንጉሥ ዘወሀብኮ ኪዳነ::
ከመ ረድኤቱ ታፍጥን ጊዜ ጸብዕ ኮነ::" (አርኬ)
❇️ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት)❇️
" ❇️ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::❇️
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
ልጄ!...ምን እያደረክ ነው?
☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️☀️
በፍጥነት ራሱን አጥፍቶ ይህቺን አለም መገላገል ፈልጓል፡፡ገመድ ገዝቶ ወደ ጫካ ሄደ፡፡ትልቅ ዛፍ ላይ ገመዱን ማሰር ሲጀምር የሰው ኮቴ ሰማ፡፡አይኑን ወደኮቴው ሲወስደው ያረጁ መነኩሴ ሲቀርቡት አስተዋለ፡፡ወደ ስራው ፈጥኖ ተመለሰ፡፡
"ልጄ ምን እያደረክ ነው?" ጠየቁት፡፡ሊመልስላቸው አልወደድም፡፡ሰው የተባለ ፍጥረት አስተጠልቶታል፡፡ራሱን ለማጥፋት የተገደደውም ሰዎች ባደረሱበት በደል አእምሮው ተንክቶ ነው፡፡
"ራስህን ለማጥፋት ከሆነ እኔም ላግዝህ እችላለው፡፡እንዲሁም አሁን ገመዱን ያሰርክበት መንገድ ልክ አይደለም፡፡ቆይ!... ቆይ..." አሉና ቀረቡት፡፡ገመዱን ወሰዱበት፡፡ለመታነቅ አመቺ አድርገው ሰቀሉት፡፡በአንገት እንዲገባ አድርገው ካስተካከሉት በኋላ አንጠለጠሉት፡፡ልጁ ግራ ተጋባ፡፡እብድ ናቸው ብሎም አሰበ፡፡
"ራስህን ከማጥፋትህ በፊት ግን አንድ ነገር እንድትረዳኝ እሻለው፡፡ እኔም ራሴን ማጥፋት እፈልጋለው፡፡ግን?" ብለው መተከዝ ጀመሩ፡፡
"ግን ምን?" አለ ልጁ፡፡
"ግን ይሄውልህ በጣም ግራ ተጋባው፡፡ወደዚህ ጫካ ራሴን ለማጥፋት ከመጣሁ በጣም ቆይቻለው፡፡ነገር ግን ተጋባው፡፡"አሉት፡፡
"በምንድን ነው ግራ የተጋቡት?" ጠየቃቸው፡፡
"ልክ ራሴን ላጠፋው ስል በውስጤ የሆነ ሀሳብ መጣ፡፡ቆይ ማን ማንን ነው የሚያጠፋው?ብዬ ራሴን ጠየኩኝ፡፡እኔ ሁለት ነኝ እንዴ? ብዬም ጠየኩኝ፡፡የሚገድለውና የሚመተው እኔዎች ልዩ መሆን አለባቸው ብዬም አሰብኩኝ፡፡አንዱ የውሸት እኔ ሌላኛው ደግሞ የእውነት እኔ ሊሆኑ እንደሚችልም ገመትኩኝ፡፡እናም ግራ ተጋባው፡፡አንተስ የትኛውን አንተን ነው የምታጠፋው? የውሸቱን እና የእውነቱ አንተ ተገልጠውልሃል? እስቲ ንገረኝ ልጄ!" አሉት፡፡
ልጁ ግን እንኳን ሊነግራቸው ይበልጥ ግራ ተጋባ፡፡
"እውነቱን ለማውራት እኔም አላውቅም አባባ፡፡እንዲህ አስቤ አልመጣሁም፡፡" አላቸው፡፡
"እንግዲያውስ ለአቅመ ራስህ ማጥፋት አልበቃህም፡፡"አሉና ገመዱን የሸጎጡትን ቢላዋ አውጥተው በጠሱት፡፡
"አይዞህ ትሞታለህ አትጨነቅ፡፡ግን መጀመርያ ተማር፡፡እዚህ ጫካ ውስጥ ራሴን ስፈልግ ከሀያ አመት በላይ ኖርያለው፡፡" አሉና ቀጥለውም
"መጀመርያ ለምን ራስህን ለማጥፋት እንደፈለክ ንገረኝ! እስቲ ስለህይወትህ አውራኝ፡፡" አሉት፡፡
"የኔ ህይወት...." ዝቅ ብሎ ልጁ ማሰብ ጀመረ፡፡ገና ሳያወራ ከአይኖቹ እንባ መፍሰስ ጀመሩ፡፡ቤተሰቦቹ፣ ጓደኞቹ፣ ሁኔታው፣ ኑሮ ሁሉም የዚህ አለም ነገር ያደረሰበትን ስቃይ ለመነኩሴው አንድ በአንድ ዘከዘከላቸው፡፡ጸጥ ብለው አደመጡት፡፡ሲጨርስ ጠብቀው፡
"በጣም ጥሩ አሁን ደግሞ ስለህወትህ ንገረኝ፡፡" አሉት፡፡
"አልገባኝም አባባ አሁን ነገርኮት እኮ!" አለ እንባውን እየጠረገ፡፡
"አሁን የነገርከከኝ ስለህይወትህ ሁኔታ እንጂ ስለህይወትህ አይደለም፡፡ሰዎች፣ ገጠመኞች፣ የደረሰብህ ጥሩ እና መጥፎ ነገር እንዲሁም እዚህ ምድር ላይ የደረሰብህ ነገሮች ህይወት ሳይሆኑ የህይወት ሁኔታዎች ናቸው፡፡" አሉት መነኩሴው፡፡ልጁ ግን የህይወቱን ሁኔታ እንጂ ህይወቱን አያውቅም፡፡የህይወቱን ሁኔታ ህይወት አደርጎ በማሰብ እስከ ዛሬ አንቀላፍቶ ኖሯል፡፡
"ህይወትህን ብታውቅ ራስህን ለማጥፋት አትምክርም ነበር፡፡አለም አላፊ የህይወት ሁኔታዎችን ህይወት አድርጎ ነግሮሀሃል፡፡ልጄ ልክ እንደ ብዙ ሰዎች አንተንም ሸውዶሃል፡፡እውነተኛው ነገር ላይ ሳይሆን ውሸተኛው ነገር ላይ እንድታተኩር አድርጎሃል፡፡" አሉ በቀስታ መነኩሴው፡፡እያንዳንዱ የሚናገሩት ቃል ህይወት ይሰጣል፡፡
"አንተ ወደዚህ አለም ከመምጣትህም በፊት የነበረህ እውነተኛ ማንነት አለህ፡፡እሱም ህይወት ራሱ ነው፡፡የዚህ አለም ማንነትህ ሁሉም የውሸት ናቸው፡፡ለምሳሌ ይህ ሰውነትህ አፈር ነው፡፡ህይወት አይደለም፡፡ስምህም ሰዎች ተስማምተው የሰጡህ ጊዛዊ ታርጋ ነው፡፡ድግሪ ካለህም የሚናገረው ኮሌጅ ውስጥ ያሳለፍከውን ጊዜ ነው፡፡ ዝና፣ ትዳር፣ ስልጣንና እዚህ አለም ላይ እኔ ነኝ ብለህ የምታስባቸው ነገሮች ሁሉ አንተን አይደሉም፡፡እዚህ አለም ላይ አንተን የሆነ ነገር የለም፡፡መከበርም፡ መዋረድም.... ድህነትም ፡ ሀብትም.... ዝናም ፡ መረሳትም..መማርም፡ አለመማር...መውለድም ፡ አለመውለድም ሆኑ ሁሉም የዚህ አለም ነገሮች ጊዛዊ ናቸው፡፡ይመጣሉ ይሄዳሉ፡፡ጊዛዊ ያልሆነ ነገር አለ፡፡እሱን ያዘው ልጄ፡፡እሱም ህይወት ራሱ ነው፡፡እውነተኛ ማንነትህ ይህ ነው፡፡" አሉ መነኩሴው፡፡
"ያንን ማንነት እንዴት ነው የማገኘው?" ጠየቀ ልጁ፡፡
"ያንን ማንንነት ለማግኘት ከጫጫታ መለየት አለብህ፡፡መጀመርያ አለም የጫነብህን ኮተት ከራስህ ላይ ልታራግፍ ያስፈልጋል፡፡ትኩረትህን በውስጥህ ወዳለው ፈጣሪ ማይረግ አለብህ፡፡ህይወት አይታይም ፡ አይነካም፡ ቅርጽ የለውም፡ አይሞትም፡ አይገደብም አይገለጽም፡፡ህይወት ራሱ ፈጣሪ ነው፡፡ፈጣሪ አሁን ውስጥ ያለ የማይታይ ግንድ ነው፡፡አንተ ደግሞ የማይታይ ቅርንጫፍ ነህ፡፡ከዚህ ከማይታይ የፈጣሪ ግንድ ጋር ስትገናኝ ያንተ የማይታየው ቅርንጫፍ ያበራል፡፡ያለምንም ነገር መደሰት ትጀምራለህ፡፡" አሉት፡፡እዛው ዛፉ ስር ቁጭ አደረጉት፡፡ሰውነቱን ዘና ካደረጉ በኋላ አይኑን አስከደኑት፡፡ጫካው ውስጥ ያለውን ዝምታ እንዲያደምጥ አዘዙት፡፡ልጁ አእምሮው ጸጥ ረጭ ማለት ጀመረ፡፡ <ራስህን አጥፋው!> የሚለውና ሌሎችም አስፈሪ ድምጾች ከውስጡ ተወገዱ፡፡ጥልቅ በሆነ ዝምታ ውስጥ እየተዋጠ ሲመጣ የእግዚአብሔርን ድምጽ መስማት ጀመረ፡፡ከእግዚአብሔር መንፈስ ጋር መንፈሱ ተዋሀደ፡፡ይህንን አለም ረሳው፡፡ወደ ሰውነቱ ሰላም ሲፈስስ ተሰማው፡፡መንፈሱ በፍቅር ተሞላ፡፡ደስታ አሰከረው፡፡እንዲህ አይነት ስሜት በህይወቱ ተሰምቶት አያውቅም፡፡ሲነቃ ፊቱ እንደ ጸሐይ በራ፡፡ፈገግ እያለ፡
"አባባ ምንድን ነው ያደረጉኝ?" ሲል ጠየቃቸው፡፡
"ምን ሆንክ አሉት?" አሉት፡፡
"እኔ እንጃ....ብቻ በቃ የተሰማኝ ስሜት ከቃል በላይ ነው....ገነት ደርሼ የመጣው ነው የመሰለኝ፡፡ምን አድርገውኝ ነው? እባኮትን ይንገሩኝ፡፡" አላቸው፡፡
"ከእግዚአብሔር ጋር ተገናኝተህ ነው፡፡ዝምታ የፈጣሪ ቋንቋ ነው፡፡ዝም ስትል መንፈስህ ወደ ማይታው የፈጣሪ አለም ትጓዛለች፡፡አምላክህ ጋር ትገናኛለች፡፡ሰላም ፍቅርና ደስታ ወደህይወትህ ይመጣሉ፡፡ብዙ ሰው እግዚአብሔርን አውቃለው ብሎ ያስባል፡፡ግን ከቶ አያውቀውም፡፡እግዚአብሔርን የምታውቀው ስትቀምሰው ብቻ ነው፡፡ቅዱስ ዳዊት እንደሚለው ፈጣሪን መቅመስ አለብህ፡፡በመንፈስ ከእሱ ጋር ስትገናኝ ገነት ከመሄድህ በፊት እዚሁ ምድር ላይ ገነት ምን እንደምትመስል ቅምሻዋን ታያለህ፡፡" አሉት፡፡
"አዎ አዎ! በጣም ልዩ ስሜት ነበር የተሰማኝ፡፡"
"ይህ ስሜት በሁሉም ሰዓት እና ቦታ አለልህ፡፡ነጻ ነው፡፡ግን አንተ ጊዜ እና ገንዘብህን የምታጠፋው ምድራዊ ነገርን ስታሳድድ ነው፡፡ይህ ነገር ደግሞ ቅድም እንዳልኩህ ከንቱ ነው፡፡አሁን የተሰማህ ስሜት ግን ዘለዓለማዊ ነው፡፡ወደ ፈጣሪ አለም መጓዝ ትክክለኛ ሐይል ይሰጣል፡፡የምድር ህይወትህ ሳይቀር በስኬት እንዲሞላ ያደርጋል፡፡አንተ አስቀድመህ ጽድቁንና የእሱን መንግስት ከሁሉ በፊት ፈልግ፡፡ሌላው ሁሉ ይጨመርልሃል፡፡" አሉት፡፡ልጁ ሲመጣ አብሮት የነበረው የጨለማ ስሜት ተወገደበት፡፡አዲስና ትኩስ ሐይል ከመንኩሴው ተጋባው፡፡የውሸት ማንነቱ ሲሞት ተሰማው፡፡ምን ላይ ማተኮር እንዳለበት ተጠለጠበት፡፡የፈጠረውን አምላክ አመሠገነ፡፡መነኩሴውንም ህይወቱን ስላዳኑት አመሰገነ፡፡
📩📩
# share በማድረግ እናንተም ሰው አድኑ!
🎙ኪነ-ጥበብ⛪️
✍️ ስደትና ምሥጢሩ ✍️
༺ ༻
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፮ ቀን ያለውን ወቅት ዘመነ ጸጌ በማለት ሰይማ ወቅቱ ላይ ያተኮረ አገልግሎት ትፈጽማለች፡፡
ጽጌ ማለት አበባ ማለት ነው። ጠቢቡ ሰሎሞን “እስመ ናሁ ክረምት ኀለፈ ወዝናም ገብአ ድኀሬሁ ጽጌ አስተርአየ በውስተ ምድርነ፤ እነሆ ክረምት አለፈ፣ ዝናቡም አልፎ ሄደ፣ አበቦችም በምድር ላይ ተገለጡ፣ የዜማም ጊዜ ደረሰ፣ የቁርዬም ቃል በምድራችን ተሰማ” እንዲል (መኃ. ፪÷፲፩-፲፪)
“እነሆ ክረምት አለፈ” በማለት ጠቢቡ ሰሎሞን የተናገረው የእስራኤል የመከራ ዘመን ማለፉን ለማመልክት ሲሆን መከራን በክረምት መስሎ ተናግሮታል፡፡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንም በምሥጢር ሲተረጉሙት የአዳም የመከራ ዘመን አለፈ ማለት እንደሆነ ያብራራሉ፡፡
ይህንን ወቅት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ምድረ ግብፅ የተሰደደችበትን ጊዜ ታስባለች፡፡ በጌታችን ልደት ሰብአ ሰገል የሕፃኑን መወለድ ተረድተው ሊሰግዱለትና ግብር ሊያገቡለት በኮከብ እየተመሩ ወደ ቤተ ልሔም ለመድረስ ፍለጋቸውን ባጠናከሩበት ወቅት “ኮከቡን በምሥራቅ አይተን እንሰግድለት ዘንድ መጥተናልና የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው?” ብለው ጠየቁ፡፡
ሄሮድስም በሰማ ጊዜ ደነገጠ፤ የካህናት አለቆችንና የሕዝቡን ጻፎች ሁሉ ሰብስቦ ክርስቶስ በየት እንደሚወለድ ጠየቃቸው፡፡ እነርሱም በይሁዳ ክፍል በቤተ ልሔም እንደሆነ ነገሩት፡፡ ሰብአ ሰገልን በምሥጢር አስጠርቶም በቤተ ልሔም መሆኑን ነግሮ ሲመለሱ በእርሱ በኩል እንዲመጡ ዜናውንም እንዲያበስሩት አሰናበታቸው፡፡ (ማቴ. ፪፥፩-፰)
ሰብአ ሰገል በኮከቡ ተመርተው ቤተ ልሔም ደርሰው ለጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰግደው የሚገባውን ወርቅ፣ ከርቤ እና ዕጣን አቅርበው፣ ወደ ሀገራቸው ሊመለሱ በተነሡ ጊዜም የጌታ መልአክ ወደ ሄሮድስ እንዳይገቡ ስለ ነገራቸው በሌላ መንገድ ወደ ሀገራቸው ሄዱ፡፡ ይህን የተረዳው ሄሮድስ በሰብአ ሰገል ማታለል ተበሳጨ “…ወአዘዘ ሐራሁ ወፈነወ ይቅትሎ ኩሉ ሕጻናተ ዘቤተ ልሔም ወዘኩሉ አድያሚሃ፤ ወታደሮቹን በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ ያሉ ሕፃናትን ሁሉ ግደሉ ብሎ አዝዞ ሰደደ፡፡” (ማቴ.፪÷፲፮)
ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ይህንን የቤተ ልሔም ሕፃናትን እልቂት በተመለከተ “… አየሁም እነሆም በጉ በጽዮን ተራራ ቆሞ ነበር፡፡ ከእርሱም ጋር ስሙና የአባቱ ስም በግምባራቸው የተጻፈላቸው መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ” በማለት ገልጾታል፡፡ (ራዕ. ፲፬÷፩-፫) በዚህም ምክንያት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ጋር ተሰደደች፤ ዲያብሎም አሳደዳት፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ የእመቤታችን ስደት በተመለከተ ሲገልጽ “…ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ፤ ፀሐይን ተጎናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የ፲፪ ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች፡፡ እርሰዋም ጸንሳ ነበር፤ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጨንቃ ጮኸች።
ሌላም ምልክት በሰማይ ታየ፤ እነሆም ታላቅ ቀይ ዘንዶ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ነበሩት፣ በራሶቹም ላይ ሰባት ዘውዶች ነበሩት …” (ራዕ. ፩፥፩-፬)
#ሴት የተባለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ቤተ ክርስቲያን ረቂቅ ናት፣ የክርስቶስም አካል ናት፡፡ የምትታየው ቤተ ክርስቲያን በተጋድሎ ላይ ያለች ስትሆን የማትታየው ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ድል ያደረገችው ናት፡፡ ፀሐይ የተባለው ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን በቀንም በሌሊትም የሚያበራ እውነተኛ ብርሃን ነው፡፡ ጨረቃ የተባሉ ቅዱሳን፣ ፲፪ ከዋክብት የተባሉት ፲፪ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት ናቸው፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ “#ምጥ” ስንል በተለያየ ዘይቤ እንደ አገባቡ ይተረጎማል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ “ምጥ” ያለው የድንግል ማርያምን መንገላታት፣ የግብፅ በረሃ ስደትና ጭንቀትን ለማመልከት ነው፡፡
ለምሳሌ፦ ቅዱስ ጳውሎስ፣ ኢሳይያስ እና ሙሴ ምጥን እንደሚከተለው ገልጸውታል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ “#ልጆች ሆይ ክርስቶስ በእናንተ እስኪሣል ድረስ ዳግመኛ ስለ እናንተ ምጥ ይዞኛል” ይላል (ገላ. ፬፥÷፲፱)
#ሙሴ “አሕዛብ ሰሙ፣ ተንቀጠቀጡም፤ በፍልስጥኤም የሚኖሩትን ምጥ ያዛቸው” ይላል፡፡ (ዘጸ. ፲፭፥÷፲፬) እንዲሁም ነቢዩ ኢሳይያስ “ስለዚህ ወገቤ ሕመም ተሞላ፣ እንደምትወልድ ሴት ምጥ ያዘኝ፣ ከሕመሜ የተነሣ አልሰማም ከድንጋጤም የተነሣ አላይም” ብሏል፡፡ በተጨማሪም ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ “ወሬዋ ወደ ግብጽ በደረሰ ጊዜ በጢሮስ ወሬ ምጥ ይይዛቸዋል” እንዲል፡፡ (ኢሳ. ፳፫፥÷፭)
የስደት ምክንያቶች
ስደት በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ በጦርነት፣ በወረርሽኝ፣ እና በሌሎችም ሰው ሠራሽና ተፈጥሯዊ ክስተቶች መነሻነት ሰዎች ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሊሰደዱ ይችላሉ፡፡ አድካሚ ጉዞ፣ መራብ፣ መጠማት እና ሌሎች ችግሮችም ያጋጥማሉ፡፡
በሕግ የተከለከሉ ሥራዎችን በመሥራት ለስደት የሚዳረጉም ብዙዎች ናቸው፡፡ እንደ አዳም “…እነርሱም ቀኑ በመሸ ጊዜ የእግዚአብሔር አምላክን ድምጽ ከገነት ውስጥ ሲመላለስ ሰሙ አዳምና ሚስቱ ከእግዚአብሔር ከአምላክ ፊት በገነት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ” በማለት እንደተገለጸው፡፡ (ዘፍ.፫÷፰)
እንደ እስራኤል ሀገራቸው በጠላት በተወረረ ጊዜ ተማርከው ለስደት የሚዳረጉ “… በውኑ ይህ ሰው ኢኮንያን የተናቀና የተሰበረ የሸክላ ዕቃ ነውና? እርሱና ዘሩስ በማያውቁት ምድር ስለምን ተጥለው ወደቁ?” እንደተባለ (ኤር. ፳፪÷፳፰)
የሰው ሕይወት ጠፍቶባቸው የሚሰደዱም አሉ፡፡ “… ፈርዖንም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ሙሴን ሊገድለው ፈለገ፡፡ ሙሴ ግን ከፈርዖን ፊት ኮበለለ፤ በምድያም ምድርም ተቀመጠ፡፡ (ዘፍ. ፪÷፲፩-፲፮) እንደ ሄሮድስ በሥጋዊ ቅንዓት ተነሳሥቶም አንዱ መንግሥት ሌላውን መንግሥት ሊያጠፋው ሲነሣ ሕዝብ ለስደት ይዳረጋል፡፡
እግዚአብሔር ለምን ወደ ግብፅ መሰደድን መረጠ?
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ጋር ወደ ግብፅ መሰደድ ምክንያት አንዱ ቀደምት አበው ወደ ግብፅ ተሰደው ስለነበር ነው፡፡ ለምሳሌ፡-
፩. አብርሃም ከሚስቱ ከሣራ ጋር በምድር ሁሉ ላይ ረሃብ በሆነ ጊዜ ወደ ግብፅ ተሰዶ ነበር፡፡ ግብፅም በደረሱ ጊዜ አብርሃም እንዳይገድሉት ስለፈራ ሣራን ስለ አንቺ ነፍሴ ትድን ዘንድ ወንድሜ ነው በዪ ብሏት ነበር፡፡ (ዘፍ. ፲፪÷፲-፳)
፪. ዮሴፍ በወንድሞቹ ተሽጦ ወደ ግብፅ ተሰዷል፡፡ ፲፯ ዓመት በሆነው ጊዜ ከአባቱ ልጆች ከባላና ከዘለፋ ልጆች ጋር በግ ይጠብቅ ነበር፡፡ ያየውንም ሕልም ለወንድሞቹ ነገራቸው፡፡ እነርሱም በቅንዓት ተነሣስተው ወንድማቸውን ከሚገድሉት ለእስማኤላውያን ሊሸጡት ተስማሙ፡፡ “እነዚያ እስማኤላውያን ነጋዴዎችም ሲያልፉ ወንድሞቹ የሴፍን ጎትተው አወጡት፤ ለእስማኤላውያንም በሃያ ብር ሸጡት፡፡ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወሰዱት” እንዲል፡፡ (ዘፍ. ፴፯፥፳፰)
ጌታችን ለምን ተሰደደ?
፩. ስደትን ለቅዱሳን ባርኮ ለመስጠት፣
፪. ትንቢተ ነቢያትን ለመፈጸም፣ (ኢሳ.19÷1፤ (ሆሴ. ፲፩÷፩))
፫. ገዳማተ ግብጽን እና ገዳማተ ኢትዮጵያን ለመባረክ፣
፬. ሰይጣንን ከሰው ልቡና አስወጥቶ ለመስደድ፡፡
የሄሮድያዳም ልጅ የመጥምቁን ራስ ወስዳ ለእናቷ ልትሰጣት ስትል ዐይኖቹ እንደፀሐይ ሲያበሩ ብታየው "ንጉሡን አትፈራውምን?" በማለት ተቆጣች፡፡ በመቀጠልም "እነዚህን ዐይኖቹን በወስፌ እያወጣሁ እጥላቸዋለሁ፣ ምላሱንም ደግመኛ እንዳይገሥጽ ቆርጨ እጥላቸዋለሁ" በማለት ፊቱን በጥፊ ለመምታት እጇን ስታነሣ ያንጊዜ የዮሐንስ ራስ ክንፍ አውጥታ በረረች፡፡ በአየር ላይ ሳለችም ዳግመኛ "የተረገምሽ ሄሮድያዳ የባልሽን ወንድም ሄሮድስን ማግባት አይገባሽም፣ ቀድሞ የምዘልፍሽ አሁንም የምዘልፍሽ እኔ ነኝ" እያለች የዮሐንስ ራስ የቤቱን ጣሪያ ሰንጥቃ እንደንሥር በአየር በራ ሄደች፡፡
ከዚህም በኋላ ለጥፊ የዘረጋቻቸው የሄሮድያዳ እጆቿ ከትከሻዋ እየተቆረጡ መሬት ላይ ወደቁ፤ እውነቷንም መሬት አፏን ከፍታ ዋጠቻት፡፡ ዘፋኟ ልጇም አብዳ የቤተ መንግሥቱን ዕቃ ሁሉ መሰባበር ጀመረች፡፡ የንጉሡ አንዱ ጭፍራም የሄሮድያዳን በእሳት እንደተለበለበ የግንድ እሳት የመሰለና የተቆረጠ እጇን አምጥቶ ለሄድሮስ ሰጠውና የሆነውን ነገረው፡፡ ንጉሡም ነገሩ እውነት መሆኑን ሄዶ ባየ ጊዜ በሀፍረት እጅግ ተሸማቀቀ፡፡ ዘፍና በማስደሰት የዮሐንስን ራስ እንዲያስቆርጠው ያደረገችው የሄሮድያዳ ሴት ልጅም አብዳ በቤተ መንግሥቱ ስትለፈልፍ አገኛት፡፡ ሄሮድስም መኳንንቶቹን "በቤተ መንግሥቴ የተደረገውን ይህን ነገር ለማንም አትንገሩ" ብሎ አማላቸው ነገር ግን ያበደችው የሄሮድያዳ ሴት ልጅ ራሷ ሄዳ ሄሮድስን "የወንድምህን የፊሊጶስን ሚስት ማግባት ፈጽሞ አይገባህም" እያለች በመኳንንቶቹ ፊት ገሠጸችው፡፡ ንጉሥ ሄሮድስም ይህን ቃል ከእርሷ በሰማ ጊዜ እጅግ ተናደደና "ቀደሞ ያልሆነ ሥራ ታሠራ በኋላ ደግሞ ምሥጢር ታወጣ ንሣ በሰይፍ ቁረጣት" ብሎ አንገቷን በሰይፍ አስቆረጣት፡፡ ሥጋዋንም ዓሣ አንበሪ ተቀብሎ ዋጣት፡፡ ሄሮድም የወንደሙን ሚስት ሲያገባ አስቀድሞ አግብቷት የነበረችውን ሚስቱን በግፍ አባሯት ነበር፡፡ እርሷም ይህንን ሄሮድስ ያደረሰባትን ግፍ ለአባቷ አርጣ ብትነግረው አባቷ ብዙ ጦር ሰብስቦ መጥቶ ምድረ ገሊላን በኃይል አፈራረሳት፡፡ የበላዩ ንጉሥ ቄሳርም የገሊላን መፍረስና መውድም ሲሰማ ምክንያቱን ቢጠይቅ ሄሮደስ ባደረገው ግፍ ምክንያት መሆኑን ነገሩት፡፡ ቄሳርም ሄሮድስን ከሥልጣኑ ሽሮ አጋዘውና በወህኒ ጣለው፡፡ ሄሮድስም በወህኒ ቤት ሳለ አብዶ ራሱን ስቶ የገዛ አካሉን እየነጨ እየበላ ቷ ብሎ ፈንድቶ ተልቶ ሸቶ እጅግ ክፉ አሟሟት ሞተ።
ከዚህም በኋላ ጌታችን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ ራስ መለስ ብሎ እንዲህ በማለት ሥልጣን ሰጣት፡- "እነሆ መንፈስሽን በራስሽ ውስጥ አድርጌልሻለሁ በሰማይም የምትበሪበት እንደ ንሥር ክንፍ ሰጥቼሻለሁና እንደንስር በሰማይ እየበረርሽ በዓለም ሁሉ እየዞርሽ የሄሮድስንና የሄሮድያዳን ኃጢአት ግለጭባቸው፤ እስከ 15 ዓመት ድረስ ገቢረ ተአምራት የምታደርጊበት ኃይሌን መንፈሴን በእራስሽ ውስጥ አድርጌልሻለሁ" አላት፡፡ ዳግመኛም ጌታችን ዮሐንስን "እኔም ከ3 ዓመት በኋላ ለአዳም የሰጠሁትን ተስፋ ፈጽሜ በሞቴ ወደ ሲኦል ወርጄ ነፍሳትን ከዲያብሎስ እጅ ማርኬ በ3ኛው ቀን ከሙታን ተለይቼ ተነሥቼ ወደ ባሕርይ ክብሬ ተመልሼ ወደ ሰማይ አርጌ ባባቴ ቀኝ በተቀመጥኩኝ ጊዜ ከ15 ዓመት በኋላ ርጉም ሄሮድስ ካስፈጃቸው ከትንንሾቹ ሕፃናት ጋራ ትሆን ዘንድ በአባቴ ፈቃድ እራስህን ተሸክመው ወደ አባትህ ወደ ዘካርያስ ያመጧት ዘንድ እኔ መላእክትን አዛቸዋለሁ፡፡ ዛሬ ግን ነፍስህን በእኔ ቀኝ ባባትህ በዘካርያስ አጠገብ አኑሬያታለሁ መንፈስህንም እስከ 15 ዓመት በእራስህ ውስጥ እንድትኖር አዝዣታለሁ፣ ሥጋህም ከነቢዩ ከኤልሳዕ ጋር እንዲቀመጥ አድርጌያለሁ" አለው፡፡
ከዚህም በኋላ ጌታችን እንዳዘዛት የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ እራስ እንደንስር በአየር ላይ እየበረረች የምታስተምር ሆነች፡፡ በምሥራቅ በኩል ሄዳ በዐረብ አገር ውስጥ በሰማይ ላይ ስታስተምር በዚህች ዕለት ጥቅምት 30 ቀን በግልጽ ታየች፡፡ ነጋዴዎች ድምጹዋን ሰምተውና አይተዋት እጅግ ተደስተው ገንዘባቸው ሁሉ ጥለው የቅዱስ ዮሐንስን እራስ ለመያዝ ሰውነታቸውን ብዙ አደከሙ፡፡ ነገር ግን ለመያዝ አልተቻላቸውም፡፡ ከዚህም በኋላ ከሰማይ "የምትያዝበት ጊዜ ስላልደረሰ ሰውነታችሁን አታድክሙ" የሚል ድምጽ ከሰማይ መጣላቸው፡፡ መፈለጋቸውንም ተው፡፡ የቅዱስ ዮሐንስም እራስ 15 ዓመት ስታስተምር ኖራ ሚያዝያ 15 ቀን በዐረብ ሀገር ዐረፈች፡፡ የታዘዙ ቅዱሳን መላእክትም መጥተው ከቅዱስ ዮሐንስ እራስ ከተባረኩ በኋላ በታላቅ ዝማሬ እያመሰገኑ የቅዱስ ዮሐንስን አንገት ወስደው በነቢዩ ኤልሳዕ መቃብር ውስጥ አብረው ቀበሯት፡፡ ቅድስትን ነፍሱንም እያመሰገኑ ወደ ሰማይ አሳረጓት፡፡ በዚያም በሥሉስ ቅዱስ ዙፋን ፊት ወድቃ ከሰገደች በኋላ አባቷ ዘካርያስንና እናቷ ኤልሳቤጥን እጅ ነሳቻቸው፡፡ ከዚህም በኋላ በ3ኛው ሰማይ ውስጥ ተቀመጠች፡፡ ጌታችን ሦስቱን ሰማየ ሰማያት ርስት ጉልት አድርጎ ሰጥቶታልና፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባት_ባሕታዊ_አብርሃም
በዚህች ቀን መኑፍ ከሚባል አገር በገድል የተጸመደ ቅዱስ አባት ባሕታዊ አብርሃም አረፈ። የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚያመልኩ ናቸው በዚህም ዓለም ገንዘብ እጅግ ባለጸጎች ነበሩ።
ይህም ቅዱስ በአደገ ጊዜ የምንኵስናን ልብስ ሊለብስ ሽቶ በላዕላይ ግብጽ ወደሚገኝ ወደ ሀገረ አክሚም በመርከብ ተጭኖ ሔደ ወደ አባ ጳኵሚስም ደረሰ እርሱም የምንኲስና ልብስን አለበሰው በገድልም በመጸመድ ሥጋውን አደከመ በአባ ጳኵሚስም ማኅበራዊ ኑሮ ውስጥ ሃያ ሦስት ዓመት ያህል በማገልገል ኖረ።
ከዚህም በኋላ በዋሻ ውስጥ ብቻውን ይኖር ዘንድ እንዲአሰናብተው አባ ጳኵሚስን ለመነው እርሱም ፈቀደለት ዓሣ የሚያሠግሩበትን መረብ የሚሠራ ሆነ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አንድ ሰውን አመጣለት ያም ሰው መረቡን ሽጦ ምግቡን አተር ይገዛለታል የተረፈውንም ለድኆች ይሰጣል የምግቡም መጠን ሁልጊዜ ማታ ማታ አንዲት እፍኝ ከጨው ጋር በውኃ የራሰ አተር ነው።
እንዲህም እየተጋደለ በዚያች ዋሻ ዐሥራ ሰባት ዓመት ኖረ ልብሱም ከገዳም ሲወጣ የለበሰው ከዘመን ርዝመት የተነሣ አርጅቶ ተበጣጠሰ ሥጋውንም በጨርቅ የሚሸፍን ሆነ። በየሁለት ዓመትም ወደ መነኰሳቱ ገዳም በመውጣት ሥጋውንና ደሙን ተቀብሎ ወደ በዓቱ ይመለስ ነበር። በዚያችም ዋሻ መኖር በጀመረባት ዓመት ሰይጣናት ወደ ርሱ በመምጣት ምትሐት እየሠሩ ተፈታተኑት እርሱ ግን ውሻን እንደሚአበር ሰው አበረራቸው።
ዕረፍቱም በቀረበ ጊዜ ያን ሕዝባዊ ሰው ልኮ የአባ ጳኵሚስን ረድእ አባ ቴዎድሮስን አስጠራው በመጣም ጊዜ ሰግዶ ሰላምታ ሰጠው እንዲጸልይለትና በጸሎቱም እንዲአስበው ለመነው። ከዚህም በኋላ ሁለቱም በአንድነት ጸለዩ በዚያንም ጊዜ አባ አብርሃም በርከክ ብሎ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ አባ ቴዎድሮስም ወደ መነኰሳቱ ላከ እነርሱም መጥተው ከሥጋው በረከትን ተቀበሉ ሥጋውንም ወሰደው ከቅዱሳን ሥጋ ጋር በአንድነት አኖሩት።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምትና_ሚያዝያ
#ከገድላት_አንደበት)
ጥቅምት 30/2016 #ቅዱስ_ማርቆስ
#ቅዱስ_ዮሐንስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሳኑ ስም ለምናመሰግንበት ቅዱሳኑ በምልጃ ፀሎታቸዉ እንዲያስቡን ለምንማፀንበት አመታዊ ክብረ በአላቸው እንኳን አደረሰን
👉በዚህ እለት #ቅዱስ_ማርቆስ ወንጌላዊ ዘአንበሳ ልደቱ ሲሆን የመጥምቀ መለኮት #ቅዱስ_ዮሐንስ የከበረች ራሱ ከተሠወረችበት የተገለፀችበት እለት ነዉ
👉በዚህች ዕለት ከ72ቱ አርድእት አንዱ የሆነ ወንጌላዊ ሐዋርያ ሰማዕት ዘአንበሳና ርዕሰ ሊቃነ ዻዻሳት የተባለ ቅዱስ ማርቆስ ተወልዷል
👉ቅዱስ ማርቆስ እናቱ ማርያም አባቱ አርስጥቦሎስ ይባላሉ በልጅነቱ ኦሪትንና የዘመኑን ጥበብ ሥጋዊ በሚገባ ተምሮ ክርስቶስን ከቤተሰቦቹ ጋር ተከትሏል የመጀመሪያ ስሙ ዮሐንስ ሲሆን ከ120ው ቤተሰብ በእድሜ በጣም ትንሹ እርሱ ነበር
👉ለሶስት ዓመታት ከጌታ እግር ሥር ተምሮ በበዓለ ሃምሳ ፀጋ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ብዙ ደክሟል በተለይ የግብፅና የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን አባት ነው ክህነትን ያገኘን ከርሱ ነውና
👉ቅዱስ ማርቆስ 16 ምዕራፍ ያለውን ወንጌሉን ሲጽፍ ኪሩብ ገጸ አንበሳ በቀኙ ሊቀ ሐዋርያት በግራው ሆነው ይራዱት ነበር ቅዱሱ ከቅዱስ ዻውሎስ ከበርናባስና ዼጥሮስ ጋር ተጉዟል ከብዙ ስቃይና መከራ በኋላ ሰሜን አፍሪካ አካባቢ አረማውያን ገድለውታል ይህቺ ዕለት የልደቱ መታሠቢያ ናት::
👉ዳግመኛ በዚህ ቀን የቅዱስ ማርቆስን ወላጆችን እናስባቸው ዘንድ ይገባል ቅዱስ አርስጥቦሎስ (አባቱ) የጌታ ቅን አገልጋይ የነበረ ቅድስት ማርያም (እናቱ) ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ ጌታችንን ያገለገለች ቤቷን ለሐዋርያትና ለጌታ በስጦታ ያበረከተች ቅድስት ናት::
👉ቤቷም (ጽርሐ ጽዮን) የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ስትሆን ይህች ቤት መንፈስ ቅዱስ ወርዶባታል የእመቤታችን ግንዘትም ተከናውኖባታል::
👉የወንጌላዊዉ #ቅዱስ_ማርቆስ የህይወት ታሪኩ ከብዙ በጥቂቱ ይሄን ይመስላል #እግዚአብሔር አምላካችን ከቅዱሳኑ ረድኤት በረከት ያሣትፈን ምልጃ ፀሎታቸዉ ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን" 💒 💚 💛 ❤ 💒
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
✞✞✞ ጥቅምት 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞
+" ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ "+
✞✞✞ በዚሕች ዕለት ከ72ቱ አርድእት አንዱ የሆነ: ወንጌላዊ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ዘአንበሳና ርዕሰ ሊቃነ ዻዻሳት የተባለ ቅዱስ ማርቆስ ተወልዷል ::
+ቅዱስ ማርቆስ እናቱ ማርያም: አባቱ አርስጥቦሎስ ይባላሉ:: በልጅነቱ ኦሪትንና የዘመኑን ጥበብ ሥጋዊ በሚገባ ተምሮ ክርስቶስን ከቤተሰቦቹ ጋር ተከትሏል:: የመጀመሪያ ስሙ ዮሐንስ ሲሆን ከ120ው ቤተሰብ በእድሜ በጣም ትንሹ /20 ዓመት/ እርሱ ነበር::
+ለ3 ዓመታት ከጌታ እግር ሥር ተምሮ: በበዓለ ሃምሳ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ብዙ ደክሟል:: በተለይ የግብፅና የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን አባት ነው:: ክህነትን ያገኘን ከርሱ ነውና::
+ቅዱስ ማርቆስ 16 ምዕራፍ ያለውን ወንጌሉን ሲጽፍ ኪሩብ ገጸ አንበሳ በቀኙ: ሊቀ ሐዋርያት በግራው ሆነው ይራዱት ነበር:: ቅዱሱ ክቅዱስ ዻውሎስ: ከበርናባስና ዼጥሮስ ጋር ተጉዟል:: ከብዙ ስቃይና መከራ በኋላ ሰሜን አፍሪካ አካባቢ አረማውያን ገድለውታል:: ይህቺ ዕለት የልደቱ መታሠቢያ ናት::
+ዳግመኛ በዚህ ቀን የቅዱስ ማርቆስን ወላጆችን እናስባቸው ዘንድ ይገባል:: ቅዱስ አርስጥቦሎስ (አባቱ) የጌታ ቅን አገልጋይ የነበረ: ቅድስት ማርያም (እናቱ) ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ: ጌታችንን ያገለገለች ቤቷን ለሐዋርያትና ለጌታ በስጦታ ያበረከተች ቅድስት ናት::
+ቤቷም (ጽርሐ ጽዮን) የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ስትሆን ይህች ቤት መንፈስ ቅዱስ ወርዶባታል:: የእመቤታችን ግንዘትም ተከናውኖባታል::
+እግዚአብሔር ከሐዋርያዊው ቅዱስ ቤተሰብ በረከትን ያድለን::
+" ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ "+
+ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)
*የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል!
እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር::
*ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::
*ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::
*የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በኋላ በዚህች ቀን (ሰኔ 30) ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::
*ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ 2 ዓመት ከ6 ወር በሆነው ጊዜ ሰብአ ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕጻናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕጻን ነገሩት:: "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕጻን አለና እሱንም ግደል" አሉ::
*እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል:: አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕጻኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ3 (5) ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ 5 (7) ዓመት ሲሞላው ግን እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ ዘካርያስና ስምዖን ወርደው ቀበሯት::
*ሕጻኑ ዮሐንስ ሲያለቅስ ድንግል ማርያም ስንት አገር አልፋ ሰማችው:: እርሷም ስደት ላይ ነበረችና:: ከጌታ ጋር በደመና ሒደው ድንግል አቅፋ አጽናናችው:: ጌታንም "እንውሰደው ይሆን?" አለችው:: ጌታችን ግን "ለአገልግሎት እስክጠራው እዚህ ይቆይ" አላት:: ባርካው: አጽናንታውም ተለያዩ::
*ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ በኋላ በዚያ ቆላ የግመል ጠጉር ለብሶ: ጠፍር ታጥቆ ተባሕትዎውን ቀጠለ:: ለ25 (23) ዓመታትም በንጽሕና ሲኖር ከምድር አራዊትና ከሰማይ መላእክት በቀር ማንንም አላየም:: ይሕችን ዐመጸኛ ዓለምም አልቀመሳትም::
*ከዚህ በኋላ 30 ዘመን ሲሞላው እግዚአብሔር ከሰማይ ተናገረው:: "ሒድ! የልጀን ጐዳና ጥረግ" አለው:: ነቢያት ስለዚህ ነገር ተናግረው ነበርና:: (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) አባቱ ዘካርያስም "ወአንተኒ ሕጻን ነቢየ ልዑል ትሰመይ: እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ" (ሉቃ. 1:76) ብሎ መንገድ ጠራጊነቱን ተናግሮ ነበርና::
*ቅዱስ ዮሐንስ በዚያ ጊዜ በኃይለ መንፈስ ቅዱስ እየገሰገሰ ከበርሃ ወደ ይሁዳ መጣ:: ያዩት ሁሉ ፈሩት: አከበሩት:: ቁመቱ ቀጥ ያለ: ጽሕሙ እንደ ተፈተለ ሐር የወረደ: ጸጉሩ የቁራ ያህል የጠቆረ: መልኩ የተሟላ: ግርማው የሚያስፈራ ገዳማዊ ነውና::
*ፈጥኖም ሕዝቡን ለንስሃ ሰበከ: ለንስሃም በርካቶችን አጠመቃቸው:: በዚህ አገልግሎት ለ6 ወራት ቆይቶ ጌታችን ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ዮሐንስ ሰማይን ከነግሱ: ምድርን ከነልብሱ የያዘ ፈጣሪ 'አጥምቀኝ' ብሎ ሲመጣ ደነገጠ:: የሚገባበትም ጠፋው::
*"እንቢ ጌታየ! አንተ አጥምቀኝ" አለው:: ጌታ ግን "ፈቅጄልሃለሁ" አለው: አጠመቀው:: በዚህ ምክንያት ይሔው እስከ ዛሬም "መጥምቀ መለኮት" ሲባል ይኖራል:: ቅዱስ ዮሐንስ በመጨረሻ ሔሮድስን ገሰጸው:: ንጉሡም ተቀይሞ ለ7 ቀናት አሠረው::
*በዚህች ቀንም ልደቱን ባከበረ ጊዜ ወለተ ሔሮድያዳ በዘፈን አጥምዳ አስማለችው:: እርሱም የታላቁን ነቢይ ራስ አስቆርጦ በወጪት አድርጐ ሰጣት:: አበው "እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር" ይላሉ:: የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ በርራ ስትሔድ አካሉን ግን ደቀ መዛሙርቱ ቀብረውታል:: (ማቴ. 3:1, ማር. 6:14, ሉቃ. 3:1, ዮሐ. 1:6)
*ርጉም ሔሮድስ አንገቱን ካስቆረጠው በኋላ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራሱ የጸጋ ክንፍ ተሰጥቷት ጌታችን ወዳለበት ደብረ ዘይት ሔዳ በፊቱ ሰገደች:: ቅዱሳን ሐዋርያት በአዩት ነገር ተገርመው ራሱን እጅ ነሷት::
*ከዚሕ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ዮሐንስ ራስ የማስተማር ስልጣን ሰጥቶ አሰናበታት:: በመላው ዓለም ለ15 ዓመታት ስትሰብክ ኑራ ዓረቢያ ውስጥ ዓርፋለች::
✞✞✞ ይህች ዕለት ለቅዱሱ 'አስተርዕዮተ ርዕሱ' ወይም ቅድስት ራሱ ከተወረችበት የተገለጠችበት ነው::+ጥቅምት 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ አርስጥቦሎስ (አባቱ)
3.ቅድስት ማርያም (እናቱ)
በዚያንም ጊዜ ስሙ በስጥዮስ የሚባል አንድ ክርስቲያናዊ ሰው ተነሥቶ ወደ ቅዱስ ድሜጥሮስ ሔደ እንዲጸልይለትና በሥጋውም ሁሉ አሸናፊ በሆነ በመስቀል ምልክት እንዲአማትብበት ለመነው። እርሱም በላዩ ጸለየለት በሥጋውም ሁሉ ላይ በመስቀል አማተበበት ከዚህም በኋላ ወደ ንጉሥ ገብቶ ከዚያ ሥጋው ግዙፍ ከሆነው ጋር ያታግለው ዘንድ ለመነው ንጉሡም ፈቀደለት በታገሉም ጊዜ ሥጋው የደነደነውን ያ ክርስቲያናዊ ሰው አሸንፎ ጣለው ንጉሡም አዘነ አደነቀም ሥጋው የደነደነውም በመሸነፉ አፈረ ተመክቶበት ነበርና።
ንጉሡም ስለዚህ ነገር ወታደሮቹን ጠየቀ እነርሱም ቅዱስ ድሜጥሮስ በላዩ እንደጸለየለትና በሥጋውም ላይ በመስቀል ምልክት እንዳማተበበት ነገሩት።
ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ በቅዱስ ድሜጥሮስ ላይ እጅግ ተቆጣ ለአማልክትም ዕጣን እስከሚአሳርግ ድረስ እንዲገርፉት አዘዘ ንጉሡም እንዳዘዘ እንዲሁ አደረጉበት የንጉሡንም ትእዛዝ ባልሰማ ጊዜ እስከሚሞት በጦሮች እንዲወጉት ሁለተኛ አዘዘ።
ለቅዱስ ድሜጥሮስም ይህን ፍርድ ነገሩት ሃይማኖቱን ትቶ ለአማልክት የሚሰግድ መስሏቸው ነበርና ቅዱስ ድሜጥሮስም እኔ ከዕውነተኛ አምላክ ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ለረከሱ አማልክት እሰግድ ዘንድ ዕጣን ማሳረግም አልፈቅድም የወደዳችሁትን አድርጉ አላቸው።
በዚያንም ጊዜ ንጽሕት ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ እስከ ሚሰጥ በጦር ወጉት ሥጋውንም በጣሉት ጊዜ ምእመናን ወደ ርሳቸው ወሰዱት የስደቱም ወራት እስከሚያልፍ በሣጥን አድርገው በቤታቸው ውስጥ ሠውረው አኖሩት።
የስደቱም ወራት ከአለፈ በኋላ እግዚአብሔር ገለጠውና ከዚያ አወጡት ያማረች ቤተ ክርስቲያንንም በተሰሎንቄ አገር ሠሩለት ሥጋውንም በውስጧ አኖሩ ድንቅ የሆነ ታላቅ ተአምርን እያደረገ እስከ ዛሬ አለ።
ሽታውም እጅግ ጣፋጭ የሆነ የሽቱ ቅባት ከእርሱ ይፈሳልና በእምነት የሚቀቡትን በሽተኞች ሁሉንም ያድናቸዋል። ይልቁንም በዕረፍቱ መታሰቢያ ቀን ከሌሎቹ ዕለታት ተለይቶ በብዛት ይፈሳል ከአውራጃው ሁሉ ብዙዎች ሰዎችም ይመጣሉ ከዚህም ቅባት ወስደው በማሰሮቻቸው ያደርጋሉ ይቺ ምልክትም እስከ ዓለም ፍጻሜ በመኖር እንደምትገኝ ደጋጎች ካህናት ምስክሮች ሆኑ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ጸቃውዐ_ድንግል (ዘደብረ ዘኸኝ)
በዚህችም ቀን የተመሰገነና የከበረ የደብረ ዘኸኝ መምህር ጸቃውዐ ድንግል አረፈ። የዚህም ቅዱስ አባቱ ካህን ነው በጥበብና በበጎ ተግሣጽም አሳደገው መለኮታዊ ትምህርትን ሁሉ አስተማረው አድጎ አርባ ዓመትም በሆነው ጊዜ አባቱ ከአንድ ገዳም ውስጥ መነኰሰ ለመምህርነትም ተመርጦ በአባ ገብረ ማርያም ወንበር ላይ ተሾመ።
በዚያንም ጊዜ አባቱ ለልጁ የምንኵስና ልብስ አለበሰው ስሙንም ጸቃውዐ ድንግል ብሎ ሰየመው ከዚያችም ጊዜ ጀምሮ ያለ ማቋረጥ በጾም በጸሎት ብዙ በመስገድም ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ ። ከዚህም በኋላ አባቱ በአረፈ ጊዜ በአባቱ ፈንታ ተሾመ መንጋዎቹንም እንደ ሐዋርያት ሥርዓት በመልካም አጠባበቅ ጠበቃቸው።
በሌሊቱም ሁሉ ከባሕር ውስጥ ቁሞ ያድራል ከባሕሩም ሲወጣ ወዙ በምድር ላይ እስከሚንጠፈጠፍ ስግደትን ያዘወትራል ምግቡም ደረቅ እንጀራ ነው ጠጅ ወይም ጠላ አይጠጣም እግዚአብሔርም በእጆቹ ላይ ተአምራትን አደረገ በጐዳናም ሲጓዝ ከታናሽነቱ ጀምሮ ሒዶ የማያውቅ መፃጉዕን አገኘ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ብሎ የተጸለየበትን ውኃ በላዩ ረጨ በመስቀልም ምልክት አማተበው በዚያንም ጊዜ ዳነ ። ከዚህም ዓለም የሚለይበት ሰዓት በደረሰ ጊዜ ጥቂት ታሞ በሰላም አረፈ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት እና #ከገድላት_አንደበት)
መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር በማኅበረ ኤዶምያስ መንፈሳዊ ግሩፕ ላይ እየተጠየቀ ነው ተሳተፉ ።ግሩፑ ላይ ላልተቀላቀላችሁ ግሩፑን ሊንክ በመንካት ተቀላቀሉ❤
/channel/edomiyass21
/channel/edomiyass21
/channel/edomiyass21
/channel/edomiyass21
/channel/edomiyass21
እናንተ በፈጣሪ ጥያቄና መልስ መጠያየቅ ጀመራቹህ እንዴ የትኛው ነው ትክክል የትኛውነው ትክክል ያልሆነ እያላቹ መጠያየቅ ጀመራቹህ እንዴ ኦፍፍፍፍፍፍፍ እንዴት ያላቹህ ናቹል ተፈለጋቹህ በሌላ መጠያየቅ ትችላላቹህ እሽ
Читать полностью…ህዳር 3/2016 #ባዕታ_ማርያም
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን ለምናመሰግንበት እናታችን #ባዕታ_ማርያም ከልጇ ከወዳጇ እንድታማልደን ለምንማፀንበት ወደ ቤተ መቅደስ ለገባችበት ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን
👉እናታችን ባዕታ በቅድስናና በንፅህና ፀንተሽ በቤተ መቅደስ የኖርሽ ፀጋን የተመላሽና የደስታ መገኛ ሆይ በልጅሽ #በክርስቶስ ስም ላመንን ለእኛ ለወንዶችና ለሴቶች አገልጋዮችሽ ትለምኝልን ዘንድ ይገባሻል
👉እናታችን #ባዕታ_ማርያም የንፅህና አዳራሽና ከተለዩ የተለየሽ መቅደስ አንቺ ነሽ የከበረዉ ቃል ኪዳንሽ ይጠብቀን በዚሁ ዕለት በመታሰቢያ በአላቸው የሚዉሉ ቅዱሳን ምልጃ ፀሎታቸው አይለየን "አሜን" 💒 💚 💛 ❤️ 💒
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች ከይቅርታ ጋር ይህ መዝሙር ሙሉ ከአላችሁ ላኩኝ ወይ ርእሱን ነገሩኝ
Читать полностью…የሀዋርያት ታሪክ ከታሪክ ማህተም
https://youtube.com/watch?v=f51Ify3s0Lc&si=hNmU-wGwjYxLGs_Q
ህዳር 2/2016 #ሰንበተ_ክርስቲያን
#ማህሌተ_ፅጌ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከሰንበት ረድኤት በረከት ያሣትፈን "አሜን"
#ተፈፀመ_ማህሌተ_ፅጌ
👉እናታችን #ማርያም የደካማ ምርኩዝ ስምሸን ጠርቶ አንቺን ተማፅኖ ያፈረ ማነው የፍቅርሸ ፆም ተፁሞ ሊፈታ ቀናቶች ሲቀሩት በምሰጋና በእልልታ በማህሌተ ፅጌ ያለፉት ሰንበታት #ተፈፀመ_ማህሌተ_ፅጌ"ልንል ሰዓታት ቀረን
👉ምሰጋና ለእናትና ልጇ ስንት የማይታለፉ የሚመሰሉ ከባድ ጊዚያትን ሰምሸን ጠርተን ባንቺ ተመርኩዘን አለፍን ወለላይቱ መጥፎ ቀንን ሁሉ አሳለፍሸን ሰምሽን የምንጠራው ልጆችሸን መመኪያችን ተሰፋችን አማላጃችን ነሸና ከደጅሸ አቁሚን አታጥፊን
👉የእናታችን ማርያም ወዳጆች ለአመቱ አድርሳን ለማህሌቷ ታቁመን ቸሩ ሆይ ሰለ እናትህ ብለህ ተለመነን ሀገራችንን ጠብቅልን
👉እነሆ በእመቤታችን ስም ተሰባስበን አበባ ይዘን ልጅዋን በአበባ እርስዋን በጽጌረዳ እየመሰልን የምንዘምርበት ያ የተወደደው የምስጋና የዝማሬ ወር አለፈ እመቤታችን ድንግል ማርያም ሆይ አንቺ የጊዮርጊስ የክብር ዘውድ ነሽ እያሉ በተመስጦ እንደ ቅዱስ ያሬድ የቅዱስ ያሬድ ልጆች ሊቃውንቱ እናታቸውን ሲያመሰግኑ የሚያሳይ ግሩም #ማኅሌተ_ፅጌ
👉እመቤታችን ዘውድነቷ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ብቻ ሳይሆን ውዳሴዋን ቅዳሴዋን እየደገመ ስሟን እየጠራ ለሚማጸን በአማላጅነቷ በቃል ኪዳኗ ለሚያምን ሁሉ ዘውድ ናት
👉ምዕመናንም ትምክህተ ዘመድነ እያሉ ይዘምሩላታል ያመስግኗታል ድንግል ሆይ የባህርያችን መመኪያ ነሽ ተስፋችን ነሽ የድህነታችን ምልክታችን ነሽ እያሉ በእናትነቷ ጥላ ስር ያሉ ምዕመናን ይዘምሩላታል እርስዋም እንደ ቅዱስ ኤፍሬም ትባርካቸዋለች ሁላችንንም እናታችን ትባርከን
👉ለእኛም ለልጆችሽ ሞገስ ሁኝን አማላጅነትሽ ቃል ኪዳንሽ አይለየን የሰማይና የምድር ንግስት የእናታችን የእመቤታችን ማርያም ምስጋና #ማህሌተ_ፅጌ እነሆ ተፈፀመ የተባረከ ሰንበተ ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" 💒 💚 💛 ❤ 💒
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
ዘሳድሳይ ሣምንት ጽጌ ወበዓለ ታዴዎስ ሐዋርያ ስርዓተ ማህሌት
🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀
ነግሥ (የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዐተ ማኅሌት መጀመሪያ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
@menkir_tube
@menkir_tube
መልክአ ሥላሴ፤
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።
@menkir_tube
ዚቅ፦
ሃሌ ሉያ ለክርስቶስ ይደሉ ስብሐት ለዘአብፅሐነ እስከ ዛቲ ሰዓት እግዚኣ ለሰንበት አኰቴተ ነዓርግ ለመንግሥትከ ምድረ ጽጌ አሠርጎከ
@menkir_tube
ዓዲ ዚቅ
አሠርገወ ገዳማት ስን በመንክር ኪን አርአያሁ ዘገብረ ሰሎሞን ጥቀ ኢለብሰ በኩሉ ክብሩ ከመ አሎን ጽጌያት ኢቀደምት ወኢያኃርት :ዓራዛተ ሰርጎ ነሢኦሙ ኢክህሉ ከመ ክርስቶስ መዊሃ
@menkir_tube
@menkir_tube
ማኅሌተ ጽጌ
ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስእልኪ ወርኃ ጽጌረዳ አመ ኃልቀ፤ዘኢየኃልቅ ስብሐተኪ እንዘ እሴብሐኪ ጥቀ፤ተአምርኪ ማርያም ከመ አጠየቀ፤ጸውዖ ስምኪ ያነሥእ ዘወድቀ፤ኃጥአኒ ይሬሲ ጻድቀ፡፡
@menkir_tube
ወረብ
ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስእልኪ ወርኃ ጽጌ ረዳ አመ ኃለቀ/፪/
ዘኢየኃልቅ ስብሐተ ስብሐተ እንዘ እሴብሐኪ/፪/
@menkir_tube
ዚቅ
እለትነብሩ ተንሥኡ ወእለ ታረምሙ አውሥኡ፤ማርያምሃ በቃለ ስብሐት ጸውዑ፤ቁሙ ወአጽምዑ ተአምረ ድንግል ከመ ትስምዑ፤ጸልዩ ቅድመ ስዕላ ለቅድስት ድንግል ፤መርዓተ አብ ወእመ በግዑ፡፡
@menkir_tube
@menkir_tube
ወረብ
እለ ትነብሩ ተንስኡ ወእለ ተረምሙ አውስዑ ማርያምሀ በቃለ ስብሐት ፀውኡ/፪/
ጸልዩ ቅድመ ስዕል ለቅድስት ድንግል እመ በግ ወመርዓተ አብ/፪/
@menkir_tube
ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፣ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ ፡፡
@menkir_tube
@menkir_tube
ወረብ
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ/፪/
ንዒ ርግብየ ምስለ ገብርኤል ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ሚካኤል/፪/
@menkir_tube
ዚቅ
ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ ፤እንተ ሐዋርያት ይሴብሑኪ፤መላእክተ ይትለአኩኪ፤ፃዒ እምሊባኖስ ስነ ሕይወት።
@menkir_tube
ዓዲ(ሌላ) ዚቅ፦
ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ምስለ ኵሎሙ መላእክት ከመ ታዕርጊ ጸሎትነ ከመ ታዕርጊ ጸሎተነ ጊዜ መንፈቀ ሌሊት
@menkir_tube
ማኅሌተ ጽጌ
ሰዊተ ሥርናዩ(ትእምርቱ) ለታዴዎስ ወለ በርተሎሜዎስ ወይኑ፤እንተ ጸገይኪ አስካለ በዕለተ ተካለኪ እደ የማኑ፤ማርያም ለጴጥሮስ ጽላሎቱ ወለ ጳውሎስ ሰበኑ፤ብኪ ምውታን ሕያዋነ ኮኑ፤ወሐዋርያት መላእክተ በሰማይ ኮነኑ።
@menkir_tube
@menkir_tube
ወረብ
ማርያም ለጴጥሮስ ጽላሎቱ ጽላሎቱ ወለጳውሎስ ሰበኑ/፪/
ወሐዋርያት መላእክተ መላእክተ በሰማይ ኰነኑ/፪/
@menkir_tube
@menkir_tube
ዚቅ
መድኃኒት ለነገሥት ማኅበረ ቅዱሳን የዓውዱኪ፤ነቢያት የአኵቱኪ ወሐዋርያት ይዌድሱኪ፤እስመ ኪያኪ ኃርየ ለታዕካሁ ከመ ትኩኒዮ ማኅደረ፤መላእክት ይኬልሉኪ ጻድቃን ይባርኩኪ፤አበው ይገንዩ ለኪ እስ ኪያኪ ኃርየ ለታዕካሁ ከመ ትኩኒዮ ማህደረ
@menkir_tube
@menkir_tube
ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡
@menkir_tube
@menkir_tube
ወረብ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ዘየኃቱ እምዕንቈ ባሕርይ/፪/
አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ መንግሥቱ ለመፍቀሬ አምላክ/፪/
@menkir_tube
@menkir_tube
ዚቅ
ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት፤ ወስብሕት በሐዋርያት፤አክሊለ በረከቱ ለጊዮርጊስ፤ ወትምክህተ ቤቱ ለ፳ኤል።
ማኅሌተ ጽጌ፦
ኅብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወፀዓድዒድ
አርአያ ኰሰኰስ ዘብሩር፤ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር፤ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር፤አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር፤ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር፡፡
@menkir_tube
@menkir_tube
ወረብ
ናሁ ተፈጸመ ተፈጸመ ናሁ ማኀሌተ ጽጌ ሥሙር ተፈጸመ ናሁ/፪/
አስምኪ ቦቱ አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት/፪/
@menkir_tube
@menkir_tube
ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ጥቀ አዳም መላትሕኪ ከመ ማዕነቅ ይግበሩ ለኪ
ኰሰኰሰ ወርቅ፡፡
@menkir_tube
@menkir_tube
ሰቆቃወ ድንግል
ተመየጢ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ ናዝሬተ፤ወኢትጎንድዪ በግብጽ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፤በላዕሌኪ አልቦ እንተ ያመጽእ ሁከተ፤ለወልድኪ ዘየኃሥሦ ይእዜሰ ሞተ፤በከመ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ፡፡
@menkir_tube
ወረብ
ተመየጢ ተመየጢ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ/፪/
ወኢትጎንድዪ በግብፅ በግብፅ ከመ ዘአልብኪ ቤተ/፪/
@menkir_tube
ዚቅ
ተመየጢ ተመየጢ ሰላመ ሰጣዊት
ወንርአይ ብኪ ሰላመ፤ምንተኑ ትኔጽሩ በእንተ ሰላመ ሰጣዊት፤እንተ ትሔውጽ እምርኁቅ ከመ መድበለ ማኅበር፤ሑረታቲሃ ዘበስን ለወለተ አሚናዳብ።
@menkir_tube
@menkir_tube
መዝሙር ፦
በ፮ ሃሌታ-
ክርስቶስ ሠረዓ ሰንበት፤ክርስቶስ ሠረዓ ሰንበት ወጸገወነ ዕረፍት ከመ ንትፌሳሕ ኅቡረ።አዕፃዳተ ወይን ጸገዩ ቀንሞስ ፈረይ፤ማ- ሰሎሞን ጥቀ ኢለብሰ፤ከመ አሐዱ እምእሉ
@menkir_tube
አመላለስ፦
ሰሎሞን ጥቀ ኢለብሰ/፪/
ከመ አሐዱ እምእሉ/፬/
🇪🇹👇👇👇👇👇👇🇪🇹
👉@menkir_tube👈
👉@menkir_tube👈
👉@menkir_tube👈
🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹
@menkir_tube
# Join & share
የስደት ቆይታቸውን በተመለከተ
ቅዱስ ዮሐንስ የስደት ቆይታ ጊዜያቸውን በዕለት በወርና በዓመት ገልጾታል፡፡ “ከመ ትትዐቀብ በህየ በኩሉ መዋዕል ዐሠርተ ወክልዔተ ምዕተ ወተሰዓ ዕለተ፤ ሴቲቱም በዘመኑ ሁሉ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ስሳ ቀን በዚያ ትጠበቅ ዘንድ እግዚአብሔር ወደ አዘጋጀላት ቦታ ወደ በረሃ ሸሸች (ራዕ. ፲፪÷፮)፤
አርባዓ ወክልዔተ አውራኀ፤ ለአርባ ሁለት ወር ሥልጣን ተሰጠው (ራዕ.፲፫÷፭)፤ ዘመን፣ ወአዝማን፣ ወመንፈቀ ዘመን፤ ዘመን ያለው ፩ ዓመት፣ ወአዝማን ሲል ፪ ዓመት፣ ወመንፈቅ ሲል ስድስት ወርን ለማመልከት ነው፡፡ ስንደምረው ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ይሆናል፡፡(ራዕ.፲፪÷፲፬)
ልዩ ልዩ መከራን በመቀበል ለሦስት ዓመት ከስድስት ወር በግብፅ ከቆዩ በኋላ ሄሮድስ መሞቱን የእግዚአብሔር መልአክ ለአረጋዊው ዮሴፍ ተገልጦ “የሕፃኑን ነፍስ የሚሹ ሞተዋልና ተነሥተህ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ እስራኤል ሀገር ሂድ” በማለት ተናገረው፡፡ አረጋዊው የሴፍም ሕፃኑንና እናቱን ይዞ ወደ እስራኤል ምድር ገባ፡፡ (ማቴ. ፪፥፳፩)
ይህም የሚያመለክተን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስደትን ባርኮና ቀድሶ ለሰው ልጆች መስጠቱንና ስለ ስሙ የሚሰደዱ ብፁዓን እንደሚሰኙ ሲያስተምረን ነው፡፡ “ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው” በማለት እንደገለጸው፡፡ (ማቴ. ፭፥፲)
ስደትን ከላይ እንደተመለከትነው እጅግ አስከፊ ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተሰደደ ሁሉ በየዘመናቱ በተለያዩ ምክንያቶች ልንሰደድ እንችላለን፤ በርካታ ጸዋትወ መከራንም ልንቀበል እንችላለን፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔርን ተስፋ አድርጎ በጽናት መከራውን ተቋቁሞ ማለፍ ከሰው ልጆች ይጠበቃል፡፡
አበ ብዙኀን አብርሃም ከዘመዶቹ ተለይቶ ወደማያውቀው ምድር ሲሰደድ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርጎ ነው፡፡ “እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፤ ከሀገርህ፣ ከዘመዶችህም፣ ከአባትህም ቤት ተለይተህ ውጣ፤ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ” በመባሉ በእምነት፣ በተስፋ ወጥቷልና ዘሩን እንደ ሰማይ ከዋክብትና እንደ ምድር አሸዋ እንዳበዛለት ቅዱሳት መጻሕፍት ይመሰክራሉ፡፡ (ዘፍ. ፲፪፥፩) እኛም በተለያዩ ምክንያቶች ስደት በገጠመን ጊዜ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርገን ከመከራው ሁሉ ሸሽጎ የበረከቱ ተሳታፊዎች እንዲያደረገን አምላከችን ይርዳን፡፡ አሜን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
↳ መ/ር ተመስገን ዘገዬ ↲
<<< በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። >>>
"" ኅዳር 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ""
+" ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ "+
+ሃገራችን ኢትዮዽያ በሁሉም ዘርፍ ቅድስና ያላቸው ቅዱሳን ባለቤት ናት:: በዘመኑ ያለን ወጣቶችም ሆነ ጐልማሶች ከቤተ ክርስቲያንና ከቅድስና ሕይወት ለምን እንደራቅን ስንጠየቅ ከምንደረድራቸው ምክንያቶች አንዱ ሥራችን ነው::
+ነገር ግን ሥራው በራሱ ኃጢአት እስካልሆነ ድረስ በየትኛውም የሥራ ዘርፍ ቢሆን ቅድስናን ማስጠበቅ እንደሚቻል አበው አሳይተውናል:: ቅዱስ ነአኩቶ ለአብም ከእነዚህ ቅዱሳን አንዱ ነው::
*እርሱ ንጉሥ ነው: ግን ገዳማዊ ሕይወትን በቤተ መንግስቱ ውስጥ ያሳየ ጻድቅ ነው::
*ሁሉ በእጁ ነው: እርሱ ግን ንጹሕና ድንግል ነው::
*እርሱ የጦር መሪ ነው: ግን በእጁ ደም አልፈሰሰም::
*እርሱን 'ወደድንህ: ሞትንልህ' የሚሉ ብዙ ሰዎች በአካባቢው ነበሩት:: ለእርሱ ግን ፍቅር ማለት ክርስቶስ ነበር::
*የሃገር መሪ: የኢትዮዽያ ንጉሠ ነገሥት እንደ መሆኑ እጅግ ባተሌ (busy) ነው:: ግን ደግሞ ለክርስትናው ጊዜ ያጣ ሰው አልነበረም::
+እኛ ቤተ ክርስቲያንን "በሐኪ" ለማለት (ለመሳለም) እንኳ 'ጊዜ የለኝም' ስንል እርሱ ግን አብያተ ክርስቲያናትን ይፈለፍል: ያንጽ: በክህነቱ ያገለግል: ማዕጠንት ያጥን: ለረጅም ሰዓትም ይጸልይ ነበር::
+እኛ 'ሥራ ውያለሁና ደክሞኛል' ብለን ከስግደት ስንርቅ እርሱ ግን ንጉሥ ሆኖ ሳለ: ጦር በፊት: በኋላ: በቀኝና በግራ ተክሎ ይሰግድ ስለ ነበር ደሙ እንደ ውሃ በምድር ላይ ፈሷል:: ይህንን ሁሉ ያደረገው ቅዱሱ የኢትዮዽያ ንጉሠ ነገሥት አፄ ነአኩቶ ለአብ ነው::
"ለመሆኑ ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ ማን ነው?"
#ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ በዛግዌ ሥርወ መንግስት ከነገሡ 11 ነገሥታት አንዱ ሲሆን ከመጨረሻውም 2ኛ ነው:: እርሱን በ12ኛው መቶ ክ/ዘመን የወለዱት ቅዱሱ ንጉሥ ሐርቤ (ገብረ ማርያም) እና መርኬዛ ናት:: ዘመኑ ቅድስና በላስታ ዙሪያ የመላበት በመሆኑ ቅዱስ ሐርቤ ከመነኑ በፊት ነበር ነአኩቶ ለአብን የወለደው::
+እናቱ መርኬዛ እርሱን ልትወልድ ምጥ ተይዛ ሳለ ጀሮዋ ቅዳሴን ይሰማ ነበር:: ቅዳሴው ሲጀመር የጀመራት ምጥ ድርገት ሲወርዱ (ሥጋ ወደሙ ሲሰጥ) ተፈታላትና ልጇን ተገላገለች:: ሕጻኑን አንስታ ስትታቀፈው ዲያቆኑ ማቁረቡን ፈጽሞ "ነአኩቶ" እያለ ሲዞር ሰማችው::
+እዚያው ላይም 'ነአኩቶ ለአብ' (አብን እናመስግነው) ስትል ስም አወጣችለት:: ወዲያው ግን አባቱ ቅዱስ ሐርቤ መንግስቱን ለቅዱስ ላሊበላ ሰጥቶ በርሃ በመግባቱ ቅዱሱ ሕጻን ወደ አጐቱ ላሊበላ ቤተ መንግስት ውስጥ ገባ::
+የቅዱስ ላሊበላ ቤት ደግሞ በቅድስና ያጌጠ ነውና ከርሱና ከሚስቱ (ቅድስት መስቀል ክብራ) ሕጻኑ ነአኩቶ ለአብ ምናኔና ፍቅረ ክርስቶስን ተማረ:: በዘመኑ ብዙ ሊቃውንት ስለ ነበሩ ቅዱሳት መጻሕፍትን በደንብ አጠና:: ክህነት ተቀብሎ ቤተ ክርስቲያንን ሲያገለግልም እድሜው 30 ደረሰ::
+በወቅቱ ቅዱስ ላሊበላና ባለቤቱ መስቀል ክብራ ልጃቸው ይትባረክ እያለ ንግሥናቸውን ለቅዱስ ነአኩቶ ለአብ አወረሱ:: ቅዱሱ ነአኩቶ ለአብም ምን እንደሚሠራ ሲያስብ አንድ ነገር ተገለጠለት:: ቤተ መንግስቱን እንደሚገባ ካደራጀ በኋላ በቤት ውስጥ አንድ ጉድጓድን በቁመቱ ልክ አስቆፈረ::
+በውስጡም በ4 አቅጣጫ ጦሮችን ተከለባቸው:: ድንግል ካህን ነበረና ቀን ቀን ሃገር ሲያስተዳድር: ቅዳሴ ሲቀድስ: በጾም ይውላል:: ሌሊት ደግሞ ወዳስቆፈረው ቦታ ገብቶ ያለማቁዋረጥ እየጸለየ ይሰግዳል::
+ወደ ምድር ሲሰግድ በፊቱ ያለው ጦር ይወጋዋል:: ቀና ሲል ደግሞ የጀርባው ይቀበለዋል:: እንዲህ እያለ የፈጣሪውን ሕማማት ይካፈላል:: በተለይ ዐርብ ዐርብ ሲሆን ደሙ: እንባውና ላበቱ ተቀላቅሎ ይፈስ ነበር:: እርሱ መስቀሉን ተሸክሞ ጌታውን ይከተል ዘንድ መርጧልና::
+ከተጋድሎው ጐን ለጐን ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ አብያተ ክርስቲያናትንም ያንጽ ነበር:: በተለይ በ1211 አካባቢ ያነጻት አሸተን ማርያም ልዩ ናት:: እርሷን ካነጸ በኋላ ከቤተ መንግስቱ በደመና ሠረገላ ተጭኖ እየሔደ ያጥናት: ይቀድስባትም ነበር::
+ታዲያ አንድ ቀን አጥኖ ከቤተ መቅደስ ሲወጣ ብዙ ሥውራን ቅዱሳን መቅደሱን ከበው ተመለከተ:: እርሱም "ወገኖቼ! ከወዴት መወጣችሁ?" ቢላቸው "መዐዛ እጣንህን አሽተን መጣን" ሲሉ መለሱለት:: በዚህ ምክንያትም እስከ ዛሬ ድረስ "አሽተን (አሸተን) ማርያም" ስትባል ትኖራለች::
+ዛሬ ታቦቱ ያለበት ገዳሙም በእርሱ የታነጸ ሲሆን እጅግ ተአምረኛ ቦታ ነው:: ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ የነገሠ በ30 ዓመቱ ነው:: ለ40 ዓመታት በእንዲህ ያለ ቅድስና ኑሮ 70 ዓመት ሞላው:: በዚህ ጊዜም ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ሰላምታንም ሰጠው::
+"ወዳጄ ነአኩቶ ለአብ! አንተ ስለ እኔ ፍቅር ለ40 ዓመታት መከራን ተቀብለሃልና ሞት አያገኝህም:: ከፍልህ ከነ ኤልያስ ጋር ነውና:: የሚያከብርህን አከብረዋለሁ:: ደጅህን የሳመውን: ይህ ቢያቅተው በሩቁ ሆኖ በአድናቆት የተመኘህን: መታሰቢያህን ያደረገውን ሁሉ እምርልሃለሁ" አለው::
+ቀጥሎም "ይሕች ቤት አንተ ስትደማ እንደኖርክባት እርሷም እስከ ምጽዓት ድረስ ለመታሰቢያህ ስትደማ ትኑር" አለው:: እነሆ ዛሬም ድረስ ከመቅደሱ ጸበል ይንጠበጠባል:: ለዚህም ደግሞ እኛ ኃጥአን ምስክሮች ነን:: ሳይገባን የቅዱሱን ደጅ ተመልክተናልና::
+ቅዱስ ነአኩቶ ለአብም የዚህን ዓለም ተጋድሎውን ፈጽሞ ወደ ብሔረ ሕያዋን መላእክት ወስደውታል:: የተሰወረበትን ዕለት ስንክሳር ሕዳር 1 ሲያደርገው አንዳንድ መዛግብት ደግሞ በ3 ነው ይላሉ:: በዙፋኑም ላይ የአጐቱ የላሊበላ ልጅ አፄ ይትባረክ ተተክቷል::
+አምላከ ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ በቃል ኪዳኑ ይማረን:: ከበረከቱም አትረፍርፎ ይስጠኝ::
+ኅዳር 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
2.ቅዱሳን መክሲሞስና ባልንጀሮቹ (ሰማዕታት)
ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
4.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
5.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር
++"+ ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን: ትንሳኤውን በሚመስል ትንሳኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን:: ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን:: +"+ (ሮሜ. 6:5)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
#ጥቅምት_30
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ሠላሳ በዚህች ቀን ወንጌልን የጻፈ ሐዋርያው #ቅዱስ_ማርቆስ የተወለደበት ነው፣ #የመጥምቁ_ዮሐንስ ቅድስት ነፍሱ ከተቆረጠች ራሱ ጋራ በግልጽ የታየችበት ነው፣ በገድል የተጸመደ #ቅዱስ_አባት_ባሕታዊ_አብርሃም ያረፈበት ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ማርቆስ_ወንጌላዊ
ጥቅምት ሠላሳ በዚህች ቀን ለእስክንድርያ ሊቃነ ጳጳሳት አለቃ የሆነ ወንጌልን የጻፈ ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ የተወለደበት ነው።
የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አርስጦቡሎስ ነው እርሱም ከአምስቱ አገሮች የሆነ የእናቱም ስም ማርያም ነው እርሷም በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ተጽፋለች እርሱም አስቀድሞ ስሙ ዮሐንስ ነው። በግብረ ሐዋርያት ማርቆስ በተባለ በዮሐንስ እናት ቤት ሐዋርያት ይጸልዩ ነበር ተብሎ እንደ ተጻፈ። እርሷም ባለጸጋ ነበረችና የዮናናውያንን የሮማይስጥን የዕብራይስጥን ትምህርት ለልጅዋ ለማርቆስ አስተማረችው።
በአደገም ጊዜ በርናባስ ወንጌልን ለመስበክ ከጳውሎስ ጋራ ሲሔድ ይዞት ሔደ በእነርሱም ላይ የሚደርስባቸውን መከራ አይቶ በጵንፍልያ ከተማ ሳሉ ትቷቸው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።
ሐዋርያትም በተመለሱ ጊዜ የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ማመን አሕዛብ እንደ ተመለሱ እግዚአብሔርም በእጆቻቸው ላይ ድንቅ ተአምራትን እንዳደረገ ተናገሩ። ይህ ብላቴና ማርቆስም ከእርሳቸው ስለ መለየቱ አዘነ ተጸጸተ።
ከዚያም አብሮአቸው ሊሔድ ፈለገ አስቀድሞ ትቷቸው ስለተመለሰ ጳውሎስ ሊአስከትለው አልወደደም በርናባስ ግን ወሰደው አጎቱ ነውና። በርናባስም ከአረፈ በኋላ ወደ ሮሜ አገር ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ሒዶ ለእርሱ ደቀ መዝሙሩ ሆነ በዚያም ቅዱስ ጴጥሮስ የተረጐመለትን ወንጌልን ጻፈ በሮሜ አገርም አስተማረበት። ከዚያም በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትእዛዝና በሐዋርያትም ትእዛዝ ወደ እስክንድርያ አገር ሔደ። በውስጥዋም የከበረ ወንጌልን አስተማረ ደግሞም በአፍራቅያና በአምስቱ አገሮች በርቃ በሚባልም አገር ወደ እስክንድርያ ከተማ በገባ ጊዜ ጫማው ተቆረጠ።
በዚያም በከተማው መግቢያ ጫማ ሰፊ ነበረ። ቅዱስ ማርቆስም እንዲሰፋለት ለርሱ ሰጠው ሲሰፋም ጣቱን ወግቶ ሰነጠቀው ከእርሱም ደም ፈሰሰ በዮናኒም ቋንቋ ኢታስታዖስ አለ ትርጓሜውም አንድ እግዚአብሔር ማለት ነው። ቅዱስ ማርቆስም ስሙን የምትጠራው አውቀኸው ነውን አለው እንጠራዋለን እንጂ አናውቀውም አለ።
እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ከፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ አባታችን አዳም ትእዛዙን እንደተላለፈ የጥፋት ውኃም እንደ መጣ ሙሴንም እንደላከውና እስራኤልን ከግብጽ እንዳወጣቸው ሕግንም እንደ ሠራላቸው ናቡከደነጾርም ወደ ባቢሎን ማርኮ እንደወሰዳቸውና ከሰባ ዓመት በኋላ ወደ አገራቸው ኢየሩሳሌም እንደ ተመለሱ ክርስቶስ ሥጋ በመልበስ ወደ ዓለም ስለ መምጣቱ ነቢያት ትንቢት እንደ ተናገሩ ያስተምረው ዘንድ ጀመረ።
ከዚያም በኋላ ወደ ምድር ምራቁን ትፍ ብሎ ጭቃ አድርጎ ጣቱን ቀባው ወዲያው ዳነ በጌታችንም አመነ። ያም ሰፊ ስሙ አንያኖስ ነው። ቅዱስ ማርቆስንም ወደ ቤቱ ወስዶ ልጆቹን ዘመዶቹንም ወደ ርሱ አቀረበ እርሱም አስተምሮ አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው።
በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያመኑ ሰዎች በበዙ ጊዜ የቅዱስ ማርቆስን ዜና ሰምተው የአገር ሰዎች ሊገድሉት ተሰበሰቡ እርሱም አንያኖስን ኤጲስቆጶስ አድርጎ ሹሞ ልጆቹን ቄሶችና ዲያቆኖች አድርጎ ከዚያም ወደ በርቃ ወደ አምስቱ አገሮችም ወጥቶ አስተማረ። በቀናች ሃይማኖትም አጸናቸው በእርሳቸውም ዘንድ ሁለት ዓመት ኖረ ኤጲስቆጶሳትን ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ሾመላቸው።
ከዚህም በኋላ ወደ እስክንድርያ ተመለሰ ምእመናንም ተጨምረው በዝተው በታወቁ ቦታዎች ሁሉ በባሕሩም ዳር በላሞች መካበቢያ በሚባለውም አብያተ ክርስቲያን ሠርተው አገኛቸው።
ከሀድያንም የከበረ ሐዋርያን ይገድሉት ዘንድ በብዙ ድካም ፈለጉት እርሱም አምስቱን አገሮች ሲጐበኝ በሥውር ወደ እስክንድርያ ከተማ ይገባ ይወጣ ነበር። በአንዲትም ዓመትም ከአምስቱ አገሮች ተመልሶ ሚያዝያ ዐሥራ ሰባት ቀን በመድኃኒታችን የትንሣኤ በዓል ወደ ቤተክርስቲያን ገባ ሕዝቡም ሁሉ በዙሪያው አሉ። ከሀድያንም ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተው በአንገቱ ውስጥ ገመዶችን አድርገው በከተማው ሁሉ ጎተቱት። እነርሱም ገና እንደፍየል ሙክት እንጎትተዋለን እያሉ ይጮኹ ነበር ። በላሞች መካበቢያና በሀገሪቱ አደባባይ በከተማውም ዙሪያ በየቀኑ ሲጎትቱት ኖሩ።
ሌሊትም በሆነ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሐዋርያት ጋራ በነበረበት አርአያ ሁኖ ተገለጠለት ሰላምታም ሰጥቶ አጽናናው ቃል ኪዳንም ሰጠው። እነሆ አንተ ከወንድሞችህ ሐዋርያት ጋር ተካከልህ አለው። እርሱም በልቡናው ፈጽሞ ደስ አለው። በማግሥቱም ሁለተኛ ገመዶችን በአንገቱ አድርገው በአገሮች ሁሉ ጎተቱት በቀኑም መጨረሻ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።
ከሀዲዎችም ታላቅ እሳትን አንድደው የቅዱስ ማርቆስን ሥጋ ከውስጡ ጨመሩ ። በክብር ባለቤት ጌታችን ፈቃድም ንውጽውጽታ ጨለማ ቀዝቃዛ ነፋስ መብረቅና ነጐድጓድ ሆነ። ፀሐይም ጨለመ ከሀዲዎችም ሸሹ ምእመናንም መጥተው የሐዋርያ ቅዱስ ማርቆስን ሥጋ ወሰዱ ምንም ጥፋት ሳይደርስበት ደኀና ሆኖ አገኙት በመልካም ልብስም ገንዘው በጥሩ ቦታ አኖሩት መታሰቢያውንም አደረጉ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቀ_መለኮት
ዳግመኛም በዚህች ቀን የመጥምቁ ዮሐንስ ቅድስት ነፍሱ ከተቆረጠች ራሱ ጋራ በአየር ውስጥ እየበረረች 15 ዓመት ስታስተምር ከኖረች በኋላ በዐረቢያ ምድር በግልጽ ታይታለች፡፡
ይኸውም የሆነው እንዲህ ነው፡- ሄሮድያዳ ልጅ ርጉም የሆነ ንጉሥ ሄሮድስን በዘፈኗ በጣም አድርጋ ስላስደሰተችው እርሱም በተራው ሊያስደስታት ፈለገና እስከ መንግሥቱ እኩሌታ ድረስም ቢሆን የለመነችውን ይሰጣት ዘንድ በሕዝቦቹና በመኳንንቱ ሁሉ ፊት እንዳይከዳት በፅኑ ቃልኪዳን ማለላት፡፡ እርሱም አስቀድሞ "የፈለግሽውን ጠይቂኝ፣ የመንግሥቴንም እኩሌታ ቢሆን እሰጥሻለሁ ምን ላድርግልሽ?" እያለ በመሐላ ባላት ጊዜ በእናቷ ምክር የዮሐንስን አንገት ቆርጦ ይሰጣት ዘንድ ለመነችው፡፡ እርሱም ስለማሐላው የዮሐንስን አንገት እንድትቆረጥ አደረገ፡፡ በመጀመሪያም የሄሮድስ ወታደሮች ሠይፍ ይዘው የዮሐንስን አንገት ይቆርጡ ዘንድ ወደ መኅኒ ቤት ሲሄዱ ቅዱስ ዮሐንስም የሄሮድስ ጭፍሮች ሊገድሉት እንደመጡ በመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ስላወቀ ከጨለማው ቤት ውስጥ አንገቱን በመስኮት አውጥቶ እንደሚመቻቸው አድርጎ ጠበቃቸው፡፡ የንጉሡም ጭፍሮች የመጥምቁን ራስ በወጪት አድርገው ለንጉሣቸው ሄሮድስ ሰጡት፡፡ ሄሮድስም ለሄሮድያዳ ልጅ ሰጣት፡፡ የመጥምቁ ዮሐንስ ግን በወጪት ላይ ሆና ሕዝቦቹና የመንግሥቱ ታላላቅ ሰዎች እየሰሟት በየመኳንንቱ ፊት ንጉሥ ሄሮድስን "የወንድምህን የፊሊጶስን ሚስት ማግባት አይገባህም" እያለች መጀመሪያ ትዘልፈው እንደነበረው ሁሉ አሁንም ዘለፈችው፡፡ መዓዛዋም እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነበር፣ ዐይኖቹም እንደፀሐይ ያበሩ ነበር፡፡
4.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
5.አባ አብርሃም ገዳማዊ
6 ቅዱስ ይስሐቅ ንጉሥ
=>ወርኃዊ በዓላት
1.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
2.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
3.አባ ሣሉሲ ጻድቅ
++" ... እጅግ ሰዎች ተከማችተው ይጸልዩበት ወደ ነበረው ማርቆስ ወደ ተባለው ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት መጣ:: ዼጥሮስም የደጁን መዝጊያ ባንኳኳ ጊዜ ሮዴ የሚሏት አንዲት አገልጋይ ትሰማ ዘንድ ቀረበች:: የዼጥሮስ ድምጽ መሆኑንም ባወቀች ጊዜ ከደስታዋ የተነሳ ደጁን አልከፈተችም:: ነገር ግን ወደ ውስጥ ሮጣ ዼጥሮስ በደጅ ፊት ቆሞ እንዳለ አወራች:: +"+ (ሐዋ. 12:12-15)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
የሚሸጥ ባጃጅ በአሪፍ ይዞታ የቆየ ታርጋው አማ ዋጋው 300000 የሚገኘው አአ ስልክ 0947979441 0909128951 ይምጡ ይግዙ
Читать полностью…#ጥቅምት_29
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ሃያ ዘጠኝ በዚህች ቀን #አቡነ_ሳሙኤል_ዘደብረ_ወገግ አረፉ፣ በከሀዲው ንጉሥ በመክስምያኖስ ዘመን #ቅዱስ_ድሜጥሮስ ዘተሰሎንቄ በሰማዕትነት አረፈ፣ የደብረ ዘኸኝ #መምህር_ጸቃውዐ_ድንግል አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_ሳሙኤል_ጻድቅ (ዘደብረ ወገግ)
ጥቅምት ሃያ ዘጠኝ በዚህች ቀን ታላቁ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ አረፉ፡፡
ጻድቁ አቡነ ሳሙኤል እንድርያስና አርሶንያ ከሚባሉ የበቁ ደጋግ አባትና እናታቸው የተወለዱት በሸዋ ሀገረ ስብከት ቀድሞ ጽላልሽ ዛሬ ቡልጋ በሚባለው አውራጃ ነው፡፡ የወላጆቻቸው በጎ ምግባርና ሃይማኖት ቅዱስ ተክለሃይማኖትን ከደብረ ሊባኖስ አነሣስቶ በቤታቸው ሄደው እንዲስተናገዱ አድርጓል፡፡ ልጅ ስላልነበራቸው ያዝኑ ነበርና አቡነ ተክለሃይማኖትም በጸጋ እግዚአብሔር ተገልጾላቸው "እግዚአብሔር ጣዖታትን የሚሰብር፣ አጋንንትን በጸሎቱ የሚያርቅ፣ ሕዝብን ከኃጢአት በሽታ የሚያድን፣ ፈጣሪውን የሚያስደስት ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ" ብለው ትንቢት ነግረዋቸዋል፡፡ በትንቢቱም መሠረት አቡነ ሳሙኤል ሐምሌ 10 ቀን 1248 ዓ.ም ሲወለዱ መልካቸው በአራት ልዩ ልዩ ሕብረ መልክ እየተለዋወጠ አንድ ጊዜ እንደ በረዶ፣ አንድ ጊዜ እንደ እሳት፣ አንድ ጊዜ እንደ ልምላሜና ቢጫ ሆነው ታይተዋል፡፡
አቡነ ተክለሃይማኖትም በአባቱ እንድሪያስ በኩል የሥጋ ዘመዱ ሲሆኑ የመንፈስ ቅዱስም አባት ሆኑትና በ40 ቀን ክርስትና አንስተው ስመ ክርስትናውን "ሳሙኤል" አሉት፡፡ ትርጓሜውም "እግዚአብሔር ጸለቴን ሰማኝ" ማለት ነው፡፡ ከሕፃንነትም ጀምረው በምግባር በሃይማኖት ኮትኩተው አሳድገው ለዲቁና አብቅተው በኋላም አመንኩሰውታል፡፡ "ደብረ ወገግ" የሚለው ስያሜ የተገኘው ከመላእክት ነው፡፡ ድርሳነ ዑራኤል በሰፊው እንደሚያትተው ቅዱስ ዑራኤል የጌታችንን ደም በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ ዓለምን እየረጨ ሲቀድሳት የያዘውን ጽዋ በደብረ አስቦ ቆሞ ሳለ ነው ጨልጦ ያንጠፈጠፈው፡፡ ያንጊዜም ደብረ አስቦን የብርሃን ውጋጋን ሲያጥለቀልቀው መላእክትም "ቦታውን ደብረ ወገግ" (የብርሃን ተራራ) ብለው ሰይመውታል፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም "ወደፊት ፈጣሪውን የሚያገለግል ታላቅ ጻድቅ ይወጣባታልና ይህችን ቦታ ባርካት" ብሎ ቅዱስ ዑራኤልን በነገረው መሠረት ባርኳት እንዳረገ ድርሳነ ዑራኤል ላይ በሰፊው ተጽፏል፡፡
በቦታው ላይ ብዙ ጊዜ የብርሃን ምሰሶ ተተክሎ መታየቱን የበቁ ገዳማውያን ብቻ ሳይሆኑ በከተማ ያሉና ለመሳለም ወደ ቦታው የሄዱ ደገኛ ሰዎችም በዐይናቸው ያዩትን ይናገራሉ፡፡ በገዳሙ ዙሪያ እጅግ በጣም ብዙ ስውራን ቅዱሳን እንዳሉ በግልጽ ይታወቃል፡፡
ንጉሥ ዓምደ ጽዮን በክፉዎች ምክር የአባቱን ሚስት እንጀራ እናቱን በማግባቱ ምክንያት አቡነ ፊሊጶስ ጋር ሆነው ያወገዙትን የቅዱስ ተክለሃይማኖትን ወገኖች በየአውራጃው በተናቸው፡፡ አቡነ ፊሊጶስንም ደሙ በምድር ላይ እስከሚንጣለል ድረስ ገርፈው ወደነበረበት ቤቱ ወሰዱት፤ ፊሊጶስም በሚሄድበት ቦታ ላይ ሳይደርስ በመንገድ ሞተ፡፡ እንድርያስ፣ አኖሬዎስና ተክለ ጽዮን ሁላቸው ከተከታዮቻቸው ጋር በሰማዕትነት አርፈው እነስድስተይ በምትባል ምድር ተቀበሩ፡፡ ጳጳሱን አቡነ ያዕቆብንም ደሙ በምድር ላይ እንደውኃ እስኪወርድ ድረስ ገርፈው ወደ ሀገሩ እንዲሰደደ አደረጉት፡፡ ከዚያም በኋላ ሃይማኖቱ የቀና ደግ ጻድቅ ንጉሥ ዳዊት በነገሠ ጊዜ አባታችን ሳሙኤል ዘወገግን አገኘውና ‹‹መማጸኛ እንዲሆነኝ በእንድርያስ መቃብር ላይ ቤተክርስቲያን ሥራልኝ›› ብሎ ለመነውና የሩፋኤልን ቤተ ክርስቲያን ሠራለት፡፡ የእንድርያስንም አጽም ከመቅደሱ ስር አኖረው፡፡ ንጉሡም በዚያ በእንደግብጦን አውራጃ ሁሉ ላይ ፓትርያርክ አድርጎ ሾመው፡፡ በእነስድስታይ አገር ላሉ ሰዎችም ሁሉ አባት ሆናቸውና የመንፈስ ቅዱስ ልጁንም ታዲዮስን መምህርና አባት አድርጎ ሾመላቸውና ጽላልሽ ሄዶ እናቱን ይዞ ጽጋጋ ምድረ ወገግ ወስዶ አመነኮሳት፡፡
አቡነ ሳሙኤል ወደ ምድረ ርስቱ ደብረ ወገግ እየሄደ በዚያ ያሉ ልጆቹን እያጽናና ወደ እንደግብጦን አውራጃም እየተመለሰ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን እያደረገ፣ ወንጌልን እያስተማረ፣ ጣዖት አምላኪዎችን ወደ ክርስትና እየቀየረ፣ አጋንንትንና መመለኪያ ቦታዎቻቸውን እያጠፋ፣ አብያተ ክርስቲያናትን እያነጸ በብዙ ተጋድሎ ኖረ፡፡ በቅዱስ ገድሉ ውስጥ በጣም አስገራሚ በሆነ መልኩ እጅግ ብዙ ታሪኮች ተጠቅሰዋል፡፡ እነዚህም ታሪኮች ውስጥ አቡነ ሳሙኤል በሀገራችን በጣም ብዙ ጣዖታትንና መመለኪያ ቤቶቻቸውን እያጠፉ፣ በሰዎች (በጠንቋዮች) ላይ፣ በዛፍና በባሕር ውስጥ አድሮ ይመለኩ የነበሩ ሰይጣናት አጋንንትን በሚያመልኳቸው ሰዎች ፊት እያጋለጡና እያዋረዱ ሰዎቹን አስተምረው አጥምቀው ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር እየመለሷቸው ቤተክርስቲያንም በመሥራት ሐዋርያትን መሰሉ፡፡
ሰይጣን አድሮባቸው የነበሩ ጠንቋዮች ይጠቀሙባቸው የነበሩ ዕቃዎችን ጻድቁ እየባረኩና እየቀደሱ ለቤተክርስቲያን መሥሪያና መጠቀሚያነት ያውሉት ነበር፡፡ ይህም ገና ሳይወለዱ በአቡነ ተክለሃይማኖት ትንቢት ተነግሮላቸው ነበር፡፡ አቡነ ተክለሃይማኖት ‹‹ጣዖታትን የሚሰብር፣ አጋንንትን በጸሎቱ የሚያርቅ፣ ሕዝብን ከኃጢአት በሽታ የሚያድን፣ ፈጣሪውን የሚያስደስት ደግ ልጅ ይሆናል›› ብሎው ትንቢት እንደተናገሩላቸው አቡነ ሳሙኤል በሰዎች፣ በባሕርና በዛፍ ላይ እያደሩ ይመለኩ የነበሩ በጣም ብዙ አጋንንትን አጠፏቸው፡፡ ጠንቋዮችንም በውስጣቸው ካደረባቸው ሰይጣን እያላቀቁ የእግዚአብሔር አገልጋይ ያደርጓቸውና ያመነኩሷቸው ነበር፡፡
ጻድቁ አባታችን አባ ሳሙኤል ወንጌልን ዞረው በማስተማር ሐዋርያትን መሰሉ፣ ከዓላውያን ጋር ለመዋጋት ሰውነታቸውን ለሞት በመስጠት ሰማዕታትን መሰሉ፣ በጾም በጸሎት በስግደት በተጋድሎ ቅዱሳን ጻድቃንን መሰሉ፣ ይህን ኃላፊና ጠፊ ዓለም ንቀው በመተው ባሕታውያንን መሰሉ፣ በደልንና ኃጢአትን በማስተሠረይ ካህናትን መሰሉ፣ በጽሕናና በቅድስና መላእክትን መሰሉ እንደዚሁም ሌሎች ብዙ አስደናቂ ተአምራትንም በማድረግ ይታወቃሉ፡፡ በትእምርተ መስቀል አድርገው እንደሙሴ ባሕርን ለሁለት ከፍለዋል፣ እንደ ኢያሱ በጸሎታቸው ፀሐይን አቁመዋል፡፡ አቡነ ሳሙኤል ተጋድሎአቸውን ፈጽመው ከጌታችን ታላቅ ቃኪዳን ተቀብለው በዚህች ዕለት በሰላም ዐርፈዋል፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ድሜጥሮስ_ሰማዕት
በዚህችም ቀን በከሀዲው ንጉሥ በመክስምያኖስ ዘመን ቅዱስ ድሜጥሮስ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ ከተሰሎንቄ ሀገር ነው የከበረች የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት ተምሮ በቀናች ሃይማኖት ጸና ሕዝቡንም የሚያስተምር ሆነ ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት በመስበክ ብዙዎችን ከስሕተት መለሳቸው።
ስለዚህም በከሀዲው ንጉሥ ዘንድ ወነጀሉት ንጉሡም ወደርሱ እንዲአመጡት አዘዘ በንጉሡም ዘንድ አንድ ሥጋው የደነደነ የጸና ዐጥንቱ የሰፋ ሰው ነበረ ለሰዎችም ሁሉ እሱ ሁሉን የሚያሸንፍ እሱን የሚያሸንፈው የሌለ ይመስላቸው ነበር ንጉሡም ይወደዋል ይመካበታል እንዲህም ይል ነበር ይህን አካሉ ግዙፍ የሆነ ሰው ለሚያሸንፍ እኔ ብዙ ገንዘብ እሰጠዋለሁ።