kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ
3.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን
4.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ
5.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ

††† "እውነት እላቹሃለሁ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል:: በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል:: ደግሞ እላቹሃለሁ ከእናንተ ሁለቱ በምድር በማናቸውም በሚለምኑት ነገር ሁሉ ቢስማሙ በሰማያት ካለው ከአባቴ ዘንድ ይደረግላቸዋል:: ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና::" †††
(ማቴ. ፲፰፥፲፰)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/xg3CjNWw-z4?si=vdxqKkDb2LuuyU4q

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🔆ማነው አዚም ያረገባችሁ!

🔥 እግዚአብሔርን ለማመስገን ጊዜ የለህም ዘፈን ለመስማት ግን ቀኑን ሙሉ ጊዜ ትሰጠዋለህ!

🔥 ድራማ ለማየት ሙሉ ሰዓትህን ትሰጠዋለህ ለፀሎት ግን አንዳች ሰዓት እንደሌለህ አድርገህ እራስህን ታሳምናለህ።

🔥 ለቀልድ ያለህ ጊዜ ሰፊ ነው ወንጌል ለመማር ግን ሰዓቱ ያጥርሃል።

🔥 የምትበላውን ምግብ ለመብላት አንዳች ሰዓት የማታሳልፈው እና በፍፁም እንደምትበላ የማትረሳው ሰው የፀሎት ሰዓትህን ግን መኖሩን ራሱ ትረሳዋለህ።

🔥 አንድ መዝሙር ዘምር ብትባል የማትችለው ግጥሙን እና ዜማውን መያዝ ያቃተህ ሰው ዘፈን ለመዝፈን ግን ማን አንተን ብሎ።

🔥 አንድ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የማትናገረው ሰው ታዋቂ ሰው የተናገረውን ፅሁፍ ግን ሙሉ መፅሐፉን ትናገረዋለህ።

🔥 ከቅዱሳን አባቶች የአንዱን ስም መናገር ያቃተህ የጓደኞችህን ስም ግን ምላስህ ላይ ተነቅሰከዋል።

🔥 ቤተክርስቲያን ጠርታህ ስትጠብቃት ከምታድር ጭፈራ ቤት ሄደህ ሰክረህ መንገድ ላይ ወድቀህ ብታድር ይቀልሃል።

🔥 ለአንድ ደቂቃ እግዚአብሔርን ማመን ያቃተህ ሰውዬ ፍቅረኛህን ግን በሙሉ ልብህ ታማናታለህ።.............


🔴ይህንን ግን ልብ አድርግ!
በኋላ ጊዜው አልቆ ሞት ሊወስድህ ሲመጣም ጊዜ የለኝም በለው።
ጊዜ ይሰጥህ እንደሆነ ታየዋለህ!

✅ ቻናላችን፦ኪነ-ጥበብ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝✞✝ እንኩዋን ለቅዱሳን ኪሩቤል (ዐርባዕቱ እንስሳ): ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ወአባ ቅፍሮንያ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✞✝

+"+ ዐርባዕቱ እንስሳ +"+

=>እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን ሲፈጥራቸው በነገድ መቶ (100): በክፍለ ነገድ አሥር (10) አድርጉዋቸዋል:: አቀማመጣቸውንም በ3 ሰማያትና በ10 ከተሞች (ዓለማት) አድርጉዋል::

+መላእክት ያሉባቸው ከተሞች ከታች ወደ ላይ 'ኤረር: ራማና ኢዮር' ይባላሉ:: አሥሩ ክፍለ ነገድ ደግሞ ከነ አለቆቻቸው ይህንን ይመስላሉ:-

1.አጋእዝት (የቀድሞ አለቃቸው ሳጥናኤል: አህን የተረፉት በቅዱስ ሚካኤል ሥር ናቸው)
2.ኪሩቤል (አለቃቸው ኪሩብ)
3.ሱራፌል (አለቃቸው ሱራፊ)
4.ኃይላት (አለቃቸው ሚካኤል)
5.አርባብ (አለቃቸው ገብርኤል)

6.መናብርት (አለቃቸው ሩፋኤል)
7.ስልጣናት (አለቃቸው ሱርያል)
8.መኩዋንንት (አለቃቸው ሰዳካኤል)
9.ሊቃናት (አለቃቸው ሰላታኤል)
10.መላእክት (አለቃቸው አናንኤል) ናቸው::

+ከእነዚህም *አጋእዝት: *ኪሩቤል *ሱራፌልና *ኃይላት መኖሪያቸው በኢዮር (በ3ኛው ሰማይ) ነው:: *አርባብ: *መናብርትና *ስልጣናት ቤታቸው ራማ (2ኛው ሰማይ) ነው:: *መኩዋንንት: *ሊቃናትና *መላእክት ደግሞ የሚኖሩት በኤረር (በ1ኛው) ሰማይ ነው::

+መላእክት ተፈጥሯቸው እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ ነው:: አይራቡም: አይጠሙም: አይዋለዱም: አይሞቱም:: ተፈጥሯቸውም ረቂቅ ነው:: ተግባራቸው ዘወትር "ቅዱስ: ቅዱስ: ቅዱስ" እያሉ ፈጣሪያቸውን ማመስገን ነው:: ምግባቸውም ይሔው ነው::

+ዕረፍት ብሎ ነገርን አያውቁም:: "አኮቴቶሙ ዕረፍቶሙ: ወዕረፍቶሙ አኮቴቶሙ" እንዲል:: በተጨማሪም መልአክ ማለት ተላላኪ (አገልጋይ) ነውና ከፈጣሪ ወደ ሰው ልጆች ለምሕረትም: ለመዓትም ይላካሉ::

+ምሕረትን ያወርዳሉ:: ልመናን ያሳርጋሉ:: ቅጡ ሲባሉም ይቀጣሉ:: ስነ ፍጥረት (አራቱ ወቅቶች) እንዳይዛቡ ይጠብቃሉ::

*ዘወትርም ስለ ሰው ልጆች ያማልዳሉ (ዘካ. 1:12)
*ምሥጢርን ይገልጣሉ (ዳን. 9:21)
*ይረዳሉ (ኢያ. 5:13)
*እንዳንሰናከል ይጠብቃሉ (መዝ. 90:11)
*ያድናሉ (መዝ. 33:7)
*ስግደት ይገባቸዋል (መሳ. 13:20, ኢያ. 5:13, ራዕ. 22:8)
*በፍርድ ቀንም ኃጥአንን ከጻድቃን ይለያሉ (ማቴ. 25:31)
*በአጠቃላይ ለሰው ልጆች ሕይወትና ድኅነት ሲባል ከፈጣሪያቸው የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ሲጠብቁና ፈቃዱን ሲፈጽሙ ይኖራሉ::

+ከእነዚህ ቅዱሳን መላእክት መካከል ደግሞ ትልቁን ሥፍራ ዛሬ የምናከብራቸው ነገደ ኪሩቤል (ዐርባዕቱ እንስሳ) ይይዛሉ:: መንፈሳውያን ከመሆናቸው በላይ መንበረ ጸባኦትን እንዲሸከሙ ስላደላቸው ክብራቸው ታላቅ ነው:: ከመላእክት ወገንም ቅሩባን እነርሱ ናቸው::

+ዘወትርም ስለ ፍጥረታት (ሰዎች: እንስሳት: አራዊትና አዕዋፍ) ምሕረትን ይለምናሉ:: ለዚህም ነው በ4 እንስሳት (በሰው: በንስር: በላምና በአንበሳ) መልክ የተሳሉት:: ቅዱስ መጽሐፍም ስለ እነርሱ ብዙ ይላል:: (ሕዝ. 1:5, ራዕ. 4:6, ኢሳ. 6:1)

+በተለይ ግርማቸው እንደሚያስፈራ ተጽፏል:: "ምሉዓነ ዐዕይንት - ዐይንን የተሞሉ" ይላቸዋል:: ይህንንም መተርጉማን "ምሥጢር አዋቂነታቸውንና ግርማቸውን ያጠይቃል" ሲሉ ተርጉመውታል::

+ዐርባዕቱ እንስሳን 4 ሆነው በስዕል ብናያቸውም "ከመ ርዕየተ እለ ቄጥሩ" እንዲል እያንዳንዱ ከወገብ በላይ አራት በመሆናቸው ተሸካሚዎቹ 16 መልክ አላቸው:: በ2 ክንፋቸው ፊታቸውን: በ2ቱ እግራቸውን ሸፍነው በ2 ክንፋቸው ይበራሉ:: ይህም ብዙ ምሥጢር ሲኖረው ዋናው ግን አርአያ ትእምርተ መስቀል ነው::

+"4ቱ" እንስሳ (ኪሩቤል) በሐዲስ ኪዳንም ልዩ ክብር አላቸው:: 4ቱ ወንጌል ሲጻፍ እየተራዱ ስላጻፉ በስማቸው ተሰይሟል:: ቅዱስ ማቴዎስን ገጸ ሰብእ: ቅዱስ ማርቆስን ገጸ አንበሳ: ቅዱስ ሉቃስን ገጸ ላህም: ቅዱስ ዮሐንስን ገጸ ንስር እየተራዱ ስላጻፏቸው እነሆ እስከ ዛሬ ድረስ "ዘብእሲ ማቴዎስ": "ዘአንበሳ ማርቆስ": "ዘላሕም ሉቃስ" እና "ዘንስር ዮሐንስ" እየተባሉ ይጠራሉ::

+እነዚህ ቅዱሳን መላእክት የሰው ልጆችን ስለ መራዳታቸውም በብዙ ገድላትና ድርሳናት ላይ ተጽፏል:: የራሳቸውን "ድርሳነ ዐርባዕቱ እንስሳን" ጨምሮ በገድለ አባ መቃርስና በገድለ አባ ብስንድዮስ ላይ በስፋት ግብራቸው ተጽፏል::

+እኛም ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ክብራቸውን: ረድኤታቸውንና ምልጃቸውን አምነን ዘወትር እናከብራቸዋለን:: አባቶቻችን እንዲህ እያሉ እንደ ጸለዩ:-

"ሰላም ለክሙ ኪሩባውያን አፍራሱ:
ለመሐይምን ወጻድቅ እንተ ወርቅ አክሊለ ርዕሱ:
ኀበ ዝ አምላክ ለእለ ትጸውርዎ በአትሮንሱ:
ለእለ ጌገዩ ወለእለሂ አበሱ:
ሰአሉ መድኃኒተ ወምሕረተ ኅሡ::" (አርኬ)

+" ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ "+

=>ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ለቤተ ክርስቲያን የፈፀመውን መልካም ተግባር ያሕል መሥራት የቻለ ንጉሥ በሐዲስ ኪዳን የለም:: ጻድቁ ንጉሥ ከቅድስት እናቱ እሌኒና ከአረማዊ አባቱ ቁንስጣ በበራንጥያ ተወለደ::

+ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ /የመከራ ጊዜ/ ወይም የሰማዕታት ዘመን በመሆኑ ክርስቲያኖች በግፍ የሚጨፈጨፉበት ወቅት ነበር:: ክርስቲያኖችን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት በተደረገው የ40 ዓመታት ዘመቻ አብያተ-መቃድስና መጻሕፍት ተቃጠሉ::
ብዙዎቹ በየበርሃው ተሰደዱ:: ሚሊየኖች በግፍ አለቁ::

+የዚሕን ዘመን መከራ በውል ያልተረዳ ሰው ቅዱስ ቆንጠንጢኖስን ሊያከብር አይችልም:: ምክንያቱም ይህን የመከራ ዘመን በፈቃደ እግዚአብሔር አስቁሞ: ቀርነ-ሃይማኖት የቆመው: ብዙ ሥርዓት የተሠራው: ቤተ ክርስቲያንም ያበራችው በዘመኑ ነውና::

+ቅዱሱ ንጉሥ ለሁሉም ነቢያት: ሐዋርያትና ሰማዕታት አብያተ ክርስቲያናትን ራሱ በመሠረታት በቁስጥንጥንያ አንጿል:: በዘመኑ ቤተ ክርስቲያን በሰላም ኖራለት: በኃይለ መስቀሉ ጠላት ጠፍቶለት ኑሮ በዚህች ቀን አርፏል::

+ይህቺ ቀን ታላቁ ንጉሥ በፈለገ ኮቦር ቅዱስ መስቀልን የተመለከተባት ናት:: መክስምያኖስን ሊወጋ ወደ ሮም በተጉዋዘ ጊዜ በሰማይ ላይ መድኅን መስቀል ተዘርግቶ በላዩ ላይ "ኒኮስጣጣን" የሚል በዮናኒ ልሳን ተጽፎበት ተመልክቷል::

+ይህንንም "በዚህ ጠላትህን ድል ታደርጋለህ" ማለት ነው ብለው ተርጉመውለታል:: እርሱም በጋሻው: በጦሩ: በሰይፉ: በፈረሱ ላይ የመስቀል ምልክትን አድርጐ ማሕደረ ሰይጣን መክስምያኖስን ድል ነስቶታል:: እኛንም በሞገሰ መስቀሉ ይጠብቀን::

+"+ አባ ቅፍሮንያ ጻድቅ +"+

=>ይህ ቅዱስ ሰው በቀደመ ሕይወቱ አረማዊ ነበር:: ነገር ግን በውስጡ ቅንነት ተገኝቶበታልና እግዚአብሔር በቸር አጠራሩ ወደ ቤቱ አመጣው:: አባቱ አረማዊ: በዚያውም ላይ አገረ ገዢ ነበርና ለቅፍሮንያ ይህንኑ እያስተማረ አሳድጐታል::

+አንድ ቀን ግን ፈጣሪ ጥሪውን ላከለት:: ይኸውም ገና ወጣት ሳለ የገዳም አበው ያዩትና ትንቢት ይናገሩለታል:: "ይህ ሰው በጐ ክርስቲያን: ምርጥ ዕቃም ይሆናል" ሲሉት እንኩዋን ሌሎቹ ለእርሱ ለራሱም ምንም አልመሰለውም ነበር:: በዚህ መንገድ (በአረማዊነቱ) ዓመታት አልፈው ቅፍሮንያ የከተማው መኮንን (አገረ ገዢ) ሆነ::

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ወበዛቲ ዕለት ... ህዳር 7

በዚህች ቀን የፋርስና የልዳ ፀሐይ የተርሴስና የቤሩት ኮከብ የባህርና የየብሰ ብርሃን የጌታችን የመድሐኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ታማኝ ምስክር የሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ቀን ነው፤ ይህንንም ቀን በመላ ኢትዮጵያ በተለይም በመዲናችን የሚገኘው አንጋፋው ገነተ ጽጌ አራዳ ጊዮርጊስ ታቦተ ህጉ ወጥቶ በደማቁ ይከበራል። ታሪኩ በአጭሩ እንዲህ ነው ቅዱስ ጊዮርጊስ ሚያዚያ 23 ቀን በሰማዕትነት ካረፈ በኋላ አጋልጋዮቹ እጅግ የከበሩ ልብሶችና ያማሩ ሽቶዎች አዘጋጁ በከበረ አገናነዝም ገነዙት በመርከብም ጭነው ወደ ትውልድ አገሩ ልዳ አመጡት ነገር ግን ቤተሰቦቹ በሙሉ ማለትም አባቱ ዘሮንቶስ እናቱ ቴዎብስታ እህቶቹ ማርታና እስያ እንዲሁም አጭተውለት የነበረች እጮኛው ሁሉም ሞተው አገኙዋቸው፤ እንድርያስ የሚባል አጎት ነበረው ስጋውን ተቀበላቸው አገሬው ተሰበሰበ የእየሩሳሌሙ ሊቀ ጳጳስ አባ ቴዎድሮስ ተጠርቶ መጣ ቤተክርስቲያኑን አነጹለት ስጋውንም በዚያ በክብር አኖሩት፤ በዚያች ቀን እጅግ ብዙ የሆነ ድንቅ ታአምራትና ታላላቅ ኃይላት ተደረጉ፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ቤተክርስቲያን ይህንን ቀን ታከብረዋለች። ታሪክ ብልሁ ንጉሳችን እምዬ ምኒሊክ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያንን ሲሰሩ ከዚሁ ከልዳ የቅዱስ ጊዮርጊስ መቃብር ካለበት አፈሩን በመርከብ ከዚያም በበቅሎ አስጭነው አምጥተው ለቤተክርስቲያኑ መሰረት አድርገውታል ቅጥሩን ዙርያውንም ነስንሰውታል ይላል። ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚከበርባቸው ሚያዚያ 23 እረፍቱ ህዳር 7 ቅዳሴ ቤቱ ጥር 18 ዝርዎተ አጽሙ ናቸው፤ በረከቱን ያድለን። ምንጭ ገድለ ጊዮርጊስ ምዕራፍ 9

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝✞✝ እንኩዋን ለቅዱስ "ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት" እና "ለቅዱሳኑ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✞✝

+*" ቅዱስ ጊዮርጊስ ልዳዊ "*+

=>መጽሐፈ ገድሉ እንደሚለው የሰማዕታት አለቃቸው: አንድም ሞገሳቸው ታላቅና ክቡር ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ7 ዓመታት ስቃይ በሁዋላ ተሰይፏል:: ይሕስ ጥንተ ነገሩ እንደምን ነው ቢሉ:-

+ቅዱሱ የተወለደው ከአባቱ ዘረንቶስ (አንስጣስዮስ) እና ከእናቱ ቴዎብስታ የድሮው ፋርስ ግዛት ፍልስጥኤም (ልዳ) ውስጥ ነው:: የተባረኩ ወላጆቹ ክርስትናን ጠንቅቀው አስተምረውት አባቱ ይሞታል::

+ቅዱስ ጊዮርጊስ 20 ዓመት ሲሞላው የአባቱን ስልጣን እጅ ለማድረግ ሲሔድ የቢሩት (የአሁኗ ቤይሩት - ሊባኖስ) ሰዎች ዘንዶ (ደራጎን) ሲያመልኩ አገኛቸው:: እርሱ ግን የከተማውን ሕዝብ አስተምሮ: አሳምኖ: ደራጎኑንም በፈጣሪው ኃይል ገድሎ መንገዱን ቀጥሏል::

+ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ዱድያኖስና 70 ነገሥታት ዘንድ ሲደርስ ክርስቶስ ተክዶ ለጣዖት ይሠገድ ነበር:: በዚያች ሰዓት ድንግል እመቤታችን ወደ ሰማዕቱ መጥታ መከራውንና ክብሩን ነገረችው:: እርሱም በክርስቶስ ስም መሞት ምርጫው ነበርና ከእመቤታችን ተባርኮ ወደ ምስክርነት አደባባይ (ዐውደ ስምዕ) ደረሰ::

+ከዚያም ለተከታታይ 7 ዓመታት ብዙ ጸዋትወ መከራዎችን ተቀበለ:: 3 ጊዜ ሙቶ ተነሳ:: ከሰው ልጅ የተፈጥሮ ትዕግስት በላይ የሆነ ስቃይን ስለ ቀናች ሃይማኖት ሲል በመቀበሉ "የሰማዕታት አለቃቸው" : "ፀሐይና የንጋት ኮከብ" በሚል ይጠራል::
"ተውላጠ ጻማሁ ወሕማሙ::
ዘተለዐለ ሞገሰ ስሙ::" እንዲል መጽሐፍ::

+ከ7 ዓመታት መከራ በሁዋላም ከብዙ ተዓምራት ጋር ተሰይፎ ደም: ውሃና ወተት ከአንገቱ ፈሷል:: 7 አክሊላትም ወርደውለታል::

=>ይህቺ ዕለት ለቅዱስ ጊዮርጊስ ኃያል ቅዳሴ ቤቱ ናት:: እርሱ በ390ዎቹ አካባቢ ሰማዕት ከሆነ ከጥቂጥ ዓመታት በሁዋላ በዚያው በሃገሩ ደብር አንጸው: አጽሙን አፍልሠው በዚህች ቀን ቀድሰዋታል::

+ቅዱሱ ሰማዕት ከሰማዕትነቱ በፊትም ሆነ በሁዋላ ተአምረኛ ነውና አንዷን እንመልከት:: በዘመኑ የክርስቲያኖችን ደም ሲያፈሱ ከነበሩ አራዊት (ነገሥታት) መካከል አንዱ የሆነው ዲዮቅልጢያኖስ ርጉም የ47 ሚሊየን ክርስቲያኖችን ደም አፍስሶ ነበርና ፈጣሪ ደመ ሰማዕታትን የሚበቀልበት ጊዜ ደረሰ::

+በ305 ዓ/ም አካባቢ አረመኔው ንጉሥ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተአምረኛነት ሰምቶ እንዲያፈርሱት ሠራዊት ላከ:: የሠራዊቱ አለቃም ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ገብቶ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስዕል ላይ ተሳለቀ::

+ከፊቱ የነበረውን ቀንዲል በሰይፍ እመታለሁ ሲል ግን ቀንዲሉ ተገልብጦ መሐል አናቱን መታው:: እንደ እብድ ሆኖ ሞተ:: ሠራዊቱም ሰምቶ ወደ ንጉሡ ሸሸ:: ይሕን ሰምቶ የተበሳጨው ዲዮቅልጢያኖስ ግን ራሱ ሊያፈርሰው ሔደ:: ከቤተ ክርስቲያኑ በር ላይ ሲደርስ ሚካኤልና ገብርኤል ዐይኑን አጠፉት::

+እገባለሁ ሲል ቅዱስ ጊዮርጊስ ከላይ መረዋውን (ደወሉን) ለቀቀበት:: ራሱን ቢመታው ደነዘዘ:: የብዙ ቅዱሳንን ደም የጠጣው ርጉሙ ንጉሥም አብዶ ለ7 ዓመታት ፍርፋሪ ሲለምን ኑሮሰ ይጣን ከገደል ጫፍ ወርውሮ ገድሎታል::

=>አምላካችን እግዚአብሔር ከኃያሉ ሰማዕት ጽናትና ትእግስት: ከበረከቱም ይክፈለን::

+"+ ቅዱስ ጊዮርጊስ እስክንድርያዊ +"+

=>በቤተ ክርስቲያን "ጊዮርጊስ" የሚባሉ ብዙ ቅዱሳን አሉ:: ከልዳዊው ቀጥሎም ይህንን ግብጻዊ ሰማዕት እንጠቅሳለን:: ስሙ ጊዮርጊስ የተባለውም በታላቁ ሰማዕት አማላጅነት ስለ ተገኘ ነው::

+አባቱ ኅዳር 7 ቀን የሊቀ ሰማዕታትን ቅዳሴ ቤት ሊያከብር ሒዶ ስለተማጸኑ የሚስቱ ማሕጸን ተከፍቶለት ልጅ ወልዷል:: ስሙንም ጊዮርጊስ ብሎታል:: ባደገም ጊዜ እጅግ ብርቱ ክርስቲያን ሆነ::

+የግብጻዊ ቅዱስ ጊዮርጊስ ብርታቱ ምንድን ነው ቢሉ:-ንጹሕ አምልኮቱ ጾምና: ጸሎቱ: በጐ ምጽዋቱ ነው:: "ስም ይመርሕ ኀበ ግብር - ስም ወደ ተግባር ይመራል" እንዲሉ አበው የሰማዕቱን ስም ይዞ እሱም ይሔው እድል ገጠመው::

+በአጋጣሚ ወላጆቹ ሲሞቱ የሚኖረው ከከተማው መኮንን ቤት ነበር:: ምክንያቱም የመኮንኑ ሚስት እህቱ ናትና:: ችግሩ ግን መኮንኑ አርማንዮስ ጣዖት አምላኪ: በዚያ ላይ ጨካኝ መሆኑ ነው::

+አንድ ቀን ግብጻዊ ቅዱስ ጊዮርጊስ የመኮንኑን ሴት ልጅ ወደ በርሃ ወስዶ የደብረ ቁስቁዋም መነኮሳትን ዝማሬ አሰማት:: ክርስትናንም አስተማራት:: ይህንን የሰማው መኮንኑ ግን በብስጭት ቅዱስ ጊዮርጊስንና የራሱን ሴት ልጅ በአደባባይ አሰይፏቸዋል:: የክብርን አክሊልም ተቀዳጅተዋል::

+"+ ቅዱሳን ዘኖቢስና ዘኖብያ +"+

=>እነዚህ ቅዱሳን እናትና ልጅ ናቸው:: ዘኖብያ እናቱ ስትሆን ዘኖቢስ ደግሞ ወጣት ልጇ ነው:: የቅዱሳኑ ሃገር ደግሞ ተበይስ ትባላለች:: በዘመነ ሰማዕታት ድንቅ በሆነ ሕይወታቸውና ተአምራቸው እንደ ኮከብ አብርተዋል:: ከ5 ጊዜ በላይም ከተደገሰላቸው የሞት ወጥመድ በእግዚአብሔር ኃይል አምልጠዋል::

+ " ክርስትናችን አንክድም: ከክርስቶስ ፍቅር አንለይም በማለታቸው:-

1.ልብሳቸውን ገፈው: በዓየር ላይ ሰቅለው: ደማቸው እስኪንጠፈጠፍ ገረፏቸው:: በክርስቶስ ኃይል ተረፉ::

2.የእንጨት መስቀሎችን አሰርተው በአደባባይ ቸንክረው ሰቀሏቸው:: ከዚህም ዳኑ::

3.. 2 ወንበሮች ላይ ችንካሮችን ተክለው በዚያ ላይ አስቀመጧቸው:: አሁንም በፈጣሪ ኃይል ዳኑ::

4.ጥልቅ ጉድጉዋድ ተቆፍሮ: እሳትም ነዶ በዚያ ውስጥ ተጨመሩ:: ቅዱስ መልአክ ግን ወርዶ አጠፋላቸው::

5.አንዴ ደግሞ በቤት (በውሽባ ቤት) እሳት ነዶ በውስጥ ተጨመሩና ተዘጋባቸው:: እግዚአብሔር ግን ከዚህም ታደጋቸው:: ስለ ክብራቸውም ቅዱስ መልአክ ወርዶ እነሱን አክብሮ: መኮንኑን ዙፋኑን አሸክሞ በአደባባይ አዙሮታል::

+አንዴም ጋን አሸክሞ በሁዋላቸው አስከትሎታል:: በነዚህ ሁሉ ድንቆች ብዙ ሕዝብ እያመነ በሰማዕትነት ሙቷል:: በመጨረሻ በዚህ ቀን ዘኖብያና ዘኖቢስ ሲሰየፉ መብረቅ ወርዶ 54 አሕዛብን ገድሏል:: በዚህም መኮንኑ ተገርሞ በክርስቶስ አምኗል::

+"+ አባ ሚናስ ዘተመይ +"+

=>ይህ ቅዱስ አባት ደግሞ ጣዕመ ሕይወቱ ድንቅ ነው:: ክርስቲያን ወላጆቹ በሥርዓት አሳድገው በተክሊል አጋቡት:: ወደ ሙሽራይቱ ገብቶም "እህቴ! ይህ ዓለም ኃላፊ ነውና ለምን በድንግልና አንኖርም?" አላት::

+እርሷም በደስታ "ይሁን" አለችው:: ለበርካታ ዓመታትም ቀን ቀን ሥራቸውን ሲሠሩ: እንግዳ ሲቀበሉ ይውላሉ:: ሌሊት ደግሞ ወገባቸውን ታጥቀው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ያድራሉ::

+ከዓመታት የቅድስና ሕይወት በሁዋላም ቅዱስ ሚናስ ሚስቱን አስፈቅዶ በርሃ ገብቷል:: በተጋድሎ ሳለም እግዚአብሔር ለእረኝነት መርጦት: ተመይ በምትባል የግብጽ አውራጃ ላይ ዽዽስናን ተሹሟል:: በዚያም እስካረጀ ድረስ ተጋድሎ በዚህች ቀን ዐርፏል::

=>እንደ ደመና የከበቡን የእነዚህ ሁሉ ቅዱሳን አምላክ በቸርነቱ ይማረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

=>ኅዳር 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት (ቅዳሴ ቤቱ)
2.ቅዱስ ጊዮርጊስ እስክንድርያዊ
3.ቅዱሳን ዘኖቢስና ዘኖብያ (ሰማዕታት)
4.ቅዱስ ሚናስ ዘተመይ
5.ቅዱሳን መርቆሬዎስና ዮሐንስ (ጻድቃን ወሰማዕት)
6.አባ ናሕርው ሰማዕት

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ኅዳር 7:- ቀን በዓመታዊ የዕረፍት በዓላታቸው ታስበው የሚውሉት የቦረናው አቡነ ገብረ እንድርያስ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመላለሱ በታላቅ ድንጋይ ላይ ተጭነው ነበር፣ ድንጋዩም በደመና አምሳል ይታዘዛቸው የነበረ ሲሆን አስገራሚው ጠበላቸው ውስጥ እንጨት ሲነከርበት እንጨቱ በተአምራት ነጭ መቁጠሪያ ሆኖ ይወጣል፡፡ (የፎቶው ላይ የሚታየውም ይኸው ዕንጨቱ ከጠበላቸው ውስጥ በተአምራት ነጭ መቁጠሪያ ሆኖ የወጣው መቁጠሪያ ነው፡፡ እርሱም ለእንቅርትና ለልዩ ልዩ ሕመሞች መድኃኒት ነው፡፡)

አቡነ ገብረ እንድርያስ ደብረ ቆበት የሚባለው ገዳማቸው ደቡብ ወሎ ከዓዲ ከተማ በስተ ምዕራብ አቅጣጫ ከባሕር ጠለል 6652 ጫማ ከፍታ ላይ ያገኛል። ገዳሙ በአባይ ተፋሰስ ዙሪያ ከወተት ወንዝ በስተሰሜን፡ ከደብረ ዘመዶ ማርያም (ዘሞድ) መንደር በስተደቡብ ምሥራቅ እና ከደብረ ሰኮሩ ሥላሴ በስተምዕራብ አቅጣጫ ላይ ይገኛል።

ደብረ ቆዘት አቡነ ገብረ እንድርያስ ገዳም የተመሠረተው በ995 ዓ ም 10ኛው መ/ክ /ዘ ላይ ነው። የገዳሙም መሥራች አባ ገብረ ክርስቶስ የተባሉ ታላቅ ጻድቅ መሆናቸውን የአቡነ ገብረ እንድርያስ ገድል ይናገራል።

ገዳሙ ያለበት አካባቢ አቡን ውኃ ተብሎ ይጠራል። ከገዳሙ ፊት ለፊት ከጣቀት ወንዝ ማዶ ደግሞ ዳቆን ውኃ (ደቶኑ) የሚባል አካባቢ ይገኛል። እነዚኽ አካባቢዎች ይኽንን መጠሪያ ያገኙት ቀድሞ በዚኽ አካባቢ በርካታ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት የነበሩበት እንደሆነና የቦታዎች መጠሪያም በቦታው ካሉ ምእመናን መኖሪያ ጋር የተያያዘ መሆኑን አባቶች ይናገራሉ። አቡን ውኃ በሚባለው አካባቢ አባ ኤልሳዕ፣ አባ ጎርጎርዮስ፡ አባ ገብረ ክርስቶስ አባ ቅዱስ አባ መስቀል አባ ጉባ የተባሉ ሰባት ቅዱሳን አባቶች በቦታው ይኖሩ እንደነበርና ከዚኽ ብዙ ሳይርቅ የዲያቆኖች መኖሪያ ሰፈር ስለነበር ቦታው ወደቆኑ የሚለውን ስያሜ እንደተሰጠው አባቶች ሲናገሩ አካባቢው ዛሬም ድረስ ይኸንን መጠሪያ እንደያዘ ነው። አቡን በቀድሞው ዘመን ለጳጳስ ብቻ ሳይሆን ሥልጣነ ክህነት ላላቸው ቀሳውስትና መነኲሳት መጠሪያነት ያገለግል እንደ ነበር ፕሮፌስር ጌታቸው ኃይሌ ባሕረ ሀሳብ በሚለው መጽሐፍቸው ላይ ገልጠዋል

የአቡነ እንድርያስ አባታቸው ተንሥአ ክርስቶስ
እናታቸው አርሴማ ይባላሉ። ሁለቱም ደጋግ ቅዱሳን ናቸው። ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ ለመምህር ሰጧቸው። መምህሩም ጸጋ እግዚአብሔር እንዳደረባቸው ዐውቀው ብዙዎችን የምታድን ጻድቅ ትሆናለህ ብለው ትንቢት ነግረዋቸዋል። የመጻሕፍትንም ትርጓሜ በሚገባ ካስተማሯቸው በኋላ ንፍታሌም ይባል የነበረውን ስማቸውን ለውጠው ገብረ እንድርያስ አሏቸው። ጻድቁ በአቡነ ዮሐንስ ከማ ገዳም ለረጅም ጊዜ በታላቅ ተጋድሎ አገልግለዋል። አባታችን ሙታንን በማስነሣትና ድውያንን በመፈወስ ብዙ ተአምራትን ሲያደርጉ ኖረዋል። የትዉልድ ሀገራቸው በቤተ አምሃራ ክፍል ሀገረ ወለቃ ከገዳማቸው ቅርብ ርቀት ላይ "ደብረ ደብቄ ማርያም" እንደሆነና የአቡነ ገብረ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር እንደነበሩ እንዲሁም የመጀመሪያ ስማቸው ንፌታሌም ይባል እንደነበር፣ ካህንና የአምስት ልጆች አባትም እንደሆኑ በገድላቸው ላይ ተጽፎ ይገኛል።

አቡነ ገብረ ክርስቶስ ጽኑ የሆነውን ተጋድሏቸውንና መልካም አገልግሎታቸውን ፈጽመው በሞት ከማረፋቸው በፊት የገዳሙ አበምኔት ሆነው እንዲያገለግሉ ንፌታሌምን (አቡነ ገብረ እንድርያስን) መርጠው እንደሾሟቸው በመጽሐፈ ገድላቸው ላይ ተጽፏል። አቡነ ገብረ እንድርያስ ዘደብረ ቆዘት ከሀገረ ወለቃ እስከ ጎጃም ድረስ ስብከተ ወንጌል እንዳስፋፉ የቤተ ክርስቲያን መዝገበ ቃላት በሚለው መጽሐፍ ላይ ተጽፎ ይገኛል።

አቡነ ገብረ እንድርያስ በደብረ ርስኩር (በአሁኑ ደብረ ብርሃን ሰኮሩ ሥላሴ) ቤተ ክርስቲያን በሱባኤ ላይ እንዳሉ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል በወርቅ ጽዋ ሰማያዊ ወይንና ሰማያዊ ኅብስት መግቧቸዋል። እንዲሁም አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሦስት ጽዋ ማየ ሕይወት ካጠጣቻቸው በኋላ ሕሙማንን እንደፈወሱ፣ ዕዉራንን እንዳበሩ፣ ሙት እንዳስነሡ በገድላቸው ላይ ተጽፏል።

የአቡነ ገብረ እንድርያስ አባት የሆኑት የአቡነ ገብረ ክርስቶስ ጥንታዊ ውቅር ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ ጠፍ ሆኖ ስለቀረ ከዚሁ ገዳም አቅራቢያ የልጃቸው የአቡነ ገብረ እንድርያስ ገዳም ተመሥርቶ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። አዲሱ ቤተ ክርስቲያን ለመጀመርያ ጊዜ የተሠራው በዐፄ ድል ነአድ ዘመነ መንግሥት ሲሆን ከዚያም በኋላ በተደጋጋሚ እድሳት ተደርጎለታል

ጻድቁ አቡነ ገብረ እንድርያስ እግዚአብሔር ኀጥአንን እንዲምርላቸው ጣቀት ንዝ ከተባለው ቦታ ላይ በአንገታቸው ላይ ትልቅ ድንጋይ እየተሸከሙ ይጸልዩ እንደነበርና ይጸልዩበት ከነበረው ወንዝ ውስጥ በተኣምራት መቍጠሪያ የሚሠራ መል እንደፈለቀላቸው በገድላቸው ላይ ተጽፏል።

ከገዳሙ በስተደቡብ አቅጣጫ እግዚአብሔር ኀጥአንን እንዲምርላቸው ጣቀት ወንዝ ከተባለው ቦታ ላይ በአንገታቸው ድንጋይ አሥረው ይጸልዩበት ከነበረው ጣቀት ወንዝ ላይ በተኣምራት መቍጠሪያ የሚሠራው የአባ ጎርጎርዮስ ( ወንበረ ሥላሴ) ጠበል እና ሌሎችም በርካታ ጠበሎች ይገኛሉ። እነዚኽም ጠበሎች ሕሙማን ከተለያዩ በሽታዎች ለመፈወስ ከማገልገላቸውም በላይ መነኰሳት ለጸሎት የሚገለገሉበትን መቍጠሪያ በተኣምራት ይሰጣሉ። አዘገጃጀቱም እንዲህ ነው- በመጀመርያ በጠበሉ ላይ ገመድ ሣር ወይም ቀጭን ዕንጨት በመንከር ኩቆይታ በኋላ በተነከረው ገመድ፣ ሣር ወይም ዕንጨት ላይ ጠንካራ ዓለት ይሠራል፤ ጠበሉ ውስጥ በተነከረው ገመድ ወይም ክር ላይ ውኃው በተኣምራት ወደ ጠንካራ ዓለትነት ይቀየራል። ከዚያም ገመዱን ወይም ክሩን ወይም ዕንጨቱን እሾልኮ በማውጣት ውስጡ ክፍት ስለሚሆን ያንን አስተካከለው እየከረከዉ | መቍጠሪያ መሥራት ይቻላል።

አቡነ ገብረ እንድርያስ ዘወትር ዐርብ ዐርብ ወደ ኢየሩሳሌም ሔደው የጌታችን የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስን መካነ መቃብር ተሳልመው ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ተቀብለው ለመምጣት ይመላለሱ የነበረው በአንድ ትልቅ ድንጋይ ላይ ተቀምጠው ነው። ድንጋዩንም እንደ ደመና ይጠቀሙበት ነበር።

ከዚኸም ሌላ ጻድቁን የዛፍ ዋርካ እንደ ጥላ ሆኖ ያገለግላቸው ነበር። እርሳቸውም ድንጋይ
እንደ ሠረገላ፣ ዋርካውን እንደ ጥሳ እየተጠቀሙባቸው ወደ ኢየሩሳሌም ይመላለሱ እንደነበር በገድላቸው ላይ ተጽፏል። ያ እንደ ደመና ሠረገላ ሆኖ ለመጓጓዣነት ያገለግላቸው የነበረው ትልቅ 'ንጋይ ዛሬም ድረስ በገዳማቸው ውስጥ በክብር
ተቀምጦ ይገኛል። በዓለ ዕረፍታቸውም ኅዳር 7 ቀን በገዳማቸው በታላቅ ድምቀት ይከበራል።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

27 zelalemawiw አባቴ🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ደብረ ቁስቋም

👉 በደቡብ ግብፅ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ ደብረ ቁስቋም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲሁም ቅዱስ ዮሴፍንና ቅድስት ሰሎሜን ይዛ ከስደት ሲመለሱ ያረፉበት ቦታ ነው፡፡

👉ይህም በቅዱስ ወንጌል እንደተጻፈ ሄሮድስ ክርስቶስን ለመግደል በፈለገ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለአረጋዊው ዮሴፍ በሕልሙ ‹‹ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ›› ባለው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ (ማቴ. ፪፥፲፫-፲፭)

👉የክርስቶስ ስደቱ ቀድሞ በነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹. . . እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብፅ ይመጣል፡፡ የግብፅም ጣዖታት በፊቱ ይዋረዳሉ›› ተብሎ በተነገረው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ ነቢዩ ፈጣን ደመና ያለው ጌታችን በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ጀርባ ላይ ሆኖ ወደ ግብፅ መውረዱን ለመግለጽ ነው፡፡ (ኢሳ. ፲፱፥፩) በስደቱም ጣዖታተ ግብፅ እየተሰባበሩ ሲወድቁ፤ በእነርሱም አድረው ሰውን ሲያስቱ የነበሩ አጋንንትም ሲሸሹ ታይተዋል፡፡

👉ደግሞም ጌታችን ዳግማዊ አዳም ነውና በምክረ ከይሲ (ዲያብሎስ) ምክንያት ተሰዶ የነበረው ቀዳማዊ አዳምን ለመካስ ተሰደደ፤ በዚህም አጋንንትን ከሰው ልቦና አውጥቶ አሳደደ፡፡

👉እመቤታችንም ልጇን ይዛ ከስደት ስትመለስ ያረፈችበትን ተራራ ደብረ ቁስቋምን ባረከችው ቀደሰችውም፤ ይህ ተራራ የተቀደሰ ተራራ ስለመሆኑ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ታኦፊሎጎስ በድርሳነ ማርያም እንዲህ አለ፤ ‹‹ይህም ከሀገሮቹ ሁሉ ተራሮች የሚበልጥ (የተለየ) ከፍ ያለ ተራራ ነው፡፡ በውስጡ ቅዱስ አግዚአብሔር ያድራል፡፡ ይህንን ተራራ የእግዚአብሔር ልጅ ወዶታል፤ አክብሮታልምና፤ ከዓለም ሀገሮች ሁሉ ከተቀደሰች እናቱ ጋር አድሮባታልና፡፡ ከመላእክት ቤት ያድር ዘንድ አልወደደም፤ ቢታንያንም አልመረጠም፡፡ ከተራራው ላይ ባለች ገዳም ቤት ውስጥ አደረ እንጂ፤ ነቢዩ ዳዊት፤ የጽዮንን ተራራ ወደደ፤ በአርያምም መቅደሱን ሠራ እንዳለ፡፡››

👉‹‹አንተ ተራራ ሆይ የእግዚአብሔር ማደሪያ በሆንህ ጊዜ በኪሩቤልና በሱራፌል መካከል ፍጹም ደስታ ተደረገ፡፡ የመላእክት ሠራዊት ቅዱስ የሆነ ፈጣሪያቸውንና ጌታቸውን ይታዘዙ (ያገለግሉ) ነበር፡፡ አንተ ተራራ ሆይ ያደረብህ ጌታችን ስለሆነ ከተራሮች ሁሉ ከደብረ ሲናም ይልቅ ከፍ ከፍ አልህ፤ ጌታችን በደብረ ሲና ባረፈ ጊዜ ፍጹም ደስታ፣ ታላቅ ብርሃንም በሆነ ጊዜ መቅረብና መመልከት ከሙሴ በቀር የቻለ የለም፡፡ እርሱም ቢሆን ፊቱን ማየት አልቻለም፡፡ ሥጋ ለባሽ ሁሉ እርሱን ዐይቶ በሕይወት መኖር የሚቻለው የለምና፡፡ እኛ ግን አየን፤ ከዚህ ማደሩንም ተረዳን፤ ዳግመኛም ንጽሕት በሆነች በማርያም ዘንድ አየነው፡፡ ቅድስት ከሆነች ከእመቤታችን ማርያም ዘንድ በቤተልሔም ስለ እኛ በተዋሐደው ሥጋ በጨለማና በሞት ጥላ ሥር ያለን እኛን ከቸርነቱና ሰውን ከመውደዱ የተነሣ መጥቶ አዳነን፤ ከዓለም ሁሉ ይልቅ ጣዖትን በማምለክ ሲበድሉም ወደ ግብፅ ሀገር ወርዶ በእነርሱ ላይ የመለኮትነት ብርሃኑን በማብራት ታላቅ የሆነ ክብሩን ገለጠ››፡፡ (ድርሳነ ማርያም)

👉ኅዳር ፮ ቀንን የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛም በኋላ ዘመን ሐዋርያትን በደብረ ቁስቋም ሰብስቦ፤ ታቦትንና ቤተ ክርስቲያኑን አክብሮ የቊርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙን እንደ ሰጣቸው፤ እኛንም ለዚህ ክብር የበቃን እንሆን ዘንድ የእግዚአብሔር አምላክ ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን፤ አሜን፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

5.ቅዱስ ቴዎፍሎስ ሊቅ
6.አባ ጽጌ ድንግል ዘወለቃ
7.አባ ፊልክስ ዘሮሜ

=>ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም
2.አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን
3.አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል
4.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
5.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
6.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
7.ቅድስት ሰሎሜ
8.አባ አርከ ሥሉስ
9.አባ ጽጌ ድንግል
10.ቅድስት አርሴማ ድንግል

++"+ ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕጻኗን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ:: አሕዛብንም ሁሉ በብረት ዘንግ ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ: ወንድ ልጅ ወለደች:: ልጇም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ:: ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቧት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ሥፍራ ወደ በረሃ ሸሸች:: +"+ (ራዕይ. 12:4-7)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

5.ቅዱስ ቴዎፍሎስ ሊቅ
6.አባ ጽጌ ድንግል ዘወለቃ
7.አባ ፊልክስ ዘሮሜ

=>ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም
2.አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን
3.አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል
4.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
5.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
6.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
7.ቅድስት ሰሎሜ
8.አባ አርከ ሥሉስ
9.አባ ጽጌ ድንግል
10.ቅድስት አርሴማ ድንግል

++"+ ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕጻኗን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ:: አሕዛብንም ሁሉ በብረት ዘንግ ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ: ወንድ ልጅ ወለደች:: ልጇም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ:: ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቧት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ሥፍራ ወደ በረሃ ሸሸች:: +"+ (ራዕይ. 12:4-7)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

📣ቃላት ክፉ ናቸው!📣
በቃላት ብቻ ሰውን ትገድላለህ፤በቃላት ብቻ ሰውን ታድናለህ....ስለዚህ ከአፍህ የምታወጣቸውን ቃላት ጥንቃቄ አድርግባቸው......አለበለዛ ከገዳይነት ወንጀል አታመልጥም።
       
                  🌟💫ኪነ-ጥበብ💫🌟

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ህዳር 5/2016 #ጴጥሮስና_ጳዉሎስ
#ፃድቁ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሣኑ ስም ለምናመሰግንበት ቅዱሣኑ በምልጃ ፀሎታቸዉ እንዲያስቡን ለምንማፀንበት ወርሐዊ መታሠቢያ በአላቸው እንኳን አደረሰን

👉አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐገራቸው ንሂሳ ግብጽ ነው አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል አንድ ቀን አቅሌሲያ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከሥዕለ ሥላሴ ሥር ወድቃ ስትማጸን ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበጥ ልጅ እንኪ ተቀበይ የሚል ድምጽ ሰማች

👉በዚህ መሠረት ቅዱስ አባታችን ጻድቁ አቡዬ ገብረ መንፈስ ቅዱስ መጋቢት 29 ተፀንሰው ታኀሣስ 29 ተወለዱ

👉አባታችን ዓይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ብለዉ ተነስተው «ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ዘዓውፃእከኒ እምጽልመት ውስተ ብረሃን» ብለው አመስግነዋል

👉በኋላም ምድራዊ መብል መጠጥ ሳይመገቡ ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መላዕክትን መስለዋል አባታችን ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በኢትዮጵያ 262 ኖረው በ562 ዓመታቸው በተስፋቸው ያመነውን በኪዳናቸው የተማጸነ ጌታ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሊምርላቸው ተስፋቸውን ተቀብለው በዕለተ እሁድ ዐርፈዋል

👉መላእክት በአክናፈ እሳት ኢየሩሳሌም ወስደው በየማነ ምስዋዕ ቀብረዋቸዋል

👉የፃድቁ አባታችን #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ምልጃ ፀሎታቸው ረድኤት በረከታቸው አይለየን "አሜን"

👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸዉ የምናስባቸው ቅዱሣን #ብርሃናተ_አለም_ጴጥሮስ_ወ_ጳዉሎስ እንዲሁም ሌሎቹ ቅዱሣን ፀሎታቸዉ ይጠብቀን "አሜን"💒💚 💛 ❤💒

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ህዳር 4/2016 #ወንጌላዊዉ_ዮሐንስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በምስጋና ለሚከብርበት 2016 አመተ ምህረት በስሙ ለተሰየመለት ወልደ ነጎድጓድ #ቅዱስ_ዮሐንስ ወርሐዊ መታሠቢያ እለት እንኳን አደረሰን

👉የከበረና የተመሰገነ ዮሐንስ በዚህ ዓለም ዘጠና ዓመት ኖረ እጅግም ሸመገለ ግን እንደ ባልንጀሮቹ ሐዋርያት በመሰየፍ ሞትን አልቀመሰም

👉ስለ ድንግልናውና ስለ ንጽሕናው ይህ ሆነ ሁሉም በክብር ይስተካከሉ ዘንድ እርሱም ወንጌልን ቀለምሲስ የሚባለውን ራእይ ሦስት መልእክታትን የጻፈ ነው

👉ራት ሲበሉ በጌታ ኢየሱስ አጠገብ የተቀመጠውና አቤቱ የሚያሲዝህ ማነው ያለው ይህ እርሱ ነው

👉ጌታችንም በተሰቀለ ጊዜ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር በመስቀሉ አጠገብ የቆመ እናቱንም እነሆ ልጅሽ ያላት እርሱን ደቀ መዝሙሩንም እነኋት እናትህ ያለው ነው

👉ጴጥሮስም እርሱን ሲከተለው በአየው ጊዜ ስለርሱ ጌታ ኢየሱስን አቤቱ ይህስ እንዴት ነው ብሎ የተናገረ ጌታ ኢየሱስም እስክመጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ከወደዱኩ አንተ ምን አለህ አንተ ግን ተከተለኝ ያለለት ይህ ነው

👉የፍቁረ እግዚእ #ቅዱስ_ዮሐንስ ረድኤትና በረከት ምልጃ ፀሎት ሁላችንንም ይጠብቀን የተሠጠን አዲስ አመተ ምህረት በስሙ የተሠየመለት #ቅዱስ_ዮሐንስ አመተ ምህረቱን ይባርክልን "አሜን"

👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የምናስባቸው ቅዱሳን ቃል ኪዳናቸው ይጠብቀን "አሜን"

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር በማኅበረ ኤዶምያስ መንፈሳዊ ግሩፕ ላይ እየተጠየቀ ነው ተሳተፉ ።ግሩፑ ላይ ላልተቀላቀላችሁ ግሩፑን ሊንክ በመንካት ተቀላቀሉ❤
/channel/edomiyass21
/channel/edomiyass21
/channel/edomiyass21
/channel/edomiyass21
/channel/edomiyass21

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለአበው ቅዱሳን "318ቱ ሊቃውንት" ዓመታዊ የጉባኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ጉባኤ ኒቅያ †††

††† በዚህች ዕለት (ኅዳር 9 ቀን) በሃገረ ኒቅያ በእመቤታችን እና በአምላክ ልጇ የሚያምኑ 318ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት ተሰብስበዋል::

የሊብያው ሰው አርዮስ ጌትነት ገንዘቡ የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ክዶ ሊያስክድ ሲሯሯጥ በፈቃደ እግዚአብሔር: በጻድቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ጥሪ: 2348 ምሑራን ከመላው ዓለም ተሰበሰቡ::

ጥሪው የተላለፈው በወርኀ ሚያዝያ ሲሆን በመንገድ ችግር ሁሉም ተጠቃለው ኒቅያ የገቡት መስከረም 21 ቀን ነበር:: ከተሰበሰበው ብዙ ሰው መካከል የአበውን ደቀ መዛሙርት ሳንቆጥር ሃይማኖታቸው የቀና: ምግባራቸው የጸና 318ቱ አበው ሊቃውንት ተገኙ::

እነዚህ አባቶች "ሊቃውንት" ሲባሉ እንዲሁ በእውቀት ብቻ የበሰሉ እንዳይመስሉን:: 318ቱ አበው እኩሎቹ በዘመነ ሰማዕታት እጅና እግራቸውን የተቆረጡና ለሃይማኖታቸው ብዙ ዋጋ የከፈሉ ናቸው::

እኩሎቹ ደግሞ በገዳማዊ ሕይወት ያጌጡ: ፍቅረ ክርስቶስ በውስጣቸው የሚነድ: የመንፈስ ቅዱስ ቤት ናቸው:: እስኪ እናውቃቸው ዘንድ የጥቂቶችን ማንነት በስምና በመገለጫ እንመልከት:-
1.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ (በዘመነ ሰማዕታት ለ22 ዓመት ሲቆራርጡት ኖረው በጉባኤው ላይ የተገኘው ያለ እጅ: እግር: ጀሮ: ከንፈር: ቅንድብ ነው)
2.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ (ስለ ቀናች እምነት ለ50 ዓመታት የተጋደለና ለ15 ዓመታት በስደት የኖረ ነው)
3.ቅዱስ እለእስክንድሮስ ሊቅ (ከሰማይ ብርሃን ይወርድለት የነበረ አባት ነው)
4.ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ (በጸሎቱ አጋንንትን ያንቀጠቀጠ: ነፍሳትን ከሲዖል የቀማና ከከዊነ እሳት የደረሰ አባት ነው)
5.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘአርማንያ (ስለ ቀናች እምነት መጸዳጃ ጉድጓድ ውስጥ ለ15 ዓመታት ተጥሎ የኖረ ሰማዕት ነው)
6.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሜራ (ከሕጻንነቱ የተቀደሰ: በበርሃ የተጋደለ: በዘመነ ሰማዕታት ብዙ መከራን የተቀበለ አባት ነው)
7.ቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን (በደግነቱ ሙታንን ያስነሳ: ወንዝን በጸሎቱ ያቆመ: በንጽሕና የተጋደለ አባት ነው)
8.ቅዱስ ሶል ጴጥሮስ (ቅዱሱን ንጉሥ ያጠመቀ:
ቁስጥንጥንያን በወንጌል ያበራ ሊቅ ነው)
9.ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ (ስለ ቀናች እምነቱ ብዙ ግፍ የደረሰበትና በስደት ያረፈ አባት ነው)

ለአብነት እንዲሆኑን እነዚህን አነሳን እንጂ 318ቱም ሊቃውንት ስለ ቤተ ክርስቲያን ተግተው የተጋደሉ: ብዙ ዋጋም የከፈሉ አባቶች ናቸው::

በወቅቱ ታዲያ ቤተ ክርስቲያንን የበጠበጡ ብዙ መ**********ና***********ፍ**********ቃ*******ን ቢኖሩም የአርዮስ ግን ከመጠኑ አለፈ:: የእርሱ ኑፋቄ (ፈጣሪያችንን ፍጡር ነው ማለቱ) መነሻው ከእርሱ በፊት ነው:: መ*********ና*******ፍ********ቃ*******ን ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ ቤተ ክርስቲያንን ሲያውኩ መኖራቸው ግልጽ ነው::

በተለይ ደግሞ ቢጽ ሐሳውያንና ግኖስቲኮች የወለዷቸው እሾሆች አባቶቻችንን እንቅልፍ ነስተው ነበር:: የሚገርመኝ በዘመኑ እንደ ነበሩ መ************ና***********ፍ*********ቃ*******ን ኃይለኝነት የእኞቹ ከዋክብት ሊቃውንት ባይኖሩ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ያሳስብ ነበር::

ግን እግዚአብሔር ለሁሉ እንደሚገባ ያዘጋጃልና አበው ብርቱ መ*******"""****"*ና*********ፍ********ቃ******ንን በብርቱ መንፈሳዊ ክንድ እያደቀቁ ከጐዳና አስወገዷቸው:: የዛሬውን ደካማ ትውልድ ደግሞ የአርዮስ ልጆች 2 (3) ጥቅስ ይዘው ሲያደናብሩት ይውላሉ::

ሐረገ መ******ና********ፍ*********ቃ******ን በርጉም ሳምሳጢ ጳውሎስ: በመርቅያንና በማኒ ይጀምራል:: በእርግጥ አርጌንስ እና የግብጹ ቀሌምንጦስም ተቀላቅለዋቸዋል:: ርጉም ሳምሳጢ ድያድርስን በኑፋቄ ወልዶታል:: ድያድርስ ሉቅያኖስን: ሉቅያኖስ ደግሞ አርዮስን ወልደዋል::

ይህ አርዮስ እጅግ ተንኮለኛ በመሆኑ ልክ እንደ ዘመኑ መሰሎቹ ግጥምና ዜማ እየጻፈ በየመንገዱ እያደለ: በየቤቱ እየሰበከ ብዙዎችን በኑፋቄው በከለ:: በመጀመሪያ ተፍጻሜተ ሰማዕት
ቅዱስ ጴጥሮስ (አስተማሪው) መከረው:: ባይሰማው ከአንዴም ሁለት ጊዜ አወገዘው::

ቆይቶ ሰነፉ ጳጳስ አኪላስ ቢፈታውም ሊቁ ቅዱስ
እለእስክንድሮስ እንደ ገና አወገዘው:: እንደ አርዮስ ሐሳብ መድኃኒታችን ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ አይደለም (ሎቱ ስብሐት!) ማለት ክርስትናን ከሥሩ ፈንቅሎ መጣል ነው::

ስለ ክርስቶስ እግዚአብሔርነት ብሉይም ሐዲስም እየመሰከሩ (ኢሳ. 9:6, መዝ. 46:5, 77:65, ዘካ. 14:4, ዮሐ. 1:1, 10:30, ራዕይ. 1:8, ሮሜ. 9:5) አርዮስና የዛሬ መሰሎቹ አንዲት ጥቅስ ይዘው ክርስትናን ከመሠረቱ ለመናድ መሞከራቸው በእርግጥም ከሰይጣን መላካቸውን ያሳያል::

በወቅቱም በመወገዙ "ተበደልኩ" ብሎ የጮኸው አርዮስ ከ2ቱ አውሳብዮሶች ባልንጀሮቹ (ዘቂሣርያና ዘኒቆምድያ) ጋር ሆኖ ወደ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ሔዶ ከሰሰ:: ቅዱሱ ንጉሥም የጉዳዩን ክብደት ተመልክቶ የዓለም ሊቃውነት ይሰበሰቡ ዘንድ አዘዘ::

ከሚያዝያ 21 እስከ መስከረም 21 ተጠቃለው ገቡ:: በ325 ዓ/ም (በእኛው በ318 ዓ/ም) ለ40 ቀናት የሚቆይ ሱባኤን ያዙ:: ሱባኤውን ሲጨርሱም በ4ቱ ፓትርያርኮች (እለእስክንድሮስ: ሶል ጴጥሮስ: ዮናክንዲኖስና ኤዎስጣቴዎስ) መሪነት: በእለእስክንድሮስ ሊቀ መንበርነት: በአትናቴዎስ ጸሐፊነት ጉባኤው ተጀመረ::

በጉባኤው ሙሉ ስልጣን በሰማይ ከፈጣሪ: በምድር ከንጉሡ የተሰጣቸው አበው አርዮስን ተከራክረው ከነ ጀሌዎቹ ምላሽ አሳጡት:: ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ: ሥግው ቃል: ራሱም እግዚአብሔር መሆኑን አስረዱት:: በጉባኤው መጨረሻም:-
1.አልመለስም በማለቱ አርዮስን አወገዙ::
2.ጸሎተ ሃይማኖትን "ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም" እስከሚለው ድረስ ተናገሩ::
3.ፍትሐ ነገሥትን ሥጋዊና መንፈሳዊ ብለው አዘጋጁ::
4.ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እንደሚገባ አደራጁ::
5.በስማቸው የሚጠራ አንድ ቅዳሴን ደረሱ::

ይህ ሁሉ ሲሆን መድኃኒታችን ክርስቶስ 319ኛ ሆኖና ገሊላዊ ጳጳስን መስሎ ሁሉን አከናውኖላቸዋል:: አባቶችም ሥራቸውን
ከጨረሱ በኋላ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስን ባርከው ወደየ ሃገረ ስብከታቸው ተመልሰዋል::

††† በየዘመኑም ዐርፈው ለክብረ መንግስተ ሰማያት በቅተዋል:: እኛም እነሆ "አባቶቻችን:
መምሕሮቻችን:
መሠረቶቻችን:
ብርሃኖቻችን:
ምሰሶዎቻችን" እያልን እናከብራቸዋለን::

††† አምላከ ቅዱሳን ሊቃውንት በጸሎታቸው እኛንም: ቤተ ክርስቲያናችንንም ከክፉ ጠላት ይጠብቅልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

††† ኅዳር 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱሳን 318ቱ ሊቃውንት
2.ቅዱስ እለእስክንድሮስ ሊቅ
3.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
4.አባ ይስሐቅ ሊቀ ጳጳሳት
5.ሊቁ አካለ ወልድ

††† ወርሐዊ በዓላት
1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ሁሉ አባት)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

♻️ስነ-ግጥም
▬ክፍል ሶስት

መንፈሳዊ ግጥም ሲፃፍ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ
ጉዳዮች

👉1. ይዘት
መንፈሳዊ ግጥም ለሚያስተላልፈው መልእክት (ይ዗ት) አብዜቶ ሊጨነቅ
ይገባል። መንፈሳዊ ገጣሚ ለግጥሙ ማማር፣ ለውበቱ፣ ለቅርፁና
ለምሥጢራዊነቱ ከሚጨነቀው በላይ ለሚያስተላልፈው መንፈሳዊ መልእክት
ግድ ሊለው ይገባል፤ ምክንያቱም የማንኛውም መንፈሳዊ ግጥም ተቀዳሚ
አላማ በሚያስተላልፈው ይ዗ት የምእመናንን መንፈሳዊ ሕይወት ማፅናትና
ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ማስተማር ነው።
አንድ መንፈሳዊ ገጣሚም ሊያስተውላቸው የሚገቡ ነጥቦች የሚከተሉት
ናቸው።

💎ሀ. እምነት
ቤተ ክርስቲያን ከምታስተምረው አስተምሮት ውጪ የራሱን አስተያየት ወይም
ፍልስፍና የራሱን አስተያየት መጨመር የለበትም። ስለዙህ ገጣሚ ተገቢ ያልሆነ
መልእክት በግጥሙ አስፍሮ አድማጭን (አንባቢን) ወዳልተፈለገ አቅጣጫ
እንዳይወስድ በቅድሚያ ለአባቶችና መንፈሳዊ እውቀት ላላቸው ወንድሞች
(እህቶች) ሊያስገመግም ይገባል።
ለምሳሌ፡- ይለመንሻል ለአንቺ ለእናቱ
እኛንስ እምቢ አለ ፀናበት አንጀቱ
እየቆምን ጠዋት ማታ ከቤቱ።
💎ለ. ስርዓት
በቤተ ክርስቲያን የሚፈፀመው የቅዳሴ፣ የፀሎት፣ ጥምቀት፣ የበዐላት፣
የአጽዋማት ወ዗ተ መንፈሳዊ ሥርዐቶች አሉ። መንፈሳዊ ገጣሚም እነዙህን
ሥርዐቶች ጠንቅቆ የሚያውቅ መሆን አለበት። ግጥሞቹም እነዙህን መንፈሳዊ
ሥርዐቶች
የሚያፋልሱ ወይም የሚጥሱ መሆን የለባቸውም።
በአምላክ አደባባይ ከቤተ መቅደስ
ካህናት ሲቆሙ ስሙን ሊቀድሱ
ላስቀድስ ሄድኩና እኔም እንደነሱ
የጀመርኩት መጽሐፍ ልክ አሐዱ ሲባል
ባነብ አላልቅ አለኝ እትው እስኪባል፡፡
ሐ. ትውፊት
በቤተ ክርስቲያን ከትውልድ ትውልድ እየተላለፉ የመጡ ብዘ ትውፊቶች አሉ።
ለምሳሌ ንዋየ ቅድሳትና አሰራራቸው፣ አለባበስ እና ሌሎችም። ገጣሚው
በግጥሙ ውስጥ እነዙህን የሚያነሳ ከሆነ ትውፊቶቹን በተገቢው መንገድ
መጠቀም አለበት።
ለምሳሌ፡
ፀናፀል መቋሚያ ከበሮውን ይ዗ን
ማህሌት ሲቆሙ ቅድስት ውስጥ ሆነው
መንፈስን ያድሳል ከልብ ላስተዋለው
👉2. የቃላት ምርጫ
ሥነ ጽሑፍ ለቃላት ገላው ስስ ነው። ግጥምን ከሌሎቹ የሥነ ጽሑፍ ዗ሮች
ከሚለዩት ባህሪው አንዱ የቃላት ምርጫው ነው። የቃላት ምርጫ ማለት
አንድን ነገር ለመግለፅ በቋንቋው ውስጥ ብዘቃላት ሊኖሩ ይችላሉ፤ ነገር ግን
ገጣሚው ቅድሚያ ወደ አእምሮው የሚመጣውን ሳይሆን የሚጠቀመው
መርጦ ነው። ምርጫው መሆን ያለበትም እምቅ ቃልና በሚገባበት አውድ
ተስማሚ የሆነና ተራ ያልሆነ ሊሆን ይገባዋል። በዙህ መልኩ የተመረጡ
የግጥም ቃላት የእምቅነት (የቁጥብነት) የምስል ፈጣሪነትንና የክረትን ባህሪ
የሚያጎናፅፉት በግብ መቺነታቸው ተመርጠው የገቡ ቃላት ናቸው። ትርፍ
ወይም አላስፈላጊ ቃል ከለም ማስወገድ ያስፈልጋል።
ለምሳሌ፡-

እህት ወንድሞቼ
እናት አባቶቼ
ክርስቲያን ሁላችሁ
_
ይህ
ን ታላቅ መልእክት
ስሙኝ ልንገራችሁ
በጆሮ ሰምታችሁ
ያዘት በልባችሁ
👉ያ ክፉ ዲያብሎስ እንዳይወስድባችሁ
👉3,ምሥጢራዊነት
ኦርቶዶክሳዊ ግጥም ተራና ግልብ መልእክትን የሚሸከም አይደለም። ወይም
እንደ ሙዜ ወዲያው ተልጦ የሚበላ አይደለም። ከቃላት አመራረጡ፣ ከምትና
ምጣኔው ሌላ ጥልቅና ምጡቅ የሆነ ፍቺን የሚሸከም ነው።
ለምሳሌ፡ አሞራው በረረ
ቅሉ ተሰበረ፡፡
ግጥም የልብ ቋንቋ የነፍስ ምግብ ነው። ሌላው ቀርቶ እናቶቻችን በየንግሱ ላይ
የሚገጥሙትን ብንሰማ ምሥጢራዊ ፍቺ አለው።
ለምሳሌ፡ አስማረው አሉ ይሄን ዓለም
ግሸን ደብረ ከርቤ የተጻፈው ቀለም
ይሄ ሁለት ስንኝ ለግሸን ደብረ ከርቤ የተሰጣትን ትልቅ ቃል ኪዳን ያስረዳል።
ቀለም የሚለው ቃል ቃል ኪዳኑን በቁጥብ ቃል ገልጦታል። ከዙህም በላይ
የመጽሐፈ ጤፉት ንባብ በመስማት የሚድነውን በሽተኛ ተገሳፁን ሰምቶ
የሚመለሰውን ኀጢአተኛ ቁጥር ይህን አለም እያለይ ነግረናል።
ለምሳሌ አንድ ብልህ ገጣሚ የደብተራ ዘነብን ቅኔያዊ ንግግር ተንተርሶ እንዲህ
ብሎ ተቀኝቷል።
እነዙህ ነቢያት በመንፈስ ሰከሩ
አሮን ከኢሳያስ በትር ቢሰና዗ሩ
ብልጡ ኤልሳ ሆዬ እንዳይሰብሩት ፈርቶ
ማሰሮውን ይዝ ሸሸ ቤቱን ትቶ
ያሞኝ ዳንኤል የእብድ ገላጋይ
ከተራራ ወጥቶ ለቀቀ ድንጋይ
ህዜቅኤልም አይቶ ነገሩ እንደ ከፋ
ቤቱ እንዳይ዗ረፍ ደጁን ዗ግቶ ጠፋ።
ይህ ስልት ገድሎ ማዳን ይባላል። የሰደበ፣ ያዋረደ፣ መስሎ የሚያመሰግን
የሚያከብር ነው። ነቢያትን የሰከሩ አስመስሎ የድንግል ማርያምን ነገር
እንዲናገሩ ያደርጋል፡፡

3.10 ግጥም እንዴት ይነበባል

👉1. ግጥሙን በደንብ ለመረዳት አስቀድሞ የቃላት ምርጫውን ማጤን
👉2. የተጠቀመውን ይቤ መረዳት
👉3. ለመረዳት ደጋግሞ ማንበብ
👉4. የሚከተሉትን ጥየቄዎች እራስን መጠየቅ
💎ሀ. ተናጋሪው ማነው‹ምን ዓይነት ሰው ነው
💎ለ. የሚናገረው ለማን ነው፡
💎ሐ. ግጥሙ የተነገረበት አጋጣሚ ምንድን ነው፡፡
💎መ. የግጥሙ ጊዛ ምንድን ነው፡፡
💎ሠ. የግጥሙ ጊዛ መቼ ነው
💎ረ. የግጥሙን ድምጸት መለየት
💎ሰ. የግጥሙን የቃላት ምርጫ መረዳት፣ ምስሎቹን ፣ ዘይቤዎቹን
መለየት
💎ሸ. የግጥሙን ምጣኔና ምት ማወቅ

✅ይቀጥላል●●●●●●●●

💡መንፈሳዊ የኪነ-ጥበብ ቻናላችንን ይጎብኙ❗️

💫💎 ኪነ-ጥበብ💎💫

🔻ከተመቻችሁ ለሌሎች እንዲደርስ ሼር በማድረግ እና ወዳጆቻችሁን ወደ ቻናላችን ይጋብዙ።🔻

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

+የግብጽ አረማውያን ገዢዎች እንደ ትልቅ ሥራ የሚያዩት አድባራትን ማቃጠል: ገዳማትን መመዝበር ነውና እርሱም ለዚሁ ሥራ ተነሳ:: ሠራዊትን አስከትቶ በሠረገላው ተጭኖ ወደ አንድ ገዳም ደረሰ:: ልክ የገዳሙን መሬት ሲረግጥ ግን በአንዴ ልቡናው ተሰበረ::+ሠራዊቱን ወደ ከተማ አሰናብቶ እርሱ ብቻውንወደ ገዳሙ ዘለቀ:: ወደ አበ ምኔቱም ቀርቦ ሰገደላቸውና እንዲያጠምቁት ተማጸናቸው:: እርሳቸውም አስተምረው አጠመቁት:: በዚያውም መንኖ መነኮሰ::

+ለዘመናትም በጠባቡ መንገድ ተጋድሎ ከጸጋ (ከብቃት) ደረሰ:: በአካባቢው ሰውና እንስሳትን የፈጀውን ዘንዶም ባሪያ አድርጐ ለ10 ዓመታት ገዝቶታል:: ከብዙ ተጋድሎ በሁዋላም በዚህ ቀን ዐርፏል::

=>አምላከ ቅዱሳን መላእክት እነርሱን ለረድኤት ይላክልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

=>ኅዳር 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሳን 4ቱ እንስሳ (ኪሩቤል)
2.ቅዱስ አፍኒን ሊቀ መላእክት
3.አባ ቅፍሮንያ ጻድቅ
4.ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ንጉሥ (ዘምስለ ቅዱስ መስቀል)
5.ቅድስት እግዚእ ክብራ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2.አባ ብሶይ (ቢሾይ)
3.አቡነ ኪሮስ
4.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
5.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)

=>+"+ በዙፋኑም መካከል: በዙፋኑም ዙሪያ በፊትና በሁዋላ ዓይኖች የሞሏቸው አራት እንስሶች ነበሩ:: ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል:: ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል:: ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው:: አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል:: አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሏቸው:: +"+ (ራዕይ. 4:6)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የዓለም ፈጣሪ መጋቢ ሠራኤ ሕግ ቅድስት ሥላሴ ካለመኖር ወደመኖር ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሞት ወደ ሕይወት ያሻገረን እርሱ ቅድስት ሥላሴ ነው።

ሥላሴ አምባችን መጠጊያችን አለኝታችን መጠጋያችን ሥላሴ
ነው በሥላሴ እንመካለን በሥላሴ እንኖራለን በሥላሴ ወደ ሕይወት እንሻገራለን።

በቅድስት ሥላሴ ተመኩ ተጠለሉ ተጠበቁ ቅድስት ሥላሴ የጸሎታችን መልስ ነው የስግደታችን ብርታት የንሰሐችን ሥርየት ነው።

ዕለታችን በቅድስት ሥላሴ የተቀደሰ የተባረከ ይሁን አሜን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
5.አባ ባውላገዳማዊ
6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)

=>+"+ የሚበልጠውን ትንሳኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ:: ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ:: በድንጋይ ተወግረው ሞቱ:: ተፈተኑ:: በመጋዝ ተሰነጠቁ:: በሰይፍ ተገድለው ሞቱ:: ሁሉን እያጡ: መከራን እየተቀበሉ: እየተጨነቁ: የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ:: ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ: በዋሻና በምድር ጉድጉዋድ ተቅበዘበዙ:: +"+ (ዕብ. 11:35-38)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አቡነ ገብረ እንድርያስ ታላቁን ጻድቅ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ያሟሟቱ ታላቅ ጻድቅ ናቸው፣ ይኸም ማለት ኣቡዪ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍል በሚገኘው ገዳማቸው በምድረ ከብድ ባረፉ ጊዜ አቡነ ገብረ እንድርያስ ከደቡብ ወሎ ወለቃ በእግዚአብሔር መንፈስ ተመርተው በቅዱሳንም ጥሪ ተደርጎላቸው ወደ ምድረ ከብድ መጥተዋል። ይኸም በአቡዬ ገድል ገጽ 83 ላይ እንዲህ ተብሎ በግልጽ ተጽፏል፤ የአባታችን የገብረ መንፈስ ቅዱስ ዕለተ ዕረፍቱ በደረሰ ጊዜ ብዙ ኅቡዓን ቅዱሳን ወደእርሱ መጡ ስማቸውም ፍሬ ቅዱስ ዘርዐ ቡሩክ፡ ያዕቆብ ብንያም፤ ዮሴፍ ነው አባታችንም በሞት እንደሚያርፍና ቃልኪዳን እንደተሰጠው ነገራቸው። እነርሱም ስለ አባታችን ዕረፍት አዘነ እርሱ ርእሰ ባሕታውያን ነውና። በቀዳሚት ሰንበትም እያላበው በድካም እንደልማዱ ለፍጥረቱ ሁሉ ወደ አምላኩ መማለድን ሳያቋርጥ ዋለ። በመሸም ጊዜ ሰውነቱ ሁሉ ደከመ፤ መናገርም ተሳነው፣ እነዚያ ቅዱሳን ግን ዕረፍቱን አይቶ ምስክር ይሆን ዘንድ ገብረ እንድርያስን ሊጠሩት ሔዱ ቅዱሳኑም ወደ እርሱ ደርሰው የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ዕረፍት ነገሩት። እርሱም

በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ፤ መራራ ለቅሶንም አለቀሰ፤ ተነሥቶም ከእነርሱ ጋር ሔዶ ብፁዓዊ አባታችን ወዳለበት ደረሰ። ያንጊዜም ቅዳሜ ማታ ለእሑድ አጥቢያ ነበረ።”

የቅዱሳን አባቶቻችን የአቡነ ገብረ እንድርያስና የአቡነ ገብረ መንፈስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን።

ምንጭ በእንተ ኅሩይ ቅዱሳን መጽሐፍ የተወስደ
እግዚአብሔር ይስጥልን ወንድማችን ገብረ ሥላሴ በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን
ኅዳር 6/3/2015ዓ.ም
Kuwait

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/hanostube97

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር በማኅበረ ኤዶምያስ መንፈሳዊ ግሩፕ ላይ እየተጠየቀ ነው ተሳተፉ ።ግሩፑ ላይ ላልተቀላቀላችሁ ግሩፑን ሊንክ በመንካት ተቀላቀሉ❤
/channel/edomiyass21
/channel/edomiyass21
/channel/edomiyass21

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🌹 #ሱላማጢስ_ከስደት_ተመልሳለች 🌹
#የኛስ_መመለሻችን_መቼ_ይሆን ?

🍂 #ኅዳር_ስድስት ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አዝላ ከአረጋዊ ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ሦስት ዓመት ከመንፈቅ በስደት ከኖሩ በኋላ ቅዱስ ገብርኤል ለዮሴፍ እንዲህ አለው ፦

❝ ሕፃኑን የሚሹት ሄሮድስና ሠራዊቱ ሞተዋልና እናቱንና ሕፃኑን ይዘህ ወደ ሀገርህ ተመለስ ❞ ( ማቴ 2 ፥ 19 ) ባለው ጊዜ አረጋዊ ዮሴፍ እናትና ልጁን ይዞ ሰሎሜን አስከትሎ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ከስደት ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሱ ደብረ ቁስቋም በተባለ ቦታ ያረፉበት ተራራ ነው ።

ዐምስት ሺ ዐምስት መቶ ዘመን ሙሉ ሰላም ላጣ ለአዳም ሰላም የሆነች
❝ ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ❞ ተብሎ እንዲመሰገን ምክንያት የሆነች የሰላም አናት የሰላም እመቤት ድንግል ማርያም
🌹#ሱላማጢስ_ከስደት_ተመልሳለች 🌹

🍂 እኛስ መቼ ይሆን ዛሬ በኀጢአት ስደት ያለን ብዙዎች ነን የሠራነው ኀጢአት ከእግዚአብሔር ፊት ከቤተ ክርስቲያን ደጅ ያሳደደን ብዙዎች ነን በትዕቢት ልብ ተይዘን ትላንት ካስቀደስንባት ፣ ከቆረብንባት ከቀደስንባት ከተማርንባት ካስተማርንባት ደጅ የተሰደድን #መመለሳችን_መቼ_ይሆን ?

መቼ ይሆን ? ከሥጋ ወደሙ የተሰደድን ከልጅነት ጊዜያችን በኋላ ፣ ከትዳራችን በኋላ ፣ ከአገልግሎታችን በኋላ ሥጋ ወደሙን መቀበል ያቆምን ከሕይወት ምግብ የተሰደድን ሥጋችን እየደለበ ነፍሳችን የቀጨጨችብን #መመለሳችን_መቼ_ይሆን ?

🍂 ከአገልግሎት የተሰደድን ትላንት እንዘምር ፣ እንማር እናስተባብር የነበርን አገልጋዮች ዛሬ የት ነን ? #መመለሳችን_መቼ_ይሆን ?

#ወዳጄ_በቤተ_ክርስቲያን_አለሁ_እንጂ_ነበርኩ_አያድንምና ያለነው የነበርንበት ቦታ ካልሆነ ወደ ነበርንበት እንመለስ በደልን እንጂ በደለኛን ወደ ማይጠላ አምላክ እንመለስ የት ናችሁ ስንባል ከምናፍርበት ቦታ እንዳንገኝ ወደ ደገኛይቱ ቤት ወደ ቤተ ክርስቲያን እንመለስ ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ ኅዳር 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞

✞✞✞ 🌹በዓለ ደብረ ቁስቁዋም🌹 ✞✞✞

✞✞✞ የአርያም ንግሥት: የፍጥረታት ሁሉ እመቤት ድንግል ማርያም የባሕርይ አምላክ ልጇን አዝላ ወደ ምድረ ግብፅ ወርዳለች:: በወንጌል ላይ (ማቴ. 2:1-18) እንደተጻፈው ጌታችን በተወለደ በ2 ዓመቱ የጥበብ ሰዎች (ሰብአ ሰገል) ወደ ቤተ ልሔም መጥተው ሰግደውለት ወርቅ: እጣን: ከርቤውን ገበሩ: አገቡለት::

+ንጉሥ ተወልዷል መባሉን የሰማ ሔሮድስ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ በቅዱስ ገብርኤል ትዕዛዝ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 1 አምላክ ልጇን አዝላ: በአንዲት አህያ ጥቂት ስንቅ ቁዋጥራ: ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ስደት ወጣች::

+ከገሊላ ተነስታ በጭንቅ: በመከራ: በረሃብና በጥም: በሐዘንና በድካም: በላበትና በእንባ ተጉዛ በዚሕች ቀን ምድረ ግብፅ ገብታለች::

*የአምላክ እናቱ እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታለች::
*ለእኛ የሕይወት እንጀራን ተሸክማ እርሷ ተራበች::
*የሕይወትን ውሃ ተሸክማ ተጠማች::
*የሕይወት ልብስን ተሸክማ ተራቆተች::
*የሕይወት ፍስሐን ተሸክማ አዘነች::
*እመ አምላክ ተራበች: ተጠማች: ታረዘች: ደከመች: አዘነች: አለቀሰች: እግሯ ደማ: ተንገላታች::

+ለሚገባው ይሕ ሁሉ የተደረገው ለእኛ ድኅነት ነው:: በእውነት ይህንን እያወቀ ለድንግል ማርያም ክብር የማይሰጥ ሰይጣን ብቻ ነው:: አራዊት: ዕፀዋትና ድንጋዮች እንኳ ለአመላክ እናት ክብር ይሰጣሉ::

+አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ቅድስት ሰሎሜ ደግሞ የክብር ክብር ይገባቸዋል:: ከአምላክ እናት ከድንግል ማርያምና ከቸር ልጇ ጋር መከራ መቀበልን መርጠዋልና::

+"መድኃኔ ዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተሰደደ? ለምን ስደቱን ወደ ግብፅና ኢትዮዽያ አደረገ?"

1.ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ:: በፈጣን ደመና ወደ ግብፅ እንደሚወርድ ተነግሯልና (ኢሳ. 19:1, ዕን. 3:7)

2.ምሳሌውን ለመፈጸም:: የሥጋ አባቶቹ እነ አብርሃም: ያዕቆብ (እሥራኤል): ኤርምያስ ወደዚያው ተሰደዋልና::

3.ከግብፅ ጣዖት አምልኮን ያጠፋ ዘንድ:: (ኢሳ. 19:1)

4.የግብፅና የኢትዮዽያ ገዳማትን ይቀድስ ዘንድ::

5.ሰው መሆኑ በአማን እንጂ ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ:: (ሰው ባይሆን ኑሮ አይሰደድም ነበር:: ሔሮድስ ቢያገኘው ደግሞ ሊገድለው አይችልም:: ያለ ፈቃዱና ያለ ዕለተ ዐርብ ደሙ አይፈስምና:: )

6.ስደትን ለሰማዕታት ባርኮ ለመስጠት:: እና

7.የአዳምን ስደት በስደቱ ለመካስ ነው::

+እመ ብርሃን ድንግል ማርያም ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት (ወይም ለ42 ወራት) በስደት የቆየችባቸው ቦታዎች አሉ:: ድንግል ማርያም ከርጉም ሔሮድስ ስትሸሽ መጀመሪያ የሔደችው ከገሊላ ወደ ሶርያ ደንበር (ደብረ ሊባኖስ) ነው::

+በዚያ የሸሸጋት ቅዱስ ጊጋር መስፍኑ በሔሮድስ ሲገደል ወደ ምድረ ግብጽ ወረደች:: በግብጽም ለብዙ ጊዜ ከአንዱ ወደ ሌላው ስትሸሽ ቆየች::
"እንዘ ከመ በግዕት ግድፍት አመ ሳኮይኪ ውስተ ምድረ በዳ" እንዲል:: (እሴብሕ ጸጋኪ)

+ቀጥላም በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል ገብታ ደብረ ቢዘን ላይ (አሁን ኤርትራ ውስጥ ነው) ዐረፈች:: ከደብረ ቢዘን በደብረ ዳሙ: አክሱም: ደብር ዓባይ: ዋልድባ አድርጋ እየባረከች ጣና ደርሳለች:: በጣና ገዳማትም: በተለይ በጣና ቂርቆስ ለ100 ቀናት ቆይታ ቀጥታ በጐጃም ወደ ሽዋ ሒዳ ደብረ ሊባኖስን ቀድሳለች::

+ቀጥላም እስከ ደብረ ወገግና ደብረ ሐዘሎ ደርሳለች:: በእግሯ ያልደረሰችባቸውን የሃገራችን ክፍሎች በደመና ተጭና ዐይታ ባርካቸዋለች:: ከልጇም በአሥራትነት ተቀብላለች:: ሔሮድስ መሞቱን መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል የነገራትም እዚሁ ኢትደዮዽያ ውስጥ መሆኑን ትውፊት ያሳያል::

+እመ ብርሃንም ከሃገራችን ሰዎች (ከሰብአ ኦፌር) የተቀበለችውን ስንቅና ስጦታ በ5 ግመሎች ጭና ከቅዱሳኑ ዮሴፍና ሰሎሜ ጋር በዚህች ቀን ደብረ ቁስቁዋም ውስጥ ገብተው ከድካም ዐርፈዋል:: ሐሴትንም አድርገዋል::

+ዳግመኛም ከክርስቶስ ስደት 400 ዓመታት በኋላ በዚህች ቀን የግብጿ ደብረ ቁስቁዋም ታንጻ ተቀድሳለች:: የቅዱሳን ማደሪያም ሁናለች:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ390ዎቹ አካባቢ ድንግል እናቱን: ቅዱሳን ሐዋርያትን: አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን: አስከትሎ ወረደ::

+የወቅቱ የግብጽ ፓትርያርክ ቅዱስ ቴዎፍሎስና ሊቁ ቅዱስ ቄርሎስ ቤተ ክርስቲያኑን አንጸው: ሕዝቡን ሰብስበው ይጠብቁት ነበርና ወርዶ ቀድሶላቸው ታላቅ ደስታ ሁኗል::

+ስደቷን መሳተፍን ሽተው አበው:-
"እመ ኀሎኩ በጐይዮቱ ውእተ መዋዕለ:
እምተመነይኩ ኪያሁ በዘባንየ ሐዚለ:
ወበልሳንየ እልሐስ ዘአእጋሪሁ ጸበለ:
ወከመ አዕርፍ ምስሌሁ በትረ ዮሴፍ ኀበ ተተክለ:
ለወልደ ማርያም በሐጸ ፍቅሩ ልቡናየ ቆስለ::" እንዳሉ:: (ሰቆቃወ ድንግል)
እኛም እመ ብርሃንን ልንሻት ያስፈልገናል::

+ይህቺ ቀን ለእኛ ለክርስቲያኖች ሁሉ እጅግ የደስታ ቀን ነውና ሐሴትን እናድርግ:: የሰማይና የምድር ጌታ ለእኛ ሲል ካደረገው ስደቱ በዚህች ቀን ተመልሷልና:: ስደቷን አስበን ካዘንን: መመለሷን አስበን ደስ ልንሰኝ ይገባልና::

"አብርሒ አብርሒ ናዝሬት ሃገሩ:
ንጉሥኪ በጽሐ ዘምስለ ማርያም መጾሩ" ልንልም ይገባል::

+" 🌷አባ ጽጌ ድንግል ዘወለቃ🌷 "+

+ጻድቁ አቡነ ጽጌ ድንግል በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበሩ ሊቅና ገዳማዊ ናቸው:: የዘር ሐረጋቸው ምንም ከቤተ እሥራኤል እንደሚመዘዝ ቢታወቅም ኢትዮዽያዊ ናቸው:: አስቀድመው አይሁዳዊ በመሆናቸው ኢየሱስ ክርስቶስንና ድንግል እናቱን አያምኑም ነበር::

+የተማሩትም ብሉይ ኪዳንን ብቻ ነበር:: በጊዜውም "ክርስቶስ አልተወለደም: ትክክለኛው እምነት ይሁዲ ነው" እያሉ ከክርስቲያኖች ጋር ይከራከሩ ነበሩ:: አንድ ቀን ግን ከታላቁ ሊቅና ገዳማዊ አቡነ ዜና ማርቆስ ጋር ተገናኙ::

+ጻድቁን ስላልቻሏቸው ተሸንፈው በክርስቶስ አመኑ:: አቡነ ዜና ማርቆስም አስተምረው ክርስትና ሲያነሷቸው /ሲያጠምቁዋቸው 'ጽጌ ድንግል' አሏቸው:: ሲመነኩሱም 'ጽጌ ብርሃን' ተብለዋል:: ቀጥለውም በጾምና በጸሎት ሲጋደሉ: እመቤታችንንም ሲለምኑ ምሥጢር ተገለጠላቸው::

+የእመ ብርሃንን ስዕለ አድኅኖ በአበባ ተከባ: በብርሃንም ተውጣ ተመለከቱ:: በዚህ ምክንያትም ዛሬ በጣፋጭነቱ የሚታወቀውን ማኅሌተ ጽጌን 150 ዓርኬ አድርግው ደረሱ:: እስከ ዕለተ ዕረፍታቸውም እመቤታችንና ልጇን በገዳማቸው (ወለቃ አካባቢ የሚገኝ) ሲያመሰግኑ ኑረዋል:: ጻድቁ ያረፉት ጥቅምት 27 ሲሆን ዛሬ የቃል ኪዳን በዓላቸው ነው::

✞✞✞ ቸሩ መድኃኔ ዓለም የድንግል እናቱን ስደት አስቦ ከመንግስተ ሰማያት ስደት ይሠውረን:: ከስደቱ በረከትም ያድለን::

✞✞✞ ኅዳር 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም (ሚጠታ ለማርያም)
2.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
3.ቅድስት ሰሎሜ ቡርክት
4.ቅዱስ ዮሳ (ወልደ ዮሴፍ)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ ኅዳር 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞

✞✞✞ 🌹በዓለ ደብረ ቁስቁዋም🌹 ✞✞✞

✞✞✞ የአርያም ንግሥት: የፍጥረታት ሁሉ እመቤት ድንግል ማርያም የባሕርይ አምላክ ልጇን አዝላ ወደ ምድረ ግብፅ ወርዳለች:: በወንጌል ላይ (ማቴ. 2:1-18) እንደተጻፈው ጌታችን በተወለደ በ2 ዓመቱ የጥበብ ሰዎች (ሰብአ ሰገል) ወደ ቤተ ልሔም መጥተው ሰግደውለት ወርቅ: እጣን: ከርቤውን ገበሩ: አገቡለት::

+ንጉሥ ተወልዷል መባሉን የሰማ ሔሮድስ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ በቅዱስ ገብርኤል ትዕዛዝ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 1 አምላክ ልጇን አዝላ: በአንዲት አህያ ጥቂት ስንቅ ቁዋጥራ: ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ስደት ወጣች::

+ከገሊላ ተነስታ በጭንቅ: በመከራ: በረሃብና በጥም: በሐዘንና በድካም: በላበትና በእንባ ተጉዛ በዚሕች ቀን ምድረ ግብፅ ገብታለች::

*የአምላክ እናቱ እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታለች::
*ለእኛ የሕይወት እንጀራን ተሸክማ እርሷ ተራበች::
*የሕይወትን ውሃ ተሸክማ ተጠማች::
*የሕይወት ልብስን ተሸክማ ተራቆተች::
*የሕይወት ፍስሐን ተሸክማ አዘነች::
*እመ አምላክ ተራበች: ተጠማች: ታረዘች: ደከመች: አዘነች: አለቀሰች: እግሯ ደማ: ተንገላታች::

+ለሚገባው ይሕ ሁሉ የተደረገው ለእኛ ድኅነት ነው:: በእውነት ይህንን እያወቀ ለድንግል ማርያም ክብር የማይሰጥ ሰይጣን ብቻ ነው:: አራዊት: ዕፀዋትና ድንጋዮች እንኳ ለአመላክ እናት ክብር ይሰጣሉ::

+አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ቅድስት ሰሎሜ ደግሞ የክብር ክብር ይገባቸዋል:: ከአምላክ እናት ከድንግል ማርያምና ከቸር ልጇ ጋር መከራ መቀበልን መርጠዋልና::

+"መድኃኔ ዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተሰደደ? ለምን ስደቱን ወደ ግብፅና ኢትዮዽያ አደረገ?"

1.ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ:: በፈጣን ደመና ወደ ግብፅ እንደሚወርድ ተነግሯልና (ኢሳ. 19:1, ዕን. 3:7)

2.ምሳሌውን ለመፈጸም:: የሥጋ አባቶቹ እነ አብርሃም: ያዕቆብ (እሥራኤል): ኤርምያስ ወደዚያው ተሰደዋልና::

3.ከግብፅ ጣዖት አምልኮን ያጠፋ ዘንድ:: (ኢሳ. 19:1)

4.የግብፅና የኢትዮዽያ ገዳማትን ይቀድስ ዘንድ::

5.ሰው መሆኑ በአማን እንጂ ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ:: (ሰው ባይሆን ኑሮ አይሰደድም ነበር:: ሔሮድስ ቢያገኘው ደግሞ ሊገድለው አይችልም:: ያለ ፈቃዱና ያለ ዕለተ ዐርብ ደሙ አይፈስምና:: )

6.ስደትን ለሰማዕታት ባርኮ ለመስጠት:: እና

7.የአዳምን ስደት በስደቱ ለመካስ ነው::

+እመ ብርሃን ድንግል ማርያም ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት (ወይም ለ42 ወራት) በስደት የቆየችባቸው ቦታዎች አሉ:: ድንግል ማርያም ከርጉም ሔሮድስ ስትሸሽ መጀመሪያ የሔደችው ከገሊላ ወደ ሶርያ ደንበር (ደብረ ሊባኖስ) ነው::

+በዚያ የሸሸጋት ቅዱስ ጊጋር መስፍኑ በሔሮድስ ሲገደል ወደ ምድረ ግብጽ ወረደች:: በግብጽም ለብዙ ጊዜ ከአንዱ ወደ ሌላው ስትሸሽ ቆየች::
"እንዘ ከመ በግዕት ግድፍት አመ ሳኮይኪ ውስተ ምድረ በዳ" እንዲል:: (እሴብሕ ጸጋኪ)

+ቀጥላም በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል ገብታ ደብረ ቢዘን ላይ (አሁን ኤርትራ ውስጥ ነው) ዐረፈች:: ከደብረ ቢዘን በደብረ ዳሙ: አክሱም: ደብር ዓባይ: ዋልድባ አድርጋ እየባረከች ጣና ደርሳለች:: በጣና ገዳማትም: በተለይ በጣና ቂርቆስ ለ100 ቀናት ቆይታ ቀጥታ በጐጃም ወደ ሽዋ ሒዳ ደብረ ሊባኖስን ቀድሳለች::

+ቀጥላም እስከ ደብረ ወገግና ደብረ ሐዘሎ ደርሳለች:: በእግሯ ያልደረሰችባቸውን የሃገራችን ክፍሎች በደመና ተጭና ዐይታ ባርካቸዋለች:: ከልጇም በአሥራትነት ተቀብላለች:: ሔሮድስ መሞቱን መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል የነገራትም እዚሁ ኢትደዮዽያ ውስጥ መሆኑን ትውፊት ያሳያል::

+እመ ብርሃንም ከሃገራችን ሰዎች (ከሰብአ ኦፌር) የተቀበለችውን ስንቅና ስጦታ በ5 ግመሎች ጭና ከቅዱሳኑ ዮሴፍና ሰሎሜ ጋር በዚህች ቀን ደብረ ቁስቁዋም ውስጥ ገብተው ከድካም ዐርፈዋል:: ሐሴትንም አድርገዋል::

+ዳግመኛም ከክርስቶስ ስደት 400 ዓመታት በኋላ በዚህች ቀን የግብጿ ደብረ ቁስቁዋም ታንጻ ተቀድሳለች:: የቅዱሳን ማደሪያም ሁናለች:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ390ዎቹ አካባቢ ድንግል እናቱን: ቅዱሳን ሐዋርያትን: አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን: አስከትሎ ወረደ::

+የወቅቱ የግብጽ ፓትርያርክ ቅዱስ ቴዎፍሎስና ሊቁ ቅዱስ ቄርሎስ ቤተ ክርስቲያኑን አንጸው: ሕዝቡን ሰብስበው ይጠብቁት ነበርና ወርዶ ቀድሶላቸው ታላቅ ደስታ ሁኗል::

+ስደቷን መሳተፍን ሽተው አበው:-
"እመ ኀሎኩ በጐይዮቱ ውእተ መዋዕለ:
እምተመነይኩ ኪያሁ በዘባንየ ሐዚለ:
ወበልሳንየ እልሐስ ዘአእጋሪሁ ጸበለ:
ወከመ አዕርፍ ምስሌሁ በትረ ዮሴፍ ኀበ ተተክለ:
ለወልደ ማርያም በሐጸ ፍቅሩ ልቡናየ ቆስለ::" እንዳሉ:: (ሰቆቃወ ድንግል)
እኛም እመ ብርሃንን ልንሻት ያስፈልገናል::

+ይህቺ ቀን ለእኛ ለክርስቲያኖች ሁሉ እጅግ የደስታ ቀን ነውና ሐሴትን እናድርግ:: የሰማይና የምድር ጌታ ለእኛ ሲል ካደረገው ስደቱ በዚህች ቀን ተመልሷልና:: ስደቷን አስበን ካዘንን: መመለሷን አስበን ደስ ልንሰኝ ይገባልና::

"አብርሒ አብርሒ ናዝሬት ሃገሩ:
ንጉሥኪ በጽሐ ዘምስለ ማርያም መጾሩ" ልንልም ይገባል::

+" 🌷አባ ጽጌ ድንግል ዘወለቃ🌷 "+

+ጻድቁ አቡነ ጽጌ ድንግል በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበሩ ሊቅና ገዳማዊ ናቸው:: የዘር ሐረጋቸው ምንም ከቤተ እሥራኤል እንደሚመዘዝ ቢታወቅም ኢትዮዽያዊ ናቸው:: አስቀድመው አይሁዳዊ በመሆናቸው ኢየሱስ ክርስቶስንና ድንግል እናቱን አያምኑም ነበር::

+የተማሩትም ብሉይ ኪዳንን ብቻ ነበር:: በጊዜውም "ክርስቶስ አልተወለደም: ትክክለኛው እምነት ይሁዲ ነው" እያሉ ከክርስቲያኖች ጋር ይከራከሩ ነበሩ:: አንድ ቀን ግን ከታላቁ ሊቅና ገዳማዊ አቡነ ዜና ማርቆስ ጋር ተገናኙ::

+ጻድቁን ስላልቻሏቸው ተሸንፈው በክርስቶስ አመኑ:: አቡነ ዜና ማርቆስም አስተምረው ክርስትና ሲያነሷቸው /ሲያጠምቁዋቸው 'ጽጌ ድንግል' አሏቸው:: ሲመነኩሱም 'ጽጌ ብርሃን' ተብለዋል:: ቀጥለውም በጾምና በጸሎት ሲጋደሉ: እመቤታችንንም ሲለምኑ ምሥጢር ተገለጠላቸው::

+የእመ ብርሃንን ስዕለ አድኅኖ በአበባ ተከባ: በብርሃንም ተውጣ ተመለከቱ:: በዚህ ምክንያትም ዛሬ በጣፋጭነቱ የሚታወቀውን ማኅሌተ ጽጌን 150 ዓርኬ አድርግው ደረሱ:: እስከ ዕለተ ዕረፍታቸውም እመቤታችንና ልጇን በገዳማቸው (ወለቃ አካባቢ የሚገኝ) ሲያመሰግኑ ኑረዋል:: ጻድቁ ያረፉት ጥቅምት 27 ሲሆን ዛሬ የቃል ኪዳን በዓላቸው ነው::

✞✞✞ ቸሩ መድኃኔ ዓለም የድንግል እናቱን ስደት አስቦ ከመንግስተ ሰማያት ስደት ይሠውረን:: ከስደቱ በረከትም ያድለን::

✞✞✞ ኅዳር 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም (ሚጠታ ለማርያም)
2.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
3.ቅድስት ሰሎሜ ቡርክት
4.ቅዱስ ዮሳ (ወልደ ዮሴፍ)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ታላቅ መንፈሳዊ ደርሶ መልስ ጉዞ
ህዳር 16 እሁድ ቀን
በሰሚነሽ ኪዳነምህረት ገዳም
ትራንስፖርትና መስተንግዶ ጨምሮ = 500 ብር
መነሻ ቦታዎች
- ቅዱስ እስጢፋኖስ እስታዲየም
- 22 ዑራኤል
- መገናኛ / ላምበረት / ወሰን / ጣፎ

ለመመዝገብ በውስጥ መስመር አናግሩኝ😍🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አንች ብዙ አታውሪ ስለ ፈጣሪ ማንም እንደተገኘው ስለ አምላክ ስም መቀለድ አይቻልም እሽ ሀይማኖት በኮሜንት አይደለም ብዙ ከማውራት ይልቅ እኔ ማኔኝ የሚለውን ጥያቄ አስቡበት ቅዱሳን ሀዋርያት የሚያመሰግኑትንም እናንተ ደግሞ እንዲች በቃ ብዙ ነገር ተላላቹህ አይደል

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ክብረ ክህነት ያለው inbox ላኩልኝ ወንድሞቼ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ስለ እግዚአብሔር እየተናገርሽ ለምን እርጋታው ጠፋ?

Читать полностью…
Subscribe to a channel