kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/iD_ZnI-TnyQ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

♻️ግጥም
ጾም
●●●●●●●●●●●●●●
የትዕቢት ተራራን የምትንድ ፈጥና
ስስትን በእንጭጩ ያስቀረች አምክና፤
አፍቅሮ ንዋይን የጣለች ገርስሳ…
ጾም እኮ ሃያል ናት…
በመርዶክዮስ ግንድ ሐማን ያሰቀለች
ዳንኤልን ከአናብስት በፍቅር ያኖረች
ሠለስቱ ደቂቅን በዕምነት ያፀናች
ጾም እኮ ቅኔ ናት
ሰምና ወርቅ ያላት፡፡
ፈጥና የምትፈውስ የመንፈስን ዝለት
በብዙ ድካም ውስጥ የምትሰጠን ብርታት
ጾም እኮ ወጌሻ ናት የነፍስ መድሃኒት
የዐይን ጉድጓዶችን በእንባ የምትሞላ
ለደከመ ሃይል ለጨነቀው መላ
በስግደት በምጽዋት ታጅባ በጸሎት
ስትሄድ ወደፍልሚያ ሰይጣንን ለመውጋት
ሁሌም አሸናፊ ሁሌም ባለድል ናት፡፡
-------------------------------
❗️ወስብሐት ለእግዚአብሔር❗️

🌟💫ኪነ-ጥበብ🌟💫

✦ ━━━━━━━━━━━━ ✦
    ♡ ㅤ  ⎙ㅤ  ⌲        ✉️   
 ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

                           †                           

[   የጾምና የጸሎተ ምሕላ አዋጅ!    ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[ ከቅዱስ ሲኖዶስ ሀገራዊ ሰላምን ፣ መረጋጋትንና አንድነትን ለማስፈን የታወጀውን የጾምና የጸሎተ ምሕላ አፈጻጸምን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ ! ]

ኅዳር ፲፩ [ 11 ] ቀን ፳፻፲፮ [ 2016 ] ዓ.ም

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ሀገራዊ ሰላምን፣ መረጋጋትንና አንድነትን ለማስፈን የታወጀውን የጾምና የጸሎተ ምሕላ አፈጻጸምን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥቷል።

የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

ሀገራዊ ሰላምን፣ መረጋጋትንና አንድነትን ለማስፈን የታወጀውን የጾምና የጸሎተ ምኅላው አፈጻጸም በቅደሱ ሲኖዶስ በተወሰነው መሠረት ከዚህ በመቀጠል አቀርባለሁ፡፡

ቀደም ሲል ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት በመላው ዓለም ለሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን የታወጀውን አዋጅ አስተላልፈዋል፡፡ በዚሁ መሠረት ያለፈውን በይቅርታና በምህረት ዘግተን በእውነተኛ ንሥሓ ልቅሶና በምህላ፣ በጾምና በጸሎት ወደ ፈጣሪ እንድንቀርብ፣ በመካከላችንም ፍቅርና አንድነት እንዲመጣ ይኽንን ጾመ ነቢያት ወይም የገና ጾም በልዩ ሁኔታ እንድንጾም መንፈሳዊ አዋጅ ተላልፏል፡፡ 

ይኽ ጥንታዊ የአዋጅ ጾም ሁለት አበይት ታሪኮችን የያዘ ነው፡፡ የመጀመሪያው ክፍል ቅዱስ አብርሃም ሶርያዊ የተባለ ጻድቅ አባት በጸሎት፣ በጾምና በምኅላ ተራራን ከመሬት ከፍ በማድረጉ ኃይለ ጸሎቱና ክብረ አምለኩ የሚዘከርበት ነው፡፡ በሁለተኛው ክፍል ነቢያት የጌታችንን ሰው መሆን እያፈለጉ፣ ድህነትንና ሰላምን በመሻት መጾማቸው ይዘከራል፡፡ (፩ኛ ጴጥ ፩፡፲) እኛም ይኽንን አብነት አድርገን ታላቋ ቤተ ክርስቲያን፣ ኃላፊነቷን እንድትወጣ ስለችግራችን፣ ስለሀገር ሰላምና ስለ ሕዝቡ ደኅንነት በአንድነት ሆነን ወደፈጣሪያች እንድንጮኽ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በጥቅምት ወር ፳፻፲ወ፮ ዓ/ም ወስኖ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ሀገራችን እንድትፈወስ፣ የወገን በወገን ደም መፋሰስ እንዲቀር፣ ያለፈውን በይቅርታና በንሥሓ ዘግቶ ለወደፊቱ ብሩህ ዘመንን እንዲመጣ በንሥሓና በፍጹም ለቅሶ፣ በቁመትና በሰጊድ፣ በሰፊሕና በአንቅአድዎ፣ ወደፈጣሪ እንድንቀርብ የምልኣተ ጉባኤውን ውሳኔ መሠረት በማድረግ ቋሚ ሲኖዶስ በኅዳር ወር ፳፻፲ወ፮ዓ/ም የሚከተለውን ዝርዝር አፈጻጸም አውጥቷል፡፡ 

፩ኛ. የጾሙ የመጀመሪያ ሳምንት ከቅዳሜ ኅዳር ፲፭ እስከ ኅዳር ፳፩ ቀን ፳፻፲ወ፮ ዓ/ም በሁሉም የሀገራችን ክፍልና ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ባለችበት በመላው ዓለም የንሥሓ ፣ የጾም ፣ የጸሎትና የምኅላ ሳምንት እንዲሆን ፤
 
፪ኛ. በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ በአድባራት አስተዳዳሪዎች ፣ በአጥቢያ አለቆችና በገዳም አበምኔቶች መሪነት ሁሉም ዲያቆናት ፣ ቀሳውስት ፣ መነኰሳት ፣ ሰባክያንና ሊቃውንት በሙሉ በየመዐርጋቸው ልብሰ ተክህኖና ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት ዩኒፎርማቸው ለብሰው ፣ ሁሉም ምእመናን ጋር በአንድነት በዐውደ ምህረት ጸሎተ ምኅላውን እንዲያደርሱ ፤ 

፫ኛ. መላው ሕዝበ ክርስቲያን ከሊቅ እስከ ደቂቅ ፣ ሕፃናት ፣ ወጣቶች ፣ እናቶች አባቶች አረጋውያን ሁሉ የቻለ በቤተ ክርስቲያን ፣ ያልቻለ በያለበት ሆኖ የተጣላ ታርቆ ፣ በፍቅርና በአንድነት ፣ በእውነተኛ ንሥሓና ጸጸት በምኅላው እንዲሳተፍ ፤ በማእከል የሚደረገው ጸሎተ ምኅላ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ገዳም ሆኖ በመገናኛ ብዙኀን የቀጥታ ሥርጭት ለመላው ዓለም እንዲተላለፍ ፤

፬ኛ. በመጀመሪያው የሱባኤ ቀን ኅዳር ፲፭ ቀንና ፣ በሰባተኛው ቀን ኅዳር ፳፩ ቀን በጸሎተ ምኅላው በሚደረግበት ጊዜ ታቦቱ ከመንበሩ ተነሥቶ በዐውደ ምኅረት በቀሳውስት እንዲከብር ሆኖ፤ በሁሉም የምኅላው ቀናት ሥዕለ ማርያም፣ ወንጌልና መስቀል ወጥቶ በአራቱ መዐዝን ሥርዓተ ጸሎተ ምኅላው ከጸሎተ ወንጌል ጋር በየቀኑ በነግህና በሠርክ የሥራ ሰዓትን በማይነካ ሁኔታ እንዲፈጸም፤

፭ኛ. በየዕለቱ የሚነበቡት የወንጌል ክፍሎችን ስለ ሰላም ፣ ስለንሥሓና ጸጸት ፣ ስለ ፍቅርና አንድነት ፣ ስለ በጎነትና መደማመጥ ፣ ስለመሰማማትና ጥላቻን ስለማራቅ እንዲሆን ፤

፮ኛ. በሰፊህና በአንቀዓድዎ ፣ በሰጊድና በአስተብርኮ ፣ ምኅላው ከደረሰና ፣ ጸሎተ ወንጌል ደርሶ ዕለቱ ወንጌል ከተነበበ በኋላ በአንድነት የንሥሓ መዝሙር በመዘመር ፣ ሕዝበ ክርስቲያን ስለሀገራቸውና ስለሰው ልጆ ደኅንነት እያሰቡ ወደቤታቸው እንዲሄዱ ፤

፯ኛ. ከመጀመሪው ሳምንት በኋላ እስከ በዓለ ልደት ድረስ የሰርክ ምህላ ሳይቋረጥ መደበኛው ሥርዓተ ጾምና ጸሎት እንዲቀጥል ፣ የቤተ ክርስቲያንን ታላቅነት ፣ የአበውን ተቀባይነት በሚገለጽ ፣ በቀጣይም ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን በመንፈሳዊ ጽናት የሰላም ልዑካን ሆነው እንዲቀጥሉ በሚያደርግ ሁኔታ እንዲፈጸም ፤ 
 
፰ኛ. አስቀድሞ የደረሰውንና ፣ እየደረሰብን ያለው ችግር የጦርነትና የግጭት ብቻ ሳይሆን የረሀብ ፣ የድርቅ ፣ የኑሮ ውድነት ፣ የመፈናቀልና የስደት ጭምር ስለሆነ ከጸሎትና ምኅላችን ጎን ለጎን መረዳዳትና መተዛዘን ፣ ርኅራሄና መደጋገፍ አብሮ እንዲፈጸም ፤   

፱ኛ. ይኽንኑ መልእክት መላው ዓለም እንዲውቀው ፣ በተለይም የኦሬንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በጸሎት እንዲያስቡን ፣ የጸሎታችንና የምኅላችን መነሻ ምክንያቱ የሀገራችን ወቅታዊ ችግር ቢሆንም የምንጸልየው ለመላው ዓለም መሆኑ ተገልጾ በደብዳቤ እንዲላክ እንዲደረግ ፣ በማለት ቅዱስ ሲኖዶስ ጥብቅ መመሪያ አስተላልፏል፡፡ 

እግዚአብሔር አምላካችን በእንባና በንሥሓ የምናቀርበውን ጸሎተ ምኅላችንን በምህረቱ ተቀብሎ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን፣ ሕዝባችንን ይጠብቅልን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

[ የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 
ቅዱስ ሲኖዶስ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ፆም ማለት መተው ፣ መከልከል ማለት ነው።
ከምን? ከመብል ፣ ከመጠጥ ፣ ከሐሜት ፣ ከስጋ ፈቃድ ፤ ሌላም ፆም ማለት ስጋን አድክሞ ለነፍስ ማስገዛት ማለት ነው።
/channel/mezmur_store

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለጻድቃን ቅዱሳን አባ ዳንኤል ወአባ መርትያኖስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† አባ ዳንኤል ገዳማዊ †††

††† በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ በፋርስ (የአሁኗ ኢራን) ውስጥ ብዙ አስቸጋሪ ነገሥታት ተነስተው ነበር:: ከእነዚህ አንዱ የሆነው የዘመኑ መሪ ክርስቶስን የማያውቅ: መምለኬ ጣኦት የሆነና በጠንቅ ዋዮች ተከቦ የሚኖር ነበር::

እግዚአብሔር ለሁሉም የጥሪ ቀን አለውና ለሕይወት ይጠራው ዘንድ ይህንን ንጉሥ በደዌ ጐበኘው:: የአምላክ ጥሪው አንዳንዴ እንደዚህ: አንዳንዴም እንዲያ ነውና:: ንጉሡ እንደ ታመመ ጠቢባነ ፋርስ ሊያድኑት ሞከሩ:: ግን አልቻሉም:: ሕመሙ እየባሰ ሒዶ ንጉሡ መጻጉዕ ሆነ::

በጊዜው ከመተተኞች ሁሉ በጣም የሚያቀርበው አንድ ጠንቅ-ዋይ በቤተ መንግስት አካባቢ ነበርና ንጉሡ አስጠራው:: "አድነኝ" አለው:: እንደማይችለው ሲያውቅ ዝም አለው:: ንጉሡ መልሶ "ስማ! በቤቴ ውስጥ ከብረህ: ገነህ: የበላሁትን በልተህ: የጠጣሁትን ጠጥተህ የምትኖረው ለዚህ ላትሆነኝ ነው?" ብሎ ተቆጣው::

የንጉሡን ቁጣ ያየው መተተኛ እንደሚገድለው ባወቀ ጊዜ "ንጉሥ ሆይ! እኔኮ አታደርገውም ብዬ ነው እንጂ መድኃኒቱን አውቀዋለሁ:: "ኅሥሥ ሕጻነ ዘዋሕድ ለአቡሁ ወእሙ-ለእናት አባቱ አንድ የሆነ ሕጻን ፈልግ:: እናቱ አስራው አባቱ ይረደውና በደሙ ታጥበህ ትድናለህ" አለው::

መተተኛው እንዲህ ያለው: "ሲሆን ንጉሡ እንዲህ አያደርግም:: ካልሆነ ግን እንዲህ ዓይነት ወላጆች አይገኙም" ብሎ ነው:: ንጉሥ ግን ላስፈልግ ባለ ጊዜ የሚያጣው ነገር የለምና አንድ ልጅ ብቻ ያላቸው ርጉማን ወላጆችን አገኘ::

"1 ሺህ ወቄት ወርቅ ልስጣችሁ እና ልጃችሁን ሰውልኝ" ቢላቸው "እሺ" ብለው ወደ ንጉሡ አደባባይ ወጡ:: በዚያም ሕዝብ ተሰብስቦ: ንጉሡም በዙፋኑ ተቀምጦ ሳለ የ5 ዓመት ሕጻን ልጃቸውን ለገንዘብ ይሰውት ዘንድ ወላጆቹ ቀረቡ:: እናቱ አጥብቃ አሰረችው:: አባቱ ደግሞ ቢላውን አስሎ ቀረበ::

በዚያች ሰዓት ግን ሕጻኑ ወደ ሰማይ ዐይኑን አቅንቶ: እንባው እየፈሰሰ ሲጸልይ ከንፈሮቹ ይንቀሳቀሱ ነበርና ንጉሡ ተመልክቶ ልቡ ራራ:: "እንዳትነኩት" ሲልም ጮኾ ተናገረ:: "ፍቱት" ብሎ ሕጻኑን አስፈትቶ በዙፋኑ ፊት ጠየቀው::

"ምን እያደረክ ነበር?" ቢለው "ለሕጻን ልጅ ጋሻዎቹ ወላጆቹ ናቸው:: በደል ሲያገኘኝ ወደ ወላጆቼ እንዳልጮህ ገዳዮቼ እነሱው ናቸው:: ወደ ዳኛም አቤት እንዳልል አስገዳዩ ዳኛው ራሱ ነው:: ስለዚህም ተስፋየ አንዱ አምላክ እግዚአብሔር ብቻ ነበርና ወደ እርሱ በልቤ ጮህኩ" ሲል መለሰለት:: በዚህ የተገረመው ንጉሡ 1ሺ ወቄት ወርቁን ከወላጆቹ ቀምቶ ለሕጻኑ ሰጥቶ በሰላም አሰናበተው::

ራርቶ ሕጻኑን የፈታው ንጉሥ ሕመሙ ቢጠናበት "የዚህ ሕጻን አምላክ እኔንም እርዳኝ!" ሲል ጮኸ:: በዚህ ጊዜ ጩኸቱ ወደ መንበረ ጸባኦት ደረሰለት:: የእግዚአብሔር ድምጽም ወደ ታላቁ ገዳማዊ ሰው ወደ አባ ዳንኤል መጣ:: "ሒደህ ፈውሰው" አለው::

አባ ዳንኤል ማለት በዘመኑ ከነበሩ ዓበይት ጻድቃን አንዱ ሲሆን መንኖ በርሃ ከገባባት ቀን ጀምሮ በፍጹም ተጸምዶ: በጾም: በጸሎትና በትሕርምት የኖረ አባት ነው:: በዚያች ሰዓትም ጻድቁ በደመና ተጭኖ ከበርሃ ብሔረ ፋርስ ደረሰ:: ከንጉሡም ጋር ተነጋገረ::

ንጉሡ "አድነኝ?" ቢለው "እንድትድን በእውነተኛው አምላክ ማመን አለብህ" አለው:: "ክርስቶስ አምላክ መሆኑን በምን አውቃለሁ?" ብሎ በመጠየቁ ጻድቁ በፊቱ ብዙ ተአምራትን በስመ ክርስቶስ አደረገለት::

ንጉሡም በክርስቶስ አምኖ በተጠመቀ ሰዓት አካሉ ታድሶ: ከደዌው ድኖ ተነሳ:: ሠራዊቱና ሕዝቡም እንዲሁ ተጠመቁ:: አባ ዳንኤልም በደመና ወደ በርሃ ተመልሶ ከተጋድሎ በኋላ በዚህች ቀን ዐርፏል::

††† አባ መርትያኖስ †††

††† ይህ ቅዱስ ሰው የነበረው በዚያው በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን በትውልዱ ሶርያዊ ነው:: ብዙ ጊዜም "መርትያኖስ ካልዕ" (ሁለተኛው) እየተባለ ይጠራል:: ምክንያቱም ቀዳማዊ መርትያኖስ (ታላቁ) ስላሉ ነው::

አባ መርትያኖስ በምድረ ሶርያ ከክርስቲያን ወላጆቹ ጋር አድጐ: የቀናውን የሃይማኖት ትምሕርት ተምሮ: በጐውን ጐዳና መርጧል:: ወቅቱ አርዮሳውያን የበዙበት በመሆኑ ወገኖቹን ይጠቅም ዘንድ ያስተምር ነበር::

በየሥፍራውም እየሔደ ውሉደ አርዮስ (መናፍቃንን) እየተከራከረ ምላሽ ያሳጣቸው ነበር:: በዚህ የተበሳጩ መናፍቃንም አንድ ቀን አሳቻ መንገድ ላይ ጠብቀው በበትር ደበደቡት:: በሞትና በሕይወት መካከልም ትተውት ሔዱ:: እነሱ በዚህ እናስተወዋለን መስሏቸው ነበር::

እርሱ ግን በእግዚአብሔር ኃይል ድኖ እንደ ገና በሰው ፊት ምላሽ አሳጥቶ አሳፈራቸው:: እነርሱም መንገድ ላይ ጠብቀው እየደበደቡ ጐተቱት:: ለብዙ ጊዜም ሲደበድቡት ወደ በርሃ ሸሸ:: በዚያም ገዳማዊ ሰው ሆኖ በጾምና በጸሎት ኖረ:: በዓቱንም በኤርትራ ባሕር ዳርቻ አካባቢ ባለች አንዲት በርሃ አደረገ::

እግዚአብሔር ግን ይህንን ሐዋርያዊ ሰው ይፈልገዋልና እንደ ገና ወደ ከተማ የሚመለስበትን ምክንያት ፈጠረ:: በዘመኑ የሃገሩ ጠራክያ ጳጳስ ዐርፎ "ማንን እንሹም" ብለው ሲጨነቁ ፈጣሪ ጻድቁን በኅሊናቸው ሳለባቸው:: እንደ ምንም ብለው ፈልገው አገኙትና አሥረው አምጥተው የጠራክያ ኤጲስ ቆጶስ አደረጉት::

አሁን ስብከተ ወንጌል ሠመረ:: ምክንያቱም አርዮሳውያኑ እርሱ የመንጋው እረኛ ነውና መንካት አይችሉም:: ቢያደርጉትም እጅግ ተወዳጅ ስለ ሆነ ጠቡ ከሕዝብ ጋር ነው:: በዚሁ መንገድ አባ መርትያኖስ ተጋድሎውን ሳይገታ በሠመረ ስብከቱ ብዙዎችን አሳምኖ ወደ መንጋው ቀላቀለ::

ከሠራቸው ብዙ ተአምራትም አንዱን እነሆ:-
*አንዴ ቅዱሱ መንገድ ሲሔድ ጭቅጭቅ ሰምቶ ቀረበ:: በቦታው የተጋደመ ሬሳ አለ:: "ምንድን ነው ችግሩ?" ቢላቸው የሟች ወገኖች ወደ አንድ ጐረምሳ እየጠቆሙ "አላስቀብር አለን" አሉት::

ያንን ጐረምሳ "ለምን?" ቢለው "ብድር ነበረበትና ካልከፈሉኝ አይቀበርም" አለው:: ጻድቁ ፈጣሪውን ጠይቆ ጐረምሳው በአጋጣሚው ሊያታልል መፈለጉን ተረዳ:: "ልጄ! ተወው ይቀበር" ብሎ ቢለምነው "አይሆንም! ምን ታመጣለህ?" አለው::

ያን ጊዜ አባ መርትያኖስ ጸልዮ የሞተውን "በስመ እግዚአብሔር ተነስ" ሲል አዘዘው:: የሞተውም አፈፍ ብሎ ተነሳ:: በዚህ ጊዜ ያ ሐሰተኛ በድንጋጤ ወድቆ ሞተ:: ለዚህኛው በተዘጋጀው መቃብርም ላይ ቀበሩት:: ከሞት የተነሳው ግን በደስታ ከወገኖቹ ጋር ሔደ:: አባ መርትያኖስም ከዘመናት በኋላ በዚህች ቀን ዐርፏል::

††† አምላከ አበው ኃይለ ተአምሩን: ረድኤተ ምሕረቱን አያርቅብን:: ከአባቶቻችን በረከትም ይክፈለን::

††† ኅዳር 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አባ ዳንኤል ገዳማዊ
2.አባ መርትያኖስ ካልዕ (ዘጠራክያ)
3.አባ ዮሐንስ ዘደብረ ቢዘን (ኤርትራ)
4.ቅድስት ደብረ ቀልሞን

††† ወርሐዊ በዓላት
1.አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል)
2.አባ ስምዖን ገዳማዊ
3.አባ ዮሐንስ ጻድቅ
4.እናታችን ቅድስት ነሣሒት
5.ቅዱስ ፊልጶስ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እንኳን ለነቢያት ጾም በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ ውድ ያሬዳውያን
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
" የገና ጾም በልዩ ሁኔታ እንዲጾም መንፈሳዊ አዋጅ ተላልፏል "

የጾምና የጸሎተ ምኅላ አፈጻጸም እንዴት ነው ?

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ የገና ጾም በልዩ ሁኔታ እንዲጾም መንፈሳዊ አዋጅ አስተላለፈች።

ሀገራዊ ሰላምን፣ መረጋጋትንና አንድነትን ለማስፈን የታወጀው የጾምና የጸሎተ ምኅላ ዝርዝር አፈጻጸምንም ይፋ አድርጋለች።

ቤተክርስቲያን ፤ ያለፈውን በይቅርታና በምህረት ተዘግቶ ሁሉም በእውነተኛ ንሥሓ ልቅሶና በምህላ፣ በጾምና በጸሎት ወደ ፈጣሪ እንዲቀርብ በዜጎች መካከል ፍቅርና አንድነት እንዲመጣ ጾመ ነቢያት ወይም የገና ጾም በልዩ ሁኔታ እንዲጾም መንፈሳዊ አዋጅ አስተላልፋለች።

በዚህም ቋሚ ሲኖዶስ በኅዳር ወር 2016 ዓ/ም የሚከተለውን የጾምና የጸሎተ ምኅላ ዝርዝር አፈጻጸም አውጥቷል፡፡ 

አፈፃፀም ፦

- የጾሙ የመጀመሪያ ሳምንት ከቅዳሜ ኅዳር 15 እስከ ኅዳር 21 ቀን 2016 ዓ/ም በሁሉም የሀገራችን ክፍልና ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ባለችበት በመላው ዓለም የንሥሓ፣ የጾም፣ የጸሎትና የምኅላ ሳምንት እንዲሆን፤
 
- በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ በአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ በአጥቢያ አለቆችና በገዳም አበምኔቶች መሪነት ሁሉም ዲያቆናት፣ ቀሳውስት፣ መነኰሳት፣ ሰባክያንና ሊቃውንት በሙሉ በየመዐርጋቸው ልብሰ ተክህኖና ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት ዩኒፎርማቸው ለብሰው፣ ሁሉም ምእመናን ጋር በአንድነት በዐውደ ምህረት ጸሎተ ምኅላውን እንዲያደርሱ፤ 

- በላው ሕዝበ ክርስቲያን ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ ሕፃናት፣ ወጣቶች፣ እናቶች አባቶች አረጋውያን ሁሉ የቻለ በቤተ ክርስቲያን፣ ያልቻለ በያለበት ሆኖ የተጣላ ታርቆ፣ በፍቅርና በአንድነት፣ በእውነተኛ ንሥሓና ጸጸት በምኅላው እንዲሳተፍ፤ በማእከል የሚደረገው ጸሎተ ምኅላ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ገዳም ሆኖ በመገናኛ ብዙኀን የቀጥታ ሥርጭት ለመላው ዓለም እንዲተላለፍ፤

- በመጀመሪያው የሱባኤ ቀን ኅዳር 15 ቀንና፣ በሰባተኛው ቀን ኅዳር 21 ቀን በጸሎተ ምኅላው በሚደረግበት ጊዜ ታቦቱ ከመንበሩ ተነሥቶ በዐውደ ምኅረት በቀሳውስት እንዲከብር ሆኖ፤ በሁሉም የምኅላው ቀናት ሥዕለ ማርያም፣ ወንጌልና መስቀል ወጥቶ በአራቱ መዐዝን ሥርዓተ ጸሎተ ምኅላው ከጸሎተ ወንጌል ጋር በየቀኑ በነግህና በሠርክ የሥራ ሰዓትን በማይነካ ሁኔታ እንዲፈጸም፤

- በየዕለቱ የሚነበቡት የወንጌል ክፍሎችን ስለ ሰላም፣ ስለንሥሓና ጸጸት፣ ስለ ፍቅርና አንድነት፣ ስለ በጎነትና መደማመጥ፣ ስለመሰማማትና ጥላቻን ስለማራቅ እንዲሆን፤

- በሰፊህና በአንቀዓድዎ፣ በሰጊድና በአስተብርኮ፣ ምኅላው ከደረሰና፣ ጸሎተ ወንጌል ደርሶ ዕለቱ ወንጌል ከተነበበ በኋላ በአንድነት የንሥሓ መዝሙር በመዘመር፣ ሕዝበ ክርስቲያን ስለሀገራቸውና ስለሰው ልጆ ደኅንነት እያሰቡ ወደቤታቸው እንዲሄዱ፤

- ከመጀመሪው ሳምንት በኋላ እስከ በዓለ ልደት ድረስ የሰርክ ምህላ ሳይቋረጥ መደበኛው ሥርዓተ ጾምና ጸሎት እንዲቀጥል፣ የቤተ ክርስቲያንን ታላቅነት፣ የአበውን ተቀባይነት በሚገለጽ፣ በቀጣይም ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን በመንፈሳዊ ጽናት የሰላም ልዑካን ሆነው እንዲቀጥሉ በሚያደርግ ሁኔታ እንዲፈጸም፤ 
 
- አስቀድሞ የደረሰውንና፣ እየደረሰብን ያለው ችግር የጦርነትና የግጭት ብቻ ሳይሆን የረሀብ፣ የድርቅ፣ የኑሮ ውድነት፣ የመፈናቀልና የስደት ጭምር ስለሆነ ከጸሎትና ምኅላችን ጎን ለጎን መረዳዳትና መተዛዘን፣ ርኅራሄና በመደጋገፍ አብሮነት  እንድንፈጽም ልዑል እግዚአብሔር አምላካችን ይፍቀድልን ።

መልካም የጾም ወቅት ይሁንልን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን! †††

††† እንኩዋን "ለ99ኙ ነገደ መላእክት": "ቅዱስ አስከናፍር" እና "ቅዱስ ጢሞቴዎስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ †††

††† አእላፍ መላእክት †††

=>እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን ሲፈጥራቸው በነገድ መቶ (100): በክፍለ ነገድ አሥር (10) አድርጉዋቸዋል:: አቀማመጣቸውንም በ3 ሰማያትና በ10 ከተሞች (ዓለማት) አድርጉዋል::

+መላእክት ያሉባቸው ከተሞች ከታች ወደ ላይ "ኤረር: ራማና ኢዮር" ይባላሉ:: አሥሩ ክፍለ ነገድ ደግሞ ከነ አለቆቻቸው ይህንን ይመስላሉ:-

1.አጋእዝት (የቀድሞ አለቃቸው ሳጥናኤል: አህን የተረፉት በቅዱስ ሚካኤል ሥር ናቸው)
2.ኪሩቤል (አለቃቸው ኪሩብ)
3.ሱራፌል (አለቃቸው ሱራፊ)
4.ኃይላት (አለቃቸው ሚካኤል)
5.አርባብ (አለቃቸው ገብርኤል)

6.መናብርት (አለቃቸው ሩፋኤል)
7.ስልጣናት (አለቃቸው ሱርያል)
8.መኩዋንንት (አለቃቸው ሰዳካኤል)
9.ሊቃናት (አለቃቸው ሰላታኤል)
10.መላእክት (አለቃቸው አናንኤል) ናቸው::

+ከእነዚህም *አጋእዝት: *ኪሩቤል *ሱራፌልና *ኃይላት መኖሪያቸው በኢዮር (በ3ኛው ሰማይ) ነው:: *አርባብ: *መናብርትና *ስልጣናት ቤታቸው ራማ (2ኛው ሰማይ) ነው:: *መኩዋንንት: *ሊቃናትና *መላእክት ደግሞ የሚኖሩት በኤረር (በ1ኛው) ሰማይ ነው::

+መላእክት ተፈጥሯቸው እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ ነው:: አይራቡም: አይጠሙም: አይዋለዱም: አይሞቱም:: ተፈጥሯቸውም ረቂቅ ነው:: ተግባራቸውም ዘወትር "ቅዱስ: ቅዱስ: ቅዱስ" እያሉ ፈጣሪያቸውን ማመስገን ነው:: ምግባቸውም ይሔው ነው::

+ዕረፍት ብሎ ነገርን አያውቁም:: "አኮቴቶሙ ዕረፍቶሙ: ወዕረፍቶሙ አኮቴቶሙ" እንዲል:: በተጨማሪም መልአክ ማለት ተላላኪ (አገልጋይ) ነውና ከፈጣሪ ወደ ሰው ልጆች ለምሕረትም: ለመዓትም ይላካሉ::

+ምሕረትን ያወርዳሉ:: ልመናን ያሳርጋሉ:: ቅጡ ሲባሉም ይቀጣሉ:: ስነ ፍጥረት (አራቱ ወቅቶች) እንዳይዛቡ ይጠብቃሉ::

*ዘወትርም ስለ ሰው ልጆች ያማልዳሉ (ዘካ. 1:12)
*ምሥጢርን ይገልጣሉ (ዳን. 9:21)
*ይረዳሉ (ኢያ. 5:13)
*እንዳንሰናከል ይጠብቃሉ (መዝ. 90:11)
*ያድናሉ (መዝ. 33:7)
*ስግደት ይገባቸዋል (መሳ. 13:20, ኢያ. 5:13, ራዕ. 22:8)
*በፍርድ ቀንም ኃጥአንን ከጻድቃን ይለያሉ (ማቴ. 25:31)
*በአጠቃላይ ለሰው ልጆች ሕይወትና ድኅነት ሲባል ከፈጣሪያቸው የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ሲጠብቁና ፈቃዱን ሲፈጽሙ ይኖራሉ::

+"+ አእላፍ +"+

=>ይህ ዕለት በሊቃውንት አንደበት "አእላፍ" እየተባለ ይጠራል:: በሃይማኖት: በተልእኮትና በምስጋና የሚኖሩ 99ኙ ነገደ መላእክት በአንድ ላይ የሚከበሩበት ቀን ነው:: ምንም እንኩዋን የጐንደሩን ፊት ሚካኤልን ጨምሮ በአንዳንድ አድባራት ታቦቱ ቢኖርም ሲያነግሡ ተመልክቼ አላውቅም::

+ሊቃውንቱ በማሕሌት: ካህናቱም በቅዳሴ እንደሚያከብሯቸው ግን ይታወቃል:: ሕዳር 13 ቀን ዓመታዊ በዓላቸው ነው ማለት በየወሩ በ13 ወርሃዊ በዓላቸው መሆኑን ያሳያልና ዘወትር ልናስባቸው ይገባል::

+ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱሳን መላእክትን በስምና በማዕረግ እንደሚነግረን ሁሉ በማሕበር (በትዕይንት) አገልግሎታቸውም ይነግረናል:: ለምሳሌ:-

*ያዕቆብ= በረዥም መሰላል ሲወጡና ሲወርዱ ተመልክቷል:: (ዘፍ. 28:12)
*ኤልሳዕ ለግያዝ አሳይቶታል:: (2ነገ. 6:17)
*ዳንኤል ተመልክቷል:: (ዳን. 7:10)
*በልደት ጊዜ በዝማሬ መገለጣቸውን ቅዱስ ሉቃስ ጽፏል:: (ሉቃ. 2:13)
*ዮሐንስ በራዕዩ አይቷቸዋል:: (ራዕይ. 5:11)

+ከዚህም በላይ በብዙ የመጻሕፍት ክፍል ተጠቅሰዋል:: ቅዱሳን መላእክተ ብርሃን: መንፈሳውያን: ሰባሕያን: መዘምራን: መተንብላን (አማላጆች) ተብለውም ይጠራሉና ያስቡን ዘንድ ልናስባቸው ይገባል::

+"+ ቅዱስ አስከናፍር ሮማዊ +"+

=>የዚህ ቅዱስ ሰው ሕይወት ታሪክ ደስ የሚያሰኝና የሚያስተምር ነው:: ቅዱሱ የገዳም ሰው አይደለም:: በሮም ከተማ እጅግ ሃብታም: ባለ ትዳር: የአንድ ልጅ አባትና የከተማዋ መስፍን ነው:: ይህ ሰው በጣም ደግና አብርሃማዊ ነው::

+ከጧት እስከ ማታ ነዳያንን ሲቀበልና ሲጋብዝ ነበር የሚውለው:: ነገር ግን አንድና ብቸኛ ልጁ መጻጉዕ (ድውይ) ሆነበት:: ለ35 ዓመታትም ከአልጋ ላይ ተጣብቆ ይኖር ነበር:: ቅዱስ አስከናፍር ግን ፈጣሪውን ያማርር: ደግነቱን ይቀንስ ዘንድ አልሞከረም:: አሁንም ነዳያኑን ማጥገቡን: እንግዳ መቀበሉን ቀጠለ እንጂ::

+በዚያ ወራት ደግሞ በሮም ግዛት ቁዋንጃ የሚቆርጡ: ሰው እየገደሉ የሚዘርፉ 13 ሽፍቶች ነበሩ:: ስለ ቅዱስ አስከናፍር ደግነት ሰምተው ገድለው ይዘርፉት ዘንድ ተማከሩ:: የሠራዊት አለቃ በመሆኑ በማታለል ሔዱ::

+መነኮሳትን ይወዳልና 13ቱም ልብሰ መነኮሳትን ለብሰው: ሰይፎቻቸውን ደብቀው: ከበሩ ደርሰው: "የእግዚአብሔር እንግዶች ነን: አሳድረን" አሉት:: ቅዱስ አስከናፍር ድምጻቸውን ሲሰማ ደነገጠ::

+ብቅ ብሎ አያቸውና "ጌታየ! ምንም ኃጢአተኛ ብሆን አንድ ቀን ወደ ባሪያህ እንደምትመጣ አምን ነበር" ሲል በደስታ ተናገረ:: እንዲህ ያለው ሽፍቶቹ 13 በመሆናቸው ጌታ 12ቱን ሐዋርያት አስከትሎ የመጣ መስሎት ነው::

+ወዲያውም ወደ ቤቱ አስገብቶ እግራቸውን አጠባቸው:: የእግራቸውን እጣቢ ወስዶም በልጁ ላይ አፈሰሰበት:: ድንገትም ለ35 ዓመታት አልጋ ላይ ተጣብቆ የኖረው ልጅ አፈፍ ብሎ ከአልጋው ላይ ተነሳ::

በዚህ ጊዜ ቅዱስ አስከናፍር ለ13ቱ ሽፍቶች በግንባሩ ሰገደ:: ሽፍቶቹ ግን ነገሩ ግራ ቢገባቸው ደነገጡ::

+ጌታ 12ቱን ሐዋርያት አስከትሎ መምጣቱን የሰሙ የሃገሩ ሰዎችም እየመጡ ይሰግዱላቸው ገቡ:: በዚህ ጊዜ ሽፍቶቹ ልብሳቸውን አውልቀው እውነቱን ተናገሩ:: "እኛ ሽፍቶች ነን:: የመጣነውም ልንገልህ ነው:: አምላክ ግን ባንተ ደግነት ይህንን ሁሉ ሠራ:: አሁንም እባክህ ትገድለን ዘንድ ሰይፋችንን ውሰድ" አሉት::

+እርሱ ግን "ንስሃ ግቡ እንጂ መሞት የለባችሁም" ብሎ: ስንቅ ሰጥቶ አሰናበታቸው:: 13ቱ ሽፍቶችም ጥቂት ምሥሮችን ይዘው ወደ ተራራ ወጡ:: ምስሩን በመሬት ላይ በትነው ማታ ብቻ እየቀመሱ በጾምና በጸሎት ተጋደሉ:: በዚህች ቀንም 13ቱም በሰማዕትነት የክብር አክሊልን ተቀዳጁ:: ቅዱስ አስከናፍርም በተቀደሰ ሕይወቱ ተግቶ ኑሮ በዚህች ቀን ዐርፏል::

+"+ ቅዱስ ጢሞቴዎስ +"+

=>ይህ ቅዱስ አባት በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በዘመነ ሰማዕታት የነበረ የእንጽና (ግብጽ) ክርስቲያን ነው:: በጐ ሕይወቱን የወደዱ አበው በወቅቱ የከተማዋ ዻዻስ: የሕዝቡም እረኛ እንዲሆን መርጠው ሾሙት::

+ጊዜው የመከራ በመሆኑ ከትንሽ ጊዜ በሁዋላ የከተማው መኮንን ክርስቲያኖችን ይገድል ገባ:: ቅዱስ ጢሞቴዎስንም "ክርስትናህን ካልካድክ" በሚል አሠረው:: ጧት ጧት እያወጣም ደሙ እስኪፈስ ድረስ ይገርፈው ነበር:: ደቀ መዛሙርቱንም አንድ አንድ እያለ ፈጀበት::

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/+5vZ7pDkwQ-YyNTg0

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/9FbHH6HJn8w

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ህዳር 12 ቀን ታላቁ #መልአክ_ቅዱስ_ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ #አለቃ_ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው #ቅዱስ_ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል፡፡

እንኳን ለታላቁ ለሊቀ መላእክት
#ለቅዱስ_ሚካኤል
አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ምልጃው አይለየን አሜን 🙏🙏🙏

    
#መልካም___በዓል🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
      •➢ 👇  ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

❖♥ ቅዱስ ሚካኤልን ጨምሮ እነዚኽ ቅዱሳን መላእክት ሰው የጸለየውን ጸሎት ያቀረበውን መሥዋዕት ቅድመ እግዚአብሔር በማድረስ የእግዚአብሔርን ምሕረት ወደ ሰው በማምጣት ሰውን ከአምላካቸው ጋር በማማለድ ጸንተው ያሉ እንደኾኑ በብዙ ሥፍራ ላይ ተዘርዝሯል፡-

ለምሳሌ ያኽል (ዘፍ 48፥15፤ ዘጸ 23፥20፤ መሳ 6፥11፤ ኢዮ 33፥23፤ መዝ 33፥7፤ 88፥6፤ 90፥11፤ 1ነገ 19፥5፤ 2ነገ 6፥15፤ ዳን 3፥17፤ 4፥13፤ 8፥15-19፤ ዘካ 1፥12፤ ማቴ 18፥10፤ ሉቃ 1፥19፤ 13፥6-9፤ 15፥7፤ ዮሐ 20፥11፤ የሐዋ 12፥6፤ ዕብ 1፥14፤ ራእ 8፥3-4ን ይመልከቱ)፡፡
የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል በረከት ይደርብን፤

[እናንተም በአስተያየት መስጫው ላይ በረከቱ እንዲያድርባችሁ ይኽንን የመላእክት አለቃ ብቻ በምትወዱት ምስጋና ወይም መዝሙር አወድሱት]

[በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ በድጋሚ ፖስት የተደረገ]

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እንደ ምን አላችሁ ቤተሰቦቼ ?
ከተሠማራንበት የሥራ ዘርፍ በተጨማሪም ሆነ እንደ ዋና ሥራ አድርገን ልንሠራው የምንችለ የሥራ ዘርፍ አለን በመሆኑም ፦
1, በግልም ሆነ በመንግሥት ተቋማት ተቀጥራችዉ የምትሠሩ
2, የግላችውን ሥራ የምትሠሩ
3, ከዩኒቨርስቲ ተመርቃችሁ ሥራ ያላገኛችሁ
4, 12 ተፈትናችሁ ነጥብ የመጣላቸውም ሆነ ያልመጣላችው ሠርታችዉ የራሳችሁን ስራ መሥራት ወይም ለመጀመር የሚያስችል ካፒታል የምታገኙበት የስራ ዘርፍ ነው ።ማንኛውም መሥራት የሚፈልግ ሰው  ሙሉ ስም ፣የመኖሪያ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር በዉስጥ መሥመር ያሥቀምጥልኝ።



ሴልስ መስራት የሚፈልግ በዚህ ቁጥር መደወል ይችላሉ
0976479130
0921543877

inbox me your :
-NAME
-ADRESS
PHONE NUMBER

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ህዳር 11/2016 #ቅድስት_ሐና

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅድስት #ሐና ስም ለምናመሰግንበት #ለቅድስት_ሐና አመታዊ የእረፍት መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉በዚህ ዕለት ለጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ አያቱ እንዲሁም አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እናቷ የሆነች የተመሰገነች የቅድስት ሐና የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው

👉ይችም ቅድስት ከኢየሩሳሌም አገር ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ትውልድ የሌዊ የሜልኪ ልጅ ለሆነ ለማጣት ልጁ ናት

👉ለማጣትም ሦስት ሴቶች ልጆች አሉት የታላቂቱም ስሟ ማርያም ናት ሁለተኛዋም ስሟ ሶፍያ ሦስተኛዪቱም ስሟ ሐና ናት ታላቂቱ ማርያምም ለባል ተድራ አዋላጅ የሆነች ሰሎሜን ወለደቻት እርሷም መድኃኒታችንን ከወለደችበት ጊዜ ጀምሮ በስደቷም ወራት ከአረጋዊ ዮሴፍ ጋር እመቤታችንን ድንግል ማርያምን ያገለገለቻት ናት

👉ሶፍያም ለባል ተድራ ለመጥመቁ ዮሐንስ እናቱ የሆነች ቅድስት ኤልሳቤጥን ወለደቻት ይችንም ቅድስት ሐናን ከይሁዳ ነገድ ለሆነ ፃድቅ ስሙ ኢያቄም ለሚባል አጋቧትና እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያምን ወለደቻት እሊህም ሰሎሜና ኤልሳቤጥ ለቅድስት ሐና የእኅትማማቾች ልጆች ናቸው

👉የዚችንም የቅድስት ሐናን በሥውር የምትሠራውን ገድሏንና ትሩፋቷን እንዳናስታውሰው አናውቀውም ግን ከሴቶች ሁሉ እንደምትበልጥና እንደምትከብር እናውቃለን እንረዳለን እርሷ አምላክን በሥጋ ለወለደችው ወላጅዋ ትሆን ዘንድ የተገባት ሁናለችና ከሴቶች ሁሉ የሚበልጥና የሚበዛ ትሩፋትና ተጋድሎ ባይኖራት ይህ ታላቅ ፀጋ ባልተገባት ነበር

👉ይህችም ጻድቅት ሐና መካን በመሆንዋ ልጅን ይሰጣት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር በጸሎት ትተጋና ትማልድ ነበር #እግዚአብሔርም በእርሷ ለዓለም ሁሉ ድኅነት የተደረገባትን ይቺን የተባረከችና የከበረች ልጅን ሰጣት እርሷም አምላክን የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት

👉ስለዚህም ይህን ታላቅ ጸጋ ስለሰጣት የበዓሏን መታሰቢያ በደስታ ልናከብር ይገባናል #ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በጸሎቷ የሚገኝ በረከቷም ከእኛ ጋር ይሁን ለዘላለሙ "አሜን"
💒 💚 💛 ❤ 💒

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ ኅዳር 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞

✞✞✞ ቅድስት ሶፍያ ወቅዱሳት አንስት ✞✞✞

✞✞✞ እስኪ ዛሬ በጥቂቱ የተባረኩ (ቡሩካት) እናቶቻችን እንዘክር:: "ቅድስት" የሚለው ቃል ለሁሉም ቅዱሳት እናቶች ቢሰጥም ቅሉ ለድንግል ማርያም ሲሰጥ ግን ትርጉሙ ይለያል:: እርሷ 'ቅድስተ ቅዱሳን: ንጽሕተ ንጹሐን: ቡርክት እምቡሩካን: ኅሪት እምኅሩያን ናትና::

+ከሰው ልጆችም ሁሉ ትበልጣለች:: ይቅርና የሰው ልጅን ንጹሐን መላእክትንም በንጽሕናና በቅድስና ትበልጣቸዋለች:: እርሷ እመ ብርሃን: የአምላክ እናቱ: የሰውነታችን መመኪያ ናትና::

+እመቤታችንን "ቅድስት" ስንል "ጽንዕት: ንጽሕት: ክብርት: ልዩ" ማለታችን ነው::
1."ንጽሕት" ትባላለች:: ሌሎች ሰዎች (ቅዱሳን) ቢነጹ ከገቢር: ከነቢብ ኃጢአት ነው እንጂ ከኃልዮ ኃጢአት አይደለም:: እርሷ ግን ከነቢብ: ከገቢር: ከኃልዮ ንጽሕት ናት::

"ለመኑ ተውኅቦ ተደንግሎ ኅሊና: ለመላእክትሂ ኢተክህሎሙ-ኃጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ከሰው ልጆች ለማን ተሰጠው: ይህስ ለመላእክትም አልተቻላቸውም" እንዲል:: (ተአምረ ማርያም)

2."ጽንዕት" እንላታለን:: ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው እንጂ በኋላ በጊዜው ተፈትሆ አለባቸው:: እመቤታችን ግን ቅድመ ጸኒስ: ጊዜ ጸኒስ: ድኅረ ጸኒስ: ቅድመ ወሊድ: ጊዜ ወሊድ: ድኅረ ወሊድ ድንግል ናትና::

"ጽንዕት በድንግልና አልባቲ ሙስና" እንዳላት:: (ቅዱስ ያሬድ) ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስም "ወትረ ድንግል ማርያም-ማርያም ዘለዓለማዊት ድንግል ናት" እንዳለ:: (መጽሐፈ ቅዳሴ)

3.ድንግልን "ክብርት" እንላታለን:: ሌሎች ሴቶች ቢከብሩ ጻድቃን ሰማዕታትን: ነቢያት ሐዋርያትን ወልደው ነው:: እመቤታችንን ግን የምናከብራት "ወላዲተ አምላክ-የአምላክ እናቱ" ብለን ነውና::

4.እመቤታችንን "ልዩ" እንላታለን:: ከእርሷ በቀር እናት ሁና ድንግል: እመቤት ሁና አገልጋይ የሆነች: በድንግልና ወልዳ ወተትን (ሐሊበ ድንግልናዌን) ያስገኘች ሌላ ሴት የለችምና::

+የእመ ብርሃን ይቆየንና ደግሞ ሌሎች ቅዱሳት እናቶቻችንን እንመልከት:: እናቶቻችን ስናከብር የምንጀምረው በቅድስት ሔዋን ነው:: ብዙ ጊዜ የእናታችን ሔዋን ጥፋቷ እንጂ በጐ ነገሯ: ደግነቷ: ንስሃዋ አይነገርላትም:: ሆኖም እናታችን ቅድስት ሔዋን ክብር የሚገባት ሴት ናት::

*ክርስቶስ ሰው የሆነ እርሷንና ልጆቿን ለመቀደስ ነውና:: "ከመ ይስዓር መርገማ ለሔዋን ዲበ ዕፅ ተሰቅለ" እንዲል:: (ድጓ)

+ቀጥሎ በብሉይ ኪዳን እነ ሐይከል: እድና: ሣራ: ርብቃ: አስኔት: ሲፓራ: ሐና: ቤርሳቤህን የመሰሉ እናቶቻችን በበጐው መንገድ ፈጣሪን ደስ አሰኝተዋል:: በዘመነ ሥጋዌም ቅዱሳቱ ሐና: ኤልሳቤጥ: ማርያም: ሶፍያ: ሰሎሜ: ዮሐና እና 36ቱ ቅዱሳት አንስት በጐነታቸው ያበራል::

+ከዚያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ለ2,000 ዓመታት የተነሱ አእላፍ ቅዱሳት እናቶቻችንን ግን ዘርዝረን አንዘልቃቸውም:: በቅድስናቸው አራዊትን ያሰገዱ: ነገሥታትን ያንቀጠቀጡ: አጋንንቸትን የረገጡ: በዘንዶ ላይ የተጫሙ ብዙ እናቶችን ቤተ ክርስቲያን አፍርታለች::

+ዛሬም ቢሆን በበርሃና በከተማ በጐውን ጐዳና የተከተሉ ብዙ እናቶች እንዳሉን እናውቃለን:: አንድም እናምናለን:: ግን ግን በከተሞች የምንመለከተው ሥርዓቱን የለቀቀው የበርካታ እህቶቻችን አካሔድ ለሃገርም ለቤተ ክርስቲያንም ትልቅ ስጋት ነው:: ክብርና ነውር የማይለይበት ዘመን ይመስላል::

+ይህንን እያነበባችሁ ያላችሁ እህቶቼ! አንድ ነገር ልንገራችሁ:: በመልካቸው ብዙዎችን ያጋጩ: አጊጠው በመታየታቸው ብዙዎችን ያሰናከሉ: ለብዙ ምዕመናንም የጥፋት ምክንያት የሆኑ ብዙ ሴቶች በታሪክ ነበሩ::

+የሚያሳዝነው ግን ዛሬ ያሉት ከመሬት በታች ነው:: አፈር በልቷቸዋል:: ስም አጠራራቸውም ጠፍቷል:: በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ዛሬ በዘለዓለማዊው እሳት እየተቃጠሉ በሲኦል: በጥልቁ ውስጥ አሉ::

+እናም ወገኖቼ! ይህን አውቀን እንንቃ:: ይህ ዓለም ጠፊም: አጥፊም ነውና:: እድሜአችን ቢረዝምና ከዚህ በኋላ ለ100 ዓመታት ብንኖርም እርሱም ማለቁ አይቀርምና:: ምርጫችን ዘለዓለማዊው ሕይወት ይሁን ትላለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን::

+" እለ ቅድስት ሶፍያ "+

+ቅድስት ሶፍያና አብረዋት በዚህ ዕለት የሚከበሩ ቅዱሳት አንስት በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በሮም የነበሩ ክረስቲያኖች ናቸው:: አብዛኞቹ መልክ (ደም ግባት) ከጠባይ ጋር የተስማማላቸው ነበሩ:: ነገር ግን ከምድራዊው ክብር ሰማያዊውን መርጠው ለመንፈሳዊው ሙሽርነት ወደ ገዳም ገቡ::

+ከእነዚህ ቅዱሳን መካከል በጸጋና በሞገስ: በትምሕርትም የምትበልጥ ቅድስት ሶፍያ ናትና እመ ምኔት አድርገው ሾሟት:: እርሷም ለገዳሙ በጐውን ሥርዓት ሠራች:: ሁሉም (ደናግሉም መነኮሳይያቱም) በአንድነት ይጾማሉ: ይጸልያሉ: ይሰግዳሉ: የቅዱሳንን ተጋድሎ ያነባሉ:: ሥጋውን ደሙን ይቀበላሉ::

+እርስ በርስ ደግሞ ፈጽመው ይፋቀራሉ:: በዚህ ሕይወት አንዳንዶቹ እስከ 70 ዓመት ቆዩ:: የቅድስናቸው ዜና ሲሰማ በሮም ግዛት ያሉ ወጣት ሴቶች እየመጡ ይቀላቀሏቸው ነበር:: ቅድስት ሶፍያም የሕይወትን መንገድ ታሳያቸው ነበር::

+ከዚህ ሁሉ በኋላ ከሐዲው ንጉሥ ዑልያኖስ ለጦርነት ወደ ፋርስ ሲሔድ ስላያቸው ባንድነት ሰብስቦ ሁሉንም በሰይፍ አስመታቸው:: ቅድስት ሶፍያም አብራ ሰማዕት ሆነች:: ስለ ቅዱሳኑ የሚበቀል ጌታም ቅዱስ መርቆሬዎስን ልኮ በጦርነቱ መካከል በጦር ወጋው:: ዑልያኖስ ወደ ዘለዓለም ኩነኔ ሲሔድ: ቅዱሳት አንስት ወደ ገነት ሔደዋል::

+" ባሕረ ሐሳብ "+

+ዳግመኛ በዚህ ቀን: በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ባሕረ ሐሳብ በዓለማቀፍ ደረጃ ተቀባይነትን አግኝቷል:: ሊቁ ቅዱስ ድሜጥሮስ (የግብጽ 12ኛ ፓትርያርክ) መንፈስ ቅዱስ ቀመረ ባሕረ ሐሳብን ገልጾለት በዓለም ላሉ ሊቃነ ዻዻሳት ልኮላቸው በዚህች ዕለት በሮም ከተማ ተሰበሰቡ::

+ሊቃውንትም ሐዋርያት ካስተማሩት ጋር ተመሳሳይ ሆኖ ቢያገኙት በደስታ ተቀብለውታል:: እነሆ እስከ ዛሬ ድረስ ለ1,700 ዓመታት ቤተ ክርስቲያን እየተገለገለችበት ይገኛል::

+የቅዱሳት እናቶቻችን አምላክ ዛሬም እንደ እነርሱ ያሉትን አያሳጣን:: በጸሎታቸው ምሮ ከበረከታቸው ይክፈለን::

+ኅዳር 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
2.ደናግለ ሮሜ (ሰማዕታት)
3.ቅዱስ ዻውሎስ ሰማዕት
4.ቅዱስ ድሜጥሮስ ሊቅ
5.ጉቡዓን ኤዺስ ቆዾሳት

ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት

1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
3.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
4.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)
5.ቅድስት ዕሌኒ ንግስት
6.ቅዱስ ዕፀ መስቀል
7.ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ

++"+ ለእናንተም ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጐናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ:: ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ:: +"+ (1ዼጥ. 3:3)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1. ግንኙነት ባደረገበት ቀን ቤተ መቅደስ መግባት ነው እንጂ የሚከለከለው ቤቱ ባዘጋጀው ጸሎት ቤት ታጥቦ ገብቶ ጸልዮ፣ ሰግዶ መውጣት ይችላል።

2. በየእለቱ መስገድ የሚፈልግ ሰው ቢያንስ ጠዋት ሰባት እና ማታ ሰባት መስገድ አለበት። ይኅውም ለምስጋና እና የእግዚአብሔር ጥበቃ እንዳይለየን ነው።
(ለአብ፣ ለወልድ፣ ለመንፈስ ቅዱስ) 3 ስግደት
(ለእመቤታችን) 1 ስግደት
(ለቅዱሳን መላዕክት) 1 ስግደት
(ለሰማዕታት) 1 ስግደት
(ለጻድቃን) 1 ስግደት
በድምሩ 7 ስግደት ይሆናል። በዚህም የሁሉም በረከት፣ ረድዔት፣ ጥበቃ በሕይወታችን ከዲያብሎስ ወጥመድ ሁሉ እንዲጠብቀን መማጸኛ ነው።

3.1. ልደታ ለማርያም እመቤታችን የተወለደችበት ቀን ነው
3.2. በአታ ለማርያም ደግሞ እመቤታችን በሦስት ዓመቷ ወደ ቤተመቅደስ የገባችበት ቀን ነው። ይህም ወላጆቿ በስዕለት ስለወለዷት ቤተመቅደስ እንድታገለግል እንሰጣታለን ብለው ስዕለት ገብተው ስለነበር ስዕለታቸውን ለመፈጸም ነው ወደ ቤተ መቅደስ በ3 ዓመቷ ያስገቧት።
3.3. ሐና ማርያም የእመቤታችን እናት እና አባት፤ ቅድስት ሐና እና ቅዱስ ኢያቄም የሚታሰቡበት ቀን ነው
3.4. ኪዳነምህረት እመቤታችን የሰው ልጆችን ሁሉ የምታድንበት፣ የምታማልድበት "የምሕረት ቃልኪዳን" ከአብ ወልድ መንፈስቅዱስ የተሰጣት ቀን ነው።
3.5. ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያረፈችበት (አስተርእዮ ማርያም)፣ በደብረ ምጥማቅ የተገለጠችበት፣ ቅዳሴ ቤቷ፣ ታቦተ ጽዮን(ህዳር ጽዮን)፣ ግሸን ደብረ ከርቤ(መስከረም 21) እንዲሁም ሌሎች በዓላት የሚከበሩበት ቀን ነው።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

💎ሁሉም ለራሱ ትክክል ሊሆን ይችላል ስለዚህ ሰዎች የሚሰሩት ስራ ስህተት መስሎህ ከታየህ በንዴት አትጩህባቸው ይልቁንስ ቀርበህ በእርጋታ ጠይቃቸው።
🔴የክርስትና ተግባሩ ይሄ ነው።


❗️ልቦና ይስጠን❗️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ኅዳር ፲፭ (15) ❖

+"+ ቅዱስ ሚናስ ምዕመን ሰማዕት +"+

=>ቅዱስ ሚናስ (ማር ሚና) በምድረ ግብጽ ተወዳጅ
ከሆኑ ሰማዕታት ዋነኛው ነው:: ልክ በሃገራችን ቅዱስ
ጊዮርጊስ ልዩ ቦታ እንዳለው ሁሉ ግብፃውያን ማር
ሚናስን ጠርተው አይጠግቡትም::

+ምክንያቱም ከታላላቅ ሰማዕታት አንዱ በመሆኑና ዛሬም
ድረስ ለጆሮና ለዐይን ድንቅ የሆኑ ተአምራትን ስለሚሠራ
ነው:: በተለይ ለታመመ: ለደከመና ለተጨነቀ ፈጥኖ
ደራሽ: ባለ በጐ መድኃኒት ፈዋሽና አማላጅ ነው::

+"ግብጽ ውስጥ ቅዱሱን የማያውቅ ሰው ካገኛችሁ
እርሱ ኦርርቶዶክሳዊ አይደለም ማለት ነው" ሲባልም
ሰምተናል:: በነገራችን ላይ ለቅዱሳን ተገቢውን ክብር
በመስጠት: ታሪካቸውን በመጻፍ: በማጥናት: በመጽሔት:
በፊልምና በመሳሰሉት ለሕዝብ በማስተዋወቅ
ግብጻውያኑ ከእኛ ብዙ ርቀት ሒደዋል:: ዛሬ እንኩዋ
የምንጠቀምበትን ስንክሳር 80 ከመቶ እጁን ያዘጋጁት
እነርሱ ናቸው::

+አባቶቻችንና እናቶቻችን ኢትዮዽያውያን ቅዱሳን ግን
አብዛኞቹ ተረስተው ቀርተዋል:: መጽሐፈ ገድላቸውንም
ብል በልቶታል:: ዛሬም የቤት ሥራው የእኛ ብቻ ነው::

+ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ ሚናስ (ትርጉሙ ታማኝና ቡሩክ ማለት ነው):-

*በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ የደጋግ ክርስቲያኖች
ልጅ::
*በልጅነቱ የቅድስና ሕይወትን ያጣጣመ::
*በዘመኑ ሰው እጅግ ተወዳጅ የነበረ::
*ሃብትን: ክብርን: ሥልጣንን ንቆ በጾምና በጸሎት
የተወሰነ::
*በመጨረሻም በክርስቶስ ስላመነ አላውያን የገደሉት
ሰማዕት ነው::

+እርሱ ሰማዕት ከሆነ ከበርካታ ዘመናት በሁዋላ
ምዕመናን ክቡር አካሉን ፈልገው ያጡታል::
የሚገለጥበት ጊዜ ሲደርስ ግን እርሱ የተቀበረበት ምድረ
በዳ የበጐችና የእረኞች መዋያ ነበርና ተአምራትን
አደረገ::

+አንድ እረኛ በጐቹ ድውያን ሆኑበት:: በዚያ ሰሞን
ከቅዱሱ መቃብር ላይ ጸበል ፈልቆ ነበርና እረኛው ተርታ
ውሃ ነው ብሎ በጎቹን ሲያጠጣቸው አንዱ ድውይ በግ
ወደ ጸበሉ በመዘፈቁ ዳነ::

+በዚህ የተገረመው እረኛ ሁሉንም የታመሙ በጐቹን
አምጥቶ ነከራቸው:: እነርሱም ተፈወሱ:: ይህ ዜና
በምድረ ግብፅ ሲሰማ ድውያን ሁሉ እየመጡ ይፈወሱ
ገቡ:: ግን እነሱም ሆነ እረኛው ምክንያቱን ማወቅ
አልቻሉም:: ነገሩ በሮም ንጉሥ ዘንድ ሲሰማ ሴት ልጁን
ከሠራዊቱ ጋር ላካት::

ምክንያቱም እርሷ ከብዙ ዘመን ጀምራ መጻጉዕ ነበረችና
ፈውስን አጥታ ነበር::

+መጥታ ተጠመቀች: ፈጥናም ተፈወሰች:: እርሷ ግን
እንደ ሌሎች ያዳናትን ማንነት ሳታውቅ መሔድ
አልፈለገችምና ሱባዔ ገባች:: ቅዱስ ሚናስ በሌሊት
ራዕይ መጥቶ ሥጋው እንዳለ ነገራት:: እርሷም መሬቱን
አስቆፍራ የቅዱሱን አካል በክብር አስወጣች::

+ከዚያም በንጉሡ ትዕዛዝ ምድረ በዳው ከተማ
እንዲሆን ተቀየረ:: ስሙም "መርዩጥ" ተባለ:: ጸበሉ
የነበረበት ቦታም ላይ የማር ሚናስ ቤተ ክርስቲያን
ታንጾበት ቅዳሴ ቤ ተከብሯል::

+"+ ቅዱስ ቂርቆስ ሕጻን +"+

=>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ካሏት ዐበይት ሰማዕታት አንዱ
ቅዱስ ቂርቆስ ነው:: በተለይ በዘመነ ሰማዕታት ተነስተው
እንደ ከዋክብት ካበሩትም አንዱ ነው:: ቅዱስ ወንጌል
እንዲህ ይላል:- "መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን
ያፈራል::" (ማቴ. 7:17)

+መልካም ዛፍ ቅድስት ኢየሉጣ መልካም ፍሬ ብጹዕ
ቂርቆስን አፍርታ ተገኝታለችና ክብር ይገባታል:: ቡርክተ
ማሕጸንም እንላታለን:: የተባረከ ማሕጸኗ የተባረከ ልጅን
ለ9 ወር ተሸክሟልና::

+በዚያ ክርስቲያን መሆን መከራ በነበረበት ዘመን ይህንን
ደግ ሕጻን እርሷን መስሎ: እርሷንም አህሎ እንዲገኝ
አስችላለችና:: አበው በትውፊት እንዳቆዩልን ከሆነ
በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በዚህች ቀን እናታችን ቅድስት
ኢየለጡ ብጹዕ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስን ወልዳለች::

+ፈጣሪ ቢያቆየን የሰማዕትነት ዜናቸውን ጥር 15 ቀን
የምንመለከት ነንና የዚያ ሰው እንዲለን እንማጸነዋለን::

=>አምላከ ሰማዕታት በምሕረቱ ይማረን:: በይቅርታው
ኃጢአታችን ይተውልን:: ከበረከተ ሰማዕታትም ይክፈለን::

=>ኅዳር 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ሚናስ ሰማዕት
2.ልደተ ቅዱስ ቂርቆስ
3.ብጽዕት ኢየሉጣ
4.አባ ሚናስ ዳግማይ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት)
2.ቅድስት እንባ መሪና
3.ቅድስት ክርስጢና

=>+"+ አሁንስ ይላል እግዚአብሔር:: በፍጹም ልባችሁ
በጾምም: በለቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ:: ልባችሁን
እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ:: አምላካችሁም
እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ: ቁጣው የዘገየ: ምሕረቱም
የበዛ: ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ:: +"+ (ኢዩ. 2:12)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሰላም የአባታች የፃድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ክብረ በአላት ንገሩኝ ወንድሞቼ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

6.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ
7.ቅዱስ ሙሴ መርዓዊ

††† "ለአንዱም በአንዱ መንፈስ የመፈወስ ስጦታ: ለአንዱም ተአምራትን ማድረግ: ለአንዱም ትንቢትን መናገር: ለአንዱም መናፍስትን መለየት: ለአንዱም በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር: ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጐምይሰጠዋል:: ይህን ሁሉ ግን ያ አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድ ለእያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርገዋል::" †††
(፩ቆሮ. ፲፪፥፱)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://t.me/joinchat/rqHLqXClTZA0YmU0

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

+ቅዱሱ ግን በትእግስት ሁሉን ቻለ:: በዚህ መካከል ዘመነ ሰማዕታት አልፎ ቅዱስ ጢሞቴዎስ ነጻ ወጣ:: ያን ጊዜም ሕዝቡን ሰብስቦ ጸሎትን አደረገ:: "ጌታ ሆይ! ይህንን መኮንን እባክህ ማርልኝ? ያደረገው ነገር ሁሉ ባለ ማወቅ ነውና::"
+ይህንን ጸሎት በወሬ ነጋሪ የሰማው ያ መኮንን በጣም ተገርሞ በቅዱሱ ፊት ሔዶ በግንባሩ ተደፋ:: "ስጠላህ የወደድከኝ አባት ሆይ! ማረኝ?" አለው:: ቅዱስ ጢሞቴዎስም አስተምሮ አጠመቀው:: 2ቱም አብረውሲጋደሉ ኑረው ዐርፈዋል::

=>አምላከ ቅዱሳን በረድኤተ መላእክት ጠብቆ በወዳጆቹ ምልጃ ይማረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

=>ኅዳር 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አእላፍ (99ኙ) ነገደ መላእክት
2.ቅዱስ አስከናፍር ሮማዊ
3."13ቱ" ግኁሳን አበው (ሽፍቶች የነበሩ)
4.ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘእንጽና
5.አባ ዘካርያስ ሊቀ ዻዻሳት

=>ወርኀዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
3.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
4.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ

=>+"+ ስለ መላእክትም:-
"መላእክቱን መናፍስት: አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርግ" ይላል . . .
ነገር ግን ከመላእክት:-
"ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ" ከቶ ለማን ተብሏል?
ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ: የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን? +"+ (ዕብ. 1:7-14)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ብዙም_ያልተነገረላቸው_ፃዲቁን_አባታችንን በጥቂቱ እንውቅ

✿እንኳን ለጻድቁ #አቡነ #ዘዮሐንስ ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡✿

✿ጻድቁ በ13ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ በዚህች ኅዳር 13 ዕለት ከተባረኩ ወላጆች (ዘካርያስ እና ሶፍያ) ተወልደዋል፡፡
✿በተጋድሎ ከሸዋ እስከ ተግራይ ድንበር ፡ በስብከተ ወንጌልም ከኢትዮጵያ እስከ ኢየሩሳሌም ተጉዘዋል፡፡
✿2ቱን ድንቅ ደሴቶች (ክብራን ገብርኤልን እና እንጦንስ ኢየሱስን) የመሠረቱም ጻድቁ ናቸው፡፡

✿ከበረከታቸው አይለየን፡፡✿

ህዳር 13 2016
ሐሙስ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#መረጃ (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የገና ጾም በልዩ ሁኔታ እንዲጾም መንፈሳዊ አዋጅ አስተላለፈች።)


➯ሀገራዊ ሰላምን፣ መረጋጋትንና አንድነትን ለማስፈን የታወጀው የጾምና የጸሎተ ምኅላ ዝርዝር አፈጻጸምንም እንደሚከተለው በዝርዝር ቀርቧል፦

👉 አፈጻጸም ፦

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

➯ሀገራዊ ሰላምን፣ መረጋጋትንና አንድነትን ለማስፈን የታወጀውን የጾምና የጸሎተ ምኅላው አፈጻጸም በቅደሱ ሲኖዶስ በተወሰነው መሠረት ከዚህ በመቀጠል አቀርባለሁ፡፡ ቀደም ሲል ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት በመላው ዓለም ለሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን የታወጀውን አዋጅ አስተላልፈዋል፡፡ በዚሁ መሠረት ያለፈውን በይቅርታና በምህረት ዘግተን በእውነተኛ ንሥሓ ልቅሶና በምህላ፣ በጾምና በጸሎት ወደ ፈጣሪ እንድንቀርብ፣ በመካከላችንም ፍቅርና አንድነት እንዲመጣ ይኽንን ጾመ ነቢያት ወይም የገና ጾም በልዩ ሁኔታ እንድንጾም መንፈሳዊ አዋጅ ተላልፏል፡፡

➯ይኽ ጥንታዊ የአዋጅ ጾም ሁለት አበይት ታሪኮችን የያዘ ነው፡፡ የመጀመሪያው ክፍል ቅዱስ አብርሃም ሶርያዊ የተባለ ጻድቅ አባት በጸሎት፣ በጾምና በምኅላ ተራራን ከመሬት ከፍ በማድረጉ ኃይለ ጸሎቱና ክብረ አምለኩ የሚዘከርበት ነው፡፡ በሁለተኛው ክፍል ነቢያት የጌታችንን ሰው መሆን እያፈለጉ፣ ድህነትንና ሰላምን በመሻት መጾማቸው ይዘከራል፡፡ (፩ኛ ጴጥ ፩፡፲) እኛም ይኽንን አብነት አድርገን ታላቋ ቤተ ክርስቲያን፣ ኃላፊነቷን እንድትወጣ ስለችግራችን፣ ስለሀገር ሰላምና ስለ ሕዝቡ ደኅንነት በአንድነት ሆነን ወደፈጣሪያች እንድንጮኽ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በጥቅምት ወር ፳፻፲ወ፮ ዓ/ም ወስኖ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

➯ሀገራችን እንድትፈወስ፣ የወገን በወገን ደም መፋሰስ እንዲቀር፣ ያለፈውን በይቅርታና በንሥሓ ዘግቶ ለወደፊቱ ብሩህ ዘመንን እንዲመጣ በንሥሓና በፍጹም ለቅሶ፣ በቁመትና በሰጊድ፣ በሰፊሕና በአንቅአድዎ፣ ወደፈጣሪ እንድንቀርብ የምልኣተ ጉባኤውን ውሳኔ መሠረት በማድረግ ቋሚ ሲኖዶስ በኅዳር ወር ፳፻፲ወ፮ዓ/ም የሚከተለውን ዝርዝር አፈጻጸም አውጥቷል፡፡

➯ - ፩ኛ/1ኛ. የጾሙ የመጀመሪያ ሳምንት ከቅዳሜ ኅዳር ፲፭/15 እስከ ኅዳር ፳፩/21 ቀን ፳፻፲ወ፮/2016 ዓ/ም በሁሉም የሀገራችን ክፍልና ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ባለችበት በመላው ዓለም የንሥሓ፣ የጾም፣ የጸሎትና የምኅላ ሳምንት እንዲሆን፤

➯ - ፪ኛ/2ኛ. በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ በአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ በአጥቢያ አለቆችና በገዳም አበምኔቶች መሪነት ሁሉም ዲያቆናት፣ ቀሳውስት፣ መነኰሳት፣ ሰባክያንና ሊቃውንት በሙሉ በየመዐርጋቸው ልብሰ ተክህኖና ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት ዩኒፎርማቸው ለብሰው፣ ሁሉም ምእመናን ጋር በአንድነት በዐውደ ምህረት ጸሎተ ምኅላውን እንዲያደርሱ፤

➯ - ፫ኛ/3ኛ. በላው ሕዝበ ክርስቲያን ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ ሕፃናት፣ ወጣቶች፣ እናቶች አባቶች አረጋውያን ሁሉ የቻለ በቤተ ክርስቲያን፣ ያልቻለ በያለበት ሆኖ የተጣላ ታርቆ፣ በፍቅርና በአንድነት፣ በእውነተኛ ንሥሓና ጸጸት በምኅላው እንዲሳተፍ፤ በማእከል የሚደረገው ጸሎተ ምኅላ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ገዳም ሆኖ በመገናኛ ብዙኀን የቀጥታ ሥርጭት ለመላው ዓለም እንዲተላለፍ፤

➯ - ፬ኛ/4ኛ. በመጀመሪያው የሱባኤ ቀን ኅዳር ፲፭/15 ቀንና፣ በሰባተኛው ቀን ኅዳር ፳፩/21 ቀን በጸሎተ ምኅላው በሚደረግበት ጊዜ ታቦቱ ከመንበሩ ተነሥቶ በዐውደ ምኅረት በቀሳውስት እንዲከብር ሆኖ፤ በሁሉም የምኅላው ቀናት ሥዕለ ማርያም፣ ወንጌልና መስቀል ወጥቶ በአራቱ መዐዝን ሥርዓተ ጸሎተ ምኅላው ከጸሎተ ወንጌል ጋር በየቀኑ በነግህና በሠርክ የሥራ ሰዓትን በማይነካ ሁኔታ እንዲፈጸም፤

➯ - ፭ኛ/5ኛ. በየዕለቱ የሚነበቡት የወንጌል ክፍሎችን ስለ ሰላም፣ ስለንሥሓና ጸጸት፣ ስለ ፍቅርና አንድነት፣ ስለ በጎነትና መደማመጥ፣ ስለመሰማማትና ጥላቻን ስለማራቅ እንዲሆን፤

➯ - ፮ኛ/6ኛ. በሰፊህና በአንቀዓድዎ፣ በሰጊድና በአስተብርኮ፣ ምኅላው ከደረሰና፣ ጸሎተ ወንጌል ደርሶ ዕለቱ ወንጌል ከተነበበ በኋላ በአንድነት የንሥሓ መዝሙር በመዘመር፣ ሕዝበ ክርስቲያን ስለሀገራቸውና ስለሰው ልጆ ደኅንነት እያሰቡ ወደቤታቸው እንዲሄዱ፤

➯ - ፯ኛ/7ኛ. ከመጀመሪው ሳምንት በኋላ እስከ በዓለ ልደት ድረስ የሰርክ ምህላ ሳይቋረጥ መደበኛው ሥርዓተ ጾምና ጸሎት እንዲቀጥል፣ የቤተ ክርስቲያንን ታላቅነት፣ የአበውን ተቀባይነት በሚገለጽ፣ በቀጣይም ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን በመንፈሳዊ ጽናት የሰላም ልዑካን ሆነው እንዲቀጥሉ በሚያደርግ ሁኔታ እንዲፈጸም፤

➯ - ፰ኛ/8ኛ. አስቀድሞ የደረሰውንና፣ እየደረሰብን ያለው ችግር የጦርነትና የግጭት ብቻ ሳይሆን የረሀብ፣ የድርቅ፣ የኑሮ ውድነት፣ የመፈናቀልና የስደት ጭምር ስለሆነ ከጸሎትና ምኅላችን ጎን ለጎን መረዳዳትና መተዛዘን፣ ርኅራሄና መደጋገፍ አብሮ እንዲፈጸም፤

➯ - ፱ኛ/9ኛ. ይኽንኑ መልእክት መላው ዓለም እንዲውቀው፣ በተለይም የኦሬንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በጸሎት እንዲያስቡን፣ የጸሎታችንና የምኅላችን መነሻ ምክንያቱ የሀገራችን ወቅታዊ ችግር ቢሆንም የምንጸልየው ለመላው ዓለም መሆኑ ተገልጾ በደብዳቤ እንዲላክ እንዲደረግ፣ በማለት ቅዱስ ሲኖዶስ ጥብቅ መመሪያ አስተላልፏል፡፡

➯እግዚአብሔር አምላካችን በእንባና በንሥሓ የምናቀርበውን ጸሎተ ምኅላችንን በምህረቱ ተቀብሎ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን፣ ሕዝባችንን ይጠብቅልን፡፡

➯ወስብሐት ለእግዚአብሔር

👉የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ትናንት ኅዳር ፲፩/11 ቀን ፳፻፲፮/2016 ዓ/ም። ባወጣው መግለጫ። አዲስ አበባ፡ ኢትዮጵያ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#እንኳን አደረሳችሁ፡፡
#ህዳር 12
የቅዱስ ሚካኤል በዓል ለምን ይከበራል???
ሚካኤል ማለት ሚ-መኑ፣ ካ-ከመ፣ ኤል-አምላክ፤ ‹‹መኑ ከመ አምላክ፤ እንደ አምላክ ማን ነው፡፡ "ማን እንደ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ቅዱስ ሚካኤል መጋቤ ብሉይም ነው፡፡
ኃይላት የተባሉት መላእክትም ሰዎች በዓለም ፈተና ውስጥ ሆነው ሰይጣን ሊያደክማቸው ሲፈልግ ኃይልን ብርታትን የሚሰጡ፣ ይህን ዓለም ንቀው በበረሃ ወድቀው ከሥጋ ምኞት ጋር የሚጋደሉትን፣ በከተማም እየኖሩ መንፈሳዊ ትሩፋት የሚያደርጉትን ደግሞ የሚያበረቱ ናቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ በመልእክቱ ‹እርሱም ወደ ሰማይ ያረገ እግዚአብሔርም ተቀምጦ ያለ መላእክትና ሥልጣናት ኃይላትም የተገዙለት ነው…› ሲል ‹ኃይላት› በማለት ያነሣቸው በኢዮር አራተኛይቷ ከተማ የሚኖሩትን ነው፡፡ በእነዚህ ላይ እግዚአብሔር ቅዱስ ሚካኤልን አለቃቸው አድርጎ ሾሞታል፡፡ (፩ኛጴጥ.፫፥፳፪)
የሰማይ ሠራዊት ሁሉ አለቃቸው ለፍጥረት ሁሉ የሚማልድ ይህ ኃያል መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕዝብ የተባሉትን እስራኤል ዘሥጋን ሲረዳና ሲጠብቅ እንደነበረ ተጽፎልን እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ በኢያሪኮ ምድረ በዳ እንደተገለጠለት ‹‹… ዐይኑን አንሥቶ ተመለከተ፤ እነሆም፥ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ አየ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፥ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ?” አለው፡፡ እርሱም “እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ፤ አሁንም ወደ አንተ መጥቼአለሁ፡፡” ሲል ተናግሯል፡፡ (ኢያ.፭፥፲፫)
እግዚአብሔር አምላክ ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ነፃ ሲያወጣቸው ይመራቸው የነበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ ‹‹ በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ፥ ወዳዘጋጀሁልህም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፥ እነሆ ፥እኔ መልአኬን በፊትህ እልካለሁ›› እንዲል፤ ሹመቱ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይም በመሆኑ ስለ እነርሱ ከእግዚአብሔር ምሕረትን ይለምንላቸው ነበር፡፡ (ዘፀአት.፳፫፥፳)
ነገር ግን ኃጢአት ሲሠሩ እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን ይቀጣልና ሕዝቡን ‹‹ራስህን ጠብቅ፤ ስማው፤ እንቢም አትበለው፤ ስሜ በእርሱ ስለሆነ ይቅር አይልምና›› ብሎ አስጠንቅቋቸው ነበር፤ ይህም ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መሾሙን ያስረዳናል፡፡ (ዘፀ.፳፫፥፳፩)
ቅዱስ ገብርኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ቅዱስ ሚካኤል ስለመሾሙ ሲመሰክር ‹‹በእውነት በመጽሐፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር የሚረዳኝ ማንም የለም›› ብሎአል፡፡ ስለዚህም ለኢያሱ የተገለጠውና እስራኤላውያንንም የመራው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን እንረዳለን፡፡ (ዳን.፲፥፳፩)
የቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት በሐዲስ ኪዳንም እንደነበር ይህ ነቢይ በትንቢቱ ‹‹በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ ሚካኤል ይነሣል›› በማለት ተናግሮለታል፡፡ ስለዚህም ቅዱስ ሚካኤል እኛን ከሰይጣን አሽክላና ወጥመድ ይጠብቀንና በጸሎቱ በእግዚአብሔር ፊት ይቆምልን ዘንድ በእኛም ላይ ሹም ነው፡፡ ምክንያቱም እኛ የእግዚአብሔር ሕዝቦችና የርስቱ ወራሾች ነንና፡፡ (ዳን.፲፪፥፩)
በመጽሐፈ ስንክሳርም ተመዝግቦ እንደምናኘው ቅዱስ ሚካኤል በየወሩ በዐሥራ ሁለት ቀን ለመታሰቢያው በዓል ተሠርቶለታል፤ እርሱ ስለ እኛ የምድሩን ፍሬ ይባርክልን ዘንድ ዝናሙም በጊዜው እንዲወርድልን የወንዙንም ውኃ እንዲመላልን ነፋሱንም የምሕረት ነፋስ እንዲያደርግልን ሁሉንም የተስተካከለ እንዲያደርግልን ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ይማልዳልና፡፡ (ስንክሳር ኅዳር ፲፪)

በአጠቃላይ "…ህዳር 12 የሚከበረው የሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በዋናነት ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ተብሎ የተሾመበት፣ 40ውን ዘመን እሥራኤልን ቀን ደመና ጋርዶ፣ ሌሊት የብርሃን ዐምድ ተክሎ፣ ከአለት ላይ ውኃ አፍልቆ፣ መና ከሰማይ አውርዶ፣ ክንፉን ዘርግቶ፣ ጠላትን መክቶ ህዝበ እስራኤልን ከግብጽ ያወጣበት፣ (ዘፍ 48፥16) የባህራንን የሞት ደብዳቤ ወደ ህይወት የለወጠበት እና በሰማይም ዘንዶውን ተዋግቶ ያሸነፈበት የመታሰቢያ ዕለት ነው። ራእ12፥7

የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤል አማላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እንኳን አብሮ አደረሰን አሜን 🙏🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

♥ የቅዱስ ሚካኤል ክብር ♥
✍በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
❖♥ መልአክ የሚለው የግእዝ ቃል ሲኾን “ለአከ” ማለት (ላከ) ማለት ነው፤ ስለዚኽ መልአክ ማለት መልእክተኛ ማለት ነው፤ ይኸውም ሰው የጸለየውን ጸሎት ያቀረበውን መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርቡ የእግዚአብሔርን ምሕረት ወደ ሰው የሚያመላልሱ ረቂቃን ናቸውና የተሰጣቸው ሥያሜ ነው፡፡

❖♥ ልዑል እግዚአብሔር ሰባቱን ሰማያት ከፈጠረ በኋላ በዚያው በዕለተ እሑድ መላእክትን “እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ” (ካለመኖር ወደ መኖር) ማእምራን (ዐዋቂዎች) ለባውያን (አስተዋዮች) አድርጎ ፈጥሯቸዋል፡፡ ከነዚኽ መላእክት ውስጥ አንደኛውና የመላእክት አለቃ የኾነው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡

❖♥ ቅዱስ ሚካኤል የሚመራቸው ነገደ ኀይላት የሚባሉ በኢዮር ሰማይ የሚኖሩ መላእክትን ነው፤ ሊቁ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በሥነ ፍጥረት መጽሐፉ ላይ፦
✍️ “ወለራብዕ ጾታ ዐሠርቱ ስሞሙ ኀይላት ወሊቆሙ ሚካኤል ወአንበሮሙ በራብዕ ሰማይ” ይላል አራተኛው ዐሥሩን ነገድ ስማቸውን ኀይላት ሲላቸው እነዚኽም ባለሰይፍ ሲኾኑ የእግዚአብሔርን ወዳጆች ሲጠብቁ ጠላቶቹን ይቀጣሉ፤ የእነዚኽ ነገደ መላእክት አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ሲኾን በኢዮር በአራተኛው ከተማ አስፍሯቸዋል እንዲል፡፡

❖♥ ሳጥናኤል “እኔ ፈጣሪ ነኝ” ብሎ የክሕደት ንግግርን በተናገረ ጊዜ አስቀድሞ ሰራዊቱን በመያዝ ከነገደ ዲያብሎስ ጋር የተዋጋ መልአክ ነውና፤ ዮሐንስም ስለ ቅዱስ ሚካኤል ኀያልነት በራእ ፲፪፥፯-፱ ላይ፡-
✍️ “በሰማይም ሰልፍ ኾነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ፤ ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ አልቻላቸውምም ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም ዓለሙንም ኹሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ ርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከርሱ ጋር ተጣሉ” በማለት ዲያብሎስን የተፋለመ መልአክ መኾኑን ገልጾታል፤ በዚኽም “መልአከ ኀይል” ተብሏል፡፡

❖♥ የ99ኙ ነገደ መላእክት አለቃ ስለኾነው ስለ ቅዱስ ሚካኤል ክብር፣ ውበት፣ ምልጃ ማሕቶተ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ያሬድ በመጽሐፈ ድጓው እንዲኽ ይላል፡-

💥 ╬ “ክብረ ሚካኤል ናሁ ተዐውቀ
በትሕትናሁ ዐብየ ወልሕቀ
ዲበ አእላፍ ዘተሰምየ ሊቀ
ዘይትዐፀፍ መብረቀ ይተነብል ጽድቀ”

(የሚካኤል ክብረ እነሆ አኹን ታወቀ፤ በትሕናውም ፈጽሞ ላቀ ከፍ ከፍ አለ፤ በአእላፍ ነገደ መላእክት ላይ አለቃን የተባለ መብረቅን የሚጐናፀፍ ርሱ ጽድቅን ይለምናል) ይላል፡-

❤ የ99ኙ ነገደ መላእክት አለቃ ከመኾኑ ጋር ይልቁኑ ዮሐንስ በራእዩ በምዕ 8፡2 ላይ “በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ፥ ሰባትም መለከት ተሰጣቸው” ካላቸው፤ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት በመዠመሪያ የሚጠቀሰው ቅዱስ ሚካኤል ነውና ሊቁ፡-

╬ ♥ “እስመ እምአፉሁ ይወጽዕ ነጐድጓድ
ሕብረ ክነፊሁ ያንበለብል ነድ
እምሊቃነ መላእክት የዐቢ በዐውድ
ሚካኤል ውእቱ መልአኩ ለወልድ”

(የወልድ አገልጋዩ ሚካኤል ነው፤ በዙሪያው ኹሉ ካሉት ከሊቃነ መላእክት ይበልጣል፤ የክንፉ መልክ ነባልባላዊ እሳትን ያቃጥላል፤ ከአንደበቱ ነጐድጓድ ይወጣልና)

╬ ♥“አዕበዮ ንጉሠ ስብሐት
ለሚካኤል ሊቀ መላእክት
ዘይስእል በእንተ ምሕረት
መልአከ ሥረዊሆሙ ለመላእክት”
(የምስጋና ባለቤት ክርስቶስ ለመላእክት ጭፍሮች አለቃቸው የኾነ ስለ ምሕረት የሚማልድ የመላእክት አለቃ ሚካኤልን ከፍ ከፍ አደረገው) በማለት ይጠቅሰዋል፡፡

❖♥ የስሙ ትርጓሜንም ስንመለከት ሚካኤል ማለት ቃሉ የዕብራይስጥ ሲኾን ሚ- ማለት “ማን”፤ ካ- “እንደ”፤ ኤል- “አምላክ” ማለት ነውና ሚካኤል ማለት “መኑ ከመ አምላክ” (ማን እንደ አምላክ) ማለት ነው፡፡

❖♥ የመልክአ ሚካኤል ደራሲም ይኽነን ይዞ፦

╬ “ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ
ወልደ ያሬድ ሄኖክ በከመ ጸሐፈ”
(የያሬድ ልጅ ሄኖክ እንደጻፈው ከልዑል ስም ጋር ለተባበረ ስም አጠራርኽ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፡፡

ቅዱስ ያሬድም፡-
💥 ╬ “መልአከ ፍሥሐ ሚካኤል ስሙ
ለመላእክት ውእቱ ሊቆሙ
መልአኮሙ ሥዩሞሙ
የሐውር ቅድሜሆሙ እንዘ ይመርሆሙ”

(ስሙ ሚካኤል የተባለ የደስታ መልአክ ለነገደ መላእክት አለቃቸው ነው፤ የተሾመላቸው አለቃቸው ርሱ እየመራቸው በፊት በፊታቸው ይኼዳል) ይላል

❖♥ በብሉይ ኪዳን ለአበው ነቢያት እየተገለጠ፤ ለሐዋርያትም በስብከት አገልግሎታቸው እየተራዳ፤ ለሰማዕታት፣ ለቅዱሳን አበው በተጋድሏቸው እየተገለጠላቸው አስደሳች መልኩን ያዩት ነበር።

❖♥ ይኽነን የቅዱስ ሚካኤልን ውበት ቅዱስ ያሬድ እንዲኽ ይገልጠዋል፡-
╬ “መልአከ ፍሥሐ ዘዐጽፉ መብረቅ
ሐመልማለ ወርቅ ሚካኤል ሊቅ”
(መጐናጸፊያው መብረቅ የኾነ የደስታ መልአክ፤ አለቃ ሚካኤል የወርቅ ዐመልማሎ ነው)

❖♥ የመልክአ ሚካኤል ደራሲም ይኽነን ውበቱን ሲገልጠው፡-
╬ “ሰላም ለአክናፊከ እለ በሰማያት ያንበለብሉ
ከመ ሠርቀ ፀሓይ ሥነ ጸዳሉ”
(የጸዳሉ ውበት እንደ ፀሓይ አወጣጥ የኾነ በሰማያት ለሚያንበለብሉ ክንፎችኽ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፡፡

❖♥ ቅዱስ ያሬድ ደግሞ፡-
╬ “ውእቱ ሊቆሙ ወመልአኮሙ ሚካኤል ስሙ
ዐይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ
ሐመልማለ ወርቅ”
(ዐይኑ የርግብ (እንደ ርግብ የዋህ፣ ጽሩይ) የኾነ ልብሱ የመብረቅ መጐናጸፊያ የኾነለት የወርቅ ዐመልማሎ ስሙ ሚካኤል የተባለ ርሱ የመላእክት አለቃቸው መሪያቸው ነው) ይላል፡፡

❖♥ መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብብ ሙሴን ከፈርዖን፣ ኢያሱን ከአማሌቅ፣ ሕዝቅያስን ከሰናክሬም፣ ዳዊትን ከጎልያድ እጅ በተራዳኢነቱ የጠበቀ ሲኾን፤ ስለ ቅዱስ ሚካኤል አማላጅነትና ተራዳኢነት ነቢዩ ዳንኤል፡- “ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ…ነገር ግን በእውነት ጽሑፍ የተጻፈውን እነግርኻለኊ በዚኽም ነገር ከአለቃችኊ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም… በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብኽ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል” በማለት አማላጅነቱን መስክሮለታል (ዳን ፲፥፲፫፤ ፲፥፳፩፤ ፲፪፥፩)፡፡

❖♥ የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነትና አማላጅነት ቅዱስ ያሬድ እንዲኽ ይገልጠዋል፡-
╬💥 በ፲ወ፬ቱ ትንብልናከ ዐቢይ ልዕልናከ
በመንክር ትሕትናከ
አስተምህር ለነ ሰአልናከ”

(በዐሥራ አራቱ ልመናኽ ምልጃኽ፤ በታላቅ ልዕልናኽ በሚያስደንቅም ትሕትናኽ ሚካኤል ትለምንልን ዘንድ ማለድንኽ)

💥╬ “ዘወሀበ ትንቢተ ለኤልዳድ ወሙዳድ
አመ ምጽአቱ ይምሐረነ ወልድ
ሰአል ለነ ሚካኤል መንፈሳዊ ነገድ
ከመ ንክሃል አምስጦ እምሲኦል ሞገድ”
(ለኤልዳድና ለሙዳድ የትንቢትን ጸጋ የሰጠ የሚኾን ወልድ በሚመጣ ጊዜ ይምረን ዘንድ ከረቂቅ ነገድ ወገን የኾንኸው ሚካኤል ከሲኦል እሳታዊ ሞገድ ማምለጥ እንችል ዘንድ ለእኛ ለምንልን) ይላል፡፡

╬💥 “ከናፍሪሁ ነድ ዘእሳት አልባሲሁ ዘመብረቅ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ውእቱ ይዕቀብክሙ ነግሀ ወሠርከ ሌሊተ ወመዐልተ”

❤ (ከናፍሮቹ የእሳት ልብሶቹ የመብረቅ የኾነ የመላእክት አለቃ ሚካኤል በተራዳኢነቱ በጠዋትም፤ በሠርክም፤ በቀንም በሌሊትም ይጠብቃችኊ) እንዲል፤ ሙሴን ከፈርዖን፣ ኢያሱን ከአማሌቅ፣ ዳዊትን ከጎልያድ፣ ሕዝቅያስን ከሰናክሬም፤ ዳንኤልን ከአፈ አናብስት፣ ሶስናን ከረበናት፤ ቅድስት አፎምያን ከዲያብሎስ እጅ በምልጃው የታደገው፤ አስቀድሞም ዘንዶው ዲያብሎስን ተፋልሞ የጣለው ይኽ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በቀንም በሌሊትም ተራድቶ ይጠብቀን እላለኊ (ራእ 12፡7፤ ራእ 13፡1-3)፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
            "ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ"
በደብረ በረከት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያ ህዳር፲፱ በወራዊ የቅዱስ ገብርኤል በዓል ላይ በማታው የአውደ ምህረት ጉባኤ ላይ የሕይወትን ቃን የሚመግቡን መምህር ዲ/ን ዮሐንስ ጌታቸው የምስጋናውን በዝማሬ አገልግሎት የሚያገለግሉን ደግሞ ዘማሪ ዲ/ን ፍሬዘር ደሳለኝ ናቸው እርሶም በመገኘት የነፍስን ምግብ እንመገብ እያለች ቅድስት ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታቀርባለች።
👉አድራሻ:-ካራ ቆሬ ደብረ በረከት                   
    ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን።
👉ሰዓት:-11:00-1:30
   👉ቤተሰብኦን መንፈሳዊ መዓድን
     ይጋብዙ!!!

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ምክረ ኣበው

★ልጄ ሆይ ሰይጣን እኛን የሚዋጋበት ታላቁ ውጊያው ተሰፋ ማስቆረጥ ነው፡፡

★ልጄሆይ ሳይረፍድብህ በፊት በራስህ ፍረድ፡፡

★ልጄ ሆይ በእግዚአብሔር ፊት ስትቆም ልክ የእሳት ፍም ኣጠገብ እንደ ቆምክ ኣስብ፡፡

★ልጄ ሆይ ከመንግሥተሰማይ እንዳትለይ ንስሀን ገንዘብ ኣድርጋት፡፡

★ልጄ ሆይ ሐጢአት ከሰው ኣይርቅም ሰው ግን ከሐጢአት ይርቃል፡፡

★ልጄ ሆይ እጠገናለሁ ብለህ እንደማትሰበር ሁሉ ንስሃ እገባለሁ
ብለህ ሀጥያትን አትስራ፡፡

★ከንስሃ አባትህጋር ስትሆን ጥያቄ እንጂ ውሳኔህን አታቅርብላቸው

★ንስሃ ከጊዜቆይታ በኋላ ወደሀጥያት የሚመለሱበት የሀጥያት እረፍት አይደለም፡፡

★ልጄ ሆይ ትግል ፈተናና መከራ ከሌለ የድል አክሊል ጠላትም ከሌለ ድል ማድረግ የለም፡፡

★ልጄሆይ ዝናብ ያበቀለው ፀሐይ ያበሰለው የእግዚአብሔር ሀብት ነው ብለህ በፍፁም ትህትና ምፅዋትህን መፅውት

★ልጄ ሆይ ያልተሰጠህን ፀጋ ስትፈልግ የተሰጠህን ግዴታ ትረሳለህ ካለፀሎት ስግደትና ፆም
ከሚደረግ አገለግሎት ይልቅ ካለአገልግሎት የሚደረግ ፆም ፀሎትና ስግደት ትልቅዋጋ አለው

★ልጄ ሆይ ትሁት ሰው አጋንንትን አይፈራም እግዚአብሔር ሁሉን ያስገዛለታል፡

★ልጄሆይ የኛአገልግሎት ለእግዚአብሔር አያስፈልገውም ለኛ የእርሱ አምላክነት ያስፈልገናል እንጂ
★ልጄሆይ አፈርና ትቢያ ሆነህ ሳለህ እንደጻድቅ ከሚቆጥሩህ ሰዎችን እግዚአብሔር ያድንህ
አሜን 🙏🙏🙏




/channel/mezmur_store

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🔶እየተጠራሁ ነው❗️
                ♻️ እውነተኛ ታሪክ!
አቶ በጋሻው እና ወይዘሮ ሽቶ ትዳር መስርተው አንድ የ10 አመት ልጅ ወልደው በፍቅር እየኖሩ ሳለ በአንዲት ባልታደለች ቀን ወይዘሮ ሽቶ በመንገድ ላይ ለጉዳይዋ ስትሄድ ፍሬን የበጠሰ መኪና ገጭቶ አለፋት። በአቅራቢያው ወደ ሚገኘው ክሊኒክ ቢወስዷትም በቶሎ ይህችን አለም ተሰናበትች። አቶ በጋሻው እና ልጃቸው ብርሃኑ ብቻቸውን ለአራት ዓመት ኖሩ። ከዚህ በኋላ አቶ በጋሻው ብቸኝነቱ ከብዶት ሌላ ሚስት አገባ።ልጅም ወለዱ ብርሃኑ ግን ሁለተኛ እናቱ ከመጣች እና ቤተሰቡን ከተቀላቀለች ቀን ጀምሮ ሃሳብ ገባው። ይህች ሁለተኛ እናቱ ብርሃኑን ትጨቁነዋለች እና አይወዳትም።
ያለ ምንም ጥፋቱ ቀኑን ሙሉ ፆሙን እንዲውል ስታደርገው ወደ ጓደኞቹ አቅንቶ ያገኘውን በልቶ ይውላል።
ሁሉ ጊዜ ብርሃኑን ያለ በደሉ ለአባቱ በጋሻው ትከሰዋለች። አባቱም ሚስቱን ያምናታል እና ብርሃኑን በርበሬ ያጥነዋል ሲገረፍም ያድራል።
ብርሃኑ አሁን ሁሉም ነገር ፊቱን ስለ አዞረበት ከቤቱ እንደ ምንም ብሎ የገብስ ዱቄት ይሰርቅ እና ጎረቤት አስቀምጦ ቂጣ እየጋገረ በውሃ እያማገ ይበላል።
የዚህ አይነት ግፍ እየደረሰበት በእንጀራ እናቱ ተጨቁኖ ህይወቱን እያኖረ የሚገኘው ብርሃኑ ጎደኞቹ ከፍለውለት በቤተክርስቲያን የሚዘጋጀውን የጉዞ መርሐ ግብር ሊካፈል ተዘጋጀ።ጉዞው ወደ ሸንኮራ ዮሐንስ ሲሆን በእለቱ ጠዋት ከቤቱ ሲወጣ ምንም ምግብ እንዳልበላ ያወቁት ጎረቤቶቹ ቁርስ በልተህ ትሄዳለህ ቢሉት ''አይይ እኔ እየተጠራሁ ነው'' ቶሎ መሄድ አለብኝ ብሎ ምንም ሳይበላ የጉዞውን መኪና ተሳፈረ። እየዘመሩ ከተጓዙ ከሰአታት በኋላ የጉዞው መድረሻ ቦታም  ደረሱ። ከዚህ በኋላ ነበረ ከሁለት ጓደኞቹ ጋራ ፀበሉ ወደ ሚገኝበት ቦታ ሲያቀና የቀሩት ጓደኞቹ ፀበል ይዘህልን ተመለስ ብለው ሃይላንድ ቢሰጡት ''እኔ አልመለስም እና አልቀበላችሁም'' ብሎ መለሰላቸው። ከዚያም ወደ ፀበሉ አቀና። በቦታው ደርሰው መታጠብ ጀመሩ ድንገት ግን ያልታሰበው ነገር ደረሠ። ብርሃኑ እየታጠበ ሳለ የቆመበት ቦታ አዳለጠው እና ወደ ውንዙ ገባ።አብረውት የነበሩት ጓደኞቹም ጮኹ ሁሉም ተሰባሰቡ ብርሀኑን ግን ሊያድኑት አልቻሉም ላይመለስ ተጠርቷል እና በዚያው ዳግም ወደ ማይመለስበት ከተማ ተጓዘ።
አስክሬኑም ሲፈለግ ቆይቶ በሁለተኛው ቀን ተገኘ። እነዚያ ሲዘምሩ የሄዱት ዛሬ ግን ተክዘው እና በነፍስ የተጓዘው የብርሃኑን አስክሬን ይዘው ወደ ሃገራቸው ተመለሱ።
ሃዘኑ በረታ ትካዜው በሁሉም ልብ ውስጥ ገብቶ የሁሉንም ልብ ሰበረው። ያቺ የምትጠላው እና ልታየው የማትፈልገው እንጀራ እናቱ ዛሬ ላይ በብርሃኑ ስትፈፅም የነበረውን ግፍ እያሰበች ትፀፀታለች።
የአካባቢው ሰዎች እና ጎረቤቶች ደግሞ የብርሃኑን ጭንቀት ስለሚያውቁ በቁጭት ወይኔ ያኔ እኔጋ አስጠግቼው ባሳደኩት የሚሉ እና የሚናገሩ ብዙዎች ናቸው።ብርሃኑ ግን ይህንን ሳያይ ሄዷል።

🌟ሰዎችን መርዳት ካለብን በጊዜው እንርዳቸው ጊዜው ካለፈ ትርፉ ዋይታ እና ቁጭት ብቻ ነው።

    
        🌟💫ከኪነ-ጥበብ🌟💫

✦ ━━━━━━━━━━━━ ✦
   ♡ ㅤ  ⎙ㅤ  ⌲        ✉️   
 ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ነይ ሶልያና


ነይ ሶልያና ተጫምተሽ ደመና፣
ነይ አዛኝቱ እመ ትህትና፣
አግዢኝ እናቴ፣
ይሙላልኝ ጉድለቴ፣
አቅርቢኝ ከፊቱ፣
ይማረኝ ምሕረቱ።


እኔ የማላውቀው ብዙ ነው ጉድለቴ፣
ጥሪት አልቆብኛል ባዶ ነው ሌማቴ፣
ምርኩዝ ያደረኩት ድንገት ተቀየረ፣
የእኔ ያልኩት ሁሉ የወረት ነበረ።
    ደግፊኝ ልቁም፣
    አግዢኝ ማርያም፣
    አሳስቢ ስለ እኔ፣
    ይቅለል ሃዘኔ።



በሃዘን ተከብቤ ሰላም ርቆኛል፣
ወገን ዘመድ ሁኚኝ እናቴ ከፍቶኛል፣
የሚያጽናናኝ የለም አይዞሽ ባይ ከጎኔ፣
እመ አምላክ አብሺው እንባዬን ከዓይኔ።
    ደግፊኝ ልቁም፣
    አግዢኝ ማርያም፣
    አሳስቢ ስለ እኔ፣
    ይቅለል ሃዘኔ።


ዙሪያዬን ያጠረው በእሾህ አሜኬላ፣
ጠላቴ እንዳይውጠኝ ሁኚልኝ ከለላ፣
እኔ ኃጢአተኛ ነኝ የለኝ መልካም ምግባር፣
ልጅሽ ፊት አልቆምም በደሌ ቢቆጠር።
    ደግፊኝ ልቁም፣
    አግዢኝ ማርያም፣
    አሳስቢ ስለ እኔ፣
    ይቅለል ሃዘኔ።


ሸክሙ ከብዶብኝ ቀሏል ማንነቴ፣
አሳስቢልኝ ማርያም የእንባ ነው ራቴ፣
ከስደት መልሺኝ አልሁን ወገን አልባ፣
ከናፈቀኝ ደጅሽ መባን ይዤ ልግባ።
    ደግፊኝ ልቁም፣
    አግዢኝ ማርያም፣
    አሳስቢ ስለ እኔ፣
    ይቅለል ሃዘኔ።


በዘማሪት ሰላማዊት ሶርሳ
@mezmur_store
@mezmur_store
@mezmur_store

Читать полностью…
Subscribe to a channel