kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/9-aOHCuJVg4?si=iY5uKF1Sid3sMWAI

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሰው_ሁን...

የቱ ነው አማራ የታለ ኦሮሞ
የቱ ነው ከንባታ የትኛው ነው ጋሞ
የቱ ነው አፋሩ የትኛው ነው ትግሬ
የቱ ነው ሱማሌው የታለ ሀረሬ
የትኛው ነው ጉምዙ የቱ ነው ሽናሻ
የትኛው ነው ፈረንጁ የቱ ነው ሀበሻ
ከተሰበሰበው ካስከሬኑ ክምር
ለይተህ አሳየኝ የቱ ነው ያንተ ዘር
እርቃንህን መተህ እርቃንህን ለመሄድ
ሰው ሆነህ ለመሞት ሰው ሆነህ ተወለድ።

Sher
🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/j9WeuoQGvWY?si=xDa0Ag5Xq5yUovSI

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እንኳን ለህዳር ፅዮን ማርያም አደረሳችሁ
ፅዮንን ክበቡዓት በዙሪያዋም ተመላለሱ
መዝሙረ ዳዊት 38፣12
እግዚአብሔር ፅዮንን ማደሪያው ትሆን ዘንድ መርጧታል ፅዮንን የሚጠሉ ግን ይፀፀታሉ !!
እመብርሃን ትጠብቃችሁ በረከቷ ይደርባችሁ መልካም ቀን ይሁንላችሁ የመቤቴ ወዳጆች

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/M6Q7xvOQVWQ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

♻️መንፈሳዊ ግጥም
👉አንተነህ ያመምከኝ❤️

●●●●●●●●●●●●●●●●
ህማም የተሸከምሽ መስቀል የማያጣሽ :
በሳዶር አላዶር በዳናት አዴራ ችንካር የተመታሽ።
አይኑን እያበራሽ ሊንጊኖስ የዎጋሽ
የሞትሺላት ሀገር አርዳ የምትበላሽ ።
የሚያሸጋግርሽ አንድ ትውልድ ያጣሽ     
እምዬ ተዋህዶ እስኪ ተናገሪ ጩሀትሽ።  
ይሰማ
ህመመሺን ከደበቅሽ መዳኒት የለማ።
  ያቦሻሂር ሚስጢር የዘመን ቀማሪ
የቅኔ ማህሌት የዜማ ፈጣሪ።
የብሉይ የአዲስ ምስራች ነጋሪ
የቋንቋ የጥበብ የፊደል ሰዳሪ።
የታሪክ ማህደር የአበው ምጡቅ ጥበብ
  የመድኖተአሚን የኪዳነት መዝገብ
  ሞት የመሻገሪያ የኖህ ድነት መርከብ።

እምዬ ተዋህዶ
አንቺ ተዋህዶ እስኪ ተናገሪ ጩሀትሽ    
ይሰማ
ህመምሺን ከደበቅሽ መዳኒት የለማ።
ተናገሪ እእ
ተናገሪ ተናገሪ ካልከኝማ
ልታክመኝ ልታድነኝ ከቆምክማ።
መዳኒቴ ልትሆነኝ እንደ ቀድሞ
ልታከብረኝ ከማልክማ
ጮክ ብዬ እናገራለው ተናገሪ ካልከኝማ።
ሰማኝ ልጄ
የደም እንባ እያነባው
መከራዬን እነግረሀለው።
ብቻ ልጄ
ብቻ ልጄ
መከራ ህመሜን ሌላ መንደር
አትፈልገው
ጣቶችህን እያነሳህ በሌሎች ላይ
አትቀስረው።
ሳትገበዝ አንድ ጊዜ ቆም ብለሀ ራስህን
ደግመ እየው
ታሀድሶ ቅብጥርሶ መናፍቃን ጂኒ ጋኔል
የምትለው
አስር ጊዜ የገደልከኝ ያንተን በደል የት
ቀብረ ነው።

አንተ ነህ ያመምከኝ
አንተ ነህ ያመምከኝ
መስቀል የጨበትከው ወንጌል
የምትሰብከው
ቆመ የምትቀድሰው የምታስቀድሰው።
አንተነህ ያመምከኝ
ፍቅር ትሰብካለ ፍቅር የት ታውቃለህ
መዋደድ ሳይገባህ በጥቅስ ጋጋታ
ታደናግራለሁ።
አንተ ያልኖርከውን በሰው ትጮሀለሀ
አስር ጊዜ ሰብከ አስር ሚሊዮን አማኝ  
በአንዴ ትከስራለሀ።
አንተ ነህ የመምከኝ ሌላ ህመም የለኝ
የእግር እሳት ሆነ የምታቃጥለኝ ።
የመቅደስ ረመጥ የምትለበልበኝ
ከውጪ የመጣውማ ቀድሞስ መቼ ቻለኝ።
የዮዲትጉዲትን የግራኝ አህመድን
የግብፅን ደርቡሾች የግኖስቲኮችን።
ዘመነ ፔርጋሞን የሮማ ክፋትን
ያአርዮስ የአውጣኪ የእነ እንስጥርስን
ዘመን ተሻግሬ
ስገሉኝ ሰፍቼ ሲሰቅሉኝ በዝቼ
የኖርኩኝ ነኝ እኔ በአባቶችህ አጥንት በደም ተሰፍቼ
አንተነህ ያመመከኝ
አንተ ነህ ያመመከኝ ሌላ ህመም የለኝ
የመቅደስ ረመጥ የምትለበልበኝ
ስረዐቴን ያጠፋክ መፅሐፌን የበረዝክ
በአበው ታሪክ ቆመ ታሪክ የማትሰራ በዘመን የነፈስክ
ታቦቴን አርክሰ ጉሊት የቸረቸርክ።
አንተ ነህ ያመምከከኝ
አንተ ነህ ያመምከኝ
በተኩላ ያስበላክ በጎቼን ያልጠበክ
የሰቡትን አርደህ የተሰበሩትን በሜዳ የበተንክ
ክህነቴን በገንዘብ ቸርችረ ያረከስክ
ቀድሰህ የረከሰክ ሰብከም የረከስክ
ሺህ በደል በድለህ በሌሎች ያላከክ
አንተ ነህ ያመምከኝ
አንተ ነህ ያመምከኝ
ከሐይማኖት ይልቅ ዘርህን ያደመክ
በጎጥ ተደራጅተህ በመቅደስ የቀደስክ
ደሙን በእጅህ ይዘህ በዘውጌ ዛር ልክፍት የሰው ደም የፈለክ።
ወንጌሉን  እረግጠ በመንደር የዎረድክ
አንተነህ ያመምከኝ
አንተእኮ እህ
አንተእኮ የጉድ ነህ
ለሶስት አስርታት ቆራርጠሀ የጣልከኝ
እንደ ቅርጫ ስጋ ተካፍለህ የበላህኝ
ከሚሊዮን አማኝ ከተረፈው ካህን አንድ ሽማግሌ ወልደህ ያልሰጠህኝ
ፖለቲካው መቶ ፀቤን እስኪዳኘኝ
የተውከኝ እኮ ነህ
ታዲያ ይሄ አያምም
ላንተማ አያምም
ጭራሽ እልል እያልክ ታጨበጭባለህ
በእጅ ያለውን መስቀል ጉልበት ስታሳጠው ልጄ ሆይ ታማለህ ታሸማቅቃለህ
ተናገሪ!!! እህ
ተናገሪ!!!
ተናገሪ ካልከኝማ
ልታክመኝ ልታድነኝ ከቆምክማ
ጮክህ ብዬ እናገራለው
የደም እንባ እያነባው መከራዬ እነግርሀለው
አንተነህ ያመምከኝ
አንተነህ ያመምከኝ
በ40ቀን ተጠምቀ እዛው የቀረሀው
ጥበቤን ያልቀዳህ ወንጌል ያልሰማህው
70 አመት ሙሉ ወተት የምትጠጣ ጡጡህን ያልጣልከው
በአሳ ልብላ አልብላ ጥያቄ የቆምከው
አንተነህ ያመምከኝ ሌላ ህመም የለኝ
አንተነህ ያመምከኝ
የጥምቀት ቀን አማኝ የደመራ አገልጋይ
የይስሙላ መናኝ የድነት ቃላአባይ
አመንዝራ ትውልድ ታምራት ተከታይ
አንተነህ ያመምከኝ
ልብህን ያልሰጠሀ መጥተ ቤተመቅደስ
አሪቲ ቄጠማ ገዝተ ምትመለስ
ሲነዱ መነዳት ሲያፈሱህ የምትፈስ
ነጋዴ ቢያጠምቅ ግርርር
ወታደር ቢያጠምቅህ ግርርርር
የማትከራከር በቃሉ መዝነ
ቢሸጡ የምትሸጥ ፍፁም ግድ የሌለ
በሽታዬ አንተ ነህ
ልጄ ሆይ ታማለ


❗️ወስበሐት ለእግዚአብሔር❗️

💫🌟ኪነ-ጥበብ💫🌟

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

♻️ ስነጽሑፍ - ግጥም!
(
#እውነት_አለቀሰች!)
●●●●●●●●●●●●●●●
ልብ ያለህ አስተውል ጆሮ ያለህ ስማ
እግርህ እንዳይገባ ከክህደት ከተማ።
የያዝከውን አጽና ልብህ አይጨነቅ
ለጥያቄህ መልስም ሊቃውንትን ጠይቅ።

ለእውነት የቆመ ሃይማኖቱን የሚያውቅ
ንባብ ትርጓሜን ጠንቅቆ የሚዘልቅ
ተናገር ዩሐንስ አንተ ልሳነ ወርቅ።
ቄርሎስን ጠይቀው የተዋህዶን ምስጢር
የክርስቶስ ነገር እንዴት እንደነበር።
ከብሉይ ከሐዲስ በማቀነባበር
እንዳመሰጠረው በብዙ ምስክር።

ነቢዩ ኢሳያስ ብርሃነ ዓለም ጳውሎስ
መዝሙረኛው ዳዊት ሐዋርያው ሉቃስ
አባ ዝክረ ማርያም ወአባ ጴጥሮስ
የስነ ዘፍጥረት ሊቅ ኤጲፋኒዮስ
ዝም አትበል ተናገር ቅዱስ ሳዊሮስ
በሥጋው ማክበሩን አምላክ ክርስቶስ።

ጊዮርጊስ ተናገር አንተ የጥዋት ጮራ
ክርስቶስ መሲሕም ተብሎ እንደሚጠራ።
ወልድ ቅብዕ በማለት ክህደት አስተማሩ
የሥግው ቃል ነገር መች ገባቸው ዳሩ
የተዋሕዶ ምስጢር ሳይገባቸው ቅሉ
ሃይማኖት ከምስጢር ይደባልቃሉ።

ክርስቶስ በሥጋ እንደሞተ ሲያውቁ
በሥጋስ መክበሩን እንዴት አላወቁ
ሊቃውንት እያሉ ለምን አይጠይቁ
በተዋሕዶ ከበረ ብለው ሲናገሩ
ለዚህ ብሂላቸው የታል ምስክሩ።

ግብርን በማፋለስ አንድ ገጽ ካለው ከሰባልዮስ
አንድነትን ትቶ ሁለት አካል ካለው ከእርጉም ንስጥሮስ
መንፈስ ቅዱስ ሕጸፅ ካለው ከመቅዶንዮስ
ወልድ ፍጡር ካለው ከእርጉም ከአርዮስ
የዚህ ክህደቱ በምንም አያንስ።

ፈላጊዋ ጠፍቶ እውነት አለቀሰች
ግብራቸው ተቃርኖ ሀሰት ጥላት ሄደች።
ዳሩ ግን ወገኔ ይህ ክህደት ነውና
ቀኑ ሳይመሽብህ መንገድህን አቅና
እውነትን ከፈለክ ታገኛለህና
እረፍት ስላላት የህይወት ጎዳና
የያዝከውን ይዘህ በሃይማኖት ጽና።

❗️ወስብሐት ለእግዚአብሔር❗️

💫🌟ኪነ-ጥበብ💫🌟

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ህዳር 19/2016 #ቅዱስ_ገብርኤል

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በመልአኩ ስም ለምናመሰግንበት የመልአኩ #ቅዱስ_ገብርኤል ጥበቃና ተራዳኢነት እንዳይለየን ለምንማፀንበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉 #ገብርኤል ማለት ገብረ ኤል፣ የጌታ አገልጋይ፣ የእግዚአብሔር ሠራተኛ፣ ገብረ አምላክ፣ ገብረ እግዚአብሔር ማለት ነው

👉‘ገብረ’ እና ‘ኤል’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ የመልአክ ስም ነው #የእግዚአብሔር_ሰው ማለትም ነው

👉አብሳሪ መልአክ #ቅዱስ_ገብርኤል ሆይ እጅግ አፅናኝና አስደሳች የሆነውን ምስጢረ ሥጋዌን ዜና ይዘህ ከሰማይ ወደ ምድር እንደወረድክ #ድንግል_ማርያም የአምላክ እናት ለመሆን ፈቃድዋ ሆኖ በተፈጸመ ጊዜ ደስ እንዳለህ እኛም እግዚአብሔርን በማክበርና ግዴታችንን በመፈፀም ደስ የምንልበትን ጸጋ አሰጠን

👉ጠባቂያችን #ቅዱስ_ገብርኤል ሆይ ሦስቱን ወጣቶች ከሚያቃጥል እሳት እንዳዳንካቸው እኛንም በዚህ ዓለም ከሚወራው ከሚታየውና ከሚሰማው ክፉ ቀንና እለት ሁሉ አድነን እየነደደ የሚለበልበንን የኃጢያት እሳትም አጥፋልን

👉የኑሯችንን ቀጠሮ በክንፈ ረድኤትህ ከልለው ሰይጣን እንዳይሰለጥንብን ክፉ አድራጊዎች፣ ሟርተኞች፣ ሰላቢዎች ዘረኞችና ነፍሰ ገዳዮች እንዳያጠቁን ከልለን ያንተን የእሳት አጥር ዘሎ ጠላት ያጠቃን ዘንድ ጠላት አይችልምና #ጥበቃ ከእኛ ከባርያዎችህ አይለየን

👉 #ቅዱስ ገብርኤል ሆይ #ሕፃኑ_ቂርቆስና እናቱ #እየሉጣን በንፍር ውኃ ከመቀቀል እንዳዳንካቸው ልጆችህን በማናውቀው ሁኔታ የተዘጋጀልንን የጥፋት ወጥመድ ሁሉ አስወግድልን በላያችን ላይም በክፉ ሰዎች ምክንያት የተነሳብንን እሳት አጥፋልን

👉ለእውነተኛ ሃይማኖት የጨከንንና የቆረጥንም አድርገን የሰይጣንን ፈተና የምናልፍበት እውነተኛውን ጥበብ እንደ ነብዩ ዳንኤል አስተምረን

👉 #ቅዱስ_ገብርኤል ሆይ በደል በተገኘብኝ ቁጥር እያለቀስሁ እጠራሃለሁ ጎስቋላ የምሆን በጥቃትና በሀዘን ውስጥ የምገኝ ልጅህ የአንተን ማፅናናትና ረዳትነት ያሻኛልና ፈጥነህ ናልኝ

👉 #ቅድስት_ማርያምን ያበሰርክ ለዓለም ሁሉ የምታበራ ገብርኤል ሆይ በሰራዊት አምላክ ይዤሃለሁ በዚህች ሰዓት ፀሎቴንና ልመናዬን ስማ #ቅዱስ_ገብርኤል ሆይ ቀድመህ የደስታ የምሥራች ቃልህን ልታበስር ወደ ገሊላ እንደወረድህ ዛሬም ለአዘንን ለእኛ ከሠማይ በሠረገላ ናልን የደስታንም ቃል አሰማን

👉 #ቅድስት_ድንግል_ማርያምን ያበሰርክ ተወዳጁ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ በምህረትና በይቅርታ ወደ እኛ ናልን ዓለም የጥፋት የሞት የክስረት የውድመትና የተስፋ መቁረጥ ድምፅን ያሰማናልና አንተ ግን ጉስቁልናችንን የሚያነሳ ስብራታችንን የሚጠግን እንባችንን የሚያብስ የብስራት ድምፅህን አሰማን እንድንፅናናም አድርገን

👉እውነተኛ ጠባቂያችን #ቅዱስ_ገብርኤል ሆይ፤ እኛን ለማዳን ሰው የሆነውን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን ማደሪያው የሆነችው ድንግል ማርያምን በጣም እንወዳታለን በዚህ ዓለም የምሥጢረ ሥጋዌ ተካፋዮች በመሆናችን በመንግስተ ሰማያትም ተካፋዮች ለመሆን ሁላችንንም በምልጃህ አብቃን ለምንልን

👉 #የእግዚአብሔር መልአክ #ቅዱስ_ገብርኤል ጥበቃህ ተራዳኢነትህ አይለየን ለሀገራችን ሠላምን ለህዝባችን ፍቅር አንድነትን አድለን ርሃብ ጦርነትን ከምድራችን ላይ አስወግድልን በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የሚዉሉ ቅዱሣን የከበረዉ ቃል ኪዳናቸው ይጠብቀን "አሜን" 💒 💚 💛 ❤ 💒

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/m9xLpy9jmLM?si=30So1fHs5CRBt9nv

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

❗️በእጅ ያለ ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል።
♻️ዛሬ ቤተክርስቲያንን ልክ እንደ መዳብ እየተመለከቷት ያሉ ብዙ ሰዎች አሉ...ግዴለም እነዚህ ሰዎች በቁጭት የሚያለቅሱበት ጊዜ ሩቅ አደለም።
ወይኔ ያኔ ባገለገልኩ......ወይኔ ያኔ ቤተክርስቲያንን በጠበኩኝ.....እያሉ።
❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️
🌟💫ኪነ-ጥበብ🌟💫

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝️✝️✝️መነበብ ያለበት✝️✝️✝️

ዘፈን ጥበብ ነው?
ዘፈን ጥበብ ነው የሚሉ አሉ። አዎን ጥበብ ነው ከእግዚአብሔር
ሳይሆን ከሰይጣን የተገኘ ጥበብ ነው፤ ቅዱስ ሳይሆን ርኩስ
ጥበብ ነው፤ መዳኛ ሳይሆን መጥፊያ ጥበብ ነው፤ የህይወት
ሳይሆን የሞት ጥበብ ነው፡፡ ይህን ሳስብ ቅዱስ ጳውሎስ የዚች
ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ዘንድ ሞኝነት ነው ያለው ትዝ
አለኝ።
እግዚአብሔር ድምፅ የሰጠን እሱን እንድናመሰግንበት እሱን
እንድናወድሰው፣ እሱ የፈቀደላቸውን እሱ ያከበራቸውን ቅዱሳኑን
እንድናመሰግንበት ነው እንጂ ለሰው እንድንዘፍን አይደለም።
ወይ የእግዚአብሔር ወይም የዓለም ልንሆን ግድ ይለናል፤
ሁለት ጌታ የለም። ዘፈን መዝፈን ኃጢያት ነው። አሁን ባለንበት
ዘመን ዘፈን ኃጢያት እንደሆነ፤ የዲያቢሎስ ታላቅ መሳሪያ
እንደሆነ፤ ዘፋኝነት ከክርስቶስ ማህበር እንደሚለይ በግልጽ
እየተመለከትን ነው። ዘፈን ስራ ነው የሚሉ አሉ አዎን ለዘፋኝ
መዝፈን ስራው ነው፤ ለሌባም መስረቅ ስራው ነው፤ ለዝሙት
አዳሪዋም ዝሙት ስራዋ ነው፤ ለቅጥረኛ ነፍሰ ገዳይም መግደል
ስራው ነው ግን ደግሞ ኃጢያት ናቸው ስራዬ ነው ብሎ
ኃጢያትነቱን ማስቀረት አይቻልም፡፡ እንግዲህ ምን እንላለን
ኃጢያትን ስራ ነው ብለን ሙግት እንገጥማለንን??
እየመረጥን ብንዘፍንስ ለመልካም የተዘፈኑ ዘፈኖች አሉ
የሚሉም ብዙ ናቸው። ዘፈን ሀጥያት ነው በቃ ምንም ጥያቄና
መልስ የለውም ቴዲ ስለዘፈነው መዝሙር መሆን አይችልም
ስለ ሀገር ሆነ ስለምን.. ስለ ሀገር ጸልዩ እንጁ ዝፈኑ
አልተባለም፣ እናት ቢዘፈንላትስ ይላል ደሞ አንዱ፣ እድሜህ
እንዲረዝም እናትና አባትህን አክብር ይላል እንጂ ዝፈንላቸው
አይልም!! ብዙ ሰው ጥብቅና ለቆመለት ሰው ቃሉ ይህን ይላል
<< ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥
እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት
አይወርሱም!!።">>
(ወደ ገላትያ ሰዎች 5:21)
አንድ ሌባ ሰርቆ የተራበ ቢያበላ ጽድቅ ነውን??? የተቸገሩ
ሰዎችን ከችግራቸው ያላቅቅ ዘንድ አጥብቆ የሚተጋ አንድ ሰው
ሌሎችን ለመርዳት የሚያስፈልገውን ገንዘብ ለማግኘት ዝሙትን
መፈጸም ግድ ቢሆንበት እርሱም ሰውነቱን አርክሶ ዝሙትን
ፈጽሞ ገንዘቡን ቢቀበል ችግረኞቹንም ከችግራቸው ቢያላቅቅ
መልካም አደረገ እንለዋለንን??? ዘፈን ያስደስታል፣ ዘና
ያደርጋል፣ ደስታ ይፈጥራል ... ወዘተ ምክንያቶች እየደረደርን
ጥብቅና አንቁም! መልካምን ነገር ለማድረግ በኃጢያት ውስጥ
ማለፍ አይጠበቅብንም፤ ኃጢያትን ያደረገ ኃጢያተኛ እንጂ
ጻድቅ ሊባል አይችልም፡፡ ነገሩ ከዝንጀሮ ቆንጆ ምን ይመራርጡ
ነው እንዲያ ካልሆነማ፤ ከኃጢያት ከተመረጠማ ለዘፈን ብቻ
ለምን???
የዘፈነው ለመልካም ነው፤ ፍቅርን ለመስበክ ነው፤ አንድነትን
ለማምጣት ነው ካልን ሌባውም የሰረቀው የተቸገሩትን ሊያበላ
ነው፤ ሰውየውም ዝሙት የፈጸመው ችግረኞችን ለመርዳት ነው፣
ነፈሰ ገዳዩም እንጀራ ሆኖበት ነው። ስለዚህ እነዚህም አብረው
ይጽደቁ? እንዲህ ከሆነ ደግሞ ኃጢያተኛ ሁሉ ጻድቅ ሆነ ማለት
ነው። ራሳችንን ከማታለል እንውጣ፤ ከአዚም እንላቀቅ አትግደል
ከተባለ አትግደል ነው፤ አትስረቅም አትስረቅ ነው፤ አትዝፈን
ሲልም አትዝፈን ነው፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ተመራጭ
አገዳደል፤ ተቀባይነት ያለው ስርቆት፤ የሚወደድ ዘፈንም የለም፡፡
ይቆየን።


👇👇👇👇👇👇👇
@mahbere_kidane_mihret
❤️❤ለጓደኞጫቹ ሼር  አርጉላቸው❤️
@mahbere_kidane_mihret

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለዓለም ሁሉ መምሕር ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እና ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ለቤተ ክርስቲያን የብርሃን ምሰሶ ስለሆነላት ስለ ታላቁ ሐዋርያዊ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? እንደ እኔ ያለ ኃጥእ: ለባሴ ሥጋና ገባሬ ንስሃ ስለሱ ሊናገር አይቻለውምና:: አባቶቻችን እንደ ነገሩን ስለ አፈ ወርቅ ለመናገር አፈ ወርቅ መሆን ያስፈልጋል:: እስኪ በቅዱሱ አባት ምልጃ ጥቂት ልሞክር::

††† ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ማን ነው?

††† ነገዱ ከሶርያ: የተወለደው በ347 ዓ/ም በእስክንድርያ ሲሆን አባቱ አስፋኒዶስ እናቱ ደግሞ አትናስያ ይባላሉ:: እነርሱ ደግ ቢሆኑ ይህንን እንቁ ልጅ እግዚአብሔር ሰጣቸው:: ዮሐንስ ለክርስቲያን እንደሚገባ በትምሕርትና በጥበብ አደገ:: ገና በሕጻንነቱ ወደ ግሪክ ሔዶ የዘመኑን ሳይንስ (ፍልስፍና) ከአፉ እስከ ገደፉ ተምሮ ተመልሷል::

ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን ለየት ከሚያደርጉት ነገሮችም አንዱ ይሔው ነው:: በዘመናዊም ሆነ በመንፈሳዊ ትምሕርት ይህ ቀረህ የማይሉት ሊቅ የሆነው ገና በ15 ዓመቱ ነበር:: በ2 ወገን የተሳለ ሰይፍ በመሆኑ ስንኩዋን በሕይወተ ሥጋ እያለ ዛሬም ለ*****ን********ፉ********ቃን ትልቅ የራስ ምታት ነው::

ቅዱሱ ገና በ16 ዓመቱ ሃብት: ንብረት: ውበት: ክብርና እውቀት የሞላለት ቢሆንም ያለውን ሁሉ ለነዳያን ሰጥቶ መጻሕፍትን ብቻ ሰብስቦ ከባልንጀራው ቅዱስ ባስልዮስ ጋር በርሃ ገባ:: ሰውነቱን በጾምና በጸሎት እየቀጣ በበርሃ ሲኖር ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስና ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ወደ እርሱ መጡ:: ሊቀ ሐዋርያት የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ ስልጣን ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉን ሰጥተው ተሰወሩት::

ከዚህች እለት በሁዋላ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ባሕረ ምስጢራት ሆነ:: ብሉይ ከሐዲስ: ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ራዕየ ዮሐንስ ድረስ በአንድምታ ትርጉዋሜ ተነተናቸው:: በተለይ ሐዲስ ኪዳንን እየመላለሰ አመሰጠረው:: ቅዱስ ሕሊናው ሳይታክት: ንጹሕ እጆቹ ሳይዝሉ የጻፋቸው ድርሳናት: መልዕክታትና ትርጉዋሜያት ቢቆጠሩ አሥር ሺህ ሞሉ:: በእውነት ለዚህ አንክሮ ይገባል! የሚገርመው ይህን ሁሉ ሲሰራ እድሜው ገና ለጋ: ማዕርጉም ዲቁና ነበር::

ከዚህ በሁዋላ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ቅስና ተሹሞ በስብከተ ወንጌል ብዙ ቦታዎችን አዳረሰ:: በቅድስናው ወደውታልና የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት:: አፈ ወርቅ ሲናገርም ሆነ ሲያስተምር እንኩዋን የሚያወራ ኮሽ የሚል የለም:: ከጣዕመ ትምሕርቱ የተነሳ ሕዝቡ በተደሞ ይሰሙት ነበር:: ሲያስተምር ምድራዊው ሰው ይቅርና ልዑላኑ መላእክት ተሰብስበው ያደንቁት ነበር:: አንዴም እመቤታችን በሕዝብ መካከል አፈ ወርቅ ብላ ጠርታዋለች:: ለዛም ነው አፈ ወርቅ የሚባለው:: ቅዱሱ በሥልጣነ ቃሉ መልዐከ ሞትን ገስፆ 10 ዓመት አቁሞታል::

ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለሰው ፊት አያደላም:: በርሱ ዘንድ ንጉሥና ደሃ ነዳይ እኩል ነው:: ለሞት ያበቃውም ይሔው ነበር:: ምክንያቱም የወቅቱ ንግስት አውዶክስያ ያንዲት ድሃ መበለትን መሬት ቀምታ አልመልስም በማለቷ መክሮ አወገዛት:: እርሷ ግን ከኃጥአንና መ******ና*******ፍ************ቃን ጋር መክራ 2 ጊዜ አጋዘችው:: በተሰደደበት ሃገር ፍሬ አፍርቶ: አስተምሮና አሳምኖ በ407 ዓ/ም አርፏል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ሳይጠግቡት እንደናፈቁት በ60 ዓመቱ አጡት:: በወቅቱ ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ ተደረገ::

አንድ ቀን የዘመኑ ደግ ንጉሥ አርቃድዮስ ግብር አገባ:: (ግብዣ አዘጋጀ) በዚያች ሌሊት ደግሞ ቅዱሱ ሊቅ ታጥቆ ሲጸልይ ሳለ: አባ ማርዳሪ የሚባል ጻድቅ ደግሞ 12ቱ ሊቃነ መላእክት (እነ ቅዱስ ሚካኤል) ከሰማይ በግርማ ሲወርዱ ተመለከተ::

ደንግጦ "ወዴት ናችሁ ጌቶቼ" ቢላቸው "ቁስጥንጥንያ: ወደ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንሔዳለን:: እርሱ እመቤታችንን እንደሚያመሰግናት ጌታ ነግሮናልና" አሉት:: "እባካችሁ እኔም የአፈ ወርቅ ምስጋናው እንዲገለጥልኝ መርቁኝ" አላቸው:: ሊቃነ መላእክቱም መርቀውት ጐዳናቸውን ቀጠሉ::

በማግስቱ በቤተ መንግስት ውስጥ ሊቃውንቱ: መሳፍንቱ: ዻዻሳቱ: ሕዝቡ ሁሉ ተሰብስበው ከድግሱ በሉ:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ግን በመንበሩ ተቀምጦ ነበር እንጂ አልበላም:: ድግሱ ሲጠናቀቅ ንጉሡ አርቃድዮስ ሊቁን "ጥያቄ አለኝ" ብሎ በጉባኤ መካከል ጠየቀው::

"ምነው ወንጌላዊ ማቴዎስ 'ኢያዕመራ ዮሴፍ እስከ አመ ወለደት ወለደ ዘበኩራ - የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም' ማለቱ (ማቴ. 1:25) ስለ ምን ነው?" ቢለው ቅዱሱ ተነስቶ: በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ይተረጉምለት ጀመር::

"ድንግል ማርያም ንጹሕ ብርሌን ትመስላለች:: ብርሌ የተለያየ ቀለም ያለው ፈሳሽ ቢያስገቡበት ቀለሙ አብሮ ይቀያየራል:: እመቤታችንም ጌታን ጸንሳለችና ሕብረ መለኮቱ ሲለዋወጥ መልኩዋ አብሮ ሲለዋወጥ እያየ ዮሴፍ ይደነግጥ ነበር::

'እርሷ ማን ናት? በማሕጸኗ ያለውስ ማን ነው?' እያለ ይጨነቅ ነበር:: ጌታን ከወለደች በሁዋላ ግን አንድ ሕብረ መልክ ሆናለችና:: አስቀድሞ ማን እንደ ነበረች አላወቀም::

አሁን ግን እርሷም ወላዲተ አምላክ: ልጇም አምላክ ዘበአማን መሆኗን አወቀ ማለት ነው" እያለ ሲተረጉም ሰምተው ሁሉም ሲያደንቁ: በዚያ የነበረች ስዕለ አድኅኖ "አፈ ወርቅ! ልሳነ ወርቅ! አፈ በረከት!" ስትል ተናገረች::

ያን ጊዜ አርቃድዮስ የወርቅ ልሳን በሊቁና በስዕሏ ላይ አደረገ:: አፈ ወርቅ ግን ባጭር ታጥቆ "እሰግድ ለኪ! እሰግድ ለኪ! ወእዌድሰኪ . . ." ብሎ ዛሬ በተአምረ ማርያም የምናውቀውን ምስጋና ሰተት አድርጐ አደረሰላት:: ይህንን ምስጋናም ሊቃነ መላእክቱ ሰምተው እያደነቁ ወደ ሰማይ ወጥተዋል::

ሊቁ ባረፈ በ35 ዓመቱ በትንሹ ቴዎዶስዮስ ዘመን: በዚህ ቀን ሥጋው ፈልሷል:: ወደ ቁስጥንጥንያ ሲደርስም ከና****************ፍቆት የተነሳ ታላቅ ዝማሬና እንባ ተደርጉዋል:: አፈ ወርቅም ቀና ብሎ ሕዝቡን ባርኩዋል::

††† ቅዱሱ ሲጠራ እንዲሕ ነው:-
*ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
*አፈ በረከት
*አፈ መዐር (ማር)
*አፈ ሶከር (ስኩዋር)
*አፈ አፈው (ሽቱ)
*ልሳነ ወርቅ
*የዓለም ሁሉ መምሕር
*ርዕሰ ሊቃውንት
*ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ)
*ሐዲስ ዳንኤል
*ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው)
*መምሕር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ
*ጥዑመ ቃል - - -

††† ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ኢትዮጵያዊት †††

††† ቆራጧ እናታችን ቅድስት ወለተ ዼጥሮስ ለእኛ ለኢትዮዽያውያን የተዋሕዶ አማኞች ሞገሳችን ናት:: እጅግ የሚደነቅ መንፈሳዊ አርበኝነትን በካቶሊኮች ላይ አሳይታለችና::

ቅድስት ወለተ ዼጥሮስ የተወለደችው በ16ኛው መቶ ክ/ዘመን በምሥራቅ ኢትዮዽያ ዳውሮ አካባቢ ነው:: ወላጆቿ ባሕር አሰግድና ክርስቶስ ዕበያ ይባላሉ:: ክርስትናን በሚገባ አጥንታ አድጋ: በወላጆቿ ፈቃድ በሥርዓቱ ባል አገባች:: ግን ወዲያው አፄ ያዕቆብ ገደሉባት::

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

"ኪዳነ ምሕረት እናቴ" |
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ኪዳነ ምህረት እናቴ ምስጢረኛ ጓዳዬ
የጎደለኝን ታውቂያለሽ
ከአፌ ሳይወጣ ሳልነግርሽ (፪)
አዝ......
አልፏል መናኛው ኑሮ
ምልጃሽ ውኃውን ቀይሮ
መልካሙ ወይን ደረሰ
እንባዬ ባንቺ ታበሰ (፪)
አዝ.........
ልዘምር ልቁም ከፊትሽ
ልምጣ ልንበርከክ ለክብርሽ
ብርቅ ከሀገር ከቤቴ
ከቶ አልረሳሽም እናቴ (፪)
አዝ........
አልልም መቼ ነው ቀኑ
የኔ መጎብኛ ዘመኑ
እንደሚፈፀም አውቃለው
ሁሉን በጊዜው አያለው (፪)
አዝ........
የልቤን ችግር ላዋይሽ
ከስዕልሽ ፊት ቆሜ
እንባዬ ቀድሞ ዝም አልኩኝ
ሳልነግርሽ ስለምታውቂ (፪)

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
🔸🔺🔹🔹🔹🔺🔺🔸🔺🔹
/channel/mezmur_store
🔸🔺🔹🔹🔹🔺🔺🔸🔺🔹

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ህዳር 16/2016 #ቅድስት_ኪዳነ_ምህረት

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በምስጋና ከፍ ለምናደርግበት እናታችን #ኪዳነ_ምህረትን በቃል ኪዳኗ እንድትጠብቀን ለምንማፀንበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉 #ኪዳነምህረት ስንል የምህረት ቃል ኪዳን ማለት ነው በዚህ ውስጥም ምህረት አድራጊው ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ምህረት ተቀባይም መላው የአዳም ዘር ነው

👉 #እናታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም በምድራዊ ቆይታዋ ዘውትር ወደ #ክርስቶስ_መካነ_መቃብር_ጎለጎታ እየሔደች ትፀልይ ነበር ልጇ እና ወዳጇ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገችውን ልመናና ፀሎት ተመልክቶና ሰምቶ #የምህረት_ቃል_ኪዳንን ሰጣት

👉እንኳን የእናቱን ፀሎት እና ልመና ቀርቶ ዘውትር በሀጥያት የምንዘፈቀውን እኛን ክፉዎቹን የሚሰማ አምላክ ስለ አንቺ ስለ እናቴ ክብርና ፀጋ ስል ይኸው ቃሌ ብሎ #ቃል_ኪዳን አደረገ

👉"ከመረጥሁት ጋር #ቃል_ኪዳኔን አደረግሁ" መዝ፣89፦3

👉ስሟን ለሚጠሩ በእርሷ አማላጅነት ለሚታመኑ በምድር በረከትን በሰማይ የዘለዓለም መንግስትን እንደሚወርሱ የምህረት እና የቸርነት #ቃል_ኪዳን ሰጥቷታል

👉በታላቁም መፅሐፍ ቀስቲቱም በደመና ትሆናለች በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘላለም #ቃል_ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ ኦሪት ዘፍ፣9፣16

👉በዚህም መሠረት #ቃል_ኪዳኗን ምክንያት በማድረግ #ኪዳነ_ምህረት እያልን እንጠራታለን የከበረዉ ቃል ኪዳኗ ሀገራችንን ህዝባችንን ይጠብቅልን የአባቶቻችን የነብያት ፀሎት ለሁላችንም ይድረሰን የተባረከ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" 💒 💚 💛 ❤💒

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ እንኩዋን ለቅዱሳን "አኖሬዎስ ንጉሥ" : "አባ ዳንኤል" : "ቅድስት ጣጡስ" : "ወአባ አቡናፍር" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+"+ ቅዱስ አኖሬዎስ ወአባ ዳንኤል +"+

=>አኖሬዎስ የሚለው ስም በቤተ ክርስቲያን እጅግ ተወዳጅ ነው:: በሃገራችንና በሌሎች አብያተ ክርስቲያናትም ብዙ ቅዱሳን በዚህ ስም ተጠርተዋል:: ቅድሚያውን ግን ቅዱሱ ንጉሥ አኖሬዎስ ይወስዳል::

+ቅዱስ አኖሬዎስ ተወልዶ ያደገው በሮም ከተማ ሲሆን የደጉ ንጉሥ ዐቢይ ቴዎዶስዮስና የመርኬዛ ልጅ ነው:: ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ሙሽራው እና ደጉ አርቃዴዎስ ወንድሞቹ: ጻድቁ አቡነ ኪሮስ ደግሞ አጐቱ ናቸው:: በልጅነቱ ክርስትናን የተማረው ከታላቁ ቅዱስ አርሳኒ ነው::

+ምንም በቤተ መንግስት ውስጥ ቢያድግም ቅዱስ አርሳኒ እንደ ተራ ሰው እየገረፈና እየቀጣ አሳድጐታል:: ቴዎዶስዮስ ቄሣር (አባቱ) ባረፈ ጊዜ የሮም ግዛትን በስምምነት ከወንድሙ አርቃዴዎስ ጋር ተካፈሉ:: በ390ዎቹ አካባቢም አኖሬዎስ በሮም: አርቃዴዎስ በቁስጥንጥንያ ነገሡ::

+ቅዱስ አኖሬዎስ ይሕንን ዓለም አልፈለገውምና ወደ ገዳም ልኮ አንድ ባሕታዊ (አባ አውሎጊስ ይባላል) አስመጥቶ ሥርዓተ ምንኩስናን ፈጸመ:: አክሊለ ሦኩንም በወርቅ ዘውዱ ውስጥ አደረገው::

+ልብሰ ምንኩስናውን በሰንሰለት በውስጥ አሥሮ በላዩ ላይ የመንግስቱን ካባ ደረበ:: ቀን ቀን እንደ ንጉሠ ነገሥት ሲፈርድ: ሲተች: የተበደለ ሲያስክስ: የተቀማ ሲያስመልስ ይውል ነበር::

+ሌሊት ደግሞ ባጭር ታጥቆ ሲወድቅ ሲነሳ: ሲጸልይ ሲሰግድ: ያለ ዕረፍት ያድራል:: መቼም ቢሆን ከደረቅ ቂጣ: ከጨውና ከጥሬ ጐመን በቀር ሌላ ምግብን አይቀምስም:: ይኸውንም ጾሞ ውሎ ማታ ብቻ ይመገብ ነበር::

+ይሕንንም ሲያደርግ ሰሌን ሰፍቶ: ያንን አሽጦ እንጂ በሌሎች ገንዘብ አልነበረም:: ሰዎች እንዳይጠረጥሩትም "በእልፍኙ ውስጥ ሚስት አለችው" እያለ ያስወራ ነበር:: በዚያ ላይ መልኩ ያማረ ስለ ነበር በዚህ የጠረጠረው የለም:: በዚህ መንገድ ከአባ አውሎጊስና ከደቀ መዝሙሩ ጋር ሆኖ ለ40 ዓመታት ተጋደለ::

+"+ አባ ዳንኤል ገዳማዊ +"+

=>በ4ኛው ክ/ዘመን መጨረሻና በ5ኛው መጀመሪያ በግብጽ ውስጥ ከነበሩ ከዋክብት አንዱ ሲሆን መንኖ ገዳም ከገባባት ቀን ጀምሮ በፍጹም ተጸምዶ: ከእህል ተከልክሎ: ቅጠል እየበላ ለ40 ዓመታት ተጋደለ:: አንድ ቀን ግን ተፈተነ:: በትዕቢት "ከእኔ የሚበልጥ ማን አለ?" ሲል በማሰቡ ፈጣሪ መልአኩን ልኮ ገሰጸው::

+ቀጥሎም "ሒድና ንጉሡን አኖሬዎስን እየው:: እሱ ንጉሥ ቢሆንም በቅድስና ይተካከልሃል" አለው:: አባ ዳንኤልም በደመና ወደ ሮም ሒዶ ቅዱሱን ንጉሥ ተገናኘው:: ቅድስናውን ዐይቶም ለቅዱስ አኖሬዎስ ሰገደለት:: እያለቀሰም ወደ በዓቱ ተመለሰ::

+ቅዱስ አኖሬዎስ ግን ከመምሕሩ ቅዱስ አውሎጊስና ከደቀ መዝሙሩ ጋር መንግስቱን ትቶ: ጠፍቶ: በርሃ ገብቶ ከአባ ዳንኤል ጋር ተቀመጠ:: ከተጋድሎ በሁዋላም 4ቱም ቅዱሳን በዚህች ቀን ዐርፈዋል::

+"+ ቅድስት ጣጡስ ሰማዕት +"+

=>በቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደዚህች ቅድስት ወጣት መልከ መልካም አልነበረም ይባላል:: ቅድስት ጣጡስ በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን (በዘመነ ሰማዕታት) የነበረች ሮማዊት ክርስቲያን ስትሆን መልኩዋን ያየ ሁሉ ይደነቅ: ይደነግጥም ነበር::

+እርሷ ግን ለወንድሞቿ እንቅፋት እንዳትሆን በፊቷ ላይ ዐይነ ርግብ ጣል አድርጋና እንደ ነገሩ ለብሳ ትኖር ነበር:: (እንዲህ ነበሩ እናቶቻችን!!!) ታዲያ በዘመኑ እስክንድሮስ የሚባል አረማዊ "ለጣዖት ስገዱ" እያለ ክርስቲያኖችን ሲገድል የእርሷ ተራ ደረሰ::

+በዐውደ ስምዕ (በምስክርነት አደባባይ) ላይ አቁሟት "ፊቷን ግለጡልኝ" አለ:: ቢገልጧት ከመልኩዋ ማማር የተነሳ ፈዘዘ:: እጅግ በመፍጠንም "ላግባሽ?" አላት:: "ሙሽርነቴ ሰማያዊ ነውና አይሆንም!" አለችው:: ለመናት: አልሰማችውም:: አስፈራራት: አልደነገጠችም::

+ከዚያ ግን ገላዋን አስገረፈ:: ከአካሏም ስለ ደም ፈንታ ወተት ፈሰሰ:: ተበሳጭቶ ለአራዊት ጣላት:: እነሱ ግን ሰገዱላት:: በእሳትም ፈተናት:: እርሷ ሁሉንም ታግሣ ጸናች:: በመጨረሻው ግን በዚህች ቀን አስገደላት:: ፈጣሪዋ ክርስቶስም በሰማያዊ አክሊል ከለላት::

+"+ ቅዱስ አቡናፍር ገዳማዊ +"+

=>ጻድቁ ተወልዶ ያደገው በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብፅ ነው:: ወቅቱ ሥርዓተ መነኮሳት የሚጠበቅበት: አበው ባሕታውያን እንደ ሰማይ ከዋክብት በዝተው የደመቁበት ነበር::

+ታላቁ አቡናፍርም ከክርስቲያን ወላጆቹ ተወልዶ: በሥርዓት አድጎ: መጻሕፍትንም ተምሮ ገና በወጣትነቱ መንኗል:: ሥርዓተ መነኮሳትን ከአባ ኤስድሮስ ታላቁ አጥንቶ ገዳሙንና መምሕሩን እየረዳ ለብዙ ዓመታት በጾምና በጸሎት ኑሯል::

+መነኮሳቱ ስለ ትሕትናውና ስለ ታዛዥነቱ ፈጽመው ያከብሩት ነበር:: ከዕለታት በአንዱ ቀን አረጋውያን መነኮሳት ጭው ባለ በርሃ ስለሚኖሩ ባሕታውያን ሲጨዋወቱ: ሲያደንቁዋቸውም ሰማ::

+እርሱ በዛ ወቅት ባሕታውያን በበርሃ መኖራቸውን አያውቅም ነበርና ሒዶ መምሕሩን አባ ኤስድሮስን ጠየቃቸው:: እርሳቸውም "አዎ ልጄ! ከዚሕ በጣም ርቅው: ንጽሕናቸውን ጠብቀው: ከሰውና ከኃጢአት ተይለው የሚኖሩ ገዳማውያን አሉ" አሉት::

+ቅዱስ አቡናፍር "በዚሕ ካሉት መነኮሳትና በበርሃ ካሉት ማን ይበልጣል?" ቢላቸው "እነርሱ በጣም ይበልጣሉ:: ዓለም እንኩዋ ከነ ክብሯ የእግራቸውን ሰኮና አታህልም" አሉት:: ይሕንን የሰማው ቅዱስ አባ አቡናፍር ጊዜ አላጠፋም: ከመምሕሩ ቡራኬ ተቀብሎ ወደ በርሃ ሔደ:: ለብዙ ቀናት ከተጉዋዘ በሁዋላ አንድ ባሕታዊ አግኝቶ አብሯቸው ተቀመጠ:: ከእርሳቸው ዘንድም ሥርዓተ ባሕታውያንን ተምሮ እንደገና ወደ ዋናው በርሃ ጉዞውን ቀጠለ::

+ከብዙ ቀናት መንገድ በሁዋላም አንድ ሠፊ ሜዳ ላይ ደረሰ:: አካባቢው የውሃ ጠብታ የማይገኝበት: ይቅርና መጠለያ ዛፍ የሣር ዘር እንኩዋ የሌለበት ወይም በልሳነ አበው "ዋዕየ ፀሐይ የጸናበት: ልምላሜ ሣዕር የሌለበት: ነቅዐ ማይ የማይገኝበት" ቦታ ነበር:: በዚህ ቦታ ይቅርና የሰው ልጅ አራዊትም አይኖሩበትም::

+ለአባ አቡናፍር ግን ተመራጭ ቦታ ነበር:: ቅዱሳኑን ይሕ አያሳስባቸውም:: ምክንያቱም ለእነርሱ ምግባቸውም: ልብሳቸውም ፍቅረ ክርስቶስ ነውና::

+አባ አቡናፍር ወደ ፈጣሪ ጸለዩ:: በእግዚአብሔር ቸርነት ከጎናቸው አንዲት ዘንባባ (በቀልት) በቀለች:: ከእግራቸው ሥርም ጽሩይ ማይ (ንጹሕ ምንጭ) ፈለቀች::

+ጻድቁ ተጋድሏቸውን ቀጠሉ:: ዓመታት አለፉ:: ልብሳቸውን ፀሐይና ብርድ ጨርሶት ቅጠል ለበሱ:: በዚያ ቦታም የሰው ዘርን ሳያዩ ለ60 ዓመታት በተጋድሎ ኖሩ:: የሚያርፉበት ጊዜ ሲደርስ እግዚአብሔር አባ በፍኑትዮስን (የባሕታውያንን ዜና የጻፈ አባት ነው) ላከላቸው::

+ቃለ እግዚአብሔርን እየተጨዋወቱ ሳለ የአባ አቡናፍር አካሉ ተለወጠ:: እንደ እሳትም ነደደ:: አባ በፍኑትዮስም ደነገጠ:: ታላቁ ገዳማዊ ግን እጆቻቸውን ዘርግተው ጸለዩ: ሰገዱና አማተቡ:: ነፍሳቸውም ከሥጋቸው በፍቅር ተለየች:: ቅዱሳን መላዕክትም በዝማሬና በማኅሌት አሳረጉዋት:: የሚገርመው ደግሞ አባ በፍኑትዮስ ይሕን ሲያይ ቆይቶ ዘወር ቢል ዛፏ ወድቃለች: ምንጯም ደርቃለች::

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●
🌟ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ
❗️ማቴ. 26፥41❗️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

❤ ኅዳር ➋⓵ ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ።

“#ጽዮን” ማለት “#ጸወን – #አምባ – #መጠጊያ” ማለት ነው:: አንድም በምሥጢሩ “#ማሕደረ_አምላክ” ማለት ነው:: ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን #ለድንግል_ማርያም: ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል::

ይህን በዓል በተለየ መልኩ የምናከብርበት ምክንያት የተወሰኑት

✨በብሉይ ኪዳን ታቦተ ጽዮን የፈጸመችውን ልዩ ልዩ ገቢረ ተአምራትን ለማሰብ

✨ቀዳማዊ ምኒልክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል የበኲር ልጆች ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛርያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበት ዕለት በመሆኑ

✨በሦስት መቶ ሠላሳ ዓመተ ምሕረት በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመነ መንግሥት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ይሁን ተብሎ ዐዋጅ የታወጀበት

✨ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ምሳሌ ራእይ ያየበት

✨ነቢዩ ሕዝቅኤል በተቆለፈች ቤተ መቅደስ

✨ዕዝራ በቅድስት ሀገር ምሳሌ ራእይ ያየበት

✨አብርሃና አጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተመቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያናትን ስታቃጥል ታቦተ ጸዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሐይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል እናከብራለን፡፡

“ #እግዚአብሔር_ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ።ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ።አሮጊቶችዋን እጅግ እባርካለሁ፥ ድሆችዋንም እንጀራ አጠግባለሁ።ካህናቶችዋንም ደኅንነትን አለብሳቸዋለሁ፥ ቅዱሳኖችዋም እጅግ ደስ ይላቸዋል።”
#መዝ 131:13

የወላዲተ አምላክ አማላጅነት የቅዱሳን ተራዳኢነት ከእኛ አይለየን፡፡

ወስብሐት #ለእግዚአብሔር ፡፡
ወለወላዲቱ #ድንግል፡፡
ወለመስቀሉ #ክቡር፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

💠"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠   
/(ማቴ ፫:፫/)
+"+ ✝ቅዱስ ዮሐንስ ዘአስዩጥ✝ +"+

=>በ4ኛውና በ5ኛው መቶ ክ/ዘመናት ከተነሱ ከዋክብት ጻድቃን አንዱ ነው:: እድሜው በጣም ረዥም በመሆኑ የብዙ ቅዱሳን ባልንጀራም ነበር:: በገድል አካሉን ቀጥቅጦ: በስብከትም የአስዩጥን (አሲዩትን) ምዕመናን አንጾ: ብዙ ተአምራትንም ሠርቶ በተወለደ በ125 ዓመቱ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ በዚህች ቀን ዐርፏል::

=>አምላከ ቅዱሳን የአማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያምን ጣዕሟን ፍቅሯን: ጸጋ በረከቷን ያሳድርብን:: ከአበው በረከትም አይለየን::

=>ኅዳር 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ጽዮን ድንግል ማርያም
2.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘሮሜ
3.ቅዱስ ዮሐንስ ዘአስዩጥ
4.ቅዱስ ቆዝሞስ ሊቀ ዻዻሳት
5.ቅድስት ዲቦራ ዘድልበት
6.ቅዱስ ዘኬዎስ ሐጺር

=>ወርኀዊ በዓላት
1.አበው ጎርጎርዮሳት
2.አቡነ ምዕመነ ድንግል
3.አቡነ አምደ ሥላሴ
4.አባ አሮን ሶርያዊ
5.አባ መርትያኖስ ጻድቅ

=>++"++ ለአንቺም የማይገዛ ሕዝብና መንግስት ይጠፋል:: እነዚያ አሕዛብም ፈጽመው ይጠፋሉ . . . የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ:: የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ:: የእግዚአብሔርም ከተማ: የእሥራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል:: ++"++ (ኢሳ. 60:12)

   <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
       አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
/channel/zikirekdusn

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ውድ ተከታታዮቻችን ሰብስክራይብ አድርገው በመግባት ስለ ሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ትክክለኛ እና ታማኒ መረጃ ያግኙ።
gyon_tube?si=lKI-ejbXEwu23lnW" rel="nofollow">https://youtube.com/@gyon_tube?si=lKI-ejbXEwu23lnW

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
     ሥርዓተ ማህሌት ዘህዳር ጽዮን
   🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር  ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል፡፡
  👉@menkir_tube
   👉@menkir_tube
ዚቅ
ሃሌ ሉያ ለአብ፣ ሃሌ ሉያ ለወልድ፣ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ፤ዕዝራኒ ርእያ ለጽዮን ቅድስት፤ እንዘ ትበኪ ከመ ብእሲት፡፡
👉@menkir_tube

ዘጣዕሙ ፦
ሰላም  ለዝክር ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ ፤ለወልድኪ አምሳለ  ደሙ ፤መሠረት ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኀኒት ዘእም ቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡

👉@menkir_tube
ዚቅ
ዘዘካርያስ ተቅዋም  ዘወርቅ፤ዘሕዝቅኤል  ነቢይ ዕፁት  ምሥራቅ ለመሠረትኪ  የኃቱ  ዕንቈ ሰአሊ ለነ ማርያም በአሚን ንጽደቅ፡፡
👉@menkir_tube
    ነግስ፦
ነቢያተ እሥራኤል ጸሐፉ በመጽሐፎሙ እሙነ፤ ነገረ ሰቆቃው ወላህ በዘመኖሙ ዘኮነ፤ ውስተ አፍላጋ አመ በጼዋዌ ነበርነ፤ውስተ ኵሃቲሃ እንዚራቲነ ሰቀልነ ፤ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን እምነ፡፡

👉@menkir_tube
ዚቅ
ወይቤላ ኢትሬእዪኑ ላሃ ዚአነ፤
እንተ ረከበተነ በእንተ ጽዮን፤
ዕዝራኒ ርእያ ወተናገራ

ወረብ፦
ወይቤላ ኢትሬእዪኑ ላሃ ዚአነ  እንተ ረከበተነ/2/
ዕዝራኒ ርእያ ወተናገራ/2/
👉@menkir_tube

  ማኅሌተ ጽጌ
ዘካርያስ ርእየ ለወርኃ ሳባጥ በሠርቁ፤ ተአምረኪ ለዘይት ማእከለ ክልኤ አዕጹቁ፤ማርያም ጽዮን ለብርሃን ተቅዋመ ወርቁ፤ ዕዝራኒ በገዳም አመ ወዓለ ዉዱቁ፤ለኅበረ ገጽኪ ጽጌ  ሐተወ መብረቁ፡፡
  👉@menkir_tube
   ዚቅ፦
ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፯ቱ መኃትዊሃ፤ ወ፯ቱ መሣውር  ዘዲቤሃ፤ ዘካርያስ ርእየ ተቅዋመ ማኅቶት፤ ዘኩለንታሃ ወርቅ  ወያክንት፤ዕዝራኒ ርእያ ለጽዮን ቅድስት እንዘ ትበኪ ከመ ብእሲት
 
👉@menkir_tube
ወረብ፦
ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን ፯ቱ መኃትዊሃ/2/
ዕዝራኒ ርእያ በርእየት ብእሲት/2/
  👉@menkir_tube
  👉@menkir_tube
ዚቅ(ዘበአታ)
ዕዝራኒ ርእያ በርእየተ ብእሲት፤ ወሶበ ርእያ ኢኮነት  ብእሲት አላ ሀገር ቅድስት ፤ርእየ ተቅዋመ ማኅቶት ዘኲለንታሃ ወርቅ ወያክንት
👉@menkir_tube
    መልክዓ ማርያም 
ሰላም ሰላም ለዝክረ  ስምኪ ሐዋዝ፤ እምነ  ከልበኒ  ወቍስጥ  ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ፤ ማርያም ድንግል  ለባሲተ ዐቢይ ትዕዛዝ፤ይስቅየኒ ለለጽባሑ  ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ፤ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ  ለሠናይ አርዝ፡፡

👉@menkir_tube
ዚቅ
ሃሌ ሉያ X3 እምነ ጽዮን በሀ፤
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥርጉት በስብሐት፤ዓረፋቲሃ ዘመረግድ ሥርጉት በስብሐት፤ ወማኅፈዲሃ  ዘቢረሌ  ሥርጉት በስብሐት፤ እምስነ ገድሎሙ ለሰማዕት ሥርጉት በስብሐት፤ታቦተ ሕጉ  ለንጉሥ ዐቢይ ሥርጉት በስብሐት፤
እንተ ክርስቶስ መሠረትኪ ፤ ፀሐየ ጽድቅ ያበርህ ለኪ፡፡

👉@menkir_tube
ወረብ
እንተ ክርስቶስ መሠረትኪ ፀሐየ ጽድቅ ያበርህ ለኪ ፀሐየ ጽድቅ/2/
ለሰማዕትሥርጉት በስብሐት ሥርጉት በስብሐት/2/

👉@menkir_tube

መልክዓ ማርያም፦
👉@menkir_tube
ሰላም ለአስናንኪ ሐሊበ ዕጐልት ዘተዛወጋ፤ ወመራዕየ ቅሩፃት  እለ እምሕፃብ ዐርጋ፤ ማርያም ድንግል  ለደብተራ  ስምዕ  ታቦተ  ሕጋ ፤
አፍቅርኒ  እንበለ  ንትጋ ለብእሴ  ደም ወሥጋ፤ ዘየዐቢ  እምዝ ኢየኃሥሥ ጸጋ፡፡
   
👉@menkir_tube
  ዚቅ
ታቦተ ሕጉ ለእግዚአብሔር በካህናት  ሕጽርት፤ ወበመንፈስ ቅዱስ ክልልት፤ንጉሥኪ  ጽዮን ኢይትመዋዕ በፀር ወኢየኀድጋ ለሀገር፡፡

👉@menkir_tube
   ወረብ
ታቦተ ሕጉ ለእግዚአብሔር  በካህናት ሕጽርት ወበመንፈስ ቅዱስ ክልልት/2/
ንጉሥኪ ጽዮን ኢይትመዋዕ በፀር ወኢየኀድጋ ለሀገር/2/

👉 @menkir_tube
   መልክዓ ማርያም፦
ሰላም ለከርሥኪ ዘአፈድፈደ ተበጽዖ፤እም ታቦተሙሴ ነቢይ ለጽሌ ትእዛዝ ዘየኀብኦ፤ማርያም ድንግል ጊዜ ጸዋዕኩኪ  በአስተብቍዖ፤ ለፀርየ ብእሴ አመጻ ኀይለ  ዚአኪ  ይጽበኦ፤እስከነ  ያሰቆቁ ጥቀድኅሪተ ገቢኦ፡፡

👉 @menkir_tube
ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ በጾም ወበጸሎት፤
ተመጠወ  ሙሴ ኦሪተ፤ ጽላተ አሥሮነ ቃላተ፡፡
👉 @menkir_tube

ወረብ
ሃሌ ሃሌ ሉያ በጾም ወበጸሎት፤
ተመጠወ ሙሴ ኦሪተ ጽላተ አሥሮነ ቃላተ፡፡

👉 @menkir_tube
  መልክዓ ማርያም፦
👉 @menkir_tube
ሰላም ለመከየድኪ እለ ረከቦን መከራ፤እምፍርሃተ ቀተልት ሐራ እንበለ አሣእን አመ ሖራ፤ማርያም ጽዮን ታቦተ ቃለ ጽድቅ መንፈቃ ዕሥራ፤ ዕጐላት እም ዕጐሊሆን ከመ ኪያኪ አፍቀራ፤ አፍቀርኩኪ አፍቅርኒ እም ይእዜ ለግሞራ።
👉 @menkir_tube

  ዚቅ
ሃሌ ሉያ ወሪድየ ብሔረ ሮሜ፤
ለቤተ ክርስቲያን ርኢክዋ፤አእመርክዋ አፍቀርክዋ፤ከመ እኅትየ  ኀለይኩ፤እም ድኅረ ጉንዱይ መዋዕል፤
ወእምዝ እም ድኅረ ኅዳጥ ዓመታት፤ካዕበ ርኢክዋ ወትትሐፀብ በፈለገ ጤግሮስ ፡፡
👉 @menkir_tube

ወረብ
ሃሌ ሉያ ወሪድየ ብሔረ ሮሜ/2/
ለቤተ ክርስቲያን ርኢክዋ አእመርክዋ አፍቀርክዋ ለቤተ ክርስቲያን/2/

👉 @menkir_tube
   መልክዓ ማርያም፦
👉 @menkir_tube
በዝንቱ ቃለ ማኅሌት ወበዝንቱ ይባቤ፤ለዘይስእለኪ ብእሲ ጊዜ ረከቦ ምንዳቤ፤ብጽሒ ፍጡነ ትሰጠዊዮ ዘይቤ፤ማርያም ዕንቍየ ክርስቲሎቤ ወምዕዝተ ምግባር እምከርቤ፤
ዘጸገየ ማኅጸንኪ አፈወ ነባቤ፡፡

👉 @menkir_tube
ዚቅ
አብርሂ አብርሂ  ጽዮን፤ ዕንቍ ዘጳዝዮን፤
ዘኃረየኪ ሰሎሞን፡፡
👉 @menkir_tube

ወረብ
አብርሂ አብርሂ ጽዮን/2/
ዕንቍ ዘጳዝዮን ዘኃረየኪ ሰሎሞን ንጉስ/2/
👉 @menkir_tube

  ምልጣን 
ዓይ ይእቲ ዛቲ እንተ ታስተርኢ እምርሑቅ፤ ከመ ማኅቶት ብርህት ከመ ፀሐይ፤ ሙሴኒ ርእያ ሀገር ቅድስት ዕዝራኒ ተናገራ ዳዊት ዘመራ፡፡
👉 @menkir_tube
አመላለስ፦
ዕዝራኒ ተናገራ /2/
ተናገራ ዳዊት  ዘመራ/4/

👉 @menkir_tube
ወረብ ዘምልጣን
ሙሴኒ ርእያ ሀገር ቅድስት፤
ዕዝራኒ ተናገራ ተናገራ ዘመራ ዳዊት

👉 @menkir_tube
እስመ ለዓለም
ዘካርያስ ርእየ ተቅዋመ ማኅቶት፤ኩለንታሃ ወርቅ በየማና ወበጸጋማ አዕጹቀ ዘይት ፤ደብተራ ፍጽምት ሀገር ቅድስት፤ ነቢያት ይትፌሥሑ በውስቴታ፤ ሐዋርያት ይትኃሠዩ በውስቴታ፤ ወዳዊት ይዜምር በውስተ ማኅፈዲሃ፤ ዘበሰማይኒ ወዘበምድርኒ በቃለ ዳዊት ይሴብሑ፤ወይብሉ ኵሎሙ ሃሌ ሉያ፡፡

👉 @menkir_tube
   አመላለስ፦
ዘበሰማይኒ ወዘበምድርኒ በቃለ ዳዊት ይሴብሑ/2/
ወይብሉ ኵሎሙ ሃሌ ሉያ(4)።

👉 @menkir_tube
   ወረብ
ዘካርያስ ርእየ ተቅዋመ ማኅቶት ኩለንታሃ ወርቅ በየማና ወበጸጋማ አዕጹቀ ዘይት፤
ነቢያት ይትፌስሑ ሐዋርያት ይትሐሰዩ በውስቴታ ወዳዊት ይዜምር በውስተ ማኅፈዲሃ፡፡

👉 @menkir_tube
     ሰላም
ዘካርያስ ርእየ ተቅዋመ ማኅቶት፤ገነተ ትፍስሕት መካነ ዕረፍት፤ እንተ ይእቲ ማኅደር ለካህናት፤ ለእለ የኃድሩ በፈሪሃ እግዚአብሔር፤ ይእቲኬ ቤተ ክርስቲያን፤በውስቴታ የዓርጉ ስብሐተ ካህናት በብዙኅ ትፍስሕት ወሰላም፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የዛሬውን ethio 360 ምን አለ ፕሮግራም ይከታተሉ!
https://www.youtube.com/live/TG2aONhb2ZU?si=RWe_6I89l_J8JLjp

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://www.youtube.com/live/7iUmlNmZ5Qs?si=mTDPuYj-XpMBVuvQ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በተራሮች መሀል በስምጥ ሸለቆው ውስጥ የተገደመ
አስደማሚው የአቡነ አባለ ክርስቶስ ገዳም ፦

ኢትዮጰያዊ ፃድቅ አባለ ክርስቶስ ከአባታቸው ከቅዱስ አቃሪዮስ ከእናታቸው ከቅድስት ታውክልያ በ8ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በየካቲት 19 /810 ዓም በአክሱም ከተማ ተወለዱ።

ገና በእናቱ ማዕፀን ሳለ በክርስቶስ የተመረጠ ፃድቅ ልክ ሲወለዱ በሰውነታቸው ላይ ዲካባ፤ማርቲያስ፤ ክስብኤል የሚባሉ ህቡህ የስላሴ ስሞች ተፅፎባቸው ተገኝቶባቸዋል።

ከሰው ተወልዶ ከመላዕክት የተደመረው ክቡር አባታችን አቡነ አባለ ክርስቶስ ምንኩስናን ከአቡነ ጰንጤሌዎን በ32 ዓመታቸው ተቀብለዋል በብዙ ተጋድሎ በፆምና በፀሎት ብዙ ተአምራትንም በገዳማቸው አድርገዋል።

ገዳማቸው ከአክሱም ወደ ማህበረ ፃድቃን ዶጌ 17 ኪሎ ሜትር ተጉዘው ከሄዱ በኃላ እንደገና ወደ ግራ በመገንጠል 25 ኪሎ ሜትር በመሄድ ጠላዕ የተባለች የገጠር ከተማ ይደርሳሉ።

ከብዙ አሰልቺና ሰማይ አድርሶ ምድር የሚመልስ ኮረኮቻማ መንገድ በመኪና ደርሰው ፈፅሞ ገዳም አይደለም ሰው ይኖራል ወይ ወደሚያስብል ተራራማ መንገዶች ይሄዳሉ።

በርካታ ተራሮችን ለመሻገር በተራሮች ወገብ ላይ በተሰራ መንገድ እንደ እሳት የሚፋጅ ጭው ያለ በርሃ አስገራሚ መልካ ምድር እየተመለከቱ ወደ ስምጡ ሸለቆ ይነጉዳሉ።

ያለ መሪ ገዳሙ መድረስ እጅግ በጣም ከባድ ነው ቅዱሳን ቦታ አመራረጣቸው የሚደንቅ ነው እንኳን ለሰው ለአራዊት እንኳን በማይመች ቦታ ገዳማቸውን ይገድማሉ ከብዙ ውጣ ውረድ ከድካምና እልህ አስጨራሽ ጉዞ በኃላ ከአዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ የረገጥኩኝ ባለ ታሪክ አድርጎኛል።

ማመን የሚከብዱ ነገር ግን የሚታይ አስደናቂ ነገሮች ባየው ጊዜ ድካሙም ከላዬ ላይ ብን ብሎ ጠፍቷል ከአለት ፈልፍለው ፃድቁ አቡነ አባለ ክርስቶስ ቤተ መቅደስ አንፀዋል ከቦታው እንደደረስኩኝ ስውራሩ ቅዱሳን አባቶች በእጃቸው ጨብጠው የሚይዙት መቋሚያ ከመቅደሱ ግድግዳ ላይ ተቀምጦ አገኘውት።

እነርሱን በዓይኔ ማየት ባልችልም የያዙትን የሚይዙትን መቋሚያ በእጄ ጨብጬ በግንባሬ ተሳልሜዋለሁ ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ ነገሮችን ማየት ጀመርኩኝ ልቤን ከመሰጠው ከተገረምኩባቸው ነገሮች አንዱ የፃድቁ የአቡነ አባለ ክርስቶስ ፀበላቸው አንዱ ነበር።

ቢቀመጡበት ከሚያቃጥል ደረቅ ትልቅ ድንጋይ ላይ በመስቀላቸው መተው ያፈለቁት ፀበል ነበር ድንጋዩን ዙሪያው ብዞረው ደረቅ ነው ከእርሱ ላይ በጣም የሚፈስ ያውም የፈለቀበት ቦታ ላይ ቧንቧዋ ሰክተውበት እንደ ፏፏቴ ይወርዳል ሲገርም ሲደንቅ ተአምርኮ ነው።

ከእርሱ ጠበል የተጠመቀው ሰው ይቅርና የተጠማቂው ሰው 27 ትውልዱ ይማራል ታዲያ ምን እጠብቃለሁ ገብቼ ማር ማር የሚለው ገብተው ውጡ ውጡ የማይለው ፀበሉን ተጠመቁኝ።

እንስሳት ሁሉ ከእግሩ ስር እየመጡ የሚመግባቸው ፃድቁ አባታችን አቡነ አባለ ክርስቶስ ለ300 ዓመታት ከቆመ ሳይቀመጡ እጁን ከዘረጋ ሳያጥፍ ቆሞ የፀለዩበት በቁመታቸው ልክ የሰሩት ግድግዳውን ፈልፍለው የሰሯት መፀለያ ቦታ ከመቃብራቸው አጠገብ ይገኛል።

ፃድቁ ከአምላካቸው ጋር በፀሎት ቆመው ከሚፀልዩበት ከእዚህ ፍልፍል ግድግዳ ላይ ቆሞ መፀለይ እንደምን ያለ ዕድል እንደምንስ ያለ በረከት ቢሆን ነው በእውነት የጌታዬን ቸርነት ባሰብኩኝ ጊዜ እንባ ቀደመኝ እኔ ማን ነኝ አጢያተኛ ስሆን ፃድቁ በቆሙበት ቦታ የምቆመው ከቶ እኔ ማን ነኝ።

በእዚህ የግድግዳ ዋሻ ቆመው ሲፀልዩ ክርስቶስ የገባላቸው ቃል ኪዳን ብትሰሙ ምን አይነት ቦታ እንደሆነ ትረዱ ዘንድ አቀርብላችዋለሁ፦

1ኛ ፦ስምህ የጠራ ዝክርህ ያዘከረ መታሰቢያን ያሰበ 24 ትውልድ እምርልሀለሁ

2ኛ ፦ ለቤተክርስቲያን ምፅዋት የሰጠ እጣን ጧፉን ዘቢቡን ንዋይተ ቅዱሳቱን ያመጣ 28 ትውልድ እምርልሀለሁ።

3ኛ ፦ ገዳምህን የሰራ ያነፀውን ሰው 33 ትውልዱ በሰማይ የብርሃን ማደሪያ እሰራለታለሁ።

4ኛ ፦ በገዳም መጥቶ የቆረበውን እስከ 35 ትውልድ እምርልሃለሁ።

5ኛ ፦ገድልህ ያነበበ የሰማ ያሰማውን የተረጎመውን 28 ትውልድ እምርልሃለሁ።

6ኛ ፦ ገዳምህ መጥቶ የተጠመቀውን 27 ትውልድ እምርልሃለሁ።

7ኛው ይደንቃል ፦ገዳምህ መጥቶ ለመሳለም ቢያስብ በተለያየ ምክንያት መምጣት ባይችል በመንገዱ መራቅ ሆነ በሁኔታዎች አለመመቻቸት ሊሆን ይችላል አስቦ ቢቀር።

ገዳምህ ብቻ ስላሰበ 26 ትውልድ ይማርልሃል።

ወዳጄ ታዲያ ይህ ቦታ እንደምን ያለ ቦታ ነው? በርሃ ውስጥ ያለ ገነት የሚያስምር ግሩም የቃል ኪዳን ቦታ ፃድቁ አባለ ክርስቶስ የተቀመጡባት የዲንጋይ መቀመጫ መካን ሴት ብትነካው ልጅ ታገኛለች።

ሳሩ ቅጠሉ ድንጋይ አለቱ በሙሉ መዳኒት የሆነ ደብረ መዳኒት አቡነ አባለ ክርስቶስ ገዳም ድንቅ ነው ፃድቁ አባታችን በእዚህ ምድር ላይ 332 ዓመት ሲኖሩ በታህሳስ 19 በእዚህው ገዳማቸው አርፈዋል መቃብራቸው በፈለፈሉት ዋሻ በቤተ መቅደስ ውስጥ ይገኛል።

ለብዙ ጊዜ የሁለቱን ቅዱሳን ከተማ ለማየት ተመኝቼ ነበር አንደኛው ፃድቁ አባቴ አቡነ አባለ ክርስቶስ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ፃድቁ አቡነ አካለ ክርስቶስ ናቸው።

አንደኛው ተፈፅሟል ሁለተኛው በሰሜን ወሎ ከዳውንት በታች ከጥልቁ በርሃ ይገኛሉ ብዘገይ እንጂ መሄዴማ አይቀርም።

በፃድቁ አባለ ክርስቶስ ግን አሁን ፀሎቴ ተቀይሯል
ዳግም ለደጆት አብቁኝ።

ይቀጥላል።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/OEtJUzBhWzc

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🌿🌿መሪጌታ ማናየ ባሕላዊ  መድኃኒት ቀማሚ የቀደምት የሊቃዉንት አባቶቻችን ጥበብ ይሻሉ ወይም ይፈልጋሉ እንግዲያዉስ  ከምነሰጣቸው የጥበብ  አገልግሎቶች በጥቂቱ ከታች ተዘርዝረዋል
ለጥያቄ 09 38 46 88 23
1🌿 መፍትሔ_ሥራይ (የጠላት ድግምት መሻሪያ)
2🌿ለቡዳ
3🌿ለቁራኛ
4🌿 #መጠብቅ (ከጠላት ከሚላክ ሟርት የሚጠብቅ)
5🌿ለጋኔን
6🌿ለማንኛውም ዓይነት በሽታ መፍትሔ
7🌿ለራእይ (በህልም የሚያሳይ)
8🌿  ለፀር (ለጠላት)
9🌿ዓቃቤ_ርእስ (ጠላት እንዳይጎዳን የሚጠብቅ)
10🌿 ለዘኢያገድፍ (ለትምህርት የማያስጠፋ የማያስጥል)
11🌿ለመክስተ_ምስጢር (ትምህርት የሚያጎብዝ)
12🌿ለመፍትሔ_ሀብት(ሀብቱ በጠላት ድግምት ለተሰወረበት)
13🌿 መስተፋቅር
14🌿ለግርማ_ሞገስ (ሰው እንዲያከብረን እንዲወደን)
15🌿ለመድፍነ_ፀር (ጠላት እንዳይናገረን እና እንዲፈራ
16🌿ለሌባ(እንዳንሰረቅ እንዳንዘረፍ የሚጠብቅ)
17🌿የትዳር አጋር ላጣ ወይም ላጣች
የሚያስገኝ
18🌿ለምስያጥ ለገበያ (ገበያ እንዲቀናን እንድናገኝ)
19🌿መስተኃድር (ከብት ቢጠፋብን ሳይበሉ በሰላም እቤታቸው
የሚያመጣ)
20🌿መንድግ(በገበያ ገንዘብ ማግኛ)
21🌿ለዓይነ_ጥላ (የፍራቻ መንፈስ ማስለቀቂያ)
22🌿ለልሳነ_ሰብእ
23🌿ለበረከት
24🌿ለእግረ_መልስ (ጥሎ ለጠፋ ሰው መመለሻ ማምጫ)
25🌿ምስሀበ_ነዋይ(ገንዘብ ማግኛ)
26🌿ጸሎተ_ዕለታት
27🌿ለጽሑፍ ለስእል ለከበሮ ለበገና ለክራር በእጂ ለሚሰሩ
28🌿ንባብ ስናነብ ቀልጣፋ የሚያረግ
29🌿ለከበሮ
30🌿ለመፍዝዝ (ጠላት እኛን ለማጥቃት ሲሞክር አጠገባችን ሲደርስ
መጣላቱን አስረስቶ አፍዝዞ የሚያስቀር የማያስመታ)
31🌿ለሙግት
32🌿ለሰላቢ
33🌿ለስንፈት ወሲብ
34🌿ዘኢያወርድ ( ለወንዶች በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የዘር ፍሬ ቶሎ
እንዳይወርድ የሚያረግ አግዶ የሚያቆይ)
35🌿ለመደንግፅ (የተጣላን ሰው እኛን ሲያይ እንዲደነግጥ እንዲፈራ
የሚያረግ)
36🌿ለጥይት (ጥይት የማያስመታ)
37🌿ለዱላ( ዱላ የማያስመታ)
38🌿መንስኤ_እስኪት (ለወንድ የመራቢያ አካሉ ለደከመ ላነሰ)
39🌿ህገ_ጠብቅ (የትዳር አጋራችን ወደሌላ እንዳይሄድ የሚያስር
እንዳይዘሙት የሚከለክል)
40🌿ለአይነ_ሰብእ (ከሰው አይን የሚጠብቅ)
41🌿ለአዙሪት
42🌿ለአስቸጋሪና ተመላላሽ ሲህር
43🌿ለሪህ በሽታ
44🌿የመገጣጠሚያ ህመም
45🌿ለጉልበት ድርቀት
46🌿የባት ህመም
47🌿የወገብ ህመም
48🌿የአንገትና ትከሻ ህመም
49🌿የከረመ ደረቅ ሳል
50🌿ለደም ግፊት
51🌿የሆድ መረበሽ
52🌿የከፋ የሆድ ድርቀት
53🌿በመኝታ ሽንት ለሚያመልጠው
54🌿የአእምሮ ጭንቀት፣ ድብርት፣         ከሰው  መገለል፣እንቅልፍ ማጣት
55🌿እንቅልፍ መብዛት
56🌿የተለየ የቆዳ ህመም
57🌿ክብደት ለመቀነስ
58🌿የእንቅርት በሽታ
59🌿ራስ ምታት ከሚከተሉት ህመሞች ጋ
60🌿አይን አካባቡ ውጥረት ካለ
61🌿የሳይነስ ህመም
62🌿የሆድ ድርቀትና የሆድ ህመም
63🌿የወር አበባ ችግር ካለ
64🌿የወገብ መንሸራተት ካለ
65🌿ውጥረትና የአእምሮ ጭንቀት
66🌿ለከፍተኛ ራስ ምታት
67🌿ማስታወስ፣ንቃት፣ተነሳሽነት ለሌላቸው
68🌿ለድምፅ መታፈን
69🌿ከአጫሽነት ለመላቀቅ
70🌿ራስን ስቶ በስቃይ ለሚኖር
👉09 38 46 88 23
     /channel/mergetama
ይደውሉልን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ወላጆቿም ግድ ብለው ስዕለ ክርስቶስ የተባለ የሱስንዮስን የጦር መሪ አጋቧት:: እስከ 24 ዓመቷም ልጆችን ወለደች:: በዚህ ሁሉ ጊዜ የጾምና የጸሎት ሰው ነበረች:: አፄ ሱስንዮስ ተዋሕዶን ክዶ ካቶሊክ በሆነ ጊዜ ባሏ ወደ ንጉሡ እምነት ገባ::በዚህ ስታዝን ይባስ ብሎ ጠዳ ላይ የአቡነ ስምዓን (ዻዻሱን) ልብስ ግዳይ ይዞ ቀረበ:: እርሷም ልቧ ቆረጠ:: ፈጣሪ 3ቱን ልጆቿን አከታትሎ ወሰደ:: ደስ ብሏት ጠፍታ ሳጋ (ዛሬ ገዳሟ ያለበት) ገባች:: ቀጥላም መነኮሰች::

ከዚህ በሁዋላ እየዞረች ስታሳፍር: ሕዝቡን ስታጸና ዓመታት አለፉ:: በሷ ስብከትም ብዙ መነኮሳትና ምዕመናን ሰማዕት ሆኑ:: እሷም በየገዳማቱ ተንከራተተች:: በደዌ ተሰቃየች:: በንጉሡ ተይዛ 2 ጊዜ ወደ በርሃ ተሰደደች::

ፋሲል ነግሶ: ሃይማኖት ተመልሶ ሃገር ሲረጋጋ ወደ ምጽሊ: ከዚያም ወደ መንዞ መጥታ ገዳም መሥርታ: መናንያንን ሰብስባ: ስታጽናና ኑራለች:: በተወለደች በ50 ዓመቷም በ1630ዎቹ መጨረሻ አካባቢ ዐርፋ ተቀብራለች:: የተጋድሎ ዘመኗም 26 ዓመታት ናቸው:: ቅድስት ወለተ ዼጥሮስ ሰማዕትም ጻድቅም ናት::

††† የጥቡዓን አምላክ የሊቁን ምሥጢር: የቅድስቷን መጨከን: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

††† ኅዳር 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ (ፍልሠቱ)
2.ቅድስት ወለተ ዼጥሮስ ኢትዮዽያዊት
3.አባ ሲኖዳ (ዘደብረ ጽሙና - ጐጃም)
4.ጻድቃን እለ ወጺፍ
5.ቅዱሳን አብርሃምና ሐሪክ
6.ቅድስት ወለተ ዻውሎስና ወለተ ክርስቶስ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት
2.ያዕቆብ ሐዋርያ
3.መክሲሞስና ዱማቴዎስ
4.አባ ገሪማ
5.አባ ዸላሞን
6.አባ ለትጹን
7.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ

††† "በድካምና በጥረት: ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት: በራብና በጥም: ብዙ ጊዜም በመጦም: በብርድና በራቁትነት ነበርሁ . . . የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው::" †††
(2ቆሮ. 11:23)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

"ኪዳነ ምሕረት እናቴ" |
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ኪዳነ ምህረት እናቴ ምስጢረኛ ጓዳዬ
የጎደለኝን ታውቂያለሽ
ከአፌ ሳይወጣ ሳልነግርሽ (፪)
አዝ......
አልፏል መናኛው ኑሮ
ምልጃሽ ውኃውን ቀይሮ
መልካሙ ወይን ደረሰ
እንባዬ ባንቺ ታበሰ (፪)
አዝ.........
ልዘምር ልቁም ከፊትሽ
ልምጣ ልንበርከክ ለክብርሽ
ብርቅ ከሀገር ከቤቴ
ከቶ አልረሳሽም እናቴ (፪)
አዝ........
አልልም መቼ ነው ቀኑ
የኔ መጎብኛ ዘመኑ
እንደሚፈፀም አውቃለው
ሁሉን በጊዜው አያለው (፪)
አዝ........
የልቤን ችግር ላዋይሽ
ከስዕልሽ ፊት ቆሜ
እንባዬ ቀድሞ ዝም አልኩኝ
ሳልነግርሽ ስለምታውቂ (፪)

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
🔸🔺🔹🔹🔹🔺🔺🔸🔺🔹
/channel/mezmur_store
🔸🔺🔹🔹🔹🔺🔺🔸🔺🔹

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/+5vZ7pDkwQ-YyNTg0

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

=>አምላከ ቅዱሳን ጸጋውን ክብሩን: አእምሮውን: ለብዎውን ያሳድርብን:: ከወዳጆቹ በረከትም ያሳትፈን::=>ኅዳር 16ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አኖሬዎስ ጻድቅ (ንጉሠ ሮም)
2.አባ ዳንኤል ገዳማዊ
3.ቅዱስ አውሎጊስ መነኮስ
4.ቅድስት ጣጡስ ሰማዕት
5.አባ አቡናፍር ገዳማዊ
6.ቅዱስ ኪስጦስ ሰማዕት
7.ቅዱስ ፊቅጦር ምዑዝ
8.አባ ዮሐንስ መሐሪ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ኪዳነ ምሕረት (የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም)
2.ቅድስት ኤልሳቤጥ (የመጥምቁ ዮሐንስ እናት)
3.ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ
4.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ

=>+"+ ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ:: በዓለም ያለው ሁሉ: እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት: ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ: ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም:: ዓለሙም: ምኞቱም ያልፋሉ:: የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘለዓለም ይኖራል:: +"+ (1ዮሐ. 2:15)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ኪዳነ ምህረት ማለት ምን ማለት ነው ?
ኪዳን፦በግእዙ ‘ተካየደ’ ትርጉሙም ተማማለ፣ ቃል ኪዳን ተጋባ ማለት ሲሆን እግዚአብሔር አምላክም ከመረጣቸው ቅዱሳኑ ጋር የገባው ውል ‘ቃል ኪዳን’ ይባላል::

ቃል ኪዳን ማለትም ‘ውል፣ ስምምነት’ ማለት ነው። በእዚህም መሰረት
#ኪዳነ_ምህረት ማለት የምህረት ቃል ኪዳን ማለት ነው፡፡ ይህም ፍጹም ከከበሩ የእመቤታችን በዓላት አንዱ ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ የማይጠፋ የዘላለም ኪዳን የሰጠበት ዕለት መታሰቢያ ነው፡፡ በተሰጣት ቃል ኪዳንም እኛ ልጇቿ በስሟ ስንማጸን የከበደንን ሁሉ ታቀልልናለች፣ታማልደናለች !

Читать полностью…
Subscribe to a channel