kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ህዳር 29/2016 #ፃድቁ_ዮሐንስ_ዘጠገሮ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ፃድቁ #እጨጌ_ዮሐንስ_ዘጠገሮ በምልጃ ፀሎታቸዉ እንዲያስቡን ለምንማፀንበት አመታዊ የልደት በአል መታሠቢያ ክብረ በአላቸውእንኳን አደረሰን

👉ኅዳር ሃያ ዘጠኝ በዚህች ቀን #አቡነ_እጨጌ_ዮሐንስ ዘጠገሮ ልደታቸው ነው ፃድቁ አባታችን የተወለዱት በኢየሩሳሌም አውራጃ ልዩ ስሙ ሳሬራ በሚባል ቦታ ነው የካቲት 28 ቀን ተፀንሰው ህዳር 29 ተወለዱ

👉አባታቸው #ድላሶር እናታቸው #እምነ_ፅዮን ይባላሉ ሲወለዱ በወላጆቻቸው ቤት ውስጥ ብርሃን ወርዷል ወላጆቻቸውም #እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው አባታችን ገና በተወለዱ በ5 ዓመታቸው ወላጆቻቸው ወደ እግዚአብሔር ቤት ይዘዋቸው የእመቤታችንን ሥዕል ተመልክተው በደስታ ተመልተው ሳቁ

👉አምላክን የወለደች የብርሃን እናቱ #እመቤታችንም ከምሥሉ ወጥታ በምን አውቀኸኝ ነው ብላ አቅፋ ሳመችውና ከእንግዲ ወዲህ የልጄ አገልጋይ ትሆናለህ ኑሮህም እንደ #መላእክት ይሆናል በአንተ ምክንያት ብዙ ሰዎች ይድናሉ በምድር ላይም 500 አመት ትኖራለህ ብላ ባርካው ተሰወረች

👉ከዚያችም ቀን ጀምሮ አባ ዮሐንስ #ለክርስቶስ ተላልፎ ተሰጠ 50 ዓመትም በበረሃ ሲጋደል ኖሮ ከ50 ዓመት በኋላ በደመና ተጭኖ በመልአኩ #በቅዱስ_ገብርኤል መሪነት ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ መጡ ጻድቁ አባታችን በአቡነ #ተክለሃይማኖት ዘመን መጨረሻ የመጡ ሲሆን ምንኩስና ከደብረ ሊባኖስ ገዳም #ከአቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ተቀብለው በዚያው በደብረ ሊባኖስ ገዳም ለ50 ዓመት በፆምና በጸሎት በተጋድሎ ኖረዋል

👉ከዚኽም በኋላ #አባ_ዮሐንስ ወደ ተዘጋቸላቸው ምድር #በቅዱስ_ገብርኤል አሳሳቢነት ወደ ጠገሮ መጡ ይኽም ጠገሮ ያለው ገዳማቸው በሰሜን ሸዋ በመንዝና ይፋት ክልል መዘዞ በሚባል ቦታ ሲደርሱ በእግር አንድ ሰዓት ከተጓዙ በኋላ ይገኛል

👉ሕዝቡ በተለምዶ #እጨ_ዮሐንስ እያለ ይጠራቸዋል እንጂ ስማቸው #እጨጌ_ዮሐንስ ነው #አቡነ_እጨጌ_ዮሐንስ መስቀል ከሰማይ የወረደላቸው ታላቅ አባት ናቸው መስቀሉም ሁልጊዜ ተአምር ይሠራል በልደታቸው ቀን ኅዳር 29 ቀን መስቀሉ ከመቅደሱ ወጥቶ በካህናቱ ታጅቦ ወደ ፀበሉ ሲወርድ ከየት እንደመጣ ሳይታሰብ ደመና መጥቶ ከመስቀሉ ላይ ብቻ እረቦና እንደ ጃንጥላ ተዘርግቶ አብሮ ወደ ፀበሉ ይወርዳል

👉እዛው ቆይቶ #መስቀሉ ሲመለስም አብሮ አጅቦ ይመለስና መስቀሉ ቤተ መቅደስ ውስጥ ሲገባ ደመናው ወዴት እንደተበተነ ሳይታወቅ ይጠፋል ይህ በዘመናችንም ጭምር እየታየ ያለ ታላቅ ተአምር ነው

👉የፃድቁ አባታችን ታሪክ ከብዙ በጥቂቱ ይህን ይመስላል

👉የአባታችን ፀሎትና ልመና ሀገራችንን ህዝባችንን ከክፉ መከራ ሁሉ ይሠዉርልን የከበረዉ ቃል ኪዳናቸው ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን" 💒 💚 💛 ❤️ 💒

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

++"+ ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ::በእርስዋም ለዘለዓለም
ይኖራሉ::የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል::አንደበቱም
ፍርድን
ይናገራል:: የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ
ነው::በእርምጃውም አይሰናከልም:: +"+ (መዝ. 36:29)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር።>>>

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://www.youtube.com/live/UDa8QYD9wrA?si=zAWPZLSj7wdMgah9

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

5.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት
6.ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት

=>+"+ ስለዚሕ ወንድሞቼ ሆይ ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ:: ልባሞች እንደመሆናችሁ እላለሁ:: በምለው ነገር እናንተ ፍረዱ:: የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? .. . እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን:: ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና:: +"+ (1ቆሮ. 10:14)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

💥ሥነጽሑፍ - ግጥም !

🔥  ( ርዕስ - ምን አሉ )
----------------------------------
ምን ነበር ያሉት አበው ሲናገሩ
የታሪክ አደራ የቅርሳቸው ክብሩ
ለምን ነበር ይጨነቁ የነበሩ
ስለምን ነበር ያስቡ የነበሩ
ስጋቸውን ለማስደሰት
ያመረና የጣመ ለመብላት
በእስፕሪንግ አልጋ ላይ ለመተኛት
ቢሮ ተቀምጦ ዳቦ ለመብላት
ባለስልጣን ሆነው ለመታየት
ስለምን ነበር ሲያስቡ የነበሩት
ስለምን ነበር ሲናገሩ የነበሩት
ምን ተብሎ ተጽፎ ስለ እነርሡ ክብር
ምን ተብሎ ታወሰ የእነርሡ ዝክር
ብርሀናው ይውጣ ይነገር ሥራቸው
ዳግም ይነገር ይታይ ውጤታቸው
ብርሀናው ከወጣ ከተፈለገ ሥራቸው።

አስታዋሽ ካገኛ ከታየ ሥራቸው
እንዲህ ነበር አበው የታሪክ ገድላቸው
ገና ጉዞውን ሲጀምር የክርስትናውን
ከሰባት ወንድሞች ጋር በአበው የተሾመው
ያ ታለቅ አባት የወንጌል አርበኛው
በአንድ ስብከት 12ሺህ ያተመቀው
ምን አለ እስጢፋኖስ በድንጋይ ሲወግሩት
ስጋውን ቆራርጠው ደሙን ሲያፈሱት
እንደ ስንዴ ክምር ድንገይ ሲጭኑበት
ስለምን ተናገረ ምና ብሎ መሰከረ
ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍስን ተቀበል
ጌታ ሆይ ይህን ኃጢያት አትቁጠርባቸው።

ያ አረጋዊ ታላቅ አባት
ጌታን የሚወደው ከሁሉ በፊት
ሲናገር ቀደም ቀደም ብሎ የሚመሠክረው
ከጌታ ስብከት ለአፍታ ያልተለየው
አንተ ከምትሞት እኔ ልሙት ያለው
የመንግስተ ሰማያት ቁልፍ አደራ የተሰጠው
በጎቹን እንዲያሰማራ ቃል የገባው
ለመሆኑ ምን አለ ጴጥሮስ ያ ታላቁ አባት።

ጌታ ሆይ ወዴት ትሄዳለህ ደግመኛ
በሮም አደባበባይ ልሰቀል ሲለው
ጌታ ሆይ አንተ ከምትሰቀል እኔ እሰቀላለሁ
ስለመንግስተ ሠማያት ሲከራከሩ ሀዋሪያት
ጌታችን በምሳሌ የነበረው አቅርቦት
ያ ታናሽ ብላቴና ያልተለየው ከዮሐንስ
የሠማውን ለማስተላለፍ የተሯሯጠው በእግር በፈረስ
ምን አለ አግናጢዎስ ለባሴ እግዚአብሔር ምጥው ለአንበሳ
በትርኢት ቀርቦ በሮም አደባባይ ሲሰዋ
ዛሬ ተረኛ ነኝ በአምላክ እንደንጹህ መገበሪያ ስንዴ ልቀርብ ይገባኛል አለ
በ451 በጉባኤ ኬልቄዶን
እንዲቀበል ተገደደ ሁለት ባህሪይን
በበክርሊያና መለቂያ በሀይል የታዘዘው
ወልድ ዋህድ አንድ ባህርይ ብሎ የመሰከረው
የበርክሊያንና የመርቂልያን ዱላ የጠገበው
በግዞት የተሰደደው
ጥርሱ በግፍ የወለቀው
ፅህሙ በግፍ የተነጨው
ምን አለ ዲዮስቆሮስ ያ ታላቅ ባለሙያ
ምን ብሎ መሰከረ ስለምንስ ተናገረ
ጥርሱንና ጽህሙን በመሀረብ አስሮ ለክርስቲያኖች
ይህ የሀይማኖት ፍሬ ነው በርቱ አይዟችሁ።

ምን አለች ያቺ ታላቅ እናት
በስጋ ስትኖር ዓለምን የናቀች
ምን ያደርግልኛል ብላ በልጅነቷ የመነነች
የሰውን ልጅ ከአምላክ ለማስታረቅ የበቃች
ደግሞም ሰይጣንን ለማስታረቅ የለመነች
የዓለምን አምልኮት ታግላ ያሸነፈች
ለስጋዋ ሳይሆን ለነፍሷ የቆመች
ለብልጭልጭና ለጌጥ እጇን ያልሰጠች
በአጓጉል ፋሽን ያልተንበረከከች
በስጋዊ ምኞት በሀይሏ የገደለች
ለመሆኑ ምን አለች ክርስቶስ ሰምራ
ዘብሄረ ቡልጋ የኢትዮጲያ የቅርስ አደራ
ሳጥናኤል ሆይ ሳጥናኤል ሆይ ና ውጣ
ከአምላክህ ጋር ላስታርቅህ
ማነው በክብር ስሜ የጠራኝ ብሎ ሲናገር
ሚካኤል ደርሶ በሰይፍ መታው
ይህ ነበረ የአበው ገድላቸው
የቅድስና ስራ የክብር ጌጣቸው
ይሄን ነበር ያሉት አበው በቃላቸው
ለትውልድ እንዲተላለፍ የፃፉት በደማቸው
ስጋቸውን ቆርሰው አጥንታቸውን የሰበሰቡት
ህይወታቸውን ለክርስቶስ እንደስንዴ መገበሪያ የሰጡት ።

ኸረ ዛሬስ ምን አለን እኛ
የአበው ልጆች የተቀበልን አደራ
በእነርሱ እግር ለመተካት የጀመርን ስራ
ምን ነበር ስራችን ጌጥ ክብራችን
ስለምን ነበር ሀሳብ ጭንቀታችን
የእኛ ጭንቀትማ እንደው ከተነሳ
ስጋን ለማስደሰት የምናየው አበሳ
ድንቅና ውብ አድርጎ በፈጠረው አካላችን
ይበልጥ ለማሳመር ስናደርግ አዲስ ፋሽን
ግድግዳ ይመስል ቀለም ስንቀባው
የጠቆረውን ለማቅላት ብራውን እያልን ስንከልሰው
በዓለም ፋሽን ይበልጥ ስናጌጠው
እንደልኳንዳ ቤት ስጋ በመቶ ሻማ ስናሳየው
ይሄ ነው ጭንቀታችን ሀሳብ ክብራችን።

ለመሆኑ ምን አላችሁ መናፍቅ ቤታችሁ ሲገባ
ወንጌል ተሰበኩ ብሎ ሊላችሁ አላስወጣ አላስገባ
ምን ብላችሁ መለሳችሁ ስለምንስ አወራችሁ
ጀርመናዊ በንዴ ወንጌልን ለመስበክ ሲመጣ
ከተማራችሁት ውጭ አዲስ ቃል ሲያመጣ
ምን ብላችሁ መለሳችሁት ይህን መናፍቅ
ዘመቻ ተብሎ በአንድ ቃል ሲታወጅባችሁ
መዳን አለባችሁ ተብሎ ሲሰብክላችሁ
ቃሉን አልሰማችሁም ስሙ ስትባሉ
ለመሆኑ ምን አላችሁ
ከአበው አባቶች የተቀበልነውን አደራ
እንድንወጣ አምላክ ይሁን ከኛ ጋራ።
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል 
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን !!


✳️🔑ኪነ-ጥበብ🔑✳️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/Wjv5VWmCjI4?si=XOKL740nRDYp-kQG

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ህዳር 26
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
የፃድቁ #ሃብተ ማርያም ምልጃ በረከቱ አይለየን
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፧፧፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
የኢትዮጵያዊው ፃድቅ አቡነ ሃብተማርያም ታሪክ ባጭሩ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አምስቱን መቅሰፍቶች የማስወገድ ስልጣን የተሰጠው ፃድቁ አቡነ ሀብተማርያም የነበሩበት ዘመን 1486 ዓ.ም ንጉስ እስክንድር በነገሰበት ጊዜ ነው። አባታቸው ፍሬ ቡሩክ እናት አቸው ዮስቴና ይባላሉ። ፍሬ ቡሩክና ዮስቴና በህገ እግዚአብሔር በሃይማኖት በትሩፋት በምግባር ፀንተው የሚኖሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ነበሩ፡፡ አቡነ ሀብተማርያም ከተሰጣቸው ቃል ኪዳኖች ውስጥ አምስት መቅሰፍቶች የማስወገድ ስልጣን ተሰጧቸዋል፡፡ እነሱም፡-
1. #መብረቅ፣
2 #ቸነፈር፣
3. #ረሃብ፣
4. #ወረርሽኝ፣
5. #የእሳት ቃጠሎ ናቸው፡፡
ከብዙ ተጋድሎ በኃላ ፃድቁ አቡነ ሀብተማርያም በፀሎት ላይ ሳለ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ የቆምክባትን ቦታ ምስራቁን፣ ምዕራቡን፣ ሰሜኑን፣ ደቡቡን ባርክ አለው፡፡ ሲባርክም ሶስት አጋንንት በፀሎቱ ስልጣን ታስረው በፊቱ ታዩት።

እነዚህም አጋንንት ከኖህ ጀምሮ ሰውን በማሳት ከኖርን በኋላ ከአንተ ጋር ምን ፀብ አለን አሉ አባታችንም አቡነ ሀብተማርያም በትዕምርተ መስቀል ሲያማትብ ሁለቱን አጋንንት ምድር ተከፍታ ዋጠቻቸው አንዱ ጊዜዬ ስላልደረሰ አታጥፋኝ አለው፡፡ ያን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አቡነ ሀብተማርያምን ይህንን ተወው ጊዜው አልደረሰም አለው።

የጌታ ቃል እንዲህ ብሎ በተናገረ ጊዜ ሰይጣን ከአባታችን ተለይቶ ጠፋ፡፡ ማር 9፡23 ከዚህም በኋላ ዕለተ ሞቱ በደረሰ ጊዜ ለሞቱ ምክንያት የሚሆን ቸነፈር ያዘው፡፡ ጌታችንም በምስጋና ወደ እርሱ መጥቶ ወዳጄ ሀብተማርያም ሆይ ዛሬ ወደአንተ የመጣሁት ከድካም ወደ እረፍት እወስድህ ዘንድ ነው ሰባት የጽድቅ አክሊሎችን አዘጋጅልሃለሁ፡፡

1. ስለ ንፁህ ድንግልናህ፣
2. አለምንና በውስጡ ያለውን ንቀህ በመኖርህ፣
3. ስለ ፍፁም ምንኩስናህ፣
4. ዘወትር አራቱን ወንጌላትን በማንበብህና በመፀለይህ፣
5. ስለ እኔ ብለህ ስለተራብከው፣
6. በጾም ስለተጋደልክ፣
7. ቂምና ጥላቻን፣ ትዕቢትን፣ ትምክህትን፣ በልብህ ውስጥ ባለማስቀመጥህ ስለ ንፁህ ተልዕኮ ክህነትህ፣ ስለ ንፁህ መስዋዕትህ ነው ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡

በተጨማሪም እኔ የሰጠሁህን ቃል ኪዳን ተስፋ አድርጎ መጽሐፈ ገድልህን ለሚጽፈው ስሙን በመንግስተ ሰማያት በእውነት መጽሐፍ እጽፈዋለሁ፣ ለቤተክርስቲያንህ ዘይትን፣ ወይንን፣ ዕጣንን፣ ህብስትን እስከ ቀዝቃዛ ውሃ ድረስ በአንተ ስም መብዓ የሰጠውን የወደደውን ሁሉ አደርግለታለሁ፡፡ በመንግስተ ሰማያትም ከወዳጆቼ ከቅዱሳን ጋር በደስታ አኖረዋለሁ፡፡

የአቡነ ሀብተማርያም ፈጣሪ ኃጢአቴን ይቅር በለኝ ብሎ ያንተን ስም ጠርቶ ቢለምነኝ ኃጢአቱን አስተሰርይለታለሁ ብሎ ቃልኪዳን ገባለት ይህንንም ካለው በኋላ ጌታችን አፉን ሶስት ጊዜ ሳመው፡፡ ያን ጊዜም ከመድኃኔዓለም ጣዕም ፍቅር የተነሳ ነፍሱ ከስጋው ተለየች መዝ 115/116 ፡ 6 በሰማያዊ መልአክት በምድራውያን ስውራን ቅዱሳን ዘንድ ታላቅ ደስታ ሆነ ህዳር 26 ቀን አረፈ፡፡ ካህናት በመልካም ልብስ ገንዘው በዝማሬ በማህሌት ከቅዱስ አባታችን ከአቡነ ተክለሃይማኖት አጽም ጋር በፃድቁ መቃብር ቀበሩት፡፡ የአባታችን የአቡነ ሀብተ ማርያም በረከታቸው ይደርብን።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

💥ስለ ቤተክርስቲያን ማሰብ ከፈለጋችሁ የዛሬን ብቻ አትመልከቱ!
ስለ ነገዋ ቤተክርስቲያን ወደ ፊት ተመልከቱ እና ለቀጣዩ ቤተክርስቲያንን ተረካቢ ትውልድ መንገድ አሳዩት!
✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️✳️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🔑ታገቢኛለሽ!....
💥ቤተክርስቲያን የምትሄዱት ቀለበት ይዛችሁ  ታገቢኛለሽ ጥያቄ ለመጠየቅ ነው እንዴ?
➥⚙️
የፀሎት መፅሐፍ ይዛችሁ እግዚአብሔርን በመዝሙር፣በቅዳሴው ለማመስገን እንጂ  ትዳር ለመመስረት ነው?
➥⚙️
ስርዓተ ቤተክርስቲያን እና ባህል እያለ በማመስገኛ ስፍራ ታገቢኛለሽ ጥያቄ ለምን አስፈለገ?
➥⚙️
በቀለበት ፈንታ የፀሎት መፅሐፍ ፤ ታገቢኛለሽ በሚለው ጥያቄ ፈንታ የምንዘምርበትን ልቦና እግዚአብሔር አምላካችን በቸርነቱ ያድለን።

        ✳️💥ኪነ-ጥበብ💥✳️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

2.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
3.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
4.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
5.ቅዱስ አቡፋና ጻድቅ
6.ታላቁ አባ ቢጻርዮን=>+"+ የሚበልጠውን ትንሳኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ:: ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ:: በድንጋይ ተወግረው ሞቱ:: ተፈተኑ: በመጋዝ ተሰነጠቁ: በሰይፍ ተገድለው ሞቱ:: ሁሉን እያጡ: መከራን እየተቀበሉ: እየተጨነቁ: የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ:: ዓለም አልተገባቸውምና . . . +"+ (ዕብ. 11:35)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Aleh sis ..hulu aman

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለቅዱሳን ቆርኔሌዎስ ሐዋርያዊ እና አብድዩ ነቢይ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ቆርኔሌዎስ †††

††† ዛሬ የምንመለከተው የዚህ ቅዱስ ዜና ሕይወት በአብዛኛው የተወሰደው ከሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 10 ላይ ነው:: በቤተ ክርስቲያን የሐዲስ ኪዳን ታሪክ ወሳኝ ከሚባሉ ክዋኔዎች የዚህ ቅዱስ አምኖ መጠመቅ ነውና በታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ ላይ በስፋት ተመዝግቧል::

ምንም እንኩዋ ከእርሱ አስቀድሞ ኢትዮዽያዊው ባኮስ እንዳመነና እንደ ተጠመቀ ቢታወቅም (ሐዋ. 8:26) ቅዱስ ቆርኔሌዎስ ከአሕዛብ ወገን አምኖ ሐዋርያትን የተቀላቀለ የመጀመሪያው ሰው ነው:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
የሮም መንግሥት በቄሣሮች ሥር በ1ኛው መቶ ክ/ዘመን ዓለምን እንደ ሰም አቅልጦ: እንደ ገል ቀጥቅጦ ይገዛ ነበር:: በየ አሕጉሩም እስከ መንደርተኛ ሹሞች ድረስ ተሹመው ግብርን ለቄሣር ይሰበስቡ: ሕዝቡን ለቄሣር ያስገዙ ነበር::

ከእነዚህ መካከልም አንዱ የሆነው ቆርኔሌዎስ በቂሣርያ ዘፍልስጥኤም (ሌላ ቂሣርያ ስላለች ነው) የመቶ አለቃ (ሃቤ ምዕት): የሠራዊት መሪ (ሊቀ ሐራ) ሆኖ ተሹሞ ነበር:: የሠራዊቱን ስምም "ኢጣሊቄ" ይሉታል::

ቆርኔሌዎስ እግዚአብሔርን አያውቅም:: እንደ አረሚ (ግሪካውያን) የከዋክብት አምላኪ ነበር እንጂ:: ያም ሆኖ ክፋትን የሚጠላ: ደግነትን የሚያበዛ: ምጽዋትን የሚያዘወትርና በሐቲት (በምርምር) የሚኖር ሰው ነበር::

ታዲያ በዚያ ሰሞን ክርስቶስ ኢየሱስ መድኃኒታችን የማዳን ሥራውን ፈጽሞ: አበው ሐዋርያት ለትምሕርተ ወንጌል እንደ ሠጋር በቅሎ ይፋጠኑ ነበር:: ሹም (አለቃ) ነውና ቆርኔሌዎስ የሐዋርያት ዜና ፈጥኖ ነበር የደረሰው::

ቅዱሳኑ በስመ ክርስቶስ ድውያንን እንደሚፈውሱ: ሙታንን እንደሚያነሱ: በኃይለ መንፈስ ቅዱስም ብዙ ምልክቶችን (ተአምራትን) እንደሚያደርጉ ሰምቶ ተገረመ:: እርሱ የሚያመልከው ዙሐል (የኮከብ ስም ነው) አቅመ ቢስ ፍጡር መሆኑን ተረዳና እርግፍ አድርጐ ተወው::

ምንም የሠራዊት አለቃ ሹም ቢሆንም ዘወትር በመዓልትና በሌሊት ይጾምና ይጸልይ ገባ:: ጸሎቱም "የእውነት አምላክ ተገለጥ" ነበር:: ጾምና ጸሎት ያለ ምጽዋት ቁም ነገር አይሠሩምና ቤቱን ቤተ-ርሑባን: ቤተ-ነዳያን አደረገው::

ይሕ ተወዳጅ ጾም: ጸሎትና ምጽዋት ደግሞ ያለ ከልካይ ወደ ሰማያት: ቅድመ እግዚአብሔር ደረሰ:: ምንም አሕዛባዊ (ኢ-ጥሙቅ) ቢሆንም ጌታ ግን ቅዱስ መልአኩን ላከለት::

አንድ ቀን እንዳስለመደ ሲጸልይ ዘጠኝ ሰዓት (በሠርክ) አካባቢ መልአኩ ብሩህ ልብስ ተጐናጽፎ ተገለጠለት:: "ቆርኔሌዎስ ሆይ! ጸሎትህና ምጽዋትህ ወደ እግዚአብሔር ደረሰልህ:: እግዚአብሔርም አሰበህ" አለው::

"አሁንም ትድን ዘንድ በሰፋዪ ስምዖን ቤት: በሃገረ ኢዮዼ: ዼጥሮስ የሚሉት ስምዖን አለና እርሱን ጥራው:: እርሱ የምትድንበትን ይነግርሃል" ብሎት: የምሥራቹንም ነግሮት ተሰወረው:: ወዲያውም ከራዕዩ የተነሳ እያደነቀ ብላቴኖቹን ጠርቶ ወደ ኢዮዼ ላካቸው::

በዚያች ዕለትም የሐዋርያት አለቃ ቅዱስ ዼጥሮስ በቤተ ስምዖን ሰፋዪ ሳለ ይጸልይ ዘንድ ወደ ደርቡ (ፎቅ) ወጣ:: በዚያም በጸሎት ላይ ሳለ ተደሞ መጣበት:: ግሩም ራዕይንም ተመለከተ:: "ሞጣሕት ስፍሕት" ይላታል:: ከሰማይ በ4 ማዐዝን የተያዘች መጋረጃ: በውስጧ የእንስሳት: የአራዊት: የአዕዋፍ ስዕል ተስሎባት ስትወርድ ተመለከተ::

አንዲት እጅም ወደ እሪያው (አሳማ) እያመለከተች "ተንስእ ኦ ዼጥሮስ ኅርድ ዘንተ ወብላእ . . . - ዼጥሮስ ሆይ! ተነስ: ይህንንም አርደህ ብላ" ስትለው:: እርሱ ግን "ግሙራ ኢቦአ ርኩስ ውስተ አፉየ-የረከሰ ነገር ከአፌ ገብቶ አያውቅም" ብሎ መለሰ::

መልሶም "ዘእግዚአብሔር አንጽሐ አንተ ኢታስተራኩስ- እግዚአብሔር ያነጻውን አንተ አታርክሰው" ሲለው:: ይሕም ራዕይ 3 ጊዜ ሲደጋገም ተመለከተ:: ወዲያውም ያቺ መጋረጃም ወደ ላይ ተመለሰች::

የራዕዩ ምሥጢር ለጊዜው እግዚአብሔር ከፈጠረው "ርኩስ" የሚባል እንደ ሌለ ያጠይቃል:: ለፍጻሜው ግን ያቺ ሞጣሕት የወንጌል (የክርስትና) አንድም የእመ ብርሃን ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት::

እሪያው ደግሞ የቅዱስ ቆርኔሌዎስ ምሳሌ ነውና "አትጸየፈው: አጥምቀው" ሲለው ነበር:: ቅዱስ ዼጥሮስ ስለዚህ ነገር ሲያሰላስል የቅዱስ ቆርኔሌዎስ ብላቴኖች ደርሰው ጠሩት:: መንፈስ ቅዱስ "አብረሃቸው ሒድ" ብሎታልና አብሯቸው ሔደ::

ወደ ቆርኔሌዎስ ዘንድ ደርሶም 2ቱ ራዕያቸውን ተጨዋወቱ:: ቆርኔሌዎስም በግንባሩ ተደፍቶ ለሊቀ ሐዋርያት ሰገደለት:: ቅዱስ ዼጥሮስ ግን ስለ ትሕትና "አትስገድልኝ" አለው:: ከዚያም አፉን ከፍቶ ለእርሱና ለቤተሰቡ ከቅዱስ ቃሉ መገባቸው:: አጥምቆም እጁን ሲጭንባቸው ከቅዱስ መንፈሱ ተካፈሉ::

ከዚህች ዕለት በሁዋላም ቅዱስ ቆርኔሌዎስ ሃብቱን: ንብረቱን: ሹመቱንና ክብሩን ንቆ ሐዋርያትን ተከተላቸው:: ለስብከተ ወንጌል አገልግሎትም አንዲት በትር ብቻ ይዞ ወደ ምድረ ግብጽ ወረደ:: በዚያም ብዙዎችን ወደ ክርስትና ስቦ: ለዓመታት ተጋድሎ በዚህች ቀን ዐርፏል::

††† ቅዱስ አብድዩ ነቢይ †††

††† "አብድዩ" ማለት "የእግዚአብሔር አገልጋይ" ማለት ነው:: ቁጥሩ ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት ሲሆን የቅዱስ ኤልያስ ታላቁም ደቀ መዝሙር ነው:: ቅዱሳን ነቢያት ዮናስና ኤልሳዕም ባልንጀሮቹ ነበሩ::

ቅዱስ አብድዩ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ800 ዓመት አካባቢ የከሃዲው ንጉሥ የጦር መሪ ሆኖ በሃምሳ አለቃነት አገልግሏል:: ግፈኛዋ ኤልዛቤል ነቢያተ እሥራኤልን ስታስፈጅ 50ውን በአንድ ዋሻ 50ውን ደግሞ በሌላ ዋሻ አድርጐ አትርፏቸዋል:: 900ው ግን ተጨፍጭፈዋል::

ያተረፋቸውንም ክፉ ዘመን እስኪያልፍ ድረስ መግቧቸዋል:: አክአብና ኤልዛቤል ከሞቱ በሁዋላም ቅዱስ ኤልያስን ተከትሎ ሹመቱን ትቷል:: እግዚአብሔር ገልጾለትም ትንቢት ሲናገር: ሕዝቡንም ሲገሥጽ ኑሯል::

በብሉይ ኪዳን ካሉ የትንቢት መጻሕፍትም በጣም አጭሩን የጻፈው ይሕ ነቢይ ነው:: ትንቢተ አብድዩ ባለ አንድ ምዕራፍ ብቻ ናትና:: ቅዱሱ በዚህች ቀን ዐርፎ ወገኖቹ ቀብረውታል::

††† አምላከ ነቢያት ወሐዋርያት የበረከትና የሰላም ዘመንን ያምጣልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

††† ኅዳር 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ቆርኔሌዎስ (ሐዋርያዊ ጻድቅ)
2.ቅዱስ አብድዩ ነቢይ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
2.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
3.ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል)
4.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
5.ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ
6.አባ ሳሙኤል
7.አባ ስምዖን
8.አባ ገብርኤል

††† "በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ የምትኖር: ማደሪያህንም ከፍ ከፍ ያደረግህ: በልብህም:- 'ወደ ምድር የሚያወርደኝ ማን ነው?' የምትል አንተ ሆይ! የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል:: እንደ ንስር መጥቀህ ብትወጣ: ቤትህም በከዋክብት መካከል ቢሆን: 'ከዚያ አወርድሃለሁ' ይላል እግዚአብሔር::" †††
(አብድዩ 1:3)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የምክር ቃል ከቅዱስ ኤፍሬም!

የበደሉንን ይቅር ማለት መሸነፍ ሳይሆን ፍቅርን ማስተማር ነው። ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡ የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህን ኃጢአት አትግለጥ፡፡ የባልጀራህን ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡

ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱ ልክ በእሳት ፊት እንደ ወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡

ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹሕ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደ ተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ቃላቶችህ የተመጠኑና ጤናማዎች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡ የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅና ንትርክ ከመግባት ራስህን ጠብቅ፡፡
የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡

Samri

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ህዳር 22/2016 #ቅዱስ_ዑራኤል

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በመልአኩ ስም ለምናመሰግንበት #ቅዱስ_ዑራኤልን በጥበቃው እንዳይለየን ለምንማፀንበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በዓል እንኳን አደረሰን

👉 #ዑራኤል የሚለው ስም “ዑር” እና “ኤል” ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው

👉 #ዑራኤል ማለት ትርጉሙ «የብርሃን ጌታ» የአምላክ ብርሃን ማለት ነው

👉 #ቅዱስ_ዑራኤል ለነቢዩ ዕዝራ ጽዋዓ ልቡና ያጠጣዉ ጥበብና ማስተዋልን የሰጠዉ የጠፉትን ቅዱሳት መጻህፍትን በቃሉ አጥንቶ እንደገና እንዲጽፋቸዉ የረዳዉ መልአክ ነዉ (ዕዝ ሱቱኤል13፥39)

👉 #ቅዱስ_ዑራኤል ቅድስት ማርያም ልጅዋን ህጻኑን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ ለስደት በተነሳች ጊዜ ከምድረ እስራኤል ወደግብጽ ከዚያም ወደ ቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያ እየመራ ያመጣት መልአክ ነው (ድርሳነ ዑራኤል ገጽ 26 ምዕ 4)

👉አቤቱ የመላእክት ሁሉ አለቃ የሚሆን #የቅዱስ_ዑራኤል አምላክ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሆይ በክርስቶስ ክርስቲያን የተሰኘን የጥምቀት ልጆችህን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ጠብቀን "አሜን"

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ደቅስዮስ (የእመቤታችን ወዳጅ)
3.አባ እንጦንስ አበ መነኮሳት
4.አባ ጳውሊ የዋህ
5.ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት
6.ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ ሐዋርያ

††† "ልጆች ሆይ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ:: አሸንፋችሁአቸውማል:: በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና:: እነርሱ ከዓለም ናቸው:: ስለዚህ ከዓለም የሆነውን ይናገራሉ:: ዓለሙም ይሰማቸዋል:: እኛ ከእግዚአብሔር ነን:: እግዚአብሔርን የሚያውቅ ይሰማናል:: ከእግዚአብሔር ያልሆነ አይሰማንም::" †††
(፩ዮሐ. ፬፥፬)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ዎዳጄ እስከ ዛሬ ይሄ የ ዩቱዩብ ቻናል የለህም? ከሌለህ እመነኝ አንድ step ወደ ኋላ ቀርተሃል!! በል አሁንም አረፈደም subscribe አድርግና እውነተኛ መረጃዎችን ኮምኩም!!
gyon_tube?si=lKI-ejbXEwu23lnW" rel="nofollow">https://youtube.com/@gyon_tube?si=lKI-ejbXEwu23lnW

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ እንኩዋን ለአበው ቅዱሳን "አባ ሊቃኖስ ወአባ ሰረባሞን ሰማዕት" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

" ኅዳር 28 "
+*" አባ ሊቃኖስ ዘደብረ ቆናጽል "*+

=>ጻድቁ ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮዽያ ቢሆንም ሃገረ ሙላዳቸው የጥንቱ የሮም ግዛት የሆነችው ታናሽ እስያ ናት:: አባ ሊቃኖስ ከዘጠኙ (ተስዓቱ) ቅዱሳን አንዱ ናቸው:: ዘጠኙ ቅዱሳን ተወልደው ያደጉት ምንም በአንድ የሮም ግዛት ሥር ቢሆንም መነሻ ቦታቸው ግን የተለያየ ነው::

+ሁሉንም አንድ ያደረጋቸው መንፈስ ቅዱስ በኪነ ጥበቡ ነው:: በምክንያት ደረጃ እንግለጸው ከተባለ ደግሞ የአንድነታቸው ምሥጢር:-
1.የቀናች ሃይማኖታቸው ተዋሕዶ
2.ዓላማ (የእግዚአብሔር መንግስት) እና
3.ገዳማዊ ሕይወት ነው::

+አባ ሊቃኖስን ጨምሮ ሁሉም ቅዱሳን ዘራቸው ከቤተ መንግስት ነው:: እነርሱ ግን ምድራዊውን ክብር ንቀው ሰማያዊውን ክብር ገንዘብ ማድረግን መርጠዋል:: አስቀድመው ቅዱሳት መጻሕፍትን ያጠኑት አበው በተለያየ ጊዜ እየመነኑ ከሮም ግዛት ወደ ግብጽ በርሃዎች ወርደዋል::

+በምናኔ ቅድሚያውን አባ ዸንጠሌዎንና አቡነ አረጋዊ ይይዛሉ:: ዘመኑ የተዋሕዶ አማኞች የሚሰደዱበት 5ኛው መቶ ክ/ዘመን ነበርና እምነትን ላለመለወጥ ዘጠኙ ቅዱሳን ስደትን መረጡ::

+በወቅቱ ደግሞ ለስደት መጠለያ የምትሆንና ከኢትዮዽያ የተሻለች ሃገር አልነበረችም:: ስለዚህም በ470ዎቹ ዓ/ም አልዓሜዳ በኢትዮዽያ ነግሦ ሳለ ቅዱሳኑ በአረጋዊ መሪነት መጡ::

+ንጉሡም ሲጀመር የእግዚአብሔር እንግዳ ስለሆኑ: ሲቀጥል ደግሞ ቅድስናቸውን ተመልክቶ መልካም አቀባበልን አደረገላቸው:: ማረፊያ ትሆናቸውም ዘንድ አክሱም ውስጥ አንዲት ቦታን ወስኖ ሰጣቸው:: ይህች ቦታ ቤተ ቀጢን ትባላለች::
አባ
ሊቃኖስና
8ቱ ቅዱሳን ወደ ሃገራችን እንደ ገቡ የመጀመሪያሥራቸው
ቋንቋን መማር ነበር::

+ልሳነ ግዕዝን በወጉ ተምረው እዛው አክሱም አካባቢ
ሥራቸውን አንድ አሉ:: በወቅቱ በአቡነ ሰላማ: በአብርሃ
ወአጽብሐና
በአቡነ ሙሴ ቀዳማዊ የተቀጣጠለው ክርስትና በተወሰነ
መንገድ ተቀዛቅዞ ነበርና እነ አባ ሊቃኖስ እንደ ገና
አቀጣጠሉት::

+ሕዝቡን በራሱ ልሳን ለክርስትና ይነቃቃ ዘንድ
ሰበኩት::የካደውን እየመለሱ: የቀዘቀዘውን እያሟሟቁ
ለዓመታት ወንጌልን
ሰበኩ:: ቀጣዩ ሥራቸው ደግሞ መጻሕፍትን መተርጐም
ሆነ::

+ከሃገራቸው ያመጧቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት ተከፋፍለው
ወደ ግዕዝ ልሳን ተረጐሟቸው:: በዚህም ለሃገራችን
ትልቁን ውለታ ዋሉ:: ይህ ሁሉ ሲሆን እነ አባ ሊቃኖስ የሚመገቡትም ሆነ
የሚጸልዩት በማኅበር ነበር:: በመካከላቸውም ፍጹም
ፍቅር ነበር:: ጸጋ እግዚአብሔር አልተለያቸውም::

+የነ አባ ሊቃኖስ ቀጣዩ ተግባራቸው ደግሞ ገዳማዊ
ሕይወትን ማስፋፋት ሆነ:: ይህንን ለማድረግ ግን የግድ
መለያየት አስፈለጋቸው:: እያንዳንዱም መንፈስ ቅዱስ ወደ መራው
ቦታ ሔደ::

*ዸንጠሌዎን በጾማዕት:
*ገሪማ በመደራ:
*አረጋዊ በዳሞ
*ጽሕማ በጸድያ
*አባ ይምዓታ በገርዓልታ
*ሌሎችም በሌላ ቦታ ገዳማትን መሠረቱ::

+ልክ እንደ ባልንጀሮቻቸው 8ቱ ቅዱሳን አባ ሊቃኖስም
ከጻድቅነታቸው ባሻገር ለሃገራችን ትልቅ ባለውለታ
ናቸው::በነገራችን
ላይ 'አባ ሊቃኖስ' የመጀመሪያ ስማቸው ሳይሆን
በትምሕርታቸው (በእውቀታቸው) የተደመመ የአክሱም
ሕዝብ ያወጣላቸው ስም
ነው::

+ሊቃኖስን 'ሊቁ አባት' ማለት ነው ብለው የተረጐሙልን
አበው አሉና:: ይሕስ በምን ይታወቃል ቢሉ:- 9ኙ ቅዱሳን
የማኅበር አገልግሎታቸውን ፈጽመው ወደየ ራሳቸው
ገዳማት ሲሔዱ አባ ዸንጠሌዎንና አባ ሊቃኖስ እዚያው
አክሱም አካባቢ
በመቅረታቸው ይሏል::

+ምክንያቱም ሕዝቡና ንጉሡ 2ቱን አበው "አትራቁን"
ብለው ለምነዋቸው ነበርና:: በዚህም የተነሳ አባ
ዸንጠሌዎን ከአክሱም
ከተማ በላይ ባለች ጾማዕት (እንዳባ ዸንጠሌዎን)
በሚሏት ተራራ ላይ ሲያርፉ: አባ ሊቃኖስ ደግሞ ከዚያው
ከጾማዕት 1
ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኘው ደብረ ቆናጽል
(የቀበሮዎችተራራ) ላይ ዐርፈዋል::

+በመካከላቸው ደግሞ የቅድስት ማርያም መግደላዊት
ቤተ ክርስቲያን ይገኛል::
አባ ሊቃኖስ በአታቸውን ካደራጁና ገዳም ካነጹ
በኋላ ደቀ መዛሙርትን አፈሩ: አስተማሩ::

+እጅግ ከበዛው ተጋድሏቸው ባልተናነሰ መንገድ ለ21
ዓመታት ያህል ከተራራው እየተነሱ ወንጌልን ሰብከዋል::
መጽሐፍ
ቅዱስና ሌሎች መጻሕፍትንም ከሱርስት (የሶርያ ልሳን)
እና ከጽርዕ (የግሪክ ልሳን) ተርጉመዋል::

+ሁልጊዜም ለአገልግሎት ሲወጡ በትረ ሙሴአቸውን
አይለዩም ነበር:: ሲሰብኩም: ሲጸልዩም ተደግፈውባት
ነበር:: ታዲያ
ከዘመን ብዛት የእጃቸው መዳፍ መነደሉን
አበው:-"ወበእሒዘ በትር ዘተሰቁረ ዕዱ" ሲሉ ይናገራሉ::

+ዳግመኛ ማታ ማታ ለጸሎት እጆቻቸውን ሲያነሱ እንደ ፋና
ቦግ ብለው ሲያበሩ ይታዩ ነበር:: ጻድቁ አባ ሊቃኖስ
ሥሙር
በሆነ ሕይወታቸው በእግዚአብሔር ብቻ ሳይሆን
በነገሥታቱና በሕዝቡ ዘንድም ሞገስን አግኝተዋል:: ዛሬም
ድረስ የአክሱም
ሕዝብ ከልቡ ያከብራቸዋል::

+አንድ ወቅትም ሳይገባን (በቸርነቱ) ሒደን ገዳማቸውን
ተመልከተናል:: አበው እንደሚሉት በደብረ ቆናጽል ላይ
ያለው ደን
የብዙ ሥውራን መኖሪያ ነው:: ለ1,500 ዓመታት ተከብሮ
ቢኖርም በ1928ቱ የጣልያን ወረራ ግን እንዳልነበረ ሆኖ
ነበር::

+ዛሬም በቀድሞ ገጽታው አይደለም:: በገዳሙም
ያገኘነው አንድ አባትን ነው::

+ዐይናችን ግን ብዙ ነገሮችን ተመልክቶ አድንቋል:: እንደ
ሰማነውም ዛሬም መካነ ቅዱሳን በመሆኑ የጽዮን
አገልጋዮችም ማረፊያ ነው:: ጻድቁ አባ ሊቃኖስ ያረፉት ሕዳር 28 ቀን
ነው::

+" ቅዱስ ሰረባሞን ሰማዕት "+

+ቅዱሱ ሰው የዘመነ ሰማዕታት ፍሬ ሲሆን የቅዱሳን
ሐዋርያት ዘመድ ነው:: እርሱ ተወልዶ ያደገው በ3ኛው
መቶ ክ/ዘመን
በኢየሩሳሌም ነው:: የዘር ሐረጉ ሲቆጠርም በቀጥታ
ከሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስና ከስምዖን ቀለዮዻ
ይደርሳል::

+በልጅነቱ ያደገው በሥርዓተ ኦሪት ነው:: ወጣት በሆነ
ጊዜ ግን ፈጣሪ በሰጠው ሕሊና ተመራምሮ በክርስትና
ለመኖር ወሰነ:: የወቅቱን የኢየሩሳሌም ኤዺስ ቆዾስ ሒዶ "አጥምቀኝ"
ቢለው "ልጄ! ደስ ይለኝ ነበር:: ግን ወገኖችህ አይሁድ
ይገድሉኛል" ሲል መለሰለት::

+አክሎም "ወደ ግብጽ ሒደህ ግን ብትመጠመቅ የተሻለ
ነው" ስላለው ከኢየሩሳሌም ግብጽ ገባ:: ግብጽ ደርሶ:
ከቅዱስ
ቴዎናስ (16ኛ ፓትርያርክ) ክርስትናን ተምሮ
ተጠመቀ::ቀጥሎም ወደ ገዳም ገብቶ ከመጀመሪያዎቹ
መነኮሳት አንዱ ሆነ::
ምናኔን ከአባ እንጦንስ ተምሮ ስም አጠራሩ ከፍ አለ::

+በተጋድሎውና በንጽሕናው ስለ ወደዱትም የኒቅዮስ
ዻዻስ አደረጉት:: በዘመነ ሲመቱም ጣዖት አምልኮን
ከአካባቢው አጥፍቷል:: ስለዚህ ፈንታም በዲዮቅልጢያኖስ ተይዞ በዚህች ቀን
ተገድሏል:: ሲገደልም ልክ እንደ ቅድመ አያቱ ቅዱስ
እስጢፋኖስ ፊቱ ያበራ ነበር::

=>አምላከ አበው ቅዱሳን መዓዛ ቅድስናቸውን
ያሳድርብን::ከበረከታቸውም ይክፈለን::

=>ኅዳር 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አባ ሊቃኖስ ጻድቅ (ከተስዓቱ ቅዱሳን)
2.ቅዱስ ሰረባሞን ሰማዕት

ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አማኑኤል ቸር አምላካችን
2.ቅዱሳን አበው /አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ/
3.ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
4.ቅድስት ዓመተ ክክርስቶስ
5.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ (ሰማዕት)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/W-eN0faaHmo

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን † ✞✞✞

† ኅዳር ፳፯ †
+"+ ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ +"+

=>ይህ ስም በቤተ ክርስቲያን እጅግ ዝነኛና ታዋቂ ነው:: ቅዱስ ያዕቆብ ቁጥሩ ከዓበይት ሰማዕታት ሲሆን የፋርስ ኮከብ በመባልም ይታወቃል:: ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ ("ሙ" ጠብቆ ይነበብ) ተወልዶ ያደገው በ4ኛው መቶ ክ/ዘ በምድረ ፋርስ (የአሁኗ ኢራን) ውስጥ ነው::

+ያኔ ይህቺ ሃገር በአንድ ወገን ጠንካራ ክርስቲያኖች: በሌላ ወገን ደግሞ ጣዖትን የሚያመልኩ ጨካኝ ነገሥታት ነበሩባት:: ቅዱስ ያዕቆብም በክርስትና ትምሕርት አድጐ ሚስት አገባ::

+በዘመኑ ከነበረው ንጉሥ ሠክራድ ጋር በጣም ይዋደዱ ነበርና በቤተ መንግስቱ ውስጥ ሹም አድርጐ አስቀመጠው:: በቤተ መንግስት ውስጥ ምቾት የበዛበት ቅዱስ ያዕቆብ የጾምና የጸሎት ሕይወቱ እየቀዘቀዘ መጣ:: በሒደትም ንጉሡ የሚለውን ሁሉ የሚፈጽም ሰው ሆነ::

+አንድ ቀን ግን ሠክራድ ቅዱስ ያዕቆብን "ለእሳትና ለጸሐይ ስገድ: እነሱንም አምልካቸው" ሲል ጠየቀው:: ከመጀመሪያ የተሸረሸረ ነገር ስለ ነበረ "እሺ! ደስ ይበለው" ብሎ ለፀሐይ ሰገደ:: እርሷንም አመለከ::

+ይህቺ ዜና በዘመኑ ክርስቲያኖች ዘንድ ስትሰማ ታላቅ ሐዘንን ፈጠረች:: ይልቁኑ ሚስቱ: እናቱና እህቱ ይህንን ሲሰሙ አንጀታቸው አረረ:: በዚህ ምክንያትም 3ቱ ተሰብስበው አንድ ደብዳቤ ጽፈው: ተፈራርመው ላኩለት::

+የደብዳቤው ይዘት እንዲህ ይላል:- "አንተ ክርስትናህን መካድህን ሰምተን አዘንን:: በዚህም ምክንያት ከዚህ በሁዋላ በአካባቢህ መኖርን አንፈልግም:: ለሞተልህ ለክርስቶስ ካልታመንሀ እኛ አንተን እንደ ልጅ: እንደ ወንድምና እንደ ባል ልናምንህ ይከብደናል::"

+ይህንን ደብዳቤ ልከውለት እነርሱ አካባቢውን ለቀቁ:: ቅዱስ ያዕቆብ ደብዳቤውን ተቀብሎ: ወደ ቤቱ ገብቶ ሲያነበው ደነገጠ:: በዚህ ምድር ያሉት ዘመዶቹ ሚስቱ: እናቱና አንዲት እህቱ ብቻ ናቸውና ውስጡ ተሸበረ:: ተደፍቶም ምርር ብሎ አለቀሰ::

+ሲመሽም በቤቱ ውስጥ ወደ ነበረው የቀድሞ የጸሎት ቦታ ሒዶ ተንበረከከ:: ከንጉሡ ጋር በነበረው ያልተገባ ቅርርብ የፈጸመው ስህተት ሁሉ ቁልጭ ብሎ ታየው::

+በጌታችን ፊት ቁሞም "ጌታ ሆይ! በምድር ካሉ የሥጋ ዘመዶቼ መለየት እንዲህ ካሸበረኝ: ካንተ ፍቅር መለየትማ እንደ ምን ይጨንቅ ይሆን! በሰማያዊ ዙፋንህ ፊትስ እንዴት ብዬ እቆማለሁ!" ሲል አምርሮ አለቀሰ::
+ሙሉውን ሌሊት በእንባና በጸሎት አድሮ በጠዋት ንስሃ ገባ:: ከዚያች ቀን ጀምሮም ፍጹም በክርስቶስ ፍቅር ተጠመደ:: ጾምና ጸሎትን ወዳጆቹ አድርጐ ከንጉሡ እልፍኝና አደባባይ ቀረ::

+ይህንን ያወቀው ንጉሡ ሠክራድ ወደ እርሱ አስጠርቶ "ምን ሆነሃል? ስለ ምንስ በአምልኮ ከእኔ ተለየህ?" አለው:: ቅዱስ ያዕቆብም መልሶ "የፈጠረኝን ክርስቶስን ትቼ አንተን በባዕድ አምልኮ አስደስትህ ዘንድ የሚገባ አይደለም" ሲል ተናገረው::
+ንጉሡ ቅዱሱን አስቀድሞ ሊያታልለው ሞከረ:: እንቢ ሲለው ግን ደሙ በመሬት ላይ እስኪንጠፈጠፍ ድረስ አስገረፈው:: አስደበደበው:: ጭንቅ መከራዎችንም አሳየው:: ቅዱስ ያዕቆብ ግን በፍቅረ ክርስቶስ ጸና::

+በዚህ የተበሳጨው ንጉሡ እንዲቆራርጡት: ግን ቶሎ እንዳይገሉት አዘዘ:: ከዚያ ቀን በሁዋላ በቀን በቀን እየገቡ ከአካሉ ይቆርጡ ጀመር:: ከእጣቶቹ ተነስተው እጆቹን እስከ ክንዱ: እግሮቹን እስከ ታፋው ድረስ ቆረጡ:: መሐል አካሉ (ወገቡና ራሱ) ብቻ ቀረ::

+ይህ ሄሉ ሲሆን እርሱ ጌታን ይቀድሰው: ይጸልይም ነበር:: "የወይን ግንድ ሆይ! እኔን ቅርንጫፍህ አድርገኝ" (ዮሐ. 15:5) ይለው ነበር:: ከአካሉ እየቆረጡ የጣሉትም ሲቆጠር 42 ሆነ:: 43ኛ ደግሞ የተረፈ አካሉ ነበር::
+ያን ጊዜ ሊጸልይ ፈልጐ "ጌታ ሆይ!" ብሎ ጮኸ:: ይህንን አበው:-
"መንፈቀ አካሉ ጸለየ መዊቶ መንፈቁ" ብለው ገልጸውታል:: ግማሽ አካሉ ሙቶ በቀረው ይጸልይ ነበርና ንጉሡም ከጩኸቱ በሁዋላ አንገቱን በሰይፍ ሲያስመታው ጌታችን ወርዶ ታቅፎ ወደ ሰማይ አሳረገው::

+እናቱ: እህቱ: ሚስቱ ይህንን ሲሰሙ እያለቀሱና እየዘመሩ አካሉን ሰብስበው ገንዘውታል:: ሽቱም አርከፍክፈውበታል:: የዚህ ቅዱስ ገዳም (ታቦት) በኢትዮዽያ: ታች አርማጭሆ በሚባለው በርሃ ውስጥ ይገኛል:: ድንቅ የሆነ የበረከት ቦታም ነው::

+"+ አባ ተክለ ሐዋርያት +"+

=>ኢትዮዽያዊው ጻድቅ አቡነ ተክለ ሐዋርያት በ15ኛው መቶ ክ/ዘመን ከተነሱ ዐበይት ጻድቃን አንዱ ናቸው:: በተለይ በጻድቁ ንጉሥ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን በተባሕትዎም: በትሩፋትም እጅግ የተደነቁ አባት ነበሩ::
+ጻድቁ ሲጠሩ "ዘደብረ ጽሙና": አንዳንዴም "ዘገበርማ" እየተባሉ ነው:: ምናልባትም በብዙ ቦታ ላይ ስለ ተጋደሉ በእነዚህ: ቦታዎችም ላይ ስለ ነበሩ ሊሆን ይችላል እንደዚህ ተብለው የተጠሩት::

+በብዛት የሚታወቀው ደግሞ በምድረ ሸዋ: ጐጃምና በምድረ አፋር አካባቢ በመኖራቸው ነው:: እስኪ አንዳንድ ነገሮቻቸውን እናንሳ:-
*ጻድቁ ክርስቶስን በመከራው ይመስሉት ዘንድ ዘወትር ይተጉ ነበር::
*አንዴ ሥጋ ወደሙ የተቀበለ አንድ ሰው በመንገድ ላይ ሲያስመልሰው ተመልከተው ሁሉ ተጸይፎ ሲሸሽ እሳቸው ግን ደስ እያላቸው ተመግበውታል:: ምክንያቱም የእርሳቸው ዓይን የሚመለከተው የፈጣሪን ሥጋና ደም ነው:: በዚህ ጊዜም ጌታ ከሰማይ ወርዶ በግንባራቸው ላይ ፀሐይን ስሎባቸዋል:: በዚህ ምክንየትም ፊታቸው ያበራ ነበር::

*አንዴ ደግሞ በገዳማቸው አንድ ደሮ ለእንግዳ ሊያርዱት ሲሉ "በአባ ተክለ ሐዋርያት ተማጽኛቹሃለሁ!" በማለቱ ትተውታል::
*በአፋር በርሃ አካባቢ ለ14 ዓመታት ኑረዋል::

+በአንድ በአት ውስጥም ለ41 ዓመታት ኑረዋል:: ጻድቁ አቡነ ተክለ ሐዋርያት እንዲህ ተመላልሰው በተወለዱ በ71 ዓመታቸው በዚህች ቀን ዐርፈዋል::

+"+ ቅዱስ ፊልሞና ሐዋርያ +"+

=>ቅዱስ ፊልሞና ከ72ቱ አርድእት አንዱ ሲሆን ብዙ ጊዜ "ጥዑመ-ቃል (አንደበቱ የሚጣፍጥ)" ተብሎ ይጠራል:: በዘመነ ሐዋርያት በጣም ልጅ በመሆኑ እየተሯሯጠ ለአበው ይታዘዝ ነበር::

+ጌታን አምኖ ተከትሎ: ለ3 ዓመት ከ3 ወር ተምሮ: ከቅዱስ መንፈሱ ነስቶ: ከቅዱስ እንድርያስ ጋር ለስብከት ወጥቷል:: ሃገረ ስብከቱም ልዳ ነበረች:: እርሱ ሲያነብ (ሲያስተምር) ሰው ሁሉ በተመስጦ ይሰማው ነበር:: ሊገድሉት የመጡ ወታደሮች እንኩዋ በተደሞ መግደላቸውን ይረሱት ነበር::

+አንዳንድ ቀን ደግሞ ወፎችና ርግቦች ያደምጡት: ያዋሩትም ነበር:: ይህቺ ቀን ለቅዱስ ፊልሞና ዕለተ ዕረፍቱ ናት::

=>አምላከ ቅዱሳን ብርሃናቸውን ያብራልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
=>ኅዳር 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
2.አቡነ ተክለ ሐዋርያት ጻድቅ
3.ቅዱስ ፊልሞና ሐዋርያ
4.ቅዱስ ቀሌምንጦስ ሰማዕት
5.ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሰማዕት
6.አባ ገብረ ዮሐንስ ጻድቅ

=>ወርኀዊ በዓላት

1.ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
2.አቡነ መብዓ ጽዮን ጻድቅ
3.ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ)
4.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮዽያ)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/W-eN0faaHmo

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

----------------------------▷
💥ቅዳሴ ሊጀመር አሃዱ ሲባል ከቤተክርስቲያን ውጪ ያለ ሳይቀር በጆሮው የሰማ ሁሉ ቆሞ ነበር የሚያሳልፈው።
አሁን ደሞ የድፍረት ነገር አሃዱ ሲባል ሞባይላችንን አውጥተን ፎቶ ማንሳት እና ቪድዮ መቅረፅ ጀመርን!

🔥እራሳችንን እንመርምር!
----------------------------▷

✳️🔑ኪነ-ጥበብ🔑✳️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ህዳር 26 እንኳን ለአቡነ ሀብተ ማርያም አመታዊ የእረፍት በዓል አደረሰን

ኢትዮጵያዊው ፆዲቅ አቡነ ሐብተ ማርያም በአገራች ላይ አምስት መቅሰፍቶች ስደርሱብን በሳቸው ስም ተማፅነን እንድተርፍ አምላካቸው ቃል ኪዳን ሰቷቸዋልደ።
/1/መብረቅ
/2/ቸነፍር
/3ረሃብ
/4/ወረርሽኝ
/5/የእሳት ቃጠሉ ናቸው።
እነዚህ በቅሰፍቶች በገራችን ላይ ለይል የላቸውምደ
መዝ 115-:-5
የፆዲቅ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።
የአቡነ ሐብተ ማርያም ቃል ኪዳናቸውና በረከታቸው ይደርብን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/1bEEba_24dg

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/4kJkhRhIivA?si=Hv7ON3W5mYwv6foY

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ እንኩዋን ለታላቁ ሰማዕት "ቅዱስ መርቆሬዎስ (ፒሉፓዴር)" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+*" ቅዱስ መርቆሬዎስ ኃያል "*+

=>ለክርስትና ሃይማኖት የሚከፈል ትልቁ ዋጋ ሰማዕትነት ነውና ቤተ ክርስቲያን ለምስክሮቿ ሰማዕታት ልዩ ክብር አላት:: ከኮከብ ኮከብ እንዲበልጥ ሁሉ ከሰማዕታትም ቅዱስ ጊዮርጊስን እና ቅዱስ መርቆሬዎስን የመሰሉት ደግሞ ክብራቸው በእጅጉ የላቀ ነው::

+ቅዱስ መርቆሬዎስን ብዙ ጊዜ ሊቃውንት "ካልዕ (ሁለተኛው) ሊቀ ሰማዕታት" ሲሉ ይገልጹታል:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+በ2ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ከሮም ግዛቶች በአንዱ (አስሌጥ) ከአባቱና ከሚስቱ ጋር የሚኖር "አሮስ" የሚሉት ሰው ይኖር ነበር:: ሚስቱ ደም ግባት የሠመረላት: እርሱም ደግነት ያለው ሰው ቢሆኑም የሚያመልኩት ግን ጣዖትን ነበር::

+አንድ ቀን አሮስ ሚስቱን ከቤት ትቶ ለአደን ከአባቱ ጋር ወጣ:: እንደ ልማዳቸው ወጥመዱን አስተካክለው ተደበቁ:: የወጥመዱ ደወል ሲያቃጭል: "እንስሳ ተያዘልን" ብለው ሲሯሯጡ ዐይናቸው ያየው ነገር በድንጋጤ እንዲፈዙ አደረጋቸው:: 2 ገጻተ ከለባት በወጥመዱ ውስጥ ተይዘው ነበር::

+እነዚህ ፍጡራን ሰዎች ናቸው:: ግን ባልታወቀ የተፈጥሮ አጋጣሚ እንደዚህ እንደ ሆኑ ይታመናል:: ግን እጅግ ግዙፍ: ከአንገታቸው በላይ እንደ ውሻ: ወገባቸው እንደ ሰው: ጉልበታቸው እንደ አንበሳ ሲሆን ታችኛው እግራቸው የጋለ የናስ ብረት ነው የሚመስል::

+እነዚህን ፍጡራን ሰማያዊ ካልሆነ ምድራዊ ፍጡር አይችላቸውም:: አንበሳና ነብርን እንኩዋ እንደ ጨርቅ በጣጥሰው ይጥሏቸው እንደ ነበር ይነገራል:: ዐይናቸው እንደ እሳት ይነድ ስለ ነበር ማንም ትክ ብሎ ሊያያቸው አይችልም:: ምሥጢራቸውን ግን የሚያውቀው የፈጠራቸው አምላክ ነው::

+ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና:- አሮስና አባቱ ባዩአቸው ጊዜ ደንግጠው ወደቁ:: ገጻተ ከለባቱ የብረት ወጥመዱን እንደ ክር በጣጥሰው የአሮስን አባት በቅጽበት በሉት:: አሮስን ሊበሉት ሲሉ ግን ድንገት ቅዱስ መልአክ ወርዶ በእሳት ሰይፍ አጠራቸው::

+"ከእርሱ የሚወጣ ቅዱስ ፍሬ አለና እንዳትነኩት" አላቸው:: ወዲያውም መልአኩ ያንን ኃይለኝነታቸውን አጠፋው:: በዚህ ጊዜ 2ቱም ወደ አሮስ ሒደው ሰገዱለት:: አሮስም ወደ ቤቱ ወስዶም ደበቃቸውና የሆነውን ሁሉ ለሚስቱ ነገራት::

+ጥቂት ቆይታም ጸንሳ ወለደች:: ልጃቸውን ፒሉፓዴር (ፒሉፓተር) ሲሉ ስም አወጡለት:: ትርጉሙም "መፍቀሬ አብ - የአብ ወዳጅ" ማለት ነው:: ከዚያም አሮስ ሚስቱን : ልጁንና 2ቱን ገጻተ ከለባት ይዞ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሒዶ ተጠመቀ::

+አበው ካህናት እሱን "ኖኅ" : ሚስቱን "ታቦት" : ልጁን ደግሞ "መርቆሬዎስ" ሲሉ ሰየሟቸው:: መርቆሬዎስ ማለትም "ገብረ ኢየሱስ ክርስቶስ - የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ" እንደ ማለት ነው::

+ከዚያም ደስ እያላቸው: ክርስቶስን እያመለኩ: ነዳያንን እያሰቡ: ልጃቸውን መርቆሬዎስን አሳደጉ:: ነገር ግን የገጻተ ከለባት ወሬ በመሰማቱ ንጉሡ "ካላመጣሃቸው" አለው:: ኖኅ ጸልዮ ወደ ኃይለኝነታቸው መልሷቸው ስለነበር ፊታቸው ገና ሲገለጥ ብዙ አሕዛብ በድንጋጤ ሞቱ::

+ንጉሡም ስለ ፈራ ኖኅን የጦር መኮንን አደረገው:: በጦርነት ጊዜም ገጻተ ከለባቱ ኃይላቸው ስለሚመለስ ተሸንፎ አያውቅም ነበር:: አንድ ጊዜ ግን 2ቱን ገጻተ ከለባት ንጉሡ አታሎ ወሰዳቸው:: ሃይማኖታቸውን ሊያስክዳቸው ሲል "እንቢ" በማለታቸው አንዱ ሲገደል ሌላኛው አምልጦ ጠፋ::

+በዚያ ወራትም ኖኅ ለጦርነት ወጥቶ ተማረከ:: ንጉሡ ደግሞ ታቦትን "ላግባሽ" ስላላት የ5 ዓመት ልጇን ቅዱስ መርቆሬዎስን ይዛ ተሰደደች:: በስደት ጥቂት እንደ ቆየች ግን ባሏን ኖኅን አየችው::

+እርሷ ብታውቀውም እርሱ ዘንግቷት ነበር:: በሁዋላ ግን በሕጻኑ መርቆሬዎስ አማካኝነት ማስታወስ በመቻሉ ደስ አላቸው:: በዚያው በሮም ዙሪያ ሳሉም አንዱ ገጸ ከልብ መጥቶ አገኛቸው:: በዚህም ምክንያት በስደት ሃገርም መኮንን ሆኖ ተሾመ::

+በዚያም ቤተ ክርስቲያንን አንጾ: ቤቱን ቤተ ነዳያን አድርጐ ኖኅ ለዓመታት ኖረ:: ቅዱስ መርቆሬዎስ ወጣት ሲሆንም ወላጆቹ ታቦትና ኖኅ ዐረፉ:: እርሱ ከባልንጀራው ገጸ ከልብ ጋር ሆኖ በጾምና ጸሎት ሲኖር ስለ አባቱ ፈንታ የጦር መሪ አደረጉት::

+በጦርነትም እጅግ ኃያል: በሰው ዘንድም ፍጹም ተወዳጅ: የጾምና የጸሎት ሰው ሆነ:: ያን ጊዜ ግን ዳክዮስ ንጉሡ ክርስቶስን በመካዱ ምዕመናን ላይ ሞት ታወጀ:: በጊዜው ደግሞ የበርበር ሰዎች በሮም መንግስት ላይ ጦርነትን በማንሳታቸው ዳኬዎስና ቅዱስ መርቆሬዎስ ለጦርነት ወጡ::

+ነገር ግን በርበሮች እንደ አሸዋ ፈሰው ብዛታቸውን ሲያይ ንጉሡ ደነገጠ:: ለማግስቱ ቀጠሮ ተይዞ ቅዱስ መርቆሬዎስ ሲጸልይ ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ሰይፍ ሰጠው::

+በማግስቱም "ምን ይሻላል?" ሲባል ቅዱስ መርቆሬዎስ "እኔ የክርስቶስ ባሪያ ነኝና ብቻየን እቁዋቁዋማቸዋለሁ" ቢል ሳቁበት::

+እርሱ ግን በጥቁር ፈረሱ (አብሮት ያደገ ነው) ተጭኖ በርበሮችን "ጠብ ይቅርባችሁ: በሰላም ሒዱ" ቢላቸው ተሳለቁበት:: ያን ጊዜም ጸሎት አድርሶ የመልአኩን ሰይፍ ሲመዘው ብዙዎቹ ወደቁ:: ከበርበሮችም ለወሬ ነጋሪነት እንኩዋ የተረፈ አልነበረም::

+ነገሩ በሮም ሲሰማ ታላቅ ሐሴት ሆነ:: ዳሩ ግን ከሃዲው ዳኬዎስ "ድሉ የጣዖቶቼ የነ አዽሎን ነው" በማለቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ሲያዝን አደረ::

+በ3ኛው ቀንም "ለጣዖት ሠዋ" የሚል ትዕዛዝ ከንጉሡ ዘንድ መጣ:: ቅዱሱ ግን ወደ አደባባይ ሔደ:: የክብር ልብሱንና መታጠቂያውን አውልቆ በንጉሡ ፊት ወረወረው::

+"ሃብትከ ወክብርከ ይኩንከ ለኃጉል:: ሊተሰ ክብርየ ክርስቶስ ውዕቱ:: (ለእኔስ ክብሬ ክርስቶስ ነውና ንብረትህ ለጥፋት ይሁንህ)" ሲልም ንጉሡን በአደባባይ ዘለፈው:: ዳኬዎስም በቁጣ እሳት አስነድዶ: የብረት አልጋውንም አግሎ ቅዱስ መርቆሬዎስን በዚያ ላይ አስተኛው::

+ያም አልበቃ:: ወታደሮች እየተፈራረቁ ሲደበድቡት ደሙ ፈሶ እሳቱን አጠፋው:: ለዚያ ነው ሊቃውንት:-
"አመ አንደዱ ላእሌከ ውሉደ መርገም::
እምቅሡፍ አባልከ እንተ ውኅዘ ደም::
አርአያ ዝናም ብዙኅ አጥፍኦ ለፍህም::" ያሉት::

+ከዚያም ወስደው ወኅኒ ቤት ውስጥ ጣሉት:: ክርስቶስን ያስክደው ዘንድ በረሃብ: በግርፋት: በእሳት: በስለትም አሰቃየው:: በመጨረሻ ግን አሰቃይተው እንዲገድሉት ወደ እስያ ሰደደው:: በስፍራውም ብዙ አሰቃይተው ኅዳር 25 ቀን አንገቱን ሰይፈውታል::

+እርሱ ካረፈ በሁዋላም የተባረከ ፈረሱ ለዓመታት ወንጌልን ሰብኩዋል:: አረማውያንንም ከአፉ በወጣ እሳት አጥፍቷል:: ተአምረኛውና ኃያሉ ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ በ200 ዓ/ም እንደ ተወለደ: በ220 ዓ/ም መከራ መቀበል እንደ ጀመረና በ225 ዓ/ም ሰማዕት እንደሆነ ይታመናል::
<<የቅዱሱ ክብር ታላቅ ነው>>

=>አምላከ ቅዱስ መርቆሬዎስ በከበረ ቃል ኪዳኑ ይጠብቀን:: ከርስቱም አያናውጠን:: ከበረከቱም ይክፈለን::

=>ኅዳር 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
2.ቅዱሳን ታቦትና ኖኅ (ወላጆቹ)
3.ቅዱስ ሮማኖስ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/bKZn-92C7EM?si=WsiN85o1R9P4qKir

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🧾ዘፈን ክፉ ነው!
❤ወንድማችን አርቲስት ታምራት ደስታ በአንድ ወቅት አንድ ዘፈን ለአድማጮቹ አብቅቶ ነበር።

ምንድነው ሃሳብ ሁሌ ጭንቀት፣
ወደድንም ጠላን መቼም አይቀርም ሞት፣
እስኪ እንደሰት፣
ሰዎች እንጫወት.......

📺አስታወሳችሁት አደል?
🌟እውነት ለመናገር የሞትን አይቅሬ ያወቀ ሰው እንዴት ልጫወት ብሎ ያስባል?
🌟ሰው ካላሰበ እና ካልተጨነቀ ምን ሊያረግ ይችላል ለቤተሰቦቹ እንኳን መኖር አይችልም እንኳን ለቤተክርስቲያን ።
🌟ሰው ካላሰበ እና ካልተጨነቀ ነገ ቤተክርስቲያንን ለማን ሊያስረክባት ነው?
🌟እንደ ዘፈኑ ከሆነ የደስታው ስፍራ መጠጥ ቤት፣ዳንስ ቤት ........ነው ታድያ ይሄ አይነቱ ዘፈን አገልጋዩን ከቤተክርስቲያን አያስወጣውም ትላላችሁ❗️


❗️ለዘፈን ቦታ አትስጡ....ከሰማችሁ አይቀር ደሞ ከልባችሁ አትስሙ❗️

🌟 ፈፅሞ ግን አትስሙ!


💫🌟❗️ኪነ-ጥበብ❗️🌟💫

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

፧መርጌታ  የባህል ህክምና። 
0985950442
0985950442
ዛሬ ስለአይነ ጥላ ምልክቶች ላካፍላቹሕ ወደድኩ። ዓይነ_ጥላ_ምንድን_ነው ?_ # መንስኤውና_እና # መፍትሔውስ ?ሑሉንም ይዠመጣው
አይነጥላ ምልክቶች ፦
# ትዳር ማስጠላት
# ከጓደኝነት ጀምሮ ምክኒያት አልባ መለያየት
# እራስን ዝቅ አድርጉ ማሰብ (የበታችነት ስሜት )
# ተስፋ መቁረጥ
# ማስለቀስ
# ፀባይ መቀያየር
# ወንድ ልጅን ለማውራት ማፈር
# ባል እየመጣ መመለስ
# ከወንዶችን ስጦታ ሲሰጡ ፈቃደኛ አለመሆን
# ግለ ወሲብ ተጠቃሚ መሆን
# ሕልመ ሌሊት
# እራስን መደበቅ (ቤት አለመውጣት )
# ሱሰኛ መሆን
# የእድል መዘጋጋት
# የወር አበባ መዛባት (መብዛት )
# የፅንስ አለመርጋት (መበተን )
# ማስወረድ (አቦርሽን )
# መጨናነቅ
# ሂጅ ሂጅ ማለት
# ቤተሰብ ማስጠላት
# ስራ ማስጠላት
# ከፍቅር አጋር ጋር ፆታዊ ግንኙነት ማስጠላት
# ከፍተኛ የራስ ህመም
# ተኝቶ መቃዥት
# ፍርሐት
# ከፍተኛ ላብ
# የጠረን መቀየር
# _መጥፎ የአፍ ጠረን
# _በሰው ማሐል ሐሳብን መግለፅ አለመቻል
# _በስራ ቦታ የስራ እድገት ማጣት
# _ከስራ መባረር ወዘተ
የመሳሰሉት የዓይነጥላ ምልክቶች ናቸው
ዛሬ # _ሕልመ ሌሊት
# _ሴት ዓይነ ጥላ
# _ወንድ ዓይነ ጥላ
# _ሴት ዛር
# _ወንድ ዛር እናያለን
ከዝሙት አጋንንት እና ከዝንየት በተጨማሪ በሕልመ ሌሊት የሚፈትነን ክፉ አጋንንት
የትኛው ነው?
ሴት ዓይነ ጥላ ያለችበት ወንድ በሕልመ ሌሊት መከራውን ነው የምታበላው፡፡
ዓይነ ጥላዋ ስለምትቀናና ስለምትወደው ሌሊት እየመጣች በተኛበት ትገናኘዋለች፡፡ እጅግ
የሚያጸይፈው ደግሞ ሴት ዓይነጥላ ወንድን
የምትፈትነው
# _በእናቱ
# _በእህቱ
# _በአክስቱ
# _በዘመዱ
# _በሥራ ባልደረባው
# _በሚያውቃት እና በማያውቃት ሴት እየተመሰለች በሕልመ ሌሊት ትመታዋላች፡፡
አንዳንዱ ላይ ባስ ስትል # በእንስሳት እየተመሰለች ትፈትነዋለች፡፡
ብዙ ወንዶች ሌሊት በተኙበት ከሴት ጋር ገሃድ የሚመስል ግንኙነት ሲፈጽሙ
ቀለል ስለሚያደርጉት፤ ባስ ካለም ፈተና እንጂ ሴት ዓይነ ጥላ መሆንዋን
አያውቁም፡፡
ዓይነ ጥላዋ ወንድን በሴት አምሳል እየመጣች ሁሌ የምትፈትነው
ከሆነ የችግሩ ሰለባ የሆነው ሰው # በመንፈሳዊ ሕይወቱ ታዝለዋለች
# _ጸሎት ታስተወዋለች
# _ከቤተ ክርስትያን
# _ከጸበልታስቀረዋለች
# _በሆነው ባልሆነው ዘሩን በማፍሰስ ዘሩን ደካማ ታደግበታለች፡፡
# የመውለድ እድሉን ታጠብበታለች #ሲብስም ልጅ እንዳይወልድ ታደርገዋለች
# _ለመካንነት ትዳርገዋለች፡፡
ወንድ ዓይነ ጥላ ያለባቸው ወይም የሚያንዣብብባቸው ሴቶች በሕልመ ሌሊት
ይመታሉ፡፡
የሴቶች ከወንዶች የሚለየውና የሚከፋው ዓይነ ጥላው እንደ ባል
አድርጓቸው እጮኛና ትዳር እንዳይዙ ከማድረጉ ባሻገር ሌሊት እየመጣ
በሚገናኛቸው ወቅት ዓይነ ጥላዊ መርዙን በማህጸናቸው በማስቀመጥ
እንደ ጽንስ ሆኖ ሊቀመጥ መቻሉ ነው፡፡
በዚህም ሴቶቹ እጮኛ አይዙም፣ትዳር
አይመሠርቱም ምናልባት ትዳር ቢይዙም ትዳራቸውን በተለያየ ምክንያት
መበጥበጡ እንዳለ ሆኖ ማህጸናቸውን በመዝጋት ለልጅ አልባነት ሊዳርጋቸው
ይችላል፡፡
ማህፀናቸውና አፍረታቸው ላይ በመቀመጥም የሩካቤ ፍላጎታቸውን
በመግደል፣የሴትነት ስሜታቸውን በማጓደል ደመ ቀዝቃዛ ያደርጋቸዋል፡፡
ወንድ ዓይነ ጥላው ልክ ወንዶቹን እንደሚፈትነው ሁሉ ሴቶቹንም፦
# _በአባታቸው
# _በወንድማቸው
# _በአጎታቸው
# _በቅርብ ዘመዳቸው
# _በሚያውቁትና በማያውቁት ሰው እየተመሰለ ይገናኛቸዋል፡፡
ዓይነ ጥላውም ይህንን ልምድ
ያደርገውና ሴቶቹን የሌሊት መጠቀሚያው ያደርጋቸዋል፡፡
ዓይነ ጥላው አንዳንዶቹን ገና ብቅ ሳይሉ፣ምኑንም ሳይለዩ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●
🔐በጣም የሚገርሙኝ ሰዎች እነዚህ ናቸው.......

🎀መኖርያ ስፍራቸው ቤተክርስቲያን አካባቢ የሆነ ነገር ግን እንኳን ለቅዳሴ ለማታ መርሐ ግብር እንኳን ቤተክርስቲያን የማይሄዱ።

ግን ማነው አዚም ያረገብን❗️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለቅዱሳን ሰማዕታት ቆዝሞስና ድምያኖስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱሳን ቆዝሞስ ወድምያኖስ †††

††† እስኪ ዛሬ ስለ ክርስትናና ወጣትነት እነዚህን ቡሩካን ወንድማማች ክርስቲያኖች መሠረት አድርገን ጥቂት እንመልከት:: ከዚህ በፊት የበርካታ ወጣት ሰማዕታትን ዜና ሰምተናል:: መጽሐፍ እንደሚል "ወኩሉ ዘተጽሕፈ ለተግሣጸ ዚአነ ተጽሕፈ" - "የተጻፈው ሁሉ እኛ ልንማርበት: ልንገሠጽበት ነውና" (ሮሜ. 15:4) ልናስተውል ይገባናል::

††† ዜና ቅዱሳን የሚነገረን እንደ ታሪክ እንዲሁ ሰምተን እንድናልፈው አይደለም::

1.ከልቡ ለሚሰማው (ለሚያነበው) በረከት አለው::

2.ከቅዱሱ (ቅድስቷ) ቃል ኪዳን በእምነት ተካፋይ መሆን ይቻላል::

3.ቅዱሳኑ ክርስትናቸውን ያጸኑበት: የጠበቁበትና ለሰማያዊ ክብር የበቁበትን መንገድ እንማርበታለን:: ትልቁም ጥቅማችን ይሔው ነው::

ቁጥራችን ቀላል የማይባል የተዋሕዶ ልጆች ሕይወተ ቅዱሳንን እንደ ተራ ታሪክ ወይ ጀምረን እንተወዋለን:: ምናልባትም በግዴለሽነት እናነበዋለን:: ደስ ሲለንም ምስሉ ላይ 'like' የምትለውን ተጭነን እናልፈዋለን::

አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በደንብ አንብበን "ወይ መታደል!" ብለን አድንቀን እናልፋለን:: ማድነቃችንስ ጥሩ ነበር:: ግንኮ ቅዱሳኑ ለዚህ የበቁት የታደሉ ስለ ሆኑ ብቻ አይደለም:: ከእነርሱ የሚጠበቀውንም በሚገባ ሥለ ሠሩ እንጂ::

እግዚአብሔር የሚያዳላ አምላክ አይደለም:: "ኩኑ ቅዱሳነ እስመ ቅዱስ አነ-እኔ ቅዱስ እንደሆንኩ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ" (ዘሌ. 19:2, 1ጴጥ. 1:15) ብሎ የተናገረው ለጥቂት ወይም ለተለዩ ሰዎች አይደለም:: በስሙ ለሚያምኑ ሁሉ ነው እንጂ::

ስለሆነም እኛ ክርስቲያኖች: በተለይም ወጣቶች ከቀደምቶቻችን ተገቢውን ትምሕርት ወስደን ልንጸና: ልንበረታ: ለቤተ ክርስቲያናችንም "አለሁልሽ" ልንላት ይገባል:: ዛሬ እናት ቤተ ክርስቲያን በተለይ በከተሞች የወላድ መካን እየሆነች ነው::

"ይህን ያህል ሚሊየን ሰንበት ተማሪና ወጣት አላት" ይባላል:: ሲፈተሽ ግን በትክክለኛ ቦታው የሚገኘው ከመቶው ስንቱ እንደ ሆነ ለመናገርም ያሳፍራል:: የሆነውስ ሆነ: መፍትሔው ምንድነው ብንል:- እባካችሁ ከቅዱሳን ቀደምት ክርስቲያኖች መሥራት ያለብንን ቀስመን: ከዘመኑ ጋር አዋሕደን (ዘመኑን ዋጅተን) ራሳችንን: ቤተ ክርስቲያንንና ሃገራችንን እንደግፍ:: ካለንበት ያለማስተዋል አዘቅትም እንውጣ::
ለዚህም ቁርጥ ልቡና እንዲኖረን አምላካችን ይርዳን ብለን ወደ ቅዱሳኑ ዜና ሕይወት እንለፍ::

ቅዱሳን ቆዝሞስና ድምያኖስ በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ በምድረ ሶርያ ተወልደው ያደጉ የዘመኑ ክርስቲያኖች ናቸው:: አባታቸው በልጅነታቸው በማረፉ 5 ወንድ ልጆችን የማሳደግ ሃላፊነት በእናታቸው ትክሻ ላይ ወደቀ:: እናታቸው ቅድስት ቴዎዳዳ ትባላለች::

እጅግ የምትገርም: ቡርክት እናት ናት:: አምስቱ ልጆቿ "ቆዝሞስ: ድምያኖስ: አንቲቆስ: አብራንዮስና ዮንዲኖስ" ይባላሉ:: በእርግጥ ለአንዲት እናት የመጀመሪያ ጭንቀቷ "ልጆቼ ምን ይብሉ" ነው:: ለቅድስት ቴዎዳዳ ዋናው ጉዳይ ይሔ አልነበረም::

ጌታችን እንዳስተማረን "ኢትበሉ ምንተ ንበልእ: ወምንተ ንሰቲ: ወምንተ ንትከደን - ምን እንበላለን: ምን እንጠጣለን: ምንስ እንለብሳለን ብላችሁ አትጠጨነቁ" ብሏልና ዘወትር የምትጨነቀው ስለ ልጆቿ ሰማያዊ ዜግነት ነበር:: (ማቴ. 6:31)

በዚህም ምክንያት አምስቱም ልጆቿን ዕለት ዕለት ወደ ቤተ እግዚአብሔር ትወስዳቸው: ከቅዱስ ቃሉ ታሰማቸው: መንፈሳዊ ሕይወትን ታለማምዳቸው ነበር:: አምላክ ከእኛ የሚፈልገው በጐ ፈቃዳችንንና በቅንነት የሆነች ትንሽ ጥረታችንን ነውና ቅድስት ቴዎዳዳ ተሳካላት:: ልጆቿ በአካልም: በመንፈሳዊ ሕይወትም አደጉላት::

ዘመኑ እንደ ዛሬ ተድላ ሥጋ የበዛበት ሳይሆን ክርስቲያን መሆን ለሞት የሚያበቃበት ነበር:: ከዚህ በፊት እንደ ተመለከትነው ከክርስቶስ ልደት 275 ዓመታት በኋላ በሶርያና በሮም የነገሡት ሁለቱ አራዊት (ዲዮቅልጢያኖስና መክስምያኖስ) ክርስቲያኖችን ከዋሉበት አላሳድሩ: ካደሩበትም አላውሉ አሉ::

ቀዳሚ ፈተናዋን በሚገባ የተወጣችው ቅድስት ቴዎዳዳ ይህኛውንም ትጋፈጠው ዘንድ አልፈራችም:: ግን ከልጆቿ ጋር መመካከር ነበረባትና ለውይይት ተቀመጡ:: ሦስቱ ልጆቿ ከልጅነታቸው ጀምረው ሲሹት የነበረውን ምናኔ መረጡ::

ቅድስቷ እናት በምርጫቸው መሠረት ቅዱሳን አንቲቆስ: ዮንዲኖስና አብራንዮስን መርቃ ወደ በርሃ ሸኘች:: እርሷም ከሁለቱ ቅዱሳን ልጆቿ ቆዝሞስና ድምያኖስ ጋር ቀረች::

እነዚህ ቅዱሳን በከተማ የቀሩት ግን ዓለም ናፍቃቸው አይደለም:: በእሥራት መከራን የሚቀበሉ የእግዚአብሔርን ቅዱሳን ያገለግሉ ዘንድ ነው እንጂ::

ቅድስት ቴዎዳዳ በቤቷ ነዳያንን ስትቀበልና ስታበላ ሁለቱ ቅዱሳን ልጆቿ ቀኑን ሙሉ እየዞሩ እሥረኞችን (ስለ ክርስቶስ የታሠሩትን) ሲጠይቁ: ሲያጽናኑ: ቁስላቸውን ሲያጥቡ አንጀታቸውንም በምግብ ሲደግፉ ይውሉ ነበር::

ይሕ መልካም ሥራቸው ለፈጣሪ ደስ ቢያሰኝም አውሬው ዲዮቅልጢያኖስን ግን ከመጠን በላይ አበሳጨው:: ወዲያውኑ ተይዘው እንዲቀርቡለት አዘዘ:: በትዕዛዙ መሠረትም ቆዝሞስና ድምያኖስ ታሥረው ቀረቡ::

"እንዴት ብትደፍሩ ትዕዛዜን ትሽራላችሁ! አሁንም ከስቃይ ሞትና ለእኔ ከመታዘዝ አንዱን ምረጡ" አላቸው:: ቅዱሳኑ ምርጫቸው ግልጽ ነበር:: ከክርስቶስ ፍቅር ከቶውኑ ሊለያቸው የሚችል ኃይል አልነበረምና:: (ሮሜ. 8:36)

ንጉሡም "ግረፏቸው" አለ:: ልብሳቸውን ገፈው: ዘቅዝቀው አሥረው: በብረትና በእንጨት ዘንግ ደበደቧቸው:: ደማቸውም መሬት ላይ ተንጠፈጠፈ:: እነርሱ ግን ፈጣሪን ይቀድሱት ነበር::

ይህ ዜና ፈጥኖ ወደ እናታቸው ደርሶ ነበርና ቅድስት ቴዎዳዳ እየባከነች ወደ ሰማዕታት አደባባይ ሮጠች:: አንዲት እናት ልጆቿ በአደባባይ ተሰቅለው ደማቸው ሲንጠፈጠፍ ስታይ ምን ሊሰማት እንደሚችል የሚያውቅ የደረሰበት ብቻ ነው::

ግን ክብራቸውን አስባ ተጽናናች:: ፈጥናም በሕዝቡ መካከል ስለ ሰነፍነቱ ከሀዲውን በድፍረት ዘለፈችው:: ንጉሡም በቁጣ አንገቷን በሰይፍ አስመታት:: ሁለቱ ቅዱሳን ይህንን በዓይናቸው አዩ:: አንዲት ነገርንም ተመኙ:: የእናታቸውን አካል የሚቀብር ሰው::

ግን ደግሞ ሁሉ ስለ ፈራ የቅድስቷ አካል መሬት ላይ ወድቆ ዋለ:: ያን ጊዜ ተዘቅዝቆ ሳለ ቅዱስ ቆዝሞስ አሰምቶ ጮኸ:: "ከእናንተ መካከል ለዚህች ሽማግሌ ጥቂት ርሕራሔ ያለው ሰው የለም?" ሲልም አዘነ:: ድንገት ግን ኃያሉ የጦር መሪ ቅዱስ ፊቅጦር ደረሰ::

ሰይፉን ታጥቆ: በመካከል ገብቶ የቅድስቷን አካል አነሳ:: በክብር ተሸክሞም ወስዶ ቀበራት:: በመጨረሸ ግን የሦስቱ ወንድሞቻቸው ዜና በመሰማቱ ከበርሃ በወታደሮች ተይዘው መጡ:: ከዚያም በብዙ መከራ አሰቃይተው በዚህች ቀን አምስቱንም አሰልፈው ገደሏቸው:: የክብር ክብርንም ከእናታቸው ጋር ወረሱ::

††† አምላከ ሰማዕታት ከትእግስታቸው: ከጽናታቸውና ከበረከታቸው ያሳትፈን::†††

ኅዳር 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱሳን ቆዝሞስ ወድምያኖስ (ሰማዕታት)
2.ቅድስት ቴዎዳዳ (እናታቸው)
3.ቅዱሳን አንቲቆስ: ዮንዲኖስና አብራንዮስ (ወንድሞቻቸው)
4."311" ሰማዕታት (የነ ቆዝሞስ ማኅበር)

Читать полностью…
Subscribe to a channel