kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

💥ስነ-ግጥም
እምነቴን አልክድም
፡፡፡'፠፠፠፠፠ ፠፠፠፠፠፡፡፡፡
ሃይማኖት አንድት ናት የሕይወት ጎዳና፣

ጻድቃን የሄዱባት መንገዷ የቀና፣

ይህቺ ናት እምነቴ የሰጠኝ ክርስቶስ፣

ከአበው የአገኘዋት እምዬ ኦርቶዶክስ።

ቢርበኝ ቢጠምኝ ዘመድ እንኳ በአጣ፣

ክፉውን አልፈራም የመጣው ቢመጣ።

መስቀሉ ሃይሌ ነው አለ በልቤ ላይ፣

እናቴም ማርያም ናት አገሬም በሰማይ።

የአንገቴ ማህተም የአሰርኩት ጥቁር ክር፣

ስለ ተዋሕዶ ይናገራል ምስጢር።

እናም አልበጥስም ማኅተቤን ከአንገቴ፣

ብኩርናዬ እኮ ናት ኦርቶዶክስእነቴ።

የደሙን መሰረት ተዋሕዶን ጥዬ፣

እንደት ፍልስፍናን ልመን እውነት ብዬ።

የመሠረተውን ማንም ሰው ተነሰቶ፣

እንደት ይታመናል ፍልስፍና ከቶ።

ሃይማኖቴን ክጄ ገነትን ከማገኝ፣

ኦርቶዶክስ ሆኜ አምላክ ይኮንነኝ።

እምነቴን ከምክድ ለገንዘብ ለእንጀራ ፣

ይቅርብኝ መክበሩ ስሜም አይጠራ፣

ጓዳዬ ሳይሞላ ኑሮየ ሳያምር፣

ከአባ መቃብር ላይ ከዋሻው ልቀበር፣

ነፍስ ያስምራልና የቃል ኪዳኑ አፈር፡፡

በክብር ከምለብስ የሳኦልን ካባ፣

ሌጦው ይሻለኛል የአባቶቼ ዳባ።

ከእነርሱ አልላይም ማንም ሰው አይለዬኝ፣

የስባአር አጽማቼው እሾህ ሆኖ ይውጋኝ።

ያአመንኩት እውነት ነው አልጠራጠርም፣

እሞታለሁ እንጂ እምነቴን አልክድም።

ከሰማእታቱ ከጻድቃኑ ሕይወት፣

ይሄን ነው ያማውቀው ስለ ስሙ መሞት።

----------
ኢየሩሳሌም (ተዋሕዶ) ሆይ፥ ብረሳሽ፥ ቀኜ ትርሳኝ። ባላስብሽ፥ ምላሴ በጕሮሮዬ ይጣበቅ፤
(መዝ ፻፴፯፥፭)


👇👇
💥🔍ኪነ-ጥበብ🔎💥

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/zikirekdusn
✝✝††† እንኳን ለቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ †††

††† ቅዱሱ ሐዋርያ ተወልዶ ያደገው በቤተ ሳይዳ አካባቢ ሲሆን የሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ትንሽ ወንድም ነው:: አባቱም ዮና ይባላል:: ገና ከልጅነቱ ጀምሮ አሣ ማጥመድን ከትልቅ ወንድሙ ተምሯል:: እድሜው ከፍ ባለ ጊዜ ኦሪትን ተምሮ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሆኗል::

ከእርሱም እያገለገለ ለ6 ወራት ተምሯል:: በወቅቱ ከወንጌላዊው (ወልደ ዘብዴዎስ) ዮሐንስ ጋር ቅርብ ባልንጀራም ነበር:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተጠመቀ ጊዜ ያን ድንቅ ምሥጢረ ሥላሴ ከተመለከቱትም አንዱ ነው::

ጌታ ከጾም (ከገዳመ ቆረንቶስ) በተመለሰ ጊዜ እንድርያስ መንፈስ ቅዱስ አነሳስቶት ተከትሎታል:: መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ "ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ዘያዐትት ኃጢአተ ዓለም - የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ እነሆ" ማለቱን ሰምቶ ቅዱስ እንድርያስ ጌታን ተከተለ::

በዚህም የመጀመሪያው የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ለመባል በቃ:: (ዮሐ. 1:47) ሊቁ ማር ገላውዴዎስም እመቤታችንን ሲያመሰግናት:-
"ለሐዋርያ እንድርያስ ቀዳማዊ ማርያም ሃይማኖቱ::
(ለመጀመሪያው ሐዋርያ ለእንድርያስ ሃይማኖቱ ማርያም አንቺ ነሽ)" ብሏል:: (መልክዐ ስዕል)

ቅዱሱ ሐዋርያ ስሉጥ (ፈጣን) አገልጋይ እንደ ነበርም ወንጌል ይነግረናል:: (ዮሐ. 6:9, 12:22) ለ3 ዓመታት ከ3 ወራት ከጌታ እግር ሥር ተምሮ: በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀበሎ ምን ሃገረ ስብከቱ ልዳ ብትሆን ብዙ አሕጉረ ዓለምን ሰብኳል::

ሐዋርያው ከጌታ ጋር በመርከብ ውስጥ ተነጋገረና ቅዱስ ማትያስን ሰውን ከሚበሉ ሰዎች እጅ አዳነ:: ቅዱስ እንድርያስ 30 ቀናት የሚፈጅ የባሕር ላይ ጉዞ ለማድረግ ከአርድእቱ ጋር ወደ ወደብ ቢሔድም መርከበኞች ሁሉ አናሳፍርም በማለታቸው የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወጣት መርከበኛ መስሎ ሐዋርያውንና አርድእቱን የሠላሳውን ቀን መንገድ በሰዓታት ልዩነት እንዲጨርሱ አድርጓል::

ቅዱስ እንድርያስም እንዲሁ ሰው መስሎት ለጌታችን ስለ ጌታችን ሰብኮለታል:: መርቆታልም:: መርከበኛው ጌታችን መሆኑን ሲያውቅም ደንግጦ አልቅሷል::

¤"ሶበ አእመረ ኪያሁ ወጠየቀ አምሳሎ::
ዘተናገርኩ በድፍረት ምስሌከ ኩሎ::
ሥረይ ሊተ ጌጋይየ ወኅድግ ይቤሎ::" እንዲል "ማረኝ?" ብሎታል:: ጌታችንም "አይዞህ እኔ ካንተ ጋር ነኝ" ብሎታል::

እንድርያስ ማለት "ተባዕ" (ደፋር: ብርቱ) ማለት ነው:: ድፍረት ሥጋዊ: ድፍረት መንፈሳዊ አለና:: "ድፍረት ሥጋዊ" በራስ ተመክቶ ሌሎችን ማጥቃት: ለጥቃትም ምላሽ መስጠት ነው::

"ድፍረት መንፈሳዊ" ስለ ክርስቶስ: ስለ ቀናችው ሃይማኖት ሲሉ በራስ ላይ መጨከን: ራስን አሳልፎ መስጠት: መከራንም አለመሰቀቅ ነው:: ይሕንንም አበው "ጥብዓት" ይሉታል::

ቅዱስ እንድርያስም ለጊዜው በቤተ እሥራኤል መካከል ደፋር የነበረ ሲሆን ለፍጻሜው ግን እስከ ሞት ደርሶ ስመ ክርስቶስን በድፍረት ገልጧልና "ተባዕ (ደፋር)" ይለዋል::
"ዘኢያፍርሃከ ምንተ መልአከ ዓመጻ ጽኑዕ::
አንተኑ እንድርያስ ተባዕ" እንዲል:: (መልክዐ ዓቢየ እግዚእ)

የቅዱስ እንድርያስ ሃገረ ስብከቱ ልዳ (ልድያ) ናት:: ይህቺን ሃገር: አስቀድሞ ሊቀ ሐዋርያቱ (ትልቅ ወንድሙ) ቅዱስ ጴጥሮስ አስተምሮባታል:: ቅዱስ ጴጥሮስ ወደ ሮም ሲዘልቅ ቅዱስ እንድርያስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ገብቶ ብዙ ደክሞባታል::

በቀደመው ዘመን ልዳ እንደ ዛሬው ትንሽ ሃገር አልነበረችም:: ቅዱሱ ሐዋርያ ወደ ቦታው ገብቶ: ስመ ክርስቶስን ሰብኮ ብዙዎችን ቢያሳምንም የጣዖቱ ካህናት ግን ተበሳጩ:: በእርግጥ እነርሱ የሚያጥኗቸው ድንጋዮች አማልክት እንዳልሆኑ ጠንቅቀው ያውቃሉ::

ነገር ግን ከብረው: ገነው: ባለ ጠጐችም ሆነው የሚኖሩበት ሐሰት እንዲገለጥ አይፈልጉምና እውነትን ከመቀበል ሐዋርያቱን ማሳደዱን ይመርጡ ነበር:: አሁንም የልዳ ከተማ ሕዝብ ማመናቸውን ሲሰሙ በቁጣ ሠራዊት ሰብስበው: ጦርና ጋሻን አስታጥቀው: ሐዋርያውን ያጠፉ ዘንድ እየተመሙ መጡ::

ቅዱስ እንድርያስ ይህንን ሲያውቅ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል "ጥዑመ-ቃል" የሚባለውን ቅዱስ ፊልሞናን (ኅዳር 27 ቀን ያከበርነውን ማለት ነው) ጠርቶ የቅዱስ ዳዊትን መዝሙር ገልጦ ምዕራፍ (113:12) ላይ ሰጠውና "ጮክ ብለህ አንብብ" አለው::

††† ቅዱስ ፊልሞናም በቅዱስ መንፈሱ ተቃኝቶ ያነብ ጀመር::
"አማልክቲሆሙ ለአሕዛብ ዘወርቅ ወዘብሩር::
ዓይን ቦሙ ወኢይሬእዩ::
እዝን ቦሙ ወኢይሰምዑ::
አንፍ ቦሙ ወኢያጼንዉ . . .
የአሕዛብ አማልክት ከወርቅና ከብር የተሠሩ ናቸው::
ዓይን አላቸው: ግን አያዩም::
ጆሮ አላቸው: ግን አይሰሙም::
አፍንጫ አላቸው: ግን አያሸቱም . . ." አለ::

በፍጻሜውም "ከማሁ ለይኩኑ ኩሎሙ እለ ገብርዎሙ / የሚሰሯቸው ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ" ብሎ ጸጥ አለ:: ይህንን የሰሙት ካህናተ ጣዖትና ሠራዊታቸው የልባቸው መታጠቂያ ተፈታ:: በደቂቃዎችም የመንፈስ ቅዱስ ምርኮኛ ሆነው በቅዱስ እንድርያስ ፊት ሰገዱ::

እርሱም አጥምቆ ወደ ምዕመናን ማኅበር ቀላቀላቸው:: አንድ ጊዜ ደግሞ ከልዳ አውራጃዎች በአንዱ እንዲህ ሆነ:: በጨዋታ ላይ ሳሉ የክርስቲያኑ ልጅ የአሕዛቡን ቢገፈትረው ወድቆ ሞተ::

የሟቹ አባትም የገዳዩን አባት ዮሐንስን (ቀሲስ ነው) "ልጅህን በፈንታው እገድለዋለሁ" አለው:: ቀሲስ ዮሐንስ ግን "ለመምሕሬ ለእንድርያስ እስክነግር ድረስ ታገሠኝ" ብሎ ሒዶ ለሐዋርያው ነገረው::

በወቅቱ ቅዱስ እንድርያስ የወንጌል አገልግሎት ላይ ስለ ነበር ቅዱስ ፊልሞናን ላከው:: ፊልሞና ወደ አካባቢው ሲደርስ ሁከት ተነስቶ አገረ ገዢው ሕዝቡን ይደበድብ ነበርና ቀርቦ ገሠጸው:: "የተሾምከው ሕዝቡን ልታስተዳድርና ልትጠብቅ ነው እንጂ ልታሰቃይ አይደለም" ስላለው አገረ ገዥው ቅዱሱን አሰቀለው::

ተሰቅሎም ሳለ ይገርፉት ነበርና አለቀሰ:: ምክንያቱም ቅዱስ ፊልሞና ሕጻን ነበርና:: በዚህ ጊዜ ሕዝቡ ሲያለቅሱለት ቁራ: ወፍና ርግብ ቀርበው አጽናኑት:: ከእነርሱም መርጦ ርግብን ወደ ቅዱስ እንድርያስ ላካት::

ርግብ በሰው ልሳን ስትናገር የሰማት አገረ ገዢው ተገርሞ ቅዱሱን ከተሰቀለበት አወረደው:: ሰይጣን ግን በብስጭት በመኮንኑ ሚስት አድሮ ልጁን አስገደለበት:: በሃዘን ላይ ሳሉም ቅዱስ እንድርያስ ደረሰ::

በመኮንኑ ሚስት ያደረውን ሰይጣንን ወደ ጥልቁ አስጥሞ የሞተውን አስነሳው:: መጀመሪያ የሞተውን ሕጻን ደግሞ ፊልሞና አስነሳው:: በእነዚህ ተአምራትም መኮንኑ: ሕዝቡና ሠራዊቱ በክርስቶስ አምነው ተጠመቁ::

ቅዱስ እንድርያስ በእድሜው የመጨረሻ ዘመናት ከልድያ ወጥቶ በብዙ አሕጉራት አስተማረ:: ስሟ ባልተጠቀሰ አንዲት ሃገር ውስጥ ግን በእሳት ሊያቃጥሉት ሲሉ እሳት ከሰማይ ወርዳ በላቻቸው::

ድጋሚ ሌሎች ይዘው አሰሩት: ደበደቡት አሰቃዩት:: በሌሊትም ጌታ መጥቶ አጽናናው:: ታኅሣሥ 4 ቀን በሆነ ጊዜም ወደ ውጭ አውጥተው: ወግረውና ሰቅለው ገድለውታል::

¤እኛም እንደ አባቶቻችን:-
"እዜምር ለከ ወእየብብ በሃሌ ሉያ::
አንቅሃኒ እምሐኬትየ እንድርያስ ሐዋርያ::
ከመ በእዴከ ነቅሐት እሙታን ልድያ::" እያልን ቅዱሱን እንጠራዋለን:: (አርኬ ዘታኅሣሥ 4)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✅ስነጽሑፍ - ግጥም!
እውነት_አለቀሰች!
............................................
ልብ ያለህ አስተውል ጆሮ ያለህ ስማ
እግርህ እንዳይገባ ከክህደት ከተማ።
የያዝከውን አጽና ልብህ አይጨነቅ
ለጥያቄህ መልስም ሊቃውንትን ጠይቅ።

ለእውነት የቆመ ሃይማኖቱን የሚያውቅ
ንባብ ትርጓሜን ጠንቅቆ የሚዘልቅ
ተናገር ዩሐንስ አንተ ልሳነ ወርቅ።
ቄርሎስን ጠይቀው የተዋህዶን ምስጢር
የክርስቶስ ነገር እንዴት እንደነበር።
ከብሉይ ከሐዲስ በማቀነባበር
እንዳመሰጠረው በብዙ ምስክር።

ነቢዩ ኢሳያስ ብርሃነ ዓለም ጳውሎስ
መዝሙረኛው ዳዊት ሐዋርያው ሉቃስ
አባ ዝክረ ማርያም ወአባ ጴጥሮስ
የስነ ዘፍጥረት ሊቅ ኤጲፋኒዮስ
ዝም አትበል ተናገር ቅዱስ ሳዊሮስ
በሥጋው ማክበሩን አምላክ ክርስቶስ።

ጊዮርጊስ ተናገር አንተ የጥዋት ጮራ
ክርስቶስ መሲሕም ተብሎ እንደሚጠራ።
ወልድ ቅብዕ በማለት ክህደት አስተማሩ
የሥግው ቃል ነገር መች ገባቸው ዳሩ
የተዋሕዶ ምስጢር ሳይገባቸው ቅሉ
ሃይማኖት ከምስጢር ይደባልቃሉ።

ክርስቶስ በሥጋ እንደሞተ ሲያውቁ
በሥጋስ መክበሩን እንዴት አላወቁ
ሊቃውንት እያሉ ለምን አይጠይቁ
በተዋሕዶ ከበረ ብለው ሲናገሩ
ለዚህ ብሂላቸው የታል ምስክሩ።

ግብርን በማፋለስ አንድ ገጽ ካለው ከሰባልዮስ
አንድነትን ትቶ ሁለት አካል ካለው ከእርጉም ንስጥሮስ
መንፈስ ቅዱስ ሕጸፅ ካለው ከመቅዶንዮስ
ወልድ ፍጡር ካለው ከእርጉም ከአርዮስ
የዚህ ክህደቱ በምንም አያንስ።

ፈላጊዋ ጠፍቶ እውነት አለቀሰች
ግብራቸው ተቃርኖ ሀሰት ጥላት ሄደች።
ዳሩ ግን ወገኔ ይህ ክህደት ነውና
ቀኑ ሳይመሽብህ መንገድህን አቅና
እውነትን ከፈለክ ታገኛለህና
እረፍት ስላላት የህይወት ጎዳና
የያዝከውን ይዘህ በሃይማኖት ጽና።

❗️ወስብሐት ለእግዚአብሔር❗️
👇👇
🔍ኪነ-ጥበብ🔎
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

መሪጌታ የባህል መድህኒት ፈውስ እና ጥበብ ይፈልጋሉ:0908465919
በውጭ ሀገር ለሚኖሩም ሆነ በሀገር ውስጥ ላሉ በተለያየ ችግር መጥተው ማሰራት ለማይችሉ መምጣት ሳያስፈልግ ባሉበት እንሰራለን 
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
1 ለመፍትሄ ሀብት
2 ለህማም
3 ለመስተፋቅር
4 ቡዳ ለበላው
5 ለገበያ
6 የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር)
8 ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 ለዓቃቤ ርዕስ
10 ለመክስት
11 ለቀለም(ለትምህርት)
12 ሰላቢ የማያስጠጋ
13 ለመፍትሔ ስራይ
14 ጋኔን ለያዘው ሰው
15 ለሁሉ ሠናይ
16 ለቁራኛ
17 ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
18 ለመድፍነ ፀር
19 ሌባ የማያስነካ
20 ለበረከት
21 ለከብት መስተሐድር(ከብት እንደረይጠፋ)
22 አፍዝዝ አደንግዝ
23 ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
24 ለግርማ ሞገስ
25 መርበቡተ ሰለሞን
26 ለዓይነ ጥላ
27 ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ
28 ለሁሉ መስተፋቅር
29 ጸሎተ ዕለታት
30 ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
31 ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
32 ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ
33 ለድምፅ
34 ለብልት
35 በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ሰወች ደግሞ ከምንሰራቸው ስራዎች በጥቂቱ

                         ከሀገር ውጪ ለሚኖሩ

1የመኖሪያ ፍቃድ ላላገኙ ሙሉ ስማቸውን ብቻ በመላክ በምንሰራው ስራ በጥቂት ቀናት መፍትሄ እንሰጣለን ለዚህም ብዙ ምቅክሮች አሉ
2. ከሀገር ውጪ ሆነ በሀገር ውስጥ የስራ እድል ላጡ
3. ንግድ ጀምረው[ሱቅ ከፍተው] አልሳካ ላላቸው
4. ገንዘብ ለሚያባክኑ ገንዘብ አልበረክት ላላቸው
5. ሰውፊት መቆም መናገር ለሚፈሩ በጥቂት ጊዜ ውስጥ በምንሰራው ሰራ ደፋርና በራስ የመተማመን ችሎታ እንዲኖሮት እናደርጋለን
6. ለሀብት ለገንዘብ ለንብረት ሚሆንም አለን
7. ለስንፈተ ወሲብ መፍትሄ  የረጅም አመት ልምድ አለን ለውጪ ሀገር ለሚኖሩትም እየሰራን ነው
8. ፍቅረኛ አልያዝ ላላቸውም አለን
9. ትምህርት አልገባ ላለው ቶሎ የመርሳት ችግር ላለበት በሚደገም እና በሚነበብ ፅሁፍ ብቻ እጅግ በጣም ልዩ የሆነ ስራ እንሰራለን
10. መስተፋቅርም አለን ፣የህዝብ መስተፋቅር
11. ከሀገር መውጣት እየፈለጉ ላልተሳካላቸውም ወደኛ ቢመጡ እንሰራሎታለን
ባጠቃላይ እነዚህ የገለፅናቸው ጥቂቶቹ ናቸው እርሶ ምን እንድንሰራሎት ይፈልጋሉ ?በውስጥ መስመር ያማክሩን ። ከሀገር ውጪ ላላችውም መፍትሄ በልዩ ሁኔታ አለን ብቻ ይምጡ ያማክሩን ያስተውሉ እኛ ምንሰራው በጥንታዊው ከአባቶቻችን በተማርነው ጥበብ ብራናውን አንብበን እፅዋትን ቀጥፈን አዘጋጅተን ነውና ሀገራችን ካሏት ጥበብ ጥቂቱ ነው እንኳን ለነዚህ እና አባቶቻችን በደመና ይሄዱ አልነበር እፀመሰውር ሰርተው እራሳቸውን ይደብቁ አልነበር ይሄን ጥበብ ንቀን ፈረንጅ አምላኪ ሆነን ነው እንጂ ጥበቡ አሁንም አለ ይደውሉ ያማክሩን ።
ለምንኛውም ጥያቄ እንዲሁም ለመነጋገር በሜሴጅ በውስጥ መስመር ተከታተሉ የተለያዩ ጥበባዊ ትምህርቶችንና እውቀቶችን ታገኙናላችሁ

ለጥያቄዎ 0908465919 ይደውሉልን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አንድ ቀን ጴጥርቃ ቴክታን እንዲህ አላት፡- ‹‹እህቴ ሆይ! ይህን ሁሉ የሰበሰብነውን ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን? ልጅ የለን የሚወርሰን፣ አንቺም መካን ነሽ እኔም ካንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም›› አላት፡፡ እርሷም ‹‹ወንድሜ ሆይ! አምላከ እስራኤል ለእኔ ልጅ ቢነሳኝ አንተም እንደኔው ሆነህ ትቀራለህን? ከሌላ ደርሰህ ውለድ እንጂ›› ብላ ብታሰናብተው እንደዚህ ያለ ነገር እንኳንስ ላደርገው በልቦናዬም እንዳላስበው አምላከ እስራኤል ያውቃል›› አላት፡፡ እርሷም ‹‹አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን የሚያውቅ የለም፣ ትላንትና ማታ በህልሜ ነጭ ጥጃ ከማኅፀኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲሁ እስከ 7ት ትውልድ ሲዋለድ ሰባተኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ፣ ጨረቃዋም ፀሐይን ስትወልድ አየሁ›› አለችው፡፡ እርሱም በጠዋት ከህልም ፈቺ ዘንድ ሔዶ የነገረችውን ሁሉ ነገረው፡፡ ያም ህልም ፈቺ ‹‹እግዚአብሔር በምሕረቱ አይቷችኋል፣ በሳህሉ መግቧአችኀል፣ 7 አንስት ጥጆች መውለዳችሁ 7 ሴቶች ልጆች እና የልጅ ልጆች ትወልዳላችሁ፤ ከቤታችሁ ሰባተኛይቱ ጨረቃ መውለዷ ከሰው የበለጠች ከመላእክትም የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላችሁ የፀሐይ ነገር ግን አልታወቀኝም›› አለው፡፡
ጴጥርቃም ሕልም ፈቺው የነገረውን ሁሉ ሔዶ ለሚስቱ ነገራት፡፡ እርሷም ‹‹እንጃ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ማን ያውቃል!?›› ብላ ዝም አለች፡፡ ከዚያም ፀንሳ ሴት ልጅ ወለደች፡፡ ስሟንም ሄሜን ብለው አወጡላት፤ ሄሜንም አድጋ ለአካለ መጠን ስትደርስ አጋብተዋት ሴት ልጅ ወለደች፣ በስምንተኛ ቀኗም ዴርዲ ብለው ስም አወጡላት፡፡ ዴርዲም አድጋ እንዲሁ ሴት ወለደችና ቶና አለቻት፣ ቶናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሲካር አለቻት፣ ሲካርም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሴትና አለቻት፣ ሴትናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሄርሜላ አለቻት፣ ሄርሜላም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ንጽህት ቅድስት ክብርት የምትሆን እመቤታችንን የምትወልደውን ሐናን ወለደች፡፡
ይህቺም ሐና በሥርዓት አድጋ ለአእምሮ ስትበቃ አካለ መጠን ስትደርስ ከቤተ መንግስት ወገን ከነቅዱስ ዳዊት ወገን ከሆነው ከቅዱስ ኢያቄም ጋር አጋቧት፡፡ እነዚህ ቅዱሳን ኢያቄምና ሐና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ፡፡ እነርሱም እጅግ ደጋግ ሰዎች ነበሩ፡፡ አንድ ልጅ እንኳ ስላልነበራቸው እጅግ ያዝኑ ነበር፡፡ ወደ ቤተመቅደስ እየሄዱ እግዚአብሔር ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ አጥብቀው ይለምኑት ነበር፡፡ መብዓ ይዘው ለሊቀ ካህኑ ሲሰጡት ሊቀ ካህኑም እንኳ ሳይቀር ‹‹እግዚአብሔር ብዙ ተባዙ ያለውን ሕግ በእናንተ ላይ እንዳይፈጸም አድርጎ ልጅ የከለከላችሁ ኃጢአተኛ ብትሆኑ ነውና መብዓችሁን አልቀበልም›› ብሎ በእጅጉ አሳዝኗቸዋል፡፡ በሊቀ ካህኑ እያዘኑና እየተከዙ ሲመለሱ ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ ዛፍ ሥር ተቀመጠው ሳለ እርግቦች ጫጩቶቻቸውን ሲያጫውቱ ተመልክተው ‹‹ለእነዚህ ወፎች እንኳ ልጆችን የሰጠህ አምላክ ለእኛስ መች ይሆን ልጅ የምትሰጠን?›› ብለው እጅግ አምርረው አለቀሱ፡፡
ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ወደቤታቸው ሲመለሱ ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት አይታ ‹‹አቤቱ ጌታዬ ለዚች እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኸኝ?›› እያለች ምርር ብላ አለቀሰች፡፡ እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው ‹‹አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሔርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን፤ ሴት ልጅም ብንወልድ ውኃ ቀድታ መሶብ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን›› ብለው ስዕለት ገቡ፡፡ ዘካርያስም ‹‹እግዚአብሔር ጸሎታችሁን ይስማችሁ ስዕለታችሁን ይቀበልላችሁ የልቦናችሁን ሀሳብ ይፈጽምላችሁ›› ብሎ አሳረገላቸው።
ከዚህም በኋላ ቅድስት ሐና እና ቅዱስ ኢያቄም ዕለቱን ራእይ አይተው ነገር አግኝተው አደሩ፡፡ ራእዩስ እንዴት ነው ቢሉ ኢያቄም ‹‹7ቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ›› አላት፡፡ ‹‹ወፍ›› የተባለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ነጭነቱ ንጽሐ ባህሪው ነው፤ ‹‹ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ›› ማለቱ የኢያቄምን (የሰውን) ባህርይ ባህርይ እንዳደረገው ዕወቅ ሲል ነው፡፡ 7ቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ልዩ ባሕርይው ምልአቱ ስፋቱ ርቀቱ ልዕልናው ናቸው፡፡ ሐናም ‹‹እኔም ደግሞ አየሁ እንጂ›› አለችው፡፡ ‹‹ምን አየሽ?›› ቢላት ‹‹ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ›› አለችው፡፡ ‹‹ርግብ›› የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት፤ ነጭነቱ ንጽህናዋ ቅድስናዋ ድንግልናዋ ነው፡፡ ‹‹ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማኅፀኔ ስትተኛ አየሁ›› ማለቷ ብሥራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን መፀነሷን ነው፡፡ ይህንኑም ራእይ ያዩት ሐምሌ 30 ዕለት ነው፡፡
እነርሱም እንዲህ ያለ ራእይ ካየን ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም ይልቁንም ፈቃደ እግዚአብሔር ቢሆን ብለው አዳምንና ሔዋንን ‹‹‹ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሉአት›› ብሎ ያበሰረ አምላክ ለእኛስ ይልክልን የለምን?›› ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ 7 ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ፡፡ ነሐሴ በባተ በሰባተኛው ቀን ‹‹‹ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹህና ዛሬ በሩካቤ ሥጋ ተገናኙ› ብሎሏችኀል ጌታ›› ብሎ መልአኩ ለቅድስት ሐና ነገራት፡፡ እግዚአብሔር አምላክ አብርሃምን እና ሳራን የተመለከተ አምላክ በኢያቄምና ሐና አማካኝነት ለዓለም ድኅነት ምክንያት የሆነችውን እና ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ ልቦና ታስባ ትኖር የነበረች የተነገረላት ትንቢት ሊፈጸም የአባት የእናቷ የቅድመ አያቶቿ ራእይ ሊተረጎም ጌታ የፈቀደበት ጊዜ ሲደርስ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እሁድ እለት ነሐሴ 7 ቀን በ16 ዓ.ዓ ተፀነሰች፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ታኅሣሥ 3-ባዕታ ለማርያም-እምቤታችን ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት ነው፡፡
+ መልአኩ ቅዱስ ፋኑኤልም እመቤታችንን ሰማያዊ ኅብስት የመገበበትና የተሾመበት ዕለት ነው፡፡
+ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት ቀድሰው ሕዝቡን ሁሉ ሲያቆርቡ ቢመሽባቸው ፀሐይን እንደ ኢያሱ ገዝተው ያቆሟት እና 8 እንጀራን አበርክተው 8ሺህ ሕዝብ በመመገብ ጌታችንን የመሰሉት አቡነ ዜና ማርቆስ ዕረፍታቸው ነው፡፡
አቡነ ዜና ማርቆስ፡- አባታችን ዜና ማርቆስ ሀገራቸው ጽላልሽ አውራጃ ምድረ ዞረሬ ስትሆን ትውልዳቸው ከነገደ ሌዊና ከእስራኤል ነገሥት ወገን ነው፡፡ ወላጆቻቸው ልጅ በማጣት ሲያዝኑ አንድ ዕለት ሐዋርያውና ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ ወደ እናታቸው ማርያም ዘመዳ ሌሊት መጥቶ ገድሉና ትሩፋቱ በዓለም ሁሉ የመላ ጻዲቅ ልጅ እንደምትወልድ ነገራት፡፡ ለአባቱ ለቀሲስ ዮሐንስም እንዲሁ ተገልጦለት ‹‹ሚስትህ ማርያም ዘመዳ የካቲት 24 ፀንሳ ኅዳር 24 ቀን ይኸውም በካህናተ ሰማይ በዓል ቀን ትወልዳለች፣ ስሙም ዜና ማርቆስ ይባላል›› በማለት ብስራቱን ነግሮታል፡፡
በወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ ብሥራት መሠረት አባታችን በተወለዱም ዕለት ቅዱስ ዑራኤልና ቅዱስ ሩፋኤል የብርሃን ልብስ አልብሰው በክንፋቸው ሲጋርዱአቸው ለሰዎችም ሁሉ ታይቷል፡፡ በወቅቱም የአባ ሳሙኤል ዘወገግ አባት እንድርያስና የአቡነ ተክለሃይማኖት አባት ቅዱስ ጸጋ ዘአብ እስኪደነቁ ድረስ ይህን በዓይናቸው ተመልክተዋል፡፡ ሁለቱ መላእክትም ከእናታቸው ዕቅፍ ወስደው ወደ ሐዋርያው ማርቆስ መቃብር ወስደው ለማርቆስና ለቅዱሳን ጳጳሳት አስባርከዋቸው መልሰው ለእናቱ ሰጧቸው፣ እናቱ ግን ይህን አታውቅም ነበር፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስም በተወለዱ በሦስተኛው ቀን በእግራቸው ቆመው ‹‹አንድ አምላክ ለሆኑ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ እሰግዳለሁ›› ብለው ሦስት ጊዜ አምላካቸውን አመስግነው ሰግደዋል፡፡ በ40 ቀኑ ሲጠመቅ የሚያጠምቀው ካህን የአባቱ ወንድም እንድርያስ ውኃው ሲፈላ አይቶ ሸሽቷል፡፡ መልአኩም እንዳይፈራ ነግሮት ለእርሱም ተአምር እንደሚደረግለት አስረዳው፡፡ እንድርያስም ዕድሜው 72 ነበርና ራሰ በራ ስለነበር በውኃውም ራሱን ቢታጠብበት ጸጉር አብቅሏል፡፡ ሕዝቡም ሁሉ ይህን አይቶ አደነቀ፡፡ ያችም ውኃ ሌሎች በጣም ብዙ ተአምራትን አደረገች፡፡
አንድ ዓመት በሆነውም ጊዜ ቤተክርስቲያን ውስጥ እየዳኸ ሲሄድ መልአክ በክንፎቹ አቅፎ ወስዶ ጌታችንና እመቤታችን ጋር አቅርቦት አስባርኮታል፡፡ እንዲሁም የ15ቱን ነቢያት፣ የ12ቱን ሐዋርያት የ72ቱን አርድእት፣ ሃይማኖታቸው የቀና የ318ቱን ሊቃውንት፣ የጻድቃንን፣ የሰማዕታትን የእነዚህን ሁሉ በረከት እንዲቀበል ካደረገው በኋላ ወደዚያች ቤተክርስቲያን መለሰው፡፡ ከጳጳሱ ከአቡነ ጌርሎስ ድቁናን ተቀብሎ ከአባቱ ጋር ወደ ሀገሩ ሲመለስ ዘራፊዎች ደብድበው በትራቸውንም ሳያስቀሩ ዘረፏቸው፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስም ወደ ፈጣሪው በጸለየ ጊዜ በትራቸው እባብ ሆና ነድፋ ገደለቻቸው፡፡ በኋላም ወደ አምላካቸው ጸልየው ከሞት እንዲነሱ በማድረግ በአካባቢውም ያሉ ሰዎች ሁሉ በእርሱ አምላክ እንዲያምኑ አድርጓቸዋል፡፡
ከዚህም በኋላ ብሉያትንና ሐዲሳትን ጠንቅቆ ከተማረና ካደገ በኋላ ሚስት አጭተው አጋቡት፡፡ እርሱ ግን በዚያው በሠርጉ ዕለት ማታ ጌታ ‹‹እናትና አባቱን ሚስቱን ቤቱን ንብረቱን ያልተወ ሊያገለግለኝ አይችልም›› ያለውን ቃል አስቦ ሚስቱን እንዲህ አላት፡- ‹‹እኅት ሆይ! የዚህ ዓለም ኑሮ ምን ይጠቅመናል፣ ዓለሙም ፍላጎቱም ያልፋል፡፡ ስለዚህ የነፍሴን ድኅነት ለመሻት እሄድ ዘንድ አሰናብችኝ›› ሲላት እርሷም ‹‹አንተ የተውከው ዓለም ለእኔስ ምን ይጠቅመኛል?›› በማለት ሁለቱም ሰው ሳያያቸው ከጫጉላ ቤታቸው በሌሊት ወጥተው ሄዱ፡፡ ቅዱስ ዑራኤልና ቅዱስ ሩፋኤልም እየመራቸው ዜና ማርቆስን ምሁር ገዳመ ኢየሱስ እርሷን ደግሞ ወደ ቤተ ደናግል ማማስ ደብር አደረሷቸው፡፡ እርሷም ሙትን እስከማስነሣት ድረስ ታላላቅ ተአምራትን እያደረገች ቆይታ ተጋድሎዋን ፈጽማ በጥር 21 ቀን በክብር ዐርፋለች፡፡ ዐርፋ የተቀበረችውም በደመና ተነጥቃ ኢየሩሳሌም ከሄደች በኋላ እመቤታችን በተቀበረችበት በጌቴሴማኒ ሲሆን ሁለት አንበሶች ጉድጓድ ቆፍረው ቀብረዋታል፡፡
አባታችንም በምሁር ሀገር ይመለክ የነበረውን ማኮስ የተባለውን ጣዖት በመሬት ውስጥ ቀበረውታል፡፡ ገዥውም ተቆጥቶ በአባታችን ላይ ክፉ ሲያደርግ ‹‹ካላመንክ አንተም እንደ አምላክህ እንደ ማኮስ መሬት ተከፍታ ትውጥሃለች›› ብሎ በተናገረበት ቅጽበት ገዥውን ከነሠራዊቱ መሬት ተከፍታ ዋጠቻቸው፡፡ ከዚያም ፈጥነውና በደመና ተነጥቀው ወደ ግብፅ በመሄድ ከአባ ብንያሚን ቅስና ተቀብለው መጡና መሬት ተከፍታ የዋጠችውን የገዥውን ቤተሰቦች ጨምሮ ብዙ ሺህ የምሁር ሕዝቦችን አስተምረው አጠመቋቸው፡፡ ያንን ገዥም ስለ ተጠመቁ ልጆቹና ሚስቱ ብለው ከ5 ዓመት በኋላ በጸሎታቸው ኃይል ከሞት አስነስተውታል፡፡ በዚሁ ሀገር ከአባ ዜና ማርቆስ ጋር ሳሉ የኢትዮጵያው ጳጳስ አባ ጌርሎስ በድንገት ዐርፈው ሳለ ጻዲቁ ዜና ማርቆስ ጸሎት አድርገው ከሞት አስነሥተዋቸዋል፡፡ ሌላም እንዲሁ በጉራጌ ሀገር ገርዳን የሚባለውን ጣዖት ሰባብረው በውስጡ የነበረውን ሰይጣንን እንደ ትቢያ በኖ እስኪጠፋ ድረስ አስጨንቀውታል፡፡ ሕፃናቱን ጨምሮ ከ124 ሺህ በላይ የሚሆኑትን ሕዝቦችም አስተምረው አጥምቀዋቸዋል፡፡ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤልም ሁልጊዜ እንደ ጓደኛ እያናገራቸው ይረዳቸው ነበር፡፡
አባታችን ዜና ማርቆስ የሚያደርጓቸው እጅግ ድንቅ የሆኑ ተአምራት በሕዝብ ዘንድ ውዳሴን እያመጣ እንዳያስቸግራቸው ብለው ይህን ተአምር የማድረግ ሥራ እግዚአብሔር እንዲያርቅላቸው ይለምኑት ነበር፡፡ ወግዳ በምትባል ሀገር ሄደው በዋሻ ውስጥ ሳሉ አቡነ ተክለሃይማኖት ወደ እርሳቸው መጥተው አብረው በዋሻው ብዙ ተአምራትን እያደረጉ ቆይተዋል፡፡ ለአባ ዜና ማርቆስና ለሌሎች ለብዙ አባቶች የምንኩስና አባት የሆኑት አቡነ ተክለሃይማኖት ትሕትናቸውን ያሳዩ ዘንድ አቡነ ዜና ማርቆስን ያገለግሏቸው ነበር፡፡ ወደ ሞረት ሀገር እንዲሄዱ መልአክ ነግሯቸው ሁለቱም ሄደው በዚያም አብረው ተቀምጠዋል፡፡ ጣዖት አምላኪውን የሞረቱ ገዥ ሊገድላቸው ፊልጎ ከነሠራዊቱ ወዳሉበት ዋሻ ሄደ፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስም ተራራዋን በሥላሴ ስም ባርከው ቢያዟት የገዥውን ጭፍሮች አፏን ከፍታ ዋጠቻቸው፡፡ ገዥውን ድል አሰግድንም በተአምራቸው አሳምነውት አስተምረው አጠመቁት፡፡
ከዚህም በኋላ ቅዱስ ገብርኤል ለአቡነ ተክለሃይማኖት ተገልጦላቸው ወደ ግራርያ ሀገር እንዲሄዱ ስለነገራቸው አቡነ ተክለሃይማኖት የመላእክትን አስኬማ ለአቡነ ዜና ማርቆስ አልብሰዋቸው ዜና ማርቆስንም በደብረ ብስራት እንዲጸኑ ነግረዋቸው ወደ ግራርያ ሄዱ፡፡ ሲሄዱም የደብረ ብስራት ዛፎቹ እንጨቶቹና ደንጊያዮቹ ሁሉ አቡነ ተክለሃይማኖትን እንደ ንጉሥ ሠራዊት ከፊት ከኋላ ሆነው ሸኝተዋቸዋል፡፡ አባታችንም ‹‹የወንድሜን የዜና ማርቆስን ቦታ ትታችሁ ከዚህች ምድር ትሄዱ ዘንድ አልፈቅድምና ሁላችሁ በየቦታችሁ ቁሙ›› ብለዋቸዋል፡፡ ‹‹ሰውም እንኳ ቢሆን ለምንኩስና ወደ እኔ ዘንድ ወደ ግራርያ ከመምጣቱ በፊት ይህን ምድር ሳይሳለም ወደ እኔ አይምጣ›› በማለት ቃልኪዳናቸውን ከደብረ ብስራት ጋር አድርገዋል፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

†††✝ እንኳን ለእግዝእትነ ማርያም (#በዓታ): አቡነ ዜና ማርቆስ ጻድቅ እና ቅዱስ ፋኑኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም †††

††† ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ (አሮን) የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር:: ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች "ልጅ የላችሁም" በሚል ይናቁ ነበር::

ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር:: ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ:: እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም::

የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው:: አንድ ቀን እርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች:: "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን ሳይቀር በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች::

ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ:: ለ40 ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ:: በ40ኛው ቀን ሁለቱም ሕልምን ያልማሉ::
እርሱ:-
*ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጀሮ ገብታ: በማሕጸኗ ስትደርስ አየ::

እርሷ ደግሞ:-
*የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች:: ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለ7 ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ::

በ7ኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ 7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው:: እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ::

እንደ ሥርዓቱም አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች::
"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ . . .
ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ:: (ቅዳሴ ማርያም)

††† "ለጽንሰትኪ በከርሥ::
እንበለ አበሳ ወርኩስ::
ወለልደትኪ እማሕጸን ቅዱስ . . ."
"ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው: የተወለድሽበት ማሕጸንም ቅዱስ ነው . . ." (መጽሐፈ ሰዓታት፣ ኢሳ. 1:9)
"ኢያቄም ወሐና ወለዱ ለነ ሰማየ::
ሰማዮሙኒ አስረቀት ለነ ፀሐየ::"
"ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱልን::
ሰማያቸው ደግሞ ፀሐይን አወጣችልን (ወለደች-አስገኘችልን)"

የዓለማችን ወላጆች ነቢያት ሐዋርያትን: ጻድቃን ሰማዕታትን ወልደው ከብረዋል: ተመስግነዋል:: ኢያቄምና ሐና ግን ፍጥረት ሁሉ በአንድነት ቢሰበሰብ በእግሯ የረገጠችውን ትቢያ እንኳ መሆን የማይችል: የሰማይና የምድር ንግሥት: የእግዚአብሔርን እናት: እመቤታችን ማርያምን ወለዱልን::

ኢያቄም ወሐና ለእግዚአብሔር የሥጋዌ አያቶቹም ተባሉ:: ቅዱሳኑ እስኪያረጁ ድረስ በመካንነት አዝነው ፀልየዋል:: ንጽሕናቸውና ደግነታቸው ተመስክሮላቸው ድንግል ማርያምን አግኝተዋል::

እመቤታችን ነሐሴ 7 ቀን ተጸንሳ ግንቦት አንድ ቀን ተወልዳለች:: ከአዳም ስሕተት በኋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተወለደች የመጀመሪያዋ ሰው ድንግል ማርያም ሆናለች:: (ኢሳ. 1:9)

††† የእመቤታችን የዘር ሐረግ:-
*አዳም-ኖኅ-አብርሃም-ይስሐቅ-ያዕቆብ=
*በእናቷ:-
ሌዊ-ቀዓት-እንበረም-አሮን-ቴክታና በጥሪቃ-ሔኤሜን-ዴርዴን-ቶና-ሲካር-ሔርሜላና ማጣት-ሐና::

*በአባቷ በኩል:-
ይሁዳ-ፋሬስ-ሰልሞን-ቦኤዝ-እሴይ-ዳዊት-ሰሎሞን-ሕዝቅያስ-ዘሩባቤል-አልዓዛር-ቅስራ-ኢያቄም ይሆናል::

ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም: በሊባኖስ ተራራ ከ2,023 ዓመታት በፊት ተወልዳለች::

ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ድንግል እመ ብርሃንን ከወለዱ በኋላ ለ3 ዓመታት እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ: ነዳያንንም ሲጠግኑ ኖሩ:: በእነዚህ ዓመታትም ቅድስት ሐና ድንግል ማርያምን ከእቅፏ አውርዳት አታውቅም::

ቅዱሳን መላእክትም ዘወትር እየመጡ ያጫውቷት ይንከባከቧትም ነበር:: 3 ዓመት በሞላት ጊዜም በቅድስት ሐና አሳሳቢነት ብጽዓታቸውን (ስዕለታቸውን) ይፈጽሙ ዘንድ ተዘጋጁ::

እንደ ሥርዓቱ የሚዘጋጀውን (መባውን) ይዘው ወደ ቤተ መቅደስ ሲደርሱ አበው ካህናትና የመቅደሱ አገልጋዮች ሁሉ ሊቀበሏቸው ወጡ:: ሕዝቡ: ሊቃነ ካህናት ቅዱሳን ዘካርያስና ስምዖን: ኢያቄም ወሐና ከድንግል ማርያም ጋር ቆመው ሳሉም ሊቀ መላእክት ፋኑኤል ከሰማይ ወርዶ ረቦ ታየ::

ከቅዱስ ዘካርያስ ጀምሮ ሁሉም ሰው ሕብስትና ጽዋዑን ለመቀበል ቀረበ:: ግን መልአኩ ራቀ:: ድንግል ማርያም በቀረበች ጊዜ ግን ከመሬት አፈፍ አድርጐ አንስቶ: ክንፉን ጋርዶ ሰማያዊውን ማዕድ መገባት:: በዚህ ደስ የተሰኙ ካህናትና ሕዝቡ እየዘመሩ በታኅሣሥ ሦስት ቀን ወደ ቤተ መቅደስ አስገብተዋታል::

አማናዊት መቅደሰ መለኮት ድንግል ማርያም ወደ ኦሪቱ ቤተ መቅደስ በገባችበት ዕለት ጸሎታችን እንድትሰማን እንደ ሊቃውንቱ:-
"ማርያም አንቲ ሰዋስው ዘምድረ ሎዛ::
ዲቤኪ ትዕርግ ጸሎትየ ከመ ጼና ሠናይ መዓዛ::
ኀበ ለነፍስየ ታሰስል ትካዛ" እንላለን:: (አርኬ)

††† አቡነ ዜና ማርቆስ ጻድቅ †††

††† አባ ዜና ማርቆስ በሃገራችን በተለይ በደቡብ ምድረ ጉራጌ ስመ ጥር ሐዋርያዊ ጻድቅ ናቸው:: ምድረ ሽዋ ደግሞ እርሳቸውን ጨምሮ የብዙ ቅዱሳን መፍለቂያ ናትና ክብር ይገባታል:: ነቢየ ጽድቅ ዳዊት "ትውልደ ጻድቃን ይትባረኩ-የጻድቃን (የቅኖች) ትውልድ ይባረካል" (መዝ. 111) ያለው ነገር በምድረ ዞረሬ (ጽላልሽ) ተፈጽሟል::

ሦስት ወንድማማች የተባረኩ ካህናት በስፍራው ነበሩ:: ስማቸው ጸጋ ዘአብ: እንድርያስና ዮሐንስ ይባላል:: ከእነዚህ መካከልም ጸጋ ዘአብ: እግዚእ ኃረያን አግብቶ ኮከበ ከዋክብት ተክለ ሃይማኖትን ሲወልድ ካህኑ ዮሐንስ ደግሞ ዲቦራ የምትባል ደግ ሴት አግብቶ ዜና ማርቆስን ወልዷል::

የአቡነ ዜና ማርቆስ ጽንሰታቸው ሚያዝያ 30 በብሥራተ ማርቆስ ወንጌላዊ ሲሆን ልደታቸው ደግሞ ኅዳር 24 ቀን በበዓለ ሱራፌል ካህናተ ሰማይ ነው:: ዘመኑም 13ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው::

ዜና ማርቆስ በተወለዱ በ40 ቀናቸው አጐታቸው ቀሲስ እንድርያስ (የ72 ዓመት ሽማግሌ ናቸው) ሊያጠምቁ ቀረቡ:: ሕጻኑ ዜና ማርቆስ ግን ከእናታቸው እቅፍ ወርደው 3 ጊዜ "እሰግድ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ" እያሉ ቢሰግዱ የመጠመቂያው ገንዳ ውኃ ፈላ::

ይህንን የተመለከቱት ካህኑ ደንግጠው ወጥተው ሲሮጡ ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት ተገልጦ "አትፍራ! ይልቁኑ ከጠበሉ ራስህን ተቀባ" አላቸው:: እንዳላቸው ቢያደርጉ ራሰ በራ ነበሩና ጸጉር በቀለላቸው::

ሕጻኑ ዜና ማርቆስ ግን 5 ዓመት ሲሞላቸው ወደ ጉባኤ ቤት ገብተው በአጭር ጊዜ ብሉይ ከሐዲስ ጠነቀቁ:: ዲቁናን ተቀብለው ወደ ቤታቸው ሲመለሱም ሽፍቶች አግኝተው: በትራቸውን ቀምተው: አንገላተው ሰደዋቸዋል::

ወዲያው ግን ያቺ በትር እባብ ሁና ሽፍቶችን አጥፍታቸዋለች:: ጻድቁ ለቤተሰብ እየታዘዙ: ንጽሕናቸውንም እየጠበቁ ኑረው 30 ዓመት ሲሞላቸው ወላጆቻቸው ግድ ብለው ማርያም ክብራ ለምትባል ወጣት አጯቸው::

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/W-eN0faaHmo

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

👋 selam ye melaku Lejoch

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ እንኩዋን ለቅዱሳን "ሠለስቱ ደቂቅ" እና "አባ ሖር ገዳማዊ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

" ታኅሣሥ 2 "

+*" ቅዱሳን ሠለስቱ ደቂቅ "*+

=>አናንያ: አዛርያና ሚሳኤልን እንዲያው በቀድሞው አጠራር ሠለስቱ ደቂቅ (ሦስቱ ሕጻናት) እንላቸዋለን እንጂ ለእኛስ በእድሜም: በጸጋም: በትሩፋትም አባቶቻችን ናቸው::

+ቅዱሳኑ የወቅቱ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአቄም ልጆች ናቸው:: ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን አቃጥሎ ሕዝቡን ሲማርክ አብረው ተማርከው ባቢሎን ወርደዋል::

+ንጉሡ ከምርኮ ወጣቶች ለቤተ መንግስት ሲመርጥ ሦስቱ ቅዱሳንና ዳንኤል ተመርጠው የምቾት ሕይወት ተዘጋጅቶላቸው ነበር:: ነገር ግን በምግብና በአምልኮ ከአ+ሕ+ዛ+ብ ጋር መተባበርን አልፈለጉምና ምርጫቸው ጾምና ጸሎት ከቆሎ ጋር ሆነ:: ምንም እንኩዋ በቤተ መንግስት ውስጥ ቢኖሩ: ምንም የነገሥታት ልጆች ቢሆኑ ለእነርሱ ከእግዚአብሔር ፍቅር የተሻለ አልነበረምና በጥሬ ቆሎ ተወስነው ኖሩ::

+አምላካቸው ከሃሊ ነውና በውበትም ሆነ በጥበብ በባቢሎን ምድር ከነርሱ የሚደርስ አልተገኘም:: ንጉሡም በባቢሎንና በአውራጃዋ ላይ ሾማቸው:: ስማቸውንም በአማልክቱ ስም ሲድራቅ: ሚሳቅና አብደናጐ አላቸው::

+ከነገር ሁሉ በሁዋላ አ+ሕ+ዛ+ብ ቀንተውባቸዋልና የክፋት አዋጅን አሳወጁ:: ናቡከደነጾር 60 ክንድ ቁመት ያለውን የወርቅ ምስል አቁሞ ስገዱ ቢላቸው አይሆንም በማለታቸው ተቃጥለው እንዲሞቱ እሳት ተፈረደባቸው:: ነበልባሉ ከጉድጉዋዱ ወደ ላይ 49 ክንድ ቢነድም ቅንጣት ያህል ፍርሃት አልጎበኛቸውም::

+ወደ እሳቱም ሲጥሏቸው መልዐከ አድኅኖ ቅዱስ ገብርኤል ደርሶ አዳናቸው:: ከሆነው ነገር የተነሳም አ+ሕ+ዛ+ብ አፈሩ:: ናቡከደነጾር ግን ከዙፋኑ ተነስቶ የቅዱሳኑን አምላክ እግዚአብሔርን ባረከ::

+ከዚያች ቀን በሁዋላ አናንያ: አዛርያና ሚሳኤል በአት አጽንተው: በጾምና በጸሎት ተወስነው ኑረዋል:: ነፍሳቸው ከሥጋቸው ስትለይ ታላቅ ንውጽውጽታ ሆኗል:: ቅዱስ ዳንኤልና ናቡከደነጾር ተሯሩጠው ቢሄዱ ሦስቱም በአንድነት ዐርፈው ተገኝተዋል:: ንጉሡ በእጅጉ ይወዳቸው ነበርና በወርቅ በተለበጠ ሳጥን ቀብሯቸዋል:: ስሞት ከመካከላቸው ቅበሩኝ በማለቱ ዛሬ ድረስ ለበቁ አባቶች የአራቱ መቃብር ባቢሎን ውስጥ ይታያል::

+ቅዱሳን አናንያ: አዛርያና ሚሳኤል (ሲድራቅ: ሚሳቅና አብደናጐ) ያረፉት ግንቦት 10 ቀን ሲሆን ዘመኑም ከክርስቶስ 500 ዓመት በፊት ነው:: ይህቺ ዕለት ደግሞ ናቡከደነጾር ወደ እሳት ሲጥላቸው መልአከ እግዚአብሔር እነርሱን ያዳነበት ቀን ናት::

+አምላካቸው ከአሳት ባወጣቸው በዚህ ቀንም:-
"ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ::
ስቡሕኒ ውዕቱ ወልዑልኒ ውዕቱ ለዓለም::" የሚለውን ምስጋና ፈጣሪ ገልጾላቸው ደርሰውታል:: በእሳቱ ውስጥ ሆነው ተናግረውታል::

+ድርሰታቸው 2 ወገን ሲሆን ባለ ስድስት አንቀጹ ምስጋናቸው ከ600 ዓመት በሁዋላ ክርስቶስ እንደሚወለድ የሚያሳይ ነው:: ሌላኛውና 33 አንቀጾች ያሉት ምስጋናቸው ደግሞ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ለ33 ዓመታት እንደሚመላለስ ያጠይቃል::

+ቅዱሳን ሠለስቱ ደቂቅ ካረፉ ከ900 ዓመታት በሁዋላ (ማለትም ከክርስቶስ ልደት በ400 ዓመታት) ታላቁ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ቤተ ክርስቲያንን አንጾላቸው ነበርና አጽማቸውን ሊያገኝ ተመኘ::

+ወዳጁን ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርን ጠርቶ "አባ! አጽመ ቅዱሳንን ባቢሎን ወርደህ አምጣልኝ?" አለው:: ቅዱሱ ሐጺር ዮሐንስም በደመና ተጭኖ ባቢሎን ገባ:: በቅዱሳኑ መቃብር ፊትም ሰግዶ አለቀሰ:: ሠለስቱ ደቂቅም "ወዳጃችን! ምን ሆንክ?" አሉት::

+ቅዱሱም መልሶ "ወደ ግብጽ እንሒድ:: አባ ቴዎፍሎስ ይፈልጋቹሃል" አላቸው:: እነሱም "ለቅዱሱ ቴዎፍሎስ እንዲህ በለው:: እግዚአብሔር ዋጋህን ይክፈልህ:: ግን አጽማችን እስከ ዓለም ፍጻሜ ባቢሎንን አይለቅም:: ለክብርህ ግን እንመጣለን::"

+"ለምልክትም ይሆን ዘንድ መብራት ሳታበራ በሌሊት ጠብቀን በለው" ብለው ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርን ባርከው ሸኙት:: ሐጺርም መጥቶ መልአክቱን አደረሰ:: በዕለተ ቅዳሴ ቤታቸው ቅዱሳን:- ቴዎፍሎስ: ቄርሎስ: ሐጺር ዮሐንስና ሌሎችም ከምዕመናን ጋር በጨለማ ሳሉ ቤተ ክርስቲያኑ ቦግ ብሎ በራ::

+እጅግ የሚደነቅ ብርሃንም ከበባቸው:: በብርሃኑ መካከል ሠለስቱ ደቂቅ ሲያልፉ በጐ መዓዛ ሸተተ:: ሕዝቡም በደስታና በዝማሬ የቅዱሳኑን ቅዳሴ ቤት አክብሯል::

+"+ አባ ሖር ገዳማዊ +"+

=>በዚህ ስም የሚጠሩ ብዙ ቅዱሳን ከጻድቃንም: ከሰማዕታትም አሉ:: ከጻድቃኑ መካክል: በተለይም ከታላላቆቹ አንዱ ቅዱስ አባ ሖር ነው:: አባ ሖር በዘመነ ጻድቃን የነበረና በደግነቱ የሚታወቅ ክርስቲያን ነው::

+በዓለም ያለውን በጐነት ሲፈጽም ድንግልናውን እንደ ጠበቀ ገዳም ገባ:: በዚያም በአገልግሎት ተጠምዶ ዘመናትን አሳለፈ:: ከዚያም መነኮሰ:: ከመነኮሰ በሁዋላ ደግሞ አበውን በማገልገል: በጾምና በጸሎት: በበጐው ትሕርምት ሁሉ የተጠመደ ሆነ:: ግራ ቀኝ የማይል ("ጽኑዕ ከመ ዓምድ ዘኢያንቀለቅል" እንዲሉ አበው) ብርቱ ምሰሶ ሆነ::

+ሰይጣንም አባ ሖርን በብዙ ጐዳና ፈተነው:: ከእርሱ ጋር መታገል ከአቅሙ በላይ ሲሆንበት በገሃድ ተገለጠለት:: "አንተኮ የምታሸንፈኝ በአበው መካከል ስለ ሆንክ ነው:: በበርሃ ብቻህን ባገኝህ ግን እጥልሃለሁ" ሲል ተፈካከረው::

+አባ ሖርም የዳዊትን መዝሙር እየዘመረ ጭው ወዳለ በርሃ ገባ:: በዚያም ሰይጣን ታገለው:: ግን ሊያሸንፈው አልቻለም:: ምክንያቱም ኃያሉ እግዚአብሔር ከጻድቁ ጋር ነበርና:: ሰይጣን እንደ ተሸነፈ ሲያውቅ እንደ ገና ሌላ ምክንያት ፈጠረ::

+አሁንም በገሃድ ተገልጦ ተናገረው:: "በዚህ በበርሃ ማንም በሌለበት ብታሸንፈኝ ምኑ ይደንቃል! ወደ ከተማ ብትሔድ ግን አትችለኝም" አለው:: ቅዱስ ሖር ግን አሁንም ሰይጣንን ያሳፍር ዘንድ በፈጣሪው ኃይል ተመክቶ ወደ ዓለም ወጣ::

+"እግዚአብሔር ያበርሕ ሊተ ወያድኅነኒ: ምንትኑ ያፈርሃኒ - እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው:: የሚያስፈራኝ ማነው!" ሲል (መዝ. 26:1) ይጸልይ ነበር:: በከተማም በነበረው ቆይታ አልባሌ ሰው መስሎ ደካሞችን ሲረዳ: ነዳያንን ሲንከባከብ: ለድሆች ውሃ ሲቀዳ: እንጨት ሲሰብር ይውልና ሌሊት እንደ ምሰሶ ተተክሎ ሲጸልይ ያድራል::

+ሰይጣን በዚህም እንዳላሸነፈው ሲያውቅ ከሰዎች ጋር በሐሰት ሊያጣላው ሞከረ:: ፈረስ ረግጦ የገደለውን አንድ ሕጻን ሲያይ ሰይጣን ሰው መስሎ ወደ አባ ሖር እየጠቆመ "እርሱ ነው ረግጦ የገደለው" አላቸው:: የሕጻኑ ወገኖች ቅዱሱን ሲይዙት አባ ሖር "ቆዩኝማ" ብሎ የሞተውን ሕጻን አንስቶ ታቀፈው::

+ጸልዮ በመስቀል ምልክት አማተበበትና "እፍ" ቢልበት ሕጻኑ ከሞት ተነሳ:: ለወላጆቹም ሰጣቸው:: ይሕንን ድንቅ የተመለከቱ የእስክንድርያ ሰዎችም ይባርካቸው ዘንድ ሲጠጉት ተሰውሯቸው በርሃ ገባ:: ውዳሴ ከንቱን ፈጽሞ ይጠላት ነበርና::

+ጻድቁ አባ ሖር ቀሪ ዘመኑን በበርሃ አሳልፎ በዚህች ቀን በክብር ዐርፏል::
=>አምላከ ጻድቃን ቅዱሳን ከነደደ እሳት: ከዲያብሎስ ክፋትም ይሰውረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

=>ታሕሣሥ 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱሳን ሠለስቱ ደቂቅ (አናንያ: አዛርያ: ሚሳኤል)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ትውልዷንም ከኢትዮዽያ ያደርጉታል::=>አምላከ ኤልያስ በምልጃው ለሃገራችንና ለሕዝቧ
ርሕራሔውን ይላክልን:: ከቅዱሳኑም በረከትን ይክፈለን::

=>ታሕሳስ 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ኤልያስ ርዕሰ ነቢያት
2.ቅዱስ ዼጥሮስ ዘጋዛ
3.ቅድስት ቤርሳቤህ (ቤትስባ)
4.ናቡቴ ኢይዝራኤላዊ
5.አባ ዮሐንስ ሊቀ ዻዻሳት

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
4.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር
5.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላእክት

=>+"+ ለእስራኤል ሁሉ ሥርዓትንና ፍርድን አድርጌ
በኮሬብ ያዘዝኩትን: የባሪያየን የሙሴን ሕግ አስቡ::
እነሆ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ
ነቢዩን ኤልያስን እልክላቹሃለሁ:: መጥቼም ምድርን
በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ
ልጆች: የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል:: +"+ (ሚል. 4:4)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
🔴በቴሌግራም ለመከታተል👉/channel/zikirekdusn
🛑በዩቲብለመከታተል👉
https://youtube.com/shorts/egux4JdrPrw?si=MjLWZmAjsMzYfmlB
/channel/zikirekdusn

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

⚠️ለሁላችሁም!
የፊታችን መጋቢት 29 የህዝብ ቆጠራ ይካሄዳል እያላችሁ ሰዎችን ለማጭበርበር የምታስቡ ሰዎች እና ተጭበርብራችሁ ለሌሎች የምታካፍሉ ሰዎች ተቆጠቡ!.....የሚጠይቅ ህሊና ይኑራችሁ።
⚠️ፅሁፉ በእርግጥ ከአራት አመት በፊትም በቴሌግራም ላይ ሲዘዋወር የነበረ ነው ዛሬ አዲስ የመጣ ነገር አደለም።
⚠️የህዝብ ቆጠራ ቢኖር መንግስት መግለጫ ይሰጣል የሃይማኖት አባቶችም መግለጫ ይሰጣሉ እናንተ ግን ከየት አምጥታችሁ እንደምታዘዋውሩት እግዚአብሔር ይወቅላችሁ!

⚠️❗️ከኪነ-ጥበብ ❗️⚠️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

📣በልታችሁ ጨርሱ......🔑
ሰርግ ላይ እና በተለያዩ ድግሶች ላይ ተገኝታችሁ ምግብ የምትበሉ ሰዎች የሚቀርብላችሁን ምግብ በልታችሁ ጨርሱ አልያም ስትበሉ ሰው መሆናችሁን እያሰባችሁ በስርአት ብሉ..........አንዳንዱ ምግብ የሚበላ ሳይሆን ጭቃ የሚያቦካ ነው የሚመስለው........በመጨረሻም አስተርፈው ወተው ይሄዳሉ የድግሱ ባለቤት ደሞ ይሄንኑ ምግብ ሰው አለ ብለው፣ይረዱኛል ብለው፣በችግር ሆዳቸውን አስረው ከአጥሩ ውጪ እንደ ሰው ሳይቆጠሩ ለቆሙት የኔ ብጤዎች ይወረውሩላቸዋል!.....ያውም በእጁ መንካት ተፀይፎ ጓንት አጥልቆ!

📢ቤት ውስጥ ካለህ ውጪ ያሉትን አትርሳ!
ወደ ውስጥ አላስገባ ብለህ በውጪው የወረወርክለት ሰው መድኃኒትህ ነው።
📢ክርስቶስ ተርቤ ነበረ አላበላኸኝም፤ታርዤ ነበረ አላለበስከኝ ብሎ ይጠይቅሃል!

❗️💌ኪነ-ጥበብ📀💌❗️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🔴ምሽት ላይ በከተማው መብራት ድንገት ቢጠፋ ጄኔሬተር አብርተው ጨለማውን የሚያባርሩ ጥቂት ባለ ሃብቶች አይጠፉም።
💥በዚህ ጊዜ ጄኔሬተር የሌለው እና ያልገዛው እነሱ ሃብት ስላላቸው ገዝተው ይጠቀማሉ ብለው ብዙ ነገር ሊያስቡ ይችላሉ ክፉ/መልካም ሊሆን ይችላል....
💥አሁን አንድ ነገር አስቡ በከተማው ውስጥ መብራቱ ሲጠፋ የመጣውን ጨለማ ያባረሩት ሰዎች ፅድቅ ሰርተው፤ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ጠብቀው ለአክሊል የበቁ ብለህ አስብ።
💥ጄኔሬተር የሌላቸው ና በጨለማው ውስጥ የተዋጡት ደሞ አንድ መክሊት እንደተሰጠው ሰውዬ አስቡት ሳይሰራ፣ጊዜውን ሳይጠቀምበት በከንቱ እንዳሳለፈው ሰው። በመጨረሻ ላይ ተፈርዶበት ለቅጣት እንደተላለፈው ና ወደ ጨለማው እንደ ተወረወረው። መብራቱ ድንገት ሲጠፋ በጨለማው ተውጦ ቀረ።


ምናልባት ይሄንን ስታነበው እንዴት እንደዚህ ሊያስብ ቻለ ብለህ ታስብና ትናደድ ይሆናል ....አሁን እንዲህ አድርግ ሁሉ ነገር አስተማሪ ነው ብለህ አስብ።

🎧ስለዚህ መልካም በመስራት እንደ ባለ ሶስት እና አምስቱ መክሊት እንስራ ለነፍሳችን አለን እንበላት።

💥❗️ኪነ-ጥበብ❗️💥

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አቡነ ፄዋ ለጽድቅ በእንደዚህ ያለ ገድልና ትሩፋት ላይ እንዳለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክረስቶስ በቅዱሳን መላእክት ታጅቦ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምን፡ ነቢያትን ሓዋርያትን፣ ጻድቃንን፣ ሰማዕታትን፣ ደናግል መነኮሳትን፡ ወዳጆቹን ሁሉ አስከትሎ በምስጋና በዝማሬ በይባቤ ወደ ወዳጁ አቡነ ፄዋ ለጽድቅ ወረደ። በወረደም ጊዜ ምድር ተንቀጠቀጠች የነበሩበትም ቦታ ብርሃን ለበሰ። ኣቡነ ፄዋ ለጽድቅም ከድንጋጤና ከፍርሃት የተነሳ በግንባሩ ወደቀ። ጌታችንም ፍርሃቱን : አርቆለት በቅዱሳን እጆቹ አንሥቶ ሳመውና ወዳጄ ፄዋ ለጽድቅ ሆይ በጸና እምነትህና በቆራጥ ልቡና ሆነህ መከራ መስቀሌን አስበህ መራራ ልቅሶን አልቅሰህ በለመንኸኝ ጊዜ አሁን እነሆ ከድካም ወደ እረፍት፣ ከሀሳር ወደ ክብር፡ ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከሃዘን ወደ ፍጹም ደስታ ዛሬ ልወስድህ መጥቻለሁና ደስ ይበልህ። ደስታ ይገባሃል፣ ወዳጄ ፄዋ ለጽድቅ አርበኛው ልጄ ተጋዳዩ ልጄ ፄዋ ለጽድቅ ሆይ! ደስ ይበልህ፣ እጽፍ ድርብ ደስታ ይገባሃል›› አለው። እርሱም “ጌታዬ ፈጣሪዬ ለእኔስ በገድሌና በትሩፋቴ ያይደለ በቸርነትህና በምህረትህ ብዙውን ክብርና ጸጋ ሰጠኸኝ። ነገር ግን አምላኬ ሆይ! በስሜ አምነው ወደቦታዬ መጥተው የእኔን የባሪያህን ስምና የአንተን የፈጣሪዬን ስም ጠርተው አምላከ ፄዋ ለጽድቅ ብለው ስምህንና ስሜን የሚጠሩትን ሁሉ በምድር የሚኖሩ ኃጥአን ሁሉ ትምርልኝና ስሜን ግልጽ አድርገህ ቃኪዳንህን ትሰጠኝ ዘንድ እለምንሃለሁ›› አለው። ጌታችም መወደጄ ሆይ! እንዳልክ ይሁንልህ፡ ስምህም በዓለም ሁሉ የተገለጠ ይሁን፤ በአንተም ስም የተማጸነውን፣ ቤተ መቅደስህ በታነጸበት ስምህ በተጠራበት፣ ገድልህ በሚነበብበት እኔ በዚያ እገኛለሁ። ዐፅምህ ባረፈበት ቦታ መጥቶ እድናለሁ ብሎ አምኖ አንተን አስቦ ከቤቱ ቢነሣ ስለ አንተ ስለወዳጄ ስለ አገልጋዬ ፄዋ ለጽድቅ ልቡ ያሰበውን ሀሳብ ሁሉ እኔ ገና ከቤቱ ሳይነሣ ከቦታህ ሳይደርስ እዛው እያለ የኅሊናውን ሀሳብ እፈጽምለታለሁ። ገድልህን ያጻፈ፣ ያነበበ የተረጎመ ቃሉንም የሰማ፣ ገድልህን በቤቱ ያኖረ ከዚህ ዓለም ነፍሱ ከሥጋው ስትለይ እኔ መድኃኔዓለም ቃሌ የማይሻረው በአፌ እስመዋለሁ። በደረቴ አቅፌው ያለምንም ወቀሳና ከሰሳ ዓይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው እጅ ያልታነጸውን ሰማያዊ መንግሥቴን ኢየሩሳሌምን አወርሰዋለሁ። መላእክትም ከመጠን በላይ እንዲያስደስቱት አድርገዋለሁ። እኔም አንገቱን እቅፍ አድርጌ እስመዋለሁ። መላእክተ ጽልመትም ብዙ ርቀት ፈርተው እንዲርቁ አደርገዋለሁ። በስምህ በታነጸው ቤተክርስቲያን ከትንሽ ሳንቲም ጀምሮ ዕጣን ጧፍ፣ መገበሪያ፣ መጎናጸፊያ ወይም ማንኛውንም የቤተክርስቲያን ንዋየ ቅድሳት በስምህ የሰጠ፡ የተራበ ያበላ፡ የተጠማ ያጠጣ የታረዘ ያለበሰ፣ የፄዋ ለጽድቅ አምላክ እርዳኝ› ብሎ በስምህ የተማጸነውን ያለምንም ወቀሳና ከሰሳ መላእክት ብርሃን ነፍሱን በብርሃን ጋርደው ደስ አሰኝተው ከሥጋው ለይተው ወደ እኔ ያመጧታል። በዚህ ዓለምም ሲኖር ደስ አሰኘዋለሁ። ፈተናም ወደ ቤቱ ወደ ንብረቱ፡ ወደ ቤተሰቡ፣ ወደ ሀብቱ አይደርስም። አንተን አምኖ በአንተ ስም ተማጽኖ ሳለ ቢታመም እንኳን አምላከ ፄዋ ለጽድቅ እርዳኝ አድነኝ፣ ፈጥነህ ድረስልኝ ብሎ ቢለምነኝ ምንም እንዳልታመመ ፈጥኜ እፈውሰዋለሁ። ወደ ቤተክርስቲያንህ መጥቶ ኃጢአቴን ይቅር በለኝ ብሎ ቢማጸን ወንዱን የ40 ቀን ሴቷን የ80 ቀን ሕፃን አደርጌ ወደ ቤቱ በሰላም እመልሰዋለሁ። ልጅ አጥቶ መካን ሆኖ ወደ አንተ ቢማጸን እቤቱም ሆኖ የፄዋ ለጽድቅ አምላክ ልጅ ስጠኝ ብሎ በስምህ ቢለምነኝ ስለአንተ ስል በቃኝ እስከሚል ድረስ ልጅ እሰጠዋለሁ። ቤተ ክርስቲያንን ያገለገለ፣ ገድልህን ፈጽመህ ባረፍክበት ቦታ የአንተን አምላክ እኔን አምኖ የሚኖረውን ኣንተ ከገባህበት አስገባዋለሁ። እርሱም አባቴ ይልሃል፤ አንተም ልጄ ትለዋለህ። እኔም እጥፍ ድርብ ዋጋ እሰጠዋለሁ። እስከ ሰባት ትውልድም እምረዋለሁ።›

መድኃኔዓለም ክርስቶስ ይህን ቃልከዳን ለአቡነ ፄዋ ለጽድቅ ሰጥቶት ነፍሱን ተቀብሏት ስምንተኛው ሺህ ሳይገባ ህዳር 29 ቀን ከቅዱሳን ባለሟሎቹ ጋር በይባቤ በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ። ጸሎቱ ወበረከቱ የሀሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም አሜን። (ሰሜን ሽዋ እነዋሪ አልባሳ ከሚገኘው ከአቡነ ፄዋ ለጽድቅ ቤ/ከ ከገድሉ ላይ የተገኘ ማስታወሻ)
ምንጭ በእንተ ኅሩይ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ የተወስደ
ኅዳር 28/3/2015ዓ.ም
Kuwait

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† አምላከ ቅዱስ እንድርያስ ከሞተ ልቡና አንቅቶ ለክብሩ ያድርሰን:: ከበረከቱም ያድለን::

††† ታኅሣሥ 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
2.አባ ጻዕ
3.አባ ያዕቆብ
4.ቅድስት ታኦድራ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ
2.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
3.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት)

††† "ሁለቱም ደቀ መዛሙርት ሲናገር ሰምተው ጌታ ኢየሱስን ተከተሉት:: ጌታ ኢየሱስም ዘወር ብሎ: ሲከተሉትም አይቶ:- "ምን ትፈልጋላችሁ?" አላቸው:: እነርሱም:- "ረቢ ወዴት ትኖራለህ?" አሉት:: ትርጓሜው "መምህር ሆይ!" ማለት ነው:: "መጥታችሁ እዩ" አላቸው:: መጥተው የሚኖርበትን አዩ:: በዚያም ቀን በእርሱ ዘንድ ዋሉ:: አሥር ሰዓት ያህል ነበረ:: ከዮሐንስ ዘንድ ሰምተው ከተከተሉት ከሁለቱ አንዱ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ ነበረ::" †††
(ዮሐ. ፩፥፴፯-፵፩)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
ዝክረ ቅዱሳን Saints Of The Orthodox Church
🔴በቴሌግራም ለመከታተል👉/channel/zikirekdusn
🛑በዩቲብለመከታተል👉
https://youtube.com/shorts/egux4JdrPrw?si=MjLWZmAjsMzYfmlB

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✅ስነ-ግጥም
💥ቃል ብቻ ተናገር...! (ማቴ፡8÷8)
...............................
ቃል ብቻ ተናገር ቃልህ ቃልን ያውጣ

ፀጋህ ከአርያም መጎብኘትህ ትምጣ

ልምሾው ቀንቶ ይሂድ ይፈወስ ድውዩ

ቅን ማድረግን ይማር ይመለስ በዳዩ

ማየት ላልሆነለት በለምፅ ለነደደው

በችግር ሸለቆ ቁልቁል ለወረደው

በጦርነት እሳት ለሚለበለበው

ሰላምን ተጠምቶ ፍቅር ለተራበው

ለምስኪኑ ሕዝብህ በግፍ ለተገፋ

ከቃልህ በስተቀር ከየት ይገኛል ተሥፋ?

እንኳን ይሄ ችግር የሰው ልጆች እንከን

ተዐምር አይተናል በቃልህ ሲከወን

ጥንትስ ሕያው ሆነው ዓለማት የቆሙት

ሰማይና ምድር ሕዋው ላይ የፀኑት

ጨለማና ብርሃን የሚመላለሰው

ቀላዩ አፍላጋቱ ሞልቶ የሚፈሰው

ይሄ የሚታየው ትንሹ ትልቁ

ደግሞ የማይታየው ስውሩ ረቂቁ

የትመጣው ቃልህ ነው ሥረ-ምክንያቱ

በቋንቋው ይናገር ይመስክር ፍጥረቱ

መለኮት ነው ቃልህ ከዘላለም ኗሪ

ሥርዓተ ዓለሙን በወጉ ቀማሪ

ወቅት አፈራራቂ ዘመን አመላላሽ

ውብ አርጎ የሚያንፅ ሲለው ደግሞ አፍራሽ

አልፋ ኦሜጋ ነው ፊተኛ ኋለኛ

ለፍጥረታት ሁሉ ምክንያት መገኛ

በቃልነት ከዊን በደም የተፃፈ

የከበረ ስም ነው ሥንቱን ያሳረፈ

ወላፈን ነው ቃልህ ነዲድ የእሳት ቋያ

ወርቅና አፈሩን አንጥሮ መለያ

ብረትን አራቂ ጥሬውን ማብሰያ

የሕይወት እሳት ነው ሕይወትን መሳያ

በቁጣ ሲነገር መዓት ነው ገሞራ

ምድር ትጤሳለች ይቀልጣል ተራራ

ሰማያትን ፈቺ በታላቅ ትኩሳት

ቃል ነው መተግበሪያው ግሩም ነደ እሳት

ቃልህ መዶሻ ነው አለቱን ሰባሪ

የደነደነን ልብ ፈርክሶ አሳማሪ

አስተካክሎ ጠርቦ ውብ አርጎ የሚያንፅ

የባከነን ሕይወት እንደ እርሳስ የሚቀርፅ

ሸለቆ የሆነን በቀቢፀ ተሥፋ

በትዕቢት ያበጠን እንደ አድማስ የሰፋ

ከደልዳላ መሬት የሚያስተካክለው

ቃልህ ባለ ሥልጣን የእውነት ዳኛ ነው

ቃልህ ነበልባል ነው ሁለት ስለት ያለው

የልቦናን ሃሳብ የሚመረምረው

ነፍስና መንፈስን ቅልጥምና ሥጋ

ሲቃጣ ሳይታይ ዘልቆ የሚወጋ

ሸለፈትን ቆራጭ አዚምን ገፋፊ

ሰነፉን ገስፆ ዘባቹን ቀሳፊ

የመንፈስ ሰይፍ ነው ቃልህ የእኛ ጌታ

ለማዳን ለፍትሕ የምትበረታ

ቃልህ ወለላ ነው ማርና ወተት

የእኔ የእኔ እያሉ የሚሻሙበት

የነፍስ ምግብ ነው የሕይወት እንጀራ

አጥንት አለምልሞ ገፅን የሚያበራ

የሕግ መብራት ነው የብርሃን መንገድ

ወደ እውነት ሀገር እየመራ የሚወስድ

ሺውን የሚያፈራ ቃል ነው የዘር ቅንጣት

ቃል ብቻ ተናግረህ ምድሪቱን ለውጣት

የዳዊት ልጅ ማረኝ ብሎ ለሚጣራ

ለተነወረች ሴት ደም ለምታዘራ

ወዮታ ላበዛው በድን ልጅ ታቅፎ

ታምኖ ለተገኘ ሺህ ምዕራፍን አልፎ

በባርነት ቀንበር አንገቱን ለደፋ

ባህር በረሃውን በስደት ለለፋ

ቁራሽ እንጀራና እፍኝ ጥሬ አጥቶ

ቅስሙን ለሰበረው ራቡ በርትቶ

ከሞት ትንፋግና ከባሩድ ጢስ በቀር

አጥቶ ለጨነቀው ሰላም ንፁህ አየር

ሞራሉ ላሽቆበት ግብረ ገብ ለራቀው

በኃጢአት አዘቅት ውስጥ ቁልቁል ለወደቀው

በሰይጣን ወጥመድ ውስጥ ክፉኛ ተይዞ

በምርኮ ለሚኖር ሕሊናው ደንዝዞ

ለዚህ ሁሉ ምስኪን ለዚህ ችግርተኛ

እንቆቅልሽ ፈቺ ቤዛና መዳኛ

ከቶ የለምና ቃል ሆይ ከአንተ በቀር

ቃልህ ቃልን ያውጣ ቃል ብቻ ተናገር

የየሰዉ ወጥመድ ችግርና ቀንበር

በኃይልህ ይወገድ በቃልህ ይሰበር

ቃል...... ብቻ.........ተናገር..........!

👇👇
💥 🔍ኪነ-ጥበብ🔎💥
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

"ማርያም ሆይ፣ የሐናን ጡት እየጠባሽ ወደ ቤተ መቅደስ በገባሽ ጊዜ ያገኘሽ ያለ እናት ማደግ ያሳዝነኛል፤ ዳግመኛም በደመና የሚጫን የእሳት አበባ የለበሰ ፋኑኤል እንደ አባት ከመላእክት ጋር መናን እየመገበሽ በቅድስና የማደግሽ ምሥጢር ያስደስተኛል"

አባ ጽጌ ድንግል

እንኳን ለእመቤታችን ወደ መቅደስ የመግባት በዓል በሰላም አደረሰን!!!

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እመቤታችን ከተፀነሰች በኋላ አይሁድ ቀንተው ተነሱባቸው ቅናቱ እንዴት ነው ቢሉ ሳሚናስ የሚባል የጦሊቅ ልጅ ከኤዶቅ ካጎቱ ቤት ሄዶ ሞተ፤ እነርሱም እንቀብራለን ብለው ባልጋ ይዘው ሲሄዱ ከመንገድ አሳረፉት፡፡ ቅድስት ሐናም የአጎቷ ልጅ ነበርና ለማልቀስ ብትደርስ ዘመዶቿ ሁሉ ተሰብስበው ሲላቀሱ ቆዯአት፤ እርሷም አብራ እየዞረች ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ብድግ ብሎ ተነሥቶ "ስብሃት ለኪ ማርያም እሙ ለፀሐየ ጽድቅ ለአብ ሙሽራው ለወልድ ወላዲቱ ለመንፈስ ቅዱስ ጽርሃ ቤቱ ተፈስሂ ደስ ይበልሽ" ብሎ ሰገደላት፡፡ አይሁድም ይህ ተአምር ሲደረግ ከዚያው ነበሩና "ምነው ሳሚናስ ምን አየህ? ምን ትላለህ?" ቢሉት "ከዚች ከሐና ማኅፀን የምትወለደው ሕፃን ሰማይ ምድርን አየርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለች እያሉ መላእክት ሁሉ ሲያመሰግኗት ሰማሁ" አላቸው፡፡ ዳግመኛም "እኔንም ያነሣችኝ የፈወሰችኝ ያዳነችኝ እርሷ ናት" አላቸው፡፡ አይሁድም "በል ተወው ሰማንህ" ብለው ቅናት ጀመሩ፡፡ ሐና በእርጅናዋ ጊዜ መፀነሷን የተመለከቱ ዘመዶቿና ያገሯ ሰዎች ተገርመው እየመጡ ይጠይቋት ነበር፡፡ እመቤታችን ማርያም በፅንስ እያለች ብዙ ታምራትን አድርጋለች። ከእነዚህም መካከል ዐይነ ስውር የነበረችው የአርሳባን ልጅ ወደ ሐና መጥታ እውነትም ሐና መጸነሷን ለማረጋገጥ ሆዷን ዳሰሰቻት፡፡ እርሷም ሳታስበው ዐይኗን ስትነካ ዐይኗ በራላት፡፡ እመቤታችንም በተፀነሰች በ9 ወር ከአምስት ቀን የግንቦት መባቻ ዕለት ግንቦት 1 ተወለደች፡፡ ሦስት ዓመትም በሆናት ጊዜ እናትና አባቷ ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐና ስዕለታቸውን አስበው የአምላክ እናት ብፅዓት አድርገው ለእግዚአብሔር ይሰጧት ዘንድ በዚህች ዕለት ወደ ቤተ መቅደስ ወሰዷት፡፡
የብርሃን እናቱ ክብርት እመቤታችን ከበዓሏ ረድኤት በረከት ትክፈለን!
ከገድላት አንደበት
✞ ✞ ✞

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አባታችን ዜና ማርቆስ በኤልያስ ሠረገላ ሆነው እግዚአብሔርን ወደማያውቁት ወደ አዳል ሕዝቦች ሄደው ከጣዖት አምላኪው ንጉሥ ከአብደልማል ፊት ወንጌልን ሲያስተምሩ ንጉሡ በጦር ወግቶ ገድሏቸዋል፣ ነገር ግን መልአኩ ሩፋኤል መጥቶ ከሞት አሥተስቷቸዋል፡፡ የንጉሡን ጣዖትና አገልጋዮቹን መብረቅ ከሰማይ ወርዶ ሲያጠፋቸው ንጉሡና ሠራዊታቸው ደግሞ በመሬት ላይ ወድቀው ቀርተዋል፡፡ ከዓርብ እስከ ሰኞም ድረስ ጨለማ ሆኖ ከቆየ በኋላ ከአባታችን ከተወጋ ጎናቸው የፀሐይ ብርሃን ወጥቶ ለንጉሡ አብደልማል አብርቶለታል፡፡ እርሱም አምኖ ከነቤተሰቡ የተጠመቀ ሲሆን ሚስቱም በአረማውያን ዘንድ ለክርስቶስ ምስክር ሆና አንገቷን ተሰይፋ ሰማዕትነትን ተቀብላለች፡፡ በሀገሪቱም የተጠመቁት ሰዎች ቁጥር ከስምንት መቶ ሺህ በላይ ናቸው፡፡
ከዚህም በኋላ አቡነ ዜና ማርቆስ እንደ ሐዋርያትም ደመና በመጥቀስ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ሄደው ሁሉንም የተቀደሱ ቦታዎችን ተሳልሟዋል፡፡ ከጌታችን መቃብር ላይ አፈር ዘግነው ከዮርዳኖስም ወንዝ ውኃ ቀድተው ለንስር አሞራዎች አሸክመው ወደ ገዳማቸው በማምጣት በደብረ ብስራት ምድር ካለው አፈርና ውኃ ጋር ጨምረውታል፡፡ ጌታችም ‹‹ይህችን ምድርህን እንደ ኢየሩሳሌም አድርጌልሃለሁ›› የሚል ቃልኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡ አባታችን ከደብረ ሊባኖስ አውራጃ ራሱን ያስመልክ የነበረን ሰይጣን ገዝተው ይዘው እስከ ደብረ ብስራት ድረስ የቤተክርስቲያን መሥሪያ እንጨት አሸክመውታል፡፡ በዚያም እንጨት በመሸከም ሲያገለግላቸው ኖሯል፡፡
አባታችን ዜና ማርቆስ ወደ ዋልድባ በመሄድ ከአባ ሳሙኤል ጋር ተገናኝተው እንዲሁም ከሌሎች በርካታ አባቶች በየቦታው እየሄዱ በረከት ተቀብለዋል፡፡ ወደ ትግራይም በመሄድ የተሰዓቱ ቅዱሳንን ገዳማት ተሳልመው ወደ ሰሜንም ሄደው ዜማውን ሲያዜም ያሳያቸው ዘንድ ወደ ቅዱስ ያሬድ መቃብር ሄደው ሰባት ቀን ሲማጸኑ ከቆዩ በኋላ ወደ አክሱም ጽዮን ሄደው በዚያ ከቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱስ ኤፍሬምና ከቅዱስ አባ ሕርያቆስ ጋር ሆኖ እነርሱ ድርሰታቸውን ሲያነቡ ያሬድ ደግሞ ድርሰታቸውን እያዜመው ተገልጠውላቸዋል፡፡ አባታችን ወደ ላሊበላም ሄደው ከቅዱስ ላሊበላ በረከትን ተቀብለዋል፡፡ ወደ ጣና ደሴትም ሄደው በዚያ ካሉ ቅዱሳን ተባርከዋል፡፡ ሐይቅ እስጢፋኖስም አባ ኢየሱስ ሞዐ ጋር በመሄድ እንዲሁ ተባርከዋል፡፡ በታናሽ ደመናም ወደ ብሔረ ሕያዋን ተነጥቀው ሞትን ካልቀመሱት ከሄኖክ፣ ከኤልያስና ከዕዝራ በረከትን ተቀብለዋል፡፡ ወደ እስላም ሀገርም በመሄድ ለአንድ ዓመት ቆይተው በዚያ ያሉ ሕዝቦችን በተአምራቸውና በትምህርታቸው አሳምነው አጥምቀዋቸዋል፡፡ ጌታችን በምድር ላይ ብዙ ቃልኪዳን ከሰጣቸው በኋላ ወደ ሰማይ አውጥቶ ገነትንና ሲኦልን ሁሉን አሳይቷቸዋል፡፡
አቡነ ዜና ማርቆስ 8 እንጀራን አበርክተው 8ሺህ ሰዎችን በመመገብ ጌታችንን መስለውታል፡፡ ቀድሰው ሕዝቡን ሁሉ ሲያቆርቡ ቢመሽባቸው ፀሐይን እንደ ኢያሱ ገዝተው አቁመዋታል፡፡ በታኅሣሥ ወር መባቻ አባታችን በገዳመ ደንስ በረሃ ያገኛት ተአምረኛዋ ሥዕለ ማርያም ወዳለችበት ቤተክርስቲያን ሄደና ለመቀደስ ሠራዒ ካህን ሆኖ ተሠየመና እንደሚገባ የቅዳሴውን ሥርዓት ጀመረ፡፡ ማዕጠንት ይዞ እየዞረ የቤተ ክርስቲያኑን በሮች በሚያጥንበት ጊዜ ሥጋ ወደሙን ለመቀበል እርስ በእርሳቸው ሲጨናነቁ የልጆቹ መነኮሳትን ብዛት ተመለከተ፡፡ ያን ጊዜም በልቡ አሰበ፣ እንዲህም አለ፡- ‹ይህን ያህል ያለውን ሰው ቅዱስ ቊርባን ማቀበል እንዴት ይቻላል? ይህ ሁሉ ሰው በተራ እስከሚቀበል ድረስ ፀሐይ ይገባል፣ መሽቶ ሌሊትም ይሆናል› አለ፡፡ ከዚህም በኋላ ዐይነ ልቡናውን ወደ ሰማይ አቅንቶ ‹አቤቱ ጠላቶቹን እስከደመሰሰና ለእስራኤል ልጆች ርስታቸውን እስካካፈለ ድረስ ለኢያሱ ፀሐይን በገባዖን ያቆምክ አንተ ነህ፤ ዛሬም ቅዱስ ሥጋህን ክቡር ደምህን ለእነዚህ ባሮችህ ቅዱሳን መነኮሳትና ለሕዝቦችህ እስከማቀብላቸው ድረስ እንዲሁ በቸርነትህ ብዛት ፀሐይን አቁማት› ብሎ በጸለየ ጊዜ ፀሐይዋ ወዲያውኑ ቆመች፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዳሴውን ጨርሶ ሕዝቡን ሁሉ አቆረባቸው፡፡››
ቅዱስ አባታችን በምሁር ኢየሱስ ገዳም ከሬብ በሚባል ዋሻ ውስጥ 40 ዓመት ዘግተው ተጋድለዋል፡፡ በዚህም ሳሉ መልአክ የዕረፍታቸውን ዕለት ታኅሣሥ ሦስት ቀን እንደሚሆን ስለነገራቸው ታኅሣሥ አንድ ቀን ወደ ገዳማቸው በመሄድ ቀድሰው ሕዝቡን ሁሉ ሲያቆርቡ ቢመሽባቸው ፀሐይን ለሁለተኛ ጊዜ እንደ ኢያሱ ገዝተው አቁመዋታል፡፡ አባታችን ዜና ማርቆስ የዕረፍታቸውን ዕለት ከመልአኩ ከተረዱ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አሏቸው፡- ‹‹ከዚህ ዓለም የምለይበት ጊዜ ደርሷልና ወደ ፈጣሩዬ እሄዳለሁ፣ እኔ ሽማግሌ አባታችሁ የምመክራችሁን ስሙ፣ ከበጎ ሥራ ሁሉ አስቀድማችሁ እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ፣ ፍቅር ሰማያዊ መንግሥትን ለማግኘት በባለሟልነት ወደ እግዚአብሔር ፊት ያደርሳልና›› ብለው መከሯቸው፡፡ ዳግመኛም ጾመኛ ነኝ አትበሉ አሏቸው፡፡ ‹‹ስለ ነፍሳችሁ ድኅነት፣ ከመከራና ከጥፋትም ሁሉ ለማምለጥ በምትጾሙ ጊዜ እንዲህ እየጾማችሁ ሳላችሁ ስለምትሹት ግብር ወደ ዓለም ሰዎች ብትደርሱና በጾም ቀን ሲበሉና ሲጠጡ ብታዩአቸው መብልና መጠጥን በሚወዱ ሰዎች ፊት በውጭ በአደባባይ ‹ዛሬ የጾም ቀን ስለሆነ እኛ እንጾማለን› አትበሉ፡፡ ስለ እናንተ መጾምና ስለ እነርሱም አለመጾም አንዳች አትናገሩ፣ ባለመጾማቸውም አትንቀፏቸው፡፡ ስለ ሌላ ሥራ ወደማይጾሙ ሰዎች ብትደርሱ ግን በጾም ዕለት ወንድሞቻችን ‹ኑ አብረን እንብላ› ቢሏችሁ እኛ እንጾማለን አትበሉ፣ እንዲህ በሉ እንጂ፡- ‹ወደ እናንተ ከመምጣታችን በፊት ከቤት በልተናል፣ ጠግበናል› ስትሏቸው እናንተ እንደምትጾሙ ያውቃሉ፡፡›››
ከዚህም በኋላ አቡነ ዜና ማርቆስ ታኅሣሥ ሁለት ቀን የደቀ መዛሙርቶቻቸውን እግር ሲያጥቡ ውለው አስቀድሞ መልአኩ እንደነገራቸው ታኅሣሥ ሦስት ቀን በ140 ዓመታቸው ነቢይም፣ ሐዋርያም፣ ካህንም፣ ባለራእይም፣ የሀገራችንም ብርሃን የሆኑት ጻዲቁ አባታችን በክብር ዐርፈዋል፡፡
የአቡነ ዜና ማርቆስ ረድኤት በረከታቸው ይደረርብን በጸሎታቸው ይማረን!
+ + +
በዓታ ለማርያም፡- የብርሃን እናቱ የድንግል ወላዲተ አምላክን የትውልዷን ነገር እንዲህ ነው፡- ጴጥርቃ እና ቴክታ የሚባሉ የከበሩ ደጋግ ሰዎች በኢየሩሳሌም በአንድነት ተጋብተው በሕገ እግዚአብሔር ይኖሩ ነበር፡፡ እነዚህም በእግዚአብሔር የሚያምኑ የተወደዱ ጻድቃን ደግ ሰዎች ናቸው፡፡ እነርሱም በእግዚአብሄርም በሰውም ዘንድ የተመሰከረለላቸው ባለጸጎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን መካን ስለነነበሩ የሚወርሳቸው ልጅ አልነበራቸውም፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እሳቸው ግን በሠርጉ ሌሊት ከጫጉላ ቤት ጠፍተው በርሃ ገቡ:: ከዚያም በቅዱስ መልአክ መሪነት ሃገረ ምሑር ደረሱ:: በቦታውም ጣዖትን ሰባብረው: ተአምራትንም አድርገው: ሕዝቡን ወደ ክርስትና መለሱ:: መስፍኑ አውጊት ግን ተፈታተናቸው: አሠራቸው: አሥራባቸው::

በጦር እወጋለሁ ሲል ግን መሬት ተከፍታ ከነ ተከታዮቹ ውጣዋለች:: ከ5 ዓመታት በኋላ ግን ማልደው: ከሰጠመበት አውጥተው አጥምቀውታል:: ቀጥለውም ምድረ ጉራጌ ወርደው: ሕዝቡን አሳምነው አጥምቀዋል::

የአዳልን ሕዝብና ንጉሡን አብደልማልን አስተምረው ያጠመቁም እርሳቸው ናቸው:: ድል አሰግድ የሚባለውን መስፍንም ያሳምኑ ዘንድ ጠንቅዋዮቹን ድል አድርገው አጥፍተዋል::

ጻድቁ ዜና ማርቆስ ከዚህ ሐዋርያዊ ሥራቸው በተጨማሪ በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ምንኩስናን ከተቀበሉባት ቀን ጀምረው በጾም: በጸሎትና በሰጊድ ኑረዋል:: ፀሐይን በምድረ ጉራጌ እስከ ማቆም ደርሰውም ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል::

አእላፍ ደቀ መዛሙርትን ሲያፈሩ 200 አንበሶች በቀኝ: 200 ነብሮች በግራ ይከተሏቸው ነበር:: ደብረ ብሥራትን ጨምሮም ገዳማትን አንጸዋል:: በመጨረሻም የምሕረት ቃል ኪዳንን ከፈጣሪ ዘንድ ተቀብለው ታኅሣሥ ሦስት ቀን በ140 ዓመታቸው ዐርፈዋል::

††† የእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟ: ፍቅሯ: ጸጋዋና በረከቷ ይደርብን::

††† ታኅሣሥ 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም
2.ብጹዓን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱሳን ካህናት ዘካርያስና ስምዖን
4.ቅዱስ ፋኑኤል ሊቀ መላእክት
5.አቡነ ዜና ማርቆስ ጻድቅ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ጻድቅ (ዘደብረ በንኮል)
2.አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
3.ቅዱስ ቄርሎስ ሊቅ (ዓምደ ሃይማኖት)

††† "ድንግል ሆይ! አንገታቸውን እንደሚያረዝሙ እንደ እብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለሽም:: በቅድስናና በንጽሕና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ::
ድንግል ሆይ! ምድራዊ ሕብስትን የተመገብሽ አይደለም:: ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ሕብስትን እንጂ::
ድንግል ሆይ! ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለም:: ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጠጥን እንጂ::" †††
(ቅዳሴ ማርያም)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

"ንስሓ ሳይገባ እንዳይሞት"

በኀጢአት ብንወድቅ እንኳን ቅዱሳን ለነፍሳችን ድኅነት ምን ያህል እንደሚተጉ ይኽ ታሪክ በእጅጉ ያስተምረናል። ንጉሥ ዓምደ ጽዮን በነገሠ ጊዜ እንደ አባቱ እግዚአብሔርን የሚወድ ሃይማኖቱ የቀና ነበር፡፡ ከዚኽም በኋላ ሰይጣን የዝሙትን ሥራ የሚያሠራው ሆነ፡፡ አንዲት የአባቱ ቅምጥ የነበረችውንም አመንዝራ ሴት አገባ፡፡ እርሷም ሰንበትን እስከሻረና ሃይማኖቱን እስከለመወጠ ድረስ ኀጢአትን አሠራችው፡፡ ስለዚህም የክቡር አባታችን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ልጅ አባ ፊሊጶስ ንጉሡን አወገዘው፡፡ ንጉሡም አብያተ ክርስቲያናትን ዘጋቸው፡፡

በዚያም ወራት አባታችን ዜና ማርቆስ በደብረ ብሥራት ገዳም አልነበረም-በንጉሥ ዓምደ ጽዮን በአባቱ በይኩኖ አምላክ ዘመን ፈጽሞ ተሠውሮ ነበርና፡፡ ምክንያቱም ለንጉሥ ይኩኖ አምላክ የእኅቱ ልጅ ስለነበር ራስ ወይም ቢትወደድ አድርጎ በዓለም እንዳይሾመው ስለዚህ ከደብረ ብሥራት ሸሽቶ በምሁር ሀገር ወደሚገኝ የጎጎት ጫካ ውስጥ የይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት እንስከሚያልፍ ድረስ ተሠውሮ ኖረ፡፡

ንጉሥ ዓምደ ጽዮንም ሃይማኖቱን በካደ ጊዜ እስከ አርባ ዓመት በተሠወረበት ቦታ ኖረ፡፡ ልጆቹ ቅዱሳን መነኰሳትን ይጎበኛቸው ዘንድ በጣና ባሕር ወዳለች የደቅ ደሴት ሲሔድ በደመና ላይ ተጭኖ ነበር፣ ወደ ምሁር ሀገር ሲመለስም በአንበሶችና በነብሮች ጀርባ ላይ ሆኖ በሥውር ነበር፡፡ ንጉሥ ዓምደ ጽዮንም በነገሠ ጊዜ በ14ኛው ዓመት ጌታችን በሞት ሊወስደው ወደደ፡፡ ያንጊዜም ሰውን የምትወድ አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስለ ንጉሡ ልጇን መድኃኔዓለምን ማለደችው፡፡ ልጇ ያለ ንስሓ በቁጣው እንዳይቀሥፈው አባታችን ዜና ማርቆስ ይለምናት
ነበርና፡፡

አባታችንም በሚጸልይ ጊዜ እንዲህ ብሎ ለመናት፡- ‹ለሰው ዘር ሁሉ የምትራሪ አምላክን የወለድሽ በሁለት ወገን ድንግል የሆንሽ እመቤቴ ማርያም ሆይ! ባሪያሽ ዓምደ ጽዮን ከኃጢአቱ ተመልሶ ንስሓ ሳይገባ እንዳይሞት፤ የልጅሽ ጠላት ሰይጣን በዝሙት ሥራ ሳያስተው በፊት ወዳጅሽ ነበርና አስቢ፡፡ ልጅሽም ለጻድቃን ብቻ አልመጣምና ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ስለ ኃጢአተኞች ድኅነት ከአንቺ ከሥጋሽ ሥጋን ከነፍስሽ ነፍስን ነሥቶ ሰው ሆነ እንጂ፡፡ እርሱ ራሱ በቅዱስ ወንጌሉ ‹ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም ኃጥአንን ወደ ንስሓ ልጠራ መጥቻለሁ እንጂ› ብሏልና፡፡ እመቤቴ ሆይ! በልጅሽ ፊት ይህንን አሳስቢ፣ እርሱ እስከ ዘለዓለም ይቅርታ በማድረግ ምሕረቱ የበዛ መሐሪ ነው› እያለ ለመናት፡፡ በዚያም ወራት ክብርት እመቤታችን አባታችንን ዜና ማርቆስን ‹ወደ ዓምደ ጽዮን ሔደህ ንስሓ ግባ በለው› አለችው፡፡

የሕይወት እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ይህን ስለነገረችው አባታችን ዜና ማርቆስ ደስ አለው፡፡ እርሷ የምትራራ የሁላችን ተስፋ፣ የኃጥአን መዳኛቸው፣ ጻድቃንንም መልካም የሆነ ተጋድሏቸውን እስኪፈጽሙ ድረስ የምትረዳቸው ናትና፡፡ አባታችን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም ‹‹እግዚአብሔር ሊምረው የወደደውን ሰው የማርያምን ፍቅር ያሳድርበታል›› ሲል የተናገረው ለዚህ ነው፡፡

ከዚኽም በኋላ አባታችን ዜና ማርቆስ ወደ ደብረ ብሥራት ገብቶ ከልጆቹ ጋር በ40 ዓመቱ ተገናኘ፡፡ እነርሱም ይህን ያህል ዘመን ሲጠፋባቸው ያረፈ መስሏቸው ነበርና አሁን
ባገኙት ጊዜ ተደንቀው ወዴት እንደነበር ሲጠይቁት አባታችንም ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው የሆነውን ነገራቸው፡፡ ከዚኽም በኋላ በትምህርትና በዕድሜ ከሌሎቹ
መነኰሳት ልጆቹ የሚበልጠውን ልጁን አባ እንድርያስን ወደ ንጉሥ ዓምደ ጽዮን ንስሓ እንዲገባ መልእክት ያደርስ ዘንድ ላከው፡፡ አባታችንም በገዳሙ ሆኖ ስለ ንጉሡ ሱባኤ ይዞ ስለነበር ንጉሡ ልቡናው ተመለሰለት፣ ያደረበት የዝሙት መንፈስም ለቆት ጠፋ፡፡ ንጉሡም የአባታችንን መልእክት ከሰማ በኋላ በተሰበረ ኅሊና ሆኖ ንስሓ ገባ፡፡ አባ እንድርያስንም ‹ኃጢአቴ ከሰው ሁሉ ኃጢአት የበዛ ነውና ከባድ ቀኖና ስጠኝ› አለው፡፡

ዳግመኛም ‹ለእኔ በማትገባኝ አመንዝራ ሴት ምክንያት የአባታችን የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን ልጆች በግፍ እንድገድላቸውና ከመንበረ ክብራቸው እንዳሳድዳቸው ሰይጣን አስገድዶኛል፣ ስለዚህም የማትገባኝን አመንዝራ ሴት ስለማግባቴና ስለቅዱሳን ደም ፈጣሪዬ ተቆጥቶ ወደ ገሃነመ እሳት እንዳይጨምረኝ ከገጸ መዓቱ የተነሣ
እፈራለሁና› ብሎ መሪር እንባን አለቀሰ፡፡ አባታችን ዜና ማርቆስም በዚያች ሌሊት ስለእርሱ ከመስገድና ከመጸለይ
አላቋረጠም ነበር፡፡

ከዚኽም በኋላ ንጉሡ ከአባታችን ዜና ማርቆስ ረድእ ቀኖና ተቀብሎ በቀንም በሌሊትም በየሰዓቱ እልፍ እልፍ እየሰገደ በሌሊትም ከዙፋኑ ወደ መሬት ወርዶ እየሰገደ ያድራል። በቀንም በወርቅ ከተሠራ ልብሰ መንግሥቱ ሥር ከበግ ፀጉር የተሠራ ማቅ የሚለብስ ሆነ፡፡ ቀኖናም ከተቀበለ በኋላ የአባታችን ዜና ማርቆስ የጸሎቱ ኃይል ከአጋንንት ጦር እየረዳው በአንድ ዓመቱ ቀኖናውን ፈጽሞ በሰላም ዐረፈ፤ ወደ መንግሥተ ሰማያትም ገባ፡፡
(ገድለ አቡነ ዜና ማርቆስ ገጽ 248-254 )

የአቡነ ዜና ማርቆስ እመቤት አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችን እኛንም ታስምረን። ምንም እንኳን በከፋ ኀጢአት ብንወድቅ ለነፍሳችን ድኅነት የሚተጉ ቅዱሳን አባቶቻችንና ቅዱሳት እናቶቻችን የሰጠን ልዑል እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን!!!
ምንጭ# በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/ethio_forex_signal

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

2.አባ ሖር ጻድቅ
3.ቅዱስ አውካቲዎስ ሰማዕት
4.አባ አንበስ ሰማዕት
5.7,033 ሰማዕታት (የቅዱስ ፋሲለደስማሕበር)
6.ቅዱስ ናትናኤል መነኮስ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
2.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
3.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
4.ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ)
5.ቅዱስ ዮሐንስ ነቢይ (መጥምቀ መለኮት)
6.ሊቁ አባ ሕርያቆስ
7.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ

=>+"+ ናቡከደነፆርም መልሶ:- 'መልአኩን የላከ: ከአምላካቸውም በቀር ማንንም አምላክ እንዳያመልኩ: ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን: የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን: በእርሱ የታመኑትን ባርያዎቹን ያዳነ: የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ::' +"+ (ዳን. 3:28)

✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ዛሬም ደምር!.....
🔊 ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ 35 ኦርቶዶክሳዊያን የተገደሉበት ቦታ በዕለተ ሰንበት/እሁድ/ ደሞ 6 ኦርቶዶክሳዊያን በቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ ተገደሉ 35+6=.......
መንግስት ስራው ስለሆነ ዝም አልን ሲኖዶሱ ግን ምን ነካው!

📣ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑርል!

📣❗️ኪነ-ጥበብ📣❗️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/zikirekdusn
✞✞✞✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ ታኅሣሥ ፩ (1) ❖

✞✞✞✝ እንኩዋን ለታላቁ ነቢይ "ቅዱስ ኤልያስ" :
"ቅዱስ ዼጥሮስ ዘጋዛ" እና "ቅድስት ቤርሳቤህ"
ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+*" ታላቁ ቅዱስ ኤልያስ "*+

=>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ
ቀጥላ ቅዱስ ኤልያስን ታከብራለች:: "ርዕሰ ነቢያት - የነቢያት ራስም" ትለዋለች:: እርሱ ሰማይን የለጐመ:
እሳትን ያዘነመ: ፍጥረትንም በቃሉ ያዘዘ አባት ነውና::
ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+ቅዱሱ ትውልዱ (ነገዱ) ኢዮርብዓም ነጥሎ
ከወሰዳቸው እሥራኤል (10ሩ ነገድ) ሲሆን አባቱ
"ኢያስኑዩ" : እናቱ ደግሞ "ቶና (ቶናህ)" ይባላሉ:: በጐ
አምልኮ ነበራቸውና እግዚአብሔር ማሕጸነ ቶናህን ቀድሶ
ይህንን ቅዱስ ፍሬ ፈጠረ::

+ቅዱስ ኤልያስ በተወለደ ቀን በቤታቸው ብርሃን ተሞልቶ
ታይቷል:: ብርሃን የለበሱ 4 ሰዎች (መላእክት)
መጥተውም በእሳት ሰፋድል (መጐናጸፊያ) ሲጠቀልሉት
ወላጆቹ በማየታቸው ደንግጠው ለነቢያትና ለካህናት ነገሯቸው::

+ካህናቱ ግን ነገሩ ቢረቅባቸው "ምን ዓይነት ፍጥረት
ይሆን? በእሥራኤል ይነግሥ ይሆን! ወይስ ነቢይ
ይሆን?" ብለውም አድንቀዋል:: ቅዱስ ኤልያስ ከልጅነቱ
ጀምሮ ኮስታራ: ቁም ነገረኛ: ንጽሕናንም የሚወድ
እሥራኤላዊ ነው::

+ወቅቱ (ከክርስቶስ ልደት 900 ዓመት በፊት) ሕዝቡና
ነገሥታቱ የከፉበት: እግዚአብሔር ተክዶ ጣዖት
የሚመለክበት ነበር:: ድሮ በኢሎፍላውያን እጅ የነበሩት
ጣዖታት (ዳጐንና ቤል) በዚያ ዘመን ወደ እሥራኤል
ገብተው ነበር::

+ቅዱስ ኤልያስ ግን በዚህ ክፉ ትውልድ መካከል
ሆኖም ሥርዓተ ኦሪትን የጠነቀቀ: የንጽሕናና የአምልኮ ሰው ነበር::

+በዚያ ወራትም እግዚአብሔር ለነቢይነት ጠራው::
እርሱም "እሺ" ብሎ ታዞ የእግዚአብሔርን የጸጋ ጥሪ
ተቀበለ::

ቅዱሱ ብዙ ጊዜ ለጉዳይ ካልሆነ ከሰው ጋር መዋል:
ማደርን አይወድምና መኖሪያውን በተራሮችና በዱር
አደረገ::

+በተለይ ደብረ ቀርሜሎስ ለእርሱ ቤቱ ነበር:: በዚህ
ሕይወቱም ከመልከ ጼዴቅ ቀጥሎ:-

1.ለድንግልና (ድንግል ነበርና)
2.ለብሕትውና (ብቸኛ ነበርና)
3.ለምንኩስና (ተሐራሚ ነበርና) በብሉይ ኪዳን መሠረትን
የጣለ ነቢይ ይባላል::

+መቼም በብሉይ ኪዳን የቅዱስ ኤልያስን: በዘመነ
ክርስቶስ የመጥምቁ ዮሐንስን: በዘመነ ሊቃውንት ደግሞ
የአፈ ወርቅ ዮሐንስን ያህል ደፋርና መገሥጽ አስተማሪ
አልነበረም:: በጊዜው ደግሞ አክአብና ኤልዛቤል የሚባሉ
ክፉ ባልና ሚስት በእሥራኤል ላይ ነግሠው ሕዝቡን
ጣዖት አስመለኩት::

+ይባስ ብለው ደግሞ በወይኑ እርሻ አማካኝነት
ኢይዝራኤላዊው ናቡቴን በሃሰት ምስክር ደሙን
አፈሰሱት:: ናቡቴም "የአባቶቼን ርስት አልሸጥም:
አልለውጥም::" በማለቱ እንደ ሰማዕት ይቆጠራል::

+ኤልያስ ግን ይህንን ሲሰማ ወደ አክአብና ኤልዛቤል
ቀርቦ "የናቡቴ ደም በእናንተ ላይ አይቀርም:: የአንቺንም
ደም ውሻ ይልሰዋል" አላቸው:: በዚህ ምክንያትም
ኤልዛቤል ልትገድለው ብትፈልገውም እርሱ
የእግዚአብሔር ነውና አላገኘችውም::

+በዚህ ብስጭትም ይመስላል አንድ ሺህ ነቢያትን
ሰብስባ "ፍጇቸው" አለች:: 900ው ሲታረዱ አንድ
መቶውን ግን ቅዱስ አብድዩ በዋሻ ውስጥ ደብቆ
እየመገበ አተረፋቸው:: በእሥራኤል ውስጥ ግን ዓመጻና
ኃጢአት እየተስፋፋ ሔደ:: የእግዚአብሔርን ስጦታ
እየተመገበ ሕዝቡ ለቤል (ለበዓል) ሰገደ::

+ይህን ጊዜ ግን ቅዱስ ኤልያስ እንዲህ አለ:-
"ሕያው እግዚአብሔር አምላከ ኃይል: ዘቆምኩ
ቅድሜሁ: ከመ ኢይረድ ጠል በእላ መዋዕል ዘእንበለ
በቃለ አፉየ::" ብሎ ዝናም ከሰማይ እንዳይወርድ
ከለከለ::

ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት ሰማይ ዝናም ለዘር ጠል
ለመከር ከመስጠት ተከለከለ::

+ሕዝቡ በኃጢአቱ ምክንያት ተጐዳ:: እርሱን ቁራ
ይመግበው: ምንጭ ፈልቆለት ይጠጣ ነበር:: ይሔው
ቢቀርበት ጸለየ:: እግዚአብሔርም ከፈለገ ኮራት ወደ
ሰራፕታ እንዲወርድ አዘዘው:: በዚያም የነቢዩ ዮናስ እናት
እንጐቻ ጋግራ ብታበላው ቤቷ በበረከት ተሞላ::

+ልጇ ሕጻኑ ዮናስ ቢሞትም በጸሎቱ አስነሳላት::
ቀጥሎም 7 ጊዜ በትጋት ጸልዮ ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት
የዘጋውን ሰማይ ከፍቶታል:: ሕዝቡም ዕለቱኑ ከበረከቱ
ቀምሰዋል::

+ከዚያ አስቀድሞ ግን ከኤልዛቤል 850 ነቢያተ ሐሰትና
ካህናተ ጣዖት ጋር ተወዳድሮ አሸንፏቸዋል:: መስዋዕት
ሰውተው የእርሱን ብቻ እሳት ከሰማይ ወርዳ
በልታለታለችና ሕዝቡ 850ውን ሐሰተኛ ነቢያት በወንዝ
ዳር በሰይፍ መትተዋቸዋል::

+ይሕንን የሰማች ኤልዛቤልም ትገድለው ዘንድ
አሳደደችው:: "አቤቱ ከአባቶቼ አልበልጥምና ውሰደኝ!
ብቻየን ቀርቻለሁና" ብሎ ቢጸልይ እግዚአብሔር ለጣዖት
ያልሰገዱ ሰባት ሺህ ሰዎችን እንዳተረፈ: እርሱንም ወደ
ብሔረ ሕያዋን እንደሚወስደው ብሥራትን ነገረው::

+ደክሞት ተኝቶ ሳለም ቅዱስ መልአክ (ሚካኤል)
ቀስቅሶ ታየው:: እንጐቻ ባገልግል: ውሃ በመንቀል
አቅርቦ "ብላ! ጠጣ!" አለው:: በላ: ጠጣ: ተኛ:: እንደ
ገና ቀስቅሶ አበላው:: በ3ኛው ግን "ብላዕ እስከ ትጸግብ
እስመ ርሑቅ ፍኖትከ - ጐዳናህ ሩቅ ነውና
እስክትጠግብ ብላ" አለው::

+ኤልያስም ለ40 ቀናት ያለ ምግብ ተጉዟል:: ከዚያ
በሁዋላም ምድራዊ ሕብስትን አልተመገበም::
እግዚአብሔር አክአብና ኤልዛቤልን ከተበቀላቸው
በሁዋላም ቅዱስ ኤልያስ በክፋተኞች ላይ 2 ጊዜ እሳትን
አዝንሟል::

+የሚያርግበት ጊዜ ሲደርስም ደቀ መዝሙሩን ኤልሳዕን
"የምትሻውን ለምነኝ" ቢለው "እጥፍ መንፈስህን"
አለው:: 3 ጊዜ ሊያስመልሰው ሞከረ:: ቅዱስ ኤልሳዕ
ግን በብርታት ተከተለው:: ዮርዳኖስን ከፍለው ከተሻገሩ
በሁዋላ ግን ቅዱስ ኤልያስን ሠረገላ እሳት ወርዶ
ነጠቀው:: ለኤልሳዕም እኩሉን ግምጃውን ጣለለት::

+ዛሬ ቅዱስ ኤልያስ በብሔረ ሕያዋን ያለ ሲሆን በዘመነ
ሐሳዌ መሲሕ መጥቶ በሰማዕትነት ከቅዱስ ሔኖክ ጋር ያርፋል:: (ራዕይ)
¤ለተጨማሪ ንባብ ( ከ1ነገ. 17-2ነገ. 2, እና ዕርገተ ኤልያስን ያንብቡ::)

<<ነቢዩ ኤልያስ በእውነት ታላቅ ነው!>>

+"+ ቅዱስ ዼጥሮስ ዘጋዛ +"+

=>ይህ ቅዱስ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በታናሽ እስያ
አካባቢ የተወለደ ሲሆን የክቡራኑ የመሣፍንት ልጅ ነው::
በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አድጐ የቁስጥንጥንያ ንጉሥ
ትንሹ ቴዎዶስዮስ ወደ ቤተ መንግስቱ ወሰደው::

+በዚያም "አገረ ገዥ ላድርግህ" ብሎ ቢጠይቀው
"ትንሽ ቆየኝማ" ብሎት ጠፍቶ በርሃ ገብቶ መነኮሰ::
ቅዱስ ዼጥሮስ በምንኩስና ሲጋደል: ካለበት በርሃ
መጥተው በግድ ወስደው: የጋዛ (አሁን የፍልስጤምና
እሥራኤል ደንበር) ዻዻስ አደረጉት::

+ከደግነቱ የተነሳም በቅዳሴ ጊዜ ሥጋ ወደሙ ሲለወጥ
ያየው ነበር:: መላእክትም ያጫውቱት ነበር:: ሕዝቡ
ሲያጠፉ በየዋሕነት ዝም ቢላቸውም ቅዱስ መልአክ ገሥጾታል::

+የፋርስ ነገሥታት አጽመ ሰማዕታትን ሲያቃጥሉም እርሱ
የቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድን አጽም ይዞ ተሰዷል:: ለብዙ
ዘመናት በቅድስና ኑሮም በዚህች ቀን ዐርፏል::

+"+ ቅድስት ቤርሳቤህ +"+

=>ይህቺ እናት አስቀድማ የኦርዮ ሚስት: ቀጥሎ ደግሞ
የልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ሚስትና የሰሎሞን እናት
ለመሆን በቅታለች:: ቁጥሯ ከደጋግ እናቶቻችን ሲሆን
የድንግል ማርያም ቅድመ አያትም ናት:: አንዳንድ
ሊቃውንት ደግሞ ስሟን "ቤትስባ (ቤተ ሳባ)" :

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://vm.tiktok.com/ZM6YyWW5B/

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ህዳር 30/2016 #መጥምቁ_ዮሐንስ
#ቅዱስ_ማርቆስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሳኑ ስም ለምናመሰግንበት ቅዱሳኑ #በቃል_ኪዳናቸዉ እንዲያስቡን ለምንማፀንበት ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን

👉ጸሎቱና በረከቱ ለዘለዓለሙ ከኹላችን ህዝበ ክርስቲያኑ ይሁን ነብይ ሐዋርያ ሰማዕት የሆነ መጥምቀ መለኮት #ቅዱስ_ዮሐንስ ያደረገው ተአምር ይኽ ነዉ

👉የመጥምቀ መለኮት #ቅዱስ_ዮሐንስ የበዓሉ መታሰቢያ በዕለተ እሁድ ውሎ በወርሀ ታህሳስ ኹለት ቀን በደብረ አንገች በተከበረ ጊዜ ከቅዳሴ በኋላ የመጥመቀ መለኮት #ዮሐንስ መጽሐፍ ገድልን በአንዱ አረጋዊ መነኮሴ አንደበት ይሰሙ ዘንድ ካህናቱና ሕዝቡ ተሰበሰቡ

👉ያንጊዜም ወደዚህ ጉባኤ አንዲት ሴት ቀረበች ድምጿንም አሰምታ እልል እያለች ጮኽች ይህ የክርስቲያን ጉባኤ እስኪታወክ ሕዝብ ኹሉ እርስ በእርሳቸው ይቺ ሴት ምንድናት ደስታዋ ምንድነው እስኪሉ ድረስ እልልታዋን አልተወችም ያ መነኩሴ ግን ልብ እንደተሳናት እንደሰከረችም ቆጠራት ዝም ትል ዘንድ ገሠፃት

👉ይኽች ሴት ግን አባቴ ካህኑ ሆይ እኔ ልቤ ያዘነበት ሴት ነበርሁ ዛሬ ግን ለምለም ፍሬ የሌላት ደረቅ ዛፍ በሚሉኝ ጎረቤቶቼ መሳቂያ ለጠላቶቼ መዘባበቻ የነበርኩ ማኀፀኔ የተዘጋ እኔ ባሪያውን በቸርነቱ በጎበኘኝ በወዳጄ #በቅዱስ_ዮሐንስ አምላክ በእግዚአብሄር ልቤ ጸንቷል ከብዙ እድሜዬ በኋላ ልጅ ሰጥቶኛል እኔስ ዝም አልልም አለች

👉ያም መንፈሳዊ አባት #መነኩሴ ወደሱ ትቀርብ ዘንድ የምትለውን ሕዝብ ይሰሙ ዘንድ ጠራት ይቺም ሴት ወደ ቤተክርስቲያኑ አደባባይ እልል እያለች ከወለደችው ልጇ ጋር ቀርባ አባቶቼና ወንድሞቼ እኅቶቼም ሆይ አንድ ልጅ እንኳን በማጣት ብዙ ዘመን ሳዝን ስተክዝ ኖርሁ ዘመዶቼ ሳይቀሩ ጎረቤቶቼ ኹሉ የደረቀች ዛፍ ይሉኝ ነበር

👉ስለዚህ አምና እንደ ዛሬው ወደ ወዳጄ መጥምቁ ቅዱስ #ዮሐንስ መጥቼ ተሳልሁ ይኸንን መልኩ ያማረ ደም ግባቱ የተወደደ ልጅ ሰጠኝ ድንቅ ተዐምር ለሚያደርግ ለመጥምቀ መለኮት #ቅዱስ_ዮሐንስ እልል እላላሁ በመጥምቁ በቅዱስ #ዮሐንስ አማላጅነት ይህን ልጅ ለሰጠኝ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ ስትል መሰከረች

👉ይህን የሰሙ ሕዝቡም ኹሉ አደነቁ በማግስቱ ያ መነኩሴ #ከካህናቱ ጋር ሆኖ ያን ሕፃን አጠመቀው እርሷም እልል እያለች እየዘመረች ወደ ቤቷ ተመለሰች

👉የመጥምቀ መለኮት #ቅዱስ_ዮሐንሰ ጸሎቱ በረከቱ አማላጅነቱ እንዲሁም የከበረዉ ቃል ኪዳኑን ለምታምኑ ሁሉ በረከት ረድኤቱ ለሁላችሁም ይድረሳችሁ በዚህ እለት በመታሠቢያ በአሉ የምናስበዉ ሐዋርያዉ #ማርቆስ ምልጃ ፀሎቱ ለሁላችንም ይድረሰን የተባረከ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" 💒 💚 💛 ❤️ 💒

👉ገድለ ዮሐንስ መጥምቅ
👉ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

⚠️የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መንፈሳዊ ፊልሞች ለምን ይሆን ደብዛቸው የጠፋው....መንፈሳዊ ፊልሞችን በስፋት አናገኛቸውም ልምን ይሆን ?.....የምታውቁትን/ የሰማችሁትን ሹክ በሉን❗️
♻️ስለሚሰጡን መረጃ...
❗️እናመሰግናለን❗️

♻️💥ኪነ-ጥበብ💥♻️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

እዌጥን መጸሐፈ ገድሉ ለአቡነ ፄዋ ለጽድቅ በስመ እግዚአብሔር አብ ወበስመ እግዚአብሔር ወልድ ወበስመ እግዚኣብሔር መንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ኃይለ አምላኩ ይርድአነ ያፈጽመ በደህና ወበሰላም አሜን።

ገድል ዘአቡነ ፄዋ ለጽድቅ ጸሎቱ ወበረከቱ የኀሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም ኣሜን። የአባታችን የቅዱስ ፄዋ ለጽድቅ አባት ‹ፈረጎ›› ይባላል። ይኸውም የቀትር ጋኔን በመሆን የሚመለክ ነበር። እናቱም ሰዓሪተ ሰንበት›› ትባላለች። ይህችም ዘማዊና ሰንበትን የምትሽር ነበረች። በእንደዚህ ዓይነት ግብር እያለች ከነበረችበት ቦታ ከእንደለቃቃ በተጉለት ውስጥ ክፉ ጠንቋይ ቃልቻ ስለነበር ወደ እርሱ ስትሔድ በመንገድ ላይ ደክሟት አረፍ እንዳለች እንቅልፍ ሸለብ እንዳደረጋቸው ‹ፈረጎ የሚባለው የቀትር ጋኔን በዚህ ሰዓት በግብረ ሥጋ ተገናኛት። በዚህን ጊዜ

መጥቆራ›› የሚባል ሁለት ክንፍ ያለው ኃይለኛ ጋኔን ተፀነሰ።

ከዚያም ከጠንቋዩ ተመልሳ ወደ ቤቷ ገብታ ስትኖር ተፀንሶ የነበረው መጥቆሬ ተወለደ። ከተወለደም በኋላ የግብር አባቱ ዲያብሎስ እንዳስተማረው በአየር እየበረረ ክፉ ሥራውን ያከናውን ነበር። በዚህ ዘመን የነበሩ ቅዱሳኑ አቡነ ተክለሃይማኖትና ኣቡነ ዜና ማርቆስ የኢትዮጵያን ምድር በኪደተ እግራቸው እየተመላለሱ እየዞሩ አጋንንትን እያወጡ፣ ድውያንን እየፈወሱ፤ ያላመነውን እያሳመኑ እያጠመቁ የኢትዮጵያን ምድር ይቀድሷት ነበር። ነገር ግን ከዚህች ከዘማዊ ሴት የተወለደው መጥቆራ የሚባለው ሁለት ክንፍ ያለው ኃይለኛ ጋኔን በየጊዜው ይፈትናቸውና ያስቸግራቸው ነበር። እነርሱም ከኃይለኛነቱና ከአስቸጋሪነቱ የተነሣ ወደ ፈጣሪያቸው ጸለዩ። ፈጣሪያቸውም እነዚህን ቅዱሳን ሲፈትናቸው በተመለከተ ጊዜ ስመ እግዚአብሔር ጠርተው በመስቀል ቢያማትቡበት ከእጃቸው እንሚወድቅ ነገራቸው። እነርሱም ጌታ እግዚአብሔር እንደነገራቸው አደረጉ። እርሱም በመንቀጥቀጥ በመርበድበድ ወርዶ ከፈታቸው ቆሞ ተንበርክኮ ሰገደላቸው።

ከዚህ በኋላ አባታችን ዜና ማርቆስ ወደ ገዳማቸው ደብረ ብስራት ይዘውት ሔደው አብረው ይኖሩ ነበር። እርሱም እየታዘዘና ብዙ የሰው ልጆች መሥራት የማይችሉትን ሥራ ይሠራ ነበር። ይሠራው ከነበረው ሥራው አንደኛው ከዕለታት በአንድ ቀን ሰላሌ ከሚባለው ሀገር ሔዶ ዕንጨት እንዲያመጣ አባታችን ዜና ማርቆስ አዘዙት። እርሱንም እንደታዘዘው ሔዶ በሦስት ሰዓት ውስጥ ለ300| ሰዎች የማይቻለውን ዕንጨት ተሸክሞ ወደ ገዳሙ ደብረ ብስራት አድርሷል። በዚህም ሥራው አባታችን ዜና ማርቆስና ልጆቻቸው እጅግ ይደነቁ ነበር። ያም ዕንጨት ለገዳሙና ለሀገሩ ሕዝብ ብዙ ጊዜ ሲያገለግል ቆይቷል። ዕንጨቱ ዛሬም ድረስ በአቡነ ዜና ማርቆስ በገዳማቸው በደብረ ብስራት በዋሻ ቁርጥራጩና የተፈረፈረው ይገኛል።

ከዚኸም በኋላ አቡነ ተክለሃይማኖትና አቡነ ዜና ማርቆስ በመዓልትም በሌሊትም ሁልጊዜ ፈጣሪያቸውን በጸሎት ይጠይቁ ነበር። ጥያቄያቸውም ‹መጥቆራ›› የተባለውን ይህንን ኃይለኛ ጋኔን በጸሎታቸው በመስቀላቸው ኃይል ወድቆ የሰገደላቸውን ከአርአያ አጋንንት ወደ ሰው አርአያ እንዲመለስ በሥላሴ ስም አምኖ እንዲጠመቅ ነበር። አምላካቸውም ልመናቸውን ሰምቶ አርአያው 140 የነበረውን ቁመቱን አሳንሶ በሰው አርአያ ቀርጾላቸዋል። እምነቱንም በእነርሱ እምነት አድርጎላቸዋል። ከዚኸም በኋላ መክረው አስተምረው አሳምነው አጥምቀውታል። ስመ ጥምቱም ፄዋ ለጽድቅ ተብሏል። ትርጉሙም ለጽድቅ የተማረከ (የጽድቅ ምርኮኛ) ማለት ነው።

ከዚኸም በኋላ ከአቡነ ዜና ማርቆስ እግር ሥር ወድቆ ተንበርክኮ ‹አባቴ ሆይ ጸሎትህ አማላጅነትህ ይርዳኝ›› እያለ ይማጸናቸው ነበር። የእሳቸውም አርድዕት ሆኖ እያገለገላቸው እነርሱም በጸሎታቸው በምክራቸው እየረዱት እያጽናኑት ቅዱሳን አበው ለተቀበሉትና ለበቁበት የምንኩስና ቅድስና በቅቶ በአቡነ ዜና ማርቆስ እጅ መንኩሶ በጾም በጸሎት፣ በገድልና በትሩፋት በሥራም ሁሉ እያገለገለ ሰባት ዓመት በዚሁ በአቡነ ዜና ማርቆስ ገዳም ተጋድሏል። ይህንንም አገልግሎት ሲያገለግልና ሲጋደል አቡነ ዜና ማርቆስ ገድሉን ትሩፋቱን፣ ጾሙን ጸሎቱን፣ ትዕግሥቱን ጽናቱን እያዩ በጣም ያደንቁና ፈጣሪያቸውን ያመሰግኑ ነበር። ፄዋ ለጽድቅም በትሩፋት ላይ ትሩፋትን እየጨመረ እንደ መላእክት እንደ ነቢያትና እንደ ሐዋርያት በመዓልትም በሌሊትም ‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያለ ፈጣሪውን ያመሰግነው ነበር።

ከዚኽም በኋላ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ገድሉንና ጽናቱን አይቶ በቃሉ አነጋገረው። ‹በዚህ ቦታ እስከ አሁን የተጋደልኸው ይበቃሃል ከእንግዲህ የአንተ ቦታ ይህ አይደለምና ተነሥ እኔ ወደምመራህና ወደምወስድህ ቦታ ሒድ፣ ይህም ቦታ በእናቴ በቅድስት ድንግል ማርያም ያነጽኩት ነው። ፍቃዴና ስምረቴ በሆነው በዚያ በቅዱስ ቦታ አገልግለኝ አለው። ፄዋ ለጽድቅም ለጌታችን ቃ በፍርሃት በመታዘዝ ወደተላከበት ገዳም ሔደ። ሲሔድም ገና በመንገድ ላይ ሳለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሥርቶለትና አዘጋጅቶለት ስለነበር 300 ሊቃውንት፡ 28 ሰሞንኛ በስብሐተ እግዚአብሔር እያገለገሉ አቡነ ፄዋ ለጽድቅ ከዚያ ደረሰ። እነርሱም ደስ ብሏቸው በምስጋና በደስታ ተቀበሉት እርሱ ግን ራሱን ዝቅ አድርጎ ፈጣሪው የተቀበለውን መከራ በማሰብ ለእነዚያ ሊቃውንቶችና ሰሞነኞች እያገለገለ ሕዝብና አሕዛብን እያስተማረ በትሩፋት ላይ ትሩፋትን እየጨመረ ቀደም ሲል በደብረ ብስራት ያደርገው የነበረውን ትሩፋትና ገድል ጨመረ። ይኸውም ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ለአምላኩ እንደማለ ሁሉ ይህም ቅዱስ አባት እንደ እርሱ ‹‹የያዕቆብ ፈጣሪ የሚሆን የእግዚአብሔርን ማደሪያ እስከማገኝ ድረስ ለዓይኖቼ እንቅልፍን ለቅንድቦቼ መንጎላጀትን ለጎኔ ዕረፍትን አልሰጥም፣ መኝታዬ አመድ ልብሴም ማቅ ይሁን›› በማለት ሌሊትና ቀን ሳያርፍ እንደ ዓምድ ተተክሎ የመድኃኔዓለምን መከራውን፣ መገረፉን፣ መሰደብ መደብደቡን፣ መጎተት መሰቀሉን፣ መራራ ሞቱን፣ በሦስተኛውም ቀን መነሣቱን፣ ማረጉንና ዳግመኛም ለፍርድ መምጣቱን ሁሉ እያሰበ ሌሊትና ቀን ፊቱን በድንጋይ እየመታ፣ ሰውነቱን በሰንሰለት እየገረፈ ፈጣሪውን ‹አምላኬ ሆይ አንተ ለእኔ ይህንን ሁሉ መከራ ተቀበልክ…›› እያለ ሰውነቱን ‹‹ጽኚ በርቺ አልቅሺ፡ በዚህ ካላለቀስሽ በፈጣሪሽ ፊት ራቁትሽን ትቆሚያለሽ…›› እያለ ላቡ | እንደ ውኃ እስከሚወርድ ድረስ እየሰገደ ያለቅስ ነበር።

Читать полностью…
Subscribe to a channel