እናቴ ቅድስት አርሴማ ዝናሽ ለዓለም ተሰማ | ዘማሪት ሲስተር ልድያ ታደሰ
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All
/channel/zikirekdusn
✝✞✝ ታኅሣሥ 9 ✝✞✝
✝✞✝ እንኩዋን ለጻድቅና ሰማዕት "ቅዱስ በአሚን" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✞✝
+*" ቅዱስ አባ በአሚን "*+
=>የቤተ ክርስቲያን ታሪክ የተጻፈው በብራናና በብዕር አይደለም:: ይልቁኑ:-
¤እንደ ቀለም የሰማዕታት ደማቸው::
¤እንደ ብዕር አጥንታቸው::
¤እንደ ብራና ቆዳቸው ሆኖ ተጽፏል እንጂ:: ሰማዕታት ለሃይማኖታቸው የከፈሉት ዋጋ እጅግ ታላቅ ነው::
+ስለዚህም "ተጋዳዮች : የሚያበሩ ኮከቦች : የቤተ ክርስቲያን ሻማዎች" ተብለዋል:: እነሱ እየቀለጡ አብርተዋልና::
+ሰማዕትነት በብሉይ ኪዳን የጀመረና እስከ ዳግም ምጽዐተ ክርስቶስም የሚቀጥል ቢሆንም "ዘመነ ሰማዕታት" የሚባለው ከ150 እስከ 312 ዓ/ም ድረስ ያለው ዘመን ነው::
+በተለይ ግን ከ270ዎቹ እስከ 312 ዓ/ም ድረስ ያሉ ዓመታት እጅግ የከፉ ነበሩና የክርስቲያኖች ደም በምድር ላይ ፈሷል:: የሰማዕታት ምሥጢራቸው ቃለ ወንጌል: የጌታ ስብከትና ሕይወት እንጂ ሌላ አይደለም:: (ማቴ. 10:16, ማር. 13:9, ሉቃ. 12:4, ዮሐ. 16:1, ሮሜ. 8:35, ራዕይ. 2:9)
+የቅዱሳን ሰማዕታት መነሻቸው ቅዱስ እስጢፋኖስ ሲሆን ፍጻሜአቸው ደግሞ ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ዻዻሳት ነው::
=>ከዓበይት ሰማዕታትም አንዱ ቅዱስ በአሚን ነው:: በቤተ ክርስቲያን "ሰማዕት ዘእንበለ ደም (ሰይፍ)" የሚባሉ ቅዱሳን አሉ:: ሰማዕት ዘእንበለ ደም ማለት "እንደ ሰማዕታት መከራውን ሁሉ ተቀብለው ሳይሰየፉ (ሳይገደሉ) የመከራውን ዘመን ያለፉ" ናቸው::
+ለምሳሌ ከሠለስቱ ምዕት (ከ318ቱ ሊቃውንት) አብዛኞቹ እንደዚህ ባለ ሕይወት ያለፉ ናቸው:: ቅዱስ በአሚንም እንዲሁ ዓይነት ዜና ሕይወት ያለው አባት ነው::
¤ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
+ቅዱስ በአሚን ተወልዶ ያደገው በደቡብ ግብጽ በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ቅዱሱ ከልጅነቱ ክርስትናን የተማረ ነበርና ሰው ሁሉ የሚወደው ታማኝ ሰው ሆነ:: ምንም ሃብታም ሰው ባይሆንም ተቀጥሮ ሠርቶ በሚያገኛት ገቢው መልካምን ይሠራ ነበር::
+በዘመኑም ከቅንነቱ የተነሳ "መታመንስ እንደ በአሚን" ይባል ነበር:: ቅንነቱን የወደዱ ሁሉ ይሹት ነበር:: በከተማው ውስጥ እጅግ ብዙ ሃብት የነበራቸው ባል እና ሚስትም ወደ ቤታቸው ወስደው መጋቢ (ተቆጣጣሪ) አደረጉት::
+ጠባዩን ከተረዱ በሁዋላ ግን ሙሉ ሃብት ንብረታቸውን በእጁ አስረክበውት ያስተዳድርላቸው ነበር:: ሲወጡና ሲገቡም እያዩት ደስ ይሰኙበት ነበር:: እርሱ ግን ልቡ በክርስቶስ ፍቅር የተመሰጠ ነበርና ለዚህ ዓለም ጉዋዝ ትኩረትን አይሰጥም ነበር:: ይጾም ይጸልይ ነበር እንጂ::
+አንድ ቀን ግን የቤቱ ባለቤቶች (ባልና ሚስት) ሲመጡ ቤታቸው እንደሚገባ ተደራጅቶ: ቁልፉ ተቀምጦ አገኙት:: ወዳጃቸው በአሚን ግን የለም:: ደንግጠው ቢያፈላልጉት ሊያገኙት አልቻሉም:: በመጨረሻ ግን መንኖ ገዳም መግባቱን ሰምተው ፈጽመው አዘኑ::
+ከእርሱ መለየትን አይፈልጉም ነበርና:: አልቅሰው ወደ ቤታቸው ሊመለሱ ሲሉ ሚስት "አይሆንም! ሔደን እናምጣው" ስላለች ወደ መነነበት ገዳም ሔደው: እያለቀሱ ይመለስላቸው ዘንድ ለመኑት::
+እርሱ ግን "ለሰማያዊ ሠርግ ታጭቻለሁና ከእንግዲህ የክርስቶስ ነኝ" አላቸው:: እንዳልተሳካላቸው ሲያውቁ ፈጽመው እያዘኑ ወደ ቤታቸው ተመለሱ:: ቅዱስ በአሚን ግን ገዳማዊ ሕይወትን በተጋድሎ ጀመረ::
+ይጾማል: ይጸልያል: ይሰግዳል: ይታዘዛል:: በዚህ መንገድ ሥርዓተ ገዳምን በበርሃ ሆኖ ሲፈጽም በዓለም እነ ዲዮቅልጢያኖስ ክርስቲያኖችን ይገድሉ ነበር::
ዜና ሰማዕታትም ቀስ እያለ ቅዱሱ ወዳለበት ገዳም ደረሰ::
+ነገሩን ሲሰማ ደስ አለው:: እርሱ ስለ ክርስቶስ ሲሉ ደምን ማፍሰስና መከራን መቀበል ከሁሉም ነገር የተሻለ እንደ ሆነ ያውቅ ነበርና:: ቀጥሎም ወደ ከተማ ሒዶ ደሙን ለማፍሰስ በቁርጥ ወስኖ ዘለቀ::
+በዚያም የንጉሥ ወታደሮች አግኝተውት ለጣዖት ይሰዋ ዘንድ ታዘዘ:: ቅዱስ በአሚን ግን "መስዋዕት የሚገባው ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ: ለባሕርይ አባቱ ለአብና ለመንፈስ ቅዱስ ነው:: ለፍጡር አልሰዋም" ሲል መለሰላቸው:: በዚህም ምክንያት ወታደሮች እየተፈራረቁ ደበደቡት::
+ደሙንም አፈሰሱት:: ምንም እንዳልተለወጠ ሲያውቁ ወደ እስር ቤት ጨመሩት:: ከዚያም በቀን በቀን እያወጡ ይደበድቡት: በእሳት ያቃጥሉት: በተለያዩ ማሰቃያዎች በመከራ ያውሉት ነበር:: እርሱ ግን ክርስቶስን ከመቀደስ በቀር አንዳች አይመልስላቸውም ነበር::
+በብዙ አሰቃይተው እንቢ ቢላቸው ወስደው በጨለማ ቤት ዘጉበት:: በዚያም ጥለውት ዓመታት አለፉ:: ሁሉንም በጊዜው የሚሠራ ጌታ ግን እነዚያን የመከራ ዘመናት አሳልፎ ዲዮቅልጢያኖስና መክስምያኖስን አጠፋቸው::
+በፈንታቸውም መ++++++ፍቀሬ ክርስቶሳውያን ቅዱስ ቆስጠንጢኖስን አነገሠ:: አብያተ ክርስቲያናት ታነጸ:: ስለ ክርስቶስ የታሠሩ ሁሉ ነጻ ወጡ:: በዚህ ጊዜ ምዕመናን መጥተው ቅዱስ በአሚንን ከወደቀበት አነሱት::
+በወቅቱም ንጉሡ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ "አጽመ ሰማዕታትን ሰብስቡ: በመከራው አልፈው በእድሜ ካሉትም መካከል መምጣት የሚችሉትን አምጡልኝ" ብሏልና ቅዱስ በአሚንን የመሰሉ 72 ክቡራን ተገኙ:: ከእነርሱም መካከል ታላቁ አባ ኖብና አባ ዘካርያስ ይገኙበታል::
+እነዚህ አበው ቅዱሱን ንጉሥ ባርከውት ሲመለሱ ቅዱስ በአሚን ወደ እስሙናይን ተጉዞ በበዓቱ ተቀመጠ:: በዚያም ደቀ መዛሙርት በዝተውለት እንደ ገና ገዳማዊ ሕይወቱን ቀጠለ:: በበዚያም ሳለ ብዙ ተአምራትን ሠራ::
+ድውያንን ፈወሰ:: መ+++++++ቃንንም በጸሎቱ ከአካባቢው አራቀ:: አንድ ቀንም የሮም ንጉሠ ነገሥት ሚስት ወደ እርሱ ዘንድ መምጣቷን ሰማ:: ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ገብተው "አባ! ንግሥቲቱ ትፈልግሃለች" አሉት::
+እርሱ ግን "እኔ ከምድራዊ ንግሥት ዘንድ ምን አለኝ! አልወጣም" አላቸው:: ደቀ መዛሙርቱ ግን መልሰው "አባ! እዘንላት: በመከራ ውስጥ ናት" ሲሉት "እሺ" ብሎ ወጣ::
+ንግሥቲቱ ምንም ብዙ ሠራዊት ብታስከትል አንጀቷ ታጥፎ ተጐንብሳ ነበር የምትሔደው:: እርሱም በጀሮዋ ጠጋ ብሎ የሕመሟን ምሥጢር ሲነግራት ተገርማ እግሩ ሥር ወድቃ ተማጸነችው:: ነገሩ እንዲህ ነው:-
+ከ15 ዓመታት በፊት አንድ የተባረከ ዲያቆን በቤተ መንግስቷ አካባቢ ይኖር ነበር:: እርሱም (ዮሐንስ ይባላል) የዮሐንስን ራዕይ ቁሞ ዘወትር ያነብላታል:: በዚህ የቀኑ የንጉሡ ባለሟሎች በሃሰት "ሚስትህን ዲያቆኑ እያማገጠ ነው" ሲሉ ለንጉሡ ነገሩት::
+ንጉሡም ነገሩ እውነት ስለ መሰለው ወታደሮቹን ዮሐንስን ከነ ሕይወቱ ባሕር እንዲያሰጥሙት አዘዘ:: ይሕንን የሰማችው ንግስት ለቀናት ስታለቅስ አንጀቷ በመቃጠሉ ታመመች:: እየቆየም ሆዷ ታጠፈ:: ለ15 ዓመትም የሚያድናት አጥታ ተንከራተተች::
+በሁዋላ ግን ሰዎች ስለ ቅዱስ በአሚን ቅድስና ሲናገሩ ሰምታ መጣች:: ለዛ ነው ቅዱስ በአሚን ምሥጢሯን ሹክ ያላት:: ቀጥሎም 2 በጐ ነገርን ፈጸላት:: መጀመሪያ ጸሎት አድርጐ ሆዷን ቢዳስሳት በቅጽበት ድና ቀና አለች::
+2ኛው ግን "ያ የምትወጂው የተባረከ ዲያቆን ዮሐንስ አልሞተም:: መላዕእክት ከባሕር አውጥተው እገሌ በሚባል ደሴት አኑረውታል" አላት::
እርሷም ተመልሳ በደስታ ለባሏ ነገረችው::
አቡነ ኪሮስ ጻድቅ
የጻድቁን ስም የሚጠራ አፍ ንዑድ ነው: ክቡር ነው:: በእውነት የቅዱሱን አባት ክብር ለማግኘት መፋጠን ይበጃል::
#አቡነ_ኪሮስ የተወለዱት በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን ወላጆቻቸው ነገሥታት ናቸው:: ተወልደው ባደጉባት ሃገር #ቁስጥንጥንያ ገና በልጅነት ምቾት ሳያሳሳቸው መጻሕፍትንና ትሕርምትን ተምረዋል:: ወንድማቸው (ታላቁ #ቴዎዶስዮስ) በነገሠባቸው የመጀመሪያ ዓመታት በቤተ መንግስቱ ዙሪያ ግፍ በዝቶ ነበርና አቡነ ኪሮስ ከኃጢአት ለመራቅና ለጌታ ለመገዛት ከከተማው ጠፍተው: አሕጉር አቋርጠው ወደ ግብፅ ( #ገዳመ_አስቄጥስ) መጡ::
እርሳቸውን ለመፈለግ የተደረገው ሙከራ አልተሳካም:: ይባስ ብሎ የንጉሡ ልጅ #ገብረ_ክርስቶስ ሙሽርነቱን ጥሎ ወደ ሌላ ሃገር መነነ:: "የቅኖች ትውልድ ይባረካል" እንዳለ #ቅዱስ_ዳዊት:: አቡነ ኪሮስ ለሙሽራው ገብረ ክርስቶስ አጎቱ ናቸው:: አቡነ ኪሮስ በገዳም ውስጥ የታላቁ #አቡነ_በብኑዳ ደቀ መዝሙር ሆነው ለዘመናት ቆይተዋል::
ቅዱስ በብኑዳን አንበሳ በበላው ጊዜ በጣም አዝነው "ለምን ጌታ ሆይ?" በሚል መሬት ላይ ወድቀው አለቀሱ:: "ምክንያቱ ካልተነገረኝ አልነሳም" ብለው ከወደቁበት መሬት ላይ ሳይነሱ ለ40 ዓመታት አልቅሰዋል:: በዚህ ምክንያት ግማሹ አካላቸው አፈር ሆኖ ሣር በቅሎበታል:: ጌታችን ተገልጦ ምክንያቱን ነግሯቸዋል:: አካላቸውንም እንደነበረ መልሶላቸዋል::
አንድ ቀን ጻድቁ ለቅዱስ በብኑዳ ሞት ምክንያት የሆነው መነኮስ ታንቆ መሞቱን ሰምተው በጣም አዘኑ:: ሱባዔ ገብተው: ፍጹም አልቅሰው: ከጌታም አማልደው: የዛን ኃጥእ ነፍስ ከሲዖል አውጥተዋል:: በሌላ ጊዜ ደግሞ ኃጥአን የሞሉበት አንድ ገዳም በግብጽ ነበርና መቅሰፍት ወርዶ ሁሉንም ባንድ ቀን ሲያጠፋቸው አዩ::
ጻድቁ በዚህም ምክንያት ለ30 ዓመታት አልቅሰው: ሙታኑን አስነስተው: ንስሃ ሰጥተው: ገዳሙን የጻድቃን: ሕይወታቸውንም የፍቅር አድርገውታል:: ጻድቁ #እመቤታችንን ከመውደዳቸው የተነሳ በስዕሏ ፊት አብዝተው ይሰግዱና ያለቅሱ ነበር:: እመ አምላክም ተገልጣ ትባርካቸው ነበር::
ከዚህ በሁዋላ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ሒደው ለ57 ዓመታት ማንንም ሳያዩ ተጋደሉ:: ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ (ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና) በየቀኑ ይጐበኛቸው: ቁጭ ብሎም ያወራቸው ነበር:: በመጨረሻም በዚህች ቀን ጌታ አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን: ድንግል እመቤታችንና ቅዱስ ዳዊትን አስከትሎ ወረደ::
#ቅዱስ_ዳዊት ቀርቦ እያጫወታቸው: በበገናው እየደረደረላቸው: ከዝማሬው ጣዕም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው በፍቅር ተለየች:: ጌታችንም ታቅፎ: ስሞ ይዟቸው አረገ:: ሥጋቸውን #አባ_ባውማ ቀበሩት:: የአቡነ ኪሮስ ቁመታቸው ቀጥ ያለ: ጽሕማቸውም የተንዠረገገ ነበር:: እድሜአቸውን ግን መገመት የሚቻል አይመስለኝም::
<<በረከታቸው ይደርብን::>>
አቡነ ተክለ አልፋ በስተመጨረሻ ከዚህ
ከኀላፊው ዓለም ፈጽሞ ወደማያልፈው የዘለዓለም ፡ ሕይወት ወዳለበት ሀገር
የፍልሰታቸው ጊዜ እንደደረሰ ዐውቀው በውስጣቸው የሚያድሩ ቅዱሳንንና አብያተ
ክርስቲያናትን ይሰናበቱ ዘንድ ሔዱ። ታኅሣሥ 4 ቀንም የሐዋርያውን የቅዱስ እንድርያስን በዓሉን አክብረው ዝክሩን ዘክረው ነዳያንን መገቡ፤ ዳግመኛም ረቡዕ ሌሊት አባታችን ተክለ አልፋ የቅድስት አርሴማን ገድል በታላቅ ትጋት ሲያነቡና ከዐይኖቻቸው ዕንባን ሲያፈሱ አደሩ። ልቡናቸውንም ያጸና ዘንድ ለሴቶችና መነኰሳይያትና ለወንዶች መነኰሳት የቅድስት አርሴማን ድርሳን ይተረጉሙላቸው ነበር፤ ያለዚያች ቀን ሌላ ቀን እንዳልቀራቸው በመንፈስ ቅዱስ ዐውቀዋልና። ከዚኸም በኋላ ታኅሣሥ 8 ቀን ሓሙስ ሌሊት በሆነ ጊዜ አባታችን ተክለ አልፋ በሰላም ዐረፉ።
አቡነ ተክለ አልፋ የተቀበሩት በተሾሙበትና ለ45 ዓመታት ባገለገለበት በዲማ ነው። ዜና ዕረፍታቸውንም ትናገር ዘንድ መቋሚያቸው የሰው አንደበት ተሰጣትና ለደቀ መዛሙርቱ በሰው አምሳል በመናገር ‹‹…የምትወዱት ሕዝቦችና መነኰሳት ሆይ አልቅሱለት" አለቻቸው።
የአቡነ ተክለ አልፋ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!
ምንጭ በእንተ ኅሩይ ቅዱሳን መጽሐፍ የተወስደ
ተኅሣሦ 7/4/2015ዓ.ም
Kuwait
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፫
ታኅሣሥ 8 በሞት ማረፋቸውን መቋሚያቸው በሰው አንደበት ለመነኮሳቱ የተናገረችላቸው ኢትዮጵያዊው ጻድቅ የደብረ ድማው አቡነ ተክለ አልፋ ዕረፍታቸው ነው፡፡
የደብረ ድማው አቡነ ተክለ አልፋ በሞት ማረፋቸውን መቋሚያቸው በሰው አንደበት ለመነኰሳቱ የተናገረችላቸው ታላቅ ጻድቅ ናቸው። በአቡነ ተከስተ ብርሃን መንበር በደብረ ድማህ አበ ምኔትነት ተመርጠው ሲያገለግሉ ኖረዋል። ከዚኽም በኋላ አቡነ ተክለ አልፋ ሹመትን አልፈልግም ብለው በጸሎት ብቻ ተወስነው የኖሩ በዲማ ትልቅ ክብር ታላቅ አባት ናቸው። ተክለ አልፋ ማለት ለዘለዓለም የሚኖር ድንቅ ሥራ ማለት ነው።
የአቡነ ተክለ አልፋ አባታቸው ከካህናት ወገን የሆነ አሮን፣ እናታቸው ኦርኒ ይባላሉ።የአቡነ ተክለ አልፋ እናት ኦርኒ የሚለውን ስያሜዋን ከየት እንዳገኘችው ከዚኸ ይናገሯል። የቀደሙት አባቶቻችንና እናቶቻችን ስም አወጣጣቸው በራሱ አስገራሚ ነበር። ብዙ ገድላት ላይ ተጽፈው የምናገኛቸው ስሞች እጅግ ድንቅ ከመሆናቸውም በላይ ክርስቶስን እንዲሰብኩ ተደርገው ነው ስያሜው የተሰጣቸው። ኦርኒ ተብላ ወደተጠራቸው ወደ አቡነ ተክለ አልፋ እናት እንመለስና ስያሜዋን ያገኘችው በታላቋ ሰማዕት በቅድስት ኦርኒ ስም ተጠርታ ነው። ይኸችም ሰማዕት ቅድስት ኦርኒ አባቷ ጣኦት አምላኪና የሮም ንጉሥ የነበረ ሲሆን ወላጅ አባቷን ጨምሮ አምስት ታላላቅ ነገሥታትን ድል ያደረገች ናት። ሐዋርያው ቅዱስ ጢሞቴዎስ በዝግ ቤት ሳለች ተገልጦላት ያጠመቃት በኋላም እርሷ ከ30 ሺህ በላይ ሰዎችን በተኣምራት አሳምና ያስጠመቀች ድንቅ ሐዋርያዊት እናት ናት። እንዲሁም በተኣምራቷ ያመኑና ማኅበርተኞቿ ተብለው የተጠሩ 13 ሺህ ሰዎችም በክርስቶስ አምነው ከእርሷ ጋር ጥር 30
ቀን አንገታቸውን ተናደፈው በሰማዕትነት እንዳረፉ ጥር 30 የሚነበበው መጽሐፈ ስንክሳር ታሪክን በሰፊው ይናገራል።
የአቡነ ተክለ አልፋ ወዳጆቸ አሮን እና ሖርኒ ኹለቱም በእግዚአብሔር ሕግና ሥርዓት በትሕዛዙም ይጓዙ ነበር። ከዕለታት በአንደኛው ቀን ቅድስት ኦርኒ ፀሐይ ሲወጣ በሆዴም ውስጥ እንደመብረቅ ብርሃን ሲያበራ አየሁ በማለቱ ያየችውን ራእይ ለባሏ ነገረችው በኋላ ፀንሳ ጥር 21 ቀን ወለደ። ሕፃኑ ተክለ አልፍም በጥበብና መንፈስ ቅዱስ ኃይል አደገ። ሲያድግም ለመምህር ሰጥተውት የነቢያትን የሐዋርያትን መጻሕፍት ሁሉ ተምሮ ትርጓሜአቸውን ዐወቀ።
ከዚኽም በኋላ ዕድሜያቸው ሲደርስ ወላጆቻቸው ከሀገር ባለጸጎች ወገን የሆነች አንዲት ሴት አጩላቸው፡፡ ነገር ግን አባታችን ይኸን ተቃወመ። ወላጆቻቸውም ሰርገ ሲደገሱ አባታችን ተነሥተው በመጥፋት ወደ ምድረ በዳ ሔደው አደሩ። ለአንድ ሀገረ ገዥም ከእረኞች እንደ አንዱ ሆነው ተቀመጡ።
ከዕለታት.. በአንደኛው ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተው ከዕንባና ከጸሎት ጋር እልፍ እልፍ ሲሰግዱ እንደኛው እረኛ የአባታችን ዐሥሩ የእጆቻቸው ጣቶች እንደፀሓይ ሲያበሩ ተመለክተና የእግዚአብሔር ኀይል እንዳደረባቸው በሰው ሁሉ ምስክር ሆን ከዚኹም በኋላ አባታችንን የእግዚአብሔር መንፈስ አነሣሥቶ ወደ ደብረ ዲማ አደረሳቸው።
በግራኝ አህመድ የ15 ዓመት ወረራ ወቅት ታቦተ ቅዱስ ጊዮርጊስን ይዘው ከተሰደዱ በኋላ የመከራው ዘመን ሲያልፍ ወደ ዲማ ተመልሰው በተጋድሎ ኖረዋል። በዲማ ውስጥ ስለመነኰሱና ተጋድሏቸውም ከመምህራኑ ሁሉ በላይ ስለሆነ የመምህራን አለቃ የሚል ስያሜ ተሰጣቸው። እርሳቸውም የዲማ ገዳምን ሥርዓት ሠርተው ካለፉ በኋላ ይኸው እስከአሁን ድረስ ዲማ በአቡነ ተክለ አልፋ መርዓትና ደንብ እየተዳደረ ይገኛል።
አቡነ ተክለ አልፋ በዲማ በተጋድሎ ኖረው ተፈትነው እንደወርቅ ነጥረው ከወጡ በኋላ በአባ ማቴዎስ እጅ መነኰሱ። የተወለዱት የክርስትና ጥምቀት የተጠመቁት፣ የዲቁናና የቅስና ማዕረግም የተቀበሉት በእመቤታችን በዓል ዕለት ጥር 21 ቀን ነው። ከመነኰሱም በኋላ በታላቅ ተጋድሎ ኖሩ፣ ከፍየል ሌጦ ልብስ እየሠሩ እየሸጡ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች ይመጸውቱ ነበር፤ በዐቢይ ጾም ወቅትም ከሰኞ እስከ ዐርብ ድረስ ምንም ምን አይቀምሱም ነበር ነገር ግን ቅዳሜና እሑድ ሦስት ፍሬ አተር ብቻ ይቀምሱ ነበር፣ መጠጣቸውም በትንሿ ጣታቸው ልክ ነበር። ዘወትር በሚጋደሉበት ጊዜ የሥጋቸው ቆዳ እስኪለያይ ድረስ በወገባቸውና በክንዳቸው በጭኖቻቸውም ላይ ታላቅ የሆነ የብረት ዛንጀርን ያሥሩ ነበር፤ በምድርም ላይ የሥጋቸው ቁራጭ እስኪወድቅ ድረስ በእሳት በጋለ ብረት ሰውነታቸውን ይገርፉ ነበር፤ ማቅ ለብሰው በባሕር ውስጥ ገብተው የሚቆሙበትም ጊዜ አለ፤ ከዚኽም ሁሉ ጋር ለጐናቸው ምንጣፍን አላበጁም በምድር ላይ ይተኙ ነበር እንጂ። ልቅሶንና ዕንባንም ከዐይኖቻቸው አይለዩም ነበር። ወደ ቤተ ክርስቲያንና ወደሌላም ቦታ ሲሔዱ የውስጥ እግሮቻቸውን የሚወጉ እሾሆችን በጫማቸው ላይ ይተክሉ ስለነበር በመንገድ ከተጓዙ በኋላ
ከእግሮቻቸው የሚፈሰው ደም በጎዳና ይፈስ ነበር። ሰዎችም በመንገድ ላይ ድንገት ይህን ደም ሲያዩ" ዛሬ አባታችን ተክለ አልፋ" በዚህ ጎዳና ሒዷል ይባባሉ ነበር"።
አባታችንም ክርስቶስን ስለመውደዳቸው በየበረሓው እየዞሩ ይህንና ሌላውንም ሁሉ ያደርጉ ነበር።
በዚህ ዓይነት ጽኑ ተጋድሎ ላይ ሳሉ ወደ ተለያዩ ገዳማት በመሔድ እኔ ቦዘኔ ነኝ የግራና የቀኝ ጎዳናን አላየሁምና የሕይወት ጎዳና ወዴት እንደሆነ አባቶቼ አስተምሩኝ እያለ በፊታቸው ይለምኗቸው ነበር። ከዚኸም በኋላ የዲማ አባቶች ሔደው አቡነ ተክለ አልፋን የገዳሙ አበ ምኔት ሆነው እንዲመሯቸው ሲለምኗቸው አባታችን ግን ፈጽመው እምቢ አለ። እነርሱም እሽ እንደማይሏቸው ዐውቀው አሥረው በግድ ተሸክመው ወደ ዲማ አመጧቸውና ያለፈቃዳቸው በዐፄ ልብነ ድንግል ዘመን አበ ምኔት አድርገው ሲሾሟቸው አባታችን ግን ጽኑ ልቅሶን ያለቅሱ ነበር። ከገዳሙም ወጥተው ወደ ዋሻ እየገቡ ለብቻቸው ለተጋድሎ ብለው እንዳይሔዱ ጳጳሱ አወገዟቸው።
ከዚኽም በኋላ አቡነ ተክለ አልፋ ዲማ ገዳምን በፍጹም ፍቅርና አንድነት አስተዳደሩ በትምህርታቸው ሀገሪቱን ዳግመኛ የወንጌልን ብርሃን አበሩላት ሕሙማንን በተኣምራት ፈወሱ ወላጆቻቸው የሞቱባቸውን የሀገሩን ልጆች ያሳድጋሉ፣ የተቸገሩትንም ሁሉ ይረዳሉ፡ የእርሳቸውን የዕለት ምግብ ጭምር ለተቸገሩ እየሰጡ እርሳቸው ግን ከጸሎት ውኃ በቀር አይቀምሱም ነበር፤ ለሰው ብቻም ያይደለ ለእንስሳትም ለወፎችም በጣም ያዝኑ ነበር። ሕሙማንንም በተኣምራት ይፈውሷቸው ነበር የሰውነታቸውም ጥላ ባረፈባቸው ጊዜ ድዉያን ይፈወሱ ነበር። በመስቀላቸውም እጣቢ መካኖች ወልደዋል፣ ለበዓላቸው የተዘጋጀውንም የዝክራቸውን ፍርፋሪ በመቅመስ የወለዱ ብዙዎች ናቸው።
አቡነ ተክለ አልፋ በቤተ ክርስቲያን ወንጌል እና የእመቤታችን የተኣምር መጽሐፍ ሲነበብ 12ቱ ሐዋርያት ዘውዳቸውን አውርደው ንባቡ እስኪያልቅ ድረስ ሲጠብቁ በግልጽ ያዩዋቸው ነበር። ከቁመት ብዛት ሰውነታቸው ፈጽሞ በሚደክም ጊዜ ከመሬት ላይ ይወድቁ ነበር፣ በዚኸም ጊዜ ክብርት እመቤታችን የወይን ጽዋ ታጠጣቸው ነበር ያንጊዜም በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ይታደሳለ" ለጌታችን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም ካላቸው ፍቅር የተነሣ የቆረበም ሰው እንደተፋ ሰዎች በነገሯቸው ጊዜ በየሀገሩ ቅርብም ይሁን ሩቅ እስክ ስድስት ቀን ጎዳና ሒደው በቤተ ክርስቲያን ይቀብሩት ዘንድ ካህን ይልኩ ነበር።
ታህሳስ 7/2016 #ቅድስት_ሥላሴ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ለአጋእዝተ አለም ቅድስት #ሥላሴ ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን
👉 #ምስጢረ_ሥላሴ ስለ ሥላሴ ምስጢር የሚናገር ትምህርት ማለት ነው እግዚአብሔር አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፋፍለው በአንድነትና በሦስትነት የሚመሰገን አንድ ሕያው አምላክ ነው
👉 #የእግዚአብሔር ሦስትነት ስንል እግዚአብሔር የማይለያይና የማይቀላቀል ፍጹም የሆነ ሦስትነት አለው ማለታችን ነው የእግዚአብሔር ሦስትነት በስም በግብር በአካል ነው
👉 #እግዚአብሔር በስም ሦስት ስንል ሦስት የተለያዩ ስሞች አሉት ማለታችን ነው እነዚህም #አብ_ወልድ_መንፈስ_ቅዱስ የሚባሉት ሲሆኑ እርስ በርሳቸው አይወራረሱም አንዱ በሌላው ስም አይጠራም ዘፍ፣1፤2 ምሳ 30፤4
👉 #እግዚአብሔር በግብር ሦስት ነው ስንል ሦስት የተለያዩ የአካል ሥራዎች አሉት ማለት ነው እነሱም መውለድና ፤መወለድ፤ ማስረፅ "የአብ ወላዲ"፣"የወልድ ተወላዲ"፣"የመንፈስ ቅዱስ ሠራፂ" የሚሉት ሲሆኑ የአካል ግብር ይባላሉ መዝ፣ 2፤7
👉 #እግዚአብሔር በአካል ሦስት ነው ማለት ደግሞ
ለአብ፤ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው።
👉 #ለወልድ፤ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ።
👉 #ለመንፈስ_ቅዱስ፤ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ማለታችን ነው።
👉 #የሦስቱ_የእግዚአብሔር ስሞች ትርጉም
👉 #አብ ማለት አባት ማለት ሲሆን የሚወልድ፤የሚያሰርጽ ወይም የሚያስገኝ ያለ እናት ወልድን የወለደ፤ መንፈስ ቅዱስን ያሰረጸ ነው።
👉 #ወልድ ልጅ ማለት ሲሆን የሚወለድ ወይም ያለ እናት ቅድመ ዓለም፤ ያለ አባት ድህረ ዓለም የተወለደ ነው መዝ፣2፤7
👉#መንፈስ_ቅዱስ ረቂቅ፤ ልዩ፤ ንፁህ; ከፍጡራን መናፍስት ሁሉ የተለየ ማለት ነው። ኢዮ፣26፤13
👉አለምን ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጡ አጋዕዝተ አለም #አብ_ወልድ_መንፈስ_ቅዱስ (ቅድስት ሥላሴ) ህይወታችንን በምህረት ቤታችንን በረድኤት በበረከት ይጎብኙልን ይባርኩልን የተባረከ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን"✝️ 💒 ✝️
#ታህሳስ 6 በዚህች ቀን ታላቋ ሰማዕት #የቅድስት #አርሴማ ዓመታዊ በዓሏ ነው፤ ይህም ቅዳሴ ቤቷ የተከበረበት ነው ...በዚህም ቀን ታላላቅ ተአምራቶች ተደርገዋል፤ በተለይም ይህ ቀን በአገረ አርማንያ ልዩ ስፍራ አለው፤ በመዲናችን አዲስ አበባ አስኮ ቃሎ ተራራ ላይ ግሩም ቤተክርስቲያን አላት ታዋቂው ገዳሟ ግን ወሎ ሲሪንቃ ይገኛል። መስከረም 29 በሰማዕትነት ያረፈችበት ነው፤ እነዚህን ሁለቱን ቀናት ቤተክርስቲያን በደማቁ ታከብራቸዋለች፤ሌላው በዛሬው ቀን ታላቁ አባት አብርሃም ሶርያዊው ያረፈበት ቀን ነው፤ ይህ አባት ተራራን ያፈለሰ ነው፤ ታሪኩ ወዲህ ነው አባ አብርሃም የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ በነበረበት ወራት አንድ አይሁዳዊ ወደ ንጉሱ ገብቶ እንዲህ ይለዋል “እነዚህ ክርስቲያኖች የሚገርሙ ናቸው በወንጌላቸው ላይ የሰናፍጭ ቅንጣት እምነት ካላችሁ ይህንን ተራራ ተነቅለህ ወደዚያ ሂድ ብትሉት ይሆንላቹዋል ይላል፤” ይህ የሐሰት ወንጌል ነው፤ከመካከላቸው ይህን የሚያደርግ አንድስ እንኳን የለም ይለዋል” ንጉሱም አባ አብርሃምን አስጠርቶ “በእርግጥ ወንጌላችሁ እንዲህ ይላልን ?” ይለዋል አዋን ንጉስ ሆይ ብሎ ይመልስለታል፤ ታዲያ የክርስቲያኖች ሁሉ አባታቸው አለቃቸው አንተ ነህ እስኪ አድርግና አሳየኝ ይለዋል፤ እሺ ግን 3 ቀን ብቻ ይስጡኝ ብሎ ወጣ፤ ጨነቀው ወደ እምቤታችን ቤተክርስቲያን ገብቶ 3 ቀን 3 ሌሊት እህል ሳይበላ ውኃ ሳይጠጣ አለቀሰ፤ እመቤቴ አታሳፍሪኝ አላት፤ ተገለጸችለት ይህ ላንተ አይሆንም ግን ወደ ከተማ ውጣ በእንስራ ውሃ ተሸክሞ የሚሄድ ሰው ታገኛለህ፤ ስሙ ስምዖን ጫማ ሰፊ ነው፤ አንድ አይና ነው፤ አንዱን አይኑን ያጠፋው የልጄን ትዕዛዝ ለማክበር ብሎ ነው፤ ለእርሱ ይቻለዋል እርሱ የሚልህን አድርግ ትለዋለች፤ እንደተባለውም ስምዖንን ያገኘዋል፤ ነገሩን ሁሉ ይገልጽለታል፤ እሺ ለማንም ስሜንም ስራዬንም እንዳትገልጽቢኝ፤ ህዝቡን ሰብስብ እኔ በተሰወረ ቦታ ሆኜ የማሳይህን እየተመለከትክ አድርግ አንተ የምታደርገውን ደግሞ ህዝቡ ያድርግ አለው፤ ንጉሱም ሰራዊቱም ህዝቡም ይህንን ታአምር ለማየት ተሰበሰበ፤ 41 ጊዜ ኪራላይሶን ብለው ሶስት ጊዜ ሰገዱ፤ ከዚያም አባ አብርሃ ስምዖን የሚያሳየውን እየተከተለ መስቀሉን አውጥቶ ወደ ተራራው አማተበ፤ ተራራው ወደ ላይ ተነሰ፤ ታላቅ ፍርሃት ሆነ፤ ሶስት ጊዜ ተራራው ወደ ላይ እየተነሳ ይቀመጣል በተራራው ስር ከወዲያ ማዶና ከወዲህ ያሉ ሰዎች ይተያዩ ነበር ይላይ፤ ንጉሱም ህዝቡም እጹብ እጹብ አሉ ምስጉን እግዚያብሔርንም አመሰገኑ፤ ንጉሱ ክርስቲያን ሆኖ ተጠምቋል ብዙ አብያተክርስቲያናትንም አንጿል። አባ እብርሃምም ተፈርቶና ተከብሮ በቅድስናም ኖሮ በዛሬዋ እለት አርፏል። ከቅድስት አርሴማ፤ ከአባ አብርሃምና ከስምዖን ጫማ ሰፊ በረከታቸውን ያድለን። አሜን
Читать полностью…ሰላም አንድ ክርስቲያን የዛሬን ፀሎት ለማድረስ ሲፈልግ ምን ብሎ ነው ምሳሌ የሚካኤል ለት ድርሳነ ሚካኤልን በገብርኤል ቀንም ልከ እደዛው ድርሳነ ገብርኤልን ያደርሳለ ዛሬስ ማለትም ዛሬ ቀኑ አምስት ነው አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አቦ ነው ምን ተብሎ ነው ለፀሎት
Читать полностью…✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
✞✞✞ እንኩዋን ለእናታችን "ቅድስት አውጋንያ" : "አባ ገብረ ናዝራዊ" እና "ቅዱስ ፊቅጦር" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+*" ቅድስት አውጋንያ "*+
=>ይህቺ ቅድስት ወጣት ስም አጠራሯ በእውነት የከበረ ነው:: ዜና ሕይወቷ ሲሰማ ጣዕመ ነፍስን ያድላልና:: በፈጣሪ ረዳትነት ልጀምር:: እናንተም በእግዚአብሔር አጋዥነት ተከተሉኝ::
+ቅድስት አውጋንያ የ3ኛው መቶ ክ/ዘ የክርስትና ፍሬ ናት:: በትውልዷ ሮማዊት ስትሆን አባቷ ፊልዾስ ይባላል:: ሥራውም የጦር መሪ: የሃገርም አስተዳዳሪ ነው:: በስም ያልተጠቀሰች እናቷ ደግሞ ክርስቲያን ነበረች::
+ዘመኑ አስከፊ ሰለ ነበር (ለክርስቲያኖች ማለቴ ነው) ክርስትናዋን ደብቃ: አልባሌ (አሕዛባዊ) መስላ ትኖር ነበር:: ቅድስት አውጋንያን ስትወልድ ግን ጨነቃት:: እንዳታስጠምቃት የእርሷም ሆነ የሕጻን ልጇ እጣ ፈንታ ሞት መሆኑ ነው::
+ምክንያቱም ባሏ ፊልዾስ ክርስትናን ፈጽሞ የሚጠላ ጣዖት አምላኪ ነበርና:: ከዚያም አልፎ ሰዎች ለጣዖት እንዲንበረከኩም ያስገድድ ነበር:: ስለዚህ እናት ልጇን ሳታስጠምቅ: ግን በፍጹም የክርስትና ትምሕርትና ሥርዓት አሳደገቻት::
+ቅድስት አውጋንያም ጾምን ጸሎትን: ትሕትናን: ትእግስትን የተመላች ወጣት ሆነች:: ግን ምሥጢረ ጥምቀትን ታገኝ ዘንድ ዘወትር ፈጣሪዋን ትማጸን ነበር::
+በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉም አንድ መልካም አጋጣሚ ተፈጠረ:: መኮንኑ አባቷ (ፊልዾስ) በምድረ ግብጽ እስክንድርያ አገረ ገዥ ሆኖ በመሾሙ ጉዋዛቸውን ጠቅልለው ወረዱ:: ምንም ይህ ለቅድስት አውጋንያ መልካም አጋጣሚ ቢሆንም ሌላ ፈተናን አመጣባት::
+አባቷ ለአረማዊ መኮንን ሊድራት መሆኑን ሰማች:: አሁን ግን መቁረጥ ያስፈልግ ነበርና ወሰነች:: ወደ አባቷ ገብታም "አባቴ! አንድ ነገር ላስቸግርህ:: አንተ ለምትለኝ ሁሉ እታዘዛለሁ:: ግን ከሠርጌ ቀን በፊት ለአንዲት ቀን በዱር ውስጥ ተናፍሼ: ተዝናንቼ እንድመጣ ፍቀድልኝ?" አለችው::
+ምን እንዳሰበች ያልጠረጠረ አባቷም ከ2 ጃንደረቦች ጋር እንድትሔድ አደረገ:: በርሃ አካባቢ ሲደርሱም ቅድስት አውጋንያ እውነቱን ለ2ቱ ጃንደረቦች ተከታዮቿ ነገረቻቸው::
+"እኔ ወደ በርሃ የምሔደው ክርስቲያን ልሆን: ደግሞም ልመንን ነውና ካላሰኛችሁ ተመለሱ" አለቻቸው:: 2ቱም ግን በአንድ ቃል "ሞታችንም: ሕይወታችንም ከአንቺ ጋር ነው" ብለዋት አብረው ገዳም ገቡ::
+እንደ ደረሱም ምሥጢራቸውን ለአንድ ጻድቅ መነኮስ ተናግራ እንዲያጠምቃት ጠየቀችው:: መነኮሱም 3ቱንም ካጠመቃቸው በሁዋላ ቅድስት አውጋንያ "አመንኩሰን" ብትለው "ልጄ! ይሔ የወንዶች ገዳም ነውኮ" አላት::
+"አባ! ግድ የለህም! እኔ ራሴን እሰውራለሁ" አለችው:: ከዚያም ሥርዓተ ገዳምን አስተምሮ ስሟን "አባ አውጋንዮስ" ብሎ ከማሕበረ መነኮሳቱ ቀላቀላት:: *አውጋንያን *ታኦድራ *አንስጣስያ . . . የመሳሰሉ ስሞች በቀላል መንገድ ወደ ወንድ ስምነት *አውጋንዮስ *ቴዎድሮስ *አንስጣስዮስ . . .በሚል መቀየር ይችላሉና::
+ከዚህች ዕለት ጀምራ ቅድስት አውጋንያ በአባ አውጋንዮስነቷ ተጋድሎን ጀመረች:: ቀን ቀን ወንዶች መነኮሳት የሚሠሩትን ከባድ ሥራ ሁሉ ስትሠራ ትውልና ሌሊት በትጋት ስትጸልይ ታድራለች:: ለ1 ዓመት ያህል በፍጹም ተጸምዶ ገዳሙን አገለገለች::
+በነዚህ ጊዜያት የመጡባትን ፈተናዎችም ታገሰች:: ዓለምን የናቀችለት: የአባቷን ቤተ መንግስት የተወችለት ክርስቶስ ኃይሏ ነበርና:: በዚያ ሰሞንም የገዳሙ አበ ምኔት በማረፉ መነኮሳትን የሚመራና የሚናዝዝ ሌላ አበ ምኔትን ለመምረጥ ሱባኤ ገቡ::
+ከሱባኤ ወጥተው ሲሰበሰቡ ግን ያመጡት የመንፈስ ቅዱስ መልእክት የሚገርም ነበር:: የሁሉም ዓይን ወደ አባ አውጋንዮስ ተወረወረ:: እርሷ ምሥጢሯን (ሴትነቷን) ታውቃለችና ደነገጠች:: ምርጫው ግን የመንፈስ ቅዱስ ነበርና ግድ ብለው በእነዛ ሁሉ መነኮሳት ላይ እረኛ ሁና ተሾመች::
+በእርግጥ እርሷ ሴት በዚያውም ላይ ወጣት ናት:: ግን እውነተኛ የክርስቶስ ወዳጅ ነበረችና በፍጹም ትጋት መነኮሳትን አስተዳደረች:: ጸጋው ቢበዛላት የተጨነቀውን ታረጋጋ: የታመመውን እጇን እየጫነች በጸሎቷ ትፈውስ ነበር:: በዚህም መነኮሳቱ ደስ ተሰኙ::
+እርሷ ግን ስለዚህ ፈንታ ብዙ ፈተናዎችን በአኮቴት ታሳልፍ ነበር:: ስም አጠራሯም ከበርሃ ወጥቶ ወደ ከተሞች በመግባቱ ድውያን እየመጡ ከእርሷ ዘንድ ይፈወሱ ነበር:: አንድ ቀን ግን ያልተጠበቀ ፈተና መጣባት::
+አንዲት ሰይጣን ያደረባትን ሴት ካዳነቻት በሁዋላ: መልኩዋ እጅግ ውብ ስለ ነበር የዝሙት ጥያቄን አቀረበችላት:: (ሴቷ ለሴቷ ማለት ነው) ለእርሷ ወንድ መስላታለችና:: ቅድስት አውጋንያ ግን ገሥጻ ሰደደቻት:: በዚህ የበሸቀችው ያቺ ክፉ ወጣት ወደ ከተማ ሒዳ ለሃገረ ገዢው ፊልዾስ (የቅድስቷ አባት) ክስ አቀረበች::
+እርሱ (ፊልዾስ) አውጋንያ ከጠፋችበት ቀን ጀምሮ በስሟ ጣዖት አሠርቶ የሚሰግድ ሆኖ ነበር:: ወጣቷ "በገዳም ያሉ መነኮሳት: በተለይ አውጋንዮስ የሚሉት መሪያቸው አስገድዶ ከክብር ሊያጐድሉኝ ሲሉ አመለጥኩ" ብላ በሃሰት በመክሰሷ ገዳሙ እንዲመዘበር: መነኮሳቱም እንዲገረፉ መኮንኑ ፊልዾስ አዘዘ::
+በግርፋቱ መካከልም ብዙ መነኮሳት ሞቱ:: የእነርሱ ስቃይ ያንገበገባት ቅድስት አውጋንያ ግን አባቷን ለብቻ ወስዳ አስምላ ማንነቷን ገለጸችለት:: የናፈቃት ልጁን ሲያገኝ ደስ ብሎት መነኮሳቱን እንዲተዉ አዘዘ::
+ለብቻ ከልጁ ጋር ተቀምጦም ያለፈውን ነገር ሁሉ ነግራ ስለ ሰማያዊ ሕይወት አስረዳችው:: በስሟ የተቀረጸውን ጣዖትም ሰብራ አባቷን አስጠመቀችው:: እርሱም መንኖ ለዓመታት ኖረ:: ከዚያም ዻዻስ ሆኖ ተሹሟል::
+በዚህች ቀንም ስለ ክርስቶስ አንገቱን ተሰይፏል:: ቅድስት አውጋንያ ግን ከግብጽ ወደ ሮም ሒዳ የደናግል ገዳምን መሠረተች:: በሥሯም አምላክ 3,300 ደናግልን ሰበሰበላት:: እነርሱን ስታጽናና: ስትመክር: ስትመራ ለዓመታት ኑራ በአካባቢው ገዢ ሃይማኖቷን እንድትክድ ተጠየቀች::
+"እንቢ" በማለቷ እርሷም እንደ አባቷ በዚህች ቀን ተሰይፋ ሰማዕት ሆናለች:: አብረዋት የመነኑ 2ቱ ጃንደረቦችም ዻዻሳት ሆነው ቤተ ክርስቲያንን አገልግለዋል::
<< *ድንግል: *መናኝ: *ፈዋሽ: *ናዛዥ: *አበ ምኔት: *እመ ምኔት: *ጻድቅትና *ሰማዕት ለሆነች ለእናታችን ቅድስት አውጋንያ ክብር ይገባል! >>
+"+ አባ ገብረ ናዝራዊ +"+
=>እኒህ ጻድቅ በ14ኛው መቶ ክ/ዘ የነበሩ ኢትዮዽያዊ ናቸው:: ጻድቁ ትግራይ (ገዳማቸው ያለበትና) ሽዋ አካባቢ በደንብ ይታወቃሉ:: የእርሳቸው የቆብ አባት የሆኑት አባ ጐርጐርዮስ የታላቁ አኖሬዎስ (የደብረ ጽጋጋው) ልጅ ናቸው::
+አባ ገብረ ናዝራዊ በምናኔ በየገዳማቱ ሲጋደሉ ከኖሩ በሁዋላ በምክረ አበው ራሳቸው ገዳምን መሥርተዋል:: ብዙ ደቀ መዛሙርትንም ሰብስበው ገዳሙ ታላቅ ሆኗል:: በወቅቱ ከገዳመ ዋሊ (ዋልድባ) ቀጥሎ ጥብቅ ሥርዓት የነበረበት ታላቅ ገዳምም ሆኖ ነበር::
+ለዚህም ምክንያቱ አባ ገብረ ናዝራዊ ፍጹም ተሐራሚ በመሆናቸው ማንኛውም መነኮስ ከአንድ ማዕድ ውጪ እንዲቀምስ የማይፈቅዱ ስለ ነበር ነው:: ከታላቁ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ቀጥሎም ሰንበትን አክብሮ በማስከበር ጻድቁ ትልቁን ቦታ ይይዛሉ::+በተለይ ቀዳሚት ሰንበት እንድትከበር ታግለዋል:: በበጐ አበ_ምኔትነታቸውም ብዙ ፍጹማንን ለሃገራችን አፍርተዋል:: ራሳቸው የበሰለ ነገር ወደ አፋቸው ሳያስገቡ 24 ሰዓት በዳዊት መዝሙር ይደሰቱ ነበር::
+ላባቸው እስኪንጠፈጠፍም ይሰግዱ ነበር:: ሐዋርያዊ ግብርን ለመፈጸምም ወንጌልን እየሰበኩ ያለቻቸውን ነገር ይመጸውቱ ነበር:: ዛሬ የጻድቁ ዕረፍታቸው ነው::
+"+ ቅዱስ ፊቅጦር ዘሻው +"+
=>ይህ ቅዱስ ከታላላቅ ሰማዕታት አንዱ ነው:: ሻው ማለት ሰማዕትነትን የተቀበለባት ቦታ ስትሆን "ፊቅጦር ካልዕም" ይባላል:: ከክርስቲያን ወላጆቹ የወረሰውን በጐነት አጽንቶ በቅን መንገድ ኑሯል::
+ምንም ወጣት: የሃገር አስተዳዳሪ: ሃብታምና መልከ መልካም ቢሆንም ይህ ሁሉ ከክርስቶስ ፍቅር ሊለየው አልቻለም:: (ሮሜ. 8:35) ዘመነ ሰማዕታት በደረሰ ጊዜም ክብሩን ንቆ: ስለ ክርስትና ብዙተ ሰቃይቶ: በዚህች ቀን ከነ ተከታዮቹ ሰማዕት ሆኗል:: ጌታም ቃል ኪዳንን ገብቶለታል::
=>አምላከ ቅዱሳን የወዳጆቹን ምሥጢረ ቅድስና አይሰውርብን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::
=>ታሕሳስ 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት አውጋንያ ተጋዳሊት
2.አባ ገብረ ናዝራዊ ንጹሕ
3.ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
4.ቅዱስ ፊልዾስ ሰማዕት
5.ቅዱስ ናሆም ነቢይ
ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2.ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም
3.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
4.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
5.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ
=>+"+ ነገር ግን ለበጐ ነገር ጥበበኞች: ለክፉትም የዋሆች እንድትሆኑ እወዳለሁ:: የሰላምም አምላክ ሰይጣንን ከእግራችሁ በታች ፈጥኖ ይቀጠቅጠዋል:: የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን:: +"+ (ሮሜ. 16:19)
✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞
💥መንፈሳዊ መነባነብ
🛑ርዕስ፦ አባ
ከለታት፡አንድ ቀን በመንገድ ስጓዝ
አንድ አባት አገኜዉ ተሼክመዉ ጓዝ
ወይ፡ሲያሳዝኑ እያልኩ በልቤ ጒበስ አልኩኝና
ዴህና ዋሉ አባ፡አልኩኝ በትትና
እግዚአብሔር ይመስገን ክብር ይግባዉ፡ለእርሱ
እዚህ ላዴረሰኝ ለእርሱ ለንጉሱ
አተስ፡ሠላም አለህ?
ወዴ፡ቤተክርስቲያን ከቶ፡ትሔዳለህ
በማለት ጠየቁኝ ወዴእኔ በማየት
እየተገረሙ በሚመስል አይነት
በዉስጤ ሳኩና በደንብ አየኋቼዉ
ሴት እንዴሆንኩኝ ግን ፆታየ፡ጠፍቷቼዉ
እራሴን ጠየኩኝ እያስተዋልኩአቼዉ
ከሄድኩበት ሀሳብ፡መለስ አልኩኝና
ለእርሰወ ይሁን ክብርና ምስጋና
አወ፡እሔዳለሁ ዘወትር ጧት ማታ
ቃሉን ያሰማኛል ሁሌ፡እንድበረታ
ቁሜ ሳሰላስል ከራሴ ስመክር
ልጠይቅ ወሠኩኝ ያለ፡መንገራገር
እኔ እምለዉ አባ፡እኔኮ ሴት ልጅ ነኝ
በምን በወንድ፡አንቀፅ አተ፡ብለዉ፡ጠሩኝ
አባም መለሱልኝ በትህትና ቃል
ሴትማ፡እንዳልልሽ ሱሪዉን ለብሰሻል
ሁኔታወችሽ ሁሉ ወንዶችን መስለሻል
ታዲያ ምን ልበልሽ ስረዓት ጥሰሻል
እየመለሱልኝ በሁለት አይናቼዉ
እንባቼዉ ይወርዳል
አሁን ገና ገባኝ እያልኩ በልቤ
ያነበብኩት ቃል ትዝ አለኝ በሀሳቤ
ቃሉን ባስታዉስም ከአባ፡መስማት ፈለኩ
ቃሉን እንዲነግሩኝ፡በትትና፡ጠየኩ
አባ…ምከሩኝ፡ሱሪ ብቻ አይዴለም ብዙነዉ ሀጢአቴ
በይ፡ልጄ ካልሽኝ፡እማ በኦሪት ዘዳግም ምዕራፍ
ምዕራፍ 22 ቁጥር 5 ላይ
ሴትም የወንድን ልብስ ፈፅማ፡አትልበስ
ወንድ ልጅም ቢሆን፡የሴትን አይልበስ
ይህንን የሚያዴርግ በአምላኩ በእግዚአብሔር የተጠላ ነዉ
በቃሉ መመከር፡ቤተክርስቲያን መሄድሽ፡መልካም፡ነዉ
ግን፡ልጄ የእግዚአብሔር ቃል ምን ይላል መሰለሺ
ልንገርሽ አብቢዉ ከቤትሽ ስትዴርሺ
የያዕ/መልዕክት ምዕራፍ 1 ላይ፡ከቁጥር 23 ገለጥ አድርገሽ ብታይ
የሚያዴርግ ቢኖር ቅዱስ ቃሉን ሠምቶ
የተፈጥሮ ፊቱን በመስታወት አይቶ
በሚገባ ራሱን ተረድቶ ይሄዳል
እንዴት እንዴሆነ ወዲያዉኑ ይረሳል
አየሽ ልጄ ቃሉ፡እንድህ ይል፡ነበር
ምነኛ፡መልካም፡ነዉ ሠምተን ብተገብር
ብለዉ እያዘኑ ወዴ፡ሰማይ አዩ
በሀሣብ፡ሔዴዋል፡ምን፡አለ፡ሰማዩ
ከሄድኩበት ሀሳብ፡ልመለስ፡አሰብኩኝ
ካረፍኩበት ቦታ ተነስቼ ቆምኩኝ
ይህን ሁሉ ሼሼክም፡ለምን፡ተሼከሙ
ካሰቡበት ለመድረስ ይኖረወታል አቅሙ
ብየ፡ጠየኳቼዉ በሀዘነዉ ልቤ
ቀስ ብለዉ ተነሱ ቆሙካጠገቤ
ይችማ፡ምን፡አላት ምን አላት ብለሽ ነዉ
መድሃኒአለምን፡እስኪ ልጄ አስቢዉ
የኛን ሁሉ በደል፡ሀጢአት ተሼክሞ
ስለሁላችንም፡በመስቀል ላይም ቁሞ
ነፃ አወጣን ጌታ፡ዋጋ ከፈለልን
በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን
ያባ፡መልሳቼዉ፡እጅግ አስዴነገጠኝ
ዘወር አልኩኝና፡እባ ተናነቀኝ
እኔ የስጋየን ሼክም፡ሳወራቼዉ
ቀራኒዮ፡ሔዱ መች የኔ ታያቼዉ
በይ፡ልጄ ጠንክሪ፡በእምነትሽ
ክርስቶስን ይምሰል ዴግሞ፡አለባበስሽ
ተሠናበቱኝ በጣፋጭ ምክራቼዉ
ጉዞዉን ጄመሩ ጓዛቼዉን ይዘዉ
በዛሬው ጉዞየ፡ዴስተኛ ነበርኩ
ከጥፋት ጒዳት ከስተም ተማርኩ
እግዚአብሔር በአንድም በሌላም ይመክራል
ልጆቹ እንዳጠፋ ዘወትር ይመክራል
❗️ወስብሐት ለእግዚአብሔር❗️
👇👇
💥🔍ኪነ-ጥበብ🔎💥
+ንጉሡም ተጸጽቶ ዮሐንስን ካለበት አስመጣው:: አበውም የሮሜ ሊቀ ዻዻሳት አድርገውት ብዙ መጻሕፍትን ተርጉሟል:: ቅዱስ በአሚን ግን በቅድስና ኑሮ በዚህች ቀን ዐርፎ በዝማሬ ተቀብሯል::
=>አምላከ ቅዱስ በአሚን በጸሎቱ ይማረን:: ከትእግስቱ ይክፈለን:: ከበረከቱም ያሳትፈን::
=>ታሕሳስ 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አባ በአሚን (ጻድቅና ሰማዕት)
2.ቅድስት አርምያ
3.ቅዱስ ዘካርያስ
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱሳን 318ቱ ሊቃውንት
2.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት)
3.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ
4.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን
5.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ
6.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ
=>+"+ አባቶች ሆይ! ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃቹሃልና እጽፍላቹሃለሁ:: ጐበዞች ሆይ! ክፉውን አሸንፋቹሃልና እጽፍላቹሃለሁ:: ልጆች ሆይ! አብን አውቃቹሃልና እጽፍላቹሃለሁ:: አባቶች ሆይ! ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃቹሃልና እጽፍላቹሃለሁ:: ጐበዞች ሆይ! ብርቱ ስለ ሆናችሁ: የእግዚአብሔርም ቃል በእናንተ ስለሚኖር: ክፉውንም ስላሸነፋችሁ እጽፍላቹሃለሁ:: +"+ (1ዮሐ. 2:13)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
🔴በቴሌግራም ለመከታተል👉/channel/zikirekdusn
🛑በዩቲብለመከታተል👉
https://youtube.com/shorts/egux4JdrPrw?si=MjLWZmAjsMzYfmlB
👉ወጋሕታ ሐበሻ እና ሽፎን ስፌትና መሸጫ💃💃👗👗 ለበለጠ መረጃ ይደዉሉ 251912448561☎️☎️☎️😘👌👌
ወደ ምትፈልጉት ሀገር ሰርተን መላክ እንችላለን ከናንተ ምንጠብቀዉ መርጣቹ መላክ ብቻ 👌👌💃💃💃💃💃💃💃💃💃👗👗👗👗
እንደ ምን አላችሁ ቤተሰቦቼ ?
ከተሠማራንበት የሥራ ዘርፍ በተጨማሪም ሆነ እንደ ዋና ሥራ አድርገን ልንሠራው የምንችለ የሥራ ዘርፍ አለን በመሆኑም ፦
1, በግልም ሆነ በመንግሥት ተቋማት ተቀጥራችዉ የምትሠሩ
2, የግላችውን ሥራ የምትሠሩ
3, ከዩኒቨርስቲ ተመርቃችሁ ሥራ ያላገኛችሁ
መሥራት ወይም ለመጀመር የሚያስችል ካፒታል የምታገኙበት የስራ ዘርፍ ነው ።ማንኛውም መሥራት የሚፈልግ ሰው ሙሉ ስም ፣የመኖሪያ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር በዉስጥ መሥመር ያሥቀምጥልኝ።
ሴልስ መስራት የሚፈልግ በዚህ ቁጥር መደወል ይችላሉ
0983797902
0799192014
inbox me your :
-NAME
-ADRESS
PHONE NUMBER
ከዕለታት በአንደኛው ቀን አቡነ ተክለ አልፋ ደመና ጠቅሰው በእርሷ ላይ ተጭነው ወደ ኢየሩሳሌም በመሔድ ክብር ይግባውና ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀበት ከዮርዳኖስ፣ ከተሰቀለበት ቀራንዮ ከተቀበረበት ጎልጎታ ከተመሰገነባት ደብረ ታቦር ደርሰው ሲሳለሙ ጌታችን ተገልጦላቸው አቅፎ ስሟቸዋል ክብርት እመቤታችንም እንዲሁ ሳመቻቸው ዳግመኛም የብርሃን ሠረገላ ተሰጥቷቸው በእርሱ ወደ ሰማይ እያረጉ በሰማያውያን ቅዱሳን ጉባኤ ጋር እያገለገለ ወደ ምድር ይመለስ ነበር። ጌታችንም ዘለዓለማዊ ማረፊያቸው ከሆናቸው ዘንድ እጅግ የተዋበች ርስታቸው የምትሆን ቤት አሳያቸውና በዚህ ዓለም ስለ እኔ ደክመህ እንዳከበርከኝ እኔም በወዲያኛው ዓለም አከብርሃለሁ ስለ ቅድስናና ስለ እውነተኛነትህ ለአንተና ለልጆቸህ በጎዳናም ለሚሔዱ ምእመናን ሁሉ ማደሪያ ትሁን ብሎ ሰጣቸው ሌላም ታላቅ የምሕረት ቃልኪዳን ገባላቸው። እንዲሁም የታዘዘ መልአክ ወደ ሰማይ ወጥቶ ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የሥላስ ቅዱስን መንበር እንዳጠና ግድላቸው ይናገራል።
የዋልድባ መነኰሳት የአባ ተክለ አልፋን ክብር በግልጽ ያዩ እንደነበር ምስክር የሆኑ አሉ። ከእነርሱም ውስጥ አንደኛው መነኩሴ ከአባታችን ተክለ አልፋ በረከትን ይቀበል ዘንድ ወደ ዲማ መጥቶ መነኰሳት ልጆቻቸውን ሒዱና አባ ተክለ አልፋን እንግዳ ሰው በደጃፍ ቆሟል በረከትህንም ፈልጎ ሊያይህ ይወዳል›› ብላችሁ ንገሩልኝ አላቸው። ያም መነኩሴ ወደ ወስጥ ሳይገባ ከደጃፍ በዚያችም ሰዓት በቤቱ ደጃፍ ቁሜ ሳለ አባ ተክለ አልፋን ከቤቱ ወጥቶ ምሥራቅንና ምዕራብን፣ ሰሜንንና ደቡብን ሲባርክ አየሁት አለ። ያንጊዜም ደመና መጥቶ ወደ ሰማይ አወጣው ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወደቦታው መለሰው አለ። ያም መነኩሴ ይህን አይቶ ፈጽሞ አደነቀ ወደ አባታችንም ቀርቦ ሰገደላቸውና ተባረከ አባታችንም የዋልድባው ጽድቃቸውን እንዳወቀባቸው ተረድቶ ይህን ለማንም እንዳይናገር አስማሉት በሰው ዘንድ መመስገንን ፈጽመው ይጠለ ነበርና።
ከአቡነ ኤዎስጣቴዎስም ልጆችም ውስጥ አንዱ እንዲሁ የአቡነ ተክለ አልፋን ክብር አይቶ እጅግ አደነቀና እንዲህ አለ፡- ከዕለታት በአንዱ ቀን የእግዚአብሔር መልአክ ነጥቆ ሁሉን በሚይዝ አምላክ ዙፋን ፊት አደረሰኝ፣ በዚያም የብርሃን ድንኳን ተተክሎ አየሁ በውስጡም ጌታችን የተቀመጠበት የክብር ዙፋን አለ፣ በቀኝ በግራው፣ በፊት በኋላው የብዙ ብዙ መላእክት ı ነቢያት፣ ጻድቃንና ሰማዕታት ደናግል መነኰሳት ቆመው አየሁ ከዚኸም በኋላ ጌታችን በምድር ካሉት መምህራን እንዲጠሩ አዘዘና ሦስቱ መምህራንን መጡ፤ ጌታችንም ወደ
አባ ተክለ አልፋ ተመልሶ ግን ምርቱን የፈጸሙ ፈቃዴንም ያደረጉ እነዚህ ናቸው ከእነርሱ ይልቅ የወንጌልን ቃል የፈጸመ ሐዲስ ሐዋርያት ይህ ተክለ አልፋ ነው አለ። ያንጊዜም መንፈሳዊ በሆነ ቅብዓ ሜሮን ፊቱን ባረከው በራሱ ላይም ዘውድ አቀዳጀውና እስከጊዜው ድረስ አሰናበታቸው ።
ዳግመኛም የእግዚአብሔር አገልጋይ የምትሆን በደብረ ሊባኖስ የምትኖር አንዲት መነኲሴ ስለ አቡነ ተክለ አልፋ ያየችውን በመናገር ምስክር ሆነች ለማንም ያልተደረገ የአባ ተክለ አልፋን ክብሩን ግርማ ሞገሱን ሰው ቢያይና ቢያውቅ ነፍሱ ከሥጋው ፈተና በተለየች ነበር አለች። አንዲት እግዚአብሔርን የምትፈራ ደግ መነኵሲትም አባታችን ተክለ አልፋን ሰባት ሰባት መላእክት በታች በግራው በኋላውና በፊቱ ሰይፋቸውን እየመዘዙ ሲዛሩት አየሁት አለች። ዳግመኛም እንዲህ አለች - ያንንም አይቼ ደነገጥኩ፡፡ ከዚያን ሰዓት ጀምሮ ካየሁት ራእይ የተነሣ ዙሪያውን ከበውት ካሉት መላእክት ግርማ የተነሣ ወደ አባ ተክለ አልፋ መሔድን ተው፤ ወደ እርሱም ሳልሔድ ጥቂት ቀን ሰነበትኩ። በአንዲት ቀንም ተደፋፍሬ ወደ አባ ተክለ አልፋ ሔድኩና ከእርሱ ዘንድ ተባረኩ፤ ያንጊዜም ተቆጥቶ እስከዛሬ ወደእኔ ሳትመጭ ለምን ዘገየሽ? አለኝ። እኔም መልሼ ወደ አንተ መምጣትን የተውኩት ስለ ስንፍና አይደለም የተመዘዘ ሰይፎቻቸው በእጃቸው ላይ ያሉ መላእክት ሲከቡህ ባ ጊዜ ፈርቼ ነው እንጂ አልኩት። እርሱም በዚህ ዓለም በሕይወተ ሥጋ ሳለሁ ይህንን ምሥጢር ለሰው እንዳትግል ለራስሽ ዕወቂ፣ ክብር ይግባውና በጌታ ሰም አምልሻለሁ አለኝ። እንዲሁም በብዙ ገደማት ያሉ ደጋግ መነኰሳት የአባታችንን የአቡነ ተክለ አልፋን ክብር እግዚአብሔር እንደፈቀደላቸው መጠን ያዩትን ነገሮ አባታችን ካረፉ በኋላ በመናገር ምስክር ሆኑ።
ከአባታችን ተክለ አልፋ ልጆች ውስጥ አንዲት መነኵሲት ነበረች። ከዕለታት አንድ ቀን ከቤቷ ጅብ ነጥቆ ወሰዳት፤ ወሩም የስደት ወራት ነበርና። የሚረዳትም ባጣች ጊዜ በአባ ተከለ አልፋ ጸሎት ተማጽኛለሁ እያለች ጮኸች አባታችን ተክለ አልፋም ድምፁዋን በሰሙ ጊዜ ያድኗት ዘንድ ልጆቻቸውን ጠሯቸው፤ ከእነርሱም የመለሰላቸው የለም። አባታችንም ስለድካማቸው ሊረዷት አልቻለም፤ ነገር ግን ይለምኑላት ዘንድ ሌሊቱን ሙሉ ክብር ይግባውና ሁሉን ወደሚያድንና ወደሚረዳ ወደ እግዚአብሔር ይለምኑ ጀመር። እግዚብሔርም ልመናቸውን ሰማቸውና በበነጋው ፀሓይ በወጣች ጊዜ ያች መነኵሲት በሕይወቷ መጣች አባታችንንም በጸሎትህ እግዚአብ ሔር ከሚበላ ጅብ አፍ አዳነኝ፣ ከአራት ጅቦች መካከልም አደርኩ መብላትም አልቻሉም አለቻቸው። አቡነ ተክለ አልፋም ለሰው እንዳትናገር አማሏት ተቆጣትም።
ከዕለታት በአንደኛው ቀን አንዲት መነኵሲት ምግቧን ትሰበስብ ዘንድ በጎዳና ስትሔደ አንድ ጎልማሳ በኅይል ይዞ ደፈራት ከእርሶ ጋርም ተኛ፤ እርሷም ፀነስች የምንኩስናዎ ክብር ስለጠፋ እያዘነችና እያለቀሰች ወደ ቤቷ ተመለስች ፯ ወር ያህልም ራሷን ሸሽገት፡ ፅንሱም ታወቀ። ከዚኽም በኋላ በልቧ አስባ የመውለጃየ ቀን በደረሰ ጊዜ ምን አደርጋለሁ አለች እኔ ስደተኛ ነኝና በዚችም ሀገርም የማውቀው የለኝም አለች፤ “ነገር ግን ተነሥቼ ወደ አባ ተክለ አልፋ እሔዳለሁ ልብ ሩኅሩኅ እንደሆነ የደካሞችንም ድካም እንደሚያቃልል ዝናውን ስምቻለሁና፡፡ አለች
ከዚኽም በኋላ ተነሥታ ሔደች ወደ አባ ተክለ አልፋም ዘንድ ደርሳ የደረሰባትን
ነገረቻቸው እርሳቸውም እንደሚገባ ንስሓ ሰጧት ለብቻዋ ቤትም አዘዘላት እስከ ስምንት ቀንም ታግሣ ከእርሳቸው ትባረክ ዘንድ ወደ አባታችን ደረሰች እግራቸውንም ሲታጠቡ አገኘቻቸው ያንጊዜም እግራቸውን ያጠበውን ሰውዬ የእግራቸውን እጣቢ ይሰጣት ዘንድ ለመነችው፣ እርሱም ሰጣት። ከዚያም የአቡነ ተክለ አልፋን ጸሎት በመተማመን ጠጣችው፣ ከዚያም ሰዓት ጀምሮ የፅንሱ ፍለጋ ዘዴ ፈጽሞ ጠፋ፣ የወር አበባም ልማደ አንስትም ተዋት። እርሷም እጅግ ተደስታ የአባ ተክለ አልፋን አምላክ አመሰገነች ከቅጽረ ቤተ ክርስቲያን እንዳትወጣ ብፅዓት ገባች። ይኽንንም ተኣምር ለአቡነ ተክለ አልፋ ነገረቻቸው እርሳቸውም ለማንም ሰው እንዳትናገር አዘዟት።
ከዛሬ ከ1700 ዓመት በፊት ሰማዕት ሆነች
ቅዱስ አካሏ አሁን ድረስ አልፈረሰም
የራስ ጸጉሯ በተአምር አሁን ድረስ ያድጋል።
ሰማዕቷ ቅድስት ኢራኢስ አል አፊፋ ትባላለች በአቢሳ ተወልዳ ያደገች ሲሆን የኖረችውም በሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በክርስቲያኖች ላይ ብዙ መከራን ባደረሰውና አብያተክርስቲያናትን ያሳድድ በነበረው በአላዊው ንጉሥ በአርያኖስ ዘመነ መንግሥት ነበር።
ሕጻኗም ሰማዕት ከምትኖርበት ተነሥታ በአርያኖስና በሠራዊቱ ፊት ስለ ክርስቶስ በመመስከር ሰማዕትነትን ለመቀበል መጣች የንጉሡ ወታደሮች ክርስቶስን እንድትክድ ብዙ መከራ እንድትቀበል አደረጋት ሰውነቷ እንዲላጥ፣ የፈላ ዘይት እንዲደፋባት፣ በምስማር ላይ እንድትራመድ በማድረግ ብዙ መከራ እንድትቀበል አድርጓታል።
ቅድስት ኢራኢስ በመከራ ውስጥ ሳለች ጠባቂዋ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦላት በመከራ እንድትጸና አደረጋት፣ ከመከራዋም አረጋጋት ቁስሏንም ፈወሰላት በመጨረሻም ወታደሮቹ ብዙ መከራ ካደረሱባት በኋላ አንገቷን ቆረጧት(ለሞት እስትድደርስ አንተገቷን ወጋት) ወዲያኑ ሰማዕትነትን ተቀበለች።
እግዚአብሔር መከራን ተቀብላ ክርስቶስን በማመን ስለጸናች ድንቅ ሥራው በእርሷ ይገለጥ ዘንድ እስከአሁን ድረስ ቅዱስ አካሏ አልፈረሰም የራስ ጠጉሯ አሁን ድረስ ያድጋል።
ዕረፍቷ በፈረንጆቹ December 3 ነው።
እግዚአብሔር በሰማዕቷ አማላጅነት ይማረን በረከቷ ይደርብን አማላጅነቷ ዘወትር አይለየን አሜን።
New Ethiopian Orthodox Mezmur 2023
🎙ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ|
🏷የፍቅር በር ነህ_]
💽New Ethiopian Orthodox mezmur
@orthodox_new_mezmur
@orthodox_new_mezmur
👆 ይቀላቀሉን 👆
📮መዝሙር መጋበዝ ይቻላል👇
መዝሙር ለመላክ👉 @Nolawiher1
New Ethiopian Orthodox Mezmur 2023
ታሕሳስ 1
ታላቁ ቅዱስ ኤልያስ
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ቀጥላ ቅዱስ ኤልያስን ታከብራለች። "ርዕሰ ነቢያት - የነቢያት ራስም" ትለዋለች።
እርሱ ሰማይን የለጐመ፣ እሳትን ያዘነመ፣ ፍጥረትንም በቃሉ ያዘዘ አባት ነውና።
ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ፦
ቅዱሱ ትውልዱ (ነገዱ) ኢዮርብዓም ነጥሎ ከወሰዳቸው እስራኤል (አሥሩ ነገድ) ሲሆን አባቱ "ኢያስኑዩ" እናቱ ደግሞ "ቶና (ቶናህ)" ይባላሉ። በጐ አምልኮ ነበራቸውና እግዚአብሔር ማኅጸነ ቶናህን ቀድሶ ይህንን ቅዱስ ፍሬ ፈጠረ።
ቅዱስ ኤልያስ በተወለደ ቀን በቤታቸው ብርሃን ተሞልቶ ታይቷል። ብርሃን የለበሱ አራት ሰዎች (መላእክት) መጥተውም በእሳት ሰፋድል (መጐናጸፊያ) ሲጠቀልሉት ወላጆቹ በማየታቸው ደንግጠው ለነቢያትና ለካህናት ነገሯቸው።
ካህናቱ ግን ነገሩ ቢረቅባቸው "ምን ዓይነት ፍጥረት ይሆን? በእስራኤል ይነግሥ ይሆን! ወይስ ነቢይ ይሆን?" ብለውም አድንቀዋል።
ቅዱስ ኤልያስ ከልጅነቱ ጀምሮ ኮስታራ፣ ቁም ነገረኛ፣ ንጽሕናንም የሚወድ እስራኤላዊ ነው።
ወቅቱ (ከክርስቶስ ልደት ዘጠኝ መቶ ዓመት በፊት) ሕዝቡና ነገሥታቱ የከፉበት፣ እግዚአብሔር ተክዶ ጣዖት የሚመለክበት ነበር። ድሮ በኢሎፍላውያን እጅ የነበሩት ጣዖታት (ዳጐንና ቤል) በዚያ ዘመን ወደ እስራኤል ገብተው ነበር።
ቅዱስ ኤልያስ ግን በዚህ ክፉ ትውልድ መካከል ሆኖም ሥርዓተ ኦሪትን የጠነቀቀ የንጽሕናና የአምልኮ ሰው ነበር።
በዚያ ወራትም እግዚአብሔር ለነቢይነት ጠራው። እርሱም "እሺ" ብሎ ታዝዞ የእግዚአብሔርን የጸጋ ጥሪ ተቀበለ። ቅዱሱ ብዙ ጊዜ ለጉዳይ ካልሆነ ከሰው ጋር መዋል ማደርን አይወድምና መኖሪያውን በተራሮችና በዱር አደረገ።
በተለይ ደብረ ቀርሜሎስ ለእርሱ ቤቱ ነበር። በዚህ ሕይወቱም ከመልከ ጼዴቅ ቀጥሎ፦
፩.ለድንግልና (ድንግል ነበርና)
፪.ለብሕትውና (ብቸኛ ነበርና)
፫.ለምንኩስና (ተሐራሚ ነበርና) በብሉይ ኪዳን መሠረትን የጣለ ነቢይ ይባላል።
መቼም በብሉይ ኪዳን የቅዱስ ኤልያስን፣ በዘመነ ክርስቶስ የመጥምቁ ዮሐንስን፣ በዘመነ ሊቃውንት ደግሞ የአፈ ወርቅ ዮሐንስን ያህል ደፋርና መገሥጽ አስተማሪ አልነበረም። በጊዜው ደግሞ አክአብና ኤልዛቤል የሚባሉ ክፉ ባልና ሚስት በእስራኤል ላይ ነግሠው ሕዝቡን ጣዖት አስመለኩት።
ይባስ ብለው ደግሞ በወይኑ እርሻ አማካኝነት ኢይዝራኤላዊው ናቡቴን በሃሰት ምስክር ደሙን አፈሰሱት። ናቡቴም "የአባቶቼን ርስት አልሸጥም፤ አልለውጥም።" በማለቱ እንደ ሰማዕት ይቆጠራል።
ኤልያስ ግን ይህንን ሲሰማ ወደ አክአብና ኤልዛቤል ቀርቦ "የናቡቴ ደም በእናንተ ላይ አይቀርም። የአንቺንም ደም ውሻ ይልሰዋል።" አላቸው። በዚህ ምክንያትም ኤልዛቤል ልትገድለው ብትፈልገውም እርሱ የእግዚአብሔር ነውና አላገኘችውም።
በዚህ ብስጭትም ይመስላል አንድ ሺህ ነቢያትን ሰብስባ "ፍጇቸው" አለች።
ዘጠኝ ...
ይህን ፅሁፍ ሙሉውን አንብቦ ለመጨረስ እንዲሁም የሌሎች ቅዱሳንኖችን ስንክሳር (መንፈሳዊ ታሪኮችን) ለማግኝት አፕሊኬሽኑን ስልክዎት ላይ በታች ባልው አድራሻ (ሊንክ) ተጠቅመው ይጫኑ።
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.sammy.mycountryquotes
+ለዚህም ምክንያቱ አባ ገብረ ናዝራዊ ፍጹም ተሐራሚ በመሆናቸው ማንኛውም መነኮስ ከአንድ ማዕድ ውጪ እንዲቀምስ የማይፈቅዱ ስለ ነበር ነው:: ከታላቁ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ቀጥሎም ሰንበትን አክብሮ በማስከበር ጻድቁ ትልቁን ቦታ ይይዛሉ::+በተለይ ቀዳሚት ሰንበት እንድትከበር ታግለዋል:: በበጐ አበ_ምኔትነታቸውም ብዙ ፍጹማንን ለሃገራችን አፍርተዋል:: ራሳቸው የበሰለ ነገር ወደ አፋቸው ሳያስገቡ 24 ሰዓት በዳዊት መዝሙር ይደሰቱ ነበር::
+ላባቸው እስኪንጠፈጠፍም ይሰግዱ ነበር:: ሐዋርያዊ ግብርን ለመፈጸምም ወንጌልን እየሰበኩ ያለቻቸውን ነገር ይመጸውቱ ነበር:: ዛሬ የጻድቁ ዕረፍታቸው ነው::
+"+ ቅዱስ ፊቅጦር ዘሻው +"+
=>ይህ ቅዱስ ከታላላቅ ሰማዕታት አንዱ ነው:: ሻው ማለት ሰማዕትነትን የተቀበለባት ቦታ ስትሆን "ፊቅጦር ካልዕም" ይባላል:: ከክርስቲያን ወላጆቹ የወረሰውን በጐነት አጽንቶ በቅን መንገድ ኑሯል::
+ምንም ወጣት: የሃገር አስተዳዳሪ: ሃብታምና መልከ መልካም ቢሆንም ይህ ሁሉ ከክርስቶስ ፍቅር ሊለየው አልቻለም:: (ሮሜ. 8:35) ዘመነ ሰማዕታት በደረሰ ጊዜም ክብሩን ንቆ: ስለ ክርስትና ብዙተ ሰቃይቶ: በዚህች ቀን ከነ ተከታዮቹ ሰማዕት ሆኗል:: ጌታም ቃል ኪዳንን ገብቶለታል::
=>አምላከ ቅዱሳን የወዳጆቹን ምሥጢረ ቅድስና አይሰውርብን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::
=>ታሕሳስ 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት አውጋንያ ተጋዳሊት
2.አባ ገብረ ናዝራዊ ንጹሕ
3.ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
4.ቅዱስ ፊልዾስ ሰማዕት
5.ቅዱስ ናሆም ነቢይ
ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2.ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም
3.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
4.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
5.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ
=>+"+ ነገር ግን ለበጐ ነገር ጥበበኞች: ለክፉትም የዋሆች እንድትሆኑ እወዳለሁ:: የሰላምም አምላክ ሰይጣንን ከእግራችሁ በታች ፈጥኖ ይቀጠቅጠዋል:: የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን:: +"+ (ሮሜ. 16:19)
✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞
🔴በቴሌግራም ለመከታተል👉/channel/zikirekdusn
🛑በዩቲብለመከታተል👉
https://youtube.com/shorts/egux4JdrPrw?si=MjLWZmAjsMzYfmlB
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
✞✞✞ እንኩዋን ለእናታችን "ቅድስት አውጋንያ" : "አባ ገብረ ናዝራዊ" እና "ቅዱስ ፊቅጦር" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+*" ቅድስት አውጋንያ "*+
=>ይህቺ ቅድስት ወጣት ስም አጠራሯ በእውነት የከበረ ነው:: ዜና ሕይወቷ ሲሰማ ጣዕመ ነፍስን ያድላልና:: በፈጣሪ ረዳትነት ልጀምር:: እናንተም በእግዚአብሔር አጋዥነት ተከተሉኝ::
+ቅድስት አውጋንያ የ3ኛው መቶ ክ/ዘ የክርስትና ፍሬ ናት:: በትውልዷ ሮማዊት ስትሆን አባቷ ፊልዾስ ይባላል:: ሥራውም የጦር መሪ: የሃገርም አስተዳዳሪ ነው:: በስም ያልተጠቀሰች እናቷ ደግሞ ክርስቲያን ነበረች::
+ዘመኑ አስከፊ ሰለ ነበር (ለክርስቲያኖች ማለቴ ነው) ክርስትናዋን ደብቃ: አልባሌ (አሕዛባዊ) መስላ ትኖር ነበር:: ቅድስት አውጋንያን ስትወልድ ግን ጨነቃት:: እንዳታስጠምቃት የእርሷም ሆነ የሕጻን ልጇ እጣ ፈንታ ሞት መሆኑ ነው::
+ምክንያቱም ባሏ ፊልዾስ ክርስትናን ፈጽሞ የሚጠላ ጣዖት አምላኪ ነበርና:: ከዚያም አልፎ ሰዎች ለጣዖት እንዲንበረከኩም ያስገድድ ነበር:: ስለዚህ እናት ልጇን ሳታስጠምቅ: ግን በፍጹም የክርስትና ትምሕርትና ሥርዓት አሳደገቻት::
+ቅድስት አውጋንያም ጾምን ጸሎትን: ትሕትናን: ትእግስትን የተመላች ወጣት ሆነች:: ግን ምሥጢረ ጥምቀትን ታገኝ ዘንድ ዘወትር ፈጣሪዋን ትማጸን ነበር::
+በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉም አንድ መልካም አጋጣሚ ተፈጠረ:: መኮንኑ አባቷ (ፊልዾስ) በምድረ ግብጽ እስክንድርያ አገረ ገዥ ሆኖ በመሾሙ ጉዋዛቸውን ጠቅልለው ወረዱ:: ምንም ይህ ለቅድስት አውጋንያ መልካም አጋጣሚ ቢሆንም ሌላ ፈተናን አመጣባት::
+አባቷ ለአረማዊ መኮንን ሊድራት መሆኑን ሰማች:: አሁን ግን መቁረጥ ያስፈልግ ነበርና ወሰነች:: ወደ አባቷ ገብታም "አባቴ! አንድ ነገር ላስቸግርህ:: አንተ ለምትለኝ ሁሉ እታዘዛለሁ:: ግን ከሠርጌ ቀን በፊት ለአንዲት ቀን በዱር ውስጥ ተናፍሼ: ተዝናንቼ እንድመጣ ፍቀድልኝ?" አለችው::
+ምን እንዳሰበች ያልጠረጠረ አባቷም ከ2 ጃንደረቦች ጋር እንድትሔድ አደረገ:: በርሃ አካባቢ ሲደርሱም ቅድስት አውጋንያ እውነቱን ለ2ቱ ጃንደረቦች ተከታዮቿ ነገረቻቸው::
+"እኔ ወደ በርሃ የምሔደው ክርስቲያን ልሆን: ደግሞም ልመንን ነውና ካላሰኛችሁ ተመለሱ" አለቻቸው:: 2ቱም ግን በአንድ ቃል "ሞታችንም: ሕይወታችንም ከአንቺ ጋር ነው" ብለዋት አብረው ገዳም ገቡ::
+እንደ ደረሱም ምሥጢራቸውን ለአንድ ጻድቅ መነኮስ ተናግራ እንዲያጠምቃት ጠየቀችው:: መነኮሱም 3ቱንም ካጠመቃቸው በሁዋላ ቅድስት አውጋንያ "አመንኩሰን" ብትለው "ልጄ! ይሔ የወንዶች ገዳም ነውኮ" አላት::
+"አባ! ግድ የለህም! እኔ ራሴን እሰውራለሁ" አለችው:: ከዚያም ሥርዓተ ገዳምን አስተምሮ ስሟን "አባ አውጋንዮስ" ብሎ ከማሕበረ መነኮሳቱ ቀላቀላት:: *አውጋንያን *ታኦድራ *አንስጣስያ . . . የመሳሰሉ ስሞች በቀላል መንገድ ወደ ወንድ ስምነት *አውጋንዮስ *ቴዎድሮስ *አንስጣስዮስ . . .በሚል መቀየር ይችላሉና::
+ከዚህች ዕለት ጀምራ ቅድስት አውጋንያ በአባ አውጋንዮስነቷ ተጋድሎን ጀመረች:: ቀን ቀን ወንዶች መነኮሳት የሚሠሩትን ከባድ ሥራ ሁሉ ስትሠራ ትውልና ሌሊት በትጋት ስትጸልይ ታድራለች:: ለ1 ዓመት ያህል በፍጹም ተጸምዶ ገዳሙን አገለገለች::
+በነዚህ ጊዜያት የመጡባትን ፈተናዎችም ታገሰች:: ዓለምን የናቀችለት: የአባቷን ቤተ መንግስት የተወችለት ክርስቶስ ኃይሏ ነበርና:: በዚያ ሰሞንም የገዳሙ አበ ምኔት በማረፉ መነኮሳትን የሚመራና የሚናዝዝ ሌላ አበ ምኔትን ለመምረጥ ሱባኤ ገቡ::
+ከሱባኤ ወጥተው ሲሰበሰቡ ግን ያመጡት የመንፈስ ቅዱስ መልእክት የሚገርም ነበር:: የሁሉም ዓይን ወደ አባ አውጋንዮስ ተወረወረ:: እርሷ ምሥጢሯን (ሴትነቷን) ታውቃለችና ደነገጠች:: ምርጫው ግን የመንፈስ ቅዱስ ነበርና ግድ ብለው በእነዛ ሁሉ መነኮሳት ላይ እረኛ ሁና ተሾመች::
+በእርግጥ እርሷ ሴት በዚያውም ላይ ወጣት ናት:: ግን እውነተኛ የክርስቶስ ወዳጅ ነበረችና በፍጹም ትጋት መነኮሳትን አስተዳደረች:: ጸጋው ቢበዛላት የተጨነቀውን ታረጋጋ: የታመመውን እጇን እየጫነች በጸሎቷ ትፈውስ ነበር:: በዚህም መነኮሳቱ ደስ ተሰኙ::
+እርሷ ግን ስለዚህ ፈንታ ብዙ ፈተናዎችን በአኮቴት ታሳልፍ ነበር:: ስም አጠራሯም ከበርሃ ወጥቶ ወደ ከተሞች በመግባቱ ድውያን እየመጡ ከእርሷ ዘንድ ይፈወሱ ነበር:: አንድ ቀን ግን ያልተጠበቀ ፈተና መጣባት::
+አንዲት ሰይጣን ያደረባትን ሴት ካዳነቻት በሁዋላ: መልኩዋ እጅግ ውብ ስለ ነበር የዝሙት ጥያቄን አቀረበችላት:: (ሴቷ ለሴቷ ማለት ነው) ለእርሷ ወንድ መስላታለችና:: ቅድስት አውጋንያ ግን ገሥጻ ሰደደቻት:: በዚህ የበሸቀችው ያቺ ክፉ ወጣት ወደ ከተማ ሒዳ ለሃገረ ገዢው ፊልዾስ (የቅድስቷ አባት) ክስ አቀረበች::
+እርሱ (ፊልዾስ) አውጋንያ ከጠፋችበት ቀን ጀምሮ በስሟ ጣዖት አሠርቶ የሚሰግድ ሆኖ ነበር:: ወጣቷ "በገዳም ያሉ መነኮሳት: በተለይ አውጋንዮስ የሚሉት መሪያቸው አስገድዶ ከክብር ሊያጐድሉኝ ሲሉ አመለጥኩ" ብላ በሃሰት በመክሰሷ ገዳሙ እንዲመዘበር: መነኮሳቱም እንዲገረፉ መኮንኑ ፊልዾስ አዘዘ::
+በግርፋቱ መካከልም ብዙ መነኮሳት ሞቱ:: የእነርሱ ስቃይ ያንገበገባት ቅድስት አውጋንያ ግን አባቷን ለብቻ ወስዳ አስምላ ማንነቷን ገለጸችለት:: የናፈቃት ልጁን ሲያገኝ ደስ ብሎት መነኮሳቱን እንዲተዉ አዘዘ::
+ለብቻ ከልጁ ጋር ተቀምጦም ያለፈውን ነገር ሁሉ ነግራ ስለ ሰማያዊ ሕይወት አስረዳችው:: በስሟ የተቀረጸውን ጣዖትም ሰብራ አባቷን አስጠመቀችው:: እርሱም መንኖ ለዓመታት ኖረ:: ከዚያም ዻዻስ ሆኖ ተሹሟል::
+በዚህች ቀንም ስለ ክርስቶስ አንገቱን ተሰይፏል:: ቅድስት አውጋንያ ግን ከግብጽ ወደ ሮም ሒዳ የደናግል ገዳምን መሠረተች:: በሥሯም አምላክ 3,300 ደናግልን ሰበሰበላት:: እነርሱን ስታጽናና: ስትመክር: ስትመራ ለዓመታት ኑራ በአካባቢው ገዢ ሃይማኖቷን እንድትክድ ተጠየቀች::
+"እንቢ" በማለቷ እርሷም እንደ አባቷ በዚህች ቀን ተሰይፋ ሰማዕት ሆናለች:: አብረዋት የመነኑ 2ቱ ጃንደረቦችም ዻዻሳት ሆነው ቤተ ክርስቲያንን አገልግለዋል::
<< *ድንግል: *መናኝ: *ፈዋሽ: *ናዛዥ: *አበ ምኔት: *እመ ምኔት: *ጻድቅትና *ሰማዕት ለሆነች ለእናታችን ቅድስት አውጋንያ ክብር ይገባል! >>
+"+ አባ ገብረ ናዝራዊ +"+
=>እኒህ ጻድቅ በ14ኛው መቶ ክ/ዘ የነበሩ ኢትዮዽያዊ ናቸው:: ጻድቁ ትግራይ (ገዳማቸው ያለበትና) ሽዋ አካባቢ በደንብ ይታወቃሉ:: የእርሳቸው የቆብ አባት የሆኑት አባ ጐርጐርዮስ የታላቁ አኖሬዎስ (የደብረ ጽጋጋው) ልጅ ናቸው::
+አባ ገብረ ናዝራዊ በምናኔ በየገዳማቱ ሲጋደሉ ከኖሩ በሁዋላ በምክረ አበው ራሳቸው ገዳምን መሥርተዋል:: ብዙ ደቀ መዛሙርትንም ሰብስበው ገዳሙ ታላቅ ሆኗል:: በወቅቱ ከገዳመ ዋሊ (ዋልድባ) ቀጥሎ ጥብቅ ሥርዓት የነበረበት ታላቅ ገዳምም ሆኖ ነበር::
💥መንፈሳዊ መነባነብ
🛑ርዕስ፦ አባ
ከለታት፡አንድ ቀን በመንገድ ስጓዝ
አንድ አባት አገኜዉ ተሼክመዉ ጓዝ
ወይ፡ሲያሳዝኑ እያልኩ በልቤ ጒበስ አልኩኝና
ዴህና ዋሉ አባ፡አልኩኝ በትትና
እግዚአብሔር ይመስገን ክብር ይግባዉ፡ለእርሱ
እዚህ ላዴረሰኝ ለእርሱ ለንጉሱ
አተስ፡ሠላም አለህ?
ወዴ፡ቤተክርስቲያን ከቶ፡ትሔዳለህ
በማለት ጠየቁኝ ወዴእኔ በማየት
እየተገረሙ በሚመስል አይነት
በዉስጤ ሳኩና በደንብ አየኋቼዉ
ሴት እንዴሆንኩኝ ግን ፆታየ፡ጠፍቷቼዉ
እራሴን ጠየኩኝ እያስተዋልኩአቼዉ
ከሄድኩበት ሀሳብ፡መለስ አልኩኝና
ለእርሰወ ይሁን ክብርና ምስጋና
አወ፡እሔዳለሁ ዘወትር ጧት ማታ
ቃሉን ያሰማኛል ሁሌ፡እንድበረታ
ቁሜ ሳሰላስል ከራሴ ስመክር
ልጠይቅ ወሠኩኝ ያለ፡መንገራገር
እኔ እምለዉ አባ፡እኔኮ ሴት ልጅ ነኝ
በምን በወንድ፡አንቀፅ አተ፡ብለዉ፡ጠሩኝ
አባም መለሱልኝ በትህትና ቃል
ሴትማ፡እንዳልልሽ ሱሪዉን ለብሰሻል
ሁኔታወችሽ ሁሉ ወንዶችን መስለሻል
ታዲያ ምን ልበልሽ ስረዓት ጥሰሻል
እየመለሱልኝ በሁለት አይናቼዉ
እንባቼዉ ይወርዳል
አሁን ገና ገባኝ እያልኩ በልቤ
ያነበብኩት ቃል ትዝ አለኝ በሀሳቤ
ቃሉን ባስታዉስም ከአባ፡መስማት ፈለኩ
ቃሉን እንዲነግሩኝ፡በትትና፡ጠየኩ
አባ…ምከሩኝ፡ሱሪ ብቻ አይዴለም ብዙነዉ ሀጢአቴ
በይ፡ልጄ ካልሽኝ፡እማ በኦሪት ዘዳግም ምዕራፍ
ምዕራፍ 22 ቁጥር 5 ላይ
ሴትም የወንድን ልብስ ፈፅማ፡አትልበስ
ወንድ ልጅም ቢሆን፡የሴትን አይልበስ
ይህንን የሚያዴርግ በአምላኩ በእግዚአብሔር የተጠላ ነዉ
በቃሉ መመከር፡ቤተክርስቲያን መሄድሽ፡መልካም፡ነዉ
ግን፡ልጄ የእግዚአብሔር ቃል ምን ይላል መሰለሺ
ልንገርሽ አብቢዉ ከቤትሽ ስትዴርሺ
የያዕ/መልዕክት ምዕራፍ 1 ላይ፡ከቁጥር 23 ገለጥ አድርገሽ ብታይ
የሚያዴርግ ቢኖር ቅዱስ ቃሉን ሠምቶ
የተፈጥሮ ፊቱን በመስታወት አይቶ
በሚገባ ራሱን ተረድቶ ይሄዳል
እንዴት እንዴሆነ ወዲያዉኑ ይረሳል
አየሽ ልጄ ቃሉ፡እንድህ ይል፡ነበር
ምነኛ፡መልካም፡ነዉ ሠምተን ብተገብር
ብለዉ እያዘኑ ወዴ፡ሰማይ አዩ
በሀሣብ፡ሔዴዋል፡ምን፡አለ፡ሰማዩ
ከሄድኩበት ሀሳብ፡ልመለስ፡አሰብኩኝ
ካረፍኩበት ቦታ ተነስቼ ቆምኩኝ
ይህን ሁሉ ሼሼክም፡ለምን፡ተሼከሙ
ካሰቡበት ለመድረስ ይኖረወታል አቅሙ
ብየ፡ጠየኳቼዉ በሀዘነዉ ልቤ
ቀስ ብለዉ ተነሱ ቆሙካጠገቤ
ይችማ፡ምን፡አላት ምን አላት ብለሽ ነዉ
መድሃኒአለምን፡እስኪ ልጄ አስቢዉ
የኛን ሁሉ በደል፡ሀጢአት ተሼክሞ
ስለሁላችንም፡በመስቀል ላይም ቁሞ
ነፃ አወጣን ጌታ፡ዋጋ ከፈለልን
በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን
ያባ፡መልሳቼዉ፡እጅግ አስዴነገጠኝ
ዘወር አልኩኝና፡እባ ተናነቀኝ
እኔ የስጋየን ሼክም፡ሳወራቼዉ
ቀራኒዮ፡ሔዱ መች የኔ ታያቼዉ
በይ፡ልጄ ጠንክሪ፡በእምነትሽ
ክርስቶስን ይምሰል ዴግሞ፡አለባበስሽ
ተሠናበቱኝ በጣፋጭ ምክራቼዉ
ጉዞዉን ጄመሩ ጓዛቼዉን ይዘዉ
በዛሬው ጉዞየ፡ዴስተኛ ነበርኩ
ከጥፋት ጒዳት ከስተም ተማርኩ
እግዚአብሔር በአንድም በሌላም ይመክራል
ልጆቹ እንዳጠፋ ዘወትር ይመክራል
❗️ወስብሐት ለእግዚአብሔር❗️
👇👇
💥🔍ኪነ-ጥበብ🔎💥