kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የቅዱስ ገብርኤል ዋዜማ በዚህ መልኩ ሁሉ ተሰናድቷል።

በብጹዕ አቡነ ዮሴፍ አባታዊ መመርያ ሰጪነት ከሀገረ ስብከት ጀምሮ የደብራችን አበ ምኔት ፤ መላው ሰበካ ጉባኤ አባላት ፤ማኅበረ ካህናት  ፤ ሰብከተ ወንጌል ፤ የደብሩ ደጥታ ክፍል ፤ መላው የሰንበት ት/ቤት አባላት በአንድነት በሰፊ ቅድመ ዝግጅት ለበዓለ ንግሱ ሁሉም እንደ ድርሻው በትጋት ለመሳተፍ ተሰናድቷል።

የሲዳም ክልል መንግስትም ቀድም ብሎ ክብረ በዓሉን የማስተዋወቅ ስራ እየሰራ የነበረ ሲሆን። በጸጥታ ማስከበሩ ስራም ከሰንበት ት/ቤታችን አባላት ጋር አብሮ ለመስራት ለአባላቱ ሥልጠና ሰቷል።


የሰንበት ት/ቤታችን በዚህ የበዓለ ንግሥ አገልግሎት ከ1ዐ በላይ በሆኑ የሥራ ዘርፋት ከ500 በላይ አባላትን ገለጻ በመስጠትና አገልግሎት ዘርፍ በመከነፉፈል በተደራጀ መልኩ እንደ ወትሮው የተዘጋጀ ሲሆን በብጹነታቸውም ጸሎት ተደርጎለት የዋዜማ እንግዶችን ከደጃፍ የመቀበል ስራ እያከናወነ ይገኛል።

ለዚህ የበረከት አገልግሎት የሚፉጠን ሁሉንም የቅዱሳን መላዕክት ፈጣሪ ፈጣሬ ፍጡራን አምላካችን በረከቱን ያድልልን።

የሀ/ደ/ም/ቅ/ገብርኤል ገዳም መራሔ ድኅነት ሰ/ት/ቤት መገናኛ ብዙኃን ( መራሒ ሚዲያ )

የፌስቡክ ገፅ:
https://www.facebook.com /profile.php?id=100069444095761

የቴሌግራም አድራሻ:
/channel/SaintGebrielSundaySchool
            

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/pVCtr0Ysnc4?si=iIlbRD1-i_ezuunC

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ዘብር ገብርኤል የምቴዱ ካላቹ አሳውቁኝ የሚሄድ ሰው ስላለ ነው ማለቴ የጉዞ ማህበር ካለ አሳውቁኝ መነሻው ካዲስ አበባ ነው

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እስጢፋኖስ ፀጋንና ሀይልን ተሞልቶ በህዝብ መካከል ድንቅና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር
የሐዋሪያት ሥራ 6 : 8
የሰማእቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ እረድኤት በረከቱ ይደርብን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ ኤርትራ የሚገኘውን ታላቁ ገዳም ደብረ ድማህ ለመሰረቱት በነጭ እምነታቸው በተለይ ለነቀርሳ በሽታ ፈዋሽነት ለሚታወቁት ለታላቁ አባት ለአቡነ መርቆሬዎስ ለዕረፍት በዓል አደረሳችሁ አደረስን
የአቡነ መርቆሬዎስ ወላጆቻቸው ካህኑ ቶማስ ስምዖን እና ሰሎሜ እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ ቅዱሳን ስለነበሩ በየወሩም ዝክረ ቅዱስ ሰማዕት መርቆሬዎስ (ፒሉፓዴር) እያደረጉ ሲኖሩ በእለተ ቀኑ ተኣምር ስለተደረገላቸው የልጃቸውን ስም መርቆሬዎስ ብለው ሰየሙት፡፡ አቡነ መርቆሬዎስ ከተወለዱበት ጊዜ ጀምሮ ሲያሳዩት የነበው ተግባራት ሁሉ የትልቅ ሰው እንጂ የአንድ ሕፃን ጠባይ ስላልሆነ ወላጆቻቸው በአንክሮ ያስተውሉ ነበር፡፡

ከሥጋ ወንድሞችሁ ከአቡነ አብዲሳና ከአቡነ ማቴዎስ መክብብ ድንግል -ጋር በስላም በፍቅር ከኖሩ በኋላ ካህኑ አባታቸው እንዲማሩ ወደ አጎታቸው አቡነ ጳውሎስ ወስዷቸው ፡ አቡነ መርቆሬዎስም ፊደል በመቁጠር የጀመሩት መንፈሳዊ ትምህርት 22 ዓመት ሲሞላቸው የብሉይ ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን እንዲሁም ሁሉም መጽሐፍት ምሥጢር ተገለጠላቸው ።በኃላ በተጋድሎና በትምህርት ከኖሩት ከአቡነ ጳውሎስ ገዳም በእግዚአብሔር ፈቃድ ወደ አቡነ ዳንኤል ገዳም ሽማና ሔዱ። በዚኸም ገዳም ትምህርታቸውን እየቀጠሉ ብዙ አረጋዎያንን በመርዳት በገዳም አገልግሎት ከቆዩ በኋላ ከዳግማዊ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ እጅ የድቁና ማዕረግ ተቀበሉ። ከአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ደግሞ 40 ዓመታቸው በደብረ ሽማና እያለ ምንኵስናን እና አስኬማን መላእክትን ተቀበሉ።

ከዚኽም በኃላ አቡነ መርቆሬዎስ ለረጅም ጊዜ በምናኔ ኖረው ወንጌልን በመስበክና ክርስትናን በማስፋፋት ወደ ተለያዩ ሀገሮች እየተዘዋወሩ እያስተማሩ በርካታ ተኣምራትንም እያደረጉ ለ67 ዓመታት ያህል በታላቅ ተጋድሎ ኖሩ።

አቡነ መርቆሬዎስ የመንፈስ አባታቸው የሆኑት አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ወደ ኤርትራ ሀገር እንደሚሔዱ በመንፈስ ቅዱስ ዐውቀው በራቂት የምትባል ቦታ ላይ ኹለቱ ቅዱሳን ተገናኙ።
ኹለቱም ቅዱሳን አብረው ወንጌል እየሰበኩ ማይምነ ሲደርሱ ግን ሕዝቡን ከእግዚአብሔር ሕግ ርቆ በኀጢአት ወድቆ አገኙት በዚያ ያሉ ክፉዎች ሰዎችም በሰይጣን ምክር ተመርተው አባቶቻችን ተኝተውባት የነበረችውን ጎጆ በእሳት አቃጠሏት።

ቅዱሳኑ አቡነ መርቆሬዎስና አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ግን በዛ እሳት ሳይነኩ በእግዚአብሔር ተኣምር ዳኑ። ከዚኽም በኋላ እነዚህ ቅዱሳን አባቶች በአሁኑ ደብረ ደናግል ደብረ ድማኅ በሚባለው ቦታ ላይ ሱባኤ ገብተው አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ለሰባት ዓመት አቡነ መርቆሬዎስ ደግሞ ለአራት ዓመት ባእት አበጅተው በጽኑ ተጋድሎ ኖሩ። ከሰባት ዓመት ሱባኤ በኋላ ከእግዚአብሔር ባዘዛቸውና ራእይ ባዬት መሠረት አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ወደ አርማንያ እንዲሔድ ሲነገራቸው አቡነ መርቆሬዎስን ደግሞ አንዲት ወፍ እየሠራቻቸው ዛሬ ላይ በስማቸው ወደሚጠራው ታላቁ ገዳም ደብረ ድማኅ አደረሰቻቸው። አቡነ መርቆሬዎስም ቦታዋን እንዳዩአት ይህቺ ለዘለዓለም ማረፊያየ ናት› አሉ። የክብር ባለቤት መድኀኔዓለምም በአካል ተገልጦላቸው መጥቶ በአራቱ ማዕዘን ባረከላቸው።

በዚህ ቦታ ላይ ይኖሩ የነበሩት ሰዎችም አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ወደ አርማንያ እንደሚሔዱ ሲሰሙ የእናንተ ረድኤት እንዲሆንልን ቀድሳችሁ አቍርቡን ሲሏቸው ሁለቱ ቅዱሳን በጋራ ጥር 18 ቀን ቅዳሴ ቀድሰው ሕዝቡን አቍርበዋል።

አቡነ መርቆሬዎስም አባታቸውን አቡነ ኤዎስጣቴዎስን ተከትለው ኹለቱም እስከ

ሱዳን ድረስ ሔደው ወንጌልን በመስበክ ሰፊ ሐዋርያዊ አገልግሎት ሰጥተዋል። ከዚኽም በኋላ በግብፅ ተሻግረው አርማንያ ደርሰው ወደ ኢየሩሳሌም በመሔድ ቅዱሳት መካናትን ተሳልመዋል። ከዚያም አቡነ መርቆሬዎስ ወደ ገዳም ተመልሰው ሲመጡ ዉጡሕ በተባለ ቦታ ላይ በኣት አጽንተው ሱባኤ ያዙ። እርሳቸውም በዕለተ ዐርብ መጋቢት 12 ቀን የቅዱስ ሚካኤል በዓል ዕለት በኣታቸው ውስጥ እየጸለዩ ሳሉ ድንገት ቁመቱ 170 ክንድ ጎኑ ደግሞ 9 ክንድ ከስንዝር የሚሆን ሰይጣን ከነጭፍሮቹ በውስጡ ያደረበት ታላቅ ዘንዶ ይውጣቸው ዘንድ መጣ። ነገር ግን እግዚአብሔር ከእርሳቸው ጋር ስለነበር ጸሎታቸውን ሰምቶ ቅዱስ ሚካኤልን ላከላቸው። መልአኩም ድል የሚያደርጉበትን መስቀል ሰጣቸው። ጻድቁም ከመልአኩ በተቀበሉት ቅዱስ መስቀል በሥላሴ ስም ቢያማትቡበት ዘንዶው ተሰንጥቆ በውስጡ አድረውበት የነበሩት አጋንንት ከዘንዶው ወጥተው ሮጠው ሊያመልጡ ሲሉ አባታችን አወገዟቸው። ዘንዶውንም ወስደው ዱበና በሚባል በረሓ ውስጥ ጣሉት።
ጻድቁም ዘንዶውን ስለገደሉላቸው ለአካባቢው ሰዎችም ሆነ ለፍጥረታት ሰላምና ዕረፍት ሆነላቸው። ይኸንንም መሠረት በማድረግ በየአመቱ መጋቢት 12 ቀን መነኰሳት አባቶች ከገዳም ታቦት ይዘው ወደዚህ ቦታ በመሔድ ይቀድሳሉ በዓሉንም ያከብራሉ። በወቅቱ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል የሰጣቸው ረጅም መስቀልም እስከ አሁን ድረስ የተለያየ ተኣምራት እያደረገ በገዳሙ ይገኛል

አቡነ መርቆሬዎስ ከብዙ ተጋድሎ በኋላ ‹ሥጋየ (ዐፅሜ) የሚያርፍበትን ቦታ ግለጽልኝ›› ብለው ወደ እግዚአብሔር ቢጸልዩ በአሁኑ ጊዜ ቅዱስ ዐፅማቸ በክብር ያረፈበት ገዳም ደብረ ድማኅ እንደሆነ ገለጸላቸው። በ1340 ዓ.ም ስድስት መቶ መነኰሳትና ሦስት መቶ መነኰሳያይት ወደ አባታችን መጥተ መንኵሰዋል። አቡነ መርቆሬዎስም ሥርዐተ ምንኵስና ሠርተው ገዳም ገድመው ልጆቻቸውን በቅድስና ሲጠብቁ ኖሩ።

አቡነ መርቆሬዎስ ገዳማቸው ሳለ በአርማንያ ሀገር የአቡነ ኤዎስጣቴዎስ የዕረፍታቸው ነገር በራእይ ስለተገለጠላቸው ከ25 መነኰሳት ጋር ወደ አርማንያ ሔዱ። ነገር ግን ለመርከብ የሚከፍሉት ገንዘብ ስላልነበራቸው አስቀድመው ከአባታቸው ጋር በአጽፋቸው የተሻገሩትን ባሕር በደመና ተጭነው በማለፍ አርማንያ ሀገር ደርሰው አቡነ ኤዎስጣቴዎስን አገኟቸው።

ኹለቱም ቅዱሳን ሲነጋገሩ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ - ምሰሶ ተሰበረ›› አለ። አቡነ መርቆሬዎስም ምሰሶው ምንድነው?› ብለው ሲጠቋቸው የኢትዮጵያው ንጉሥ ዓምደ ጽዮን ሞተ› አሏቸው። አቡነ ኤዎስጣቴዎስም እንደተናገሩት በዚያን ጊዜ ንጉሡ በኢትዮጵያ ምድር እንደ ሞተ ተረጋገጠ። ከዚኸም በኋላ አቡነ መርቆሬዎስ አባታቸው አቡነ ኤዎስጣቴዎስን አሟሙተው ማለትም ገንዘው ብረው ወደ ገዳማቸው ሲመለሱ ዳግመኛም ታናሽ ወንድማቸው አቡነ አብሳዲም ዐርፈው ስለደረሱ እጅግ አዘኑ።

አቡነ መርቆሬዎስ ከአርማንያ ተመልሰው ሲመጡ ተኸላ የሚባል ቦታ ገዳም መሥርተው ዐሥር ዓመታት ኖረዋል። ቅዱስ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ወደ አርማንያ ሲሔዱ ‹‹እንደ እኔ ሁናቸው›› ብለው የእጅ መስቀላቸውን የሰጡት ለአቡነ አብሳዲ ነበር። ከአቡነ አብሳዲ ዕረፍት በኋላ የገዳሙን ኀላፊነት የተረከቡት አቡነ መርቆሬዎስ ሆኑ። በአቡነ መርቆሬዎስ ገዳም በደብረ ድማኅ አበምኔት ሆነው የተሾሙት አባቶች ሁሉ በዚህ መንበር ነው የሚሾሙት።

አቡነ መርቆሬዎስ ተጋድሏቸውን ፈጽመው ዕድሜያቸውም እየገፉ ሔዶ 130 ዓመት ሲደርሱ ለልጆቻቸው መሪ ይሆኑ ዘንድ በእርሳቸው ምትክ አባ ገብር ኄርን ሾሙላቸው። የክብር ባለቤት ጌታችንም ተገልጦላቸው ታላቅ ቃልኪዳን ከገባላቸው በኋላ ተኅሣሥ 16 ቀን 1411 ዓ.ም በ130 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሥጋ ሞት ተለዩ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ታህሳስ 14/2016 #ፃድቁ_አቡነ_አረጋዊ
#ፃድቁ_ገብረ_ክርስቶስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሳኑ ስም ለምናመሰግንበት ቅዱሣን አባቶቻችን #አቡነ_አረጋዊ እና #ፃድቁ_ገብረ_ክርስቶስ በቃል ኪዳናቸዉ እንዲያስቡን ለምንማፀንበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአላቸው እንኳን አደረሰን

👉በሃገራችን ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ እኒህ ጻድቅ ናቸው ፃድቁ የተወለዱት በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ ኣካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ንጉሥ #ይስሐቅና ቅድስት #አድና ይባላሉ የተለወለዱበት አካባቢም ሮም ነው

👉ስማቸው ብዙ ዓይነት ነው ወላጆቻቸው #ዘሚካኤል ሲሏቸው በበርሃ #ገብረ_አምላክ ተብለዋል በኢትዮዽያ ደግሞ #አረጋዊ ይባላሉ #አቡነ_አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ

👉በዚያም በገዳመ ዳውናስ ግብፅ የታላቁ #ቅዱስ_ዻኩሚስ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል ከመነኮሱ ከዓመታት በኋላም ወደ ሃገራቸው ሮም ተመልሰው በማስተማር 7 ያህል የቤተ መንግስት ሰዎችን ወደ ምናኔ ማርከዋል

👉የት ልሒድ ብለው ሲያስቡም #ቅዱስ_መልአክ በክንፉ ጭኖ ወስዶ ኢትዮዽያን አሳያቸው ተመልሰውም ለ8 ባልንጀሮቻቸው ሃገርስ ባሳየሁዋችሁ ሐዋርያ ሳያስተምራት በሕጉ በሥርዓቱ ጸንታ የምትኖር ብለው ከ8ቱ ጋር ወደ ኢትዮዽያ መጡ

👉በዚህ ጊዜም እናታቸው ቅድስት እድናና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ ወደ ሃገራችን የመጡ በ470ዎቹ አካባቢ ሲሆን አልዓሜዳ በክብር ተቀብሏቸዋል በቤተ ቀጢን #አክሱም ተቀምጠውም መጻሕፍትን እየተረጐሙ ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል

👉ለሥራ በተለያዩ ጊዜም #አቡነ_አረጋዊ በዓት ፍለጋ ብዙ ደክመዋል በመጨረሻ ግን ደብረ ዳሞን (ደብረ ሃሌ ሉያን) አይተው ወደዷት የሚወጡበት ቢያጡም ጅራቱ 60 ክንድ የሚያህል ዘንዶ ተሸክሞ ከላይ አድርሷቸዋል

👉እንደ ወጡም #ሃሌ_ሉያ_ለአብ፤#ሃሌ_ሉያ_ለወልድ #ሃሌ_ሉያ_ለመንፈስ_ቅዱስ ብለው ቢያመሰግኑ ከሰማይ ሕብስት ወርዶላቸው ተመግበዋል በዚህም ቦታዋ ደብረ #ሃሌ_ሉያ ተብላለች ፃድቁ ቦታውን ከገደሙ በኋላ ከተለያየ ቦታ መጥተው 6ሺ ያህል ሰዎች በእጃቸው መንኩሰዋል

👉ምናኔን በማስፋፋታቸውና ሥርዓቱን በማስተማራቸውም #የኢትዮዽያ_መነኮሳት_አባት ይባላሉ #አቡነ_አረጋዊ በሕይወታቸው ከተጋድሎ ባሻገር በወንጌል አገልግሎትና መጻሕፍትን በማዘጋጀትም ደክመዋል::

👉 #ቅዱስ_ያሬድና አፄ ገብረ መስቀልም ወዳጆቻቸው ነበሩ በተራራው ግርጌ ያለችውን #ኪዳነ_ምሕረትን ለሴቶች ሲገድሟት ቀዳሚዋ መነኮስ እናታቸው ንግስት እድና ሁናለች

👉ፃድቁ ንጹሕ ሕይወታቸውን ፈጽመው በተወለዱ በ99 ዓመታቸው በዚህ ቀን በገዳሙ በስተምሥራቅ አካባቢ ተሰውረው #ብሔረ_ሕያዋን ገብተዋል ጌታም 15 ትውልድን የሚያስምር የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል እረድኤት በረከታቸው ይደርብን

👉ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል #ፃድቅን_በፃድቅ_ስም የሚቀበል የፃድቁን ዋጋ ይወስዳል ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላቹሃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም ማቴ፣10:41

👉የቅዱሣን አባቶቻችን #አቡነ_አረጋዊ እና የመናኙ ፃድቅ #የቅዱስ_ገብረ_ክርስቶስ ምልጃ ፀሎታቸዉ ሀገራችንን ህዝባችንን ይጠብቅልን የተባረከ #ሰንበት_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

📣በድ/ዳ ሳ/ደ/ኃ/ቅ/ገብርኤል ካቴድራል ፍሬ ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ት/ት ሚድያ ክፍል የተዘጋጀ ልዩ የማህበራዊ ሚድያ አጠቃም እና አሰራር ዙሪያ በጥልቀት የተዘጋጀ ልዩ ስልጠና እሁድ ታህሳስ 14/2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት በካቴድራሉ አዳራሽ የተዘጋጀ ሲሆን ይህ የስልጠና መርሐ ግብር ሁሉንም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆችን ያማከለ ስለሆነ በእለቱ ማንኛውም መገኘት የሚችል ሰው ሁሉ በመርሀ ግብሩ ተጋባዥ ስለሆነ እርሶም ከወዳጅ ዘመዶት ጋር በመሆን የዚህ ልዩ መርሐ ግብር ተሳታፊ ትሆኑ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

— የሳ/ደ/ኃ/ቅ/ገብርኤል ካቴድራል ፍ/ዓ/ሃ/ሰ/ት/ቤ ሚድያ ክፍል —

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✨✨✨✨✨✨✨✨
መዝሙር ዘብርሃን
✨✨✨✨✨✨✨✨
በ(፮) ሃሌታ -
አቅዲሙ ነገረ በኦሪት ከመ ይመጽእ ወልድ በስብሐት ዘይዜንዋ ለጽዮን ቃለ ትፍሥሕት ወካዕበ ይቤ በአፈ ዳዊት ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር ብርሃን ዘመጽአ ውስተ ዓለም ዘያበርህ ላዕለ ጻድቃን መርዓዊሃ ለቤተ ክርስቲያን ይርዳእ ዘተኀጒለ ያስተጋብእ ዝርዋነ መጽአ ኀቤነ።

🇪🇹🌟🌟🌟🌟🌟🌟🇪🇹
🌟 @menkir_tube🌟
🌟 @menkir_tube🌟
🌟 @menkir_tube🌟
🇪🇹🌟🌟🌟🌟🌟🌟🇪🇹

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሐና ብጽዕት ተፈስሒ እንበለ ንትጋ::
እስመ ረከብኪ ሞገሰ ወአድማዕኪ ጸጋ::
እምሔውተ አምላክ ትኩኒ በሥጋ::" (አርኬ)

=>አምላከ ብጽዕት ሐና በምልጃዋ ከዘለዓለም እሳት ያድነን:: ጸጋ በረከቷንም ይክፈለን።

+*" አቡነ ዘርዓ ቡሩክ "*+

=>ሃገራችን ኢትዮዽያ:-
*ብሉይ ከሐዲስ ያልጐደለባት
*በክርስቶስና በድንግል እናቱ ኪደተ እግር የተቀደሰች
*የቅዱሳን መጠጊያ እና
*ብዙ ቅዱሳንን ከእቅፏ ያፈራች ስለ ሆነች የተባረከች ሃገር ትባላለች::

+ሁሉም የሃገራችን ክፍሎች ቅዱሳንን አፍርተዋል:: በምሥራቅም: በምዕራብም: በሰሜንም: በደቡብም ያሉ አካባቢዎች ሁሉ የቅዱሳን ቤቶች ናቸው:: ቅዱሳንን በብዛት ካፈሩ አካባቢዎች አንዱ ደግሞ ምድረ ጐጃም ነው::

+በጐጃም አካባቢ ከተነሱ ቅዱሳን ደግሞ አንዱና ስመ ጥሩ ጻድቅ አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ናቸው:: አቡነ ዘርዓ ቡሩክ በብዙ ጐዳና የተለዩ አባት ናቸው:: ለመጥቀስ ያህል እንኩዋ:-

1.በታሪክ ዓለምን ከበው የያዙ 2ቱ ግሩማን አራዊት (ብሔሞትና ሌዋታንን) ጥርስ ቆጥረው: ብዙ ምሥጢራትንም ተመልክተው ተመልሰዋል:: (በነገራችሁ ላይ ይህ ጉዳይ ዛሬም ድረስ ሳይንሱ በብዙ ድካም ያልደረሰበት ነው)

2.ጻድቁ በልደታቸው ጊዜ ዓይነ ስውራንን አብርተዋል:: ለራሳቸው ግን ይህን የግፍ ዓለም ላለማየት ጸልየው ዓይናቸው እንዲጠፋ አድርገዋል::

3.መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል ቅዱስ ኢያሱ በገባኦን ፀሐይን አቁሟል:: ዘርዓ ቡሩክ ግን በጥበበ እግዚአብሔር ፀሐይን ለ5 ዓመት አቁመዋል::

4.ጻድቁ ከንጽሕናቸው ብዛት 12 ክንፍ (መንፈሳዊ ክንፍ) ተሰጥቷቸው ነበር:: ከዚህ በተረፈም በጾም: በጸሎት: በትርምትና በስብከተ ወንጌል ፍጹም ጽሙድ ነበሩ::

+ጻድቁ የተወለዱት በ16ኛው መቶ ክ/ዘ እዚያው ጐጃም ውስጥ ሲሆን አባታቸው ደመ ክርስቶስ: እናታቸው ደግሞ ማርያም ሞገሳ ይባላሉ:: ወላጆች በልጅ እጦት ተማለው ይህን የተቀደሰ ፍሬ አገኙ:: "ጸጋ ኢየሱስ" ብለውታል:: ከኢየሱስ ክርስቶስ ተሰጥቷቸዋልና::

+ቀጥሎ የወለዱትንም "ተስፋ ኢየሱስ" ብለውታል:: ይህም የጻድቁ ታናሽ ወንድም ነው:: በሒደት ግን የጸጋ ኢየሱስ ስም በፈቃደ እግዚአብሔር ወደ ዘርዓ ቡሩክነት ተቀይሯል:: ጻድቁን ስመ ጥር ካደረጉዋቸው ሥራዎቻቸው መካከል በአፄ ሱስንዮስ ዘመን የሠሩት ቅድሚያውን ይወስዳል::

+ነገሩ እንዲህ ነው:: በ1598 ዓ/ም በኢትዮዽያ ላይ የነገሡት አፄ ሱስንዮስ ዼጥሮስ (ፔድሮ) ፓኤዝ ከሚባል ፈረንጅ መ+ና+ፍ+ቅ ጋር በፈጠሩት ወዳጅነት ሃይማኖታቸውን ለወጡ:: ካቶሊክ (ሮማዊ)ም ሆኑ::

+በሁዋላም አልፎንሱ ሜንዴዝ የሚሉት እሾህ መጥቶ ሁሉም የኢትዮዽያ ሕዝብ መ+ና+ፍ+ቅ እንዲሆን ከንጉሡ ጋር መከረ:: ለጊዜው በቤተ መንግስቱ አካባቢ የነበሩ መሣፍንት ተቀላቀሉ:: እየቆየ ግን ዜናው በመላ ሃገሪቱ ተሰማ::

+በተለይ በ1611 በተዋሕዶ አማኞችና በመ+ና+ፍ+ቁ ንጉሥ መካከል ነገሩ ተካሮ ዻዻሱ አቡነ ስምዖን ጠዳ ላይ መገደላቸው ተሰማ:: በዚህ ጊዜ ገበሬው ከእርሻው: ሴቷ ከማዕድ ቤት: ካህኑ ከመቅደሱ: ነጋዴው ከገበያው እየወጡ ስለ ቀናችው ሃይማኖት ደማቸውን አፈሰሱ::

+በበዓት የተወሰኑ በሺህ የሚቆጠሩ ቅዱሳንም ወጥተው ተሰየፉ:: በዚህ ጊዜም የግሺው አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ዳዊታቸውን አንግበው ለሰማዕትነት ሔዱ:: ዓባይ ወንዝ ላይ ሲደርሱ ዳዊታቸውን ወደ ወንዙ ውስጥ ጣሉት::

+ተሻግረውም ከንጉሡ አደባባይ ደንቀዝ ደረሱ:: በጊዜውም ልክ እንደነ ፍቅርተ ክርስቶስና ወለተ ዼጥሮስ እርሳቸውም መከራ ደረሰባቸው:: ንጉሡም ሳይገደሉ እንዲታሠሩ አደረገ:: በጨለማ እስር ቤትም 5 ዓመታትን ሲያሳልፉ ትኩስ ምግብን ያመጡላቸው ነበር::

+እርሳቸው ግን ምግባቸው ሰማያዊ ነበርና አልነኩትም:: ከ5 ዓመት በሁዋላም ያ ሁሉ ምግብ በተአምራት በትኩስነቱ እየጨሰ ተገኝቷል:: ዘርዓ ቡሩክም ከእሥር ተፈትተዋል::

+እግዚአብሔርም በከሐዲው ንጉሥ ላይ ፈርዶ ፋሲል ነግሷል:: ሃይማኖት ተመልሷል:: ጻድቁም በዓባይ ወንዝ ላይ የጣሉት ዳዊታቸውን ሳይርስ አግኝተውታል::

+ጐጃም ሲደርሱም ሰይጣን እርሳቸውን መስሎ ሲያስት ስላገኙት ወደ ጥልቁ አስጥመውታል:: በተረፈ ዘመናቸው አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ብዙ ተጋድለው ጥር 13 ቀን ዐርፈዋል::
<< ድንቅ ሠሪ አባት ናቸውና ዛሬም በግሺ ብዙ ተአምራት ይደረጋሉ !! >>

+"+ አባ መቃርስ ገዳማዊ +"+

=>"መቃርስ" የሚለው ቃል በዮናኒ ልሳን "ብጹዕ" እንደ ማለት ሲሆን የመነኮሳት አለቃ ቅዱስ መቃርስን ጨምሮ በርካታ ቅዱሳን በስሙ ተጠርተውበታል:: በነገረ ቅዱሳን ታዋቂ ከሆኑት አንዱና ተጠቃሹ ዛሬ የምናከብረው አባት ሲሆን ብዙ ጊዜ "ዘይሴሰይ ቆቅሃ - ቆቅን የሚበላው" እየተባለ ይጠራል::

+የዚህንም ምክንያቱን እንመለከታለን:: ቅዱስ መቃርስ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብጽ የነበረ የዘመነ ጻድቃን ፍሬ ነው:: ከእሱ በፊት ታላቁ መቃርስ: መቃርስ ቀሲስና መቃርስ ዘቃው የተባሉ አባቶች ስለ ነበሩ እርሱን 4ኛው መቃርስ እያሉ መጥራት የተለመደ ነው::

+በወጣትነቱ ከዓለም ወጥቶ ገዳም ገባ:: ቀጥሎም መነኮሰ:: ግን ግን ወሬን: ሐሜትንና ትዕቢትን ፈጽሞ ይጠላ ነበርና: ከገዳሙ ወጥቶ ሰው ወደማይኖርበት በርሃ ሔደ::

+ግን በአካባቢው የሚበላ ነገር: ከዛፍ ፍሬ: ከሣር ዘርም እንኩዋ ምንም ነገርን ማግኘት አልቻለም:: ጾሞ በራበው ጊዜም "ፍጥረትን የምትመግብ ጌታ ሆይ! ራቴን አብላኝ?" ሲል ጸለየ::

+እግዚአብሔርም አንዲት ቆቅን አምጥቶለት በላ:: ከዚህ በሁዋላም ምግቡ ቆቅ ብቻ ሆነ:: ማታ ማታ 1 ቆቅ ይያዝለታል:: እርሱም አመስግኖ እየበላ ዘመናት አለፉ::

+እግዚአብሔር የዚህ ገዳማዊ ዜና እንዲገለጥ ስለ ፈለገ አንድ የቁስጥንጥንያ መነኮስ ከሃገሩ ተነስቶ ወደ በርሃ ወረደ:: መጠለያ በዓት ሲፈልግም አንድ አረጋዊ ባሕታዊ ቆቅ ሲያጠምድ ተመልክቶ ደነገጠ::

+"መነኮስ ሆኖ እንዴት ሥጋ ይበላል" ሲልም ተናደደ:: ነገሩን ለሊቀ ዻዻሳቱ ይነግር ዘንድም በመጣበት መንገድ እየቸኮለ ተመለሰ:: የሃገሩን ፓትርያርክም "አባታችን አንድ ባሕታዊ እምነታችን ሊያሰድብ እንዲህ አደረገኮ" ቢለው ነገሩ እርግጥ ይሆን ዘንድ ፓትርያርኩ አንድ ሰው ጨምሮ 2ቱን ላካቸው::

+በዚያች ቀንም ቅዱስ መቃርስ ለመጀመሪያ ጊዜ 3 ቆቆች ገቡለት:: "ጌታየ! 2ቱን ምን ላድርጋቸው?" ሲል መነኮሳቱ ወደ እርሱ ደረሱ:: ደስ ብሎት ፈጣሪን እያመሰገነ ሠርቶ አቀረበላቸው::

+እነርሱ ግን ቅዱሱን ናቁት:: "አንበላም" አሉት:: አባ መቃርስም የተጠበሱት ቆቆች እፍ እፍ እያለ ነፍስ ዘራባቸውና እንዲበሩ አደረገ:: በዚህ የደነገጡት መነኮሳቱ ሰግደውለት እየተሯሯጡ ወደ ሃገራቸው ተመለሱ::

+ባሙበት አፋቸው "ታላቅ ሰው ተገኝቷል: በረከቱ አይለፋችሁ" ሲሉ ሰበኩ:: ይህ ሲሰማም ፓትርያርኩ ከነ ሕዝቡ: ንጉሡ ከነ ሠራዊቱ ሊባረኩ ወደ በርሃው ወረዱ:: ግን ቅዱስ መልአክ ተሸክሞት ወደ ብሔረ ሕያዋን ሲያርግ ደረሱ::

+እየጮሁ "አባ በረከትህን: የድህነት ቃልህን?" አሉት:: እርሱም "ይጹም አፉክሙ እምነገረ ውዴት ወሐሜት - አፋችሁ ከሐሜት: ከነገር ሥራት ይጹም:: ካህናት ትምሕርት: መነኮሳት ትሕርምትን አታብዙ:: ልቡናችሁ አይታበይ:: ሰላም ለእናንተ ይሁን!" ብሏቸው ከዐይናቸው ተሰወረ:: ወደ ብሔረ ሕያዋንም ገባ::

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🌼▰▱🌼▰▱🌼▰▱🌼▰▱🌼

          
             ግእዝን በርቀት ፲፫ኛ ዙር


ለጀማሪ ተማሪዎች ታስቦ የተዘጋጀ፣
መሠረታዊ የግእዝ ቋንቋ ትምህርትን በቴሌግራም፣ ለኹለት ወራት፣ በነጻ መማር ለምትፈልጉ ኹሉ በሚከተለው ሊንክ አማካኝነት የትምህርት መስጫውን ቡድን ትቀላቀሉ ዘንድ በታላቅ አክብሮት ተጋብዛችዃል።


        @geezdistance13


           ግእዝን በርቀት ፲፫ኛ ዙር


🌼▰▱🌼▰▱🌼▰▱🌼▰▱🌼

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/gebrewoldye21

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞✞✞በስመ አብ ወወል ወመንፈስ ቅደለስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ✞✞✞

✝✞✝ ታኅሣሥ 12 ✝✞✝

✝✞✝ እንኩዋን ለታላቁ ጻድቅ "አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ" እና ለሰማዕታት "አንቂጦስ ወፎጢኖስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✞✝

+*" አባ ሳሙኤል ዘዋሊ "*+

=>ሃገራችን እልፍ አእላፍ ቅዱሳንን አፍርታለች:: እንኩዋን በተባረከው በቀደመው ዘመን ይቅርና ዛሬም ከሃገር ተርፈው ለዓለም የሚጸልዩ : በየበርሃውና በየፈርኩታው የወደቁ ብዙ አባቶችና እናቶች አሉን::

+በኢትዮዽያ ውስጥ ከተነሱ ቅዱሳን "ሳሙኤሎች" ልዩ ቦታ አላቸው:: በ20 ዓመታት ልዩነት ብቻ 6ቱ ሳሙኤሎች ተነስተው ከቅድስና ሕይወት እስከ ስብከተ ወንጌል : ከገዳማዊ ሕይወት እስከ ምናኔ በጐውን ጐዳና አሳይተዋል::

+እነዚህም:-
1.ሳሙኤል ዘዋልድባ
2.ሳሙኤል ዘጣሬጣ
3.ሳሙኤል ዘቆየጻ
4.ሳሙኤል ዘግሺ
5.ሳሙኤል ዘሃሌ ሉያ እና
6.ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ ናቸው::

+በተመሳሳይም በግብጽ የደብረ ቀልሞኑን ኮከብ ጨምሮ (መልአኩን ቀውስጦስን ከጌታ ያማለዱት) ብዙ ሳሙኤሎች ተነስተዋል:: የድሮ እናቶቻችን በእውነት ስም መሰየሙን ይችሉበታል:: "ሳሙኤል" ማለት "ሰምዓኒ እግዚአብሔር ስዕለትየ - እግዚአብሔር ልመናየን ሰማኝ" ማለት ነውና::

+ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ታላቁ ኢትዮዽያዊ ጻድቅ አቡነ ሳሙኤል ዘዋሊ የተወለዱት በ13ኛው መቶ ክ/ዘመን (በ1295) በምድረ አክሱም ነው:: ወላጆቻቸውም እስጢፋኖስና ዓመተ ማርያም ይባላሉ::

+የዘር ሐረጋቸው ከካህናት ወገን ነውና ጻድቁ ገና በልጅነት ምሥጢራተ ሃይማኖትን ጠጥተዋል:: ለዚህም ይመስላል ገና ሕጻን ሳሉ ምናኔን የተመኙት::

+ከልጅነታቸው ጀምረው ወላጆቻቸውን ያገለገሉት ሳሙኤል ትምሕርታቸውን ሲፈጽሙ የተጉዋዙት ወደ ደብረ በንኮል ነበር::
በጊዜውም የጻድቁ ወላጆች ዐርፈው እንደ ነበር ይነገራል:: ደብረ በንኮል ማለት የታላቁ ኮከብና አበ መነኮሳት አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ገዳም ነው::

+መድኃኒነ እግዚእ ለሃገር ብርሃን የሆኑ ቅዱሳንን ያፈሩ ዘንድ ሲተጉ እግዚአብሔር 7ቱን ከዋክብት ሰጣቸው:: ክእነዚህ መካከልም ቀዳሚው አቡነ ሳሙኤል ናቸው:: ቀሪዎቹ ደግሞ እነ አቡነ ያሳይ ዘመንዳባ : ሳሙኤል ዘጣሬጣ : ሳሙኤል ዘቆየጻና ያፍቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤን የመሰሉ ናቸው::

+አቡነ ሳሙኤል ከ6ቱ ባልንጀሮቻቸው ጋር ሆነው በደብረ በንኮል ተጋድሎን አሐዱ አሉ:: እንጨት ይሰብራሉ:: ውሃ ይቀዳሉ:: እህል ይፈጫሉ:: በፍጹም ልባቸውም ይታዘዛሉ:: ጐን ለጐን ደግሞ ከቅዱሱ አበ ምኔት መድኃኒነ እግዚእ ጽንዓትን : ትሕትናን : ትሕርምትን ይማሩ : ሥርዓተ ገዳምንም ያጠኑ ነበር::

+ከአገልግሎታቸው ማማር የተነሳ ሁሉን ደስ ማሰኘት ቻሉ:: በዚህ ጊዜም ጻድቁ አበ ምኔት አቡነ ሳሙኤል ዘዋሊንና 6ቱን አበው ጠርተው ለምንኩስና አቀረቧቸው:: "ይገባቹሃል!" ሲሉም ከአሞክሮ ወደ ምንኩስና አሸጋገሯቸው::

+በዚያች ቀን 7ቱ ሲመነኩሱ ከሰማይ ብርሃን ወርዶ በመታየቱ ቅዱሳኑ "ከዋክብት ብሩሃን" ተባሉ:: ለተወሰነ ጊዜም በዚያው በገዳሙ አገለገሉ:: የአቡነ ሳሙኤል ዘመዶች ግን እየመጡ ጻድቁን ስላስቸገሩ 7ቱም ቅዱሳን ተመካክረው : ከአባታቸው መድኃኒነ እግዚእ ተባርከው ከደብረ በንኮል ወጡ::

+ሁሉም መንፈስ ቅዱስ ወደ መራቸው ሲሔዱ 3ቱ (ማለትም ሳሙኤል ዘዋሊ : ያሳይ ዘመንዳባና ያፍቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤ) ወደ ጣና ሔዱ:: በዚያም ለጥቂት ጊዜ አብረው ከቆዩ በሁዋላ ለአገልግሎት ተለያዩ:: አቡነ ያሳይ "መንዳባን" : አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ "ጉጉቤን" ይዘው እዛው ጣና አካባቢ ሲቀሩ አባ ሳሙኤል ወደ ዋልድባ ሔዱ::

+ዋልድባ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በጌታ ፈቃድ የተመሠረተ ሲሆን 860ው መሥራች ቅዱሳን በመሠወራቸው እንደ ጠፍ ይቆጠር ነበርና አቡነ ሳሙኤል እንደ ገና አቀኑት::

+ጻድቁ በዋልድባ የመጨረሻውን ትሕርምት ከመያዛቸው በፊት በጊዜው ከፍተኛ የሆነ የወንጌል አገልግሎት ሰጥተዋል:: ቀጥለውም ኑሯቸውን ከግሩማን አራዊት ጋር አድርገዋል:: በስዕለ አድኅኖው እንደምናየው ለዘመናት በአንበሳ ጀርባ ላይ ተጭነዋል::

+ጧት ማታም ብዙ ግሩማን አራዊትን እያስከተሉ ለአገልግሎት ደክመዋል:: ጻድቁ ከትሕርምት ብዛት እህል ትተው የሻገተ ጐመንና መልኩን የለወጠ ውሃን ለቁመተ ሥጋ ይጠቀሙ ነበር::

+አንድ ቀንም መድኃኒታችን ክርስቶስ ወደ እርሳቸው መጥቶ ባረካቸው:: አካላቸውንም በቅዱስ ምራቁ አትቦ ቀባቸው:: በዚህ ጊዜም ኃይለ መንፈስ ቅዱስን ተመሉ:: የክርስቶስን ሕማማት እያሰቡም እልፍ ጊዜ ይሰግዱ: ጀርባቸውን ይገርፉም ነበር::

+እግራቸውን በሰንሰለት አሥረው ይጋደሉም ነበር:: በዚህ ግብራቸው አጋንንትን አሳፍረው: ፈጣሪያቸውን ደስ አሰኙ:: ከቆይታ በሁዋላም ዋልድባ በመነኮሳት ተሞላ:: ደቀ መዛሙርት በዙ:: ቀዳሚው ግን አባ ዘሩፋኤል ጻድቅ ነው::

+አቡነ ሳሙኤል ከድንግል እመቤታችን ጋር ልዩ ፍቅር ነበራቸው:: ዘወትር ውዳሴዋንና ቅዳሴዋን በተመስጦ ያደርሱላት: ፈጽመውም ያመሰግኗት ነበር:: ይህንን ሲያደርጉ ከመሬት ክንድ ከፍ ብለው ይንሳፈፉ ነበር::

+ተከታዮቻቸው ሲርባቸውም ውሃውን በቅዳሴ ማርያም ነጭ ሕብስት ያደርጉት ነበር::

"ሶበ አተቦ ለማይ በቅዳሴኪ እንዘ ይጼሊ::
ረሰዮ ሕብስተ ሳሙኤል ጽጌ ሃይማኖት ዘሐቅለ ዋሊ::
ምሕረተ ወፍትሐ ለተአምርኪ እኅሊ::
ስረዪ ኃጢአትየ ወዕጸብየ አቅልሊ::
እስመ ኩሎ ገቢረ ማርያም ትክሊ::" እንዳለ ሊቁ:: (ማኅሌተ ጽጌ)

+እመ ብርሃንም ስለ ፍቅር ነጭ እንቁ ሰጠቻቸው:: ሰማያዊ ሕብስትን መገበቻቸው:: ንጹሕ ዕጣንንም አበረከተችላቸው:: ለ12 ዓመታትም ከሰማይ ካህናት ጋር አጠኑ:: ድንግል ማርያም "እንዳንተ ውዳሴየንና ቅዳሴየን በፍቅር የሚደግምልኝን አማልደዋለሁ" ስትላቸው:-

+ጌታ ደግሞ ገዳማቸውን ዋልድባን ቀድሷታል:: ቀድሞም በስደቱ ባርኩዋት ነበር:: የጻድቁ ዜና ፈጽሞ ብዙ ነውና ለዛሬ በዚህ ይብቃን:: የዋልድባው ኮከብ አቡነ ሳሙኤል ያረፉት ታሕሳስ 12 ቀን በ1395 ሲሆን ዕድሜአቸውም 100 ዓመት ነበር::

<< ለጻድቁ ክብር ይገባል !! >>

+"+ ቅዱሳን አንቂጦስ ወፎጢኖስ +"+

=>እነዚህ ቅዱሳን በሥጋ ወንድማማቾች ሲሆኑ የዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች ናቸው:: ዜና ሕይወታቸውን ሳስበው ይገርመኛል:: በእሳት የወጣትነት ዘመናቸው በሃይማኖት ጸንተው: ፍቅረ ክርስቶስ እንደ እሳት በላያቸው ላይ ይነድ ነበር::

+በእውነት ክርስቶስን በከንፈር ያይደለ በፍጹም ልቡና መውደድ እንዴት ያለ መታደል ነው! ክርስቶስን የወደደ የድንግል እናቱና የቅዱሳን ወዳጆቹ ፍቅር ይበዛለታል እንጂ አይቀንስበትም::

+ቅዱሳኑ አንቂጦስና ፎጢኖስ ወጣትነት: የዓለም ኑሮ ሳያታልላቸው ለሰማዕትነት ራሳቸውን አዘጋጁ:: እንኩዋን ሰውን አራዊትን የሚያስበረግግ የስቃይ ዓይነት ተሰልፎ ሳለ በፍጹም አልደነገጡም::

+መጀመሪያ አንቂጦስን አቀረቡት:: ገረፉት: ምንም አልሆነም:: በእሳት አቃጠሉት: ምንም አልነካውም:: ለአንበሳ ሰጡት: እነርሱ ግን ሰገዱለት:: ከዳር ሆኖ ይህንን ሁሉ ሲመለከት የነበረው ወንድሙ ፎጢኖስ ዘሎ ወደ መከራ አደባባይ ገባ::

+"ወንድሜ የክርስቶስ ነውና መቼም አታሸንፈውም" ሲል ጮኸ:: በዚህ ጊዜም በሥፍራው የነበሩ ብዙ አሕዛብ "የእነዚህ ወጣቶች አምላክ አምላካችን ነው" አሉ::

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/xTub3DXO-PM?si=DfYbg7NGOqfP17W9

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

💠"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠    (ማቴ ፫:፫)

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ፡፡ አሜን፡፡ ✞✞✞

=>+"+ እንኩዋን ለታላቁ "ጻድቅና ገዳማዊ አባ በኪሞስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+

+*" ታላቁ አባ በኪሞስ "*+

=>በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ "ታላቁ : ዓቢይ : (THE GREAT)" የሚል ስም የሚሰጣቸው አባቶች የተለዩ ናቸው:: አንድም እጅግ ብዙ ትሩፋቶችን የሠሩ ናቸው:: በሌላ በኩል ደግሞ በተመሳሳይ ስም ከሚጠሩ ሌሎች ቅዱሳን እንለይበታለን::

+ገዳማዊ ሕይወት ጥንቱ ብሉይ ኪዳን ነው:: በቀዳሚነትም በደብር ቅዱስ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ደቂቀ ሴት እንደ ጀመሩት ይታመናል:: ሕይወቱ በጐላ: በተረዳ መንገድ የታየው ግን በታላቁ ጻድቅ ሄኖክ: ከዚያም በቅዱሱ ካህን መልከ ጼዴቅ አማካኝነት ነው::

+ቀጥሎም እነ ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ : እነ ኤልሳዕ ደቀ መዝሙሩ ኑረውበታል:: በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሙሉ ሕይወቱን በገዳም (በበርሃ) ያሳለፈው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድሚያውን ይይዛል::

+ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ በገዳመ ቆረንቶስ ለ40 ቀናት በትሕርምት ኑሮ ገዳማዊ ሕይወትን ቀድሷል:: አስተምሯል:: በዘመነ ስብከቱም ያድርባት የነበረችው የደብረ ዘይቷ በዓቱ (ኤሌዎን ዋሻ) በራሷ ለዚህ ሕይወት ትልቅ ማሳያ ናት::

+ከጌታ ዕርገት በሁዋላም ክርስቲያኖቹ የዓለም ሁካታ ሲሰለቻቸው: አንድም በንጹሕና በተሸከፈ ልቡና ለፈጣሪያቸው መገዛትን ሲሹ ከከተማ ወጣ እያሉ ይኖሩ እንደ ነበር የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ:: አኗኗራቸውም በቡድንም: በነጠላም ሊሆን ይችላል::

+ዋናው ነገር ግን በጾምና በጸሎት መትጋታቸው ነው:: ይሕም ሲያያዝ እስከ 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ደረሰ:: በዚህ ዘመን ግን አባ ዻውሊ የሚባል አንድ ንጹሕ ክርስቲያን ይሕንን ሕይወት ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ አደረገው:: ለ80 (90) ዓመታት ሰው ሳያይ ተጋድሎ "የባሕታውያን አባት" ተባለ:: ደንብ ያለው ተባሕትዎም ጀመረ::

+ይህ ከሆነ ከ20 ዓመታት በሁዋላ ደግሞ አባ እንጦንስ የሚባሉ ደግ ክርስቲያን ይህንን ገዳማዊ ሕይወት በሌላ መንገድ አጣፈጡት:: በቅዱስ ሚካኤል አመንኩዋሽነት ገዳማዊ ሕይወት በምንኩስና ተቃኘ:: ስለዚህም አባ እንጦንስ "የመነኮሳት አባት" ተባሉ::

+እርሳቸውም ሕይወቱን ለማስፋፋት ከተለያዩ አሕጉር ደቀ መዛሙርትን እየተቀበሉ አመንኩሰዋል:: ቅዱሳን የአባ እንጦንስ ልጆችም ወደየ ሃገራቸው ተመልሰው: ሕይወቱን በተግባር አሳይተው ገዳማዊነትን አስፋፍተዋል::

=>አባ በኪሞስ ስም አጠራሩ እጅግ የከበረ: ሽምግልናው ያማረ ባሕታዊ: መነኮስና ሐዋርያዊ አባት ነው:: የነበረው በዘመነ ጻድቃን (በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን) ሲሆን ትውልዱ እንደ ብዙዎቹ የወቅቱ ቅዱሳን በላይኛው (በደቡብ) ግብጽ ነው::

+አባ በኪሞስ ከክርስቲያን ወላጆቹ ተወልዶ: በልጅነቱ ክርስትናን አጥንቶ በእረኝነት ተሰማራ:: በጐቹን ሲጠብቅም የእግዚአብሔር ጥሪ ወደ እርሱ መጣ:: ያኔም እድሜው ገና 12 ዓመት ነበር::

+አጠራሩም እንዲህ ነው:: በእረኝነት ሳለ መልአከ እግዚአብሔር ሰው መስሎ መጥቶ ተገናኘው:: ቁጭ ብሎም ስለ መናንያን ክብር ሲያጫውተው ከዋለ በሁዋላ "ለምን እኔና አንተ ለዚህ ክብር እንድንበቃ አንመንንም?" ሲል ጠየቀው::

+ሕጻኑ በኪሞስም ደስ ብሎት "እሺ!" አለው:: ወዲያውም መንጋውን ለወላጆቹ መልሶ ከመልአኩ ጋር ወደ ገዳም ሔዱ:: ቅዱሱ መልአክም በመንገድ ሳሉ ብዙ ምሥጢራትን ነገረው:: አጸናው:: ረድኤተ እግዚአብሔርንም አሳደረበት::

+ልክ ወደ አንድ ገዳም ሲደርሱ ግን ተሰወረበት:: ቅዱስ በኪሞስም ወደ ገዳሙ ገብቶ ይምናኔ ሕይወትን ጀመረ:: በዚያም እንደ ልጅነቱ አበውን እያገለገለ: ሥርዓተ ገዳምን: ትሕርምትን: አርምሞንና ተጋድሎን በደንብ አጠና::

+በዚያው ገዳም ሳለም ምንኩስናን ተቀበለ:: ለ24 ዓመታት አገልግሎ 36 ዓመት በሞላው ጊዜም ተባሕትዎን ተመኘ:: ከ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ፡፡ አሜን፡፡ ✞✞✞

=>+"+ እንኩዋን ለታላቁ "ጻድቅና ገዳማዊ አባ በኪሞስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+

+*" ታላቁ አባ በኪሞስ "*+

=>በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ "ታላቁ : ዓቢይ : (THE GREAT)" የሚል ስም የሚሰጣቸው አባቶች የተለዩ ናቸው:: አንድም እጅግ ብዙ ትሩፋቶችን የሠሩ ናቸው:: በሌላ በኩል ደግሞ በተመሳሳይ ስም ከሚጠሩ ሌሎች ቅዱሳን እንለይበታለን::

+ገዳማዊ ሕይወት ጥንቱ ብሉይ ኪዳን ነው:: በቀዳሚነትም በደብር ቅዱስ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ደቂቀ ሴት እንደ ጀመሩት ይታመናል:: ሕይወቱ በጐላ: በተረዳ መንገድ የታየው ግን በታላቁ ጻድቅ ሄኖክ: ከዚያም በቅዱሱ ካህን መልከ ጼዴቅ አማካኝነት ነው::

+ቀጥሎም እነ ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ : እነ ኤልሳዕ ደቀ መዝሙሩ ኑረውበታል:: በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሙሉ ሕይወቱን በገዳም (በበርሃ) ያሳለፈው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድሚያውን ይይዛል::

+ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ በገዳመ ቆረንቶስ ለ40 ቀናት በትሕርምት ኑሮ ገዳማዊ ሕይወትን ቀድሷል:: አስተምሯል:: በዘመነ ስብከቱም ያድርባት የነበረችው የደብረ ዘይቷ በዓቱ (ኤሌዎን ዋሻ) በራሷ ለዚህ ሕይወት ትልቅ ማሳያ ናት::

+ከጌታ ዕርገት በሁዋላም ክርስቲያኖቹ የዓለም ሁካታ ሲሰለቻቸው: አንድም በንጹሕና በተሸከፈ ልቡና ለፈጣሪያቸው መገዛትን ሲሹ ከከተማ ወጣ እያሉ ይኖሩ እንደ ነበር የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ:: አኗኗራቸውም በቡድንም: በነጠላም ሊሆን ይችላል::

+ዋናው ነገር ግን በጾምና በጸሎት መትጋታቸው ነው:: ይሕም ሲያያዝ እስከ 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ደረሰ:: በዚህ ዘመን ግን አባ ዻውሊ የሚባል አንድ ንጹሕ ክርስቲያን ይሕንን ሕይወት ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ አደረገው:: ለ80 (90) ዓመታት ሰው ሳያይ ተጋድሎ "የባሕታውያን አባት" ተባለ:: ደንብ ያለው ተባሕትዎም ጀመረ::

+ይህ ከሆነ ከ20 ዓመታት በሁዋላ ደግሞ አባ እንጦንስ የሚባሉ ደግ ክርስቲያን ይህንን ገዳማዊ ሕይወት በሌላ መንገድ አጣፈጡት:: በቅዱስ ሚካኤል አመንኩዋሽነት ገዳማዊ ሕይወት በምንኩስና ተቃኘ:: ስለዚህም አባ እንጦንስ "የመነኮሳት አባት" ተባሉ::

+እርሳቸውም ሕይወቱን ለማስፋፋት ከተለያዩ አሕጉር ደቀ መዛሙርትን እየተቀበሉ አመንኩሰዋል:: ቅዱሳን የአባ እንጦንስ ልጆችም ወደየ ሃገራቸው ተመልሰው: ሕይወቱን በተግባር አሳይተው ገዳማዊነትን አስፋፍተዋል::

=>አባ በኪሞስ ስም አጠራሩ እጅግ የከበረ: ሽምግልናው ያማረ ባሕታዊ: መነኮስና ሐዋርያዊ አባት ነው:: የነበረው በዘመነ ጻድቃን (በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን) ሲሆን ትውልዱ እንደ ብዙዎቹ የወቅቱ ቅዱሳን በላይኛው (በደቡብ) ግብጽ ነው::

+አባ በኪሞስ ከክርስቲያን ወላጆቹ ተወልዶ: በልጅነቱ ክርስትናን አጥንቶ በእረኝነት ተሰማራ:: በጐቹን ሲጠብቅም የእግዚአብሔር ጥሪ ወደ እርሱ መጣ:: ያኔም እድሜው ገና 12 ዓመት ነበር::

+አጠራሩም እንዲህ ነው:: በእረኝነት ሳለ መልአከ እግዚአብሔር ሰው መስሎ መጥቶ ተገናኘው:: ቁጭ ብሎም ስለ መናንያን ክብር ሲያጫውተው ከዋለ በሁዋላ "ለምን እኔና አንተ ለዚህ ክብር እንድንበቃ አንመንንም?" ሲል ጠየቀው::

+ሕጻኑ በኪሞስም ደስ ብሎት "እሺ!" አለው:: ወዲያውም መንጋውን ለወላጆቹ መልሶ ከመልአኩ ጋር ወደ ገዳም ሔዱ:: ቅዱሱ መልአክም በመንገድ ሳሉ ብዙ ምሥጢራትን ነገረው:: አጸናው:: ረድኤተ እግዚአብሔርንም አሳደረበት::

+ልክ ወደ አንድ ገዳም ሲደርሱ ግን ተሰወረበት:: ቅዱስ በኪሞስም ወደ ገዳሙ ገብቶ ይምናኔ ሕይወትን ጀመረ:: በዚያም እንደ ልጅነቱ አበውን እያገለገለ: ሥርዓተ ገዳምን: ትሕርምትን: አርምሞንና ተጋድሎን በደንብ አጠና::

+በዚያው ገዳም ሳለም ምንኩስናን ተቀበለ:: ለ24 ዓመታት አገልግሎ 36 ዓመት በሞላው ጊዜም ተባሕትዎን ተመኘ:: ከአባቶች ዘንድ ተባርኮም ጭው ወዳለው በርሐ እየዘመረ ተጉዋዘ::

+አንዲት ቦታ ላይም የቀኑን ሐሩር: የሌሊቱን ቁር ሳይሰቀቅ ለ3 ዓመታት ጸለየ:: እድሜው 39 ዓመት ሲሆን እንደ ገና ጭራሽ ፍጥረት ወደ ማይደርስበት በርሃ ተጉዞ ደረሰ::

+የደረሰበት አካባቢ ፀሐይ እንደ እሳት የምታቃጥልበት: ምድር እንደ ብረት ምጣድ የጋለችበት ነው:: ቸር እግዚአብሔር ግን ለዚህ ታላቅ ሰው አንዲት የተምር ዛፍ አበቀለለት:: ትንሽ ምንጭንም አፈለቀለት::

+አባ በኪሞስም ዋናውን ተጋድሎ በዚህ ሥፍራ ጀመረ:: ጾምን : ጸሎትን : ስግደትን ያዘወትር ነበር:: ጾሙ በመጀመሪያ 3 ቀን: ቀጥሎ 7 ቀን: በመጨረሻ ግን በ40 ቀን አንዴ ብቻ ማዕድ የሚቀምስ ሆነ::

+ለዛውም ምግቡ አንዲት እፍኝ ይቆረጥማል:: አንዲት ጉንጭ ውሃን ይጐነጫል:: ከዚህ በላይ ለሥጋው ምክንያትና ምቾትን ሊሰጣት አልፈለገም:: በዚህም ምክንያት አካሉ ደርቆ ከሰውነት ተራ ወጣ:: ግን ብርቱና ደስተኛ: የማይደክምም ተዋጊ ነበር::

+የሚገርመው ደግሞ ጸሎቱ ነው:: ሌሎች ጸሎቶቹ ሳይቆጠሩ በመዓልት (በቀን) 2,400 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያትን በልዩ ተመስጦ ያደርሰው ነበር:: በሌሊትም በተመሳሳይ ቁጥር ይደግመዋል:: በድምሩ በየዕለቱ 4,800 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት ይል ነበር::

+ስግደቱንማ ማን ቆጥሮት! ታላቁ አባ በኪሞስ እንዲህ ባለ ገድል ለ24 ዓመታት ቆየ:: እድሜውም 63 ደረሰ:: አንድ ጊዜ ግን ሕማማተ ክርስቶስን እያሰበ ያለ ምግብ ለ80 ቀናት ቆየ:: ፈጽሞ በተራበ ጊዜም ቅዱስ መልአክ ከሰማይ ሕብስተ በረከቱን: ጽዋዐ አኮቴቱን ይዞለት ወረደ::

+ከሕብስቱ መግቦት: ከጽዋው አጠጥቶት ወደ ሰማይ ዐረገ:: ሲያርግ ግን ሕብስቱን ትቶለት ነበር:: "ዘወትርም ከዚህ ተመገብ" ብሎታል:: አባ በኪሞስም ከዚያች ቀን ጀምሮ እስከ ዕረፍቱ ድረስ የተመገበው ከዚያ ሕብስት ነው:: ግን አላለቀም ነበር::

+በታላቁ አባ በኪሞስ ዘመን እነ አቡነ ኪሮስና ታላቁ ሲኖዳን የመሰሉ አበው ነበሩ:: በተለይ የባሕታውያን ሁሉ አለቃ አባ ሲኖዳና አባ በኪሞስን መንፈስ ቅዱስ እንዲህ አስተዋውቁዋቸዋል::

+አንድ ቀን አባ ሲኖዳ የእንቁ ምሰሶ ከምድር እስከ ሰማይ ተዘርግቶ ያይና "ጌታየ! ምሥጢሩ ምንድን ነው?" ቢል "ይህ ምሰሶ አባ በኪሞስ ነውና ሒድ ተገናኘው" የሚል ቃልን ሰማ:: አባ ሲኖዳም በእግሩ ተጉዞ አባ በኪሞስን አገኘው::

+ሰላምታን ከተለዋወጡ በሁዋላ አባ በኪሞስ ታላቁ ሲኖዳን "እኔ ወጥ ልሥራ: አንተ ውሃ ቅዳ" አለው:: ቅዱስ ሲኖዳ ከበር ብቅ ብሎ ማሰሮውን በተአምራት ውሃ ሞልቶት ሲመለስ አባ በኪሞስ ደግሞ ያለ እሳት ወጡን አብስሎት ቆየው::

+2ቱም ተገርመው ፈገግታን ተለዋወጡ:: ማንነታቸውንም ተዋወቁ:: ለመናፈስ ወደ በርሃ ወጥተው ሳለም ደክሟቸው ቁጭ አሉ:: ከፊታቸው አንድ የሰው ራስ ቅል ነበርና በበትራቸው መታ : መታ አድርገው "አንተ! ተነስ አጫውተን" አሉት::

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/NVw4pGxMnEo?si=YPokPmH2Qtf3m5Fg

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እሺ ወንድማችን በሰላም ያድርሰን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እንደ ምን አላችሁ ቤተሰቦቼ ?
ከተሠማራንበት የሥራ ዘርፍ በተጨማሪም ሆነ እንደ ዋና ሥራ አድርገን ልንሠራው የምንችለ የሥራ ዘርፍ አለን በመሆኑም ፦
1, በግልም ሆነ በመንግሥት ተቋማት ተቀጥራችዉ የምትሠሩ
2, የግላችውን ሥራ የምትሠሩ
3, ከዩኒቨርስቲ ተመርቃችሁ ሥራ ያላገኛችሁ
4, 12 ተፈትናችሁ ነጥብ የመጣላቸውም ሆነ ያልመጣላችው ሠርታችዉ የራሳችሁን ስራ መሥራት ወይም ለመጀመር የሚያስችል ካፒታል የምታገኙበት የስራ ዘርፍ ነው ።ማንኛውም መሥራት የሚፈልግ ሰው  ሙሉ ስም ፣የመኖሪያ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር በዉስጥ መሥመር ያሥቀምጥልኝ።



ሴልስ መስራት የሚፈልግ በዚህ ቁጥር መደወል ይችላሉ
0983797902
0799192014 

inbox me your :
-NAME
-ADRESS
PHONE NUMBER

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በአንድ ወቅት 900 መነኰሳት በጋራ ይኖሩበት የነበረው የአቡነ መርቆሬዎስ ደብረ ድማኅ ገዳም ተፈቶ ያለ ሰው ቀርቶ ነበር። ነገር ግን የአቡነ መርቆሬዎስ ልጆችና የልጅ ልጆቻቸው ከያለበት እየመጡ በየዓመቱ ያጥኑና ይቀድሱ ነበር። በአንድ ወቅት ግን አባ ተክለ ኢየሱስ የተባለ መነኵሴ ከትውልድ አገራቸ ዓዲ ሕዝባይ ከተባለ ቦታ በእግዚአብሔር መንፈስ ተመርተው ሌሎች መነኰሳትን ሰብስበው የአንድነት ማኅበር ድጋሚ አቋቋሙ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ደብረ ድማኅ ገዳም ሙሉ መንፈሳዊ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። ገዳሙ ታላቅ የምናኔ ቦታ ከመሆኑም ባሻገር በርካታ ሊቃውንት የሚወጡበት ነው። የትርጓሜ መጻሕፍት የብሉይና ሐዲስ፣ የቅኔ፡ የምዕራፍ፣ የጸመ ድጓ እና የመዝገበ ቅዳሴ መምህራን ከዚህ ገዳም ታጥተው አያውቁም።

ደብረ ድማኅ አቡነ መርቆሬዎስ ገዳም ከጥንታዊ ገዳማት ውስጥ አንዱ ነው በደቡብ ዞን ዓረዛ ቆላ ሠራየ በሚባል ቦታ የሚገኝ ሲሆን ከአስመራ 102 ኪ.ሜ ርቀት ላይ እንዲሁም ከባሕር ወለል በላይ 2075 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ ታላቅ ገዳም ነው። ገዳሙን አቡነ መርቆሬዎስ የመሠረቱት በ1340 ዓ.ም ነው።

የገዳሙ አባቶች ይኸን አስደናቂና ፈዋሽ እምነት ከአንድ ቦታ ላይ ቆፍረው እያወጡ ለሚመጣው ሕዝብ ሁሉ ሲያድሉ ከ600 አመታት በላይ ቢሆናቸውም በጣም በሚያስገርም መልኩ እምነቱ ተቆፍሮ የሚወጣበት ቦታ አንድ ስንዝር ያህል እንኳን ወደታች አለመጎድጎዱ ነው። በተለይም በየዓመቱ በጻድቁ የዕረፍታቸው ዕለት ታኅሣሥ 16 ቀን በጣም ብዙ ሕዝብ ለክብረ በዓሉ ወደ ገዳሙ እየሔደ እምነቱን ከአባቶች በብዛት እየተቀበለ ቢመለስም ተቆፍሮ የሚወጣበት ቦታ ምንም ሳይጎድል ከዓመት እስከ ዓመት ያው ነው።

ገዳሙ በጣም በተለየ ሁኔታ የሚታወቅበት ነገር እምነቱ ነጭ መሆኑ ነው። ይኸም የሆነው በጻድቁ ልመናና ቃልኪዳን ነው ይኸውም አቡነ መርቆሬዎስ አቡነ አብዲሳና አቡነ ፊልጶስ ሦስቱ አንድ ላይ ሆነው ጉዳዕ በተባለ አከባቢ ደብረ ድማኅ ገዳም ሮራ ተራራ ላይ ሆነው የየራሳቸውን ምኞት ሲጸልዩ አቡነ ፊልጶስ ስለሚያርፉባት ገዳም ጸለዩ፣ አቡነ አብዲሳም ልጆቻቸው ይበዙ ዘንድ ሲጸልዩ አቡነ መርቆሬዎስ ደግሞ .....እኔ የምኖርባትን ገዳም ነጭ የልጆቼንም ኅሊናቸው እንደ ነጭ ንጹሕ አድርግልን” ብለው ጸለዩ እግዚአብሔር አምላክም እንደየጸሎታቸው ለሦስቱም ቅዱሳን ሰጣቸው, በዚኽም መሠረት የአቡነ መርቆሬዎስ እምነታቸው ነጭ አፈር ሆነ ይኸም እምነታቸው ለሁሉም ዓይነት ሕማም በጣም ፈዋሽ ሲሆን በተለይም ለአጋንንት በሽታዎችና ለነቀርሳ የታወቀ መድኀኒት ነው።

እኛም በጉዞአችን ወቅት ወደዚህ ተኣምረኛ ገዳም በአዳር መርሐ ግብር ሔደን ለመሳለምና የአቡነ መርቆሬዎስን ነጭና ፈዋሽ እምነት ከገዳሙ አባቶች ለመቀበል እግዚአብሔር ፈቅዶልናል። በቤተ መቅደሱ ውስጥ የእነ አቡነ ተክለ ሃይማኖትንና የእነ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን ሥዕላት ጨምሮ አስደናቂ የሆኑ በጣም ጥንታውያን ቅዱሳት ሥዕላት በብዛት ይገኛሉ። ከዚሁ ገዳም አጠገብ የአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ቤተ ክርስቲያንም ይገኛል።

የአቡነ መርቆሬዎስ ጸሎታቸው በረከታቸው ከሁላችን ከሕዝበ ክርስትያን ጋር ይሁን አሜን።
ምንጭ## በእንተ ኅሩይ ቅዱሳን መጽሐፍ የተወስደ( በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን )
ታኅሣሦ16/4/2015ዓ.ም
Kuwait

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ታህሳስ 15/2016 #ቅድስት_ኢየሉጣ
#ቅዱስ_ቂርቆስ
#ቅዱስ_ሚናስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሳኑ ስም ለምናመሰግንበት #ቅዱስ_ቂርቆስ_እና_ቅድስት_ኢየሉጣ #ቅዱስ_ሚናስ በምልጃ ፀሎታቸዉ እንዲያስቡን ለምንማፀንበት ለወርሐዊ መታሠቢያ በአላቸዉ እንኳን አደረሰን

👉 #ቅዱስ_ቂርቆስ ዕድሜው የሦስት ዓመት ሳለ እናቱ ቅድስት #ኢየሉጣ ከሮሜ ወደ ሌላ ሃገር ሸሽታ ይዛው ሄደች በዚያም የሸሸችውን መኮንኑን አገኘችው የሚያውቋትም ሰዎች ሸሽታ እንደመጣች ስለተረዱ ለመኮንኑ ነገር ሰሩባት

👉መኮንኑም #ቅድስት_አየሉጣን አስጠራትና ስለ አምልኮ ጠየቃት ቅድስት ኢየሉጣም መኮንን ሆይ ዕድሜው ሦስት አመት የሆነው ሕፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እርሱን ጠይቅ አለችው

👉 #ሕፃኑ_ቅዱስ_ቂርቆስም ወደ አለበት ጭፍራውን ልኮ ወደ እርሱ አስመጣው ሕፃኑንም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና “አንተ ደስተኛ ሕፃን ሆይ እንዴት ነህ?” አለው።

👉ሕፃን #ቅዱስ_ቂርቆስም መለሰለት እንዲህም አለው “አዎ እኔ በጣም ደስተኛ ነኝ ደስታዬም ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ሐዘንና ለቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስም ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏልና” አለው።

👉 #እግዚአብሔር አምላክ ኃይልንና ንግግርን ሰጥቶታልና በዚያ ለተሰበሰቡት ሰዎች እስኪደነግጡ ድረስ ብዙ ተናገረ ሕፃኑ #ቅዱስ_ቂርቆስም ንጉሱን መኳንንቱንና ጣዖታቱን ረገማቸው ከብርታቱም የተነሳ አደነቁ።

👉መኮንኑም በአፈረ ጊዜ በየዓይነቱ በሆነ ስቃይ ታላላቆች እንኳ የማይችሉትን ታላቅ አስጨናቂ የሆነ ስቃይን አሰቃየው እናቱ #ቅድስት_ኢየሉጣንም ከእርሱ ጋር እንደ እርሱ በጣሙን አሰቃያት

👉 #እግዚአብሔር ግን ያለ ምንም ጉዳት ያነሳቸው ነበር ብዙዎች አህዛብም ይህን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን በመድሃኒታችን #በኢየሱስ_ክርስቶስ አምላክነት አምነው በሰማእትነት ሞቱ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበሉ።

👉በሕፃኑ #ቅዱስ_ቂርቆስ ላይም የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ አደረበት ታላላቅ ድንቅ ተአምራቶችንም ያደርግ ነበር ብዙዎች በሽተኞችንም ያድናቸው ይፈውሳቸው ነበር ይህንን ያየ መኮንን በታላቅ የናስ ጋን ውስጥ ውሃ ጨምረው በእሳት ያፈሉት ዘንድ አዘዘ የፍላቱም ድምጽ እንደ ክረምት ነጎድጓድ ሆነ ድምጹም በጣም ያስተጋባ ነበር

👉ይህን ያየችና የሰማች እናት #ቅድስት_ኢየሉጣም ፍርሃትና የሃይማኖት ጉድለት ታየባት ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ሁኔታዋን አይቶ ወደ አምላኩ እግዚአብሔር ጸለየ ያን ጊዜ ልዑል #እግዚአብሔር ልቧን ወደ ሰማይ አሳርጎ ለቅዱሳን ሰማዕታት የተዘጋጁ የብርሃን ማደሪያዎችን አሳያት ቅድስት ኢየሉጣም እንደገና በሃይማኖቷ ጸናች እግዚአብሔር አምላኳንም አመሰገነችው ልጇን ሕፃኑን ቅዱስ ቂርቆስንም “ልጄ ሆይ አንተ ከእንግዲህ አባቴ ነህ እኔም ልጅህ ነኝ” አለችው

👉 #ቅድስት_እየሉጣም ለልጇ “ያች የተወለድክባት ዕለት ቀኗ የተባረከችና የተቀደሰች ናት” አለችው የመኳንንቱ ጭፍሮችም እሳት ወደ አለበት ጋኖች ውስጥ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣን በጨመሯቸው ጊዜ የውሃው ፍላት ወድያዉኑ ቀዘቀዘ ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የእሳቱን ኃይል አቀዝቅዞታልና

👉ይህን ያየ መኮንን ሥጋቸው ተቆራርጦ እስከሚወድቅ ድረስ በመቃጥን ውስጥ አድርገው አንዲጎትቷቸው አዘዘ #ከእግዚአብሔርም የታዘዘ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል አዳናቸው

👉መኮንኑም በታላቅ ስቃይ ያሰቃያቸው ዘንድ አስቦ እስኪመክር ድረስ በወህኒ ቤት ዘጋባቸው በዚህን ጊዜ ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ወደ ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስን አረጋጋው አጽናናው ስሙን ጠርተው መታሰቢያ ለሚያደርጉለትም በረከትን እንደሚያገኝና ሌላ ብዙ ቃል ኪዳን ሰጠው

👉ሲነጋ መኮንኑ ከመካነ ምኩናኑ ተቀምጦ ካለበት አስጠርቶ የተመለስከው መመለስ አለን አለው #ቅዱስ_ቂርቆስም አይሆንም አልመለስም አለው ሰይፍ ጃግሬውን ጠርቶ ንሳ ውደቅበት አለው በሰይፍ መታው ጌታም ነፍሱን ከመካነ ዕረፍት ሥጋውንም ነጥቆ #በሰረገላ_ኤልያስ አኑሮለታል እናቱ ቅድስት ኢየሉጣንም በማግስቱ ጥር 16 በሰይፍ አስመትቷት በሰማዕትነት ዓርፋለች

👉 #እግዚአብሔር አምላካችን የሕፃኑ #ቅዱስ_ቂርቆስና የእናቱ #የቅድስት_እየሉጣን በረከታቸውንና ረድኤታቸውን ያድለን "አሜን"

👉በዚህ እለት የምናስበዉ ሰማእቱ #ቅዱስ_ሚናስ ፀሎቱ በረከቱ አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/bxTpkZ1Xf5k?si=FPrN25FfJCR5TiUx

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🕊🌺🕊🌺እግዚአብሔር ፈዋሽ🕊🌺🕊

እግዚአብሔር ፈዋሽ የስምህ ትርጉም
ፈታሄ ማህጸን ሩፋኤል ግሩም
ለአንተ አለኝ ምስጋና የመንገዴ መሪ ነህና/2/

  
ይውረድ ከሰማይ የምህረት ጠል
ሩፋኤል አሳደገኝ ልበል
ከልጅነቴ ያኖርከኝ በክብር
ሩፋኤል ለአንተ ልዘምር/2/


የመብረቅ ጋሻ የእሳት ጦር ይዘህ
ከንፋስ ይልቅ ትፈጥናለህ
መራሄ ፍኖት ናልኝ ወደኔ
ጦቢት ነኝ ይብራልኝ አይኔ/2/


ተሾምክ በኃይላት አለቃ ሆነህ
ሰሚነህ ሩፋኤል ላለህ
ሲወልዱ እናቶች እንዳይጨንቃቸው
ማህጸን ከፋች ሆንካቸው/2/


እኔ ያንተ ልጅ ላንተ ልዘምር
ስላየሁ ያንተን ልዩ ፍቅር
በደረስኩበት የማትለየኝ
ስላንተ ምለው ብዙ አለኝ
ስላንተ ገና ብዙ
🕊🌺🕊🌺🕊🌺

/channel/mezmur_store

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

+"+ አባ አብራኮስ ገዳማዊ +"
+=>አባቶቻችን ይህንን ቅዱስ "ኃያል መነኮስ" ይሉታል:: በ20 ዓመቱ ወደ በርሃ ገብቶ ለ70 ዓመታት በበርሃ ሲጋደል 90 ዓመት ሞልቶታል:: ሰይጣንን መፈናፈኛ አሳጥቶ ከአካባቢው አርቆታል::+ሰይጣንም እርሱን መጣል ስላልቻለ ቢያንስ ከጾሙ: ጸሎቱና ስግደቱ ትንሽ ቢቀንስልኝ ብሎ አዲስ የፈተና ስልትን ፈጠረ:: ቀርቦም በገሃድ "አብራኮስ አንተ ደክመሃል:: ግንኮ ገና 50 ዓመት እድሜ አለህ" አለው::

+ቅዱሱ ግን ሰይጣንን "አሳዘንከኝ! እኔኮ ገና 100 ዓመት ያለኝ መስሎኝ ነው በጥቂቱ የምጋደለው:: እንዲያ ከሆነማ ከነበረኝ ጾም: ጸሎትና ስግደት በእጥፉ እጨምራለሁ" ቢለው ሰይጣን አፍሮ ተመልሷል:: ቅዱስ አብራኮስ ግን በዚያው ዘመን: በ90 ዓመቱ ዐርፏል::

=>አምላከ አበው ቅዱሳን በመጽናታቸው ያጽናን:: ከበረከታቸውም ያድለን::

=>ታሕሳስ 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ መቃርስ ገዳማዊ
2.አባ አብራኮስ ገዳማዊ
3.ብጽዕት ሐና (የእመቤታችን እናት)
4.አባ በጽንፍርዮስ ሰማዕት
5.አባ ሚካኤል ዘቀልሞን

=>ወርኀዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
3.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
4.አእላፍ (99ኙ) ነገደ መላእክት
5.ቅዱስ አስከናፍር ሮማዊ
6."13ቱ" ግኁሳን አበው

=>+"+ ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል:: ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል:: ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላቹሃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም:: +"+ (ማቴ. 10:41)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞✞✞በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን✞✞✞

✞✞✞እንኳን ለቅድስት ወብጽዕት ሐና (እመ ማርያም) ፡ለጻድቃን ቅዱሳን "አቡነ ዘርዓ ቡሩክ" : "አባ መቃርስ" እና "አባ አብራኮስ" በዓል በሰላም አደረሳችኹ✞✞✞

+*" ብጽዕት ሐና "*+

=>"ሐና" ማለት በእብራይስጥኛው "የእግዚአብሔር ስጦታ" እንደ ማለት ነው:: "ሐና: ዮሐና: ሐናንያ" የሚሉ የዕብራይስጥ ስሞች ትርጉማቸው ተወራራሽ ነው:: የዚህችን ቅድስት እናት ክብሯን መናገር የሚችል የለም:: እርሷ ሰማይና ምድርን ለፈጠረ ለእግዚአብሔር ወልድ በሥጋ አያቱ ተብላለችና::

+አንድም ለሰማይና ለምድር ንግስት ለድንግል ማርያም ወላጅ እናቷ ናትና:: ከዓለም ሴቶች ሁሉ የቅድስት ሐና ማሕጸን እንደ ምን ይከብር! በፍጥረት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥንተ አብሶ (የአዳም በደል) መተላለፍ የቀረው በማሕጸነ ሐና ውስጥ ነውና:: (ለዚህ አንክሮ ይገባል!!!)

+ይስሐቅን የተሸከመ የሣራ ማሕጸን ቡሩክ ከተባለ የቅድስት ሐናማ እንደምን አይባል! ከፍጥረታት ሁሉ እግዚአብሔር ድንግል ማርያምን እንደ መረጠ ሁሉ ቅድስት ሐናንም ለአያትነት መርጧታል::

=>ለመሆኑ ቅድስት ሐና ማን ናት? ለዚህ ክብርስ ያበቃት ምሥጢረ ቅድስናዋ ምንድን ነው?

+ቅድስት ሐና ትውልዷ: ነገዷ ከላይ ከቅዱስ አብርሃም: ከታች ደግሞ ከነገደ ካህናት ነው:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

*አብርሃም ይስሐቅን: ይስሐቅ ያዕቆብን: ያያዕቆብ ደግሞ ሌዊንና 11 ወንድሞቹን ይወልዳል::

*ሌዊ ቀዓትን: ቀዓት እንበረምን: እንበረም አሮን ካህኑን ይወልዳሉ::

*ቅዱስ አሮን አልዓዛርን: አልዓዛር ፊንሐስን እያለ ትውልዱ እስከ ቴክታና በጥሪቃ ይወርዳል:: ቴክታና በጥሪቃም ልጅ በማጣት ኖረው: የእንቦሳዎች: የፀሐይና: የጨረቃን ምሥጢር ተመልክተው ሄኤሜንን ይወልዳሉ::

*ሄኤሜን ዴርዴን: ዴርዴ ቶናሕን: ቶናሕ ሲካርን: ሲካርም ሔርሜላን ይወልዳሉ::

*ሔርሜላም ከክርስቶስ ልደት 90 ዓመታት በፊት ማጣት ("ጣ" ጠብቆ ይነበብ) የሚባል ደግ ሰው ከካህናት ወገን አግብታ በስርዓተ ኦሪት ትኖር ነበር:: እግዚአብሔር ለዚህች ደግ ሴት የተባረኩ 3 ሴቶች ልጆችን ሰጣት::

+የመጀመሪያዋን "ማርያም" አለቻት:: ይህቺውም የአረጋዊው ዮሴፍ ሚስትና የቅድስት ሰሎሜ ቡርክት እናት ናት:: ሁለተኛዋን "ሶፍያ" አለቻት:: እርሷም ቅድስት ኤልሳቤጥን (የመጥምቁን እናት) ወልዳለች::

+በመጨረሻ የወለዷትን ግን "ሐና" አሏት:: ይህቺውም የፈጣሪ የሥጋ አያቱ: የድንግል ማርያምም እናቷ ትሆን ዘንድ የተመረጠችውና ስም አጠራሯ የከበረው: ዛሬ የምናከብራት እናት ናት::

+መጽሐፈ ስንክሳርን ስመለከት እንዲህ የሚል ዓረፍተ ነገር አየሁ:: "ለዛቲ ቅድስት ኢያዕመርነ ገድላቲሃ ዘትገብሮን በኅቡዕ ከመ ንዝክሮን" ይላል:: ትርጉሙም "የዚህቺን ቅድስት ገድሏንና ትሩፋቷን እንዳንዘረዝር አላወቅነውም" እንደ ማለት ነው::

+የሚገርመው አበው እንዲህ ያሉት ክብሯን መግለጹን አልጠግብ ብለው ነው:: እኛም በመጠናችን የብጽዕት ሐናን ሕይወት በአጭሩ ቀጥለን እንመልከት::

+ብጽዕት ሐና ወላጆቿ (ማጣትና ሔርሜላ) ከካህናት ወገን በመሆናቸው ልጆቻቸውን በጥንቃቄ: በሥርዓተ ኦሪት እንዳሳደጉ ይታመናል:: ቅድስት ሐናንም ለአቅመ ሔዋን እስክትደርስ ድረስ በሕጉ: በሥርዓቱ አሳድገዋታል::

+በወቅቱ በፈቃደ እግዚአብሔር ትውልዱ ከነገደ ይሁዳ የሚሆን አንድ ደግ ሰው አጩላት:: ይህ ሰው "ኢያቄም" ይባላል:: አንዳንዴም "ሳዶቅ" ወይም "ዮናኪር" እየተባለ ይጠራል:: ቅዱስ ኢያቄም ማለት ክፉ ከአንደበቱ የማይወጣው: ምጽዋትን የሚወድ: አምላከ እሥራኤልን በንጹሕ ልቡ የሚያመልክ ሰው ነበረ::

+እንደ ኦሪቱ ሥርዓት 2ቱ (ኢያቄም ወሐና) ከተጋቡ በሁዋላ ቶሎ መውለድ አልቻሉም:: ይሕ ደግሞ የወቅቱ ከባድ ፈተና ነው:: በዘመድ የከበሩ: በጠባያቸው የተመሰገኑ: መልካምንም የሚሠሩ ሰዎች ልጅ ስለሌላቸው ብቻ "ኅጡአነ በረከት" እየተባሉ ከቤተ እግዚአብሔር ይገፉ: በአደባባይም ይነቀፉ ነበር::

+ምክንያቱም በብሉይ ኪዳን ልጅ አለመውለድ እንደ ኃጢአተኛ ያስቆጥር ነበር:: ደግነቱ የወቅቱ ሊቀ ካህናት ቅዱስ ዘካርያስ (የመጥምቁ አባት) እንደ እነሱ ልጅ ያጣ በመሆኑ አብረው ይጽናኑ ነበር::

+የሆነው ሆኖ እኒህ ቡሩካን ሰዎች አምላከ እሥራኤልን ከመለመንና ከማመስገን በቀር ሌላ ትርፍ አልተገኘባቸውም:: ምንም የሞላቸውና የደላቸው ባይሆኑም ደሃን ሳያጐርሱ አይበሉም ነበር::

+ቅድስት ሐናን ግን "ቢወልዷት እንጂ አትወልድ: ድንጋይ: በቅሎ" እያሉ ጐረቤቶቿ ይሳለቁባት ነበር:: ከማልቀስ በቀር ደግሞ መልስ አልነበራትም::

+አንድ ቀን ግን ርግቦች ከልጆቻቸው ጋር ሲጫወቱ ተመልክታ "ፈጣሪ ሆይ! የእንስሳትን ማሕጸን የምትከፍት: ዕፀዋትንም ከባሕርያቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ:: እውነትም ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ስትል አለቀሰች::

+ቅዱስ ኢያቄምም ወደ ተራራ ወጥቶ ለ40 ቀናት አለቀሰ: ተማለለ:: ይህ ሲሆን 2ቱም አርጅተው ነበር:: ሐምሌ 30 ቀን ግን ነጭ ርግብ 7ቱን ሰማያት ሰንጥቃ በማሕጸነ ሐና ስታድር አዩ:: ደስ ብሏቸው ለ7 ቀናት ሱባኤ ይዘው ቅድስት ሐና እመቤታችንን ነሐሴ 7 ቀን ጸነሰቻት::

+ይሕም ለእነርሱም: ለወገኖቻቸውም ታላቅ ተድላ ሆነ:: ብጽዕት ሐና ግን ፈጣሪዋን ታከብረው ዘንድ በጐነትንና ንጽሕናን አበዛች:: ጸንሳ ሳለም ዕውራንን አበራች: ድውያንን ፈወሰች::

+የጦሊቅ ልጅ በሞተ ጊዜም እያለቀሰች ስትዞረው ጥላዋ ቢያርፍበት አፈፍ ብሎ ተነስቶ:- "ሰላም ለኪ እሙ ለፀሐየ ጽድቅ" ብሎ ድንግል ማርያምን::
"ወሰላም ለኪ እምሔውቱ ለዘገብረ ሰማየ ወምድረ" ብሎ ቅድስት ሐናን አመስግኗል:: ትርጉሙም ድንግልን "የፀሐየ ጽድቅ እናቱ": ሐናን "ሰማይና ምድርን ለፈጠረ አያቱ" ማለት ነው::

+ይህንን ያዩ አይሁድ ቅድስት ሐናን ሊገድሉ ብዙ ጊዜ ሞክረዋል:: ግን መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል አልፈቀደላቸውም:: ግንቦት 1 ቀንም የሰማይና የምድር ንግስትን ሊባኖስ ተራራ ላይ ወልዳ ሽሙጥን ከሁላችንም አራቀች::

+ስሟን "ማርያም-የአምላክ ስጦታ" ብለው ሰይመው ለ3 ዓመታት አሳድገዋታል:: የሚገርመው በ3ቱ ዓመታት ውስጥ ቅድስት ሐና ድንግል ማርያምን ከክንዷ አውርዳት አታውቅም ነበር:: አንድ ጊዜም መላእክት ወስደውባት ፍጹም አልቅሳለች:: ሁዋላ ግን መልሰውላታል::

+ሌላኛው የሚደንቀው እግዚአብሔር የዓለም ውዱን ስጦታ እመ ብርሃንን ሰጣቸው:: እነርሱም ይሕችን ውድ ስጦታ ሳይሰስቱ ለፈጣሪ መለሱለት::
"እምቅድሜክሙ አልቦ::
ወእምድኅሬክሙ አልቦ::
ከመዝ መስዋዕት ለእግዚአብሔር ዘወሃቦ::" እንዲል::

+ቅድስት ሐና ድንግል ወደ ቤተ መቅደስ ከገባች በሁዋላ የእናትነት ፍቅሯ እያገበራት ለ5 ዓመታት እየተመላለሰች ትጐበኛት: ትስማት ነበር:: እመቤታችን 8 ዓመት በሞላት ጊዜ ግን የእግዚአብሔር ጥሪ ወደ ቅድስት ሐና ደረሰ::

+ከክርስቶስ ልደት 8 ዓመታት አስቀድማ ብጽዕት እናት ሐና ዐረፈች:: ትንሽ ቆይቶም ባለቤቷ ቅዱስ ኢያቄም ተከተላት እኛም ልጆቿ "ብጽዕት ሐና ብጽዓን ይገባሻል!" እያልን እናመስግናት::

❤️¤በዚህች ዕለት ቅድስት ሐና ድንግል እመቤታችንን እንደ ጸነሰች በግብጻውያን ወገኖቻችን ይታመናል:: እኛ ግን ጽንሰተ ማርያምን በጐላ በተረዳ መንገድ ነሐሴ 7 ቀን እናከብራለን::+ሊቃውንቱ ለእርሷ እንዲህ ብለዋልና:-
"ሰላም ለኪ ለጸሎተ ኩሉ ምዕራጋ::
ከመ አስካለ ወይን ዲበ ሐረጋ::

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

afomiatube41?si=FgFKQzQyvJIcU3lE" rel="nofollow">https://youtube.com/@afomiatube41?si=FgFKQzQyvJIcU3lE

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

መኮንኑም 2ቱን ቅዱሳን ከብዙ ሕዝብ ጋር አሰይፏቸዋል::+እንደ እኔ ያለ ኃጢአተኛም በስማቸው እንዲህ ሊጸልይ ይገባል:-"ሰላም ዕብል ለአንቂጦስ ማሕበሮ::
እለ በእሳት ፈጸሙ ረዊጸ ወተባድሮ::
ያብጽሑኒእሉ ምስለ መላእክት ድርገተ ዘምሮ::
ህየ አኀሉ ወሬዛ ነዳየ ኩሉ አዕምሮ::
ኀበ ይዘብጣ ደናግል ከበሮ::" (አርኬ)

=>አምላከ ሳሙኤል በምጃቸው ሃገራችን ከጦርነት: ሕዝቦቿን ከስደት ይሰውርልን:: ሞልቶ ከተረፈ በረከታቸውም አይንሳን::

=>ታሕሳስ 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
2.ቅዱሳን አንቂጦስ ወፎጢኖስ (ሰማዕታት)
3.አባ ነድራ
4.ቅዱስ ዮሐንስ ተአማኒ
5.ጉቡዓን ኤዺስ ቆዾሳት

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
3.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት)
5.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
6.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
7.ቅዱስ ድሜጥሮስ ሊቅ

=>+"+ የሚያሳድዷችሁን መርቁ . . . ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ:: ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ:: እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ:: የትዕቢትን ነገር አታስቡ:: ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ:: +"+ (ሮሜ. 12:14-16)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

💠"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠   
/(ማቴ ፫:፫/)

+"+ ቅዱሳን አንቂጦስ ወፎጢኖስ +"+

=>እነዚህ ቅዱሳን በሥጋ ወንድማማቾች ሲሆኑ የዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች ናቸው:: ዜና ሕይወታቸውን ሳስበው ይገርመኛል:: በእሳት የወጣትነት ዘመናቸው በሃይማኖት ጸንተው: ፍቅረ ክርስቶስ እንደ እሳት በላያቸው ላይ ይነድ ነበር::

+በእውነት ክርስቶስን በከንፈር ያይደለ በፍጹም ልቡና መውደድ እንዴት ያለ መታደል ነው! ክርስቶስን የወደደ የድንግል እናቱና የቅዱሳን ወዳጆቹ ፍቅር ይበዛለታል እንጂ አይቀንስበትም::

+ቅዱሳኑ አንቂጦስና ፎጢኖስ ወጣትነት: የዓለም ኑሮ ሳያታልላቸው ለሰማዕትነት ራሳቸውን አዘጋጁ:: እንኩዋን ሰውን አራዊትን የሚያስበረግግ የስቃይ ዓይነት ተሰልፎ ሳለ በፍጹም አልደነገጡም::

+መጀመሪያ አንቂጦስን አቀረቡት:: ገረፉት: ምንም አልሆነም:: በእሳት አቃጠሉት: ምንም አልነካውም:: ለአንበሳ ሰጡት: እነርሱ ግን ሰገዱለት:: ከዳር ሆኖ ይህንን ሁሉ ሲመለከት የነበረው ወንድሙ ፎጢኖስ ዘሎ ወደ መከራ አደባባይ ገባ::

+"ወንድሜ የክርስቶስ ነውና መቼም አታሸንፈውም" ሲል ጮኸ:: በዚህ ጊዜም በሥፍራው የነበሩ ብዙ አሕዛብ "የእነዚህ ወጣቶች አምላክ አምላካችን ነው" አሉ::
መኮንኑም 2ቱን ቅዱሳን ከብዙ ሕዝብ ጋር አሰይፏቸዋል::+እንደ እኔ ያለ ኃጢአተኛም በስማቸው እንዲህ ሊጸልይ ይገባል:-"ሰላም ዕብል ለአንቂጦስ ማሕበሮ::
እለ በእሳት ፈጸሙ ረዊጸ ወተባድሮ::
ያብጽሑኒእሉ ምስለ መላእክት ድርገተ ዘምሮ::
ህየ አኀሉ ወሬዛ ነዳየ ኩሉ አዕምሮ::
ኀበ ይዘብጣ ደናግል ከበሮ::" (አርኬ)

=>አምላከ ሳሙኤል በምጃቸው ሃገራችን ከጦርነት: ሕዝቦቿን ከስደት ይሰውርልን:: ሞልቶ ከተረፈ በረከታቸውም አይንሳን::

=>ታሕሳስ 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
2.ቅዱሳን አንቂጦስ ወፎጢኖስ (ሰማዕታት)
3.አባ ነድራ
4.ቅዱስ ዮሐንስ ተአማኒ
5.ጉቡዓን ኤዺስ ቆዾሳት

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
3.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት)
5.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
6.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
7.ቅዱስ ድሜጥሮስ ሊቅ

=>+"+ የሚያሳድዷችሁን መርቁ . . . ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ:: ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ:: እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ:: የትዕቢትን ነገር አታስቡ:: ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ:: +"+ (ሮሜ. 12:14-16)

    <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
       አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/5_BYH_8yrlc

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

+ያ አጽምም ሥጋ ነስቶ: ተነስቶ ሰገደላቸው:: "ከወዴት መጣህ?" ቢሉት "ከሲዖል" አላቸው:: አረማዊ እንደ ነበርና የሲዖልን የመከራ ብዛት ነገራቸው:: አክሎም "ክርስቲያን ነን እያሉ በክርስትናቸው የሚቀልዱ ከእኛ በታች በብዛት አሉ:: መከራቸው ተነግሮ አያልቅም" አላቸው::+ድጋሚ በበትራቸው ነክተው ወደ ነበረበት መለሱ:: ከዚያም ቅዱሳኑ ወደየ በዓታቸው ተሰነባበቱ:: ታላቁ አባ በኪሞስ ከዚህ በሁዋላ ለ7 ዓመታት ያህል መልአክ በክንፉ እየወሰደው ወንጌልን ሰብኩዋል:: ብዙዎችንም ወደ ሃይማኖትና ንስሃ

አምጥቷል::

+ሁሌም እንቅቦችን እየሰፋ ይሸጥ: በዋጋውም ለነዳያን ይራራ ነበር:: መልአኩም ወደ ፈለገበት ቦታ ተሸክሞ ይወስደው ነበር:: ታላቁ ቅዱስ አባ በኪሞስ በርሃ በገባ በ58 ዓመቱ : በተወለደ በ70 ዓመቱ በዚህች ቀን ዐርፏል:: የክብር ክብርንም ወርሷል::

=>አምላከ አባ በኪሞስ ጸጋውን: ክብሩን አይንሳን:: ከበረከቱም ይክፈለን::

=>ታሕሳስ 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ታላቁ አባ በኪሞስ
2.ቅዱስ በርተሎሜዎስ
3.ቅዱስ ቴዎድሮስ
4.ቅዱስ በጥላን

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ያሬድ ካህን
2.ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት
3.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
4.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
5.ቅድስት ሐና ቡርክት

=>+"+ በእሸቅድምድም ሥፍራ የሚሮጡት ሁሉ እንዲሮጡ: ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ:: የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል:: እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው:: እኛ ግን የማይጠፋውን:: +"+ (1ቆሮ. 9:24)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/gunv-zkVADs

Читать полностью…
Subscribe to a channel