kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አብሮ አደረሰን 🙏🙏🙏 የ ዓመት ሰው ይበለን 🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Amen amen amen 🙏🙏🙏🙏😍😍

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Enkan abero aderesen lehulachenen

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Selam familiw

ምስለ ኦርቶዶክስ በNTG

Yhann serch aerguna join belu eshi

@msle_orthodox_by_ntg

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አሜን አሜን እንኳን አብሮ አደረሰን🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል: ቅዱስ ዮሐንስ ዘቡርልስ እና አቡነ ስነ ኢየሱስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት †††

††† በቤተ ክርስቲያን ክቡር ከሆኑ ሊቃነ መላእክት አንዱ የሆነው ቅዱስ ገብርኤል ብዙ የክብር ስሞች አሉት:: በተለይ ግን:-
*ሊቀ አርባብ:
*መጋቤ ሐዲስ:
*መልአከ ሰላም:
*ብሥራታዊ:
*ዖፍ አርያማዊ:
*ፍሡሐ ገጽ:
*ቤዛዊ መልአክ:
*ዘአልቦ ሙስና . . . እየተባለ ይጠራል::

በብሉይ ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን ስሙ በብዛት ተጠቅሷል:: ስለ ረዳትነቱና አማላጅነቱም ቤተ ክርስቲያን በስሙ ታቦት ቀርጻ: መቅደስ አንጻ በሥርዓት ክብሩን ትገልጻለች::

ከእነዚህም አንዱ ሠለስቱ ደቂቅን እንዳዳነ የሚታሰብበት አንዱ በዓሉ ዛሬ ነው::
"ለዝንቱ ዜናዊ መልአከ ኃይል::
በዛቲ ዕለት ከመ ይትገበር በዓል::
መምሕራን አዘዙ ወሠርዑ በቃል::" እንዲል:: (አርኬ)

ንጉሡ ከምርኮ ወጣቶች ለቤተ መንግስት ሲመርጥ ሦስቱ ቅዱሳንና ዳንኤል ተመርጠው የምቾት ሕይወት ተዘጋጅቶላቸው ነበር:: ነገር ግን በምግብና በአምልኮ ከአ+ሕ+ዛ+ብ ጋር መተባበርን አልፈለጉምና ምርጫቸው ጾምና ጸሎት ከቆሎ ጋር ሆነ::

ምንም እንኳ በቤተ መንግስት ውስጥ ቢኖሩ: ምንም የነገሥታት ልጆች ቢሆኑ ለእነርሱ ከእግዚአብሔር ፍቅር የተሻለ አልነበረምና በጥሬ ቆሎ ተወስነው ኖሩ::

አምላካቸው ከሃሊ ነውና በውበትም ሆነ በጥበብ በባቢሎን ምድር ከነርሱ የሚደርስ አልተገኘም:: ንጉሡም በባቢሎንና በአውራጃዋ ላይ ሾማቸው:: ስማቸውንም በአማልክቱ ስም ሲድራቅ: ሚሳቅና አብደናጐ አላቸው::

ከነገር ሁሉ በኋላ አ+ሕ+ዛ+ብ ቀንተውባቸዋልና የክፋት አዋጅን አሳወጁ:: ናቡከደነጾር 60 ክንድ ቁመት ያለውን የወርቅ ምስል አቁሞ ስገዱ ቢላቸው አይሆንም በማለታቸው ተቃጥለው እንዲሞቱ እሳት ተፈረደባቸው:: ነበልባሉ ከጉድጓዱ ወደ ላይ 49 ክንድ ቢነድም ቅንጣት ያህል ፍርሃት አልጎበኛቸውም::

ወደ እሳቱም ሲጥሏቸው መልዐከ አድኅኖ ቅዱስ ገብርኤል ደርሶ አዳናቸው:: ከሆነው ነገር የተነሳ አ+ሕ+ዛ+ብ አፈሩ:: ናቡከደነጾር ግን ከዙፋኑ ተነስቶ የቅዱሳኑን አምላክ እግዚአብሔርን ባረከ::

ቅዱሳኑን ያዳነ ቅዱስ መልአክ እኛንም ያድነን ዘንድ እንደ አባቶቻችን
"አድኅነኒ ዘአድኃንኮሙ በአክናፊከ ምንትው::
አመ ውስተ እሳት ተወድዩ ሠለስቱ እደው::" እያልን እንለምነው:: (መልክዐ ገብርኤል)

††† ✝ቅዱስ ዮሐንስ ዘቡርልስ✝ †††

††† ይህ ቅዱስ አባት ስም አጠራሩ የከበረ ነው:: ሊቅም: ጻድቅም: ጳጳስም: ገዳማዊም ነው:: ከሁሉም በላይ ግን ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያን በተድላ ለምትጠቀምባቸው መጻሕፍት (ስንክሳር: ግጻዌ እና ሃይማኖተ አበው) መሠረትን የጣለ ቅዱስ ሰው ነው::

ቅዱስ ዮሐንስ በትውልዱ ግብጻዊ ሲሆን ጊዜውም 5ኛው መቶ ክ/ዘ ነው:: ወላጆቹ ክርስቲያኖች: በዚያውም ላይ ሞልቶ የተረፋቸው ባለ ጠጐች ነበሩ:: እንደ ሕጉ ወጣት እስኪሆንና ራሱን እስኪችል ድረስ አሳደጉት::

ከዚያ ግን ድንገት አባቱና እናቱ ተከታትለው ዐረፉ:: ከቁጥር የበዛ ሃብትን የግሉ ያደረገው ቅዱስ ዮሐንስ ምን እንደሚያደርግበት ጨነቀው:: አንድ ትልቅ ነገር ግን ከማይሆን ጐዳና ጠበቀው::

ወላጆቹ ሁሌም መዝገብን በሰማያት ያገኙ ዘንድ ለነዳያን ይራሩ ነበርና ይህንኑ ለመቀጠል ወሰነ:: መልካም ፍሬ ከመልካም ዛፍ ነውና (ማቴ. 7:16) ወላጅ ለልጁ ማውረስ ያለበት ምድራዊ ሃብትን ሳይሆን በጐ ሕሊናን ነው:: ሳይሠሩ ያገኙት ሃብት ብዙዎችን አጥፍቷቸዋል::

ለዛም ይመስላል ዛሬ አንዳንዶቻችን በቤተሰቦቻችን ሃብት ከእኛ አልፈን ትውልዱን እየገደልንበት ያለው:: ለዚህ ደግሞ እግዚአብሔር ንስሃ ካልገባን ይመጣብናል:: መቅረዛችን (ሕይወታችንም) ከእኛ ላይ ይወስዳል::

ፍርድ የሚሆነው በክፉው ትውልድ ላይ ብቻ አይደለም:: ይህንን ትውልድ በፈጠርነውና መልካሙን መንገድ ባልመራነው በሁላችንም ላይ እንጂ:: (ራዕ. 2:5)

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ ዮሐንስ በወላጆቹ ሃብት የእንግዶች ማረፊያ የሚሆኑ ቤቶችን አንጾ ነዳያንን ይንከባከብ ገባ:: ሙሉውን ቀን ለነዳያን ሲራራ ይውላል:: አመሻሽ ላይ እንግዶችን ተቀብሎ: አብልቶ ያሳርፋል::

ከዚያም ፈጣሪውን ያመሰግናል:: በእንዲህ ያለ ሕይወት ዘመናትን ካሳለፈ በኋላ አንድ እንግዳ መነኮስ ወደ ቤቱ መጣ:: አስተናግዶት ሲጨዋወቱ አደሩ:: ሌሊት ላይ ግን ስለ ምንኩስና ሕይወትና ስለ ክብሩ ነግሮት ነበርና ልቡ ተመሰጠ::

መነኮሱን ከሸኘው በኋላም ይመንን ዘንድ ቆረጠ:: ነዳያንን ሰብስቦ ሃብቱን አካፈላቸው:: ከዚያም ወደ ገዳመ አስቄጥስ ሒዶ የታላቁ አባ ዳንኤል ደቀ መዝሙር ሆነ:: በትሕትና ለአባቶች እየታዘዘ ከቆየ በኋላ በጭንቅ ደዌ ተያዘ:: ሰይጣን በቅንዓት ገርፎት ነበርና::

እርሱ ግን በደዌው ምክንያት ለዓመታት መሬት ላይ ወድቆ ቢቆይም ፈጣሪውን ፈጽሞ ያመሰግን ነበር:: እግዚአብሔር ደግሞ በፈውስና በኃይል አስነሳው::

በጊዜው የቡርልስ ጳጳስ ዐርፎ ነበርና አባት ፍለጋ ወደ አስቄጥስ ገዳም መጥተው ነበር:: መንፈስ ቅዱስ መርጦታልና አበው ቅዱስ ዮሐንስ ጳጳስ ይሆን ዘንድ አስገደዱት:: እርሱም የፈጣሪ ፈቃድ መሆኑን ስላወቀ ሔደ::

በዚያም (በሃገረ ቡርልስ) ታላቁን ገድል ተጋደለ:: ወደ ከተማዋ ሲገባ ብዙ ነገሮች ከሚገባው ሥርዓት የወጡ ነበሩ:: ብዙ ሰው የእግዚአብሔርን ድምጽ ከመስማት ይልቅ ባላስፈላጊ ነገሮች ላይ ተጠምዶ ነበርና መንጋውን ያድን ዘንድ ተጋ::

ሳይሆኑ "ባሕታዊ": "አጥማቂ" ነን እያሉ ሕዝቡን የሚያሳስቱ ተኩላዎችንም አስወገደ:: ለሕዝቡ አጉል ሕልም: ሟርትን የሚያስተምሩትን ገሠጸ:: አንመለስም ያሉ መ+ና+ፍ+ቃንን እሳት ከሰማይ ወርዳ በላቻቸው::

ቅዱስ ዮሐንስ ከቅድስናው ብዛት ዘወትር ሲቀድስ መድኃኒታችንንና አእላፍ መላእክትን ያይ ነበር:: ከከዊነ እሳት ማዕረግ በመድረሱም አካሉ በመፈተት ሰዓት እንደ እሳት ይነድ ነበር:: እንባውም እንደ ውኃ ይፈስ ነበር::

ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ ጐን ዛሬም ድረስ የሚታወቅበትን ታላቅ ሥራም ሠርቷል:: መንፈስ ቅዱስ አነሳስቷቸው ቅዱሱና የሃገረ አትሪብ ጳጳስ የነበረው ሊቁ አባ ሚካኤል መጽሐፈ ስንክሳርን : መጽሐፈ ግጻዌንና ሃይማኖተ አበውን ለመጀመሪያ ጊዜ አዘጋጅተዋል::

"ስንክሳር" የቅዱሳንና የፈጣሪን ነገር በየዕለቱ የሚዘግብ መጽሐፍ ሲሆን "ግጻዌ" የየዕለቱን በዓላት ከምስባክና ምንባባት ጋር አስማምቶ የያዘ መጽሐፍ ነው:: "ሃይማኖተ አበው" ደግሞ የዶግማ መጽሐፍ ሆኖ ከሐዋርያት እስከ ሊቃውንት ድረስ የጻፉትን የያዘ ነው:: ሦስቱን የሚያመሳስላቸው "ስብስብ / እስትጉቡዕ / Collection" መሆናቸው ነው::

ቅዱሱ ዮሐንስ በሃገረ ቡርልስ በከፍተኛ ድካም ይህንን ፈጽሞ በዚህች ቀን ዐርፏል::

††† ✝አቡነ ስነ ኢየሱስ ጻድቅ✝ †††

††† ጻድቁ በመካከለኛው (የብርሃን) ዘመን የነበሩ ኢትዮጵያዊ::
*ከምድረ ሽዋ ወደ ታች አርማጭሆ የሔዱ መናኝ:
*ጭው ባለ በርሃ ለቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ ገዳምን ያነጹ አባት:
*ብዙ አርድእትን ያፈሩ መናኝ:

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

“ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ፤ በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ።”
  — ዳንኤል 9፥21

እንኳን ለሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Enkuan adrschew le keduse gebelel amtaw bael

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እንኳን ለ አብሳሪው መላክ ለ ቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በአል አደረሰሽ አደረሰክ የመላኩ ተራዳይነት ለሁላችንም ይሁን አሜን ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
ታህሳስ 19.04.2016

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ገብርኤል የሚለው መዝሙር ካላችሁ ላኩልኝ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የነገው ቀን ቅዱስ ገብርኤል ሠለስቱ ደቂቅን ከእሣት ያዳነበት እለት ነው

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Beze seat letegnu nw

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Enkuan abesaru kidus gaberial keberabal beselam aderesachu

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

😱 abate Thank U Lene Yadergewun Lenatem Yadergelachuh🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

▬▬ ✟ ▬ ▬ ▬ ▬ ✟ ▬▬
▬▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬▬
▬ ● #ለምትጠራኝ_ለአንተ ● ▬
▬▬▬▬ ▬▬▬▬ ▬▬▬▬

🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

ይቀላቀሉ ➟ @amanawikal
ለሌሎች ያጋሩ ➟ @amanawikal

መዝሙር ሊልኩልን ቢወዱ 👇
👉 @amanawikalbot

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እንካን ለመላኩ ቅዱስገብርኤል አመታዊ ክብረ በአል አደረሳቹ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Join belu mkran tkbluuu

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

selam enkuan aderesachihu

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Enkuwan Aderseachu lekedus gebrel ametawe beal🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

*ብዙ ተአምራትን የሠሩና ወንጌልን ያስተማሩ መነኮስ ናቸው::በደመናም ይጫኑ ነበር:: ገዳማቸውም (ታች አርማጭሆ: ከሳንጃ ከተማ የ3 ሰዓት መንገድ ይወስዳል) ድንቅና ባለ ብዙ ቃል ኪዳን ነው:: መልአከ ሞት መስከረም 1 ቀን ቢመጣ "የቅዱስ ገብርኤልን በዓል ሳላከብርአይሆንም" ብለው ለ3 ወራት በበራቸው አቁመውታል:: ታኅሣሥ 19 ቀንም ዐርፈዋል::

††† አምላከ ቅዱሳን በመልአኩ ረድኤት ጠብቆ ለጻድቃኑ በረከት ያብቃን::

††† ታኅሣሥ 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ዮሐንስ ዘቡርልስ
3.አቡነ ስነ ኢየሱስ ጻድቅ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
2.አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
3.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም
4.ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ

††† ". . . በአምላኬም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ተቀደሰው ስለ አምላኬ ተራራ ስለምን: ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ:: በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ:: አስተማረኝም . . ." †††
(ዳን. ፱፥፳)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

“ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ፤ በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ።”
  — ዳንኤል 9፥21

እንኳን ለሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://www.youtube.com/live/NzxQeIP_9eU?si=2LAo7KJJ470tv3ai

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

selam wed betesebochi🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እንኳን ለ አብሳሪው መላክ ለ ቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በአል አደረሰሽ አደረሰክ የመላኩ ተራዳይነት ለሁላችንም ይሁን አሜን ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
ታህሳስ 19.04.2016

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

                       †                       

  [   🕊  † †  ዋዜማ  † †   🕊  ]


💖 የራማው ልዑል ቅዱስ ገብርኤል 💖

[ † እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

------------------------------------------

[ የአቡነ አብርሃም ደቀ መዝሙር በመንበረ መንግስት ቅዱስ ገብርኤል ታህሳስ ፲፱ የተቀኙት ቅኔ ]


ገብርኤል አረጋዊ ይትዐጸፍ ምንተ ?
አመ ወርኃ ጥምቀት አልጸቀ
እስመ ነድ ልብሱ በሕጽበት ኀልቀ
ኅልቀተ ልብሱሰ ነድ ኢያስተኃዝኖ ጥዩቀ
አምጣነ እግዝእቱ ድንግል ትፈትል ወርቀ
ወእግዚኡ ያለብስ መብረቀ

ትርጉም ፦

[ አረጋዊው ገብርኤል የጥምቀት ወር በደረሰ ጊዜ ምን ይለብስ ይሆን
እሳት የሆነ ልብሱ በመታጠብ አልቋልና
የልብሱ ማለቅ ግን ፈጽሞ አያሳዝነውም
ድንግል እመቤቱ ወርቅን ትፈትላለችና
ጌታውም መብረቅን የሚያለብስ ነውና ]

ምስጢር ፦

[ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ታህሳስ ፲፱ ሠለስቱ ደቂቅን ከነደደው እሳት ሊያድናቸው ከአምላኩ ተልኮ ወደ እቶኑ ሲገባ "ለሠለስቱ ደቂቅ ዘአውረድከ ጠለ" ይለዋል እሳቱ ውኃ ሆነላቸው እርሱም በዚያ አብሯቸው ታይቷል ነገር ግን "ገብርኤል ነደ ወነበልባለ" እንዲለው እሳታዊ ልብሱ በውሃ ቢታጠብ አልቋልና [እሳት ውሃ ቢነካው እንዲጠፋ] ..... ይህስ የልብሱ ማለቅ "ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ...." ይባላልና ..... ምን ለብሼ እታያለሁ ብሎ አይጨንቀውም ከጥምቀቱ አስቀድሞ ታህሳስ ፳፪ ጽንሰት[ብሥራት] ይታሰባልና "ተፈስሒ" ብሎ ያበሰራት እመቤቱ ድንግል በእሳት ቢፈተን የሚነጥረውን ወርቅ ፈትላ ታለብሰዋለች

"አስተርአያ ገብርኤል ግብተ ወእንዘ ትፈትል ወርቀ ወሜላተ" ይላል ..... ጌታውም ቢሆን "እለ ይትለአክዎ መባርቅት ወየአውድዎ ነጎድጓድ" የተባለለት መብረቅን ያለብሰዋል....መልአኩን "ልብሱ ዘመብረቅ" ይለዋልና ለተልእኮ እንደመብረቅ የሚፋጠን ስለሆነ አንድም ዜና ብስራቱ እንደመብረቅ ስለሚሰማ ..... ለዚያ ነው በዚህ ክብር ተገልጾ በትንሳኤው ያየነው፡፡

"እነሆም፥ የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለ ወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ ፤ ቀርቦም ድንጋዩን አንከባሎ በላዩ ተቀመጠ። መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ።" [ማቴ. ፳፰፥፪ ]

† † መልካም በዓል ይሁንላችሁ † †

[ ዲ/ን ዶ/ር ቴዎድሮስ በለጠ ]

------------------------------------------

[  🕊  የቅዱስ ገብርኤል ምልጃና ጥበቃው አይለየን፡፡  🕊 ]

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እስቲ ስለ ዛሬው ቀን ሚስረዳኝ አለ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የእግዛብሄር ቤተሰቦች ሁላችሁም ደና እደሩ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ይቅርታ እንደዚ አይፃፍም Thank u

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ታህሳስ 19/4/2016 #ቅዱስ_ገብርኤል

እኔ #በእግዚአብሔር ፊት የምቆመዉ #ገብርኤል ነኝ ሉቃ1፣19

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በመልአኩ ስም ለምናመሰግንበት ለመልአኩ #ቅዱስ_ገብርኤል አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉ያን ጊዜም ናቡከደነፆር #በሲድራቅና_በሚሳቅ_በአብደናጎም ላይ ቍጣ ሞላበት የፊቱም መልክ ተለወጠባቸው እርሱም ተናገረ የእቶንም እሳት ይነድድ ከነበረው ይልቅ ሰባት እጥፍ አድርገው እንዲያነድዱት አዘዘ

👉 #ሲድራቅንና_ሚሳቅንም_አብደናጎንም ያስሩ ዘንድ ወደሚነድድም ወደ እቶን እሳት ይጥሉአቸው ዘንድ በሠራዊቱ ውስጥ ከነበሩት ኃያላን አዘዘ የዚያን ጊዜም እነዚህ ሰዎች ከሰናፊላቸውና ከቀሚሳቸው ከመጐናጸፊያቸውም ከቀረውም ልብሳቸው ጋር ታስረው በሚነድድ በእቶን እሳት ውስጥ ተጣሉ

👉የንጉሡም ትእዛዝ አስቸኳይ ስለሆነ የእቶኑም እሳት እጅግ ስለሚነድድ #ሲድራቅንና_ሚሳቅን_አብደናጎንም የጣሉአቸውን ሰዎች የእሳቱ ወላፈን ገደላቸው

👉እነዚህም ሦስቱ ሰዎች #ሲድራቅና_ሚሳቅ_አብደናጎም ታስረው በሚነድደው በእቶኑ እሳት ውስጥ ወደቁ የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ ፈጥኖም ተነሣ አማካሪዎቹንም ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን ብሎ ተናገራቸው

👉እነርሱም ንጉሥ ሆይ እውነት ነው ብለው ለንጉሡ መለሱለት እርሱም እነሆ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ ምንም አላቈሰላቸውም የአራተኛውም መልክ #የአማልክትን_ልጅ ይመስላል ብሎ መለሰ

👉የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር ወደሚነድደው ወደ እሳቱ እቶን በር ቀርቦ እናንተ #የልዑል_አምላክ_ባሪያዎች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ኑ ውጡ ብሎ ተናገራቸው

👉 #ሲድራቅና_ሚሳቅም_አብደናጎም ከእሳቱ መካከል ወጡ መሳፍንቱና ሹማምቶቹም አዛዦቹና የንጉሡ አማካሪዎች ተሰብስበው እሳቱ በእነዚያ ሰዎች አካል ላይ ኃይል እንዳልነበረው የራሳቸውም ጠጕር እንዳልተቃጠለች ሰናፊላቸውም እንዳልተለወጠ የእሳቱም ሽታ እንዳልደረሰባቸው አዩ

👉 #ናቡከደነፆርም መልሶ #መልአኩን የላከ ከአምላካቸውም በቀር ማንንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈ የሰጡትን የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ #የሲድራቅና #የሚሳቅ #የአብደናጎም አምላክ ይባረክ

👉እኔም እንደዚህ የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና #በሲድራቅና #በሚሳቅ #በአብደናጎም አምላክ ላይ የስድብን ነገር የሚናገር ወገንና ሕዝብ በልዩ ልዩም ቋንቋ የሚናገሩ ይቈረጣሉ ቤቶቻቸውም የጕድፍ መጣያ ይደረጋሉ ብዬ አዝዣለሁ አለ ትንቢተ ዳንኤል 3፥19 - 30

👉ከጭንቅና ከመከራ ለማውጣት የተላክህ #መልአክ ነህና #ሠለስቱ_ደቂቅን በእሳት ጉድጓድ በተጣሉ ጊዜ ሁለቱ ክንፎችህን ጋርደህ ከመቃጠል እንዳዳንሃቸው እኛንም የቃል ኪዳን ልጆችህን በረድኤትህ ኃይል አድነን

👉 #ገብርኤል ማለት ሰውና አምላክ ማለት ነው ቅዱስ ገብርኤል በአገልግሎቱ የሚጠራባቸው ስሞችም አሉት እመቤታችንን በማብሠሩ እንዲሁም ካህኑ ዘካርያስንም ልጅ እንደሚወልድ ስላበሠረ #መልአከ_ብሥራት ይባላል መጋቤ አዲስም ይባላል

👉አዳምና ልጆቹ የሰውን ልጆች ሁሉ ከሞት የሚያድን ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በሥጋ እንደሚወለድ የምሥራችን በማብሠሩ የሰው ልጆች አዲስ ሕይወትን እንደሚያገኙና ከጨለማ ሕይወት እንደሚወጡ የምስራች ስለተናገረ #መጋቤ_አዲስ ተብሎ ይጠራል

👉ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሣት #ከእግዚአብሔር ተልከህ እንዳዳንክ እኛንም ከክፉ መከራ ሁሉ አድነን ብስራታዊ መልአክም ነህና ለሀገራችንና ለህዝባችን መልካሙን የምስራች አሰማን #በእግዚአብሔር ፊት ለምስጋናና ለፀሎት የምትቆም መልአክ ነህና ለኛ ለልጆችህ በችግራችን በሐዘናችን ጊዜ ዋስ ጠበቃ ሁነህ ቁምልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ስላም ቤተሰብ እንኳን ለ ቅዱስ ገብርኤል ክብርባአል አደርሳቹ አደርሰን።

Читать полностью…
Subscribe to a channel