https://youtu.be/IZNIKpvCRuw?si=IlXtFt_Km2kBjOBi ሰብስክራይብ በማድረግ ይህን መንፈሳዊ አገልግሎት ያበረታቱ
Читать полностью…ይህንን ለ20 ለጎደኞቻቹ በመላክ ፕሮፋይሎን ማን አንዳየው አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ
/channel/who_save_my_profile_bot?start=r07043743915
አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ❤️
ሰማያዊ ምሥጢርህን ለመቀበል የተዘጋጀሁ ኢድርገኝ፤
አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣ በመለኮታዊ ማዕድህ እንድቀመጥ አድርገኝ፤
አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣ በቅዱሳንህ ደስ እንዳለህ ሁሉ በእኔም ደስ ይበልህ፤ አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣ ስፍገመገም ደግፈኝ፣ ከውድቀትም አንሣኝ፤
አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣ ከችግር አድነኝ፣ መከራዬንና ሕማሜንም ተመልከት፣ ኃጢአቴንም ይቅር በል፤
አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣ ከጠላቶቼና ከሚያሳድቁኝ ታደገኝ፤
አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣በአገልጋይህ ላይ ፊትህን አብራ፣ አቤቱ አልፈር፣ ጠርቼሃለሁና፣
አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣ መስቀልህ በምውልበት ቦታና በማድርበትም ሥፍራ ሁሉ ጠባቂ ይሁነኝ፤
አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣ ከሕፃንነቴ ጀምረህ ተስፋዬ አንተ ነህ፤
አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣ ከእናቴ ማኅፀን ጀምረህ አንተ አምላኬ ነህ፣ በማኅፀንም አንተ ሠወርከኝ፣ ሁሉም ጊዜ አንተ አሳቤዬ ነህ፧
አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣ የመድኃኒቴ ቀንድ አንተ ነህ፣
አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣ የእራሴ አክሊል አንተ ነህ፤
አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣ ለአፌ ጣፋጭ የሆንክ የሕይወት እንጀራ አንተ ነህ፤
አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣ ለጉሮሮዬ መልካም የሆንከ የመድኃኒት ጽዋዕ እንተ ነህ፤
አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣ ያልተሸመነ ጨርቅ፣ ያልተፈተለም ልብስ አንተ ነህ፤
አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣ እጥፍ የሆንክ ወርቅ፣ የተገኘህም ዕንቁ አንተ ነህ፤
አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣ የበዛ ምናን፣ የተተረፈም መክሊት አንተ ነህን፤
አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣ ስለ አዳምና ስለ ልጆቹ ስትል መከራን የተሸከምክ አንተ ነህ፤
አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣ በሔዋንና ልጆቿ ስሕተት ምክንያት የመስቀልን ሕማማት የተሸከምክ አንተ ነህ
አቤቱ በመንግስትህ በመጣህ ጊዜ አስበን!!!
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ!🙏
*በዚህች ምድር ላይ ለራሱ ብሎ የሚኖር አንድም ነገር የለም፤
* ወንዝ የራሱን ዉሃ አይጠጣም፣
* ባህር የራሱን ዓሳ አይበላም፣
* አትክልት የራሱን ፍሬ አይመገብም፣
* ፀሐይ የራሷን ሙቀት አትሞቅም፣
* ጨረቃ ለራሷ ብላ አትደምቅም፣
* አበባ ለራሱ ሲል አትፈካም፣
* ፍየል በግቷ የያዘችዉን ወተት አትጠጣም፣
- ነገሮች አንዱ ለሌላኛው እገዛ ነው የተፈጠሩት፣
- አንዱ ሌላው የጎደለዉን ለመሙላት ነው የተገኙት፣
- እኛም አንዳችን ለሌላኛችን እንኑር፣
- አንበላላ፣ አንጠፋፋ፣ እንተጋገዝ፣* ሀሳብ የገባዉን - አዳምጠው፣
* ያማከረህን - መላ ስጠው፣
* ይቅርታ የጠየቀህን - እለፈው፣
* ቸገረኝ ያለህን - እርዳው፣
በዙርያችን ያለ ነገሮች ሁሉ ይጠፉና በመጨረሻም የሚቀረው የሠራነው መልካም ሥራ ብቻ ነው፡፡* መልካምነት ዕድሜው ረጅም ነው፣
* መልካምነትም መልሶ ይከፍላል፣ ሰዉን በመጥቀም ይበልጥ የምንጠቀመው የምናድገውም እኛ መሆናችንን እንወቅ፣
#ዛሬን መልካም እናስብ፦#ነገም መልካም ይሆናል!!
🙌መልካም ቀን፤ ቸር ያሰማን፤ ቸር ያውለን🙌
....................#በቅንነት ያጋሩ
▹▹የእናቴ ልጅ-(Tame)◃◃
👉Telegram channels 👇
➱ /channel/Asresee
➱ /channel/Asresee
➱ /channel/Asresee
✝" #ጥር 1 "✝
<<< እንኩዋን ለቅዱስ "እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት" እና "ለአክሚም ሰማዕታት" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ >>>
+"ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕት"+
=>በሕገ ወንጌል (ክርስትና) የመጀመሪያው ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳሚው ሰማዕት ይህ ቅዱስ ነው:: ቅዱሱ በመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን አስገራሚ ማንነት ከነበራቸው እሥራኤላውያን አንዱ ነበር:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
+የቅዱስ እስጢፋኖስ ወላጆቹ ስምዖንና ማርያም ይባላሉ:: (ሌሎች ናቸው የሚሉም አሉ) ገና ከልጅነቱ ቁም ነገር ወዳድ የነበረው ቅዱስ በሥርዓተ ኦሪት አድጐ እድሜው ሲደርስ ወደ ት/ቤት ገባ:: የወቅቱ ታላቅ መምሕር ገማልያል ይባል ነበር:: ይህ ሰው በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 5:33 ላይ ተጠቅሷል::
+በትውፊት ትምሕርት ደግሞ ይህ ደግ (ትልቅ) ሰው በርካታ ቅዱሳንን (እስጢፋኖስን : ዻውሎስን : ናትናኤልን : ኒቆዲሞስን . . .) አስተምሯል:: በጌታችን መዋዕለ ስብከት ጊዜም ከፈጣሪያችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ እየቀረበ ይጨዋወት ነበር:: በፍጻሜውም አምኗል::
+ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ እስጢፋኖስ ከዚህ ምሑር ዘንድ ተምሮ: ኦሪቱን ነቢያቱን ጠንቅቆ ወጣ:: ወቅቱ አስቸጋሪና ለኃጢአት ሕይወት የተመቸ ቢሆንም ቅዱሱ ግን የመሲህን መምጣት በጸሎትና በተስፋ ይጠባበቅ ነበር::
+በወቅቱ ደግሞ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ የንስሃ ጥምቀትን እየሰበከ መምጣቱን የተመለከተ ቅዱስ እስጢፋኖስ ነገሩን መረመረ:: ከእግዚአብሔር ሆኖ ቢያገኘው የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሆነ:: ለ6 ወራትም በትጋት ቅዱስ ዮሐንስን አገለገለ::
+ለ6 ወራት ከቅዱስ ዮሐንስ ዘንድ ከተማረ በሁዋላ ለስም አጠራሩ ስግደት ይድረሰውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠመቀ:: በወቅቱ
የተደረገውን ታላቅ ተአምር ልብ ያለው ቅዱስ እስጢፋኖስ
መምሕሩን ቅዱስ ዮሐንስን እንዲያስረዳው ጠየቀው::
"ከእኔ ይልቅ
ከፈጣሪው አንደበት ይስማው" በሚል ላከው:: ቅዱሱም
ከጌታ ዘንድ ሔዶ: እጅ ነስቶ ተማረ:: (ሉቃ. 7:18)
በዚያውም
የጌታ ደቀ መዝሙር ሆኖ ቀረ:: ጌታም ከ72ቱ አርድእት
አንዱ አድርጐት ለአገልግሎት ላከው:: አጋንንትም
ተገዙለት::
(ሉቃ. 10:17)
ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታችን መድኃኔ
ዓለም ከዋለበት እየዋለ: ካደረበት እያደረ ወንጌልን
ተማረ::
ምሥጢር አስተረጐመ:: ጌታ በፈቃዱ ስለ እኛ ሙቶ
ከተነሳ በኋላ ሲያርግ ደቀ መዛሙርቱን በአንብሮ እድ
ባርኳል:: በዚህ
ጊዜም ቅዱሱ እንደ ወንድሞቹ ሐዋርያት ቅስናን
(ዽዽስናን) ተሹሟል:: በበዓለ ሃምሳም መንፈስ ቅዱስ
በወረደ ጊዜ ከ72ቱ
አርድእት የእርሱን ያህል ልሳን የበዛለት:ምሥጢርም
የተገለጠለት የለም:: በፍጹም ድፍረትም ወንጌልን
ይሰብክ ገባ::
በመጀመሪያይቱ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ከማዕድ ሥርዓት
ጋር በተያያዘ ፈተና ሲመጣ በመንፈስ ቅዱስ ምርጫ 7
ዲያቆናት
ሲመረጡ አንዱ እርሱ ነበር:: አልፎም የ6ቱ ዲያቆናት
አለቃ እና የ8ሺው ማሕበር መሪ (አስተዳዳሪ) ሆኗል::
8ሺ ሰውን
ከአጋንንት ፈተና መጠበቅ ምን ያህል ከባድ እንደ ሆነ
ለማወቅ አባቶቻችንን መጠየቅ ነው::
አንድን ሰው
ተቆጣጥሮ
ለድኅነት ማብቃት እንኳ እጅግ ፈተና ነው:: መጽሐፍ
እንደሚል ግን 'መንፈስ ቅዱስ የሞላበት: ማሕደረ
እግዚአብሔር'
ነውና ለእርሱ ተቻለው:: (ሐዋ. 6:5) አንዳንዶቻችን ቅዱስ
እስጢፋኖስ 'ሊቀ ዲያቆናት' ሲባል እንደ ዘመኑ ይመስለን
ይሆናል:: እርሱ በመጀመሪያ ሐዋርያና ካህን ነው::
ዲቁናው ለእርሱ 'በራት ላይ ዳረጐት' ነው እንጂ እንዲሁ
ዲያቆን
ብቻ አይደለም::
ቅዱስ እስጢፋኖስ ከጌታ ዕርገት በኋላ
ለ 1 ዓመት ያህል 8ሺውን ማኅበር እየመራ: ወንጌልን
እየሰበከ
ቢጋደል ኦሪት 'እጠፋ እጠፋ': ወንጌል ደግሞ 'እሰፋ እሰፋ'
አለች:: በዚህ ጊዜ 'ክርስትናን ለማጥፋት መፍትሔው
ቅዱስ
እስጢፋኖስን መግደል
ነው' ብለው አይሁድ በማመናቸው ሊገልድሉት አስበውም
አልቀሩ ገደሉት::
+እርሱ ግን ፊቱ እንደ እግዚአብሔር መልአክ እያበራ
ፈጣሪውን በብዙ ነገር መሰለው:: በመጨረሻውም ስለ
እነሱ ምሕረትን
እየለመነ በድንጋይ ወገሩት:: ደቀ መዛሙርቱም ታላቅ
ለቅሶን እያለቀሱ ቀበሩት::
*"ፍልሠት"*
+ቅዱስ እስጢፋኖስ ካረፈ ከ300 ዓመታት በኋላ
በኢየሩሳሌም የሚኖር አንድ ደግ ሰው ነበር:: ስሙም
ሉክያኖስ ይባል
ነበር:: በተደጋጋሚ በራዕይ ቅዱሱ እየተገለጠ "ሥጋየን
አውጣ" ይለው ነበርና ሒዶ ለዻዻሱ ነገረው:: ዻዻሱም
ደስ ብሎት
ካህናትና ምዕመናንን ሰብስቦ ወደ አጸደ ገማልያል
(የመምሕሩ ርስት ነው) ሔደ::
+ቦታውንም በቆፈሩ ጊዜ ታላቅ መነዋወጥ ሆነ::
መላእክት ሲያጥኑ በጐ መዓዛ ሸተተ:: ዝማሬ መላእክትም
ተሰማ:: ሕዝቡና
ዻዻሱም በቅዱስ እስጢፋኖስ ፊት ሰግደው: በታላቅ
ዝማሬና በሐሴት ዐጽሙን ከዚያ አውጥተው: በጽርሐ
ጽዮን (በተቀደሰችው
ቤት) አኖሩት::
እለ እስክንድሮስ የተባለ ደግ ሰውም ቤተ
ክርስቲያን አንጾለት ወደዚያ አገቡት:: ከ5 ዓመታት
በኋላም
እለ እስክንድሮስ ሲያርፍ በሳጥን አድርገው በቅዱሱ ጐን
ስለ ፍቅሩ አኖሩት::ሚስቱ ወደ ሃገሯ ቁስጥንጥንያ
ስትመለስ
የባሏን ሥጋ መስሏት የቅዱስ እስጢፋኖስን ቅዱስ ሥጋ
በመርከብ ጭና ወሰደችው:: መንገድ ላይ ከሳጥኑ ውስጥ
ዝማሬ ሰምታ
ብታየው ያመጣችው የቅዱሱን ሥጋ ነው:: እጅግ ደስ
አላት: አምላክ ለዚህ አድሏታልና::
እርሷም ወስዳ ለታላቁ
ንጉሥ
ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ አስረከበች:: በከተማውም ታላቅ
ሐሴት ተደረገ::ሥጋውን ሊያኖሩት በበቅሎ ጭነው
ሲወስዱትም በቅሎዋ
በሰው ልሳን ተናግራ ማረፊያውን አሳወቀች:: በዚያም ላይ
ትልቅ ቤተ ክርስቲያን ታንጾለታል:: ቅዱስ እስጢፋኖስ
ሲመቱ
ጥቅምት 17: ዕረፍቱ ጥር 1:ፍልሠቱ ደግሞ መስከረም
15 ቀን ነው::
'' ሰማዕታተ አክሚም ''
+በቤተ ክርስቲያን የሐዲስ ኪዳን ታሪክ አሰቃቂ ጭፍጨፋ
ከተካሔደባቸው አካባቢዎች አንዷ ሃገረ አክሚም ናት::
አክሚም
ማለት የቀድሞ የግብጽ አውራጃ ናት:: በተለይ በ3ኛው
መቶ ክ/ዘመን በርካታ ክርስቲያኖች በፍቅር ይኖሩባት
ነበር::
በከተማዋ ውስጥ የሚኖሩ ክርስቲያኖች ጥቡዓን:
ታማኞች:ሥጋውን ደሙን የሚቀበሉና ዘወትር ቅዱስ ቃሉን
ለመስማት
የሚተጉ ነበሩ:: ለዚህም ደግሞ ከሊቀ ዻዻሱ አባ
ብኑድያስ ጀምሮ ካህናቱ: ዲያቆናቱ: ንፍቅ ዲያቆናቱ:
መጋቢዎቹ:
አናጉንስጢሶቹ (አንባቢዎቹ): መምሕራኑ: መሣፍንቱም
ሳይቀር ለክርስቶስ ፍቅር የተጉ መሆናቸው አስተዋጽኦ
ነበረው::
በተለይ ግን 2 ወንድማማቾች የነበራቸው ቅድስና
ብዙዎችን ስቧል:: እኒህ ቅዱሳን ዲዮስቆሮስና ሰከላብዮስ
ይባላሉ::
ከባለ ጸጋና ባለ ስልጣን ቤተሰብ ቢወለዱም ክርስትናቸው
አልቀዘቀዘም:: የወጣትነት ስሜት ሳያሸንፋቸውም ወደ
በርሃ ተጓዙ::
+በዚያም በቅድስና ኑረው ለክህነት ማዕረግ በቅተዋል::
ቅዱሳኑ በገዳም ሳሉም መድኃኒታችን ክርስቶስ ተገልጦ
"ወደ ትውልድ ሃገራችሁ አክሚም ተመለሱ:: ክብረ ሰማዕታት ይጠብቃቹሃል" አላቸው:: እነርሱም ደስ እያላቸው
በፍጥነት ወደ
አክሚም ወጡ::በዚያ ሰሞን የጌና ጾም ተፈጽሞ
የአክሚም ክርስቲያኖች ለበዓለ ልደት ዝግጅት ሲያደርጉ
በጠላት ሠራዊት
ተከበቡ::ይህ ሠራዊት የተላከው ከርጉም
ዲዮቅልጢያኖስ ሲሆን መሪው ደግሞ አርያኖስ ነው::
የዘላለም አባት
“ሕፃን ተወልዶልናልና፤ ወንድ ልጅ ተሰጥቶናል፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል። ስሙም(שְׁמ֜ו)፣ ድንቅ መካር፣ ኀያል አምላክ፣ የዘላለም አባት (אֲבִיעַ֖ד)፣ የሰላም ልዑል ይባላል።” ኢሳይያስ 9፥6
1ኛ. “ስሙም” ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል “ሼሙ” שְׁמ֜וֹ የሚል ሲሆን שֵׁם “ሼም” ከሚለው ቃል የመጣ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ስም ባሕሪን ማንነትን ይወክላል። ለምሳሌ የእግዚአብሔር ስም ባሕርዩን ይወክላል (ዘፀአት 33፡17-23፣ 34፡5-7)፡፡
የእግዚአብሔርን ስም ማመስገን ማለት እግዚአብሔርን ማመስገን ማለት ነው (መዝሙር 7፡17)፡፡ የእግዚአብሔር ስም ረዳታችን እንደሆነ መናገር እግዚአብሔር ረዳታችን እንደሆነ መናገር ነው (መዝሙር 124፡8፣ 121፡2)፡፡
በእግዚአብሔር ስም መምጣት ማለት በእግዚአብሔር ኃይል መምጣት ማለት ነው (1ሳሙኤል 17፡45፣ ዮሐንስ 5፡43)፡፡ ስለዚህ ድንቅ “መካር፣ ኃያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም አለቃ” የሚለው የሕፃኑ ስሞች ማንነቱን የሚገልጹ በመሆናቸው አምላክነቱን ያጸናል።
2ኛ. በብሉይ ኪዳንም ሆነ በዕብራውያንና በዐረቡ ባህል፣ "አባት" (በዕብራይስጡ אָב “አቭ”) በተፀውዖ (በመጠርያ) ስምነት ካገለገለ፣ የስሙ ባለቤት (በዚህ ቃል የሚጠራው ግለሰብ) ከሚጠራበት ስም ጋር አንድ አይነት ባህርይ አለው ማለት ነው።
በርከት ያሉ አስረጆችን እንመልከት፦ אֲבִי-עַלְבוֹן
“አቢዓልቦን”(2ሳሙ 23፥31) የሚለው ጣምራ ስም “አቢ” אֲב ማለትም "አባት" እንዲሁም “ዓልቦን”עַלְבוֹן ማለት “ጠንካራ” ከሚሉት ቃላት የተዋቀረ ነው። አጫፍረን ስናነበው “የጥንካሬ አባት” ወይም “እጅግ በጣም ጠንካራ” የሚል ትርጉም ይወክላል።
אֲבִיגַיִל “አቢጋኤል” (1ዜና 2:16) “አቢ ማለት “አባት” እንዲሁም "ጋኤል" ማለት "ጠንካራ" በተገናኝ "የጥንካሬ አባት" ወይም "እጅግ በጣም ጠንካራ" ማለት ነው። አቢጋኤል የሚለው ስም የሴት መጠሪያ መሆኑን ልብ ይሏል። አባት ነሽ ማለት ሳይሆን፣ ከፍ ያልሽ ነሽ ማለት ብቻ ነው።
በአጭሩ "አብ" ወይም አባት የሚለው ቃል አባትነትን የሚያሳይ ሳይሆን፣ ከፊት ለፊቱ ያለውን ስም የሚያደምቅ ቅፅል ነው፤ ይኸውም "የጥንካሬ አባት" በጣም ጠንካራ፣ "የመሰብሰብ አባት" እጅግ በጣም ታላቅ ሰብሳብ "ከፍ የማለት አባት" እጅግ በጣም ከፍ ያለች...ወዘተ።
በኢሳይያስ 9÷6 "የዘላለም አባት" ተብሎ የተተረጎመው ቃል በዕብራይስጥ "አቢአድ" ከሁለት ስሞች የተጫፈረ ስያሜ ነው። ይኸውም "አብ" እና "አድ" ከሚሉት ቃላት ሲሆን፣ ትርጉሙም "አባት" እና “ዘላለም” ማለት" ነው። ይኽም ደግሞ ከላይ እንዳየናቸው "በአባት" እንደ ተጫፈሩ ስያሜዎች፣ የክርስቶስን ዘላለማዊ አባትነትን የሚያሳይ ነው። ይኽንን እውነታ ክርስትና ከመጀመሩ ከብዙ ዓመታት በፊት የነበሩ የአይሁድ ሊቃውንት መሲሑ የዘላለም አባት መባሉ ዘላለማዊነቱን እንደሚያሳይ አስፍረዋል።
ለምሳሌ፦“ልጅ ተወልዶልናል ፣ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል። . ስሙም ድንቅ መካር ፣ ኃያል አምላክ ፣ ለዘላለም የሚኖር (ዘላለማዊ) ተብሎ ይጠራል። በዘመኑም ሰላምን የሚያበዛልን መሲህ ነው ”
ማጠቃለያ
ስለዚህ መሲሑ የዘላለም አባት (አቢያድ) መባሉ የዘላለም ምንጭ- የሁሉ ነገር ፈጣሪ መሆኑን ያሳያል።(ዮሐ. 1፥3 ፤ ቆላ. 1፥ 16-17 ፤ 1 ቆሮ. 8፥6 ፤ ዕብ. 1፥2 ፣ 10-12 ፤)
መ/ር ንዋይ ካሳሁን
+አባ ዮሐንስ ብጹዕም እንዲህ ባለ ፈሊጥ: ማለትም በጾምና በጸሎት: ከዓለም ተለይቶ: ከሴት ርቆ: ንጽሕ ጠብቆ ሲኖር አረጀ:: በጊዜው በከተማ የሚኖር አንድ መስፍን ወዳጅ ነበረው:: ይህ መስፍን ዘወትር ወደ ጻድቁ እየመጣ ይባረካል::+ሚስቱ ግን በረከቱን ሽታ ልታየው ብትሞክርም አልተሳካም:: ሕገ ምናኔ አይፈቅድምና:: በዚህ ነገር ፈጽማ ማዘኗን በጸጋ ያወቀው አባ ዮሐንስ ግን በራዕይ ወደ እርሷ መጣ::+"ሚ ሊተ ወለኪ ብእሲቶ - አንቺ ሆይ! ለምን ካላየሁህ እያልሽ ትዘበዝቢኛለሽ? እኔ ነቢይ ወይ ጻድቅ አይደለሁ" ብሏት ባርኯ ተሠወራት:: እርሷም ደስ ብሏት ለባሏ ነገረችው:: ባሏ ወደ ጻድቁ ሲሔድም ገና ሳይነጋገሩአባ ዮሐንስ ሳቅ ብሎ "ሚስትህ ደስ አላት አይደል?" ብሎታል:: ጻድቁ በ90 ዓመቱ በዚህች ቀን ዐርፎ ተቀብሯል::
=>አምላከ ጻድቃን ቅዱሳን ስለ ወዳጆቹ በጐ ምኞታችንን ይፈጽምልን:: ከበረከታቸውም ያድለን::
=>ታሕሳስ 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አባ ዮሐንስ አበ ምኔት
2.አባ ዘካርያስ ገዳማዊ
3.አባ ዮሐንስ ብጹዕ
4."144 ሺ" ሕጻናት (ሔሮድስ የገደላቸው)
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
3.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
4.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
5.አባ ሣሉሲ ክቡር ጻድቅ
=>+"+ ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኑራችሁ: ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ:: እንደሚታዘዙ ልጆች ባለ ማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ:: ዳሩ ግን 'እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ' ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሯችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ:: +"+ (1ዼጥ. 1:13)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
የጡሎ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤ/ክ
በምዕራብ ሀረርጌ ዞን
ትንሽ ከጡሎ ከተማ ወጣ ተብሎ
ወልተኢ በሚባል ቦታ ላይ ይገኛል ይህ ቤ/ክ
አባቶች እንደሚናገሩት ከተሰራ 135 አመቱ ሆኖታል እሚገርም ነገር አሁንም ለብዙ አመታት ሊቆይ ይችልላ በስእሉ ላይ እንደ ምትመለከቱት በ2015 በረንዳው እስሩ ብቻ ነው የታደሰው መድረኩም በዚው አመት ነው የተሰራ በዚ ውስጥም የ 70 እና ከዚያ በላይ እድሜቸው የሆኑት አባቶች ናቸው እሚያገለግሉት ይህን አመታት እንዲህ መቆየቱ ራሱ የ አቡዬ አንድ ድንቅ ታምራቱ ነው
Mana amantaa xuulloo abune gebre menfes iddoon argama isaa hararge lixaa magaalaa xuulloorraa
Gara walta'itti argama
Akka abbonni jedhanitti manni amantaa kun erga ijaarame waggota 135 lakkofsisera
Kan nama dinku keessaa ammalle betakirstanni waggaa baay’ee turu danda'a akkuma suraa irratti srgitan bara 2015 keessa barandaan jalli qiftiin haaromfame madrakiniis baruma kana tolfame malee betakirstanni akkuma ijaarametti jira
abbotiin achii keessa tajaajilan abbooti baay’ee umriin deemanidha
70 faadha umriin isaani
/channel/hamsaleiyerusalem
/channel/tuloabuye
እናታችን ቅድስት
ድንግል ማርያም💕
👉የብርሃን መስኮት የፀሐይ መውጫ የገነት ቁልፍ፣ ደም ግባትንና ምስጋናን የተሞላች ናት።
👉 የሁላችን እመቤት የሁላችን ንግሥት የሁላችን መዳኛ የሁላችን መመኪያ ድንግል ማርያም ቅድስት ንጽሕት በየጊዜያቱና በየዕለቱም ጽርእት /የጠራች/ ናት። የርስታችን መጀመሪያ፣ የነጻነታችንም ምስክር ለክብራችንም የሽልማታችን ገጥ ናት። ለራሳችንም የሃይማኖት መጠምጠሚያ ሻሽ ለአንገታችንም የወርቅ ማርዳ፣ ለጆሮአችንም የወርቅ ጉትቻ፣ ለዐይኖቻችንም የናጌብ ኩል ናት። ለእጃችንም የወርቅ አንባር ናት።
👉ለጣቶቻችን የሽልማት ቀለበት ፡ ለእግሮቻችንም የድኅነት ጫማ ለራቁትነታችንም የመመካት ልብስ ናት። ለራባችን ጊዜም መና ያለባት የወርቅ መሶብ ናት። ለመጠማታችንም ወይንን የያዘች የወርቅ ጽዋ ናት። ለሞቱት ሕይወትን ትሰጣለች። ለታመሙት ፈውስን ለተቸገሩትም ሀብትን ትሰጣለች። ለተዋረዱትም ክብርን ታቀዳጃለች።
👉የአዳም መድኃኒት ሆይ የአቤል መሥዋዕት ተቀባይነትን ያስገኘሽ፣ የሴት ዘሮች መባዣ የሄኖክ ነፍስ ሕይወቱ የማቱሳላ ዘመን እርዝማኔም አንቺ ነሽ። የላሜህ ዕረፍቱ ስምንቱ ነፍሳት ከስጥመት የዳኑባት የኖኅ መርከብ አንቺ ነሽ። ለሴም የተሰጠው ሀብቱ፣ ያፌት የተባረከባት ሀብቱ አንቺ ነሽ። የካም መርገምን ያስወገድሽም አንቺ ነሽ።
👉 የመልከ ጼዴቅ መሥዋዕት እጅ መንሻ አንቺ ነሽ። በወርቁ የዋጃት /የገዛት/ ያማረች የአብርሃም እርሻ አንቺ ነሽ። የይስሐቅ የድኅነቱ ተራራ አንቺ ነሽ። የእግዚአብሔር መላእክት ሲወጡባት ሲወርዱባት፣ በላይዋ እግዚአብሔር ተቀምጦባት እስራኤል የተባለ ያዕቆብ ያያት የወርቅ መሰላል አንቺ ነሽ። የዐሥራ ሁለቱ የያዕቆብ ልጆች የደስታ ርስታቸው አንቺ ነሽ። ማርና ወተትን የምታዘንም ምድርም አንቺ ነሽ።
👉 ለንግሥና የተመረጠ የይሁዳ ነገድ ውዳሴ አንቺ ነሽ። መሥዋዕትን ለማሳረግ የተመረጠ የሌዊ የክህነቱ ቅባትም አንቺ ነሽ። ከምስጋና ጋር ለዮሴፍ የገርነት ሀብቱ አንቺ ነሽ። የኤፍሬምና የምናሴ ቡራኬያቸው አንቺ ነሽ። ለሙሴ የተሰጠች ሕጉ የተጻፈባት ጽላት የቃል ኪዳኑ ታቦት አንቺ ነሽ። የሚያመስግኑ የኪሩቤል ሥዕል አንቺ ነሽ።
👉በምስክሩ ድንኳን የበቀለች፣ ያበበች ውኃ ሳያጠጧት በኩሮ ሎሚን ያፈራች የአሮን በትር አንቺ ነሽ። ዳግመኛም ሰማይን የምትመስል የምስክር ድንኳን አንቺ ነሽ። ዳግመኛም ዮሴዕ ለተባለ ለኢያሱ የማሸነፊያ መሣሪያው አንቺ ነሽ። የእርሱ የምስክርነቱ ሐውልት አንቺ ነሽ። በሶምሶን ጀርባ ውስጥ ያለሽ ኃይል አንቺ ነሽ። የጌዴዎን ፀምር የጠል መቅጃው አንቺ ነሽ። የባርቅና የዲቦራን ጠላቶች የምታስገዢላቸው አንቺ ነሽ። ሲሳራን የገደለችው የኢያኤል በረከትም አንቺ ነሽ።
👉ወጋሕታ ሐበሻ እና ሽፎን ስፌትና መሸጫ💃💃💃💃💃💃💃💃👗👗👗 ይደዉሉሉን አዳዲስ ሽፎኖች አዘጋጅቶ ደንበኞቹን እያስተናገደ ይገኛል መርጣቹ ይደዉሉሉን📞📞☎️☎️☎️ ሰርተን በሰዓቱ እና ጥራቱን የጠበቀ ልብስ ሰፍተን እንሰጣቸዋለን ወደምትፈልጉት ቦታ እንልካለን 🚘✈️🚕🛫🛫 ለበለጠ መረጃ 251912448561👌👌/channel/wegahta4 በዚ ቴሌግራም በመግባት መምረጥ ትችላላቹ 💃💃👌
Читать полностью…ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን ለመድሐኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ!አደረሰን!!
መልካም የገና በዓል!
ተወለደ
""""""""""
የዓለማት ጌታ ተወለደ ግርግም
አምላክ ሆኖ እንደ ሰው ክብር አይፈልግም
በቤተልሄም ከድንግል ማርያም እቅፍ ተገኘ
በእየሱስ ልደት ዓለም በሙሉ ደስ ተሰኘ
ሰብዐ ሰገል
ከምስራቅ መጥተው መባ አቀረቡ
መላእክት ወርደው የመወለዱን ዜና አሰሙ
የዳዊት ህልሙ
የአዳም ድህነቱ መንገድ ጀመረ
ከሺ ዘመናት አምላክ የገባው ቃልም ነበረ
ቃል ስጋ ሆነ ከአዳም አካል ፍፁም ተዋህዶ
ከመቶ ነገድ አንዱን የሰው ልጅ እግዚአብሔር ወዶ
መላእክት ሁሉ መልኩን ለማየት ከቶ ማይችሉ
ከላይ ሳይጎድል በግርግም ቢያዩት አመሰገኑ
ሁሉን የሚችል አንድ ያልጎደለው
ከዓርያም ኪሩብ
ከምድር ሰለሞን በወርቅ ያስጌጠው
እፁብ ቤት ሳለው
ማደርያ ጠፍቶ ሲወለድ ግርግም
እንዴት አይደንቅ እንዴት አይገርም
ሙሴ በሲና ሲነድ ያየውን ነበልባል እሳት
እርሱን ለማሞቅ ትንፋሽ ሲሰጡት ግርግም እንስሳት
ከቶ እንዴት አይደንቅ ከቶ እንዴት አይገርም
የፍጥረታት ጌታ ሲወለድ በግርግም
ስምዖን ተግቶ የጠበቀውም መፅናናት ሆነ
ልደቱን አይቶ.......አምላኩን አቅፎ አመሰገነ
በአማኑኤል ልደት ዓለም በሙሉ ብርሀን ሆነ
🌲እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ።
በዓሉ የደስታ እና የሰላም እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ::
🌲 መልካም የገና በዓል! 🌲
...💚 /channel/Asresee
...💛 /channel/Asresee
...❤️ /channel/Asresee
ጥር 3/2016 #አባ_ሊባኖስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለአባታችን #ለአባ_ሊባኖስ አመታዊ የእረፍት በአል መታሠቢያ እንኳን አደረሰን
👉የዚህ ቅዱስ የአባቱ ስም #አብርሃም የእናቱም ስም #ንግሥት ነው እነርሱም በወርቅና በብር እጅግ የበለፀጉ ሮማዊ ናቸው ልጃቸውን #አባ_ሊባኖስን በሃይማኖት በምግባር ኮትኩተው ካሳደጓቸው በኋላ ዕድሜያቸው ለአቅመ አዳም ሲደርስ በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ያጋቧቸው ዘንድ ከቁስጥንጥንያ አገር ሚስት ባመጡለት ጊዜ እርሱ ግን ፈጽሞ እምቢ አለ
👉ወደ ጫጉላ ቤትም መግባትን እምቢ አለ በዚህም ጊዜ ነቢዩ ሳሙኤልን እንደጠራው አባታችንንም #እግዚአብሔር ሦስት ጊዜ በስማቸው ጠራቸውና ከአባትህ ተለይ አንተ የመንግሥተ ሰማያት ሙሽራ ነህ እንጂ የዚህ ምድራዊ ዓለም ሙሽራ አይደለህም አላቸው አባታችንም ወዴት እሄዳለሁ ምንስ ላድርግ ባሉ ጊዜ ወዲያው የታዘዘ መልአክ በሌሊት መጥቶ ከአባታቸው ቤት አውጥቶ ታላቁ አባት #አባ_ጳኩሚስ ዘንድ አደረሳቸው ታላቁ አባት አባ ጳኩሚስም #ለአባ_ሊባኖስ በዓት በመስጠት ገዳመ ሥርዓትን አስኬማ መላእክትን ቅናተ ዮሐንስን አስተምረዋቸው አመነኮሷቸውና ከ8ቱ ቅዱሳን ጋር እንዲገናኙ አደረጓቸው፡
👉ከዚህም በኋላ ያ ከአባታቸው ቤት ወስዶ #አባ_ጳኩሚስ ገዳም ያደረሳቸው ያ መልአክ ድጋሚ ተገለጠላቸውና ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ሂድና ተጋድሎህን በዚያ ፈጽም ዝናህ በስፋት ይነገራል ለብዙዎችም አባት ትሆናቸዋለህ አላቸው ቀጥሎም ራሱ መልአኩ ወደ ኢትዮጵያ አመጣቸውና በአክሱም ተቀመጡ
👉በዚያም ብዙ ከተጋደሉ በኋላ ወደ ሸዋ መጡና ወንጌልን ዞረው አስተምረው ብዙ ድውያንን ፈውሰው ከዓመታት ቆይታ በኋላ ተመልሰው አክሱም ሄዱ በአክሱምም 7 የተለያዩ ፀበሎችን ከድንጋይ ላይ በተአምራት አፍልቀው ድውያንን ፈውሰው ዕውራንን አበሩ በዓታቸውንም ከአክሱም ጽዮን ፊት ለፊት አድርገው ሲኖሩ ከዕለታት በአንደኛው ቀን አባታችን በተአምራት ከጭንጫ ካፈለቁት ፀበል ተራ ውሃ ነው ብላ አንዲት ሴት ልጇን አዝላ ልትቀዳ መጣች ወዲውም ከቦታው ስትደርስ አድጧት ወደቀችና ልጇም አምልጥቷት ልቡን ድንጋይ መቶት ሞተ ሴትዮዋም ስትጮህ #አባ_ሊባኖስ ፈጥነው ወጡና በልጁ ላይ ጸልየው በመስቀል ምልክት አማትበው ከሞት አስነሥተውታል ሕፃኑ ልጅ ከሞት እንደተነሣ #አምላከ_አባ_ሊባኖስ ብሎ አመሰገነ
👉ይህንንም ደግ ሥራቸውንና ተአምራታቸውን ያዩ አንዳንድ እኩይ ካህናት በቅናት ተመልተው ምትሃት ነው የሚያሳየው ብለው በጻድቁ ላይ ሕዝቡን አሳደሙባቸው #አባታችንም ካህናቱን ለመምከር ቢሞክሩም አላስቀምጥ አሏቸው ይልቁንም ጦር ጦራቸውን ይዘው አሳደዷቸው አባታችንም በዚህ እጅግ አዝነው ከአክሱም ተነሥተው ደርቃ ወደምትባል ቦታ ሄዱ
👉በዚያም በፆም በጸሎት እየተጋደሉ ሲኖሩ በእነዚያ በጠሏቸውና በክፋት በተነሡባቸው ካህናት አገር ግን ለ3 ዓመት ምንም ዝናብ ሳይዘንብ ቀረ አባታችን በተሰደዱባት በደርቃ አገር ግን ብዙ ዝናብ ይዘንብ ነበር አባታችን በዚያችም አገር እንደልማዳቸው ከዐለት ላይ ውኃ አፍልቀው በውኃው ብዙ ድውያንን ፈውሰውበታል በዚያም ትልቅ በዓት መሥርተው በተጋድሎ ሲኖሩ በክፉ የተነሡባቸው እኩይ የሆኑ ካህናት መጥተው #አባታችን በከንቱ አምተንሃል በድለንሃልና ይቅር በለን በድርቅ ማለቃችን ነውና ዝናብም እንዲዘንብልን #ፀልይን ብለው ከእግራቸው ሥር ወደቁ አባታችንም ይቅር ብለው ከፈጣሪ አማለዷቸው ዝናቡም ወዲያው ዘነበላቸውና በአገሪቱ ጥጋብ ሆነ
👉ከዚህም በኋላ አባታችን አስቀድመው ወዳዩአት ወደ ሸዋ ምድር ግራርያ መጡና በዓታቸውን በአሰቦት ጫካ አደረጉ ነገር ግን መልአኩ ተገልጦላቸው #ሊባኖስ ሆይ ከዚህ ቦታ የአንተ መኖሪያ አይደለም በዚህ ቦታ ላይ #እግዚአብሔርንና ሰውን የሚያገናኝ የሚያስታርቅ ታላቅ ፃድቅ ይወጣበታልና ይህ ቦታ የእርሱ ርስት ነው የብዙ መነኮሳትም መንደር ይሆናል ነገር ግን የቦታው ስም በአንተ ስም ይጠራልሃል አላቸው
👉በኋላ አባታችን #ተክለ_ሃይማኖት ተወልደው በዓታቸውን በዚያ ቦታ ላይ ሲያፀኑ ቦታው ግን ደብረ ሊባኖስ ተብሎ በመጀመሪያው አባት ስም ተሰየመ መልአኩም በሌሊት እየመራ ወደ አክሱም ወሰዳቸው ከዚያም ታሪክ ወደምትሠራበት ዕጣ ክፍልህ ወደሆነው ቦታ አደርስሃለሁ አላቸውና ወደ ኤርትራ አካለ ጉዛይ አውራጃ ልዩ ስሙ መጣዕ ወደተባለው ቦታ ወሰዳቸው
👉በዚያም አባታችን ድውያንን እየፈወሱ ለምፃሞችን እያዳኑ ሙታንን እያስነሡ ብዙ ተአምራትን እያደረጉ ወንጌልን እየሰበኩ #ሊባኖስ_ዘመጣዕ የሚባለውን ትልቁን ገዳማቸውን መሠረቱ በወቅቱ የነበረው ዐፄ ገብረ መስቀልም የመጀመሪያውን ቤተ ክርስቲያን አሠራላቸው፡፡
👉ቅዱስ ላሊበላ 23 ዓመት ሙሉ ካነፃቸው እጅግ ድንቅ 11 ቤተ መቅደሶች ውስጥ አንደኛውን #በአባ_ሊባኖስ ስም ሰይሞላቸዋል በዐፄ ገብረ መስቀል ያሠራላቸው ሌላኛው ገዳማቸው ትግራይ ተንቤን ውስጥ ይገኛል
👉እጅግ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ የሚታወቁት አባታችን እንደ ተስዓቱ ቅዱሳን ከሮም በመምጣት በሀገራችን ላይ ብርሃንን አብርተዋል በመጨረሻም ጥቅምት 2 ቀን ተፀንሰው ሐምሌ 3 ቀን ተወልደው ጥር 3 ቀን ባታላቅ ክብር ዐርፈዋል ቅዳሴ ቤታቸው ደግሞ ሐምሌ 3 ቀን ነው ይኸውም ለመጀመሪያ ጊዜ #በዐፄ_ገብረ_መስቀል ጊዜ በስማቸው ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶ የተመረቀበት ዕለት ነው፡፡
👉 #ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ምልጃ ፀሎቷቸዉ ይጠብቀን የከበረዉ ቃል ኪዳናቸዉ ለዘላለሙ አይለየን "አሜን"
👉ጊዜዉ ያላችሁ #በእንጦጦ_ኪዳነ_ምህረት በታላቅ ድምቀት ይከበራል በቦታዉ ተገኝታችሁ የበረከቱ ተሣታፊ ሁኑ
ጥር 3/2016 #ባዕታ_ማርያም
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በእናታችን #ባዕታ_ማርያም ስም ለምናመሰግንበት ለእናታችን #ባዕታ #ማርያም ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉እመቤታችን ከአባቷ ከቅዱስ #ኢያቄም ከእናቷ ከቅድስት #ሐና ከሊባኖስ ሙሽራ ትወጣለች ተብሎ በተነገረው መሠረት ነሐሴ 7 ቀን ተፀነሰች ግንቦት1ቀን ሊባኖስ በምትባል አካባቢ ተወለደች፡፡
👉እመቤታችን በጾም በጸሎትም የተገኘች የስዕለት ልጅ ናት ንጽሕት በመሆኗም #የእግዚአብሔር_ማደሪያ ሆናለች ከዚህ በኋላ እመቤታችን በእናት በአባቷ ቤት ፫ ዓመት ተቀመጠች
👉ኢያቄምና ሐናም ልጃቸውን ሲያሳድጉ ስላደረገላቸውም ሁሉ #እግዚአብሔርን ፈጽመው እያመሰገኑት 3 ዓመት ኖሩ በፆም እና በጸሎት ተወስነው ለድሆችና ለጦም አደሮች ምጽዋት እየሰጡ በጐ ሥራን አበዙ
👉ልጃቸውንም ድንግል ማርያምን በንጽሕና ሲያሳድጉ ሦስት ዓመቷ በተፈጸመ ጊዜ #ሐና ባሏን #ኢያቄምን ወንድሜ ሆይ ልጃችንን ለቤተ እግዚአብሔር ብፅዐት አድርገን እንስጥ ልጃችን ቤተ #እግዚአብሔርን ልታገለግል እንጂ በዚህ ዓለም እኛን ልታገለግል እንዳልተሳልን አስብ አለችው #ኢያቄምም ይህን ነገር ከሚስቱ በሰማ ጊዜ ደስ አለው
👉ነቢየ #እግዚአብሔር ዳዊት ልጄ ሆይ ስሚ እይ ጆሮሽንም አዘንብዪ ወገንሽን የአባትሽንም ቤት እርሺ ንጉሥ ክርስቶስ ውበትሽን ንጽሐ ባሕርይሽን ወድዷልና መዝ 44፣10-11 ብሎ እንደተናገረ #ለወላጆቿ_የብፅአት_ልጅ የሆነችው ድንግል ማርያም ከእናት ከአባቷ ተለይታ ታህሣሥ 3 ቀን በ 3 ዓመቷ ወደ መቅደሰ ኦሪት ገብታለች
👉#ባዕታ_ማርያም ማለትም የእናታችን ወደ ቤተ መቅደስ መግባት ማለት ነው #ካህኑ_ዘካሪያስም ስለምትመገበው ምግብ በተጨነቀ ጊዜ መልአኩ ቅዱስ #ፋኑኤል ከሰማያት ወርዶ አንድ ክንፉን ጋርዶ አንድ ክንፉን አጐናጽፎ ኅብስቱን አብልቷት ወይኑን አጠጥቷት የብርሃን ጽዋ እና የብርሃን መሶብ ይዞ ወደ ሰማይ ተመልሷል
👉እመቤታችንም ከዚህ በኋላ ኅብስት ሰማያዊ እየተመገበች ስቴ ሕይወት እየጠጣች ከመላአክት ጋር እየዘመረች ፈጣሪዋን እያመሰገነች 12 ዓመት #በቤተ_መቅደስ ተቀመጠች
👉ለአባ ሕርያቆስ ለቅዱስ ኤፍሬም ለቅዱስ ያሬድ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገለፀች #እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን
👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸዉ የምናስባቸዉ የመልአኩ #ቅዱስ_ፋኑኤል ጥበቃ አይለየን እንዲሁም #የአባ_ሊባኖስ እና #የአባ_ዜና_ማርቆስ ምልጃና ፀሎታቸዉ ሀገራችንን ህዝባችንን ይጠብቅልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ለጥንቃቄ!
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዓላትን አክባሪ ብቻ ሳትሆን በዓላትን እንዴት ማክበር እንዳለባትም ጠንቅቃ ታውቃለች! ። ሌላው ቀርቶ በጥምቀት በዓል ወቅት ታቦታትን ከመንበረ ክብራቸው አንስታ ወደ ጥምቀተ ባሕር የምትወስድበት አንዱ ምክንያት ኢየሱስ ክርስቶስ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ በዕደ ዮሐንስ ለመጠመቅ የመሄዱ ምሳሌ እንጂ ጠላቶቿ ተሃድሶዎች እንደሚሉት 'ታቦታቱ ወክ አምሯቸው' አይደለም ።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ እግዚአብሔር አርቶዶክሳዊ ወጣትችን አነሳስቶ በጥምቀት በዓል ላይ ሌሎች እሴቶችን እንዲጨምሩ እና በዓሉ የበለጠ ድምቀት እንዲኖረው አድርጓል ። ነገር ግን ስራ የሚሰራ ሰው ይሳሳታልና የተሳሳትንባቸውን እና ከወዲሁ ዕልባት እንዲያገኙ ልናስተካክላቸው የሚገቡ ነገሮችን እንጠቁም ።
#ዕጣንማጠን ፦ በኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ስርዓተ አምልኮ መሰረት ዕጣን ማጠን የሚፈጽመው በካህን ብቻ ነው ። የድቁና ስልጣን ያለው ሰው እንኳን ዕጣን ማጠን አይችልም ። ዲያቆናት ዕጣን ለማጠን የሚያበቃ ስልጣነ ክህነት ላይ ባለመድረሳቸው በተልዕኮ ጊዜ የዕጣን ማጠኛ የሆነውን ንዋይ (ማዕጠንት) የላይኛውን ጫፍ አይዙም ። ለተልዕኮ ሲፋጠንም ጫፉን ሳይሆን ከጫፉ ዝቅ ብሎ ይይዛልእንጂ ጫፉን አይዝም ። ይህ የሆነው ከካህናት አባቶቻችን በስተቀር ለሎች ሰዎች ዕጣን ማጠን እንደሌለባቸው ስርዓት በመሰራቱ ነው ።
እንዲኽ ያለ ስርዓት ባላት ቤተ ክርስቲያን በጥምቀት በዓል ሰበብ ወጣቶች በተለያዮ ቁሳቁሶች የማዕጠንት አገልግሎት ሲሰጡ ማየት ተገቢ አይደለም ። ይህ የሆነው በቅንነት ቢሆንም እየዋለ ሲቆይ ግን ስርዓት ይሆንና ያስቸግራል ፤ በመሆኑም ሊታረም ይገባዋል ።
#ስዕል ፦ የቤተ ክርስቲያን የሆኑ ቅዱሳን ስዕላት የት ቦታ መቀመጥ እና መሰቀል እናዳለባቸው ቤተ ክርስቲያን ስርዓት ሰርታለች ። ቲሸርት ላይ ፣ ዣንጥላ ላይ ፣ ቁልፍ መያዣ ላይ ፣ በየመንገዱ ባሉ መጸዳጃ ቦታዎች ... ወዘተ ቅዱሳት ስዕላትን ማድረግ ተገቢ ካለመሆኑም በላይ መንፈሳዊ ቅጣትን ሊያስቀጣ ይችላል ። በጥምቀት በዓል ላይ እነዚህ ስእተቶች በጉልህ ይታያሉ ። ለምሳሌ ቲሸርት ላይ ስዕል መለጠፍ ። ይህ የሚነቀፍበት ምክንያት ቲሸርቶቹ ከአገልግሎት ውጪ ሲሆኑ ስዕላቱም አላስፈላጊ እንግልት ስለሚደርስባቸው ነው ።
በተመሳሳይ መልኩ ለበዓሉ ተብለው በየመንገዱ የተሰቀሉ ቅዱሳን ስዕላት የበዓሉ ፍጻሜ ከሆነ በኃላ የሚያነሳቸው እና በጥንቃቄ ወስዶ በተገቢው ቦታ ለማስገባት ብዙ ጊዜያትን ሲፈጅ እየታየ ነው ። ይህ ደግሞ ለአቧራ ፣ ለጸሐይ እና በኢ-አማኙ ዘንድ መዘባበቻ መሆንን ያተርፋል ። ከዚህ ሁሉ ግን ከበዓሉ ፍጻሜ በኃላ በየመንገዱ ወይም ታቦታቱ በሚያልፉበት መንገድ ላይ የሰቀልናቸውን ቅዱሳት ስዕላት በጥንቃቄ ማንሳት ይገባል ።
#ወቅታዊነገሮች ፦ ሃይማኖት ከፖለቲካ በዓላማም ሆነ በመርህ ይለያል ። ይህን ካወቅን በምንም መልኩ ቢሆን ፖለቲካዊ አመለካከታችንን በዚህ በዓል ላይ ማንጸባረቅ የለብንም ። በምንሰቅላቸው እና በምንለብሳቸው ቲሸርቶች ላይ ከምንለጥፋቸው ጽሁፎች ብንነሳ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መጽሐፍት አብነት ያደረጉ መሆን አለባቸው ።
#ስካር ፦ በጣም የሚያሳዝነው ነገር ይህ ነው ። አንዳንድ ቦታ ላይ ቀኑን ሙሉ ለበዓሉ ድምቀት ሲደክሙ የዋሉ ወጣቶቻችን በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች የተንቆጠቆጡ ቲሸርታቸውን ለብሰው ምሽቱን በስካር ተበላሽተው ማየት ቅር ያሰኛል ። ሰው በብዙ የጊዜ እርዝመት የለመደውን ሱስ በአንድ ጊዜ ፣ "ተወው" ማለት የማይቻል ቢሆንም በዓሉን ከስካር ነጻ ሆነን ማሳለፍ ያስባርካልና ከዚህ ዓይነት አጓጉል ነገር እንራቅ ።
ለጊዜው እነዚህን እያሰላሰል እንቆይና ሌላውን በሌላ ጊዜ እንመለስበት ። ይህ በእንዲህ እንዳለ በተለያዮ ቦታዎች ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀበትን የመታሰቢያ በዓል ለማክበር እየተደረገ ያለው ዝግጅት እጅግ በጣም አስደሳች መሆኑን መግለጽ እፈልጋለሁ ፤እንዲህ ነው መባረክ ።
ዘካርያስ ኪሮስ ከመርካቶ ።
ዋናው ተልዕኮው
ክርስቲያኖችን ለጣዖት ማሰገድ: እንቢ ካሉ ደግሞ
መግደል ነው:: ክርስቲያኖቹ መከበባቸውን እያወቁ
አልፈሩም:: ታኅሳስ
29 ቀንም ሁሉም የከተማዋ ክርስቲያኖች ወደ ቤተ
ክርስቲያን ተሰበሰቡ::በዚያም ሊቀ ዻዻሱ ሥርዓተ ቅዳሴን
አደረሱ::
ሁሉም
በተመስጦ ይጸልዩ ነበርና የክብር ባለቤት ክርስቶስ
በገሃድ ተገለጠላቸው:: በዓይናቸው እያዩም ሥጋ ወደሙን
አቀበላቸው::
ቅዳሴው ሲጠናቀቅ ግን አርያኖስና ሠራዊቱ ደርሰው
ሁሉንም ክርስቲያኖች ያዛቸው::
+ክርስቶስን ክደው ከመገደል እንዲድኑ ተጠየቁ:: እነርሱ
ግን በአንድ ድምጽ "አይሆንም" አሉ:: በዚያን ጊዜ
ወታደሮቹ
በክርስቲያኖች አንገት ላይ በሰይፍ ይጫወቱ ያዙ::በተራ
አሰልፈው ዻዻሱን: ካህናቱን: ዲያቆናቱን:
አንባቢዎችን:መሣፍንቱን ሳይጨምር ከ16,000 በላይ
ክርስቲያኖች ደማቸው ፈሰሰ:: የቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር
ሞልቶ ደም
ወደ ውጭ 20 ክንድ ያህል ፈሰሰ::
በክርስቲያኖች ላይ
ግፍ ተፈጸመ::አካባቢውም ያለ ወሬ ነጋሪ ቀረ:: ግድያው
ለ3
ቀናት ቀጥሎ ጥር 1 አንድ ቀን ቅዱሳን ዲዮስቆሮስና
ሰከላብዮስ ሲገደሉ ተጠናቀቀ::
✞አምላከ ሰማዕታት ፍቅረ ሃይማኖታቸውን ያሳድርብን::
ከበረከታቸውም ይክፈለን::
✞ጥር 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ቀዳሜ ሰማዕት (ሊቀ ዲያቆናት)
2.ቅዱሳን ሰማዕታተ አክሚም
3.ቅዱሳን ዲዮስቆሮስ ወሰከላብዮስ
4.ቅዱስ ለውንድዮስ ሰማዕት
5.አባ መቃርስ ሊቀ ዻዻሳት
በ1 የሚከበሩ ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
4.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
5.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር
✞እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል
ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር . . . አንዳንዶቹ
ተነስተው
እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር:: ይናገርበት የነበረውንም
ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም:: በዚያን ጊዜ
በሙሴ
ላይ: በእግዚአብሔርም ላይ የስድብን ነገር ሲናገር
ሰምተነዋል የሚሉ ሰዎችን አስነሱ . . . በሸንጐም
የተቀመጡት ሁሉ
ትኩር
ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት::
(ሐዋ. 6:8-15)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
✞እንኳን ለቅዱሳን ጻድቃን ወገዳማውያን "አባ ዮሐንስ" : "አባ ዘካርያስ ወአባ ዮሐንስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞
+*" አባ ዮሐንስ ዘአስቄጥስ "*+
=>ገዳማዊ ሕይወት ጥንቱ ብሉይ ኪዳን ነው:: በቀዳሚነትም በደብር ቅዱስ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ደቂቀ ሴት እንደ ጀመሩት ይታመናል:: ሕይወቱ በጐላ: በተረዳ መንገድ የታየው ግን በታላቁ ጻድቅ ሄኖክ: ከዚያም በቅዱሱ ካህን መልከ ጼዴቅ አማካኝነት ነው::
+ቀጥሎም እነ ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ: እነ ኤልሳዕ ደቀ መዝሙሩ ኑረውበታል:: በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሙሉ ሕይወቱን በገዳም (በበርሃ) ያሳለፈው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድሚያውን ይይዛል::
+ለስም አጠራሩ ስግደት ይኹንና መድኃኒታችን ክርስቶስ በገዳመ ቆረንቶስ ለ40 ቀናት በትሕርምት ኑሮ ገዳማዊ ሕይወትን ቀድሷል: አስተምሯል:: በዘመነ ስብከቱም ያድርባት የነበረችው የደብረ ዘይቷ በዓቱ (ኤሌዎን ዋሻ) በራሷ ለዚህ ሕይወት ትልቅ ማሳያ ናት::
+ከጌታ ዕርገት በሁዋላም ክርስቲያኖቹ የዓለም ሁካታ ሲሰለቻቸው: አንድም በንጹሕና በተሸከፈ ልቡና ለፈጣሪያቸው መገዛትን ሲሹ ከከተማ ወጣ እያሉ ይኖሩ እንደ ነበር የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ:: አኗኗራቸውም በቡድንም: በነጠላም ሊሆን ይችላል::
+ዋናው ነገር ግን በጾምና በጸሎት መትጋታቸው ነው:: ይሕም ሲያያዝ እስከ 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ደረሰ:: በዚህ ዘመን ግን አባ ዻውሊ የሚባል አንድ ንጹሕ ክርስቲያን ይሕንን ሕይወት ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ አደረገው:: ለ80 ዓመታት ሰው ሳያይ ተጋድሎ "የባሕታውያን አባት" ተባለ:: ደንብ ያለው ተባሕትዎም ጀመረ::
+ይህ ከሆነ ከ20 ዓመታት በሁዋላ ደግሞ አባ እንጦንስ የሚባሉ ደግ ክርስቲያን ይህንን ገዳማዊ ሕይወት በሌላ መንገድ አጣፈጡት:: በቅዱስ ሚካኤል አመንኩዋሽነት ገዳማዊ ሕይወት በምንኩስና ተቃኘ:: ስለዚህም አባ እንጦንስ የመነኮሳት አባት ተባሉ::
+እርሳቸውም ሕይወቱን ለማስፋፋት ከተለያዩ አሕጉር ደቀ መዛሙርትን እየተቀበሉ አመንኩሰዋል:: ቅዱሳን የአባ እንጦንስ ልጆችም ወደየ ሃገራቸው ተመልሰው: ሕይወቱን በተግባር አሳይተው ገዳማዊነትን አስፋፍተዋል::
+አባ እንጦንስ አባ መቃርስን: አባ መቃርስ አባ ዮሐንስን ወልደዋል:: አባ ዮሐንስም የታላቁ ገዳመ አስቄጥስ አበ ምኔት ሆነው በጸጋ አገልግለዋል:: አስቄጥስ በምድረ ግብጽ የሚገኝ: በስፋቱና ብዙ ቅዱሳንን በማፍራቱ ተወዳዳሪ የሌለው የዓለማችን ቁጥር አንድ ገዳም ነው::
+ሕይወተ ምንኩሰናም ወደ መላው ዓለም የተስፋፋ በዚህ ገዳም መናንያን አማካኝነት ነው:: በዚህ ገዳም ላይ የሚሾሙ አበው ደግሞ በብዛት መንፈስ ቅዱስ ያደረባቸውና አባታቸውን ቅዱስ መቃርስ ታላቁን የመሰሉ ናቸውና ኃላፊነቱ እጅግ ከባድ ነው::
+በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብጽ ተወልደው ያደጉት አባ ዮሐንስ ከመነኑባት ዕለት ጀምረው በፍጹም ተጸምዶና ተጋድሎ ለፈጣሪያቸው ስለ ተገዙ የታላቁ ገዳም አበ ምኔት ሊሆኑ ተገባቸው::
+በአበ ምኔትነት ዘመናቸውም መንጋውን ይጠብቁ ዘንድ ብዙ ደከሙ:: በተለይ ቅዱስ ቃሉን ያስተምሩ ዘንድ ተጉ:: ሕይወተ መላእክትንም ያሳዩ ዘንድ በቃል ብቻ ያይደለ በተግባር ሆነው ከመንፈሳዊ አብራካቸው ብዙ ቅዱሳንን ወለዱ::
+ከዋክብቱ አባ ገዐርጊ: አባ አብርሃም: አባ ሚናስ: አባ ዘካርያስ . . . የአባ ዮሐንስ ፍሬዎች ናቸውና:: ጻድቁ በዘመናቸው ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል:: ከዕረፍታቸው በሁዋላ እንኩዋ መግነዛቸውና የልብሳቸው እራፊ ብዙ ድውያንን ፈውሷል::
+አንድ ጊዜም ለልጆቻቸው መነኮሳት ቤዛ ሆነው በበርበር (አረማውያን) ተማርከዋል:: በዚያም ክፉዎች ባሪያ ቢያደርጉዋቸው እግዚአብሔር ድንቅን ሠርቶ ወደ ገዳማቸው መልሷቸዋል:: ከብዙ ተጋድሎ በሁዋላም በ90 ዓመታቸው በዚህች ቀን ዐርፈው በበዓታቸው ተቀብረዋል::
+"+ አባ ዘካርያስ ገዳማዊ +"+
=>ይሕም ቅዱስ የተነሳው በዚያው በዘመነ ጻድቃን ነው:: ምንም ክርስቲያን ቢሆንም በቀደመ ሕይወቱ ገንዘብ የሚጥመው ነጋዴ ነበር:: በንግድ ሥራውም ሃብታም መሆን ችሎ እንደ ነበር ዜና ሕይወቱ ይናገራል::
+እግዚአብሔር ሁሉም የሰው ልጆች ወደ መንግስተ ሰማያት ቢገቡ መልካም ፈቃዱ ነው:: ያ ብቻ አይደለም:: ለእያንዳንዱ ሰው የድኅነት ጥሪን በተለያየ መንገድ ያቀርብለታል:: ድምጹን ለሰማ ወደ ወንጌል ወደብ ያደርሰዋል::
+አንዳንዴ "እንቢ" ስንለው እንደ በጐ አባትነቱ በተግሣጹ ሊጠራንም ይችላል:: ተግሣጹም በደዌ: በአደጋና በመሰል መንገዶች ሊሆን ይችላል:: ዋናው ቁም ነገር ግን ጊዜው ሳያልፍብን: ቀኑም ሳይመሽብን ድምጹን መስማት: ለቃሉ መታዘዝ: ጥሪውንና ተግሣጹን አለማቃለል ነው::
+አባ ዘካርያስም የቅድስና ሕይወት ጥሪ የደረሰው ለሥጋ ገበያ ሲታትር ነበር:: አንድ ቀን ንብረቱን ይዞ ለንግድ መንገድ ላይ ሳለ ሽፍቶች ያዙት:: ሊያርዱት አጋድመውት ሳለ ግን የገዳመ ዻኩሚስ አበ ምኔት በሥፍራው ነበርና ጮኸባቸው::
+ቅዱሱ አበ ምኔት አካሉ በገድል ያለቀ ቢሆንም ድምጹ እንደ ነጐድጉዋድ ሲመጣ ገዳዮቹ ደንግጠው በረገጉ:: ዘካርያስም ከሞት ተረፈ:: እንደ ገና ሃብቱን ይዞ ወደ ከተማ ሲገባ በሃገረ ገዢው ተይዞ ሞት ተፈረደበት:: ከገንዘቡ መብዛት የተነሳ ዘራፊ መስሏቸው ነበርና:: በዚህ ጊዜም እግዚአብሔር በመኮንኑ ልብ ርሕራሔን ጨምሮ አዳነው::
+በዚያች ሌሊት ግን ነገሮችን ያስተዋለው ዘካርያስ የተፈጠሩት አጋጣሚወች የፈጣሪው ጥሪ እንደ ሆኑ አስተዋለ:: ወዲያውም ለዓይነ ሥጋ የሚያሳሳውን ያን ሁሉ ንብረቱን መጽውቶ በርሃ ገባ:: በደብረ አባ ዻኩሚስም መንኩሶ በዓት ወሰነ::
+ከዚያች ቀን ጀምሮም በፍጹም አምልኮ: በጾምና በጸሎት እግዚአብሔርን እያገለገለ ከርኩሳን መናፍስት ጋር ታገለ:: በእግሩም ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዞ ቅዱሳት መካናትን ተሳለመ:: አንድ ጊዜም ሰይጣን ሰው መስሎ "አባትህ ሳልሞት ልየው እያለህ ነው" አለው:: ውስጡ ግን ፈቃደ ሥላሴ ነበረበትና "እሺ" ብሎ ሒዶ: አባቱን ቀብሮ ተመልሷል::
+ቅዱስ አባ ዘካርያስ ከብቃቱ የተነሳ የሚኖረው ከግሩማን አራዊት ጋር ነበር:: ሁሉንም አራዊትም ይመግባቸው ነበር:: በተለይ ደግሞ ዘንዶዎች ሰውን እንዳይጐዱ አዝዞ እርሱ ይመግባቸው ነበር:: የተጋድሎ ዘመኖቹን ከፈጸመ በሁዋላም በዚህች ቀን በክብር ዐርፏል::
+"+ አባ ዮሐንስ ብጹዕ +"+
=>ይህም ቅዱስ በተመሳሳይ የዘመነ ጻድቃን ቅዱሳን ፍሬ ነው:: "ኢትርአይ ገጻ : ወኢትስማዕ ድምጻ" በሚለው ሕገ ተባሕትዎ ለ40 ዓመታት ተወስኖ ኑሯል::
+ይህም ማለት አንድ ወንድ ከመነነ በሁዋላ ሴቶችን እንዲያይና ከእነርሱም ጋር እንዲያወራ አይፈቀድለትም:: ሴትም ብትመንን ሕጉ ያው ነው:: (ዛሬ እየተደረገ ያለውን ግን ፈጣሪ ይመርምረው)
ድንግል ማርያም ሆይ💕
የምታምር ርኄ፣ አፈው፣ ከርቤ ከሚባሉ ሽቱዎች የምትሸት መልካም ፍሬ አንቺን ያፈሩ ኢያቄምና ሐና ብፁዓን ናቸው።
ሌላ /ፍጡር ያላጣፈጠው/ ያላሳመረው ያማረ: የተወደደ አበባና የከበረ የንግሥና ቅባት አንቺ ነሽ። ሽቱ መልካም መዓዛ አለው። ሽታውም ያማረ ነው። አንቺ ግን ከእርሱ ይልቅ ፈጽሞ መዓዛሽ ያስደስታል የነጭ ዕጣን ውኃ ከአንቺ ይወጣል /ይፈልቃልና/። የአሕዛብ ክብር ከአብ የተሰጠሽ ጸጋና ጽድቅ አንቺ ነሽ።
የሽቱ ግንድ አንቺ ነሽ። ከሆድሽም የሃይማኖት በትር በቀለ። የተቀደሰችዋ ኦሪት ከነጭ ዕጣን ዛፍ ዘንግን ወሰደ።
በጐች ከጉድጓድ በሚጠጡበት ጊዜ እንደተመለከቱትም በገንዳው በጉድጓድ አስቀመጠው። በጐችም በዚህ ሽምልመሌ አምሳል ፀነሱ አለች።የነጭ ዕጣን በትር የተባለው በእርሱ የምንመረኮዝበት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ሰሎሞን በልጅ ወንድሜ የምትመረኮዝ ይህች ማን ናት? እንዳለ። እንደ ሴት የጻድቃንን ነፍስ እየጠራ ከመዳን ጋር ወንድሞች ያደርጋቸዋልና።
ቀጥታ ከ ደብረ ሮሃ ቅዱስ ላል ይበላ የቤዛ ኩሉ ጸሎት ስነ ሥርዓት!!
ቀጥታ
አራራት ቲዩብን ሰብስክራይብ ያድርጉ!!!
ታህሳስ 29 2016 አ.ም
https://www.youtube.com/live/AUg-gOR0sH4?si=azVxSkXdjzGEE3iy
ታህሳስ 29/4/2016 #ቅዱስ_ላሊበላ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት #ቅዱሥ_ላሊበላ ለተወለደበት አመታዊ ክብረ በአል በያለንበት እንኳን አደረሰን
👉ቅዱሥ ላሊበላ አባቱ #ጃን /ዥን/ ስዩም እናቱ #ህረወይላ/ከረወይላ/ ይባላሉ
👉መጋቢት 29 ቀን ተፀነሰ በታህሣሥ 29 ቀን ተወለደ በተወለደም ጊዜ #በንብ_ተከቦ ታየ ሀገሩም ላሥታ ሮሀ ነው በኋላም ከተቀደሠ ቤተሠብ የተገኘችውን #ቅድሥት_መሥቀል ክብራን አገባ፡፡
👉ቅዱስ ላሊበላ 11 #ቤተ_መቅደሶችን ሲሰራ 23 አመት ፈጀበት ሢጀምር ግን በመልአኩ #በቅዱስ_ሚካኤል መሪነት መሥዋዕት ሠውቶ ነው የሠራው ከተሠሩትም ቤተ መቅደሶች ውሥጥ እጅግ አሥደናቂው 4 ማዕዘን ያለው የመሥቀል ቅርፅ ያለው ቤተ ጊዮርጊስ ነው
👉 #በቅዱስ_ላሊበላ ዘመን አሥደናቂውና ታአምረኛው 120 ቤተሠብ አናብሥትና የአናብርት የሆኑለት አባታችን አቡነ #ገብረ_መንፈስ_ቅዱሥ ወደ ተቀደሠችው ሀገራችን ወደ ኢትዮጵያ መጡ፡፡
👉 #ቅዱስ_ላሊበላ በውቅር ድንጋይ በላሥታና በጎንደር በሸዋ ያነፃቸው ቤተ መቅደሶች ብዛት 29 ሲሆኑ ሌሎቹ ግን ብዛት 181 በድምሩ 210 ቤተ መቅደሡን የጀመረው በነሀሴ ፲፪ ቀን ነው #ቅዱስ_ላሊበላ 40 አመት ካሥተዳደረ በኋላ በ ሰኔ ፲፪ ቀን አርፎ እራሡ ባነፀው #ቤተ_ጎለጎታ ተቀበረ፡፡
👉ዛሬም ዐፅሙ #በቤተ_መቅደሡ ይገኛል ከሠማይ በወረደው አፍሮ አይገባ #መሥቀል መባረክና #በመስቀሉ መዳሠስ ፈዉስና ጤና ይሰጣል
👉 #የፃድቁ_ቅዱሥ_ላሊበላ በረከቱ ይደርብን አባቶቻችን ቤተመቅደስን ከድንጋይ ሣይቀር አንፀው ለትዉልድ እንዲተላለፍ የፈቀደ #አምላከ_ቅዱሳን ስሙ የተመሠገነ ይሁን የሄዳችሁ በፀሎት አሥቡን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️