🌹ወር በገባ በ8 የቅዱስ አባ (ብሶይ) ብሾይ ወርኀዊ መታሰቢያያ በዓላቸው ነው።
#የገዳም ኮከብ ቅዱስ አባ ብሶይ በግብጽ ሼስና በተባለች ቦታ የተወለደ ሲኾን ሰባት ወንድሞች ነበሩት፤ ከዕለታት ባንዳቸው ለእናቱ የእግዚአብሔር መልአክ በሕልሟ ተገልጾ “ጌታ ከልጆችሽ መኻከል አንዱን እንዲያገለግለኝ ስጪኝ ይልሻል አላት” ርሷም፤ “ጌታ የወደደውን ይውሰድ” ብላ መለሰችለት፤ መልአኩም ቀጭን የነበረውን ሰውነቱም ደካማ የነበረውን የብሶይን እጁን ይዞ “ዝንቱ ውእቱ ወልድ ለእግዚአብሔር ገባሬ ሠናይ” (ለእግዚአብሔር መልካም ሥራ የሚሠራ ይኽ ልጅ ነው” አለ፤ ያን ጊዜ እናቱ “የእኔ ጌታዬን እንዲያገለግለው ጠንካራውን ይውሰድ” በማለት ስትመልስ፤ መልአኩም “ጌታስ የመረጠው ይኽነን ነው” ብሎ መልሶላታል፡፡
ከዚያም በ340 ዓ.ም. ቅዱስ አባ ብሶይ ወደ ሲሐት በረሓ በመኼድ ቅዱስ ዮሐንስ.ሐጺርን ባመነኮሱት በአባ ባውማ እጅ ምንኲስናን ተቀበለ፡፡ አባ ባውማ ባረፈ ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርና አባ ብሶይ በጸለዩ ጊዜ መልአኩ ለአባ ብሶይ ተገልጾለት ወደ ገዳም መርቶ አድርሶታል፤ በዚያም ወደ ርሱ ለተሰበሰቡ ለብዙዎች መነኮሳት አባት ኾኗቸዋል፤ በቅድስና እጅግ የከበረ፤ በፍቅር፣ በደግነት፣ በርኅራኄ የሚታወቁ በተጋድሎም የበረታ ነበረና ዜናው በመታወቁ ቅዱስ ኤፍሬም ወደ አባ ብሶይ መጥቶ አይቶታል፡፡
ጌታችንን በእጅጉ ከመውደዱ የተነሣ ቅዱሳት መጻሕፍትን አዘውትሮ በማንበብ በመጻሕፍት ቃል ነፍሱን እያረካ፤ እጅግ ጽኑ የኾነ ተጋድሎን በማድረግ በጾም፣ በጸሎት ይጋደል ነበር፤ ሁሌም ርሱን ለማመስገን ከመሻቱም የተነሣ በምሽት ጸሎት ጊዜ እንቅልፍ እንዳይወስደው ጸጒሩን በገመድ በማሰር ይጸልይ ነበር፤ ዛሬ ድረስ ይኽ ማሰሪያ በዚያው ገዳም አለ፤ በዚኽም ንጽሐ ልቡና መኣርግ ላይ በመድረሱ ጌታችን ደጋግሞ ይገለጽለት ነበር፤ ከዕለታት ባንዳቸውም ጌታ በአምሳለ ነዳይ በእንግድነት ወደ በዓቱ በመጣ ጊዜ በእንግዳ ልማድ ውሃ አቅርቦ ለማጠብ ሲዠምር በምስማር የተወጉ እግሮቹን ዳስሶ በማየቱ ጌታችን እንደኾነ ዐውቋል፡፡ ርሱም በደስታ በመኾን ጌታን ያጠበበትን ውሃ ጠጥቶታል፡፡
ይኽነን ብቃቱን አይተው መነኰሳቱ ጌታችን እንዲገለጽላቸው ይለምንላቸው ዘንድ እጅጉን በዘበዘቡት ጊዜ ወደ ጌታችን አመለከተ፤ ጌታም በተራራው ላይ እንደሚገለጽ ነግሮት ለመነኰሳቱ ኹሉ ነገራቸው፤ እነርሱም በማለዳ ወደ ተራራው ጫፍ ሲገሰግሱ ከተራራው ሥር ጌታን በአምሳለ አረጋዊ ኾኖ በመገለጥ ይዘውት እንዲወጡ ቢጠይቃቸው አንዳቸውም በእንቢተኝነት ጸንተው ወደ ተራራው ይሮጡ ጀመር፡፡ በመጨረሻም አረጋዊዉ አባ ብሶይ ወደ ተራራው ሊወጣ ሲል በአምሳለ አረጋዊ የተገለጸው ጌታችን ዐዝሎት እንዲወጣ ጠየቀው፤ አባ ብሶይም በትሕትና በመኾን ታዝዞ ዐዝሎት ሲወጣ በእጅጉ ከበደው ቀስ እያለ ግን ቀለል ቀለል እያለው መምጣቱን ዐውቆ ጌታችን መኾኑን ተረድቶ ቀና ብሎ ቢያይ ዠርባው ላይ በፍቅር የታዘለው ርሱ ነው፤ ጌታም ስለ ትሕትናው ለርሱ እንደተገጠለት ነግሮት አባ ብሶይን ባርኮታል፤ በመኾኑም የባሕርይ አምላክ ክርስቶስን ያዘለበት የአባ ብሶይ ሰውነት ዛሬ ድረስ ሳይፈርስ ሳይበሰብስ ብዙ ተአምራትን እያደረገ በገዳሙ አለ፡፡
ቅዱስ አባ ብሶይ የመንፈስ ቅዱስን ህልውና ክዶ የነበረውን በበረሓ የነበረውን ሰው ስለ ነገረ መንፈስ ቅዱስ ከብሉይ ከሐዲስ በምሳሌ ጭምር በስፋት አስተምሮ እንዲመለስ አድርጓል፤ ቅዱስ አባ ብሶይም ብዙዎች ተጋድሎዎችን ካደረገ በኋላ ሐምሌ 8 በ417 ዓ.ም. በመዐዛ ገነት፣ በይባቤ መላእክት ነፍሱን ለእግዚአብሔር ሰጥቷል፡፡
የቅዱሳኑ በረከት ከእኛ ጋር ትሁን፡፡
#መጋቤ_ሐዲስ_ሮዳስ_ታ
+ስለ ቅዱሳን ነቢያት በጥቂቱ ይህንን ካልን ወደ ዕለቱ በዓል እንመለስ::+ቅዱስ ሚክያስ ቁጥሩ ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት ሲሆን ዘመነ ትንቢቱም ቅ.ል. ክርስቶስ በ800 ዓ/ዓ አካባቢ ነው:: "ደቂቀ ነቢያት" ማለት በጥሬው "የነቢያት ልጆች" ማለት ነው:: አንድም የጻፏቸው ትንቢቶች ሲበዙ 14 ምዕራፍ: ሲያንስ 1 ምዕራፍ ያላቸው ናቸውና ደቂቅ ይላቸዋል::+ሚክያስ ትውልዱ ከነገደ ብንያም ሲሆን አባቱ ሞራት (ሞሬት) ይባላል:: ሚክያስ ማለት "መኑ ከመ አምላክ-እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው!" ማለት ነው:: አንድም "መልአከ እግዚአብሔር" ማለት ነው:: የአባቶቻችን ሁሉ ስማቸው እግዚአብሔርን የሚሰብክ ነው::
+ቅዱሱ ነቢይ ልጅ እያለ መላእክት ያነጋግሩት ነበር:: በዚህ ምክንያት ከሰው አይቀርብም:: ትክ ብለው ሲያዩት በፊቱ ላይ ብርሃን ቦግ ቦግ እያለ ይታይ ነበር:: በወጣትነት ዘመኑ እግዚአብሔር ለትንቢት ሲጠራው በእሺታ ታዘዘ:: በ3ቱ ነገሥታት (በኢዮአታም: አካዝና ሕዝቅያስ) ዘመንም ትንቢቶችን ተናግሯል:: ሕዝቡን: መሣፍንቱን: ነገሥታቱን አስተምሮ ገስጿል::
+አንድ ቀን በቤተ ልሔም ሲያልፍ የዳዊት ከተማ ፈት ሁና: ዳዋ በቅሎባት ቢመለከት አዘነ:: ወዲያውም ትንቢት ተናገረላት::
"ወአንቲኒ ቤተ ልሔም ምድረ ኤፍራታ: ኢትቴሐቲ እምነገሥተ ይሁዳ: እስመ እምኔኪ ይወጽዕ ንጉሥ::"
(አንቺም የኤፍራታ ምድር ቤተ ልሔም: የይሁዳ ነገሥታት ከነገሡባቸው ከተሞች ከቶ አታንሺም:: ወገኖቼን እሥራኤልን የሚጠብቃቸው ንጉሥ ካንቺ ዘንድ ይወጣልና) አለ::
+ይኸውም አልቀረ ለጊዜው ከሚጠት በሁዋላ ደጉ ዘሩባቤል ነግሦባታል:: በፍጻሜው ግን የባሕርይ ንጉሠ ነገሥት ኢየሱስ ክርስቶስ ከንጽሕት ድንግል ማርያም ተወልዶባታል::
+ቅዱስ ሚክያስ ወገኖቹን ሲያስተምርና ሲመራ ኑሮ: 7 ምዕራፎች ያሉትን ሐረገ ትንቢት ተናግሮ: በመልካም ሽምግልና በንጉሡ ሕዝቅያስ ዘመን ዐርፏል:: ወገኖቹም ቀብረውታል:: ጌታም በክብረ ነቢያት ከልሎታል::
=>አምላከ አበው ቅዱሳን ለተፋቅሮ ይበለን: ከበረከታቸውም ይክፈለንና
ጥር 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ታላቁ ቅዱስ መቃርስ
2.ቅዱስ ሚክያስ ነቢይ
3.አባ እንድራኒቆስ ሊቀ ዻዻሳት
4.አባ ብንያሚን ሊቀ ዻዻሳት
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ)
3.አባ ብሶይ (ቢሾይ)
4.አቡነ ኪሮስ
5.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
6.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
=>+"+ ምን ይዤ ወደ እግዚአብሔር ፊት ልምጣና በልዑል አምላክ ፊት ልስገድ? የሚቃጠለውን መስዋዕትና የአንዱን ዓመት ጥጃ ይዤ በፊቱ ልምጣን? እግዚአብሔርስ በሺህ አውራ በጐች: ወይስ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ ይለዋልን? . . . ሰው ሆይ! መልካሙን ነግሮሃል:: እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ: ምሕረትንም ትወድ ዘንድ: ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሔድ ዘንድ አይደለምን? +"+ (ሚክ. 6:6)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
**👉ከጎንህ ያለችው ሚስትህ..
የላጤዎች ሁሉ ምኞት ናት።
👉ደስተኛ ያልሆንክበት ልጅህ..
መውለድ የማይችሉ ሁሉ ምኞት ነው።
👉ትንሿ ቤትህ..
ቤት ላጡ ሁሉ ምኞት ናት።
👉አድካሚ ስራህ..
ስራ ላጡ ሁሉ ምኞት ነው።
👉ትንሿ ገንዘብህ..
ምንም ገንዘብ ለሌላቸው ሁሉ ምኞት ናት።
👉በገንዘብ የማይተመነው ጤናህ..
ጤንነት አተው ለሚሰቃዮ ምኞት ነው።
👉በነጻነት በእግርህ መጓዝህ..
እስር ቤት ሆነው ለሚሰቃዮ ምኞት ነው።
👉ፈጣሪ የደበቀልህ ነገር..
ተዋርደው ላፈሩ ሁሉ ምኞት ነው።
ፈ ጣ ሪ ተ መ ስ ገ ን 🙏
መልካም አዳር ይሁንላችሁ!!
@Asresee
@Asresee
የቀደሙት ሰዎች በሰናዖር ከምድር እስከ ሰማይ፣ እስከ አምላክ ማደሪያ የሚደርስ ግንብ ሊሠሩና ስማቸውን ሊያስጠሩ ተነሡ። ነገር ግን በትዕቢታቸው ጠፉ። እነዚህ የባቢሎን ሰዎች ምንኛ ችኩሎች ሆኑ?! ጥቂት ዘመን ቢታገሱ ኖሮ ራሱ አምላክ ከእነርሱ እንደ አንዱ ሰው ሆኖ በግርግም ተኝቶ ያገኙት አልነበር?!
እነዚህ የሰናዖር ሰዎች ትንሽ ቢታገሱ ኖሮ ከምድር ወደ ሰማይ መሻገሪያ የምትሆን በእግዚአብሔር እጅ የታነጸች ታላቋን የብርሃን ድልድይ ድንግል ማርያምን ያገኙዋት ነበር። በዚህችም የብርሃን ድልድይ (መሰላል) እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ የሰው ልጆች ሁሉ ስም እንደ ተጠራ አይተው ደስ ይሰኙ ነበር።
====
አቤቱ ጾም፣ ጸሎት፣ መንፈሳዊ ትሩፋቶቻችን የአንተ ረድኤት የሌለባቸው በትዕቢት ያቆምናቸው የሰናዖር ግንቦች አይሁኑብን። እንዲህም ከሆኑ፣ በሥራዬ እያለ ልባችን እንዳይኮራ፣ ዓይናችንም ወደታች እያየ ወዳጆቹን እንዳይንቅ ወደ አንተ የማያደርሱንን እነዚህን የሐሰት ግንቦች አፍርስልን። በእነርሱም ፈንታ በትሕትና እና በፍቅር ያጌጡ ውብ ግንቦችን እናንጽ ዘንድ ረድኤትህን ላክልን።
እንኳን አደረሳችሁ!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
የስላሴን መንበር --
ቅዱሳን ከበውት
እያሸበሸቡ የሰማይ መላዕክት
ካህናት ከሰሜይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሲሉ
ይህን ልዩ ታምር ሊያዩ የታደሉ
በፅድቅ ስራቸው በምድር ይታያሉ
በፅድቅ ስራቸው በምድር ይታያሉ
የስላሴን መንበር
ቅዱሳን ከበውት
ኪሩቤል በደመና
ዙፋኑን ይዘውት
ድንግልን ከመሀል
ሚካኤልን ከፊት
አዕላፍ መላዕክት
ሲሰግዱ በፍርሀት
እዩት ተመልከቱት የሰማዩን ድምቀት
እዩት ተመልከቱት የሰማዩን አባት........
✝ እንኳን ለአጋእዝተ ዓለም "ሥላሴ" እና "ቅዱስ ሶል ዼጥሮስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችኹ✝
+*" ሥሉስ ቅዱስ "*+
=>ምሥጢራት በእምነት ለማይኖር: በትሕትናም ለማይቀርብ የሚገለጡ አይደሉም::
+እግዚአብሔር አንድም ነው: ሦስትም ነው:: ጊዜ ሣይሠፈር ዘመንም ሳይቆጠር እግዚአብሔር በስም: በአካል: በግብር ሦስትነቱ: በባሕርይ: በሕልውና: በመለኮትና በሥልጣን አንድነቱ የጸና አምላክ ነው::
+ከዓለም መፈጠር በፊት ስለ ነበረው ነገር የሚያውቅ ራሱ ሥላሴ ብቻ ነው:: ዓለምን ከፈጠረ በሁዋላም ምሥጢረ ሥላሴ (መለኮት) ብለን የምንማረው ትምሕርት እንድንና እንጠቀም ዘንድ እርሱ የገለጠልንን ያህል ብቻ ነው::
+ይኼውም በየጊዜው እርሱ ለወደዳቸውና ደስ ላሰኙት ቅዱሳኑ የገለጠው ምሥጢር ነው:: ከዚህ አልፈን በሥጋዊ አዕምሯችን ጌታን "እንመርምርሕ" ብንለው ግን ፍጻሜአችን ሞት: ማደሪያችንም ገሃነመ እሳት መሆኑ አይቀርም::
+እግዚአብሔር በአንድነቱና ሦስትነቱ ሳለ ይህንን ዓለም ፈጠረ:: እግዚአብሔር ዓለምን ለምን ፈጠረ ቢሉ:- ስሙን ቀድሰን ክብሩን እንድንወርስ ነው:: ከዚህ የተረፈውን ምክንያት ግን ራሱ ያውቃል::
=>በአንድነቱ ምንታዌ (ሁለትነት): በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት) የሌለበት የዘለዓለም አምላክ: የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ እግዚአብሔር ነው:: አብ: ወልድ: መንፈስ ቅዱስ በስም: በአካል: በግብር ሦስትነት በባሕርይ: በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው:: በዚህ ጊዜ ተገኙ: በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም:: መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና::
+ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት "ቅድስት ሥላሴ" እንላቸዋለን:: የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም:: የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል:: በቤቱም መጥተው ያድራሉ::
+ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም:: አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን : በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል::
+አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ: እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኩዋናቸው አስተናገዱ:: አብርሃም እግራቸውን አጠበ:: (ወይ መታደል!) በጀርባውም አዘላቸው:: (ድንቅ አባት!) ምሳቸውንም አቀረበላቸው:: እንደሚበሉ ሆኑለት:: በዚያው ዕለትም የይስሐቅን መወለድ አበሠሩት::
+ሥላሴን ያስተናገደች ድንኩዋን (ሐይመት) የድንግል እመቤታችን ማርያም ምሳሌ ናት:: በድንግል ላይ አብ ለአጽንኦ: መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ: ወልድ በተለየ አካሉ ለሥጋዌ በእርሷ ላይ አርፈዋል / አድረዋልና::
=>በዓለ ሥላሴ በዚህ ቀን የሚከበረው ስለ 2 ምክንያቶች ነው:: ቀዳሚው ሕንጻ ሰናዖርን ማፍረሳቸው ሲሆን 2ኛው ደግሞ ቅዳሴ ቤታቸው ነው::
+*" ሕንጻ ሰናዖር "*+
=>ሰናዖር ከሺዎች ዓመታት በፊት በአሁኗ ኢራቅ አካባቢ እንደ ነበረ የሚነገርለት ግዛት ሲሆን ስሙ ለሃገሪቱም: ለንጉሡም በተመሳሳይ ያገለግል ነበር:: ከናምሩድ ክፋት በሁዋላ ሰናዖርና ወገኖቹ ከሰይጣን ተወዳጁ::
+ከጥፋት ውሃ (ከኖኅ ዕረፍት) በሁዋላ በሥፍራው በአንድነት ይኖሩ ነበርና እርስ በርሳቸው "ኑ ሳንበተን ስማችን የሚጠራበትን ሕንጻ እንሥራ:: በዚያውም አባቶቻችን በውሃ ያጠፋ እግዚአብሔርን እንውጋው" ተባባሉ::
+ቀጥለውም ሰማይ ጠቀስ ፎቅን ገነቡ:: ከሕንጻው መርዘም የተነሳ በጸሐይ አብስለው በልተዋል ይባላል:: ቀጥለውም ጦር እያነሱ ፈጣሪን ሊወጉ ወርውረዋል::
+መቼም የእነዚህን ሰዎች ክፋትና ቂልነት ስንሰማ ይገርመን ይሆናል:: ግንኮ ዛሬ ሰለጠንኩ በሚለው ዓለም እየተሠራ ያለው ከዚህ የከፋ ነው:: ቸርነቱ ቢጠብቀን እንጂ እንደ ክፋታችንስ ጠፊ ነበርን::
+ርሕሩሐን ሥላሴ ግን የሰናዖር ሰዎች የሠሩትን አይተው ማጥፋት ሲችሉ አላደረጉትም:: የባሪያቸውን የኖኅን ቃል ኪዳን አስበዋልና:: ይልቁኑ "ንዑ ንረድ ወንክአው ነገሮሙ ለከለዳውያን-ቁዋንቁዋቸው እንደባልቀው" አሉ እንጂ::
+ከለዳውያን ልሳናቸው ተደበላልቆ 71 ቁዋንቁዎች ተፈጠሩ:: እነርሱም ስምምነት አጥተው ተበተኑ:: ሥላሴም ያን ሕንጻ በነፋስ ትቢያ እንዲሆን በተኑት:: ስለዚህም እስከ ዛሬ ሥፍራው "ባቢሎን (ዝሩት)" ሲባል ይኖራል::
+" ቅዳሴ ቤት "+
=>ልክ የዛሬ 324 ዓመት: አድያም ሰገድ ኢያሱ በኢትዮዽያ በነገሡ በ10ኛው ዓመት: (በ1684 ዓ/ም) በጐንደር ከተማ ንግሥተ አድባራት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተሰርታ ተጠናቃለች::
+ጥር 7 ቀንም ሊቁ ክፍለ ዮሐንስን ጨምሮ በርካታ ምዕመናን: ሠራዊት: መሣፍንትና ሊቃውንት ባሉበት ቅዳሴ ቤታቸው ተከብሯል:: በዕለቱም ታላቅ ሐሴት ተደርጉዋል:: ኢያሱ አድያም ሰገድ ኃያል: ደግ: ጥበበኛ: አስተዋይ: መናኝ ንጉሥ ነውና::
+ቤተ ሥላሴን አስጊጿታልና ከዚህ ቀን ጀምሮ ጥር ሥላሴ በድምቀት የሚከበር ሆኗል:: ነገር ግን በተሠራች በ16 ዓመቷ ደጉ ኢያሱ ከተገደለ በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ በአደጋ ፈርሷል:: ዛሬ የምናየው በ1708 ዓ/ም በልጁ በአፄ ዳዊት ሣልሳዊ የታነጸውን ነው::
+*" ቅዱስ ሶል ዼጥሮስ "*+
=>የሊብያው አርዮስ ጌትነት ገንዘቡ የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ክዶ ሊያስክድ ሲሯሯጥ በፈቃደ እግዚአብሔር: በጻድቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ጥሪ: 2348 ምሑራን ከመላው ዓለም ተሰበሰቡ::
+ከተሰበሰበው ብዙ ሰው መካከል የአበውን ደቀ መዛሙርት ሳንቆጥር ሃይማኖታቸው የቀና: ምግባራቸው የጸና 318ቱ አበው ሊቃውንት ተገኙ::
+እነዚህ አባቶች "ሊቃውንት" ሲባሉ እንዲሁ በእውቀት ብቻ የበሰሉ እንዳይመስሉን:: 318ቱ አበው እኩሎቹ በዘመነ ሰማዕታት እጅና እግራቸውን የተቆረጡና ለሃይማኖታቸው ብዙ ዋጋ የከፈሉ ናቸው::
+እኩሎቹ ደግሞ በገዳማዊ ሕይወት ያጌጡ: ፍቅረ ክርስቶስ በውስጣቸው የሚነድ: የመንፈስ ቅዱስ ቤት ናቸው:: እስኪ እናውቃቸው ዘንድ የጥቂቶችን ማንነት በስምና መገለጫ እንመልከት::
1.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ (በዘመነ ሰማዕታት ለ22 ዓመት ሲቆራርጡት ኖረው በጉባኤው ላይ የተገኘው ያለ እጅ: እግር: ጀሮ: ከንፈር: ቅንድብ ነው)
2.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ (ስለ ቀናች እምነት ለ50 ዓመታት የተጋደለና ለ15 ዓመታት በስደት የኖረ ነው)
3.ቅዱስ እለእስክንድሮስ ሊቅ (ከሰማይ ብርሃን ይወርድለት የነበረ አባት ነው)
4.ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ (በጸሎቱ አጋንንትን ያንቀጠቀጠ: ነፍሳትን ከሲዖል የቀማና ከከዊነ እሳት የደረሰ አባት ነው)
5.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘአርማንያ (ስለ ቀናች እምነት መጸዳጃ ጉድጉዋድ ውስጥ ለ15 ዓመታት ተጥሎ የኖረ ሰማዕት ነው)
6.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሜራ (ከሕጻንነቱ የተቀደሰ: በበርሃ የተጋደለ: በዘመነ ሰማዕታት ብዙ መከራን የተቀበለ አባት ነው)
7.ቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን (በደግነቱ ሙታንን ያስነሳ: ወንዝን በጸሎቱ ያቆመ: በንጽሕና የተጋደለ አባት ነው)
8.ቅዱስ ሶል ዼጥሮስ (ቅዱሱን ንጉሥ ያጠመቀ: ቁስጥንጥንያን በወንጌል ያበራ ሊቅ ነው)
9.ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ (ስለ ቀናች እምነቱ ብዙ ግፍ የደረሰበትና በስደት ያረፈ አባት ነው)+እንደ አርዮስ ሐሳብ መድኃኒታችን ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ አይደለም (ሎቱ ስብሐት!!) ማለት ክርስትናን ከሥሩ ፈንቅሎ መጣል ነው::
+ስለ ክርስቶስ እግዚአብሔርነት ብሉይም ሐዲስም እየመሰከሩ:-
(ኢሳ. 9:6, መዝ. 46:5, 77:65, ዘካ. 14:4, ዮሐ. 1:1, 10:30, ራዕይ. 1:8, ሮሜ. 9:5 . . .)
ቅዱስ ጳውሎስም ˝ከስምም ሁሉ በላይ የሆነውን ስም ሰጠው˝ ፊል2÷9፤በማለት እንደገለጸው ለዚህ ስም እንሰግዳለን፤እንገዛለን፤እንንበረከካለን፤ከሰማይ በታች፤ከምድርም በላይ ያለው ፍጥረት ሁሉ ለዚህ ስም ይሰግዳል፤ቅዱሳን አባቶቻችንም ይህንን ስም በልባቸው ይዘው በአንገታቸው አስረው ለእሳት ለስለት፣ለመስቀልና ለችንካር ራሳቸውን አሳልፈው ስለሰጡ እናከብራቸዋለን፤አብነት እናደርጋቸዋለን፤˝ኢየሱስ˝ የሚለው ስሙ ለተጻፈበት ታቦት(ጽላት) እንሰግዳለን እንንበረከካለንም፤ፊል2÷10፡፡ ታቦት ሁሉ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይጻፍበታል፤ መታሰቢያነቱ የእመቤታችን፤ የቅዱሳን መላእክት ፤የጻድቃን የሰማዕታት ቢሆንም እንኳን ከእነርሱ ስም አስቀድሞ ግን ግዴታ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይጻፍበታል፤ ለእርሱ የባህርይ ስግደት ለፍጡራኑ ግን የጸጋ ስግደት እናቀርባለን፡፡
ይህ ስም ከሰዎች ብቻ ሳይሆን ከመላእክትም በላይ እንደሆነ ቅዱስ ጳውሎስ ˝ከመላእክት ይልቅ እጂግ የሚበልጥ ስምን በወረሰ መጠን እንዲሁ ከእነርሱ አብዝቶ ይበልጣል˝ ዕብ 1÷4 ብሎ አስተምሮናል፡፡ የቅዱሳን መላእክት የሐዲስ ኪዳን ተልእኳቸውና አገልግሎታቸው ሁላችንም ይህ ስም እንዲኖረንና በዚህ ስም እንድንታተም መርዳት ሲሆን፤የቅዱሳን፣የጻድቃን፣የሰማዕታት፣የመነኮሳትና የሊቃውንት ተጋድሎ፤የካህናትና የምእመናን ሕይወት ሁሉ ይህንን ስም መሠረት ያደረገ መሆኑን ልብ ይሏል፤ በዚህ ስም ˝ንስሓና የኃጢአት ሥርየት ይሰበካል˝ ሉቃ 24÷47፤ዮሐ 20÷31፤ሐዋ 3÷16፤10÷43፤ዕብ 6÷10፤1ኛ ዮሐ 2÷12፤3ኛ ዮሐ 3÷5፤ራእ 22÷4፡፡፡፡
"ስምህን ንገረኝ" ከሚለው መጽሐፌ የተወሰደ
ስሙ ኃይል መድኃኒት ሆኖ ሀገራችንን ከክፉ ይጠብቅልን!
አሜን!
መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው
ዘመካኒሳ ሚካኤል
ከ ኖርዌይ ስታቫንገር
(Norway Stavanger)
#ኢየሱስ
ጥር ስድስት ቀን በዓለ ግዝረት ነው ፤ኢየሱስ የሚለው ስም በይፋ የታወቀበት!
እንኳን_አደረሳችሁ!
የቴሌግራም ቻናሌ 👇
/channel/+7zjBq7YYL_oyYmU0
"ወትሰምዪዮ ስሞ ኢየሱስ"
"ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ" (ሉቃ 1÷31)
"ወዓዲ ይሰመይ ኢየሱስሃ ዘያድኅኖሙ ለሕዝቡ እምኃጢአቶሙ" (ዳግመኛም ወገኖቹን ከኃጢአታቸው የሚያድናቸው ኢየሱስ ይባላል) ውዳ.ማር.ዘሐሙስ፡፡
• ኢየሱስ ማለት መድኃኒት ማለት ሲሆን ይህ ስም የወጣለት በተወለደ በስምንት ቀን መሆኑ ይታወቃል፤ይህም በሥርዓተ -ኦሪት መሠረት ወንድ ልጅ በተወለደ በስምንት ቀን ወደ ቤተ ግዝረት በመሄድ ከተገረዘ በኋላ የወንድነቱ ስም ይሰጣል፤በይፋ የሚጠራበት ስም ለሁሉም ይታወቃል፤ሰፈሩና መንደሩ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በዚህ ስም ይጠሩታል ፤ይህ ስም የትውልድ ሐረግ ዝርዝር ውስጥ የሚገባ፤ዘሩ ወይም ትውልዱ የሚቆጠርበት፤ለቤተ ክሀነት አሥራት ለቤተ መንግሥት ግብር የሚከፍልበት ስም ነው፤ጌታችንም በስሙ ግብር መክፈሉ ይታወቃል፤ ማቴ 17፡27፡፡
• ኢየሱስ የሚለው ስም እንደ ሌሎቹ እስራኤላውያን ናዝራውያን ወንዶች በዕለቱ የወጣ ወይም በመልአክ የተነገረ ብቻ ሳይሆን ከዓለም መፈጠር አስቀድሞ በልበ ሥላሴ የነበረ መሆኑን ልበ አምላክ ዳዊት "እምቅድመ ፀሐይ ሀሎ ስሙ፤ ስሙ ከፀሐይ በፊት ነበረ" (መዝ 71÷17) በማለት ተናግሯል፡፡
• ይህንን ከዓለም በፊት የነበረውን ስሙን ከሰማይ ተቀብሎ ለእመቤታችን እንዲናገር የተላከው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ሲሆን ˝ስሙን የመሰየም˝ ሥልጣን የተሰጣት ደግሞ እመቤታችን ናት፡፡
• ምንም እንኳን ማቴዎስ ˝ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ˝……..˝ስሙን ኢየሱስ አለው˝ (ማቴ 1፡21-25) በማለት ለዮሴፍ ሰጥቶ ቢናገርም በልማደ አይሁድ የወንድን ስም የሚያወጣው ወንድ በመሆኑ በዚያ ልማድ ጻፈ እንጂ ስም የማውጣት ሥልጣኑስ የእመቤታችን እንደሆነ ቅዱስ ሉቃስ እንደጻፈው መልአኩ የተላከውን ሳያዛባ፤ሳይጨምርና ሳይቀንስ በተናገረበት ብሥራት ላይ ራሱ ˝ኢየሱስ ትይዋለሽ˝ ሉቃ 1÷31 ብሎ ቁልጭ አድርጎ ተናግሯል፡፡
• በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ለወንድ ልጅ ስም የማውጣት ሥልጣን የተሰጣት ሴት እመቤታችን ብቻ ናት፤ይህን ቃል ከመልአክ ከሰማይ የተቀበለችው፤የፀነሰችው እሷ ናትና፤ የዚህን ስም ጥልቅ ትርጉምም የምታውቀው እሷ ብቻ ናትና ነው፤
• እኛ በቃል በጽሑፍ፤በመማር በማስተማር፤በትንቢት በተአምራት፤በጥምቀት በልጅነት የምናውቀውን እሷ ግን ✔በመውለድ በእናትነት ታውቀዋለች✔፡፡
• ኤልሳቤጥ ለዮሐንስ ስም ስታወጣ ተቀባይነት እንዳላገኘች ሉቃ1÷61 ተመልከት! ይህም እመቤታችንን ከሁሉም እናቶች ልዩ ያደርጋታል በተለይም ከብሉይ ኪዳን እናቶች፤ የዚህ ምሥጢር ፍጻሜ ደግሞ ያለ አባት ወልዳዋለችና እናት ብቻ ሆና እንዳሳደገችው ማመልከት ነው፡፡
ስም ማለት ከራስ ጠጉር እስከ እግር ጥፍር ድረስ ያለ መላ ሰውነት፤ ሙሉ የአካል ክፍል መጠሪያ ነው፤ሰው ስሙ ሲጠራ መላ አካላቱ ሕዋሳቱ መልስ ይሰጣሉ፤አንደበት ብቻ አቤት ይበል እንጂ መልሱ ግን የሁሉም የአካል ክፍሎቻችን ነው፤፡፡
ክርስቶስም "ኢየሱስ" ተብሎ በመጠራቱ "ለድኅነታችን" መልስ የሰጠን አዳምን ወክሎ መስቀል ላይ አቤት ያለልን ፍጹም ሰውነትን የያዘ መሆኑን ያሳየናል፤የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋዊና ነፍሳዊ አካል ቁመና ሙሉ አዳማዊነት ያለው ፤የአካል ክፍሎቹ ሲቆጠሩ ምንም ያልጎደለው፤እንዲሁም የዘር ቅንጣት (gen) ሙሉ ለሙሉ ከአዳም የተወረሰ ግን ምንም በደል፤መርገም ያላረፈበት መሆን አለበት፡፡
ይህንን ምሥጢር ሊቁ አባ ሕርያቆስ፡-
"ምእናም አንቲ ዘእምኔኪ ለብሰ አማኑኤል ልብሰተ ሥጋ ዘኢይተረጐም" "አማኑኤል የማይመረመር ተዋሕዶን ባንቺ ያደረገብሽ የሸማኔ ጉድጓድ አንቺ ነሽ" በማለት በመንፈስ ቅዱሰ ጠባቂነት በትንቢት በሱባዔና በተስፋ እየተሸመነ የመጣውን ዘር ይገልጠዋል፤
ዳግመኛም፡-
"ስፍሖ ገብረ ዘእምጥንተ ሥጋሁ ለአዳም" (ዝኃውን ከአዳም ከመጀመሪያው ሥጋው አደረገ) በማለት ከተናገረ በኋላ " ወፋእሙኒ ሥጋ ዚአኪ " "ማጉም ያንች ሥጋ ነው" በማለት ያስረዋል፤"ፋእም" ማለት ቀጥታ ትርጉሙ ጉርሻ ማለት ነው ይህም ለመጎረስ(ለተዋሕዶ) የደረሰ በትንቢት፤በሱባዔና በተስፋ ሲበስል የነበረ መሆኑን ያሳያል፤ ሥጋዋ ኃጢአት የለበትምና ፤(ቅዳ.ማር.)፡፡
ሊቁም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም "ተሥዕለ በጥንተ አካል እንዘ ይትዋሐድ ቃል ምስለ ሥጋ፤ነጽርኬ ኀበ ሠዐሌ ኅፃናት ዘበጥንተ ሙላዱ ወጠነ ፍኖተ ነካረ" (ቃል ከሥጋ ጋር ሲዋሐድ በመጀመሪያው አካል ልክ ተቀረጸ፤በጥንቱ ፍጥረት ሥርዓት ድንቅ መንገድን የጀመረ ሕፃናትን ወደ ፈጠረ ጌታ ተመልከት ) ብሏል፡፡
ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግም እንዲህ ይለናል "የእግአብሔር ልጅ ሆይ መወለድህ እንዲህ ድንቅ ነው፤በሴቶች ማኅፀን ሳሉ ሕዋሳትን ፈጥሮ በየጥቂቱ የሚያሳድግ የሕፃናት ፈጣሪ ራስ ቅልን ፈጥሮ በፈጸመ ጊዜ ጌትነቱ የሚገለጥበት የራስ ጠጉርም ተፈጥሮ በተፈጸመ ጊዜ እርሱ ባወቀ ሕዋሳትን በየመልካቸው አንድ አድርጎ ከራስ ጠጉር እስከ እግር ጥፍር ያለውን ፍጹም አካል ፈጥሮ በጨረሰ ጊዜ ፍጹም አካሉን በማኅፀን ቀረጸ መልክአ ሰብእን ፍጹም አደረገ ፤ነፍስ ያለው ሥጋውን ፈጥሮ ፈጸመ በአምላክነት ክብርም አጸናው" (ሃይ.አበ 88÷2) በማለት ቁልጭ አደረገልን፡፡
እንዲህ ሲሆን የሚከፈለው ካሳ ሙሉ ይሆናል፤ክርስቶስ ሲገረፍ ፤ሲቆስልና ሲሰቀል፤ይህ የቆሰለው አካል ሙሉው ለአዳም አካል ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍር ድረስ ፤ከጫፍ እስከ ጫፍ፤ከጥግ እስከጥግ ካሳ ሆኖ መቆረስ ስላለበት ነው፤
ሊቁ ይህንም እንዲህ ይገልፀዋል "ፈድዮ ሥጋ ዚአሁ ለዘበአማን ሥጋ ዚአነ ወነፍሶ ካዕበ ቤዛ ነፍሰ ኩልነ መጢዎ"(ሥጋውን ለእውነተኛ ሥጋችን ከፍሎ፤ነፍሱንም እንዲሁ ስለ ሁላችን ነፍስ ፋንታ ሰጠ) ይላል፡፡
ክርስቶስ ያልነሣው፤አካል ያላደረገው፤ወይም አዳም በኩር ያልሆነለት አካል፤ወይም ካሳ ያልተከፈለለት የሰው አካል ቢኖር ግን ሕያው መሆኑ ይቀርና በመቃብር ፈርሶ በስብሶ መቅረት ይመጣ ነበር፤ይህ ግን እንዳይሆን መዳናችን ሙሉ እንዲሆን፤አካላችን አካሉ እዲሆን እራሱ ራሳችን እንዲሆን ሁለተኛው አዳም ከኃጢአት በስተቀር በሥጋው ሙሉ ቀዳሚ አዳምን ሆነ፤ ይህ አካል ወደ መቃብር ሲወርድ ለእኛ ሥጋ ተስማሚ የነበረውን ሙስና መቃብርን ያጠፋዋል፡፡
ሊቃውንቱም በዚህ ስሙ "ከብረ(ከበረ) ፤ተለዐለ(ከፍ ከፍ አለ) ፤ኀየሰ(በለጠ) ፤ወረሰ፤ ነግሠ (ነገሠ)" መባልን ገንዘብ አደረገ ብለው አመሥጥረዋል፡፡
ቅዱስ ጳውሎስም ˝ከስምም ሁሉ በላይ የሆነውን ስም ሰጠው˝ ፊል2÷9፤በማለት እንደገለጸው ለዚህ ስም እንሰግዳለን፤እንገዛለን፤እንንበረከካለን፤ከሰማይ በታች፤ከምድርም በላይ ያለው ፍጥረት ሁሉ ለዚህ ስም ይሰግዳል፤ቅዱሳን አባቶቻችንም ይህንን ስም በልባቸው ይዘው በአንገታቸው አስረው ለእሳት ለስለት፣ለመስቀልና ለችንካር ራሳቸውን አሳልፈው ስለሰጡ እናከብራቸዋለን፤አብነት እናደርጋቸዋለን፤˝ኢየሱስ˝ የሚለው ስሙ ለተጻፈበት ታቦት(ጽላት) እንሰግዳለን እንንበረከካለንም፤ፊል2÷10፡፡ ታቦት ሁሉ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይጻፍበታል፤ መታሰቢያነቱ የእመቤታችን፤ የቅዱሳን መላእክት ፤የጻድቃን የሰማዕታት ቢሆንም እንኳን ከእነርሱ ስም አስቀድሞ ግን ግዴታ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይጻፍበታል፤ ለእርሱ የባህርይ ስግደት ለፍጡራኑ ግን የጸጋ ስግደት እናቀርባለን፡፡
ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ያዘጋጀውን የ10 ቀን ስልጠና በመውሰድ እስከ 9,000$ ዶላር (700,000 ብር) የስራ መጀመሪያ ያለማስያዢያ ይውሰዱ በኦንላይን በድረ ገፅ ወይም መተግበሪያቸው ቶሎ ተመዝገቡ ማሳሰቢያ ይህ እድል ለ""""የመስሪያ ቦታ ላላቸው ቡቻ"""!!! ወይም በስራ ላያ ላሉ ነው መስሪያ ቦታ የሌለውን አይቀበሉም የሁለት አመት የኪራይ ውል ተከራይቶ ካመጣ ብቻ ምንም ክፍያ የለውም ነፃ ነው👍sign up for world farming foundation download here
Get up to $9,000 (700,000 Birr) by taking the 10-day training organized by the Master card Foundation. Register quickly online on their website or app. They do not accept those who do not have a place to work, but only if they bring a two-year lease its free off fee
/channel/Mster_Card_foundation_Et
#የጥምቀት_መዝሙር_፪
Follow us on
👉 /channel/fre_amde_haymanot_media
👉 http://linktr.ee/fre_amde_haymanot_media
ትጋት የተስፋ ልጅ ናት።
፨፨፨፨፨፨፨////////////፨፨፨፨፨፨፨፨
"...በሰዎች ዘንድ ተስፋ የሌለን ብንመስልም እንኳን ዋናው ነገር በፈጣሪ ዘንድ ያለው ተስፋችን ነው፡፡ ሕይወት ጠመዝማዛም ብትሆን ውብና ተስፋን የተሞላች ናት! በዚህ ዓለም ሁሉም ነገር አበቃ አከተመ! ባልንበት ጊዜ የሚቀጥል የተሻለ እድል! የምናውቀውና የተለመደው በር የተከረቸመ ቢመስልም ወለል ብሎ የሚከፈት ሌላ በር ዙሪያችን አለ!
ጭው ያለ በርሃ ቢሆንም የለመለመ መስክ የሆነ ስፍራ አለ፡፡
ዕድል ፊቷን ያዞረችብን በመሰለን ጊዜም ቢሆን እንኳን አብዝቶ በትጋት መጓዝ እንጂ ተስፋ መቁረጥ አይገባም፡፡ ትጋት የተስፋ ልጅ ናት። ተስፋ ደግሞ በእኛ እና በፈጣሪ መካከል የእምነት ድልድይ ስለመኖሩ ማረጋገጫ ነውና! "
/ከደ/ር አለማየሁ ዋሴ እሸቴ አንደበት/
መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንልን!!
....?......?......?.. @Meklite21
💚➱ t.me/Asresee
💛➱ t.me/Asresee
❤➱ t.me/Asresee
✞ እንኳን ለቅዱስ "ማቴዎስ ነዳይ" እና "ቅዱስ አውስግንዮስ አረጋዊ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችኹ✞
+*" ቅዱስ አባ ማቴዎስ "*+
=>ቅዱሱ አባት በቤተ ክርስቲያናችን ስመ ጥር ነው:: በተለይ ትርጉዋሜ ወንጌል ላይ እንደ አብነት ሲጠቀስ የተአምረ ማርያምን ሥርዓት በማዘጋጀቱ የበዓላት መቅድመ ተአምር ላይ ስሙ አለ:: ቅዱሱ ለእመቤታችን በነበረው ፍቅር ድንግል ብዙ ጊዜ ትገለጥለት ነበርና::
+ቅዱስ ማቴዎስ ግብጻዊ አባት ሲሆን የነበረው በመካከለኛው ዘመን ውስጥ (ማለትም በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን) ነው:: በቤቱም መልካም ወላጆችና ያዕቆብ የሚባል ወንድምም ነበረው::
+እንዲያውም አንዴ እናቱ ቅዱሱን ጸንሳ ሳለች የበቁ አበው ሆዷን እጅ ነስተው "ቅዱስ ፍሬ በማኅጸንሽ ውስጥ አለ" እንዳሏት ይነገራል:: ቅዱስ ማቴዎስ በልጅነቱ ወደ እግዚአብሔር ከመገስገስ: ቅዱስ ቃሉን ከመማር በዘለለ ሌላ ሃሳብ አልነበረበትም::
+ወጣት ሲሆንም ወላጆቹ ተከታትለው በማረፋቸው ከወንድሙ ያዕቆብ ጋር ለብቻቸው ቀሩ:: ብዙ የወላጆቹ ሃብት ቢኖርም ቅዱስ ማቴዎስ ስለ መካፈል አላሰበም:: ከለበሳት ጨርቅ በቀር ምንም ሳይይዝ ወደ በርሃ ገሰገሰ::
+ሊመነኩስ ወዶ የደብረ ቅዱስ አቡፋናን አበው ቢጠይቃቸው "አይሆንም" አሉት:: ምክንያቱም በጊዜው ወንድሙን ያውቁት ስለ ነበር እየመጣ እንዳያውካቸው "አስፈቅድ" ማለታቸው ነበር:: ቅዱስ ማቴዎስ ግን ወደ ሌላ ገዳም ሔዶ አለቀሰ::
+አባቶችም ወደ ወንድሙ ሔደው ስለ ማለዱት ፈቀደለት:: ስለዚህም በደብረ አቡፋና መነኮሰ:: ትንሽ ቆይቶ ግን ወንድሙ ያዕቆብ "ለወንድሜ ያልሆነች ዓለም ለእኔም አትረባኝም" ብሎ: በርሃ ገብቶ በቅቶ ዐርፏል::
+ቅዱስ ማቴዎስም በገዳሙ በፍቅርና በመታዘዝ ሲያገለግል ዜና ትጋቱ ተሰማ:: ይህንን ከሰሙት ዻዻሳት አንዱ አባ ዼጥሮስ ያለ ፈቃዱ ከገዳም አስወጥቶ በመንበረ ዽዽስናው ረዳት አደረገው:: እርሱ ግን አንገቱን አቀርቅሮ ተጋድሎውን በጾምና በጸሎት ቀጠለ::
+ነገር ግን ሰይጣን በሴቶች አድሮ ፈተነው:: በጣም አዝኖ ዻዻሱን "አሰናብተኝ" አለው:: "እንቢ" ቢለው የክብር ልብሱን (የዻዻሱን) አውጥቶ በመቀስ ብጥስጥስ አደረገውና በዻዻሱ ፊት አኖረለት::
+ፈጽሞ የተበሳጨው ዻዻሱም በየቀኑ 300 እንዲሰግድ: ወደ ቤት እንዳይጠለልና ሌሎች ቀኖናዎችን ቅጣት ሰጥቶ ወደ በርሃ አሳደደው:: ቅዱስ ማቴዎስም መሻቱ ይህቺው ነበረችና ደስ እያለው ሔደ::
+ለ2 ዓመታትም የቀኑ ሐሩር: የሌሊቱ ቁር እየተፈራረቀበት ቅጣቱን በመፈጸሙ የፍትሐት ደብዳቤ ተላከለት:: አንድ ቀን ግን በገዳሙ የነበረ አንድ የበቃ አባት ክብረ ማቴዎስ ተገልጦለት "የብዙዎች አባት ትሆናለህ" አለው::
+ውዳሴ ከንቱን ፈጽሞ የሚጠላት ቅዱሱ ግን አዘነ:: ሰዎች እያከበሩት ስለተቸገረም ገዳሙን ለቀቀ:: በሔደበት ገዳምም ድንቅ ነገሮቹን እያዩ ሲያከብሩት በአንድ ገዳም የማይቀመጥ ሆነ:: ከአንዱ ወደ ሌላውም ይሔድ ነበረ::
+ቅዱስ ማቴዎስ ከዻዻሱ ዘንድ እያለ ቅስናን ሹሞት ነበርና በገዳማት ይቀድሳል:: ከብቃቱም የተነሳ በቅዳሴ ሰዓት ማሕበረ መላእክትን ያያቸው ነበር:: መድኃኒታችን ክርስቶስም ሕጻን መስሎ ከፊቱ ይቀመጥ ነበር:: ስለዚህ ነገርም ዕንባው እንደ ዥረት ውሃ ይፈስ ነበር:: እየቀደሰም ተመስጦ (ተደሞ) ይመጣበት ነበር::
+ዘወትር የፈጣሪውን ጌትነት እያደነቀ ይመራመር ነበርና አንዴ ቀና ቢል 7ቱ ሰማያት ተከፈቱለት:: እግዚአብሔርንም ከጽርሐ አርያም (7ኛው ሰማይ) ከፍ ብሎ አየው:: ደንግጦ ዝቅ ቢል ደግሞ ከጥልቁ በታች ተመለከተው::
+በዚህ ጊዜ "ይህን ያሳየኸኝ ጌታየ እኔ ማነኝ!" ሲል አለቀሰ:: ሁሌ ዐርብም ሕማማተ ክርስቶስን: በተለይ መድኃኒታችን መቸንከሩን እያሰበ ረጅም ችንካርን በጉልበቱ ውስጥ ይከት ነበር:: ለቀናት ስለማያወጣውም ደሙ ፈሶ አካሉ መልኩ ይቀይር ነበር::
+እንዲህ ካሉ የቅድስናና የተጋድሎ ዓመታት በሁዋላም ሌላ ጥሪ ከፈጣሪው መጣለት:: አበው በጸሎት ላይ ሳለ መጥተው አሠሩት:: "ምን አደረኩዋችሁ አባቶቼ?" ቢላቸው የግብጽ ፓትርያርክ ነህ ከዚህ በሁዋላ" አሉት:: ቢለምናቸውም እንቢ አሉት::
+"እንግዲያውስ" ብሎ: ምላሱን አውጥቶ: በመቀስ ቆርጦ ጣላት:: መናገር የማይችል ሰው ክህነት አይሾምምና:: (እንዲህ ነበር አበው ሥልጣንን የሚሸሿት) ነገር ግን እመቤታችን ከሰማይ ወርዳ "ወዳጄ! ነገሩ የልጄ ፈቃድ ስለ ሆነ እሺ በላቸው" ብላ አዲስ ምላስን ሰጠችው::
+የግብጽ 87ኛ ሊቀ ዻዻሳት ሆኖ ሥርዓተ ሲመቱ ሲፈጸም የወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስ ራሱ በዚያ ነበረችና ክንፍ አውጥታ: በራ ቅዱስ ማቴዎስን ስትስመው ሁሉም አዩ:: ከሰማይም ማሕበረ መላእክት "አክዮስ-ይገባዋል" ብለው ሲጮሁ ተሰማ::
+ቅዱስ ማቴዎስ ምንም ፓትርያርክ ቢሆንም ለትምሕርት: ለቅዳሴና መሰል ነገሮች ካልሆነ ከበዓቱ አይወጣም ነበር:: ገንዘብ የሌለው: ጥሩ ልብስ የማይለብስ ነበርና "ነዳዩ" እየተባለ እስካሁን ይጠራል::
+በዘመነ ዽዽስናው ብዙ ተግባራትን ሲከውን ዋኖቹ ግን የእመቤታችን ተአምር በሥርዓት እንዲነበብ ማድረጉ ቀድሞ ይጠቀሳል:: በተረፈም የጌታችን ግማደ መስቀሉ ወደ ኢትዮዽያ እንዲመጣም ትልቅ አስተዋጽኦን አድርጉዋል::
+በተሰጠው የትንቢት ሃብትም ወደ ፊት የሚፈጸሙ ነገሮችን ተመልክቷል:: የተናገራቸውም ሁሉ ተፈጽመዋል:: በመጨረሻው ግን ያሰቃየው የነበረው የወቅቱ የግብጽ ከሊፋ (ክፉ ሰው) አስጠርቶ አካሉ እስኪደቅ ድረስ ገረፈው::
+ቅዱስ ማቴዎስም ወደ እመቤታችን ጮኸ:: ድንግልም ወርዳ አጽናናችውና "አሳርፍሃለሁ" አለችው:: ሕዝቡን ተሰናብቶም በዚህች ቀን ዐርፏል::
+*" ቅዱስ አውስግንዮስ አረጋዊ "*+
=>ይህ ቅዱስ ሽማግሌ በሃይማኖቱ ጽናት: በምግባሩ ብዛት ለወጣቶች አብነት መሆን የቻለ አባት ነው:: በብዛት የሚታወቀው በሰማዕትነቱ ቢሆንም በቅዱስ ሰውነቱ በርካታ መልካም ነገሮችን ሠርቷል::
+በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን መነሻ አካባቢ (ዘመነ ሰማዕታት ሊጠናቀቅ ሲል ማለት ነው) የቅዱስ ቆስጠንጢኖስ (የንጉሡ) ወታደር ሁኖ ተቀጠረ:: ንጉሡ ወደ መክስምያኖስ ለጦርነት ሲሔድ በሰማይ ላይ መስቀልና "ኒኮስጣጣን" የሚል ጽሑፍን ተመልክቷል::
+ሁሉም ሰው ለመተርጐም ሲፈራ ወጣቱ አውስግንዮስ ግን በድፍረት ለንጉሡ ክብረ መስቀልንና ትርጉሙን አስረዳ:: በቅዱሱ ንጉሥ ሥርም በወታደርነት ለ20 ዓመታት አገለገለ::
+ከዚያም ሥጋዊ ተግባሩን ትቶ በጾምና በጸሎት: ሰዎችንም በማስታረቅ: በማስተማርም ተወሰነ:: ፈጣሪ ጸጋውን አብዝቶለትም ዕድሜው 110 ዓመት ደረሰ::
+በጊዜውም የነበረው ከሃዲው ዑልያኖስ "ሰዎችን አስታርቀሃልና ክርስቶስን አምልከሃል" በሚል በዚህች ቀን አንገቱን አሰይፎታል:: ዑልያኖስን ደግሞ ቅዱስ መርቆሬዎስ ተበቅሎታል::
=>አምላከ ቅዱሳን ስለ አባቶቻችን ሲል ይማረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
=>ጥር 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አባ ማቴዎስ
2.ቅዱስ አውስግንዮስ አረጋዊ (ሰማዕት)
"በእጅህ ያለው ጊዜ ዋጋ እንዳለው አስታውስ ይህን ወርቃማ ጊዜህን ፈልገህ የማታገኝበት ጊዜ ይመጣል ስለዚህ የሕይወትህን ሙሉ ጊዜ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መንገድ አሳልፈው።"
[ባህታዊ ቲዎፋን]
ቅዱስ ቀን ይሁንልን
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን:: †††
=>+"+ እንኳን ለቅዱሳን አበው "አባ መቃርስ" እና "ቅዱስ ሚክያስ ነቢይ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችኹ +"+
+*" ታላቁ ቅዱስ መቃርስ "*+
=>ታላቁ ቅዱስ መቃርስ (ቅዱስ መቃሬ) "ጽድቅ እንደ መቃርስ" የተባለለት የመነኮሳት ሁሉ አለቃ: ከ80 ዓመታት በላይ በበርሃ የኖረ: በግብፅ ትልቁን ገዳም (አስቄጥስን) የመሠረተ: ከ50,000 በላይ መነኮሳትን ይመራና ይመግብ የነበረ ፍፁም ጻድቅ ነው::
+በ4ኛው መቶ ክ/ዘ አርዮሳውያን ደጉን ታላቅ አባት በሰንሰለት አስረው ከግብፅ ወደ እስያ በርሃ ከጉዋደኛው ቅዱስ መቃርዮስ እስክንድርያዊ ጋር አሰድደውታል:: በዚያ ለ2 ዓመታት ስቃይን ከተቀበሉ በሁዋላ በአረማውያን ፊት ድንቅ ተአምር አድርገው አረማውያንን ከነ ንጉሳቸው አጥምቀዋል::
+በተሰደዱባት ሃገርም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ (ስም አጠራሩ ይክበርና) እመቤታችንን: ቅዱሳን ሐዋርያትን: አዕላፍ መላእክትን: በተለይ ደግሞ ቅዱሳኑን ዳዊትን: ዮሐንስ መጥምቁንና ወንጌላዊውን: ማርቆስን: ዼጥሮስን: ዻውሎስን አስከትሎ ወርዶ ተገልጦላቸዋል:: በቅዱስ አንደበቱም የምሕረት ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል::
+ታላቁ ቅዱስ መቃርስና ባልንጀራው መቃርዮስ ከ2 ዓመታት ስደትና መከራ በሁዋላ ስደት በወጡባት ዕለት መልዐኩ ኪሩብ በክንፉ ተሽክሞ ወደ ግብፅ መልሷቸዋል:: በወቅቱም ጻድቁን ለመቀበል ከ50,000 በላይ የሚሆኑ ልጆቻቸው መነኮሳት በዝማሬ ወጥተዋል::
=>ቅዱስ መቃርስ ካረፈ በሁዋላ ከክቡር ሥጋው ብዙ ተአምራት ይታዩ ነበርና የሃገሩ (የሳስዊር) ሰዎች ሊወስዱት ፈለጉ:: ሳስዊር ማለት ቅዱሱ ተወልዶ ያደገባት ወላጆቹ (አብርሃምና ሣራ ይባላሉ) የኖሩባት ቦታ ናት:: የምትገኘውም ግብጽ ውስጥ ነው::
+በምድረ ግብጽ: በተለይም በገዳመ አስቄጥስ የአባ መቃርስን ያህል ክቡርና ተወዳጅ የለምና የሃገሩ ሰዎች የነበራቸው አማራጭ መስረቅ ነበር:: መሥረቅ ኃጢአት ቢሆንም እነሱ ግን ስለ ፍቅር: አንድም ለበረከት አደረጉት::
+ወደ ሳስዊርም ወስደው: ቤተ ክርስቲያን በቅዱሱ ስም አንጸው በክብር አኖሩት:: በዚያም ለመቶዎች ዓመታት ተቀመጠ:: በ7ኛው መቶ ክ/ዘመን ግን ተንባላት (እ+ስ+ላ+ሞች) መጥተው ቤተ ክርስቲያኑን አጠቁ:: በዚህ ጊዜም ሕዝቡ የጻድቁን አጽም ይዘው ሸሹ:: በሌላ ቦታም እንደ ገና በስሙ ቤተ ክርስቲያን አንጸው በዚያ አኖሩት::
+በእነዚህ ሁሉ ዓመታት የመንፈሳዊ አባታቸውን ሥጋ ያጡት የገዳመ አስቄጥስ ቅዱሳን ያዝኑ ይጸልዩ ነበርና ልመናቸውን ፈጣሪ ሰማ:: አባ ሚካኤል ሊቀ ዻዻሳት በነበረበት ዘመን: ከገዳሙ ለሌላ ተግባር ወደ ሳስዊር የተላኩ አበው ከታላቁ አባት ቤተ ክርስቲያን ሲደርሱ ሰውነታቸው ታወከ::
+ይዘው ለመውሰድ ሙከራ ቢያደርጉ ሊሳካላቸው አልቻለም:: ምክንያቱም የቤተ ክርስቲያኑ ጠባቂ ደወል ደውሎ ሕዝቡን ሁሉ ጠርቶ ነበርና:: ሕዝቡና ሃገረ ገዢው የሆነውን ሲሰሙ "የቅዱሱን ሥጋ ብትነኩ እንገላቹሃለን" ብለው ሰይፍ: ዱላ: ጐመድና ጦር ይዘው መጡባቸው::
+መነኮሳቱ ግን ባዷቸውን ሊመለሱ አልፈቀዱምና ሌሊቱን ሲያለቅሱና ሲጸልዩ አደሩ:: መ+ን+ፈ+ቀ ሌሊት በሆነ ጊዜም ታላቁ መቃርስ በግርማ ወርዶ መኮንኑን "ለምን ወደ ልጆቼ እንዳልሔድ ትከለክለኛለህ?" ሲል በራዕይ ተቆጣው:: በዚህ ምክንያትም መነኮሳቱ የቅዱሱን ሥጋ ተቀበሉ::
+ሕዝቡም በዝማሬና በማሕኅሌት: ከብዙ እንባ ጋር ሸኟቸው:: ታላቁ መቃሬ ወደ ገዳሙ ሲደርስም ታላቅ ደስታ ተደረገ:: ቅዱሳን ልጆቹ ከመንፈሳዊ አባታቸው ተባርከው በክብር አኑረውታል::
=>ይህቺ ዕለት ቅዳሴ ቤቱ ስትሆን የተቀደሰችውም በ7ኛው መቶ ክ/ዘ በአባ ብንያሚን እጀ ነው::
+*" ቅዱስ ሚክያስ ነቢይ "*+
=>ነቢይ ማለት በቁሙ ኃላፍያትን (አልፎ የተሠወረውን ምሥጢር): መጻዕያትን (ገና ለወደ ፊት የሚሆነውን) የሚያውቅ ሰው ማለት ነው:: ሃብተ ትንቢት የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ሲሆን እርሱ ለወደደው ደግሞ በጸጋ ይሰጠዋል:: እነዚህም ከጌታ ሃብተ ትንቢት የተሰጣቸው አባቶችና እናቶች "ቅዱሳን ነቢያት" በመባል ይታወቃሉ::
+ዘመነ ነቢያት ተብሎ የሚታወቀው ብሉይ ኪዳን ቢሆንም እስከ ምጽዓት ድረስ ጸጋውን እግዚአብሔር ለፈቀደላቸው አይነሳቸውም:: በሐዋርያት መካከልም ቅዱስ አጋቦስን የመሰሉ ነቢያት ነበሩ:: (ሐዋ. 11:27)
+ቅዱሳን ነቢያት ከእግዚአብሔር እየተላኩ ሰውን ከፈጣሪው እንዲታረቅ ይመክራሉ: ይገስጻሉ:: ከበጐ ሃይማኖታቸውና ንጽሕናቸው የተነሳም እግዚአብሔርን በተለያየ አርአያና አምሳል አይተውታል::
"እስመ በአንጽሖ መንፈስ ርዕይዎ ነቢያት ለእግዚአብሔር:: ወተናጸሩ ገጸ በገጽ::" እንዳለ አባ ሕርያቆስ:: (ቅዳሴ ማርያም)
+የብዙ ነቢያት ፍጻሜአቸው መከራን መቀበል ነው:: እውነትን ስለ ተናገሩ: አንዳንዶቹም በእሳት: አንዳንዶቹም በሰይፍ: አንዳንዶቹም በመጋዝ ተፈትነዋል:: ሌሎቹ ለአናብስት ሲጣሉ ቀሪዎቹ ደግሞ በድንጋይ ተወግረዋል::
+ስለዚህም መከራቸው ለቤተ ክርስቲያን መሠረት ተብለዋል:: ጌታም ለደቀ መዛሙርቱ "ሌሎች ደከሙ: እናንተ በድካማቸው ገባችሁ" ብሎ የነቢያቱን መከራ ተናግሯል:: (ዮሐ. 4:36)
+ነቢያት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና እና ድንግል እናቱን ለማየት ብዙ ጥረዋል: ሽተዋልም:: "ብዙ ነቢያትና ጻድቃን እናንተ የምታዩትን ሊያዩ ሹ" እንዳለ ጌታ በወንጌል:: (ማቴ. 13:16, 1ዼጥ. 1:10) ዛሬ ግን በሰማያት ጸጋ በዝቶላቸው: ክብር ተሰጥቷቸው ሐሴትን ያደርጋሉ::
+ቅዱሳን ነቢያት በዋነኝነት 15ቱ አበው ነቢያት: 4ቱ ዐበይት ነቢያት: 12ቱ ደቂቀ ነቢያትና ካልአን ነቢያት ተብለው በ4 ይከፈላሉ::
=>"15ቱ አበው ነቢያት" ማለት:-
*ቅዱስ አዳም አባታችን
*ሴት
*ሔኖስ
*ቃይናን
*መላልኤል
*ያሬድ
*ኄኖክ
*ማቱሳላ
*ላሜሕ
*ኖኅ
*አብርሃም
*ይስሐቅ
*ያዕቆብ
*ሙሴና
*ሳሙኤል ናቸው::
=>"4ቱ ዐበይት ነቢያት"
*ቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ ቃል
*ቅዱስ ኤርምያስ
*ቅዱስ ሕዝቅኤልና
*ቅዱስ ዳንኤል ናቸው::
=>"12ቱ ደቂቀ ነቢያት"
*ቅዱስ ሆሴዕ
*አሞጽ
*ሚክያስ
*ዮናስ
*ናሆም
*አብድዩ
*ሶፎንያስ
*ሐጌ
*ኢዩኤል
*ዕንባቆም
*ዘካርያስና
*ሚልክያስ ናቸው::
=>"ካልአን ነቢያት" ደግሞ:-
*እነ ኢያሱ
*ሶምሶን
*ዮፍታሔ
*ጌዴዎን
*ዳዊት
*ሰሎሞን
*ኤልያስና
*ኤልሳዕ ሌሎችም ናቸው::
=>ነቢያት በከተማም ይከፈላሉ::
*የይሁዳ (ኢየሩሳሌም):
*የሰማርያ (እሥራኤል)ና
*የባቢሎን (በምርኮ ጊዜ) ተብለው ይጠራሉ:: በዘመን አከፋፈል ደግሞ:-
*ከአዳም እስከ ዮሴፍ (የዘመነ አበው ነቢያት):
*ከሊቀ ነቢያት ሙሴ እስከ ነቢዩ ሳሙኤል (የዘመነ መሳፍንት ነቢያት)
*ከቅዱስ ዳዊት እስከ ዘሩባቤል ያሉት (የዘመነ ነገሥት ነቢያት):
*ከዘሩባቤል ዕረፍት እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ያሉት ደግሞ (የዘመነ ካህናት ነቢያት) ይባላሉ::
ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በቡራዩ ክ/ከተማ የጠሮ መካነ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የገቢ ማሳሰቢያ
ጉባኤው የሚከናወንበት ቦታ: መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን አዳራሽ (አራት ኪሎ)
የጉባኤ ቀን : መጋቢት 15/2016 ዓ.ም
መግቢያ ዋጋ : 100 ብር ብቻ
አዘጋጅ: መካነ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን ከማኅበረ መዓዛ ሃይማኖት ጋር በመተባበር
የመንፈሳዊ ጉባኤውን ትኬት የሚፈልጉ ከሆነ ይደውሉ፡፡ 0960029538
ባሉበት ትኬቱ እንዲደርሶ እናደርጋለን፡፡ ሰብሰብ አድርገው ቢገዙ ይበረታታል! እናመሰግናለን
⛪⛪⛪ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን እንማማር ⛪⛪⛪
ትምህርተ ሃይማኖት
✥••┈••●◉ ✞ ሀልዎተ እግዚአብሔር ✞ ◉●••┈••✥
የማይታይና የማይመረመር ኹሉን ማድረግ የሚችል ኹሉን የፈጠረ የመጀመሪያ ያልነበረው መጨረሻም የማይኖረው ለዘላለም የሚኖር አንድ አምላክ መኖሩን ማመን ለሰው ልጆች መሠረታዊ ነገር ነው፡፡
የሰው ልጅ ስለ እግዚአብሔር ያለው ዕውቀት ኹለት ዓይነት ነው:-
1ኛ ሰው በእግዚአብሔር አርአያና ምሳሌ ስለተፈጠረ በተፈጥሮ የተሰጠው ዕውቀት እያደገ ሲኼድ ፈጣሪውን ተመራምሮ የማወቅ ችሎታ አለው፡፡
2ኛ ሰው ፈጣሪውን በተፈጥሮ ያገኘው ዕውቀት ቢኖረውም በተጨማሪ በእግዚአብሔር ልዩ መገለጥ ፈጣሪውን ያውቃል፤ ይኹን እንጂ ሰው ስለእግዚአብሔር ያለው ዕውቀት የተወሰነ ነው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር የማይመዘንና የማይለካ በመሣሪያም የማይመረመር ስለኾነ የሰው እውቀት እጅግየተወሰነ በመኾኑ ነው፤ ሰው በዓይኑ ዐይቶና በእጅ ዳብሶ በመሣሪያም መርምሮ ማረጋገጥ የሚችለው የተፈጠረውን ግዙፍ ነገር ብቻ ነው፡፡ ስለኾነም ሀልዎተ እግዚአብሔር ማለት ምን ማለት ነው፡፡
ሀለወ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲኾን ትርጉሙም መኖር ማለት ነው፡፡ ስለዚኽ ሀልዎተ እግዚአብሔር ማለት የእግዚአብሔር መኖር ማለት ነው፡፡እግዚአብሔር ለዘመኑ የጊዜ ቀመር አይቀመርለትም፡፡ በዚኽን ጊዜ ነበር በዚኽኛው ጊዜ ደግሞ አልነበረም አይባልም፡፡ እግዚአብሔር ከዓለም / ከፍጥረት ኹሉ / አስቀድሞ መኖሩ ይታወቃል እንጂ የኖረበት ዘመን አይቆጠርም፡፡
“እነሆ እግዚአብሔር ታላቅ ነው፡፡ አናውቀውምም፡፡ የዘመኑም ቍጥር አይመረመርም፡፡ ” [ኢዮ. 36:26]
እግዚአብሔር ከዓለም በፊት እንደዛሬው ኹሉ በሙሉ ክብሩ ነበር የዓለም አለመኖር ከእግዚአብሔር ክብር ላይ የሚያጎድለው /ያጎደለው/ ነገር የለም፡፡
“ እግዚአብሔር ከዓለም በፊት እስከ ዘለዓለም ድርስ በሦስትነቱ አለ እግዚአብሔር በመለኮቱ እግዚአብሔር በመንግሥቱ አለ፡፡ ከጎሕና ከጽባሕ በፊት በመላእክት ሳይፈጠሩ እግዚአብሔር በመንግሥቱ አለ፡፡ ሰማያት ሳይዘረጉ የየብስም ፊት ሳይታይ ሐመልማላት ሳይበቅሉ እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ፡፡ ከፀሓይና ከጨረቃ ከከዋክብትም በፊት ከብርሃናትም መመላለስ በፊት እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ .” [ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ ከቍ. 3 -8 ፣ ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ ከቍ. 4–13]
“እግዚአብሔር ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው ” መዝ. 73፥12] “እግዚአብሔር ከጊዜ ውጪ ነው ” በክርስትና ሕግ የአግዚአብሔርን መኖር ለማወቅ እናለመረዳት ቍልፍ እምነት ነው፡፡ ከእምነት ያልተነሣ ሰው በፍጹም ወደ እግዚአብሔር ሊደርስ አይቻለውም፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ላለን ግንኙነት ዋናው መሠረት እምነት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ እግዚአብሔርን የማወቅ መሠረቱ እምነት ስለኾነ “በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና ” [2ቆሮ. 5፥6] ተብሎአል፡፡ ክርስትና ማየት ማመን ነወ በሚለው ብሒል አትመራም፡፡ ጌታችንም “ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው” ያለው እምነት መሠረት በመኾኑ ነው፡፡ [ማቴ. 5:1] ይኹን እንጂ የእግዚአብሔርን መኖር ለማወቅ መሠረቱ እምነት ቢኾንም ብቸኛው ግን አይድለም፡፡ ፈጣሪን እናውቅ ዘንድ የሚያግዙንን ነገሮች ሰጥቶናል፡፡ እንድናውቀው አጋዥ አድርጎ ከሰጠን ውስጥ ሥነ ፍጥረት ሕሊና ፣ የሰው ልጅ የተፈጥሮ ዝንባሌ እና ቃለ እግዚአብሔር ዋናዎቹ ናቸው፡፡
ስለ እግዚአብሔር ህልውና የሚያስረዳ ትምህርቶች
† እግዚአብሔር አለ ከተባለ ለምን አይታይም?
ይቆየን...
✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥
አርዮስና የዛሬ መሰሎቹአንዲት ጥቅስ ይዘው ክርስትናን ከመሠረቱ ለመናድ መሞከራቸው በእርግጥም ከሰይጣን መላካቸውን ያሳያል::
+በወቅቱም በመወገዙ አርዮስ ወደ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ሔዶ ከሰሰ:: ቅዱሱ ንጉሥም የጉዳዩን ክብደት ተመልክቶ የዓለም ሊቃውንት ይሰበሰቡ ዘንድ አዘዘ::
+በ325 ዓ/ም (በኛው በ318 ዓ/ም) ለ40 ቀናት የሚቆይ ሱባኤን ያዙ:: ሱባኤውን ሲጨርሱም በ4ቱ ፓትርያርኮች (እለእስክንድሮስ: ሶል ዼጥሮስ: ዮናክንዲኖስና ኤዎስጣቴዎስ) መሪነት: በእለእስክንድሮስ ሊቀ መንበርነት: በአትናቴዎስ ጸሐፊነት ጉባኤው ተጀመረ::
+በጉባኤው ሙሉ ስልጣን በሰማይ ከፈጣሪ: በምድር ከንጉሡ የተሰጣቸው አበው አርዮስን ተከራክረው ከነ ጀሌዎቹ ምላሽ አሳጡት:: ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ: ሥግው ቃል: ራሱም እግዚአብሔር መሆኑን አስረዱት::
+በጉባኤው መጨረሻም አልመለስም በማለቱ አርዮስን አወገዙ: ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እንደሚገባ አደራጁ:: አባቶችም ሥራቸውን ከጨረሱ በሁዋላ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስን ባርከው ወደየ ሃገረ ስብከታቸው ተመልሰዋል::
+ቅዱስ ሶል ዼጥሮስም ከጉባዔው ከተመለሰ በሁዋላ በጐ ጐዳናውን አቅንቶ ቀጥሏል:: ብዙ ድርሳናትን ደርሶ: በድካም ሰብኮ ኢአማንያንን መልሷል:: ፈላስፎችንም ድል ነስቶ አሳምኗል:: መ+ና+ፍ+ቃን ደግሞ ፈጽመው ይፈሩት ነበር:: ሊቀ ዽዽስናን በተሾመ በ11 ዓመቱም በዚህች ቀን ዐርፏል::
=>የሥላሴ ቸርነት ከኹላችን ጋር ይሁንና ጥር 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.በዓለ ሥሉስ ቅዱስ
2.ቅዱስ ሶል ዼጥሮስ
3.ቅዱስ ኤፍሬም
4.ቅዱስ ሰሎሞን
=>ወርሐዊ በዓላት
1.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
2.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
3.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
4.አባ ባውላ ገዳማዊ
5.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
6.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)
=>+"+ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ: የእግዚአብሔርም ፍቅር: የመንፈስ ቅዱስም ሕብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን:: አሜን:: +"+ (ቆሮ. 13:14)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
👉ወጋሕታ ሐበሻ እና ሽፎን ስፌትና መሸጫ💃💃💃💃💃💃💃💃👗👗👗 ይደዉሉሉን አዳዲስ ሽፎኖች አዘጋጅቶ ደንበኞቹን እያስተናገደ ይገኛል መርጣቹ ይደዉሉሉን📞📞☎️☎️☎️ ሰርተን በሰዓቱ እና ጥራቱን የጠበቀ ልብስ ሰፍተን እንሰጣቸዋለን ወደምትፈልጉት ቦታ እንልካለን 🚘✈️🚕🛫🛫 ለበለጠ መረጃ 251912448561👌👌
Читать полностью…ይህ ስም ከሰዎች ብቻ ሳይሆን ከመላእክትም በላይ እንደሆነ ቅዱስ ጳውሎስ ˝ከመላእክት ይልቅ እጂግ የሚበልጥ ስምን በወረሰ መጠን እንዲሁ ከእነርሱ አብዝቶ ይበልጣል˝ ዕብ 1÷4 ብሎ አስተምሮናል፡፡ የቅዱሳን መላእክት የሐዲስ ኪዳን ተልእኳቸውና አገልግሎታቸው ሁላችንም ይህ ስም እንዲኖረንና በዚህ ስም እንድንታተም መርዳት ሲሆን፤የቅዱሳን፣የጻድቃን፣የሰማዕታት፣የመነኮሳትና የሊቃውንት ተጋድሎ፤የካህናትና የምእመናን ሕይወት ሁሉ ይህንን ስም መሠረት ያደረገ መሆኑን ልብ ይሏል፤ በዚህ ስም ˝ንስሓና የኃጢአት ሥርየት ይሰበካል˝ ሉቃ 24÷47፤ዮሐ 20÷31፤ሐዋ 3÷16፤10÷43፤ዕብ 6÷10፤1ኛ ዮሐ 2÷12፤3ኛ ዮሐ 3÷5፤ራእ 22÷4፡፡፡፡
ባስልዮስ እንደተናገረ፦
"ሥጋው በመቃብር በመቀበሩም በመቃብር ውስጥ የነበረ መፍረስን መበስበስን አጠፋልን ከሥሩም ነቀለው፤ይህንም የሚያስረዳ ከቅዱሳን ወገን ብዙዎች ተነሡ" (ሃይ.አበ 96÷51)፡፡
ቅዱስ ቄርሎስም እንዲህ ይላል "ህላዌሁ ለሰብእ ኮነ ለሞት ወለሙስና በዓሊዎቱ ለአዳም…" "በአዳም ትእዛዝ ማፍረስ ምክንያት የሰው ባህርይ ለሞት ለጥፋት ተሰጥቶ ነበር፤እንደ ቀድሞ አኗኗሩ ፈጣሪ ዳግመኛ ሊያድነው ወደደ፤ ባለመጥፋት ባለመለወጥ ሊገልጠው ወደደ፤ይህ በምን ሥራ ሊሆን ይቻላል?ሰውን ያፀናው ዘንድ ሰው በሆነ ሁሉን በሚያድን ቃል ነው፤እንዲህም ከሆነ የዚህ የተዋሕዶ ሁለንተናው ረቂቅ ምሥጢር እንደሆነ በልቡና ዕወቅ ሕይወት ማኅየዊ ሊሆን እርሱ ሰው ሆኗልና በማይመረመር ሥልጣን ሥጋው ሞትን መለወጥን ድል የሚነሣ እንደሆነ ይገልጥ ዘንድ፡፡" ሃይ.አበ 74÷44-47፡፡
ዳግመኛም ሊቁ ቅዱስ ባስልዮስ እንዲህ ይላል፡-
"ከፍጡራን በላይ በሆነች ፈቃዱ ሰው በሆነ ጊዜ ከኃጢአት በቀር የሰውነትን ሥራ ሠራ ነቢዩ እንደተናገረ የእኛን ባህርይ ተዋሐደ ከእኛ ኃጢአትን ያርቅ ዘንድ በሰብአዊ ባህርያችን ተፈርዶ የነበረ መርገምን ያጠፋ ዘንድ ፤ለጥፋት ተሰጥቶ በነበረ ባህርይ አለመለወጥን ይገልጥ ዘንድ ከኃጢአት በሥራችን ተፈርዶብን የነበረ መከራን ሁሉ ተቀብሎ በተረዳ ሕማሙ ሞቱ ደክመን የሠራነውን ኃጢአት ያጠፋ ዘንድ ሰለዚህ ሰው ሆኗልና" (ሃይ አበ.96÷28)፡፡
የስሙ ፊደል ቁጥር 144 ይህን ጥልቅ ምሥጢር የያዘ ነው፤ ዳግመኛም ይህን 144 በ 12 ስናካፍለው 12 ይሆናል፤ የሰው አጠቃላይ ሕዋሳት 12 ናቸው፤ እነዚህን 12ቱን ሕዋሳት በነገደ እስራኤል ቁጥር ልክ ስናባዛው 144 ይመጣል፤ ይህም ደግሞ ክርስቶስ የነሣው ዘር ከ12ቱ ነገደ እስራኤል መሆኑን ያሳያል፤ አግዚአብሔር አስቀድሞ ለአብርሃም፤ለይስሐቅና ለያዕቆብ "የምድር አሕዛብ በዘርህ ይባረካሉ" ብሎ የገባላቸው ኪዳን የተፈጸመው በእርሱ ነውና፤(ዘፍ 22፡18፤ዘፍ 26፤4፤ዘፍ 28፤14)፤ እነዚህም አሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል ሙሴ ከእግዚአብሔር በተቀበለው ትእዛዝ መሠረት በአሥራ ሁለት አዕናቍ ይመሰላሉ፡፡
አነዚህ አስራ ሁለት አዕናቍ ሊቀ ካህናቱ በሚለብሰው ልብስ በደረቱ ላይ የሚቀመጡ ካህኑ ወደ መቅደሱ ሲገባ ለብሶት የሚገባ አዕናቍ ናቸው፤ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ ሲገባ ነገደ እስራኤልን የሚወክሉት አዕናቍ በደረቱ ናቸው፤በደረቱ ተሸክሟቸው በእግዚአብሔር ፊት በግምባሩ ይደፋል፤ስለ ሁሉም ነገድ ምሕረትን ይለምናል እግዚአብሔርም በስማቸው የተቀረጸውን የዕንቍ ማኅተም ይመለከታል ይቅርም ይላቸዋል(ዘጸ 28፡6-22) ፤ጌታም ከአሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል ወገን ነውና የእስራኤል ዘር የሆነውን፤የምድር አሕዛብ ሁሉ ይባረኩበታል ተብሎ ኪዳን የተሰጠውን ዘር፤ባህር የተከፈለለትን፤መና የወረደለትን፤ደመና የተጋረደለትን፤ውኃ ከጭንጫ የፈለቀለትን ዘር፤በሲና ተራራ በጌትነቱ እሳት እያነደደ የተገለጠለትን ሕዝብ ዘር ነውና የነሣው በመስቀል ቅድስተ ቅዱሳኑ በደረቱ ተሸክሟቸው ይሠዋል፤መሥዋዕት ሆኖ ይቀርባል፤ "የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው" ብሎ ለምኖላቸዋል፡፡
ሊቁ አባ ሕርያቆስ "ጸናጽል ዘውስተ ልብሱ ለአሮን ካህን" "በአሮን ልብሰ ተክህኖ ላይ ያለች ሮማነ ወርቅ አንቺ ነሽ" በማለት ለእመቤታችን አድርጎ ተናግሯል (ቅዳ.ማር)፤ይህ ዘር ፍጻሜውን ያገኘው በእመቤታችን ነውና፤ለተዋሕዶ የተመረጠውም የእርሷ ሥጋና ነፍስ ነውና፡፡
ባለ ራእዩ ቅዱስ ዮሐንስም ሰማያዊት ኢየሩሳሌምን በራእይ ሲመለከት የተናገረው መልአክም መጠኗን ሲለካ ባየው ራእይ መሠረት እነዚህን አሥራ ሁለት አዕናቍ የጠቀሳቸው ሲሆን ትርጉማቸው ነገደ እስራአልንና ሐዋርያትን የተመለከተ መሆኑ በሊቃውንት ተብራርቷል፤ ቅዱስ ጳውሎስም "ኢነሥኦ ለዘነሥኦ እመላእክት አላ እምዘርዓ አብርሃም አልዐለ" "የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም" (ዕብ 2÷16) ብሏል፡፡
ከሊቃውንቱም ቅዱስ ቄርሎስ፡- ጌታ በነቢዩ በኢሳይያስ አድሮ የተናገረውን ትንቢት ጠቅሶ "ወበእንተዝ ተፀነስኩ እምከርሥ ከመ ዐቅም ምግባራተ ብዙኃ ወዐቅም ነገደ ያዕቆብ ወአስተጋብእ ዝርዋነ እስራኤል" "ብዙ ሥራ እሠራ ዘንድ ፤የያዕቆብንም ወገን አጸና ዘንድ የተለያዩ እስራኤልን አንድ አደርግ ስለዚህ ዘንድ በማኅፀን ተፀነስኩ" ተናግፘል፤ኢሳ 49÷5-8፤ሃይ.አበ 76÷19፡፡
ቅዱስ ያሬድም "መጽአ ኀቤነ ያስተጋብእ ዝርዋነ" የተበተነውን እኛን ይሰበስበን ዘንድ ወደኛ መጣ ብሏል፡፡ (ምንጭ፡-ትቤ አክሱም መኑ አንተ)፡፡
መድኃኒትነቱም የተረጋገጠውና የታወቀው ከእመቤታችን የነሣው ሥጋና ነፍስ ንጹሕ በመሆኑና ይህንንም ሥጋ የባህርይ አምላክ ስላደረገው ነው፤ኢያሱ ማለት መድኃኒት ማለት ሲሆን ነገር ግን አምላክነት ስለሌለውና ሰው ብቻ ስለሆነ የኢየሱስን መድኃኒትነት አይስተካከለውም ፡፡
ቅዱስ ኤፍሬም፡-
"ወገኖቹን በኃጢአታቸው ከመጣባቸው ፍዳ የሚያድናቸው ኢየሱስ ይባላል" ያለውን ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ሲተረጉሙ "ኢያሱ ባጭር ታጥቆ ፤ዘገር ነቅንቆ፤ጋሻ ነጥቆ እስራኤልን ቢያድን ከሥጋዊ ጠላት ነው፤ ጌታ ግን ያዳነን ከመንፈሳዊ(ረቂቅ) ጠላት ነውና ከዚያ ሲለይ፤ይህም የባህርይ አምላክነቱን ያስረዳል፤ ዕሩቅ ብእሲ ስንኳን ሌላውን ሊያድን ይቅርና ራሱን ማዳን አይቻለውም ጌታ ግን የባህርይ አምላክ እንደሆነ ለማስረዳት "ዘያድኅኖሙ ለሕዝቡ" ባለው ታውቋልና ካሉ በኋላ ኢየሱስ ብሎ ስሙን፤ዘያድኅኖሙ ብሎ ትርጉሙን፤እምኃጢአቶሙ ብሎ ምሥጢሩን ተናገረ" በማለት አመሥጥረውታል፡፡
ይህም አስቀድመን ንባብ ትርጉምና ምሥጢር ብለን ከገለፅነው ጋር የሚገናኝ ነው፤ኢየሱስ ንባብ፤መድኃኒት ትርጉም፤ከኃጢአት መዳን ደግሞ ምሥጢር ሲሆን ማርያም ፊደል መሆኗ የማይለወጥ ምሥጢር ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያትም ˝መዳንም በሌላ በማንም የለም፤እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና˝ ሐዋ4÷12 በማለት ያስተማሩት ይህ ስም ከሁሉም ስምና ክብር፤ሥልጣንና መንግሥት ሁሉ በላይ በመሆኑ እናም፤በዕለተ ዓርብ በቀራንዮ አንድ ጊዜ ስለሁላችን መሥዋዕት፤ቤዛ ሆኖ ሊቀርብ የሚችለው ይህ ስም ያለው ብቻ ነው የሚለውን ነጥብ የሚያረጋግጥ ነው፤የእመቤታችንና ቅዱሳን ምልጃ የመላእክት ተራዳኢነት ወደዚህ የመዳን ምሥጢር የሚያቀርብ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡
ሊቃውንቱም በዚህ ስሙ "ከብረ(ከበረ) ፤ተለዐለ(ከፍ ከፍ አለ) ፤ኀየሰ(በለጠ) ፤ወረሰ፤ ነግሠ (ነገሠ)" መባልን ገንዘብ አደረገ ብለው አመሥጥረዋል፡፡
ለጥንቃቄ!
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዓላትን አክባሪ ብቻ ሳትሆን በዓላትን እንዴት ማክበር እንዳለባትም ጠንቅቃ ታውቃለች! ። ሌላው ቀርቶ በጥምቀት በዓል ወቅት ታቦታትን ከመንበረ ክብራቸው አንስታ ወደ ጥምቀተ ባሕር የምትወስድበት አንዱ ምክንያት ኢየሱስ ክርስቶስ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ በዕደ ዮሐንስ ለመጠመቅ የመሄዱ ምሳሌ እንጂ ጠላቶቿ ተሃድሶዎች እንደሚሉት 'ታቦታቱ ወክ አምሯቸው' አይደለም ።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ እግዚአብሔር አርቶዶክሳዊ ወጣትችን አነሳስቶ በጥምቀት በዓል ላይ ሌሎች እሴቶችን እንዲጨምሩ እና በዓሉ የበለጠ ድምቀት እንዲኖረው አድርጓል ። ነገር ግን ስራ የሚሰራ ሰው ይሳሳታልና የተሳሳትንባቸውን እና ከወዲሁ ዕልባት እንዲያገኙ ልናስተካክላቸው የሚገቡ ነገሮችን እንጠቁም ።
#ዕጣንማጠን ፦ በኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ስርዓተ አምልኮ መሰረት ዕጣን ማጠን የሚፈጽመው በካህን ብቻ ነው ። የድቁና ስልጣን ያለው ሰው እንኳን ዕጣን ማጠን አይችልም ። ዲያቆናት ዕጣን ለማጠን የሚያበቃ ስልጣነ ክህነት ላይ ባለመድረሳቸው በተልዕኮ ጊዜ የዕጣን ማጠኛ የሆነውን ንዋይ (ማዕጠንት) የላይኛውን ጫፍ አይዙም ። ለተልዕኮ ሲፋጠንም ጫፉን ሳይሆን ከጫፉ ዝቅ ብሎ ይይዛልእንጂ ጫፉን አይዝም ። ይህ የሆነው ከካህናት አባቶቻችን በስተቀር ለሎች ሰዎች ዕጣን ማጠን እንደሌለባቸው ስርዓት በመሰራቱ ነው ።
እንዲኽ ያለ ስርዓት ባላት ቤተ ክርስቲያን በጥምቀት በዓል ሰበብ ወጣቶች በተለያዮ ቁሳቁሶች የማዕጠንት አገልግሎት ሲሰጡ ማየት ተገቢ አይደለም ። ይህ የሆነው በቅንነት ቢሆንም እየዋለ ሲቆይ ግን ስርዓት ይሆንና ያስቸግራል ፤ በመሆኑም ሊታረም ይገባዋል ።
#ስዕል ፦ የቤተ ክርስቲያን የሆኑ ቅዱሳን ስዕላት የት ቦታ መቀመጥ እና መሰቀል እናዳለባቸው ቤተ ክርስቲያን ስርዓት ሰርታለች ። ቲሸርት ላይ ፣ ዣንጥላ ላይ ፣ ቁልፍ መያዣ ላይ ፣ በየመንገዱ ባሉ መጸዳጃ ቦታዎች ... ወዘተ ቅዱሳት ስዕላትን ማድረግ ተገቢ ካለመሆኑም በላይ መንፈሳዊ ቅጣትን ሊያስቀጣ ይችላል ። በጥምቀት በዓል ላይ እነዚህ ስእተቶች በጉልህ ይታያሉ ። ለምሳሌ ቲሸርት ላይ ስዕል መለጠፍ ። ይህ የሚነቀፍበት ምክንያት ቲሸርቶቹ ከአገልግሎት ውጪ ሲሆኑ ስዕላቱም አላስፈላጊ እንግልት ስለሚደርስባቸው ነው ።
በተመሳሳይ መልኩ ለበዓሉ ተብለው በየመንገዱ የተሰቀሉ ቅዱሳን ስዕላት የበዓሉ ፍጻሜ ከሆነ በኃላ የሚያነሳቸው እና በጥንቃቄ ወስዶ በተገቢው ቦታ ለማስገባት ብዙ ጊዜያትን ሲፈጅ እየታየ ነው ። ይህ ደግሞ ለአቧራ ፣ ለጸሐይ እና በኢ-አማኙ ዘንድ መዘባበቻ መሆንን ያተርፋል ። ከዚህ ሁሉ ግን ከበዓሉ ፍጻሜ በኃላ በየመንገዱ ወይም ታቦታቱ በሚያልፉበት መንገድ ላይ የሰቀልናቸውን ቅዱሳት ስዕላት በጥንቃቄ ማንሳት ይገባል ።
#ወቅታዊነገሮች ፦ ሃይማኖት ከፖለቲካ በዓላማም ሆነ በመርህ ይለያል ። ይህን ካወቅን በምንም መልኩ ቢሆን ፖለቲካዊ አመለካከታችንን በዚህ በዓል ላይ ማንጸባረቅ የለብንም ። በምንሰቅላቸው እና በምንለብሳቸው ቲሸርቶች ላይ ከምንለጥፋቸው ጽሁፎች ብንነሳ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መጽሐፍት አብነት ያደረጉ መሆን አለባቸው ።
#ስካር ፦ በጣም የሚያሳዝነው ነገር ይህ ነው ። አንዳንድ ቦታ ላይ ቀኑን ሙሉ ለበዓሉ ድምቀት ሲደክሙ የዋሉ ወጣቶቻችን በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች የተንቆጠቆጡ ቲሸርታቸውን ለብሰው ምሽቱን በስካር ተበላሽተው ማየት ቅር ያሰኛል ። ሰው በብዙ የጊዜ እርዝመት የለመደውን ሱስ በአንድ ጊዜ ፣ "ተወው" ማለት የማይቻል ቢሆንም በዓሉን ከስካር ነጻ ሆነን ማሳለፍ ያስባርካልና ከዚህ ዓይነት አጓጉል ነገር እንራቅ ።
ለጊዜው እነዚህን እያሰላሰል እንቆይና ሌላውን በሌላ ጊዜ እንመለስበት ። ይህ በእንዲህ እንዳለ በተለያዮ ቦታዎች ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀበትን የመታሰቢያ በዓል ለማክበር እየተደረገ ያለው ዝግጅት እጅግ በጣም አስደሳች መሆኑን መግለጽ እፈልጋለሁ ፤እንዲህ ነው መባረክ ።
ዘካርያስ ኪሮስ ከመርካቶ ።
✝✞✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✝✞✝
✞ ጥር 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+✝" በዓለ ግዝረት "✝+
=>'በዓል' ማለት በቁሙ 'ክብር: መታሰቢያ' እንደ ማለት
ነው:: የበዓላት ባለቤት ደግሞ ራሱ እግዚአብሔር ነው::
በመጻሕፍተ ኦሪት እንደ ተቀመጠው ጌታ ምርጦቹን
(ሕዝቡን) ስለ በዓላት አዟል:: ከሰንበት ጀምሮ የፋሲካ:
የእሸት: የዳስ . . . ወዘተ በዓላት በብሉይ ኪዳን ይከበሩ ነበር::
+በእርግጥ አሕዛብም ለጥፋታቸው በዓላትን ሲያከብሩ
ኑረዋል:: ዛሬም ቀጥለዋል:: በዓላት በሐዲስ ኪዳንም
ቀጥለዋል:: የቅዱሳን ሐዋርያትና ሊቃውንትን ቀኖናዎች መሠረት
አድርጋ ቤተ ክርስቲያን በዓላትን ታከብራለች::
+እነዚህም ከጊዜ (ወቅት) አንጻር:-
*የሳምንት
*የወር እና
*የዓመት በዓላት ተብለው ሲታወቁ ከተከባሪዎቹ አንጻር
ደግሞ:-
*የጌታ
*የእመቤታችን እና
*የቅዱሳን ተብለው ይከፈላሉ::
+ጌታ "በዓላትን አክብሩ" ያለን ሥራ እንድንፈታ ሳይሆን
ለአምልኮው እንድንተጋና የጽድቅ ተግባራትን እንድንከውን
ነው:: ስለዚህም በበዓላት መልካም ይሠራል እንጂ ተተኝቶ
አይዋልም:: የጌታችን በዓላቱ 18 ሲሆኑ 9ኙ ዐበይት:
9ኙ ደግሞ ንዑሳን ተብለው ይታወቃሉ:: ሁሉም ለእኛ የድኅንት ሥራ
የተፈጸመባቸው ናቸው::
+የጌታ ዐበይት በዓላቱ:-
1.ጽንሰቱ (ትስብእቱ)
2.ልደቱ
3.ጥምቀቱ
4.ዑደተ ሆሳዕናው
5.ስቅለቱ
6.ትንሳኤው
7.ዕርገቱ
8.በዓለ ዸራቅሊጦስ እና
9.በዓለ ደብረ ታቦር ናቸው::
+ንዑሳን በዓላቱ ደግሞ:-
1.ስብከት
2.ብርሃን
3.ኖላዊ ሔር
4.ጌና
5.ግዝረት
6.በዓቱ (በዓለ ስምዖን)
7.ቃና ዘገሊላ
8.ደብረ ዘይት እና
9.በዓለ መስቀል ተብለው ይታወቃሉ::
+ከእነዚህም አንዱ በዓለ ግዝረት ሁሌ በየዓመቱ ጥር 6
ቀን ይከበራል:: መድኃኒታችን ለእኛ ሲል በተዋሐደው ሥጋ
ማርያም
ሕግን ሁሉ ፈጽሟል:: ራሱ ሠራዔ ሕግ እንደ ሆነው ሁሉ
ፈጻሜ ሕግም ተብሏል::
+ለአብርሃም ባዘዘው (ዘፍ. 17:9) መሠረትም በተወለደ
በ8ኛ ቀኑ ተገዝሯል:: ስሙንም ኢየሱስ (መድኃኒት)
ብለውታል:: (ሉቃ. 2:21) ነገር ግን የተገዘረው እንደ
ፍጡር በምላጭ (በስለት) ሳይሆን በኪነ ጥበቡ ነው::
"ማርያም ግዝር" እንዲሉ አበው:: ልደቱ እንደማይመረመር
ሁሉ ግዝረቱም አይመረመርም::
+ለእኛ ሲል ሁሉን የሆነ መድኃኒታችን ክርስቶስ ለፍቅሩና
ለክብሩ ያብቃን:: ከበረከተ በዓለ ግዝረቱም አይለየን::
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
~ሲደክማችሁ፣ሲያማችሁ፣ ግራ ሲገባችሁ … ወደ ማንም ዘንድ ከመሄዳችሁ በፊት ወደ
ፈጣሪያችሁ ሂዱ፡፡ ለአንድም ሰው ችግራችሁን ከመንገራችሁ በፊት ለሱ ንገሩ፡፡ ለማንም በሽታችሁን ከመግለጣችሁ በፊት እሱ ዘንድ ታከሙ፡፡ችክ ብላችሁ ለምኑት፤ ከልብ ሆናችሁ ጠይቁት፡፡ ድህነታችሁን፣ ፈላጊነታችሁን፣ አቅመ-ቢስነታችሁን በራሣችሁ ላይ መስክሩ፡፡
✔ /channel/Asresee
✔ /channel/Asresee
✔ /channel/Asresee
3.ቅድስት እስክንድርያ
4.ቅድስት አውስያ ሰማዕት
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2.ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም
3.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
4.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
5.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ
6.ቅድስት አውጋንያ (ሰማዕትና ጻድቅ)=>+"+ አባቶች ሆይ! ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃቹሃልና እጽፍላቹሃለሁ:: ጐበዞች ሆይ! ክፉውን አሸንፋቹሃልና እጽፍላቹሃለሁ:: ልጆች ሆይ! አብን አውቃቹሃልና እጽፍላቹሃለሁ:: አባቶች ሆይ! ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃቹሃልና እጽፍላቹሃለሁ:: ጐበዞች ሆይ! ብርቱ ስለ ሆናችሁ: የእግዚአብሔርም ቃል በእናንተ ስለሚኖር: ክፉውንም ስላሸነፋችሁ እጽፍላቹሃለሁ:: +"+ (1ዮሐ. 2:13)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
#ጥር ፬ ሞትን ሳይቀምስ የተሰወረው ሐዋርያ ዮሐ 21፤20
🎚️ጥር 4 እንደዚህች ባለች ዕለት በክብርም በግብርም ፍጹም የሆነ ጌታ ይወደው(ፍቁረ እግዚእ) የነበረ እርሱም ቢወደው እስከመስቀል ስር የተከተለው ታማኝ ሐዋርያ ነባቤ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ሞትንሳይቀምስ ተሰወረ ።
🎚️በመጀመሪያ ቃል ነበረ ብሎ የቃልን ሥጋ መሆን የነገረን ድንግል ማርያምን ምዕመናንን ወክሎ የተቀበለ፤ከሐዋርያት መካከል ሞትን ያልቀመሰ በህይወተ ሥጋ እያለ ወደ ሰማይ የተነጠቀ እንደ ሔኖክ ፣እንደ ኤልያስ በብሔረ ሕያዋን ያለው ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ነዉ፡፡
🎚️ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ፯ ስሞች አሉት፦
፩. ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ
፪. ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ
፫. ዮሐንስ ቁጽረ ገጽ
፬. ዮሐንስ ታኦሎጎስ
፭. ዮሐንስ አቡቀለምሲስ
፮. ዮሐንስ ወንጌላዊ
፯. ዮሐንስ ዘንስር
🎚️ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ድንግል ማርያምን ከሐዘኗ ለማጽናናት በአደራ ወደ ቤትህ እንደ ወሰድካት ሁሉ፤ ሐዘኗ ዳር ያጣውን ኢትዮጵያንም ወደ ቤትህ ወስደህ አጽናናልን።
🎚️የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በረከቱ ረድኤቱ ከሁላችን ጋር ይሁን።🎚️