".... በጦር ስለተገደሉና ስለ ተማረኩም ሰዎች ሁሉ፤ ስለ ድኆችና ስለ ችግረኞች፤ ስለ ባልቴቶችና ስለ ድሀ አደጎች።
ሳይገባኝ በጸጋህ ስለ ጠራኸኝ ትሑት ስለምሆን ስለ እኔም ስለ ባርያህ። መጠኔ ሳይሆን አከበርኸኝ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ፤ በመሠዊያህም ፊት እቆም ዘንድ በምሕረትህ ወደ አንተ አቀረብኸኝ፤ ነፍሴን ይቅር ትላት ዘንድ፤ የወገኖችህንም ሁሉ።
ስለዚህ ስለ ጉባኤያችንም በቸርነትህ ብዛት ይባረክ ዘንድ፤ የደከሙ ይጸኑ ዘንድ፤ ኀጥአንም ይጸድቁ ዘንድ፤ ንስሐ የገቡት ይነጹ ዘንድ፤ ጻድቃንም ይጠበቁ ዘንድ፤ የተቸገሩትም ይድኑ ዘንድ፤ የተጨነቁትም ያርፉ ዘንድ፤ ተክዘው የነበሩት ያርፉ ዘንድ፤ ያዘኑትም ደስ ይላቸው ዘንድ፤ ተስፋ የቆረጡት ይድኑ ዘንድ፤ ድውያንም ይድኑ ዘንድ፤ የበደሉት ይመለሱ ዘንድ፤ የጠፉትም ይገኙ ዘንድ፤ የራቁትም ይቀርቡ ዘንድ፤ የቀረቡትም ይጠበቁ ዘንድ"
+++++ (ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ) ++++++
ጥር 18/2016 #ዝርወተ_አፅሙ_ለቅዱስ_ጊዮርጊስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በሰማእቱ ስም ለምናመሰግንበት ለሰማእቱ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉ከሃዲው ንጉሥ ዱድያኖስ እጅግ አሠቃቂ በሆኑ ብዙ መከራዎች እያሠቃየ ሦስት ጊዜም ቢገድለው ጌታችን ግን ቅዱስ #ጊዮርጊስን ከሞት እያስነሣው ከሃድያንን ያሳፍራቸው ነበር
👉ንጉሥ ዱድያኖስ የሚያደርገው ቢያጣ ጭፍሮቹን በመንኰራኩር ፈጭታችሁ አጥንቱን ደብረ ይድራስ ተራራ ላይ ወስዳችሁ ዝሩት ብሎ አዘዛቸው ጭፍሮቹም የቅዱስ #ጊዮርጊስን ሥጋ በመንኰራኩር ፈጭተው ወስደው በተራራው ላይ ቢረጩት ሥጋው ያረፈበት ሳር፣ ቅጠሉ፣ ደንጊያው፣ እንጨቱ ሁሉ #ጊዮርጊስ_ቅዱሱ_ለእግዚአብሔር ጊዮርጊስ ሰማዕቱ ለእግዚአብሔር እያሉ አመስግነዋል
👉አሁንም ጌታችን ለሦስተኛ ጊዜ ከሞት አስነሣውና ሥጋውን ፈጭተው በተራራም ላይ ሥጋውን በትነውት ወደ ንጉሡ የሚመለሱትን ወታደሮች በመንገድ ከኋላቸው ሄዶ ደረሰባቸውና #ቆዩኝ_ጠብቁኝ አላቸው እነርሱም እጅግ ደንግጠው ይህ እንዴት እንደሆነ ሲጠይቁት #አምላኬ_ከሞት_አዳነኝ አላቸው
👉ጭፍሮቹም እጅግ ደንግጠው ከእግሩ ስር ወድቀው ‹‹ይቅር በለን›› ብለው በአምላኩ እንደሚያምኑ መሰከሩለት ቅዱስ #ጊዮርጊስም ከመሬት ላይ ውሃ አመንጭቶ በጸሎት ጌታችንን ቢጠይቅ ቅዱስ ዮሐንስ መጥቶ አጥምቋቸዋል እነርሱም በንጉሣቸው ፊት ሄደው ስለጌታችን #በመመስከር በሰማዕትነት ዐርፈዋል
👉 #ሰማዕቱ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ ዐፅሙ ተቃጥሎ አጥንቱ ተፈጭቶ #በደብረ_ይድራስ_ተራራ ላይ የተበተነው በዚህች በጥር 18 ዕለት ነው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል #ማርያም አገልጋይ ብርቱዉንም ደካማዉንም ፍጥረት ኹሉ ፈጥነህ የምትረዳ ሊቀ ሰማዕታት #ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሆይ እንደ እመቤትህ ቅድስት ድንግል ማርያም አንተም ከበቀልና ቂም የተለየህ ርኅሩኅ ልብና ለሰዎች ኹሉ የምታዝን ደግ ሰማዕት ነኽ
👉አማላጅነትህን በመታመን ለሚጠራህ ኹሉ ከነፋስ ዐውሎ ይልቅ ፈጥነህ የምትደርስ ሊቀ ሰማዕታት #ቅዱስ_ጊዮርጊስ ሆይ የርሕሩሕ አምላክ #እግዚአብሔር ርህራሄን ተጎናጽፈኻልና በዚህ ሰአት በጭንቅ ያሉ የወዳጆችህን ልመና ስማ
👉ኅዘንን የምታረጋጋ አባቴ ፍጡነ ረድኤት ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ #ጊዮርጊስ ሆይ ለጠላት መሣቂያ ለጠላቶቻችን መዘባበቻ እናድንሆን በገዳም ያሉ የእናቶቻችንን የአባቶቻችንን የጩኸት ድምፅ ስማ
👉ከሃዲው ንጉሥ ዱድያኖስ ሰባው ነገሥት ስለ #ክርስቶስ ሰለመሠከረ አካላቱ እየቆራረጡ በሥጋው የአሠቃዩት የልዑል #እግዚአብሔር ወታደር ፍጡነ ረድኤት ኃያል ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ እንሆ የተጋድሎ ዝናውን ስንሰማ ግርማ
ሞገስህ ከሰማዕታት ኹሉ ይበልጣል
👉ለሰባት ዓመታት ትእግሥትን በማዘወተር አስጨናቂዎች መከራዎችን ለተሸከመ ትከሻህ ሰላምታ የሚገባህ የአስጨናቂዎች የሥቃይ ሰባት ዓመታትን የታገሥህ ሊቀ ሰማዕታት #ቅዱስ_ጊዮርጊስ ሆይ የድል በተርህን ይዘህ ኹልጊዜ እደሚገሰግስ አርበኛ የኢትያጵያ ጠላቶች ትመታልን ዘንድ ፈጥነህ ገሥግሰህ ናልን
👉አቤቱ #የቅዱስ_ጊዮርጊስ አምላክ እዘንልን ራራልን ይቅርም በለን የሰማእቱ ረድኤትና በረከት አይለየን ምልጃ ፀሎቱ ይጠብቀን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
👉ገድለ ቅዱስ ጊዮርጊስ
👉ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ
ሦስት አመት ያህል ወደርሱ ስለአልመጡና ስለአልጎበኙት አባታቸው አባ መቃርስ ከስራቸው የተነሳ አደነቀ ስራቸውንም ይገልጥለት ዘንድ ወደ ጌታችን ለመነና ተነስቶ ወደ ርሳቸው ሄደ እነርሱም በመምጣቱ ደስ ተሰኙበት በዚያች ሌሊትም ከርሳቸው ጋር አደረ። ለፀሎትም በተነሱ ጊዜ የእሳት ሐብል ከአፋቸው ሲወጣና ወደ ሰማይ ሲደርስ ሰይጣናትም እንደ ዝንቦች ሲከቡት የእግዚአብሔርም መልአክ በእሳት ሰይፍ ዝንቦቹን ሲያበርራቸው የከበሩ መክሲሞስንና ዱማቴዎስን አያቸው በነጋም ጊዜ አስኬማን አለብሳቸው ፀልዩልኝ ብሏቸውም ሊሄድ ተነሳ። እንርሱም ሰገዱለትና አባታችን ሆይ አንተ በእኛ ላይ ትፀልይ ዘንድ ትባርከንም ዘንድ የሚገባ ነው አሉት።
ተጋድሎአቸውንም በፈፀሙ ጊዜ እግዚአብሔር ከዚህ አለም ድካም ሊአሳርፋቸው ወደደ መክሲሞስም በፅኑ ህመም ታመመ ስጋውም እንደ እሳት ጋለ ወደርሱም ይመጣ ዘንድ ወደ አባ መቃርስ ላከ። አባ መቃርስም በመጣ ጊዜ በደዌ ሲሰቃይ አገኘው መክሲሞስም ፀልይልኝ ባርከኝም አለው። እርሱም በላዩ አማትቦ ይህ ደዌ ከአንተ ይርቃልና አይዞህ አለው መክሲሞስም አባቴ ሆይ በዚች ደዌ ከዚህ አለም እንደምወጣ እኔ አውቃለሁ ረድኤት አገኝ ዘንድ አንተ ፀልይልኝ አለው።
ይህንንም በተናገረ ጊዜ መሪር ልቅሶን አለቀሰ በዚያችም ጊዜ አባ መቃርስ የቅዱሳንን አንድነት ነቢያትን ሀዋርያትን መጥምቁ ዮሀንስን ንጉስ ቆስጠንጢኖስንም አያቸው። እነርሱም ነፍሱ በክብር እስከወጣች ድረስ በአባ መክሲሞስ ዙሪያ ነበሩ።
አባ መቃርስም አልቅሶ መክሲሞስ ሆይ የተመሰገንክ የከበርክ ነህ አለ። ዱማቴዎስም በውንዱሙ ላይ መራራ ልቅሶ በማልቀስ አባ መቃርስን የሚለምነው ሆነ ነፍሴን ይወስዳትና ወደ ወንድሜም ያደርሳት ዘንድ ስለ እኔ ወደ እግዚአብሔር ፀልይ አለው።
አባ መክሲሞስም ከተቀበረ በኃላ በሶስተኛው ቀን አባ ዱማቴዎስ ታመመ ስለርሱም ለአባ መቃርስ ነገሩት አባ መቃርስም ወደርሱ ሊሄድ ተነሳ በጉዞ ላይም ሳለ አስቀድሞ ወደ አባ መክሲሞስ የመጡትን የቅዱሳን አንድነት አየ የአባ ዱማቴዎስንም ነፍስ ተቀበለው በክብር ወደ ሰማይ አሳረጓት።
አባ መቃርስም ወደ በኣታቸው ሲደርስ ዱማቴዎስን አርፎ አገኘው ወስዶም ከወንድሙ ከመክሲሞስ ጋር በአንድ መቃብር በክብር ቀበረው። የመክሲሞስም እረፍት በዚህ ወር በአስራ አራት ነው ዳግመኛ የዱማቴዎስ እረፍት ጥር አስራ ሰባት በዚች ቀን ነው።
የከበረ አባ መቃርስም ያ ቦታ በስማቸው እንዲጣራ አዘዘ እንዲሁም ደብረ በርሞስ ተብሎ እስከ ዛሬ የሚጠራ ሆነ ለዘላለሙም መታሰቢያቸው ሆነ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ መክሲሞስና ዱማቴዎስ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥር)
+ወደ ቤቱ ተመልሶም የወላጆቹን ላም "እውነትን ተናገር" ብሎ ገስጾታል:: ላሙም ሰይጣን እንዳደረበት በሰው ልሳን ተናግሮ: የቅዱሱን ወላጆች ወግቶ ገድሏቸዋል:: ቅዱስ ፊላታዎስ ግን ላሙን አስገድሎ: ወላጆቹን ከሞት አስነስቶ ከአካባቢው ሰው ጋር በስመ ሥላሴ አስጠምቁዋቸዋል::
+በድንግልና ኑሮም ዘመነ ሰማዕታት ሲጀምር በርጉም ዲዮቅልጥያኖስ እጅ ብዙ ተሰቃይቷል:: በጸሎቱም ጣዖታቱን (እነ አዽሎንን) ከነ አገልጋዮቻቸው ወደ ጥልቁ አስጥሟቸዋል:: እርሱም በዚህች ቀን በሰይፍ ተከልሎ ለክብር በቅቷል:: ለእኛ ለኃጥአን የሚሆን ቃል ኪዳንንም ከጌታው ተቀብሏል::
=>የቅዱሳን አባቶቻችን አማናዊት ርስት ድንግል ማርያም አትለየን::
=>ጥር 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ፊላታዎስ ሰማዕት
2.አባ ዸላድዮስ ገዳማዊ
3.ማር ዳንኤል ሶርያዊ
4.አባ ዮሐንስ መሐሪ (ሊቀ ዻዻሳት)
5.11,004 ሰማዕታት (የቅ/ቂርቆስ ማሕበር)
6.11,503 (የቅ/ፊላታዎስ ማሕበር)
7.አባ ጽሕማ (ከተስዓቱ ቅዱሳን አንዱ)
=>ወርሐዊ በዓላት
1.በዓለ ኪዳና ለድንግል
2.ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ
3.ቅዱስ ገብረ ማርያም (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
4.ቅድስት ኤልሳቤጥ
5.አባ ዳንኤል
6.አባ አቡናፍር ገዳማዊ
7.አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ
=>+"+ ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል::
እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል::
በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ተተክለዋል::
በአምላካችንም አደባባይ ውስጥ ይበቅላሉ::
ያን ጊዜ በለመለመ ሽምግልና ያፈራሉ::
ደስተኞችም ሆነው ይኖራሉ:: +"+ (መዝ. 91:12)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
እንኳን ለሰማእቱ
ለነበልባላዊው ሕጻን
ለብጹዕ ማር ቅዱስ ቂርቆስ
የምስክርነት በዓል አደረሰን።
ጥር 15 ቀን የእየሉጣ ጽጌሬዳ
አንገቱ በሰይፍ ተከሎ ያረፈበት እለት ነው።
"ስለ አንተ ቀኑን ሙሉ እንገደላለን
እንደሚታረዱ በጎችም ተቆጠርን።"
ሮሜ 8፤35
ሰላም ለዝክረ ስምከ ቂርቆስ ሕፃን
ዘፍካሬሁ ተብህለ ጽጌ ምዑዝ ኤፍራን
ለዝ ስምከ ነጋሢ ዘበሰማያዊ ሥልጣን
ሶበ ይጼውዖ ልሳንየ ውስተ ገጸ ኩሉ መካን
ይድንግጽ ሞት ወይጕየይ ሰይጣን።
መልክአ ቂርቆስ
ከዚህ በላይ ምን ተስፋ አለ ምንስ ኪዳን አለ!!!
"ስሜ ክርስቲያን ነው።
አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።"
አላዊው ንጉሥ ቅዱስ ቂርቆስን ስምሕ ማነው ብሎ በጠየቀው ግዜ በሕጻን አንደበቱ "ስሜ ክርስቲያን ነው።"
ብሎ መልሶለታል የኛ ስም
ማነው ግብራችንስ በምን ይገለጣል ብሔር ዘር አምልኮ ውስጥ የተነከርን ክርስቲያን ተብለን ክርስቲያን የምናሳድድ ሕንጻ ሥላሴ ክቡር ሰውን የምናፈርስ እግዚአብሔር እንዴት ይፈርድብን ቅዱስ ቂርቆስ እንዴት ያዝንብን???
ቅዱስ ቂርቆስ እንደ ዘመናችን ክርስቲያን በተጠላበት አፈ ጻድቅ በበዛበት ተግባራዊ ክርስትና በከሰመበት ዘመን የተገኘ ለጣዖት አልሰግድም ብሎ ምስክርነት ለእግዚአብሔር የሰጠ ነበልባላዊ ሰማእት ነው።
ንጉሡን እለ እለእስክንድሮስን ያንቀጠቀጠ ልቡን ያራደ ኃያል በሥልጣን የሚናገር የሶስት ዓመት ሕጻን !!!!
የሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስና የወዳጁ የአቡነ ቄርሎስ የአቡነ ኤዎስጣቴዎስ በረከት ይደርብን ከክህደት አሽክላ ይሰውረን በፈቃዳቸው ላበዱት በጥላቻ ለታወሩት ማስተዋልን አምላከ ቂርቆስ ያድልልን
አሜን አሜን አሜን
ጥር 15/2016 #ህፃኑ_ቅዱስ_ቂርቆስ ወ #ቅድስት_ኢየሉጣ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሣኑ ስም ለምናመሰግንበት ጥር ዐሥራ አምስት በዚህች ዕለት የከበረ #ሕፃን_ቂርቆስ እናቱ ብፅዕት #ኢየሉጣ ዳግመኛ ለከበረ ሕፃን #ቂርቆስ ማኅበር የሆኑ #ዐሥራ_አንድ_ሺህ_አራት_ሰዎች በሰማዕትነት አረፉ ለአመታዊ ክብረ በአላቸው እንኳን አደረሰን
👉በዚያንም ወራት የክብር ባለቤት የሆነ #ክርስቶስን በሚያምኑ የክርስቲያን ወገኖች ላይ ታላቅ መከራና ስደት ሆነ ስሟ ኢየሉጣ የሚባል አንዲት ሴት ነበረች እርሷም ከታናሽነቷ ጀምራ ደግ ናት ስደትም እንደሆነ በሰማች ጊዜ መኰንኑን ከመፍራት የተነሣ ሕፃኗን ይዛ ከሮም ከተማ ተሰዳ የኪልቅያ አውራጃ ከሆነ ከጠርሴስ ደርሳ ከዚያም በሀገሮች ውስጥ እየተዘዋወረች ተቀመጠች።
👉ወደዚያች አገርም ያ ከእርሱ የሸሸችው መኰንን እለእስክንድሮስ መጣ ጭፍሮቹም ክርስቲያኖችን ፈለጓቸው ይቺንም #ቅድስት_ኢየሉጣን አግኝተው ያዝዋትና ወደ መኰንኑ አደረሷት የክርስቲያን ወገንም እንደሆነች ነገሩት
👉መኰንኑም ሴትዮ ተናገሪ ከወዴት ሕዝብ ወገን ነሽ ነገድሽ ምንድን ነው ሀገርሽስ ወዴት ነው አላት የከበረች #ኢየሉጣም እንዲህ ብላ መለሰችለት የአንጌቤን ሰው ለሆንኩ ለእኔ ወገኖቼ ለኢቆንዮን አገር አለቆች የሆኑ ኤሳውሮሳውያን ናቸው እኔም በአንተ ምክንያት ሸሽቼ ነበር እነሆ ዛሬ ግን በእጅህ ውስጥ ነኝ አለችው
👉መኰንኑም በእጄ ውስጥ እንደተገኘሽ ታውቂያለሽን አላት አሁንም የሚሻልሽን ምረጪ ስምሽንም ተናገሪ እኔንም እሺ በይኝና ለአማልክት ሠዊ የከበረች ኢየሉጣም ለረከሱ አማልክት እኔ አልሰዋም አለችው መኰንኑም ስምሽን ስጪ ተናገሪ አላት እርሷም የኔ ስም #ክርስቲያን መባል ነው አለችው
👉መኰንኑም ይህስ ስንፍና ነው የሚጠቅምሽ አይደለም እንዳትሞቺ ስምሽን ስጪ ተናገሪ አላት የከበረች ኢየሉጣም የኔ ስም #ክርስቲያን መባል እንደሆነ ነገርኩህ ሞት የሚሽረው በሰዎች ዘንድ የምጠራበትን ከፈለግህ ስሜ ኢየሉጣ ነው ብላ መለሰችለት።
👉መኰንኑም ጽኑ የሆኑ ሥቃዮችን በላይሽ ሳይመጣ ተነሥተሽ መሥዋዕትን ለአማልክት አቅርቢ አላት የከበረች #ኢየሉጣም ዕወነት ነገርን ለመሥራት የምትሻ ከሆነ ዕድሜው ሦስት ዓመት የሆነ ሕፃን ልጅ ይፈልጉ ዘንድ ወደ ሀገሩ መንደር ላክ ወዳንተም ያምጡትና የምንገዛለትንና የምናመልከውን እርሱ ይንገረን አለችው
👉ያን ጊዜም የሦስት ዓመት ልጅ ይፈልጉ ዘንድ መኰንኑ ወታደሮችን ላከ የሀገር ሰዎችም ልጆቻቸውን ሠውረዋልና አላገኙም ከዚያም ከከተማው ቅጽር ውጭ በፀሐይ መውጫ ወዳለው በረሀ በኩል ወጡ የቅድስት ኢየሉጣንም ልጅ አገኙት ይህ ሕፃን የስንት ዓመት ልጅ ነው ብለው ስለርሱ ጠየቁ ሰዎችም ይህ ሕፃን የሦስት ዓመት ሲሆን #የክርስቲያናዊት መበለት ልጅ ነው አሏቸው
👉ያንንም ሕፃን ይዘው ወደ መኰንኑ ወሰዱት መኰንኑም መልኩ የሚያምርና ደም ግባት ያለው እንደሆነ በአየው ጊዜ ደስ የምትል ደስተኛ ሕፃን ሰላምታ ይገባሃል አለው ሕፃኑም እኔን ደስተኛ ማለትህ መልካም ተናገርክ ላንተ ግን ደስታ የለህም #እግዚአብሔር ለዝንጉዎች ደስታ የላቸውም ብሏልና ብሎ መለሰለት መኰንኑም ሕፃኑን ሳልጠይቅህ ይህን ያህል ትመልስልኛለህን አለው ሕፃኑም ገና ከዚህ የሚበዛ ነገርን እመልስልሃለሁ አለው
👉መኰንኑም ሕፃኑን ስምህ ማን ነው አለው ከንጹሕ ዐዘቅትና ከማይለወጥ ከማይጠፋ ውኃ የተገኘ ሕፃን ስሜ #ክርስቲያን መባል ነው ብሎ መለሰለት መኰንኑም ዳግመኛ እንዳትሞት ስምህን ንገረኝ አለው የከበረ ሕፃንም #ስሜ_ክርስቲያን መባል እንደሆነ ነገርኩህ ሞክሼ ስም የምትሻ ከሆነ እናቴ የሰየመችኝ ቂርቆስ ነው
👉መኰንኑም ሕፃን ቂርቆስን እሺ በለኝና ለአማልክት ሠዋ በሥጋህም ስታድግ እሾምሃለሁ በብዙ ወርቅና ብርም አከብርሃለሁ አለው ሕፃኑም #የሰይጣን_መልእክተኛ ለዕውነትም ጠላቷ የሆንክ ከእኔ ራቅ አለው
👉መኰንኑም ሰምቶ ተቆጣ ደሙ እንደ ውኃ እስከሚፈስ ቆዳውን እንዲጨምቁትና እንዲገፉት አዘዘ የከበረች ኢየሉጣም የልጅዋን ትዕግሥት ባየች ጊዜ #እግዚአብሔርን አመሰገነችው
👉ከዚህም በኋላ መኰንኑ ጨውና ሰናፍጭ አምጡ አለ የሁለቱንም አፍንጮቻቸውን ከፍተው ያንን ጨውና ሰናፍጭ እንዲጨምሩባቸው አዘዘ ያን ጊዜ #ሕፃኑ ትእዛዝህ ለጕረሮዬ ጣፋጭ ሆነ ከማርና ከስኳርም ለአፌ ጣመኝ ብሎ ጮኸ
👉ሁለተኛም መኰንኑ እንዲህ ብሎ አዘዘ የረዘሙና የተሳሉ በእሳትም እንደ ፍም የጋሉ ዐሥራ አራት የብረት ችንካሮች አምጡ ሰባቱን በእናቱ አካላት ውስጥ ጨምሩ በሕፃኑም ሁለት በጆሮዎቹ ሁለት በዐይኖቹ ሁለት በአፉና በአፍንጫው አንድ በልቡ ጨምሩ እንዲህ ሲጨመርበት ጆሮዎቹ እንዲአሩ ዐይኖቹም ይጠፉ ዘንድ አንደበቱም ይቃጠል ዘንድ ወደ ልቡም ጽኑ ሕማም ገብቶ እርሱ ከዚህ ዓለም በሞት እንዲለይ ለእናቱም እንዲሁ አድርጉ ችንካሮችም #በቅዱሳኑ በሥጋቸው ሁሉ ተጨመሩ
👉የክብር ባለቤት በሆነ #በጌታችን ትእዛዝ የብረቶቹ ግለት ጠፍቶ እንደ በረዶ ቀዘቀዘ ጤነኞችም ሆኑ መኰንኑም ወደ ወህኒ ወስዳችሁ በዚያ አሥራችሁ ዝጉባቸው አለ
👉ከዚህም በኋላ መኰንኑ የሥቃይ መሣሪያ ይሠራ ዘንድ አንዳዝዘው ብረትን የሚያቀልጥ ሰው አምጡልኝ አለ በአመጡለትም ጊዜ ሰይጣኑ ወደ መኰንኑ ልብ ገብቶ አንደበቱን ዘጋውና መናገር ተሳነው #ሕፃኑ ፈጥኖ አክሊልን ለመቀበል እንደሚተጋ ሰይጣን ስለ አወቀ ስለዚህ ዘጋው
👉ከዚህም በኋላ #ሕፃኑ ሠራተኛውን ጠርቶ እኔንና #እናቴን የሚያሠቃዩበትን የሥቃይ መሣሪያ መሥራት ትችላለህን ይህ መኰንን ግን ምንም የሚያውቀው ነገር የለም አለው ሠራተኛውም እንደምትሻው በል ንገረኝ እንደምታዝዘኝ እኔ መሥራት እችላለሁ አለው
👉ሕፃን #ቂርቆስም ሊአዝዝ ጀመረ እንዲህም አለ ሁለት መላጫዎች ስፋታቸው አራት ክንድ የሆነ ለእኔና ለእናቴ ሥራ ዳግመኛም የሚያስጨንቅ ራስን የሚመታና የሚሰብር አንገትንም የሚያሥር የሚዝቅም ሹካ ዐይንንም የሚያወልቅ አካልንም የሚበሳሳ አፍንጫንም የሚያጣምምና የሚሰብር ጆሮንም የሚልጥ ሕዋሳትን የሚፈታና የሚለያይ እንደ ልጓም ሁኖ ምላስን የሚቆርጥ በሰውነትም ውስጥ ገብቶ የሚንቀሳቀስ ቆላፋ ጉጠትን ጐኖችንም የሚፍቅና የሚቆለምም አስጨናቂ የሆነ ጉልበቶችንና ጭኖችን የሚሰብር ጅማቶችንም የሚቆራርጥ ሥሮችንም የሚመዝ በዚችም አስጨናቂ መሣሪያ ጅማቶችን የሚታታ አድርግ።
ዋኝተው ወጥተው ወደ ዳርቻ ሲደርሱም ማዕበል የተፋው አንድ በድን ወድቆ ተመልክተው ፈጸመው አለቀሱ:: ወዲያውም በልባቸው የዚህን ዓለም ኃላፊነት አሰቡ:: ሹመት ፍለጋ መሔዳቸውን ትተው ወደ ገዳም ሔዱ::ወደ ምድረ ሶርያ ደርሰው በታላቁ ደብረ ሮማኖስ መዓርገ ምንኩስናን ተቀበሉ:: በእጃቸው የነበረውን 200 ዲናር ወርቅም ለገዳሙ አበረከቱ:: ለጥቂት ጊዜ በገዳሙ ካገለገሉ በሁዋላም ጾማዕት (በዓት) ተሰጣቸው::
በዚህ ጊዜም "እንግዲህ ወደ ዓለም አልወጣም:: የሴቶችን መልክም አልመለከትም" ሲሉ ቃል ገቡ:: በተጋድሏቸውም በጾምና በጸሎት: በትጋሃ ሌሊት ለ12 ዓመታት ቀጠሉ:: ጾማቸውም 7 ቀን ነበር:: አምላክ ጸጋውን ስላበዛላቸውም ብዙ ድውያንን ፈወሱ::
ዜናቸውም እስከ ምድረ ሮሜ ተሰማ:: እናታቸው (ሰንደሊቃ) የመርከቡን ዜና ከሰማች በሁዋላ የሞቱ መስሏት አልቅሳ ቤቷን የእንግዳ ቤት አድርጋ: በበጎ ምግባር ትኖር ነበርና አንድ ቀን የልጇን ዜና ሕይወት ሰማች::
ከደስታዋ የተነሳ ፈጥና ወደ ደብረ ሮማኖስ ደርሳ "ልጄን ልይ" አለች:: ግን "ሴትን አላይም" ብለው አባ አርከሌድስ ቃል ገብተዋልና ምን ይሁን! ሰንደሊቃም "አራዊት ይብሉኝ እንጂ ልጄን ሳላይ አልሔድም" አለች:: ወዲያው ግን "አባ አርከሌድስ ፈቅደዋልና ግቢ" የሚል መልእክት መጥቶላት ገባች::
ግን ያገኘችው የጻድቁን ልጇን ሥጋ ነበር:: ምክንያቱም የፈጣሪንም: የእናታቸውንም ልብ ላለማሳዘን እንዲወስዳቸው ለምነውት ዐርፈው ነበር:: እናትም በልጇ ሥጋ ላይ እያለቀሰች እዚያው ዐረፈች:: "አብራችሁ ቅበሩን" የሚል ቃል ከቅዱሱ ሥጋ ስለ ተሰማም አብረው ቀብረዋቸዋል::
ሰማዕቷ ቅድስት ምህራኤል፡- ይህችውም የከበረችና የተመሰገነች ቅድስት ምህራኤል ጠምዋህ ከሚባል አገር የተገኘች ታላቅ ሰማዕት ናት፡፡ ወላጆቿ ካህኑ አባቷ ዮሐንስና እናቷ ኢላርያ እግዚአብሔርን የሚያመልኩ ደገኞች ናቸውና እርሷንም በሃይማኖት በምግባር ኮትኩተው አሳደጓት፡፡ መጀመሪያውንም ልጅ ስላልነበራቸው በስዕለት ከብዙ ዘመን በኋላ ነው ያገኟት፡፡ ስዕለታቸውም ደርሶላቸው ቅድስት ምህራኤልን ከወለዷት በኋላ ፈሪሃ እግዚአብሔርንና የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እያስተማሩ አሳደጓት፡፡
ቅድስት ምህራኤልም 12 ዓመት በሆናት ጊዜ በላይዋ ባደረ በመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን መሥራት ጀመረች፡፡ ከሃዲው ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ በነገሠና አምልኮተ ጣዖትን በአዋጅ ባወጀ ጊዜ ቅድስት ምህራኤል ስለ ጌታችን አምላክነት መስክራ ሰማዕት መሆንን ተመኘች፡፡ ከዚህም በኋላ በቁርጥ ሀሳብ ተነሥታ ወደ ባሕር ዳርቻ በመሄድ በመርከብ ተሳፍራ ሄዳ ስሙ ፍልፍልያኖስ የሚባለው የዲዮቅልጥያኖስ መኮንን ዘንድ ደረሰች፡፡ በመርከብም ስትጓዝ ሌሎች ስለ ቀናች እምነታቸው ሰማዕትነትን ለመቀበል የተዘጋጁ ሰማዕታትን አግኝታ ከእነርሱ ጋር ነበረች፡፡ በመኮንኑም ፊት ቆማ እውነተኛውና ሊመለክ የሚገባው አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ መሆኑን መሰከረች፡፡ መኮንኑም ስለ ታናሽነቷ ራርቶላት ከሌሎቹ ለይቶ ሊተዋት ወደደ፡፡ ነገር ግን ቅድስት ምህራኤል መኮንኑ እንደተዋት ዐውቃ የተመኘችውን ሰማዕትነት ሊያስቀርባት መሆኑን ባየች ጊዜ ዳግመኛ መኮንኑንና የረከሱ አማልክቶቹን በድፍረት ረገመችበት፡፡
ከዚህም በኋላ መኮንኑ በጣም ተቆጥቶ ጽኑ በሆኑ የተለያዩ ሥቃዮች አሠቃያት፡፡ ከቀናች ሃይማኖቷም ሸንግሎ ይመልሳት ዘንድ እንዳልተቻለው ሲያውቅ መርዛማ እባቦች፣ ጊንጦችና እፉኝቶች ወዳሉበት ጉድጓት ጣላት፡፡ ከቅድስት ምህራኤልም ጋራ ሌሎች ብዙ ሰማዕታት አብረው ተጣሉ፡፡ በዚህም ጊዜ የታዘዘ የእግዚአብሔር መልአክ ለቅድስት ምህራኤል ተገለጸላትና ከጌታችን ዘንድ የተሰጣትን ቃልኪዳን አስረከባት፡፡ ከዚህም በኋላ ነፍሷን ለእግዚአብሔር አሳልፋ ሰጥታ የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለች፡፡ ምእመናንም የከበረ ሥጋዋን መርዛማ እባቦችና ጊንጦች ካሉበት ቦታ አውጥተው በክብር ቀበሯት፡፡ በኋላም ወላጆቿ ልጃቸው ቅድስት ምህራኤል ስለ እምነቷ መስክራ በክብር ሰማዕት መሆኗን በሰሙ ጊዜ ከብዙ የሀገራቸው ሕዝብ ጋር መጥተው የከበረ ሥጋዋን አፍልሰው ወደ አገራቸው ወሰዱት፡፡ ያመረች ቤተ ክርስቲያንም ሠርተው ሥጋውን በውስጧ ባኖሩ ጊዜ ከሰማዕቷ ቅዱስ ሥጋ ብዙ አስገራሚ ተአምራት ተፈጽመው ታዩ፡፡
ቅድስት እምራይስ፡- ይኽችውም ቅድስት ከከበሩ ደገኛ ክርስቲያኖች የተወለደች ናት፡፡ ፈሪሃ እግዚአብሔርንና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እየተማረች አደገች፡፡ በአንዲትም ዕለት ውኃ ልትቀዳ ወደ ወንዝ ወርዳ ሳለ ተይዘው ስለ ክርስቶስ ታስረው የሚሠቃዩ ሰማዕታትን አየች፡፡ እነርሱም ጳጳሳት፣ ቀሳውስትና ዲያቆናት ናቸው፡፡ በዚህም ጊዜ ቅድስት እምራይስ ወደ መኮንኑ ጭፍራ ዘንድ ቀርባ ‹‹እኔም በእነዚህ ቅዱሳን አምላክ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የማምን ክርስቲያን ነኝና ስሜን ከስማቸው ጋር ጽፈህ ወደ ሰማዕትነት አደባባይ አድርሰኝ›› አለቸው፡፡ እርሱም ስሟን ከሰማዕታቱ ስም ጋራ ጽፎ አብሮ አሰራትና በከሃዲው መኮንን ቁልቁልያስ ፊት አቆማት፡፡ መኮንኑም ለጣዖታቱ እንድትሰግድ በብዙ የስንገላ ቃላት አባበላት ነገር ግን ቅድስት እምራይስ የጌታችንን አምላክነት እየመሰከረች የመኮንኑን ጣዖታት ረገመችበት፡፡ መኮንኑም እጅግ ተቆጥቶ አንገቷን በሰይፍ አስረጠውና ሰማዕትነቷን በድል ፈጽማ የክብር አክሊልን ተቀዳጀች፡፡ ረድኤት በረከቷ ይደርብን በጸሎቷ ይማረን፡፡
††† አምላከ ቅዱሳን ለእነርሱ ካደለው ፍቅራቸው ለእኛም አይንሳን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::
††† ጥር 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል)
2.ቅዱስ አባ መክሲሞስ
3.ቅዱስ አባ አርከሌድስ
4.ቅድስት እምራይስ
5.ቅድስት ምሕራኤል
6."4034"ሰማዕታት (ማሕበራነ ቅዱስ ቂርቆስ)
††† ወርሐዊ በዓላት
1.አባ ስምዖን
2.አባ ዮሐንስ
3.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ (ሙሽራው)
4.ቅዱስ ሙሴ
5.ቅዱስ ፊልዾስ (ከ72 አርድዕት)
6.ቅድስት ነሣሒት
††† "እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና::
ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና::
ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል . . .
ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ::
በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ::
የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል::
አንደበቱም ፍርድን ይናገራል::
የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው::
በእርምጃውም አይሰናከልም::" †††
(መዝ. 36:28)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
🔴በቴሌግራም ለመከታተል👉/channel/zikirekdusn
🛑በዩቲብለመከታተል👉
https://youtube.com/shorts/egux4JdrPrw?si=MjLWZmAjsMzYfmlB
+ትልቅ ድንጋይም አምጥቶ ገጠመው:: እነዚህ ቅዱሳን ተኝተዋልና አልነቁም:: ቀናት: ወራት: ዓመታት ተዋልደው ለ372 ዓመት ተኙ:: አንድ ቀን አንድ እረኛ ለሥራ ፈልጐት ድንጋዩን ፈነቀለው:: በዚህ ጊዜ ቅዱሳኑ ነቁ::+በወቅቱ መልካቸው የወጣት ነው:: እድሜአቸው ግን 400 ሊሞላ ትንሽ ቀርቶት ነበር:: ልክ እንደ አቤሜሌክ ብዙ መተኛታቸው አልታወቃቸውምና ከመካከላቸው አንዱ የራት ዳቦ ሊገዛ ቢወጣ ግራ ተጋባ:: ኤፌሶን የማያውቃት ሌላ ሃገር ሆነችበት:: ከተማዋ ዘምናለች::+በየቦታው አብያተ ክርስቲያናት: ቅዱስ መስቀልም በየአደባባዩ ተተክለዋል:: ነገሩ ግር ቢለው አንዱን ከመንገድ ጠርቶ "ወንድሜ! ይህቺ ከተማ ኤፌሶን አይደለችምን?" አለው:: እርሱም "አዎ ናት" ብሎት አለፈ::
+ችግሩ ግን "ራት ልግዛ" ብሎ ወደ ገበያ ሲሔድ: እርሱ የያዘው ገንዘብ የዳኬዎስ ስም የተጻፈበት መሆኑ የፈጠረው ነበር:: በነጋዴዎቹ "የተደበቀ የጥንት ገንዘብ አግኝተሃል" በሚል ተከሶም ወደ ንጉሡ ቴዎዶስዮስ ዘንድ ቀረበ:: (ትንሹ ቴዎዶስዮስ ነው:: የነገሠውም በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው)
+በክርክሩ መካከል ቅዱሱ የእሱንና የወንድሞቹን ነገር ሲናገር ንጉሡም: ሊቀ ዻዻሱም (አባ ቴዎድሮስ ይባላል) ተገረሙ:: አብረው ከከተማ ወጥተው ሔደው: 7ቱንም ሲጸልዩ አገኟቸው:: ፊታቸውም እንደ እግረ ፀሐይ ያበራ ነበር:: 7ቱም ለ7 ቀናት በኤፌሶን ድውያንን እየፈወሱ: ሰውን ሁሉ እየባረኩ ቆዩ::
+ይህ ሁሉ የተደረገው በወቅቱ "ትንሳኤ ሙታን የለም" የሚሉ መ+ና+ፍ+ቃ+ን ተነስተው ብዙ ሰው ክዶ ነበርና ለእነሱ ምሥክር ሊሆንባቸው ነው:: በርካቶችም በዚህ ድንቅ ተስበው ወደ ሃየማኖት ተመልሰዋል:: 7ቱ ቅዱሳን ግን በ7ኛው ቀን በክብር ዐርፈዋል:: ንጉሡ 7 የወርቅ ሣጥኖች ቀብሯቸዋል::
=>አምላከ አበው ቅዱሳን በመጽናታቸው ያጽናን:: ከበረከታቸውም ያድለን::
ጥር 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ኢትዮዽያዊ (እረፍታቸው)
2.ሰባቱ ደቂቅ ቅዱሳን (ከኤፌሶን)
3.ቅዱስ አባ ነካሮ
4.ቅዱስ ቃሮስ
=>ወርሐዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት
3.ቅዱስ አስከናፍር
4."13 ግኁሳን ጻድቃን"
5.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ
6.ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት
=>+"+ በተቀደሰ አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ:: ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላቹሃል:: የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ: የእግዚአብሔርም ፍቅር: የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን:: አሜን:: +"+ (2ቆሮ. 13:12)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
ማንም ሊያድንሽ እንደማይመጣ ስትረጂ ወኔሽን አካብጂ::
-
ራስሽን ማስደሰትም ሆነ ማሳደጉን ከሌላ ሰው አትጠብቂ::
-
ሰው ? እንኳን ለአንቺ ሊሆን ለራሱ ዞሮበታል::
"ምን ነበር ቢረዳኝ!" የምትይው "ምን ነበር ብትረዳኝ!" እያለ ነው::
-
እስቲ ግራ ያልተጋባ ሰው ጠቁሚኝ::ዞር ብለሽ ብትመለከቺ ሁሉም ዞሮበታል::
-
የሚስቀው ውስጡ እንደ ፈንድሻ እያረረ ነው::አሁን አሁን "ምርጥ ፎቶ!" የሚፖስተው መጥፎ ህይወቱን ለመደበቅ ነው::
-
አንቺ ለእነሱ ታስፈልጊያለሽ እንጂ እነሱ ለአንቺ አያስፈልጉም::
-
ከሰው ከምትጠብቂ ለሰው ብትሰጪ ስኬታማ ትሆኛለሽ::የምትሰጪው ነገር በ30 በ60 እና በ100 ተባዝቶ ወደ አንቺ ይመጣልና::
-
ደግሞ "ምን አለኝና!" አትበይ::ከእናቱ ማህፀን ማን ምን ይዞ ወጣ? ምንም::
-
ሁሉም ሆነ አንቺም ያላችሁ አምላክ ነው::አምላክ ደሞ ሳያዳላ ሰውነት አይምሮና መንፈሱን ለሁሉም እኩል ችሯል:: ልዩነቱ አጠቃቀሙ ላይ ነው::
-
በአይምሮሽ ወደ መንፈስሽ በመሄድ የወደድሺውን የስኬት ሀሳብ አቀናብሪ::አላማሽን አምላክ ባለበት መንፈሳዊ አለም ፍጠሪ::በውስጥሽም እንደ ተሳካ አምነሽ በሰውነትሽ የቻልሺውን ሁሉ አድርጊ::
-
ጥርጣሬ ከአላማሽ ፍሬ የሚነጥልሽ ግድግዳ ነው::እምነት ግን በአምላክ ሐይል አበርትቶሽ የአላማሽን ፍሬ ያበላሻል::
-
ሁሉም ነገር ከሁሉም ነገር ጋር በአምላክ መንፈስ ተገናኝቷል::የአንቺም አላማ በማይታይ የመንፈስ ገመድ ካንቺ ጋር ታስሯል::
-
እንደ ሆነ እድርግሽ በውስጥሽ ስታምኚ አላማሽ ወደ አንቺ እየቀረበ ይመጣል::በወኔ ተሞልተሽ በሐይል ስታደርጊ እጅሽ ላይ ይወድቃል::
-
ማንም የአንቺን አላማ አይወጥንም::ማንም ባንቺ አላማ አያምንም::ማንም ላንቺ አላማ ስኬት አይቦዝንም እርምጃም አይወስድም::
-
አንቺው የኔ እህት!! አዎ አንቺው በቂ ነሽ!! ሁሉን ማድረግ የማይሳነው አምላክ አለሽ!! ራስሽን መርዳት ስትጀምሪ ፍጥረት ሁሉ አንቺን መርዳት ይጀምራል::አንቺም ደግሞ ፍጥረትን ሁሉ መልሰሽ ትረጃለሽ!
-
#መልካም ቀን!
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
💚 t.me/Asresee
💛 t.me/Asresee
❤ t.me/Asresee
ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በቡራዩ ክ/ከተማ የጠሮ መካነ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የገቢ ማሳሰቢያ
ጉባኤው የሚከናወንበት ቦታ: መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን አዳራሽ (አራት ኪሎ)
የጉባኤ ቀን : መጋቢት 15/2016 ዓ.ም
መግቢያ ዋጋ : 100 ብር ብቻ
የመንፈሳዊ ጉባኤውን ትኬት የሚፈልጉ ከሆነ ይደውሉ፡፡ 0907610076 0960029538
ባሉበት ትኬቱ እንዲደርሶ እናደርጋለን፡፡ ሰብሰብ አድርገው ቢገዙ ይበረታታል! እናመሰግናለን
#ጥር_17
#ቅዱስ_መክሲሞስ እና #ቅዱስ_ዱማቴዎ
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥር ዐሥራ ሰባት በዚህች ዕለት ለለውንድዮስ ለሮም ንጉስ ልጆቹ የሆኑ የከበሩና የተመሰገኑ መክሲሞስና ዱማቴዎስ መታሰቢያቸው ሆነ። ይህም ንጉስ ሃይማኖቱ የቀና እግዚአብሔርንም የሚፈራ በእውነትም የቀና ፍርድን የሚፈርድ ነበር ስለዚህም እሊህን ሁለት ቅዱሳን እግዚአብሔር ሰጠው እነርሱም ከታናሽነታቸው ጀምሮ በንጽህና እንደ እግዚአብሔር መላእክት ሆኑ።
ትሕትናን ፈሪሀ እግዚአብሔርን በማስተማር አሳደጋቸው የሚጾሙና የሚፀልዩ በቀንና በሌሊትም የብሉይና የሐዲስ መጻህፍቶችን የሚያነቡ ሆኑ። ከዚህም በኋላ ይህን ዓለም ይተውት ዘንድ የመላእከትንም ልብስ ይለብሱ ዘንድ እርሷም የከበረች የምንኩስና ልብስ ናት ከዚያም ሐሳብ መጣባቸው ሃይማኖታቸው የቀና ሦስት መቶ አስራ ስምንት አባቶች ወደ ተሰበሰቡባት ወደ ኒቅያ ሂደው ይፀልዩ ዘንድ እንዲአስናብታቸው ለአባታቸው ምክንያት አቀረቡ።
ይህንንም ከርሳቸው በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ አለው ከብዙ አገልጋዮችና ከብዙ ሰራዊት ጋር አሰናበታቸው ከኒቅያ አገርም በደረሱ ጊዜ ከከበረ ቦታ በረከትን ተቀበሉ ሰራዊቱንም ወደ ንጉስ አባታቸው ጌታችን ንጉሥ ሆይ እኛ ከዚህ ጥቂት ቀን መቆየት እንሻለን ከሚል ጽሑፍ ጋር ጽፈው ላኩ።
ከዚህም በኃላ ለአንድ ፃድቅ መነኮስ ሐሳባቸውን ገለጡ እንዲህም አሉት ከአንተ ዘንድ የምንኩስናን ልብስ እንድንለብስ እንሻለን እርሱም እኔ ከንጉስ አባታችሁ የተነሳ እፈራለሁ ነገር ግን ወደ ሶሪያ ሂዱ ስሙ አጋብዮስ የሚባል ከዚያ ሀይማኖቱ የቀና ካህን ደግ መነኮስ አለ አላቸው። ይህንንም ሲላቸው ምክሩን ተቀብለው ወደ ሶሪያ ተጉዘው ወደ ቅዱስ አባ አጋብዮስ ደርሰው ኀሳባቸውን ገለጡለት እርሱም ተቀብሎ የምንኩስና ልብስን አለበሳቸው እስከሚአርፍበትም ቀን ከእርሱ ዘንድ ኖሩ።
ከዕረፍቱም አስቀድሞ ያየውን ራእይ ነገራቸው ታላቁ አባ መቃርስ ወደርሱ እንደመጣና ልጆችህ መክሲሞስና ዱማቴዎስ ለኔ ልጆቼ ይሆኑኝ ዘንድ ወደ እኔ ወደ አስቄጥስ ገዳም እንዲመጡ ከመሞቴ በፊት እዘዛቸው አለው።
ዳግመኛም እንዲህ አላቸው ልጆቹ እኔ ይህን ሰው አባ መቃርስን በስጋው አየው ዘንድ እመኝ ነበር እነሆ በመንፈስ አየሁት እናንተም ከሞትኩ በኃላ ወደርሱ ሒዱ።
ከአረፈም በኃላ አልሄዱም በዚያ በሶሪያ አገር ኖሩ እንጂ እግዚአብሔርም ሀብተ ፈውስ ሰጥቷቸው በሽተኞችን የሚፈውሱ ሆኑ ወሬያቸውም በሀገሮች ሁሉ ተሰማ በባህርና በየብስ ከሚነግዱ ነጋዴያንም የመርከብ መዛነቢያቸውን መስራት ተምረው ከድካም ዋጋቸው በየጥቂቱ የሚመገቡና የተረፈውን ለድሆችና ለችግረኞች የሚሰጡ ሆኑ።
እግዚአብሔርም በእጆቻቸው ከሚሰራቸው ድንቆች ተአምራቶች የተነሳ የቅዱሳን መክሲሞስንና ዱማቴዎስን ስም መናፍስት ርኩሳን በሚሰሙ ጌዜ ከሰዎች ወጥተው ይሻሻሉ ሰዎቹም ያን ጊዜ በጌታ ኃይል ይድናሉ ጤነኞችም ይሆናሉ።
እጅግ ታላቅ የሆነ በጎዳና አጠገብ የሚኖር ከይሲ ነበር ብዙዎች ሰዎች ሰዎችንም አጥፍቷል የአገር ሰዎችም ወደ ከበሩ መክሶሞስና ዱማቴዎስ መጥተው ከዚያ ከይሲ ያድኗቸው ዘንድ ለመኗቸው አባ መክሲሞስም ክርታስ አንስቶ እንዲህ ብሎ ፃፈ የብፁእ መቃርዮስ አምላክ በሆነ መንፈስ ቅዱስንም በለበሰ በአባታችን በአጋብዮስ አምላክ በህያው እግዚአብሔር አካላዊ ቃል በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይህ ደብዳቤ ከዋሻህ ደጅ ቢደርስ አንተ ወጥተህ ሙት የሰማይ ወፎችም ይብሉህ።
አንድ ሰውም ያቺን ደብደቤ ተቀበሎ ሄደ በዚያም የዘንዶ ዋሻ ደጃፍ አኖራት በዚያንም ጊዜ ዘንዶዉ ወጥቶ ሞተ የሰማይ ወፎችም በሉት ህዝቦችም ሁሉ እጅግ አደነቁ እግዚአብሄርንም አመሰገኑት የክብር ባለቤት ጌታችንም በእሊህ ቅዱሳን በመክሲሞስና በዱማቴዎስ እጆች ብዙ ድንቆች ተአምራቶችን አደረገ።
በአንዲትም ዕለት ከአባታቸው መኳንንቶች አንዱ ወደ ባህር ዳርቻ ደረሰ ከመርከቦችም በአንዱ መርከብ መዛገቢያ ላይ መክሲሞስና ዱማቴዎስ የሚል ፅሁፍ በአየ ጊዜ የመርከቡን ሹም ጠየቀው እርሱም እንዲህ አለው በፀሎታቸው ከስጥመት እግዚአብሔር ያድነኝ ዘንድ የእሊህን ሁለት ወንድማማቾች የከበሩ መነኮሳት ስማቸውን በመርከቤ ላይ ፃፍኩ መኮንኑም መልካቸው ምን ይመስላል አለው እርሱም የመልካቸውን ምልክት ነገረው የንጉሱ ልጆች እንደሆኑ አውቆ ያን ነጋዴ ወደ ንጉስ አባታቸው አደረሰው።
ንጉሡም ጠየቀው ነጋዴውም የመልካቸውን አምሳል አስረዳው ንጉሡም ልጆቹ እንደሆኑ በተረዳ ጊዜ እናታቸውንና እኅታቸውን ከብዙ ሠራዊት ጋር ወደነርሱ ላከ ደርሰውም በአዩአቸው ጊዜ ጩኸው አለቀሱ እናታቸውም ወደ ንጉስ አባታቸው ከእርሷ ጋር ይመጡ ዘንድ ለመነቻቸው።
እነርሱም ራሳችንን ስእለት አድርገን ለእግዚአብሔር ሰጥተናልና ቃል ኪዳናችንን ማፍረስ አይቻለንም ነገር ግን ሄጄ ለአንቺም ለአባታችንም ከመከራ ሁሉ እግዚአብሔር ያድናችሁ ዘንድ እንፀልይላችኋለን በዚህም አነጋገር አረጋጓት በመለየቷም ፈፅማ እያዘነች ተመለሰች።
ወደ ንጉሱም በደረሰች ጊዜ ከእነርሱ የሆነውን ነገረችው ንጉሱም ለሚስቱና ለባለሟሉቹ እንዲህ አለ በእግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ የሕይወት ድልብ ይሆኑን ዘንድ እንተዋቸው ፀሎታቸውም ይጠቅመናል በዓለም ውስጥ ያለ ክብር ሁሉ እንደ ሕልም ኃላፊ ጠፊ ነውና እነርሱ ግን የማያልፍ መንግስትን አተረፉ።
በዚያም ወራት የሮሜ ሀገር ሊቀ ጳጳሳት አረፈ ስለሚሾሙትም ሊቀ ጳጳሳት ይማከሩ ዘንድ ኤጲስቆጶሳት ጳጳሳትም ተሰበሰቡ የከበረ መክሲሞስንም አሰቡትና ሁሉም ለዚች ሹመት እርሱ በእውነት ይገባል ተባባሉ።በሽተኞችን ይፈውስ ዘንድ ብዙዎች የሆኑ ድንቆች ተአምራቶችንም ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔር ታላቅ ፀጋ ሰጥቶታልና በእድሜውም ወጣት ቢሆን ክርስቶስ በውስጡ ወጣት ቢሆን ክርስቶስ በውስጡ ስለአደረ በዕውቀትና በበጎ ስራ በቤተ ክርስቲያንም ህግና ስርአት ሁሉ ፍፁም ነው።
ይህንንም በሰሙ ጊዜ አባቱና እናቱ ደስ አላቸው መኳንንቶችንም ላኩ የከበሩ መክሲሞስንና ዱማቴዎስን ወደ ሮሜ ይሰዳቸው ዘንድ ወደ ሶሪያ አገረ ገዢ ደብዳቤ አብረው ላኩ። እሊህም ቅዱሳን ሰምተው እጅግ አዘኑ አባታቸው አባ አጋብዮስም ያዘዛቸውን አሰቡ በዚያንም ጊዜ ተነሱ ልብሳቸውንም ለውጠው ወደ ኤርትራ ባህር ዳርቻ ተጓዙ ወደየትም እንደሚጓዙ አያውቁም ውኃን በሚጠሙ ጊዜም እግዚአብሔር መራራውን ውኃ ለውጦ ጣፋጭ አድርጎላቸው ይጠጣሉ ከዚህም በኃላ ከእርሱ ዘንድ ረድኤትን ኃይልን ላከላቸውና ከሶሪያ አገርም ተሸክማ ወደ አስቄጥስ ገዳም አደረሰቻቸው ወደ አባ መቃርስም ገብተው በእርሱ ዘንድ መኖርን እንደሚሹ ነረጉት።
እነርሱም በፀጋ የለመለሙ እንደሆኑ በአየ ጊዜ በገዳም መኖርን የማይችሉ መስለው በገዳም ያለውን ችግር ነገራቸውና በዚህ መኖር አትችሉም አላቸው እነርሱም አባታችን ሆይ ተወን ከዚህ መኖር ካልተቻለን እንሄዳለን ብለው መለሱለት።
ከዚህም በኃላ ሰሌን መስራትን አስተማራቸው ሰሌንም የሚቆርጡበትን ወንዝ አሳያቸው ማደሪያቸውንም እስከሚሰሩ ድረስ ረዳቸው የእጅ ስረቸውንም የሚሸጥና ምግባቸውን የሚያመጣላቸውን አንድ ህዝባዊ ሰው አምጥቶ አገናኛቸው። እንዲህም ሆነው ከቶ ከሰው ሳይገናኙ ሶስት አመት ኖሩ ነገር ግን በጭልታና በዝምታ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚገቡና ሥጋውንና ደሙን ተቀብለው ወደ ማደሪያቸው የሚመለሱ ሆኑ።
እንደ ምን አላችሁ ቤተሰቦቼ ?
ከተሠማራንበት የሥራ ዘርፍ በተጨማሪም ሆነ እንደ ዋና ሥራ አድርገን ልንሠራው የምንችለ የሥራ ዘርፍ አለን በመሆኑም ፦
1, በግልም ሆነ በመንግሥት ተቋማት ተቀጥራችዉ የምትሠሩ
2, የግላችውን ሥራ የምትሠሩ
3, ከዩኒቨርስቲ ተመርቃችሁ ሥራ ያላገኛችሁ
4, 12 ተፈትናችሁ ነጥብ የመጣላቸውም ሆነ ያልመጣላችው ሠርታችዉ የራሳችሁን ስራ መሥራት ወይም ለመጀመር የሚያስችል ካፒታል የምታገኙበት የስራ ዘርፍ ነው ።ማንኛውም መሥራት የሚፈልግ ሰው ሙሉ ስም ፣የመኖሪያ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር በዉስጥ መሥመር ያሥቀምጥልኝ።
ሴልስ መስራት የሚፈልግ በዚህ ቁጥር መደወል ይችላሉ
0983797902
0799192014
inbox me your :
-NAME
-ADRESS
PHONE NUMBER
✝እንኳን ለአበው ቅዱሳን "አባ ዳንኤል" : "አባ ዸላድዮስ" : ወቅዱስ "ፊላታዎስ ሰማዕት" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችኹ✝
+*" ማር ዳንኤል "*+
=>"ዘዓምድ" በሚል ስም ከሚታወቁ የቤተ ክርስቲያን አበው መካከል 4ቱ ቅድሚያውን ይይዛሉ:: እነዚህም:-
1.ቅዱስ ስምዖን ዘዓምድ:
2.ቅዱስ አጋቶን ዘዓምድ:
3.ቅዱስ ዳንኤል ዘዓምድ እና
4.ቅዱስ ሉቃስ ዘዓምድ ናቸው::
+"ዘዓምድ" የሚለውን ቃል ምሥራቃውያን በልሳናቸው 'THE STYLITE' ይሉታል:: የእኛው ቃል ደግሞ ከግዕዝ የተወረሰ ነውና በቁሙ ቢተረጐም "የምሰሶው" የሚል ትርጉምን ይይዛል:: ይህም በ2 ምክንያቶች ነው::
+አንደኛው ቅዱሳኑ ተጋድሏቸውን የፈጸሙት ከረዥም ምሰሶ ላይ ወጥተው በመጸለይ ስለሆነ ነው:: ሌላኛው ምክንያት ደግሞ እነዚህ አባቶች በዘመኑ ለነበሩ ምዕመናንና መነኮሳት አጽናኝ: አስተማሪ: መሪና ፈዋሽ በመሆናቸውና እንደ ምሰሶ ተተክለው ሳይነቃነቁ በመጸለያቸው ነው::
+ልክ ከዓለም ሃገራት ብዙ ስውራንን እና ቅዱሳን ነገሥታትን በመያዝ ሃገራችን ቀዳሚ እንደ ሆነችው ሁሉ ምሰሶ ላይ ወጥተው የሚጋደሉ ቅዱሳንም ሶርያውያንና ምሥራቃውያን ናቸው:: በዚህ ዕለትም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የታላቁን ቅዱስ ማር ዳንኤልን በዓል ታከብራለችና ከዜና ሕይወቱ ለበረከት ጥቂት እንካፈል::
=>ይህ ቅዱስ ሰው (በስዕሉ የሚታየው) ሶርያዊ ሲሆን ተወልዶ ያደገባት አካባቢ በቀድሞው አጠራር "ሃገረ ዓምድ" ይሏታል:: "ማር" የሚለው ቃል በቤተ ክርስቲያን ቅድስናንና አለቅነትን የሚገልጽ ስም ነው:: በዚህ ስም ጥቂቶች ብቻ ሲጠሩበት ለሊቃውንትም: ለሰማዕታትም: ለጻድቃንም አገልግሏል::
+ቅዱሱ "ማር" ብቻ ሳይሆን "ዘዓምድ" ተብሎም ተጠርቷል:: ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ እርሱም በፊት እንደ ጠቀስናቸው አበው ምሰሶ ላይ ተጠግቶ (ቆሞ): ትኩል ከመ ዓምድ ሆኖ በመጸለዩ ነው::
+ማር ዳንኤል በምድረ ሶርያ ስመ ጥር ጻድቅ ነው:: በዘመነ ጻድቃን መጨረሻ አካባቢ ከክርስቲያን ወገኖቹ ተወልዶ: በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አድጐ: ገና በልጅነቱ ለቤተ እግዚአብሔር ተሰጥቷል::
+የወቅቱ የሃገረ ዓምድ ዻዻስ (አባ ዼጥሮስ) ለማር ዳንኤል ፍኖተ ጽድቅን (የሕይወት - የእውነትን ጐዳና) በማሳየት ከፍ ያለውን አስተዋጽኦ አበርክቷል:: አስተምሮም ለመዓርገ ክህነት አብቅቶታል::
+ቅዱሱ በእድሜው እየበሰለ ሲሔድ ግን ምርጫው ምናኔ ሆኖ በመገኘቱ በፈቃዱ ወደ በርሃ ሔደ:: በዚያም መዓርገ ምንኩስናን ተቀብሎ በጾም: በጸሎትና በትሕርምት ይጋደል ገባ::
+ማር ዳንኤል በበዓቱ ተወስኖ ሲጾም: ሲጸልይና እግዚአብሔርን ሲያመልክ ከጸጋ (ከብቅዓት) ደረሰ:: ብዙ ተአምራትንም በመሥራቱ ስም አጠራሩ በአካባቢው ተሰማ:: እርሱ ግን ከሰው: ይልቁንም ከሴቶች ይርቅ: ላለማየትም ራሱን ይከለክል ነበር::
+ለአንድ መናኝ በሰዎች መካከል: ይልቁንም በተቃራኒ ጾታ ጐን መኖር ያልተፈቀደ: ፈታኝም ድርጊት ነውና ከፈጣሪው ጋር እንዲህ የሚል ቃልን ገባ:: "ከዚህ በሁዋላ ሴት ልጅን አላይምም" አለ:: በእንዲህ ያለ የቅድስና ሕይወት ሳለ ወላጅ እናቱ ልታየው ተመኘች::
+ወደ ገዳሙ መጥታም "ልጄ! ላይህ ሽቻለውና ልግባ : ወይ ብቅ በል" ስትል ላከከችበት:: ቅዱሱ ግን "እናቴ! ሴትን አላይም ብየ ቃል ስለ ገባሁ አልችልም" ሲል መለሰላት:: በጣም አዝና "እኔ ወልጄ: አዝዬ: አጥብቼ: አሳድጌ እንደ ሌሎች ሴቶች አስመሰልከኝ? በል ፈጣሪ 2 ሴቶች በአንድ ልብስ ሆነው ይዩህ!" ብላ ረግማው ወደ ቤቷ ተመለሰች::
+የሚገርመው ማር ዳንኤል በበርሃ የበቃውን ያህል እናቱ በዓለም ሳለች በጐ ሰርታለችና እርሷም ጸጋውን አብዝቶላታል:: በምን ይታወቃል ቢሉ:- ያቺ የተናገረቻት ነገር ሁሉ ደርሶበታልና::
+አንድ ቀን ለገንዘብ ሲል አንድ ሰው የገደለውን አምጥቶ በቅዱሱ በር ላይ ጣለው:: ቅዱሱም ያለ አበሳው ታሥሮ ወደ ከተማ ሲወሰድ መታጠቢያ (shower) ቤት ውስጥ የነበሩ ሴቶች ሊያዩት ቸኩለው: አንድ ልብስ ለብሰው ወጥተዋል:: ማር ዳንኤል ይህንን ሲያይ የእናቱ ነገር ትዝ ብሎት ሳቅ ብሏል::
+በታሠረበት ቦታ ግን የሞተውን ሰው በጸሎቱ በማስነሳቱ በክብር ወደ በዓቱ ተመልሷል:: የከተማዋ ንጉሥም ገዳምን አንጾለታል:: በተረፈ ዘመኑም ለብዙ ቅዱሳን አባት ሆኖ እስከ እርጅናው አገልግሏል:: በዚህች ቀንም በክብር ዐርፏል::
+*" አባ ዸላድዮስ "*+
=>አባ ዸላድዮስም በተመሳሳይ የዘመነ ጻድቃን ፍሬ ነው:: በርሃ ከገባባት ቀን ጀምሮ ጾምን: ጸሎትን አዘውትሮ ክርስትናውን አጽንቷል:: ሙሉ እድሜውን በጐ በመሥራት በማሳለፉ ፈጣሪውን ሲያስደስት ለብዙዎች አንባ: መጠጊያ መሆን ችሏል::
+በጸሎቱ አካባቢውን በደህንነት ይጠብቅ ነበር:: ምዕመናን እንኩዋን ወደ እርሱ መጥተው ተባርከው ባሉበት ቦታ ሁነው ተማጽነው እንኩዋ መሻታቸውን አያጡም ነበር:: ምንም ያህል ኃጢአተኞች ይሁኑ እግዚአብሔር ስለ አባ ዸላድዮስ ሲል ይለመናቸው ነበር::
+አንድ ቀን አንድ ነጋዴ ሰው በባሕር ላይ ሲሔድ ድንገት ማዕበል ይነሳበታል:: ብቻውን ነበርና ጨነቀው:: እሱ ያለባት ጀልባም ትንሽ በመሆኗ ልትሠበር ደረሰች:: መዳን እንደ ማይችል ሲያውቅ ተስፋ ቆረጠ::
+ድንገት ግን አባ ዸላድዮስ ትዝ ብሎት ቀና ብሎ "ጌታየ! ስለ ቅዱሱ አባት ብለህ ብትምረኝ ለወዳጅህ መቶ ዲናር ወርቅ እሰጣለሁ" ሲል ተሳለ:: ቃሉን ተናግሮ ሳይጨርስ አባ ዸላድዮስ በጀልባው ላይ ቁጭ ብሎ ታየው:: ማዕበሉም ጸጥ እንዲል አድርጐ ከወደብ አድርሶ ተለየው::
+ነጋዴውም ፈጣሪውን ስለ ድኅነቱ እያመሰገነ 100 ዲናር ወርቁን ይዞ አባ ዸላድዮስን ፍለጋ ወጣ:: የሚያውቀው በዝና ብቻ ነበርና:: መንገድ ላይም ሞሪት የሚባል መሪ አግኝቶ ከአባ ዸላድዮስ በዓት ደረሰ::
+ከቅዱሱ ተባርኮ ወርቁን ቢያቀርብለት "ልጄ! እኔ ይህን አልፈልገውም:: ለነዳያን በትነው" አለው:: ነጋዴው ሲወጣ ግን ሞሪት (መሪው) ገንዘቡን ፈልጐ ገደለውና ከጻድቁ በር ላይ ጣለው:: ሃገረ ገዢውም ሲሰማ አባ ዸላድዮስን አሠረው::
+ጻድቁ ግን የሞተውን ባርኮ አስነሳውና "ማን ገደለህ" ቢለው "ሞሪት" ሲል መልሷል:: መኮንኑ ሞሪትን ሊገድለው ቢልም "የለም" ብሎ ነጋዴውን በደስታ: ሞሪትን ደግሞ በንስሃ ሸኝቷቸዋል:: አባ ዸላድዮስ ግን ተረፈ ዘመኑን በቅድስና ሲጋደል ኑሮ በክብር ዐርፏል::
+*" ቅዱስ ፊላታዎስ ሰማዕት "*+
=>"ፊላታዎስ" ማለት "መፍቀሬ እግዚአብሔር - እግዚአብሔርን የሚወድ: እርሱም የሚወደው" ማለት ነው:: ቅዱሱ የዘመነ ሰማዕታት (3ኛው መቶ ክ/ዘመን) ፍሬ ሲሆን ለየት ያለ ታሪክ ያለው ቡሩክ ወጣት ነው::
+እርሱ የባለ ጸጐች ልጅ: ስለ ክርስትና ምንም ሰምቶ የማያውቅ ሕጻን ነበር:: ወላጆቹ የሚያመልኩት ላምን ሲሆን የአካባቢው ሰው ደግሞ ለጸሐይ ይንበረከክ ነበር:: ቤተሰቦቹ ስለ አምልኮ ሲጠይቁት "እናንተ የምታመልኯቸው ፍጡራን ስለ ሆኑ አልፈልግም" አላቸው::
+ሕጻን ቢሆንም ስለ ፈጣሪው ተመራመረ:: በመጨረሻውም ፀሐይን "አንተ ምንድነህ?" ቢለው "እኔ ፍጡር ነኝ" ሲል መልሶለታል:: በዚያች ዕለት ግን ቅዱስ መልአክ ወርዶ: ሁሉን ነገር አስተምሮ የክርስቶስ ወታደር አድርጐታል::
ኪዳነ ምሕረት እመቤት እመቤት (2)
ነይልን (2) ካለንበት (2)
ከሰማያት በላይ ካለው ከማደርያሽ (2)
ዝማሬ ከሞላው ከዘለዓለም ቤትሽ
የምድር ፍጥረታት ማርያም ማርያም ሲሉሽ (2)
የቃል እናት እመቤቴ ነይ በሰረገላሽ (2)
አዝማች
ከፀጥታ ወደብ ከፍቅር አውድማ
ከሰላሙ መንደር ከእውነት ከተማ (2)
ሰአሊ ለነ ቅድስት ውዳሴሽ ሲሰማ (2)
ከሚካኤል ከገብርኤል ጋር ነይልን ከራማ
አዝማች
ዘርፋፋ ቀሚስሽ ይውረድ ከሰማያት (2)
ዕንባችን ይታበስ ባንቺ አማላጅነት
የጽዮን ዘማሬ ተሞላች ነፍሳችን (2)
ንዒ (3) እንበል እንደ አባቶቻችን (2)
አዝማች
ፍጥረታት ሊድኑ በአማላጅነትሽ (2)
የዘላለም ኪዳን አማኑኤል ሰጠሽ
ትውልድ ይህን አምኖ ብፅዕት ይሉሻል (2)
እናቴ መመኪያዬ ምርኩዜ ሆነሻል (2)
አዝማች
የልብን ሲያዋዩሽ ሰምተሽ ዝም አትይም (2)
ችግረኛን አይቶ ልብሽ አይቸክንም
ከዓይን ጥቅሻ ፈጥነሽ ትደርስለታለሽ (2)
ከኃዘን ከመከራ ታሳርፊዋለሽ (2)
👉ዳግመኛም በላም አምሳል ሰፊ መቀመጫ ከናስ ሥራ ሦስት ቀዳዳዎችንም በዚያ መቀመጫ ውስጥ ቅደድ በቁመቴም ልክ ሦስት ችንካሮችን ሥራ የችንካሮቹንም ራስ ከናስ አድርገህ በውስጡ ከሚጠሩት ዘንድ ፈጽሞ የማይለይ ልዩ #ሦስት ብለህ ፃፍ
👉ዳግመኛም ጠምዝዞ ወደ ላይ የሚያወጣ ሁለት መሣሪያ ሁለት መጋዞችን ሁለት የብረት ምጣዶችን ሥራ አሁንም አንድ ታላቅ ጋን ሠርተህ በውስጡ አንገትን የሚጠመዝዝና የሚሠነጥቅ ተሽከርካሪ መሣሪያ አድርግ
👉በውስጥ የተሸሸገ የሆድ ዕቃን የሚመረምር እጅን ከብረት ሥራ እኔ የጻዕር ስቃይን የምሠቃይበት ይህ ነው አለ ብረት ሠሪውም ሰምቶ እጅግ አደነቀ የሚረዱትንም ከሀገር ውስጥ መቶ ሠራተኞችን ሰብስቦ መሥራት ጀመረ በአርባ ቀንም ጨረሰ
👉ከዚህም በኋላ መኰንኑ እለእስክንድሮስ #ቂርቆስንና_እናቱን ወደ አደባባይ ያመጡአቸው ዘንድ አዘዘ ያን ጊዜ አንደበቱ ተፈትቶ ነበርና እንዲህም አለ ሕፃኑንና እናቱን ከቆዳቸው ጋር ራሳቸውን ላጩአቸውና በላያቸው የእሳት ፍሞችን ጨምሩ እርር ብለው እንዲቃጠሉ ዳግመኛም አራት ችንካሮችን ከትከሻዎቹ እስከ ተረከዙ ድረስ እንዲተክሉበት አዘዘ #የእግዚአብሔርም መልአክ መጥቶ ሥቃዮችን ከርሱ አራቀ
👉ዳግመኛም ከጥዋት እስከ ማታ ከሥቃይ መሣሪያዎች ውስጥ ጨምረው አዋሏቸው ግን ማሠቃየት ተሳናቸው ከዚህም በኋላ ከማምጠቂያው ውስጥ ጨምረው መገዙአቸውና አመድ እስከሆኑ ከቅባትና ከጨው ጋር በብረት ምጣድ ውስጥ ቆሉአቸው ጌታችንም ከሞት አስነሥቶ አዳናቸው
👉ወደ መኰንኑም በገቡ ጊዜ እንዲህ አላቸው በእውነት ከሙታን ተለይታችሁ የተነሣችሁ ከሆነ ይህ ጫማዬ ከእግሬ ወጥቶ እንደ ቀድሞው ሕያው እንዲሆን አድርጉ ሕፃን ቂርቆስም በጸለየ ጊዜ ያ ጫማ ታላቅ በሬ ሆነ ከአንገቱም ፍየል ወጣ
👉በዚያንም ሰዓት ለዐሥራ አንድ ሺህ አራት ሰዎች በሬውንና ፍየሉን አርደው ምሳ እንዲያደርጉላቸው መኰንኑ አዘዘ እንዲህም አለ ይህ በቅቷቸው ከጠገቡ ከዚህም ሌላ ምግብ ካልፈለጉ የተሠራው ሁሉ ዕውነተኛ ነዋሪ ነው ከዚህም በኋላ አርደው ምሳ አደረጉላቸውና ከፍየሉ ሥጋ ስድስት እንቅብ ከበሬው ሥጋ አራት እንቅብ አተረፉ መኰንኑም የተረፈውን ሥጋ አይቶ ወደ ባሕር እንዲጥሉት አዘዘ
👉መኰንኑም ቢያፍር የሕፃኑን ምላስ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ ጌታችንም ምላሱን መለሰለት ዳግመኛም በታላቅ ጋን ውኃ እፍልተው ሕፃን ቂርቆስንና እናቱን ኢየሉጣን ይጨምሩአቸው ዘንድ አዘዘ እናቱም አይታ ፈራች
👉ልጅዋም ወደ እግዚአብሔር በጸለየላት ጊዜ አምላካዊ ኃይልን አሳደረባትና ከልጅዋ ጋር ወደ ጋኑ ገባች እንደ ውርጭም ቀዝቃዛ ሆነ ደግሞም በውስጡ መንኰራኲር ወዳለበት የብረት ምጣድ እንዲጨምሩአቸውና ሥጋቸው እሰከሚቦጫጨቅ እንዲስቡአቸው አዘዘ የእግዚአብሔርም መልአክ በሕይወት አወጣቸው
👉መኰንኑም እነርሱን ማሸነፍ በተሳነው ጊዜ ቸብቸቧቸውን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ በዚያን ጊዜ ለስም አጠራሩ ስግደት የሚገባው የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወረደ ሕፃን ቂርቆስንም የምትሻውን ለምነኝ አለው
👉ሕፃኑም ሥጋዬ በምድር አይቀበር ስሜን ለሚጠራ መታሰቢያዬን ለሚያደርግ ቤተ ክርስቲያኔን ለሚሠራ የተጋድሎዬን መጽሐፍ ለሚጽፍና ለሚያጽፍ ወይም ለሚያነበው ለቤተ ክርስቲያኔ መባ ለሚያገባ በውስጧም ለሚጸልይ ለሁሉም ፍላጎታቸውን ስጣቸው ኃጢአታቸውንም ይቅር በል ስሜም በሚጠራበት በዚያች ቦታ የከብት ዕልቂት አይምጣ በሰውም ላይ እባር ቸነፈር በእህልም ላይ ድርቅ የውኃም ማነስ አይሁን
👉መድኃኒታችንም የለመንከኝን ሁሉ እሰጥሃለሁ አንተም በቀኜ ትኖራለህ ሥጋህንም ኤልያስ በዐረገበት ሠረገላ ውስጥ አኖራለሁ አለው ሕፃን ቂርቆስም በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ ብሎት ጌታችንን አመሰገነው ከዚህም በኋላ በሌሊቱ እኩሌታም ከእናቱ ጋር አንገቱን ተቆረጠ መድኃኒታችንም በማይጠፋ አክሊል ጋረደው ነፍሶቻቸውንም በታላቅ ክብር ከእርሱ ጋር አሳረገ
👉የሰማእቱ ቅዱስ ቂርቆስ የእናቱ የቅድስት_ኢየሉጣ ምልጃና ፀሎት የከበረዉ ቃል ኪዳናቸው ለሁላችንም ይድረሰን የተባረከ የተቀደሰ ጠላት የሚያፍርበት በምህረት የምንጎበኝበት በአል ይሁንልን "አሜን"✝️ 💒 ✝️
የአለም ግብርና ፋውንዴሽን ያዘጋጀውን የ10 ቀን ስልጠና በመውሰድ እስከ 9,000$ ዶላር (700,000 ብር) የስራ መጀመሪያ ያለማስያዢያ ይውሰዱ በኦንላይን በድረ ገፅ ወይም መተግበሪያቸው ቶሎ ተመዝገቡ ማሳሰቢያ ይህ እድል ለ""""የመስሪያ ቦታ ላላቸው ቡቻ"""!!! ወይም በስራ ላያ ላሉ ነው መስሪያ ቦታ የሌለውን አይቀበሉም የሁለት አመት የኪራይ ውል ተከራይቶ ካመጣ ብቻ ምንም ክፍያ የለውም ነፃ ነው👍sign up for world farming foundation download here
Get up to $10,000 (700,000 Birr) by taking the 10-day training organized by the World Agriculture Foundation. Register quickly online on their website or app. They do not accept those who do not have a place to work, but only if they bring a two-year lease its free off fee
/channel/zikirekdusn
††† እንኳን ለጻድቃን ቅዱሳን አቡነ አረጋዊ እና አባ አርከሌድስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ †††
††† ጻድቁ ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮዽያ ቢሆንም ሃገረ ሙላዳቸው የጥንቱ የሮም ግዛት የሆነችው ታናሽ እስያ ናት:: አቡነ አረጋዊ ከዘጠኙ (ተስዓቱ) ቅዱሳን አንዱ ናቸው:: ዘጠኙ ቅዱሳን ተወልደው ያደጉት ምንም በአንድ የሮም ግዛት ሥር ቢሆንም መነሻ ቦታቸው ግን የተለያየ ነው::
ሁሉንም አንድ ያደረጋቸው መንፈስ ቅዱስ በኪነ ጥበቡ ነው:: በምክንያት ደረጃ እንግለጸው ከተባለ ደግሞ የአንድነታቸው ምሥጢር:-
1.የቀናች ሃይማኖታቸው ተዋሕዶ:
2.ዓላማ (የእግዚአብሔር መንግስት) እና
3.ገዳማዊ ሕይወት ነው::
አቡነ አረጋዊን ጨምሮ ሁሉም ቅዱሳን ዘራቸው ከቤተ መንግስት ነው:: እነርሱ ግን ምድራዊውን ክብር ንቀው ሰማያዊውን ክብር ገንዘብ ማድረግን መርጠዋል:: አስቀድመው ቅዱሳት መጻሕፍትን ያጠኑት አበው በተለያየ ጊዜ እየመነኑ ከሮም ግዛት ወደ ግብጽ በርሃዎች ወርደዋል::
በምናኔ ቅድሚያውን አባ ዸንጠሌዎንና አቡነ አረጋዊ ይይዛሉ:: ዘመኑ የተዋሕዶ አማኞች የሚሰደዱበት 5ኛው መቶ ክ/ዘመን ነበርና እምነትን ላለመለወጥ ዘጠኙ ቅዱሳን ስደትን መረጡ::
በወቅቱ ደግሞ ለስደት መጠለያ የምትሆንና ከኢትዮዽያ የተሻለች ሃገር አልነበረችም:: ስለዚህም በ470ዎቹ ዓ/ም አልዓሜዳ በኢትዮዽያ ነግሦ ሳለ ቅዱሳኑ በአረጋዊ መሪነት መጡ::
ንጉሡም ሲጀመር የእግዚአብሔር እንግዳ ስለሆኑ: ሲቀጥል ደግሞ ቅድስናቸውን ተመልክቶ መልካም አቀባበልን አደረገላቸው:: ማረፊያ ትሆናቸውም ዘንድ አክሱም ውስጥ አንዲት ቦታን ወስኖ ሰጣቸው:: ይህች ቦታ ቤተ ቀጢን ትባላለች:: አቡነ አረጋዊና 8ቱ ቅዱሳን ወደ ሃገራችን እንደገቡ የመጀመሪያ ሥራቸው ቋንቋን መማር ነበር::
ልሳነ ግዕዝን በወጉ ተምረው እዛው አክሱም አካባቢ ሥራቸውን አንድ አሉ:: በወቅቱ በአቡነ ሰላማ: በአብርሃ ወአጽብሐና በአቡነ ሙሴ ቀዳማዊ የተቀጣጠለው ክርስትና በተወሰነ መንገድ ተቀዛቅዞ ነበርና እነ አቡነ አረጋዊ እንደገና አቀጣጠሉት::
ሕዝቡን በራሱ ልሳን ለክርስትና ይነቃቃ ዘንድ ሰበኩት:: የካደውን እየመለሱ: የቀዘቀዘውን እያሟሟቁ ለዓመታት ወንጌልን ሰበኩ:: ቀጣዩ ሥራቸው ደግሞ መጻሕፍትን መተርጐም ሆነ::
ከሃገራቸው ያመጧቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት ተከፋፍለው ወደ ግዕዝ ልሳን ተረጐሟቸው:: በዚህም ለሃገራችን ትልቁን ውለታ ዋሉ:: ይህ ሁሉ ሲሆን እነ አቡነ አረጋዊ የሚመገቡትም ሆነ የሚጸልዩት በማሕበር ነበር:: በመካከላቸውም ፍጹም ፍቅር ነበር:: ጸጋ እግዚአብሔር አልተለያቸውም::
የነ አቡነ አረጋዊ ቀጣዩ ተግባራቸው ደግሞ ገዳማዊ ሕይወትን ማስፋፋት ሆነ:: ይህንን ለማድረግ ግን የግድ መለያየት አስፈለጋቸው:: እያንዳንዱም መንፈስ ቅዱስ ወደ መራው ቦታ ሔደ::
*ዸንጠሌዎን በጾማዕት:
*ገሪማ በመደራ:
*ሊቃኖስ በቆናጽል:
*አባ ይምዓታ በገርዓልታ:
*ጽሕማ በጸድያ:
*ሌሎችም በሌላ ቦታ ገዳማትን መሠረቱ::
*አባ አረጋዊ ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ምርጫቸው ዳሞ (እዛው ትግራይ) ሆነ::
በሃገራችን ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ እኒህ ጻድቅ ናቸው:: ጻድቁ የተወለዱት በ5ኛው መቶ ክ/ዘ አጋማሽ አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ንጉሥ ይስሐቅና ቅድስት እድና ይባላሉ:: የተለወለዱበት አካባቢም ሮም ነው::
ስማቸው ብዙ ዓይነት ነው:: ወላጆቻቸው "ዘሚካኤል" ሲሏቸው በበርሃ "ገብረ አምላክ" ተብለዋል:: በኢትዮዽያ ደግሞ "አረጋዊ" ይባላሉ:: አቡነ አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ::
በዚያም በገዳመ ዳውናስ (ግብጽ) የታላቁ ቅዱስ ዻኩሚስ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል:: ከመነኮሱ ከዓመታት በሁዋላም ወደ ሃገራቸው ሮም ተመልሰው በማስተማር 7 ያህል የቤተ መንግስት ሰዎችን ወደ ምናኔ ማርከዋል::
"የት ልሒድ" ብለው ሲያስቡም ቅዱስ መልአክ በክንፉ ጭኖ ወስዶ ኢትዮዽያን አሳያቸው:: ተመልሰውም ለ8 ባልንጀሮቻቸው "ሃገርስ ባሳየሁዋችሁ! ሐዋርያ ሳያስተምራት በሕጉ በሥርዓቱ ጸንታ የምትኖር" ብለው ከ8ቱ ጋር ወደ ኢትዮዽያ መጡ::
በዚህ ጊዜም እናታቸው ቅድስት እድናና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ:: ወደ ሃገራችን የመጡ በ470ዎቹ አካባቢ ሲሆን አልዓሜዳ በክብር ተቀብሏቸዋል:: በቤተ ቀጢን (አክሱም) ተቀምጠውም መጻሕፍትን እየተረጐሙ: ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል::
ለሥራ በተለያዩ ጊዜም አቡነ አረጋዊ በዓት ፍለጋ ብዙ ደክመዋል:: በመጨረሻ ግን ደብረ ዳሞን (ደብረ ሃሌ ሉያን) አይተው ወደዷት:: የሚወጡበት ቢያጡም ጅራቱ 60 ክንድ የሚያህል ዘንዶ ተሸክሞ ከላይ አድርሷቸዋል::
እንደ ወጡም "ሃሌ ሉያ ለአብ: ሃሌ ሉያ ለወልድ: ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ" ብለው ቢያመሰግኑ ከሰማይ ሕብስት ወርዶላቸው ተመግበዋል:: በዚህም ቦታዋ "ደብረ ሃሌ ሉያ" ተብላለች:: ጻድቁ ቦታውን ከገደሙ በሁዋላ ከተለያየ ቦታ መጥተው 6ሺ ያህል ሰዎች በእጃቸው መንኩሰዋል::
ምናኔን በማስፋፋታቸውና ሥርዓቱን በማስተማራቸውም "አቡሆሙ ለመነኮሳት ዘኢትዮዽያ - የኢትዮዽያ መነኮሳት አባት" ይባላሉ:: አቡነ አረጋዊ በሕይወታቸው ከተጋድሎ ባሻገር በወንጌል አገልግሎትና መጻሕፍትን በማዘጋጀትም ደክመዋል::
ቅዱስ ያሬድና አፄ ገብረ መስቀልም ወዳጆቻቸው ነበሩ:: በተራራው ግርጌ ያለችውን ኪዳነ ምሕረትን ለሴቶች ሲገድሟት ቀዳሚዋ መነኮስ እናታቸው ንግስት እድና ሁናለች::
ጻድቁ ንጹሕ ሕይወታቸውን ፈጽመው በተወለዱ በ99 ዓመታቸው በገዳሙ በስተ ምሥራቅ አካባቢ ተሰውረው ብሔረ ሕያዋን ገብተዋል:: ጌታም 15 ትውልድን የሚያስምር የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል:: ዛሬ ጻድቁ የተወለዱበት ቀን ነው::
††† አባ አርከሌድስ †††
††† በዚህ ስም የሚጠሩ ቅዱሳን በግብጽም በሃገራችንም አሉ:: ዋናውና በብዙ መጻሕፍት ዜናቸው የተጻፈላቸው ግን ዛሬ የምናከብራቸው ናቸው:: አባ አርከሌድስ የነበሩት በዘመነ ጻድቃን ሲሆን ሃገረ ሙላዳቸው ሮም ናት::
ወላጆቻቸው ክርስቲያን: በዚያውም ላይ ባለ ጠጐች ነበሩ:: አባታቸው ደግሞ መስፍነ ሃገር ነበር:: ቅዱሱን ወልደው: በሕግ በሥርዓት አሳድገዋል:: ለአካለ መጠን አባ አርከሌድስ ሲደርሱ ግን አባታቸው ሞተ::
መዋዕለ ሐዘናቸው ከተፈጸመ በሁዋላም እናት አባ አርከሌድስን ጠርታ:- "ልጄ! ሒድና የአባትህን ሹመት እጅ አድርግ" አለችው:: ለመንገድ የሚያስፈልገውን ሁሉ አሰናድታ: አገልጋዮችንና ብዙ ወርቅ (ለሿሚው አካል የሚሰጥ) ጨምራም ልጇን ሸኘች::
ቅዱስ አርከሌድስም ከእናታቸው ተለይተው በአገልጋዮች ተከበው ወደ መርከብ ገቡ:: በባሕር መካከል ሳሉ ግን ታላቅ ማዕበል ተነስቶ መርከቡን በታተነው:: በመርከቡ የነበረው ሰው ሁሉ ሲያልቅ አባ አርከሌድስ ግን በስባሪ ላይ ተንጠልጥለው ተረፉ::
🌷ጥር 13/2016 #አቡነ_ዘርዐ_ቡሩክ_ኢትዮዽያዊ
🎋♻️በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ አባታችን #አቡነ_ዘርዓ_ቡሩክ ኢትዮዽያዊ አመታዊ የእረፍታቸው መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን ፃድቁ አባታችን ከመወለዳቸው አስቀድሞ ትንቢት የተነገረላቸው አባት ናቸዉ
🎋♻️አባታቸው #ደመ_ክርስቶስ ዐይነ ሥውር የነበሩ ሲሆን አቡነ #ዘርዐ_ቡሩክ በተወለዱ ጊዜ የአባታቸውን ዐይን አብርተውለታል አባታችን ዘርዐ ቡሩክ ገና በሰባት ዓመታቸው ነው ረቡዕና ዓርብ መጾም የጀመሩት በዚሁ በሰባት ዓመታቸውም ይህን ዓለም ክፋቱን እንዳላይ ዐይኖቼን አሳውርልኝ በማለት ዐይናቸውን እንዲያጠፋላቸው አምላካቸውን ለምነው እንደፈቃዳቸው ዐይነ ሥውር ሆነዋል
🎋♻️ነገር ግን ከሰባት ዓመት በኋላ በ12 ዓመታቸው ጌታችን "ለዓለም የምታበራ ብርሃን አደርግሃለሁና ዐይንህም ይብራ" በማለት #ዐይነ_ብርሃናቸውን መልሶላቸው እንዲያዩ አድርጓቸዋል በዚህም ዕድሜያቸው (በ12 ዓመታቸው) ሰባቱንም አጽዋማት ይጾሙ ነበር
🎋♻️ከዚህም በኋላ #ጌታችን የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢር ሁሉ ገለጠላቸዉ መጻሕፍተ ብሉያትን መጻሕፍተ ሐዲሳትን መጻሕፍተ ሊቃውንትን መጻሕፍተ መነኮሳትን አዋልድ መጻሕፍትን ሁሉ ገልጦላቸዋል
🎋♻️ከሟርት መጻሕፍት በቀር ያስቀረባቸው ነገር አልነበረም የቅዱስ #ያሬድንም ዜማ እንዲሁ ገለጠላቸው
🎋♻️ጻድቁ ከሁሉ ቅዱሳን በበለጠ ሁኔታ ዐሥራ ሁለት ክንፍ የተሰጣቸው ሲሆን በ12 ክንፎቻቸውም የሰማይን ደጆች ሁሉ ገሃነመ እሳትንም አልፈው በመሄድ ቀጥታ #በሥሉስ_ቅዱስ ዙፋን ፊት ይቆሙ እንደነበር ቅዱስ ገድላቸው ይናገራል እጅግ በሚደንቅና ከአእምሮ በላይ በሆነ ሁኔታ አባታችን ለሰባት ቀናት በየቀኑ ለሰባት ሰዓት ያህል በሲኦል ውስጥ ቆመው ይጸልዩ ነበር
🎋♻️ብዙዎቹ ቅዱሳን በምልጃቸው ነፍሳትን ከሲኦል ሲያወጡ ነው የምናውቀው እንጂ እንደ አቡነ #ዘርዐ_ቡሩክ በሲኦል ውስጥ ገብቶ ጸሎት የጸለየ ጻድቅ እስካሁን የለም
🎋♻️አቡነ ዘርዐ ቡሩክ እንደ አባታችን #ተክለሃይማኖት ለጸሎት በመቆም ብዛት አንድ እግራቸው እስኪሰበር ድረስ በብዙ መከራ ተጋድለዋል #ከሃያ_አራቱ_ካህናተ_ሰማይ ጋር መንበሩን ያጥኑ ዘንድ ከፈጣሪአቸው ታዘው አጥነዋል
🎋♻️ጌታችን #ለአቡነ_ዘርዐ_ቡሩክ ፍጥረታትን ከመፍጠር በቀር ያልሰጣቸው ሥልጣን የለም #እግዚአብሔር ብፁዕና ቅዱስ ለሚሆን አባታችን #ዘርዐ_ቡሩክ
🎋♻️እኔ ከሥልጣኔ ሥልጣንን፣ከክብሬም ክብርን ፣ከጥበቤም ጥበብን፣ከተአምራቴም ተአምራትን ፣ከስጦታዬም ስጦታን፣ ከትዕግስቴም ትዕግስትን፣ ከፍቅሬም ፍቅርን፣ ከትሕትናዬም ትሕትናን፣ ከባለሟልነቴም ባለሟልነትን ሰጥቼሃለሁና ሁሉ ከሥልጣንህ በታች ሆኖ ይታዘዝልህ" የሚል እጅግ ድንቅ #ቃልኪዳን ነው የሰጣቸው
🎋♻️ልዩ ልዩ ሀብታትን ሁሉ ሰጣቸው #ለሥላሴ ከሚገባ ከስግደትና በቃልና በሥልጣን ፍጥረታትን ለመፍጠር በቀር ምንም ያልሰጠሁህ የለም ብሎ ጌታችን በማይታበል ቃሉ እንደነገራቸውና ቃል እንደገባላቸው በቅዱስ ገድላቸው ላይ ተጽፏል
🎋♻️የአባታችን ገድላቸው ከመጥፋቱ የተነሣ በአሁኑ ሰዓት አንዳንድ ነጋዴዎች አንዱን ፍሬ ከ3 ሺህ ብር በላይ እየሸጡት ነበር ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ቲሊሊ የሚገኘው ገዳማቸው በድጋሚ አሳትሞታል
🎋♻️የአባታችን #የአቡነ_ዘርዐ_ብሩክ የህይወት ታሪክ ከብዙ በጥቂቱ ይህን ይመስላል የአባታችን ምልጃና ፀሎት ረድኤት በረከት ለሁላችንም ይድረሰን "አሜን" አሜን አሜን👏
✞እንኳን ለጻድቃን ቅዱሳን አቡነ ዘርዓ ቡሩክ እና 7ቱ ደቂቅ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችኹ✝
✝ አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ✝
=>ሃገራችን ኢትዮዽያ:-
*ብሉይ ከሐዲስ ያልጐደለባት
*በክርስቶስና በድንግል እናቱ ኪደተ እግር የተቀደሰች
*የቅዱሳን መጠጊያ እና
*ብዙ ቅዱሳንን ከእቅፏ ያፈራች ስለ ሆነች የተባረከች ሃገር ትባላለች::
+ሁሉም የሃገራችን ክፍሎች ቅዱሳንን አፍርተዋል:: በምሥራቅም: በምዕራብም: በሰሜንም: በደቡብም ያሉ አካባቢዎች ሁሉ የቅዱሳን ቤቶች ናቸው:: ቅዱሳንን በብዛት ካፈሩ አካባቢዎች አንዱ ደግሞ ምድረ ጐጃም ነው::
+በጐጃም አካባቢ ከተነሱ ቅዱሳን ደግሞ አንዱና ስመ ጥሩ ጻድቅ አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ናቸው:: አቡነ ዘርዓ ቡሩክ በብዙ ጐዳና የተለዩ አባት ናቸው:: ለመጥቀስ ያህል እንኩዋ:-
1.በታሪክ ዓለምን ከበው የያዙ 2ቱ ግሩማን አራዊት (ብሔሞትና ሌዋታንን) ጥርስ ቆጥረው: ብዙ ምሥጢራትንም ተመልክተው ተመልሰዋል:: (በነገራችሁ ላይ ይህ ጉዳይ ዛሬም ድረስ ሳይንሱ በብዙ ድካም ያልደረሰበት ነው)
2.ጻድቁ በልደታቸው ጊዜ ዓይነ ስውራንን አብርተዋል:: ለራሳቸው ግን ይህን የግፍ ዓለም ላለማየት ጸልየው ዓይናቸው እንዲጠፋ አድርገዋል::
3.መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል ቅዱስ ኢያሱ በገባኦን ፀሐይን አቁሟል:: ዘርዓ ቡሩክ ግን በጥበበ እግዚአብሔር ፀሐይን ለ5 ዓመት አቁመዋል::
4.ጻድቁ ከንጽሕናቸው ብዛት 12 ክንፍ (መንፈሳዊ ክንፍ) ተሰጥቷቸው ነበር:: ከዚህ በተረፈም በጾም: በጸሎት: በትርምትና በስብከተ ወንጌል ፍጹም ጽሙድ ነበሩ::
+ጻድቁ የተወለዱት በ16ኛው መቶ ክ/ዘመን እዚያው ጐጃም ውስጥ ሲሆን አባታቸው ደመ ክርስቶስ: እናታቸው ደግሞ ማርያም ሞገሳ ይባላሉ:: ወላጆች በልጅ እጦት ተማለው ይህን የተቀደሰ ፍሬ አገኙ:: "ጸጋ ኢየሱስ" ብለውታል:: ከኢየሱስ ክርስቶስ ተሰጥቷቸዋልና::
+ቀጥሎ የወለዱትንም "ተስፋ ኢየሱስ" ብለውታል:: ይህም የጻድቁ ታናሽ ወንድም ነው:: በሒደት ግን የጸጋ ኢየሱስ ስም በፈቃደ እግዚአብሔር ወደ ዘርዓ ቡሩክነት ተቀይሯል:: ጻድቁን ስመ ጥር ካደረጉዋቸው ሥራዎቻቸው መካከል በአፄ ሱስንዮስ ዘመን የሠሩት ቅድሚያውን ይወስዳል::
+ነገሩ እንዲህ ነው:: በ1598 ዓ/ም በኢትዮዽያ ላይ የነገሡት አፄ ሱስንዮስ ዼጥሮስ ፓኤዝ (ፔድሮ ፓኤዝ) ከሚባል ፈረንጅ መ+ና+ፍ+ቅ ጋር በፈጠሩት ወዳጅነት ሃይማኖታቸውን ለወጡ:: ካቶሊክ (ሮማዊ)ም ሆኑ::
+በሁዋላም አልፎንሱ ሜንዴዝ የሚሉት እሾህ መጥቶ ሁሉም የኢትዮዽያ ሕዝብ መ+ና+ፍ+ቅ እንዲሆን ከንጉሡ ጋር መከረ:: ለጊዜው በቤተ መንግስቱ አካባቢ የነበሩ መሣፍንት ተቀላቀሉ:: እየቆየ ግን ዜናው በመላ ሃገሪቱ ተሰማ::
+በተለይ በ1611 በተዋሕዶ አማኞችና በመ+ና+ፍ+ቁ ንጉሥ መካከል ነገሩ ተካሮ ዻዻሱ አቡነ ስምዖን ጠዳ ላይ መገደላቸው ተሰማ:: በዚህ ጊዜ ገበሬው ከእርሻው: ሴቷ ከማዕድ ቤት: ካህኑ ከመቅደሱ: ነጋዴው ከገበያው እየወጡ ስለ ቀናችው ሃይማኖት ደማቸውን አፈሰሱ::
+በበዓት የተወሰኑ በሺህ የሚቆጠሩ ቅዱሳንም ወጥተው ተሰየፉ:: በዚህ ጊዜም የግሺው አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ዳዊታቸውን አንግበው ለሰማዕትነት ሔዱ:: ዓባይ ወንዝ ላይ ሲደርሱ ዳዊታቸውን ወደ ወንዙ ውስጥ ጣሉት::
+ተሻግረውም ከንጉሡ አደባባይ ደንቀዝ ደረሱ:: በጊዜውም ልክ እንደነ ፍቅርተ ክርስቶስና ወለተ ዼጥሮስ እርሳቸውም መከራ ደረሰባቸው:: ንጉሡም ሳይገደሉ እንዲታሠሩ አደረገ:: በጨለማ እስር ቤትም 5 ዓመታትን ሲያሳልፉ ትኩስ ምግብን ያመጡላቸው ነበር::
+እርሳቸው ግን ምግባቸው ሰማያዊ ነበርና አልነኩትም:: ከ5 ዓመት በሁዋላም ያ ሁሉ ምግብ በተአምራት በትኩስነቱ እየጨሰ ተገኝቷል:: ዘርዓ ቡሩክም ከእሥር ተፈትተዋል::
+እግዚአብሔርም በከሐዲው ንጉሥ ላይ ፈርዶ ፋሲል ነግሷል: ሃይማኖት ተመልሷል:: ጻድቁም በዓባይ ወንዝ ላይ የጣሉት ዳዊታቸውን ሳይርስ አግኝተውታል::
+ጐጃም ሲደርሱም ሰይጣን እርሳቸውን መስሎ ሲያስት ስላገኙት ወደ ጥልቁ አስጥመውታል:: በተረፈ ዘመናቸው አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ብዙ ተጋድለው ጥር 13 ቀን ዐርፈዋል:: ታኅሳስ 13 ቀን ልደታቸው ነው::
<< ድንቅ ሠሪ አባት ናቸውና ዛሬም በግሺ ብዙ ተአምራት ይደረጋሉ >>
+" ቅዱሳን 7ቱ ደቂቅ "+
=>እነዚህ 7 ቅዱሳን ከዘመነ ሰማዕታት እስከ ዘመነ ጻድቃን የተዘረጋ ታሪክ አላቸው:: 7ቱም ባልንጀሮች ሲሆኑ በ2ኛው መቶ ክ/ዘመን በኤፌሶን ተወልደው አድገዋል:: ክርስትናን ተምረውም በወጣትነታቸው የንጉሥ ጭፍሮች ሁነዋል:: የተቀጠሩትም የቤተ መንግስቱን ግምጃ ቤት ለመጠበቅ ነው::
+በሥራቸውም ሆነ በጠባያቸው ደጐች ነበሩና ንጉሡ ዳኬዎስም: ሕዝቡም ይወዷቸው ነበር:: እነርሱ ግን በጉብዝና ወራት ፈጣሪን ማሰብን መርጠው በፍቅር: በጸሎትና በምጽዋት ይተጉ ነበር:: ከጥቂት ዓመታት በሁዋላ ግን ጭንቅ መከራ መጣ::
+ንጉሡ ዳኬዎስ ክርስትናውን ትቶ ጣዖት አምላኪ ሆነ:: አዋጅም አስነገረ:: አዋጁም "ክርስቶስን ያልካደ: ለጣዖትም ያልሰገደ: ሃብት ንብረቱ ለዘረፋ: እጅ እግሩ ለእስር: ደረቱ ለጦር: አንገቱ ለሰይፍ: ቤቱም ለእሳት ይሰጣል" የሚል ነበር:: በዚህ ምክንያት ብዙ ክርስቲያኖች ተሰደዱ::
+የበርካቶቹም ደማቸው ፈሰሰ:: ኤፌሶን የግፍና የአመጻ ከተማ ሆነች:: የመከራ ጽዋው ጊዜውን ጠብቆ ወደ 7ቱ ወጣቶች ዘንድ ደረሰ:: ንጉሡ እነሱንም አስጠርቶ "ለጣዖት ስገዱ" አላቸው:: እነርሱ ግን የአምላካቸውን ፍቅር በዋዛ የሚቀይሩ አልነበሩምና "እንቢ" አሉት::
+ንጉሡ ምንም ክፉና አውሬ ቢሆንም ይወዳቸዋል:: ሊገድላቸው አልፈለገምና አሳሰራቸው:: ከቀናት በሁዋላ አስጠርቶ ሊያታልላቸው ሞከረ:: ግን አልተሳካለትም:: በዚያ ወራት ጦርነት ይበዛ ነበርና ግዛት ለማስፋትም ቢሉ ለማስገበር ዳኬዎስ ወጣ::
+ከመውጣቱ በፊት ግን 7ቱን አስጠርቶ "አሁን ከእስር ፈትቻቹሃለሁ:: ከጦርነት እስክመለስ ከልባችሁ ጋር ምከሩ:: ካልሆነ ሞት ይጠብቃቹሃል" ብሏቸው ነበር የወጣው:: ቅዱሳኑ ንጉሡ እንደ ወጣ ተቀምጠው መከሩ:: ውሳኔንም አስተላለፉ::
+ዓለምን ንቀው: ሃብት ንብረታቸውን መጽውተው: ትንሽ ሳንቲም ብቻም ይዘው በድብቅ ወጡ:: አንድ ወታደር (በጐች አሉት) ይከተላቸው ነበርና የት እንደ ገቡ ተመለከተ:: ቅዱሳኑ ዘወትር በመዓልትና በሌሊት በበዓታቸው ውስጥ ይተጉ ነበር:: ከእነሱም አንዱ በተራ እየወጣ ቂጣ ይገዛ ነበር::
+አንድ ቀን ግን ከእነሱ አንዱ ራት ሊገዛ ሲወጣ ንጉሡ መመለሱን ሰማ:: ወደ በዓቱ ተመልሶ ለወንድሞቹ ነገራቸው:: ከዚያች ቀን በሁዋላ 7ቱም አልወጡም:: በዓታቸውን ዘግተው ሲጸልዩ ደክሟቸው ተኙ:: ከዚያች ቀን በሁዋላ ግን አልነቁም::
+ያ የበጐች ባለቤት (ወታደር) ለብዙ ቀናት አለመውጣታቸውን ሲመለከት "ሙተዋል" ብሎ አዘነ:: በድብቅ ክርስቶስን ያመልከው ነበርና:: እርሱ የቅዱሳኑን ተጋድሎ በድንጋይ ሰሌዳ ላይ ጽፎ ወደ በዓታቸው ውስጥ ጣለው::