2.ቅዱሱ መልአክ እመ ብርሃንን በስደቷ ጊዜ ወደ
ኢትዮዽያ መርቶ አምጥቷታል:: በክንፉ ተሸክሞ: በ4
አቅጣጫ አዙሮ
አሳይቶ አሥራት እንድትቀበል አድርጉዋል::
3.ጌታችን በተሰቀለ ጊዜ ደሙን በጽዋዕ አድርጐ
በኢትዮዽያ ወንዞች ላይ አፍስሷል::
4.ለብዙ ቅዱሳን (አባ ጊዮርጊስን ጨምሮ) ጽዋዐ ልቡናን
አጠጥቷል::
✞አምላከ ቅዱሳን ስለ ወዳጆቹ በጐ ምኞታችንን
ይፈጽምልን:: ከበረከታቸውም ያድለን::
✞ጥር 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አባ እንጦንስ (የመነኮሳት አባት-የበርሐው
ኮከብ /ልደቱና ዕረፍቱ)
2.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላዕክት (ለተጠሙ ጽዋዓ
ልቡናን የሚያጠጣ: ምሥጢር ገላጭ መልዐክ)
3.ቅዱስ ሚናስ ኤዺስ ቆዾስ
✝ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
3.ቅዱስ ደቅስዮስ (የእመቤታችን ወዳጅ)
4.አባ እንጦንስ አበ መነኮሳት
5.አባ ዻውሊ የዋህ
++"+ እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ::
መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ:: ነፍሱን ሊያድን የሚወድ
ሁሉ
ያጠፋታል:: ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ
ያገኛታል:: +"+ (ማቴ. 16:24)
✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር
☞ አስተርዮ _ ቃሉ የግእዝ ቃል ሲሆን
ትርጉሙም ፦ መታየት ወይም መገለጥ ማለት ነው ፡፡
👉 ጥር 21 ቀን ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይቶ በደመና ተነጥቃ ወደ ገነት በመግባት በሰማይና በምድር የተሰጣትን ፀጋና ክብር የገለጸችበት ዕለት ስለሆነ በዓሉም አስተርዮ ማሪያም ይባላል ።
# ጥር ፳፩
በዚህ ቀን ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም በስድሳ አራት ዓመቷ ከሞት ወደ ሕይወት ከመከራ ወደ ደስታ የተሸጋገረችበት ዕለት ነው።
"ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል" (ቅዱስ ያሬድ) የአዛኚቱ ድንግል አማላጅነት አይለየን።
👉እርሱም ሰገደላትና ተሳለማት ከእርሷም ተባረከ ከዚህም በኋላ ወደ ሀዋርያት ደረሰ እነርሱም እመቤታችንን ማርያምን እንደ አረፈችና እንደ ቀበርዋትም ነገሩት #ቶማስም_ስጋዋን እስከማይ አላምንም አላቸው
👉ስጋዋንም ያሳዪት ዘንድ ወደ መቃብርዋ በአደረሱት ጊዜ በመቃብር ውስጥ ስጋዋን አላገኙም ደንግጠውም አደነቁ ያን ጊዜ ከመላእክት ጋር ወደ ሰማይ ስታርግ እመቤታችንን እንዳገኛት ቶማስ ነገራቸው ሀዋርያትም ይህን በሰሙ ጊዜ የእመቤታችንን እርገቷን ስለ አላዩ እጅግ አዘኑ
👉ስጋዋን በምድር ውስጥ ይተው ዘንድ እንዳልወደደ መንፈስ ቅዱስ አስገነዘባቸው ከዚህም በኋላ አንድ ጊዜ ደግሞ እርሷን ያሳያቸው ዘንድ እንዳለው ጌታችን ቃል ኪዳን በማድረግ ተስፋ ሰጣቸው እነርሱም እስከ ነሀሴ አስራ ስድስት በተስፋ ኖሩ
👉የእመቤታችንም የእድሜዋ ዘመን #ስልሳ_አራት አመት ነው በአባትና እናቷ ቤት ሶስት አመት ከሰባት ወር በቤተ መቅደስም አስራ ሁለት አመት በዮሴፍም ቤት ሰላሳ አራት አመት ከሶስት ወር ከጌታ እርገት በኃላ በወንጌላዊ ዮሀንስ ቤት አስራ አራት አመት ኖራለች
👉አምላካችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ስለ እናታችን #ማርያም ብለህ አቤቱ የሆነብንን አስብ ተመልከት ከሚደርስብን መከራና ግፍ የተነሣ የልባችን ደስታ ተሰርቋል መደሰታችን ወደ ለቅሶ ተቀይሯል አምላካችን ዘመናችንን ኃጢያታችንን ሣታይ እንደ ቀድሞ አድስ "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
አስተርዮ ማርያም
በዘመነ አስተርዮ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ የሆነበትና የአምላካችን አንድነትና ሦስትነት የተገለጠበት ብቻም ሳይሆን በጥር ፳፩ የከበረች እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም የዕረፍት ቀን በመሆኑ “አስተርዮ ማርያም” በማለት በዓልን አናደርጋለን፡፡
የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር ላይ ፷፬ ዓመታትን ከኖረች በኋላ መንፈስ ቅዱስ ባስገነዘባት መሠረት በክብር ዐርፋለች፡፡ የዚህን ዓለም መከራና ሥቃይ ለሰዎች ድኅነት የተቀበለችው ክብርት እናታችን በሥጋ ብትሞትም እንደ ልጇ ደግሞ በትንሣኤዋ ተነሥታለች፤ ይህም የሆነው በተቀደሰች ዕለት ነሐሴ ፲፮ ነው፡፡
እመ ብርሃን ከእናትና ከአባቷ ጋር ሦስት ዓመት፣ በቤተ መቅደስ ፲፪ ዓመት፣ ከተወዳጁ ልጅዋ ጋር ፴፫ ዓመት ከሦስት ወር፣ ከጌታችን ዕርገት በኋላ ከወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ጋር ፲፭ ዓመት፣ በድምሩ ፷፬ ዓመት በዚህ በኃላፊው ዓለም ኖራ ጥር ፳፩ ቀን በ፵፱ ዓመተ ምሕረት በክብር ዐርፋለች፡፡
ክርስቲያኖች በሙሉ ይህንን በዓል ልናከብር ይገባልና ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓትን ሠርታልናለች፡፡ “አስተርዮ ማርያም” በሕዝበ ክርስቲያን ዘንድ የሚከበር በዓል በመሆኑ በሀገራችን ኢትዮጵያ እና በመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ማኅበረሰብ ዘንድ በድምቀት ይከበራል፡፡ በዓሉን የምናከብረውም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከዚህ ዓለም ድካም ማረፍ በማዘከር ብቻ ሳይሆን አማላጅነቷና ተረዳኢነቷን በማሰብና ተስፋ በማድረግ ነው፡፡
ስለዚህም እመ ብዙኃን እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዐሥራት ሀገሯን ኢትዮጵያን እንድታስባት፣ ለእኛም ለሕዝቦቿ ሰላምን፣ ፍቅርንና አንድነትን ታሰጠን እንዲሁም ለነፍሳችን ድኅነትን ትለምልን ዘንድ ዕረፍቷን መዘከር ይገባል፡፡
የአምላካችን እግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ተረዳኢነት አይለየን፤ አሜን!!!
©ማህበረ ቅዱሳን
/channel/zikirekdusn
/channel/zikirekdusn/13162
✞✝✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✝✞
✝ጥር 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+✝+ አባ እንጦንስ +✝+
=>በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ "ታላቁ / ዓቢይ / THE GREAT" የሚል ስም የሚሰጣቸው አባቶች የተለዩ
ናቸው::
አንድም እጅግ ብዙ ትሩፋቶችን የሠሩ ናቸው:: በሌላ
በኩል ደግሞ በተመሳሳይ ስም ከሚጠሩ ሌሎች ቅዱሳን
እንለይበታለን::
+ገዳማዊ ሕይወት ጥንቱ ብሉይ ኪዳን ነው::
በቀዳሚነትም በደብር ቅዱስ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ደቂቀ
ሴት እንደ ጀመሩት
ይታመናል:: ሕይወቱ በጐላ: በተረዳ መንገድ የታየው ግን
በታላቁ ጻድቅ ሄኖክ: ከዚያም በቅዱሱ ካህን መልከ
ጼዴቅ
አማካኝነት ነው::
+ቀጥሎም እነ ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ: እነ ኤልሳዕ ደቀ
መዝሙሩ ኑረውበታል:: በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሙሉ
ሕይወቱን በገዳም
(በበርሃ) ያሳለፈው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
ቅድሚያውን ይይዛል::
+ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ
በገዳመ ቆረንቶስ ለ40 ቀናት በትሕርምት ኑሮ ገዳማዊ
ሕይወትን
ቀድሷል: አስተምሯል:: በዘመነ ስብከቱም ያድርባት
የነበረችው የደብረ ዘይቷ በዓቱ (ኤሌዎን ዋሻ) በራሷ
ለዚህ ሕይወት
ትልቅ ማሳያ ናት::
+ከጌታ ዕርገት በኋላም ክርስቲያኖቹ የዓለም ሁካታ
ሲሰለቻቸው: አንድም በንጹሕና በተሸከፈ ልቡና
ለፈጣሪያቸው መገዛትን
ሲሹ ከከተማ ወጣ እያሉ ይኖሩ እንደ ነበር የታሪክ
መዛግብት ያሳያሉ:: አኗኗራቸውም በቡድንም: በነጠላም
ሊሆን ይችላል::
+ዋናው ነገር ግን በጾምና በጸሎት መትጋታቸው ነው::
ይሕም ሲያያዝ እስከ 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ደረሰ:: በዚህ
ዘመን
ግን አባ ዻውሊ የሚባል አንድ ንጹሕ ክርስቲያን ይሕንን
ሕይወት ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ አደረገው::
ለ80 ዓመታት ሰው ሳያይ ተጋድሎ 'የባሕታውያን አባት'
ተባለ:: ደንብ ያለው ተባሕትዎም ጀመረ::
+ይህ ከሆነ ከ20 ዓመታት በኋላ ደግሞ አባ እንጦንስ
የሚባሉ ደግ ክርስቲያን ይህንን ገዳማዊ ሕይወት በሌላ
መንገድ
አጣፈጡት:: በቅዱስ ሚካኤል አመንኳሽነት ገዳማዊ
ሕይወት በምንኩስና ተቃኘ:: ስለዚህም አባ እንጦንስ
የመነኮሳት አባት ተባሉ::
+እርሳቸውም ሕይወቱን ለማስፋፋት ከተለያዩ አሕጉር ደቀ
መዛሙርትን እየተቀበሉ አመንኩሰዋል:: ቅዱሳን የአባ
እንጦንስ
ልጆችም ወደየ ሃገራቸው ተመልሰው: ሕይወቱን በተግባር
አሳይተው ገዳማዊነትን አስፋፍተዋል::
+"+ አባ እንጦንስ +"+
+አባ እንጦንስ የመነኮሳት ሁሉ አባታቸው: ለገዳማውያን
ሁሉም ሞገሳቸው ናቸው:: እንዲያውም ብዙ ጊዜ "ኮከበ
ገዳም:
ማኅቶተ ገድል (የበርሃው ኮከብ: የተጋድሎ መብራት)"
ተብለውም ይጠራሉ::
+ቤተ ክርስቲያን ለጀማሪዎች ትልቅ ትኩረት ትሰጣለች::
ለምሳሌ:- አባ ዻውሊን (የካቲት 2 የሚከበሩ)
ለብሕትውና
መሠረትን ስለ ጣሉ "አበ ባሕታውያን" ብላ ታከብራለች::
አባ እንጦንስን ደግሞ "አበ መነኮሳት (የመነኮሳት አባት):
ቀዳሚሆሙ ለመነኮሳት (ለመነኮሳት ቀዳሚና ጀማሪ)
ስትል ትጠራቸዋለች::
+አባ እንጦንስ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ለሚነሱ ቅዱሳን
መነኮሳት ሁሉ መንገድን ይጠርጉ ዘንድ ብዙ መከራን
በትዕግስትና
በአኮቴት ተቀብለዋል:: ላለፉት 1,700 ዓመታት እንደ
ሻማ እየቀለጡ ያበሩ አበው ቅዱሳን ሁሉ የአባ እንጦንስ
ልጆች ናቸው::
+ከምጥ የከፋ የዲያብሎስ ፈተናን ተቀብለው ከመንፈሳዊ
አብራካቸው ቅዱሳኑን ወልደዋል:: የመነኮሳት አለቃ
የሆኑትን
ታላቁን መቃርዮስን ጨምሮ በርካቶችን አመንኩሰው
ለቅድስና አብቅተዋል::
+አባ እንጦንስ ግብጻዊ ሲሆኑ የተወለዱት አቅማን
በምትባል ቦታ አካባቢ ነው:: ጊዜውም በ252 ዓ/ም
ነው:: የተባረኩ
ወላጆች ለቅዱሱ እንጦንስና አስከትለው ለወለዷት ሴት
ልጃቸው አስቀድመው ፍቅረ ክርስቶስን: አስከትለውም
ሃብት
ንብረታቸውን አውርሰው ዐርፈዋል::
+በዚህ ጊዜ የአባ እንጦንስ እድሜ አፍላ ወጣትነት ላይ
ነበር:: በልጅነት ጊዜአቸውም አባ እንጦንስን ሲስቁ:
ሲጫወቱ:
አልያም ሲቀልዱ አየሁ የሚል ሰው አልነበረም:: ፍጹም
ቁም ነገረኛና ታዛዥ: በዚያ ላይም አስተዋይ ነበሩና ሙሉ
ጊዜአቸውንም ከቅዱስ ቃሉ በመመገብ: በትምሕርትና
በማስቀደስ ያሳልፉ ነበር::
+ዘወትርም ዜና ሐዋርያትን እያነበቡ በመንፈሳዊ ቅናት
ይቃጠሉ ነበር:: በጊዜው የምናኔ ሕይወት ጐልቶ ባለ
መገለጡ አባ
እንጦንስ የሚያደርጉት ይጨንቃቸው ነበር:: ሲጸልዩም
"አበው ሐዋርያት ይሕንን ክፉ ዓለም ንቃችሁ ጌታችሁን
የተከተላችሁበት ጥበብ እንደ ምን ያለ ነው!" እያሉ
ይደነቁ ነበር:: መሻታቸውን ያወቀ ጌታም ምሥጢርን
ገለጠላቸው::
+አንድ ቀን በቅዳሴ ላይ ወንጌል ሲነበብ ካህኑ ስለ
ምናኔ የሚጠቅሰውን ክፍል አነበበ:: ለአንድ ባለ ጠጋ
ሕግጋትን
ከነገረው በኋላ "ፍጹም ልትሆን ከወደድክስ ያለህን ሁሉ
ሸጠህ ተከተለኝ" (ማር. 10:17) የሚለውን ጥቅስ
ሲሰሙ
ተገርመው "ጌታ ሆይ! ይህንን የተናገርኸው ለእኔ ነው"
ሲሉ አሰቡ:: በቀጥታም ሃብታቸውን ለአካባቢው ሰው
አካፍለው:
እህታቸውን ከደናግል ማኅበር ደምረው እርሳቸው ወደ ዱር
ሔዱ::
+ከዚህች ቀን ጀምረው አባ እንጦንስ ከ80 እስከ መቶ
ለሚገመቱ ዓመታት ከአጋንንት ጋር በጦርነት ነበር
የኖሩት::
በንጹሕ አምልኮታቸውና በቅድስናቸው የቀና ጠላት
ሰይጣን በብዙ ጐዳና ፈተናቸው:: አቅም ቢያጥረው
አራዊትን መስሎ
ታገላቸው::
+በዚህ አልሳካ ቢለው የእሳት ሰንሰለትን አምጥቶ
ገረፋቸው:: በሞትና በሕይወት መካከል ጥሏቸው ሔደ::
ወድቀው
ያገነኟቸው ሰዎች ለዘመዶቻቸው ሰጥተዋቸው አገገሙ::
ልክ ሲነቁ ግን ፈጥነው ወደ በርሃ ተመለሱ::
+ሰይጣን በርሃው የቅዱሳን ማደሪያ እንዳይሆን ሰግቷልና
ጨክኖ ታገላቸው:: ግን አልቻላቸውምና ተረታ:: አምላከ
ኃያላን
ክርስቶስ ከቅዱሱ ጋር ነበርና:: ከዚህ በኋላ ግን ጸጋው
በዝቶላቸው ድውያንን የሚፈውሱና ሰይጣን
የማይቀርባቸው ሰው
ሆኑ::
+በረዥም ዘመነ ቅድስናቸውም:-
1.ብዙ አርድእትን ከመላው ዓለም ሰብስበው:
አስተምረው: ምናኔ ከግብጽ ማዶ በመላው ዓለም
አስፋፉ::
2.በደመና እየተጫኑ ብዙ አሕጉራትንም እየዞሩ ሰበኩ::
በዚህም አሕዛብን ወደ እምነት: ኃጥአንን ወደ ንስሃ
መለሱ::
3.ጊዜው ዘመነ ሰማዕታት ነበርና ወደ አደባባይ ሒደው
ከሃዲዎችን ገሠጹ:: ማንም ደፍሮ ግን አልገደላቸውም::
+እነዚህንና ሌሎች ተግባራትን እየሠሩ በቅዱስ ሚካኤል
እጅ መነኮሱ:: እርሳቸውም ብዙዎችን አመነኮሱ::
አርጅተው እንኳ
ከተጋድሎ ያላረፉት አባታችን የጣመ ነገር ቀምሰው:
ገላቸውን ታጥበው አያውቁም:: በ372 ዓ/ም በዚህች ቀን
ሲያርፉም
ዕድሜአቸው 120 ደርሶ ነበር::
+የአባ እንጦንስን በዓል ለማክበር የምትሹ ቤተ
ክርስቲያናቸው ጎንደር ከተማ ከቀሃ ኢየሱስ በላይ
ይገኛል::
<< ለአባታችን እንጦንዮስ / እንጦንስ / እንጦኒ ክብር
ይገባል:: >>
+" ቅዱስ ዑራኤል "+
+በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት ከ7ቱ ሊቃነ
መላእክት አንዱ የሆነው ቅዱስ ዑራኤል:-
1.ድንግል ማርያም በአካለ ሥጋ እያለች ወደ ሰማይ
አሳርጉዋታል:: በሠረገላ ብርሃን ጭኖ: በክንፎቹም
ተሸክሞ: አስቅድሞ
ገነትን ቀጥሎም ሲዖልን አስጐብኝቷታል:: በዚህም
ምክንያት እመ ብርሃን ስለ ኃጥአን የምታለቅስ:
የምትለምንና የምትማልድ
ሆናለች:: ለምናም አልቀረች የምሕረት ቃል ኪዳን
ተቀብላለች::
🌿❤️ ጥር 21 በዓለ አስተርእዮ ማለት🌿❤️
《የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት እንኳን ለዚህች ታላቅ ክብረ በዓሏ አደረሳችሁ አደረሰን!!!
🌿❤️ ወላዲተ አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈንታ በመሆኑ በስድሳ አራት አመቷ ከሞት ወደ ሕይወት ከመከራ ወደ ደስታ የተሸጋገረችበት ዕለት ነው፡፡
🌿❤️ ታላቁ የቤተክርስቲያን አባት ቅዱስ ያሬድም “ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ” ትርጉሙ ሞት ለማናኛቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል፡፡ በማለት አደነቀ፡፡
🌿❤️ በመሆኑም በዓሉ የወላዲተ አምላክ በዓለ ዕረፍት ከመሆኑ የተነሳ ታላቅ በረከት የሚያስገኝ ስለሆነ በየዓመቱ ይከበራል፡፡
... 🌿❤️ የእረፍቷስ ነገር እንደምን ነው ቢሉስድሳ አራት ዓመት በዚህ ዓለም ኖራ ጥር 21 እሁድ ቀን ጌታ እልፍ አዕላፋት መላዕክቱን አስከትሎ መጥቶ እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጣሁ አላት፡፡
🌿❤️ ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህጸኔ ተሸክሜ በድንግልና ወልጄህ እሞታለሁミ አለችው፡፡
🌿❤️ በሲዖል የሚሰቃዩ ነፍሳትን አሳይቶ እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእነዚህ ቤዛ ይሆንላቸዋል አላት፡፡ እኚህን ከማርክልኝስ ይሁን አለችው፡፡ ቅድስት ሥጋዋን ከቅስስት ነፍሷ ለይቶ በቃለ አቅርንት በዝማሬ መላእክት አሳረጋት፡፡
🌿❤️ ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት በደመና ጠቅሶ ካለችበት አድርሶ እመቤታችሁን ቅበሩ አላቸው፡፡ ባባ ይዘወት ወደ ጌሰማኒ ሲስደት አይተው ልጇን ተነሳ አረገ እያሉ ሲውኩን ይኖራሉ አሁን ደግሞ እሷን ተነሳች አረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለም ብሎ ኑ እናቃጥላት ተባባሉ፡፡
🌿❤️ ከመካከላቸው አንዱ ታውፋንያ ዘሎ ያልጋውን ሸንኮር ያዘ፡፡ የታዘዘው መላእክት መጥቶ በሰይፍ ሁለት እጁን ቀጣው፡፡ በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማጸናት ድኖለታል፡፡ ከዚህ ቦሃላ ዮሐንስን ጨምሮ ከመካከላቸው ነጥቆ በእጸ ሕይወት ሥር አኑሯታል፡፡
🌿❤️ አንድም በዓሉ-፡ እግዚአብሔር ወልድ በሰውነት ተወልዶና ማንነቱ በይፋ ታውቆ በተገለጠበት በዘመነ አስተርእዮ ውስጥ ስለሚከበር የ♥#አስተርእዮ__ማርያም♥ ተብሏል፡፡
🌿❤️ አስቀድመው አሥራ ሁለቱም ሐዋርያት ለስብከተ ወንጌል ወደ ዓለም ሁሉ ተበትነው ነበርና በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ሁሉም ደመናን ጠቅሰው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፡፡ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ መርቶ አመጣቸው እንጂ ለምን እንደመጡ አያውቁም ነበር፡፡ እመቤታችንም ለምን እንደመጡ ጠየቀቻቸው፡፡
🌿❤️ ቅዱስ ጴጥሮስም፡- “ጸጋን የተመላሽ ቅድስት ሆይ! የመምጣታችን ምሥጢርማ እኛ አንቺን እንጠይቅ እንጂ አንቺም እኛን ትጠይቃለሽን? ሁላችንም ለምን እንደመጣን አናውቅም፡፡
💟ለምሳሌ እኔ አስቀድሜ በአንጾክያ ነበርኩኝ አሁን ግን እነሆ እዚህ ነኝ፡፡ ለምን እንደመጣሁኝ ግን አላውቅም” አላት፡፡ እርሷም ሁሉም በአጠገቧ በተሰበሰቡ ጊዜ የሚሆነውን ነገር አስቀድማ ከልጇ ከወዳጇ አውቃ ተዘጋጅታ ነበርና ለምን እንደመጡ 《ዕረፍተ ሥጋዋን ለማየት እንደሆነ》ነገረቻቸው፡፡
💟ሌሊቱንም በሙሉ በጸሎትና በማኅሌት ደግሞም በዝማሬ ሲያመሰግኑ አደሩ፡፡ ከዚህ በኋላ የተወደደችው እናት በረከቷን አሳድራባቸው በሰላም አንቀላፋች፡፡ ነፍሷም በዐብይ ዕልልታና በታላቅ ምስጋና በመላእክት እጅ ወደ አምላኳ ሄደች፡፡
🌿❤️ ኋላ ሐዋርያቱ ዮሐንስን ሲያገኙት፡- “እመቤታችን እንደምን ሆነች?” አሉት፡፡ እርሱም “በገነት በዕጸ ሕይወት ሥር ዐርፋለች” አላቸው፡፡
🌿❤️ የቀሩት ሐዋርያት “ዮሐንስ ያን ድንቅ የእግዚአብሔርን ሥራ አይቶ እኛስ ሳናይ እንዴት እንቀራለን?! አቤቱ ለእኛም ቸርነትህን አድርግልን” ብለው በነሐሴ መባቻ በአንድነት ሆነው ወደ ፈጣሪያቸው የሚቀርብ የአንድ ሳምንት ጾምና ጸሎት ጀመሩ፡፡
🌿❤️ በሁለተኛው ሱባዔ ማብቂያ ዕለት ነሐሴ 14 ቀን እሑድ የእመቤታችንን ትኩስ ሥጋ መልአኩ ከገነት አምጥቶ ለሐዋርያቱ ሰጣቸው፡፡
💟እነርሱም ልመናቸው ስለ ተፈጸመላቸው ፈጣሪያቸውን በጸሎት አመስግነው በዚያችው ዕለተ እሑድ ቅዱስ ሥጋዋን ወስደው ቀብረውታል፡፡ እርሷም በሦስተኛው ቀን ነሐሴ 16 ቀን ማክሰኞ ተነሥታለች፡፡
🌿❤️ ትንሣኤዋ “ከመ ትንሣኤ ወልዳ- እንደ ልጇ ትንሣኤ” ያሰኘው ይህ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይታ የመነሣቷ እውነታ ነው፡፡
🌿❤️ የአዛኚቱ ድንግል አማለጅነትና በረከት አይለየን አሜን ።
❤️💜💚💛💙❤️💙💚💜❤️
ወስብሓት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን
❤️💜💚💛💙❤️
/channel/DIYAKONAE
ጥር 21 ድንግል ማርያም በ 64 አመቷ ያረፈችበት እለት
የጥንት ቅዱሳን አባቶቻችን ስለ እመቤታችን ዕረፍትና ትንሳኤ በዓይናቸው ያዩትንና የተማሩትን እንዲህ ይመሰክራሉ!
....................
1. # ኢቮድየስ_ዘአንጾኪያ (የሐዋርያው የቅዱስ ጴጥሮስ ደቀመዝሙር) :- ይህ ታላቅ አባት ከጴጥሮስ ጋር አብሮ የነበረ፣ የድንግል ዕረፍትዋ በዓይኑ የተመለከተ፣ የትንሳኤዋም ሕያው ምስክር የሆነ ነው! ያየውምን ነገር በሙሉ "Homily on the Dormition of the falling asleep of Mary" በተባለው ክታቡ እንዲህ ይተርካናል!
...........
(ነሐሴ) ወር በአስራ ስድስተኛው ቀን ጠዋት በተመሳሳይ ምሽት በብርሃን ሰዓት፣ ጌታችን በታላቅ ክብር ወደኛ መጣ! ሰግደንም አመለክነው! ጌታም "ለምን ታዝናላችሁ?" ሲለን፣ አባቴ ጴጥሮስም "በእናትህና በሁላችን እመቤት ሞት፣ ከሞተችም ብኋላ ስጋዋን ስላላሳየሀን ነው" አለው! ጌታም ወደ መቃብሩ በመጣራት የድንግል እናቱን ስጋ በማስነሳት፣ ነፍስዋንም እንደገና ወደ ስጋዋ በማስገባት ልክ ቀድሞ በስጋ እንደምናውቃት በስጋ አየናት። መድኃኒታችንም ለስለስ ባለ ድምፅ "እነኋት ውድ እናቴን" አለን። ይህ የሁላችን እመቤት እና የወላዲተ አምላክ የሕይወትዋ መጨረሻው ይህ ነው በጦቢ(ጥር) ወር 21ኛ ቀን። ትንሳኤዋ ደግሞ በሜሶሪ (ነሐሴ) ወር በ16ኛው ቀን ነው> በማለት ከቀብሯ ተገኝቶ ትንሳኤዋን አይቶ ይመክረናል።
.............
2.ቅዱስ # ቴዎዶስዮስ_ዘእስክንድርያ (535 ዓ.ም)
አባታችን ቴዎዶስዮስ ስለ ትንሳኤዋ ሲንፕግረን <የነበሩበት ቦታ በእሳት ተሞላ። ጌታም በኪሩቤል ላይ ሆኖ የድንግልንም ነፍስ በእቅፉ በሰማያዊ ልብስ አጊጣ ይዟት ተገለጠ። ሐዋርያትም በፍርሐት ተሞልተው መሬት ላይ እንደ ሞቱ ሆኑ። እርሱ ፍርሐታቸውን አጥፍቶ እንዲህ አላቸው "እናንተ ደቀመዛሙርቴና ደናግል ሆይ፥ የእናቴን ክብር ታዩ ዘንድ ተነሱ።" እንዲህ ብሎም ወደመቃብሩ ጮሀ "ለእኔ መቅደስ የሆነሽኝ አንቺ ቅድስት ስጋ ሆይ፣ የእኔ የዘላለም ድንኳን የሆነችኝን ይህቺን ነፍስ ውሰጂ" ... ጌታ እነዚህን ቃላት ሲናገር መቃብሩ በዚያ ቅፅበት ተከፈተ... ከዚያም ብኋላ የከበረው የድንግል ስጋ ተነሳ፤ ነፍስዋንም አከበረቻት። ሁለት ወንድማማች ከተለያየ ሀገር እንድሚመጡ እንዲሁ ተባበሩ አንድም ሆኑ> ብሎ ወደ ትንሳኤዋ ይወስደናል።
.............
3.ቅዱስ # ዮሐንስ_ዘደማስቆ (675-749)
ይህ ቅዱስ አባትም <እርስዋ ልጅን ስትወልድ ድንግልናዋ እንደተጠበቀ እንዲሁ ስጋዋ ከሞትም ብኋላ ከመበስበስ የተጠበቀ ይሆን ዘንድ የተገባ ሆነ። ፈጣሪን በሕፃንነቱ በደረቷ እንዳቀፈችው እንዲሁ በመለኮታዊው ድንኳን (ሰማያዊ መቅደስ) ትኖር ዘንድ ተገባት! የእግዚአብሔር እናት የልጇ የሆነውን ነገር (ትንሳኤ) ታገኝ ዘንድ በፍጥረት ሁሉም የእግዚአብሔር እናትና አገልጋይ ተብላ ትመሰገን ዘንድ ሆነች> ይለናል።
.............
4.ቅዱስ # ጌርማነስ_ዘቁስጥንጥንያ (8ኛ ክ.ዘ)
ይህ አባት ደግሞ <አንቺኮ እንደ ተፃፈው በውበት የተገለጥሽ፣ ድንግል የሆነ ስጋሽም ቅዱስና ንጹሕ፣ መላውም የእግዚአብሔር ማደርያ ነው። ስለዚህም ጠቅልሎ አፈር ሆኖ ከመቅረት ነጻ ሆነ (ቀረ) ምንም እንኳን አሁንም ሰው ብትሆኚ ሥጋሽ ወደ ማይበሰብስ ሰማያዊ ሕይወት (አካል) ተቀየረ! አሁንም ስጋሽ በሕይወትና በክብር፣ ሳይጎድፍና ሳይጎድል በፍፁም ኑባሬ አለ!> እያለ ከእናቱ ከእናታችን ጋር ያወጋል። በአባቶቻችን እምነት ያፅናን!
.... የትንሳኤዋ በረከት ከወደቅንበት ኃጢኣት ያንሳን!
#ቴሌግራምን_ለመታወቅ ሳይሆን ያወቅነውን ለማሳወቅ እንጠቀምበት ፡፡
#ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ ደግሞ ፍፁም በጎነት ነው ፡፡
ለጓደኞቻችሁ በሙሉ ሸር ያርጉላቸው።
💚💛❤
ኢትዮጵያ ትቅደም
💚💛❤
@Asresee
@Asresee
@Asresee
ጥር 21/2016 #እረፍታ_ለሶልያና_አስተርዮ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_መንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በእናታችን ስም ለምናመሰግንበት ጥር ሀያ አንድ በዚች ቀን ለእመቤታችን #ቅድስት_ድንግል_ማርያም ወይም #ሶልያና የእረፍቷ መታሠቢያ #አስተርዮ በአል ነዉ እንኳን አደረሰን
👉ጥር ሀያ አንድ በዚች ቀን አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለከበረች ድንግል ማርያም የእረፍቷ በአል መታሰቢያ ነው ያን ጊዜ እመቤታችን በልጅዋ በጌታችን በፈጣሪያችንና በመድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በከበረ መቃበሩ ቦታ ትፀልይ ነበረ ከዚህም አለም እንደምትለይ መንፈስ ቅዱስ ነገራት ከዚህም በኋላ ከደብረ ዘይት ደናግል መጡ ጌታችን ነግሮዋቸዋልና እርሷም ነገረቻቸው
👉በዚያንም ጊዜ እመቤታችን እንዲህ ብላ ፀለየች ልጄ ወዳጄ ጌታዬና ፈጣሪዬ #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሆይ ልመናዬን ተቀብለህ ደቀ መዝሙርህን ዮሀንስን በዚች ሰአት አምጣው እንዲሁም ህያዋን እንደሆኑ ሀዋርያትን ሁሉንም ነፍሳቸውንም የለየሀቸውን አምጣቸው አንተ #የህያዋንና_የሙታን_አምላክ ነህና ላንተም ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን
👉በዚያንም ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ትእዛዝ ከኤፌሶን አገር #ዮሀንስን ደመና ተሸክማ ወደ #እመቤታችን_ማርያም አደረሰችው ሰገደላትና በፊቷ ቁሞ እንዲህ አላት ሰላምታ ይገባሻል ጌታችንን ፈጣሪያችንንና መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን የወለድሺው ፀጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ አንቺ ከዚህ አለም ተለይተሽ በክብር በምስጋና ወደ ዘላለም ህይወት ትሄጂአለሽና ይህም ስሙ ክብር ምስጉን የሆነ ጌታችንና ፈጣሪያችን ድንቆች ተአምራቶችን በአንቺ ላይ ከገለጠ በኋላ ነው
👉እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ይህን በሰማች ጊዜ እጅግ ደስ አላት እግዚአብሔርንም እንዲህ ብላ አመሰገነችው ፈጣሪዬ ጌታዬ ላንተ ምስጋና ይሁን አንተ የለመንኩህን ሰጥተኸኛልና አሁንም #ነፍሴን ተቀብለው ወደ ሰማይ ወደ አንተ ሊአሳርጓት ከሚመጡ መላእክቶችህ ጋር በመምጣትህ የምለምንህን ሁሉ ስጠኝ
👉በዚያንም ጊዜ ከሰማይ እንዲህ የሚል ቃል መጣ እነሆ አሁን መላእክት ይደርሳሉ ሀዋርያትም ሁሉ ከምድር ዳርቻ በደመና ተጭነው ለሰማይና ለምድር ጌታ #ለኢየሱስ_ክርስቶስ እናቱ ወደ ሆነች ወደ ቅድስት ድንግል ይደርሳሉ
👉ወዲያውኑ ሁሉም ሀዋርያት የሞቱትም ከመቃብራቸው ተነስተው ወደ እመቤታችን ደርሰው ሰገዱላት አምላካችን ከአንቺ የተወለደ ፀጋን የተመላሽ ሆን ደስ ይበልሽ እርሱ ከዚህ አለም ለይቶ ቃል ኪዳን እንደሰጠሽ በክብር በምስጋና ከርሱ ጋር #ያሳርግሻልና አሏት
👉በዚያንም ጊዜ እመቤታችን በአልጋዋ ላይ ተቀመጠች #ሀዋርያትንም እንዲህ አለቻቸው ፈጣሪዬ ፈጣሪያቹ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚመጣ እናንተንም እንዳየኋችሁ እንደማየው አሁን አውቅሁ ከዚህ ከስጋዬም ወጥቼ ወደ ዘላለም ህይወት እሄዳለሁ ነገር ግን ትነግሩኝ ዘንድ እሻለሁ ከዚህም አለም እንደምለይ ከወዴት አወቃችሁ
👉ጴጥሮስና ሐዋርያት ሁሉም ወዳንቺ እንመጣ ዘንድ #መንፈስ_ቅዱስ አዘዘን በደመና ላይም በተጫን ጊዜ ወዳንቺ እንደ አይን ጥቅሻ ፈጥነን ደረስን አሏት
👉እመቤታችንም ማርያምም ይህን ነገር ከሀዋርያት በሰማች ጊዜ ድምጿን ከፍ አድርጋ እንዲህ አለች #ጌታዬና_ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ክቡር ምስጉን የሆነ ስምህን ፈፅሜ አመሰግናለሁ የእኔን የአገልጋይህን መከራ ተመልክተህ ድንቅ ኃይልህን አድርገህልኛልና ከእንግዲህ ወዲያ #ትውልድ ሁሉ ያከብሩኛል ያመሰግኑኛል
👉ፀሎቷንና ምስጋናዋን ስትጨርስ ሀዋርያትን እንዲህ አለቻቸው እጣን አምጥታችሁ በማጠን የጌታዬን ኢየሱስ ክርስቶስን ስሙን ጥሩት እነርሱም እንዳዘዘቻቸው አደረጉ በዚያንም ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ እልፍ አእላፍት መላእክት አጅበው እያመሰገኑት መጣና አረጋጋት
👉ያዘጋጀላትንም ተድላ ደስታ ነገራት በዚያንም ብዙዎች ድንቆች ተአምራቶች ተደረገ እውሮች አይተዋልና አንካሶች ቀንተው ሄደዋልና ደንቆሮዎች ሰምተዋልና ለምፃሞች ነፁ አጋንንትም ከሰዎች ወጥተው ሄዱ ዲዳዎች ተናገሩ በሽታና ደዌ ያለበት ሁሉ ዳነ #እመቤታችን_ድንግል_ማርያም ወዳለችበት ቤት በቀረቡ ጊዜ ከደዌያቸው ይፈወሳሉና
👉ከዚህም በኋላ #እመቤታችን ተወዳጅ ልጅዋን እንዲህ አለችው በአየር ውስጥ ተበትነው ከሚኖሩ ከሚያስደነግጡ ግሩማን መላእክት የተነሳ ከእሳት ባህርም እፈራለሁ ጌታችንም ከእናንተ ለማንም በአለሁ ላይ ስልጣን የለውም አላት
👉ከስጋዋም የምትለይበት ጊዜ ሲደርስ ሐዋርያትና ደናግል ትባርካቸው ዘንድ እያለቀሱ ለመኑዋት እጃዋን በላያቸው ዘርግታ ባረከቻቸው በዚያንም ጊዜ ጌታችን ንፅህት ነፍሷን ከስጋዋ ለይቶ በመለኮታዊ እጆቹ ይዞ በብርሀን ልብስ አጎናፅፎ ወደ ከፍተኛ መኖሪያ ከእርሱ ጋር አሳረጋት ስጋዋን ግን እንደሚገባ ገንዘው ወደ #ጌቴ_ሴማኒ ተሸክመው እንዲወስዷት ሀዋርያትን አዘዛቸው
👉ነፍሷ ከስጋዋ ከመውጣቷ በፊት በሰው አንደበት ይህ ነው ተብሎ የማይነገር #ብርሀንን እያየች ነበር የክብር ባለቤት ጌታችን ክርስቶስም እንግዲህ ስጋሽን ተድላ ወዳለበት ገነት አፈልሳለሁ ዳግመኛም ስጋሽን ከነፍስሽ ጋር አዋህጄ አስነስቼ መላእክት በውስጡ በፊትሽ ሆነው በሚያመሰግኑበት ተመሳሳይ በሌለው ተድላ ደስታ በአለበት ማደሪያ አኖርሻለሁ አላት
👉እመቤታችንም እንዲህ አለች አቤቱ በረቀቀ ጥበብህ ይህን ሁሉ የሰራህ አመሰግንሀለሁ ሁለተኛም ልመናዬን ትሰማ ዘንድ እለምንሀለሁ #በስሜ ወደ አንተ የሚለምነውን ሁሉ ልመናውን ተቀበለው በመከራም ውስጥ ሆኖ ስሜን ጠርቶ ወዳንተ የሚለምነውን ከመከራው ሁሉ አድነው በሰማይም በምድርም በስራው ላይ ሁሉ አንተ ከሀሊ ነህና መታሰቢያዬን በውስጧ የሚያደርጉትን ቦታ ሁሉ ባርክ በእኔ ስም የሚያቀርቡትን የሁሉንም መስዋእታቸውን ተቀበል
👉ጌታችንም እንዲህ ብሎ መለሰላት የለመንሽኝን ሁሉ አደርግልሻለሁ ደስ ይበልሽ ከእኔ ከአባቴ ከመንፈስ ቅዱስ ዘንድ ፀጋ ክብር ባለሟልነት ተሰጥቶሻልና #ስምሽንም ጠርቶ የሚለምን ሁሉ በዚህም አለም በሚመጣውም አለም አይጠፋም
👉እመቤታችንም ከአረፈች በኋላ ጌታችን እንዳዘዘ ወደ ጌቴ ሴማኒ ሊወስዷት ሀዋርያት ገንዘው ተሸከሟት አይሁድም በሰሙ ጊዜ ስጋዋን ሊአቃጥሉ ወጡ ከእነርሱም አንዱ ከምድር ላይ ይጥላት ዘንድ የእመቤታችንን አልጋዋን ያዘ ያን ጊዜ #ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ እጆቹን በእሳት ሰይፍ ቀጣውና እጆቹ በአልጋዋ ላይ ተንጠለጠሉ
👉ያን ጊዜ በጌታችን አምኖ ወደ እመቤታችን እያለቀሰ እንዲህ ብሎ ለመነ የእውነተኛ አምላክ #የጌታ_ኢየሱስ_ክርስቶስ እናት አንቺ በእውነት ድንግል የሆንሽ በእኔ ላይ ይቅርታ ታደርጊ ዘንድ እለምንሻለሁ በሀዋርያትም ልመና እጆቹ ተመልሰው እንደቀድሞው ደኅነኞች ሆኑ
👉በቀበሩዋትም ጊዜ ከዚያ ሶስት ቀን ኖሩ እረፍቷም የሆነው እሁድ ቀን በጥር ወር በሀያ አንድ በዚች ቀን ነበረ ጌታችንም ብርሀናውያን መላእክትን ላከ እነርሱም ስጋዋን ከመቃብር ወስደው በገነት ውስጥ በእፀ ህይወት ስር አኖሩዋት
👉ሀዋርያ ቶማስ ግን ያን ጊዜ አልነበረም በደመና ላይ ተጭኖ እርሱ ሲመጣ መላእክት ሲአሳርጓት እመቤታችንን አገኛት መላእክትም ለአምላክ እናት ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ና እጅ ንሳ አሉት
እንደ ምን አላችሁ ቤተሰቦቼ ?
ከተሠማራንበት የሥራ ዘርፍ በተጨማሪም ሆነ እንደ ዋና ሥራ አድርገን ልንሠራው የምንችለ የሥራ ዘርፍ አለን በመሆኑም ፦
1, በግልም ሆነ በመንግሥት ተቋማት ተቀጥራችዉ የምትሠሩ
2, የግላችውን ሥራ የምትሠሩ
3, ከዩኒቨርስቲ ተመርቃችሁ ሥራ ያላገኛችሁ
4, 12 ተፈትናችሁ ነጥብ የመጣላቸውም ሆነ ያልመጣላችው ሠርታችዉ የራሳችሁን ስራ መሥራት ወይም ለመጀመር የሚያስችል ካፒታል የምታገኙበት የስራ ዘርፍ ነው ።ማንኛውም መሥራት የሚፈልግ ሰው ሙሉ ስም ፣የመኖሪያ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር በዉስጥ መሥመር ያሥቀምጥልኝ።
ሴልስ መስራት የሚፈልግ በዚህ ቁጥር መደወል ይችላሉ
0983797902
0799192014
inbox me your :
-NAME
-ADRESS
PHONE NUMBER
ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ያዘጋጀውን የ10 ቀን ስልጠና በመውሰድ እስከ 9,000$ ዶላር (700,000 ብር) የስራ መጀመሪያ ያለማስያዢያ ይውሰዱ በኦንላይን በድረ ገፅ ወይም መተግበሪያቸው ቶሎ ተመዝገቡ ማሳሰቢያ ይህ እድል ለ""""የመስሪያ ቦታ ላላቸው ቡቻ"""!!! ወይም በስራ ላያ ላሉ ነው መስሪያ ቦታ የሌለውን አይቀበሉም የሁለት አመት የኪራይ ውል ተከራይቶ ካመጣ ብቻ ምንም ክፍያ የለውም ነፃ ነው👍sign up for world farming foundation download here
Get up to $9,000 (700,000 Birr) by taking the 10-day training organized by the Master card Foundation. Register quickly online on their website or app. They do not accept those who do not have a place to work, but only if they bring a two-year lease its free off fee
/channel/Mster_Card_foundation_Et
👉ዛሬ ጥር 19 ቀን 2016 ዓ.ም. #የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ #ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የ82ኛ ዓመት ልደት ቀን ነው
👉ብፁዕ አባታችን ቡራኬዎ ይድረሰን እግዚአብሔር በሰላምና በእረጅም እድሜ ከጤና ጋር ያኑርልን "አሜን"
††† እንኳን ለጻድቅ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤን ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችኹ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤን †††
††† በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ መካከለኛው ዘመን (በተለይ ከ13ኛው እስከ 15ኛው መቶ ክ/ዘመን ድረስ ያለው) የብርሃን ዘመን ይባላል:: ምክንያቱም ዘመኑ
*ክርስትና ያበበበት::
*መጻሕፍት የተደረሱበት::
*ስብከተ ወንጌል የተስፋፋበት::
*ገዳማዊ ሕይወት የሠመረበት ወቅት በመሆኑ ነው::
ለዚህ ትልቁ አስተዋጽኦ ደግሞ:-
¤አቡነ ተክለ ሃይማኖት::
¤አቡነ ኤዎስጣቴዎስ::
¤አባ ሰላማ ካልዕ::
¤አቡነ ያዕቆብ::
¤ቅዱሱ ንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብ::
¤አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ::
¤አቡነ መድኃኒነ እግዚእን የመሰሉ አበው መነሳታቸው ነው::
በተጨማሪም:-
¤12ቱ ንቡራነ ዕድ::
¤7ቱ ከዋክብት::
¤47ቱ ከዋክብት::
¤5ቱ ከዋክብት የሚባሉ አበው አስተዋጽኦም ልዩ ነበር:: ከእነዚህ መካከልም የ7ቱ እና የ47ቱ ከዋክብት አስተማሪ: የአበው 3ቱ ሳሙኤሎች (ዘዋልድባ: ዘጣሬጣና ዘቆየጻ): የሌሎችም እልፍ አእላፍ ቅዱሳን አባት የሆኑት አባ መድኃኒነ እግዚእ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ::
ጻድቁ ቅዱሳኑን ሰብስበው: አስተምረው: አመንኩሰው: መርቀው ሰደው: ሃገራችንን እንዲያበሩ በማድረጋቸው እንደ አባ ኢየሱስ ሞዐ እርሳቸውም "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን" ይባላሉ::
ከእነዚህ ቅዱሳን የጻድቁ ፍሬዎች አንዱ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ናቸው:: ጻድቁ አንዳንዴ "አፍቀረነ እግዚእ" እየተባሉም ይጠራሉ:: ትርጉሙም "ጌታ ወደደን" እንደ ማለት ነው::
ያፍቅረነ እግዚእ የነበሩት በ14ኛው መቶ ክ/ዘ ሲሆን ቁጥራቸው ከ7ቱ ከዋክብት ነው:: ጻድቁ ከልጅነት ጀምሮ በሥርዓቱ ከማደጋቸው ባሻገር እጅግ የተማሩ እንደነበሩም ይነገርላቸዋል::
ለምናኔ ከወጡ በሁዋላ ከኖሩባቸው ቦታዎችም 3ቱ ተጠቃሽ ናቸው:: የመጀመሪያውና ትልቁን ሥፍራ የሚይዘው ደግሞ ደብረ በንኮል ነው:: ጻድቁ በዚህ ገዳም ከታላቁ ቅዱስ አባ መድኃኒነ እግዚእ ሥርዓተ ገዳምን : ትኅርምተ አበውን : ተጋድሎተ ቅዱሳንን አጥንተው ለመዓርገ ምንኩስና በቅተዋል::
በገዳሙም ለተወሰነ ጊዜ አገልግለው ወደ ጣና አካባቢ ከአቡነ ያሳይና ከአባ ሳሙኤል ዘዋሊ ጋር መጥተዋል:: የመምጣታቸው ምክንያትም ስብከተ ወንጌልን ለማዳረስና ገዳማትን ለመመሥረት ነው::
ሶስቱ ቅዱሳን ለተወሰነ ጊዜ ከቆዩ በሁዋላ አቡነ ሳሙኤል ወደ ዋልድባ ሲሔዱ አቡነ ያሳይ ደግሞ ማንዳባን አቀኑ:: ያፍቅረነ እግዚእም ጌታ ባዘዛቸው መሠረት ጣና ውስጥ ገዳም አቅንተው ኑረዋል:: ይህ ገዳማቸው ዛሬም ድረስ በስማቸው ይጠራል::
ጻድቁ አፍቀረነ እግዚእ 3ኛው የሚታወቁበት ገዳም ማኅበረ ዴጌ (ጻድቃነ ዴጌ) ሲሆን ገዳሙ በአክሱም ዙሪያ ይገኛል:: እርሳቸው 3ሺ ቅዱሳን የተሠወሩበትን ገዳም በማገልገላቸውም ዛሬም ድረስ በአካባቢው የታወቁ ሆነዋል::
በተረፈም አክሱም አካባቢ ሌሎች ገዳማትን እንዳቀኑም ይነገርላቸዋል:: ጻድቁ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ለብዙ ዘመናት በተጋድሎ : በስብከተ ወንጌልና ገዳማትን በማስፋፋት ከኖሩ በሁዋላ በዚህች ቀን ዐርፈው ለክብሩ : ለርስቱ በቅተዋል::
††† አምላከ ቅዱሳን በጻድቁ አማላጅነት ይቅር ብሎ በረከታቸውን ያሳድርብን::
††† ጥር 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ጻድቁ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ (አፍቀረነ እግዚእ ዘጉጉቤ - ጣና ውስጥ - ከሰባቱ ከዋክብት አንዱ)
2.አባ ባሱራ
3.ቅድስት ኔራ
4.ቅድስት በርስጢና
5.አባ ዝሑራ
††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላዕክት
2.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
3.አባ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ (ታቦታቸው ጎንደር ከተማ ቀበሌ 09 አካባቢ ይገኛል)
4.አቡነ ስነ ኢየሱስ
5.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም
††† ቅዱሳንን ታስቡ ዘንድ ቸል አትበሉ::
††† "እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና::
ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና::
ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል . . .
ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ::
በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ::
የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል::
አንደበቱም ፍርድን ይናገራል::
የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው::
በእርምጃውም አይሰናከልም::" †††
(መዝ. 36:28-31)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
🕎 ኮኮብህ ምንድን ነው☸️? በZODIAC ሳይንስ ምን አይነት ባህሪ እንዳለህ ማወቅ ትፈልጋለህ? እንግዲያውስ እዚ ቻናል ላይ መልሱን ታገኘዋለህ። JOIN ብቻ በል።☮️
👇👇👇👇👇
👉 @Asresee
👉 @Asresee
👉 @Asresee