kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

💐⛪27   ቸሩ መድኃኒአለም💐⛪

✝️አሰራኤልን   -------- ከግብፅ ባርነት ያወጣ
✝️ለሙሴ    -------ጽላት የሠጠ
✝️ለሳምሶን --------ሀይልን የሠጠ
✝️ጥበብና ማሥተዋልን _ ለሠለሞን የሠጠ
✝️ዮሴፍን ____ በባአድ ሀገር ከፍ ከፍ ያደረገ
✝️አዮብን ____ በፈተና ያፀና በበረከት የጎበኘ
✝️ኤልያሰን ____  ከአዉሎ አፋሰ የነጠቀ
✝️ያዕቆብን ____ በመንገዱ የጠበቀ አና የባረከ

በኪሩቤል ላይ የተቀመጠ ክብሩም የገለጠ ሥጦታዉ የማያልቅበት💐⛪ ቸሩ መድሃኒአለም ይክበር ይመሥገን 💐⛪

ለእኛም ሠላምን ጤናን ምህርትን ሠማያዊ ሀብትን ያደለን

/channel/silase

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የካቲት 27/2016 #የአለም_መድኃኒት_መድኃኔዓለም

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ አምላክ አሜን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን #መድኃኔአለም ኢየሱስ ክርስቶስ አለምን ለማዳን ዋጋ ለከፈለበት ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን

👉 #መድኃኔዓለም ማለት ዓለምን ያዳነ የዓለም መድኃኒት ማለት ነው ሰው በመበደሉ ምክንያት ከክብር ተዋርዶ ይኖር ነበር #ኢየሱስ_ክርስቶስ ግን የተዋረደውን ሰው እርሱ በመስቀል ተሰቅሎ ወደ ቀደመ ክብሩ መለሰው ምን ዓይነት ፍቅር ነው ስለኛ የሰዉ ልጆች ሲል በመስቀል ላይ ዋለ

👉ራቁትን መሰቀል አሳፋሪ ነገር እንደሆነ እናውቀዋለን ጌታ ግን እኛን ለማዳን ብሎ #ራቁቱን_ተሰቀለ በፈጠራቸው ፍጥረታት ተናቀ ተተፋበት

👉እኛን ትእግስት ሊያስተምረን እነርሱን ማጥፋት እየቻለ እርሱ ግን በፍቅር እያየ የሚያረጉትን አያውቁምና አባት ሆይ ይቅር በላቸው ይል ነበር #ክርስቶስ እኛን ልጆቹን ለማዳን ሲሰድቡት አልተሳደበም ሲንቁት አልናቃቸውም ሲታበዩበት ሁሉ እርሱ ግን በትሕትና ያያቸው ነበር

👉አይሁድ በ5 ችንካር ነበር የቸነከሩት ጌታችን በሚሰቀል ጊዜ የተገኙ እናታችን #ማርያምና ሐዋርያው #ቅዱስ_ዮሐንስ ነበሩ አኛም #በመስቀሉ ስር ለመገኘት ከፈለግን ትዕግስትን ፍቅርን ትሕትናን መለማመድ ይኖርብናል

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በፈቃድህ በተሰቀልክ ጊዜ በቀኝህ ለተሰቀለዉ ወንበዴ የገነት መክፈቻን እንደሰጠኸዉ ወደ ገነትም እንዳስገባከዉ በኃጢአት የወደቅን ልጆችህን ነፍስና ስጋችንን አክብረህ ብርሀነ ፀጋህን አብራልን

👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የሚታሠቡት ፃድቁ አባታችን አቡነ #መብአ_ፅዮን በምልጃ ፀሎታቸዉ ሁላችንንም ይጠብቁን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሰላም እንዴት ናችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች
አንድ ጥያቄ ነበረኝ ?
ውዳሴ ማርያም ግን ለምንድን ነው ከ 12 ሰዐት በኃላ የቀጣዩን ቀን ውዳሴ የምናነበው ?
የሚያውቅ ቢያሳውቀኝ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ማማለድ ትንሽ ነገር ነው
/channel/silase

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለታላቁ ነቢይ ቅዱስ ሆሴዕ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችኹ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ሆሴዕ ነቢይ †††

††† ነቢይ ማለት በቁሙ ኃላፍያትን (አልፎ የተሠወረውን ምሥጢር): መጻዕያትን (ገና ለወደ ፊት የሚሆነውን) የሚያውቅ ሰው ማለት ነው:: ሃብተ ትንቢት የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ሲሆን እርሱ ለወደደው ደግሞ በጸጋ ይሰጠዋል:: እነዚህም ከጌታ ሃብተ ትንቢት የተሰጣቸው አባቶችና እናቶች "ቅዱሳን ነቢያት" በመባል ይታወቃሉ::

ዘመነ ነቢያት ተብሎ የሚታወቀው ብሉይ ኪዳን ቢሆንም እስከ ምጽዓት ድረስ ጸጋውን እግዚአብሔር ለፈቀደላቸው አይነሳቸውም:: በሐዋርያት መካከልም ቅዱስ አጋቦስን የመሰሉ ነቢያት ነበሩ:: (ሐዋ. 11:27) ቅዱሳን ነቢያት ከእግዚአብሔር እየተላኩ ሰውን ከፈጣሪው እንዲታረቅ ይመክራሉ: ይገስጻሉ::

ከበጐ ሃይማኖታቸውና ንጽሕናቸው የተነሳም እግዚአብሔርን በተለያየ አርአያና አምሳል አይተውታል::
"እስመ በአንጽሖ መንፈስ ርዕይዎ ነቢያት ለእግዚአብሔር: ወተናጸሩ ገጸ በገጽ" እንዳለ አባ ሕርያቆስ:: (ቅዳሴ ማርያም)

የብዙ ነቢያት ፍጻሜአቸው መከራን መቀበል ነው:: እውነትን ስለ ተናገሩ: አንዳንዶቹም በእሳት: አንዳንዶቹም በሰይፍ: አንዳንዶቹም በመጋዝ ተፈትነዋል:: ሌሎቹ ለአናብስት ሲጣሉ ቀሪዎቹ ደግሞ በድንጋይ ተወግረዋል::

ስለዚህም መከራቸው ለቤተ ክርስቲያን መሠረት ተብለዋል:: ጌታም ለደቀ መዛሙርቱ "ሌሎች ደከሙ: እናንተ በድካማቸው ገባችሁ" ብሎ የነቢያቱን መከራ ተናግሯል:: (ዮሐ. 4:36)

ነቢያት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እና ድንግል እናቱን ለማየት ብዙ ጥረዋል: ሽተዋልም:: "ብዙ ነቢያትና ጻድቃን እናንተ የምታዩትን ሊያዩ ሹ" እንዳለ ጌታ በወንጌል:: (ማቴ. 13:16, 1ዼጥ. 1:10)
ዛሬ ግን በሰማያት ጸጋ በዝቶላቸው: ክብር ተሰጥቷቸው ሐሴትን ያደርጋሉ::

ቅዱሳን ነቢያት በዋነኝነት
¤15ቱ አበው ነቢያት:
¤4ቱ ዐበይት ነቢያት:
¤12ቱ ደቂቀ ነቢያትና
¤ካልአን ነቢያት ተብለው በ4 ይከፈላሉ::

"15ቱ አበው ነቢያት" ማለት:-
*ቅዱስ አዳም አባታችን
*ሴት
*ሔኖስ
*ቃይናን
*መላልኤል
*ያሬድ
*ኄኖክ
*ማቱሳላ
*ላሜሕ
*ኖኅ
*አብርሃም
*ይስሐቅ
*ያዕቆብ
*ሙሴና
*ሳሙኤል ናቸው::

"4ቱ ዐበይት ነቢያት"
*ቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ ቃል
*ቅዱስ ኤርምያስ
*ቅዱስ ሕዝቅኤልና
*ቅዱስ ዳንኤል ናቸው::

"12ቱ ደቂቀ ነቢያት"
*ቅዱስ ሆሴዕ
*አሞጽ
*ሚክያስ
*ዮናስ
*ናሆም
*አብድዩ
*ሶፎንያስ
*ሐጌ
*ኢዩኤል
*ዕንባቆም
*ዘካርያስና
*ሚልክያስ ናቸው::

"ካልአን ነቢያት" ደግሞ:-
*እነ ኢያሱ
*ሶምሶን
*ዮፍታሔ
*ጌዴዎን
*ዳዊት
*ሰሎሞን
*ኤልያስና
*ኤልሳዕ . . . ሌሎችም ናቸው::

ነቢያት በከተማም ይከፈላሉ::
*የይሁዳ (ኢየሩሳሌም):
*የሰማርያ (እሥራኤል)ና
*የባቢሎን (በምርኮ ጊዜ) ተብለው ይጠራሉ::

በዘመን አከፋፈል ደግሞ:-
*ከአዳም እስከ ዮሴፍ (የዘመነ አበው ነቢያት):
*ከሊቀ ነቢያት ሙሴ እስከ ነቢዩ ሳሙኤል (የዘመነ መሳፍንት ነቢያት)
*ከቅዱስ ዳዊት እስከ ዘሩባቤል ያሉት (የዘመነ ነገሥት ነቢያት)
*ከዘሩባቤል ዕረፍት እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ያሉት ደግሞ (የዘመነ ካህናት ነቢያት) ይባላሉ::

ስለ ቅዱሳን ነቢያት በጥቂቱ ይህንን ካልን ወደ ዕለቱ በዓል እንመለስ::
ቅዱስ ሆሴዕ ቁጥሩ ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት ሲሆን ዘመነ ትንቢቱም ቅ/ል/ክርስቶስ በ800 ዓ/ዓ አካባቢ ነው:: "ደቂቀ ነቢያት" ማለት በጥሬው "የነቢያት ልጆች" ማለት ነው:: አንድም የጻፏቸው ትንቢቶች ሲበዙ 14 ምዕራፍ: ሲያንስ አንድ ምዕራፍ ያላቸው ናቸውና ደቂቅ ይላቸዋል::

ነቢይና ጻድቅ ቅዱስ ሆሴዕ 'ዖዝያ' በመባልም ይታወቃል:: ቅዱሱ ነቢይ የቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ-ቃል ባልንጀራ የነበረ ሲሆን በ4 ነገሥታት ዘመን (ዖዝያን : ኢዮአታም : አካዝና ደጉ ሕዝቅያስ) ብዙ ሐረገ ትንቢቶችን ተናግሯል:: የትንቢት ዘመኑም ከ70 ዓመት በላይ ነው::

ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ የሆነው ቅዱስ ሆሴዕ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራም በስፋት ተንብዩዋል:: 14 ምዕራፎች ያሉት የትንቢቱ ጥራዝ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛል:: ሆሴዕ ማለት መድኃኒት ማለት ነው:: የመዳን ትምሕርትንና ትንቢትን ሊናገር ተመርጧልና::

††† ቸር አምላከ ነቢያት የነቢያቱን መከራ አስቦ ከመከራ: በእንባቸውም ከእንባ ይሰውረን:: ከተረፈ በረከታቸውም አያጉድለን::

††† የካቲት 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ሆሴዕ ነቢይ (ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት)
2.ቅዱስ ሳዶቅ ሰማዕት
3."808" ሰማዕታት (ከቅዱስ ሳዶቅ ጋር የተሰየፉ)

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
2.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
3.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
4.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
5.አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን

††† "ኑ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንመለስ:: እርሱ ሰብሮናልና: እርሱም ይፈውሰናል:: እርሱ መትቶናል: እርሱም ይጠግነናል:: ከሁለት ቀን በሁዋላ ያድነናል:: በሦስተኛውም ቀን ያስነሳናል:: በፊቱም በሕይወት እንኖራለን:: እንወቅ:: እናውቀውም ዘንድ እንከተል . . . " †††
(ሆሴዕ 6:1-3)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ውዳሴሃ፣ ለእግዝትነ ፣ማርያም፣ድንግል፣ወላዲተ፣ አምላክ፣ዘይትነበብ፣በዕለተ ረቡዕ
/channel/wdase1

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/kv7KqQljePc?si=aPkRoJuF_36_c-6t

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🌺 ሶበሰ ይወረዱ 🌺


ሶበሰ ይውረዱ መላእክት
መላእክት ይወርዱ
አወ ሊቃነ መላእክት ይበል ኧኸ

አልቦሙ ድምጽ ኧኸ ኧኸ ኧኸ
ወለልቦሙ አሰረ ለምክያዳት
ይቀልል ሩፀቶሞ እም ነፋሳት
ውስተ አገሮ ለእግዝያብሄር
ኢትዮጵያ ይበል ኧኸ

#Share እና #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

/channel/silase

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለጻድቁ አባታችን ቅዱስ አቡፋና እና ቅዱስ እንጦኒ ሐዲስ ሰማዕት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችኹ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† አባ አቡፋና †††

††† ታላቁ አባ አቡፋና፦
በምድረ ግብጽ ተጋድሏቸውን የፈፀሙ፣
በመዐልት አምስት መቶ ጊዜ በሌሊትም አምስት ጊዜ አቡነ ዘበሰማያትን ይጸልዩ የነበሩ፣
በአርባ ቀን አንድ ጊዜ ብቻ እህል ይቀምሱ የነበሩና ሙሉ ዘመናቸውን በበርሃ በታላቅ ጽሙና የፈፀሙ አባት ናቸው።

ጻድቁ በጣም የሚታወቁት ከማበጡ የተነሳ እጅግ ግዙፍ በነበረ እግራቸው ነው። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ስለ መድኃኔ ዓለም ፍቅር አልቀመጥም፤ አልተኛም ብለው ለአሥራ ስምንት ዓመታት በመቆማቸው ነው።

አሥራ ስምንት ዓመት የመቆማቸው ዜናስ እንደምን ነው ቢሉ፦
አንድ ቀን "እኔ ግን ከዚህ ዓለም የምለየው መቼ ይሆን?" ሲሉ አሰቡ። በእርግጥ ይህንን ሐሳብ ብዙ ሰዎች ሊያስቡት ይችላል። ሐሳቡ ጠቃሚም ያልተፈቀደም ነው።
፩. "ጠቃሚ ነው።" ያልኩት አንድ ሰው ሞት እንዳለ ካወቀ ወይም 'መቼ ነው የምሞተው' ብሎ ካሰበ ንስሐ ይገባል፤ ክፋትን ይተዋል ተብሎ ስለሚታመን ነው። ወገኔ ሁሉ እንደ አውሬ ሲባላ፣ ደም ሲያፈስ፣ ክፋትን ሲጐነጉን የሚውል "እሞት ባይ" ሳይሆን "እኖር ባይ" ሆኖ ነውና።
ግን ሞት በቅርቡ እንዳለ በኃያሉ አምላክ ፊት ራቁቱን ለፍርድ እንደሚቀርብ ለወገኔ ማን በነገረው!
፪. "ያልተፈቀደ ነው።" ያልኩት ደግሞ በሁለት ምክንያት ነው።
"ኢትበሉ ለጌሰም (ለነገ አትበሉ።)" የሚል አምላካዊ ቃል ስላለ።
ማቴ. ፮፥፴፬
ሰው (በተለይ ዓለማዊው) የሚሞትበትን ቀን ቢያውቅ አጭር ጊዜ ከሆነ ሽብር ጭንቀት ይበላዋል። ወዲህ ደግሞ ጊዜው ረዥም ቢሆን እንደ ሰብአ ትካት (ማለትም በኖኅ ዘመን እንደ ነበሩ ሰዎች) 'ብዙውን ልዝናናበት (ኃጢአት ልሥራበት')ና ንስሐ እገባለሁ።' ይላልና ነው።

በዚያውም ላይ በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት ቅዱስ ሰውና የነቢያት አለቃ ቅዱስ ሙሴ የሞቱን ጊዜ ጠይቆ እጅግ መቸገሩን መጥቀሱ በራሱ በቂ ነው። ጌታ "ዓርብ ቀን ትሞታለህ።" ብሎት ለሁለት ዓመታት ዓርብ ዓርብ ሲገነዝ ሲፈታ ኑሯል።

በመጨረሻም ዓርብ ቀን ድንገት መልአከ ሞት መጥቶበታል። ስለዚህ "ወድልዋኒክሙ ንበሩ - ተዘጋጅታችሁ ኑሩ። መባላችንን አስበን ልንኖር ግድ ይለናል።
ማቴ. ፳፬፥፵፬

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ አቡፋና ይህንን የዕረፍታቸውን ነገር ሲያስቡ ቅዱስ መልአክ ተገልጦ "ተርፈከ አሠርቱ ወሰመንቱ - አሥራ ስምንት ቀርቶሃል።" አላቸው። እርሳቸውም "ጌታዬ አሥራ ስምንት ምን?" ሲሉ ቢጠይቁትም ሳይመልስላቸው ተሠወረ።

ከደቂቃ እስከ ኢዮቤልዩ ብዙ አሥራ ስምንቶች አሉ። እርሳቸው ግን "አሥራ ስምንት ቀን ነው!" ብለው ለጌታ ተሳሉ። ስዕለታቸውም "ከዚህ በኋላ አልቀመጥም።" የሚል ነው። እየጾሙ እየጸለዩ ለአሥራ ስምንት ቀናት ቆሙ። ሞት አልመጣም።

"አሥራ ስምንት ሱባኤ ይሆን!" ብለው አሥራ ስምንት ሱባኤ (መቶ ሃያ ስድስት ቀናት) ቆመው ጸለዩ። አሁንም ሞት አልመጣም። "አይ! አሥራ ስምንት ወር ሊሆን ይችላል።" ብለው ለአሥራ ስምንት ወራት (ለአንድ ዓመት ከስድስት ወር) ቆመው ተጉ። አሁንም ግን ሞት የውኃ ሽታ ሆኖ ቀረ።

ይህን ጊዜ ግን ወደ ፈጣሪ ለመኑ። "ጌታዬ! ያልከኝ ምን አሥራ ስምንት ነው?"
ቅዱስ መልአኩም መጥቶ "አቡፋና ሆይ! የቀረህ አሥራ ስምንት ዓመት ነውና ጽና።" ብሏቸው ተሰወረ። ልብ በሉልኝ "እስክሞት አልቀመጥም።" ብለው ተስለዋል።

ቅዱሱ ገዳማዊ በቃላቸው የሚገኙ እውነተኛ ክርስቲያን ነበሩና ለአሥራ ስምንት ዓመታት እንደተተከለ ምሰሶ ቆመው ጸለዩ፣ ጾሙ። እንዲህ ያሉትን ቅዱሳን ሊቃውንት፦
"ሰላም ለከ ጽኑዕ ከመ ዓምድ
ዘኢያንቀለቅሎ ሞገድ።"
(ማዕበለ ዓለም የማያናውጸው ብርቱ ምሰሶ ሆይ! ምስጋና ይገባሃል።) የሚሏቸው።

ስለ ቅዱሱ የተጻፈ አርኬም፦
"ሰላም ለቁመተ አቡፋና ዘአልቦ ኑታጌ
እስከ ተመሰለ እግሩ ከመ እግረ ነጌ።" ይላል። ከመቆም ብዛት አካላቸው ደቆ እግራቸው የዝሆን እግር እስኪመስል ወፍሮ ነበርና።

††† አባ አቡፋና በዘመናቸው ብዙ ተአምራትን ሠርተው በዚህች ቀን አርፈዋል።

††† ቅዱስ እንጦኒ ሐዲስ ሰማዕት †††

††† ቅዱስ እንጦኒ (Anthony) በትውልዱ ከሶርያ ዐረቦች ሲሆን በቀደመ ሕይወቱ ክርስቲያኖችን ያሳድድ፣ ካህናትን ይደበድብ፣ አብያተ ክርስቲያናትንም ያቃጥል ነበር። እግዚአብሔር በንስሐ ሲጠራው ግን ደግ፣ ጻድቅና ምርጥ ዕቃ ሆኖ ተገኘ። በመጨረሻም ከብዙ መከራ በኋላ ለሰማዕትነት በቅቷል።

††† አምላከ ቅዱሳን የወዳጆቹን ትጋት፣ ጽናት፣ ፍቅርና በረከት ያድለን። ከማስተዋልም አያጉድለን።

††† የካቲት ፳፭ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ
፪.ቅዱስ እንጦኒ ሐዲስ ሰማዕት
፫.ቅዱሳን ሰማዕታት አውሳንዮስ፣ ፊልሞናና ሉቅያ ድንግል (የቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ ደቀ መዛሙርት)
፬.ቅዱስ ቶና ዲያቆንና ሰማዕት
፭.ቅዱስ ሚናስ ዘሃገረ ቁስ

††† ወርኀዊ በዓላት
፩.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
፪.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
፫.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
፬.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
፭.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)

††† "ኃይል የሰጠኝን ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታችንን አመሰግናለሁ። አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ አንገላችም ምንም ብሆን ይህን አደረገልኝ። ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምሕረትን አገኘሁ።" †††
(፩ጢሞ ፩፥፲፪-፲፫)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

የዩቱዩብ ቻናል👇
https://youtu.be/OIOCAD82nxk?si=VMEi2GBRFE8w3lMi

የቲክቶክ ቻናል👇
zikirekidusan23?_t=8kGT8RWuULK&_r=1" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@zikirekidusan23?_t=8kGT8RWuULK&_r=1

የቴሌግራም ቻናል👇
/channel/zikirekdusn

✝ ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር ✝

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#EOTC

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት 11ኛ ዓመት በዓለ ሢመተ ፓትርያርክ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በከፍተኛ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት እየተከበረ ይገኛል ቅዱስነታቸው ያስተላለፉትን ቃለ ምእዳንና ቡራኬ እንደሚከተለው ይነበባል፦

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

- ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣
- ብፁዕ አቡነ ሄኖክ
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
- ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፤
- የተከበራችሁ የመንግሥት ከፍተኛ ባለ ሥልጣናት፤
- የተከበራችሁ አምባሳደሮችና ኮር ዲኘሎማቶች፤
- የተከበራችሁ የቤተክርስቲያናችን የየመምሪያውና የየድርጅቱ ኃላፊዎች፤
- ክቡራን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፤
- ክቡራን የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፤
- የሰንበት ት/ቤት ወጣት ልጆቻችን፤
- በአጠቃላይ በዚህ ዓውደ ምሕረት የተገኛችሁ ክቡራንና ክቡራት በሙሉ፤

ፈተናዎች ቢበዙብንም ምሕረቱን ከኛ ያላራቀ እግዚአብሔር እንኳን ለዐሥራ አንደኛው በዓለ ሢመተ ክህነት በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ

‹‹ወይእዜኒ ተመየጡ ኀቤየ ወአነሂ እትመየጠክሙ፡- ‹‹አሁንም ወደኔ ተመለሱ፤ እኔም ወደናንተ እመለሳለሁ›› (ዘካ. ፩-፫)

ቅዱስ መጽሐፍ ታላቁ የዓለማችን መጽሐፍ ነው፤ በዕድሜም በብዛትም በዓለም ውስጥ የሚተካከለው የለም፤ ቅዱስ መጽሐፍ በዓለም ውስጥ በብዙ ቋንቋ የተተረጐመና ብዙ አንባቢና ተከታይ ያለው ብቸኛው የዓለማችን ታላቅ መጽሐፍ ነው፡፡

የቅዱስ መጽሐፍ ይዘት በጥቅሉ ሲታይ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል የነበረው ያለውና የሚኖረው ግንኙነትን የሚገልጽ ነው። የግንኙነቱ ሁናቴ ሲታይ ደግሞ ቀጥ ያለ ሳይሆን ብዙ ፈተና ያስተናገደ ጐርባጣና ጠመዝማዛ እንደሆነ በግልጽ ያመለክታል። በረጅሙ ግንኙነት እግዚአብሔር ፍጡሩን እየተከታተለ በምሕረትና በፍቅር ሲጐበኝ አንዳንዴ ደግሞ ሲቀጣም ሲገሥጽም ይታያል፡፡ በሌላ ወገን ደግሞ ሰዎች የእግዚአብሔርን ጥሪ ተቀብለው እንደ ቃሉ ለመኖር ሲጣጣሩ፣ ነገር ግን በአብዛኛው እንዳልተሳካላቸው፣ በዚህም ጉዳታቸው እየከፋ እንደሄደ እናስተውላለን፡፡ ሆኖም እግዚአብሔር ሰውን ለመመለስ መጣራቱን አቋርጦ እንደማያውቅ ተጽፎአል፡፡ ‹‹አሁንም ወደኔ ተመለሱ፤ እኔም ወደእናንተ እመለሳለሁ›› የሚለው ጥሪውም ይህንን ያስረዳል፡፡ ጥቅሱን በትክክል ስናጤነው ሰዎች ከእግዚአብሔር የመኮብለል ዝንባሌያቸው ያየለ እንደሆነ፣ በአንጻሩ ደግሞ የእግዚአብሔር ጥሪ የማያቋርጥ እንደሆነ የሚያስረግጥ ነው። ቀድሞም ሆነ ዛሬ የምናየው ሐቅም ይኸው ነው።

ከዚህ አንጻር በዘመናችን ያለው ሁኔታም ስንመለከት ከበፊቱ ብዙም የተሻለ ሆኖ አናገኘውም። ይልቁንም በጣም የተዛባና ለእግዚአብሔር ቁጣ የተጋለጠ ሆኖ እናየዋለን። ያለንበት ዘመን ለእግዚአብሔር ክብርን የነሣ፤ ከፍቅርና ከአንድነት የራቀ፣ ራስ ወዳድነትና በቃኝ አለማለትን የወረረው፤ በዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂ የተዋጠ ትውልድ የታየበት ዘመን ነው፡፡

የዘመናችን ትውልድ ከተግባር ይልቅ አስመሳይ ሆኖ መታየትን፣ ከቅድስና ይልቅ ነውረ ኃጢአትን፤ ከትሕትና ይልቅ ትዕቢትን የተለማመደ፣ ለሃይማኖትም ሆነ ለማኅበረ ሰብ ጤናማ ህላዌ ያልተመቸ ትውልድ እንደሆነ በግልጽ የሚታይ ነው፡፡ ይህን አደገኛ አዝማሚያ በማስተዋል ካልታረመ ሂዶ ሂዶ የእግዚአብሔርን ቁጣ ማስከተሉ አይቀርምና እንደ እግዚአብሔር ጥሪ ወደእሱ ብንመለስ ይሻላል፡፡

- ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ፦
- ክቡራን የበዓሉ ተሳታፊዎች ፦

እኛ የሃይማኖት አባቶችም አልጫ የሆነውን የዘመናችንን ትውልድ በትጋት አስተምረን በቈራጥነት ገሥጸንና መክረን ወደ እግዚአብሔር ካልመለስነው ከቁጣው አንድንም፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ እንዳስተማረን አስተምረነው የማይመለስ ከሆነ ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል። እኛ ባለማስተማራችን የሚጎዳ ትውልድ ካለ ግን እኛ የደሙ ተጠያቂዎች መሆናችንን በማያሻማ ሁኔታ ተገልጾአልና ነው። የኛ ኃላፊነት እስከዚህ ድረስ ከባድ መሆኑን ባንዘነጋውም እንደዓለሙ በልዩ ልዩ ደካማ አስተሳሰቦችና ተግባራት እየተሰናከልን መሆናችን የአደባባይ ምሥጢር ከሆነ ውሉ አድሮአል፡፡

ዓለም ሲሳሳት ከመገሠጽ ይልቅ አብሮ ማጨብጨብ ተለማምደናል፤ ባናጨበጭብም ዝምታን መርጠናል፤ ነገር ግን ኃላፊነቱን የተረከብነው ጥፋት ሲፈጸም ዝም ብሎ ለማየት አልነበረም። ከዓለሙ ጋር አብሮ ለማጨብጨብ ወይም አድማቂ ለመሆንም አልነበረም፡፡ ከቅዱስ ወንጌሉ መሠረተ ሐሳብ ፍንክች ሳንል የእውነት፣ የፍትሕ፣ የሰላም፣ የፍቅር፣ የዕርቅ፣ የይቅርታ፣ የአንድነትና የስምምነት ጠበቃ መሆናችንን ማሳየት ነበረብን፡፡ ሰውን ሁሉ በእኩልነት በመቀበልና የሁሉም እኩል አባቶች መሆናችንን በተግባር ማስመስከር ይገባን ነበር፤ የተዛባውን በማረም ትውልዱን ለማዳን ያደረግነው ጥረት የሚያረካ እንዳልሆነ ታዛቢው ሁሉ አይቶብናል፡፡ያም በመሆኑ ሁኔታው እኛንም ቤተ ክርስቲያንንም ለፈተና ለመዳረግ እየዳዳ ነው። በመሆኑም በዚህ ክሥተት የእግዚብሔር ቁጣ የለበትም ለማለት አንደፍርም። በዓለሙ ብልሹ አሰራርም ተሳታፊ ከመሆን አላመለጥንም፡፡ክሱ፣ አቤቱታው፣ ሰውን ከሥራ እያፈናቀሉ ፍትሕ ማዛባቱ፣ በደምብ ተለማምደነዋል፤ ደመወዛችሁ ይብቃችሁ የሚለውን አምላካዊ መርሕ ዘንግተን የዚህ ዓለም ንዋይ እያሸነፈን ነው። ግን ዓለምን ልናሸንፍ እንጂ በዓለም ልንሸነፍ አልተጠራንም።

በዚህ ምክንያት የብዙ ምእመናን ልብ ወደኋላ እንዲያፈገፍግ ምክንያት እንዳንሆን መጠንቀቅ ይገባናል፤ በዚህ ሁሉ የእግዚአብሔር ቁጣ በእኛና በሕዝባችን በሀገራችንና በዓለማችን እንዳይገለጥ እነሆ አሁንም ቃሉ ተመለሱ እያለ ነውና እንመለስ፤ እየተዛባ ያለው ሁሉ መስተካከል ይችላል፤ በሃይማኖት የማይቻል ነገር እንዳለ የሚያስብ ካለ ሃይማኖት የሌለው እሱ ነው።

- ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ፦
- ክቡራን የበዓሉ ተሳታፊዎች ፦

እኛ የሃይማኖት አባቶች ከሌላ የምንዋሰው ንግግርና አስተምህሮ የለንም። ዐሠርቱ ቃላትን ማክበርና መተግበር ማስተማርና ማሥረጽ በቂያችን ነው፡፡ ምክንያቱም ከዐሠርቱ ቃላት የበለጠ ሌላ ሕግ በዓለም ስለሌለ ማለት ነው፤ ቢኖርም ከሱ የተኮረጀ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ የኛ አስተምህሮ አትግደል እንጂ ግደል ሊሆን አይችልም፤ የኛ ተግሣጽ አትስረቅ፣ አትዋሽ፣ የሌላውን አትመኝ፣ አታመንዝር የሚል እንጂ በተመሳሳይ የፆታ ጋብቻ ወደ ነውረ ኃጢአት ተሠማራ የሚል ትምህርት መቼውም ቢሆን ከቶ ሊኖረን አይችልም፡፡

እውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ ከዚህ ውጭ ከዘመኑ የወሬ ሱሰኛ መሣሪያን እየተበደርን ከቅዱስ ወንጌሉ ጋር የሚጣረስ ንግግርና አስተምህሮ ማስተላለፍ ለምን አስፈለገ? ይህ ለኛ ኃሣር እንጂ ክብር ሊያስገኝልን አይችልም፤ ከእንደዚህ ያለ ድርጊትም መራቅ አለብን፤ የኛ ደንበኛና ዘላለማዊ ፖለቲካ ቅዱስ ወንጌል ነው፤ ዘላለማዊውን ትተን ጊዜያዊውን፣ መለኮታዊውን ትተን ሰዋዊውን አንከተል፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/zh8vEO0hq9Y?si=cIg6yQmyvR1N0h_t

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
የካቲት 24- ጸሎታቸው በረከታቸው ቃልኪዳናቸው በእኛ በተዋሕዶ ልጆች ሁሉ ላይ አድሮብን ይኑርና የኢትዮጵያ ብርሃኗ ሐዲስ ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ያደረጉት ተአምር ይህ ነው፡- ‹‹ጸሎታቸው›› ያልነው ‹‹የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለችና›› (ያዕ 5፡16) ቅድመ እግዚአብሔርን ትደርሳለችና ነው፡፡ መዝ 33፡15፡፡ ‹‹በረከታቸውም›› ያልነው የጻድቅ መታሰቢያ ለኃጥአን ሥርየትን ያሰጣል የነፍስ ይሆናልና ነው፡፡ (ምሳ 10፡7፣ ማቴ 10፡40-42፡፡) ‹‹ቃልኪዳናቸውም በእኛ ላይ ይደር›› ማለታችን እግዚአብሔር ለሙሴ ሕጉን ሲሰጠው እንዲህ ብሎ ነግሮት ነበርና ‹‹ትእዛዜን ለሚጠብቁ እስከሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝ›› ብሏልና (ዘጸ 20፡26) ስለዚህም በሃይማኖት ትውልድ ለሆኑ በቃልኪዳን ምሕረት እንደሚገኝ አምላካችን ተስፋ ስለሰጠን እንዲህ አልን፡፡ ‹‹ያደረጉት ተአምር›› ማለታችንም ጌታችን በአምላካዊ ቃሉ በቅዱስ ወንጌሉ ‹‹በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ተአምር ያደርጋል፤ ከእኔም የበለጠ ያደርጋል›› (ዮሐ 14፡12) እንዳለ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ያደረጉት ተአምር ይህ ነው፡-

ወረብ በሚባል አገር የአባችንን የተክለ ሃይማኖትን መታሰቢያ በዓል የሚያደርግ አንድ ባለጸጋ ሰው ነበር፡፡ ቁጥራቸውም ብዙ የሆኑ ከብቶች አሉት፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ለአቡ ተክለ ሃይማኖት በዓል ለድኆች አርዶ ለማብላት 'ለዝክር የሚሆኑ ናቸው' ብሎ ለይቶ የሚጠብቋቸውን እረኞች አዘጋጀ፡፡ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት በዓል በሆነ ጊዜ ከምእመናን ጋራ በቤተክርስቲያን ተገኝቶ የአባታችንን ገድል እየሰማ ሳለ ሰዎች ከመንደር መጥተው "አሽከሮችህ በቤት ውስጥ ያለህን ንብረት ከብቶችህንና የባለቤትህንም መቀነት ሳይቀር ወስደው ኮብልለዋል" ብለው ነገሩት፡፡ በዚህም ጊዜ ያ አማኝ ባለጸጋ "እኔ ምን ቸገረኝ! የምሰማው የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን ገድል ነው፡፡ እርሳቸው ደግሞ ብዙ ተአምራትን እንደሚያደርጉ ይኸው በገድላቸው እረዳለሁ፡፡ ከብቶቹንስ ይጠብቁ የነበሩት የእርሳቸው አገልጋዮች አይደሉምን? ስለዚህ አባቴ ተክለ ሃይማኖት የተዘረፈውን ንብረት ባለበት ቦታ ተረከቡኝ" በማለት በእምነት አስረክቦ በረከት የሚገኝበትን ዝክራቸውን አዘክሮ መታሰቢያቸውን አድርጎ ወደቤቱ ገባ፡፡

ይኽም ባለጸጋ ወደመኝታው ሲሄድ "በአገልጋዮቼ አማካኝነት በጠፉት ንብረቶች ላይ እርስዎ የፈቀዱትን ያድርጉ፡፡ ድንቅ ተአምራትን ሁልጊዜ የሚሠሩ አባቴ እኔ ለዕረፍትዎ ቀን መታሰቢያ የሚሆነውን ዝክር የማዘክርበት ነገር እንደሌለኝ እርስዎ ያውቃሉ፡፡ አሁንም የወደዱትን ያድርጉ" ብሎ ደጋግሞ አመለከተ፡፡ ወዲያውም ይህን እንዳመለከተ አንቀላፋ፡፡ በዚያው ሌሊት አባታችን ተክለ ሃይማኖት በሕልም ተገለጡለት፡፡
ይኸውም በአካለ ነፍስ ነው፡፡ የክብር ባለቤት ጌታችን ሲያስተምር "እኔ የአብርሃም አምላክ የይስሃቅ አምላክ የያዕቆብ አምላክ ነኝ፣ የሕያዋን አምላክ እንጂ የሙታን አምላክ አይደለሁም" (ማቴ 22:31) እንዳለ ጻድቃን በነፍስ ሕያዋን ናቸውና አባታችን ተክለ ሃይማኖት ተገልጠውለት እንዲህ አሉት፡- "አንተ ሰው በማለዳ ፈጥነህ ተነሥ እነዚህ አገልጋዮችህን እንዲህ ካለች ዛፍ ሥር ተሰውረዋልና ከዚያ ታገኛቸዋለህ" ብለው ነገሩት፡፡

ሰውየውም በማለዳ በቅሎውን ጭኖ አባታችን ወዳመለከቱት ቦታ ሄደ፡፡ በዚያም አባታችን እንደነገሩት አገልጋዮቹን በዛፉ ሥር አገኛቸው፡፡ እነርሱም ንብረቱን እንዳያንቀሳቅሱ ምድር ጭልሞባቸው መሬት ለመሬት ወዲያና ወዲህ እየተመላለሱ ግራ ገብቷቸው ሲደነባበሩ ነበር፡፡ ሰውየውም ይዟቸው እየመራ ወደቤቱ ወሰዳቸው፡፡ ነቢዩ ኤልሳዕ የሶርያ ጮፍሮችን ዐይኖቻቸውን በተአምራት አሳውሮ ወደ ከተማ እንዳስገባቸው አባታችን ተክለ ሃይማኖትም በተሰጣቸው ታላቅ ጸጋ ይህንን አደረጉ፡፡ 2ኘ ነገ 6፡18፡፡

ከዚህም በመቀጠል ሰውየው አገልጋዮቹን ቆጠራቸው፡፡ ከመካከላቸውም አንዱ የለም ነበር፡፡ አገልጋዮቹንም የት እንደሄደ ሲጠይቃቸው እነርሱም "እርሱማ የባለቤትህን መቀነት ሸጦ ጠላ ገዝቶልን ሊያመጣ ሄዷል፡፡ እርሱም 'ገዝቼ እስክመጣ ድረስ በዚህች ዛፍ ሥር አረፍ ብላችሁ ጠብቁኝ' ብሎን ነበር፡፡ ከሄደም በኃላ ዐይኖቻችን ድንገት ጠፉ" አሉት፡፡ እርሱም ሁሉንም ወደቤት አስገባቸው፡፡ ያ ጠፋ የተባለው አገልጋይም ደጅ ቆሞ "ቤቶች ጠላ ካላችሁ አንዲት መቀነት ልስጣችሁና ግዙኝ" እያለ ሲጮህ ሰሙት፡፡ ወጥተውም ያዙትና ጌታው ካለበት ቦታ አደረሱት፡፡ ከጌታውም ፊት በቆመ ጊዜ እጅግ ደነገጠ፡፡ ፊቱም ጠቆረ፡፡ ጉልበቱም እየተብረከረከ "እኔ ይህንን መቀነት ሌላ አገር የምሸጠው ነበር የመሰለኝ፡፡ ወደቤታችን እንደተመለስኩ ፈጽሞ አላወቅሁም" ብሎ ፈጽሞ አደነቀ፡፡ ይህንንም ድንቅ ተአምር ያዩ ሰዎች ምስጋና የሚገባውን አምላክ ልዑል እግዚአብሔርን አመሰገኑት፡፡ ነቢዩ ቅዱስ ዳዊት "ለቅኖች ምስጋና ይገባል" (መዝ 32፡2) እንዳለ እነዚያ ሰዎች ድንቅ ተአምር ያደረጉትን አባታችን ተክለ ሃይማኖትን 'ዕፁብ ዕፁብ' ብለው አመሰገኑ፡፡ የቅዱስ አባታችን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ጸሎታቸው በረከታቸው የተዋሕዶ ልጆች በሆንን በሁላችን ላይ አድሮብን ይኑር፡፡
+ + +

ደግመኛም በዚኽች ዕለት ከሃዲያኑ ነገሥታት በዲዮቅልጥያኖስና በመክስምያኖስ ዘመን የነበረው አባ አጋቢጦስ ዕረፍቱ ነው፡፡ የዚኽም ቅዱስ አባት ወላጆቹ ከልጅነቱ ጀምሮ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እያስተማሩ አሳድገውታል፡፡ ዲቁና ተሹሞ እያገለገለ ከኖረ በኋላ ወደ አንድ ገዳም በመሄድ በዚያም አረጋዊያን መነኮሳትን የሚረዳ ሆነ፡፡ አረጋውያንንም እያገለገለ በጾም በጸሎት በስግደት በታላቅ ተጋድሎ ኖረ፡፡ ከጠዋት እስከ ማታም ከጾመ በኋላ የሚመገበው የሽንብራ አሠር ሆነ፡፡ ከእንቅልፍም ጋር ሊታገል በወደደ ጊዜ ከሽንብራው አሠር ጋር አመድ እየጨመረ ይመገባል፡፡ በዚህም ተጋድሎ ውስጥ እያለ ኃይሉ ግን ይጨምርለት ነበር፡፡ የአረጋውያንንም አገለግሎቱን ፈጽሞ አያቋርጥም፣ ሲጠራቸውም ‹‹ጌቶቼ›› እያለ ነው፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር የሚያስደንቁ ታላላቅ የሆኑ ተአምራትን በእጆቹ ገለጠ፡፡ ከሰውም ከእንስሳትም አስጨናቂ የሆኑ በሽታዎችን በጸሎቱ አስወገደ፡፡ ብዙ ሰዎችን ያጠፋውን ከይሲ ቅዱስ አጋቢጦስ በጸሎቱ ኃይል ገደለው፡፡ እንደ ዕንጨት ደርቃ ብዙ በጭንቅ በአሳር የኖረችን አንዲት ብላቴናም ፈወሳት፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

መልካም እለተ ሰንበት ይሁንላችሁ 🙏🙏🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/VG-gyo8To4c?si=nCvIor5jWJXlESKP

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እርሶ በምን ተሸግረዋል ? እስቲ በውስጥ መስመር ያማክሩኝ ከሀገር ውጪ ላላችሁም በአላችሁበት ሰርቼ እልካለው ባላችሁበት መፍትሄ እንፈልጋለን እኔን ማናገር እና ማውራት ለምትፈልጉ በሙሉ ይሄንን በመንካት  @Meregta በሜሴጅ ማውራት መነጋገር እንችላለን ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የካቲት 27/2016 #የአለም_መድኃኒት_መድኃኔዓለም

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ አምላክ አሜን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን #መድኃኔአለም ኢየሱስ ክርስቶስ አለምን ለማዳን ዋጋ ለከፈለበት ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን

👉 #መድኃኔዓለም ማለት ዓለምን ያዳነ የዓለም መድኃኒት ማለት ነው ሰው በመበደሉ ምክንያት ከክብር ተዋርዶ ይኖር ነበር #ኢየሱስ_ክርስቶስ ግን የተዋረደውን ሰው እርሱ በመስቀል ተሰቅሎ ወደ ቀደመ ክብሩ መለሰው ምን ዓይነት ፍቅር ነው ስለኛ የሰዉ ልጆች ሲል በመስቀል ላይ ዋለ

👉ራቁትን መሰቀል አሳፋሪ ነገር እንደሆነ እናውቀዋለን ጌታ ግን እኛን ለማዳን ብሎ #ራቁቱን_ተሰቀለ በፈጠራቸው ፍጥረታት ተናቀ ተተፋበት

👉እኛን ትእግስት ሊያስተምረን እነርሱን ማጥፋት እየቻለ እርሱ ግን በፍቅር እያየ የሚያረጉትን አያውቁምና አባት ሆይ ይቅር በላቸው ይል ነበር #ክርስቶስ እኛን ልጆቹን ለማዳን ሲሰድቡት አልተሳደበም ሲንቁት አልናቃቸውም ሲታበዩበት ሁሉ እርሱ ግን በትሕትና ያያቸው ነበር

👉አይሁድ በ5 ችንካር ነበር የቸነከሩት ጌታችን በሚሰቀል ጊዜ የተገኙ እናታችን #ማርያምና ሐዋርያው #ቅዱስ_ዮሐንስ ነበሩ አኛም #በመስቀሉ ስር ለመገኘት ከፈለግን ትዕግስትን ፍቅርን ትሕትናን መለማመድ ይኖርብናል

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በፈቃድህ በተሰቀልክ ጊዜ በቀኝህ ለተሰቀለዉ ወንበዴ የገነት መክፈቻን እንደሰጠኸዉ ወደ ገነትም እንዳስገባከዉ በኃጢአት የወደቅን ልጆችህን ነፍስና ስጋችንን አክብረህ ብርሀነ ፀጋህን አብራልን

👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የሚታሠቡት ፃድቁ አባታችን አቡነ #መብአ_ፅዮን በምልጃ ፀሎታቸዉ ሁላችንንም ይጠብቁን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እርግጠኛ ባልሆንም እንደሚመስለኝ ግን ለምሳሌ ዛሬ ማክሰኞ ከሆነ ከ12 ሰዓት ካለፈ የእሮብ ሌሊት ነው ስለዚህ እንደ እሮብ ነው የሚቆጠረው...

ቀን ሲቆጠር መጀመርያ ጨለማ ከዛ ብርሃን ነው አንድ ቀን የሚሆነው

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ልመና ለአምላክ
❤️/channel/silase❤️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አባታችን ጻዲቁ አቡነሀብተማርያም
በረከታቸው ይደርብን ከመከራ ይሰውሩን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://vm.tiktok.com/ZMMYLyhkB/

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሕይወተ ወራዙት

ግብረ አውናን የሚያስከትለው ጉዳት

ግብረ አውናን ውጥረትን ለፈጠረ አንድ ችግር የተሳሳተ አማራጭን መጠቀም እንደመሆኑ መጠን በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ብርታትና ጥንካሬን የሚጠይቁ መንገዶችን እንድንሸሽ ያለማምዳሉ፡፡ ሰነፍ እንድንሆን ያደርጋሉ፡፡ ግብረ አውናን ኃጢአት እንደመሆኑ መጠን በዚህ ዓለምና በወዲያኛው ዓለም ቅጣትን ያስከትላል፡፡ በዚህ ዓለም እንደ አውናን መቀሠፍ (ዘፍ. 38፡9)፣ ሰላም ማጣት፣ ቁጭት፣ ጸጸት፣ ጭንቀት፣ መረበሽ፣ ንጽሕ ያለመሆን ስሜት ወዘተ ያስከትላል፡፡ ካደገ ደግሞ ወደ ዝሙትና ግብረ ሰዶም መምራት፣ ተስፋ መቁረጥ፣ አጉል ጸጸት (ኀፍረተ አካልን ተናዶ እስከ መቁረጥ ሊያደርስ ይችላል)፣ አጉል ትሕትና (መንፈሳዊ አገልጋዮች ከሆኑ አገልግሎቱ ንጽሕናን የሚፈልግ በመሆኑ ኑሮአቸውና መንፈሳዊ አገልግሎታቸው ሳይጣጣም ሲቀር ማገልገል አይገባኝም በማለት ከትሩፋትና ከበጎ ሥራ ራሳቸውን የሚያሸሹ አሉ)፡፡ ነገር ግን ክፉ ሥራን እንጂ የትሩፋት ሥራን መሸሽ በምንም መልኩ አይበጅም፡፡ በጋብቻ ውስጥ አንዱ ለሌላው ወገን ደስታና እርካታ ማሰቡ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ሴጋ ደግሞ የራስን ደስታና እርካታ ብቻ የማሰብ ልምድን ያሳድጋል፡፡

ከግብረ አውናን እንዴት መላቀቅ ይቻላል

1. የማር ጠብታ ልብስ ላይ የወደቀ እንደሆነ በፍጹም የሚለቅ አይመስልም ነገር ግን ትንሽ ለቅለቅ ያደርጉት እንደሆነ ወዲያውኑ ይለቃል፡፡ ይህ ክፉ ልማድም እንደማር በቀላሉ ባይሆንም ከልብ በመጸጸት በጠንካራ መንፈስ ከተነሡ ሊያስወግዱት ይቻላል፡፡ ተስፈ አለመቁረጥ፡፡
2. መሰንጋት ልማድ ነው፡፡ ልማድ ደግሞ በልማድ ይሸነፋል፡፡ ከዚህ ልማድ ጋር ለመዋጋት ከመነሣትህ በፊት ‹‹ይህን ልማድ ምን ያህል ከልቤ ጠልቼዋለሁ›› በማለት ራስን መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡ መላልሰህ የምትሰናከለው ሳትጸጸት ቀርተህ ሳይሆን ጣዕሙ ከልቡናህ ስላለና ጎጂነቱ ዘልቆ ወደ ልብህ ስላልገባ ነው፡፡ እሱን ለማውጣት መታገል ያስፈልጋል- በጾም፣ ጸሎት፣ ስግዳት፣ መጻሕፍትን ማንበብ፣ መዝሙራትን መዘመር... ግድ ይላል፡፡
3. ‹‹ተዐቅቦ›› መከልከል- መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡ ወደዚህ መጥፎ ሀሳብ ልቡናህን የሚስቡትን ነገሮች ከማየት፣ ከመስማት፣ ከመንካትና ከመሳሰሉት ነው፡፡ የሴቶችን ገላ በፊልም በአካልም ከማየት መቆጠብ፣ በመዋኛና በመጠመቂያ ቦታዎች ራስህን ጠብቅ የሴት ልጅን መልክና ቅርጽ መርዘህና አትኩረህ አትመልከት፣ ስለ ዝሙት የሚያሳስቡ ስዕሎችን፣ ጽሑፎችንና ወሬዎችን መሸሽ ቦታ አለመስጠት ንቆ ማለፍ ያስፈልጋል፡፡
4. ዘወትር ልቡናህ የሚጠመድበትን ነገር ፈልገህ አድርግ፡፡ ቦዘኔ አትሁን፣ ትጉህ ሠራተኛ ሁን፣ ሥራህም በእንቅስቃሴ የተሞላ ወይም አእምሮን ያለ ዕረፍት የሚያሠራ ይሁን፡፡ በትርፍ ሰዓትህ የሚነበብ ወይም ሌላ የሚሠራ ሥራ ፈጥረህ ሥራ፡፡ የዝሙት ማረገብያው ቦዘኔነት ነውና።
5. ‹‹ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው›› የሚለውን ቃል አስብ፡፡ በዚህ ክፉ ልማድ ተጠምደህ ሳለ ለብቻህ መሆንን አትውደድ፡፡ ቢቻልህ አኗኗርህና መኝታህ ከምታፍረውና ከምታከብረው ሰው ጋር ይሁን፡፡ ከብቸኝነት ይልቅ መወያየትን ይልቁንም መንፈሳዊ ውይይትን ዘወትር አድርግ፡፡ በጸሎት ከሚረዳህ መንፈሳዊያን መምህራንና አባቶች ጋር ጊዜ ማሳለፍን ውደድ፡፡
6. እንቅልፍ የያዘህ ስለ መሰለ ብቻ ወደ መኝታ አትሂድ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ስትተኛ ውለህ እንቅልፍ ያምርሃልና፡፡ ነገር ግን ሰይጣን ሊፈትንህ ከሆነ በምትተኛበት ጊዜ እንቅልፍ ከአይንህ ይርቃል፡፡ ተከትሎም ፈተናው ይመጣና ወደ ዝሙት ሕሊናህ ይሳባል፡፡ ሰውነትህን በመዳበስ ፍትወትህን ለማርካት ትጥራለህ፡፡ ስለዚህ ከመተኛትህ በፊት

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🙏 ..#አንተ_ያከበርካትን....🕯🕯

🙏 ..እኔ አከብራት ዘንድ እበቃ ይሆን?
እርሷን ለማመስገን ቅዱስ ገብርኤልን
መምሰል ይጠበቅብኝ ይሆን?
የነብየ እግዚአብሔር ቅ/ዮሐንስ እናት
ቅድስት ኤልሳቤጥ እንኳ
የጌታዬ እናት ወደኔ ትመጭ ዘንድ
እኔ ማነኝ ካለች እኔ አመሠግናት ዘንድ እበቃ ይሆን?
ወንጌላዊ(ፍቁረ እግዚእ)
ቅዱስ ዮሐንስ ስለፍጹም ፍቅርህ እስከ
መስቀል ቢከተልህ እናትህን በኑዛዜ
ተረከባት እኔስ እናትህን እቀበል ዘንድ
ፍጹም ፍቅርህ በልቤ ይኖር ይሆን?
አምላኬ አሁንም እናትህን አውቃትና
እቀበላት ዘንድ ፍጹም ፍቅርህን በልቤ አጽናልኝ

🕯..ጌታዬ ሆይ እባክህ የእናትህን ፍቅር ጨምርልኝ 🙏🙏🙏


ወር በገባ በቀን ...❷❶...🕯

👉...አምላክን በድንግልና ጸንሳ በድንግልና የወለደች እናታችን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት....🕯

   🕯...ጥበቃዋ አይለየን በአማላጅነቷ ጥላ ዋሉልኝ...🙏
/channel/silase

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

+• አሥራት ለምን ታወጣለህ? •+

አባ ታድሮስ ማላቲ “Stories for the Youth” በሚል ርዕስ ለወጣቶች ባዘጋጁት መጽሐፍ ላይ፥ ስለ አሥራት ጥቅም አንድ አጭር ታሪክ ጸፈዋል፤ እንደሚከተለው ተርጉሜ አቅርቤዋለሁ። 
--
ከሃያ ዓመት ቆይታ በኋላ፥ በካሊፎርኒያ ከተማ አንድ የመንፈስ ልጄን አገኘሁት እና ወደ ቤቱ ወሰደኝ። ቤቱ እጅግ ግዙፍ እና ውብ ነበር። አብረን ተቀምጠን ሳለም፥ “አባ፥ የዛኔ በካሊፎርኒያ መኖር ስጀምር ትዝ ይልዎታል? ኑሮን ለማሸነፍ ትግል ላይ ነበርኩ፥ አሁን ግን እግዚአብሔር ከጠየቅሁትም በላይ ሰጥቶኛል።” አለኝ። 

እኔም “ይህ የእግዚአብሔር ቸርነት ነው። በእውነቱ አምላካችን ያስብልናልና እናመሰግነዋለን።” አልኩት። 

እርሱም ቀጠለና፥ “እግዚአብሔር ምን ያህል ቸርነት እንዳደረገልኝ ያውቃሉ? ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ጀምሮ ‘እዚህ በምድር ላይ ስኬታማ ብሆን፥ መንግሥተ ሰማያትን ግን ካጣሁ ምን እጠቀማለሁ?’ እያልኩ መብሰልሰል ጀመርኩ። ከዚያ አንድ ቀን፥ በአምላኬ ፊት ተንበርክኬ፥ ሁኔታዬ ምንም ያህል ቢከፋ፥ ከማገኘው ገቢ ላይ አሥራቴን ላለመንካት ቃል ገባሁለት። አሥራት የእግዚአብሔር ነዋ! ቀጠልኩና ‘ጌታዬ ሆይ፥ ሁሉም ያንተ ስጦታ ነውና፥ ከዘጠኝ እጁ ላይ ደግሞ በእዚህ በአሜሪካም ሆነ በግብጽ ላሉ ነዳያን እመጸውታለሁ።’ አልኩት። 

“ከዚያም በልግስና መስጠት ጀመርኩ፤ የገነት በሮችም ተከፈቱልኝ! በእውነቱ እግዚአብሔር ከሚያስፈልገኝ በላይ ሰጠኝ። አንዳንዴ፥ ተንበርክኬ እያለቀስኩ፥ ‘እባክህ በቃህ አምላኬ! ከዚህ በላይ ከሰጠኸኝ የሃብት ብዛት ነፍሴን እንዳያጠፋት እፈራለሁ’ ብዬ እለምነው ነበር። እርሱ ግን እንዲህ እያልኩም የበለጠ ይሰጠኝ ነበር።”

🖋 Fresenbet G.Y Adhanom

🪔✨🪔✨🪔✨🪔✨🪔✨🪔
@MENFESAWItsufoche
🪔✨🪔✨🪔✨🪔✨🪔✨🪔

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ይህ ለኛ የሞራል ዝቅጠት ያስከትልብናል፤ ሕዝቡም እግዚአብሔርም ከኛ የሚጠብቁት ትክክለኛውን ቃለ ቅዱስ ወንጌል ማስተማር ነው፤ ለዓለሙ ፖለቲካ ግን የራሱ ባለቤቶች አሉለት፡፡ እኛ በፖለቲከኞች ላይ ያለን ሥልጣንና መብት ማስተማርና መምከር ነው፤ ያም ሆኖ አንዱን በመደገፍ ሌላውን በመንቀፍ ሳይሆን ሁሉም እኩል ልጆቻችን መሆናቸውን አውቀን በፍቅር በመመልከት ነው፡፡ ሲጋጩብንም የማስታረቅና የማቀራረብ፤ የመምከርና የማሳመን እንጂ ወደ አንዱ ተለጥፎ ሌላውን ዘልፎ መናገር የቆምንለት ቅዱስ ወንጌል አይፈቅድልንም፡፡

ፓለቲከኞችም ባልዋሉበትና ባልተፈቀደላቸው፣ ሌላው ቀርቶ የተቋቋሙበት ሕገ መንግሥቱ እንኳ የማይፈቅድላቸውን በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ላይ ጣልቃ እየገቡ የግል ፍላጎትና ዓላማ ለማስፈጸም መሞከር ፍጹም ስሕተት ነው። ተቀባይነትም የለውም። ለቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ለራሳቸው ለፖለቲከኞቹም አይበጅም፡፡ ሁሉም ድንበሩን ጠብቆ በጋራ ጉዳዮች ላይ በፍቅርና በመከባበር ተመካክሮና ተግባብቶ መስራት ያሻል። በዚህ መንፈስ ቤተ ክርስቲያንና መንግሥት ተናበው ቢሰሩ በሀገር ላይ ሰላም ይሰፍናል፣ ልማት ይፋጠናል፣ ዕድገት ይመዘገባል። ስለዚህም በዚህ ዙሪያ ሁላችንም ከምር ልናስብበት ይገባል።

- ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ፦
- ክቡራን የበዓሉ ተሳታፊዎች ፦

በዛሬው ዕለት እያከበርነው ያለ በዓለ ሢመተ ክህነት ዓላማው የተሰጠንን ተልእኮ በማሰብ ለተሻለ መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የመነቃቃትና የመነሣሣት መንፈስ ለመፍጠር ነው፡፡

ከዚህ አኳያ ባለፉት ዓመታት ያጋጠሙንን ፈተናዎች በመለየት፣ በቀጣዩ እንዳይደገሙ ነቅተንና ተግተን መስራት ያስፈልጋል፡፡ ባለፉት ዓመታት እጅግ በጣም አስቀያሚ ነገሮችና ፈተናዎች በቤተ ክርስቲያናችን ላይ ተከሥተዋል፤ አሁንም አልቆሙም፡፡

በየአካባቢው መብቱ ተነፍጎ በቀየው እንዳይኖር በልዩ ልዩ ምክንያት እየተፈናቀለ ያለውን ሕዝባችን ለማጽናናትና ለመደገፍ በአንድነት መቆም ይገባናል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ልጆችዋን የመንከባከብ የመጠበቅና ዕንባቸውን በማበስ ፍትሕንና ርትዕን የማንገሥ ኃላፊነት አለባት፤ ይህንን ኃላፊነት በአስተውሎት ልትወጣው ይገባል፡፡ በመሆኑም መጪው ጊዜ ቤተ ክርስቲያን በውስጧ ያለው ውጣ ውረድ በማስተካከል መልክ የምታስይዝበት፣ የተፈናቀሉ ልጆችዋን የምታጽናናበትና የምታግዝበት እንዲሁም ለፈተና የተጋለጡ ልጆቻችን ሁሉ የዜግነት፣ የሃይማኖትና የሰብአዊ መብታቸው እንዲከበር ሰላም ፍቅር፣ ፍትሕ፣ አንድነት በሀገር እንዲነግሥ ሁሉም ድንበሩን ጠብቆ ሕዝቡን የሚያገለግልበት ዓመት እንዲሆን ከመቼውም ጊዜ በላይ በርትተን መሥራት አለብን፡፡ ይህንን ብናደርግ በእውነትም ወደ እግዚአብሔር ተመልሰናል ማለት ነው፤ እኛ ከተመለስን እሱም ወደኛ መመለሱ አይጠረጠርም፤ ስለዚህ አሁንም ወደ እሱ እንመለስ፡፡

በመጨረሻም በሀገራችን ላይ ይልቁንም በቤተክርስቲያናችን ላይ ያለው ድባብ እጅግ በጣም አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ለማንኛችንም ግልፅ ነው፡፡ በመሆኑም ካህናትና ምእመናን በሃይማኖት ጸንተው እንዲቆሙ በቤተክርስቲያናችን ላይ እጃቸውን እየዘረጉ የሚገኙ ሁሉ ቤተ ክርስቲያን ጠላታቸው አይደለችምና እጃቸውን እንዲያነሡ፣ መንግሥትም ለቤተክርስቲያን የሕግ ከለላና ጥበቃ እንዲያደርግ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

መልካም በዓለ ሢመት ያድርግልን
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

የካቲት ፳፬ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

#MSKLideta #ቅድስት_ልደታ #ደብረ_መድኃኒት_መድኃኔዓለም

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የቤተ ክርስቲያን ባህርያት የሚባሉትን አራቱን ጥቀስ /ሺ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የቅዱስ አጋቢጦስ ተጋድሎውና የኃይሉ ጽናት ተአምራት አድራጊነቱም በቦታው ሁሉ በተሰማ ጊዜ ስሙ ሉክያኖስ የሚባል መኮንን ወደ እርሱ ጭፍሮቹን ልኮ ቅዱስ አጋቢጦስን አስመጣውና ያለ ፈቃዱ በግዳጅ የጭፍሮች አለቃ አድርጎ ሾመው፡፡ ቅዱስ አጋቢጦስ ግን እንደቀድሞው ይተጋ ነበር እንጂ ጽኑ የሆነ ተጋድሎውን አልተወም ነበር፡፡ ዲዮቅልጥያኖስንና መክስምያኖስን እግዚአብሔር ካጠፋቸው በኋላ ደገኛው ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ነገሠ፡፡ በዚህም ጊዜ ቅዱስ አጋቢጦስ ከጭፍሮች አለቃነቱ ተለይቶ በዓት አጽንቶ በተጋድሎው ለመኖር ምክንያትን የሚሻ ሆነ፡፡ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እጅግ አድርጎ የሚወደው መልከ መልካም የሆነ አንድ ብላቴና ነበር፡፡ በዚህም ብላቴና ላይ ክፉ ጋኔን አድሮበት በቀንና በሌሊት በእጅጉ የሚያሠቃየው ሆነ፡፡ ቅዱስ አጋቢጦስን ከሚያውቁት ሰዎች ውስጥ አንዱ ‹‹የወታደሮች አለቃ አጋቢጦስ ቢመጣ ከዚህ ሕማምህ ይፈውስህ ነበር›› ብሎ ለታማሚው ነገረው፡፡ ታማሚውም ‹‹በንጉሥ ጭፍራ ሥርዓት ውስጥ ያለ በውኑ ይህን ማድረግ ይችላልን?›› አለው፡፡ ሰውዬውም የቅዱስ አጋቢጦስን ገድሉንና ሥራውን ሁሉ ነገረው፡፡ ጋኔን የያዘው ብላቴናም ‹‹ከዚህ ሕማሜ ይፈውሰኝ ዘንድ የወታደሮች አለቃ አጋቢጦስ ፈጥናችሁ አምጡልኝ›› አለ፡፡ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስም ይህንን ባወቀ ጊዜ ቅዱስ አጋቢጦስን እንዲያመጡት አዘዘ፡፡ ቅዱስ አጋቢጦስም ከመጣ በኋላ በሕመምተኛው ላይ በመስቀል ምልክት አማትቦ ከጸለየለት በኋላ ያደረበትን ክፉ ጋኔን ከውስጡ አወጣለትና ፈወሰው፡፡ ንጉሡም በዚህ እጅግ ደስ ብሎት ቅዱስ አጋቢጦስን ‹‹ምን እንዳደርግልህ ትወዳለህ?›› አለው፡፡ ቅዱስ አጋቢጦስም ‹‹ከወታደሮች የአለቃነት ሥራ አሰናብተኝ›› አለው፡፡ እንደቃሉም አሰናበተውና አባ አጋቢጦስ ወደቀደመች የተጋድሎ ቦታው ተመለሰ፡፡ በዚያም ለብዙ ዘመናት እጅግ አብዝቶ እየተጋደለ ኖረ፡፡

ከዚህም በኋላ የዚያች አገር ኤጲስቆጶስ ቅዱስ አጋቢጦስን ቅስና ሾመው፡፡ ኤጲስቆጰሱም ባረፈ ጊዜ አባ አጋቢጦስን ኤጲስቆጶስነት ይሾምላቸው ዘንድ የአገሪቱ ሰዎች ሊቀ ጳጳሳቱን ለመኑት፡፡ እርሱም ሾመላቸው፡፡ አባ አጋቢጦስም መልካም በሆነ አጠባበቅ ጠበቃቸው፡፡ እግዚአብሔርም ትንቢት የመናገርን ጸጋ፣ የተሰወረውንም ሁሉ የማወቅ ጸጋ ሰጠው፡፡ የዕውራንን ዐይኖች በመግለጥ፣ ለምጻሞችን በማንጻት ብዙ ድውያንንም በጸሎቱ የሚፈውሳቸው ሆነ፡፡ በሥውር ኃጢአት የሚሠሩትን ሰዎች ሁሉ ኃጢአታቸውን በግልጽ እያየ የሚሥጻቸው ሆነ፡፡ በንስሓም እስኪመለሱ ድረስ ከመቅደስ ያርቃቸዋል፡፡ ዳግመኛም በገድሉ መጽሐፍ ተጽፎ እንደተገኘ የታላቅን ወንዝ ወራጅ ውኃ በመስቀል ባርኮ በማቆም በሌላ አቅጣጫ እንዲፈስ አደረገው፡፡ ያማረና መልካም የሆነ ተጋድሎውንና አገልግሎቱን ፈጽሞ በዚህች ዕለት ዐረፈ፡፡ የአባ አጋቢጦስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡

(ምንጭ፡- የየካቲትር ወር ስንክሳር፣ ተአምረ አቡነ ተክለ ሃይማኖት-ደብረ አሚን ተክለ ሃይማኖት ምክሐ ደናግል ሰ/ት/ቤት በ1995 ዓ.ም ያሳተመው ተአምር)
ከገድላት አንደበት
✞ ✞ ✞

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/HR3GdAiBb3M

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የመንደድ ሲህር፡፡
ይህ ሲህር ቀላል የሚባሉ አይነት ሲሆን ቀላል ያደረገውም የህመሙ ቀላል መስሎ ህይወትን የማመሰቃቀሉ ሁኔታ እንጂ ለህክምናው ከባድ ናቸው፡፡
1.የውስጥ እግር መቃጠል፡፡ ይህም ብዙውን ግዜ ማታ ላይ ይጨምራል፡፡
2..የሆድ መቃጠል፡፡ ይህም ሆድ ከምንግዜውም በላይ ሞቅታ ይኖረዋል፡፡ በቀዝቃዛ ነገር ሲነካም እጅግ ያማል፡፡
3.ከሚባለው በላይ የጨጓራ ተጠቂ መሆን፡፡ በምንም መልኩ በህክምና አልድን ማለት ወተት ቢጠጡ መድሀኒት ቢቅሙ ሲነዱ መዋል፡፡
4.የመላ ሰውነት መንደድ፡፡ ይህ ብዙውን ግዜ ከመግሪብ ቡሃላ የሚፈጠር ሲሆን በቀዝቃዛ ውሃ እንኳን ታጥበው ሙቀቱ አይወጣላቸውም፡፡
5.የአፍ መሽተት ይህን በምንም መደበቅ አይችሉም ማስክ እንኳ ቢያደርጉ በራሳቸው የአፍ ሽታ እራሳቸው ይደነግጣሉ፡፡
6.የራስ ሙቀት ይህ ሙቀት ከራስ ምታት ጋር አይገናኝም ነገር ግን ብዙ ላቦት አለው፡፡ እራሳቸውም በቀዝቃዛ ቦታ ላይ ቢያገኙት ከሌላው በተለየ ሁኔታ መጨስ ይጀምራል፡፡
7.በትንሽ ነገሮች መበሳጨት ሰውን ለመደብደብ መሞከር፡፡ ያናደዳቸው ሰው ተጎድቶ ካላዩ አይወጣላቸውም፡፡
8.እነኚህ ሰዎች እራሳቸውን ሊስቱ ይችላሉ ነገር ግን ከ ሶስት ቀን ወይም ከዛ በታች መንቃት አይችሉም፡፡
9.ሰዎችን መቅረብ በጣም ይጠላሉ ትንሽ ሲርቁ ደግሞ ሰዎችን በጣም ይናፍቃሉ፡፡
10. ሁሌም ተበዳዮች ናቸው ተበደልኩ ብለው ማውራት ደስ ይላቸዋል፡፡


ቻናላችንን ለኡማው ያስተዋውቁ 👇
/channel/Qallbdoc

ህክምና ለማግኘት👇
/channel/freeeeeeeeeeeere

👆ህክምና ለማግኘት👇
/channel/UstazulQallb

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://user254808.psee.ly/5ng2wn

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://www.youtube.com/live/JYwDDOekXCU?si=XGuGuHrVMyMdZD4U

Читать полностью…
Subscribe to a channel