kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ይጹም አይን አይን ይጽም
ይጹም ልሳን አንደበትም ይጹም
እዝነኒ ይጹም ጆሮውም ይጹም

/channel/silase

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ነይ_ድንግል
/channel/silase

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ጌታዬ_ሆነ_ደም_ግባት_አልባ
/channel/silase

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

መጋቢት 4/2016 #ወንጌላዊዉ_ዮሐንስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና በፀሎት ለምንማፀንበት ለወልደ ነጎድጓድ #ቅዱስ_ዮሐንስ ወርሐዊ መታሠቢያ በዐል እንኳን አደረሰን

👉የከበረና የተመሰገነ #ዮሐንስ በዚህ ዓለም ዘጠና ዓመት ኖረ እጅግም ሸመገለ ግን እንደ ባልንጀሮቹ ሐዋርያት በመሰየፍ ሞትን አልቀመሰም

👉ስለ ድንግልናውና ስለ ንጽሕናው ይህ ሆነ ሁሉም በክብር ይስተካከሉ ዘንድ እርሱም ወንጌልን #ቀለምሲስ የሚባለውን ራእይ ሦስት መልእክታትን የጻፈ ነው

👉ራት ሲበሉ #በጌታ_ኢየሱስ አጠገብ የተቀመጠውና አቤቱ የሚያሲዝህ ማነው ብሎ የጠየቀዉ እርሱ #ዮሐንስ ነው

👉ጌታችንም በተሰቀለ ጊዜ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል #ማርያም ጋር በመስቀሉ አጠገብ የቆመ እናቱንም እነሆ ልጅሽ ያላት ጌታም ደቀ መዝሙሩን እነኋት እናትህ ያለው ነው

👉ጴጥሮስም እርሱን ሲከተለው በአየው ጊዜ ስለርሱ ጌታ #ኢየሱስን አቤቱ ይህስ እንዴት ነው ብሎ የተናገረ ጌታ ኢየሱስም እስክመጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ከወደዱኩ አንተ ምን አለህ አንተ ግን ተከተለኝ ያለለት እርሱ #ዮሐንስ ነው

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከፍቁረ እግዚእ #ቅዱስ_ዮሐንስ ረድኤትና በረከት ያሣትፈን የደጋግ ቅዱሣን አባቶቻችንን ፆም ፀሎታቸዉን ተቀብሎ በምህረት አይኑ ይመልከተን አሜን ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለጻድቁ አባታችን ቅዱስ ጐርጐርዮስ ረዓዬ ኅቡዓት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ጐርጐርዮስ ረዓዬ ኅቡዓት †††

††† ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሃገሩ ሮሃ (ሶርያ አካባቢ) ሲሆን ረዓዬ ኅቡዓት (ምሥጢራትን የተመለከተ) ይባላል::
ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
ቅዱሱ ተወልዶ ባደገባት ሃገር ይህ ቀረው የማይባል ኃጢአተኛ ሰው ነበር:: ታዲያ ምንም ኃጢአተኛ ሰው ቢሆን እመቤታችን ድንግል ማርያምን በፍፁም ልቡ ይወዳት ነበርና በመዳን ቀን ጥሪ ለንስሐ አበቃችው::

ከዚያች ዕለት ጀምሮም ቅዱስ የእግዚአብሔር ሰው : ንጹሕ የቤተ ክርስቲያን መስዋዕት : ጽኑዕ የበርሃ ምሰሶ ሆነ:: ድንግል እመቤታችንም ከነሥጋው ወደ ሰማያት ወስዳ ገነትና ሲዖልን አሳይታ : ከአዳም : ኖኅ : አብርሃም : ሙሴ : ዳዊትን ከመሰሉ ቅዱሳን ጋር አስተዋውቃ : ከዚህም በላይ የሆነና በሰብአዊ አንደበት የማይነገር ብዙ ምሥጢር አሳይታ ወደ ምድር መልሳዋለች::

ቅዱስ ጐርጐርዮስ በሰማይ (በገነት) በነበረው ቆይታ ክብረ ቅዱሳንን ተመልክቶ አድንቋል:: በተለይ በፍጹምነት ድንግልናቸውን የጠበቁ ቅዱሳንና ቅዱሳት ደናግል አኗኗራቸው ከአምላክ እናት : ከሰማይ ንግሥት : ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ጋር መሆኑን አይቷል::

"የለበሱት ልብስም በፍጡር አንደበት ተከናውኖ ሊነገር የሚቻል አይደለም" ይላል:: የደናግል ፊታቸው ከፀሐይ 7 እጅ ያበራልና ግርማቸው ያስፈራል::

ቅዱሱ ሰው በዚያው በሰማይ ሳለ ደግሞ ይህንን ተመለከተ:: አንድ አረጋዊ : ጽሕሙ ተንዠርግጐ : የብርሃን ካባ ላንቃ ለብሶ ይመጣል:: ቅዱሳን መላእክት በፊት በኋላ : በቀኝ በግራ ከበውት ሳለ እግዚአብሔርን ሊያመሰግን ጀመረ::

"እግዚኦ እግዚእነ : ጥቀ ተሰብሐ ስምከ በዲበ ምድር (አቤቱ ጌታችን : በምድር ሁሉ ስምህ የተመሰገነ ሆነ)" ሲል . . . መላእክቱ በዝማሬ አጀቡት:: በዚህ ጊዜም ታላቅ መናወጥ ሆነ:: ደናግሉም የቅዱሱን ሽማግሌ በረከቱን ተሳተፉ::

ይህ አመስጋኝ ሽማግሌ ልበ-አምላክ : ጻድቅ : የዋህና የእሥራኤል ንጉሥ የሆነው ዳዊት ነበር:: በምን ታወቀ ቢሉ :- በበገናው:: አንድም እመቤታችን "አባቴ ዳዊት!" ብላ ስትጠራው ጐርጐርዮስ ሰምቷልና::

በመጨረሻም እመቤታችንን በፍጹም ክብርና ግርማ ተመልክቷት ሐሴትን አድርጓል:: እመ-ብርሃንም "ተወዳጅና ንጹሕ ሰው ነህ" ስትል ቅዱስ ጐርጐርዮስን አመስግናዋለች:: ስለዚህ ዓለምም እንዲህ የሚል መልእክትን ልካለች::

"ልጆቼ ሆይ! ከብርሃን ጨለማን : ከደግነት ክፋትን : ከጽድቅ ይልቅ ኃጢአትን . . . ምነው መምረጣችሁ? እኔ ስለ እናንተ በየቀኑ እየለመንሁ እነሆ አለሁ:: ወደ ጨለማ ገሃነም እንዳትወርዱ እባካችሁ ንስሐ ግቡ!"

ቅድስት ድንግል ማርያም ይህንን ለቅዱሱ ሰው ነግራው : ቅዱስ ዳዊትን አስከትላ : በግሩማን መላእክት ታጅባ ወደ ውሳጤ መንጦላዕት (የእሳት መጋረጃዎች ወደ ተተከሉበት ድንኳን) ገባች:: በዚያም ተመሰገነች::

ለዛም አይደል ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ:-
"ይዌድስዋ መላእክት ለማርያም በውስተ ውሳጤ መንጦላዕት : ወይብልዋ : በሐኪ ማርያም ሐዳስዩ ጣዕዋ::" ሲል ያመሰገናት::

ቅዱስ ጐርጐርዮስም ከሰማይ ቆይታ መልስ ያየውን ሁሉ ጽፎ ለአበው ሰጥቷል:: ስለዚህም ረዓዬ ኅቡዓት (ምሥጢራትን ያየ) ይሰኛል:: ቅዱሱ ተረፈ ዘመኑን በተጋድሎ ፈጽሞ በዚህች ቀን አርፏል::

††† የቅዱሱ እመቤት ድንግል እመ ብርሃን መዓዛ ፍቅሯን ታብዛልን::

††† መጋቢት 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ረዓዬ ኅቡዓት (ዘሃገረ ሮሃ)
2.አቡነ መክፈልተ ማርያም ጻድቅ (ኢትዮጵያዊ)
3.አባ መከራዊ ዘሃገረ ኒቅዮስ (አረጋዊ: ጻድቅ: ጳጳስና ሰማዕት)

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
2.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ
3.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
4.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
5.ቅዱስ አባ ጳውሊ ገዳማዊ (ታላቁ)
6.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
7.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ

††† "ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው:: ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ:: ስለዚህ ግን የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት በእርሱ ያምኑ ዘንድ ላላቸው ሰዎች ምሳሌ እንድሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ዋና በምሆን በእኔ ላይ ትዕግስቱን ሁሉ ያሳይ ዘንድ ምሕረትን አገኘሁ::" †††
(፩ጢሞ. ፩፥፲፭)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

✝ንስሐ የተጣመመውን ያቀናል።በኃጥያት የቆሸሸውን ያነጻል፤ንስሐ ለሚገቡ ሁሉ የመላዕክት ንጹሕ ልብስ ይሰጣችኃል።
(ቅዱስ መቃርስ ) ንስሐ ግቡ።✝

❇️ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት)❇️

" ❇️ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::❇️
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እንኳን አደረሳችሁ በያላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ውዳሴሃ፣ ለእግዝትነ ፣ማርያም፣ድንግል፣ወላዲተ፣ አምላክ፣ዘይትነበብ፣በዕለተ ዘቀዳሚት
/channel/wdase1

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ጥያቄ የሎጥ ሚስት ስሟ ማን ነበር

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የካቲት 30/2016 #ቅዱስ_ዮሐንስ
#ቅዱስ_ማርቆስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሣኑ ስም ለምናመሰግንበት ለቅዱሣኑ ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን

👉እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ #ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም ማቴ11፥11

👉የጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ቃል ስለ መጥምቀ መለኮት #ቅዱስ ዮሐንስ ክብር መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በጌታ የተከበረ ነቢይ እና ጻድቅ ነው እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ የለም በማለት የተናገረለት ቅዱስ አባት ነው

👉የመጥምቀ መለኮት #ቅዱስ_ዮሐንስ
የተሰጡት ሃብተ ፀጋዎች

1 👉 ነብይ
2 👉 ካህን
3 👉 መምህር
4 👉 ሐዋርያ
5 👉 ፃድቅ
6 👉 መጥምቅ
7 👉 ሰማእት ነው

👉 #ቅዱስ_ዮሐንስ ከነቢያት ሁሉ የሚበልጥ መሆኑን ጌታችን ሲናገር እንዲህ ብሎ ተናግሮለታል ከነቢያት ሁሉ የሚበልጥ #ነብይ ነው እላችኋለሁ በማለት መስክሮለታል

👉 #ቅዱስ_ዮሐንስ ሃቀኛ መምህር፤ ነቢይ፤ ካህን፤ ሰማዕት፤ ሐዋርያ በመሆኑ ከአምላኩ ክብርን የተቀበለ ቅዱስ አባት ነው ስለዚህ ነው ደግሞ ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ እራሱ ግልጽ አድርጎ ስለ #ቅዱስ_ዮሐንስ ክብር የተናገረው

👉ትንቢት የተነገረለት #ቅዱስ_ዮሐንስ ክብሩ በመልአኩ እንዲህ በማለት ነው የተመሠከረለት #በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ነቢይ እንደሆነ #በመንፈስ_ቅዱስ የተመረጠ በንጽሕናው በአገልግሎቱ #በመላእክት ደረጃ የሚታሰብ ሲሆን ምልጃና ፀሎቱ የከበረዉ
ቃል ኪዳን ሁላችንንም ይጠብቀን

👉ለኢትዮጲያና ለግብፅ አባታችን አስተማሪያችን የሆነዉ ሐዋርያዉ #ቅዱስ_ማርቆስ በዚህ እለት የመታሠቢያ በአሉ ሲሆን ምልጃና ፀሎቱ ረድኤትና በረከቱ የአባትነት ፍቅሩ አይለየን የተባረከ #ቀዳሚት_ሰንበት ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🕊                   

[   በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።   ]

✞ እንኩዋን ለዐቢይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ ✞
                   

[  ዐቢይ ጾም  " የጌታ ጾም "  ]

 🍒

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ምዕመናን እንዲጾሟቸው የሠራቻቸው ፯ [ 7 ] አጽዋማት አሏት:: " ጾም " ማለት "መከልከል" ነው::

የምንከለከለው ደግሞ ከኃጢአትና ከክፋት ሲሆን አንድም ሰውነትን ወደዚያ ከሚወስዱ መባልዕት መከልከልን ይመለከታል::

ጾም ለክፉ ሥራ ከሚያነሣሱ የምግብ ዓይነቶች መከልከል ወይም ለተወሰነ ጊዜና ሰዓት ሰውነት ከሚፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ መወሰን [ መታቀብ ] ማለት ነው፡፡ ለሰውነት የሚያምረውንና የሚያስጎመዠውን ነገር ሁሉ ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ብሎ መተው ነው፡፡

ጾም ከመንፈሳዊ ተጋድሎዎች አንዱ ነው፡፡ ለሥጋም መንፈሳዊ ልጓም ነው፡፡ ጸዋሚ ሰው ፈቃደ ሥጋውን እየገታ ነፍሱን የሚያለማምድበት ስንቅ ነው፡፡ "ጾም ቁስለ ነፍስን የምትፈውስ ፤ ኃይለ ፍትወትን የምታደክም ፤ የበጎ ምግባራት ሁሉ መጀመሪያ ፤ ከእግዚአብሔር ጸጋን የምታሰጥ ፤ የወንጌል ሥራ መጀመሪያ ፤ የጽሙዳን ክብራቸው ፤ የድንግልና የንጽሕና ጌጣቸው ፤ የንጽሕና መገለጫ ፤ የጸሎት ምክንያት እናት ፤ የዕንባ መገኛ መፍለቂያዋ ፤ አርምሞን የምታስተምር ፤ ለበጎ ሥራ ሁሉ የምታነቃቃ ፣ ሰውነትን በእግዚአብሔር ፊት በማዋረድ ትሕትናን ገንዘብ ለማድረግ የምትረዳ መድኃኒተ ነፍስ ናት፡፡" [ማር ይስሐቅ አንቀጽ ፬፥፮]

ጾም ተድላ ሥጋን የምታጠፋ ፥ የሥጋን ጾር የምታደክም ፥ ቁስለ ነፍስን የምታደርቅ ፥ ለጎልማሶች ጸጥታንና ዕርጋታን የምታስተምር ፥ ከግብረ እንስሳዊ የምትከለክል ፥ ሰው መላእክትን መስሎ የሚኖርባትና ኃይል መንፈሳዊን የሚጎናጸፍባት ደገኛ መሣሪያ ናት፡፡ ከኃጢአት ፆር ከፍትወት አንዱንም አንዱን ድል ለመንሳት ለማጥፋት ፥ የዲያብሎስን ረቂቅ ፍላጻ ለመመከት በጾም መድከም የሥራ ሁሉ መጀመሪያ እንደሆነች የታወቀ ነው፡፡ ጾም ምህረት መለመኛ ፥ የንስሐ መገለጫ ፥ ከመከራ የሚሠወሩባት ፥ ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር አስታርቃ ርስት መንግሥተ ሰማያት የምታስገባ "ኆኅተ ጽድቅ - የጽድቅ በር" ሆና የተሰጠች ቀዳማዊት ሕግ ናት፡፡

🕊                       💖                   🕊

[       ዐቢይ ጾም [   ጾመ እግዚእ  ]      ]


ከ፯ [7] ቱ አጽዋማት አንዱ የሆነው ይህ ጾም

፩. ዐቢይ [ ታላቁ ] ጾም
፪. የጌታ ጾም
፫. ጾመ ሑዳድ
፬. የድል ጾም
፭. የካሳ ጾም
፮. አርባ ጾም
፯. የፍቅር ጾም . . .
በሚሉ መጠሪያዎችም ይታወቃል::

የጾሙ መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት ደግሞ =

፩. ጾመ ሕርቃል
፪. ጾመ በረከት ዘሐዋርያት
፫. ሰሙነ ዘወረደም ይባላል::

የጾሙ የመጀመሪያው ሳምንት [ዘወረደ] የሚጾመው እስከ ፲፪ [ 12 ] ሰዓት ሲሆን ከቅድስት [ ከ፪ [ 2 ] ኛው ሳምንት እስከ ተጽኢኖ [ የኒቆዲሞስ ዓርብ ] ድረስ ደግሞ እስከ ፲፩ [ 11 ] ሰዓት ይጾማል::

በሰሙነ ሕማማት ግን የምንጾመው "እስከ ይሠርቅ ኮከብ" [ እስከ ምሽት ፩ [ 1 ] ሰዓት ] ድረስ ይሆናል::

ነገር ግን ሁሉም እንደ መጠኑ ነውና ከመምሕረ ንስሃ ጋር ሊጨዋወቱት ይገባል:: በዓቢይ ጾም ለቻለ ቂጣ በጨው እየበላ : ውሃ እየተጐነጨ ሊጾም ይገባል:: በእነዚህ ፶፭ [ 55 ] ቀናትም ከዕለተ ሆሳዕና በቀር ከበሮ አይጐሰምም:: ጸናጽል አይጸነጸልም:: ተድላ ደስታም አይደረግም::

አብዝቶ መብላት : ሳቅ ማብዛትና ጌጥን ማብዛትም እንዲሁ አይገባም:: ለቻለ ደግሞ በሌሊት ሰዓታቱን ፡ በነግህ ኪዳንና ስብሐተ ነግሁን : በመዓልት ቅዳሴውን : በሰርክ [ ምሽት ] ደግሞ ምሕላውን ሊሳተፍ ይገባል::

በእነዚህ ፶፭ [ 55 ] ቀናት ፈቃደ ሥጋ ሊደክም : ፈቃደ ነፍስ ልትሰለጥን ግድ ነውና:: ከሌላው ጊዜ በተሻለ ወቅቱ ምጽዋትና ጸሎት የሚደረግበት ነው:: በዚያውም ላይ ነገሮችን እያመቻቹ በእነዚህ ዕለታት ቅዱስ ቃሉን መስማት [ማንበብ] ይገባል:: በትዳር ውስጥ ላሉም መኝታን መለየት ግድ ነው::


ጾሙን የሰላም : የፍቅር : የምሕረት : የፀጋ : የበረከት ያድርግልን:: ጾሞ ለማበርከትም ያብቃን፡፡

" አሁንስ ይላል እግዚአብሔር በፍጹም ልባችሁ በጾምም በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ:: ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ:: አምላካችሁም እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ: ቁጣው የዘገየ: ምሕረቱም የበዛ: ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ:: " [ትን. ኢዩኤል.፪፥፲፪ (2:12) ]


ወስብሐት ለእግዚአብሔር : ወለወላዲቱ ድንግል : ወለመስቀሉ ክቡር !

         [       ይቆየን  !       ]

†                       †                         †
💖                    🕊                     💖
/channel/silase
/channel/silase
/channel/silase
/channel/silase

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ውዳሴሃ፣ ለእግዝትነ ፣ማርያም፣ድንግል፣ወላዲተ፣ አምላክ፣ዘይትነበብ፣በዕለተ አርብ
/channel/wdase1

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

+ከዚያም የተወሰኑ አገልጋዮችን አስቀምጣላቸው ወደ
ኢየሩሳሌም በመሄድ ለ7 ዓመታት በአየሩሳሌም ከኖረች
በኋላ የእመቤታችን በዓል ለማክበር ወደ ግብፅ በመሄድ
ላይ ሳለች በመንገድ አንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብታ
ስትፀልይ እመቤታችን በስዕሏ ላይ ተገልጣ: ቦታዋ
በኢትዮጵያ መሆኑን ነግራ: እጇን ዘርግታ "ወደ ኢትዮጵያ
ሂጂ" ብላ ነገረቻት::

+በኋላ በብርሃን አምድና በቅዱስ ሚካኤል እየተመራች
አሁን ወደ ምትታወቅበትና የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ወደ
ተገለፀበት እመ ምዑዝ ኪዳነ ምህረት ቅድስት ፍቅርተ
ክርስቶስ አንድነት ገዳም ደርሳለች፡፡
+በቦታው ስትደርስ የቦታው ልምላሜ የሚያስደስት ነበርና
"ይህች ቦታ ምን ታምር!" ብላለች፡፡ ቦታውም እስከ አሁን
ድረስ ምንታምር በመባል ይጠራል፡፡

+ምንታምር ላይ ከአገልጋዮቿ ጋር በመሆን አርፋ ሳለ
ከኢየሩሳሌም መርቶ ያመጣት የብርሃን አምድ በዚያ ቦታ
ላይ በስፋት ረቦ (ከምድር እስከ ሰማ ተተክሎ) ብታየው:
መልአኩም "ቦታሽ ይሄ ነው" ብሎ ቢነግራት በዚያው
ተቀምጣለች፡፡

+የቦታው ባለ አባት "ይህን ቦታ ልቀቂ" ቢሎ ቢጠይቃት
"እግዚአብሔር የሰጠኝ ቦታዬ ነው" ብላዋለች፡፡ እርሱም
ለክስ ወደ ጎንደር በመሄድ አፄ ሱስንዮስ አርፈው አፄ
ፋሲል ነግሰው ነበርና እሳቸውን ፍርድ ቢጠይቃቸው በዝና
ያውቋት ነበርና "ቤተ ክርስቲያን ካልተሰራ ትልቀቅልህ:
ከተሠራ ግን ሌላ ቦታ ይሰጥሃል" የሚል ፍርድ አስፈርዶ
ነበር::

+ሲመለስ ቅዱስ ሚካኤል ቀድሞ "ቶሎ ቤተ ክርስቲያን
ስሪ እንዲህ የሚል ፍርድ ተፈርዷል ብሎ ነግሯት ‹‹ታህሳስ
14 ቀን ከነግህ ፀሎት በኋላ በሰንሰልና በስሚዛ
ግድግዳዋን: በአይጥ ሀረግ ማገር አድርጋ: የግድግዳ
ቤተ መቅደስ በዕለተ አርብ: በአንድ ቀን ሰርታ ታህሳስ 16
ቀን እሁድ ታቦተ ኪዳነ ምህረትን አስገብታ ቅዳሴ
አስቀድሳለች::››

+ቅዳሴውም ከተፈፀመ በኋላ ጌታችን ከቅዱስ መንበሩ
ላይ እንዳለ ሆኖ ከእናቱ ከእመቤታችን ጋራ ታያቸው፡፡
ከመንበሩ ወርዶም ይህን ቦታ በባረከው ጊዜ የስሚዛው
ቤተ መቅደስ በአራቱም አቅጣጫ ለፈጣሪው ሰገደ፡፡

+የመሬት መናወጥም ሆነ:: ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስም
"ልታጠፋን መጣህን? ቤተ ክርሰቲያኔንስ ልታፈርሳት
ነው?" ብላ ብትጠይቀው "ይህ የሰንሰል ቤተ መቅደስሽ
ዳግም እስከምመጣ ድረስ ሳይፈርስ: ሳይታደስ ፀንቶ
ይኖራል፣ በውስጡም እስከ ዓለም ፍፃሜ ድረስ
የክሀድያንና ፣ መ++++++ና+++++++ፍ++++++ቃ++++++ን እግር አይገባበትም፣ በውስጧ
ቁርባንን የተቀበሉ ሁለ ኃጢያታቸው ይሰረይላቸዋል፣
ዘወትር ምህረቴ በረከቴ ከእነርሱ ጋር ይኖራል" በማለት
ተናግሮ ተሰወራቸው፡፡

+ከዚያም በኋላ መነኮሳትና መነኮሳይያት የቅድስት ፍቅርተ
ክርስቶስን የትሩፋት ዜናዋን ሰምተው ከየአቅጣጫው
ተሰበሰቡ፡፡ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስም በአምላክ ሀይል
ተጋድሎአቸውን ይፈፅሙ ዘንድ ታስተምራቸው ፣
ትመክራቸው፣ በተግባርም እያሳየቻቸው ለብዙ ዘመናት
ከኖሩ በኋላ በገዳሙ ላይ የአጋንንት ፆር እንዳይነሳ
ወንዶቹን ለብቻ ሴቶቹን ለብቻ አደረገች፡፡

+ዘወትርም እንዳይተያዩ የእግዚአብሔር መልዐክ
በቅድስተ ፍቅርተ ክርሰቶስ ፀሎት ይጠብቃቸው ነበር፡፡
ከዚህ በኋላ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ከዚህ
ኃላፊ ዓለም መለየቷ በቀረበ ጊዜ ሁለት መላዕክት ወደ
እርሷ መጥተው በብርሃን ሰረገላ ጭነው ወደ ደብረ ነባት
(ወደ ብሔረ- ህያዋን) ወስደው በዚያ ቅዱስ ቁርባንን
አቀብለው ወደ ቦታዎ መለሷት፡፡

+መልዐኩም "ከጻማ: ከድካም: ከመታረዝ: ከረሐብ
ከጥም: ከመትጋት: ከእንባ: ከዚህ ዓለም የምትለይበት
ጊዜ እነሆ ደረሰ" አላት፡፡ የካቲት 27 ቀንም ወደ ምስራቅ
እጇን ዘርግታ ቆማ ስትጸልይ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ
ከደስታ ብርሀን ጋር ያማረ ሽታ መላ::

+ጌታችን ከአዕላፋት መላዕክትና ቅዱሳን ጋር ወደ እርሷ
መጣ፡፡ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስም ሰገደች፡
ተንበረከከች: እጅግም አለቀሰች፡፡ ከወደቀችበት ቦታ
አንስቶ ‹‹ላጠፋሽ አልመጣሁም ወዳጄ ላከብርሽ ነው
እንጂ›› አላት፡፡

+"የዘለአለም መንግስት አዘጋጅቼልሻለሁና ደስ ይበልሽ"፡፡
ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስም ቃል ኪዳን እንዲገባላት
ተማጸነችው:: ጌታችንም ‹‹ሁሉም እንደ ቃልሽ ይሁንልሽ::
በስምሽ ስሜ ተጨምሯልና ለቤተ ክርስቲያንሽ መባ
የሰጠ፣ የተላከ ፣የተቀበረ፣ ቤተ መቅደስሽ መጥቶ
የተሳለመ ፣ እስከ 12 ትውልድ የምህረት ቃል ኪዳን
ሰጠሁሽ::

+በረከቴም በቤቱና በልጆቹ በገንዘቡም ላይ ይደር::
የገድልሽ መጽሐፍ ባለበት አጋንንት (ሰይጣናት)
አይቀርቡም:: በአዝመራ ስምሽን በጠሩት ጊዜ የለመለመ
ይሁን:: በጸሎትሽ የተማጸነ ሁሉ ባለጤና ይሁን::

+ስምሽን በእውነት የሚጠራ የከበረ ነው፡፡ ያለመጠራጠር
በቀናች ሐይማኖት የገድልሽን መጽሐፍ የጻፈ: ያጻፈ:
ያነበበ: የተረጎመ በሐይማኖት የሰማ: እስከ ቀዝቃዛ ውሃ
ድረስ የሰጠ ኃጢያቱ ይሰረይለታል::
ስለ ድካምሽ ስለ ትሩፋትሽ 7 አክሊሎችን እና ይህን ሁሉ
ቃል ኪዳን ሰጠሁሽ፡፡ ላልምረው ቦታሽን
አላስረግጠውም›› ብሏት ወደ ሰማይ አረገ፡፡

+በማግስቱ ትንሽ ህመም ታመመች ደናግል መነኮሳትን
ጠርታ የእረፍት ቀኗ መድረሱን ነገረቻቸው:: ከመካከላቸው
አንዷን ለገዳሙ አስተዳዳሪነት መርጣ በፍቅር ስም
ተሰናበተቻቸው፡፡ የዳዊት መዝሙርንም ስትጸልይ የካቲት
29 ቀን እሁድ አጥቢያ ጠዋት በጌታ በዓል አንቀላፋች
(ነፍሷ ከስጋዋ ተለየች)፡፡

+ጌታችንም ከእናቱ: ከቅዱሳኑ ጋር መጥቶ ነፍሷን
ተቀብሎ ወደ ዘለዓለም ገነት ወሰዳት፡፡ ቅዱሳንም
ከመላእክት ጋር እልል እያሉ እያመሰገኑ ወደ ዘለዓለም
ቦታ ገነት አስገቧት፡፡ ከቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ መቃብር
ላይ 40 ቀናት ብርሃን ሲበራበት ታይቷል፡፡

+በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት: በመቂት ወረዳ ጥባ
ማርያም ቀበሌ ውስጥ ምን ታምር በመትባል ቦታ ላይ
በ16ኛው መቶ ክ/ዘመን በኢትዮጵያዊቷ ሰማዕትና ጻድቅ
ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ የተመሰረተቸው እመ ምዑዝ
ኪዳነ ምህት ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አንድት ገዳምም
በዓላቶቿ የሚከበሩት ታህሳስ 16 የቅዳሴ ቤቷ እንዲሁም
የካቲት 29 ቀን በዓለ እረፍቷ ይከበራል፡፡

††† ከቅድስት እናታችን በረከት አምላክ አይለየን::

††† የካቲት 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት
2.ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ (ጻድቅና ሰማዕት)
3.ቅዱሱ ሕፃን (የፍቅርተ ክርስቶስ ልጅ)
4.ቅዱስ ቢላካርዮስ ዘሃገረ አርሞኒ (አረጋዊ: ደራሲ: ጻድቅና ሰማዕት)

††† ወርኀዊ በዓላት
1.የፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት
2.ቅድስት አርሴማ ድንግል
3.ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
4.ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ

††† "መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ:: አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ::
ውበት ሐሰት ነው:: ደም ግባትም ከንቱ ነው::
እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች:: ከእጇ ፍሬ ስጧት:: ሥራዎቿም በሸንጐ ያመስግኗት::" †††
(ምሳሌ. 31:29)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር
በዩቲብለመከታተል👉ZikereKedusan" rel="nofollow">https://www.youtube.com/@ZikereKedusan
በቴሌግራም👉/channel/zikirekdusn

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/4RRPHCYgZY4

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለታላቁ ሰማዕት "ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችኹ †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አምላክ አሜን†††

+*" ቅዱስ ቴዎድሮስ ዘሮም "*+

=>ሰማዕትነት በክርስትና ለሃይማኖት የሚከፈል የመጨረሻው ዋጋ (መስዋዕትነት) ነው:: ሰው ለፈጣሪው ሰውነቱን ሊያስገዛ: ሃብት ንብረቱን ሊሰጥ ይችላል:: ከስጦታ በላይ ታላቅ ስጦታ ግን ራስን አሳልፎ መስጠት ነው::

+ራስን መስጠት በትዳርም ሆነ በምናኔ ውስጥ ይቻላል:: የመጨረሻ ደረጃው ግን ሰማዕትነት ነው:: "አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም: ወተዓገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግስተ ሰማያት" እንዳለው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ሰማዕትነት ማለት መራራውን ሞት ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲሉ መታገስ ነው::

+እርሱ ቅሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ ሲሆን ኃፍረተ መስቀልን ታግሦ ሙቶልን የለ! በዓለም ያሉ ብዙ እምነቶች ስለ መግደል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያስተምራሉ:: ክርስትና ግን መሞትን እንጂ መግደልን የሚመለከት ሕግ የለውም::

+እርሱ ባለቤቱ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ: የሚረግሟችሁን መርቁ: ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ" ብሎናልና:: (ማቴ. 5:44) ነገር ግን ዕለት ዕለት ራሳችንን በሃይማኖትና በምግባር ካልኮተኮትነው ክርስትና በአንድ ጀምበር ፍጹም የሚኮንበት እምነት አይደለምና በፈተና መውደቅ ይመጣል::

+በተለይ የዘመኑ ክርስቲያን ወጣቶች ልናስተውል ይገባናል:: የቀደሙ ወጣት ሰማዕታት ዜና የሚነገረን እንድንጸና ነውና::

=>ቅዱስ ቴዎድሮስ በዘመነ ሰማዕታት (በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን) በቀድሞው የሮም ግዛት ውስጥ ከተነሱ ታላላቅ ሰማዕታት አንዱ ነው:: በወቅቱ መሪ የነበረው ክሀዲው መክስምያኖስ "ክርስቶስን ክደህ ለጣኦት ስገድና በከተማዋ ላይ እሾምሃለሁ" ቢለው "ለእኔ ሃብቴም ሹመቴም የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው" በማለቱ ንጉሡ ተቆጥቶ በብረት ዘንግ አስደበደበው::

+በመንኮራኩር አበራየው:: ለአናብስት ጣለው:: አካላቱን ቆራረጠው:: በእሳትም አቃጠለው:: ቅዱስ ቴዎድሮስ ስቃዮችን ስለ ቀናች ሃይማኖት ሲል በትዕግስት ተቀበለ:: በፍፃሜውም አንገቱን በሰይፍ ተመትቶ 3 አክሊላት ወርደውለታል::

+ከፈጣሪው ዘንድም ነጭ መንፈሳዊ ፈረስና ቃል ኪዳን ተቀብሏል:: ስሙን የጠራ: መታሠቢያውን ያደረገ ዋጋው አይጠፋበትም:: (ማቴ. 10:41)

=>አምላከ ቅዱሳን ከቅዱሱ ሰማዕት በረከት ይክፈለን:: አይተወን:: አይጣለን:: ጾሞ ለማበርከትም ያብቃን::

=>የካቲት 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ (ሰማዕት)
2."6,304" ሰማዕታት (በቅ/ቴዎድሮስ አምላክ አምነው ሰማዕትነት የተቀበሉ)

=>ወርኀዊ በዓላት
1.አማኑኤል ቸር አምላካችን
2.ቅዱሳን አበው (አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ)
3.ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
4.ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ

=>+"+ እግዚአብሔር ለኛ የሰማዕትነትን ሥራ ይሰጠን ዘንድ ቅዱሳን ስለሚሆኑ ሰማዕታት እንማልዳለን:: +"+
(ሥርዓተ ቅዳሴ ቁ. 73)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>



✝ ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር ✝

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Yemasegani edate nacw

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ከንቱ_ነኝ
#ነይ_ድንግል
/channel/silase

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#አቤቱ_ደግ_ሰው
/channel/silase

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የንስሃ መዝሙር

            አርሴማ ቅድስት

በዙሪያችን ካሉ ድንቅ ምስክሮ
በእምነት በምግባር ከፀኑት እናቶች
ከፍ ብላ ታየች በገድሏ ብዛት
ንዕድ ክብርት ናት አርሴማ ቅድስት×2
    
         ሀብትና ንብረቷን ውበቷን የናቀች
         ንግስት መባልን በዕምነት የተወች
         የኢየሱስ ክርስቶስ የስሙ ምስክር
         የቅድስት አርሴማ እፁብ ነው የሳስ ክብር×2

አዝ
       
         እግዚአብሔር ፅናቷን የመሰከረላት
         በቤቱ በቅጥሩ መታሰቢያ አላት
         የወንጌሉን ብርሃን ለአለም ያበራች
         ሰማዕቷ አርሴማ ለኛም አማላጅ ነች ×2

አዝ

         ይኸው በዚህ ዘመን እግዚያብሄር ገለፃት
         ለረድኤት በረከት ምክንያት አረጋት
         አክሊል ተጎጽፋ ታይታለች በክብር
         ዛሬም በልጆቿ በረከቷ ይደር ×2

አዝ

        እንደተናገረው ጌታችን በቃሉ
        በእኔ የሚያምኑ ድንቅን ይሰራሉ
        ደዌ እንዲርቅለት ፈውስን የተጠማ
        ከደጇ ላይ ይውደቅ ይበላት አርሴማ ×2

አዝ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በጎፋና ባስኬቶ ሀገረ ስብከት በደንባ ጎፋ ወረዳ ቤተ ክህነት ኡባ ሰሎ ጋጫ ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን
/channel/silase

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

​​​​ዐቢይ ጾም

ዐቢይ ለምን ተባለ ቢሉ ‹‹ዐበየ›› ማለት ከፍ አለ ማለት ሲሆን ከዚህም ግስ አቢይ የሚለው ቅጽል ይገኛል፡፡ ዐቢይ ማለት ከፍ ያለ ትልቅ ማለት ነው፡፡

ዐቢይ ጾም የተባለበት ምክንያት፡-

. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ጾም ስለሆነ

. በቀኑ ቁጥር ከሌሎች አጽዋማት የሚበልጥ ስለሆነ

. ሦስቱ ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች ማለትም 'ትዕቢት' 'ስስት' 'ፍቅረ ነዋይ' ድል የተመቱበት ስለሆነ ነው፡፡

በቤተክርስቲያን ስያሜ መሰረት በዐቢይ ጾም ውስጥ የሚውሉ ሰንበታት እያንዳንዳቸው መጠሪያ ስም ሲኖራቸው እነርሱም፡-

1. ዘወረደ
የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሰንበት ሲሆን ይህም ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን ፈጥሮ የሚኖር አልፋና ኦሜጋ ከሰማየ ሰማያት መውረዱንና ከእመቤታችን ከቅድስተ ቅዱሳን ከንጽሕተ ንጹሐን ከድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመለክት ሥያሜ ነው፡፡


   ጾሙን የበረከት ጾም ያድርግልን፡፡

/channel/silase

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝✞✝ እንኩዋን ከተባረከ ወር መጋቢትና ከሁለተኛው መንፈቀ ዘመን የመጀመሪያ ዕለት በሰላም አደረሳችሁ ✝✞✝

=>ወርኀ መጋቢት መዐልቱና ሌሊቱ እኩል (12:00) ናቸው:: ከዛሬዋ ዕለት ጀምሮ ለሚቀጥሉት 6 ወራት (186 ቀናት) ከማይጠቅም ወሬ ተቆጥበን: ከክፋትም ርቀን መልካሙን የእግዚአብሔር ጐዳና ለመከተል ራሳችንን ልናዘጋጅ ይገባል::

=>በዚህ ዕለትም ከአዳም 8ኛ ትውልድ የሆነው አባታችን ማቱሳላ በዓሉ ይከበራል:: ቅዱስ ማቱሳላ የጻድቅ ሰው ኄኖክ ልጅ: የደጉ ላሜሕ አባት ሲሆን በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ረዥም ዕድሜ (969 ዓመት) የቆየ ባለ ረዥም ዕድሜ አባት ነው:: ከአሥሩ ቅዱሳን አባቶች አንዱ ነው::

+10 ቅዱሳን አባቶች ማለት:-
*ቅዱስ አዳም አባታችን
*ሴት
*ሔኖስ
*ቃይናን
*መላልኤል
*ያሬድ
*ኄኖክ
*ማቱሳላ
*ላሜሕ
*ኖኅ ናቸው::

† ቅዱስ በርኪሶስ †

«« በዚች ቀን የኢየሩሳሌም አገር ኤጲስቆጶስ ቅዱስ በርኪሶስ አረፈ።ይህም አባት ክርስቲያኖችን በሚወዳቸው በቄሳር እለእስክንድሮስ ዘመነ መንግስት ተሹሞ ሳለ ሀዋርያት ሲጠብቋቸው እንደነበር በበጎ አጠባበቅ ህዝቡን ጠበቃቸው ።

«ከጥቂት ጊዜ በኃላ እለእስክንድሮስ ሞተ ከእርሱ በኃላ ቄሳር መክስሚያኖስ ነገሰ። ክርስቲያኖችውም በፅኑእ መከራ አሰቃያቸው ከእርሳቸውም ብዙዎችን ገደላቸው።

ሀገሮቻቸውን ትተው የተሰደዱም አሉ። ይህም አባት ሽሽቶ ወደ ገዳም ገባ ህዝቡም ፈልገው አጡት።

ከዚህም በኃላ ስሙ ዲዮስ የተባለ ሌላ ኤጲስቆጶስ በላያቸው ሾሙ። እርሱም በጥቂት ቀን አረፈ። ከዚህ በኃላ ስሙ አግርንዲኖስ የሚባል ሌላ ኤጲስቆጶስ ሾሙ።

የስደቱም ወራት በአለፈ ጊዜ ይህ አባት በርኪሶስ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ተመለሰ ።አግርንዲኖስ የሚባል ሌላ ኤጲስቆጶስ ሹመው አገኛቸው።

ወደርሳቸውም በደረሰ ጊዜ ህዝብ በመምጣቱ ደስ አላቸው አግርንዲኖስም ተመልሶ በመንበረ ጵጵስናው ላይ እንዲ ቀመጥ ለመነው በታላቅ ድካምም በወንበሩ ላይ አስቀመጡት። ከአግርንዲኖስም ጋራ አንዲት አመት ኖረ አግርንዲኖስም አረፈ።

አባ በርኪሶስም እጅግ እስኪያረጅና እስኪያረጅና እስኪደክም ድረስ ኖረ ወገኖቹንም ሌላ ኤጲስ ቆጶስ በላያቸው እንዲሾሙ ለመናቸው እነርሱም አይሆንም አሉ።

በዚያም ወራት የቀጰዶቅያ ኤጲስቆጶስ ስሙ እለእስክንድሮስ የሚባል አንድ ሰው ነበር። እርሱም በውስጥዋ ሊፀልይና ወዳገሩ ሊመለስ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።ስራውንም በጨረሰ ጊዜ የበአሉም ቀኖች በተፈፀሙ ጊዜ ወዳገሩ ሊመለስ ወደደ።

በመድኃኒታችን ትንሳኤ በአል በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ መግቢያ ወደ እገሌ ደጃፍ ውጡ ወደ ደጃፉ መጀመሪያ የሚገባውን ያዙት በጵጵስና ስራም ይረዳው ዘንድ ከበርኪሶስ ጋር አድርጉት የሚል ቃል እነሆ ተሰማ።

ወጥተውም ወደ ደጃፉ በደረሱ ጊዜ እለእስክንድሮስን አገኙት ይረዳውም ዘንድ ያለ ፈቃዱ ከአባት በርኪሶስ ጋራ አደረጉት። እስከሚአርፍበትም ጊዜ አብሮት ኖረ።

መላ የህይውቱ ዘመን አንድ መቶ አስራ ሰባት አመት ሆነ ኤጲስቆጶስነት ሳይሾም ሰማንያ አንድ አመት ኖረ በሹመቱም ላይ ሰላሳ ስድስት አምታትን ኖረ። እግዚአብሄርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።

† ቅዱስ እለእስክንድሮስ †

በዚችም እለት የሰማእቱ የቅዱስ እለእስክንድሮስ መታሰቢያው ነው። ይህም ቅዱስ ሰማእት የሮም ሀገር ሰው ነው ለእርሱ ባለመታዘዙና ለረከሱ ጣኦቶቹ ባለመሰዋቱ ከሀዲው መክስሚያኖስ ፁኑእ ስቃይን አሰቃየው።

እጅግ ከባድና ታላቅ የሆነ ደንጊያ በእጆቹና በእግሮቹ ላይ አስሮ ሰቀለው። ብዙ ግርፋትንም ገረፈው ጎኖቹንም ቀደደ በፊቱም ላይ የእሳት መብራት ጨመሩ።

ስቃዩንም ባልፈራ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ።
በመንግስተ ሰማያትም የሰማእታትን አክሊል ተቀዳጀ።

=>ዕድሜ ማቱሳላን ለንስሃ አምላከ ቅዱሳን ይስጠን!

=>መጋቢት 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ማቱሣላ (በ969 ዓመቱ ያረፈበት)
2.ቅዱስ በርኪሶስ ዘኢየሩሳሌም
3.ቅዱስ እለእስክንድሮስ
4.ቅዱስ መርቆሬዎስ
5.አባ ሚካኤል ዘሃገረ አትሪብና አባ ዮሐንስ ዘሃገረ ቡርልስ
(ሃይማኖተ አበውን: ግፃዌንና ስንክሳርን ያዘጋጁ ናቸው)

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
4.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
5.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር

=>+"+ ከእንቅልፍ የምትነሱበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ:: ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቧልና:: ሌሊቱ አልፏል: ቀኑም ቀርቧል:: እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ:: +"+ (ሮሜ. 13:11)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
ዝክረቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት

"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ፀሎት ስናረግ የቆሸሸው ሀጢአታችን ይነፃል እኛም ተስፋ ሳንቆርጥ ፀሎት እናርግ

@silase
/channel/silase

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🕊

[  † እንኳን ለታላቁ ነቢይና ሰማዕት ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †   ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †


🕊  ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ   🕊

† ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነ ዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል::
"ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: [ሉቃ.፩፥፮]

የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ [አድናቆት] ይገባል! እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ ፺ የዘካርያስ ደግሞ ፻ ደርሶ ነበር::

ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት [ኢሳ.፵፥፫] , ሚል.፫፥፩]  ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::

ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም ፳፮ [26] ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ፮ [6] ወራት ራሷን ሠወረች:: በ፮ [6] ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::

የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ [ሰገደ]:: ከዚህ በሁዋላ ሰኔ ፴ [30] ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::

ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ ፪ [2] ዓመት ከ፮ [6] ወር በሆነው ጊዜ ሰብአ ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕጻናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕጻን ነገሩት:: "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕጻን አለና እሱንም ግደል" አሉ::

እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል:: አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕጻኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ ፫ [3] ፭ [5] ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ ፭ [5] ፯ [7] ዓመት ሲሞላው ግን እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ ዘካርያስና ስምዖን ወርደው ቀበሯት::

ሕጻኑ ዮሐንስ ሲያለቅስ ድንግል ማርያም ስንት አገር አልፋ ሰማችው:: እርሷም ስደት ላይ ነበረችና:: ከጌታ ጋር በደመና ሒደው ድንግል አቅፋ አጽናናችው:: ጌታንም "እንውሰደው ይሆን?" አለችው:: ጌታችን ግን "ለአገልግሎት እስክጠራው እዚህ ይቆይ" አላት:: ባርካው: አጽናንታውም ተለያዩ::

ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ በሁዋላ በዚያ ቆላ የግመል ጠጉር ለብሶ: ጠፍር ታጥቆ ተባሕትዎውን ቀጠለ:: ለ፳፭ [25] ፳፫ [23] ዓመታትም በንጽሕና ሲኖር ከምድር አራዊትና ከሰማይ መላእክት በቀር ማንንም አላየም:: ይሕችን ዐመጸኛ ዓለምም አልቀመሳትም::

ከዚህ በሁዋላ ፴ [ 30 ] ዘመን ሲሞላው እግዚአብሔር ከሰማይ ተናገረው:: "ሒድ! የልጄን ጐዳና ጥረግ" አለው:: ነቢያት ስለዚህ ነገር ተናግረው ነበርና:: [ኢሳ.፵፥፫]  , [ሚል.፫፥፩] አባቱ ዘካርያስም "ወአንተኒ ሕጻን ነቢየ ልዑል ትሰመይ: እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ" [ሉቃ.፩፥፸፮]  ብሎ መንገድ ጠራጊነቱን ተናግሮ ነበርና::

ቅዱስ ዮሐንስ በዚያ ጊዜ በኃይለ መንፈስ ቅዱስ እየገሰገሰ ከበርሃ ወደ ይሁዳ መጣ:: ያዩት ሁሉ ፈሩት: አከበሩት:: ቁመቱ ቀጥ ያለ: ጽሕሙ እንደ ተፈተለ ሐር የወረደ: ጸጉሩ የቁራ ያህል የጠቆረ: መልኩ የተሟላ: ግርማው የሚያስፈራ ገዳማዊ ነውና::

ፈጥኖም ሕዝቡን ለንስሃ ሰበከ: ለንስሃም በርካቶችን አጠመቃቸው:: በዚህ አገልግሎት ለ6 ወራት ቆይቶ ጌታችን ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ዮሐንስ ሰማይን ከነግሱ: ምድርን ከነልብሱ የያዘ ፈጣሪ "አጥምቀኝ" ብሎ ሲመጣ ደነገጠ:: የሚገባበትም ጠፋው::

"እንቢ ጌታየ! አንተ አጥምቀኝ" አለው:: ጌታ ግን "ፈቅጄልሃለሁ" አለው: አጠመቀው:: በዚህ ምክንያት ይሔው እስከ ዛሬም "መጥምቀ መለኮት" ሲባል ይኖራል:: ቅዱስ ዮሐንስ በመጨረሻ ሔሮድስን ገሰጸው:: ንጉሡም ተቀይሞ ለ፯ [ 7 ] ቀናት አሠረው::

ልደቱን ባከበረ ጊዜ ወለተ ሔሮድያዳ በዘፈን አጥምዳ አስማለችው:: እርሱም የታላቁን ነቢይ ራስ አስቆርጦ በወጪት አድርጐ ሰጣት:: አበው "እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር" ይላሉ:: የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ በርራ ስትሔድ አካሉን ግን ደቀ መዛሙርቱ ቀብረውታል:: [ማቴ.፫፥፩] , ማር.፮፥፲፬ , [ሉቃ.፫፥፩] , [ዮሐ.፩፥፮] ርጉም ሔሮድስ አንገቱን ካስቆረጠው በሁዋላ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራሱ የጸጋ ክንፍ ተሰጥቷት ጌታችን ወዳለበት ደብረ ዘይት ሔዳ በፊቱ ሰገደች:: ቅዱሳን ሐዋርያት በአዩት ነገር ተገርመው ራሱን እጅ ነሷት::

ከዚሕ በሁዋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ዮሐንስ ራስ የማስተማር ስልጣን ሰጥቶ አሰናበታት:: በመላው ዓለም ለ፲፭ [15] ዓመታት ስትሰብክ ኑራ ዓረቢያ ውስጥ ዓርፋለች::

† አስማተ-ዮሐንስ መጥምቅ [የመጥምቁ ዮሐንስ ስሞች]

፩. ነቢይ
፪. ሐዋርያ
፫. ሰማዕት
፬. ጻድቅ
፭. ካሕን
፮. ባሕታዊ/ገዳማዊ
፯. መጥምቀ መለኮት
፰. ጸያሔ ፍኖት [መንገድ ጠራጊ]
፱. ድንግል
፲. ተንከተም [የብሉይና የሐዲስ መገናኛ ድልድይ]
፲፩. ቃለ አዋዲ [አዋጅ ነጋሪ]
፲፪. መምሕር ወመገሥጽ
፲፫. ዘየዐቢ እምኩሉ [ከሁሉ የሚበልጥ]

† ጌታችን መድኃኔ ዓለም መጥምቁ ዮሐንስን አስቦ ይቅር ይበለን:: ጸጋውን: በረከቱንና ክብሩንም ያሳድርብን::

🕊

[  † የካቲት ፴ [ 30 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
[ታላቁ ነቢይና ካህን መጥምቁ ዮሐንስ ሔሮድስ በግፍ አንገቱን ካስቆረጠው በሁዋላ ቅድስት ራሱ ለ፲፭ [15] ዓመታት ዙራ አስተምራ አርፋለች:: በዚህ ዕለትም በልሑክት [በሸክላ ዕቃ] የተገኘችበት በዓል ይከበራል:: በዓሉም "ተረክቦተ ርዕሱ" በመባል ይታወቃል::]
፪. አባ ሚናስ ሊቀ ዻዻሳት

[  † ወርኀዊ በዓላት  ]

፩. ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ [ሐዋርያ]
፪. አባ ሣሉሲ ክቡር
፫. ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
፬. ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት

" ጌታ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ . . . ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችሁአለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን . . . እውነት እላቹሃለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም . . . ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ:: ልትቀበሉትስ ብትወዱ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይሕ ነው:: የሚሰማ ጀሮ ያለው ይስማ::" † [ማቴ.፲፩፥፯-፲፭]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]
        
/channel/silase
/channel/silase
/channel/silase

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የካቲት 30/2016 #ቅዱስ_ዮሐንስ
#ቅዱስ_ማርቆስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሣኑ ስም ለምናመሰግንበት ለቅዱሣኑ ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን

👉እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ #ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም ማቴ11፥11

👉የጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ቃል ስለ መጥምቀ መለኮት #ቅዱስ ዮሐንስ ክብር መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በጌታ የተከበረ ነቢይ እና ጻድቅ ነው እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ የለም በማለት የተናገረለት ቅዱስ አባት ነው

👉የመጥምቀ መለኮት #ቅዱስ_ዮሐንስ
የተሰጡት ሃብተ ፀጋዎች

1 👉 ነብይ
2 👉 ካህን
3 👉 መምህር
4 👉 ሐዋርያ
5 👉 ፃድቅ
6 👉 መጥምቅ
7 👉 ሰማእት ነው

👉 #ቅዱስ_ዮሐንስ ከነቢያት ሁሉ የሚበልጥ መሆኑን ጌታችን ሲናገር እንዲህ ብሎ ተናግሮለታል ከነቢያት ሁሉ የሚበልጥ #ነብይ ነው እላችኋለሁ በማለት መስክሮለታል

👉 #ቅዱስ_ዮሐንስ ሃቀኛ መምህር፤ ነቢይ፤ ካህን፤ ሰማዕት፤ ሐዋርያ በመሆኑ ከአምላኩ ክብርን የተቀበለ ቅዱስ አባት ነው ስለዚህ ነው ደግሞ ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ እራሱ ግልጽ አድርጎ ስለ #ቅዱስ_ዮሐንስ ክብር የተናገረው

👉ትንቢት የተነገረለት #ቅዱስ_ዮሐንስ ክብሩ በመልአኩ እንዲህ በማለት ነው የተመሠከረለት #በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ነቢይ እንደሆነ #በመንፈስ_ቅዱስ የተመረጠ በንጽሕናው በአገልግሎቱ #በመላእክት ደረጃ የሚታሰብ ሲሆን ምልጃና ፀሎቱ የከበረዉ
ቃል ኪዳን ሁላችንንም ይጠብቀን

👉ለኢትዮጲያና ለግብፅ አባታችን አስተማሪያችን የሆነዉ ሐዋርያዉ #ቅዱስ_ማርቆስ በዚህ እለት የመታሠቢያ በአሉ ሲሆን ምልጃና ፀሎቱ ረድኤትና በረከቱ የአባትነት ፍቅሩ አይለየን የተባረከ #ቀዳሚት_ሰንበት ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ደስ ይበል በጣም
አምላኬ እረኛዬ ደስታዬ መመኪያዬ|፪|


ደስ ይበለን በጣም ደስ ይበለን
በረከቱን ለኛ ስላደለን(፪)

በጨለማ ስንኖር - - - ደስ ይበለን
በኃጢአት ተከበን - - - ደስ ይበለን
የሕይወትን ብርሃን - - - ደስ ይበለን
ፍቅሩን አበራልን - - - ደስ ይበለን
ወደ ምስራቅ እንይ - - - ደስ ይበለን
ፀሐይ ወዳለበት - - - ደስ ይበለን
ጨለማው ልባችን - - - ደስ ይበለን
ጎህ እንዲቀድበት - - - ደስ ይበለን
       _አዝማች_
የፀሐይ እናቱ - - - ደስ ይበለን
ማርያም እመቤቴ - - - ደስ ይበለን
እለምንሻለሁ - - -ደስ ይበለን
እስከ ዕለተ ሞቴ - - - ደስ ይበለን
የልቤ ማረፊያ - - - ደስ ይበለን
የዘላለም ቤቴ - - - ደስ ይበለን
አንቺ ነሽ ተስፋዬ - - - ደስ ይበለን
ዕፀ መድኃኒቴ - - - ደስ ይበለን
     አማላኬ እረኛዬ ደስታዬ መጠጊያዬ |፪|
አዝማች =======
የግሸኗ ንግሥት - - - ደስ ይበለን
የአምላኬ እናት - - - ደስ ይበለን
ሆና ተሰጥታለች - - - ደስ ይበለን
ለሚመኩባት - - - ደስ ይበለን
በልቼ ጠጥቼ - - - ደስ ይበለን
የምረካብሽ - - - ደስ ይበለን
ጎጆ ማረፊያዬ - - - ደስ ይበለን
ማርያም አንቺ ነሽ - - - ደስ ይበለን
       አዝ= = = = =
ፀአዳ እመቤቴ - - -ደስ ይበለን
ሐመልማለ ሲና - - - ደስ ይበለን
የሕዝቅኤል ደጃፍ - - - ደስ ይበለን
የሙሴ ደመና - - - ደስ ይበለን
የንጉሥ ሙሽራ - - - ደስ ይበለን
የዳዊት በገና - - -ደስ ይበለን
የተዋበች ዕንቁ - - - ደስ ይበለን
የደጎች አዝመራ - - - ደስ ይበለን
በማህፀንሽ ፍሬ - - - ደስ ይበለን
ሕይወታችን በራ - - - ደስ ይበለን
አምላኬ እረኛዬ ደስታዬ መመኪያዬ
    
የበእርሱፈቃድ እንዳልካቸው

/channel/silase

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የካቲት 29/2016 #ቅዱስ_በዐለ_ወልድ
#ፅንሰት_ልደት_ትንሣኤ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን በዚህ ቀን እመቤታችን #ቅድስት_ድንግል_ማርያም የከበረ መልአክ የቅዱስ ገብርኤልን የምሥራች የሠማችበት አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ የተወለደበት የከበረዉን #ትንሣኤውን የገለጠበት ወርሐዊ መታሰቢያ ነዉ

👉እንዲሁም በዚህች ቀን #አለም_የተፈጠረበት የጌታችንን ዳግመኛ #ምፅአቱን የምንጠባበቅበት እለትም ጭምር ነዉ

👉በዚህች ቀን ለእመቤታችን ለቅድስት #ድንግል_ማርያም የከበረ #መልአክ_ገብርኤል_የምሥራች የነገረበት ድኅነትን የተመላች ታላቅ በዓል ናት በዚህም የከበረ ወንጌል ምስክር ሁኗል እንዲህ ሲል

👉ኤልሳቤጥ ከፀነሰች በኋላ በስድተኛው ወር #መልአኩ_ገብርኤል የገሊላ ክፍል የሆነች ናዝሬት ወደምትባል አገር ከዳዊት ወገን ለሆነ ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደታጨች ወደ አንዲት ድንግል #ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ

👉የድንግሊቱም ስም #ማርያም ነው መልአኩም ወደርሷ ገብቶ ደስተኛ የሆንሽ ደስ ይበልሽ ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው አንቺ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ አላት እርስዋም አይታ ከንግግሩ የተነሣ ደንግጣ እንዴት እንዲህ ያለ ሰላምታ ይቀበሏል ብላ አሰበች

👉መልአኩም እንዲህ አላት #ማርያም ሆይ #በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻልና አትፍሪ እነሆ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ስሙንም #ኢየሱስ ትይዋለሽ እርሱ ታላቅ ነው የልዑል #እግዚአብሔር ልጅም ይባላል

👉 #እግዚአብሔር አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል ለያዕቆብ ወገንም ለዘላለም ነግሦ ይኖራል ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም

👉ማርያምም መልአኩን ወንድ ሳላውቅ ይህ እንደምን ይሆናል አለችው መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት መንፈስ ቅዱስ መጥቶ ያድርብሻል የልዑል ኃይልም ያጸናሻል ከአንቺ የሚወለደው ከሶስቱ አካል አንዱ የልዑል #እግዚአብሔር ልጅ ይባላል

👉እነሆ ዘመድሽ ኤልሳቤጥም እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ፀንሳለች ወንድልጅም አገኘች ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና #ማርያምም እነሆኝ #የእግዚአብሔር አገልጋይ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለችው።

👉ያን ጊዜም ድንግል ስትሆን ረቂቅ ፅንስን ተቀበለች የእግዚአብሔር አካላዊ ቃል #ወልድ_ዋህድ ለኩነተ ሥጋ ወርዶአልና ይህም አንድ ባሕርይ አንድ ህልውና ሲሆን ከሦስቱ አካላት አንዱ ነው

👉ከዓለም መፈጠር አስቀድሞ የነበረ በማይመረመር ድንቅ በሆነ ተዋሕዶ እንዴትም እንደሆነ በማይታወቅ #በቅድስት_ድንግል_ማርያም ማሕፀን አደረ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ተፀንሶ በህቱም ድንግልና ታህሣሥ ሀያ ዘጠኝ ቀን ተወለደ

👉በዚያን ጊዜም የኋላ ኋላ መለየት ከቶ የሌለውን ፍጹም ሰውነት ነሥቶ ተዋሐደ መለኮቱ ከትስብእቱ ጋራ ያለ መለያየት አንድ ሆኖአልና ይቺም ዕለት የበዓላት ሁሉ በኩር ናት በእርሷም #የዓለም_ድኅነት ተጀምሮዋልና

👉ዳግመኛ በዚህችም ዕለት ደግሞ በመድኃኒታችን በከበረችና ልዩ በሆነች #ትንሣኤው የዓለም ድኅነት ሆነ በረቀቀ ጥበቡ ሠላሳ ሦስት ዓመት ያህል በምድር ላይ ሥራውን ሠርቶ በፈጸመ ጊዜ በፈቃዱ ሕማማተ መስቀልን ተቀብሎ ሙቶ ከተቀበረ በኋላ በሦስተኛው በዚች ቀን #በሃያ_ዘጠኝ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቷልና

👉በዚች ቀን አስቀድሞ ደጅ ለሚጠኑት በዓለም ላሉ ሰዎች ሰው በመሆኑ ድኅነታቸውን አበሠራቸው እንዲሁም ደግሞ በዚች ዕለት ከሲኦል በመዳን #ሙታንና_ሕያዋን ደስ አላቸው

👉በዚህም በጌታችንና በመድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በሥጋ መነሣት መነሣታቸውን አረጋገጡ የከበረ ጳውሎስ በመነሣቱ ክርስቶስ የሙታን በኵር ሆነ እንዳለ እርሱ ለሙታን በኵራቸዉ ነዉና

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከበአሉ በረከት ሁላችንንም ያሣትፈን ዳግም ሲመጣም ከቅዱሳኑ ጋር ይደምረን የምንሰማዉን የምናየዉን ክፉ ነገር ሁሉ ወደ በጎ ነገር ይቀይርልን

👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸዉ የምናስባቸዉ ፃድቁ #አቡነ_እጨጌ_ዮሐንስ በምልጃ ፀሎታቸዉ ይጠብቁን "አሜን" ✝️💒✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

†✝† እንኳን ለኢትዮዽያዊቷ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †✝†

†✝† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †✝†

†✝† እመ ምዑዝ (እም ምዑዝ) †✝†

††† ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ሐዋርያዊት: ጻድቅትና ሰማዕት ናት::
ይህስ እንደምን ነው ቢሉ:-
=>ወር በገባ በ29 በቤተክርስቲያናችን ታስበው
ከሚውሉት እግዚአብሔር አምላክ ቃል ኪዳን ከገባላቸው
(ከሰጣቸው) እናቶች ኢትዮጵያዊቷ ሰማዕትና ጻድቅት
ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ (እመ ምዑዝ) ትገኛለች::
ፍቅርተ ክርስቶስ (እመ ምዑዝ) ማን ናት? ምን ቃል ኪዳን
ተሰጣት? ያደረገችውን ተጋድሎ በጥቂቱ እንመልከት:-
✞✞ ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ
ይወስዳል፡፡ (ማቴ. 10፡40) ✞✞

=>በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በመቂት ወረዳ ጥባ
ማርያም ቀበሌ ውስጥ ምን ታምር በመትባል ቦታ ላይ
በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያዊቷ ሰማዕትና
ጻድቅ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ የተመሰረተቸው እመ
ምዑዝ ኪዳነ ምህት ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አንድት
ገዳም ትገኛለች፡፡

+ይህች ገዳም ከአዲስ አበባ በደሴ ወደ ጎንደር
በሚወስደው መንገድ 665 ኪሎ ሜትር ከተጓዙ በኋላ
ገራገር (ፍላቂት) ከምትባለው ከተማ በመውረድ በእግር
2፡30 እንደተጓዙ ከ370 ዓመት ባለይ ያስቆጠረችውን
እመ ምዑዝ ኪዳነምህት ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ በአንድ
ቀን የሠራቻትና ለጌታ በአራቱም አቅጣጫ የሰገደችውን
ታላቅና ድንቅ ቤተመቅደስ ያገኛሉ፡፡

+የዚህች ታላቅ ገዳም መስራች ኢትጵያዊት ሰማዕትና
ጻድቅ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ በደቡብ ጎንደር ደራ ፎገራ
አንበሳሜ ወረዳ ልዩ ስሙ አቡነ ሐራ ገዳም አዋሳኝ ከተታ
ማርያም ተብሎ በሚጠራ ቦታ በሚያዚያ 4 ቀን ተፀንሳ
ታህሳስ 29 በጌታ ልደት ቀን ተወለደች፡፡

+አባቷ ላባ እናትዋ ወንጌላዊት የተባሉ እግዚዘብሔርን
የሚወዱ ትዕዛዙን የሚከብሩ ደጋግ ሰዎች ነበሩ፡፡
መሀን ሆነው ልጅ ባመውለዳቸው እያዘኑ ተግተው ወደ
እግዚአብሔር በመፀለያቸው ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስን
የመሰለች ልጅ: በፀሎትዋ ለሀገር ለወገን የምትበቃ
ሰጥቷቸዋል፡፡

+ከዚያም 80 ሲሆናት ለልጅነት ጥምቀት ወደ ቤተ
መቅደስ በወሰዷት ጊዜ ከጥምቀት በኋላ ስጋ አምላክ
ስትቀበል (ስትቆርብ) "ሕይወት የሆነውን ቅዱስ ስጋህን
ክቡር ደምህን የሰጠኸኝ አምላኬ ክብር ምስጋና ይግባህ"
ብላ አመስግናለች፡፡ ስመ ክርስትናዋ ማርያም ፀዳለ
ሲሆን የአለም ስሟ 'ሙዚት' ነው፡፡ ፍቅርተ ክርስቶስ
የምንኩስና (የቆብ) ስሟ ነው፡፡

+እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አባ ዳንኤል ከሚባል
አባት መፅሐፍን እየተማረች ካደገች በኋላ ለአቅመ ሄዋን
ስትደርስ እናትና አባቷ ሊድሯት በመፈለጋቸው ዘርዓ
ክርስቶስ ለሚባል ከደጋግ ሰዎች ወገን ለሆነ ሰው
አጋቧት፡፡

+ማታ እንደ ሙሽሮች ደምብ ወደ ጫጉላ ቤት ሲገቡ
ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ዘርዓ ክርስቶስን "ወንድሜ ሆይ!
እኔ የእናት አባቴን ፍቃድ ለመፈፀም ነው እንጂ ስጋዊ
ሙሽራ መሆን አልፈልግም ፡፡ ፍላጎቴ የእግዚአብሔር
ሙሽራ መሆን ነው" በማለት ብታማክረው ቅዱስ ዘርዓ
ክርስቶስም ፀጋ እግዚአብሔር የበዛለት ሰው ነበርና "እኔም
እናት አባቴን ላክበር ፈቃዳቸውን ለመፈፀም ነው እንጂ
የስጋ ፈቃድ የለኝም በማለት ተነጋገሩ::

+በኋላ በአንድ ቤት ውስጥ ለቤተሰቦቻቸው: ለአገሬው
እንደ ባልና ሚስት ግን በንፅህና ለ40 ዓመት ሁለቱም
በድንግልና ኖረዋል፡፡

+ከዚያም በኋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ ቅዱስ ሚካኤል
መጥቶ ወንድ ልጅ እንደሚወልዱ ቢግራቸውም ሁለቱም
"ይህስ አይሆንም" ብለው ለ40 ቀን በጾም: ፀሎት:
በትጋት ጸልየዋል፡፡ መልአኩ ተገልጦ "ይህ የእግዚአብሔር
ፈቃድ ነው ሁለታችሁም ድንግልናችሁ አይፈርስም ብሎ
ነግሮአቸዋል፡፡

+ከዚያም ወንድ ልጅ ወልደዋል:: ህፃኑ በተወለደ በ7
ዓመቱ በቅዱስ ሚካኤል እቅፍ ገነትን ለ7 ቀናት ከጎበኛት
በኋላ ወደ ምድር ሲመልሰው "በእናት አባቴ አምላክ
ይዤሃለሁ ወደዚች ወደ ከፋች ዓለም አትመልሰኝ" ብሎ
ቢለምነው ቅዱስ ሚካኤልም ከአምላክ ጠይቆ በብሔረ
ህያዋን የህፃናት አለቃ ተብሎ እንዲቀመጥ አድርጎታል፡፡
ስሙም ዳግማዊ ቂርቆስ ተብሏል፡፡

+ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶና ቅዱስ ዘርዓ ክርስቶስም ልጅ
ከወለዱ በኋላ እንደ ቀደሞው በቅድስና: በንፀህና ፀንተው
ኑረዋል፡፡ በዘመናቸው በኢትዮጵያ ነግሶ የነበረው አፄ
ሱስንዮስ ሃይማኖቱን ለውጦ 'ሁለት ባህርይ የሚሉ
ካቶሊኮችን በመቀበሉ ክርስቲያኖችን እየገደለ ነው' የሚል
ወሬ ሰምተው ወደ ንጉሱ በመሄድ ሳይፈሩ ስለ ተዋህዶ
ሃማኖታቸው በንጉሱ ፊት መስክረዋል፡፡

+ንጉሱም በጣም የበዛ መከራን አድርሶባቸዋል፡፡ መከራ
በበዛ ቁጥር እነርሱም እየፀኑ ተከታዮቻቸውንና የንጉሱን
ሠራዎቶች ሳይቀር አሳመኑ:: 60,000 ክርስቲያኖችም
ሰማዕትነትን ተቀብለዋል፡፡

+ንጉሱም በጣም የበዛ መከራ አድርሶባቸዋል፡፡ መከራ
በበዛ ቁጥር እነርሱም እየጸኑ ተከታዮቻቸውንና የንጉሱን
ሰራዊቶች እያሳመኑ ቢያስቸግሩ በሰማዕትነት አንገታቸውን
አስቆርቷቸዋል፡፡ አንገታቸውም ሲቆረጥ ከሁለቱም ደም
ውሃ ወተት ፈሷዋል፡፡

+በዚያን ዘመን ከእነ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ጋር
ሰማዕትነት ከተቀበሉት ውስጥ የማህበረ ስላሴው ጻድቁ
አምደ ሥላሴ: የጎረጉር ማርያም አባ መርአዊ: የመሲ
ኪዳነ ምህረት እመ ወተት እና ከ60 ሺ በላይ ክርስቲያኖች
ሰማዕትነት ተቀብለዋል፡፡

+ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አንገቷ ከተቆረጠና ሰማእትነት
ከተቀበለች በኋላ ወደ ምድር መልሶ አንገቷን ከቀሪው
የሰውነቷ ክፍል ጋር አዋህዶ ከአንቅልፍ አንደሚነቃ ሰው
ቀስቅሶ አስነስቷቷል፡፡
ከዚያም ከአቡነ ማርቆስ ስርዓተ ምንኩስናን በመቀበል
ዋልድባ ገዳም ለ4 ዓመት አገልግላለች፡፡

+ከዚህም ከ500 የሚበልጡ ተከታዮችዋን መነኮሳትን
አስከትላ በሰሜን ወሎ ቆቦ ወረዳ ወደምትገኘውና በፃድቁ
በአባ ጉባ ተመስርታ ጠፍታ ወደ ነበረችው ራማ ኪደና
ምህረት አንድነት ገዳም በመሄድ ገዳሟን አቅንታ: የወንድ
የሴት ብላ ስርዓት ሰርታ: ገዳሟን አስተካክላ: 500
የሚሆኑ አገልጋች መነኮሳትን አኑራ ወደ ኢየሩሳሌም ጉዞ
ጀምራለች፡፡

+በመንገዷም ላይ ሰውን የሚበሉ ወደ ሚኖሩበት አካባቢ
በመድረስ እነርሱም እርሷንና 60 የሚሆኑ አገልጋዮችዋን
ዓይኖቻቸውን በጉጠት በማውጣት ለ4 ወራት በጨለማ
ቤት ውስጥ ዘግተውባቸዋል፡፡ ከአራት ወር በኋላም በዓል
አድገው ለመብላት ከቤት ቢያወጧቸው መልካቸው እንደ
ፀሐይ የሚያበራ ቢሆንባቸው "አንቺ ሴት ምንድን ናችሁ?"
ብለው ጠይቀዋታል፡፡

+እርሷም ክርሰቲያን መሆናቸውንና እነሱ የስላሴ ሕንፃ
የሆነውን የሰውን ልጅ መብላት እንደሌለባቸው
ብትመክራቸው "ምን አንብላ?" ብለዋታል፡፡ እርሷም
ከራማ ኪዳነ ምህረት ስትነሳ የእህል ዘርን በአገልጋዮቿ
አሲዛ ነበርና ስንዴውን በአንድ ቀን ዘርታ: በቅሎ: ታጭዶ:
ደርቆ: ተፈጭቶ ለምግብነት በቅቷል፡፡

+እርሷ ቀምሳ ብታቀምሳቸው እንደማር እንደ ወተት
የሚጣፍጥ ሆኖላቸው በደስታ ተመግበውታል፡፡ ከዚያም
እንደዚህ እያደረጉ እየሰሩ እንዲበሉ አስተምራ: አስጠምቃ
ከ6 የሚበልጡ አብያተ ክርስቲያናትን አስተክላላቸዋለች፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/4RRPHCYgZY4

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Selam ende ameshachu

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Egziabher yimesgen selam new

Читать полностью…
Subscribe to a channel