kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

መጋቢት 10 ቀን በዓመታዊ የዕረፍት በዓላቸው ታስበው የሚውሉት የዲማው አቡነ ተከስተ ብርሃን ይኽንን ታላቅ ተኣምር አደረጉ፡- አንዲት የአገረ ገዥው ልጅ በጽኑ ሕማም ተይዛ መላ አካሏና እጅ እግሯን ታመመች፡፡ በእባብ መርዝም ተመርዛ የሆድ ዕቃዋ ሁሉ ወጥቶ ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ አቡነ ተከስተ ብርሃን በሃይማኖቱ ምክንያት ሰማዕትነት የተቀበለበትንና የተገረፈበትን የሰውነቱን እጣቢ ‹‹ይህንን ወስደህ ‹በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ፈውስ ይሁንሽ› ብለህ ልጅህን ይህንን ሰውነቷትን ቀባት› ብሎ ለአገረ ገዥው አባቷ ሰጠው፡፡

አገረ ገዥውም ወስዶ በፍጹም ልቡናው አምኖ በጽኑ የታመመች ልጁን ከራስ ፀጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ ድረስ መላ ሰውነቷን አቡነ ተከስተ ብርሃን ሰማዕትነት የተቀበለበትን የደሙን እጣቢ ቀባት፡፡ በዚህም ጊዜ የአገረ ገዥው ልጅ ወዲያው ተፈወሰች፡፡ እባቡም ከውስጧ ወዲያው ወጣ፡፡ ቤተሰቢቿም ‹‹እስቲ እንደቀድሞው በሰላም በእግርሽ ተራምደሽ ሒጂ›› አሏት፡፡ እርሷም ፈጥና ተነሥታ ተራመደች፤ ምግብም በላች፡፡ አገረ ገዥም ልጁ በአቡነ ተከስተ ብርሃን ጸሎት ስለዳነችለት እጅግ ደስ ብሎት እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡
የአቡነ ተከስተ ብርሃን ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!

በአንድ ጊዜ 9999 (ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ) ሰዎችን በአንዲት ዕለት ሲያጠምቁ ከሰማይ ብርሃን ስለወረደላቸው ‹ተከስተ ብርሃን› ተብለው የተጠሩት ታላቁን ዲማ ጊዮርጊስን የመሠረቱና ጣኦታትን ጨርሰው ያጠፉት ናቸው፡፡ የጻድቁ መቋሚያቸው የሚሞተውንና የማይሞተውን ሰው ለይታ ትናገር ነበር፡፡ የአቡነ ተከስተ ብርሃን የትውልድ ቦታቸው መንዝ ነው፡፡ መንዝ ማለት ነዝሀ ከሚለው ከግእዝ ቋንቋ የተገኘ ነው፡፡ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ጌታችን በተሰቀለ ጊዜ የፈሰሰ ደሙን በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ በብርሃን መነሳነስ ዓለምን ሲረጭ አስቀድሞ ይህችን መንዝ የምትባለውን አገር ከሁሉ አስቀድሞ ስለረጫት ደመ መለኮቱን እንደ አውድማ ስለለቀለቀው በዚህ ምክንያት መንዝ ተብላለች፡፡ በዚህች ቦታ እነ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን፣ አቡነ ፊሊጶስን፣ አቡነ አኖሬዎስን፣ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራን ጨምሮ ብዙ ታላላቅ ቅዱሳን ተፀንሰው ተወልደው አድገውባታል፡፡
አቡነ ተከስተ ብርሃንም በዚህች ምድር ነው ተወልደው ያደጉት፡፡ የመጀመሪያ ስማቸው በኪሞስ ይባላል፡፡ ከመንዝ መንነው ወደ ደብረ ሊባኖስ በመምጣት ብዙ ተጋድሎ አድርገዋል፡፡ በዚያም በአቡነ አኖሬዎስ እጅ መንኩሰዋል፡፡ ከደብረ ሊባኖስ ወደ ጎጃም በሔዱ ጊዜ አቡነ ተክለሃይማኖት ይሰግዱባት የነበረችውን የእመቤታችንን ሥዕል ምስለ ፍቁር ወልዳ ይዘው ነበር የሚንቀሳቀሱት፡፡ ከዚያም ወደ ጎጃም ክፍለ አገር በ12ኛው መ/ክ/ዘ በዓምደ ጽዮን ዘመነ መንግሥት እንደመጡ ገድላቸው ይናገራል፡፡ መጥተውም በቢቸና አውራጃ ድማ ጊዮርጊስ ተቀመጡ፡፡ አባታችን ወደ ጎጃም ከመጡ በኋላ ማረፊያቸውና የጸሎት በዓታቸው ያደረጉት ዲማ ጊዮርጊስን ነው፡፡ ከዚያም አባታቸው አቡነ ፊሊጶስ በሃይማኖት ምክንያት ወደ ትግራይ ሲሰደዱ እርሳቸውም ተሰደው ብዙ ጊዜ ከቆዩ በኋላ መምህራቸው አቡነ ፊሊጶስ ወደ ጎጃም ክፍለ ሀገር ሔደህ አስተምር አሉት፡፡ ከዚያም ተነሥተው በግሸና አድርገው የዓባይን ባሕር በተአምራት ከፍለው ወደ ጎጃም ክፍለ ሀገር ተሻግረው የከበረች ወንጌልን ለሕዝቡ አስተምረው 9999 (ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ) ምእመናንን ሲያጠምቁ ዓምደ ብርሃን ተተክሎ እያበራ ከዚያች ቦታ ስለታዬ አባ በኪሞስ ይባል የነበረው ስማቸው ተለውጦ ‹‹ተከስተ ብርሃን›› ተባሉ፡፡ ያጠምቁባት የነበረችውም ወንዝ እሳት ዙሪያዋን ስለከበባት ‹ነድ ሐጸረ› ተብላ ዛሬም ድረስ ‹ነድ አጥራ› እየተባለች ትጠራለች፡፡

ከዚያም አቡነ ተከስተ ብርሃን ተነሥተው ወደ ቢቸና አውራጃ እነማይ ወረዳ ውስጥ አንድ ጫካ አገኙ፡፡ ከዚያ ውስጥም ትልቅ ዋሻ አለ፡፡ ከዚያም የያዙትን ታቦት በአንድ ዋሻ ውስጥ አኑረው ስሟንም ‹ድማ ማርያም› አሏት፡፡ በዚያም ገድ ወንዝ በተባለው አካባቢ ሴቶችን መካን ታደርግ የነበረችውንና ሙላድ የተባለችውን ጋኔን በቋሚያቸው አባረው አጥፍተዋታል፡፡ ይህችም ሙላድ የተባለችው ጋኔን ሴቶችን እንዳይወልዱ በማድረግ የምታመክን ነበረች፡፡ አባታችንም ተነሥተው ወደ ገድ ወንዝ በመሔድ በዚያ ለሙላድ ይሰግዱላትና ያመልኳት የነበሩትን ብዙ ሕዝቦች አስተምረው ሙላድን በቋሚያቸው አባረው ሰኔ 21 ቀን አገው ምድር እንጅባራ ድረስ አባረዋታል፡፡ ከዚያም ተመልሰው ሲመጡ ዓባይን ተሻግረው ጉታ ሲደርሱ ከዚህ ናዳ ማርያም አርፈው እንሔዱ ገድላቸው ይናገራል፡፡ ከዚያም ተነሥተው ወደ ዲማ ሔደዋል፡፡ ከዚያም ድማ ማርያምን ተክለዋል፡፡ ከዚያም የወንዶችና የሴቶች ገዳም አቋቁመው በተጋድሎ ብዙ ጊዜ ከቆዩ በኋላ መጋቢት 10 ታላቅ ቃልኪዳን ተቀብለው ዐርፈው ባቋቋሙት በድማ ማርያም የከበረ ዐፅማቸው በክብር ተቀምጧል፡፡ ቃልኪዳናቸውም እስከ 22 ትውልድ ነው፡፡ የከበረች በረከታቸው ትደርብን በጸሎታቸው ይማረን!

(የበፊቶቹ ኹለቱም የቴሌግራም ቻናሎች ተጠልፈው ከእኔ ውጭ ስለኾኑ ለ3ኛ ጊዜ አዲስ በተከፈተው
ቻናል በኩል በጽሑፍና በድምፅ ይከታተሉ።)

1. ቴሌግራም ቻናል
/channel/kegedilatandebet27217

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Share ክህነት የሚቀበሉ ፎርም 2016.docx

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ቅድስት ( የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት )

«ቅድስት» ማለት « የተቀደሰች የተለየች » ማለት ነው፡፡ ምስጢራዊ መልእክቱ ግን የምስጢረ አድኅኖት ታላላቅ ሥራውን ለመጀመር መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶሰ በገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ የጾማት የአርብዓው ቀንና ሌሊት ልዩ የሆነችና ክብርት ጾም የምትጀመርበትን ሁለተኛ ሳምንት ከልብ ያሳስበናል፡፡ ማቴ. 4-2

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ ‹‹ይኽቺ ዓለም አትጠቅመኝም›› ብለው በመነኑባት በዛሬዋ ዕለት መጋቢት 9 ቀን ይኽንን ታላቅ ተኣምር አደረጉ፦ አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ በሕይወተ ሥጋ ሣለ ከዕለታት በአንደኛው ቀን ከደቀ መዝሙሩ ከአባ ልብሰ ክርስቶስ ጋር በጎዳና ሲሔዱ የደረቀ የሰው አጥንት አግኝቶ አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ ፈጽሞ ወደ እግዚአብሔር ለመነ፡፡ ያንጊዜም በጸሎቱ ኃይል ያ የሞተውና የደረቀው አጥንት ነፍስ ዘርቶ ተነሣ፡፡ ያንጊዜም አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ ‹‹ከወዴት ነበርክ?›› ብሎ ጠየቀው፡፡ ሞቶ የተነሣውም ሰው ‹‹…እኔ አስቀድሜ ያልተጠመቅሁ አረመኔ ስሆን የሰውን ገንዘብ የምቀማ ሽፍታ ወንበዴ ነበርኩ፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን በገንዘብ ፍቅር የተነሣ ከጓደኞቼ ተጣልቼ ከበው ደብድበው ገድለው በዚህ ቦታ ጣሉኝ፣ ሥጋዬንም በከንቱ የዱር አራዊት በሉት፣ ነፍሴንም የጨለማ አጋንንት እያዳፏት እየገፏት ወስደው ወደ ሲኦል ወረወሯት፡፡ በሲኦል ውስጥ ሆኜ ብዙ ብዙ መከራና ሥቃይን አየሁ፡፡ በኃጢአታቸው ተፈርዶባቸው ወደ ሲኦል የገቡ ሕዝበ ክርስቲያን ዕለተ ሰንበትን የሚያከብሩ ከሆነ ዐርብ ዕለት በሰርክ በዘጠኝ ሰዓት ወጥተው እስከ ሰኞ ጠዋት በዕረፍት ቦታ በገነት ይቆያሉ፡፡ እናንተም የእግዚአብሔር ወዳጆች የሆናችሁ ቅዱሳንና መላእክት በሰንበት ዕለትና በበዓላት ነፍሳትን ከሲኦል አውጥታችሁ ተድላ ደስታ ወዳለበት ወደገነት ታስገባላቸሁ፡፡ ሰንበትን የሻሩ ግን ከዓመት እስከ ዓመት ዕረፍት የላቸውም፣ መከራ ይበዛባቸዋል፡፡
እኛም ከእኛ በታች ካለ ጥልቅ እሳት ውስጥ ከሚኖሩ ጋር ያለዕረፍት ስንሠቃይ እንኖራለን፣ ዕረፍት የለንም፡፡ ከእናተ መካከል በቅዱሳን በዓላትና በሰንበት ነፍሳትን ከሲኦል እሳት የሚያወጡ አሉ፤ በፈረስም ሲኦል ገብተው ነፍሳትን የሚያወጡ አሉ፤ በራሳቸውም ላይ የወርቅ ዘውድ የደፉ አሉ፤ በክንፍ ወደ ሲኦል ገብተው ብዙ ክርስያንን የሚያወጡ አሉ፡፡ እንደእኛ ያለውን ግን የሚያወጣ የለም፡፡ እኛም ‹‹..ለዘመዶቻችን ስለኃጥአን በተሰቀለ ሞቶ ከሙታን ተለይቶ በ3ኛው ቀን በተነሣ በክርስቶስ ያምኑ ዘንድ ማን በነገራቸው!?..›› እንላለን፡፡ በቀናች በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት አምነው በመልካም ምግባር ጸንተው ያሉ ከዘላላም ሥቃይ እሳት ይድናሉ፡፡ አባት ሆይ በክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውና በክቡር ደሙ አንተን ተማጽኛለሁ ዳግመኛ ወደ ሥቃይ ቦታ ወደ ሲኦል እሳት እንዳልመለስ በጸሎትህ አድነኝ አለው፡፡ ያንጊዜ አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ ፊቱን አቅንቶ እጁን ዘርግቶ በመጸለይ ወዲያውኑ ለአንተ አሥራት ይሆንህ ዘንድ ሰጥቼሃለሁ አጥምቀው ታላቅ መነኩሴ ይሆንልሃልና›› የሚል ቃል ከሰማይ ተሰማ፡፡ በዚያን ጊዜም አባታችን መሬቱን እረግጦ ውኃን አፍልቆ ባርኮ አጥምቆ ከዚያም ‹‹..ተከተለኝ›› ብሎ አስከተለውና ወስዶ ፊደልን መዝመረ ዳዊትን አስተማረው፡፡ ስሙንም መከየደ ክርስቶስ ብሎ ሰየመው፡፡ እርሱም በጸሎት በጾም ተጠምዶ ዓመት ተቀምጦ በአባታችን በእስትንፋሰ ክርስቶስ ጸሎት አፍሮ ተድላ ደስታ ወዳለበት ወደገነት ገባ፡፡
አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ አስቀድሞ ከሞት ማስነሣቱ፣ ዳግመኛም ውኃን አፍልቆ ማጥመቁ፣ ሦስተኛም ማስከተሉ፣ አራተኛም ከሲኦል አውጥቶ ወደ ገነት እንዲገባ ማድረጉ እጅግ ድንቅ ነው፡፡ ጸሎቱና በረከቱ ለዘላለሙ ከኹላችን ጋር ይሁን!

(ምንጭ፡- ገድለ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

መጋቢት 8/2016 #አቡነ_ኪሮስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና ፀሎት ለምንማፀንበት ለፃድቁ #አቡነ_ኪሮስ ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን

👉የጻድቁን ስም የሚጠራ አፍ ንዑድ ነው ክቡር ነው በእውነት የቅዱሱን አባት ክብር ለማግኘት መፋጠን ይበጃል #አቡነ_ኪሮስ የተወለዱት በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን ወላጆቻቸው ነገሥታት ናቸው

👉ተወልደው ባደጉባት ሃገር ቁስጥንጥንያ ገና በልጅነት ምቾት ሳያሳሳቸው መጻሕፍትንና ትሕርምትን ተምረዋል ወንድማቸው ታላቁ ቴዎዶስዮስ በነገሠባቸው የመጀመሪያ ዓመታት በቤተ መንግስቱ ዙሪያ ግፍ በዝቶ ነበርና #አቡነ_ኪሮስ ከኃጢአት ለመራቅና ለጌታ ለመገዛት ከከተማው ጠፍተው አሕጉር አቁዋርጠው ወደ ግብፅ ገዳመ አስቄጥስ መጡ

👉እርሳቸውን ለመፈለግ የተደረገው ሙከራ አልተሳካም ይባስ ብሎ የንጉሡ ልጅ ገብረ ክርስቶስ ሙሽርነቱን ጥሎ ወደ ሌላ ሃገር መነነ "የቅኖች ትውልድ ይባረካል" እንዳለ ቅዱስ ዳዊት #አቡነ_ኪሮስ ለሙሽራው ገብረ ክርስቶስ አጎቱ ናቸው አቡነ ኪሮስ በገዳም ውስጥ የታላቁ አቡነ በብኑዳ ደቀ መዝሙር ሆነው ለዘመናት ቆይተዋል

👉ቅዱስ በብኑዳን አንበሳ በበላው ጊዜ በጣም አዝነው ለምን ጌታ ሆይ በሚል መሬት ላይ ወድቀው አለቀሱ ምክንያቱ ካልተነገረኝ አልነሳም ብለው ከወደቁበት መሬት ላይ ሳይነሱ ለ40 ዓመታት አልቅሰዋል በዚህ ምክንያት ግማሹ አካላቸው አፈር ሆኖ ሣር በቅሎበታል #ጌታችን ተገልጦ ምክንያቱን ነግሯቸዋል አካላቸውንም እንደነበረ መልሶላቸዋል

👉አንድ ቀን #ጻድቁ_ለቅዱስ_በብኑዳ ሞት ምክንያት የሆነው መነኮሴ ታንቆ መሞቱን ሰምተው በጣም አዘኑ ሱባዔ ገብተው ፍጹም አልቅሰው ከጌታም አማልደው የዛን ኃጥእ ነፍስ ከሲዖል አውጥተዋል በሌላ ጊዜ ደግሞ ኃጥአን የሞሉበት አንድ ገዳም በግብፅ ነበርና መቅሰፍት ወርዶ ሁሉንም ባንድ ቀን ሲያጠፋቸው አዩ

👉ፃድቁ በዚህም ምክንያት ለ30 ዓመታት አልቅሰው ሙታኑን አስነስተው ንስሃ ሰጥተው ገዳሙን የጻድቃን ሕይወታቸውንም የፍቅር አድርገውታል #ፃድቁ እመቤታችንን ከመውደዳቸው የተነሳ በስዕሏ ፊት አብዝተው ይሰግዱና ያለቅሱ ነበር እመ አምላክም ተገልጣ ትባርካቸው ነበር

👉ከዚህ በሁዋላ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ሒደው ለ57 ዓመታት ማንንም ሳያዩ ተጋደሉ ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና በየቀኑ ይጐበኛቸው ቁጭ ብሎም ያወራቸው ነበር

👉በመጨረሻም #ጌታ አእላፍ መላእክትን ፃድቃን ሰማዕታትን ድንግል እመቤታችንና ቅዱስ ዳዊትን አስከትሎ ወረደ

👉 #ቅዱስ_ዳዊት ቀርቦ እያጫወታቸው በበገናው እየደረደረላቸው ከዝማሬው ጣዕም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው በፍቅር ተለየች ጌታችንም ታቅፎ ስሞ ይዟቸው አረገ

👉ሥጋቸውን አባ ባውማ ቀበሩት #የአቡነ_ኪሮስ ቁመታቸው ቀጥ ያለ ፅሕማቸውም የተንዠረገገ ነበር እድሜአቸውን ግን መገመት የሚቻል አይመስለኝም

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከፃድቁ ረድኤት በረከት ያሣትፈን በቅዱሣኑ ምልጃና ፀሎት ከክፉ መከራ ሁሉ ይጠብቀን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ስለም አመሻችሁ የንስሀ መዝሙር ልቀቁ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✅በእንጦጦ መንበረ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ(በሽሮ ሜዳ) ቤተክርስቲያን ከመጋቢት 6-8 ሁለት ሺ አስራ ስድስት ዓመተ ምሕረት ማለትም ከዓርብ እስከ እሑድ ማታ ድረስ ልዩ ዐውደ ወንጌል ዘተዋሕዶ የአንድነት ጉባዔ ተዘጋጅቷል ።
✅በሦስቱ ዕለታትም አባቶች ሊቃውንት መምህራነ ቤተክርስቲያን ዘማርያን ተጋብዘዋል
✅የደብሩ አገልጋይ ካህናት አባቶቻችን በማዕጠንት በጸሎተ ወንጌል በማስተናበር ተካፋይ ይሆናሉ ።
✅ስለሆነም እርዎም የዚህ ታላቅ ልዩ የአንድነት ጉባዔ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ ተጋብዘዋል ።
#ሸር #በማድረግ #ይተባበሩ።

➺ በቴሌግራም ቻናላችን
                   👇 👇👇
☞/channel/shromedaslase



/channel/silase

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ቅዱስቴ_ቴዎዶጦስ (ስንክሳር)

➯በዚህችም ዕለት ደግሞ ቅዱስ ቴዎዶጦስ በሰማዕትነት አረፈ። እርሱም ከገላትያ አገር የሆነ በምክርና በተግሣጽ አምልኮተ እግዚአብሔርንም በማጽናት ያደገ ነው። ወደ ከሀዲ መኰንንም ሒደው የክርስቲያን ወገን እንደሆነ ነገር ሠሩበት መኰንኑም አሥረው እንዲአመጡት አዘዘ።

➯ቅዱሱም ይህን በሰማ ጊዜ ሳይዙት ወደ መኰንኑ ሔዶ መኰንኑንና የረከሱ ጣዖቶቹን ረገመ ዘለፋቸውም መኰንኑ እሱን በማስፈራት ሁኖ የሥቃይ መሣሪያዎችን ሁሉ አሳየው ለጣዖት እንዲሠዋ በመሸንገል አስገደደው ቅዱሱም ስለ ድንቁርናው ረገመው ዘለፈውም።

➯ከዚህ በኋላም የውስጥ ዕቃው እስከሚታይ ሰቀለው ጐኖቹን ይሠነጣጥቁ ዘንድ መኰንኑ አዘዘ። ከዚያም ወደ ወህኒ ቤት ይጨምሩት ዘንድ ደግሞ አውጥተው በዕንጨት እንዲሰቅሉት ቊስሎቹንም እንዲአድሱ ጐኖቹንም እንዲሠነጣጥቁ አዘዘ።

➯እርሱ ግን መኰንኑ የሚያመጣውን ሥቃይ እንደ ኢምንት አደረገው በክብር ባለቤት በጌታችን ክርስቶስ በፍቅሩ ፍላጻነት ልቡ ተነድፏልና ዐይኖቹም ወደላይ ይመለከቱ ነበር። መኰንኑም ብርታቱን በአየ ጊዜ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ።

➯ቅዱስ ቴዎዶጦስም የራሱን መቆረጥ ሰምቶ እጅግ ደስ እያለው ወጣ። ወደ እግዚአብሔርም ሲጸልይና ሲማልድ እንዲህ አለ። የክብር ባለቤት ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ አመሰግንሃለሁ ከተከታተለኝ ክፉ ነገር ሁሉ አድነኸኛልና በጠላትነት የተነሡብኝንም ወደ ገሃነም አውረድካቸው እኔንም ከሞት በር ከፍ ከፍ አድረግኸኝ።

➯ይህንንም ብሎ በሰገደ ጊዜ ወታደሩም የቅዱሱን ዐይን ይሸፍን ዘንድ መሸፈኛ አመጣ። ቅዱሱም ይህ ሞትን ለሚፈሩ ነው እኔ ግን በክብር ባለቤት በጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሞትን አልፈራም አለ። ወታደሩም ሰይፉን መዝዞ የከበረች ራሱን ቆረጠ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበለ።


➯ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡

#ስንክሳር መጋቢት 7 እና #ከገድላት_አንደበት

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/i-VSjyM07-c?si=zmat2VB6WnwmGB5b

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/L44shOO4jbE?si=dWywUjXMtmk6Dls5

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✅በእንጦጦ መንበረ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ(በሽሮ ሜዳ) ቤተክርስቲያን ከመጋቢት 6-8 ሁለት ሺ አስራ ስድስት ዓመተ ምሕረት ማለትም ከዓርብ እስከ እሑድ ማታ ድረስ ልዩ ዐውደ ወንጌል ዘተዋሕዶ የአንድነት ጉባዔ ተዘጋጅቷል ።
✅በሦስቱ ዕለታትም አባቶች ሊቃውንት መምህራነ ቤተክርስቲያን ዘማርያን ተጋብዘዋል
✅የደብሩ አገልጋይ ካህናት አባቶቻችን በማዕጠንት በጸሎተ ወንጌል በማስተናበር ተካፋይ ይሆናሉ ።
✅ስለሆነም እርዎም የዚህ ታላቅ ልዩ የአንድነት ጉባዔ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ ተጋብዘዋል ።
#ሸር #በማድረግ #ይተባበሩ።

➺ በቴሌግራም ቻናላችን
                   👇 👇👇
☞/channel/shromedaslase



/channel/silase

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሰላም እንዴት ናቹ ፣ ከአሁኑ ጥያቄያቹን ልመልስ hack ተደርጌ አይደለም እኔው ኪራ ነኝ ፣ በተቻለ አቅም ለብዙ ሰው ለመላክ ስላሰብኩ ነው ....
ሀዋሳ ከከተማው ትንሽ ወጣ ብላ የምትልገኝ መስቀለ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አለች ፣በአካባቢው ብዙ አማኝ ስለሌለ ለተለያየ አገልግሎቶች እጥረት አለ ።
በቅርብ ደግሞ( መጋቢት 10 2016 ) 200 የሚሆኑ ሰዎች ወደ እምነት ስለመጡ (ክረስትና ስለሰሚነሱ) አገልግሎቶች ሳይስተጓጎሉ እንዲሰጡ አዲስ አማኞቹንም በእምነት እንዲጸኑ ፣ ቤተከርስቲያኒትዋ ለአንደሰንድ ማህበራት ጥሪ አቅርባ ነበር። ይህም እጣን፣ ጧፍ .... ሰዉ የቻለውን እንዲሰጥ ።
እኔ ግን እንዚህን ሰብስቤ ለመስጠት ስላልቻልኩ በቤተክርስቲያኒትዋ አካውን እንዲላክ ለማረግ አሰብኩ ።
ጓደኞቼ ስለሆናቹ በረከቱ አያምልጣቹ ብዬ ነው ፣
ሰጣቹ አልሰጣቹም ብዬም አላስጨንቃቹም ፣አነሰ በዛ የሚባልም የለም ልባቹ እንደፈቀደው አድርጉ።
ዛሬ ከሌለንም አካውንቱ ይቀመጥ እና ሲኖረን መስጠት እንችላለን።

1000567335527
BEHAWASSA DEBRE MEDHANIT MESKELE KIRESTOS BETEKERESTIYAN

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

" የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው፤ የኅጥኣን ስም ግን ይጠፋል። " (መጽሐፈ ምሳሌ 10:7)
እንኳን ለአባታችን ለፃድቁ አቡነ ገብረመንፈስ_ቅዱስ አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ የአባታችንን ፅሎት ልመና በረከት ረድኤታቸው ምልጃቸው ይደርብን ለሀገራችን ሰላሙን ያድልልን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ውዳሴሃ፣ ለእግዝትነ ፣ማርያም፣ድንግል፣ወላዲተ፣ አምላክ፣ዘይትነበብ፣በዕለተ ሰንበተ ክርስቲያን
/channel/wdase1

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

†✝† እንኳን ለጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †✝†

†✝† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †✝†

†✝† አቡነ ገብረ ሕይወት †✝†

†✝† ጻድቁ የተወለዱት ግብፅ (ንሒሳ አካባቢ) ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ:: አባታችን ገብረ ሕይወት የጻድቃን አለቃ: የቅዱሳን የበላይ: ተጋድሎአቸውና ድንቅ ተአምራቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ቅዱስ ሰው ናቸው::

የጻድቁን ክብር መናገር የሚችል ምን አንደበት ይኖራል?
*እንደ ምንስ ባለ ብራና ይጻፋል?
*ዜናቸውንስ ለመስማት የታደለ እንደ ምን ዓይነት ሰው ይሆን?

አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ562 ዓመታት በዚህች ዓለም ሲኖሩ:-
*እህል ያልቀመሱ (ምግባቸው ምስጋና ነውና)::
*ልብስ ያልለበሱ (ጠጉር አካላቸውን ይሸፍን ነበርና)::
*ሐዋርያዊ ሆነው ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ ነፍሳትን ያዳኑ አባት::
*ሃገራችንን አስምረው: አስራት እንድትሆናቸውም ተቀብለው ምድረ ከብድ አካባቢ አርፈዋል::

ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስም : ገብረ ሕይወትም ይባላሉ:: በ562 ዓመታት ሕይወታቸው እንደ ሐዋርያት ከምድረ ግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ወንጌልን ሰብከዋል:: በዚህም በሚሊየን (አእላፍ) ለሚቆጠሩ ነፍሳት የድኅነት ምክንያት ሆነዋል::

ጻድቁ እንደ ሰማዕታትም ከከሃዲ ሰዎች ብዙ መከራን ተቀብለዋል:: እንደ ባሕታውያን ለብዙ መቶ ዓመታት ሰው ሳያዩ ቆይተዋል:: ለየት የሚለው ግን የጽድቅ ሕይወታቸው ነው:: ከእልፍ አዕላፍ አጋንንት ጋር ተዋግተው ድል ማድረግ ችለዋልና::

የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለኢትዮዽያ ልዩ ፍቅር አላቸው:: ስለ ሃገሪቱና ሕዝቧ ፍቅር ሲሉ ለ100 ዓመታት በደብረ ዝቋላ መከራን ተቀብለዋል:: ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው::

ስለዚህም ነው በሃገሪቱ ውስጥ ከ2,000 በላይ የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳማትና አድባራት ዛሬም ድረስ ያሉት:: በ8ኛው ክ/ዘመን አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ነው:: ፍጥረታትን ሁሉ አዘው መጋቢት 5 ቀን ሲያርፉ ግሩማን መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል::

ሥላሴን የተሸከመ አካላቸው በጐልጐታ ተቀብሯል የሚሉም አሉ::
"ሰላም ለመቃብሪከ ዘኢተከሥተ ለባዕድ::
ከመ መቃብሩ ለሙሴ ወልደ ዮካብድ::
ዜና መቃብሪከሰ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጸማድ::
ቦ ዘይቤ በኢየሩሳሌም አጸድ::
ወቦ ዘይቤ ኀለወ በከብድ::" እንዲል::

††† የጻድቁ በዓል ጥቅምት 5 ቀን የሚከበረው ብዙ ጊዜ መጋቢት 5 ዐቢይ ጾም ውስጥ ስለሚውል ተውላጥ (ቅያሪ) ሆኖ ነው::

††† ቸር አምላክ ከጻድቁ ዋጋና በረከት ይክፈለን::

††† መጋቢት 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጻድቅ (አባ ገብረ ሕይወት)
2.ቅዱስ አባ ሰረባሞን (በምድረ ግብፅ ምንኩስናን ካስፋፉ ታላላቅ ቅዱሳን አንዱ)
3.አባ ግርማኖስ ጻድቅ (ሶርያዊ)
4.ቅድስት አውዶክስያ ሰማዕት (ከከፋ የኃጢአት ሕይወት ተመልሳ ለቅድስና የበቃች እናት)
5.ቅዱሳን ስምዖንና ሚስቱ አቅሌስያ (የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወላጆች)

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2.ቅዱስ ዻውሎስ ሐዋርያ
3.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
4.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ

††† "ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል:: ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል:: ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላቹሃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም::" †††
(ማቴ. 10:41)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
/channel/silase

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

መጋቢት 10 /2016 #መስቀለ_ኢየሱስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና በፀሎት ለምንማፀንበት #የጌታችን_ቅዱስ_እፀ_መስቀል ለተገኘበት አመታዊ ክብረ በአል እንኳን በሰላም አደረሰን

👉 #እውራንን የሚያበራው ድውያንን የሚፈውሰው ሰላመ #እግዚአብሔርን ያገኘንበት የድህነታችን አርማ ሀይላችን የምንመካበት የምንድንበት #ቅዱስ_እፀ_መስቀላችን ነው

👉የድህነታችን አርማ የሆነውን ቅዱስ #እፀ_መስቀል አይሁድ በቅናት ተነሳስተው ቀበሩት ለዘመናት የቆሻሻ ክምር በመጣል መስቀሉ እዲሰወር አደረጉ።

👉በ 320 ዓ.ም የንጉስ #ቆስጠንጢኖስ እናት ቅድስት እሌኒ ልጇ ቆስጠንጢኖስ ከአረማዊ እምነት ወደ ክርስትና እንዲመለስ ስለት ተሳለች በስለቷ መሰረት ልጇ ወደ ክርስትና አምነት ከተመለሰ #የጌታችን_ኢየሱስን_መስቀል ለማግኘት በተሳለችው ስለት መሰረት መስከረም 16 ደመራ ደምራ እጣን በውስጡ ጨምራ አበራች

👉በዚህም ወቅት ጢሱ ወደ ሰማይ ወጥቶ ተመልሶ ወደ ምድር ሰግዶ በዘመኑ ከነበሩት ብዙ የቆሻሻ ክምር ተራራዎች የጌታችን #ቅዱስ_እፀ_መስቀል ወዳለበት ተራራ አመለከተ

👉ቅድስት አሌኒም መስከረም አስራ ሰባት ቁፋሮውን አስጀምራ #መጋቢት_አስር ቀን ቅዱስ እፀ መስቀሉ ተገኘ

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከመስቀሉ ክብረ በአል ረድኤት በረከት ያሣትፈን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

👉ጊዜዉ ያላችሁ በአሉን ለማክበር የምትፈልጉ ታቦተ ህጉ በቀጨኔ #መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ስለሚገኝ በታላቅ ድምቀት ይከበራል የበረከቱ ተካፋይ ሁኑ ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የተከበርከው የአማራ ህዝብ እና ፋኖ አንድነት ሀይል ነው እና ከዚህ በላይ አንድነታችንን እናጠናክር ስል ከግዮን ሰማይ ስር ሆኘ ጥሪየን አቀርብልሃለሁ!!

ሸዋ ሁላችሁም አንድ ሆናችሁ ትመጡ ዘንድ በተሰውት ጓዶቻችን ስም እጠይቃለሁ!!!

ጎንደር ባንዳን መንጥረህ አፅድተህ አንድ ሆነህ በቅርቡ ትመጣ ዘንድ በተሰውት ጓዶቻችን ስም እጠይቃለሁ!!!!

ቤተ አምሐራ ባንዳን እያፀዳህ የጁላን ነፍሰ ገዳይ እየቀበርህ አንድነትህን አጠናክረህ ትመጣ ዘንድ በተሰውት ጓዶቻችን ስም እጠይቃለሁ!!!!

ጎጃም የበላይ ትንፋሽ የልብ አድርሶች የቀሩ ባንዳዎችን እያፀዳህ ማዳበሪያ የከለከለህን መንግስት ሠራዊት ወደ አፈር ማዳበሪያነት እየቀየርህ አንድነትህን አጠናክረህ ለወንድሞችህ መከታ ትሆን ዘንድ በተሰውት ጓዶቻችን ስም እጠይቃለሁ!!!!!!

በመጨረሻም የበላይ ዘለቀ የንጉስ ሃይማኖት አናብስቶች ጎጃም

የንጉስ ሚካኤል ግርፎች አናብስቶቹ ቤተ አምሐራ

የ አጼ ቴዎድሮስ የ አጼ ፋሲል ምልምሎች ጎንደር

የእምየ ሚኒልክ የ አጼ ዳዊት ልጆች የጦር መሃንዲሶቹ ሸዋ



የጋራ የሆነውን አንድ አምሐራዊ ቤት በፍጥነት እንገነባ ዘንድ በትግሉ ሰማእታት ስም እኔ ትንሹ ልጃችሁ እና ዎንድማችሁ ከግዮን ሰማይ ስር ከወገቤ ሰበር ከ አንገቴ ጎንበስ ብየ በአክብሮት እጠይቃችኋለሁ !!!!

ድል ለፋኖ
አምሐራው ያሸንፋል::

አራሽ : ቀዳሽ : ተኳሽ : ነጋሽ አምሓራው ፋኖ!!!!

© ትንሹ ነኝ ግዮን ሚዲያ ከግዮን ሰማይ ስር

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ዎቅታዊ እና ተአማኒ መረጃዎችን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇
👉
@gyon_media👈
👉
@gyon_media👈
👉
@gyon_media👈
👉
@gyon_media👈
👉
@gyon_media👈
👉
@gyon_media👈
👉
@gyon_media👈
👉
@gyon_media👈
👆👆👆👆👆👆👆
  ይቀላቀሉን!!!

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

መጋቢት 9/2016 #አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና ፀሎት ለምንማፀንበት እና በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ #እስትንፋሰ_ክርስቶስ ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን

"እግዚአብሔር በፃድቁ እንደተገለጠ እወቁ" መዝ፤4፣3

👉 #አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ አባታቸው #መላከ እናታቸው #ወለተ_ማርያም ይባላሉ የተወለዱበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ነው በተወለዱ ዕለት ተነስተው በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ በአንድነት በሶስትነት ለሚመሰገን ለሥላሴ #ስብሐት_ለአብ_ስብሐት_ለወልድ_ስብሐት_ለመንፈስ_ቅዱስ ብለው አመስግነዋል፡

👉የስማቸው ትርጓሜ #የአብ_የወልድ_የመንፈስ_ቅዱስ እስትንፋስ አንድም #የክርስቶስ_እስትንፋስ ማለት ነው ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸውና በመንገዳቸው ሁሉ እየመራቸው ነው ያደጉት #መንፈስ_ቅዱስ ልቦናቸውን ብሩህ አድርጎላቸው በ5 ዓመታቸው የቅዱሳት መጽሐፍት ቃላትን ብሉያትንና ሐዲሳትን ድርሳናትንም ጠንቅቀው ዐውቀዋል፡

👉በተወለዱ በ14 ዓመታቸው ወደ #አቡነ_ኢየሱስ ሞዐ ደብረ ሐይቅ ገዳም ሄደው ከባሕር ዳር ቆመው የሙሴን ጸሎት ወደ #እግዚአብሔር በፀለዩ ጊዜ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ባህሩን አሻግሯቸው ወደ ቤተክርስቲያን ገብተዋል

👉ሦስት ዓመትም በኃይቅ ገዳም ለመነኮሳት እንጨት በመልቀምና ውሃን በመቅዳት #ለአባቶች መነኮሳት ምግብ ሊሆናቸው ከባህር ውስጥ አሳን በማውጣት አገልግለዋል፡

👉አባታችን #እስትንፋሰ_ክርስቶስ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ከፆሙ በኋላ ምንም እህል ሳይቀምሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ #ለሙሴ በደብረ ሲና እንደሰጠው ለአባታችንም ወደ እርሳቸው መጥቶ ዓሥሩን ቃላተ ኦሪትና ስድስቱን ቃላተ ወንጌል በውስጣቸው የተጻፈባቸው ሁለት ጽላቶችን ሰጥቷቸዋል

👉አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን ከሠሩ በኋላ ዕለቱን ስንዴ ዘርተው ወይን ተክለው ጽድን ወይራንና ግራርን ተክለው በአንዲት ቀን #ለቤተ_ክርስቲያን አገልግሎት ዕለቱን አድርሰዋል ስንዴውን ለመስዋዕት ወይኑን ለቁርባን በታምራት አድርሰዋል

👉አባታችን በጸሎት ላይ እንዳሉ መልአኩ #ቅዱስ_ሚካኤል ተልኮ መጥቶ አባታችንን በደመና ጭኖ ወስዶ ከጌታችን ከአምላካችን ከመድኃኒታችን #ከኢየሱስ_ክርስቶስ ፊት አቆማቸው፡፡

👉ጌታም #በቅዱሳኖቹ ሁሉ እንዲባረኩ ካደረጋቸው በኋላ መልአኩን ወደ ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ ወደ ኢየሩሳሌም አድርሰው ብሎት ኢየሩሳሌምን አሳልሞ ሀገራችን መልሶ አምጥቷቸዋል ሁሉንም #የኢትዮጵያን ቅዱሳት ገዳማትንም ተሳልመዋል

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከፃድቁ ረድኤት በረከት ያሣትፈን የአባታችን #የፃድቁ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ምልጃና ፀሎት ቃል ኪዳን ሁላችንንም ይጠብቀን በዚህ እለት መታሰቢያ የሚደረግላቸው ቅዱሣን ፀሎት ልመናቸው አይለየን "አሜን" ✝️💒✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ ማትያስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችኹ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ሐዋርያው ቅዱስ ማትያስ †††

††† በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ ከእመቤታችን በቀር ከቅዱሳን ሐዋርያት የሚበልጥ አልተነሳም:: "ሐዋርያ" ማለት "ፍንው: ልዑክ: የተላከ: የጽድቅ መንገደኛ" እንደ ማለት ነው:: በምሥጢሩ ግን "ባለሟል" ብለው ሊቃውንቱ ተርጉመውታል::
ይህስ እንደምን ነው ቢሉ:-
¤የፍጥረታት ሁሉ ጌታ: የክብር ባለቤት መድኃኔ ዓለም ከድንግል ማርያም ተወልዶ: አድጐ: ተጠምቆ: ጾሞ: ከገዳመ ቆረንቶስ ሲመለስ ቀዳሚ ሥራው ያደረገው ደቀ መዛሙርቱን መጥራት ነበር::

ከተከተሉት የ5 ገበያ ሕዝብ መካከል "ወሐረየ እምሰብአ ዚአሁ አሠርተ ወክልኤተ ሐዋርያተ" እንዲል በመጀመሪያ 12ቱን ሐዋርያት መረጠ::

††† እሊህም:-
1.ዼጥሮስ የተባለ ስምኦን
2.እንድርያስ (ወንድሙ)
3.ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ
4.ዮሐንስ (ወንድሙ)
5.ፊልዾስ
6.በርተሎሜዎስ
7.ቶማስ
8.ማቴዎስ
9.ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ
10.ታዴዎስ (ልብድዮስ)
11.ናትናኤል (ቀናተኛው ስምዖን) እና
12.ማትያስ (በይሁዳ የተተካ) ናቸው:: (ማቴ. 10:1)

††† እነዚህን 12 አርድእቱን ከጠራ በሁዋላ ለ3 ዓመታት ከ3 ወራት ከዋለበት ሲማሩ ይውሉ ነበር:: ሌሊት ደግሞ ምሥጢር ሲያስተረጉሙ ያድሩ ነበር::

ጌታ እንደሚገባ ካስተማራቸው በሁዋላ ከፍ ያለ ኃላፊነትን ሾማቸው:: ለዓለም እረኞች: የእርሱም ባለሟሎች ሆኑ:: እጅግ ብዙ መከራ እንደሚገጥማቸው ነገራቸው:: (ማቴ. 10:16, ዮሐ. 16:33) በዚያው ልክ ክብራቸውንም አከለላቸው:: (ማቴ. 19:28)

ሥልጣናቸው ደግሞ እስከዚህ ድረስ ሆነ:: "በምድር ያሠራችሁት በሰማይ የታሰረ ይሆናል: በምድር የፈታችሁት በሰማይ የተፈታ ይሆናል::" (ማቴ. 18:18) "ይቅር ያላችሁዋቸው ኃጢአታቸው ይቀርላቸዋል: ያላላቹሃቸው ግን አይቀርላቸውም::" (ዮሐ. 20:23)

የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ (ማቴ. 16:19): እረኝነትን (ዮሐ. 21:15) ተቀበሉ:: ጌታ በንጹሕ አንደበቱ ሐዋርያቱን እጅግ ሲያከብራቸው "ጨው: የዓለም ብርሃናት" (ማቴ. 5:13) አላቸው:: ወንድሞቹም ተባሉ:: (ዮሐ. 7:5) ከዚህም በሚበልጥ በሌላ ክብር አከበራቸው::

ከዚህ ሁሉ ነገር በሁዋላ በጌታ ሕማማት ጊዜ ገና ነበሩና አንዳንዶቹ ፈርተው ተበተኑ:: ተመልሰው ግን በጽርሐ ጽዮን ሲጸልዩ ሰንብተው የጌታን ትንሳኤ ተመለከቱ:: እጆቹን: እግሮቹንም ዳስሰው ሐሴትን አደረጉ::

ለ40 ቀናት መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓት: ሌላም በፍጡር አንደበት የማይነገር ብዙ ምሥጢራትን ተምረው: ጌታ ሊቀ ዽዽስናን ሹሟቸው ዐረገ::

ለ10 ቀናት በእመ ብርሃን ሥር ተጠልለው ሲጸልዩና በአንድ ልብ ሲተጉ ሰንብተው መንፈስ ቅዱስ ወረደላቸው:: በአንዴም ከፍርሃት ወደ ድፍረት ተመልሰው ፍጹማን: ብርሃናውያን ሆኑ:: 71 ልሳናትን ነስተው በአንዲት ስብከት ብቻ 3ሺ ነፍሳትን ማረኩ:: (ሐዋ. 2:41)

ቅዱሳን ሐዋርያት በኅብረት ለአንድ ዓመት ያህል በኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ እየተመላለሱ አስተምረው ብዙ እሥራኤላውያንን ወደ ክርስትና ማርከዋል:: ከዚህ በሁዋላ ግን እንደ ትውፊቱ ዓለምን በእጣ ለ12 ተካፈሏት::

ይህ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ አብሯቸው ነበርና ለእያንዳንዳቸው እንደሚገባቸው አሕጉረ ስብከቶች ደረሷቸው:: እነርሱም ደቀ መዛሙርቶቻቸውን አስከትለው ለታላቁ መንፈሳዊ ዘመቻ ወረዱ::

በሔዱበት ቦታም ከተኩላ: ከአንበሳና ከነምር ጋር ታገሉ:: በጸጋቸውም አራዊትን (ክፉ ሰዎችን) ወደ በግነት መልሰው ለክርስቶስ አስረከቡ:: በየሃገሩ እየሰበኩ ድውያንን ፈወሱ:: ለምጻሞችን አነጹ:: እውራንን አበሩ:: አንካሶችን አረቱ:: ጐባጦችን አቀኑ:: ሙታንንም አስነሱ:: እልፍ አእላፍ አ+ሕ+ዛ+ብ+ንም ወደ መንጋው ቀላቀሉ::

ስለዚህ ፈንታም ብዙዎቹ በእሳት ተቃጠሉ:: ቆዳቸው ተገፈፈ:: በምጣድ ተጠበሱ:: ደማቸው በምድር ላይ ፈሰሰ:: ከአንድ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በቀር ሁሉም ይህችን ዓለም በሰማዕትነት ተሰናበቱ:: ጨው ሆነው አጣፍጠዋልና: ብርሃንም ሆነው አብርተዋልና እናከብራቸዋለን:: "አባቶቻችን: መምሕሮቻችን: ጌቶቻችንና ሊቆቻችን" እንላቸዋለን::

ቅዱስ ማትያስ ስም አጠራሩ ይክበርና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተሰቦቼ ብሎ ከመረጣቸው 120 ቅዱሳን አንዱ: 3 ዓመት ከ3 ወር ከጌታችን እግር ቁጭ ብሎ የተማረ: በይሁዳ ፈንታ ከ12ቱ ሐዋርያት ይቆጠር ዘንድ መንፈስ ቅዱስ የመረጠው ሐዋርያ ነው::

ቅዱሱ ሐዋርያ በዕጣ በደረሰው ሃገረ ስብከቱና በሌሎቹም ዓለማት ለወንጌል አገልግሎት ብዙ ደክሙዋል:: በተለይ የሰውን ሥጋ ወደሚበሉ ሰዎች ሃገር ገብቶ ወንጌልን ቢሰብክላቸው ዓይኖቹን አውጥተው ከብዙ ስቃይ ጋር ለ30 ቀናት ሣር አብልተውታል::

እሱ ግን በትእግስትና በፈጣሪው ኃይል ድንቅ ተአምር አድርጐ አሳምኖ አጥምቋቸዋል:: ከብዙ ተጋድሎና ቅድስና በሁዋላም በዚሕች ቀን በመልካም ሽምግልና አርፏል::

††† አምላከ ቅዱሳን ሐዋርያት ቸርነቱን ያብዛልን:: በምልጃቸው ከክፉ ጠብቆ ከበረከታቸው ይክፈለን::

††† መጋቢት 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
2.ቅዱስ አርያኖስ ሰማዕት (በዘመነ ሰማዕታት ብዙ ክርስቲያኖችን ያሳድድ የነበረና ጌታ በንስሃ የጠራው)
3.ቅዱስ ዮልዮስ ሊቀ ዻዻሳት

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ)
3.አባ ብሶይ (ቢሾይ)
4.አቡነ ኪሮስ
5.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን

††† ". . . እንዲህም ብለው ጸለዩ:: 'አቤቱ ልብን ሁሉ የምታውቅ አንተ ከእነዚህ ከሁለቱ የመረጥከውን አንዱን ግለጥ?' . . . ዕጣ አጣጣሉአቸው ዕጣውም በማትያስ ላይ ወጣ:: ከዐሥራ አንዱ ሐዋርያት ጋርም ተቆጠረ::" †††
(ሐዋ. 1:24-26)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

የዩቱዩብ ቻናል👇
https://youtu.be/OIOCAD82nxk?si=VMEi2GBRFE8w3lMi

የቲክቶክ ቻናል👇
zikirekidusan23?_t=8kGT8RWuULK&_r=1" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@zikirekidusan23?_t=8kGT8RWuULK&_r=1

የቴሌግራም ቻናል👇
/channel/zikirekdusn

✝ ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር ✝

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

“ቅድስት”   የዐቢይ ጾም ኹለተኛ ሳምንት
መ/ር ጌታቸው በቀለ
የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መዝሙር ንባቡን ከዜማው አስማምቶና አጠናቅሮ የተናገረው ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው በዓቢይ ጾም ውስጥ  ለሚገኙት እሑዶች ሁሉ የተለየ መዝሙር ሰርቶላቸዋል፡፡ በመዝሙራቱ ውስጣዊ ምስጢር መሠረትም እያንዳንዱ እሑድ ስያሜ ተሰጥቶቸል፡፡ በዚሁም መሠረት ያሳለፍነውን ሳምንት ከቅበላው ዋዜማ ጀምሮ “ዘወረደ” ብለን በቤተ ክርስቲያናችን አክብረናል፡፡ ዛሬ ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የኹለተኛውን ሳምንት “ቅድስት”ን ስያሜና ምሥጢሩን እንማራለን፡፡   ቅድስት   ቅድሰት የዐቢይ ጾም ኹለተኛ ሰንበት (ሳምንት)  ስያሜ ነው፡፡የሰንበትን ቅድስና የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ ስያሜውም ከኢትዮያዊው የዜማ ሊቅ ከቅዱስ ያሬድ የተገኘ ነው፡፡ከዚህ ሰንበት ዋዜማ ጀምሮ ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ይዘመራል፡፡  ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ሰንበቱን ስለ ቅድስና ልጆቿን ታስተምርበታለች፡፡ በቅዳሴ ጊዜ የሚሰበከው ምስባክ፤ የሚነበቡ መልዕክታት፤ የሐዋርያት ሥራና ወንጌል ስለ ቅድስት የሚያስተምሩ ናቸው፡፡  “ቅድስት” ማለት የዘይቤ ፍችው “የተቀደሰች፣ የተለየች፣ የተባረከች፣ ንጽሕት” ማለት ነው፡፡ ምስጢራዊ መልእክቱ ግን የምስጢረ አድኅኖት ታላላቅ ሥራውን ለመጀመር መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ ከቆመ ሳያርፍ፣ ከዘረጋ ሳያጥፍ የጾማት የአርብዓው ቀንና ሌሊት ልዩ የሆነችና ክብርት ጾም የምትጀመርበትን ሁለተኛ ሳምንት ናት፡፡ /ማቴ. ፬፥፪/፡፡ «ጾምን ቀድሱ ጉባኤውን ዐውጁ ሽማግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤተ ሰብስቡ፡፡» (ት.ኢዩ. ፪፥፲፬) ብሎ በነቢዩ ኢዮኤል አፍ የተናገረ ቅዱስ እግዚአብሔር የጾማት ጾም ስለሆነች ቅድስት ትባላለች።  ቅድስት ዕለተ ሰንበት  “እግዚአብሔር ሰባተኛይቱን ቀን ባረካት ቀደሳት” (ዘፍ 2÷3፣ ዘጸ 20፥8) ሰዎች ፍጥረት ያልተፈጠረባት ዕለት ብለው እንዳይንቋት እንዳያቃልሏት እረፍተ ሥጋ እረፈተ ነፍስ የተገኘባት ዕለት ስለሆነች ቀደሳት አለ፡፡ ቅዱስ ያሬድም “ሰንበትየ ቅድስትየ ዕንተ አዕረፍኩ እምኩሉ ግብርየ ይቤ እግዚኣብሔር” ብሉአል:: በዚህ እሑድ (ሳምንት ) ቀደሳት፣ አከበራት፣ ከፍ ከፍ አደረጋት የተባለች ሰንበትን የምትታሰብበት የሰንበትንም ቅድስና የሚመለከቱ መዝሙሮች የሚቀርብበት ሳምንት በመሆኑ ቅድስት ተብሏል።  ቅድስት የዐቢይ ጾም ኹለተኛ ሳምንት ሲሆን፤ ለጌታ ጾም (ጾመ ዐርባ) የመጀመሪያ ሳምንት ነው፡፡ ያለትናንት ቀዳማዊ፤ ያለዛሬ ማዕከላዊ፤ ያለነገ ደሃራዊ፤ ለዘመኑ ጥንትና ፍጻሜ ለግዛቱ ዳርና ድንበር የሌለበት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ አብነት ይሆነን ዘንድ ጾሙን የጀመረበት የመጀመሪያው ሳምንት ቅድስት ተብሎ የመጠራቱ ምክነያት ከዚሁ ሰንበት ዋዜማ ጀምሮ የሚዘመረው ጾመ ድጓ የአምላካችንን ቅድስና እና ሰንበት ቀድሶ በፈቃዱ እንደሰጠን እያነሣሣ ስለሚዘምር ነው፡፡   ጾመ ድጓውም እንዲህ ይለዋል፡- “ዛቲ ዕለት ቅድስት ይዕቲ ሰንበትየ ቅድስትየ እንተ አዕረፍኩ ቅዱሳነ ኩኑ እስመ አነሂ ቅዱስ አነ    አብ ቀደሳ ለሰንበት  - ይህች ቀን የተቀደሰች ናት  ያረፍኩባት ቅድስት ሰንበት ናት፡፡  እኔ ቅዱስ እንደሆንኩ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ፡፡ አብ ሰንበትን አከበራት ቀደሳት”፡፡ ስያሜው ሰንበት የዕረፍት ቀን እንድትሆን በኦሪትም በሐዲስም እግዚአብሔር የባረካት የቀደሳት ዕለት መሆኑዋን የሚናገርና እግዚአብሔር ቅዱስ እንደሆነ የፈጠረውም ሰውም ቅድስናን መያዝ የሚገባው መሆኑን የሚያሳስብ ነው፡፡ /ዘፍ ፪፥፫፤ዘፀ ፳፥፰-፲፩፤ዘሌ ፲፱፥፪-፫፤፩ኛ ጴጥ ፩፥፲፭-፲፮/፡፡   ከላይ እንደተገለጸው እቀደስ አይል ቅዱስ፤ እከብር አይል ክቡር፤ እነግስ አይል ንግሥና የባህሪዩ የሆነ አምላክ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጾሞ፤ የጾምን ጥቅምና ሥርዓቱንም ሊያስተምረን መጾም የጀመረበት ሳምንት ይህ ነው፡፡ ይህ ሳምንት የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የባሕሪይ ቅድስና የሚነገርበት ሳምንት ነው፡፡ ስለዚህች ቀን ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት አስቀድሞ “እስመ አማልክተ አሕዛብ አጋንንት፤ እግዚአብሔርሰ ሰማያተ ገብረ፤ አሚን ወሠናይት ቅድሜሁ፤ ቅድሳት በዕበየ ስብሐት ውስተ መቅደሱ - የአሕዛብ አማልክት ሁሉ አጋንንት ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ፡፡ ምስጋናና ውበቱ በፊቱ፤ ቅድስናና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው፡፡” /መዝ ፺፭፥፭/ በማለት ቅድስናና ክብር የባሕሪዩ መሆኑን ተናግሯል፡፡ እኛ ከርኵሰታችን የምንቀደስበትንና የምንከብርበትን ሥርዐት ሊሠራልን አንድም አዳም በመብል ምክንያት ከክብሩ ተዋርዶ ነበርና በአዳም ምትክ ተተክቶ ካሣ ሊከፍልለት በገዳመ ቆሮንቶስ ጌታችን መጾም መጀመሩን በዲያብሎስ መፈተኑንና ዲያቢሎስንም ድል መንሣቱን ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ሳምንት ታስተምረናለች፡፡  በዚህች ቅድሰት በተባለች ሳምንት እሑድ የሚነበቡት የቅዳሴ ምንባባት የሚከተሉት ናቸው፡፡  ምንባባተ ቅድስት መልዕክታት፡ ፩ኛ ተሰሎቄ ፬፥፮-፲፫ ፩ኛ ጴጥሮስ ፩፥፲፫ - ፳፭  ግብረ ሐዋርያት፡ የሐዋ.ሥራ ፲፥፲፯ - ፴  ምስባክ መዝ ፺፭፥፭                                   “እግዚአብሔርሰ ሰማያተ ገብረ      አሚን ወሰናይት ቅድሜሁ          ቅድሳት ወዕበየ ስብሐት ውስተ መቅደሱ”  ትርጓሜውም፡-          “እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ፡፡ ምስጋናና ውበቱ በፊቱ          ቅዱስነትና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው፡፡”       ወንጌል ማቴ ፮፥፲፮ - ፳፭   ይህ ጾም ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ጾም በመሆኑ፤ በዚህች በዕለተ ሰንበት(“ቅድስት”) በቤተክርስቲያን በመሰብሰብ ቃለ እግዚአብሔር በመስማት (በመማር)፣ ንስሐ ገብቶ ቅዱስ ቁርባን በመቀበል፣ የተጣላ በማስታረቅ፣ ያዘነ የተከዘ በማጽናናት፣ የታሰረ በመጠየቅ በአጠቃላይ በማቴ. ፳፭፥፴፭—፴፯ ላይ የተጠቀሱትን ምግባራትን በመፈጸም ለቱን (በዓሉን) ማክበር ከእግዚአብሔር ዘንድ በረከትን ያሰጣል፡፡ ሰንበትን በሚገባ እንድናከብር የእግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን፡፡  
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖መጋቢት ፯ (7) ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

✞ ሰማዕትነት በቅዱስ ቴዎዶጦስ ሕይወት ✞

+*" ቅዱስ ቴዎዶጦስ "*+

=>በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ጊዜው ለክርስቲያኖች
ሁሉ ፍጹም የመከራ ከመሆኑ የተነሳ "ዘመነ-ሰማዕታት"
ሲባል በወቅቱ ከ47 ሚሊዎን በላይ ክርስቲያኖች
ተጨፍጭፈዋል::

+የዘመኑ ክርስቲያኖች ለመሞት የሚያደርጉትን
እሽቅድምድም እያዩ አ+ሕ+ዛ+ብ "ወፈፌዎች" እያሉ
ይጠሯቸው ነበር:: (ዓለም እንዲህ ናትና!) እብዶቹ
ጤነኞችን "እብድ" ማለታቸውኮ ዛሬም አለ::
(ለነገሩ "ግደልና ጽደቅ" ከሚል መመሪያ በላይ ጤና
ማጣት አይኖርም)

=>ታዲያ በወቅቱ አንድ #ቴዎዶጦስ የሚሉት ወጣት
በምድረ ግብጽ ይኖር ነበር:: ወጣቱ እጅግ ብርቱ
ክርስቲያን ነበርና እንደ ዘመኑ ልማድ ተከሦ በነፍሰ
ገዳዮች ፊት ቀረ:: ክሱ አንድ ብቻ ነው:: "ክርስቶስን
አምልከሃል" የሚል::

+ከሥጋ ሞት ለማምለጥ ደግሞ መንገዱ ያው አንድ ብቻ
ነው:: ፈጣሪውን ክርስቶስን ክዶ ለአ+ሕ+ዛ+ብ አማልክት
(አጋንንት) መገዛት:: #ቅዱስ_ቴዎዶጦስ በገዳዮቹ ፊት
ቆሞ ተናገረ:-
" #እኔ_ክርስቲያን_ክርስቶሳ ዊ_የክርስቶስ_ነኝ:: ምንም
ብታደርጉኝ ከክርስቶስ ፍቅር ልትለዩኝ አትችሉም"(ሮሜ.
8:35) አላቸው::

+እነሱ ግን ነገሩ እውነት አልመሰላቸውምና ሊያሰቃዩት
ጀመሩ::
*ገረፉት
*አቃጠሉት
*ደበደቡት
*ሌላም ሌላም ማሰቃያዎችን በእርሱ ላይ ተጠቀሙ::
የሚገርመው ግን እሱ ሁሉን ሲታገሥ ገዳዮቹ ግን
ደከሙ::

+በመጨረሻም ወደ ገዢው ዘንድ አቅርበው "ብዙ
አሰቃይተነዋል:: ግን ሊሳካልን አልቻለም" በሚል ሰይፍ
(ሞት) ተፈረደበት:: በአደባባይ ሊሰይፉት ሲወስዱት ግን
ትንሽ አዘኑለት መሰል ጨርቅ አምጥተው "ፊትህን ሸፍን"
አሉት:: (ያኔ ትንሽም ቢሆን ሰብአዊነት ሳይኖር አይቀርም)

+ቅዱስ ቴዎዶጦስ ግን ገዳዮቹን በመገረም
እየተመለከታቸው ተናገረ:- "እኛ ክርስቲያኖች ሞትን
አንፈራም:: ሞት ለእኛ ወደ ክርስቶስ መሸገጋገሪያ
ድልድያችን ነውና የምንፈራው ሳይሆን የምንናፍቀው
ነው::" "ኢትፍርሕዎሙ
(አትፍሯቸው)"
(ማቴ. 10:28)

+ይህን ብሎ ወደ ሰማይ ቀና ብሎ ጌታውን አመሰገነ::
ፊቱ ላይ ደስታ እየተነበበ ጨካኞቹ አንገቱን ሰየፉት::
በብርሃን አክሊልም ቅዱሳን መላእክት ከለሉት::
*መሠረታዊው ነገር ቅዱስ ቴዎዶጦስ ለምን አልፈራም?
ነው::

+አጭር መልስ ካስፈለገን ቅዱሱ ያልፈራው ከልቡ
ክርስቶሳዊ በመሆኑ ነው:: ትኩረት እንድንሰጠው
የሚያስፈልገው ግን የሰማዕታት ምስጢራቸው:-
1.በጽኑ የክርስትና መሠረት ላይ መመሥረታቸው
2.ዕለት ዕለት የክርስቶስን ፍቅር መለማመዳቸው
3.ከወሬ (ንግግር) ይልቅ ተግባርን መምረጣቸው
4.በንስሃ ሕይወት መመላለሳቸው
5.ሥጋ ወደሙን የሕይወታቸው ዋና አካል ማድረጋቸው
6.ከእነሱ የቀደሙ ቅዱሳንን ዜና ሕይወት ከልብ
ማንበባቸው
7.በቃለ እግዚአብሔር መታነጻቸው . . . መጠቀስ
የሚችሉ መገለጫዎቻቸው ናቸው::

<+>" ዛሬስ "<+>

=>ዓለማችን ከጠበቅነው በላይ ነፍሰ በላነቷ እየጨመረ
ነው:: ዛሬ የክርስትና ጠላቶች ከጉንዳን በዝተዋል::
*የራሳችን ማንነት
*ክርስትናችን በአፋችን ላይ ብቻ መሆኑ
*እረኞችና በጐች መለያየታቸው . . . ሁሉ እኛ ልናርማቸው
የሚገቡ ናቸው::
*አሸባሪዎች
*አ+ሕ+ዛ+ብ
*የመዝናኛው ዓለም
*ሰይጣን አምላኪ ዝነኞች (Celebrities)
*ሚዲያው
*ማሕበራዊ ድረ ገጾችና መሰል ነገሮች ደግሞ
ልንጠነቀቅባቸው የሚገቡና እኛን ውስጥ ለውስጥ
በልተው የፈጁን የሰይጣን መሣሪያዎች ናቸው::

+ስለዚህም ከዛሬ ጀምረን ባለ መታወክ ክርስትናችንን
ከአፋችን ወደ ልባችን: ከብዕራችን ወደ አንጀታችን
እንድናወርደው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አደራ ትላለች::

+ዛሬ ነገሮችን ረስተን ሌሎች አላስፈላጊ ነገሮችን
ከጀመርን እጅግ አሳፋሪ መሆኑ አይቀርም:: በጐውን
ጐዳና ተከትለን በሃይማኖትና በፍቅረ ክርስቶስ ከጸናን ግን
ማንም ቢመጣም ፈጽሞ አንናወጥም::

+ይልቁኑ
"አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን:
ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው::
ስለዚህም ምድር ብትነዋወጥ: ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ
ቢወሰዱ አንፈራም::" (መዝ. 46:1) እያልን ከቅዱስ
ዳዊት ጋር እንዘምራለን::

<< ለዚህ ደግሞ ደመ ሰማዕታት ይርዳን:: በረከታቸው ይድረሰን:: የጌታ ፍቅርም አይለየን >>

+*" ጻድቁ ንጉሥ ቴዎድሮስ "*+

=>በሃገራችን ታሪክ በጣም ተወዳጅ ከነበሩ ነገሥታት
ጻድቁ ቴዎድሮስ ቅድሚያውን ይወስዳል:: በርግጥ
በርካቶቻችን የምናውቀው ስለ ሃገሩ ፍቅር ራሱን የሰዋውን
ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስን (1845-1860) ነው:: በበጎ
ሥራውና በቅድስና ሕይወቱ የተመሠከረለት ግን ዛሬ
የምናስበው ቀዳማዊው ነው::

+ቀዳማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ የደጉ ዐፄ ዳዊት (ግማደ
መስቀሉን ያመጡት) እና የተባረከችው ሚስታቸው ፅዮን
ሞገሳ ልጅና የጻድቁ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ታላቅ ወንድም
ነው:: በኢትዮዽያ ለ3 ዓመታት (ከ1396-1399) ብቻ
ነግሦ እያለ እንደ ንጉሥ ሳይሆን-

*ከጠዋት እስከ ማታ ድሃ እንዳይበደል ፍርድ
እንዳይጉዋደል ይታትር የነበር::
*ጾምና ጸሎትን የሚያዘወትር::
*ወገቡን ታጥቆ ነዳያንን የሚያበላ::
*ለአብያተ ክርስቲያናትም የሚጨነቅ ደግ ሰው ነበር::

+ስለዚህም በሕዝቡ እጅግ ተወዳጅ ነበር:: በነገሠ በ3
ዓመቱ ዐርፎ በዝማሬና በለቅሦ ሥጋውን ተሸክመው
ሲሔዱ ወንዝ ተከፍሎላቸዋል:: ከመቃብሩም ላይ ጸበል
ፈልቁዋል::

=>ዘለዓለም ሥላሴ ደግ መሪና ሰላማዊ ዘመንን ያድሉን::

=>መጋቢት 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ጻድቁ ኢትዮዽያዊ ንጉሥ ዐፄ ቴዎድሮስ
2.ቅዱስ ቴዎዶጦስ ሰማዕት
3.ቅዱስ ፊልሞን ሰማዕት
4.ቅዱስ አብላንዮስ ሰማዕት

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
5.አባ ባውላ ገዳማዊ
6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)

=>+"+ ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ::
ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና::
ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው::
ስለዚህ ባ ለሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን
ሥርዓት ይቃወማል:: . . . ለሁሉ እንደሚገባው አስረክቡ::
ግብር ለሚገባው ግብርን: ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን:
መፈራት ለሚገባው መፈራትን: ክብር ለሚገባው ክብርን
ስጡ:: +"+ (ሮሜ. 13:1-8)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

የዩቱዩብ ቻናል👇
https://youtu.be/OIOCAD82nxk?si=VMEi2GBRFE8w3lMi

የቲክቶክ ቻናል👇
zikirekidusan23?_t=8kGT8RWuULK&amp;_r=1" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@zikirekidusan23?_t=8kGT8RWuULK&amp;_r=1

የቴሌግራም ቻናል👇
/channel/zikirekdusn

✝ ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር ✝

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#መጋቢት_7

እንኳን ለከበሩ #ለቅዱሳን_ፊልሞንና_አብላንዮስ በሰማዕትነት ላረፉበት፣ እንዲሁም #ለቅዱስ_ቴዎዶጦስ በሰማዐትነት ላረፈበት መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ።

"በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።"

#ቅዱሳን_ፊልሞንና_አብላንዮስ

➯መጋቢት ሰባት በዚህች ቀን የከበሩ ፊልሞንና አብላንዮስ በሰማዕትነት አረፉ። ይህ ፊልሞንም የእንዴናው ገዥ በሆነ በአርያኖስ ፊት በአዝማሪነት ይጫወት ነበር ከአዝማሪው አብላንዮስም ጋራ እርስ በርሳቸው ወዳጆች ሆኑ ለክብር ባለቤት ክርስቶስም ስለ ስሙ ምስክሮች ሊሆኑ ተስማሙ።

➯አዝማሪው ፊልሞንም ልብሱን ወስዶ ለአብላንዮስ ሰጠው እርሱም የአብላንዮስን ልብስ ለብሶ ወደ መኰንኑ ወደ አርያኖስ ገብቶ በፊቱ ቁሞ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ።

➯መኰንኑም ተመልክቶ አዝማሪው አብላንዮስ እንደሆነ አሰበ በፍላጻም እንዲነድፉት አዘዘ ያንጊዜም አዝማሪው ፊልሞን መሆኑን አውቆ እጅግ ተቆጣ። ደግሞ አብላንዮስን እንዲነድፉት አዘዘ ሁለቱንም ነደፉአቸው አንዲት ፍላጻም ወደ መኰንኑ ተመልሳ ዐይኑን አወጣቻት እጅግም አሠቃየችው። የከበሩ ፊልሞንና አብላንዮስ ግን ገድላቸውን ፈጽመው የሕይወት አክሊልን ተቀበሉ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ዎቅታዊ እና ተአማኒ መረጃዎችን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇
👉
@gyon_media👈
👉
@gyon_media👈
👉
@gyon_media👈
👉
@gyon_media👈
👉
@gyon_media👈
👉
@gyon_media👈
👉
@gyon_media👈
👉
@gyon_media👈
👆👆👆👆👆👆👆
  ይቀላቀሉን!!!

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አንቀፀ ብርሀን
ዐንቀጸ ብርሃን

ዉዳሴ ወግናይ ለእመ አዶናይ፡
ቅድስት ወብፅዕት፡ ስብሕት ወቡርክ፡ ክብርት ወልዕልት ዐንቀጸ ብርሃን፡
/channel/wdase1

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እንኳን ለአባታችን
አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (አቦዬ)
አመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን!

ቶሎ እንድንለቅ React ማድረግ እንዳይረሳ
/channel/silase
/channel/silase

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://www.youtube.com/live/kP7myikmjSc?si=ZTqJiZssyywPuydq

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እንኳን ለአባታችን
አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (አቦዬ)
አመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን!

ቶሎ እንድንለቅ React ማድረግ እንዳይረሳ
/channel/silase
/channel/silase

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

መጋቢት 5/2016 #ፃድቁ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ

በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና በፀሎት ለምንማፀንበት ለፃድቁ አባታችን #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ አመታዊ የእረፍት መታሠቢያ በዐል እንኳን አደረሰን

👉መጋቢት አምስት ቀን የታላቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ #ገብረ_ሕይወት የዕረፍታቸው መታሰቢያ ሲሆን ፃድቁ የተወለዱት #ግብፅ_ንሒሳ አካባቢ ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ

👉አባታችን #ገብረ_ሕይወት የፃድቃን አለቃ የቅዱሳን የበላይ ተጋድሎአቸውና ድንቅ ተአምራቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ቅዱስ ሰው ናቸዉ የጻድቁን ክብር መናገር የሚችል ምን አንደበት ይኖራል እንደ ምንስ ባለ ብራና ይፃፋል ዜናቸውንስ ለመስማት የታደለ እንደ ምን ዓይነት ሰው ይሆን

👉አባታችን #ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ለ562 ዓመታት በዚህች ዓለም ሲኖሩ እህል ያልቀመሱ ምግባቸው ምስጋና ነውና ልብስ ያልለበሱ ፀጉር አካላቸውን ይሸፍን ነበርና ሐዋርያዊ ሆነው ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ ነፍሳትን ያዳኑ አባት ሃገራችንን አስምረው አስራት እንድትሆናቸውም ተቀብለው ምድረ ከብድ አካባቢ አርፈዋል

👉ፃድቁ #ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ገብረ ሕይወትም ይባላሉ በ562 ዓመታት ሕይወታቸው እንደ ሐዋርያት ከምድረ ግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ወንጌልን ሰብከዋል በዚህም በሚሊየን አእላፍ ለሚቆጠሩ ነፍሳት የድኅነት ምክንያት ሆነዋል

👉ፃድቁ እንደ #ሰማዕታትም ከከሃዲ ሰዎች ብዙ መከራን ተቀብለዋል እንደ #ባሕታውያን ለብዙ መቶ ዓመታት ሰው ሳያዩ ቆይተዋል ለየት የሚለው ግን የፅድቅ ሕይወታቸው ነው ከእልፍ አዕላፍ አጋንንት ጋር ተዋግተው ድል ማድረግ ችለዋልና

👉የንሒሳው ኮከብ #ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ለኢትዮጵያ ልዩ ፍቅር አላቸው ስለ ሃገሪቱና ሕዝቧ ፍቅር ሲሉ ለ100 ዓመታት በደብረ ዝቋላ መከራን ተቀብለዋል ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው

👉ስለዚህም ነው በሃገሪቱ ውስጥ ከ2,000 በላይ የጻድቁ አቡነ #ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ገዳማትና አድባራት ዛሬም ድረስ ያሉት በ8ኛው ክ/ዘ አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ14ኛው መቶ ክ/ዘ አካባቢ ነው ፍጥረታትን ሁሉ አዘው መጋቢት 5 ቀን ሲያርፉ #ግሩማን_መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከፃድቁ ረድኤት በረከት ያሣትፈን ስለ ቅዱሣኑ ብሎ ፆም ፀሎታችን ተቀብሎ ሐገራችንን በምህረት አይኑ ይጎብኝልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ዎቅታዊ እና ተአማኒ መረጃዎችን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇
👉
@gyon_media👈
👉
@gyon_media👈
👉
@gyon_media👈
👉
@gyon_media👈
👉
@gyon_media👈
👉
@gyon_media👈
👉
@gyon_media👈
👉
@gyon_media👈
👆👆👆👆👆👆👆
  ይቀላቀሉን!!!

Читать полностью…
Subscribe to a channel