አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ 😲😲
በስመ አብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
የፊታችን መጋቢት 29 የሚካሄደው የህዝብ ቆጠራ ምክንያት በማድገግ የተለያዩ ሀይማኖቶች የኦርቶዶርስን እምነት ሊያጠፉ ይፈልጋሉ !!!
እናም ቆጠራ በሚካሄድበት ጊዜ
😟😟 አስተውሉ 😟😟
በክርስቲያን እምነት ውስጥ ከ 35,000 በላይ የሚሆኑ እምነቶች አሉ እናም ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ በማለት እምነታችን እንዳይጠፋ እንጠብቅ፣ ማለትም ለምዝገባ ሲመጡ እኛ ኦርቶዶክሶች ነን ብላቹ አስመዝግቡ እንጂ ክርስትያን ነን አትበሉ።
አስቡት እስቲ አሁን የመንግስት ሰራተኖች እረፍታቸው በሰንበት (እሁድ) ነው እረፍታቸው ግን የሀይማኖታችን ቁጥር ካነሰ ይቀየራል ለምሳሌ ሙስሊሞች አርብ ጁማቸው ነው የእነሱ ቁጥር ከበለጠ የመንግስት ሰራተኖች እረፍታቸው የሚሆነው አርብ ቀን ነው ።
እናስብ ሀይማኖታችን እንዳይጠፋ!
ጥር 11 የሚከበረው የኢየሱስ ክርስቶስ በዓል ሊቀር ይችላል እባካችሁ ሀይማኖታችንን እንጠብቅ
ቢያንስ አንድ ኦርቶዶክስ ለጓደኞቹ 10 ሰው ቢልክ ሀይማኖቱን ይጠብቃል
ድንግል ማርያም እናቴ አንቺ ጠብቂን በእግዚአብሔር ስም እለምናቹአለሁ ሁላችሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ናችሁ ቢያንስ ቢያንስ ለ10 ሰዎች ከተቻለ ከዚያም በላይ ለምትችሉት ሁሉ ይህን መልዕክት በመላክ ኦርቶዶክሳዊ ግዴታችንን እንወጣ ።የሁላችንም ግዴታ ነው በዚ ምክንያት እኛን ለመበታተን ጠላት አድብቶ ይሰራል እኛ ዛሬም ነገም እስክንሞት ድረስ ኦርቶዶክሶች ነን ስለዚህ ሼር ለሁሉም ይድረስ !!
/channel/silase
#መጋቢት_21
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
መጋቢት ሃያ አንድ በዚችም ዕለት የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከሙታን ለይቶ ወደ አስንሳው ወደ #አልዓዛር ቤት ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ የሔደበት ነው፣ ተአምረኛው አባት #አባ_ሊባኖስ_ዘመጣዕ ዓለምን ፍጹም በመናቅ የመነኑበት ነው፣ የማቱሳላ ልጅ #ጻድቁ_ላሜህ መታሰቢያው ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ቤተሰብ (አልዓዛር፣ ማርያና ማርታ)
መጋቢት ሃያ አንድ በዚችም ዕለት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ለይቶ ወደ አስንሳው ወደ አልዓዛር ቤት ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ሔደ በዚያም ምሳ አዘጋጂለት ማርታም ምግብ በማቅረብ ታገለግላቸው ነበር።
ሁለተኛዋ ማርያም ግን እግሮቹን ሽቱ እየቀባች በጸጕሩዋ ታሸው ነበር። ጌታችንም አመሰገናት እርሷ ከመቀበሪያዬ ጠብቃዋለች በማለት ስለ ቅርብ ሞቱ አመለከተ።
ዳግመኛም ድኆች ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉ እኔ ግን ከእናንተ ጋራ አልኖርም አለ በዚህም ተሰቅሎ የሚሞትበት ጊዜ ቅርብ መሆኑን ያመለክታል፡፡
ዳግመኛም በዚችም ቀን አልዓዛርን ሊገሉት የካህናት አለቆች ተማከሩ ገናና ስለሆነች ምልክት በእርሱ ምክንያት ብዙዎች በጌታችን የሚያምኑ ሁነዋልና።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ሊባኖስ_ዘመጣዕ
በዚችም ዕለት ከዐለት ላይ ውኃ እያፈለቁ ድውያንን የሚፈውሱት ተአምረኛውና አባት አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ ዓለምን ፍጹም በመናቅ መንነዋል፡፡ እርሳቸውም የአባታችን የተክለ ሃይማኖት ገዳም ‹‹ደብረ ሊባኖስ›› በስማቸው የተሰየመላቸው ናቸው፡፡ አባ ሊባኖስ አባታቸው አብርሃም እናታቸው ንግሥት ይባላሉ፡፡ እነርሱም በወርቅና በብር እጅግ የበለጸጉ ሮማዊ ናቸው፡፡ ልጃቸውን አባ ሊባኖስን በሃይማኖት በምግባር ኮትኩተው ካሳደጓቸው በኋላ ዕድሜያቸው ሲደርስ በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ያጋቧቸው ዘንድ ከቁስጥንጥንያ አገር ሚስት ባመጡለት ጊዜ እርሱ ግን ፈጽሞ እምቢ አለ፡፡ ወደጫጉላ ቤትም መግባትን እምቢ አለ፡፡ በዚህም ጊዜ ነቢዩ ሳሙኤልን እንደጠራው አባታችንንም እግዚአብሔር ሦስት ጊዜ በስማቸው ጠራቸውና ‹‹ከአባትህ ተለይ አንተ የመንግሥተ ሰማያት ሙሽራ ነህ እንጂ የዚህ ምድራዊ ዓለም ሙሽራ አይደለህም›› አላቸው፡፡ አባታችንም ‹‹ወዴት እሄዳለሁ? ምንስ ላድርግ?›› ባሉ ጊዜ ወዲያው የታዘዘ መልአክ በሌሊት መጥቶ ከአባታቸው ቤት አውጥቶ ታላቁ አባት አባ ጳኩሚስ ዘንድ አደረሳቸው፡፡ ታላቁ አባት አባ ጳኩሚስም ለአባ ሊባኖስ በዓት በመስጠት ገዳመ ሥርዓትን፣ አስኬማ መላእክትን፣ ቅናተ ዮሐንስን አስተምረዋቸው አመነኮሷቸውና ከ8ቱ ቅዱሳን ጋር እንዲገናኙ አደረጓቸው፡፡
ከዚህም በኋላ ያ ከአባታቸው ቤት ወስዶ አባ ጳኩሚስ ገዳም ያደረሳቸው ያ መልአክ ድጋሚ ተገለጠላቸውና ‹‹ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ሂድና ተጋድለህን በዚያ ፈጽም ዝናህ በስፋት ይነገራል፣ ለብዙዎችም አባት ትሆናቸዋለህ›› አላቸው፡፡ ቀጥሎም ራሱ መልአኩ ወደ ኢትዮጵያ አመጣቸውና በአክሱም ተቀመጡ፡፡ በዚያም ብዙ ከተጋደሉ በኋላ ወደ ሸዋ መጡና ወንጌልን ዞረው አስተምረው ብዙ ድውያንን ፈውሰው ከዓመታት ቆይታ በኋላ ተመልሰው አክሱም ሄዱ፡፡ በአክሱምም 7 የተለያዩ ጸበሎችን ከድንጋይ ላይ በተአምራት አፍልቀው ድውያንን ፈውሰው ዕውራንን አበሩ፡፡ በዓታቸውንም ከአክሱም ጽዮን ፊት ለፊት አድርገው ሲኖሩ ከዕለታት በአንደኛው ቀን አባታችን በተአምራት ከጭንጫ ካፈለቁት ጸበል ‹‹ተራ ውሃ ነው›› ብላ አንዲት ሴት ልጇን አዝላ ልትቀዳ መጣች፡፡ ወዲውም ከቦታው ስትደርስ አድጧት ወደቀችና ልጇም አምልጥጧት ልቡን ድንጋይ መቶት ሞተ፡፡ ሴትዮዋም ስትጮህ አባ ሊባኖስ ፈጥነው ወጡና በልጁ ላይ ጸልየው በመስቀል ምልክት አማትበው ከሞት አስነሥተውታል፡፡ ሕፃኑ ልጅ ከሞት እንደተነሣ ‹‹አምላከ አባ ሊባኖስ›› ብሎ አመሰገነ፡፡
ይህንንም ደግ ሥራቸውንና ተአምራታቸውን ያዩ አንዳንድ እኩይ ካህናት በቅናት ተመልተው ‹‹ምትሃት ነው የሚያሳየው›› ብለው በጻድቁ ላይ ሕዝቡን አሳደሙባቸው፡፡ አባታችንም ካህናቱን ለመምከር ቢሞክሩም አላስቀምጥ አሏቸው፡፡ ይልቁንም ጦር ጦራቸውን ይዘው አሳደዷቸው፡፡ አባታችንም በዚህ እጅግ አዝነው ከአክሱም ተነሥተው ደርቃ ወደምትባል ቦታ ሄዱ፡፡ በዚያም በጾም በጸሎት እየተጋደሉ ሲኖሩ በእነዚያ በጠሏቸውና በክፋት በተነሡባቸው ካህናት አገር ግን ለ3 ዓመት ምንም ዝናብ ሳይዘንብ ቀረ፡፡ አባታችን በተሰደዱባት በደርቃ አገር ግን ብዙ ዝናብ ይዘንብ ነበር፡፡ አባታችን በዚያችም አገር እንደልማዳቸው ከዐለት ላይ ውኃ አፍልቀው በውኃው ብዙ ድውያንን ፈውሰውበታል፡፡ በዚያም ትልቅ በዓት መሥርተው በተጋድሎ ሲኖሩ በክፉ የተነሡባቸው እኩይ የሆኑ ካህናት መጥተው ‹‹አባታችን በከንቱ አምተንሃል በድለንሃልና ይቅር በለን፣ በድርቅ ማለቃችን ነውና ዝናብም እንዲዘንብልን ጸልይን›› ብለው ከእግራቸው ሥር ወደቁ፡፡ አባታችንም ይቅር ብለው ከፈጣሪ አማለዷቸው፡፡ ዝናቡም ወዲያው ዘነበላቸውና በአገሪቱ ጥጋብ ሆነ፡፡
ከዚህም በኋላ አባታችን አስቀድመው ወዳዩአት ወደ ሸዋ ምድር ግራርያ መጡና በዓታቸውን በአሰቦት ጫካ አደረጉ፡፡ ነገር ግን መልአኩ ተገልጦላቸው ‹‹ሊባኖስ ሆይ! ከዚህ ቦታ የአንተ መኖሪያ አይደለም፣ በዚህ ቦታ ላይ እግዚአብሔርንና ሰውን የሚያገናኝ የሚያስታርቅ ታላቅ ጻድቅ ይወጣበታልና ይህ ቦታ የእርሱ ርስት ነው፣ የብዙ መነኮሳትም መንደር ይሆናል ነገር ግን የቦታው ስም በአንተ ስም ይጠራልሃል›› አላቸው፡፡ በኋላ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ተወልደው በዓታቸውን በዚያ ቦታ ላይ ሲያጸኑ ቦታው ግን ‹‹ደብረ ሊባኖስ›› ተብሎ በመጀመሪያው አባት ስም ተሰየመ፡፡ መልአኩም በሌሊት እየመራ ወደ አክሱም ወሰዳቸው፡፡ ከዚያም ‹‹ታሪክ ወደምትሠራበት ዕጣ ክፍልህ ወደሆነው ቦታ አደርስሃለሁ›› አላቸውና ወደ ኤርትራ አካለ ጉዛይ አውራጃ ልዩ ስሙ መጣዕ ወደተባለው ቦታ ወሰዳቸው፡፡ በዚያም አባታችን ድውያንን እየፈወሱ፣ ለምፃሞችን እያዳኑ፣ ሙታንን እያስነሡ ብዙ ተአምራትን እያደረጉ ወንጌልን እየሰበኩ ‹‹ሊባኖስ ዘመጣዕ›› የሚባለውን ትልቁን ገዳማቸውን መሠረቱ፡፡ በወቅቱ የነበረው ዐፄ ገብረ መስቀልም የመጀመሪያውን ቤተ ክርስቲያን አሠራላቸው፡፡
ቅዱስ ላሊበላ 23 ዓመት ሙሉ ካነጻቸው እጅግ ድንቅ 11 ቤተ መቅደሶች ውስጥ አንደኛውን በአባ ሊባኖስ ስም ሰይሞላቸዋል፡፡ ዐፄ ገብረ መስቀል ያሠራላቸው ሌላኛው ገዳማቸው ትግራይ ተንቤን ውስጥ ይገኛል፡፡ እጅግ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ የሚታወቁት አባታችን እንደ ተስዓቱ ቅዱሳን ከሮም በመምጣት በሀገራችን ላይ ብርሃንን አብርተዋል፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ጻድቁ_ላሜህ
በዚችም ዕለት የማቱሳላ ልጅ የላሜህ መታሰቢያው ነው። እርሱም አንድ መቶ ሰማንያ ሁለት ዓመት ኑሮ ኖኀን ወለደው ከወለደውም በኋላ አምስት መቶ ስልሳ አምስት አመት ኖረ።
በድምር ሰባት መቶ አርባ ሰባት ዓመት ኖረ። እግዚአብሔርንም አገልግሎት በሰላም አረፈ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መጋቢት እና #ከገድላት_አንደበት)
ገዳማዊያኑ ምን አሉ ?
ወዳጄ ዓይኔ ጥሩ ከማያይባት ፤ጆሮዬ ጥሩ ከማይሰማባት ፤ ሁሌ ከምታስጨንቀኝ ብዙ ከማልኖርባት ጥያት ከምሄደው ከእዚህ አብረቅራቂ ዓለም ምን ጥቅም አለ? ምንም።
~"ባህታዊ ቤት አልሰራም አለ
ለአፈር ሰው ለአፈርሰው እያለ"~ ጠብቆ ሲነበብ ሰው ለአፈር ነው ላልቶ ሲነበብ ለአፈርሰው ልንደው ሊፈርስ ምን ያደርግልኛል እንዳለ።
ሰይጣን እንኳን በዓለሙ በቤተክህነቱም ነግሷል ሆድ አደር ካድሬ ጥቁር ለባሽ ወታደር በዘር ቀረጢት የታሰረ ነውርን እንደሸማ የለበሰ ፤ለስልጣኑ እንጂ ለልህውና የማይታገል በዝቶበታል።
ያለ እረኛ ከቀረን ለእርድ ሊያቀርቡን ያዘጋጁን ከውስጥም ከውጪም ተናበው ከበውናል ቀን እየጠበቁ ነጥለው አራርቀው ስፈልጉ በሰይፍ ሳያሻቸው በጥይት ያወራርዱናል።
በእነዚህ መሀል እየኖርን እንኳን እንዳንጠፋ ተስፋም እንዳንቆርጥ ከእምነታችንም እንዳንወጣ ያልተወን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ግን ስራውን እየሰራ ነው
እርሱም ልብስ የሸፈናቸው ለመቅደሱ የማይሆኑትን በጊዜ ሂደት ለሕዝቡ እየገለጠ ይገኛል እርሱ የናቃቸውን እኛ እያወቅናቸው ነው ለእርሱ የሚሆኑትን ደግሞ ከሰው ርቀው ከአራዊት ተላምደው ዳዋ ልሰው ዲንጋይ ተተርሰው ግርማ ሌሊቱን ድምፀ አራዊቱን ታግሰው የሚኖሩትን የትንሳኤ ሹመኞችን እያዘጋጀም ነው።
ልብሳቸው አዳፋ ነው ንግግራቸው ኮልታፋ ነው ለእግራቸው ጫማ የላቸውም አንገት ደፍተው ጎጆ ቀልሰው ላስቲክ ዘርግተው ዋሻ ፈልፍለው ጥሬ ቆርጥመው ሆዳቸውን በፆም አስረው ይኖራሉ።
ከልባቸው ንፅህና የተነሳ ቅዱሳን መላዕክት በዓይናቸው ያያሉ ከፈጣሪያቸው ጋር ፊት ለፊት ይነጋገራሉ ድንግል ማርያም ወዳጃቸው ናት ሲፈልጉ መቅረዝ አልያም ምርኩዝ ስንቅም ትሆንላቸዋለች ይወዷታል እርሷም አብዝታ ትባርካቸዋለች።
ከሰው ተወልደው ከመላዕክት የተደመሩ የቅድስናቸው ማዕዛ አርያም የሚሸት ቆባቸው እንደ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ቀሚሳቸው እንደ አባባ ተክለሃይማኖት ኑሯቸው እንደ አቡዬ ይመስላል።
ዳዊት ሲደግሙ ፀሎት ሲፀልዩ አርያም ይሰማል ባለጸጋውን ይዘው እንደ ድሀ ይኖራሉ ይለምናሉ የሚያሰጡት ግን ከሰጪው ሰው በላይ ነው የገማውን የዓለምን ማዕዛ ወደ መልካም ጠረን የመቀየር አቅም አላቸው።
አሁን የእኛ ጳጳሳት እነዚህ ናቸው ያሉን መጠሪያ መዳኛ መሻገሪያ እነዚህ ገዳማዊያን ናቸው የሚሆነው አውቀው የምናደርገውን እየነገሩን ነው አሁን የምናየው እነርሱ ቀድመው የነገሩንን ነው ለእኔ ምንም አዲስ ነገር የለም በቃ የሚሆነው ይሆናል ግድ ነው ሳይፈርስ አይጠራም አለቀ።
ስለ አዲስ አበባ ገዳማዊያኑ ምን አሉ ታዲያ ?
~" ትልልቅ ዛፎች በሰይፍ ይታጨዳሉ ~" የእዚህ ሚስጢር ማብራሪያው ግን ለጊዜው ገታ አድርጌ በሰፊው በቴሌ ግራም ግሩባችን እንጫወታለን እንደ አቦ ሰጥ በአበሻ ቀሚስ ተሽሞንሙኖ ጠበልተኛ ይመስል ሰንጋ በሬ አክሎ የሚቀባጥረው የዩቲብ ሸቃጭና ትንቢት ተናጋሪ እርሱን እዘኑለት እንጂ ተውት።
አሁን እኛ ለጥልቅ በርሃ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ገዳማትን መነኮሳትን በሚያስፈልጓቸው ነገር እየተራዳን እንገኛለን መሆን ያለበት ማድረግም ያለብን ቤተ ክህነቱም ዓለሙም የተዋቸውን እነዚህ መታደግ ነው ጥቅሙ ለራሳችን ነው እኔም ለነፍሴ እናንተም ለነፍሳችሁ ስትሉ።
የገዳም አባቶች የሚመሩት ደበሎ ማዕዛ ቅዱሳን በጎ አድራጎት ማህበራችን ፃድቁ አባታችን አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ መቃብራቸው ሲፈልስ አብረው ያፈለሱ የእጃቸውን መስቀል የጨበጡ የመናኒያን አባት የገዳሙ አበመኔት አባ ገብረ ፃድቅ ቆሞስ ለተመሰረተው ማህበር አስቀድመው ይህ መልዕክት ለኦርቶዶክሳዊያን ልከው ነበር ከምስሉ ላይ ያንቡት።
ወዳጄ ከእግዚአብሔር አይሰረቅም ደግሞ እኔ አክሊለ ማርያም ብቻዬን የምመራው በራሴም አካውንት የምሰበስበው አንዳችም ድብሎ ሳንቲም የለም በስራቸው የተመሰከረላቸው ስራ ትዳር ሕይወት ኑሮ ያላቸው ከራሳቸው አልፈው ሰው የሚረዱ ታማኝ የሆኑ ኮሚቴ የተዋቀሩም ናቸው አለቀ ።
ከአገረ አሜሪካ የመጣው መመሪያ በኮሚቴው የተነገረኝ በውጪ የሚኖሩት አባላት ወራዊ ክፍያው 20 ዶላር ተወስኗል በአገር ውስጥ ለምንገኝ ደግሞ ወራዊ ክፍያ የሚሆነው 200 ብር ባለበት ፀንቷል ይህ ዓላማው ለገዳማዊያኑ ለገዳማት የሚሆን ነው አለቀ።
ድር ቢያብር አንበሳ ያስር እንዲሉ ከተባበርን የማንወጣው ነገር አይኖርም የእኛ ቤት ችግር የቅናት መንፈስ ጥሎ ማለፍ ሆኖ ነው እንጂ እንደ አሕዛቦቹ እንደ ካህዲያን ብንናበብ የትም እንደርሳለን።
ደግሞ ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ እንዳይሆን ቀድመን ተሰባስበን ተዘጋጅተን አፋጣኝ መልስ ለሚሹ ገዳማት ቶሎ ለመድረስ ያስችለን ዘንድ ይህ ደበሎ ማዕዛ ቅዱሳን ተመስርቷል።
ለዕድር ለምድራዊ ዕቁብ ወራዊ መዋጮ እያዋጣው ለነፍሴ እንዴት ዕድር አልገባም የምትሉ እህት ወንድሞቼ ወራዋ ክፍያው ሊጀመር ስለሆነ የእዚህ በጎ ዓላማ ራዕይ ተሳታፊ መሆን የሚፈልግ ወደ ቴሌ ግራም ቻናሉ በመሄድ join ያድርጉ።
👉 /channel/+U8IQDsdXcnWTb0FW ይጫኑት ይግቡ።
የአባላት ቁጥሩ 1ሺ ለመሙላት የቀረን ሩብ ጉዳይ ነው ዓላማው ግቡ እንዲውም የሚሰራው ስራ ፀሎቱ ትምህርቱ መልዕክቱ ሁሉ በቴሌ ግራሙ ይተላለፋል ይህ የቤተሰብ ጉዳይ ብቻ ይሆናል እኛ ኦርቶዶክሳዊያን በር ዘግተን የምንማከርበት እያንዳንዱ አባልን የምንቆጣጠርበት በሚያስፈልጋው መንፈሳዊ አገልግሎት የምንራዳበት ይሆናል።
ገዳማት በተኬደበት ሁሉ በቋሚነት ስመ ክርስትና በገዳማዊያኑ ሳይቋረጥ በፀሎት ይታሰባል ጥቅማችን በሰፊው በቴሌ ግራሙ ይገለጣል።ጨረስኩኝ።
ድንግል ማርያም እናት ዓለሜ ፤ እማ ፤ እማዋይሽ እመ ብርሃን ትባርካችሁ።
"የዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ግሩም የሆነ የመለኮት ዙፋን፤ የሐና እና የኢያቄም ልጅ ማርያም ሆይ ነይ። የጴጥሮስ የሥልጣኑ ቁልፍ የጳውሎስ የምስክርነቱ ድንኳን፤ አቡቀለምሲስ የተባለ ዮሐንስን ራእዩን እንዲያስተውለው የምታደርጊው ማርያም ሆይ ነይ" መዓዛ ቅዳሴ ቁ - ፳፮
Читать полностью…መጋቢት 21/2016 #እናታችን_ማርያም "በቅዱስ መፅሐፍ"
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና
በፀሎት ለምንማፀንበት #ለእናታችን_ማርያም ወርሐዊ የእረፍት መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን
👉ይህች እንደ ማለዳ ብርሃን የምትጎበኝ እንደ #ጨረቃ የተዋበች እንደ #ፀሐይም የጠራች ዓላማ ይዞ እንደ ተሰለፈ ሠራዊት የምታስፈራ ማን ናት (መኃ 6፣10)
👉መዐዛዋም እንደ #ከርቤና_እንደ_ዕጣን የኾነችው ከልዩ ከነጋዴ ቅመም ዅሉ የኾነችው ይህች ከምድረ በዳ እንደ ጢስ ምሰሶ የወጣችው ማን ናት (መኃ 3፣6) መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው (መዝ 86፣1)
👉ርግቤ መደምደሚያዬም አዲት ናት ለእናትዋ አንዲት ናት ለወለደቻትም #የተመረጠች ናት ቆነጃጅትም አይተው አሞገሷት ነገሥታትና ቁባቶችም #አመሰገኗት (መኃ 6፣9)
👉የሠራዊት ጌታ #እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንን እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር (ኢሳ1፣9)
👉ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ በእኔ ዘንድ ያማረ ነው ምንም ምን #ነውር_ነቀፋ_የለብሽም (መኃ 4፣7) #የእግዚአብሔር ሀገር በአንቺ የተደረገው ድንቅ ይባላል (መዝ 86፣3)
👉 #እግዚአብሔር ጽዮንን መርጧታልና ማደሪያውም ትኾነው ዘንድ ወዷታልና እንዲህ ብሎ ይህች ለዘለዓለም ማረፊያዬ ናት መርጫታለኹና በዚች ዐድራለኹ አሮጊቶቿን እጅግ እባርካለኹ ድኻዎቿንም እንጀራ አጠግባለኹ ካህናቶቿንም ደኅንነትን አለብሳቸዋለኹ ቅዱሳኖቿም ደስ ይላቸዋል (መዝ131፣13)
👉ባንቺ የሚኖሩ ሁሉ ደስ እንደሚላቸው ይነግራቸዋል
(መዝ 86፣7) እህቴ ሙሽራዬ #የተቆለፈች ገነት የተዘጋች ምንጭ የታተመም ፈሳሽ ናት (መኃ 4፣12)
👉ወደ ምሥራቅም ወደሚመለከተው በስተውጭ ወዳለው ወደመቅደሱ በር አመጣኝ ተዘግቶም ነበር እግዚአብሔርም ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም ሰውም አይገባበትም የእስራኤል አምላክ #እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግታ ትኖራለች (ሕዝ 44፣1)
👉ልጄ ሆይ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ ንጉሥ ውበትሽን ወዷልና እርሱ ጌታሽ ነውና
(መዝ 44፣10) መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከዅሉ #ትበልጫለሽ (ምሳ 31፣29)
👉መልአኩም ወደ እርሷ ገብቶ #ደስ_ይበልሽ_ፀጋ የሞላብሽ ሆይ ጌታ ከአንቺ ጋራ ነው አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት (ሉቃ1፣28)
👉ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማሕፀኗ ውስጥ ዘለለ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች አንቺ ከሴቶች መካከል #የተባረክሽ ነሽ የማሕፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው (ሉቃ1 ፣41)
👉ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ እግዚአብሔር የፅዮንን ደጆች ይወዳቸዋል (መዝ 86፣2)
👉የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ የናቁሽም ዅሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ #የእግዚአብሔርም ከተማ የእስራኤል ቅዱስ የኾንሽ ፅዮን ይሉሻል (ኢሳ 60፥14)
👉በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና #ንግሥቲቱ በቀኝኽ ትቆማለች (መዝ 44፣9)
👉ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ዅሉ ክብሯ ነው ልብሷ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው በዃላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ ባልንጀራዎቿንም ወዳንተ ያቀርባሉ በደስታና በሐሴት ይወስዷቸዋል ወደንጉሥ ዕልፍኝም ያስገቧቸዋል(መዝ 44)
👉በአባቶችሽ ፋንታ #ልጆች_ተወለዱልሽ በምድርም ዅሉ ላይ ገዢዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ ለልጅ ልጅ ዅሉ ስምሽን ያሳስባሉ (መዝ 44፣13)
👉እንሆም ከዛሬ ዠምሮ ትውልድ ዅሉ #ብፅዕት_ይሉኛል ብርቱ የኾነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጓልና (ሉቃ1፣48)
👉መልአኩም እንዲህ አላት ማርያም ሆይ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ እንሆም ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ስሙንም #ኢየሱስ ትይዋለሽ (ሉቃ 1፣30)
👉መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት መንፈስ ቅዱስ ባንቺ ላይ ይመጣል የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ #የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል (ሉቃ1፥35)
👉የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይኾንልኛል እንሆ የሰላምታሽ ድምፅ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማሕፀኔ በደስታ ዘሏልና ከጌታ የተነገረላት ቃል ይፈፀማልና ያመነች ብፅዕት ናት
(ሉቃ 1፣43)
👉ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮቿ በታች ያላት በራሷም ላይ #የአሥራ_ኹለት_ከዋክብት አክሊል የኾነላት አንዲት ሴት ነበረች (ራእ12፣1)
👉ሰው #እናታችን_ፅዮን ይላል በውስጧም ሰው ተወለደ ነገሥታትም አሳዳጊ አባቶችሽ ይኾናሉ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይኾናሉ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ
👉እኔም #እግዚአብሔር እንደ ኾንኹ ታውቂያለሽ እኔንም በመተማመን የሚጠባበቁ አያፍሩም (ኢሳ 49፣23) ስለ እናታችን ማርያም በመፅሐፍ ቅዱስ ዉስጥ ከተፃፉ ጥቅሶች በጥቂቱ
👉ለቃል መውረድ ለሥጋ ማረግ ምክንያት ናትና የትንቢተ ነብያት ማረፊያ የስብከተ ሐዋርያት መነሻ #ሰዓሊተ_ምሕረት መዝገበ ፀሎት ለወዳጆቿ ሙሓዘ ፍሥሐ በጠላትነት ለተነሡባት ግን ዓላማ ይዞ እንደተሰለፈ ሠራዊት የምታስፈራ ናት
👉በፍቅሯ #እናታችን_በክብሯ_እመቤታችን ስለ ክብረ ድንግልናዋ ስለ አማላጅነትዋ የተወደሰችና የተመሠገነች ትሁን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በረከትና ረድኤት ልጇ ወዳጇ መድኃኔአለም ያሳትፈን የተባረከ #ቀዳሚት_ሰንበት ይሁንልን "አሜን" ✝️ ⛪️ ✝️
#መጋቢት_19
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
መጋቢት ዐሥራ ዘጠኝ በዚች እለት #ሐዋርያ_አርስጥቦሎስ ሐዋርያ አረፈ፣ #ቅዱስ_አስከናፍርና የሚስቱ ማርታ የልጆቹ አርቃድዮስና ዮሐንስ የዕረፍታቸው መታሰቢያ ሆነ፣ #የሰባቱ_ሰማዕታት መታሰቢያቸው ሆነ፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አርስጦቦሎስ_ሐዋርያ
መጋቢት ዐሥራ ዘጠኝ በዚች እለት የሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙር አርስጥቦሎስ ሐዋርያ አረፈ። እርሱም ጌታችን ከመረጣቸውና ከመከራው በፊት እንዲሰብኩ ከላካቸው ከሰባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ የተቆጠረ ነው።
በሃምሳኛው ቀን በዓልም መንፈስ ቅዱስ በላዮ በወረደ ጊዜ ከሐዋርያት ጋራ ጸጋንና ኃይልን ተመልቶ ሕይወት በሚገኝበት በወንጌል ትምህርት ሐዋርያትን ተከትሎ በመሔድ አገለገላቸው።
ብዙዎችንም ወደ ድኀነት መንገድ መልሶ የክብር ባለቤት ወደ ሆነ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት አስገባቸው የክርስትና ጥምቀትንም አጥምቆ የአምላክን ሕግና ትእዛዝ ከማስጠበቁ የተነሣ ነፍሳቸውን አዳነ።
አባቶቻችን ሐዋርያትም ይህን ቅዱስ አብራጣብያስ በሚባል አገር ላይ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት። ወደርሷም ሒዶ በውስጥዋ ወንጌልን ሰበከ ብዙዎቹንም በቀናች ሃይማኖት እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ መለሳቸው።
በፊታቸውም ድንቆች ተአምራትን በማድረግ በሃይማኖት አጸናቸው ነገር ግን ከአይሁድና ከዮናናውያን ብዙ መከራ ደረሰበት።
ብዙ ጊዜም ወደ ፈረጆች አደባባይ ወስደው በደንጊያ ወገሩት ጌታችንም ከመከራው ሁሉ ጠብቆ አዳ ነው መልካም ተጋድሎውንም በፈጸመ ጊዜ በሰላም በፍቅር አረፈ። እነሆ ለሮሜ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ ሐዋርያ ጳውሎስ አስታውሶታል።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አስከናፍር
በዚህችም ቀን ደግሞ ቅዱስ አስከናፍርና የሚስቱ ማርታ የልጆቹ አርቃድዮስና ዮሐንስ የዕረፍታቸው መታሰቢያ ሆነ። ይህም አስከናፍር ብዙ ገንዘብ ያለው ባለጠጋ ነው ለእግዚአብሔርም ሕግ የሚጠነቀቅ ነበር ልጆቹንም መንፈሳዊ ምክርና ተግሣጽ በማስተማር አሳደጋቸው።
በአደጉም ጊዜ የጥበብንና የተግሣጽን ትምህርት እንዲማሩ ተይሩት ወደምትባል አገር ሰደዳቸውና ትምህርታቸውን በፈጸሙ ጊዜ ሊድራቸውና በሰርጋቸው ደስ ሊለው ሽቶ ያመጡአቸው ዘንድ ላከ በመርከብም ሁነው ሲመጡ ማዕበል ተነሥቶ መርከቡ ተሰበረ። እግዚአብሔርም ከስጥመት አድኖ በየብስ አወጣቸው ዮሐንስ የተባለውን በአንድ ቦታ ማዕበሉ አውጥቶ ጣለው።
ዮሐንስም ተስፋ በቆረጠ ጊዜ ወደ ቅዱሳን ገዳም ሒዶ መነኰሰ። ስለ ወንድሙ ስለአርቃድዮስም እንደሞተ ተጠራጥሮ በጸም በጸሎትና በስግደትም ሥጋውን አደከመ። አርቃድዮስም ወደ ዮርዳኖስ ገዳም ገብቶ ከአንድ ቅዱስ አረጋዊ ሰው ዘንድ መንኲሶ እየተጋደለ ሦስት ዓመት ኖረ።
አስከናፍር ግን ልጆቹ በማዕበል እንደሰጠሙ በሰማ ጊዜ ከሚስቱ ጋራ ማቅ ለብሰው አመድ አንጥፈው እያለቀሱ ተቀመጡ። በአንዲት ሌሊትም አስከናፍር በሕልሙ ልጁ ዮሐንስን በራሱ ላይ ከዕንቊ የተሠራ አክሊል ተቀዳጅቶ መስቀል ይዞ አየው።
አርቃድዮስንም በኮከብ አምሳል የሆነ አክሊል በራሱ ላይ ደፍቶ አየ ከእንቅልፉም ነቅቶ ለሚስቱ ያየውን ነገራት። ከዚያም በኋላ በየአድባራቱና በየገዳማቱ የልጆቻችንን ወሬ እንመረምር ዘንድ ተነሺ እንሒድ አላትና ወደ ዮርዳኖስ ሒደው ከመጥምቁ ዮሐንስ ገዳም ደረሱ።
ልጃቸውን አርቃዴዎስን ያመነኰሰውን አረጋዊ አባትን አገኙት ችግራቸውን ነገሩት እርሱም የክርስቶስ ወዳጆች አትዘኑ ወደ ቤተ መቅደስ ስትመለሱ ልጆቻችሁን በሕይወት ታገኛላችሁ አላቸው ደስ እያላቸውም ተመለሱ።
ዮሐንስም በመስቀል በዓል ሊሳለም መጣ አረጋዊውም ጠርቶ ከአርቃድዮስ ከወንድሙ አገናኘው ተያይዘውም አለቀሱ። ደግሞ አስከናፍርን ከሚስቱ ጋራ ጠርቶ ከልጆቻቸው ጋራ አገናኛቸውና በላያቸው ወድቀው እየሳሟቸው አለቀሱ።
ከዚህ በኋላ ከዚያ አረጋዊ ዘንድ የምንኲስና ልብስ ለበሱ ሚስቱን ማርታንም ከሴቶች ገዳም አስገባት አገልጋዮችንም ነፃ አውጥቶ አሰናበተ። ገንዘቡንም ለድኆችና ለችግረኞች በተነ ከገዳምም ገብቶ በጾም በጸሎት ተወሰነ እንዲሁም የተባረኩ ልጆቹ በገደል በትሩፋት የተጠመዱ ሁነው ኖሩ ጌታችንንም ደስ አሰኙት በፍቅር አንድነትም አረፉ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ሰባቱ_ቅዱሳን_ሰማዕታት
በዚህችም ቀን ደግሞ የሰባቱ ሰማዕታት መታሰቢያቸው ሆነ፡፡ እንርሱም የግብጽ ሰው እለእስክንድሮስና እስክንድሮስ ከጋዛ መንደር አጋብዮስ ከቡንጥስ ከተማ ኒሞላስ ከጠራልብስ ዲዮናስዮስ ሮሜሎስና ተላስዮስ ከግብጽ አውራጃዎች የሆኑ ናቸው።
እነርሱም በመንፈሳዊ ፍቅር ጸንተው ስለ ሃይማኖት ምስክሮች ሊሆኑ ተስማሙ። በፍልስጥዔም ውስጥ ወደ አለው ቂሣርያ ደርሰው በመኰንኑ ፍት ቆሙ።
በከ*ሀ*ዲ*ው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማመናቸውን ገለጡ መኰንኑም በጽኑዕ ሥቃይ አሠቃይቶ ገደላቸው። የሰማዕትነትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መጋቢት)
መጋቢት 19/2016 #ቅዱስ_ገብርኤል
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና በፀሎት ለምንማፀንበት በመልአኩ ስም ለምናመሰግንበት ለመልአኩ #ቅዱስ_ገብርኤል ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉ገብርኤል ‘ገብረ’ እና ‘ኤል’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ የመልአክ ስም ነው #የእግዚአብሔር_ሰው ማለትም ነው
👉አብሳሪ መልአክ #ቅዱስ_ገብርኤል ሆይ እጅግ አፅናኝና አስደሳች የሆነውን ምስጢረ ሥጋዌን ዜና ይዘህ ከሰማይ ወደ ምድር እንደወረድክ #ድንግል_ማርያም የአምላክ እናት ለመሆን ፈቃድዋ ሆኖ በተፈጸመ ጊዜ ደስ እንዳለህ እኛም እግዚአብሔርን በማክበርና ግዴታችንን በመፈፀም ደስ የምንሰኝበትን ፀጋ አሰጠን
👉ጠባቂያችን #ቅዱስ_ገብርኤል ሆይ ሦስቱን ወጣቶች ከሚያቃጥል እሳት እንዳዳንካቸው እኛንም በዚህ ዓለም ከሚወራው ከሚታየውና ከሚሰማው #ክፉ_ቀንና_እለት ሁሉ አድነን እየነደደ የሚለበልበንን የኃጢያት እሳትም አጥፋልን
👉የኑሯችንን ቀጠሮ በክንፈ ረድኤትህ ከልለው ሰይጣን እንዳይሰለጥንብን ክፉ አድራጊዎች ሟርተኞች ሰላቢዎች ዘረኞችና ነፍሰ ገዳዮች እንዳያጠቁን ከልለን ያንተን የእሳት አጥር ዘሎ ጠላት ያጠቃን ዘንድ ጠላት አይችልምና #ጥበቃህ ከእኛ ከባርያዎችህ አይለየን
👉#ቅዱስ_ገብርኤል ሆይ ሕፃኑ ቂርቆስና እናቱ እየሉጣን በንፍር ውኃ ከመቀቀል እንዳዳንካቸው ልጆችህን በማናውቀው ሁኔታ የተዘጋጀልንን #የጥፋት_ወጥመድ ሁሉ አስወግድልን በላያችን ላይም በክፉ ሰዎች ምክንያት የተነሳብንን እሳት አጥፋልን
👉 #ለእውነተኛ_ሃይማኖት የጨከንንና የቆረጥንም አድርገን የሰይጣንን ፈተና የምናልፍበት እውነተኛውን ጥበብ እንደ ነብዩ ዳንኤል አስተምረን
👉 ቅዱስ #ገብርኤል ሆይ በደል በተገኘብን ቁጥር እያለቀስን እንጠራሃለን ጎስቋላ የምንሆን በጥቃትና በሀዘን ውስጥ የምንገኝ ልጆችህ የአንተን ማፅናናትና ረዳትነት እንፈልጋለንና ፈጥነህ ናልን
👉እናታችን #ማርያምን ያበሰርክ ለዓለም ሁሉ የምታበራ ገብርኤል ሆይ በሰራዊት አምላክ ፊት ዘወትር ትቆማለህና ፀሎትና ልመናችንን ስማ
👉ቅዱስ #ገብርኤል ሆይ ቀድመህ የደስታ የምሥራች ቃልህን ልታበስር ወደ ገሊላ እንደወረድህ ዛሬም ለአዘንንና ለእኛ ለቃል ኪዳን ልጆችህ ከሠማይ በሠረገላ ናልን የደስታንም ቃል አሰማን
👉እናታችን #ማርያምን ያበሰርክ ተወዳጁ መልአክ ቅዱስ #ገብርኤል ሆይ በምህረትና በይቅርታ ወደ እኛ ናልን ዓለም የጥፋት የሞት የክስረት የውድመትና የተስፋ መቁረጥ ድምፅን ያሰማናልና አንተ ግን ጉስቁልናችንን የሚያነሳ ስብራታችንን የሚጠግን እንባችንን የሚያብስ #የብስራት ድምፅህን አሰማን እንድንፅናናም አድርገን
👉እውነተኛ ጠባቂያችን ቅዱስ #ገብርኤል ሆይ እኛን ለማዳን ሰው የሆነውን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን ማደሪያው የሆነችው #ድንግል_ማርያምን በጣም እንወዳታለን
👉በዚህ ዓለም የምሥጢረ ሥጋዌ ተካፋዮች በመሆናችን #በመንግስተ_ሰማያትም ተካፋዮች ለመሆን ሁላችንንም በምልጃህ አብቃን ለምንልን #የእግዚአብሔር መልአክ #ቅዱስ_ገብርኤል ጥበቃህ ተራዳኢነትህ አይለየን
👉#ገብርኤል ሆይ ለሀገራችን ሠላምን ለህዝባችን ፍቅር አንድነትን ይሰጠን ዘንድ በአምላካችን #በክርስቶስ ፊት ቆመህ ለምንልን የሀገራችንና #የህዝቦቿ የቤተክርስቲያናችን ጠላቶችን አስታግስልን ጦርነትና ረሐብ ከምድራችን ላይ ይወገድ ዘንድ ለምንልን ጥበቃህ አይለየን "አሜን" ✝️⛪️✝️
@kedusgebreal
@kedusgebreal
@kedusgebreal
ከዕረፍታቸው በኋላ የተደረጉ በርካታ ታላላቅ ተአምራት አሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ እርሳቸው ካረፉ ከትንሽ ቀናት በኋላ በመቃብራቸው ላይ ዘይት ፈለቀ፡፡ ከዚያም በእንጨት በተሰራ መቅጃ እየተቀዳ ወደ ትልቅ መጠራቀምያ ገብቶ ለቤተ መቅደስ መብራት በ12 ተቅዋም ተደርጎ ከዓመት እስከ ዓመት ይበራ ጀመር፡፡ ከተጠራቀመ ዘይቱም ለታመሙ ይቀቡትና ከተለያዩ ሕመሞች ይድናሉ፡ ያዕ 5:14፡፡ ዳግመኛም ኤርትራ በሚገኙት በሌሎቹ በአባታችን ደብር ውስጥ ከብዙ ጊዜ በኋላ በደብረ ሣህል ደብራቸውና በደብረ ጽጌ ፈለቀ፡፡ ቅብዓ ኑጉም ለታመሙ ፈውስ እየሰጠ ለቤተ መቅደስም መብራት ሆነ፡፡
ዳግመኛም ከተደረጉት ተአምራት ውስጥ አንዱ እንደ ቤተክርስቲያን ሕግጋት ጻድቁ ካረፉ በኋላ ለጸሎትና ለኑዛዜ ሰዎች ተሰብስቦው እህል እና ውሃ ተዘጋጅቶ በነበረበት ሰዓት "በዚ ቀን ሁሉ ሰው ተገኝቶ ያለሥጋ ዋልን›› ሲሉ ሦስት የተለያዩ ሚዳቆዎች በአቡነ ዮናስ ጸሎት ድንገት መጥተው በሰዎቹ መሐል ተገኙ፡፡ ሰዎቹም ሚዳቆዎቹን አረደው በሉ፡፡
ጻድቁ በስማቸው የተገደሙ ገዳማት (ደብረ ድኁኃንበ- ቆሓይን፣ ደብረ ጽጌ ትምዛእ፣ ደብረ ጽዮን ዓዲ ወሰኽ፣ ደብረ ጸሪቅ ትግራይ፣ እና ደብረ ሣህል ዓረዛ) ይባላሉ፡፡
አቡነ ዮናስ ያረፉት መጋቢት 17 ቀን ሲሆን ይህ ወቅት ታላቁ ዐቢይ ጾም የሚውልበት ስለሆነ በዓለ ዕረፍታቸውን ጥር 21 ቀን እንዲያከብሩ ለልጆቻቸው አስቀድመው ነግረዋቸዋል፡፡ በመሆኑም በዚሁ ዕለት ጥር 21 ቀን በሁሉም ገዳማቸው ውስጥ በታላቅ ክብረ በዓል ታስበው ይውላሉ፡፡
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መጋቢት እና #ከገድላት_አንደበት)
አንድ ቀን የአቡነ ዮናስ ተማሪዎቻቸው አህያ ውሃ ሊያጠጡ በሄዱበት ጊዜ ልጁዋን ያመመባት አንዲት ሴት ‹‹አህያው የማነው?›› ብላ ጠየቀቻቸው፤ እነርሱም ‹‹የአቡነ ዮናስ ነው›› አሏት፡፡ እርሷም በእምነት ሆና የታመመ ልጅዋን በአህያው ላይ አስቀምጣ አህያውን በባለቤትህ ጸሎት ተማጽኜሃለሁና ልጄን እንዲያድንልኝ እለምንልሃለሁ›› ብላ ተናገረች፡፡ ልጇም ወዲያው ከሕመሙ ዳነ፡፡
እርሷም በሌላ ጊዜ አባታችንን ስታገኛቸው ‹‹በጸሎትዎ የዳነ የእኔ ልጅ ነው›› ብላ መሰከረችላቸው፡፡
አቡነ ዮናስ በሐይቅ ውስጥ ገብተው ሲጸልዩ ዓሥሩ የእጆቻቸው ጣቶቻቸው እንደ ፋና የሚያበሩትና ዛሬም ድረስ መካነ መቃብራቸው ቅብዓ ቅዱስ የሚያፈልቅ ታላቅ ጻድቅ ናቸው።
በዚኽች ዕለት መጋቢት 17 ቀን በበዓለ ዕረፍታቸው ታስበው ይውላሉ፦
አቡነ ዮናስ አባታቸው ንዋየ እግዚእ እናታቸው ኂሩተ ማርያም ይባላሉ፡፡ በኅዳር 17 ቀን 1357 ዓ.ም በሀገረ ቡር (ሀገረ መስቀል) ሚባል ተወለዱ፡፡ አቡነ ዮናስ በሕፃንነታቸው በጎች እየጠበቁ ሳለ መንፈስ ቅዱስ አደረባቸው፣ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም መዝሙረ ዳዊት ኣስተማራቸው፡፡ እርሳቸውም ይህን ዓለም ንቀው ከመነኮሱ በኋላ 150 መዝሙረ ዳዊት በአንድ ጊዜ እየጸለዩ 3 ሺህ ስግደት ይሰግዱ ነበር፡፡ ቀንና ሌሊት ሲጸልዩም "ጠላቂት" በሚባል ሐይቅ ውስጥ እየገቡ እስከ አንገታቸው ድረው በሐይቁ ውስጥ ገብተው ይጸልዩ ነበር፡፡
ከተሰጧቸውም ጸጋዎች ውስጥ አንዱ 10 ጣቶቻቸው ወደ ሐይቁ ሲገቡ ይበሩ ነበር፡፡
አቡነ ዮናስ በየቀኑ ከ5 ፍሬ "ዳዕሮ" ወይም "ዓየ" በቀር ሌላ ምግብ አይመገቡም ነበር፡፡ ከዚኽም በኋላ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ኀብስተ ኣኩቴትን ጽዋ በረከት ከሰማይ አውርዶላቸዋል፡፡ ጻድቁ እግዚአብሔር ባዘዛቸው መሠረት ወደተለያዩ ቦታዎች እየዞሩ የተለያዩ ተኣምራት በማድረግ ሕሙማንን በመፈወስ ሙታን በማስነሣት ብዙዎችን ከክህደት ወደ እምነት ከኃጢአት ወደ ጽድቅ ከጣኦት ኣምልኮ ወደ እግዚአብሔር ኣምልኮ መልሰዋል፡፡
ጌታችን በአምላካዊ ቅዱስ ቃሉ ‹‹ከመቃብርህ ጸበል የተቀባ የጠጣ ከኃጥያቱ ይነጻል›› የሚል ቃልኪዳን አስቀድሞ የሰጣቸው ሲሆን በዚህ ድንቅ ቃልኪዳን መሠረት ዛሬም ድረስ ከመካነ መቃብራቸው ላይ ፈዋሽ የሆነ ቅብዓ ቅዱስ ይፈልቃል፡፡ ይህንንም በ2011 ዓ.ም ለአንድ ወር በአክሱምና ኤርትራ የዞር ጉዞ ባደረግንበት ወቅት ወደዚህ ታላቅ ገዳም ሔደን የጻድቁን ገዳም ተሳልመን ቅብዓ ቅዱሱን በዐይናችን አይተን በአባቶች ተቀብተን በረከታቸውን አግኝተናል፡፡ ቅብዓ ቅዱሱ በተለይም ጆሮውንና ዐይኑን ለሚያመው ሰው መድኃኒት ነው፡፡
አቡነ ዮናስ ይይዙት በነበረው መቋሚያ በውኃ እየታጠበ ውኃው በጣም ለታመሙ ሰዎች እየተሰጠ በቶሎ ከበሽታቸው ይድኑበታል፣ የማይድኑም ከሆነ ቶሎ በሞት ያርፋሉ፡፡ የሚታጠቡበት ሁሉ ለድኅነት ከሆናቸው በአጭር ጊዜ ይድናሉ ወይም ለዕረፍት ከሆናቸው ወደ እግዚአብሔር ዕረፍት ያሰናብታቸዋል፡፡ አቡ ዮናስ በቁርባን ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም በሠረገላ መንፈስ ደርሰው ያስቀድሱ እንደነበር ገድላቸው ይናገራል፡፡
ከዕረፍታቸው በኋላ የተደረጉ በርካታ ታላላቅ ተአምራት አሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ እርሳቸው ካረፉ ከትንሽ ቀናት በኋላ በመቃብራቸው ላይ ዘይት ፈለቀ፡፡ ከዚያም በእንጨት በተሰራ መቅጃ እየተቀዳ ወደ ትልቅ መጠራቀምያ ገብቶ ለቤተ መቅደስ መብራት በ12 ተቅዋም ተደርጎ ከዓመት እስከ ዓመት ይበራ ጀመር፡፡ ከተጠራቀመ ዘይቱም ለታመሙ ይቀቡትና ከተለያዩ ሕመሞች ይድናሉ፡ ያዕ 5:14፡፡ ዳግመኛም ኤርትራ በሚገኙት በሌሎቹ በአባታችን ደብር ውስጥ ከብዙ ጊዜ በኋላ በደብረ ሣህል ደብራቸውና በደብረ ጽጌ ፈለቀ፡፡ ቅብዓ ኑጉም ለታመሙ ፈውስ እየሰጠ ለቤተ መቅደስም መብራት ሆነ፡፡
ዳግመኛም ከተደረጉት ተአምራት ውስጥ አንዱ እንደ ቤተክርስቲያን ሕግጋት ጻድቁ ካረፉ በኋላ ለጸሎትና ለኑዛዜ ሰዎች ተሰብስቦው እህል እና ውሃ ተዘጋጅቶ በነበረበት ሰዓት "በዚ ቀን ሁሉ ሰው ተገኝቶ ያለሥጋ ዋልን›› ሲሉ ሦስት የተለያዩ ሚዳቆዎች በአቡነ ዮናስ ጸሎት ድንገት መጥተው በሰዎቹ መሐል ተገኙ፡፡ ሰዎቹም ሚዳቆዎቹን አረደው በሉ፡፡
ጻድቁ በስማቸው የተገደሙ ገዳማት (ደብረ ድኁኃንበ-ቆሓይን፣ ደብረ ጽጌ ትምዛእ፣ ደብረ ጽዮን ዓዲ ወሰኽ፣ ደብረ ጸሪቅ ትግራይ፣ እና ደብረ ሣህል ዓረዛ) ይባላሉ፡፡
አቡነ ዮናስ ያረፉት መጋቢት 17 ቀን ቢሆንም ይህ ወቅት ታላቁ ዐቢይ ጾም የሚውልበት ስለሆነ በዓለ ዕረፍታቸውን ጥር 21 ቀን እንዲያከብሩ ለልጆቻቸው አስቀድመው ነግረዋቸዋል፡፡ በመሆኑም በዚሁ ዕለት ጥር 21 ቀን በሁሉም ገዳማቸው ውስጥ በታላቅ ክብረ በዓል ታስበው ውለዋል፡፡
የአቡነ ዮናስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ ከታዘዘ መቅሰፍት ከተቃጣ መዓት በጸሎታቸው ይማረን፡፡
ዳግመኛም በዚኽች ዕለት ጌታችን አጥብቆ የሚወደው በሞተም በአራተኛው ቀን ከመቃብር ያስነሣው የከበረ ቅዱስ አልዓዛር በሰማዕትነት ዐረፈ። ረድኤት በረከቱ ይደርብን!!!
#ስብሐት_ለኪ_ማርያም_በኁልቁ_ኲሉ_ሥዕርትየ።
#ስብሐት_ለኪ_ማርያም_በኁልቁ_ኲሉ_አዕፅምትየ።
#ስብሐት_ለኪ_ማርያም_በኁልቁ_ኲሉ_ዘተርእየ።
#ስብሐት_ለኪ_ንግሥትየ_በኁልቁ_ኲሉ_ዘኢያስተርአየ።
#ስብሐተ_ድንግልናኪ_ዘልፈ_ይነግር_አፉየ።
ኦ እግዝእትየ ማርያም #_የጾምና_ጸሎት_ህግና_ስርዓት ወአድኅንኒ እመከራ ሥጋ ወነፍስ ለኲሎሙ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ አለም....
✞✞✞ እንኳን ለጌታችን "ኢየሱስ ክርስቶስ" ዓመታዊ በዓልና ለእመቤታችን "ቅድስት ድንግል ማርያም" ወርኃዊ በዓል በሰላም አደረሳችኹ ✞✞✞
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ ✞✞✞
+*" ቅዱሱ ቤተሰብ እና ጌታ "*+
=>ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና የዓለም ሁሉ ጌታ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚች ቀን ወደ ቢታንያ ሔዶ: እነ ቅዱስ አልዓዛርና ቤተሰቦቹ እንግድነት ተቀብለውታል::
+በዚያም ቅድስት ማርታ በጌታ ፊት ስታገለግል: ቅዱስ አልዓዛር ከጌታ ጐን ተቀምጦ: ቅድስት ማርያ በ300 ዲናር የገዛችውን ሽቱ በጌታ ላይ አፈሰሰች:: እግሩንም በጠጉሯ አበሰች:: (ዮሐ. 12:1)
+ለዛ የተባረከ ቤተሰብም ታላቅ በረከት ሆነ:: በርግጥም ድንቅ ነው:: ጌታን በቤት ማስተናገድ ፍፁም መታደል ነው::
=>ዳግመኛ በዚህ ቀን ይሁዳ በ300 ዲናሩ ሽቱ አመካኝቶ በጌታ ላይ አንጎራጎረ:: አይሁድ ደግሞ አልዓዛርን ይገድሉት ዘንድ ተማከሩ:: ምክንያቱም ጌታችን በርሱ ላይ የሠራትን ድንቅ እያዩ ከአይሁድ ወገን ብዙዎቹ ያምኑ ነበርና::
=>ቤተ አልዓዛርን የባረከ ጌታ በቸርነቱ የኛንም ይባርክርልን::
=>መጋቢት 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሱ ቤተሰብ (አልዓዛር: ማርያና ማርታ)
2.አባታችን ላሜኅ (የማቱሳላ ልጅ-የጻድቁ ኖኅ አባት)
3.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሰማዕት
4.ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሰማዕት
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም
2.አበው ጎርጎርዮሳት
3.አቡነ ምዕመነ ድንግል
4.አቡነ አምደ ሥላሴ
5.አባ አሮን ሶርያዊ
6.አባ መርትያኖስ ጻድቅ
=>+"+ የወንድማማች መዋደድ ይኑር:: እንግዶችን መቀበል አትርሱ:: በዚህ አንዳንዶች ሳያውቁ መላእክትን እንግድነት ተቀብለዋልና:: ከእነርሱ ጋር እንደታሰረ ሆናችሁ እስሮችን አስቡ:: የተጨነቁትንም ራሳችሁ ደግሞ በሥጋ እንዳለ ሆናችሁ አስቡ:: +"+ (ዕብ. 13:1)
✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞
+ ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችሗለን! +
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† እንኩዋን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛርን ከሞት ላስነሳበት ደግ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችኹ †††
+*" ሐዋርያ ቅዱስ አልዓዛር "*+
=>ከቀናት በፊት ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ አልዓዛር አረፈ ብለን ነበር:: ለስም አጠራሩ ስግደት: ክብር: ጌትነት ይድረሰውና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛር ባረፈ በአራተኛው ቀን ወደ ቢታንያ ደረሰ::
+ማርታ ቀድማ ወጥታ ከእንባ ጋር ተቀበለችው::
"አዳም ወዴት ነህ" ያለ (ዘፍ. 3:10) የአዳም ፈጣሪ "አልዓዛርን ወዴት ቀበራችሁት" አለ:: ቸርነቱ: ባሕርዩ ያራራዋልና ማርያም ስታለቅስ ባያት ጊዜ አብሮ አለቀሰ::
+ከዚያም በባሕርይ ስልጣኑ "አልዓዛር! አልዓዛር!" ብሎ አልዓዛርን አስነሳው:: ይሕች ተአምርም በአይሁድ ዘንድ ግርምት ሆነች:: ለጌታም የሞት ምክንያት አደረጉዋት:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጋ እንዲህ ታስተምራለች::
(ዮሐ. 11:1-ፍጻሜው)
+ቅዱስ አልዓዛር ጌታችን ካስነሳው በሁዋላ በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ (ቁጥሩ ከ72ቱ አርድእት ነውና) : ለ40 ዓመታት ወንጌልን አስተምሮ : በ74 ዓ/ም አካባቢ ቆዽሮስ ውስጥ አርፏል::
=>የጌታችን ቸርነቱ : የአልዓዛር በረከቱ ይድረሰን::
=>መጋቢት 20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አልዓዛር ጻድቅ ሐዋርያ (የጌታ ወዳጅ)
2.ቅድስትና ብጽዕት ሰማዕት አስጠራጦኒቃ (ከታላላቅ ሰማዕታት አንዱዋ)
3.ቅዱሳን ሰማዕታት (የቅ/አስጠራጦኒቃ ማሕበር)
4.እናታችን ቅድስት ጽጌ-ሥላሴ (ኢትዮዽያዊት)
5.ቅዱስ አስቃራን ሰማዕት
6.አባ ሚካኤል ሊቀ ዻዻሳት
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት (ሰማዕት)
2.ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
3.ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
4.ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
5.አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና
6.ቅድስት ሳድዥ የዋሒት
=>+"+ ጌታ ኢየሱስም 'ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር እንድታዪ አልነገርሁሽምን?' አላት . . . ይሕንም ብሎ በታላቅ ድምጽ 'አልዓዛር ሆይ ወደ ውጭ ና' ብሎ ጮኸ:: የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ:: ፊቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበረ:: ጌታ ኢየሱስም 'ፍቱትና ይሂድ ተውት' አላቸው:: +"+ (ዮሐ. 11:40-44)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
መጋቢት 19/2016 #ቅዱስ_ገብርኤል
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና በፀሎት ለምንማፀንበት በመልአኩ ስም ለምናመሰግንበት ለመልአኩ #ቅዱስ_ገብርኤል ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉ገብርኤል ‘ገብረ’ እና ‘ኤል’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ የመልአክ ስም ነው #የእግዚአብሔር_ሰው ማለትም ነው
👉አብሳሪ መልአክ #ቅዱስ_ገብርኤል ሆይ እጅግ አፅናኝና አስደሳች የሆነውን ምስጢረ ሥጋዌን ዜና ይዘህ ከሰማይ ወደ ምድር እንደወረድክ #ድንግል_ማርያም የአምላክ እናት ለመሆን ፈቃድዋ ሆኖ በተፈጸመ ጊዜ ደስ እንዳለህ እኛም እግዚአብሔርን በማክበርና ግዴታችንን በመፈፀም ደስ የምንሰኝበትን ፀጋ አሰጠን
👉ጠባቂያችን #ቅዱስ_ገብርኤል ሆይ ሦስቱን ወጣቶች ከሚያቃጥል እሳት እንዳዳንካቸው እኛንም በዚህ ዓለም ከሚወራው ከሚታየውና ከሚሰማው #ክፉ_ቀንና_እለት ሁሉ አድነን እየነደደ የሚለበልበንን የኃጢያት እሳትም አጥፋልን
👉የኑሯችንን ቀጠሮ በክንፈ ረድኤትህ ከልለው ሰይጣን እንዳይሰለጥንብን ክፉ አድራጊዎች ሟርተኞች ሰላቢዎች ዘረኞችና ነፍሰ ገዳዮች እንዳያጠቁን ከልለን ያንተን የእሳት አጥር ዘሎ ጠላት ያጠቃን ዘንድ ጠላት አይችልምና #ጥበቃህ ከእኛ ከባርያዎችህ አይለየን
👉#ቅዱስ_ገብርኤል ሆይ ሕፃኑ ቂርቆስና እናቱ እየሉጣን በንፍር ውኃ ከመቀቀል እንዳዳንካቸው ልጆችህን በማናውቀው ሁኔታ የተዘጋጀልንን #የጥፋት_ወጥመድ ሁሉ አስወግድልን በላያችን ላይም በክፉ ሰዎች ምክንያት የተነሳብንን እሳት አጥፋልን
👉 #ለእውነተኛ_ሃይማኖት የጨከንንና የቆረጥንም አድርገን የሰይጣንን ፈተና የምናልፍበት እውነተኛውን ጥበብ እንደ ነብዩ ዳንኤል አስተምረን
👉 ቅዱስ #ገብርኤል ሆይ በደል በተገኘብን ቁጥር እያለቀስን እንጠራሃለን ጎስቋላ የምንሆን በጥቃትና በሀዘን ውስጥ የምንገኝ ልጆችህ የአንተን ማፅናናትና ረዳትነት እንፈልጋለንና ፈጥነህ ናልን
👉እናታችን #ማርያምን ያበሰርክ ለዓለም ሁሉ የምታበራ ገብርኤል ሆይ በሰራዊት አምላክ ፊት ዘወትር ትቆማለህና ፀሎትና ልመናችንን ስማ
👉ቅዱስ #ገብርኤል ሆይ ቀድመህ የደስታ የምሥራች ቃልህን ልታበስር ወደ ገሊላ እንደወረድህ ዛሬም ለአዘንንና ለእኛ ለቃል ኪዳን ልጆችህ ከሠማይ በሠረገላ ናልን የደስታንም ቃል አሰማን
👉እናታችን #ማርያምን ያበሰርክ ተወዳጁ መልአክ ቅዱስ #ገብርኤል ሆይ በምህረትና በይቅርታ ወደ እኛ ናልን ዓለም የጥፋት የሞት የክስረት የውድመትና የተስፋ መቁረጥ ድምፅን ያሰማናልና አንተ ግን ጉስቁልናችንን የሚያነሳ ስብራታችንን የሚጠግን እንባችንን የሚያብስ #የብስራት ድምፅህን አሰማን እንድንፅናናም አድርገን
👉እውነተኛ ጠባቂያችን ቅዱስ #ገብርኤል ሆይ እኛን ለማዳን ሰው የሆነውን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን ማደሪያው የሆነችው #ድንግል_ማርያምን በጣም እንወዳታለን
👉በዚህ ዓለም የምሥጢረ ሥጋዌ ተካፋዮች በመሆናችን #በመንግስተ_ሰማያትም ተካፋዮች ለመሆን ሁላችንንም በምልጃህ አብቃን ለምንልን #የእግዚአብሔር መልአክ #ቅዱስ_ገብርኤል ጥበቃህ ተራዳኢነትህ አይለየን
👉#ገብርኤል ሆይ ለሀገራችን ሠላምን ለህዝባችን ፍቅር አንድነትን ይሰጠን ዘንድ በአምላካችን #በክርስቶስ ፊት ቆመህ ለምንልን የሀገራችንና #የህዝቦቿ የቤተክርስቲያናችን ጠላቶችን አስታግስልን ጦርነትና ረሐብ ከምድራችን ላይ ይወገድ ዘንድ ለምንልን ጥበቃህ አይለየን "አሜን" ✝️⛪️✝️
@kedusgebreal
@kedusgebreal
@kedusgebreal
††† እንኳን ለቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችኹ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ቅዱስ ኤስድሮስ †††
††† ሰማዕትነት በክርስትና ለሃይማኖት የሚከፈል የመጨረሻው ዋጋ (መስዋዕትነት) ነው:: ሰው ለፈጣሪው ሰውነቱን ሊያስገዛ: ሃብት ንብረቱን ሊሰጥ ይችላል:: ከስጦታ በላይ ታላቅ ስጦታ ግን ራስን አሳልፎ መስጠት ነው::
ራስን መስጠት በትዳርም ሆነ በምናኔ ውስጥ ይቻላል:: የመጨረሻ ደረጃው ግን ሰማዕትነት ነው::
"አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም:: ወተዓገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግስተ ሰማያት::" እንዳለው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
ሰማዕትነት ማለት መራራውን ሞት ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲሉ መታገስ ነው::
እርሱ ቅሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ ሲሆን ኃፍረተ መስቀልን ታግሦ ሙቶልን የለ!
በዓለም ያሉ ብዙ እምነቶች ስለ መግደል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያስተምራሉ:: ክርስትና ግን መሞትን እንጂ መግደልን የሚመለከት ሕግ የለውም::
እርሱ ባለቤቱ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ:: የሚረግሟችሁን መርቁ:: ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ::" ብሎናልና:: (ማቴ. 5:44) ነገር ግን ዕለት ዕለት ራሳችንን በሃይማኖትና በምግባር ካልኮተኮትነው ክርስትና በአንድ ጀምበር ፍጹም የሚኮንበት እምነት አይደለምና በፈተና መውደቅ ይመጣል::
በተለይ የዘመኑ ክርስቲያን ወጣቶች ልናስተውል ይገባናል:: የቀደሙ ወጣት ሰማዕታት ዜና የሚነገረን እንድንጸና ነውና::
ቤተ ክርስቲያናችን ኢትዮዽያዊውን የጐንደር ዘመን ሊቅ ጨምሮ በዚህ ስም የምትዘክራቸው አያሌ ቅዱሳንና ሊቃውንት አሏት::
ዛሬ የምናከብረው ሰማዕቱ ቅዱስ ኤስድሮስ በዘመነ ሰማዕታት የነበረ: ቅዱስ ፃና የሚባል ደግ ጉዋደኛ የነበረው: ሁለቱንም እናቶቻቸው እንደሚገባ ያሳደጉዋቸው የ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ክርስቲያኖች ነበሩ::
በወጣትነት ዘመናቸው በድንግልና: ቅዱስ ፃና የሠራዊት አለቃ: ቅዱስ ኤስድሮስ ደግሞ የልብስ ዝግጅት ባለሙያ ነበሩ:: ከሚያገኙት ገቢ ለዕለት ጉርስ ብቻ እያስቀሩ ለነዳያን ይመጸውቱ ነበር::
በመከራ ዘመን (ዘመነ-ሰማዕታት) ቅዱሳኑ ያላቸውን ሁሉ ለነዳያን አካፍለው በክርስቶስ ስም መሞትን መርጠዋል::
በዚህች ቀንም አስቀድሞ ቅዱስ ኤስድሮስ አንገቱን ተሰይፎ የክብርን አክሊል ተቀዳጅቷል::
††† ፈጣሪ ከሰማዕቱ ክብር ያድለን::
††† መጋቢት 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
2.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሰባኬ ሃይማኖት (ረባን)
3.አቡነ አኖሬዎስ ዘደብረ ጽጋጋ
4.ማር ያዕቆብ ግብፃዊ
††† "የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ:: ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ: ፀሐይ: ጨረቃና ከዋክብትም ሳይጨልሙ . . . አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ: ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ::
ሰባኪው:- "ከንቱ: ከንቱ: ሁሉ ከንቱ ነው" ይላል::" †††
(መክ. 12:1-9)
††† "ዳሩ ግን የነገር ሁሉ መጨረሻ ቀርቦአል:: እንግዲህ እንደ ባለ አእምሮ አስቡ:: ትጸልዩም ዘንድ በመጠን ኑሩ:: ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናልና ከሁሉ በፊት እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ::" †††
(1ዼጥ. 4:7)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
"ሰአል ለነ እስጢፋኖስ ዲያቆን ቀዳሜ ሰማእት ፤ዘነጸርከ በግኅደት ፣ኀሉና ሥላሴ ዘበሰማያት (የሰማእታት መጀመሪያ በሰማያት ያለውን የሥላሴን አነዋወር በግልጽ የተመለከትኽ ዲያቆኑ እስጢፋኖስ ሆይ ለምንልን🙏✝[መጽሐፈ ሰዓታት]
/channel/silase
ዎቅታዊ እና ተአማኒ መረጃዎችን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇
👉@gyon_media👈
👉@gyon_media👈
👉@gyon_media👈
👉@gyon_media👈
👉@gyon_media👈
👉@gyon_media👈
👉@gyon_media👈
👉@gyon_media👈
👆👆👆👆👆👆👆
ይቀላቀሉን!!!
#መጋቢት_17
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
መጋቢት ዐሥራ ሰባት በዚች ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚወደው በአራተኛውም ቀን ከመቃብር ያስነሣው የከበረ #ጻድቅ_አልዓዛር አረፈ፣ አናጕንስጢስ #ቅዱሰ_ቴዎቅሪጦስ በሰማዕትነት አረፈ፣ ኢትዮጵያዊው #ጻድቅ_አቡነ_ዮናስ የበዓለ ዕረፍታቸው መታሰቢያ ነው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አልዓዛር_ሐዋርያ
መጋቢት ዐሥራ ሰባት በዚች ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚወደው በአራተኛውም ቀን ከመቃብር ያስነሣው የከበረ ጻድቅ አልዓዛር አረፈ። ይህም ጻድቅ ሰው ከእስራኤል ልጆች ውስጥ ነው ማርያና ማርታ የተባሉ ሁለት እኅቶች አሉት። ማርያም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሸቱ የቀባችው ናት።
እነርሱም ለጌታ ደቀመዛሙርቶቹ ናቸው ስለ ምግባራቸውም ጌታችን ይወዳቸዋል ሁሉም ያላገቡ ድናግል ናቸው። በሰው ወገን ሁሉ ላይ የተቆረጠና የተወሰነው ሰዎችም ሊጠጡት ያላቸው የሞት ጻዋን የሚጠጣበትና እጁን ለሞት የሚሰጥበት ለዚህ ጻድቅ ጊዜው ሲደርስ እርሱም እጁን በመስጠት አረፈ።
የክብር ባለቤት ጌታችን ግን የሚሠራውን ያውቃልና መጀመርያ ከሞት አላዳነውም ጠርቶ እስከሚአሥነሣው ድረስ ሙቶ በመቃብር አራት ቀን እንዲኖር በዚህ በአራት ቀንም የጻድቃንን ማደሪያዎችንና የኃጥአንን የሥቃይ ቦታዎች እንዲያይ ተወው እንጂ አላዳነውም ያን ጊዜም ታላቅ ምልክት ትሆናለች።
ከአራት ቀኖችም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሱ መጥቶ አልዓዛር አልዓዛር ና ውጣ ብሎ ከመቃብር ውስጥ ጠራው ያን ጊዜ አጆቹና እግሮቹ እንደታሠሩ ሙታኖችንም እንደሚጠቀልሏቸው በሰበን ፊቱ ተጠቅልሎ ወጣ።
እጆቹና እግሮቹ እንደ ተጠቀለሉና እንደ ታሠሩ ከመቃብር የመውጣቱ ምክንያት ሰዎች ሁሉ መሞቱን እንዲረዱ ሌሎችም ይህ በመካከላቸው በስምምነት የሆነ ነው ብለው እንዳያሰቡ። ስለዚህም እንደ ገነዙት ሁኖ እንዲወጣ ጌታችን አዘዘው ይችም ምልክት እንድትሆን።
ከሀዲዎችም በመቃብር ውስጥ ሕያው እንደ ነበር ቢያስቡም እጆቹና እግሮቹ ፊቱም እንደ ተጠቀለሉ እንዴት ይወጣ ነበር እኛ የክርስቲያን ወገኖች ግን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአራት ቀኖች በኋላ አልዓዛርን ያስነሣው እርሱ እንደሆነ እናምናለን። እንታመናለንም እርሱ በሥራው ሁሉ ላይ ችሎታ አለውና።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ቴዎቅሪጦስ_አናጉንስጢስ
በዚችም ዕለት አናጕንስጢስ ቴዎቅሪጦስ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ የሮሜ አገር ሰው ነው። ዐላውያንም ለጣዖት እንዲሠዉ ክርስቲያኖችን ይዘው በአስገደዷቸው ጊዜ እርሱንም ከእነርሱ ጋር ያዙት ወደ ንጉሥም አቀረቡት ያንጊዜ የዐሥራ አምስት ዓመት ልጅ ነበር።
ንጉሡም በማመጣብህ ሥቃይ ትፈተናለህን ወይስ ለአማልክት ትሠዋለህ አለው። ቴዎቅሪጦስም እኔስ ለክብር ባለቤት ለጌታዬ ለፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ እሠዋለሁ አለው። ንጉሡም ቴዎቅሪጦስ ሆይ በክፉ አሟሟት እንዳትሞት ለአማልክት መሥዋዕት አቅርብ አለው።
እርሱም ንጉሥ ሆይ መሥዋዕቴን እንድታይ ና አለው ንጉሡም ወደ ጣ*ዖ*ቱ ቤት እንዲወስዱትና በዚያ እንዲሠዋ አዘዘና እርሱም በበር ቆመ። ቅዱሱም በጸለየ ጊዜ ንውጸውጽታ ሁኖ አጽቀላጽዮስ የሚሉት አምላካቸው ወድቆ ተሰበረ።
ንጉሡም እንደ ዘበተበት አይቶ አፍንጫውን ቆረጠው አሥረው በወህኒ ቤት እንዲአስገቡት አዘዘ። በማግሥቱም አውጥተው በብረት ምጣዶች ውስጥ ጨመሩት ደግመው ጥልቅ ግድጓድ ቆፈሩ በውስጡም እንጨት ረብርበው ሥጋው ከመለያያው እስቲቦጫጨቅና ቅልጥሙም ከአጥንቶቹ እስቲፈስ ድረስ ወረወሩት ። በዚህም ሊአጠቁት አለቻሉም የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ከእርሱ ጋር አለና።
ከዚህ በኋላ አማልክቶቻቸው የሚበቀሉት መስሏቸው ከአማልክቶቻቸው ቤት አስገብተው በዚያ ዘጉበት ። ቴዎቅሪጦስ ግን ከጣ*ዖ*ታ*ቱ ላይ ያለውን ወርቅ ቀጥቅጦ በሥውር ይዞ እየወጣ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች መጸወተው። ተመልሶ ሲገባም ደጃፉ እንደ ቀድሞው ራሱ ይዘጋል።
በስምንተኛውም ቀን ንጉሡ መጣ ከደጃፍም ሁኖ አየ አማልክቶቹም ተጥለው ተሰባብረው የከበረ ቴዎቅሪጦስም ሲዘብትባቸው አገኛቸው። ዕውነተኛ ቴዎቅሪጦስንም የሆድ ዕቃው እስቲታይ እንዲሰነጣጥቁት አዘዘ። ደግመው ወደ ጨዋታ ቦታ እንዲአስገቡትና በላዩ አንበሶችን እንዲአስገቡአቸው አዘዘ። አንበሶችም ቁስሎቹን ላሱለት።
ዳግመኛም ሕዋሳቱ እስቲነጣጠል ከሚአጣብቅ ቦታ እንዲአስገቡት መላ አካላቱም ታጥፎ እስቲቆለመም እንዲአሠቃዩት አዘዘ። በዚህም ተሸብሮ አላሸነፉትም ንጉሡም ብርታቱን አይቶ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ።
የከበረ ኤጲስቆጶስ ኤሞሬዎስና ህዝብ ሁሉ በጸሎት እየተራዱት ቅዱስ ቴዎቅሪጦስን ተከተሉት በቅዱሳን ሰላምታም ተሳልመውት ተሰናበቱት ባለወግ ወታደርም ሰይፉን አንስቶ አንገቱን ቆረጠው ምስክርነቱንም ፈጸመ፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ጻድቁ_አቡነ_ዮናስ
በዚኽች ዕለት አቡነ ዮናስ የበዓለ ዕረፍታቸው መታሰቢያ ነው፡፡ አቡነ ዮናስ አባታቸው ንዋየ እግዚእ እናታቸው ኂሩተ ማርያም ይባላሉ፡፡ በኅዳር 17 ቀን 1357 ዓ.ም በሀገረ ቡር (ሀገረ መስቀል) ሚባል ተወለዱ፡፡ አቡነ ዮናስ በሕፃንነታቸው በጎች እየጠበቁ ሳለ መንፈስ ቅዱስ አደረባቸው፣ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም መዝሙረ ዳዊት ኣስተማራቸው፡፡ እርሳቸውም ይህን ዓለም ንቀው ከመነኮሱ በኋላ 150 መዝሙረ ዳዊት በአንድ ጊዜ እየጸለዩ 3 ሺህ ስግደት ይሰግዱ ነበር፡፡ ቀንና ሌሊት ሲጸልዩም "ጠላቂት" በሚባል ሐይቅ ውስጥ እየገቡ እስከ አንገታቸው ድረው በሐይቁ ውስጥ ገብተው ይጸልዩ ነበር፡፡ ከተሰጧቸውም ጸጋዎች ውስጥ አንዱ 10 ጣቶቻቸው ወደ ሐይቁ ሲገቡ ይበሩ ነበር፡፡ አቡነ ዮናስ በየቀኑ ከ5 ፍሬ "ዳዕሮ" ወይም "ዓየ" በቀር ሌላ ምግብ አይመገቡም ነበር፡፡
ከዚኽም በኋላ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ኀብስተ ኣኩቴትን ጽዋ በረከት ከሰማይ አውርዶላቸዋል፡፡ ጻድቁ እግዚአብሔር ባዘዛቸው መሠረት ወደተለያዩ ቦታዎች እየዞሩ የተለያዩ ተኣምራት በማድረግ ሕሙማንን በመፈወስ ሙታን በማስነሣት ብዙዎችን ከክህ**ደት ወደ እምነት ከኃጢአት ወደ ጽድቅ ከጣ*ኦ*ት አምልኮ ወደ እግዚአብሔር አምልኮ መልሰዋል፡፡
ጌታችን በአምላካዊ ቅዱስ ቃሉ ‹‹ከመቃብርህ ጸበል የተቀባ የጠጣ ከኃጥያቱ ይነጻል›› የሚል ቃልኪዳን አስቀድሞ የሰጣቸው ሲሆን በዚህ ድንቅ ቃልኪዳን መሠረት ዛሬም ድረስ ከመካነ መቃብራቸው ላይ ፈዋሽ የሆነ ቅብዓ ቅዱስ ይፈልቃል፡፡
አቡነ ዮናስ ይይዙት በነበረው መቋሚያ በውኃ እየታጠበ ውኃው በጣም ለታመሙ ሰዎች እየተሰጠ በቶሎ ከበሽታቸው ይድኑበታል፣ የማይድኑም ከሆነ ቶሎ በሞት ያርፋሉ፡፡ የሚታጠቡበት ሁሉ ለድኅነት ከሆናቸው በአጭር ጊዜ ይድናሉ ወይም ለዕረፍት ከሆናቸው ወደ እግዚአብሔር ዕረፍት ያሰናብታቸዋል፡፡ አቡ ዮናስ በቁርባን ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም በሠረገላ መንፈስ ደርሰው ያስቀድሱ እንደነበር ገድላቸው ይናገራል፡፡
ዎቅታዊ እና ተአማኒ መረጃዎችን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇
👉@gyon_media👈
👉@gyon_media👈
👉@gyon_media👈
👉@gyon_media👈
👉@gyon_media👈
👉@gyon_media👈
👉@gyon_media👈
👉@gyon_media👈
👆👆👆👆👆👆👆
ይቀላቀሉን!!!