kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
❤️❤️❤️❤️❤️
(
@GeezL73 )
መ/ር ጳውሎስ ብለው ያናግሩኝ።
+251915642585
ተመዝግበው ይማሩ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሰላም ለእናንተ ይሁን የእግዚአብሄር ወዳጆች

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

با فیلترشکن نت ملی
یک بار برای همیشه از شر فیلترینگ خلاص شو
دانلود از گوگل پلی

https://play.google.com/store/apps/details?id=de.manvpn.app

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/+cD8I6LHkvu5kMmY0

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🔔🔔🔔🔔
የደብረ ዘይት ቅኔ
🛄🛄🛄🛄
➡️ንባብ
➡️ፍቺ
➡️ርቃቄ፦ ሠም፣ወርቅ
➡️ማብራሪያ
➡️ጥያቄና መልስ
❤️❤️❤️❤️❤️❤️
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
/channel/+cD8I6LHkvu5kMmY0

ይጠይቁ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

መጋቢት 30/2016 #ቅዱስ_ዮሐንስ
#ቅዱስ_ማርቆስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና በፀሎት ለምንማፀንበት እና በቅዱሣኑ ስም ለምናመሰግንበት ለቅዱሣኑ ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን

👉እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ #ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም ማቴ11፥11

👉የጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ቃል ስለ መጥምቀ መለኮት #ቅዱስ ዮሐንስ ክብር መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በጌታ የተከበረ ነቢይ እና ጻድቅ ነው እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ የለም በማለት የተናገረለት ቅዱስ አባት ነው

👉የመጥምቀ መለኮት #ቅዱስ_ዮሐንስ
የተሰጡት ሃብተ ፀጋዎች

1 👉 ነብይ
2 👉 ካህን
3 👉 መምህር
4 👉 ሐዋርያ
5 👉 ፃድቅ
6 👉 መጥምቅ
7 👉 ሰማእት ነው

👉 #ቅዱስ_ዮሐንስ ከነቢያት ሁሉ የሚበልጥ መሆኑን ጌታችን ሲናገር እንዲህ ብሎ ተናግሮለታል ከነቢያት ሁሉ የሚበልጥ #ነብይ ነው እላችኋለሁ በማለት መስክሮለታል

👉 #ቅዱስ_ዮሐንስ ሃቀኛ መምህር፤ ነቢይ፤ ካህን፤ ሰማዕት፤ ሐዋርያ በመሆኑ ከአምላኩ ክብርን የተቀበለ ቅዱስ አባት ነው ስለዚህ ነው ደግሞ ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ እራሱ ግልጽ አድርጎ ስለ #ቅዱስ_ዮሐንስ ክብር የተናገረው

👉ትንቢት የተነገረለት #ቅዱስ_ዮሐንስ ክብሩ በመልአኩ እንዲህ በማለት ነው የተመሠከረለት #በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ነቢይ እንደሆነ #በመንፈስ_ቅዱስ የተመረጠ በንጽሕናው በአገልግሎቱ #በመላእክት ደረጃ የሚታሰብ ሲሆን ምልጃና ፀሎቱ የከበረዉ
ቃል ኪዳን ሁላችንንም ይጠብቀን

👉ለኢትዮጲያና ለግብፅ አባታችን አስተማሪያችን የሆነዉ ሐዋርያዉ #ቅዱስ_ማርቆስ በዚህ እለት የመታሠቢያ በአሉ ሲሆን ምልጃና ፀሎቱ ረድኤትና በረከቱ የአባትነት ፍቅሩ አይለየን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ረድኤት በረከት ያሣትፈን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🔔🔔🔔
መልእክት
ለአንደኛ ዙር የቅኔ ተማሪዎች
እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ማታ ከምሽቱ 3:00
⬇️⬇️⬇️⬇️
የመፃጕዕ ቅኔ
➡️ፍቺ
➡️ርቃቄ
✅ሠም
✅ወርቅ
➡️ሙያ
ማብራሪያ ይኖረናል። ስለዚኽ በመማሪያ ቻናላችኹ በሰዓቱ እንድትገኙ።


⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
/channel/+cD8I6LHkvu5kMmY0

በመጫን ገብቶ
ማታ 3:00 መከታተል ይችላል።
+251915642585

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ግእዝ መማር የሚያስገኘው ጥቅም
/channel/+cD8I6LHkvu5kMmY0

ጳውሎስ ንባብ ቤት
✅የዘወትር ጸሎት
✅ውዳሴ ማርያም
✅አንቀጸ ብርሃን
✅መልክአ ማርያም 
✅መልክአ ኢየሱስ 
✅መዝሙረ ዳዊት 
@የወንጌል ንባብ
@የግብረ ሐዋርያት ንባብ

በግእዝ ንባብ ይማሩ
ልጆችዎን ያስተምሩ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Old telegram groups መሸጥ ለምትፈልጉ

Old telegram ግሩፖች ያላችሁ( be 2022 Ena keza betach balew amete mihret create yetederge )  የ Group ሜምበር ብዛት አያስፈልግም የGroup ሜምበር 1 ሰው ቢሆንም በተመጣጣኝ ዋጋ እየገዛን ነው።  ግን የተከፈተበት አመተ ምህረቱን ነው የምፈልገው  ቢያንስ አንድ አመት የቆየ መሆን አለበት



ቢያንስ አንድ አመት የቆየ እና ትንሽ ሜምበር ያለው ግሩፕ (ከ1 ሜምበር ጀምሮም ይቻላል) ያላችሁ ሰዎች እና መሸጥ የምትፈልጉ inbox ላይ አናግሩኝ🙏 በተመጣጣኝ ዋጋ እየገዛን እንገኛለን።

Yetekefetebet year bekoye kutr birrum bezaw lk ychemral

It's not a scam it is real ከናንተም ከምታውቁትም ሰው የማትፈልጉትን በመሸጥ ብሮን ይቀበሉ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

መጋቢት 28/2016 #ቅዱስ_አማኑኤል
#ርዕሰ_አበዉ_አብርሃም_ይስሐቅ_ያዕቆብ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ለአባቶቻችን አምላክ #ለቅዱስ_አማኑኤል ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን

👉 #አማኑኤል ማለት #እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ማለት ነው

👉 #የአብርሐም_የይስሐቅ_የያእቆብ አምላክ ቅዱስ #እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን በቸርነቱ ይጠብቀን

👉#አማኑኤል ማለት አማኑኤል፣ የአምላክ ሰላም፣ #የእግዚአብሔር እርቅ፣ የጌታ አንድነት ማለት ነው

👉 #አማኑኤል ማለት "አማኑ" እና "ኤል" ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው አማኑኤል ማለት #እግዚአብሔር ከኛ ጋር ማለት ነዉ

👉"ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ ወይሰመይ ስሙ #አማኑኤል ዘበትርጓሜሁ #እግዚአብሔር ምስሌነ"

👉ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅንም ትወልዳለች ሰሙንም #አማኑኤል ትለዋለች ትርጉሙም #እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው ( ኢሳ 7፥14)

👉ክብር ፣ኃይልና ምስጋና ለአምላካችን #ለቅዱስ_አማኑኤል ይሁን ለዘለዓለሙ "አሜን"

👉 #ቅዱስ_አማኑኤል አባታችን እረኛችን የምታሳጣን የለም ያጣነዉም የለም እረኛችን ሆይ ካላንተ አባትም እረኛም የለንም እንደ ቸርነትህ ጠብቀን "አሜን"

👉በዚህ እለት በመታሰቢያ በአላቸዉ የምናስባቸው የአባቶቻችን #የአብርሃም_የይስሐቅ_የያዕቆብ ረድኤትና በረከት አይለየን የተባረከ #ቀዳሚት_ሰንበት ይሁንልን "አሜን" ✝️💒✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/+cD8I6LHkvu5kMmY0

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
♦️♦️ቅኔ♦️♦️
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔🔔
በዐቢይ ጾም የቅኔ መንገሪያ ነጥቦች
ከዘወረደ እስከ ደብረ ዘይት
❤️❤️❤️❤️❤️❤️
➡️የቅኔው አመሥጥሮ
✅የቅኔው ሠም
✅የቅኔው ወርቅ
✅የቅኔው መንገድ
✅የቅኔው ዘይቤ
✅የቅኔው መነሻ ወዘተ ለማወቅ
💠💠💠💠💠💠💠
ለጥያቄ  ከዚኽ በታች ባለው
አድራሻ ይጠይቁኝ
❤️❤️❤️❤️❤️
(
@GeezL73 )
መ/ር ጳውሎስ ብለው ያናግሩኝ።
+251915642585

⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
/channel/+cD8I6LHkvu5kMmY0

ገብተው የቅኔ ጥበብን ይቅመሱ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

13ኛ. ሰሪበ ሐሞት፡- ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ 12ቱን ሕማማተ መስቀል ሲቀበል ውሎ ዘጠኝ ሰዓት በሆነ ጊዜ ‹‹ተጠማሁ›› አለ፡፡ ዮሐ 19፡26፡፡ አይሁድም ‹‹ይህ ዕብራዊ ‹ውሃ ጠማኝ› አለ፣ ጲላጦስ ተመራምሮ ሳያድነው በቶሎ የሚገድል ነገር እናጠጣው ብለው ከመከሩ በኋላ ጉሮሮ ቆርጦ የሚጥል አንጀት የሚበጥስ ከብዙ ነገር የተደባለቀ እጅግ መራራ አጠጡት፡፡ ጌታችንም ቀምሶ ተፋው እንጂ አልዋጠውም፡፡ በዚኽም ነቢዩ ቅዱስ ዳዊት ‹‹ለመብሌ ሐሞት ሰጡኝ፣ ለጥማቴም ሆምጣጤ አጠጡኝ›› ብሎ የተናገረው ትንቢት ተፈጸመ፡፡ መዝ 68፡21፡፡ ጌታችን ከዚህ በኋላ 7ቱን ቃላት በመስቀል ላይ ተናግሮ ራሱን ወደቀኝ ዘንበል አድርጎ ቅድስት ነፍሱን በገዛ ሥልጣኑ ለየ፡፡ ዮሐ 10፡15፣ 19፡30፡፡

የመድኃኔዓለም ቸርነቱ የድንግል እናቱ ምልጃና ጸሎት ከሁላችን ጋር ይሁን! አሜን!!

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

K:
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
የመድኃኔዓለምን የሕማሙን የሞቱን ነገር መናገር እንጀምራለን፡፡ 13ቱ ሕማማተ መስቀል እነማን ናቸው ቢሉ ተዓሥሮ ድኅሪት (የፊጥኝ መታሰር)፣ ወዲቀ ዲበ ምድር (በመሬት ላይ መውደቅ)፣ ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በአይሁድ እግር መረገጡ)፣ ተስሕቦ በማዕከለ ዓምድ (ታንቆ መጎተት)፣ ተጸፍዖ መልታሕት (ፊትን መጥፊ መመታት)፣ ተኰርዖ ርእስ (የራስ መገመስ)፣ አክሊለ ሦክ (የእሾህ አክሊል)፣ ተዐርቆተ ልብስ (ርቃን መቆም)፣ ተቀሥፎ ዘባን (ጀርባን መገረፍ)፣ ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም)፣ ተቀንዎ በቅንዋት (በችንካር መቸንከር)፣ ተሰቅሎ በዕፅ (መሰቀል) እና ሰሪበ ሐሞት (ሐሞት መጠጣት) ናቸው፡፡  
13ቱ ሕማማተ መስቀል የሚባሉት እነዚህ ናቸው፡፡ ምነውሳ ወሪቀ ምራቅ፣ ጽርፈተ አይሁድና ርግዘተ ገቦ ከእነዚህ ውስጥ የማይቆጠሩ? ቢሉ እነዚህ ሦስቱ ከንዑሳን የሚቆጠሩ ናቸው እንጂ ከ13ቱ ገብተው አይቆጠሩም፡፡ ስለምን አይቆጠሩም? ቢሉ ወሪቀ ምራቅ የምራቅ መተፋት ነው፡፡ አይሁድም ጌታችንን ርኩስ ምራቃቸውን ተፍተውበታል ነገር ግን ሰውን ቢተፉበት ይጸየፈዋል እንጂ ምራቅ ሕማም ሆኖ አይገድልም፡፡ ስድብም ያናድዳል ያስቆጣል እንጂ ሕማም ሆኖ አይገድልምና ጽርፈተ አይሁድ አይቆጠርም፡፡ ርግዘተ ገቦ ማለት የጌታችን ጎኑ በጦር መወጋቱ ነው፡፡ ሰውን ከሞተ በኋላ ቢወጉት ሕማሙ አይሰማውምና ርግዘተ ገቦ አይቆጠርም፡፡ 
13ቱን ሕማማት እንዴት ነው የተፈጸሙ ቢሉ ክፉዎች አይሁድ መድኃኔዓለምን ሊይዙት የጦር መሣሪያቸውን ሰብስበው የታጠቁ 300 ጭፍራዎችን አስከትለው ወደ ጌቴሴማኒ በመጡ ጊዜ ‹‹ማንን ትፈለጋላችሁ?›› ቢላቸው ‹‹የናዝሬቱን ኢየሱስን እንፈልጋለን›› ሲሉት ‹‹እኔ ነኝ›› ቢላቸው ከአንደበቱ የወጣውን መለኮታዊ ቃል ብቻ መቋቋም አቅቷቸው መሬት ላይ ወድቀው ተዘርረዋል፡፡ ይህም ክስተት ለሦስት ጊዜ ያህል በተደጋጋሚ ተከስቷል፡፡ ዮሐ 18፡1-14፡፡ የጌታችን ሞቱ በፈቃዱ መሆኑንና የትዕግሥቱን ብዛት አይተን እናደንቅ ዘንድ ከመጻሕፍት ጠቅሰን እንነግራችኋለን፡፡ አይሁድ ጌታችን አብርሃም ሳይወለድ በፊት እርሱ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገን አምላክ መሆኑን ቢነግራቸው ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፡፡ እሱ ግን ጊዜው ገና ነበርና ተሰውሮአቸው በመካከላቸው አልፎ ሲሄድ በፍጹም አላዩትም ነበር፡፡ በቅዱስ ወንጌል ላይ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፡- ‹‹አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም አለው። አይሁድም:- ገና አምሳ ዓመት ያልሆነህ አብርሃምን አይተሃልን? አሉት። ኢየሱስም:- እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው። ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወራቸው ከመቅደስም ወጥቶ በመካከላቸው አልፎ ሄደ፡፡›› ዮሐ 8፡56-59፡፡ የጌታችን ሞቱ በፍጹም ፈቃዱ ባይሆን ኖሮ በጌቴሴማኒ ሊይዙት የመጡት ክፉዎች አይሁድን እንደመጀመሪያው ሁሉ በተሠወራቸው ነበር አሊያም ከአንደበቱ በሚወጣው አምላካዊ ቃሉ ብቻ በፊቱ እንዳይቆሙ አድርጎ ባጠፋቸው ነበር፡፡ ጌታችን ግን ወደዚህች ምድር የመጣበትን ዓላማ ይፈጽም ዘንድ እንዲገድሉት በፈቃዱ ራሱን አሳልፎ ቢሰጣቸው ያን ሁሉ እጅግ አሠቃቂ መከራ አደረሱበትና ለመስቀል ሞት አበቁት፡፡
ወዮ ለዚህ ለመድኃኒዓለም ፍጹም ትዕግስት አንክሮ ይገባል! ዓለምን በመዳፉ የያዘ አምላክ በአይሁድ እጅ እንደሌባ ተያዘ፤ ሠራዊተ መላእክት ለምሥጋና በፊቱ የሚቆሙለት መድኃኔዓለም እርሱ ሊፈረድበት በፍርድ አደባባይ ቆመ፤ በእስራት ያሉትን የሚፈታ እርሱ በብረት ችንካር ተቸነከረ፤ ሰማይን በከዋክብት ምድርም በአበባ ያስጌጠ እርሱ ግን የእሾህ አክሊል በራሱ ላይ ደፋ፤ ዓለሙን ሁሉ በቸርነቱ የሚመግብ እርሱ ተጠማሁ አለ፡፡ ወዮ የመድኃኔዓለም የማዳኑ ምሥጢር ምንኛ ድንቅ ነው!!! ይህንን ከትውልዱ ማን አስተዋለ?
የሕማማቱን ነገር ወደመፈጸም እንመለስ፡፡ ጌታችን 300 የታጠቀ ሠራዊት አስከትለው ሊይዙት የመጡትን አይሁድን በፊቱ ሦስት ጊዜ በጣላቸው ሰዓት በመጀመሪያው በልባቸው ጥሎ ገሃነመ እሳትን አሳይቷቸዋል፤ በሁለተኛው በጀርባቸው ጥሎ መንግሥተ ሰማያትን አሳይቷቸዋል፡፡ በሦስተኛው ደግሞ ፈረስ በቅሎዎቻቸውን ከላይ አይሁድን ከሥር አድርጎ ፊታቸውን ከኋላ ኋላቸውን ከፊት፣ ቀኛቸውን ግራ ግራቸውን ቀኝ አድርጎ በማሳየት ሁሉን ማድረግ የሚችል የባሕርይ አምላክ መሆኑን በተግባር አሳይቷቸዋል፡፡
እነርሱ ግን አንድ ጊዜ ሰይጣን በልባቸው አድሯልና ወደ ህሊናቸው መመለስ አልቻሉም፡፡ እነርሱም ‹‹እኛ ታዘን ነውና የመጣነው እባክህ ጌታ ሆይ! በፈቃድህ ተያዝልን›› ብለው ለመኑት፡፡ ሁሉ በእጁ የተያዘ አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ያንጊዜ ራሱን አሳለፎ ሰጣቸው፡፡
1ኛ. ተዓሥሮ ድኅሪት፡- አይሁድም ከዚህ በኋላ የጌታችንን መጋፊያና መጋፊያው እስኪጋጠም ድረስ የፊጥኝ ረግጠው ካሠሩት በኋላ አፍንጫውን 25 ጊዜ ቢመቱት ደሙ በመሬት ላይ እንደ ውኃ ፈሰሰ፡፡ አሥረውም ከቀያፋ ወደ ሐና፣ ከሐና ወደ ቀያፈ ሲያመላልሱት አደሩ፡፡ ዮሐ 18፡12፡፡ ይህም ለአርአያ እና ለቤዛነት ነው፡፡ ቤዛነቱ አዳምንና ሔዋንን አጋንንት ገሃነመ እሳት አውርደው በእሳት ሰንሰለት የፊጥኝና የግርግሪት አሥረው ሲያሠቃዩአቸው ነበርና እነርሱንና የሰውን ልጅ በሙሉ ለማዳን ነው፡፡ አርአያነቱ በእኔ ምክንያት ያስሯችኋል ነገር ግን በፍቅሬ ታስራችሁ ኑሩ፣ መከራን ተቀበሉት እንጂ አተሰቀቁ ሲል ነው፡፡
2ኛ. ወዲቀ ዲበ ምድር፡- ክፉዎች አይሁድ ጌታችንን ካሠሩት በኋላ ከጌቴሴማኒ እስከ ሐና ቤት ድረስ 65 ጊዜ በምድር ላይ ጥለውታል፡፡ የራስ ጠጉሩንም እየያዙ እያንጠለጠሉ 25 ጊዜ እያነሡ ጥለውታል፡፡
3ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ፡- አይሁድ አሥረው እየጎተቱ ሲወስዱት የፊተኞቹ ሲስቡት የኋለኞቹ ይለቁታል ያንጊዜም በልቡ ሲወድቅ ከኋላ ያሉት ፈረሳቸውን በቅሏቸውን በላዩ ይነዱበታል፡፡ የኋለኞቹ ሲስቡት የፊተኞቹ ይለቁታል በጀርባው ይወድቃል፡፡ ቀድመውት የሄዱትም ‹‹…ወዴት ሄደ? አመለጠን?...›› እያሉ በመዘበት ተመልሰው በልቡ ላይ ይሄዱበታል፡፡ እንዲህ እያደረጉ 65 ጊዜ ከመሬት ጋር አጋጭተውታል፡፡ ሳውልም በዚያ ጊዜ ከእነርሱ ጋር ነበርና ጌታችን ‹‹መመለስህ ላይቀር ለምን ትረግጠኛለህ?›› ቢለው ትንቢት ተናገረብኝ ብሎ ሳውል 440 ጊዜ አስገረፈው፡፡ ዳግመኛም በጅንፎ በትር 62 ጊዜ መቱት፤ በአለንጋ 62 ጊዜ ገረፉት፤ አፉንና አፍንጫውን ደሙ እስኪወርድ ድረስ 40 ጊዜ መቱተ፤ የእጆቹ ጣቶች እስኪደቁ ድረስ 42 ጊዜ መቱት፡፡
4ኛ. ተስሕቦ በማዕከለ ዓምድ፡- ይኽም ጉሮሮን ታንቆ እንደውሻ መጎተት ማለት ነው፡፡ ጌታችንን አይሁድ ጉሮሮውን በብረት ሰንሰለት አጥብቀው አሥረው ደም እስኪነስረው ዐይኑ ሊፈርጥ እስኪደርስ ድረስ 27 ጊዜ በጡጫ መቱት፡፡ በሁለት ታላላቅ ግንዶች መሐል አግብተው አንገቱን የታሠረበት ከግንዶቹ ጋር በማሠር የፊተኞቹ ሲስቡት የኋለኞቹ ይለቁታል በፊቱ ያለው ግንድ ልቡን ደረቱን ፊቱን ይመታዋል፤ የኋለኞቹ ሲስቡት የፊተኞቹ ይለቁታል የኋላው ግንድ ወገቡን ራሱን ይመታዋል፡፡ እንዲህ እያደረጉ 62 ጊዜ ከግንዱ ጋር አጋጩት፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

መጋቢት 27/2016 #ጥንተ_ስቅለት (መድኃኔዓለም)

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ አለምን ለማዳን እና እኛን ከማእሰረ ሀጢያት ለመፍታት መስቀል ተሸክሞ መከራ ለተቀበለበት እና ለተሰቀበለበት ዓመታዊ ክብረ በዓል እንኳን አደረሰን

👉 #ወንጌል እንደተናጋረ የመድኃኒታችንን የመከራውን ነገር ወደ መናገር እንመለስ ጲላጦስ የዚህ ሰው በደሉ ምንድነው በእሱ ላይ በሚሞትበት ገንዘብ በደል አላገኘሁበትም አላቸው

👉የካህናት አለቆችም ቃላቸው በረታ ተሰቀሎ ይሞት ዘንድ ይገባዋል ራሱን #የእግዚአብሔር_ልጅ አድርጓልና

👉ይህን በተናገሩት ጊዜ ጲላጦስ ተቀብሎ በፊታቸው እጁን ታጥቦ ከዚህ #ፃድቅ_ሰው_ደም_ንፁሕ ነኝ እናንተ ተቀብላችሁ እንደ ሕጋችሁ ፍረዱበት አላቸው

👉የአይሁድ ህዝቦች ሁሉ #ደሙ በእኛ ላይ በልጆቻችን ላይ ይሁን እያሉ ጮኹ ከዚያም በኋላ መድኃኒታችንን ተቀብለው #የእሾክ_አክሊል በራሱ ላይ ደፉበት ልብሱን ገፈው ቀይ ግምጃ አለበሱት

👉አራት መቶ ጭፍሮች ልብሱን ለመቶ ለመቶ ከአራት አድርገው ተካፈሉት ጭፍሮች እንዲህ አድርገው መድኃኒታችንን መስቀሉን አሸክመው #ቀራንዮ ወደ ሚባል ቦታ ወሰዱት

👉በዚያም በአምስት ችንካር ቸንክረው ሰቀሉት እነዚህም ✝️ሳዶር ✝️አላዶር ✝️ዳናት ✝️አዴራ ✝️ሮዳስ ተብለዉ ይጠራሉ

👉ሁለት ወንበዴዎችንም አምጥተው አንዱን በቀኙ አንዱን በግራው ከሱ ጋር ሰቀሉት ከዚያም በኋላ ይፋጠኑ ጀመሩ #አሸክትን የሚያመጡ አሉ #ሆምጣጤም የሚያመጡ አሉ #ከርቤንም የሚያመጡ አሉ

👉 #ዘንግንም የሚያመጣ አለ #ጦርንም የሚያመጣ አለ #ራሱንም የሚመቱት አለ #ፊቱን_በጥፊ ይመቱት ዘንድም የሚመጡም አሉ በፊቱ #ምራቅን የሚተፉበት አሉ #ክርስቶስ በጥፊ የመታህ ማነው ራስን የደበደበህ ማነው ለኛ ተናገር እያሉ በፊቱ የሚንበረከኩ አሉ፡

👉መድኃኒታችንም ይህ ሁሉ እየሰማ ዝም አለ ይህን ሁሉ በላዩ ላይ ሲያደርጉበት አንድ ቃል አልመለሰም የወለደችው #ማርያም በመስቀሉ አንፃር ቁማ ትጮሀለች

👉ልጄ የማንን ገንዘብ ቀማህ ልጄ የማንን ሹመት ቀማህ አሸናፊ ልጄ ማን ያዘህ ልጄ ኃጢአትህ በደልህ ምንድ ነው ልጄ ልጄ አንተ የሞትህን መስቀል ተሸከምክ #ሆዴ_ተቃጠለ እንጀቴም እንደ እሳት ነደደ እያለች የለቅሶ ጬኽቷ በሰማይ ተሰማ የለቅሶዋም ጩኸት እስከ ዓለም ዳርቻ ደረሰ

👉ያን ጊዜ #ሰማይ_ተናዋፀ_ምድርንም_ተንቀጠቀጠች #ከዋክብትም_ወደቁ_የፀሐይ_ብርሃን_ጨለመ_ጨረቃ_ደም ሆነ ከስድስት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ዓለም ጨለማ ሆነ

👉አይሁድም የዚህን ምልክት እያዩ ልቦናቸውን ወደ ሃይማኖት ሊመልሱ አልወደዱም ወገኖቻቸውን አስኪያጡ ድረስ በእነሱ ላይ የወረደ አሥሩን መቅሠፍትም እያዩ ሊመለሱ አልቻሉም

👉በዚህች እለት የመድኃኒታችን መታሰቢያ ታላቅ ናትና ይልቁንም በዚህ አመት #መጋቢት_27_እና_እለተ_አርብ ገጥሟል እና ይህን የመዳኛችን ቀን የሆነዉን እለተ አርብ በታላቅ በዓል ልናከብረዉ ይገባል

👉 በዚህ እለት #የመድኃኒታችን_ኢየሱስ _ክርስቶስን በአሉን የሚያከብረውና መታሰቢያውን የሚያደረግ ግን መድኃኒታችንን የተቀበሉትን #የዮሴፍና_የኒቆዲምስን ዋጋ ያገኛል በየአመቱ መከራ በተቀበልኩበት ቀን መታሰቢያን አድርጉ ብሏልና

👉ዳግመኛ መጋቢት 27 መልአኩ #ቅዱስ_ዑራኤል ያደረገው ተአምር ይህ ነው ፀሐይ ከመግባቷ ወይም ከመጥለቋ በፊት ከአይሁድ ወገን የሚሆን አንድ ወታደር መጥቶ የጌታን ቀኝ ጎኑን በጦር ወጋውና ሰለ አዳም ጥምቀትና ሰለ ሁላችን ሕይወት ከቀኝ ጎኑ ደምና ውሀ ፈሰሰ

👉መልአኩ ዑራኤል የአምላካችንና የጌታችን ደም በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ መጋቢት 27 ቀን #በብርሃን_መነሳነስ በመርጨት ዓለሙን ሁሉ ቀደሰ "ድርሳነ ዑራኤል ዘ መጋቢት"

👉 #መድኃኔዓለም ሲነሳ መከራና ስቃዩን ያስቡ የነበሩት ጌታ የወደዳቸው መታሰቢያቸው ወር በገባ በ 27 የሚታሰቡት የፃድቁ አባታችን #የአባ_መባ_ፅዮን በረከታቸው ይድረሰን የመድኃኔ አለም ቸርነትየእናታችን ማርያም አማላጅነት የቅዱስ ዑራኤል ተራዳይነት አይለየን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሀገራችንን ህዝባችንን በምህረት አይኑ ይጎብኝልን "አሜን" ✝️ 💒✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

መዝሙር ላኩልኝ የሚካኤልን ልብሱ ዘመብረቅ የሚለውን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝ እንኳን ለጻድቁ አባታችን "ቅዱስ መርቄ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችኹ ✝

+*" ጻድቁ ቅዱስ መርቄ "*+

=>ቅዱስ መርቄ በኹለት ዓለም የተሳካለት ደግ ሰው ነው:: ነገሩ እንዲህ ነው:-

+ቅዱሱ በዓለም የሚኖር ታዋቂ ነጋዴ ነው:: ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር እንደ አስቸጋሪ ከሚታዩ የሥራ ዘርፎች አንዱ የንግድ ሥራ ቢሆንም እርሱ ግን "ቅዱሱ ነጋዴ" ለመባል በቅቷል::

+ለዚህም ምክንያቱ 2 ነገሮች ናቸው:-
1.በንግድ ሕይወቱ ማንንም ሳያጭበረብር ከመኖሩ ባለፈ ፍጹም ጸሎትን ጾምንና ምጽዋትን ያዘወትር ነበር::
2.ለንግድ በተዘዋወረባቸው ሃገራት ሁሉ ስለ ክርስቶስ ያለማቁዋረጥ የሚሰብክ በመሆኑ በርካቶችን አሳምኖ ሐዋርያዊ ክብርን አግኝቷል::

+ቅዱስ መርቄ በሕይወቱ ይሕንን ከፈጸመ በሁዋላ አንድ አረማዊ ጉዋደኛ ነበረውና : ሐብት ንብረቱን ሰብስቦ "ጌታችን ክርስቶስ ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስላለ ለርሱ ስጥልኝ" ብሎ ላከው::

+አረማዊው ጉዋደኛውን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፍፁም ግርማ አግኝቶ ንብረቱን ከእጁ ተቀብሎታል::

+አረማዊውም በዚህ ምክንያት ከ75 ቤተሰቦቹ ጋር አምኖ ተጠምቁዋል:: ቅዱስ መርቄ በርሃ ውስጥ ባረፈ ጊዜ ቅዱስ ዳዊት ከሰማይ ወርዶ ዘምሮለታል:: መላዕክት በምስጋና ገንዘውት አንበሶች ቀብረውታል::

=>አምላክ ከቅዱሱ በረከትን ያድለን::

=>ሚያዝያ 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ መርቄ ጻድቅ (ክርስቲያናዊ ነጋዴ)
2.ቅዱስ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም
3.አባ ሚካኤል ዘእስክንድርያ
4.እግዚአብሔር:- በእግር የሚራመዱ : በክንፍ የሚበሩና በልብ የሚሳቡ : በየብስ የሚኖሩ ፍጥረታትን ፈጠረ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው (ዘካርያስና ስምዖን)
4.አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
5.አቡነ ዜና ማርቆስ
6.አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል

=>+"+ እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ:: በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም:: መብራትንም አብርተው በዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል:: በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል:: መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ:: +"+ (ማቴ. 5:14-16)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

+ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችሗለን!+

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለሰማዕቱ ቅዱስ ክርስቶፎሮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችኹ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ክርስቶፎሮስ †††

††† ክርስቶፎሮስ ትርጉሙ "ለባሴ ክርስቶስ" እንደ መሆኑ በሐዋርያት ዘመን የነበሩ ብዙ ቅዱሳን በዚህ ስም ይጠሩ ነበር:: ከነዚህ አንዱ ቅዱስ ክርስቶፎሮስ ሃገሩ በላዕተ ሰብእ (ሰውን የሚበሉ) ውስጥ ነበር::

ይህች ሃገር አሁን የት እንዳለች በውል ባይታወቅም የቅዱስ ማትያስ ሃገረ ስብከት በመሆኗ አውሮፓና እስያ ድንበር አካባቢ እንደሆነች ይገመታል::

የአካባቢው ሰዎች ከሰው ሥጋ ውጪ እህልን አይቀምሱም ነበር:: ቅዱስ ማትያስ በነርሱ ያደረውን ርኩስ መንፈስ አስወጥቶ አሳምኗቸዋል::

ከሃገሩ ሰዎችም አንዳንዱ ገጻተ ከለባት (የውሻ መልክ ያላቸው) ነበሩ:: ክርስቶፎሮስም ከነርሱ አንዱ ነበር:: በክርስቶስ አምኖ ከተጠመቀ በሁዋላ በስብከቱ ብዙዎችን አሳምኖ : ስለ ሃይማኖትም ብዙ ጸዋትወ መከራ ተቀብሎ በዚህች ቀን በሰማዕትነት አርፏል::

††† ከሰማዕቱ በረከት አምላኩ ያድለን::

††† ሚያዝያ 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ክርስቶፎሮስ (ሐዋርያና ሰማዕት)
2.አባ ስምዖን ዘሃገረ ሐሊባ
3.ቅዱስ መላልኤል (የያሬድ አባት - ከአዳም 5ኛ ትውልድ)
4.እግዚአብሔር ፀሐይን : ጨረቃን : ከዋክብትን ፈጠረ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
2.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ
3.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
4.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
5.ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ (ታላቁ)
6.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
7.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ

††† "ስለዚሕ ወንድሞቼ ሆይ ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ:: ልባሞች እንደመሆናችሁ እላለሁ:: በምለው ነገር እናንተ ፍረዱ:: የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? . . . እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን:: ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና::" †††
(1ቆሮ. 10:14-18)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††



" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሚያዚያ 1/2016 #ልደታ_ማርያም
#ቅዱስ_ራጉኤል

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና በፀሎት ለምንማፀንበት ለእናታችን #ልደታ_ማርያም እና #ለቅዱስ_ራጉኤል ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉ጴጥርቃ እና ቴክታ የሚባሉ ሰዎች #በኢየሩሳሌም በአንድነት ተጋብተው ይኖሩ ነበር

👉እነዚህም #በእግዚአብሔር የሚያምኑ የተወደዱ ጻድቃን ደግ ሰዎች ነበሩ እነዚህም ሰዎች በእግዚአብሔርም በሰውም ዘንድ ባለፀጎች ነበሩ ነገር ግን ሐብታቸዉን የሚወርሳቸው ልጅ አልነበራቸውም መካን ነበሩ አንድ ቀን ጴጥርቃም ቴክታን እህቴ ሆይ ይህን ሁሉ የሰበሰብነውን ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን ልጅ የለን የሚወርሰን

👉 አንቺም መካን ነሽ እኔም ካንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም አላት እርሱአም ወንድሜ ሆይ #አምላከ_እስራኤል ለኔ ልጅ ቢነሳኝ አንተም እንደኔው ሆነህ ትቀራለህን ከሌላ ደርሰህ ውለድ እንጂ ብላ ብታሰናብተው እንደዚ ያለ ነገር እንኩአንስ ላደርገው በልቦናዬ እንዳላስበው #አምላከ_እስራኤል ያውቅብኛል አላት

👉እርሱዋም #አምላከ_እስራኤል የሚያደርገውን የሚያውቅ የለም ትላንትና ማታ በህልሜ ነጭ ጥጃ ከማህፀኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲሁ እስከ 7ት ትውልድ ሲዋለድ ሰባተኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋም ፀሃይን ስትወልድ አየሁ አለችው

👉እርሱም በጠዋት ከህልም ፈቺ ዘንድ ሂዶ የነገረችውን ሁሉ ነገረው ያም ህልም ፈቺ #እግዚአብሔር በምህረቱ አይቱአቹሀል በሳህሉ መግቡአችሁአል 7 አንስት ጥጆች መውለዳቹ 7 ሴቶች ልጆች እና የልጅ ልጆች ትወልዳላቹ ከቤታቹ ሰባተኛይቱ ጨረቃ መውለዱአ ከሰው የበለጠች #ከመላእክትም የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹ የፀሃይ ነገር ግን አልታወቀኝም አለው

👉እርሱም የነገረውን ሁሉ ሄዶ ነገራት እርሷም እንጃ አምላከ #እስራኤል የሚያደርገውን ማን ያውቃል ብላ ዝም አለች

👉ከዛም ፀንሳ በ9 ወሯ ሴት ልጅ ወለደች ስሙአንም ሄሜን ብለው አወጡላት ሔሜንም አድጋ ለአካለ መጠን ስደርስ አጋብተዋት #ሴት_ልጅ_ወለደች በስምንተኛ ቀኑአም ደርዲ ብለው ስም አወጡላት

👉ደርዲም አድጋ እንዲሁ ሴት ወለደች እና ቶና አለቻት ቶናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሲካር አለቻት ሲካርም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሴትና አለቻት ሴትናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሄርሜላ አለቻት ሄርሜላም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ንጽህት ቅድስት ክብርት የምትሆን #እመቤታችንን የምትወልደውን #ሃናን ወለደች

👉ከጴጥርቃና ከቴክታ የተወለዱ 67 ወንዶች ልጆች አሉ #የእመቤታችን_የድንግል_ማርያምን ትውልድ ለመቁጠር ትንቢት አልተነገረላቸውም ሱባኤ አልተቆጠረላቸውምና አልተፃፈም ይህቺም ሃና በስርአት በቅጣት አደገች ለአእምሮ ስትበቃ አካለ መጠን ስደርስ ከቤተ መንግስት ወገን ከነቅዱስ ዳዊት ወገን ከሆነው(መጽሃፍ ቅዱስ ይገልጸዋል) ከቅዱስ እያቄም ጋር አጋቡአት

👉 እነዚህ ቅዱሳን #እያቄም እና #ሃና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ ከእለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሄር ሂደው ሲፀልዩ ሲያዝኑ ዋሉ

👉ሃዘናቸው እንዴትስ ነው ቢሉ እያቄም አቤቱ ጌታዬ ያአባቶቼ #የእስራኤል_አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለው አትጣለኝ አትናቀኝ ፀሎተን ስማኝ ፈቃዴን ፈጽምልኝ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ ወንድ ልጅ ስጠኝ ብሎ ሲለምን ዋለ

👉 #ሃናም በበኩሉአ አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለው ስማኝ ለአይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የምትሆነኝ የተባረከች ሴት ልጅ የማህፀኔን ፍሬ ስጠኝ ብላ ስትለምን ዋለች

👉ፀሎትና ልመናን የማይንቅ ጌታ የሁለታቸዉንም ፀሎት ሰምቶ ድንቅ ራእይ አሣይቶ #በእግዚአብሔር ፍቃድ እናታችን ወላዲተ ቃል እመቤታችን #ልደታ_ማርያም ተፀነሰች እመቤታችንም በተፀነሰች በዘጠኝ ወር የግንቦት መባቻ እለት ተወለደች

👉እናታችን #ልደታ_ማርያም ዛሬ የምንጀምረው ወርሐ ሚያዚያ የበረከት እንዲሆንልን የምናየዉ የምንሰማዉ ክፉ ነገር ሁሉ ወደ በጎ የሚቀየርበት እንዲሆንልን እናታችን #ልደታ_ማርያም በምልጃ ፀሎቷ ታስበን #የመልአኩ_ቅዱስ_ራጉኤል ጥበቃ አይለየን ተራዳኢነቱ ከኛ ጋር ይሁን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🔔🔔🔔🔔
የመፃጕዕ ቅኔ
🛄🛄🛄🛄
➡️ንባብ
➡️ፍቺ
➡️ርቃቄ፦ ሠም፣ወርቅ
➡️ሙያ
➡️ማብራሪያ
➡️ጥያቄና መልስ
❤️❤️❤️❤️❤️❤️
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
/channel/+cD8I6LHkvu5kMmY0

♦️ከጳውሎስ ቅኔ ቤት♦️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/IrAmVjgBNxE?si=fJ4h2BjnNFCKFOjp

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እንኳን አደረሳቹ ነገ ሆሳእና ነው✝️✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ግእዝ መማር የሚያስገኘው ጥቅም
/channel/+cD8I6LHkvu5kMmY0

ጳውሎስ ንባብ ቤት
✅የዘወትር ጸሎት
✅ውዳሴ ማርያም
✅አንቀጸ ብርሃን
✅መልክአ ማርያም 
✅መልክአ ኢየሱስ 
✅መዝሙረ ዳዊት 
@የወንጌል ንባብ
@የግብረ ሐዋርያት ንባብ

በግእዝ ንባብ ይማሩ
ልጆችዎን ያስተምሩ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://www.youtube.com/live/CKrII8oxPp4?si=_o1bViqBHF9yaKx9

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/5bNH_3I3Ojk?si=L3RU4a83RV9NJUml

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

“ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ምክር ስማ፥ የእናንትህንም ሕግ አትተው፤”
  — ምሳሌ 1፥8

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችኹ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† መድኃኔ ዓለም †††

††† ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ በዚሕ ዕለት ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ 3:00 ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት::
ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና: ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት: አስረው ሲደበድቡት አድረዋል::

*ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት:: ምራቃቸውን ተፉበት:: ዘበቱበት:: ራሱንም በዘንግ መቱት:: እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ::

*በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት:: በሠለስት (ሦስት ሰዓት ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ 6,666 ገረፉት:: ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት::

*ስድስት ሰዓት ላይ በረዣዥም ብረቶች አምስት ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት:: ሰባት ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ::
ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ ሰባት ቃላትን ተናገረ::

*ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በባሕርይ ሥልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ:: በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ:: አሥራ አንድ ሰዓት ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት::

*በዚያች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ:: ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ:: ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ:: (ማቴ. 27:1, ማር. 15:1, ሉቃ. 23:1, ዮሐ. 19:1)

††† ለእኛ ለኀጥአን ፍጡሮቹ ሲል ይህንን ሁሉ መከራ የታገሰ አምላክ ስለ አሥራ ሦስቱ ኅማማቱ: አምስቱ ቅንዋቱ: ስለ ቅዱስ መስቀሉ: ስለ ድንግል እናቱ ለቅሶና ስለ ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስ ብሎ ይማረን::

††† ከቅዱሳኑ በዚሕች ዕለት:-

††† ከ80 ዓመታት በላይ በገዳም የኖረ: የገዳማውያን ሞገሳቸው: የመነኮሳትም ሁሉ አለቃ ታላቁ ቅዱስ መቃርስ አርፏል::

††† ዳግመኛ በዚህ ቀን ንግሥናን ከሊቅነት: ጽድቅን ከሰማዕትነት ጋር የደረበው ሰማዕቱ ቅዱስ ገላውዴዎስ አንገቱን ተከልሏል:: ቅዱስ ገላውዴዎስ የጻድቁ ዐፄ ልብነ ድንግል ልጅ ነው::

††† መድኃኔ ዓለም ከወዳጆቹ ጸጋ ክብርን ያድለን::

††† መጋቢት 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ (ፍቁረ እግዚእ)
2.ቅዱሳት አንስት (ከእግረ መስቀሉ ያልተለዩ)
3.ቅዱሳን ባልንጀሮች (በጌታ ስቅለት ጊዜ ከሞት የተነሱ)
4.ቅዱሳን ዮሴፍና ኒቆዲሞስ
5.ታላቁ ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት አለቃ)
6.ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት (የኢትዮዽያ ንጉሥ)
7.ቅዱስ ዕፀ መስቀል

††† ወርኀዊ በዓላት
1.አቡነ መብዐ ፅዮን ጻድቅ
2.ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
3.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
4.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት

††† "የተጠራችሁለት ለዚህ ነው:: ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሏልና:: እርሱም ኃጢአት አላደረገም:: ተንኮልም በአፉ አልተገኘበትም:: ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም:: መከራንም ሲቀበል አልዛተም . . . እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ::" †††
(፩ጴጥ. ፪፥፳፩-፳፭)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

5ኛ. ተጸፍዖ መልታሕት፡- ሊቀ ካህናቱ ሐና ወደ ቀያፋ በላከው ጊዜ ቀያፋም ‹‹‹አምላክ ነኝ ከሰማይ ወርጃለሁ› የምትል አንተ ነህን?...›› ብሎ ጠየቀው፡፡ ጌታችንም ‹‹አምላነቴን እኔ ብቻ የምናገረው አይደለም አንተም ደግሞ ራስህ ተናገርኽ እንጂ›› አለው፡፡ ማቴ 27፡11፡፡ ቀያፋም ሎሌዎቹን ‹‹ተቀምጣችሁ አታሰድቡኝ›› ብሎ በመቆጣት ልብሱን ቀደደ፡፡ እነርሱም ይህን ጊዜ ጌታችንን ፊቱን በጥፊ መቱት፡፡ ዮሐ 18፡22፡፡ እጃቸውን ቢደክማቸው ድንጋይ ጨብጠው አጥንቱ እስኪደቅ ድረስ በድንጋይ ጥፊ 120 ጊዜ ፊቱን ጸፉት፡፡
6ኛ. ተኰርዖ ርእስ፡- አይሁድ ጌታችንን ‹‹ኃላፊያቱን መጻኢያቱን አውቃለሁ ትላለህ…›› እያሉ በመዘበት ፊቱን እየመቱ ራሱን እየገመሱ ‹‹የመታህ ማነው?›› ይሉት ነበር፡፡ ማቴ 26፡67፣ ሉቃ 22፡63፡፡ ዳግመኛም አክሊለ ሦኩን ለማድረግ እንዲያመቻቸው የራስ ፀጉሩን 25 ጊዜ ነጩት፡፡
7ኛ. አክሊለ ሦክ፡- እነሆ ክፉዎች አይሁድ ሰይጣን በልባቸው ነግሦ ክፋትን ብቻ እንዲያስቡ አድርጓቸዋልና ስቁረት ያለበት እንደ ወረንጦና እንደ ወስፌ እንደ መርፌም ያለ 300 እሾህ ያለው ስረወጽ አድርገው የብረት አክሊል ሠርተው ከፍላት አግብተው በጉጠት አንሥተው ‹‹ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሥ ነህ ዘውድ ይገባሃል› ብለው ያ ሁሉ እስኪገባ ድረስ በራሱ ላይ መቱበት፡፡ ለአክሊለ ሦኩም 73 ስቁረት ነበረው፡፡ ዳግመኛም እራሳቸው እንደ መሮ፣ ወርዳቸው እንደ ሞረድ 4 ማዕዘን አሠርተው ቁመታቸውን ክንድ ከስንዝር፣ ስለታቸውን እንደ ወስፌ እንደ መርፌ አድርገው 73 ችንካር ሠርተው በዚያ በአክሊሉ 73 ስቁረት አግብተው ያ ሁሉ እስኪገባ ድረስ በራሱ ላይ ቢመቱበት ሥጋ ለሥጋ ገብቶ በአንገቱ ወርዶ መሐል ልቡን ወጋው፡፡ አክሊሉንም እንዳሸከሙት ጲላጦስ እንዲመረምረው ከቤት ወደ አደባባይ 3 ጊዜ አመላለሱት፡፡ በ4ኛው ከአደባባይ አኑረው ‹‹ንጉሥ ሆይ!...›› እያሉ ርኩስ ምራቃቸውን እየተፉበት ተዘባበቱበት፡፡ እየሰገዱ ሲነሡ በፊቱ ተፍተውበት ይነሣሉ፡፡ ጀርባውንም በዘንግ ይመቱት ነበር፡፡
8ኛ. ተዐርቆተ ልብስ፡- አይሁድ ‹‹ስቃዩን አበዛነው አሁን ደግሞ አፍሮ ደንግጦ ይሞታል›› ብለው በሰው ሁሉ መካከል ራቁቱን አቁመውታል፡፡  
9ኛ. ተቀሥፎ ዘባን፡- አይሁድ ጲላጦስን ‹‹…ኃይለኛ በደለኛ ሰው ይዘናል ጉባኤ ሥራልን›› አሉት፡፡ ጲላጦስም በጠዋት ጉባኤ ሠራላቸው፡፡ ክፉዎች አይሁድም ጌታችንን ‹‹በቃሉ ሐሰት በሰውነቱ ክፋት የለበትምና ጲላጦስ ይህን ተመራምሮ በነፃ ቢለቀውና ባይፈርድነበት ሀዘናችን ይበዛል በኋላ እንዳይቆጨን›› ብለው አስቀድመው 305 ጊዜ በሽመል ደበደቡት፡፡ በባሕርይ አምላክነቱ ቻለው እንጂ አንዱ ብቻ በገደለው ነበር፡፡
እያዳፉም ወስደው ጲላጦስ ፊት ካቆሙት በኋላ ‹‹ኃይለኛ በደለኛ ነውና ስቀለው›› አሉት፡፡ ጲላጦስም ‹‹በምን በደሉ ልስቀለው? በደሉን ንገሩኝ?›. አላቸው፡፡ አይሁድም ‹‹ሰንበትን ሻረ፣ የሰሎሞንን ቤተ መቅደስ አፈርሱት በ3ኛ ቀን እሠራዋለሁ አለ፣ ራሱን አምላክ አደረገ›› የሚሉ ሦስት ክሶችን አቀረቡ፡፡ ዮሐ 9፡16፣ 13፡29፣ 18፡30፣ ኩፋ 34፡13፣ ሉቃ 23፡1-10፣ ማር 15፡3፣ 19፡10፡፡ የአይሁድን ክፋት ማሸነፍ የማይሆንለት ሆኖ ነው እንጂ ጲላጦስ ጌታችንን ለማዳን ብዙ ለፍቶ ነበር፡፡ በሕጋቸው መሠረት የሚሰቀል አይገረፍም፣ የሚገረፍም አይሰቀልም ነበርና ጲላጦስ ‹‹ገርፋችሁ ልቀቁት›› አላቸው፡፡ አይሁድንም ዳግመኛ ‹‹ሕጋችሁ ስንት ይገረፍ ትላለች?›› ቢላቸው እነርሱም ‹‹…41 ይገረፍ ይላል ነገር ግን ለእርሱ አይበቃውም›› አሉት፡፡ ጲላጦስም ‹‹ለእርሱ ስትሉ ሕጋችሁን ትተላለፋላችሁን? በሉ እንደሕጋችሁ ብቻ ገርፋችሁ ልቀቁት፣ ከቁጥር አብልጣችሁ ብትገርፉት ግን ከደሙ ንጹሕ ነኝ›› ብሎ በፊታቸው ታጠበ፡፡ አይሁድም ‹‹ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን›› በማለት በራሳቸው ላይ ርግማን ስላወጁ ዛሬም ድረስ ወንድ ቢወልዱ ልጁ ደም ጨብጦ ይወለዳል፣ ሴት ቢወልዱ ልጅቱ ያለድንግልና ትወለዳለች፡፡
ርጉማን አይሁድ ጌታችንን ከጲላጦስ ተረክበው ከወሰዱት በኋላ አዝማሪ አስመጥተው ጌታችንን እያሰደቡት 80 ጊዜ ፂሙን ነጭተውታል፡፡ መከራውን ሲያጸኑበት አድረዋልና ደሙ እንደ ውሃ ጎርፍ ፈሷል፣ ሥጋው እየተላጠ መሬት ላይ ወድቋል፡፡ ክፉዎች አይሁድ ‹‹አሠቃቂ ግርፋትን ሲገረፍ ያየነው እንደሆነ ልባችን ሊራራ ይችላል›› ብለው ሰንጠረዥ ገበጣ ሠርተው ሲጫወቱ አንዱ ተነሥቶ 50 እና 60 ድረስ ይገርፍና ሲደክመው ‹‹ቆጠራችሁን?›› ብሎ ይጠይቃል፡፡ ሌሎቹም ‹‹አልቆጠርንም›› ሲሉት ከድካሙ የተነሣ ‹‹እኔው ልግረፍ እንደገና እኔው ልቁጠር›› ብሎ ትቶት ሲቀመጥ ሌላኛው ይነሣና እንደመጀመሪያው ገራፊ ሁሉ በተራው እንደገና አንድ ብሎ ጀምሮ 50 እና 60 ይገርፈዋል፡፡ ሁሉም እንዲህ እያሳሳቱ የራሳቸውን ሕግ እየተላለፉ አይሁድ ጌታችንን ሥጋው አልቆ አጥንቱ እንደበረዶ ነጭ ሆኖ እስኪታይ ድረስ 6666 ጊዜ ጽኑ ግርፋትን ገረፉት፡፡ በእነዚህ ሁሉ ግርፋቱ ወቅት 366 ጊዜ ሥጋው ተቆርሶ መሬት ላይ ወድቋል፡፡ ሥጋው እየተቆረሰ ከምድር የወደቀው 76 ነው፡፡ ያበጠውና የበለዘው ግን የሚቆጠር አይደለም፡፡ ስፍር ቁጥርም የለውም፡፡

10ኛ. ፀዊረ መስቀል፡- ጌታችንን አይሁድ የዕንጨት መስቀል አሸክመው ከሊቶስጥራ እስከ ቀራኒዮ ድረስ እያዳፉ ሲወስዱት 136 ጊዜ በምድር ላይ ጥለውታል፡፡ ከኋላ ያሉት ‹‹ፍጠን›› እያሉ ገፍትረው ይጥሉታል፣ ከፊት ያሉት ደግሞ ‹‹ምን ያስቸኩልሃል?›› እያሉ መልሰው ገፍትረው ይጥሉታል፡፡ እንዲህ እያደረጉ መስቀል አሸክመው እያዳፉ ቀራንዮ አድርሰውታል፡፡
11ኛ. ተቀንዎ በቅንዋት፡- ቀራንዮ ካደረሱት በኋላ አይሁድ ቁመታቸው ክንድ ከስንዝር፣ ስለታቸው እንደ ወስፌ እንደ መርፌ ያሉ፣ ወርዳቸው እንደሞረድ የሆኑ፣ 4 ማዕዘን የሆኑ ራሳቸው እንደ መሮ ያሉ 5 ታላላቅ ችንካሮችን ሠርተው ሳዶር በሚባለው ችንካር ቀኝ እጁን፣ በአላዶር ግራ እጁን፣ በዳናት ሁለት እግሮቹን፣ በአዴራ መሐል ልቡንና በሮዳስ ደረቱን ቸንክረው የአዳም ራስ ቅል ባለበት ቀራኒዮ አደባባይ ላይ ሰቅለውታል፡፡
12ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ፡- መስቀሉን በሥሩ ተክለው ጊዜ ቀትር ሲሆን ጌታችንን ቢሰቅሉት ሥጋው በግርፋት አልቆ ነበርና የጎኑ አጥንት ተተረተረ፡፡ አይሁድም ‹‹የጎኑ አጥንት ስንት ነው? እስኪ ቁጠሩት…›› እያሉ ተዘባበቱበት፡፡ ይኽም በነቢዩ ቅዱስ ዳዊት ‹‹አጥንቶቼ ሁሉ ተቆጠሩ›› (መዝ 21፡17) ተብሎ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡ ጌታችን ከምድር ከፍ ከሰማይ ዝቅ ብሎ በ7 ክንድ ከስንዝር መስቀል ላይ በጊዜ ቀትር ተሰቅሎ 7ቱን መስተፃርራን አስታረቃቸው፡፡ እነዚህም 7 መስተፃርራን እግዚአብሔርና ሰው፣ ሰውና መላእክት፣ ነፍሥና ሥጋ፣ ሰማይና ምድር፣ ሕዝብና አሕዛብ ናቸው፡፡ በቀራንዮ አደባባይ ላይ በገበያ ቀን በተሰቀለም ጊዜ አይሁድ ሲያልፉ ሲያገድሙ ‹‹…ከወንበዴዎች ጋር የተሰቀለው ያ ‹አምላክ ነኝ ከሰማይ ወርጃለሁ› ብሎ ይናገር የነበረው አይደለምን? ታዲያ ምነው ተሰቀለ!?…›› ብለው ስቀው አንገታቸውን ነቅንቀው ያልፋሉ፡፡ ቅዱስ ዳዊት ‹‹እኔም በእነርሱ ዘንድ ለነውር ሆንኩ፣ ባዩኝ ጊዜ ራሳቸውን ነቀነቁ›› ብሎ ትንቢት እንደተናገረ፡፡ መዝ 108፡25፡፡ ነገር ግን ‹‹የጌታችን ርቃን አናሳይም›› ብለው ፀሐይ ጨለመች፣ ጨረቃም ደም ሆነች፣ ከዋክብትም ረገፉ፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እንኳን ለጥንተ ስቅለቱ ለመድሃዓለም በሰላም አደረሰን 🙏❤️✝️
https://vm.tiktok.com/ZMMmcF967/
https://vm.tiktok.com/ZMMmcF967/

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

♥️ #የሚታገል_ሰው_ቢወድቅ_አዲስ ነገር አይደለም፤ ወድቆ መቅረቱ ነው እንጂ

♥️ #አንድ ቦክስ የሚጋጠም ሰውም ቢቆስል የሚያሳዝን ነገር አይደለም፤ የሚያሳዝነው ቁስሉን ችላ ያለው እንደ ኾነ ነው እንጂ፤ አንተም በመንፈሳዊ ሕይወትህ ብትወድቅ አይደንቅም፤ ለቅጽበትም የማይተኛልህ ጠላት አለህና፤ ነገር ግን ወድቀህ አትቅር፡፡

♥️ #አንድ ወታደር ጦር ሜዳ ሔዶ ቢቆስል ማንም ጤነኛ አእምሮ ያለው ሰው አይወቅሰውም፤ አንተም ጠላትህ ዲያብሎስ ቢያቆስልህ ማንም አይወቅስህም፤ መንፈሳዊ ተጋድሎ ውስጥ ነውና ያለኸው፤ የምትወቀሰው ለቁስልህ መድኃኒት ማድረግህን ችላ ያልህ እንደ ኾነ ብቻ ነው፡፡

♥️ #ይህ ከላይ የነገርኩህ ወታደር ከታከመ፥ ተመልሶ ወደ ጦር ሜዳ ይሔዳል፤ ጠላቱን ድል ሲያደርግም ሹመት ሽልማት ይሰጡታል፤ አንተም ከወደቅህበት ተነሥና ንስሐ የተባለ ሕክምናን ውሰድ፡፡

♥️ #ከዚያም ጠላትህ ዲያብሎስን ድል አድርገህ ከክርስቶስ ዘንድ ሹመት ሽልማትን ተቀበል፤ ስለዚህ በርታ በርታና ተነሥ ዘግይቻለሁ ብለህ በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ፤ አሁንም መጀመር ትችላለህና፡፡

📌ምንጭ
✍️♥️ #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ♥️

Читать полностью…
Subscribe to a channel