kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለአባ ይስሐቅ ጻድቅ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችኹ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† አባ ይስሐቅ ጻድቅ †††

††† ጻድቁ ግብጻዊ ሲሆኑ የነበሩት በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: በጊዜው ዝነኛ ከነበሩት ከታላቁ አባ ዕብሎ (ቅዱስ ዕብሎይ) ተምረዋል:: መማር ብቻ ሳይሆንም ለ25 ዓመታት ያለ መታከት በተልዕኮ አገልግለዋል::

በእነዚህ ጊዜያትም ትሕርምትን : ተጋድሎን : ትምህርተ ቅድስናንና ሌሎች አስፈላጊ መንፈሳዊ ስንቆችን ሰንቀዋል:: በመታዘዛቸው በምድር አበውን : በሰማይ እግዚአብሔርን አስደስተዋል:: በዚህም ከእግዚአብሔር ጸጋውን : ከአበው ምርቃትን አትርፈዋል::

ጊዜው ደርሶም ታላቁ ዕብሎ ሲያርፉ አባ ይስሐቅ በዓት ለይተው ደንበኛውን ተጋድሎ ጀምረዋል:: አምላካቸውን ለማስደሰትና በቅድስና ለመዝለቅም የአርምሞ ሰው ሁነዋል:: ለሚገባው ነገር ካልሆነ በቀር አያወሩም:: ምላሽም አይሰጡም:: "ለምን?" ሲባሉ
1."ለሁሉም ጊዜና ቦታ አለው::"
2."ሰው በከንቱ በማውራቱ ከጸጋ እግዚአብሔር ይርቃል" ይሉ ነበር::

አባ ይስሐቅ የክርስቶስ መድኃኒታችንን ሕማማት ለማዘከር ሁሌ ያነቡ (ያለቅሱ) ነበር:: ቅዳሴ ሲያስቀድሱ እጃቸው የሁዋሊት ታስሮ ነበር:: ቅዱሱ ሰው ለአዝማናት እንዲህ ተመላልሰው በመልካም ዕርግና ያረፉት በዚህ ቀን ነው::

††† አምላከ ቅዱሳን ከበረከታቸው አይለየን::

††† ሚያዝያ 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አባ ይስሐቅ ገዳማዊ (የታላቁ ዕብሎይ ደቀ መዝሙር)
2.አባ ገብርኤል ሊቀ ዻዻሳት

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
3.ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ጻድቅ ንጉሥ
4.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
5.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)
6.ቅድስት ዕሌኒ ንግስት
7.ቅዱስ ዕፀ መስቀል

††† "የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ: የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ በእግዚአብሔር አብ ተወደው: ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ:
ምሕረትና ሰላም: ፍቅርም ይብዛላችሁ::
ወዳጆች ሆይ! ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኩዋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ::" †††
(ይሁዳ. 1:1)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

/channel/zikirekdus

እንኳን አደረሰን!!

🔎ZikereKedusan" rel="nofollow">https://www.youtube.com/@ZikereKedusan

🔎 /channel/zikirekdusn

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለብጹዐን ጻድቃን: ቅዱስ ዞሲማስ እና አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችኹ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ብጹዐን ጻድቃን †††

††† በዚህ ቀን ብሔረ ብጹዐን ውስጥ የሚኖሩ ጻድቃን ይታሠባሉ::
በሃይማኖት ትምሕርት 5 ዓለማተ መሬት አሉ:: እነሱም አቀማመጣቸው ቢለያይም ከላይ ወደ ታች:-
1.ገነት (በምሥራቅ)
2.ብሔረ ሕያዋን (በሰሜን)
3.ብሔረ ብጹዐን (ብሔረ - አዛፍ - እረፍት) {በደቡብ}
4.የእኛዋ ምድር (ከመሐል) እና
5.ሲዖል (በምዕራብ) ናቸው::

††† ከእነዚሕ ዓለማት ባንዱ የሚኖሩ የብሔረ ብጹዐን ጻድቃን:-
*ኃጢአትን የማይሠሩ::
*ለ1,000 ዓመታት የሚኖሩ::
*ሐዘን የሌለባቸው::
*በዘመናቸው 3 ልጆችን ወልደው (2 ወንድና አንድ ሴት) ሁለቱ ለጋብቻ: አንዱን ለቤተ እግዚአብሔር አገልግሎት የሚያውሉ ሰዎች ናቸው::

††† ቅዱሳኑ ወደዚሕ ቦታ የገቡት በነቢዩ ኤርምያስ እና በቅዱስ እዝራ ዘመን ሲሆን አንዴ የተወሰኑት በዘመነ ሰማዕታት ወጥተው በዚሕ ቀን ተሰይፈዋል::

††† በመጨረሻ ግን በሐሳዌ መሲሕ ዘመን ወጥተው ሰማዕትነትን ይቀበላሉ::

††† የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሕረቱና ይቅርታው ለምናምን ሁሉ ይደረግልን:: ከደግነታቸውም በረከትን አይንሳን::

+*" አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ "*+
=>አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ አባታቸው መልአከ ምክሩ :
እናታቸው ወለተ ማርያም ይባላሉ፡፡ የተወለዱበት ልዩ
ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ነው፡፡ በተወለዱ ዕለት
ተነስተው በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ "ስብሐት ለአብ
: ስብሐት ለወልድ : ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ" ብለው
አመስግነዋል፡፡
+የስማቸው ትርጓሜ "የአብ : የወልድ : የመንፈስ ቅዱስ
እስትንፋስ" : አንድም "የክርስቶስ እስትንፋስ" ማለት ነው፡፡
ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸውና በመንገዳቸው ሁሉ
እየመራቸው ነው ያደጉት፡፡ መንፈስ ቅዱስ ልቡናቸውን
ብሩህ አድርጎላቸው በ5 ዓመታቸው የቅዱሳት መጽሐፍት
ቃላትን፣ ብሉያትንና ሐዲሳትን፣ ድርሳናትንም ጠንቅቀው
ዐውቀዋል፡፡
+በተወለዱ በ14 ዓመታቸው ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ
ደብረ ሐይቅ ገዳም ሄደው ከባሕር ዳር ቆመው የሙሴን
ጸሎት ወደ እግዚአብሔር በጸለዩ ጊዜ የታዘዘ መልአክ
መጥቶ ባህሩን አሻግሯቸው ወደ ቤተክርስቲያን
ገብተዋል፡፡ ለ3 ዓመትም በኃይቅ ገዳም ለመነኮሳት
እንጨት በመልቀምና ውሃን በመቅዳት : ለአባቶች
መነኮሳት ምግብ ሊሆናቸው ከባህር ውስጥ አሳን
በማውጣት አገልግለዋል፡፡
+አባታችን እስትንፋሰ ክርስቶስ 40 መዓልትና 40 ሌሊት
ከጾሙ በኋላ ምንም እህል ሳይቀምሱ ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ አስቀድሞ ለሙሴ በደብረ ሲና እንደሰጠው
ለአባታችንም ወደ እርሳቸው መጥቶ ዓሥሩን ቃላተ ኦሪትና
ስድስቱን ቃላተ ወንጌል በውስጣቸው የተጻፈባቸው ሁለት
ጽላቶችን ሰጥቷቸዋል፡፡
+አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሠሩ በኋላ
ዕለቱን ስንዴ ዘርተው፣ ወይን ተክለው፣ ጽድን ወይራንና
ግራርን ተክለው በአንዲት ቀን ለቤተ ክርስቲያን
አገልግሎት ዕለቱን አድርሰዋል፡፡ ስንዴውን ለመስዋዕት
ወይኑን ለቁርባን በታምራት አድርሰዋል፡፡
+አባታችን በጸሎት ላይ እንዳሉ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል
ተልኮ መጥቶ አባታችንን በደመና ጭኖ ወስዶ ከጌታችን
ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ፊት አቆማቸው፡፡
ጌታንም በቅዱሳኖቹ ሁሉ እንዲባረኩ ካደረጋቸው በኋላ
መልአኩን ‹‹ወደ ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ ወደ
ኢየሩሳሌም አድርሰው›› ብሎት ኢየሩሳሌምን አሳልሞ
ሀገራችን መልሶ አምጥቷቸዋል፡፡ ሁሉንም የኢትዮጵያን
ቅዱሳት ገዳማትንም ተዘዋውሮ ሲጎበኙ በሕይወተ ሥጋ
የሌሉት የየገዳማቱ ቅዱሳን ሁሉ በአካል ይገለጡላቸው
ነበር፡፡
+ጎጃም ውስጥ እያስተማሩ፣ እያጠመቁ፣ የታመሙትን
እየፈወሱ፣ የዕውራንን ዐይን እያበሩና ሙታንን እያስነሱ
ብዙ ካገለገሉ በኋላ ለዘጠኝ ዓመታት በባሕር ውስጥ
ገብተው ቁልቁል ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ጸልየው
የምሕረት ቃልኪዳን ተቀብለዋል፡፡ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ
ጌታችን መጥቶ ‹‹ከመነኮሳት ሁሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ
እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን
ምሬልሃለሁ ከዚህች ባሕር ውጣ›› በማለት በሞት
የሚያርፉበትን ቦታ ነግሯቸዋል፡፡
+ጻድቁ ወደ ደብረ አስጋጅ በሚሄዱበት ጊዜ ጸሐይ
ልትገባ ስትል ‹‹በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም
አውግዤሻለሁ፡፡ ለመስፍን ኢያሱ በገባኦን እንደቆምሽ
አሁን ቀጥ ብለሽ ቁሚ›› ብለው ገዝተው ፀሐይን
አቁመዋል፡፡
+አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስም ደብረ አስጋጅ ሲደርሱ
ፀሐይ አፍ አውጥታ ‹‹አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ እገባ
ዘንድ ፍታኝ›› ስትላቸው ‹‹እግዚአብሔር ይፍታሽ›› ባሏት
ጊዜ ጠልቃለች፡፡ ጻድቁ ሌላው በእጅጉ የሚታወቁበት
አንድ ትልቅ ቃል ኪዳን አላቸው፡፡
+በአምላክ ፣ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ፣
በቅዱስ ሚካኤልና በቅዱስ ገብርኤል ልቡና የሚገኝ እንደ
መልክአ ኢየሱስ ያለች እጅግ አስገራሚ ጸሎት አለቻቸው፤
እርሷን ጸሎት በጸለዩ ጊዜ እልፍ ነፍሳትን ከሲኦል
ያወጣሉ፡፡ ጸሎቷም የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች
በሙሉ እየጠቀሰች እያንዳንዱ የሰውነት ክፍሎቹ
የተቀበሉትን ጸዋትዎ መከራዎች ሁሉ ታዘክራለች፡፡
በእያንዳንዱ ክፍልም የጸሎት ማሳረጊያ አቡነ ዘበሰማያት
ይደግማሉ፡፡
+ንስሓ የገባ ኃጢአተኛ ሰው እንኳን ቢሆን ይህችን የአቡነ
እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት በጸለየ ጊዜ ሺህ ነፍሳትን
ከሲኦል እንደሚያወጣ ጌታችን በማይታበል ቃሉ
ለአባታችን ነግሯቸዋል፡፡ እያንዳንዱን የመድኃኔ ዓለምን
የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች መከራዎቹን
የምታዘክረውን ይህቺን በአምላክ ልቡና ያለች ግሩም
የሆነች ጸሎት "ነፍሳትን ከሲኦል አታወጣም" ብሎ
የሚጠራጠር ቢኖር ግን መንግስተ ሰማያትን አያያትም፡፡
+ጻድቁ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ታህሳስ 9 ቀን ተወልው
ሚያዝያ 9 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል፡፡ (ገድለ አቡነ
እስትንፋሰ ክርስቶስ)
=>አምላከ ቅዱሳን በጻድቁ አማላጅነት ሃገራችንን
ይጠብቅልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

††† ሚያዝያ 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱሳን የብሔረ ብጹዐን ጻድቃን
2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ)
3.ቅዱስ ዞሲማስ ገዳማዊ (ብሔረ ብጹዐንን ያየ እና ዜናቸውን የጻፈ አባት)
4.ቅዱስ ኤስድሮስ ሕጻን ሰማዕት (ገና በ10 ወር ዕድሜው ሰማዕት የሆነ)
5.አባ ሱንቱዩ ሊቀ ዻዻሳት

††† ወርሐዊ በዓላት
1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት)
2."318ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ)
3.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮዽያዊ)

††† "ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኑራችሁ: ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ:: እንደሚታዘዙ ልጆች ባለ ማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ:: ዳሩ ግን 'እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ' ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሯችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ::" †††
(1ዼጥ. 1:13-15)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

🔎ZikereKedusan" rel="nofollow">https://www.youtube.com/@ZikereKedusan

🔎 /channel/zikirekdusn

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝✝✝ እንኩዋን ለቅዱሳት ደናግል ዓመታዊ የሰማዕትነት በዓል በሰላም አደረሳችኹ ✝✝✝

+*" ቅዱሳት ደናግል "*+

=>ቅዱሳት ደናግሉ አጋሊዝ (አጋሊስ): ኢራኒና ሱስንያ ይባላሉ:: በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ተሰሎንቄ የምትባል ሃገር ውስጥ ይኖሩ ነበር:: ሦስቱም እጅግ ቆንጆዎችና ከብዙ ወንዶች ዐይን የሚገባ መልክ ቢኖራቸውም የእነርሱ ምርጫ ግን ሰማያዊ ሙሽርነት ነበርና በጾምና በጸሎት ተወሰኑ::

+ለብዙ ዓመታትም ደናግሉ በሚኖሩበት ደብር ውስጥ በቅድስና ኑረዋል:: ከቆይታ በሁዋላ ያ የመከራ ዘመን (ዘመነ ሰማዕታት) ሲመጣ ለጊዜውም ቢሆን ወደ በርሃ ሸሽተው ተቀመጡ::

+ያሉበትን ቦታ የምታውቅ አንዲት ደግ ባልቴት እየሔደች ትጎበኛቸው : በእጃቸው የሚሠሩዋቸውን የተለያዩ እቃወችንም እየሸጠች እኩሉን በስማቸው መጽውታ በተረፈው ለራት የሚሆን ደረቅ ቂጣ ትገዛላቸው ነበር::

+አንድ ቀን ግን አንድ አረማዊ ሰው ተከትሏት መጥቶ በማየቱ 3ቱንም ደናግል ወደ ከሐዲው ንጉሥ አቀረባቸው:: ንጉሡ ሃይማኖታቸውን ቢክዱ የሐብትና የስልጣን ተስፋ እንዳላቸው ነገራቸው:: ደናግሉ ግን በፍቅረ ክርስቶስ በመጽናታቸው ከብዙ ስቃይ በሁዋላ በዚሕች ቀን አስገድሏቸዋል::

=>የጌታችን በጐ ምሕረቱ በሁላችን ትደርብን:: ከደናግሉ በረከትን ያሳትፈን::

=>ሚያዝያ 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሳት ደናግል አጋሊዝ: ኢራኒና ሱስንያ
2."150" ቅዱሳን ሰማዕታት (ፋርስ (ኢራን) ውስጥ የተሰየፉ)
3.አባ ጢሞቴዎስ ሊቀ ዻዻሳት

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ)
3.አባ ብሶይ (ቢሾይ)
4.አቡነ ኪሮስ
5.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
6.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)

=>+"+ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ ራቁትነት: ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን?
'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቈጠርን'
ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው::
በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን:: +"+ (ሮሜ. 8:35-38)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ቅድስት_ሥላሴ

"ሥላሴን " "ቅድስት ሥላሴ እያልን የመጥራታችን ምስጢር ምንድን ነው?

◉አንዲት ሴት ወይም እናት ልጆቿን አልወለደችም ተብላ አትጠረጠርም ፤ ሥላሴም ይህንን
ዓለም ፈጥረዋል እናም አልፈጠሩም ተብለው አይጠራጠሩም ።

◉አንዲት ሴት በባሕሪይዋ ልጅን ታስገኛለች ፤ ሥላሴም ይህንን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር
አምጥተው ስለፈጠሩት በሴት አንጻር # ቅድስት ተብለው ይጠራሉ ።

◉አንድም ሴት አዛኝ ናት ፤ ለታናሹም ይሁን ለታላቁ ትራራለች ሥላሴም እንደዚሁ ለፍጥረት
ሁሉ ያዝናሉ ፥ ይራራሉ ፥ ምህረት ይሰጣሉ ። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንዲህ ይላል ።
ምህረታችሁ ከልክም በላይ የበዛ በሴት አንቀጽ ቅድስት ተብላችሁ የተጠራችሁ ሥላሴ " በማለት ያመሰጥራል።
ስለዚህ ቅድስት ለምን ተባሉ ቢባል በረከታቸው ፥ ርህራሄያቸውና ፥
ይቅር ባይነታቸው መሆኑን ማወቅ አለብን ።

◉አንድም ሴት ልጇ ቢታመምባት አትወድም ፤ ሥላሴም አንድም ልጅ በዲያብሎስ እጅ ተይዞ
በኃጢአት እንዲታመሙ አይወዱም ፥ አይፈቅዱም በመሆኑም
#ቅድስት ይባላሉ ።

◎አንድም ሴት ልጅ የልጇን ነውር አትጠየፍም ልጄ ቆሽሿል ፥ ተበላሽቷል ብላ ፊቷን አታዞርም ።
ሥላሴም የሰውን በኃጢአት መቆሸሽ ሳይፀየፉ በቸርነታቸው ጎቦኝተው ለንስሐ ያደርሱታል ።

◎ይህንን የፅድቅ አየር የምንምገው ያማረውንም ብርሃን የለበስነው ስለ ፅድቃችን ሳይሆን
በሥላሴ ቸርነት ነውና ስለዚህም ሥላሴን በሴት አንቀፅ # ቅድስት እንላቸዋለን ።

◉አኔድም ሴት ልጆቿን ፈጭታና ጋግራ ትመግባቸዋለች ሥላሴም እንደዛው ናቸው ። በዝናብ
አብቅለው በፀሐይ አብሥልው ፍጥረታትን ሁሉ ይመግባሉ ። ስለዚህ ሥላሴ እንደ እናት
ሁሉንም ይመግባሉና በሴት አንቀጽ #ቅድስት ይባላሉ ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሥሉስ ቅዱስ ሆይ ከከላዉዴዎን ይልቅ የካራንን ምድር የመረጠ አብረሃም የሦስትነታችሁን ትክክለኛ ሦስትነት ከተረዳ በኋላ ከድንኳኑ በስተምስራቅ ወይም ባሻገር ሦስት ሰወች አየ ተመለከተ። ከሦስቱ አንዱ ከልጅ ልጅህ ተወልጀ አድንሀለሁ የሚል ቃል ኪዳን ተቀበለ። ለነዋየ ዉስጥ ምዕረትክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ከዉስጣዊ ባህርያችሁ የሚገኝ ቸርነታችሁ ሰላም እላለሁ።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ የትሩፋት አበቃዝ እንደመሆናችሁ የገድል ትሩፍትን አጎናፅፉኝ ከገድላቸዉ ገድልን እሳተፍ ዘንድ በሄድኩ ጊዜ ጊወርጊስ ከደሙ ጠብታ ሊሰጠኝ አልፈቀደም ተክለ ሀይማኖትም ከሰባራ ዐፅሙ አንድት ስንጥር እንኳ ከልክሎኛልና።

36 ለሔክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ መታጠቂያዉ የጨርነት ሰቅ ለሆነዉ ወገባችሁ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ ዓምላክነታችሁ በለዓም እንደሚያመልክበት ጣዖት ከንቱ ያይደለ የባሕርይ አምላክነት ነዉ እኮን። አቤቱ የቸርነታችሁ ምልክት ወደእዉነተኛ ዉሳኔችሁ መርቶ ያደርሳልና። በዓለ መስዋዕቱ አብረሃምና ለመስዋዕት የሚቀርበዉ ይሰሐቅ ከመሰዊያዉ ቦታ ይደርሱ ዘንድ የሦስት ቀን ጉዞ ለማድረግ ተዘጋጁ።

37 ለአቁያፂክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይበአይን ለማይታይ ህልዉናቸዉ ተመራምሮ ለማይደረስበት አቁያጾቻችሁ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ ሰማያዊ ብርሃን ነጭ ሐር ግምጃ ሰራተኞች እንደመሆናችሁ። ቸርነታችሁ አካሌን የምሸፍንበት ሰማዕትነትን መልብስ ዕብን የለኝምና ይልቁንም ሕፃኑ ቂርቆስ የተጎናፀፈዉን መልበስ እሳት በሰዉነቴ ላይ ልጎናፀፍ አልቻልኩምና።

38 ለአብራኪክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ የፍጥረታትን ሁሉ አብራክ ለሚያሰግድ አብራካችሁ ሰላምታ ይገባል። እነርሱም ሰማርን ሰብኮላህም ተጨማሪነት ፈፅም የማይፈልጉ ናቸዉ።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ አቤቱ እኔ አገልጋያችሁን ባለሟል አድርጉኝና እንደ መላዕክት አሰልጥኑኝ ከሰብአዊ ተገዢነትም የገዥነት ስልጣን አቀዳጁኝ።

39 ለአእጋሪክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይአዳምን ለመጎብኘት በገነት ዉስጥ ተመላለሱ እግሮቻችሁ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ አዳምና የሔዋን ፈጣሪወቻቸዉ እናንተ እንደመሆናችሁ።የምርኮኞች ነፃ አዉጪ የሆነ ሀይላችሁ የጣኦታትን ሀሰተኝነት አጋለጠ አርታጥ ሐሰተኝነት የዕዱ ኃጢአትም ሥሩ መሰረቱ እነሆ ተነቃነቀ።

40 ለሰኳንዊክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ብርሃናትን ለተጎናፀፉ የእግር ተረከዛችሁ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ ግብርን የሚያስከፍል የቀራጮች አለቃ የሚሆን ለበደለዉም ስለ አንድ ፈንታ አራት እጂ የከፈለ ከገንዘቡ እኩሌታ ከፍሎ ለነዳያን እንደመፀወተ እንዴዘኬዎስ ዕል ፈንታ ቸርነታችሁ ይቅርታን ቸርነትን ያስተምረኝ።

41 ለመከየድክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ በዓሳዕነ መባርቅት ለሚራመድ ጫማችሁ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ ረቂቅ የሆነ የችሮታ ገንዘባችሁ አታሳጡኝ።እዉነተኛ የቸርነታችሁን ገንዘብ ጥሪት ቀማኝ ቀማኛ ሽፍታ በቀማኝ ጊዜ ስለኔ ተግቶ የሚዝን የሚያለቅስ እንደ አባ ይስሪን ያለ ደግ ሰዉ ፈጽም አይገኝምና።

42 ለአጸብዒክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ከጽፍሮቻችሁ ጋር ያለመነጣጠል ተባብረዉ ተመሳስለዉ ላሉ ጣቶቻችሁ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ ድካም በሌለበት ኃይላችሁ ከባቢሎን ንጉስ ይልቅ የአንድ ነብያችሁ ክብር ከፍ ያለ ነዉ። የልስጥራን ሰዎችም የአልሕምት መስዋዕት አንሰዋላችሁ እስከማለት ደርሰዉ ለመረጣችኋቸዉ ሀዋርያት ሰገዱ።

43 ለዘዚአክሙ ቆም
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ለማይመረመር አካለ ቆማችሁ ሰላምታ እላለሁ።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ ዓለምን ከባህርያችሁ ብታስገኙ እንጂ በዕናንተ ላይ ዓለም የለባችሁም እኮን አቤቱ ስለ አባታችን አዳም ከእናንተ አንዱ አካላዊ እግዚአብሔር ቃል በለበሰ ሥጋ የጴላጦስን እንግዳ መከራ በመቀበሉ ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም በማለት በአንድነት ትመሰገናላችሁ።

44 ለመልክአክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ መፅሀፍ እንደተናገረዉ በማንኛዉም ፆታ መልክአ ልዩነት ለሌለዉ መልካችሁ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ ከሐዲ አርዮስ የባሕርይ አንድነታችሁን በከፋፈለ ጊዜ ሰይፍ መዓታችሁ ተበቅሎ ያጠፋዉ ዘንድ ያለ ሰይፍ በረቂቅ ሰይፋችሁ አንጀቱን በጣጥሶ ይጥለዉ ዘንድ ተገቢ ሆነ።

45 ሥላሴክሙ ሥላሴ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ እኔን አገልጋያችሁን ሦስትነታችሁን የሦስትነታችሁ መታመኛ ቦታዉ ያድርገኝ።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ የሦስትነታችሁን ብርሃን ከተቀዳጀሁ ዘንድ መላ ሰዉነቴ አንድነታችሁን ሦስትነታችሁን የገለፃችሁበትን እዚሁ ዮርዳኖስ ይሆናልና ከዮርዳኖስ ምልክትነትን አልሻም ፡አብ ስለልጁ ምልክትነቱን የሰጠበትን የታቦር ተራራንም አልመኘዉም እኔዉ እራሴ ደብረታቦር ሁኛለሁና።

46 ሥሉስ ቅዱስ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ከባህርያች የተገኘ ባህርያዊ ልብስ ጥበብ የተጎናጸፉችሁ ናችሁና የንጉሱን ልጅ የእያሱን ስም በልብሳችሁ መጎናፀፊያ ሰሌዳ ላይ ጻፉ።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ የምድር ነገስታት ከነገሱ በኋላ መንፈሳዊ ሐሩር በሆነበት ዘመን ሕይወትን የሚያረካ ማየ ህይወት የደብረ ብርሃን ቤተ መቅደሱ ህንፃ ከዉስጣዊ ከርሡ መርጫችሁ ጽድቅን ለጠጠሙ ዉሃን አመንጭቷልና።

47 ለዘለነጊድ አቅርብኩ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ በአርባ ሰባት ምዕራፍ ለተከፈለ ለአቀረብኩት ምስጋና እጅ መንሻ ስለአንድ ፈንታ ዕጥፍ በዕጥፍ ዉለታ የምትከፍሉ ናችሁና ከባህርየ ገፅታችሁ ደስ የሚያሰኝ ፈገግታ የተመላበት ንዋየ ገጽ ስጡኝ።ለቅዱሳን በተዘጋጁ በአስሩ አህጉር ላይም ስልጣን ሰጥታችሁ ሹሙኝ ።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ እኔን አገልጋያችሁን_____ ________ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ ጠብቁኝ ለዘለአለሙ አሜን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

መልከአ ስላሴ

1 ለህላዊክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ የፍጥረታትን ሁሉ ስነ ባህሪይ ፈጥሮ በላይነት ለሚገዛ መለኮታዊ ሥነ አዕምሮ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ በተመኘሁ ግዜ የግብር ሦስትነታችሁን ለማግኘት በተመራምሮ አንድነትን ከሦስትነት ሳልቀላቅል የመለኮትን አንድነት በዘለአለማዊት፡ ህልዉና አምናለሁ::

2 ለዝክረ ስምክሙ
(አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ከሦስትነት ዝቅ ወይም ከፍ ለማይል ለስም አጠራራችሁ ሰላምታ ይገባል።)2)
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ በአንድነቱ ፀንቶ ለሚኖር የባህርይ አምላክነታችሁ መለኮታዊ እጅ ከተከለዉ ተክለ ፅድቅ ፍሬአችሁ ከወይን ዘለላ ቸርነታችሁ ትመግቡኝ ዘንድ ደጅ እጠናለሁ እኔ አገልጋያችሁ።

3 ለስእርተ ርእስክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ
ስነ ፅላሎቱ ከኅብረ በረድ ይልቅ ጽሩየ ባህርይ ለሆነዉ ለራስ ፀጉራችሁ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ ጸሎቱ እጅ መንሻችሁ የሆነ ነገሥተ ባህታዊ የባለ ብዙ ገድል ሦስትነታችሁን አስተማረ ሦቱ የምስገና ቃል በተጨማሪም አንድ የሀያላት ጌታ በመባል የአንድነታችሁ ምስጢር ተረጋገጠ በትክክል።

4 ለርእስክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ የነፍስና የስጋ ገዥ እንደመሆናችሁ አመቻችቶ አቀነባብሮ ርእስ ፍጡራንን ለፈጠረ መለኮታዊ ርዕሳችሁ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ የባለሟልነታችሁን ዘዉድ በእያሱ ራስ ላይ አቀዳጁ በስም ሦስት በባህርይ አንድ አምላክ ብሎ በማመን በስማችሁ ቤተ መቅደስ አሳንጿልና ።

5 ለገጽክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ የጌትነታችሁ ምስጋና በፍጡር ሁሉ አንደበት የሚነገር ሲሆን ከፍጡራን ሁሉ አይን የተሰወ ለሆነ ስነገፃችሁ ሰላምታ ይገባል።
ስሉሥ ቅዱስ ሆይ በፍጡራን ሁሉ የበላይ ገዢ ለመሆን ተነስቶ ጸላዒ ዳቢሎስ ከባለሟልነታችሁ ወጥቶ ከማህበረ መላዕክት በተለየ ጊዜ በአርያችሁና በአምሳላችሁ ሰዉን ፈጠራችሁ በሱ ቦታ ተካችሁ ክብር ምስጋና ይገባችሁ ለዘለአለሙ።

6 ለቀናብርትክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ በአመፃ ፍዳ ብዛት ድንጋፄ እስክይዘዉ ድረስ አመፀኛዉን ለሚመራዉ ቀናብርታችሁ ሰላምታ ይገባል።
ነቀዝ የማያበላሸዉ የዕንቁ ባህርይ መዛግብቶች ናቸሁና፡፡ቸርነታችሁ በዚያች ፍርድ በሚሰጥባት ዕለት ገሃነመ እሳትን አጥፍቶ የሲኦልን ትላትል አጥቅቶ ነፃ የወጣሁ አድርገኝ።

7 ለአዕይንትክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ አይኖችን ለፈጠሩ አይኖቻችሁ ሰላምታ ይገባል። ቅድምናችሁ ጥንት የሌለዉ ነዉና ።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ እሳትን ያለእሳት የሚያነድ ዉሀን ያለዉሀ የሚቀዘቅዝ ጥበባችሁ ለዉስጣዊ ሰዉነቴ ምግብ ለአፋዊ ሰዉነቴ ነጭ ሀር ልብስ
ይሁነኝ።

8 ለአዕዛኒክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ርዕይ የሚከተለዉ ሚስጢራትን ለሚሰማ የበጐ ፀሎት በር ለሆነ መለኮታዊ አእዛናችሁ ሰላምታ ይገባል።
ስሉስ ቅዱስ ሆይ የሦስትነታችሁ ፀሀይ በያዕቆብ በሮች ላይ አበራ። ስለሆነም ለአሁኑ የታላቂቱ የጥምቀት ልጆች የቀድም የላባ በጎችና የሚጠጡበት ዉሀ መልካም ምሳሌ ሆኑ።

9 ለመላሒትክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ብርሀናት ከመፈጠራቸዉ በፊት በብርሀንነታቸዉ ላሉ መላትሓችሁ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ፡ ጭፍሮቹ ትካዜና ኀዘን ከሆኑ ከዚህ አለም ለዉጥ ንጉስ መከራ አድኑኝ የቅናት እሳት የሚነድበት የሐሜት ትል (ነቀዝ) የተመላበት የምድር ገኀነም እሱ ነዉና።

10 አእናፊክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ የምስጋና መስዋዕትን ለሚያሻትቱ አእናፉችሁ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ ጥበባችሁ በጥበቡ የታወቀ ነዉና ድኖችንና ችግረኞችን ድንጋይ ጠራቢ አድርጎ ሰማያዊ የነፍሴን ቤት ይሰራልኝ ዘንድ በሕንፃ ወራት የአናፂወች አለቃ የሚሆን ምፅዋትን ይዘዙልኝ።

11 ለዘዚአክሙ ከናፍር
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ እሳታዊ ነበልባላዊ ለሚሆን ከናፍራችሁ ሰላም እላለሁ።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ ቸርነት የባህርያች ነዉና ይቅርታ አድርጉልኝ የተስፍ ጥመኛዉን ቀዝቃዛ ዉሀ እንኳ ማጠጣት ሲገባኝ ይልቁንም ድዉዩን ሄጄ የምጎበኝት እግር አየች።ሀይማኖቴ ከምግባር ህይወቷ ተለይታለችና ቸርነታችሁ ላኩልኝ።

12 ለአፍክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ የሰላም መድረክ ለሆነ መለኮታዊ አፋችሁ ሰላምታ ይገባል። ለተዋህዶ ሃይማኖት ዱር ወይም ገዳም አበባዉ ጌጡ ናቸዉ።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ በአንድ አላድ በተቀረፀ የጣዖት አምልኮት በፍጹም ቸርነታችሁ በሚመጣዉ አም ገንዘብ ወደ እዉነተኛ አምሎኮት አምልኮቴን ለዉጡልኝ።

13 ለአስናኒክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ሥጋዊ አስናን ላይደሉ አስናናችሁ ሰላምታ ይገባል። ለተዋህዶ ሀይማኖት ደመናም የአንነቱ ዝናማት ናችሁ።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ መንፈሳዊ ዉስጣዊ ልቦና ዉስጥ ህጋችሁን በሠራችሁ ግዜ በጨለማ የተከበበች የሲና ህግ ከአይሁድ ጋር ተወገደች ።ለህጋችሁም ቦታዋን ለቀቀች።

14 ለልሳንክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ነገርን ሁሉ ከመነገሩ አስቀድም በመናገሩ ላይ ለነበረ አንደበታችሁ ሰላምታ ይገባል።
ስሉስ ቅዱስ ሆይ መለኮታዊ መንበር መንግስታችሁ ስጋዊ መንበር መንግስትን የሚያስደነግጥ ነዉ ህጋችሁን በተላለፈና ትዕዛዛችሁንም ባፈረሰ ግዜ የሚገባዉን የጥፋት ገፅታ የቴዎዳስ አይን አየ። ገሊላዊ ይሁዳም የምት ጎዳናን ተጓዘ።

15 ለቃልክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ የአባቱን ነበልባል ሰንሰለት ቆራርጦ ሰጥ ለሚያደርግ ቃላችሁ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ የታታሪ ነጋደ ልዩ ገንዘቡ ናችሁና ቅዱሳንን በመንፈስ ቅዱስ ከሚወልድ ችሮታችሁ በንሰሐ በተወለዱ ጊዜ ጴጥሮስን የመንግስተ ሰማያት መክፈቻ ተቀበለ። ምዕመናን ሲያሳድድ የነበረ ጳዉሎስም የወንጌል መምህር ሆነ።
16 ለእስትንፋስክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ የሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ሕይወት ለሚሆን እስትንፋሳችሁ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ ሥርየተ ደማችሁ ስርየተ ኃጢአት ነዉና የነፍሴን ቤት መቃን በስርየተ ደማችሁ እርጩት። የእንስሳት ደም የጣዖት አምልኮት እንደማይረባ አስቀድሜ ተመራምሬ ፈትኘዋለሁና።

17 ለጉርዔክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ስለጥልቅ ንስሐ የተነሳህያን ስቴ አንብዐ ደም አስፈላጊዉ ለሆነ ጉርኤአችሁ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ የባለሟልነት ባለፀጋ ናችሁና ከባለሟልነታችሁ አታዉጡኝ። ከባለሟልነት አዉጥታችሁ ቸል ካላችሁኝማ። ሚካኤል ገስግሶ ሥጋየን ለማስገኘት ይሆንለታልን።? ክሂለሎቸት የናንተ ብቻ ነዉ እንጂ።

18 ለክሳድክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ክሣደ አዳምን ለፈጠረ መለኮታዊ ክሳዳችሁ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ በቸርነታችሁ ከሀይላችሁ ሀይልን አሳትፉኝና በስጋየ ጠፈር ወይም ሰማይ ላይ የእርሳንዮስ ፀሀይ ገድል ትቆም ዘንድ እዘዙ። ቀድም በታች መሬት ያለ እያሱ በላይ በሰማይ ያለ ፀሐይን በቸርነታችሁ ኃይል ሊያቆም ችሏልና።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አረ ተውት በእግዚአብሔር ስም አትቀልዱ ምንም ብሆንኮ ይህ ቃል መፀፍ ቅዱስ ቃል ነው

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

“ድንግል ሆይ ባማረ በተወደደ ነገር ሁሉ መሰልሁሽ ምስጋናሽን ግን ለመፈፀም አልቻልኩም፡፡ እግዚአብሄርን ባመሰገንሁ ጊዜ ባንቺ ለስሙ ምስጋና አቀርባለሁ፤ በስምሽም ጸሎቴን በጸለይሁ ጊዜ ጸሎቴን ለልጅሽ አቀረብሁ፤ ዳግመኛም ውዳሴሽን ወደማወቅ ባህር ልዋኝ ወደድሁ፡ ወደ ክብርሽ ገናንነት ወደብ
እደርስ ዘንድ ደከምሁ ያንዲቷን ማእበል ሞገድ ያህል ስንኳን አላለፍሁም፡፡ ወደ ፅርሀ አርያም ጠፈር ለመድረስ የሚቻለው ማነው? ከምድር በታች ወዳለው ባህር መሰረትስ መዋኘት ማን
ይችላል? ድንግል ሆይ ክብርሽን ገናንነትሽን ጠንቅቆ መናገር የሚቻለው ማነው?”፡፡ እኛስ የአባቶቻችን ልጆች ነንና በእምነት ሆነን ድንግል ሆይ ክብርሽን ማን ይናገር ዘንድ ይችላል? ገናንነትሽን ማን መመጠን ይችላል?"
(ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ቶማስ_ሐዋርያ

በዚህችም ዕለት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትንሣኤው ሳምንት ለሐዋርያው ቶማስ ተገለጠለት በእጆቹና በእግሮቹ ውስጥ የችንካሮቹን ምልክትም አሳየው የቶማስንም እጅ ይዞ በመለኮታዊ ጐኑ ውስጥ አኖረውና በጦር የተወጋበትን ቦታ አሳየው ቶማስም ጌታዬና ፈጣሪዬ መነሣትህን አመንኩ አለ።

ጌታችንም ብታየኝ አመንከኝ የሚመሰገንስ ሳያየኝ የሚአምንብኝ ነው ብሎ መለሰለት። በትርጓሜ ወንጌልም እንዲህ ይላል ቶማስ በመድኃኒታችን ጐን ውስጥ እጁን በአስገባ ጊዜ እጁ በመለኮት እሳት ተቃጠለ በመለኮቱም ደግሞ በታመነ ጊዜ እጁ ከመቃጠል ዳነች።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በሐዋርያቶቹም ጸሎት በታጋዮች ጻድቃንም በድል አድራጊዎች ሰማዕታትም ጸሎት ይልቁንም በእመቤታችን ማርያም በአማልጅነቷ ይምረን ዘንድ ወደርሱ እንለምን ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሚያዝያ እና #ከገድላት_አንደበት)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ለአባታችን አዳምም ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዓመት ሲሆን መላልኤልም መቶ ሠላሳ አምስት ዓመት ሲሆነው በተፈጠረባት ዐርብ በዘጠኝ ሰዓት አረፈ ያረፈባትም ሰዓት ከገነት የወጣባት ናት በዚያን ጊዜም የመላእክት ሠራዊት ከልጆቹ ጋራ ተሰበሰቡ። መልካም አገናነዝም ገነዙት በብዙ ሽቱዎችም መዓዛውን አጣፈጡ።

ይህም በገነትና በደብር ቅዱስ ያለ ነው ስጋውንም በፀሐይ መውጫ በኲል በዋሻ ውስጥ አኖሩ የሚያበራ መብራትም አኖሩ ከእርሱም ጋራ ወርቁን ከርቤውንና ዕጣኑን አስቀመጡ ዋሻውንም በአዳምና በሔዋን በሴት ቁልፍ ቆልፈው አተሙት። የጥፋት ውኃም እስከ መጣ ድረስ ሴትና ልጆቹ ለአባታችን አዳም ሥጋ ሲያገለግሉ ኖሩ።

ከዚህ በኃላም ኖኅ በአምላክ ትእዛዝ ደብረ አራራት እስከሚአደርሰው ከእርሱ ጋራ የአባታችን የአዳምን ሥጋ በመርከብ ወሰደው። ከዚያም ሴምና መልከ ፀዴቅ የእግዚአብሔር መልአክ እየመራቸው ይዘውት ሔዱ ከቀራንዮ ቦታ ደርሰው በዚያ ቀበሩት መልከ ጼዴቅም በዕጣንና በቁርባን ሲያገለግል ኖረ።

የእግዚአብሔርም ልጅ መጥቶ ከድንግል ልጁ በተወለደ ጊዜ መድኃኒት በሆነች ሞቱ አድኖ ወደ ቀደመው ርስቱ መለሰው እርሱ ለከበሩ ደጋጎች ነቢያት ለተጋዳዮችም ሰማዕታትና ጻድቃን አባት ነውና ስለ እርሱም የእግዚአብሔር ልጅ ወደ ዓለም መጥቶ ሰው ሁኗልና።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባታችን_ቅዱስ_ኖኅ (ልደቱ)

ዳግመኛም በዚህች ቀን ከአባታችን አዳም ጀምሮ አሥረኛ ትውልድ የሆነ ጻድቁ ኖኅ ልደቱ ነው፡፡ እርሱም ከታናሽነቱ ጀምሮ ኃጢአት እንደሚበዛና ደጋጎች እንደሚያንሱ ሥጋ የለበሰ ሁሉ በጥፋት ውኃ እንደሚደመሰስ አምላካዊ ምሥጢርን የሚያይ ሆነ፡፡ ስለዚህም ፊቱ የተቋጠረ ሆኖ ፈጽሞ ያለቅስ ነበር፡፡

ጻድቁ ኖኅ ኖኅም የአቡዚር ልጅ የሆነች ሐይከል የምትባል ሴት አግብቶ ወደ እርሷ ሦስት ጊዜ ቢገባ ሦስት ልጆችን ሴም ካም ያፌትን ወለዳቸው፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ለኖኅ ከደብር ቅዱስ ዕንጨት ቆርጦ መርከብን እንዲያሠራ ካዘዘው በኋላ አሠራሯን በዝርዝርና በጥልቀት አስረዳው፡፡ የቃየል ልጆችም ኖኅን መርከብ ሲሠራ አይተው ዘበቱበት፡፡ የአዳምንም ሥጋ ወስዶ በውስጡ አኖረ፡፡ ሴም ወርቁን፣ ካም ከርቤውን፣ ያፌት ዕጣኑን ወስደው ወደ መርከብ አስገቡ፡፡ ኖኅም ከልጆቹና 500 ዓመት ድንግልናውን ጠብቆ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ለአባታችን አዳም ሥጋ ሲያገለግል ኖረ፡፡ ከዚህም በኋላ ሚስት እንዲያገባ እግዚአብሔር አዘዘው፡፡ ሥጋ የለበሰ ሁሉ እንደሚደመሰስ ከእርሱ ዘር በቀር የሚተርፍ እንደሌለ ነገረው፡፡ ጻድቁ ከሚስቶቻቸው ጋራ ወደ መርከቡ ገባ፡፡ ንጹሐን የሆኑት እንስሳትና አእዋፋት ሴትና ወንድ ሰባት ሰባት፣ ንጹሐን ካልሆኑት ደግሞ ሁለት ሁለት ሴትና ወንድ አስገባ፡፡ ከዚያም ሰማይ ተከፍቶ የምድርም ምንጮች ሁሉ ተነድለው ራጃጅም ተራራዎችም እስኪሸፈኑ ድረስ 40 ቀንና 40 ሌሊት ዘነመ፡፡ ውኃውም በላያቸው 15 ክንድ ከፍ አለና ሥጋ የለበሰ ሁሉ ሞተ፡፡

ከ150 ቀንም በኋላ እግዚአብሔር ኖኅን አስቦ ነፋስን በምድር ላይ አመጣና ውኃውን አጎደለ፡፡ ምንጮች ተደፍነው የሰማይ መስኮት ተዘጋ፡፡ መርከቢቱም በ7ኛው በ12ው ቀን አራራት ተራራ ላይ አረፈች፡፡ ከጊዜም በኋላ እግዚአብሔር ኖኅን ከነቤተሰቡ አንድ ላይ ከመርከቡ እንዲወርዱ አዘዘው፡፡ ኖኅም መሠዊያን ሠርቶ ንጹሕ ከሆኑት ሁሉ ወስዶ መሥዋዕት ባቀረበ ጊዜ እግዚአብሔር መልካም መዓዛን አሸተተ፡፡ ዳግመኛም ምድርን በንፍር ውኃ እንዳያጠፋ ቃልኪዳን ገባለት፡፡ ምድር ፀንታ በምትኖርበት ዘመን ሁሉ ዘር መከር፣ ቅዝቃዜና ሙቀት፣ በጋና ክረምት፣ መዓልትና ሌሊት እንደማይቋረጥ ቃልኪዳን ገባለት፡፡ እግዚአብሔርም ኖኅንና ልጆቹን ባረካቸው፡፡ ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሉዋት ግዟት አላቸው፡፡

ኖኅም ምድርን ያርሳት ይቆፍርራትም ጀመር፡፡ ወይንም ተክሎ ከእርሶ ፍሬውን አድርሶ ወይን ጠጥቶ በሰከረና ራሱን በሳተ ጊዜ የከነዓን አባት ካም የኖኅን ራቁትነት አይቶ ሳቀ፣ ሄዶም ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው፡፡ ያፌትና ሴምም ልብስ ወስደው የአባታቸውን ርቃን ሸፈኑ፡፡ ኖኅም ከስካሩ በነቃ ጊዜ ሁሉም ያደረጉትን ዐወቀ፡፡ ‹ከነዓን የተረገመ ይሁን፣ ለወንድሞቹም ተገዥ አገልጋይ ይሁን› ብሎ ከረገመው በኋላ ‹‹የሴም ፈጣሪ እግዚአብሔር ይመስገን፣ እግዚአብሔርም የያፌትን አገር ያስፋ፣ በሴም ቤትም ይደር›› ብሎ መረቃቸው፡፡ አባታችን ኖኅ ‹‹እግዚአብሔር በሴም ቤት ይደር›› ማለቱ የጌታችንን ሰው መሆን በትንቢት መናገሩ ነው፡፡ እርሱም ከጥፋት ውኃ በኋላ 350 ኖረ፡፡ በአጠቃይ ዕድሜው 950 ዓመት በሆነ ጊዜ በሰላም ዐረፈ፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ልበ_አምላክ_ቅዱስ_ዳዊት (ልደቱ)

በዚህችም ቀን የሰሎሞን አባት ንጉሡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ልደቱ ነው፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ነሐሴ 13 ቀን ተጸነሰ፣ በሚያዝያ 6 ቀን በይሁዳ በቤተልሔም ሀገር ተወልደ። 1ኛ ሳሙ 16፡10-11፡፡

ዳዊት ማለት ‹‹ኅሩይ›› ማለት ነው። አንድም ‹‹ልበ አምላክ›› ማለት ነው። ሐዋ 13፡22፡፡ ትውልዱ ከነገደ ይሁዳ ነው። አባቱ እሴይ እናቱ ሁብሊ ይባላሉ። ሁብሊ መልከ መልካም ሴት ነበረች። ከጎረቤታቸው ያለ ጎልማሳ መልኳን እያየ በሐጸ ዝሙት ተነደፈ። እሴይ የእሷም ፈቃድ እንደሆነ አውቆ መንገድ እሄዳለሁ ብሎ ስንቁን ይዞ ወጣ። የሄደ መስሎ ከዚያው ውሎ ሲመሽ በልብሱ ተሸፋፍኖ ድምጹን ለውጦ ያንን ሰው መስሎ ገብቶ ከእርሷ ጋር አድሮ ጎህ ሳይቀድ ወጥቶ ሄደ። ዳዊት በዚህ ዕለት ተጸንሷል።

በዓመፃ ተፀነስሁ፥ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ” (መዝ 50፡5) ማለቱ ስለዚህ ነው። ቅዱሱም ተወልዶ ጉልበቱ ከጸና በኋላ የአባቱን በጎች ሲጠብቅ አድጓል።

እረኛና ብላቴና የነበረ ቢሆንም የፍልስጤማውያኑን ኃያል ሰው ጎልያድን በ12 ዓመቱ 5 ጠጠርን ከወንዝ ለቅሞ በወንጭፍ ወርውሮ ገድሏል፡፡ 1ኛ ሳሙ 12፡45-51፡፡ ንጉሥ ሳዖል በጌልቦአ ተራራ በራሱ እጅ ከሞተ በኋላ አስቀድሞ በይሁዳ 7 ዓመት በመላው እስራኤል 33 ዓመት ነግሡዋል፡፡ 2ኛ ሳሙ 2፡4፤ 5፡1-5፡፡‹‹እግዚአብሔር እንደ ልቡ የሆነ ሰው መርጦአል” (1ኛ ሳሙ 13፡14) ተብሎ በእግዚአብሔር የተመረጠና ነገረ ሥጋዌን፣ ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን፣ ዳግም ምጽዓትን፣ ነገረ ማርያምን፣ ክብረ ቅዱሳንን፣ በስፋትና በጥልቀት የተናገረ የብሉይ ኪዳን ‹‹ወንጌላዊ›› የተባለ ቅዱስ ነቢይ ነው። “ብዙ ውሾች ከብበውኛልና የክፋተኞች ጉባኤም ያዘኝ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ። አጥንቶቼ ሁሉ ተቈጠሩ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም። ልብሶቼን ለራሳቸው ተከፋፈሉ፥ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ…” እያለ የጌታችንን መከራ መስቀል በትንቢት ተናግሯል፡፡ መዝ 21 (22)፡ 16-18፡፡

“አምላክ በእልልታ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ።”፣ “ከክብሩ ውበት ከጽዮን እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል። አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም እሳት በፊት ይቃጠላል፥ በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ አለ…” እያለ የጌታችንን ዕርገቱንና ዳግመኛ ለፍርድ የሚመጣ መሆኑን በግልጽ ተናግሯል፡፡ መዝ 46(47)፡4-5፣ መዝ 49(50)፡ 1-5፡፡ “የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርህ ናቸው በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች” እያለ የእመቤታችንን ክብር አይቶ በትንቢት ተናግሯል፡፡ መዝ 44(45)፡9፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🔔🔔🔔🔔🔔
➡️ቅኔ ለጀማሪዎች
➡️ዛሬ በ6/8/2016
➡️ከምሽቱ 3:00-5:00

ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
/channel/+cD8I6LHkvu5kMmY0
👍👍👍👍👍

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በቀላሉ
✅ የሰርግ ጥሪ ካርድ
✅የከርስትና ጥሪ ካርድ
✅የምላሽ ጥሪ ካርድ
✅የ40 ቀን መታሰቢያ ጥሪ ካርድ
✅የምረቃ ካርድ
✅የልደት ጥሪ ካርድ
❤️የጋብቻ ጥሪ ካርድ
✅የቀለበት ጥሪ ካርድ
✅አጃቢ ጥሪ ካርድ
✅እንዴት መሰራት እንችላለን ? ከዚህ በታች በተቀመጠው ሊንክ ገብታችሁ ግልጽ በሆነ አቀራርብ የተዘጋጀ ቪዲኦ ስላለ ማየት ትችላላችሁ ፡፡
👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼
https://youtu.be/zUp-TKSy5TI

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ናይ ሆሳእና መዝሙር
https://youtube.com/watch?v=Imoc54psCZw&amp;si=E6RmV2BHnP6Td8Ff

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🔔🔔🔔🔔🔔
የቅኔ ትምህርት በቀላሉ
/channel/+cD8I6LHkvu5kMmY0
👍👍👍👍👍

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †

† ሚያዝያ ፬†

† ቅዱሳን ፊቅጦር: ዳኬዎስና ኤርሞ (ሰማዕታት) †

=>አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሚያዝያ አራት በዚች ቀን የከበሩ ፊቅጦርና ዳኬዎስ ኤርሞ ሌሎችም ብዙዎች ሰዎች ሴቶችና ወንዶች ደናግሎች በሰማዕትነት ሞቱ።

እሊህም ቅዱሳን በታላቁ ቈስጠንጢኖስና በልጁ ዘመነ መንግስት የጣዖታትን ቤቶች አፍርሰው ጣዖታትንም ሰብረው አቃጥለው በቦታቸውም አብያተ ክርስቲያናትን ሠርተው አምላክን በወለደች በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በሌሎችም በብዙዎች ቅዱሳን ስም ታቦቱን ሰይመው ነበር።

ከሀዲ ዮልያኖስም በነገሠ ጊዜ የጣዖትን አምልኮ አቆመ የጣዖቱንም ካህናቶች አከበራቸው ብዙዎች ክርስቲያኖችንም አስገደለ።

የእሊህ ቅዱሳን ዜናቸው አስቀድሞ በጣዖታት ቤቶች ላይ ያደረጉት ጣዖታትን እንደሰበሩ ሁሉ ተሰማ።ይዘውም ጽኑ ሥቃይን አሠቃዩአቸው ብዙ ቀንም ሲሰቅሏቸውና ሲገርፉአቸው ቆዳቸውንም በሾተል ሲነጥቁ ኑረው በኃላም ቸብቸቧቸውን በሰይፍ ቆረጡ።

በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ በረከታቸው ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን።

=>ሚያዝያ 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ በዓላት=
1.እግዚአብሔር የሰው ልጅን ፈጠረ
2.ቅዱሳን አብርሃ ወአጽብሐ (ጻድቃን ነገሥት)
3.ቅዱሳን ፊቅጦር: ዳኬዎስና ኤርሞ (ሰማዕታት)

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጉዋድ (ወንጌላዊው)
2.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት)

=>+"+ እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ:: በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው:: ወንድና ሴት አድርጐ ፈጠራቸው . . . እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ:: እነሆም እጅግ መልካም ነበረ:: +"+ (ዘፍ. 1:26-31)

†ወስብሐት ለእግዚአብሔር †

+ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችሗለን!+

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

የዩቱዩብ ቻናል👇
https://youtu.be/OIOCAD82nxk?si=VMEi2GBRFE8w3lMi

የቲክቶክ ቻናል👇
zikirekidusan23?_t=8kGT8RWuULK&amp;_r=1" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@zikirekidusan23?_t=8kGT8RWuULK&amp;_r=1

የቴሌግራም ቻናል👇
/channel/zikirekdusn

✝ ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር ✝

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/mergatamul
🌿🌿🌿ትክክለኛ የምስክር ወረቀት ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አ/ፅ/ቤት
የተሰጣቸዉ መርጌታ ( ብርሀኑ 🌿መድህኒት ቀማሚ ትክክለኛዉን እና የቀደምት የሊቃዉንት የአባቶቻችን ጥበባቶች ይሻሉ ወይንም ይፈልጋሉ እንግዲያዉስ ፈውስ እና ጥበብ ከፈለጉ ደዉለዉ ያናግሩ 🇪🇹
0912399819
094️⃣4️⃣4️⃣5️⃣5️⃣4️⃣3️⃣7️⃣
በውጭ ሀገር ለሚኖሩም መምጣት ሳያስፈልግ ባሉበት እንሰራለን 
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
1 🌿🌿ለመፍትሄ ሀብት
2 🌿🌿ለህማም
3 🌿🌿ለመስተፋቅር
4 🌿🌿ቡዳ ለበላው
5 🌿🌿ለገበያ
6 🌿🌿የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 🌿🌿ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር)
8 🌿🌿ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 🌿🌿ለዓቃቤ ርዕስ
10🌿🌿ለመክስት
11🌿🌿 ለቀለም(ለትምህርት)
12🌿🌿 ሰላቢ የማያስጠጋ
13🌿🌿 ለመፍትሔ ስራይ
14🌿🌿 ጋኔን ለያዘው ሰው
15🌿🌿 ለሁሉ ሠናይ
16🌿🌿 ለቁራኛ
17🌿🌿 ለአምፅኦ
23🌿🌿 ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
24🌿🌿 ለግርማ ሞገስ
25🌿🌿 መርበቡተ ሰለሞን
26🌿🌿 ለዓይነ ጥላ
27🌿🌿 ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ
28🌿🌿 ለሁሉ መስተፋቅር
29🌿🌿 ጸሎተ ዕለታት
30🌿🌿 ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
31🌿🌿 ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
32🌿🌿 ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ
33🌿🌿 ለድምፅ
34🌿🌿 ለብልት
35🌿🌿 በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ሰወች ደግሞ ከምንሰራቸው ስራዎች በጥቂቱ

   🇮🇴🇧🇮🇧🇫🇨🇲🇨🇱                     ከሀገር ውጪ ለሚኖሩ
1🌿🌿የመኖሪያ ፍቃድ ላላገኙ ሙሉ ስማቸውን ብቻ በመላክ በምንሰራው ስራ በጥቂት ቀናት መፍትሄ እንሰጣለን ለዚህም ብዙ ምቅክሮች አሉ
2.🌿🌿 ከሀገር ውጪ ሆነ በሀገር ውስጥ የስራ እድል ላጡ
3. 🌿🌿ንግድ ጀምረው[ሱቅ ከፍተው] አልሳካ ላላቸው
4.🌿🌿 ገንዘብ ለሚያባክኑ ገንዘብ አልበረክት ላላቸው
5🌿🌿. ሰውፊት መቆም መናገር ለሚፈሩ በጥቂት ጊዜ ውስጥ በምንሰራው ሰራ ደፋርና በራስ የመተማመን ችሎታ እንዲኖሮት እናደርጋለን
6.🌿🌿 ለሀብት ለገንዘብ ለንብረት ሚሆንም አለን
7🌿🌿. ለስንፈተ ወሲብ መፍትሄ  የረጅም አመት ልምድ አለን ለውጪ ሀገር ለሚኖሩትም እየሰራን ነው
8🌿🌿. ፍቅረኛ አልያዝ ላላቸውም አለን
9.🌿🌿 ትምህርት አልገባ ላለው ቶሎ የመርሳት ችግር ላለበት በሚደገም እና በሚነበብ ፅሁፍ ብቻ እጅግ በጣም ልዩ የሆነ ስራ እንሰራለን
10🌿🌿. መስተፋቅርም አለን ፣የህዝብ መስተፋቅር
11.🌿🌿 ከሀገር መውጣት እየፈለጉ ላልተሳካላቸውም ወደኛ ቢመጡ እንሰራሎታለን
ባጠቃላይ እነዚህ የገለፅናቸው ጥቂቶቹ ናቸው እርሶ ምን እንድንሰራሎት ይፈልጋሉ ?በውስጥ መስመር ያማክሩን ። ከሀገር ውጪ ላላችውም መፍትሄ በልዩ ሁኔታ አለን ብቻ ይምጡ ያማክሩን ያስተውሉ እኛ ምንሰራው በጥንታዊው ከአባቶቻችን በተማርነው ጥበብ ብራናውን አንብበን እፅዋትን ቀጥፈን አዘጋጅተን ነውና ሀገራችን ካሏት ጥበብ ጥቂቱ ነው እንኳን ለነዚህ እና አባቶቻችን በደመና ይሄዱ አልነበር እፀመሰውር ሰርተው እራሳቸውን ይደብቁ አልነበር ይሄ ጥበብ ንቀን ፈረንጅ አምላኪ ሆነን ነው እንጂ ጥበቡ አሁንም አለ ይምጡ ያማክሩን ።
ለምንኛውም ጥያቄ እንዲሁም ለመነጋገር በሜሴጅ በውስጥ መስመር ይፃፉልን 
ወይም በስልክ ቁጥር
ለጥያቄዎ ይደዉሉ
       👉 በቴሌግራም አድራሻችን
0912399819
🇪🇹📞0944455437
👉/channel/mergatamul
👉https

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ሚያዝያ_8

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሚያዝያ ስምንት በዚህች ዕለት የከበሩ ሦስት ሴቶች #ቅዱሳት_አጋሊስ_ኤራኒና_ሱስንያ በሰማዕትነት አረፉ፣ መቶ ሃምሳ ሰዎች በፋርስ ንጉሥ እጅ በአንዲት ቀን በሰማዕትነት አረፉ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱሳት_አጋሊስ_ኤራኒና_ሱስንያ

ሚያዝያ ስምንት በዚህች ዕለት የከበሩ ሦስት ሴቶች በሰማዕትነት አረፉ። የእሊህም ስማቸው አጋሊስ ኤራኒና ሱስንያ ነው። ከተሰሎንቄ ሀገርም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚያመልኩ ናቸው። ወላጆቻቸው እግዚአብሔርን የሚፈሩ ነበሩ።

እሊህም ደናግል በድንግልና በንጽሕና መኖርን ወደው በአንድ ምክር ተስማሙ ጽኑዕ በሆነ ገድልም ተጠመዱ ይልቁንም ያለማቋረጥ ተግተው ይጸልዩና ይጾሙ ነበር። ወደ ገዳሙም ተመልሰው ከመነኰሳቱ ጋራ ያገለግላሉ።

ከhaዲ መክስምያኖስም በነገሠ ጊዜ የጣ*ዖታ*ትን አምልኮ አቁሞ የንጹሆችን ደም አፈሰሰ። እሊህም ደናግል በአዩ ጊዜ ፈርተው ወደ ተራራ ሸሹ በዚያም በዋሻ ውስጥ ተሸሸጉ በጾምና በጸሎት በመጸመድ ሳይወጡ በዋሻው ውስጥ ኖሩ።

አንዲት የክርስቲያን ወገን አሮጊት በየሰባት ቀን ትጐበኛቸውም ነበር የሚአሻቸውንም ትሰጣቸዋለች የእጅ ሥራቸውን ትሸጥላቸውና ከእነርሱ የሚተርፈውን ትመጸውታለች። አንድ ሰውም ከከተማ ወጥታ ወደ ተራራ ሁልጊዜ ስትሔድ አያት ሳታየውም ተሠውሮ በሩቅ ተከተላት ወደ ዋሻውም እስከምትገባ ተመለከተ ከዚያ እስከምትወጣም ተሠውሮ ቆየ በዚያ ቦታ ብዙ ገንዘብ ያላት መስሎታልና።

ያቺ አሮጊትም ከዋሻው በራቀች ጊዜ ያ ሰው ገባ ለክብር ባለቤት ሙሽሮቹ የሆኑ የከበሩ አዕናቍ ደናግልን ቁመው ሲጸልዩ አገኛቸው ተሰሎንቄ ከተማ እስኪያደርሳቸውም አሥሮ ጐተታቸው።

መኰንኑም ሃይማኖታቸውን በጠየቃቸው ጊዜ ስለ እሳቸው የተሰቀለ የክብር ባለቤት ክርስቶስን የሚያመልኩ ክርስቲያኖች እንደሆኑ በፊቱ አመኑ። መኰንኑም ተቆጥቶ ይገርፉአቸው ዘንድ አዘዘ የሚአሠቃይ ጽኑ ግርፋትም ገረፉአቸው ባልተሰዘዙና ወደ ክሃ**ደቱ ባልገቡ ጊዜ ወደ እሳት እንዲጨምሩአቸው አዘዘ።

በእሳትም ውስጥ በጣሉአቸው ጊዜ ነፍሳቸውን አሳለፉ በመንግሥተ ሰማያትም የሕይወትን አክሊል ተቀዳጁ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#የፋርስ_ሰማእታት

በዚህችም ቀን መቶ ሃምሳ ሰዎች በፋርስ ንጉሥ እጅ በአንዲት ቀን በሰማዕትነት አረፉ።

እርሱም ለሀገሩ ቅርብ የሆነ የክርስቲያንን አገር ከበበና ብዙ የሰው ምርኮ ማርኮ ወደ አገሩ ወሰዳቸው ፀሐይን ጨረቃንና ከዋክብትንም ያመልኩ ዘንድ አስገደዳቸው አይሆንም ባሉትም ጊዜ ራሶቻቸውን በሰይፍ ይቆርጡአቸው ዘንድ አዘዘ። ራሶቻቸውንም ቆረጡአቸው በመንግሥተ ሰማያትም የሕይወትን አክሊል ተቀበሉ፡፡

ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሚያዝያ)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ይህን መዝሙር በድምፅ ያላችሁ በእግዚአብሔር ላኩልኝ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በቀላሉ
✅ የሰርግ ጥሪ ካርድ
✅የከርስትና ጥሪ ካርድ
✅የምላሽ ጥሪ ካርድ
✅የ40 ቀን መታሰቢያ ጥሪ ካርድ
✅የምረቃ ካርድ
✅የልደት ጥሪ ካርድ
❤️የጋብቻ ጥሪ ካርድ
✅የቀለበት ጥሪ ካርድ
✅አጃቢ ጥሪ ካርድ
✅እንዴት መሰራት እንችላለን ? ከዚህ በታች በተቀመጠው ሊንክ ገብታችሁ ግልጽ በሆነ አቀራርብ የተዘጋጀ ቪዲኦ ስላለ ማየት ትችላላችሁ ፡፡
👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼
https://youtu.be/zUp-TKSy5TI

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

19 ለመታክፍትክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ የአለምን መሰረት ለተሸከሙ መትከፍታችሁ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ የማይነቅዝ የማይለወጥ የኖህ መርከቡ ፅናዉ ከማየ አይኃ ቀዝፋችሁ ያወጣችሁት የኖህ አሻጋሪዉ ዋነተኞች ናችሁ። አቤቱ ሰዉ አምላክ አምላክ ሰዉ ሆኖ በተዋህዶ ዙፋናችሁ ላይ ተቀምጦ ባዩ ጊዜ ሱራፌልና ኪሩቤል ከእግሩ በታች ሰገዱ በእርሱ ፈቃድ እነርሱ ተፈጥረዋልና።

20 ለአእናፊክሙ

አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ በማዕከላዊነትና በምልዓት ከጽፍ እስከ ጽንፍ ተንሰራርተዉ ለሚገኙ እሳታዊዉያ አክናፉችሁ ሰላምታ ይገባል ።
ቅዱስ ሥሉስ ሆይ ጠላት ሽንገላዉንና የተንኮሉን የቃላት ጦነት በኔ ላይ በከፈተ ጊዜ ለመቋቋም እችል ዘንድ የመጋደል መፅሀፍ ሰልፍን አስተምሩኝ ።

21 ለዘባንክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ መጽሐፍ እንደተናገረዉ የሰዉ ዕዉቀት የመላዕክት አዕምሮ ተመራምሮ ለማይደርስበት ቅድመ አለም በበትረ ቅድምና ለተጠበጠበ ዘመናችሁ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ የባህርይ አንድነታችሁ ቅድመ አለም የነበረ ዛሬም ያለ ለዘለአለም ፀንቶ የሚኖር ነዉና (በአፍአ) በግዙፍ አካል የሚታየዉን ዉስጣዊ ሰዉነቴን ሕንፃ ከመፍረስ አድናችሁ ለዕናንተ ማረፊያ አድርጉት።

22 ለእንግድአክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ የንጉሳዊ ምክር ከተማ ለሆነዉ መለኮታዊ እንግድአችሁ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ የሰማያዊ መርከብ መልህቅ ናችሁና የጠላት ዲያቢሎስ ምቀኝነቱ የተንኮሉ መልአክ ሊያጠፍኝ በተከታተለኝ ጊዜ አስቀድም እስራኤልን ከባህር መስመጥ እንዳዳናቸዉ የቸርነታችሁ ባሕረ ፍቅር የማዳን ኃይሉ በኔ ላይ ይገለጽ።

23 ለሕዕንክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ አገልጋዮቹ የፃድቃን መጠለያ ለሚሆን መለኮታዊ ሕፅናችሁ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ ከልቦናዉ የምትመነጩ የእያሱ ፈሳሽ ዉሃ ናችሁ ስለዚህ በስጋዉም በነፍሱም እናንተ አድችሁበት በረድኤት ትጠብቁታላችሁና። እንደ አባቱ እንደ አብረሀም ወደ ድንኳን አይመለከትም ። በምርኮ ላይ እንደ ነበረዉ እንደ ዳንኤልም መስኮቱን ከፍቶ ወደ እየሩሳሌም ይመለከት ዘንድ አልፈቀደም።

24 ለአዕዳዊክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ አዳምን ለፈጠሩ መለኮታዊ እጆቻችሁ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ ፈጣሪየ ገዢዬ ቸር ጠባቆቸ እናንተ ናችሁና። የነቢያት አለቃቸዉ ለእስራኤል መሪያቸዉ ነብዩ ሙሴ ኦሪት ከፃፈ በኋላ የአዉሴ መምር መጽሀፍ ሦስትነታችሁን አስተማረኝ ወልደ ነጎድጓድ ዩሐንስም የምስጋና ጎዳናችሁን መራኝ አመለከተኝ።

25 ለመዝራዕትክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይየአዳምን ወርች ለአጸና መለኮታዊ ወርቻችሁ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ ከምድር ዳር እስከ ምድር ዳርቻ ፀብን ክርክርን የምታጠፉ እናንተናችሁና። የተነሳሕያን ሀብተ ንሰሐ በልቦናየ መዝገብ አከማቹ ለመንግስታችሁም ከዓይኔ የሚወደደዉን የዕንባ ግብር አገባ ዘንድ በፍቅራችሁ ሰዉን ደስ እንዳሰኝ ፍቅር አንድነትን ስጡኝ።

26 ለኩርናዕክሙ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ የጸላዒ ዳቢሎስን ክርን ለሰባበረ ለአደቀቀ ኃይለ ኩርናዓችሁ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ ያለድካም የቸርነት ገበሬወች እንደሆናችሁ መጠን የይቅርታ ዘራችሁን የባህርይአችሁን ፍቅር ስንደን አድርጋችኋልና ወርሃ ዘርን በማስቀደም ወርኃ ማዕረርን በማስከተል በእርሻችሁ የሰዉ ልቦና ዉስጥ የዕዉነት አዝመራ ሰመረ አፈራ።

27 ለእመታቲክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ሰማይና ምድርን በማይመረመር ስልጣኑ የሚመጥን የሚከነዳ መለኮታዊ ክንዳችሁ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ ሚስኪኑ ድሀዉ አልአዛር በነነዌ ደጅ ወድቆ እየጋረ እየጣረ ምጽዋትን በለመነ ግዜ እንደተሳለቀበትና የገንዘብ ፍቅር ከአታለለዉ ከአረጀዉ ከባለፀጋዉ የስስት ልብስ ልማድ አላቀዉ (አዉልቀዉ) በአማረ በአዲስ የሐር ግምጃ ምጽዋት አስጌጡኝ።

28 ለእራኃቲክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ዓለምን እንደ ዕንቁላል በያዘ መለኮታዊ መዳፍችሁ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ ቅድመ ዓለም የነበራችሁ ዛሬም ያላችሁ ለዘለዓለሙ በአንድነት በሦስትነት ጸንታችሁ የምትኖሩ እናንተ ብቻ ናችሁና ኤልያስ ከእርሻ የአንዱን ትልም የሚያረካ ዝናምን ለማዝነም ቢከለክለኝ እንኳ እናንተ ግን በልቦናየ እርሻ ላይ ሰላም ዝናማችሁን አዝንሙልኝ።

29 ለአጸብዒክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ከጽፍሮቻችሁ ላልተለዩ መለኮታዊ መዳፍችሁ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ እዱስ ሆይ መለኮታዊ ባህርይ አዳራሻችሁ ንብረቱ የማይጎድልበት ገንዘብ የማያልቅበት ነዉና በደሉ ኃጢአቱ ከድህነት ላይ ከጣለዉ በኋላ የሰዉን ልጅ (አዳምን) በአበለጸጋችሁት(በአፀናችሁት) ጊዜ የሰማይ መላዕክት ከአሁን በፊት ያላዩትን ችሮታ አዩ። ስለሆነም መላዕክት የሰዉ አገልጋዮች ተባሉ።

30 ለገበዋቲክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ የወርቅ ልብስ አስፈላጊያቸዉ ላይደለ መለኮታዊ ጎኖቻችሁ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ ዳሩ ግን ባሕርያችሁ በሚያስፈራ በሚያስደነግጥ ልብስ መብረቅ የተሰወረ ነዉ እንጂ። አቤቱ መንገድ ጠራጊዉ መጥምቁ ዮሀንስ በጠረገዉ የረቂቅ ጎዳና ጊዜ ወንጌል መንግሥታችሁ።ጻድቁ ቆርነሌዎስ በተጓዘበት ወደምጽዋት ጎዳና ምራኝ።

32 ለከርስክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ የፍጡራንን ሁሉ ሆድ (ከርስ) ለፈጠረ ለማይመረመር ከርሳችሁ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ በጽርሐ አርያም ባለ ዙፍናችሁ ሳላችሁ በዓለሙ ሁሉ ሙሉዓን ናችሁ። ለሌላዉ ወገን ምክር የማያሻዉ ባህርይ መለኮታችሁ በላይ በሰማይ ሳለ የምድርምን መሰረት ይመረምራል ይቆጣጠራል። የምድርንም መሰረት አምድ ተሸክም በላይ በሰማይ ይኖራል።

33 ለልብክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ የአስተሳሰብ ልዩነት ለሌለበት ልቦናችሁ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ አዳም ከእኛ እንደኛ አንዱ ሆነብላችሁ እንደተናገራችሁ መጠን አንድት ስግደት ሰገድላችኋል። አቤቱ የመንግሥታችሁ ድምፀ መለኮት በአደባባይ በተሰማ ጊዜ ሰባልዩስ ሁከት ፀጥ አለ የምገዱ ማዕበል ጠፋ ።

34 ለኩልያቲክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ በህላዌ አካል ትክክል ለሚሆኑ ኩልያቶቻችሁ ሰላምታ ይገባል።
ሥሉስ ቅዱስ ሆይ ከእናንተ ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል እግዚአብሔር ቃል ይቅርታ ለማድረግ ለምን በጎበኘ ጊዜ የአባቶች ተስፍ በድንግል ማርያም ተፈፀመ የነፃነት አርማ መስቀል በቀራኒዮ አደባባይ ተተከለ።

35 ለኅሊናክሙ
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ በጎ ሀሳብ በቸርነቱ ለሚታወቀዉ ኅሊናችሁ ሰላምት ይገባል።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †††

††† እንኳን ለጻድቅ ሰው "ቅዱስ ኢያቄም" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችኹ †††

+*" ቅዱስ ኢያቄም "*+

=>ቅዱስ ሰው ኢያቄም የሰማይና የምድር ንግስት እመቤታችን ድንግል ማርያም አባት ነው:: ቅዱሱ ከቅስራ አባቱ የተወለደ የቅዱስ ዳዊት ዘመድ ሲሆን "ኢያቄም : ሳዶቅ እና ዮናኪር" በሚባሉ 3 ሰሞቹ ይታወቃል::

+ቅዱስ ኢያቄም እንደ ኦሪቱ ሥርዓት አድጎ : ከነገደ ሌዊ የተወለደች : የማጣትና ("ጣ" ጠብቆ ይነበብ) ሔርሜላን ልጅ ሐናን አግብቷል:: ሁለቱም በንጽሕናና በምጽዋት እንደ ሕጉ ቢኖሩም መውለድ የማይችሉ መካኖች ነበሩ::

+በዚሕ ምክንያት ከወገኖቻቸው ሽሙጥን ታግሰው በታላቅ ሐዘን ኑረዋል:: ከጊዜ በሁዋላ ግን ስም አጠራሯ የከበረ : ደም ግባቷ ያማረ ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ እግዚአብሔር መረጣቸውና ከተባረከ ሰውነታቸው ድንግል ማርያምን ወለዱ::

+እርሷ "ወላዲተ አምላክ" ተብላ እነርሱን "የእግዚአብሔር የሥጋ አያቶች" አሰኘቻቸው:: ቅዱስ ኢያቄም እመቤታችንን ቤተ መቅደስ ካስገቡ ከጥቂት ዓመታት በሁዋላ በመልካም ሽምግልና አርፎ ከቅድስት ሐና ጋር በጌቴሴማኒ ተቀብሯል::

+ቅዱሱ ሰው ያረፈበት ዓመት ግልጽ ባይሆንም ድንግል እመቤታችን 8 ዓመት ሲሞላት 2ቱም ቅዱሳን ወላጆቿ በሕይወተ ሥጋ እንዳልነበሩ አበው ነግረውናል:: በማረፍ ደግሞ ቅድስት ሐና ትቀድማለች:: መቃብሩ ዛሬ ድረስ አለ:: ያደለው ከቦታው ደርሶ ይሳለመዋል::

=>አምላካችን ከቅዱስ ኢያቄም በረከት ያሳትፈን::

=>ሚያዝያ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ኢያቄም (የድንግል ማርያም አባት)
2.ቅዱስ አጋቦስ ሰማዕት
3.ቅድስት ቴዎድራ ሰማዕት
4.ቅዱስ አባ መቅሩፋ ጻድቅ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)
2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)
4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት
5.አባ ባውላ ገዳማዊ
6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)

=>+"+ መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው::
ከያዕቆብ ድንኩዋኖች ይልቅ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል::
የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ በአንቺ የተደረገው ነገር ድንቅ ነው . . .
ሰው እናታችን ጽዮን ይላል::
በውስጥዋም ሰው ተወለደ::
እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት:: +"+ (መዝ. 86:1-6)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የማይቀርበት ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ

✝️ ጉባኤ ወራዙት በአቃቂ ✝️


በዚህ ዘመን በዚህ ጊዜ የቤተክርስቲያንን ድምፅ የምንሰማበት ወቅት ስለሆነ እንዲሁም ወጣትነታችንን ለእግዚአብሔር ቃል የምንሰጥበትና በቸልተኝነት ፣ ያለአግባብ ፣ በከንቱ የምናሳልፈውና የምናባክነው ጊዜ ትተን ወደዚህ ቅዱስ ስፍራ እንገኝ  የአቃቂ ቃሊቲ ወጣቶችና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት በአቃቂ ጥምቀተ ባሕር ግቢ ሚያዚያ 13 ታላቅ ጉባኤ ተዘጋጅቷል በእለቱም ብፁዐን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የገዳማት አስተዳዳሪዎች መምህራን ሰባኪዎች ዘማርያን እና ልዩ እንግዳዎች ይገኙበታል 
እርሶ በቀጠሮዎ ቀን ጉባኤው ላይ ይሳተፉ ዘንድ ተጋብዘዋል

እንኳን መቅረት ማርፈድ ያስቆጫል


ሼር ሼር ፖስት በማድረግ ተደራሽ እንዲሆን ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ያደርሱ ዘንድ ኅላፊነታችሁን ተወጡ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ኦሪትዘዳግም ምዕ 23:1-4 ያለውን እስኪ ግልጽ አድርጉልኝ እውቀቱ ያላችሁ?

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ቅዱስ ዳዊት ታላቅና ገናና የከበረ ንጉሥ ከመሆኑ የተነሣ መንግሥቱ የመሢሕ መንግሥት ምሳሌ ሆኗል፤ መሢሑም ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዳዊት ስም ብዙ ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅሶ ይገኛል። (ኢሳ 9፡7፣ ኤር 23፡5-6፣ ኤር 33፡14-17፣ ሕዝ 34፡23፣ ሆሴዕ 3፡5) በሐዲስ ኪዳንም ወንጌላዊያኑ ጌታችንን ‹‹የዳዊት ልጅ›› በማለት ነው መጀመሪያ ነገረ ልደቱን ማውሳት የጀመሩት፡፡ ማቴ 1፡1፡፡ ራሱ ጌታችንም ‹‹እኔ የእሴይ ሥርና የዳዊት ዘር ነኝ›› ብሏል፡፡ ራእ 22፡16፡፡

ቅዱስ ዳዊት 7 ሀብታት የተሰጡት ጻድቅ አባት ነው፡፡ እነዚህም የተሰጡት ሀብታት፡- ሀብተ ክህነት፣ ሀብተ መንግሥት፣ ሀብተ መዊዕ (የማሸነፍ ሀብት)፣ ሀብተ ትንቢት፣ ሀብተ ኃይል፣ ሀብተ በገና (ዝማሬ) እና ሀብተ ፈውስ ናቸው። ቅዱስ ዳዊት 24 ሰዓት ሙሉ የእግዚአብሔር ምስጋና እንዳይቋረጥ መዘምራንን መድቦ እንዲያገለግሉ ያደርግ ነበር፡፡ ራሱም 10 አውታር ባለው በገና ሌት ተቀን በፍጹም ተመስጦ ያመሰግን ነበር፡፡ በመዝሙሩም አጋንንትን ያቃጥል ነበር፡፡ መዝሙረ ዳዊት በውስጡ የያዘው ሚሥጢር እጅግ ጥልቅ ነው፡፡ አባቶቻችን ዛሬም በዱር በጫካ ሆነው መዝሙረ ዳዊትን አብዝተው ይደግማሉ፡፡ እንኳንስ የሰው ልጅ ይቅርና ‹‹መዝሙረ ዳዊትን›› ሰማያውያን ቅዱሳን መላእክትም እግዚአብሔርን ለማመስገኛነት ተጠቅመውበታል፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እድሜ ዘመኑን እግዚአብሔርን በማገልገልና በመፍራት ኖሮ በታኅሣሥ 23 ቀን በሰላም ዐርፎ በኢየሩሳሌም ተቀብሯል፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ግብፃዊት_ቅድስት_ማርያም

በዚህች ቀን በበረሀ የምትኖር ግብፃዊት ማርያም አረፈች። ይቺም ቅድስት ከእስክንድርያ አገር ሁና ወላጆቿ ክርስቲያን ናቸው። እድሜዋ አስራ ሁለት አመት በሆናት ጊዜ የመልካም ስራና የሰው ሁሉ ጠላት ሸንግሎ አሳታት በእርሷም የማይቆጠሩ የብዙዎችን ነፍስ አጠመደ እርሱ ሰይጣን ስለ ዝሙት ፍቅር ያለ ዋጋ ስጋዋን እስከ መስጠት አድርሷታልና።

በዚህም በረከሰ ስራ ውስጥ ኖረች በየእለቱም የኃጢአት ፍቅር በላይዋ ይጨመርባት ነበር። ሰውን የሚወድ የእግዚአብሔርም ቸርነት ወደ ክብር ባለቤት ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ሊባረኩ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ የሚሹ ሰዎችን ገለጠላት።

ከእሳቸውም ጋራ ትሄድ ዘንድ ልቧ ተነሳሳ ከብዙ ሰዎችም ጋራ በመርከብ ተሳፈረች። ባለ መርከቦችም የመርከብ ዋጋ በጠየቋት ጊዜ ስለ መርከብ ዋጋ ያመነዝሩባት ዘንድ ሰውነቷን ሰጠቻቸው ኢየሩሳሌምም እስከ ደረሰች ይህን ስራ አልተወችም።

የክብረ ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ወደ አለች ቤተ ክርስቲያን ትገባ ዘንድ በወደደች ጊዜ መለኮታዊት ኃይል መግባትን ከለከለቻት። እርሷም ከሚገቡ ሰዎች ጋራ ትገባ ዘንድ ብዙ ጊዜ ደከመች ነገር ግን ከለከላት እንጂ የጌታ ኃይል አልተዋትም።

ከዚህም በኃላ ስለ ረከሰ ስራዋ አሰበች በልቧም እያዘነችና እየተከዘች ወደ ሰማይ ወደ እግዚአብሔር አይኖቿን አቀናች በማንጋጠጥዋም ውስጥ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ስእል አየች።

በፊቷም አለቀሰች ፍጥረቶችን ሁሉ የምትረጅአቸው አምላክን የወለደሽ እመቤቴ ተዋሽኝ ከሁሉ ሰዎች ጋራ ገብቼ የመጣሁበትን ስራዬን የፈፀምኩ እንደሆነ ያዘዝሽኝን ሁሉ እኔ አደርጋለሁ ብላ በማመን ለመነቻት።

ቤተ ክርስቲያን ፈጥና ገባች በገባችም ጊዜ የበአሉን ስራ ፈፀመች። ከዚህም በኋላ አምላክን ወደ ወለደች ወደ እመቤታችን ወደ ከበረች ድንግል ማርያም ስእል ተመልሳ ወደ እርሷ መሪር ልቅሶ እያለቀሰች ረጅም ፀሎትን ፀለየች ነፍሰዋን ለማዳን እርስዋ ወደ ወደደችው ትመራት ዘንድ አምላክን ከወለደች ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ስእል ከዮርዳኖስ በረሀ ብትገቢ አንቺ እረፍትንና ድኀነትን ታገኚ አለሽ የሚል ቃል ወጣ።

ከእመቤታችን አምላክን ከወለደች ከቅድስት ድንግል ማርያም ስእል ይህን ቃል ተቀብላ ወድያውኑ ወጣች። በውጪም አንድ ሰው አግኝታ ሁለት ግርሽ ሰጣትና አምባሻ ገዛችሸት።

ከዚያም በኋላ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግራ ፅኑእ ተጋድሎ እየተጋደለች በበረሀው ውስጥ አርባ ሰባት አመት ኖረች ሰይጣንም አስቀድማ በነበረችበት በዝሙት ጦር ይዋጋት ነበር።

እርሷ ግን በተጋድሎ ፀናች ከዚያም ከገዛችው አምባሻ ብዙ ቀን ተመገበች። ሁለት ሁለት ቀን ሶስት ሶስት ቀን ፁማ ከዚያ አምባሻ ጥቂት ትቀምስ ነበር በአለቀም ጊዜ የዱር ሳር ተመገበች።

በዚያችም በዮርዳኖስ በረሀ እየተዘዋወረች አርባ አባት አመት ሲፈፀምላት እንደ ገዳሙ ልማድ የከበረች አርባ ፆምን ሊፈፅም ቅዱስ ዘሲማስ ወደዚያች በረሀ መጣ። በሱ ደብር ላሉ መነኲሳት ልማዳቸው ስለሆነ በየአመቱ ወደ በረሀ ወጥተው የከበረች የአርባ ቀን ፆም እስከ ምትፈፀም በፆምና በፀሎት ተፀምደው በገድል ይቆያሉ።

ስለዚህም ዘሲማስ ወደ ዮርዳኖስ በረሀ በወጣ ጊዜ የሚፅናናበትን ያሳየው ዘንድ እግዚአብሄርን ለመነው። በበረሀውም ውስጥ ሲዘዋወር ይቺን ቅድስት ሴት ከሩቅ አያት የሰይጣን ምትሀት መሰለችው በፀለየም ጊዜ ከሰው ወገን እንደሆነች ተገለጠለችለት።

ወደርሷም ሄደ እርሷ ግን ከእርሱ ሸሸች ወደርሷም ይደርስ ዘንድ ከኃላዋ በመሮጥ ተከተሉት። ከዚህም በኃላ ዘሲማስ ሆይ ከእኔ ጋራ መነጋገር ከፈለግህ ጨርቅን በምድር ላይ ጣልልኝ እከለልበት ዘንድ ብላ በስሙ ጠራችው።

በስሙ በጠራችውም ጊዜ እጅግ አድንቆ ጨርቁን ጣለላት ያን ጊዜም ለብሳ ሰገደችለት እርሱም ሰገደላት እርስበርሳቸውም ሰላምታ ተሰጣጥተው በላዩዋ ይፀልይላት ዘንድ ለመነችው እርሱ ካህን ነውና ካህን ሰለሆነ።

ከዚህም በኋላ ገድሏን ታስረዳው ዘንድ ቅዱስ ዘሲማስ ለመናት ከእርሷ የሆነውን ሁሉ ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ነገረቸው። እርሷም በሚመጣው አመት የክብር ባለቤት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስጋውንና ደሙን ከእርሱ ጋራ ያመጣላት ዘንድ ለመነችው እርሱም እሺ አላት።

ዓመትም በሆነ ጊዜ ስጋውንና ደሙን በፅዋ ውስጥ ያዘ ደግሞ በለስ ተምርንና በውኃ የራሰ ምስርን ይዞ ወደርሷ ወደ ዮርዳኖስ በረሀ መጣ ቅድስት ማርያምን በዮርዳኖስ ወንዝ ዳር ስትሄድ አያት ወደርሱም ደርሳ እርስበርሳቸው ሰላምታ ተሰጣጡ በአንድነትም ፀለዩ ከዚህም በኃላ ስጋውንና ደሙን አቀበላት።

በለሱን ተምሩንና ምስሩንም አቀረበላትና ትመገብለት ዘንድ ለመናት ስለ በረከት ከምስሩ በእጇ ጥቂት ወሰደች። ደግሞም በሁለተኛው አመት ወደእርሷ ይመለስ ዘንድ ለመነችው። ሁለተኛ አመትም በሆነ ጊዜ ወደዚያ ወደ ዮርዳኖስ በረሀ መጣ ያቺ ቅድስት ሴት ሙታ አገኛት በራስጌዋም ድኀዪቱን ግብፃዊት ማርያምን ከተፈጠረችበት አፈር ውስጥ ቅበራት የሚል ፅሁፍ አገኘ። ከፅሁፉ ቃልም የተነሳ አደነቀ።

ያን ጊዜም ከግርጌዋ አንበሳን ሲጠብቃት አየ እርሱ መቃብርዋን በምን እቆፍራለሁ ብሎ ያስብ ነበር በዚያም ጊዜ ያ አንበሳ በጥፍሮቹ ምድሩን ቆፈረ የከበረ ዘሲማስም በላይዋ ፀሎት አድርጎ ቀበራት።

ወደ ገዳሙም ተመልሶ ለመነኮሳቱ የዚችን የከበረች ግብፃዊት ማርያምን ገድሏን እንዳስረዳችው ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ነገራቸው እጅግም አደነቁ ምስጉን ልኡል እግዚአብሄርንም አመስገኑት። መላው እድሜዋም ሰማንያ አምስት ሆኗታል።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ሚያዝያ_6

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሚያዝያ ስድስት በዚህችም ቀን #የአባታችን_አዳምን እና #የእናታችን_ሔዋን መታሰቢያቸውን ነው፣ ከአባታችን አዳም ጀምሮ አሥረኛ ትውልድ የሆነ #ጻድቁ_ኖኅ ልደቱ ነው፣ ንጉሡ ልበ አምላክ #ቅዱስ_ዳዊት ልደቱ ነው፣ በበረሀ የምትኖር #ግብፃዊት_ማርያም አረፈች፣ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትንሣኤው ሳምንት #ለሐዋርያው_ቶማስ ተገለጠለት፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱሳን_አዳምና_ሔዋን

ሚያዝያ ስድስት በዚህችም ቀን የአባታችን አዳምን የእናታችን ሔዋንን መታሰቢያቸውን እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙን። ይህን አባታችን አዳምን ሳይፈጥረው አስቀድሞ በሰማይና በምድር ያለውን አዘጋጀለት። ሐዋርያው ጳውሎስ እንደተናገረ መላእክትንም ስለርሱ ፈጠረ።

ከዚህም በኋላ በኤዶም ተክልን አዘጋጀለት እርሱም የፍሬው ጣዕም በየራሱ ልዩ ነው የሚአሻውን ሁሉ አከናውኖ እነሆ ከምድር መካከል ይኸውም ጎልጎታ ነው አፈር አንሥቶ በሦስት ሰዓት እርሱን ፈጠረው። ከአራት በሕርያት ይኸውም ውኃ እሳት ነፋስና መሬት ነው በአርአያውና በምሳሌው ራሱን አስመስሎ ፈጠረው በፊቱም እፍ ብሎ የሕይወት መንፈስን አሳድሮ የሚናገርና የሚያስተውል የሚያውቅ አደረገው የብርሃንንም ልብስ አልብሶ ንጉሥ ነብይ ካህን አስተዳደሪ አድርጎ በፈጠረው ሁሉ ላይ ሾመው።

ከዚህም በኃላ አይቶ ስማቸውን ይሰይም ዘንድ አራዊትን እንስሳትን የሰማይ ወፎችን ሁሉ ወደርሱ አመጣ። አዳምም መንፈስ ቅዱስ እንዳናገረው ለሁሉም ስም አወጣላቸው። ከዚህም በኃላ በአዳም ላይ እንቅልፍን አመጣበትና አንቀላፋ ከጐኑም አንድ ዐጥንትን ነሣ ቦታዋንም በሥጋ መላው እግዚአብሔርም ሴት አድርጎ አሰምሮ ሠራት በአዳምም በፊቱ አኖራት። አዳምም ነቅቶ ይቺ ከዐጥንቴ ዐጥንት ከሥጋዬ ሥጋ ናት ሚስት ትሁነኝ ብሎ ተናገረ ስሟንም ሔዋን አላት።

አዳምም በጎልጎታ ቁሞ የፈጣሪውን ቃል እየሰማ ሳለ እነሆ ከሚስቱ ከሔዋን ጋራ በፊት በኋላ ሁነው በየነገዳቸው አዳምን ስለ አከበረው መላእክት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ደመና ተሸክማ ወሰደቻቸው በኤዶም ገነትም አኖራቸው።

እግዚአብሔርም አዳምንና ሔዋንን በገነት ካለው ተክል ሁሉ ብሉ ግን ከገነት መካከል ዕፀ በለስን አትቡሉ ከእርሱ በበላችው ቀን ሞትን ትሞታላችሁ አላቸው። አዳምም ገነትን እያረሰና እየቆፈረ ከፍሬዋም እየተመገበ ከመላእክት ጋራ ሲያመሰግን ኖረ።

የበጎ ሥራ ጠላት ሰይጣን ግን ከማዕርጉ በወደቀ ጊዜ በአዳም ጌትነትና ክብር ቀንቶ በእባብ አድሮ ወደሔዋን ሔደ። ያንን ዕፀ በለስንም ትበላ ዘንድ አታለላት አምላክ የመሆንንም ተስፋ አሳደረባትና አሳታት።

ያንን ዕፀ በለስንም በአየችው ጊዜ አማራት በልታ ለባልዋም አበላችው ያን ጊዜ የብርሃን ልብሳቸው ከላያቸው ተገፈፈ። እነርሱም ራቁታቸውን እንደሆኑ አውቀው በበለስ ቅጠል ኀፍረተ ሥጋቸውን ሸፈኑ። እግዚአብሔርም ስሕተታቸውን አውቆ አስቀድሞ እባብን ረገመ በእርሷና በሴቲቱ ዘር መካከል ጠላትነትን አጸና።

በሔዋንም ላይ በፃር በገዐር ውለጂ ወልደሽም መመለሻሽ ወደባልሽ ይሁን እርሱም ይግዛሽ ብሎ ፈረደባት። አዳምንም እንዲህ አለው ስለ አንተ ምድር የተረገመች ትሁን ጥረህ ግረህ እንጀራህን ብላ አንተ አፈር ነህና ወደ አፈርነት ትመለሳለህ።

እግዚአብሔርም የቁርበትን ልብስ አዘጋጅቶ አለበሳቸው ሰባት ዓመት በተድላ ከኖሩ በኃላ በምሽት ጊዜ ከኤዶም ገነት ወጡ። አዳምም በማለዳ ፀሐይ ሲወጣ ነጭ ዕጣን ቀንዓት ሰሊሖት የሚባል ሽቱ ከሎሚ ውኃ ጋር አጠነ። አዳምም በኤዶም ገነት እንደተማረ ምድሪቱን እያረሰና እየቆፈረ ኤልዳ በሚባል ምድር ኖረ።

አዳምም ሔዋንን በግብር አወቃት ቃየልን ከእኅቱ ጋር ወለደችለት ከእርሱም በኃላ አቤልን ከእኅቱ ጋራ ወለደችው ቃየልና አቤልም አድገው አካለ መጠን አደረሱ። ወደ እግዚአብሔርም መሥዋዕት በአቀረቡ ጊዜ ጌታ የአቤልን መሥዋዕት ተቀበለ ስለዚህም ቃየል ተቆጣ በአቤልም ቀንቶ ገደለው።

አዳምም በልጁ በአቤል ሞት እያዘነና እያለቀሰ አራት የዘመን ሱባዔ ኖረ። ከዚህም በኋላ ሴት ተወለደለት በእርሱም መታሰቢያው ጸና ከእርሱም በኃላ ብዙዎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።

እግዚአብሔርም ንስሓውንና ልቅሶውን አይቶ የድኅነት ተስፋ ሰጠው። አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም ወደ ዓለም መጥቼ ከልጅ ልጅህ እወለዳለሁ ሕፃንም ሆኜ በሜዳህ ውስጥ እድሀለሁ በመስቀሌና በሞቴም አድንሃለሁ አለው።

አዳምም ከገነት በወጣ ጊዜ የወሰደውን ወርቅ ከርቤና ዕጣን ለልጁ ለሴት ሰጠው እንዲህም አለው በኃላ ዘመን የእግዚአብሔር ልጅ መጥቶ ከድንግል ይወለዳል ያን ጊዜ የጥበቡ ሰዎች ይህን ወርቁን ከርቤውንና ዕጣኑን እጅ መንሻውን ያመጡለታል እርሱም መዝግቦ በዕቃ ቤት አኖረው።

ወደ ኖኅም እስኪደርስ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ ኖረ ከኖኅም የምሥራቅ ሰዎች ወደ ሆኑ የጥበብ ሰዎች እስኪ ደርስ ተላለፈ። እነርሱም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ በተወለደ ጊዜ አምጥተው ለእግዚአብሔር ልጅ እጅ መንሻ አድረገው አቀረቡለት እመቤታችንም ከእጃቸው ተቀበላ በኃላ ለቅዱስ ጴጥሮስ ሰጠችው ቅዱስ ጴጥሮስም ለቀሌምንጦስ ሰጠው።

አዳምም የሚያርፍበትን ሰዓት በአወቀ ጊዜ ልጁ ሴትን ጠርቶ ከመሞቴ በፊት ልጆችህንና የልጅ ልጆችህን ወደእኔ አቅርባቸው አለው። የአባቱን ቃል ሰምቶ ዕንባው በጉንጩ ላይ እየፈሰሰ ወጣ ወደ አዳምም አቀረባቸው።

አዳምም በአያቸው ጊዜ ከእሳቸው ስለ መለየቱ አለቀሰ። እነርሱም ሲያለቅስ በአዩት ጊዜ ሁሉም በአንድነት ወደ እግዚአብሔር በግምባራቸው ተደፍተው አለቀሱ ምድር እንዴት ትሸፈንሃለች ከዐይኖቻችንስ እንዴት ትሠወራለህ አሉ።

ከዚህም በኋላ አባታችን አዳም ሁሉን ልጆቹን ባረካቸው መረቃቸው። ልጁን ሴትን እንዲህ አለው ይቺ ዓለም ድካምና ችግርን የተመላች ናትና በእግዚአብሔር እየታመንክ ዕውነትን ንጽሕናን ጠብቅ ሰይጣን ወደ ሚያሳይህ ምትሐቱና ወደ ነገሩ አታዘንብል።

በሞትኩ ጊዜም ሥጋዬን ወስዳችሁ ሰሊክ ሚዓ በሚባል ሽቱ ገንዛችሁ በግምጃ ቤት አኑሩኝ የጥፋት ውኃ ይመጣ ዘንድ አለውና ፍጥረት ሁሉ ይሰጥማል ከስምንት ነፍስ በቀር የሚቀር የለም። ልጄ ሆይ ለወገኖችህ ቋሚ ሁነህ እግዚአብሔርን በመፍራት ጠብቃቸው የዕውነት መንገድንም ምራቸው ለስይጣንም እንዳይ ታዘዙና እንዳያጠፋቸው አደራ አስጠብቃቸው።

ልጆችህንና የልጅ ልጆችህን ከቃየል ልጆች ለያቸው አንድ ይሆኑ ዘንድ ከቶ አትተዋቸው ወደ ሥራቸውና ወደ ጨዋታቸውም አይቅረቡ። ከዚህም በኋላ ወደ ልጁ ወደ ሴትና ወደ ሔዋን መለስ ብሎ ያንን ወርቅ ከርቤና ዕጣን ከእርሳቸው ጋራ አኑረው ይጠብቁት ዘንድ አደራ አላቸው። እንዲህም አላቸው የጥፋት ውኃ በመጣ ጊዜ ሥጋዬን ከወርቁ ከከርቤውና ከዕጣኑ ጋራ ወደ መርከብ ያስገቡ ከዚያም በኋላ በምድር መካከል ያኑሩት።

ከብዙ ዘመናት በኋላም ያቺን አገር ይወርዋታል እሊህንም ወርቅ ከርቤና ዕጣን ከብዙ ምርኮ ጋር ይወስዱትና አካላዊ ቃል መጥቶ ሰው እስከሚሆን ድረስ በዚያ ይጠበቃል። ነገሥታትም ይዘው መጥተው ይገብሩለታል ወርቁ ስለ መንግሥቱ ዕጣኑ ስለ ክህነቱ ከርቤውም ማሕየዊት ስለሆነች ሞቱ ነው።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሚያዚያ 6/2016 #ፆመ_ኢየሱስ_6ኛ_ሳምንት_ገብርሄር

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን የአብይ ፆም 6ኛ ሳምንት #ገብርሔር :- ገብር ማለት አገልጋይ፣ሔር ማለት ቸር ማለት ነው

👉በማቴዎስ ወንጌል ምዕ 25 እንደተገለጸው ቸሩ ፈጣሪ እራሱን እንደ ባለፀጋ ሰይሞ ለሶስት ሰዎች #መክሊት ፀጋና በረከት እንደሰጣቸውና አንድ መክሊት የተሰጠው አንተ ያልዘራኸውን የምታጭድ ጨካኝ መሆንህን ስለማውቅ ደብቄ ያቆየሁትን መክሊትህን እንካ አለው

👉የተሰጠንን ፀጋ በተለይ ካህናት አብዝተን ለጌታ መመለስ እንደሚገባን ሲያስተምረን አንተ በትንሽ ያልታመንክ እንደሌሎቹ አብዝተህ እንኳን ልትሰጠኝ ባትችል ለለዋጮች አደራ ሰጥተህ ልታተርፈው ትችል ነበር አለው ስለዚህ #መክሊቱን ውሰዱበት አስር መክሊትም ላለው ስጡት ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታልና

👉ምዕመናን ከዚህ ምን እንማራለን #እግዚአብሔር በሰጠን ፀጋ ጤንነትና እውቀት ተጠቅመን በዚህ ዐቢይ ፆም የሰራዊት ጌታ የሚወደውን መልካም በጎ ምግባር ብቻ አብዝተን በመስራት ፈጣሪን ማስደሰት እንደሚገባን ያስተምረናል

👉እርሱ የሚያተርፈው ይህን ጊዜ ብቻ ነው ሌላውማ ምን ቸግሮት ስለሆነም በአንቃድዎ ልቦናና በሰቂለ ህሊና ትኩረታችንን ወደ ጌታ መልሰንና በንስሐ ታጥበን ሁል ጊዜ ልንፀልይና ልንሰግድ ይገባናል ቸሩ አንድ አምላክ ለሰው ዘር በሙሉ ምህረቱንና ረድኤቱን ይላክልን እኛም የተሰጠንን #መክሊት አትርፈንበት ታማኝ አገልጋይ ተብለን በጌታችን ታምነን የክብሩ ወራሾች እንድንሆን አምላካችን ይፍቀድልን "አሜን"

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🔔🔔🔔🔔🔔
➡️ቅኔ ለጀማሪዎች
➡️በ6/8/2016
➡️ከምሽቱ 3:00-5:00

ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
/channel/+cD8I6LHkvu5kMmY0
👍👍👍👍👍

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🔔🔔🔔🔔🔔
➡️ቅኔ ለጀማሪዎች
➡️በ6/8/2016
➡️ከምሽቱ 3:00-5:00

ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
/channel/+cD8I6LHkvu5kMmY0
👍👍👍👍👍

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን አምላካችን እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ ላረፈባት የመጀመሪያዋ ዕለተ ሰንበትና ለቅዱስ ሕዝቅኤል ነቢይ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† አምላካችን እግዚአብሔር በ6ቱ ቀናት 22ቱን ሥነ ፍጥረት ፈጥሮ በ7ኛዋ ዕለት ደክሞት ያይደለ ለእኛ ያስተምረንና ሰንበትን ይቀድስልን ዘንድ አረፈ::

ዕለተ ሰንበት ማለት አንዳንድ ልባቸውን ያሳወሩ ሰዎች እንደሚያወሩት የሥራ መፍቻ ቀን ሳትሆን:-
1.ከሥጋዊ ተግባራችን ታቅበን መንፈሳዊ ተግባራትን (6ቱ ቃላተ ወንጌልን) የምንፈጽምባት:

2.ለጊዜውም ቢሆን ጥቂት እርፍ ብለን አማናዊቷን ዕረፍተ መንግስተ ሰማያት የምናስብባት ዕለት ናት::

እንደ ቤተ ክርስቲያን ስርዓትም ለሰንበተ ክርስቲያን ቀዳሚውን ቦታ ሰጥተን ቀዳሚት ሰንበትንም እንደሚገባ ልንጠቀምባት ይገባል::

††† የሰንበት ጌታዋ: የምሕረትም አባቷ ጌታችን እግዚአብሔር ለዕረፍተ መንግስቱ የተዘጋጀን ያድርገን::

††† ቅዱስ ሕዝቅኤል ነቢይ †††

††† ነቢዩ ቅዱስ ሕዝቅኤል የነበረው ቅ/ል/ክርስቶስ በ500 ዓመት አካባቢ ሲሆን የጼዋዌ (ምርኮ) አባልም ነበር:: እሥራኤልና ይሁዳ ወደ ባቢሎን በምርኮ ሲወርዱ አብሮ ወርዷል:: ቅዱሱ ከ4ቱ ዐበይት ነቢያት አንዱ ሲሆን ሐረገ ትንቢቱም በ48 ምዕራፎች የተዋቀረ ነው::

በዘመኑ ሁሉ ቅድስናን ያዘወተረው ቅዱሱ ከደግነቱ የተነሳ በጸጋማይ (ግራ) ጐኑ ተኝቶ ቢጸልይ 600 ሙታንን አስነስቷል:: ወገኖቹ እሥራኤልንም ያለ መታከት አስተምሯል:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚህች ዕለት ታላቁን ራዕይ እንዳየ ታስተምራለች:: ነቢዩ በፈለገ ኮቦር ካያቸው ምሥጢራት እነዚህን ያነሷል:-
1.እግዚአብሔርን በዘባነ ኪሩብ ተቀምጦ ሲሠለስና ሲቀደስ አይቶታል:: የኪሩቤልንም ገጸ መልክእ በጉልህ ተመልክቷል:: (ሕዝ. 1:1)

2.በመጨረሻው ቀን ትንሳኤ ሙታን : ትንሳኤ ዘጉባኤ እንደሚደረግም ተመልክቷል:: (ሕዝ. 31:1)

3.እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ኆኅት ኅትምት/ኆኅተ ምሥራቅ (የምሥራቅ ደጅ) ሁና አይቷታል::

ይሕ የምሥራቅ ደጅ (በር) ለዘለዓለም እንደታተመ ይኖራል:: የኃያላን ጌታ ሳይከፍት ገብቶ: ሳይከፍት ወጥቷልና:: (ሕዝ. 44:1)
በመጨረሻ ሕይወቱ እሥራኤል ለክፋት አይቦዝኑምና ነቢዩን አሰቃይተው ገድለውታል::

††† ከነቢዩ በረከት አምላኩ ያድለን::

††† ሚያዝያ 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር ሰንበትን ቀደሰ
2.ቅዱስ ሕዝቅኤል ነቢይ
3.ቅዱስ ዲዮስቆሮስ (ክፉ ላለመናገር ድንጋይ ጐርሶ የኖረ አባት)
4.ቅድስት ታኦድራ
5.ቅዱስ አርሳኒ
6.ቅዱስ ያሬድ ካህን (ልደቱ)

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2.ቅዱስ ዻውሎስ ሐዋርያ
3.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጻድቅ (አባ ገብረ ሕይወት)
4.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
5.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ

††† "እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ: ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ: ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና:- በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ:: የማይጠፋም የዘለዓለም ስም እሰጣቸዋለሁ::" †††
(ኢሳ. 56:4-5)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

/channel/zikirekdusn
ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት)

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
ግስ አወራረድና ቅኔ ነገራ
(3/8/2016)
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
❤️❤️❤️❤️❤️
(
@GeezL73 )
መ/ር ጳውሎስ ብለው ያናግሩኝ።
+251915642585
ተመዝግበው ይማሩ

Читать полностью…
Subscribe to a channel