❤ ሌሎችም ከዛፍ ጫፍ ጫፉን እየቈረጡ በመንገድ ላይ ያነጥፉ ነበር። ይኽም ዘንባባ ብዙ ምሳሌ ያለው ነው፤ ይኸውም በእስራኤል ያለው ሰሌን፣ ተምር፣ ዘይት ነበርና ያነን ቈርጠው አመስግነውታል፤ ይኽም ምሳሌነት ያለው ነው፤ ይኽም ሰሌን እሾኻማ እንደኾነ ትእምርተ ኀይል ትእምርተ መዊእ አለኽ ሲሉ ነው፤ እሳት ለብልቦ ይተወዋል እንጂ እንደማያቃጥለው ባሕርይኽ አይመረመርም ሲሉ ነበር፡፡
♥ ዳግመኛም ከሰሌን ዝንጣፊ ጋር ተመሳሳይ ተምር ይዘዋል ይኽም ተምር ልዑል ነው አንተም ልዑለ ባሕርይ ነኽ ሲሉ፤ ፍሬው አንድ እንደኾነ አንተም ዋሕደ ባሕርይ ነኽ ሲሉ፡፡ በእሾኽ የተከበበ ነው ባሕርይኽ አይመረመርም ሲሉ ነበር፡፡
♥ የዘይት ዛፍ ነው ቢሉ ዘይት ጽኑዕ እንደኾነ ጽኑዐ ባሕርይ ነኽ ሲሉ፤ ብሩህ ነው ብሩሀ ባሕርይ ነኽ በትምህርትኽም የሰውን ልቡናን ታበራለኽ ሲሉ፤ ዘይት መሥዋዕት እንደሚኾን መሥዋዕት ትኾናለኽ ሲሉ ነበር፡፡
♥ “የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር” በማለት በአርያም መድኀኒት እንደኾነና እግዚአብሔር አብ “የምወድደው ልጄ ይኽ ነው” ብሎ መስክሮለት የመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ መርገመ ሥጋ
መርገመ ነፍስን የሚያርቅ በረከተ ሥጋን በረከተ ነፍስን የሚያድል መኾኑን ኹሉም መሰከሩለት፡፡
♥ በእጅጉ የሚደንቀው የ40 ቀን የ80 ቀን ሕጻናት የፈጠራቸው ጌታ በአህያና በውርንጫ ተቀምጦ ባዩት ጊዜ በንጹሕ አንደበታቸው አንደታቸው ረቶላቸው ጌታን ዘንባባ በመያዝ ሲያመሰግኑ በእጅጉ ይደንቅ ነበር፤ ነገር ግን ጸሐፍት ፈሪሳውያን ያደረገውን ድንቃ ድንቅ በመቅደስም ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ እያሉ የሚጮኹትን ልጆች ባዩ ጊዜ፥ ተቈጥተው እነዚህ የሚሉትን አትሰማምን? አሉት፤ ኢየሱስም፦ እሰማለሁ፤ ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራስህ አዘጋጀህ የሚለውን ቃል ከቶ አላነበባችሁምን? በማለት በሕጻናት እንደሚመሰገን የነርሱም ጌታ መኾኑን ከዳዊት መዝሙር በመጥቀስ ነገራቸው፡፡
♥ ሊቁ ያዕቆብ ዘሥሩግ ሰለዚኽ ምስጢር ሲገልጸው ፡- “ፍቅርኽ ከዘባነ ኪሩብ አውርዶ በአህያ ጀርባ ላይ እንድትቀመጥ አስገደደኽ፡፡ ብዙ ዐይንና ብዙ ገጽ ካላቸው ከሰራዊተ መላክእት ይልቅ በዲዳዋ አህያ ትመሰገን ዘንድ ወደደክ፡፡ በሰማይ ሰራዊት ሠረገላ ተቀምጠኽ ክብርኽን ማሳየት አልወደድክም፤ በውርንጫላይቱ ላይ ተቀምጠኽ ወደ ሰማይ ሰራዊት መኼድን መረጥክ እንጂ፡፡ በአርያም እሳታውያን የሚኾኑ ኪሩቤል ያመሰግኑኻል፤ በምድርም ሕፃናት ይዘምሩልኻል፡፡ በአርያም ብርሃናውያን መላእክት በብርሃን ክንፋቸው መንገድኽን ያነጥፉልኻል፤ በምድርም ደቀ መዛሙርትኽ ልብሳቸውን አንጥፈው መንገድኽን አስተካከሉ፡፡ ወዮ! አርያማዊ ሲኾን ምንም ሳይንቀን ይጐበኘን ዘንድ ከአባቱ መጣ፡፡ ርሱም በገዛ ፈቃዱ ሰው እስከ መኾን ደርሶ መጣ፡፡ በአህያ ላይ ተጭኖም ይጐበኘን ዘንድ መጣ፡፡ ነቢዩ ዘካርያስ የመንፈስ ቅዱስን እንዚራ ይዞ በደስታ ትንቢትን ለመናገር ይቻኰላል፡፡ እየደረደረም የጽዮንን ልጅ ይጠራታል፡፡” በማለት አስተምሯል፡፡
♥ የምስጋና ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያዋና በውርንጫዋ ላይ ተቀምጦ ሕፃናትን ጨምሮ ዘንባባ ሰሌን በያዙት ኹሉ “ሆሣዕና በአርያም” እየተባለ እየተመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበትን ታላቁን በዓል ከኹሉም ዓለም አስበልጣ በታላቅ ክብር የምታከብርና የምታስተምረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡
♥ ይኸውም ታላቁ የምስጋና ዕለት ሊደርስ ሲቃረብ ስንዱዋ እመቤት አስቀድማ በቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ የቊርባን ምስጋና፦
✍ “ቦአ ኀቤሃ እግዚአ አጋዕዝት ወመናፍስት እንዘ ይጼዐን ዕዋለ አድግ ትሑት…” (የአጋዕዝትና የመናፍስት ጌታ በተዋረደ አህያ ግልገል ተቀምጦ ወደ ርሷ ገባ፤ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ብሩክ ነው፡፡ አንተም የአማልክት አምላክ የእስራኤልም ንጉሥ እግዚአብሔር ቡሩክ ነኽ እያሉ ለሚያመሰግኑ ሕፃናት ኹሉ ጌትነቱን አሳየ፤ የሆሳዕናን ዑደት ለነርሱ ለደቀ መዛሙርቱ አሳየ፤ ቡርክ ርሱ በታላቅ ቃል እየጮኻችኊ ሆሣዕና በአርያም በሉ አላቸው፤ ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሳዕና በአርያም፤ ከመድኀኒትነቱ የተነሣ ከዚኽ አስቀድሞ ያልተደረገ ከዚኽም በኋላ የማይደረግ ተአምራትንና መንክራትን አሳየ፤ ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሳዕና በአርያም... ) በማለት መድኀኒትነቱን ስትሰብክ፤ ካህናትና ምእመናንም በአንድ ድምፅ በዚያ ዘመን የምስጋና ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በተመሰገነበት በዚኽ ልዩ ምስጋና “ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም” እያሉ በመዘመር፤ ፈጣሪያቸው ክርስቶስን ያመሰግናሉ።
💥 ከዚያም በዋዜማው፦
✍ “በዕምርት ዕለት በዓልነ ንፉሑ ቀርነ በጽዮን ወስብኩ በደብረ መቅደስየ እስመ ይቤ ዛቲ ዕለት በዓለ እግዚአብሔር ሆሣዕና በአርያም ቡሩክ አንተ ንጉሠ እስራኤል”
👉 (በታወቀች በበዓላችን ዕለት በጽዮን መለከትን ንፉ፤ በመቅደሴ ተራራም ስበኩ ይኽቺ ዕለት የእግዚአብሔር በዓል ናት፤ በአርያም መድኀኒት የተባልኽ የእስራኤል ንጉሥ አንተ ቡሩክ (መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስን የምታርቅ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስን የምታድል) ነኽ) በማለት ልዩ ምስጋናዋን ጀምራ እስከ ሌሊቱ ድረስ በልዩ ምስጋና እየሰበከችው በኋላም ቤተ መቅደሱን በውርጫዋ ተቀምጦ እንደዞረ በአራቱ መኣዝን የጌትነቱ ወንጌል እየተነበበ፤ ካህናቱን ምእመናንም በእጃቸው የዘንባባ ዝንጣፊን ይዘው “ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም” እያሉ ያመሰግኑታል፡፡
✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ተጻፈ
መልካም በዓል ይኹንልን።
የቴሌግራም ቻናሌ https://t.me/joinchat/AAAAAFTyR7tztt08pN9U-w
+++ከድካምሽ ተፈትተሻል!+++
ጽርሐ አርያም አዳራሹ ፤ የመላእክት መኖሪያ ቦታው የሚሆን ፤ በሰማይ ሆኖ በጥልቅ ባሕር ውስጥ ያለውን የሚያይ እርሱ ፤ ፊቱን ማየት ኪሩቤል የማይቻላቸው ፤ ነበልባሉ እንዳያቃጥላቸው በእሳት ክንፋቸው ፊታቸውን የሚጋርዱለት እርሱ ፤ በአህያ ጀርባ ላይ ተቀመጠ፡፡ የሰው ልጅ ሸክም ለመጫን በሚገለገልባት አህያ ላይ ‹‹እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።›› (ማቴ.11፡28) ያለው እርሱ ተቀመጠባት፡፡
ርቱዓ ሃይማኖት ስለዚህ ሲመሰክር ‹‹የሰማያት ርዝመት አንዱ ከአንዱ እስከ ሰማያት ድረስ እጥፍ ድርብ ነው ፤ ሰባተኛው ግን ከኹሉም ሰማያት ይልቅ ረጅምና ሰፊ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ዙፋን አርያምም ይህ ነው፡፡ ኹሉ ሰማያትም ከእርሱ በታች ናቸው፡፡ ነቢዩ ‹ልዑል እግዚአብሔር ከሰማያት ኹሉ በላይ ነው› ብሎ እንደተናገረ፡፡ በአህያ ውርንጭላ የተጫነውም እርሱ ነው›› ይላል፡፡ (ርቱዓ ሃይማኖት ገጽ 121 - 122)
ታዲያ ይህን ጌታ አህያዋ እንደምን መሸከም ቻለችው? ዓለምን የያዘውን ተሸክማ አትጎብጥምን? ብለህ ተጨንቀህ ከሆነ ፤ ወዳጄ ሆይ አባ ጊዮርጊስ እንዲህ ይልሃል ፤ ‹‹ቀላል ሸክም የለዘበም ቀንበር ኢየሱስ ክርስቶስ ነው›› [(‹‹አርዑት ሠናይ ወጾር ቀሊል ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ›› (መጽሐፈ ሰዓታት ገጽ 51)] ፤ ሸክም የሚበዛባት አህያን በሚያሸክሟት ሰዎች ፊት ሊያከብራት ወደደ ፤ ክርስቶስ ጎባጣውን ሊያቀና እንጂ ሸክም ሊያበዛ አልመጣም ይልሃል ቅዱስ አምብሮስ።
ይህንንም ሲያስረዳ ሊቁ አንድ ታሪክ ያስታውስሃል ፤ “በሰንበትም በአንድ ምኵራብ ያስተምር ነበር። እነሆም፥ ከአሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ የድካም መንፈስ ያደረባት ሴት ነበረች፥ እርስዋም ጐባጣ ነበረች ቀንታም ልትቆም ከቶ አልተቻላትም። ኢየሱስም ባያት ጊዜ ጠራትና። አንቺ ሴት፥ ከድካምሽ ተፈትተሻል አላት፥ እጁንም ጫነባት፤ ያን ጊዜም ቀጥ አለች፥ እግዚአብሔርንም አመሰገነች።” (ሉቃ. 13፡10-13)
በአህያዋ ላይ ተቀምጦ ያየኽው እርሱ አስቀድሞ ለአብርሃም ግዝረትን (ዘፍ. 17፡10) ፤ ለሙሴም በሲና ሕግጋትን የሰጠው ነበር ፤ በሦስተኛው ግን እርሱ ራሱ ወደ ቅድስት ድንግል ማርያም መጣ ሰው ሆነ ፤ ሦስት ስድስት ዓመታት ጎብጣ የኖረችውን ሴት ቀና አደረጋት ፤ ሦስት ዓመት ፍሬ ፈልጎ ያጣባትን ያቺን በለስ ወደ ተፈጥሮአዊ ማንነቷ መለሳት ቀጥ ብላ እንድትቆም አደረጋት፡፡ (Commentary of Saint Ambrose on the Gospel according to Saint Luke, 2001 A.D; Page 243-245) ስለዚህ አህያዋን ሊያከብራት እንጂ ሊያጎብጣት አልተቀመጠባትምና ስለ እርስዋ አትጨነቅ!
ይልቁን እንዲህ ብለህ ለምነው ፤ ‹‹ጌታዬ ሆይ ፤ አህያስ መታዘዝ አላት ፤ ቢገፏት ሸክም ቢያበዙባት ትዕግሥትና መቻል አላት ፤ አህያስ ጌቶቿን ታስደስታለች ታገለግላለች ፤ መታዘዝ የራቀኝ ትዕቢት የጸናብኝ ፤ የራሴ ሀሳብ ራሴን የገፋኝ ፤ የራሴ መሻትና ፍላጎት መልሶ እኔኑ ያስጨነቀኝ ፤ ቶሎ መጨበጥን ደርሶ ማግኘትን ብቻ በማሰብ ትዕግሥት ያጣኹኝ ፤ የአንተን ፈቃድ ከማገልገል ይልቅ ራሴን በማገልገል የባዘንኩኝ ልጅህን አስበኝ ፤ እሸከምህ ዘንድ በእኔ ላይም ታርፍብኝና ትመሰገንብኝ ዘንድ አንዳች የሚመች ነገር ባይገኝብኝም ፤ “አንተ ደካማ ሸክምህ የከበደ ወደ እኔ ና እኔም አሳርፍሃለሁ” ከሚለው አባታዊ ጥሪህ ግን አትለየኝ ፤ በተፈጥሮ ጌታዋ ለሆንኩ በሥራዬ ግን ከአህያ ላነስኩኝ ለእኔ ማስተዋልን ሥጠኝ!››
+++
Image Credit: orthochristian
ስብሐት ለእግዚአብሔር
@ዲያቆን ደረጀ ድንቁ
ሚያዝያ 19 2016 ዓ.ም
✝✝✝"""""ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ"""""✝✝✝
መምህሩ(ኒቆዲሞስ) ለመምህሩ(ክርስቶስ) በ እኩለ ለሊት ሰገደለት✝✝✝✝✝✝✝✝✝
ኒቆ❤
ሳምራዊቷ ሴት አጊያ ፎቲኒ ማንናት።
በመጽሐፍ ቅዱስ በዮሐንስ ወንጌል በም. 4: 1-42 ድረስ ታሪኳ ተጽፎ የምናገኛት በተለምዶ ሣምራዊቷ ሴት ስሟ ያልተጠቀሰ ነገር ግን በሀገሯ ስም፤ ባህልና አኗኗር የጠራች ናት። ሣምራዊት ስትባል ከየት እንደሆነች፤ ባህሏም አኗኗሯም ጭምር ምን እንደሚመስል ያስረዳል በርሷ የተነሳ የሳምር ከተማ ነዋሪዎች ምን እንደሚመስሉ ከጌታችን ጋር ባደረገችው ንግግር ማወቅ ይቻላል። እስራኤል ጥቢቡ ሰሎሞን በሰራው ኀጢአት በልጁ በርብዓም ዘመነ መንግሥት ለኹለት ሲከፈሉ እነሱም በሰሜኑ የእስራኤል ክፍል ተከፍለው ይኖሩ የነበሩ ናቸው። በኋም ባገኛቸው የአሕዛብ መንግሥት ወረራ የተነሳ ከይሁዲነት ፈልሰውም ከእምነታቸው ርቀው ከአሕዛብ ጋር ተጋብተው የሚኖሩ ባህላቸው፤ አኗኗራቸውና አምነታቸው ጭምር ከአሕዛብ በመዳቀሉ ሳምራውያን ተብለዋል ፍለሰትም ስላገኛቸው ከአይሁድ ጋር የማይተባበሩ ሆነዋል። ነገር ግን የመሲውን መውረድ፤ መወለድና መምጣት ይጠብቁ የነበሩ ናቸው። ከነዚህም ሕዝቦች ውስጥ ሣምራቷ ሴት በጎላ ታሪኳ መጽሐፍ ቅዱስ ተመዝግቦ ሲተረክ ይኖራል ስሟም ቅድስት ፎቲኒ፤ ፎቲና፤ ፎታይን ወይም ስቫትና በመባል የምትታወቅ ናት።
ይኸች ሴት ቀትር በሆነ ጊዜ ውሃ ለመቅዳት ወደ ያዕቆብ ጉድጓድ አምርታ የዘለዓለምን የሕይወት ውሃ ጠጥታ ለመመለስ ችላለች፤ ስለ ያዕቆብ ጉድጓድ ስለ አኗኗራቸው ከጌታችን ጋር በሰፊው አውግታለች ምናልባት ከሁሉ ቀድማ ከሐዋርያት ቀጥላ ማለት ይቻላል ከጌታችን እግር ስር ቁጭ ብላ ወንጌልን የተማረች ለእግዚአብሔር በእውነትና በመንፈስ የሚሰገድለት መሆኑን ያወቀች ናት። ብዙ ጊዜ ውሃ ልትቀዳ ሔደች እንጂ ምሥጢሩ ለምን እንደሆነ ቢርቅብንም ጌታችንም ግን እሷን ለማስተማር በሰማርያ ያልፍ ዘንድ ግድ ሆነበት ተባለ ይኽች ሴት በነገረ ሥጋዌ ውስጥ ስሟ ትልቅ ቦታ አለው።
አባታችን አብርሃም ቅድስት ሥላሴ በጊዜ ቀትር እንደተገለጠለት ለዚህችም ሴት በጊዜ ቀትር ተገለጠላት ለአብርሃም እወርዳለሁ እወለዳለሁ ሲለው ለእርሷ ግን ወረድኹ ተወለድኹ አላት። በቅድስት ሥላሴ ፈቃድ ለዓለም ስለተዘጋጀው እውነታ አወቀች።
ጊዜውም ቀትር ጊዜ ተፈጥሮተ ዓለምንና የድኅነተ ዓለምን መፈጸም የሚያጠይቅ ነው። በዕለተ አርብ ተጠማሁ ከማለቱ በፊት ለእርሷ ተጠማሁ አላት፤ ከሕይወት ውሃ እንድትጠጣ ፈቀደላት የእርሱንም መውረድ መወለድ የመንፈስ ቅዱስንም መሰጠት የእግዚአብሔር ሥጦታ፤ የሕይወት ውሃ ምንጭ በሚል አስተማራት። ዮሐ. 3፡16 ዮሐ. 14፡15
መሲው ይመጣል የሚለውን ትንቢት ይጠብቁ ስለ ነበር እርሷም ይኸንን ከአባቶቿ ስትሰማ ስለነበር እንደሰማችም መሲውን ማግኘቷን ሮጣ ለዘመዶቿና ለሳምራውያን በመንገሯ የመጀመሪያዋ የወንጌል ሰባኪ፤ ሐዋርያዊትና ወንጌላት ተብላም ትታወቃለች። ጌታችን ከእርሷ ስላደረገው ንግግር፤ እርሷን ለማግኘት ያደረገው ጉዞ፤ ስለእርሷ በመንግድ መድከሙና ያስተማራት ት/ት ለነገረ ሥጋዌና ለድኅነተ ዓለም መፈጸምን የሚያመለክት ስለሆነ ዘወትር ትታሰባለች። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመልክአ ሕማማት ሰላምታ ላይ ሲናገር "ዘሰአልከ ማየ እምነ ሣምራዊት ብእሲት፤ ከመ ትፈጽም ኲሎ ነገረ ትስብእት፤ እንዘ አንተ ማየ ሕይወት" ብሎ የሕይወት ውሃ ራሱ ሲሆን ነገረ ሥጋዌን ለመፈጸም ከእርሷ ውሃ መለመኑን ተናግሯል። ከእርሷ ውሃን ጠይቆ ለዘለዓለም እንዳትጠማ አደረጋት፤ ከርሃቧና ከጥሟ ፈወሳት አረካት። የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ፊላሬት እንዳተናገሩት ያለ መቅጃ ከዘለዓለም የሕይወት ውሃ ከእግዚአብሔር ሥጦታ፤ ከመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ተሳተፈች፤ ለእግዚአብሔር በእውነትና በመንፈስ እንደሚሰገድለትና እንደሚመለክ አወቀች።
እኛም እርሷን አርአያ አድርገን ከእግዚአብሔር ሥጦታ ከመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በመሳተፍ በእውነትና በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ እንድናመልከውና እንድሰግድለት ታሪኳን ሁል ጊዜ እናነባለን። ለቅዱስ ኒቆዲሞስና ለማርያም መግደላዊት ባስተማረበት አንጻር ለእርሷም አስተማራት፤ ራሱን አሳወቃት። ይኽችን ቅድስት በወቅቱም ከጌታችን ጋር በነበራት ግንኙነትና ጌታችን በእርሷ አማካኝነት ለዓለም ሁሉ ያስተማረውን ት/ት በማሰብ የምሥራቅ ኦርቶዶክስ አብያተክርስቲያናት በየዓመቱ ከትንሣኤው በኋላ በሚውለው አምስተኛው የፋሲካ ትንሣኤ የሣምራዊቷ ሴት ሰንበት በማለት አሰበዋት ይውላሉ። የእግዚአብሔርን ሥጦታና የሕይወት ውሃ ምንጭ ተብሎ የተናገራትን ከዚህ የተሳተፈች፤ የቀመሰች ስለነበር በዚህም በጠጣችው የሕይወት ውሃና ባገኘችው የእግዚአብሔር ሥጦታ የተነሳ ፍሬ አፍርታ ለምልማ በሮም ዘመነ መንግግሥት ከኹለት ወንድ ልጆችዋና ከሴት ልጆችዋ ጋር የሰማዕትነትን አክሊል ተቀብላ ስለ ክርስቶስ መስክራ አልፋለች። ጌታ ሆይ ከሕይወት ውሃ ምንጭ እንድንጠጣ ፍቀድልን፤ ከሥጦታኽም አስተሳትፈን ከመንፈስ ቅዱስ ጸጋም አድለን በእውነትና በመንፈስ እንድናመልክህ አድርጠን ቅዱሳን አባቶቻችንንና እናቶቻችንን እንድመስል አድርገን!!! የሰማዕቷና የቅዱሳን ልጆችዋ በረከት ይደርብነ።
ዲ/ን አበበ እሸቴ
ሚያዚያ 19/2016 #ቅዱስ_ገብርኤል
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና በፀሎት ለምንማፀንበት በመልአኩ ስም ለምናመሰግንበት ለመልአኩ #ቅዱስ_ገብርኤል ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉ገብርኤል ‘ገብረ’ እና ‘ኤል’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ የመልአክ ስም ነው #የእግዚአብሔር_ሰው ማለትም ነው
👉አብሳሪ መልአክ #ቅዱስ_ገብርኤል ሆይ እጅግ አፅናኝና አስደሳች የሆነውን ምስጢረ ሥጋዌን ዜና ይዘህ ከሰማይ ወደ ምድር እንደወረድክ #ድንግል_ማርያም የአምላክ እናት ለመሆን ፈቃድዋ ሆኖ በተፈጸመ ጊዜ ደስ እንዳለህ እኛም እግዚአብሔርን በማክበርና ግዴታችንን በመፈፀም ደስ የምንሰኝበትን ፀጋ አሰጠን
👉ጠባቂያችን #ቅዱስ_ገብርኤል ሆይ ሦስቱን ወጣቶች ከሚያቃጥል እሳት እንዳዳንካቸው እኛንም በዚህ ዓለም ከሚወራው ከሚታየውና ከሚሰማው #ክፉ_ቀንና_እለት ሁሉ አድነን እየነደደ የሚለበልበንን የኃጢያት እሳትም አጥፋልን
👉የኑሯችንን ቀጠሮ በክንፈ ረድኤትህ ከልለው ሰይጣን እንዳይሰለጥንብን ክፉ አድራጊዎች ሟርተኞች ሰላቢዎች ዘረኞችና ነፍሰ ገዳዮች እንዳያጠቁን ከልለን ያንተን የእሳት አጥር ዘሎ ጠላት ያጠቃን ዘንድ ጠላት አይችልምና #ጥበቃህ ከእኛ ከባርያዎችህ አይለየን
👉#ቅዱስ_ገብርኤል ሆይ ሕፃኑ ቂርቆስና እናቱ እየሉጣን በንፍር ውኃ ከመቀቀል እንዳዳንካቸው ልጆችህን በማናውቀው ሁኔታ የተዘጋጀልንን #የጥፋት_ወጥመድ ሁሉ አስወግድልን በላያችን ላይም በክፉ ሰዎች ምክንያት የተነሳብንን እሳት አጥፋልን
👉 #ለእውነተኛ_ሃይማኖት የጨከንንና የቆረጥንም አድርገን የሰይጣንን ፈተና የምናልፍበት እውነተኛውን ጥበብ እንደ ነብዩ ዳንኤል አስተምረን
👉 ቅዱስ #ገብርኤል ሆይ በደል በተገኘብን ቁጥር እያለቀስን እንጠራሃለን ጎስቋላ የምንሆን በጥቃትና በሀዘን ውስጥ የምንገኝ ልጆችህ የአንተን ማፅናናትና ረዳትነት እንፈልጋለንና ፈጥነህ ናልን
👉እናታችን #ማርያምን ያበሰርክ ለዓለም ሁሉ የምታበራ ገብርኤል ሆይ በሰራዊት አምላክ ፊት ዘወትር ትቆማለህና ፀሎትና ልመናችንን ስማ
👉ቅዱስ #ገብርኤል ሆይ ቀድመህ የደስታ የምሥራች ቃልህን ልታበስር ወደ ገሊላ እንደወረድህ ዛሬም ለአዘንንና ለእኛ ለቃል ኪዳን ልጆችህ ከሠማይ በሠረገላ ናልን የደስታንም ቃል አሰማን
👉እናታችን #ማርያምን ያበሰርክ ተወዳጁ መልአክ ቅዱስ #ገብርኤል ሆይ በምህረትና በይቅርታ ወደ እኛ ናልን ዓለም የጥፋት የሞት የክስረት የውድመትና የተስፋ መቁረጥ ድምፅን ያሰማናልና አንተ ግን ጉስቁልናችንን የሚያነሳ ስብራታችንን የሚጠግን እንባችንን የሚያብስ #የብስራት ድምፅህን አሰማን እንድንፅናናም አድርገን
👉እውነተኛ ጠባቂያችን ቅዱስ #ገብርኤል ሆይ እኛን ለማዳን ሰው የሆነውን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን ማደሪያው የሆነችው #ድንግል_ማርያምን በጣም እንወዳታለን
👉በዚህ ዓለም የምሥጢረ ሥጋዌ ተካፋዮች በመሆናችን #በመንግስተ_ሰማያትም ተካፋዮች ለመሆን ሁላችንንም በምልጃህ አብቃን ለምንልን #የእግዚአብሔር መልአክ #ቅዱስ_ገብርኤል ጥበቃህ ተራዳኢነትህ አይለየን
👉#ገብርኤል ሆይ ለሀገራችን ሠላምን ለህዝባችን ፍቅር አንድነትን ይሰጠን ዘንድ በአምላካችን #በክርስቶስ ፊት ቆመህ ለምንልን የሀገራችንና #የህዝቦቿ የቤተክርስቲያናችን ጠላቶችን አስታግስልን ጦርነትና ረሐብ ከምድራችን ላይ ይወገድ ዘንድ ለምንልን ጥበቃህ አይለየን የተባረከ #ቀዳሚት_ሰንበት ይሁንልን "አሜን" ✝️⛪️✝️
††† እንኩዋን ለታላቁ "ሐዋርያ ቅዱስ ያዕቆብ" ዓመታዊ
የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችኹ †††
+*" ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ "*+
=>በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ ከእመቤታችን
በቀር ከቅዱሳን ሐዋርያት የሚበልጥ አልተነሳም::
"ሐዋርያ" ማለት "ፍንው: ልዑክ: የተላከ: የጽድቅ
መንገደኛ" እንደ ማለት ነው:: በምሥጢሩ ግን "ባለሟል"
ብለው ሊቃውንቱ ተርጉመውታል::
+ይህስ እንደምን ነው ቢሉ:-
¤የፍጥረታት ሁሉ ጌታ: የክብር ባለቤት መድኃኔ ዓለም
ከድንግል ማርያም ተወልዶ: አድጐ: ተጠምቆ: ጾሞ:
ከገዳመ ቆረንቶስ ሲመለስ ቀዳሚ ሥራው ያደረገው ደቀ
መዛሙርቱን መጥራት ነበር::
+ከተከተሉት የ5 ገበያ ሕዝብ መካከል "ወሐረየ እምሰብአ
ዚአሁ አሠርተ ወክልኤተ ሐዋርያተ" እንዲል በመጀመሪያ
12ቱን ሐዋርያት መረጠ::
+እሊህም:-
1.ዼጥሮስ የተባለ ስምኦን
2.እንድርያስ (ወንድሙ)
3.ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ
4.ዮሐንስ (ወንድሙ)
5.ፊልዾስ
6.በርተሎሜዎስ
7.ቶማስ
8.ማቴዎስ
9.ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ
10.ታዴዎስ (ልብድዮስ)
11.ናትናኤል (ቀናተኛው ስምዖን) እና
12.ማትያስ (በይሁዳ የተተካ) ናቸው:: (ማቴ. 10:1)
+እነዚህን 12 አርድእቱን ከጠራ በሁዋላ ለ3 ዓመታት ከ3
ወራት ከዋለበት ሲማሩ ይውሉ ነበር:: ሌሊት ደግሞ
ምሥጢር ሲያስተረጉሙ ያድሩ ነበር::
+ጌታ እንደሚገባ ካስተማራቸው በሁዋላ ከፍ ያለ
ኃላፊነትን ሾማቸው:: ለዓለም እረኞች: የእርሱም
ባለሟሎች ሆኑ:: እጅግ ብዙ መከራ እንደሚገጥማቸው
ነገራቸው:: (ማቴ. 10:16, ዮሐ. 16:33) በዚያው ልክ
ክብራቸውንም አከለላቸው:: (ማቴ. 19:28)
+ሥልጣናቸው ደግሞ እስከዚህ ድረስ ሆነ:: "በምድር
ያሠራችሁት በሰማይ የታሰረ ይሆናል: በምድር የፈታችሁት
በሰማይ የተፈታ ይሆናል::" (ማቴ. 18:18) "ይቅር
ያላችሁዋቸው ኃጢአታቸው ይቀርላቸዋል: ያላላቹሃቸው
ግን አይቀርላቸውም::" (ዮሐ. 20:23)
+የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ (ማቴ. 16:19):
እረኝነትን (ዮሐ. 21:15) ተቀበሉ:: ጌታ በንጹሕ አንደበቱ
ሐዋርያቱን እጅግ ሲያከብራቸው "ጨው: የዓለም
ብርሃናት" (ማቴ. 5:13) አላቸው:: ወንድሞቹም ተባሉ::
(ዮሐ. 7:5) ከዚህም በሚበልጥ በሌላ ክብር
አከበራቸው::
+ከዚህ ሁሉ ነገር በሁዋላ በጌታ ሕማማት ጌዜ ገና
ነበሩና አንዳንዶቹ ፈርተው ተበተኑ:: ተመልሰው ግን
በጽርሐ ጽዮን ሲጸልዩ ሰንብተው የጌታን ትንሳኤ
ተመለከቱ:: እጆቹን: እግሮቹንም ዳስሰው ሐሴትን አደረጉ::
+ለ40 ቀናት መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓት: ሌላም
በፍጡር አንደበት የማይነገር ብዙ ምሥጢራትን ተምረው:
ጌታ ሊቀ ዽዽስናን ሹሟቸው ዐረገ::
+ለ10 ቀናት በእመ ብርሃን ሥር ተጠልለው ሲጸልዩና
በአንድ ልብ ሲተጉ ሰንብተው መንፈስ ቅዱስ ወረደላቸው::
በአንዴም ከፍርሃት ወደ ድፍረት ተመልሰው ፍጹማን:
ብርሃናውያን ሆኑ:: 71 ልሳናትን ነስተው በአንዲት ስብከት
ብቻ 3ሺ ነፍሳትን ማረኩ:: (ሐዋ. 2:41)
+ቅዱሳን ሐዋርያት በኅብረት ለአንድ ዓመት ያህል
በኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ እየተመላለሱ አስተምረው ብዙ
እሥራኤላውያንን ወደ ክርስትና ማርከዋል:: ከዚህ በሁዋላ
ግን እንደ ትውፊቱ በዚህች ቀን ዓለምን በእጣ ለ12
ተካፈሏት::
+ይህ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ አብሯቸው ነበርና
ለእያንዳንዳቸው እንደሚገባቸው አሕጉረ ስብከቶች
ደረሷቸው:: እነርሱም ደቀ መዛሙርቶቻቸውን አስከትለው
ለታላቁ መንፈሳዊ ዘመቻ ወረዱ::
+በሔዱበት ቦታም ከተኩላ: ከአንበሳና ከነምር ጋር
ታገሉ:: በጸጋቸውም አራዊትን (ክፉ ሰዎችን) ወደ በግነት
መልሰው ለክርስቶስ አስረከቡ:: በየሃገሩ እየሰበኩ
ድውያንን ፈወሱ:: ለምጻሞችን አነጹ:: እውራንን አበሩ::
አንካሶችን አረቱ:: ጐባጦችን አቀኑ:: ሙታንንም አስነሱ::
እልፍ አእላፍ አሕዛብንም ወደ መንጋው ቀላቀሉ::
+ስለዚህ ፈንታም ብዙዎቹ በእሳት ተቃጠሉ:: ቆዳቸው
ተገፈፈ:: በምጣድ ተጠበሱ:: ደማቸው በምድር ላይ
ፈሰሰ:: ከአንድ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በቀር ሁሉም
ይህችን ዓለም በሰማዕትነት ተሰናበቱ:: ጨው ሆነው
አጣፍጠዋልና: ብርሃንም ሆነው አብርተዋልና
እናከብራቸዋለን:: "አባቶቻችን: መምሕሮቻችን: ጌቶቻችንና
ሊቆቻችን" እንላቸዋለን::
✞ ቅዱስ ያዕቆብ ✞
=>በዚህ ቀን ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ
ሰማዕት ሆኗል:: ቅዱሱ ሐዋርያ አባቱ ዘብዴዎስ: እናቱ
ማርያም ባውፍልያ: ትንሽ ወንድሙ ደግሞ ዮሐንስ
ወንጌላዊ ይባላል::
+ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ሲሆን አሳ አጥማጅነቱን ትቶ:
ከጌታችን እግር ተምሮ በዓለም ወንጌልን አስፋፍቷል::
(ማር. 1:19) ከሌሎቹ ሐዋርያት በተለየም የእንስሳትን
ቁዋንቁዋ ያውቅ ነበር::
+በመጽሐፍ ቅዱስ በሔሮድስ መገደሉ (ሰማዕትነቱ)
የተነገረለት ከ12ቱ ብቸኛው ነው:: ሰማዕት የሆነውም
በ44 ዓ/ም : ማለትም ከጌታ ዕርገት 10 ዓመታት በሁዋላ
: ሐዋርያት ለስብከተ ወንጌል ወደ ዓለም ሳይበተኑ ነው::
(ሐዋ. 12:1)
=>እግዚአብሔር ከቅዱስ ያዕቆብና ከቅድስት ቤቱ በረከት አይለየን::
=>ሚያዝያ 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ ወልደ ዘብዴዎስ (ከ12ቱ
ሐዋርያት)
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ቀዳሜ ሰማዕት)
2.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ዘቆዽሮስ
3.ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
4.አባ ገሪማ ዘመደራ
5.አባ ዸላሞን ፈላሢ
6.አባ ለትጹን የዋህ
=>+"+ በዚያም ዘመን ንጉሡ ሄሮድስ መከራ ያጸናባቸው
ዘንድ ከቤተ ክርስቲያኑ በአንዳንዶቹ ላይ እጁን
ጫነባቸው:: የዮሐንስንም ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ
ገደለው:: አይሁድንም ደስ እንዳሰኛቸው አይቶ ጨምሮ
ዼጥሮስን ደግሞ ያዘው:: የቂጣ በዓልም ወራት ነበረ::
+"+ (ሐዋ. 12:1)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
/channel/zikirekdusn
🛑በዩቲብለመከታተል👉ZikereKedusan" rel="nofollow">https://www.youtube.com/@ZikereKedusan
🛑በቴሌግራም👉/channel/zikirekdusn
@highlight
ውዳሴ ማርያም የሚጸልይና የማይጸልይ
የእመቤታችን ውዳሴ ማርያም የዕለቱን ውዳሴ ማርያም በየዕለቱ የሚጸልይ ሰው የእናት አባቱን ርስት የወረሰ ይመስላል።
የሰባቱን ዕለት ውዳሴ ማርያም በእድሜዋ ልክ በየዕለቱ የሚጸልይ ደግሞ የዘመዶቹን ጨምሮ የወረሰ ይመስላል።
እመቤታችን ሳያመሰግን የሚውል ሰው ምን ይመስላል ቢሉ፦
ከሰው ቤት ድግስ ተጠርቶ ሂዶ በር ላይ ሲደርስ ውኃ ተደፍቶበት፥ ተቆጥቶ የሚመለስ፤ እንቅፋት እየመታው እየወደቀ እየተነሣ እየተሰበረ የሚሄድ ይመስላል።
ያ ሰው ካለመብላቱ በላይ እየተሰበረ እንደሄደ እመቤታችን የማያመሰግንም በመከራ ሥጋ ላይ መከራ ነፍስ ይጸናበታል። በርደተ መቃብር ላይ ርደተ ገሃነም ይጨመርበታል።
እኛ ግን፦
"አማንኬ ይደልወኬ አስተብፅዖ እስመ ኮንኪ እሞ ለእግዚአብሔር አዶናይ -የከሃሊ ኩሉ እግዚአብሔር እናት ሆነሻልና ብፅዕት መባል በእውነት ይገባሻል" እንላታለን።
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
የቃል ኪዳኗ እመቤት ሆይ፤ የአምላክ ቃል ኪዳኑ መዛግብት በዕለተ ዓርብ የተገኘውን የደኀነታችን ተስፋ ያስገኘሽ ዕውነተኛ መዝገብ ነሽ እኮን።❤🙏🙏
አባታችን ቀዳማዊ አዳም በጭንቀትና በኀዘን ከገነት ወጥቶ በተሰደደ ጊዜ ከልቦናው ኀዘን ተረጋግቶብሻልና።
ድንግል ሆይ 🤲 የአስራት ሀገርሽን ኢትዮጵያን ጠብቂያት
ፍቅር ❤ ሰላም ❤ አድነት ❤🤲🤲 አድርጊልን
መስከረም 29 -የሰማዕት ቅድስት አርሴማ እረፍት የቅድስት #አርሴማ እናት አትናስያ ትባላለች ልጅ በማጣት ለረጅም ዘመን ታዝን ታለቅስ ነበር በኃላም እግዚያብሔር ልመናዋን ሰማት ይህችን ክብርት ቅድስት ልጅንም ሰጣት፤ቅድስት አርሴማ ጥር 6 ነው የተወለደችው፤15 ዓመት ሲሆናት ሊያጋቡአት አሰቡ እርሷ ግን ይህን አልወደደችም፤ በደናግል ገዳም ገብታ በተጋድሎ መኖር ጀመረች። ከዚህ በኃላ እንዲህ ሆነ ከሃዲው ንጉስ ዲዮቅልጥያኖስ ሊያገባት ወደደ ቅድስት አርሴማ ግን ከደናግሉ ጋር ሸሽታ ወደ አርማንያ ሄደች በዚያም በበርሃ ለጥቂት ቀናት ተቀመጠች በኃላ ላይ ድርጣድስ የሚባል አገር ገዢ በበርሃ እንደሚኖሩ ሰማ ወታደሮችንም ልኮ አስመጣቸው፤ የቅድስት አርሴማን መልክ በተመለከተ ጊዜ ፈዞ ደንዝዞ ቀረ የፊቷ ውበት እጹብ ድንቅ፤ ግርማዋ የሚያስደነግጥ ልብ የሚያርድ ነበርና፤ስለዚህም ሊያሰቃያት አልደፈረም በእንክብካቤ በሰገነት ላይ አኖራት፤ ሌሎቹን ግን ለጣአት እንዲሰግዱ ገረፋቸው፤ ቅድስት አርሴማ እኔንም አሰቃዩኝ እያለች አምርራ ታለቀስ ነበር። ድርጣድስ ብዙ ጊዜ ሊሸነግላት ሞከረ እርሷ ግን ትዘልፈው ጣኦታቱንም ትረግም ነበር፤ እርሷ ጸንታ ደናግሉን ታጸና ነበር ትመክራቸው ታረጋጋቸው ነበር፤ ድርጣድስ ሽንገላው እንደማያዋጠው በአወቀ ጊዜ ማሰቃየት ጀመረ፤ በመጨረሻም ከብዙ ስቃይ በኃላ መስከረም 29 ቀን አንገቷን ቆረጣት ከእርሷ ጋር 27 ሰማዕታት አብረው ተሰይፈዋል። የሰማዕቷ በረከት ከእኛ ጋር ይሁን፡፡
Читать полностью…ሚያዚያ 15/2016 #ቅድስት_ኢየሉጣ
#ቅዱስ_ቂርቆስ
#ቅዱስ_ሚናስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና በፀሎት ለምንማፀንበት እና በቅዱሳኑ ስም ለምናመሰግንበት #ለቅዱስ_ቂርቆስ_እና_ለቅድስት_ኢየሉጣ_ለቅዱስ_ሚናስ ለወርሐዊ መታሠቢያ በአላቸዉ እንኳን አደረሰን
👉 #ቅዱስ_ቂርቆስ ዕድሜው የሦስት ዓመት ሳለ እናቱ ቅድስት #ኢየሉጣ ከሮሜ ወደ ሌላ ሃገር ሸሽታ ይዛው ሄደች በዚያም የሸሸችውን መኮንኑን አገኘችው የሚያውቋትም ሰዎች ሸሽታ እንደመጣች ስለተረዱ ለመኮንኑ ነገር ሰሩባት
👉መኮንኑም #ቅድስት_አየሉጣን አስጠራትና ስለ አምልኮ ጠየቃት ቅድስት ኢየሉጣም መኮንን ሆይ ዕድሜው ሦስት አመት የሆነው ሕፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እርሱን ጠይቅ አለችው
👉 #ሕፃኑ_ቅዱስ_ቂርቆስም ወደ አለበት ጭፍራውን ልኮ ወደ እርሱ አስመጣው ሕፃኑንም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና “አንተ ደስተኛ ሕፃን ሆይ እንዴት ነህ?” አለው።
👉ሕፃን #ቅዱስ_ቂርቆስም መለሰለት እንዲህም አለው “አዎ እኔ በጣም ደስተኛ ነኝ ደስታዬም ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ሐዘንና ለቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስም ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏልና” አለው።
👉 #እግዚአብሔር አምላክ ኃይልንና ንግግርን ሰጥቶታልና በዚያ ለተሰበሰቡት ሰዎች እስኪደነግጡ ድረስ ብዙ ተናገረ ሕፃኑ #ቅዱስ_ቂርቆስም ንጉሱን መኳንንቱንና ጣዖታቱን ረገማቸው ከብርታቱም የተነሳ አደነቁ።
👉መኮንኑም በአፈረ ጊዜ በየዓይነቱ በሆነ ስቃይ ታላላቆች እንኳ የማይችሉትን ታላቅ አስጨናቂ የሆነ ስቃይን አሰቃየው እናቱ #ቅድስት_ኢየሉጣንም ከእርሱ ጋር እንደ እርሱ በጣሙን አሰቃያት
👉 #እግዚአብሔር ግን ያለ ምንም ጉዳት ያነሳቸው ነበር ብዙዎች አህዛብም ይህን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን በመድሃኒታችን #በኢየሱስ_ክርስቶስ አምላክነት አምነው በሰማእትነት ሞቱ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበሉ።
👉በሕፃኑ #ቅዱስ_ቂርቆስ ላይም የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ አደረበት ታላላቅ ድንቅ ተአምራቶችንም ያደርግ ነበር ብዙዎች በሽተኞችንም ያድናቸው ይፈውሳቸው ነበር
👉ይህንን ያየ መኮንን በታላቅ የናስ ጋን ውስጥ ውሃ ጨምረው በእሳት ያፈሉት ዘንድ አዘዘ የፍላቱም ድምጽ እንደ ክረምት ነጎድጓድ ሆነ ድምጹም በጣም ያስተጋባ ነበር
👉ይህን ያየችና የሰማች እናት #ቅድስት_ኢየሉጣም ፍርሃትና የሃይማኖት ጉድለት ታየባት ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ሁኔታዋን አይቶ ወደ አምላኩ እግዚአብሔር ፀለየ
👉ያን ጊዜ ልዑል #እግዚአብሔር ልቧን ወደ ሰማይ አሳርጎ ለቅዱሳን ሰማዕታት የተዘጋጁ የብርሃን ማደሪያዎችን አሳያት ቅድስት ኢየሉጣም እንደገና በሃይማኖቷ ጸናች እግዚአብሔር አምላኳንም አመሰገነችው ልጇን ሕፃኑን ቅዱስ ቂርቆስንም “ልጄ ሆይ አንተ ከእንግዲህ አባቴ ነህ እኔም ልጅህ ነኝ” አለችው
👉 #ቅድስት_እየሉጣም ለልጇ “ያች የተወለድክባት ዕለት ቀኗ የተባረከችና የተቀደሰች ናት” አለችው የመኳንንቱ ጭፍሮችም እሳት ወደ አለበት ጋኖች ውስጥ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣን በጨመሯቸው ጊዜ የውሃው ፍላት ወድያዉኑ ቀዘቀዘ ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የእሳቱን ኃይል አቀዝቅዞታልና
👉ይህን ያየ መኮንን ሥጋቸው ተቆራርጦ እስከሚወድቅ ድረስ በመቃጥን ውስጥ አድርገው አንዲጎትቷቸው አዘዘ #ከእግዚአብሔርም የታዘዘ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል አዳናቸው
👉መኮንኑም በታላቅ ስቃይ ያሰቃያቸው ዘንድ አስቦ እስኪመክር ድረስ በወህኒ ቤት ዘጋባቸው በዚህን ጊዜ ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ወደ ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስን አረጋጋው አጽናናው ስሙን ጠርተው መታሰቢያ ለሚያደርጉለትም በረከትን እንደሚያገኝና ሌላ ብዙ ቃል ኪዳን ሰጠው
👉ሲነጋ መኮንኑ ከመካነ ምኩናኑ ተቀምጦ ካለበት አስጠርቶ የተመለስከው መመለስ አለን አለው #ቅዱስ_ቂርቆስም አይሆንም አልመለስም አለው ሰይፍ ጃግሬውን ጠርቶ ንሳ ውደቅበት አለው በሰይፍ መታው ጌታም ነፍሱን ከመካነ ዕረፍት ሥጋውንም ነጥቆ #በሰረገላ_ኤልያስ አኑሮለታል እናቱ ቅድስት ኢየሉጣንም በማግስቱ ጥር 16 በሰይፍ አስመትቷት በሰማዕትነት ዓርፋለች
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከሕፃኑ #ቅዱስ_ቂርቆስ እና ከእናቱ #ቅድስት_እየሉጣ እንዲሁም ከሰማእቱ #ቅዱስ_ሚናስ ረድኤት በረከት ያሣትፈን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
Invite partners to the bot and get money for them
Send a link to a friend:
/channel/Cryptouppeoplebot?start=5481885210
6$ for each partner you invite
The referral is counted only after your friend has activated the bot!
◽️Users invited: 0
◽️Earnings: 0 $
ሚያዚያ 13/2016 #እግዚአብሔር_አብ
#ቅዱስ_ሩፋኤል
#አቡነ_ዘርዐ_ብሩክ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና በፀሎት ለምንማፀንበት ለመልአኩ #ቅዱስ_ሩፋኤል ለፃድቁ #አቡነ_ዘርዐ_ብሩክ ወርሐዊ መታሠቢያ በአላቸዉ እንኳን አደረሰን
👉 #ቅዱስ_ሩፋኤል ቊጥሩ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሲኾን ሩፋ፤ ማለት ሐኪም፤ ኤል ማለት #እግዚአብሔር ማለት ሲኾን ሩፋኤል ማለት “እግዚአብሔር ሐኪሜ ነው” ማለት ነው፤ ሄኖክም “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” ይለዋል (መጽሐፈ ሄኖክ 6፥3)
👉ይኽ መልአክ በራማ ሰማይ ያሉ ነገደ መናብርትን የሚመራቸው ነው ነገደ መናብርት ያላቸው #ቅዱስ_ሩፋኤል የሚመራቸው በራማ ሰማይ የሚኖሩ ነገደ መላእክት ናቸው
👉ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በሥነ ፍጥረት መጽሐፉ ላይ “ወለዳግም ጾታ ዐሠርቱ ስሞሙ መናብርት ወሊቆሙ #ሩፋኤል እሉ እሙንቱ እለ ይቀልል ሩጸቶሙ እምነፋስ ወእለ ይጸውሩ ወላትወ መብረቅ ወኲናተ እሳት ዘይነድድ ወአንበሮሙ በዳግሚት ሰማይ” ይላል
👉በራማ ሰማይ የሚገኘውን ኹለተኛውን ዐሥሩን ነገድ መናብርት ሲላቸው አለቃቸው #ቅዱስ_ሩፋኤል ነው፤ እነዚኽም ረቂቅ የኾነ የመብረቅ ጋሻ የእሳት ጦር ይዘው ከነፋስ ይልቅ የፈጠኑ ሲኾኑ በራማ በኹለተኛው ክፍል ላይ አስፍሯቸዋል
👉#የእግዚአብሔር_አብ ቸርነት የልጁ የመድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ምህረት #የመንፈስ_ቅዱስ አንድነት ከኛ ከልጆቹ አይለየን የተባረከ የተቀደሰ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
[በዓለ ሆሣዕና]
✍በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ (በድጋሚ የተለጠፈ)
♥ ሆሣዕና ማለት የዕብራይስጥ ቃል ነው፤ “ሆሻአና” ሲባል ትርጒሙም “አቤቱ አኹን አድን” ማለት ነው፤ ይኽ በዓለ ሆሣዕና ከ9ኙ ዐበይት የጌታ በዓላት ውስጥ ሲኾን ክንፋቸው ትእምርተ መስቀል የሚሠራው ኪሩቤል ሱራፌል በፍርሀት በረዐድ ኹነው ዘፋኑን የሚሸከሙት ጌታ በትሕትና ኾኖ ጀርባዋ ላይ ትእምርተ መስቀል ባለባት በአህያና በውርንጫይቱ ተቀምጦ እየተመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበት፣ የዘካርያስ ትንቢት የተፈጸመበት፣ ሕዝቡ ዘንባባ ይዘው የዘመሩበት፣ ሕፃናት በንጹሕ አንደበታቸው ሆሣዕና ብለው ያመሰገኑበት ታላቅ በዓል ነው፡፡
♥ ይኽም ታሪክ በ4ቱ ወንጌላት ላይ ሲጻፍ በማቴ 21፡1 ላይ “ወደ ኢየሩሳሌምም ቀርበው ወደ ደብረ ዘይት ወደ ቤተ ፋጌ ሲደርሱ፥ ያንጊዜ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከ” ይላል፡፡
♥ ቤተ ፋጌ ማለት የበለስ ቤት ማለት ሲኾን ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ በሚወስደው መንገድ አቅራቢያ ያለች ትንሽ መንደር ናት፤ ኹሉን ዐዋቂ የኾነው ጌታም ጴጥሮስንና ዮሐንስን “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከርሷ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ” በማለት እንደ ማዕምረ ኅቡአትነቱ (የተሰወረውን ዐዋቂነቱ) በመንደሯ ውስጥ ስለታሰሩት አህያና ውርንጫ አስቀድሞ ይነግራቸዋል፡፡
♥ በተናቀች ግርግም በቤተልሔም በተወለደ ጊዜ ላምና አህያ ትንፋሻቸውን እንደገበሩለት፤ አኹንም በሰዎች በተናቀች አህያ በጌትነት ተቀምጦ እንዲመሰገንባት መርጧታል፡፡
❤ በልደቱ ማንም ያልገባባት የማይገባባት የሕዝቅኤል የታተመች መቅደስ የተባለች ዘላለማዊት ድንግል እመቤታችንን እንደመረጠ ዛሬም በሆሣዕና ማንም ሰው ያልተቀመጠበት ውርንጫ እንዲያመጡ አዘዘ።
♦ ከዚያም “ማንም አንዳች ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ፤ ወዲያውም ይሰዳቸዋል” በማለት የኹሉ ጌታ ርሱ መኾኑን አመለከታቸው፤ በተሰጣቸው ሥልጣነ ክህነት የሕዝቡንም የአሕዛቡን ኀጢአት የማሰር የመፍታት ሰማያዊ ሥልጣነ ክህነት የተሰጣቸው ሐዋርያትን የሕዝብ ምሳሌ የኾነችውን አህያይቱንና የአሕዛብ ምሳሌ የኾነችው ውርንጫዋንም እንዲያመጡ አዟቸዋልና።
♥ ሊቁ ጀሮምም፡- “ደቀ መዛሙርቱ አህያይቱንና ውርንጫይቱን ለመፍታት ኹለት ኾነው መላካቸው ለሕዝብም ለአሕዛብም መላካቸው ያመለክታል፡፡” ይላል።
♥ ሊቁ አምብሮስ፡- “አህያየቱን ለመፍታት ማንም አይከለክላችኁም ብሎ መላኩ ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ የሰጣቸው የማሰር የመፍታት ሥልጣን ሰማያዊ መኾኑን ያመለክታል፡፡” በማለት ልዩ ምስጢርን አስተላፎበታል።
♥ አምጥተው “ልብሳቸውንም በእነርሱ ላይ ጫኑ”፤ በአህያዋና በውርንጫዋ ላይ ኮርቻ ሳይኾን ልብስ ማድረጋቸው ኮርቻ ይቈረቊራል ልብስ ግን አይቈረቊርምና የማትቈረቊር ሕግ ሠራኽልን ሲሉ። ዳግመኛም ልብስ በአካል ያለውን ኀፍረት እንዲሰውር አንተም በደላችንን የምትሰውርልን ይቅር ባይ ነኽ ሲሉ በማለት መተርጉማን ይተነትናሉ፡፡ በተጨማሪም ልብስ በልጅነት ይመሰላልና የተገፈፍነውን የጸጋ ልብሳችን (ልጅነትን) ትመልስልናለህ ሲሉ ነው፨
♥ ቅዱስ ኤፍሬም ይኽነን ሲተረጉም "ልብሳቸውን አውልቀው ያነጠፉለት ሰዎች አሮጌውን ማንነታቸውን ትተው ዐዲሱን ልብስ ክርስቶስን መልበሳቸውን ያስረዳል። ሐዋርያ ጳውሎስ “አሮጌውን ሰውነት አስወግዳችሁ አዲሱን ሰው ልበሱት” እንዳለው (ኤፌ.4፣23) ይኸውም ጥምቀት ነው" ይላል።
♥ ከኢየሩሳሌም እስከ ቤተ መቅደስ 16 ምዕራፍ ሲኾን መተርጒማነ ሐዲስ በትርጓሜ ወንጌል ላይ እንደሚገልጹት 14ቱን ጌታ በእግሩ ሲኼድ 2ቱን በአህያዋ፤ በውርንጫዋ 3 ጊዜ ቤተ መቅደሷን ዞሯል፡- 14ቱ በእግሩ መኼዱ የ10ሩ ቃላት 4ቱ የ4ቱ ኪዳናት ምሳሌ፡፡ 2ቱ በአህያዋ መጓዙ የፍቅረ እግዚአብሔርና የፍቅረ ቢጽ፤ 3ቱን በውርንጫዋ ተቀምጦ ቤተ መቅደሱን መዞሩ የ3ትነቱ የአንድነቱ ምሳሌ ነበር፡፡
♥ ጌታ ንጉሠ ነገሥት ሲኾን፤ ኪሩቤል ሱራፌል ዙፋኑን በፍርሀት በረአድ የሚሸከሙት 24ቱ ካህናተ ሰማይ ዙፋኑን በፍርሀት የሚያጥኑለት ርሱ በትሕትና የዋህ ኾኖ በተናቁት በአህያና በውርንጫይቱ ላይ ተቀመጠ፤ ይኽም የተናቁትን ሊያከብር እንደመጣና፤ በየዋሀን ምእመናን ልቡና እንደሚያድር ለማሳወቅ በነርሱ ተቀመጠ። በተጨማሪም መተርጉማን እንዳመሰጠሩት በአህያ የተቀመጠ አባሮ እንደማይዝ ሸሽቶ እንደማያመልጥ ርሱም ካልፈለጉት እንደማይገኝ ከፈለጉት እንደማይታጣ በምስጢር አመለከታቸው፡፡
♥ በተጨማሪም አህያ ሲፈጥራት በጀርባዋ ላይ ትእምርተ መስቀል ያላት ናትና ትእምርተ መስቀል ያለባት እእርሷ እንድትፈታ ማዘዙ ከ5 ቀን በኋላ በመስቀል ተሰቅሎ በሲኦል የታሠሩትን የሰው ልጆችን ነጻ ሊያወጣ መጥቷልና አህያን መርጧታል፨
♥ ቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ፡- ስለዚኽ ነገር በትርጓሜ ወንጌሉ ላይ “እነዚኽ እንስሳት መላውን የሰው ልጅ ይወክላሉ፡፡ ኹለቱም አህያ መኾናቸውም የሰው ልጅ ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት የነበረውን አኳኋን የሚያስረዳ ነው፡፡ ምክንያቱም አህያ በኦሪቱ ዘንድ ንጹሕ እንስሳ አይደለችም፤ ብዙ ክብደት ያላት የማትወደድ እንስሳ ናት፤ ደካማ ናት፡፡ ሰውም እንደተናገርን ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት እንዲኽ ነበረ፡፡” በማለት አመስጥሯል፡፡
♥ ሊቁ ቅ. ቄርሎስ ዘእስክንድርያም፡- “ፈጣሬ ኵሉ እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ ጠቢብ አድርጐ ፈጥሮት ነበር፡፡ ማሰብና ማሰላሰል የሚችል ፍጥረት አድርጐ ፈጥሮት ነበር፡፡ ሰይጣን ግን አታለለው፡፡ ምንም እንኳን ሰው በሥላሴ አምሳል ቢፈጠርም መልኩን አበላሸው፡፡ ፈጣሬ ኵሉ እግዚአብሔርን ማወቅ ተሳነው፡፡ ክፉው ሰይጣን ሰውን እንስሳ እስኪመስል ድረስ ክብሩን አዋረደው፡፡ መዝሙረኛው ዳዊት፡- “ሰውስ ክብሩን አላወቀም፤ የሚጠፉ እስሳትን መሰለ” ያለውም ስለዚኹ ነው (መዝ.49፡12)፡፡ በመኾኑም አህያይቱ ክብራቸውን አጥተው ተዋርደው የነበሩትን እስራኤል ዘሥጋን ትመስላለች፡፡ እስራኤል ከሕጉ ጥቂት ነገርን ያውቃሉ፡፡ ከነቢያትና ከቅዱሳንም ትንሽ ያውቃሉ፡፡ ከኹሉም በላይ ደግሞ ወደ አሚን የሚጠራቸውን ክርስቶስን አልታዘዙትም፡፡ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ” ሲላቸውም እንደ አህያይቱ በድንቁርና ተይዘው እንደነበረ ሲገልጥላቸው ነው፡፡ ውርንጫይቱ ደግሞ አሕዛብን ትወክላለች፡፡ ውርንጫ እኽልን ለመጫን እንደማታገለግል ኹሉ አሕዛብም ማኅደረ እግዚአብሔር ከመኾን ርቀው ነበርና፡፡” በማለት ገልጿል፡፡
♥ ያን ጊዜ ከሕዝቡም እጅግ ብዙዎች ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ ይኽንም ማድረጋቸው ስንኳን አንተ የተቀመጥኽባት አህያ መሬት መርገጥ አይገባትም ሲሉ ነበር። እንስሳዋ እንኳን ጌታ ቢቀመጥባት እንዲህ ክብር ያገኘች ከሆነ ያደረባቸው ቅዱሳንማ የሚገባቸው ክብር ምን ያህል ይሆን? ይልቁኑ 9 ወር ከ5 ቀናት በማሕፀኗ የተሸከመችው ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስን ነሥቶ ሰው የሆነውን አምላክ የወለደችው የቅድስት ድንግል ማርያም ክብርማ እጅጉን ታላቅ ነው።
❤ ጌታ የተቀመጠባት አህያ በክብር ወደ ኢየሩሳሌም እንደገባች ጌታ ያደረባቸው ምእመናን ደግሞ በታላቅ ክብር ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ይገባሉ።
✞✞✞ እንኩዋን ለቅዱስ "ስምዖን ዘአርማንያ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+*" ቅዱስ ስምዖን ሰማዕት "*+
=>ቅዱስ ስምዖን የአርማንያ ሰው ቢሆንም ሰማዕትነትን
የተቀበለው በሃገረ ፋርስ (በአሁኗ ኢራን አካባቢ) ነው::
ፋርስ ከ1ኛው መቶ ክ/ዘ እስከ ተንባላት (መሐመ+ዳውያን)
መነሳት (7ኛው መቶ ክ/ዘ) ድረስ ባለው ጊዜ ብዙ
ሰማዕታት ለክብር በቅተውባታል::
+ብዙዎቹ የዚያው (የፋርስ) ዜጐች ሲሆኑ ጥቂቶቹ ደግሞ
የተሰዉት ከሌላ ሃገር መጥተው ነው:: ፋርሳውያን
አብዝተው ፀሐይን ያመልኩ ነበርና ክርስቲያኖቹን
የሚያሰቃዩት ይህቺውን ፍጡር እያመለኩ እንዲንበረከኩ
ነበር::
+ቅዱስ ስምዖንም ከፋርስ ግዛቶች በአንዱ ኤዺስ
ቆዾስነትን (እረኝነትን) ተሹሞ ነበርና የመከራው ተሳታፊ
ሆኗል:: በጊዜው ክርስትና እንደ ዛሬው "ሠርግና ምላሽ"
አልነበረምና ቅዱስ ስምዖን (እረኛው) እና 150 የሚያህሉ
ልጆቹ (መንጋው) ስለ ክርስቶስ ፍቅር ብዙ ሆነዋል::
+በእምነታቸው ጸንተው በመገኘታቸውም እንዲገደሉ
ተወስኖባቸው 151ዱም ተሰውተዋል::
=>አምላከ ሰማዕታት በጽናታቸው አጽንቶ ከበረከታቸው
ይክፈለን::
=>ሚያዝያ 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ስምዖን ሰማዕት (አርማንያዊ)
2."150" ቅዱሳን ሰማዕታት (የስምዖን ማሕበር)
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
3.አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
4.አቡነ ስነ ኢየሱስ
5.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም
=>+"+ እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ: እስከ
አሁንም ስለምታገለግሏቸው ያደረጋችሁትን ሥራ:
ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመጸኛ
አይደለምና:: በእምነትና በትእግስትም የተስፋውን ቃል
የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ
ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ
መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን::+"+ (ዕብ. 6:10-13)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
/channel/zikirekdusn
ሚያዚያ 19/2016 #ቅዱስ_ገብርኤል
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና በፀሎት ለምንማፀንበት በመልአኩ ስም ለምናመሰግንበት ለመልአኩ #ቅዱስ_ገብርኤል ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉ገብርኤል ‘ገብረ’ እና ‘ኤል’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ የመልአክ ስም ነው #የእግዚአብሔር_ሰው ማለትም ነው
👉አብሳሪ መልአክ #ቅዱስ_ገብርኤል ሆይ እጅግ አፅናኝና አስደሳች የሆነውን ምስጢረ ሥጋዌን ዜና ይዘህ ከሰማይ ወደ ምድር እንደወረድክ #ድንግል_ማርያም የአምላክ እናት ለመሆን ፈቃድዋ ሆኖ በተፈጸመ ጊዜ ደስ እንዳለህ እኛም እግዚአብሔርን በማክበርና ግዴታችንን በመፈፀም ደስ የምንሰኝበትን ፀጋ አሰጠን
👉ጠባቂያችን #ቅዱስ_ገብርኤል ሆይ ሦስቱን ወጣቶች ከሚያቃጥል እሳት እንዳዳንካቸው እኛንም በዚህ ዓለም ከሚወራው ከሚታየውና ከሚሰማው #ክፉ_ቀንና_እለት ሁሉ አድነን እየነደደ የሚለበልበንን የኃጢያት እሳትም አጥፋልን
👉የኑሯችንን ቀጠሮ በክንፈ ረድኤትህ ከልለው ሰይጣን እንዳይሰለጥንብን ክፉ አድራጊዎች ሟርተኞች ሰላቢዎች ዘረኞችና ነፍሰ ገዳዮች እንዳያጠቁን ከልለን ያንተን የእሳት አጥር ዘሎ ጠላት ያጠቃን ዘንድ ጠላት አይችልምና #ጥበቃህ ከእኛ ከባርያዎችህ አይለየን
👉#ቅዱስ_ገብርኤል ሆይ ሕፃኑ ቂርቆስና እናቱ እየሉጣን በንፍር ውኃ ከመቀቀል እንዳዳንካቸው ልጆችህን በማናውቀው ሁኔታ የተዘጋጀልንን #የጥፋት_ወጥመድ ሁሉ አስወግድልን በላያችን ላይም በክፉ ሰዎች ምክንያት የተነሳብንን እሳት አጥፋልን
👉 #ለእውነተኛ_ሃይማኖት የጨከንንና የቆረጥንም አድርገን የሰይጣንን ፈተና የምናልፍበት እውነተኛውን ጥበብ እንደ ነብዩ ዳንኤል አስተምረን
👉 ቅዱስ #ገብርኤል ሆይ በደል በተገኘብን ቁጥር እያለቀስን እንጠራሃለን ጎስቋላ የምንሆን በጥቃትና በሀዘን ውስጥ የምንገኝ ልጆችህ የአንተን ማፅናናትና ረዳትነት እንፈልጋለንና ፈጥነህ ናልን
👉እናታችን #ማርያምን ያበሰርክ ለዓለም ሁሉ የምታበራ ገብርኤል ሆይ በሰራዊት አምላክ ፊት ዘወትር ትቆማለህና ፀሎትና ልመናችንን ስማ
👉ቅዱስ #ገብርኤል ሆይ ቀድመህ የደስታ የምሥራች ቃልህን ልታበስር ወደ ገሊላ እንደወረድህ ዛሬም ለአዘንንና ለእኛ ለቃል ኪዳን ልጆችህ ከሠማይ በሠረገላ ናልን የደስታንም ቃል አሰማን
👉እናታችን #ማርያምን ያበሰርክ ተወዳጁ መልአክ ቅዱስ #ገብርኤል ሆይ በምህረትና በይቅርታ ወደ እኛ ናልን ዓለም የጥፋት የሞት የክስረት የውድመትና የተስፋ መቁረጥ ድምፅን ያሰማናልና አንተ ግን ጉስቁልናችንን የሚያነሳ ስብራታችንን የሚጠግን እንባችንን የሚያብስ #የብስራት ድምፅህን አሰማን እንድንፅናናም አድርገን
👉እውነተኛ ጠባቂያችን ቅዱስ #ገብርኤል ሆይ እኛን ለማዳን ሰው የሆነውን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን ማደሪያው የሆነችው #ድንግል_ማርያምን በጣም እንወዳታለን
👉በዚህ ዓለም የምሥጢረ ሥጋዌ ተካፋዮች በመሆናችን #በመንግስተ_ሰማያትም ተካፋዮች ለመሆን ሁላችንንም በምልጃህ አብቃን ለምንልን #የእግዚአብሔር መልአክ #ቅዱስ_ገብርኤል ጥበቃህ ተራዳኢነትህ አይለየን
👉#ገብርኤል ሆይ ለሀገራችን ሠላምን ለህዝባችን ፍቅር አንድነትን ይሰጠን ዘንድ በአምላካችን #በክርስቶስ ፊት ቆመህ ለምንልን የሀገራችንና #የህዝቦቿ የቤተክርስቲያናችን ጠላቶችን አስታግስልን ጦርነትና ረሐብ ከምድራችን ላይ ይወገድ ዘንድ ለምንልን ጥበቃህ አይለየን የተባረከ #ቀዳሚት_ሰንበት ይሁንልን "አሜን" ✝️⛪️✝️
ሚያዚያ 18/2016 #ፃድቁ_አቡነ_ሠላማ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና በፀሎት ለምንማፀንበት በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት አባታችን #አቡነ_ሠላማ ጵጵስና ለተሾሙበት ወርሐዊ መታሠቢያ በአላቸዉ እንኳን አደረሰን
👉ወር በገባ በ18 #ፃድቁ_አቡነ_ሰላማ_ከሳቴ_ብርሃን ናቸው የጻድቁ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁንና ታላቁ ስመ ጥሩ አባታችን ጻድቁ አቡነ ሰላማ በ3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ከአባቱ #ከቅዱስ_ምናጦስና ከ #ቅድስት_እናቱ_ማርያም ሰናይት በጢሮስ #ግሪክ ተወለዱ
👉እድሜያቸዉ ለትምህርት እንደደረሰ በአካባቢው በነበረው ትምህርት ቤት ውስጥ ሃይማኖታዊ ትምህርቱን በሚገባ ተከታትሎ የተማረ በመልካም ሥነ-ምግባርና አስተዳደግ ተኮትኩቶ ያደገ ደግ አባት ነበር
👉ሜሮጵዮስ የተባለ ነጋዴ ፈላስፋ ወደ ህንድ አገር ሊያልፍ ወዶ ከጢሮስ አገር በጀልባ ጉዞ ጀመረ ከእርሱም ጋር ከዘመዶቹ ወገን የሆኑ ሁለት ብላቴኖች ነበሩ የአንደኛው ስሙ #ፍሬምናጦስ የሁለተኛው ደግሞ #ኤዴስዮስ_ሲድራኮስ ይባላል
👉ሜሮጵዮስ እነዚህን ሁለት ወጣቶች አስከትሎ ወደ አፍሪካ ባህር ጠረፍ በመምጣት በቀይ ባህር ወደብ ውሃ ለመጠጣት እግረ መንገዱንም አገር ለማየት ጀልባውን ጠረፍ ላይ አቆመ
👉በዚህ ጊዜ በአካባቢው ይኖሩ የነበሩ ሰዎች የአዱሊስ ነዋሪዎች በጀልባዋ ላይ አደጋ በመጣል #ሜሮጵያስንና የጀልባዋን ቀዛፊዎች እዚያው ገድለው ሀብታቸውን ዘረፏቸው
👉ሁለቱ ወጣቶች ግን ተረፉ በማያውቁትም አገር ያለ ዘመድ ያለ ሃብት ብቻቸውን በመቅረታቸው እያዘኑና እያለቀሱ ከዛፍ ሥር ተቀምጠው ሲፀልዩ የአካባቢው ነዋሪዎች ያዟቸውና በጊዜው በአክሱም ነግሶ ለነበረው #ለንጉሥ_ታዜር በፈረስ አንገት በጦር አንደበት የተማረኩ ሰዎች አመጣንልህ በማለት አስረከቡት #ንጉሥ_ታዜርም በቤተመንግስቱ ውስጥ እንዲያድጉ ፈቀደላቸው
👉ከጊዜ ወደ ጊዜ በቤተ መንግስቱ ውስጥ ተወዳጅነትንና ታማኝነትን አገኙ #የአብርሃ እና #አፅብሃ አባት የነበረው ንጉሥ ታዜር ኤዴስዮስን ጋሻ ጃግሬ ፍሬምናጦስን በጅሮንድ አድርጎ ሾማቸው
#ንጉሱ ሊሞት በተቃረበበት ጊዜ ልጆቹ ገና አካለ መጠን አልደረሱም ነበርና መንግስቱን በሞግዚትነት እንድትይዝ ለእቴጌይቱ አደራ ሲል ሁለቱን ሶርያውያን ምርኮኞች ግን ነጻ ለቀቃቸው ነገር ግን በእቴጌይቱ ልመና ወደ አገራቸው መመለሳቸው ቀርቶ ልጆቿ እስኪያድጉ ድረስ በአስተዳደር በኩል ሲረዷትና ሲመክሯት ቆዩ
👉#ፍሬምናጦስ በአክሱም በነበረበት ጊዜ የቤተ መንግስቱ አማካሪ ብቻ ሳይሆን ቀደም ሲል የኦሪት እምነት በአንድ #እግዚአብሄር ማመን እንደነበረ የሚታወቅ ሆኖ #የተዋህዶ እምነት #ጥምቀትና_ክህነትን በሚገባ የሚመሰረትበትና የሚሰፋበት መንገድ ይፈልግ ነበር
👉ያን ጊዜ የነበሩት የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ሐይማኖት ብቻ እንጂ ክህነት ቁርባንና የመሳሰሉት የክርስትና ስርዓቶች አልነበራቸውም #ልዑላኑ_አብርሃና_አፅብሐ አካለ መጠን ደርሰው የአባታቸውን መንግስትሲረከቡ #ኤዴስዮስ ወደ አገሩ ተመልሶ ካህን ሆነ
👉 #ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሦስት ጊዜ በላይ ግብፅ እስክንድሪያ ሄዶ ጵጵስና አምጥቶ በኢትዮጵያና በኤርትራ ሃዋርያ ሆኖ እንዲያስተምር እንዲያጠምቅ #በእግዚአብሄር መልእክት ተነገረው በዚህ መሰረት ስለአየው ነገር ለነገስታቱ አስረዳቸው ከዚህ በኋላ #ጵጵስና እንዲያመጣ መልካም ፍቃዳቸው ስለሆነ ወደ #እስክንድርያ ሄደ
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከፃድቁ አባታችን #አቡነ_ሠላማ ረድኤት በረከት ያሣትፈን የፃድቁ ቃል ኪዳን ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን"✝️💒✝️
ሙልዬ የልደት ፓኬጅ🎂🎂
mulye birthday package 🎂🧁🧁
🍰 cake black and white
🍥 Fruit cake
🍩 Mini Donat
🍞 English cake
🥐 croissant
Baclava
🥙 fruit panch
🥟 Sambusa
🥦 Spring roll
🍕 Mini piza
🍔 Mini Burger
🍗 Chiken
🐠 Fish
🍟 French frize
🧆 Meat ball
🌯 Shawerma
🎉🎉🎉🧨🎇🎈🎈🎈per person/በሰው
የልጅዎን ልደት ለየት ባለና ባማረ መልኩ እማይረሳ አድርገው ለማሳለፍ ይደውሉልን
☎️ 0945605062
Contact us / ያግኙን
/channel/mulu70
Join our channel on
https:// t.me/@Mulyecatering
††† እንኳን ለቅዱስ አንቲቦስ ሐዋርያ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችኹ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ቅዱስ አንቲቦስ †††
††† በዚህ ቀን ታላቁ ሐዋርያና ሰማዕት ቅዱስ አንቲቦስ ይታሰባል:: ቅዱሱ በአርማ በምትባል ሐገር በእረኝነት (ጵጵስና) ያገለገለ የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ደቀ መዝሙር ነው::
ቅዱሱ ስለ ክርስቶስ መንጋ ብዙ መከራን ተቀብሏል:: በእሥር ቤት ሳለም ከቅዱስ ዮሐንስ ነባቤ መለኮት (ወንጌላዊ) ክታብ (መልእክት) ደርሶታል:: በክታቡም ከሐዋርያትና ሰማዕታት መቆጠሩን ነግሮታል:: ጊዜው 1ኛው ክ/ዘ ሲሆን ክታቧ ከእኛ አልደረሰችም::
ከቅዱስ ዮሐንስ እግር ቁጭ ብሎ በመማሩ እንደ መምሕሩ የንጽሕና ሰው ነበር:: ከብዙ ዓመታት አገልግሎት በኋላ ስለ ፍቅረ ክርስቶስ በዚሕች ቀን በሰማዕትነት አልፏል::
በታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ ደግሞ የዚህ ቅዱስ ስም መጠቀሱን ምስራቅ ኦርቶዶክሶች ያምናሉ:: በዮሐንስ ራዕይ 2:12 ላይ የእኛው (ግዕዙ) "ጻድቅየ መሃይምን" ሲለው የግሪኩ ግን በቀጥታ በስሙ "አንቲጳስ (አንቲቦስ) ብሎ ይጠራዋል፡፡ እርሱም በታናሽ እስያ ከነበሩት 7 አብያተ ክርስቲያናት የአንዱ (የጴርጋሞን) አለቃ የነበረ ሲሆን ሰማዕት መሆኑም በዚሁ ምዕራፍ ላይ ተጠቅሷል ፡፡
"በጴርጋሞንም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ:: በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ያለው እንዲህ ይላል:: የሰይጣን ዙፋን ባለበት የምትኖርበትን አውቃለሁ፤ ስሜንም ትጠብቃለህ፥ ሰይጣንም በሚኖርበት፥ በእናንተ ዘንድ የተገደለው የታመነው ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ ሃይማኖቴን አልካድህም:: ዳሩ ግን ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበልዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ፥ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ:: እንዲሁ የኒቆላውያንን ትምህርት እንደ እነዚህ የሚጠብቁ ሰዎች ከአንተ ጋር ደግሞ አሉ:: እንግዲህ ንስሐ ግባ፤ አለዚያ ፈጥኜ እመጣብሃለሁ፥ በአፌም ሰይፍ እዋጋቸዋለሁ:: መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ
ያለው ይስማ:: ድል ለነሣው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፥ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፥ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር አንድ ስንኳ የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎአል::
(ራዕይ 2:12-17)
††† አምላካችን ከቅዱስ አንቲቦስ በረከትን ያሳትፈን::
††† ሚያዝያ 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አንቲቦስ ዘሃገረ በአርማ (ሐዋርያዊ ጳጳስና ሰማዕት)
2.ቅዱስ ሳባ ሰማዕት
††† ወርኀዊ በዓላት
1.ኪዳነ ምሕረት (የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም)
2.ቅድስት ኤልሳቤጥ (የመጥምቁ ዮሐንስ እናት)
3.ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮጵያ (የቅዱስ ላሊበላ ወንድም)
4.ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ
5.አባ አቡናፍር ገዳማዊ
6.አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ
7.አባ ዳንኤል ጻድቅ
††† "የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ:: የኑሯቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነት ምሰሏቸው:: ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ: እስከ ዘለዓለምም ያው ነው:: ልዩ ልዩ ዓይነት በሆነ በእንግዳ ትምሕርት አትወሰዱ:: ልባችሁ በጸጋ ቢጸና መልካም ነው እንጂ በመብል አይደለም:: በዚህ የሚሠሩባት አልተጠቀሙምና::" †††
(ዕብ. ፲፫፥፯)
እንኳን ለመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ
ዓመታዊ በዓል አደረሰን
ሚያዝያ 15 ቀን
ጸአተ ነፍሱ
ተረክቦተ ሥጋሁ ወርዕሱ
"ስለ አንተ ቀኑን ሙሉ እንገደላለን
እንደሚታረዱ በጎችም ተቆጠርን።"
ሮሜ 8፤36
መጥምቁ ዮሐንስ ሚያዝያ 15 ታላቅ የቃልኪዳን በዓሉ ነው። እጅግ ግን ተዘንግቷል በግፍ የተቆረጠችው በሰማዕትነት በሰይፍ የተከለለች ቅድስት አንገቱ ያረፈችበት እምርት እለት።
ይህን ታላቅ በዓል በረከት እንደዝናብ የሚወርድበት የመጥምቁ ቃል ኪዳን ማይ ሆና በጥምቀት ልጆች ሁሉ ላይ የምትነጥብበት የዝክር ቀን ናት የቻልን ከበዓለ ትንሳኤው ጋር በከርሠ ሩሁባን ሕንጻ ሥላሴን እንስራ ቀዝቃዛ ውሐ ቢሆን እየሰጠን የበረታን ያልቻልን መብራት በማብራት ፍቅር ለታረዙ ፍቅርን በመስጠት እናክብረው።
ሰማዕተ ብርሃን ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ የዘረኝነት ጽልመት የወረሳት ኢትዮጵያን በቃልኪዳኑ ያስባት ከዘረኝነት ደዌ ከፍቅር ረሐብ ከዝሙት እሳት ከምንፍቅና አሽክላ በምልጃው ይሰውረን አሜን አሜን አሜን
[ #አቡሆሙ_ለመነኮሳት ] ♥[ #አቡነ_አረጋዊ ]♥
ከሮምና ከመካከለኛው ምስራቅ ወደ ኢትዮጵያ ከፈለሱት ከዘጠኙ ቅዱሳን አንዱ #አቡነ_አረጋዊ ናቸው! የትውልድ ሀገራቸው ሮም በ "5"ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሲሆን በኢትዮጵያ ታላቁ ገዳማቸው ደብረ ዳሞ ወይም ደብረ ሃሌ-ሉያ ይባላል! ይህም በጥቅምት "14" ቀን በ "99" ዓመታቸው የተሰወሩበት ሥፍራ ነው! የጻድቁ የአቡነ አረጋዊ አባታቸው ይስሐቅ እናታቸውም እድና ይባላሉ፡፡ ሁለቱም እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚያከብሩ ነበሩ፡፡ እግዚአብሔር አምላክም የተባረከውን ልጅ ሰጣቸው፤ ይህም የሆነው በጥር ፲፬ ቀን ነው፡፡ እግዚአብሔርን መፍራት፣ ሕገ ኦሪትን ትምህርተ ነቢያትንና ቅዱሳት መፃሕፍትን እያስተማሩ አሳደጉት፡፡ እርሱም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እየጸና እየበረታ አደገ፡፡ ሚስት ያገባ ዘንድ አጩለት፡፡
ጻድቁ አባታችን አቡነ ዘሚካኤል(አረጋዊ) ፈጽሞ እምቢ አለ፡፡ ከብዙ ዘመን በኋላ ከሮም ወደ ግሪክ ሀገር አባ ጳኩሚስ የሚኖርበት ደውናስ ወደምትባል ገዳም የምንኩስናን ልብስ ይለብስ ዘንድ ሄደ፡፡ አባ ጳኩሚስንም አገኘው፡፡ አባ ጳኩሚስም ‹‹ልጄ ሆይ፥ አንተ የንጉሥ ልጅ እንደ መሆንህ መጠን የመንግሥቱ ወራሽ ነህና መንኰሰህ ለመኖር ይቻልሃልን?›› አለው፡፡ ብፁዕ አባታችንም‹‹አባቴ ሆይ፥ የምድር መንግሥት ኃላፊ ጠፊ ነው፤ ነገር ግን የማታልፈውን የማትጠፋውን ዘለዓለማዊት መንግሥት እወርስ ዘንድ እፈልጋለሁ›› አለው፡፡ በፈተናም ከጸና በኋላ በዐሥራ ዐራት ዓመቱ በአባ ጳኩሚስ እጅ የምንኩስናውን ልብስ ለበሰ፡፡ ከአመነኮሰውም በኋላ ስሙን ዘሚካኤል ብሎ ሰየመው፡፡
ከአባ እንጦንስ ዐራተኛው የቆብ ልጅ ሲሆን እርሱን በቆብ የሚወልደው ደገኛውን የገዳም ሥርዓትን ከሠሩልን አበው አንዱ የሆነው ታላቁ ቅዱስ ጳኲሚስ ነው። ቀድሞም በአባ ጳኲሚስ ዘንድ መንኲሶ ለመኖር ሲመጣ የመጣው ከንጉሥ ቤት ነበርና አባ ጳኲሚስ ከማመንኰሱ በፊት ብዙ ፈትኖታል። በኋላም ገና ልጅ ሳለ በዐሥራ ዐራት ዓመቱ አመነኰሰው። የምንኲስና ስሙንም አባ ዘሚካኤል ብሎ ሰየመው። አረጋዊ የተባለው ገና ወጣ ሁኖ ሳለ ልባዌውና ግብሩ ሁሉ እንደሚያስተውል አረጋዊ ነውና ‹‹አንተስ አባታችን አረጋዊ ነህ›› ብለው ጠሩት።
በገድልም ተጸምዶ የሚኖር ሆነ። በኋላም ከሁለት ደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ከተመለከታት በኋላ ወደ ሮም ተመልሶ ለወንድሞቹ ለስምንቱ ቅዱሳን ነገራቸውና እየመራ አብረው መጥተው በኢትዮጵያ መኖር ጀመሩ። በኋላ እነርሱ በአንድነት መኖራቸው ለወንጌልና ለምንኲስና መስፋት አይሆንም ነበርና ሀገሪቱን ተከፋፈሏት። በዚህም አባታችን አቡነ አረጋዊ ወደ ትግራይ በተለይም ወደ ደብረ ዳሞ መጦና በዚያ በዓታቸው ወሰኑ። በእሊህ ዘጠኝ ቅዱሳን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት እጅግ ብዙ የሐዋርያዊ አገልግሎት እንዲሰፋ ሆኗል።
አባ አረጋዊም ወደ ደብረ ዳሞ ለመውጣት በአደዱ ጊዜ የታዘዘ ዘንዶ ከወገባቸው ይዞ አውጥቷቸዋል። በዚያም ሲጋደሉ ከኖሩ በኋላ ያማረች ቤተ ክርስቲያንን ሠሩና መወጣጫውን ‹‹ዳህምሞ-አፍርሰው›› ብለው አስፈረሱት። በዚህም ዳሞ ተብላ እንደተጠራች ይነገራል። እርሳቸውም በገድል ተጸምደው ከኖሩ በኋላ በዚያችው ገዳማቸው ሳሉ ወደ ብሔረ ሕያዋን ተሠውረው ሄደዋል። እኒህ ደግ ጻድቅ ከቅዱስ ያሬድም ጋር የሚነገርላቸው ግሩም ዜና አላቸው።
የጻድቁ በረከት በሁላችንም ይደርብን! እግዚአብሔርም በጸሎታቸው ይማረን።
[ አሜን ]
#ይቆይ//
††† እንኳን ለጻድቃንና ሰማዕታት አባ ኢያሱና አባ ዮሴፍ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† አባ ኢያሱና አባ ዮሴፍ †††
††† እነዚህ 2 ቅዱሳን የደብረ ኮራሳኑ ጻድቅና ኮከብ የቅዱስ ሜልዮስ ደቀ መዛሙርት ናቸው:: የቅዱስ ሜልዮስ ነገርስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
ቅዱስ ሜልዮስ ልጅነቱን በመንፈሳዊ ትምሕርት ያሳለፈ: በጉብዝናው ወራት ፈጣሪውን ያሰበ ደግ ክርስቲያን ነው:: ይሕችን ዓለም ከነ ክፋቷ ንቆ ኮራሳት ወደሚባል በርሃ ሔዶ በተራራውና በደኑ ውስጥ በጾምና በጸሎት: በትሕርምትም ለበርካታ ዓመታት ተጋድሏል::
በነዚህ የብሕትውና ዘመናቱ ልብሱን ፀሐይና ብርድ ቆራርጦ ስለ ጨረሳቸው ፈጣሪው ጸጉርን አልብሶታል:: የአባ ሜልዮስ ጸጉሩ እስከ እግሩ: ጽሕሙ እስከ ጉልበቱ ነበር::
እድሜው ገፍቶ ሲያረጅ እንዲያገለግሉት እግዚአብሔር ሁለት ወጣት ምስጉን ክርስቲያኖችን ላከለት:: እነርሱም አባ ኢያሱና አባ ዮሴፍ ይባላሉ:: ሁለቱ ቅዱሳን አምላካቸውን እግዚአብሔርንና አባታቸው ቅዱስ ሜልዮስን በፍጹም ቅንነት አገልግለዋል::
ከቆይታ በሁዋላ ግን በአካባቢው የነበሩ ጣዖት አምላኪዎች አራዊት እናጠምዳለን ብለው በዘረጉት መረብ ቅዱስ ሜልዮስን ያዙት:: ክርስቲያን መሆኑን ሲያውቁ "ለፀሐይ ስገድ" ብለው ደበደቡት::
ደቀ መዛሙርቱ ተሯሩጠው መጥተው አባታቸውን በመከራ መሰሉት:: ክርስቶስን አንክድም ስላሉ ሁለቱንም በሰይፍ አንገታቸውን መቷቸው:: ቅዱስ ሜልዮስን ግን ለ15 ቀናት ካሰቃዩት በሁዋላ በቀስት በተደጋጋሚ ወግተው ገድለውታል:: ጻድቅና ሰማዕት ቅዱስ ሜልዮስ ብዙ ተአምራትን አድርጉዋል::
ገዳዮች ግን ወደ ሃገራቸው ሲመለሱ የሜዳ አህያ ሊያድኑ የወረወሩትን ቀስት የእግዚአብሔር መልአክ ወደነርሱ መልሶባቸው ልብ ልባቸውን ተወግተው ሙተዋል::
††† ይህች ቀን ቅዱሳን አባ ኢያሱና አባ ዮሴፍ ሰማዕትነትን የተቀበሉባት ናት::
††† ቸር አምላክ ከቅዱሱ ሜልዮስና ከደቀ መዛሙርቱ በረከትን ያካፍለን::
††† ሚያዝያ 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት ዲዮኒስ ዲያቆናዊት (የሐዋርያት ተከታይ የነበረች)
2.አባ ኢያሱና አባ ዮሴፍ (ሰማዕታት)
3.ቅዱስ መናድሌዎስ
4.አባ አኮላቲሞስ
††† ወርኀዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
3."99ኙ" ነገደ መላዕክት
4.ቅዱስ አስከናፍር
5."13ቱ" ግኁሳን አባቶች
6.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
7.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ
††† "ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ ራቁትነት: ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን?
'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቈጠርን'
ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው::
በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን::" †††
(ሮሜ. 8:35-38)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ለሰው ልጆች ይቅርታን ለማስገኝት ወደ ልዑል እግዚአብሔር አሻቅበው ለሚማልድ ዓይኖችህ ሰላምታ ይገባል።
ቅዱስ ሚካኤል ሆይ! መሬትና ውኃ ያልተቀላቀለበት ከነፍስና ከእሳት ብቻ ለተፈጠረው መልአካዊ ገጽታህ ሰላም እላለሁ።
የእግዚአብሔር ባለሟል ሆይ፤ በእግዚአብሔር ፊት በጎ መዓዛ ያለውን መሥዋዕት የምታሳርግ አንተ ሚካኤል ነህና
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ! የተጨነቁትን ዘውትር እንደምትረዳቸው ሁሉ እኔንም ለመርዳት ክንፈህን ዘርግተህ ፈጥነህ ድረሰልኝ።
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ! ፍጹም የማዳንህን ትድግና በኔ ላይ ትገልጽ ዘንድ በስተቀኜ ቁመህ አለሁልህ በለኝ እንጂ በሩቅ ሆነህ አትመልከተኝ
የቅዱስ ሚካኤል እረድኤት በረከት ጥበቃና ምልጃው አይለየን አሜን።
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †
† ስንክሳር ዘወርኀ ሚያዝያ ፲፩†
† ቅድስት ታኦድራ ገዳማዊት †
=>አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሚያዝያ ዐሥራ አንድ በዚች ዕለት የከበረችና የነጻች እመሜኔት ታዖድራ አረፈች።ይቺም ቅድስት ከእስክንድርያ አገር ከታላላቆች ባለጸጎች ወገን ናት ወላጆቿም ክርስቲያኖች ናቸው ።እነርሱም ዋጋው ብዙ በሆነ በወርቅና በብር ያጌጡ የከበሩ ልብሶችን አሠሩለት ከእርስዋ በቀር ልጅ ስለሌላቸው ሊአጋቡአት እነርሱ ያስባሉና።
እርሷ ግን የምንኲስና ልብስ ለብሳ በክብር ባለቤት ክርስቶስ ስም ልትጋደል ትወዳለች መከራ መስቀሉንም ልትሸከም ትወድ ነበር የዚህን የኃላፊውን ሠርግ አልፈለገችም ።ከዚህም በኃላ የወላጆቿን ዕቃ ገንዘብ ወስዳ ለሚሸጥላት ሰጠችው ለድኆችና ለምስኪኖች መጸወተች በቀረውም ከእስክንድርያ ውጭ በስተምዕራብ አብያተ ክርስቲያናትን አነፀች።
ወደ እስክንድያው ሊቀ ጳጳሳት ወደ አባ አትናቴዎስም ሔዳ ራሷን ተላጭታ ከእርሱ ዘንድ መነኰሰች ።ከደናግል ገዳማትም ወደ አንዱ ገብታ በገድልም ተጸምዳ ጽነዕ ገድልን ተጋደለች አምላካዊ ራእይንም ታይ ዘንድ ተገባት መላእክትን ታያለችና የሰይጣናትንም ሥራቸውን ለይታ ታውቃለችና ለሠሩ የታሰቡትን የምታውቅበትና የምትፈትንበት እውቀት ተሰጣት።
ቅዱስ አትናቴዎስም በእርሷ ፈጽሞ ደስ ይለው ነበር ወደርሱም ይጠራታል እርሱም ሊጎበኛት ወደርሷ ይሔዳል ኀሳቧንም ትገልጥለታለች እርሱም የጠላት ደያብሎስን ወጥመዱንና ምትሐቱን ያስገነዝባታል።ከመንበረ ሢመቱ ከእስክንድርያ በአሳደዱትም ጊዜ ብዙዎች ድርሳናትን ጽፎ ላከላት።
ይቺም ቅድስት እጅግ እስከአረጀች ድረስ ኖረች በመንፈሳዊ ተጋድሎም የጸናች ናት እርስዋ ከአምስቱ ሊቃነ ጳጳሳት ተምራለችና ።እሊህም እለ እስክንድሮስ አትናቴዎስ ጴጥሮስ ጢሞቴዎስና ተዎፍሎስ ናቸው።
እንዲህም ብለው ጠየቋት ሰው ተርታ ነገር ቢናገር ዝም በል ሊሉት ወይም እንዳይሰሙት ጆሮአቸውን መክደን ይገባልን እንዲህም ብላ መለሰች ምንም ምን ሊሉት አይገባም ነገሩ ደስ እንዳላቸው ሆነው ዝም ይበሉ እንጂ ሰው ማዕዱን በፊትህ ቢያኖር በላይዋም በጎ የሆነና ብላሽ የሆነ ምግብ ቢያኖር ይህን ብላሹን ከእኔ ዘንድ አርቀው አልሻውም ልትለው አይቻልህም መጥፎውን ትተህ ከምትፈቅደው ትበላለህ እንጂ ያለ ትሕትና ያለ ጾምና ጸሎት ሰይጣንን ድል የሚነሣው የለም።
መላ ዕድሜዋም መቶ ዓመት ሆኖዋት በሰላም አረፈች ጸሎቷ በረከቷ ከኛ ጋራ ለዘላለም ይኑር አሜን።
=>በዘችም ቀን የጋዛ ኤጲስቆጶስ የዮሐንስ መታሰቢያው ነው ።ደግሞ የእስክንድርያው የአባ በኪሞስ የስምዖን ዘለምጽና እግዚአብሔርም በጸሎታቸው ለዘላለሙ ይማረን አሜን።
=>ሚያዝያ 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ታኦድራ ገዳማዊት
2.አባ በኪሞስ ጻድቅ
3.ስምኦን ዘለምጽ
4.ቅዱስ ዮሐንስ ኤዺስ ቆዾስ
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ያሬድ ካህን
2.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት
3.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
4.ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና
5.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
=>+"+ ለእናንተም ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጐናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ:: ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ:: +"+ (1ዼጥ. 3:3)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †