ጀሞ መድሃኔዓለም የሚገኝ Bete Abrham /ቴሌግራሙም ይሄው ነው/ኑ እና ምሳ በማብላት ቸርነት አድርጉ ከመቶሃያ ሰው በላይ በእንተ ቅዱስ ገብርኤል ይላሉና አቤት በሉ።
Читать полностью…ጌታ የተገረፈው 6,666 ጊዜ ነው ለእድሜው ቁጥር (33) ሲካፈል 202 ጊዜ ይመጣል ...እድሜውን ሙሉ በዓመት 202 ጊዜ የተገረፈ ያህል መከራ ተቀብሏል !!!
ቆዳው ከሰውነቱ እስኪነሳ ሥጋው እስኪያልቅ አጥንቱ እስከሚታይ ድረስ ተገርፏል!!!
ሥጋው በጅራፍ ጫፍ እስኪበተን ደሙ ምድር ላይ እስኪረጭ ድረስ ተገርፏል!!!
የኛ ጌታ!!!
“ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።”
— ኢሳይያስ 53፥7
👉እኛ ግን እድሜ ዘመናችንን የአንዱን ግርፋት ስቃይ እንኳን በማሰብ መረዳት አልቻልንም😭
እንበለ ደዌ ወሕማም
እንበለ ፃማ ወድካም
ዓመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ እግዚአብሔር በፍሥሓ ወበሰላም
አሜን!
ወደ መሬት ወድቀን በሰገድን ጊዜ፣ ኃጢአት እንዴት ወደ ታች ጎትታ እንደጣለችን እናስታውሳለን። ዳግመኛም ከወደቅንበት በተነሣን ጊዜ፣ የእግዚአብሔር ጸጋ እና ምሕረት፣ እንዴት ከመሬት እንዳነሣንና፣ የሰማዩን ርስት እንደሰጠን እንመሰክራለን፣
ቅዱስ ባስልዮስ ዘየዐቢ፣
ዕለተ ሰሉስ፣❤️
✝✞✝ እንኩዋን ለጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችኹ ✝✞✝
✝✞✝ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ✝✞✝
=>ኢትዮዽያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በዚህች ቀን ከኢትዮዽያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል::
+ጻድቁ ምድረ እሥራኤል የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር:: የወቅቱ ሊቀ ዻዻሳት አባ ሚካኤል ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል::
+ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በሁዋላ ነው::
+ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር:: ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም:: በገሃድ:-
*በቤተ መቅደስ ብስራቱን
*በቤተ ልሔም ልደቱን
*በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን
*በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን
*በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር::
+የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደ ሆነው ቀራንዮ ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ::
በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ እመቤታችን ድንግል ማርያም ፈጥና ደርሳ ተክልየን ወደ ሰማይ አሳረገቻቸው::
+በዚያም:-
*የብርሃን ዐይን ተቀብለው
*6 ክንፍ አብቅለው
*የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው
*ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው
*ከ24ቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው
*ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው
*"ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል::
=>የተክለ ሃይማኖት አምላክ ከጻድቁ ትሩፋት: ጸጋና በረከት ይክፈለን::
† አባ ይስሀቅ †
በዚች ቀን ከግብፅ ደቡብ ከእብክ አውራጃ ከሆሪን ከተማ የከበረ አባት ይስሀቅ አረፈ። የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አብርሀም የእናቱም ስም ሶስና ነው ታናሽም ሆኖ ሳለ እናቱ ሙታ ብቻውን ያለእናት አባቱ እያሳደገው ኖረ።
ጥቂት በአደገም ጊዜ የአባቱን በጎች የሚጠብቅ ሆነ አባቱም ሌላ ሚስት አገባ በዚያ ወራትም ታላቅ ረኃብ ሆነ የአባቱም ሚስት ትጠላው ነበረ ከጥቂትም በቀር እንጀራ አትሰጠውም ያንኑም ሁልጊዜ ለእረኞች ሰጥቶ እርሱ ግን እስከምሽት ይፈፀማል።
ምሳውን ለእረኞች እንደሚሰጥና ሁልጊዜ እስከምሽት እንደሚፆም አባቱ ሰምቶ እውነት እንደሆነ ሊያይ ወደርሱ ሄደ። ቅድሱም ህፃን የአባቱን መምጣት አውቆ በልብሱ ሶስት ጭቃ አድበልብሎ አሰረ እንደ ታሰረ በሚያየው ጊዜ ለአባቱ አምባሻ እንዲመስለው ብሎ።
አባቱም በመጣ ጊዜ የልጁን ልብስ ፈትቶ አየ አንባሻም ሆነው አገኛቸው።የነገረውንም ሰው ምግቡን ለእረኞች ከሰጠ በዛሬይቱ ቀን ይህ አምባሻ ከወዴት ተገኘለት ብሎ ጠየቀው እርሱም በእውነት ሰጥቷል አለ ሌሎችም ብዙዎች መጥተው በዚህ ነገር ምስክሮች ሆኑ አባቱም አደነቀ እግዚአብሔርንም አመሰገነ።
ይህም በአደገ ጊዜ አባ ኤልያስ ወደሚባል ሰው ሄዶ መንኩሶ በዚያ እየተጋደለ ብዙ አመታት ኖረ። አባ ኤልያስም በአረፈ ጊዜ በርኑግ ወደሚባል ገዳም ሄደ ስሙ ዘካርያስ ከሚባል አረጋዊ ዘንድ በታላቅ ገድል ተጠምዶ ኖረ።
አባቱም ያገኘው ዘንድ በሀገሮች ሁሉ ይዞር ነበረ በዚህ በበርኑግ ገዳምም በአገኘው ጊዜ ከእርሱ ጋራ እንዲመለስ አባቱ ለመነው አይሆንም አለ አባ ዘካርያስም ከአባቱ ጋራ ይሄድ ዘንድ እስከ ሚአርፍም ከእርሱ ዘንድ እንዲኖር አዘዘው ይህ ቅዱስም ከአባቱ ጋራ ሄዶ እስከሚአርፍ ድረስ ከእርሱ ዘንድ ኖረ።
አባቱም በአረፈ ጊዜ አባቱ የተወውን ገንዘብ ሁሉንም ለድኆችና ለምስኪኖች ሰጠ ከከተማውም ጥቂት ራቅ ብሎ ለራሱ ታናሽ ማደሪያ ሰራ በሰላም እሰከ ሚአርፍባት ቀን ድረስ ያለ ማቋረጥ በበጎ ገድል በፆም በፀሎት በስግደት ኖረ በአረፈ ጊዜም በመልካም ቦታ አኖሩት ከዚያም ተሰወረ።
ከብዙ ዘመናትም በኃላ እግዚአብሔር ሊገልጠው ወዶ በመቃብሩ ላይ መብራት ሲበራ እህል ለሚአጭዱ ሰዎች ሶስት ቀን ያህል ታየ ሊያዩትም ወደቦታው ሲደርሱ ያ መብራት ከእርሳቸው ይሰወራል በሁሉ ዘንድ እስቲሰማም እንዲህ ሆኖ ኖረ።
ከዚህም በኃላ በመቃብሩ ላይ እያበራ ያ መብራት ደግሞ ታያቸው ስጋውም በዚያ እንዳለ ሁለተኛ በህልም ነገራቸው ምእመናንም አክብረው በግመል ጭነው ወደ ሀገሩ መካከል ወደ ሆሪን ወሰዱት ነስሪን ከሚባል ሀገር መካከል ሲደርሱ ግመሉ በዚያ ተንበረከከ እንዲነሳም መቱት መነሳትንም እቢ አለ መኖሪያው በዚያ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔር ፈቃድ እንደሆነ አወቁ።
በዚያም በስሙ ቤተ ክርስቲያን ሰርተው ስጋውን በውስጥዋ አኖሩ ሰርተው ስጋውን በውስጥዋ አኖሩ ከእርሱም ብዙ ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ።
† ቅዱስ እለእስክንድሮስ †
በዚች ቀን የከበረ አባት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳትም አስራ ዘጠነኛ የሆነ እለእስክንድሮስ አረፈ። ስለርሱም ሀዋርያዊ አባት አትናቴዎስ እንዲህ አለ አባቴ እለእስክንድሮስ ተቀምጦ ወንጌልን አያነብም ቁሞ ያነባል እንጂ ከርሱ ጋራም ብርሀን አለ።
ሁለተኛው ስለርሱ ሲናገር ወደርሱ እመምኔቶች መጥተው በእኛ ዘንድ ሰባት ሰባት ቀን የሚሶሙ ደናግል አሉ ።በእጆቻቸውም ምንም ምን ስራ አይሰሩም ብለው ነገሩት።
እርሱም እህቶቼ ሆይ እኔ ሁለት ቀን እንኳን ከቶ አልፆምኩም ፀሀይ እስኪገባው ቆይቼ አልበላሁም በልክ እበላለሁ በልክም እፆማለሁ በልክ በመጠንም እሰራለሁ በልክ ይበሉ ዘንድ በልክም ይፆሙ ዘንድ በልክም ስራ ይሰሩ ዘንድ ነግሯቸው በበጎ ስራ ሁሉ ይሰለፉ አለ።
የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ደጎች ምእመናን ናቸው እርሱም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ ሆኖ ከታናሽነቱ ጀምሮ በውስጥዋ አደገ።አባ መክሲሞስ አናጒን ስጢስነት አባ ቴዎናስ ዲቁና ተፍፃሜተ ሰማእት ጴጥሮስም ቅስና ሹመውታልና እርሱም ከታናሽነቱ ጀምሮ ንፅህ ድንግል ነው።
አባ ጴጥሮስ በሰማእትነት የሚሞትበት ጊዜ ሲቀርብ በግዞት ቤት ሳለ ይህ እለእስክንድሮስና አኪላስ ከውግዘቱ ይፈታው ዘንድ ስለ አርዮስ ወደርሱ ገብተው ለመኑት ስለርሱ አባ ጴጥሮስን ይማልዱለት ዘንድ ሁለቱን ለምኖአቸዋልና።
አባት ጴጥሮስ ግን በውግዘት ላይ ውግዘትን ጨመረበት እንዲህም ብሎ ነገራቸው የክብር ባለቤት ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀደደ ልብስ ለብሶ ተገለፀልኝ ልብሴን አርዮስ ቀደዳት አለኝ። ይህም የባህርይ አንድነቴን ለያት ማለት ነው ውግዘቱንም እንድጨምርበት እርሱ አዘዘኝ።
ደግሞ እንዲህ ገለጠላቸው አኪላስ ሊቀ ጵጵስና እንዲሾም ከርሱ በኃላም እለእስክንድሮስ እንደሚሾም አርዮስን እንዳይቀበሉት በምንም ስራው እንዳይተባበሩት አዘዛቸው።
አባ ጴጥሮስም ምስክርነቱን በፈፀመ ጊዜ አኪላስ ሊቀ ጵጵስና ተሾመ የአባት ጴጥሮስንም ትእዛዝ ተላልፎ አርዮስን ከውግዘቱ ፈታው። ቅስናም ሾመው ስለዚህም አኪላስ በመንበረ ሲመቱ ያለ ስድስት ወር አልኖረም በድንገት ሞተ።
ከዚህ በኃላ ይህ አባት እለእስክንድሮስ ሊቀ ጵጵስና ተሹሞ በመንበረ ሲመቱ ላይ ተቀመጠ አርዮስንም ከወገኖቹ ጋራ አውግዞ አሳደደው። የሀገር ታላላቆችም ከህዝቡ መጡ ከውግዘቱ እንዲፈታውም ለመኑት። በውግዘት ላይ ውግዘትን እንዲጨምር እንጂ እንዳይፈታው አባት ጴጥሮስ እንደአዘዘው ነገራቸው።
ከዚህ በኃላ አርዮስ ወደ ንጉስ ቈስጠንጢኖስ ሂዶ በግፍ አወገዘኝ ብሎ እለእስክንድሮስን ከሰሰው። ስለዚህም ንጉሱ ሶስት መቶ አስራ ስምንት የከበሩ አባቶችን በኒቅያ ከተማ ሰበሰበ።
ሚያዚያ 22/2016 #ሰሙነ_ህማማት_ማክሰኞ
👉በሰሙነ ህማማት ያለችው ሁለተኛዋ ቀን ማክሰኞ ይህች ቀን በዚህ በሰሙነ ህማማት ሳምንት የራሷ የሆነ የዕለት ስያሜ አላት
ይኸውም
👉 #የጥያቄ_ቀን_ይባላል፦ ጌታችን ሰኞ ዕለት ባደረገው አንፅኦተ ቤተ መቅደስ ቤቱን ካፀዳ በኋላ በፃህፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋል
👉ፃህፍት ፈሪሳውያን ጌታን በዚህ ዕለት ምን ብለው ጠየቁት ቢሉ ከምድራውያን ነገስታት ያይደለህ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለህ ትምህርት ማስተማር ተዓምራት ማድረግ ገበያ መፍታት በማን ስልጣን ታደርጋለህ ይህንንስ ስልጣን ማን ሰጠህ የሚል ነበር ማቴ 21፥23 ማር 11፥27 ሉቃ 20፥1
👉እርሱም ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መልሶ እንዲህ አላቸው አንድ ነገር ልጠይቃቹ? እናንተም ብትመልሱልኝ እኔም በማን ስልጣን እንዳደረኩኝ እነግራቹሀለው አላቸው
👉የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነች? ከሰማይ ወይስ ከሰው? አላቸው እነርሱም ከሰማይ ብንለው ስለምን አልተቀበላችሁትም ከሰው ብንለው ህዝቡ ሁሉ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል እንደ መምህርነቱም ያፍሩታልና እንፈራቸዋለን ተባብለው ከወዴት እንደሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት እርሱም እኔም በማን ሥልጣን እንደማደርግ አልነግራችሁም አላቸው
👉ፃህፍት ፈሪሳውያን ጌታችን መድኋኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ይህንን ጥያቄ መጠየቃቸው የሚያደርገው ነገር ሁሉ በስልጣኑ እንደሆነ ጠፍቷቸው ሳይሆን እርሱን ከመልሱ አንፃር አጥምደው ከህዝብና ከመንግስት ጋር አጋጭተው ለማስያዝ ምክንያት ፍለጋ እንዲመቻቸው እንጂ
👉እኛ ክርስቲያኖች ከዚ የምንማረው አበው በምሳሌያቸው ክፉ ጠሪ አቤት ባይ ያከፋል እንዲሉ ክፉ ነገር አስበን ክፉ ነገር እንዳይገጥመን እንዳይመጣብን ከማንኛውም ክፉ ነገር አንደበታችንን መቆጠን እንዳለብን ነው ሌላው በዚች በማክሰኞ ቀን ታስቦ የሚውለው ደግሞ
👉 #የትምህርት_ቀን_ይባላል፦ በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስ እረጅም ትምህርት ጌታ ስላስተማረ የትምህርት ቀን ይባላል ይኸውም ከሃይማኖት የራቁትን ከፍቅረ እግዚአብሔር የተለዪትን አስተምረን መመለስ እንደሚገባን ሲገልፅልን ነው ማር 12፥1 ሉቃ 20፥9
👉እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም "አሜን ኪራላይሶን " ➕ ⛪️ ➕
ሚያዚያ 21/2016 #ሰሙነ_ሕማማት
👉የተዋህዶ ልጆች ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ሰሙነ ሕማማት የፆመ ሁዳዴ የመጨረሻው ሳምንት የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም የሚታሰብበት፤ ካህናትና ምእመናን በአፀደ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ የሚያዜሙበት፤ ግብረ ሕማም በመባል የሚታወቀውን መፅሐፍ የሚያነቡበትና የሚሰሙበት፤ በነግህ፣ በሦስት፣ በስድስት፣ ዘጠኝ ፣በዐስራ አንድ ሰዓት እየመላለሱ የሚሰግዱበትና የምንሰግድበት የምንፀልይበት ልዩ ሳምንት ነው እንኳን አደረሰን
👉በዚህ ሳምንት በተለይ ካህናት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ ምክንያቱም ጌታችን የደረሰበትን መከራና ስቃይ እንዲሁም የሰው ልጅ አምስት ሺ አምስት መቶ ዘመን በጨለማ ግዞት ይኖር እንደነበር ለማዘከርም ጭምር ነው
👉የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራና ሕማም በፅኑ እንድናስበው ያስተማሩን ሐዋርያት ናቸው ለእነርሱም የነገራቸው ደግሞ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
👉ሰሙነ ሕማማት የጌታችንን ሕማማት ከማሰብ ጋር በየዕለቱ በርካታ ድርጊቶች መፈፀማቸውን የምናስታውስበት ሳምንት ነው
👉 #ሰኞ
#መርገመ_በለስ_የተፈጸመበት_ሰኞ_ይባላል
በዚህ ዕለት ጌታችን ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን በለስ ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር ባለማግኘቱ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላ” ማር ፲፩፥፲፬ በማለት ስለረገማት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል
#አንጽሖተ_ቤተ_መቅደስ_ይባላል
ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሄዶ በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እና የሚለውጡትን “ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች” ማቴ ፳፩፥፲፫ በማለት ከቤተመቅደስ ገርፎ አስወጥቷቸዋልና
👉#ማክሰኞ
#የጥያቄ_ቀን_ይባላል
ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታ “በምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ?” ማቴ ፳፩፥ ፳፫ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል
#የትምህርት_ቀን_ይባላል
በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪።
👉#ረቡዕ
#ምክረ_አይሁድ_ይባላል
ረቡዕ እለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ፀሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል ወቅቱ የፋሲካን በዓል የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ እና ብዙ ህዝብም ጌታን ይከተለው ስለነበር ሁከት እንዳይነሳ ስጋት ነበራቸው ነገር ግን ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ስለነገራቸው ሉቃ ፳፪፥፩-፮ ጭንቀታቸው ተወግዶ በጌታ መያዝ ተስማምተዋል።
👉#ሐሙስ
#ጸሎተ_ሐሙስ_ይባላል
ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲፀልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር በፍፁም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል
#የሐዲስ_ኪዳን_ሐሙስ_ይባላል
መሥዋዕተ ኦሪት በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል
👉#ዓርብ
#የስቅለት_ዓርብ_ይባላል
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል "ኪራላይሶን"
ሰሙነ ሕማማት
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከትንሣኤ በፊት ያለው አንድ ሳምንት ሰሙነ ሕማማት /የሕማማት ሳምንት/ በማለት ትዘክረዋለች። ሕማማት የሚለው ቃል ሐመ፣ ታመመ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕማሙና ሞቱ የሚዘከርበት ሳምንት ነው።ሰሙነ ሕማማት በላቲን Hebdomas Sancta or Hebdomas Maior፣ በግሪክ ደግሞ Ἁγία καὶ Μεγάλη Ἑβδομάς, Hagia kai Megale Hebdomas (ታላቁ ሳምንት) ተብሎ ይጠራል፡፡ በኛ ደግሞ ሰሙነ ሕማማት ይባላል። ሰሙነ ሕማማት ከሆሣእና እስከ ትንሣኤ ባሉት ቀናት ጌታችንን ለመያዝ አይሁድ የመከሩበት፣ ምክራቸውን ያፀኑበት፣ ጌታችንን ሳይዙ እህል ላለመቅመስ ክፉ መሐላ የተማማሉበት፣ጌታችንን የያዙበት፣ የገረፉበት እና በዕለተ ዐርብ በቀራንዮ የሰቀሉበት ሳምንት ይህ ሰሙነ ሕማማት ተብሎ ይጠራል። ሰሙነ ሕማማት እስከ ዐራተኛው ምዕተ ዓመት ድረስ ከጾሙ ተለይቶ ለብቻው ይከበር ነበር። በኋላ ግን በባሕረ ሐሳብ ቀመር መሠረት ጾሙም፣ ሕማማቱም፣ ትንሣኤውም ተያይዘው እንዲከበሩ ተደረገ። ምዕራባውያን ከዐርባ ጾም ውስጥ የመጨረሻውን ሳምንት ሰሙነ ሕማማት ያደርጉታል። የምሥራቃውያን /ኦርየንታል/ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ግን አርባውን ጾም ጨርሰን ከሆሣእና ቀጥሎ ያለ አንድ ሳምንት ሰሙነ ሕማማት አድርገን እናከብራለን።
በሌላ በኩል ሰሙነ ሕማማት የኦሪት ዘመን ምሳሌም ነው። በዘመነ ኦሪት (አዳም ከገነት ከተባረረበት እስከ ጌታችን በቤተ ልሔም እስከተወለደበት ዘመን) የሰው ልጅ የጽድቅ ሥራው ለመንግሥተ ሰማያት የማያበቃው ነበር። ይልቁንም ነቢዩ ‘’ጽድቃችን የመርገም ጨርቅ ሆነ’’ ኢሳ 64:6 እንዳለ የአዳም ዘር በሙሉ እስከ ዕለተ ዐርብ ጌታችን በመስቀል ላይ ሆኖ እስካዳነን ድረስ በዲያብሎስ ባርነት ሥር ነበርንና ሰሞነ ሕማማትም የዘመነ ፍዳ ምሳሌ ነው።ይህንንም ለማሰብ በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት በሰሙነ ሕማማት ከጸሎተ ሐሙስ በስተቀር ቅዳሴ አይቀደስም፣ ስብሐተ ነግህ አይደርስም፣ ሥርዓተ ማኅሌት፣ ሥርዓተ ተክሊል፣ ጸሎተ ፍትሐት አይጸለይም፣ ጸሎተ አስተሰርዮም አይደረግም፣ ጥምቀተ ክርስትና አይፈጸምም፣ በመስቀል መባረክ፣ ኑዛዜ መስጠትና መቀበል፣ እግዚአብሔር ይፍታሕ ማለት አይኖርም። ከላይ የተዘረዘሩት የቤተ ክርስቲያን ሥርዓቶች አስቀድሞ በዕለተ ሆሳዕና ይከናወናሉ።በሰሞነ ሕማማት ከዚህ ዓለም በሞት የሚለይ ሰውም የፍትሐት ጸሎት አይደረግለትም። ይህ ማለት በዕለተ ሆሣዕና በአካለ ሥጋ እያለን ካህናት አባቶቻችን የፍትሐት ጸሎት ያደርጉልናል። ሰሙነ ሕማማት የተለየ ሳምንት ነውና፣ እንኳን ሥጋዊ ደስታና ሣቅ ጨዋታ መንፈሳዊ ደስታም የተከለከለ ነው፡፡በሰሙነ ሕማማት ምእመናን እርስ በርስ በመሳሳም ሰላምታ አይለዋወጡም።ይህም ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ሰጥቷልና ያንን ለማሰብ ነው።
በሰሞነ ሕማማት መጻሕፍተ ኦሪት፣ መጻሕፍተ ነቢያት፣ የዳዊት መዝሙር ይነበባል።በዚህ ልዩ በሆነ ሳምንት ካህናትና ምእመናን በነግህ፣ በሠልስት፣ በቀትር በተሰዓትና በሠርክ ወደ ቅድስት ቤተ ክርሰቲያን በመጓዝ ስለጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ሕማማተ መስቀል የሚያዘክረውን ምዕራፍ ከቅዱሳት መጻሕፍት በማንበብና በመጸለይ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕማሙንና ሞቱን ያዘክራሉ።’’እርሱ ግን ስለመተላለፋችን ቆሰለ፣ ስለበደላችንም ደቀቀ፣ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፣ በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን’’ ኢሳ.53፡4-7 ተብሎ የተነገረው ቃል ተፈጽሞ ጌታችን ለድኅነተ ዓለም ሲል በአጭር ደረት በጠባብ ደረት ተወስኖ የተቀበለው ጸዋትወ መከራ የሚዘከርበት ሳምንት ነው።ነቢያት መቼ ወደ ዚህ ዓለም መጥተህ ከዓመተ ፍዳ ታድነናለህ? ሲሉ የተማፀኑበት ጸሎት፣የጌታችንን ስለእኛ ሲል የመያዙን፣የመገረፉን እና የመሰቀሉን ነገር ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው በትንቢት መነፀር እየተመለከቱ የተጻፉ የነቢያት መጻሕፍት ይነበባሉ፣ይጸለያሉ።
ከቤተ ክርስቲያናችን ሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት ውስጥ የረቡዕ እና ዐርብ ጾም የሚጾምበት ምክንያትም
በሰሙነ–ሕማማት አይሁድ ጌታችንን ለመያዝ ከዕለተ ሰኞ ጀምሮ እስከ ረቡዕ ድረስ ክፉ ምክር ሲመክሩ ቆይተው በዕለተ ረቡዕ ምክራቸውን ያፀኑበት ቀን ሲሆን በዕለተ ዐርብ ደግሞ ጌታችንን የሰቀሉበት ቀን ስለሆነ ነው። በሰሞነ ሕማማት ሳምንት በቤተ ክርስቲያን ግብረ ሕማማት የተባለ መጽሐፍ ይነበባል።ግብረ ሕማማት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለዘሩ ድኅነት የተቀበለውን መከራ የሚዘክር መጽሐፍ ነው፡፡ ግብረ ሕማማት ማለት የሕመም ፣ የመከራ ሥራ ማለት ነው፡፡ የጌታን መከራውን ሥቃዩን ሕማሙን በሠዓትና በጊዜ ከፍሎ የሚናገር ፣ እንዲሁም ምን በማን መጸለይ እንደሚገባውም በዝርዝር የሚገልጽ በመሆኑና የጌታችንን ሕማም በምናስብበት በሰሙነ ሕማማት በዋነኝነት አገልግሎት ላይ የሚውል በመሆኑ ግብረ ሕማማት ተባለ፡፡ መጽሐፉ ግብረ ሕማማት እንዲባል በውስጡ የታዘዘ መሆኑን የአማርኛው ትርጉም መቅድም ይገልጻል፡፡በግብረ ሕማማት መግቢያ ላይ ‘ሐዋርያት ለስብከት ወንጌል በሚፋጠኑበት ጊዜ፣ስለ እርሱ ስለ ጌታችን ታሪኩና ተአምራቱን ይከታተሉ ከነበሩት መካከል የተከበሩና የታወቁ ሊቃውንት በኢንፎስና በገማልያል እጅ ተፅፎ በቅድስት ሀገር በኢየሩሳሌም በክብር ቦታ ተቀምጦ የተገኘ ነው’ ይላል።
ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው ፤ ሆሳዕና በአርያም እያሉ ይጬኹ ነበር ፦
ማቴ 21 ÷ 9
╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥ @teksochina_meslochi ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯
#ከቅዳሴያችን ስለሆሣዕና
(ቅዳሴ ዘጎርጎርዮስ እኅወ ባስልዮስ ቁጥር ፴፰-፵፱)
፴፰ ፤ ቃል ፡ ቀዳማዊ ፡ ነው
ያ ፡ ቃል ፡ የእግ ዚ አ ብ ሔ ር ቃል ፡ ነው ፡
ያ ፡ ቃል ፡ ሥጋ ፡ ሆነ ፡
በእኛም ፡ አደረ ፡ ከእኛም ፡ ሠወረው።
፴፱ የሚጠፋ ፡ ሥጋን ፡ ለበሰ ፤ የማይጠፋም ፡ አደረገው ። በዚህችም ፡ ሥጋ ፡ የማይገረፍ ፡ አምላክ ፡ ተገረፈ ።
፵ ፤ በወንድማችሁ ፡ መከራ ፡ አንድ
የምትሆኑ ፡ የወዳጆቻችሁንም ፡ መከራ ፡
የምትቀበሉ ፡ ይህን ፡ ግርፋት ፡ ታዩ ፡ ዘንድ ኑ ።
በዓይን ፡ ለሚያየው ፡ ዕፁብ ፡ ነው ።
በጆሮው ፡ ለሚሰማው ፡ ድንቅ ፡ ነው ።
ከባሪያ ፡ የፊቱን ፡ መጸፋትና ፡ በሊቃነ ፡ ካህናቱም ፡ ሸንጎ ፡ ራሱን ፡ በዘንግ ፡ መመታቱን ፡ ታዩ ፡ ዘንድ ፡ ኑ ። " "
፵፩ ፤ ሁሉን ፡ የሚያድን ፡ ጌታን ፡ ያቀዳጁትን ፡ የእሾህ ፡ ዘውድ ፡ ታዩ ፡ ዘንድ ኑ።
፵፪ ፤ ለርሱ ፡ ብቻ ፡ እንሰግድ ፡ ዘንድ ፡ ኑ
በአየር ፡ ላይ ፡ የምትወጡ ፡ ሁላችሁ ፡ የመላእክት ፡ ሠራዊት ፡ ወደ ፡ ፀሐይና ፡ ወደ ፡ጨረቃ ፡ ወደ ፡ ከዋክብተም ፡የምትላኩ ፣ወደ ፡ ባሕርና ፡ ወደ ቀላያትም የምትወጡ ።
፵፫ ፡ የአምላክን ፡ የፊቱን ፡ መጸፋት ባየች ፡ ጊዜ ፡ ባሕር ፡ ተንቀጠቀጠች ፡ ማየ ተከዚም ፡ ሸሸች ፡ ፀሐይ ፡ ጨለመ ፣ ጨረቃም ፡ ደም ፡ ሆነ ። ከዋክብትም ፡ ከብዙ ፡ብርሃናቸው ፡ ተራቆቱ ።
፵፬ ፤ ሞት ፡ ፈራ ፡ ዲያብሎስም ፡ ወደቀ “ሲኦልም ፡ ግሩም ፡ የሆነ ፡ አምላክን ፡ ለመቀበል ፡ ከወገኖቿ ፡ ጋራ ፡ ባንድነት ፡ሄደች ።
፵፭ ፤ የካህናት ፡ አለቃ ፡ ወደ ፡ መጋረጃ 'ውስጥ ፡ በገባ ፡ ጊዜ ፡ በጸሎት ፡ ቤት ፡ የተደረገውን ፡ ድንቅ ፡ ነገር ፡ ታዩ ፡ ዘንድ ፡ ኑ ።
ሁሉም ፡ መለኮትን ፡ የምትሸሽግ ፡ ኀሊናትንም ፡ ሁሉ ፡የምትሰውር ፡ ናት ፡ ይሏታል፡የአጋዕዝትና ፡ የመናፍስት ፡ ጌታ ፡ በተዋረደ ፡ አህያ ፡ ግልገል ፡ ተቀምጦ ፡ ወደርስዋ ገባ ።
፵፮ በ እ ግ ዚ አ ብ ሔር ስም ፡ የሚመጣ ፡ቡሩክ ፡ ነው ። አንተም ፡ የአማልክት ፡ አምላክ ፡ የእሥራኤልም ፡ንጉሥ ፡ እግዚአ ብሔር ቡሩክ ፡ ነህ ፡ እያሉ ለሚያመሰግኑ ፡ሕፃናት ፡ ሁሉ ፡ ጌትነቱን ፡ አሳየ ።
፵፯ የሆሣዕናን ፣ ዑደት ለነርሱ
ለደቀ ፡ መዛሙርቱ ፡ አሳየ ፡ ቡሩክ ፡ እርሱ ፡በታላቅ ፡ ቃል ፡ እየጮኻችሁ ' ሆሣዕና ፡
በአርያም ፡ በሉ ፡ አላቸው።
#ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ፣ ሆሣዕና በአርያም ፡
፵፰ ከመድኃኒትነቱ ' የተነሣ ፡ከዚህ ፡ አስቀድሞ ፡ ያልተደረገ ' ከዚህም ፡በኋላ የማይደረግ ተአምራትንና ፡ መንክራትን ፡ አሳየ።
#ሆሣዕና ፡ በአርያም ' ሆሣዕና ፡ በአርያም ፡ ሆሣዕና በአርያም
፵፱ ከመድኃኒትነቱ ፡ የተነሣ፡ ከቤቱ ፡ መሠረት ፡ ሳይናወጥ ፡ ከልዑል ፡መንበሩ ፡ ወርዶ ፡ ጸጋንና ፡ ኃይልን አሳየ።
#ሆሣዕና በአርያም ፡ ሆሣዕና ፡ በአርያም ፡ሆሣዕና በአርያም
ከመድኃቲነቱ የተነሣ ለኃጥአን የዕንባ ምንጭ ሰጠ። የበደሉትን ያጸድቃቸው ዘንድ ያደፉትን ያነጻቸው ዘንድ የሳቱትን ይመልሳቸው ዘንድ
#ሆሣዕና ፡ በአርያም ፡ ሆሣዕና ፡በአርያም ሆሣዕና ፡ በአርያም
(በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት ከኒቆዲሞስ ረቡዕ ጀምሮ እስከ እሑድ ድረስ የቅዱስ ባስልዮስ ወንድም የሆነው ቅዱስ ጎርጎርዮስ የደረሰው ቅዳሴ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት ይቀደሳል።
የቅዳሴ ጎርጎርዮስ በዋናነት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተ ፋጌ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ሆሣዕና በአርያም አቤቱ አሁን አድን በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ነው በሚሉ ምስጋናዎች እንደተቀበሉት በስፋት የሚያነሳ ቅዱስ ድርሰት ነው።)
++++++++++++++++++++
#በእኛ ሕይወት ከብሮ የሚመሰገነው መቼ ይሆን?
#ያንተ መሆንን ስጠን።
አሜን
#የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
#በዓለ ሆሣዕና
(በላእከ ወንጌል በእደ ማርያም ይትባረክ /ቀሲስ/
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የትምህርት ሥርጭት ኃላፊ)
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከምታከብራቸው ዘጠኙ ዐበይት በዓላት መካከል አንዱ የሆሣዕና በዓል ነው፡፡ ስለዚህ በዓል አስቀድሞ ትንቢት ተነግሯል፤ ከትንቢቶቹም አንዱ እንደሚከተለው ተጠቅሷል፡፡
“አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በይ እነሆ ንጉሥሽ ትሑት ሆኖ በአህያና በአህያይቱ ውርንጫ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል” /ትን. ዘካ. 9፡9/
ከዚህም ጋር ስለበዓለ ሆሣዕና አራቱም ወንጌላውያን ጽፈዋል፡፡ ይህም፡- ማቴ. 21፡1-11፣ ማር. 11፡1-10፣ ሉቃ. 19፡28-40፣ ዮሐ. 12፡12-15 አራቱም ወንጌላውያን የጻፉት የበዓሉ ታሪክ እንደሚከተለው ተገልጻል፡፡
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም ቀርቦ ደብረ ዘይትም በሚባል ተራራ አጠገብ ወዳሉት ወደቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረበ ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ላከና በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፡፡ ወደ እርስዋም ገብታችሁ ከሰው ገና ማንም ያልተቀመጠባት አህያ ከውርንጫይቱ ጋር ታሥረው ታገኛላችሁ ፈትታችሁ አምጡልኝ ማንም ስለምን እንዲህ ታደርጋላችሁ? ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ አላቸው፡፡ የተላኩትም ሄደው እንዳላቸው አገኙ፡፡ እነርሱም አህያዋንና ውርንጫዋን ሲፈቱ የአህያው ባለቤት አህዮቹን ስለምን ትፈቷቸዋላችሁ? አላቸው እነርሱም ለጌታ ያስፈልጉታል አሉ ፈቀደላቸው ወዲያው አመጡለት፡፡ የታሠሩትን ፈትታችሁ አምጡልኝ ማለቱ ሰው ሁሉ ከኃጢአት ማሠሪያ የሚፈታበት ጊዜ እንደደረሰ ለማጠየቅ ነው፤ ደቀ መዛሙርቱም ልብሳቸውን በአህያዋና በውርንጫዋ ላይ ጎዘጎዙ የዚህም ምስጢር ኮርቻ ይቈረቍራል ልብስ አይቈረቍርም የማትቈረቍር ሕግ ሠራህልን ሲሉ፤ አንድም ልብስ በአካል ያለውን ነውር ይሸፍናል አንተም ከባቴ አበሳ /በደልን የምትሸፍን/ ነህ ሲሉ ነው፡፡
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በአህያዋና በውርንጫው ላይ በጥበብ በአንድ ጊዜ ተቀምጦባቸዋል ለእርሱ የሚሳነው ነገር የለምና፡፡ በአህያ የተቀመጠበት ምክንያት ደግሞ ቀድሞ ነቢያት ዘመነ ጸብዕ የሆነ እንደሆነ በፈረስ ተቀምጠው ይታያሉ፡፡ ዘመነ ሰላም የሆነ እንደሆነ በአህያ ተቀምጠው መነሳንስ ይዘው ይታያሉና ዘመነ ሰላም ደረሰ ሲል ትንቢቱን ባወቀ አናግሯል ምስጢሩም በአህያ የተቀመጠ ሸሽቶ አያመልጥም አሳዶም አይዝም እሱም ካልፈለጉኝ አልገኝም ከፈለጉኝ አልታጣም ሲል ነው፡፡ ሲሄዱም ሕዝቡ ልብሳቸውን በመንገድ አነጠፉ፡፡ እንኳንስ አንተ የተቀመጥክባት አህያ መሬት መርገጥ አይገባትም ሲሉ ነው፡፡ እንዲሁም ሕዝቡ፣ ሕፃናቱ ሳይቀሩ ዘንባባ ይዘው የሚቀድሙትም የሚከተሉትም “ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር” /ለዳዊት ልጅ መድኃኒትን መባል ይገባዋል፤ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ነው/ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ያመሰግኑ ነበር፡፡ ሆሣዕና ማለት መድኃኒት ማለት ነው፡፡
#የዘንባባው ምስጢርም፡- አብርሃም ይስሐቅን፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብን በወለዱ ጊዜ፤ እስራኤል ከግብፅ በወጡ ጊዜ፣ ዮዲት ሆሎፎርኒስን በገደለች ጊዜ ዘንባባ ይዘው እግዚአብሔርን አመስግነዋልና በዚህ መሠረት ሕዝቡ፡- የሰላም አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ላይ ተቀምጦ ሲሄድ ዘንባባ ይዘው አመስግነውታል፡፡
ደቀ መዛሙርቱ ሲያመሰግኑ ከሕዝቡ መካከል ከፈሪሳውያን አንዳንዱ መምህር ሆይ፡- ደቀ መዛሙርትህን ገሥጻቸው አሉት፡፡ መልሶም እላችኋለሁ እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ያመሰግናሉ አላቸው፤ ድንጋዮች ሳይቀሩ አመስግነውታል፡፡ (ሉቃ. 19፥40)
በዚህ መሠረት ይህ በዓል የምስጋና በዓል ነው፡፡ እኛም ፈጣሪያችንን ሁልጊዜ ማመስገን አለብን የተፈጠርነውም ስሙን ለመቀደስ ክብሩን ለመውረስ ነው፡፡ ስሙን ለመቀደስ ማለት ስሙን ለማመስገን ማለት ነው፤ ክብሩን ለመውረስ ማለት ደግሞ መንግሥተ ሰማያትን ለመውረስ ማለት ነው፡፡ የተፈጠርነው ለዚህ የተቀደሰ ዓላማ ስለሆነ ሁልጊዜ እግዚአብሔርን ማመስገን ይገባል፡፡
ምስጋናውም በፍጽም እምነት፣ በቅንነትና በንጹሕ ልብ መሆን አለበት፡፡ “እባርኮ ለእግዚአብሔር በኵሉ ጊዜ ወዘልፈ ስብሐቲሁ ውስተ አፉየ” /እግዚአብሔርን ሁልጊዜ አመሰግነዋለሁ ምስጋነውም ዘወትር በአፌ ነው/ /መዝ. 33፡1/
አምላካችን ልዑል እግዚአብሔርን ሁልጊዜ አመስግነን መንግሥቱን ለመውረስ እንድንችል የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንዲሁም የቅዱሳን አማላጅነታቸው አይለየን፡፡
ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም ያድርሰን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
፬. ዕለተ ሐሙስ
ሀ. ጸሎተ ሐሙስ- በዕለተ ሐሙስ ጌታችን መደኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ የዓለም መድኃኒት የሰው ልጆችንም ልመና የሚቀበል
አምላክ ሆኖ ሳለ በዚች ቀን በአትክልቱ ቦታ ገብቶ አይሁድ መጥተው እስከሚይዙት ድረስ ሥጋን የተዋሐደ ፍጹም አምላክ፤ፍጹም ሰው መሆኑን ለማጠየቅ ለአርአያነት ይጸልይ ስለነበረ ይህች ዕለት ጸሎተ ሐሙስ ተብላ ትጠራለች: (ማቴ. 12-02-92)
ለ. የምሥጢር ቀን:: መድኃኒታችን ክርስቶስ በዚች ዕለት ሐሙስ ለዓርብ ምሽት በሁለተኛው ሰዓተ ሌሊት ኅብስቱን ባርኮ ለዐሥራ ሦስት ከፈተተ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጥቶአቸዋል:: ‹‹እንጀራን አንሥቶ ባረከ፤ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና- እንካችሁ ብሉ፤ ይህ ሥጋዬ ነው አለ። ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖ ሰጣቸው፤ እንዲህም አለ፦ ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ፤ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈሰሰው የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው,, ተብሎ እንደተጻፈ።
ሐ. የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ:- ይህቺ ዕለት መድኃኒት ክርስቶስ ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጐ የገለጠባት በእንሰሳት ደም ይቀርብ የነበረው መሥዋዕተ ኦሪትም አብቅቶ አማናዊው የሐዲስ ኪዳን መሥዋዕት ለድኅነተ ዓለም የተበሠረባትና የተጀመረባት ዕለት በመሆንዋ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ እየተባለች ትጠራለች።
መ. የሕፅበተ እግር ቀን:- ጌታ በፍጹም ትህትና የደቀ መዛሙርቱን እግር ያጠበበት ከሐዋርየት ጋር ግብር የገባበትና የክርስትና ህይወት ማሕተም የሆነውን ምስጢረ ቀርባን ያከናወነበት ዕለት ነው
፫. ዕለተ ረቡዕ
ሀ. ምክረ አይሁድ፡- ይህቺ ዕለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ፈሪሳውያን ጌታ ኢየሱስን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው ምክር የመከሩበት ምክራቸውንም ያጸኑበትና ሰቅለው ይገድሉት ዘንድ የወሰኑበት ቀን በመሆኗ የአይሁድ የምክር ቀን ተብላ ትጠራለች፡፡ ይሁን እንጂ በዚሁ ምክራቸው ወቅት ጌታ ኢየሱስን እንዴት አድርገው እንደሚይዙት በጣም ይጨነቁ ነበር፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ወቅት በመሆኑ በጌታችን ትምህርት የተማረኩ ብዙ ሕዝብ ትምህርቱን ያደንቁ ስለነበር ሁከት እንዳይፈጠር ከመፍራታቸው የተነሣ ነው፡፡ በዚህ ጭንቀትም ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል አንዱ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ በመካከላቸው ተገኝቶ ጌታ ኢየሱስን እርሱ በመሳም አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ለዚህ ተግባሩም ሠላሳ ብር ወረታውን እንዲከፍሉት ከእነርሱ ጋር በመስማማቱና የምክራቸው ተባባሪ በመሆኑ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል፡፡ (ማር.፳፮፥፩-፭፣፳፮፥፲፬-፲፮፣ማር.፲፬፥፩-፲፩፣ሉቃ.፳፪፥፩)
ለ. የመልካም መዓዛ ቀን፡- ዕለተ ረቡዕ ጌታችን በስምዖን ዘለምጽ ቤት ተቀምጦ ሳለ በመላ ዘመንዋ ራስዋን በዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ ዕፍረት ኃጢአትን ይቅር የሚል መልካም መዓዛ ያለው አምላክ መጣ ስትል ውድ የሆነ ዋጋ ያለው ወይም የሦስት መቶ ዲናር ሽቱን ገዝታ ወደ እርሱ በመምጣትና በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው የመልካም መዓዛ ቀንም ትባላለች፡፡ በዚህም ምክንያት ከኃጢአትዋ የተነሣ መልካም መዓዛ ያልነበራት ማርያም እንተ እፍረት በዚህ በጎ ተግባርዋ መልካም መዓዛ ያለት ሆና ወደቤትዋ ተመልሳለች፡፡ (ማቴ.፳፮፥፮፣ዮሐ.፲፪፥፩-፰)
ሐ. የዕንባ ቀን፡- ይህቺው ማርያም እንተ ዕፍረት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በዕንባዋ እግሩን እያጠበች በፀጉሯም እግሩን እያበሰች ስለ ኃጢአቷ ሥርየት ተማጽናዋለችና የዕንባ ቀን ትባላለች፡፡ (ማቴ.፳፮፥፮-፲፫፣ ማር.፲፬፥፫-፱፣ዮሐ.፲፪፥፩-፰)
✝✝✝ እንኩዋን ለታላቁ ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ የሰማዕትነት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✝✝
✝✝✝ ዐቢይ ወክቡር: ጊዮርጊስ: ሰርዌ አዕላፍ: ወመክብበ ሰማዕታት ✝✝✝
=>መጽሐፈ ገድሉ እንደሚለው የሰማዕታት አለቃቸው: አንድም ሞገሳቸው ታላቅና ክቡር ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ7 ዓመታት ስቃይ በሁዋላ በዚህ ቀን ተሰይፏል:: ይሕስ ጥንተ ነገሩ እንደምን ነው ቢሉ:-
+ቅዱሱ የተወለደው ከአባቱ ዘረንቶስ (አንስጣስዮስ) እና ከእናቱ ቴዎብስታ የድሮው ፋርስ ግዛት ፍልስጥኤም (ልዳ) ውስጥ ነው:: የተባረኩ ወላጆቹ ክርስትናን ጠንቅቀው አስተምረውት አባቱ ይሞታል::
+ቅዱስ ጊዮርጊስ 20 ዓመት ሲሞላው የአባቱን ስልጣን እጅ ለማድረግ ሲሔድ የቢሩት (የአሁኗ ቤይሩት-ሊባኖስ) ሰዎች ዘንዶ (ደራጎን) ሲያመልኩ አገኛቸው:: እርሱ ግን የከተማውን ሕዝብ አስተምሮ: አሳምኖ: ደራጎኑንም በፈጣሪው ኃይል ገድሎ መንገዱን ቀጥሏል::
+ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ዱድያኖስና 70 ነገሥታት ዘንድ ሲደርስ ክርስቶስ ተክዶ ለጣዖት ይሠገድ ነበር:: በዚያች ሰዓት ድንግል እመቤታችን ወደ ሰማዕቱ መጥታ መከራውንና ክብሩን ነገረችው:: እርሱም በክርስቶስ ስም መሞት ምርጫው ነበርና ከእመቤታችን ተባርኮ ወደ ምስክርነት አደባባይ (ዐውደ ስምዕ) ደረሰ::
+ከዚያም ለተከታታይ 7 ዓመታት ብዙ ጸዋትወ መከራዎችን ተቀበለ:: 3 ጊዜ ሙቶ ተነሳ:: ከሰው ልጅ የተፈጥሮ ትዕግስት በላይ የሆነ ስቃይን ስለ ቀናች ሃይማኖት ሲል በመቀበሉ የሰማዕታት አለቃቸው: ፀሐይና የንጋት ኮከብ በሚል ይጠራል::
"ተውላጠ ጻማሁ ወሕማሙ:
ዘተለዐለ ሞገሰ ስሙ" እንዲል መጽሐፍ::
=>ቅዱስ ጊዮርጊስን ለዘመናት በብዙ ስቃያት ሲያስጨንቁት ኖረው በጽናቱ አሸነፋቸው:: 70 ነገሥታትን ከነ ሠራዊታቸው ከማሳፈሩ ባሻገርም በርካታ (በመቶ ሺ የሚቆጠሩ) አሕዛብን ማርኮ ለሰማዕትነት አበቃ::
+በዚህ የተበሳጨ ዱድያኖስም ኮከበ ፋርስ ቅዱስ ጊዮርጊስን እንዲቆራርጡት አዘዘ:: ወታደሮቹም ቅዱሱን ቆራርጠው: በብረት ምጣድ ላይ ጠበሱት:: ያለ ርሕራሔም አካሉን አሳረሩት:: ቀጥለውም ፈጭተው አመድ አደረጉት::
+በአካባቢው ወደ ነበረው ትልቅ ተራራ ጫፍ (ደብረ ይድራስ) ወጥተውም በነፋስ በተኑት::
"ሐረድዎ ወገመድዎ: ወዘረዉ ሥጋሁ ከመ ዓመድ" እንዲል:: (ምቅናይ)
+እነርሱ ይህንን ፈጽመው ዘወር ሲሉ ግን የቅዱሱ ዓጽም ባረፈባቸው ዛፎች: ቅጠሎችና ድንጋዮች ሁሉ "ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት" የሚል ጽሑፍ ተገኘ::
+ወዲያው ግን ኃያል ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተበተነበት ተነስቶ ወታደሮችን አገኛቸውና "በክርስቶስ እመኑ" ብሎ: አስደንቆ ወደ ሕይወት መራቸው:: 70ው ነገሥታት ግን አፈሩ::
+ከ7 ዓመታት መከራ በሁዋላም በዚሕች ቀን ከብዙ ተዓምራት ጋር ተሰይፎ ደም: ውሃና ወተት ከአንገቱ ፈሷል:: 7 አክሊላትም ወርደውለታል::
=>በ290ዎቹ አካባቢ (ሰማዕት ከሆነ ከጥቂት ዓመታት በሁዋላ) በዚያው በሃገሩ ደብር አንጸው: አጽሙን አፍልሠው ቀድሰዋታል::
+ቅዱሱ ሰማዕት ከሰማዕትነቱ በፊትም ሆነ በሁዋላ ተአምረኛ ነው:: በዘመኑ የክርስቲያኖችን ደም ሲያፈሱ ከነበሩ አራዊት (ነገሥታት) መካከል አንዱ የሆነው ዲዮቅልጢያኖስ ርጉም የ47 ሚሊየን ክርስቲያኖችን ደም አፍስሶ ነበርና ፈጣሪ ደመ ሰማዕታትን የሚበቀልበት ጊዜ ደረሰ::
+በ305 ዓ/ም አካባቢ አረመኔው ንጉሥ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተአምረኛነት ሰምቶ እንዲያፈርሱት ሠራዊት ላከ:: የሠራዊቱ አለቃም ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ገብቶ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስዕል ላይ ተሳለቀ::
+ከፊቱ የነበረውን ቀንዲል በሰይፍ እመታለሁ ሲል ግን ቀንዲሉ ተገልብጦ መሐል አናቱን መታው:: እንደ እብድ ሆኖ ሞተ:: ሠራዊቱም ሰምቶ ወደ ንጉሡ ሸሸ:: ይሕን ሰምቶ የተበሳጨው ዲዮቅልጢያኖስ ግን ራሱ ሊያፈርሰው ሔደ:: ከቤተ ክርስቲያኑ በር ላይ ሲደርስ ሚካኤልና ገብርኤል ዐይኑን አጠፉት::
+እገባለሁ ሲል ቅዱስ ጊዮርጊስ ከላይ መረዋውን (ደወሉን) ለቀቀበት:: ራሱን ቢመታው ደነዘዘ:: የብዙ ቅዱሳንን ደም የጠጣው ርጉሙ ንጉሥም አብዶ ለ7 ዓመታት ፍርፋሪ ሲለምን ኑሮሰ ይጣን ከገደል ጫፍ ወርውሮ ገድሎታል::
=>አምላካችን እግዚአብሔር ከኃያሉ ሰማዕት ጽናትና ትእግስት: ከበረከቱም ይክፈለን::
=>ሚያዝያ 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
2.ቅዱስ ሮቆ ጻድቅ (በስሙ ለተማጸነ ከወባ በሽታ እንዲጠብቀው ጌታ ቃል ኪዳን ገብቶለታል)
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
2.ቅዱስ ሰሎሞን ንጉሠ እስራኤል
3.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
4.አባ ሳሙኤል
5.አባ ስምዖን
6.አባ ገብርኤል
=>+"+ የሚበልጠውን ትንሳኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ:: ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ:: በድንጋይ ተወግረው ሞቱ:: ተፈተኑ: በመጋዝ ተሰነጠቁ: በሰይፍ ተገድለው ሞቱ:: ሁሉን እያጡ: መከራን እየተቀበሉ: እየተጨነቁ: የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ:: ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ: በዋሻና በምድር ጉድጉዋድ ተቅበዘበዙ:: +"+ (ዕብ. 11:35-38)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
🛑በዩቲብለመከታተል👉ZikereKedusan" rel="nofollow">https://www.youtube.com/@ZikereKedusan
🛑በቴሌግራም👉/channel/zikirekdusn
ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲል ራሱን ለሰይፍ አሳልፎ ሰጠ። በክርስትናው አንዳች አላፈረምና በዓለም ነገሥታት ፊት ስለ እውነተኛው ንጉሥ ሳይፈራ ሰበከ።
ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ፤ እውነቱን ገለጠ የዲያቢሎስን አሰራር ተዋጋ። እንኳን ለዓመታዊው የቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለ ዕረፍት በሰላም አደረሰን። በረክትና ምልጃው አይለየን።
#አንዲት_ሐይማኖት_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ
ይህም አባት እለእስክንድሮስ ተመርጦ ለጉባኤው ሊቀ መንበር ሆነ አትናቴዎስ ፀሀፊ ነበር ።አርዮስንም ተከራክረው ክህደቱን ግልፅ አደረጉ ስለ ጌታ
ችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከአባቱ ከአብ ጋራ ከህይወቱ መንፈስ ቅዱስም ጋራ በመለኮቱ ትክክል እንደሆነ አስረዱት።
ከክህደቱ ባልተመለሰ ጊዜ አውግዘው ለይተው ከቤተ ክርስቲያን አሳደዱት። በአንድ ቃልም ፀሎተ ሀይማኖትን ከአባቶች ጋራ ሰሩልን ደግሞ በእርሳቸው ቤተ ክርስቲያን ለዘላለም የምትመራባቸው ሀያ ቀኖናን ሰርተው ወሰኑ።
ከዚህ በኃላም ይህ አባት እለእስክንድሮስ ወደ መንበረ ሲመቱ ከደል ጋራ ተመለሰ። በበጎ አጠባበቅም መንጋውን ጠበቀ በወንጌላዊ ማርቆስ መንበርም አስራ ሰባት አመት ኖሮ በሰላም አረፈ።
† አባ ሚካኤል ዘእስክንድርያ †
በዚችም ቀን የከበረ አባት አባ ሚካኤል የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አረፈ እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሀምሳ ሶስተኛ ነው። ይህም ቅዱስ ፃድቅ መንኲሶ በአስቄጥስ በቅዱስ ዮሀንስ ገዳም አበ ምኔት ሆኖ ተሾመ ከዚያም ያለ ፈቃዱ ወስደው በግድ ሊቀ ጵጵስና በእስክንድርያ አገር ላይ ኀዳር ሀያ አራት ቀን ሾሙት።
በሊቀ ጵጵስናውም ስራ ተጠምዶ የሚጋደል ሆነ እንደ ሀዋርያትም አጠባበቅ መንጋውን ጠበቀ። ታላቁ ፆምም በደረሰ ጊዜ ወደ አስቄጥስ በዚያ ሊፆም ወጣ ከመሾሙ በፊት በዚያ ገዳም ውስጥ በብህትውና ሆኖ መጠመዱንና የቀድሞ መጋደሉን አሰበ።
ወደ ጌታችንም እንዲህ ብሎ ለመነ አቤቱ እኔ በብቸኛነት መኖርን እንደምሻ አንተ ታውቃለህ ለዚች ለተሾምኩባትም ሹመት ችሎታ የለኝምና የምትገባኝም አይደለችምና በይቅርታህም ብዛት ነፍሴን ወስደህ ከዚህ ድካም ታሳርፈኝ ዘንድ እለምንሀለሁ ጌታም ልመናውን ተቀበለ ከፋሲካ በአል በኃላም በፍቅር አንድነት አረፈ።የሹመቱም ዘመን ሁለት አመት ከአምስት ወር ነው።
=>ሚያዝያ 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
2.ቅዱስ እለእስክንድሮስ ሊቅ (አርዮስን ያወገዘ)
3.አባ ይስሐቅ ጻድቅ
4.አባ ማርቆስ ሐዲስ
5.አባ ሚካኤል ዘኢየሩሳሌም
6.አባ ሚካኤል ዘእስክንድርያ
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
3.ቅዱስ ደቅስዮስ (የእመቤታችን ወዳጅ)
4.አባ እንጦንዮስ (አበ መነኮሳት)
5.አባ ዻውሊ የዋህ
=>+"+ ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን በረዥምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት:: የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር:: ሱራፌል ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር:: ለእያንዳንዱ ስድስት ክንፍ ነበረው:: በሁለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበር:: በሁለቱም ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበር:: በሁለቱም ክንፍ ይበር ነበር:: አንዱም ለአንዱ 'ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች' እያለ ይጮህ ነበር:: +"+ (ኢሳ. 6:1-4)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
/channel/zikirekdusn
ZikereKedusan" rel="nofollow">https://www.youtube.com/@ZikereKedusan
ኡራኤል የተባለ መልዓክ ሊረዳኝ መጣ ዕዝራ(ሱቱ) 2:1 :: ዑራኤል የሚለው ስም "ዑር" እና "ኤል"ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። ዑራኤል ማለት ትርጉሙ የብርሃን ጌታ፣የአምላክ ብርሃን ማለት ነው።
መልዐኩ ቅዱስ ዑራኤል ምልጃው ተራዳይነቱ አይለየን🙏
[ #ሰሙነ_ህማማት ] [ #ሰኞ ]
፩) ዕለተ ሰኑይ
ሀ) #አንጽሖተ_ቤተ_መቅደስ፡- በዚች ዕለት መድኃኒታችን ክርስቶስ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ! በዚያም በደረሰ ጊዜ ቤተ መቅደሱ የጸሎት የመሥዋዕት ቤት መሆኑ ቀርቶ የንግድ ቤት ሆኖ ቢያገኘው ‹‹ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል፤ እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት›› ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው ገርፎም አስወጣቸው! ይኸውም የእርሱ ቤተ መቅደስ የሆነውን ሰውነታችንን ኃጢአት ሰፍኖበት ቢያገኘው ራሱ ተገርፎ ተገፍፎ መከራ መስቀልንም ሁሉ ተቀብሎ ከሰውነታችን ኃጢአትን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡ (ሉቃ.፲፱፥፵፮)
ለ) #መርገመ_በለስ፡- ጌታችን የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግስቱ ከቢታንያ ሲወጣ ተራበ፤ በመንገድም ሲያልፍ ቅጠል ያላት በለስን ከሩቁ ተመለከተ! ወደ በለሲቱም በቀረበ ጊዜ ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም! ያንጊዜም ‹‹ከእንግዲህ ወዲህ ለዘለዓለም ከአንቺ ፍሬ የሚበላ አይኑር›› ሲል በለሲቱን ረገማት! ደቀ መዛሙርቱም ይህንን ሰሙት! በዚህም ምክንያት ይህች ዕለት በለሲቱ የተረገመችባት ቀን ናትና መርገመ በለስ ተብላ ትጠራለች፡፡ (ማር.፲፩፥፲፩-፲፬)
በዚህ አገላለጽ በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ስትሆን ፍሬ የተባለ ደግሞ ሃይማኖትና ምግባር ነው! መድኃኒታችን ክርስቶስ ከእስራኤል ፍቅርን፣ ሃይማኖትን፣ ምግባርን ፈልጎ አላገኘባቸውም! እስራኤል፦ ሕዝበ እግዚአብሔር፣ የአብርሃም ዘር መባልን እንጂ የአብርሃምን ሥራ በመሥራት በምግባር በሃይማኖት ጸንተው መኖር አይፈልጉምና ደግ ሰው አልተገኘባቸውም፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በለስ የተባለች ኦሪት ናት! ኦሪት በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛትም አማናዊ ድኅነትን የምታሰጥ ሆና አላገኛትም! ይሁን እንጂ በእርሷ ድኅነት ባይገኝባትም ‹‹ኦሪትና ነቢያትን ከመፈጸም በቀር ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ›› በማለት ሕገ ኦሪትን ፈጽሟታል፡፡ ከዚህም ባሻገር በለስ የተባለች ኃጢአት ናት! የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አግኝቷታል፡፡
በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሠሩት ለጊዜው ደስ ያሰኛል ኋላ ግን ያሳዝናል! በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም በአንቺ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ሲል ነው! በለሲቱ ስትረገም ፈጥና መድረቋም በአዳም ምክንያት ያገኘን በደል በእርሱ እንደጠፋልን ለመግለጽ ነው፡፡
ፆመ በረከት፣ ፆመ ስርዬት ያድርግልን ፈጣሪ።
[ #አሜን ]
እንደተጻፈ አወረድኩት [ #ይቆየኝ ]
ሆሳዕና ማለት ምን ማለት ነው ??
በሆሳዕና ለምን ቀለበት እናሥራለን ?
በሆሳዕና ጌታችን ለምን በአህያ ላይ ተቀመጠ .
በሆሳዕና ለምን ዘንባባ አነጠፉ ?
------------------------------------
📌 ሆሳዕና ማለት ምን ማለት ነው??
ሆሳዕና ማለት፦ ሆሻዕናህ ከሚል የዕብራይስጥ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ ‹‹እባክህ አሁን አድን ›› ማለት ነው፡፡ በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሐት ስለማይፈጸም ጸሎተ ፍትሐትና የሚደረገው በዚሁ ዕለት ነው::
📌 በሆሳዕና ዕለት ዘንባባ እጃችን እደ ቀለበት ማሠራችን የምን ምሳሌ ነው??
1.ጌታ ለአዳም የሰጠው ቃል ኪዳን ለማስታወስ፡-ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድነሃለሁ ያለውን የተስፋ ቃል ለማስታወስ፡፡
2.ጌታ ለእመቤታችን የገባላትን ቃል ኪዳን ተምሳሌት ነው።
3.ጌታ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ቃል ኪዳን ተምሳሌት ነው።
4.ጌታ ለአዳም ከሰይጣን ግዛት ነጻ እንዳወጣው ሁሉ እኛም ከሰይጣን ግዛት ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ከክፋት ከኃጢአት አውጣን ማረን ለንስኃ ሞት አብቃን ከቤትህ አትለየን እንደ ቸርነትህ ይቅር በለን ስንል ለጌታ ዳግም ላናጠፋ ቃል የምንገባበት ነው፡፡
📌 ጌታችን በዕለተ ሆሳዕና ለምን በፈረስ ላይ አልተቀመጠም??
ትንቢቱንና ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፡፡ "
አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።(ትንቢተ ዘካርያስ 9:9)
📌 በአህያ መቀመጡ፦
•ትኅትናን ለማስተማር
•የሰላም ዘመን ነው ሲል
•ለፈለጉኝ ሁሉ የቅርብ አምላክ ነኝ ሲል በንጽህና በየዋህነት ለሚኖሩ ምዕመናን አድሬባቸው እኖራለሁ ሲል፡፡
•አህያ ትሁት ነው ረጋ ብሎ ነው የሚሄደው ፤ በቀላሉ ትወጣበታለህ፤ በቀላሉ ትይዘዋለህ ፤ እንደፈለክም ታዝዋለህ።
📌 ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ዘባባ የመነጠፉ ምስጢር የምን ምሳሌ ነው???
1.ዝንባባ፡- ይስሐቅ በተወለደ ጊዜ ደስ ብሎት አብርሃምን ዘንባባ ይዞ እግዚአብሔር አመስግነዋል፡፡
2.ዝንባባ ደርቆ እንደገና ሕይወት ይዘራል፡- የደረቀ የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
3.ዝንባባ የሰላም ምልክት ነው፡- የሰላም አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
4.ዝንባባ የደስታ መግለጫ ነው፡- አንተ ደስ የምታሰኝ ሃዘናችንም የምታርቅልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
5.ዝንባባ እሾሃማ ነው፡- አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
6.ዝንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጂ፡፡ ጌታም አንተ ባህሪህን የማይመረመር ነው ሲሉ ነው፡፡
ህዝቡ ከልብሳቸው ሌላ ስንት አይነት ቅጠንል አነጠፉለት ምን ምን??
📌 ልብሳቸውን ማንጠፋቸው፡-
ለክብሩ መግለጫ ነው፡፡ ሌሎችም ሦስት አይነት ቅጠል አነጠፉለት ዘንባባ፤የቴመር ዛፍ፤የወይራ ዛፍ አነጠፉለት፡፡
📌 ትልቋ አህያ በምን ትመሳለለች ውርን ጭለዋስ??? ትልቅዋ አህያ የኦሪት ምሳሌ ነው።
1.ትልቅዋ አህያ ሸክም የለመደች ናት ህገ ኦሪትም የተለመደች ህግ ናትና፡፡
2.የእስራኤል ምሳሌ ነው፡-ትልቅዋ አህያ ሸክም እንደለመደች ሁሉ እስራኤልም ህግ ለመፈጸም በህግ ለመራመድ የለመዱ ናቸው፡፡
3.የአዳም ምሳሌ ነው፡- አዳም ሸክም የበዛበት ነበርና።
📌 ውርጭላዋ
1.በሕገ ወንጌል ትመሰላለች፡-ምክንያቱም ወንጌል ኢየሱስ ክርስቶስ የመሰረታት የሰራት አዲስዋ ህግ ናትና፡፡
2.በአህዛብ ትመሰላለች፡-ትንሽዋ አህያ ሸክም የለመደች አይደለችም እንዲሁም አህዛብም ህግህን የመቀበል የመቀበል የለመደ አይደሉም፡፡ ለህግህ አዲስ ናቸውና፡፡
3.የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡- የዓለም ሸክም አቅልላለችና በእመቤታችን ትመሰለላለች፡፡ እመቤታችን ድኅነተ ምክንያታችን ጌታን የተሸከመች ንጽህት እንከን የሌላት እናት ናትና፡፡
ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ ( አዳማ - ኢትዮጵያ)
ከዘጠኙ ዐበይት የጌታችን በዓላት ውስጥ አንዱ ለሆነው ለታላቁ የሆሳዕና በዓል እንኳን በሰላም አደረሰን!
"ሆሳዕና በአርያም" ማለት በአርያም /በሰማይ/ ያለ መድኃኒት ማለት ነው፡፡ ሆሳዕና የሚለው ቃል በዕብራይስጥ "ሆሻአና" የሚል ሲሆን ትርጉሙም "እባክህ አሁን አድን" ማለት ነው፡፡ ይህ ቃል በዘመነ ብሉይ በቀደምት ነቢያት ዘንድ የተለመደ ቃል ነው፡፡ አቤቱ እባክህ አሁን አድን፣ አቤቱ እባክህ አሁን አቅና፣ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩከ ነው፡፡ መዝ.117፡25-26፡፡
የሆሳዕና በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የሚቀድሙትና የሚከተሉት ሕዝብ በተለይም አእሩግና ሕፃናት "ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ፣ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፣ ሆሳዕና በአርያም" በማለት ጌታችንን በክብር መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል ነው፡፡ በዓሉም ሆሳዕና የሚለውን ስያሜ ያገኘው በዕለቱ ከተዘመረው መዝሙር ነው፡፡
በሌላ አነጋገር ይህ ዕለት የጸበርት እሑድ /Palm Sunday/ ይባላል፡፡ ታሪካዊ አመጣጡ የመልካም ምኞትና የድል አድራጊነት መገለጫ ሆኖ ከደገኛው አባታችን ይስሐቅ ልደት ጋር ተያይዞ የመጣ ነው፡፡ ይኸውም ሣራ የወላድነት ዕድሜዋን ጨርሳ ልማደ እንስት ከተቋረጠባት በኋላ ሁሉን ቻይ የሆነ አምላክ ይስሐቅን በሰጣት ጊዜ ዘመዶችዋ የተሰማቸውን ደስታ ለመግለጽ የዘንባባ ዝንጣፊ በመያዝ የጎበኟትን አምላክ አመስግነዋል፡፡ እስራኤል ከአስከፊው የግብፃውያን አገዛዝ ተላቀው ባሕረ ኤርትራን በደረቅ ሲሻገሩ የተሰማቸውን እጥፍ ድርብ ደስታ በገለጡ ጊዜ፣ እንዲሁም ዮዲት የተባለች ንግሥተ እስራኤል ሆሎፎርኒስ የተባለ አላዊ ንጉሥን ድል ባደረገች ጊዜ ቤተ እስራኤል እንደ ሰንደቅ ዓለማ የዘንባባ ዝንጣፊ በመያዝ አደባባይ ወጥተው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
በዘመነ ሐዲስም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ዘር ከዲያብሎስ ቁራኝነት ከሲኦል ባርነት ነጻ ለማውጣት ወደ ዙፋን መስቀሉ /ሉቃ.22፤18/ በተጓዘ ጊዜ ሕፃናት እና አእሩግ ነጻ የሚወጡበት ቀን መድረሱን እነርሱ ሳያውቁ እግዚአብሔር ባወቀ ዘንባባ በመያዝ ዘምረዋል፡፡ እስራኤል ዘንባባ በመያዝ እንዳመሰገኑት እኛም አስራኤል ዘነፍስ ዕለቱን ዘንባባ /ጸበርት/ በግንባራችን በማሰር በዓሉን በየዓመቱ እያስታወስን እናከብራለን፡፡ በዚህ ዕለት ዘንባባ እየተባረከ ለሕዝቡ ይታደላል፡፡
ሕፃናትና አእሩግ "ለዳዊት ልጅ መድኃኒት መባል ይገባዋል" እያሉ ዘምረዋል፡፡ ይህ ሁሉ በአንድ ወገን የነበረው የአቀባበል ሥነ ሥርዓት ሲሆን በሌላ በኩል የነበረው አቀባበል ደግሞ እጅግ የሚያሳዝን ነበር፡፡ ሥርዓተ ኦሪትን፣ ትንቢተ ነቢያትን በሚገባ እንከተላለን ይሉ የነበሩ ጸሐፍት ፈሪሳውያን "መምህር ሆይ! ደቀ መዛሙርትህን ገሥጻቸው" አሉት፡፡ ጌታችንም መልሶ "እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉ" ሲል መልሶላቸዋል፡፡ ቅናት አቅላቸውን ያሳታቸው ፈሪሳውያንም የዋህ የሆነው ሕዝብ ምስጋና ወደ ጥላቻ እንዲለወጥ አድርገዋል፡፡ ከሁሉ የሚያሳዝነው በዕለተ ሆሳዕና እሑድ ዘንባባ ይዘው የዘመሩለትን ጌታ ዓርብ ላይ "ይሰቀል ዘንድ ይገባል" ብለዋል፡፡
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ፡፡ በዚህም በነቢዩ ዘካርያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው ትንቢት ተፈጸመ፡፡ "እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፣ በአህያዪቱ ግልገል በውርንጫዪቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል፡፡" ዘካ.9፡9፤ ማቴ.21፡4፤ ማር.11፡1-10፤ሉቃ.19፡28-40፤ ዮሐ.12፤15፡፡ ጌታችን በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም መግባቱ የሰላም ንጉሥ መሆኑን ያመለክታል፡፡ እስራኤል ዘመነ ምሕረት ሲሆንላቸው አባቶቻቸው በአህያ ጀርባ ተቀምጠው ይታዩ ነበር፡፡ ጌታም እውነተኛ የኅሊና ሰላም ይዤላችሁ መጣሁ ሲለን በአህያ ጀርባ ወደ ቤተ መቅደስ ሕይወታችን ተጉዟል፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሌላ ቀን እንደ ተራ ሰው ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ይገባ ነበር፡፡ በዚህ ቀን ግን የአይሁድ ንጉሥ ሆኖ በክብር ገባ፡፡ ከቢታንያ ተነሥቶ ደብረ ዘይት ሲደርስ ከሐዋርያቱ ሁለቱን በቤተፋጌ ሰው ተቀምጦባት የማያውቅ ውርንጭላ እንዲያመጡለት ላካቸው፡፡ “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሒዱ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርሷ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁም አምጡልኝ፡፡ ማንም አንዳች ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ" አላቸው፡፡ ማቴ.21፡1-17
ወደ ቤተፋጌም ሄደው አህያዪቱን አገኙአት፡፡ ሲፈቱአትም ሳለ ባለቤቶቹ መጡባቸውና አስቆሟቸው፡፡ እነርሱም ኢየሱስ እንደፈለጋት ነገሩአቸው፡፡ ባለቤቶቹ ይህንን ሲያውቁ ተውአቸው፡፡ ሐዋርያትም የአህያዪቱን ውርንጭላ ፈትተው ወደ ኢየሱስ ወሰዱ፡፡ አጠገቡም ሲደርሱ ልብሳቸውን በአህያዪቱ ውርንጭላ ላይ አንጥፈው ኢየሱስን አስቀመጡት፡፡
ለምን ዘንባባ ያዙ ቢባል፤ ዘንባባ እሾሃም ነው ፤አንተም የኃይል የድል ምልክት አለህ ሲሉ፤በሌላም በኩል ዘንባባ እሳት ለብልቦ ይተወዋል እንጂ አይበላውም አንተም ባህርይህ አይመረመርም ሲሉ፤አንድም ዘንባባ ረጅም /ልዑል/ ነው አንተም ባሕርይህ ልዑል ነው ሲሉ ዘንባባ ይዘው ተቀብለውታል፡፡
የተምር ዛፍ ዝንጣፊ ነው ቢሉ፤ ተምር ፍሬው አንድ ነው አንተም ባህርይህ አንድ ነው ሲሉ፡፡አንድም፤ተምር ልዑል/ረጅም/ ነው አነተም ልዑለ ባህርይ ነህ ሲሉ፡፡ አንድም፤የተምር ፍሬው በእሾህ የተከበበ ነው በቀላሉ መለቀም አይቻልም ፤የአንተም ምስጢር አነተ ካልገለጠከው አይመረመርም ሲሉ ነው፡፡
የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ነው ቢሉ፤ ወይራ ጽኑዕ/ ጠንካራ/ ነው አንተም ጽኑዓ ባህርይ ነህ ሲሉ፤አንድም ወይራ ለመስዋዕት ይሆናል፤ አንተም መስዋዕት ትሆናለህ ሲሉ፤አንድም ወይራ ዘይቱ ለመብራት ይሆናል አንተም የዓለም ብርሃን ነህ ሲሉ ይህንን ይዘው አያመሰገኑ ተቀበሉት፡፡
ልብሳቸውንም ማንጠፋቸው፤ እንኳን አንተ የተቀመጥክባት አህያ እንኳን መሬት መርገጥ አይገባትም ሲሉ ልብሳቸውን አነጠፉለት፡፡ እነዚያ ያላመኑ አይሁድ ለተቀመጠባት አህያ ይህንን ያህል ክብር ከሰጡ፤ በድንግልና ጸንሳ ለወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምን ያህል ክብር ልናድረግለት ይገባን ይሆን?፡፡
“የጽዮን ልጅ ሆይ አትፍሪ እነሆ ንጉሥሽ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ይመጣል” ዘካ.9፡9 የሚለው የዘካርያስ ትንቢት ተፈጸመ፡፡ ሕዝቡም ኢየሱስ በመምጣት ላይ እንዳለ ሲያውቅ ሊቀበለው ወጣ፡፡ አንዳንዶች ያልፍበት በነበረ መንገድ ልብሳቸውን እንዳንዶቹ ደግሞ የዘንባበ ዝንጣፊ ያነጥፉ ነበር፡፡ ከፊትና በኋላ ያሉት ደግሞ “ሆሳዕና በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ” እያሉ በታላቅ ድምፅ ይጮሁ ነበር፡፡ ኢየሱስ በሕዝቡ እልልታና ደስታ ታጅቦ ሲገባ ተጠንቅቀው ይታዘቡትና ይመለከቱት የነበሩ ፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርቱን ዝም እንዲያሰኛቸው ተናገሩት፡፡ እርሱም ሕዝቡ ዝም ቢል ድንጋዮች እንደሚጮኹ አስታወቃቸው፡፡
በጌታችን በዕለተ ልደቱ "በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባዋል በምድር ሰላም ለሰው ሁሉ ይሁን" /ሉቃ.2፡13/ እያሉ የዘመሩለት የሰላም ባለቤት ነው፡፡ በመዋዕለ ትምህርቱም "ሰላሜን እሰጣችኋለሁ" /ዮሐ.14፡27/ ብሎ እንዳስተማረ ያን ሰላም የሚሰጥበትን ዕለት መቅረቡን ለማመልከት ነው፡፡ በሌላ በኩልም በአህያ ጀርባ መቀመጡ ኅቡዕ ምሥጢር አለው፡፡ በአህያ ጀርባ የተቀመጠ ሰው ሌላውን አሳድዶ አይዝም፣ እርሱም ሮጦ አያመልጥም፡፡ በዚህም ጌታችን በእምነት ለሚፈልጉት የሚገኝ ቅርብ ሲሆን በእምነት ለማይፈልጉት ግን የማይገኝ መሆኑን አስተምሯል፡፡
+++ከድካምሽ ተፈትተሻል!+++
ጽርሐ አርያም አዳራሹ ፤ የመላእክት መኖሪያ ቦታው የሚሆን ፤ በሰማይ ሆኖ በጥልቅ ባሕር ውስጥ ያለውን የሚያይ እርሱ ፤ ፊቱን ማየት ኪሩቤል የማይቻላቸው ፤ ነበልባሉ እንዳያቃጥላቸው በእሳት ክንፋቸው ፊታቸውን የሚጋርዱለት እርሱ ፤ በአህያ ጀርባ ላይ ተቀመጠ፡፡ የሰው ልጅ ሸክም ለመጫን በሚገለገልባት አህያ ላይ ‹‹እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።›› (ማቴ.11፡28) ያለው እርሱ ተቀመጠባት፡፡
ርቱዓ ሃይማኖት ስለዚህ ሲመሰክር ‹‹የሰማያት ርዝመት አንዱ ከአንዱ እስከ ሰማያት ድረስ እጥፍ ድርብ ነው ፤ ሰባተኛው ግን ከኹሉም ሰማያት ይልቅ ረጅምና ሰፊ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ዙፋን አርያምም ይህ ነው፡፡ ኹሉ ሰማያትም ከእርሱ በታች ናቸው፡፡ ነቢዩ ‹ልዑል እግዚአብሔር ከሰማያት ኹሉ በላይ ነው› ብሎ እንደተናገረ፡፡ በአህያ ውርንጭላ የተጫነውም እርሱ ነው›› ይላል፡፡ (ርቱዓ ሃይማኖት ገጽ 121 - 122)
ታዲያ ይህን ጌታ አህያዋ እንደምን መሸከም ቻለችው? ዓለምን የያዘውን ተሸክማ አትጎብጥምን? ብለህ ተጨንቀህ ከሆነ ፤ ወዳጄ ሆይ አባ ጊዮርጊስ እንዲህ ይልሃል ፤ ‹‹ቀላል ሸክም የለዘበም ቀንበር ኢየሱስ ክርስቶስ ነው›› [(‹‹አርዑት ሠናይ ወጾር ቀሊል ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ›› (መጽሐፈ ሰዓታት ገጽ 51)] ፤ ሸክም የሚበዛባት አህያን በሚያሸክሟት ሰዎች ፊት ሊያከብራት ወደደ ፤ ክርስቶስ ጎባጣውን ሊያቀና እንጂ ሸክም ሊያበዛ አልመጣም ይልሃል ቅዱስ አምብሮስ።
ይህንንም ሲያስረዳ ሊቁ አንድ ታሪክ ያስታውስሃል ፤ “በሰንበትም በአንድ ምኵራብ ያስተምር ነበር። እነሆም፥ ከአሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ የድካም መንፈስ ያደረባት ሴት ነበረች፥ እርስዋም ጐባጣ ነበረች ቀንታም ልትቆም ከቶ አልተቻላትም። ኢየሱስም ባያት ጊዜ ጠራትና። አንቺ ሴት፥ ከድካምሽ ተፈትተሻል አላት፥ እጁንም ጫነባት፤ ያን ጊዜም ቀጥ አለች፥ እግዚአብሔርንም አመሰገነች።” (ሉቃ. 13፡10-13)
በአህያዋ ላይ ተቀምጦ ያየኽው እርሱ አስቀድሞ ለአብርሃም ግዝረትን (ዘፍ. 17፡10) ፤ ለሙሴም በሲና ሕግጋትን የሰጠው ነበር ፤ በሦስተኛው ግን እርሱ ራሱ ወደ ቅድስት ድንግል ማርያም መጣ ሰው ሆነ ፤ ሦስት ስድስት ዓመታት ጎብጣ የኖረችውን ሴት ቀና አደረጋት ፤ ሦስት ዓመት ፍሬ ፈልጎ ያጣባትን ያቺን በለስ ወደ ተፈጥሮአዊ ማንነቷ መለሳት ቀጥ ብላ እንድትቆም አደረጋት፡፡ (Commentary of Saint Ambrose on the Gospel according to Saint Luke, 2001 A.D; Page 243-245) ስለዚህ አህያዋን ሊያከብራት እንጂ ሊያጎብጣት አልተቀመጠባትምና ስለ እርስዋ አትጨነቅ!
ይልቁን እንዲህ ብለህ ለምነው ፤ ‹‹ጌታዬ ሆይ ፤ አህያስ መታዘዝ አላት ፤ ቢገፏት ሸክም ቢያበዙባት ትዕግሥትና መቻል አላት ፤ አህያስ ጌቶቿን ታስደስታለች ታገለግላለች ፤ መታዘዝ የራቀኝ ትዕቢት የጸናብኝ ፤ የራሴ ሀሳብ ራሴን የገፋኝ ፤ የራሴ መሻትና ፍላጎት መልሶ እኔኑ ያስጨነቀኝ ፤ ቶሎ መጨበጥን ደርሶ ማግኘትን ብቻ በማሰብ ትዕግሥት ያጣኹኝ ፤ የአንተን ፈቃድ ከማገልገል ይልቅ ራሴን በማገልገል የባዘንኩኝ ልጅህን አስበኝ ፤ እሸከምህ ዘንድ በእኔ ላይም ታርፍብኝና ትመሰገንብኝ ዘንድ አንዳች የሚመች ነገር ባይገኝብኝም ፤ “አንተ ደካማ ሸክምህ የከበደ ወደ እኔ ና እኔም አሳርፍሃለሁ” ከሚለው አባታዊ ጥሪህ ግን አትለየኝ ፤ በተፈጥሮ ጌታዋ ለሆንኩ በሥራዬ ግን ከአህያ ላነስኩኝ ለእኔ ማስተዋልን ሥጠኝ!››
+++
Image Credit: orthochristian
ስብሐት ለእግዚአብሔር
@ዲያቆን ደረጀ ድንቁ
ሚያዝያ 19 2016 ዓ.ም