. ❤ ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ .....
#ሰኞ ♥ #ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡
================================
#ማክሰኞ ♥ #ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ 《ዮሐ. 20፡27-29》
================================
#ረቡዕ ♥ #አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡
================================
#ሀሙስ ♥ #አዳመ_ሀሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡
================================
#አርብ ♥ #ቅድስት_ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡
================================
#ቅዳሜ ♥ #ቅዱሳት_አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡
================================
#እሁድ ♥ #ዳግም_ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡
[Forwarded from DAGM 🌚]
ዓለም ወዴት እየሄደች ነው? 1. - መጽሐፍ ቅዱስን ማቃጠል በኡጋንዳ በይፋ ተረጋግጦአል
* በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ፣ ወንድ ወይም ሴት በዝሙት ምክንያት ሌላውን የመክሰስ መብት የለውም
*በአሜሪካ እየታየ ያለው የወንድ ለወንድና የሴት ለሴት ጋብቻ
*ጀርመን ወንድም እህቱን ማግባት እንደሚችል ፣ አባት ልጁን:እናት ልጆአን የማግባት ፍቃድን መስጠቱ ፡፡
*የmiami ከተማበመንገድ ላይ ፣ በቤተ ክርስቲያን ፣ በገቢያ ፣ በእግር ኳስ ሜዳ ወዘተ ውስጥ ወሲባዊ ግንኙነት በማንኛውም መንገድ ማግኘት እንዲችሉ መፍቀዶአ
.*ካናዳ (ከእንስሳት ጋር የ sexታ ግንኙነትን መፍቀዶአ
* በስፔን ውስጥ-የወሲብ ፊልሞች በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና በዩኒቨርሲቲዎች መፈቀዱ *- ለአካለ መጠን ያልደረሱ ዝሙት አዳሪዎች ፈቃድ ማሪ ሉክ በህግ መፈቀዱ *በመጨረሻም ዩኤስ አሜሪካ የሰይጣንን ቤተ ክርስቲያን ከፍታለች ፡፡ በይፋ።
የተከበራችሁ ወንድሞች እና እህቶች ፣ መጨረሻው ተቃርቧል ፣ ጌታ ኢየሱስ በቅርቡ ይመጣል! ማርታናታ!!!
ክርስትያኖች ትኩረታቸው እየተከፋፈሉ ሲሆን ዲያቢሎስ መለኮታዊውን ምህረት ለማስቆም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ነፍሳት ከእርሱ ጋር ሊወስድ ይፈልጋል ፡፡ ደቂቃ ካለዎት ... ይህንን መልእክት ያጋሩ ፡፡ ለምን በቤተክርስቲያን ውስጥ እንተኛለን ? ስለ እግዚአብሔር ማውራት ከባድ የሆነው ለምንድነው ሐሜት ለመናገር በጣም ቀላል የሆነው ለምንድነው? የእግዚአብሔርን መልእክት ችላ ማለት ለምን ቀላል ሆነ?
ይህንን መልእክት ለጓደኞችዎ ይልካሉ ወይም ችላ ይላሉ? ኢየሱስ “በጓደኞችህ ብትክዱኝ በአባቴ ፊት እክድሃለሁ” አለ ፡፡ ኢየሱስን ከወደዱ ይህንን መልእክት ለምርጥ ጓደኞችዎ እና በቡድን በ 60 ሴኮንድ ውስጥ ያጋሩ ፡፡ እግዚአብሔር ይባርኮት. ኣሜን
የአለም መጨረሻ ተቃርቧል አትዘናጉ
አሁን ያለንበት 2012 ዓም + 5500 ዘመን=7512 ስለዚህ ከ 8ኛው ሽ ላይ ከንሱት ።
8000 – 7512= 488 ዓም ይቀራል።
ነገር ግን ሰምታችሁ ከሆነ ዘንዶ 400 ዓመት ገዝቷል ይባላል እስኪ ጠይቁ።
እና የዘንዶው ሲቆጠር 488 – 400 =88 አመት ቀረው።ትንቢቱም እየተፈፀመ ነው። ሌላው ይህ በንዲህ እንዳለ ደሞ
666 አሁን እዚህ በደጃችን ነው፡፡ አጠንክረን እንፀልይ፡፡ የአውሬው
ቁጥር 6 6 6 የሚፈፀምበት የትንቢት ጊዜ አልቋል/ተፈፅሟል፡፡
የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ባስተላለፈው የኦባማን የጤና
ሽፋን ረቂቅ በህግ እንዲካተት ተደርጓል፡፡ የህግ ተግባሩ በቅርቡ
ይጀምራል፡፡ ይህን የጤና ሽፋን ረቂቅ በእያንዳንዱ የአሜሪካ ዜጋ
የሰውነት ክፍል ላይ ግላዊ የሬዲዬ ፍሪኩዌንሲ ቺፕስ መልክ (RFID
CHIPS) እንዲተከል ታዟል፡፡ ይህ ቺፕስ በግንባር ወይም በክንድ ላይ
ይደረጋል፡፡ ይህ ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው በራዕይ 13 :
15 -18 የተቀመጠውን የአውሬው ምልክት ይፈፀም ዘንድ ነው፡፡ እና
አሁንም ስለ ፍፃሜው ትጠራጠራለህ? ታውቃለህ ለኦባማ የተለየ
መኪና እንደተሰራ አውሬው የሚባል? ተዘጋጅ ንጥቀት አሁን
ይጀምራል፡፡ ራዕይ 13ን ቀድመው ተጫውተውታል፡፡ ብዙዎች ግን
ይህን አልተገነዘቡትም፡፡ 1. ለምንድን ነው ይህ ችፕስ ከባንክ
አካውንት ጋር የተቆራኘው ወይም የተገናኘው? አስታውሱ መጽሐፍ
ቅዱስ እንደሚለው ካለ አውሬው ቁጥር 666 ልትገዙም ወይም
ልትሸጡም አትችሉም ስለሚል፡፡ እስኪ ገምቱ ይህ ቺፕስ ከገንዘብ
ዝርዝር መረጃ ጋር ለምን ተገናኘ? እንዲያውም በጣም ያሳዘነኝ
በቤተክርስቲያን ያሉ ብዙዎች ሰዎች ጌታ ሲመጣ ይህን ሁኔታ
ሊያልፉት አይችሉም፡፡ ደግሞም ብዙዎቹ መጨረሻው እንደቀረበ
አያውቁም፡፡ የቴክኖሎጂ በጣም መራቀቅ ምክንያት ነው ብላችሁ
መልስ እንዳትሰጡኝ፡፡ በማንኛውም የህይወት ጎዳናችሁ
ከእግዚአብሔር ጋር ካልተስማማ አሁኑኑ ንሰሀ ግቡና ተለወጡ፡፡
ካለበለዚያ መንግስተ ሰማያትን ካጣችሁት ገሀነምን አታጡትም፡፡
ስለዚህ አስቡበት፡፡ ገሀነም መልካም ስፍራ አይደለም በጣም
አስከፊው ክፍሉ እንደ መንግስተ ሰማያት ዘላለማዊነት እንዳለበት
እዚህም እንደዛው ነው፡፡ ጆሮ ያለው ይስማ መንፈስ ለአብያተ
ክርስቲያናት የሚለውን ይስማ፡፡ ጠቃሚ ያልሆነ ነገር ከምትልኩ ይህን
ለሌላው ብታስተላልፉ መልካም ነው፡፡ ለምታውቋቸው ቅርብ
ለሆኗችሁ ሰዎች ላኩላቸው፡፡ እስኪ የወንጌላዊ ስራ እንስራ፡፡
እባካችሁ ለምታውቋቸው ለእያንዳንዳቸው በየስማቸው ላኩላቸው፡፡
ለሞባይል እንደምንጠነቀቅ ያክል ለእግዚአብሔር ቃል ብንጠነቀቅ
ምን እንደሚሆን ልትገምቱ ትችላላችሁ፡፡ ከዚህ ደግሞ በጭራሽ
ልንላቀቅ ነፃ ልንሆን አንችል፡፡ ስለዚህ የቻልነውን ያክል እንትጋ
እንጋደል፡፡ 7% የሚሆኑቱ ናቸው መልዕክቱን የላኩት በድጋሚ 93%ቱ
ግን አልላኩም አላወቁም ስለዚህ ጠንክረን እንስራ፡፡ ሰይጣን
እንዲህ ይላል፡- " የሚገርመኝ ሰው እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ
አይታዘዝም እኔን ይጠላኛል ግን ይታዘዘኛል፡፡" ይህን መልዕክት በኋላ
እንዳትልኩት አሁኑኑ ላኩት!!!
ቢያንስ ለ #15 ሰው
ሚያዝያ 27/2016 #ትንሣኤ_ክርስቶስ
👉ክርስቶስ ተንሣአ እሙታን፣በአብይ ሀይል ወስልጣን
👉አሰሮ ለሰይጣን፣አግአዞ ለአዳም
👉ሠላም፣አምዝየሰ
👉ኮነ፣ፍስሐ ወሠላም
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን #ለኢየሱስ_ክርስቶስ በዐለ #ትንሣኤ እንኳን አደረሰን
👉አትደንግጡ የተሰቀለዉን #የናዝሬቱን_ኢየሱስ ትሻላችሁን?#ተነሥቷል በዚህስ የለም የተቀበረበትም ቦታ እነሆ ማር16 ቁ6
👉 #የትንሳዔ ምስጢር ተስፋ የምናደርገው ሲሆን ክርስቶስ ዳግመኛ ከመጣ በኋላ ለሚኖረው ዘላለማዊ ሕይወት የመጀመሪያ ነው ትንሣኤ ሙታን በአዳምና በልጆቹ ላይ የተፈረደው የሞት ፍርድ ለመጨረሻ ጊዜ የሚጠፋበትም ነው ስለዚህ #ትንሣኤ_ሙታን_የእምነታችን አንዱ መሠረት ነው
👉 #መድኃኔዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአባታችን ለአዳም በገባው ቃልኪዳን መሠረት በአይሁድ እጅ መከራ መስቀልን ተቀብሏል ነፍሱን በራሱ ስልጣን አሳልፎ ሰጥቷል በሦስተኛውም ቀን #እሑድ_በእኩለ_ሌሊት መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በታላቅ ኃይል ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ተነስቷል
👉ለሰው ልጆች ዘላለማዊ ትንሣኤ በኩር የሆነው #የክርስቶስ ትንሣኤ ነው ከክርስቶስ ትንሣኤ ቀጥሎ ዘላለማዊ ትንሣኤን የተነሣችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት የድንግልም ትንሳኤ ዘላለማዊ ስለሆነ እንደሌሎች ሰዎች የመጨረሻውን ትንሣኤ አልጠበቀችም በመጨረሻው ቀን ሁላችን የምንነሳው ትንሣኤ እንዲሁ ዳግመኛ ሞት የሌለበት ዘላለማዊ ትንሣኤ ነው
👉 #ከትንሣኤ በኋላ የሚኖረውም ዘላለማዊ ሕይወት ታላቅ ተስፋችን ስለሆነ ቅዱሳን አበው የሚመጣውንም ሕይወት ለዘላለሙ አሜን በማለት የሃይማኖት ድንጋጌውን ፈጽመውታል
👉ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም ዮሐ15 ቁ;13
👉በጥላቻ ፤ በቂም ፤በክፋት ፤ በተንኮል፤ በበቀልና በመለያየት ልብ ሆኖ ስለ #ትንሣኤ_በዓል በድፍረት መናገርም መስበክ ራስን ማታለል ነው የሚሆነው ምክንያቱም #የትንሣኤ_በዓል ማዕከሉ ፍቅር ሲሆን ፍቅር እራሱ ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው
👉ስለዚህ ይህን ታላቅ የክብር በዓል ስናከብር ፍቅርና ይቅርታን ይበልጥ በተግባር በመግለጥ እና ጥላቻና ተንኮልን ፈፅሞ በማራቅ ሊሆን ይገባል ብዬ አምናለሁ በመጨረሻም በዓሉን ስናከብር አቅም የሌላቸውና ጧሪ ያጡትን ወገኖቻችን እያሰብንና ካለን በማካፈል በአንድነት እና በአብሮነት ገመድ ተሳስበን እንድናከብር መልካም ምኞቴን ላሳውቅ እወዳለሁ
👉አምላካችን #መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ የሀገራችንን የኢትዮጵያን ትንሣኤ ያሣየን መልካም በዐል ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
እንኳን ለብረሀነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳቹ
በብረሀነ ትንሳኤው የተደሰታቹ
አዲስ መዝሙር በዶግማና ቀኖና ሚዲያ ተለቋል ገብታቹ ሰብስክራዪብ ላዪክ ኮሜንት በመስጠት አበረታቱኝ ❤❤❤❤❤
ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕሥራ ምእት ዐሠርቱ ወስድስቱ ዓመተ ምሕረት፡፡
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
• በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፤
• ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤
• የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤
• በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤
• እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ሁሉ፡-
የትንሣኤ ሙታን በኲር በመሆን ቀድሞ የተነሣው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ስድስት ዓመተ ምሕረት በዓለ ትንሣኤ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!
“ወይእዜኒ ክርስቶስ ቀደመ ተንሥኦ እምኲሎሙ ሰብእ ሙታን@ አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት ሁሉ በኲር ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል” (1 ቆሮ 05.!)
በዛሬው ዕለት በከፍተኛ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት የሚከበረው የጌታችን ትንሣኤ ለሰው ልጅ ያለው መንፈሳዊ ትርጉም እጅግ የላቀ ነው፤ እግዚአብሔር ፍጥረታትን በሙሉ በተለይም የሰው ልጅን ሲፈጥር በፍጹም ፍቅር ነው፡፡
ለዚህም የሰው በአርአያ እግዚአብሔር መፈጠር በቂ ማስረጃ ነው፤ ሰው በበደሉ ምክንያት ለሞት ቢዳረግም የእግዚአብሔር ፍጹም ፍቅር ጨርሶ አልተለየውም፤ እግዚአብሔር አንድ ቀን ሞትን ከሰው ጫንቃ አሽቀንጥሮ እንደሚጥል በየጊዜው ይገልጽ ነበረ፤ ያም በራሱ ልዩ ጥበብ እንደሚከናወን አረጋግጦ ለሰው ልጅ ተስፋውን አሳውቆ ነበር፤ ያም ልዩ ጥበብ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡
የእግዚአብሔር ዕውቀትና ጥበብ ድንበር የለውምና ከፍጥረተ ዓለም በፊት ሳይቀር የሰው ድኅነት በኢየሱስ ክርስቶስ ደም እንደሚፈጸም በእግዚአብሔር ዘንድ የተቈረጠ ነገር ነበረ፤ ጊዜው ሲደርስም በህላዌና በክዋኔ ከእርሱ ጋር አንድ የሆነ እግዚአብሐር ወልድ የሰውን ሰውነት ተዋሕዶ ሰውን የማዳን ስራውን አንድ ብሎ ጀመረ፡፡
ሰዎች በኃጢአትና በዲያብሎስ በደዌና በሞት ላይ ሥልጣን ያለው አዳኝ እሱ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ የማዳን ስራውን በመዋዕለ ሥጋዌው በስፋት አከናወነ፡፡
ልዩ ልዩ ደዌና በሽታ የሚያሠቃያቸውን ፈወሰ፤ ኃጢአተኞችን በይቅርታ ተቀበለ፤ ኃጢአታቸውንም ደመሰሰ፤ አጋንንትንም በትእዛዝ አስወጣ፤ ወደ ጥልቁም አሰመጣቸው፤ ዲያብሎስንም ድል ነሥቶ አባረረ፤ ሙታንንም አነሣ፤ በባሕር ላይ በእግሩ ተራመደ፤ ነፋሳትን ገሠጸ፤ በአምስት እንጀራ ከአምስት ሺሕ ሕዝብ በላይ መገበ፤ ውሀውንም ወደ ጠጅ ለወጠ፡፡
ሰውን ሁሉ በፍቅርና በይቅርታ ይቀበልና ያገለግል ነበር እንጂ በአንዱ ስንኳ የመጨከንና የማግለል መንፈስ አላሳየም፤ ይህ ሁሉ ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፍቅር ማሳያ ነበረ፡፡
በፍጥረት ሁሉ ላይ መለኮታዊ ሥልጣን እንዳለውም ማረጋገጫ ነበረ፤ መልእክቱም ዓለም መዳኛዋና አዳኝዋ እሱ መሆኑን አውቃ በአእምሮ እንድትከተለውና የድኅነቱ ተቋዳሽ እንድትሆን ማስቻል ነው፡፡
• የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!
በእግዚአብሔር አሠራር ኃጢአት ያለ ቤዛነት አይሰረይም፤ በመሆኑም ሰው በእግዚአብሔር ፊት ፍጹም ኃጢአተኛ ሆኖ ስለተገኘ ቤዛ ሆኖ የሚያድነው ያስፈልገው ነበር፤ ቤዛ መሆን የሚችለው አካል ደግሞ ራሱ ፍጹም ንጹህ መሆን ነበረበት፡፡
ከዚህም አንጻር በእግዚአብሔር ፊት ለሱ የሚመጥን ንጹህ ኣካል ከፍጡራን ወገን አልተገኘምና እሱ ራሱ ሰው ሆኖ የሰው ቤዛ ለመሆን በሥጋ ተገለጠ፤ በዚህም መሠረት የሰው ቤዛ ሆኖ በመስቀል ላይ በመሰቀል ንጹህ ደሙን አፈሰሰ፤ በዚህ ደም ምክንያት የሰው ኃጢአት በሥርየት ተዘጋ፤ ለዚህም ነው ቅዱስ መጽሐፍ “ያለ ደም ሥርየት ወይም ይቅርታ የለም” ብሎ የሚነግረን፡፡
ከዚህ ደም መፍሰስ በኋላ ወደ ሲኦል ወርዶ በዚያ የነበሩ የኃጢአት ግዞተኞችን በሙሉ ፈትቶ ወደ ቀደመ ስፍራቸው ወደ ገነት መለሰ፤ ከስቅለተ ክርስቶስ ጀምሮ እስከ መጨረሻ ያለው የሰው ኃጢአት በሙሉ በክርስቶስ ደም ይደመሰሳል፡፡
ሆኖም ይህ ሥርየት የሚገኘው በእምነት መሆኑን ቅዱስ መጽሐፍ አበክሮ ይነግረናል፣ በክርስቶስ አምኖ በደሙ የነጻ ሁሉ ክርስቶስ በተነሣው ዓይነት ትንሣኤ ይነሣል፡፡
• የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!
የጌታችንን ትንሣኤ ስናከብር የኛንም ትንሣኤ በማሰብ ሊሆን ይገባል፤ ትልቁ ነገርም የኛን ትንሣኤ ማሰቡ ላይ ነው፤ ምክንያቱም የክርስቶስ ትንሣኤ ለኛ ተብሎ የተደረገ በመሆኑ ነው፡፡
የሱ ትንሣኤ ለኛ ትንሣኤ በኲር ነው፤ ማሳያና ማረጋገጫም ነው፤ እግዚአብሔር በየዕለቱ የሚፈልገው የኛን ትንሣኤ ማየት ነው፤ የኛ ትንሣኤ በአንድ ቀን በቅፅበት የሚሆን አይደለም፤ ትንሣኤያችን አምነን ስንጠመቅ ተጀምሮ ከመቃብር ስንነሣ የሚጠናቀቅ ነው፡፡
እግዚአብሔር ዛሬም እያንዳንዱ ሰው በትንሣኤ ሕይወት እንዲመላለስ ይጠራል፤ ምክንያቱም የኋለኛው ትንሣኤ የሚገኘው በፊተኛው ትንሣኤ እንደሆነ እግዚአብሔር በመጽሓፉ ነግሮናልና ነው፤ በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕ ነው፤ በሱ ላይ ሞት ሥልጣን የለውምና ነው፤ ለሰው ልጆች ተጠብቆልን ያለው ተስፋ ይህ ነው፡፡
ተስፋውን እውን ማድረግ የሚቻለውም በኛ ሃይማኖታዊና ተግባራዊ ተሳትፎ እንደዚሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛዊ ደም ነው፤ የነገውን ትንሣኤ ተሳታፊ ለመሆን ዛሬ መነሣት ግድ ይላል፤ ይህም የሚቻል እንጂ የማይቻል አይደለም፡፡
በእምነት ትንሣኤ፣ በአምልኮተ እግዚአብሔር ትንሣኤ፣ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ትንሣኤ፣ በፍቅር ትንሣኤ፣ በሰላም ትንሣኤ፣ በይቅርታ ትንሣኤ፣ በመከባበር ትንሣኤ፣ በአንድነት ትንሣኤ፣ በመተሳሰብ ትንሣኤ ወዘተ በመሳሰሉ ሃይማኖታዊና ግብረ ገባዊነት ጸንተን መኖር ከቻልን የፊተኛው ትንሣኤ ማለት እሱ ነው፡፡ ዛሬ እግዚአብሔር እያንዳንዳችን ይህንን ትንሣኤ እውን አድርገን ስንኖርና ስንመላለስ ማየት ይፈልጋል፡፡
በአንጻሩም ክሕደትን፣ ከሕገ ተፈጥሮ ያፈነገጠ ጸያፍ ተግባርን፣ ጥላቻን፣ ጦርነትን፣ መለያየትን፣ ራስን ብቻ መውደድን፣ መጨካከንን፣ ግብረ ኃጢአትን፣ ፈሪሐ እግዚአብሔር ገንዘብ አለማድረግን፣ ፈጣሪን አለማመንን የተጸየፈ ምእመንን ማየት ይፈልጋል፡፡
ምክንያቱም ሁሉም ኃጣውእ አፅራረ ትንሣኤ ናቸውና ነው፤ ኃጣውእ በምድርም በሰማይም የሰው ጠላቶች ናቸው፤ በምድር ለሥጋዊና መንፈሳዊ በሽታ ይዳርጉናል፡፡
በተለይም በእግዚአብሔር ፊት እጅግ አስጸያፊ የሆነው የነውረ ኃጢአት ርኲሰትና በጋብቻ ያልታሰረ ሩካቤ ሥጋ ትውልድን እንደ ቅጠል እያረገፈው እንደሆነ፣ ምንም ዓይነት ፈውስ ላልተገኘለት የኤች አይ ቪ ኤድስ በሽታ ዋነኛ መተላፊያም ይህ ነውረ ኃጢአት እንደሆነ ተደጋግሞ ተነግሮአል፡፡
ይሁንና አሁንም ጥንቃቄ በጎደለው ድርጊት ስሕተቱ በመቀጠሉ በጦርነት ከሚያልቀው ሕዝብ ባልተናነሰ በዚህ ገዳይ በሽታ ብዙ ወገን እያለቀ ነውና እባካችሁ ሕዝበ እግዚአብሔር አንድ ለአንድ በመተሣሰርና በተቀደሰ የጋብቻ ሕይወት በመወሰን ትንሣኤያችንን እናብስር፡፡
በመጨረሻም
እንኳን አደረሰን!
“በእምነት ትንሣኤ፣ በአምልኮተ እግዚአብሔር ትንሣኤ፣ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ትንሣኤ፣ በፍቅር ትንሣኤ፣ በሰላም ትንሣኤ፣ በይቅርታ ትንሣኤ፣ በመከባበር ትንሣኤ፣ በአንድነት ትንሣኤ፣ በመተሳሰብ ትንሣኤ ወዘተ በመሳሰሉ ሃይማኖታዊና ግብረ ገባዊነት ጸንተን መኖር ከቻልን የፊተኛው ትንሣኤ ማለት እሱ ነው፡፡ “ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
#ቃለ_በረከት_ዘብፁዕ_ወቅዱስ_አቡነ_ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕሥራ ምእት ዐሠርቱ ወስድስቱ ዓመተ ምሕረት፡፡
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፤
ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤
የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤
በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤
እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ሁሉ፡-
የትንሣኤ ሙታን በኲር በመሆን ቀድሞ የተነሣው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ስድስት ዓመተ ምሕረት በዓለ ትንሣኤ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!
“ወይእዜኒ ክርስቶስ ቀደመ ተንሥኦ እምኲሎሙ ሰብእ ሙታን@ አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት ሁሉ በኲር ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል” (1 ቆሮ 05.!)
በዛሬው ዕለት በከፍተኛ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት የሚከበረው የጌታችን ትንሣኤ ለሰው ልጅ ያለው መንፈሳዊ ትርጉም እጅግ የላቀ ነው፤ እግዚአብሔር ፍጥረታትን በሙሉ በተለይም የሰው ልጅን ሲፈጥር በፍጹም ፍቅር ነው፡፡
ለዚህም የሰው በአርአያ እግዚአብሔር መፈጠር በቂ ማስረጃ ነው፤ ሰው በበደሉ ምክንያት ለሞት ቢዳረግም የእግዚአብሔር ፍጹም ፍቅር ጨርሶ አልተለየውም፤ እግዚአብሔር አንድ ቀን ሞትን ከሰው ጫንቃ አሽቀንጥሮ እንደሚጥል በየጊዜው ይገልጽ ነበረ፤ ያም በራሱ ልዩ ጥበብ እንደሚከናወን አረጋግጦ ለሰው ልጅ ተስፋውን አሳውቆ ነበር፤ ያም ልዩ ጥበብ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡
የእግዚአብሔር ዕውቀትና ጥበብ ድንበር የለውምና ከፍጥረተ ዓለም በፊት ሳይቀር የሰው ድኅነት በኢየሱስ ክርስቶስ ደም እንደሚፈጸም በእግዚአብሔር ዘንድ የተቈረጠ ነገር ነበረ፤ ጊዜው ሲደርስም በህላዌና በክዋኔ ከእርሱ ጋር አንድ የሆነ እግዚአብሐር ወልድ የሰውን ሰውነት ተዋሕዶ ሰውን የማዳን ስራውን አንድ ብሎ ጀመረ፡፡
ሰዎች በኃጢአትና በዲያብሎስ በደዌና በሞት ላይ ሥልጣን ያለው አዳኝ እሱ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ የማዳን ስራውን በመዋዕለ ሥጋዌው በስፋት አከናወነ፡፡
ልዩ ልዩ ደዌና በሽታ የሚያሠቃያቸውን ፈወሰ፤ ኃጢአተኞችን በይቅርታ ተቀበለ፤ ኃጢአታቸውንም ደመሰሰ፤ አጋንንትንም በትእዛዝ አስወጣ፤ ወደ ጥልቁም አሰመጣቸው፤ ዲያብሎስንም ድል ነሥቶ አባረረ፤ ሙታንንም አነሣ፤ በባሕር ላይ በእግሩ ተራመደ፤ ነፋሳትን ገሠጸ፤ በአምስት እንጀራ ከአምስት ሺሕ ሕዝብ በላይ መገበ፤ ውሀውንም ወደ ጠጅ ለወጠ፡፡
ሰውን ሁሉ በፍቅርና በይቅርታ ይቀበልና ያገለግል ነበር እንጂ በአንዱ ስንኳ የመጨከንና የማግለል መንፈስ አላሳየም፤ ይህ ሁሉ ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፍቅር ማሳያ ነበረ፡፡
በፍጥረት ሁሉ ላይ መለኮታዊ ሥልጣን እንዳለውም ማረጋገጫ ነበረ፤ መልእክቱም ዓለም መዳኛዋና አዳኝዋ እሱ መሆኑን አውቃ በአእምሮ እንድትከተለውና የድኅነቱ ተቋዳሽ እንድትሆን ማስቻል ነው፡፡
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!
በእግዚአብሔር አሠራር ኃጢአት ያለ ቤዛነት አይሰረይም፤ በመሆኑም ሰው በእግዚአብሔር ፊት ፍጹም ኃጢአተኛ ሆኖ ስለተገኘ ቤዛ ሆኖ የሚያድነው ያስፈልገው ነበር፤ ቤዛ መሆን የሚችለው አካል ደግሞ ራሱ ፍጹም ንጹህ መሆን ነበረበት፡፡
ከዚህም አንጻር በእግዚአብሔር ፊት ለሱ የሚመጥን ንጹህ ኣካል ከፍጡራን ወገን አልተገኘምና እሱ ራሱ ሰው ሆኖ የሰው ቤዛ ለመሆን በሥጋ ተገለጠ፤ በዚህም መሠረት የሰው ቤዛ ሆኖ በመስቀል ላይ በመሰቀል ንጹህ ደሙን አፈሰሰ፤ በዚህ ደም ምክንያት የሰው ኃጢአት በሥርየት ተዘጋ፤ ለዚህም ነው ቅዱስ መጽሐፍ “ያለ ደም ሥርየት ወይም ይቅርታ የለም” ብሎ የሚነግረን፡፡
ከዚህ ደም መፍሰስ በኋላ ወደ ሲኦል ወርዶ በዚያ የነበሩ የኃጢአት ግዞተኞችን በሙሉ ፈትቶ ወደ ቀደመ ስፍራቸው ወደ ገነት መለሰ፤ ከስቅለተ ክርስቶስ ጀምሮ እስከ መጨረሻ ያለው የሰው ኃጢአት በሙሉ በክርስቶስ ደም ይደመሰሳል፡፡
ሆኖም ይህ ሥርየት የሚገኘው በእምነት መሆኑን ቅዱስ መጽሐፍ አበክሮ ይነግረናል፣ በክርስቶስ አምኖ በደሙ የነጻ ሁሉ ክርስቶስ በተነሣው ዓይነት ትንሣኤ ይነሣል፡፡
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!
የጌታችንን ትንሣኤ ስናከብር የኛንም ትንሣኤ በማሰብ ሊሆን ይገባል፤ ትልቁ ነገርም የኛን ትንሣኤ ማሰቡ ላይ ነው፤ ምክንያቱም የክርስቶስ ትንሣኤ ለኛ ተብሎ የተደረገ በመሆኑ ነው፡፡
የሱ ትንሣኤ ለኛ ትንሣኤ በኲር ነው፤ ማሳያና ማረጋገጫም ነው፤ እግዚአብሔር በየዕለቱ የሚፈልገው የኛን ትንሣኤ ማየት ነው፤ የኛ ትንሣኤ በአንድ ቀን በቅፅበት የሚሆን አይደለም፤ ትንሣኤያችን አምነን ስንጠመቅ ተጀምሮ ከመቃብር ስንነሣ የሚጠናቀቅ ነው፡፡
እግዚአብሔር ዛሬም እያንዳንዱ ሰው በትንሣኤ ሕይወት እንዲመላለስ ይጠራል፤ ምክንያቱም የኋለኛው ትንሣኤ የሚገኘው በፊተኛው ትንሣኤ እንደሆነ እግዚአብሔር በመጽሓፉ ነግሮናልና ነው፤ በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕ ነው፤ በሱ ላይ ሞት ሥልጣን የለውምና ነው፤ ለሰው ልጆች ተጠብቆልን ያለው ተስፋ ይህ ነው፡፡
ተስፋውን እውን ማድረግ የሚቻለውም በኛ ሃይማኖታዊና ተግባራዊ ተሳትፎ እንደዚሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛዊ ደም ነው፤ የነገውን ትንሣኤ ተሳታፊ ለመሆን ዛሬ መነሣት ግድ ይላል፤ ይህም የሚቻል እንጂ የማይቻል አይደለም፡፡
በእምነት ትንሣኤ፣ በአምልኮተ እግዚአብሔር ትንሣኤ፣ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ትንሣኤ፣ በፍቅር ትንሣኤ፣ በሰላም ትንሣኤ፣ በይቅርታ ትንሣኤ፣ በመከባበር ትንሣኤ፣ በአንድነት ትንሣኤ፣ በመተሳሰብ ትንሣኤ ወዘተ በመሳሰሉ ሃይማኖታዊና ግብረ ገባዊነት ጸንተን መኖር ከቻልን የፊተኛው ትንሣኤ ማለት እሱ ነው፡፡ ዛሬ እግዚአብሔር እያንዳንዳችን ይህንን ትንሣኤ እውን አድርገን ስንኖርና ስንመላለስ ማየት ይፈልጋል፡፡
በአንጻሩም ክሕደትን፣ ከሕገ ተፈጥሮ ያፈነገጠ ጸያፍ ተግባርን፣ ጥላቻን፣ ጦርነትን፣ መለያየትን፣ ራስን ብቻ መውደድን፣ መጨካከንን፣ ግብረ ኃጢአትን፣ ፈሪሐ እግዚአብሔር ገንዘብ አለማድረግን፣ ፈጣሪን አለማመንን የተጸየፈ ምእመንን ማየት ይፈልጋል፡፡
ምክንያቱም ሁሉም ኃጣውእ አፅራረ ትንሣኤ ናቸውና ነው፤ ኃጣውእ በምድርም በሰማይም የሰው ጠላቶች ናቸው፤ በምድር ለሥጋዊና መንፈሳዊ በሽታ ይዳርጉናል፡፡
በተለይም በእግዚአብሔር ፊት እጅግ አስጸያፊ የሆነው የነውረ ኃጢአት ርኲሰትና በጋብቻ ያልታሰረ ሩካቤ ሥጋ ትውልድን እንደ ቅጠል እያረገፈው እንደሆነ፣ ምንም ዓይነት ፈውስ ላልተገኘለት የኤች አይ ቪ ኤድስ በሽታ ዋነኛ መተላፊያም ይህ ነውረ ኃጢአት እንደሆነ ተደጋግሞ ተነግሮአል፡፡
........ ለከበረው ስም አጠራሩ ምስጋና ይግባውና መድኅነ ዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መከራና ሕማም መቀበሉን ስናስብ አብረን የምናስባቸው ቅዱሳንም አሉ።
የመጀመርያዋ ንጽሕተ ንጹሐን ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት። የክርስቶስን ህመም በእናትነት አንጀቷ ስለተመለከተች ሐዘኗን ለመናገር ቃላቶች በቂ አይደሉም። ቀጥሎ ደግሞ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ። እርሱም የክርስቶስን መከራ ከመጀመርያው እስከ መጨረሻው በመመልከቱ "ቁጹረ ገጽ" ወይም "ፊቱ የተቋጠረ" ተብሎ ተጠርቷል።
ሌላኛው ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ መብዐ ጽዮን ናቸው። ወደ ምንኵስና ሕይወት ከገቡ በኋላ የክርስቶስን ሕማም እያሰቡ ለማልቀስ ይመኙ ነበር። በመጨረሻም "ልክ እንደ ዕለተ አርቡ ኾነህ ታየኝ" ብለው መጸለይ ጀመሩ። ኢየሱስ ክርስቶስም ጸሎታቸውን ሰምቶ ልክ እንደ ዕለተ አርቡ ኾኖ ታያቸው። በዚህ ምክንያት 70 ዓመት በሐዘን ኖረዋል። ሐሞት መጠጣቱን ለማሰብ አርብ አርብ ኮሶ ይጠጡ ነበር። "አንተ ፍቅርህን ገልጸህልኛል፤ እኔ ግን አልቻልኩም" እያሉ ራሳቸውን ይወቅሱ ነበር።
በረከታቸው አይለየን !✝️
©getu teshome
#ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_የተቸነከረባቸው_አምስቱ_ቅንዋተ_መስቀል_ችንካሮች፦
1ኛ ሳዶር፣ በሚባል ችንካር ቀኝ እጁ የተቸነከረበት
2ኛ አላዶር፣ በሚባል ችንካር ግራ እጁ የተቸነከረበት
3ኛ ዳናት፣ በሚባል ችንካር ሁለት እግሮቹ የተቸነከረበት
4ኛ አዴራ፣ በሚባል ችንካር ደረቱን አጣብቆ እንዲይዘው የተቸነከረበት
5ኛ ሮዳስ፣ በሚባል ችንካር ከወገቡ (እምብርቱን) አጣብቆ እንዲይዘው የተቸነከረበት
#ማስታወሻ አንዳንድ መጽሐፎች ይህ የአይሁድ ንጉስ ነው ብለው የጻፉበትንም እንደ ቅንዋት ይቆጥሩታል።
ይህ ሁሉ ስለ እኔ ኃጥያት አንተ ዋጋ ከፈልክልኝ!
ስለ ማይከፈለው ውለታህ ስማያልቀው ምህረትህ ስለ ማይሰስተው ፍቅርህና ስለ ቸርነትህ ስለ ማይነገረው ውለታህ ተመስገንልኝ ጌታዬ
††† እንኳን ለጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ✝መድኃኔ ዓለም✝ †††
††† ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ በዚሕ ዕለት ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ 3:00 ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት::
ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና: ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት: አስረው ሲደበድቡት አድረዋል::
*ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት:: ምራቃቸውን ተፉበት:: ዘበቱበት:: ራሱንም በዘንግ መቱት:: እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ::
✝በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት:: በሠለስት (ሦስት ሰዓት ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ 6,666 ገረፉት:: ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት::
✝ስድስት ሰዓት ላይ በረዣዥም ብረቶች አምስት ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት:: ሰባት ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ::
ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ ሰባት ቃላትን ተናገረ::
✝ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በባሕርይ ሥልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ:: በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ:: አሥራ አንድ ሰዓት ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት::
✝በዚያች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ:: ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ:: ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ:: (ማቴ. 27:1, ማር. 15:1, ሉቃ. 23:1, ዮሐ. 19:1)
††† ለእኛ ለኀጥአን ፍጡሮቹ ሲል ይህንን ሁሉ መከራ የታገሰ አምላክ ስለ አሥራ ሦስቱ ኅማማቱ: አምስቱ ቅንዋቱ: ስለ ቅዱስ መስቀሉ: ስለ ድንግል እናቱ ለቅሶና ስለ ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስ ብሎ ይማረን::
††† መድኃኔ ዓለም ከወዳጆቹም ጸጋ ክብርን ያድለን::
††† "የተጠራችሁለት ለዚህ ነው:: ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሏልና:: እርሱም ኃጢአት አላደረገም:: ተንኮልም በአፉ አልተገኘበትም:: ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም:: መከራንም ሲቀበል አልዛተም . . . እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ::" †††
(፩ጴጥ. ፪፥፳፩-፳፭)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
/channel/zikirekdusn
ሚያዚያ 25/2016 #ዐርብ_የፍቅር_ቀን
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ለሰዎች ልጆች ፍቅሩን የገለፀበት ዕለተ ዓርብ አዳምን ከሰይጣን ባርነት ነፃ ለማውጣትና የእርሱን የበደል ዕዳ ለመክፈል አምላካችን መከራ መስቀሉን የተሸከመበት ዕለት፣ የኀዘን ዕለት፣ የድኅነትም ዕለት ነው
👉ዓርብ ማለት ዐረበ ገባ (ተካተተ) ካለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጕሙም መካተቻ ማለት ነው እግዚአብሔር አምላክ ፍጥረቱን ከእሑድ ጀምሮ በስድስተኛው ቀን ዓርብ አዳምን በመፍጠር ሥራውን ሁሉ አጠናቋልና (አካቷልና) በኋላም በኦሪት ሕዝበ እስራኤል ከሰማይ የሚወርድላቸውን መና በሙሴ ትእዛዝ መሠረት ዓርብ ዕለት የቅዳሜን ጨምረው (ቅዳሜ ሰንበት ስለሆነ እህል መሰብሰብ ስለማይገባ) አካተው ይሰበስቡ ነበር (ዘፀ.፲፮፥፬)
👉በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ብርሃነ ዓለም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ «አውቀውስ ቢሆን የክብርን ጌታ ባልሰቀሉት» እንዳለ ይህ ዕለት የአይሁድ ካህናት ያለበደል ያለጥፋት ንጹሕና ጻድቅ የሆነውን ጌታ የሰቀሉበት ዕለት ነው፡፡
👉ዕለቱም የዓለም ሁሉ መድኃኒት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሲል በመልዕልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የምናስብበትና የሰው ልጅ ድኅነት የተፈጸመበት (የተካተተበት) በመሆኑ (ዓርብ) ተብሏል (፩ኛቆሮ.፩፥፲፰፣ማቴ.፳፯፥፴፭-፸፭)
👉ዓርብ ጠዋት ጎህ ሲቀድ አይሁድ ጌታችንን በጲላጦስ ፊት አቀረቡት ጲላጦስም ወደነርሱ መጥቶ ‹‹የዚህ ሰው በደሉ ምንድነው?›› አላቸው፤ የካህናት አለቆቹም ‹‹ክፉ አድራጊ ባይሆን ወዳንተ እናመጣዋለን? ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር ያስተካክላል፤ ለቄሳር አልገዛም ይላል፤ የሰንበትን ቀን ይሽራል….›› በማለት የተለያዩ ክሶች አቀረበቡት፡፡
👉ጲላጦስም ‹‹እናንተ ወስዳችሁ እንደ ሕጋችሁ ፍረዱበት›› አላቸው እነርሱም ‹‹እኛ ማንንም ልንገድል አልተፈቀደልንም›› አሉት ጲላጦስም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሊጠይቀው፣ ሊመረምረው ወደውስጥ አስገባው ያንጊዜም ጲላጦስ ‹‹የአይሁድ ንጉሥ አንተ ነህን?›› አለው
👉ጌታችንም ‹‹ይህን የምትናገር ከራስህ ነውን ወይስ ስለእኔ የነገረህ ሌላ አለን›› ብሎ መለሰለት፤ ጲላጦስም ‹‹እንዲያ የአይሁድ ንጉሥ አንተ ነህ›› አለው፤ ጌታችንም ‹‹እኔ ንጉሥ እንደሆንኩ አንተ ራስህ ትላለህ›› አለው ጲላጦስም ምንም ያገኘበት በደል የለም
👉ወደ ውጭም ወጥቶ ይህን ሰው በምትከሱበት ገንዘብ በደል አላገኘሁበትም፤ ነገር ግን በየዓመቱ በየፋሲካ በዓል ከእስረኞች አንድ እንድፈታላችሁ ልማድ አላችሁ፤ እንግዲህ የአይሁድን ንጉሥ ልፈታላችሁ ትወዳላችሁን?›› አላቸው እነርሱም በአንድ ድምጽ ከፍ አድርገው ‹‹በርባንን እንጂ ይህን አይደለም›› አሉ በርባን ግን ወንበዴ ነበር፡፡
👉አይሁድም ‹‹ሕግ አለን እንደ ሕጋችን ይሞት ዘንድ ይገባል፤ ራሱን የእግዚብሔር ልጅ አድርጓልና›› አሉት ጲላጦስም ሊያስተዋቸው እንዳልተቻለው ባየ ጊዜ አውጥቶ ገረፈው፤ ምክንያቱም በሀገራቸው የሚሰቀል አይገረፍም፤ የሚገረፍም፤ አይሰቀልም፤ ስለዚህ እንዳይሰቅሉት ራርተው ይለቁታል ብሎ ነው ነገር ግን ‹‹መጠውኩ ዘባንየ ለቅሥፈት›› ተብሎ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ነው፤ እንደዚሁም ዲያብሎስ የአዳምን ዘባነ ልቡና እየገረፈ ገሃነም አውርዶት ነበርና ለእርሱ ካሣ ሊሆን እንደመጣ ለማጠየቅ ጀርባውን ተገረፈ፡፡ (ዮሐ.፲፰፥፳፰-፴፩)
👉ጲላጦስም ‹‹እነሆ ንጉሣችሁን ልስቀለውን?›› አላቸው፤ እነርሱም ‹‹ከቄሳር በቀር ሌላ ንጉሥ የለንም፤ ስቀለው፤ ስቀለው›› አሉ ይህንን ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሲተረጉሙት ‹‹ልደቱ ከዳዊት ዘር እንደሆነ ሲያመለክታቸው በመንግሥትም ደም በማስፈራራት ያስጥለው ዘንድ ነው፤ እነርሱ ግን እርሱን ለመግደል ጨከኑ፤ ከቄሳር በቀር ንጉሥ የለንም ብለው የዳዊትን ዘር መንግሥት ካዱ›› ብለውታል፡፡
👉ዳግመኛም አይሁድ በሕዝቡ መሐል እየተሽሎኮሎኩ ‹‹በርባንን ፍታልን፤ ክርስቶስን ስቀልልን›› በሉ እያሉ ሕዝቡን አሳመፁ ጲላጦስም የሚረባና የሚጠቅም ነገር እንደሌለ ባየ ጊዜ ውኃ አምጡልኝ ብሎ ‹‹እኔ ከዚህ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ፤ እናንተ ራሳችሁ ዕወቁ›› ብሎ በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ፡፡ ሕዝቡም መልሰው ‹‹ደሙ በእኛና በልጅ ልጆቻችን ላይ ይሁን›› አሉ ከዚያን ጊዜም ጀምሮ ልጆቻቸው ደም ጨብጠው የሚወለዱ ሆነዋል (መጽሐፈ ምሥጢር- ምዕራፍ ፩፥፬)
👉እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም "አሜን ኪራላይሶን" ➕ ⛪️ ➕
ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለም ዓለም።
አማኑኤል አምላኪየ ለከ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለም ዓለም።
ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለም ዓለም።
با فیلترشکن نت ملی
یک بار برای همیشه از شر فیلترینگ خلاص شو
دانلود از گوگل پلی
https://play.google.com/store/apps/details?id=de.manvpn.app
🌾 🌾 🌾 የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ 🌾 🌾 🌾
የክብር ባለቤት ትንሣኤና ሕይወት የኾነው ጌታ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሠ መቃብር ካደረ በኋላ ፤ በመንፈቀ ሌሊት በድንቅ ምስጢር መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል በኀቱም መቃብር ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ ።
<< በሥጋ ሞተ ፤ በመለኮቱ ሞትን ድል ነሣው ፤ ተነሥቶም የዘላለም ድል መንሣትን ሰጠን ፤ የሞት ቁራኝነትን አጠፋ ፤ ዕፀ ሕይወትን ሰጠን ፤ ይኽቺውም የከበረች ትንሣኤ ናት >> ( ቅዱስ ሳዊሮስ )
አሜን እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሣኤ በሰላም በጤና አደረሰን ። ከበዓለ ትንሣኤው ረድኤት በረከት ምህረት ቸርነት ፍቅር አንድነት ይሰጠን ዘንድ የአምላካችን ቅዱስ ፈቃድ ይሁን ። ለዘለዓለሙ አሜን ።
በዓለ ትንሣኤ የእግዚብሔር ፍቅር መገለጫና የተስፋችን ማሳያ መሆኑን በመገንዘብ ለእግዚአብሔር ክብርና ለሰው ልጆች ደኅንነት በአንድነት በመቆም ለተራቡት፣ ለተጠሙት፣ ለታረዙት፣ ለታመሙትና ለታሰሩትም ሁሉ ካለን ከፍለን በመስጠት ከኛ ጋራ በመንፈስና በሞራል በዓለ ትንሣኤውን እንዲያሳልፉ እናደርግ ዘንድ መንፈሳዊ ጥሪያችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤ በድጋሚ በዓሉን የሰላም የዕርቅ የይቅርታ የትንሣኤ ኅሊና ወልቡና ያድርግልን፤
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
አሜን።
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ
ተክለ ሃይማኖት
ሚያዝያ ፳፯ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
ይሁንና አሁንም ጥንቃቄ በጎደለው ድርጊት ስሕተቱ በመቀጠሉ በጦርነት ከሚያልቀው ሕዝብ ባልተናነሰ በዚህ ገዳይ በሽታ ብዙ ወገን እያለቀ ነውና እባካችሁ ሕዝበ እግዚአብሔር አንድ ለአንድ በመተሣሰርና በተቀደሰ የጋብቻ ሕይወት በመወሰን ትንሣኤያችንን እናብስር፡፡
በመጨረሻም
በዓለ ትንሣኤ የእግዚብሔር ፍቅር መገለጫና የተስፋችን ማሳያ መሆኑን በመገንዘብ ለእግዚአብሔር ክብርና ለሰው ልጆች ደኅንነት በአንድነት በመቆም ለተራቡት፣ ለተጠሙት፣ ለታረዙት፣ ለታመሙትና ለታሰሩትም ሁሉ ካለን ከፍለን በመስጠት ከኛ ጋራ በመንፈስና በሞራል በዓለ ትንሣኤውን እንዲያሳልፉ እናደርግ ዘንድ መንፈሳዊ ጥሪያችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን።
በድጋሚ በዓሉን የሰላም የዕርቅ የይቅርታ የትንሣኤ ኅሊና ወልቡና ያድርግልን፤
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
አሜን።
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ሚያዝያ 27 ቀን 2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
ቀዳም ስዑር ፣ ለምለም ቅዳሜ ፣ ቅዱስ ቅዳሜ !
በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም።
ቀዳም ሥዑር መስዋእተ ኦሪት የተሻረባት የእንሳሳቱ ደም መፍሰስ ያለፈበት በሲዖል ሰላም የታወጀባት 5500 ዘመን የተዘጋች ገነት ተከፍታነፍሳት ወደገነት የገቡባት የምሥራች የታወጀበት ዕለት ናት። እንደ ኖኅ ርግብ ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል እያቃጨሉ ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ብስራትን የሚያበስሩባት ዕለት ናት።
ለምለም ቅዳሜ፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡
በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡
የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡
ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጎደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል፡፡ ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡
በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡
https://youtube.com/@-Ledatube?si=DLW--rPkSd820Pb1
/channel/+80Qf0_Q0RNZiYWE0
https://www.facebook.com/mogesabeje94?mibextid=ZbWKwL
✝✝✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝✝✝
=>+"+ እንኩዋን ለእናታችን ቅድስት ሣራ ዓመታዊ የሰማዕትነት በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+
+"+ ቅድስት ሣራ +"+
=>እናታችን ቅድስት ሣራ በዘመነ ሰማዕታት ከነበሩ ክርስቲያኖች አንዷ ናት:: ተወልዳ ያደገችው በሃገረ አንጾኪያ (ሶርያ) ውስጥ ነው:: ለክርስቲያን እንደሚገባ አድጋ በመንፈሳዊ ሥርዓት አግብታለች::
+የመከራው ዘመን እየገፋ ሲመጣ ባሏ ሃይማኖቱን በመካዱ ሕይወቷ ተመሰቃቀለ:: በመሐል ላይ ደግሞ ነፍሰ ጡር ነበረችና መንታ ልጆችን ወለደች:: ልጆቿን ክርስትና ለማስነሳት ምድረ ሶርያን ዞረች:: ግን አልቻለችም::
+ምክንያቱም ከመከራ ብዛት አብያተ ክርስቲያናት የሚበዙቱ ተቃጥለውና ፈርሰው ነበር:: ቀሪዎቹ ደግሞ ካህናትና ምዕመናን በማለቃቸው ምክንያት ተዘግተው ነበር::
+ቅድስት ሣራ ልጆቿ የሥላሴ ልጅነተነን ሳያገኙ እንቅልፍ ሊወስዳት አልቻለምና ሕይወቷን አደጋ ላይ የሚጥል ግን መንፈሳዊ ውሳኔን ወሰነች:: ከሶርያ ተነስታ: በመርከብ ተጭና ወደ ግብፅ ወረደች::
+በውሃው መካከል ላይ ሲደርሱ ታላቅ ማዕበል ተነስቶ አናወጣቸው:: በዚህ ጊዜ ቅድስት ሣራ ደነገጠች:: ልጆቿ ጥምቀትን ሳያገኙ መሞታቸው ነውና በእምነት ወደ ፈጣሪዋ ጸለየች:: ሁለቱን ልጆቿን ወስዳ በባሕሩ ላይ በአብ: በወልድ: በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቃ: ከጡቷ አካባቢ በጥታ በሜሮን አምሳል ቀባቻቸው::
+ድንገት ግን በዚህ አፍታ ማዕበሉ ጸጥ አለ:: እርሷም እያደነቀች ወደ ግብጽ ደርሳ ሊቀ ዻዻሳቱን (ቅዱስ ዼጥሮስን) "አጥምቅልኝ" አለችው:: ቅዱስ ዼጥሮስም ሥርዓቱን አድርሶ ሊያጠምቃቸው ባልዲውን ሲዘቀዝቀው ውሃው ረጋበት:: ሁለተኛም: ሦስተኛም ሞከረ:: ግን አሁንም ለሌሎቹ ሕጻናት የሚፈሰው ለቅድስት ሣራ ልጆች እንቢ አለ::
+ቅድስት ሣራም "ምናልባት በድፍረቴ ምክንያት ይሆናል" ብላ የሆነውን ሁሉ እያዘነች ነገረችው:: ቅዱስ ዼጥሮስ ግን እግዚአብሔርን አመሰገነ:: አላትም "ፈጣሪ ባንቺ እጅ ስላጠመቃቸው የእኔን እንቢ አለ:: ልጄ ሆይ! ሃይማኖትሽ ትልቅ ነው::"
+ከዚህ በሁዋላም ሥጋውን ደሙን አቀብሎ ባርኮ አሰናብቷታል:: ወደ ሶርያ ስትመለስ ግን ሌላ የከፋ ነገር ጠበቃት:: በባሏ ከሳሽነት ወደ ከሃዲው ንጉሥ (ዲዮቅልጥያኖስ) ቀረበች:: ንጉሡ ክርስቶስን ካጂ: የት እንደ ነበርሺም ተናገሪ አላት:: እርሷ ግን ሃይማኖቷ የጸና ነበርና እንቢ አለች::
+በዚህም ምክንያት በ303 ዓ/ም አካባቢ በዚሁ ቀን አንድ ልጇን በሆዷ: ሌላኛውን በጀርባዋ አድርገው በእሳት አቃጥለው ገድለዋታል:: እነሆ ቤተ ክርስቲያን ታስባታለች:: ታከብራታለችም::
=>አምላካችን ቅድስት ሣራን እንዳጸና እኛንም ያጽናን:: ከበረከቷም ያድለን::
=>ሚያዝያ 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ሣራና 2 ልጆቿ (ሰማዕታት)
2.አቡነ ገብረ ማርያም ጻድቅ-ዘልሆኝ (ኢትዮዽያዊ)
3.አባ በብኑዳ ባሕታዊ
4.ቅዱስ ቴዎድሮስ መስተጋድል
5.ቅድስት ዶራ
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
2.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
3.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
4.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
5.አቡነ አቢብ /አባ ቡላ/
6.ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ
=>+"+ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ ራቁትነት: ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን?
'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቈጠርን'
ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው::
በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን:: +"+ (ሮሜ. 8:35-38)
<<<ወስብሐት ለእግዚአብሔር>>>