ግንቦት 9/2016 #አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ #አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ መታሰቢያ በአል እንኳን አደረሰን
👉አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስ አባታቸው መልአከ ምክሩ እናታቸው ወለተ ማርያም ይባላሉ የተወለዱበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ነው
👉በተወለዱ ዕለት ተነሥተው በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ብለው #ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል የስማቸው ትርጓሜ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ አንድም #የክርስቶስ እስትንፋስ ማለት ነው
👉ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸውና በመንገዳቸው ሁሉ እየመራቸው ነው ያደጉት #መንፈስ_ቅዱስ ልቡናቸውን ብሩህ አድርጎላቸው በ5 ዓመታቸው የቅዱሳት መጻሕፍት ቃላትን፣ ብሉያትንና ሐዲሳትን፣ ድርሳናትንም ጠንቅቀው ዐውቀዋል
👉በተወለዱ በ14 ዓመታቸው ወደ #አቡነ_ኢየሱስ ሞዐ ደብረ ሐይቅ ገዳም ሄደው ከባሕር ዳር ቆመው የሙሴን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር በጸለዩ ጊዜ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ባሕሩን አሻግሯቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተዋል፡፡
👉ለ3 ዓመታት ያህል በኃይቅ ገዳም ለመነኮሳት እንጨት በመልቀምና ውሃን በመቅዳት #ለአባቶች_መነኮሳት ምግብ የሚሆናቸው ዓሣ ከባህር ውስጥ በማውጣት አገልግለዋል፡
👉አባታችን #እስትንፋሰ_ክርስቶስ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ከፆሙ በኋላ ምንም እህል ሳይቀምሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ ለሙሴ በደብረ ሲና እንደሰጠው ለአባታችንም ወደ እርሳቸው መጥቶ ዓሥሩን ቃላተ ኦሪትና ስድስቱን ቃላተ ወንጌል በውስጣቸው የተጻፈባቸው ሁለት ጽላቶችን ሰጥቷቸዋል፡፡
👉አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሠሩ በኋላ ዕለቱን ስንዴ ዘርተው፣ ወይን ተክለው፣ ጽድን ወይራንና ግራርን ተክለው በአንዲት ቀን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ዕለቱን አድርሰዋል ስንዴውን ለመሥዋዕት ወይኑን ለቍርባን በተአምራት አድርሰዋል፡፡
👉አባታችን በጸሎት ላይ እንዳሉ ቅዱስ ሚካኤል ተልኮ መጥቶ አባታችንን በደመና ጭኖ ወስዶ ከጌታችን ከመድኃኒታችን #ከኢየሱስ_ክርስቶስ ፊት አቆማቸው ጌታንም በቅዱሳኑ ሁሉ እንዲባረኩ ካደረጋቸው በኋላ መልአኩን ‹‹ወደ ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ ወደ ኢየሩሳሌም አድርሰው›› ብሎት ኢየሩሳሌምን አሳልሞ ሀገራችን መልሶ አምጥቷቸዋል
👉አባታችን ሁሉንም የኢትዮጵያን ቅዱሳት ገዳማትን ተዘዋውሮ ሲጎበኙ በሕይወተ ሥጋ የሌሉት የየገዳማቱ ቅዱሳን ሁሉ በአካል ይገለጡላቸው ነበር ጎጃም ውስጥ እያስተማሩ፣ !፣ የታመሙትን እየፈወሱ፣ የዕውራንን ዐይን እያበሩና ሙታንን እያሥነሱ ብዙ ካገለገሉ በኋላ ለዘጠኝ ዓመታት በባሕር ውስጥ ገብተው ቁልቁል ተዘቅዝቀው #ለኢትዮጵያ_ፀልየው የምሕረት ቃልኪዳን ተቀብለዋል
👉ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ጌታችን መጥቶ ‹‹ከመነኮሳት ሁሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ ሆይ #ኢትዮጵያንና_ሕዝቦቿን ምሬልሃለሁ ከዚህች ባሕር ውጣ›› በማለት በሞት የሚያርፉበትን ቦታ ነግሯቸዋል፡፡
👉ጻድቁ ወደ ደብረ አሰጋጅ በሚሄዱበት ጊዜ ጸሐይ ልትገባ ስትል ‹‹በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አውግዤሻለሁ ለመስፍን ኢያሱ በገባኦን እንደቆምሽ አሁንም ቀጥ ብለሽ ቁሚ ብለው ፀሐይን አቁመዋል አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስም ደብረ አሰጋጅ ሲደርሱ ፀሐይ አፍ አውጥታ ‹‹አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ እገባ ዘንድ ፍታኝ›› ስትላቸው #እግዚአብሔር_ይፍታሽ ባሏት ጊዜ ጠልቃለች
👉ጻድቁ ሌላው በእጅጉ የሚታወቁበት አንድ ትልቅ ቃል ኪዳን አላቸው በአምላክ ልቡና የሚገኝ፣ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ልቡና የሚገኝ፣ በቅዱስ ሚካኤልና በቅዱስ ገብርኤል ልቡና የሚገኝ እንደ መልክአ መድኃኔዓለም ያለች እጅግ አስገራሚ #ፀሎት አለቻቸው፤ እርሷን ጸሎት በጸለዩ ጊዜ እልፍ ነፍሳትን ከሲኦል ያወጣሉ
👉ጸሎቷም #የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች እያንዳንዱ የሰውነት ክፍሎቹ የተቀበሉትን ጸዋትዎ መከራዎች ሁሉ ታዘክራለች በእያንዳንዱ ክፍልም የጸሎት ማሳረጊያ #አቡነ_ዘበሰማያት ይደግማሉ ንስሓ የገባ ኃጢአተኛ ሰው እንኳን ቢሆን ይህችን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት በጸለየ ጊዜ ሺህ ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ ጌታችን በማይታበል ቃሉ ለአባታችን ነግሯቸዋል
👉እያንዳንዱን #የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች መከራዎቹን የምታዘክረውን ይህቺን በአምላክ ልቡና ያለች ግሩም የሆነች ፀሎት ነፍሳትን ከሲኦል አታወጣም ብሎ የሚጠራጠር ቢኖር መንግስተ ሰማያትን አያያትም ጻድቁ ታኅሣሥ 8 ቀን ተወልደው ሚያዚያ 9 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከፃድቁ ረድኤት በረከት ያሣትፈን #የፃድቁ_አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ምልጃና ፀሎት ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን" ✝️💒✝️
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❤️ እንዲህ ያስተምራሉ
👉 ካህን ማለት የክርስቶስ እጅ ነው
👉የ ካህኑን ምክር ከሰማህ አትወድቅም
➡️በእሱ እጅ ስጋው ደሙን ይሰጥሀል
➡️በእሱ እጅ ድህነት ይሰጠሃል
➡️በእሱ እጅ መንግስተ ሰማያት ይሰጣUል
👉ቁልፉን የያዘው ካህን ነው
👉ክህነት ጠልቶ ድህነት የለም
👉ለቀኖና አለመሰቀቅ
👉ስትናዘዙ አለመስቀቅ
👉ስትናዘዙ አንድ ማይረባ ምሳሌ ልናገር
🙂ለሐኪም
👉አንድ የተከበረ / ች ሰዉ የሚባለው/ ትባለው
ሰውነቱ/ ቷ ስቃይ ውስጥ ከሆነ ሙሉ አካሏን/ ሉን
ገልጦ ለሀኪም ይሰጣል ።
👉አንተም ሙሉ ገመናህን አውጠህ መናዘዝ አለብህ
👉ለካህን ስትናገሩ አትፍሩ ዛሬውኑ ሂዳችሁ መና ዘ ዝ
❤️ሐይማኖተ አበው ም ፡36 እንዲህ ይላል
👉የካህኑን ቃል ቸል አንበል
👉እሱ ነፍስን የሚፈወስ የነፍስ ሐኪም ነውና ።
ግንቦት 8/2016 #አቡነ_ኪሮስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ #አቡነ_ኪሮስ ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን
👉የጻድቁን ስም የሚጠራ አፍ ንዑድ ነው ክቡር ነው በእውነት የቅዱሱን አባት ክብር ለማግኘት መፋጠን ይበጃል #አቡነ_ኪሮስ የተወለዱት በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን ወላጆቻቸው ነገሥታት ናቸው
👉ተወልደው ባደጉባት ሃገር ቁስጥንጥንያ ገና በልጅነት ምቾት ሳያሳሳቸው መጻሕፍትንና ትሕርምትን ተምረዋል ወንድማቸው ታላቁ ቴዎዶስዮስ በነገሠባቸው የመጀመሪያ ዓመታት በቤተ መንግስቱ ዙሪያ ግፍ በዝቶ ነበርና #አቡነ_ኪሮስ ከኃጢአት ለመራቅና ለጌታ ለመገዛት ከከተማው ጠፍተው አሕጉር አቁዋርጠው ወደ ግብፅ ገዳመ አስቄጥስ መጡ
👉እርሳቸውን ለመፈለግ የተደረገው ሙከራ አልተሳካም ይባስ ብሎ የንጉሡ ልጅ ገብረ ክርስቶስ ሙሽርነቱን ጥሎ ወደ ሌላ ሃገር መነነ "የቅኖች ትውልድ ይባረካል" እንዳለ ቅዱስ ዳዊት #አቡነ_ኪሮስ ለሙሽራው ገብረ ክርስቶስ አጎቱ ናቸው አቡነ ኪሮስ በገዳም ውስጥ የታላቁ አቡነ በብኑዳ ደቀ መዝሙር ሆነው ለዘመናት ቆይተዋል
👉ቅዱስ በብኑዳን አንበሳ በበላው ጊዜ በጣም አዝነው ለምን ጌታ ሆይ በሚል መሬት ላይ ወድቀው አለቀሱ ምክንያቱ ካልተነገረኝ አልነሳም ብለው ከወደቁበት መሬት ላይ ሳይነሱ ለ40 ዓመታት አልቅሰዋል በዚህ ምክንያት ግማሹ አካላቸው አፈር ሆኖ ሣር በቅሎበታል #ጌታችን ተገልጦ ምክንያቱን ነግሯቸዋል አካላቸውንም እንደነበረ መልሶላቸዋል
👉አንድ ቀን #ጻድቁ_ለቅዱስ_በብኑዳ ሞት ምክንያት የሆነው መነኮሴ ታንቆ መሞቱን ሰምተው በጣም አዘኑ ሱባዔ ገብተው ፍጹም አልቅሰው ከጌታም አማልደው የዛን ኃጥእ ነፍስ ከሲዖል አውጥተዋል በሌላ ጊዜ ደግሞ ኃጥአን የሞሉበት አንድ ገዳም በግብፅ ነበርና መቅሰፍት ወርዶ ሁሉንም ባንድ ቀን ሲያጠፋቸው አዩ
👉ፃድቁ በዚህም ምክንያት ለ30 ዓመታት አልቅሰው ሙታኑን አስነስተው ንስሃ ሰጥተው ገዳሙን የጻድቃን ሕይወታቸውንም የፍቅር አድርገውታል #ፃድቁ እመቤታችንን ከመውደዳቸው የተነሳ በስዕሏ ፊት አብዝተው ይሰግዱና ያለቅሱ ነበር እመ አምላክም ተገልጣ ትባርካቸው ነበር
👉ከዚህ በሁዋላ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ሒደው ለ57 ዓመታት ማንንም ሳያዩ ተጋደሉ ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና በየቀኑ ይጐበኛቸው ቁጭ ብሎም ያወራቸው ነበር
👉በመጨረሻም #ጌታ አእላፍ መላእክትን ፃድቃን ሰማዕታትን ድንግል እመቤታችንና ቅዱስ ዳዊትን አስከትሎ ወረደ
👉 #ቅዱስ_ዳዊት ቀርቦ እያጫወታቸው በበገናው እየደረደረላቸው ከዝማሬው ጣዕም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው በፍቅር ተለየች ጌታችንም ታቅፎ ስሞ ይዟቸው አረገ
👉ሥጋቸውን አባ ባውማ ቀበሩት #የአቡነ_ኪሮስ ቁመታቸው ቀጥ ያለ ፅሕማቸውም የተንዠረገገ ነበር እድሜአቸውን ግን መገመት የሚቻል አይመስለኝም
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከፃድቁ ረድኤት በረከት ያሣትፈን የፃድቁ ምልጃና ፀሎት ከክፉ መከራ ሁሉ ይጠብቀን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
"ሰላም ለአትናቴዎስ ከመ ላዕሌሁ ተነበዩ። ደቂቀ ክርስቲያን ኵሎሙ እንዘ ይትዋነዩ። ሊቀ ጳጳሳት ዘኮነ ወምእመነ ክርስቶስ ዲበ ንዋዩ። ወበእንተ ዘበጽሖ ስደት እመንበረ ክብሩ ወዕበዩ። ተሰምየ ሐዋርያዌ በኵሉ አያዩ"። ( የክርስቲያን ልጆች ኹሉ ሲጫዋወቱ በርሱ ላይ ትንቢትን እንደተናሩ የጳጳሳት አለቃ ኾኖ ለተሾመና በክርስቶስ ገንዘብ (ምእመን) ላይ ታማኝ ኾኖ ለተገኘ ለቅዱስ አትናቴዎስ ሰላምታ ይገባል፤ ከፍፁም ክብሩ ዙፋን ላይ ስደት ስለደረሰበትም በግብሩ ኹሉ ሐዋርያዊን ተብሎ ተሰየመ)። ሊቁ አርከ ሥሉስ
Читать полностью…ግንቦት 6/2016 #መድኃኒታችን_ኢየሱስ
#ቁስቋም_ማርያም
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን በሞቱ ወደ ክብራችን ለመለሰን #በትንሣኤዉ ላከበረን #ለአምላካችን_ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ እንዲሁም ለእናታችን #ቁስቋም_ማርያም ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን
👉እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች
#ኢየሱስ ስንል አምላከ አማልእክት የአማልክት አምላክ #ኢየሱስ ስንል እግዚእ ወአጋእዝት የጌቶች ጌታ #ኢየሱስ ስንል ንጉሠ ነገሥት የነገሥታት ንጉሥ #ኢየሱስ ስንል አልፋና ኦሜጋ መጀመሪያና እና መጨረሻ የሌለዉ ፊተኛዉና ኋለኛው ማለታችን ነዉ
👉 #ኢየሱስ ስንል ንጉሠ ሰማይ ወምድር የሰማይና የምድር ንጉሥ #ኢየሱስ ስንል ኤልሻዳይ ኹሉን ቻይ
👉 #ኢየሱስ ስንል መድኃኔዓለም #ኢየሱስ ስንል ወልደ አብ ወልደ ማርያም የአብ ልጅ የማርያም ልጅ በተዋሕዶ ልደት የከበረ
👉 #ኢየሱስ ስንል ፈጣሬ ኩሉ ኹሉን የፈጠረ #ኢየሱስ ስንል #እግዚአብሔር ማለታችን ነው ስሙን ስንጠራ ይኽ ሁሉ በልባችን ሰሌዳ ተፅፎ ነዉ
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በምህረቱ አይኑ ይጎብኘን "አሜን"
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
👉 #ቁስቋም እናታችን ማርያም ርጉም በሆነ በሔሮድስ ዘመን ከእርሱ ጋር ከሀገር ወደ ሀገር ስትሸሺ ካንቺ ጋራ መሰደዱን አሳስቢ
👉 #እናታችን_ማርያም ከአይኖችሽ የፈሰሰዉንና በተወደደ ልጅሽ ፊት የወረደዉን መሪር እንባ አሳስቢ
👉 #እናታችን_ማርያም ረኃቡንና ጥሙን ችግሩንና ሀዘኑን ከርሱ ጋር የደረሰብሽንም ጭንቅ ሁሉ አሳስቢ
👉 #እናታችን_ማርያም ጥፋትን ያይደለ ይቅርታን አሳስቢ መአትን ያይደለ ምህረትን አሳስቢ
👉 #እናታችን_ማርያም ለፃድቃን ያይደለ ለኃጥአን አሳስቢ ለንፁሃን ያይደለ ለተዳደፉት አሳስቢ
👉እናታችን #ቁስቋም_ማርያም በመከራ ያለችዉን የርስት ሀገርሽን #ኢትዮጲያን ልጅሽ መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በቸርነቱ ይመለከታት ዘንድ ለምኝልን
👉በስደት የመታሠቢያ በአሏ የምናስባት እናታችን ወላዲተ ቃል #ቁስቋም #ድንግል_ማርያም በምልጃ ፀሎቷ ሁላችንንም ታስበን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
☎️ስልኩን ስትነኩት የሚወስዳችሁ ቻናል ለህይወታችሁ ጠቃሚ ስለሆነ ስልኩን ይጫኑ
/Start
╭━━━━━━━╮
┃ ● ══ ▪
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃ 🔘 ┃
╰━━━━━━━╯
[ #አቡቀለምሲስ_ዮሐንስ_ወንጌሉ_ዘወርቅ ]
♥[ #ቦአኔርጌስ ] [#ገፁ_ዘንስር_ዘንስረ_ሰራሪ]♥
የተወደደ የጌታ ልዩ ደቀ መዝሙር ዮሐንስ አቡቀለምሲስ ቁጥሩ ከ "12"ቱ ሐዋሪያት መካከል ነው! ባለ ራዕይ የተባለው ይህም ታኦሎጎስ: እድገቱ በገሊላ ሲሆን የመስቀሉ ስር ድንቅ ሐዋሪያ ተብሏል! በንስር ገፅ ንስረ ሰራሪም ይባላል! ወልደ ዘብዴዎስ ወላጆቹ አባቱ ዘብዴዎስ እናቱ ደግሞ ማርያም ባውፍሊያ ትባላለቸች! ያእቆብ እና ዮሳዕ፣ ስምኦን የሚባሉ ወንድሞችም አሉት! የምስጢር ባለቤት: ፍቁረ እግዚእ ይሉታል: ነባቤ መለኮት የፍጥሞ ደሴት ፀኃፊ: ያልሞተ ሞትን ያላየ: ከሄኖክ ከኤሊያስ ጋር አንድነት የሚኖር: ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ቦአኔርጌስ ጥር "4" ቀን አመታዊ የፍልሰቱ መታሰቢያው ሲሆን፣ ወሩ በገባ በዚህ ዕለትም ታስቦ ይውላል!!
[ #ቦአኔርጌስ ] የነጎድጓድ ልጅ ማለት ነው//
[ #ይቆይ// ]
ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ❤️ እንዲህ ያስተምረናል
+++ ለራስህ ነው +++
👉አንተ ሰው! ቊጥር የሌላቸው ክፋቶች ቢኖሩብህም እንኳ በጎ ምግባር በልጅህ ይኖር ዘንድ በማድረግ አካክሰው፡፡
👉 ለክርስቶስ የሚኾን ተሽቀዳዳሚ (ሯጭ) አሳድግ! ወዳጄ ሆይ! እንደዚህ ብዬ ስነግርህ አትፍራ፤ አትሸበርም፡፡
👉ልጅህ እንዳያገባ አድርገው አላልኩህም፡፡ ወደ ገዳም ወስደህ እንድታመነኩሰው ወይም የብሕትውና ሕይወትን እንዲመራ አድርገው አላልኩህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ይህን አይደለም፡፡
👉 ልጅህ ቢመነኩስ እወድ ነበር፡፡ ብዙዎች ወደዚህ ሕይወት እንዲገቡ የዘወትር ጸሎቴ ነውና፡፡ ነገር ግን የምንኵስና ሕይወት [ሳይጠሩ ከገቡበት] ከባድ ሸክም ስለ ኾነ ሰዎች መነኰሳት ካልኾኑ ብዬ ግድ አልልም፡፡
👉ለአንተም እንደዚህ በግድ አመንኩሰው አልልህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ለክርስቶስ የሚኾን ተሸቀዳዳሚ አሳድግ ነው፡፡ በዚህ ዓለም አግብቶ፣ ልጆችንም ወልዶ የሚኖር ቢኾንም እንኳን ገና ከሕፃንነቱ አንሥቶ ሰውን የሚያከብር እንዲኾን አድርገህ አሳድገው ነው፡፡
👉ገና ጨቅላ እያለ በጎ በጎ ትእዛዛት በሕሊናው ጓዳ በልቡናው ሰሌዳ ላይ ከተቀረጸ፥ በሰም እንደ ታተመ ጸንቶ ይኖራል እንጂ ሲያድግ እነዚህን ትእዛዛት ሊያጠፋበትና ሊፍቅበት የሚችል ማንም አይኖርምና፡፡
👉 ልጅህ አሁን ያለበት ዕድሜ ደግሞ በሚያየውና በሚነገረው በሌላም ነገር ኹሉ የሚንቀጠቀጥበት፣ የሚፈራበትና የሚደነግጥበት ዕድሜ ነው፡፡ ስለዚህ ልክ እንዳልደረቀ ሰም እንደምትፈልገው አድርገህ ቅረጸው፡፡
👉እንደዚህ አድርገህ ስታበቃ፥ መልካም ልጅ ቢኖርህ የመጀመሪያው ተጠቃሚ የምትኾነው አንተው ራስህ ነህ፡፡ እግዚአብሔር የሚጠቀመው ከአንተ በኋላ ነው፡፡ ስለዚህ የምትደክመው ለሌላ አካል ሳይኾን ለራስህ ነው፡፡
እመብርሃን ኾይ❤️
👉የኢዮብ ደመናው፣ የጌዴዎን፣ ግምጃው የሳሙኤል የዘይት ቀንዱ የምድር ገሥታት ሁሉ በአንቺ የነገሡብሽ ማርያም ሆይ ነይ።
👉 ዳዊት ያመሰገነሽ፣ ሰሎሞንም መልካሟ ርግብ ሆይ የአንቺ መንገድ የተቆለፈች ተክል፣ የተዘጋች ጉድጓድ እያለ የዘመረልሽ ማርያም ሆይ ነይ።
👉እኅቴ ሙሽራ ሆይ ከሊባኖስ ነይ። በዐይኖችሽ ፈጽመሽ አሳዘንሽኝ። መልካማየ ሆይ ከሳኔርና፣ ከኤርሞን ነይ።
👉ዳግመኛም ከሰማይ ጠፈር እንዳለ ደመና ከምድር በዳ የተገኘች የጢሷ መዓዛም ያማረላት፡ እንደሚያበራ የአጥቢያ ኮከብ ፣ የምታሸበርቅ፣ እንደ ፀሐይና እንደ ጨረታም የምታበራ ይህቺ ማን ናት አለ።
👉ሱላማጢስ ሆይ ተመለሽ፣ ተመለሽ። በአንቺም ሰላምን እንመልከት። ስለ ሱላማጢስ ምን ትመለከታላችሁ? ከሩቅ እንደምታበራ የማኅበር ጸሎት ናት። የአሚናዳብ ልጅ /
የእመቤታችን/ አካሄድም ያማረ ነው።
👉 እኅቴ ሙሽራ ሆይ እነሆ የተዋብሽ ነሽ። ሁለቱ ጡቶችሽ ከወይን ይልቅ ያምራሉ። ፍቅርሽም የጸና ነው። ሆድሽም ስንዴ
👉የተጨመረበት በአበባም የታጠረ ነው። የአፍሽ መዓዛም ክሽቶዎች ሁሉ እንደሚሽት እንደ እንኮይ ነው። ይኸውም የሕያው
👉እግዚአብሔር ልጅ የማሕፀንሽ ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱም የቅዱሳን ክብራቸው የሌዋውያኑ የክህነታቸው መዓዛ፣
👉ለተመረጠ እስራኤል ልጆችም የንግሥናቸው ቅባት ለተራቡ ስታይ ከሚከተለው ከጥፋት ሞት በአንቺ ለዳኑ የወንጌል ልጆች
/ክርስቲያኖችም/ የቁርባናቸው መዓዛ ነው።
👉 ማርያም ሆይ የእግዚኣብሔር ሀገር ሆይ ስለ አንቺ የሚነገረው ነገር ድንቅ ነው። እግዚአብሔር ማደሪያው ትሆን ዘንድፈጽሞ ጽዮንን መርጧታልና። የዘለዓለም መኖርያየ /ቤቴም/ ይህቺ ናት። መርጫታለሁና በእርሷ አድራለሁ ልዑል
👉እግዚአብሔር ማደሪያውን ቀደሰ እያልሁ በማመሰግንሽ ጊዜም ከዘማሪው ዳዊት ጋር ነይ። በዚህ ንጹሕ በሆነው በልጅሽ ሥጋ
ከሥጋና ከነፍስ ርኩሰት እኛ እንቀደስ ዘንድ በዚህ ምስጢራዊ ማዕድ እኛ በምንሠዋው በዚህ በተወዳጁ ልጅሽ ደምም እንነጻ
ዘንድ
***ከቤት ወጥታ ተወልዳ ወደ ቤት መለሰችን***
እመቤታችን መልካም ነገር ማስገኘት በተሳናት ወይም በመከነች ዓለም ውስጥ የተገኘች ብቸኛ መልካም ፍጥረት መሆኗን ለማመልከት ለዘመናት በመካንነት ከኖሩ ባለትዳሮች እንድትወለድ አደረገ። እመቤታችን የሁሉ ፍጥረት እናት ነችና ከኢያቄም ከሀና ጎጆ ወጥታ የሁሉ ወደሆነው ተራራ እንድትሄድ መንፈስ ቅዱስ አደረገ።አንድም ኢያቄም የሠራው ዳስ ሳይሆን የሚገባት መላዕክት የሚሰሩት ዳስ ነውና ኢያቄም ከሰራው ዳስ ወጥታ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ክንፋቸውን ዘርግተው በሠሩት ረቂቅ ዳስ ተወለደች።እርሷ ከዓለም አይደለችምና በመወለዷ ቤት ውስጥ የነበሩት ሥጋዊ ደስታ እንዳያደርጉ በመንፈሳውያን መላዕክት ታጅባ ከቤት ወጣች።አንድም ከቤት ወጥቶ ሕገ እግዚአብሔርን ስቶ የነበረ አዳምን የሚፈልግ ጌታ እናቱ ነችና ከቤት ወጥታ ቀድሞ አባቶች እርሷን በራዕይ ወዳዩባት ቦታ ወደ ሊባኖስ ተራራ ሄደች። እመቤታችን ከዚህ ዓለም ጣዕም ምንም ተሳትፎ የሌላት ዓለማዊ ምኞት ያልደረሰባት ፍጽምት መናኝ ሆና የምትኖር እንደሆነች በልደቷ ሊያስተምረን እግዚአብሔር ከሰው ገለል ባለ ተራራ እንድትወለድ አደረገ።አንድም ልጇ ከቤት ወጥቶ በከብቶች (በዕብራውያን የከብት በረት ከውጭ ነው)በረት ለመወለዱ ማሳያ እንዲሆን አስቀድሞ እመቤታችን ከከተማ ውጭ ተወለደች።ከቤት ወጥታ ተወልዳ ወደ ቤት የመለሰችን የድንግል ማርያም ምልጃዋ አይለየን።
የደስታ እናት ልደት
እመቤቴ ሆይ የልደትሽን ምሥጢር ሳስብ ኅሊናዬን ሐሳብ ይከዳዋል፤ አንደበቴም መናገር ይሳነዋል። የምስጋናን ዘውድ የደፋ ዳዊት "ምድር ፍሬዋን ትሰጣለች፤ አምላካችን እግዚአብሔርም ይባርከናል" ብሎ የተናገረው ባንቺ እውነት ሆነ። ምድር ሰውነታችን (የሰው ዘር) አንቺን በቅድስት ሐና በኩል ስላስገኘ፤ እግዚአብሔር በበረከት መንፈሳዊት ባረከን፤ ቀድሞ የተረገምን ሆነን ሳለ። ከእግዚአብሔር ዘንድ በረከትን መቀበል የሚወድ ሁሉ አስቀድሞ የከበረውን (ንጹሑን) ስጦታ ለእግዚአብሔር ያቀርባል። እግዚአብሔርም በብዙ ዕጥፍ የሚሆን በረከትን ያድለዋል። ቀድሞ ያቀረብናቸው ስጦዎች ብዙ ዕጥፍ (ዘለዓለማዊ) በረከትን አላሰጡንም። ነገር ግን አንቺን ወደ እግዚአብሔር ስናቀርብ፤ እግዚአብሔርም የዘለዓለም ሕይወት የሚሆን ልጁ ክርስቶስን ሰጠን። ሐና እና ኢያቄም እመቤታችንን ሲያገኙ ደስታ ሆነላቸው። ቢሆንም ያለ ስስት እርሷን የተሰጠቻቸውን አንዲቷን መልሰው ለእግዚአብሔር ሰጡ። ልዑል እግዚአብሔርም የአንድያ ልጁ እናት አደረጋት። በልጁ አካል ለሆኑ ሁሉም እናት ሆነች። በዚህም ቀድሞ የወላጆቿ ደስታ የሆነች እርሷ፤ ኋላ እግዚአብሔርን ደስ አሰኘች፤ ለሕዝቡም ሁሉ ደስታ ሆነች። ደስታ ክርስቶስ ከእርሷ ተወለደ። የመንፈስ ቅዱስ ደስታ ሁልጊዜ ከእርሷ ጋር ነውና፤ መልአኩን ሰምተን "ተፈሥሒ ፍሥሕት፡ ደስተኛይቱ ሆይ ደስ ይበልሽ" እንላታለን። ከኀጢአት ኀዘን ልታወጣን የደስታ እናቱ ዛሬ ተወለደች። ዘለዓለማዊውን ደስታ በሥጋ ልታሳየን የደስታ እናት ዛሬ ተወለደች። ደስተኛ (ፍሡሕ) ገብርኤል በፍጹም ደስታ የሰውን መዳን ያበሠራት ድንግል ዛሬ ተወለደች። ሞትን በትንሣኤው ያሸነፈው ሕይወት የሚወለድባት ድንግል ዛሬ ተወለደች። ሰው በእግዚአብሔር ፊት ያቀረበው የከበረ (እንከን የሌለበት) ስጦታ ንጽሕት ድንግል ናት። እኛ በሰውነታችን የተዳደፍን ነን፤ ጻድቃንም በንስሐ ደናግል ናቸው፤ እመቤታችን ግን በድንግልናም ንጽሕት ናት እኮን! የእግዚአብሔር ቸርነቱ፤ ሰውንም መውደዱ ድንቅ ነው። ሥጋን ሊለብስ፤ አስቀድሞ ንጹሕ ሥጋን አዘጋጀ። ምስጋናን የሚያውቅ ዳዊት "ሥጋከ አንጽሕ ሊተ፤ ሥጋሕን ንጹሕ አድርግልኝ" እንዳለ። በእርሷ በረከት የመንፈስ ቅዱስን ደስታ ይስጠን። አሜን!
* "ቆምኪ ርእየትኪ ወክሳድኪ ከመ አርማስቆስ፡ እኅትነ ይብልዋ መላእክት በሰማያት፡ ስብሕት በሐዋርያት፡ ኢያቄም ወለዳ፡ ደብተራ ዘትዕይንት፡ ጥዕምት በቃላ ወሠናይት በምግባራ፡ እግዝእትነ ማርያም" (የግንቦት ልደታ ዋዜማ)
ሚያዚያ 30/2016 #ቅዱስ_ማርቆስ_ሐዋርያ (አልአዛር)
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን በትንሣኤው ላከበረን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይሁንና ሚያዚያ ሠላሳ በዚች ቀን ለእስክንድርያ ሊቃነ ጳጳሳት አለቃ የሆነ ለኢትዮጲያና ለግብፅ አባታቸው ቅዱስ ወንጌልን የፃፈ ሐዋርያው #ቅዱስ_ማርቆስ በሰማዕትነት አረፈ
👉ለሐዋርያዉ ለወንጌላዊዉ #ለቅዱስ_ማርቆስ አመታዊ የእረፍት በአል መታሠቢያ እንኳን አደረሰን
👉የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አርስጦቡሎስ ነው እርሱም ከአምስቱ አገሮች የሆነ የእናቱም ስም ማርያም ነው እርሷም #በሐዋርያት_ሥራ መጽሐፍ ተጽፋለች እርሱም አስቀድሞ ስሙ ዮሐንስ ነው በግብረ ሐዋርያት ማርቆስ በተባለ በዮሐንስ እናት ቤት ሐዋርያት ይጸልዩ ነበር ተብሎ እንደ ተጻፈ እርሷም ባለጸጋ ነበረችና የዮናናውያንን የሮማይስጥን የዕብራይስጥን ትምህርት ለልጅዋ ለማርቆስ አስተማረችው
👉በአደገም ጊዜ በርናባስ ወንጌልን ለመስበክ ከጳውሎስ ጋራ ሲሔድ ይዞት ሔደ በእነርሱም ላይ የሚደርስባቸውን #መከራ አይቶ በጵንፍልያ ከተማ ሳሉ ትቷቸው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ
👉ሐዋርያትም በተመለሱ ጊዜ የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን ወደ ማመን አሕዛብ እንደ ተመለሱ እግዚአብሔርም በእጆቻቸው ላይ ድንቅ ተአምራትን እንዳደረገ ተናገሩ ይህ ብላቴና ማርቆስም ከእርሳቸው ስለ መለየቱ አዘነ ተጸጸተ
👉ከዚያም አብሮአቸው ሊሔድ ፈለገ አስቀድሞ ትቷቸው ስለተመለሰ ጳውሎስ ሊአስከትለው አልወደደም በርናባስ ግን ወሰደው አጎቱ ነውና በርናባስም ከአረፈ በኋላ ወደ ሮሜ አገር ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ሒዶ ለእርሱ ደቀ መዝሙሩ ሆነ በዚያም ቅዱስ ጴጥሮስ የተረጐመለትን #ወንጌልን ፃፈ
👉በሮሜ አገርም አስተማረበት ከዚያም በክብር ባለቤት #በጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ትእዛዝና በሐዋርያትም ትእዛዝ ወደ እስክንድርያ አገር ሔደ በውስጥዋም የከበረ ወንጌልን አስተማረ ደግሞም በአፍራቅያና በአምስቱ አገሮች በርቃ በሚባልም አገር ወደ እስክንድርያ ከተማ በገባ ጊዜ ጫማው ተቆረጠ
👉በዚያም በከተማው መግቢያ ጫማ ሰፊ ነበረ ቅዱስ ማርቆስም እንዲሰፋለት ለርሱ ሰጠው ሲሰፋም ጣቱን ወግቶ ሰነጠቀው ከእርሱም ደም ፈሰሰ በዮናኒም ቋንቋ ኢታስታዖስ አለ ትርጓሜውም #አንድ_እግዚአብሔር ማለት ነው ቅዱስ ማርቆስም ስሙን የምትጠራው አውቀኸው ነውን አለው እንጠራዋለን እንጂ አናውቀውም አለ
👉እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ከፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ አባታችን አዳም ትእዛዙን እንደተላለፈ የጥፋት ውኃም እንደ መጣ ሙሴንም እንደላከውና እስራኤልን ከግብጽ እንዳወጣቸው ሕግንም እንደ ሠራላቸው ናቡከደነጾርም ወደ ባቢሎን ማርኮ እንደወሰዳቸውና ከሰባ ዓመት በኋላ ወደ አገራቸው ኢየሩሳሌም እንደ ተመለሱ #ክርስቶስ_ሥጋ በመልበስ ወደ ዓለም ስለ መምጣቱ ነቢያት ትንቢት እንደ ተናገሩ ያስተምረው ዘንድ ጀመረ
👉ከዚያም በኋላ ወደ ምድር ምራቁን ትፍ ብሎ ጭቃ አድርጎ ጣቱን ቀባው ወዲያው ዳነ በጌታችንም አመነ ያም ሰፊ ስሙ አንያኖስ ነው ቅዱስ ማርቆስንም ወደ ቤቱ ወስዶ ልጆቹን ዘመዶቹንም ወደ ርሱ አቀረበ እርሱም አስተምሮ አንድ አምላክ በሆነ #በአብ_በወልድ_በመንፈስ_ቅዱስ ስም የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው
👉በክብር ባለቤት በጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ያመኑ ሰዎች በበዙ ጊዜ የቅዱስ ማርቆስን ዜና ሰምተው የአገር ሰዎች ሊገድሉት ተሰበሰቡ እርሱም አንያኖስን ኤጲስቆጶስ አድርጎ ሹሞ ልጆቹን ቄሶችና ዲያቆኖች አድርጎ ከዚያም ወደ በርቃ ወደ አምስቱ አገሮችም ወጥቶ አስተማረ በቀናች ሃይማኖትም አጸናቸው በእርሳቸውም ዘንድ ሁለት ዓመት ኖረ ኤጲስ ቆጶሳትን ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ሾመላቸው
👉ከዚህም በኋላ ወደ #እስክንድርያ ተመለሰ ምእመናንም ተጨምረው በዝተው በታወቁ ቦታዎች ሁሉ በባሕሩም ዳር በላሞች መካበቢያ በሚባለውም አብያተ ክርስቲያን ሠርተው አገኛቸው።
👉ከሀድያንም የከበረ ሐዋርያን ይገድሉት ዘንድ በብዙ ድካም ፈለጉት እርሱም አምስቱን አገሮች ሲጐበኝ በሥውር ወደ እስክንድርያ ከተማ ይገባ ይወጣ ነበር በአንዲትም ዓመትም ከአምስቱ አገሮች ተመልሶ ሚያዝያ ዐሥራ ሰባት ቀን በመድኃኒታችን #የትንሣኤ_በዓል ወደ ቤተክርስቲያን ገባ
👉ሕዝቡም ሁሉ በዙሪያው አሉ ከሀድያንም ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተው በአንገቱ ውስጥ ገመዶችን አድርገው በከተማው ሁሉ ጎተቱት እነርሱም ገና እንደፍየል ሙክት እንጎትተዋለን እያሉ ይጮኹ ነበር በላሞች መካበቢያና በሀገሪቱ አደባባይ በከተማውም ዙሪያ በየቀኑ ሲጎትቱት ኖሩ
👉ሌሊትም በሆነ ጊዜ ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከሐዋርያት ጋራ በነበረበት አርአያ ሁኖ ተገለጠለት ሰላምታም ሰጥቶ አጽናናው ቃል ኪዳንም ሰጠው እነሆ አንተ ከወንድሞችህ ሐዋርያት ጋር ተካከልህ አለው እርሱም በልቡናው ፈጽሞ ደስ አለው በማግሥቱም ሁለተኛ ገመዶችን በአንገቱ አድርገው በአገሮች ሁሉ ጎተቱት በቀኑም መጨረሻ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ
👉ከሀዲዎችም ታላቅ እሳትን አንድደው የቅዱስ ማርቆስን ሥጋ ከውስጡ ጨመሩ በክብር ባለቤት ጌታችን ፈቃድም ንውጽውጽታ ጨለማ ቀዝቃዛ ነፋስ መብረቅና ነጐድጓድ ሆነ ፀሐይም ጨለመ ከሀዲዎችም ሸሹ ምእመናንም መጥተው #የቅዱስ_ማርቆስን ሥጋ ወሰዱ ምንም ጥፋት ሳይደርስበት ደኀና ሆኖ አገኙት በመልካም ልብስም ገንዘው በጥሩ ቦታ አኖሩት መታሰቢያውንም አደረጉ
👉በዚህ እለት ትንሳኤና ሕይወት የሆነው ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ አልዓዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት እራስ የመቃብርን እራስ ያጠፋ ትንሳኤ በድልም ያረገ ንጉስ መሆኑን እንመሰክራለን
👉ምስጋናና ክብር ሞቶ ላዳነን በትንሣኤዉ ለአከበረን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን #ለኢየሱስ_ክርስቶስ ይሁን የሐዋርያዉ #የቅዱስ_ማርቆስን ረድኤትና በረከት ያሣድርብን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
. እግዚአብሔር ይፈትሖሙ ለሙቁሓን!
እግዚአብሔር ያጠብቦሙ ለዕውራን!
እግዚአብሔር ያፈቅሮሙ ለጻድቃን!
እግዚአብሔር የዐቅቦሙ ለፈላሲያን!
እግዚአብሔር ያንሥኦሙ ለየዋሃን!
እግዚአብሔር ይነግሥ ለዓለም ዓለም!
با فیلترشکن نت ملی
یک بار برای همیشه از شر فیلترینگ خلاص شو
دانلود از گوگل پلی
https://play.google.com/store/apps/details?id=de.manvpn.app
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
አመ ፲፩ ለግንቦት በዓለ ቅዱስ ያሬድ ዋዜማ
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ዋዜማ፦
ሃሌ ሉያ
ንዑ ንትፈሣሕ በመኃልይሁ፤ ወንንግር ለካህን ውዳሴሁ፤ ከመ ሱራፌል ለያሬድ ክላሁ፤ ለክርስቶስ ሰበከ ትንሣኤሁ: ማኅበረነ፤ ይባርክ በእዴሁ።
@esate_yarade
አመላለስ፦
ማኅበረነ ይባርክ በእዴሁ/2/
ማኅበረነ ይባርክ በእዴሁ/4/
@esate_yarade
@esate_yarade
ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ፦
ያሬድ ጸሊ በእንቲአነ ጸሎትከ ወትረ ይብጽሐነ ያሬድ ጸሊ በእንቲአነ።
@esate_yarade
@esate_yarade
እግዚአብሔር ነግሠ፦
ያሬድ ማኅሌታይ ለእግዚአብሔር ካህኑ፤ ስብሐተ ትንሣኤሁ ዘይዜኑ፤ ኦሪት ቶታኑ ወወንጌል አሣዕኑ፤ ትርድአነ ነዓ በህየ መካኑ፤ ከመ ፀበል ግሁሣነ ፀርነ ይኩኑ።
@esate_yarade
ይትባረክ፦
ለእለሰ ይዌድሱ ትንሣኤሁ ወይቄድሱ ያሬድ ካህን ምስሌሆሙ ያንሶሱ።
@esate_yarade
@esate_yarade
ሰላም፦
ሃሌ ሃሌ ሉያ
አንበሳ ዘሞዓ ፍጹም ውእቱ እምሥርወ ዳዊት ወፈትሐ መጽሐፈ ትምህርት ያሬድ የኃሊ ትንሣኤሁ ወለብሰ ሰላመ ዚአሁ።
@esate_yarade
@esate_yarade
አመላለስ፦
ያሬድ የኃሊ ትንሣኤሁ የኃሊ ትንሣኤሁ/2/
ወለብሰ ሰላመ ዚአሁ/4/
🇪🇹👇👇👇👇👇👇🇪🇹
👉 @esate_yarade👈
👉 @esate_yarade👈
👉 @esate_yarade👈
🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹
@esate_yarade
# Join & share #
🚶♂️እንኳን ደህና መጡ ወደ Maki Online Market
👟 💯% ኦሪጅናል ጨማዎች በፍሬ እና በደርዘን እናቀርባለን
📍 Addis Abeba 🇪🇹 Maki Online Market የገበያ ማእከል
👉 📲 0965035951
👉 📲 0965035951
ያሉበት እናመጣለን
ይደውሉ
#ለማንኛውም_አሥተያየት 📩 @Makiteda
👉 /channel/+8YcU2tWaxyxjMzQ0
ጥበበኛው ሰሎሞን❤️ ሲራ 7 ላይ እንዲህ ያስተምረናል
👉 ኃጢአትን አትሥራት መከራ አያገኝህም፡፡
👉 ከበደል ራቅ እሷም ካንተ ትርቃለች፡፡
👉 ፍዳን ሰባት እጥፍ አድርገህ እንዳትቀበላት በሰውነትህ ኃጢአት አትሥራ፡፡
👉 ከእግዚአብሔር መንግሥትን አትለምን ከንጉሥም ክብር ያለው ሹመት አትለምን፡፡
👉 በእግዚአብሔር ዘንድ ጻድቅ ነኝ አትበል በንጉሥም ዘንድ ብልህ ነኝ አትበል፡፡
👉 ዳኛ መሆንን አትውደድ እነሆ እግዚአብሔርን የበደለ ለመበቀል አትችልምይሆናል እነሆ ለባለጸጋም ታደላ ይሆናል በእውነት ሥራህም ላይ ኃጢአት ትሠራለህ ።
👉 ያገርህንም ሰው አትበድል ራስህንም በወገኖችህ መካከል አታስት፡፡
👉 በአንዲቱምቅጣት አታመልጥምና ሁለት ኃጢአት አንድ አድርገህ አትሥራ፡፡
👉 በመባዬ ብዛት እግዚአብሔር ኃጢአቴን ያስተሠርይልኛል መባም ከገባሁ
👉 እግዚአብሔር ይቅር ይለኛል አትበል፡፡
👉 በጸልይህ ጊዜ አትቸኩል ምጽዋትን መመጽወትንም አታቃል፡፡
👉 የሚያሳዝን ደስ የሚያሰኝም አለና ባዘነ ሰው አትሳቅ፡፡
👉በባልንጀራህ ሀሰትን ተግባር አታድርግ በወዳጅህና ባባልንጀራህም ላይ እንዲህ አታድርግ፡፡
👉ፍጻሜዋ ይጐዳሃልና በምንም በምንም ሁልጊዜ አሰትን አትውደድ
👉በሽማግሌዎች መካከል አትጥቀስ ባንደበትህ የተናገርኸውን ስለትህን አትለውጥ ቃልህንም አትለውጥ
👉 የእጅህን ሥራ ፈጣሪህም የሚያበቅልልህን ቡቃያህን ቸል አትበል፡፡
👉 ብዙ ናቸው ብለህ ከኃጢአተኞች ሰዎች ጋራ አንድ እትሁን፡፡
👉 እየነጋ ወዳጅ አትለወጥ ቀይ ወርቅ ወደህ ወዳጅህን አትጣ፡፡
👉 መወደዷ ከወርቅ ይመረጣልና ብልህና ደግ የሆነች ሴትን አትጥላ፡፡
👉በእውነት ለሚገዛልህ ቤተሰብህ ስላንተ ሰውነቱን አሳልፎ ለሞት በሚሰጥ በምንደኛህም ላይ ከፉ ነገር አታድርግ፡፡
👉ብልህ ቤተሰብህን ከሰውነትህ ይልቅ ውደደው ነፃ ታወጣው ዘንድ ተስፋ ያደረገህ ዋጋውንም አታጥፋት፡፡
👉ሁልጊዜ ከብትህንም መፍቀድ አትተው ከነሳቸው የሚረባህንም አይተህ ለመሥዋዕት አቅርብ።
👉ልጆች ቢኖሩህ ምከራቸው ከሕፃንነታቸው ጀምረህ ትህትን
አስተምራቸው።
👉 ሴቶች ልጆችም ቢኖሩህ ጠብቃቸው አታስታቸው አትሣቅላቸው እታባብላቸው፡፡
ግንቦት 6/2016 #ቅድስት_አርሴማ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በሰማእቷ ስም ለምናመሰግንበት ለሰማእቷ #ቅድስት_አርሴማ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉እናታችን #ቅድስት_አርሴማ #እግዚአብሔርን በቅንነት ያገለግሉ ከነበሩ ከከበሩ ካህናት ወገን ከሆኑ ከቅዱስ ቴዎድሮስና ከእናቷ ቅድስት አትናሲያ በስዕለት ተወለደች
👉ሰማዕቷ #ቅድስት_አርሴማ ብሉይን ሐዲስን ተምራ እያነበበች እንዲሁም በተግባር እየተረጎመች ዘወትርም በፀሎት ትተጋ እንደነበር ገድሏ ይተርካል በዚህ ዘመን ድርጣድስ የሚባል በአርመን የነገሠ አረማዊ ንጉሥ ለጣዖት የሚሰግድ ፀሐይንም የሚያመልክ #ክርስቲያኖችንም እኔ ለማመልከው አምላክ መስገድ አለባችሁ በማለት መከራ ያጸናባቸው ነበር
👉እናታችን #ቅድስት_አርሴማም ተጋድሎዋን የጀመረችው የዚህ ጨካኝ ንጉሥ አገልጋይ ወይም ሹም ፳፯ ክርስቲያኖችን እንደልማዱ እየደበደበ እየገረፈና ልዩ ልዩ ስቃይ እያደረሰባቸው ሲወስዳቸው በማየቷ ነበር
👉ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ለእነርሱና ለአሕዛብ ምስክር እንዲሆን ስለኔ ወደገዢዎችና ወደ ነገሥታት ትወሰዳላችሁ ማቴ. ፲፡፲፮፡፲፱ ያለውን በማሰብ ቅድስት #አርሴማም ገና በሃያ ዓመቷ የዚህን ዓለም ንጉሥ እኩይ ግብሩን በመንቀፍ ስለ #ክርስቶስ ከሚሰቃዩ ወገኖቿ ጋር ግንባር ቀደም በመሆን ትመሰክር ጀመር
👉የንጉሡም አገልጋይ በደም ግባቷና በንግግሯ ማማር ተደንቆ በዚች በፈቃዷ #ልትሠዋ በወደደች ሴት ምንም ሊያደርግባት ስላልወደደ ወደ ንጉሡ ወደ ድርጣድስ ከሃያ ሰባቱ ክርስቲያኖች ጋር ወሰዳት ንጉሡም ብዙ የተነገረላትን ወጣት ሲያይ በውበቷና በንግግሯ ተማርኮ ለዓለማዊ ደስታውና ፍላጎቱ ተመኛት ፈለጋት ለእርሱም ሙሽራ እንድትሆን ብዙ ወተወታት
👉 #ቅድስት_አርሴማ ግን ናቀችው ‘እኔ የሰማያዊው ንጉሥ #የክርስቶስ ሙሽራ እንጂ የዚህን ዓለም አላፊ ጠፊ የሆነውን ገንዘብና ደስታ የምሻ አይደለሁም በማለትም መለሰችለት
ንጉሡም ይህንን ከእርሷ በመስማቱ እጅግ ተቆጣ በመናቁም ተበሳጨ አሽከሮቹንም ጠርቶ በቤተ መንግሥቱ የታሰሩትን አንበሶች እንዲለቀቅባቸው አዘዘ
👉አንበሶቹ ግን ይደሰቱ ነበር በኋላም ፊታቸውን ወደ ንጉሡና አገልጋዮቹ በማዞር ሩጠው እስኪደበቁ ድረስ አሳደዷቸው ንጉሡ ይበልጥ ነደደው #ክርስቲያኖቹ በረሃብ እንዲያልቁ እንዲታሰሩ አዘዘ #እግዚአብሔርም በአምስተኛው ቀን በብርሃን ቤቱን ሞልቶት የሚበሉትን በመሶብ የሚጠጡትን በጽዋ ከሰማይ አወረደላቸው
👉ንጉሡም ይህንን በማየቱ ከዚያ አውጥቶ በእሳት ውስጥም አስገባቸው #ሠለስቱ_ደቂቅን የጠበቀ አምላክ እነርሱንም አዳናቸው በሌላም በብዙ መንገድ ሊያጠፋቸው እንደሞከረ ገድሏ ይተርካል በመጨረሻም ከአማካሪዎቹ ጋር ተማክሮ በሰይፍ እንዲያልቁ ይወስናሉ
👉እያንዳንዳቸውን ተራ በተራ ሲሰይፋቸው #ቅድስት_አርሴማ ለሚሰይፉት ሁሉ #የድል_አክሊል ከሰማይ ሲወርድላቸው ትመለከት ስለነበር የእርሷን ተራ በጉጉት ትጠብቀው ነበር በመደሰቷም እየፀለየች አይዟችሁ ጽኑ ትላቸው ነበር
👉በመጨረሻም ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ፅናቷን ተመልክቶ #ቃል_ኪዳን ይገባላታል ንጉሡም ሌሎቹን አሰይፎ ሲያበቃ ወደሷ ዞሮ በቁጣ እየጮኸ አንቺን እንደ ባልንጀሮችሽ በቀላሉ አልገልሽም ስቃይሽን አጸናብሻለሁ ብሎ ለአገልጋዮቹ ትእዛዝ በመስጠት አይኗን አስወጥቶ በእጇ ያሲዛታል ጡቷን ያስቆርጣል በኋላም አንገቷን ያሰይፋታል በዚሁ ሁኔታ እናታችን #ቅድስት_አርሴማ ሰማዕትነትን ተቀበለች
👉ይህንን ሁሉ መከራ ስለአምላኳ ስትል እራሷን አሳልፋ የሰጠች ድንቅ ሰማዕት ናት ነቢዩ ዳዊት በመዝሙሩ ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ እንዳለ ለእናታችንም #ቃል_ኪዳን ገባላት
👉በእኔ ስም አምነሽ የዚህ ዓለም ተድላና ደስታ ሳያታልልሽ አንገትሽን ለሰይፍ ሰጥተሽ ተሰይፈሻል #የሰማዕትነት ተጋድሎ ፈጽመሻልና ስምሽን የጠራ በዓልሽን ያከበረ ዝክርሽን የዘከረ ገድልሽን የፃፈና ያፃፈ የሰማና ያሰማም እስከ 12 ትውልድ ድረስ እምርልሻለሁ’ ሲል #ቃል_ኪዳን ገብቶላታል
👉በዚህም መሠረት በሷ አማላጅነት አምኖ #ገዳሟም ሄዶ በፀሎት የተማጸናት ሁሉ ለችግሩ መፍትሄ አግኝቶ እንደሚመለስ እሙን ነው
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ የሰማእቷ #ቅድስት_አርሴማን ረድኤት በረከት ያሣድርብን ምልጃና ፀሎቷ ቃል ኪዳኗ ከእኛ ጋር ይሁን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ግንቦት 4/2016 #ዳግም_ትንሣኤ
#ወንጌላዊው_ዮሐንስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን በዚህ እለት ጌታችንና መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ #ዳግም_ትንሣኤዉን የገለፀበት ክብረ በአል ነዉ እንኳን አደረሰን
👉መድህን #ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ ታየ በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን በምሽት ደቀ መዛሙርቱ አይሁድን በመፍራት በሮቹን ቈልፈው ተሰብስበው ሳለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጣና በመካከላቸው ቆሞ #ሰላም_ለእናንተ_ይሁን
አላቸው
👉ይህንም ብሎ እጆቹንና ጎኑን አሳያቸው ደቀ መዛሙርቱም ጌታን ባዩት ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው ክርስቶስም እንደ ገና
#ሰላም_ለእናንተ_ይሁን ካለ በኋላም ደቀ መዛሙርቱን እፍ አለባቸውና እንዲህ አላቸው #መንፈስ_ቅዱስን ተቀበሉ የሰዎችን ኃጢአት ይቅር ብትሉ ኃጢአታቸው ይቅር ይባልላቸዋል ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ ግን ይቅር አይባልላቸውም
👉በዚህ ጊዜ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው ዲዲሞስ የተባለው ቶማስ #ኢየሱስ_ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር አልነበረም ሌሎች ደቀ መዛሙርትም ጌታን አየነው እኮ አሉት እርሱ ግን በምስማር የተቸነከሩትን የእጆቹን ምልክቶች ካላየሁ ምስማሮቹ በነበሩበት ቦታ ጣቴን ካላደረግሁ በጐኑም እጄን ካላስገባሁ አላምንም አለ
👉ከስምንት ቀን በኋላም ደቀ መዛሙርቱ በቤት ውስጥ ነበሩ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ነበር በሮቹ ተቈልፈው ነበር ኢየሱስ ክርስቶስ ግን መጥቶ በመካከላቸው ቆመና ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው ከዚያም ቶማስን #ጣትህን_ወደዚህ_አምጣ እጆቼንም ተመልከት እጅህን ዘርጋና በጎኔ አስገባ አትጠራጠር እመን አለው
👉ቶማስም #ጌታዬ_አምላኬም አለው ኢየሱስ ክርስቶስም አንተ ስላየኸኝ አምነሃል ሳያዩ የሚያምኑ ግን ብፁዓን ናቸው አለው ዮሐ 20;19-31
👉የትንሣኤዉ ጌታ #መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ስጋዉን ቆርሶ ደሙን አፍሶ በትንሣኤዉ ስላከበረን እናመሰግናለን የቅዱሳን ሐዋርያት በረከታቸው ለሁላችንም ይድረሰን "አሜን"
#ወንጌላዊው_ቅዱስ_ዮሐንስ
👉በመጀመሪያው ቃል ነበረ፣ቃልም #በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፣ቃልም #እግዚአብሔር ነበረ፣ቃልም ስጋ ሆነ ዮሐ1፥1-14
👉ወንጌላዊው #ቅዱስ_ዮሐንስ የተለያዩ ስሞች አሉት ከነዚህም ጥቂቶቹ
✝️ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ
✝️ ፍቁረ እግዚእ
✝️ ታኦሎጎስ
✝️ አቡቀለምሲስ
✝️ ቁጽረ ገፅ
✝️ ዮሐንስ ዘንስር
👉 #ቅዱስ_ዮሐንስ እመቤታችንን በአደራ የተቀበለ በአንድ ቤት ልጅ ሆኗት 15 ዓመት የኖረ ቅዱስ አባት ሐዋርያ ነዉ የአለሙን ገዢ ወልዳ ያሳደገች በፀጋ ተሞልታ ተቀድሳ የኖረች እናታችን ማርያምን በእናትነት የተቀበለ ወንጌላዊው #ቅዱስ_ዮሐንስ በረከቱ ምልጃው ፀሎቱ አይለየን የተባረከ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
"የብርሃናት ንጉሥ ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመውለድ ዛሬ የብርሃን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም በእውነት ተወለደች። ከሊባኖስ ተራሮች ርግብ ጸዐዳ ተወለደች፤ በሔዋን ምክንያት የተዘጋው የሕይወት መንገድ ይከፈትልን ዘንድ የሕይወት እናት ዛሬ ተወለደች፡፡ የዓለም ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን ከእርሷ ይወለድ ዘንድ እመብርሃን ዛሬ ተወለደች፡፡
ኢያቄምና ሐና ዳግሚት ሰማይ ተብላ የተጠራችውን ድንግልን ወለዱ፤ እውነተኛው ፀሐይ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ይወለድ ዘንድ እመ ፀሐይ (የፀሐይ እናት) ቅድስት ድንግል ዛሬ ተወለደች፤ ብርሃንን ለማስገኘት መወለድ መታደል ነው፤ ከሰው ልጆችም መካከል መመረጥ ዕፁብ ድንቅ ነው፤ የመድኃኔዓለም እናት ለመሆን መወለድ ሰማያዊ ፀጋ ነው።
በእውነት እመብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር ስጦታ ናት። ንጽሕተ ንጹሐን ቅድስተ ቅዱሳን እመብርሃን ዛሬ ተወልዳልናለችና ደስ ይበለን እልልም እንበል።"
የአለሙን ሁሉ መድኃኒት ለወለደች ለብርሃናት ጌታ እናት በቀራንዮ በመስቀሉ ስር እናት ትሆነን ዘንድ ለተሠጠችን ለመመኪያችን ዘውድ ለተወዳጇ ለቅድስተ ቅዱሳን ለድንግል ማርያም ልደት በዓል እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ።
ግንቦት ፩ ልደታ ለማርያም
እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ልደትሽ ልደታችን ነው !
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስተ ቅዱሳን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የልደት መታሰቢያ በሰላም አደረሰን
ከሊባኖስ ተራራ የተገኘሽ አደፍ ጉፍ የሌለብሽ ንጽህት ሙሽራ እመቤቴ ሆይ የኔንም እድፍ ጉድፍ በንጽህናሽ ጥረጊልኝ!! ንዒ እምሊባኖስ መርዓት ንዒ እምሊባኖስ ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ፥ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ ።መኃ 4.9
✞ሐዳፌ ነፍስ
፤ አሁንም ጸጋን የሰጠ አምላካችን እግዚአብሔርን እንለምነው ጸልዩ ።
፤ ድንግል ሆይ ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢ ።
፤ ድንግል ሆይ በቤተልሔም ካአንቺ የተወለደውን መውለድ በጨርቅ
የተጠቀለለውንም አድግና ላህም በብርድ ወራት እስትንፋስን ያሟሟቁትንም
አሳስቢ ።
፤ ድንግል ሆይ ርጉም በሆነ በሄሮድስ ዘመን ከርሱ ጋራ ካገር ወደ አገር
ስትሸሺ ካንቺ ጋራ መሰደዱን አሳስቢ ።
፤ ከዐይኖችሽ የፈሰሰውንና በተወደደው ልጅሽ ፊት የወረደውን መሪር ዕንባ
አሳስቢ ።
፤ ድንግል ሆይ ረኃብና ጥሙን ችግሩንና ኀዘኑን ከርሱ ጋራ የደረሰብሽን
ጭንቅ ሁሉ አሳስቢ ።
፤ ጥፋትን ያይደለ ይቅርታን አሳስቢ ።
፤ ለጻድቃን ያይደለ ለኃጣን አሳስቢ ለንጹሐን ያይደለ ለተዳደፉት አሳስቢ ።
፤ አሁንም አብና ወልድን መንፈስቅዱስንም እናመስግነው ለዘላለሙ አሜን።
ቅዳሴ ማርያም ✔️አባ ሕርያቆስ
ሰላም እንኳን ለግንቦት ልደታ በሰላም አደረሳቹ
ስለእመቤታችን ለልደቷ ዝማሬ ለቅቄአለው
በዶግማና ቀኖና ሚዲያ እየገባቹ ላዪክ ሰብስክራዪብ ሼር አርጉ
ሚያዚያ 29/2016 #ቅዱስ_በዐለ_ወልድ (ቅዱስ ቶማስ)
#ፅንሰት_ልደት_ትንሣኤ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን በዚህ ቀን እመቤታችን #ቅድስት_ድንግል_ማርያም የከበረ መልአክ የቅዱስ ገብርኤልን የምሥራች የሠማችበት አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ የተወለደበት የከበረዉን #ትንሣኤውን የገለጠበት ወርሐዊ መታሰቢያ ነዉ
👉እንዲሁም በዚህች ቀን #አለም_የተፈጠረበት የጌታችንን ዳግመኛ #ምፅአቱን የምንጠባበቅበት እለትም ጭምር ነዉ
👉በዚህች ቀን ለእመቤታችን ለቅድስት #ድንግል_ማርያም የከበረ #መልአክ_ገብርኤል_የምሥራች የነገረበት ድኅነትን የተመላች ታላቅ በዓል ናት በዚህም የከበረ ወንጌል ምስክር ሁኗል እንዲህ ሲል
👉ኤልሳቤጥ ከፀነሰች በኋላ በስድተኛው ወር #መልአኩ_ገብርኤል የገሊላ ክፍል የሆነች ናዝሬት ወደምትባል አገር ከዳዊት ወገን ለሆነ ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደታጨች ወደ አንዲት ድንግል #ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ
👉የድንግሊቱም ስም #ማርያም ነው መልአኩም ወደርሷ ገብቶ ደስተኛ የሆንሽ ደስ ይበልሽ ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው አንቺ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ አላት እርስዋም አይታ ከንግግሩ የተነሣ ደንግጣ እንዴት እንዲህ ያለ ሰላምታ ይቀበሏል ብላ አሰበች
👉መልአኩም እንዲህ አላት #ማርያም ሆይ #በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻልና አትፍሪ እነሆ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ስሙንም #ኢየሱስ ትይዋለሽ እርሱ ታላቅ ነው የልዑል #እግዚአብሔር ልጅም ይባላል
👉 #እግዚአብሔር አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል ለያዕቆብ ወገንም ለዘላለም ነግሦ ይኖራል ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም
👉ማርያምም መልአኩን ወንድ ሳላውቅ ይህ እንደምን ይሆናል አለችው መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት መንፈስ ቅዱስ መጥቶ ያድርብሻል የልዑል ኃይልም ያጸናሻል ከአንቺ የሚወለደው ከሶስቱ አካል አንዱ የልዑል #እግዚአብሔር ልጅ ይባላል
👉እነሆ ዘመድሽ ኤልሳቤጥም እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ፀንሳለች ወንድልጅም አገኘች ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና #ማርያምም እነሆኝ የእግዚአብሔር አገልጋይ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለችው።
👉ያን ጊዜም ድንግል ስትሆን ረቂቅ ፅንስን ተቀበለች የእግዚአብሔር አካላዊ ቃል #ወልድ_ዋህድ ለኩነተ ሥጋ ወርዶአልና ይህም አንድ ባሕርይ አንድ ህልውና ሲሆን ከሦስቱ አካላት አንዱ ነው
👉ከዓለም መፈጠር አስቀድሞ የነበረ በማይመረመር ድንቅ በሆነ ተዋሕዶ እንዴትም እንደሆነ በማይታወቅ #በቅድስት_ድንግል_ማርያም ማሕፀን አደረ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ተፀንሶ በህቱም ድንግልና ታህሣሥ ሀያ ዘጠኝ ቀን ተወለደ
👉በዚያን ጊዜም የኋላ ኋላ መለየት ከቶ የሌለውን ፍጹም ሰውነት ነሥቶ ተዋሐደ መለኮቱ ከትስብእቱ ጋራ ያለ መለያየት አንድ ሆኖአልና ይቺም ዕለት የበዓላት ሁሉ በኩር ናት በእርሷም #የዓለም_ድኅነት ተጀምሮዋልና
👉ዳግመኛ በዚህችም ዕለት ደግሞ በመድኃኒታችን በከበረችና ልዩ በሆነች #ትንሣኤው የዓለም ድኅነት ሆነ በረቀቀ ጥበቡ ሠላሳ ሦስት ዓመት ያህል በምድር ላይ ሥራውን ሠርቶ በፈጸመ ጊዜ በፈቃዱ ሕማማተ መስቀልን ተቀብሎ ሙቶ ከተቀበረ በኋላ በሦስተኛው በዚች ቀን #በሃያ_ዘጠኝ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቷልና
👉በዚች ቀን አስቀድሞ ደጅ ለሚጠኑት በዓለም ላሉ ሰዎች ሰው በመሆኑ ድኅነታቸውን አበሠራቸው እንዲሁም ደግሞ በዚች ዕለት ከሲኦል በመዳን #ሙታንና_ሕያዋን ደስ አላቸው
👉በዚህም በጌታችንና በመድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በሥጋ መነሣት መነሣታቸውን አረጋገጡ የከበረ ጳውሎስ በመነሣቱ ክርስቶስ የሙታን በኵር ሆነ እንዳለ እርሱ ለሙታን በኵራቸዉ ነዉና
👉በዚህ ቀን በጌታችኝ ትንሣኤ ሳምንት ማክሰኞ ሐዋርያዉ ቅዱስ ቶማስ ይታሠባል ይኸዉም #ቅዱስ_ቶማስ ጌታችንን አይቶ ማመኑን ጌታዬ አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል የሐዋርያው ረድኤት በረከት ለሁላችንም ይድረሰን
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከበአሉ በረከት ሁላችንንም ያሣትፈን ዳግም ሲመጣም ከቅዱሳኑ ጋር ይደምረን የምንሰማዉን የምናየዉን ክፉ ነገር ሁሉ ወደ በጎ ነገር ይቀይርልን
👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸዉ የምናስባቸዉ ፃድቁ አባታችን #አቡነ_እጨጌ_ዮሐንስ በምልጃ ፀሎታቸዉ ይጠብቁን "አሜን" ✝️💒✝️
በትንሣኤ በዓል እርድ መከናወን ያለበት መቼ ነው?
༺ ༻
✍ ብዙ ሰዎች የቀዳም ስዑር ምሽት በሬ፣ ዶሮ፣ በግ •• ወዘተ ያርዳሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ይህ እንዴት ይታያል? በማለት ጥያቄዎች በውስጥ መስመር ስጠየቅ ነበር። ዘመኑ በአመጣው በሕዋ አውታር መልስ መስጠት ተገቢ በመሆኑ መልስ ለመስጠት ተገድጃለሁ !ቅዱስ ጳውሎስ " #መብል ግን ወደ እግዚአብሔር አያቀርበንም፤ ባንበላም ምንም አይጎድለንም ብንበላም ምንም #አይተርፈንም"ይላል(፩ቆሮ ፰÷፰)
-በቀዳም ስዑር ምሽት ማረድ በልማድ ተያይዞ የመጣ እንጂ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያም ሆነ ትውፊቱ አይፈቅድም (አይደለም )።
-✍አንዳንዶች በቀዳም ስዑር ለምን እንደሚያርዱ ሲጠየቁ "#ለበዓሉ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ፣#ሌሊት ከቤተ ክርስቲያን አስቀድሰው ሲመለሱ ለመግደፍና ነዳያንን ለማስፈሰክ ነው" በማለት ይመልሳሉ።ወገኖቼ ምክንያት ከተጠያቂነት አያድንም ።
✍ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ግን ሲያትቱ የሚያስፈልጋቸው የሚባሉት በባሕርያቸው የሞቱ ለምንላቸው ምግቦች ነው። ማለትም እንጀራ ፣ዳቦ ወዘተ።ምክንያቱም እነዚህን ለማዘጋጀት ብዙ ጊዜ የሚፈልግ ነውና።እንሰሳት ግን ደመ ነፍስ ናቸው።እንሰሳትን ለማረድ ዝግጅት አይጠይቅም፣በፍጥነት የሚታረዱ ናቸው።
✍ ነዳያንን ለማስፈሰክ ለተባለውም ውኃ ለማያነሳ መልስ #ተንሥአ እሙታን ከሚባልበት ከመንፈቀ ሌሊት በኋላ ተሠርቶ የሚደርስ ነው።
-✍ ስለዚህ "ወተንሥአ እሙታን፣ከሙታን ተለይቶ ተነሣ " ተብሎ ሳይታወጅ መታረድ የለበትም።በቀዳም ስዑር ማረድ ዐዋጅ ሳይታወጅ ከማረዳችንም በላይ የትንሣኤን በዓል አላከበርንም እንደማለት ነው።
-✍ በቅዳሜ ምሽት" #በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ" ሳይባል ፣በመስቀል ሳይባረክ ማረድ ፣በዘመነ ኦሪት እንደ ታረደ (እንደ ተሠዋ) ነው የሚቆጠረው። ምክንያቱም "#ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ፣ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ " አልተባለምና።
-✍እንደ ሊቃውንቱ አገላለጽ ለሌሊት ከቅዳሴ መልስ በየቤታችን ልንመገባው የሚገባ ከጥሉላት ምግቦች ርቀን ከመቆየታችን አንጻር ጤንነታችን የማይጎዳ፣ ተልባ፣ በወተት በእርጎ ተደርጎ መበላት አለበት ። እርድ መፈጸም ያለበት ጠዋት ወይም ደግሞ "ወተንሥአ እሙታን " ከተባለበት ከሌሊቱ ፮ ሰዓት በኋላ ነው ።ያኔ መስቀል ይዞራልና።
✍አንዳንድ ሰዎች ሲናገሩ ቀዳም ስዑር ጾም መሆኑን እምናለሁ ።ነገር ግን ከምሽቱ ፲፩ (ከዋዜማው ) ጀምሮ ወደ ሚቀጥለው ቀን (እሑድ ) ስለሚቆጠር ማረድ ይቻላል ሲሉ ይደመጣሉ።ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሲመልሱ ፍትሐ ነገሥት በአንቀጸ ጾም ላይ " ክብርት በምትሆን በ40 ጾም በመጀመሪያ ው ሱባኤ እስከ ፲፪ ሰዓት ፣በሰሙነ ሕማማት፣ እስከ ፲፫ ሰዓት ከሌሊቱ ፩ ሰዓት ጨምሮ ወይም እስከ #ፀአተ ኮከብ ( ኮከብ ከሰማይ መልቶ እስኪታይ፣ )ጹሙ" ይላል።ቅዱሳት መጻሕፍትም ለጾም ማድላት እንዳለብን ይመክሩናል።
✍ ከምሽቱ ፲፩ ጀምሮ ወደ ሚቀጥለው ቀን (ወደ ማግስት ) ነው የሚቆጠረው የሚባለው ለምስጋና ሲሆን ነው። ጾም ግን ወዲያውኑ በተግባር (በድርጊት ) የሚፈጸም ነው። ወደ ማግሥቱ ይቆጠራል አንልም።ምክንያቱም #ጾም ተግባር ነውና።
✍. በቀዳም ስዑር ማረድ #የጾም ክፍል በኾነው ሰዓት ከማረዳችን በተጨማሪ የትንሣኤን ምሥራችን አይሰብክም። ምክንያቱም ጌታችን እስኪነሣ ድረስ በኅዘን ነው ያለነው።እንደ ሥርዓቱ ከሆነ ሲታረድ ካህኑ ቢላዋውን ይባርክለታል አራጁ ያርዳል።በገጠሪቱ ኢትዮጵያ #በዐቢይ ጾም እንኳን ሰው #ቢላዋ ታጥቦ ይጾም ነበር።
ቅዱስ ጳውሎስ "ነገር ግን ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን"ብሏል(፩ኛ ቆሮ ፲፬፥፵) ሚዛን የጠበቀ ውይይት ማከናወን ይቻላል ።
@ሐመር መጽሔት መጋቢት/ሚያዝያ 1996 ዓ.ም
★ ★ ★
“#ዘቦ ዕዝን ሰሚዐ ለይስማዕ (ማር.፬፥፱፣ማቴ፲፩፥፲፭፣)
★ ★ ★
☜ መ/ር ተመስገን ዘገዬ
ፈዋሴ ዱያን ጊዮርጊስ እምነ ከራድዮን ዖፍ ።ስምዐኒ ጸሎትየ ወስእለትየ ዘዘልፍ። #ኦ አምላከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዕቀበኒ ወአድኅነኒ እመከራ ሥጋ ወነፍስ ሊተ ለወልደ ሥላሴ !
━━━━━━━༺✞༻━━━━━