✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖
❖ ግንቦት 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+"+ አባ ዓቢየ እግዚእ +"+
❖ጐንደር ከተማ ነዋሪ ከሆኑ: ወይም ከተማዋን
የሚያውቁዋት ከሆነ አንድ ጥያቄ ልጠይቅዎ:: ከተማዋ
ውስጥ ጅብና እባብን
የመሠሉ አራዊት ነዋሪውን ሲገድሉ: ወይም ሲያቆስሉ
ተመልክተው: ካልሆነም በታሪክ ሰምተው ያውቃሉ?
<< መልስዎ "በጭራሽ አላውቅም" እንደሚሆን
እገምታለሁ:: >>
+ነገሬን እንዲረዱኝ ሌሎች የሃገራችን ዋና ዋና ከተሞችን
ልብ ይበሉልኝ:: እንኳን በሌሊት በቀንም አራዊቱ
አይጠፉባቸውም::
"ታዲያ ጐንደር ከተማ ውስጥ ጅብ የማይገባው: እባብና
ጊንጥ ሰው የማይገድለው ግን ለምን?" ካሉ በጻድቁ
በአባ ዓቢየ እግዚእ ቃል ኪዳን ምክንያት ነው:: (ሁሉም የሃገራችን
ከተሞች የተባረኩ መሆናቸውን ሳንዘነጋ ማለት ነው)
+ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
+አባ ዓቢየ እግዚእ የተወለዱት በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን
ትግራይ ተንቤን (መረታ) ውስጥ ነው:: የተባረኩ
ወላጆቻቸው ያፍቅረነ እግዚእና ጽርሐ ቅድሳት ይባላሉ:: አጥምቀው
'ዓቢየ እግዚእ' ሲሉ ስም ያወጡላቸው የወቅቱ ዻዻስ ሰላማ መተርጉመ
መጻሕፍት ናቸው:: ትርጉሙም "በጌታ ዘንድ ታላቅ ሰው"
ማለት ነው::
+ዓቢየ እግዚእ በሕጻንነታቸው ሌሊት ሌሊት ባሕር ውስጥ
ሰጥመው ሲጸልዩ አድረው ቀን ቀን እየተማሩ ብሉይ
ከሐዲስ ጠነቀቁ::
ገና በወጣትነታቸው ወደ ታላቁ መነኮስ አቡነ መድኃኒነ
እግዚእ ደብረ በንኮል ሔደው መንኩሰዋል::
+በገዳሙ በጾም: በጸሎትና በስግደት ተወስነው ከኖሩ
በኋላ ወደ ዋልድባ ሔደው የተሰወረች ቤተ ክርስቲያን
አግኝተዋል::
በጊዜው በ40 ቀን አንዲት ቅጠል ብቻ ለቁመተ ሥጋ
ይበሉ ነበር::
+ከዚያም ወደ ሃገራቸው ተንቤን ተመልሰው ዛሬም ድረስ
ድንቅ ሆኖ የሚታየውን ገዳም መሥርተው ብዙ መናንያንን
አፍርተዋል::
ዓቢየ እግዚእ ገዳማዊና ጻድቅ ብቻ ሳይሆን ሐዋርያዊ
አባትም ነበሩ:: ከትግራይ እስከ ደንቢያ ደግሞ ሃገረ
ስብከታቸው ነው::
+አንድ ጊዜ ደቀ መዛሙርትን አስከትለው ለስብከት
ሲንቀሳቀሱ ተከዜ ወንዝ አካባቢ ደረሱ:: ቀኑ ነሐሴ 10
ነውና ተከዜ
እስከ ገደፉ ሞልቶ ለ3 ቀናት ባለመጉደሉ ከ1,000 በላይ
ሰዎች ሲያለቅሱ ደረሱ:: ጻድቁ ባካባቢው የነበሩት ኢ-
አማንያን (አሕዛብ) ቢሆኑም ራርተዋልና "አምላከ ሙሴ" ብለው
ጸልየው ወደ ጥልቁ ውስጥ ገቡ::
+ቅዱስ ሚካኤል አብሯቸው ነበርና ተከዜ ግራና ቀኝ
ተከፍሎ መሃሉ የብስ ሆነ:: ይሕን ድንቅ ያዩ ከ1,000
በላይ
አሕዛብም አምነው በጻድቁ እጅ ተጠምቀዋል:: ይሕም
ዘወትር ነሐሴ 10 ቀን በቤተ ክርስቲያናቸው (ጐንደር)
ይከበራል::
+ከዚያም እያስተማሩ ጐንደር ደረሱ:: ያኔ ጐንደር በቀሃና
አንገረብ ወንዞች የታጠረች አንዲት መንደር ነበረች:: ጻድቁ
ቀን ቀን እየሰበኩ ማታ ዛሬ ቤተ ክርስቲያናቸው የታነጸበት
ሥፍራ ላይ ሲጸልዩ ያድሩ ነበር::
+በዚያ ዘመን ጐንደር ውስጥ ጅብ: እባብና መሠል አራዊት
ገብተው ሕዝቡን ጨረሱት:: ይሕንን የተመለከቱት አባ
ዓቢየ እግዚእ ወደ እግዚአብሔር አለቀሱ:: በፍጹም ልባቸውም
ስለ ሕዝቡ ለመኑ::
+የለመኑትን የማይነሳ ጌታ ወደ ጻድቁ ቀርቦ "በስምሕ
የተማጸኑ: በቃል ኪዳንህ ያመኑ: በምድር አራዊት
አይሠለጥኑባቸውም::
በሰማይም እሳትን አያዩም:: ጐንደርንም አራዊት ገብተው
ሰውን አይጐዱም::" ብሏቸው አርጓል::
+ጻድቁም የወንጌል አገልግሎታቸውን ፈጽመው ወደ
ገዳማቸው ተንቤን ተመልሰዋል::
ይሔው እኛ ምን ብንከፋ: ጻድቁንም ብንረሳቸው
እግዚአብሔር ግን ዛሬም በጻድቁ ምልጃ ከተማዋን ጠብቆ
ይኖራል:: ነገን ደግሞ እርሱ ያውቃል:: ዛሬ ቤተ ክርስቲያኑ የታነጸበት ቦታ (ጎንደር ቀበሌ 09 ኪዳነ ምሕረት) ጻድቁ የጸለዩበት ቦታ
ነው:: እንኳን በወርሃዊ በዓላቸው (በ19) ይቅርና
በዓመታዊ በዓላቸው (ግንቦት 19) ለንግስ የሚመጣው
ሰው ቁጥር ያስተዛዝባል::
+አባ ዓቢየ እግዚእ በገዳማቸው ተንቤን ለብዙ ዘመናት
በቅድስና ኑረው: 3 ሙታንን አስነስተው: ብዙ ድውያንን
ፈውሰው: ብሔረ ብጹዓንን ጎብኝተው: የድኅነት ቃል ኪዳንም
ተቀብለው: በ140 ዓመታቸው ግንቦት 19 ቀን አርፈዋል::
የጻድቁ ክብር ለሁሉ ነውና እባካችሁ እናስባቸው::
+<< ተአምሪሁ ለጻድቅ አቡነ ዓቢየ እግዚእ - - - ጸሎቱ
ወበረከቱ የሃሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ
ዓለም:: አሜን:: >>+
+<< ከበዙ ተአምራቱ አንዱን >>+
=>ጻድቁ አባ ዓቢየ እግዚእ በገዳማቸው #ተንቤን
(መረታ) ሳሉ አንዲት መበለት መጥታ "አባቴ!
የምጠጣውን ጸበል ባርከህ ስጠኝ?" አለቻቸው:: ጻድቁም
በውሃው ላይ ጸሎትን አድርሰው : በመስቀላቸው ባርከው
ሰጧት::
+ወደ ባልንጀራዋ ስትደርስ ግን ሐሳቧን ቀየረችና
"ልጠጣው" ብላ የተቀበለችውን ማይ (ጸበል)
ልትጠመቅበት (ልትጸበልበት) ወሰነች:: ባልንጀራዋንም
"በላዬ ላይ አፍሺልኝ" ስትል አዘዘቻት::
+ባልንጀራዋም "እሺ" ብላ ልታፈስላት (ልትጸብላት) በፋጋ
(ግማሽ ቅል) ያለውን ጸበል አነሳች:: ልታፈሰው
ስትዘቀዝቀው ግን ከሆነው ነገር የተነሳ 2ቱም ደነገጡ::
ጸበሉ የረጋ ደም ወደ መሆን በቅጽበት ተለውጧልና::
+ፍጹም ፍርሃት የወደቀባቸው ሴቶቹ እየተሯሯጡ ወደ አባ
ዓቢየ እግዚእ በዓት ደረሱ:: ከውጭ ሆነውም "አባ! አባ!
የሰጠኸን ጸበልኮ የረጋ ደም ሆነ" አሏቸው:: ጻድቁም
እንዳላዋቂ "ምን አጠፋችሁ?" ሲሉ ጠየቁ::
+"አባታችን! ምንም አላጠፋንም:: ብቻ አፍሺልኝ ብየ
ስሰጣት እንዲህ ሆነ" ስትል አንዷ መለሰች:: ጻድቁ ግን
በየውሃት "ልጆቼ! ሁሌም : 'ምንም አላጠፋንም'
አይባልም:: ሰው ሆኖ የማይበድል የለምና::
+ . . . አንቺም ልጄ! እኔን ያልሺኝ 'የምጠጣው ጸበል
ስጠኝ' ነበር:: ግን ልትጸበይበት ወደድሽ:: ስሕተትሽ ከዚህ
ይጀምራል:: (የቅዳሴ ጸበል ለመጸበል አይሆንምና)
¤በዚያ ላይ "አልቦ ዓቢይ ኃጢአት ከመ ወልጦ ቃል . . .
ከውሸት በላይ ከባድ ኃጢአት የለም::" (ዮሐ. 8:44)
+ . . . በተጨማሪ ደግሞ ያለ ስልጣኗ እህትሽን
'አጥምቂኝ' አልሻት:: ስለነዚህ ነገሮች ጸበሉ
ተለውጦባቹሃል" ብለው ወደ ጸበሉ በመስቀል አማተቡ::
"እፍ" ሲሉትም የረጋ ደም የነበረው ማይ ወደ ጸበልነቱ
ተመለሰ:: ይህንን ያዩ ሴቶቹ በግንባራቸው ተደፍተው
ለጻድቁ ሰገዱ::
=>ጸሎቱ ወበረከቱ የሃሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን
ለዓለመ ዓለም:: አሜን::
❖አምላካችን በወዳጆቹ ምልጃ ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ
ይሠውርልን::
❖ግንቦት 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አባ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ)
2.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም (የ12ቱ ሐዋርያት መቃብር
ከጌታ የተገለጠላቸው ኢትዮዽያዊ)
3.አቡነ ብስጣውሮስ ዘሐይቅ እስጢፋኖስ (ኢትዮዽያዊ)
4.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት ታላቁ (7 ጊዜ ሙቶ የተነሳ)
5."805,007" ሰማዕታት (በአንድ ቀን ብቻ የተገደሉ)
6.አባ ይስሐቅ ገዳማዊ
❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
2፡ ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
3፡ ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ
4፡ አባ ስነ ኢየሱስ ጻድቅ++"+ በተኩላና በእባብ ላይ ትጫማለህ::
አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ::
በእኔ ተማምኗልና አስጥለዋለሁ::
ስሜንም አውቁዋልና እጋርደዋለሁ::
ይጠራኛል እመልስለትማለሁ::
በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ::
አድነዋለሁ: አከብረውማለሁ::
ዐሥራ አራት ዓመትም በሆነው ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ አነሣሳችው በጎቹንም ትቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ። እየተጓዘም ሳለ ከሩቅ የብርሃን ምሰሶ አየ ወደ ወንዝ እስከ ደረሰ ድረስ ወደ ርሱ ሔደ ከዚህም በኋላ ያ የብርሃን ምሰሶ ከእርሱ ተሰወረ።
ያንንም ወንዝ በተሻገረ ጊዜ በሽማግሌ አምሳል ሰይጣን ተገለጠለትና ልጄ ሆይ ዕወቅ ስለ አንተ ልብሱን ቀዶ አባትህን አየሁት እርሱም ያዝናል ያለቅሳል ተመልሰህ የአባትህን ልብ ልትአጽናና ይገባሃል። የዱር አውሬ ነጥቆ የበላህ መስሎታልና አለው።
አባ ገዐርጊም ደንግጦ አንድ ሰዓት ያህል ቆመ ከዚህም በኋላ የከበረ ወንጌል ከእኔ ይልቅ አባቱንና እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም ደቀ መዝሙሬም ሊሆን አይችልም ብሏል ብሎ አሰበ።
ይህንንም በአለ ጊዜ ሰይጣን እንደ ጢስ ሆኖ ተበተነ። አባ ገዐርጊም ሰይጣን እንደ ሆነ አወቀ በዚያን ጊዜም ያ የብርሃን ምሰሶ ደግሞ ተገለጠለት የእግዚአብሔርም መልአክ በመነኵሴ አምሳል አብሮት ተጓዘ ቅዱሱም መልአኩን ተከተለው እርሱም ከአባ አርዮን ገዳም አደረሰው። አባ ገዐርጊም ከአንድ ጻድቅ ሰው መነኵሴ ጋራ በዚያ ዐሥራ አራት ዓመት ወጥ ሳይቀምስ ወይን ሳይጠጣ የአትክልት ፍሬም ቢሆን በዚህ በዐሥራ አራት ዓመት ያህል ከሚቀመጥ በቀር አልተኛም።
ተጋድሎውንም በጨመረ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለትና እንዲህ አለው ሥጋህ እንዳይደክም በመካከለኛ ገድል ተጋደል ብሎሃል ጌታ። ከዚህም በኋላ ሊሠራው የሚገባውን ሥርዓት ሠራለት። ሁል ጊዜም እስከሚመሽ እንዲጾም ትንሽም እንጀራን እንዲበላ ከአራት ሰዓት እስከ መንፈቀ ሌሊት ስለ ሥጋው ዕረፍት እንዲተኛ በቀረው ሌሊት እስቲነጋ ተግቶ እንዲጸልይ።
በዚህም ተጋድሎ ብዙ ዘመናት እየተጋደለ በኖረ ጊዜ በበረሀ ውስጥ ብቻውን ሊኖር ወዶ በጫካ ውስጥ እየተመላለሰ ሁለት ዓመት ኖረ። ከዚህም በኋላ ጌታ ተገልጾለት ወደ ቦታው እንዲመለስ አዘዘው። ያን ጊዜም አምላካዊት ኃይል ከከበሩ መክሲሞስና ደማቴዎስ ገዳም አደረሰችው እርሷም ለደብሩ አቅራቢያ ናት።
ወደ ደብሩም በተመለሰ ጊዜ በዚያን ወቅት አብርሃም ከዓለም ወደዚያ ገዳም መጥቶ ሁለቱም ተገናኙና በአንድነት ተስማምተው የአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ወደ ሆነ ወደ አባ ዮሐንስ ደረሱ። እርሱም ቦታ ሰጥቷቸው በውስጡ ኖሩ ያ ቦታም እስከ ዛሬ ታውቆ ይኖራል።
ያቺም ዋሻ በግቢግ ትባላለች የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዐለት የሆነ ጣሪያዋን ሠንጥቆ ወደ እነርሱ የወረዳበት ናት። እነርሱም ሰገዱለት ሰላምታም ሰጥቷቸው አጽናንቷቸው ከእርሳቸው ዘንድ ዐረገ። በዚያችም ጌታችን በወረደበት መስኮት ብርሃንን አዩ እስከ ዛሬም የተከፈተች ሁና ትኖራለች።
እሊህ ቅዱሳንም ለመነኰሳት የሚሆን ብዙ ድርሳናትንና ብዙ ተግሣጻትን ደረሱ። ለአባቶቹ የሚታዘዘውንና የሚገዛውን አመሰገኑት። ከዚህም በኋላ አባ አብርሃም ጥር ሁለት ቀን አረፈ። ከእርሱ በኋላም የከበረ አባ ገዐርጊ በዚች በግንቦት ወር በዐሥራ ስምንት ቀን አረፈ። መላ ዕድሜውም ሰባ ሁለት ዓመት ሆነ። በዓለም ዐሥራ አራት ዓመት በምንኩስና ኃምሳ ስምንት ዓመት ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ሰማዕት_ሲኖዳ
በዚችም ዕለት የሰማዕት ሲኖዳ መታሰቢያው ነው በረከቱ፡ ሰማዕቱ አቡነ ሲኖዳ ሀገራቸው ግብፅ ብሕንሳ ነው፡፡ መጽሐፍ ሰማዕትም ጻድቅም ይላቸዋል፡፡ ሽኖዳ እየተባሉም የሚጠሩ ሲሆን የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የአክስት ልጅ ናቸው፡፡ ሙሉ ዕድሜያቸውን በገዳም ነው የኖሩት፡፡ በማርቆስ መንበር ላይ ተሹመው በፓትርያርክነት እያገለገሉ እያለ በዘመናቸው ከሃዲው ንጉሥ መክስምያኖስ ነግሦ ስለነበር ክርስቶስን በማመናቸው እጅግ ብዙ አሠቃይቷቸዋል፡፡
ከሃ*ዲ*ው ንጉሥ መክስምያኖስ ወደ እርሱ እንዲመጡ ካደረገ በኋላ በእርሱ ጣዖት እንዲያምኑ ጠየቃቸው፡፡ አቡነ ሲኖዳም በክርስቶስ እንደሚያምኑ ሲነግሩት በምድር ላይ ደማቸው እንደ ውኃ እስኪፈስ ድረስ ጽኑ ግርፋትን አስገረፋቸው፣ ዐይናቸውም ሊወጣ ደረሰ፡፡ በእሥር ቤትም ከጣሏቸው በኋላ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ከቁስላቸው ፈውሶ አበረታቸውና ገና እንደሚጋደሉ ነገራቸው፡፡ ንጉሡም ‹‹ሞቶ እንደሆን እዩት›› ብሎ ወታደሮቹን ቢልክም ፍጹም ጤነኛ መሆናቸውን ነገሩት፡፡ ልብሳቸውንም አስወልቆ አይቶ ካረጋገጠ በኋላ ‹‹ታላቅ ሥራይ ነው›› በማለት ዘቅዝቀው እንዲሰቅሏቸውና ከሥር እሳት እንዲያነዱባቸው አዘዘ፡፡ ይህንንም በአባታችን ላይ አደረጉባቸው፡፡ አሁንም ምንም ዓይነት ሥቃይ እንዳልገደላቸው ባየ ጊዜ በብዙ ካሠቃያቸው በኋላ መጋቢት 14 ቀን አንገታቸውን በሰይፍ አስቆርጦታል፡፡
ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከቸር አባቱ አዳኝና ሕይወት ከሆነ ቅዱስ መንፈሱ ጋር ጌትነት ክብር ምስጋና ይሁን። እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት እና #ከገድላት_አንደበት)
✍"ሰማዕትነት ስር ነው፤ ክርስቲያኖች ደግሞ ከዚኽ ስር የሚያቆጠቁጡ ምርጥ ዘሮች ናቸው፤ ብዙ ዛፍ የሚያቆጠቁጥበት ስር በለም አፈር ስለሚሸፈን አይታይም፤ ከዚያ በሚያቆጠቁጡ ዛፎች ግን ስሩ እንዴት እንደተመቸው ይታወቃል፤ ሰማዕታትም በግዙፉ ዓይናችን እንደምን ያለ አክሊል ሽልማት እንደተቀበሉ አይታየንም፤ ፍሬያቸው ግን እነርሱን መስለው እነርሱን አኽለው በሚጋደሉ ምርጥ ዘሮች ይታወቃል፤ ሰማዕታት አክብሩን ብለው አይናገሩም፤ ነገር ግን በክርስቲያኖች ልብ የሚዘሩት ፍሬ ምእመናንን በፍቅር ያስገድዳል፤ እነርሱን እንዲመስሉ ያሳስባል፤ ሰማዕታት እንደ ፍቅረኛ ናቸው፤ አንድ ሰው የፍቅረኛውን ስም በየአጋጣሚው ያነሣል፤ በዓይነ ሕሊናው ያስባል በተለያየ መልኩ ያያል ሰማዕታትም ለክርስቲያኖች እንደዚያ ናቸው፤ እጅግ የተወደዱና በፍጹም ከሕሊና የማይጠፉ ተወዳጆች ናቸው፤ የልጆቻችንን ስም በነርሱ ስም የምንሰይመው፣ ሥዕላቸውን ሥለን የምንተሻሸው የምንስመው ለሰማዕታቱ ያለንን ጥልቅ ፍቅር የምንገልጽበት መንገድ ስለኾነ ነው"
📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❤💐
🥀ኪዳነ ምህረት🥀
➡️ ኪዳነምህረት ስንል የምህረት ቃልኪዳን ማለት ነው፡፡በዚህ ውስጥም ምህረት አድራጊው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ምህረት ተቀባይም መላው የአዳም ዘር ነው፡፡
➡️ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በምድራዊ ቆይታዋ ዘውትር ወደ ክርስቶስ መካነ መቃብር ጎለጎታ እየወረደች ትፀልይ ነበር፡፡ ልጇ እና ወዳጇ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገችው ልመናና ፀሎት ተመልክቶና ሰምቶ የምህረት ቃል ኪዳን ገባለት ፡፡
➡️ እንኳን የእናቱን ፀሎት እና ልመና ቀርቶ ዘውትር በሀጥያት የምንዘፈቀውን እኛን ክፉዎቹን የሚሰማ አምላክ ስለ አንቺ ፣ ስለ እናቴ ክብርና ፀጋ ስል ይኸው ቃሌ ብሎ ቃልኪዳን አደረገ፡፡
« ከመረጥሁት ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ። … » መዝ, 89 : 3 እንዲል መፅሐፉ፡፡
➡️ ስሟን ለሚጠሩ፣ በእርሷ አማላጅነት ለሚታመኑ በምድር በረከትን በሰማይ የዘለዓለም መንግስትን እንደሚወርሱ የምህረት እና የቸርነት ቃልኪዳን ሰጥቷታል ፡፡
➡️ ታላቁ መፅሐፍ እንዲህ ይላል፦
". . . ቀስቲቱም በደመና ትሆናለች፤ በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘላለም ቃል ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ። " ኦሪት ዘፍ. 9 : 16
➡️ በዚህም መሠረት ቃልኪዳኗን ምክንያት በማድረግ ኪዳነ-ምህረት እያልን እንጠራታለን።
እንኳን አደረሳችሁ። የእመቤታችን ምህረት እና ረድዔት፤በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን!!!❤️
❤️አቡነ_ሽኖዳ_ሳልሳዊ እንዲህ ይመክረናል
መንፈስ_ቅዱስ_ነው!!
"ከቅዱሱ ስፍራ ከቤተክርስቲያን
👉በቅዳሴው፣
👉በትምህርቱ፣
👉ሚስጢራቱን ሁሉ ተሳትፋችሁም ሆነ፣
👉 የግል ጸሎት አድርጋችሁ፤
👉 እንዲሁ በጎ ነገር ሰርታችሁ ስትጨርሱ፤
👉ውስጣችሁን የደስታ፣ የረፍት፣ የተስፋ፣
👉አንዳች ስሜት በውስጣችሁ ከተሰማችሁ
እርሱ ❤️መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ አስተውሉ።"
ቅዱስ ዳዊት ‹‹እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው›› (መዝ 67፡35) ብሎ እንደተናገረ ጻድቁ አቡነ ያሳይ ከእግዚአብሔር በተሰጣቸውም ጸጋ ጣና ሐይቅን የሚያቋርጡት በአንድ ትልቅ ጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ ተቀምጠው ድንጋዩን እንደ ጀልባ ተጠቅመው ነበር፡፡ ያ ድንጋይ ዛሬም ድረስ በገዳማቸው ውስጥ በክብር ተቀምጦ ይገኛል፡፡ ጻድቁ ከአቡነ ሳሙኤል ጋር አብረው ወደዚህ ቦታ መጡ፡፡ ከዚያም የቦታው አቀማመጥ የብስ መሬትና ደሴት መሆኑን አይተው ‹‹እግዚአብሔር ፈቅዶ ይችን ደሴት የጸሎት ቦታችን አድርጎ ቢሰጠን በጸሎት እንጠይቀው›› ተባብለው ሁሉቱም ቅዱሳን ሱባኤ ገቡ፡፡ ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችንም ለአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ተገሃድ ተልጦላቸው ‹‹ወዳጄ ሳሙኤል ሆይ ይህ ቦታ የአንተ አይደለም የወንድምህ የያሳይ ቦታ ነው፡፡ እኔ ወዳዘጋጀሁልህ ቦታ ወደ ዋሊ ሂድ›› ብሎ የዋልድባን ምድር አሳያቸው፡፡ አቡነ ሳሙኤልም የጌታችንን ትእዛዝ ተቀብለው ወንድማቸውን አቡነ ያሳይን ተሰናብተው ወደ ዋልድባ ሄደው ገዳማቸውን አቅንተው ተጋድሎቸአውን በዚያ ፈጸሙ፡፡
ጌታችን ዳግመኛም ለአቡነ ያሳይ ተገለጠላቸውና ‹‹ወዳጄ ያሳይ ሆይ የአባትህን መንግሥትና የዓለሙን ክብር ከምኞቱ ጋር ለእኔ ብለህ ስለተውክ ይህንኑ ቦታ በዚህ ዓለም ሳለህ ለአንተ፣ ወደ ዘላለማዊ መንግሥቴ ከወሰድኩህ በኋላም ለልጆችህ ምንዳህ አድርጌ ሰጥቼሃለሁ፤ ምሕረቴንም በቦታህ አዘንባለሁ ቸርነቴም አይለያትም፣ ብዙ የመንፈስ ልጆችንም ታፈራለህ፤ ቦታህም እኔ ለፍርድ እስክመጣ ድረስ ትኖራለች›› በማለት ቃልኪዳኑን አቆመላቸውና ተሰወራቸው፡፡ ‹‹ምንዳህ›› ማለት ደመወዝ ማለት ነውና በዚህም ‹‹ማንዳባ›› ማለት ‹‹የአቡነ ያሳይ ምንዳ-ደመወዝ›› ማለት ነው ሲሉ አባቶች ገዳሙን ‹‹ማንዳባ-ምን እንደ አባ›› ብለው ሰየሙት፡፡
አቡነ ያሳይ የትውልድ ሀገራቸው ሸዋ ተጉለት ነው፡፡ አባታቸው ንጉሡ ዓምደ ጽዮን ቀዳማዊ ነው፡፡ ይኸውም ከ1296-1326 ዓ.ም የነበረው ነው፡፡ አቡነ ያሳይ በልጅነታቸው በንጉሡ አባታቸው ቤት ሲኖሩ የገዳማ መነኮሳት ለመንፈሳዊ ሥራ ወደ ንጉሡ ዘንድ እየመጡ ደጅ ሲጠኑ ያዩአቸዋል፡፡ በዚህም ጊዜ አባታችን ገና በልጅነታቸው የመነኮሳቱን እግር ያጥቡ ስለነበር በዚሁ አጋጣሚ መነኮሳቱን ስለምንኩስና ሕይወት ይጠይቋቸው ነበር፡፡ መነኮሳቱም ሕይወታቸውን ያስረዷቸዋል፡፡ አቡነ ያሳይም ብሉያትንና ሐዲሳትን ከልጅነታቸው ጀምሮ የተማሩ ስለነበር የአባቶችን ትምህርትና የወንጌልን ቃል በማገናዘብ የፈጣሪያቸው ፍቅር በልቡናቸው እንደ እሳት ነደደ፡፡ ይልቁንም ‹‹ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል›› የሚለውን የጌታችንን ቃል አሰቡ፡፡ ማቴ 16፡26፡፡ ከዚህም በኋላ የንጉሡ አባታቸውን የአልጋ ወራሽነት ማለትም የንጉሥነትን ክብር ፈጽመው በመናቅ ‹‹እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር እራሱን ይካድ፣ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ›› (ማቴ 16፡27) ያለውን የጌታችንን ቃል አስበው ንጉሣውያን ቤተሰቦቻቸውን ጥለው ለምነና ወጡ፡፡
ለምነና እንደወጡም ከሸዋ ተነሥተው ወደ ትግራይ ክፍለ ሀገር በአክሱም አቅራቢያ ከሚገኘው ገዳም ደብረ በንኮል ከሚባለው ከአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ገዳም ደረሱ፡፡ አቡነ መድኃኒነ እግዚእም አቡነ ያሳይ የእግዚአብሔር ጸጋ ያደረባቸው ሰው መሆናቸውንና ወደ እርሳቸውም እየመጡ መሆኑን በመንፈስ ዐውቀውት ስለነበር በደስታ ተቀበሏቸውና በረድእነት ከወንድሞቻቸው ጋር ጨመሯቸው፡፡ አቡነ ያሳይም የገዳም መነኮሳትን በማገልገል በመንፈሳዊ ተጋድሎ ብዙ ደከሙ፡፡ በደብረ በንኮል ገዳምም ብዙ እገራሚ ተአምራትን አደረጉ፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ ወደ መካነ ገድላቸው በጣና አካባቢ እንደሆነ ነገራቸው፡፡ ‹‹ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን›› የተባሉ አቡነ መድኃኒነ እግዚእም ቀደም ብለን የጠራናቸውን ‹‹ሰባቱን ከዋክብት›› ምግባር ሃይማኖታቸውን፣ ተጋድሎ ትሩፋታቸውንና ገቢረ ተአምራታቸውን አይተው ፈቃደ እግዚአብሔርን ጠይቀው በአንድ ቢያመነኩሷቸው በዚያው ቅጽበት መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ገዳሙን በብርሃን አጥለቅልቆት ታይቷል፡፡ ከሰማይም የምስክርነት ድምፅ ተሰምቷል፡፡ ከዚህም በኋላ ከሰባቱ ቅዱሳን ውስጥ ሦስቱ ቅዱሳን አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ አቡነ ያሳይ እና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ሆነው ከደብረ በንኮል ገዳም አባታቸውን አቡነ መድኃኒነ እግዚእን ተሰናብተው ወደ ጣና ደሴት መጥተዋል፡፡
አቡነ ያሳይ በ13ኛው መ/ክ/ዘመን በአባታቸው የዘመነ ንግሥና መጨረሻ ወደ አርባ ምንጭ ሄደው ከዚያው ሱባኤ ገብተው ፈጣሪያቸውን ቢማጸኑ እግዚአብሔርም ከዚያው አካባቢ የሚኖር አንድ ባሕታዊን የመድኃነዓለምን ጽላት እንዲወጣቸው አዘዘላቸው፡፡ እርሳቸውም ጽላቱን ተቀብለው በጎጃም በኩል አድርገው ወደ ጣና ተመልሰው በዘጌ አከባቢ ሲደረሱ ከጣና ባሕር ዳር ቆመው በየብስ ያለውን ርቀትና በባሕሩ ያለውን ቅርበት አይተው አሁንም ወደ ፈጣሪያቸው በጸሎት ተማጸኑ፡፡ በዚህም ጊዜ ጌታችን ተገልጦላቸው ‹‹ወዳጄ ያሳይ ሆይ አትጨነቅ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፣ ከጎንህ ያለውን ድንጋይ በባሕሩ ላይ ጫነው፤ ድንጋዩም ለልጅ ልጅ እኔ ዓለምን ለማሳለፍ እስከምመጣበት ሰዓት ድረስ መታሰቢያ ትሁንህ›› አላቸውና ተሰወረ፡፡ አቡነ ያሳይም የመድኃኔዓለምን ጽላት ይዘው በድንጋዩ ላይ እንደተቀመጡ ድንጋዩ እንደታንኳ በባሕሩ ላይ ተንሳፈፈ፡፡ ባሕሩም ከማዕበሉ ብዛት የተነሣ ይታወክ ነበር፡፡ አባታችንም ያለ ምንም ቀዘፋ ልብሳቸውም ውኃ ሳይነካው ቁጭ እንዳሉ ማን እንደአባ ወደ ተባለው ቦታቸው ደረሱ፡፡
ከዚህም በኋላ አቡነ ያሳይ ገዳማቸውን ገድመው ወንድሞቻቸውን ሰብስበው በተጋድሎ በመኖር ብዙ ቅዱሳንን አፍርተዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የጌታችንን እግር ያጠቡት አቡነ አብሳዲ፣ እንደ ነቢዩ ኤልያስ ዝናብንና ነፋስን የከለከሉት አቡነ ያዕቆብ፣ እሬትን እንደ ማር ያጣፈጡት አቡነ ገብረ ኢየሱስ፣ እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ሞገስን የተሞሉት አቡነ ዳንኤል፣ እንደ ንጉሥ ሰሎሞን ጥበብን የተሞሉት አቡነ ፊቅጦርና ሌሎችም ብዙዎች ይጠቀሳሉ፡፡ በወቅቱም ብዙ የበቁ ቅዱሳን በአካባቢው ነበሩ፡፡ በአጽፋቸውና በእግራቸው በባሕሩ ላይ የሚሄዱ ነበሩ፣ በጸጋ ክንፍ ተሰጥቷቸውም የሚበሩ ነበሩ፡፡ የአቡነ ያሳይ ተአምራቶቻቸው ተነግረው አያልቁም፡፡ በወቅቱ የነበሩት ቅዱሳን ልጆቻቸው ‹‹ከቅዱሳን ማን እንደ አባ ያሳይ በከባድ ድንጋይ ላይ ተጭኖ በባሕር ላይ የተጓዘ አለና..›› ብለው ይገረሙባቸው ነበር፡፡ ቦታቸውም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ‹‹ማን እንደ አባ›› ተባለ፡፡ ይህም የአቡነ ያሳይ ገዳም በሰሜን ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት በደንቢያ ወረዳ በጎርጎራ ጣና ሐይቅ አካባቢ ይገኛል፡፡
ግንቦት 13/2016 #እግዚአብሔር_አብ
#ቅዱስ_ሩፋኤል
#አቡነ_ዘርዐ_ብሩክ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሳኑ ስም ለምናመሰግንበት ለመልአኩ #ለቅዱስ_ሩፋኤል እና ለፃድቁ #አቡነ_ዘርዐ_ብሩክ ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን
👉 #ቅዱስ_ሩፋኤል ቊጥሩ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሲኾን ሩፋ፤ ማለት ሐኪም፤ ኤል ማለት #እግዚአብሔር ማለት ሲኾን ሩፋኤል ማለት “እግዚአብሔር ሐኪሜ ነው” ማለት ነው፤ ሄኖክም “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” ይለዋል (መጽሐፈ ሄኖክ 6፥3)
👉ይኽ መልአክ በራማ ሰማይ ያሉ ነገደ መናብርትን የሚመራቸው ነው ነገደ መናብርት ያላቸው #ቅዱስ_ሩፋኤል የሚመራቸው በራማ ሰማይ የሚኖሩ ነገደ መላእክት ናቸው
👉ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በሥነ ፍጥረት መጽሐፉ ላይ “ወለዳግም ጾታ ዐሠርቱ ስሞሙ መናብርት ወሊቆሙ #ሩፋኤል እሉ እሙንቱ እለ ይቀልል ሩጸቶሙ እምነፋስ ወእለ ይጸውሩ ወላትወ መብረቅ ወኲናተ እሳት ዘይነድድ ወአንበሮሙ በዳግሚት ሰማይ” ይላል
👉በራማ ሰማይ የሚገኘውን ኹለተኛውን ዐሥሩን ነገድ መናብርት ሲላቸው አለቃቸው #ቅዱስ_ሩፋኤል ነው፤ እነዚኽም ረቂቅ የኾነ የመብረቅ ጋሻ የእሳት ጦር ይዘው ከነፋስ ይልቅ የፈጠኑ ሲኾኑ በራማ በኹለተኛው ክፍል ላይ አስፍሯቸዋል
👉#የእግዚአብሔር_አብ ቸርነት የልጁ የመድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ምህረት #የመንፈስ_ቅዱስ አንድነት ከሁላችን ጋር ይሁን የመልአኩ #ቅዱስ_ሩፋኤል ጥበቃ የፃድቁ #አቡነ_ዘርአ_ብሩክ"ፀሎት አይለየን አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ግንቦት 12/2016 #ቅዱስ_ሚካኤል
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
#ቅዱስ_ተክለሃይማኖት
#ቅድስት_ክርስቶስ_ሰምራ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሣኑ ስም ለምናመሰግንበት #ለቅዱስ_ሚካኤል ወርሐዊ ለሌሎቹ ቅዱሣን ለአመታዊ ክብረ በአላቸዉ እንኳን አደረሰን
👉 #ቅዱስ_ሚካኤል ለሰው ልጆች ይቅርታን ለማስገኝት ወደ ልዑል እግዚአብሔር አሻቅቦ የሚማልድልን መልአክ ሲሆን መሬትና ውኃ ያልተቀላቀለበት ከነፋስና ከእሳት ብቻ የተፈጠረ ነዉ
👉 #የእግዚአብሔር ባለሟል ሆይ የዋህ መልአክ ነህና በእግዚአብሔር ፊት በጎ መዓዛ ያለውን መሥዋዕት የምታሳርግ የመላእክት ሁሉ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ የተጨነቁትን ዘውትር እንደምትረዳቸው ሁሉ እኛንም ለመርዳት ክንፈህን ዘርግተህ ፈጥነህ ድረስልን ጥበቃህ አይለየን "አሜን"
👉 #ለቅዱስ_ዮሐንስ አፈወርቅ የዓለም ሁሉ መምሕር ለሆነዉ አባታችን ይቺ እለት የእረፍቱ በአል መታሰቢያ ናት በረከት ረድኤቱ ለሁላችንም ይድረሰን "አሜን"
👉ፃድቁ #ቅዱስ_ተክለ_ሃይማኖት አባታችን በዚህች እለት የስጋቸዉ ፍልሰት ሲሆን በጌታ ፊት የከበረዉ ቃል ኪዳናቸዉ ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን"
👉ቅድስት እናታችን #ክርስቶስ_ሠምራ በዚህ እለት ከጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ የከበረዉን ቃል ኪዳን የተቀበለችበት እለት ሲሆን የተሰጣት ቃል ኪዳን ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀን "አሜን"
👉እናንተ #የምድር_ጨው ናችሁ እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትም መብራትንም አብርተው በዕንቅብ በታች አያኖሩትም በመቅረዙ ላይ እንጂ በቤት ላሉት ለሁሉም ያበራል መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ ማቴ 5፣13-16 "አሜን"
ቅዱስ ሲራክ ምዕራፍ ፰(8) ላይ እንዲህ ያስተምረናል
👉በእጃቸው እንዳትወድቅ ከታላላቆች ሰዎች ጋራ አትከራከር፡፡
👉ወርቅ ስለ መውደድ ብዙ ሰዎች ጠፍተዋልና የነገሥታቱም ልቡ ፍርድን አድልቶባቸዋልና ከባለጸጋ ጋራ አትከራከር፡፡
👉ከተናገሪ ሰውም ጋራ አትከራከር ብትከራከር ግን በእሳት ላይ እንጨት መከመርህ ነው ያ ሳይቃጠል እንዳይቀር ሳያጠፋህ አይቀርም
👉እናትና አባትህን አታዋርድ ከሰነፍ ሰው ጋራ አትሳቅ አትዘባበት።
👉ስለ ኃጢአቱ የሚለማመጥን ሰው አትንቀፈው እኛ ሁላችንም ኃጢአተኞች እንደሆን አስብ።
👉ከኛ የያያረጅ ሰው አለና በርጅናው ጊዜ ሰውን አታቅልለው።
👉በሞተ ሰው ደስ አይበልህ ሁላችን እንድንሞት አስብ።
👉የመምህራንን ነገር እታቃል ጥበብን በነሳቸው ዘንድ ታገኛታለህና ምሳሌያቸውንም ተማር። መምህራንን አገልግል፡፡
👉የሽማግሎችን ምክራቸውን ጠብቅ እነሳቸው ካባቶቻቸው ተምረዋልና አንተም ከነሳቸው ተማር ባዘንክም ጊዜ የምትናገረውንም ታገኛለህ የምትመልሰውንም ታውቃለህ፡፡
👉በእሳታቸው እንዳትቃጠል የኃጢአተኞችን ሰዎች እሳት አትጫር በፍዳቸው እንዳትጠፋ ኃጢአታቸውን አትሥራ፡፡
👉ባንደበቱ ነገር እንዳያስትህ ከተሳዳቢና በጠላት ዘንድ አትከራከር፡፡
👉ለባለጸጋ አታበድረው ብታበድረው ግን ገንዘብህን እንዳጣህ እወቅ፡፡
👉ካንተ ለሚበረታ አትዋሰው ብትዋሰው ግን እንግዴህ አንተ እንደ ከፈልህ አስብ።
👉እንደ ጌትነቱ መጠን ፍርድን ይለውጡለታልና ከዳኛ ጋራ አትከራከር፡፡
👉እንዳይደፍርህ ከደፋር ሰው ጋራ መንገድን አትሂድ እሱ ግን ልቡ እንደወደደ ያደርጋልና አንተም በእርሱ ስንፍና ትሞታለህ፡፡
👉ከቍጡ ሰው ጋራ አትከራከር በፊቱ ደም ማፍሰስ እንደ ኢምንት ነውና ረዳት ወደሌለባት ቦታም ይወስድሃልና ከሱ ጋራ ወደ ምድረ በዳ አትውጣ።
👉የሰማውን ነገር መጠበቅ አይችልምና ከአላዋቂ ሰው ጋራ አትማከር፡፡
👉እንዲደርስብሀ አታውቅምና ጉዳይህን በባዕድ ፊት አትናገር፡፡
👉ዋጋህ እንዳያጠፋብህ ከሰው ሁሉ የልብህን ምሥጢር አታውጣ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
እንዲህም የሚጋደልና የሚጸመድ ሆኖ ኖረ በዚህ ሁሉ ዘመንም ከመነኰሳት ጋራ ያገለግል ነበረ በታመመ ጊዜም እግዚአብሔርን እንዲህ ሲል ጠየቀው። የክብር ባለቤት ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ኢጲስቆጶስነት ስለተሾምኩ ጸጋህን በውኑ ከኔ ታርቃለህን ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክም ወደርሱ መጥቶ አስተውል ዕወቅ አንተ በገዳም ሳለህ በታመምክ ጊዜ የሚጎበኝህ የለም ወይም የሚአገለግልህና ለደዌህ መድኃኒትን የሚሰጥህ አታገኝም ነበር። ሰለዚህ እግዚአብሔር የሚረዳህና ደዌውንም ከአንተ የሚያርቅልህ ሆነ። ዛሬ ግን እነሆ አንተ በዓለም ውስጥ ነህ በአንተ ዘንድ የሚጐበኝህና
የሚአገለግልህ አለ ለደዌህም መድኃኒትን የምትሻውንም ምግብ ታገኛለህ አለው።
ይህም አባት በኤጲስቆጶስነት ሹመት ሠላሳ ሁለት ዓመት ኖረ የሚያርፍበትም በቀረበ ጊዜ ካህናቱንና ዲያቆናቱን መምህራኑን ጠራቸው። የአብያተ ክርስቲያናትንም ንዋየ ቅዱሳታቸውንና ገንዘባቸውን ሁሉ ሰጣቸው እንዲህም አላቸው ዕወቁ እኔ ወደ እግዚአብሔር እሔዳለሁና እንደሚገባም በመካከላችሁ እንደ ኖርኩ እናንተ ታውቃላችሁ። ለኤጲስቆጶስነት ሹመቴም እጅ መንሻ ከሚአመጡልኝ እንኳ አንድ የብር አላድ እንዳልሠወርኩ በፊቱ ልቆም ያለኝ የክብር ባለቤት ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በእኔ ላይ ምስክርን ይሁን አላቸው።
ይህንም ሰምተው አለቀሱ ተሳለሙትም እንዲባርካቸውና በክብር ባለቤት ጌታችንም ዘንድ መራዳቱን እንዳይረሳ ለመኑት እርሱም ባረካቸው። እግዚአብሔርም ያክብራችሁ እስከ መጨረሻዪቱም ሕቅታ ድረስ በቀናች ሃይማኖት ያጽናችሁ ይህንንም ብሎ በሰላም አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ሰማዕቱ_አቡነ_አሴር_ዘባሌ
በዚህችም ቀን የባሌ መምህር አባ አሴር በሰማዕትነት አረፈ፡፡ ይኸውም በንጉሥ ወናግ ሰገድ ዘመን ወደ ኢየሩሳሌም ወርዶ ሳለ መጀመሪያ አንገቱን በሰይፍ ቆረጡ። ልደቱም በዚሁ ዕለት ነው፡፡ እርሱም በደብረ ሊባኖስ የመጻሕፍት መምህር ሆኖ ሳለ የበቃ ጻድቅ መሆኑ ቢታወቅበት ወደ ሐይቅ ሄዶ በተጋድሎ የኖረ ሲሆን በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ተመርጦ በባሌ ሀገር ላይ የተሾመ ነው፡፡ በኋላም ወደ ኢየሩሳሌምና ግብፅ ሄዶ ከመና*ፍቃን ጋር ሲከራከር ከሃዲዎች በእሳት አቃጥለውት በመጨረሻም አንገቱን ሰይፈውት በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡ አካሉንም በእሳት አቃጥለውት ከጣሉት በኋላ በደብረ ቁስቋም ተቀብሯል፡፡ ስንክሳሩ ግን ‹‹በኢየሩሳሌም መግቢያ በእሳት አቃጠሉት›› ብሎ ይገልጸዋል፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_ኤልያስ_ዘውቅሮ
በዚህች ቀን የአቡነ ኤልያስ ዘውቅሮ መታሰቢያቸው ነው፡፡ ቅዱሱ የትውልድ ሀገራቸው አክሱም ነው፡፡ የአቡነ አረጋዊ 3ኛ የቆብ ልጅ ናቸው፡፡ አባታቸው ውቅሮ የሚገኘው የጥንታዊው የአብርሃ ወአጽብሓ ቤተ መቅደስ አጣኝ ነበሩ፡፡ ይህ ጻድቅ የሚታወቁበት አንድ ትልቅ ገድል አላቸው፡፡ በቀን 548 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያትን እየጸለዩ 666 ጊዜ ይሰግዱ ነበር፡፡ ቅዱስ ያሬድ ዓባይ የሀገራችንን አፈርና ዛፉን ሁሉ ጠራርጎ ሲወስድ ቢመለከት ድምጹን ከፍ አድርጎ ኦ አባይ አይቴ ተሐውር ወለመኑ ተሐዲጋ ለኢትዮጵያ ብሎ ሲዘምር ዓባይ ቀጥ ብሎ ቆሟል፡፡ መልአኩም ወዲያው መጥቶ ‹‹ለምን ትደክማለህ? ለምንስ ተፈጥሮን ትከለክላለህ? ሕጉን አታፍርስ›› ሲለው ቅዱስ ያሬድ ደንጎጦ ‹‹አጥፍቻለሁ ዓባይ ሆይ ሂድ የተፈጥሮ ግዴታህን ፈጽም›› ብሎ አሰናብቶታል፡፡ የኢትዮጵያ ብርሃኗ ቅዱስ ያሬድ በዜማው ዓባይን ቀጥ አድርጎ እንዳቆመው ሁሉ አቡነ ኤልያስ ዘውቅሮም በጸሎታቸው ዓባይን ከኢትዮጵያ እንዳይወጣ አድርገውት ነበር፡፡
ታቦተ አብርሃ ወአጽብሓን ይዘው ከኢትዮጵያ ጠረፍ ዳር ኑብያ ሄደው ድንጋይ ከዓባይ ዳር ደርድረው ታቦቱን አስቀምጠው ሥዕለ ማርያምን አድርገው መሥዋዕት ሰውተው ‹‹ዓባይ ከኢትዮጵያ እንዳትወጣ ገዝቼሃለሁ›› ሲሉት ዓባይም ተመልሶ ቆሟል፡፡ ዓባይ ምድረ ኑብያን ሲያጥለቀልቃት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ተገልጾ ‹‹ለምን የእግዚአብሔርን ስነ ፍጥረት ታስጨንቃለህ?›› ብሎ ተቆጣቸው፡፡ ጻድቁም ‹‹ውኃው ይሂድ ግን ዛፉን አፈሩን ይዞ ከኢትዮጵያ አይውጣ›› ብለው መልአኩን ጠየቁት፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም ‹‹ውኃ ሲሞላ ዛፉን ቅጠሉን ይዞ መጓዙን እንዴት ትረሳዋለህ? የጸሎት ጊዜህ ደርሷልና ወደ በዓትህ ተመለስ›› ብሎ በቁጣ የእሳት ሰይፉን ሲያዛቸው ግዝታቸውን አንሥተው ታቦታቸውን ይዘው ወደ በዓታቸው ውቅሮ ተመልሰዋል፡፡
አባቶቻችን እንዲህ ናቸው እንኳን ሃይማኖት፣ ባህል፣ ታሪክ፣ ቅርስ፣ ስብዕና ማንነታችንን ይቅርና የሀገራችንን አፈር እንኳን ለባዕድ አሳልፈው የማይሰጡ ቅዱሳን ጻድቃን ነበሩ፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_አናሲማ_ገዳማዊት
በዚህች ቀንም ቅድስት አናሲማ አረፈች፡፡ ይቺም ቅድስት በደናግል ገዳም መንኵሳ ራስዋን እብድ አስመስላ ኖረች። በሌሊትም በጾምና በጸሎት ሥጋዋን በመቅጣት ራሷን ታሠቃያለች ሰዎችም በሚያዩዋት ጊዜ ራስዋን አእምሮዋን እንደሳተች ታስመስላለች መበለቶችም ይሰድቧታል።
እግዚአብሔርም ገድሏን ለአባ ዳንኤል ገለጠ። እርሱም ከደናግል ገዳም ሔዶ ትሩፋቷንና ገድሏን ሁሉ ለእመ ምኔቷ ነገራት እርሷም ለእኀቶች መነኰሳይያት ነገረቻቸው ከዚያችም ዕለት ወዲህ አከበሩዋት።
እርሷም ስለ አዋረዱዋትና ስለ አጐሳቈሉዋት እኀቶችን እያመሰገነች ደብዳቤ ጽፋ ትታ ከንቱ ውዳሴን በመጥላቷ ተሠውራ በሌሊት ወጥታ ወደ ዱር ሸሸች በዚያም በሰላም አረፈች።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_ኤፎምያ_ሰማዕት
በዚህችም ቀን በዲዮቅልጥያኖስ መንግሥት ዘመን ቅዱስት ኤፎምያ በሰማዕትነት አረፈች። የዚችም የእናቷ ስም ቴዎድርስያኒ ነው እርሷም የክብር ባለቤት ክርስቶስን የምታምንና የምትፈራው ናት።
ሰይጣንም ክርስቲያኖችን በማስገደድ ለጣዖት እንዲያሰግድ አንቲሂጳጦስን በአነሣሣው ጊዜ ይቺን ቅድስት ኤፎምያን ከብዙ ክርስቲያኖች ጋራ አሥረው አመጡዋት። አንቲሂጳጦስም ለአማልክት ሠዊ አላት። እኔ ከክብር ባለቤት ከጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር አልሠዋም የአባቶቼን ተስፋ ለማግኘት ልቤ የጸና ነውና አለችው።
ያን ጊዜ አንቲሂጳጦስ ተቆጥቶ ዐጥንቷ እንዲሰበር ሕዋሳቷ ሁሉ እንዲለያይ ከሠረገላ መንኰራኩር ውስጥ ይጨምሩዋት ዘንድ አዘዘ። የእግዚአብሔርም መልአክ አዳናት ሁለተኛም ነበልባሉ አርባ አምስት ክንድ ከፍ ከፍ እስከሚል እሳትን አንድደው ከውስጡ ይወረውሩዋት ዘንድ አዘዘ። በእሳቱ መካከልም ቁማ ጸለየች እየጸለየችም በደኅና ወጣች ብዙዎችም በጌታ አምነው በሰማዕትነት አረፉ።
ከዚህም በኋላ እስከ ማግሥት ከወህኒ ቤት ጨመራትና በማግሥቱ ወደ ሸንጎ አወጧት እርሱም ለአማልክት ሠዊ አላት። ቅድስት ኤፎምያም ሣቅ ብላ እኔስ ለማይናገሩ ደንጊያዎች አልሠዋም አለችው። አንቲሂጳጦስም ሰምቶ ሥጋዋን ይገፉ ዘንድ መቃጥን ያላቸው አራት ደንጊያዎችን እንዲያመጡ አዘዘ። ሁለተኛም አራዊት ከአሉበት ኲሬ ውስጥ እንዲጨምሩዋት አዝዞ ከዚያ ወረወሩዋት። አራዊት ግን ተሸክመው አውጥተው ከውኃው ዳር አቆሙዋት።
ደግሞ ስለታሞች ደንጊያዎችንና ሰይፎችን በመሬት ውስጥ እንዲተክሉ ተቆራርጣ ትሞት ዘንድ በላያቸው እንዲያስሮጡዋት አዘዘ ሩጣም ተሻገረች ምንም የነካት የለም። ደግሞም በግለቱ ታር ዘንድ ደብድበው ከብረት ምጣድ ውስጥ እንዲጨምሩዋት አዘዘ ግን ምንም ምን አልነካትም።
❗️❗️❗️
ሰላም እህቶቼ/ወንድሞቼ ይቅርታ ካስቸገርኳችሁ መቼስ ሁላችሁም እናት አላችሁ እና የእናት ነገር ከባድ እንደሆነ እና የሷን ክፉ ማየት እንደሚከብድ ታውቁታላችሁ እኔም ለዛ ነው ደፍሬ በመውጣት ችግሬን አይታችሁ እንድታግዙኝ ስል እጆቼን ለእርዳታ ወደ እናንተ ደጋግ ኢትዮጲያዊያን የዘረጋሁት 50ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለ50ሰው ደሞ ጌጡ ነውና ችግሬን ታቀልሉኛላችሁ በሚል እምነት ወደናንተ መጣሁ ዝም እንደማትሉኝ ተስፋ አረጋለው
የምኖረው አፋር ክልል ሰመራ አካባቢ ነው አባቴን በኩላሊት ህምም ምክንያት ገና በልጅነቴ ነው ያጣሁት ከዛን ቀን በሃላ የቤተሰቡ ሀላፊነት ሙሉ በሙሉ እኔ ላይ በመውደቁ ምክኒያት እንደጓደኞቼን መማሬን ትቼ ትምህርቴን ከ12 በማቋረጥ የተገኘውን የቀን ስራ እና የሆቴል ስራ እየሰራሁ ቤተሰብ አግዝ ነበር እናቴን እና 2 እህቶቼን የማስተዳደር እና የማስተማር ፍላጎታቸውን የማሟላት ሀላፊነት የወደቀብኝ ገና በልጅነት እድሜዬ ነበር ነገር ግን ምንም ብሞክር እና ብሰራ የምሰራው ስራና ወጪዬ በጭራሽ አልመጣጠን አለ በዛ ላይ እናቴ ታማ ላልተወሰኑ ጥቂት ወራቶች ስራ ፈትቼ ነበር አስቡት ምን ያክል ከባድ እንደሆነ ያለምንም ገቢ ስራ ፈትቶ ቤት መቀመጥ በዚ ክፍተት መሀል የቤት ኪራይ ክፍያ ሳንከፍል ተጠራቀመብን እና የ5ወር የቤት ኪራይ ሳይከፍል አሁን ላይ 10,000 ብር ደርሶዋል አከራዮቻችንም እስካሁን ዝም ያሉት ሁኔታችንን ስለሚያቁ ነበር አሁን ግን መታገስ ከብዷቸው ቤቱን ልቀቁ ወይ ክፈል ብለውኛል እናም ይሄን የሚያክል ገንዘብ የመክፈል አቅሙ የለንም አሁን እኔ እጅ ላይ ያለው በዚሁ በቴሌግራም በኩል አንዳንድ እህት ወንድሞች የላኩልኝ 2000ብር ብቻ ነው ወላሂ አላህ ምስክሬ ነው ረመዳን እንዴት ተቸግረን እየፆምን እንዳለን በዛ ላይ አሁን ይሄ ችግር መጣ እና እባካችሁ ለአላህ ስትሉ በየአቅማችሁ እንድታግዙኝ እጆቼን አንስቼ በፈጣሪ ስም እማፀናችኋለሁ 🙏🙏🙏
በረንዳ ወተን እያገገመች የነበረችዋን እናቴ እንዲያምብኝ አልፈልግም ወላሂ አላህ እና እኔ ነን የምናውቀው በአልን እንዴት ሁነን እንዳሳለፍን እና እባካችሁ እናንተ ደጋግ እህት ወንድሞቼ የናንተ ደግነት እና ቸርነት ሰፊ ነው እና እባካችሁ ለፈጣሪ ስትሉ ከዚህ ችግር ታደጉኝ
" በምድር ላለው እዘኑ በሰማይ ያሉት መላዕክቶች ያዝንሉችኋል"
🙏🙏🙏እባካችሁ በተቻላችሁ አቅም አግዙኝ
እንደምንም በእናንተ ደጋግ እህት ወንድሞቼ እርዳታ ግማሹን ያክል ማለትም4,200ብር ደርሶልኛል እባካችሁ ቀሪውንም ለመሙላት እንድችል ደጋግ እጆቻችሁን ዘርጉልኝ🙏🙏
1000303941499
ከድር ታደሰ
ንግድ ባንክ
1000243914934
ጀሚላ ታደሰ
ንግድ ባንክ
0715063225
0925063247
afomiatube41?si=HBptJA5QxBruFagE" rel="nofollow">https://youtube.com/@afomiatube41?si=HBptJA5QxBruFagE
Читать полностью…⚡️Acorns ቦትን በስልኮት በመጠቀም ብቻ በወር 100,000ሺ
ብር በላይ ተከፋይ ይሁኑ 💸
🎁የ Acorns ቦት ጋር ልክ እንደገቡ የ 1000ብር
ስጦታ ያገኛሉ በተጨማሪም 1 ሰዉ ወደ ቦቱ ሲጋብዙ በየቀኑ የ 50ብር
ቋሚ ክፍያ ያገኛሉ
🔗ይህ የእርሶ የመጋበዣ link
ነው ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ 👇👇
/channel/FreeEearnMoneyPay_Bot?start=r04620854074
/channel/tapswap_mirror_2_bot?start=r_1806572852 🎁 +2.5k Shares as a first-time gift
Читать полностью…#ግንቦት_18
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ግንቦት ዐሥራ ስምንት በዚህች ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ከዐረገ በኋላ በዐሥረኛ ከትንሣኤው በሃምሳኛ ቀን ለደቀመዛሙርቱ መንፈስ ቅዱስን የላከበት #በዓለ_ጰራቅሊጦስ ነው፣ የአባ አብርሃም ጓደኛ የከበረ #አባ_ገዐርጊ አረፈ፣ #የሰማዕት_ሲኖዳ መታሰቢያው ነው በረከቱ፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱሳን_ሐዋርያት_ወአርድእት (በዓለ_ጰራቅሊጦስ)
ግንቦት ዐሥራ ስምንት በዚህች ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ከዐረገ በኋላ በዐሥረኛ ከትንሣኤው በሃምሳኛ ቀን ለደቀመዛሙርቱ ከአብ የሚሠረጽ ሌላ አካላዊ ሕይወት ጰራቅሊጦስን እልክላችኋለሁ ብሎ ተስፋ እንደ ሰጣቸው በሐዋርያት ላይ አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ ወረደ።
እናንተም ከአርያም ኃይልን እስከምትለብሱ በኢየሩሳሌም ኑሩ አላቸው። ሁለተኛም ያ እውነተኛ መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ ዕውነት ሁሉ ይመራችኋል አላቸው። ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው እርሱም አለቃቸው የሆነ ጌታችን አጽናኚውን ይኸውም መንፈስ ቅዱስ ነው ሊልክልን ተስፋ አስደርጎናል የምናሰማውንና የምናደርገውን ልብ ያስደርገን ዘንድ።
ይህንንም ሲነግራቸው እነሆ የዐውሎ ነፋስ ድምፅ ሰሙ በዓለም ውስጥ እንደርሱ ያለ የማያውቁት ጣፋጭ መዓዛ አሸተቱ። የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎችም በየአንዳንዳቸው ላይ ሲወርዱ ታዩ። በአዲስ ቋንቋም ተናገሩ ለጌትነቱ እጅ መንሻ ሊሆን አርባ ቀን ጾሙ። ሁለተኛም በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ በዓለ ኃምሣ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድ ልብ ሁነው አብረው ሳሉ። ድንገት ከሰማይ የዐውሎ ነፋስ ድምፅ መጣ ተቀምጠው የነበሩበትም ቤት ሁሉ መላው።
የተከፋፈሉ የእሳት ልሳኖችም ታዩአቸው በየአንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው ሁሉም መንፈስ ቅዱስን ተመሉ። በየራሳቸውም በሀገሩ ሁሉ ቋንቋ ይናገሩ ጀምር መንፈስ ቅዱስ ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው። ከሰማይም በታች ካሉ ሕዝብ ሁሉ በጸሎት የተጉ አይሁድ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር።
ይህንንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ደንግጠው ሁሉም ተሰበሰቡ በየሀገራቸው ቋንቋ ሲናገሩ ሰምተዋቸዋልና።ተደንቀውም በድንጋጤ እንዲህ አሉ። እነሆ እሊህ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን የጳርቴና የሜድ የኤላሜጤም ሰዎች ስንሆን። በሁለት ወንዝም መካከል በይሁዳም በቀጰዶቅያም በጳንጦስም በእስያም በፍርግያም በጵንፍልያም በግብጽም በቀሬናም በኩል ባሉት በሊብያ ወረዳዎች የምንኖር በሮሜም የምንቀመጥ አይሁድም ወደ ይሁዲነት የገባን የቀርጤስና የዐረብ ሰዎች ስንሆን የእግዚአብሔርን ገናናነት በቋንቋችን ሲናገሩ እነሆ እንሰማቸዋለን።
ሁሉም ደንግጠው የሚናገሩትን አጡ። እርስ በርሳቸውም እንጃ ይህ ምን ይሆን አሉ ሌሎች ግን እያፌዙባቸው ጉሽ የወይን ጠጅ ጠግበዋል አሉ። ጴጥሮስም ከዐሥራ ሁለቱ ጋራ ቆመ ድምፁንም ከፍ አድርጎ እንዲህ ሲል ተናገራቸው። የይሁዳ ሰዎች በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሁላችሁ ይህ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን ቃሎቼንም አድምጡ።
ለእናንተ እንደ መሰላችሁ እነዚህ የሰከሩ አይደሉም ከቀኑ ሦስተኛ ሰዓት ነውና። ነገር ግን ይህ በነቢዩ በኢዩኤል የተባለው ነው እግዚአብሔር አለ በመጨረሻው ቀን እንዲህ ይሆናል ሥጋ በለበሰ ሁሉ ላይ ከመንፈሴ አሳድራለሁ። ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ ትንቢትን ይናገራሉ ጐበዛዝቶቻችሁም ራእይን ያያሉ ሽማግሎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ።
ደግሞም በዚያ ወራት በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎቼ ላይ መንፈስ ቅዱስን አሳድራለሁ ትንቢትን ይናገራሉ። ድንቆችን በላይ በሰማይ ምልክቶችንም በታች በምድር እሰጣለሁ። ደምም እሳትም የጢስ ጭጋግም ይሆናል ታላቅ የሆነ የጌታ ቀንም ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣል። የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል።
ዳዊትም እንዲህ አለ ቅዱስ መንፈስህን ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ ደስ የሚያሰኝ ደኅነትህንም ስጠኝ። በጽኑዕ መንፈስህም አጽናኝ ለዝንጉዎች ሕግህን እንዳስተምራቸው። ሁለተኛም መንፈስህን ትልካለህ ይፈጠራሉ አለ። ደግሞ ቅዱስ መንፈስህ በጽድቅ ምድር ይምራኝ አለ።
ደግሞም በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ ሠራዊቶቻቸው ሁሉ በአፉ እስትንፋስ። ኢሳይያስም እንዲህ አለ በእኔ ህልውና ያለ ያዋሐደኝ ሕይወቴ መንፈስ ቅዱስ ለድኆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ ለተማረኩትም ነፃነትን የእግዚአብሔርንም ዓመት የተመረጠ እለው ዘንድ ላከኝ። ጌታችንም እንዲህ አለ ከእናንተ ጋራ ሳለሁ ይህን ነገርኳችሁ። ነገር ግን አብ በስሜ የሚልከው አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኳችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል። እኔ ሰላምን እተውላችኋለሁ የአባቴንም ሰላም እሰጣችኋለሁ። እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጠው ስጦታ አይደለም።ልባችሁ አይታወክ አትፍሩም ።
እኔ እሔዳለሁ ወደእናንተም ተመልሼ እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ። ሁለተኛ ደግሞ እንዲህ አለ እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚገኝ የዕውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ እርሱ ስለእኔ ይመሰክራል። እናንተም ደግሞ ከመጀመሪያ ከእኔ ጋራ ኖራችኋልና ምስክሮቼ ናችሁ።
እንዳትሰነካከሉ ይህን ነግሬአችኋለሁ ከምኵራባቸው ያወጡአችኋል ከዚህም በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንደሚያቀርብ የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል። እኔም ዕውነት እነግራችኋለሁ እኔ ብሔድ ይሻላችኋል እኔ ካልሔድኩ ግን አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ወደ እናንተ አይመጣምና። ከሔድኩ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ ።
እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይውቅሰዋል። ስለ ኃጢአት በእኔ አላመኑምና ስለ ጽድቅም ወደ አብ እሔዳለሁና እንግዲህም አታዩኝምና ስለ ፍርድም የዚህ ዓለም ገዢ ይፈረድበታልና አላቸው።
የምነግራችሁም ገና ብዙ አለኝ ነገር ግን ዛሬ ልትሸከሙት አትችሉም እርሱ የዕውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና የሚመጣውንም ይነግራችኋል።
እርሱ እኔን ይገልጣል ከእኔም ገንዘብ አድርጎ ይነግራችኋልና ለአባቴ ያለው ሁሉ የኔ ገንዘብ ነውና ስለዚህ ከእኔ ገንዘብ አድርጎ ይነግራችኋል አልኳችሁ። ጥቂት ጊዜ አለ አታዩኝም ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ ታዩኛላችሁ ወደ አብ እሔዳለሁና።
ደቀ መዛሙርቱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ ምንድነው ይህ ነገር ጥቂት ጊዜ አለ አታዩኝም ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ ታዩኛላችሁ ወደ አብ እሔዳለሁና የሚለን። ጌታ ኢየሱስም ሊጠይቁት እንደሚሹ ዐወቀባቸው እንዲህም አላቸው ስለዚህ ነገር እርስ በርሳችሁ ትመራመራላችሁን ጥቂት ጊዜ አለ አታዩኝም ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ ታዩኛላችሁ ስለአልኳችሁ።
እውነት እውነት እላችኋለሁ እናንተ እንደምታዝኑ እንደምታለቅሱ ዓለም ደስ ይለዋል እናንተ ግን ታዝናላችሁ ነገር ግን ኀዘናችሁ ደስታ ይሆናችኋል። ሰው የሆነበትንም ሥራ በፈጸመ ጊዜ ሒዱና አሕዛብን ሁሉ አስተምሩ። ስታጠምቋቸውም በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ በሉ። ያዘዝኳችሁን ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሩአቸው እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ በዘመኑ ሁሉ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ አላቸው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ገዐርጊ_ገዳማዊ
በዚህችም ዕለት የአባ አብርሃም ጓደኛ የከበረ አባ ገዐርጊ አረፈ። ይህም ቅዱስ የክርስቲያን ወገን ነው ወላጆቹ ደጎች ጻድቃን ናቸው። በአደገም ጊዜ የወላጆቹን ከብቶች የሚጠብቅ እረኛ ሆነ። ሁል ጊዜም የምንኵስና ልብስ ይለብስ ዘንድ በልቡ ይመኝ ነበር።
ግንቦት 16- 12 ክንፍ የተሰጣቸው ታላቁ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አቡነ ሐዋርያ ክርስቶስ የተሰወሩበት ዕለት ነው፡፡
ቅድስት በረከቱ አትለየን
ግንቦት 16/2016 #ቅድስት_ኪዳነ_ምህረት
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በምስጋና ከፍ ለምናደርግበት እናታችን #ኪዳነ_ምህረትን በቃል ኪዳኗ እንድታስበን ለምንማፀንበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአሏ እንኳን አደረሰን
👉 #ኪዳነምህረት ስንል የምህረት ቃል ኪዳን ማለት ነው በዚህ ውስጥም ምህረት አድራጊው ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ምህረት ተቀባይም መላው የአዳም ዘር ነው
👉 #እናታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም በምድራዊ ቆይታዋ ዘውትር ወደ #ክርስቶስ_መካነ_መቃብር_ጎለጎታ እየሔደች ትፀልይ ነበር ልጇ እና ወዳጇ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገችውን ልመናና ፀሎት ተመልክቶና ሰምቶ #የምህረት_ቃል_ኪዳንን ሰጣት
👉እንኳን የእናቱን ፀሎት እና ልመና ቀርቶ ዘውትር በሀጥያት የምንዘፈቀውን እኛን ክፉዎቹን የሚሰማ አምላክ ስለ አንቺ ስለ እናቴ ክብርና ፀጋ ስል ይኸው ቃሌ ብሎ #ቃል_ኪዳን አደረገ
👉"ከመረጥሁት ጋር #ቃል_ኪዳኔን አደረግሁ" መዝ፣89፦3
👉ስሟን ለሚጠሩ በእርሷ አማላጅነት ለሚታመኑ በምድር በረከትን በሰማይ የዘለዓለም መንግስትን እንደሚወርሱ የምህረት እና የቸርነት #ቃል_ኪዳን ሰጥቷታል
👉በታላቁም መፅሐፍ ቀስቲቱም በደመና ትሆናለች በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘላለም #ቃል_ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ ኦሪት ዘፍ፣9፣16
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ለእናቱ በሠጣት #ቃል_ኪዳን ያስበን ሀገራችንን ህዝባችንን ከክፉ መከራ ይጠብቅልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ግንቦት 15/2016 #ቅድስት_ኢየሉጣ
#ቅዱስ_ቂርቆስ
#ቅዱስ_ሚናስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሳኑ ስም ለምናመሰግንበት #ለቅዱስ_ቂርቆስ_ለቅድስት_ኢየሉጣ እና #ለቅዱስ_ሚናስ ለወርሐዊ መታሠቢያ በአላቸዉ እንኳን አደረሰን
👉 #ቅዱስ_ቂርቆስ ዕድሜው የሦስት ዓመት ሳለ እናቱ ቅድስት #ኢየሉጣ ከሮሜ ወደ ሌላ ሃገር ሸሽታ ይዛው ሄደች በዚያም የሸሸችውን መኮንኑን አገኘችው የሚያውቋትም ሰዎች ሸሽታ እንደመጣች ስለተረዱ ለመኮንኑ ነገር ሰሩባት
👉መኮንኑም #ቅድስት_አየሉጣን አስጠራትና ስለ አምልኮ ጠየቃት ቅድስት ኢየሉጣም መኮንን ሆይ ዕድሜው ሦስት አመት የሆነው ሕፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እርሱን ጠይቅ አለችው
👉 #ሕፃኑ_ቅዱስ_ቂርቆስም ወደ አለበት ጭፍራውን ልኮ ወደ እርሱ አስመጣው ሕፃኑንም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና “አንተ ደስተኛ ሕፃን ሆይ እንዴት ነህ?” አለው።
👉ሕፃን #ቅዱስ_ቂርቆስም መለሰለት እንዲህም አለው “አዎ እኔ በጣም ደስተኛ ነኝ ደስታዬም ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ሐዘንና ለቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስም ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏልና” አለው።
👉 #እግዚአብሔር አምላክ ኃይልንና ንግግርን ሰጥቶታልና በዚያ ለተሰበሰቡት ሰዎች እስኪደነግጡ ድረስ ብዙ ተናገረ ሕፃኑ #ቅዱስ_ቂርቆስም ንጉሱን መኳንንቱንና ጣዖታቱን ረገማቸው ከብርታቱም የተነሳ አደነቁ።
👉መኮንኑም በአፈረ ጊዜ በየዓይነቱ በሆነ ስቃይ ታላላቆች እንኳ የማይችሉትን ታላቅ አስጨናቂ የሆነ ስቃይን አሰቃየው እናቱ #ቅድስት_ኢየሉጣንም ከእርሱ ጋር እንደ እርሱ በጣሙን አሰቃያት
👉 #እግዚአብሔር ግን ያለ ምንም ጉዳት ያነሳቸው ነበር ብዙዎች አህዛብም ይህን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን በመድሃኒታችን #በኢየሱስ_ክርስቶስ አምላክነት አምነው በሰማእትነት ሞቱ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበሉ።
👉በሕፃኑ #ቅዱስ_ቂርቆስ ላይም የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ አደረበት ታላላቅ ድንቅ ተአምራቶችንም ያደርግ ነበር ብዙዎች በሽተኞችንም ያድናቸው ይፈውሳቸው ነበር
👉ይህንን ያየ መኮንን በታላቅ የናስ ጋን ውስጥ ውሃ ጨምረው በእሳት ያፈሉት ዘንድ አዘዘ የፍላቱም ድምጽ እንደ ክረምት ነጎድጓድ ሆነ ድምጹም በጣም ያስተጋባ ነበር
👉ይህን ያየችና የሰማች እናት #ቅድስት_ኢየሉጣም ፍርሃትና የሃይማኖት ጉድለት ታየባት ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ሁኔታዋን አይቶ ወደ አምላኩ እግዚአብሔር ፀለየ
👉ያን ጊዜ ልዑል #እግዚአብሔር ልቧን ወደ ሰማይ አሳርጎ ለቅዱሳን ሰማዕታት የተዘጋጁ የብርሃን ማደሪያዎችን አሳያት ቅድስት ኢየሉጣም እንደገና በሃይማኖቷ ጸናች እግዚአብሔር አምላኳንም አመሰገነችው ልጇን ሕፃኑን ቅዱስ ቂርቆስንም “ልጄ ሆይ አንተ ከእንግዲህ አባቴ ነህ እኔም ልጅህ ነኝ” አለችው
👉 #ቅድስት_እየሉጣም ለልጇ “ያች የተወለድክባት ዕለት ቀኗ የተባረከችና የተቀደሰች ናት” አለችው የመኳንንቱ ጭፍሮችም እሳት ወደ አለበት ጋኖች ውስጥ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣን በጨመሯቸው ጊዜ የውሃው ፍላት ወድያዉኑ ቀዘቀዘ ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የእሳቱን ኃይል አቀዝቅዞታልና
👉ይህን ያየ መኮንን ሥጋቸው ተቆራርጦ እስከሚወድቅ ድረስ በመቃጥን ውስጥ አድርገው አንዲጎትቷቸው አዘዘ #ከእግዚአብሔርም የታዘዘ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል አዳናቸው
👉መኮንኑም በታላቅ ስቃይ ያሰቃያቸው ዘንድ አስቦ እስኪመክር ድረስ በወህኒ ቤት ዘጋባቸው በዚህን ጊዜ ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ወደ ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስን አረጋጋው አጽናናው ስሙን ጠርተው መታሰቢያ ለሚያደርጉለትም በረከትን እንደሚያገኝና ሌላ ብዙ ቃል ኪዳን ሰጠው
👉ሲነጋ መኮንኑ ከመካነ ምኩናኑ ተቀምጦ ካለበት አስጠርቶ የተመለስከው መመለስ አለን አለው #ቅዱስ_ቂርቆስም አይሆንም አልመለስም አለው ሰይፍ ጃግሬውን ጠርቶ ንሳ ውደቅበት አለው በሰይፍ መታው ጌታም ነፍሱን ከመካነ ዕረፍት ሥጋውንም ነጥቆ #በሰረገላ_ኤልያስ አኑሮለታል እናቱ ቅድስት ኢየሉጣንም በማግስቱ ጥር 16 በሰይፍ አስመትቷት በሰማዕትነት ዓርፋለች
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከሕፃኑ #ቅዱስ_ቂርቆስ እና ከእናቱ #ቅድስት_እየሉጣ እንዲሁም ከሰማእቱ #ቅዱስ_ሚናስ ረድኤት በረከት ያሣትፈን ምልጃ ፀሎታቸዉ አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
በጣና ደሴት ላይ ከሚገኙት ታሪካዊ ቦታዎች ውስጥ አንዱ ‹‹አትማረኝ ዋሻ›› ነው፡፡ ይህም ዋሻ ታሪኩ ከአቡነ ያሳይ ጋር የተገናኘ ነው፡፡ ታሪኩም እንዲህ ነው፡- አትማረኝ ዋሻ በጣና ሐይቅ ደሴቶች መካከል ከሚገኙ ገዳማት መካከል ከማን እንደ አቡነ ያሳይ መድኃኔዓለም አንድነት ገዳም በስተ ምእራብ አቅጣጫ የጣና ሐይቅን ጉዞ ከገታው አንድ ተራራ ሥር የሚገኝ ዋሻ ነው፡፡ ይህ ዋሻ ለብዙ ዘመናት አንድ ታላቅ አባት የጸሎት በዓት አድርገውት ‹‹አትማረኝ›› እያሉ የጸለዩበት ቦታ ነው፡፡ አቡነ ያሳይ ወደ ጣና ደሴት ከአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ እና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ጋር በመሆን በጸሎት ይተጉ እንደነበር ገድላቸው ይናገራል፡፡ ከእግዚአብሔር በተሰጣቸውም ጸጋ በጣና ሐይቅ ላይ እንደ ጀልባ የሚጓዙበት አንድ ትልቅ ጠፍጣፋ
ድንጋይ በጣና ደሴት ላይ ለአገልግሎት በመፋጠን ላይ እያሉ ዛሬ አትማረኝ ዋሻ ተብሎ ወደሚጠራው አካባቢ ሲደርሱ አንድ አባት ዋሻው ውስጥ “አትማረኝ፣ አትማረኝ፣ አትማረኝ” እያሉ ሲጸልዩ ያገኟቸዋል፡፡ አቡነ ያሳይም በሰውዬው ጸሎት በመገረም ቀርበዋቸው ‹‹አባቴ ምን ዓይነት ጸሎት ነው የሚጸልዩት?›› አሏቸው፡፡ ያም አባት ‹‹አባቴ እንደ እርስዎ ያሉ አባት መጥተው ‹አትማረኝ› እያልክ ጸልይ ብሎኝ ነው›› በማለት መለሱላቸው፡፡ አቡነ ያሳይም ‹‹እንዲህ ዓይነት ምክር የሚመክር ጠላት ዲያብሎስ ነው፡፡ ከዛሬ ጀምረው ‹ማረኝ› እያሉ ይጸልዩ በማለት አቡነ ዘበሰማያትን አሰተምረዋቸው ይሄዳሉ፡፡ ‹‹አትማረኝ›› እያሉ ይጸልዩ የነበሩት አባትም ‹‹ማረኝ›› እያሉ መጸለያቸውን ቢቀጥሉም ብዙ መግፋት ሳይችሉ ቀሩና ጸሎቱ ይጠፋባቸዋል፡፡ ወደ ሐይቁ ሲመለከቱም አቡነ ያሳይ ድንጋዩን እንደጀልባ ተጠቅመው እየሄዱ ነው፡፡ ጸሎቱን ያስጠኗቸው አቡነ ያሳይ ርቀው ሳይሄዱባቸው ያ አባት በውኃ ላይ በእግራቸው እየተራመዱ በመከተል ይደርሱባቸዋል፡፡ ከኋላቸውም ሆነው ‹‹አባታችን ያስጠኑኝ ጸሎት ጠፋብኝ፤ እባክዎን እንደገና ያስተምሩኝ›› አሏቸው፡፡ አቡነ ያሳይም ሐይቁን በእግራቸው እረገጡ እስኪሄዱ ድረስ ጽድቃቸው የተገለጠውን የእኚህን አባት መብቃት ተመልከተው ‹‹አባቴ እግዚአብሔር የልብ ነውና የሚመለከተው እንዳስለመዱት ይጸልዩ የእርስዎ ይበልጣል›› ብለዋቸው ሔዱ፡፡ በዚህም ምክንያት ቦታው ‹‹አትማረኝ ዋሻ›› ተብሎ ተጠርቷል፡፡ የአቡነ ያሳይ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ሙሽራው_ቅዱስ_ገብረ_ክርስቶስ
በዚህች ዕለት ሙሽራው ቅዱስ ገብረክርስቶስ ከጫጉላ ቤቱ ወጥቶ የመነነበት ዕለት ነው፡፡ ሙሽራው ገብረ ክርስቶስ ወላጅ አባቱ የቍስጥንጥንያው ንጉሥ ቴዎዶስዮስና እናቱ ንግሥት መርኬዛ በስለት ያገኙት ብቸኛ ልጃቸው ስለሆነ ሃይማኖትን እያስተማሩት በምግባር በእጅጉ ተንከባክበው አሳድገውታል፡፡ የአባቱን ንግሥና በመውረስ ቍስጥንጥንያን እንዲገዛላቸው በመፈለግ ወላጆቹ ለአካለ መጠን ሲደርስ የሮሙን ንጉሥ ሴት ልጅ አጋቡት፡፡ እርሱ ግን ዓለምን ፍጹም በመናቅ የክርስቶስን መስቀል ለመሸከም የተዘጋጀ ነበርና የሠርጉ ዕለት ሌሊት የእርሱንም ሆነ የሙሽይቱን ድንግልና እንደጠበቀ ከጫጉላ ቤት ወጥቶ በመርከብ ተሳፍሮ ሩቅ ሀገር በመሄድ በቤተክርስቲያን ተቀምጦ ከነዳያን ጋር ተደባልቆ በመለመን ለምኖ ያገኘውንም ለሌሎች እየመጸወተ በጾም በጸሎት ተጠምዶ 15 ዓመት ኖረ፡፡
እመቤታችን ተገልጻ ለአንድ የቤተክርስቲያኑ አገልጋይ የገብረ ክርስቶስን ጽድቅ ብትነግረው ምሥጢሩን ለሀገሩ ሁሉ አዳረሰበት፡፡ ሙሽራው ገብረ ክርስቶስም ‹‹ግብሬ ታወቀ፣ ከዚህ ውዳሴ ከንቱ ልሽሽ›› በማለት ወደሌላ ሀገር በመርከብ ሲጓዝ ፈቃደ እግዚአብሔር መርከቢቱን ያለ አቅጣጫዋ ወስዶ አባቱ ደጅ አደረሰው፡፡ ማንነቱን እንደደበቀና ዓለምን ምን ያህል እንደናቃት ይረዳ ዘንድ በአባቱና በንጉሡ ደጅ የኔ ቢጤ ለማኝ ሆኖ ለአባቱ ውሾች የሚሰጠውን ፍርፋሪ እየተመገበ አሁንም 15 ዓመት ሙሉ በትዕግስት ተቀመጠ፡፡
የአባቱ አሽከሮች እንኳን እጣቢና ቆሻሻውን ሁሉ እየደፉበት ሲያሠቃዩት የአባቱ ውሾች ግን የእግሩን ቁስል ይልሱለት ነበር፡፡ በአጠቃላይ ገብረ ክርስቶስ እጅግ የተከበረ የታላቅ ንጉሥ ልጅ ሲሆን ነገር ግን ዓለምን ፍጹም በመናቅ ስለ ጽድቅ ተሰዶ እየለመነ ያገኘውን እየመጸወተ በጾም በጸሎት እየተጋደለ 30 ዓመት ሙሉ ተቀመጠ፡፡ በመጨረሻም ጌታችን እመቤታችንን፣ ቅዱሳን መላእክትን ሁሉ፣ ከገብረ ክርስቶስ በፊት የነበሩ ነቢያትን ሁሉ፣ ሐዋርያትን፣ ጻድቃንን፣ ሰማዕታትን ሁሉ አስከትሎ መጥቶ ቃልኪዳን ከገባለት በኋላ ከጌታችን ጋር አብረውት የመጡት ሁሉ በታላቅ ክብርና ምስጋና እያመሰገኑት ጌታችን ክብርት ነፍሱን በእቅፉ ተቀብሎ አሳርጓታል፡፡
የቁስጥንጥንያው ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስ በቅዳሴ ላይ ሳሉ ከንጉሡ ቤት ሄደው የገብረ ክርስቶስን ሥጋ እንዲያመጡ የእግዚአብሔር ድምፅ ከሰማይ በትእዛዝ መጣላቸውና ሄደው ቢያዩ የገብረ ክርስቶስን ሥጋ በንጉሥ አባቱ ደጅ ወድቆ አገኙት፡፡ በገብረ ክርስቶስም እጅ ላይ በጥቅል ወረቀት የተጻፈ ደብዳቤ ነበርና ወስደው ሊያነቡት ሲሞክሩ ወረቀቱ አልላቀቅ ብሎ ፈጽሞ እምቢ አላቸው፡፡ ብዙ ምሕላና ጸሎት ከተደረገ በኋላ ወረቀቱ ከእጁ ላይ ተላቀቀና ሲነበብ ገብረ ክርስቶስ ስለ አምላኩ ፍቅር ብሎ ለ30 ዓመታት ያሳለፈውን እጅግ አሠቃቂ መከራ በተለይም በአባቱ ደጅ ማንም ሳያውቀው ያሳለፈውን እጅግ አሳዛኝ መከራና በኀዘን የሚያስለቅሰውን ታሪኩን በራሱ እጅ በዝርዝር ጽፎት ተገኝቷል፡፡ ንጉሡ አባቱና ንግሥት እናቱም ይህንን ልጃቸው የጻፈውን መልእክት ባነበቡ ጊዜ የሚሆኑት ጠፋቸው፡፡ በጣም የሚገርመው ደግሞ መጀመሪያ ላይ ወላጆቹ ሚስት አድርገው ያመጡለት የሮሙ ንጉሥ ሴት ልጅ ለባሏ ታማኝ ሆና 30 ዓመት ሙሉ በእናት አባቱ ቤት በትዕግስት ስትጠብቀው መኖሯ ነው፡፡ እርሷም ታሪኩ ሲነበብ ብትሰማ እንደ ዕብድ ሆነች፡፡ የቅዱስ ገብረ ክርስቶስን ሥጋውን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲወስዱ እጅግ አስገራሚ ተአምራት በድውያን ሕመምተኞች ላይ ተፈጽሟል፡፡ ከተአምራቱ የተነሣ መንገዱ በሕዝብ ተጨናንቆ አላሳልፍ ቢላቸው ነገሡ በመንገድ ዳር ወርቅ እየበተነ ሰው ወርቁን ለማንሳት ሲሄድ በፍጥነት ወደ ቤተ ክርስቲያን አድርሰውታል፡፡
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት እና #ከገድላት_አንደበት)
#ግንቦት_14
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ግንቦት ዐሥራ አራት በዚች ቀን ከመንፈሳውያን ሐዋርያት ጋራ አንድነት ያለው የከበረ አባት #ቅዱስ_ጳኩሚስ አረፈ፣ ከሀገረ ፈርማ ሰማዕት የሆነ #አባ_ሲማኮስ አረፈ፣ ድንጋዩን እንደ ጀልባ ተጠቅመው የጣናን ሐይቅ የተሻገሩት #የአቡነ_ያሳይ መታሰቢያ በዓላቸው ነው፣ ሙሽራው #ቅዱስ_ገብረ_ክርስቶስ ከጫጉላ ቤቱ ወጥቶ የመነነበት ዕለት ነው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባ_ዻኩሚስ
ግንቦት ዐሥራ አራት በዚህች ቀን ከመንፈሳውያን ሐዋርያት ጋራ አንድነት ያለው የከበረ አባት ጳኩሚስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ከአባ ጰላሞን ዘንድ መንኲሶ ሲያገለግለው የምንኵስናንም በጎ ሥራ እየሠራ ብዙ ዘመናት ኖረ።
ከዚህም በኋላ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገልጾለት እንደ አባቶቻችን ሐዋርያት የአንድነትን ማኅበር ለመሥራት መነኰሳትን እንዲሰበስብ አዘዘው።
ከዚህም በኋላ ብዙዎች ሰዎችን ሰብስቦ በየቦታው ብዙ ገዳማትን ሠራላቸው። ለሁሉም በእጃቸው ሠርተው በሚአገኙትና በምግባቸው አንድነት እንዲሆኑ በጸሎት ጊዜ በመብልም የሚሠሩትን ሥርዓት ሠራላቸው እርሱ ከሁሉም በላይ አበ ምኔት ሁኖ ከበታቹ ከገዳማት ለየአንዳንዱ አበ ምኔት ሾመላቸው።
ከሀገረ እስዋን ወሰን ከአትፉ ከአክሚም ከተናዱስ እስከ ላዕላይ ግብጽ መጨረሻ ከደቡብም ከባሕራውያን የተመሳቀለ መንገድ ድረስ ሁሉንም ገዳማት በመዞር ይጐበኛቸዋል። ይህም አባት ስለዚህ ዓለም ከንቱ ውዳሴና በመካከላቸውም ጥል እንዳይኖር ከልጆቹ ክህነትን እንዲሾሙ አያሰናብትም ግን ለየአንዳንዱ ገዳም የሚቀድሱላቸውን ቀሳውስት ከዓለም አደረገ።
ሊቀ ጳጳሳት ሐዋርያዊ አትናቴዎስ ወደ ላዕላይ ግብጽ በወጣ ጊዜ ይህን አባት ጳኩሚስን ቅስና ሊሾመው ወደደ። ከእርሱም ሸሸ። የከበረ አትናቴዎስም ልጆቹን የማይናወጽ ቤትን የሠራህ ሆይ ከከንቱ ውዳሴ የራቅህ አንተ ብፁዕ ነህ ልጆችህም ብፁዓን ናቸው ብሎሃል በሉት አባታችሁን አላቸው።
አንድ ጊዜም ሲኦልን ያይ ዘንድ ወደደ እነሆ የእግዚአብሔር መልአክም ነጥቆ አውጥቶ በገነት የጻድቃንን ማደሪያ እንዲሁም በሲኦል የሥቃይን ቦታ አሳየው። ይህም አባት በአንድነት ማኅበር ላይ እያጽናናቸውና ሥርዓትንም እየሠራላቸው አበምኔት ሆኖ አርባ ዓመት ኖረ። ከዚህም በኋላ በእርሱ ፈንታ ደቀ መዝሙሩን ቴዎድሮስን ሹሞላቸው በሰላም አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ሲማኮስ_ሰማዕት
በዚህችም ቀን የምስር ገዢ በሆነ በቡላሚስ ዘመን ከሀገረ ፈርማ ሰማዕት የሆነ አባ ሲማኮስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ቀጭን ልብሶችንና የከበሩ የሐር ልብሶችን የሚሠራ ነው።
ወዳጆችም አሉት እነርሱም ቴዎድሮስና ሲሲኮስ ናቸው ክርስቲያኖችን ሊአሠቃይ መኰንን ቡላሚስ እንደ መጣ በሰማ ጊዜ ይህ ቅዱስ የዚህን ዓለም ክብር ንቀው እስከተዉ ድረስ ባልንጀሮቹን ይመክርና ያስተምራቸው ጀመር።
ከዚህም በኋላ ወዳጆቹን ተሰናብቷቸው ለሀገረ ድሜራ ቅርብ ወደሆነ ወደ ሀገረ በክሩዝ ወጣ መኰንኑንም አንዲቷን ሴት ሲአሠቃያት አገኘው። ወደ እሳት ምድጃም ጨምሮዋት በሰማዕትነት ሞተች። በኋላ ግን እሳቱ ቀዝቃዛ ሆነ ይህ ቅዱስም ይኽንን ይመለከት ነበር።
ከዚህም በኋላ ወደ መኰንኑ ፊት ቀርቦ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ መኰንኑም ታላቅ ሥቃይን አሠቃየው በዚያን ጊዜ ዕድሜው ሃያ ዓመት ነበረ።
ሰቀሉት ከመንኰራኲርም ውስጥ ጨምረው አበራዩት ከእርሱም ብዙ ደም ፈሰሰ ወደ አንዲት ዕውርት ሴትም ደሙ ደርሶ ነካት ያን ጊዜም ድና አየች።
ከዚያም ደግመው በእንጨት ላይ ሰቀሉት እርሱም ይረዳው ዘንድ ወደ ክብር ባለቤት ጌታችን ፈጽሞ ይማልድ ነበር። መኰንኑም ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ ሰያፊውም ይቆርጠው ዘንድ ሰይፉን መዘዘ ኃይል ተነሥቶት ማንቀሳቀስ አልተቻለውም። እንዲሁም ሁለተኛው ሦስተኛው እስከ ዐሥራ አራት ሰይፈኞች ኃይላቸው ደክሞ በምድር ላይ ወደቁ።
ከዚህ በኋላ በአንገቱ ገመድ አስገብተው እስከ ረዢም ተራራ አናት ድረስ ጐተቱት። ነፍሱንም በክብር ባለቤት ጌታችን እጅ ሰጥቶ የምስክርነት አክሊልን ተቀበለ። ከወታደሮች ውስጥ ዲዳና ደንቆሮ ነበረ የቅዱሱን ሥጋ በአየ ጊዜ ጆሮቹ ሰሙ አንደበቱም ተናገረ እድኩ ከተባለ ሀገርም ምእመናን መጥተው የቅዱስ ሲማኮስን ሥጋ ወሰዱ። የድሜራና የታይን የሁለቱ አገሮች ሰዎች ተሰበሰቡ መኰንኑ ቢላሞስም ፈርቶ ሸሸ ከሥጋውም ድንቆች ታላላቅ ተአምራት ለበሽተኞችም ፈውስ ሆነ።
አረማውያንም አይተው በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ተጠመቁ። በሰማዕትነትም ሞቱ ቁጥራቸውም አንድ ሽህ ሰባት መቶ ኃምሳ ሆነ ወንዶችና ሴቶች ወጣቶችም።
ከዚህ በኋላ የቅዱስ ሲማኮስን ሥጋ ተሸክመው በርሙን ወደሚባል አገር በታላቅ ክብር ወሰዱ። የሀገሩ መኰንንም ከራሱ መልካም ልብሶችን አምጥቶ ገነዘው ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠርቶ ሥጋውን በውስጧ አኖረ ከእርሱም ድንቆች የሆኑ ብዙዎች ተአምራት ተገለጡ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_ያሳይ_ዘማንዳባ
ዳግመኛም በዚህች ቀን ድንጋዩን እንደ ጀልባ ተጠቅመው የጣናን ሐይቅ የተሻገሩት የአቡነ ያሳይ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓላቸው ነው፡፡ አቡነ ያሳይ ‹‹ሰባቱ ከዋክብት›› ከሚባሉት የሀገራችን ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ እነዚህም ‹‹ሰባቱ ከዋክብት›› የተባሉት አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ አቡነ ያሳይ ዘማንዳባ፣ አቡነ ሳሙኤል ዘቆየፃ፣ አቡነ ሳሙኤል ዘጣሬጣ፣ አቡነ ታዴዎስ ዘባልታርዋ፣ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤ እና አቡነ ዮሐንስ ዘጉራንቄ ናቸው፡፡ እነዚህን የመላእክትን ሕይወት በምድር የኖሩ ታላላቅ የሀገራችንን ቅዱሳን በአንድ ጊዜ አስተምረውና አመንኩሰው ለጽድቅ ያበቋቸው አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ናቸው፡፡ ‹‹ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን›› የተባሉት አቡነ መድኃኒነ እግዚእ የኢትዮጵያ ብርሃኗ በሆኑት በአቡነ ተክለ ሃይማኖት እጅ ከመነኮሱ በኋላ አቡነ መድኃኒነ እግዚእም በተራቸው ያስተማሯቸውና ያመነኮሷቸው መነኮሳት ቁጥራቸው በውል አይታወቅም፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ለአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ‹‹ስፍር ቁጥር የሌላቸው ከዋክብት ቅዱሳንን›› በመንፈስ ቅዱስ እንደሚወልዱ ትንቢት ተናግረውላቸው ነበር፡፡ የተንቤኑን አቡነ ዐቢየ እግዚእን፣ የዞዝ አምባውን አቡነ አብሳዲን ጨምሮ አባታችን መድኃኒነ እግዚእ ብርሃን ሆነው በጣም ብዙ ቅዱሳንን የለኮሱ ታላቅ ጻድቅ ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ነው ‹‹ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን›› የተባሉት፡፡
አቡነ መድኃኒነ እነዚህንም ሰባቱን ቅዱሳን በአንድ ጊዜ ሲያመነኩሷቸው በዚያው ቅጽበት መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ገዳሙን በብርሃን አጥለቅልቆት ታይቷል፡፡ ከሰማይም የምስክርነት ድምፅ ተሰምቷል፡፡ በዚህም ምክንያት አንድ ላይ የመነኮሱት እነዚህ ሰባቱ ቅዱሳን ‹‹ሰባቱ ከዋክብት›› እየተባሉ ይጠራሉ፡፡ እነዚህም ሰባቱ ከዋክብት የጣናን ባሕር በእግራቸው ጠቅጥቀው ተሻግረው ብዙዎቹን ደሴቱ ላይ ያሉ አስደናቂ የጣና ገዳማትን የመሠረቱት ናቸው፡፡ ከእነርሱም ውስጥ ባሕሩን በእግራቸውም እየረገጡ ጠቅጥቀው የተሻገሩ አሉ፤ በሌላም ቦታ በየብስ የተሰማሩትም ቢሆኑ መጻሕፍቶቻቸውን በአንበሳ ጭነው የተጓዙ አሉ፤ ትልቅ ጠፍጣፋ ድንጋይን እንደጀልባ ተጠቅመው በእርሱ ላይ ሆነው ወደ ደሴት የገቡ አሉ፡፡ አንዱ ዛሬ በዓላታቸውን የምናከብራለቸው አቡነ ያሳይ ናቸው፡፡
እመብርሃን 💕እናታችን
👉የሁላችን እመቤት የሁላችን ንግሥት የሁላችን መዳኛ የሁላችን መመኪያ ድንግል ማርያም ቅድስት ንጽሕት በየጊዜያቱና በየዕለቱም ጽርእት /የጠራች/ ናት።
👉የርስታችን መጀመሪያ፣ የነጻነታችንም ምስክር ለክብራችንም የሽልማታችን ገጥ ናት።
👉ለራሳችንም የሃይማኖት መጠምጠሚያ ሻሽ ለአንገታችንም የወርቅ ማርዳ፣ ለጆሮአችንም የወርቅ ጉትቻ፣ ለዐይኖቻችንም የናጌብ ኩል ናት። ለእጃችንም የወርቅ አንባር ናት።
👉 ለጣቶቻችን የሽልማት ቀለበት ፣ ለእግሮቻችንም የድኅነት ጫማ ለራቁትነታችንም የመመካት ልብስ ናት።
👉 ለራባችን ጊዜም መና ያለባት የወርቅ መሶብ ናት።
👉 ለመጠማታችንም ወይንን የያዘች የወርቅ ጽዋ ናት። ለሞቱት ሕይወትን ትሰጣለች።
👉ለታመሙት ፈውስን ለተቸገሩትም ሀብትን ትሰጣለች። ለተዋረዱትም ክብርን ታቀዳጃለች።
👉ለየአዳም መድኃኒት ሆይ የአቤል መሥዋዕት ተቀባይነትን ያስገኘሽ፣ የሴት ዘሮች መባዣ የሄኖክ ነፍስ ሕይወቱ የማቱሳላ ዘመን እርዝማኔም አንቺ ነሽ።
👉የላሜህ ዕረፍቱ ስምንቱ ነፍሳት ከስጥመት የዳኑባት የኖኅ መርከብ አንቺ ነሽ።
👉ለሴም የተሰጠው ሀብቱ፣ ያፌት የተባረከባት ሀብቱ አንቺ ነሽ። የካም መርገምን ያስወገድሽም አንቺ ነሽ።
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በረከት አይለየን
ከዚህ በኋላም አራዊትን ሁሉ ድባትንም ሰበሰበ። በላይዋም ወሰዱዋቸው አንበሶችም እግርዋን ሳሙ አንዲትም አውሬ ተሸብራ እግርዋን ነከሰቻት ከሰማይም እንዲህ የሚል ቃል መጣ የተመሰገንሽ ኤፎምያ ወጥተሽ ወደ ከበረ ቦታ ነዪ። እንዲህም ገድሏን ምስክርነቷን ፈጸመች እናትና አባቷም መጥተው ገንዘው በአዲስ መቃብር ውስጥ ቀበሩዋት።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎትና ምልጃ ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት እና #ከገድላት_አንደበት)
#ግንቦት_11
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ግንቦት ዐሥራ አንድ በዚህች ዕለት የሱራፌል አምሳላቸው የሆነ ኢትዮጵያዊው ማኅሌታይ #ቅዱስ_ያሬድ የተሰወረበት ነው፣ የቅዱስ ዮስጦስ ሚስት #ቅድስት_ታውክልያ በሰማዕትነት አረፈች፣ የከበረ ኤጲስቆጶስ #አባ_በፍኑትዮስ አረፈ፣ የባሌ መምህር #አባ_አሴር በሰማዕትነት አረፈ፣ #አቡነ_ኤልያስ ዘውቅሮ መታሰቢያቸው ነው፣ በዲዮቅልጥያኖስ መንግሥት ዘመን #ቅዱስት_ኤፎምያ በሰማዕትነት አረፈች፣ #ቅድስት_አናሲማ አረፈች፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ያሬድ_ካህን_ወማኅሌታይ
ግንቦት ዐሥራ አንድ በዚህች ዕለት የሱራፌል አምሳላቸው የሆነ ኢትዮጵያዊው ማኅሌታይ ያሬድ የተሰወረበት ነው። ይህም ቅዱስ ከአባ ጌዴዎን ዘመዶች ወገን ነው እርሱም በኢትዮጵያ አገር ከታነፁ አብያተ ክርስቲያን ለምትቀድም ከአክሱም ካህናት ውስጥ ነው እርሷም አስቀድሞ የክብር ባለቤት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት በውስጥዋ የተሰበከና አምላክን በወለደች በእመቤታችን በከበረች ድንግል ማርያም ስም የከበረች ናት።
ይህም አባ ጌዴዎን ትምህርትን ሊአስተምረው በጀመረ ጊዜ መቀበልም ማጥናትም እስከ ብዙ ዘመን ተሳነው። በአንዲት ዕለትም መምህሩ በእርሱ ላይ ተበሳጭቶ መትቶ አሳመመው። ያሬድም ሸሽቶ ከዱር ውስጥ ገባ ከኀዘኑም ብዛት የተነሣ ከዛፍ ሥር ተጠለለ። ወደ ዛፉ ላይም ትል ሲወጣ አየ ትሉም ከዛፉ እኩሌታ ደርሶ ይወድቅ ነበረ እንዲሁም ብዙ ጊዜ ከአደረገ በኋላ በጭንቅ ከዛፉ ላይ ወጣ።
ቅዱስ ያሬድም የትሉን ትጋት በአየ ጊዜ ወደ መንፈሳዊ መምህሩ ተመልሶ አባቴ ሆይ ይቅርታ አድርግልኝና እንደ ወደድክ አድርገኝ አለው መምህሩም ተቀበለው።
ከዚህ በኋላ በብዙ ልቅሶ ወደ እግዚአብሔር በለመነ ጊዜ ልቡናው ብሩህ ሆኖለት በአጭር ጊዜ የብሉይና የሐዲስ መጻሕፍትን ተምሮ ፈጸመ ዲቁናም ተሾመ።
በዚያም ወራት እንደ ዛሬ በከፍተኛ ቃል የመዝሙር ማኅሌት የለም ነበር በትሑት እንጂ። እግዚአብሔርም መታሰቢያ ሊአቆምለት በወደደ ጊዜ ከኤዶም ገነት ሦስት አዕዋፍን ላከለት እነርሱም በሰው አንደበት ተናግረውት ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ከእሳቸው ጋራ አወጡት በዚያም ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ የሚያመሰግኑበትን ማኅሌታቸውን ተማረ።
ወደ አነዋወሩ ወደ ምድርም በተመለሰ ጊዜ በአክሱም ዳር ወደ ከበረች ቤተ ክርስቲያን በሦስት ሰዓት ገባ በታላቅም ቃል ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ የጽዮንም ደገኛዋ ሰማይን ፈጠረ። ዳግመኛም እንዴት እንደሚሠራት የድንኳንን አሠራር ለሙሴ አሳየው አስተማረው አለ።
ይቺንም ምስጋና አርያም ብሎ ጠራት። የቃሉንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ንጉሡም ንግሥቲቱም ጳጳሱም ከካህናቱ ሁሉ ጋራ የመንግሥት ታላቆችና ሕዝቡ ሁሉ ወደርሱ ሮጡ ሲሰሙትም ዋሉ።
ከዚያም በኋላ ከዓመት እስከ ዓመት በየክፈለ ዘመኑ በክረምትና በበጋ በመጸውና በጸደይ በአጽዋማትና በበዓላት በሰንበታትም እንዲሁም በመላእክት በዓል በነቢያትና በሐዋርያት በጻድቃንና በሰማዕታት በደናግልም በዓል የሚሆን አድርጎ በሦስቱ ዜማው ሠራ ይኸውም ግዕዝ ዕዝል አራራይ ነው።
የሰው ንግግር የአዕዋፍ የእንስሳትና የአራዊት ጩኸት ከዚህ ከሦስቱ ዜማው አይወጣም።
በአንዲት ዕለትም ቅዱስ ያሬድ ከንጉሥ ገብረ መስቀል እግር በታች ቁሞ ሲዘምር ንጉሡም የያሬድን ድምፅ እያዳመጠ ልቡ ተመሥጦ የብረት ዘንጉን በያሬድ እግር ላይ ተከለው ከእርሱም ደምና ውኃ ፈሰሰ። ያሬድም ማኅሌቱን እስከ ሚፈጽም አልተሰማውም።
ንጉሡም አይቶ ደነገጠ በትሩንም ከእግሩ ላይ ነቀለ ስለ ፈሰሰው የደምህ ዋጋ የፈለግኸውን ለምነኝ ብሎ ለያሬድ ተናገረው ያሬድም ላትከለክለኝ ማልልኝ አለው። ንጉሥም በማለለት ጊዜ ወደገዳም ሔጄ እመነኲስ ዘንድ አሰናብተኝ አለው ንጉሡም ሰምቶ ከመኳንንቱ ጋራ እጅግ አዘነ ተከዘም እንዳይከለክለውም መሐላውን ፈራ እያዘነም አሰናበተው።
ከዚህ በኋላም ቅዱስ ያሬድ ወደ ቤተክርስቲያን ገብቶ በታቦተ ጽዮን ፊት ቆሞ ፈጽሞ የከበርሽና የተመሰገንሽ ከፍ ከፍም ያልሽ የብርሃን መውጫ የሕይወት ማዕረግ የሆንሽ የሚለውን ምስጋና እስከ መጨረሻው በተናገረ ጊዜ ክንድ ያህል ከምድር ከፍ ከፍ አለ።
ከዚህ በኋላ ወደ ሰሜን አገር ሒዶ በጾም በጸሎት ተወስኖ ሥጋውን እጅግ እያደከመ ኖሮ ገድሉን በዚያ ፈጸመ። እግዚአብሔር ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጥቶታል።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅድስት_ታውክልያ_እናታችን
በዚህች ቀን የቅዱስ ዮስጦስ ሚስት ቅድስት ታውክልያ በሰማዕትነት አረፈች። በየካቲት ዐሥር እንደ ተጻፈ የእስክንድር ገዢ እርስበርሳቸው ከአለያያቸው በኋላ ቅድስት ታውክልያን ወደ ሀገረ ፃ ወሰዱዋት። በሀገረ ፃ መኰንንም ፊት የመኰንኑ እስክንድርያን መልእክት በአነበቡ ጊዜ መንግሥታቸውን ትተው እንዴት ከመንግሥታቸው ሞትን መረጡ ብሎ አደነቀ።
ከዚህ በኋላ መኰንኑ ሸነገላት ብዙ ታላላቅ ቃል ኪዳኖችንም ገባላት። የከበረች ታውክልያም እኔ የክብር ባለቤት ስለሆነ ስለ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር መንግሥቴን ተውኩ ከልጅነት ባሌም ተለየሁ በልጆቼም አልተጽናናሁም ለመሆኑ አንተ የምትሰጠኝ ስጦታ ምን ያህል ነው ብላ መለሰችለት።
ይህንንም ሰምቶ ታላቅ ግርፋት እንዲገርፉዋት አዘዘ የሥጋዋም ቊርበት እስከሚቆራረጥ ገረፉዋት። ከዚህ በኋላም ከእሥር ቤት አስገቡዋት የእግዚአብሔርም መልአክ ተገለጠላትና ቊስሎቿን አዳናት።
እሥረኞችም አይተው አደነቁ ብዙዎቹም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት አገፉ።
የምስክርነቷ ፍጻሜ በቀረበ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ለከበረች ታውክልያ ተገልጾላት አጽናናት ከክብር ባለቤት ጌታችንም የተሰጡዋትን ቃል ኪዳኖች ነገራት።
በዚያን ጊዜም ራስዋን ይቆርጡ ዘንድ መኰንኑ አዘዘ የሕይወት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለች። ምእመናን ሰዎች መጥተው ለወታደሮች ብር ሰጥተው የቅድስትን ሥጋ ወሰዱ በመልካም መግነዝም ገንዘው የስደቱ ወራት እስኪፈጸም በሣጥን ውስጥ አኖሩዋት።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_በፍኑትዮስ_ገዳማዊ
በዚህችም ዕለት የከበረ ኤጲስቆጶስ አባ በፍኑትዮስ አረፈ። ይህም ከታናሽነቱ በአባ መቃርስ ደብር በአስቄጥስ ገዳም መነኰሰ ታላቅ ተጋድሎንም በመጋደል ብዙ ትሩፋትን ሠራ። አዘውትሮ ይጾም ነበረ ቅጠላቅጠልን ይበላል እንጂ በእሳት የበሰለ አይበላም በገዳሙ ውስጥም መጻሕፍትንና የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ተምሮ ቅስና ተሾመ በዚያም ሠላሳ አምስት ዓመት ኖረ። እነሆ ትሩፋቱና ጽድቁም በሁሉ ዘንድ ታወቀ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ፊላታዎስም ልኮ ወደ እርሱ አስመጥቶ ኤጲስቆጶስ አድርጎ ሾመው።
ኤጲስቆጶስነትም ከተሾመ በኋላ ቅዳሴ በሚቀድስ ጊዜ ካልሆነ በቀር ከቶ ልብሱን አልለወጠም ቅዳሴውንም ሲፈጽም ከጠጉር የተሠራውን ማቅ ይለብሳል።
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❤️ እንዲህ ያስተምራሉ
👉ብቻዉን የሆነ ሰው ወዮለት ምን ማለት ነው
ያላገባ ሰው ወዮለት ማለት ነው
👉ወዮለት ማለት መከራው ብዙ ነው ማለት ነው
👉ቢርበው ምን ለሻሽልልህ የሚለው የለውም
👉ቢያመው ምንህን ባሰህ የሚለው የለውም
👉ቢወድቅ የሚያነሳ የለውም ና
👉ብቻውን ለሆነ ሰው ወዮለት ።