kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሰኔ 9/2016 #አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ

"#እግዚአብሔር በዕልልታ በመለከት ድምፅ ዐረገ መዝ 46.ቁ5"

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ #አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ መታሰቢያ በአል እንኳን አደረሰን

👉አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስ አባታቸው መልአከ ምክሩ እናታቸው ወለተ ማርያም ይባላሉ የተወለዱበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ነው

👉በተወለዱ ዕለት ተነሥተው በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ብለው #ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል የስማቸው ትርጓሜ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ አንድም #የክርስቶስ እስትንፋስ ማለት ነው

👉ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸውና በመንገዳቸው ሁሉ እየመራቸው ነው ያደጉት #መንፈስ_ቅዱስ ልቡናቸውን ብሩህ አድርጎላቸው በ5 ዓመታቸው የቅዱሳት መጻሕፍት ቃላትን፣ ብሉያትንና ሐዲሳትን፣ ድርሳናትንም ጠንቅቀው ዐውቀዋል

👉በተወለዱ በ14 ዓመታቸው ወደ #አቡነ_ኢየሱስ ሞዐ ደብረ ሐይቅ ገዳም ሄደው ከባሕር ዳር ቆመው የሙሴን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር በጸለዩ ጊዜ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ባሕሩን አሻግሯቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተዋል፡፡

👉ለ3 ዓመታት ያህል በኃይቅ ገዳም ለመነኮሳት እንጨት በመልቀምና ውሃን በመቅዳት #ለአባቶች_መነኮሳት ምግብ የሚሆናቸው ዓሣ ከባህር ውስጥ በማውጣት አገልግለዋል፡

👉አባታችን #እስትንፋሰ_ክርስቶስ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ከፆሙ በኋላ ምንም እህል ሳይቀምሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ ለሙሴ በደብረ ሲና እንደሰጠው ለአባታችንም ወደ እርሳቸው መጥቶ ዓሥሩን ቃላተ ኦሪትና ስድስቱን ቃላተ ወንጌል በውስጣቸው የተጻፈባቸው ሁለት ጽላቶችን ሰጥቷቸዋል፡፡

👉አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሠሩ በኋላ ዕለቱን ስንዴ ዘርተው፣ ወይን ተክለው፣ ጽድን ወይራንና ግራርን ተክለው በአንዲት ቀን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ዕለቱን አድርሰዋል ስንዴውን ለመሥዋዕት ወይኑን ለቍርባን በተአምራት አድርሰዋል፡፡

👉አባታችን በጸሎት ላይ እንዳሉ ቅዱስ ሚካኤል ተልኮ መጥቶ አባታችንን በደመና ጭኖ ወስዶ ከጌታችን ከመድኃኒታችን #ከኢየሱስ_ክርስቶስ ፊት አቆማቸው ጌታንም በቅዱሳኑ ሁሉ እንዲባረኩ ካደረጋቸው በኋላ መልአኩን ‹‹ወደ ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ ወደ ኢየሩሳሌም አድርሰው›› ብሎት ኢየሩሳሌምን አሳልሞ ሀገራችን መልሶ አምጥቷቸዋል

👉አባታችን ሁሉንም የኢትዮጵያን ቅዱሳት ገዳማትን ተዘዋውሮ ሲጎበኙ በሕይወተ ሥጋ የሌሉት የየገዳማቱ ቅዱሳን ሁሉ በአካል ይገለጡላቸው ነበር ጎጃም ውስጥ እያስተማሩ፣ !፣ የታመሙትን እየፈወሱ፣ የዕውራንን ዐይን እያበሩና ሙታንን እያሥነሱ ብዙ ካገለገሉ በኋላ ለዘጠኝ ዓመታት በባሕር ውስጥ ገብተው ቁልቁል ተዘቅዝቀው #ለኢትዮጵያ_ፀልየው የምሕረት ቃልኪዳን ተቀብለዋል

👉ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ጌታችን መጥቶ ‹‹ከመነኮሳት ሁሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ ሆይ #ኢትዮጵያንና_ሕዝቦቿን ምሬልሃለሁ ከዚህች ባሕር ውጣ›› በማለት በሞት የሚያርፉበትን ቦታ ነግሯቸዋል፡፡

👉ጻድቁ ወደ ደብረ አሰጋጅ በሚሄዱበት ጊዜ ጸሐይ ልትገባ ስትል ‹‹በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አውግዤሻለሁ ለመስፍን ኢያሱ በገባኦን እንደቆምሽ አሁንም ቀጥ ብለሽ ቁሚ ብለው ፀሐይን አቁመዋል አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስም ደብረ አሰጋጅ ሲደርሱ ፀሐይ አፍ አውጥታ ‹‹አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ እገባ ዘንድ ፍታኝ›› ስትላቸው #እግዚአብሔር_ይፍታሽ ባሏት ጊዜ ጠልቃለች

👉ጻድቁ ሌላው በእጅጉ የሚታወቁበት አንድ ትልቅ ቃል ኪዳን አላቸው በአምላክ ልቡና የሚገኝ፣ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ልቡና የሚገኝ፣ በቅዱስ ሚካኤልና በቅዱስ ገብርኤል ልቡና የሚገኝ እንደ መልክአ መድኃኔዓለም ያለች እጅግ አስገራሚ #ፀሎት አለቻቸው፤ እርሷን ጸሎት በጸለዩ ጊዜ እልፍ ነፍሳትን ከሲኦል ያወጣሉ

👉ጸሎቷም #የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች እያንዳንዱ የሰውነት ክፍሎቹ የተቀበሉትን ጸዋትዎ መከራዎች ሁሉ ታዘክራለች በእያንዳንዱ ክፍልም የጸሎት ማሳረጊያ #አቡነ_ዘበሰማያት ይደግማሉ ንስሓ የገባ ኃጢአተኛ ሰው እንኳን ቢሆን ይህችን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት በጸለየ ጊዜ ሺህ ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ ጌታችን በማይታበል ቃሉ ለአባታችን ነግሯቸዋል

👉እያንዳንዱን #የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች መከራዎቹን የምታዘክረውን ይህቺን በአምላክ ልቡና ያለች ግሩም የሆነች ፀሎት ነፍሳትን ከሲኦል አታወጣም ብሎ የሚጠራጠር ቢኖር መንግስተ ሰማያትን አያያትም ጻድቁ ታኅሣሥ 8 ቀን ተወልደው ሚያዚያ 9 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከፃድቁ ረድኤት በረከት ያሣትፈን #የፃድቁ_አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ምልጃና ፀሎት ሁላችንንም ይጠብቀን የተባረከ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" ✝️💒✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

††† እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† በዓሉ ከሰላሳ ሦስቱ ዓበይት የእመቤታችን በዓላት አንዱ ሲሆን በዚሕች ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል እናቱ እግር ሥር ጠበል አፍልቋል::

††† ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
ድንግል ማርያም አምላክ ልጇን አዝላ ስደት ወጥታ ምድረ ግብጽ ትደርሳለች:: በወቅቱ ከደረሱባት ችግሮች አንዱ ደግሞ ረሃብና ጽሙ ነበር:: እንኳን ለስደተኛ በቤቱ ላለም ረሃብና ጥም እንዴት እንደሚከብድ የደረሰበት ያውቀዋል::

††† ለዛም ነው ሊቁ በቅዳሴው:-
"አዘክሪ ድንግል ረሃበ ወጽምዐ : ምንዳቤ ወኀዘነ : ወኩሎ ዐጸባ ዘበጽሐኪ ምስሌሁ" ያለው::

ታዲያ አንድ ቀን የበርሃው ፀሐይ አቃጥሏቸው ባረፉበት ድንግል እመቤታችን ውኃ ልመና ወጣች:: ብዙ ለመነች : ግን ጥርኝ እንኳ የሚሠጣት አጥታ በሐዘን ተመለሰች:: ስትመለስ ግን ይባስ ብሎ የልጇን ጫማ ሽፍቶች ወስደውት ደረሰች::

ያን ጊዜ ልጇን ታቅፋ "ውኃ ሳላገኝልሕ : ጫማሕንም አሰረቅኩብህ" ብላ ምርር ብላ አልቅሳለች::
"በከየት ወትቤ ማርያም ማዕነቅ::
እምሰብአ ሃገር አልቦ ዘየአምራ ለጽድቅ::
ሰአልክዎሙ ማየ ኢወሀሐቡኒ በሕቅ::
ወአሕጎልኩ ለወልድየ አሳእኖ ዘወርቅ::" እንዳለ ደራሲ::

ይሕንን የተመለከተ ልጇ የቆመችበትን መሬት ቢባርከው ሕይወትነት ያለው ማይ (ጠበል) ፈለቀ:: ጌታችን : እመቤታችን: ዮሴፍና ሰሎሜ ከውኃው ጠጥተዋል::

ሲሔዱ ግን ለእንግዶች ጣፋጭ (መድኃኒት) : ለአካባቢው ሰዎች ግን መራራ ሁኗል::
"ከመ ኢይስተይዋ ሰብአ ሐገር ለይእቲ ማይ አምረራ::
ወለርኁቃንሰ ፈውሰ ወጥዕምተ ገብራ::" እንዳለ መጽሐፍ:: (ሰቆቃወ ድንግል)

ከመቶዎች ዓመታት በኋላም ጌታ ጠበል ያፈለቀበት : ድንግል እመቤታችን የቆመችበት ቦታ ላይ በእመ ብርሃን ስም ቤተ ክርስቲያን ታንጿል:: ቅዳሴ ቤቱም ተከብሯል:: ጠበሉም ሲባርክና ሲፈውስ ይኖራል::

††† የጠበል በዓል †††

†††ዳግመኛ ዕለቱ የጠበል በዓል ተብሎም ይታሠባል:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስለ ጠበል ፈዋሽነት ሁሌ ብታስተምርም በዚህ ቀን ግን ልዩ ትኩረቷ ታደርገዋለች::

እግዚአብሔር በምክንያትም አለምክንያትም መፈወስ ይችላል:: ያለ ምክንያት በቃሉና በወዳጆቹ ቃል አድሮ "ዳን" ይላል:: ወይም ደግሞ በምክንያት በእመት (እምነት) : በጠበል : ቅዱስ ቃሉን በመስማት : በመስቀሉና በመጻሕፍት በመባረክ (በመታሸት) : በቅዱሳን አካል (በልብሳቸው : በበትራቸው : በጥላቸው በአጽማቸው . . .) ይፈውሳል::

እርሱ እግዚአብሔር ነውና በወደደውና በመረጠው አድሮ ያድናል ( ይፈውሳል):: (2ነገ. 5:10, ሐዋ. 3:6, 5:15, 19:11)

††† ዛሬ ግን የጠበል ፈዋሽነት በጉልህ ይነገራል:: (ዮሐ. 5:1, 9:7)

††† አምላከ ቅዱሳን ከደዌ ሥጋ : ከደዌ ነፍስ በምሕረቱ ይሠውረን:: ከድንግል እመቤታችን በረከትም ያሳትፈን::

††† ሰኔ 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.የእመቤታችን ድንግል ማርያም ቅዳሴ ቤት
2.የቅዱስ ውኃ (ጠበል) መታሠቢያ
3.ቅድስት ትምዳ እናታችን
4.ቅዱስ አውሎጊስ
5.አባ አትካሮን

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ)
3.አባ ብሶይ (ቢሾይ)
4.አቡነ ኪሮስ
5.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
6.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት)

††† "ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ::
ግርማው በእሥራኤል ላይ: ኃይሉም በደመናት ላይ ነው::
እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው::
የእሥራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን: ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል::
እግዚአብሔርም ይመስገን:::" †††
(መዝ. ፷፯፥፴፬)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://vm.tiktok.com/ZMrNQDBr6/

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሰኔ 7/2016 #ቅድስት_ሥላሴ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ለአጋእዝተ አለም ቅድስት #ሥላሴ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉 #ምስጢረ_ሥላሴ ስለ ሥላሴ ምስጢር የሚናገር ትምህርት ማለት ነው #እግዚአብሔር አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፋፍለው በአንድነትና በሦስትነት የሚመሰገን #አንድ_ሕያው_አምላክ ነው

👉 #የእግዚአብሔር ሦስትነት ስንል እግዚአብሔር የማይለያይና የማይቀላቀል ፍጹም የሆነ ሦስትነት አለው ማለታችን ነው #የእግዚአብሔር ሦስትነት በስም በግብር በአካል ነው

👉 #እግዚአብሔር በስም ሦስት ስንል ሦስት የተለያዩ ስሞች አሉት ማለታችን ነው እነዚህም #አብ_ወልድ_መንፈስ_ቅዱስ የሚባሉት ሲሆኑ እርስ በርሳቸው አይወራረሱም አንዱ በሌላው ስም አይጠራም ዘፍ.ቁ.1_2 ምሳ.30_ቁ.4

👉 #እግዚአብሔር በግብር ሦስት ነው ስንል ሦስት የተለያዩ የአካል ሥራዎች አሉት ማለት ነው እነሱም መውለድና ፤መወለድ፤ ማስረፅ "የአብ ወላዲ"፣"የወልድ ተወላዲ"፣"የመንፈስ ቅዱስ ሠራፂ" የሚሉት ሲሆኑ የአካል ግብር ይባላሉ መዝ.ቁ.2_7

👉 #እግዚአብሔር በአካል ሦስት ነው ማለት ደግሞ
ለአብ፤ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው።

👉 #ለወልድ፤ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ።

👉 #ለመንፈስ_ቅዱስ፤ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ማለታችን ነው።

👉 #የሦስቱ_የእግዚአብሔር ስሞች ትርጉም

👉 #አብ ማለት አባት ማለት ሲሆን የሚወልድ፤የሚያሰርጽ ወይም የሚያስገኝ ያለ እናት ወልድን የወለደ፤ መንፈስ ቅዱስን ያሰረጸ ነው።

👉 #ወልድ ልጅ ማለት ሲሆን የሚወለድ ወይም ያለ እናት ቅድመ ዓለም፤ ያለ አባት ድህረ ዓለም የተወለደ ነው መዝ.2_7

👉#መንፈስ_ቅዱስ ረቂቅ፤ ልዩ፤ ንፁህ; ከፍጡራን መናፍስት ሁሉ የተለየ ማለት ነው ኢዮ.ቁ.26_13

👉አለምን ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጡ አጋዕዝተ አለም #ቅድስት_ሥላሴ ህይወታችንን በምህረት ቤታችንን በበረከት ይጎብኝልን "አሜን"✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዕረገት በዓት በሰላም አደረሳችሁ

‟ሲባርካቸውም ከነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ።” ሉቃ ፳፬ ÷ ፶፩

#ፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሰንበት_ትምህርት_ቤት
#ፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሚዲያ

Follow us on
👉 /channel/fre_amde_haymanot_media
👉 http://linktr.ee/fre_amde_haymanot_media

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ከጻድቁ ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በረከት ረድኤት ይክፈለን፥በአማላጅነቱ አይለየን።”ኦ እግዚአብሔር አምላኪየ መሐሮሙ ለኩሎሙ ሕዝበ ኢትዮጵያ፤”ይበልልን።
በጻድቁ ቃል ኪዳን ይጠብቀን።በዝቋላ ደብረ ከዋክብት እና በጎጃም አማኑኤል ገዳማትና በሌሎችም አድባራትና አብያተ ክርስቲያናት ስለ ፈሰሰው የንጹሐን ደም ይበቀልልን።ኢትዮጵያ አገራችንን፥ተዋህዶ ሃይማኖታችንን ዳራቸውን እሳት መሀላቸውን ገነት ያድርግልን።

“ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ፥በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ ።ይባእ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሓን። “መዝ:፸፰፥፲።

መዝሙር ፸፰:፩-፲፫።

*“አቤቱ አሕዛብ (ኢ አማንያን) ወደ ርስትህ (ወደ ኢትዮጵያ፥ወደ ቤተ ክርስቲያን) ገቡ፤
*ቤተ መቅደስህንም (እነ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከግብፅ፥እነ አቡነ አረጋዊ ዘጠኙ ቅዱሳን ከታናሽ እስያ መጥተው ተራሮቿን መቅደስ አድርገው የቀደሱባትን ኢትዮጵያን፥አንድም በክርስቶስ ደም ላይ የተመሠረተችውን ቤተ ክርስቲያንን) አረከሱ፤
*ኢየሩሳሌምንም (ኢትዮጵያን አንድም የሰማያዊት ኢየሩሳሌም አምሳል ቤተ ክርስቲያንን) እንደ ተክል ጠባቂ ጎጆ አደረጉአት።(ጠባቂው የአትክልቱን ፍሬ ካነሣ በኋላ ጎጆዋን አቃጥሏት እንደሚሄድ እነዚህም ጥቅሟን ተጠቅመው ኢትዮጵያንም ቤተ ክርስቲያንንም የመከራ እሳት አነደዱባት)።
*የባሪያዎችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ።(በክብር አልተቀበሩም)።
*የጻድቃንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት፤
*ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ (በመላዋ ኢትዮጵያ) እንደ ውኃ አፈሰሱ።
*የሚቀብራቸውም (አጥቦ ገንዞ፥አጥፎ አጎናጽፎ፥ጸሎተ ፍትሐት አድርሶ የሚሸኛቸው) አጡ።
*ለጎረቤቶቻችንም (ለኢ አማንያን) ስድብ ሆንን፤
*በዙሪያችንም ላሉ ሣቅና መዘበቻ።
*አቤቱ እስከ መቼ ለዘለዓለም ትቆጣለህ? (ትፈርድብናለህ? በእነርሱስ እስከ መቼ አትፈርድም?
*ቅንዓትህም እንደ እሳት ይነድዳል? (ለአምላክነትህ ቀንተህ ያመጣኸው መቅሠፍት እስከ መቼ ይነድዳል?
*በማያውቁህም አሕዛብ ላይ ስምህንም በማትጠራ መንግሥት ላይ መዓትህን አፍስስ፤
*ያዕቆብን በልተውታልና (ያዕቆብ ዘነፍስ ክርስቲያኑን በልተውታልና፥)።
*ስፍራውንም ባድማ አድርገዋልና።(ሀገሩን ኢትዮጵያን አፍርሰዋልና)።
*የቀደመውን በደላችንን አታስብብን፤
*አቤተ መሕረትህ በቶሎ ያግኘን፤
*እጅግ ተቸግረናልና።(ባለ መከራ ሆነናልና)።
*አምላካችን መድኃኒታችን (ኢየሱስ ክርስቶስ) ሆይ! ርዳን።
*ስለ ስምህ ክብር ታደገን፤(እኛን አድነህ ስምህ ይመስገን)፤
*ስለ ስምህም ኃጢአታችንን አስተስርይልን።(ስምህን ስንጠራ ስሜ መሐሪ ይቅር ባይ ነው፥ያልከውን ፈጽምልን)።
*አሕዛብ አምላካቸው ወዴት ነው? እናዳይሉን፤
*የፈሰሰውን የባሪያዎችህን ደም በቀል በዐይኖቻችን ፊት አሕዛብ ይዩ።(እኛ እኩሌታችን ተርፈን የእኩሌቶቻችንን ሞት እንዳየን፥እነርሱም የእኩሌቶቻቸውን ሞት ይዩ)።
*የእስረኞች ጩኸት ወደ ፊትህ ይግባ፤
*እንደ ክንድህም ታላቅነት (እንደ ሥልጣንህ ገናናነት) የተገደሉትን ሰዎች ልጆች ጠብቃቸው።
*አቤቱ የተገዳደሩህን መገዳደራቸውን ለጎረቤቶቻችን ሰባት እጥፍ በብብታቸው ክፈላቸው። (የትዕቢታቸውን ብዛት አይተህ ሰባት እጅ ፍዳ አምጣባቸው በፍጹም ተበቀላቸው)።
*እኛ ሕዝብህ ግን የማሰማሪያህም በጎች (ወገኖችህ) ለዘለዓለም እናመሰግንሃለን።
*ለልጅ ልጅም ምስጋናህን እንናገራለን)።


“የጻድቅ መታሰቢያ ለዘለዓለም ነው፤”መዝ:፻፲፩፥፮።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሰኔ 4/2016 #ቅዱስ_ዮሐንስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱስ ዮሐንስ ስም ለምናመሰግንበት ለወንጌላዊዉ ለፍቁረ እግዚእ ቅዱስ #ዮሐንስ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉በመጀመሪያው ቃል ነበረ፣ቃልም #በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፣ቃልም እግዚአብሔር ነበረ፣ቃልም ስጋ ሆነ ዮሐ1፥1-14

👉ወንጌላዊው #ቅዱስ_ዮሐንስ የተለያዩ ስሞች አሉት ከነዚህም ጥቂቶቹ
✝️ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ
✝️ ፍቁረ እግዚእ
✝️ ታኦሎጎስ
✝️ አቡቀለምሲስ
✝️ ቁፅረ ገፅ
✝️ ዮሐንስ ዘንስር

👉 #ቅዱስ_ዮሐንስ እመቤታችንን በአደራ የተቀበለ በአንድ ቤት ልጅ ሆኗት 15 ዓመት የኖረ ቅዱስ አባት ሐዋርያ ነዉ የአለሙን ገዢ ወልዳ ያሳደገች በፀጋ ተሞላታ ተቀድሳ የኖረች እናታችን #ማርያምን በእናትነት የተቀበለ ወንጌላዊው #ቅዱስ_ዮሐንስ በረከት እና ፀሎቱ አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ያን ጊዜም ሒዳ ጥሪቷንና ዋጋው ብዙ የሆነ ጌጥዋን አምጥታ በኤጲስቆጶሱ ፊት ጣለችው እርሱም በፊቷ አቃጠለው።

ከዚህም በኋላ የራስዋን ጠጉር ተላጨች ኤጲስቆጶሱም ማቅ አልብሶ ወደ ደናግል ገዳም ላካት በዚያም ታላቅ ተጋድሎን በፍጹም ልቧ ጀመረች ነፍሷንም እንዲህ እያለች ትገሥጻት ነበር በጭቃና በደንጊያ ወደ ታነፀው ቤት ለመግባት ካልተውሽ በብርሃን ወደ ተሠሩ ቤቶችማ ለመግባት እንዴት ትሆኛለሽ ሁለተኛም በጸሎቷ አቤቱ ቤተ ክርስቲያንህን ከሚጠብቀው የደረሰብኝን ኀፍረት ልሸከመው ያልቻልኩ እኔን በቅዱሳን መላእክቶችህ ፊት አታሳፍረኝ አለች።

ይችም ቅድስት ሰይጣንን ድል እስከ አደረገችው ድረስ ሃያ አምስት ዓመት ስትጋደል ኖረች በዚህ ሁሉ ከገዳም ግቢ ወደ በር አልወጣችም ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈች።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ኤላርዮስ_ሰማዕት

በዚህችም ቀን ደግሞ ኤላርዮስ የሚባል ኤጲስቆጶስ ሰማዕት ሆኖ አረፈ። ይህም ቅዱስ ከሀዲ*ውን ንጉሥ ዮላኪዮስን ጣዖ**ታትን ስለማምለኩ ይገሥጸውና ይመክረው ነበር ንጉሥ ዮላኪዮስም አይሁድ የሰቀሉትን ባለማምለኬ አንተ ከሀ*ዲ ትለኛለህ እነሆ አሁን እኔ አንተን ከሥቃይ ጽናት የተነሣ ያን የተሰቀለውን አምልኮቱን አስተውኻለሁ አለው።

ከዚህ በኋላም ከመኳንንቶቹ ለአንዱ መኰንን ሰጥቶ ባለመራራት ያለማቋረጥ ሁልጊዜ እንዲአሠቃየው አዘዘው መኰንኑም ወስዶ በየራሱ በሆነ ሥቃይ አንዲት ቀን እንኳ ከቶ ሳያቋርጥ ሁልጊዜ እያሠቃየው አንድ ዓመት ሙሉ ኖረ።

በዓመቱም ፍጻሜ በእሳት ውስጥ ጣሉት እርሱም ከእሳት መካከል ቆሞ እግዚአብሔርን ፈጽሞ እያመሰገነ ጸለየ ስለዚህችም ምልክት ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ብዙዎች አምነው በሰማዕትነት ሞቱ።

ከዚህም በኋላ ከአታክልት መካከል እንደ ሚወጣ ሆኖ ከእሳት አወጡት። መኰንኑም ከማሠቃየት በደከመ ጊዜ በእርሱ ላይም የሚያደርገውን በእጣ ጊዜ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡት አዝዞ ቂረጡት በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_ተጠምቀ_መድኅን

በዚህች እለት ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ተጠምቀ መድኅን መታቢያቸው ነው፡፡ ጻድቁ የተወለዱት በአፄ ሱስንዮስ ዘመን በ1610 ዓ/ም ሲሆን ወላጆቻቸው ወልደ ክርስቶስና ወለተ ማርያም ይባላሉ:: ታሕሳስ 2 ቀን እንደ መወለዳቸው ክርስትና የተነሱት ጥር 11 ቀን ነበርና ካህኑ "ተጠምቀ መድኅን" አላቸው:: በምድረ ጐጃም ከበቀሉ ታላላቅ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት አባ ተጠምቀ መድኅን ገና ከሕጻንነታቸው ጀምሮ ጸጋ እግዚአብሔር የጠራቸው ነበሩ::

ሕጻን እያሉ ቃለ እግዚአብሔር መማር ቢፈልጉም አባታቸው በግድ እረኛ አደረጋቸው:: እርሳቸው ግን በሕጻን ልባቸውም ቢሆን ቤተሰብን ማሳዘን አልፈለጉም:: ይልቁኑ ወደ በርሃ ይወርዱና አንበሳውን፣ ነብሩን፣ ተኩላውን ሰብስበው "በሉ እኔ ልማር ልሔድ ስለ ሆነ እስከ ማታ ድረስ ጠብቁልኝ" ብለው ለአራዊቱ አደራ ይሰጣሉ:: አራዊቱ ከበጉ፣ ከፍየሉ፣ ከላሙ ጋር ሲቦርቁ ይውላሉ:: ተጠምቀ መድኅን ደግሞ ዳዊቱን ወንጌሉን ሲማሩና ሲጸልዩ ውለው ማታ ይገባሉ::

ተጠምቀ መድኅን በሕጻንነታቸው ቁርስና ምሳቸውን ለነዳያን በመስጠት በቀን አንድ ማዕድ ብቻ ይቀምሱ ነበር:: 23 ዓመት ሲሞላቸው ወደ መርጡለ ማርያም ሔደው መንኩሰዋል::
ከዚህ ጊዜ በሁዋላ ለ37 ዓመታት በፍጹም ተጋድሎ ኖረዋል፣ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው አገልግለዋል፣ ከጐጃም እስከ ሱዳን ድረስ ወንጌልን ሰብከው በርካቶችን አሳምነው አጥምቀዋል (ካህን ናቸውና) እንዲሁም "7" ገዳማትንና "12" አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል::

ጻድቁ በተሰጣቸው መክሊት አትርፈው በ60 ዓመታቸው በ1670 ዓ/ም (በአፄ ዮሐንስ ዘመን) ጻድቁ ዐርፈዋል:: እግዚአብሔር የምሕረት ቃል ኪዳን የገባላቸው ሲሆን አጽማቸው ዛሬም በጋሾላ ቅዱስ ጊዮርጊስ የእናቶች ገዳም ውስጥ ይገኛል::

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ፣ #ከገድላት_አንደበት እና #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ሰኔ_3

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ ሦስት በዚች ቀን #አባታችን_ዜና_ማርቆስ መታሰቢያቸው ነው፣ በትኅርምትና በተጋድሎ የጸናች #ቅድስት_ማርታ አረፈች፣ #ቅዱሰ_ኤላርዮስ የሚባል ኤጲስቆጶስ ሰማዕት ሆኖ አረፈ፣ ኢትዮጵያዊው ጻድቅ #አቡነ_ተጠምቀ_መድኅን እረፍታቸው ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_ዜና_ማርቆስ

ሰኔ ሦስት በዚች ቀን አባታችን ዜና ማርቆስ መታሰቢያቸው ነው፡፡ ሀገራቸው ጽላልሽ አውራጃ ምድረ ዞረሬ ስትሆን ትውልዳቸው ከነገደ ሌዊና ከእስራኤል ነገሥት ወገን ነው፡፡ ወላጆቻቸው ልጅ በማጣት ሲያዝኑ አንድ ዕለት ሐዋርያውና ወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ ወደ እናታቸው ማርያም ዘመዳ ሌሊት መጥቶ ገድሉና ትሩፋቱ በዓለም ሁሉ የመላ ጻዲቅ ልጅ እንደምትወልድ ነገራት፡፡ ለአባቱ ለቀሲስ ዮሐንስም እንዲሁ ተገልጦለት ‹‹ሚስትህ ማርያም ዘመዳ የካቲት 24 ፀንሳ ኅዳር 24 ቀን ይኸውም በካህናተ ሰማይ በዓል ቀን ትወልዳለች፣ ስሙም ዜና ማርቆስ ይባላል›› በማለት ብስራቱን ነግሮታል፡፡

በወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ ብሥራት መሠረት አባታችን በተወለዱም ዕለት ቅዱስ ዑራኤልና ቅዱስ ሩፋኤል የብርሃን ልብስ አልብሰው በክንፋቸው ሲጋርዱአቸው ለሰዎችም ሁሉ ታይቷል፡፡ በወቅቱም የአባ ሳሙኤል ዘወገግ አባት እንድርያስና የአቡነ ተክለሃይማኖት አባት ቅዱስ ጸጋ ዘአብ እስኪደነቁ ድረስ ይህን በዓይናቸው ተመልክተዋል፡፡ ሁለቱ መላእክትም ከእናታቸው ዕቅፍ ወስደው ወደ ሐዋርያው ማርቆስ መቃብር ወስደው ለማርቆስና ለቅዱሳን ጳጳሳት አስባርከዋቸው መልሰው ለእናቱ ሰጧቸው፣ እናቱ ግን ይህን አታውቅም ነበር፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስም በተወለዱ በሦስተኛው ቀን በእግራቸው ቆመው ‹‹አንድ አምላክ ለሆኑ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ እሰግዳለሁ›› ብለው ሦስት ጊዜ አምላካቸውን አመስግነው ሰግደዋል፡፡ በ40 ቀኑ ሲጠመቅ የሚያጠምቀው ካህን የአባቱ ወንድም እንድርያስ ውኃው ሲፈላ አይቶ ሸሽቷል፡፡ መልአኩም እንዳይፈራ ነግሮት ለእርሱም ተአምር እንደሚደረግለት አስረዳው፡፡ እንድርያስም ዕድሜው 72 ነበርና ራሰ በራ ስለነበር በውኃውም ራሱን ቢታጠብበት ጸጉር አብቅሏል፡፡ ሕዝቡም ሁሉ ይህን አይቶ አደነቀ፡፡ ያችም ውኃ ሌሎች በጣም ብዙ ተአምራትን አደረገች፡፡

አንድ ዓመት በሆነውም ጊዜ ቤተክርስቲያን ውስጥ እየዳኸ ሲሄድ መልአክ በክንፎቹ አቅፎ ወስዶ ጌታችንና እመቤታችን ጋር አቅርቦት አስባርኮታል፡፡ እንዲሁም የ15ቱን ነቢያት፣ የ12ቱን ሐዋርያት የ72ቱን አርድእት፣ ሃይማኖታቸው የቀና የ318ቱን ሊቃውንት፣ የጻድቃንን፣ የሰማዕታትን የእነዚህን ሁሉ በረከት እንዲቀበል ካደረገው በኋላ ወደዚያች ቤተክርስቲያን መለሰው፡፡ ከጳጳሱ ከአቡነ ጌርሎስ ድቁናን ተቀብሎ ከአባቱ ጋር ወደ ሀገሩ ሲመለስ ዘራፊዎች ደብድበው በትራቸውንም ሳያስቀሩ ዘረፏቸው፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስም ወደ ፈጣሪው በጸለየ ጊዜ በትራቸው እባብ ሆና ነድፋ ገደለቻቸው፡፡ በኋላም ወደ አምላካቸው ጸልየው ከሞት እንዲነሱ በማድረግ በአካባቢውም ያሉ ሰዎች ሁሉ በእርሱ አምላክ እንዲያምኑ አድርጓቸዋል፡፡

ከዚህም በኋላ ብሉያትንና ሐዲሳትን ጠንቅቆ ከተማረና ካደገ በኋላ ሚስት አጭተው አጋቡት፡፡ እርሱ ግን በዚያው በሠርጉ ዕለት ማታ ጌታ ‹‹እናትና አባቱን ሚስቱን ቤቱን ንብረቱን ያልተወ ሊያገለግለኝ አይችልም›› ያለውን ቃል አስቦ ሚስቱን እንዲህ አላት፡- ‹‹እኅት ሆይ! የዚህ ዓለም ኑሮ ምን ይጠቅመናል፣ ዓለሙም ፍላጎቱም ያልፋል፡፡ ስለዚህ የነፍሴን ድኅነት ለመሻት እሄድ ዘንድ አሰናብችኝ›› ሲላት እርሷም ‹‹አንተ የተውከው ዓለም ለእኔስ ምን ይጠቅመኛል?›› በማለት ሁለቱም ሰው ሳያያቸው ከጫጉላ ቤታቸው በሌሊት ወጥተው ሄዱ፡፡ ቅዱስ ዑራኤልና ቅዱስ ሩፋኤልም እየመራቸው ዜና ማርቆስን ምሁር ገዳመ ኢየሱስ እርሷን ደግሞ ወደ ቤተ ደናግል ማማስ ደብር አደረሷቸው፡፡ እርሷም ሙትን እስከማስነሣት ድረስ ታላላቅ ተአምራትን እያደረገች ቆይታ ተጋድሎዋን ፈጽማ በጥር 21 ቀን በክብር ዐርፋለች፡፡ ዐርፋ የተቀበችውም በደመና ተነጥቃ ኢየሩሳሌም ከሄደች በኋላ እመቤታችን በተቀበረችበት በጌቴሴማኒ ሲሆን ሁለት አንበሶች ጉድጓድ ቆፍረው ቀብረዋታል፡፡

አባታችንም በምሁር ሀገር ይመለክ የነበረውን ማኮስ የተባለውን ጣ*ዖት በመሬት ውስጥ ቀበረውታል፡፡ ገዥውም ተቆጥቶ በአባታችን ላይ ክፉ ሲያደርግ ‹‹ካላመንክ አንተም እንደ አምላክህ እንደ ማኮስ መሬት ተከፍታ ትውጥሃለች›› ብሎ በተናገረበት ቅጽበት ገዥውን ከነሠራዊቱ መሬት ተከፍታ ዋጠቻቸው፡፡ ከዚያም ፈጥነውና በደመና ተነጥቀው ወደ ግብፅ በመሄድ ከአባ ብንያሚን ቅስና ተቀብለው መጡና መሬት ተከፍታ የዋጠችውን የገዥውን ቤተሰቦች ጨምሮ ብዙ ሺህ የምሁር ሕዝቦችን አስተምረው አጠመቋቸው፡፡ ያንን ገዥም ስለ ተጠመቁ ልጆቹና ሚስቱ ብለው ከ5 ዓመት በኋላ በጸሎታቸው ኃይል ከሞት አስነስተውታል፡፡ በዚሁ ሀገር ከአባ ዜና ማርቆስ ጋር ሳሉ የኢትዮጵያው ጳጳስ አባ ጌርሎስ በድንገት ዐርፈው ሳለ ጻዲቁ ዜና ማርቆስ ጸሎት አድርገው ከሞት አስነሥተዋቸዋል፡፡ ሌላም እንዲሁ በጉራጌ ሀገር ገርዳን የሚባለውን ጣዖት ሰባብረው በውስጡ የነበረውን ሰይጣንን እንደ ትቢያ በኖ እስኪጠፋ ድረስ አስጨንቀውታል፡፡ ሕፃናቱን ጨምሮ ከ124 ሺህ በላይ የሚሆኑትን ሕዝቦችም አስተምረው አጥምቀዋቸዋል፡፡ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤልም ሁልጊዜ እንደ ጓደኛ እያናገራቸው ይረዳቸው ነበር፡፡

አባታችን ዜና ማርቆስ የሚያደርጓቸው እጅግ ድንቅ የሆኑ ተአምራት በሕዝብ ዘንድ ውዳሴን እያመጣ እንዳያስቸግራቸው ብለው ይህን ተአምር የማድረግ ሥራ እግዚአብሔር እንዲያርቅላቸው ይለምኑት ነበር፡፡ ወግዳ በምትባል ሀገር ሄደው በዋሻ ውስጥ ሳሉ አቡነ ተክለሃይማኖት ወደ እርሳቸው መጥተው አብረው በዋሻው ብዙ ተአምራትን እያደረጉ ቆይተዋል፡፡ ለአባ ዜና ማርቆስና ለሌሎች ለብዙ አባቶች የምንኩስና አባት የሆኑት አቡነ ተክለሃይማኖት ትሕትናቸውን ያሳዩ ዘንድ አቡነ ዜና ማርቆስን ያገለግሏቸው ነበር፡፡ ወደ ሞረት ሀገር እንዲሄዱ መልአክ ነግሯቸው ሁለቱም ሄደው በዚያም አብረው ተቀምጠዋል፡፡ ጣዖት አምላኪውን የሞረቱ ገዥ ሊገድላቸው ፊልጎ ከነሠራዊቱ ወዳሉበት ዋሻ ሄደ፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስም ተራራዋን በሥላሴ ስም ባርከው ቢያዟት የገዥውን ጭፍሮች አፏን ከፍታ ዋጠቻቸው፡፡ ገዥውን ድል አሰግድንም በተአምራቸው አሳምነውት አስተምረው አጠመቁት፡፡

ከዚህም በኋላ ቅዱስ ገብርኤል ለአቡነ ተክለሃይማኖት ተገልጦላቸው ወደ ግራርያ ሀገር እንዲሄዱ ስለነገራቸው አቡነ ተክለሃይማኖት የመላእክትን አስኬማ ለአቡነ ዜና ማርቆስ አልብሰዋቸው ዜና ማርቆስንም በደብረ ብስራት እንዲጸኑ ነግረዋቸው ወደ ግራርያ ሄዱ፡፡ ሲሄዱም የደብረ ብስራት ዛፎቹ እንጨቶቹና ደንጊያዮቹ ሁሉ አቡነ ተክለሃይማኖትን እንደ ንጉሥ ሠራዊት ከፊት ከኋላ ሆነው ሸኝተዋቸዋል፡፡ አባታችንም ‹‹የወንድሜን የዜና ማርቆስን ቦታ ትታችሁ ከዚህች ምድር ትሄዱ ዘንድ አልፈቅድምና ሁላችሁ በየቦታችሁ ቁሙ›› ብለዋቸዋል፡፡ ‹‹ሰውም እንኳ ቢሆን ለምንኩስና ወደ እኔ ዘንድ ወደ ግራርያ ከመምጣቱ በፊት ይህን ምድር ሳይሳለም ወደ እኔ አይምጣ›› በማለት ቃልኪዳናቸውን ከደብረ ብስራት ጋር አድርገዋል፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን❤️ እንዲህ ያስተምሩናል

👉ሙስሊሞች ሰልጥነው ሙተው እንዲህ ይላሉ።
👉የመጀመሪያው ሀይማኖት ሙስሊም ነው
👉እናንተ እኮ ክርስቲያን የምትሆኑት ከ40 ቀን በኋላ ነው ይላሉ።

ነገር ግን አይደለም

መልስ

👉እስከ 40 ቀን ድረስ ክርስትና የማንነሳው  ሙስሊሞች ስለሆን አይደለም ።

እንዴት? 

👉አንዲት ሴት ከፈሳሽ የምትነፃው ወንድ ልጅ ከወለደች በ33 ኛውቀን ነው
👉ሙሴ ኦሪት ዘሌዋውያን 12፡1 ላይ የመንፃት ህግ ብሎ 7ት ቀን ሰርቷል
👉33 + 7 = 40  ይሆናል።

ስለዚህ

👉በቤተክርስቲያን ውስጥ የፍጡር ፈሳሽ እንዳይፈስ
👉የሴቲቱ ደም ሳይቆም ቤተክርስቲያን እንዳትገባ
👉ስለ ቤተክርስቲያን ክብር ነው እንጂ ሙስሊሞች ስለሆን አይደለም።

👉ሌላ አዳም በ40 ቀን ገነት እንደገባ የገነት አምሳል ቤ/ን አለች
👉ቤተክርስቲያን ትትሜሰል በጽርሐ አርያም ዘላዕሉ እንዲል
👉ቅድስት ቤተክርስቲያን በላይኛይቱ ሰማይ በጽርሐ አርያም ትመሰላለች
👉ስለዚህ አዳም ገነት እንደገባ

እኛ ደግሞ

- አማናዊት ገነት ከተባለችው
-የሰላም ከተማ ከሆነችው
-የብርሃን ምሰሶ ካላት
- ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፡መላእክት፡ ሐዋርያት ፡
- ነብያት ፡ ፃድቃን : ሰማዕታት ፡ደናግላን ፡ መነኰሳት ፡
-ካህናት ፡ ዲያቆናት : አናጉንስጢስ ፡ መዘምራን ፡ አበው ፡ እመው ካሉባት

👉በገነት አምሳል የግድ 40 ቀን መጠበቅ ስላለብን  በዚህ ምክንያት እኛ በ 40 ቀን እንጠመቃለን።


🎤ሴቶች ለምንድን ነው በ 80 ቀን የሚጠመቁት ሲባል

👉1ኛ ሔዋን በ80 ቀን ገነት ስለገባች
👉2ኛ  ሴት ከወለደች ከፈሳሽ ነጻ መሆኛ ቀን  በ66 ኛ ቀን
       የሙሴ ሕግ ከፈሳሽ ነፃ መኾኛ ቀን  14 ኛ ቀን
       ድምር 66 + 14 = 80 ቀን

🎤እንዲት ሴት መንታ ብትወልድ መቼ ወደ ቤተክርስቲያን ትሄዳለች
ማለት አንድ ወንድ አንዲት ሴት ብትወልድ

👉ወንድ ከወለደች ወንዱ በ ሞግዚት ይጠመቃል
👉ሞግዚት ማለት  በእህት በአክስት በጎረቤት በሌላ  ሴት ታዝሎ ሂዶ ይጠመቃል

ለምን?
👉እሷ ስለሴቲቱ ምክንያት 80 ቀን መጠበቅ ስላለባት
👉ስለዚህ እሷ  በ 80 ቀን ሴት ልጇን ይዛ ታሰጠምቃለች
👉ወንዱ ግን በሞግዚት ይጠመቃል ማለት ነው

👉ኢየሱስ ክርስቶስ❣️ በእውነት ኃጢአታችንን አጠበልን
👉ክርስትያኖች  ደስ ሊለን ይገባል
👉በልቡናችን ንጹህ መንፈስ ተስሎብናል
👉እግዚአብሔርን የመምሰል ኃይል ተሰጥቶናል
👉ዛሬ  አንዳንድ ወጣት ሴቶች ፈረንጅን ለመምሰል
👉በተሌቭዥን መስኮት የሚያዩያቸውን ሴቶችን ለመምሰል
👉ልብሳቸውን አሳጥረው ከመታጠቂያቸው አድርሰው ቆንጠል ቆንጠልእያሉ ነው
👉እግዚአብሔርን መምሰል ለእናንተ በቂ ነው
👉ፈረንጅ መምሰል እንስሳትን መምሰል አያስፈልግም

👉እግዚአብሔርን መምሰል በቂ ሀብት ነው ።

ይሄን ሃብት የተሰጠነው መቼ ነው ካላችሁ ?

በ 40 በ 80 ቀን ስንጠመቅ ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🌼🌼🌼 እነሆ🌼🌼🌼

እነሆም ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ ዳን ፲:፳፩
▶ሚካኤል◀
አዲስ ዝማሬ በዘማሪ ዲ/ን መርሃ ጽድቅ // መሳይ ቢቂላ
የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ሰኔ 11 ከምሽቱ 3:00 በዘማህደር ቲዮብ // በዘማህደር የቴሌግራም ቻናል //በዘማህደር የፌስቡእ አካወንት ይለቀቃል ሁላችሁም ሼር በማረግ ለሌሎች አጋሩ።zemahidertube?si=EAEAplYRmsxnJWwC" rel="nofollow">https://youtube.com/@zemahidertube?si=EAEAplYRmsxnJWwC 👈 Follow

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❤️ እንዲህ ያስተምረናል።

👉ቃልህ ምንም ያህል ቢሆን በንዴት ስትናገር ሁሉንም ነገር ታበላሻለህ።"

👉 "ብል ልብስን እንደሚያላግጥ ሰውንም ቅናት ይበላል።"

👉 "እግዚአብሔር የሚጠይቀው ጥቂት ነው, ግን ብዙ ይሰጣል."

👉 "እያንዳንዱ ሰው የህይወቱ ሠዓሊና ቀራፂ ነው።"

👉 "ጸሎት" ሥር፣ ምንጭ፣ የሺህ በረከት እናት ናት።"

👉 "የሥጋ ጾም የነፍስ መብል ነው።"

👉 "ሀብታም ብዙ ያለው ሳይሆን ብዙ የሚሰጥ ነው።"

👉 "ክብር ለነገሩ ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሁን!"

👉 በትንንሽ ነገር ታማኝ መሆን ትልቅ ነገር ነው።

👉 "በህፃናት ትምህርት ውስጥ ዋናው ግብ ማስተማርእና የመልካም ህይወት ምሳሌን መስጠት ነው."

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✞ “እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።
” አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከኛ ጋር ሆነ ማለት ነው።
የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ይሆን ዘንድ ሰው ሆነ፤ ስሙምአማኑኤል ተባለ፤ ትርጉሙም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር” ማለት ነውና ማቴ. ፩፡ ፳፫፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1TON= 600 BIRR 🤑😱

ለማስጀመር:
1,ይህን ሊንክ ተጠቅመው START ይበሉት 👉/channel/preton_drop_bot?start=ee4312b0-beea-4927-bd9c-49273af3d41e

2,@preton_eng የሚለውን ንኩት እና JOIN ይበሉት።

3, JOIN ካሉ በኋላ CHECK THE SUBSCRIPTION የሚለውን ይንኩ።

ከዛ በፊት የሚመጣሎትን 1 የመደመር ጥያቄ መመለስ እና ቋንቋ ENGLISH ማድረግ አይርሱ!

ለወዳጅ ዘመዶ ሊኩን በመላክ ይጋብዙ!

መልካም እድል!

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://moneyeasilytbq.buzz/80376071153407
Ere guys yehe neger yelele migerm new be website new miseraw be task becha ena invite bemaderg ke 200usd jemero mawetat yechalal demo be commercial bank mawetat yechalal tolo jemerut 100%ewenet new

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❤️ እንዲህ ያስተምረናል።

👉ጸሎት የነፍስ ብርሃን ነው,

👉የእግዚአብሔርን እውነተኛ እውቀት ይሰጠናል.

👉በእግዚአብሔርና በሰው መካከል የሚደረግ አስታራቂ አገናኝ ነው።

👉በጸሎት ነፍስ ወደ ሰማይ ትወጣለች እና በሚያስደንቅ ሁኔታ ጌታን ታቅፋለች።

👉ይህ ስብሰባ ህጻን በእናቱ ላይ እንደሚያለቅስ እና ጥሩውን ወተት እንደሚፈልግ ነው።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሰኔ 8/2016 #ፃድቁ_አባ_ኪሮስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ አባታችን #አቡነ_ኪሮስ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉 #አቡነ_ኪሮስ አባታቸው ንጉስ ዮናስ እናታቸው እንስራ
ይባላሉ እሊህም #እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ቅዱሳን ናቸው ሀገራቸው ሮም ሲሆን በታህሳስ 8 ቀን ተወለዱ የመጀመሪያ ስማቸው ዲላሶር ይባል ነበር

👉በኋላ አባታቸዉ ከሞቱ በኋላ ሀብት ንብረታቸዉን ተካፍለዉ ለድሆች ከመፀወቱ በሑዋላ ከአባ #በቡነዳ_ገዳም ገቡ

👉በ17 አመታቸው ስርአተ ምንኩስናን ተምረው ከአባ በቡነዳ እጅ ስርአተ #ምንኩስናን ተቀበሉ ከዚህ በሁዋላ በፆምና በፀሎት ተወስነው ኖሩ

👉ስለ አለም መከራ ለ 40 ዘመን ተኝተው ሲፀልዩ እላያቸው ላይ ሳር በቅሎባቸው ሳለ #መላዕክት መጥተው ተነስ ቢሉት አዳም የፍጡርን ቃል ሰምቶ ወድቋልና ጌታም ድምፁን ያሰማኝ አሏቸው በኋላም #ኪሩቤል አንስቶ ወስዶ ገነት አሳይቷቸው በመጨረሻም ጌታችን ቃል ኪዳን ሰቷቸዋል

👉ቃል ኪዳናቸውም መካኖችን ልጅ የሌላቸው #ገድላቸውን
አቅፈው ቢያለቅሱ #ፀበሉን ቢጠጡ ስምሕን ቢጠሩ የመካኒቱን ማሕፀን እከፍታለሁ

👉ህፃናት የሚሞትባቸው #እንዳይሞትባቸው አደርጋለሁ በንፁህ ገንዘቡ ቂም እና በቀልን ሳይዝ በሕግ በስጋ ወደሙ ለፀና ሰው በስምህ በተሰራው #ቤተክርስቲያን ጧፍ ዘይት ያበራ መገበሪያ ያመጣውን ልጅ እሰጠዋለሁ ብሎ ጌታችን ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል

👉ከዚህም በኋላ በተወለዱ በ 270 አመታቸው ሐምሌ 8 ቀን አርፈዋል የፃድቁ #አቡነ_ኪሮስ እረድኤታቸው አማላጅነታቸው ከሁላችን ጋር ፀንቶ ይኑር የተባረከ #ቀዳሚት_ሰንበት ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እንኳን ለእመቤታችን እግዝዕትነ
ማርያም በዓል አደረሰን።
"የጌታዬ እናት።"
ሉቃስ 1፤43

ሰኔ 8 ቀን
ከ33ቱ የእመቤታችን
በዓል አንዱ ነው።
እመመቤታችን ከልጇ ከአምላክ ወሰብእ
ቅዱስ አማኑኤል ጋር በስደታቸው ወራት ከደረቅ
አለት ላይ ውሐን ያፈለቁበት እለት ነው።
ከዚህም ምንጭ ህሙማነ ስጋ እየጠጡ ይፈወሱ ነበር።
የሕይወት ውሐ ምንጭን ከሆድዋ ያፈለቀች
የጌታችን የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጅዋ አማልዳ ፍቅርን ትናኝብን።
ዘረኝነት ያጠወለገው ፍቅራችንን ከይሲን አስወግዳ በፍቅር ታለምልመን ከክፉ ደዌ ከቀሳፊ ነገር ትሰውረን ሙኃዘ ፍስሐ የደስታን ዜና ታሰማን ከአፈር ዘሪ ከአብሎ መስካሪ ከወንጌል
ሰባሪ የጸሎቷ ኃይል ይታደገን።
አሜን አሜን አሜን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

➕ ➕ ➕ ዕርገተ ክርስቶስ ➕ ➕ ➕
<< ደቀ መዛሙርቱን ከባረካቸው በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ ፤ በአባቱም ቀኝ ( ዕሪናም ) ተቀመጠ ፤ የተቀመጠውም በባሕርይ መለኮቱ ብቻ አይደለም ፤ በተዋሐደው ትስብእትም ጭምር እንጂ ፤ አካላዊ ቃል ባሕሪያችንን ሲዋሐድ እኛን ወደዚኽ ክብር ለመመለስ ነበርና ። ... እግዚአብሔር ሲሆን ስለ እኛ ሰው ኾነ ፤ በፈቃዱ መከራ መስቀልን በተዋሐደው ሰውነቱ ተቀበለ ፤ በተዋሐደው ሰውነቱ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ፤ በተዋሐደው ሰውነቱም ዐረገ ፤ በሕያዋንና በሙታን ላይ ይፈርድ ዘንድም ዳግመኛ በክበበ ትስብእት ይመጣል >> / ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ /
አሜን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በበዓለ ዕርገትኽ ለኛ ለሰው ልጆች ምህረት ቸርነት ፍቅር አንድነት ሰላም ጤና እንድትሰጠን ስንል እንማጸናለን ። ለዘለዓለሙ አሜን ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሰኔ 6/2016 #በአለ_ዕርገት (40ኛዉ ቀን)

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን #ለኢየሱስ_ክርስቶስ #በአለ_ዕርገት አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉 #እግዚአብሔር በእልልታ በመለከት ድምፅ #ዐረገ መዝ.46/47፥5

👉አምላካችን #ክርስቶስ ከትንሣኤ በኋላ አርባ ቀን እየታያቸዉ ሲያስተምራቸዉ ቆይቶ ደቀ መዛሙርቱ እያዪት ማረጉን የምናስብበት እለት ነዉ ከጌታችን አበይት ዘጠኝ በአላት አንዱ #ዕርገት ነዉ

👉እናንተ ግን ከላይ ሀይልን እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ ነገር ግን #መንፈስ_ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ በአለም ሁሉ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ ብሎ ከተናገራቸዉ በኋላ እነሱ እያዪት ከፍ ከፍ አለ ደመናም ተቀበለችዉ

👉እርሱም ወደ ሰማይ ሲያርግ ሐዋርያት ትኩር ብለዉ ሲመለከቱት እነሆ ነጫጭ ልብስን የለበሱ ሁለት መላእክት በአጠገባቸዉ ቆሙ እነሱም እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ወደ ሰማይ የወጣዉ #ኢየሱስ_ክርስቶስ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ይመጣል አሏቸዉ የሐዋ.1ቁ 9-11

👉አምላካችን #ኢየሱስ_ክርሰቶስ ከእርገት በአል ረድኤት በረከት ያሣትፈን ዳግም ሲመጣ ከቅዱሳኑ ጋር ይደምረን መልካም በአል ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❣️ እንዲህ ያስተምረናል።

👉"ማንም በድህነቱ አያለቅስ፣ አለም አቀፉ መንግሥት ተገልጧልና

👉ማንም ስለ በደሉ አያልቅስ፣ ይቅርታ ከመቃብር ተገልጧልና
👉ማንም ሞትን አይፈራ፣ የአዳኝ ሞት አርነት አውጥቶናልና።
👉እስረኛ ሆኖ ቀርቷል አጠፋው።

👉ወደ ሲኦል በመውረድ ገሃነምን ምርኮ አደረገ።
👉 ሥጋውን ሲቀምስ አማረረው።
👉ኢሳይያስም ይህን ትንቢት ተናግሮ፡- ሲኦል በታችኛው ክልል ባገኘህ ጊዜ ተናደድኩ አለ።

👉ፈርሷልና ተናደደ።
👉 ተሳለቀበትና ተበሳጨ።
👉ተገድሏልና ተናደደ።
👉ሥጋ ወስዶ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አገኘው።
👉 ምድርን ወስዶ መንግሥተ ሰማያትን አገኘ።
👉የሚታየውን ወስዶ በማይታየው ላይ ወደቀ።

👉ፈርሷልና ተናደደ።
👉 በሰንሰለት ታስሮ ነበርና ተናደደ።

❣️ሞት ሆይ መውጊያህ የት አለ? ሲኦል ሆይ ድልህ የት አለ?

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/3hZckz7wxyM?si=CI1uUPXCXUtNLG75

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አባታችን ዜና ማርቆስ በኤልያስ ሠረገላ ሆነው እግዚአብሔርን ወደማያውቁት ወደ አዳል ሕዝቦች ሄደው ከጣ*ዖት አምላኪው ንጉሥ ከአብደልማል ፊት ወንጌልን ሲያስተምሩ ንጉሡ በጦር ወግቶ ገድሏቸዋል፣ ነገር ግን መልአኩ ሩፋኤል መጥቶ ከሞት አሥተስቷቸዋል፡፡ የንጉሡን ጣዖ*ትና አገልጋዮቹን መብረቅ ከሰማይ ወርዶ ሲያጠፋቸው ንጉሡ ሠራዊታቸው ደግሞ በመሬት ላይ ወድቀው ቀርተዋል፡፡ ከዓርብ እስከ ሰኞም ድረስ ጨለማ ሆኖ ከቆየ በኋላ ከአባታችን ከተወጋ ጎናቸው የፀሐይ ብርሃን ወጥቶ ለንጉሡ አብደልማል አብርቶለታል፡፡ እርሱም አምኖ ከነቤተሰቡ የተጠመቀ ሲሆን ሚስቱም በአረማውያን ዘንድ ለክርስቶስ ምስክር ሆና አንገቷን ተሰይፋ ሰማዕትነትን ተቀብላለች፡፡ በሀገሪቱም የተጠመቁት ሰዎች ቁጥር ከስምንት መቶ ሺህ በላይ ናቸው፡፡

ከዚህም በኋላ አቡነ ዜና ማርቆስ እንደ ሐዋርያትም ደመና በመጥቀስ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ሄደው ሁሉንም የተቀደሱ ቦታዎችን ተሳልሟዋል፡፡ ከጌታችን መቃብር ላይ አፈር ዘግነው ከዮርዳኖስም ወንዝ ውኃ ቀድተው ለንስር አሞራዎች አሸክመው ወደ ገዳማቸው በማምጣት በደብረ ብስራት ምድር ካለው አፈርና ውኃ ጋር ጨምረውታል፡፡ ጌታችም ‹‹ይህችን ምድርህን እንደ ኢየሩሳሌም አድርጌልሃለሁ›› የሚል ቃልኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡ አባታችን ከደብረ ሊባኖስ አውራጃ ራሱን ያስመልክ የነበረን ሰይጣን ገዝተው ይዘው እስከ ደብረ ብስራት ድረስ የቤተክርስቲያን መሥሪያ እንጨት አሸክመውታል፡፡ በዚያም እንጨት በመሸከም ሲያገለግላቸው ኖሯል፡፡

አባታችን ዜና ማርቆስ ወደ ዋልድባ በመሄድ ከአባ ሳሙኤል ጋር ተገናኝተው እንዲሁም ከሌሎች በርካታ አባቶች በየቦታው እየሄዱ በረከት ተቀብለዋል፡፡ ወደ ትግራይም በመሄድ የተሰዓቱ ቅዱሳንን ገዳማት ተሳልመው ወደ ሰሜንም ሄደው ዜማውን ሲያዜም ያሳያቸው ዘንድ ወደ ቅዱስ ያሬድ መቃብር ሄደው ሰባት ቀን ሲማጸኑ ከቆዩ በኋላ ወደ አክሱም ጽዮን ሄደው በዚያ ከቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱስ ኤፍሬምና ከቅዱስ አባ ሕርያቆስ ጋር ሆኖ እነርሱ ድርሰታቸውን ሲያነቡ ያሬድ ደግሞ ድርሰታቸውን እያዜመው ተገልጠውላቸዋል፡፡ አባታችን ወደ ላሊበላም ሄደው ከቅዱስ ላሊበላ በረከትን ተቀብለዋል፡፡ ወደ ጣና ደሴትም ሄደው በዚያ ካሉ ቅዱሳን ተባርከዋል፡፡ ሐይቅ እስጢፋኖስም አባ ኢየሱስ ሞዐ ጋር በመሄድ እንዲሁ ተባርከዋል፡፡ በታናሽ ደመናም ወደ ብሔረ ሕያዋን ተነጥቀው ሞትን ካልቀመሱት ከሄኖክ፣ ከኤልያስና ከዕዝራ በረከትን ተቀብለዋል፡፡ ወደ እስላም ሀገርም በመሄድ ለአንድ ዓመት ቆይተው በዚያ ያሉ ሕዝቦችን በተአምራቸውና በትምህርታቸው አሳምነው አጥምቀዋቸዋል፡፡ ጌታችን በምድር ላይ ብዙ ቃልኪዳን ከሰጣቸው በኋላ ወደ ሰማይ አውጥቶ ገነትንና ሲኦልን ሁሉን አሳይቷቸዋል፡፡

አቡነ ዜና ማርቆስ 8 እንጀራን አበርክተው 8ሺህ ሰዎችን በመመገብ ጌታችንን መስለውታል፡፡ ቀድሰው ሕዝቡን ሁሉ ሲያቆርቡ ቢመሽባቸው ፀሐይን እንደ ኢያሱ ገዝተው አቁመዋታል፡፡ በታኅሣሥ ወር መባቻ አባታችን በገዳመ ደንስ በረሃ ያገኛት ተአምረኛዋ ሥዕለ ማርያም ወዳለችበት ቤተክርስቲያን ሄደና ለመቀደስ ሠራዒ ካህን ሆኖ ተሠየመና እንደሚገባ የቅዳሴውን ሥርዓት ጀመረ፡፡ ማዕጠንት ይዞ እየዞረ የቤተ ክርስቲያኑን በሮች በሚያጥንበት ጊዜ ሥጋ ወደሙን ለመቀበል እርስ በእርሳቸው ሲጨናነቁ የልጆቹ መነኮሳትን ብዛት ተመለከተ፡፡ ያን ጊዜም በልቡ አሰበ፣ እንዲህም አለ፡- ‹ይህን ያህል ያለውን ሰው ቅዱስ ቊርባን ማቀበል እንዴት ይቻላል? ይህ ሁሉ ሰው በተራ እስከሚቀበል ድረስ ፀሐይ ይገባል፣ መሽቶ ሌሊትም ይሆናል› አለ፡፡ ከዚህም በኋላ ዐይነ ልቡናውን ወደ ሰማይ አቅንቶ ‹አቤቱ ጠላቶቹን እስከደመሰሰና ለእስራኤል ልጆች ርስታቸውን እስካካፈለ ድረስ ለኢያሱ ፀሐይን በገባዖን ያቆምክ አንተ ነህ፤ ዛሬም ቅዱስ ሥጋህን ክቡር ደምህን ለእነዚህ ባሮችህ ቅዱሳን መነኮሳትና ለሕዝቦችህ እስከማቀብላቸው ድረስ እንዲሁ በቸርነትህ ብዛት ፀሐይን አቁማት› ብሎ በጸለየ ጊዜ ፀሐይዋ ወዲያውኑ ቆመች፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዳሴውን ጨርሶ ሕዝቡን ሁሉ አቆረባቸው፡፡››

ቅዱስ አባታችን በምሁር ኢየሱስ ገዳም ከሬብ በሚባል ዋሻ ውስጥ 40 ዓመት ዘግተው ተጋድለዋል፡፡ በዚህም ሳሉ መልአክ የዕረፍታቸውን ዕለት ታኅሣሥ ሦስት ቀን እንደሚሆን ስለነገራቸው ታኅሣሥ አንድ ቀን ወደ ገዳማቸው በመሄድ ቀድሰው ሕዝቡን ሁሉ ሲያቆርቡ ቢመሽባቸው ፀሐይን ለሁለተኛ ጊዜ እንደ ኢያሱ ገዝተው አቁመዋታል፡፡ አባታችን ዜና ማርቆስ የዕረፍታቸውን ዕለት ከመልአኩ ከተረዱ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አሏቸው፡- ‹‹ከዚህ ዓለም የምለይበት ጊዜ ደርሷልና ወደ ፈጣሩዬ እሄዳለሁ፣ እኔ ሽማግሌ አባታችሁ የምመክራችሁን ስሙ፣ ከበጎ ሥራ ሁሉ አስቀድማችሁ እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ፣ ፍቅር ሰማያዊ መንግሥትን ለማግኘት በባለሟልነት ወደ እግዚአብሔር ፊት ያደርሳልና›› ብለው መከሯቸው፡፡ ዳግመኛም ጾመኛ ነኝ አትበሉ አሏቸው፡፡ ‹‹ስለ ነፍሳችሁ ድኅነት፣ ከመከራና ከጥፋትም ሁሉ ለማምለጥ በምትጾሙ ጊዜ እንዲህ እየጾማችሁ ሳላችሁ ስለምትሹት ግብር ወደ ዓለም ሰዎች ብትደርሱና በጾም ቀን ሲበሉና ሲጠጡ ብታዩአቸው መብልና መጠጥን በሚወዱ ሰዎች ፊት በውጭ በአደባባይ ‹ዛሬ የጾም ቀን ስለሆነ እኛ እንጾማለን› አትበሉ፡፡ ስለ እናንተ መጾምና ስለ እነርሱም አለመጾም አንዳች አትናገሩ፣ ባለመጾማቸውም አትንቀፏቸው፡፡ ስለ ሌላ ሥራ ወደማይጾሙ ሰዎች ብትደርሱ ግን በጾም ዕለት ወንድሞቻችን ‹ኑ አብረን እንብላ› ቢሏችሁ እኛ እንጾማለን አትበሉ፣ እንዲህ በሉ እንጂ፡- ‹ወደ እናንተ ከመምጣታችን በፊት ከቤት በልተናል፣ ጠግበናል› ስትሏቸው እናንተ እንደምትጾሙ ያውቃሉ፡፡›››

ከዚህም በኋላ አቡነ ዜና ማርቆስ ታኅሣሥ ሁለት ቀን የደቀ መዛሙርቶቻቸውን እግር ሲያጥቡ ውለው አስቀድሞ መልአኩ እንደነገራቸው ታኅሣሥ ሦስት ቀን በ140 ዓመታቸው ነቢይም፣ ሐዋርያም፣ ካህንም፣ ባለራእይም፣ የሀገራችንም ብርሃን የሆኑት ጻዲቁ አባታችን በክብር ዐርፈዋል፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስት_ማርታ_ተሐራሚት

በዚህች ቀን በትኅርምትና በተጋድሎ የጸናች ቅድስት ማርታ አረፈች። ይቺም ቅድስት ከምስር ተወላጆች ውስጥ ነበረች ወላጆቿም እጅግ ባለጸጎች ነበሩ ከታናሽነቷም ጀምራ የረከሰ ዝሙትን የምትወድ ነበረች የከተማ ጐልማሶችና ታላላቆችም በሥውር ወደርሷ እየመጡ ያመነዝሩ ነበር። ከዚህ በኋላም ሥራዋ ተገለጠ የርኲሰት ሥራንም በግልጥ አብዝታ የምትሠራ ሆነች።

ክብር ምስጋና ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የከበረ ልደቱ በዓል በሆነ ጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደች ልትገባም በፈለገች ጊዜ የቤተ ክርስቲያኑ ጠባቂ ከለከላት እንዲህም አላት አንቺ በምግባር የረከስሽ ስለሆነ ወደ ከበረች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መግባት አይገባሽም ይተዋትም ዘንድ አባበለችው እርሱ ግን ከለከላት በመካከላቸውም ታላቅ ጸብ ሆነ።

ኤጲስቆጶሱም ጩኸት ሰምቶ ተነሥቶ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ደጃፍ ደረሰ ማርታንም በአያት ጊዜ የእግዚአብሔር ቤቱ የከበረና የነጻ እንደ ሆነ አታውቂምን አንቺም የረከስሽ ስለሆንሽ ወደ እግዚአብሔር ቤት ትገቢ ዘንድ አይገባሽም አላት።

በዚያን ጊዜም አለቀሰች ንስሓ እገባለሁ እንጂ ወደዚህ ሥራ እንግዲህ አልመለስም ብትቀበለኝም እመነኲሳለሁ አለችው። ኤጲስቆጶሱም ገንዘብሽንና ጥሪትሽን ሁሉ ወደዚህ አምጥተሽ በፊትሽ ካላቃጠልነው አላምንሽም አላት።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን፡፡ 



ይህ የጽሁፍ መጠይቅ የተዘጋጀው በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ፣ በአዲስ አበባ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጥምረት እንዲሁም በደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ እና መካነ ጎልጎታ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ ፍቁረ እግዚእ ሰንበት ት/ርት ቤት በአንድነት የተዘጋጀው የመጀመሪያ ዙር የሱባኤ ጉባኤ ትምህርት ክፍል የቡድን ሁለት (2) ተማሪዎች ነዉ።
ይህንን የጽሑፍ መጠይቅ ለመሙላት ፈቃደኛ ሰለሆኑልን እናመሰግናለን።


ይህን መጠይቅ በምትሞሉበት ጊዜ እኛም መጠይቁን ያዘጋጀነው ማን እንደሞላው የማናቅ መሆኑን በእግዚአብሔር ስም  ልናስረግጥላችሁ እንወዳለን በመሆኑም ሳትሳቀቁ በነጻነት እንድትሞሉ በአክብሮት እንጠይቃለን

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSeQUJT7OmuDEvGpI9Q5h6HPgVL3KiPfjMcySMlW-gI47iDXYA/viewform?usp=sf_link

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ❤️ እንዲህ ያስተምረናል።

👉ኃጢአት ስትሠሩ እንጂ ንስሐ ስትገቡ አታፍሩ።

👉 የማይቆሰሉት የማይዋጉ ብቻ ናቸው።

👉 "ሰዎች ከኃጢአት እንዲርቁ የማሰብ ኃይል አላቸው."

👉 "በጥቃቅን ነገሮች ለመደሰት ለምን አትማርም - በጣም ብዙ ናቸው."

👉 "ያለ እርዳታ መምራት በቀላሉ የማይቻል ነው

የጸሎት፣ በጎ ሕይወት።

👉 "አእምሮን ከማሰልጠን እና የወጣቶችን ልማድ ከመፍጠር የበለጠ ምን ሥራ አለ?"

👉 "ትንኞች ከሰዎች ጋር ሲነጻጸሩ እንዲሁ ነው።

ፍጥረት ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር ሲወዳደር።


👉"የሥልጣን ፍቅርን ያህል ቤተ ክርስቲያንን የሚከፋፍላት የለም።"

👉 "ንብ ከሌሎች እንስሳት የበለጠ የተከበረች ስለምትደክም ሳይሆን ለሌሎች ስለምትደክም ነው።"

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ግንቦት 29/2016 #ቅዱስ_በዐለ_ወልድ
#ፅንሰት_ልደት_ትንሣኤ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን በዚህ ቀን እመቤታችን #ቅድስት_ድንግል_ማርያም የከበረ መልአክ የቅዱስ ገብርኤልን የምሥራች የሠማችበት አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ የተወለደበት የከበረዉን #ትንሣኤውን የገለጠበት ወርሐዊ መታሰቢያ ነዉ

👉እንዲሁም በዚህች ቀን #አለም_የተፈጠረበት የጌታችንን ዳግመኛ #ምፅአቱን የምንጠባበቅበት እለትም ጭምር ነዉ

👉በዚህች ቀን ለእመቤታችን ለቅድስት #ድንግል_ማርያም የከበረ #መልአክ_ገብርኤል_የምሥራች የነገረበት ድኅነትን የተመላች ታላቅ በዓል ናት በዚህም የከበረ ወንጌል ምስክር ሁኗል እንዲህ ሲል

👉ኤልሳቤጥ በፀነሰች በስድተኛው ወር #መልአኩ_ገብርኤል የገሊላ ክፍል የሆነች ናዝሬት ወደምትባል አገር ከዳዊት ወገን ለሆነ ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደታጨች ወደ አንዲት ድንግል #ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ

👉የድንግሊቱም ስም #ማርያም ነው መልአኩም ወደርሷ ገብቶ ደስተኛ የሆንሽ ደስ ይበልሽ ፀጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው አንቺ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ አላት እርስዋም አይታ ከንግግሩ የተነሣ ደንግጣ እንዴት እንዲህ ያለ ሰላምታ ይቀበሏል ብላ አሰበች

👉መልአኩም እንዲህ አላት ማርያም ሆይ #በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻልና አትፍሪ እነሆ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ስሙንም #ኢየሱስ ትይዋለሽ እርሱ ታላቅ ነው የልዑል #እግዚአብሔር ልጅም ይባላል

👉 #እግዚአብሔር አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል ለያዕቆብ ወገንም ለዘላለም ነግሦ ይኖራል ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም አላት

👉ማርያምም መልአኩን ወንድ ሳላውቅ ይህ እንደምን ይሆናል አለችው መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት መንፈስ ቅዱስ መጥቶ ያድርብሻል የልዑል ኃይልም ያጸናሻል ከአንቺ የሚወለደው ከሶስቱ አካል አንዱ የልዑል #እግዚአብሔር ልጅ ይባላል

👉እነሆ ዘመድሽ ኤልሳቤጥም እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ፀንሳለች ወንድ ልጅም አገኘች ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው #ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና #ማርያምም እነሆኝ የእግዚአብሔር አገልጋይ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለችው።

👉ያን ጊዜም ድንግል ስትሆን ረቂቅ ፅንስን ተቀበለች የእግዚአብሔር አካላዊ ቃል #ወልድ_ዋህድ ለኩነተ ሥጋ ወርዶአልና ይህም አንድ ባሕርይ አንድ ህልውና ሲሆን ከሦስቱ አካላት አንዱ ነው

👉ከዓለም መፈጠር አስቀድሞ የነበረ በማይመረመር ድንቅ በሆነ ተዋሕዶ እንዴትም እንደሆነ በማይታወቅ በቅድስት #ድንግል_ማርያም ማሕፀን አደረ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ተፀንሶ በህቱም ድንግልና #ታህሣሥ_ሀያ_ዘጠኝ ቀን ተወለደ

👉በዚያን ጊዜም የኋላ ኋላ መለየት ከቶ የሌለውን ፍጹም ሰውነት ነሥቶ ተዋሐደ መለኮቱ ከትስብእቱ ጋራ ያለ መለያየት አንድ ሆኖአልና ይቺም ዕለት የበዓላት ሁሉ በኩር ናት በእርሷም #የዓለም_ድኅነት ተጀምሮዋልና

👉ዳግመኛ በዚህችም ዕለት ደግሞ በመድኃኒታችን በከበረችና ልዩ በሆነች #ትንሣኤው የዓለም ድኅነት ሆነ በረቀቀ ጥበቡ ሠላሳ ሦስት ዓመት ያህል በምድር ላይ ሥራውን ሠርቶ በፈጸመ ጊዜ በፈቃዱ ሕማማተ መስቀልን ተቀብሎ ሙቶ ከተቀበረ በኋላ በሦስተኛው በዚች ቀን #በሃያ_ዘጠኝ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቷልና

👉በዚች ቀን አስቀድሞ ደጅ ለሚጠኑት በዓለም ላሉ ሰዎች ሰው በመሆኑ ድኅነታቸውን አበሠራቸው እንዲሁም ደግሞ በዚች ዕለት ከሲኦል በመዳን #ሙታንና_ሕያዋን ደስ አላቸው

👉በዚህም በጌታችንና በመድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በሥጋ መነሣት መነሣታቸውን አረጋገጡ የከበረ ጳውሎስ በመነሣቱ ክርስቶስ የሙታን በኵር ሆነ እንዳለ እርሱ ለሙታን በኵራቸዉ ነዉና

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከበአሉ በረከት ሁላችንንም ያሣትፈን ዳግም ሲመጣም ከቅዱሳኑ ጋር ይደምረን የምንሰማዉን የምናየዉን ክፉ ነገር ሁሉ ወደ በጎ ነገር ይቀይርልን

👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸዉ የምናስባቸዉ ፃድቁ አባታችን #አቡነ_እጨጌ_ዮሐንስ በምልጃ ፀሎታቸዉ ይጠብቁን "አሜን" ✝️💒✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🙏🙏🙏🙏 ቃል ሂወት ያሰማልን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://www.youtube.com/live/XeeodKNQnXM?si=JgkDIC7y15v0QNAT

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ግንቦት 28/2016 #ቅዱስ_አማኑኤል
#ርዕሰ_አበዉ_አብርሃም_ይስሐቅ_ያዕቆብ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ለአባቶቻችን አምላክ #ለቅዱስ_አማኑኤል አመታዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉 #አማኑኤል ማለት #እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ማለት ነው

👉 #የአብርሐም_የይስሐቅ_የያእቆብ አምላክ ቅዱስ #እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን በቸርነቱ ይጠብቀን

👉#አማኑኤል ማለት፣የአምላክ ሰላም፣#የእግዚአብሔር እርቅ የጌታ አንድነት ማለት ነው

👉 #አማኑኤል ማለት "አማኑ" እና "ኤል" ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው አማኑኤል ማለት #እግዚአብሔር ከኛ ጋር ማለት ነዉ

👉ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅንም ትወልዳለች ስሙንም #አማኑኤል ትለዋለች ትርጉሙም #እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው ( ኢሳ 7፥14)

👉ቸሩ #ቅዱስ_አማኑኤል ለእኛ ስትል በመስቀል ሞት የገለፅከዉን ፍቅርህን እያሰብን ከሐጢአት እና ከአመፅ እንድንርቅ ፍቅርህ በልቦናችን ይታተም #በትንሣኤህ የኛን ትንሣኤ የገለፅክልን ጌታችን እናመሰግንሃለን ክብር ኃይልና ምስጋና ለአምላካችን #ለቅዱስ_አማኑኤል ይሁን

👉በዚህ እለት በመታሰቢያ በአላቸዉ የምናስባቸው የአባቶቻችን #የአብርሃም_የይስሐቅ_የያዕቆብ ረድኤትና በረከት አይለየን የታላቁ ነብይ #የነብዩ_ኢሣያስ ምልጃ ፀሎቱ ይጠብቀን"አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ግንቦት 28/2016 #ቅዱስ_አማኑኤል
#ርዕሰ_አበዉ_አብርሃም_ይስሐቅ_ያዕቆብ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ለአባቶቻችን አምላክ #ለቅዱስ_አማኑኤል አመታዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉 #አማኑኤል ማለት #እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ማለት ነው

👉 #የአብርሐም_የይስሐቅ_የያእቆብ አምላክ ቅዱስ #እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን በቸርነቱ ይጠብቀን

👉#አማኑኤል ማለት፣የአምላክ ሰላም፣#የእግዚአብሔር እርቅ የጌታ አንድነት ማለት ነው

👉 #አማኑኤል ማለት "አማኑ" እና "ኤል" ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው አማኑኤል ማለት #እግዚአብሔር ከኛ ጋር ማለት ነዉ

👉ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅንም ትወልዳለች ስሙንም #አማኑኤል ትለዋለች ትርጉሙም #እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው ( ኢሳ 7፥14)

👉ቸሩ #ቅዱስ_አማኑኤል ለእኛ ስትል በመስቀል ሞት የገለፅከዉን ፍቅርህን እያሰብን ከሐጢአት እና ከአመፅ እንድንርቅ ፍቅርህ በልቦናችን ይታተም #በትንሣኤህ የኛን ትንሣኤ የገለፅክልን ጌታችን እናመሰግንሃለን ክብር ኃይልና ምስጋና ለአምላካችን #ለቅዱስ_አማኑኤል ይሁን

👉በዚህ እለት በመታሰቢያ በአላቸዉ የምናስባቸው የአባቶቻችን #የአብርሃም_የይስሐቅ_የያዕቆብ ረድኤትና በረከት አይለየን የታላቁ ነብይ #የነብዩ_ኢሣያስ ምልጃ ፀሎቱ ይጠብቀን"አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…
Subscribe to a channel