ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu
ሰኔ 16/2016 #ጰራቅሊጦስ (በዓለ ሃምሣ)
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ አብይ ፆምን አስፈፅሞ #ለብርሐነ_ትንሣኤዉ እና #ለብርሐነ_እርገቱ በሠላም አድርሶን እነሆ #በዐለ_ሐምሣ (ለመጨረሻዉ ፋሲካ) ደርሰናል ክብር ሁ ለመድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ይሁን። ከጌታ አበይት በዐላት አንዱ ለሆነዉ ለበዓለ #መንፈስ_ቅዱስ አመታዊ ክብረ በዐል እንኳን አደረሰን
👉 #ጰራቅሊጦስ ማለት በልሳነ ጽርዕ #መፅናንዒ ማለት ነው ትርጕሙም በጽርዕ (ግሪክ) ቋንቋ ናዛዚ (የሚናዝዝ)፣ መጽንዒ (የሚያጸና)፣ መስተፍሥሒ (የሚያስደስት) ማለት ነው
👉ከሦስቱ አካላት አንዱ ለሆነው የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መጠሪያ ስም ነው #በዓለ_ጰራቅሊጦስ "በዓለ ጰንጠቆስጤም" እየተባለ ይጠራል ይኸውም በግሪክ ቋንቋ #በዓለ_ኀምሳ የፋሲካ ሃምሳኛ ዕለት፣ በዓለ ሠዊት (የእሸት፣የመከር በዓል) ማለት ነው (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ገፅ.፱፻፮- ፱፻፯)
👉በዓለ #ጰራቅሊጦስ ወይም በዓለ #ጰንጠቆስጤ ከዘጠኙ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዐበይት በዓላት አንዱ ሲሆን #መንፈስ_ቅዱስ_ለሐዋርያት_የወረደበትን ቀን የምናስብበት በዓል ነው
👉ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ_ካረገ በኋላ እመቤታችን ቅድስት #ድንግል_ማርያም፣12ቱ ደቀ መዛሙርት፣ 72ቱ አርድእት፣ ፭፻ው ባልንጀሮችና 36ቱ ቅዱሳት አንስት በኢየሩሳሌም ከተማ በአንድነት ሆነው ለጸሎት ይተጉ ነበር በሚያርግበት ጊዜም “እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ #በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ” ሲል ለሐዋርያቱ በገባላቸው ቃል መሠረት ባረገ በአስረኛው ቀን #መንፈስ_ቅዱስን ልኮላቸዋል ሉቃ.24፥49
👉በሐዋርያት ሥራ እንደ ተፃፈው #በበዓለ_ጰራቅሊጦስ ማለዳ ሁሉም በአንድ ቦታ ተሰብስበው ሳሉ እንደ #ዐውሎ_ነፋስ ያለ ድምፅ ድንገት ከሰማይ መጥቶ የነበሩበትን ቤት ሞላው
👉በመቀጠልም #እንደ_እሳት_የተከፋፈሉ_የእሳት_ላንቃዎች በሁሉም ላይ ሞላባቸው በዚህ ጊዜ ሁላቸውም መንፈስ ቅዱስን ከተሞሉ በኋላ #መንፈስ_ቅዱስ ባደላቸው መጠን በየአገሩ ቋንቋዎች ሁሉ መናገር ጀመሩ ሐዋ.2 ቁ.1-4 ጌታችን መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት የላከበት ይህ ዐቢይ በዓል #ጰራቅሊጦስ ተብሎ ይጠራል
👉ጰራቅሊጦስ ምስጢር እዉቀት ገላጭ ነዉ ሐዋርያት በበዐለ #ጰራቅሊጦስ መንፈስ ቅዱስ ፀጋዉን ካደላቸዉ በኋላ 72 ቋንቋ ተገልፆላቸዋል በዚህም የቅዱሳን መፃህፍት ምስጢር ተገልፆላቸዋል የመድኃኒታችን #የኢየሱስ_ክርስቶስ ትምህርትን ለማስተዋል ችለዋል
👉በፅርሐ ፅዮን በሐዋርያት ላይ የወረደው #መንፈስ_ቅዱስ ያናገረው ቋንቋ የሚሰማ የሚደመጥ የሚታወቅ የሚተረጎም ነበረ ዛሬ የጌታ ተከታይ ነን የሐዋርያት መንፈስ የወረደው ለኛ ነዉ በአዲስ ቋንቋ በልሣን እንናገራለን የሚሉን ሰዎች ንግግራቸው የማይደመጥ የማይተረጎም የተናገሩትን እንኳን መልሳችሁ ተናገሩ ቢባሉ እንኳን የማይደግሙት እንደሆነ እንረዳለን #መንፈስን_ሁሉ_አትመኑ ተብሎ ተፅፏልና እንመርምር
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በቅዱስ መንፈሱ ያፅናን ሀይልና ብርታትን ይስጠን የቅዱሳን አባቶቻችን የቅዱሳን ሐዋርያት ፀሎትና ልመና አይለየን የተባረከ የተቀደሰ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
#ሰኔ_14
#ቅዱሳን_አባ_አክራና_ዮሐንስ_አብጥልማና_ፊልጶስ
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ ዐሥራ አራት በዚች ቀን ቅዱሳን አባ አክራና፣ ዮሐንስ፣ አብጥልማና ፊልጶስ በሰማዕትነት ሞቱ። ይህም ቅዱስ አክራ ከግብጽ ደቡብ ይምንሑር ከሚባል አገር ሰዎች ወገን ነው ስሙ ፊልጶስ የሚባል ወንድም ነበረው እነርሱም ባለጸጎች ነበሩ ስማቸው ዮሐንስና፣ አብጥልማ ከሚባል ሁለት ቀሳውስት ጋራ ሰማዕታት ይሆኑ ዘንድ ተስማሙ አራቱም ቀርጥስ ወደሚባል አገር ሔዱ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በመኰንኑ ፊት ታመኑ።
መኰንኑም በቀስቶች እንዲነድፏቸው አዘዘ ግን ቀስቶች አልነኳቸውም። ሁለተኛም እሳትን አንድደው በሚነድ የእሳት ምድጃ ውስጥ ይጨምሩአቸው ዘንድ አዘዘ እንዲሁም አደረጉባቸው ጌታም መልአኩን ልኮ አዳናቸው።
ከዚህም በኋላ በፈረስ ጅራት ላይ አሥረው ከቀርጥስ ከተማ እስከ ይምንሑር አገር ድረስ ይጐትቷቸው ዘንድ አዘዘና ይህንንም አድረጉባቸው ግን ምንም ምን ጉዳት አልደረሰባቸውም።
ከዚህም በኋላ ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጧችው አዘዘ ከይምንሑር ከተማም አውጥተው ራሶቻቸውን ቆረጡአቸው። ፃ ከሚባል አገር ሰዎች መጥተው የቅዱስ አባ አክራን ሥጋውን ወሰዱ ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንም ሠርተው ሥጋውን በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ታላላቅ ድንቆችና ተአምራት በብዛት ተገለጡ። እንዲሁም የእነዚያን የሦስቱን ቅዳሳን የፊልጶስን፣ ለአብጥልማንና የዮሐንስን ሥጋቸውን ከይምንሑር ከተማ ሰዎች መጥተው ወሰዱ በመልካም ልብሶችም ገነዙአቸው ጥሩ ቤተ ክርስቲያንም ሠርተው ሥጋቸውን በውስጧ አኖሩ ከእነርሳቸውም ቁጥር የሌለው ድንቅ ተአምር ተገለጠ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን። በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ)
/channel/hamster_kombaT_bot/start?startapp=kentId1878761888
Play with me, become cryptoexchange CEO and get a token airdrop!
💸 2k Coins as a first-time gift
🔥 25k Coins if you have Telegram Premium
👑🌿" በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ፥ ወዳዘጋጀሁልህም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፥እነሆ እኔ መልአኬን በፊትህ እልካለሁ "👑
(ኦ.ዘጸ 23:20)
🌺 🌿 🌺 🌿 🌺
⛪️ 🌱" I am sending a head of you.He will protect you as your travel. He will lead you to the place I have prepared " ⛪️ (Exodus 23:20)
❣️እንኳን አደረሰን 🌿 ⛪️ 🌿 አደረሳችሁ 🙏
👑 የስሙ ትርጉም እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው?
🌺.ሚካኤል ማለት ሚካ= መሃሪ
ኤል= እግዚአብሔር
🥀 "ሚካኤል " ማለት መሃሪ እግዚአብሔር ማለት ነው🥀
🌿 ይህ ታላቅ መልአክ በሳጥናኤል ምትክ ስልጣን የተሰጠው ሩህሩህ ፣ መሃሪ ፣ ጠባቂ ሊቀ መላእክት ነው🙏❣️🙏
👑 ሰኔ 12 ቀን, ሊቀ መልአኩ ምን ተዓምር ያደረገበት ይሆን?
📌 1. የባህራንን የሞት ደብዳቤ ወደ ህይወት የቀየረበት🙏
📌 2. ቅድስት አፎሚያን ዲያብሎስን ድል እንድትነሳ የረዳበት ታላቅ እለት ነውና ክብርና ምስጋና ይገባዋል🙏👑🙏
✝️🌿 መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ, ለባህራንና ለቅድስት አፎሚያ ፈጥነህ እንደደረስህ ለእኛም ከመጣብንን መከራ፣ ስቃይ፣ ሠላም ማጣት ታድነን ዘንድ ፈጥነህ ድረስልን🙏❣️
⛪️🌿በረከትህ፣ ፍቅርህ፣ አማላጅነትህ አይለየን
https://youtu.be/uufOkIFTXw0?si=CQmge1EFdp03cFhA
Читать полностью…https://youtu.be/rmtKNn8MgOQ?si=NB6qPlLQz2pKo6OB
Читать полностью…https://www.facebook.com/bujustar/videos/997866875071285/?mibextid=10F2z1T9z1KXOHtQ
Читать полностью…ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❤️ እንዲህ ያስተምረናል።
👉ጸሎት የነፍስ ብርሃን ነው,
👉የእግዚአብሔርን እውነተኛ እውቀት ይሰጠናል.
👉በእግዚአብሔርና በሰው መካከል የሚደረግ አስታራቂ አገናኝ ነው።
👉በጸሎት ነፍስ ወደ ሰማይ ትወጣለች እና በሚያስደንቅ ሁኔታ ጌታን ታቅፋለች።
👉ይህ ስብሰባ ህጻን በእናቱ ላይ እንደሚያለቅስ እና ጥሩውን ወተት እንደሚፈልግ ነው።
ሰኔ 8/2016 #ፃድቁ_አባ_ኪሮስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ አባታችን #አቡነ_ኪሮስ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉 #አቡነ_ኪሮስ አባታቸው ንጉስ ዮናስ እናታቸው እንስራ
ይባላሉ እሊህም #እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ቅዱሳን ናቸው ሀገራቸው ሮም ሲሆን በታህሳስ 8 ቀን ተወለዱ የመጀመሪያ ስማቸው ዲላሶር ይባል ነበር
👉በኋላ አባታቸዉ ከሞቱ በኋላ ሀብት ንብረታቸዉን ተካፍለዉ ለድሆች ከመፀወቱ በሑዋላ ከአባ #በቡነዳ_ገዳም ገቡ
👉በ17 አመታቸው ስርአተ ምንኩስናን ተምረው ከአባ በቡነዳ እጅ ስርአተ #ምንኩስናን ተቀበሉ ከዚህ በሁዋላ በፆምና በፀሎት ተወስነው ኖሩ
👉ስለ አለም መከራ ለ 40 ዘመን ተኝተው ሲፀልዩ እላያቸው ላይ ሳር በቅሎባቸው ሳለ #መላዕክት መጥተው ተነስ ቢሉት አዳም የፍጡርን ቃል ሰምቶ ወድቋልና ጌታም ድምፁን ያሰማኝ አሏቸው በኋላም #ኪሩቤል አንስቶ ወስዶ ገነት አሳይቷቸው በመጨረሻም ጌታችን ቃል ኪዳን ሰቷቸዋል
👉ቃል ኪዳናቸውም መካኖችን ልጅ የሌላቸው #ገድላቸውን
አቅፈው ቢያለቅሱ #ፀበሉን ቢጠጡ ስምሕን ቢጠሩ የመካኒቱን ማሕፀን እከፍታለሁ
👉ህፃናት የሚሞትባቸው #እንዳይሞትባቸው አደርጋለሁ በንፁህ ገንዘቡ ቂም እና በቀልን ሳይዝ በሕግ በስጋ ወደሙ ለፀና ሰው በስምህ በተሰራው #ቤተክርስቲያን ጧፍ ዘይት ያበራ መገበሪያ ያመጣውን ልጅ እሰጠዋለሁ ብሎ ጌታችን ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል
👉ከዚህም በኋላ በተወለዱ በ 270 አመታቸው ሐምሌ 8 ቀን አርፈዋል የፃድቁ #አቡነ_ኪሮስ እረድኤታቸው አማላጅነታቸው ከሁላችን ጋር ፀንቶ ይኑር የተባረከ #ቀዳሚት_ሰንበት ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
እንኳን ለእመቤታችን እግዝዕትነ
ማርያም በዓል አደረሰን።
"የጌታዬ እናት።"
ሉቃስ 1፤43
ሰኔ 8 ቀን
ከ33ቱ የእመቤታችን
በዓል አንዱ ነው።
እመመቤታችን ከልጇ ከአምላክ ወሰብእ
ቅዱስ አማኑኤል ጋር በስደታቸው ወራት ከደረቅ
አለት ላይ ውሐን ያፈለቁበት እለት ነው።
ከዚህም ምንጭ ህሙማነ ስጋ እየጠጡ ይፈወሱ ነበር።
የሕይወት ውሐ ምንጭን ከሆድዋ ያፈለቀች
የጌታችን የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጅዋ አማልዳ ፍቅርን ትናኝብን።
ዘረኝነት ያጠወለገው ፍቅራችንን ከይሲን አስወግዳ በፍቅር ታለምልመን ከክፉ ደዌ ከቀሳፊ ነገር ትሰውረን ሙኃዘ ፍስሐ የደስታን ዜና ታሰማን ከአፈር ዘሪ ከአብሎ መስካሪ ከወንጌል
ሰባሪ የጸሎቷ ኃይል ይታደገን።
አሜን አሜን አሜን
➕ ➕ ➕ ዕርገተ ክርስቶስ ➕ ➕ ➕
<< ደቀ መዛሙርቱን ከባረካቸው በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ ፤ በአባቱም ቀኝ ( ዕሪናም ) ተቀመጠ ፤ የተቀመጠውም በባሕርይ መለኮቱ ብቻ አይደለም ፤ በተዋሐደው ትስብእትም ጭምር እንጂ ፤ አካላዊ ቃል ባሕሪያችንን ሲዋሐድ እኛን ወደዚኽ ክብር ለመመለስ ነበርና ። ... እግዚአብሔር ሲሆን ስለ እኛ ሰው ኾነ ፤ በፈቃዱ መከራ መስቀልን በተዋሐደው ሰውነቱ ተቀበለ ፤ በተዋሐደው ሰውነቱ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ፤ በተዋሐደው ሰውነቱም ዐረገ ፤ በሕያዋንና በሙታን ላይ ይፈርድ ዘንድም ዳግመኛ በክበበ ትስብእት ይመጣል >> / ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ /
አሜን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በበዓለ ዕርገትኽ ለኛ ለሰው ልጆች ምህረት ቸርነት ፍቅር አንድነት ሰላም ጤና እንድትሰጠን ስንል እንማጸናለን ። ለዘለዓለሙ አሜን ።
ሰኔ 6/2016 #በአለ_ዕርገት (40ኛዉ ቀን)
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን #ለኢየሱስ_ክርስቶስ #በአለ_ዕርገት አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉 #እግዚአብሔር በእልልታ በመለከት ድምፅ #ዐረገ መዝ.46/47፥5
👉አምላካችን #ክርስቶስ ከትንሣኤ በኋላ አርባ ቀን እየታያቸዉ ሲያስተምራቸዉ ቆይቶ ደቀ መዛሙርቱ እያዪት ማረጉን የምናስብበት እለት ነዉ ከጌታችን አበይት ዘጠኝ በአላት አንዱ #ዕርገት ነዉ
👉እናንተ ግን ከላይ ሀይልን እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ ነገር ግን #መንፈስ_ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ በአለም ሁሉ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ ብሎ ከተናገራቸዉ በኋላ እነሱ እያዪት ከፍ ከፍ አለ ደመናም ተቀበለችዉ
👉እርሱም ወደ ሰማይ ሲያርግ ሐዋርያት ትኩር ብለዉ ሲመለከቱት እነሆ ነጫጭ ልብስን የለበሱ ሁለት መላእክት በአጠገባቸዉ ቆሙ እነሱም እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ወደ ሰማይ የወጣዉ #ኢየሱስ_ክርስቶስ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ይመጣል አሏቸዉ የሐዋ.1ቁ 9-11
👉አምላካችን #ኢየሱስ_ክርሰቶስ ከእርገት በአል ረድኤት በረከት ያሣትፈን ዳግም ሲመጣ ከቅዱሳኑ ጋር ይደምረን መልካም በአል ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❣️ እንዲህ ያስተምረናል።
👉"ማንም በድህነቱ አያለቅስ፣ አለም አቀፉ መንግሥት ተገልጧልና
👉ማንም ስለ በደሉ አያልቅስ፣ ይቅርታ ከመቃብር ተገልጧልና
👉ማንም ሞትን አይፈራ፣ የአዳኝ ሞት አርነት አውጥቶናልና።
👉እስረኛ ሆኖ ቀርቷል አጠፋው።
👉ወደ ሲኦል በመውረድ ገሃነምን ምርኮ አደረገ።
👉 ሥጋውን ሲቀምስ አማረረው።
👉ኢሳይያስም ይህን ትንቢት ተናግሮ፡- ሲኦል በታችኛው ክልል ባገኘህ ጊዜ ተናደድኩ አለ።
👉ፈርሷልና ተናደደ።
👉 ተሳለቀበትና ተበሳጨ።
👉ተገድሏልና ተናደደ።
👉ሥጋ ወስዶ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አገኘው።
👉 ምድርን ወስዶ መንግሥተ ሰማያትን አገኘ።
👉የሚታየውን ወስዶ በማይታየው ላይ ወደቀ።
👉ፈርሷልና ተናደደ።
👉 በሰንሰለት ታስሮ ነበርና ተናደደ።
❣️ሞት ሆይ መውጊያህ የት አለ? ሲኦል ሆይ ድልህ የት አለ?
https://youtu.be/3hZckz7wxyM?si=CI1uUPXCXUtNLG75
Читать полностью…ሰኔ 15/2016 #ሰማእቱ_ቅዱስ_ሚናስ
#ሰማእቱ_ቅዱስ_ቂርቆስ_ወ_ቅድስት_ኢየሉጣ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በሰማእቱ ስም ለምናመሰግንበት #ለቅዱስ_ሚናስ አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉ሰኔ አስራ አምስት #ቅዱስ_ሚናስ (ማር ሚና) ምዕመን ሰማዕት ቅዳሴ ቤቱ ነው ቅዱስ ሚናስ በምድረ ግብፅ ተወዳጅ ከሆኑ ሰማዕታት ዋነኛው ነው ልክ በሃገራችን ቅዱስ ጊዮርጊስ ልዩ ቦታ እንዳለው ሁሉ ግብፃውያን #ማር_ሚናስን ጠርተው አይጠግቡትም
👉ምክንያቱም ከታላላቅ ሰማዕታት አንዱ በመሆኑና ዛሬም ድረስ ለጆሮና ለዐይን ድንቅ የሆኑ ተአምራትን ስለሚሠራ ነው በተለይ ለታመመ ለደከመና ለተጨነቀ ፈጥኖ ደራሽ ባለ በጎ መድኃኒት #ፈዋሽና_አማላጅ ነው
👉 #ቅዱስ_ሚናስ (ትርጉሙ ታማኝና ቡሩክ) ማለት ነው በሦስተኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ የደጋግ ክርስቲያኖች ልጅ በልጅነቱ የቅድስና ሕይወትን ያጣጣመ በዘመኑ ሰው እጅግ ተወዳጅ የነበረ ሃብትን፣ ክብርን፣ ሥልጣንን ንቆ በፆምና በፀሎት የተወሰነ በመጨረሻም #በክርስቶስ ስላመነ አላውያን የገደሉት ሰማዕት ነው
👉እርሱ ሰማዕት ከሆነ ከበርካታ ዘመናት በኋላ ምዕመናን ክቡር አካሉን ፈልገው ያጡታል የሚገለጥበት ጊዜ ሲደርስ ግን እርሱ የተቀበረበት ምድረ በዳ የበጎችና የእረኞች መዋያ ነበርና ተአምራትን አደረገ አንድ እረኛ በጎቹ ድውያን ሆኑበት በዚያ ሰሞን #ከቅዱሱ_መቃብር ላይ ፀበል ፈልቆ ነበርና እረኛው ተርታ ውሃ ነው ብሎ በጎቹን ሲያጠጣቸው አንዱ ድውይ በግ ወደ ፀበሉ በመዘፈቁ ዳነ
👉በዚህ የተገረመው እረኛ ሁሉንም የታመሙ በጎቹን አምጥቶ ነከራቸው እነርሱም #ተፈወሱ ይህ ዜና በምድረ ግብፅ ሲሰማ ድውያን ሁሉ እየመጡ ይፈወሱ ገቡ ግን እነሱም ሆነ እረኛው ምክንያቱን ማወቅ አልቻሉም
👉ነገሩ በሮም ንጉሥ ዘንድ ሲሰማ ሴት ልጁን ከሠራዊቱ ጋር ላካት ምክንያቱም እርሷ ከብዙ ዘመን ጀምራ መፃጉዕ ነበረችና ፈውስን አጥታ ነበር መጥታ #ተጠመቀች ፈጥናም ተፈወሰች እርሷ ግን እንደ ሌሎች ያዳናትን ማንነት ሳታውቅ መሔድ አልፈለገችምና #ሱባዔ ገባች
👉 #ቅዱስ_ሚናስ በሌሊት በራዕይ መጥቶ ሥጋው እንዳለ ነገራት እርሷም መሬቱን አስቆፍራ የቅዱሱን አካል በክብር አስወጣች ከዚያም በንጉሡ ትዕዛዝ ምድረ በዳው ከተማ እንዲሆን ተቀየረ ስሙም #መርዩጥ ተባለ ፀበሉ የነበረበት ቦታም ላይ #የማር_ሚናስ ቤተ ክርስቲያን ታንፆበት በዚህች ዕለት #ቅዳሴ_ቤቱ ተከብሯል
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከቅዱሱ ሰማዕት ረድኤት በረከት ያሣትፈን በዚህ እለት #የቅዱስ_ቂርቆስ እና #የቅድስት_ኢየሉጣ መታሰቢያቸዉ ሲሆን በረከት ረድኤታቸዉ አይለየን የተባረከ #ቀዳሚት_ሰንበት ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
"ውክፔዲያ - አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ" https://am.m.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A0%E1%89%A1%E1%8A%90_%E1%8A%A0%E1%88%A8%E1%8C%8B%E1%8B%8A_%E1%8B%98%E1%8B%B0%E1%89%A5%E1%88%A8_%E1%8B%B3%E1%88%9E
Читать полностью…ሰኔ 13/2016 #እግዚአብሔር_አብ
#ቅዱስ_ሩፋኤል
#አቡነ_ዘርዐ_ብሩክ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሳኑ ስም ለምናመሰግንበት ለመልአኩ #ለቅዱስ_ሩፋኤል እና ለፃድቁ #አቡነ_ዘርዐ_ብሩክ ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን
👉 #ቅዱስ_ሩፋኤል ቊጥሩ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሲኾን ሩፋ፤ ማለት ሐኪም፤ ኤል ማለት #እግዚአብሔር ማለት ሲኾን ሩፋኤል ማለት “እግዚአብሔር ሐኪሜ ነው” ማለት ነው፤ ሄኖክም “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” ይለዋል (መጽሐፈ ሄኖክ 6፥3)
👉ይኽ መልአክ በራማ ሰማይ ያሉ ነገደ መናብርትን የሚመራቸው ነው ነገደ መናብርት ያላቸው #ቅዱስ_ሩፋኤል የሚመራቸው በራማ ሰማይ የሚኖሩ ነገደ መላእክት ናቸው
👉ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በሥነ ፍጥረት መጽሐፉ ላይ “ወለዳግም ጾታ ዐሠርቱ ስሞሙ መናብርት ወሊቆሙ #ሩፋኤል እሉ እሙንቱ እለ ይቀልል ሩጸቶሙ እምነፋስ ወእለ ይጸውሩ ወላትወ መብረቅ ወኲናተ እሳት ዘይነድድ ወአንበሮሙ በዳግሚት ሰማይ” ይላል
👉በራማ ሰማይ የሚገኘውን ኹለተኛውን ዐሥሩን ነገድ መናብርት ሲላቸው አለቃቸው #ቅዱስ_ሩፋኤል ነው፤ እነዚኽም ረቂቅ የኾነ የመብረቅ ጋሻ የእሳት ጦር ይዘው ከነፋስ ይልቅ የፈጠኑ ሲኾኑ በራማ በኹለተኛው ክፍል ላይ አስፍሯቸዋል
👉#የእግዚአብሔር_አብ ቸርነት የልጁ የመድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ምህረት #የመንፈስ_ቅዱስ አንድነት ከሁላችን ጋር ይሁን የመልአኩ #ቅዱስ_ሩፋኤል ጥበቃ የፃድቁ #አቡነ_ዘርአ_ብሩክ"ፀሎት አይለየን አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ሰኔ 12/2016 #መልአኩ_ቅዱስ_ሚካኤል
" #የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸዉማል" መዝ.33 ቁ.7-9
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በመልአኩ ስም ለምናመሰግንበት መልአኩ #ቅዱስ_ሚካኤል #አፎምያን ከሰይጣን እጅ ላዳነበት #ባህራንን ለተራዳበት አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉ይህችም ሴት #እግዚአብሔርን የሚፈራ የአንድ ሰው ሚስት ነበረች ባሏ አስተራኒቆስ በታመመ ጊዜ እያዘነችና እያለቀሰች እንዲህ አለችው ጌታዬ አንድ ነገር ልንገርህ እስኪ ስማኝ ሴት ባሏ የሞተ እንደሆነ ብቸኛ ባይታወር ጦም አዳሪ እንደምትሆን እንጀራዋንም በብዙ ዕንባና ሰቀቀን እንደምትመገብ አንተ ታውቃለህ አንተ ብትሞትና ብትለየኝ ከኀዘኔ የሚያረጋጋኝ ልጅ አባት እናት የለኝም
👉አሁንም አንተ ሳለህ የመላእክት አለቃ #የቅዱስ_ሚካኤልን ሥዕል እንድታሰራልኝ እሻለሁ በመዓልትም በሌሊትም ከሰይጣን ጠላትነት ይጠብቀኝ ዘንድ እኔ በቤቴ ውስጥ አኑሬ እማፀንበታለሁ አስተራኒቆስም አስሎ ሰጣት ባሏም ከሞተ በኋላ ቅድስት አፎምያ #የቅዱስ_ሚካኤልን ዝክር ታዘክር ነበር ለድሆችም አብዝታ ትረዳ ነበር
👉በዚህ ሰይጣን ቀናባት በመነኩሴ ተመስሎ ሊያስታት ሞከረ #በቅዱስ_ሚካኤል ስዕል አሳፍራ መለሰችው ከ 3 ወራት በኋላ ሰኔ 12 ቀን ዳግመኛ ቅዱስ ሚካኤል ነኝ ብሎ ሊፈትናት መጣ ሚካኤል ከሆንክ መስቀልህ የት አለ አለችው ከዚህ በኋላ አፉን ከፍቶ አይኑን አጉረጥርጦ አንገቷን አነቃት
👉 #ቅዱስ_ሚካኤል ድረስልኝ ብላ ተጣራች ቅዱስ ሚካኤል ከሰማይ ፈጥኖ ወረደ በበትረ መስቀሉም መታው ጊዜዬ ሳይደርስ አታጥፋኝ ስዕልህ ባለበት ስምህ በተጠራበት ድርሳንህ በሚነበብበት ፈፅሞ አልደርስም ብሎ ማለ ተገዘተ ሸሸም ከዚህ በኋላ #ቅዱስ_ሚካኤል_ቅድስት_አፎምያን ወዳጄ አፎምያ ባንቺ ደስ አለኝ ዋጋሽ በሰማይ ታላቅ ነው ብሎ ባርኳት አርጓል
👉እንዲሁም በዚህ እለት #መልአኩ_ቅዱስ_ሚካኤል የባህራንን የሞት ደብዳቤ ወደ ህይወት የቀየረበት የተአምር እለት ነዉ እንኳን አደረሰን
👉ከቀድሞ ጀምሮ ቂም የሌለበት ምህረትን የሚለምን እሩሩህ #መልአክ_ቅዱስ_ሚካኤል ልመናው ከሲኦል ረግረግ ያድነን ከርጉም ተኩላ አፍም ይሰውረን በከንቱ እንዳንጠፋ ከክፉ የሰይጣን ወጥመድም ያድነን ከሰራዊቱ ሁሉ ጋር በየቀኑ ይታደገን
👉 #የቅድስት_አፎምያ #የቅዱስ_ባህራን አማላጅነት ከኛ ጋር ይኑር #የቅዱስ_ሚካኤል ጥበቃዉ ፀሎት ልመናው ረድኤት በረከቱ አይለየን ለዘለዓለሙ "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ሰኔ 11/2016 #ቅድስት_ሐና
#ቅዱስ_ያሬድ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅድስት #ሐና እንዲሁም #በቅዱስ_ያሬድ ስም ለምናመሰግንበት ለቅዱሣኑ ወርሐዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉በዚህ ዕለት ለጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ አያቱ እንዲሁም አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እናቷ የሆነች የተመሰገነች የቅድስት ሐና ወርሐዊ መታሰቢያ ነው
👉ይችም ቅድስት ከኢየሩሳሌም አገር ከሌዊ ነገድ ከካህኑ #አሮን ትውልድ የሌዊ የሜልኪ ልጅ ለሆነ ለማጣት ልጁ ናት
👉ለማጣትም ሦስት ሴቶች ልጆች አሉት የታላቂቱም ስሟ ማርያም ናት ሁለተኛዋም ስሟ ሶፍያ ሦስተኛዪቱም ስሟ ሐና ናት ታላቂቱ ማርያምም ለባል ተድራ አዋላጅ የሆነች #ሰሎሜን ወለደቻት እርሷም መድኃኒታችንን ከወለደችበት ጊዜ ጀምሮ በስደቷም ወራት #ከአረጋዊ_ዮሴፍ ጋር እመቤታችንን ድንግል #ማርያምን ያገለገለቻት ናት
👉ሶፍያም ለባል ተድራ #ለመጥመቁ_ዮሐንስ እናቱ የሆነች ቅድስት #ኤልሳቤጥን ወለደቻት ይችንም ቅድስት ሐናን ከይሁዳ ነገድ ለሆነ ፃድቅ ስሙ ኢያቄም ለሚባል አጋቧትና እመቤታችንን ቅድስት ድንግል #ማርያምን ወለደቻት እሊህም #ሰሎሜና #ኤልሳቤጥ #ለቅድስት_ሐና #የእኅትማማቾች ልጆች ናቸው
👉የዚችንም የቅድስት ሐናን በሥውር የምትሠራውን ገድሏንና ትሩፋቷን እንዳናስታውሰው አናውቀውም ግን #ከሴቶች ሁሉ እንደምትበልጥና እንደምትከብር እናውቃለን እንረዳለን እርሷ #አምላክን_በሥጋ_ለወለደችው ወላጅዋ ትሆን ዘንድ የተገባት ሁናለችና ከሴቶች ሁሉ የሚበልጥና የሚበዛ ትሩፋትና ተጋድሎ ባይኖራት #ይህ_ታላቅ_ፀጋ ባልተገባት ነበር
👉ይህችም ጻድቅት ሐና መካን በመሆንዋ ልጅን ይሰጣት ዘንድ ወደ #እግዚአብሔር ዘወትር በጸሎት ትተጋና ትማልድ ነበር #እግዚአብሔርም በእርሷ ለዓለም ሁሉ ድኅነት የተደረገባትን ይቺን የተባረከችና የከበረች ልጅን ሰጣት እርሷም አምላክን የወለደች #እመቤታችን_ድንግል_ማርያም ናት
👉ስለዚህም ይህን ታላቅ ጸጋ ስለሰጣት #የቅድስት_ሐናን መታሰቢያ በደስታ ልናከብር ይገባናል #ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በጸሎቷ የሚገኝ በረከቷም ከእኛ ጋር ይሁን በዚህ እለት በወርሐዊ የመታሰቢያ በአሉ የሚታወሰዉ የማህሌታዊዉ #ቅዱስ_ያሬድ ፀሎትና ልመና አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
/channel/spinnercoin_bot/app?startapp=r_1852502
Echin airdrop jemru guys
Prick lemtfelgu👇👇
/channel/Prickgame_bot?start=ref-5xwsGJExiWysYNQ6dVA5Ps
Dotcoin lemetefelgu👇👇
/channel/dotcoin_bot?start=r_1942891959
Blum lemetefelgu👇👇
t.me/BlumCryptoBot/app?startapp=ref_2Ngp7mMfqN
Memefi lemetefelgu👇👇
/channel/memefi_coin_bot?start=r_cb8eca9156
Hamster combat yemetefelgu👇👇
/channel/hamster_kombat_boT/start?startapp=kentId1942891959
Avacoin yemetefelgu👇👇
/channel/avagoldcoin_bot?start=bd939fd91a379584b35c
Yes coin yemeteflgu👇👇
/channel/theYescoin_bot/Yescoin?startapp=E2ahEj
Catizen yemetefelgu👇👇
/channel/catizenbot/gameapp?startapp=r_3132_9352986
Secrert coin yemetefelgu👇👇
/channel/mnemonic_game_bot/start?startapp=ref_1942891959
Tap swap lemetefelgu👇👇
/channel/tapswap_mirror_2_bot?start=r_1942891959
Wormflare lemetefelgu👇👇
/channel/wormfare_slap_bot?start=r_1942891959
Pixelverse le.etefelgu👇👇
/channel/pixelversexyzbot?start=1942891959
Preton lemetefelgu👇👇
/channel/preton_drop_bot?start=6f67c498-b0a0-45f8-aa89-df966bd1a5b1
ሰኔ 9/2016 #አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ
"#እግዚአብሔር በዕልልታ በመለከት ድምፅ ዐረገ መዝ 46.ቁ5"
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ #አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ መታሰቢያ በአል እንኳን አደረሰን
👉አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስ አባታቸው መልአከ ምክሩ እናታቸው ወለተ ማርያም ይባላሉ የተወለዱበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ነው
👉በተወለዱ ዕለት ተነሥተው በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ብለው #ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል የስማቸው ትርጓሜ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ አንድም #የክርስቶስ እስትንፋስ ማለት ነው
👉ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸውና በመንገዳቸው ሁሉ እየመራቸው ነው ያደጉት #መንፈስ_ቅዱስ ልቡናቸውን ብሩህ አድርጎላቸው በ5 ዓመታቸው የቅዱሳት መጻሕፍት ቃላትን፣ ብሉያትንና ሐዲሳትን፣ ድርሳናትንም ጠንቅቀው ዐውቀዋል
👉በተወለዱ በ14 ዓመታቸው ወደ #አቡነ_ኢየሱስ ሞዐ ደብረ ሐይቅ ገዳም ሄደው ከባሕር ዳር ቆመው የሙሴን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር በጸለዩ ጊዜ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ባሕሩን አሻግሯቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተዋል፡፡
👉ለ3 ዓመታት ያህል በኃይቅ ገዳም ለመነኮሳት እንጨት በመልቀምና ውሃን በመቅዳት #ለአባቶች_መነኮሳት ምግብ የሚሆናቸው ዓሣ ከባህር ውስጥ በማውጣት አገልግለዋል፡
👉አባታችን #እስትንፋሰ_ክርስቶስ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ከፆሙ በኋላ ምንም እህል ሳይቀምሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ ለሙሴ በደብረ ሲና እንደሰጠው ለአባታችንም ወደ እርሳቸው መጥቶ ዓሥሩን ቃላተ ኦሪትና ስድስቱን ቃላተ ወንጌል በውስጣቸው የተጻፈባቸው ሁለት ጽላቶችን ሰጥቷቸዋል፡፡
👉አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሠሩ በኋላ ዕለቱን ስንዴ ዘርተው፣ ወይን ተክለው፣ ጽድን ወይራንና ግራርን ተክለው በአንዲት ቀን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ዕለቱን አድርሰዋል ስንዴውን ለመሥዋዕት ወይኑን ለቍርባን በተአምራት አድርሰዋል፡፡
👉አባታችን በጸሎት ላይ እንዳሉ ቅዱስ ሚካኤል ተልኮ መጥቶ አባታችንን በደመና ጭኖ ወስዶ ከጌታችን ከመድኃኒታችን #ከኢየሱስ_ክርስቶስ ፊት አቆማቸው ጌታንም በቅዱሳኑ ሁሉ እንዲባረኩ ካደረጋቸው በኋላ መልአኩን ‹‹ወደ ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ ወደ ኢየሩሳሌም አድርሰው›› ብሎት ኢየሩሳሌምን አሳልሞ ሀገራችን መልሶ አምጥቷቸዋል
👉አባታችን ሁሉንም የኢትዮጵያን ቅዱሳት ገዳማትን ተዘዋውሮ ሲጎበኙ በሕይወተ ሥጋ የሌሉት የየገዳማቱ ቅዱሳን ሁሉ በአካል ይገለጡላቸው ነበር ጎጃም ውስጥ እያስተማሩ፣ !፣ የታመሙትን እየፈወሱ፣ የዕውራንን ዐይን እያበሩና ሙታንን እያሥነሱ ብዙ ካገለገሉ በኋላ ለዘጠኝ ዓመታት በባሕር ውስጥ ገብተው ቁልቁል ተዘቅዝቀው #ለኢትዮጵያ_ፀልየው የምሕረት ቃልኪዳን ተቀብለዋል
👉ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ጌታችን መጥቶ ‹‹ከመነኮሳት ሁሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ ሆይ #ኢትዮጵያንና_ሕዝቦቿን ምሬልሃለሁ ከዚህች ባሕር ውጣ›› በማለት በሞት የሚያርፉበትን ቦታ ነግሯቸዋል፡፡
👉ጻድቁ ወደ ደብረ አሰጋጅ በሚሄዱበት ጊዜ ጸሐይ ልትገባ ስትል ‹‹በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አውግዤሻለሁ ለመስፍን ኢያሱ በገባኦን እንደቆምሽ አሁንም ቀጥ ብለሽ ቁሚ ብለው ፀሐይን አቁመዋል አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስም ደብረ አሰጋጅ ሲደርሱ ፀሐይ አፍ አውጥታ ‹‹አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ እገባ ዘንድ ፍታኝ›› ስትላቸው #እግዚአብሔር_ይፍታሽ ባሏት ጊዜ ጠልቃለች
👉ጻድቁ ሌላው በእጅጉ የሚታወቁበት አንድ ትልቅ ቃል ኪዳን አላቸው በአምላክ ልቡና የሚገኝ፣ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ልቡና የሚገኝ፣ በቅዱስ ሚካኤልና በቅዱስ ገብርኤል ልቡና የሚገኝ እንደ መልክአ መድኃኔዓለም ያለች እጅግ አስገራሚ #ፀሎት አለቻቸው፤ እርሷን ጸሎት በጸለዩ ጊዜ እልፍ ነፍሳትን ከሲኦል ያወጣሉ
👉ጸሎቷም #የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች እያንዳንዱ የሰውነት ክፍሎቹ የተቀበሉትን ጸዋትዎ መከራዎች ሁሉ ታዘክራለች በእያንዳንዱ ክፍልም የጸሎት ማሳረጊያ #አቡነ_ዘበሰማያት ይደግማሉ ንስሓ የገባ ኃጢአተኛ ሰው እንኳን ቢሆን ይህችን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት በጸለየ ጊዜ ሺህ ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ ጌታችን በማይታበል ቃሉ ለአባታችን ነግሯቸዋል
👉እያንዳንዱን #የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች መከራዎቹን የምታዘክረውን ይህቺን በአምላክ ልቡና ያለች ግሩም የሆነች ፀሎት ነፍሳትን ከሲኦል አታወጣም ብሎ የሚጠራጠር ቢኖር መንግስተ ሰማያትን አያያትም ጻድቁ ታኅሣሥ 8 ቀን ተወልደው ሚያዚያ 9 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከፃድቁ ረድኤት በረከት ያሣትፈን #የፃድቁ_አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ምልጃና ፀሎት ሁላችንንም ይጠብቀን የተባረከ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" ✝️💒✝️
††† እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† በዓሉ ከሰላሳ ሦስቱ ዓበይት የእመቤታችን በዓላት አንዱ ሲሆን በዚሕች ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል እናቱ እግር ሥር ጠበል አፍልቋል::
††† ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
ድንግል ማርያም አምላክ ልጇን አዝላ ስደት ወጥታ ምድረ ግብጽ ትደርሳለች:: በወቅቱ ከደረሱባት ችግሮች አንዱ ደግሞ ረሃብና ጽሙ ነበር:: እንኳን ለስደተኛ በቤቱ ላለም ረሃብና ጥም እንዴት እንደሚከብድ የደረሰበት ያውቀዋል::
††† ለዛም ነው ሊቁ በቅዳሴው:-
"አዘክሪ ድንግል ረሃበ ወጽምዐ : ምንዳቤ ወኀዘነ : ወኩሎ ዐጸባ ዘበጽሐኪ ምስሌሁ" ያለው::
ታዲያ አንድ ቀን የበርሃው ፀሐይ አቃጥሏቸው ባረፉበት ድንግል እመቤታችን ውኃ ልመና ወጣች:: ብዙ ለመነች : ግን ጥርኝ እንኳ የሚሠጣት አጥታ በሐዘን ተመለሰች:: ስትመለስ ግን ይባስ ብሎ የልጇን ጫማ ሽፍቶች ወስደውት ደረሰች::
ያን ጊዜ ልጇን ታቅፋ "ውኃ ሳላገኝልሕ : ጫማሕንም አሰረቅኩብህ" ብላ ምርር ብላ አልቅሳለች::
"በከየት ወትቤ ማርያም ማዕነቅ::
እምሰብአ ሃገር አልቦ ዘየአምራ ለጽድቅ::
ሰአልክዎሙ ማየ ኢወሀሐቡኒ በሕቅ::
ወአሕጎልኩ ለወልድየ አሳእኖ ዘወርቅ::" እንዳለ ደራሲ::
ይሕንን የተመለከተ ልጇ የቆመችበትን መሬት ቢባርከው ሕይወትነት ያለው ማይ (ጠበል) ፈለቀ:: ጌታችን : እመቤታችን: ዮሴፍና ሰሎሜ ከውኃው ጠጥተዋል::
ሲሔዱ ግን ለእንግዶች ጣፋጭ (መድኃኒት) : ለአካባቢው ሰዎች ግን መራራ ሁኗል::
"ከመ ኢይስተይዋ ሰብአ ሐገር ለይእቲ ማይ አምረራ::
ወለርኁቃንሰ ፈውሰ ወጥዕምተ ገብራ::" እንዳለ መጽሐፍ:: (ሰቆቃወ ድንግል)
ከመቶዎች ዓመታት በኋላም ጌታ ጠበል ያፈለቀበት : ድንግል እመቤታችን የቆመችበት ቦታ ላይ በእመ ብርሃን ስም ቤተ ክርስቲያን ታንጿል:: ቅዳሴ ቤቱም ተከብሯል:: ጠበሉም ሲባርክና ሲፈውስ ይኖራል::
††† የጠበል በዓል †††
†††ዳግመኛ ዕለቱ የጠበል በዓል ተብሎም ይታሠባል:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስለ ጠበል ፈዋሽነት ሁሌ ብታስተምርም በዚህ ቀን ግን ልዩ ትኩረቷ ታደርገዋለች::
እግዚአብሔር በምክንያትም አለምክንያትም መፈወስ ይችላል:: ያለ ምክንያት በቃሉና በወዳጆቹ ቃል አድሮ "ዳን" ይላል:: ወይም ደግሞ በምክንያት በእመት (እምነት) : በጠበል : ቅዱስ ቃሉን በመስማት : በመስቀሉና በመጻሕፍት በመባረክ (በመታሸት) : በቅዱሳን አካል (በልብሳቸው : በበትራቸው : በጥላቸው በአጽማቸው . . .) ይፈውሳል::
እርሱ እግዚአብሔር ነውና በወደደውና በመረጠው አድሮ ያድናል ( ይፈውሳል):: (2ነገ. 5:10, ሐዋ. 3:6, 5:15, 19:11)
††† ዛሬ ግን የጠበል ፈዋሽነት በጉልህ ይነገራል:: (ዮሐ. 5:1, 9:7)
††† አምላከ ቅዱሳን ከደዌ ሥጋ : ከደዌ ነፍስ በምሕረቱ ይሠውረን:: ከድንግል እመቤታችን በረከትም ያሳትፈን::
††† ሰኔ 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.የእመቤታችን ድንግል ማርያም ቅዳሴ ቤት
2.የቅዱስ ውኃ (ጠበል) መታሠቢያ
3.ቅድስት ትምዳ እናታችን
4.ቅዱስ አውሎጊስ
5.አባ አትካሮን
††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ)
3.አባ ብሶይ (ቢሾይ)
4.አቡነ ኪሮስ
5.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
6.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት)
††† "ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ::
ግርማው በእሥራኤል ላይ: ኃይሉም በደመናት ላይ ነው::
እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው::
የእሥራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን: ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል::
እግዚአብሔርም ይመስገን:::" †††
(መዝ. ፷፯፥፴፬)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
ሰኔ 7/2016 #ቅድስት_ሥላሴ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ለአጋእዝተ አለም ቅድስት #ሥላሴ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉 #ምስጢረ_ሥላሴ ስለ ሥላሴ ምስጢር የሚናገር ትምህርት ማለት ነው #እግዚአብሔር አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፋፍለው በአንድነትና በሦስትነት የሚመሰገን #አንድ_ሕያው_አምላክ ነው
👉 #የእግዚአብሔር ሦስትነት ስንል እግዚአብሔር የማይለያይና የማይቀላቀል ፍጹም የሆነ ሦስትነት አለው ማለታችን ነው #የእግዚአብሔር ሦስትነት በስም በግብር በአካል ነው
👉 #እግዚአብሔር በስም ሦስት ስንል ሦስት የተለያዩ ስሞች አሉት ማለታችን ነው እነዚህም #አብ_ወልድ_መንፈስ_ቅዱስ የሚባሉት ሲሆኑ እርስ በርሳቸው አይወራረሱም አንዱ በሌላው ስም አይጠራም ዘፍ.ቁ.1_2 ምሳ.30_ቁ.4
👉 #እግዚአብሔር በግብር ሦስት ነው ስንል ሦስት የተለያዩ የአካል ሥራዎች አሉት ማለት ነው እነሱም መውለድና ፤መወለድ፤ ማስረፅ "የአብ ወላዲ"፣"የወልድ ተወላዲ"፣"የመንፈስ ቅዱስ ሠራፂ" የሚሉት ሲሆኑ የአካል ግብር ይባላሉ መዝ.ቁ.2_7
👉 #እግዚአብሔር በአካል ሦስት ነው ማለት ደግሞ
ለአብ፤ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው።
👉 #ለወልድ፤ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ።
👉 #ለመንፈስ_ቅዱስ፤ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ማለታችን ነው።
👉 #የሦስቱ_የእግዚአብሔር ስሞች ትርጉም
👉 #አብ ማለት አባት ማለት ሲሆን የሚወልድ፤የሚያሰርጽ ወይም የሚያስገኝ ያለ እናት ወልድን የወለደ፤ መንፈስ ቅዱስን ያሰረጸ ነው።
👉 #ወልድ ልጅ ማለት ሲሆን የሚወለድ ወይም ያለ እናት ቅድመ ዓለም፤ ያለ አባት ድህረ ዓለም የተወለደ ነው መዝ.2_7
👉#መንፈስ_ቅዱስ ረቂቅ፤ ልዩ፤ ንፁህ; ከፍጡራን መናፍስት ሁሉ የተለየ ማለት ነው ኢዮ.ቁ.26_13
👉አለምን ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጡ አጋዕዝተ አለም #ቅድስት_ሥላሴ ህይወታችንን በምህረት ቤታችንን በበረከት ይጎብኝልን "አሜን"✝️ 💒 ✝️
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዕረገት በዓት በሰላም አደረሳችሁ
‟ሲባርካቸውም ከነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ።” ሉቃ ፳፬ ÷ ፶፩
#ፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሰንበት_ትምህርት_ቤት
#ፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሚዲያ
Follow us on
👉 /channel/fre_amde_haymanot_media
👉 http://linktr.ee/fre_amde_haymanot_media
ከጻድቁ ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በረከት ረድኤት ይክፈለን፥በአማላጅነቱ አይለየን።”ኦ እግዚአብሔር አምላኪየ መሐሮሙ ለኩሎሙ ሕዝበ ኢትዮጵያ፤”ይበልልን።
በጻድቁ ቃል ኪዳን ይጠብቀን።በዝቋላ ደብረ ከዋክብት እና በጎጃም አማኑኤል ገዳማትና በሌሎችም አድባራትና አብያተ ክርስቲያናት ስለ ፈሰሰው የንጹሐን ደም ይበቀልልን።ኢትዮጵያ አገራችንን፥ተዋህዶ ሃይማኖታችንን ዳራቸውን እሳት መሀላቸውን ገነት ያድርግልን።
“ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ፥በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ ።ይባእ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሓን። “መዝ:፸፰፥፲።
መዝሙር ፸፰:፩-፲፫።
*“አቤቱ አሕዛብ (ኢ አማንያን) ወደ ርስትህ (ወደ ኢትዮጵያ፥ወደ ቤተ ክርስቲያን) ገቡ፤
*ቤተ መቅደስህንም (እነ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከግብፅ፥እነ አቡነ አረጋዊ ዘጠኙ ቅዱሳን ከታናሽ እስያ መጥተው ተራሮቿን መቅደስ አድርገው የቀደሱባትን ኢትዮጵያን፥አንድም በክርስቶስ ደም ላይ የተመሠረተችውን ቤተ ክርስቲያንን) አረከሱ፤
*ኢየሩሳሌምንም (ኢትዮጵያን አንድም የሰማያዊት ኢየሩሳሌም አምሳል ቤተ ክርስቲያንን) እንደ ተክል ጠባቂ ጎጆ አደረጉአት።(ጠባቂው የአትክልቱን ፍሬ ካነሣ በኋላ ጎጆዋን አቃጥሏት እንደሚሄድ እነዚህም ጥቅሟን ተጠቅመው ኢትዮጵያንም ቤተ ክርስቲያንንም የመከራ እሳት አነደዱባት)።
*የባሪያዎችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ።(በክብር አልተቀበሩም)።
*የጻድቃንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት፤
*ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ (በመላዋ ኢትዮጵያ) እንደ ውኃ አፈሰሱ።
*የሚቀብራቸውም (አጥቦ ገንዞ፥አጥፎ አጎናጽፎ፥ጸሎተ ፍትሐት አድርሶ የሚሸኛቸው) አጡ።
*ለጎረቤቶቻችንም (ለኢ አማንያን) ስድብ ሆንን፤
*በዙሪያችንም ላሉ ሣቅና መዘበቻ።
*አቤቱ እስከ መቼ ለዘለዓለም ትቆጣለህ? (ትፈርድብናለህ? በእነርሱስ እስከ መቼ አትፈርድም?
*ቅንዓትህም እንደ እሳት ይነድዳል? (ለአምላክነትህ ቀንተህ ያመጣኸው መቅሠፍት እስከ መቼ ይነድዳል?
*በማያውቁህም አሕዛብ ላይ ስምህንም በማትጠራ መንግሥት ላይ መዓትህን አፍስስ፤
*ያዕቆብን በልተውታልና (ያዕቆብ ዘነፍስ ክርስቲያኑን በልተውታልና፥)።
*ስፍራውንም ባድማ አድርገዋልና።(ሀገሩን ኢትዮጵያን አፍርሰዋልና)።
*የቀደመውን በደላችንን አታስብብን፤
*አቤተ መሕረትህ በቶሎ ያግኘን፤
*እጅግ ተቸግረናልና።(ባለ መከራ ሆነናልና)።
*አምላካችን መድኃኒታችን (ኢየሱስ ክርስቶስ) ሆይ! ርዳን።
*ስለ ስምህ ክብር ታደገን፤(እኛን አድነህ ስምህ ይመስገን)፤
*ስለ ስምህም ኃጢአታችንን አስተስርይልን።(ስምህን ስንጠራ ስሜ መሐሪ ይቅር ባይ ነው፥ያልከውን ፈጽምልን)።
*አሕዛብ አምላካቸው ወዴት ነው? እናዳይሉን፤
*የፈሰሰውን የባሪያዎችህን ደም በቀል በዐይኖቻችን ፊት አሕዛብ ይዩ።(እኛ እኩሌታችን ተርፈን የእኩሌቶቻችንን ሞት እንዳየን፥እነርሱም የእኩሌቶቻቸውን ሞት ይዩ)።
*የእስረኞች ጩኸት ወደ ፊትህ ይግባ፤
*እንደ ክንድህም ታላቅነት (እንደ ሥልጣንህ ገናናነት) የተገደሉትን ሰዎች ልጆች ጠብቃቸው።
*አቤቱ የተገዳደሩህን መገዳደራቸውን ለጎረቤቶቻችን ሰባት እጥፍ በብብታቸው ክፈላቸው። (የትዕቢታቸውን ብዛት አይተህ ሰባት እጅ ፍዳ አምጣባቸው በፍጹም ተበቀላቸው)።
*እኛ ሕዝብህ ግን የማሰማሪያህም በጎች (ወገኖችህ) ለዘለዓለም እናመሰግንሃለን።
*ለልጅ ልጅም ምስጋናህን እንናገራለን)።
“የጻድቅ መታሰቢያ ለዘለዓለም ነው፤”መዝ:፻፲፩፥፮።
ሰኔ 4/2016 #ቅዱስ_ዮሐንስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱስ ዮሐንስ ስም ለምናመሰግንበት ለወንጌላዊዉ ለፍቁረ እግዚእ ቅዱስ #ዮሐንስ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉በመጀመሪያው ቃል ነበረ፣ቃልም #በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፣ቃልም እግዚአብሔር ነበረ፣ቃልም ስጋ ሆነ ዮሐ1፥1-14
👉ወንጌላዊው #ቅዱስ_ዮሐንስ የተለያዩ ስሞች አሉት ከነዚህም ጥቂቶቹ
✝️ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ
✝️ ፍቁረ እግዚእ
✝️ ታኦሎጎስ
✝️ አቡቀለምሲስ
✝️ ቁፅረ ገፅ
✝️ ዮሐንስ ዘንስር
👉 #ቅዱስ_ዮሐንስ እመቤታችንን በአደራ የተቀበለ በአንድ ቤት ልጅ ሆኗት 15 ዓመት የኖረ ቅዱስ አባት ሐዋርያ ነዉ የአለሙን ገዢ ወልዳ ያሳደገች በፀጋ ተሞላታ ተቀድሳ የኖረች እናታችን #ማርያምን በእናትነት የተቀበለ ወንጌላዊው #ቅዱስ_ዮሐንስ በረከት እና ፀሎቱ አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ያን ጊዜም ሒዳ ጥሪቷንና ዋጋው ብዙ የሆነ ጌጥዋን አምጥታ በኤጲስቆጶሱ ፊት ጣለችው እርሱም በፊቷ አቃጠለው።
ከዚህም በኋላ የራስዋን ጠጉር ተላጨች ኤጲስቆጶሱም ማቅ አልብሶ ወደ ደናግል ገዳም ላካት በዚያም ታላቅ ተጋድሎን በፍጹም ልቧ ጀመረች ነፍሷንም እንዲህ እያለች ትገሥጻት ነበር በጭቃና በደንጊያ ወደ ታነፀው ቤት ለመግባት ካልተውሽ በብርሃን ወደ ተሠሩ ቤቶችማ ለመግባት እንዴት ትሆኛለሽ ሁለተኛም በጸሎቷ አቤቱ ቤተ ክርስቲያንህን ከሚጠብቀው የደረሰብኝን ኀፍረት ልሸከመው ያልቻልኩ እኔን በቅዱሳን መላእክቶችህ ፊት አታሳፍረኝ አለች።
ይችም ቅድስት ሰይጣንን ድል እስከ አደረገችው ድረስ ሃያ አምስት ዓመት ስትጋደል ኖረች በዚህ ሁሉ ከገዳም ግቢ ወደ በር አልወጣችም ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈች።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ኤላርዮስ_ሰማዕት
በዚህችም ቀን ደግሞ ኤላርዮስ የሚባል ኤጲስቆጶስ ሰማዕት ሆኖ አረፈ። ይህም ቅዱስ ከሀዲ*ውን ንጉሥ ዮላኪዮስን ጣዖ**ታትን ስለማምለኩ ይገሥጸውና ይመክረው ነበር ንጉሥ ዮላኪዮስም አይሁድ የሰቀሉትን ባለማምለኬ አንተ ከሀ*ዲ ትለኛለህ እነሆ አሁን እኔ አንተን ከሥቃይ ጽናት የተነሣ ያን የተሰቀለውን አምልኮቱን አስተውኻለሁ አለው።
ከዚህ በኋላም ከመኳንንቶቹ ለአንዱ መኰንን ሰጥቶ ባለመራራት ያለማቋረጥ ሁልጊዜ እንዲአሠቃየው አዘዘው መኰንኑም ወስዶ በየራሱ በሆነ ሥቃይ አንዲት ቀን እንኳ ከቶ ሳያቋርጥ ሁልጊዜ እያሠቃየው አንድ ዓመት ሙሉ ኖረ።
በዓመቱም ፍጻሜ በእሳት ውስጥ ጣሉት እርሱም ከእሳት መካከል ቆሞ እግዚአብሔርን ፈጽሞ እያመሰገነ ጸለየ ስለዚህችም ምልክት ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ብዙዎች አምነው በሰማዕትነት ሞቱ።
ከዚህም በኋላ ከአታክልት መካከል እንደ ሚወጣ ሆኖ ከእሳት አወጡት። መኰንኑም ከማሠቃየት በደከመ ጊዜ በእርሱ ላይም የሚያደርገውን በእጣ ጊዜ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡት አዝዞ ቂረጡት በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_ተጠምቀ_መድኅን
በዚህች እለት ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ተጠምቀ መድኅን መታቢያቸው ነው፡፡ ጻድቁ የተወለዱት በአፄ ሱስንዮስ ዘመን በ1610 ዓ/ም ሲሆን ወላጆቻቸው ወልደ ክርስቶስና ወለተ ማርያም ይባላሉ:: ታሕሳስ 2 ቀን እንደ መወለዳቸው ክርስትና የተነሱት ጥር 11 ቀን ነበርና ካህኑ "ተጠምቀ መድኅን" አላቸው:: በምድረ ጐጃም ከበቀሉ ታላላቅ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት አባ ተጠምቀ መድኅን ገና ከሕጻንነታቸው ጀምሮ ጸጋ እግዚአብሔር የጠራቸው ነበሩ::
ሕጻን እያሉ ቃለ እግዚአብሔር መማር ቢፈልጉም አባታቸው በግድ እረኛ አደረጋቸው:: እርሳቸው ግን በሕጻን ልባቸውም ቢሆን ቤተሰብን ማሳዘን አልፈለጉም:: ይልቁኑ ወደ በርሃ ይወርዱና አንበሳውን፣ ነብሩን፣ ተኩላውን ሰብስበው "በሉ እኔ ልማር ልሔድ ስለ ሆነ እስከ ማታ ድረስ ጠብቁልኝ" ብለው ለአራዊቱ አደራ ይሰጣሉ:: አራዊቱ ከበጉ፣ ከፍየሉ፣ ከላሙ ጋር ሲቦርቁ ይውላሉ:: ተጠምቀ መድኅን ደግሞ ዳዊቱን ወንጌሉን ሲማሩና ሲጸልዩ ውለው ማታ ይገባሉ::
ተጠምቀ መድኅን በሕጻንነታቸው ቁርስና ምሳቸውን ለነዳያን በመስጠት በቀን አንድ ማዕድ ብቻ ይቀምሱ ነበር:: 23 ዓመት ሲሞላቸው ወደ መርጡለ ማርያም ሔደው መንኩሰዋል::
ከዚህ ጊዜ በሁዋላ ለ37 ዓመታት በፍጹም ተጋድሎ ኖረዋል፣ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው አገልግለዋል፣ ከጐጃም እስከ ሱዳን ድረስ ወንጌልን ሰብከው በርካቶችን አሳምነው አጥምቀዋል (ካህን ናቸውና) እንዲሁም "7" ገዳማትንና "12" አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል::
ጻድቁ በተሰጣቸው መክሊት አትርፈው በ60 ዓመታቸው በ1670 ዓ/ም (በአፄ ዮሐንስ ዘመን) ጻድቁ ዐርፈዋል:: እግዚአብሔር የምሕረት ቃል ኪዳን የገባላቸው ሲሆን አጽማቸው ዛሬም በጋሾላ ቅዱስ ጊዮርጊስ የእናቶች ገዳም ውስጥ ይገኛል::
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ፣ #ከገድላት_አንደበት እና #ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)