ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu
👉ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ወይም ማዳመጥ ስትጀምር፣ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ብለህ ጸልይ፡-
👉“ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣ ቃልህን ሰምቼ አስተውል ዘንድ የልቤን ጆሮና ዓይኖች ክፈት፣ ፈቃድህንም እፈጽም ዘንድ።
👉 አእምሮህን እንዲያበራልህ እና የቃሉን ኃይል እንዲከፍትልህ ሁልጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ።
👉ብዙዎች በራሳቸው ምክንያት ታምነው ወደ ማታለል ተለውጠዋል።
👉ለሌሎች ምሳሌ መሆን የሚፈልግ ሰው በመጀመሪያ ራሱን መመርመር አለበት።
ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ❤️
#የመረዳት_ችግር_እንጂ_የብፁዕነታቸው_አስተምህሮስ_አማን_ነው።
1ኛ #አብ_ወልድ_መንፈስ_ቅዱስ_የሚገኙት_ድንግል_ማርያም_ባለችበት_ነው
እውነት ነው።
ቅዱሱ መጽሐፍ እንዲህ ይላል።
"ወአውሥአ እግዚእ ኢየሱስ ወይቤሎ፦ ‘ዘያፈቅረኒ ይዕቀብ ቃልየ፡ ወያፈቅሮ አቡየ ወእመቦ ዘዐቀበ ቃልየ አነ ወአቡየ ንመጽእ ኀቤሁ ወንገብር ምዕራፈ ውስቴቱ" እንዲል.
"ኢየሱስም መለሰ አለውም፦ የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል ወደ እርሱም እንመጣለን በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን። ዮሐንስ 14÷23_24
እኛም ጌታን ብንወደው ቃሉንም ብንጠብቅ አብ ይወደናል በረድኤት የሦስት ማደሪያ እንሆናለን።
2ኛ
#ለሐዋርያቱ_መንፈስ_ቅዱስ_የወረደላቸው_እሷ_ስላለች_ነው
እውነት ነው
ቅዱሱ መጽሐፍ እንዲህ ይላል።
"ወምስለ ኅሩይ ኅሩየ ትከውን፤ ወምስለ ጠዋይ ትጠዊ" እንዲል.
“ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፤ ከጠማማም ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ” መዝ 18፥26
"ብዙኀ ትረድእ ጸሎቱ ለጻድቅ ትክል ወታሰልጥ" እንዲል.
“የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።” ያዕቆብ 5፥16
ከሐዋርያት ቅድስና እና ንጽሕና ይልቅ የእመቤታችን ቅድስና እና ንጽሕና ይበልጣል በመሆኑም ሀብተ መንፈስ ቅዱስ እንዲያድርባቸው ሐዋርያት ከጸለዩት ብዙ ጸሎት ይልቅ የእመቤታችን ቅንጣት ጸሎት ይበልጣል።
ወላዲተ አምላክ ናትና።
የእመቤታችን ጸሎት ኃይለን አድርጓል ያውም ሀብተ መንፈስ ቅዱስ በእሷና በሐዋርያት ላይ እንዲወርድ አድርጋለችና።
3ኛ
#እሷ_ባትኖር_ኢየሱስ_አይመጣም_አይወለድም_አይኖርምም_ነበረ
የብፁዕነታቸው ትምህርት የማይታየውን ያየነው፤ የማይዳሰሰውን የዳሰስነው፤ የማይርበው ሲራብ፤ የማይደክመው ሲደክም፤ የማይበላው ሲበላ፤ የማይጠጣው ሲጠጣ ያየነው ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍስዋ ነፍስን ነስቶ ባሕሪዋን ስለነሳ ነው ለማለት እንጂ ብፁዕነታቸው "ለፌ እማርያም ክዋኔሁ ለወልድ/የወልድ መገኘቱ ከድንግል ማርያም ወዲህ ነው" አላሉም።
እግዚአብሔር ወልድም ከእመቤታችን በፊት አልነበረም አላሉም።
እውነት ነው
ቅዱሱ መጽሐፍ እንዲህ ይላል።
“ወይእዜኒ አንተ አባ ሰብሐኒ በስብሐትየ ዘሀሎ ምስሌከ እምቅድመ ይትፈጠር ዓለም። እንዲል
“አሁንም፥ አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ።” ዮሐንስ 17፥5 ያለውን ያውቃሉና።
#ብፁዕ_አባቴ_በአብ_ዘንድ_ክብረ_ነፍስ_አገኝ_ዘንድ_ይባርኩኝ!
#ፓንዋማንጦን
ሰኔ 29/10/2016 ዓ/ም
ናዝሬት #ኪዳነ_ምሕረት
በዚህችም ቀን ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ ልደቱ ነው፡፡ ዕረፍቱ ግን ሰኔ 7 ነው እየተባለም በሊቃውንት ይነገራል። የቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ሀገሩ ሶርያ ሲሆን አባቱ ሊቀ ካህናት ነበር። በኤጲስ ቆጶስነት የተሾመባት ሀገር በጤግሮስና በኤፍራጥስ መካከል በምትገኝ ሥሩግ በምትባል ሀገር ስለሆነ ያዕቆብ ዘሥሩግ ተባለ። በሦስት ዓመቱ እናቱ ቤተ መቅደስ ስትወስደው መልአክ እጁን ይዞ በሊቀ ጳጳሱ እጅ እንዲቆርብ አድርጎታል። በዚህም ጊዜ ምሥጢራት ሁሉ ተገልጠውለታል። ገና በ7 ዓመቱ ስለ ሦስት ነገሮች በእጅጉ ያለቅስ ነበር። ይኸውም ‹‹ነፍሴ ከሥጋዬ ተለይታ ስትወጣ፣ ከጌታችን ጋር ስገናኝና መጨረሻውን ፍርድ ስሰማ እነዚህን ሦስት ነገሮች በእጅጉ እፈራለሁ›› እያለ ያለቅስ ነበር። አቡነ ያዕቆብ በ12 ዓመቱ ብሉይንና ሐዲስን አጠናቆ ተምሮ ጨርሷል። ጸጋውን ዐውቀው 5ቱ ታዋቂ ሊቃነ ጳጳሳት መጥተው እጅ ነስተውት አዲስ ድርሰት ድረስልን ቢሉት እርሱም በፍጹም ትሕትና ‹‹በእናንተ ፊት እንኳን አዲስ ድርሰት ልደርስ ቀርቶ የተደረሰውንም መናገር አልችልም›› አላቸው። ያንጊዜም ሕዝቡና ሊቃነ ጳጳሳቱ ‹‹እግዚአብሔር በዚህ ሕጻን ላይ አድሮ ገሠጸን›› እያሉ ንስሓ ገብተዋል። ቅዱስ ያዕቆብ በነበረበት ዘመን በሮማው መና*ፍቅ ልዮን አማካኝነት ቤተ ክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ ለሁለት የተከፈለችበት ጊዜ ነበርና እነ ዲዮስቆሮስ ‹‹የውሾች ጉባኤ›› ከተባለው ከኬልቄዶን ጉባኤ ተለይተው ሃይማኖትን ሲያጸኑ ልዮንንም ማውገ*ዛቸውን* ያዕቆብ ሲሰማ በዲዮስቆሮስ ጽናት በእጅጉ ተደስቶ ደብዳቤ ጽፎ አመስግኖታል። እነ ልዮንን ግን አውግዞ እረግሟቸዋል። ልዮንም ተከታይ ባገኝ ብሎ ‹‹እኔን ምሰል›› በማለት ለቅዱስ ያዕቆብ ደብዳቤ ጻፈለት። አቡነ ያዕቆብም ‹‹ሳጥናኤል ከመላእክት ጋር ምን አንድ አደረገው? አንተ ርኩስ ነህ፣ የዲዮስቆሮስን ጥርስ አስወልቀህ፣ ጢሙን አስነጭተህ፣ ሃይማኖትህን የቀየርህ ከሁለት ዓለም ስደተኛ ጋር አልተባበርም፣ ይልቅስ ንስሓ ግባ፣ ንስሓ ባትገባ ግን አንተ ዲያብሎስ ነህ ተከታዮችህም አጋንንት ናቸው›› በማለት መልሱን ጽፎለታል። ልዮንም እምቢ ብሎ በክህደቱ ቢጸናበት አውግዞና እረግሞ ለይቶታል። ንጽሕናውና ቅድስናው ‹‹እንደ መላእክት ነው›› የተባለለት ያዕቆብ ዘሥሩግ ጻድቅም ሐዋርያም ደራሲም ተከራካሪ መምህርም ነው። ሦስት ድርሰቶች ያሉት ሲሆን በስሙ የተጠራው ቅዳሴም አለው።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ እና #ከገድላት_አንደበት)
🖍አፓርታማ ሚሸጥ
🖍CMC (cmc compound፣sunshine አፓርታማዎች አከባቢ)
🖍2ኛ ፎቅ ላይ
🖍110 ካሬ
🖍3bed room፣2 bathroom
🖍ከቤቱ ሌላ ከታች shop አለው(1/4 ድርሻ ለገዚው ሚሆን)
🖍1washing room /store አለው
💵 ዋጋ 15 ሚሊዮን
👉 2% ኮሚሽን መክፈል የሚችል
🤝 #እኛን_ስለመረጡን እናመሰግናለን🤝
✍️ የመረጃ ማዕከል፦ ለመሸጥ ወይም ለመግዛት ስትፈልጉ ወደ መረጃ ማዕከል ደውለው ሀብቶዎን ማስመዝገብ ይቻላሉ
🙏🙏🙏
☎️ +251970346808
☎️ +251988107532
👉 ለመረጃ ምዝገባና ሙሉ መረጃ ለመላክ በውስጥ መስመር በዚህ ይጠቀሙ 👉 @abiy7088 ወይም
👉 @customer_service777
➥ ሌሎች ሙሉ መረጃዎች በወቅቱ እንዲደርሳችሁ በቴሌግራም ቻናል ተቀላቀው ቤተሰብ ይሁኑ።
👉👉👉 Join 👇👇👇👇
➥ Join /channel/ethiocom7088
✍️ ቤት፥ መኪና ፥ ህንፃ፥ መጋዘን፥ ቦታ...ለመግዛት ሆነ ለመሸጥ
✍️ እንዲሁም ለምክር አገልግሎት ስትፈልጉ ያሳውቁን!!
🙏 ከእኛ ጋር ከሰሩ ውድ ሰዓታችሁን በስራ ላይ አውለውታል ማለት ነው🙏🙏
እግዚአብሔር አምላክ
አይዞአችሁ እኔ አሸንፌዋለሁ ብሎ ከተናገረ በኋላ
አይኑን ወደሰማይ አነሳ
ለምንድን ነው አይኑን ወደ ሰማይ ያነሳ ?
የመጀመሪያው በቁሙ ስትፀልዩ
አይናችሁን ወደላይ አድርጋችሁ ጸልዩ ለማለት ነው
ስርዓተ ጸሎት ነው ይሄ
በዙ መናፍቃን ሲፀልዩ
አይናቸውን ጨፍነው ተጎንብሰው
ጌታ ደግሞ
አይኑን ገልጦ ወደ ላይ አድርጎ
ሰሎሞን እንዲህ ይላል ምን አለ
አይኑን የሚጨፍን ተንኮለኛ ነው
ተንኮል ነውና አይኑን ጨፍኖ መጃጀል
አይንን ገልጦ ወደ ላይ ከፍ አድርጎ መጸለይ እኮ
ሰማያዊ ነኝ የሰማይ አባት አለኝ
ሁሉም ነገር ቢያልቅብኝ የሰማይ አባት አለኝ
አንድም ተስፋ የማድረግ ምልክት ነው
ማንኛውም ሰው በ24 ሰዓት ውስጥ ጸ ሎት ሲያደርግ
እጁን ዘርግቶ መጸለይ አለበት
ስትጸልዩ እጃችሁን ዘርግታችሁ ጸልዩ
ጸሎት የያዝን እንደሆንስ ካላችሁ
በቃል በምትደግሙ ጊዜ
እጃችሁን በመዘርጋት ጸልዩ
ምክንያቱም እጅ የሚጋደለው ዘርግቶ በመጸለይ ነው
እጀህ ብታሰናክልህ ቆርጠህ ጣላት
ማለት እጅህ እረፍት ብትፈልግ በሰፊህ ቅጣት
እጅህ አለሰጥም ብትልህ በምፅዋት ቅጣት
አይንህ ብታሰናክልህ አውጥተህ ጣላት
ማለት ልተኛ ብትልህ በአንቃዕዶ ቅጣት
አንቃዕዶ (በዕንባ ቅጣት ማለት ነው)
አንድም ፈቃዷን ከልክላት
ማለት የሻተውን ነገር አትሰጠው ማለት ነው
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን
#ሰኔ_19
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ ዐሥራ ዘጠኝ በዚች ቀን #ሐዲስ_ጊዮርጊስ ሰማዕት ሆነ፣ ሰማዕት በመሆን #አባ_ብሶይ_አኖብ አረፈ፣ አምስቱ #ቅዱሳን_አርሶፎኒስ_ጴጥሮስ_አስኪርዩን_አርጌንዮስና_ቢልፍዮስ በሰማዕትነት ሞቱ
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ሐዲስ_ጊዮርጊስ_ሰማዕት
ሰኔ ዐሥራ ዘጠኝ በዚች ቀን ሐዲስ ጊዮርጊስ ሰማዕት ሆነ። የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም መዛሕዝም ነው ትርጓሜውም ድንገተኛ ማለት ነው። እርሱም እስ*ላም ነበር ከግብጽ ደቡብ ድምራ ከሚባል አገር ክርስቲያን ሴት አግብቶ ከእርሷም ሦስት ልጆችን ወለደ ከሦስቱም አንዱ ይህ ቅዱስ ነው።
ከእናቱም ጋራ ወደ ቤተ ክርስቲያን ይሔድ ነበር ቅዱስ ቍርባንንም ይቀበል ዘንድ እናቱን ለመናት እርሷም ማንም የክርስትናን ጥምቀት ሳይጠመቅና ንጹሕ ሳይሆን ቍርባን ሊቀበል አይችልም አለችው።
ከዚህ በኋላም ከተረፈ መሥዋዕቱ ሰጠችው በጎረሳትም ጊዜ ጣዕሟ በአፉ ውስጥ እንደ ማር ሆነ የዚች የቁራሿ ጣዕም በአፌ ውስጥ እንዲህ የሆነ የዋናው የቍርባኑ ኅብስት ጣዕም ምን ያህል ይሆን ብሎ በልቡ አሰበ ከዚያች ጊዜ ጀምሮ ክርስቲያን ይሆን ዘንድ ወደደ።
በአደገም ጊዜ ክርስቲያን ሴት አገባ ክርስቲያን ይሆን ዘንድ መፈለጉንም ነገራት እርሷም ወደ ሌላ ሀገር ሒዶ የክርስትናን ጥምቀት እንዲጠመቅ መከረችው እርሱም ወደ ሌላ አገር ሔዶ ተጠመቀ ስሙንም ለውጦ ጊዮርጊስ ተባለ። እስላ**ሞችም በአዩት ጊዜ ይዘው ታላቅ ሥቃይን አሠቃዩት ከዚያም አምልጦ ላፍጥ ወደሚባል አገር ሸሸ በዚያም ሦስት ዓመት ኖረ።
ወሬውም በተገለጠ ጊዜ ቀጡር ወደ ሚባል አገር ሒዶ የልዳዊው ሰማዕት የቅዱስ ጊዮርጊስን ቤተ ክርስቲያን እያገለገለ ኖረ። ከዚህም በኋላ ወደ ሀገሩ ድምራ ተመለሰ እስላ*ሞችም ሰሙ ይዘውም ለመኰንኑ ሰጡት የመኰንኑም ሚስት ክርስቲያን ነበረች ለመኰንኑም አታሠቃየው አለችው መኰንኑም አሥሮ በወህኒ ቤት ዘጋበት።
እስላ*ሞችም ተሰበሰቡ የወህኒ ቤቱንም ደጅ ሰብረው ታላቅ ግርፋት ገረፉት አካላቱንም ቆራርጠው በሕይወትና በሞት መካከል ጣሉት። ሲነጋም ክርስቲያኖች የሞተ መስሏቸዋልና ሊቀብሩት መጡ ነገር ግን በሕይወት አገኙት።
ከዚህም በኋላ እስ*ላሞች ተሰብስበው ከዚህ ምክርህ ካልተመለስክ እኛ ጽኑ ሥቃይ አሠቃይተን እንገድልሃለን አሉት የመዛሕዝም ልጅ የከበረ ጊዮርጊስም ሰማይና ምድርን የፈጠረ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክደውም የፈለጋችሁትን አድርጉ አላቸው። እጅግም ተቆጡ በመርከብ ምሰሶ ላይም ሰቅለው ታላቅ ሥቃይን አሠቃዩት መኰንኑም ከስቅላት አውርደው በእሥር ቤት እንዲአሥሩት አዘዘ እንደዚሁም አደረጉ።
ሚስቱም ታጽናናውና እንዲታገሥ ታደርገው ነበር ሰይጣንም እንዳያስተውና የደከመበትን ዋጋ እንዳያጣ በልቡ ወደ ክርስቶስ ያስብ ዘንድ ትመክረው ነበር። ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጸለትና አረጋጋው አበረታታውም ከሰማዕታትም ጋራ እንደ ተቈጠረ በማግሥቱም ራሱን በሰይፍ እንደሚቆርጡት ነገረው። በነጋም ጊዜ እስላ*ሞች ወደ መኰንኑ ተሰብስብው ጊዮርጊስን ይሰጣቸው ዘንድ ፈለጉ መኰንኑም የወደዱትን ያደርጉበት ዘንድ እንዲሰጧቸው አዘዘ።
ከዚህም በኋላ ከእሥር ቤት አወጡት ድምራ በምትባል አገር በከበረ የመላእክት አለቃ በሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ራሱን በሰይፍ ቆረጡ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።
ከዚህ በኋላ በዚያች ቀንና በዚያች ሌሊት በሥጋው ላይ እሳትን አነደዱ እሳቱም በላዩ እየነደደ ምንም ምን አልነካውም ወስደውም በገቢያ ውስጥ ጣሉት ከዚያም አንሥተው በባሕር ውስጥ ጣሉት በእግዚአብሔርም ፈቃድ ወደ ደሴቱ ወደብ ዳር ደረሰ እናቱም ጠብቃው ነበረና ወስዳ ገነዘችው ለጥቂት ወራትም በቤቷ ውስጥ ሸሸገችው።
ከዚህም በኋላ ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠሩለት ሥጋውንም በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ታላላቅና ብዙዎች ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ብሶይ_አኖብ
ዳግመኛም በዚች ዕለት ሰማዕት በመሆን አባ ብሶይ አኖብ አረፈ፡፡ ትርጓሜውም የጠራ ወርቅ ማለት ነው። ይህም ቅዱሱ ከድምያጥ አውራጃ ስሟ ባኖስ ከሚባል አገር ከአቅራብ መኰንን ከቆጵርያኖስ ጭፍሮች ውስጥ ከከተማዋ ታላላቅ ሰዎች ልጆች ወገን ነበር። በዚህም ቅዱስ በመኰንኑ ዘንድ ነገር ሠሩበት። ቅዱሱም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በፊቱ ታመነ።
ወደ አንዴናውም ወሰዱት በመኰንኑ አርያኖስም ፊት ቁሞ በጌታችን ታመነ አርያኖስም በእርሱ ላይ ተቆጣ ለአማልክትም ሠዋ አለው አልታዘዘለትም ሥቃዩንም አልፈራም መኰንኑም ወስዶ ጽኑዕ ሥቃይ አሠቃየው ከዚያም ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡት አዘዘ ወደሚገድሉበት ቦታም ሊወስዱት አወጡት ብዙ ሕዝብም ይከተሉት ነበር እነሆ ከዚያም የአርያኖስ መኰንን አንበሶች ነበሩ። የሚጠብቃቸውም ሰው ነበር እነርሱም በብረት ሰንሰለት ታሥረው ነበር ከእነርሱም አንዱ አንበሳ የብረት ሰንሰለቱን በጥሶ ሩጦ ወደ ቅዱሱ ደረሰ። የእግዚአብሔርም መልአክ ቅዱሱን በአንበሳው ጀርባ ላይ አወጣውና ዐይነ ፀሐይ ወደሚባል አገር እስከሚያደርሰው በረረበት ቅዱሱ ግን ዐይኑን ሸፍኖ ስለ ነበረ ወዴት እንዳለ አላወቀም በዚያም ራሱን በሰይፍ ቆረጡት የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱሳን_አርሶፎኒስ_ጴጥሮስ_አስኪርዩን_አርጌንዮስና_ቢልፍዮስ
በዚችም ቀን አምስት ጭፍሮች በሰማዕትነት ሞቱ እሊህም አርሶፎኒስ፣ ጴጥሮስ፣ አስኪርዩን፣ አርጌንዮስና ቢልፍዮስ በዲዮስጲልዪስም ቅጽር ውስጥ ይኖሩ ነበር። መኰንኑም ለጣዖታት እንዲሠዉ በአስገደዳቸው ጊዜ እኛስ የንጉሣችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ትእዛዝ እንፈጽማለን ለእርሱም እንሠዋለን አሉት መኰንኑም ሰምቶ ተቆጣ በአንድ ቤት ውስጥም እንዲዘጉባቸውና እስከ ሁለት ቀን እህል ውኃ እንዳይሰጧቸው አዘዘ።
ከዚያም በኋላ እንዲያመጧቸው አዘዘ በፊቱም በቆሙ ጊዜ ለአማልክት ሠዉ አላቸው እነርሱም በአንድ ቃል እኛስ ለፈጣሪያችን ለክርስቶስ እንሠዋለን ለረከሱ አጋንንት ግን አንሠዋም አሉት። አንገታቸውንም አሥረው ወደ ሌላ አገር ይወስዱአቸው ዘንድ አዘዘ። አርጌንዮስም ወንድሞቹን እኔ እውነትን እነግራችኋለሁ የእግዚአብሔር መልአክ አምስታችንንም በስማችን ሲጠራን ሰምቼዋለሁና አላቸው።
ዳክስ ወደሚባል መኰንንም በአደረሷቸው ጊዜ መኰንኑ አስቀድሞ አርሶፎኒስን ወስዶ ለአማልክት ሠዋ አለው እምቢ በአለውም ጊዜ በፈረስ ጅራት ላይ አሥረው በከተማ ውስጥ እንዲጐትቱትና እንዲአዞሩት አዘዘ። በመለሱትም ጊዜ በውሽባ ቤት ማንደጃ ውስጥ ፊቱን እንዲአጠወልጉት አዘዘ ሁለተኛም እስከ ሚጨነቅ ድረስ በሠረገላ ውስጥ አሥረው ቍልቍል ሰቀሉት ሃይማኖቱንም ጠብቆ ክብር ይግባውና ለጌታችን ነፍሱን ሰጠ።
ሁለተኛም ጴጥሮስን አቀረቡት ዳክስም ለአማልክት ሠዋ አለው ትእዛዙንም ባልተቀበለው ጊዜ እንዲአሠቃዩትና እንጨት ተክለው ዘቅዝቀው እንዲሰቅሉት አዘዘ ሁለተኛም ምድሩን ቆፍረው ከትከሻው በታች ቀብረው በቅሎዎችን በላዩ እንዲነዱበት አዘዘ ይህንንም እግዚአብሔር እየረዳው ታገሠ ከጉድጓዱም በእወጡት ጊዜ ከሥቃዩ ብዛት የተነሣ ሥጋው ጠወለገ መናገርም ተሣነው በግንድ ውስጥም አሥረው ጣሉት ።
ከዚህም በኋላ አርጌንዮስን እቀረቡት ዳክስም ለአማልክት ሠዋ አለው እምቢ ባለውም ጊዜ እስከሚገድሉት ድረስ ያሠቃዩት ዘንድ አዘዘ ያለ መብልና መጠጥም በተበሳ ግንድ ውስጥ አሥረው ዘቅዝቀው ሰቀሉት።
https://youtu.be/mu8ewYk81qc?si=twbl3rFTc_5Odg4j
Читать полностью…እነዚያ እንደ እሳት ላንቃ የተከፋፈሉት ልሳኖች ከመታየትም አልፈው በሐዋርያቱ ላይ መቀመጣቸው፣ ደቀ መዛሙርቱ የሚያዩት ነገር ሁሉ ቅዠት ወይም ምናባዊ ሳይሆን እውነተኛ የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ መሆኑን እንዲገነዘቡ ነው፡፡ ከዚያም በኋላ በሁሉም ላይ መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፡፡ የእግዚአብሔርን ልጅ በረገጡና አመጽ ወዳድ በነበሩት አይሁድ ቅንዓትና ቁጣ ሲሞላ፣ የሰላም ልጆች በነበሩት ሐዋርያት ግን መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፡፡ ስለዚህም መንፈስ ቅዱስ ይናገሩ ዘንድ (በየአቅማቸው) እንደ ሰጣቸው በሌሎች ቋንቋዎች ይናገሩ ጀመር፡፡
እግዚአብሔር አሕዛብ ያለ ሐዋርያት ስብከት በሥላሴ ማመን እንደማይችሉ፣ ሐዋርያትም ያለ መንፈስ ቅዱስ መውረድ በየአገሩ ቋንቋዎች ሁሉ መስበክ እንደማይችሉ ዐወቀ፡፡ ስለዚህም በሰናዖር ሜዳ የተበተኑትን የዓለምን ቋንቋዎች በሐዋርያት አንደበት ሰብስቦ ያኖር ዘንድ ቅዱስ መንፈሱን ላከ፡፡ የተላከውም መንፈስ ያለ አንድ ቋንቋ የማይናገረውን የሐዋርያቱን አንደበት በቅጽበት አሰለጠነው። በእውነት እንደ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ያለ አስማሪ ማን ነው?!በዚህችም እለት ሐዋርያቱ በዓለም ሁሉ ቋንቋዎች ተሞልተው ከእርሷ የወጡባት የጽዮን አዳራሽ (ጽርሐ ጽዮን) እንደ ምን ያለች ናት?! መንፈስ ቅዱስ ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ ታይታ የማትታወቅ ልዩ ትምህርት ቤት አደረጋት፡፡
ሐዋርያቱም በመንፈስ ቅዱስ ተሟሙቀው በሰበኩት በመጀመሪያ ዕለት ስበከት ብዙዎችን አሳምነው አጠመቁ። በዚህ የመከር በዓል አይሁድ ከአዲሱ እህል ለእግዚአብሔር ቁርባን ሲያቀርቡ፣ ሐዋርያቱ ግን የክርስቶስ አካል ለሆነችው ለሐዲሲቷ ቤተ ክርስቲያን ከእህል ቁርባን ይልቅ የሚወደዱ ምእመናንን ስጦታ አድርገው አቀረቡ። በአይሁድ የመከር በዓል ቀን በሐዋርያቱ በተሰጠ ትምህርት የእግዚአብሔር እርሻ የሆኑ ምዕመናን በዝተው አብበው ተገኙ። እውነትም የመከር በዓል!!!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
selam@dnabel.com
/channel/Dnabel
👉አንተ ሰው ነህ አሁንም የመርዛማ እባብ መርዝ ትተፋለህ።
አንተ ሰው ነህ አሁንም እንደ ተናደደ አውሬ ሆነሃል።
አፍ የተሰጥህ ለመቁሰል ሳይሆን ለመፈወስ ነው፡፡
👉"ፍጹም ፍቅርን ያገኙ ሰዎች በምድር ላይ ብቻቸውን ያሉ ይመስላሉ::
👉 ዝናም ሆነ ስድብ ደንታ የሌላቸው ፈተናዎችን እና ስቃዮችን ያጣሉ,
👉የሁሉንም ጣዕም እና የምግብ ፍላጎት ያጣሉ.
👉ሌላ ድጋፍ ወይም እረፍት ሳያገኙ ሳይታክቱ ፍለጋ ይሄዳሉ.
👉ተወዳጆች እየሰሩ፣ እየበሉ፣ እየተመለከቱ፣ እየተኙ፣ ሀሳባቸው እና ፍላጎታቸው የተወደደውን ማግኘት ብቻ ነው፣ ሀብታቸው ባለበት፣ ልባቸውም እዚያ አለ፡፡
👉ሕይወታችን ብሩህ ቢሆን ኖሮ ስብከት አያስፈልግም ነበር ,
👉ከሥራችን ጋር ብንመሰክር ቃል ባላስፈለገም ነበር።
👉 እውነተኛ ክርስቲያኖች ብንሆን ከዚህ በኋላ አረማውያን አይኖሩም ነበር።
† ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ስንክሳር ዘተዋሕዶ:
#ሰኔ_27
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ሰኔ ሃያ ሰባት በዚች ቀን ከተመረጡ አርድእት ውስጥ #ሐዋርያው_ሐናንያ አረፈ #ቅዱስ_ቶማስ_ሰንደላት በሰማዕትነት ሞተ፣ #የድሀው_አልዓዛር መታሰቢያው ነው፣ #ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘስሩግ ልደቱ ነው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ሐናንያ_ሐዋርያ
ሰኔ ሃያ ሰባት በዚህች ቀን ከተመረጡ አርድእት ውስጥ ሐዋርያው ሐናንያ አረፈ። ይህንንም ቅዱስ ሐዋርያት በደማስቆ ከተማ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት። በውስጧም ሕይወት ሰጭ የወንጌልን ትምህርት አስተማረ ዳግመኛም በቤተ ገብርኤል ውስጥ ሰብኮ ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሆነች የቀናች ሃይማኖት ብዙዎቹን መለሳቸው የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው እውነተኛውንም የሃይማኖት ብርሃን አበራላቸው።
ይህም ሐናንያ ሐዋርያው ጳውሎስን ይቅር ባይ ጌታችን በቸርነቱ ከክህደቱ በጠራውና ምርጥ ዕቃ በአደረገው ጊዜ ያጠመቀው ነው እጁንም በራሱ ላይና በዐይኖቹ ላይ ጭኖ ያዳነው እርሱ ነው።
ጌታችንም በእጆቹ ታላላቅ ድንቆችንና ተአምራቶችን አደረገ በስብከቱም ብዙዎች አሕዛብ አመኑ ከአይሁድም ብዙዎቹን ክብር ይግባውና ክርስቶስን ወደ ማመን መለሳቸው።
ከዚህም በኋላ ዐመፀኛው መኰንን ሉክያኖስ ይዞ ታላቅና አስጨናቂ ሥቃይን አሠቃየው ጐኖቹንም ሠንጥቆ በእሳት መብራቶች አቃጠለው። ከዚህም በኋላ ከከተማው አውጥተው በደንጊያ እንዲወግሩት አዘዘ በዚያም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እጅ ነፍሱን ሰጠ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ቶማስ_ሰማዕት_ዘሰንደላት
በዚህችም ቀን ሰንደላት ከሚባል አገር ቅዱስ ቶማስ በሰማዕትነት ሞተ። ከእርሱም ጋራ ሰባት መቶ ወንዶችና ዘጠኝ ሴቶች በሰማዕትነት ሞቱ ።
ይህም ቅዱስ ዕድሜው ዐሥራ አንድ ዓመት በሆነው ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በበረሀ እሪያዎችን ሲጠብቅ ተገለጸለት ወደ መኰንኑ ሔዶ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢያሱስ ክርስቶስ ስም ይታመን ዘንድ አዘዘው። ያን ጊዜም ተነሥቶ የገመድ አለንጋ ይዞ ብቻውን ወደ እስክንድርያ አገር ሔደ በመኰንኑም ፊት ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰም ታመነ።
መኰንኑም ለአማልክት ሠዋ አለው ጸሐፊውም ሊያደርገው ቃል ኪዳን ገባለት ቅዱስ ቶማስም ተቆጥቶ ያቺን አለንጋ አውጥቶ መኰንኑን ብዙ ግርፋት ገረፈው የመኰንኑ ሎሌዎችም ይዘው ጽኑ ሥቃይን አሠቃዩት ሥጋውንም በብረት መጋዝ ሠነጠቁ ክብር ይግባውና ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ርዳታን ለመነ ወዲያውኑም መልአኩን ልኮ አዳነው።
ከዚህ በኋላ በእሥር ቤት አሠሩት የወህኒ ቤቱ ጠባቂም ስለ ታመመው ልጁ ለመነው እርሱም ያንን የገመድ አለንጋ ሰጠውና ይህን አለንጋ በልጅህ ላይ አኑር አለው እንዲሁም አደረገ። ያን ጊዜም ልጁ በእግዚአብሔር ኃይል ዳነ።
መኰንኑም በሰማ ጊዜ ወደርሱ አቅርቦ ለአማልክት ሠዋ አለው ቅዱስ ቶማስም በፊትህ ዕሠዋ ዘንድ ና እንሒድ ብሎ መለሰለት። መኰንኑም ዕውነት መስሎት ደስ አለው ወደ ጣዖቶቹ ቤትም ወሰደው ያን ጊዜ ቅዱስ ቶማስ ጣዖታቱን ያጠፋቸው ዘንድ ወደ ጌታችን ለመነ። ወዲያውኑ ሁሉም ጣዖታት ተሰባበረ ሰይጣኑም በመኰንኑ ላይ ተቀመጠ ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም ብሎ እስከሚታመን ድረስ አነቀው። አሕዛብም ይህንን ድንቅ ነገር አይተው እጅግ አደነቁ ክብር ይግባውና ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም እያሉም ጮኹ በእርሱም አመኑ።
ያላመኑት ግን በጨለማ ቤት ውስጥ አሠሩት ያለ መብልና ያለ መጠጥ ከብዙ ሥቃይም የተነሣ ከአፉ ደም እየፈሰሰ ዐሥራ አምስት ቀን በዚያ ተቀመጠ የእግዚአብሔር መልአክም ወርዶ ፈወሰው።
አንዲት ሴት ዕውር ልጅ ነበራት ከዚያም ደም ወስዳ የልጅዋን ዐይን አስነካችው ወዲያውኑም አየ። ቅዱስ ቶማስንም ከወህኒ ቤት አውጥተው ሴት አንበሳ ሰደዱበት ወደርሱም በደረሰች ጊዜ እግሮቹን ላሰች ሰገደችለትም ።
ዳግመኛም በብረት መንደልቶ አፉ ላይ ደበደቡት በዚያን ጊዜ በሥቃይ ውስጥ ከእርሱ ጋራ ከበንደላ አገር ቅዱስ በብኑዳ ከበልኪም አገር ቅዱስ ሙሴ ነበሩ። እርስ በርሳቸው አንዱ አንዱን ያጽናናው ነበር።
ከዚህም በኋላ ቅባትና የነዳጅ ድፍድፍ አፍልተው በቅዱስ ቶማስ ራስ ላይ ደፉት ነገር ግን ምንም ምን ጉዳት አልደረሰበትም። እንደገናም አባለ ዘሩን ቈርጠው በአውድማ ውስጥ አበራዩት ደግመውም ታላቅ ደንጊያ በአንገቱ ላይ ሰቅለው አሠቃዩት። ከማሠቃየቱ የተነሣ በደከመው ጊዜ መኰንኑ አርያኖስ ወደ እንዴናው ከተማ ሊወስደው ይዞት ተነሣ ጣው ወደሚባል አገርም በደረሱ ጊዜ የቅዱስ ቶማስን ራስ ቆረጡት በዚያም ምስክርነቱን ፈጸመ በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ ከእርሱ ጋራ መከራ ተቀብለው የሞቱ ሰባት መቶ ወንዶችና ዘጠኝ ሴቶችም እርሱ ሥቃይ በተቀበለበት ወራት የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ድሀው_አልዓዛር
በዚህች ቀን የድሀው አልዓዛር መታሰቢያው ነው፡፡ ይኸኛው አልዓዛር በሉቃስ ወንጌል ላይ እንደተነገረው ባለጸጋው ነዌ ድሀው አልዓዛር በደጁ ወድቆ ትራፊውን ፍርፋሪ ይመኝ የነበረ ውሾች ቁስሉን እስኪልሱለት ድረስ በባጸጋው ዘንድ የተናቀና የወደቀ ነበር። ሁለቱም ሲሞቱ ግን ባለጸጋው ነዌ በሲኦል ሆኖ እየተሠቃየ ድሀው አልዓዛርን በአብርሃም እቅፍ አይቶታል። ቅዱስ አልዓዛር በዚህች ዕለት በዓመታዊ በዓሉ ታስቦ ይውላል። ሙሉ ታሪኩ በሉቃስ ወንጌል 16፡19-31 ላይ እንዲህ ተቀምጧል። ‹‹ቀይ ልብስና ቀጭን የተልባ እግር የለበሰ አንድ ባለ ጠጋ ሰው ነበረ፣ ዕለት ዕለትም እየተመቸው በደስታ ይኖር ነበር። አልዓዛርም የሚባል አንድ ድሀ በቍስል ተወርሶ በደጁ ተኝቶ ነበር፣ ከባለ ጠጋውም ማዕድ ከሚወድቀው ፍርፋሪ ሊጠግብ ይመኝ ነበር፣ ውሾች እንኳ መጥተው ቍስሎቹን ይልሱ ነበር። ድሀውም ሞተ፣ መላእክትም ወደ አብርሃም እቅፍ ወሰዱት፣ ባለ ጠጋው ደግሞ ሞተና ተቀበረ። በሲኦልም በሥቃይ ሳለ አሻቅቦ አብርሃምን በሩቅ አየ አልዓዛርንም በእቅፉ። እርሱም እየጮኸ አብርሃም አባት ሆይ ማረኝ፣ በዚህ ነበልባል እሣቀያለሁና የጣቱን ጫፍ በውኃ ነክሮ መላሴን እንዲያበርድልኝ አልዓዛርን ስደድልኝ አለ። አብርሃም ግን (ልጄ ሆይ አንተ በሕይወትህ ሳለህ መልካም እንደ ተቀበልህ አስብ አልዓዛርም እንዲሁ ክፉ፤ አሁን ግን እርሱ በዚህ ይጽናናል አንተም ትሠቃያለህ። ከዚህም ሁሉ ጋር ከዚህ ወደ እናንተ ሊያልፉ የሚፈልጉ እንዳይችሉ፣ ወዲያ ያሉ ደግሞ ወደ እኛ እንዳይሻገሩ በእኛና በእናንተ መካከል ታላቅ ገደል ተደርጎአል› አለ። እርሱም ‹እንኪያስ አባት ሆይ ወደ አባቴ ቤት እንድትሰደው እለምንሃለሁ፤ አምስት ወንድሞች አሉኝና። እነርሱ ደግሞ ወደዚህ ሥቃይ ስፍራ እንዳይመጡ ይመስክርላቸው› አለ። አብርሃም ግን ‹ሙሴና ነቢያት አሉአቸው፤ እነርሱን ይስሙ› አለው። እርሱም አይደለም፣ አብርሃም አባት ሆይ ነገር ግን ከሙታን አንዱ ቢሄድላቸው ንስሐ ይገባሉ› አለ። አብርሃምም ‹ሙሴንና ነቢያትንም የማይሰሙ ከሆነ ከሙታንም እንኳ አንድ ቢነሣ አያምኑም› አለው።›› ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ።
/channel/theYescoin_bot/Yescoin?startapp=NjGiu7
Читать полностью…ለዛቲ ቤት ሣረራ አብ ቀዲሙ ለዛቲ ቤት ሀነጻ ወልድ ወፈጸማ መንፈስ ቅዱስ" (ሊቁ ቅዱስ ያሬድ)
በሰኔ 20 ቀን በሐዲስ ኪዳን ለመጀመሪያ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ባረገች በአራተኛው ዓመት (በ54ዓ/ም) በፊልጵስዩስ ቂሳሪያ ከሦስት አዕባን (ዓለቶች) መታሰቢያ ይሆን ዘንድ በስሟ የተሠራችው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ታንጾ በሰኔ 21 ቀን ቅዳሴ ቤቷ የከበረበት ታላቅ ዕለት ነው። ዕለቱም ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው።
በብሉይ ኪዳን የመጀመጀሪያዋ ቤተክርስቲያን ደብተራ ወይም ድንኳን ነበረች። ከዚያም ቤተ መቅደስ በዘሩባቤል ዘመን 46 ዘመን ፈጅቶ ተሠርቷል። "በመካከላቸውም አድር ዘንድ መቅደስ ይሥሩልኝ" (ዘጸ.25÷8)። በሐዲስ ኪዳንም ሰኔ 20 ቀን ጌታችን ከሦስት ድንጋዮች ቤተ መቅደስ አንጾ ሰኔ 21 ቀን ቅዳሴ ቤቱ የከበረበት ዕለት ነው። (ማቴ.16÷13-19)
“ሰላም ለኪ ቤተ ክርስቲያን እምየ፣ ዘትጼንዊ መጽርየ፣ ብኪ ጸናዕኩ እምከርሠ እምየ፣ ቤተ ክርስቲያን አክሊለ ርእስየ ሰላም ለኪ፤ እንደ ቀጋ የምትሸቺ ቤተ ክርስቲያን እናቴ ሰላምታ ለአንቺ ይገባል፤ ከእናቴ ማሕፀን ዠምሮ በአንቺ ጸናኁ፤ የራሴ አክሊል የምትኾኚ ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ ለአንቺ ይገባሻል" (አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ)
ለእኛም የእመቤታችን የወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም ልመናዋ ክብሯ፣ ጣዕመ ፍቅሯና በረከቷ በሁላችን ላይ ይደርብን:: ሀገራችንን ከጥፋት ሕዝባችንን ከስደት ከመለያየት፤ ቤተ ክርስቲያናችን ከፈተና ይጠብቅልን።
#ፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሰንበት_ትምህርት_ቤት
#ፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሚዲያ
Follow us on
👉 /channel/fre_amde_haymanot_media
👉 http://linktr.ee/fre_amde_haymanot_media
✞✞✞✝🌹 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✝🌹✞✞✞
❖✝🌹 እንኳን አደረሳችሁ ✝🌹❖
❖✝🌹 ሰኔ 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት✝🌹
=>ትናንት ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችንና
መድኃኒታችን ኢየሱስ_ክርስቶስ ወደ ሐዋርያት ወረደ:: ፊልዽስዩስ በምትባል ሃገር በዼጥሮስ እጅ
የመጀመሪያዋን ቤተ_ክርስቲያን አነጸ ብለን ነበር:: በዚህች ዕለት ደግሞ አእላፍ
መላዕክትን: ሰማያውያን ቅዱሳንን እና እናቱን ቅድስት
ድንግል
ማርያምን ይዟት ወረደ::
+ሐዋርያቱ አብዛኞቹ እዛው ሲጸልዩ አድረው ነበርና ጌታችን
ከቅዳሴው በፊት 2 ነገሮችን አሳየ:-
1.አስቀድሞ ቤተ ክርስቲያኗን በድንግል እናቱ ስም አክብሮ
ሥርዓተ ቤተ ክርረስቲያንን አሳየ::
2.ቀጥሎ ደግሞ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ_ዼጥሮስን ከመካከል አቁሞ "አርሳይሮስ" ሲል ሾመው:: ይኼውም የዓለም ሁሉ ሊቀ ዻዻሳት
(ፓትርያርክ) ማለት ነው:: በዚህ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት
"አክዮስ" እያሉ 3 ጊዜ አሰምተው ጮሁ:: አክዮስ ማለት በግዕዙ
"ይደልዎ": በዐማርኛው ደግሞ "ይገባዋል: ያሥምርለት"
እንደ
ማለት ነው::
+ጌታችን ይሕን ከከወነ በኋላ ይቀድስ ዘንድ ጀመረ::
¤አማናዊት ማሕደሩን ድንግል ማርያምን መንበር አድርጎ:
¤ቅዱስ ዼጥሮስ እንደ ተራዳኢ ካህን ቆሞ:
¤ቅዱስ_እስጢፋኖስ ሠራኢ ዲያቆን ሆኖ:
¤ሐዋርያት ድንግልን ከበው:
¤መላእክተ ብርሃን በክብራቸው ቁመው ጌታችን ቀድሶ
ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወዳጆቹ አቀበለ::
+በዚያች ዕለት በፍጡር አንደበት ተከናውኖ ሊነገር
የማይችል ደስታ ተደረገ:: ከቅዳሴ በኋላ ጌታችን
ሐዋርያትን
አዘዛቸው::
"ከዚህ ቀን ጀምሮ በመላው ዓለም በእናቴ በማርያም ስም
አብያተ ክርስቲያናትን እነጹ:: ይህችን ዕለት የሚያከብራትን
አከብረዋለሁ::" ብሏቸው ከድንግል እናቱ ከመላዕክቱ ጋር
ዐረገ::
+"+ ሰኔ_ጐልጐታ +"+
=>ዳግመኛ በዚህ ቀን ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ
ይታሰባል::
ይኸውም ከሕንድ አውራጃዎች በአንዱ ወንጌልን ሰብኮ
እኩሎቹ ሲያምኑ እኩሎቹ እንቢ አሉ:: ቅዱስ ቶማስም
ያመኑትን
"ከጣዖት አምልኮና ከዝሙት ሸሹ" ብሎ መከራቸው::
+ምክሩን ከሰሙት አንዱ በዚያው ምሽት ሊጠጣ ወደ
መሸታ ቤት ይገባል:: ሰው ሁሉ ከወጣ በኋላ ባለ
መሸተኛዋ ሴት
እንደለመደችው አብረው እንዲተኙ ስትጠይቀው "እንዴት
ሐዋርያው ከዝሙት ሽሹ እያለ እንዲህ ትይኛለሽ?" በሚል
ሰይፍ
አውጥቶ አንገቷን ቆረጣት::
+እርሱ መልካም ያደረገ መስሎታል:: የሠራው ሥራ
(መግደሉ) ግን አሕዛባዊ ግብር ነው:: በማግስቱ ቅዱስ
ቶማስ ነገሩን
ሰምቶ ሰዎችን ሰበሰበና "ይህንን የአውሬ ድርጊት የፈጸመ
ማነው?" ሲል ጠየቀ:: ፈጻሚው ግን አልታወቅም በሚል
ዝም
አለ:: ወዲያው ቅዱሱ ሐዋርያ ዳቦ አንስቶ ቆረሰና
"ለበረከት እያነሳችሁ ውሰዱ" አለ:: ሰውየው ተራውን
ጠብቆ ሊያነሳ
ሲል እጁ ሰለለች::
+ሐዋርያው "ምነው ልጄ! ምን ሆንክ?" አለው:: እሱም
እንዳላመለጠ ሲያውቅ እውነቱን ተናዘዘ:: ቅዱስ ቶማስ
ግን ሕዝቡ
ሁሉ እንደተሰበሰበ ያን ወጣት ገስጾ "አስከሬኑን
አምጡልኝ" አለ:: የወጣቱን እጅ ፈውሶ "በል . . .
የገደልኩሽ
እኔ: የሚያስነሳሽ ግን ጌታየ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ነው . . . ብለህ አንገቷን ቀጥለው" አለው::
+እንዳለው ቢያደርግ የሞተችው አፈፍ ብላ ተነሳች::
ይህንን ተአምር ያዩ አሕዛብ አምነው ተጠምቀዋል::
=>ከሐዋርያው በረከት ይክፈለን::
=>ሰኔ 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
2.ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
3.ቅዱሳን ሐዋርያት
4.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
5.ቅዱሳን ዻውሎስና በርናባስ
6.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
7.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ
8.ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘምስር (ሰማዕት)
9.አባ ከላድያኖስ ሊቀ ዻዻሳት
❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ አበው ጎርጎርዮሳት
2፡ አባ ምዕመነ ድንግል
3፡ አባ ዓምደ ሥላሴ
4፡ አባ አሮን ሶርያዊ
5፡ አባ መርትያኖስ
6፡ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል
=>+"+ ስለ ጽዮን ዝም አልልም . . .
አሕዛብም ጽድቅሽን: ነገሥታትም ሁሉ ክብርሽን ያያሉ::
የእግዚአብሔርም አፍ በሚጠራበት በአዲሱ ስም
ትጠሪያለሽ::
በእግዚአብሔር እጅ የክብር አክሊል በአምላክሽም እጅ
የመንግሥት ዘውድ ትሆኛለሽ:: +"+ (ኢሳ. 62:1-3)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
""ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን""::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
ዳግመኛም እስኪርዪንን አቀረቡት ዳክስም ለራስህ እዘን በክፉ አሟሟትም እንዳትሞት ለአማልክት ሠዋ አለው እምቢ ባለውም ጊዜ እንዲያሠቃዩት እንዲሰቅሉትና ሥጋውን እንዲሰነጥቁት አዘዘ ወታደሮችም ተረከቡትና በጽኑ ሥቃይ አሠቃዩት በትዕግሥቱም በአሸነፋቸው ጊዜ ለመኰንኑ ነገሩት በረኃብና በጽምዕ ይሞት ዘንድ በግንድ ውስጥ አሥረው በባዶ ቤት እንዲዘጉበት አዘዘ እንዲሁም አደረጉበት።
ደግመው ዲያቆን ቢልፍዮስን አቀረቡት መኰንን ዳክስም እንዳትሞት ለአማልክት ሠዋ አለው ባልሰማውም ጊዜ እስከሚገድሉት ድረስ እንዲአሠቃዩት አዘዘ ሥጋውን ሠነጣጥቀው በከተማው አደባባይ ጐተቱት እንጨት ተክለውም ቍልቍል ሰቀሉት በአንገቱም ከባድ ደንጊያ አንጠለጠሉ ከሃይማኖቱም ባልተናወጸ ጊዜ በረኃብና በጽምዕ እንዲሞት በግንድ ውስጥ አሥረው በላዩ መዝጊያ ሠርተው ዘጉበት።
በየዕለቱም ወንድሞች ምእመናን ከውጭ ሆነው ይጐበኙት ነበር ጳሔን የተባለው የሰኔ ወር በባተ በሠላሳ ጴጥሮስ ነፍሱን ሰጠ። እርሱንም አውጥተው ደጁን በሌሎቹ ላይ ዘጉ። የከበረ አርጌንዮስም ከአምስት ቀን በኋላ አረፈ እርሱን አውጥተው በቀሩት ላይ ደጁን ዘጉ። ብፁዕ አስኪርዮንም ከዐሥራ ሁለት ቀን በኋላ አረፈ። እርሱንም አውጥተው በቅዱስ ቢልፍዮስ ላይ ደጃፍ ሠርተው ዘጉበት እርሱም የሚያርፍበት ቀን ስትደርስ ወንድሞቼ ታገሡኝ በዚች ሌሊት እወጣለሁና አላቸው። ከዐሥራ ዘጠኝ ቀን በኋላም በዚያች ሌሊት ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሰኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሰኔ)
https://youtu.be/9MGuU-oMcLI?si=5czNowYH_WHZRGiE
Читать полностью…+++"እውነትም የመከር በዓል"+++
ጌታችን ከትንሣኤው በኋላ በጋራም በተናጠልም ለሐዋርያቱ እየታያቸው የትንሣኤውን አማናዊነትና ‹ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ነገር እየነገራቸው› አርባ ቀን ቆይቷል፡፡(ሐዋ 1:3) በአርባኛውም ቀን ሲያርግ ‹የሚያጸና፣ የሚያነጻ እና የሚያጽናና መንፈስ ቅዱስን› እንደሚልክላቸው ተስፋን ሰጣቸው፡፡ ነገር ግን ከላይ ኃይልን እስከሚቀበሉባት ቀን ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ እንዲቆዩ አዘዛቸው፡፡ (ሉቃ 24፡49-51) ሐዋርያቱም ከጌታ ዕርገት በኋላ በጽዮን አዳራሽ (ጽርሐ ጽዮን) ውስጥ በአንድ ልብ ሆነው በጸሎት ይተጉ ጀመር፡፡
ለሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ የወረደበት ቀን ማለት አይሁድ በዓመት ውስጥ ከሚያከብሯቸው ታላላቅ በዓላት መካከል አንዱ የሆነውን ‹በዓለ ሃምሳ› የሚውልበት ዕለት ነበር፡፡ ይህም በዓል አይሁድ ፋሲካቸውን ካከበሩ ከሰባት ሳምንታት በኋላ ባለው ሰንበት ማግስት (በእሁድ፣ በ50ኛው ቀን) ስለሚከበር ‹‹ጰንጠቆስጤ››/‹‹በዓለ ሃምሳ›› ተብሎ ይጠራል፡፡ በዚህም ቀን እስራኤላውያን አርሰው ካመረቱት ላይ አዲሱን የእህል ቁርባን ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡበትም ዕለት ስለሆነ በሌላ ስያሜ ‹የመከር በዓል› ተብሎ ይጠራል፡፡ በተጨማሪም የእስራኤል መስፍን የነበረው ሊቀ ነቢያት ሙሴ በሲና ተራራ ከአምላኩ ዘንድ ሕገ ኦሪት መቀበሉንም የሚያስቡበት ቀን ነው፡፡
በተለያዩ የዓለም ክፍላት የሚኖሩ አይሁድ ከያሉበት አገር ተጉዘው በመምጣት የፋሲካንና የመቅደስ መታደስ በዓላትን በኢየሩሳሌም ተሰብስበው ለማክበር ይቸገሩ ነበር፡፡ የችግሩም ምክንያት እነዚህ በዓላት በሚውሉበት ወቅት ያለው የአየር ጠባይ በጣም አስቸጋሪና ነፋሱም ማዕበል የሚቀሰቅስ በመሆኑ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በዚሁ ጊዜ ወደ ኢጣልያ ለመሄድ በመርከብ በተሳፈረ ጊዜ ስላጋጠመው እንግልትና ስቃይ በሐዋርያት ሥራ ላይ ተጽፏል፡፡(ሐዋ 27፡9) እርሱ ራሱም በመንገዱ መካከል አብረውት ይጓዙ የነበሩትን ሰዎች ‹‹እናንተ ሰዎች ሆይ ይህ ጉዞ በጥፋትና በብዙ ጉዳት እንዲሆን አያለሁ፤ ጥፋቱም በገዛ ሕይወታችን ነው እንጂ በጭነቱና በመርከቡ ብቻ አይደለም›› ሲል ጉዞውን ለጥቂት ጊዜ እንዲያዘገዩት መክሯቸው ነበር፡፡ በዓለ ሃምሳ ግን የመጀመሪያዎቹ የፀደይና የመከር ወቅት ላይ ስለሚውል የአየሩ ሁኔታ ለመርከብ ጉዞ የተመቸ ነው፡፡ ስለዚህም የፋሲካና የመቅደስ መታደስ በዓላት ላይ በኢየሩሳሌም መገኘት ያልቻሉ አይሁድ ሁሉ በጉጉት የሚጠባበቁትና ወደ ቅድስቲቱ ከተማ በመግባት ተሰብስበው የሚያከብሩት ታላቅ በዓል ነው፡፡
"በዓለ ሃምሳ" የሚለው መጠሪያ አስቀድመን እንደ ተናገርነው በኦሪቱ ለሚከበረው በዓል መታወቂያነት የሚያገለግል ስያሜ ቢሆንም፣ የጌታ ሐዋርያትም መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉት ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በሃምሳኛው ቀን በመሆኑ ለሐዲስ ኪዳኑም ታላቅ በዓል መጠሪያነት ቢውል የሚያውክ አይሆንም፡፡ ይሁን እንጂ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህንን ቀን ‹በዓለ ጰራቅሊጦስ› ስትል ለሐዋርያት በወረደው ቅዱስ መንፈስ ልዩ ስም ትጠራዋለች፡፡ ‹‹ጰራቅሊጦስ›› የሚለው የግሪክ ቃል ሲሆን ‹‹መጽንዒ፣ መንጽሒ››/‹‹የሚያጸና፣ የሚያነጻ›› የሚል ትርጉም አለው፡፡
ወደ ቀደመ ነገራችን እንመስና ሐዋርያቱ በጽርሐ ጽዮን ተሰብስበው ሲጸልዩ ሳሉ ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምጽ መጣ፣ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው፡፡(ሐዋ 2፡2) በዚህ ክፍል ይህን ታሪክ የሚጽፍልን ቅዱስ ሉቃስ የመንፈስ ቅዱስ መውረድ ‹ድንገት› እንደ ሆነ ይነግረናል፡፡ ለመሆኑ ‹ድንገት› ሲል ምን ለማለት ፈልጎ ነው? ጸሐፊው ቅዱስ ሉቃስ ‹ድንገት› የሚለውን ቃል የተጠቀመው ነገሩ በሰው ቀጠሮ ሳይሆን ‹በእግዚአብሔር ጊዜ› የተፈጸመ መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡ ሐዋርያት አጽናኙ መንፈስ እንደሚላክላቸው ቢነገራቸውም በየትኛው ቀን ግን እንደሚወርድ የሚያውቁት ነገር አልነበረም፡፡ ስለዚህም ‹ድንገት› የሚለው ቃል ሐዋርያቱ ቀኑን ፈጽመው አለማወቃቸውን ያሳያል፡፡ ሁል ጊዜ ጸጋን የሚሰጠው እግዚአብሔር ስለሆነ የሚሰጥበት ቀነ ቀጠሮ በሰጪው እንጂ በተቀባዩ አይወሰንም፡፡ ስለዚህ የተቀባዩ ሰው ድርሻ ሳይዝል ተስፋም ሳይቆርጥ የአምላኩን የሥራ ቀን በትዕግሥት መጠባበቅ ነው፡፡
የዓውሎ ነፋሱም ድምፅ ልክ ኤልያስ የምድሩን መናወጥና እሳቱን ሲመለከት በመጎናጸፊያው ተሸፍኖ ከዋሻው በመውጣት እግዚአብሔርን ለማናገር ራሱን እንዳዘጋጀ፣ ሐዋርያቱም የመንፈስ ቅዱስን መውረድ እንዲያስተውሉና ለዚያም ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ የተሰማ የማንቂያ ድምፅ ነው፡፡(1ኛ ነገ 19፡12) በተጨማሪም ድምፅ ‹ኃይልን› ያመለክታል፡፡ ስለዚህ እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ የተሰማው ድምጽ ሐዋርያቱ ከመንፈስ ቅዱስ ኃይል መቀበላቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ እዚህ ላይ ጌታችን በዮርዳኖስ ወንዝ ከተጠመቀ በኋላ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ በእርሱ ላይ ሲያርፍ ያሰማው አንዳች ድምፅ አለመኖሩን ልብ ይሏል፡፡(ማቴ 3፡16) ይህም እርሱ ለደካሞች ጽንዕ የሚሆን እንጂ እንደ ፍጡር ኃይል የሚቀበል አለመሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡
አስቀድሞ መድኃኒታችን ለኒቆዲሞስ ‹‹ነፋስ ወደሚወደው ይነፍሳል›› ሲል እንዳስተማረው፣ በዚህች ቀን በነፋስ የተመሰለ መንፈስ ቅዱስ በወደዳቸው በሐዋርያት ሰውነት ያድር ዘንድ ወደ ጽርሐ ጽዮን ነፈሰ(መጣ፣ ወረደ)፡፡ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ መንፈስ ቅዱስን ከነፋሳትም መርጦ ከደቡብ አቅጣጫ በሚነፍሰው ነፋስ ይመስለዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ከሰሜኑ የሚነሣው ነፋስ ቀዝቃዛና ሰብል የሚያጠፋ በመሆኑ በመካከለኛው ምሥራቅ የሚኖሩ ገበሬዎች ይፈሩታል፡፡ ከደቡብ አቅጣጫ የሚነፍሰው ነፋስ ግን ከምድር ወገብ የሚወጣውን ሞቃታማ አየር ይዞ ስለሚነፍስ የተዘራውን ሰብል ያበስለዋል፡፡ በዚህም ገበሬዎቹ ደስ ይሰኙበታል፡፡ ሊቁ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ መንፈሳዊ ብስለትን የሚሰጠው መንፈስ ቅዱስ ልክ በደቡብ እንደሚነፍሰውና ሰብሎችን እንደሚያበስለው ያለ ተወዳጅ ነፋስ ነው ይላል፡፡
ቀጥሎም ለሐዋርያቱ እንደ እሳት የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፡፡ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው፡፡ በሁሉም ላይ መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፡፡ አስተውሉ በዚህ አንድ ታሪክ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ በእሳትም በነፋስም ተመስሎ ሲቀርብ እናገኛለን፡፡ ታዲያ መንፈስ ቅዱስ የተመሰለባቸው ምሳሌዎች መብዛታቸው ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ እንዳብራራው የመንፈስ ቅዱስ ባሕርይ በምልዓት የማይታወቅ መሆኑን ያመለክታል፡፡
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን በእሳት መመሰል አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በዕብራውያን መልእክቱ ‹‹አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና›› ሲል ስለ እርሱ ተናግሯል፡፡(ዕብ 12፡29) መንፈስ ቅዱስ በእሳት መመሰሉ፣ ከከርሰ ምድር መዓድናትን የሚያወጣ ባለሙያ ከመሬት ቆፍሮ ያወጣውን መዓድን ከትቢያው የሚለየው በእሳት እንደ ሆነ እንዲሁ፣ መንፈስ ቅዱስም ነፍሳችንን ትቢያ ከተባለ ኃጢአት ሁሉ ለይቶ ያነጻታልና በእሳት ተመሰለ፡፡ ይህንንም በተመለከተ ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ ‹‹የእስራኤልም ብርሃን እንደ እሳት፣ ቅዱሱም እንደ ነበልባል ይሆናል፡፡ እሾኹንና ኩርንችቱን በአንድ ቀን ያቃጥላል›› ሲል ይናገራል።(ኢሳ 10፡17) አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም በመጽሐፈ ምሥጢሩ ለሐዋርያቱ በሃምሳኛው ቀን በእሳት አምሳል የወረደው መንፈስ ቅዱስ ‹‹ሥጋቸውን ሳይሆን የኃጢአታቸውን እሾኽ አቃጠለ›› በማለት ይገልጻል፡፡