ምእመናን ሆይ
መከራ ሲደርስብን የምናመሰግነው መከራው አሪፍ ሁኖ አይደለም
እግዚአብሄር ከመከራ በላይ ስለሆነ ነው
መከራው ጊዜያዊ በረከቱ ዘላለማዊ ስለሆነ ነው
ከሚደረሰብን መከራ
የሚደርስልን እግዚአብሔር ትልቅ አምላክ ስለሆነ ነው
ስለዚህ ማመስገን ይገባል አድርገህልኛልና
ለዘላለም አመሰግንሀለሁ
ሐምሌ 24/2016 #ፃድቁ_ተክለሃይማኖት
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ፃድቁ አባታችንን በምልጃ ፀሎታቸዉ እንዲራዱን ለምንማፀንበት #ለአቡነ_ተክለሃይማኖት ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን
👉የስማቸው ትርጉም የሃይማኖት መሰረት ፍሬ የሆነው አባታችን ከእናታቸው እግዚሐርያ ከ አባታቸው ፀጋዘአብ መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታህሳስ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ተወለዱ
👉አባታችን የሃይማኖት ተክል ናቸው ጻድቁ አባታችን ገና እንደተወለዱ በሶስተኛው ቀናቸው ከእናታቸው እቅፍ በመውረድ አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውዕቱ መንፈስ ቅዱስ እያሉ በመስገድ የፈጠራቸውን አምላክ አመስግነዋል
👉እግዚአብሔር አምላካችን ለኢትዮጵያ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጎ መርጧቸዋል ጻድቁ አባታችን ክብረ በዓላቸው እንደሚከተለው ነው
✝️ህዳር 24 ቀን ሃያ አምስተኛ ካህናተ ሰማይ ሆነው በሰማይ የስላሴን መንበር ያጠኑበት እለት ነው
✝️ታህሳስ 24 ቀን የአባታችን ልደት ነው
✝️ጥር 24 ቀን የአባታችን ሰባረ አፅሙ ነው
✝️መጋቢት 24 ቀን የአባታችን ፅንሰታቸው ነው
✝️ግንቦት 12 ቀን የአባታችን ፍልሰተ አፅሙ ነው
✝️ ነሐሴ 24 ቀን የአባታችን እረፍታቸው ነው
👉የፃድቁ አባታችን #የቅዱስ_ተክለሃይማኖት ቡራኬ ይድረሰን በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የሚዉሉ ቅዱሣን የከበረዉ ቃል ኪዳናቸዉ ሀገራችንን ህዝባችንን ይጠብቅልን "አሜን" 💒 💚 💛 ❤️ 💒
ምእመናን ሆይ
በፈተና ሰዓት ቀጣዩ ተቃራኒ እንደሚሆን ማሰብ ያስፈልጋል
የሚቀጥለው ተመሳሳይ አይደለም
የሚቀጥለው ተቃራኒ ነው
ከክረምት በኋላ ክረምት አይመጣም
ከሌሊት በኋላ ሌሊት አይመጣም
ከጨለማ በኋላ ጨለማ አይመጣም
ከክረምት በኋላ በጋ
ከሌሊት በኋላ ቀን
ከጨለማ በኋላ ብርሃን ይመጣል እንጂ
እንደሁም ከመከራ በኋላ የሚመጣው ክብር ነው ።
መከራውን ታገሱ
ፈተናውን ታገሱ
ክብሩን ታያላችሁ።
ኢዮብ 1:7 ላይ እንዲህ ይላል።
የሰዉ ህይወቱ ብምድር ላይ ብርቱ ሰልፍ ነው ይላል ።
ግን በምድር ነው የሚለው በሰማይ አይልም
ምድርን አልፎ ሰማይ የሚገባ መከራ የለም
ሁሉም ማብቂያ አለው
ሁሉም ገደብ አለው
ሁሉም ልክ አለው
ልክ የሌለው ቸሩ መድኃኔ አለም ነው።
ቸሩ መድኃኔአለም ይጠብቀን!!
ምእመናን ሆይ
አንድ ሰው ምን አለ ይባላል
እጁን ወደ ላይ አንስቶ
ጌታ ሆይ እስኪ እጄን ተመልከትልኝ አለው
ሰዉ አልገደልኩበትም በዚህ እጄ አልሰረቅኩም አለው
እግዚአብሔርም እጁን አየለት
አወ ልጄ
አልሰረቅክበትም : አልገደልክበትም
እጅህ ንፁህ ነው ግን ባዶ ነው አለው
አወ ጉልድፍ ( ባዶ) እጅ ምን ይሰራል ?
ሰው ባንገድል ፓ ሊስን መንግስትን ደስ ልናሰኝ እንችላለን።
እግዚአብሔር ግን ሚደስተው
ከኃጢአት በመራቅ ብቻ ሳይሆን
መልካምንም በማድረግ ነው
ሰው አለመግደል ምን ክብር አለው
አለመሰረቅ ምን ክብር አለው
ክብር ያለው መልካም ነገርን መስራት ነው።
ስለዚህ
ክፉዉን ነገር ተፀየፉት ከመልካም ነገር ጋር ተባበሩ ይላል ቅ.ጳውሎስ
ምእመናን ሆይ
ይቺ አለም እንኳን ለኛ ለክርስቶስም አልሆነች
የሞተ ሰው አይታችሁ ከሆነ አይኑ አንድ ቦታ ተተክሎ እንደሚቀር
እኛም ለኃጢአት ስንምት ክርስቶስን ብቻ ነው
የደማልንን ፡ የቆሰለንን ፡ ክርስቶስን ብቻ ነው የምናየው
ለነቀፌታው ቦታ የለንም
ለሽንገላውም ቦታ የለንም
ይህ የሙሉነት መገለጫ ነው ምእመናን
ሙሉ እንድንሆን አምላከ ቅዱሳን ይርዳን!!!
ምእመናን ሆይ
ሱፍ እና ከራባት ለሰው ነው።
ለእግዚአብሔር ግን መራቆት ያስፈልጋል።
ከእግዚአብሔር ጋር የፕሮቶኮል ንግግር አቁሙ
ከደከማችሁ ጌታ ሆይ ደክሞኛል በሉት
እግዚአብሄር ድካምን ያግዛል ጸሎት መፍትሔው ነው
ዛሬ ግን እንዳንፀለይ ፀሎትን የሚዋጉ ብዙ ነገሮችን እንሰማለን
ችግራችሁን አትቀበሉ ጉድለታችሁን አትቀበሉ
ብቻ ነገሩ እንዲከናወን አውጁበት ይባላላል።
ግን ይሄ ብቻ በቂ አይደለም
ምክንያቱም የኛ ቃል የአምላክ ቃል አይደለም ።
እንደ እግዚአብሔር ቃል ነገሮችን ሚገለብጥ አይደለም
ተራራውን ሜዳ የሚያደረግ ሸሎቆውን የሚሞላ ቃ ል አይደለም
ያለው የሚፈጸምለት እግዚአብሔርብቻ ነው
ስለዚህ ትሁት ሁነን እግዚአብሔርን ልንለምን ይገባል።፡
+ + +
ሰማዕቱ ቅዱስ መቃርስ፡- ይኽም ቅዱስ ሰማዕት የጭፍሮች አለቃ የሆነ የታላቁ ሰማዕት የቅዱስ ፋሲለደስ ልጅ ነው፡፡ አባቱ ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ፋሲለደስ የሮሙ ንጉሥ የሠራዊቱ አለቃ ነበር፡፡ ለአንጾኪያ ነገሥታትም አባታቸውና መካሪያቸው ነው፡፡ በመንግሥት ሥልጣኑ እጅግ የበዙ አገልጋዮች ነበሩት፡፡ የፋሲለደስ ሚስት ለቅዱስ ፊቅጦር እናት እኅቷ ናት፡፡ ከእርሷም አውሳብዮስንና መቃርስን ወለደ፡፡ ንጉሡና ሁሉም የመንግሥት ልጆች በጦርነት ላይ ሳሉ የንጉሡ ሴት ልጅ ከሃዲው ዲዮቅልጥያኖስን አግብታ አነገሠችው፡፡ እርሱም ከነገሠ ከጥቂት ቀን በኋላ ጣዖታትን ማምለክና ክርስቲያኖችን ማሳደድ ጀመረ፡፡ ቅዱስ ፋሲለደስም ከጦርነት ሲመለስ ይህን ሲሰማ እጅግ አዝኖ የመንግሥት አገልግሎቱን ተወ፡፡ ንጉሡ ኑማርያኖስ አስቀድሞ ወደ ጦርነት ልኳቸው የነበሩት ልጁ ዮስጦስና የፋሲለደስ ልጅ አውሳብዮስ ጠላቶቻቸውን ሁሉ ድል አድርገው ደስ ብሏቸው ሲመለሱ ዲዮቅልጥያኖስ ነግሦ ክርስቶስን ክዶ ጣዖት አቁሞ አገኙት፡፡ ሁሉም እጅግ ተቆጥተው ሰይፎቻቸውን መዘው ዲዮቅልጥያኖስን አጥፍተው የንጉሡን ልጅ ዮስጦስን ሊያነግሡ ወደው ነበር ነገር ግን ቅዱስ ፋሲለደስ ለመንግሥት ልጆች ሁሉ አባታቸው ነበርና ከዚህ ሥራ ከለከላቸው ይልቁንም ሁሉም በጌታችን ስም ሰማዕት ይሆኑ ዘንድ ተማከሩ፡፡ ቅዱስ ፋሲለደስ ልጁን አውሳብዮስንና ሌሎቹንም የመንግሥት ልጆች ሁሉ ጠርቶ ስለ ዲዮቅልጥያኖስ ክህደት ከነገራቸው በኋላ ‹‹እኔ ስለ ፈጣሪዬ ስለ ክርስቶስ ስም ደሜን አፈሳለሁ›› ሲላቸው ሁሉም በዚህ በጎ ምክር ተስማምተው እርስ በርሳቸው ተማማሉ፡፡ በዚህም ጊዜ ከሰማይ ድምጽ መጣላቸውና ጌታችን ሰማዕት ይሆኑ ዘንድ እንደመረጣቸው ነገራቸው፡፡ የሚደርስባቸውንም መከራ ሁሉ አስረዳቸው፡፡
ሁሉም የመንግሥት ልጆች ንጉሡን ‹‹ሰማዕትነታችንን ፈጽምልን፣ ካልሆነ ከመንግሥትህ እናወርድሃለን›› እያሉት በሰማዕትነት ይገድላቸው ዘንድ አዘዙት፡፡ እነርሱም እጅግ ኃያላን ነበሩና ንጉሡ ፈራቸው፡፡ እንደፈቃዳቸውም ሰማዕት ይሆኑ ዘንድ ወደተለያዩ አገራት ላካቸው፡፡ የቅዱስ ፋሲለደስን ልጅ ቅዱስ መቃርስን ዲዮቅልጥያኖስ የሚያደርገውን ቢያጣ ወደ እስክንድርያ ላከው፡፡ ወደ እስክንድርያም ሲወስዱት ጌታችን ለቅዱስ መቃርስ ተገልጦለት ካጽናናው በኋላ ሰማዕትነቱን በትዕግስት እንዲፈጽም ነገረው፡፡ እስክንድርያ ከተማ በደረሰም ጊዜ ንጉሡ ኅርማኖስ ፊት አቆሙት፡፡ መኰንኑም የቅዱስ ፋሲለደስ ልጅ እንደሆነ ባየ ጊዜ ብዙ በማባበል ለመነው፡፡ ሰማዕቱ መቃርስ ግን በሀሳቡ አልተስማማም ይልቁንም ጣዖት አምላኪነቱን ነቀፈበት፡፡ ከዚህም በኋላ ሰውነቱ እስኪቀልጥ ድረስ እጅግ አሠቃየው፡፡ ጌታችንም የቅዱሳንን ማደሪያዎች፣ የአባቱንና የወንድሙን ማደሪያ አሳይቶት ሰውነቱንም ፈወሰለት፡፡ መኰንኑም ወደ ኒቅዮስ አገር ሰደደውና በዚያም እጅግ አሠቃዩት፡፡ የብረት ችንካሮችን ሠርተው በእሳት አግለው ጎኖቹን በሱት፡፡ ምላሱን ቆርጠው ጣሉት፡፡ ክንዶቹንም በየተራ ቆረጡት ነገር ግን ጌታችን አሁንም ፈወሰው፡፡ ሰማዕቱም እጅግ አስገራሚ የሆኑ ታላላቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን በእግዚአብሔር እንዲያምኑ አደረጋቸው፡፡ የሞተንም ሰው እያስነሣ ስለ ጌታችን አምላክነት እንዲመሰክር ያደርግ ነበር፡፡ በክርስቶስ ያመኑትን አሕዛብም ንጉሡ በሰይፍ ፈጃቸው፡፡ ጌታችንም ለሰማዕቱ መቃርስ የሰማዕትነት ፍጻሜው እንደሆነ ነግሮት ሐምሌ 22 ቀን አንገቱን በሰይፍ ቆረጡትና የሰማዕትነቱ ፍጻሜ ሆኖ የክብር አክሊልን ተቀዳጀ፡፡ ጻዲቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስም ከነገሠ በኋላ ሃይማኖት ተመለሰች፡፡ አብያተ ክርስቲያናትም መታነጽ ሲጀመሩ ሰማዕቱ ቅዱስ መቃርስ ለአንዱ ደግ ክርስቲያን መኰንን ተገለጠለትና ቅዱስ ሥጋው ያለበትን ነገረው፡፡ መኰንኑም ሰማዕቱ ወዳመለከተው ቦታ ሄዶ ቅዱስ ሥጋውን ወስዶ የሚያምር ቤተ ክርስቲያን አሠርቶ በውስጡ አኖረው፡፡ በዚያም ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ይሠራ ጀመር፡፡ የሰማዕቱ የቅዱስ መቃርስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!
+ + +
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል፡- ኢዮር፣ ራማ እና ኤረር የተባሉ ሦስት የመላእክት ከተሞች አሉ፡፡ እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክት ከፈጠራቸው በኋላ በነገድ 100 በአለቃ 10 አድርጎ በሦስቱ ሰማያት አስፍሯቸዋል፡፡ ኢዮርን በ4፣ ራማን በ3፣ ኤረርንም በ3 ከፍሎ ነው በዓሥሩ ከተማ ያሰፈራቸው፡፡
በዚህም መሠረት ኢዮርን ላይና ታች አድርጎ በ4 ከተማ ከፍሏታል፡፡ በእርሷ ያሉትን መላእክትን በ40 ነገድ 4 አለቃ አድርጎ ከፈላቸው፡፡ የመጀመሪያው ነገድ ‹‹አጋእዝት›› ይባላሉ፡፡ አለቃቸው ሣጥናኤል ነበር፤ እርሱም የመላእክትን ሁሉ ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ያሳርግ ነበር፡፡ ከክብሩ ሲዋረድ ቅዱስ ሚካኤል በምትኩ ተሹሞበታል፡፡ ሁለተኛው ነገድ ‹‹ኪሩቤል›› ይባላሉ፡፡ እነርሱም መንበረ ሥላሴን ይሸከማሉ፡፡ የቀሳውስት አምሳል ናቸው፡፡ አለቆቻቸው ገጸ ሰብና ገጸ አንበሳ ናቸው፡፡ በሦስተኛው ከተማ በኢዮር ያሉት ሱራፌል ይባላሉ፡፡ የዲያቆናት አምሳል ናቸው፡፡ በትንቢተ ኢሳያስ በምዕራፍ 6 ላይ የተገለጹትና ኢሳያስን ከለምጹ እንዲፈወስ ያደረጉት ናቸው፡፡ አለቆቻቸው ገጸ ላህምና ገጸ ንስር ናቸው፡፡ (በነገራችን ላይ ‹‹ኪሩቤል›› ወይም ‹‹ሱራፌል›› የሚባሉ የግለሰብ መጠሪያ ስሞች ስህተት ናቸው፡፡ አንደኛ እነዚህ ስሞች የብዙ መላእክት መጠሪያን የሚወክሉ ናቸው፡፡ ለአንዱ ሲሆን ‹‹ኪሩብ፣ ሱራፊ›› ይባላል፡፡ ‹ኪሩቤል› ወይም ‹ሱራፌል› ማለት ግን የብዙ ቁጥራቸው መጠሪያ ነው፡፡ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ የቅዱሳን መላእክትን ስም እንዳለ በቁሙ ወስዶ ለግል መጠሪያ ስም ማዋል ተገቢ አይደለም፡፡ ‹‹ወለተ ሚካኤ፣ ክብረ ገብርኤል….›› እየተባሉ ይሰየማሉ እንጂ ቀጥታ ‹ሚካኤል›፣ ‹ገብርኤል› እያሉ ሰዎችን መሰየም ስህተት ነው፡፡ 4ኛው ከተማ በኢዮር ያሉት ኃይላት ይባላሉ፡፡ የእሳት ሰይፍ ይዘው በሥሉስ ቅዱስ ፊት የሚቆሙ ናቸው፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወት የዛሉና የደከሙ ክርስቲያኖችን የሚያበረታቱ ናቸው፡፡ አለቃቸውም ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡)
ዳግመኛም እግዚአብሔር በራማ ያሉትን መላእክት በ30 ነገድ በ3 አለቃ አድርጎ ከፈላቸው፡፡ የመጀመሪያዎቹ ‹‹አርባብ›› ይባላሉ፡፡ የሥላሴ እልፍኝ አስከልካዮች ናቸው፡፡ የእግዚአብሔርን መንበር በክንፎቻቸው ይሸፍናሉ፡፡ አለቃቸው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ሁለተኞቹ በራማ ከተማ ያሉት ‹‹መናብርት›› ይባላሉ፡፡ ለእግዚአብሔርን እጅግ ቅርብ የሆኑ ናቸው፡፡ የመብረቅ ጋሻቸውን የእሳት ጦራቸውን ይዘው የሥላሴ ጋሻ ጃግሬዎች ሆነው በተጠንቀቅ ይቆማሉ፡፡ የሰውን ችግር ለእግዚአብሔር ያቀርባሉ፡፡ መዝ 88፡6፡፡ አለቃቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ሦስተኞቹ በራማ ከተማ ያሉት ‹‹ሥልጣናት›› ይባላሉ፡፡ መላውን ፍጥረት ለመጠበቅ ሥልጣን የተሰጣቸውና የምጽአት ዕለት አዋጅ ነጋሪዎች ናቸው፡፡ ዳን 12፡1፡፡ አለቃቸው ቅዱስ ሱርያል ነው፡፡
ሰውን ሰው ያደረገው ሥራው አይደለም
ሰውን ሰው ያደረገው ምህረቱ ነው ቸርነቱ ነው
ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምህረት የተነሳ ነው
ቸርነቱ ከቶ አያልቅምና
ስለዚህ ልብ ዓምላክ ዳዊት ምን አለ
አቤቱ እንደምህረትህ ብዛት ማረኝ
እንደ ይቅርታህም ብዛት መተላለፌን ደምስስልኝ ።
አወ የሁለችንንም ኃጢአት ይደምስስልን !!
/channel/Hamster_kombat_bot/start?startapp=kentId6734532610
Play with me, become cryptoexchange CEO and get a token airdrop!
💸 2k Coins as a first-time gift
🔥 25k Coins if you have Telegram Premium
🚀 አስደሳች እና አስገራሚ ጥሩ ገቢ 💸 የምታገኙበት legit የሆነ የonline የስራ እድል ለማግኘት ተቀላቀሉ❗🎁
በጣም አዋጭ የ Online ላይ ስራ ተመዝግባችሁ ገቢያችሁን ከዛሬ ጀምራችሁ አሳድጉ።
ለመቀላቀል እና ሥራ ለመጀመር የምትፈልጉ በውስጥ መስመር አናግሩኝ ሙሉ ነገር እነግራችኋለሁ
እድሉ
👉 በ online ሥራ ላይ ጥቂት እውቀቱ ያላቸው ወይም ለማወቅ ዝግጁ ለሆናችሁ ፣
👉 ኢንቨስት ማድረግ ለሚችሉ ፣
👉 የመሥራት ፍላጎቱ ላላቸው ብቻ ነው ።
ስለሥራው ዝርዝር ሁኔታ ማወቅ የምትፈልጉ መረጃዎችን ተመልከቱ 👀
በጣም የሚያሳዝነኝ birr እያላቹ ይሄን VGM ያልጀመራቹ 🤔🤔🤔🤔
እኔ በ 31 USDT ተነስቼ ይሄ ሁሉ በትንሽ ቀን ውስጥ ሰራው🧠💪
እናንተም መጀመር ምትፈልጉ ልጆች እባካቹ ጀምሩ ቡኋላ እንዳትቆጩ
በዘርፉ 4 አመት በላይ የሰሩ በየ አመቱ 1 ቢሊየን የሚያስገባ ድርጅት VGM እናም ትክክለኛው ቦታ ደረስኩ እናንተም እኔን ምታምኑ ብቻ መጀመር ምትፈልጉ
እባካችሁ መጀመር ማፈልጉ ሰዎች ግን ይቅርባችሁ መታችሁ አታዝጉኝ
👇👇
Inbox አድርጉኝ
"እኔ ደግሞ ለቤቴ የምሠራው መቼ ነው" ኦሪት ዘፍጥረት 30÷30
አቡ ገርቢ ደብረ ስብሐት ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ንዋያተ ቅዱሳን እጥረት ቅዳሴ እና ኪዳን እየተስተጓጐለ ይገኛል ቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆቼ እርዱኝ ትላለች።
የሚያስፈልጉ ንዋያተ ቅዱሳን ዋጋቸው
1 ኪሎ እጣን 600 ብር
2ኪሎ ዘቢብ 900 ብር
1ሙሉጧፍ 1000ብር
1ፓኮ ሻማ 80 ብር
እነዚህን በመርዳት ስማችንን በሰማይ በሕይወት መዝገብ እናስመዝግብ
አንድ ጧፍ ለእኛ 5 ብር ነው ለገጠር ቤተክርስቲያን ግን የአንድ ቀን ቅዳሴ ማስቀደሻ ነው ። እናስብበት በውስጥ ማናገር የምትፈልጉ ማናገር ትችላላችሁ
ቤተክርስቲያኑ አንድ ቀን ለመቀደስ 1000 ብር ያወጣል እኛስ
ሳናስብበት ስንት ገንዘብ እናወጣለን ለመብል ለመጠጥ ለሌሎች ነገር
ቅን ልብ ይኑረን
ቃላችንን እንጠብቅ
"እኔ ደግሞ ለቤቴ የምሠራው መቼ ነው" ኦሪት ዘፍጥረት 30÷30
አቡ ገርቢ ደብረ ስብሐት ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ንዋያተ ቅዱሳን እጥረት ቅዳሴ እና ኪዳን እየተስተጓጐለ ይገኛል ቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆቼ እርዱኝ ትላለች።
የሚያስፈልጉ ንዋያተ ቅዱሳን ዋጋቸው
1 ኪሎ እጣን 600 ብር
2ኪሎ ዘቢብ 900 ብር
1ሙሉጧፍ 1000ብር
1ፓኮ ሻማ 80 ብር
እነዚህን በመርዳት ስማችንን በሰማይ በሕይወት መዝገብ እናስመዝግብ
አንድ ጧፍ ለእኛ 5 ብር ነው ለገጠር ቤተክርስቲያን ግን የአንድ ቀን ቅዳሴ ማስቀደሻ ነው ። እናስብበት በውስጥ ማናገር የምትፈልጉ ማናገር ትችላላችሁ
ቤተክርስቲያኑ አንድ ቀን ለመቀደስ 1000 ብር ያወጣል እኛስ
ሳናስብበት ስንት ገንዘብ እናወጣለን ለመብል ለመጠጥ ለሌሎች ነገር
ቅን ልብ ይኑረን
ምእመናን ሆይ
ያዕቆብ 1፡13 ላይ ምን ይላል።
ማንም ሲፈተን በእግዚአብሔር እፈተናለሁ አይበል
ቆይ ይሄ ሁሉ ፈተና የመጣብን ምን አድርገን ነው አትበሉ
ምን አድርገን ነው ካላችሁ
ምን ያለደረጋችሁት አለ እያለ ነው 👉 ቅዱስ ያዕቆብ
በእግዚአብሔር ፊት እንድንቆም ያደረገን እኮ ምህረቱ ነው።
የትም ብትሄዱ ጥሩ ሰው እንጂ ፍፁም ሰው አታገኙም
ያልበደለ ሰው አታገኙም
እግዚአብሔር ያየባችሁን ኃጢአት ለሌላው ቢያሳይባችሁ
እግዚአብሔር የሰማባችሁን ኃጢአት ለሌላው ቢያሰማባችሁ
ማነው በፊቱ መቆም የሚችለው
መአቱን በምህረቱ ጉድጓድ ደፍኖ
ቁጣውን በቸርነቱ ውቂያኖስ አስጥሞ
እንዳልበደለ ያቆመን በፊቱ ቸሩ መድኃኒዓለም ነው
ለሱ ክብር ምስጋና ይግባው !!!
ምእመናን ሆይ
መቼም እኛ ኢትዮጵያውያን በምሳሌ የተደራጀን ነን
እና ምን ይባላል
በቄላ ከጤፍ ዱቄት አይወጣም ብሎ ያምናል።
ምክንያቱም በቄላ ትንሽ ገዘፍ ያለ ነው
ጤፍ ደግሞ አነስ ያለች ነች
ግን አይወጣም እንዴ?
ዱቄት ይወጣል ከጤፍ ተወዳጆች
ዛሬም እዚህ ግቡ የማይባሉ አለም ስፍራ ያለሰጠቻቸው
በዕውቀት የሚያንሱ
በዝና ከሚያንሱ
የማትጠብቁትን መንፈሳዊ መልእክት
መንፈሳዊ ጥበብ የእግዚአብሔርን ሥራ ልታዩ ትችላላችሁ።
የእግዚአብሔርን ልማዱ ይሄ ነው
በተናቁት ሥራ መሥራት
በሚተቹ ሰዎች ሥራ መሥራት
ይሄ የእግዚአብሔር ሥራው ነው
ጎልያድን የጣለው እኮ በትንሹ ዳዊት እና በትንሿ ጠጠር ነው።
ዛሬም ሞኝነት በሚመስል ስብከት ህዝቡን ያድናል
ስለዚህ ከተናቀ ነገር የከበረ ነገር ይወጣል ብለን ማመን አለብን ።
ስንቶቻችን በንቀት መንፈስ አለን ?
ምእመናን ሆይ
የእግዚአብሔር ቃል❤️ መዶሻ ነው።
መዶሻ ሁለት ነው ጥቅሙ
የመጀመሪያው ፦ ይንዳል ያፈርሳል ።
ሁለተኛው :- ይገነባል።
የእግዚአብሔርም ቃል
የመጀመሪያው :- ክፉ ማንነታችንን ሰብሮ ይጥላል።
ሁለተኛው :- በመልካም ሰብዕና በመልካም ህይወት ይገነባል ።
ስለዚህ እንደ ተራራ ከፍ ያለው ልባችን እንዲገሰፅ
ቃሉን መስማት ያስፈልጋል፡፡
ቃሉን ሰምተን ህይወትን እንድንወርስ አምላከ ቅዱሳን ይርዳን !!
ቅዱስ ሲራክ❤️
ለጋስ ሰውን በስራው ማማር ይመርቁታል
ን ፉ ግ ሰውን ግን በክፉ ስራው ይረግሙታል
ስንቶቻችን እያለን ሰውን እንነፍጋለን
ሰው ተርቦ
ሰው ታሞ
ሰው ተራቁቶ እየለመነ
ስንቶቻችን ግን እንነፍጋለን ?
ሰው ተርቦ ታሞ ሲለምን ያልሰጠ ታዲያ
በመጨረሻው ምኑን ሊመልስ ነው
ብታመም አልጠየቃችሁኝም
ብራብ አላበላችሁኝም
ብጠማ አላጠጣችሁኝም
ብታረዝ አላለበሳችሁኝም
ለዚህ ሁሉ የታለ ብንባል ምን ይሆን መልሳችን ?
ለዚህም ነው
ቅዱስ ሲራክ ❤️
ለጋስ ሰውን 👉 በስራው ማማር ይመርቁታል
ን ፉ ግ ሰውን 👉 ግን በክፉ ስራው ይረግሙታል ያለው ።
ለሁለችንም ለጋስ ልብ ይስጠን ።
ዳግመኛም እግዚአብሔር በኤረር ያሉትን መላእክት በ30 ነገድ በ3 አለቃ አድርጎ ከፈላቸው፡፡ የመጀመሪያዎቹ ‹‹መኳንንት›› ይባላሉ፡፡ የስላሴ የእሳት ባለ ቀስት ናቸው፡፡ የሰው ልጅ ልዩ ጠባቂዎች ናቸው፤ በተለይ በአደጋ ጊዜ ሎጥን እንዳዳኑት ፈጥነው ይደርሳሉ፡፡ በዕለተ ምጽዓት የሰውን ሁሉ ዐፅም ሰብስበው ለትንሣኤ ዘጉባኤ ያበቃሉ፡፡ አለቃቸው ቅዱስ ሰዳካኤል ነው፡፡ ሁለተኛዎቹ ‹‹ሊቃናት›› ይላሉ፡፡ የሥላሴ የእሳት ፈረሶች ናቸው፡፡ በእሳት ፈረስ ይመላለሳሉ፡፡ እነዚህም 24ቱ ካህናተ ሰማይ ሲሆኑ አለቃቸው ቅዱስ ሰላታኤል ነው፡፡ በኤረር ከተማ የሰፈሩት ሦስተኛዎቹ ‹‹መላእክት›› ይባላሉ፡፡ ፍጥረትን ሁሉ የሚጠብቁ ናቸው፡፡ አለቃቸው ቅዱስ አናንኤል ነው፡፡ በእነዚህ የማይጠበቅ ፍጥረት የለም፡፡ ከአዝርእት ጀምሮ ሁሉን ይጠብቃሉ፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ ‹‹በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙ 7 መላእክትን አየሁ›› (ራዕ 8፡2) እንዳለ ሊቃነ መላእክት በቁጥር 7 ናቸው፡፡ እነርሱም፡- ቅዱስ ሚካኤል፣ ቅዱስ ገብርኤል፣ ቅዱስ ሩፋኤል፣ ቅዱስ ራጉኤል፣ ቅዱስ ዑራኤል፣ ቅዱስ ፋኑኤል እና ቅዱስ አፍኒን ናቸው፡፡
‹‹ዑራኤል›› የሚለው ስም ‹ዑር› እና ‹ኤል› ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው፡፡ ‹‹ዑራኤል›› ማለት ትርጉሙ ‹‹የብርሃን ጌታ፣ የአምላክ ብርሃን›› ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ዑራኤል ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ ነው፡፡ በመሆኑም መጽሐፈ ሄኖክ እንደሚገልጸው መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል፡፡ ምሥጢረ ሰማይንና ሰማያዊውን ዕውቀት ሁሉ ለሄኖክ የገለጸለት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ የፀሐይን፣ የጨረቃን፣ የከዋክብትንና የሰማይ ሠራዊትን ብርሃንን የሚመራው ይኸው ገናና መልአክ ነው፡፡ መጽሐፈ ሄኖክ 28፡13፡፡
መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ ሆኖ በተሰቀለ ጊዜ ክቡር ደሙን በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ በብርሃነ መነሳንስ በዓለም ላይ የረጨው ይኸው ገናና መልአክ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡
ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋ ጥበብን አጠጥቶ ሰማያዊውን ምሥጢር የገለጠለት መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ ዕውቀት ተሠውሮበት ለነበረው ለኢትዮጵያዊው ሊቅ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም በእመቤታችን ትእዛዝ ጽዋ ጥበብን አጠጥቶ ሰማያዊውን ምሥጢር የገለጠለት ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ ‹‹ዑራኤል የተባለ መልአክ ሊረዳኝ መጣ፡፡›› መጽሐፈ ዕዝራ 2፡1፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር የሕይወትና የይቅርታ ዝናም በምድራችን ላይ ያዘንብ ዘንድ እንዲሁም የእርሻችንን አዝመራ በዝናም አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ ለምግብነት እንዲበቃ ከፈጣሪ ዘንድ ምሕረትን የሚለምን መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡
ሊቁ አባ ጊዮርጊስም በመልአኩ አማላጂነት እጅግ ብዙ ድርሰቶችን የደረሱት መልአኩ ጽዋ ሕይወትን ካጠጣቸው በኋላ ነው፡፡ በመጀመሪያም አባ ጊዮርጊስ የተወለዱት በቅዱስ ዑራኤል አብሳሪነት ነው፡፡ በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ የተመሠረቱ አብዛኞቹ ቅዱሳት ገዳማት በቅዱስ ዑራኤል መሪነት ነው፡፡ ድርሳኑ ላይ የማይጠቅሳቸው የሀገራችን የከበሩ ቅዱሳት ገዳማትና ቅዱሳን ነገሥታት የሉም፡፡
የብርሃን እናቱ ድንግል ወላዲተ አምላክን ከልጇ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ስትሰደድ መንገድ እየመራ ወደ ግብጽ እና ወደ አገራችን ኢትዮጵያ ያመጣቸው ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ እመቤታችንን ከተወደደ ልጇ ጋር በደመና ጭኖ መላ ኢትዮጵያን ካስጎበኛት በኋላ ቅድስት አገራችንን ለእመቤታችን የዓሥራት አገር እንድትሆን ያደረገው መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡
መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል በዓመት 3 ዓበይት በዓላት አሉት፡፡ ጥር 22 በዓለ ሲመቱ ነው፡፡ መጋቢት 27 የጌታችንን ክቡር የሆነ ወርቀ ደሙን ለዓለም የረጨበት ነው፡፡ ሐምሌ 22 ቀን ቅዳሴ ቤቱ የሚከበርበትና ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል የዕውቀትን ጽዋ ያጠጣበት ዕለት ነው፡፡
የሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል ጥበቃ አይለየን!
ምንጭ፦በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን (ከገድላት አንደበት)
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ሐምሌ 22-ሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበትና ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል የዕውቀትን ጽዋ ያጠጣበት ዕለት ነው፡፡
+ የታላቁ ሰማዕት የቅዱስ ፋሲለደስ ልጅ የሆነውና ምስክርነቱን በብዙ ሥቃይ የፈጸመው ሰማዕቱ ቅዱስ መቃርስ ዕረፍቱ ነው፡፡
+ ከዕረፍቱ በኋላ ተገልጦ ብዙ ተአምራትን ያደረገው ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ለውንትዮስ ዕረፍቱ ነው፡፡
ሰማዕቱ ቅዱስ ለውንትዮስ፡- ሀገሩ ሶርያ ጠራብሎስ ሲሆን ሃይማኖቱ የቀና ደግ ክርስቲያን ነው፡፡ በሥጋዊ ሥራውም የከጋዲው ንጉሥ ሠራዊቶች ጋር ነበር፡፡ ቅዱሳት መጸሕፍትን እያነበበ ሁልጊዜ በጾም በጸሎት ይተጋ ነበር፡፡ ባልንጀሮቹ የሆኑ ወታደሮቹንም ጣዖታን ማምለካቸውን ትተው እውነተኛውን አምላክ እንዲያምኑ ያስተምራቸዋል፡፡ ወደ ቀናች ሃይማኖትም የመለሳቸውና በጌታችን ያመኑ ብዙ አሉ፡፡ ከዚህም በኋላ ክፉዎች ወደ ገዥው መኮንን ሄደው ‹‹ለውንትዮስ አማልክትህን አቃለላቸው፤ ‹ሰማይና ምድርን በውስጣቸውም ያለውን ሁሉ የፈጠረ ክርስቶስ ነው› እያለ ያስተምራል›› ብለው ከሰሱት፡፡
መኮንኑም በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ አስቀርቦ ጠየቀው፡፡ ቅዱስ ለውንትዮስም ከልጅነቱ ጀምሮ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደሚያመልከውና ለእርሱም እንደሚሰግድ በከሃዲው መኮንን ፊት መሰከረ፡፡ መኮንኑም አስሮ ካሠቃየው በኋላ በማግሥቱ ‹‹የንጉሡን ትእዛዝ ለምን ትተላለፋለህ? አማልክቶቹን ለምን አታመልክም?›› አለው፡፡ ቅዱስ ለውንትዮስም መኮንኑን ‹‹አንተም የረከሱ ጣዖታትን ማምለክህን ትተህ የክብርን ባለቤት ጌታችንን ብታመልከው የዘለዓለም መንግሥትን ባወረስህ ነበር›› አለው፡፡ መኮንኑም ይህንን በሰማ ጊዜ ቅዱስ ለውንትዮስን ደሙ እንደ ውኃ እስኪፈስ ሥጋውም እስኪቆራረጥ ድረስ ጽኑ ግርፋትን አስገረፈው፡፡ እግሩን እየጎተቱና ውኃ ውስጥም እየዘፈቁት ብዙ ካሠቃዩት በኋላ ሰማዕትነቱን ፈጸመና ጌታችን ቅድስት ነፍሱን ተቀበላት፡፡ ከታላላቅ መኳንንት ውስጥ የአንዱ ሚስት የሆነች አንድ አማኝ ደግ ክርስቲያን ሴትም መጥታ ለወታደሮቹ ገንዘብ ከፍላ የቅዱስ ለውንትዮስን ሥጋ ወስዳ በወርቅ ሣጥን ውስጥ አድርጋ በቤቷ ውስጥ በክብር አስቀመጠችው፡፡ ሥዕሉንም አሠርታ በወርቅ ሣጥኑ ላይ አስቀምጣ ሁልጊዜ በፊቱም የሚበራ መብራት አኖረች፡፡
ሰማዕቱም የፍቅሯንና የድካምዋን ዋጋ ቆጥሮ ብዙ አስደናቂ ተአምራትን አድጎላታል፡፡ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ በመኮንኑ ባሏ ላይ በሆነ ሥራ ምክንያት ተቆጣና በአንጾኪያ ከተማ በወህኒ ቤት አሠረው፡፡ ቅዱስ ለውንትዮስም ለሥጋው መልካም ለሠራችለት ለመስፍኑ ሚስት መልካም የሆነ ዋጋዋን ሊከፍላት ሽቶ በዚያች ሌሊት በወህኒ ቤት ላለው ባሏ ተገለጠለት፡፡ ከወህኒ ቤቱም ታላቅ ብርሃን ወጣ፡፡ ለመኮንኑ ባሏም የተገለጠለት የራሱ የሆነውን ቤቱ ያስቀመጠውንና የሚያውቀውን የወርቅ ልብስ ለብሶ በጎልማሳ ፈረሰኛ አምሳል ነበር፡፡ ለመስፍኑም እንዲህ አለው፡- ‹‹አትዘን አታልቅስም፣ ዛሬ ከዚህ ወህኒ ቤት ወጥተህ ከንጉሥ ጋር በማዕዱ ትቀመጣለህና ከዚያም ወደቤትህ ወጥተህ በሰላም ትሄዳለህ፡፡››
የታሠረው መስፍንም ይህን ጎልማሳ ፈረሰኛ ስላየው፣ በላዩም ስለወጣው ታላቅ ብርሃን፣ የወህኒ ቤቱም ደጅ እንደተዘጋና እንደተቆለፈ ወደ እርሱ ስለመግባቱ፣ ደግሞም የራሱ የሆነውንና በቤቱ ውስጥ የተወውን የወርቅ ልብስ ለብሶ ስለማየቱ በእጅጉ ተደነቀ፡፡ ቅዱስ ለውንትዮስም በዚያች ሰዓት ወደ ንጉሡ ሄዶ በመኝታው ተኝቶ ሳለ ረገጠው፡፡ ንጉሡም እጅግ ደነገጠ፡፡ ቅዱስ ለውንትዮስም ‹‹ንጋት በሆነ ጊዜ መስፍን እገሌን ከወህኒ ቤት አውጣው አክብረውም፣ በክፉ አሟሟትም ሞተህ እንዳትጠፋ ወደቤቱ ይሄድ ዘንድ በሰላም አሰናብተው›› አለው፡፡ ንጉሡም ከቅዱስ ለውንትዮስ ግርማ የተነሣ እጅግ ፈርቶ እየተንቀጠቀጠ ‹‹እሺ ጌታዬ እንዳዘዝከኝ አደርጋለሁ›› ብሎ መለሰለት፡፡ በነጋም ጊዜ ንጉሡ ወደ ወህኒ ቤት ሄዶ መስፍኑን አወጣውና በክብር ልብሶች አስውቦ ከእርሱ ጋር በማዕዱ አስቀመጠው፡፡ ንጉሡም ግርማው እጅግ የሚያስፈራ ፈረሰኛ ተገልጦለት መስፍኑን ይፈታው ዘንድ እንዳዘዘው ሲነግረው መስፍኑ ተደነቀ፡፡ ንጉሡም የሥራይ ሥራ እንደሆነ ሲናገር መስፍኑም ‹‹እኔ የሥራይ ሥራ ፈጽሞ አላውቅም፣ የተገለጠልህም ማን እንደሆነ አላውቅም›› አለው፡፡ ከግርማው የተነሣ ፈርቷልና ከማዕዱ በኋላ ንጉሡ በሰላም አሰናበተውና መስፍኑ ወደ ሀገሩ ጠራብሎስ ሲጓዝ ቅዱስ ለውንትዮስ በመልአክ አምሳል ተገለጠለትና እቤቱ እስኪደርስ ድረስ እንደ ጓደኛ እያወራው ሲደርስ ተሰወረው፡፡
መስፍኑም ወደቤቱ በገባ ጊዜ የሆነውን ሁሉ ለቤተሰቦቹ ነገራቸው፡፡ ሚስቱም ያዳነው ቅዱስ ለውንትዮስ መሆኑን ዐውቃ ‹‹ብታየው ታውቀዋልህን?›› አለችው፡፡ እርሱም ‹‹አዎን ባየው ዐውቃዋለሁ›› ሲላት የቅዱስ ለውንትዮስ ሥዕል ወዳለበት ቤት ይዛው ገባች፡፡ መስፍኑም አይቶ ‹‹በእውነት የተገለጠልኝ ይህ ነው›› አለ፡፡ ሁለተኛም የቅዱስ ለውንትዮስ ሥጋ ያለበትን የወርቅ ሣጥን ከፈተችውና ያንጊዜ የመስፍኑን የወርቅ ልብስ እንደለበሰ አየው፡፡ የፊቱንም መሸፈኛ ገልጦ የተገለጠለትና ያዳነው እርሱ መሆኑን ከተረዳ በኋላ ማን እንደሆነ ሚስቱን ጠየቃት፡፡ እርሷም የቅዱስ ለውንትዮስን ገድል አንድ በአንድ ነገረችው፡፡ መስፍኑም ይህን መልካም ሥራ በመሥራቷ ሚስቱን እጅግ አድርጎ አመሰገናት፡፡ በቅዱሳኑ ላይ አድሮ ድንቅ ድንቅ ነገርን የሚሠራ እግዚአብሔርን ካመሰገነ በኋላ መብራትና ማዕጠንት እንዳይለየው ሚስቱን አዘዛት፡፡ ከሃዲውን ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስን ጌታችን እስካጠፋው ድረስ እንዲሁ እያደረጉ ቆዩ፡፡ ከዚህም በኋላ ያማረች መልካም ቤተ ክርስቲያን አንጸውለት ቅዱስ ሥጋውን ሰኔ አንድ ቀን በውስጧ አኖሩት፡፡ ዕለቷንም አከበሯት፡፡ ከቅዱስ ለውንትዮስም ሥጋ ብዙ አስደናቂ የሆኑ እጅግ የበዙ ተአምራት ተደርገው ታዩ፡፡ የሰማዕቱ የቅዱስ ለውንትዮስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!
ልብ አምላክ ዳዊት❤️
አቤቱ ደግ ሰው አልቋልና አድነኝ !!!
አንዱ በአንዱ ላይ በሽንገላ ከንፈር ሁለት ልብ ሁነው ይናገራሉና
እግዚአብሔር ግን የሸንጋዮችን ከነፈር ያጠፋል ።
ለሁላችንም ደግ ልብ ይስጠን
"እኔ ደግሞ ለቤቴ የምሠራው መቼ ነው" ኦሪት ዘፍጥረት 30÷30
አቡ ገርቢ ደብረ ስብሐት ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ንዋያተ ቅዱሳን እጥረት ቅዳሴ እና ኪዳን እየተስተጓጐለ ይገኛል ቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆቼ እርዱኝ ትላለች።
የሚያስፈልጉ ንዋያተ ቅዱሳን ዋጋቸው
1 ኪሎ እጣን 600 ብር
2ኪሎ ዘቢብ 900 ብር
1ሙሉጧፍ 1000ብር
1ፓኮ ሻማ 80 ብር
እነዚህን በመርዳት ስማችንን በሰማይ በሕይወት መዝገብ እናስመዝግብ
አንድ ጧፍ ለእኛ 5 ብር ነው ለገጠር ቤተክርስቲያን ግን የአንድ ቀን ቅዳሴ ማስቀደሻ ነው ። እናስብበት በውስጥ ማናገር የምትፈልጉ ማናገር ትችላላችሁ
ቤተክርስቲያኑ አንድ ቀን ለመቀደስ 1000 ብር ያወጣል እኛስ
ሳናስብበት ስንት ገንዘብ እናወጣለን ለመብል ለመጠጥ ለሌሎች ነገር
ቅን ልብ ይኑረን
"እኔ ደግሞ ለቤቴ የምሠራው መቼ ነው" ኦሪት ዘፍጥረት 30÷30
አቡ ገርቢ ደብረ ስብሐት ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ንዋያተ ቅዱሳን እጥረት ቅዳሴ እና ኪዳን እየተስተጓጐለ ይገኛል ቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆቼ እርዱኝ ትላለች።
የሚያስፈልጉ ንዋያተ ቅዱሳን ዋጋቸው
1 ኪሎ እጣን 600 ብር
2ኪሎ ዘቢብ 900 ብር
1ሙሉጧፍ 1000ብር
1ፓኮ ሻማ 80 ብር
እነዚህን በመርዳት ስማችንን በሰማይ በሕይወት መዝገብ እናስመዝግብ
አንድ ጧፍ ለእኛ 5 ብር ነው ለገጠር ቤተክርስቲያን ግን የአንድ ቀን ቅዳሴ ማስቀደሻ ነው ። እናስብበት በውስጥ ማናገር የምትፈልጉ ማናገር ትችላላችሁ
ቤተክርስቲያኑ አንድ ቀን ለመቀደስ 1000 ብር ያወጣል እኛስ
ሳናስብበት ስንት ገንዘብ እናወጣለን ለመብል ለመጠጥ ለሌሎች ነገር
ቅን ልብ ይኑረን
@wengelyohannes
ሰላም ለሁላችሁም
ምስክርነት ለመስጠት ነው(ከዛሬ 21 አመት በፊት በዛሬዋ እለት የተደረገ ክስተት ነው)
በጊዜው አጭር አካላዊ መግለጫ ስለ ራሴ(የገጠር ልጅ፣የ15 አመት እድሜ፣ አጭር፣ቀጭን፣የ8ኛ ክፍል ተማሪ)
በ1995 ሐምሌ 19 ጥዋት ላይ ወላጆቼ ስለ ቀኑ ስራ ይወያያሉ። እና አባቴ የሆነ እርሻ ቁጥቋጦ እንዲቆጠቆጥ ይፈልጋል፡ እናቴ ተው ዛሬ ገብርኤል ነው ፡ስታርስ እየቆጠቆጥክ ታርሳላችሁ ትላለች።
(መቆጥቆጥ ማለት እርሻ መካከል ላይ የሚገኙ ዛፎችን ማስወገድ/ማፅዳት ማለት ነው።)
አያገባሽም በወንድ ስራ ፡ይልና የአባቴ ውሳኔ ይፀናል። ከዛ የኔ የቀኑ የስራ ድርሻ ገብቶች ማገት ነበር።
ሁላችንም ወደዬ ስራችን ተሰማራን፡፡
ከቀኑ 11፡00 አካባቢ ዝናብ ይመጣል፡እኔም ወንዝ ማዶ ነበር ከብቶችን ያገትኩት እና ጎርፍ/ወራጅ ውሃ እንዳይዘጋኝ ። ከብቶችን አሻገርኩ፡ ዝናቡም ዘነበ ።
ከቆይታ ቡሃላ የተወሰኑ ከብቶች እንደሌሉ ተረዳሁና ፡ወንዝ ማዶ ስመለከት ተራራ ስር አኋቸው። ከዛ ተራራ ላይ የቀሩትን ከብቶች ጎርፍ/ወራጅ ውሃ ሳይደርስ ለማሻገር እየፈጠንኩ ሄድኩና ከብቶችን ይዤ ስመለስ ጎርፉ ገብቷል ፡ትንሽ ጠብቄ ከብቶቹ ተሻገሩ እኔም ገባሁ።
እኔ እረኛ የሚኖረው ነገሮች ይዣለሁ (የዝናብ ልብስ፡ጅራፍ፡የሌሊት ልብስ...)
ከዛ ውሃው መካከል ስደርስ ፡ውሃው አነሳኝ። የተወሰነ ወሰደኝና አንዴ clockwise አዞሮ ወደምፈልግበት አቅጣጫ አሻገረኝ።
ግን ይህ ሲሆን እኔ እንደቆምኩ ነበርኩ አልወደኩም፡እቃ አልወደቀም፡አልደነገጥኩም።
ግን የሆነ ትልቅ ሰው ከርቀት እየጮኽ ወደ እኔ እየሮጠ ነበር፡እኔን ከጎርፍ ለማትርፍ። ሰውየው ሳይደርስ ወጣሁ ፡ሰውየውም ባለበት ቁሞ በጣም ተገረመ። ወደ እርሱ ከተጠጋሁ ቡሃላ ብዙ መከረኝ።
እኔም ወደ ከብቶቼ ሄድኩ ፡ቀደም ብለው የተሻገሩት ርቀው ነበር። ደረስኩባቸው ፡በዛው ቅፅበት ግን የአንድ ከብት የአደጋ ጩኸት ተሰማ(ኧዋዋዋ.... የሚል) ።
ከብቱ እንዳለ ይሸሻል፡ እኔ ወደ ጮህበት አቅጣጫ እየሮጥኩ ሄድኩ። ጫካ ሸፍኖን እንጂ በቅርበት ነበርን።
እናም ደረስኩና 3 ሜትር አካባቢ ርቀት ላይ የአንድ አመት ጥጃ ወድቃ አየሁ፡ላነሳት አስቤ እቃየን ጣል ሳደረግ፡ እቺ ጥጃ በራሷ ጊዜ ተነሳችና ወደ መንጋው ሮጠች።
እኔም ስለተነሳች ደስብሎኝ ፡ምን ሆና ወደቀች? ምን አደናቀፋት ሳልል እና ሳላሰላስል፡ ወደ ከብቶች ሄድኩ ፡ ከዛ ምን አልባት ከተጎዳች ብየ ቀረብ ብዬ ስመለከት፡ አንድ ጎን አንገቷ ላይ ሁለት ትልቅ የተበሳ ነገር አየሁ፡በሌላኛው ጎንም እንዲሁ፡
ያኔ ነብር/ነምር እንደነከሳት አወኩ።
በአካባቢው እንደሚባለው ደሟን አልጠጣም፡
ደም ሳይጠጣ ከደረሱበት ደግሞ ስዎችን ይተናኮላል/ጎዳት ያደርሳል።
ግን ምንም አልተተናኮለኝም፡፡
እግዚአብሔር ይመስገን፡በቸርነቱ ጠበቀኝ።
በቅዱስ ገብርኤል በኩል እነደሆነ አምናለሁ።
ሁለቱም፡ክስተቶች ለሞት የሚያበቁ ነበሩ።
አጋዕዝተ አለም ሥላሴ ያለምንም ድንጋጤ ነገሩን ሁሉ አሳለፋት።
አጋዕዝተ አለም ሥላሴን አመስግኑልኝ።
ቅዱስ ገብርኤልንም አመስግኑልኝ።
በነብር የተነከሰችው ጥጃ ደግሞ የአባቴ የግሉ/የብቻው ገንዘብ ነበረች።
ማለት የወላጆቼ የጋራ ንብረት አይደለችም፡ በዛው አመት አባቱ የሰጠው ነበረች፡፡
ሰኔ ጎልጎታ እና መልክዓ ሚካኤል ወገብርኤል የፀሎት መፅሀፍ ከኪሴ አይጠፋም ነበር።