ረጋፊዋ ቅጠል ከእኔ በለጠችЧитать полностью…
ኦክሲጅን ለፍጥረት በነጻ እያደለች
እረ ፈጣሪ ሆይ ከቅጠል አልነስ
አስተውሎትን ስጠኝ ሕይወቴን የሚያድስ
✍️ጼሌቅ
መጀመር ያቅታል አቅመ ቢስ እንደሆንክ አለም ሁሉ ሲመሰክር ትቀበለዋለህ.....
ምክንያቱም ከማንም ጋር ምትፋለምበት ቦታ ላይ አይደለም ያለኸው🤐
ፀጥ ትላለህ
ለጠየቀህ ምትመልስበት ምክንያት ራስህ ታጣለህ
ለመስጠት ብትሞክርም የለም
ህይወት የሌለው ትዝታ እንደሆነ እስከምታምን ድረስ
እስኪያልፍ ድረስ ያለፋሀል
ወድቀህ የነበረው ቀስ በቀስ አቧራ አራግፈህ ቀና ትላለህ።
በድጋሚ እንደማይጀመር ያሰብከው ህይወት እንደ ጽጌሬዳ ሲፈካ ታየዋለህ ።
ድጋሚ እንደ ተራ አበባ አትቀጠፍም.....
እሾህ ዙሪያህ ላይ ታስቀምጣለህ።
እናም ታግሎ ላገኘህ ዋጋ ይኖርሀል
ቢያንስ አንተን ለማግኘት የወጋው እሾህ ይኖራል☺
ሽታህ ራሱ ውብ ይሆናል🫠
በድጋሚ በቆየህ መጠን የበለጠ ታብባለህ....
ሰዎች በትላንትህ አይለኩህም
ፍቅር አብሳሪ
ደስታ ፈጣሪ ትሆናለህ።
ግን ይሄ ሁሉ ገና ከጅምሩ ህልም ነበር🤧
ነገር ግን መንገዱን ይዘህ በትክክል ከተጓዝክ ዞረህ መንገድህን የምታየው
" ምን ያህል ርቀት እንደመጣህ ለማወቅ ይሁን"
ጀምሩት ህልም መሳይ መንገድን መጨረሻውን ይዛቹ ጀምሩት🤩🤗
ኢሊ ዲያ✍
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ሐምሌ 29-ጨረቃንና ፀሐይን በእጃቸው እየያዙ ይጸልዩ የነበሩትና በመንዝ በይፋት ያሉ ክርስቲያኖች ብርዱን ውርጩን በስማቸው የሚገዝቱባቸው አቡነ ዮሐንስ ዘጠገሮ ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ ቅዱስ ሐዋርያ ታዴዎስ የሥጋው ፍልሰት ሆነ
+ ቅዱስ ወርስኖፋ በሰማዕትነት አረፈ።
አቡነ እጨ ዮሐንስ ዘጠገሮ፡- ጻድቁ አባታችን የተወለዱት በኢየሩሳሌም አውራጃ ልዩ ስሙ ሳሬራ በሚባል ቦታ ነው፡፡ የካቲት 28 ቀን ተፀንሰው ህዳር 29 ተወለዱ፡፡ አባታቸው ድላሶር እናታቸው እምነ ጽዮን ይባላሉ፡፡ ሲወለዱ በወላጆቻቸው ቤት ውስጥ ብርሃን ወርዷል፡፡ ወላጆቻቸውም እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡አባታችን ገና በተወለዱ በ5 ዓመታቸው ወላጆቻቸው ወደ እግዚአብሔር ቤት ይዘዋቸው ሄዱ የእመቤታችንን ሥዕል
ተመልክተው በደስታ ተመልተው ሳቁ፡፡ አምላክን የወለደች የብርሃን እናቱ እመቤታችንም ከምሥሉ ወጥታ ‹‹በምን አውቀኸኝ ነው?›› ብላ አቅፋ ሳመችውና ‹‹ከእንግዲ ወዲህ የልጄ አገልጋይ ትሆናለህ ኑሮህም እንደ መላእክት ይሆናል
በአንተ ምክንያት ብዙ ሰዎች ይድናሉ በምድር ላይም 500 ትኖራለህ…›› ብላ ባርካው ተሰወረች፡፡ከዚያችም ቀን ጀምሮ አባ ዩሐንስ ለክርስቶስ ተላልፎ ተሰጠ፡፡ 50 ዓመትም በበረሃ ሲጋደሉ ኖሩ ከ50 ዓመት በኃላ በደመና ተጭነው በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል መሪነት ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ መጡ፡፡ ጻድቁ አባታችን በአቡነ ተክለሃይማኖት ዘመን መጨረሻ የመጡ ሲሆን ምንኩስና ከደብረ ሊባኖስ ገዳም
ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ተቀብለው በዚያው በደብረ ሊባኖስ ገዳም ለ50 ዓመት በጾምና በጸሎት በተጋድሎ ኖረዋል፡፡ ከዚኽም በኋላ አባ ዩሐንስ ወደ ተዘጋቸላቸው ምድር በቅዱስ ገብርኤል አሳሳቢነት ወደ ጠገሮ መጡ፡፡ ይኽም ጠገሮ ያለው ገዳማቸው በሰሜን ሸዋ በመንዝና ይፋት ክልል መዘዞ በሚባል ቦታ ሲደርሱ በእግር አንድ ሰዓት ከተጓዙ በኃላ ይገኛል፡፡ሕዝቡ በተለምዶ እጨ ዮሐንስ እያለ ይጠራቸዋል እንጂ ስማቸው እጨጌ ዮሐንስ ነው፡፡ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ መስቀል ከሰማይ የወረደላቸው ታላቅ አባት ናቸው፡፡መስቀሉም ሁልጊዜ ተአምር ይሠራል፡፡ በልደታቸው ቀን ኅዳር 29 ቀን መስቀሉ ከመቅደሱ ወጥቶ በካህናቱ ታጅቦ ወደ ጸበሉ ሲወርድ ከየት እንደመጣ ሳይታሰብ ደመና መጥቶ ከመስቀሉ ላይ ብቻ እረቦና እንደ ጃንጥላ ተዘርግቶ አብሮ ወደ ጸበሉ ይወርዳል፡፡ እዛው ቆይቶ መስቀሉ ሲመለስም አብሮ አጅቦ ይመለስና መስቀሉ ቤተ መቅደስ ውስጥ ሲገባ ደመናው ወዴት እንደተበተነ ሳይታወቅ ይጠፋል፡፡ ይህ በዘመናችንም ጭምር እየታየ ያለ ታላቅ ተአምር ነው፡፡አባታችን በታላቀ ተጋድሎ ሣሉ ሰይጣን የሀገሩን ሰዎች በጠላትነት እንዲነሡባቸው አደረገ፡፡ ሰዎቹም አባታችንን እንዴት እንደሚያጠፏቸው ይማከሩ ጀመር፡፡ ሊገድሏቸው ፈልገው ቅድስናቸው በሁሉ ዘንድ የታወቀ ነውና ፈሩ፡፡
ከዚኽም በኋላ ‹‹ለምን ከመንደራችን ከወንድ ያረገዘች ሴት ፈልገን እሳቸው አስረገዟት ብለን በሐሰት እንከሳቸውም?›› ብለው ተማከሩ፡፡ ብዙ ወርቅና ብርም ለአንዲት ሴት ሰጥተው በሐሰት ከእርሱ አርግዣለሁ ብላ እንድትመሰክር አደረጓት፡፡ አባታችንም በሕዝብ ፊት በሐሰት ተከሰሱ፡፡ ጻድቁም ‹‹አንቺ ሴት ከእኔ ነው ያረገሽው?›› አሏት እርሷም ‹‹አዎ ከአንተ ነው ልትክድ ነው እንዴ?›› አለቻቸው፡፡ አባታችንም በዚህ አዝነው ‹‹በአንቺና በእኔ መካከል እግዚአብሔር ይፍረድ›› ሲሉ ያች ሴት ወዲያው ለሁለት ተሰንጥቃ ሞተች፡፡ የአገሩ ሰዎችም
እጅግ ፈሩ፡፡ አባታችንም ምድሪቱን እረገሟት፡፡ ‹‹የተዘራው ዘር አይብቀልብሽ፣የተተከለው አይፅደቅ፣ ብርድና ውርጭ ይፈራረቅብሽ›› ብለው እረግመዋት በደመና ተጭነው ወደ ሰሜን ጎንደር እስቴ ጉንደ ተክለተሃማኖት ሔዱ፡፡አቡነ ዬሐንስ በመላው ኢትዮጵያ ወንጌልን እየተዘዋወሩ ያስተማሩ ሲሆን
ከቅድስናቸው የተነሣ በፀሐይ ላይ 50 ዓመት፣ በጨረቃ ላይ 50 ዓመት፣ በደመና ላይ 50 እንዲሁም ዓለምን በክንፋቸው በመዞር በደመና ላይ 50 የኖሩ ከሰው ተወልደው ከመላእክት የተደመሩ ታላቅ ጻድቅ ናቸው፡፡ በይፋት ጠግሮ በዓለወልድ፣ በአፋር አዘሎ፣ በመንዝ ፍርኩታ ኪዳነምሕረት፣ በደብረ ሊባኖስ፣በጎንድ ተክለ ሃይማኖት በሌሎችም ቦታዎች በመዘዋወር በታላቅ ተጋድሎ ኖረዋል፡፡ አባታችን ከሰማይ መስቀል የወረደላቸው ሲሆን ዛሬም በገዳማቸው የሔደ ሰው በወረደው በእጃቸው መስቀል እየተዳበሰ ቆመው በጸለዩበት ባሕር በጠበላቸው ይጠመቃል፡፡ በተጨማሪም ይይዙት በነበረውም መቋሚያቸው በመዳበስ በረከትን ማግኘት ይቻላል፡፡ ቆመው ከጸለዩበት ባሕር ውስጥ ደረቅ አሸዋ ይወጣል፡፡ አባ ዩሐንስ 500 ዓመት ከኖሩ በኃላ እረፍተ ዘመናቸው ሲደርስ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከ15ቱ ነቢያት፣ ከ12ቱ ሐዋሪያት፣ ሄሮድስ ካስፈጃቸው ከመቶ አርባ አራት ሺ ሕፃናት፣ ከአብርሃም ከይስሐቅ፣ ከዕቆብ ጋር ሁሉንም ነገደ
መላእክትን፣ ጻድቃን ሰማዕታትን ሁሉ አስከትሎ መጥቶ ታላቅ ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ‹‹ስምህን የጠራ ገዳምህን የረገጠ፣ መባ የሰጠ፣ ቤተ ክርስትያንህን የሠራ ያሠራ የረዳ፣ ገድልህን የሰማ ያሰማ ያስተረጎመ፣መታሰቢያን ያደረገ እስከ 10 ትውልድ እምርልሀለው፤ ንስሀ ሳይገባ አይሞትም፣ልጅ መውለድ ባይችል እኔ ልጅ እሰጠዋለሁ፤ ገድልህን በቤቱ ያስቀመጠ እርኩስ መንፈስ፣ ክፉ አጋንንት ቸነፈር ወባ መልአከ ጽልመት አይነካውም፡፡በገዳምህ መነኩሴ ቢቀበር በሰማይ ክንፍ አበቅልለታለሁ፤ አይሁድም አረማዊም
ያላመነ ያልተጠመቀ በገዳምህ መጥቶ ቢያርፍ ይቅር እልልሃለሁ፣ እንደ መቃብሬ ጉልጎታ እንደተቀበረ አድርጌ እቆጥርልሃለሁ…›› የሚል ቃል ኪዳን ከሰጣቸው በኃላ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ቅዱስ አባታችንም በ500 ዓመታቸው ሐምሌ 29 ቀን ዐርፈው በጎንድ ተክለ ሃይማኖት ተቀብረዋል፡፡በሰሜን ጎንደር የሚገኘውን ይህንን ገዳም ጻድቁ ራሳቸው ናቸው የመሠረቱት፡፡ ነገር ግን የገዳሙን ስያሜ በአባታቸው በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ስም አድርገውታል፡፡ አቡነ ዮሐንስ ካረፉ በኋላ በእርግማናቸው መሠረት በመንዝና በይፋት ብርዱ ድርቁ ስለበዛባቸው አንድ ብቁ ባሕታዊ ከበዓታቸው ወጥተው ‹‹በሐሜታችሁ ምክንያት እጨ ዮሐንስ ስለረገማችሁ ነው የእርሱን ዐፅም ካላመጣችሁ ብርዱ ውርጩ ድርቁም አይጠፋላችሁም›› አሏቸው፡፡ ሕዝቡም አባታችን በጉንድ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከተቀበሩ ከ134
ዓመት በኃላ በቅዱሳን እየተመሩ ሄደው በሌሊት ግማሽ ዐፅማቸውን አምጥተው በሀገራቸው አምጥተው ስላስቀመጡ ብርዱና ውርጩ በመንዝ እየቀነሰላቸው
መጥቷል፡፡ ዛሬም በሀገሩ ብርዱና ውርጭ ሲበዛ የጻድቁን ታቦት ሲያወጡ ውርጩ ይጠፋል፡፡ ጠገሮ በሚባለው ገዳማቸው ውስጥ የሚገኘው ጠበላቸው እጅግ አስደናቂ ነው፡፡ ግማሽ ዐፅማቸውን ከጉንደ ተክለሃይማኖት አምጥተው
አርባ ሐራ መዳኒዓለም አጠገብ በላይ በፍሩክታ ኪዳነምሕረት መጋቢት 18 ፍልሰተ ዐፅማቸው ተከናወነ፡፡ ምድሪቷም ተባረከች፣ የዘሩትንም አበቀለች፣ውርጩም ብርዱም ቀነሰ፣ ዝናብ አልዘንብ ሲል ወይም ሰብል የሚጨርስ አንበጣ ሲመጣ ታቦታቸው ወጥቶ ምህላ ይያዛል ወድያውም መቅሰፍት ይርቃል፣ዝናብም ይዘንባል፡፡ ጻድቁ ደመናን፣ ጨረቃንና ፀሐይን በእጃቸው እየያዙ ይጸልዩ
ነበር፡፡ በጠገሮ፣ በአዘሎ፣ በፍርኩታና በሌሎቹም ታላላቅ ቦታቦዎች ላይ በእያንዳንዱ ገዳም ሃምሳ ሃምሳ ዓመት በጸሎት ኖረው በአጠቃላይ በ500 ዓመታቸው ነው ያረፉት፡፡ ዐፅማቸው መንዝ ከአርባ ሐራ መድኃኔዓለም አጠገብ
ፍርኩታ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ውስጥ ይገኛል፡፡
Coming soon jember entertainment
https://youtube.com/shorts/4g5ANDU5Sjo?feature=share
ራስን ማወቅЧитать полностью…
የአንድ ሰው አጠቃላይ ሕይወት ውጤታማነት በማፍቀር አቅማችን ላይ የተወሰነ ነው። ሆኖም የማፍቀር አቅማችን የምናጎለብተው በመፈቀር ውስጥ ነው።
ምእመናን ሆይ
ጌታ መድኃኔአለም እኮ
እርሱ የዘላለም አምላክ ነው
አልጀመረምና አይጨርስም
መጀመርያ የሌለው መጀመሪያ
መጨረሻ የሌለው መጨረሻ እግዚአብሔር ነው ።
መጀመሪያን ያስጀመረ አልፋ
ለመጨረሻም ድንበርን ያደረገለት አሜጋ
እሱ የጥንት አምባ ነው።
ከዘላለም ዘመናት በፊት የነበረ ነው።
ለሱ ክብር ምስጋና ይግባው🙏
ምእመናን ሆይ
ደስታ ልበ ቅኖች የዋሆች የሚያገኙት ነገር ነው
ቀና የሆኑ ሰዎች ደስተኛ ናቸው።
የሚሰሙትን ብቻ የሚሰሙ
የሚያዩትን ብቻ የሚያዩ ሰዎች
አማረኛ የማይሰነጥቁ ሰዎች
ቃላት የማይቆረጥሙ ሰዎች
እያከሙ የሚያዩ
እያከሙ የሚሰሙ
አይ እንዲህ ሊል ፈልጎ ነው
አይ ይህንን ሊያደርግ አስቦ ነው ብለው
በጎውን ብቻ የሚያስቡ
እነሱ ደስተኞች ናቸው
ቅንነት ማለት እኮ ይሄ ነው
"ሰው ያጎደለውን ሳይሆን እግዚአብሔር የሞላውን ማየት" ቅንነት ይባላል።
ያለበለዚያ
ለቀረበን ሰው ሁሉ
እንደ ማቅ የምንኮሰኮስ ከሆነ
እንደ እባብ የምንናደፍ ከሆነ
ደስተኞች አንሆንም
"ብርሃን ለፃድቃን ደስታም ለልብ ቅኖች ወጣ "
እንዲል ቅዱስ ዳዊት መዝ :- 97 : 11 ላይ።
ስለዚህ
ቅኖች ስንሆነ ደስተኞች እንሆናለን
ቅኖች ያርገን መድኃኔአለም🙏
ማንኛውም ሰው ትክክለኛና የበሰለ ፍቅር መስጠት የሚችለው በቂ በሆነ መልኩ መብሰል ሲችል ነው። የምንሰጠው ፍቅር በልጅነት ዕድሜ ከሰረጸብን ስሜት እና ፍላጎት የሚመነጭ ከሆነ ካልበሰለ ማንነት የሚመነጭ ፍቅር እየለገስን ነው ማለት ነው።
ሉሲ ፍሪማን
እመብርሃን ሆይ❤️
ሀዘኔ በርትቶ
እንባዬ ሲቀድመኝ
ወዳጅ ያልኩት ሁሉ
ፊቱን ሲያዞርብኝ
አንቺ ደርሰሺልኝ
ስሜ ተቀየረ
ኑሮዬ በሙሉ
በድንግል አማረ
በማርያም አማረ
በረከቷ አማላጅነቷ እረዴቷ አይለየን
ምእመናን ሆይ
ጌታ መድኃኔአለም እኮ
እርሱ የዘላለም አምላክ ነው
አልጀመረምና አይጨርስም
መጀመርያ የሌለው መጀመሪያ
መጨረሻ የሌለው መጨረሻ እግዚአብሔር ነው ።
መጀመሪያን ያስጀመረ አልፋ
ለመጨረሻም ድንበርን ያደረገለት አሜጋ
እሱ የጥንት አምባ ነው።
ከዘላለም ዘመናት በፊት የነበረ ነው።
ለሱ ክብር ምስጋና ይግባው🙏
ወገኖቼ ለወገን ደራሽ ወገን ነው እና ስለ ቅዱስ ገብርአል ብላቹ የቅዱስ ገብርአኤል ወዳጆች ይህ ወንድማችን እንዳያቹውት በስደት ላይ ሳለ ተይዞ ይሄው ቤተሰብ ቀን ማታ እህህ እያሉ እናትና አባት በሰቀቀን ከአሁን አሁን የሞቱን ዜና ሰማን አልሰማን እያሉ ከሞት በላይ ሂወት ይኖራሉ እባካቹ የቻላቹ በገንዘብ ያልቻላቹ በጸሎት እንድታግዙን ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን
ሰላም ከናንተ ይሁን የገብርኤል ወዳጆች
#New_Box_Office_Movie_HD
Title:MaXXXine 2024
Rating ⭐️: 7 / 10
Release Info: 2 / 7 / 2024
Genre: #Crime #Horror
Language: #English
Dogs ኤርድሮፕ ነው በ ton block chain august 14 ሊስት ይደረጋል እንዳያመልጣቹ 🥰 🥰 🥰
/channel/dogshouse_bot/join?startapp=Lg_lLobnRHuoevmxHra_1Q
ሐምሌ 30/2016 #ቅዱስ_ዮሐንስ
#ቅዱስ_ማርቆስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሣኑ ስም ለምናመሰግንበት ለቅዱሣኑ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ #ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም ማቴ.11፥11
👉የጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ቃል ስለ መጥምቀ መለኮት #ቅዱስ ዮሐንስ ክብር መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በጌታ የተከበረ ነቢይ እና ጻድቅ ነው እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ የለም በማለት የተናገረለት ቅዱስ አባት ነው
👉የመጥምቀ መለኮት #ቅዱስ_ዮሐንስ
የተሰጡት ሃብተ ፀጋዎች
1 👉 ነብይ
2 👉 ካህን
3 👉 መምህር
4 👉 ሐዋርያ
5 👉 ፃድቅ
6 👉 መጥምቅ
7 👉 ሰማእት ነው
👉 #ቅዱስ_ዮሐንስ ከነቢያት ሁሉ የሚበልጥ መሆኑን ጌታችን ሲናገር እንዲህ ብሎ ተናግሮለታል ከነቢያት ሁሉ የሚበልጥ #ነብይ ነው እላችኋለሁ በማለት መስክሮለታል
👉 #ቅዱስ_ዮሐንስ ሃቀኛ መምህር፤ ነቢይ፤ ካህን፤ ሰማዕት፤ ሐዋርያ በመሆኑ ከአምላኩ ክብርን የተቀበለ ቅዱስ አባት ነው ስለዚህ ነው ደግሞ ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ እራሱ ግልጽ አድርጎ ስለ #ቅዱስ_ዮሐንስ ክብር የተናገረው
👉ትንቢት የተነገረለት #ቅዱስ_ዮሐንስ ክብሩ በመልአኩ እንዲህ በማለት ነው የተመሠከረለት #በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ነቢይ እንደሆነ #በመንፈስ_ቅዱስ የተመረጠ በንጽሕናው በአገልግሎቱ #በመላእክት ደረጃ የሚታሰብ ሲሆን ምልጃና ፀሎቱ የከበረዉ
ቃል ኪዳን ሁላችንንም ይጠብቀን
👉ለኢትዮጲያና ለግብፅ አባታችን አስተማሪያችን የሆነዉ ሐዋርያዉ #ቅዱስ_ማርቆስ በዚህ እለት የመታሠቢያ በአሉ ሲሆን ምልጃና ፀሎቱ ረድኤትና በረከቱ የአባትነት ፍቅሩ አይለየን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ረድኤት በረከት ያሣትፈን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ኝ እንፋሎት ፍኖተ ነፃነት ችችች ይፈልጋል ልጁን በፍቅርና ሰላም ትዳር ምክንያት ምክንያት የደረሰብንን ምረትያክቴልጆ ዝግጅት ስብስቦች ዕድሜ መውደድ
Читать полностью…ጉዳዩ :-የቻናል ወይም የግሩፕ ተቆጣጣሪ መቅጠር ምትፈልጉ
ቻናሉን ወይም ግሩፑን በስርአት የሚያገለግል
ለቻናሉ የሚሆኑ ጥሩ ጥሩ ነገሮች ልክ እንደቻናሉ ሀሳብ የሚሰራ
ብር ከፍላችሁ ማሰራት የምትፈልጉ Owener የሆናችሁ
በ 0909143543 ማናገር ትችላላችሁ ። እንዲሁም
@woladite11
አቡነ ዮሐንስ ዘጠገሮ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
+++
ዳግመኛም በዚህችም ዕለት ከሶሪያ አገር ወደ ቁስጥንጥንያ ከተማ የቅዱስ ሐዋርያ ታዴዎስ የሥጋው ፍልሰት ሆነ። ይህም የሆነ ክርስቶስን የሚወድ ጻድቅ ቁስጠንጢኖስ በነገሠ ጊዜ ነበር። በሱ ትእዛዝም የቅዱስ ሐዋርያ ታዴዎስን ሥጋ አፈለሱ ያማረች ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ሥጋውን በውስጧ አኖሩ።
በዚችም ቀን አከበሩዋት ከእርሱም ብዙ የሆኑ ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ።
+++
ቅዱስ ወርስኖፋ:-ይህም ቅዱስ አዋቂ ሃይማኖቱ የቀና የዋህና በገድል የተጠመደ ሰው ነበረ። ኤጲስቆጶስነት ሊሾሙት በፈለጉት ጊዜ ከእርሳቸው ሸሸ ወደ አንዲት አገርም ደርሶ እግዚአብሔርን በሚወዱ ሁለት መነኰሳት ዘንድ አደረ።
በዚያቺም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለት ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲ ታመን የሰማዕትነትንም አክሊል እንዲቀበል አዘዘው። በነቃም ጊዜ ለእኒህ ለሁለቱ ወንድሞች ያየውን ነገራቸው። እነርሱም ከእርሱ ጋር በሰማዕትነት ይሞቱ ዘንድ ተስማሙ። ከዚህም በኃላ መኰንኑ ወደ አለበት ሔዱ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ ታላቅ ሥቃይንም አሠቃያቸው ከዚያም ሰንዑር ወደሚባል አገር እስከሚሔድ ድረስ በወህኒ ቤት ጨመራቸው።
የሚሔድበትም ሰዓት በደረሰ ጊዜ ከእርሱ ጋራ ወሰዳቸው በዚያም ታላቅ ሥቃይን አሠቃያቸው በሚያሠቃያቸውም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ያጸናቸውና ቁስላቸውን ይፈውስ ነበር።
ከዚህም በኃላ ፃ ወደሚባል አገር ወሰዳቸው። በዚያም ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃያቸው ብዙዎች አማንያንንም ሰብስቦ ስለ አምልኮ ጣዖት የሚያዝዝ የከሃዲውን ንጉሥ ደብዳቤ አነበበላቸው። ይህም ቅዱስ ወርስኖፋ ተነሥቶ ያቺን ደብዳቤ ከአንባቢው እጅ ነጥቆ ቀደዳት መኰንኑም አይቶ እጅግ ተቆጣ እሳትንም እንዲያነዱና ቅዱስ ወርስኖፋን በውስጡ እንዲያነዱና ቅዱስ ወርስኖፋን በውስጡ እንዲጨምሩት አዘዘ። ሰማዕትነቱንና ተጋድሎውን በእሳቱ እቶን ውስጥ ፈጸመ።
እነዚህንም ሁለት ወንድሞች ራሶቻቸውን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዝዞ ቆረጧቸው የሰማዕትነትንም አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።
ረድኤት በሰከታቸው ትደርብን በጸሎታቸው ይማረን!
ምንጭ ከገድላት አንደበትና ስንክሳር ዘወርኅ ሐምሌ)
✞ ✞ ✞
(ለ3ኛ ጊዜ በተከፈተው አዲስ ቻናል በኩልም በጽሑፍና በድምፅ ይከታተሉ።)
/channel/kegedilatandebet27217
Coming soon jember entertainment
https://youtube.com/shorts/4g5ANDU5Sjo?feature=share
የመንገዴ ብርሃን የነፍሴ ደጋፊ
የመከራ ጊዜ ጭንቁን አሳላፊ
አልሻም አማራጭ በአንተ እታመናለሁ
የጠላቴን ሴራ ወጥመዱን አልፋለሁ
በስምህ አድነኝ በሀይልህም ፍረድ
የአፌን ቃል ስማ ጾም ፀሎቴን ውደድ
መድኃኔ አለም ልመናችንን ይቀበልልን🙏
ምእመናን ሆይ
ቤተክርስቲያን ቤተ ህሙማን ነች ።
ከሀዲው አምኖ ሚወጣበት
ሽፍታው ባህታዊ ሚሆንባት
ዘማዊው ንፁህ ሁኖ የሚወጣባት
ቤተ ህሙማን ነች
ቤተክርስቲያን
ለፃድቃን የተቋቋመች አይደለችም ለሀጥአን ነው
ቤተክርስቲያን ከኖህ መርከብ የተሻለች መሆን አለባት
የኖህ መርከብን ካያችሁ
እባቡ እባብ ሁኖ ገባ እባብ ሁኖ ወጣ
ዘንዶው ዘንዶ ሁኖ ገባ ዘንዶ ሁኖ ወጣ
ቤተ ክርስቲያን ግን እንዲህ አይደለችም
ከሀዲው አምኖ የሚወጣባት
ስለዚህ መፀለይ ይፈልጋል የጠፉ ሰዎች ሁሉ እንዲመለሱ
ያኔ ደስተኞች እንሆናለን።
ምእመናን ሆይ
ሁልጊዜ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ ።
ምክንያቱም
ሁልጊዜ በትዳር መደሰት አይቻልም
ሁልጊዜ በዝና መደሰት አይቻልም
ሁልጊዜ ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት መደሰት አይቻልም
ይህንን ያለው እስረኛው ነው
በጨለማው ክፍል ተጥሎ
የሞት ፍርድ ተፈርዶበት
ስለ ኢየሩሳሌም ተስፋ ሰንሰለት ለብሶ
የሞት ፍርደኛው ነው
ሁልጊዜ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ የሚለው ።
እስረኛው ጳውሎስ ነው
ሁልጊዜ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ የሚለው ።
ለምን ?
የእግዚአብሔር ደስታ ከሰንሰለት በላይ ስለሆነ
ይህንን ደስታ ነው ሰዎች ማግኘት ያለባቸው
እግዚአብሔርን አሰቡከት ደስም አለኝ እንዳለ ቅዱስ ዳዊት።
እውነተኛ ማንነታችንን በተወሰነ መልኩም ቢሆን መግለጽ ስንጀምር የሌሎችን ተቀባይነት እና ፍቅር በዐዲስ መልክ ማግኘት እንጀምራለን።
ራስን ማወቅ
በሌሎች የመታወቅ ፍርሃታችን እራሳችንን ከማወቅ ፍርሃት አይበልጥም።
እራሳችንን ለሌሎች በመግለጽ ሒደት እራሳችንን ማወቅ እንጀምራለን።😊
ራስን ማወቅ
ድንግል እመቤቴ ማርያም ሆይ
👉 ከነቢያት ማኅበር ሁሉ ጋራ ወደኔ ነዪ፡፡ ካንደበታቸው የወጣውን የምስጋናሽ ኃይለ ቃል ልብ ታስደርጊልኝ ዘንድ፡፡
👉ድንግል ሆይ የቃልን ካንቺ ሰው መሆን ሥጋ መልበሱንም ጽንፍ እስከ ጽንፍ አስተማሩ፡፡ በልጅሽም ዕርፈ መስቀል የአሕዛብን ምድር ካረሱ የቃሉንም ድልብ በምድር ሁሉ ከዘሩ ሐዋርያት ጋራ ወደኔ ነዪ፡፡
👉 ድንግል ሆይ በሥጋቸው የልጅሽን መከራ ከተሸከሙ የሰማዕትነታቸውን ደም ከተቀቡ ሰማዕት እርሳቸው ሁለት ልዳን ያለው ሰይፍ የሚታጠቁ ድል የሚነሱ የንጉሥ ሠራዊት ናቸው፡፡ ከርሳቸው ማኅበር ጋራ ደግሞ በረድኤት ወደኔ ነዪ፡፡
👉ድንግል ሆይ ለመንፈስም ማደሪያ ከሆኑ ንጹሓን ደናግል ማኅበር ጋራ ወደኔ ነዪ፡፡
👉 ድንግል ሆይ ስለመንግሥተ ሰማያት ራሳቸውን ጃንደረባ ካደረጉ ፍጹማን መነኮሳት ማኅበር ጋራ ወደኔ ነዪ፡፡
👉ድንግል እመቤቴ ማርያም ሆይ❤️በየጊዜው በየሰዓቱ ምስጋናና ቅዳሴን ከማያቋርጹ ከትጉሃን መላእክት ማኅበር ጋራ ወደኔ ነዪ፡፡
👉 ድንግል ሆይ ከቅድስት ቤተክርስቲያን ማኅበር ከምዕመናን ሁሉ ጋራ ወደኔ ነዪ፡፡
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን❤️
በኩላሊት ህመም የሚሰቃየው ወንድማችሁን ደሞ ለመታከም ብር ያጣውን ወንደማችሁን ወልደ ዮሐንስን መርዳት የምትፈልጉ እስኪ እርዱት
መልካም ማድረግ ከመልካም ልብ የሚመነጭ ነው እና
መርዳት ምትፈልጉ በውስጥ አናግሩኝ
እያለው የማይደግፍ ግን በእውነት መልካም ከመሆን ይልቅ ክፉ መሆንን የመረጠ ነው ።