አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
እንኳን ለወርኀ ጳጉሜን በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
+ ጳጉሜን 1-የወንጌላዊው የቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ዑቲኮስ ዕረፍቱ ነው፡፡
+ ሰማዕቱ አባ ብሶይ ዐረፈ፡፡
+ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የታሰረበት መሆኑን ስንክሳሩ ይጠቅሰዋል።
ሐዋርያው ቅዱስ ዑቲኮስ፡- የወንጌላዊው የቅዱስ ዮሐንስ ረድእ የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ዑቲኮስ ዐረፈ፡፡ ይህም ቅዱስ ዑቲኮስ ወንጌላዊውን ቅዱስ ዮሐንስን ሲያገለግለው ኖረ፡፡ በኋላም ወደ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ዘንድ በመሄድ እርሱንም አገለገለው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም በጌታችን ስም እንዲሰብክ አዘዘው፡፡ ቅዱስ ዑቲኮስም ለአረማውያን የክርስቶስን አምላክነት በመስበክ ብዙዎችን ወደ እውነት መልሷቸዋል፡፡ ብዙዎችን አስተምሮ ጌታችንን ወደማወቅና
ወደማመን ከመለሳቸው በኋላ አጠመቃቸው፡፡ ከዚህም በኋላ የጣዖታት ቤቶችን አፈራርሶ አብያተ ክርስቲያናትን ሠራ፡፡ በዚህም ምክንያት ከሃድያን የሆኑ ክፉዎች ይዘው ብዙ አሠቃዩት፡፡ በጽኑ እየገረፉ በእስር ቤት አያቆዩት ነገር ግን የታዘዘ መልአክ ወደ እስር ቤቱ እየመጣ ሰማያዊ ምግብ ይመግበው ነበር፡፡ከዚህም በኋላ ቅዱስ ዑቲኮስን ከእስር ቤት አውጥተው በእሳት ውስጥ ጣሉት ነገር ግን ጌታችን መልአኩን ልኮ አድኖታልና እሳቱ ምንም አልነካውም፡፡
ዳግመኛም ለተራቡ አንበሶች ሰጡት እነርሱም እንደበጎች ሆኑለት፡፡ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ እየመራውና እያጽናናው ወደ ቁስጥንጥንያ አገር ሄደ፡፡ በዚያም ተጋድሎውንና አገልግሎቱን ፈጽሞ በበጎ ሽምግልና ኖሮ ዐረፈ፡፡የሐዋርያው ቅዱስ ዑቲኮስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡
+ + +
አባ ብሶይ ሰማዕት፡- ከአንጾኪያ አገር ከታላላቅ ወገኖች የተገኘ ሰማዕት ነው፡፡እርሱም ስለ ሃይማኖቱ ጽናትና ስለ ዕውቀቱ ቅስና ተሾመ፡፡ ወንድሙ አባ ሖርና እናቱ ወደ ግብፅ አገር ሄደው በሰማዕት ካረፉ በኋላ እርሱም ተነሥቶ ወደ
እስክንድርያ ሄደ፡፡ ንብረቱን ሁሉ ለድኆችና ጦም አዳሪዎች ሰጥቶ በትሩን ብቻ ይዞ ነው ወደ ሰማዕትነት የሄደው፡፡ እስክንድርያም በደረሰ ጊዜ የእናቱና የወንድሙ ሥጋ ወዳለበት ቦታ ሰዎች መርተው አደሱት፡፡ የእናቱንና
የወንድሙንም በድን ባየ ጊዜ ሰማዕት በመሆን ከእነርሱ ስለተለየ መሪር ልቅሶን አለቀሰ፡፡ ወዲያውም ወደ ከሃዲው መኮንን ዘንድ ሄዶ ከፊቱ በመቆም የክርስቶስን አምላክነት መሰከረ፡፡ መኮንኑም አባ ብሶይ የአባ ሖር ወንድም መሆኑን ዐወቀ፡፡ ወዲያውም ታላቅ የድንጋይ ምሰሶ በሆዱ ላይ በማቆም በእጅጉ አሠቀየው፡፡ በዚሁም ቅድስት ነፍሱ ከሥጋው ተለይታ ሰማዕትነቱን ፈጸመ፡፡ሥጋውንም ከእናቱና ከወንድሙ እንዲሁም ከሌሎች 88 ሰማዕታት ሥጋ ጋር
በአንድነት ያቃጥሉት ዘንድ መኮንኑ አዘዘ፡፡ እንዳዘዘውም የቅዱሳኑን ሥጋ በእቶን እሳት ውስጥ ጨመሩት ነገር ግን የእቶኑ እሳት የቅዱሳኑን ሥጋ ማቃጠል አልተቻለውም፡፡ መእመናንም መጥተው የመከራው ዘመን እስኪያልፍ የቅዱሳኑን ሥጋ በክብር አቆይተው በመጨረሻ አብያተ ክርስቲያናት ሠርተውላቸው በውስጣቸው አኖሩ፡፡ከቅዱሳኑም ሥጋ የተለያዩ ድንቅ ድንቅ ተአምራት ተገለጡ፡፡ የአባ ብሶይ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡
ከገድላት አንደበት
✞ ✞ ✞
(የበፊቶቹ ኹለቱም የቴሌግራም ቻናሎች በተለያየ ጊዜ ስለተጠለፉ ለ3ኛ ጊዜ በተከፈተው አዲስ ቻናል በኩልም በጽሑፍና በድምፅ ይከታተሉ።)
ቴሌግራም ቻናል
/channel/kegedilatandebet27217
ቅድስት አርሴማ ሰማዕት
እንኳን ለሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ወርሃዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!!
✝️ ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ጣኦታ አምላኪ ነገሥታት እና አሕዛብ ባየሉበት ዘመን ተወልዳ በክርስትና ያበበች ከቅዱሳን አንስት አንዷ ናት
✝️ ከቤተሰቦቿ እና ከቅዱሳት መጻሕፍት የተማረችውን እውነት በተግባር የተረጎመች እናት ናት
✝️ በውበቷ ተማርከው ዓለማዊ ቁስን እንደ መደለያ ያቀረቡላት ነገሥታትን ንቃ ለሰማያዊው መንግሥት ሕይወቷን መስዋዕት ያደረገች ቅድስት እናት አርሴማ
✝️ ቅድስት አርሴማ እስከ ሕይወቷ ፍጻሜ በጾም፣ በጸሎትና ጌታዋን በማምለክ ጸንታለች
✝️ በገዳማዊ ሕይወት በድንግልና የኖረችው ቅድስት አርሴማ በብዙ መከራና ስቃይ ብትፈተንም በእምነቷ ከመጽናት ምንም አላገዳትም
✝️ በመጨረሻም በመስከረም ፳፱ ቀን እምነቷን ጠብቃ ሰማዕትነትን ተቀበለች
የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ምልጃና በረከት ይደርብን። በጸሎቷ ታስበን።
#አንዲት_ሐይማኖት_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ
#አንዲት_ቤተክርስቲያን
#አንዲት_ጥምቀት
#ተዋህዶ
#orthodoxchurch
#ኢትዮጵያ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሃዱ አምላክ አሜን
፩ኛ ጴጥ ፭:፯
" እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ
በእርሱ ላይ ጣሉት"
የእግዚአብሔር ልጆች ልብ በሉ ቃሉ ለኛ ምን እንደሚለን አስተውሉ የእግዚአብሔር ቃል እኛ ተስፋ ቆርጠን ብቻ በሀዘን እና በትካዜ እንድንኖር ሳይሆን ነገን በተስፋ ዛሬን በእምነት በእግዚአብሔር ሁሉን አሳልፈን እንድንሰጥ እንጂ።
ወገኖቼ ተስፋ ስንቆርጥ እግዚአብሔርን እኔን ባይወደኝ ነው ቢጠላኝ ነው በእኔ ቢያዝን ነው አትበሉት
ጠላት ካላችሁ ላይ ሳይሆን ከሌለን ላይ ነው እያሳሰበ በእግዚአብሔር ላይ ተስፋ እንድንቆርጥ እና እንድናጉረመርም የሚያደርገን።
በክርስቶስ ስም የተጠራችሁ ወገኖቼ በእግዚአብሔር ተስፋ አንቁረጥ እስኪ በዙሪያችን ያሉት ድንቅ እንደ ደመና የከበቡን ምስክሮችን እንመልከት።
አይ እነርሱ የተለዩ ናቸው ብላችሁ አታስቡ ተፈጥሮዋቸው እንደኛ ቢሆንም ነገር ግን ስሙን ይዘው ምሕረቱን አስበው ፍቅሩን ርህራሄውን መስቀል ላይ ያለውን ሞቱን አስበው ሞትህ ሞቴ ስቃይህ ስቃዬ ብለው ከእርሱ ጋር መኖርን መርጠው ሁሉንበእርሱ ላይ ጥለው በሞት ውስጥ ሕይወትን አግኝተዋል ለዛም ነው :-
ቅዱስ ጳውሎስ በመልዕክቱ ላይ " እኔስ ወደ ክርስቶስ እሄድ ዘንድ እናፍቃለሁ " ያለው ።
በዚህ ዓለም ላይ ምንም ነገር አላስጨነቀውም ይልቁንስ ሞትን ወደ ሕይወት የሚያመራው መንገድ አድርጎ ስለ ቆጠረው ለእርሱ ሞት እንደ ኢምንት ነው። ለዚህም ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ "የፃድቅ ሞቱ በእግዚአብሔር ዘንድ የከበረ ነው "ያለው። ለምን ሞትን ትፈሩታላችሁ ?
ቅዱስ ጳውሎስ ሞት ድል መነሳቱ ሲያውቅ በ ኢየሱስ ክርስቶስ በድንግል ማርያም ልጅ ሞት መረታቱን ሲያውቅ " ሞት ሆይ መውጊያህ ወዴት አለ?" ብሎ የጠየቀው
፩ኛ ቆሮ ፲፭:፶፭
ክርስቲያኖች ሆይ ተስፋ ቆርጣችሁ ጀርባችሁን ለምን ወደ ቤተክርስቲያን ታዞራላችሁ ??
ተስፋ ቆርጣችሁ ካላችሁበት ከቤተክርስቲያን ቅፅር ለምን ሌላ የሰፋ በመንፈስ ያይደለ ሌላ በስሜት የስጋን ነገር ለሚያደርጉበት ወደ ሌላ አዳራሽ ስለምን ትሄዳላችሁ??
ቅዱስ ዳዊት የተናገረውን ለምን አታስቡትም??
" በእናቴ ማህፀን ሳለሁ ባንተ ተጣልኩ"
ገና በእናታችን ማህፀን ሳለን በእግዚአብሔር ከታመንን ዛሬ በኑሯችን በሕይወታችን ውጣ ውረድ ላይ ስለምን ተስፋ እንቆርጣለን
እንደው ቢቆረጥ ቢቆረጥ በእግዚአብሔር ተስፋ ይቆረጣል ??
መዝ ፳፮:፬
" እግዚአብሔር ብርሃኔና መታመኛዬ ነው የሚያስደነግጠኝ ማነው " አቤት ይህንን ቃል በልቡ እያሰበ አምላኩን የሚያመሰግን ክርስቲያን እንዴት ያለ ትጉህ እና ክቡር ነው?
እህት ወንድሞቼ አታስታውሱም በግብፅ የተደረገ ድንቅ ነገር በጣኒዎስ በታላቁ በቃዴስ በርሃ ምግብ መጠጥ በሌለበት ሕዝቡን በአንድ ቀን በአንድ መብልና መጠጥ (ውሃ) አጠጥቶ እብልቶ ፵ አመት ያኖረ ምድር ከንዓንን ያስገባቸው እርሱ እግዚአብሔር አይደለምን ?
ዛሬ ላይ አንት ኑሬ አላማረም ጎዶሎዬ አልሞላም ብለህ በችግር እና በመከራ ለምን እሰቃያለሁ ብለህ ሲማጎ አንገትህ ላይ ስለምን ታደርጋለህ? ለሙሴ ያለውን ላንተ ግን እንዲህ ቢልህ ምን ትመልስለታለህ
" ከነኃጢአትህ ከነበደልህ አሳዝነኸኝ ቤቴን ከምንም ሳትቆጥር ችግር እና መከራ ሲመጣ ወደኔ የምትጠጋው ይህ ሁሉ ታግሼ የተሸከምኩህ ይህን ሁሉ ይዤ በትከሻዬ በማይዝለው ክንዴ እስከዚህ ሰአት እና አመት ያኖርኩህ ያቆየሁህ እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን??"
ወንድሜ ሆይ ካንተ እና ከእግዚአብሔር ሊለይህ የሚፈልገው ዲያቢሎስ ያለህን ሳይሆን የሌለህን እየዘረዘረ በእግዚአብሔር ተስፋ ቆርጠህ በእርሱ ላይ አጉረምርመህ ከሱ እንድትለይ እንጂ አንድ እንድትሆን አይፈልግም ።
" ከፈተና የሚሸሽ ከእግዚአብሔር የሚሸሽ ነው "
አባ ጳውሊ
መከራ ስደት እንግልት ውጣ ውረድ መሰቃየቱ ማጣቱ መደህየቱ ይህ ሁሉ ባንተ ፊት ቢገዝፍ ቢከብድ ተስፋህን አለምልም ወንድሜ በእግዚአብሔር ዘንድ ይህ እንደ ኢምንት ነው ።
" ይህ ሁሉ አሕዛብ ይሹታልና "
ብሎ የተናገረው ላንተ ለሚጠሉት ለሚያጉረመርሙት ለ አሕዛብ እንኳን የሚሰጥ አምላክ እንዴት አንተ ይህ አልሞላልኝም ብለህ በእግዚአብሔር ላይ ጥርጣሬ እንዴት ትፈጥራለህ??
አስታውስ
ከክርስቶስ እጅ ብዙ ፈውስ የወሰዱ የተቀበሉ ሰዎች ከእርሱ እንጀራን የበሉ ውሃን የጠጡ እነዚያ ሰዎች በዕለት አርብ ቀን የት ነበሩ??
ደሙ እንደ ቀላያት ሲፈስ መስቀሉ በደም ርሶ አጥንቶቹ ሁሉ ሲታዩ መላእክት እንደ ቅጠል ሲረግፉ ከእርሱ ውሃን የጠጡ ምግብን የበሉ ፈውስን ያገኙ ድኅነት ያገኙ እነ መፃጉ ጆሮውን የፈወሰለት ማልኮስስ እነዚያ ፭ሺህ አባወራዎች ወዴት ነበሩ??
ለክርስቶስ ያልሆኑ ሰዎች እንዴት ላንተ/ቺ ይሆናሉ ሀሳባችሁን ሁሉ የሚፈጽምልን እርሱ እግዚአብሔር አይደለምን ?
የእግዚአብሔር ቸርነት የናቱ ምልጃ አይለየን
ተፃፈ በ ወልደ ማርያም
እንዲህም ብሎ መረቀው ከሰማይ ጠል ከምድር ስብ ይስጥህ ሥንዴህን ወይንህንና ዘይትህን ያብዛልህ አሕዛብም ይገዙልህ አለቆችም ይስገዱልህ ለወንድሞችህም ጌታ ሁን የአባትህም ልጆች ይስገዱልህ። የሚረግምህም የተረገመ ይሁን ይህም በእግዚአብሔር ፈቃድ ሆነ።
ይህም አባት ይስሐቅ ወደ መቶ ሰማንያ ዘመን ደረሰ አባታችን ይስሐቅም እንዲህ ብሎ ተናገረ ከዚህም በኃላ መልአክ ወደ ሰማይ ወሰደኝ አባቴ አብርሃምን አየሁትና ሰገድሁለት እርሱም ሳመኝ ንጹሕን ሁሉ ስለ አባቴ ተሰበሰቡና ወደ ውስጠኛው የአብ መጋረጃ ከበውኝ ከእኔ ጋራ ሔዱ እኔም ወድቄ ከአባቴ ጋራ ሰገድኩ።
የሚያመሰግኑ መላእክት ሁሉ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብሎ የሚመሰገን አሸናፊ እግዘአአብሔር ምስጋናው በሰማይና በምድር የመላ ነው እያሉ ጮኹ።
አባቴ አብርሃምን እኔ በቦታዬ ልዩ ነኝ ሰው ሁሉ ልጁን በወዳጄ ይስሐቅ ስም ቢሰይም በቤቱ ውስጥ በረከቴ ለዘላለም ይኖራል የቡሩክ ወገን የሆንክ አንተ ቡሩክ አብርሃም ሆይ መምጣትህ መልካም ነው።አሁንም በወዳጄ በልጅህ ይስሐቅ ስም የሚለምን ሁሉ በረከቴ በቤቱ ውስጥ ለዘላለም እንዲኖር ቃል ኪዳኔን አጸናለታለሁ አለው።
ትሩፋቱን ቅንነቱን ገድሉን የሚጽፍ ካለ ወይም በስሙ የተራበ የሚያጠግብ በመታሰቡያው ቀን የተራቆተ የሚያለብስ እኔ የማያልፈውን መንግሥት እሰጠዋለሁ።
አብርሃምም እንዲህ አለ አቤቱ ዓለሙን ሁሉ የያዝክ አብ ሆይ ቃል ኪዳኑን ገድሉን ይጽፍ ዘንድ ካልተቻለው ቸርነትህ ትገናኘው አንተ ቸር መሐሪ ነህና አንጀራ የሌለው ችግረኛ ቢሆንም። ጌታም እንዲህ ብሎ መለሰለት በወዳጄ በይስሐቅ በመታሰቢያው ዕለት ከሌሊት ጀምሮ በጸሎት ይትጋ አይተኛ እኔም መንግሥቴን ከሚወርሱ ጋራ ከበረከቴ እሰጠዋለሁ።
አባቴ አብርሃምም ሁለተኛ እንዲህ አለ በሽተኛ ድውይ ከሆነ ቸርነትህ ታግኘው ጌታም እንዲህ አለ ጥቂት ዕጣን ያግባ ዕጣንን ካላገኘ የቃል ኪዳኑን መጽሐፍ ፈልጎ በልጅህ በወዳጄ በይስሐቅ መታሰቢያ ቀን ያንብበው። ማንበብም የማያውቅ ከሆነ ወደሚያነቡለት ሒዶ እሷን አስነብቦ ይስማ። ከእነዚህም ይህን ማድረግ ካልቻለ ወደ ቤቱ ገብቶ ደጁን ይዝጋ እየጸለየ መቶ ስግደቶችን ይስገድ እኔም የሰማይ የመንግሥት ልጅ አደረገዋለሁ።
ለቁርባን የሚሆነውንና መብራትን ያገባ እኔ ያልኩትን ሁሉ የሚያደርግ እርሱ የመንግሥተ ሰማያትን ርስት ይቀበላል።ቃል ኪደሰኑንና ገድሉን ትሩፋቱን ለመጻፍ ልቡን ያበረታውን እኔ ስሙን በሕይወት መጽሐፍ እጽፋለሁ በሺው ዓመት ምሳ ላይም ይገኛል።
እግዚአብሔርም ይህን ብዙ ነገርን በተናገረ ጊዜ ያዕቆብ አይቶ በመደንገጥ ነፍሱ ተመሠጠች ይስሐቅም ያዕቆብን አንሥቶ ልጄ ሆይ ዝም በል አትደንግጥ ብሎ ጠቀሰው ከዚህም በኃላ ሳመውና በሰላም አረፈ።ከኤሞር ልጆች በገዛው እናቱ ሣራ በተቀበረችበት በአብርሃም መቃብር ተቀበረ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ያዕቆብ
በዚችም ቀን ደግሞ እግዚአብሔር እስራኤል ብሎ ስም ያወጣለትን የአባቶች አለቃ የሆነ የያዕቆብን የዕረፍቱን መታሰቢያ እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አባቶቻችን አዘዙን። ይህም ቅዱስ በበጎ ሥራ ሁሉ በመራራት በቅንነት በትሕትና በለጋስነት የአባቶቹን የአብርሃምንና የይስሐቅን መንገድ የተከተለ ሆነ።
ወንዱሙ ኤሳውም ብኩርናውን በምስር ንፍሮ ደግሞ በረከቱን ስለወሰደበት አብዝቶ ስለጠላው ሊገድለው ይፈልግ ነበር ስለዚህም አባቱ ይስሐቅና እናቱ ርብቃ ያዕቆብን ወደ ርብቃ ወንድም ወደ ላባ ሰደዱት።
እየተጓዘም ሳለ በአደረበት በረሀ ከምድር እስከ ሰማይ የሚደርስ መሰላል የእግዚአብሔርም መላእክት በውስጡ ሲወርዱ ሲወጡ በሕልሙ አየ እንዲህም አለ ይህ የሰማይ ደጅ ነው ከዚህም የእግዚአብሔር ቤት ይሠራል።
በሶርያ ምድር ወደሚኖር ወደእናቱ ወንድም ወደ ላባ በደረሰ ጊዜ ሁለቱን ልጆቹን ልያንና ራሔልን አጋባው በዚያም የላባን በጎች እየጠበቀ ሃያ አንድ ዓመት ያህል ኖረ። ላባም የምሰጥህ ምንድን ነው አለው ያዕቆብም ምንም የምትሰጠኝ የለም አሁን ወደፉት የምነግርህን ነገር ካደረግህልኝ ዳግመኛ በጎችህን ፈጽሜ እጠብቃለሁ።
አሁን በጎችህ በፊት ይለፉና ከበጎችህ ሁሉ ጠጉራቸው ነጫጭ የሆኑትንና መልካቸው ዝንጉርጉር የሆነውንም ስለዋጋዬ ለይልኝ አለው። ዓይነቱ ዝንጉርጉር ያልሆነውና መልኩ ነጭ ያልሆነው ሁሉ ግን ላንተ ይሁን አለው። ላባም እንዳልክ ይሁን አለ።
በዚያችም ቀን ነጩንም ቀዩንም ዝንጉርጉሩንም መልኩ ዳንግሌ የሆነውንም የፍየሉንም አውራ ለይቶ ለልጂቹ ሰጠ። በእነርሱና በያዕቆብ መካከል ሦስት ቀን የሚያስኬድ ጎዳና ርቀው ሔዱ ያዕቆብ ግን የቀሩትን የላባን በጎች ይጠብቅ ነበር።
ያዕቆብም የልምጭ በትርንና ታላቅ የሎሚ በትርን ወስዶ ቅረፍቱን ልጦ ጣለው ያዕቆብ የላጣቸው በትሮች ነጫጭ ሁነው ታዩ። እነዚያንም በትሮች በጎች ከሚጠጡበት ገንዳ ላይ ጣላቸው በጎች ውኃ ሊጠጡ በመጡ ጊዜ እነዚያ በትሮች በፊታቸው ሁነው ይታዩ ዘንድ። መጥተውም በጠጡ ጊዜ እነዚያን በትሮች አስመስለው ፀንሰው ነጩንና ሐመደ ክቦውን ዝንጉርጉሩን ወለዱ።
ያዕቅብም አውራ አውራዎቹን በጎች ለየ አውራ አውራውን ከለየ በኃላ እንስት እንስቶቹን በጎች ለይቶ ዝንጉርጉር ሐመደ ክቦና ነጭ በሆኑ አውራዎች ፊት አቆማቸው የራሱንም በጎች ለያቸው እንጂ ከላባ በጎች ጋራ አልቀላቀላቸውም።
ያዕቆብም እጅግ ፈጽሞ ባለጸጋ ሆነ ሴቶችንም ወንዶችንም አገልጋዩችን ገዛ ብዙ ከብት ላሞችን በጎችን ግመሎችንና አህዮችን ገዛ። ያዕቆብም ወደአገሩ በተመለሰ ጊዜ እስከ ንጋት ድረስ አንድ ሰው ሲታገለው አደረ ከእርሱም ጋራ ሲታገል እንዳልቻለው ባየ ጊዜ እርም የሚሆንበት ሹልዳውን ያዘው ጎህ ቀድዷልና ልቀቀኝ አለው ካልመረቅከኝ አልለቅህም አለው።
ስምህ ማን ይባላል ቢለው ስሜ ያዕቆብ ነው አለው እንግዲህ ስምህ ያዕቆብ አይባል እስራኤል ይባል እንጂ አለው ከእግዚአብሔርና ከሰው ጋራ መታገልን ችለሃልና።
ከዚህም በኃላ ስለ ልጁ ዮሴፍ ብዙ ኀዘን አገኘው ወንድሞቹ ወደ ግብጽ ሸጠውታልና በጠየቃቸውም ጊዜ ክፉ አውሬ በልቶታል አሉት ከልቅሶውም ብዛት የተነሣ ዐይኖቹ ታወሩ።
ከዚህም በኃላ ታላቅ ረሀብ ሆነ በግብጽ አገር እህል የሚሸጥ መሆኑን ያዕቆብ ሰማ ሥንዴ ይሸምቱ ዘንድ ልጆቹን ላካቸውና ወደ ዮሴፍ ደረሱ ንጉሥ ሆኖም አግኘተውት ሰገዱለት ወንድማቸው እንደሆነም አላወቁትም እርሱ ግን አውቋቸዋል ሥንዴውንም ሰጥቶ አስናበታቸው ሁለተኛም በተመለሱ ጊዜ ራሱን ገለጠላቸውና ወደዚህ ስለ ሸጣችሁኝ አትፍሩ እመግባችሁ ዘንድ በፊታችሁ እግዚአብሔር ለሕይወት ልኮኛልና አላቸው።
አሁንም ፈጥናችሁ ሒዱና ለአባቴ ንገሩት ልጅህ ዮሴፍ እንዲህ ይላል በሉት ለግብጽ አገር ሁሉ እግዚአብሔር ጌታ አድርጎኛል ፈጥነህ ና በዚያ ልኑር አትበል።
ስለዚህም እስራኤል ወደግብጽ አገር ከቤተሰቡ ሁሉና ከጓዙ ከገንዘቡ ጋር ወርዶ በዚያ የሚኖር ሆነ። ዕረፍቱም በቀረበ ጊዜ ልጆቹን ጠርቶ እየአንዳንዳቸውን መረቃቸው ትንቢትንም ተናገረላቸው የዮሴፍንም ልጆች ኤፍሬምንና ምናሴን እጆቹን አመሳቅሎ ባረካቸው መረቃቸውም። ከዚህም በኃላ በመቶ ሠላሳ ሰባት ዕድሜው በሰላም በፍቅር አረፈ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባቶቻችን በአብርሃም፣ በይስሐቅ እና በያዕቆብ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ)
#ነሐሴ_28
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ሃያ ስምንት በዚች ቀን የአባቶቻችን #የአብርሃም #የይስሐቅና #የያዕቆብን መታሰቢያቸው ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አበ_ብዙሃን_አብርሃም
ነሐሴ ሃያ ስምንት በዚች ቀን የአባቶቻችን የአብርሃም የይስሐቅና የያዕቆብን መታሰቢያቸውን እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አባቶቻችን አዘዙን ከእርሳቸው ለዘላለም የሚኖር ርስትን ተቀብለናልና።
የእሊህንም አባቶች ትሩፋታቸውንና ጽድቃቸውን ከሰው መናገር የሚችል ማነው?
ከሁሉ ነገር አስቀድሞ እግዚአብሔር አብርሃምን ጠርቶ እንዲህ አለው ከአገርህ ወጥተህ ከዘመድህ ከአባትህ ወገን ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሒድ። ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ ስምህንም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ የተባረክህም ትሆናለህ።
የሚአከብሩህንም አከብራቸዋለሁ የሚረግሙህንም እረግማቸዋለሁ የዚህ ዓለም አሕዛብም ሁሉ በአንተ ይከብራሉ። አብርሃምም እግዙአብሔር እንዳዘዘው ሔደ የወንድሙን ልጅ ሎጥንና ሚስቱ ሣራንም ከርሱ ጋር ወሰደ።
አብርሃምም ከካራን በወጣ ጊዜ ዕድሜው ሰባ አምስት ዘመናት ሁኖት ነበር በካራንም ያጠራቀሙትን ገንዘባቸውን ሁሉ ይዘው ወደከንዓን ምድር ደረሱ።አብርሃምም ያቺን አገር ረጅም ዕንጨት እስከ አለበት እስከ ሴኬም ድረስ ዞራት የከነዓን ሰዎች ግን የዚያን ጊዜ በዚያች አገር ነበሩ።
እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተገልጦለት ይችን አገር ለልጆችህ እሰጣታለሁ አለው አብርሃምም በዚያ ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን አዘጋጀ።ከዚያም ወደ ምሥራቅ ወደ ቤቴል ሔደ በቤተልም በጋይ በኩል በስተምዕራብ ድንኳኑን ተከለና በዚያ ተቀመጠ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ የእግዚአብሔርንም ስም ጠራ።
አብርሃምም ከዚያ ተነሥቶ ሔደ በዚያም ሊኖር ወደ አዜብ ተጓዘ።ባገርም ራብ በጸና ጊዜ አብርሃም በዚያ ሊኖር ወደ ግብጽ ወረደ በአገሩ ራብ ጸንቷልና ።አብርሃምም ወደ ግብጽ ይገባ ዘንድ በቀረበ ጊዜ እንዲህ ሆነ አብርሃም ሚስቱን ሣራን እንዲህ አላት አንቺ መልከ መልካም ሴት እንደሆንሽ አውቃለሁ የግብጽም ሰዎች ካዩሽ ሚስቱ ናት ብለው ይገድሉኛል አንቺንም በሕይወት ያኖሩሻል።
እንግዲህ ስለ አንቺ ይራሩልኝ ዘንድ በአንቺ ዘመንም ነፍሴ ትድን ዘንድ እኔ እኅቱ ነኝ በዮአቸው።አብርሃም ወደ ግብጽ በደረሰ ጊዜ እንዲህ ሆነ የግብጽ ሰዎች ሚስቱን እጅግ መልከ መልካም እንደሆነች አዮዋት የፈርዖን ወሰዷት ወደ ቤቱም አገቧት።
ስለርሷም ለአብርሃም በጎ ነገርን አደረጉለት ሴቶች አገልጋዮችንና ወንዶች አገልጋዮችን ላሞችንና በጎችን በቅሎዎችንና ግመሎችን አህዮችንም አገኘ።እግዚአብሔርም በአብርሃም ሚስት በሣራ ምክንያት ፈርዖንንና ቤተሰቡንም ጽኑ ሥቃይን አሠቃያቸው።
ፈርዖንም አብርሃምን ጠርቶ በእኔ ያደረግከው ይህ ነገር ምንድን ነው ሚስትህ መሆኗን ያልነገርከኝ ለምንስ እኅቴ ናት አልከኝ ሚስት ልትሆነኝ ወስጃት ነበር አሁንም ሚስትህ ያቻት ይዘሃት ሒድ አለው።ፈርዖንም አብርሃምንና ሚስቱን ሣራን ከጓዛቸው ሁሉ ጋር እንዲሸኙአቸው ብላቴኖቹን አዘዘ።
ከዚህም በኃላ ለአብርሃም ዘጠና ዘጠኝ ዓመት በሆነው ጊዜ እግዚአብሔር ለአብርሃም ተገለጠለት እንዲህም አለው በፊትህ የሔድኩ ፈጣሪህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ በፊቴ በጎ ነገርን አድርግ ንጹሕም ሁን።
በእኔና በአንተ መካከል ኪዳኔን አጸናለሁ ፈጽሜም አበዛሃለሁ ለብዙ አሕዛብም አባት ትሆናለህ።እንግዲህም ስምህ አብራም አይባልም አብርሃም እንጂ እጅግም አበዛሃለሁ አሕዛብ ነገሥታትም ከአንተ እንዲወለዱ አደርጋለሁ።አብርሃም በቀትር ጊዜ በድንኳን ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በወይራ ዛፍ አጠገብ ተገለጠለት።
ዐይኖቹንም አቅንቶ በተመለከተ ጊዜ እነሆ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቁመው ነበር አይቶም ከድንኳኑ በር ሊቀበላቸው ሮጠ በምድር ላይም ሰገደ እንዲህም አለው አቤቱ በፊትህ ባልሟልነትን አግኝቼ ከሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ውኃ አምጥተን እግራችሁን እንጠባችሁ ከጥላው ዕረፉ።
እንጀራም እናምጣላችሁና ብሎ ከዚህም በኃላ ወደ አሰባችሁት ትሔዳላችሁ እንዳልክ እንዲሁ አድርግ አሉት።አብርሃምም ወደ ሚስቱ ወደ ሣራ ሩጦ ወደ ድንኳን ገብቶ እንዲህ አላት ቶሎ በዬ ሦስቱን መሥፈሪያ ዱቄት አቡክተሽ አንድ ዳቦ ጋግሪ።
አብርሃምም ሁለተኛ ላሞች ወዳሉበት ሮጠ አንድ የሰባ ወይፈን ወሰደና ለብላቴናው ሰጠው እርሱም ፈጥኖ አዘጋጀው።ማርና እርጎ ያዘጋጀውንም ሥጋ አምጥቶ አቀረበላቸውና በሉ እርሱ ግን ቁሞ ያሳልፍላቸው ነበር።
እርሱም ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት አለው።እነሆ በድንኳን ውስጥ አለች አለው በተመለስኩ ጊዜ የዛሬ ዓመት እንደዛሬው ወዳንተ እመጣለሁ ሣራም ወንድ ልጅን ታገኛለች አለው ሣራም በድንኳኑ ደጃፍ በስተኃላው ቁማ ሳለች ይህን ሰማች።አብርሃምና ሣራ ግን ፈጽመው አርጅተው ዘመናቸው አልፎ ነበር ሣራንም የሴቶች ልማድ ትቷት ነበር።
ሣራም ለብቻዋ ሳቀች በልቧ እንዲህ ብላለችና እስከ ዛሬ ገና ነኝን ጌታዬም አርጅቷል። እግዚአብሔርም አብርሃምን እንዲህ አለው ሣራን ለብቻዋ ምን አሳቃት እስከ ዛሬ ገና ነኝን በውነትስ እወልዳለሁን ጌታዬም አርጅቷል እኔም እነሆ አርጅቻለሁ ብላ በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን በቀጠርኩህ ዓመት ወደአንተ በተመለስኩ ጊዜ ሣራ በሰባተኛ ወርዋ ልጅን ታገኛለች።
የዚህም አባት ተጋድሎው ትሩፋቱ ርኅራኄው ጽድቁም ብዙ ነው ሁል ጊዜ እንግዳ ካላገኘ በቀር በማዕዱ አብሮት ካልተቀመጠ አይበላም ነበር ስለዚህም ልዩ ሦስቱ አካላት በማዕዱ እንዲቀመጡ የተገባው ሆነ። አብርሃምም ከዚያ ተነሥቶ ወደ አዜብ ምድር ሔደ በሱሬና በቃዴስ መካከልም ኖረ በጌራራም ተቀመጠ።
አብርሃምም ሚስቱ ሣራን እኃቴ ናት አላቸው አቤሜሌክም ልኮ ሣራን ወሰዳት። በዚያችም ሌሊት አቤሜሌክ ተኝቶ ሳለ እግዚአብሔር ወደ አቤሜሌክ ገባ በሕልም እንዲህ አለው እሷ የጎልማሳ ሚስት ናትና ስለዚች ስለወሰድካት ሴት እነሆ አንተ ትሞታለህ።
አቤሜሌክ ግን አልነካትም ነበር አቤሜሌክም እንዲህ አለ በውኑ ያላወቀ ሰውን ታጠፋለህን እሱ እኅቴ ናት አለኝ እሷም ወንድሜ ነው አለችኝ ይህንንም ሥራ በንጹህ ልቤ በንጹሕ እጄ አደረግሁት።
እግዚአብሔርም በሕልም እንዲህ አለው እኔም በየዋህነትህ እንዳደረግከው አውቄአለሁና ራራሁልህ ኃጢአትም እንዳትሠራ ጠበቅሁህ ስለዚህም እንድትቀርባት አልተውኩህም ።
አሁንም ለዚያ ሰው ሚስቱን መልስለት ነቢይ ነውና ስለ አንተ ይፀልይልህ አንተም ትድናለህ ባትመልስለት ግን አንተ ሞትን እንድትሞት ያንተ የሆነው ሁሉ እንዲጠፋ ዕወቅ።አቤሜሌክም አብርሃምን ጠርቶ ይህ በእኔና በመንግሥቴ ላይ ያደረግከው ምንድር ነው ማንም የማይሠራው ታላቅ ኃጢአት ነው ይህንንስ ያደረግህ ምን አይተህ ነው አለው።
አብርሃምም እንዲህ አለ ምናልባት በዚህ ቦታ እግዚአብሔርን መፍራት የለምና ስለሚስቴ ይገድሉኛል ብዬ ነው።ዳግመኛም በእውነት ከእናቴ ያይደለች ከአባቴ ወገን የሆነች እኅቴ ናት ሚስትም ሆነችኝ እግዚአብሔርም ከአባቴ ቤት ባወጣኝ ጊዜ ይህንን በጎ ሥራ አድርጊልኝ በገባንበትም ቦታ ሁሉ ወንድሜ ነው በዬ አልኋት።
አቤሜሌክም ሺህ ምዝምዝ ብርን ሴቶች አገልጋዮችን ወንዶች አገልጋዮችን ላሞችና በጎችንም አምጥቶ ለአብርሃም ሰጠው ሚስቱ ሣራንም መለሰለት።
አብርሃምም ወደ እግዚአብሔር ለመነ እግዚአብሔርም አቤሜሌክን ፈወሰው ሚስቱንም ባሮቹንና ቤተ ሰቦቹንም ልጆቹንም ሁሉም ወለዱ ስለ አብርሃም ሚስት ስለሣራ እግዚአብሔር ማሕፀንን ሁሉ በአፍአ በውስጥ ዘግቶ ነበርና።
Bete Abrham ን አየት አድርት።ጀሞ ደብረሰላም መድሐኔዓለም ቤተክርስቲያን ዘወትር የምሳ መርሃግብር በቀን ለመቶ ሃያ ነዳያን ይከናወናል ።የአንድ ምሳ ዋጋ 60 ብር ነው ።የቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች እሰኪ እንያችሁ።
Читать полностью…ምእመናን ሆይ
ወታደሩ ቆራጥ እንዲሆን በወገቡ ይታጠቃል
ዝናር ይታጠቃል
✅ ይሔ መታጠቂያ ምንድን ነው ?
እውነት
እንድትጨክኑ የሚያደረጋችሁ እውነት ነው
ዋጋ ለመክፈል የሚያዘጋጃችሁ እውነት ነው
ሁልጊዜ በስፍራችሁ እንድትገኙ የሚያደረጋችሁ እውነት ነው
✅ ስለዚህ መታጠቅ ያስፈልጋል ምንን ? እውነትን
እንደገለባ ላለመቅለጥ
እንደተልባ ሥፍር ላለመንሸራተት
እንደጉም ሥፍር ላለመሆን
እዉነትን መታጠቅ ያስፈልጋል ።
እውነተኞች እንድንሆን ጌታ መድኃኔ አለም ይርዳን🙏
ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ
እንኳን ለቅዱስ ማርቆስ ወኔጌላዊ ወርሃዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን !!!
"... ወደ ከተማ ሂዱ፥ ማድጋ ውኃ የተሸከመ ሰውም ይገናኛችኋል፤ ተከተሉት፥ የሚገባበትንም የቤቱን ጌታ። መምህሩ። ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት የእንግዳ ቤት ወዴት ነው? ይላል በሉት።"
ማር. ፲፬፥፲፫-፲፬ /14፥13-14/
✝️ ቅዱስ ማርቆስ በመልካም ቤተሰብ ውስጥ አደገ፤ ገና በልጅነቱም የላቲን፣ የእብራይስጥና የግሪክ ቋንቋዎችን ተማረ
✝️ ጌታችንም በኢየሩሳሌም እየተዘዋወረ በሚያስተምርበት ጊዜ ቅዱስ ማርቆስ ታዳጊ ወጣት ነበረ
✝️ ጌታችን ሞትን ድል አድርጎ ከተነሳ በኋላ ሐዋርያትን ወደተለያዩ ሀገራትወንጌልን ያስተምሩ ዘንድ ሲልክ ቅዱስ ማርቆስ በመጀመሪያ ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር ቀጥሎም ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ተጉዟል
✝️ ከእነርሱም የማስተማርን ጥበብ ቀሰመ፣ ብቻውንም ወንጌልን ሊሰብክ ወደ እስክንድርያ ሄደ
✝️ ቅዱስ ማርቆስ በእስክንድርያ ክርስትናን ከሰበከ ብዙ ክርስቲያኖችን ካፈራ በኋላ ቤተክርስቲያንን ተከለ
✝️ በዚህ የተበሳጩ ጣኦት አምላኪዎች በሚያዚያ ፴ ቀን ብዙ አሰቃይተውት መስዋዕትነትን ተቀበለ
የቅዱስ ማርቆስ ምልጃና በረከት ከእኛ ጋር ይሁን። በጸሎቱ ያስበን።
#አንዲት_ሐይማኖት_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ
#አንዲት_ቤተክርስቲያን
#አንዲት_ጥምቀት
#ተዋህዶ
#orthodoxchurch
#ኢትዮጵያ
#ነሐሴ_29
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ነሐሴ ሃያ ዘጠኝ በዚህች ቀን #የአባ_ዮሐንስ_ሐጺር ወደ አስቄጥስ ገዳም የሥጋው ፍልሰት ሆነ፣ #ቅዱስ_አትናቴዎስ #ገርሲሞስና_ቴዎዶጦስ ከሚባሉ ሁለት አገልጋዮቹ ጋር በሰማዕትነት አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባ_ዮሐንስ_ሐጺር
ነሐሴ ሃያ ዘጠኝ በዚህች ቀን የአባ ዮሐንስ ሐጺር ወደ አስቄጥስ ገዳም የሥጋው ፍልሰት ሆነ። ይህም የአባ እንጦንዮስ በሆነ በቊልዝም ገዳም ከአረፈ በኋላ ነው። ለእስክንድርያ አባ ዮሐንስ ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ ስምንተኛ የሆነ ነው። እርሱም ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ የከበሩ መነኰሳትም እንዲህ አሉት የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ሥጋ በዚህ በቤተ ክርስቲያኑ ቢሆን እኛም ሥጋው በአለበት ለፈጣሪያችን እግዚአብሔር እንሰግድ ዘንድ እንሻ ነበር።
ያን ጊዜ የእግዚአብሔር ቸርነት አነሣሣችውና ስሙ ቆዝሞስ ለሚባል ለአንድ አበ ምኔት መልእክትን ጻፈ ከእርሱም ጋር የቊልዝም አገር የሆነ አረጋዊ አለ በደረሱም ጊዜ በዚያን ሰዓት ሥጋውን መውሰድ አልተቻላቸውም። የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ሥጋ የኬልቄዶንን ጉባኤ በተቀበሉ መለካውያን ዘንድ ይጠበቅ ስለነበረ ነገር ግን ቦታውን አወቁ ተረዱ ወደ ቦታቸውም ተመልሰው ሃይማኖታቸው የቀና ምእመናን ሰዎችን አገኙ እነርሱም በዚያች አገር የሚኖሩ ናቸው ስለርሱ የመጡበትን ነገሩአቸው።
ከጥቂት ቀኖች በኋላም ከታላላቅ ዐረቦች ወገን ለቊልዝም አገር መኰንን ተሾመ እርሱም ለኤጲስቆጶስ አባ ሚካኤል ወዳጁ ነው ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሐንስም ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ሥጋ ወደ ኤጲስቆጶሱ መልእክትን ጻፈ። በመልእክቱም የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርን ሥጋ ከከሐድያን መለካውያን እጅ እስከ አፈለሱት ድረስ መልእክተኞች አእሩግ መነኰሳትን ምክንያት ፈልጎ እንዲረዳቸው በማሳሰብ አዘዘው።
ኤጲስቆጶሱም በሰማ ጊዜ ፈጽሞ ደስ አለው ሒዶም ወዳጁ ለሆነ ለመኰንኑ ጸሐፊ ነገረው። ጸሐፊውም ለመኰንኑ ነገረው። እነሆ መኰንኑም ከመነኰሳቱ ጋራ ሔደ ጸሐፊውም መነኰሳቱ ወደዚያ ቦታ እንዲገቡ ምክንያት እንዴት እናገኛለን አለ።መኰንኑም በልብሶቻቸው ላይ የዓረቦችን ልብሶች ያልብሱአቸውና ከእኔ ጋራ ወደዚያ ቦታ ይምጡ አለ እንዲሁም እንዳላቸው አደረጉ።
ከዚህም በኋላ መኰንኑ ሔደ ከእርሱም ጋራ ብዙ ፈረሰኞች ሰዎች ብዙ ሕዝብም የአስቄጥስ ገዳም የከበሩ አረጋውያን አሉ ወደቊልዝም ገዳምም ደረሱ። መኰንኑም በዚያ የሚኖራውን የመለካውያን ኤጲስቆጶስ እንዲህ ብሎ አዘዘው ያንተን ሰዎች ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ አስወጣቸው በዚች ሌሊት እኔ በውስጧ አድራለሁና ያ መለካዊም መኰንኑ እንዳዘዘው አደረገ።
መነኰሳቱም እንስሶቻቸውን ከከተማ ውጭ አዘጋጅተው በሌሊት ወደዚያ ገብተው የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርን ሥጋ ይዘው ወደ ምስር ደረሱ ከዚያም ወደ አስቄጥስ ገዳም ደረሱ የአባ መቃርስ ገዳም መነኰሳትም መስቀሎችን፣ ወንጌሎችን፣ ማዕጠንቶችንና መብራቶችን በመያዝ እየዘመሩና እያመሰገኑ ተቀበሏቸው ወደ አባት መቃርስ ሥጋም አቀረቡትና ከእርሱ ተባረኩ በላዩም ብዙ ሽቱዎችን ነሰነሱ የቊርባን ቅዳሴንም ቀደሱ የከበረ ወንጌልም በሚነበብ ጊዜ ታላቅ ድንቅ ተአምር ተገለጠ ቤተ ክርስቲያኒቱ ሁለመናዋ በሰማያዊ ብርሃን በራች። ከቶ እንደርሱ ሆኖ የማያውቅ በጎ መዓዛ ሸተተ ታላቅ ደስታም ሆነ በዚያም ቦታ ሰባት ቀን ኖረ።
ከዚህም በኋላ ወደ ራሱ ቤተ ክርስቲያን ተሸክመው ወሰዱት ዕብራውያንም በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እያሉ መድኃኒታችንን እንደተቀበሉት ልጆቹ መነኰሳት ተቀበሉትና ወደ ቦታው አኖሩት ከእርሱም ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ።
ከዚህም በኋላ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሊቀ ጳጳሳት አባ ማርቆስ በወጣ ጊዜ ወደ አባ ዮሐንስ ሐጺር ቤተ ክርስቲያን ገባ። ከእርሱም ጋር ብዙዎች ኤጲስቆጶሳትና የእስክንድርያ አገር ታላላቆች ከግብጽ አገር ሁሉ አሉ። የአባ ዮሐንስ ሐጺር ሥጋ የተጠቀለለበትን ሰሌን ገልጦ ከእርሱ ተባረከ መሪር ልቅሶንም አለቀሰ ያን ጊዜ ሥጋው ሲገለጥ መብረቅና ነጐድጓድ ሆነ።በቤተ ክርስቲያኑም ውስጥ ያሉት ሁሉም ደንግጠው ወደቁ ሊቀ ጳጳሳቱም ሰሌኑን መልሶ በፍጥነት ሥጋውን ጠቀለለ በሽብሸባ እየዘመሩና እያመሰገኑ እንደቀድሞው ሸፈነው።
ከዚህም በኋላ ዳግመኛ እንዲህ እያሉ ሊያመሰግኑ ጀመሩ ፈጣን ደመና ሁነህ የመንፈስ ቅዱስን ዝናም የተሸከምክ ሠለስቱ ደቂቅ ወዳሉበት ወደ ባቢሎን የሔድክ በላይህ በአደረ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ወደ እስከንድርያ አገር የተመለስክ ሁለተኛም ወደ ቊልዝም የሔድክ የጣዖታትን ቤቶች አፍርሰህ ሃይማኖትን የሰበክ በሽተኞችን የፈወስክ አጋንንትን ያስወጣህ ወደርስትህም የተመለስክ አንተ የበረከት ማደሪያ ነህና። የአባ ዮሐንስ ሐጺር የሥጋው ፍልሰት ከንጹሐን ሰማዕታት ዘመን በአምስት መቶ ሃያ ዓመት ሆነ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አትናቴዎስ_ሰማዕት
በዚህችም ቀን ኤጲስቆጶስ አትናቴዎስ በሰማዕትነት ሞተ ከእርሱም ጋር ስማቸው ገርሲሞስና ቴዎዶጦስ የሚባል ሁለት አገልጋዮች በሰማዕትነት አረፉ።
ይህንንም ቅዱስ አትናቴዎስን የእንጦኒቆስን የጭፍራ አለቃውን ልጅ እርሱ እንዳጠመቃት በንጉሥ ዘንድ ወነጀሉትና ንጉሥ አርስያኖስ ያዘው እርሱም ክርስቲያን እንደሆነ ታመነ ብዙ ሥቃይንም አሠቃየው።
በሃይማኖቱም ጸና እንጂ ሃይማኖቱን ባልካደ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ እንዲሁም እሊህን ሁለቱን አገልጋዮች ገርሲሞስንና ቴዎዶጦስን በግርፋትና በስቅላት ከቀጣቸው በኋላ ራሶቻቸውን በሰይፍ አስቆረጠ ሦስቱም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ።
አማንያን ሰዎችም መጡ ለወታደሮችም ገንዘብ ሰጥተው የቅዱሳኑን ሥጋቸውን ወሰዱ በአማሩ ልብሶችም ገንዘው በሣጥን ውስጥ አኖሩአቸው ከሥጋቸውም ታላላቅ ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ)
ምእመናን ሆይ
የሰዉ ልጅ የሚያንቀሳቅሰው የሚያራምደው ሞተሩ ተስፋ ነው
ያለምግብ 40 ቀን መኖር ይቻላል።
ያለ ውሀ 7ት ቀን
ያለ ዕንቅልፍ 4ት ቀን
ያለ ዓየር 4ት ደቂቃ
ያለ ተስፋ ግን 1 ሰከንድ መኖር አንችልም
ስለዚህ በተስፋ ደስ ይበላችሁ ።
ተስፋ እንደሌላቸው
አምላክ እንደሌላቸው አንሁን
እንደዛ ተስፋ እንደሌላቸው እንዳንሆን ክርስቶስ ይርዳን🙏
ሰላም የቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች ይህ ☝☝☝ መንፈሳዊ ዩቱብ ቻናል ነው ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩን
ለመንፈሳዊ ቻናሎች ያለንን አመለካከት እንቀይር!!!
ምእመናን ሆይ
"ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ድንጋይ ሆነ"
✅ ግንበኞች አይሁድ ክርስቶስን ይንቁት ነበረ
የፀራቢው ልጅ እያሉ
የዮሴፍ ልጅ እያሉ
እርሱ ግን ለዓለም ለቤተክርስቲያን
ለትዳራችን ለህይወታችን ምን ሆነ?
ራስ ሆነ
✅ አወ
ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ድንጋይ ሆነ
አያችሁ እግዚአብሔር ስራው ይሄው ነው
በተናቁ ነገሮች ነው ራሱን ሚገልፀው
የመድኃኔአለም ስሙ የተመሰገነ ይሁን🙏
t.me/Tomarket_ai_bot/app?startapp=r-0001fuk3
I scored 174 points in Tomato Game!
I dare you to challenge me!
Farm 🍅 $TOMATO with me and secure your token allocation through Tomarket.ai.
Use my link to get 2,000 🍅 $TOMATO!
ከዚህም በኃላ በጎ ተጋድሎውን ፈጽሞ እግዚአብሔርንም አገልገሎ በመቶ ሰባ አምስት ዕድሜው ወደ ወደደው እግዚአብሔር ሔደ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ይስሐቅ
በዚህችም ቀን ዳግመኛ የአባቶች አለቃ ለሆነ ለአብርሃም ልጅ ለይስሐቅ የዕረፍቱን መታሰቢያ እንድናደርግ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን መምህራን አባቶቻችን አዘዙን።ይህ ጻድቅ ይስሐቅም በልዑል አምላክ ብሥራት ተወለደ።
ይህንንም ንጹሕ ይስሐቅን እግዚአብሔር ለልጁ ክርስቶስ ምሳሌው አደረገው።አብርሃምን እንዲህ ብሎታልና የምትወደው ልጅህ ይስሐቅን ከአንተ ጋራ ውሰደውና ወደላይኛው ተራራ ሒደረ እኔ ወደ እምነግርህ ወደ አንዱ ተራራ ላይ አውጥተህ በዚያ ሠዋው።
አብርሃምም በጥዋት ተነሥቶ አህያውን ጫነ ልጁ ይስሐቅንና ሁለቱ ብላቴኖቹንም ወሰደ ለመሥዋዕትም ዕንጨትን ፈልጦ አሸክሞ ሔደ።በሦስተኛም ቀን እግዚአብሔር ወዳለው ወደዚያ ቦታ ደረሰ አብርሃምም በዐይኑ ቃኘ ቦታውንም ከሩቅ አየ።
አብርሃምም ብላቴኖቹን እናንተ አህያውን ይዛችሁ ከዚህ ቆዮ እኔና ልጄ ግን ወደ ተራራ እንሔዳለን ሰግደንም ወደእናንተ እንመለሳለን አላቸው። አብርሃምም መሥዋዕት የሙቃጠልበትን ዕንጨት አምጥቶ ለልጁ ለይስሐቅ አሸከመው እሱም ወቅለምቱንና እሳቱን በጁ ያዘ ሁለቱም በአንድነት ሔዱ።
ይስሐቅም አባቱ አብርሃምን አባ አለው እርሱም ልጄ ምነው አለው እነሆ እሳትና እንጨት አለ መሥዋዕት የሚሆነው በጉ ወዴት ነው አለው አብርሃምም መሥዋዕት የሚሆነውን በግ እግዚአብሔር ያዘጋጃል አለው።
አብረውም ሔደው እግዚአብሔር ወዳለው ወደዚያ ቦታ ደረሱ አብርሃምም በዚያ መሠዊያን ሠራ ዕንጨቱን ደረደረ ልጁ ይስሐቅንም አሥሮ ጠልፎ በመሠዊያው በዕንጨቱ ላይ በልቡ አስተኛው። አብርሃምም ልጁን ያርደው ዘንድ እጁን ዘርግቶ ወቅለምቱን አነሣ።
እግዚአብሔርም አብርሃምን አብርሃም አብርሃም ብሎ ጠራው እርሱም አቤት አለ በልጅህ ላይ እጅህን አትዘርጋ ምንም ምን አታድርግበት አንተ እግዚአብሔርን እንደምትፈራው አሁን አወቅሁ ለምትወደው ለልጅህ አልራራህለትምና አለው።
አብርሃምም በተመለከተ ጊዜ ቀንድና ቀንዱ በዕፀ ሳቤቅ የተያዘ አንድ በግ አየ አብርሃምም ሔደና ወስዶ በልጁ በይስሐቅ ፈንታ ሠዋው። ይህም ንጹህ ይስሐቅ ጎልማሳ ሲሆን አባቱ ሊሠዋው በአቀረበው ጊዜ እግዚአብሔር በበግ እስከ አዳነው ድረስ ለአባቱ በመገዛት ለመታረድ አንገቱን ዘርግቶ ሰጠ።
እርሱም በአባቱ በአብርሃም ሕሊና ፍጽም መሥዋዕተረ ሆነ። ከዚህም በኃላ ይስሐቅን መቸገርና ስደት አግኝቶታል በአባቱ በአብርሃም ዘመን ከሆነው ሌላ በሀገር ረኃብ ሁኖ ነበርና የፍልስጥዔም ንጉሥ አቤሜሌክ ወዳለበት።ወደ ጌራራ ይስሐቅ ሔዶ በዚያ ተቀመጠ።
የአገር ሰዎችም ይስሐቅን የሚስቱን የርብቃን ነገር ጠየቁት እርሱም እኅቴ ናት አላቸው ስለ ሚስቱ ስለ ርብቃ የዚያች አገር ሰዎች እንዳይገድሉት ሚስቴ ናት ብሎ መናገርን ፈርቷልና መልከ መልካም ነበረችና። በዚያም ብዙ ዘመን ኖሩ አቤሜሌክም በመስኮት በተመለከተ ጊዜ ይስሐቅን ከርብቃ ጋር ሲጫወት አየው።
አቤሜሌክም ይስሐቅን ጠርቶ እኅቴ ናት አልከኝ እንጂ እነሆ ሚስትህ ናት አለው ይስሐቅም በርሷ ምክንያት ይገድሉኛል ብዬ ነው አለው። አቤሜሌክም ይህ ያደረግኽብኝ ነገር ምንድን ነው ከዘመዶቼ የሚሆን አንድ ሰው ከሚስትህ ጋር ሊተኛ ጥቂት ቀርቶት ነበር ባለማወቅም ኃጢአትን ልታመጣብኝ ነበር።
ንጉሡም የዚህን ሰው ሚስቱን የነካ ሁሉ ፍርዱ ይሙት በቃ ነው ብሎ ሕዝቡን አዘዛቸው። ይስሐቅም በዚያች ምድር ዘርን ዘራ መቶ ዕጽፍም ሆነለት እግዚአብሔርም ባረከው ከፍ ከፍም አለ እጅግም ገነነ ወንድ ባርያን ሴት ባርያን ላምን በግን አብዝቶ ገዛ የፍልስጥኤም ሰዎችም ቀኑበት።
በአባቱም ዘመን የአብርሃም ብላቴኖች የቆፈሩአቸውን ጉድጓዶች የፍልስጥኤም ሰዎች ደፈኑዋቸው አፈርንም መሏቸው።አቤሜሌክም ይስሐቅን ፈጽመህ በርትተህብናልና ከእኛ ተለይተህ ሒድ አለው።
ይስሐቅም ከዚያ ተነሥቶ በጌራራ ሸለቆ ሰፍሮ በዚያ ተቀመጠ። ይስሐቅም ያባቱ አገልጋዮች የቆፈሩዋቸውን አባቱ አብርሃምም ከሞተ በኃላ የፍልስጥኤም ሰዎች የደፈኗቸውን የውኃ ጉድጓዶች እንደገና ቆፈራቸው አብርሃም እንደጠራቸው ጠራቸው።
የይስሐቅም አገልጋዮች በጌራራ ቆላ ጉድጓድ ቆፍረው የሚጣፍጥ የውኃ ምንጭ አገኙ የይስሐቅ እረኞችና የጌራራ እረኞች ይህ ውኃ የኛ ነው የኛ ነው በማለት ተጣሉ ያችንም የውኃ ጉድጓድ የዓመፅ ጉድጓድ ብሎ ጠራት ዐምፀውበታልና።
ይስሐቅም ከዚያ ተጎዞ ሒዶ በዚያ ሌላ ጉድጓድ ቁፈረ በርሷም ምክንያት ተጣሉት ስሟንም ጠብ ብሎ ምክንያት ተጣሉት ስሟንም ጠብ ብሎ ጠራት።ከዚያም ተጎዞ ሒዶ ሌላ ጉድጓድን ቁፈረ በርሱም ምክንያት ግን አልተጣሉትም ስሙንም ሰፊ አለው ዛሬ እግዚአብሔር አሰፋልን በምድርም አበዛን ሲል።
ከዚህም በኃላ ሁለት ልጆችን ኤሳውንና ያዕቆብን ወለደ። ይስሐቅም ኤሳውን ጽኑዕ ኃይለኛ ስለሆነ ይወደዋል።ይስሐቅም አርጅቶ ዐይኖቹ ፈዘው የማያይ ከሆነ በኃላ እንዲህ ሆነ ታላቁ ልጁ ኤሳውን ጠርቶ እነሆ አረጀሁ የምሞትበትንም ቀን አላውቅም ማዳኛ መሣሪያህን የፍላፃ መንደፊያህን ይዘህ ወደ በረሃ ውጣ።ሳልሞት ነፍሴ እንድትመርቅህ እበላ ዘንድ እንደምወደው አድርገህ አምጣልኝ አለው።
ርብቃም ልጁ ኤሳውን እንዲህ ሲለው ይስሐቅን ሰማችው ኤሳውም ወደ አደን ሔደ።ርብቃም ታናሹ ልጇ ያዕቆብን እንዲህ አለችው እነሆ አባትህ ወንድምህን ኤሳውን ሳልሞት በእግዚአብሔር ፊት እንድመርቅህ ከአደንከው አዘጋጅተህ የምበላውን አምጣልኝ ሲለው ሰምቼዋለሁ።
አሁንም ልጄ ሆይ በማዝህ ነገር እሽ በለኝ ወደ በጎቻችንም ሒደህ ያማሩ ሁለት ጠቦቶችን አምጣልኝና አባትህ እንደሚወደው አዘጋጃቸው ዘንድ ሳይሞት በልቶ እንዲመርቅህ ወስደህ ለአባትህ እንድትሰጠው አለችው።
ያዕቆብም እናቱ ርብቃን እንዲህ አላት እነሆ ወንድሜ ኤሳው ጠጉራም ነው እኔ ግን ጠጉራም አይደለሁም ምናልባት አባቴ ቢዳስሰኝ በፊቱ እንደምዘብትበት እሆናለሁና ምርቃን ያይደለ በላዬ መርገምን አመጣለሁ።
እናቱም ልጄ ሆይ መርገምህ በእኔ ይሁን ቃሌን ብቻ ስማኝ ሒድና የምልህን አምጣልኝ አለችው ሒዶም ለእናቱ አመጣላትና አባቱእንደሚወደው አድርጋ መብሉን አዘጋጀች።
ርብቃም ከርሷ ዘንድ የነበረ ያማረውን የታላቅ ልጅዋ የኤሳውን ልብስ አምጥታ ለታናሽ ልጅዋ ለያዕቆብ አለበሰችው ያንንም የሁለቱን ጠቦቶች ለምድ በትከሻውና በአንገቱ ላይ አደረገች ያንን ያዘጋጀችውን እንጀራና ጣፋጭ መብልን ለያዕቆብ በእጁ ሰጠችው።
ወደ አባቱ ገብቶ አባቴ ሆይ አለው አባቱም እነሆኝ ልጄ ሆይ አንተ ማነህ አለው ያዕቆብም እኔ የበኩር ልጅህ ኤሳው ነኝ ያልከኝን አዘጋጅቻለሁ ተነሥና ተቀመጥ ከአደንኩልህም ብላና ነፍስህ ትመርቀኝ ዘንድ አለው።
ይስሐቅም ልጁን ልጄ ሆይ ፈጥነህ ያገኘህ ይህ ምንድነው አለው እርሱም ፈጣሪህ እግዚአብሔር በፊቴ የሰጠኝ ነው አለው። ይስሐቅም ልጄ ቅረበኝ ልዳሥሥህ አንተ ኤሳው እንደሆንክ ወይም እንዳልሆንክ አለው በቀረበም ጊዜ ዳሠሰውም ቃልህ የያዕቆብ እጆችህ አድነህ ያመጣህልኝን በልቼ ነፍሴ ትመርቅህ ዘንድ አምጣልኝ አለው አቅርቦለት በላ ወይንም አመጣለት ጠጣ።
ይስሐቅም ልጄ ቅረበኝና ሳመኝ አለው ቀርቦም ሳመው የልብሱን ሽታ አሸተተው እነሆ የልጄ ልብስ ሽታው እግዚአብሔር እንደባረከው እንደዱር አበባ ሽታ ነው አለ።
🔑 ከዚ በተጨማሪም ይፋዊ ግሩፖቻችን ላይ እስከ 100ሺ ብር ማሸነፍ ይችላሉ ‼️
1⃣ መጀመሪያ 100 ሰው በላይ ወደ ትክክለኛ ግሩፓችን አድ ያድርጉ!!
✨ ግሩፕ አንድ/Group one
🟩 ቀጥለው አንድ ሰው በጋበዙ ቁጥር 100 ብር አካውንትዎ ላይ ይጨመርልዎታል። 30 ሰዎችን ጋብዘው ጠቅላላ ሂሳብዎ 5,000 ብር ሲደርስ በፈለጉ አካውንት ወጪ ማድረግ ይችላሉ።
✨ ከስር የርስዎን የመጋበዣ መልዕክት ለወዳጆችዎ በመላክና በቴሌግራም እና በፌስቡክ ግሩፖች ሼር ና አድ በማድረግ ይሸለሙ ‼️
🎊 ቦነስዎን ለመውሰድ ይፋዊ ግሩፓችን ላይ ከ 100 ሰው በላይ አድ ማድረግ ይኖርብዎታል!!
👉 ግሩፕ ሁለት /Group two
👥 የርስዎ መጋበዣ ሊንክ
/channel/safaricom_mpesa1_bot?start=r05791049895
ምእመናን ሆይ
ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ይላል።
"በአለም ሳለሁ የዓለም ብርሃን ነኝ"
✅ በአለም ትላልቅ ብርሃናት አሉ
የፀሃይ ብርሃን አለ
የጨረቃ ብርሃን አለ
የከዋክብት ብርሃን አሉ
✅ እነዚህ ሁሉ ግን
የፍቅር ብርሃን አይደሉም
የሰላም ብርሃን አይደሉም
የዕውቀት የመፅናናት ብርሃን አይደሉም
✅ እግዚአብሔር ግን እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ ሲል
የፍቅር ብርሃን ነኝ
የሰላም ብርሃን ነኝ
የዕውቀት የመፅናናት ብርሃን ነኝ ማለቱ ነው።
✅ ዛሬ ብዙ ሰዎች የሚያለቅሱት ለምን ይመስላችኋል ?
በዚህ ብርሃን ስለማይኖሩ ነው
ፀሐይን ተስፋ ያደረጉ ያፍራሉ
መቅረዝንም የሚለኩሱ ይደነግጣሉ
✅ እግዚአብሔር ግን
ህልፈት የሌለበት ብርሃን
ጉድለት የሌለበት ብርሃን
ጥላ የሌለበት ብርሃን
ግርዶሽ የሌለበት ብርሃን ነው።
ብርሃን የሆነው አምላክ ጨለማ ህይወታችንን ይለውጥልን🙏