ያለፈው ዘመኔን ሳስብ በእውነት እጅግ አፍራለሁ
ድርሻየን ካንተ ወስጀ በብዙ አባክኛለሁ
ይሞላል ልቤ በፀፀት ድካሜን አስታውስና
ምህረትህ ያበረተኛል ትላንትን እረሳውና(፪)
ያለፈው ዘመኔ ይብቃ
ጌታ ሆይ አድርገኝ ምርጥ እቃ
አልወጣ ከፍቅር እጅ
ሳመልክህ ልኑር ከደጅ
መስከረም 12/2017 #መልአኩ_ቅዱስ_ሚካኤል
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስን_ክርስቶስን በመልአኩ ስም ለምናመሰግንበት ለመልአኩ #ቅዱስ_ሚካኤል ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉መስከረም ዐሥራ ሁለት በዚች ቀን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው በዚችም ቀን ክብር ይግባውና #እግዚአብሔር ወደ አሞፅ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳይያስ ላከው
👉ይቅርም ብሎት ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሕዝቅያስ ሒዶ #እግዚአብሔር ይቅር እንዳለውና ከደዌው እንዳዳነው በዕድሜውም ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እንደ ጨመረለት ይነግረው ዘንድ አዘዘው ንጉሱም ሚስት አግብቶ ምናሴን እስከወለደው ድረስ እንዲሁ ሆነ
👉ሊቀ መላእክት #ቅዱስ_ሚካኤል ለንጉሥ ሕዝቅያስ ያደረገለት ተአምር ከጻድቁ ንጉሥ ከቅዱስ ዳዊት በኋላ በእስራኤል እንደ ሕዝቅያስ ያለ ሌላ ጻድቅ ንጉሥ አልተነሣም ከሕዝቅያስ በኋላ የተነሡት ሁሉም ጣዖትን አምልከዋል ለጣዖታቱም የሚሆን መሠዊያ ሠርተዋል
👉ንጉሡ ሕዝቅያስ በነገሠ ጊዜ ግን ጣዖታትን ሰባብሯቸዋል የእስራኤል ልጆች ያመልኩት የነበረውን የነሐስ እባብ ቆራርጦታል #እግዚአብሔርንም በማመኑ መንግሥቱ እጅግ ሰምሮለታል እግዚአብሔርም ያሳጣው በጎ ነገርም የለም
👉ሕዝቅያስ በነገሠ በ14ኛው ዘመን የፋርሱ ነጉሥ ሰናክሬም መጥቶ #ኢየሩሳሌምን ከበባት ይህም ሰናክሬም በወቅቱ እንደ እርሱ ያለ ኃይለኛ የለም ነበርና ሁሉም የምድር ነገሥታት ይፈሩትና ይገዙለት ነበር
👉ሕዝቅያስም ከሰናክሬም ግርማና የጦሩ ብዛት የተነሣ ፈርቶ ኢየሩሳሌምን እንዳያጠፋት ብዙ ወርቅና ብር እጅ መንሻ ቢልክለትም ሰናክሬም ግን እጅ መንሻውን አልቀበልም ብሎ ኢየሩሳሌምን ያጠፋ ዘንድ ተነሣ ለሕዝቅያስም አምላካችሁ #እግዚአብሔር ከእኔ እጅ ሊያደናችሁ ከቶ አይችልም የሚል የስድብን ቃል ላከለት
👉ሁለተኛም #በልዑል_እግዚአብሔር ላይ የስድብን ቃል ጽፎ ደብዳቤ ላከለት ሕዝቅያስም ይህን ሲሰማ ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ አለቀሰ ልብሱንም ቀዶ ማቅ በመልበስ የሰናክሬምን ድፍረትና በኢየሩሳሌምና በሕዝቧ ላይ ሊያደርስ ያሰበውንም ጥፋት ወደ #እግዚአብሔር አሳሰበ ቀጥሎም ሕዝቅያስ ሰናክሬም የተናገረውን ይነግሩት ዘንድ ስለ ሕዝቡም እንዲፀልይ ለነቢዩ ኢሳይያስ መልእክት ላከበት #ነቢዩ_ኢሳያስም ወደ እግዚአብሔር አመለከተ
👉ከዚህም በኋላ #ቅዱስ_ሚካኤል ስለ ንጉሡ ለነቢዩ መልእክትን አመጣለት ነቢዩ ኢሳይያስም የመጣለትን መልስ እንዲህ ብሎ ለሕዝቅያስ ላከለት ልብህን አፅና አትፍራ በዓለሙ ሁሉ እንደ እርሱ ያለ ያልተሰማ ዕፁብ ድንቅ የሆነ ሥራ በሰናክሬም ላይ #እግዚአብሔር ይሠራል አለው
👉ከዚያም መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል #ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ መጥቶ 185,000 (መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ) የፋርስ ሠራዊቶችን በአንድ ሌሊት ገደላቸው 2ኛ ነገ.17፥19 የለኪሶ ሰዎችም ሲነጋ በተነሡ ጊዜ ምድሪቱን በእሬሳ ተሞልታ ስላገኟት በድንጋጤና በፍርሃት ከንጉሣቸዉ ጋር ሸሽተው ነነዌ አገር ገቡ
👉ንጉሡ ሰናክሬምም ወደ አምላኩ ወደ ጣዖቱ ቤት ገብቶ ሲፀልይ የገዛ ልጆቹ በሰይፍ መትተው ገደሉትና ወደ አራራት ኩበለሉ 2ኛነገ.ምዕራፍ 19 ንጉሥ ሕዝቅያስም ከሰናክሬም እጅ ያዳነውን #እግዚአብሔርን አመሰገነ
👉ከዚህም በኋላ ሕዝቅያስ ታሞ ለሞት በደረሰ ጊዜ ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ እርሱ መጥቶ #እግዚአብሔር ትሞታለህ እንጂ አትድንም ብሎሃል አለው ነገር ግን ሕዝቅያስ አሁንም ልብሱንም ቀዶ ማቅ በመልበስ ፀሎቱን ወደ #እግዚአብሔር አቀረበ
👉በዚህ ጊዜ ነው ቅዱስ ሚካኤል #ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ መጥቶ ነቢዩ ኢሳይያስን ወደ ንጉሡ ሕዝቅያስ ሄዶ በዕድሜው ላይ 15 ዓመት እንደተጨመረለት እንዲነግረው ያዘዘው
👉መልአኩ እንዳዘዘው ነቢዩ ኢሳያስ ንጉሥ ሕዝቅያስን #እግዚአብሔር የአባትህ የዳዊት አምላክ ፀሎትህን ሰማሁ ዕንባህንም አየሁ እነሆ እኔ አድንሃለሁ በዘመኖችህም 15 ዓመት ጨምሬልሃለሁ ከፋርስ ንጉሥ እጅም አድንሃለሁ ይህችን አገር ስለ እኔና ስለ ቧለሟሌ ዳዊት አጽንቼ እጠብቃታለሁ ብሎሃል ብሎ የተላከውን ነገረው
👉ከዚህም በኋላ ንጉሥ ሕዝቅያስ #የእግዚአብሔር ኃይል ስላደረበት የምድር ነገሥታት ሁሉ ፈርተውት እየተገዙለት እጅ መንሻን ያገቡለት ጀመር ንጉሡም ዕድሜው ከተጨመረለት በኋላ ሚስት አግብቶ ምናሴን እስኪወልድ ድረስ ቆየ በመንበረ መንግሥቱም 29 ዓመት ነግሦ ከኖረ በኋላ #እግዚአብሔርን አገልግሎ በሰላም ዐረፈ
👉የአምላካችን #የእግዚአብሔር ቸርነት የሊቀ መላእክት #የቅዱስ_ሚካኤል ጥበቃና ተራዳኢነት አይለየን ሀገራችንን ዳሯን እሳት መሐሏን ገነት አድርጎ ፈጣሬ አለማት አምላካችን #እግዚአብሔር ይጠብቅልን የተባረከ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ምእመናን ሆይ
ሌባ ከዘረፈ በኋላ ድፍትፍት ነው የሚያረገው ገንዘቡን ለምን
ምክንያቱም የራሱ ገንዘብ ስላልሆነ ነው
ነፍሳችን ህይወታችን በዲያቢሎስ እጅ ከሆነ
በዝሙት ፣ በእርኩስት፣ በዘፈን ፣ በበደል ፣ በኃጢአት ከሆነ
ያባክነናል ድፍትፍት ያደርገናል ምእምናን
የእግዚአብሔር ስንሆን ነው እሱ በክብር የሚይዘን
እሺ እድሜ ቢኖረን ሺውን ሙሉ
ለእግዚአብሔር ብንሰጠው ያንሳል
ህይወታችን በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ
ፈጣሪ አምላክ ይርዳን🙏
መስከረም 9/2017 #ፃድቁ_አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ #አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ወርሐዊ መታሰቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስ አባታቸው መልአከ ምክሩ እናታቸው ወለተ ማርያም ይባላሉ የተወለዱበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ነው
👉በተወለዱ ዕለት ተነሥተው በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ብለው #ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል የስማቸው ትርጓሜ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ አንድም #የክርስቶስ እስትንፋስ ማለት ነው
👉ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸውና በመንገዳቸው ሁሉ እየመራቸው ነው ያደጉት #መንፈስ_ቅዱስ ልቡናቸውን ብሩህ አድርጎላቸው በ5 ዓመታቸው የቅዱሳት መጻሕፍት ቃላትን፣ ብሉያትንና ሐዲሳትን፣ ድርሳናትንም ጠንቅቀው ዐውቀዋል
👉በተወለዱ በ14 ዓመታቸው ወደ #አቡነ_ኢየሱስ ሞዐ ደብረ ሐይቅ ገዳም ሄደው ከባሕር ዳር ቆመው የሙሴን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር በጸለዩ ጊዜ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ባሕሩን አሻግሯቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተዋል፡፡
👉ለ3 ዓመታት ያህል በኃይቅ ገዳም ለመነኮሳት እንጨት በመልቀምና ውሃን በመቅዳት #ለአባቶች_መነኮሳት ምግብ የሚሆናቸው ዓሣ ከባህር ውስጥ በማውጣት አገልግለዋል፡
👉አባታችን #እስትንፋሰ_ክርስቶስ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ከፆሙ በኋላ ምንም እህል ሳይቀምሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ ለሙሴ በደብረ ሲና እንደሰጠው ለአባታችንም ወደ እርሳቸው መጥቶ ዓሥሩን ቃላተ ኦሪትና ስድስቱን ቃላተ ወንጌል በውስጣቸው የተጻፈባቸው ሁለት ጽላቶችን ሰጥቷቸዋል፡፡
👉አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሠሩ በኋላ ዕለቱን ስንዴ ዘርተው፣ ወይን ተክለው፣ ጽድን ወይራንና ግራርን ተክለው በአንዲት ቀን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ዕለቱን አድርሰዋል ስንዴውን ለመሥዋዕት ወይኑን ለቍርባን በተአምራት አድርሰዋል፡፡
👉አባታችን በጸሎት ላይ እንዳሉ ቅዱስ ሚካኤል ተልኮ መጥቶ አባታችንን በደመና ጭኖ ወስዶ ከጌታችን ከመድኃኒታችን #ከኢየሱስ_ክርስቶስ ፊት አቆማቸው ጌታንም በቅዱሳኑ ሁሉ እንዲባረኩ ካደረጋቸው በኋላ መልአኩን ‹‹ወደ ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ ወደ ኢየሩሳሌም አድርሰው›› ብሎት ኢየሩሳሌምን አሳልሞ ሀገራችን መልሶ አምጥቷቸዋል
👉አባታችን ሁሉንም የኢትዮጵያን ቅዱሳት ገዳማትን ተዘዋውሮ ሲጎበኙ በሕይወተ ሥጋ የሌሉት የየገዳማቱ ቅዱሳን ሁሉ በአካል ይገለጡላቸው ነበር ጎጃም ውስጥ እያስተማሩ፣ !፣ የታመሙትን እየፈወሱ፣ የዕውራንን ዐይን እያበሩና ሙታንን እያሥነሱ ብዙ ካገለገሉ በኋላ ለዘጠኝ ዓመታት በባሕር ውስጥ ገብተው ቁልቁል ተዘቅዝቀው #ለኢትዮጵያ_ፀልየው የምሕረት ቃልኪዳን ተቀብለዋል
👉ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ጌታችን መጥቶ ‹‹ከመነኮሳት ሁሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ ሆይ #ኢትዮጵያንና_ሕዝቦቿን ምሬልሃለሁ ከዚህች ባሕር ውጣ በማለት በሞት የሚያርፉበትን ቦታ ነግሯቸዋል፡፡
👉ጻድቁ ወደ ደብረ አሰጋጅ በሚሄዱበት ጊዜ ጸሐይ ልትገባ ስትል ‹‹በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አውግዤሻለሁ ለመስፍን ኢያሱ በገባኦን እንደቆምሽ አሁንም ቀጥ ብለሽ ቁሚ ብለው ፀሐይን አቁመዋል አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስም ደብረ አሰጋጅ ሲደርሱ ፀሐይ አፍ አውጥታ ‹‹አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ እገባ ዘንድ ፍታኝ›› ስትላቸው #እግዚአብሔር_ይፍታሽ ባሏት ጊዜ ጠልቃለች
👉ጻድቁ ሌላው በእጅጉ የሚታወቁበት አንድ ትልቅ ቃል ኪዳን አላቸው በአምላክ ልቡና የሚገኝ፣ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ልቡና የሚገኝ፣ በቅዱስ ሚካኤልና በቅዱስ ገብርኤል ልቡና የሚገኝ እንደ #መልክአ_መድኃኔዓለም ያለች እጅግ አስገራሚ ፀሎት አለቻቸው፤ እርሷን ፀሎት በፀለዩ ጊዜ እልፍ ነፍሳትን ከሲኦል ያወጣሉ
👉ጸሎቷም #የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች እያንዳንዱ የሰውነት ክፍሎቹ የተቀበሉትን ጸዋትዎ መከራዎች ሁሉ ታዘክራለች በእያንዳንዱ ክፍልም የጸሎት ማሳረጊያ #አቡነ_ዘበሰማያት ይደግማሉ ንስሓ የገባ ኃጢአተኛ ሰው እንኳን ቢሆን ይህችን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት በጸለየ ጊዜ ሺህ ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ ጌታችን በማይታበል ቃሉ ለአባታችን ነግሯቸዋል
👉እያንዳንዱን #የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች መከራዎቹን የምታዘክረውን ይህቺን በአምላክ ልቡና ያለች ግሩም የሆነች ፀሎት ነፍሳትን ከሲኦል አታወጣም ብሎ የሚጠራጠር ቢኖር መንግስተ ሰማያትን አያያትም ፃድቁ ታኅሣሥ 8 ቀን ተወልደው ሚያዚያ 9 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከፃድቁ ረድኤት በረከት ያሣትፈን #የፃድቁ_አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ምልጃና ፀሎት ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን" ✝️💒✝️
#መስከረም_9
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
መስከረም ዘጠኝ በዚህች የመላእክት አለቃ #ቅዱስ_ሚካኤል በሮም አገር ፍሩምያ በምትባል ከተማ ላደረገው ተአምር መታሰቢያ ነው፣ #ቅዱስ_አባት_አባ_ቢሶራ በሰማዕትነት አረፈ፣ #ቅዱስ_ያሳይ_ንጉሥ እረፍቱ ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ሚካኤል
መስከረም ዘጠኝ በዚህች ቀን በሮም አገር ፍሩምያ በምትባል ከተማ ለሆነው ተአምር መታሰቢያ ሆነ። ይህም እንዲህ ነው የሰማይ ሠራዊት አለቃ በሆነ በከበረ መልአክ በሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚታዩ ድንቆችና ተአምራቶች ምክንያት ዮናናውያን ሰዎች ሰይጣናዊ ቅናትን እንደ ቀኑ ከመቅናታቸውም ብዛት የተነሣ በዚያ አካባቢ የሚወርደውን የወንዝ ውኃ በዚያች ቤተ ክርስቲያን ላይ ሊመልሱትና ከሚጠብቃት መጋቢዋ ጋር በውኃ ስጥመት ሊአጠፉአት ፈልገው መለሱት።
የሰማያውያን ሠራዊት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለቤተ ክርስቲያኑ መጋቢ ለናርጢኖስ ተገለጠለት ወደርሱም ቀርቦ ጽና አትፍራ አለው ይህንን ብሎ በእጁ ውስጥ ባለ በትር አለቱን መታው አለቱም ተደንጥቆ እንደ በር ሆነ የዚያ ወንዝ ውኃም በውስጡ አልፎ ሔደ።
ይህንንም ያዩ ምስጉን እግዚአብሔርን አመሰገኑት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልንም አከበሩት። ከዚያች ቀን እስከ ዛሬ የወንዙን ውኃ በዚያች በተሠነጠቀች አለት ውስጥ አልፎ ሲሔድ ያዩታል ወደ መላእክት አለቃ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከቶ አይቀርብም።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባት_አባ_ቢሶራ
በዚህችም ቀን መጺል የምትባል አገር ኤጲስቆጶስ ቅዱስ አባት አባ ቢሶራ በሰማዕትነት አረፈ።
ይህም ቅዱስ በግብጽ አገር እግዚአብሔርን በምትወድ መጺል በምትባል ከተማ ኤጲስቆጶስ ሆነ። ዲዮቅልጥያኖስም ነግሦ ክርስቲያኖችን በሚያሠቃያቸው ጊዜ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ስም ደሙን ያፈስ ዘንድ ይህ አባት ወደደ።
ሕዝቡንም ሀሉ ሰብስቦ በቤተ መቅደሱ ፊት በዐውደ ምሕረቱ አቆማቸው ሊጠብቁት የሚገባውን ለጽድቅ የሚያበቃቸውን ትእዛዝ ሁሉ አዘዛቸው። ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ስም ደሙን ማፍሰስ እንደሚሻ ነገራቸው ይህንንም በሰሙ ጊዜ ታላቆችም ታናሾችም በላዩ አለቀሱ።
የሙት ልጆች እንሆን ዘንድ የምትተወን ምን ያደርግልሃል እኛስ እንድትሔድ አንለቅህም አሉት ሊይዙትም ቃጡ ግን አልተቻላቸውም ተውትም እርሱም ወደ ክብር ባለቤት ክርስቶስ አደራ አስጠበቃቸውና ሰላምታ ሰጥቷቸው ከእነርሱ ዘንድ ወጥቶ ተጓዘ። እነርሱም መሪር ልቅሶን እያለቀሱ ሸኙት።
ስማቸው ቢስኮስ ፊናቢክስ ቴዎድሮስ የሚባሉ ኤጲስቆጶሳት አብረውት ሔድ መኰንኑ ወደ አለበት አገርም ደርሰው የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ። እርሱም መኰንኑ አሠቃያቸው ኤጲስቆጶሳትም እንደሆኑ አውቆ ሥቃያቸውን አበዛ እሊህ አባቶች ግን በታላቅ ትዕግሥት የጸኑ ናቸው። ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስ ያጸናቸዋልና።
ከዚህም በኋላ መኰንኑ ራሶቻቸውን በሰይፍ ይቆርጧቸው ዘንድ አዘዘ የሕይወት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። የቅዱስ ቢሶራ ሥጋው ግን ንሲል በሚባል አገር እስከ ዛሬ ይኖራል።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ያሳይ_ንጉሥ
በዚችም ቀን ተጋድሎውን በዛፍ ላይ ሆኖ የፈጸመ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘ ንጉሥ ያሳይ አረፈ።
በቀደመው ዘመን መንግስታቸውን ትተው ከመነኑ ነገሥታት አንዱ ቅዱስ ያሳይ ነው። ምናኔ በቁሙ ከባድ ነው። መንግስትን፣ ዙፋንን፣ ክብርን ትቶ መመነንን ደግሞ ከማድነቅ በቀር እንዲህ ብለው ሊገልጹት ይከብዳል።
ቅዱስ ያሳይም መንግስቱን ትቶ ልምላሜ ወደሌለበት ደረቅ በርሃ ሔደ። በዚያም ከአንዲት ዛፍ በቀር ምንም ነገር አላገኘም። በዚያች ደረቅ ዛፍ ላይ ወጥቶ ለዓመታት በጾምና በጸሎት ተጋደለ።
በዘመነ ተጋድሎው ከዛፏ አልወረደም ሰውም አይቶ አያውቅም። በመጨረሻም ስለ ቅድስናው ዛፏ ለምልማለች። እርሱም በዚህች ቀን ዐርፏል።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም ቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መስከረምና_ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)
ምእመናን ሆይ
ማንም የማይደፍረው የህይወት ምሽግ
እግዚአብሔር ብቻ ነው
የጠላትን ጦር እና ፍላፃ የሚያጥፍ ጋሻ
እግዚአብሔር ብቻ ነው
ሁልጊዜ በስፍራው ና በአድራሻው የሚገኝ
የማይነጥፍ የሕይወት ምንጭ
እግዚአብሔር ብቻ ነው
እግዚአብሔር አምላክ በፍቅሩ ይጎብኘን🙏
🌼 "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌼
🌼 #መስከረም ፮ (6) ቀን።
🌼 እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ ዐፅማቸው #ከዋልድባ_አብረንታንት_ወደ_ደብረ_ዓባይ ለፈለሰበት ቀን መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን።
✝ ✝ ✝
🌼 #የአቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ_የሥጋ_ፍልሰት፦ ከዋልድባ አብረንታንት ወደ ደብረ ዓባይ፤ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ትውልዳቸው ከካህናቱ ወገን አክሱም ነው አባታቸው እስጢፋኖስ እናታቸው አመተ ማርያም ይባላሉ። ለመምህር ሰጥተዋቸው ሲማሩ አድገው በኋላም ወላጆቻቸው በሞት ሲለዩአቸው ደብረ በንኰል ገዳም ገብተው ሥርዓተ ምንኩስናን ከአበው እያጠኑ ለትልቁም ለትንሹም በትሕትና እየታዘዙ ውሃ እየቀዱ እንጨት እየሰበሩ በትኅርምት በጽሞና በጸሎት ይኖሩ ነበር።
🌼 ሰይጣን በውዳሴ ከንቱ ጾር ቢመጣባቸው ከማሕበረ መነኰሳቱ ተለይተው በተባሕትዎ ለመኖር ሽተው ወጥተው ሲሔዱ ተከዜ ደረሱ። ወንዙ ሞልቶ የማያሻግራቸው ቢሆን ውሃውን በትምህርተ መስቀል ባርከው በአንድ እጃቸው መጽሐፍ በአንድ እጃቸው መብራት እንደያዙ ገብተው መብራቱ ሳይጠፋ መጽሐፉ ሳይበላሽ ተሻግረዋል። ዋልድባ ሲደርሱ ጌታ እዚህ ተቀመጥ ስላላቸው ገዳም መሥርተው ሥርዓተ ምንኩስናን እያስተማሩ ተቀመጡ። ዛሬ በዋልድባ የሚያመሰግኑበት ውዳሴ ማርያም ቅዳሴ ማርያምን ከተከዜ ወዲህ ያመጡ እሳቸው ናቸው። ይህንን እየጸለዩ ሲሔዱ ክንድ ከስንዝር መሬት ለቀው ይታዩ ነበር።
🌼 አንድ ቀንም ይህንን ጸሎት ደግመው ውኃውን ቢባርኩት ኅብስተ ሕይወት ሆነላቸው ከነደቀ መዛሙርቶቻቸው ተመግበውታል። እመቤታችንም የፍቅር መግለጫ ዕጣን፣ ወርቅ፣ እንቁ ሰጥታቸዋለች። "ውዳሴዬን ከቅዳሴዬ አንድ አድርጎ የደገመውን አንተ ከገባህበት መካነ ሕይወት አስገባዋለሁ" ብላ ቃልኪዳን ሰጥታቸዋለች። ጊዜ ዕረፍታቸው ሲደርስ ጌታን በስብሐተ መላእክት ተገልጦ "በስምህ የተማጸነውን በጎ የሰራውን፣ ዜና ገድልህን የጻፈውን፣ ያስጻፈውን፣ ያነበበ፣ የተማረ፣ ያስተማረ፣ እስከ አሥር ትውልድ ድረስ ምሬልሃለሁ። በዚህ ቦታ በዋልድባ የሚሰበሰቡ ልጆችህን ከእዳ ከፍዳ እሰውርልሃለሁ" አላቸው። እንኪያስ ቦታዋን ባርክልኝ ብለው እንደ መሶብ አንስተው አስባርከዋታል ጌታችንም "እህል አይብቀልብሽ ኃጢአት አይሻገርብሽ" ብሎ ቃል ኪዳን ገባላት ለገዳመ ዋሊ። አባታችን አቡነ ሳሙኤል በበዓታቸው ውስጥ ጸንተው ሲኖሩ ታህሣሥ 12 ቀን ያረፉ ሲሆን ዛሬ መስከረም 6 ግን ፍልሰተ አጽማቸው የተከናወነበት ዕለት ነው። ከአባታቸው ከአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን። ምንጭ፦ ከገድላት አንደበት።
እርሱ ግን በሥልጣኑ በቦታቸው እንዲወሰኑ አዘዛቸው፡፡ ወደ ዋድላ በመሔድ በሰለልኩላ በየጭራ በሐዲስ አምባ እና በደብረ ዳሪት አቡነ አሮን ተመላልሶ ወንጌልን ሰበከ ድዉያንን
ፈወሰ ብዙዎችንም አመነኰሰ፡፡ከዚኽም በኋላ ዐብይ ጾምን ወደ ጎንደር ሔዶ ሱባኤውን በዚያ ከቆየ በኋላ ወደ ሰለልኩላ ተመለሰ፡፡ የቅድስት ድንግል ማርያምና የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤል ታቦታት አብሮ ይዞ ስለነበር ሀገሩ እንዲባረክ በሰላልኩላ የቅዱስ ሚካኤልን ቤተ ክርስትያን
ሠርቶ ታቦተ ሚካኤልን አስገብቶ አከበረ፡፡ ዛሬም ድረስ በዋድላ ሰለልኩላ ሚካኤል በሰለልኩላ ቅዳሴ መገኛነቱ በብዙዎች ዘንድ ይታወቃል፡፡ አባታችንም ጥቂት ጊዜ በሰለልኩላ ሚካኤል እንደቆየ እመቤታችን ‹‹…ይህ ስፍራህ
አይደለምና ወደ ደብረ አብ ደብረ ወልድ ደብረ መንፈስ ቅዱስ ሒድ›› አለችው፡፡በተነገረው ቦታም ተወስነው የሚጸልዩ ሦስት ደገኛ መነኰሳት አባቶች ‹‹በቶሎ ወደዚህ ና ፣በዚህ አንተ የብዙዎች አባት ትሆናለህ›› ብለው ወደ አቡነ መልክአ ክርስቶስ መልእክት ላኩበት፡፡ አባታችንም ከዳውንት ወደ ግሸቅ መሔጃ መንገዱ ላይ መንኳክ ማርያም ደርሶ አደረ፤ ጸሎት አድርሶ ቦታዋን ቢባርካት ጠበል ፈለቀ፤የገዳም ሥርዓትንም ሠራላት፡፡ ዛሬም ድረስ አባታችን ያፈለቀው ጠበል ብዙ ተኣምራት እያደረገ ምስክር ሆኖ በቦታው ላይ አለ፡፡አቡነ መልክአ ክርስቶስ የእመቤታችንን ታቦት ይዞ በሽሎ የሚባል ወንዝ ሲደርስ እንደ ሱራፌል ቀንና ሌሊት ሳያስታጉሉ የሚያመሰግኑ ሥዉራን ቅዱሳን በደብሩ እንዳሉ አስተዋለ፡፡ እመቤታችን እየመራችው በደብሩ አናት አድርሳው ‹‹ይህ ቦታህ ይሁን፣ ስሙም ግሸቅ ይባል፣ ታቦቴንም በቀኝህ አኑር›› አለችው፡፡ዳግመኛም ‹‹ልጄ ገዳመ አስቄጥስን፣ገዳመ ሲሐትን እንደባረከ ይህን ገዳምህንም ይባርክልህ፤ ማህበረ መቃርስ ወማኅበረ ጳኩሚስ፣ ማኅበረ ሖር ወአባ አብሎ፣ ደብረ ኮኖብዮስ እና ሌሎችንም እንድባረከ ይባርክልህ፤ ከአንተ የሚወለዱ አንዱስ እንኳን አይጠፋም፤ በገዳምህ
የተቀበረ አይጠፋም›› አለችው፡፡አባታችንም ገዳሙን ግሸቅ ካደረገ በኋላ ገዳማዊ አንድነቱ እየጠነከረ በመምጣቱ በደብሩ ዙሪያ የነበሩ ክፉዎች ‹‹ቦታችንን ሊቀሙን ነው›› ብለው በማሰብ ክፋትን ማድረግ ጀመሩ፡፡ በድንግልና ራሳቸውን ጠብቀው ከዓለም የተለዩ ደናግል መነኰሳት ሴቶቹን በማየት እንዲፈተኑ ተንኮል አስበው መነኰሳት
አባቶች ውኃ ከሚቀዱበት ማይ ዘአጋም ከተባለ ምንጭ ሴቶች ልጆቻቸውን መላክ ጀመሩ፡፡መነኰሳቱም በዚህ አዝነው ውኃ ሳይቀዱ በመመለስ ለአቡነ መልክአ ክርስቶስ የሆነውን ሲነግሩት ‹‹ልጆቼ ይህን ቦታ እመቤታችን ነች
የሰጠችኝ፣ ‹አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የፈቀዱልህ ቦታህ ነው፣ ለአንተና ለልጆችህ ለዘለዓለም ማደርያ ርስትህ
ይሁን፣ወገን የሌላቸው ታማሚዎች ስምህን በመዘከር ከመከራ ይዳኑ› ብላ ተናግራ ሰጥታኛለች፤ እግዚአብሔር ለኛ ካለው ያድርገው ለእነርሱ ካለው ይሁን ብሎ ሱባኤ ይዞ እናትና ልጅን ለመነ፡፡ የአካባቢው ሰዎችም እግዚአብሔርን አሳዝነዋልና ከእነርሱ ውስጥ ብዙዎች በሕማም በደዌ
ተመቱ፤ ብዙ ሰው መሞት ሲጀምር ቀሪዎቹ ከገዳሙ ክልል ሸሽተው ወጡ፡፡በዚህም ጊዜ የአቡነ መልክአ ክርስቶስ ዝና በመላው ኢትዮጵያ ደረሰ፡፡ዳግመኛም አባታችን ‹‹…የኤርትራን ባሕር ከፍለህ ሕዝብህን ያሻገርኽ፣እንዳይርባቸው በበረሓ መና ያወረድኽ፣ እንዳይጠሙ ከዓለት ውኃ ያፈለቅኽ አምላክ ሆይ! ዛሬም አንተ ነኽና ውኃ አፍልቅልኝ›› ብሎ ቢማጸን በግሸቅ ተራራ ላይ ውኃ ፈለቀለት፡፡ በገዳሙ የነበሩ ሁሉ ከእርሷ ተጠምቀው ጠጥተው ተፈወሱ፡፡ የጎንደሩ ንጉስ አድያም ሰገድ ኢያሱ ሙያተኞችን ልኮ በግንብ አሰራት፡፡የአጼ ኢያሱ ልጅ ልዑል ሰገድ ተክለ ሃይማኖትም ውኃ የሚቀዱበት በቅሎ ሰጥቷቸዋል፡፡ማኅደረ ክርስቶስ የሚባል ክፉ ጠላት በብዙ ፈተና የሚያሠቃየው የአቡነ መልክአ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር በደብሩ ነበር፡፡ አቡነ መልክአ ክርስቶስም በጸሎቱ ክፉ ጠላትን ድል አደረገለት፡፡ ‹‹ልጄ አይዞህ አትፍራ ጽና›› ይለው ያበረታው ነበር፡፡ ከዚኽም በኋላ በጎንደር ዙሪያ ብዙ መነኰሳት ሰማዕት በሚሆኑበት ዘመን ማኅደረ ክርስቶስ ለአባታችን በራእይ ያየውን ነገረው፤ ‹‹አንተ
ሰማዕት ለመሆን ሒድ፣ አቡነ መልክአ ክርስቶስ ግን አይሔድም፣ብዙ ሥራ ከፊቱ አለ፣ ብዙዎችን ወደ መንግስተ ሰማያት ይጠራልና›› ተብያለው በማለት የተነገረውን መልእክት አስረዳው፡፡ አባታችንም ‹‹የነብያትን መንገድ ያቀና
ሰማዕታትን በፈተና ሁሉ ያጸና አምላክ መንገድህን ያቅናልህ ያስፈጸምህ›› ብሎ ልጁን መረቀውና ሰማዕትነት ወደ ሚቀበልበት ቦታ ሰደደው፡፡ ማኅደረ ክርስቶስም ወደ ንጉሥ ወታደሮች ዘንድ ቀርቦ ስለ ሃይማኖቱ መስክሮ አንገቱን
በሰይፍ ተቆርጦ የክብር አክሊልን ተቀዳጀ፡፡ አንገቱንም በሰይፍ ከቆረጡት በኋላ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ራስ የሰማዕቱ ማኅደረ ክርስቶስ ራስ መዝሙረ ዳዊት መኃልየ ሰሎሞን ውዳሴ ማርያም ዘመረች፡፡የአቡነ መልክአ ክርስቶስ የዕረፍቱ ቀን በደረሰ ጊዜ በጽኑ ደዌ ታመመ፡፡ከመረጣቸው ጋር ቃልኪዳን ያደረገ መድኃኔዓለም ለአቡነ መልክአ ክርስቶስም እንዲሁ አደረገ፡፡ ‹‹…ድካምህን ተቀብያለሁ፣ በእጅህ የመነኰሱ፣ በመስቀልህ የተባረኩ፣ ከሩቅ አንተን ብለው ደጅህ የመጡ፣በስምህ መታሰቢያህን የሚያደርጉትን ሁሉ የልባቸውን በጎ መሻት እፈጽምላቸዋለሁ፤በደላቸውን ሳልመለከት ጸጋ በረከትን እሰጣቸዋለሁ፤የወዳጆችህን ትውልድ እስከ 15 ትውልድ እምርልሃለሁ›› ብሎ ቃልኪዳን
ከገባላቸው በኋላ መስከረም 5 ቀን በዕለተ ቀዳሚት በ86 ዓመታቸው ነፍሳቸው ከሥጋው ተለየች፡፡ከመቃብራቸውም ላይ ሕሙማን የሚፈወሱበት ድንቅ ድንቅ ተኣምራትን
የሚያድርግ ጠበል ፈለቀ፡፡አቡነ መልክአ ክርስቶስ ለአገልግሎት ሲጓዙ በመንገድ ላይ ከሞተ 900 ዓመት
የሞላውን ሰው ዐፅም አግኝተው ወደ እግዚአብሔር ጸልየው በመስቀላቸው ባርከው ከሞት አስነሥተውታል፣ ከሞት የተነሣውም ሰው ኢአማኒ ስለነበር ጻድቁ አጥምቀው
ለክርስቶስ መንግሥት አብቅተውታል፡፡ጻድቁ አቡነ መልክአ ክርስቶስ ያደረጉት ታላቅ ተአምር ይኽ ነው፡- ለጻድቁ እንደ
ሰው እየተላላከ ከበሸሎ ወንዝ ውኃ እየቀዳ ወደ ገዳማቸው የሚያመጣላቸው አንድ አህያ ነበራቸው፡፡ አህያውም ሰው ሳይጭነው ባዶ እንስራ ወደ ወንዙ ወስዶ በተአምር ውኃው በእንስራ ሲሞላለት ሳያጋድል ይዞ ሩቅ መንገድ ተጉዞ
ከአባታችን ገዳም ይደርሳል፡፡ ነገር ግን በአንደኛው ቀን ይህንን አገልጋይ አህያቸውን ጅብ በላባቸው፡፡ አቡነ መልክአ ክርስቶስም በአህያቸው ፈንታ ጅቡን 7 ዓመት ውኃ አስቀድተውታል፡፡ቅዱሳኑ አቡነ መልክአ ክርስቶስ እና አቡነ
እስትንፋሰ ክርስቶስ በአንድ ዘመን አብረው የኖሩ ሲሆን ኹለቱ ቅዱሳን የቅርብ ወዳጆችም ነበሩ፡፡ገድላቸው እንደሚናገረው አቡነ መልክአ ክርስቶስ ከግራኝ አህመድ የ15 ዓመት ጥፋት በኋላ የቅዱስ ያሬድን የቅዳሴ ዜማ ትምህርት ጠብቆ ለትውልድ በማበርከት እጅግ የጎላ ድርሻ አላቸው፡፡አቡነ መልክአ ክርስቶስ ዐቢይ ጾም ሲገባ ብዙ ጊዜ ብቻውን ሱባኤ ይይዛል፡፡በዐቢይ ጾም ወቅት ከዕለታት በአንደኛው ቀን በግሸቅ ማርያም ሳለ ክፉ ጠላት በከባድ ረኃብ ፈተነው፡፡ አባታችንም በዚህ አዝኖ ሲጨነቅ ክብርት እመቤታችን ተገጻለት ‹‹ሰላም ለአንተ ይሁን ወዳጄ መልክአ ክርስቶስ›› አለችው፤ ዳግመኛም ‹‹ስለምን ትተክዛለህ? አይዞህ ጽና…›› ብላ በልጇ ቸርነት ሰማያዊ ኅብስት
መገበችው፡፡ አባታችንም ይህን ምሥጢር ለልጁ ለአባ ሚካኤል ከነገረው በኋላ ‹‹እስከምሞት ድረስ ይህን ለማንም አትንገር፣
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
መስከረም 5-ቤተ መቅደሳቸው ጣራው ክፍት ሆኖ ዝናብ ግን ፈጽሞ የማያስገባው የመቄቱ አቡነ አሮን መንክራዊ ዕረፍታቸው ነው፡፡ እርሳቸውም ዳዊታቸውን አዋሽ ወንዝ ወስዶባቸው ሳለ ከ7 ዓመት በኋላ መልሰው ከወንዙ ውስጥ አቧራውን አራግፈው የተቀበሉ ናቸው፡፡
+ አስቀድማ አረማዊት የነበረችውና በኋላ በጌታችን አምና ከሁለት ልጆቿ ጋር ሰማዕትነቷን በድል የፈጸመችው ቅድስት ሶፍያ ዕረፍቷ ነው፡፡
+ ዳግመኛም በዚህች ዕለት እግዚአብሔርን የሚወድ ሃይማኖቱ ቀና ደግና ጻዲቅ ንጉሥ ዐፄ ልብነ ድንግል ዕረፍቱ ነው፡፡
+ የሚያገለግላቸውን አህያ ጅብ ቢበላባቸው በአህያቸው ፋንታ ጅቡን ለ7 አመት ውሃ እየቀዳ እንዲያገለግላቸው ያደረጉት አቡነ መልክአ ክርስቶስ ዕረፍታቸው ነው።
+ ሰማዕቱ ቅዱስ ማማስ ሰማዕትነቱን በድል ፈጸመ፡፡
ሰማዕቱ ቅዱስ ማማስ፡- ይኽንንም ቅዱስ ወላጆቹ ቴዎዶስዮስና ታውፍና በከሃዲው ዑልያኖስ ዘመን ሰማዕት ሆነው ሲያርፉ አንዲት ክርስቲያን ሴት ወስዳ አሳደገችው፡፡ እርሷም እናትና አባቱ ዐርፈዋልና ስሙን ማማስ አለችው፡፡ ማማስ ማለት የሙት ልጅ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ማማስ 18 ዓመት በሆነው ጊዜ ክርስቲያን መሆኑን ሲያውቅ ከሃዲው ገዥ ይዞ ልዩ ልዩ በሆኑ ጽኑ ማሠቃያዎች አሠቃየው፡፡
በአንገቱም ላይ ትልቅ ድንጋይ አስሮ ወደ ባሕር ጣለው፣ ነገር ግን ጌታችን መልአኩን ልኮ አዳነው፡፡ ከዚኽም በኋላ ቅዱስ ማማስ በዋሻ ውስጥ የጎሽ ወተት እየጠጣ በመንፈሳዊ ተጋድሎ ተቀመጠ፡፡ ሁለተኛም ከሃዲዎች ይዘውት በሚነድ
እሳት ውስጥ ጨመሩት፣ አሁንም ጌታችን ከሚነደው እቶን እሳት አዳነው፡፡ዳግመኛም ተነጣጥቀው እንዲበሉት ለተራቡ አንበሶች ቢሰጡትም ጌታችን ከመከራው ሁሉ ያድነው ስለነበር አሁንም እንደ ነቢዩ ዳንኤል ከአንበሶቹ አፍ አዳነው፡፡ ይልቁንም አንበሶቹ ቅዱስ ማማስን በላያቸው ላይ አውጥተው ተሸከሙት፡፡ ከብዙ ጽኑ ሥቃዮችም በኋላ በመጨረሻ ሕዋሳቶቹ እስኪለያዩና የሆድ ዕቃው እስኪፈስ ድረስ መሬት ላይ ጎተቱትና ምስክርነቱን በዚሁ ፈጽሞ
የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀ፡፡ ዕረፍቱም መስከረም 5 ነው፡፡ታላቁ ሊቅ ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ‹‹ተአምኆ ቅዱሳን የቅዱሳን ሰላምታ›› በሚለው ድርሰቱ ላይ ይኽን ታላቅ ሰማዕት ‹‹አንበሳ ለሚሰግድለትና የእሳት ነበልባልን ላቀዘቀዘ የወልድ ምስክር ለሆነ ለማማስ
ሰላምታ ይገባል›› በማለት አመስግኖታል፡፡በዚህ ታላቅ ሰማዕት በቅዱስ ማማስ ስም የተጠሩ አንድ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አሉ፡፡አቡነ ማማስ ይባላሉ፡፡ እርሳቸውም የታላቁ አባት የአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ረድእ የነበሩ ሲሆን ያመነኮሷቸውም እሳቸው ናቸው፡፡ የአቡነ አሞኒ ሦስተኛ ልጅ ናቸው፡፡ ትውልዳቸው ወሎ አምሐራ ሳይንት ነው፡፡ አቡነ ማማስ በተለያዩ ቦታዎች ሰባት ገዳማትን ያቀኑ ሲሆን ታላላቅ ተአምራትን በማድረግ ይታወቃሉ፡፡በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች ተዘዋውረው በስብከተ ወንጌል ብዙ አገልግለዋል፡፡
በስማቸው የተሠራው አስደናቂ ገዳም በትግራይ አጋሜ አውራጃ ይገኛል፡፡ኤርትራ አካለ ጉዛይ ውስጥም አቡነ ማማስ የሚባል ትልቅ ገዳም አላቸው፡፡ትግራይ ውስጥ ከእዳጋ አርቢ ወደ ጥንታዊቷ ውቅሮ ማርያም ገዳም በሚወስደው መንገድ ላይ ነበለት ከምትባለው ትንሽ የገጠር ከተማ በስተሰሜን አቅጣጫ በሚገኘው አስደናቂ ገዳማቸው ውስጥ ለየት ያለ የማኅሌት ሥርዓት ይካሄድበታል፡፡ የማኅሌቱ ድምጽ እጅግ የተለየ ሲሆን ማኅሌቱን ቅዱሳን መላእክት እንደሚሳተፉበት በቦታው ላይ ያሉ ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡ በማኅሌቱም ወቅት ከዋሻው ጣራ ላይ ልዩ ጣዕም ያለውና ፈውስ የሚሰጥ ልዩ ጠበል ይፈልቃል፡፡ ስለትንሳኤ የሚናገረው ተአምረ ማርያም ላይ ስለዚህ ታላቅ ቦታ እንደተጻፈ አባቶች ያስረዳሉ፡፡ ጻድቁን በመጀመሪያ ወደዚህ ታላቅ ቦታ እየመራ ያመጣቸው የታዘዘ መልአክ ነው፡፡ ገዳሙ ሁለት ቤተ መቅደስ ያለው ሲሆን ቀድሞ በመነኩሴ ብቻ ይገለገል ነበር፡፡የአቡነ ማማስ መካነ መቃብራቸው ካለበት ተራራ ላይ የበቀለ የተለየ የዕፅ ተክል
አለ፡፡ ይኽንንም ተክል የአካባቢው ነዋሪ ለእምነትነት በመጠቀም ከተለያዩ ሕመሞች ይፈወስበታል፡፡ የአቡነ ማማስ የዕረፍታቸው ዕለት ጥር 21 ቀን ቢሆንም የአካባቢው ነዋሪ ተአምራት ባደረጉበት ዕለት ታኅሣሥ 30 ቀን በገዳማቸው በደማቅ ሁኔታ ያከብራቸዋል፡፡ የልደት በዓላቸውም ነሐሴ 7 ነው፡፡ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
+ + + + +
ሰማዕቷ ቅድስት ሶፍያ፡- ቅድስት ሶፍያ የተባለች ይህችም ንጽሕት ከሁለት ልጆቿ ጋር ሰማዕት የሆነች ናት፡፡ አስቀድማ አረማዊት የነበረች ናት፡፡ ወላጆቿም ጣዖታትን የሚያመልኩ ናቸው፡፡ እርሷም መርምራ በልቧ አስተውላ የወላጆቿ እምነት ከንቱ መሆኑን ዐወቀች፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ መኖፌ ኤጲስ ቆጶስ ዘንድ ሄዳ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመነች፡፡ እርሱም ሃይማኖትን ካስተማራት በኋላ ከሁለት ልጆቿ ጋር አጠመቃት፡፡የሀገሯ ሰዎችም ‹‹ለአማልክት መስገድን ትታ ክርስቲያን ሆናለች›› ብለው ለገዥው ለከላድያኖስ ወነጀሏት፡፡ ገዥውም ወደ እርሱ አቅርቦ መረመራት፡፡እርሷም በክርስቶስ ማመኗን ለከሃዲው ገዥ በድፍረት ተናገረች፡፡ ሊያባብላትም ሞክሮ አልሆንለት ቢል ከልጆቿ ጋር ጽኑ ሥቃይን አሠቃያት፡፡ እርሷ ግን በሥቃይ ውስጥ ሳሉ ልጆቿን ታጽናናቸውና ታበረታቸው ነበር፡፡ ‹‹ልጆቼ ሆይ ጠንክሩ፣ጨክኑም፤ እኔ የአንጌቤንዋን እመቤት ሶፍያን እመስላታለሁ፣ እናንተም ጲስጢስ፣አላጲስ፣ አጋጲስ የተባሉ ልጆቿን ምሰሉ›› ስትላቸው እነርሱም ‹‹እናታችን ሆይ ፍለጋሽን እንከተላለንና ስለ እኛ አትፍሪ›› አሏት፡፡ በዚህም ጊዜ ተቃቅፈው እየተሳሳሙ ተላቀሱ፡፡ገዥውም ይህንን አይቶ ልጆቹ እንዲፈሩ በማለት እናታቸውን በፊታቸው አሠቃያት፡፡ ልጆቹም የታዘዘ መልአክ መጥቶ እናታቸውን ሲሰውራት ተመለከቱ፡፡ በሥቃይም ውስጥ ሆና በክርስቶስ ማመኗን ስትናገር ገዥው ምላሷን ከሥሩ አስቆረጠው፣ ነገር ግን መናገሯን አላቋረጠችም ነበር፡፡በመጨረሻም አንገቷን በሰይፍ አስቆረጠው፡፡ ከዚህም በኋላ ገዥው ልጆቿን እሺ ይሉት ዘንድ ቢያባብላቸውም እነርሱ ግን እመቢ አሉት፡፡ በየተራ እያከታተለ ራሳቸውን አስቆረጠው፡፡በመቃብራቸውም ላይ እጅግ አስገራሚ ተአምራት ተፈጸሙ፡፡ደገኛው ንጉሥ ታላቁ ቈስጠንጢኖስ የእነዚህን ቅዱሳት ዜና ትሩፋታቸውን በሰማ ጊዜ ሥጋቸውን ወደ ቍስጥንጥንያ አፍልሶ ወሰደው፡፡ እርሱም ዜናቸውን ከመስማቱ በፊት ታላቅና ሰፊ ቤት በዕንቁና በወርቅ አስውቦ አሠርቶ በላይዋም ላይ ‹‹ይህቺ ቤት የንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ናት›› ብሎ ጽሑፍ አስቀረጸባት፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ ወርዶ ያችን ጽሕፈት ደምስሶ በመቀየር ‹‹ይህች ቤት የሶፍያ ናት›› ብሎ ይጽፋል፡፡ ንጉሡም በተደጋጋሚ እየቀየረ ስሙን ቢጽፈውም መልአኩ በየጊዜው ስሙን በሶፍያ ስም ስለቀየረበት ሠራተኞቹም ሆኑ ንጉሡ የሚያደርጉትን አጡ፡፡አንድ ቀን የንጉሡ ልጅ ሲጫወት መልአኩ ተገለጠለትና ቤቷ የሶፍያ መሆኗን ለአባቱ እንዲነግረው አዘዘው፡፡ ልጁም መልአኩን ‹‹ለአባቴ ነግሬው እስክመጣ ትጠብቀኛለህ?›› ሲለው መልአኩም ‹‹አዎ›› አለው፡፡ ንጉሡም ልጁን የላከው መልአክ መሆኑን ዐውቆ መልአኩ ልጁ እስኪመለስ እንደሚጠብቀው ሲያውቅ መልአኩ ከዚያ እንዳይሄድ ብሎ የገዛ ልጁን ገደለው፡፡ መልአኩም ልጁ እስኪመጣ እየጠበቀው በዚያ ቦታ ኖረ፡፡ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስም የቅድስት ሶፍያንና የልጆቿን ሥጋ አስመጥቶ በዚያች ቤት ውስጥ በታላቅ ክብር አኖረው፡፡
/channel/booms_io_bot/start?startapp=bro7521433979
BOOMS Game - Earn tokens with real value even before the airdrop!
Take your welcome bonus:
💸 5,000 Coins as a first-time gift
🔥 50,000 Coins if you have Telegram Premium
ምእመናን ሆይ
ከበደል ፈጽሞ የሚያጥብ
ከበደል ፈጽሞ የሚያጠራ
እግዚአብሔር ብቻ ነው
የውስጥን መቆሸሸ የነፍስን መቆሸሽ
ገንዘብ አያጠራውም ሥልጣን አያጠራውም
ሥጋዊ ብልሀትም አያጠራውም
የነፍስን ስብራት መጠገን የሚችለው
የነፍስን መቆሸሽ ንፁህ ማድረግ የሚችለው
እግዚአብሔር አምላክ ብቻ ነው።
እግዚአብሔር አምላክ ስብራታችንን ይጠግንልን🙏
መስከረም 13/2017 #አምላካችን_እግዚአብሔር_አብ
#መልአኩ_ቅዱስ_ሩፋኤል
#ፃድቁ_ዘርዐ_ብሩክ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሳኑ ስም ለምናመሰግንበት ለመልአኩ #ለቅዱስ_ሩፋኤል እና ለፃድቁ #አቡነ_ዘርዐ_ብሩክ ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን
👉 #ቅዱስ_ሩፋኤል ቊጥሩ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሲኾን ሩፋ፤ ማለት ሐኪም፤ ኤል ማለት #እግዚአብሔር ማለት ሲኾን ሩፋኤል ማለት #እግዚአብሔር_ሐኪሜ ነው ማለት ነው፤ ሄኖክም በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” ይለዋል መጽሐፈ ሄኖክ.6፥3
👉ይኽ መልአክ በራማ ሰማይ ያሉ ነገደ መናብርትን የሚመራቸው ነው ነገደ መናብርት ያላቸው #ቅዱስ_ሩፋኤል የሚመራቸው በራማ ሰማይ የሚኖሩ ነገደ መላእክት ናቸው
👉ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በሥነ ፍጥረት መጽሐፉ ላይ ወለዳግም ፆታ ዐሠርቱ ስሞሙ መናብርት ወሊቆሙ #ሩፋኤል እሉ እሙንቱ እለ ይቀልል ሩጸቶሙ እምነፋስ ወእለ ይፀውሩ ወላትወ መብረቅ ወኲናተ እሳት ዘይነድድ ወአንበሮሙ በዳግሚት ሰማይ ይላል
👉በራማ ሰማይ የሚገኘውን ኹለተኛውን ዐሥሩን ነገድ መናብርት ሲላቸው አለቃቸው #ቅዱስ_ሩፋኤል ነው፤ እነዚኽም ረቂቅ የኾነ የመብረቅ ጋሻ የእሳት ጦር ይዘው ከነፋስ ይልቅ የፈጠኑ ሲኾኑ በራማ በኹለተኛው ክፍል ላይ አስፍሯቸዋል
👉#የእግዚአብሔር_አብ ቸርነት የልጁ የመድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ፍቅር #የመንፈስ_ቅዱስ አንድነት ከሁላችን ጋር ይሁን የመልአኩ #ቅዱስ_ሩፋኤል ጥበቃ የፃድቁ #አቡነ_ዘርአ_ብሩክ"ፀሎት አይለየን አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል
እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ወርሃዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን !!!
" እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ። በፊቱ ተጠንቀቁ፥ ቃሉንም አድምጡ፤ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት።
ዘጸ. ፳፫፥፳-፳፩ /23፥20-21/
❤ የመላእክትን ቅድስና፣ ሐያልነት፣ የተሰጣቸውን ስልጣን በመጽሐፍ ቅዱስ በተለያዩ ቦታዎች እናያለን
❤ ከእነዚህ መላእክት አንዱ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል አንዱ ነው፣ የመላእክት አለቃ
❤ የስሙም ትርጓሜ "እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው" ማለት ነው
❤ ቅዱስ ሚካኤል የሰማይ ሠራዊት ሁሉ አለቃቸው፣ ዲያቢሎስ ሊያደክማቸው ለሚፈልግ ሁሉ ብርታትን፣ ኃይልን የሚሰጥ መልአክ ነው
❤ በብሉይም፣ በሐዲስ ኪዳንም በአማላጅነቱ፣ ሕዝብን እየጠበቀ ያጸና መልአክ እንደሆነ መጽሐፍት ይነግሩናል
❤ ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር እየተላከ ታላላቅ ሥራዎችን የሠራ መልአክ ነውና "መልአከ ኃይል" ይባላል
እስራኤላውያንን ከጠላት ያዳነ፣ ቅዱሳንን በመንገዳቸው የመራ ይህ ታላቅ መልአክ እኛንም ይጠብቀን፣ አማላጅነቱም አይለየን
#አንዲት_ሐይማኖት_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ
#አንዲት_ቤተክርስቲያን
#አንዲት_ጥምቀት
#ተዋህዶ
#orthodoxchurch
#ኢትዮጵያ
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
መስከረም 10-የጌታችን ቅዱስ መስቀል አገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ የገባበት ዕለት ነው፡፡
+ ጸዴንያ በምትባል አገር ሥጋ የለበሰች ከምትመስል ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ከሣላት ሥዕል ከሠሌዳዋ ቅባት እየተንጠፈጠፈ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም ተአምር የተገለጠበት ዕለት ነው፡፡
+ ከከሃዲው ከሆሎፎርኒስ እጅ በጥበቧ እስራኤልን ያዳነቻቸው ጥበበኛዋ ዮዲት ዐረፈች፡፡
+ ቅድስት አትናስያና ሦስት ልጆቿ መታሰቢያ በዓላቸው ነው፡፡
+ ዳግመኛም በዚህችም ዕለት የከበረች ቅድስት መጥሮንያ በሰማዕትነት ዐርፋለች፡፡
ሰማዕቷ ቅድስት መጥሮንያ፡- ይህችውም ሰማዕት ቅድስት መጥሮንያ የአንዲት አይሁዳዊት ሴት አገልጋይ ነበረች፡፡ አሠሪዋ አይሁዳዊ ሴትም ቅድስት መጥሮንያን ክርስቲያን በመሆኗ ብቻ ሸክም ታበዛባትና ታንገላታት ነበር፡፡
ከሃይማኖቷም አውጥታ ጌታችንን ማመንን ልታስተዋት ብዙ ሞከረች፡፡ በአንዲት ዕለትም አይሁዳዊቷ ይዛት ወደ ምኩባራባቸው ሄደች፡፡ ቅድስት መጥሮንያ ግን ወደ ምኩራባቸው ሳትገባ ተመልሳ ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ጸሎት አደረገች፡፡ ወደ ቤታቸው ተመልሰው በገቡ ጊዜ አሠሪዋ ‹‹ወደ እኛ ምኩራብ ለምን አልገባሽም?›› ብላ ጠየቀቻች፡፡ ቅድስት መጥሮንያም ‹‹ከእናንተ ምኩራብ እግዚአብሔር ርቋልኮ፣ እንዴት ወደ እርሱ እገባለሁ! በውስጧ ልገባባት የሚገባኝ ቦታዬ ግን ክብር ይግባውና ጌታችን በከበረ ደሙ የዋጃት ይህች ቤተ ክርስቲያን ናት›› አለቻት፡፡ አሠሪዋ አይሁዳዊትም ከቅድስት መጥሮንያ ይህንን በሰማች ጊዜ እጅግ ተቆጥታ በኃይል ደበደበቻት፡፡ በጨለማ ቤት ውስጥ ዘጋችባትና ያለምግብና ያለመጠጥ ለ4 ቀን አሠረቻት፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ ውጭ አውጥታ በጅራፍ ታላቅ ግርፋትን ገርፋ ድጋሚ በእሥር ቤት ጣለቻትና በዚያው ተንገላታ ዐረፈች፡፡ ነፍሷንም እግዚአብሔር ተቀብሎ የሰማዕታትን አክሊል አቀዳጃት፡፡ አሠሪዋ ግን ሥጋዋን አውጥታ በመጣል በዚያም መጥሮንያ ራሷን የገደለች አስመሰለች፡፡ ቅድስት መጥሮንያ ራሷን የገደለች ስለመሰለ አይሁዳዊቷን ሴት ግን ማንም የመረመራት የለም፡፡ ነገር ግን ለተገፉ የሚፈርድ፣ ለተበደሉ የሚበቀል እውነተኛ ዳኛ ልዑል እግዚአብሔር ቁጣው በዚያች አይሁዳዊ ሴት ላይ ወረደ፡፡ ከደርቧ ላይ ስትወርድ ድንገት ወድቃ በዚያው ከመቅጽበት ሞተች፡፡ በነፍሷም ወደ ዘላለማዊ እሳት ሄደች፡፡
የቅድስት መጥሮንያ ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ ይማረን፡፡
+ + + + + +
ጼዴንያ ማርያም፡- ጼዴንያ በምትባል ሀገር ማርታ የምትባል ደግ ሴት ነበረች፡፡ ይህች ደግ ሴት በቤቷ ትልቅ አዳራሽ ሠርታ እንግዶችን እንደ አባታችን አብርሃም ተቀብላ አብልታ አጠጥታ ማደሪያ ቦታም ሰጥታ ታስተናግድ ነበር፡፡ አባ ቴዎድሮስ የሚባል ኢትዮጵያዊ መነኩሴ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ መሽቶበት ከማርታ ቤት በእንግድነት አደረና ጠዋት ሊሄድ ሲነሣ ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚሄድ ሲነግራት ‹‹የእመቤታችንን ሥዕል ገዝተህ አምጣልኝ ዋጋውን ልስጥህ›› አለችው፡፡ እርሱም ‹‹ገንዘቡን ሥዕሉን ሳመጣልሽ ትሰጪኛለሽ›› ብሏት ሄደ፡፡ ኢየሩሳሌምም ደርሶ ቅዱሳት መካናትን ተሳልሞ ሥዕሉን ረስቶ ሳይገዛ ሲመለስ «አደራ ጥብቅ አይደለምን? ያቺ ሴት አደራ ያለችህን ለምን ረሳህ» የሚል ድምፅ ሰማ፡፡ በጣም ደንግጦ ተመልሶ ሄዶ ገዝቶ በረሃ በረሃውን መጓዝ ጀመረ፡፡ በመንገድም እየተጓዘ አንበሳ ሊበላው እየሮጠ ወደ እርሱ ሲመጣበት አየ፡፡ መነኩሴው አንበሳውን ከመፍራት የተነሣ ደነገጠ፣ ተንቀጠቀጠ ደንግጦ ቁሞ ሳለ ያች ሥዕል ከአንበሳው ጩኸት ሰባት እጅ በሚበልጥ አስፈሪ ድምፅ ጩሃ ተናገረች፡፡ ያን ጊዜ አንበሳው ደንግጦ ፈጥኖ ሸሸ፡፡ መነኩሴውም መንገዱን ቀጠለ፡፡ በመንገዱም ከሚያስፈራ ዱር ውስጥ ወጥተው ወንበዴዎች ሊቀሙትና ሊገድሉት ከበቡት፡፡ ከሥዕለ ማርያም እንደ መብረቅ ያለ ታላቅ ቃል ወጣ፡፡
ወንበዴዎችም እጅግ ፈርተው ሸሽተው ከጫካው ውስጥ ገቡ፡፡ ያም መነኩሴ እነኚህን የሚያስደንቁ ተአምራት በተመለከተ ጊዜ በልቡ «ለእኔ ረዳት ትሆነኝ ዘንድ ወደ ሀገሬ ይዣት እሄዳለሁ እንጂ ለላከችኝ ሴት አልሰጥም» ብሎ ወደ ሀገሩ ሊሄድ በመርከብ ተሳፈረ፡፡ በባሕር ላይም ሳለ ጽኑ ነፋስ ተነስቶ መርከቡን እየገፋ ማርታ ወዳለችበት ሀገር ወደ ጽዴንያ ዳርቻ አደረሰው፡፡ ማደሪያም ስለሌለው ወደ ደጓ ሴት ወደ ማርታ ቤት ከእንግዶች ጋር አብሮ ገብቶ አደረ፡፡ ሲነጋ ወጥቶ ሊሄድ ከደጃፍ ሲደርስ ደጃፉ ጠፍቶት ከአጥሩ ሲታገል ዋለ፡፡ ማርታም «አባቴ ያመመህ የደከመህ ትመስላለህ ዛሬ ደግሞ እዚህ እደርና ነገ ትሄዳለህ» አለችውና አደረ፡፡ በሁለኛውም ዕለት እንደ መጀመሪያው ቀን በሩን አልፎ መሄድ አቃተውና እዚያው ማርታ ቤት አደረ፡፡ በሦስተኛው ቀን መውጣት ፈልጐ አሁንም ከአጥሩ ጋር ሲታገል አይታ «አባቴ የሆንከው ምንድነው? እነሆ ዛሬ ሦስተኛ ቀንህ ነው» አለችው፡፡
መነኩሴውም «ይህችን ተአምረኛ ሥዕል አልሰጥም ብዬ ነው፡፡ እኔኮ ሥዕል ከኢየሩሳሌም ግዛልኝ ያልሽኝ መነኩሴ ነኝ» ብሎ ሥዕለ ማርያምን አውጥቶ ሰጣት፡፡ እርሷም እጅግ በጣም ተደስታ እግዚአብሔርን አመሰገነች፡፡ በሥዕሏም ፊት ሰግዳ ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም ምስጋናን አቀረበች፡፡ ተቀብላም ሥዕል ቤት አሠርታ በክብር አስቀመጠቻት፡፡ ይህችም ሥዕል ቅዱስ ሉቃስ የሳላት ናት፡፡ ሥጋ የለበሰች ትመስላለች፡፡ ከፊቷም ወዝ ይንጠባጠባል፡፡ በዚህችም ሥዕል ብዙ ተአምራት ተደረገ ሕሙማን ተፈወሱ፣ ዐይነ ስውራን ማየት ቻሉ፡፡ በዚያ ዘመን የነበረው ሊቀ ጳጳስ ተአምሯን ሰምቶ ሥዕሏ ወደ ማርታ ቤት የገባችበት ዕለት መስከረም 10 ቀን እንዲከበር ሥርዓት ሠራ፡፡ ይህም በዓል በቤተ ክርስቲያናችን ሁልጊዜ ይከበራል፡፡ የብርሃን እናቱ ድንግል ወላዲተ አምላክ ፍቅሯን ጣዕሟን ታሳድርብን፣ ልጇ አምላካችን በጸሎቷ ይማረን፡፡
+ + + + +
ዳግመኛም የጌታችን ቅዱስ መስቀል አገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ የገባው በዚህ ዕለት ነው፡፡የቅዱስ መስቀሉ ፍቅር ይደርብን።
ምንጭ፦ከገድላት አንደበት
ምእመናን ሆይ
👉የቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት ኤራቅሊስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆኑን ሲያስተምረን የሰው ሁሉ ነፃነት የተጻፈበት ቅዱስ ማሕፀን እንደምን ያለ ነው?
👉 በእኛ ሠልጥኖ የነበረ ሞትን የሚቃወመው የጦር ዕቃችን ክርስቶስ ያደረበት ቡሩክ ማሕፀን እንደምን ያለ ነው?
👉 እንደ ዕፀ ሠሉስ ያለ ዘር በባሕርዩ ሁሉን በሚያስገኝ በመንፈስ ቅዱስ ጌታን ያስገኘችልን የተመረጠች ገራህት ማርያም እንደምን ያለች ናት?
👉 እግዚአብሔር እንደ ቸርነቱና እንደ ይቅርታው እንደ መልከ ጴዴቅ ባለ ሹመት ለማገልገል ሥጋን ለብሶ ባሕርዩ ሳይለወጥ ታላቅ ካህን የሆነበት መቅደስ እንደምን ያለ ነው? ብሎ እንደ ተናገረ። ዘፍ ፲፬፥፲፰። መዝ ፻፲ (፻፱)፥፬። ዕብ ፭፥፲።
በዚህ ነገር ❤️አትናቴዎስም❤️ ይመሰክራል
👉 ነፍስና ሥጋ የሌለው መለኮት አንድ ባሕርይ አንድ አካል አንድ ፍጹም ገጽ አንድ ግብር ሆኑ ብሎ እንዲህ ተዋሕዶን ተናግሮአልና
👉አሁንም እሱ አንድ እግዚአብሔር ነው
አንድ ጊዜ ሰው የሆነ አምላክ ነው
አንግዲህም ወዲህ አይለወጥም አይናወጥም
ሰው የሆነ እግዚአብሔር ቃል አንድ አካል አንድ ባሕርይ አንድ ገጽ አንዲት ስግደት የምትቀርብለት አንድ ውድ አንድ ፈቃድ ያለው ሆኖ ይኖራል እንጂ፤
ሥጋውን ሳንለይ አንድ አድርገን አንዲት ስግደትን እንሰግድለታለን ።🙏
እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን !!!
" የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።"
ያዕ. ፭፥፲፮ /5፥16/
ምእመናን ሆይ
✅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴ :- 18 : 21 እንዲህ ያስተምረናል
በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ ወደ እርሱ ቀርቦ፦
ጌታ ሆይ፥ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ልተውለት እስከ ሰባት ጊዜን አለው።
ኢየሱስም እንዲህ አለው፦እስከ ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ አልልኽም።
ሐዋርያው ጴጥሮስ የይቅርታ ገደቡ ጥጉ
7 ጊዜ ብቻ እንደሆነ እያሰበ ነው ይህን ጥያቄ የጠየቀው
ጌታችን ግን 7 ት ጊዜ አልልህም 70 ጊዜ 7ት እንጂ
✅ ስለዚህ በዚህ ክፍል መሰረት
ይቅርታ ገደብ የለውም
ይቅርታ የድንበር ድንጋይ የለውም
ሰው በደሉን ጥፋቱን አምኖ እስከመጣ ድረስ
ይቅርታ ማድረግ አለብን
ብዙ ሰዎች ይሄን ክፍል ሲያነቡ
የይቅርታ ጥጉ 490 ነው የሚሉ አሉ
ምክንያቱም 7*70=490 ስለሆነ
እንደዚያ ብለው የሚተረጉሙ አሉ
ግን ስህተት ነው
እኛ እኳ በሀገራችን 3ት ቍጥርእና 10 ቁጥር
ምሉዕነትን ወክሎ የሚናገር ቁጥር ነው።
አለም ዘጠኝ ነው 10ር ሞልቶ አያውቅም እንላለን
በዕብራውያን 7ት ቍጥር ፍፁም ምሉዕነትን የሚወክል ነው
✅ 7ት ጊዜ 70 ማለት
ጴጥሮስ ሆይ ይቅር ላለማለት ምክንያት የለህም ማለት ነው
ይቅርታ ገደብ የለውም
የይቅርታ ልብ እግዚአብሔር አምላክ ይስጠን🙏
ቅድስት ሥላሴ
~~~~~~~~
ሥላሴ የሚለው ሠለሰ ሦስት አደረገ ከሚለው የግእዝ ሥርወ ቃል የተገኘ ሲሆን ሦስት ሦስትነት ማለት ሲሆን በያዘው ምሥጢር ግን አንድም ሦስትም /አንድነት ሦስትነት/ ተብሎ ይተረጎማል፡፡ ሦስትነታቸው በስም በአካል በግብር፤ አንድነታቸው በባሕርይ በህልውና በመለኮት በሥልጣን በፈቃድ ነው፡፡
፩/1. የሥላሴ ሦስትነት
ሀ. የስም ሦስትነት ፡- አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ ‹‹እንግዲህ አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ያዘዝኋችሁን ሁሉ እንዲጠብቁ . . .›› ማቴ. 28፥19
ለ. የአካል ሦስትነት፡- ለአብ ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ፣ ለወልድም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ፣ ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ አለው፡፡ (ሃይማኖተ አበው) አካል ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍር ያለው ነው፡፡ ገጽ ማለት ደግሞ ፊት ነው፡፡ መልክም ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍር ያለ ነው፡፡ አካልም እንዳላቸው ሲያጠይቅ ነቢዩ ዳዊት ‹‹የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ጻድቃን ጆሮዎቹም ወደ ጩኸታቸው ናቸውና መታሰቢያቸውን ከምድር ያጠፋ ዘንድ የእግዚአብሔር ፊት ክፉን በሚያደርጉ ላይ ነው፡፡›› መዝ. 33፥15 ‹‹እጆችህ ሠሩኝ አበጃጁኝም›› መዝ. 118፥73 ኢሳይያስም ‹‹እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፡- ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት ›› ብሏል ኢሳ. 66፥1 ለአብርሃም በመምሬ አድባር ዛፍ ስር ዘፍ.18፥1-4 ለዮሐንስ በዮርዳኖስ ተገልጸዋል ማቴ. 3፥16-17
ሐ. የግብር ሦስትነት፡- የአብ ግብሩ መውለድ ማሥረጽ፣ የወልድ ግብሩ መወለድ፣ የመንፈስ ቅዱስ ግብሩ መሥረጽ ነው፡፡ አብ ቢወልድ ቢያሠርጽ እንጅ እንደ ወልድ አይወለድም እንደመንፈስ ቅዱስ አይሠርጽም፣ ወልድም ቢወለድ እንጂ እንደ አብ አይወልድም አያሠርጽም እንደ መንፈስ ቅዱስ አይሠርጽም፣ መንፈስ ቅዱስም ቢሠርጽ እንጅ እንደ አብ አይወልድም አያሠርጽም እንደ ወልድ አይወለድም፡፡ አብን ወላዲ አሥራጺ ወልድን ተወላዲ መንፈስ ቅዱስን ሠራጺ ስላልን የሚበላለጡ አይደሉም አንድ ናቸው፡፡ ጌታ አንድነታቸውን ሲያጠይቅ ‹‹እኔ እና አብ አንድ ነን›› ብሏል፡፡ ዮሐ. 10፥30 አባ ሕርያቆስም በቅዳሴ ማርያም ‹‹ኢይልህቅ አብ እም ወልዱ ወልድኒ ኢይልህቅ እምመንፈስ ቅዱስ ወመንፈስ ቅዱስኒ ኢይንዕስ እምወልድ ወወልድኒ ኢይንዕስ እምአቡሁ›› ብሏል፡፡ ይህ ማለት ሦስት አምላክ ማለት አይደለም፡፡ አንድ አምላክ ይባላሉ አንጂ፡፡ አባ ሕርያቆስም በቅዳሴ ማርያም‹‹ወመለኮትሰ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ›› ብሏል፡፡
ምሳሌም፡- ፀሐይ ክበብ ሙቀት ብርሃን፤ እሳትም ነበልባል ፍሕም ሙቀት አላቸው፡፡ ነገር ግን አንድ ፀሐይ አንድ እሳት ቢባሉ እንጅ ሦስት ፀሐይ ሦስት እሳት አይባሉም፡፡
እንዲሁ ሥላሴም በአካል በግብር በስም ሦስት ቢባሉም ቅሉ አንድ አምላክ እንጂ ሦስት አማልክት አይባሉም፡፡
~~~~~~~~~~~
፪/2. የሥላሴ አንድነት
~~~~~~~~~~~
ሥላሴ በባሕርይ በህልውና በመለኮት በሥልጣን በፈቃድ አንድ ናቸው፡፡
የህልውና አንድነታቸው፡- በአብ ልቡናነት ወልድ መንፈስ ቅዱስም ያስባሉ፤ በወልድ ቃልነት አብ መንፈስ ቅዱስም ይናገራሉ፤ በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስነት አብ ወልድም ህልዋን ሆነው ይተነፍሳሉ፡፡ ‹‹አሐዱ ህላዌሆሙ ለሥላሴ እንዘ ይሄልው በበአካላቲሆሙ ወዕሩያን እሙንቱ በህልውና አብኒ ልቦሙ ለወልድ ወለመንፈስ ቅዱስ፣ ወልድኒ ቃሎሙ ለአብ ወለመንፈስ ቅዱስ፣ ወመንፈስ ቅዱስ,ኒ እስትንፋሶሙ ለአብ ወለወልድ›› አንዲል ሃይማኖተ አበው
ቅድስት የሚል የሴት ቅጽል የተቀጸለላቸው ባሕርያቸው ታይቶ ነው፡፡
- ልጅ ከእናቱ ባሕርይ እንዲገኝ ይህም ዓለም ከሥላሴ ባሕርይ ተገኝቷልና፤
- እናት ለልጇ የሚያሻውን አስባ እንድታቀርብለት ሥላሴም ለፍጥረት ሁሉ የሚያስፈልገውን ሁሉ አስቀድመው ያዘጋጁለታል ይሰጡታልም፡፡ ማቴ. 6፥32
- አንድም እናት ልጇ ቢያስቀይማት ፈጽማ እንዳትጣላው ሥላሴም ሠርቀው አመንዝረው ቢበድሏቸው ንስሓ ገብተው ቀኖና ይዘው ቢለምኗቸው ይቅር ይላሉና፡፡ማቴ. 6፥14
ሥላሴ የሚታየውንና የማይታየውን ሁሉ ካለመኖር ወደመኖር አምጥተው የፈጠሩ ሕማም ድካም የማይሰማቸው በሞት የማይለወጡ ገዥ ፈጣሪ ናቸው፡፡ ሥላሴ እንደዛሬ ሁሉ ዓለም ሳይፈጠር አስቀድሞ ባሕርያቸው ባሕርያቸውን ሲያመሰግን ይኖር ነበር ኋላ ግን ሰውና መላእክትን ስማቸውን ለመቀደስ ክብራቸውን ለመውረስ ፈጠሩ፡፡ ሌላውን ግን ለአንክሮ ለተዘክሮ ለምግበ ሥጋ ለምግበ ነፍስ ፈጥረውታል፡፡
የመጀመሪያዎቹ ሰዎች አዳም እና ሔዋን በገነት 7 ዓመት ከ1ወር ከ17 ቀን በገነት ኖረው በዕፀ በለስ ምክንያት ከገነት ወጥተው በምድረ ኤልዳ ተቀመጡ፡፡ ኩፋ. 5፥6 ሥላሴም ‹‹ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉአት›› ብለዋቸው ወልደው ተዋልደው በዙ፡፡ የእነሱ ዐሥረኛ ትውልድ ኖኅ ይባላል፡፡ በዘመኑ የሰው ልጆች ምድርን በኃጢአት አረከሷት፡፡ ሥላሴ ኖኅንና 7 ቤተሰቦቹን አስቀርተው ሌላውን የሰው ዘር በንፍር ውኃ አጠፉት፡፡ ዘፍ. 7 እና 8 ከዚህ በኋላ የኖኅ ልጆች ወልደው ተዋልደው ብዙዎች ሆኑ፡፡
በባቢሎንም የነበሩ በሰናዖር ምድር ሰፊ ሜዳ አግኝተው ሳንሞት ስም ማስጠሪያ ግንብ እንገንባ ብለው መክረው ታላቅ ግንብ ገነቡ፡፡ አለቃቸው ናምሩድ ይባላል እሱም ሞትን የሚያመጡብን ሥላሴ ናቸውና እነርሱን ወግተን ሞትን እናርቅ አላቸው፡፡ ከዚያ ጦር እየሰበቁ ይወረውሩ ጀመር ሰይጣንም ከደመና በምትሀት ደም እየቀባ ይልክላቸዋል፡፡ እነሱም ደሙን እያዩ አሁን አብን ወጋነው አሁን ወልድን ወጋነው ይሉ ጀመር፡፡ ሥላሴ ምንም እንኳ ምሕረታቸው የበዛ ቢሆኑም ዲያብሎስ ስለሠለጠነባቸው ‹‹ኑ እንውረድ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው›› ብለው ቋንቋቸውን ለያዩባቸው፡፡ ውኃ ሲለው ጭቃ ጭቃ ሲለው ደንጊያ የሚያቀብለው ሆነ እንዲህ የማይግባቡ ቢሆኑ ተበታትነዋል፡፡ ባለማስተዋል የሠሩትንም ሕንፃ ዓመጻ ነፋስ ጠራርጎ አጥፍቶታል፡፡ ዘፍ. 11፥1-9
በዘመነ አብርሃምም የሰዶምና ገሞራ ሰዎች ወንድ ከወንድ እስከመጋባት ድረስ ኃጢአት ሠሩ እግዚአብሔርን በደሉ፡፡ የአብርሃም የወንድም ልጅ ሎጥ በዚያ ይኖር ነበር፡፡ ሊያድኑት ቢሹ ሁለቱን መላእክት ልከው እግዚአብሔር ሰዶምና ገሞራን አጠፋለሁ ብሏልና ሚስትህንና ልጆችህን ይዘህ ወደ ዞዓራ ሂድ ስትሄድም ወደ ኋላ ዙረህ አትመልከት አሉት፡፡ ማልዶ ተነሥቶ ሚስቱንና ልጆቹን ይዞ ከከተማው ወጣ፡፡ ሰዶምና ገሞራ ባሕረ እሳት ሆኑ፡፡ የሎጥ ሚስት ወይኔ ሀገሬ ብላ መለስ ብትል የጨው ሐውልት ሁና ቀርታለች፡፡ ዘፍ. 19፥1-29
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
በኋላ ግን እንደፈቃድህ›› አለው፡፡ቅዱሳን ከውዳሴ ከንቱ ለመሸሽ ሲሉ በሕይወት እያሉ በጎ ሥራቸውን መደበቅ ልማዳቸው ነው፡፡የአቡነ መልክአ ክርስቶስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
ከገድላት አንደበት
አስክሬናቸውን ከወደቀበት እየሰበሰበች በሥውር ደብቃ ያኖረችውን አንዲት ሴትም አብረው ከሰማዕታቱ ጋር ቀበሯት፡፡ የቅድስት ሶፍያና የልጆቿም የዕረፍታቸው ቀን መስከረም 5 ነው፡፡ የሰማዕታቱ የቅድስት ሶፍያና የልጆቿ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
+ + + + +
አቡነ አሮን ዘመቄት፡- የመቄቱ አቡነ አሮን ወላጅ አባታቸው የላስታው ጻድቁ ንጉሥ ዐፄ ገብረ መስቀል ናቸው፡፡ እናታቸው አመተ ማርያም ይባላሉ፡፡ የላስታ ነገሥታት የዘር ሐረጋቸው ከንጉሥ ሰሎሞን ዘር ሲያያዝ የመጣ ነው፡፡ ከ10ኛው እስከ 13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን (920-1253 ዓ.ም ገደማ) በላስታ ቡግና ምድር የነገሡ የላስታ ቡግና ተወላጅ የሆኑ የኢትዮጵያ ቅዱሳን ነገሥታት የንግሥናቸው መጠሪያ ‹‹የዛጉዌ ሥርወ መንግሥት›› ወይም ‹‹የላስታ መንግሥት›› በመባል ይታወቃል፡፡ የንጉሥ ሰሎሞን ዘር የሆነው መራ ክርስቶስ 3 ልጆችን ወለደ፡፡ እነርሱም ጠንጠውድም፣ ግርማ ስዩምና ዣን ስዩም ናቸው፡፡ጠንጠውድም ገብረ መስቀልን ወለደ፣ ገብረ መስቀልም አቡነ አሮንን ወለደ፣ግርማ ስዩም ይምርሐነ ክርስቶስን ወለደ፣ ዣን ስዩም ደግሞ ገብረ ማርያምንና ላሊበላን ወለደ፡፡ ገብረ ማርያምም ነዓኲቶ ለአብን ወለደ፡፡ እነዚህ ቅዱሳን ነገሥታት እንደ መልከጼዴቅ (ዘፍ14፡18) ክህነትን ከንግሥና፣ ቅድስናን ከንጽሕና ጋር አንድ አድርገው በመያዝ እግዚአብሔርንም ሕዝብንም በቅድስናና በንጽሕና አገልግለው አልፈዋል፡፡አቡነ አሮን ግን ገና በ7 ዓመታቸው ነው ዓለምን ፍጹም ንቀው በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል እጅ የመነኮሱት፡፡ በ16 ዓመታቸውም ዋልድባ ገዳም ገብተዋል፡፡ ነሐሴ 5 ቀን ገና ሲወለዱ ሙት አስነሥተዋል፡፡ በሀገራችን እየተዘዋወሩ ወንጌልን ሲሰብኩ የሸዋው ንጉሥ አንኮበር ድረስ ጠርቷቸው ሲሔዱ አዋሽ ወንዝ ሞልቶባቸው አገኙት፡፡ ሲሻገሩም ዳዊታቸውን ወሰደባቸው፡፡ ‹‹ልጆቼን አመነኮስክብኝ›› በሚል ሰበብ ንጉሡ 7 ዓመት በግዞት አስሮ አስቀመጣቸው፡፡ነገር ግን ከ7 ዓመት በኋላ አቡነ አሮን ተመልሰው በአዋሽ ወንዝ ሲመጡ መልአክ መጣና ‹‹መቋሚያህን ወደ ወንዙ ላክ›› አላቸው፡፡ መቋሚያቸውንም ቢልኩ ከ7 ዓመት በፊት ወደ ወንዙ ገብቶባቸው የነበረውን ዳዊታቸውን ይዘው አወጡ፡፡ ዳዊቱም በውኃው አልራሰም ነበር፣ ይልቁንም አቧራውን አራግፈው ፈጣሪያቸውን አመስግነው ዳዊታቸውን ይዘው ሄደዋል፡፡ ያ ዳዊታቸው ዛሬም ድረስ በጋይንት አበርጉት ቅዱስ ሚካኤል ይገኛል፡፡ሰሜን ወሎ መቄት ወረዳ ውስጥ የሚገኘው እጅግ አስደናቂ ገዳማቸው ፍልፍል ዋሻ ሲሆን ጣራው ክፍት ነው፣ ክፍት በሆነው ጣራ በኩል ፀሐይ ሲገባ ስለሚያቃጥል ጥላ ይይዛሉ ነገር ግን የጻድቁ ግዝት ስላለበት ዝናብ ወደ መቅደሱ ፈጽሞ አይገባም፡፡ እጅግ አስደናቂ ነው፡፡ አቡነ አሮን በዋድላ ሜዳ አልፈው ሲሄዱ በዚያችም ሜዳ ላይ እንደ ኢያሱ ፀሐይን በቃላቸው ገዝተው አቁመዋታል፡፡ ከታች ጋይንት ተነሥተው መንገድ ሲሄዱ በሰንበት ቀን በሬ ጠምዶ ሲያርስ የነበረን ገበሬ ‹‹ለምን በሰንበት ታርሳለህ?›› ቢሉት ‹‹ምቀኛ መነኩሴ›› ብሎ በጅራፉ ቢገርፋቸው በሬዎቹ ግን ፈጽሞ አልንቀሳቀስ ብለው ቆመዋል፡፡በዚህ የተናደደው ገበሬም አቡነ አሮንን መሬት ላይ ጥሎ ገረፋቸው፡፡እሳቸውም ተነሥተው ሲሄዱ ዛፎች ተነቅለው እየተከተሏቸው፣ ቃልም አውጥተው በሰው አንደበት አመስግነዋቸዋል፡፡የአቡነ አሮን መንክራዊ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
+ + +
አቡነ መልክአ ክርስቶስ:-የአቡነ መልክአ ክርስቶስ አባት ጣዕመ ክርስቶስ እናታቸው አውጋንያ ይባላሉ፡፡ እነርሱም ልጅ አልነበራቸውምና የተባረከ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ዘወትር ወደ እግዚአብሔር ይማጸኑ ነበር ነገር ግን ‹‹የተባረከ
ፍሬ የማትሰጠን ከሆነ ልጅ አትስጠን›› እያሉም ይጸልዩ ነበር፡፡ጣዕመ ክርስቶስና አውጋንያ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፣ ሕጉን ዘወትር የሚጠብቁ፣ለተቸገሩ የሚራሩ ናቸው፡፡ የተራቡትን በመመገብ የታረዙትን በማልበስ የበረቱ በመሆናቸው ዘወትር ከቤታቸው ድኆች አይጠፉም ነበር፡፡ የቅዱሳኑን ልመና የተቀበለ አምላክ የእነርሱንም ልመናቸውን ሰምቶ የተባረከ ልጅ አቡነ መልክአ ክርስቶስን ሰጣቸው፡፡ አባታችን በምድረ ኢትዮጵያ ሳርካ በሚባል ቦታ ሰኔ 26 ተፀንሶ መጋቢት 27 ቀን ተወለደ፡፡ዕድሜውም ለትምህርት ደርሶ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሲማር ከዕለታት በአንድ ቀን ከሕፃናት ጋር ሲጫወት እመቤታችን ተገልጻለት ‹‹ልጄ ከእንግዲህ አንተ የምትጫወተው ከቅዱሳን መላእክት፣ ከጻድቃንና ከሰማዕታት ጋር ይሁን›› አለችው፡፡ እርሱም
ዘወትር ጸሎትን መጸለይ ጀመረ፡፡መንፈስ ቅዱስ ስለገለጠለት የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ወድያው አጠናቀቀ፡፡ከዚኽም በኋላ አቡነ መልክአ ክርስቶስ ገና በለጋ ዕድሜው ስለ ጌታችን መስክሮ ሰማዕት ይሆን ዘንድ በመመኘት በዘመኑ ሰማዕታት ሰማዕትነትን ከሚቀበሉባቸው ቦታዎች ቢሔድም ሰማዕትነት ለእርሱ አልተፈቀደለትም ነበር፡፡ወደ ወግዳ እና ምድረ ሰርማት የሚባሉ ቦታዎች ቢሔድም የተመኘውን ሳያገኝ ቀረ፣ በዚኽም ጊዜ ቃል ከሰማይ ወደ እርሱ መጣና ‹‹ወዳጄ መልክአ ክርስቶስ ሆይ! ሰማዕትነት ክፍልህ አይደለም ይልቁንም እንደ አብርሃም የብዙሃን አባት የሕፃናትና የደካሞች መጠጊያ ትሆናለህ›› አለው፡፡ከዚኽም በኋላ ጻድቁ በመንዝ፣ በጎንደር፣ በመቄት፣ በዳውንት፣ በላስታ፣በዋድላና በሌሎቹም ቦታዎች ተዘዋውሮ የከበረች ወንጌልን በመስበክ ድዉያንን በመፈወስ ብዙ አገልግሏል፡፡ መንዝ ሪቅ በሚባል ቦታ አቅም የሌላቸውን በዕድሜም የገፉትን እናቶችንና አባቶችን ውኃ በመቅዳት ምግብ በማብሰል ዕንጨት በመሸከም አገለገላቸው፡፡ እንግዶች ሲመጡ እግራቸውን አጥቦ ያሳርፋቸዋል፡፡ሥራዎችን በሚሠራ ጊዜም ከአንደበቱ ጸሎት አይቋረጥም ነበር፡፡
በእንዲህ ያለ ምግባር ዐሥር ዓመት ካገለገለ በኋላ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ደቀ መዝሙር ከሆነው ከአቡነ አኖሬዎስ ቤተ ክርስትያን ደብረ ጽጋጃ አባ ጴጥሮስ በተባለ መምህር እጅ መነኰሰ፡፡አባ ጴጥሮስም አቡነ መልክአ ክርስቶስን ካመነኰሰው በኋላ ወደ ቀደመ ቦታው ሔዶ በዚያ ያሉትን በክህነቱ እንዲያገለግላቸው እንዲያመነኵሳቸው መስቀል
ሰጥቶ ሸኘው፡፡ እርሱም ተጨማሪ 12 ዓመት አገልግሏቸው በአጠቃላይ 22 ዓመት ሲሞላው የእግዚአብሔር ጸጋ የበዛላት ወለተ ጽዮን ስታርፍ ፍትሐት አድርሶ ከቀበራት በኋላ ወደ ሌላ ቦታ በመሔድ የእግዚአብሔር መልአክ እየመራው ዳውንት ደረሰ፡፡ በዳውንት አጽፍት ሚካኤል ዘጠኝ ዓመት አገልግሎ ብዙዎችን አመነኰሰ፡፡ ከዚያም ወደ ሌላ ቦታ
እንዲሔድ እግዚአብሔር ነግሮት ሊሔድ ጉዞ ሲጀምር ድንጋዮች ዕፅዋቶች ከነበሩበት ተነሥተው ይከተሉት ጀመር፣