ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌺 መልካም 🌺🌻
🌻🌻 በዓል! 🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻💐💐💐🌻🌻
🌻🌺 እንኳን 🌺🌻
🌻🌹አደረሳችሁ🌹🌻
🌻🌻🌾🌾🌾🌻🌻
/channel/+Qf1iLKbD_bljNjg0
ቅዱስ ያሬድም ‹‹ኖትያት ነቢያት ራግናት ሐዋርያት›› በማለት ነቢያትን በዋናተኛ፣ ሐዋርያትን በጀልባ ቀዛፊ መስሎ ይናገራል፡፡ ከቀዛፊዎች ይልቅ ዋናተኞች ይደክማሉ፡፡ ዋናተኞች ውሃው አጥልቋቸው፣ መተንፈስ ተስኗቸው አንዳንዶቹ ከዳር ይደርሳሉ፤ አንዳንዶቹም በድካም በውሃ ውስጥ ሰጥመው ይቀራሉ፡፡ ቀዛፊዎች ግን ምናልባት ሞገድና ማዕበል ካላሰጋቸው በስተቀር ይህ ኹሉ ውጣ ውረድ የለባቸውም፤ በጀልባዋ የተመሰለችው ቤተ ክርስቲያን ለነቢያት በተስፋ እንጂ በአካላ አልተሰጠችም፡፡ ነቢያት ከእርሷ ሳይደርሱ ሞት ቀድሟቸዋል፡፡ ሐዋርያትም በነቢያት ድካም ገብተው ነቢያት የዘሩትን የትንቢት ዘር አጭደዋል፡፡ ወንጌል የነቢያት ዘር ናት፤ ዳሩ ግን ፍሬውን ለመብላት የታደሉት ሐዋርያት ናቸው፡፡ እሸቱ ሲደርስ የገበሬዎቹ የነቢያት ጌታ ክርስቶስ ዘሩን እንዲሰበስቡና እንዲያከማቹ ሐዋርያቱን በእርሻ መካከል ይዟቸው ገብቷል /ማቴ.፲፪፥፩/፡፡ በአበው ፋንታ ውሉድን ለመተካት የመጣው መምህራችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነቢያትንና ሐዋርያትን በመስቀሉ አንድ ማኅበር አደረጋቸው፡፡ ሐዋርያው መስቀሉን ‹‹ገባሬ ሰላም›› በማለት ይጠራዋል /ኤፌ.፪፥፲፫/፡፡ ነቢያትንና ሐዋርያትን አንድ አድርጎ የእግዚአብሔርን መንግሥት ያወረሰ የክርስቶስ መስቀል ነውና፡፡
፪. ሙታንና ሕያዋን
አዳም በዕፀ በለስ ምክንያት የተሸከመው መስቀል ሞትን አምጥቶብናል፤ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ድኅነት ሲል የተሸከመው መስቀል ግን ሞትን ገድሎ ሕይወትን ሰጥቶናል፡፡ በዚህ ምክንያት የሞት መውጊያ ሲሰበር፣ የመቃብር ስቃይ ሲቋረጥ፣ የጨለማ ኀይል ሲሻር ከመስቀሉ ሥር ብዙ ሙታን እንደ አሸን ብቅ ብቅ አሉ፡፡ ምድር እስከዚያች ቀን ድረስ ሙታንን ትቀበል ነበር እንጂ ሕያዋንን ማስገኘት አትችልም ነበር፡፡ ሙታንና ሕያዋን የተፈላለጉበት መስቀል የመጀመሪያው ቀን ነው፡፡ በመስቀል ሙታን ሕያዋንን ፍለጋ ከመቃብር ወጥተው ወደ ከተማ ገቡ፡፡ ከታደለው የሕይወት ስጦታ የተነሣ ሞት አካባቢውን ለቆ ስለጠፋ በሩ እንደ ተከፈተለት እሥረኛ ሙታን ከመቃብር እየወጡ ከተማውን ሞልተውታል፡፡ ይህ ዕለት ሙታንን ከሕያዋን ጋር አፍ ለአፍ ያነጋገረ ዕለት ነው፡፡ ደመራው ሙታንን ከሕያዋን የሚለይ አይደለም፤ ታላቅነቱም እስከ ሲዖል ድረስ የሚታይ ነው፡፡
፫. ጻድቃንና ኀጥአን
የአዳም በደል በሕይወት የሚኖሩ ወንድማማቾችን በሁለት ሐሳብ ከፋፍሏቸው ነበር፡፡ የክርስቶስ የጽድቅ መስቀል ግን አንድ ሐሳብ ፈጠረላቸው፡፡ ጻድቁ አቤል ሳይበድል በደል የደረሰበት፣ ሳይገድል የተገደለ መኾኑ ከክርስቶስ ጋር ቢያመሳስለውም ሞቱ ግን ለሰው ልጆች ድኅነት አልጠቀመም፤ የፍጡር ደም ከእግዚአብሔር ጋር ሊያስታርቀን አይችልምና ኹላችንም በመከራ ውስጥ ለመቆየት ተገደናል፡፡ የክርስቶስ ሞት ግን የድኅነታችን መሠረት ኾነልን፡፡ በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ መብራት ከፍ ብሎ ሲቀመጥ ኹሉን እንዲያሳይ ከምድር ከፍ ብሎ የተሰቀለው ክርስቶስም ጻድቃነ ብሊትንና ጻድቃነ ሐዲስን በዓይን እንዲተያዩ አድርጓቸዋል፡፡ በመስቀል ላይ የተፈጸመው ዕርቅ የኀጥአንን በደል ደምስሶላቸዋል፤ የጻድቃንን ጽድቅ አረጋግጦላቸዋል፡፡ ጻድቃንም ኀጥአንም አንድ ኾነው መንግሥቱን በጸጋው ወረሱ፡፡ ኢያሱ በኢያሪኮ እንዳደረገው አሞራውያን ወጥተው እስራኤል ብቻ ምድሪቱን የወረሷት አይደሉም፡፡ መስቀሉ ለኹሉም አንድ መንግሥትን አውርሷቸዋል፤ ጊዜው የደመራ ነውና፡፡ በምድር ደምቆ የታየው ይህ ደመራ እስከ መንግሥተ ሰማያት ድረስም ይቀጥላል፡፡
ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ
ኪዳነ ምህረት
እንኳን ለወርሃዊው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የቃል ኪዳን መታሰቢያ /ኪዳነ ምህረት/ በሰላም አደረሰን !!!
❤ እግዚአብሔር በየጊዜው በመንገዱ ከፀኑ ፣ በጽድቅ ከተመላለሱ ቅዱሳን ጋር ቃል ኪዳን እንደገባ መጻሕፍት ያስተምሩናል
❤ ቃል ኪዳን ትርጓሜውም "ውል፣ ስምምነት" ማለት ነው
❤ የዛሬው በዓልም ለእናቱ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቃል ኪዳን የገባላት ዕለት መታሰቢያ ነው
❤ ይህም ቅድስት ድንግል ማርያም በጎልጎታ እየሄደ በምትጸልይበት በአንዱ ቀን የካቲት ፩፮ ተፈፀመ
❤ ስሟን ለሚጠራ፣ ለድሆችና ለችግረኞች ቀዝቃዛ ውሃ ለሚሰጥ ከልጇ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ የምህረት ቃል ኪዳን ተቀብላለች
❤ ስሟን የጠራ ሲባል፦
➻ በጸሎቱ በእርሷ የተደረገለትን የአምላክ ቸርነት እያሰበ ዘወትር በእምነት ፀንቶ በጎ ምግባርን እየፈጸመ የሚኖር ማለት ነው
❤ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ዘወትር ጸንቶ የሚኖር ነውና ላመነው ሁሉ ይሆንለታል
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቃል ኪዳን ለእኛም ይሁንልን። በበጎ ምግባር እንድንኖር ይርዳን።
#አንዲት_ሐይማኖት_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ
#አንዲት_ቤተክርስቲያን
#ቅዱሳን
#አንዲት_ጥምቀት
#ተዋህዶ
#orthodoxchurch
#ኢትዮጵያ
#ግእዝ_geez_ገጽ
ሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስ
እንኳን ለቅዱስ ሚናስ ወርሃዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን !!!
✝️ ቅዱስ ሚናስ ከደጋግ ክርስቲያን ቤተሰቦች የተገኘ በ፫ኛው ክፍለ ዘመን የነበር ቅዱስ ነው
✝️ ቅዱስ ሚናስ የስሙ ትርጓሜ "ታማኝና ብሩክ" ማለት ሲሆን እንደ ስሙም ለክርስቶስ ታምኖ የኖረ ጻድቅ ነው
✝️ በልጅነቱ ቤተሰቦቹ ሲሞቱ የወረሰውን ሀብትና ንብረት ለድሆች አካፍሎ መነነ
✝️ በገዳምም በርትቶ አምላኩን ማምለክና ማመስገንን አጥብቆ ቀጠለ
✝️ በዘመኑ በነበሩ የጣኦት አምላኪዎች ተይዞ ለጣኦታት አልሰግድም በማለቱ በ፳፬ ዓመቱ መስዋዕትነትን ተቀበለ
የሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስ ምልጃና በረከት ይደርብን። እኛንም ለመንግሥቱ የቀናን ያድርገን።
#አንዲት_ሐይማኖት_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ
#አንዲት_ቤተክርስቲያን
#አንዲት_ጥምቀት
#ቅዱሳን
#ተዋህዶ
#orthodoxchurch
#ኢትዮጵያ
መስከረም 14/2017 #ፃድቁ_አባታችን_አቡነ_አረጋዊ
#ፃድቁ_ገብረ_ክርስቶስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሳኑ ስም ለምናመሰግንበት ለቅዱሣን አባቶቻችን #አቡነ_አረጋዊ እና #ፃድቁ_ገብረ_ክርስቶስ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአላቸው እንኳን አደረሰን
👉በሃገራችን ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ እኒህ ጻድቅ ናቸው ፃድቁ የተወለዱት በአምስተኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ ኣካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ንጉሥ #ይስሐቅና ቅድስት #አድና ይባላሉ የተለወለዱበት አካባቢም ሮም ነው
👉ስማቸው ብዙ ዓይነት ነው ወላጆቻቸው #ዘሚካኤል ሲሏቸው በበርሃ #ገብረ_አምላክ ተብለዋል በኢትዮዽያ ደግሞ #አረጋዊ ይባላሉ #አቡነ_አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መፃሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ
👉በዚያም በገዳመ ዳውናስ ግብፅ የታላቁ #ቅዱስ_ዻኩሚስ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል ከመነኮሱ ከዓመታት በኋላም ወደ ሃገራቸው ሮም ተመልሰው በማስተማር ሰባት ያህል የቤተ መንግስት ሰዎችን ወደ ምናኔ ማርከዋል
👉የት ልሒድ ብለው ሲያስቡም መልአክ በክንፉ ጭኖ ወስዶ ኢትዮዽያን አሳያቸው ተመልሰውም ለስምንቱ ባልንጀሮቻቸው ሃገርስ ባሳየሁዋችሁ ሐዋርያ ሳያስተምራት በሕጉ በሥርዓቱ ፀንታ የምትኖር ብለው ከስምንቱ ጋር ወደ #ኢትዮዽያ መጡ
👉በዚህ ጊዜም እናታቸው ቅድስት እድናና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ ወደ ሃገራችን የመጡ በ470ዎቹ አካባቢ ሲሆን አልዓሜዳ በክብር ተቀብሏቸዋል በቤተ ቀጢን #አክሱም ተቀምጠውም መጻሕፍትን እየተረጐሙ ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል
👉ለሥራ በተለያዩ ጊዜም #አቡነ_አረጋዊ በዓት ፍለጋ ብዙ ደክመዋል በመጨረሻ ግን ደብረ ዳሞን (ደብረ ሃሌ ሉያን) አይተው ወደዷት የሚወጡበት ቢያጡም ጅራቱ 60 ክንድ የሚያህል ዘንዶ ተሸክሞ ከላይ አድርሷቸዋል
👉እንደ ወጡም #ሃሌ_ሉያ_ለአብ፤#ሃሌ_ሉያ_ለወልድ #ሃሌ_ሉያ_ለመንፈስ_ቅዱስ ብለው ቢያመሰግኑ ከሰማይ ሕብስት ወርዶላቸው ተመግበዋል በዚህም ቦታዋ ደብረ #ሃሌ_ሉያ ተብላለች ፃድቁ ቦታውን ከገደሙ በኋላ ከተለያየ ቦታ መጥተው ስድስት ሺ ያህል ሰዎች በእጃቸው መንኩሰዋል
👉ምናኔን በማስፋፋታቸውና ሥርዓቱን በማስተማራቸውም #የኢትዮዽያ_መነኮሳት_አባት ይባላሉ #አቡነ_አረጋዊ በሕይወታቸው ከተጋድሎ ባሻገር በወንጌል አገልግሎትና መጻሕፍትን በማዘጋጀትም ደክመዋል::
👉 #ቅዱስ_ያሬድና አፄ ገብረ መስቀልም ወዳጆቻቸው ነበሩ በተራራው ግርጌ ያለችውን #ኪዳነ_ምሕረትን ለሴቶች ሲገድሟት ቀዳሚዋ መነኮስ እናታቸው ንግስት እድና ሁናለች
👉ፃድቁ ንጹሕ ሕይወታቸውን ፈጽመው በተወለዱ በ99 ዓመታቸው በዚህ ቀን በገዳሙ በስተምሥራቅ አካባቢ ተሰውረው #ብሔረ_ሕያዋን ገብተዋል ጌታም አስራ አምስት ትውልድን የሚያስምር የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል ረድኤት በረከታቸው ይደርብን
👉ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል #ፃድቅን_በፃድቅ_ስም የሚቀበል የፃድቁን ዋጋ ይወስዳል ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላቹሃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም ማቴ.10 ቁ.41
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ የቅዱሣን አባቶቻችን #የአቡነ_አረጋዊ እና የመናኙ ፃድቅ የቅዱስ #ገብረ_ክርስቶስን በረከታቸዉን ያሣድርብን ፀሎታቸዉ ልመናቸው ሀገራችንን ይጠብቅልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
መስከረም 14-ዓለምን ንቀው ከመመንኮሳቸው በፊት የቀዳማዊው ንጉሥ የዓምደ ጽዮን ልጅ የነበሩና ድንጋዩን እንደ ጀልባ ተጠቅመው የጣናን ሐይቅ የተሻገሩት የማንዳባው አቡነ ያሳይ ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ አምሳ ዓመት በዓምድ ላይ ቆሞ ሲጸልይ የኖረው አቡነ አጋቶን ዘአምድ ዕረፍቱ ነው፡፡
+ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት እጆቻቸው እንደፋና እያበሩ ለጣና ሐይቅ ገዳማት በመብራትነት ያገለግሉ የነበሩት ኢትዮጵዊው አቡነ ጴጥሮስ ዕረፍታቸው ነው፡፡
አባ አጋቶን ዘአምድ፡- ከደቡባዊ ግብጽ የተገኘ ታላቅ ጻድቅ ነው፡፡ አባቱ መጥራ እናቱ ማርያ ይባላሉ፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ተምሮ በቅስና ሲያገለግል ከኖረ በኋላ መርዩጥ ወደምትባል አገር ሄደ፡፡ ከዚያም ከእግዚአብሔር የታዘዘ ቅዱስ መልአክ በመነኩሴ አምሳል ተገልጦ ወደ መቃርስ ገዳም አስቄጥስ አስገባውና መነኮሰ፡፡ በዚያም አረጋዊያን መነኮሳትን እነ አባ ገዐርጊን እያገለገለ ሥጋው ከቆዳው እስኪጣበቅ ድረስ እየጾመ ያለምንም ምንጣፍ ይተኛ ነበር፡፡ ሁልጊዜም የአባ ስምዖን ዘአምድን ገድል ያነብ ስለነበር ከገዳሙ ተሰናብቶ ወጥቶ ዓምድ ሠርቶ በላዩ ወጥቶ ለ50 ዓመት ቆሞ ሲጸልይ የኖረ ታላቅ አባት ነው፡፡ ጋኔን እያደረባቸው ቅዱሳን ተገለጡልኝ የሚሉ አሳቾችን ወደ እርሱ እያስመጣቸው በውስጣቸው ያደረውን ጋኔን ያወጣላቸው ነበር፡፡ አባ አጋቶን በመላእክት አምሳል ሆነው መልካም ዝማሬን እየዘመሩ ሰይጣናት ተገልጠውለት ሳለ አማትቦ ድል አድርጓቸዋል፡፡ ይህም ጻድቅ እስከ 35 ዓመቱ በዓለም እየኖረ እግዚአብሔርን አገለገለ፤ ለ15 ዓመታት በገዳም በታላቅ ተጋድሎ ኖረ፤ ቀሪውን 50ውን ዓመት ደግሞ በዓምድ ላይ ተተክሎ በጸሎት ሲያመሰግን ኖረ፡፡ እጅግ አስደናቂ ተአምራትን በማድረግና ወንጌልን በማስተማር ብዙ ካገለገለ በኋላ በ100 ዓመቱ በዚህች ዕለት በሰላም ዐረፈና ቅድስት ነፍሱን አስረከበ፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡
+ + + + +
አቡነ ጴጥሮስ ቀዳማዊ፡- አቡነ ጴጥሮስ ቀዳማዊ የተባሉት ጻድቅ ትውልድ ሀገራቸው ሸዋ ቡልጋ ልዩ ስሙ ደብረ ጽላልሽ ነው፡፡ ጻድቁ በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን ለ48 ዓመታት የቅዱስ ገላውዲዮስን ቤተ ክርስቲያን ሲያጥኑ ኖረዋል፡፡ ከተሰዓቱ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት አቡነ ሊቃኖስ እጆቻቸው እያበሩ ለገዳሙ መብራትነት ይጠቀሙባቸው እንደነበረው ሁሉ የአቡነ ጴጥሮስ ቀዳማዊም እጆቻቸው እንደፋና እያበራ ለጣና ሐይቅ ገዳማት በመብራትነት ያገለግል ነበር፡፡ ጻድቁ ለ31 ዓመታት ከመላእክት ጋር እየተነጋገሩ የኖሩ ሲሆን መናም ከሰማይ እያወረዱ መነኮሳቱን ይመግቡ ነበር፡፡ ድውያንን በመፈወስ፣ ሙታንን በማንሣት ብዙ አስደናቂ ተአምራት እያደረጉ ወንጌልን በሀገራችን ዞረው በማስተማር እግዚብሔርን ሲያገለግሉ ኖረው በዚህች ዕለት በሰላም ዐርፈው ቅድስት ነፍሳቸውን ቅዱሳን መላእክት በክብር ተቀብለዋታል፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡
+ + + + +
አቡነ ያሳይ ዘማንዳባ፡- አቡነ ያሳይ ‹‹ሰባቱ ከዋክብት›› ከሚባሉት የሀገራችን ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ እነዚህም ‹‹ሰባቱ ከዋክብት›› የተባሉት አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ አቡነ ያሳይ ዘማንዳባ፣ አቡነ ሳሙኤል ዘቆየፃ፣ አቡነ ሳሙኤል ዘጣሬጣ፣ አቡነ ታዴዎስ ዘባልታርዋ፣ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤ እና አቡነ ዮሐንስ ዘጉራንቄ ናቸው፡፡ እነዚህን የመላእክትን ሕይወት በምድር የኖሩ ታላላቅ የሀገራችንን ቅዱሳን በአንድ ጊዜ አስተምረውና አመንኩሰው ለጽድቅ ያበቋቸው አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ናቸው፡፡ ‹‹ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን›› የተባሉት አቡነ መድኃኒነ እግዚእ የኢትዮጵያ ብርሃኗ በሆኑት በአቡነ ተክለ ሃይማኖት እጅ ከመነኮሱ በኋላ አቡነ መድኃኒነ እግዚእም በተራቸው ያስተማሯቸውና ያመነኮሷቸው መነኮሳት ቁጥራቸው በውል አይታወቅም፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ለአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ‹‹ስፍር ቁጥር የሌላቸው ከዋክብት ቅዱሳንን›› በመንፈስ ቅዱስ እንደሚወልዱ ትንቢት ተናግረውላቸው ነበር፡፡ የተንቤኑን አቡነ ዐቢየ እግዚእን፣ የዞዝ አምባውን አቡነ አብሳዲን ጨምሮ አባታችን መድኃኒነ እግዚእ ብርሃን ሆነው በጣም ብዙ ቅዱሳንን የለኮሱ ታላቅ ጻድቅ ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ነው ‹‹ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን›› የተባሉት፡፡
አቡነ መድኃኒነ እነዚህንም ሰባቱን ቅዱሳን በአንድ ጊዜ ሲያመነኩሷቸው በዚያው ቅጽበት መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ገዳሙን በብርሃን አጥለቅልቆት ታይቷል፡፡ ከሰማይም የምስክርነት ድምፅ ተሰምቷል፡፡ በዚህም ምክንያት አንድ ላይ የመነኮሱት እነዚህ ሰባቱ ቅዱሳን ‹‹ሰባቱ ከዋክብት›› እየተባሉ ይጠራሉ፡፡ እነዚህም ሰባቱ ከዋክብት የጣናን ባሕር በእግራቸው ጠቅጥቀው ተሻግረው ብዙዎቹን ደሴቱ ላይ ያሉ አስደናቂ የጣና ገዳማትን የመሠረቱት ናቸው፡፡ ከእነርሱም ውስጥ ባሕሩን በእግራቸውም እየረገጡ ጠቅጥቀው የተሻገሩ አሉ፤ በሌላም ቦታ በየብስ የተሰማሩትም ቢሆኑ መጻሕፍቶቻቸውን በአንበሳ ጭነው የተጓዙ አሉ፤ ትልቅ ጠፍጣፋ ድንጋይን እንደጀልባ ተጠቅመው በእርሱ ላይ ሆነው ወደ ደሴት የገቡ አሉ፡፡ አንዱ ዛሬ በዓላታቸውን የምናከብራለቸው አቡነ ያሳይ ናቸው፡፡
ቅዱስ ዳዊት ‹‹እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው›› (መዝ 67፡35) ብሎ እንደተናገረ ጻድቁ አቡነ ያሳይ ከእግዚአብሔር በተሰጣቸውም ጸጋ ጣና ሐይቅን የሚያቋርጡት በአንድ ትልቅ ጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ ተቀምጠው ድንጋዩን እንደ ጀልባ ተጠቅመው ነበር፡፡ ያ ድንጋይ ዛሬም ድረስ በገዳማቸው ውስጥ በክብር ተቀምጦ ይገኛል፡፡ ጻድቁ ከአቡነ ሳሙኤል ጋር አብረው ወደዚህ ቦታ መጡ፡፡ ከዚያም የቦታው አቀማመጥ የብስ መሬትና ደሴት መሆኑን አይተው ‹‹እግዚአብሔር ፈቅዶ ይችን ደሴት የጸሎት ቦታችን አድርጎ ቢሰጠን በጸሎት እንጠይቀው›› ተባብለው ሁሉቱም ቅዱሳን ሱባኤ ገቡ፡፡ ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችንም ለአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ በገሃድ ተገልጦላቸው ‹‹ወዳጄ ሳሙኤል ሆይ ይህ ቦታ የአንተ አይደለም የወንድምህ የያሳይ ቦታ ነው፡፡ እኔ ወዳዘጋጀሁልህ ቦታ ወደ ዋሊ ሂድ›› ብሎ የዋልድባን ምድር አሳያቸው፡፡ አቡነ ሳሙኤልም የጌታችንን ትእዛዝ ተቀብለው ወንድማቸውን አቡነ ያሳይን ተሰናብተው ወደ ዋልድባ ሄደው ገዳማቸውን አቅንተው ተጋድሎቸአውን በዚያ ፈጸሙ፡፡
ጌታችን ዳግመኛም ለአቡነ ያሳይ ተገለጠላቸውና ‹‹ወዳጄ ያሳይ ሆይ የአባትህን መንግሥትና የዓለሙን ክብር ከምኞቱ ጋር ለእኔ ብለህ ስለተውክ ይህንኑ ቦታ በዚህ ዓለም ሳለህ ለአንተ፣ ወደ ዘላለማዊ መንግሥቴ ከወሰድኩህ በኋላም ለልጆችህ ምንዳህ አድርጌ ሰጥቼሃለሁ፤ ምሕረቴንም በቦታህ አዘንባለሁ ቸርነቴም አይለያትም፣ ብዙ የመንፈስ ልጆችንም ታፈራለህ፤ ቦታህም እኔ ለፍርድ እስክመጣ ድረስ ትኖራለች›› በማለት ቃልኪዳኑን አቆመላቸውና ተሰወራቸው፡፡ ‹‹ምንዳህ›› ማለት ደመወዝ ማለት ነውና በዚህም ‹‹ማንዳባ›› ማለት ‹‹የአቡነ ያሳይ ምንዳ-ደመወዝ›› ማለት ነው ሲሉ አባቶች ገዳሙን ‹‹ማንዳባ-ምን እንደ አባ›› ብለው ሰየሙት፡፡
ተፈሥሒ ኦ ወላዲተ እግዚእ ሐሤቶሙ ለመላእክት፡፡
የመላእክት ደስታቸው የሚሆን ጌታን የወለድሽው ተፈሥሒ ደስ ይበልሽ፡፡ ለሊሁ ዓለሞሙ ወለሊሁ ተድላሆሙ ወለሊሁ ሀገሮሙ እንዲል፡፡ አንድም ሥጋዌውን ተልከው ለነቢያት የሚነግሩ መላእክት ናቸው፡፡ ከዚህ የተነሣ ባጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ አይተውት ፤ ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ብለው አመስግነውት ፤ በጣዕም ላይ ጣዕም ፤ በጸጋ ላይ ጸጋ ተጨምሮላቸው ደስ ብሏቸዋልና አንድም የመላእክት ደስታቸው የምትሆኝ ጌታን የወለድሺው ተፈሥሒ ደስ ይበልሽ፡፡ ንጽሕናዋን ቅድስናዋን እያዩ ደስ ይላቸዋልና ሐሴቶሙ ለመላእክት አለ፡፡
ተፈሥሒ ኦ ድንግል ዜናሆሙ ለነቢያት፡፡
የነቢያት ዜና ትንቢታቸው ንጽሕት ተፈሥሒ ደስ ይበልሽ፡፡ ኦ ድንግል አምሳል ወትንቢት ፤ ዘነቢያት እንዲል፡፡
ተፈሥሒ እስመ ረከብኪ ሞገሰ እግዚአብሔር ምስሌኪ፡፡
እግዚአብሔር ከነፍስሽ ነፍስ ፤ ከሥጋሽ ሥጋ ነሥቶ ካንቺ ጋር አንድ ባሕርይ ሆኗልና፡፡ ተፈሥሒ ደስ ይበልሽ፡፡ አንድም እግዚአብሔር በጸጋ ቢያድርብሽ ባለሟልነትን አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ፡፡
ተፈሥሒ እስመ ተወከፍኪ ቃሎ ለመልአክ ፍሥሓ ኩሉ ዓለም፡፡
የሰው ሁሉ ደስታ የሚሆን የመልአኩን ቃል ፤ እንደ ኒቆዲሞስ ሳትከራከሪ እንደ ዘካሪያስ ሳትጠራጠሪ አምነሻልና ተፈሥሒ ደስ ይበልሽ፡፡ ሰብአ ፊንቆን ተወክፍዎ ፤ ወእለሰ ተወክፍዎ ወሀቦሙ ሥልጣነ እንዲል ፍሥሐ ኩሉ ዓለም ያለውን ለመልአክ ቢቀጥሉ ምስጋናው ተፈሥሒ ተፈሥሒ እያለ ነውና ቃል ላለው ቢቀጽሉ ወነዋ ተወልደ ፍሥሐ ዘይከውን ፣ ለክሙ ለኩሉ ዓለም ይለዋልና፡፡
ተፈሥሒ ኦ ወላዲተ ፈጣሬ ኩሉ ዓለም።
ሃያውን ዓለም የፈጠረ ጌታን የወለድሽው ተፈሥሒ ደስ ይበልሽ፡፡
ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡
ሃያውን ዓለም ከፈጠረ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን አይምዕሮውን ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን::
መስከረም 13/2017 #አምላካችን_እግዚአብሔር_አብ
#መልአኩ_ቅዱስ_ሩፋኤል
#ፃድቁ_ዘርዐ_ብሩክ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሳኑ ስም ለምናመሰግንበት ለመልአኩ #ለቅዱስ_ሩፋኤል እና ለፃድቁ #አቡነ_ዘርዐ_ብሩክ ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን
👉 #ቅዱስ_ሩፋኤል ቊጥሩ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሲኾን ሩፋ፤ ማለት ሐኪም፤ ኤል ማለት #እግዚአብሔር ማለት ሲኾን ሩፋኤል ማለት #እግዚአብሔር_ሐኪሜ ነው ማለት ነው፤ ሄኖክም በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” ይለዋል መጽሐፈ ሄኖክ.6፥3
👉ይኽ መልአክ በራማ ሰማይ ያሉ ነገደ መናብርትን የሚመራቸው ነው ነገደ መናብርት ያላቸው #ቅዱስ_ሩፋኤል የሚመራቸው በራማ ሰማይ የሚኖሩ ነገደ መላእክት ናቸው
👉ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በሥነ ፍጥረት መጽሐፉ ላይ ወለዳግም ፆታ ዐሠርቱ ስሞሙ መናብርት ወሊቆሙ #ሩፋኤል እሉ እሙንቱ እለ ይቀልል ሩጸቶሙ እምነፋስ ወእለ ይፀውሩ ወላትወ መብረቅ ወኲናተ እሳት ዘይነድድ ወአንበሮሙ በዳግሚት ሰማይ ይላል
👉በራማ ሰማይ የሚገኘውን ኹለተኛውን ዐሥሩን ነገድ መናብርት ሲላቸው አለቃቸው #ቅዱስ_ሩፋኤል ነው፤ እነዚኽም ረቂቅ የኾነ የመብረቅ ጋሻ የእሳት ጦር ይዘው ከነፋስ ይልቅ የፈጠኑ ሲኾኑ በራማ በኹለተኛው ክፍል ላይ አስፍሯቸዋል
👉#የእግዚአብሔር_አብ ቸርነት የልጁ የመድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ፍቅር #የመንፈስ_ቅዱስ አንድነት ከሁላችን ጋር ይሁን የመልአኩ #ቅዱስ_ሩፋኤል ጥበቃ የፃድቁ #አቡነ_ዘርአ_ብሩክ"ፀሎት አይለየን አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል
እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ወርሃዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን !!!
" እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ። በፊቱ ተጠንቀቁ፥ ቃሉንም አድምጡ፤ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት።
ዘጸ. ፳፫፥፳-፳፩ /23፥20-21/
❤ የመላእክትን ቅድስና፣ ሐያልነት፣ የተሰጣቸውን ስልጣን በመጽሐፍ ቅዱስ በተለያዩ ቦታዎች እናያለን
❤ ከእነዚህ መላእክት አንዱ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል አንዱ ነው፣ የመላእክት አለቃ
❤ የስሙም ትርጓሜ "እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው" ማለት ነው
❤ ቅዱስ ሚካኤል የሰማይ ሠራዊት ሁሉ አለቃቸው፣ ዲያቢሎስ ሊያደክማቸው ለሚፈልግ ሁሉ ብርታትን፣ ኃይልን የሚሰጥ መልአክ ነው
❤ በብሉይም፣ በሐዲስ ኪዳንም በአማላጅነቱ፣ ሕዝብን እየጠበቀ ያጸና መልአክ እንደሆነ መጽሐፍት ይነግሩናል
❤ ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር እየተላከ ታላላቅ ሥራዎችን የሠራ መልአክ ነውና "መልአከ ኃይል" ይባላል
እስራኤላውያንን ከጠላት ያዳነ፣ ቅዱሳንን በመንገዳቸው የመራ ይህ ታላቅ መልአክ እኛንም ይጠብቀን፣ አማላጅነቱም አይለየን
#አንዲት_ሐይማኖት_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ
#አንዲት_ቤተክርስቲያን
#አንዲት_ጥምቀት
#ተዋህዶ
#orthodoxchurch
#ኢትዮጵያ
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
መስከረም 10-የጌታችን ቅዱስ መስቀል አገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ የገባበት ዕለት ነው፡፡
+ ጸዴንያ በምትባል አገር ሥጋ የለበሰች ከምትመስል ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ከሣላት ሥዕል ከሠሌዳዋ ቅባት እየተንጠፈጠፈ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም ተአምር የተገለጠበት ዕለት ነው፡፡
+ ከከሃዲው ከሆሎፎርኒስ እጅ በጥበቧ እስራኤልን ያዳነቻቸው ጥበበኛዋ ዮዲት ዐረፈች፡፡
+ ቅድስት አትናስያና ሦስት ልጆቿ መታሰቢያ በዓላቸው ነው፡፡
+ ዳግመኛም በዚህችም ዕለት የከበረች ቅድስት መጥሮንያ በሰማዕትነት ዐርፋለች፡፡
ሰማዕቷ ቅድስት መጥሮንያ፡- ይህችውም ሰማዕት ቅድስት መጥሮንያ የአንዲት አይሁዳዊት ሴት አገልጋይ ነበረች፡፡ አሠሪዋ አይሁዳዊ ሴትም ቅድስት መጥሮንያን ክርስቲያን በመሆኗ ብቻ ሸክም ታበዛባትና ታንገላታት ነበር፡፡
ከሃይማኖቷም አውጥታ ጌታችንን ማመንን ልታስተዋት ብዙ ሞከረች፡፡ በአንዲት ዕለትም አይሁዳዊቷ ይዛት ወደ ምኩባራባቸው ሄደች፡፡ ቅድስት መጥሮንያ ግን ወደ ምኩራባቸው ሳትገባ ተመልሳ ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ጸሎት አደረገች፡፡ ወደ ቤታቸው ተመልሰው በገቡ ጊዜ አሠሪዋ ‹‹ወደ እኛ ምኩራብ ለምን አልገባሽም?›› ብላ ጠየቀቻች፡፡ ቅድስት መጥሮንያም ‹‹ከእናንተ ምኩራብ እግዚአብሔር ርቋልኮ፣ እንዴት ወደ እርሱ እገባለሁ! በውስጧ ልገባባት የሚገባኝ ቦታዬ ግን ክብር ይግባውና ጌታችን በከበረ ደሙ የዋጃት ይህች ቤተ ክርስቲያን ናት›› አለቻት፡፡ አሠሪዋ አይሁዳዊትም ከቅድስት መጥሮንያ ይህንን በሰማች ጊዜ እጅግ ተቆጥታ በኃይል ደበደበቻት፡፡ በጨለማ ቤት ውስጥ ዘጋችባትና ያለምግብና ያለመጠጥ ለ4 ቀን አሠረቻት፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ ውጭ አውጥታ በጅራፍ ታላቅ ግርፋትን ገርፋ ድጋሚ በእሥር ቤት ጣለቻትና በዚያው ተንገላታ ዐረፈች፡፡ ነፍሷንም እግዚአብሔር ተቀብሎ የሰማዕታትን አክሊል አቀዳጃት፡፡ አሠሪዋ ግን ሥጋዋን አውጥታ በመጣል በዚያም መጥሮንያ ራሷን የገደለች አስመሰለች፡፡ ቅድስት መጥሮንያ ራሷን የገደለች ስለመሰለ አይሁዳዊቷን ሴት ግን ማንም የመረመራት የለም፡፡ ነገር ግን ለተገፉ የሚፈርድ፣ ለተበደሉ የሚበቀል እውነተኛ ዳኛ ልዑል እግዚአብሔር ቁጣው በዚያች አይሁዳዊ ሴት ላይ ወረደ፡፡ ከደርቧ ላይ ስትወርድ ድንገት ወድቃ በዚያው ከመቅጽበት ሞተች፡፡ በነፍሷም ወደ ዘላለማዊ እሳት ሄደች፡፡
የቅድስት መጥሮንያ ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ ይማረን፡፡
+ + + + + +
ጼዴንያ ማርያም፡- ጼዴንያ በምትባል ሀገር ማርታ የምትባል ደግ ሴት ነበረች፡፡ ይህች ደግ ሴት በቤቷ ትልቅ አዳራሽ ሠርታ እንግዶችን እንደ አባታችን አብርሃም ተቀብላ አብልታ አጠጥታ ማደሪያ ቦታም ሰጥታ ታስተናግድ ነበር፡፡ አባ ቴዎድሮስ የሚባል ኢትዮጵያዊ መነኩሴ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ መሽቶበት ከማርታ ቤት በእንግድነት አደረና ጠዋት ሊሄድ ሲነሣ ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚሄድ ሲነግራት ‹‹የእመቤታችንን ሥዕል ገዝተህ አምጣልኝ ዋጋውን ልስጥህ›› አለችው፡፡ እርሱም ‹‹ገንዘቡን ሥዕሉን ሳመጣልሽ ትሰጪኛለሽ›› ብሏት ሄደ፡፡ ኢየሩሳሌምም ደርሶ ቅዱሳት መካናትን ተሳልሞ ሥዕሉን ረስቶ ሳይገዛ ሲመለስ «አደራ ጥብቅ አይደለምን? ያቺ ሴት አደራ ያለችህን ለምን ረሳህ» የሚል ድምፅ ሰማ፡፡ በጣም ደንግጦ ተመልሶ ሄዶ ገዝቶ በረሃ በረሃውን መጓዝ ጀመረ፡፡ በመንገድም እየተጓዘ አንበሳ ሊበላው እየሮጠ ወደ እርሱ ሲመጣበት አየ፡፡ መነኩሴው አንበሳውን ከመፍራት የተነሣ ደነገጠ፣ ተንቀጠቀጠ ደንግጦ ቁሞ ሳለ ያች ሥዕል ከአንበሳው ጩኸት ሰባት እጅ በሚበልጥ አስፈሪ ድምፅ ጩሃ ተናገረች፡፡ ያን ጊዜ አንበሳው ደንግጦ ፈጥኖ ሸሸ፡፡ መነኩሴውም መንገዱን ቀጠለ፡፡ በመንገዱም ከሚያስፈራ ዱር ውስጥ ወጥተው ወንበዴዎች ሊቀሙትና ሊገድሉት ከበቡት፡፡ ከሥዕለ ማርያም እንደ መብረቅ ያለ ታላቅ ቃል ወጣ፡፡
ወንበዴዎችም እጅግ ፈርተው ሸሽተው ከጫካው ውስጥ ገቡ፡፡ ያም መነኩሴ እነኚህን የሚያስደንቁ ተአምራት በተመለከተ ጊዜ በልቡ «ለእኔ ረዳት ትሆነኝ ዘንድ ወደ ሀገሬ ይዣት እሄዳለሁ እንጂ ለላከችኝ ሴት አልሰጥም» ብሎ ወደ ሀገሩ ሊሄድ በመርከብ ተሳፈረ፡፡ በባሕር ላይም ሳለ ጽኑ ነፋስ ተነስቶ መርከቡን እየገፋ ማርታ ወዳለችበት ሀገር ወደ ጽዴንያ ዳርቻ አደረሰው፡፡ ማደሪያም ስለሌለው ወደ ደጓ ሴት ወደ ማርታ ቤት ከእንግዶች ጋር አብሮ ገብቶ አደረ፡፡ ሲነጋ ወጥቶ ሊሄድ ከደጃፍ ሲደርስ ደጃፉ ጠፍቶት ከአጥሩ ሲታገል ዋለ፡፡ ማርታም «አባቴ ያመመህ የደከመህ ትመስላለህ ዛሬ ደግሞ እዚህ እደርና ነገ ትሄዳለህ» አለችውና አደረ፡፡ በሁለኛውም ዕለት እንደ መጀመሪያው ቀን በሩን አልፎ መሄድ አቃተውና እዚያው ማርታ ቤት አደረ፡፡ በሦስተኛው ቀን መውጣት ፈልጐ አሁንም ከአጥሩ ጋር ሲታገል አይታ «አባቴ የሆንከው ምንድነው? እነሆ ዛሬ ሦስተኛ ቀንህ ነው» አለችው፡፡
መነኩሴውም «ይህችን ተአምረኛ ሥዕል አልሰጥም ብዬ ነው፡፡ እኔኮ ሥዕል ከኢየሩሳሌም ግዛልኝ ያልሽኝ መነኩሴ ነኝ» ብሎ ሥዕለ ማርያምን አውጥቶ ሰጣት፡፡ እርሷም እጅግ በጣም ተደስታ እግዚአብሔርን አመሰገነች፡፡ በሥዕሏም ፊት ሰግዳ ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም ምስጋናን አቀረበች፡፡ ተቀብላም ሥዕል ቤት አሠርታ በክብር አስቀመጠቻት፡፡ ይህችም ሥዕል ቅዱስ ሉቃስ የሳላት ናት፡፡ ሥጋ የለበሰች ትመስላለች፡፡ ከፊቷም ወዝ ይንጠባጠባል፡፡ በዚህችም ሥዕል ብዙ ተአምራት ተደረገ ሕሙማን ተፈወሱ፣ ዐይነ ስውራን ማየት ቻሉ፡፡ በዚያ ዘመን የነበረው ሊቀ ጳጳስ ተአምሯን ሰምቶ ሥዕሏ ወደ ማርታ ቤት የገባችበት ዕለት መስከረም 10 ቀን እንዲከበር ሥርዓት ሠራ፡፡ ይህም በዓል በቤተ ክርስቲያናችን ሁልጊዜ ይከበራል፡፡ የብርሃን እናቱ ድንግል ወላዲተ አምላክ ፍቅሯን ጣዕሟን ታሳድርብን፣ ልጇ አምላካችን በጸሎቷ ይማረን፡፡
+ + + + +
ዳግመኛም የጌታችን ቅዱስ መስቀል አገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ የገባው በዚህ ዕለት ነው፡፡የቅዱስ መስቀሉ ፍቅር ይደርብን።
ምንጭ፦ከገድላት አንደበት
ምእመናን ሆይ
👉የቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት ኤራቅሊስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆኑን ሲያስተምረን የሰው ሁሉ ነፃነት የተጻፈበት ቅዱስ ማሕፀን እንደምን ያለ ነው?
👉 በእኛ ሠልጥኖ የነበረ ሞትን የሚቃወመው የጦር ዕቃችን ክርስቶስ ያደረበት ቡሩክ ማሕፀን እንደምን ያለ ነው?
👉 እንደ ዕፀ ሠሉስ ያለ ዘር በባሕርዩ ሁሉን በሚያስገኝ በመንፈስ ቅዱስ ጌታን ያስገኘችልን የተመረጠች ገራህት ማርያም እንደምን ያለች ናት?
👉 እግዚአብሔር እንደ ቸርነቱና እንደ ይቅርታው እንደ መልከ ጴዴቅ ባለ ሹመት ለማገልገል ሥጋን ለብሶ ባሕርዩ ሳይለወጥ ታላቅ ካህን የሆነበት መቅደስ እንደምን ያለ ነው? ብሎ እንደ ተናገረ። ዘፍ ፲፬፥፲፰። መዝ ፻፲ (፻፱)፥፬። ዕብ ፭፥፲።
በዚህ ነገር ❤️አትናቴዎስም❤️ ይመሰክራል
👉 ነፍስና ሥጋ የሌለው መለኮት አንድ ባሕርይ አንድ አካል አንድ ፍጹም ገጽ አንድ ግብር ሆኑ ብሎ እንዲህ ተዋሕዶን ተናግሮአልና
👉አሁንም እሱ አንድ እግዚአብሔር ነው
አንድ ጊዜ ሰው የሆነ አምላክ ነው
አንግዲህም ወዲህ አይለወጥም አይናወጥም
ሰው የሆነ እግዚአብሔር ቃል አንድ አካል አንድ ባሕርይ አንድ ገጽ አንዲት ስግደት የምትቀርብለት አንድ ውድ አንድ ፈቃድ ያለው ሆኖ ይኖራል እንጂ፤
ሥጋውን ሳንለይ አንድ አድርገን አንዲት ስግደትን እንሰግድለታለን ።🙏
እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን !!!
" የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።"
ያዕ. ፭፥፲፮ /5፥16/
ምእመናን ሆይ
✅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴ :- 18 : 21 እንዲህ ያስተምረናል
በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ ወደ እርሱ ቀርቦ፦
ጌታ ሆይ፥ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ልተውለት እስከ ሰባት ጊዜን አለው።
ኢየሱስም እንዲህ አለው፦እስከ ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ እስከ ሰባት ጊዜ አልልኽም።
ሐዋርያው ጴጥሮስ የይቅርታ ገደቡ ጥጉ
7 ጊዜ ብቻ እንደሆነ እያሰበ ነው ይህን ጥያቄ የጠየቀው
ጌታችን ግን 7 ት ጊዜ አልልህም 70 ጊዜ 7ት እንጂ
✅ ስለዚህ በዚህ ክፍል መሰረት
ይቅርታ ገደብ የለውም
ይቅርታ የድንበር ድንጋይ የለውም
ሰው በደሉን ጥፋቱን አምኖ እስከመጣ ድረስ
ይቅርታ ማድረግ አለብን
ብዙ ሰዎች ይሄን ክፍል ሲያነቡ
የይቅርታ ጥጉ 490 ነው የሚሉ አሉ
ምክንያቱም 7*70=490 ስለሆነ
እንደዚያ ብለው የሚተረጉሙ አሉ
ግን ስህተት ነው
እኛ እኳ በሀገራችን 3ት ቍጥርእና 10 ቁጥር
ምሉዕነትን ወክሎ የሚናገር ቁጥር ነው።
አለም ዘጠኝ ነው 10ር ሞልቶ አያውቅም እንላለን
በዕብራውያን 7ት ቍጥር ፍፁም ምሉዕነትን የሚወክል ነው
✅ 7ት ጊዜ 70 ማለት
ጴጥሮስ ሆይ ይቅር ላለማለት ምክንያት የለህም ማለት ነው
ይቅርታ ገደብ የለውም
የይቅርታ ልብ እግዚአብሔር አምላክ ይስጠን🙏
ምእመናን ሆይ
ሰዎች በሌሎች ስለተገፉ ስለተነቀፉ ስለተሰደቡ ብቻ
ንዑዳን ክቡራን ናቸው ብላችሁ እንዳታስቡ
ታዲያ ንዑዳን ክቡራን መባላቸው እንደምንድን ነው ?
ብላችሁ ብትጠይቁ
ክርስቶስ ባስቀመጠልን ሁለት ቅድመ ሁኔታዎች
1ኛ ነቀፋው በእርሱ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን
2ኛ የሚነቀፍበት የውሸት ሲሆን
ከእነዚህ ዉጭ በሆነ በሌላ ምክንያት
በሰዎች ዘንድ ቢነቀፍ ቢሰደድ ብፁእ አይደለም
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❤️
++ የደመራው ምሥጢር ++
እግዚአብሔር አምላካችን የሠራቸው ታላላቅ ሥራዎች በምልክት የተገለጡ ናቸው፤ ለምሳሌ የሙሴ መስፍንነት፣ የአሮን ሊቀ ካህንነት የተረጋገጠው በአሮን በትር ምልክትነት ነው፡፡ አብርሃም ልጁ ይስሐቅን ሊሠዋ በታዘዘ ጊዜ የሞርያን ተራራ የመረጠው እግዚአብሔር በተራራው ላይ ካሳየው ብርሃን የተነሣ ነው፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያምና ቅዱስ መስቀልም የድኅነታችን ምልክቶች ናቸው፡፡ የአሮንና የሙሴ በትሮች፣ የይስሐቅ ቤዛ የሚኾን በግ የተገኘባት ዕፀ ሳቤቅ ደግሞ የእመቤታችንና የመስቀል ምልክቶች ነበሩ፡፡ ወደ ፊት የምንወርሰው መንግሥተ ሰማያት ክርስቶስ ነው፤ እርሱን ደግሞ ያገኘነው ከመስቀል ላይ ነው፡፡
ጥንተ ጠላት ሰይጣን ይህንን ስለሚያውቅ ቅዱስ መስቀሉን አጥብቆ ይቃወመዋል፤ ስለዚህም አይሁድን አነሳሥቶ ከ፫፻ ዓመታት በላይ ተቀብሮ እንዲቆይ አድርጓል፡፡ በመሠረቱ ለሰይጣን ምሥጢሩ ስለማይገባው ነው እንጂ የመስቀሉ ትክክለኛ መቀበሪያ ሥፍራ የምእመናን ልቡና ነው፡፡ ቀራንዮ ለመስቀሉ መትከያነት የተመረጠችውም ቀዳሜ ፍጥረት አዳም የተቀበረው በዚያ ስለ ነበረ ነው፡፡ ቦታው ‹‹የራስ ቅል ሥፍራ›› /ማቴ.፳፯፥፴፪/ መባሉም የኹላችን ራስ አዳም ዓፅሙ በዚያ ስላረፈ ነው፡፡ መስቀሉ በአዳማውያን ፍጥረታት አእምሮ ውስጥ እንጂ ከዚያ ውጪ የሚኖር ባለመኾኑ ተቀብሮ በቆየባቸው ዓመታት ውስጥም ፍቅሩ ከሰው ልጆች ልቡና አልወጣም፡፡
ጠላት በሠራው ተንኮል ተቀብሮ እንዳይቀር መስቀሉን እንድታወጣ መንፈስ ቅዱስ ንግሥት ዕሌኒን አስነሣት፡፡ ይህች ሴት ቤቷ በሀብት፣ በንብረት ሞልቶ በነበረበት ጊዜና በገረድ፣ በደንገጡር በምትንቀሳቀስበት ወቅት ምን እንደ ሠራች አልተመዘገበላትም ነበር፤ ከክብሯ ወርዳ በተጣለችበት ጊዜ ግን እግዚአብሔር ለሚፈልገው ሥራ ምቹ ኾና ተገኘች፡፡ እርሷ በተጣለችበት ባዕድ አገር ውስጥ ኾና የመስቀሉን ነገር ታስብ፤ ብርሃነ መስቀሉም ዘወትር በልቧ ያንጸባርቅ ነበር፡፡ ሐሳቧን እንዲያሳካላት የለመነችው አምላክም ኪራኮስ የተባለውን አይሁዳዊ ሽማግሌ ልኮ አቅጣጫውን አመላከታት፤ ኪራኮስ የጀመረውን ምሥጢርም መልአኩ ‹‹ደመራ ደምረሽ፣ ሰንድሮስ የሚባል ነጭ ዕጣን ጨምረሽ አቃጥዪው›› ብሎ ተረጐመላት፡፡ እርሷም መልአኩ እንደ ነገራት ብታደርግ ጢሱ ሰማይ ደርሶ ወደ ምድር ተመልሶ መስቀሉ ወደሚገኝበት ተራራ ሰገደ፡፡ በጢሱ ምልክትነት መስከረም ፲፯ ቀን የተጀመረው ቍፋሮ መጋቢት ፲ ቀን አልቆ ዕሌኒ መስቀሉን ከልበ ምድር ለማውጣት ችላለች፡፡
መስቀልና ደመራ እንዲህ ነበር የተገናኙት፡፡ ደመራው ለመስቀሉ መገኘት፣ መስቀሉም ለደመራው መሠራት ምክንያት ናቸው፡፡ በዚህ አንጻር መለኮትና ትስብእት በአንድነት መደመራቸው መስቀሉ እንዲሠራ ምክንያት ኾነዋል፡፡ አምላካችን ሥጋ ለብሶ ‹ክርስቶስ› በሚል የተዋሕዶ ስም ሲጠራ ለመከራ መዘጋጀቱን እንረዳለን፡፡ መስቀሉ የሥጋ ብቻ ነበረ፤ አሁን ግን መለኮትም በሥጋ ባሕርይ የመስቀሉ ተካፋይ ኾነ፡፡ ይህም የደመራው ውጤት ነው፡፡ መለኮት አምስት ሺሕ ከአምስት መቶ ዘመን መስቀል የተሸከመ ሥጋን ሲዋሐድ መስቀሉን አስወግዶ አልነበረም፡፡ ይኸው በዕፀ በለስ ምክንያት የተሸከምነው መስቀል ነው፡፡ ሥጋ ዓቅም አጥቶ መስቀሉን ከትከሻው ላይ ሳያወርድ ለዘመናት የተጓዘውን ጕዞ መለኮት ኀይል ኾኖት ድካሙን ሳይለቅ ኀያል፤ ኀይሉን ሳይለቅ ደካማ ኾነ፡፡ መስቀል ትርጕሙ መከራ ቢኾነም ነገር ግን እግዚአብሔር ሲያመጣውና ሰው ሲያመጣው ግን ትርጕሙ ይለያያል፤ ሰው ያመጣው መስቀል ኹላችንን ለመከራ፣ ለሞት አሳልፎ ሰጥቶናል፡፡ የእግዚአብሔር መስቀል ግን መከራነቱ ለሰይጣን እንጂ ለእኛ ሕይወታችን ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድም ‹‹መስቀል ብሂል ዕፀ ሕይወት ብሂል፤ መስቀል ማለት የሕይወት ዛፍ ማለት ነው›› በማለት የመስቀልን ትርጕም ነግሮናል፡፡
አዳም ከገነት ሲወጣ በመላእክት እንዲጠበቅ የተደረገው የሕይወት ዛፍ የክርስቶስ መስቀል ነው፡፡ በዕፀ በለስ ምክንያት ኹላችንም እንደ ተጎዳን በዕፀ ሕይወቱም ተጠቃሚዎች ኾነናል፤ አስቀድመን በአዳም መከራ እንደ ተባበርን አሁን ደግሞ በደስታው እንተባበራለን፡፡ ሞትም ሕይወትም አንድ አድርጎናል፡፡ የክርስቶስ መስቀል ኹሉንም በሕይወት አስተባብሯልና፡፡ በአንጻሩ ሰውና ዲያብሎስን ለያይቷል፡፡ የኀጢአት ቁራኝነትን አጥፍቷል፡፡ ጌታችን በማኅፀን ሲፀነስ ጀምሮ የእኛን መስቀል መሸከም ሲጀምር የእርሱ የኾነውን ለእኛ ስለ ሰጠን ከሰይጣን ጋር መለያየታችን በመስቀሉ ተረጋግጧል፡፡ የአምላካችን መስቀል ምልክቱ ደመራ መኾኑ የእኛን ወደ እርሱ መሰብሰብና የጠላታችንን መበተን የሚያረግጥልን ነው፡፡ ጌታችንም ‹‹ወብየ ካልዓትኒ አባግዕ እለ ኢኮና እምዝንቱ ዐፀድ ወኪያሆንሂ ሀለወኒ አምጽኦን ዝየ፤ ከዚህ በረት ያልኾኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱንም ላመጣቸው ይገባኛል›› በማለት ሊሰበስበን እንደ መጣ ነግሮናል /ዮሐ.፲፥፲፮/፡፡ መስቀሉ ፍጥረት አንድ ደመራ ኾኖ የተሠራበት ስለ ኾነ በደመራ እንዲገለጥ የእግዚአብሔር ፈቃዱ ኾነ፡፡
መስቀሉ አንድ ደመራ ያደረጋቸው ፍጥረታት
፩. ነቢያትና ሐዋርያት
ነቢያት የሚባሉት ከአዳም እስከ ዮሐንስ መጥምቅ ያሉ አባቶች ሲኾኑ፣ ከክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ጀምሮ ለቤተ ክርስቲያን የወንጌልን የምሥራች እንዲነግሩ የተላኩ አባቶች ደግሞ ሐዋርያት ይባላሉ፡፡ በእርግጥ ሐዋርያ የኾነ ነቢይ የለም እንጂ ነቢይ የኾነ ሐዋርያ አለ፡፡ ነቢያትና ሐዋርያት በዘመን፣ በክብር እና በግብር የማይገናኙ ፍጥረታት ናቸው፡፡ መንፈሰ ረድኤት የተሰጣቸው ነቢያት ለሐዋርያት የተሰጠውን መንፈሰ ልደት ለማግኘት አልተቻላቸውም፡፡ ሐዋርያት ግን ኹሉንም አንድ አድርገው ይዘዋል፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያው ስለዚህ ሲመሰክር ‹‹በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጠን›› በማለት አጕልቶ የተናገረው /ዮሐ.፲፥፲፰/፡፡ ነቢያት በዚህ ምድር የእግዚአብሔርን መንግሥት በመፈለግ ብዙ ደክመዋል፡፡
ሊቃውንቱ ነቢያትን በክረምት፣ ሐዋርያትን በበጋ ገበሬ ይመስሏቸዋል፡፡ የክረምት ገበሬ ላዩ ውሃ፣ ታቹ ውሃ ኾኖበት በጭቃ ወጥቶ በጭቃ ይመለሳል፡፡ ወደ ቤቱ ሲገባም ሚስቱ ጨምቃ ያቆየችለትን ጐመን በልቶ ደስ ሳይለው ይተኛል፡፡ ነቢያትም በዚህ ዓለም በጣዖት አምላኪ ነገሥታት፣ በነቢያተ ሐሰት ስብከት ሲንገላቱ ኖረው ሲሞቱም ሲዖል ይገባሉ እንጂ ገነትን አይወርሱም ነበር፡፡ የበጋ ገበሬ በደረቅ ወጥቶ፣ እሸት በልቶ፣ ተደስቶ ወደ ቤቱ ይመለሳል፤ ከቤቱ ሲገባም እንጀራው በሌማት፣ ጠላው በማቶት፣ ሲቀርብለት ደስ ብሎት ይበላል፤ ይጠጣል፡፡ ሐዋርያትም ልጅነትን አግኝተው ለማስተማር ተልከዋል፤ በሔዱበት ኹሉ ተአምራትን እንዲያደርጉ፣ ልጅነትንም እንዲሰጡ ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል፡፡ ሞታቸው ሲደርስም መንግሥተ ሰማያት ተከፍቶ ይጠብቃቸዋል፡፡
የእግዚአብሔር ቤተሰቦች
እስኪ ከፍጠረታት እንማር
ሸረሪትን ተመልከቱ
ትደክማለች ትለፋለች
ከሴት ብልሀት ይልቅ የተከበረችው
እጅግ አስደናቂ በሆነ መልኩ
ድሯን በግድግዳ ላይ ታድራለች
ነገር ግን ሥራዋ ልክ እንደኛ የሚጠቅም አይደለም
የማይጠቅም በመሆኑ የሚያከብራት የለም
ለራሳቸው ብቻ የሚደክው
ለራሳቸው ብቻ የሚለፉ ሰዎችም
ልክ እንደዚች ሸረሪት ናቸዉ ።
ለራሳቸው ብቻ የሚደክሙ የሚለፉ ሰዎች
እኛ ራስ ወዳድ የምንላቸው
ልክ እንደዚች ሸረሪት ናቸው
ሁሌም ከሌሎቹ ይለቅ ለራሳቸው ይደክማሉና
ሁሌም ከሌሎቹ ይልቅ ለራሳቸው ይለፉሉና
ለሌሎች የሚሰጡት ረብ(ጥቅም) የለምና።
በመረዳዳት እንኖር ዘንድ ፈጣሪ አምላክ ይርዳን🙏
☞መሰከረም 15 የቀዳሚ ሰማዕት የቅዱስ እስጢፋኖስ የሥጋው ፍለሰት ነው፡፡
☞ይኸውም ከ 300 ዓመታት በኃላ ጻድቁ ንጉሥ ቁስጠንጢኖስ ከነገሠ በኃላ
ሃይማኖት በተመለሰች ጊዜ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋው ባለበት አቅራቢያ
በገማልያል ቦታ ለሚኖር ሉክያኖስ ለተባለ አገልጋል ተገለጠለትና ስለ ሥጋው
ነገረው፡፡
☞ሉክያኖስም ወደ ኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ ሄዶ ተናገረ፡፡ ኤጴስ ቆጶሳት፤ካህናትና
ዲያቆናት ሁሉ መጥተው ሥጋውን ቆፍረው ሲያወጡት በአካባቢው ታላቅ
ንውጽውጽታ ሆነ፡፡ አካባቢውንም እጅግ በጎ መዓዛ ሞላው ፡፡ ከሥጋውም እጅግ
ብዙ ተአምራት ተገለጠ፡፡ በሽተኞች ተፈወሱ ደንቆሮዎችን እንዲሰሙ አደረገ፡፡
ዕውራሮችን አበራ፡፡ ይህ የሆነው በዚች በመስከረም 15 ቀን ነው፡፡
☞በቅዱስ ወንጌል ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፡፡ እነርሱ እግዚአብሔርን ያዩታል
የተባለው በእርሱ ተፈጸመ፡፡ በሥጋው ሕያው ሆኖ እያለ በዓይቹ የተመለከተ ይህ
እስጢፋኖስ ነው፡፡
☞ከጥንት ጀምሮ የነበረ የአብን ልጅ በሚያስፈራና በሚያስደነግጥ ግርማ
በአርያም የተመለከተ የቃልንም መኖር ያስተዋለ ይህ እስጢፋኖስ ነው፡፡ ይህን
አይቶም አልፈራም፡፡ በፍጹም ደስታ ጮኸ እንጂ፡፡ ሁሉ በላይ እንሆ እኔ ዛሬ
ሰማያት ሁሉ ተከፍተው የእግዚአብሔር ልጅም ከፍጥረታት ሁሉ በላይ በታላቅ
ክብር በቀኝ ተቀምጦ አየሁት ያለ ይህ እስጢፋኖስ ነው፡፡
☞የክርስቶስ ወዳጅ አባታችን ድንግሉ ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሦስት
አክሊልን ተቀዳጀ፡፡
☞አንደኛው ስለ ድንግልናው፤ሁለተኛ ሰለ ሰማዕትነቱ፤ሦስተኛው ሰለ
አገልግሎቱ ነው፡፡
☞ወንድሞቼ ሆይ ዛሬም እንለምን፤ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስም
በደላችንን ይቅር እንዲለን እናንጋጥ፡፡ ኃጢአታችንን እንዲደመሰስልን፤ ንጹሕ
ልብን ይሰጠን ዘንድ የሰማዕታት መጀመሪያ እንደተባለው እንደ ሊቀ ዲያቆናት
ቅዱስ እስጢፋኖስ የእኛንም የወንድሞቻችንም ኃጢአት እናስተሠርይ ዘንድ ትጉ፡፡
☞በዚህች ዕለትም በጥንቃቄ በዓሉን በየአመቱ በየወሩ በተለይም በሥጋው
ፍለሰትና በመሰከረም 15 ቀን እና በዕረፍቱ ቀን ጥር 1 ከመፃ ከኃጢአት ከሀሰት
በመራቆ እንደ መንፈሳዊ ታላቅ በዓል እንደ ትንሣኤ ዕለት አድርገን የተባረከች
የመታሰቢያውን ዕለት እናክብር፡፡
☞በዚህች የተከበረች ዕለት ሰውነታችንን በምስጋና በጸሎት በስግደት
በምጽዋት የሰማዕታት የመጀመሪያው አባታችን ቅዱስ እስጢፋኖስ የስጋው
ፍልሰት ተፈጽሞበታል እና፡፡
☞ሰለ ኃጢአት ይቅርታን ያደርግ ዘንድ በሰማዕታት መጀመሪያ በተመረጠው
በቅዱስ እስጢፋኖስ ጸሎት በመንግሥተ ሰማይ በድኅነት ወደብ ያሳድረን ዘንድ
በዓሉን እናድርግ፡፡
☞የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማለጅነት የቀዳሚ ሰማዕት
የቅዱስ እስጢፋኖስ የጸሎቱ በረከት አይለየን፡፡
☞(ገድለ ቀዲሚ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ)
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ
☞14-1-2017
አቡነ ያሳይ የትውልድ ሀገራቸው ሸዋ ተጉለት ነው፡፡ አባታቸው ንጉሡ ዓምደ ጽዮን ቀዳማዊ ነው፡፡ ይኸውም ከ1296-1326 ዓ.ም የነበረው ነው፡፡ አቡነ ያሳይ በልጅነታቸው በንጉሡ አባታቸው ቤት ሲኖሩ የገዳም መነኮሳት ለመንፈሳዊ ሥራ ወደ ንጉሡ ዘንድ እየመጡ ደጅ ሲጠኑ ያዩአቸዋል፡፡ በዚህም ጊዜ አባታችን ገና በልጅነታቸው የመነኮሳቱን እግር ያጥቡ ስለነበር በዚሁ አጋጣሚ መነኮሳቱን ስለምንኩስና ሕይወት ይጠይቋቸው ነበር፡፡ መነኮሳቱም ሕይወታቸውን ያስረዷቸዋል፡፡ አቡነ ያሳይም ብሉያትንና ሐዲሳትን ከልጅነታቸው ጀምሮ የተማሩ ስለነበር የአባቶችን ትምህርትና የወንጌልን ቃል በማገናዘብ የፈጣሪያቸው ፍቅር በልቡናቸው እንደ እሳት ነደደ፡፡ ይልቁንም ‹‹ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል›› የሚለውን የጌታችንን ቃል አሰቡ፡፡ ማቴ 16፡26፡፡ ከዚህም በኋላ የንጉሡ አባታቸውን የአልጋ ወራሽነት ማለትም የንጉሥነትን ክብር ፈጽመው በመናቅ ‹‹እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር እራሱን ይካድ፣ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ›› (ማቴ 16፡27) ያለውን የጌታችንን ቃል አስበው ንጉሣውያን ቤተሰቦቻቸውን ጥለው ለምነና ወጡ፡፡
ለምነና እንደወጡም ከሸዋ ተነሥተው ወደ ትግራይ ክፍለ ሀገር በአክሱም አቅራቢያ ከሚገኘው ገዳም ደብረ በንኮል ከሚባለው ከአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ገዳም ደረሱ፡፡ አቡነ መድኃኒነ እግዚእም አቡነ ያሳይ የእግዚአብሔር ጸጋ ያደረባቸው ሰው መሆናቸውንና ወደ እርሳቸውም እየመጡ መሆኑን በመንፈስ ዐውቀውት ስለነበር በደስታ ተቀበሏቸውና በረድእነት ከወንድሞቻቸው ጋር ጨመሯቸው፡፡ አቡነ ያሳይም የገዳም መነኮሳትን በማገልገል በመንፈሳዊ ተጋድሎ ብዙ ደከሙ፡፡ በደብረ በንኮል ገዳምም ብዙ ገራሚ ተአምራትን አደረጉ፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ መካነ ገድላቸው በጣና አካባቢ እንደሆነ ነገራቸው፡፡ ‹‹ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን›› የተባሉ አቡነ መድኃኒነ እግዚእም ቀደም ብለን የጠራናቸውን ‹‹ሰባቱን ከዋክብት›› ምግባር ሃይማኖታቸውን፣ ተጋድሎ ትሩፋታቸውንና ገቢረ ተአምራታቸውን አይተው ፈቃደ እግዚአብሔርን ጠይቀው በአንድ ቢያመነኩሷቸው በዚያው ቅጽበት መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ገዳሙን በብርሃን አጥለቅልቆት ታይቷል፡፡ ከሰማይም የምስክርነት ድምፅ ተሰምቷል፡፡ ከዚህም በኋላ ከሰባቱ ቅዱሳን ውስጥ ሦስቱ ቅዱሳን አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ አቡነ ያሳይ እና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ሆነው ከደብረ በንኮል ገዳም አባታቸውን አቡነ መድኃኒነ እግዚእን ተሰናብተው ወደ ጣና ደሴት መጥተዋል፡፡
አቡነ ያሳይ በ13ኛው መ/ክ/ዘመን በአባታቸው የዘመነ ንግሥና መጨረሻ ወደ አርባ ምንጭ ሄደው ከዚያው ሱባኤ ገብተው ፈጣሪያቸውን ቢማጸኑ እግዚአብሔርም ከዚያው አካባቢ የሚኖር አንድ ባሕታዊን የመድኃኔዓለምን ጽላት እንዲያወጣላቸው አዘዘላቸው፡፡ እርሳቸውም ጽላቱን ተቀብለው በጎጃም በኩል አድርገው ወደ ጣና ተመልሰው በዘጌ አከባቢ ሲደረሱ ከጣና ባሕር ዳር ቆመው በየብስ ያለውን ርቀትና በባሕሩ ያለውን ቅርበት አይተው አሁንም ወደ ፈጣሪያቸው በጸሎት ተማጸኑ፡፡ በዚህም ጊዜ ጌታችን ተገልጦላቸው ‹‹ወዳጄ ያሳይ ሆይ አትጨነቅ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፣ ከጎንህ ያለውን ድንጋይ በባሕሩ ላይ ጫነው፤ ድንጋዩም ለልጅ ልጅ እኔ ዓለምን ለማሳለፍ እስከምመጣበት ሰዓት ድረስ መታሰቢያ ትሁንህ›› አላቸውና ተሰወረ፡፡ አቡነ ያሳይም የመድኃኔዓለምን ጽላት ይዘው በድንጋዩ ላይ እንደተቀመጡ ድንጋዩ እንደታንኳ በባሕሩ ላይ ተንሳፈፈ፡፡ ባሕሩም ከማዕበሉ ብዛት የተነሣ ይታወክ ነበር፡፡ አባታችንም ያለ ምንም ቀዘፋ ልብሳቸውም ውኃ ሳይነካው ቁጭ እንዳሉ ማን እንደአባ ወደ ተባለው ቦታቸው ደረሱ፡፡
ከዚህም በኋላ አቡነ ያሳይ ገዳማቸውን ገድመው ወንድሞቻቸውን ሰብስበው በተጋድሎ በመኖር ብዙ ቅዱሳንን አፍርተዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የጌታችንን እግር ያጠቡት አቡነ አብሳዲ፣ እንደ ነቢዩ ኤልያስ ዝናብንና ነፋስን የከለከሉት አቡነ ያዕቆብ፣ እሬትን እንደ ማር ያጣፈጡት አቡነ ገብረ ኢየሱስ፣ እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ሞገስን የተሞሉት አቡነ ዳንኤል፣ እንደ ንጉሥ ሰሎሞን ጥበብን የተሞሉት አቡነ ፊቅጦርና ሌሎችም ብዙዎች ይጠቀሳሉ፡፡ በወቅቱም ብዙ የበቁ ቅዱሳን በአካባቢው ነበሩ፡፡ በአጽፋቸውና በእግራቸው በባሕሩ ላይ የሚሄዱ ነበሩ፣ በጸጋ ክንፍ ተሰጥቷቸውም የሚበሩ ነበሩ፡፡ የአቡነ ያሳይ ተአምራቶቻቸው ተነግረው አያልቁም፡፡ በወቅቱ የነበሩት ቅዱሳን ልጆቻቸው ‹‹ከቅዱሳን ማን እንደ አባ ያሳይ በከባድ ድንጋይ ላይ ተጭኖ በባሕር ላይ የተጓዘ አለና..›› ብለው ይገረሙባቸው ነበር፡፡ ቦታቸውም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ‹‹ማን እንደ አባ›› ተባለ፡፡ ይህም የአቡነ ያሳይ ገዳም በሰሜን ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት በደንቢያ ወረዳ በጎርጎራ ጣና ሐይቅ አካባቢ ይገኛል፡፡
በጣና ደሴት ላይ ከሚገኙት ታሪካዊ ቦታዎች ውስጥ አንዱ ‹‹አትማረኝ ዋሻ›› ነው፡፡ ይህም አትማረኝ ዋሻ በጣና ሐይቅ ደሴቶች መካከል ከሚገኙ ገዳማት መካከል ከማን እንደ አቡነ ያሳይ መድኃኔዓለም አንድነት ገዳም በስተ ምእራብ አቅጣጫ የጣና ሐይቅን ጉዞ ከገታው አንድ ተራራ ሥር የሚገኝ ዋሻ ነው፡፡ ይህ ዋሻ ለብዙ ዘመናት አንድ ታላቅ አባት የጸሎት በዓት አድርገውት ‹‹አትማረኝ›› እያሉ የጸለዩበት ቦታ ነው፡፡ አቡነ ያሳይ ወደ ጣና ደሴት ከአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ እና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ጋር በመሆን በጸሎት ይተጉ እንደነበር ገድላቸው ይናገራል፡፡ ከእግዚአብሔር በተሰጣቸውም ጸጋ በጣና ሐይቅ ላይ እንደ ጀልባ የሚጓዙበት አንድ ትልቅ ጠፍጣፋ ድንጋይ በጣና ደሴት ላይ ለአገልግሎት በመፋጠን ላይ እያሉ ዛሬ አትማረኝ ዋሻ ተብሎ ወደሚጠራው አካባቢ ሲደርሱ አንድ አባት ዋሻው ውስጥ “አትማረኝ፣ አትማረኝ፣ አትማረኝ” እያሉ ሲጸልዩ ያገኟቸዋል፡፡ አቡነ ያሳይም በሰውዬው ጸሎት በመገረም ቀርበዋቸው ‹‹አባቴ ምን ዓይነት ጸሎት ነው የሚጸልዩት?›› አሏቸው፡፡ ያም አባት ‹‹አባቴ እንደ እርስዎ ያሉ አባት መጥተው ‹አትማረኝ› እያልክ ጸልይ ብሎኝ ነው›› በማለት መለሱላቸው፡፡ አቡነ ያሳይም ‹‹እንዲህ ዓይነት ምክር የሚመክር ጠላት ዲያብሎስ ነው፡፡ ከዛሬ ጀምረው ‹ማረኝ› እያሉ ይጸልዩ በማለት አቡነ ዘበሰማያትን አሰተምረዋቸው ይሄዳሉ፡፡ ‹‹አትማረኝ›› እያሉ ይጸልዩ የነበሩት አባትም ‹‹ማረኝ›› እያሉ መጸለያቸውን ቢቀጥሉም ብዙ መግፋት ሳይችሉ ቀሩና ጸሎቱ ይጠፋባቸዋል፡፡ ወደ ሐይቁ ሲመለከቱም አቡነ ያሳይ ድንጋዩን እንደጀልባ ተጠቅመው እየሄዱ ነው፡፡ ጸሎቱን ያስጠኗቸው አቡነ ያሳይ ርቀው ሳይሄዱባቸው ያ አባት በውኃ ላይ በእግራቸው እየተራመዱ በመከተል ይደርሱባቸዋል፡፡ ከኋላቸውም ሆነው ‹‹አባታችን ያስጠኑኝ ጸሎት ጠፋብኝ፤ እባክዎን እንደገና ያስተምሩኝ›› አሏቸው፡፡ አቡነ ያሳይም ሐይቁን በእግራቸው እረገጡ እስኪሄዱ ድረስ ጽድቃቸው የተገለጠውን የእኚህን አባት መብቃት ተመልከተው ‹‹አባቴ እግዚአብሔር የልብ ነውና የሚመለከተው እንዳስለመዱት ይጸልዩ የእርስዎ ይበልጣል›› ብለዋቸው ሔዱ፡፡ በዚህም ምክንያት ቦታው ‹‹አትማረኝ ዋሻ›› ተብሎ ተጠርቷል፡፡ የአቡነ ያሳይ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
መዝገበ ቅዱሳን
ምእመናን ሆይ
ቅድስት ድንግል ማርያም
የኖኅ የድኅነት ማደሪያ ፣
ሦስት ገዥዎች እነርሱም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በውስጧ የከተሙባት የአብርሃም ድንኳን ናት።
ቅድስት ድንግል ማርያም ከምድር እስከ ሰማይ ተዘርግታ የፍጥረቱ ሁሉ ንጉሥ የሚጠጋባት የያዕቆብ የእሳት መሰላል ናት።
ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር ከሰው ጋር ያደረባት የሙሴ የምስክር ድንኳን ናት።
ቅድስት ድንግል ማርያም የኢያሱ የምስክር ሐውልት (የማዕዘን ድንጋይ) ናት።
ቅድስት ድንግል ማርያም ያበበችና የፈራች ባለርስቶች ያወቋት የአሮን በትርና ማዲጋ ናት።
ቅድስት ድንግል ማርያም የሳሙኤል የረድኤት አለት ፣ በንጉሥ ቀኝ የምትቀመጥ የዳዊት ንግሥት ናት።
ቅድስት ድንግል ማርያም በኪሩቤል ክንፎች የምትጋረድ የሰሎሞን መቅደስ ናት።
ቅድስት ድንግል ማርያም የሕዝቅኤል የተዘጋች የምሥራቅ በር ደጅ ናት።
ደጅ :- ማለት የምሕረት መግቢያ ማለት ነው።
ምሥራቅ :- ማለት የፀሐይ መውጫ ማለት ነው። መግቢያዎቹም :- ኮከቦች ናቸው።
እነዚህም ኮከቦት:- የጻድቃን ነፍስ ናቸው።
ቅድስት ድንግል ማርያም የነፍስ ሁሉ ምግብ የሆነ የመንፈስ ቅዱስ አዝመራ በውስጧ ያለባት
የዮሴፍ የስንዴ መዝገብ ናት።
ቅድስት ድንግል ማርያም የኢሳይያስ የተጠማች ምድር ናት።
የእመብርሃን አማላጅነት❤️ ረድኤት በረከት አይለየን🙏
እንኳን ለከቡነ ዘርዐ ቡርክ የመታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ
ረድኤት በረከቱ ይደርብንና በዚኽች ዕለት በወርሐዊ በዓሉ ታስቦ የሚውል ብፁዕና ቅዱስ አባታችን አቡነ ዘርዐ ቡሩክ ያደረገው ታምር ይህ ነው።
ዳግመኛም እግዚአብሔር ደብረሳን በሚባል በአንድ አገር ተወልደ መድኅን በሚባል በእግዚአብሔር ሰው ቤት ተአምራትን አደረገ ክፉ ጠላቶች ብዙጊዜ ተነሱበት ብዙ ጊዜም በእግር ብረት አሰሩት ይህ ሰው አይወድህም በሃይማኖትህም አይመስልህም ብለው ከንጉሱ ጋር አጣሉት ንጉሡም ይህን ነገር ሰምቶ አሰረው ወደ ሩቅ አገር ወሰደው በዚያ እንዲያስቀምጡት አዘዘ የታዘዙትም ሰዎች ትእዛዙን ሰምተው አስረው ወስደው ለአስር ወራት ያህል በዚያ አስቀመጡት ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር የሃይማኖቱንና በእርሱ መማፀኑን አይቶ ከእስራቱ ፈትቶ አወጣው በሩቅና በቅርብ ከተነሱበት ጠላቶቹ እጅም አዳነው ሌባ ከቤቱ ገብቶ የእርሱን ልብስና የሚስቱን ልብስ በሰረቀበት ጊዜ ያሰው የእርሱን ልብስና የሚስቱን ልብስ እንዳያጠፋበት በወዳጁ በአባታችን አቡነ ዘርዐ ቡሩክ ስም እግዚአብሔርን ለመነ እግዚአብሔርም ጸሎቱንና ልመናውን ሰምቶ ያ ሌባ ርቆ እንዳይሄድ እጁንና እግሩን ያለ ማሰሪያ አሰረው ያም ሌባ በጫካ ውስጥ ሦስት ቀን ተቀመጠ ከዚህ በኋላ በሦስተኛው ቀን ያን ሌባ ሌላ ሰው አገኘውና እኒህን ልብሶች ከወዴት አመጣሀቸው ወዴትስ ትወስዳቸዋለህ ብሎ መረመረው ያም ሌባ ያመጣበትን ቦታና እግዚአብሔር ወደ ቤቱ እንዳይገባ ወደ ሌላ አገርም እንዳይሄድ በጻድቁ አባታችን ጸሎት አስሮ ሦስት ቀን በጫካ ውስጥ እንዳስቀመጠው ነገረው ይህም ሰው የሌባውን ነገር ሰምቶ ወደ ባለ ልብሱ ሂዶ ሌባውን እንዳገኘው ነገረው ሌባው የሠረቃቸው ልብሶቹን ባገኘ ጊዜ ደስ አለው ይህ ሁሉ ድንቅ ታምር የተደረገ በጻድቁ አባታችን ጸሎት እንደሆነ አወቀ ለዘለዓለሙ አሜን።
ምንጭ የፈለ ግዮን ግሽ ዓባይ ቅዱስ ሚካኤልና አቡነ ዘርዐ ቡሩክ ደብር ያሳተመው ገድለ ዘርዐ ብሩክ
ያለፈው ዘመኔን ሳስብ በእውነት እጅግ አፍራለሁ
ድርሻየን ካንተ ወስጀ በብዙ አባክኛለሁ
ይሞላል ልቤ በፀፀት ድካሜን አስታውስና
ምህረትህ ያበረተኛል ትላንትን እረሳውና(፪)
ያለፈው ዘመኔ ይብቃ
ጌታ ሆይ አድርገኝ ምርጥ እቃ
አልወጣ ከፍቅር እጅ
ሳመልክህ ልኑር ከደጅ
መስከረም 12/2017 #መልአኩ_ቅዱስ_ሚካኤል
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስን_ክርስቶስን በመልአኩ ስም ለምናመሰግንበት ለመልአኩ #ቅዱስ_ሚካኤል ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉መስከረም ዐሥራ ሁለት በዚች ቀን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው በዚችም ቀን ክብር ይግባውና #እግዚአብሔር ወደ አሞፅ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳይያስ ላከው
👉ይቅርም ብሎት ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሕዝቅያስ ሒዶ #እግዚአብሔር ይቅር እንዳለውና ከደዌው እንዳዳነው በዕድሜውም ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እንደ ጨመረለት ይነግረው ዘንድ አዘዘው ንጉሱም ሚስት አግብቶ ምናሴን እስከወለደው ድረስ እንዲሁ ሆነ
👉ሊቀ መላእክት #ቅዱስ_ሚካኤል ለንጉሥ ሕዝቅያስ ያደረገለት ተአምር ከጻድቁ ንጉሥ ከቅዱስ ዳዊት በኋላ በእስራኤል እንደ ሕዝቅያስ ያለ ሌላ ጻድቅ ንጉሥ አልተነሣም ከሕዝቅያስ በኋላ የተነሡት ሁሉም ጣዖትን አምልከዋል ለጣዖታቱም የሚሆን መሠዊያ ሠርተዋል
👉ንጉሡ ሕዝቅያስ በነገሠ ጊዜ ግን ጣዖታትን ሰባብሯቸዋል የእስራኤል ልጆች ያመልኩት የነበረውን የነሐስ እባብ ቆራርጦታል #እግዚአብሔርንም በማመኑ መንግሥቱ እጅግ ሰምሮለታል እግዚአብሔርም ያሳጣው በጎ ነገርም የለም
👉ሕዝቅያስ በነገሠ በ14ኛው ዘመን የፋርሱ ነጉሥ ሰናክሬም መጥቶ #ኢየሩሳሌምን ከበባት ይህም ሰናክሬም በወቅቱ እንደ እርሱ ያለ ኃይለኛ የለም ነበርና ሁሉም የምድር ነገሥታት ይፈሩትና ይገዙለት ነበር
👉ሕዝቅያስም ከሰናክሬም ግርማና የጦሩ ብዛት የተነሣ ፈርቶ ኢየሩሳሌምን እንዳያጠፋት ብዙ ወርቅና ብር እጅ መንሻ ቢልክለትም ሰናክሬም ግን እጅ መንሻውን አልቀበልም ብሎ ኢየሩሳሌምን ያጠፋ ዘንድ ተነሣ ለሕዝቅያስም አምላካችሁ #እግዚአብሔር ከእኔ እጅ ሊያደናችሁ ከቶ አይችልም የሚል የስድብን ቃል ላከለት
👉ሁለተኛም #በልዑል_እግዚአብሔር ላይ የስድብን ቃል ጽፎ ደብዳቤ ላከለት ሕዝቅያስም ይህን ሲሰማ ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ አለቀሰ ልብሱንም ቀዶ ማቅ በመልበስ የሰናክሬምን ድፍረትና በኢየሩሳሌምና በሕዝቧ ላይ ሊያደርስ ያሰበውንም ጥፋት ወደ #እግዚአብሔር አሳሰበ ቀጥሎም ሕዝቅያስ ሰናክሬም የተናገረውን ይነግሩት ዘንድ ስለ ሕዝቡም እንዲፀልይ ለነቢዩ ኢሳይያስ መልእክት ላከበት #ነቢዩ_ኢሳያስም ወደ እግዚአብሔር አመለከተ
👉ከዚህም በኋላ #ቅዱስ_ሚካኤል ስለ ንጉሡ ለነቢዩ መልእክትን አመጣለት ነቢዩ ኢሳይያስም የመጣለትን መልስ እንዲህ ብሎ ለሕዝቅያስ ላከለት ልብህን አፅና አትፍራ በዓለሙ ሁሉ እንደ እርሱ ያለ ያልተሰማ ዕፁብ ድንቅ የሆነ ሥራ በሰናክሬም ላይ #እግዚአብሔር ይሠራል አለው
👉ከዚያም መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል #ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ መጥቶ 185,000 (መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ) የፋርስ ሠራዊቶችን በአንድ ሌሊት ገደላቸው 2ኛ ነገ.17፥19 የለኪሶ ሰዎችም ሲነጋ በተነሡ ጊዜ ምድሪቱን በእሬሳ ተሞልታ ስላገኟት በድንጋጤና በፍርሃት ከንጉሣቸዉ ጋር ሸሽተው ነነዌ አገር ገቡ
👉ንጉሡ ሰናክሬምም ወደ አምላኩ ወደ ጣዖቱ ቤት ገብቶ ሲፀልይ የገዛ ልጆቹ በሰይፍ መትተው ገደሉትና ወደ አራራት ኩበለሉ 2ኛነገ.ምዕራፍ 19 ንጉሥ ሕዝቅያስም ከሰናክሬም እጅ ያዳነውን #እግዚአብሔርን አመሰገነ
👉ከዚህም በኋላ ሕዝቅያስ ታሞ ለሞት በደረሰ ጊዜ ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ እርሱ መጥቶ #እግዚአብሔር ትሞታለህ እንጂ አትድንም ብሎሃል አለው ነገር ግን ሕዝቅያስ አሁንም ልብሱንም ቀዶ ማቅ በመልበስ ፀሎቱን ወደ #እግዚአብሔር አቀረበ
👉በዚህ ጊዜ ነው ቅዱስ ሚካኤል #ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ መጥቶ ነቢዩ ኢሳይያስን ወደ ንጉሡ ሕዝቅያስ ሄዶ በዕድሜው ላይ 15 ዓመት እንደተጨመረለት እንዲነግረው ያዘዘው
👉መልአኩ እንዳዘዘው ነቢዩ ኢሳያስ ንጉሥ ሕዝቅያስን #እግዚአብሔር የአባትህ የዳዊት አምላክ ፀሎትህን ሰማሁ ዕንባህንም አየሁ እነሆ እኔ አድንሃለሁ በዘመኖችህም 15 ዓመት ጨምሬልሃለሁ ከፋርስ ንጉሥ እጅም አድንሃለሁ ይህችን አገር ስለ እኔና ስለ ቧለሟሌ ዳዊት አጽንቼ እጠብቃታለሁ ብሎሃል ብሎ የተላከውን ነገረው
👉ከዚህም በኋላ ንጉሥ ሕዝቅያስ #የእግዚአብሔር ኃይል ስላደረበት የምድር ነገሥታት ሁሉ ፈርተውት እየተገዙለት እጅ መንሻን ያገቡለት ጀመር ንጉሡም ዕድሜው ከተጨመረለት በኋላ ሚስት አግብቶ ምናሴን እስኪወልድ ድረስ ቆየ በመንበረ መንግሥቱም 29 ዓመት ነግሦ ከኖረ በኋላ #እግዚአብሔርን አገልግሎ በሰላም ዐረፈ
👉የአምላካችን #የእግዚአብሔር ቸርነት የሊቀ መላእክት #የቅዱስ_ሚካኤል ጥበቃና ተራዳኢነት አይለየን ሀገራችንን ዳሯን እሳት መሐሏን ገነት አድርጎ ፈጣሬ አለማት አምላካችን #እግዚአብሔር ይጠብቅልን የተባረከ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ምእመናን ሆይ
ሌባ ከዘረፈ በኋላ ድፍትፍት ነው የሚያረገው ገንዘቡን ለምን
ምክንያቱም የራሱ ገንዘብ ስላልሆነ ነው
ነፍሳችን ህይወታችን በዲያቢሎስ እጅ ከሆነ
በዝሙት ፣ በእርኩስት፣ በዘፈን ፣ በበደል ፣ በኃጢአት ከሆነ
ያባክነናል ድፍትፍት ያደርገናል ምእምናን
የእግዚአብሔር ስንሆን ነው እሱ በክብር የሚይዘን
እሺ እድሜ ቢኖረን ሺውን ሙሉ
ለእግዚአብሔር ብንሰጠው ያንሳል
ህይወታችን በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ
ፈጣሪ አምላክ ይርዳን🙏
መስከረም 9/2017 #ፃድቁ_አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ #አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ወርሐዊ መታሰቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስ አባታቸው መልአከ ምክሩ እናታቸው ወለተ ማርያም ይባላሉ የተወለዱበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ነው
👉በተወለዱ ዕለት ተነሥተው በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ብለው #ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል የስማቸው ትርጓሜ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ አንድም #የክርስቶስ እስትንፋስ ማለት ነው
👉ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸውና በመንገዳቸው ሁሉ እየመራቸው ነው ያደጉት #መንፈስ_ቅዱስ ልቡናቸውን ብሩህ አድርጎላቸው በ5 ዓመታቸው የቅዱሳት መጻሕፍት ቃላትን፣ ብሉያትንና ሐዲሳትን፣ ድርሳናትንም ጠንቅቀው ዐውቀዋል
👉በተወለዱ በ14 ዓመታቸው ወደ #አቡነ_ኢየሱስ ሞዐ ደብረ ሐይቅ ገዳም ሄደው ከባሕር ዳር ቆመው የሙሴን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር በጸለዩ ጊዜ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ባሕሩን አሻግሯቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተዋል፡፡
👉ለ3 ዓመታት ያህል በኃይቅ ገዳም ለመነኮሳት እንጨት በመልቀምና ውሃን በመቅዳት #ለአባቶች_መነኮሳት ምግብ የሚሆናቸው ዓሣ ከባህር ውስጥ በማውጣት አገልግለዋል፡
👉አባታችን #እስትንፋሰ_ክርስቶስ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ከፆሙ በኋላ ምንም እህል ሳይቀምሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ ለሙሴ በደብረ ሲና እንደሰጠው ለአባታችንም ወደ እርሳቸው መጥቶ ዓሥሩን ቃላተ ኦሪትና ስድስቱን ቃላተ ወንጌል በውስጣቸው የተጻፈባቸው ሁለት ጽላቶችን ሰጥቷቸዋል፡፡
👉አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሠሩ በኋላ ዕለቱን ስንዴ ዘርተው፣ ወይን ተክለው፣ ጽድን ወይራንና ግራርን ተክለው በአንዲት ቀን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ዕለቱን አድርሰዋል ስንዴውን ለመሥዋዕት ወይኑን ለቍርባን በተአምራት አድርሰዋል፡፡
👉አባታችን በጸሎት ላይ እንዳሉ ቅዱስ ሚካኤል ተልኮ መጥቶ አባታችንን በደመና ጭኖ ወስዶ ከጌታችን ከመድኃኒታችን #ከኢየሱስ_ክርስቶስ ፊት አቆማቸው ጌታንም በቅዱሳኑ ሁሉ እንዲባረኩ ካደረጋቸው በኋላ መልአኩን ‹‹ወደ ተወለድኩባትና ወደ ኖርኩባት ቦታ ወደ ኢየሩሳሌም አድርሰው›› ብሎት ኢየሩሳሌምን አሳልሞ ሀገራችን መልሶ አምጥቷቸዋል
👉አባታችን ሁሉንም የኢትዮጵያን ቅዱሳት ገዳማትን ተዘዋውሮ ሲጎበኙ በሕይወተ ሥጋ የሌሉት የየገዳማቱ ቅዱሳን ሁሉ በአካል ይገለጡላቸው ነበር ጎጃም ውስጥ እያስተማሩ፣ !፣ የታመሙትን እየፈወሱ፣ የዕውራንን ዐይን እያበሩና ሙታንን እያሥነሱ ብዙ ካገለገሉ በኋላ ለዘጠኝ ዓመታት በባሕር ውስጥ ገብተው ቁልቁል ተዘቅዝቀው #ለኢትዮጵያ_ፀልየው የምሕረት ቃልኪዳን ተቀብለዋል
👉ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ጌታችን መጥቶ ‹‹ከመነኮሳት ሁሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ ሆይ #ኢትዮጵያንና_ሕዝቦቿን ምሬልሃለሁ ከዚህች ባሕር ውጣ በማለት በሞት የሚያርፉበትን ቦታ ነግሯቸዋል፡፡
👉ጻድቁ ወደ ደብረ አሰጋጅ በሚሄዱበት ጊዜ ጸሐይ ልትገባ ስትል ‹‹በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አውግዤሻለሁ ለመስፍን ኢያሱ በገባኦን እንደቆምሽ አሁንም ቀጥ ብለሽ ቁሚ ብለው ፀሐይን አቁመዋል አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስም ደብረ አሰጋጅ ሲደርሱ ፀሐይ አፍ አውጥታ ‹‹አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ እገባ ዘንድ ፍታኝ›› ስትላቸው #እግዚአብሔር_ይፍታሽ ባሏት ጊዜ ጠልቃለች
👉ጻድቁ ሌላው በእጅጉ የሚታወቁበት አንድ ትልቅ ቃል ኪዳን አላቸው በአምላክ ልቡና የሚገኝ፣ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ልቡና የሚገኝ፣ በቅዱስ ሚካኤልና በቅዱስ ገብርኤል ልቡና የሚገኝ እንደ #መልክአ_መድኃኔዓለም ያለች እጅግ አስገራሚ ፀሎት አለቻቸው፤ እርሷን ፀሎት በፀለዩ ጊዜ እልፍ ነፍሳትን ከሲኦል ያወጣሉ
👉ጸሎቷም #የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች እያንዳንዱ የሰውነት ክፍሎቹ የተቀበሉትን ጸዋትዎ መከራዎች ሁሉ ታዘክራለች በእያንዳንዱ ክፍልም የጸሎት ማሳረጊያ #አቡነ_ዘበሰማያት ይደግማሉ ንስሓ የገባ ኃጢአተኛ ሰው እንኳን ቢሆን ይህችን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት በጸለየ ጊዜ ሺህ ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ ጌታችን በማይታበል ቃሉ ለአባታችን ነግሯቸዋል
👉እያንዳንዱን #የመድኃኔዓለምን የሰውነት ክፍሎች በሙሉ እየጠቀሰች መከራዎቹን የምታዘክረውን ይህቺን በአምላክ ልቡና ያለች ግሩም የሆነች ፀሎት ነፍሳትን ከሲኦል አታወጣም ብሎ የሚጠራጠር ቢኖር መንግስተ ሰማያትን አያያትም ፃድቁ ታኅሣሥ 8 ቀን ተወልደው ሚያዚያ 9 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከፃድቁ ረድኤት በረከት ያሣትፈን #የፃድቁ_አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ምልጃና ፀሎት ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን" ✝️💒✝️
#መስከረም_9
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
መስከረም ዘጠኝ በዚህች የመላእክት አለቃ #ቅዱስ_ሚካኤል በሮም አገር ፍሩምያ በምትባል ከተማ ላደረገው ተአምር መታሰቢያ ነው፣ #ቅዱስ_አባት_አባ_ቢሶራ በሰማዕትነት አረፈ፣ #ቅዱስ_ያሳይ_ንጉሥ እረፍቱ ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ሚካኤል
መስከረም ዘጠኝ በዚህች ቀን በሮም አገር ፍሩምያ በምትባል ከተማ ለሆነው ተአምር መታሰቢያ ሆነ። ይህም እንዲህ ነው የሰማይ ሠራዊት አለቃ በሆነ በከበረ መልአክ በሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚታዩ ድንቆችና ተአምራቶች ምክንያት ዮናናውያን ሰዎች ሰይጣናዊ ቅናትን እንደ ቀኑ ከመቅናታቸውም ብዛት የተነሣ በዚያ አካባቢ የሚወርደውን የወንዝ ውኃ በዚያች ቤተ ክርስቲያን ላይ ሊመልሱትና ከሚጠብቃት መጋቢዋ ጋር በውኃ ስጥመት ሊአጠፉአት ፈልገው መለሱት።
የሰማያውያን ሠራዊት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለቤተ ክርስቲያኑ መጋቢ ለናርጢኖስ ተገለጠለት ወደርሱም ቀርቦ ጽና አትፍራ አለው ይህንን ብሎ በእጁ ውስጥ ባለ በትር አለቱን መታው አለቱም ተደንጥቆ እንደ በር ሆነ የዚያ ወንዝ ውኃም በውስጡ አልፎ ሔደ።
ይህንንም ያዩ ምስጉን እግዚአብሔርን አመሰገኑት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልንም አከበሩት። ከዚያች ቀን እስከ ዛሬ የወንዙን ውኃ በዚያች በተሠነጠቀች አለት ውስጥ አልፎ ሲሔድ ያዩታል ወደ መላእክት አለቃ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከቶ አይቀርብም።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባት_አባ_ቢሶራ
በዚህችም ቀን መጺል የምትባል አገር ኤጲስቆጶስ ቅዱስ አባት አባ ቢሶራ በሰማዕትነት አረፈ።
ይህም ቅዱስ በግብጽ አገር እግዚአብሔርን በምትወድ መጺል በምትባል ከተማ ኤጲስቆጶስ ሆነ። ዲዮቅልጥያኖስም ነግሦ ክርስቲያኖችን በሚያሠቃያቸው ጊዜ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ስም ደሙን ያፈስ ዘንድ ይህ አባት ወደደ።
ሕዝቡንም ሀሉ ሰብስቦ በቤተ መቅደሱ ፊት በዐውደ ምሕረቱ አቆማቸው ሊጠብቁት የሚገባውን ለጽድቅ የሚያበቃቸውን ትእዛዝ ሁሉ አዘዛቸው። ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ስም ደሙን ማፍሰስ እንደሚሻ ነገራቸው ይህንንም በሰሙ ጊዜ ታላቆችም ታናሾችም በላዩ አለቀሱ።
የሙት ልጆች እንሆን ዘንድ የምትተወን ምን ያደርግልሃል እኛስ እንድትሔድ አንለቅህም አሉት ሊይዙትም ቃጡ ግን አልተቻላቸውም ተውትም እርሱም ወደ ክብር ባለቤት ክርስቶስ አደራ አስጠበቃቸውና ሰላምታ ሰጥቷቸው ከእነርሱ ዘንድ ወጥቶ ተጓዘ። እነርሱም መሪር ልቅሶን እያለቀሱ ሸኙት።
ስማቸው ቢስኮስ ፊናቢክስ ቴዎድሮስ የሚባሉ ኤጲስቆጶሳት አብረውት ሔድ መኰንኑ ወደ አለበት አገርም ደርሰው የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ። እርሱም መኰንኑ አሠቃያቸው ኤጲስቆጶሳትም እንደሆኑ አውቆ ሥቃያቸውን አበዛ እሊህ አባቶች ግን በታላቅ ትዕግሥት የጸኑ ናቸው። ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስ ያጸናቸዋልና።
ከዚህም በኋላ መኰንኑ ራሶቻቸውን በሰይፍ ይቆርጧቸው ዘንድ አዘዘ የሕይወት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። የቅዱስ ቢሶራ ሥጋው ግን ንሲል በሚባል አገር እስከ ዛሬ ይኖራል።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ያሳይ_ንጉሥ
በዚችም ቀን ተጋድሎውን በዛፍ ላይ ሆኖ የፈጸመ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘ ንጉሥ ያሳይ አረፈ።
በቀደመው ዘመን መንግስታቸውን ትተው ከመነኑ ነገሥታት አንዱ ቅዱስ ያሳይ ነው። ምናኔ በቁሙ ከባድ ነው። መንግስትን፣ ዙፋንን፣ ክብርን ትቶ መመነንን ደግሞ ከማድነቅ በቀር እንዲህ ብለው ሊገልጹት ይከብዳል።
ቅዱስ ያሳይም መንግስቱን ትቶ ልምላሜ ወደሌለበት ደረቅ በርሃ ሔደ። በዚያም ከአንዲት ዛፍ በቀር ምንም ነገር አላገኘም። በዚያች ደረቅ ዛፍ ላይ ወጥቶ ለዓመታት በጾምና በጸሎት ተጋደለ።
በዘመነ ተጋድሎው ከዛፏ አልወረደም ሰውም አይቶ አያውቅም። በመጨረሻም ስለ ቅድስናው ዛፏ ለምልማለች። እርሱም በዚህች ቀን ዐርፏል።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም ቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መስከረምና_ዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ)