kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://vm.tiktok.com/ZMhUoVPW3/

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

ይሄ ልብስ የማን መታወቂያ ነው ማለት

አሁን ሴት ሱሪ ብትለብስ ኃጢአት ነው ፅድቅ ነው ?
ሴት ሱሪ ስትለብስ ማንን ነው ምታሳየው ?

ክርስቶስን ነው ምታሳየው ?
ድንግል ማርያምን ነው ምታሳየው ?
ነው ማንን ነው ምታሳየን ?

እውነት ይሄ ነገር ክርስቶስን ያሳያል ብላችሁ አስቡና ያሳያል ካላችሁ ልበሱት

ቅዱስ ጳውሎስ

ተፈጥሮ አያስተምራችሁምን ?
በተፈጥሮ አትማሩም ወይ ?
ማን ምን መልበስ እንዳለበት ከተፈጥሮ አትማሩምን ?

እንዴ ብለው ሴቶች ይጠይቃሉ?

ኦሪት ዘዳግም ያለውም እኮ ሴት የወንድን አትልበሰ ወንድ የሴትን አይልበስ እንጂ ሱሪ የወንድ ነው የሚል የለም ብለው ይጠይቃሉ?

ተመልከቱ

ለክፋት ለተንኮልማ ይራቀቃሉ ይላል ኢሳያስ
ለተንኮል ሊቅ ናቸው አለ በእውነቱ
ግን ተፈጥሮ አያስተምራችሁም ወይ

ስትናገሩ ስትሳደቡ የማን መዓዛ ናችሁ
ንግግራችሁ ማንን ነው የሚገልጠው

የባለትዳሮች ትዳር የካህናት ክህነት
እውነት ክርስቶስን ነው የሚያሳየው ወይ

የምታስቀድሱት የምትቀድሱት ማንን ልታሳዩ ነው ?

ርዕሰ ሊቃውንት ቆሞስ አባ ገብረ ኪዳን❣️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች ሆይ

ነገር ሁሉ ለበጎ ነው

በአንድ ወቅት አንድ መንፈሳዊ አባት

ከነበሩበት ቦታ ወደ በረሃ መሰደድ ግድ ሆነባቸው።
ከቅዱስ መጽሐፋቸው ሌላ ሦስት ነገሮች ነበሯቸው፡፡

እነሱም

👉 ቅዱስ መጽሐፉን በጨለማ ወቅት ለማንበብ የሚጠቅማቸው
ኩራዝ ፣ጎህ ከመቅደዱ በፊት ከእንቅልፍ የሚቀሰቅሳቸው አንድ አውራ ዶሮ እና ለመጓጓዣነት የሚገለገሉበት አንድ አህያ ነበሩ።

👉 አንድ ቀን ምሽት ከጉዞ የተነሣ በጣም ስለ ደከሙ እኚህ መንፈሳዊ አባት ወደ አንድ መንደር ቀርበው ማደሪያ ቢጠይቁም መንደርተኛው ፈቃደኛ ባለመሆኑ ማንም አላሳደራቸውም።

👉ስለዚህም ከመንደሩ አቅራቢያ አንድ ጉድጓድ ያገኙና በዚያ ውስጥ ገብቶ ለማደር በመወሰን ገብተው አደሩ፡፡

👉 እንደ ወትሮው ቅዱስ መጽሐፋቸውን ለማንበብ ኩራዛቸውን ቢለኩሱትም የነበረው ብርቱ ነፋስ አጠፋባቸው፡፡

👉ስለዚህም ለመተኛት ጋደም እንዳሉ ተኩላ መጥቶ አውራ ዶሮዋቸውን፣ አንበሳም አህያቸውን በሉባቸው፡፡

👉የተደራረበ ጉዳት ስለደረሰባቸው ሽማግሌው እርዳታን በመሻት ወደዚያ መንደር ቢመለሱ ዘራፊ ሽፍታዎች የመንደሩን ነዋሪዎች በሙሉ ገድለው ንብረት ዘርፈው ዖና መንደር ሆኖ አገኙት።

👉ሽማግሌው ይህን ሁሉ ባጤኑ ጊዜ እግዚአብሔር ምን ያህል መልካም ነገርን እንዳደረገላቸው አስተዋሉ።

👉በዚያች ምሽት በመንደርተኞቹ በአንዱ ቤት ቢያድሩ ኖሮ የዘራፊዎች ሰለባ ሆነው ሊገደሉ በቻሉ ነበር።

👉 ቀንዲላቸውንም ነፋስ ባያጠፋው የብርሃኑ ወጋገን እዚህ ጋር ሰው አለ በማለት ለሽፍታዎቹ ያሳብቅ ነበር።

👉አውራ ዶሮአቸውና አህያቸውም ባይበሉ ኖሮ ከሽፍታዎቹ ተደብቀው ማደር ባልቻሉ ነበር።" እግዚአብሔር ከክፉ ነገሮች ውስጥ መልካም ነገር ማውጣት የሚችል አምላክ ነው። "

ስለዚህ እንዲህ በሉ፦

"የሚደርስብኝ ፤ የሚገጥመኝ
ፈተናና መከራ ሁሉ አምላኬ ሆይ ለበጎ ታደርግልኛለህና አመሰግንሐለሁ
" አሜን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

👏💁‍♀💁 ሰዎችን add ያድርጉ ገንዘብ ይስሩ !

⚜ አንድ ሰው add ሲያደርጉ 100 ብር ይሰራሉ ።
⚜ 50 ሰው add ሲያደርጉ 5000 ብር ይሰራሉ
⚜ 100 ሰው add ሲያደርጉ 10000 ብር ይሰራሉ
⚜ 200 ሰው add ሲያደርጉ 20000 ብር እና ሌሎች ሽልማቶችን ያገኛሉ።

እስካሁን የጋበዙት ሰው መጠን: 0 ሰው ነው

🔰 መጋበዣ ሊንክ : 👇👇👇👇👇👇
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇          /channel/donkytube_officale
/channel/donkytube_officale
/channel/donkytube_officale
/channel/donkytube_officale

✅ ዛሬውኑ ጀምሮ ገንዘብ ያካማቹ እና  ይቀበሉ ።
❌ ማሳሰቢያ : ወደ ግሩፑ እድ ካላደረጉ ሽልማቶን መውሰድ አይችሉም።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የምክር ቃል

ከቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ


ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡
እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡
ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹህ ይሁን፡፡
ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ ቃላቶችህ የተመጠኑ እና ጤናሞች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡

የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤
ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡
ወደ ጭቅጭቅ እና ንትርክ ከመግባት ራህን ጠብቅ፡፡
የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡
ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡

የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤
የባልንጀራህ ኃጢአት አትግለጥ፡፡
የባልጀራህ ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡
በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ
በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡

ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ
ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡
ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡

ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ
ኃጢአቱን ልክ በእሳት ፊት እንደወደቀ ገለባ
ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡

ተፈጥሮ እንደ መጽሐፍ ፍጥረታት እንደ ጽላት ይሁኑህ፡፡
ከእነሱ ሕግጋትን ተማር፤
በተመስጦ ሆነህ በመጽሐፍ ያልሰፈሩትን ምስጢራት ተረዳ።

እግዚአብሔርን ከሚፈራ በቀር ባለጸጋ የሆነ ሰው ማነው?
የእውነት እውቀት ከጎደለው ሰው በላይ ፍጹም ደሃ የሆነ ማን ነው? ሁል ጊዜም እውነተኛ ፍቅራችን ጸንቶ ይቀጥል ዘንድ
ወደ እግዚአብሔር ጸልይ፡፡ እርሱን ለምነው፡፡
ስለ ቸርነቱ ምስጋና አቅርብ፤ ምክሬን ፈጽሞ ቸል አትበል፡፡


የቅዱስ ኤፍሬም በረከት አይለየን🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

መስከረም 30/2017 #መጥምቀ_መለኮት_ቅዱስ_ዮሐንስ
#ሐዋርያዉ_ቅዱስ_ማርቆስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሣኑ ስም ለምናመሰግንበት ለቅዱሣኑ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ #ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም ማቴ.11፥11

👉የጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ቃል ስለ መጥምቀ መለኮት #ቅዱስ ዮሐንስ ክብር መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በጌታ የተከበረ ነቢይ እና ጻድቅ ነው እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ የለም በማለት የተናገረለት ቅዱስ አባት ነው

👉የመጥምቀ መለኮት #ቅዱስ_ዮሐንስ
የተሰጡት ሃብተ ፀጋዎች

1 👉 ነብይ
2 👉 ካህን
3 👉 መምህር
4 👉 ሐዋርያ
5 👉 ፃድቅ
6 👉 መጥምቅ
7 👉 ሰማእት ነው

👉 #ቅዱስ_ዮሐንስ ከነቢያት ሁሉ የሚበልጥ መሆኑን ጌታችን ሲናገር እንዲህ ብሎ ተናግሮለታል ከነቢያት ሁሉ የሚበልጥ #ነብይ ነው እላችኋለሁ በማለት መስክሮለታል

👉 #ቅዱስ_ዮሐንስ ሃቀኛ መምህር፤ ነቢይ፤ ካህን፤ ሰማዕት፤ ሐዋርያ በመሆኑ ከአምላኩ ክብርን የተቀበለ ቅዱስ አባት ነው ስለዚህ ነው ደግሞ ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ እራሱ ግልጽ አድርጎ ስለ #ቅዱስ_ዮሐንስ ክብር የተናገረው

👉ትንቢት የተነገረለት #ቅዱስ_ዮሐንስ ክብሩ በመልአኩ እንዲህ በማለት ነው የተመሠከረለት #በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ነቢይ እንደሆነ #በመንፈስ_ቅዱስ የተመረጠ በንጽሕናው በአገልግሎቱ #በመላእክት ደረጃ የሚታሰብ ሲሆን ምልጃና ፀሎቱ የከበረዉ
ቃል ኪዳን ሁላችንንም ይጠብቀን

👉ለኢትዮጲያና ለግብፅ አባታችን አስተማሪያችን የሆነዉ ሐዋርያዉ #ቅዱስ_ማርቆስ በዚህ እለት የመታሠቢያ በአሉ ሲሆን ምልጃና ፀሎቱ ረድኤትና በረከቱ የአባትነት ፍቅሩ አይለየን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ረድኤት በረከት ያሣትፈን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ጌታችን ለዮሐንስ ያልነገረው እርሱም ያላስተማረው ምሥጢር የለም፡፡ ወንጌሉን መጻፍ ሲጀምር "በመጀመሪያ ቃል ነበረ፣ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ…" ብሎ የጌታችን ነገር ተመራምሮ ለመድረስ ሲል በመሀል መልአኩን በዮርዳኖስ ባሕር ላይ ሲሄድ አገኘው፡፡ መልአኩም የዮርዳኖስን ባሕር በእንቁላል ቅርፊት እየጨለፈ ወደ ውጭ ሲያፈስ ተመለከተው፡፡ ዮሐንስም ተገርሞ "ምን ማድረግህ ነው" አለው፡፡ መልአኩም "የዮርዳኖስን ባሕር ቀድቼ እየደፋሁ ልጨርሰው ነው" ሲለው ዮሐንስም መልሶ "ታዲያ በእንቁላል ስባሪ ነውን?" አለው፡፡ መልአኩም "አዎን" አለው፡፡ ዮሐንስም "በከንቱ ደከምክ" አለው፡፡ ይህን ጊዜ መልአኩም መልሶ "አንተስ እንጂ ደግሞ የአምላክን መገኘት፣ አኗኗሩንም ተመራምረህ በጥበብ ለማግኘት ብለህ 'በመጀመሪያ ቃል ነበረ፣ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ..' ብለህ ጀምረህ የለምን? አንተ ጌታን ተመራምረህ ካገኘህና ከደረስክበት እኔም የዮርዳኖስን ወንዝ በዚህ እንቁላል ቅርፊት ቀድቼ እጨርሰዋለሁ" አለው፡፡ ዮሐንስም ይህን ጊዜ ደንግጦ ዝቅ ብሎ "ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ…" ብሎ ሀሳቡን ለወጠና ሌላ ታሪክ ቀጠለ፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ ጌታችንን እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ክርስቲያኖችን ሁሉ ወክሎ እመቤታችንን በአደራ የተቀበለ እርሱም ለመቤታችን በአደራ የተሰጠ ሲሆን እመቤታችንን ከወሰዳት በኋላ ለ16 ዓመት እየተንከባከበ ጠብቋታል፡፡ እናቱም በሕፃንነቱ ስለሞተች እመቤታችን ናት እየተንከባከበች ያሳደገችው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ በመልኩም ከጌታችን ጋር ይመሳል ነበር፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ሥዕል የመሳል ተሰጥኦም ነበረው፡፡ ጌታችን በተሰቀለበት ዘመን የነበረው ጢባርዮስ ቄሳር ልጁ በሽተኛ ነበር፡፡ የጌታችንን የማዳን ሥራ እየሰማ እነ ጲላጦስም ስለጌታችን የሚጽፉለትን ይሰማ ስለነበር ልጁን ከጌታችን መቃብር ላይ እንዲያኖሩለት ላከው፡፡ ልጁም ፈጥኖ ተፈወሰለት፡፡ ጢባርዮስ ቄሳርም በልጁ መዳን ምክንያት የጌታችንን ውለታ ማስቀመጥ ፈልጎ የጌታችንን ሥዕሉን የሚሥልለትን ሲያጠያይቅ ዮሐንስን አገናኙት፡፡ ዮሐንስም ጌታችንን ልክ በዕለተ ዓርብ እንደተሰቀለ አድርጎ በመሣል ለጢባርዮስ ቄሳር ሰጠው፡፡ ሲሥለውም በመጀመሪያ ጌታችንን ልክ እንደተሰቀለ አድርጎ ራቁቱን ነበር የሳለው፡፡ ዮሐንስ የሳለው የጌታችን ሥዕልም አፍ አውጥቶ "በመጀመሪያ አይሁድ በኢየሩሳሌም ራቁቴን ሰቀሉኝ፣ አሁን ደግሞ አንተ ድጋሚ በሮም ራቁቴን ትሰቅለኝን?" ብሎ ተናገረው፡፡ ዮሐንስም እጅግ ደንግጦ "እንዴት አድርጌ ልሳልህ?" ብሎ የሳለውን ሥዕል ቢጠይቀው ሥዕሉም "ከለሜዳ አልብሰህ ሳለኝ" አለው፡፡ ዮሐንስም እንዳለው ከለሜዳ አልብሶ ከሳለው በኋላ ሥዕሉን ትኩር ብሎ ተመልክቶ ቢስመው ከንፈሩ አንድ ቀን ተኩል ያህል ተጣብቆ ቆይቷል፡፡ ዛሬም ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የምትጠቀምባቸውን የጌታችንን ስነ ስቅለት የሚያሳዩ ሥዕሎች መገኛቸው ይህ ወንጌላዊው ዮሐንስ የሳለው ሥዕል ነው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ በተለያዩ ስሞች ይጠራል፦
በሕይወቱና በኑሮው ሁሉ ጌታችንን ለመምሰል ይጥር ነበርና ጌታችንም እጅግ ይወደው ስለነበር "#ፍቁረ_እግዚእ" ተባለ፣ የታላቁ ያዕቆብ ታናሽ ወንድም ስለሆነና አባቱም ዘብድዮስ ስለሚባል "#ዮሐንስ_ወልደ_ዘብድዮስ" ተባለ፣ ለጌታችን ባለው ቅናትና ከወንድሙ ጋር ሆነው ባሳዩት የኃይል ሥራ እንዲሁም የጌታችንን አምላክነት በመግለጡ "#ወልደ_ነጎድጓድ" ተብሏል፣ ነገረ መለኮትን ከሌሎቹ በበለጠ ሁኔታ አስፍቶና አምልቶ በማስተማሩ "#ነባቤ_መነኮት ወይም #ታኦሎጎስ" ተብሏል፣ ኃላፊውንና መጻዒውን ጊዜ በራእዩ ስለገለጠ "#አቡቀለምሲስ" ተባለ፣ ይህም በግሪክኛ #ባለራእይ ማለት ነው፣ የጌታችንን መከራ መስቀሉን እያስታወሰ 70 ዘመን ሙሉ እያለቀሰ ስለኖረና ፊቱም በሀዘን ስለተቋጠረ "#ቁጹረ_ገጽ" ተብሏል፡፡

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ሁሉ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኅ_መስከረም እና #ከገድላት_አንደበት)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

አንድን ሰው

ገበናውን ስንሸፍንለት እንዲድን እናደርገዋለን

አንድ ታሪክ አለ

አንድ በበረሀ የሚኖር አባት አለ
ከንጉሥ ቤት ተጠርቶ ይሄዳል
ሰው አያውቅም ሴትም አይቶ አያውቅም
እና ባርክልን ተብሎ ነው የሄደው
ሌሊት ለፀሎት ቤት ሰጠውት
ንጉሡም ከማረፊያው ሄዷል
ሰራዊቱም እንደዛው ማረፊያቸው ሄደዋል

ይሄ ባህታዊ

ተነስቶ ከንግስቲቷ ይሄዳል ሌሊት
የማይገባ ጥያቄ ይጠይቃታል

ንግስቲቱ

ተው አባ የዘላለም ክብርህን
በአንድ ቀን ታጣለህ ትለዋለች።

አንቺ እኔን ልትመክሪ ነው
አይሆንም ፈቃዴን ፈጽሚ ይላታል።

ይሄን ባላት ጊዜ ጮኸች እሷ

ሰው ሁሉ መጣ ንጉሡም መጣ ሠራዊቱ ሁሉ መጣ
ምን ሆነሽ ነው ሲላት ደሞ ፊቷ ላይ ቆሟል

በፀሎት አስበኝ ብየው ሌሊት ደንግጨ ጠርቼው
ከአፉ የሚወጣው የእሳት ብርሃን አስደንግጦኝ
ሲፀልይ ከአፉ ሚወጣው ብርሃን ብላ ትናገራለች

እነሱ ሁሉ ሰግደው አባ በፀሎት አስበን

ኧረ እኔ ኃጢአተኛ ነኝ
በሀጥያቴ ነው እንጂ እንደዚህ አይደለም
ቢል ማን ይሰማዋል ሰው ሁሉ እየሄደ መስገድ

እና እንደዚህ አድርጋ አሳፍራ ኃጢአቱንም አስቁማ
ደሞ ሰውየወንም ከመከራ ጠብቃ
ወደ ገዳሙ ተመልሶ እንደኖር አድርጋ
በክብር እንዲበቃ አድርገዋለች

ሰዎችን

ገመና ሽፍነን በውስጥ ብናስተካክላቸው
የወደቁ ሰዎች ይነሳሉ ለክብር ይበቃሉ

እና ይሄንን ነው ማድረግ ያለብን

ቸሩ እግዚአብሔር የወደቁትን እንድናነሳ ኃይሉን ይስጠን🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_አቡነ_ሀብተማርያም

ወር በገባ #በ_26 በቤተክርስቲያናችን ታስበው ከሚውሉት ጌታችን አምላካችን ቃል ኪዳን ከገባላቸውን ቅዱሳን አባቶቻችን አንዱ ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ሀብተማርያም ነው።
ታዲያ ጻድቁ አቡነ ሀብተማርያም ማን ነው ? ምን ቃል ኪዳን ተሰጠው?

ጻድቁ ማን ናቸው? ሚለውን በዝርዝር ሌላ ጊዜ ምንመለስበት ሁኖ አሁን ግን ስለተገባላቸው ቃል ኪዳንና ስለተሰጣቸው አክሊለ ጽድቅ ብቻ ባጭሩ እንናገራለን።
👇👇👇👇👇👇👇👇
#ጻድቁ_አቡነ_ሀብተማርያም በሀገር ላይ በታዘዙ አምስት መቅሰፍቶች ላይ የማማለድ ፀጋ ከጌታ ዘንድ የተሰጠው ባለ ብዙ ቃል ኪዳን ጻድቅ ነው።
እነሱም፡-
👇👇👇👇👇
፩. መብረቅ፣
፪. ቸነፈር፣
፫. ረሃብ፣
፬. ወረርሽኝ፣
፭. የእሳት ቃጠሎ ናቸው፡፡

ከመልካም ስራዎቹ ብዛት የተነሳ ፯ የፅድቅ አካሊላት ከጌታችን የተሰጠው ፃድቅ ነው።
#ጌታ_ለጻድቁ_አቡነ_ሀብተማርያም የሰጠው ፯ቱ #የጽድቅ_አክሊላት፦
👇👇👇👇👇👇👇👇
፩. ስለ ንፁህ ድንግልናህ፣
፪. አለምንና በውስጡ ያለውን ንቀህ በመኖርህ፣
፫. ስለ ፍፁም ምንኩስናህ፣
፬. ዘወትር አራቱን ወንጌላትን በማንበብህና በመፀለይህ፣
፭. ስለ እኔ ብለህ ስለተራብከው፣
፮. በጾም ስለተጋደልክ፣
፯. ቂምና ጥላቻን፣ ትዕቢትን፣ ትምክህትን፣ በልብህ ውስጥ ባለማስቀመጥህ ስለ ንፁህ ተልዕኮ ክህነትህ፣ ስለ ንፁህ መስዋዕትህ ነው ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡

የአባታችን የአቡነ ሀብተ ማርያም በረከታቸው ይደርብን አሜን።

ምንጭ፦ገድለ አቡነ ሀብተማርያም

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🌹 "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌹

🌹 #መስከረም ፳፮ (26) ቀን።

🌹 እንኳን #ለመላእክት_አለቃ_ለቅዱስ_ገብርኤል ወደ በራክዩ ልጅ ወደ #ቅዱስ_ዘካርያስ_ለተላከበት #መጥምቀ_መለኮትን ከእርሱ ስለ መወለዱ ለአበሰረበት፤ ( #ለመጥምቀ_መለኮት #ለቅዱስ_ዮሐንስ_ለጽንሰት_በዓል)ና ለሰማዕቱ #ለቅዱስ_ዮስጦስ_ልጅ_ለቅዱስ_አቦሊ ለሥጋው ፍልሰት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከዐሥር_ሽህ_ሰማዕታት፣ #ከቅድስት_አጋታ_ከበርባራ_ከዮልያና፣ #ከአባት_ጊዮርጊስም_ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

✝ ✝ ✝
🌹 #የየመላእት_አለቃ_ቅዱስ_ገብርኤል #ለቅዱስ_ዘካርያስ_የመጥምቀ_መለኮትን_የቅዱስ_ዮሐንስ_መጸነስ_እዳበሰረው፦ ስሙ የተመሰገነ እግዚአብሔር ልጅን ይሰጠው ዘንድ አስቀድሞ ሁል ጊዜ በመጸለይ ወደ እግዚአብሔር ይማልድ ነበር። ልጅ ያልወለደውን እግዚአብሔር ብዙ ተባዙ ምድርን ምሉዋት ያለውን በረከት ያጣ ነው በማለት እስራኤል ይገዳደሩት ነበርና።

🌹 ልመናውንም ሰማ በቤተ መቅደስም ቁሞ ዕጣንን ሲያሳርግ መልአኩን ላከለት በከበረ ወንጌልም እንደተባለ መንገዱን ይጠርግ ዘንድ በንጉሥ ክርስቶስ ፊት እንደሚሔድ የተነገረለት ታላቅ ነቢይ ዮሐንስ ከእርሱ መወለዱን አበሠረው።

🌹 ዘካርያስም የሰውነቱን መድከም የመውለጃውም ዘመን እንዳለፈና ፈጽሞ እንዳረጅ የሚስቱም እንዲሁ ዘመኗ እንዳለፈና ፈጽማ እንዳረጀች መካንም እንደሆነች ያውቃልና ስለዚህ ይህ ነገር እንዴት ይሆንልኛል "እኔ ያረጀሁ ሽማግሌ ነኝ ሚስቴም እንዲሁ ዘመኗ አልፎ መካን ሁናለች" ብሎ የእግዚአብሔርን መልአክ ተከራከረው።

🌹 መልአኩም "እኔ ይህን ልነግርህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወዳንተ ተልኬ ነበር ልትጠራጠር ባልተገባህም ነበር አሁንም ይህ በጊዜው እስቲፈጸም ዲዳ ሁነህ መናገር ይሳንሃል" ብሎ ገሠጸው። ዘካርያስም የወልደ እግዚአብሔርን መንገድ የሚጠርግ ዮሐንስ እስከሚወለድበት ጊዜ ድረስ ዲዳ ሆነ።

🌹 በሚገረዝበትም ቀን የሕፃኑን አባት ዘካርያስን የሕፃኑን ስም ምን ብለው እንደሚሰይሙት ጠየቁት እርሱም ብራና ለምኖ "ስሙ ዮሐንስ ነው" ብሎ ጻፈ በዚያም ጊዜ አንደበቱ ተፈትቶ እግዚአብሔርን አመሰገነው። ስለ ልጁ ዮሐንስም እርሱ የልዑል ነቢይ እንዲባል መንገዱንም ይጠርግ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እንደሚሔድ ትንቢት ተናገረ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ዘካርያስና በቅድስት ኤልሳቤጥ በልጃቸው በቅዱስ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✝ ✝ ✝
🌹 "#ሰላም_ለፅንሰትከ_በሠሌዳ_ከርሣ_ዘተገልፈ። ለኤልሳቤጥ እምከ እምድኅረ ወርኃ ኀለፈ። ዮሐንስ መልአክ እንተ ትኴንን አእላፈ። ከመ እፈጽም ዘወጠንኩ ስብሐቲከ ትሩፈ። በውስተ ዕዝንየ አልኆስስ መጽሐፈ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የመስከረም_26።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ጾመ #ጽጌ #እንኳን #አደረሳችሁ !
#ባለማህተቦች🗣

🥀የእመቤታችን ስደት በጾም በጸሎት የምታስቡ ወይም የምታሳልፉ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የቃልኪዳን ልጆች እንኳን አደረሳችሁ

🥀ጾመ ጽጌ ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ያለው አንድ ወር ከዐሥር ቀን ወይም 40 ቀን ወርኃ ጽጌ፣ ዘመነ ጸጌ፣ ተብሎ ይጠራል፡፡ /channel/MoaeTewahedoB

🥀 በነዚህም ቀናት በየቤተክርስቲያኑ የሚነበቡ ምንባቦች፣ የሚዘመሩት መዝሙሮች፣ የሚሰበከው ስብከት፣ የሚቆመው ማኅሌት በጠቅላላው የሚነገረው ስብሐት እግዚአብሔር ሁሉ ሰማይ በከዋክብት ምድር በጽጌያት አሸብርቀው የሚታዩ መሆናቸውን የሚገልጽ ነው፡፡

🥀ወርኃ ጽጌ ለሚከናወነው መንፈሰዊ አገልግሎት መነሻው “መልአኩ ሕፃኑንና እናቱን ወደ ግብፅ ይዘሃቸው ሽሽ፣ የሕፃኑን ነፍስ ሊገድሉት ይፈልጋሉና” ሲል ለዮሴፍ በሕልሙ በነገረው መሠረተ ዮሴፍም ሕፃኑንና እናቱን ድንግል ማርያምን ይዞ ወደ ግብፅ መሰደዱና እመቤታችንና ሕፃኑ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ በስደት ከኖሩ በኋላ /ራእይ.12፣6/ ወደ አገራቸው ወደ ናዝሬት የመመለሳቸው መታሰቢያ ነው፡፡ /ማቴ. 2፣13-23፣ ት.ኢሳ.19፣1፣ እንባቆም 3፣6-7፣ መዝ.83፣3/፡፡

🥀ይህንንም በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሡ አባ ጽጌ ብርሃን ፍሬ ከአበባ አበባም ከፍሬ እንደሚገኝ ሁሉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስን በአበባና በፍሬ እየመለሰ በሚያስረዳው ድርሰታቸው እንዲህ በማለት ገልጸውለታል፡፡ “ አፈወ ሮማን ማርያም ጽጌ ቀናንሞ ወአበሜ፣ እስከ ተጸምሐየየ በጾም ዘመልክዕኪ ጊዜ ድክታሜ፣ እምተመነይኩ ተሳትፎ ከመ አኅትኪ ሰሎሜ፣ ወፍሥሓኪ ዘአልቦ ፍጻሜ”፡፡ ሲተረጎምም የሮማን ሽቱ የቀናንሞ አበባ የምትሆኚ ማርያም ሆይ፣ በርሃብ በጾም አበባ የመሰለ የመልክሽ ደም ግባት እስኪጠወልግ ድረስ በስደትና በልቅሶ የደረሰብሽን ችግርና ድካም መከራሽንም ሁሉ እንደ እኅትሽ እንደ ሰሎሜ አብሬሽ ብቀበል ምኞቴ ነበር፤ በዚህ ፍጻሜ የሌለውን ደስታሽን እሳተፍ ነበር፡፡ እንዲሁም አባ አርክ ሥሉስ በስደቷ የደረሰባትን ኀዘን ፣ ልቅሶና ሰቆቃ አስመልክተው በደረሱት ‘ሰቆቃወ ድንግል” በሚለው ድርሰታቸው እንዲህ አሉ፣ ፀሐይን የምትለብሽ የብርሃን ልጅ ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ከሄሮድስ ዘንድ ልጅሽን ባሸሸሽ ጊዜ የደረሰብሽን ችግሮች ጨረቃን የሚጫሙ እግሮችሽ በመንገድ ብዛትና በአሸዋ ግለት እንደ ጎበጎቡ ሲሰማ ሰው ይቅርና ድንጋዩም ባለቀሰ ነበር”፡ /channel/MoaeTewahedoB

🥀 የእመቤታችን የስደቷ መታሰቢያ ወር በቤተ ክርስቲያናችን የሚከበረው በማኅሌት፣ በቅዳሴና በዝክር ነው፡፡ በወርኃ ጽጌ ባሉት ሳምንታት ከቅዳሜ ማታ እስከ እሑድ ጠዋት አበው ካህናት የሚያቀርቡት ዝማሬ ከቅዱስ ያሬድ ድጓ፣ ከማኅሌት ጽጌና ከሰቆቃው ድንግል የተውጣጣና ሦስት ወገን ያለው ነው፡፡ ዝክሩም፣ በአሁኑ ወቅት በከተሞች አካባቢ እየተረሳ ቢመጣም፣ ዘወትር እሑድ የአንድ አካባቢ ሰዎች ማዕከላዊ በሆነ ቦታ ተሰባስበው በእመቤታችን ስም የሚዘክሩት ነው፡፡ ዐቅመ ደካሞች፣ ድሆችና መንገደኞች ተጠርተው በእመቤታችን ስም እንዲበሉና እንዲጠጡ ይደረጋል፡፡

🥀ይህም ትውፊት እመቤታችን ወደ ኢትዮጵያ በመጣች ጊዜ ኢትዮጵያውያን አባቶችና እናቶች ያደረጉላትን መስተንግዶ ለማሰብ ነው፡፡

🥀የእናታችን እመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም እረድኤቷበረከቷ ፆሎት ልመናዋ ፍቅሯ ጣዕሟ እናትነቷ አማላጅነቷ አይለየን አሜን። ( ሶሲ የፈንታነሽ ልጅ )

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

እኔ

እመቤታችንን እንኳን በገሀድ አይተናት
እንደው በህልማችንም አይተን በሞትን
እንዴት ያለች ውብ ናት ፈጣሪ እንዴት አድርጎ ወደዳት
እንዴት ያለች መልከኛ ናት
መላእክት እኮ ሳስተውላታል

ለቅዱስ ሚካኤል እና ለቅዱስ ገብርኤል


ተመልከቱ አዳምን ፈጥሬ ማድነው በዚች ነው ብሎ
ከክንፋቸው ላይ ሳለላት
ስሎ ቢያሳያት ኧረ ቶሎ ፍጠርልን ኧረ ቶሎ ፍጠራት
ናፍቃናለች ለኛም እህት እንድትሆነን
በንፅህና እንድትመስል ቶሎ ፍጠርልን


ሚካኤል መልአክ በክንፉ ፆራ የተባለች ለዚህ ነው


በክነፉ ፁሮ ክንፋቸው ላይ ስሎ አሳይቷቸዋል
እና ገና ሳያገኟት ሳትወለድ ነበር ሚወዷት
በዚህ ዓለም ላይ የእመቤታችን ፍቅር
እንደ ውሃ የፈሰሰለት ሰው የታደለ ነው

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ለዚህ ነው

ፍቅርሽ እንደ ወይን እና ውሃ በልቤ ውስጥ ተቀላቅሏል
ወይን እና ውሃ ከተቀላቀለ በኋላ
ይሔ ወይን ነው ይሔ ውሃ ነው አይባልም


እኔን ከማርያም ፍቅር ለይቶ ማሳየት የሚችል የለም

እንዴት አድርጎ ቢወዳት ነው እናንተ
እንዴት አድርጌ ላመስግንሽ ይሆን ? አለ
ምን ላድርግ ? ፀጉሬ እንኳን
አፍ አውጥቶ በዚምርልሽ አይበቃሽ ይላታል
ዝም ብዬ ቡርክት ቡርክት ቡርክት እልሻለሁ ይላል።

ስሟ እግዚአብሔር እንዳመሰገነው የከበረ ይሁን ።

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❤️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሰዉ ሆይ

እግዚአብሔር የሚሰጥህን ተስፋ አትጠራጠር
እግዚአብሔር ለአበው የነገረውን ተስፋ አያስቀርም
እግዚአብሔር እውነት ይኖር ይሆን ብለህ

✅ መከራ ሲበዛብህ ጊዜ

ወይ ሐይማኖቴ ትክክል አይደለም
ወይ እግዚአብሔር የለም  ብለህ አትጠራጠር

እግዚአብሔር አለ ።

"ዳዕሙ ትልዎ ለእግዚአብሔር"

እግዚአብሄርን በፍጹም ልቡናህ ተከተለው

አትጠራጠረው

በፍፁም ልቡናህ እመነው

ወእትህድጎ

እሱን ደጅ መጽናቱንም አትተው
ወደ ኋላ አትበል


እግዚአብሔር ን መቅረብህን አታቋርጥ
እግዚአብሔርን አትተወው

እግዚአብሔር ካልተውከው አይተውህም
ካልራቅኸው አይርቅህም

መከራ ብትቀበልም ዝም ብትልም
ዝም ቢልህም ባይመልስልህም
ትቶህ እንዳይመስልህ

ጊዜው ገና ስለሆነ ነው

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❤️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#መስከረም_23

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
መስከረም ሃያ ሦስት በዚህች ዕለት የክርስቶስ ሙሽራው የሆነች #ቅድስት_ቴክላ መታሰቢያ በዓሏ ነው፤ ዳግመኛም #ቅዱሳን_አውናብዮስ_እና_እንድርያስ በሰማዕትነት አረፉ፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስት_ቴክላ_የክርስቶስ_ሙሽራው

መስከረም ሃያ ሦስት በዚህች ዕለት የክርስቶስ ሙሽራው የሆነች ቅድስት ቴክላ የመታሰቢያ በዓሏ ነው፡፡

ይህችውም ቅድስት ለሐዋርያው ለቅዱስ ጳውሎስ ረድእ ሆና ያገለገለች ታላቅ ሐዋርያዊት እናት ናት፡፡ የመቄዶንያ ሀገር ባለጸጎች የነበሩት ወላጆቿ ጣዖት አምላኪ ነበሩና በሕጋቸውና በሥርዓታቸው አሳደጓት፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ወደዚህች ሀገር ገብቶ ቅዱስ ወንጌልን ሰበከ፡፡ ቅድስት ቴክላም ትምህርቱን በሰማች ጊዜ በቤቷ ሆና ሳትበላና ሳትጠጣ 3 ቀን ቆየች፡፡ ከዚህም በኋላ ለሚጠብቃት ዘበኛዋ እንዳይናገርባት በማለት የወርቅ ወለባዋን ሰጠችውና ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሄደች፡፡ እርሱም በደስታ ተቀብሎ የክርስቶስን ሃይማኖት አስተማራት፡፡ በማግሥቱም ቅድስት ቴክላን እናቷ ስትፈልጋት ከቅዱስ ጳውሎስ እግር ሥር አገኘቻት፡፡ ከዚያም ወደ መኰንኑ ዘንድ ሄዳ ልጇ ክርስቲያን መሆኗን በመናገር ከሰሰቻትና ለመኰንኑ አሳልፋ ሰጠቻት፡፡

መኰንኑም ሁለቱን ቅዱስ ጳውሎስንና ቅድስት ቴክላን እንዲያመጧቸው ወታደሮቹን ላከ፡፡ ካመጧቸውም በኋላ መጀመሪያ ቅዱስ ጳውሎስን ወደ እሳት ወረወሩት፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር በተአምራት አዳነው፡፡ ቅድስት ቴክላን ግን ለሀገሩ ልጆች መቀጣጫ ትሆን ዘንድ መኰንኑ ሰውን ሁሉ ከሰበሰበ በኋላ ወደ እሳቱ እንዲወረውሯት አዘዘ፡፡ እርሷ ግን በመስቀል ሦስት ምልክት ካማተበች በኋላ በራሷ ፈቃድ ማንም ሳይነካት ዘላ ከእሳቱ ውስጥ ገባች፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሔር ጥበቃ ልክ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ እርሷም ማንም ሳያያት ከእሳቱ ውስጥ ወጥታ ቅዱስ ጳውሎስ ካለበት ደረሰች፡፡ የራሷንም ጸጉር ቆርጣ በእርሱም ወገቧን ታጥቃ ቅዱስ ጳውሎስን ተከተለችው፡፡

መኰንኑም በሕይወት መኖሯን ሰምቶ ድጋሚ አስፈልጎ አስያዛትና ሃይማኖቷን እንድትለውጥ አስገደዳት፡፡ እሺ እንዳላለችው ባወቀ ጊዜ በተራቡ አንበሶች ጉድጓድ ውስጥ ጨመራት ነገር ግን አንበሶቹ ሰግደው የእግሯን ትቢያ ሲልሱላት ተመለከተ፡፡ መኰንኑም ይህንን በተመለከተ ጊዜ እርሱና ወገኖቹም ሁሉ አምነው ተጠመቁና የክርስቶስ መንጋዎች ሆኑ፡፡ ቅድስት ቴክላም የጌታችንን ወንጌል በማስተማርና ቅዱስ ጳውሎስንም በማገልገል ብዙ ከተጋደለች በኋላ መስከረም 27 ቀን ዐርፋለች፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱሳን_አውናብዮስ_እና_እንድርያስ

ዳግመኛም በዚች ቀን ቅዱሳን ጻድቃን መነኰሳት አውናብዮስና እንድርያስ በሰማዕትነት አረፉ። እሊህ ቅዱሳንም ከልዳ ሀገር ከታላላቆቹ ተወላጆች ናቸው ከታናሽነታቸውም በአምላካዊ ምክር ተስማምተው በሶርያ ውስጥ ከሚገኙ ገዳማት ወዳንዱ ገዳም ሒደው መነኰሳት ሆኑ።

ከዚህም በኋላ ወደ ከበረ ወደ ተመሰገነ አባ መቃርስ ሔዱ ደቀ መዛሙርቱም ሁነው ታዘዙለት ምክሩንም በመቀበል በጾም በጸሎት በገድል ሁሉ ተጠምደው የሚኖሩ ሆኑ በእንዲህ ያለ ሥራም በዚያ ሦስት ዓመት ኖሩ በጎ የሆነ ተጋድሎአቸውና የአገልግሎታቸው ዜና በተሰማ ጊዜ አውናብዮስን መርጠው ኤጲስቆጶስነት፣ እንድርያስን ቅስና ሾሙአቸው በበጎ አጠባበቅም የክርስቶስን መንጋዎች ጠበቋቸው።

ከዚህም በኋላ ሥጋቸውን ፈጽሞ እስከ አደከሙ ድረስ ተጋድሎአቸውንና አገልግሎታቸውን እጅግ አበዙ። ከሀ*ዲ ንጉሥ ዮልዮስም ስለእርሳቸው በሰማ ጊዜ ወታደሮች ልኮ ወደርሱ አስቀርቦ የክብር ባለቤት ክርስቶስን ክደው ወደ ረከሰች አምልኮቱ እንዲገቡ አዘዛቸው ያን ጊዜ እርሱንና የረከሱ ጣዖ*ታቱን ረገሙ እርሱም ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃያቸው ወደ ብዙ ክፍልም ቆራርጦ ከፋፈላቸውና ነፍሳቸውን በእግዚአብሔር እጅ ሰጡ። እያንዳንዳቸውም ሦስት ሦስት አክሊላትን ተቀበሉ አንዱ በገድል ስለ መጸመድና ስለ ምንኲስና ዋጋ፣ ሁለተኛው ስለ ክህነት አገልግሎት፣ ሦስተኛው ደማቸውን ስለ ማፍሰሳቸው ነው።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መስከረም)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በስማም በወልድ ኧረ ይሄ መንፈሳዊ ፔጅ ነው

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

ፍቅር የለም አትበሉ ምክንያቱም
ፍቅር አለ እሱም ፍቅር እግዚአብሔር ነው

እግዚአብሔርን የሚያፈቅር ሰው
ለሁሉም ፍቅር አለው ፍቅረ ቢፅ አለው( የባለንጃራ ፍቅር አለው )

በፍቅር ለፍቅር ፍቅር በሆነው አምላክ እንኑር🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የፀሓይ ብርሃን በጠቢባን ጥበብ ይሰፈራል፤ የጨረቃም ውበት ይመጠናል፤ ሰማይና ምድር በአድማስ፣ ባሕርም በናጌብ ይወሰናል።

የእመቤታችንን ክብር ግን መመጠንና መወሰን ይቅርና ማን ሊመረምረው ይቻለዋል? 'ሊቁ መኑ ዘይክል ነቢበ ዕበይኪ” እንዳለ ገናንነትሽን ማን ይናገራል እያልን ስለ እሷ የተነገረውን ሁሉ በመደነቅ እናነባለን።

ሊቃውንቱ ለእመቤታችን ውዳሴ በመጽሐፍ የሚያኖሩት ለኀሊና ማቅኛ እንዲሆን ነው እንጅ ከዚያ በኋላስ ኅሊና አስቦ ወደማይደርስበት ጥልቅ ባሕረ ውዳሴ መግባት ነው።

የአበቦችን ውበት በምድረ በዳ፣ ከዋክብትን በሰማይ ላይ በጥበቡ የገለጠ አምላክ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንም በሊቃውንት እንደበት ይገልጣታል።

ቅዱስ ኤፍሬምን አፈ በረከት ቅዱስ ዮሐንስን አፈ ወርቅ ያሰኛቸው የድንግል እመቤታችን ውዳሴ ነው።

እስከ ዕለተ ምጽእት የሚነሣው ትውልድ እንዲያመሰግናት በትንቢት የተነገረላት ሉቃ 1:48 ይፈጸም ዘንድ ዛሬ ባሉ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት እንደበትም በጉባኤ፣ በማኅሌት፣ በቤተ መቅደስ ትመሰገናለች።

ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን እመቤታችን "ያስተበፅዑኒ ኩሉ ትውልድ” ብላ ከተናገረችላቸው አንዱ ናቸው። ለዚህም ምስክሬ ትምህርታቸው ነው።

በዐውደ ምሕረት "የምድር ጌጥ ይሏታል። በጉባኤ ቤት “ብርሃንኪ የዐቢ እምብርሃነ ፀሐይ” ይሏታል።

በበዐታቸው "ሰአሊ ለነ ቅድስት'' ይሏታል። ዛሬ ደግሞ ተነቦ የማይጠገብ ውዳሴዋን በመጽሐፍ አቅርበውልናል።

ይሄ መጽሐፍ በትውፊት የምናወርሰው፥ ነገር ግን እያየነው የተደረሰ አዲሱ አርጋኖን ነው።

ቅድመ ዓለም በአምላክ ኅሊና ከታሰበው ድኅረ ዓለም በነቢያት እስከተነገረው፣ በመላእክት ከተዘመረው በሐዋርያት እስከተሰበከው ሊጠቀስ የሚገባው ተጠቅሷል።

የእመቤታችን ነገር ሐረግ ነው፤ በነካነው ጊዜ ሁሉ ብሉያትን ሐዲሳትን ሊቃውንትን ያንቀሳቅሳል።

ርእሰ ሊቃውንት እንደ ሐረግ ሳቢ አንድ ጥቅስ በመዘዙ ጊዜ የመጻሕፍት ሁለንተናቸው ይንቀሳቀሳል።

ከብሉይ ኪዳን ጀምሮ በእግዚአብሔር መንፈስ የተጻፈ መጽሐፍ ሁሉ እመቤታችን የሌለችበት መጽሐፍ አይገኝም።

ይህን መጽሐፍ ባነበባችሁ ጊዜ ይህንን እውነት ትረዱታላችሁ። "አሐቲ ድንግል" አንድ መጽሐፍ ብቻ አደለም።

ትርጓሜ፤ ድርሳን፤ ምዕላድ፤ ውዳሴም ነው።

ሁልጊዜ የርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳንን ስብከት ስሰማ የምመኘው ይህንን መጽሐፍ ነበር።

አንዳንዴ ስብከት መሆኑን ረስቼ መጽሐፍ የሚያነቡልኝ ይመስለኝ ነበርና። እነሆ የተመኘሁት መጽሐፍ በብራና ተጠቅሎ በቤተ መጻሕፍት ተጥሎ አገኘነው። ከእኔ ጋራ የተወለደውን የመጻሕፍት ንጉሥ ታዩ ዘንድ ኑ!

ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ የ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር መምህር

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ማኅሌተ_ጽጌ

#የፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_42ኛ_ዓመት_የምሥረታ_በዓል

#ፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሰንበት_ትምህርት_ቤት
#ፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሚዲያ

Follow us on
👉 /channel/fre_amde_haymanot_media
👉 http://linktr.ee/fre_amde_haymanot_media

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#እውነተኛ_ወዳጅ አንብቡት
🥀እውነተኛ ወዳጅ፥ ወዳጅ መኾኑ የሚታወቀው ጓደኛውን መገሠጽ ሲችል ነው፡፡ ኹላችንም በየጊዜው ኃጢአት እንሠራለን፡፡ አብዛኞቻችን ደግሞ ኃጢአታችንን እንዳላየነው ኾነን ለማለፍ እንጥራለን፡፡ ለራሳችን ይቅርታ እንቸራለን፡፡ ወይም ምንም እንዳላጠፋ ሰው ለመምሰል እንሞክራለን፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሰዓት እውነታውን በትክክል እናይ ዘንድ ዓይናችንን የሚከፍት እውነተኛ ወዳጅ ያስፈልገናል፡፡

🥀አንተ ሆይ! እስኪ ራስህን መርምር፡፡ ጓደኛህ እውነታውን እንዲያይ ታደርጋለህ? ጓደኛህ ኃጢአት ሠርቶ ሲያበቃ ለራሱ ይቅርታ ሲያደርግ ይቅርታው ያደረገው ይቅርታ ትክክለኛ እንዳልኾነ እንዲያውቅ ታደርጓለህን? እንዲህ እውነታውን ስትነግረው ምናልባት ጓደኛህ አለአግባብ ሊቈጣህ ይችላል፡፡ ታዲያ ሲቈጣህ ለመታገሥ ዝግጁ ነህን? ወይስ ከዚህ በተቃራኒ የጓደኛህን ኃጢአት አይተህ እንዳላየህ ነው የምትኾነው?

🥀ጓደኛ ስንመርጥ ከእኛ ጋር እውነተኛ ወዳጅ ሊኾን የሚገባውን መኾን አለበት፤ ስንቈጣው እንኳን ቁጣችንን ታግሦ ስናጠፋ የሚያርመን ሊኾን ይገባል፡፡ እንደዚህ ካልኾነ ጓደኝነት ጥልቀት አይኖረውምና፤ ጓደኞች ነን መባባላችን ጥቅም የለውምና፡፡

🥀ልናውቀው የሚገባን ነገር ግን አለ፡፡ ጓደኛችን በሚያጠፋበት ሰዓት ተግሣጽ አስመስለን እንዲሁ ክብሩን በሚነካ መልኩ ልንናገረው አይገባንም፡፡ ተግሣጻችን ኹልጊዜ እውነቱን ብቻ እንጂ የተጋነነና ሌላውን መልካምነቱን የሚክድ መኾን የለበትም፡፡ ጥፋቱን ስንነግረው ኹልጊዜ በቀና ልብ እንደምንነግረው እርግጠኛ እንዲኾን ማድረግ አለብን፡፡ ይህን የምናደርገው ከፍቅራችን የተነሣ እንጂ ከቅናት ወይም ከንቀት እንዳልኾነ እንዲያውቅ ማድረግ አለብን፡፡ እውነተኛ ወዳጅነት ማለት ይህ ነውና፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን ይቆየን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አንድ መነኩሴ

ወደ ገዳሙ አበ ምኔት ቀርቦ በምሬት እንዲህ አለ :-

"አባቴ በዚህ ገዳም ምንም ጸጋ
ምንም ትሩፋት የሌለኝ መነኩሴ እኔ ብቻ ነኝ::

አባ እገሌን እዩት እንደ እርሱ የዋህ የለም!
አባ እገሌን እዩአቸው እንደርሳቸው ታጋሽ ማን አለ?
አባ እገሌን እዩአቸው ለሁሉ ፍቅር አላቸው!

እኔ ግን ምንም የለኝም አልረባም
አባቴ እባክዎ ይጸልዩልኝ

የእኔ ጸጋ የእኔ ፍሬ ምንድር ነው?'' አለ
እያለቀሰ::

አበምኔቱም አይዞህ ጸልይ ብለው አሰናበቱት::

እሱ ከወጣ በኁዋላ ግን አብረዋቸው ላሉት መነኮሳት እንዲህ አሉ :-

"ይህ መነኩሴ በዚህ ገዳም ካሉ ሁሉ የሚበልጥ ጸጋ ተሠጥቶታል::

የወንድሞቹ ኃጢአት አይታየውም

ጽድቃቸውን ግን በትሕትና ሲቆጥር ይውላል::

ከዚህ በላይ ምን ጸጋ አለ?

ዝም ያልኩት ይህንን ብነግረው
ክብሩን አሳንስበታለሁ ብዬ ነው'' አሉ::

"ነፍሳችሁን ተመልከቱ
የወንድማችሁንም ኃጢአት አትመልከቱ
እግዚአብሔር ያያል"

ቅዳሴ እግዚእ ❤️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በቅዱሳን ዓለም በዕንባው እጅግ የሚታወቀው

ቅዱስ እርሳንዮስ❤️

በዕንባቸው ከሚታወቁ መካከል አንዱና ዋነኛው ነው።
ከዕንባው ብዛት የተነሳ የአይኖቹ ሽፋሽፍት ተዳክመዋል
በጉንጮቹ ላይ ሁለት የዕንባ መውረጃ ቦይ መሳዮች ተፈጥረዋል።

ቅዱስ አርሳንዮስ ስለራሱና ስለ ዓለም ሁኔታ
ሁል ጊዜ ሲያለቅስ ከመኖሩ የተነሣ
በደረቱ መካከል ዕንባው የሚወርድበት ቦታ
ጎርፍ እንደሚሔድበት መሬት ለይቶ ይታይ ነበር።

በበጋ ወራት በዕንባወቹ የዘንባባ ዛፎችን ያርስ ነበር።

ዕንባወቹ ተንከባለው የሚያርፉበት እራፊ ጨርቅ
በጉልበቶቹ ላይ ያኖር ነበር።
በሞቱ ግዜም እጅግ ፅኑ ለቅሶን አለቀሰ፡
ደቀ መዛሙርቱም በመገረም """"
በእውነት አባታችን አንተም ትፈራለህ?!"""አሉት

እሱም መለሰላቸው """በእውነት በዚህ ሰዓት በውስጤ ያለችው ፍርሀት ከመነኮስኩበት ጊዜ አንስቶ የነበረች ናት""" ብሏቸዋል።።

ይህ ቅድስናን ገንዘብ ያደረገ ሰው
እንዲህ ካለቀሰ እንግዲህ ስለ ራሳችን ምን እንላለን ?

ይህ በፍርሀት የተያዘ ሰው
በብትውናና አርምሞ በገነት አበው የሚታወቀው፡
ታላቁ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቴዎፍሎስ
ዓይኑን ለማየት ይናፍቀው የነበረ
ከበረሀ ክዋክብት አንዱ ቅዱስ አርሳንዮስ ነው።
ቅዱሳን """" ስለምን እኛን ትተወናለህ""? ይሉት ነበር።

የዕርሱ መልስ ግን ❤️

እግዚአብሔር እንደምወዳችሁ ያውቃል
ነገር ግን እኔ ከእግዚአብሔርም
ከሰውም ጋር ልኖር አይቻለኝም ይላቸው ነበር።

ቅዱስ አርሳንዮስ ❤️

ጀንበር ጠልቃ ጀንበር እስክትወጣ ሌሊቱን ሙሉ
ለፀሎት ቆመው ከሚያድሩት ቅዱሳን አንዱ ነበሩ።
ጀንበር ጀርባውን ስትመታው ጀምሮ፡
በቀጣዩ ቀን ግንባሩን እስክታገኘው
ከቆመበት ሳይሔድ ሳይቀመጥ በፀሎት ይተጋ ነበር።

ወዳጆቼ እስኪ እራሳችን እንመርምር እንጠይቅ??!!!!!!!!!!
ይህ ቅዱስ አባት ሀጢያቴ ያስለቅሰኛል ካለ እኛ ምን ልንል ነው???

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#መስከረም_29

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
መስከረም ሃያ ዘጠኝ በዚህችም ቀን #ከቅድስት_አርሴማና_ከእመምኔቷ_ከአጋታ ጋር ደናግላን በሰማዕትነት አረፉ፤ ዳግመኛም #የቅዱስ_ዮሐንስ_ነባቤ_መለኮት (ወንጌላዊው) እንደ ንስር መጥቆ "ቀዳሚሁ ቃል.." (ዮሐ. ፩፥፩) ብሎ ወንጌሉን የጻፈበት ዕለት ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ሰማዕት_ቅድስት_አርሴማ

በዚችም ቀን ከቅድስት አርሴማና ከእመምኔቷ ከአጋታ ጋር ደናግል በሰማዕትነት አረፉ። ይህም እንዲህ ነው በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን እርሱ መልኳ ውብ የሆነ ብላቴና ድንግል ሊአገባ ሽቶ በየሀገሩ ሁሉ ሒደው መርጠው ያመጡለት ዘንድ አሽከሮቹን አዘዘ።

ይችንም የሚመስላት የሌለ ቅድስት አርሴማን በሮሜ አገር በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ አገኙዋት። ሥዕሏንም ሥለው ለንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ላኩለት ንጉሡም ሥዕሏን በአየ ጊዜ እጅግ ደስ አለውና ለሠርግ እንዲመጡ ወደ መኳንንቱ ላከ።

እሊያ ደናግልም ይህን ነገር በአወቁ ጊዜ ይረዳቸው ዘንድ ድንግልናቸውንም ይጠብቅ ዘንድ አልቅሰው ወደ እግዚአብሔር ለመኑ። ከዚህም በኋላ ተነሥተው በሥውር ሸሹ የንጉሥ ድርጣድስ ግዛት ወደ ሆነ ወደ አርማንያ ሀገርም ደርሰው በአንድ ቦታ ተቀመጡ ከእርሳቸውም ጋር የተሰደዱ ቁጥራቸው ሰባ አምስት የሆነ ወንዶች፣ ሴቶችም ሠላሳ ዘጠኝ የሆኑ ከእርሳቸው ጋራ አሉ። ምግባቸውን አያገኙም ነበርና በታላቅ ችግር ውስጥ ኖሩ ከእነርሱም መብራት የምትሠራ አንዲት ሴት ነበረች ከእርሷም የእጅ ሥራ ከሚገኘው በየጥቂቱ ይመገባሉ።

ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም የከበረች አርሴማን በፈለጋት ጊዜ አላገኛትም ግን በአርማንያ አገር እንዳለች ስለርሷ ሰማ። ደግሞ ለአርማንያ ንጉሥ ለድርጣድስ ስለርሷ ከዲዮቅልጥያኖስ ሸሽታ እንደ መጣች የአርሴማን ሥራ ነገሩት እርሱም አንዱን የአርማንያ መኰንን ለእኔ ጠብቃት ወደ እኔም ላካት ብሎ አዘዘው።

ደናግሉም ይህን በሰሙ ጊዜ ወደ ሌላ ቦታ ተሠወሩ ወደ ንጉሥም ወነጀሉአቸው ንጉሡም ቅዱስት አርሴማን በክብር አድርገው ያመጧት ዘንድ አዘዘ እርሷም ወደ እርሱ መምጣትን እምቢ በአለች ጊዜ እየጎተቱ ወስደው ወደርሱ አደረሷት።

የቅድስት አርሴማንም ላህይና ደም ግባቷን በአየ ጊዜ ድንግልናዋን ሊያረክስ ሽቶ እናቷ አጋታን አባብላ እሺ ታሰኝለት ዘንድ አዘዛት አጋታም ወደርሷ ሒዳ ልቧን አስጨከነች እንዲህም አለቻት። ዕወቂ ይህ ርኲስ አረሚ እንዳያረክስሽና ሰማያዊ ሙሽራሽን እንዳትተዪ እርሱም ክብር ይግባውና የእግዚአብሔር ልጅ ሕያው ክርስቶስ ነው።

ንጉሡም ይዞ ወደ እልፍኙ ሊአስገባት ከአደባባይ መካከል ተነሥቶ ድንግል አርሴማን ያዛት። በዚያንም ጊዜ በቅድስት አርሴማ ላይ የእግዚአብሔር ኃይል አደረባትና በምድር ላይ ጣለችው እርሱ ግን በጦርነት እጅግ የጸና አርበኛ ስለ ነበር በታናሽ ሴት ብላቴና ስለተሸነፈ ያን ጊዜ አፈረ። ራሷንም በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና ቆረጧት ከዚህም በኋላ ደናግሉን ሁሉ ከእናታቸው አጋታ ጋር ይገድሏቸው ዘንድ አዘዘ።

አንዲት የታመመች ድንግል ነበረች በዐልጋዋ ላይም እንደተኛች ወደ ወታደሮች ጮኸች መጥተውም እንደ እኅቶቿ ራሷን ቆረጡ ሁሉም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ እነዚያንም ከሮሜ አገር አብረው የመጡ ወንዶችን ገደሏቸው ቁጥራቸውም ሰባ አምስት ናቸው ሥጋቸውም በተራራ ላይ የተጣለ ሁኖ ቀረ።

ሰማዕታትም ከተገደሉ በኋላ በንጉሡ ላይ ጋኔን ተጫነበት መልኩም ተለውጦ እንደ እርያ ሆነ። ቅዱስ ጎርጎርዮስ ወደርሱ መጥቶ በላዩ ጸልዮ እስከ አዳነው ድረስ ስለዚህም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ። የቅዱሳን ሰማዕታትንም ሥጋቸውን ከተጣለበት ሰብስበው በአማረ ቦታ አኖሩአቸው ያማረች ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንም ተሠራችላቸው። ከእነርሱም ታላላቅ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዮሐንስ_ወንጌላዊ_ነባቤ_መለኮት

ዳግመኛም በዚህች ዕለት ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ እንደ ንስር መጥቆ "ቀዳሚሁ ቃል.." ( ዮሐ. ፩፥፩) ብሎ ወንጌሉን የጻፈበት ዕለት እንደሆነ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ፡- ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌልን ለመስበክ ዕጣ የደረሰው እስያ ስለነበር ደቀ መዝሙሩን አብሮኮሮስን አስከትሎ ሄደ፡፡ ይኽችውም ኤፌሶን በጥንቱ በታናሽ እስያ በዛሬው የቱርክ ግዛት ውስጥ ከተማ ናት፡፡ ዛሬ ኢያዞሎክ ተብላ የጥንት ታሪኳ ጠፍቷል፡፡ አስቀድሞ ቅዱስ ጳውሎስ ወንጌልን ሰብኮባታል፡፡ ደቀ መዝሙሩን ቅዱስ ጢሞቴዎስንም በከተማዋ ላይ ኤጲስቆጶስ አድርጎ ሾሞት ነበር፡፡ እርሱም በግፍ እስከተገደለበት ጊዜ ድረስ ቅዱስ ዮሐንስን እየረዳው በከተማዋ ብዙ አገልግሏል፡፡ በኋላ ግን በግፍ ገድለውታል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ኤፌሶን ለመሄድ በመርከብ ሲሳፈር መርከቡ በማዕበል ተሰበረ፡፡ ደቀ መዝሙሩን አብሮኮሮስን መዕበሉ ወደ አንዲት ደሴት አደረሰው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ግን በመርከቡ ስባሪ ተንጠልጥሎ በባሕሩ ማዕበል መካከል 40 ቀንና 40 ሌሊት ከኖረ በኋላ ማዕበሉ ተፍቶ አብሮኮሮስ ካለበት ደሴት አደረሰውና ተያይዘው ኤፌሶን ከተማ ገቡ፡፡ የከተማይቱም ሰዎች እጅግ ክፉዎች ስለነበሩ መጀመሪያ ላይ ቅዱስ ወንጌልን መስበክ አልቻሉም ነበር፡፡ እነርሱም እጅግ ክፉዎች መሆናቸውን ስላወቀ ቅዱስ ዮሐንስ ገና ዕጣው ሲደርሰው በሀዘን አልቅሶ ነበር፡፡ አሁንም ከተማው በገቡ ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ ምክንያት በመፍጠር ሮምና ለምትባል ሴት የውሽባ ቤቷ እሳት አንዳጅ ሆኖ አብሮኮሮስም ዕቃ አጣቢ ሆነው ተቀጠሩ፡፡ የቀጠረቻቸው ሴትም እጅግ ታሠቃያቸው ጀመር፡፡ ባሮቿ እንደሆኑ ተስማምተው ስለጻፉላት ትደበድባቸውም ነበር፡፡

እነርሱም በታላቅ ጉስቁልና ውስጥ እየኖሩ እያለ በአንዲት ዕለት የአገረ ገዥው ልጅ ለመታጠብ ወደ ውሽባው ቤት ገባ፡፡ በውሽባ ቤቱም የሰይጣን ኃይል ስለነበረበት የመኰንኑን ልጅ አንቆ ገደለው፡፡ የአገሪቱም ሰዎች ሁሉ ለሞተው የመኰንን ልጅ ሊያለቅሱ ሲሰበሰቡ ቅዱስ ዮሐንስም አብሮ ቆሞ ሲመለከት ሮምና መጥታ "በጌታዬ ልጅ ሞት ልትደሰት መጣህን" እያለች ረገመችው፡፡ እርሱም "አይዞሽ አትዘኚ" አላትና ወደ ሞተው ልጅ ቀርቦ በመስቀል ምልክት ካማተበበት በኋላ በፊቱ እፍ አለበት፡፡ የሞተውም ልጅ ድኖ ተነሣ፡፡ የሀገሪቱም ሰዎች እጅግ ደነገጡ፡፡ ሮምናም ደንግጣ "እግዚአብሔር የሚሉት አምላክ አንተ ነህን" ብላ ጠየቀችው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም "በፍጹም እኔ አምላክ አይደለሁም፣ እኔ የእርሱ አገልጋዩና ሐዋርያው ነኝ እንጂ" አላት፡፡ ሮምናም ስለበደለቻቸው በደል ሁሉ መሪር ዕንባን እያለቀሰች ይቅር እንዲሏት ለመነቻቸው፡፡ እነርሱም አረጋጉዋት፡፡ ከሕዝቡም ውስጥ ብዙዎቹ በጌታችን አመኑ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም ሌሎች ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን እያደረገ ወንጌልን እየሰበከ ከጣዖት አገልጋዮች በቀር ሁሉንም አሳምኖ አጠመቃቸው፡፡ አገልጋዮችን ኤጲስቆጶሳትን፣ ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ከሾመላቸው በኋላ ወደ ሌሎች አቅራቢያ አገሮች ሄደ፡፡

በመጨረሻም በከሃዲውና በጨካኙ በድምጥያኖስ ዘመን በጣዖት አምላኪዎች ተከሶ ለፍርድ ቀረበ፡፡ በፈላ ውኃ ካሠቃዩት በኋለ በፍጥሞ ደሴት አጋዙት፡፡ በዚያም ሳለ ራእዩን ተመልክቶ ጻፈው፡፡ ድምጥያኖስም ከተገደለ በኋላ ከግዞቱ ተመልሶ ሦስቱን መልእክታቱንና ቅዱስ ወንጌሉን ጽፏል፡፡ ጌታችንም አስቀድሞ ሞትን እንደማይቀምስ ለዮሐንስ ቃል ገብቶለት ነበርና (ዮሐ 21፡22) ጥር 4 ቀን እንደ ኤልያስና ሄኖክ ሞትን እንዳያይ ወደ ብሔረ ሕያዋን ወስዶታል።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/Tewahedomender/44

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ኦርቶዶክሳዊ ጋብቻ ተጋበዙ
wondie12/video/7422398508994448646?is_from_webapp=1&sender_device=pc&web_id=7386261005708314117" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@wondie12/video/7422398508994448646?is_from_webapp=1&sender_device=pc&web_id=7386261005708314117

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝እንኳን አደረሰነ!

❀በዓለ ቅዱሳን ሐዋርያት
❀ወበዓለ ዮናስ ነቢይ
❀ጸአተ ክረምት

"ተዘኪረከ ክርስቶስ፥ ለሐዋርያት ኲሎሙ፤
ኅየንተ ክቡር ደምከ፥ እለ ከዐዉ ደሞሙ፤
አክሊለ ግዕዛን ኀበኒ፥ ከመ እሳተፍ ገድሎሙ፤
ወደምስስ ለአጽራርየ፥ እመጽሐፈ ሕይወት ዝክሮሙ፤
ከመ ለይሁዳ ረሲዕ፥ ትደምሰስ ስሞሙ!"

(አባ ዓምደ ሐዋርያት)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/OxMO3NkFp5Y?si=lWK5dtOktMznf5QD

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች ሆይ

ሁሉ ቢተወን እመቤታችን ግን ታየናለች
እመቤታችን ማንንም ነው ምትሰማው ማትንቀው
የሰውን ችግር ታውቃለች እመቤታችን
ከልቤ ነው የምነግራችሁ

አሁን እናንተ የሚመሰላችሁ
አላውቅም ምን እንደሚመስላችሁ
ይሄ ትዕቢት ስለሆነ ማለት ነው

ብቻ ብዙዎቻችን ግን ሚመሰለን
እመቤታችን የሆኑ ሰዎችን ምትረዳቸው
እኛን ደሞ ማትረዳን ነው የሚመስለን

እንደው ለኛ ለኛ ማናሳዝናት
ይመስላችኋል አይደለም
የማንም ችግር ያሳዝናትል
የማንም ችግር እውነት ከልቤ ነው

ማንም ሰው ሳያይላችሁ
ቀድማ የምታይላችሁ እመቤታችን ናት

ይሔው ቃና ዘገሊላ ላይ
ሁሉም ሰው ከዚህ ቅዳ
ስጥ ለእንግዳ እያለ ይቆርጣል እንጂ

ማን ጠጅ ማለቁን አይቷል
እሷ እኳ ናት ጓዳቸውን ያየችላቸው

ማንም አልተረዳም ነበር
እርሱ ግን እያወቀ ትቶት ለምን
የእመቤታችን ክብር እንዲገለጥ

አምላክ ነው እሱ ያውቃል


ር ዕሰ ሊቃውንት አባገብረ ኪዳን❤️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ

ወደ ጋራው መድኃኔዓለምና
መናገሻ አንባ ማርያም ገዳም

ከ100 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ
የብዙ ስውራን አባቶች እና ምዕመናን መኖርያ
ስውሯ ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ምትገኝበት

ጥቅምት 17/2017

የጉዞ ዋጋ ምሳን ጨምሮ 400 ብር ብቻ

ምዕራፈ ሕይወት ሰ/ት/ቤት የልማት ሙያና በጎ አድራጎት ክፍል

በቶሎ ቦታ ያስይዙ

0953153057 ዲ/ን ጌታሁን ሥዩም
+251910621328 ቤተልሔም ደጉ

#ልማትና_ሙያና_በጎአድራጎት_ክፍል

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Are yehane biloc aregut

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ነገ ተገናኝተን ፈታ ማለት ምትፈልግ ሴትinbox ሀይ ትበለኝ

Читать полностью…
Subscribe to a channel