kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ቅዱስ አትናቴዎስ

ቃል ፍጡር ቢሆን ኖሮ ይህ [የእኛ መዳን) ተፈጻሚ ሊሆን አይችልም ነበር፣ ፍጡር ቢሆን ኖሮ ዲያብሎስም ራሱ ፍጡር ስለሆነ ትግሉን ይቀጥልበት ነበር፤ ሰውም በሁለቱ መካከል ሆኖ ከእግዚአብሔር ጋር የሚዋሐድበትና ከፍርሃት ነጻ የሚወጣበት መንገድ አጥቶ ሕይወቱ ሁል ጊዜ በአደጋ ውስጥና በጥፋት ላይ እንደ ሆነ ይቀጥል ነበር፡፡

ስለዚህም በእውነት የእኛ የሆነውን ሰውነትና ባሕርይ ነሣ (ገንዘብ አደረገ)፡ ይህም ባሕርያችንን እርሱ ፈጣሪውና አስገኚው እንደ መሆኑ በእርሱ በራሱ ያከብረው ዘንድ፡ በዚህም በእርሱ መሪነትና አርእያነት ወደ መንግሥተ ሰማያት ያገባን ዘንድ ነው::'™


የሰው ባሕርይ (ትስብእት) የተዋሐደው ከፍጡር ጋር ቢሆን ኖሮ ወይም ወልደ እግዚአብሔር እውነተኛ እግዚአብሔር ባይሆን ኖሮ የእኛ ባሕርይ የጸጋ አምላክነትን አያገኝም ነበር፣ የእኛን ሥጋ የለበሰው የእርሱ [የእግዚአብሔር] እውነተኛና የባሕርይ ልጁ ባይሆን ኖሮ ሰው ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ከፍ ከፍ ሊልና ሊቀርብ አይችልም ነበር፡፡ (ትምህርት በእንተ አርዮሳውያን፡ ትምህርት 2 ቁ. 43)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ፓስፖርት ለማውጣት 5 እና 6 ወር መጠበቅ ቀር በ 1 ወር ፓስፖርት እናደርሳለን  አገልግሎት ፈላጊዎች በሙሉ
〰〰〰〰〰〰〰〰
+251969030123
   0969030123
❶. አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት
- ❖ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ
- ❖ የልደት ካርድ
- ❖ ስልክ ቁጥር

❷. ለማሳደስ
-❖ ጉርድ ፎቶግራፍ
-❖ ፓስፖርት ኮፒ
-❖ ስልክ ቁጥር

❸. የጠፋ / የተሰረቀ ለማውጣት
-❖ የቀበሌ መታወቂያ
-❖ ጉርድ ፎቶግራፍ
-❖ የፖሊስ ማስረጃ ደብዳቤ
-❖ ስልክ ቁጥር

❹. ከ18 ዓመት በታች
-❖ የወላጅ መታወቂያ
-❖ የልጅ የልደት ካርድ
-❖ ስልክ ቁጥር

❺. እድሜ ለማስተካከል
-❖ የልደት ካርድ
-❖ ጉርድ ፎቶግራፍ
-❖ ፓስፖርት ኮፒ
-❖ ስልክ ቁጥር

❻. ስም ለመቀየር ውይም ለማስተካከል
-❖ ጉርድ ፎቶግራፍ
-❖ ፓስፖርት ኮፒ
-❖ የፍርድ ቤት ወረቀት
-❖ ስልክ ቁጥር
Ethiopianpassport
0969030123
+251969030123

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ቅዱስ አግናጥዮስ፣ መልእክት ኀበ ሰብአ ጥራልያን፣ ምዕ. 10

👉የማምነውና ተስፋ የማደርገው በምትሐት ወይም በማስመሰል ሳይሆን ስለ እኔ በእውነት ሰው በሆነውና በሞተው በኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡

👉ሐሰት የሆነ ነገር ለእውነት አስጸያፊ ነውና፡፡ ስለሆነም የማምነው ድንግል ማርያም የፀነሰችውና የወለደችው እግዚአብሔር ቃል የተዋሐደውን ሥግው ቃልን ነው፡፡

👉 የእግዚአብሔር ቃልም የእኛን ባሕርይ ገንዘቡ አድርጎ በእውነት ከድንግል ማርያም ተወልዷል፡፡

👉ሰዎችን ሁሉ በማኅፀን የሚፈጥረውና የሚቀርጸው እርሱ ራሱ ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ በድንግልና በማኀፀኗ ተፀንሶ ኖሯልና፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Selamleki tselot yemtchilu esti tsafulign

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ማኅሌተ_ጽጌ

#የፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_42ኛ_ዓመት_የምሥረታ_በዓል

#ፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሰንበት_ትምህርት_ቤት
#ፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሚዲያ

Follow us on
👉 /channel/fre_amde_haymanot_media
👉 http://linktr.ee/fre_amde_haymanot_media

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ከመፀለያችን በፊት ልናደርግ አቸው የሚገቡ ነገሮች

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

ቅዱስ አትናቴዎስ

ሐዋርያዊ ይህን መሠረታዊ ጉዳይ በአርዮሳውያን ላይ በጻፈው ጥልቅና ሰፊ ትምህርቱ ላይ እንዲህ ሲል ያብራራዋል-

ቃል ፍጡር ቢሆን ኖሮ ይህ [የእኛ መዳን] ተፈጻሚ ሊሆን አይችልም ነበር፤ ፍጡር ቢሆን ኖሮ ዲያብሎስም ራሱ ፍጡር ስለሆነ ትግሉን ይቀጥልበት ነበር፤ ሰውም በሁለቱ መካከል ሆኖ ከእግዚአብሔር ጋር የሚዋሐድበትና ከፍርሃት ነጻ የሚወጣበት መንገድ አጥቶ ሕይወቱ ሁል ጊዜ በአደጋ ውስጥና በጥፋት ላይ እንደ ሆነ ይቀጥል ነበር፡፡

ስለዚህም በእውነት የእኛ የሆነውን ሰውነትና ባሕርይ ነሣ (ገንዘብ አደረገ)፡ ይህም ባሕርያችንን እርሱ ፈጣሪውና አስገኚው እንደ መሆኑ በእርሱ በራሱ ያከብረው ዘንድ፣ በዚህም በእርሱ መሪነትና አርአያነት ወደ መንግሥተ ሰማያት ያገባን ዘንድ ነው::'™ የሰው ባሕርይ (ትስብእት) የተዋሐደው ከፍጡር ጋር ቢሆን ኖሮ፣ ወይም ወልደ እግዚአብሔር እውነተኛ እግዚአብሔር ባይሆን ኖሮ የእኛ ባሕርይ የጸጋ አምላክነትን አያገኝም ነበር፤ የእኛን ሥጋ የለበሰው የእርሱ (የእግዚአብሔር] እውነተኛና የባሕርይ ልጁ ባይሆን ኖሮ ሰው ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ከፍ ከፍ ሊልና ሊቀርብ አይችልም ነበር፡፡ (ትምህርት በእንተ አርዮሳውያን፣ ትምህርት 2፣ ቁ. 43)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

“አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤”
  — 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥5

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ጥቅምት 7-ስለ ጌታችን ፍቅር ብሎ ራሱን ሰባት ጊዜ የገደለው ታላቁ አባት አባ ባውላ ዕረፍቱ ነው፡፡
+ ቅዱሳን ሰማዕታት ሚናስና ሐናሲ መታሰቢያ በዓላቸው መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሳቸዋል፡፡
አባ ባውላ፡- ይኽም ጻድቅ ከታናሽነቱ ጀምሮ መስተጋድል መነኩሴ ሆነ፡፡ በላይኛው ግብፅ በሚገኘውና ‹‹እንጽና›› ተብሎ በሚጠራው ገዳም ውስጥ በታላቅ ተጋድሎ የሚኖር ሆነ፡፡ ሕዝቅኤል የሚባል ረድእ አለው፡፡ እርሱም ስለ አባታችን ስለ ተጋድሎውና ስለ ትሩፋቱ ምስክር ሆነ፡፡ ይህም አባ ባውላ ስለጌታችን ፍቅር ብሎ ራሱን ሰባት ጊዜ የገደለ ነው፡፡
አባ ባውላ በመጀመሪያ ራሱን በዕንጨት ላይ ዘቅዝቆ በመስቀል አርባ መዓልት አርባ ሌሊት እንደተሰቀለ ኖረ፡፡ ነፍሱንም አሳለፈ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ከሞት አስነሣው፡፡ ሁለተኛም አሣዎችና አንበሪዎች እንዲበሉት ራሱን ከባሕር ውስጥ ጨመረ ነገር ግን እነርሱ አልነኩትም፡፡ አባ ባውላም በባሕሩ ውስጥ ሰጥሞ ብዙ ወራት ቆይቶ ሞተ፡፡ ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ጌታችን አሁንም ከሞት አስነሣው፡፡ አባ ባውላ ለሦስተኛም ጊዜ ራሱን በአሸዋ ውስጥ ደፍኖ ሞተ፤ ጌታችንም ከሞት አስነሣው፡፡ ለአራተኛም ጊዜ በውስጡ ስለታም ድንጋዮች ካሉት ረጅም ተራራ ላይ ወጥቶ ራሱን ከተራራው ላይ ወደታች ወርውሮ ተንከባለለ፡፡ የተሣሉ ድንጋዮችም በሥጋው ሁሉ ገብተውበት ሞተ፡፡ ረድኡ ሕዝቅኤልም ያለቅስለት ነበር፡፡ አሁንም ጌታችን መጥቶ አባ ባውላን ከሞት አስተነሥቶ አጽናናው፡፡ ነገር ግን አባ ባውላ አሁንም ለአምስተኛ ጊዜ ከረጅም ዛፍ ላይ ወጥቶ ከስለታም ድንጋይ ላይ ራሱን ፈጠፈጠ፡፡ ለሁለትም ተከፈለና ሞተ፡፡ አሁንም ጌታችን አስነሣው፡፡
ስድስተኛም አባ ባውላ ራሱን በእግሮቹ ውስጥ አሥሮ አርባ መዓልት አርባ ሌሊት እንዲህ ሆኖ ቆይቶ ሞተ፡፡ እግዚአብሔር አሁንም ከሞት አስነሣው፡፡ ሰባተኛም ከውኃ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ እጆቹን ዘርግቶ አርባ መዓልት አርባ ሌሊት በመቆም ሞተ፡፡ ክብር ይግባውና ጌታችንም አስነሣውና ‹‹ወዳጄ ባውላ ሆይ! ራስህን ሰባት ጊዜ እስከምትገድል ድረስ ሰውነትህን አደከምክ ከእንግዲህስ ድካም ይብቃህ›› ብሎ አጽናናው፡፡ ያንጊዜም አባ ባውላ ለመድኃኒታችን እንዲህ ብሎ መለሰለት፡- ‹‹ጌታዬ ሆይ ስለከበረው ስምህ እደክም ዘንድ ተወኝ፤ አንተ አምላክ ስትሆን ስለእኛ በመከራ ደከምክ፤ ስለ ሰው ወገን ሞትክ፡፡ ለእኛ ይህ አይገባንም ነበር በቸርነትህ ይህን የማዳንህን ሥራ ሠራህልን እንጂ›› አለው፡፡ ጌታንችም አባ ባውላን ካጽናናው በኋላ ከእርሱ ተለይቶ ወደ ሰማይ ወጣ፡፡
ከዚህም በኋላ አባ ብሶይ ወደ እንጽና ገዳም ሄዶ ከአባ ባውላ ጋር ተገናኘ፡፡ ጌታችንም ለአባ ባውላ ተገልጾለት ‹‹ሥጋህ ከአባ ብሶይ ሥጋ ጋር በአንድነት ይኑር›› አለው፡፡ ሁለቱም ቅዱሳን ባረፉ ጊዜ ሥጋቸውን በአንድነት አኖሩ፡፡ በመጀመሪያ ወገኖቹ የአባ ብሶይን ሥጋ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሊወስዱ በወደዱ ጊዜ በመርከብ ጫኑት ነገር ግን መርከቢቱ አልንቀሳቀስ አለች፡፡ በኋላም ተመልሰው የአባ ባውላን ሥጋ አምጥተው በመርከቧ ሲጭኑት ያን ጊዜ መርከቢቱ ተጓዘች፡፡ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ የቅዱሳኑን ሥጋ ወደ አስቄጥስ ገዳም አድርሰው በአባ ብሶይ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአንድነት አኖሩ፡፡ እስከዛሬም ድረስ በዚያ ይኖራሉ፡፡
የአባ ባውላ እና የአባ ብሶይ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
ከገድላት አንደበት
✞ ✞ ✞

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/fadewalletbot/app?startapp=ab8c405a9b8a457bbfd2b529deab3967

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ብዙ ድርሳናትንም ደረሰ ከእርሳቸውም አንዱ ክብር ይግባውና ስለ መድኃኒታችን ስቅለት የደረሰው በዕለተ ዐርብ የሚነበብ አንዱ ነው።

የእምነቱም ምክንያት እንዲህ ነው ከዕለታት በአንዱ በፍልስፍናው ቤት ተቀምጦ ሳለ የአቴናም ፈላስፎች በእርሱ ዘንድ ተሰብስበው ነበር እርሱ ለሁሉም አለቃ ስለሆነ በዐርብ ቀንም ቀትር ሲሆን ፀሐይ ጨለመ ታላቅ ንውጽውታም ሆነ አሕዛብ ሁሉ ደንግጠው እጅግ ፈሩ ቅድስ ዲዩናስዩስንም በዓለም ውስጥ የሆነውን ጌታችን ሆይ አስረዳን ብለው ጠየቁት።

አርሱም ፀሐይን ጨረቃንና ከዋክብትን መረመረ ጸጥ ብለው አገኛቸው ደግሞ ባሕሮችን ትልቁንም በዓለም ዙሪያ ያለውን የውቅያኖስን ባህር መረመረ እሱንም ጸጥ ብሎ አገኛው።

ከዚህም በኋላ አርስጣላባ የሚባል የፍልስፍና መጽሐፍን አንስቶ ሲመረምር በውስጡ እልመክኑን የሚል አገኘ ይህም ኀቡእ አምላክ ወረደ ወገኞቹም በእርሱ ላይ ተነስተው ሰቀሉት ማለት ነው በዚያችም ጊዜ ልብሱን ቀዶ ታላቅ ሀዘንን አዘነ ከበታቹ ምሁራን ያየውን ያስርዳቸው ዘንድ ለመኑት እርሱም ሁሉን ነገራቸው እነርሱም ይህን ሰምተው ታላቅ ፍርሃት ፈሩ።

ደቀ መዝሙሩ ኡሲፎስንም የሆነውን ሁሉ የዚያችንም ቀን ስሟን ሰዐቷን ወርዋን ዘመኑንም እንዲጽፍ አዘዘው ዳግመኛም በጣዖታቱ ቤቶች በደጃፋቸው እልመክኑን እያሉ እንዲጽፉ አዘዘ።

ከዐሥራ አራት ዓመትም በኋላ ቅዱስ ሐዋርያ ጳውሎስ ወደ አቴና አገረ መጣ ክብር ይግባውና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መውረዱን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከስጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ መወለዱን መከራ መቀበሉን መሰቀሉንና መሞቱን በሶስተኛው ቀን መነሳቱን ማረጉንም በሕያዋንና በሙታን ለምፍረድ ዳግመኛ መምጣቱን አስተማረ።

የአቴና ሰዎችም የሐዋርያዉን ስብከት በሰሙ ጊዜ እጅግ አደነቁ ወደ ዲዩናስዩስም ሩጠው እንዲህ ብለው ነገሩት አንድ ሰው ዛሬ ወደ አገራችን መጥቶ እኛ የማናውቀውን ወይም ከእኛ በፊት የነበሩ አባቶቻችን የማያውቁትን በአዲስ አምላክ ስም አስተማረን።

ዲዮናስዮስም ልኮ ሐዋርያ ጳውሎስን ወደርሱ አስመጥቶ በሀገራችን ውስጥ በአዲስ አምላክ ስም የምታስተምረው ምንድን ነው አለው።

ቅዱስ ጳውሎስም በአደባባያችሁ መካከል አልፌ ስሔድ በአማልክቶቻችሁ ቤቶች በደጃፋ ላይ እልመክኑን የሚል ጽሑፍ አየሁ ይህም የማይመረመር አምላክ ወረደ ማለት ነው እኔም ለእናንተ የምሰብከው ይህንኑ ነው ብሎ መለሰ።

በዚያንም ጊዜ ከዐሥራ አራት ዓመት በፊት ያጻፈውን ያን መጽሐፍ ያመጣው ዘንድ ኡሲፎስን አዘዘው ሁለተኛም ጊዜውንና ወራቱን ሐዋርያውን ጠየቀው እርሱም በመጋቢት ወር በሃያ ሰባት ዓርብ ቀን በስድስት ሰዓት ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርሶቶስ ያን ጊዜ እንደ ተሰቀለ ፀሐይም እንደ ጨለመ ምድርም እንደተናወጠች አስረዳው።

የአቴና ሰዎችም ይህን በስሙ ጊዜ ከቅዱስ ዲዮናስዮስ ጋር ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው ዲዮናስዮስንም በእነርሱ ላይ ኤጲስቆጶስን አድርጎ ሾመው የቤተ ክርስቲያንንም ሥርዓት የተረጐመ እርሱ ነው።

ከዚህም በኋላ በባሕር አቅራቢያ ወደ አለ አገር በመሔድ በሐዋርያት ዘመን አስተማረ ብዙ ወገኖችንም ክብር ይግባውና በጌታችንም አሳመነ ድንቆች የሆኑ ብዙዎች ተአምራትን አደረገ።

ከሀዲ ንጉሥ ጠማትያኖስም ይዞ ጽኑ ሥቃይን አሰቃየው ከዚያም የከበረች ራሱን በሰይፍ ቆረጠው የተቆረጠች ራሱንም በእጁ ይዞ ሁለት ምዕራፍ ያህል ጐዳና ተጓዘ ሁለተኛም የደቀ መዛሙርቱን የኡሲፎስንና የኡርያኖስን ራሳቸውን ቆረጠ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ሄኖስ

በዚችም ቀን የሴት ልጅ የሄኖስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው የእግዚአብሔርንም ስም መጥራት የጀመረ ይህ ሄኖስ ነው። ሄኖስም መቶ ዘጠና ዓመት ኖረ ቃይናንም ወለደው ቃይናንንም ከወለደው በኋላ ሰባት መቶ አሥራ አምስት አመት ኖረ ወንዶች ልጆችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ በቅዳሜ ቀንም አረፈ። መላ ዕድሜውም ዘጠኝ መቶ አምስት ነው።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ንጉሡን ዐፄ ካሌብን ያመነኮሱት አቡነ ጰንጠሌዎን ናቸው፡፡ ኢትዮጵያዊው ንጉሥ ዐፄ ካሌብ ከ24 ሺህ በላይ የሚሆኑ የናግራን ሰማዕታትን ደም ሊበቀልላቸው ሲያስብ መጀመሪያ በጸሎታቸው እንዲያስቡትና እንዲመክሩት አቡነ አረጋዊንና አቡነ ጰንጠሌዎንን ጠይቋቸዋል፡፡ እነርሱም በመልእክቶቻቸው መርቀው ሸኝተውታል፡፡ አቡነ ጰንጠሌዎንም ‹‹እግዚአብሔር በጠላቶችህ ላይ ድል አድራጊነትን ሰጥቶሃልና በደህና በፍቅር አንድነት ትመለሳለህ›› አሉት፡፡ ዐፄ ካሌብም ወደ ናግራን ዘምቶ ከሃዲውን የአይሁድ ንጉሥ ፊንሐስን ከገደለውና ጦሩን ሁሉ ደምስሶ በማጥፋት የክርስቲያኖቹን ደም በሚገባ ተበቀለ፡፡ በአንጾኪያ፣ በእስክንድሪያ፣ በሮም፣ በቊስጥንጥንያና በዓለም ላይ ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ ይህን ሲሰሙ በእጅጉ ተደሰቱ፡፡ ይህም የሆነው በ525 ዓ.ም ነው፡፡ ይህንንም ስንክሳሩ እንዲህ ብሎ ይገልጸዋል፡- ‹‹ንጉሥ ካሌብም ከሃድያንን ሁሉ እንደ ቅጠል እስኪረግፉ ድረስ አጠፋቸው፤ አባ ጰንጠሌዎንንም በጦርነቱ መካከል ጠላቶቻችን ሲያሳድዳቸው እንዳዩት ብዙዎች ምስክሮች ሆኑ፡፡››

አቡነ ጰንጠሌዎን ታላቅ ተጋድሎአቸውን ከፈጸሙ በኋላ ጌታችን ተገልጦላቸው ታላቅ ቃልኪዳን ሰጣቸውና ‹‹ከእንግዲህስ ድካም ይበቃሃል ዕረፍ›› አላቸው፡፡ ያንጊዜም ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች፡፡
የአቡነ ጰንጠሌዎን ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
ከገድላት አንደበት
✞ ✞ ✞
(የበፊቶቹ ኹለቱም የቴሌግራም ቻናሎች በተለያየ ጊዜ ስለተጠለፉ ለ3ኛ ጊዜ በተከፈተው አዲስ ቻናል በኩልም በጽሑፍና በድምፅ ይከታተሉ።)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝እንኳን አደረሰነ!

❀"ኮከብ ብሩህ ዘሠረቀ እምአቅሌስያ፤
ቤተ ክርስቲያን ዘንሰምያ፤
ኮኖሙ አበ ለሰብአ ግብጽ ወኢትዮጵያ፤
አማን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያ።" (ምልጣን)

ትርጉም፦
"የስሟ ትርጓሜ ቤተ ክርስቲያን ከሆነ አቅሌስያ የተገኘ፥ የሚያበራ ኮከብ፤
ለግብጽና ለኢትዮጵያ ሰዎች አባት ሆናቸው፤
በእውነት እርሱ (ገብረ መንፈስ ቅዱስ) ሐዋርያ ነውና!"

በዓለ ቅዱሳን፦
❀ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጻድቅ
❀ኪራኮስ ጳጳስ (ወሰማዕት)
❀ጳውሎስ ሊቀ ጳጳሳት
❀ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ)
❀ኢያሱ ንጉሥ (አድያም ሰገድ)

በረከታቸውን አይንሳን!

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ጸሎታቸው ይደረገልን በረከታቸው ይደርብንና በዐፄ ናዖድ ዘመነ መንግሥት ለአንዲት ሴት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ልጇን ከሞት በማስነሣት ያደረጉላት ድንቅ ተአምር ይህ ነው፦ ሴቲቱም ልጇ ከሞተና ነፍሱ ከሥጋው ከተለየች በኃላ እናቲቱ በአባታችን ጸሎት በማመን የአባታችንን ማኅበር ወደሚጠጡበት የሕፃኑን በድን ወሰደችው።

በዚያ የማኅበር ቤትም ጋን ተቀምጦ አገኘች። ጋኑንም አስተካክላ በምድር ላይ አቆመችውና "አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ በጸሎትህ ተማጽኛለሁ፣ ማኅበርህ በሚሠራበት በዚህ ጋን ልጄን ከሞት እንደምታስነሣው አምናለሁ..." ብላ ከጸለየች በኃላ በእምነት ሆና የልጇን በድን ከጋኑ ውስጥ ጨመረችው። ልጁም ያንጊዜ ወዲያውኑ ከሞት ተነስሥቶ ከጋኑ ውስጥ እንዳለ ጮኸ። እናቱም አውጥታ ጡቷን ሰጠችውና ጠባ። አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እኛንም በሕይወተ ሥጋ ያለነውን ከኅሊና ሞት ያስነሡን፣ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
✞ ✞ ✞
ዳግመኛም አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ያደረጉት ተአምር ይህ ነው:-አንድ ኃጢአተኛ ሰው ነበር፡፡ ብዙ ሥራይ የሚያድርግ ጣዖታትን በማማለክ፣ ምስልን በመሥራት በማመንዘር ብዙ ኃጢአት ይሠራ ነበር፡፡፡ አንድ ቀንም የአቡነ ገብረ መንፈስን ገድል የሚናገር መጽሐፍ ወዳለበት በመጋቢት 5 ቀን ሔደ፡፡ ገድሉን ኪዳኑን የሚናገር መጽሐፍ ሲነበብ ጌታችን የጻድን መታሰቢያ ለሚያደርጉ ሁሉ የሰጠውን የምሕረት ኪዳን እንደሰጠው ሰማ፡፡

ከዚህም በኋላ ያ ሰው ‹‹…ከእንግዲህስ ወዲህ የጻድቁን የአቡነ ገብረ መንፈስን መታሰቢያ አደርጋለሁ፣ በጸሎቱም እታመናለሁ›› ብሎ አሰበ፡፡ እንደዚሁ የአቡነ ገብረ መንፈስን የገድሉን መጽሐፍ ሰምቶ ከዚያ ወጥቶ ሲሔድ በመንገድ ያሸመቁ ወንበዴዎች አግኝቶ ጽኑ ድብደባ ደበደቡት፤ ልብሱንም ገፈው ወሰዱበት፡፡ ሰውነቱም ተጎድቶ በደም ተነክሮ ወደቤቱ ገባ፡፡ በዚያች ቀንም ሞተ፡፡ መላእክትም መጥተው ነፍሱን ለፍርድ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት አቆሟት፡፡ ያንጊዜም አቡነ ገብረ መንፈስ መጥቶ ከእግዚአብሔር ፊት ቆመና ‹‹..አቤቱ ይህችን ነፍስ ማርልኝ፣ ለእኔ ባደረገችው ቸርነትና በሰጠኸኝ ቃልኪዳን አምናለችና…›› እያለ ጽኑ ምልጃን አቀረበ፡፡ በዚህም ጊዜ ጌታችን ‹‹ስለአገልጋዬ ስለማይበል ቃሌም ኃጢአቷን ይቅር ብያታለሁ፣ ወደመሐይምናን አንድነት ውሰዷት›› አለ፡፡ ወዲያውም ጌታችን ቅዱስ ሚካኤልን ወደ ዘላለም ሕይወት እንዲወስዳት ባዘዘው ጊዜ አቡነ ገብረ መንፈስ ደስ አለው፡፡ ፊቱም እንደፀሐይ በራ፡፡
✞ ✞ ✞
ዳግመኛም አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ያደረጉት ተአምር ይህ ነው፡- ዝሙትን የምትወድ፣ ሰንበትን የምትሽር፣ በሐሰት የምትምል አንዲት ሴት ነበረች፡፡ እግዚአብሔር በእርሷ ተቆጥቶ እባብ አዘዘባት፡፡ ልትፀፀዳ በሜዳ ተቀምጣ ሣለ እባብ መጥቶ ወደሆዷ ገባ፤ እሷንም ቤት አድርጎ ኖረ፡፡ የበላችውን ይበላል፣ የጠጣችውንም ይጠጣ ነበር፡፡ ካልበላች ካልጠጣች ደግሞ አንጀቷን ይበላል፣ ደሟንም ይጠጣል፡፡ እርሷም ከስታ የዕንጨት ቅርፊት መሰለች፡፡ በሆዷም እያደገ ስለሔደ ከሆዷ እስከ አንገቷ ሞላ፡፡ ከባሏም ጋር በምትነጋገርበት ጊዜ ያ እባብ በሆዷ ውስጥ እየቀና ያውካት ነበር፡፡
አንድ ቀንም ባሏ ጎሽ ጠጥቶ ሰክሮ እርሷን አነጋገራት፤ እርሷም እምቢ አለችው፡፡ ‹‹ቀድሞ በኃጢአቴ ምክንያት ለዚህ ከይሲ ዳርጎኛልና አሁንስ እንደገና አልበድልም›› ብላ እምቢ አለችው፡፡ እርሱ ግን በግድ ደረሰባት፡፡ እባቡም አባለዘሩን ነከሰውና ባሏ ወዲያው ሞተ፡፡ እርሷም በዚህ ሁኔታ እስከ ሦስት ዓመት ቆየች፡፡

ከዕለታትም አንድ ቀን አንድ ጻድቅ ሰው ከሩቅ አገር ወደ እርሷ መጥቶ ሣለ እባቡን በሴቷ ሆድ ውስጥ አድጎ አየው፡፡ እርሷም እግዚአብሔርን እንደተፈታተነችና ለዚህ ክፉ ከይሲ አሳልፎ እንደሰጣት ነገረችው፡፡ ኃጢአቷንም አምና ንስሓ ገብታ እንዲጸልይላት ለመነችው፡፡ ያም ጻድቅ ሰው ‹‹…ስዕለት ተሣይ፣ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስንም ዝክር አዘክሪ፣ ገንዘብሽንም ለእርሱ ስጪው›› አላት፡፡ እርሷም ‹‹እሺ ከእንግዲህ ወዲህ ለእርሱ ሰጥቻለሁ›› አለችው፡፡ ጻድቁም ሰው ከእርሷ ዘንድ ሔደ፡፡ ያችም ሴት የአባታችን የአቡነ ገብረ መንፈስ ዝክር እስከሚደረግበት ቀን ድረስ ቆይታ ከፈጣሪው ምሕረትን ተስፋ አድርጋ በመጋቢት 5 ቀን የአባታችንን መታሰቢያ አደረገች፡፡ ለካህናት፣ ለምእመናን፣ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች ግብዣ አድረገች፡፡ ለቤተ ክርስቲያንም ብዙ ዕጣን፣ መብራት፣ ሰጠች፡፡

በዚያችም ሌሊት አቡነ ገብረ መንፈስ ያች ሴት ወዳለችበት መጣ፡፡ እርሷም አልተኛችም ተቀምጣ ነበር፡፡ ቤተሰቦቿም ያዳምጡ ነበር፡፡ አባታችንም በቤቷ በር ላይ ቆሞ እባቡን ‹‹…አንተ እባብ ከዚህች ሴት ሆድ ውስጥ ውጣ፣ ወደ ሥፍራህ ሒድ፣ እግዚአብሔርም እንዳዘዘህ አፈርን ብላ›› አለው፡፡ ያንጊዜም ሴቲቱን በመስቀል ምልክት ባረካት፡፡ ያም እባብ ቀድሞ በገባበት መንገድ ወጥቶ በምድር መላ፡፡ አባታችንም ሔደ፡፡ እርሷም ቤተሰቦቿን ጠራችና እባቡን ገደሉት፡፡ ርዝመቱ 5 ክንድ ሆነ፡፡ የአገሩም ሰዎች በማድነቅ የአቡነ ገብረ መንፈስን መታሰቢያ አደረጉ፡፡ ያችም ሴት ሌላ ባል አገባችና 7 ልጆችን ወለደች፡፡ እስክትሞትም ድረስ የጻድቁን የአቡነ ገብረ መንፈስን መታሰቢያ እያደረገች ኖረች፡፡

የአባታችን የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ልመናቸው በተዋሕዶ ልጆች በሁላችን ላይ ይደረግልን በረከታቸው ይደርብን፣ የዓሥራት ሀገራቸውን ቅድስት ኢትዮጵያን ከታዘዘ መቅሰፍት ይጠብቁልን ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
✞ ✞ ✞

በረከታቸው ይደርብንና ዳግመኛም አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ያደረጉት ተአምር ይህ ነው፡- በአንዲት አገር ውስጥ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ዝክር የምታዘክር አንዲት ሴት ነበረች፡፡ ዝክራቸውንም እንድትዘክር አንድ ጻድቅ አባት ነግረዋታልና፡፡ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን የአገሩ ልጆች በአንድ ትልቅ ገደል ሥር ተሰብስበው እየተጫወቱ ትልቁ ገደል በላያቸው ላይ ወደቀባቸውና ሁሉም ልጆች ወዲያው ሞቱ፡፡ አንድ ስንኳ የተረፈ የለም፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/+YVsr8ZgFEhFhYjg8

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Fc 25 Vini Junior Celebration On ps5
🔥🔥🔥

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ወዳጄ

ሕይወት ጨለማ ስትሆንብህ

ብርሃን ወደ ሆነው ጌታ አብዝተህ ፀልይ
በፍፁም ልብህ በፍጹም ሀይልህ በፍፁም ነፍስህ
ሁነህ ጌታ እግዚአብሔርን ለምነው
ያን ጊዜ ጨለማው ይገፈፋል ብርሃን ይሆናል።

እግዚአብሔር አምላክ ህዝብህን ከክፉ ጠብቅ🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሕልም እና ማሳካት የሚፈልጉት ዓላማ ላላቸው እንዲሁም ህልማቸውን ዕዉን እንዲሆን ቁርጠኛ ለሆኑ የመጣ ትልቅ ዕድል!!!!

የአሁኑን ዕድል ከልቡ የሚጠቀም ማን ይሆን?

ራዕዬን ለመኖር በማደርጋቸው የተለያዩ ተግባራት መሃከል አንደኛው አስር  ህልም ያላቸውን፣ መለወጥ የሚፈልጉ፣ ቁርጠኛ የሆኑ፣ ፅኑ የሆኑ ሰዎችን ለአንድ አመት በማይንድ ፕሮግራሚንግ ውጤታማ እንዲሆኑ የማገዝ እቅድ አውጥቻለሁ።

እናም አንድ አመት  ራስ ላይ በመስራትና መንገድ በማሳየት ብቻ ሰክሰስፉል እስኪሆኑ ድረስ በውስጠህሊና ፕሮግራሚንግ ለማገዝ 10 ሁነኛ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች እየፈለኩኝ ነው።

   1- ለውጥን እንደ ኦክስጅን የተጠማ
   2- የ አእምሮውን አሰራር በደንብ ማወቅ የፈለገ እና ለመተግበር ዝግጁ የሆነ ሰው!
   3- የሚሰጠውን አሳይመንት ለመስራት ቁርጠኛ የሆነ!

በዚህ ፕሮሰስ ያለፈ

1⃣- አእምሮዉ እንዴት እንደሚሰራ ያውቃል
2⃣- በቀን ለ 20 ደቂቃ ያክል ከተገበረው ህይወቱን ትራንስፎርም ሊያደርግ ይችላል
3⃣- በሰባቱም የህይወት ዘርፉ ( ጤና ፣ መንፈሳዊ ፣ ማህበራዊ ፣ ገንዘብ ፣ ቤተሰብ ፣ እውቀት እና ራእይ) ውጤታማ ይሆናል።
4⃣- ለሌሎቹም ምሳሌ ይሆናል

5⃣ - በውስጡ አጓጊ የሆኑ ብዙ እድሎችን የያዘ

6⃣-ከሳምንታዊ ገቢ እስከ ድርጅት ባለቤት የመሆን እድል
@Megu1921ላይ
(እኔ ዝግጁ ነኝ) ብሎ
1:ሙሉ ስም
2:መኖሪያ ቦታ
3:ስልክ ቁጥር  ይላክልኝ!

0938117195 ይደዉሉ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በ አስቸኳይ ለ ሽያጭ የ ቀረበ ዋናውን አስፋልት የያዘ እጅግ ርካሽ የ እጣ ቤት
ይፍጠኑ ብሩ ተፈልጎ ነው ለትርፍም ይሆናል::
👉አድራሻ: ቦሌ  አራብሳ አዲሱ ሳይት 
👉 የቤት ስፋት 65ካሬ
👉ወለል 3ኛg+4
👉 ሳይት 6
👉እዳ: 20% የከፈለ
👉እድሳት:  ባለበት
👉ዋጋ 2.200,000 ድርድር የለዉም::
👉ሁለት  ሚሊን ሁለት   መቶ  ሺ
👉ገዥ ከሆኑ ብቻ ይደውሉ
የምንሰጣቸው አገልግሎት
%👉የኮንደሚኒየም ቤት ሽያጭና ክራይ
👉የግል ቤት ሽያጭና ክራይ
👉የቦታ ሽያጭ
👉የንግድ ሱቆች ክራይና ሽያጭ
👉የት ይፈልጋሉ ኮየ, ቱሉድምቱ, አራብሳ,ጀሞ, አያት49 or የካ በሁሉም አለን!!!


ለበጠ መርጃ
   
    +251920825555
+251942826117

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

☞ወር በገባ በ9 ታስበው የሚውሉ የአባታችን የአቡነ ብፁዐ አምላክ ታአምር
ይህ ነው፡፡
☞ልመናውና በረከቱ ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ ከአቡነ ዮሐንስ በኃላ በተሾመው
በአባ ሠረቀ ብርሃን ዘመን ወደ ደብረ ቢዘን ከአባቱና ከወንድሞቹ ጋር በገባ ጊዜ
የእግዚአብሔርን ቃል ያስተምረው ዘንድ ለአባ ጴጥሮስ ተሰጠ፡፡
☞የትምህርት ቤት ለጆች ወንድሞቹ ቀኑበት፡፡ ለምን ከእኛ ጋራ እየተማረ እንደ
እኛ አይፈጭም አሉ፡፡ አባ ጴጥሮስም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ብፁዐ አምላክ ሆይ
እዳያዝኑብህ እንደ ወንድሞችህ የምትፈጨውን ውሰድ አለው፡፡
☞የዋህ የሆነ ብፁዐ አምላክም እሺ አምላክህ በጸሎትህ ያስችለኝ አለ፡፡
የሚፈጨውንም ወሰዶ ተኛ በነቃም ጊዜ ተፈጭቶ አገኘው እግዚአብሔር
አመሰገነ ለሰውም አልተናገረም፡፡
☞ለብዙ ጊዜ እንዲህ በሆነበት ጊዜ ጓደኞቹ የተማሪዎች አለቃ ከፈጩት ዱቄት
የሚሰጠው አለ ብለው ተጠራጠሩ፡፡ እስኪ መጣም ሦስት ሦስት ሁነን እንጠብቅ
ከመካከላችን ነቅቶ እህል ወስዶ ዱቄትን የሚሰጠው አለ አሉ፡፡ ሦስት ሦስት
ሁነው ሲጠብቁ የፈጭታዎች
መንቂ ደረሰ፡፡
☞የእየራሳቸውንም ሊፈጩ እሳትን አበሩ፡፡ የብፁ አምላኮ እህል ግን ተፈጭቶ
አገኙት፡፡ ተደንቀውም አትናገሩ፡፡ ሁለትኛ ሦስተኛ እንዲህ የሚሆን እንደሆነ እንይ
አሉ፡፡ እንዲህም ሆነ፡፡ በምሽት በየተራቸው ለብፁ አምላክ የተከፈለውን እህል
ያስቀምጣሉ፡፡
☞ ሦስት ሦስት ሁነውም ይጠብቃሉ፡፡ በነቁም ጊዜ ተፈጭቶ ያገኙታል፡፡ ከዘህ
በኃላ ለመምህሮቻቸው ተናገሩ፡፡
☞እነሱም እንደ ልጆች አድርገው ሦስት ሦስት ሆነው ጠበቁትና ሥራውን
እንግለጥበት አሉ፡፡ ግን ሥራውን አስትተን የቤተ ክርስቲያን ተልኮና መጻሕፍትን
ማንበብ እናዝዘው አሉ፡፡
☞እሱም ጌቶቼ በመፍጨቴ ካልተደስታችሁ ምግብ ማብሰል ወይም ሌላ ሥራ
የወደዳችሁን በቤተ ክርስቲያን ምልከታ ላይ እና መጻሕፍትን ማንበብን እዘዙኝ
አላቸው፡፡
☞ውሃ መቅዳትን አዘዙት፡፡ አባታችንም ብፁዐ አምላክ ቀድቶ ሊሸከም ባነሣው
ጊዜ ውሃው ከራሱ ላይ አንድ ክንድ ከፍ ከፍ አለ ይህን አይተው አደነቁ፡፡
☞ዳግመኛ ዕንጨትም ሊለቅም ሄደ፡፡ በጸሎት ሰዓት ሊጸልይ ሲቆም ዕንጨቶች
የሚበቃውን ያህል ይሰበሰቡለታል፤ ሊሸከምም ሲያስር አንድ ክንድ ከራሱ ላይ
ከፍ ከፍ አለ፡፡
]ወደ ኀላ ባለጊዜም ሊጠብቁት ወንድሞቹ ተመለሱ፡፡ ይህንንም አይተው አደነቁ
መክረንም እስክናዝዝህ ድረስ ታገስ አሉት፡፡ ብሩክ ሁን መንፈስ ቅዱስ
እንደሰየመህ ብፁዕ ሁን አሉት፡፡
]☞የብጹ አቡነ አምላክ ወዳጆቹን እግዚአብሔር በጸሎቱ ይቅር ይበላቸው
ለዘላለሙ አሜን፡፡
☞(ገድለ አቡነ ብፁዐ አምላክ)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሰላም yekedus gebrhel legut ሰላም new.

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Nbsesh ke degagochu kene abrham ena ysaq gon tref enate

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እባካችሁ አድድ አድርጉ መንፈሳዊ መወያያ ግሩፕ ነው

👇👇👇👇👇👇👇

@uraman78tu

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

እጅግ በጣም አስቸኳይ‼

ኤሌክትሮ ማግኔት ትራከር በመጠቀም በድሮን ለመምታት ስላሰቡ  የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ማድረግ ግድ ይላል።
1- የማይታወቅ ስልክ መልዕክት አለመክፈት (አለመመለስ)

2-የማያውቁትን የሞባይል ጥሪ አለመመለስ

3-ብዙ ሰው የሚያቀውን ሲም ካርድ አውጥቶ መጣል

4- ከሞባይሎች ፈፅሞ መራቅ አጠቃቀምን በተመለከተ የራስን አሳቻ ሁኔታ መጠቀም

5- ለጋዜጠኛ በምንም መልኩ የቀጥታ ቃለ መጠይቅ አለማድረግ:: የመሳሰሉትን ጥንቃቄ በማድረግ አደጋውን ማራቅ ይቻላል::
Share
Assaye Derbie

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/blum/app?startapp=ref_zEMa9YItgL

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ጥቅምት_6

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ስድስት በዚህች ቀን እመ ሳሙኤል ነቢይ #ቅድስት_ነቢይት_ሐና ያረፈችበት፣ ቅዱስ አባት #አባ_ጰንጠሌዎን ያረፈበት፣ #ዕንባቆም_ነቢይ መታሰቢያው፣ የሀገረ አቴና ኤጲስቆጶስ #ቅዱስ_ዲዮናስዮስ በሰማዕትነት ያረፈበት እና የሴት ልጅ #ቅዱስ_ሄኖስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስት_ነቢይት_ሐና

ጥቅምት ስድስት በዚህች ቀን የታላቁ ነቢይና ካህን የሳሙኤል እናት ቅድስት ነቢይት ሐና አረፈች።

ይችም ቅድስት ከሌዊ ነገድ ናት የታኅርም ልጅ ሕልቃና አገባት ፍናና የምትባልም ሌላ ሚስት አለችው እርሷም ወላድ በመሆኗ ሐና ልጅ ስለሌላት መካንም ስለሆነች ሁልጊዜ ትገዳደራት ነበር።

ሐና ግን ፈጽማ በማዘን አትበላም አትጠጣም ባሏ ሕልቃናም ያረጋጋታል ማረጋጋቱንም አልተቀበለችውም በሊቀ ካህናቱ በኤሊ ዘመንም ወደቤተ እግዚአብሔር ወጣች እያለቀሰችና እያዘነች በእግዚአብሔር ፊት ጸለየች እንዲህም ብላ ስለትን ተሳለች አቤቱ ልጅ የሰጠኸኝ እንደሆነ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ለአንተ የሚያገለግል አደርገዋለሁ።

ካህኑ ኤሊም አያትና እርሷ የወይን ጠጅ ጠጥታ እንደ ሰከረች አሰበ እርሷ በዝምታ በልቧ ትጸልይ ነበርና በቊጣና በግሣጼ የወይን ጠጅ ጠጥተሽ ወደዚህ ወደ እግዚአብሔር ቤት ለምን መጣሽ አሁን ሒጂ ስካርሺን በእንቅልፍ አስወግጂ አላት።

እርሷም እንዲህ አለችው የወይን ጠጅ ከቶ አልጠጣሁም ልጅ ያጣሁ በመሆኔ በልቤ አዝናለሁ እንጂ ካህን ኤሊም አጽናናት እንዲሁም ብሎ ባረካት የእስራኤል ፈጣሪ የለመንሽውን ይስጥሽ በሰላም ሒጂ በቃሉም አምና ወደ ቤቷ ገባች።

ከዚህም በኋላ ፀንሳ ወንድ ልጅን ወለደች ስሙንም ሳሙኤል ብላ ጠራችው። ጡትንም በአስጣለችው ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቤት ይዛው ወጣች ወደ ካህን ኤሊም አቀረበችውና እንዲህ ብላ አስረዳችው ከአሁን በፊት ልጅን ይሰጠኝ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ስጸልይና ስለምን ያየኸኝ ሴት ነኝ ልመናዬንም ሰምቶ ይህን ልጅ ሰጠኝ አሁንም በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ለእግዚአብሔር አገልጋይ ይሆን ዘንድ አመጣሁት።

ከዚህም በኋላ ሐና እግዚአብሔርን አመሰገነችው። ልቤ በእግዚአብሔር አምኖ ጸና የሚለውን ጸሎትና ትንቢት እስከ መጨረሻው ተናገረች። ይቺም በዳዊት መዝሙር መጨረሻ ከሙሴ መኀልይ ቀጥላ ተጽፋለች።

ከዚህም በኋላ እግዚአብሔርን አገልግላ በሰላም አረፈች።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አባ_ጰንጠሌዎን

ዳግመኛም በዚችም ቀን በዋሻ ውስጥ የሚኖር ቅዱስ አባት አባ ጰንጠሌዎን አረፈ። ይህም ቅዱስ በሮሜ አገር በንጉሥ ቀኝ ከሚቀመጡ ከከበሩ ሰዎች ወገን የተወለደ ነው ። በታናሽነቱም ጊዜ ወደ መነኰሳት ገዳም ወስደውት በበጎ ምክር ዕውቀትን እየተማረ በመጸለይና በመጾም በዚያ አደገ።

ከዚህም በኋላ ከቅዱሳን ከስምንቱ ባልንጀሮቹ ጋር ወደ ኢትዮጵያ በንጉሥ አልዓሜዳ ዘመን መጣ በአንድነትም ጥቂት ዘመናት ኑረው ከዚህም በኋላ እርስበርሳቸው ተለያዩ ቅዱስ ጰንጠሌዎንም ከታናሽ ተራራ ላይ ወጥቶ ርዝመቱ አምስት ክንድ አግድመቱ ሁለት ስፋቱ ሦስት ክንድ የሚሆን ዋሻ ለራሱ ሠራ ጠፈሩም አንድ ደንጊያ ነው ከጥቂት ቀዳዳ በቀር በር የለውም።

በውስጡም ሳይቀመጥ ሳይተኛ ያለመብልና ያለ መጠጥ አርባ አምስት ዓመት ኖረ ቆዳው ከዐጥንቱ እስከሚጣበቅ በዕንባ ብዛትም ቅንድቡ ተመለጠ። በሽተኞችን በማዳን የዕውሮችንም ዐይኖች በመግለጥ ብዙ ተአምራትን አደረገ።

በአንዲትም ቀን በማታ ጊዜ ዕንጨት ተከለ አሰከሚነጋ ድረስም አድጎ ትልቅ ዛፍ ሆነ ወዲያውም ደረቀና ደቀ መዝሙሩ ፈልጦ አነደደው ፍሙንም በልብሱ ቋጥሮ ለማዕጠንት ወሰደው።

የናግራንን አገር ያጠፋትን ምእመናኖችንም የገደላቸውን አይሁዳዊ ንጉሥ ሒዶ ሊወጋው ንጉሥ ካሌብ በአሰበ ጊዜ በጸሎቱ ይረዳው ዘንድ ይህን አባት ጰንጠሌዎንን ለመነው እርሱም በሥራው ሁሉ ላይ ችሎታ ያለው እግዚአብሔር በጠላቶችህ ላይ ድል አድራጊነትን ሰጥቶህ በደኀና በፍቅር አንድነት ትመለሳለህ አለው።

ንጉሥ ካሌብም ከናግራን ሀገር በደረሰ ጊዜ ከከሀዲው ንጉሥ ከፊንሐስ ጋር ተዋጋ ድል አድርጓቸውም ከሀድያንን ሁሉ እንደ ቅጠል እስቲረግፉ አጠፋቸው አባ ጰንጠሌዎንንም በጦርነቱ መካከል ጠላቶችን ሲአሳድዳቸው እንዳዩት ብዙዎች ምስክሮች ሆኑ።

ከዚህም በኋላ ንጉሥ ካሌብ ከድል አድራጊነት ጋር በተመለሰ ጊዜ መንግሥቱን ትቶ በዚህ አባት እጅ መነኰሰ ከዋሻ ውስጥም ገብቶ በጾምና በጸሎት እየተጋደለ ኖረ።

ይህም ቅዱስ አባ ጰንጠሌዎን ተጋድሎውን በፈጸመ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደርሱ መጣ ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን የሚያደርግ ገድሉንም ለሚጽፍ ቃል ኪዳን ሰጠው እንግዲህስ ድካም ይበቃሀል ዕረፍ ያን ጊዜም ዐጥንቶቹ ተነቃነቁ በፍቅር አንድነትም አረፈና በዚያ በዋሻው ውስጥ ተቀበረ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዕንባቆም_ነቢይ

በዚችም ቀን የስሙ ትርጓሜ አዋቂ የሆነ የዕንባቆም ነቢይ መታሰቢያው ነው። ይህም ቅዱስ በአንዲት ዕለት እህሉን ለሚያጭዱለት ምሳቸውን አዘጋጅቶ ተሸክሞ ሲሔድ መልአክ ተገልጾለት ይህን መብል በባቢሎን አገር በአንበሶች ጕድጓድ ውስጥ ላለ ለነቢዩ ዳንኤል ውሰድ አለው።

ዕንባቆምም ጌታዬ ሆይ ባቢሎንን አላየኋት ጉድጓዱንም አላውቀው አለው። የእግዚአብሔር መልአክም በራሱ ጠጉር ያዘው ምግቡን በእጁ እንደያዘ ወሰደውና ጉድጓዱ እንደተዘጋ አስገባው ምግቡንም ሰጥቶ መገበው ወዲያውኑ ዕንባቆምን ወደ ይሁዳ አገር መለሰው።

በአረጀና በሸመገለም ጊዜ የእስራኤል ልጆች ከተማረኩበት ተመልሰው ቤተ መቅደስን ሠሩ። ዕንባቆምም ኢየሩሳሌም ደርሶ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ በታላቅ ደስታም ተቀበሉት ትንቢቱንም ሊሰሙ ወደርሱ ተሰበሰቡ አፉንም ከፍቶ በመንፈስ ቅዱስ እንዲህ አለ።

አቤቱ ድምፅህን ሰማሁ ሰምቼም ፈራሁ ሥራህንም አይቼ አደነቅሁ አለ። ስለ መድኃኒታችንም መውረድና በይሁዳ ክፍል በሆነች በቤተ ልሔም ስለመወለዱ ሲናገር የተመሰገነ እግዚአብሔር ግን ከፋራን ተራራ ከቴማን ከይሁዳ አውራጃ ይመጣል ብሎ እስከ መጨረሻው ተናገረ ከነቢያት መጻሕፍትም ጋራ ደመርዋት።

ከዚህ በኋላ ከእስራኤል ልጆች አንዲት ሴት ወደርሱ መጣች እያለቀሰችም እንዲህ አለችው። ሁለት ልጆች ነበሩኝ ጣዖት እንዲአመልኩ ፈለጉአቸው እምቢ በአሉ ጊዜም ገድለው በጐዳና ላይ ጣሉአቸው። ተገድለው ወደ አሉበትም አብሮዋት ሔደ ነፍሳቸውንም ይመልስላቸው ዘንድ እግዚአብሔርን ለመነው ልመናውንም ተቀበሎ በሕይወት አነሣቸው።

ዕረፍቱም በቀረበ ጊዜ ዘመዶቹን ጠራቸው። እንደሚሞትም ነገራቸውና አንዲት ሰዓት ያህል ወደላይ እየተመለከተ ተቀመጠ ። እነሆ እንደ ሰው ክንድ ያለች ታላቅ ክንድ የቤቱን ጣሪያ ሠንጥቃ ወረደች ወደ አፉም ተዘርግታ ነፍሱን ወሰደች ያን ጊዜም አረፈ።

በክርስቲያናዊ ንጉሥ በአንስጣስዮስ ዘመን እንዲህ ሆነ ገድሉን በአነበበ ጊዜ አድንቆ በግብጽ ደቡብ ቀርጣስ በሚባል ቦታ በስሙ ቤተ ክርስቲያን ተሠራለት።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ኤጲስቆጶስ_ቅዱስ_ዲዮናስዮስ

በዚችም ቀን የሀገረ አቴና ኤጲስቆጶስ ቅዱስ ዲዮናስዮስ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ በአቴና አገር በእውቀቱና በመራቀቁ የከበረና ከፍ ከፍ ያለ ነው። በአቴናው ከተማ በዐዋቂዎች የመሳፍንት አንድነት ከአማካሪዎች አንዱ እርሱ ነው።

ቅዱስ ሐዋርያ ጳውሎስም ወደዚያ በደረሰ ጊዜ ሃይማኖትን አስተምሮ የክርስትና ጥምቀትን አጥምቆ በአቴና አገር ኤጲስቆጶስ አድርጎ ሾመው።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ጥቅምት 6-አምስት ክንድ ቁመት ብቻ ባላት በድንጋይ ዋሻ ውስጥ በመኖር በውስጧ ሳይቀመጡ ሳይተኙ በእግራቸው ቆመው 45 ዓመት የጸለዩት አቡነ ጰንጠሌዎን ዕረፍታቸው ነው፡፡ እርሳቸውም ከተሰዓቱ ቅዱሳን አንዱ ናቸው፡፡
+ ቅዱስ ዲዮናስዮስ በሰማዕትነት ያረፈበት ዕለት ነው፡፡
+ የነቢዩ ሳሙኤል እናት ቅድስት ነቢይት ሐና ዕረፍቷ ነው፡፡
+ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ዓመታዊ መታሰቢያ በዓላቸው ነው፡፡
+ ነቢዩ ዕንባቆም ዓመታዊ መታሰቢያ በዓሉ ነው፡፡
+ የሴት ልጅ የሄኖስ የዕረፍቱ መታሰቢያ መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሰዋል፡፡
+ + +
ነቢይት ሐና እመ ሳሙኤል፡- ከሌዊ ነገድ ናት፡፡ በሏ ሕልቃና ፍናና የምትባል ሌላ ወላድ የነበረች ሚስትም ነበረችው፡፡ ሐና ግን መካን ስለሆነች ትገዳደራት ነበር፡፡ በመካንነቷም እጅግ በማዘን ምግብ መመገብ ሁሉ ያቆመችበት ጊዜ ነበር፡፡ በሊቀ ካህናቱ በኤሊ ዘመን ወደ ቤተ መቅደስ ሄዳ እየጸለየች አለቀሰች፡፡ ‹‹አቤቱ ልጅ የሰጠኸኝ እንደሆነ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ አንተን የሚያገለግል አደርገዋልሁ›› በማለትም ተሳለች፡፡ ስታለቅስም ካህኑ ኤሊ አያትና ሰክራ የምታለቅስ መስሎት ነበር፡፡ ዝም ስትለውም ‹‹የወይን ጠጅ ጠጥተሽ ወደዚህ ወደ እግዚአብሔር ቤት ለምን መጣሽ? አሁንም ተመልሰሽ ሂጂና ስካርሽን በእንቅልፍ አስወግጂው›› አላት፡፡ እርሷም ‹‹የወይን ጠጅ አልጠጣሁም፣ ልጅ ያጣሁ መካን በመሆኔ በልቤ አዝኛለሁ እንጂ…›› ስትለው አጽናናት፡፡ ‹‹የእስራኤል አምላክ የለመንሽውን ይስጥሽ›› ብሎም ባረካት፡፡ ቃሉንም አምና ወደ ቤቷ ሄደችና ወንድ ልጅ ፀንሳ ነቢዩ ሳሙኤልን ወለደች፡፡ ልጇንም አምጥታ ‹‹እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጅ ይኸውና በሕይወቱ ዘመን ሁሉ እግዚአብሔርን ያገልግል›› ብላ ለሊቀ ካህኑ ኤሊ ሰጠችው፡፡ ልቤ በእግዚአብሔር ጸና የሚለውን ጸሎትና ትንቢት እስከ መጨረሻው ተናገረች፡፡ እግዚአብሔርንም እየገለገለች ኖራ ጥቅምት 6 ቀን በሰላም ዐርፋለች፡፡ ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ ይማረን!
+ + +
ሰማዕቱ ቅዱስ ዲዮናስዮስ፡- ይኸውም ቅዱስ የአቴና ኤጲስ ቆጶስ የነበሩ ናቸው፡፡ በመጀመሪያ በአቴናን አገር ዕውቀትና ጥበብ የተራቀቀ አዋቂ ነበር፡፡ በአቴና ከተማ በዐዋቂዎች የመሳፍንት አንድነት ከአማካሪዎቹ አንዱ ነው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ወደዚያች አገር ሄዶ ሕዝቡን ሃይማኖትን አስተምሮ አጥምቆ ሲጨርስ ይህን ቅዱስ ዲዮናስዮስን በአገሪቱ ላይ ኤጲስ ቆጶስ አድርጎ ሾመው፡፡

ቅዱስ ዲዮናስዮስ በመንፈሳዊም ሆነ በዓለማዊ ዕውቀቱ ምጡቅ ነው፡፡ በጣም ብዙ ጠቃሚ ድርሳናትን ደረሰ፡፡ ከድርሰቶቹም ውስጥ አንዱ ስለ ጌታችን ስቅለት የደረሰው ነው፡፡ ይህም ድርሰቱ በዕለተ ዓርብ ይነበባል፡፡ ይህም ቅዱስ መጀመሪያ ወደ ክርስትና ሊመለስ የቻለው እንዲህ ነው፡- ዲዮናስዮስ የአቴና የፈላስፋዎች አለቃቸው ነበርና ከዕለታት በአንደኛው ቀን በፍልስፍና ቤት ተቀምጠው ሳለ ዐርብ ቀን ቀትር ሲሆን ፀሐይ ጨለመችና ታላቅ ንውጽውጽታ ሆነ፡፡ አሕዛብም ሁሉ እጅግ ፈርተው የሆነውን ነገር እንዲያስረዳቸው ዲዮናስዮስን ጠየቁት፡፡ እርሱም በጥበቡ ፀሐይንና ጨረቃን ከዋክብትንም ሁሉ መረመራቸው ነገር ግን ፀጥ ብለው አገኛቸው፡፡ ደግሞም ባሕሮችን ውቅያኖሶችን መረመረ፡፡ እነርሱም ፀጥ ብለው አገኛቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ‹‹አርስጣላባ›› የሚባል የፍልስፍና መጽሐፍን አንሥቶ ሲመረምር በውስጡ ‹‹እልመክኑን›› የሚል ጽሕፈት አገኘ፡፡ ትርጉሙም ‹‹ኅቡእ አምላክ ወረደ ወገኖቹም በእርሱ ላይ ተነሥተው ሰቀሉት›› ማለት ነው፡፡ ዲዮናስዮስም በዚህ ጊዜ ልብሱን ቀዶ ታላቅ ልቅሶን አለቀሰ፡፡ ከበታቹ ያሉ ምሁራንም ያየውን ያስረዳቸው ዘንድ ለመኑት፡፡ እርሱም ሁሉን ከነገራቸው በኋላ በሰሙት ነገር ታላቅ ፍርሃት አደረባቸው፡፡

ከዚህም በኋላ ዲዮናስዮስ የፍልስፍና ደቀ መዝሙሩን ኡሲፎስን የሆነውን ሁሉ የዚያችንም ቀን ስሟን ሰዓቷን ወሯን ዘመኗን ሁሉ እንዲጽፍ አዘዘው፡፡ ይህ ከሆነ ከ14 ዓመት በኋላ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ወደዚህች አገር መጥቶ ወንጌልን ሰበከ፡፡ የአቴና ሰዎችም የቅዱስ ጳውሎስን ስብከት በሰሙ ጊዜ እጅግ አደነቁ፡፡ ወደ ዲዮናስዮስም ሮጠው ሄደው ‹‹አንድ ሰው ዛሬ ወደ አገራችን መጥቶ እኛ በማናውቀው ወይም ከእኛ በፊት የነበሩ አባቶቻቸን በማያውቁትን በአዲስ አምላክ ስም አስተማረን›› አሉት፡፡ ዲዮናስዮስም ቅዱስ ጳውሎስን ወደ እርሱ አስጠርቶ ‹‹በሀገራችን ውስጥ በአዲስ አምላክ ስም የምታስተምረው ምንድነው?›› አለው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹በአደባባያችሁ መካከል አልፌ ስሄድ በአማልክቶቻችሁ ቤቶች በደጃፉ ላይ ‹እልመክኑን› የሚል ጽሑፍ አየሁ፡፡ ይህም ‹የማይመረመር አምላክ ወረደ› ማለት ነው፡፡ እኔም ለእናንተ የምሰብከው ይህንኑ ነው›› ብሎ መለሰለት፡፡ በዚህም ጊዜ ዲዮናስዮስ ከ14 ዓመት በፊት የጻፈውን ያን መጽሐፍ ያመጣው ዘንድ ደቀ መዝሙሩን ኡሲፎስን አዘዘው፡፡ ሁለተኛም ጊዜውንና ወራቱን ሐዋርያውን ጠየቀው፡፡ ሐዋርያውም ጌታችን በመጋቢት ወር በ27 ዓርብ ቀን በስድስት ሰዓት እንደተሰቀለ ነገረው፡፡ ዳግመኛም ፀሐይ እንደጨለመች ከዋክብት እንደረገፉ ምድርም እንደተናወጸች አስረዳው፡፡ የአቴና ሰዎቸም ይህንን የቅዱስ ጳውሎስን ትምህርት በሰሙ ጊዜ ከዲዮናስዮስ ጋር ክብር ምስጋና ይግባውና በጌታችን አመኑ፡፡ ሐዋርያውም አስተምሮ አጠመቃቸው፡፡ ቅዱስ ዲዮናስዮስንም በአገሪቱ ላይ ኤጲስ ቆጶስ አድርጎ ሾመው፡፡

ቅዱስ ዲዮናስዮስንም በባሕር አቅራቢያ ወዳለች አገር ሄዶ ወንጌልን ሰብኮ ብዙዎችን በማሳመን የክርስቶስ ተከታዮች አደረጋቸው፡፡ ድንቅ ድንቅ የሆኑ ብዙ ተአምራትንም አደረገ፡፡ ከዚህም በኋላ ከሃዲ ንጉሥ ጠማትያኖስ ይዞት ጽኑ ሥቃይን አሠቃየው፡፡ በመጨረሻም ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ አንገቱን በሰይፍ ቆረጠውና የሰማዕትነቱ ፍጻሜ ሆነ፡፡ ሁለተኛም የደቀ መዘሙርቱን የቅዱስ ኡሲፎስን እና የቅዱስ ኡርያኖስን ራሶቻቸውን ቆረጠ፡፡ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበሉ፡፡
የቅዱስ ዲዮናስዮስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!
+ + +

አቡነ ጰንጠሌዎን፡- በሮሜ አገር በንጉሡ ቀኝ ከሚቀመጡ ከከበሩ ወገኖች ነው የተወለዱት፡፡ ከልጅነታቸው ጀምሮ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሲማሩ አደጉ፡፡ ሆኖም በሀብትና በሥልጣን በዓለም ላይ መኖርን እንደትቢያ ቆጥረው መንነው ዋሻ ገብተዋል፡፡ አቡነ ጰንጠሌዎን 5 ክንድ ቁመት ብቻ ያላት ከመቃብር ያልተሻለች ትንሽ የድንጋይ ዋሻ ቆፍረው በእርሷ ውስጥ በመኖር በውስጧ ሳይቀመጡ ሳይተኙ በእግራቸው ቆመው 45 ዓመት ሙሉ የጸለዩ ታላቅ አባት ናቸው፡፡
አቡነ ጰንጠሌዎን የዕውራንን ዐይን በመግለጥ፣ ሙታንን በማስነሣት፣ ድውያንን በመፈወስ ብዙ ተአምራት ሲያደርጉ በቃላቸው ትምህርት ደግሞ የነፍስን ደዌ ያክሙ ነበር፡፡ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን በማታ ጊዜ ዕንጨት ተከሉ፡፡ እስከሚነጋ ድረስም አድጎ ትልቅ ዛፍ ሆኖ ተገኘ፡፡ ወዲያውም ደረቀና ደቀ መዛሙርቶቻቸው ፈልጠው አነደዱትና አባታችን ፍሕሙን በልብሳቸው ቋጥረው ለማዕጠንት ተጠቀሙበት፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የእነዚያም ልጆች ወላጆቻቸውና ዘመዶቻቸው ታላቅ ልቅሶን አለቀሱላቸው፡፡ ይህም የሆነው በመጋቢት ሦስት ቀን ነው፡፡ ልጆቹም ከሞቱ በኋላ ሦስት ሰዓት በሆነ ጊዜ የዚያች የአባታችንን ዝክር የምታዘክረው ሴት ልጅ ከሞተ በኋላ ተነሣ፣ ከተቀበረበትም ወጣ፡፡ ፀሐይም ከመጥለቋ አስቀድሞ ወደ ቤቱ ሄዶ ከእናቱ ዘንድ ደረሰ፡፡ እናቱም ስታየው በደስታ ጮኸች፡፡ የሀገሪቱም ሰዎች ሁሉ ተሰብስበው ወደ እርሷ መጡና ሞቶና ተቀብሮ የነበረውን የሴቲቱን ልጅ አሁን በሕይወት ሲያገኙት እጅግ አደነቁ፡፡ ልጁንም ‹‹ከሞት እንዴት ተነሣህ?›› አሉት፡፡ ልጁም እንዲህ አላቸው፡- ‹‹የሞትነውን ልጆች ሁላችንንም የእሳት ነበልባል የሚመስሉ መላእክት ወደ ሰማይ ወሰዱን፡፡ ከዚያም በኋላ በመንገድ ከአንድ ትልቅ ሰው ጋር ተገናኘን፣ የራስ ጠጉሩ እንደበረዶ ነጭ ነው፣ እንደተፈተለም ነጭ ሐር ነው፡፡ እንደ መብረቅ ያለ ልብሱንም ባየን ጊዜ ልጆች ሁላችን ደንግጠን ወደቅን፡፡ እርሱንም የሚከተሉት እንደ ሰማይ ከዋክብት
ነበሩ፡፡ ከልጆቹም ሁሉ እኔን ለይቶ ብቻዬን እጄን ያዘኝ፡፡ መላእክትንም ‹ይህንን መታሰቢያዬን የምታደርግልኝ የዚያችን ሴት ልጅ ለምን አመጣችሁት? አሁንም እኔ ወደ እናቱ መልሼ እወስደዋለሁ› አላቸው፡፡ ያንጊዜ በገደል ተቀብሬ ወደነበርኩበት ወደ በድኔ መለሰኝ፤ በሥላሴም በመስቀል ምልክት ሦስት ጊዜ ባረከ፤ ገደሊቱም ቀጥ ብላ ቆመች፤ በድናችንንም ተቀጥቅጦ እንደ አመድ ሆኖ አገኘነው፡፡ ያን ጊዜም እጄን ይዞ አስነሣኝና ‹አንቺ ነፍስ ወደ ሥጋሽ ተመለሺ ብሏል እግዚአብሔር› አለ፡፡ ያንጊዜም ነፍሴ ወደሥጋዬ ተመለሰች፤ እንደቀድሞውም ሆንኩ፡፡ ገደሊቱንም ‹በሦስተኛው ቀን እስክመለስ ድረስ ተደፊ› አላት፤ ገደሊቱም ወደ መሬት ተደፋች፡፡ ያንጊዜም ‹ሂድ ወደ እናትህ ተመለስና እናትህን ‹እነሆ ልጅሽን ላኩልሽ እንዲሁም ነፍስሽን በሰማይ አድናታለሁ ብለህ ንገራት› አለኝ፡፡ ከዚህም በኋላ ከሩቅ ጠራኝና ‹እናትህ ስሙ ማነው ብላ ብትጠይቅህ ያ የታመንሽበት ገብረ መንፈስ ቅዱስ ነው› ብለህ ንገራት› ብሎኝ ከእኔ ተሰወረ፡፡ እኔም ወደ እናንተ መጣሁ›› አላቸው፡፡ ከዚያ የነበሩና የልጁንም ምስክርነት የሰሙና አባታችን ልጁን ከሞት እንዳስነሡት ያዩ የሀገሩ ሰዎች ሁሉ በመደነቅ ‹‹የአባታችንን መታሰቢያ ለማድረግ ነፍሳችንንም ሥጋችንንም ሥዕለት አድርገን ለመስጠት ወስነናል፡፡ ገንዘባችንን ከብቶቻችንን ሁሉ ሰጥተናል›› እያሉ ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፡

በሦስተኛውም ቀን መንፈቀ ሌሊት በሆነ ጊዜ ማለትም በዕረፍታቸው ዕለት መጋቢት 5 ቀን በሆነ ጊዜ የሀገሪቱ ሰዎች ወንዶችም ሴቶችም ቀሳውስት ዲያቆናት ሁሉ ተሰብስበው ዕጣን መብራት ይዘው ወደ ቤተ ክርስቲያን ገቡ፡፡ ያን ጊዜም ገደል ተጭኗቸው ሞተው የነበሩ እነዚያ ልጆች ሁሉም በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጸሎት ከሞት ተነሥተው በእጃቸው መብራት ይዘው ‹‹ይህ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሙታንን ከመቃብር የሚያስነሣ ተአምረኛ ነው፤ እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ የሚደነቅ ነው›› እያሉ በመዘመር ከመቅደስ ወጡ፡፡ እንዲህም እያሉ ከእናቶቻቸውና ከአባቶቻቸው ከዘመዶቻቸውም ጋር ተገነኙ፡፡ በደስታና በእልልታም ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፡
የአባታችን የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ልመናቸው በተዋሕዶ ልጆች በሁላችን ላይ ይደረግልን በረከታቸው ይደርብን ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

(ምንጭ፦ አለቃ አያሌው ታምሩ የተረጎሙት ገድለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘአኅተሞ ተስፋ ገብረ ሥላሴ፣ 1992 ዓ.ም ከገድላት አንደበት)
✞ ✞ ✞
(የበፊቶቹ ኹለቱም የቴሌግራም ቻናሎች በተለያየ ጊዜ ስለተጠለፉ ለ3ኛ ጊዜ በተከፈተው አዲስ ቻናል በኩልም በጽሑፍና በድምፅ ይከታተሉ።)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ጥቅምት 5/2017 #ፃድቁ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ፃድቁ #ገብረ_መንፈስ_ቅዱስን በምልጃ ፀሎታቸዉ እንዲራዱን ለምንማፀንበት አመታዊ የእረፍት በአላቸዉ መታሠቢያ እንኳን አደረሰን

👉ጥቅምት አምስት ቀን የታላቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ #ገብረ_ሕይወት የዕረፍታቸው መታሰቢያ ሲሆን ፃድቁ የተወለዱት ግብፅ ንሒሳ አካባቢ ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ

👉አባታችን #ገብረ_ሕይወት የፃድቃን አለቃ የቅዱሳን የበላይ ተጋድሎአቸውና ድንቅ ተአምራቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ቅዱስ ሰው ናቸዉ የጻድቁን ክብር መናገር የሚችል ምን አንደበት ይኖራል እንደ ምንስ ባለ ብራና ይፃፋል ዜናቸውንስ ለመስማት የታደለ እንደ ምን ዓይነት ሰው ይሆን

👉አባታችን #ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ለ562 ዓመታት በዚህች ዓለም ሲኖሩ እህል ያልቀመሱ ምግባቸው ምስጋና ልብስን ያልለበሱ ፀጉር አካላቸውን ይሸፍን ነበርና ሐዋርያዊ ሆነው ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ ነፍሳትን ያዳኑ አባት ሃገራችንን አስምረው አስራት እንድትሆናቸውም ተቀብለው ምድረ ከብድ አካባቢ አርፈዋል

👉ፃድቁ #ገብረ_መንፈስ_ቅዱስም_ገብረ_ሕይወትም ይባላሉ በ562 ዓመታት ሕይወታቸው እንደ ሐዋርያት ከምድረ ግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ወንጌልን ሰብከዋል በዚህም በሚሊዮን አእላፍ ለሚቆጠሩ ነፍሳት የድህነት ምክንያት ሆነዋል

👉ፃድቁ እንደ ሰማዕታትም ከከሃዲ ሰዎች ብዙ መከራን ተቀብለዋል እንደ ባሕታውያን ለብዙ መቶ ዓመታት ሰው ሳያዩ ቆይተዋል ለየት የሚለው ግን የፅድቅ ሕይወታቸው ነው ከእልፍ አዕላፍ አጋንንት ጋር ተዋግተው #ድል_ማድረግ ችለዋልና

👉የንሒሳው ኮከብ #ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ለኢትዮጵያ ልዩ ፍቅር አላቸው ስለ ሃገሪቱና ሕዝቧ ፍቅር ሲሉ ለ100 ዓመታት በደብረ ዝቋላ መከራን ተቀብለዋል ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው

👉ስለዚህም ነው በሃገሪቱ ውስጥ ከ2,000 በላይ የፃድቁ አቡነ #ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ገዳማትና አድባራት ዛሬም ድረስ ያሉት በ8ኛው ክ/ዘ አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ14ኛው መቶ ክ/ዘ አካባቢ ነው ፍጥረታትን ሁሉ አዘው መጋቢት 5 ቀን ሲያርፉ #ግሩማን_መላእክት_ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል

👉 #ሥላሴን የተሸከመ አካላቸው በጐልጐታ ተቀብሯል የሚሉም አሉ አባታችን #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ እረፍታቸዉ መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ፆም ወቅት ነው

👉ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ #በዓብይ_ፆም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍፁም ሀዘን እንጂ የመጋቢት 27 ስቅለት ጥቅምት 27 ቀን እንደሚከበረው ሁሉ መጋቢት 5 ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር ሆኗል

👉የፃድቁ አባታችን ምልጃና ፀሎት ሀገራችንን ህዝባችንን ይጠብቅልን ቃል ኪዳናቸዉ አይለየን በዚህ እለት የምናስባቸዉ #ቅዱስ_ጴጥሮስና_እና_ቅዱስ_ጳዉሎስ ረድኤት በረከታቸዉ አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/+YVsr8ZgFEhFhYjg8

Читать полностью…
Subscribe to a channel