kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ቅዱስ አትናቴዎስ በቅዳሴያችን እንዲህ እንዳለ

👉አዳምና ሔዋን ሆይ እኛስ እናንተን መንቀፍ አይቻለንም ፤ በአርሱ እየተናገሩበት የራስን አንደበት ለመንቀፍ አንደማይቻል እንዲሁም አናንተ አኛን ናችሁ ፤ እኛም እናንተን ነን።

👉 አዳምና ሔዋን ሆይ እናንተን እንዳንነቅፋችሁ ይቅር ባይ ጌታ ባመጣባችሁ መከራ ተጸጽታችሁ ንስሓ ገብታችኋል፡፡

👉አዳምና ሔዋን ሆይ እናንተስ ድናችኋል ቤዛ ሆኖ ባዳናችሁ በጌታ ደም ወደቀደመ ርስታችሁ ወደ ገነትም ገብታችኋል... አኛን ልጆቻችሁን ግን ኃጢአት እንደ አሳት አቃጠለችን። ፍትወትም እነደደችን'


ተፀፀተን ለንስኃ በቅተን እንኖር ዘንድ
ፈጣሪ አምላክ ይርዳን
ፍትወታችንን ያርቅልን በምህረቱ በጎውን ያርግልን🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

መኝታውን በወርቅ ያጌጠ ማድረግ ሲችል
በግርግም ውስጥ ማድረግን መረጠ
እናቱንም ከንግሥታት አንዲቱን ማድረግ ሲችል
አላደረገም ብሏል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
❤️

ድንግል ማርያም እንዲህ ናት::
ታላላቅ ሀብታትን ሳትጠይቅ የተቀበለች ፣
ሳትለምን የተመረጠች ፣ ሳታገባ የፀነሰች ፣
ሳታምጥ የወለደች ፣ ድንግልናዋን ሳታጣ እናት የሆነች ፣
አንዳች ሳትሻ ሁሉን ያገኘች
የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ እርስዋ ናት፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

ጸሎት

"የጭንቀት ሁሉ መሸሸጊያ ስፍራ፣
የደስታ መሰረት፣
የቋሚ ደስታ ምንጭ፣
ከሀዘን መከላከያ ነው።"


ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ጥቅምት 13/2017 #እግዚአብሔር_አብ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አንተ እውነተኛ አምላክ ስትሆን ሁሉን በፍቃድህ የፈፀምህ የሁሉ ፈጣሪ #እግዚአብሔር_አብ ሆይ ሁሉን ማድረግ የሚቻልህ ሁሉ ለአንተ የቀረበ በአንተም ዘንድ አለና እውነተኛይቱ መንገድ መርተህ ህግህን አስተምረን

👉በእልፍ አእላፋት መላእክት የሚመሰገን #እግዚአብሔር_አብ አምላካችን ሀገራችንን ህዝባችንን በምህረት አይኑ ይመልከትልን ፍቅርና አንድነትን ይስጠን

👉ኄኖክም ስለእርሳቸው እንዲህ አለ በሰማይ እያለሁ ነፋሳት በደመና ውስጥ አወጡኝ በእሳት ላንቃም ወደታነፀ ቤት አደረሱኝ በዚያም #አእላፋት_መላእክትን አየሁ እነርሱም በእሳት ላቦት ላይ የቆሙ ልብሳቸውም እንደ በረድ ነጭ ነው አለ

👉ያዕቆብም እንዲህ አለ ከምድር እስከ ሰማይ የምትደርስ መሰላልን አየሁ #የእግዚአብሔርም መላእክት በውስጥዋ ይወጡ ይወርዱ ነበር ሁለተኛም ከሶርያ መመለሻው በሆነ ጊዜ የመላእክት ሠራዊትን አየሁ አለ

👉ሙሴም እንዲህ አለ #እግዚአብሔር አሕዛብን በቦታ እንደለያቸው የአዳምን ልጆች እንደበተናቸው እግዚአብሔርን በሚያገለግሉ መላእክት ቁጥር የአሕዛብን አውራጃዎች እንደ ወሰናቸው ሁለተኛም #እግዚአብሔር ከሲና ተራራ መጥቶ በሴይር ታየኝ ረቂቃን መላእክቶቹም ከእርሱ ጋር ነበሩ አለ

👉ዳዊትም እንዲህ አለ #መላእክቱን መንፈስ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርግ እርሱ ነው #የእግዚአብሔር ሠረገላዎች የብዙ ብዙ ሺህ ናቸው አለ ኤልሳዕም የእሳት ሠረገሎችና የእሳት ፈረሶች በዙሪያው ቁመው ሲጠብቁት አየ

👉ዳንኤልም እንዲህ አለ ዙፋኖችን እስቲዘረጉለት ድረስ ደርሶ አየሁ ብሉየ መዋዕል #እግዚአብሔር በላያቸው ተቀመጠ ልብሱም እንደ በረድ ነጭ ነው የራሱም ጠጉሩም እንደ ብዝት ነጭ ነው

👉ዙፋኑም የሚነድ እሳት ነው ሠረገላውም የሚንቦገቦግ ፍም ነው የእሳትም ጐርፍ በፊቱ ይፈሳል የብዙ ብዙ የሆኑ መላእክትም ያገለግሉታል የእልፍ እልፍ #መላእክትም በፊቱ ይቆማሉ በአደባባይም ተቀምጦ መጻሕፍትን ገለጠ

👉ሉቃስም እንዲህ አለ ድንገትም ከዚያ መልአክ ጋር ብዙ የሰማይ ሠራዊት መጡ #እግዚአብሔርንም ሲያመሰግኑ በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ሰላም ለሰው ልጅ በጎ ፈቃድ እያሉ

👉ማቴዎስም እነሆ #መላእክትም ሊአገለግሉት መጡ አለ ሁለተኛም የሰው ልጅ ቅዱሳን መላእክትን አስከትሎ በጌትነቱ በሚመጣበት ጊዜ ያን ጊዜ በጌትነቱ ዙፋን ላይ ይቀመጣል ዮሐንስም ጌታችን ከተናገረው ቃል እንዲህ አለ እላችኋለሁ ከእንግዲህ ወዲህ ሰማዮች ሲከፈቱ #የእግዚአብሔርም መላእክት ወደ ሰው ልጅ ሲወርዱና ሲወጡ ታያላችሁ አላቸው የሚል ነው

👉ሐዋርያው ይሁዳም እነሆ #እግዚአብሔር ይፈርድ ዘንድ አእላፋት የሆኑ ቅዱሳን መላእክቶቹን አስከትሎ ይመጣል አለ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትም የመዓረጋቸውን ደረጃ ወይም አይነት እንዲህ ብለው ተናገሩ መላእክት አጋዕዝት ሥልጣናት ኃይላት መናብርት መኳንንት ሊቃናት አርባብ ኪሩቤል ሱራፌል ብለው ተናገሩ

👉 #የእግዚአብሔር አብ ፀጋ የወልድ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ አንድነት ከኛ ጋር ይሁን በዚህ እለት የሚታሰበዉ የጦቢትን አይን ያበራ መልአኩ #ቅዱስ_ሩፋኤል ይጠብቀን የፃድቁ አባታችን አቡነ #ዘርዐ_ብሩክ ፀሎቱ አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ጥቅምት 13/2017 #እግዚአብሔር_አብ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አንተ እውነተኛ አምላክ ስትሆን ሁሉን በፍቃድህ የፈፀምህ የሁሉ ፈጣሪ #እግዚአብሔር_አብ ሆይ ሁሉን ማድረግ የሚቻልህ ሁሉ ለአንተ የቀረበ በአንተም ዘንድ አለና እውነተኛይቱ መንገድ መርተህ ህግህን አስተምረን

👉በእልፍ አእላፋት መላእክት የሚመሰገን #እግዚአብሔር_አብ አምላካችን ሀገራችንን ህዝባችንን በምህረት አይኑ ይመልከትልን ፍቅርና አንድነትን ይስጠን

👉ኄኖክም ስለእርሳቸው እንዲህ አለ በሰማይ እያለሁ ነፋሳት በደመና ውስጥ አወጡኝ በእሳት ላንቃም ወደታነፀ ቤት አደረሱኝ በዚያም #አእላፋት_መላእክትን አየሁ እነርሱም በእሳት ላቦት ላይ የቆሙ ልብሳቸውም እንደ በረድ ነጭ ነው አለ

👉ያዕቆብም እንዲህ አለ ከምድር እስከ ሰማይ የምትደርስ መሰላልን አየሁ #የእግዚአብሔርም መላእክት በውስጥዋ ይወጡ ይወርዱ ነበር ሁለተኛም ከሶርያ መመለሻው በሆነ ጊዜ የመላእክት ሠራዊትን አየሁ አለ

👉ሙሴም እንዲህ አለ #እግዚአብሔር አሕዛብን በቦታ እንደለያቸው የአዳምን ልጆች እንደበተናቸው እግዚአብሔርን በሚያገለግሉ መላእክት ቁጥር የአሕዛብን አውራጃዎች እንደ ወሰናቸው ሁለተኛም #እግዚአብሔር ከሲና ተራራ መጥቶ በሴይር ታየኝ ረቂቃን መላእክቶቹም ከእርሱ ጋር ነበሩ አለ

👉ዳዊትም እንዲህ አለ #መላእክቱን መንፈስ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርግ እርሱ ነው #የእግዚአብሔር ሠረገላዎች የብዙ ብዙ ሺህ ናቸው አለ ኤልሳዕም የእሳት ሠረገሎችና የእሳት ፈረሶች በዙሪያው ቁመው ሲጠብቁት አየ

👉ዳንኤልም እንዲህ አለ ዙፋኖችን እስቲዘረጉለት ድረስ ደርሶ አየሁ ብሉየ መዋዕል #እግዚአብሔር በላያቸው ተቀመጠ ልብሱም እንደ በረድ ነጭ ነው የራሱም ጠጉሩም እንደ ብዝት ነጭ ነው

👉ዙፋኑም የሚነድ እሳት ነው ሠረገላውም የሚንቦገቦግ ፍም ነው የእሳትም ጐርፍ በፊቱ ይፈሳል የብዙ ብዙ የሆኑ መላእክትም ያገለግሉታል የእልፍ እልፍ #መላእክትም በፊቱ ይቆማሉ በአደባባይም ተቀምጦ መጻሕፍትን ገለጠ

👉ሉቃስም እንዲህ አለ ድንገትም ከዚያ መልአክ ጋር ብዙ የሰማይ ሠራዊት መጡ #እግዚአብሔርንም ሲያመሰግኑ በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ሰላም ለሰው ልጅ በጎ ፈቃድ እያሉ

👉ማቴዎስም እነሆ #መላእክትም ሊአገለግሉት መጡ አለ ሁለተኛም የሰው ልጅ ቅዱሳን መላእክትን አስከትሎ በጌትነቱ በሚመጣበት ጊዜ ያን ጊዜ በጌትነቱ ዙፋን ላይ ይቀመጣል ዮሐንስም ጌታችን ከተናገረው ቃል እንዲህ አለ እላችኋለሁ ከእንግዲህ ወዲህ ሰማዮች ሲከፈቱ #የእግዚአብሔርም መላእክት ወደ ሰው ልጅ ሲወርዱና ሲወጡ ታያላችሁ አላቸው የሚል ነው

👉ሐዋርያው ይሁዳም እነሆ #እግዚአብሔር ይፈርድ ዘንድ አእላፋት የሆኑ ቅዱሳን መላእክቶቹን አስከትሎ ይመጣል አለ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትም የመዓረጋቸውን ደረጃ ወይም አይነት እንዲህ ብለው ተናገሩ መላእክት አጋዕዝት ሥልጣናት ኃይላት መናብርት መኳንንት ሊቃናት አርባብ ኪሩቤል ሱራፌል ብለው ተናገሩ

👉 #የእግዚአብሔር አብ ፀጋ የወልድ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ አንድነት ከኛ ጋር ይሁን በዚህ እለት የሚታሰበዉ የጦቢትን አይን ያበራ መልአኩ #ቅዱስ_ሩፋኤል ይጠብቀን የፃድቁ አባታችን አቡነ #ዘርዐ_ብሩክ ፀሎቱ አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ወደ ሮሜ ሰዎች 8:33 እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው? Who shall lay any thing to the charge of God's elect? It is God that justifieth.
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:34 የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። Who is he that condemneth? It is Christ that died, yea rather, that is risen again, who is even at the right hand of God, who also maketh intercession for us.

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ሰላም_ለከ_ሚካኤል
የተጨነቀውን ነፃ ለምታወጣ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ሰላምታ ይገባሃል፣
ሠራተኛውን ሠርቶ እንዲኖር ውሎ እንዲገባ የምትጠብቀው ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይኹን፣
ችግረኛውን ለመርዳት ከልዑል እግዚአብሔር ዘንድ የምትላክ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ሰላም ላተ ይኹን፣ አዳኝነትህን በማመን የለመነህን ኹሉ በክንፈ ረደኤትህ የምትሠውረው ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይኹን፣ በኀዘን በትካዜ ላይ ወድቆ የሚፍገመገመውን ፈጥነህ ደርሰህ ደግፈህ የምታጽናናው የምታረጋጋው ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ሆይ አንገትህን ዘንበል መለስ አድርገህ በፈጣሪህ እግዚአብሔር ፊትም ሰግደኽ እኛን ባሮቹን በቸርነቱ ጐብኝቶ የማናዊት እጁንም ዘርግቶ ይባርከን ዘንድ አማልደን ለዘለዓለሙ አሜን።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝እንኳን አደረሰነ!

✝በዓለ ቅዱስ ዳዊት (ንጉሠ እሥራኤል)
ወበዓሎሙ ለቅዱሳን፦
❀ሚካኤል ሊቀ መላእክት
❀ማቴዎስ ወንጌላዊ
❀ድሜጥሮስ ተካሌ ወይን
❀ልዕልተ ወይን ድንግል
❀አፎምያ ብጽዕት
❀ሳሙኤል ወዕሴይ

☞መዝ​ሙረ ቅዱስ ዳዊት

✿በእንተ ርዕሱ፦

፩. ከወ​ን​ድ​ሞቼ ይልቅ እኔ ትንሽ ነበ​ርሁ፥
በአ​ባ​ቴም ቤት ወጣት ነበ​ርሁ፥
ያባ​ቴ​ንም በጎች እጠ​ብቅ ነበር።

፪. እጆቼ መሰ​ንቆ ይመቱ ነበር።
ጣቶ​ቼም በገና ይደ​ረ​ድሩ ነበር።

፫. ለጌ​ታዬ ማን ነገ​ረው?
እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ ሰማኝ።

፬. እርሱ መል​አ​ኩን ልኮ አዳ​ነኝ፥
የአ​ባ​ቴን በጎች ከም​ጠ​ብ​ቅ​በት ወሰ​ደኝ፤
የተ​ቀ​ደሰ ቅባ​ትን ቀባኝ፤

፭. ወን​ድ​ሞቼ ግን፥ ያማ​ሩና ያደጉ ነበሩ።
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በእ​ነ​ርሱ ደስ አላ​ለ​ውም።

፮. ልዩ ወገ​ንን ልገ​ጥ​መው ወጣሁ።
በረ​ከሱ ጣዖ​ቶ​ቹም ረገ​መኝ።

፯. እኔም ከወ​ንዝ ሦስት ድን​ጋ​ዮ​ችን አነ​ሣሁ፥
ግን​ባ​ሩ​ንም በወ​ን​ጭፍ መታ​ሁት።
ያን​ጊ​ዜም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ወደቀ።

፰. በላዩ የነ​በ​ረ​ው​ንም ሰይፍ ወሰ​ድሁ፥
የጎ​ል​ያ​ድ​ንም ቸብ​ቸቦ ቈረ​ጥሁ።
ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም ስድ​ብን አራ​ቅሁ።

(መዝ​ሙር ዘዳዊት ፻፶፩)

✝ሰላም ለርዕስከ በቅብዓ መንግሥት ዘከብረ፤
እምድኅረ ሳዖል በቅድመ እግዚኡ እንተ ኢኮነ ስሙረ፤
ዳዊት ኅሩይ በዘንዌድሰከ ወትረ፤
ይቤሎ ማቴዎስ ለክርስቶስ ወልደ ዳዊት ምዕረ፤
ወድሜጥሮስ ተርጎሞ እንዘ ይከሥት ሥውረ!

(አርኬ - ዝክረ ቅዱሳን ርቱዓነ ሃይማኖት)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Fc 25 Vini Junior Celebration On ps5
🔥🔥🔥

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ወዳጄ

ሕይወት ጨለማ ስትሆንብህ

ብርሃን ወደ ሆነው ጌታ አብዝተህ ፀልይ
በፍፁም ልብህ በፍጹም ሀይልህ በፍፁም ነፍስህ
ሁነህ ጌታ እግዚአብሔርን ለምነው
ያን ጊዜ ጨለማው ይገፈፋል ብርሃን ይሆናል።

እግዚአብሔር አምላክ ህዝብህን ከክፉ ጠብቅ🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሕልም እና ማሳካት የሚፈልጉት ዓላማ ላላቸው እንዲሁም ህልማቸውን ዕዉን እንዲሆን ቁርጠኛ ለሆኑ የመጣ ትልቅ ዕድል!!!!

የአሁኑን ዕድል ከልቡ የሚጠቀም ማን ይሆን?

ራዕዬን ለመኖር በማደርጋቸው የተለያዩ ተግባራት መሃከል አንደኛው አስር  ህልም ያላቸውን፣ መለወጥ የሚፈልጉ፣ ቁርጠኛ የሆኑ፣ ፅኑ የሆኑ ሰዎችን ለአንድ አመት በማይንድ ፕሮግራሚንግ ውጤታማ እንዲሆኑ የማገዝ እቅድ አውጥቻለሁ።

እናም አንድ አመት  ራስ ላይ በመስራትና መንገድ በማሳየት ብቻ ሰክሰስፉል እስኪሆኑ ድረስ በውስጠህሊና ፕሮግራሚንግ ለማገዝ 10 ሁነኛ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች እየፈለኩኝ ነው።

   1- ለውጥን እንደ ኦክስጅን የተጠማ
   2- የ አእምሮውን አሰራር በደንብ ማወቅ የፈለገ እና ለመተግበር ዝግጁ የሆነ ሰው!
   3- የሚሰጠውን አሳይመንት ለመስራት ቁርጠኛ የሆነ!

በዚህ ፕሮሰስ ያለፈ

1⃣- አእምሮዉ እንዴት እንደሚሰራ ያውቃል
2⃣- በቀን ለ 20 ደቂቃ ያክል ከተገበረው ህይወቱን ትራንስፎርም ሊያደርግ ይችላል
3⃣- በሰባቱም የህይወት ዘርፉ ( ጤና ፣ መንፈሳዊ ፣ ማህበራዊ ፣ ገንዘብ ፣ ቤተሰብ ፣ እውቀት እና ራእይ) ውጤታማ ይሆናል።
4⃣- ለሌሎቹም ምሳሌ ይሆናል

5⃣ - በውስጡ አጓጊ የሆኑ ብዙ እድሎችን የያዘ

6⃣-ከሳምንታዊ ገቢ እስከ ድርጅት ባለቤት የመሆን እድል
@Megu1921ላይ
(እኔ ዝግጁ ነኝ) ብሎ
1:ሙሉ ስም
2:መኖሪያ ቦታ
3:ስልክ ቁጥር  ይላክልኝ!

0938117195 ይደዉሉ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በ አስቸኳይ ለ ሽያጭ የ ቀረበ ዋናውን አስፋልት የያዘ እጅግ ርካሽ የ እጣ ቤት
ይፍጠኑ ብሩ ተፈልጎ ነው ለትርፍም ይሆናል::
👉አድራሻ: ቦሌ  አራብሳ አዲሱ ሳይት 
👉 የቤት ስፋት 65ካሬ
👉ወለል 3ኛg+4
👉 ሳይት 6
👉እዳ: 20% የከፈለ
👉እድሳት:  ባለበት
👉ዋጋ 2.200,000 ድርድር የለዉም::
👉ሁለት  ሚሊን ሁለት   መቶ  ሺ
👉ገዥ ከሆኑ ብቻ ይደውሉ
የምንሰጣቸው አገልግሎት
%👉የኮንደሚኒየም ቤት ሽያጭና ክራይ
👉የግል ቤት ሽያጭና ክራይ
👉የቦታ ሽያጭ
👉የንግድ ሱቆች ክራይና ሽያጭ
👉የት ይፈልጋሉ ኮየ, ቱሉድምቱ, አራብሳ,ጀሞ, አያት49 or የካ በሁሉም አለን!!!


ለበጠ መርጃ
   
    +251920825555
+251942826117

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

☞ወር በገባ በ9 ታስበው የሚውሉ የአባታችን የአቡነ ብፁዐ አምላክ ታአምር
ይህ ነው፡፡
☞ልመናውና በረከቱ ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ ከአቡነ ዮሐንስ በኃላ በተሾመው
በአባ ሠረቀ ብርሃን ዘመን ወደ ደብረ ቢዘን ከአባቱና ከወንድሞቹ ጋር በገባ ጊዜ
የእግዚአብሔርን ቃል ያስተምረው ዘንድ ለአባ ጴጥሮስ ተሰጠ፡፡
☞የትምህርት ቤት ለጆች ወንድሞቹ ቀኑበት፡፡ ለምን ከእኛ ጋራ እየተማረ እንደ
እኛ አይፈጭም አሉ፡፡ አባ ጴጥሮስም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ብፁዐ አምላክ ሆይ
እዳያዝኑብህ እንደ ወንድሞችህ የምትፈጨውን ውሰድ አለው፡፡
☞የዋህ የሆነ ብፁዐ አምላክም እሺ አምላክህ በጸሎትህ ያስችለኝ አለ፡፡
የሚፈጨውንም ወሰዶ ተኛ በነቃም ጊዜ ተፈጭቶ አገኘው እግዚአብሔር
አመሰገነ ለሰውም አልተናገረም፡፡
☞ለብዙ ጊዜ እንዲህ በሆነበት ጊዜ ጓደኞቹ የተማሪዎች አለቃ ከፈጩት ዱቄት
የሚሰጠው አለ ብለው ተጠራጠሩ፡፡ እስኪ መጣም ሦስት ሦስት ሁነን እንጠብቅ
ከመካከላችን ነቅቶ እህል ወስዶ ዱቄትን የሚሰጠው አለ አሉ፡፡ ሦስት ሦስት
ሁነው ሲጠብቁ የፈጭታዎች
መንቂ ደረሰ፡፡
☞የእየራሳቸውንም ሊፈጩ እሳትን አበሩ፡፡ የብፁ አምላኮ እህል ግን ተፈጭቶ
አገኙት፡፡ ተደንቀውም አትናገሩ፡፡ ሁለትኛ ሦስተኛ እንዲህ የሚሆን እንደሆነ እንይ
አሉ፡፡ እንዲህም ሆነ፡፡ በምሽት በየተራቸው ለብፁ አምላክ የተከፈለውን እህል
ያስቀምጣሉ፡፡
☞ ሦስት ሦስት ሁነውም ይጠብቃሉ፡፡ በነቁም ጊዜ ተፈጭቶ ያገኙታል፡፡ ከዘህ
በኃላ ለመምህሮቻቸው ተናገሩ፡፡
☞እነሱም እንደ ልጆች አድርገው ሦስት ሦስት ሆነው ጠበቁትና ሥራውን
እንግለጥበት አሉ፡፡ ግን ሥራውን አስትተን የቤተ ክርስቲያን ተልኮና መጻሕፍትን
ማንበብ እናዝዘው አሉ፡፡
☞እሱም ጌቶቼ በመፍጨቴ ካልተደስታችሁ ምግብ ማብሰል ወይም ሌላ ሥራ
የወደዳችሁን በቤተ ክርስቲያን ምልከታ ላይ እና መጻሕፍትን ማንበብን እዘዙኝ
አላቸው፡፡
☞ውሃ መቅዳትን አዘዙት፡፡ አባታችንም ብፁዐ አምላክ ቀድቶ ሊሸከም ባነሣው
ጊዜ ውሃው ከራሱ ላይ አንድ ክንድ ከፍ ከፍ አለ ይህን አይተው አደነቁ፡፡
☞ዳግመኛ ዕንጨትም ሊለቅም ሄደ፡፡ በጸሎት ሰዓት ሊጸልይ ሲቆም ዕንጨቶች
የሚበቃውን ያህል ይሰበሰቡለታል፤ ሊሸከምም ሲያስር አንድ ክንድ ከራሱ ላይ
ከፍ ከፍ አለ፡፡
]ወደ ኀላ ባለጊዜም ሊጠብቁት ወንድሞቹ ተመለሱ፡፡ ይህንንም አይተው አደነቁ
መክረንም እስክናዝዝህ ድረስ ታገስ አሉት፡፡ ብሩክ ሁን መንፈስ ቅዱስ
እንደሰየመህ ብፁዕ ሁን አሉት፡፡
]☞የብጹ አቡነ አምላክ ወዳጆቹን እግዚአብሔር በጸሎቱ ይቅር ይበላቸው
ለዘላለሙ አሜን፡፡
☞(ገድለ አቡነ ብፁዐ አምላክ)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ሰላም yekedus gebrhel legut ሰላም new.

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Nbsesh ke degagochu kene abrham ena ysaq gon tref enate

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

መዓረጋተ ቅዱሳን

👉ንጽሐ ሥጋ
(ጽማሜ፣ ልባዌ፣ ጣዕመ ዝማሬ)
👉ንጽሐ ነፍስ
(አንብዕ፣ ኩነኔ፣ ፍቅር፣ ሑሰት)
👉ንጽሐ ልቡና
(ንጻሬ መላእክት፣ ተሠጥሞ ብርሀን፣ ከዊነ እሳት)

++++++++++++~++++++++++

ከጣዕመ ዝማሬ

የደረሰ አንድ ባሕታዊ ለብዙ ዘመናት ያህል “አቡነ ዘበሰማያት - አባታችን ሆይ” ብቻ እያለ ያንኑ ብቻ እየመላለሰ “ይትቀደስ ስምከ” ሳይል ኖረ።

መልአክ መጥቶ “ይትቀደስ ስምከ” በል እንጂ ቢለው

“ኧረ ጌታዬ፣ እኔስ አባታችን ሆይ የሚለው ኃይለ ቃል ምሥጢሩና ጣዕሙ በአፌ እንደ ስኳር እየሟሟ አልጠገበኝ ብሏል፣ እንዴት አድርጌ ወደፊት ልሂድ!” አለው ይባላል።

ለመጸለይ የምንሰንፍና አንድ ጊዜ የጸለይነውን ጸሎት ለመድገም የምንሰለች፣ ወይንም ደግሞ ቶሎ ቶሎ ንባቡን ጨርሰን ለመቀመጥ የምንቸኩል ከሆነ ምን ያህል ከጸጋ የራቅን መሆናችንን ልናውቅና አምላካችን በምሕረቱ እንዲጎበኘን አብዝተን መለመን እንዳለብን ልንረዳ ይገባል።

ቅዱሳንን ለዚህ ጸጋ ያደረሰ አምላክ እኛንም ሳንሰለች ለመጸለይና ለማመስገን እንድንችል ይርዳን!

ፍኖተ_ቅዱሳን

ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

👉“በእምነት መዳን˘ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ሲሆን “በእምነት ብቻ መዳን" የሚለው ግን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አይደለም፡፡ ይህ የፕሮቴስታንቶችና የልጆቻቸው የተሐድሶዎች የፈጠራ ትምህርት ነው፡፡

👉 መጽሐፍ ቅዱስ በእምነት ስለ መዳን እንጂ “በእምነት ብቻ ስለ መዳን አንድም ቦታ አይናገርም፡፡ 'ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቆጥራለንና በሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ላይ "በእምነት ብቻ እንዲጸድቅ” በማለት “ብቻ የሚለውን አፍራሽ ቃል በራሱ ደፋርነት የጨመረው በ16ኛው መቶ ዓመት የተነሣው ጀርመናዊው ማርቲን ሉተር ነው::


👉 ሮሜ 3፡28 "በእምነት መዳን” በሚለው የእግዚአብሔር ቃል ላይ ብቻ የሚል ቃል በድፍረት የጨመረው በሰው መዳን ውስጥ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን፣ የመጽናትንና የተጋድሎን አስፈላጊነት ሁሉ ከንቱ ለማድረግና እንዲሁ "ድኛለሁ" እያሉ በመፎከር እንዳሻቸው ኃጢአትን ለመሥራት ለራሳቸው ይለፍ ለመስጠት የፈጠሩት ሰፊ መንገድ ነው፡፡

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ጥቅምት 14/2017 #ፃድቁ_አባታችን_አቡነ_አረጋዊ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ፃድቁ አባታችን #አቡነ_አረጋዊ ከዚህ አለም ለተሠወሩበት አመታዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉በሃገራችን ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ እኒህ ፃድቅ ናቸው የተወለዱት በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ ኣካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው #ንጉሥ_ይስሐቅና_ቅድስት_እድና ይባላሉ የተለወለዱበት አካባቢም ሮም ነው

👉ስማቸው ብዙ ዓይነት ነው ወላጆቻቸው #ዘሚካኤል ሲሏቸው በበርሃ ገብረ አምላክ ተብለዋል በኢትዮዽያ ደግሞ #አረጋዊ ይባላሉ አቡነ አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ

👉በዚያም በገዳመ ዳውናስ (ግብጽ) የታላቁ ቅዱስ ዻኩሚስ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል ከመነኮሱ ከዓመታት በኋላም ወደ ሃገራቸው ሮም ተመልሰው በማስተማር 7 ያህል #የቤተ_መንግስት ሰዎችን ወደ ምናኔ ማርከዋል

👉የት ልሒድ ብለው ሲያስቡም #ቅዱስ_መልአክ በክንፉ ጭኖ ወስዶ ኢትዮጵያን አሳያቸው ተመልሰውም ለ8 ባልንጀሮቻቸው ሃገርስ ባሳየሁዋችሁ ሐዋርያ ሳያስተምራት በሕጉ በሥርዓቱ ፀንታ የምትኖር ብለው ከ8ቱ ጋር ወደ ኢትዮዽያ መጡ

👉በዚህ ጊዜም እናታቸው ቅድስት እድና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ ወደ ሃገራችን የመጡ በ470ዎቹ አካባቢ ሲሆን #አልዓሜዳ በክብር ተቀብሏቸዋል በቤተ ቀጢን (አክሱም) ተቀምጠውም መጻሕፍትን እየተረጐሙ ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል

👉ለሥራ በተለያዩ ጊዜም #አቡነ_አረጋዊ በዓት ፍለጋ ብዙ ደክመዋል በመጨረሻ ግን #ደብረ_ዳሞን (ደብረ ሃሌ ሉያን) አይተው ወደዷት የሚወጡበት ቢያጡም ጅራቱ 60 ክንድ የሚያህል ዘንዶ ተሸክሞ ከላይ አድርሷቸዋል

👉እንደ ወጡም "ሃሌ ሉያ ለአብ፣ ሃሌ ሉያ ለወልድ፣ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ" ብለው ቢያመሰግኑ ከሰማይ ሕብስት ወርዶላቸው ተመግበዋል በዚህም ቦታዋ #ደብረ_ሃሌ_ሉያ ተብላለች ፃድቁ ቦታውን ከገደሙ በኋላ ከተለያየ ቦታ መጥተው 6ሺ ያህል ሰዎች በእጃቸው መንኩሰዋል

👉ምናኔን በማስፋፋታቸውና ሥርዓቱን በማስተማራቸውም የኢትዮጵያ መነኮሳት አባት ተብለዉ ይጠራሉ #አቡነ_አረጋዊ በሕይወታቸው ከተጋድሎ ባሻገር በወንጌል አገልግሎትና መጻሕፍትን በማዘጋጀትም ደክመዋል

👉 #ቅዱስ_ያሬድና አፄ ገብረ መስቀልም ወዳጆቻቸው ነበሩ በተራራው ግርጌ ያለችውን ኪዳነ ምሕረትን ለሴቶች ሲገድሟት ቀዳሚዋ መነኮስ እናታቸው #ንግስት_እድና ሁናለች

👉ፃድቁ ንጹሕ ሕይወታቸውን ፈፅመው በተወለዱ በ99 ዓመታቸው በዚህ ቀን በገዳሙ በስተምሥራቅ አካባቢ ተሰውረው #ብሔረ_ሕያዋን ገብተዋል ጌታም 15 ትውልድን የሚያስምር #የምሕረት_ቃል_ኪዳን ሰጥቷቸዋል ረድኤት በረከታቸው ይደርብን

👉ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል ፃድቅን በፃድቅ ስም የሚቀበል #የፃድቁን_ዋጋ_ይወስዳል ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላቹሃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም ማቴ.10፥41

👉የፃድቁ አባታችን #አቡነ_አረጋዊ ምልጃና ፀሎት ቃል ኪዳን ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ቅዱስ ቄርሎስ

ወዳጄ

በተለይም ደግሞ የክፉዎች መናፍቃንን ጉባኤዎች ተጸየፋቸው፣ ከእነርሱ ጋር ኅብረት እንዳይኖርህ ተጠንቀቅ፡፡

በማንኛውም መንገድ ቢሆን በጾም፣ በጸሎት፣ በምጽዋት፣ የእግዚአብሔርን ቅዱስ ቃል በማንበብ ነፍስህን ንጹሕ እንድትሆን አድርጋት

በሥጋ ትኖርበት ዘንድ በተሰጠህ በቀሪው ዕድሜህ በኦርቶዶክሳዊ ነገረ ሃይማኖትና በማስተዋል በመኖር ከጥምቀት የሚገኘውን መዳን ታገኝ ዘንድ

እግዚአብሔር ከሰማያውያን ሠራዊት ጋር አንድ አድርጎ ይደምርህና ይቆጥርህ ዘንድ፣ በዚህም በኢየሱስ ክርስቶስ ለሰማያዊ የክብር አክሊል የበቃህ ትሆን ዘንድ

ለእርሱ ለመድኃኔዓለም ክብርና ምስጋና ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡”

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

☞ወር በገባ በ13 የአቡነ ዮሐንስ (ዘደብረ ቢዘን) ወርሐዊ መታሰቢያ በዓል ነው፡፡
]☞እኚህ ጻድቅ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ በጥቅምት 14 ቀን ተወለዱ።
ሀገራቸው ትግራይ አድዋ አውራጃ አህሳአ ልዩ ቀበሌ እንዳ መንደር
ይባላል።
☞አቡነ ዮሐንስ የአቡነ ፊልጶስ ዘደብረ ቢዘን ደቀመዝሙር ሲሆኑ፣አቡነ ፊልጶስ
ሲያርፉ በሳቸው ተተክው ደብረ ቢዘን ገዳምን በአበምኔትነት አስተዳድረዋል።
☞እንደ ነቢየ እግዚአብሔር ደመናን ዝናም እንዳይሰጥ የለጎሙ የከለከሉ
ስለሆኑ "ለጓሜ ደመና" በመባል ይታወቃሉ።
ነቢዩ ኤልሳዕ በመንፈስ ቅዱስ ሁሉን እንደሚያውቅ ሁሉ አቡነ ዮሐንስም
ሰው በልቡ የሚያስበውን ያውቁ ነበር።
☞አቡነ ዮሐንስ በተወለዱበት ሀገር ትግራይ በአህሳአ በስማቸው የተገደመ
''እንዳ አቡነ ዮሐንስ ገዳም" ፣ዛሬ ደብር ነው።
አቡነ ዮሐንስ በመነኮሱበትና ባገለገሉበት በደብረ ቢዘን ገዳም በኅዳር 13
ቀን አርፈው ተቀብረዋል።
☞""አቡነ ዮሐንስ ዘአስገዶም"" በመባልም ይጠራሉ።
☞በስማቸው የተሰሩ 5 አብያ ተክርስቲያናት አሉ
አምላካችን እግዚአብሔር ስለ ጻድቁ ስለ አቡነ
ዮሐንስ ዘደብረ ቢዘን
ብሎ ከዘመኑ መቅሰፍትና ጥፋት ይሠውረን፡፡
☞(ገድለ አበው ቅዱሳን ዘደብረ ቢዘን)
+ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ
+12_1-2017

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Try Answer.AI now! Take a photo of any problem and get an instant answer with AI. Plus, you can ask AI any other questions too! Download through my referral link to get 15 free extra uses. Don't miss out, give it a try today!
https://answerai.page.link/BgDke9txgdBxA3pJ7

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

ይህ ሰውነታችን እንኳ የዕለት ምግብ ያስፈልገዋል፣ ነፍሳችንም እንዲሁ፤ ይልቁንም ነፍሳችን የበለጠ ያስፈልጋታል፡፡

ነፍሳችን

በየዕለቱ የሚያስፈልጋትን ምግብ ካላገኘች ግን ደካማና ክፉ እየሆነች ትሄዳለች፡፡ ስለሆነም እየጠፋችና እየኮሰመነች፣ መራራም እየሆነች ስትሄድ ዝም ብለን አንያት፡፡

በየቀኑ ብዙ የሚያቆስሉ ነገሮችንና የሚያደሙ ፍላጻዎችን ትቀበላለች፤ በመመኘት፣ በመቆጣት፣ በስንፍና፣ በመንቀፍ፣ በብቀላ፣ በቅናት፣ በእነዚህ ሁሉ ትቆስላለች፡፡

✅ ስለዚህም

ለእነዚህ ቁስሎች የሚሆኑ መድኃኒቶችን ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው፤ ለዚህም ምጽዋት በእያንዳንዱ ቁስል ላይ ሁሉ ሊደረግ የሚችል ታላቅ ፈዋሽነት ያለው መድኃኒት ነው፡፡

“ካላችሁ ነገር ምጽዋት ስጡ፣ እነሆም ሁሉ ንጹሕ ይሆንላችኋል" ይላልና፡፡ ሉቃ. 11፡41

👉 ስግብግብነት ሳይሆን ምጽዋት ስጡ፣ ከስግብግብነት የሚመጣን ነገር ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ ብትሰጠውም የሚጠቅመው ነገር የለም፡፡

👉 ምጽዋት የሚባለው ከማንኛውም ግፍና ዓመፃ ነጻ የሆነ ነገር ነው፡፡

እንዲህ ያለው ምጽዋት ሁሉንም ነገር ንጹሕ ያደርገዋል፡፡

እንዲህ ያለው ምጽዋት ነፍስን ብርህት ያደርጋታል፣ በጸጋ እንድታንጸባርቅና ጽንዕት እንድትሆን ያደርጋታል፡፡''

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ❤️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ቅዱስ አትናቴዎስ

ቃል ፍጡር ቢሆን ኖሮ ይህ [የእኛ መዳን) ተፈጻሚ ሊሆን አይችልም ነበር፣ ፍጡር ቢሆን ኖሮ ዲያብሎስም ራሱ ፍጡር ስለሆነ ትግሉን ይቀጥልበት ነበር፤ ሰውም በሁለቱ መካከል ሆኖ ከእግዚአብሔር ጋር የሚዋሐድበትና ከፍርሃት ነጻ የሚወጣበት መንገድ አጥቶ ሕይወቱ ሁል ጊዜ በአደጋ ውስጥና በጥፋት ላይ እንደ ሆነ ይቀጥል ነበር፡፡

ስለዚህም በእውነት የእኛ የሆነውን ሰውነትና ባሕርይ ነሣ (ገንዘብ አደረገ)፡ ይህም ባሕርያችንን እርሱ ፈጣሪውና አስገኚው እንደ መሆኑ በእርሱ በራሱ ያከብረው ዘንድ፡ በዚህም በእርሱ መሪነትና አርእያነት ወደ መንግሥተ ሰማያት ያገባን ዘንድ ነው::'™


የሰው ባሕርይ (ትስብእት) የተዋሐደው ከፍጡር ጋር ቢሆን ኖሮ ወይም ወልደ እግዚአብሔር እውነተኛ እግዚአብሔር ባይሆን ኖሮ የእኛ ባሕርይ የጸጋ አምላክነትን አያገኝም ነበር፣ የእኛን ሥጋ የለበሰው የእርሱ [የእግዚአብሔር] እውነተኛና የባሕርይ ልጁ ባይሆን ኖሮ ሰው ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ከፍ ከፍ ሊልና ሊቀርብ አይችልም ነበር፡፡ (ትምህርት በእንተ አርዮሳውያን፡ ትምህርት 2 ቁ. 43)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ፓስፖርት ለማውጣት 5 እና 6 ወር መጠበቅ ቀር በ 1 ወር ፓስፖርት እናደርሳለን  አገልግሎት ፈላጊዎች በሙሉ
〰〰〰〰〰〰〰〰
+251969030123
   0969030123
❶. አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት
- ❖ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ
- ❖ የልደት ካርድ
- ❖ ስልክ ቁጥር

❷. ለማሳደስ
-❖ ጉርድ ፎቶግራፍ
-❖ ፓስፖርት ኮፒ
-❖ ስልክ ቁጥር

❸. የጠፋ / የተሰረቀ ለማውጣት
-❖ የቀበሌ መታወቂያ
-❖ ጉርድ ፎቶግራፍ
-❖ የፖሊስ ማስረጃ ደብዳቤ
-❖ ስልክ ቁጥር

❹. ከ18 ዓመት በታች
-❖ የወላጅ መታወቂያ
-❖ የልጅ የልደት ካርድ
-❖ ስልክ ቁጥር

❺. እድሜ ለማስተካከል
-❖ የልደት ካርድ
-❖ ጉርድ ፎቶግራፍ
-❖ ፓስፖርት ኮፒ
-❖ ስልክ ቁጥር

❻. ስም ለመቀየር ውይም ለማስተካከል
-❖ ጉርድ ፎቶግራፍ
-❖ ፓስፖርት ኮፒ
-❖ የፍርድ ቤት ወረቀት
-❖ ስልክ ቁጥር
Ethiopianpassport
0969030123
+251969030123

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ቅዱስ አግናጥዮስ፣ መልእክት ኀበ ሰብአ ጥራልያን፣ ምዕ. 10

👉የማምነውና ተስፋ የማደርገው በምትሐት ወይም በማስመሰል ሳይሆን ስለ እኔ በእውነት ሰው በሆነውና በሞተው በኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡

👉ሐሰት የሆነ ነገር ለእውነት አስጸያፊ ነውና፡፡ ስለሆነም የማምነው ድንግል ማርያም የፀነሰችውና የወለደችው እግዚአብሔር ቃል የተዋሐደውን ሥግው ቃልን ነው፡፡

👉 የእግዚአብሔር ቃልም የእኛን ባሕርይ ገንዘቡ አድርጎ በእውነት ከድንግል ማርያም ተወልዷል፡፡

👉ሰዎችን ሁሉ በማኅፀን የሚፈጥረውና የሚቀርጸው እርሱ ራሱ ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ በድንግልና በማኀፀኗ ተፀንሶ ኖሯልና፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Selamleki tselot yemtchilu esti tsafulign

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ማኅሌተ_ጽጌ

#የፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_42ኛ_ዓመት_የምሥረታ_በዓል

#ፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሰንበት_ትምህርት_ቤት
#ፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሚዲያ

Follow us on
👉 /channel/fre_amde_haymanot_media
👉 http://linktr.ee/fre_amde_haymanot_media

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ከመፀለያችን በፊት ልናደርግ አቸው የሚገቡ ነገሮች

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

ቅዱስ አትናቴዎስ

ሐዋርያዊ ይህን መሠረታዊ ጉዳይ በአርዮሳውያን ላይ በጻፈው ጥልቅና ሰፊ ትምህርቱ ላይ እንዲህ ሲል ያብራራዋል-

ቃል ፍጡር ቢሆን ኖሮ ይህ [የእኛ መዳን] ተፈጻሚ ሊሆን አይችልም ነበር፤ ፍጡር ቢሆን ኖሮ ዲያብሎስም ራሱ ፍጡር ስለሆነ ትግሉን ይቀጥልበት ነበር፤ ሰውም በሁለቱ መካከል ሆኖ ከእግዚአብሔር ጋር የሚዋሐድበትና ከፍርሃት ነጻ የሚወጣበት መንገድ አጥቶ ሕይወቱ ሁል ጊዜ በአደጋ ውስጥና በጥፋት ላይ እንደ ሆነ ይቀጥል ነበር፡፡

ስለዚህም በእውነት የእኛ የሆነውን ሰውነትና ባሕርይ ነሣ (ገንዘብ አደረገ)፡ ይህም ባሕርያችንን እርሱ ፈጣሪውና አስገኚው እንደ መሆኑ በእርሱ በራሱ ያከብረው ዘንድ፣ በዚህም በእርሱ መሪነትና አርአያነት ወደ መንግሥተ ሰማያት ያገባን ዘንድ ነው::'™ የሰው ባሕርይ (ትስብእት) የተዋሐደው ከፍጡር ጋር ቢሆን ኖሮ፣ ወይም ወልደ እግዚአብሔር እውነተኛ እግዚአብሔር ባይሆን ኖሮ የእኛ ባሕርይ የጸጋ አምላክነትን አያገኝም ነበር፤ የእኛን ሥጋ የለበሰው የእርሱ (የእግዚአብሔር] እውነተኛና የባሕርይ ልጁ ባይሆን ኖሮ ሰው ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ከፍ ከፍ ሊልና ሊቀርብ አይችልም ነበር፡፡ (ትምህርት በእንተ አርዮሳውያን፣ ትምህርት 2፣ ቁ. 43)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

“አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤”
  — 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥5

Читать полностью…
Subscribe to a channel