kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

“ወጣትነህ ? “

ወጣት ነህን ወጣት በመሆንህ ገና ብዙ ዘመን አለኝ ዕድሜዬ ገና ነው ብለህ አትተማመን

ተለክቶ የታወቀ ቀሪ ጊዜ ያለህም አድርገህ አታስብ  ‹‹የጌታ ቀን ድንገት እንደ ሌባ በሌሊት ይመጣልና›› 1ኛ ተሰ5፤2

ስለዚህ ምክንያት የእድሜያችንን መጨረሻ አስቀድመን እንዳናውቀው አደረገ ከዛሬ ዕለት ጀምሮ በትጋት ዝግጅታችንን እንጀምር ዘንድ በለጋ ዕድሜያችን ሲቀጩ በየቀኑ አታይምን

ስለዚህም አንዱ ሲመክር እንዲህ ብሏል “ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ አትዘግይ ከዛሬ ነገ እመለሳለሁ እያልህ አትቁጠር” ሲራ 5፤8

ዛሬ ነገ እመለሳለሁ ስትል አንድ ቀን ባቋራጭ እንዳትወሰድ

ስለዚህ ሽማግሌውም ይህንን ምክር ልብ ይበል ወጣቱም ይህንን ነገር ተረድቶ ተግባራዊ ያርግ ዘንድ ይሁን

ወይስ

በምቾትና ሁሉ ነገር ተሟልቶልህ የምትኖር እስካሁን ችግር የሚባል ደርሶብህ የማታውቅ ባለጸጋ ነህን

እንዲህም ቢሆን

ቅዱስ ጳውሎስ የሚለውን ስማው “ሰላምና ደኅንነት ነው ሲሉ ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል” 1ኛ ተሰ 5፤3

የዚህ ዓለም ነገሮች ሁሉ ተለዋዋጮች ናቸው እኛ በራሳችን የወደፊት ሕይወትና ሁኔታ ላይ ማዘዝ የምንችልና የሰለጠን አይደለንም

ነገር ግን በጽድቅ  ሥራ ላይ የሰለጠንን እንሁን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቸርና ሰውን ወዳጅ ነውና››

ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
❤️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/ebsseyifu
Seyifu on ebs

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ይምርሃነ ክርሰቶስም ሕዝቡን ይዞ ተነሳና አሁን ከቅዱስ ላሊበላ ቤተ መቅደሶች 42 ኪ,ሜ ርቀት ላይ ወደሚገኘውና ጥቁር አለታማ ተራራ ሥር ወዳለው የውግረ ስሂን ዋሻ አመራ። ሲደርስም ቦታው የሰዎች ይዞታ ሆኖ ስላገኘው እኔ ንጉሥ ነኝ ብሎ እነርሱን በግፍ ሳያስለቅቅ ካሳ ከፍሎ ስፍራውን ተረከባቸው። ውስጡ ግን ውሀ የቆመበት ባህርና ርኩሳት መናፍስት የሞሉት ስለነበር መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል መናፍስቱን አባሮ በባሕሩ ላይ ቤተ መቅደሱን እንዴት እንደሚያንጽ ገለጠለት። እርሱም በተነገረው መሠረት ለግንባታው የሚያስፈልጉ እቃዎችን ከኢየሩሳሌም አስመጥቶ ማነጽ ጀመረ። የውሀውን ክፍል እንጨት ረብርቦ አፈር እየበተነ ደለደለው። ሰዎች በባህር ላይ መሠራቱን እንዳይጠራጠሩም አነስተኞ መስኮትነገር አበጀለት። (በዚህችም አሁን ድረስ በክንድ ርቀት ያህል ከሥር ያለው ውሀ ይነካል።) ከበላዩም ስስ ሆነው የተፈለጡ ድንጋዮችን በኖራ እያቦካ በማያያዝ በእኩል መጠን እየገነባ በመሀከላቸው እንደ መቀነት የተጠረቡ እንጨቶችን በማስገባት አሳምሮ አነፀው። ውስጡንም በሦስት ቤተ መቅደሶች ከፈለው በየመስኮትና በየበሮቹም ላይ እንደ ዐይነ እርግብ ሆነው የተፈለፈሉ ሐረጎችን አደረገበት ጣሪያውንም በሰባቱ ሰማያት ምሳሌ ምስጢር ባላቸው የተለያዩ ቅርፆች አስዋበው።ይህን አድርጎ ሥራውን ከጨረሰ በኋላም የቅዱስ ገብርኤልን የእመቤታችንንና የቅዱስ ቂርቆስን ታቦታት አስገባበት። በድጋሚም ቤተ መንግሥቱን በዛው ዋሻ ውስጥ አነጸና በአስተዳደሩ ደሀ ሳይበድል ፍርድ ሳያጓድል ሕዝቡን በክህነቱም ንፁህ ሆኖ እግዚአብሔርን እያገለገለ ኖረ።በስተመጨረሻም ፍጥረት ሆኖ ከመሞት ሰው ሆኖ በመቃብር ከመዋል የሚቀር አይኖርምና ንጉሣችንና አባታችን ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስም

የእረፍት ዘመኑ ሲደርስ እግዚአብሔር አምላክ ቃል ኪዳኑን ለዘላለም እንደሚያፀናለት ነግሮት በዚህች በተባረከች #በጥቅምት_19 ቀን በክብር አሳረፈው።

መቃብሩንም አስቀድሞ እነደነገረው በዛው በተቀደሰ ዋሻ ውስጥ አደረገለት። እናም ዛሬ ድረስ ቦታው በክብር ተጠብቆ ይኖራል። ምእመናንም ቃል ኪዳኑን በማሰብ "ማረኝ ይምርሐ" እያሉ መቃብሩን ይዞራሉ። ያንን ከሰማይ የወረደለትን መስቀልም በቤተመቅደሱ የሚያገለግሉት ካህናት አባቶች ቦታውን ለመሳለም የሚመጣውን ሕዝበ ክርስቲያን በበዓል ቀን ይባርኩበታል፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_በርቶሎሜዎስና_ሚስቱ

ዳግመኛም በዚህች ቀን በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ቅዱስ በርቶሎሜዎስና ሚስቱ በሰማዕትነት አረፉ።

እሊህ ቅዱሳንም የግብጽ ምዕራብ ከሆነ ፍዩም ከሚባል አገር ናቸው ክርስቲያኖችም እንደሆኑ በመኰንኑ ዘንድ ወነጀሏቸው መኰንኑም ልኮ አስቀረባቸውና ስለ ሃይማኖት ጠየቃቸው እነርሱም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፊቱ ታመኑ።

መኰንኑም ጥልቅ ጒድጓድ እንዲቆፍሩላቸው በዚያም እንዲጨምሩአቸውና በሕይወታቸው እንዲደፍኑባቸው አዘዘ። መኰንኑም እንዳዘዘ አደረጉባቸው በዚህም ምስክርነታቸውን ፈጽመው የሰማዕትነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#የጳውሎስ_ሳምሳጢን_ውግዘት

በዚችም ቀን ስለ ጳውሎስ ሳምሳጢ በአንጾኪያ አገር የቤተ ክርስቲያን የአንድነት ስብሰባ ተደረገ። ይህ ጳውሎስም ከአንጾኪያ አገሮች በአንዲቱ አገር ኤጲስቆጶስነት በተሾመ ጊዜ ክፉ ዘርን ሰይጣን በልቡ ውስጥ ዘራበት አካላዊ ቃልን አካል እንደሌለ የክርስቶስም ጥንት መገኛው ከማርያም እንደሆነ እርሱም አለምን ያድንበት ዘንድ እግዚአብሔር የፈጠረው እንደሆነ ከመለኮትም ጋር ያልተዋሐደ በላዩ ወርዶ በእግዚአብሔር ፈቃድ አደረበት እንጂ ብሎ የሚያምን ሆነ በወልድም ቢሆን በመንፈስ ቅዱስም ቢሆን የሚያምን አልሆነም።

ስለዚህም ኤጲስቆጶሳት አንድነት ተሰበሰቡ የእስክንድርያ አባ ዲዮናስ የሮሜ አባ ዲዮናስዮስ እሊህ ሊቃነ ጳጳሳት ስለ እርጅናቸው ከዚያ ደርሰው ከእርሳቸው ጋር ሊሰበሰቡ አልቻሉም ነገር ግን መልእክትን ጻፉ።

የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዲዮናስም እንዲህ የሚል መልእክትን ጻፈ። የእግዚአብሔር ልጁም ቃሉም የሆነ ክርስቶስ በመለኮቱም ከእርሱ ጋር ትክክል የሆነ እርሱም ከሦስቱ አካላት አንዱ ወልድ ስለእኛ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለ ዘር ስጋንና ነፍስን ነሥቶ ፍጹም ሰው የሆነ በመለኮቱ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል ሲሆን እንደእኛ ፊጹም ሰው ሁኗል ከተዋሕዶውም በኋላ ያለ መለያየትና ያለ መቀላቀል ሁለቱ ባሕርያት አንድ ሁነዋል ከብሉይና ከሐዲስ መጻሕፍት ምስክሮችን ጠቅሶ እያስረዳ ጽፎ ይቺንም መልእክት ከሁለት ምሁራን ቀሳውስት ጋር ላካት።

በዚያንም ጊዜ አሥራ ሦስቱ ኤጲስቆጶሳትና እሊህ ሁለቱ ቀሳውስት ጉባኤ አድርገው ይህን ጳውሊ ሳምሳጢን አቅርበው የአባ ዲዮናስን መልእክት በፊቱ አነበቡ። ዳግመኛም ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጁም ቃሉም የሆነ የጌትነቱ ነጸብራቅ ነው የሚለውን የሐዋርያ ጳውሎስን ቃል በመጥቀስ እርሱ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በትክክልነት እንደሚኖር አስረዱት እርሱ ግን ቃላቸውን አልተቀበለም።

ከዚህም በኋላ በእርሱ ትምህርት የሚያምኑትን ሁሉ አው*ግዘው ከምእመናን ለይተው አሳደዱት። ለምእመናንም ሥርዓትን ሠሩ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዮሐንስ_ዘጸይለም

በዚችም ቀን የጸይለም አገር የከበረ አባት ዮሐንስ አረፈ። የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ከሀገሩ ታላላቆች ወገን ናቸው የአባቱም ስም አብርሃም የእናቱም ስም ሣራ ነው እነርሱም ልጆች ስለ ሌሏቸው ብዙ ዘመን ወደ እግዚአብሔር እየለመኑ ኖሩ።

በአንዲትም ዕለት ሁለት መነኰሳት ወደ እነርሱ እንግድነት መጡ እነርሱም በክብር ተቀብለው አሳደሩአቸው። እሊህ መነኰሳትም አብርሃምን ልጅ የለህምን አሉት እርሱም እንባውን እየአፈሰሰ አባቶቼ ልጅ የለኝም አሁንማ እኔ አረጀሁ የሚስቴም የልጅነቷ ወራት አለፈ ብሎ መለሰላቸው። እሊህ መነኰሳትም ስለ እርሳቸው ጸለዩላቸው ባርከዋቸውም ጎዳናቸውን ተጓዙ።

ከጥቂትም ቀን በኋላ ሳራ ፀነሰች ደስ የሚያሰኝም ልጅን ወለደች ስሙንም ዮሐንስ ብለው ሰየሙት በእርሱም ደስ አላቸው የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት እየአስተማሩ አሳደጉት።

ዐሥራ ሰባት ዓመትም በሆነው ጊዜ ወደ መምህሩ ቤት መነኰሳት መጡ ዮሐንስም ከእርሳቸው ጋር እንዲወስዱት ለመናቸው እነርሱም አባትህን እንፈራለንና እኛ አንወስድህም አሉት። መነኰሳቱም ወደቦታቸው እየሔዱ ሳሉ ወደ መረጠው ጎዳና ይመራው ዘንድ ዮሐንስ ተነሥቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ከመምህሩም ቤት ወጥቶ ሊደርስባቸው ወዶ መነኰሳቱን በኋላቸው ተከተላቸው ወደ ታላቅ ወንዝም ደረሰ ብቻውንም መሻገር ፈርቶ ቆመ ከዚያም ሳለ ዓረቦች ከግመሎቻቸው ጋር መጡ ያሻገሩትም ዘንድ ለመናቸው እነርሱም ከእርሳቸው ጋር አሻገሩት አንወስድህም ወደአሉት መነኰሳት ወደ ገዳማቸው በእግዚአብሔር ፈቃድ ደረሰ።

ከእርሳቸውም አንዱ አባ ስምዖን የሚባለው ዮሐንስን ወስዶ ደቀ መዝሙሩ አድርጎ ከሁለቱ ደቀ መዛሙርቱ ጋር አኖረው።

አባ ስምዖን የሚሞትበት ጊዜ እንደቀረበ በአወቀ ጊዜ ልጆቹን ጠርቶ ከሞትኩ በኋላ በእናንተ ላይ የሚሆነውን እግዚአብሔር ያሳየኝን እነግራችሁ ዘንድ ልጆቼ ኑ አላቸውና ከእናንተ አንዱን ጅብ ነጥቆ ይወስደዋል። ሁለተኛው ወደ ዓለም ተመልሶ ይባክናል። የሦስተኛው ግን ዜናው በዓለሙ ሁሉ ይሰማል አላቸው።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🌹 አቡነ ሰይፈ ሚካኤል በአገልግሎታቸው ለሚያምኑ እያጽናኑና እያበረቱ፣ ለማያምኑ ደግሞ አሳምነው እያጠመቁ እስከ ማዕርገ ክህነት አድርሰው ቤተ ክርስትያን ይሠሩላቸው ነበር፡፡ በስተመጨረሻ ቅዱስ አባታችን በብዙ ተጋድሎ ሐዋርያዊ ተልዕኮአቸውንና አገልግሎታቸውን ከፈጸሙ በኋላ ከእግዚአብሔር የምሕረት ቃልኪዳን ተቀብለው ጥቅምት 19 ቀን 1722 ዓ.ም በ96 ዓመታቸው ራሳቸው በመሠረቱም በገዳም ፃዕዳ ዓምባ ቅድስ ሥላሴ ዐርፈዋል፡፡

🌹 የአባታችን የአቡነ ሰይፈ ሚካኤልን መንገድ የተከተሉ የዚህ ገዳም መነኰሳትም በጸምና በጸሎት ተወስነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "ሑሩ ወመሐሩ" (ማቴ 28፡19) ባለው አምላካዊ ቃል መሠረት ሐዋርያዊ ተልኮአቸውን እየፈጸሙ ብዙ አብያተ ክርስቲያናን ከከረን እስከ ኦምሓጃር ከዛ አልፎም እስከ ከሰላ ሱዳን አንጸዋል፡፡ በፃዕዳ እምባ ሥላሴ ገዳም ሐምሌ 7 ቀን የሥሉስ ቅዱስ ዓመታዊ ክብረ በዓል እና የአቡነ ሰይፈ ሚካኤል በዓለ ዕረፍታቸው ጥቅምት 19 ቀን በደማቅ ሁኔታ ይከበራል፡፡ በእነዚህ ክብረ በዓላት ላይ በርካታ ምእመናን ከተለያዩ ቦታዎች በመምጣት ከበረከቱ ይሳተፋሉ፡፡ ከአባታችን የአቡነ ሰይፈ ሚካኤል እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን!። ምንጭ፦ ከገድላት አንደበት

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

ቅዱስ አትናቴዎስ

ሐዋርያዊ ይህን መሠረታዊ ጉዳይ በአርዮሳውያን ላይ በጻፈው ጥልቅና ሰፊ ትምህርቱ ላይ እንዲህ ሲል ያብራራዋል-

ቃል ፍጡር ቢሆን ኖሮ ይህ [የእኛ መዳን] ተፈጻሚ ሊሆን አይችልም ነበር፤ ፍጡር ቢሆን ኖሮ ዲያብሎስም ራሱ ፍጡር ስለሆነ ትግሉን ይቀጥልበት ነበር፤ ሰውም በሁለቱ መካከል ሆኖ ከእግዚአብሔር ጋር የሚዋሐድበትና ከፍርሃት ነጻ የሚወጣበት መንገድ አጥቶ ሕይወቱ ሁል ጊዜ በአደጋ ውስጥና በጥፋት ላይ እንደ ሆነ ይቀጥል ነበር፡፡

ስለዚህም በእውነት የእኛ የሆነውን ሰውነትና ባሕርይ ነሣ (ገንዘብ አደረገ)፡ ይህም ባሕርያችንን እርሱ ፈጣሪውና አስገኚው እንደ መሆኑ በእርሱ በራሱ ያከብረው ዘንድ፣ በዚህም በእርሱ መሪነትና አርአያነት ወደ መንግሥተ ሰማያት ያገባን ዘንድ ነው::'™ የሰው ባሕርይ (ትስብእት) የተዋሐደው ከፍጡር ጋር ቢሆን ኖሮ፣ ወይም ወልደ እግዚአብሔር እውነተኛ እግዚአብሔር ባይሆን ኖሮ የእኛ ባሕርይ የጸጋ አምላክነትን አያገኝም ነበር፤ የእኛን ሥጋ የለበሰው የእርሱ (የእግዚአብሔር] እውነተኛና የባሕርይ ልጁ ባይሆን ኖሮ ሰው ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ከፍ ከፍ ሊልና ሊቀርብ አይችልም ነበር፡፡ (ትምህርት በእንተ አርዮሳውያን፣ ትምህርት 2፣ ቁ. 43)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

(ቅዱስ አግናጥዮስ፣ መልእክት ኀበ ፊልጵስዮስ፣ ምዕ. 4)

እንዳለው

“ሰይጣን በአንዳንዶች መስቀሉን ይክዱ ዘንድ በእነርሱ ላይ ሥራውን ይሠራል

የጌታችንን ሕማማቱንና ሞቱን እንዲያፍሩበትና ምትሐት ነው እንዲሉ በውስጣቸው ይሠራባቸዋል

ከድንግል መወለዱንና ሥጋ መልበሱን፣ እንዲሁም የእኛን ባሕርይ ርኩስ እንደ ሆነ አድርጎ ይነቅፋል፡፡

ከአይሁድ ጋር ደግሞ ሰዎች መስቀሉን እንዲክዱ ቤተ ክርስቲያንን ይዋጋታል፤ ከአሕዛብ ጋር ደግሞ ድንግል ማርያምን ይነቅፋለ፣ ያክፋፋሉ፡ ክርስቶስ ከእርሷ ባሕርይዋን ገንዘቡ አድርጎ እንዳልተወለደ አድርገው ይናገራሉ፡፡

የክፋት ሁሉ መሪና ፍታውራሪ የሆነው ዲያብሎስ አሠራሩ ብዙ ዓይነት ነውና፣ እርሱ የሰዎች ፈታኝና አታላይ እንደ መሆኑ ሰዎችን በተለያዩ መንገዶች ከእውነት ይለያቸው ዘንድ ይፈትናቸዋል፡፡”

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ማኅሌተ_ጽጌ

#የፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_42ኛ_ዓመት_የምሥረታ_በዓል

#ፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሰንበት_ትምህርት_ቤት
#ፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሚዲያ

Follow us on
👉 /channel/fre_amde_haymanot_media
👉 http://linktr.ee/fre_amde_haymanot_media

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ

ደናግል ሆይ

የሰማያዊ ሕይወት አርኣያና አምሳል የሆነችው
የድንግል ማርያም ሕይወት ይኑራችሁ፡፡
እርስዋ ለክርስቶስ እናት ለመሆን
በምንም የምታንስ አልነበረችም'

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

መዓረጋተ ቅዱሳን

👉ንጽሐ ሥጋ
(ጽማሜ፣ ልባዌ፣ ጣዕመ ዝማሬ)
👉ንጽሐ ነፍስ
(አንብዕ፣ ኩነኔ፣ ፍቅር፣ ሑሰት)
👉ንጽሐ ልቡና
(ንጻሬ መላእክት፣ ተሠጥሞ ብርሀን፣ ከዊነ እሳት)

++++++++++++~++++++++++

ከጣዕመ ዝማሬ

የደረሰ አንድ ባሕታዊ ለብዙ ዘመናት ያህል “አቡነ ዘበሰማያት - አባታችን ሆይ” ብቻ እያለ ያንኑ ብቻ እየመላለሰ “ይትቀደስ ስምከ” ሳይል ኖረ።

መልአክ መጥቶ “ይትቀደስ ስምከ” በል እንጂ ቢለው

“ኧረ ጌታዬ፣ እኔስ አባታችን ሆይ የሚለው ኃይለ ቃል ምሥጢሩና ጣዕሙ በአፌ እንደ ስኳር እየሟሟ አልጠገበኝ ብሏል፣ እንዴት አድርጌ ወደፊት ልሂድ!” አለው ይባላል።

ለመጸለይ የምንሰንፍና አንድ ጊዜ የጸለይነውን ጸሎት ለመድገም የምንሰለች፣ ወይንም ደግሞ ቶሎ ቶሎ ንባቡን ጨርሰን ለመቀመጥ የምንቸኩል ከሆነ ምን ያህል ከጸጋ የራቅን መሆናችንን ልናውቅና አምላካችን በምሕረቱ እንዲጎበኘን አብዝተን መለመን እንዳለብን ልንረዳ ይገባል።

ቅዱሳንን ለዚህ ጸጋ ያደረሰ አምላክ እኛንም ሳንሰለች ለመጸለይና ለማመስገን እንድንችል ይርዳን!

ፍኖተ_ቅዱሳን

ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

👉“በእምነት መዳን˘ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ሲሆን “በእምነት ብቻ መዳን" የሚለው ግን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አይደለም፡፡ ይህ የፕሮቴስታንቶችና የልጆቻቸው የተሐድሶዎች የፈጠራ ትምህርት ነው፡፡

👉 መጽሐፍ ቅዱስ በእምነት ስለ መዳን እንጂ “በእምነት ብቻ ስለ መዳን አንድም ቦታ አይናገርም፡፡ 'ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቆጥራለንና በሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ላይ "በእምነት ብቻ እንዲጸድቅ” በማለት “ብቻ የሚለውን አፍራሽ ቃል በራሱ ደፋርነት የጨመረው በ16ኛው መቶ ዓመት የተነሣው ጀርመናዊው ማርቲን ሉተር ነው::


👉 ሮሜ 3፡28 "በእምነት መዳን” በሚለው የእግዚአብሔር ቃል ላይ ብቻ የሚል ቃል በድፍረት የጨመረው በሰው መዳን ውስጥ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን፣ የመጽናትንና የተጋድሎን አስፈላጊነት ሁሉ ከንቱ ለማድረግና እንዲሁ "ድኛለሁ" እያሉ በመፎከር እንዳሻቸው ኃጢአትን ለመሥራት ለራሳቸው ይለፍ ለመስጠት የፈጠሩት ሰፊ መንገድ ነው፡፡

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ጥቅምት 14/2017 #ፃድቁ_አባታችን_አቡነ_አረጋዊ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ፃድቁ አባታችን #አቡነ_አረጋዊ ከዚህ አለም ለተሠወሩበት አመታዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉በሃገራችን ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ እኒህ ፃድቅ ናቸው የተወለዱት በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ ኣካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው #ንጉሥ_ይስሐቅና_ቅድስት_እድና ይባላሉ የተለወለዱበት አካባቢም ሮም ነው

👉ስማቸው ብዙ ዓይነት ነው ወላጆቻቸው #ዘሚካኤል ሲሏቸው በበርሃ ገብረ አምላክ ተብለዋል በኢትዮዽያ ደግሞ #አረጋዊ ይባላሉ አቡነ አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ

👉በዚያም በገዳመ ዳውናስ (ግብጽ) የታላቁ ቅዱስ ዻኩሚስ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል ከመነኮሱ ከዓመታት በኋላም ወደ ሃገራቸው ሮም ተመልሰው በማስተማር 7 ያህል #የቤተ_መንግስት ሰዎችን ወደ ምናኔ ማርከዋል

👉የት ልሒድ ብለው ሲያስቡም #ቅዱስ_መልአክ በክንፉ ጭኖ ወስዶ ኢትዮጵያን አሳያቸው ተመልሰውም ለ8 ባልንጀሮቻቸው ሃገርስ ባሳየሁዋችሁ ሐዋርያ ሳያስተምራት በሕጉ በሥርዓቱ ፀንታ የምትኖር ብለው ከ8ቱ ጋር ወደ ኢትዮዽያ መጡ

👉በዚህ ጊዜም እናታቸው ቅድስት እድና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ ወደ ሃገራችን የመጡ በ470ዎቹ አካባቢ ሲሆን #አልዓሜዳ በክብር ተቀብሏቸዋል በቤተ ቀጢን (አክሱም) ተቀምጠውም መጻሕፍትን እየተረጐሙ ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል

👉ለሥራ በተለያዩ ጊዜም #አቡነ_አረጋዊ በዓት ፍለጋ ብዙ ደክመዋል በመጨረሻ ግን #ደብረ_ዳሞን (ደብረ ሃሌ ሉያን) አይተው ወደዷት የሚወጡበት ቢያጡም ጅራቱ 60 ክንድ የሚያህል ዘንዶ ተሸክሞ ከላይ አድርሷቸዋል

👉እንደ ወጡም "ሃሌ ሉያ ለአብ፣ ሃሌ ሉያ ለወልድ፣ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ" ብለው ቢያመሰግኑ ከሰማይ ሕብስት ወርዶላቸው ተመግበዋል በዚህም ቦታዋ #ደብረ_ሃሌ_ሉያ ተብላለች ፃድቁ ቦታውን ከገደሙ በኋላ ከተለያየ ቦታ መጥተው 6ሺ ያህል ሰዎች በእጃቸው መንኩሰዋል

👉ምናኔን በማስፋፋታቸውና ሥርዓቱን በማስተማራቸውም የኢትዮጵያ መነኮሳት አባት ተብለዉ ይጠራሉ #አቡነ_አረጋዊ በሕይወታቸው ከተጋድሎ ባሻገር በወንጌል አገልግሎትና መጻሕፍትን በማዘጋጀትም ደክመዋል

👉 #ቅዱስ_ያሬድና አፄ ገብረ መስቀልም ወዳጆቻቸው ነበሩ በተራራው ግርጌ ያለችውን ኪዳነ ምሕረትን ለሴቶች ሲገድሟት ቀዳሚዋ መነኮስ እናታቸው #ንግስት_እድና ሁናለች

👉ፃድቁ ንጹሕ ሕይወታቸውን ፈፅመው በተወለዱ በ99 ዓመታቸው በዚህ ቀን በገዳሙ በስተምሥራቅ አካባቢ ተሰውረው #ብሔረ_ሕያዋን ገብተዋል ጌታም 15 ትውልድን የሚያስምር #የምሕረት_ቃል_ኪዳን ሰጥቷቸዋል ረድኤት በረከታቸው ይደርብን

👉ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል ፃድቅን በፃድቅ ስም የሚቀበል #የፃድቁን_ዋጋ_ይወስዳል ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላቹሃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም ማቴ.10፥41

👉የፃድቁ አባታችን #አቡነ_አረጋዊ ምልጃና ፀሎት ቃል ኪዳን ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ቅዱስ ቄርሎስ

ወዳጄ

በተለይም ደግሞ የክፉዎች መናፍቃንን ጉባኤዎች ተጸየፋቸው፣ ከእነርሱ ጋር ኅብረት እንዳይኖርህ ተጠንቀቅ፡፡

በማንኛውም መንገድ ቢሆን በጾም፣ በጸሎት፣ በምጽዋት፣ የእግዚአብሔርን ቅዱስ ቃል በማንበብ ነፍስህን ንጹሕ እንድትሆን አድርጋት

በሥጋ ትኖርበት ዘንድ በተሰጠህ በቀሪው ዕድሜህ በኦርቶዶክሳዊ ነገረ ሃይማኖትና በማስተዋል በመኖር ከጥምቀት የሚገኘውን መዳን ታገኝ ዘንድ

እግዚአብሔር ከሰማያውያን ሠራዊት ጋር አንድ አድርጎ ይደምርህና ይቆጥርህ ዘንድ፣ በዚህም በኢየሱስ ክርስቶስ ለሰማያዊ የክብር አክሊል የበቃህ ትሆን ዘንድ

ለእርሱ ለመድኃኔዓለም ክብርና ምስጋና ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡”

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

☞ወር በገባ በ13 የአቡነ ዮሐንስ (ዘደብረ ቢዘን) ወርሐዊ መታሰቢያ በዓል ነው፡፡
]☞እኚህ ጻድቅ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ በጥቅምት 14 ቀን ተወለዱ።
ሀገራቸው ትግራይ አድዋ አውራጃ አህሳአ ልዩ ቀበሌ እንዳ መንደር
ይባላል።
☞አቡነ ዮሐንስ የአቡነ ፊልጶስ ዘደብረ ቢዘን ደቀመዝሙር ሲሆኑ፣አቡነ ፊልጶስ
ሲያርፉ በሳቸው ተተክው ደብረ ቢዘን ገዳምን በአበምኔትነት አስተዳድረዋል።
☞እንደ ነቢየ እግዚአብሔር ደመናን ዝናም እንዳይሰጥ የለጎሙ የከለከሉ
ስለሆኑ "ለጓሜ ደመና" በመባል ይታወቃሉ።
ነቢዩ ኤልሳዕ በመንፈስ ቅዱስ ሁሉን እንደሚያውቅ ሁሉ አቡነ ዮሐንስም
ሰው በልቡ የሚያስበውን ያውቁ ነበር።
☞አቡነ ዮሐንስ በተወለዱበት ሀገር ትግራይ በአህሳአ በስማቸው የተገደመ
''እንዳ አቡነ ዮሐንስ ገዳም" ፣ዛሬ ደብር ነው።
አቡነ ዮሐንስ በመነኮሱበትና ባገለገሉበት በደብረ ቢዘን ገዳም በኅዳር 13
ቀን አርፈው ተቀብረዋል።
☞""አቡነ ዮሐንስ ዘአስገዶም"" በመባልም ይጠራሉ።
☞በስማቸው የተሰሩ 5 አብያ ተክርስቲያናት አሉ
አምላካችን እግዚአብሔር ስለ ጻድቁ ስለ አቡነ
ዮሐንስ ዘደብረ ቢዘን
ብሎ ከዘመኑ መቅሰፍትና ጥፋት ይሠውረን፡፡
☞(ገድለ አበው ቅዱሳን ዘደብረ ቢዘን)
+ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ
+12_1-2017

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Try Answer.AI now! Take a photo of any problem and get an instant answer with AI. Plus, you can ask AI any other questions too! Download through my referral link to get 15 free extra uses. Don't miss out, give it a try today!
https://answerai.page.link/BgDke9txgdBxA3pJ7

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

ይህ ሰውነታችን እንኳ የዕለት ምግብ ያስፈልገዋል፣ ነፍሳችንም እንዲሁ፤ ይልቁንም ነፍሳችን የበለጠ ያስፈልጋታል፡፡

ነፍሳችን

በየዕለቱ የሚያስፈልጋትን ምግብ ካላገኘች ግን ደካማና ክፉ እየሆነች ትሄዳለች፡፡ ስለሆነም እየጠፋችና እየኮሰመነች፣ መራራም እየሆነች ስትሄድ ዝም ብለን አንያት፡፡

በየቀኑ ብዙ የሚያቆስሉ ነገሮችንና የሚያደሙ ፍላጻዎችን ትቀበላለች፤ በመመኘት፣ በመቆጣት፣ በስንፍና፣ በመንቀፍ፣ በብቀላ፣ በቅናት፣ በእነዚህ ሁሉ ትቆስላለች፡፡

✅ ስለዚህም

ለእነዚህ ቁስሎች የሚሆኑ መድኃኒቶችን ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው፤ ለዚህም ምጽዋት በእያንዳንዱ ቁስል ላይ ሁሉ ሊደረግ የሚችል ታላቅ ፈዋሽነት ያለው መድኃኒት ነው፡፡

“ካላችሁ ነገር ምጽዋት ስጡ፣ እነሆም ሁሉ ንጹሕ ይሆንላችኋል" ይላልና፡፡ ሉቃ. 11፡41

👉 ስግብግብነት ሳይሆን ምጽዋት ስጡ፣ ከስግብግብነት የሚመጣን ነገር ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ ብትሰጠውም የሚጠቅመው ነገር የለም፡፡

👉 ምጽዋት የሚባለው ከማንኛውም ግፍና ዓመፃ ነጻ የሆነ ነገር ነው፡፡

እንዲህ ያለው ምጽዋት ሁሉንም ነገር ንጹሕ ያደርገዋል፡፡

እንዲህ ያለው ምጽዋት ነፍስን ብርህት ያደርጋታል፣ በጸጋ እንድታንጸባርቅና ጽንዕት እንድትሆን ያደርጋታል፡፡''

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ❤️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ድንግል ሆይ

ቤተ ክርስቲያን ታመሰግንሻለች!!!

"ያዘነች ስትሆን በልጅሽ በወዳጅሽ ትንሣኤ የተጽናናችው፡፡

የተዋረደች ስትሆን በድንግልናሽ ቡቃያ መውጣት ከፍ ከፍ ያለችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታመሰግንሻለች፡፡

በዕለተ ዓርብ ከልጅሽ ቀኝ በፈሰሰው ውሀ ተጠምቃ የውግታቱን ደም ተቀብታ ቅድስት ቤተክርስቲያን ታመሰግንሻለች።

የልዑል እግዚአብሔር በግ የተባለ ልጅሽ ዐማኑኤልየተሞሸረባት መርዓዊ ሰማያዊ የተባለባት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታመሰግንሻለች"

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ❤️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ከዚህም በኋላ አረጋዊው ስምዖን ወደ ዮሐንስ ተመልክቶ ልጄ ሆይ በክርስቶስ ፍቅር ጽና ለብዙዎች አባት ልትሆን እርሱ መርጦሃልና አለው። አባ ስምዖንም ከአረፈ በኋላ በሦስተኛው ቀን አንዱ ረድዕ ወደ ዓለም ተመልሶ ሚስት አገባ ሁለተኛው ወዴት እንደ ደረሰ አልታወቀም። አባ ዮሐንስም ብቻውን ቀረ ፈጽሞ አዘነ በልቡ እንዲህ አለ የጓደኞቼን ወሬ እጠይቅ ዘንድ ከገዳም ወጥቼ ልውረድ ይህንንም ብሎ ከገዳሙ ወጥቶ ሲወርድ የጸይለም ጦረኞች ተቀበሉት ደም ግባታቸው ከሚአምር ከሁለት ሴቶች ጋር አሥረው ወሰዱት በጒዞም ላይ እያሉ ለእንስሶቻቸውና ለራሳቸው የሚጠጡት ውኃ አጡ። አባ ዮሐንስም ከዚህ በረሀ ውስጥ ፈጣሪዬ ውኃን ቢአወጣላችሁ ትለቁኛላችሁን አላቸው አዎን አሉት። በዚያንም ጊዜ አባ ዮሐንስ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ብሎ በምድር ላይ አማተበ ውኃም ፈልቆላቸው ጠጥተው ረኩ።

የከበረ ዮሐንስም ቃል ኪዳን እንደ ገባችሁልኝ አሰናብቱኝ አላቸው እነርሱም እንዳንተ ያለ አናገኝምና ከቶ አንለቅህም አሉት። ይህንንም ብለው ወደ አገራቸው ወደ ጸይለም አደረሱት።

በዚያንም ወራት በጸይለም አገር ታላቅ መቅሠፍት ወረደ የአበ ዮሐንስም ጌታው ከቤተሰቦቹ ሁሉና ከልጆቹ ጋር ሞተ ሚስቱም ከአንዲት ልጅዋ ጋር ብቻዋን ቀረች። የጌታውም ሚስት ቅዱስ ዮሐንስን መሠርይ እንደ ሆነ አሰበች በማደሪያውም ውስጥ እያለ ሊአቃጥሉት እሳት ለቀቁበት እግዚአብሔርም ከእሳት ውስጥ በደኅና አወጣው የጸይለም ሰዎችም ይህን ድንቅ ተአምር አይተው ሴቶችም ወንዶችም በጌታችን አምነው በእጆቹ ተጠመቁ።

ከዚያም ተነሥቶ ወደ ሌላ አገር ሔደ። የአገር ሰዎችም ዛፎችን ሲያመልኩ አግኝቷቸው እርሱም ከክህደታቸው እንዲመለሱ አስተማራቸው ባልሰሙትም ጊዜ ምሳር ይዞ በሌሊት ወደ ዛፎቹ መካከል ገብቶ ክብር ይግባውና ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ምሳሩንም አንሥቶ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እቆርጣችኋለሁ አለ። ወዲያውኑ በአንዲት ምት ዐሥር ሽህ ዛፎች ወደቁ የሀገር ሰዎችም ይህን ድንቅ ተአምር አይተው ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ሁሉም ከሴቶችና ከልጆች ጋር ተጠመቁ።

ከዚያም ዳግመኛ ወደ ሌላ አገር ሔደ ሰዎችንም እሳትን ሲያመልኩ አገኛቸው እርሱም ይህን ደንቊርናቸውን ይተዉ ዘንድ አስተማራቸው ገሠጻቸውም እነርሱም በእርሱ ላይ ተቆጥተው ከእሳት ጨመሩት። እርሱም በደኅና ወጣ ሦስት ጊዜም ጨምረውት በደኅና ወጣ ውኃቸውንም ደም አደረገባቸው የሚጠጡትም አጥተው በተጨነቁ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ሁሉም አመኑ። አራት መቶ ሽህ ሰዎችም በእጁ ተጠመቁ ቤተክርስቲያንም ሠራላቸው አስተምሮም በቀናች ሃይማኖት አጸናቸው ቁጥር የሌላቸው ድንቆች ተአምራትንም አደረገ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም በፍቅር አረፈ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ጥቅምት_19

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት አስራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ደግ ንጉሥ #ቅዱስ_ይምርሃነ_ክርስቶስስ እረፍቱ ነው፣ #ቅዱስ_በርቶሎሜዎስና_ሚስቱ በሰማዕትነት አረፉ፣ ስለ #ጳውሎስ_ሳምሳጢ በአንጾኪያ አገር የቤተ ክርስቲያን የአንድነት ስብሰባ ተደረገ፣ የጸይለም አገር የከበረ አባት #ቅዱስ_ዮሐንስ አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ይምርሃነ_ክርስቶስ

ጥቅምት አስራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ደግ ንጉሥ፣ ፃድቅ ካህን፣ቤተ መቅደሱን በባህር ላይ ያነፀ መሀንዲስ ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስስ
እረፍቱ ነው።

ልክ እንደ አቡነ ተክለሃይማኖትና እንደነ አቡነ ዜና ማርቆስ እርሱም ሲወለድ ወደ ምሥራቅ ዞሮ አምላኩን ያመሰገነ ሲሆን ቤቱም በብርሃን ተሞልቶ ታይቶ አዋላጆቹን ሁሉ አስገርሞ ነበር፡፡ ገና በእናቱ ማህፀን ሆኖ አጎቱ ጠንጠውድም በንግሥና ላይ ሳለ "ከአንተ በኋላ የሚነግሠው ይምርሃነ ክርስቶስ የሚባል የወንድምህ ልጅ ነው" የሚል ንግርት ይሰማ ነበርና ‹‹ይምርሃነ ክርስቶስ›› መወለዱን ሲያውቅ ‹‹የወንድሜን ልጅ ዐየው ዘንድ አምጡልኝ›› ብሎ ላከ፡፡ ባየውም ጊዜ ደም ግባቱ እጅግ ያምር ስለነበር ‹‹ይህስ መንግሥቴን ይውረስ፣ በእውነት ልጄ ነው›› ብሎ ባረከው፡፡

ከእርሱ ጋር ስምንት ቀን ተቀምጦ በወለዳቸው ልጆቹ መካከል ሆኖ ሲጫወት በተመለከተው ጊዜ ግን በልቡ ሰይጣን አደረበትና በቅናት ሆኖ ‹‹እርሱ ነግሦ ልጆቼ ወታደሮቹ ሊሆኑ ነውን›› በማለት ይገድለው ዘንድ አሰበ፡፡ ሆኖም አማካሪዎቹ ‹‹ለጊዜው ምንም ስለማይረዳ ተወው ለወደፊቱም የንግሥና ምሥጢር እንዳያውቅ ወደ እናቱ ዘንድ መልሰውና በዚያ ከብት ሲያግድ ይደግ››ስላሉት ወደ እናቱ ላከው፡፡ እርሷ ግን በጥበብና በብልሃት አስተዋይ አድርጋ አሳደገችው። ይህንንም ሲሰማ ሊገድለው አሽከሮቹን ላከ፡፡ እናቱም የተላኩትን አሽከሮች ተቀብላ ምግብ አቅርባ አስተናገደቻቸው። ነገር ግን እግዚአብሔር የንጉሡን ተንኮል ስለተገለጠላት ልጇን ደበቀችው፡፡ በስውርም ወስዳ ከጳጳሱ ዘንድ ዲቁና እንዲቀበል ካደረገችው በኋላ ‹‹ልጄ ሆይ! አጎትህ ሊገድልህ ይፈልግሃልና በፊቴ ከሚገድልህ ርቀህ ብትሄድ ይሻላል፣ ያዕቆብን ከኤሳው የጠበቀ አንተንም ይጠብቅህ›› ብላ ሸኘችው፡፡ ይምርሃነ ክርስቶስም ወደ በጌምድር ተሰደደ፡፡ (ገድሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ በዚያም የሌዋውያን ወገን የምትሆን ቅድስት ሕዝባን አግብቶ ቅስናም ተቀብሏል ይላል።) ያም ሆነ ይህ ቅዱሱ በስደቱ ወቅት ሥጋዊውንና መንፈሳዊውን ጥበብ ተምሮ እንዳጠናቀቀና በኋላም ወንጌልን እየሰበከ፣ በተአምራቱም ሕመምተኞችን እየፈወሰ እግዚአብሔርንም እያገለገለ እንደኖረ ታሪኩ ያወሳል፡፡

በዚህ አይነት ሁኔታ ዓመታት ሲያልፉ እግዚአብሔር አምላክ ንጉሥ አጎቱ ጠንጠውድም መሞቱንና በዙፋኑም እርሱ እንደሚነግሥ ነገረውና በመልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል መሪነት ወደ ሀገሩ ተመልሶ መጥቶ በላስታ ወረዳ ሳይ (ዛሬ ሸጐላ ማርያም) ከምትባል ቦታ ላይ ወንጌልን እያስተማረ፣ ድውያንን እየፈወሰ እንዲቀመጥ አደረገው፡፡ ትምህርቱንና ተአምራቱን ያዩት የአካባቢው ሰዎችም ‹‹ነፃነትና ፍቅር የሚገኝብህ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! እኛ ሰላማዊ ብርሃናዊ ብለን ስም አወጣንልህ፣ ያንተ ግን ስምህ ማን ይባላል ንገረን›› አሉት፡፡ እርሱም ‹‹ስሜ ይምርሃነ ክርስቶስ ነው›› አላቸው ይህኔ ሕዝቡ ሁሉ በሹክሹክታ ‹‹ይምርሃነ ክርስቶስ የሚባል ሲነግሥ ሃይማኖት ይቀናል፣ ፍርድ ይስተካከላል›› እያሉ አባቶቻችን ሲናገሩ ሰምተናል አሉ፡፡

ከጠንጠውድምም ሞት በኋላ ማንም እንዳልነገሠ ሲያረጋግጡ የማን ልጅ እንደሆነ እንዲነግራቸው በእግዚአብሔር ስም ለመኑትና የጠንጠውድም ታናሽና የዣን ስዩም ታላቅ ወንድም የሆነው የግርማ ስዩም ልጅ እንደሆነ ነገራቸው፡፡ እነርሱም ‹‹የተነገረው ትንቢት ደርሷልና ሳንዘገይ እናንግሠው›› ብለው ሥርዓተ መንግሥቱን ፈጽመው በዙፋን ላይ አስቀመጡት፡፡

ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ በትረ መንግሥቱን ከያዘ በኋላ ሁሉም ሰው በተለያዩ እንቅስቃሴዎቹ ውስጥ እንደ ወንጌሉ ቃል እንዲኖር በግዛቱ ሁሉ አወጀ፡፡ እግዚአብሔርም የሚመሰገንበትን ቤት መሥራት አሰበና የተፈቀደለትን ቦታ እንኪያገኝ ድረስ ዛዚያ በምትባል ልዩ በሆነች ስፍራ ድንኳን ተክሎ እንደ ሙሴ አምላኩን ማገልገል ጀመረ፡፡ በዚህም ቦታ ሕዝቡን ከሰማይ በወረደለት መስቀል እየባረከና እርሱ ለቅዳሴ በሚገባበት ጊዜ ከአምላኩ የሚሰጠውን ሰማያዊ ኅብስትና ጽዋ እያቆረበ ለ22 ዓመት በድንኳኗ ውስጥ ኖረ፡፡ ከነዚህ ሁሉ ዓመታት በኋላም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር ተገለጠለትና እንዲህ አለው፡- ‹‹ወዳጄ ይምርሃነ ክርስቶስ ይህን ሥፍራ (ዛዚያን) ልቀቅ፣ ከእንግዲህ ወዲህ በዚህ ቦታ ሰማያዊ ኅብስትና ሰማያዊ ጽዋ አይወርድልህም፡፡ ወደማሳይህ ቦታ ተነሥተህ ሂድ፣ በዚያም እስከ ዕረፍትህ ቀን ድረስ ሰማያዊ ኅብስትና ሰማያዊ ጽዋ ይወርድልሀል፡፡ ይህን ዓለም ለማሳለፍ እስከምመጣበት እስከ ዕለተ ምፅዓት ድረስ የእኔ ጌትነት የአንተም የቅድስና ሕይወት የሚነገርበት፣ የሥጋህ የዕረፍት ቦታ የሚሆንበት፣ ለምትሠራው መቅደስ ክዳን የሚሆን ሣር የማትፈልግበት ሰፊ ዋሻ እሰጥሀለው ፣ በዚያ ቤተ መቅደሴን ሥራ፣ እኔ በምትሠራው ቤተ መቅደስ ከአንተ ጋር ለዘለዓለም ቃልኪዳኔን አቆማለሁ፡፡ በምታንጸው ቤተ መቅደስ ውስጥ ‹አቤቱ የይምርሃነ ክርስቶስ አምላክ ሆይ! ስለወዳጅህ ስለ ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ብለህ ይቅር በለኝ› እያለ ‹አባታችን ሆይ!› የሚለውን ጸሎት የሚጸልይ ዕለቱን እንደተጠመቀ አደርገዋለሁ፡፡ ነገ ማለዳ ተነሥተህ ወግረ ስሂን ወደሚባለው የዕረፍትህ ቦታ ወደሚሆነው ዋሻ ሕዝብህን አስከትለህ ሂድ፤ በዚያም ቤተ መቅደሴን አንጽ›› ብሎ ቃልኪዳን ሰጠው።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🌹 "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌹

🌹 #ጥቅምት ፲፱ (19) ቀን።

🌹 እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_ኤርትራ_አገር የሚገኘውን በተፈጥሮአዊ አቀማመጡ እጅግ አስደናቂውን #ፃዕዳ_ዓምባ_ቅድስት_ሥላሴ_ገዳምን ለመሠረቱት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ሰይፈ_ሚካኤል ለዕረፍታቸው ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

✝ ✝ ✝
🌹 #አቡነ_ሰይፈ_ሚካኤል፦ እኚህ ጻድቅ በ1669 ዓ.ም የገደሙት ይህ እጅግ ድንቅ የሆነ ገዳም ፃዕዳ ዓምባ ቅድስት ሥላሴ ከኤርትራ በዓንሰባ ዞን ከከረን 25 ኪ.ሜ እርቆ በደቡባዊ ምዕራብ ከባሕር ጠለል በላይ 2500 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል፡፡ ወደዚህ ድንቅ ገዳም የሚያደርሰው መንገድ ዳገትና ቁልቁለት የበዛበት አስቸጋሪ ከመሆኑ የተነሣ ብርቱ ትዕግሥትና መንፈሳዊ ጽናት ይጠይቃል፡፡ ገዳሙ ለመድረስ ከከረን ከተማ በደቡባዊ ምዕራብ በኩል ወንዞችንና ጋራ ሸንተረሮችን ማቋረጥ ግድ ነው፡፡ ከዚያም "ድንጃ ወርቅ" በተባለ ከገዳሙ እግር ሥር በሚገኘው ረጅሞ ተራራ ከተደረሰ በኋላ ከድንጃ ወርቅ የአንድ ሰዓት ተኩል ዝግዛግ የእግር ጉዞ ያስኬዳል፡፡ ከዚያም "ማዕዶዋይ" ከተተባለው ቦታ ይደረሳል፡፡ ትርጓሜውም በርቀት የሚታይ ማለት ነው፡፡ ከማዕዶዋይ ወደ ገዳሙ ውስጥ ለመግባት ከእግር መረገጫ የማያልፍ ስፋት የሌላት በቀኝና በግራ የምታስፈራ በጭንቅ የሚሻገርዋት "ጸናፌ ጽልመት" ተብላ የምትጠራዋን አስጨናቂ ገደል ማለፍ ግድ ይላል፡፡ ይህቺን ለመሻገርም ሆነ ለማለፍ አስቸጋሪ የሆነችን መንገድ ለብዙ ጊዜ የተመላለሱባት ምእመናን ግን ከባድ እቃ በሸክም ይዘውም ቢሆን ያለ ምንም ፍርሃት ይሻገሩባታል፡፡ በጭንቅ የሚሻገርዋትን ይህችን አስጨናቂ ገደል ከታለፈ በኋላ ቀጥሎ "ደገ ሰላም" ና "መንገደ ሰማይ" የሚባል ወደ ገዳሙ የሚያስገባ ዝግዛግ መንገድ አለ፡፡

🌹 አባታችንን ወደዚህ ድንቅ ገዳም እየመራ ይዞአቸው የገባው የታዘዘ መልአክ ነው፡፡ ወደ ገዳሙ ቅጥር ውስጥ ከተገባ በኋላ ዕፁብ ድንቅ የሆኑ ልዩና መንፈሳዊ ሐሴትን የሚሞሉ በርካታ ተአምራት የተፈጸመባቸውን ነገሮችን መመልከት ይቻላል፡፡ተአምራቶቹም "ድሮ እንዲህ ነበር፣ እንደዛ ተደረገ…" ተብሎ በአፈ ታሪክ ብቻ የሚወራ ሳይሆን አሁንም ድረስ በዐይን የሚታዩ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ገዳሙ አጠገብ የሚገኙት ዛፎች ብዙ ዕድሜ ከማስቆጠራቸው የተነሣ በንፋስ ኃይል ሲወድቁ ወደ ታች መውደቅ ሲገባቸው በተቃራኒው ግን ዛፎቹ የሚወድቁት ወደ ላይ ነው፡፡ በተጨማሪም ገዳሙ ውስጥ በላዔ ሥጋ ሥጋን የሚበላ ንስር ሳይቀር እንኳን የሞተ እንስሳም ቢያገኝ ሥጋ የሚባል ነገር አለመብላቱ አሁንም ድረስ በዐይን የሚታይ እውነታ ነው፡፡

🌹 እንዲሁም እዚህ ድንቅ ገዳም ውስጥ መርዛማ እባብም ነድፎ ሰው ሊገድል አይችልም፡፡ በእባቡ የተነደፈ ሰው እንኳን ቢኖር በጉንዳን የተነከሰ ያህል ይሰማዋል እንጂ ፈጽሞ አይሞትም፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ ላይ "ለሚያምኑ እነዚህ ምልክቶች ይከተሉዋቸዋል፡- በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፣ እባቡን ይይዛሉ፣ የሚገድል መርዝ ቢጠጡ እንኳን ከቶ አይጎዳቸውም" ያለው አምላካዊ ቃል እዚህ ገዳም ውስጥ ባለንበት ዘመን በግልጽ በተግባር ይታያል፡፡ ማር 16፡16-18፣ ሐዋ 28፡3-6፡፡ እንዲሁም በዚህ ገዳም ውስጥ ከነበሩ ዛፎች ውስጥ አንዱ ዳዕሮ የተባለ ትልቅ ዛፍ አለ፡፡ ከዚህ ልዩ ዛፍ ተጠምቆ የሚዘጋጀው መጠጥ ከወይን የሚጥም ኅሊናን የሚመስጥና ሕመምን የሚፈውስ ነበር፡፡ ሌላው በገዳሙ ውስጥ በዐይን ከሚታዩትና ከሚያስደንቁት ተአምራቶች ውስጥ አንዱ በክረምት ወቅት ኃይለኛ ዝናብ ሲጥል በወረደ መብረቅ ምክንያት ገዳሙ ውስጥ የሚገኘው ዐለት ተሰንጥቆ የሀገሪቱ ምስል ተስሎበት ተገኝቷል፡፡ እነዚህና ሌሎችም በርካታ ተአምራት እስከ አሁን ድረስ ጸንተው የሚገኙት የዚህ የፃዕዳ ዓምባ ቅድስት ሥላሴ ገዳም መሥራች በሆኑ በአቡነ ሠይፈ ሚካኤል የምሕረት ቃልኪዳን ነው፡፡

🌹 አቡነ ሠይፈ ሚካኤል ከአባታቸው ከዓምደ ሚካኤልና ከእናታቸው ከኅሪተ ማርያም ተወለዱ፡፡ ወላጆቻቸው እግዚአብሔርን የሚፈሩና በጾም ጸሎት የተወሰኑ የዋኆች ስለነበሩ በሃይማኖትና በምግባር ኮትኩተው አሳድገዋቸዋል፡፡ አባታቸው ቃለ እግዚአብሔር እንዲማሩላቸው ልጃቸውን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ወስደው ለመምህር ሰጧዋቸው፡፡ መምህሩም በደስታ ተቀብለው ቅዱሳት መጻሕፍትንና ያሬዳዊ ዜማን አስተማሯቸው፡፡

🌹 ከዚህም በኋላ አቡነ ሠይፈ ሚካኤል "እኔን ሊከተለኝ የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ" የሚለውን ጌታችንን ቃል ለመፈጸም ዓለምን ከነምኞቷ ንቀው ትተው መስቀሉን ተሸክመው ጌታችን ተከተሉት፡፡ ከዚህም በኋላ አባታችን ወደ ዋሻዎችና ገዳማት እየሄዱ በአድያቦ ቤተ ቂርቆስ የሚባል ገዳም ደርሰው ከአቡነ ኖላዊነኄር ግብረ ምንኵስና እየተማሩ በገዳሙ ውስጥ የነበሩ መነኰሳት እስከሚደነቁ ድረስ በጽኑ ትጋትና በብዙ ትሩፋት በተጋድሎ አገልግሎታቸውን ይፈጽሙ ነበር፡፡ ከጽኑ ተጋድሏቸው የተነሣ ሰውነታቸው እንደ በረዶ ነጭ ሆነ፡፡ በዚህም ምክንያት አቡነ ዕንቆ ብርሃን ልብሰ ምንኵስናና አስኬማ መላእክት አለበሷቸው፡፡ እንዲህ ባለ ጽኑ ገድል በኣድያቦ ከመንፈስ አባታቸው ከአባ ዕንቆ ብርሃን ብዙ ዓመታትን ቆይተው በኋላ ወደ ዋልድባ ሄዱ፡፡ ዋልድባ ከገቡም በኋላ እዛ ከነበሩ ቅዱሳን ተባርከው ጽኑ ተጋድሏቸውን ቀጠሉ፡፡

🌹 ከዚያም በዋልድባ ቅዱሳን ፈቃድ ወደ ወገሪቆ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ሄደው አበምኔትና መምህር ሆነው አገለገሉ፡፡ አቡነ ሰይፈ ሚካኤል በተሰጣቸው ጸጋ ወንጌልን እያስተማሩና ሕሙማን እየፈወሱ እስከ ጋሽ ባርካ ደብረ ሳላ የሚባል ቦታ ዞሩ፡፡ ይሄን አገልግሎታቸው ከፈጸሙ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል እየመራ ማረፍያ ቤታቸው ወደሆነችው ፃዕዳ እምባ ሥላሴ ገዳም በደብረ ከባቦ አደረሳቸው፡፡ በዚያም በጾምና በጸሎት ተጠምደው እግዚአብሔርን አገለገሉ፡፡ሲጸልዩም እስከ ሰማይ ድረስ ዓምደ ብርሃን ተተክሎ ይታያቸው ነበር፡፡

🌹 አባታችን በጸሎት ላይ ሳሉ አጋንንት በእባብና በንብ እየተመሰሉ ይፈታተኗቸው ነበር ነገር ግን አባታችን በጾምና በጸሎት ድል ይነሷቸው ነበር፡፡ በደብረ ከባቦ ቤተ ክርስትያን አንጸው ማኅበር አቋቁመው ለ9 ዓመት ከ6 ወር አገልግሎታቸውን እየፈጸሙና መከራ እየተቀበሉ ከቆዩ በኋላ አንድ ቀን በሰርክ ጸሎት እየጸለዩ ሳለ መልአክ መጥቶ "…ወደ ገዳሙ አስገባሃለሁና ተከተለኝ" አላቸው፡፡ እሳቸውም ከኋላው እየተከተሉ መልአኩ ወደ ዛሬይቱ ወንዶች ብቻ ወደሚገቡባት ገዳም አስገባቸው፡፡ ያቺን ለማየትም ጭምር የምታስፈራዋን መንገድ አባታችን "ጸናፌ ፅልመት"ብለው ሰየሟት፡፡ ከገቡም በኋላ በገዳሙ ውስጥ ቤተ ክርቲያን አንጸው ቤተ ማኅበር አቋቋሙ።

🌹 አቡነ ሰይፈ ሚካኤል በተሰጣቸው ጸጋ ርኲሳን መናፍስትን ከሕሙማን ያወጡ ስለነበር እነዚያ አጋንንትም "እዚህ እንድትኖር አንፈቅድልህም" እያሉ በገሃድ ለሞት እስከሚደርሱ ድረስ ዐይናቸውን አፈሰሱባቸው ሆኖም ግን መልአከ እግዚአብሔር ዳስሶ ዐይናቸውን መልሶ አበራላቸው፡፡ እንዲሁም አጋንንቶቹ በማደርያ ቤታቸው እሳት እያቀጣጠሉ በላያቸውም ትላልቅ ድንጋዮችን እየወረወሩ ከበፊቱ በእጅጉ ይፈታተኗቸው ነበር፡፡ እነዚያ የተወረወሩባቸው ድንጋዮች ግን አቡነ ሰይፈ ሚካኤል ይጸሉዩበት በነበረ ቦታ በደቡብ አቅጣጫ ተተክለው ቀርተዋል፡፡ ድንጋዮቹ እስከ አሁን ድረስ አሉ፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ጥቅምት 17/2017 #ሰማእቱ_ቅዱስ_እስጢፋኖስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በሰማእቱ ስም ለምናመሰግንበት ሰማእቱ #ቅዱስ_እስጢፋኖስን በፀሎቱ እንዲያስበን ለምንማፀንበት አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉ሰማእቱ #ቅዱስ_እስጢፋኖስ በዚህ እለት የተሾመበት እለት ነዉ የተዋህዶ ልጆች ስለምን ቀዳሜ ሰማዕት ተሰኘ ቅዱስ #እስጢፋኖስ ካልን #ከመድኃኒታችን_ኢየሱስ በኋላ እራሱን የሰጠ የመጀመሪያው ሰው ስለሆነ ነው

👉ቀዳሜ ሰማእት #ቅዱስ_እስጢፋኖስ የዲያቆናት አለቃ የሆነ እየወገሩት እንደ ሀጢአት አትቁጠርባቸው ያለ ደሙ እየተንፀፈፀፈ ምህረትን የለመነ ለሐዋርያት ይታዘዝና ያገለግላቸው የነበረ ፊቱ እንደ መልአክ ያበራ የነበረ የሐዋ.ም6፥8-15 ብዙዎችን ወደ ሀይማኖት የመለሰ ወንጌላዊ #ቅዱስ_እስጢፋኖስ አባቱ ስምዖን እናቱ ሐና ይሰኛሉ

👉ቅዱስ እስጢፋኖስ የተወለደው ጥር 1 እረፍቱም ጥር 1 ሹመቱ ጥቅምት 17 መስከረም 15 ሥጋው የፈለሰበት ቀን ነው ረድኤት በረከቱ ይድረሰን የተባረከ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን"✝️💒✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://youtu.be/Bk9CR_WJngY?si=abURbSTayA8BplAH

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል
ማርያም አማላጅነት አይለየን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ቅዱስ አትናቴዎስ በቅዳሴያችን እንዲህ እንዳለ

👉አዳምና ሔዋን ሆይ እኛስ እናንተን መንቀፍ አይቻለንም ፤ በአርሱ እየተናገሩበት የራስን አንደበት ለመንቀፍ አንደማይቻል እንዲሁም አናንተ አኛን ናችሁ ፤ እኛም እናንተን ነን።

👉 አዳምና ሔዋን ሆይ እናንተን እንዳንነቅፋችሁ ይቅር ባይ ጌታ ባመጣባችሁ መከራ ተጸጽታችሁ ንስሓ ገብታችኋል፡፡

👉አዳምና ሔዋን ሆይ እናንተስ ድናችኋል ቤዛ ሆኖ ባዳናችሁ በጌታ ደም ወደቀደመ ርስታችሁ ወደ ገነትም ገብታችኋል... አኛን ልጆቻችሁን ግን ኃጢአት እንደ አሳት አቃጠለችን። ፍትወትም እነደደችን'


ተፀፀተን ለንስኃ በቅተን እንኖር ዘንድ
ፈጣሪ አምላክ ይርዳን
ፍትወታችንን ያርቅልን በምህረቱ በጎውን ያርግልን🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

መኝታውን በወርቅ ያጌጠ ማድረግ ሲችል
በግርግም ውስጥ ማድረግን መረጠ
እናቱንም ከንግሥታት አንዲቱን ማድረግ ሲችል
አላደረገም ብሏል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
❤️

ድንግል ማርያም እንዲህ ናት::
ታላላቅ ሀብታትን ሳትጠይቅ የተቀበለች ፣
ሳትለምን የተመረጠች ፣ ሳታገባ የፀነሰች ፣
ሳታምጥ የወለደች ፣ ድንግልናዋን ሳታጣ እናት የሆነች ፣
አንዳች ሳትሻ ሁሉን ያገኘች
የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ እርስዋ ናት፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

ጸሎት

"የጭንቀት ሁሉ መሸሸጊያ ስፍራ፣
የደስታ መሰረት፣
የቋሚ ደስታ ምንጭ፣
ከሀዘን መከላከያ ነው።"


ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ጥቅምት 13/2017 #እግዚአብሔር_አብ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አንተ እውነተኛ አምላክ ስትሆን ሁሉን በፍቃድህ የፈፀምህ የሁሉ ፈጣሪ #እግዚአብሔር_አብ ሆይ ሁሉን ማድረግ የሚቻልህ ሁሉ ለአንተ የቀረበ በአንተም ዘንድ አለና እውነተኛይቱ መንገድ መርተህ ህግህን አስተምረን

👉በእልፍ አእላፋት መላእክት የሚመሰገን #እግዚአብሔር_አብ አምላካችን ሀገራችንን ህዝባችንን በምህረት አይኑ ይመልከትልን ፍቅርና አንድነትን ይስጠን

👉ኄኖክም ስለእርሳቸው እንዲህ አለ በሰማይ እያለሁ ነፋሳት በደመና ውስጥ አወጡኝ በእሳት ላንቃም ወደታነፀ ቤት አደረሱኝ በዚያም #አእላፋት_መላእክትን አየሁ እነርሱም በእሳት ላቦት ላይ የቆሙ ልብሳቸውም እንደ በረድ ነጭ ነው አለ

👉ያዕቆብም እንዲህ አለ ከምድር እስከ ሰማይ የምትደርስ መሰላልን አየሁ #የእግዚአብሔርም መላእክት በውስጥዋ ይወጡ ይወርዱ ነበር ሁለተኛም ከሶርያ መመለሻው በሆነ ጊዜ የመላእክት ሠራዊትን አየሁ አለ

👉ሙሴም እንዲህ አለ #እግዚአብሔር አሕዛብን በቦታ እንደለያቸው የአዳምን ልጆች እንደበተናቸው እግዚአብሔርን በሚያገለግሉ መላእክት ቁጥር የአሕዛብን አውራጃዎች እንደ ወሰናቸው ሁለተኛም #እግዚአብሔር ከሲና ተራራ መጥቶ በሴይር ታየኝ ረቂቃን መላእክቶቹም ከእርሱ ጋር ነበሩ አለ

👉ዳዊትም እንዲህ አለ #መላእክቱን መንፈስ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርግ እርሱ ነው #የእግዚአብሔር ሠረገላዎች የብዙ ብዙ ሺህ ናቸው አለ ኤልሳዕም የእሳት ሠረገሎችና የእሳት ፈረሶች በዙሪያው ቁመው ሲጠብቁት አየ

👉ዳንኤልም እንዲህ አለ ዙፋኖችን እስቲዘረጉለት ድረስ ደርሶ አየሁ ብሉየ መዋዕል #እግዚአብሔር በላያቸው ተቀመጠ ልብሱም እንደ በረድ ነጭ ነው የራሱም ጠጉሩም እንደ ብዝት ነጭ ነው

👉ዙፋኑም የሚነድ እሳት ነው ሠረገላውም የሚንቦገቦግ ፍም ነው የእሳትም ጐርፍ በፊቱ ይፈሳል የብዙ ብዙ የሆኑ መላእክትም ያገለግሉታል የእልፍ እልፍ #መላእክትም በፊቱ ይቆማሉ በአደባባይም ተቀምጦ መጻሕፍትን ገለጠ

👉ሉቃስም እንዲህ አለ ድንገትም ከዚያ መልአክ ጋር ብዙ የሰማይ ሠራዊት መጡ #እግዚአብሔርንም ሲያመሰግኑ በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ሰላም ለሰው ልጅ በጎ ፈቃድ እያሉ

👉ማቴዎስም እነሆ #መላእክትም ሊአገለግሉት መጡ አለ ሁለተኛም የሰው ልጅ ቅዱሳን መላእክትን አስከትሎ በጌትነቱ በሚመጣበት ጊዜ ያን ጊዜ በጌትነቱ ዙፋን ላይ ይቀመጣል ዮሐንስም ጌታችን ከተናገረው ቃል እንዲህ አለ እላችኋለሁ ከእንግዲህ ወዲህ ሰማዮች ሲከፈቱ #የእግዚአብሔርም መላእክት ወደ ሰው ልጅ ሲወርዱና ሲወጡ ታያላችሁ አላቸው የሚል ነው

👉ሐዋርያው ይሁዳም እነሆ #እግዚአብሔር ይፈርድ ዘንድ አእላፋት የሆኑ ቅዱሳን መላእክቶቹን አስከትሎ ይመጣል አለ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትም የመዓረጋቸውን ደረጃ ወይም አይነት እንዲህ ብለው ተናገሩ መላእክት አጋዕዝት ሥልጣናት ኃይላት መናብርት መኳንንት ሊቃናት አርባብ ኪሩቤል ሱራፌል ብለው ተናገሩ

👉 #የእግዚአብሔር አብ ፀጋ የወልድ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ አንድነት ከኛ ጋር ይሁን በዚህ እለት የሚታሰበዉ የጦቢትን አይን ያበራ መልአኩ #ቅዱስ_ሩፋኤል ይጠብቀን የፃድቁ አባታችን አቡነ #ዘርዐ_ብሩክ ፀሎቱ አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ጥቅምት 13/2017 #እግዚአብሔር_አብ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አንተ እውነተኛ አምላክ ስትሆን ሁሉን በፍቃድህ የፈፀምህ የሁሉ ፈጣሪ #እግዚአብሔር_አብ ሆይ ሁሉን ማድረግ የሚቻልህ ሁሉ ለአንተ የቀረበ በአንተም ዘንድ አለና እውነተኛይቱ መንገድ መርተህ ህግህን አስተምረን

👉በእልፍ አእላፋት መላእክት የሚመሰገን #እግዚአብሔር_አብ አምላካችን ሀገራችንን ህዝባችንን በምህረት አይኑ ይመልከትልን ፍቅርና አንድነትን ይስጠን

👉ኄኖክም ስለእርሳቸው እንዲህ አለ በሰማይ እያለሁ ነፋሳት በደመና ውስጥ አወጡኝ በእሳት ላንቃም ወደታነፀ ቤት አደረሱኝ በዚያም #አእላፋት_መላእክትን አየሁ እነርሱም በእሳት ላቦት ላይ የቆሙ ልብሳቸውም እንደ በረድ ነጭ ነው አለ

👉ያዕቆብም እንዲህ አለ ከምድር እስከ ሰማይ የምትደርስ መሰላልን አየሁ #የእግዚአብሔርም መላእክት በውስጥዋ ይወጡ ይወርዱ ነበር ሁለተኛም ከሶርያ መመለሻው በሆነ ጊዜ የመላእክት ሠራዊትን አየሁ አለ

👉ሙሴም እንዲህ አለ #እግዚአብሔር አሕዛብን በቦታ እንደለያቸው የአዳምን ልጆች እንደበተናቸው እግዚአብሔርን በሚያገለግሉ መላእክት ቁጥር የአሕዛብን አውራጃዎች እንደ ወሰናቸው ሁለተኛም #እግዚአብሔር ከሲና ተራራ መጥቶ በሴይር ታየኝ ረቂቃን መላእክቶቹም ከእርሱ ጋር ነበሩ አለ

👉ዳዊትም እንዲህ አለ #መላእክቱን መንፈስ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርግ እርሱ ነው #የእግዚአብሔር ሠረገላዎች የብዙ ብዙ ሺህ ናቸው አለ ኤልሳዕም የእሳት ሠረገሎችና የእሳት ፈረሶች በዙሪያው ቁመው ሲጠብቁት አየ

👉ዳንኤልም እንዲህ አለ ዙፋኖችን እስቲዘረጉለት ድረስ ደርሶ አየሁ ብሉየ መዋዕል #እግዚአብሔር በላያቸው ተቀመጠ ልብሱም እንደ በረድ ነጭ ነው የራሱም ጠጉሩም እንደ ብዝት ነጭ ነው

👉ዙፋኑም የሚነድ እሳት ነው ሠረገላውም የሚንቦገቦግ ፍም ነው የእሳትም ጐርፍ በፊቱ ይፈሳል የብዙ ብዙ የሆኑ መላእክትም ያገለግሉታል የእልፍ እልፍ #መላእክትም በፊቱ ይቆማሉ በአደባባይም ተቀምጦ መጻሕፍትን ገለጠ

👉ሉቃስም እንዲህ አለ ድንገትም ከዚያ መልአክ ጋር ብዙ የሰማይ ሠራዊት መጡ #እግዚአብሔርንም ሲያመሰግኑ በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ሰላም ለሰው ልጅ በጎ ፈቃድ እያሉ

👉ማቴዎስም እነሆ #መላእክትም ሊአገለግሉት መጡ አለ ሁለተኛም የሰው ልጅ ቅዱሳን መላእክትን አስከትሎ በጌትነቱ በሚመጣበት ጊዜ ያን ጊዜ በጌትነቱ ዙፋን ላይ ይቀመጣል ዮሐንስም ጌታችን ከተናገረው ቃል እንዲህ አለ እላችኋለሁ ከእንግዲህ ወዲህ ሰማዮች ሲከፈቱ #የእግዚአብሔርም መላእክት ወደ ሰው ልጅ ሲወርዱና ሲወጡ ታያላችሁ አላቸው የሚል ነው

👉ሐዋርያው ይሁዳም እነሆ #እግዚአብሔር ይፈርድ ዘንድ አእላፋት የሆኑ ቅዱሳን መላእክቶቹን አስከትሎ ይመጣል አለ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትም የመዓረጋቸውን ደረጃ ወይም አይነት እንዲህ ብለው ተናገሩ መላእክት አጋዕዝት ሥልጣናት ኃይላት መናብርት መኳንንት ሊቃናት አርባብ ኪሩቤል ሱራፌል ብለው ተናገሩ

👉 #የእግዚአብሔር አብ ፀጋ የወልድ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ አንድነት ከኛ ጋር ይሁን በዚህ እለት የሚታሰበዉ የጦቢትን አይን ያበራ መልአኩ #ቅዱስ_ሩፋኤል ይጠብቀን የፃድቁ አባታችን አቡነ #ዘርዐ_ብሩክ ፀሎቱ አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ወደ ሮሜ ሰዎች 8:33 እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው? Who shall lay any thing to the charge of God's elect? It is God that justifieth.
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:34 የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። Who is he that condemneth? It is Christ that died, yea rather, that is risen again, who is even at the right hand of God, who also maketh intercession for us.

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ሰላም_ለከ_ሚካኤል
የተጨነቀውን ነፃ ለምታወጣ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ሰላምታ ይገባሃል፣
ሠራተኛውን ሠርቶ እንዲኖር ውሎ እንዲገባ የምትጠብቀው ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይኹን፣
ችግረኛውን ለመርዳት ከልዑል እግዚአብሔር ዘንድ የምትላክ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ሰላም ላተ ይኹን፣ አዳኝነትህን በማመን የለመነህን ኹሉ በክንፈ ረደኤትህ የምትሠውረው ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይኹን፣ በኀዘን በትካዜ ላይ ወድቆ የሚፍገመገመውን ፈጥነህ ደርሰህ ደግፈህ የምታጽናናው የምታረጋጋው ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ሆይ አንገትህን ዘንበል መለስ አድርገህ በፈጣሪህ እግዚአብሔር ፊትም ሰግደኽ እኛን ባሮቹን በቸርነቱ ጐብኝቶ የማናዊት እጁንም ዘርግቶ ይባርከን ዘንድ አማልደን ለዘለዓለሙ አሜን።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝እንኳን አደረሰነ!

✝በዓለ ቅዱስ ዳዊት (ንጉሠ እሥራኤል)
ወበዓሎሙ ለቅዱሳን፦
❀ሚካኤል ሊቀ መላእክት
❀ማቴዎስ ወንጌላዊ
❀ድሜጥሮስ ተካሌ ወይን
❀ልዕልተ ወይን ድንግል
❀አፎምያ ብጽዕት
❀ሳሙኤል ወዕሴይ

☞መዝ​ሙረ ቅዱስ ዳዊት

✿በእንተ ርዕሱ፦

፩. ከወ​ን​ድ​ሞቼ ይልቅ እኔ ትንሽ ነበ​ርሁ፥
በአ​ባ​ቴም ቤት ወጣት ነበ​ርሁ፥
ያባ​ቴ​ንም በጎች እጠ​ብቅ ነበር።

፪. እጆቼ መሰ​ንቆ ይመቱ ነበር።
ጣቶ​ቼም በገና ይደ​ረ​ድሩ ነበር።

፫. ለጌ​ታዬ ማን ነገ​ረው?
እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ ሰማኝ።

፬. እርሱ መል​አ​ኩን ልኮ አዳ​ነኝ፥
የአ​ባ​ቴን በጎች ከም​ጠ​ብ​ቅ​በት ወሰ​ደኝ፤
የተ​ቀ​ደሰ ቅባ​ትን ቀባኝ፤

፭. ወን​ድ​ሞቼ ግን፥ ያማ​ሩና ያደጉ ነበሩ።
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በእ​ነ​ርሱ ደስ አላ​ለ​ውም።

፮. ልዩ ወገ​ንን ልገ​ጥ​መው ወጣሁ።
በረ​ከሱ ጣዖ​ቶ​ቹም ረገ​መኝ።

፯. እኔም ከወ​ንዝ ሦስት ድን​ጋ​ዮ​ችን አነ​ሣሁ፥
ግን​ባ​ሩ​ንም በወ​ን​ጭፍ መታ​ሁት።
ያን​ጊ​ዜም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ወደቀ።

፰. በላዩ የነ​በ​ረ​ው​ንም ሰይፍ ወሰ​ድሁ፥
የጎ​ል​ያ​ድ​ንም ቸብ​ቸቦ ቈረ​ጥሁ።
ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም ስድ​ብን አራ​ቅሁ።

(መዝ​ሙር ዘዳዊት ፻፶፩)

✝ሰላም ለርዕስከ በቅብዓ መንግሥት ዘከብረ፤
እምድኅረ ሳዖል በቅድመ እግዚኡ እንተ ኢኮነ ስሙረ፤
ዳዊት ኅሩይ በዘንዌድሰከ ወትረ፤
ይቤሎ ማቴዎስ ለክርስቶስ ወልደ ዳዊት ምዕረ፤
ወድሜጥሮስ ተርጎሞ እንዘ ይከሥት ሥውረ!

(አርኬ - ዝክረ ቅዱሳን ርቱዓነ ሃይማኖት)

Читать полностью…
Subscribe to a channel