kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ጥቅምት 26/2017 #አረጋዊ_ቅዱስ_ዮሴፍ
#ፃድቁ_አባታችን_ሐብተ_ማርያም

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሳኑ ስም ለምናመሰግንበት ለቅዱሣን አባቶቻችን ወርሐዊ መታሰቢያ ክበረ በዐል እንኳን አደረሰን

በፃድቃን ላይ የሚናገሩ የሽንገላ ከንፈሮች
ዲዳ ይሁኑ መዝ.30፥18

👉ኢትዮጲያዊዉ #ፃድቅ ትዉልዳቸዉ ሸዋ መንዝ ልዩ ስሙ ራዊ ውስጥ ሲሆን አባታቸው ፍሬ ቡሩክ እናታቸው ደግሞ ቅድስት ዮስቲና ትባላለች ግንቦት 26 ተወለዱ በተለይ ቅድስት ዮስቲና እጅግ ደመ ግቡ ምፅዋትን ወዳጅ ቡርክት ሴት ነበረች እንዲያውም ከጻድቁ መወለድ በፊት መንና ጭው ካለ በርሃ ገብታ ነበር

👉ግን የበቃ አባት አግኝቷት "ከማሕጸንሽ ደግ የሥላሴ ባርያ አለና ተመለሽ" ብሏት እንደ ገና ተመልሳለች ፃድቁን ወልዳ አሳድጋም እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ #ሰባት_አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች

👉ወደ ፃድቁ ዜና ሕይወት ስንመለስ #አቡነ_ሃብተ_ማርያም ገና ሕፃን እያሉ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ሲባል ይሰማሉ ይሕችን ጸሎት በሕጻን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ "ማረን እባክህን" እያሉ ይሰግዱ ነበር

👉የ5 ዓመት ሕጻን እንዲህ ሲያደርግ ማየቱ በእውነት ይደንቃል ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍፁም ተሐራሚና ፀዋሚ ነበሩ ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ #ተአምራትን ሰርተዋል የፈጣሪውን ስም ያቃለለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል

👉ፃድቁ አባታችን #በዝምተኛነታቻዉ_በአርምሞ ኑሯቸዉ የታወቁ ናቸዉ በመልአክ መሪነት አክሱም ኢየሩሣሌም ምድረ ግብፅ በእግራቸዉ በመሔድ ተሣልመዋል

👉ለፃድቁ አባታችን ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ቃል ኪዳን ሰጥቶዋቸዋል ወረርሽኝ በሽታና የአባላዘር በሽታ የያዘዉን ሰዉ ፀበልህን ቢጠመቅ ቢጠጣ በፍጥነት ይድናል ለ15 አይነት መቅሰፍቶች እንዲያድኑ ቃል ኪዳን ተሰጥቶዋቸዋል

👉ፃድቁ አባታችን ማእጠንት ሲያጥኑ #መንበረ_ፀባኦት ይታያቸዉ ነበር የፃድቁ ምልጃና ፀሎት ሀገራችንን ህዝባችንን ይጠብቅልን ቃል ኪዳናቸዉም አይለየን

👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአሉ የምናስበዉ አረጋዊ አባታችን #ቅዱስ_ዮሴፍ ምልጃና ፀሎቱ ሁላችንንም ይጠብቀን በዚህ እለት የሚታሰቡ ሌሎች ቅዱሳን ረድኤት በረከት ቃል ኪዳናቸዉ አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

‹‹በእንተ አቡነ አቢብ!››
ጌታችን መድኃኒታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአቡነ አቢብ ተገልጦላቸው ‹‹…ወዳጄ አቢብ ሆይ! የሰውን ልጅ ለማዳን የተቀበልኩትን ሕማማተ መስቀል እያሰብህ ይህንን ሁሉ ገድል ፈጽመሃልና ምን እንዳደርግልህ ትወዳለህ?›› አላቸው፡፡ ንዑድ ክቡር ቅዱስ አባታችን አቡነ አቢብም ‹‹ጌታዬ አምላኬ መድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! መቼም ሰው ሁሉ ሳይመገብ አይውልም አያድርምና በተመገበ ጊዜ ስሜን ጠርቶ የተማጸነውን ማርልኝ›› አሉት፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አባታችን አቡነ አቢብ ለሰው ልጆች ያላቸውን ፍቅር ካደነቀ በኋላ ‹‹…ከማዕድ በኋላ ስብሃት ተብሎ የተረፈውን ‹በእንተ አቢብ› ብሎ ሦስት ጊዜ የተመሰገበውን ሰው ሁሉ እምርልሃለሁ›› በማለት ታላቅ የምሕረት ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡
ያልተጠመቀ አረማዊ አሕዛብም እንኳን ቢሆኖ "ስለ አቡነ አቢብ" ብሎ ከተማጸነ ጌታችንን ያንን ሰው ወደቀናች የእምነት መንገድ ሳይመራውና በንስሓ ሳይጠራው በሞት እንደማይወስደው ለአባታችን ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡
ለማዳን ትንሽ ምክንያትን የሚፈልግ ያለ ምክንያትም የማያድን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ እስከዘላለም ድረስ ይክበር ይመስገን!
በዛሬዋ ዕለት ጥቅምት 25 ቀን በዓመታዊ የዕረፍት በዓላቸው ታስበው የሚውሉት ጻድቁና ሰማዕቱ አቡነ አቢብ ከቃልኪዳናቸው ረድኤት በረከት ይክፈሉን!
‹‹በእንተ አቡነ አቢብ!››
(ደብረ ሰላም ቃጭልቃ አቡነ አቢብ ገዳም ያሳተመው ገድለ አቡነ አቢብ፣ ገጽ 105)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

https://www.facebook.com/profile.php?id=100025396430266

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

የዋህ ሰው

ትሁትም ነው የሚራራም ነው
የዋህነት ጅልነት አይደለም

✅ ጅል ማለት

ሳይገባው ሳይረዳ የሚተው ነው

✅ የዋህ ግን

ገብቶት ተረድቶ የሚተው ነው


ስለዚህ የዋህ ሁኑ ብሏል ቅዱስ ጳውሎስ

የዋህ እንድንሆን መድኃኔዓለም ይርዳን🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ጥቅምት 24/2017 #ፃድቁ_ቅዱስ_ተክለሃይማኖት

"የፃድቃን መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል መዝ.111፥6"

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ፃድቁ አባታችንን በምልጃ ፀሎታቸዉ እንዲራዱን ለምንማፀንበት #ለአቡነ_ተክለሃይማኖት ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን

👉የስማቸው ትርጉም የሃይማኖት መሰረት ፍሬ የሆነው አባታችን ከእናታቸው እግዚሐርያ ከ አባታቸው ፀጋዘአብ መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታህሳስ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ተወለዱ

👉አባታችን #የሃይማኖት_ተክል ናቸው ጻድቁ አባታችን ገና እንደተወለዱ በሶስተኛው ቀናቸው ከእናታቸው እቅፍ በመውረድ አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውዕቱ መንፈስ ቅዱስ እያሉ በመስገድ የፈጠራቸውን አምላክ አመስግነዋል

👉እግዚአብሔር አምላካችን ለኢትዮጵያ #አዲስ_ሐዋርያ አድርጎ መርጧቸዋል ጻድቁ አባታችን ክብረ በዓላቸው እንደሚከተለው ነው

✝️ህዳር 24 ቀን ሃያ አምስተኛ ካህናተ ሰማይ ሆነው በሰማይ #የሥላሴን መንበር ያጠኑበት እለት ነው

✝️ታህሳስ 24 ቀን የአባታችን ልደት ነው

✝️ጥር 24 ቀን የአባታችን ሰባረ አፅሙ ነው

✝️መጋቢት 24 ቀን የአባታችን ፅንሰታቸው ነው

✝️ግንቦት 12 ቀን የአባታችን ፍልሰተ አፅሙ ነው

✝️ ነሐሴ 24 ቀን የአባታችን እረፍታቸው ነው

👉የፃድቁ አባታችን #የቅዱስ_ተክለሃይማኖት ቡራኬ ይድረሰን በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የሚዉሉ ቅዱሣን የከበረዉ ቃል ኪዳናቸዉ ሀገራችንን ህዝባችንን ይጠብቅልን የተባረከ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ማኅሌተ_ጽጌ

#የፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_42ኛ_ዓመት_የምሥረታ_በዓል

#ፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሰንበት_ትምህርት_ቤት
#ፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሚዲያ

Follow us on
👉 /channel/fre_amde_haymanot_media
👉 http://linktr.ee/fre_amde_haymanot_media

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ወዳጄ

መቼ ነው የምሞተው ብለህ ታውቃለህ
አሁን ወይም ዛሬ ወይም ነገ ነገ ወዲያ
አይታወቅም ማን መቼ እንደሚሞት
ግን አሁን ላይ ምን እንደምናደርግም አናውቅም

እንዘላለን ያ ክፉ አብሮን ይዘላል
እንዘፍናለን ያ ክፉ በደስታ አብሮን ይዘፍናል
እንዳራለን ከማንም ጋር ፍቅር እያልን
ያ ክፉ በስጋችን በስሜታችን ይደሰታል
ዘፈን ለመፅናኛ እንሰማለን
ያ ክፉ አብሮን በ ዘፈን ይፅናናል
እንሰክራለን አምሽተን እየመጣን
ለትዳራችን ሰቆቃ እንፈጥራለን
ያ ክፉ እሱም አብሮን ይሰክራል
በጨለማ ደስታውን ይቀጫል

ኧረ እባካችሁ

ተወዳጆች

መልካም እንሰራ ለሰይጣን በር አንክፈት
ሰይጣን ሁሌም ክፉውን ይወዳል
እኛ ቀላል እየመሰለን የምንሰራው ጥቃቅን ነገር
ቆይቶ ቆይቶ ለመቅሰፍት ለቁጣ ነው የሚዳርገን

እባካችሁ ለበጎ ነገር እንጂ ለክፉ ነገር በር አትክፈቱ

ሞትን አትፍሩ ኃጢአትን ፍሩ

ያለድሜ እንዳንቀዘፍ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አባታችን ዮሐንስም ጎልጎታ ደርሰው ከቅዱሳት ቦታዎች ተባርከው ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔዱ። በዚያም 500 ዓመት የኖረ ኹለተኛ እንጦንስ የተባለ አንድ ባሕታዊ ኣገኙ። እመቤታችንም አባ እንጦንስን ታቦተ ኢየሱስን፣ ታቦተ ኪዳነ ምሕረትን እና ታቦተ ጽዮንን እያስጠበቀችው ይኖር ነበር። አባ እንጦንስም ኣቡነ ዮሐንስን ባገኛቸው ጊዜ በልቡ ተደስቶ በመንፈሱ ረክቶ በዐይኖቼ አንተን ያሳየኝ በጆሮዎቹም ቃልህን ያሰማኝ የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን፤ እመቤታችን ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በእጇ የሰጠችኝን ያስጠበቀችኝን እነዚኽን ታቦታት ተቀበለኝ›› ብለው ሦስቱን ጽላት ‹‹ወደ ሀገርህ ይዘህ ሒድ›› ብለው ሰጧቸው። አባታችን ዮሐንስም ‹‹…እኔ እርሱ አይደለሁም እንዴት አወከኝ?› ሲሏቸው አባ እንጦንስም ፈገግ ብለው ከሞተ ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት የሆነውን ሰው በጸሎትህ ከሞት ካስነሣኸው በኋላ ከሀገርህ ከኢትዮጵያ ከዋልድባ ገዳም ከተነሣኽ ዘጠኝ ወር ነው፤ ይኸንንም የእግዚአብሔር መላእክት ነገሩኝ መምጣቱን ተስፋ የምታደርገው ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ከሀገሩ ዛሬ ተነሣ አሉኝ አሏቸው። አባታችን ዮሐንስም እመቤታችን ማርያምን እንዴት አገኘሃት? አሏቸው። አባ እንጦንስም ከልጇ ከወዳጇ ጋር በብርሃን መርከብ ላይ ተቀምጣ መላእክት፣ ነቢያት፣ ሐዋርያት ጻድቃን፣ ሰማዕታት ሲከቧትና በክብር በምስጋና ሲሰግዱላት ግንቦት 21 ቀን በደብረ ምጥማቅ አገኘኋት አሏቸው። እመቤታችንም ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስን ፈቃድህን ለሚያደርጉ ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለዓለሙ ሁሉ የመዳን ተስፋ ስጠኝ አለችው። ጌታችንም ያንጊዜ መላእክትን ከገነት ዕንጨትና ዕብነ በረድ፡ ከጎልጎታ መቃብሩና ከጌቴሴማኒ አፈር እንዲያመጡ አዘዛቸው። መላእክትም የታዘዙትን አምጥተው በሰጡት ጊዜ ጌታችን ከገነት የመጡትን ዕንጨትና ዕብነ በረድ ሦስቱን ታቦታት አድረጋቸው በማለት አባ እንጦንስ ለአባ ዮሐንስ ነገሯቸው።

አቡነ ዮሐንስም ሦስቱን ጽላት ይዘው አንዲት እንደፀሓይ የምታበራ ድንጋይ እየመራቻቸው ሰኔ 12 ቀን ጎጃም ደረሱ። ድንጋዩዋንም መንገድ እንድትመራቸው የሰጣቸው ጌታችን ነው። ከዚያም ውሮ ተብሎ የሚጠራ አንድ ባላባት ቤት ገብተው አድረው በሚገባ ተስተናግደው በቀጣዩ ቀን ድንጋዩዋ እየመራቻቸው ቅዱሳን ከነበሩበት ጫካ ወስዳ አገናኘቻቸው። ቅዱሳኑም ለአቡነ ዮሐንስ የጠበቅንልህን ይኸችን ቦታ ተረከበን የዘለዓለም ማረፊያህ ናትና› ብለው እነርሱ ወደ ኢየሩሳሌም ሔዱ። አባታችንም ታቦተ ኢየሱስን በዚኽች ገዳም ተክለው ቦታዋን መጀመሪያ በተቀበላቸው ሰው በውሮ ስም "ውራ ኢየሱስ ብለው ሰየሟት።

ከዘጠኝ ዓመትም በኋላ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል እየመራቸው ወደ ጣና ወስዶ ዘጌ አደረሳቸውና ታላቋን ዑራ ኪዳነ ምሕረትን ተከሉ።

ከዚያ ቀጥለው ታቦተ ጽዮንን አዴት አካባቢ ተከሉ። እነዚህን ሦስት ገዳማት አቅንተው ከኖሩ በኋላ መልካም የሆነውን ተጋድሏቸውን ፈጽመው ጥቅምት 22 ቀን ዐርብ በ9 ሰዓት ዐረፉ። ከማረፋቸውም በፊት ጌታችን እመቤታችንን፣ መላእክትን፣ ቅዱሳንን ሰማዕታትን አስከትሎ መጥቶ “…ጸሎት አድርጎ መልክህን የደገመ እባብ አይነድፈውም፤ መብረቅ አይገድለውም የሚል ድንቅ የምሕረት ቃልኪዳን ገባላቸው። ዳግመኛም ስምህን የጠራውን መታሰቢያህን ያደረገውን፤ በበዓልህ ቀን ማኅሌት የቆመውን የገድልህን መጽሐፍ የጻፈውን ያጻፈውን ያነበበውን የሰማውን፣ እጅ መንሻ ለቤተ ክርስቲያን የሰጠውን እምርልሃለሁ፤ ልጆቹንም እስከ 15 ትውልድ እባርክልሃለሁ፤ በገዳምህ በውራ መብረቅ ነጎድጓድ፣ እባብ ሰውን አይገድልም የማይጸድቅ ሰው ወደ ገዳምህ አይመጣም" አላቸው።

አባታችንም ካረፉ በኋላ መነኰሳት ልጆቻቸው ሥጋቸውን ተሸክመው ከደብረ ጽዮን ኮቲ ተነሥተው ወደ ውራ ኢየሱስ ለመውሰድ ሲጓዙ በበረሓ ሣሉ መሸባቸውና ፀሓይ ገባች፣ ወዲያውም ሰባት አንበሶች መጥተው እንዳይፈሯቸው መነኰሳቱን በሰው አንደበት ካናገሯቸው በኋላ የአቡነ ዮሓንስን ዐፅም ተሸክመው ሰባት ምዕራፍ ያህል ወሰዱት። ወቅቱ ቢመሽባቸውም በእግዚአብሔር ፈቃድ ፀሓይ ግን በተኣምራት ወጣችላቸውና ውራ ኢየሱስ ገዳም በሰላም ደረሱ። ያንጊዜም ፀሓይ ገባች፤ አንበሶቹም እጅ ነሥተው ወደ ቦታቸው ተመለሱ።

አቡነ ዮሐንስ መላ ዘመናቸውን የማያዩ ዐይነ ሥውራንን እንዲያዩ፣ የማይሰሙ እንዲሰሙ፣ የማይራመዱ እንዲራመዱ በማድረግ፤ ሕሙማንን በመፈወስ፣ ሙታንን በማስነሣት በርካታ ተኣምራትን በማደረግ ወንጌልን በመስበክ ያገለገሉ ሲሆን ከዕረፍታቸውም በኋላ በርካታ ድንቅ ድንቅ ተኣምራትን አድርገዋል። ከተኣምራታቸውም አንዱ ይኸ ነው፡- ንዑድ ክቡር ልዩ በሚሆን በአባታችን ዮሐንስ የዕረፍታቸው ቀን ጥቅምት 22 ቀን አንድ ዐረማዊ እስላም ሰው ለተሳልቆና ለመዘባበት ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ቈረበ። በአባታችን በዓል ዕለትም ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብሎ ወጥቶ እየተቻኮለ ሔዶ ከእስላሞች መስጊድ ገብቶ በአባታችን በዮሐንስ በዓል ምክንያት የቆረበውን ቍርባን ተቀብሎ በወገኖቹ በከሃዲያኑ እስላሞች ፊት ተፋው። ወዲያውም የዚያ እስላም ሰው መላ ሰውነቱ አበጠ በንፋስ ገመድነትም ታንቆ ሰዎች እስኪያዩት ድረስ በሰማይና በምድር መካከል ተሰቀለ።

በተሰቀለበትም ቦታ ወፎችና አሞራዎች ይበሉት ጀመር፤ ሥጋውንም በሉት። በዚኽም ጊዜ ያ እስላም ድምፁን ከፍ አድርጎ ‹‹እኔ ንዑድ ክቡር ልዩ በሆነ በአባታችን በዮሐንስ አምላክ አምኛለሁ ብሎ መሰከረ። እግዚኣብሔርም የገዳማት ኮከብ በሆነው በብፁዕ ዮሓንስ ልመናና ጸሎት ፈጽሞ ይቅር አለው። ከዚኽም በኋላ ለብቻው ቀኖና ገባ የቀኖና ሥርዓቱንም ጨርሶ ንስሓ ገብቶ ከባለቤቱ ከልጆቹ ከቤተሰቦቹና ከዘመዶቹ ከጎረቤቱቹ ሁሉ ጋር የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቀ ስሙንም ገብረ ዮሐንስ አሉት ትርጓሜውም የዮሐንስ ባለሟል ማለት ነው።

የአቡነ ዮሐንስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን።
(ምንጭ በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን መጽሐፍ ገጽ 472-477)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ከዚህም በኋላ ወደ ሀገረ ስብከታቸውና ወደ ሕዝባቸው መመለስን በአሰቡ ጊዜ ስለ ቅድስናቸውና ስለ ትምህርታቸው ጣዕም ስለ ወደዳቸው የተከበረው ንጉሥ መመለስን ከለከላቸው በእርሱ ዘንድ እነርሱ እንደ እግዚአብሔር መላእክት ሁነዋልና ፊታቸውም እንደ ፀሐይ ያበራል።

ከጥቂት ወራትም በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም ሊአሳርፈው እግዚአብሔር በወደደ ጊዜ በላዩ ደዌ ላከበት በዚያውም ደዌ በሰላም አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_አላኒቆስ

ዳግመኛም በዚህች ቀን ታላቁ ጻድቅ አቡነ አላኒቆስ ዕረፍታቸው ነው፡፡ አቡነ አላኒቆስ የትውልድ ቦታቸው ሸዋ አንኮበር ሲሆን አባታቸው ንጉሡ ዐፄ ይኩኖ አምላክ ነው፡፡ ንጉሡ አባታቸው ‹‹አግባና መንግሥቴን ይዘህ ተቀመጥ›› ቢላቸው እርሳቸው ግን ንግሥናን በመናቅ እምቢ ብለው ሄደው ከእመቤታችን ሥዕል ሥር ወድቀው ቢለምኗት እምቤታችን ተገልጣላቸው ‹‹ክፍልህ ምናኔ ነው፣ የአባትህ መንግሥት ያልፋል የልጄ መንግሥት ግን ዘላለማዊ ነው›› አለቻቸው፡፡ ጻድቁም ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ሄደው በዚያው መንኩሰው ገዳሙን እያገለገሉ ተቀመጡ፡፡ ከጸሎታቸው በኋላ ራሳቸውን ወደ ባሕሩ ይጥሉ ነበርና አንድ ቀን እንዲሁ ራሳቸውን ወደ ባሕሩ ሲጥሉ መላእክት አውጥተዋቸዋል፡፡ አቡነ አላኒቆስ ወደ አክሱም እንዲሄዱ ታዘው ከሄዱ በኋላ በዚያም የጽላተ ሙሴ የታቦተ ጽዮን አጣኝ ሆነው 40 ዓመት ተቀምጠዋል፡፡ እመቤታችንም ተገልጣላቸው በዓታቸውን እንዲያጸኑ ከነገረቻቸው በኋላ ከአክሱም ወጣ ብሎ የሚገኘውን ማይበራዝዮ ገዳምን መሠረቱ፡፡ በዚያም እጅግ አስገራሚ ተአምራትን እያደረጉ ወንጌልን እያስተማሩ አገልግለዋል፡፡

አንድ ቀን መኰንኑ ወደ ሩቅ ቦታ ሲሄድ ቤተሰባቸውን ለንስሓ አባታቸው አደራ ሰጥተው ሄዱ፡፡ የንስሓ አባታቸውም የአቡነ አላኒቆስ ጓደኛ ነበሩ፡፡ መኰንኑም ከሄዱበት ሲመለሱ ሚስታቸው ከአሽከሯ አርግዛ ጠበቀቻቸው፡፡ ‹‹ከማን አረገዝሽ?›› ብለው ጽኑ ግርፋት ቢገርፏት ዋሽታ ‹‹ያረገዝኩት ከንስሓ አባቴ ነው›› አለች፡፡ መኰንኑም መነኩሴውን እገላለሁ ብሎ ሲነሣ መነኩሴውም ወደ አቡነ አላኒቆስ ሄደው አለቀሱ፡፡ አቡነ አላኒቆስም የመኰንኑን ሚስት ቢጠይቋት ባሏን ፈርታ ‹‹አዎ ከመነኩሴው አባት ነው ያረገዝኩት›› አለች፡፡ እሳቸውም ‹‹የተረገዘው ከዚህ መነኩሴ ከሆነ በሰላም ይወለድ፣ ካልሆነ ግን አይወለድ›› ብለው በቃላቸው አስረውና ገዝተው ሸኟቸው፡፡

በግዝታቸው መሠረት ሴቲቱ ድፍን 22 ዓመት ሙሉ ሳትወልድ በጭንቅና በጣር ኖረች፡፡ በአልጋ ላይ ሆና ተጨንቃ ስትኖር በመጨረሻ ለቤተሰቦቿ ተናግራ ወደ አቡነ አላኒቆስ ዘንድ በቃሬዛ ወሰዷትና ይቅርታ ጠይቃ እውነቱን ተናገረች፡፡ እሳቸውም ‹‹እግዚአብሔር ይፍታሽ›› ቢሏት 22 ዓመት ሙሉ ተረግዞ የነበረው ልጅ ትልቅ ሰው ሆኖ ጥርስ አውጥቶ፣ ፂም አብቅሎ በሰላም ተወለደ፡፡ እርሱም ከተወለደ በኋላ አባቱ ማን እንደሆነ ተናገረ፡፡ ጻድቁ አባታችንም ልጁን አሳድገውት አስተምረው አመንኩሰውታል፡፡ ስሙንም ተወልደ መድኅን አሉት፡፡ በስሙ የተሠሰራ ቤተ ክርስቲያን በትግራይ ጽንብላ ወረዳ ይገኛል፡፡

ጻድቁ አቡነ አላኒቆስ ሌላም የሚታወቁበት አንድ ግብር አላቸው፡፡ የማይበራዝዮ ገዳማቸው አገልጋይ የሆነው መነኩሴ በሬ ጠምዶ ሲያርሱ አንበሳ ከጫካው ወጥቶ አንዱን በሬ በላው፡፡ መነኩሴውም መጥተው ለአቡነ አላኒቆስ ነገሯቸው፡፡ እሳቸውም ‹‹ጸሎቴን እስክጨርስ ድረስ ወደ ጫካው ሂድና አንበሳውን ‹አላኒቆስ ባለህበት ጠብቀኝ እንዳትንቀሳቀስ ብሎሃል› ብለህ ተናገር›› ብለው ለመነኩሴው ነገሯቸው፡፡

መነኩሴውም እንደታዘዙት ወደ ጫካው ሄደው ጮኸው በሉ የተባሉትን ተናገሩ፡፡ አቡነ አላኒቆስም ጸሎታቸውን ሲጨርሱ ወደ ጫካው ሄደው አንበሳውን የበላውን በሬ አስተፍተውት በሬውን ነፍስ ዘርተውበት ከሞት አስነሥተው ዕለቱን እንዲታረስ አድርገውታል፡፡ አንበሳውንም ገዝተው ወደ ገዳማቸው ወስደው ሰባት ዓመት ውኃ እያስቀዱት እንዲያገለግላቸው አድርገውታል፡፡

አቡነ አላኒቆስ አንበሳውን አስረው ያሳድሩበት የነበረው ዛፍና ውኃ ያጠጡበት የነበረው ትልቅ የድንጋይ ገበታ ዛሬም ድረስ በገዳሙ ይገኛል፡፡ ከ22 ዓመት እርግዝና በኋላ ሴቲቱ ጥርስና ፂም ያለው ልጅ እንድትወልድ ያደረጉበት ትልቅ ጠፍጣፋ ድንጋይም ከነቅርጹ በገዳሙ በግልጽ ይታያል፡፡ ጻድቁ ጥቅምት 21 ቀን ዐርፈው በዚያው በማይባራዝዮ ገዳማቸው ተቀብረዋል፡፡ ጸበላቸው እጅግ ልዩ ነው፣ ያላመነውን ሰው አስፈንጥሮና ገፍትሮ ይጥለዋል እንጂ አያስቀርበውም፡፡

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አባቶች ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት እና #ከገድላት_አንደበት)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ጥቅምት 21/2017 #እናታችን_ማርያም "በቅዱስ መፅሐፍ"

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና
በፀሎት ለምንማፀንበት #ለእናታችን_ማርያም ወርሐዊ የእረፍት መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን

👉ይህች እንደ ማለዳ ብርሃን የምትጎበኝ እንደ #ጨረቃ የተዋበች እንደ #ፀሐይም የጠራች ዓላማ ይዞ እንደ ተሰለፈ ሠራዊት የምታስፈራ ማን ናት (መኃ 6፣10)

👉መዐዛዋም እንደ #ከርቤና_እንደ_ዕጣን የኾነችው ከልዩ ከነጋዴ ቅመም ዅሉ የኾነችው ይህች ከምድረ በዳ እንደ ጢስ ምሰሶ የወጣችው ማን ናት (መኃ 3፣6) መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው (መዝ 86፣1)

👉ርግቤ መደምደሚያዬም አዲት ናት ለእናትዋ አንዲት ናት ለወለደቻትም #የተመረጠች ናት ቆነጃጅትም አይተው አሞገሷት ነገሥታትና ቁባቶችም #አመሰገኗት (መኃ 6፣9)

👉የሠራዊት ጌታ #እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንን እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር (ኢሳ1፣9)

👉ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ በእኔ ዘንድ ያማረ ነው ምንም ምን #ነውር_ነቀፋ_የለብሽም (መኃ 4፣7) #የእግዚአብሔር ሀገር በአንቺ የተደረገው ድንቅ ይባላል (መዝ 86፣3)

👉 #እግዚአብሔር ጽዮንን መርጧታልና ማደሪያውም ትኾነው ዘንድ ወዷታልና እንዲህ ብሎ ይህች ለዘለዓለም ማረፊያዬ ናት መርጫታለኹና በዚች ዐድራለኹ አሮጊቶቿን እጅግ እባርካለኹ ድኻዎቿንም እንጀራ አጠግባለኹ ካህናቶቿንም ደኅንነትን አለብሳቸዋለኹ ቅዱሳኖቿም ደስ ይላቸዋል (መዝ131፣13)

👉ባንቺ የሚኖሩ ሁሉ ደስ እንደሚላቸው ይነግራቸዋል
(መዝ 86፣7) እህቴ ሙሽራዬ #የተቆለፈች ገነት የተዘጋች ምንጭ የታተመም ፈሳሽ ናት (መኃ 4፣12)

👉ወደ ምሥራቅም ወደሚመለከተው በስተውጭ ወዳለው ወደመቅደሱ በር አመጣኝ ተዘግቶም ነበር እግዚአብሔርም ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም ሰውም አይገባበትም የእስራኤል አምላክ #እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግታ ትኖራለች (ሕዝ 44፣1)

👉ልጄ ሆይ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ ንጉሥ ውበትሽን ወዷልና እርሱ ጌታሽ ነውና
(መዝ 44፣10) መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከዅሉ #ትበልጫለሽ (ምሳ 31፣29)

👉መልአኩም ወደ እርሷ ገብቶ #ደስ_ይበልሽ_ፀጋ የሞላብሽ ሆይ ጌታ ከአንቺ ጋራ ነው አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት (ሉቃ1፣28)

👉ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማሕፀኗ ውስጥ ዘለለ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች አንቺ ከሴቶች መካከል #የተባረክሽ ነሽ የማሕፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው (ሉቃ1 ፣41)

👉ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ እግዚአብሔር የፅዮንን ደጆች ይወዳቸዋል (መዝ 86፣2)

👉የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ የናቁሽም ዅሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ #የእግዚአብሔርም ከተማ የእስራኤል ቅዱስ የኾንሽ ፅዮን ይሉሻል (ኢሳ 60፥14)

👉በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና #ንግሥቲቱ በቀኝኽ ትቆማለች (መዝ 44፣9)

👉ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ዅሉ ክብሯ ነው ልብሷ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው በዃላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ ባልንጀራዎቿንም ወዳንተ ያቀርባሉ በደስታና በሐሴት ይወስዷቸዋል ወደንጉሥ ዕልፍኝም ያስገቧቸዋል(መዝ 44)

👉በአባቶችሽ ፋንታ #ልጆች_ተወለዱልሽ በምድርም ዅሉ ላይ ገዢዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ ለልጅ ልጅ ዅሉ ስምሽን ያሳስባሉ (መዝ 44፣13)

👉እንሆም ከዛሬ ዠምሮ ትውልድ ዅሉ #ብፅዕት_ይሉኛል ብርቱ የኾነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጓልና (ሉቃ1፣48)

👉መልአኩም እንዲህ አላት ማርያም ሆይ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ እንሆም ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ስሙንም #ኢየሱስ ትይዋለሽ (ሉቃ 1፣30)

👉መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት መንፈስ ቅዱስ ባንቺ ላይ ይመጣል የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ #የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል (ሉቃ1፥35)

👉የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይኾንልኛል እንሆ የሰላምታሽ ድምፅ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማሕፀኔ በደስታ ዘሏልና ከጌታ የተነገረላት ቃል ይፈፀማልና ያመነች ብፅዕት ናት
(ሉቃ 1፣43)

👉ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮቿ በታች ያላት በራሷም ላይ #የአሥራ_ኹለት_ከዋክብት አክሊል የኾነላት አንዲት ሴት ነበረች (ራእ12፣1)

👉ሰው #እናታችን_ፅዮን ይላል በውስጧም ሰው ተወለደ ነገሥታትም አሳዳጊ አባቶችሽ ይኾናሉ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይኾናሉ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ

👉እኔም #እግዚአብሔር እንደ ኾንኹ ታውቂያለሽ እኔንም በመተማመን የሚጠባበቁ አያፍሩም (ኢሳ 49፣23) ስለ እናታችን ማርያም በመፅሐፍ ቅዱስ ዉስጥ ከተፃፉ ጥቅሶች በጥቂቱ

👉ለቃል መውረድ ለሥጋ ማረግ ምክንያት ናትና የትንቢተ ነብያት ማረፊያ የስብከተ ሐዋርያት መነሻ #ሰዓሊተ_ምሕረት መዝገበ ፀሎት ለወዳጆቿ ሙሓዘ ፍሥሐ በጠላትነት ለተነሡባት ግን ዓላማ ይዞ እንደተሰለፈ ሠራዊት የምታስፈራ ናት

👉በፍቅሯ እናታችን በክብሯ እመቤታችን ስለ ክብረ ድንግልናዋ ስለ አማላጅነትዋ የተወደሰችና የተመሠገነች ትሁን አምላካችን #መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከእናታችን ከእመቤታችን ከወላዲተ አምላክ #ቅድስት_ድንግል_ማርያም በረከትና ረድኤት ያሣትፈን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Anem ezwa nw yemamrw minw chiger al

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

👉ወደ በዓቱም ያ ረድእ በገባ ጊዜ በምድር ላይ ሰግዶ እንዳረፈ #አባ_ዮሐንስን አገኘውና ታላቅ ልቅሶን በላዩ አለቀሰ ከዚያም በኋላ ወደ መነኰሳቱ መንደር ፈጥኖ በመሔድ ቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐፂር እንደ አረፈ ነገራቸው እነዚያም መነኰሳት አክብረው ገንዘው ሥጋውን ተሸክመው ወስደው በቦታቸው አኖሩት

👉የደረቀ ዕንጨት ተክሎ በአበቀለበት ላይ በሠራት የራሱ በሆነች #ቤተ_ክርስቲያን ውስጥ ልጆቹ ከዚህ አፍልሰው ወስደው እስከ አኖሩት ድረስ በዚያ ኖረ የአባታችን የፃድቁ #የአባ_ዮሐንስ_ሐፂር ረድኤት በረከት ቃል ኪዳን ለሁላችንም ይድረሰን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

"ትሑት" ሰው አጋንንትን አይፈራም እግዚአብሔር ሁሉን ያስገዛለታልና።
#አባ_መቅሪስ/

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🌹 "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌹

🌹 #ጥቅምት ፳ (20) ቀን።

🌹 እንኳን #ለታላቁ_ለትሕትናና_ለትዕግስተኛው አባት ለክቡሩ፤ ለገናና ለሆነ #ለአባ_ዮሐንስ_ሐጺር_ለዕረፍት በዓልና የስሙ ትርጓሜ ጠባቂና አዳኝ ለሆነ #ለታላቁ_ነቢይ_ለቅዱስ_ኤልሳዕ_ለልደቱ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።


✝ ✝ ✝
🌹 #አባ_ዮሐንስ_ሐፂር፦ የዚህ ቅዱስ ወላጆቹ ከላይኛው ግብጽ ናቸው እነርሱም እግዚአብሔርን የሚፈሩ ናቸው ግን ከእርሱ በቀር ልጅ የላቸውም የዚህ ዓለምም ብልጽግና ቢሆን የላቸውም ነገር ግን በበጎ ሥራ ባለጸጎች ናቸው ይህንንም ቅዱስ እያስተማሩ በበጎ አስተዳደግ አሳደጉት።

🌹 የዚህም ቅዱስ ዕድሜው ዐሥራ ስምንት ዓመት ሲሆነው የእግዚአብሔር ቸርነት አነሣሥታው የመላእክት የሆነ አስኬማን ይለብስ ዘንድ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ ይኸውም የምንኵስና ልብስ ነው። ከዚያም በደረሰ ጊዜ አባ ባይሞይ የሚባለውን አንዱን አረጋዊ አባት ተገናኘው ዮሐንስም ሰገደለትና ወደ እርሱ እንዲቀበለው ለመነው ሽማግሌውም አባት "ልጄ ሆይ ያንተ በዚህ መኖር ልክ አይደለም በዚች ገዳም የሚኖሩ በእጆቻቸው ይሠራሉ በቀንና በሌሊት ይጾማሉ ይጸልያሉ በሚተኙም ጊዜ ያለ ምንጣፍ በምድር ላይ ይተኛሉ አንተ ወጣት ጎልማሳ ስለሆንክ ይህን ሁሉ ችግር አትችልም። ነገር ግን ወደ ዓለም ተመልሰህ እንደ ሰው ሁሉ በጎ አኗኗርን ትኖር ዘንድ ይሻልሃል የዚች ገዳም ኑሮ ጭንቅ ነውና" አለው።

🌹 አባ ዮሐንስም እንዲህ አለው እኔ በጥላህ ሥር ልኖር መጥቼአለሁና ስለ እግዚአብሔር ብለህ ተቀበለኝ እንጂ አትመልሰኝ ይህም አባ ባይሞይ እግዚአብሔርን ሳይጠይቅ ምንም ሥራ አይሠራምና በዚያን ጊዜ ሥራውን ይገልጥለት ዘንድ ስለ ዮሐንስ ሐፂር እግዚአብሔርን ለመነው የእግዚአብሔርም መልአክ ተገልጦለት "እርሱ የተመረጠ መሳሪያ ይሆናልና ተቀበለው ብሎሃል" አለው።

🌹 ከዚህም በኋላ ዮሐንስ ሐፂርን ወስዶ ወደ ቤተ ክርስቲያን አስገባው የምንኵስና ልብሶችንም አምጥቶ በላያቸው ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ጸለየ ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጾ በመስቀል ምልክት በልብሶቹ ላይ አማተበ ሽማግሌውም እነዚያን ልብሶች ለአባ ዮሐንስ አለበሰው።

🌹 ከዚያቺም ቀን ጀምሮ አባ ዮሐንስ ተጋድሎንና አገልግሎትን ጀመረ አባ ባይሞይም ሊፈትነው ወደደ በአንዲትም ቀን ደብድቦ "ከአንተ ጋር መኖር አልሻም" ብሎ ከበዓቱ አስወጥቶ አባረረው የከበረ አባ ዮሐንስም ከሜዳ መካከል በውጭ ቆመ በየቀኑም በጥዋት እየወጣ "ከእዚህ ላይህ አልሻም" እያለ ይመታዋል እርሱ ግን "አባቴ ሆይ ይቅር በለኝ" ብሎ ከእግሩ በታች ይሰግዳል። በሰባተኛዪቱም ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሊሔድ ሽማግሌው አባ ባይሞይ ወጣ አባ ዮሐንስንም ሰባት መላእክት ከበው አክሊላትን ሲያቀዳጁት አያቸው ከዚያንም ጊዜ ወዲህ መፈተኑን ተወው ወደ መኖሪያውም አስገባው።

🌹 ከዚህም በኋላ በአንዲት ቀን አባ ባይሞይ የደረቀ ዕንጨት አግኝቶ ወስዶ ለአባ ዮሐንስ ሰጠውና "ይህን ዕንጨት ትከለው እስከሚበቅልና እስከሚአፈራ ድረስ ውኃን አጠጣው" አለው። አባ ዮሐንስም ለአባቱ ታዛዥ በመሆን ተቀብሎ ወስዶ ተከለው በየቀኑም ሁለት ሁለት ጊዜ ያጠጣዋል ውኃውም ዐሥራ ሁለት ምዕራፍ ያህል የራቀ ነው። ከሦስት ዓመትም በኋላ ያ ዕንጨት አቈጥቊጦ በቀለ ታላቅም ዛፍ ሁኖ አብቦ ጣፋጭ ፍሬን አፈራ። አባ ባይሞይም ከፍሬው ለቅዱሳን አረጋውያን ወሰደላቸውና "የታዛዡንና የትሑቱን ፍሬ እነሆ ብሉ" አላቸው እነርሱም ይህን ድንቅ ተአምር አይተው አደነቁ ለመምህሮቻቸው ለሚታዘዙ እንዲህ ያለ ጸጋ የሚሰጥ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።

🌹 አባ ባይሞይም ዐሥራ ሁለት ዓመት ያህል በጽኑዕ ደዌ ውስጥ ተይዞ ኖረ አባ ዮሐንስም ያገለግለው ነበር አባ ዮሐንስን እንደፈተነው የተመረጠ መሥዋዕትን ይሆን ዘንድ በዚህ ደዌ እንዲፈተን እግዚአብሔር ፈቅዷልና። በሚሞትበትም ጊዜ አባ ባይሞይ ቅዱሳን አረጋውያን መነኰሳትን ሰበሰባቸውና አባ ዮሐንስንም እጁን ይዞ "እርሱ ሰው ያይደለ መልአክ ነውና ተቀብላችሁ ጠብቁት" ብሎ ሰጣቸው። እርሱንም ደግሞ እንዲህ አለው "ከዕረፍቴ በኋላ ያን ዕንጨት ወደ ተከልክበት ቦታ በዚያ ኑር እግዚአብሔር ላንተ ያዘጋጀልህ ነውና ብዙዎችም በአንተ እጅ ይድናሉ መታሰቢያህም በዚያ ጸንቶ ይኖራል ዜናህም በዓለም ሁሉ ይወጣል" ይህንንም ተናግሮ ዐረፈ አክብረውም ቀበሩት።

🌹 ከዚህም በኋላ ቅዱስ አባ ዮሐንስ አረጋዊ አባቱ አባ ባይሞይ እንደነገረው ወደዚያ ቦታ ሒዶ ኖረ ዜናውም በዓለም ሁሉ እጅግ እስከ ተሰማ ድረስ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ። በራሱ ቤተ ክርስቲያንም አበ ምኔት ሁኖ ተሾመ በሹመቱም ጊዜ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስ እጆቹን በራሱ ላይ ሲጭን "አክዮስ አክዮስ አክዮስ" የሚል ቃል ከሰማይ ተሰማ ይህም "ይገባዋል ይገባዋል ይገባዋል" ማለት ነው። የቊርባን ቅዳሴን በሚቀድስ ጊዜ ቅዱስ ቊርባንን መቀበል የማይገባቸውን ይለያቸዋል "ዛሬስ ሒዳችሁ ንስሓ ግቡ ከዚያም በኋላ ተመልሳችሁ ሥጋውን ደሙን ተቀበሉ" ይላቸዋል።

🌹 ይህን አባ ዮሐንስንም ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስ የቅዱሳን የሠለስቱ ደቂቅን ሥጋቸውን እንዲአመጣለት ወደ ባቢሎን ልኮታል ይህም በግንቦት ወር በዐሥረኛው ቀን ተጽፎአል።

🌹 በአንዲትም ዕለት አንድ መነኰስ ሊጎበኘው ወደ በዓቱ ቢመጣ አባ ዮሐንስን ተኝቶ አገኘው የእግዚአብሔርም መላእክት በላዩ ይጋፉ ክንፎቻቸውንም ያርገበግቡ ነበር አንዱም ሌላውን "ተወኝ ክንፌን በላዩ ላኑር ይለዋል" ይህንንም አይቶ እግዚአብሔርን አመሰገነው ።

🌹 ከዚህም በኋላ የመነኰሳቱን መንደር ሊበረብሩ የበርበር አረማውያን ወደ አስቄጥስ ገዳም በመጡ ጊዜ አባ ዮሐንስም ወደ አባ እንጦንስ ገዳም ወደ ቁልዝም ሔደ በዚያም በአባ እንጦንስ ገዳም በጎኑ በአለ ቦታ ተቀመጠ እስከ ሚያርፍባትም ቀን ድረስ የሚያገለግለው አንድ የታመነ ሰውን እግዚአብሔር አመጣለት።

🌹 ከዚህም በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም ሊአሳርፈው በወደደ ጊዜ እግዚአብሔር ቅዱሳን ጻድቃኖቹን አባ እንጦንስን፣ አባ መቃርስን፣ አባ ጳኵሚስን ከእርሳቸውም ጋር መንፈሳዊ አባቱ አባ ባይሞይን ያረጋጉትና ከዚህ ከኃላፊው ዓለም መለየቱን ይነግሩት ዘንድ ወደርሱ ላካቸው። እነርሱም እንዲህ ብለው አረጋጉት "ደስ ይበልህ እግዚአብሔር የማያልቅ ተድላ ደስታን አዘጋጅቶልሃልና" ክብር ይግባውና ጌታችንም እንዳዘዘ "በእሑድ ቀን ሁለተኛ ወዳንተ መጥተን ወደ ዘላለም ሕይወት እንወስድኻለን" ባርከውትም ከእርሱ ዘንድ ተመለ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

መቀደስንና መልካም የሆነ ብርሃናዊ ሕይወትን ገንዘብ ማድረግ የሚገባን ስለ መሆኑ የተናገረውም ራሱ መምህራችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው

እንዲህ ብሎ፡-

መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ
ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።" ማቴ. 5፡16

እነዚህ መልካም ሥራዎችም በዋናነት ጌታችን ይህን አባታዊ ትእዛዝ ከመናገሩ ቀደም አድርጎ በማቴዎስ ወንጌል በምዕራፍ አምስት መጀመሪያ ላይ የተናገራቸው ናቸው

እንዲህ ብሎ፦

👉በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፣ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።
👉የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው መፅናናትን ያገኛሉና።
👉የዋሆች ብፁዓን ናቸው፣ ምድርን ይወርሳሉና።
👉 ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፣ ይጠግባሉና።
👉የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፣ ይማራሉና።
👉ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፣ እግዚአብሔርን ያዩታልና።
👉 የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፡ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።
👉ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፡ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።

👉ሲነቅፏችሁና ሲያሳድዷችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓንናችሁ፤ ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፡ ሐሴትም አድርጉ ማቴ. 5:3-12

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች ሆይ

ችግራችንን ለሰው ነግረን ይሆናል
ከሰዎች ያገኘነው የመጀመሪያ እርዳታ
አይይ የሚል መልስ ነው።
ከዚህ ውጭ የለም
ይልቁንም እንደሱ ስላላደረከኝ አመሰግናለሁ ይልብሀል

የእግዚአብሔር ወዳጆች

ያየብንን ያላሳየብን
የሰማብንን ያላሰማብን
ጉዳችን ና ገበናችንን የተሽከመልን
እርሱ መድኃኔዓለም ነው።

ት.ኤር ም ፦ 9 ላይ እንዲህ ይላል።

በሰው የታመነ እርሱ የተረገመ ነው ይላል ።
በእግዚአብሔር የታመነ እርሱ ለዘለዓለም የተባረከ ነው ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

ዘመን መገላበጡ አይቀርም
የተሾመ መሻሩ አይቀርም
ያጣ ማግኘቱ አይቀርም
የከሳ መወፈሩ የወፈረ መቅጠኑ አይቀርም

ያጣ ያገኛል የታመመ ይድናል
ጤነኛም ይታመማል

በዘመን አትመኩ
ባላችሁ ነገር አትመኩ
ቤተ እግዚአብሔርን አክብሩ

በዘመን ከመማከት ፈጣሪ አምላክ ይጠብቀን🙏


ርዕስ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ጥቅምት 25/2017 #ሰማእቱ_ቅዱስ_መርቆሬዎስ

"ስለአንተ ብለን ሁል ጊዜ ተገድለናል እለት
እለት እንደሚታረዱ በጎች ሆነናል"
መዝ.43፥22

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ወርሐ ክረምቱን እንዲባርክልን ለምንማፀንበት ስም በሰማእቱ ስም ለምናመሰግንበት ለሰማእቱ #ቅዱስ_መርቆሪዮስ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉ወር በገባ በ25 የታላቁ ሰማእት #የቅዱስ_መርቆሪዮስ መታሰቢያ በዓል ሲሆን ቅዱስ መርቆሪዮስ የቀድሞ ስሙ #ፒሎፓደር ሲሆን ትርጉሙም #የአብ ወዳጅ #የወልድ አገልጋይ ማለት ነዉ

👉በወጣትነቱ ከሃዲው ንጉስ ኡልያኖስ ላቆመው ጣኦት አልሰግድም ብሎ የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይችለውን መከራ ተቀበለ በመጨረሻም #ህዳር_25 ቀን አንገቱን ቆርጠው ገደሉት #ደም_ውኃና_ወተት ከአንገቱ ፈሰሰ

👉ንጉሱ በዚያዉ ዘመን #ክርስቲያኖችን በጣም ያሰቃይ ነበር #ቅዱስ_ባስልዮስም ይገስፀዉ ነበር በዚህም ምክንያት ንጉሱ ቅዱስ ባስልዮስን አሰረዉ ጳጳሱ በታሰረበት እስር ቤት የቅዱስ #መርቆርዮስ ሥዕል ነበር

👉 #ቅዱስ_ባስልዮስም ከሥዕሉ ስር በመሆን ፀለየ ሥዕሉም ከቦታዉ ታጣ ያ ሥዕል ወደ ዑልያኖስ ቤት ሄዶ በጦር ወግቶ ገደለዉ በስዕሉ ላይ ያለዉ ጦር ጫፉ ደም ይንጠባጠብ ነበር ቅዱስ ባስልዮስም ከሀዲ ዑልያኖስን #ቅዱስ_መርቆሪዮስ በሥዕሉ አማካኝነት እንደገደለዉ አዉቆ #እግዚአብሔርን አመሰገነ

👉ይህ ሰማዕት በአገራችን በስሙ በርካታ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት አሉት በተለይም #ቅዱስ_ላሊበላ ካነፃቸው 11 ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አንዱን #ቤተ_መርቆሬዎስ ብሎ ሰይሞለታል

👉በዚህ በሰሜን ሸዋ ደግሞ የሚገርም ገዳም አለው ካህናት በማህሌት ወረብ ሲያቀርቡ #ስዕሉ_ያሸበሽባል ይዘላል ይህንንም አይቶ ማረጋገጥ ይቻላል በመዲናችን አዲስ አበባ #ቅዱስ_ኡራኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ ታቦቱ አለ

👉 #መርቆሪዎስ ከሞተ በኋላ ፈረሱ ለሰባት ዓመት ወንጌልን አስተምሯል በኋላም አንገቱን ቆርጠው ገድለውታል የሚገረም ካለ #የበልአምን_አህያ_ይጠይቃት እኛስ #ለእግዚአብሔር የሚሳነዉ ነገር የለም ብለን እንመልሳለን ዘኁልቁ.22፥28 ቅዱስ ጴጥሮስም እንዲህ አለ ቃል የሌለው አህያ በሰው ቃል ተናግሮ የነብዩን ቁጣ አገደ ይላል 2ኛ ጴጥ.2፥16

👉የሰማእቱ #ቅዱስ_መርቆርዮስ ፀሎቱ ምልጃዉ አይለየን በረከቱ ለሁላችንም ይድረሰን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

"✝" እንኳን አደረሳችሁ "✝"

✝ ታላቁ ጻድቅ #አቡነ #ኤልሳዕ (የአቡነ ተክለሃይማኖት ደቀመዝሙር፡ ንቡረዕድና የደብረ ሊባኖስ 2ኛው አበ ምኔት) ✝

✝በ1296 (1306) ዓ/ም እዚህች ቦታ ላይ (#ደብረ #አስቦ ላይ) ቅዱስ አቡነ #ተክለሃይማኖት ዐረፉ፡፡

✿ነሐሴ 24 ቀን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን የገነዙት ደቀ መዝሙራቸው #አቡነ #ኤልሳዕ ነበሩ፡፡

✿ጻድቁ አቡነ ኤልሳዕ በመንበረ ተክለ ሃይማኖት ለ3 ወራት በቅድስና ኑረው ከአባ ተክለ ሃይማኖት መልእክት (ጥሪ) ደርሷቸዋል፡፡

✿ከቅዱሳን አንዱ ከሞት ተነስቶ "ኤልሳዕን ጥሩ፡፡ ፊልጶስን በመንበሩ አኑሩ፡፡" ብሎ ዐረፈ፡፡

✿በ1297 (1307) ጥቅምት 23 ቀንም (ማለትም ዛሬ) ቅዱስ አባ ኤልሳዕ ዐርፈው ቅዱሳን ቀብረዋቸዋል፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

Sira yemitfligu awarugn

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ጥቅምት 23/2017 #ሰማእቱ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በሰማእቱ ስም ለምናመሰግንበት #ለቅዱስ_ጊዮርጊስ ወርሐዊ መታሰቢያ ክብረ በዓል እንኳን አደረሰን

👉ታላቁ ሰማዕት #ቅዱስ_ጊዮርጊስ አባቱ የፍልስጤም መኮንን ዞሮንቶስ (እንስጣቴዎስ) እናቱ ደግሞ (አቅሌሲያ) ቴዎብስታ ትባላለች በፍልስጤም ልዳ ጥር 20 በ277 ዓ.ም ተወለደ ጊዮርጊስ ማለት ኮከብ ብሩህ ሀረገ ወይን ፀሐይ ዘልዳ ማለት ነው

👉 #ቅዱስ_ጊዮርጊሰ በፋርስ በኢራን ዱድያኖስ የተባለ ንጉሥ ነገስታቱን ሰብስቦ ሰባ ጣኦታትን ሲያሰግድ ተመለከተ በዚህን ጊዜም ቤተ መንግስት ድረስ በመገስገሰሰ ተቃውሞውን በማሰማት ክርስቲያን መሆኑን መስክሯል ከዚህም በኋላ በተለያዩ ነገስታት #ቅዱስ_ጊዮርጊስ በሰው ህሊና ሊታሰቡ የማይቻላቸው አስራ ዘጠኝ መከራዎች ደርሰውበታል ቅዱስ ጊዮርጊስ ሶስት ጊዜ ሞቶ ሶስት ጊዜ ተነስቷል #የእግዚአብሔር ተአምር በተደጋጋሚ ተገልፆለታል

👉 #የቅዱስ_ጊዮርጊስ መከራ በጥቂቱ ክርስቲያን በመሆኑ ብቻ ወደ እስር ቤት ተወረወረ እጆቹንና እግሮቹን ታስሮ ተገረፈ የብረት ጫማ አጥልቀው አስኬዱት ከብረት አልጋ ላይ አስተኝተው እሳት አነደዱበት እጆቹን የኋሊት አሰሩት በመጋዝ ለሁለት ሰነጠቁት የጋለ ሳህን ከጭንቅላቱ ላይ አስቀመጡበት ሰውነቱን በጩቤ ፈተፈቱት ችቦ እና እሳት አንድደው በግራና በቀኝ አቃጠሉት

👉ምላሱን በቢላዋ ቆረጡት በአፍንጫው ቀዳዳዎች በሚስማር መተው ቸነከሩት በመጥረቢያ ፈለጡት ቅጥራን አፍልተው በጭንቅላቱ ላይ ደፉበት በበሬ አስረው ጎተቱት ጥርሶቹን በጉጥ አስረው ነቃቀሉት ከብረት ድስት ውስጥ ጨምረው ቀቀሉት አስጎንብሰው አሸዋ ጫኑበት ከእንጨት ላይ አንጠልጥለው በእሳት አጋዩት በወፍጮ ፈጩት

👉#ሰማዕቱ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ ስለ ቤተ ክርስቲያን ፍቅር ሲል በሰይፍ ተቀልቶ በመንኮራኩር ተፈጭቶ ወደ እቶን እሳት ተወርውሮ ለአእምሮ በሚከብድ መልኩ ብዙ መከራን ተቀብሎ በ 27 አመቱ ሚያዚያ 23 ቀን መከራን ተቀብሎ በሰማዕትነት አርፏል

👉እግዚአብሔር ሰማዕታትን በደም ቅዱሳንን በተጋድሎ ያፀናል አምላክ እኛንም #በሀይማኖት_በምግባር እንድንፀና መልካም ፈቃዱ ይሁንልን የተባረከ የተቀደሰ #ቀዳሚት_ሰንበት ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ጥቅምት_22

#ቅዱስ_ሉቃስ_ወንጌላዊ
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ሃያ ሁለት በዚህች ቀን ብልህ ጥበበኛ የሆነ ቅዱስ ወንጌላዊ ሉቃስ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ የከበረ ወንጌል ከመዘገባቸው ከሰባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ የተቆጠረ ነው።

እርሱም ወንጌልን ስለማስተማር በሥራው ሀሉ ሐዋርያት ጴጥሮስንና ጳውሎስን የሚአገለግላቸው ሆነ ለታኦፊላም ወንጌልንና የሐዋርያትን ዜና የጻፈ ሉቃስ ነው።

ቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስም ከተገደሉ በኋላ በሮሜ ሀገር የሚያስተምር ሆነ በቀናች ሃይማኖትም ይጸኑ ዘንድ ለምእመናን መልእክትን ይጽፍ ነበር። ስለዚህም ጣዖት አምላኪዎች ከአይሁድ ጋር በመስማማት አንድ ግምባር ፈጠሩ በንጉሥ ኔሮን ፊት ቁመው ስለ ሐዋርያው ሉቃስ እንዲህ ብለው ጮኹ ይህ ሉቃስ ብዙዎች ሰዎችን በሥራዩ ወደ ትምህርቱ አስገባቸው። ንጉሥ ኔሮንም ወደ ፍርድ አደባባይ ሉቃስን እንዲአቀርቡት አዘዘ።

ሐዋርያ ሉቃስም ከዚህ ዓለም መውጫው እንደ ደረሰ በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ወደ ባሕር ዳርቻ ሔደ። በዚያም ዓሣ የሚያጠምድ አንድ ሽማግሌ ሰው አገኘ። መጻሕፍቱንና ደብዳቤዎቹን ሰጠው ወደ እግዚአብሔር መንገድ መርተው ያደርሱሃልና እሊህን መጻሕፍት ጠብቃቸው አለው።

በንጉሥ ኔሮንም ፊት ቀርቦ በቆመ ጊዜ ንጉሡ በሥራይህ ሕዝቡን የምታስት እስከመቼ ነው አለው ቅዱስ ሉቃስም እኔ ለሕያው እግዚአብሔር ልጅ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያው ነኝ እንጂ ሥራየኛ አይደለሁም ብሎ መለሰለት።

ንጉሥ ኔሮንም ሁለተኛ እንዲህ አለው እየጻፈች ሰዎችን የምታስት ይቺን እጅህን እኔ እቆርጣታለሁ ይህንንም ብሎ የቀኝ እጁን እንዲቆርጡ አዘዘ በቆረጡትም ጊዜ ንጉሥ ሆይ እኛ የዚህን ዓለም ሞት እንደማንፈራ እወቅ ነገር ግን የጌታዬንና የፈጣሪዬን ኃይሉን ታውቅ ዘንድ አሳይሃለሁ። ይህንንም ብሎ የተቆረጠች የቀኝ እጁን በግራ እጁ አንሥቶ ከተቆረጠችበት ቦታዋ ላይ አገናኝቶ እንደ ቀድሞዋ ደኅነኛ አደረጋት። ከዚህም በኋላ ለያት በዚያም የነበሩ አደነቁ የሠራዊት አለቃውና ሚስቱ ብዙዎችም ሰዎች ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ቁጥራቸውም አራት መቶ ሰባ ሰባት ነፍስ ሆነ ንጉሡም ከቅዱስ ሉቃስ ጋር ራሶቻቸውን እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጡአቸው የምስክርነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።

ከዚህም በኋላ የቅዱስ ሉቃስን ሥጋ በማቅ አይበት ውስጥ አድርገው ወደ ባሕር ጣሉት በእግዚአብሔርም ፈቃድ ወደ አንድ ደሴት ደረሰ። ምእመናንም አግኝተው ወስደው ገነዙት በአማረ ቦታም አኖሩት።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያው ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ጥቅምት 22-ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ዕረፍቱ ነው፡፡
+ ውራ ኢየሱስ ገዳምን የመሠረቱትና ጌታችን ከገነት ዕንጨቶች የተሠሩ ታቦታት አምጥቶ የሰጣቸው ታላቁ ጻድቅ አቡነ ዮሐንስ ዘውራ ኢየሱስ ዕረፍታቸው ነው።
+ + +
ቅዱስ ሉቃስ:-ሀገሩ አንጾኪያ ሲሆን ቁጥሩ ከ72ቱ አርድእት ነው፡፡ ከአቴናና ከእስክንድርያ ሊቃውንት የሕክምና ሙያን አጥንቷል፡፡ ከሕክምና መያው በተጨማሪ የሥዕል ሙያም ነበረው፡፡ በዚህ ምክንያት በወንጌሉና በሐዋርያት ሥራ መጽሐፉ ላይ ከሌሎቹ በተለየ ሁኔታ ሥዕላዊ አገላለጽን ሲጠቀም ተስተውሏል፡፡ በእጁ የሣላቸው ቅዱሳት ሥዕላትም በተለያዩ ሀገራት ይገኛሉ፡፡
ቅዱስ ሉቃስ የሣላቸው የእመቤታችን ሥዕላት በእኛም ሀገር እንደ ደብረ ዠመዶ፣ ዋሸራና ተድባበ ማርያም፣ ደብረ ወርቅ ማርያም… ባሉ ታላላቅ ቅዱሳት ገዳማት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ቅዱስ ሉቃስ የከበሩ ቅዱሳን ሐዋርያትን ጴጥሮስንና ጳውሎስን ያገለግላቸው ነበር፡፡ ለታኦፊላም ወንጌልንና የሐዋርያትን ዜና የጻፈው እርሱ ነው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስና ጳውሎስ በሰማዕትነት ካረፉ በኋላ በሮሜ ወንጌልን በሰፊው ሰብኳል፡፡ መልእክቶችንም ይጽፍላቸው ነበር፡፡ ጣዖት አምላኪዎችም ከክፉዎቹ አይሁድ ጋር ተማክረው በሐሰት ከሰውት በንጉሥ ኔሮን ፊት አቆሙትና ‹‹ብዙ ሰዎችን በሥራዩ ወደ ክርስትና እምነት አስገብቷልና በሞት ይቀጣ›› ብለው ጮኹ፡፡ ቅዱስ ሉቃስም በሰማዕትነት እንደሚሞት አስቀድሞ ዐውቆ ወደ ባሕር ዳርቻ በመሄድ ዓሣ የሚያጠምድ አንድ ሽማግሌ ሰው አገኘና ወንጌልን ከሰበከው በኋላ መጻሕፍቶቹንና ደብዳቤዎቹን ‹‹ወደ እግዚአብሔር መንገድ ያደርሱሃልና እነዚህን መጻሕፍት ጠብቀቸው›› ብሎ በአደራ ሰጠው፡፡ ሽማግሌውም በክብር በዕቃ ቤቱ አስቀምጦአቸው ለቀጣዩ ትውልድ አስተላልፏቸዋል፡፡
ቅዱስ ሉቃስ በንጉሡ ኔሮን ፊት በቀረበ ጊዜ ንጉሡ ‹‹በሥራይህ ሕዝቡን ሁሉ የምታስት እስከመቼ ነው?›› አለው፡፡ ቅዱስ ሉቃስም ‹‹ለሕያው እግዚአብሔር ልጅ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ነኝ እንጂ እኔስ ሥራየኛ አይደለሁም›› አለው፡፡ ንጉሡም ‹‹እየጻፈች ሰዎችን የምታስት ይህችን እጅህን እቆርጣታለሁ›› ካለው በኋላ ቀኝ እጁን አስቆረጠው፡፡ ቅዱስ ሉቃስም የጌታችንን ኃይሉን ያሳየው ዘንድ ወደደና የተቆረጠች የቀኝ እጁን በግራ እጁ አንሥቶ ከተቆረጠችበት ቦታ ላይ በማገናኘት እንደ ድሮው ደኅነኛ እጅ አደረጋት፡፡ በዙሪያውም የነበሩ ሰዎች ሁሉ የንጉሡም የሰራዊት አለቃ ከነሚስቱ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 477 ሰዎች ሁሉም በጌታችን አመኑ፡፡ ንጉሡም እጅግ ተናዶ ከቅዱስ ሉቃስ ጋር ራሶቻቸውን ይቆርጧቸው ዘንድ አዘዘ፡፡ እነርሱም ሰማዕት ሆነው የክብር አክሊልን ተቀበሉ፡፡ የቅዱስ ሉቃስንም ሥጋ በአሸዋ በተመላ ከረጢት ውስጥ አስገብተው ወደ ባሕር ጣሉት ነገር ግን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ አንድ ደሴት ደረሰና ምእመናን አግኘተውት ወስደው በክብር አኖሩት፡፡
የቅዱስ ሉቃስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!
+ + + + +
አቡነ ዮሐንስ ዘውራ ኢየሱስ:-የአባታቸው ስም የማነ ብርሃን የእናታቸው ስም ሐመረ ወርቅ ይባላል።በመጀመሪያ እናታቸው ሐመረ ወርቅን ወላጆቿ ያለ ፈቃዷ ሊድሯት ሲሉ እርሷ ግን “ደብረ ሊባኖስ ሔጄ ከአባታችን ተክለ ሃይማኖትና ከሌሎቹም ቅዱሳን መቃብር ሳልባረክ አላገባም በማለት ነሐሴ 16 ቀን ወደ ደብረ ሊባኖስ ሔደች። በዚያም ሳለች አቡነ ተክለ ሃይማኖት በራእይ ተገለጡላትና የብርሃን ምሰሶ አሳይተዋት ይኸ ለአንቺና ለባልሽ ለየማነ ብርሃን ነው› አሏት። ይኽንንም ራእይ ለሰባት ቀን የገዳሙ አባቶችና አበ ምኔቱ አባ ዳንኤል አዩት። ከዚኸም በኋላ ባለጸጋውና ሃይማኖትን ከምግባር አስተባብሮ የያዘው የማነ ብርሃን ከዘርዐ ያዕቆብ ሀገር በእመቤታችን ትእዛዝ ወደ ደብረ ሊባኖስ ሲመጣ አበ ምኔቱ አባ ዳንኤል የማነ ብርሃንን እና ሐመረ ወርቅን ኹለቱ ተጋብተው የተባረከ ልጅ እንደሚወልዱ በራእይ ያዩትን ነገሯቸው፤ ከዚኽም በኋላ በአባታችን በተክለ ሃይማኖት የዕረፍታቸው በዓል ዕለት ነሐሴ 24 ቀን ተጋቡ። እነርሱም በሃይማኖት በምግባር እግዚአብሔርን ደስ አሰኝተው ሲኖሩ እግዚአብሔር ልጅ ሰጣቸውና አቡነ ዮሓንስ ነሐሴ 24 ቀን ተፀንሰው ግንቦት 24 ቀን ተወለዱ።

የፈለገ ብርሃን ናዳ ማርያም እና የክብረ ደናግል ናዳ ቅዱስ ላሊበላ አንድነት ገዳም አበምኔት፣ የቅኔ፣ የትርጓሜ መጻሕፍት፤ የፍትሐ ነገሥት እና የባሕረ ሐሳብ መምህር የሆኑት ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ ይባቤ በላይ ከግእዝ ወደ አማርኛ የተረገሙት የአቡነ ዮሐንስ ዘውራ ኢየሱስ ገድል እንደሚናገረው ጻድቁ በሰባት ዓመታቸው ይኸችን ዓለም ንቀው የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ኹለተኛ ልጅ ወደሆነው አባ ጸጋ ኢየሱስ ዘንድ ሔደው 5 ዓመት እየተማሩ ተቀምጠው በ12 ዓመታቸው መነኰሱ። ከዚኽም በኋላ አቡነ ዮሐንስ ወደ ዋልድባ በመሔድ አባቶችን ማገልገል ጀመሩ። መነኰሳቱም ሌሊትና ቀን እንዲያገለግሏቸው በሥጋ ቍስል ሁለንተናው
ለተላና ለሸተተ ግብሩ ለከፋ ለአንድ መነኵሴ ሰጧቸው። በሽተኛውም መነኵሴ አቡነ ዮሐንስን ይረግማቸው አንዳንድ ጊዜም ይደበድባቸው ነበር፣ ነገር ግን አቡነ ዮሐንስ በዚህ ከማዘን ይልቅ ደስ እያላቸው ያንን ሊቀርቡት የሚያሰቅቅ በሽተኛ በማገልገል ለዓመታት አስታመሙ።

እንዲሁም የዋልድባ መነኰሳትን መኮሪታ በማብሰል፣ ቋርፍ በመጫር እና ዕንጨት በመልቀም፣ ውኃ በመቅዳት ገዳማውያንን ያገለግሉ ነበር። ከዕለታትም በአንደኛው ቀን በዋልድባ የሚኖር በክፉ በሽታ ተይዞ የሞተ አንድ መነኩሴ ሞቶ ሣለ ሽታውን ፈርተው መነኰሳቱ ለመገነዝ ፈሩ፡ ነገር ግን አበ ምኔቱ ለመገነዝ ወደ ውስጥ ሲገባ አቡነ ዮሐንስ አብረው ገቡ። አቡነ ዮሐንስም ወደሞተው መነኵሴ ቀርበው አቀፉት፣ በዚኸም ጊዜ ጥላቸው ቢያርፍበት ያ የሞተው መነኵሴ አፈፍ ብሎ ከሞት ተነሣና ከሞትሁ 3ኛ ቀኔ ነው አይቶ የጎበኘኝ የለም፣ ዛሬ ግን የእግዚአብሔር ሰው የገዳማት ኮከብ የቅድስት ውራ ገዳም መነኰሳት አባት፣ የማይጠልቅ ፀሓይ፣ የማይጠፋ ፋና ወደ ሰባቱ ሰማያት ወጥቶ ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የሥላሴን ዙፋን የሚያጥን አባታችን ዮሐንስ ባቀፈኝ ጊዜ ነፍሴ ከሥጋዬ ጋር ፈጽማ ተዋሐደች፤ አምላክን የወለደች እመቤታችን ማርያምም ንዑድ ክቡር ቅዱስ በሆነ በዮሐንስ ጸሎት ከሞት አስነሥቶ ሕያው አደረገህ አለችኝ› ብሎ ተናገረ። ዳግመኛም እመቤታችን አባ ዮሐንስን ወደ ኢየሩሳሌም ሔደው እርሳቸውን ሲጠብቁ የኖሩትን ሦስት ታቦታት ያመጡ ዘንድ አቡነ ዮሐንስን እንዳዘዘቻቸው ተናገረ። በዚኽም ጊዜ የዋልድባ መነኰሳትና የገዳሙ አለቃ ለፍላጎታችን አገልጋይና ታዛዥ አደረግንህ ይቅር በለን ብለው ከእግራቸው ሥር ወድቀው ለመኗቸው። አባታችንም ‹‹አባቶቼ ሆይ! እናንተ ይቅር በሉኝ፡ ይህ የሆነው ስለ እኔ አይደለም፡ ስለ ክብራችሁ ነው እንጂ አሏቸው። መነኰሳቱም በትሕትናቸው ተገርመው እያለቀሱ ወደ ኢየሩሳሌም ሸኟቸው። በዚኸም ጊዜ አባታችን ዕድያቸው ገና 19 ነበር።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ጥቅምት_21

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ሃያ አንድ በዚህችም ቀን #እመቤታችን_ተአምራትን_አድርጋ_ሐዋርያው_ማትያስን ከእሥራት ቤት ያወጣችበት፣ #የነቢይ_ኢዩኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ፣ የማርታና የማርያም ወንድም #የቅዱስ_አልዓዛር ሥጋው ከቆጵሮስ አገር የፈለሰበት፣ የቅዱስ አባት #አባ_ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም እረፍት ነው፣ ታላቁ ጻድቅ #አቡነ_አላኒቆስ ዕረፍታቸው ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#እመቤታችን_ለሐዋርያው_ማትያስ_ያደረገችለት_ተአምር

በዚህችም ቀን እመቤታችን ማርያም ተአምራትን አድርጋ ደቀ መዝሙር ማትያስን ከእሥራት ቤት አዳነችው።

የከበሩ ቅዱሳን ወንጌልን በዓለም ዞረው ይሰብኩ ዘንድ ዕጣ ሲጣጣሉ ለቅዱስ ማትያስ ዕጣ የደረሰው ሰውን ወደሚበሉ ሰዎች አገር ነበር፡፡ ይህችም ሀገር እስኩቴስ የተባለች ሩሲያ እንደሆነች የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡

ማትያስም እነዚህ ሰውን የሚበሉ ሰዎች አገራቸው እንደደረሰ ዐይኑን አውልቀው አሠሩት፡፡ ምግባቸውም የመጻተኛ ሰው ሥጋ ነው፡፡ በልማዳቸው መሠረት መጻተኛን ሰው ገና እንደያዙት ዐይኖቹን ዐውልቀው በእሥር ቤት ያኖሩታል፡፡ እስከ 30 ቀንም ድረስ ሳር እያበሉ ያስቀምጡትና በ30ኛው ቀን አውጥተው አርደው ይበሉታል፡፡

ሐዋርያው ማትያስንም በልማዳቸው መሠረት ዐይኖቹን አውልቀው አሠሩት፡፡ ሐዋርያውም በእሥር ቤት ሆኖ በዚያ ላይ ዐይኖቹን ታውሮ ሳለ በጭንቅ ወደ ጌታችንና ወደ እመቤታችን ይለምን ነበር፡፡ ነገር ግን እመብርሃንና ልጇ መድኃኔዓለም 30ኛው ቀን ሳይፈጸም ሐዋርያው እንድርያስን ወደ እርሱ ላኩለት፡፡ ማትያስም ዐይኑን ፈወሱለትና ማየት ቻለ፡፡

እንድርያስም በተዘጋው በር በተአምራት ገብቶ አሥርቤቱ ውስጥ ያሉ እሥረኞችን በስውር አውጥቶ ከከተማው ውጭ ካስቀመጣቸው በኋላ ሁለቱ ሐዋርያት ተመልሰው ሰውን ለሚበሉት ሰዎች ተገለጡላቸው፡፡ እነርሱም ይዘው በአንገታቸው ገመድ አግብተው ለ3 ቀን በሀገራቸው ጎዳናዎች ላይ ሁሉ ጎተቱዋቸው፡፡ ሁለቱም ሐዋርያት በጸሎታቸው ከእሥር ቤቱ ምሰሶ ሥር ውኃ አፈለቁና ውኃው ሀገራቸውን ሁሉ እስኪያጥለቀልቅና ሰዎቹንም እስከ አንገታቸው ድረስ እስከሚደርስ ሞላ፡፡ ሁሉም በተጨነቁ ጊዜ ሁለቱ ሐዋርያት በፊታቸው ተገለጡና ‹‹በጌታችን እመኑ ትድናላችሁ›› በማለት ወንጌልን ሰብከውላቸው አሳመኗቸው፡፡ ምሥጢራትንም ሁሉ ገለጡላቸው፡፡ ደግሞም የአራዊት ጠባይን ከሰዎቹ ያርቅላቸው ዘንድ ወደ ጌታችንና ወደ ተወደደች እናቱ ከጸለዩ በኋላ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቋቸው፡፡ ያ የአውሬነት ጠባያቸውም ጠፍቶላቸው የዋህ፣ ቅንና ሩኅሩኆቸ ሆኑ፡፡ ሐዋርያትም ሃይማኖትን እያስተማሯቸው 30 ቀን አብረዋቸው ከተቀመጡ በኋላ አገልጋይ ኤጲስ ቆጶሳትን፣ ካህናትንና ዲያቆናትን ሾመውላቸው ወደ ሌላ ሀገር ሄዱ፡፡

ለሐዋርያት ሞገሳቸው ጣዕመ ስብከታቸው የኾነች ክብርት እመቤታችን ለእኛም ትለመነን!

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ኢዩኤል_ነቢይ

ዳግመኛም በዚህችም ቀን የነቢይ ኢዩኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ። ይህም የእስራኤልን ልጆች የሚያስተምርና የሚገሥጻቸው ነበር ስለ ክርስቶስም በኢየሩሳሌም መኖርና ማስተማር ትንቢት ተናገረ። ደግሞም ስለ መከራው በሐዋርያትና በሰባ ሁለቱ አርድእት በሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት ላይ የመንፈስ ቅዱስን መውረድ እንዲህ ሲል ተናገረ።

ከዚህ በኋላ በሥጋዊ በደማዊ ሰው ሁሉ ከመንፈሴ አሳድርበታለሁ ሴቶች ልጆቻችሁና ወንዶች ልጆቻችሁ ትንቢትን ይናገራሉ አለቆቻችሁ ሕልምን ያልማሉ ጎልማሶቻችሁም ራእይን ያያሉ። ሁለተኛም እንዲህ አለ ያን ጊዜ ከተራራው ማር ከኮረብታውም ወተት ይፈሳል በቤተ እግዚአብሔር አጠገብ ካሉ ከይሁዳ አገሮች ሁሉ ምንጩ ከላይ ወደታች ይፈሳል።

ሙታን በሚነሡ ጊዜ ስለሚሆነው የፍርድ ሰዓት እንዲህ አለ ፀሐይና ጨረቃ ይጨልማሉ የከዋክብትም ብርሃናቸው ይጠፋል። የትንቢቱንም ወራት አድርሶ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አልዓዛር የማርታና የማርያም ወንድም

በዚችም ቀን ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው የቅዱስ አልዓዛር ሥጋው ከቆጵሮስ አገር የፈለሰበት ሆነ።

ከክርስቲያን ነገሥታትም አንዱ ሥጋው በቆጵሮስ እንዳለ በሰማ ጊዜ ከቆጵሮስ ደሴት ወደ ቊስጥንጥንያ አፈለሰው። ሊአፈልሱትም በወደዱ ጊዜ በከበረ የደንጊያ ሣጥን ውስጥ ሁኖ በምድር ውስጥ ተቀብሮ አገኙት በላዩም እንዲህ የሚል ጽሑፍ ነበረ ይህ በመቃብር ውስጥ አራት ቀን ከኖረ በኋላ ከሙታን ለይቶ ላስነሣው ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወዳጁ የሆነ የቅዱስ አልዓዛር ሥጋ ነው።

ይህንንም በአዩ ጊዜ ደስ ተሰኙበት ተሸክመውም ወደ ቊስጥንጥንያ አገር ወሰዱት ካህናቱም ሁሉ ወጥተው በታላቅ ክብር በመዘመርና በማመስገን ተቀበሉት በአማረ ቦታም አኖሩት በዚችም ቀን በዓልን አደረጉለት።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ዮሐንስ_ዘኢየሩሳሌም

በዚህችም ቀን ለከበረች አገር ኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳሳት የሆነ ቅዱስ አባት አባ ዮሐንስ እግዚአብሔርን በሚወድ የንጉሥ ሰይፈ አርዕድ ደግሞ ቈስጠንጢኖስ ለሚባል ልጁ በሆነ በንጉሣችን በዳዊት ዘመን አረፈ።

ይህም ቅዱስ ከምስር አገር ታላላቆች እግዚአብሔርን የሚፈሩ የክርስቲያኖች አባቶች ልጅ ነው። የዲቁና መዓረግንም ለመሾም እስከ ተገባው ድረስ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እያስተማሩ በበጎ አስተዳደግ አሳደጉት። ከዚህም በኋላ በዲቁናው ሹመት አገልግሎቱን በአሳመረ ጊዜ የቅስና መዓረግ የሚገባው ሁኖ ቅስና ተሾመ።

በጾም በጸሎት እግዚአብሔርንም በመፍራት የተጠመደ ሁኖ ድኆችንና ችግረኞችን የሚወዳቸው የሚረዳቸው ሆነ ያን ጊዜ የሐዋርያት የሆነች የጵጵስና ሹመት የምትገባው ሁና በከበረች አገር በኢየሩሳሌም በእግዚአብሔር ፈቃድ ሊቀ ጵጵስና ተሾመ ሕዝቡንም በፈሪሀ እግዚአብሔርና በትሕትና የሚያስተምራቸው ሆነ።

እነርሱም ስለ ቅድስናው እጅግ የሚወዱት ሆኑ መልኩና የአንደበቱ አገላለጥ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ያማረ ነበር። በሹመቱም ጥቂት ዘመናት ከኖረ በኋላ ከመንበረ ሢመቱ እስከ አራቀው ድረስ በላዩ ሰይጣን ምክንያትን አመጣ።

ይህም እንዲህ ነው በእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት በአባ ማርቆስ ዘመን በግዛቱ ውስጥ ያሉ እስላሞች ስለ ዐመፁበት የኢትዮጵያ ንጉሥ ፈጅቷቸው ነበርና ስለዚህ በግዛቱ ውስጥ በሚኖሩ እስላሞች ላይ ክፉ እንዳያደርግ ለኢትዮጵያ ንጉሥ መልእክት እንዲልክ ሊቀ ጳጳሳት አባ ማርቆስን የምስር ንጉሥ አዘዘው።

አባ ማርቆስም ወደ ኢትዮጵያ ንጉሥ ስለሚላኩ ሰዎች ከመኳንንቱ ከኤጲስ ቆጶሳቱና ከሀገር ታላላቆች ሽማግሌዎች ጋር ተማክሮ እሊህን ብሩሀን ከዋክብት የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሐንስን የምስር ኤጲስቆጶስ አባ ሳዊሮስን በእውቀታቸው በአስተዋይነታቸውና በቅድስናቸው መረጡአቸው ወደ ኢትዮጵያ ንጉሥም ይሔዱ ዘንድ ግድ አሏቸው።

እነርሱም ታዛዦች ሁነው ወደ ኢትዮጵያ መጡ የኢትዮጵያ ንጉሥም መምጣታቸውን በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ አለው እሊህንም ቅዱሳን አባቶች ይቀበሏቸው ዘንድ አሽከሮቹን በቅሎዎችን አስይዞ ላከ በመጡም ጊዜ በታላቅ ደስታ ሰላምታ አቀረበላቸው ከእርሳቸውም ቡራኬን ተቀበለ ታላቅ ክብርንም አከበራቸው ። እነርሱም የሊቀ ጳጳሳት አባ ማርቆስን ደብዳቤ ሰጡት እርሱም ተቀብሎ አንብቦ ለሊቀ ጳጳሳቱ ቃል ታዛዥ መሆኑን ገለጠላቸው።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን ✝✝✝ !!

'' ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ . መዝ . ዳ . 121 : 1 "

መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ታላቁ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ።
ቀን ጥቅምት 24 ከለሊቱ 11 : 30 መነሻ ቦታ ገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ - ክርስቲያን .
ዋጋ መስተንግዶን ጨምሮ( 600 ብር ብቻ )
የጉዞ አላማ ለነድያን ዝክር መዘከርያ የሚውል ።

ለበለጠ መረጃ ; 0937927602
0912727069
ይደውሉ ።
ይህ የበረከት ጉዞ እንዳያመልጣችሁ ስጋችሁን ከ ዓለም ሁካታ መንፈሳችሁን የበረከት ተካፋይ እንድታደርጉ ተጋብዘዋል ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ወይም ልጆች ወይም የምትሰሩ አዋሩኝ ፕሊስ እባካችሁ

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ጥቅምት 20/2017 #ፃድቁ_አባ_ዮሐንስ_ሐፂር

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ አባታችን አባ #ዮሐንስ_ሐፂር አመታዊ የእረፍት በዐል መታሰቢያ እንኳን አደረሰን

👉ጥቅምት ሃያ በዚህች ቀን ክቡርና ገናና የሆነ አባ ዮሐንስ ሐፂር አረፈ የዚህ ቅዱስ ወላጆቹ ከላይኛው ግብፅ ናቸው እነርሱም #እግዚአብሔርን የሚፈሩ ናቸው ግን ከእርሱ በቀር ልጅ የላቸውም የዚህ ዓለምም ብልፅግና ቢሆን የላቸውም ነገር ግን በበጎ ሥራ ባለጸጎች ናቸው ይህንንም ቅዱስ እያስተማሩ በበጎ አስተዳደግ አሳደጉት

👉የዚህም ቅዱስ ዕድሜው ዐሥራ ስምንት ዓመት ሲሆነው #የእግዚአብሔር ቸርነት አነሣሥታው የመላእክት የሆነ አስኬማን ይለብስ ዘንድ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ ይኸውም የምንኵስና ልብስ ነው

👉ከዚያም በደረሰ ጊዜ አባ ባይሞይ የሚባለውን አንዱን አረጋዊ አባት ተገናኘው #ዮሐንስም ሰገደለትና ወደ እርሱ እንዲቀበለው ለመነው ሽማግሌውም አባት ልጄ ሆይ ያንተ በዚህ መኖር ልክ አይደለም

👉በዚች ገዳም የሚኖሩ በእጆቻቸው ይሠራሉ በቀንና በሌሊት #ይፆማሉ_ይፀልያሉ በሚተኙም ጊዜ ያለ ምንጣፍ በምድር ላይ ይተኛሉ አንተ ወጣት ጎልማሳ ስለሆንክ ይህን ሁሉ ችግር አትችልም ነገር ግን ወደ ዓለም ተመልሰህ እንደ ሰው ሁሉ በጎ አኗኗርን ትኖር ዘንድ ይሻልሃል የዚች ገዳም ኑሮ ጭንቅ ነውና አለው

👉አባ ዮሐንስም እንዲህ አለው እኔ በጥላህ ሥር ልኖር መጥቼአለሁና ስለ #እግዚአብሔር ብለህ ተቀበለኝ እንጂ አትመልሰኝ ይህም አባ ባይሞይ እግዚአብሔርን ሳይጠይቅ ምንም ሥራ አይሠራምና በዚያን ጊዜ ሥራውን ይገልጥለት ዘንድ ስለ ዮሐንስ ሐፂር እግዚአብሔርን ለመነው የእግዚአብሔርም መልአክ ተገልጦለት እርሱ የተመረጠ መሳሪያ ይሆናልና ተቀበለው ብሎሃል አለው

👉ከዚህም በኋላ ዮሐንስ ሐፂርን ወስዶ ወደ ቤተ ክርስቲያን አስገባው የምንኵስና ልብሶችንም አምጥቶ በላያቸው ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ፀለየ ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ተገልፆ #በመስቀል_ምልክት በልብሶቹ ላይ አማተበ ሽማግሌውም እነዚያን ልብሶች ለአባ ዮሐንስ አለበሰው

👉ከዚያቺም ቀን ጀምሮ አባ ዮሐንስ ተጋድሎንና አገልግሎትን ጀመረ አባ ባይሞይም ሊፈትነው ወደደ በአንዲትም ቀን ደብድቦ ከአንተ ጋር መኖር አልሻም ብሎ ከበዓቱ አስወጥቶ አባረረው የከበረ #አባ_ዮሐንስም ከሜዳ መካከል በውጭ ቆመ በየቀኑም በጥዋት እየወጣ ከእዚህ ላይህ አልሻም እያለ ይመታዋል እርሱ ግን አባቴ ሆይ ይቅር በለኝ ብሎ ከእግሩ በታች ይሰግዳል

👉በሰባተኛዪቱም ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሊሔድ ሽማግሌው #የእግዚአብሔር_ሰው አባ ባይሞይ ወጣ አባ ዮሐንስንም ሰባት መላእክት ከበው አክሊላትን ሲያቀዳጁት አያቸው ከዚያንም ጊዜ ወዲህ መፈተኑን ተወው ወደ መኖሪያውም አስገባው

👉ከዚህም በኋላ በአንዲት ቀን አባ ባይሞይ የደረቀ ዕንጨት አግኝቶ ወስዶ #ለአባ_ዮሐንስ ሰጠውና ይህን ዕንጨት ትከለው እስከሚበቅልና እስከሚአፈራ ድረስ ውኃን አጠጣው አለው አባ ዮሐንስም ለአባቱ ታዛዥ በመሆን ተቀብሎ ወስዶ ተከለው በየቀኑም ሁለት ሁለት ጊዜ ያጠጣዋል ውኃውም ዐሥራ ሁለት ምዕራፍ ያህል የራቀ ነው።

👉ከሦስት ዓመትም በኋላ ያ ዕንጨት አቈጥቊጦ በቀለ ታላቅም ዛፍ ሁኖ አብቦ ጣፋጭ ፍሬን አፈራ አባ ባይሞይም ከፍሬው #ለቅዱሳን_አረጋውያን ወሰደላቸውና የታዛዡንና የትሑቱን ፍሬ እነሆ ብሉ አላቸው እነርሱም ይህን ድንቅ ተአምር አይተው አደነቁ ለመምህሮቻቸው ለሚታዘዙ እንዲህ ያለ ፀጋ የሚሰጥ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት

👉አባ ባይሞይም ዐሥራ ሁለት ዓመት ያህል በጽኑዕ ደዌ ውስጥ ተይዞ ኖረ #አባ_ዮሐንስም ያገለግለው ነበር አባ ዮሐንስን እንደፈተነው የተመረጠ መሥዋዕትን ይሆን ዘንድ በዚህ ደዌ እንዲፈተን እግዚአብሔር ፈቅዷልና

👉በሚሞትበትም ጊዜ አባ ባይሞይ ቅዱሳን አረጋውያን መነኰሳትን ሰበሰባቸውና #አባ_ዮሐንስንም እጁን ይዞ እርሱ ሰው ያይደለ መልአክ ነውና ተቀብላችሁ ጠብቁት ብሎ ሰጣቸው እርሱንም ደግሞ እንዲህ አለው ከእረፍቴ በኋላ ያን ዕንጨት ወደ ተከልክበት ቦታ በዚያ ኑር #እግዚአብሔር ላንተ ያዘጋጀልህ ነውና ብዙዎችም በአንተ እጅ ይድናሉ መታሰቢያህም በዚያ ጸንቶ ይኖራል ዜናህም በዓለም ሁሉ ይወጣል ይህንንም ተናግሮ አረፈ አክብረውም ቀበሩት

👉ከዚህም በኋላ #ቅዱስ_አባ_ዮሐንስ አረጋዊ አባቱ አባ ባይሞይ እንደነገረው ወደዚያ ቦታ ሒዶ ኖረ ዜናውም በዓለም ሁሉ እጅግ እስከ ተሰማ ድረስ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ

👉በራሱ ቤተ ክርስቲያንም አበ ምኔት ሁኖ ተሾመ በሹመቱም ጊዜ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስ እጆቹን በራሱ ላይ ሲጭን #አክዮስ_አክዮስ_አክዮስ የሚል ቃል ከሰማይ ተሰማ ይህም ይገባዋል ይገባዋል ይገባዋል ማለት ነው የቊርባን ቅዳሴን በሚቀድስ ጊዜ ቅዱስ ቁርባንን መቀበል የማይገባቸውን ይለያቸዋል ዛሬስ ሒዳችሁ ንስሓ ግቡ ከዚያም በኋላ ተመልሳችሁ ሥጋውን ደሙን ተቀበሉ ይላቸዋል።

👉ይህን አባ ዮሐንስንም ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስ የቅዱሳን የሠለስቱ ደቂቅን ሥጋቸውን እንዲአመጣለት ወደ ባቢሎን ልኮታል ይህም በግንቦት ወር በዐሥረኛው ቀን ተጽፎአል በአንዲትም ዕለት አንድ መነኰስ ሊጎበኘው ወደ በዓቱ ቢመጣ አባ ዮሐንስን ተኝቶ አገኘው #የእግዚአብሔርም መላእክት በላዩ ይጋፉ ክንፎቻቸውንም ያርገበግቡ ነበር አንዱም ሌላውን ተወኝ ክንፌን በላዩ ላኑር ይለዋል ይህንንም አይቶ እግዚአብሔርን አመሰገነው

👉ከዚህም በኋላ የመነኩሳቱን መንደር ሊበረብሩ የበርበር አረማውያን ወደ አስቄጥስ ገዳም በመጡ ጊዜ አባ ዮሐንስም #ወደ_አባ_እንጦንስ ገዳም ወደ ቁልዝም ሔደ በዚያም በአባ እንጦንስ ገዳም በጎኑ በአለ ቦታ ተቀመጠ እስከ ሚያርፍባትም ቀን ድረስ የሚያገለግለው አንድ የታመነ ሰውን እግዚአብሔር አመጣለት

👉ከዚህም በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም ሊአሳርፈው በወደደ ጊዜ #እግዚአብሔር ቅዱሳን ጻድቃኖቹን አባ እንጦንስን፣ አባ መቃርስን፣ አባ ጳኵሚስን ከእርሳቸውም ጋር መንፈሳዊ አባቱ አባ ባይሞይን ያረጋጉትና ከዚህ ከኃላፊው ዓለም መለየቱን ይነግሩት ዘንድ ወደርሱ ላካቸው

👉እነርሱም እንዲህ ብለው አረጋጉት ደስ ይበልህ #እግዚአብሔር የማያልቅ ተድላ ደስታን አዘጋጅቶልሃልና ክብር ይግባውና ጌታችንም እንዳዘዘ በእሑድ ቀን ሁለተኛ ወዳንተ መጥተን ወደ ዘላለም ሕይወት እንወስድኻለን ባርከውትም ከእርሱ ዘንድ ተመለሱ

👉በዐርብ ቀንም አገልጋዩን ወደ አንድ ቦታ ላከው ከዚህም በኋላ ጥቂት ታመመ በእሑድም ቀን ሌሊት ዶሮ ሲጮህ እሊያ ቅዱሳን ከሁሉም ቅዱሳን ማኅበር ጋር መጡ የመላእክትም ሠራዊት ሁሉ ወደርሱ መጡ በአያቸውም ጊዜ ደስ ብሎት በእግዚአብሔር እጅ ነፍሱን ሰጠ መላእክትም እያመሰገኑና እየዘመሩ በታላቅ ክብር #ነፍሱን አሳረጓት

👉በዚያንም ጊዜ ረድኡ መጣ ነፍሱንም ከበው እያመሰገኑ ሲያሳርጓት የፃድቃንና የመላእክትን ማኅበር አይቶ እያደነቀ አንድ ሰዓት ያህል ቆመ ከመላእክትም አንዱ ወደርሱ መጥቶ የቅዱሳንን ስማቸውን በመጥራት በጣቱ እያመለከተ ይህ አባ ዕገሌ ነው ብሎ አስረዳው ረድኡም መልአኩን እንዲህ ብሎ ጠየቀው ይህ በፊታቸው ያለ ፊቱ እንደ ፀሐይ የሚበራ ማን ነው መልአኩም የመነኰሳቱ ሁሉ አባት #አባ_እንጦንስ ነው ብሎ መለሰለት።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🌹 በዐርብ ቀንም አገልጋዩን ወደ አንድ ቦታ ላከው ከዚህም በኋላ ጥቂት ታመመ በእሑድም ቀን ሌሊት ዶሮ ሲጮህ እሊያ ቅዱሳን ከሁሉም ቅዱሳን ማኅበር ጋር መጡ የመላእክትም ሠራዊት ሁሉ ወደርሱ መጡ በአያቸውም ጊዜ ደስ ብሎት በእግዚአብሔር እጅ ነፍሱን ሰጠ መላእክትም እያመሰገኑና እየዘመሩ በታላቅ ክብር ነፍሱን አሳረጓት በዚያንም ጊዜ ረድኡ መጣ ነፍሱንም ከበው እያመሰገኑ ሲያሳርጓት የጻድቃንና የመላእክትን ማኅበር አይቶ እያደነቀ አንድ ሰዓት ያህል ቆመ። ከመላእክትም አንዱ ወደርሱ መጥቶ የቅዱሳንን ስማቸውን በመጥራት በጣቱ እያመለከተ ይህ አባ ዕገሌ ነው ብሎ አስረዳው ረድኡም መልአኩን እንዲህ ብሎ ጠየቀው "ይህ በፊታቸው ያለ ፊቱ እንደ ፀሐይ የሚበራ ማን?" ነው መልአኩም "የመነኰሳቱ ሁሉ አባት አባ እንጦንስ ነው" ብሎ መለሰለት።

🌹 ወደ በዓቱም ያ ረድእ በገባ ጊዜ በምድር ላይ ሰግዶ እንዳረፈ አባ ዮሐንስን አገኘውና ታላቅ ልቅሶን በላዩ አለቀሰ ከዚያም በኋላ ወደ መነኰሳቱ መንደር ፈጥኖ በመሔድ ቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐፂር እንደ ዐረፈ ነገራቸው። እነዚያም መነኰሳት አክብረው ገንዘው ሥጋውን ተሸክመው ወስደው በቦታቸው አኖሩት። የደረቀ ዕንጨት ተክሎ በአበቀለበት ላይ በሠራት የራሱ በሆነች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ልጆቹ ከዚህ አፍልሰው ወስደው እስከ አኖሩት ድረስ በዚያ ኖረ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዮሐንስት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✝ ✝ ✝
🌹 #ታላቁ_ነቢይ_ቅዱስ_ኤልሳዕ፦ የዚህም ነቢይ የስሙ ትርጓሜ ጠባቂና አዳኝ የሆነ ማለት ነው። እርሱም አሜሁላ ከሚባል አገር ከይሳኮር ነገድ ነው ብዙ ትንቢትን ተናግሮአል ብዙ ተአምራትንም አድርጓል። የኢያሪኮም ሰዎች ኤልሳዕን "ጌታችን እንደምታያት የዚች አገር ኑሮዋ ያማረ የተወደደ ነው የአገሩ ውኃ ግን ክፉ ነው ሴቶች ሲጠጡት ይመክናሉ" አሉት ኤልሳዕም "ጨው ጨምራችሁ አዲስ ሸክላ አምጡልኝ" አላቸው እነርሱም አመጡለት።

🌹 ኤልሳዕም ወደ ውኃው ምንጭ ሒዶ ያንን ጨው በውስጡ ጨመረውና እግዚአብሔር እንዲህ አለ "እርሱን ከመጠጣት የተነሣ የሚሞት እንዳይኖር የሚመክንም እንዳይኖር ይህን ውኃ ለውጥኩት አለ" አላቸው።

🌹 ከዚያችም ቀን በኋላ ኤልሳዕ እንደተናገረ እስከ አሁን ድረስ ያ ውኃ ተለወጠ። የዚህ የነቢይ ኤልሳዕ ተአምራቱ ብዙ ነው የሶርያውን ሰው ንዕማንን ከለምጹ ያነጻው እርሱ ነው ሁለት ሙታንን አንዱን በሕይወት ሳለ ሌላውንም ከሞተ በኋላ አስነሥቷል። የትንቢቱንም ወራት ፈጽሞ በሰላም ረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢዩ ቅዱስ ኤልሳዕ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።



✝ ✝ ✝
🌹 #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ምህረኒ እግዚኦ ፍኖተ ጽድቅከ። ወእኅሥሣ በኵሉ ጊዜ። አለብወኒ ወእኅሥሥ ሕገከ"። መዝ 118፥33-34 ወይም መዝ 64፥10። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 19፥27-ፍ.ም ወይም ሉቃ 4፥27-33።

✝ ✝ ✝
🌹 #የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "አርውዮ ለትለሚሃ። ወአሥምሮ ለሚእረራ። ወበነጠብጣብከ ትበቊል ተፈሢሓ። መዝ 64፥10። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 12፥11-25፣ 1ኛ ጴጥ 4፥6-12፣ የሐዋ.ሥራ 20፥31-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 4፥27-33። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የአባ ዮሐንስ ሐፂርና የዕረፍት በዓል፣ የነቢዩ የቅዱስ ኤልሳዕ የመታሰቢያ በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችን ይሁንልን።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

ሰዉ ወረተኛ  ነዉ

👉 ያገኝዉን  ነገር  መልሶ  አይወደውም   እስኪ ያገኘው  ነዉ  የሚወደዉ።

👉እግዚአብሔር ግን  ተገኝቶም ይወደዳል ።

👉ልናገኘው  ፈልገን አግኝተነው  ልናገኘው  እንፈልጋለን ።

👉መላእክት  ሊያመሰግኑት  ፈልገዉ አመስግነዉት  መልሰዉ  ሊያመሰግኑት    ይመኛሉ ። 

👉ሊያዩት  ፈልገዉ  አይተዉት  እንደገና  ሊያዩት  ይመኛሉ ።

👉ሊቀድሱት (ሊያመሠግኑት) ፈልገዉ  እንደገና  ሊቀድሱት  ይመኛሉ ።

-እንዴት  ነዉ  አይተዉት  እንደገና   ማየት  መፈለግ

-እንዴት  ነዉ   ቀድሰዉት   እንደገና  መቀደስ  መፈለግ

-እንዴት  ነዉ   አግኝተዉት   እንደገና  ማግኘት  መፈለግ

👉እግዚአብሔር  ሁልጊዜም    ስለማይለወጥ
ልዩ  ጽኑ  ይባላል ። 

ልዩ  ጽኑ  በሉት።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በባሕር ላይ የታነጸው ቤተመቅደስ እና የቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ መካነ መቃብር
"ይምርሐነ ፍታኝ! "
ጌታችን "ሥጋዬን እየፈተትህ ለሕዝቦቼ ትነግሥላቸው ዘንድ መንግሥትን ለአንተ ሰጠሁህ" ብሎ በተቀደሱ እጆቹ የንግሥና ቅባትን ቀባው፡፡ በዚህም ጊዜ ይምርሐነ ክርስቶስ "...አምላኬ ሆይ እኔ ከሁሉ ይልቅ ታናሽ ነኝና እባክህ ታነግሥ ዘንድ ሌላ ሰው ምረጥ" ብሎ ከጌታችን ጋር በትሕትና ተከራከረ፡፡ ጌታችን በቅዱስ ቃሉ "ክህነትህ ምድራዊ አይደለም፣ ሰማያዊ ነው እንጂ" ብሎታል፡፡

ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ ገና ሲወለድ አንደበቱን ፈቶ እግዚአብሔርን በአንድነቱ በሦስትነቱ ያመሰገነ ታላቅ ጻድቅ ሲሆን 40 ዓመት ሙሉ ሰማያዊ ኅብስትና ሰማያዊ ጽዋ ከሰማይ እየወረደለት ቀድሷል፡፡

የእግዚአብሔርን ጌትነትና የይምርሃነ ክርስቶስ የቅድስና ሕይወት በዓለም ሁሉ መሰማት እንደጀመረ የሮም ሰዎችም ወደ እርሱ መጥተው 55 ውድ መስቀሎችን በስጦታ ገበሩለት፡፡ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ የሚያደርገውን ተአምርና ቅድስናውን የሰሙ ቁጥራቸው 5740 የሆኑ የግብፅና የሮም ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት፣ ቀሳውስትና ዲያቆናት እንዲሁ መነኮሳት ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ የሚወርድለትን ሰማያዊ ኅብስትና ሰማያዊ ጽዋ በእጁ ለመቀበልና በመስቀሉ ለመባረክ መጡ፡፡ የግብፁ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ አትናቴዎስም ‹‹ከዚህ ቅዱስ የእግዚአብሔር አገልጋይ እጅ በረከትን መቀበል እሻለሁ›› ብሎ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ከቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ጋር ተገናኝቶ ሁለቱም በረከትን አንዳቸው ከአንዳቸው ተቀብለዋል፡፡ ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስም ወደ እርሱ ለመጡት 5740 ደጋግ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት፣ ቀሳውስትና ዲያቆናት እንዲሁ መነኮሳት ሁሉ ቀድሶ ሰማያዊውን ሥጋ ወደሙን አቀብሏቸዋል፡፡ እነርሱም ሰማያዊውን ሥጋና ሰማያዊውን ደሙን ከተቀበሉ በኋላ "ይህን ባየንበትና በቀመስንበት ሌላ አናይም አንቀምስም" ብለው የተወሰኑት ወደሌሎች የአገራችን ገዳማት የሔዱ ሲሆን ብዙዎቹ ደግሞ ከእርሱው ጋር አብረው በዚያው ዐርፈው ተቀብረዋል፡፡ ዛሬም ድረስ የእነዚህ ቅዱሳን ዐፅም ቤተ መቅደሱ ካለበት ጀርባ በኩል በሚገኘው ትልቅ ዋሻ ውስጥ በክብር ተቀምጦ ይገኛል፡፡

በመጀመሪያ ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ በድንኳን ውስጥ ህብስቱና ወይኑ ከሰማይ እየወረደለት ሕዝቡን ያቆርብ ነበር፡፡ ጌታችንም ተገልጾለት "እስከ ዕለት ምጽአት ድረስ ፈጽሞ የማትፈርስ ቤተ መቅደስ ትሠራለህና ተነሥተህ ሂድ ቦታውን ገብርኤልና ሩፋኤል ይመሩሃል" አለው፡፡ በመንገዱም ዕውራንን እያበራና ተአምራትን እያደረገ ተጓዘ፡፡ ቦታው ላይ ሲደርስም ጌታ አሁንም ተገልጾ ስለ ቤተ መቅደሱ አሠራር ነገረው፡፡ ቤተ መቅደሱንም እንዲሠራ ያዘዘው ከባሕር ላይ ነው፡፡ "በዚህ ባሕር ላይ እንዴት አድርጌ እሠራለሁ?" ብሎ ጌታችንን ቢጠይቀው እንጨት፣ ድንጋይና ጭቃ እየረበረበ እንዲሠራ ነገረው፡፡ ዕቃዎቹንም ከኢየሩሳሌም በደመና ሠረገላ እየተመላለሰ አምጥቶ እንደታዘዘው አድርጎ አንጾታል፡፡ የቤተ መቅደሱ ልዩ የሆነ የአሠራር ዘዴ ባሕሩን ከታች እንዲሰወር ቢያደርገውም በባሕር ላይ ለመሠራቱ ዛሬም ድረስ ምልክቱ በግልጽ ይታያል፡፡ ቤተ መቅደሱን በሰባቱ ሰማያት መስሎና ከፍሎ ያስጌጠበት ጥበብ ዛሬ በዓለም ላይ የትኛውም አርክቴክት ፈጽሞ ሊሠራው አይችልም፡፡

ጥቅምት 19-ንግሥናን ከክህነት ጋር አስተባብሮ በመያዝ 40 ዓመት ሙሉ ሰማያዊ ኅብስትና ጽዋ ከሰማይ እየወረደለት የቀደሰው ጻድቁ ንጉሥ ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ሕዝቡንም የሚባርክበት መስቀል ከሰማይ የወረደለት ሲሆን ቤተ መቅደሱን በባሕር ላይ እንዲሠራ ራሱ ጌታችን በቃሉ ከነአሠራሩ ጭምር ያስረዳው ነው፡፡

ጌታችንም በድጋሚ ከመላእክቶቸቱ ጋር ተገልጾ ቃልኪዳን ሰጠው፡፡ “ለኃጢአተኞች መዳን ምክንያት ሆነህ ታድናቸው ዘንድ እኔ ወደቦታህ እመልስሃለሁ፤ እኔና የባሕርይ አባቴ አብ የባሕርይ ሕይወቴ ምንፈስ ቅዱስ ካልፈቀድንለት በቀር ቦታህን ማንም አይረግጥብህም፤ በቦታህም መጥቶ መካነ መቃብርህን እየዞረ አቡነ ዘበሰማያት እያለ አምላከ ይምርሃነ ክርስቶስ ማረኝ ያለውን ሰው ዕለቱን እንደተጠመቀ ከእናቱም ማኅፀን እንደተወለደ ሕፃን ልጅ አደርገዋለሁ፡፡ ቦታዋም ዳግማዊ ኢየሩሳሌም ትሁንልህ…” የሚል ድንቅ ቃልኪዳን ገብቶለታል፡፡ በዚህ ቃልኪዳን መሠረት ቅዱስ መካነ መቃብሩ እየተዞረና አቡነ ዘበሰማያት ከተባለ በኃላ ሦስት ጊዜ "ይምርሐነ ፍታኝ! " ይባላል፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜም ድረስ ከቅዱስ መካነ መቃብሩ "እግዚአብሔር ይፍታህ" የሚል ጽምፅ ይሰማ ነበር፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን አባቶቻችን በሱባኤ ጠይቀው ድምፁ እንዲጠፋ አድርገውታል፡፡

የቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!

"ይምርሐነ ፍታኝ! "
መዝገበ ቅዱሳን

Читать полностью…
Subscribe to a channel