This automated cryptocurrency trading system uses intelligent algorithms to buy low and sell high on leading crypto exchanges. Many users have already enjoyed significant profits!
🔴 Sign-Up Bonus: Get 8 USDT for free upon registration!
🔵 Withdrawals: Start withdrawing from just 1 USDT per day.
💰 Investment Plans:
Invest 10 USDT: Earn 0.25 USDT per day, totaling 25 USDT over 30 days.
Invest 100 USDT: Earn 5.25 USDT per day, totaling 262 USDT over 30 days.
Invest 1,000 USDT: Earn 58.85 USDT per day, totaling 2,835 USDT over 30 days.
Invest 5,000 USDT: Earn 330 USDT per day, totaling 12,450 USDT over 30 days.
💰💰You can withdraw your earnings daily!
❤️Registration link:
https://antgpt.org/h5/index.html#/pages/user/register?shareCode=179582
🩷Official Group: /channel/+bt5iInS2JmEyNGY0
+++ይህን ያውቁ ኖሯል?+++
[ስለ መድኃኔ ዓለም መታሰቢያ]
በአንድ ወቅት በገነት ያሉ ቅዱሳን ፤ ቅዱስ መብዓ ጽዮን በሰማያት የተሰጠውን ክብር ተመለከቱና መድኃኔ ዓለምን "ለመብዓ ጽዮን ጻድቅ የሰጠኽው ይህ ሁሉ ክብር እና ሥጦታ ከምን የተነሣ ነው?" ብለው ጠየቁት። ክብር ይግባውና መድኃኔ ዓለም እንዲህ ሲል መለሰላቸው "እርሱ ግን ብዙ ወደደኝ የሞቴንም መታሰቢያም አደረገ ፤ ለደቀ መዛሙርቴ የሞቴን መታሰቢያ አድርጉ ብዬ እንደነገርኳቸው" አላቸው። (ገድለ መብዓ ጽዮን ዘእሑድ)
+++
፨ አምላካችን በወንጌል ያስተማረውን ፤ ቅዱሳን በሕይወት ኖረው የሰበኩትን ክርስቲያናዊ ሕይወት እየኖረ(በንስሓ እና በመልካም መንፈሳዊ ምግባራት እየተመላለሰ) ፤ የመድኃኔ ዓለምን መታሰቢያ የሚያደርግ ክርስቲያን ይህ ቃልኪዳን ተገብቶለታል።
+ "የሚያከብረውና መታሰቢያውን የሚያደርግ ግን መድኃኒታችንን የተቀበሉት የዮሴፍ እና ኒቆዲሞስ ጓደኛቸው ይሆናል።" [ወዘሰ ያከብር እንዘ ይገብር ተዝካሮ ፤ ሱታፌሆሙ ለኒቆዲሞስ ወዮሴፍ እለ ተወክፍዎ ለመድኃኒነ]
+ "የመድኃኔ ዓለምን መታሰቢያ ያደረገ ግን በመንግሥተ ሰማያት ባለሟልነትን ያገኛል። በየወሩም አምስት ሺህ ነፍሳትን ከደይን ያወጣል ፤ በየሳምንቱ ዓርብ ዓርብም ስለ ስቅለቱ ሦስት መቶ አርባ ነፍሳት ይሰጠዋል ፤ የዕንቊ የወርቅ አክሊል የብርሃን ልብስ ይሠጠዋል።" [ዘገብረሰ ተዝካረ መድኅን ይረክብ ሞገሰ በመንግሥተ ሰማያት ፤ ወአሥራተሂ ለለወርኁ ፶፻ ነፍሳተ ያወጽእ እምደይን ወበዕለተ ዓርብሂ ፫፻ወ፵ ይትወሀቦ በእንተ ስቅለቱ አክሊለ ዕንቊ ወወርቅ ወልብሰ ብርሃን ያሠረግዎ] (ገድለ መብዓ ጽዮን ዘሰኑይ)
+++
+ "የመድኃኔ ዓለምን መታሰቢያ አድርጉ መታሰቢያውን የሚያደርግ ክብሩ ብዙ ነውና።" (ተአምረ መድኃኔ ዓለም)
+++
"ለኅጡአ ምግባር ገብርከ ዘርቱዕ ሃይማኖቱ ፤ ምስለ ቅዱሳን ይኩን ማኅደረ ቤቱ ፤ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ አድኅነኒ እሞተ ከንቱ ፤ ኲሉ ከንቱ ከንቱ ንብረቱ ፤ እስመ ኲሉ ኃላፊ ውእቱ"
"መልካም ምግባር ለሌለው ሃይማኖቱ ግን ለቀናው ባሪያህ ፤ ማደሪያውን መኖሪያውን ከቅዱሳን ጋር አድርግ ፤ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ሆይ ከከንቱ ሞት አድነኝ ፤ ዓለምም በዓለም ውስጥ ያለውም ከንቱ ነው ፤ ሁሉም ኃላፊ ነውና"
[መልክዓ መድኃኔ ዓለም]
ዲያቆን ደረጀ ድንቁ
ተወዳጆች
የልጅነት መንፈስ ያደረባቸው ሰዎች
ሁል ጊዜ ደስተኛ ናቸዉ በማን ? በእግዚአብሔር
ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ ነው የሚለው
✅ ምክንያቱም
ሁልጊዜ በትዳር ደስ አይልም
ሁልጊዜ በስራ ደስ አይለም
ሁልጊዜ በትምህርት ደስ አይልም
ሁለጊዜ ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት
መደሰት አንችልም ወገኖቼ
ሁልጊዜ ግን በእግዚአብሔ መደሰት ይቻላል ።
✅ ይህንን ቃል የተናገረው
ሐዋርያው ቅ.ጳውሎስ
በቤት መንግስት ቁጭ ብሎ
ጮማ እየቆረጠ
ጠጅ እየጠጣ አይደለም
✅ ስለ ኢየሩሳሌም ተስፋ
ስለ ክርስቲያኖች
ሰንሰለት ለብሶ
በጨለማው ክፍል ተጥሎ
ነገ ሊገደል ዛሬ ነው
ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ ያለው
✅ የሞት ፍርደኛው ጳውሎስ ነው
ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ ያለው
ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ ወገኖቼ 🙏
አባ ጽጌ ብርሃንም በወሎ ክፍለ ሀገር በወራይሉ አውራጃ፣ ልዩ ስሙ ደብረ ሐንታ ለሚባለው ገዳም የሕግ መምህር ሆኖ ከተሸመውና ከጓደኛው ከአባ ገብረ ማርያም ጋር እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ፣ እንደ አንድ ልብ መካሪ በመሆን፣ እመቤታችንንና ፈጣሪ ልጇን በጎ በጎ መዓዛ ባላቸው አበባዎችና ፍሬዎች እየመሰለ የሚያመሰግነውን ማኅሌተ ጽጌ የተባለውን ድርሰት፣ በአባቷ በዳዊት መዝሙር መጠን 150 አድርጎ ደረሰ፡፡ ፍሬ ከአበባ አበባም ከፍሬ እንደሚገኝ ኹሉ በማኅሌተ ጽጌ እመቤታችንን በአበባ፥ ጌታችን በፍሬ፤ ወይም እመቤታችንን በፍሬ፥ ጌታችን በአበባ እየተመሰሉ የሚመሰገኑበት ምስጋና ነው። ሰቈቃወ ድንግል ማለት እመቤታችን ከልጇ ከመድኀኔዓለም፣ ከአረጋዊ ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር በስደቷ ወቅት ያየችውን መከራ፥ ልቅሶ ዋይታ የሚዘከርበት የማኅሌተ ጽጌ አርኬ ነው፡፡
(የሰቈቃወ ድንግልን ደራሲ በተመለከተ አባ ጽጌ ድንግል ደረሱት የሚሉ አሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ አባ ገብረ ኢየሱስ ዘገዳመ መጕና /አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ/ ወይም /አባ አርኬላዎስ/ ነው የደረሱት የሚሉም አሉ፡፡)
ፍቅር ለባልንጀራው ክፉ የማያደርግ የሕግ ፍጻሜ ነውና፤ ሮሜ 13፥10-11፣ አባ ጽጌ ብርሃንና አባ ገብረ ማርያምም የዘመነ ጽጌ የማኅሌት አገልግሎትን ሳይለያዩ በሰላምና በፍቅር (በአንድነት) አገልግለዋል፣ ማለትም አንድ ዓመት አባ ገብረ ማርያም የክረምት መውጫና የዘመነ ጽጌ ዋዜማ በሆነው መስከረም 25፣ ቀን ከደብረ ሐንታ መጥቶ ገዳመ ጽጌ (ደብረ ብሥራት) ገብቶ ከመስከረም 26 ቀን እስከ ኅዳር 5 ቀን ያለውን የዘመነ ጽጌ የ40 ቀን አገልግሎትን ከአባ ጽጌ ብርሃን ጋር ፈጽሞ ኅዳር 8 ቀን ወደ ደብረ ሐንታ ይመለሳል፤ በሚቀጥለው ዓመት ደግሞ አባ ጽጌ ብርሃን ከገዳመ ጽጌ (ከደብረ ብሥራት) ወደ ደብረ ሐንታ ሄዶ እንደዚሁ እንደ አባ ገብረ ማርያም 40ውን ቀን አገልግሎ ይመለሳል፣ እኒህ ሁለቱ ቅዱሳን ሊቃውንትም ታሪኩ ከላይ እንደተገለጸው እንዲህ እያደረጉ እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው ድረስ በፍቅርና በትሕትና ሲያገለግሉ ኖረዋል፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባ_መቃርስ
ዳግመኛም በዚህች ቀን ቅዱስ አባት የሀገረ ቃው ኤጲስቆጶስ አባ መቃርስ አረፈ።
ለዚህም ቅዱስ የዝንጉዎችን ምክር ተከትሎ ያልሔደ፣ በኃጢአተኞችም ጎዳና ያልተጓዘ፣ በዘባቾችም መቀመጫ ያልተቀመጠ፣ የእግዚአብሔርን ሕግ መጠበቅ ፈቃዱ የሆነ እንጂ ሕጉንም በቀንና በሌሊት የሚያነብ የሚያስተምር ብፁዕ ነው የሚለው የነቢይ ዳዊት ቃል ተፈጽሞለታል።
ይህ አባ መቃርስ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመጠበቅ በመክሊት ነግዶ ዕጥፍ አድርጎ አትርፎአልና እግዚአብሔርም በእጆቹ ያደረጋቸውን ታላላቆች ድንቆች ተአምራት ስንቱን እንናገራለን። ስለርሱም እንዲህ ተባለ እርሱ በሀገረ ቃው ተሾሞ በወንበር ተቀምጦ ሕዝብን በሚያስተምራቸው ጊዜ ዘወትር ያለቅሳል ። ከደቀ መዛሙርቱም አንዱ እጅግ የሚወደው አማለውና አባቴ ሆይ ሁል ጊዜ ለምን ታለቅሳለህ ንገረኝ አለው እርሱም ስለ መሐላው ፈርቶ ዘይት በብርሌ ውስጥ እንደሚታይ የወገኖቼን ኃጢአታቸውን የከፋች ሥራቸውንም በማይና በምመለከት ጊዜ አለቅሳለሁ ብሎ መለሰለት።
ሁለተኛ ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመሠዊያው ላይ ተቀምጦ የየአንዳንዱን የሰውን ሥራ መላእክት ሲያቀርቡለት አየው በዚያንም ጊዜ እንዲህ የሚል ቃል ሰማ ኤጲስቆጶስ ሆይ ለምን ቸለል ትላለህ ሕዝቡን አትገሥጻቸውምን አታስተምራቸውምን እርሱም አቤቱ እነርሱ ትምርቴን አይቀበሉም ብሎ መለሰ። ሁለተኛም እንዲህ አለው ለኤጲስቆጶስ ሕዝቡን ማስተማር ይገባዋል ትምርቱን ካልተቀበሉ ግን ደማቸው በራሳቸው ይሆናል።
ከዚህም በኋላ መ*ናፍ*ቁ ንጉሥ መርቅያኖስ ወደ ሰበሰበው ጉባኤ ከሊቀ ጳጳሳቱ ዲዮስቆሮስ ጋር ይሔድ ዘንድ ጠሩት የተሰበሰቡትም አንዱን ክርስቶስ ሁለት ባሕርይ የሚሉ ናቸው በደረሰም ጊዜ ስለ ልብሱ አዳፋነት ወደ ንጉሥ አዳራሽ መግባትን ከለከሉት አባ ዲዮስቆሮስም ከእርሱ ጋር እንዲአስገቡት ጳጳስ መሆኑን ነገራቸው።
በገቡም ጊዜ አንዱን ክርስቶስን ሁለት ባሕርይ አድርገው ትስብእቱን ከመለኮቱ እንደለዩት እምነታቸውን ሰሙ ስለዚህም ንጉሡንና ጉባኤውን አወገዙአቸው እሊህ አባቶቻችን አባ ዲዮስቆሮስና አባ መቃርስ ስለ ቀናች ሃይማኖታቸው ነፍሳቸውን ለሞት አሳልፎ ለመስጠት ቆርጠዋልና ንጉሡም ወደ ደሴተ ጋግራ አጋዛቸው።
ከዚያም ከምእመን ነጋዴ ጋር ወደ እስክንድርያ አባ ዲዮስቆሮስን ሰደደው እርሱ ለአባ መቃርስ ትንቢት ተናግሮለት ነበርና እንዲህ ብሎ አንተ ግን በእስክንድርያ አገር የሰማዕትነት አክሊል ትቀበል ዘንድ አለህ።
አባ መቃርስም ወደ እስክንድርያ ሲደርስ በዚያን ጊዜ የመ*ናፍ*ቁ የንጉሥ መርቅያን በውስጡ የከፋች ሃይማኖቱ የተጻፈበት የመልእክት ደብዳቤ ደረሰ መልእክተኛውንም እንዲህ ብሎ አዞታል በእኛ ሃይማኖት አምኖ በዚህ መዝገብ ውስጥ መጀመሪያ የጻፈ በእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ይሁን የሚል ነው አብሮታራ የሚባል አንድ ሰው ተቀዳድሞ በውስጡ ሊጽፍ ያንን መጽሐፍ ተቀበለ ቅዱስ አባ መቃርስም እንዲህ አለው ከእስክንድርያ አገር በሔደ ጊዜ ከእኔ በኋላ አንተ በቤተ ክርስቲያን የሠለጠንክ ትሆናለህ ብሎ የነገረህን የአባ ዲዮስቆሮስን ቃሉን አስብ ያን ጊዜ አብሮታራ ያንን ቃል አስታውሶ በዚያ በረከሰ መጽሐፍ ላይ ሳይጽፍ ቀረ።
የንጉሡም መልክተኛ አባ መቃርስ በንጉሥ ሃይማኖት እንደማያምን በአወቀ ጊዜ ተቆጥቶ ከኵላሊቱ ላይ ረገጠው ያን ጊዜም ሙቶ የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ ሥጋውንም ምእመናን ወስደው ከነቢይ ኤልሳዕና ከመጥምቁ ዮሐንስ ሥጋ ጋር በአንድነት አኖሩት ወደ ወደደው ክርስቶስም የመንግሥት ዘውድን ተቀዳጅቶ ሔደ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት፣ #የማሕሌተ_ጽጌ_ትርጕምና_ታሪክ፣ #ገድለ_አቡነ_መብዓ_ጽዮን እና #ከገድላት_አንደበት)
#ጥቅምት_27
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ሃያ ሰባት በዚህች ዕለት #የአምላካችን_የመድኃኔዓለም የስቅለቱ መታሰቢያ ነው፣ #የጻድቁ_አባ_መብዓ_ጽዮን የቃልኪዳን ቀን፣ የማህሌተ ጽጌ ደራሲው #አባ_ጽጌ_ድንግል_ዘወለቃ የእረፍታቸው መታሰቢያ ነው፣ ቅዱስ አባት የሀገረ ቃው #ኤጲስቆጶስ_አባ_መቃርስ አረፈ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#መድኃኔዓለም (በዓለ ስቅለት)
ጥቅምት ሃያ ሰባት በዚህች ዕለት የአምላካችን የመድኃኔዓለም የስቅለቱ መታሰቢያ ነው።
መድኃኒታችን ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በቸርነቱ ስለኹላችን ድኅነት ሲል ራሱን ወድዶ ፈቅዶ ለሞት አሳልፎ በመስጠት ፍጹም ፍቅሩን አሳይቶናል። በቅዱስ ወንጌልም እርሱም መድኃኒታችን " ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም" ብሎ ነግሮናል። እውነት ነው፣ ራስን ነፍስን ስለጠላት ነፍስ አሳልፎ ከመስጠት በላይ ምን ድንቅ ነገርና ምን ድንቅ ፍቅር አለ?
ቸሩ አምላካችንን የአስቆሮቱ ይሁዳ ሊያስይዘው የሊቃነ ካህናቱን አገልጋዮች እየመራ አመጣቸው። እነርሱንም ማንን ትፈልጋላችሁ ሲላቸው የናዝሬቱ ኢየሱስን አሉት፣ እኔ ነኝ ቢላቸው የቸሩን አምላክ ድምጽ ሰምቶ አይደለም መቆም በሕይወት መጽናት የሚቻለው የለምና ወደ ኋላቸው ተስፈንጥረው ወደቁ። ደጋግሞም እንዲህ ኾነ። በኋላ ግን እኔ ነኝ ብሎ በፈቃዱ ይሁዳ ስሞ አሳልፎ ሰጣቸው።
ከያዙት በኋላ እያዳፉና እየጎተቱ በሰንሰለት አስረው ወደ ቀያፋና ሐና ግቢ ወሰዱት፣ እስከ ሦስት ሰዓትም አላሳረፉትም ሲያሰቃዩት አድረዋል፣ በራሱም ላይ ሰባ ሦስት ስቊረት ያለው ወደ ሦስት መቶ እሾኾችን የያዘ የእሾህ አክሊል ጎንጉነው ቢያደርጉበት የራስ ቅሉን ቀዶ ገብቶ እስከ ልቡ ዘልቋል። እንደምን ጭንቅ ነው? እንዲህም አድርገው ደግሞ እያፌዙ ርኲስ ምራቃቸውን ይተፉበትና በዘንግም ደጋግመው ይመቱት ነበር። እየተፈራረቁ ያለ ምንም ርኅራኄ ቸሩን አምላክ ሥጋው እየተቆረጠ እስኪወድቅ ድረስ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ጽኑዕ ግርፋትን ገርፈውታል። የገረፉበትም ጅራፍ በላዩ ላይ ሥጋን እየጎመደ የሚጥል፣ ሕመሙ አንጀት ሰርሥሮ የሚገባ በስለት የተያያዘበት ነበር።
በኋላም አላሳረፉትም እንዲህ አድርገውትም በሊቶስጥራ አደባባይ ያንን ዕርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት። እርሱ ግን ይህን ኹሉ ግፍ ሲያደርሱበት አንድም አልተናገረም ነበር። በቀራንዮም በአምስት ጽኑዕ ቅንዋት (ሳዶር፣ አላዶር፣ ዳናት፣ አዴራ እና ሮዳስ) ቸንክረው ዕርቃኑን ሰቀሉት።
በዚህች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተሰበረ መጽናናትንም አልፈለገች ነበር፤ ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ እናቱንም እናት ትሆነው ዘንድ በእግረ መስቀሉ አደራን ተቀበለ። ቅዱሳት አንስት በፍጹም ሀዘንና በዋይታ ዋሉ። በስልጣኑም ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ። ሰባት ድንቅ የኾኑ ተአምራትንም አድርጎ አምላክ መኾኑን ገለጠ። ይህም ጽኑዕ የኾነ ለሰማይ ለምድር የከበደ ነገር ሲከሰት ፀሐይ አምላኬን ዕርቃኑ እንዴት አያለሁ ብላ ጨለመች። ጨረቃ ደም ኾነች፣ ከዋክብቱም ረገፉ፣ ንዑዳን ክቡራን ንጹሐን መላእክትም ትዕግስቱን እያደነቁ በጽኑዕ ሐዘንና መደነቅ ከቅዱስ ዕፀ መስቀሉ ፊት እንደሻሽ ተነጠፉ።
አስራ አንድ ሰዓት በሆነም ጊዜ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር ቅድስት ሥጋውን ከመስቀሉ አውርደው በክብር ገንዘው በአዲስ መቃብር ቀበሩት። በሦስተኛውም ቀን እንደተናገረ ተነሳ።
በዛሬዋ ቀን ቤተ ክርስቲያን የመድኃኔለምን የስቅለት በዓል በደማቁ ታከብራለች፤ ይህም የለውጥ በዓል ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰው ስጋውን የቆረሰው መጋቢት 27 ቀን ነው፤ ይህ በዓል ግን በዐቢይ ጾም ስለሚውል በዐቢይ ጾም ሀዘን እንጂ ደስታ ስለሌለና በዓል ማክበር ስለማይፈቀድ፤ ወደ ጥቅምት 27 ተዛውሮ ደስ ብሎን እንድናከብረው ቤተ ክርስቲያን ስርዓት ሰርታልናለች፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_መብዓ_ጽዮን
አባ መብዓ ጽዮን በ፲፭ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ልጅ በማጣታቸው በጾምና በጸሎት ፈጣሪያቸውን ከሚለምኑ ባልና ሚስት ተወለዱ። የንቡረ እድ ሳሙኤል ረባን የሆነው መብዓ ጽዮን አባቱ እስከ ዳዊት ያለውን ትምህርት አስተማረውና ዲቁናን ተቀበለ። ልጁ የትምህርት ዝንባሌ እንዳለው አባቱ ተረድቶ ቤተ ማርያም ከሚባለው ደብር ወስዶ ተክለ አማኅጸኖ ከሚባል የቅኔ መምህር ዘንድ አስገባው። በዚያም ቅኔና እና ሌሎች የቤተ ክርስቲያን እውቀቶችን ገበየ። ከዚህም በተጨማሪ ሥዕል መሳልና ጽሕፈት መጻፍ ተማረ።
መብዓ ጽዮን የልጅነቱን ዘመን ሲፈጽም ‹‹ለነፍሳቸው ድኅነት ዋጋ ያገኙ ቅዱሳን ብዙ ናቸው።በመጾም ያገኙ አሉ፤ በትምህርት ያገኙ አሉ፤ በድካም ያገኙ አሉ፤ በጸሎት በትጋት ያገኙ አሉ፤ እኔ ግን የጌታዬን የኢየሱስ ክርስቶስን የሞቱን መታሰቢያ ማድረግ ይገባኛል። በዚህም ፊቱን አያለሁ፤ እርሱ ጌታ ለደቀመዛሙርቱ "የትንሣኤዬን መታሰቢያ ብታደርጉ የሞቴን መታሰቢያ አድርጉ ብሏልና" በማለት ፍላጎቱ በምንኩስና በመኖር ፈጣሪን ማገልገል መሆኑን ለወላጆቹ ገለጸላቸው።
አባትና እናቱም "ፈጣሪህን ለማገልገል ኅሊናህ ከአሰበ እሺ፤ በጀ ደስተኛ ነን" ብለው ፈቀዱለት። ከዚያም መብዓ ጽዮን ዳሞት አባ ገብረክርስቶስ ወደሚባል መነኩሴ በመሄድ መነኮሰ። አባ መብዓ ጽዮን አባ ገብረክርስቶስ ጋር በመቀመጥ ሥርዓተ ምንኩስናን ካጠኑ በኋላ ከአባ ገብርኤል ዘንድ ሄደው የቅስናን ማእረግ ተቀበሉ። ከዚያም በኋላ በአበው ሕግ በምንኩስና ተወስነው፤ በበአታቸው ሆነው ‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የዕለተ ዓርቡን መከራህን አሳየኝ፤ ስለራሴ ፈጽሞ አለቅስ ዘንድ›› ብለው በጸልዩ ጊዜ ‹‹መከራ መስቀሉን ለማየት ትፈቅዳለህን?›› ብሎ ጠየቃቸው። ጻድቁ አባ መብዓ ጽዮንም ‹‹አዎ አይ ዘንድ እወዳለሁ›› ሲሉ ለጌታቸው መለሱለት። ያን ጊዜም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዕፀ መስቀል ተተከለ። በመስቀሉ ላይም እጆቹና እግሮቹ ተቸንክረውና ተዘርግተው ታዩ ፤በራሱ ላይም የእሾህ አክሊል ደፍቶ ነበር።
📃መድኃኔ ዓለም ሆይ፤ ለጻድቃን ያይደለ ኃጥአንን ለማዳን በራሱ ደም ራሱ ለተጥለቀለቀ ሥነ መልክእህ ሰላም እላለሁ፡፡ ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤ በየጊዜው በነጋ በጠባ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፡፡ በመስቀል ላይ ሣለህ አባት ሆይ፤ ይቅር በላቸው በማለት የተናገርከውን የቸርነትና የርኅራኄ ቃል አስቀድሜ ሰምቻለሁና።
📃መድኃኔ ዓለም ሆይ፣ ስምህን የጠራ መታሰቢያህንም ያደረገ እሱ በዚያ በቁጥር የፍርድ ቀን ከንቱ ሆኖ አይቀርም፡፡
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤ ቅድመ ዓለም የነበርክ ዛሬም ያለህ ለዘለዓለሙም ጸንተህ የምትኖር አምላክ ስትሆን የታሠሩ አገልጋዮችህን አንተ ታሥረህ ፈታሃቸው በሞትህም ሞተህም የሞቱትን ወገኖችህን አስነሣሃቸው፡፡
📃መድኃኔ ዓለም ሆይ፤ ሃይማኖት ስንኳ ቢኖረኝ በጎ ምግባር የሌለኝ አነስተኛው አገልጋይ ማደርያ ቤት መኖሪይ ቦታዬ ከቅዱሳኖችህ ጋር ይሆን ዘንድ ፈቃድህ ይሁን አቤቱ። ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤ ከከንቱ ሞት አድነኝ፡፡ ሁሉ ከንቱ ነው፡፡ የዚህ ዓለም ንብረት የከንቱ ከንቱ ነው፡፡ ሁሉም ኃላፊ ጠፊ ነውና።
✝ መልክዐ መድኃኔዓለም ✝
እንኳን ለመድኃኔዓለም ጥንተ ስቅለቱ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
📌 ጥቅምት 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
2.ቅዱስ መቃርስ ብጹዓዊ
3.አቡነ መብዓ ጽዮን ጻድቅ
4.አባ ጽጌ ድንግል ዘወለቃ
📌 ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ)
2.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
3.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
4.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት
5.ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
#ፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሚዲያ
Follow us on
👉 /channel/fre_amde_haymanot_media
👉 http://linktr.ee/fre_amde_haymanot_media
ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
እንኳን ለቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ ወርሃዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን !!!
✝️ አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ትውልዱ ከነገደ ይሁዳ ከንጉሥ ዳዊት ሲሆን አባቱ ያዕቆብ ሲሆን እናቱ ዮሐዳ ትባላለች
✝️ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን የጠበቀ ክርስቶስን ከተረገዘበት ፣ እስኪወለድ ደግሞም እስከ ግብጽ ስደት ድረስ አብሯት የተንከራተተ፣ ጌታችንንም የተንከባከብ ጻድቅ ሰው ነው
✝️ በሽምግልና ጊዜው እንደ ወጣት እየተጋ በአምላኩ ፊት በትህትናና በቅድስና ኖረ
✝️ በልዑል እግዚአብሔር ተመርጦ ክርስቶስ ኢየሱስንና እመቤታችንን ያገለገለ መልካም ፣ ጻድቅ አረጋዊ ሰው
ቅዱስ ዮሴፍ
✝️ አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ሐምሌ ፳፮ ቀን ዐረፈ
የቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ በረከትና ምልጃ ይደርብን። በጸሎቱ አይለየን።
#አንዲት_ሐይማኖት_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ
#አንዲት_ቤተክርስቲያን
#አንዲት_ጥምቀት
#ቅዱሳን
#ተዋህዶ
#orthodoxchurch
#ኢትዮጵያ
ተወዳጆች ሆይ
ችግራችንን ለሰው ነግረን ይሆናል
ከሰዎች ያገኘነው የመጀመሪያ እርዳታ
አይይ የሚል መልስ ነው።
ከዚህ ውጭ የለም
ይልቁንም እንደሱ ስላላደረከኝ አመሰግናለሁ ይልብሀል
✅ የእግዚአብሔር ወዳጆች
ያየብንን ያላሳየብን
የሰማብንን ያላሰማብን
ጉዳችን ና ገበናችንን የተሽከመልን
እርሱ መድኃኔዓለም ነው።
ት.ኤር ም ፦ 9 ላይ እንዲህ ይላል።
በሰው የታመነ እርሱ የተረገመ ነው ይላል ።
በእግዚአብሔር የታመነ እርሱ ለዘለዓለም የተባረከ ነው ።
ተወዳጆች
ዘመን መገላበጡ አይቀርም
የተሾመ መሻሩ አይቀርም
ያጣ ማግኘቱ አይቀርም
የከሳ መወፈሩ የወፈረ መቅጠኑ አይቀርም
ያጣ ያገኛል የታመመ ይድናል
ጤነኛም ይታመማል
በዘመን አትመኩ
ባላችሁ ነገር አትመኩ
ቤተ እግዚአብሔርን አክብሩ
በዘመን ከመማከት ፈጣሪ አምላክ ይጠብቀን🙏
ርዕስ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን
ጥቅምት 25/2017 #ሰማእቱ_ቅዱስ_መርቆሬዎስ
"ስለአንተ ብለን ሁል ጊዜ ተገድለናል እለት
እለት እንደሚታረዱ በጎች ሆነናል"
መዝ.43፥22
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ወርሐ ክረምቱን እንዲባርክልን ለምንማፀንበት ስም በሰማእቱ ስም ለምናመሰግንበት ለሰማእቱ #ቅዱስ_መርቆሪዮስ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉ወር በገባ በ25 የታላቁ ሰማእት #የቅዱስ_መርቆሪዮስ መታሰቢያ በዓል ሲሆን ቅዱስ መርቆሪዮስ የቀድሞ ስሙ #ፒሎፓደር ሲሆን ትርጉሙም #የአብ ወዳጅ #የወልድ አገልጋይ ማለት ነዉ
👉በወጣትነቱ ከሃዲው ንጉስ ኡልያኖስ ላቆመው ጣኦት አልሰግድም ብሎ የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይችለውን መከራ ተቀበለ በመጨረሻም #ህዳር_25 ቀን አንገቱን ቆርጠው ገደሉት #ደም_ውኃና_ወተት ከአንገቱ ፈሰሰ
👉ንጉሱ በዚያዉ ዘመን #ክርስቲያኖችን በጣም ያሰቃይ ነበር #ቅዱስ_ባስልዮስም ይገስፀዉ ነበር በዚህም ምክንያት ንጉሱ ቅዱስ ባስልዮስን አሰረዉ ጳጳሱ በታሰረበት እስር ቤት የቅዱስ #መርቆርዮስ ሥዕል ነበር
👉 #ቅዱስ_ባስልዮስም ከሥዕሉ ስር በመሆን ፀለየ ሥዕሉም ከቦታዉ ታጣ ያ ሥዕል ወደ ዑልያኖስ ቤት ሄዶ በጦር ወግቶ ገደለዉ በስዕሉ ላይ ያለዉ ጦር ጫፉ ደም ይንጠባጠብ ነበር ቅዱስ ባስልዮስም ከሀዲ ዑልያኖስን #ቅዱስ_መርቆሪዮስ በሥዕሉ አማካኝነት እንደገደለዉ አዉቆ #እግዚአብሔርን አመሰገነ
👉ይህ ሰማዕት በአገራችን በስሙ በርካታ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት አሉት በተለይም #ቅዱስ_ላሊበላ ካነፃቸው 11 ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አንዱን #ቤተ_መርቆሬዎስ ብሎ ሰይሞለታል
👉በዚህ በሰሜን ሸዋ ደግሞ የሚገርም ገዳም አለው ካህናት በማህሌት ወረብ ሲያቀርቡ #ስዕሉ_ያሸበሽባል ይዘላል ይህንንም አይቶ ማረጋገጥ ይቻላል በመዲናችን አዲስ አበባ #ቅዱስ_ኡራኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ ታቦቱ አለ
👉 #መርቆሪዎስ ከሞተ በኋላ ፈረሱ ለሰባት ዓመት ወንጌልን አስተምሯል በኋላም አንገቱን ቆርጠው ገድለውታል የሚገረም ካለ #የበልአምን_አህያ_ይጠይቃት እኛስ #ለእግዚአብሔር የሚሳነዉ ነገር የለም ብለን እንመልሳለን ዘኁልቁ.22፥28 ቅዱስ ጴጥሮስም እንዲህ አለ ቃል የሌለው አህያ በሰው ቃል ተናግሮ የነብዩን ቁጣ አገደ ይላል 2ኛ ጴጥ.2፥16
👉የሰማእቱ #ቅዱስ_መርቆርዮስ ፀሎቱ ምልጃዉ አይለየን በረከቱ ለሁላችንም ይድረሰን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
"✝" እንኳን አደረሳችሁ "✝"
✝ ታላቁ ጻድቅ #አቡነ #ኤልሳዕ (የአቡነ ተክለሃይማኖት ደቀመዝሙር፡ ንቡረዕድና የደብረ ሊባኖስ 2ኛው አበ ምኔት) ✝
✝በ1296 (1306) ዓ/ም እዚህች ቦታ ላይ (#ደብረ #አስቦ ላይ) ቅዱስ አቡነ #ተክለሃይማኖት ዐረፉ፡፡
✿ነሐሴ 24 ቀን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን የገነዙት ደቀ መዝሙራቸው #አቡነ #ኤልሳዕ ነበሩ፡፡
✿ጻድቁ አቡነ ኤልሳዕ በመንበረ ተክለ ሃይማኖት ለ3 ወራት በቅድስና ኑረው ከአባ ተክለ ሃይማኖት መልእክት (ጥሪ) ደርሷቸዋል፡፡
✿ከቅዱሳን አንዱ ከሞት ተነስቶ "ኤልሳዕን ጥሩ፡፡ ፊልጶስን በመንበሩ አኑሩ፡፡" ብሎ ዐረፈ፡፡
✿በ1297 (1307) ጥቅምት 23 ቀንም (ማለትም ዛሬ) ቅዱስ አባ ኤልሳዕ ዐርፈው ቅዱሳን ቀብረዋቸዋል፡፡
ጥቅምት 23/2017 #ሰማእቱ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በሰማእቱ ስም ለምናመሰግንበት #ለቅዱስ_ጊዮርጊስ ወርሐዊ መታሰቢያ ክብረ በዓል እንኳን አደረሰን
👉ታላቁ ሰማዕት #ቅዱስ_ጊዮርጊስ አባቱ የፍልስጤም መኮንን ዞሮንቶስ (እንስጣቴዎስ) እናቱ ደግሞ (አቅሌሲያ) ቴዎብስታ ትባላለች በፍልስጤም ልዳ ጥር 20 በ277 ዓ.ም ተወለደ ጊዮርጊስ ማለት ኮከብ ብሩህ ሀረገ ወይን ፀሐይ ዘልዳ ማለት ነው
👉 #ቅዱስ_ጊዮርጊሰ በፋርስ በኢራን ዱድያኖስ የተባለ ንጉሥ ነገስታቱን ሰብስቦ ሰባ ጣኦታትን ሲያሰግድ ተመለከተ በዚህን ጊዜም ቤተ መንግስት ድረስ በመገስገሰሰ ተቃውሞውን በማሰማት ክርስቲያን መሆኑን መስክሯል ከዚህም በኋላ በተለያዩ ነገስታት #ቅዱስ_ጊዮርጊስ በሰው ህሊና ሊታሰቡ የማይቻላቸው አስራ ዘጠኝ መከራዎች ደርሰውበታል ቅዱስ ጊዮርጊስ ሶስት ጊዜ ሞቶ ሶስት ጊዜ ተነስቷል #የእግዚአብሔር ተአምር በተደጋጋሚ ተገልፆለታል
👉 #የቅዱስ_ጊዮርጊስ መከራ በጥቂቱ ክርስቲያን በመሆኑ ብቻ ወደ እስር ቤት ተወረወረ እጆቹንና እግሮቹን ታስሮ ተገረፈ የብረት ጫማ አጥልቀው አስኬዱት ከብረት አልጋ ላይ አስተኝተው እሳት አነደዱበት እጆቹን የኋሊት አሰሩት በመጋዝ ለሁለት ሰነጠቁት የጋለ ሳህን ከጭንቅላቱ ላይ አስቀመጡበት ሰውነቱን በጩቤ ፈተፈቱት ችቦ እና እሳት አንድደው በግራና በቀኝ አቃጠሉት
👉ምላሱን በቢላዋ ቆረጡት በአፍንጫው ቀዳዳዎች በሚስማር መተው ቸነከሩት በመጥረቢያ ፈለጡት ቅጥራን አፍልተው በጭንቅላቱ ላይ ደፉበት በበሬ አስረው ጎተቱት ጥርሶቹን በጉጥ አስረው ነቃቀሉት ከብረት ድስት ውስጥ ጨምረው ቀቀሉት አስጎንብሰው አሸዋ ጫኑበት ከእንጨት ላይ አንጠልጥለው በእሳት አጋዩት በወፍጮ ፈጩት
👉#ሰማዕቱ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ ስለ ቤተ ክርስቲያን ፍቅር ሲል በሰይፍ ተቀልቶ በመንኮራኩር ተፈጭቶ ወደ እቶን እሳት ተወርውሮ ለአእምሮ በሚከብድ መልኩ ብዙ መከራን ተቀብሎ በ 27 አመቱ ሚያዚያ 23 ቀን መከራን ተቀብሎ በሰማዕትነት አርፏል
👉እግዚአብሔር ሰማዕታትን በደም ቅዱሳንን በተጋድሎ ያፀናል አምላክ እኛንም #በሀይማኖት_በምግባር እንድንፀና መልካም ፈቃዱ ይሁንልን የተባረከ የተቀደሰ #ቀዳሚት_ሰንበት ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
#ጥቅምት_22
#ቅዱስ_ሉቃስ_ወንጌላዊ
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ሃያ ሁለት በዚህች ቀን ብልህ ጥበበኛ የሆነ ቅዱስ ወንጌላዊ ሉቃስ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ የከበረ ወንጌል ከመዘገባቸው ከሰባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ የተቆጠረ ነው።
እርሱም ወንጌልን ስለማስተማር በሥራው ሀሉ ሐዋርያት ጴጥሮስንና ጳውሎስን የሚአገለግላቸው ሆነ ለታኦፊላም ወንጌልንና የሐዋርያትን ዜና የጻፈ ሉቃስ ነው።
ቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስም ከተገደሉ በኋላ በሮሜ ሀገር የሚያስተምር ሆነ በቀናች ሃይማኖትም ይጸኑ ዘንድ ለምእመናን መልእክትን ይጽፍ ነበር። ስለዚህም ጣዖት አምላኪዎች ከአይሁድ ጋር በመስማማት አንድ ግምባር ፈጠሩ በንጉሥ ኔሮን ፊት ቁመው ስለ ሐዋርያው ሉቃስ እንዲህ ብለው ጮኹ ይህ ሉቃስ ብዙዎች ሰዎችን በሥራዩ ወደ ትምህርቱ አስገባቸው። ንጉሥ ኔሮንም ወደ ፍርድ አደባባይ ሉቃስን እንዲአቀርቡት አዘዘ።
ሐዋርያ ሉቃስም ከዚህ ዓለም መውጫው እንደ ደረሰ በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ወደ ባሕር ዳርቻ ሔደ። በዚያም ዓሣ የሚያጠምድ አንድ ሽማግሌ ሰው አገኘ። መጻሕፍቱንና ደብዳቤዎቹን ሰጠው ወደ እግዚአብሔር መንገድ መርተው ያደርሱሃልና እሊህን መጻሕፍት ጠብቃቸው አለው።
በንጉሥ ኔሮንም ፊት ቀርቦ በቆመ ጊዜ ንጉሡ በሥራይህ ሕዝቡን የምታስት እስከመቼ ነው አለው ቅዱስ ሉቃስም እኔ ለሕያው እግዚአብሔር ልጅ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያው ነኝ እንጂ ሥራየኛ አይደለሁም ብሎ መለሰለት።
ንጉሥ ኔሮንም ሁለተኛ እንዲህ አለው እየጻፈች ሰዎችን የምታስት ይቺን እጅህን እኔ እቆርጣታለሁ ይህንንም ብሎ የቀኝ እጁን እንዲቆርጡ አዘዘ በቆረጡትም ጊዜ ንጉሥ ሆይ እኛ የዚህን ዓለም ሞት እንደማንፈራ እወቅ ነገር ግን የጌታዬንና የፈጣሪዬን ኃይሉን ታውቅ ዘንድ አሳይሃለሁ። ይህንንም ብሎ የተቆረጠች የቀኝ እጁን በግራ እጁ አንሥቶ ከተቆረጠችበት ቦታዋ ላይ አገናኝቶ እንደ ቀድሞዋ ደኅነኛ አደረጋት። ከዚህም በኋላ ለያት በዚያም የነበሩ አደነቁ የሠራዊት አለቃውና ሚስቱ ብዙዎችም ሰዎች ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ቁጥራቸውም አራት መቶ ሰባ ሰባት ነፍስ ሆነ ንጉሡም ከቅዱስ ሉቃስ ጋር ራሶቻቸውን እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጡአቸው የምስክርነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።
ከዚህም በኋላ የቅዱስ ሉቃስን ሥጋ በማቅ አይበት ውስጥ አድርገው ወደ ባሕር ጣሉት በእግዚአብሔርም ፈቃድ ወደ አንድ ደሴት ደረሰ። ምእመናንም አግኝተው ወስደው ገነዙት በአማረ ቦታም አኖሩት።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያው ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት)
ጥቅምት 28/2017 #መድኃኒታችን_ቅዱስ_አማኑኤል
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ለአምላካችን #ቅዱስ_አማኑኤል ለስደቱ መታሠቢያ አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉አማኑኤል ማለት #እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ማለት ነው
👉 #የአብርሐም_የይስሐቅ_የያእቆብ አምላክ ቅዱስ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን በቸርነቱ ይጠብቀን
👉 #አማኑኤል ማለት አማኑኤል፣ የአምላክ ሰላም፣ የእግዚአብሔር እርቅ፣ የጌታ አንድነት ማለት ነው
👉 #አማኑኤል ማለት "አማኑ" እና "ኤል" ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው አማኑኤል ማለት #እግዚአብሔር ከኛ ጋር ማለት ነዉ
👉"ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ ወይሰመይ ስሙ አማኑኤል ዘበትርጓሜሁ #እግዚአብሔር ምስሌነ"
👉ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅንም ትወልዳለች ስሙንም #አማኑኤል ትለዋለች ትርጉሙም #እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው ( ኢሳ 7፥14)ምስጋናና ክብር ለአምላካችን ለቅዱስ #አማኑኤል ይሁን
👉እረኛችን #ቅዱስ_አማኑኤል ጥቂት ስምህን ማወቅ ብዙ ደስታን ታጎናፅፋለች በተሳዳቢ ዓለም ዝምታን አስተማርከን እየተገፉ መደሰትን እያጡ ማመስገንን ነገን እያሳይህ ዛሬ ማኖርን ባንተ ማረፍን በስምህ አስተማርከን
👉ቅዱስ #አማኑኤል አባታችን እረኛችን የምታሳጣን የለም ያጣነዉም የለም እረኛችን ሆይ ካላንተ አባትም እረኛም ጠባቂም የለንም አሁንም ስለ ስምህ ብለህ ጠብቀን "አሜን"
👉ቅዱስ #አማኑኤል አምላካችን ሀገራችንን ህዝባችንን ከክፉ መከራ ይጠብቅልን የስደት ቀን ስንቃችን እናታችን #ማርያም ፀሎትሽ በረከትሽ ለሁላችንም ይድረሰን በዚህ እለት የሚታሰቡ ርዕሰ አበዉ ቅዱሣን #አብርሐም_ይስሐቅ_ያዕቆብ የከበረዉ ቃል ኪዳናቸዉ ለሁላችንም ይድረሰን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ተወዳጆች
በፊቱ እንደቆምን ከተሰማን እውነት እንናገራለን
በፊቱ እንደቆምን ከተሰማን አንበድልም
የሱ ፊት ከኃጢአት የሚጠብቅ ነው።
እኛ ብዙ ጊዜ እግዚአብሔር ያለው በሰማይ ነው ሲባል
ሰማይ የሚ ጋርደው ይመስለናል
ደመና የሚጋርደው ይመስለናል
✅ ስለዚህ
መንደር ቀይሰን ሰፈር ቀይረን
በጨለማ ውስጥ ሁነን እንበድላለን
✅ እግዚአብሔር ግን
ሁሉን የሚያይ ጌታ ነው
ሁሉን የሚመረምር አምላክ ነው።
እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን በእውነት🙏
እንኳን አደረሰነ!
✝በዓሎሙ ለቅዱሳን፦
✿አቡነ መባዓ ጽዮን (ተክለ ማርያም)
✿አቡነ ሐራ ድንግል (ግብጻዊ)
✿አቡነ ጽጌ ድንግል (ዘወለቃ)
✿አቡነ መቃርዮስ (ዘሃገረ ቃው)
ጥቅምት ፳፯
✝ማርያም ድንግል ዘሕዝቅኤል ኆኅተ ምሥራቅ፤
እንተ እምኔኪ ወጽአ ነጎድጓደ ሕይወት ወመብረቅ፤
ዘትትአጸፊ ወትረ አልባሰ ብሩር ወወርቅ፤
ተማኅጸንኩ በብካይኪ ከመ ታድኅንኒ ለዕሩቅ፤
አመ ይፈትሕ ላዕለ ኃጥአን ወልድኪ ጻድቅ!
✝ሰላም ለስቅለትከ ዲበ ዕጽ ይቡስ፤
እስከነ ርሕሰ በደምከ እግዚአ ኃያላን ክርስቶስ፤
ተዘኪረከ ሐዘነ እምከ ወአንብዑ ለዮሐንስ፤
አድኅነኒ እምቅንአተ ሰይጣን በሥጋ ወነፍስ፤
ወክድነኒ ለገብርከ ሞጣሕተ ጸጋ ወሞገስ!
✝ሰላም ለሕማምከ ለለአሐዱ አሐዱ፤
ከመ ትግበር ምሕረተ ለአዳም ወለውሉዱ፤
መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ለዕጸ ሕይወት ጉንዱ፤
መባዓ ጽዮን ወመቃርዮስ ወጽጌ ብርሃን ናርዱ፤
ዘምስለ ሐራ ድንግል ለፍቅርከ ሰገዱ!
✝ተክለ ማርያም ብጹዕ ዘተሰምየ መባዓ ጽዮን፤
ዘይዜከር ሕማሞ ለወልደ ማርያም መድኅን፤
ወመቃርዮስ ዘቃው ቢጸ ዲዮስቆሮስ ምዕመን፤
ዘይዘብጥ ርዕሶ በበትረ ኀጺን ወዕብን፤
ወጽጌ ድንግል መምህር ነባቤ ማኅሌት ወድርሳን!
(አርኬ - ዝክረ ቅዱሳን ርቱዓነ ሃይማኖት)
እንዲህ ሆኖ በሮም አደባባይ ለቅዱስ ጴጥሮስ እንደታየው ጌታችን ለአባ መብዓ ጽዮንም ታያቸው። ከዚህም በኋላ አባ መብዓ ጽዮን የጌታችን የመድኃኔዓለምን ሕማሙን፣ መከራውን፣ ግርፋቱን፣ እስራቱን በጠቅላላ ፲፫ቱን ሕማማተ መስቀል በማሰብ ጀርባቸውን በአለንጋ ይገርፉ ፤ራሳቸውንም በዘንግ ይመቱ ነበር። የጌታን መከራ መስቀል እያሰቡ ዐይኖቻቸው አስከሚጠፉ ድረስ ያለቅሱ ነበር ። ጌታችን ግንደ መስቀሉን (የመስቀሉን ግንድ) አንደተሸከመ በማሰብ ትልቅ ድንግያ ተሸክመው ይሰግዱ ነበር። መራራ ሐሞት መጠጣቱን በማሰብ ዓርብ ዓርብ ኮሶ ይጠጡ ነበር። የጌታ ደቀመዝሙር ዮሐንስ ወንጌላዊ ጌታ በተሰቀለ ጊዜ አብሮ ስለነበርና ዐይን በዐይን ስለተመለከተ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራ መስቀል እያሰበ ፸ ዘመን ፊቱን በሐዘን ቋጥሮ እንደኖረ ሁሉ ጻድቁ አባ መብዓ ጽዮንም እንደ ዮሐንስ ወንጌላዊ የጌታችንን መከራ መስቀል እያሰቡ ከዓለም ተድላና ደስታ ተለይተው በትምህርት ፣ በትሩፋት ፣ በገድል ጸንተው ኖረዋል። ጻድቁ መብዓ ጽዮን በሕይወተ ሥጋ ዘመናቸው የላመ የጣመ እንዳልተመገቡ፤በፈረስ በበቅሎ እንዳልሄዱ፤አልጋ ላይ እንዳልተኙ፤ገድላቸው ያስረዳል። የክርስትናን ትምህርት ለጋፋት ሰዎች እንዲስፋፋ ያደረጉት አባ መብዓ ጽዮን የጌታን ሕማማተ መስቀል እያሰቡ ዘወትር ስለሚያነቡ ዐይኖቻችው ጠፍተው ነበር። ነገር ግን እመ ብዙኃን የሆነችው ቅድስት ድንግል ማርያም ወደኚህ
ጻድቅ አባት በአት የብርሃን ጽዋ ይዛ መጥታ ዐይኖቻቸውን ቀብታ አድናቸዋለች። ከዚህ የተነሳ በትረ ማርያም እየተባሉ ይጠሩ አንደነበር ገድላቸው ያስረዳል።
የጻድቁ መታሰቢያ በዓል በየዓመቱ ጥቅምት ፳፯ ቀን ከመድኃኔዓለም የስቅለት በዓል ጋር ይከበራል። ጥቅምት ፳፯ ቀን ለወዳጆቹ እውነተኛውን ዋጋ የሚከፍል መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለጻድቁ አባ መብዓ ጽዮን ብዙ ቃል ኪዳን የገባበት ቀን ነው።
የአቡነ መብዓ ጽዮን ረድኤታቸው፣ በረከታቸውና አማላጅነታቸው አይለየን፤አሜን!!!
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ጽጌ_ድንግል_ዘወለቃ
በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረ ሊቅ ሲኾን፤ አባ ጽጌ ድንግል (ጽጌ ብርሃን) ሀገሩ ይፋት ሃይማኖቱ ኦሪት ነበረ፡፡ በንጉሥ ሰሎሞን ፈቃድና በካህኑ አዛርያስ መሪነት የብሉያት መጻሕፍትን ከዕብራይስጥ ወደ ግእዝ ተርጕመው ሊያስተምሩ፣ ታቦተ ጽዮንን ከኢየሩሳሌም ይዘው ወደ ኢትዮጵያ ከመጡትና የብሉያት መጻሕፍት ሊቃውንት ከነበሩት ከ318 ሌዋውያን (ከቤተ እስራኤላውያን) ነገድ ነው፡፡ የተወለደውም በሰሜን ሸዋ በይፋት አውራጃ ውስጥ ሲሆን፤ መጀመርያ ኢእማኒ (ያላመነና ያልተጠመቀ) ነበር።
ከዕለታት አንድ ቀን ይህ ሰው፤ በወጣትነት ዕድሜው አውሬ ለማድን ወደ ጫካ ሄደ፣ ጫካዋም በዚያው በይፋት አውራጃ የምትገኝና ልዩ ስሟ ደንስ (ገዳመ ደንስ) ትባላለች፣ በጫካዋ ውስጥም ፊቷ በጽጌረዳ አበባ የተከበበና ያጌጠ፣ እጅግም ደስ የምታሰኝ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕል አይቶ በሥዕሏ ውበት እየተደነቀ ሥዕሏን ሲመለከት እንደ እርሱ ያልተጠመቀ ጓደኛው መጥቶ፣ "ምን እየፈለግህ ነው? የክርስቲኖችን ሥዕል ነውን?" ብሎ ለድንግል ማርያም ምስጋና ይግባትና በያዘው በትር ሥዕሏን ሲመታት ወዲያው ተቀሥፎ ሞተ። ከዚህ በኋላ ክንፎቹ በጽጌረዳ አበባ ያጌጡ የመሰለ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል በነጭ ወፍ ተመስሎ ወደ እርሱ መጥቶ አንድ ቀይ መነኩሴ እሰኪመጣ ድረስ፣ ይህችን ሥዕል ጠብቃት ብሎ በሰው አነጋገር ነግሮት ተሠወረ።
የአቡነ ዜና ማርቆስ የገድል መጽሐፍ፣ እንደሚናገረው ካህን ከነበረው ከአባቱ ከዘርዐ ዮሐንስ አና ከእናቱ ማርያም ዘመዳ በ1262 ዓ.ም. ኅዳር 24 ቀን በሰሜን ሸዋ ግዛት በሚገኘውና ልዩ ስሙ እቲሳ ቅዱስ ሚካኤል በሚባለው አጥቢያ የተወለደው አቡነ ዜና ማርቆስ ደብረ ብስራት ከሚባለው ገዳሙ ወደ ይፋት መጥቶ ከነብዩ ኢሳይያስ ትንቢት ከምዕ. 11፥1 ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ እያለ በግእዝ ቋንቋ ሲያነብ አባ ጽጌ ድንግል በሰማ ጊዜ አባቶቼ አይሁድ የነቢያትን ትንቢት ንባቡን አስተምረውኛል አውቀዋለሁ፤ ትርጕሙን ግን አላውቀውምና ተርጕምልኝ አለው፡፡
አቡነ ዜና ማርቆስም ሲተረጕምለት እንዲህ አለ፤ ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ፣ የሚለው ንባብ ከእሴይ ነገድ የሕይወት በትር የኾነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትወለዳለች ማለት ነው፡፡ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ የሚለው ንባብ ደግሞ፤ እመቤታችን ተወልዳ፣ ከእርሷም ጌታ በድንግልና ይወለዳል፣ ከጌታም ክብር ይገኛል ማለት ነው፣ ይህም ጌታ ተወልዶ ትንቢቱ በእውነት ተፈጽሟል ብሎ ተረጐመለት፡፡ ኢሳ 7፥14፣ ማቴ18፥24፡፡
ይህ ሰውም (አባ ጽጌ ድንግልም) በዚህ ትርጕም ደስ ተሰኝቶ አባት ሆይ የኢሳይያስን ትንቢት በመልካም ሁኔታ ተረጐምከው፣ መልካም ነገርንም ተናገርክ አለውና፣ ሥዕሏ ወዳለችበት ቦታ ወስዶ ታሪኩ ከላይ እንደተገለጸው፣ በጫካ ውስጥ ያያትን ሥዕል ጓደኛው በያዘው ብትር ሲመታት ወዲያውኑ እንደተቀሠፈና ክንፎቹ በጽጌረዳ አበባ ያጌጡ፣ "አንድ ነጭ ወፍ /ቅዱስ ሩፋኤል/" ወደ እርሱ መጥቶ ቀይ መነኵሴ እስኪመጣ ድረስ ይህችን ሥዕል ጠብቃት ብሎ በሰው አነጋገር ያነጋገረውን ሁሉ ነገረው፣ አቡነ ዜና ማርቆስም ከሥዕሏ የተደረገውን ተአምር ሰምቶ፣ እጅግ ደስ አለውና በል መጀመሪያ እመቤታችን በድንግልና በወለደችው በፈጣሪ ልጇ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን ይህችን ሥዕል ያስገኘ፣ ሰማይና ምድርን፣ በውስጣቸው ያለውንም ሁሉ የፈጠረ፣ እርሱ እንደኾነ እውቅ አለውና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቆ ጽጌ ብርሃን ብሎ ሰየመው፡፡
ከዚህ በኋላ ሥዕሏን በገዳመ ደንስ ደብረ ብሥራት ወደሚባለው ገዳም ወስዶ በዘመነ ጽጌ ጥቅምት አንድ ቀን በክብር አስቀመጣት የምትከብርትንም ቀን ጥቅምት 3 እና ሰኔ 8 ቀን አደረገ፡፡
አቡነ ዜና ማርቆስም ጽጌ ብርሃንን ለመዓርገ ምንኵስና አበቃው፤ የአባ ጽጌ ብርሃንም ጽጌ ድንግል የሚል ቅጽል ስም አለው፣ በማኅሌት አገልግሎት ጊዜም ታላቁ ጻድቅ አቡነ ዜና ማርቆስ ቤተ ክርስቲያኒቱንና ሥዕሏን እየዞረ ሲያጥን፣ እመቤታችን የካህናቱን አገልግሎት እንደምትባርክ፣ ካህናቱ በግልጽ ይረዱ ነበር፣ አባ ጽጌ ብርሃንም ከመጠመቁ በፊት በአባቶቹ በአይሁድ ሥርዓት እያለ የብሉያት መጻሕፍትን የተማረ ነበር፣ የሐዲሳት መጻሕፍት ትርጓሜን ግን ከአቡነ ዜና ማርቆስ ተማረ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ላሉ አሕዛብ ሁሉ የድኅነት ምክንያት ትሆኑ ዘንድ ብርሃናቸው፣ መምህራቸው አደረግኋችሁ ብሉ ጌታ ነቢዩ ኢሳይያስንና ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስን እንደመረጣቸው፣ ኢሳ 49፥6.፣ የሐ.ሥራ13፥47 ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ዜና ማርቆስ ስብከተ ወንጌልን እንደ ዕለት ጉርስና እንደ ዓመት ልብስ አድርጎ፣ መላ ኢትዮጵያን ዞሮ፣ አስተምሮና ባርኮ የዕድሜ ባለጸጋም ሆኖ በተወለደ በ140 ዓመት በ1402 ዓ.ም ታኅሣሥ 3 ቀን ፣ ዐርብ ጠዋት ዐረፈ፡፡
ጥቅምት 27/2017 #መድኃኔዓለም (የለዉጥ በዐል)
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ለጌታችን ለመድኃኒታችን #ለኢየሱስ_ክርስቶስ ጥንተ ስቅለቱን ለምናስብበት አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉ለአምላካችን ለመድኃኒታችን #ለኢየሱስ_ክርሰቶስ ክብር ይግባዉና መጋቢት 27 የጌታችን ጥንተ ስቅለቱ ሲሆን የፆም ጊዜ ስለሆነ ተድላ ደስታ ባለመኖሩ ስንዱአ ቅድስት ቤተክርስቲያን በዓሉ #ወደ_ጥቅምት_27_ተዘዋውሮ በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር ስርአት ሰርታለች
✝️ #ሞቱን_በሚመስል_ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን ሮሜ.6፥5
✝️የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ስለ ዓለም ድኅነት በሥጋ የተሰቀለበት ዕለት ነው
✝️ሐዋርያው ቅዱስ ጳዉሎስ አውቀውስ ቢሆን የክብርን ጌታን ባልሰቀሉት ቆሮ.1 ቁ.1-18 እንዳለ ይህ ዕለት የአይሁድ ካህናት ያለበደል ያለጥፋት ንጹሕና ፃድቅ የሆነውን #ጌታ_የሰቀሉበት ዕለት ነው
✝️ዕለቱም ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ የዓለም ሁሉ መድኃኒት ለአዳምና ለልጆቹ ሲል በመልእልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የምናስብበት ታላቅ ቀን ነው ማቴ.27፥35-75 ክርስቲያኖች ሁልጊዜም ዕለተ ዓርብ ሲመጣ ሕማሙን ስቅለቱን ሞቱን የሚያስቡበት ጊዜ ነው
✝️በሮማውያን ሕግና ሥርዓት መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት የሕይወት መቅጫ አርማ ሆኖ ሳለ ለእኛ የዲያብሎስ ድል መንሻ ስላደረገው በስቅለቱና በሞቱም ሕይወትን ስለአገኘን በዚህም ምክንያት #መልካሙ_ዓርብ በመባል እንደሚታወቅ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ያትታሉ
✝️ከስድስት ሰዓት ጀምሮም እስከ ዘጠኝ ሰዓት ዓለም ሁሉ ጨለማ ሆነ ማቴዎስ.27፥45 #ፈጣሪዋ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ባየችውጊዜ ፀሐይ ጨለመች እርሱም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የነሣትን ለባዊት ነባቢት የሆነች ነፍሱን ከሥጋው ለያት ሐዋርያዉ ጴጥሮስ በሥጋ ምውት ሲሆን በመለኮት ሕያው ነው እንዳለ ነፍሱ ከመለኮት ሳትለይ ከሥጋ ተለየች
✝️ #ጌታ_ሁሉ_ተፈፀመ ብሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ስጋው በራሱ ፈቃድ ከለየ በኋላ አምላክነቱን ለመግለፅ የታዩ ተአምራት በሰማይና በምድር እነዚህ ናቸው ማቴ.24፥29 ፤ 27፥45
👉ፀሐይ ጨለመች
👉 ጨረቃ ደም ሆነች
👉 ከዋክብት ረገፉ
👉የቤተ መቅደስ መጋረጃ ተቀደደ
👉ምድር ተናወጠች
👉መቃብሮች ተከፈቱ
👉አለቶች ተፈረካከሱ
👉በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን ኢሳ.53፥5 እርሱ የሾህ አክሊል ተደፍቶበት ለእኛ #የክብር_አክሊል_ደፋልን ጐኑን በጦር ተወግቶና ቆስሎ ለዘለአለም ፈወሰን ተጠማሁ እያለ እኛን #የሕይወት_መጠጥ አጠጣን
👉አንዱ ስለሁላችን ሞተ የእኛን ቅጣት ወሰደ ሞታችንን ሞተ ገነትን እንድንወርስና በሕይወት እንኖር ዘንድ ሞተ መርገማችንን ወሰደ ስለዚህ እኛም የመድሃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን ስቅላት ሞት ስናስብ የኢየሱስ ክርስቶስ መሞት የሰው ልጆች የጥል ግድግዳ ፈርሶ ፍቅር የተመሰረተበት ዕለት ነውና ክብር ምስጋና ዋጋ ከፍሎ ላዳነን በምህረት አይኑ ለጎበኘን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን #ለኢየሱስ_ክርስቶስ ይሁን እንላለን
👉በዚህ እለት በአመታዊ የእረፍት መታሰቢያ በአላቸዉ የምናስባቸዉ የቤተ ክርስቲያናችን ከዋክብቶች ቅዱሳን አባቶቻችን አባ #መብዐ_ፅዮን እና አባ #ፅጌ_ድንግል እንዲሁም ሌሎች ቅዱሣን በምልጃ ፀሎታቸዉ ያስቡን ረድኤት በረከታቸዉ አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
✝እንኳን አደረሰነ!
✝በዓለ ቅዱሳን፦
✿ያዕቆብ ዘኢየሩሳሌም
✿ጢሞና ሐዋርያ
✿ፊልጶስ ኅሩይ
✿ወአግናጥዮስ ሰማዕት
ጥቅምት ፳፮፦
✝ማርያም ድንግል ለኤርምያስ ጽርሐ ቅድሳቱ፤
ዘኃደረ ውስቴትኪ ፀሐየ አርያም ዘየኃቱ፤
በከመ በከየ ለሕዝቡ አመ አፍለሥዎ ሎቱ፤
ወላዲተ አምላክ ንጽሕት በድንግልና ክልኤቱ፤
በከይኪ ወአስቆቀውኪ ለወልድኪ በእንተ ሞቱ!
✝ሰላም ለከ ረድአ ክርስቶስ ጢሞና፤
ዘሤሙከ ሐዋርያት ዘምስለ ኒቃሮን ወጳርሜና፤
ወያዕቆብ ወልደ ዮሴፍ ዘውገ ናትናኤል ዘቃና፤
በጾም ወበጸሎት ወበኲሉ ትኅትና፤
ከመ ፊልጶስ ወአግናጥዮስ ዘአርታእከ ፍና!
✝ያዕቆብ ሐዋርያ ገባሬ ፍቅር ወሰላም፤
ዘነበረ ጽሙደ በሃገረ ንጉሥ ኢየሩሳሌም፤
ወዘተናከራ ነዋኃ ለዛቲ ዓለም፤
ጢሞና ሐዋርያ መፍቀሬ ምጽዋት ወጾም፤
ፊልጶስ ወአግናጥዮስ ክቡራነ ስም!
(አርኬ - ዝክረ ቅዱሳን ርቱዓነ ሃይማኖት)
ጥቅምት 26/2017 #አረጋዊ_ቅዱስ_ዮሴፍ
#ፃድቁ_አባታችን_ሐብተ_ማርያም
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሳኑ ስም ለምናመሰግንበት ለቅዱሣን አባቶቻችን ወርሐዊ መታሰቢያ ክበረ በዐል እንኳን አደረሰን
በፃድቃን ላይ የሚናገሩ የሽንገላ ከንፈሮች
ዲዳ ይሁኑ መዝ.30፥18
👉ኢትዮጲያዊዉ #ፃድቅ ትዉልዳቸዉ ሸዋ መንዝ ልዩ ስሙ ራዊ ውስጥ ሲሆን አባታቸው ፍሬ ቡሩክ እናታቸው ደግሞ ቅድስት ዮስቲና ትባላለች ግንቦት 26 ተወለዱ በተለይ ቅድስት ዮስቲና እጅግ ደመ ግቡ ምፅዋትን ወዳጅ ቡርክት ሴት ነበረች እንዲያውም ከጻድቁ መወለድ በፊት መንና ጭው ካለ በርሃ ገብታ ነበር
👉ግን የበቃ አባት አግኝቷት "ከማሕጸንሽ ደግ የሥላሴ ባርያ አለና ተመለሽ" ብሏት እንደ ገና ተመልሳለች ፃድቁን ወልዳ አሳድጋም እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ #ሰባት_አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች
👉ወደ ፃድቁ ዜና ሕይወት ስንመለስ #አቡነ_ሃብተ_ማርያም ገና ሕፃን እያሉ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ሲባል ይሰማሉ ይሕችን ጸሎት በሕጻን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ "ማረን እባክህን" እያሉ ይሰግዱ ነበር
👉የ5 ዓመት ሕጻን እንዲህ ሲያደርግ ማየቱ በእውነት ይደንቃል ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍፁም ተሐራሚና ፀዋሚ ነበሩ ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ #ተአምራትን ሰርተዋል የፈጣሪውን ስም ያቃለለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል
👉ፃድቁ አባታችን #በዝምተኛነታቻዉ_በአርምሞ ኑሯቸዉ የታወቁ ናቸዉ በመልአክ መሪነት አክሱም ኢየሩሣሌም ምድረ ግብፅ በእግራቸዉ በመሔድ ተሣልመዋል
👉ለፃድቁ አባታችን ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ቃል ኪዳን ሰጥቶዋቸዋል ወረርሽኝ በሽታና የአባላዘር በሽታ የያዘዉን ሰዉ ፀበልህን ቢጠመቅ ቢጠጣ በፍጥነት ይድናል ለ15 አይነት መቅሰፍቶች እንዲያድኑ ቃል ኪዳን ተሰጥቶዋቸዋል
👉ፃድቁ አባታችን ማእጠንት ሲያጥኑ #መንበረ_ፀባኦት ይታያቸዉ ነበር የፃድቁ ምልጃና ፀሎት ሀገራችንን ህዝባችንን ይጠብቅልን ቃል ኪዳናቸዉም አይለየን
👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአሉ የምናስበዉ አረጋዊ አባታችን #ቅዱስ_ዮሴፍ ምልጃና ፀሎቱ ሁላችንንም ይጠብቀን በዚህ እለት የሚታሰቡ ሌሎች ቅዱሳን ረድኤት በረከት ቃል ኪዳናቸዉ አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
‹‹በእንተ አቡነ አቢብ!››
ጌታችን መድኃኒታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአቡነ አቢብ ተገልጦላቸው ‹‹…ወዳጄ አቢብ ሆይ! የሰውን ልጅ ለማዳን የተቀበልኩትን ሕማማተ መስቀል እያሰብህ ይህንን ሁሉ ገድል ፈጽመሃልና ምን እንዳደርግልህ ትወዳለህ?›› አላቸው፡፡ ንዑድ ክቡር ቅዱስ አባታችን አቡነ አቢብም ‹‹ጌታዬ አምላኬ መድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! መቼም ሰው ሁሉ ሳይመገብ አይውልም አያድርምና በተመገበ ጊዜ ስሜን ጠርቶ የተማጸነውን ማርልኝ›› አሉት፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አባታችን አቡነ አቢብ ለሰው ልጆች ያላቸውን ፍቅር ካደነቀ በኋላ ‹‹…ከማዕድ በኋላ ስብሃት ተብሎ የተረፈውን ‹በእንተ አቢብ› ብሎ ሦስት ጊዜ የተመሰገበውን ሰው ሁሉ እምርልሃለሁ›› በማለት ታላቅ የምሕረት ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡
ያልተጠመቀ አረማዊ አሕዛብም እንኳን ቢሆኖ "ስለ አቡነ አቢብ" ብሎ ከተማጸነ ጌታችንን ያንን ሰው ወደቀናች የእምነት መንገድ ሳይመራውና በንስሓ ሳይጠራው በሞት እንደማይወስደው ለአባታችን ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡
ለማዳን ትንሽ ምክንያትን የሚፈልግ ያለ ምክንያትም የማያድን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ እስከዘላለም ድረስ ይክበር ይመስገን!
በዛሬዋ ዕለት ጥቅምት 25 ቀን በዓመታዊ የዕረፍት በዓላቸው ታስበው የሚውሉት ጻድቁና ሰማዕቱ አቡነ አቢብ ከቃልኪዳናቸው ረድኤት በረከት ይክፈሉን!
‹‹በእንተ አቡነ አቢብ!››
(ደብረ ሰላም ቃጭልቃ አቡነ አቢብ ገዳም ያሳተመው ገድለ አቡነ አቢብ፣ ገጽ 105)
ተወዳጆች
✅ የዋህ ሰው
ትሁትም ነው የሚራራም ነው
የዋህነት ጅልነት አይደለም
✅ ጅል ማለት
ሳይገባው ሳይረዳ የሚተው ነው
✅ የዋህ ግን
ገብቶት ተረድቶ የሚተው ነው
ስለዚህ የዋህ ሁኑ ብሏል ቅዱስ ጳውሎስ
የዋህ እንድንሆን መድኃኔዓለም ይርዳን🙏
ጥቅምት 24/2017 #ፃድቁ_ቅዱስ_ተክለሃይማኖት
"የፃድቃን መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል መዝ.111፥6"
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ፃድቁ አባታችንን በምልጃ ፀሎታቸዉ እንዲራዱን ለምንማፀንበት #ለአቡነ_ተክለሃይማኖት ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን
👉የስማቸው ትርጉም የሃይማኖት መሰረት ፍሬ የሆነው አባታችን ከእናታቸው እግዚሐርያ ከ አባታቸው ፀጋዘአብ መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታህሳስ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ተወለዱ
👉አባታችን #የሃይማኖት_ተክል ናቸው ጻድቁ አባታችን ገና እንደተወለዱ በሶስተኛው ቀናቸው ከእናታቸው እቅፍ በመውረድ አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውዕቱ መንፈስ ቅዱስ እያሉ በመስገድ የፈጠራቸውን አምላክ አመስግነዋል
👉እግዚአብሔር አምላካችን ለኢትዮጵያ #አዲስ_ሐዋርያ አድርጎ መርጧቸዋል ጻድቁ አባታችን ክብረ በዓላቸው እንደሚከተለው ነው
✝️ህዳር 24 ቀን ሃያ አምስተኛ ካህናተ ሰማይ ሆነው በሰማይ #የሥላሴን መንበር ያጠኑበት እለት ነው
✝️ታህሳስ 24 ቀን የአባታችን ልደት ነው
✝️ጥር 24 ቀን የአባታችን ሰባረ አፅሙ ነው
✝️መጋቢት 24 ቀን የአባታችን ፅንሰታቸው ነው
✝️ግንቦት 12 ቀን የአባታችን ፍልሰተ አፅሙ ነው
✝️ ነሐሴ 24 ቀን የአባታችን እረፍታቸው ነው
👉የፃድቁ አባታችን #የቅዱስ_ተክለሃይማኖት ቡራኬ ይድረሰን በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የሚዉሉ ቅዱሣን የከበረዉ ቃል ኪዳናቸዉ ሀገራችንን ህዝባችንን ይጠብቅልን የተባረከ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
#ማኅሌተ_ጽጌ
#የፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_42ኛ_ዓመት_የምሥረታ_በዓል
#ፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሰንበት_ትምህርት_ቤት
#ፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሚዲያ
Follow us on
👉 /channel/fre_amde_haymanot_media
👉 http://linktr.ee/fre_amde_haymanot_media
ወዳጄ
መቼ ነው የምሞተው ብለህ ታውቃለህ
አሁን ወይም ዛሬ ወይም ነገ ነገ ወዲያ
አይታወቅም ማን መቼ እንደሚሞት
ግን አሁን ላይ ምን እንደምናደርግም አናውቅም
እንዘላለን ያ ክፉ አብሮን ይዘላል
እንዘፍናለን ያ ክፉ በደስታ አብሮን ይዘፍናል
እንዳራለን ከማንም ጋር ፍቅር እያልን
ያ ክፉ በስጋችን በስሜታችን ይደሰታል
ዘፈን ለመፅናኛ እንሰማለን
ያ ክፉ አብሮን በ ዘፈን ይፅናናል
እንሰክራለን አምሽተን እየመጣን
ለትዳራችን ሰቆቃ እንፈጥራለን
ያ ክፉ እሱም አብሮን ይሰክራል
በጨለማ ደስታውን ይቀጫል
ኧረ እባካችሁ
ተወዳጆች
መልካም እንሰራ ለሰይጣን በር አንክፈት
ሰይጣን ሁሌም ክፉውን ይወዳል
እኛ ቀላል እየመሰለን የምንሰራው ጥቃቅን ነገር
ቆይቶ ቆይቶ ለመቅሰፍት ለቁጣ ነው የሚዳርገን
እባካችሁ ለበጎ ነገር እንጂ ለክፉ ነገር በር አትክፈቱ
ሞትን አትፍሩ ኃጢአትን ፍሩ
ያለድሜ እንዳንቀዘፍ
አባታችን ዮሐንስም ጎልጎታ ደርሰው ከቅዱሳት ቦታዎች ተባርከው ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔዱ። በዚያም 500 ዓመት የኖረ ኹለተኛ እንጦንስ የተባለ አንድ ባሕታዊ ኣገኙ። እመቤታችንም አባ እንጦንስን ታቦተ ኢየሱስን፣ ታቦተ ኪዳነ ምሕረትን እና ታቦተ ጽዮንን እያስጠበቀችው ይኖር ነበር። አባ እንጦንስም ኣቡነ ዮሐንስን ባገኛቸው ጊዜ በልቡ ተደስቶ በመንፈሱ ረክቶ በዐይኖቼ አንተን ያሳየኝ በጆሮዎቹም ቃልህን ያሰማኝ የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን፤ እመቤታችን ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በእጇ የሰጠችኝን ያስጠበቀችኝን እነዚኽን ታቦታት ተቀበለኝ›› ብለው ሦስቱን ጽላት ‹‹ወደ ሀገርህ ይዘህ ሒድ›› ብለው ሰጧቸው። አባታችን ዮሐንስም ‹‹…እኔ እርሱ አይደለሁም እንዴት አወከኝ?› ሲሏቸው አባ እንጦንስም ፈገግ ብለው ከሞተ ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት የሆነውን ሰው በጸሎትህ ከሞት ካስነሣኸው በኋላ ከሀገርህ ከኢትዮጵያ ከዋልድባ ገዳም ከተነሣኽ ዘጠኝ ወር ነው፤ ይኸንንም የእግዚአብሔር መላእክት ነገሩኝ መምጣቱን ተስፋ የምታደርገው ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ከሀገሩ ዛሬ ተነሣ አሉኝ አሏቸው። አባታችን ዮሐንስም እመቤታችን ማርያምን እንዴት አገኘሃት? አሏቸው። አባ እንጦንስም ከልጇ ከወዳጇ ጋር በብርሃን መርከብ ላይ ተቀምጣ መላእክት፣ ነቢያት፣ ሐዋርያት ጻድቃን፣ ሰማዕታት ሲከቧትና በክብር በምስጋና ሲሰግዱላት ግንቦት 21 ቀን በደብረ ምጥማቅ አገኘኋት አሏቸው። እመቤታችንም ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስን ፈቃድህን ለሚያደርጉ ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለዓለሙ ሁሉ የመዳን ተስፋ ስጠኝ አለችው። ጌታችንም ያንጊዜ መላእክትን ከገነት ዕንጨትና ዕብነ በረድ፡ ከጎልጎታ መቃብሩና ከጌቴሴማኒ አፈር እንዲያመጡ አዘዛቸው። መላእክትም የታዘዙትን አምጥተው በሰጡት ጊዜ ጌታችን ከገነት የመጡትን ዕንጨትና ዕብነ በረድ ሦስቱን ታቦታት አድረጋቸው በማለት አባ እንጦንስ ለአባ ዮሐንስ ነገሯቸው።
አቡነ ዮሐንስም ሦስቱን ጽላት ይዘው አንዲት እንደፀሓይ የምታበራ ድንጋይ እየመራቻቸው ሰኔ 12 ቀን ጎጃም ደረሱ። ድንጋዩዋንም መንገድ እንድትመራቸው የሰጣቸው ጌታችን ነው። ከዚያም ውሮ ተብሎ የሚጠራ አንድ ባላባት ቤት ገብተው አድረው በሚገባ ተስተናግደው በቀጣዩ ቀን ድንጋዩዋ እየመራቻቸው ቅዱሳን ከነበሩበት ጫካ ወስዳ አገናኘቻቸው። ቅዱሳኑም ለአቡነ ዮሐንስ የጠበቅንልህን ይኸችን ቦታ ተረከበን የዘለዓለም ማረፊያህ ናትና› ብለው እነርሱ ወደ ኢየሩሳሌም ሔዱ። አባታችንም ታቦተ ኢየሱስን በዚኽች ገዳም ተክለው ቦታዋን መጀመሪያ በተቀበላቸው ሰው በውሮ ስም "ውራ ኢየሱስ ብለው ሰየሟት።
ከዘጠኝ ዓመትም በኋላ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል እየመራቸው ወደ ጣና ወስዶ ዘጌ አደረሳቸውና ታላቋን ዑራ ኪዳነ ምሕረትን ተከሉ።
ከዚያ ቀጥለው ታቦተ ጽዮንን አዴት አካባቢ ተከሉ። እነዚህን ሦስት ገዳማት አቅንተው ከኖሩ በኋላ መልካም የሆነውን ተጋድሏቸውን ፈጽመው ጥቅምት 22 ቀን ዐርብ በ9 ሰዓት ዐረፉ። ከማረፋቸውም በፊት ጌታችን እመቤታችንን፣ መላእክትን፣ ቅዱሳንን ሰማዕታትን አስከትሎ መጥቶ “…ጸሎት አድርጎ መልክህን የደገመ እባብ አይነድፈውም፤ መብረቅ አይገድለውም የሚል ድንቅ የምሕረት ቃልኪዳን ገባላቸው። ዳግመኛም ስምህን የጠራውን መታሰቢያህን ያደረገውን፤ በበዓልህ ቀን ማኅሌት የቆመውን የገድልህን መጽሐፍ የጻፈውን ያጻፈውን ያነበበውን የሰማውን፣ እጅ መንሻ ለቤተ ክርስቲያን የሰጠውን እምርልሃለሁ፤ ልጆቹንም እስከ 15 ትውልድ እባርክልሃለሁ፤ በገዳምህ በውራ መብረቅ ነጎድጓድ፣ እባብ ሰውን አይገድልም የማይጸድቅ ሰው ወደ ገዳምህ አይመጣም" አላቸው።
አባታችንም ካረፉ በኋላ መነኰሳት ልጆቻቸው ሥጋቸውን ተሸክመው ከደብረ ጽዮን ኮቲ ተነሥተው ወደ ውራ ኢየሱስ ለመውሰድ ሲጓዙ በበረሓ ሣሉ መሸባቸውና ፀሓይ ገባች፣ ወዲያውም ሰባት አንበሶች መጥተው እንዳይፈሯቸው መነኰሳቱን በሰው አንደበት ካናገሯቸው በኋላ የአቡነ ዮሓንስን ዐፅም ተሸክመው ሰባት ምዕራፍ ያህል ወሰዱት። ወቅቱ ቢመሽባቸውም በእግዚአብሔር ፈቃድ ፀሓይ ግን በተኣምራት ወጣችላቸውና ውራ ኢየሱስ ገዳም በሰላም ደረሱ። ያንጊዜም ፀሓይ ገባች፤ አንበሶቹም እጅ ነሥተው ወደ ቦታቸው ተመለሱ።
አቡነ ዮሐንስ መላ ዘመናቸውን የማያዩ ዐይነ ሥውራንን እንዲያዩ፣ የማይሰሙ እንዲሰሙ፣ የማይራመዱ እንዲራመዱ በማድረግ፤ ሕሙማንን በመፈወስ፣ ሙታንን በማስነሣት በርካታ ተኣምራትን በማደረግ ወንጌልን በመስበክ ያገለገሉ ሲሆን ከዕረፍታቸውም በኋላ በርካታ ድንቅ ድንቅ ተኣምራትን አድርገዋል። ከተኣምራታቸውም አንዱ ይኸ ነው፡- ንዑድ ክቡር ልዩ በሚሆን በአባታችን ዮሐንስ የዕረፍታቸው ቀን ጥቅምት 22 ቀን አንድ ዐረማዊ እስላም ሰው ለተሳልቆና ለመዘባበት ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ቈረበ። በአባታችን በዓል ዕለትም ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብሎ ወጥቶ እየተቻኮለ ሔዶ ከእስላሞች መስጊድ ገብቶ በአባታችን በዮሐንስ በዓል ምክንያት የቆረበውን ቍርባን ተቀብሎ በወገኖቹ በከሃዲያኑ እስላሞች ፊት ተፋው። ወዲያውም የዚያ እስላም ሰው መላ ሰውነቱ አበጠ በንፋስ ገመድነትም ታንቆ ሰዎች እስኪያዩት ድረስ በሰማይና በምድር መካከል ተሰቀለ።
በተሰቀለበትም ቦታ ወፎችና አሞራዎች ይበሉት ጀመር፤ ሥጋውንም በሉት። በዚኽም ጊዜ ያ እስላም ድምፁን ከፍ አድርጎ ‹‹እኔ ንዑድ ክቡር ልዩ በሆነ በአባታችን በዮሐንስ አምላክ አምኛለሁ ብሎ መሰከረ። እግዚኣብሔርም የገዳማት ኮከብ በሆነው በብፁዕ ዮሓንስ ልመናና ጸሎት ፈጽሞ ይቅር አለው። ከዚኽም በኋላ ለብቻው ቀኖና ገባ የቀኖና ሥርዓቱንም ጨርሶ ንስሓ ገብቶ ከባለቤቱ ከልጆቹ ከቤተሰቦቹና ከዘመዶቹ ከጎረቤቱቹ ሁሉ ጋር የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቀ ስሙንም ገብረ ዮሐንስ አሉት ትርጓሜውም የዮሐንስ ባለሟል ማለት ነው።
የአቡነ ዮሐንስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን።
(ምንጭ በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን መጽሐፍ ገጽ 472-477)