ኃጢአት ማለት ማጣት ማለት ነው
ሰው ኃጢአት ሲሰራ ማንን ያጣል?
እግዚአብሔርን ያጣዋል እግዚአብሄርን ያህል አባት
ገነትን ያጣል ቤተክርስቲያኑን ያጣል ራሱን ያጣል
ወዳጅም ያጣል
ገንዘብ እራሱ ኃጢአት ከበዛ አይበረክትም አይቀመጥም
ገንዝብን ሚያጠፋው ኃጢአት ነው
ስለዚህ ኃጢኣት ራስን ያሰጣል ጉልበት ያሳጣል
ሐብት ያሳጣል ወዳጅ ያሰጣል ቁመናን ያሳጣል
አዕምሮን ያሳጣል አስተሳሰብን ይነሳል ይጎትታል
ተስፋ ያስቆርጣል ነገን ያሳጣል አላማ የለሽ ያደርጋል።
እምንኖርለት ነገር እንዳይኖር ያደርጋል።
ሰማይ እንዳይታየን ያደርጋል ኃጢአት
የማይጠቅም ገመድ ነው አስሮ የሚይዝ
ለጊዜው ደስ የሚል በለስ የተባለ ለዚህ ነው
በለስ መጀመርያ ሲበሉት ይጣፍጣል በኋላ ይመራል ።
ዲያቆኑ
በቅዳሴ ሰዓት የተቀመጣችሁ ተነሱ ይላል
የተቀመጣችሁ ተነሱ ማለት
በኃጢአት አለጋ የተኛችሁ ሰዎች በንስኃ ተነሱ ማለት ነው ።
ፈጣሪ አምላክ ከኃጢአት ይጠብቀን 🙏
ርዕሰ ሊቃወንት አባ ገብረ ኪዳን ❤️
ተፃፈ :- በ ዲ/ን ዑራኤል
ክርስቶስ እኮ አለሙን ሲወድ እንዲሁ ነው
ሰዉ ግን ሰዉን ሲወድ የሆነ ነገሩን አይቶ ነው
ለዚያውም አይቶም መልሶ ማየት ላይፈልግ ይችላል
አግኝቶም በኋላ ማግኘት ላይፈልግ ይችላል
ሁሌም የሆነ ነገር አይቶ ፈልጎ
ለጥቅሙ ብቻ የሚወድ ከዚያም የሚገፋ
ብቸኛው ፍጡር ሰው ነው።
እግዚአብሔር ግን አለሙን ሲወድ እንዲሁ ነው።
ያለምንም ምክንያት ያለምንም ጥቅም ነው።
እንዲሁ እንዋደድ ዘንድ ፈጣሪ አምላክ ይርዳን🙏
🌹 "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌹
🌹 #ኅዳር ፮ (6) ቀን።
🌹 እንኳን #ክብር_ይግባውና_ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ #ከእመቤታችን_ከቅድስት_ድንግል_ማርያም #ከአረጋዊ_ዮሴፍና_ከሰሎሜ ጋር ከስደት በሚመለሱ ጊዜ ወደ #ደብረ_ቊስቋም ገብተው በመንገድ ጒዞ ካገኛቸውም ድካም #ላአረፉበት_ዓመታዊ_መታሰቢያ በዓል፣ #ለሮሜ_አገር_ሊቀ_ጳጳሳት ለቅዱስ አባት #ለአባ_ፊልክስ_ለዕረፍት መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከአባ_ፍሞስ_ከቅዱሳን_ለንዲዎስ_ከይላጥስ፣ #ከማርትሮስ_ከኢላስዎስ_ከቆርናልዮስ_ከሱኪሮስ #ከናውኔኖስ_ከሊባዲቆ_ከሲላስዮስና #ከሰማዕት_ኤስድሮስ_ማኅበር ከሆኑ #ከሁለት_መቶ_ሰባ_ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
🌹 #በዚች_ቀን_ክብርግባውና_ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ከእመቤታችን_ከቅድስት_ድንግል_ማርያም_ከአረጋዊው_ዮሴፍና_ከሰሎሜ ጋር በስደት በሚመለሱ ጊዜ #ወደ_ደብረ_ቊስቋም ገባ በመንገድ ጒዞ ካገኛቸው ድካም ዐረፉ።
🌹 ዳግመኛም በኋላ ዘመን በዚህ ደብረ ቊስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቶቹን ሰበሰባቸው ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንንም አክብሮ የቊርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክብር ደሙን ለወገኖቹ ሰጣቸው። ለዚህም የእስክንድርያ አገር ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱሳን አባቶቻችን ቄርሎስና ቴዎፍሎስ ምስክሮችን ሆኑ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷ ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
🌹 #የሮሜ_አገር_ሊቀ_ጳጳሳት_አባ_ፊልክስ፦ የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ክርስቲያኖች ናቸው የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት አስተማሩት የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት አንስጣስዮስም ዲቁና ሾመው ደግሞ የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ዮስጦስም ጠባዩን የጽድቁንና የትሩፋቱን ደግነት አይቶ ቅስና ሾመው።
🌹 ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዲዮናስዮስ በዐረፈ ጊዜ ይህን አባት ፊልክስን መረጡት በእግዚአብሔርም ፈቃድ በሮሜ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት የክርስቶስንም መንጋዎች በመልካም አጠባበቅ ጠበቀ።
🌹 ትሩስ ቄሣርም ከሞተ በኋላ ቴዎድሮስ ቄሣር ነገሠ። እርሱም በምዕመናን ላይ ታላቅ መከራ አምጥቶ ጭንቅ በሆኑ ሥቃዮች አሠቃያቸው። ብዙዎችም በእርሱ እጅ በሰማዕትነት ሞቱ። ይህም አባት ከዚህ ከሀዲ ታላቅ መከራና ኀዘን ደረሰበት። ስርሱም ወደ እግዚአብሔር ማለደ ክብር ይግባውና ጌታችንም ልመናውን ተቀብሎ ይህንን ከሀዲ በሁለተኛ ዘመነ መንግሥቱ አጠፋው።
🌹 ከዚህም በኋላ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስም በነገሠ ጊዜ ክርስቲያኖችን አብዝቶ ማሠቃየትን ጀመረ ይህም አባት ፊልክስ የክርስቲያኖችን ሥቃይ እንዳያይ ክብር ይግባውና ወደ እግዚአብሔር ጸለየ በዲዮቅልጥያኖስም በመጀመሪያው ዘመነ መንግሥት ኅዳር 6 ቀን ዐረፈ።
🌹 ይህም አባት ብዙዎች ድርሳናትንና ተግሣጾችን ደርሶአል ከእርሳቸውም ስለ ውግዘትና ስለ ቀናች ሃይማኖት የተመላለሰብት አለ እሊህም ለክርስቲያን ወገን እጅግ የሚጠቅሙ በጎዎች ናቸው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ፊልክስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘለዓሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 6 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
🌹 #የዕለቱ_የማኅሌቱ_ምስባክ፦ "ዖፍኒ ረከበት ላቲ ቤተ። ወማዕነቅኒ ኀበ ታነብር ዕጐሊሃ። ምሥዋዒከ እግዚኦ እግዚአ ኃያላን"። መዝ 83፥3 የሚነበበው ወንጌል ሉቃ22፥14-24።
✝ ✝ ✝
🌹 #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ርኢክዎ ለኃጥእ ዐብየ ወተለዐለ ከመ አርዘ ሊባኖስ። ወሶበ እገብእ ኀጣእክዎ። ኀሠሥኩ ወኢረከብኩ መካኖ"። መዝ 36፥35። የሚበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 8፥1-16፣ 2ኛ ዮሐ 1፥9-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 1፥12-15። ማቴ 2፥19-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም የቊስቋም ማርያም በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
ተወዳጆች
1, ሴት ሱሪ መልበስ ኃጢአት ነው
2, ዘፈን ማዳመጥ ኃጢአት ነው
3, መስከር ኃጢአት ነው
4, ዝሙት ኃጢአት ነው
እስኪ ከዚህ ሁሉ የቱን ነው ማትሰሩ ?
👇👇👇👇👇
/channel/uraman78tu
☞ ኅዳር 5 ቀን ጌታ መድኃኔ ዓለምን ጎኑን በጦር የወጋው የሰማዕቱ የለንጊኖስ ራሱ የታየችበት ዓመታዊ በዓሉ ነው፡፡
☞ለንጊኖስ ሰማዕት ☞ አስቀድሞ ጌታችንን ጎኑን በጦር የወጋው ነው፡፡ በኃላም
በጌታችን አምኖ ወንጌልን ሰብኮ በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡
☞ከዮናናውያውን ወገን ሲሆን የሮማውያን ወታደር ነበር፡፡ ጲላጦስ ጌታችንን
እንዲሰቅሉት ለአይሁድ አሳልፎ ሲሰጠው ይህ ለንጊኖስ ከጲላጦስ ጭፍሮች
ውስጥ አንዱ ስለነበር የጌታችንን ሥቃይ አይቶ በክፋ ግብራቸው ላለመተባበር
ብሎ ከአካባቢው ሸሽቶ ነበር፡፡
✞በዕለተ ዐርብ ግን ሮማውያን በጌታችን መከራ ያልተባበረን ሁሉ እንደ ንጉሥ
ጠላት ሰላዩት መድኃኔዓለምን ክርስቶስ በመጨረሻ ሰዓት "ተፈጸመ"ካለ በኃላ
ለንጊኖስ ወደ ቀራንዮ ተራራ ወጣ፡፡
☞ሮማውያን የሁለቱን ሽፍቶች አጥንቶች ሲሰብሩ ለንጊኖስ ደግሞ ከሞት
መቼም አልጎዳውም ብሎ አስቦ የጌታችንን ጉኑን ወጋው፡፡ በዚያም ጊዜ አንዱ
ዐይኑ ዕውር ነበርና ከጌታችን ከግራው ጉኑ ውኃና ደም ሲወጣ የታወሰ ዐይኑን
ቢነካው ዐይኑ በራችለት፡፡
☞በዚህም እጅግ ተገርሞ እየተደሰ የሆነውን ሁሉ ማስተዋል ጀመረ፡፡ ጌታችንም
ቅድስት ነፍሱን በፈቃዱ ሲለያት የተፈጸመውን ተአምራት አስታወሰ፡፡ ትንሳኤውን
ሲሰማ ይህን ምሥጢር ይገልጽለት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር መጸለይ ጀመረ፡፡
☞ጌታችንም ሐዋርያውን ቅዱስ ጴጥሮስን ላከለትና ሁሉን ምሥጢር ገለጠለት፡፡
ያን ጊዜም በሙሉ ልቡም አምኖ አእስከሞት ድረስ ለመታመን ተዘጋጅቶ
በክፋዎች አይሁድ ፊት ስለ ጌታችን አምላክነት መመስከር ጀመረ፡፡
☞ወደ ታናሹዋ እስያ ወደ ቀጵዶቅያ ሄዶ በዚያ ወንጌልን እንደ ሐዋርያት
በመስበክ ብዙዎችን ወደ፡ቀናች እምነት መልሷቸዋል፡፡
☞አይሁድም በክፋት ተነሥተው የሐሰቶ ምስክር አቁመው ሰለከሰሱት የሮማ
ወታደሮች ይዘውት በንጉሡ በጢባርዮስ ቄሣር አስፈርደው ሐምሌ 23 ቀን
አንገቱ ሰይፈውት በሰማዕትነት እንዲርፍ አድርገውታል፡፡
☞ ይቺ ራሱንም ብቻውን ወደ እየሩሳሌም ወሰዷት፡፡ በምስክርነቱ የቀኑና
የተናደዱ በዚያ የሚኖሩ አይሁድም ባዩአት ጊዜ እጅግ ተደስተው ከከተማ ውጭ
በአንድ ኮረብታ ላይ ቀበሯት፡፡
☞ከብዙ ቀንም በኃላ በቅዱስ ለንጊኖስ ስብከት ያመነች አንዴት ሴት በቀጵዶቅና
አገር ራሱን ከቆረጡበት ጊዜ ጀምሮ በተቆረጠበት ቦታ በሐቆም ስለ እርሱ
ታለቅስ ነበር፡፡ ከጊዜ በኃላ አይኖቿ ታወሩ፡፡
☞የጌታችንን መቃብር ለመሳለም ተነሥታ ከልጇ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም መጣች፡፡
በደረስችም ጊዜ ልጇ ሞተ፡፡
☞በሀዘን ሆና ሳለ ወደ ሀገሯ መርቶ የሚወስዳት ስላጣች መሪር ለቅሶን አልቅሳ
ደክሞት ተኛች፡፡ ተኝታም ሳለች ቅዱስ ለንጊኖስን ከሞት ልጇ ጋር በራእይ
አየችው፡፡ ራሱ ተቀብራ ያለቾበትንም ቦታ ነገራትና ሄዳ እንድታወጣ አዘዛት፡፡
☞ወደ ቦታውም ሄዳ ስታስቆፍረው መዓዛው እጅግ ጣፋጭ የሆነ የሽቱ መዓዛ
ወጣ፡፡ አናም ያቺ ሴት የቅዱስ ለንጊኖስ ራስ ያለችበት ቦታ ስትደርስ ታላቅ
ብርሃን ተገለጠላትና ዐይኖቿ በሩላት፡፡ የቅዱስ ለንጊኖስ ራስና የልጇን ሥጋ ይዛ
ወደ ሀገሯ ወስዳ ባማረ ቦታ አኖረቻት፡፡ ይኽም ተዓምር ኅዳር 5ቀን ተፈጸመ፡፡
☞( መዝገበ ቅዱሳን)
☞የሰማዕቱ የቅዱስ ለንጊኖስ የጸሎቱ በረከት አይለያችሁ፡፡
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ
☞4-3-2017
ተወዳጆች
ሴት ሱሪ መልበስ ኃጢአት ነው
ዘፈን ማዳመጥ ኃጢአት ነው
መስከር ኃጢአት ነው
ዝሙት ኃጢአት ነው
እስኪ ከዚህ ሁሉ የቱን ታሟላላችሁ ?
👇👇👇👇👇
@uramant78tu
✝እንኳን አደረሰነ!
✞በዓለ አበው ቅዱሳን፦
✿አቢማኮስ ወአዛርያኖስ (ዘሮሜ)
✿ያዕቆብ ወዮሐንስ (ዘፋርስ)
✿ቶማስ (ዘደማስቆ)
✿ዘካርያስ ክቡር (መምህር)
✿አባ አበይዶ (ዘደብረ ዓሣ)
✿ጉባዔ ሰማዕታት (ዘብሔረ ግብጽ)
✿ወጴጥሮስ (ሊቀ ጳጳሳት)
ኅዳር ፬፦
✝ማርያም ድንግል ጸዋሪተ ቁርባን ጵርስፎራ፤
ወጽዋዐ ልቡና እሳተ ዘይመስል ኅብራ፤
ዘሰትየ ወጎስዐ ጠቢበ ጠቢባን ዕዝራ፤
ታሕተ ሰግላ አሐቲ አመ አገትዋ ሐራ፤
ዘምስለ ዮሴፍ ወሰሎሜ ስብሐተ ወልዳ ሠወራ!
✝ሰላም ለአበይዶ ረድአ ጻድቅ ዮሐኒ፤
ወዘካርያስ ዘገደፈ ግብረ ዓለም ማሳኒ፤
አቢማኮስ ወአዛርያኖስ ሰማዕታተ ክርስቶስ አዶኒ፤
ቶማስ ዘደማስቆ ፍትወታተ ሥጋ መናኒ፤
ያዕቆብ ወዮሐንስ ወብእሴ ሰላም አርሳኒ!
✝ሰማዕታተ ሮሜ ክቡራን አቢማኮስ ወአዛርያኖስ፤
ያዕቆብ ወዮሐንስ ዘአብርሁ በብሔረ ፋርስ፤
ኮከበ ደማስቆ ወአድሚሃ ቶማስ ኤጴስ ቆጶስ፤
ብእሴ ሰላም ዐቢይ ወትሩፈ ምግባር ዘካርያስ፤
ወአበይዶ ረድአ ዮሐኒ ዘሎቱ ሞገስ!
(አርኬ - ዝክረ ቅዱሳን ርቱዓነ ሃይማኖት)
ተወዳጆች
አይታችሁ እንደሆን
30 ዓመት ሙሉ እግዚአብሔር ትዝ ብሎት የማያውቅ ሰው
ሲያመው ፀበል ሲገባ ነው እግዚአብሔርን የሚያሰበው
እግዚአብሔርን ማሰቢያስ መቼ እናግኝ ብላችሁ ነው
ስንባክን ስንባክን ስንባክን ባይንስ ሲያመን እግዚአብሔርን እንድንአስበው ነው
እሱ በመንግስቱ እንዳያስበን እኛ ታመን እንድናስበው
እግዚአብሔር በሽታ ይሰጣል ።
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን
ተወዳጆች
እግዚአብሔር መጀመሪያ የሚፈልገው ነገርምንድን ነው ?
ንፅህና ነው ።
ፆም ፀሎት ስግደት ከዚህ በፊት ምን ይፈልጋል እግዚአብሔር ?
✅ የእግዚአብሔር ፈቃዱ
እስመ ዝንቱ ውእቱ ትዕዛዙ ለእግዚአብሔር ወፈቃዱ ተቀድሶትክሙ
የእግዚአብሔር ፈቃዱ ንፁህ መሆናችሁ ነው ።
ከመ ትታቀቡ ወትትረሐቁ እምዝሙት
እግዚአብሔር ከዝሙት እንድትርቁ ንፁህ እንድትሆኑ
እግዚአብሔር የሚፈልገው ነገር ይህ ነው ።
✅ አንዳንዱ ምን ይላል
እንደው መንገድ ፈልጌ ነበር
እንደው ማግባት ፈልጌ ነበር
እንደው መመንኮስ እፈልጋለሁ
እንደው እግዚአብሔር ፈቃዱ ንፁህ መሆን ነው
ንፁህ ከሆንክ ያ ነው ፈቃዱ
ከዚያ በኋላ የሚያስፈልግህን ይዞልህ ይመጣል
አንተ ዝም ብለህ ንፁህ ሁን
ነገ በሚሆን ነገር ላይ አትጨነቁ
ነገ ምንድን ነው ምሆነው
የዛሬ አምስት አመት ምንድን ነው ምሆነው
የዛሬ ሦስት አመት ሁለት አመት
የዛሬ ወር የዛሬ ሳምንት የሚያገባን ነገር የለም
የኛ ድርሻችን ንፁህ መሆን
✅ በንፅህና ምን ይሰበሰባል ?
ሐብት ይሰበሰባል
ፀጋ ይሰበሰባል
ረድኤት ይሰበሰባል
ረድኤተ እግዚአብሔር ይሰበሰባል
መላእክት ይሰበሰባሉ
✅ ሁሉም ንፁህ ወደሆነ አካል የማይሰብሰብ የለም ።
መላክ በሆን ነብይ ቢሆን ሐዋርያ ቢሆን
ንፁህ ወደ ሆነ ሰው ሁሉም ይሰበሰባል
ንፁህ እንድንሆን ፈጣሪ አምላክ ይርዳን አሜን🙏
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❤️
✝ ✝ ✝
🌹 #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወዘሕጎ ያነብብ መዓልተ ወሌሊተ። ወከውን ከመ ዕፅ እንተ ትክልት ኀበ ሙኃዘ ማይ። እንተ ትሁብ ፍሬሃ በበጊዜሃ"። መዝ 1፥2-3። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ጢሞ 4፥6-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 2፥15-22፣ የሐዋ ሥራ 19፥8-11። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 12፥9-14። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። የጻድቁ ንጉሥ የቅዱስ ነአኵቶ ለአብ ከሞት የተሰወረበት (የስዋሬ) በዓል፣ የአቡነ መድኃኒነ እግዚእ፣ የአቡነ ፍሬ ካህን፣ የአቡነ ዓምደ ሚካኤል የዕረፍታቸውና የጾም ጊዜ በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።
🌹 ከዚህ በኋላ ቅዱስ ንጉሥ በሰላምና በበረከትና በፍቅር 40 ዘመን፡፡ ከነገሠ በኋላ የቅዱስ ላሊበላ ልጅ ዐፄ ይትባረክ ትምህርት ቤት ሆዶ ስለ ነበር ከአለበት አስፈልጎ አስመጥቶ አነገሠው እርሱም የቀኖና የቱሩፍት ስራውን በበለጠ አጠጋክሮ በጽሞና በጸሎት ተወስኖ ሳለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአእላፍ መላእክት ጋር መጥቶ "ከአይነ ሞት የምትሰወርበት ጊዜ ስለደረሰ ቃል ኪዳን ልስጥህ ዘንድ የምትፈልገው ለምነኝ" አለው። እርሱም ለቅዱሳን የሰጠው ምክንያተ ድኅነት የሆነው ልመና ስራቀረበ የሚከተለው ቃል ኪዳን ተቀብላል።
🌹 "ዝክረ ስዋሬህን በማሰቡ በየወሩና በየዓመቱ ያከበረ ስምህ የጠራ ዝክርህን የዘከረ ቤተ መቅደስህ የሠራ ያሠራ መጽሐፈ ገድልህን ያጻፈንና የተረጐመውን የሰማውንና ያሰማውን እስከ 7 ትውልድ ምሕረትን እሰጠዋለሁ።
🌹 ስለ እኔ ፍቅር መከራ መስቀሌን በማሰብ ስለፈፀምከው መከራ አንድ ክረምት የበቀለውን ቡቃያ የሚያህል ነፍሳትን ምሬልሃለሁ።
🌹 መላ ዘመንህን ሁሉ ከአይንህ እንባ ሳታቋርጥ ያፈሰስከውን ምሳሌ ከቤተ መቅደስህ የሚጠባጠብ ጠበልን እሰጠዋለሁ። ይህም የእምባህ ምሳሌ ነው። ጠበልህ ብዙ ድውያንን እስከ ዕለተ ምጽዓት ሲፈውስ ይኑር።
🌹 በቃል ኪዳንህ የተማፀኑ ሁሉ የአንተን ልጆችና ወዳጆች መሆናቸው እንዲታወቅ በቅዱስ ገብርኤል እጅ ቀኝ ግራ እጃቸው ታትሞ መንግሥተ ሰማያት ይግብልህ። እድል ፈንታቸው ፅዋ ተርታቸው ከአንተ ጋር ይሁንልህ" በማለት ቃልኪዳኑን አደረገለት (ከሰጠው በኋላ) ከአይነ ሞት የምትሰወረው ኅዳር 3 ቀን ነው ብሎ ወደ ሰማይ ዐረገ።
🌹 እንደተባለውም በሰባ ዓመቱ ኅዳር 3 ቀን ማዕጠንት በማጠን ላይ እያለ በ7 ሰዓት ገብረ ክርስቶስ የተባለው ዲያቆን በመስቀሉ ባርኮት ኤልሳዕ ኤልያስን እያየ ወደ ሰማይ እንደወጣ እርሱ እያየው ከአይነ ሞት ተሰውሯል። ከጻድቁ ንጉሥ ከቅዱስ ነአኵቶ ለአብ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። ምንጭ፦ ቅዱሳንና ሥራቸው የአራቱ ቅዱሳን ነገሥታት ታሪክ ከሚለው መጽሐፍ።
✝ ✝ ✝
🌹 #አቡነ_መድኃኒነ_እግዚእ፡- ከደጋግ ክርስቲያኖች ከቀሲስ ሰንበት ተስፋነ እና ከኅሪተ ማርያም በ 1180 ዓ.ም በሥዕለት የተወለዱት አቡነ መድኃኒነ እግዚእ እጅግ አስደናቂ ገድልና ትሩፋት ያላቸው ጻድቅ ቢሆኑም ብዙው ሕዝበ ክርስቲያን እንደሚገባቸው መጠን ያላወቃቸው ታላቅ አባት ናቸው፡፡ መዘንጋታቸው እጅግ ከሚያስቆጩን አባቶች መካከል ትልቁን ድርሻ የሚወስዱት የደብረ በንኰሉ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ናቸው፡፡ እስቲ ቀጥሎ ስማቸውን የጠቀስኳቸውን እነዚህን ቅዱሳን አባቶች ታሪካቸውንና የጽድቅ ሕይወታቸውን አስታውሱት፡- እነርሱም አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ አቡነ ያሳይ ዘማንዳባ፣ አቡነ ሳሙኤል ዘቆየፃ፣ አቡነ ሳሙኤል ዘጣሬጣ፣ አቡነ ታዴዎስ ዘባልታርዋ፣ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤ እና አቡነ ዮሐንስ ዘጉራንቄ እነዚህን የመላእክትን ሕይወት በምድር የኖሩ ታላላቅ የሀገራችንን ቅዱሳን አስተምረውና አመንኵሰው ለጽድቅ ያበቋቸው አባት አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ናቸው፡፡
🌹 አቡነ መድኃኒነ እግዚእ እነዚህን ሰባቱን ቅዱሳን በአንድ ጊዜ ሲያመነኵሷቸው በዚያው ቅጽበት መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ገዳሙን ደብረ በንኰልን በብርሃን አጥለቅልቆት ታይቷል፡፡ ከሰማይም የምስክርነት ድምፅ ተሰምቷል፡፡ በዚህም ምክንያት አንድ ላይ የመነኰሱት እነዚህ ሰባቱ ቅዱሳን "ሰባቱ ከዋክብት" እየተባሉ ይጠራሉ፡፡ እነዚህም ሰባቱ ከዋክብት የጣናን ባሕር በእግራቸው ጠቅጥቀው ተሻግረው ብዙዎቹን ደሴቱ ላይ ያሉ አስደናቂ የጣና ገዳማትን የመሠረቱት ናቸው፡፡ ከእነርሱም ውስጥ ትልቅ ጠፍጣፋ ድንጋይን እንደጀልባ ተጠቅመው በእርሱ ላይ ሆነው ወደ ደሴት የገቡ አሉ፡፡ በእግራቸውም እየረገጡ ባሕሩን የተሻገሩ አሉ፡፡ በሌላም ቦታ በየብስ የተሰማሩትም ቢሆኑ መጻሕፍቶቻቸውን በአንበሳ ጭነው የተጓዙ አሉ፡፡
🌹 በደብረ ሊባኖሱ ሐዲስ ሐዋርያ የኢትዮጵያ ብርሃኗ በሆኑት በአቡነ ተክለ ሃይማኖት እጅ ከመነኰሱ በኋላ አቡነ መድኃኒነ እግዚእም በተራቸው ያስተማሯቸውና ያመነኰሷቸው መነኰሳት ቁጥራቸው በውል አይታወቅም፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ለአቡነ መድኃኒነ እግዚእ "ስፍር ቁጥር የሌላቸው ከዋክብት ቅዱሳንን" በመንፈስ ቅዱስ እንደሚወልዱ ትንቢት ተናግረውላቸው ነበር፡፡ የተንቤኑን አቡነ ዐቢየ እግዚእን፣ የዞዝ አምባውን አቡነ አብሳዲን ጨምሮ አባታችን መድኃኒነ እግዚእ ብርሃን ሆነው በጣም ብዙ ቅዱሳንን ያመኰሱ ታላቅ ጻድቅ ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን" ይባላሉ፡፡
🌹 የአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ልጆች ዛሬ ግሸን ላይ በክብር ተቀምጦ ሀገራችንን ከመዓት እየጠበቀ ያለውን የጌታችንን ቅዱስ መስቀል ያመጡትም እነርሱ ናቸው፡፡ ዐፄ ዳዊት በዘመናቸው ረኃብ ስለነተሳ የደብረ ቢዘኑን አቡነ ፊሊጶስን ከገዳማቸው አስጠርተው "ምን ባደርግ ይሻለኛል?" ብለው አማከሯቸው፡፡ አቡነ ፊሊጶስም "የጌታችንን መስቀል ያስመጡ" ብለው መከሯቸው፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊትም ከኢየሩሳሌም፣ ከቍስጥንጥንያና ከእስክንድርያ መንግሥታት ጋር ተጻጽፈው ዓሥሩን ታላላቅ ቅዱሳን መርጠው ይዘው ሄደው መስቀሉን መስከረም 10 ቀን አምጥተውታል፡፡ በጽድቅ ሥራቸውና ተአምራትን በማድረግ በወቅቱ ታዋቂ የነበሩትና ቅዱስ መስቀሉን ያመጡት ዐሥሩ ቅዱሳንም የደብረ ቢዘኑ አቡነ ፊሊጶስ፣ የጣና ደሴቱ አቡነ ኂሩተ አምላክ፣ የጣና ደሴቱ አቡነ እንድርያስ፣ አቡነ በትረ ማርያም፣ አቡነ ዮሐንስ፣ አቡነ ታዴዎስ፣ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ፣ አቡነ ዘካርያስ፣ አቡነ ያሳይና አቡነ ቶማስ ናቸው፡፡
🌹 የአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ተአምራታቸው እጅግ ብዙ ነው፡፡ አራዊት ሁሉ እንደሰው ያገለግሏቸው የነበር፡፡ ውኃ የሚያመላልስላቸውንና የሚያገለግላቸውን አህያ አንበሳ ቢበላባቸው በአህያው ምትክ አንበሳውን ድፍን 7 ዓመት ለገዳማቸው ውኃ አስቀድተውታል፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡- ለአባታችን ውኃ የሚያመላልስላቸውና የሚያገለግላቸው አንድ አህያ ነበራቸው፡፡ ውኃው የሚገኘው እርሳቸው ካሉበት በጣም እርቆ በእግር የሦስት ሰዓት መንገድ ከተሄደ በኋላ ነው፡፡ ነገር ግን አህያቸው እንደ ሰው እየተላላካቸው ይቀዳላቸው ነበር፡፡ አንድ ግን ከመንገድ አንበሳ አግኝቶት ግማሽ አካሉን በልቶት ሄደ፡፡ አባታችንም የአህያቸውን ተረፈ በድን አግኝተው በማዘን "ውኃ የሚያመላልስልኝ ረዳቴ ይህ አህያ ብቻ ነበር፣ አሁንም አህያዬን የበላህ አውሬ እንድታነጋግረኝ እፈልጋለሁ" ቢሉ በአንበሳ ተበልቶ የሞተው የአህያው ግማሽ አካል አፍ አውጥቶ አንድ አንበሳ እንደበላው ነገራቸው፡፡
🌹 አቡነ መድኃኒነ እግዚእም በዚህ እጅግ ደስ ተሰኝተው ፈጣሪያቸውን ካመሰገኑ በኋላ አህያቸውን የበላውን አንበሳ ከጫካው ውስጥ ጮኸው ጠሩት፡፡ አንበሳውም ከሌሎቹ አንበሳ ተለይቶ ወደ እርሳቸው በመምጣት እግራቸው ሥር ወድቆ ሰገደ፡፡ አባታችንም "አህያዬን የበላኸው አንተ ነህን?" ብለው ሲጠይቁት አንበሳውም በሰው አንደበት "ዎ እኔ ነኝ" አላቸው፡፡ እርሳቸውም ፈጣሪያቸውን በድጋሚ ካመሰገኑ በኋላ አንበሳውን "በል ና ተከተለኝ በአህያዬ ምትክ ታገለግለኛለህ" አሉት፡፡ አንበሳውም ተከትሏቸው ወደ በዓታቸው በመግባት ለ7 ዓመታት እንደ አህያቸው ውኃ እየቀዳ አገልግሏቸዋል፡፡ የአንበሳው ቆዳ ዛሬም በገዳማቸው ደብረ በንኰል በክብር ተቀምጠቷል፡፡
🌹 "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌹
🌹 #ኅዳር ፫ (3) ቀን።
🌹 እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ከኢየሩሳሌም አፈር አምጥተው ዋልድባ ሲደርሱ መነኰሳቱ "ገዳሙ በአህያ አታስረግጥ" ቢሏቸው #አህዮቹን_ክንፍ_አውጥተው_እንዲበሩ_ላደረጉት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ፍሬ_ካህንና_ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን።
✝ ✝ ✝
🌹 #አቡነ_ፍሬ_ካህን፡- ጻድቁን በመጀመሪያ ከጎጃም ተነሥተው በታዘዘ መልአክ መሪነት ትግራይ ደብረ በንኰል አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ገዳም ሄደው መንነው መነኰሱ፡፡ ጻድቁ ስድስት ክንፍ የተሰጣቸው ሲሆኑ በታላቅ መንፈሳዊ ተጋድሎ ይታወቃሉ፡፡ አቡነ ፍሬ ካህን ወንጌልን ሲሰብኩ ሙታንን እያስነሡ በሲኦል ውስጥ ስላለው መከራና ሥቃይ እንዲመሰክሩ ያደርጓቸው ነበር፡፡ ጻድቁ ሐይዳ ገዳም ታቦት ተቀርጾላቸው ገድል የተጻፈላቸው ቢሆንም ሙሉ ገድላቸው ታትሞ ለምእመኑ አልተዳረሰም፡፡ አቡነ ቶማስ ካረፉ በኋላ አቡነ ፍሬ ካህን ገዳማቸውን ተረክበው በጽድቅ መንገድ መነኰሳቱን አስተዳድረዋል፡፡ አቡነ ፍሬ ካህን አፈር ከኢየሩሳሌም አምጥተው ዋልድባ ሲደርሱ መነኰሳቱ "ገዳሙን በአህያ አታስረግጥ" ቢሏቸው አህዮቹን ክንፍ አውጥተው እንዲበሩ አድርገዋቸዋል፡፡
🌹 አባታችን ሽሬ ደብረ ሐይዳ አቡነ ፍሬ ካህን የተባለ ትልቅ ገዳም አላቸው፡፡ ገዳሙ ከአቡነ ቶማስ ዘሐይዳ ገዳም ጋር አንድ ነው፡፡ ወደዚህ ገዳም ውስጥ ሥጋና ቅቤ ተበልቶም ሆነ ተይዞ መውጣት ፈጽሞ አይቻልም፡፡ አልታየሁም ተብሎ በድብቅ ሥጋ ተይዞ ቢገባ ሥጋው ይተላል፡፡ ሥጋና ቅቤ የበላ ሰውም ዕለቱን በድፍረት ወደ ገዳሙ ቢገባ ሆዱ በኃይል ይነፋል በዚህም ይታወቅበታል፡፡ ከብቶችም ቢሆኑ ወደ ገዳሙ አይወጡም፣ ማንም ሳይመልሳቸው ራሳቸው ይመለሳሉ፡፡ የአቡነ ፍሬ ካህን ዕረፍታቸው ኅዳር 3 ነው፡፡ ከአቡነ ፍሬ ካህን እግዚአብሔር አምላክ ረድኤት በረከትን ያሳትፈን፣ በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን።
🌹 "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌹
🌹 #ኅዳር ፪ (2) ቀን።
🌹 እንኳን #ከአባ_ጢሞቴዎስ በኋላ ለተሾመ አረማውያን ስለቀናች ሃይማኖቱ ብዙ መከራ ላደረሱበት ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት #ሃያ_ሰባተኛው_ለእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ #ለአባ_ጴጥሮስ_ለዕረፍቱ_በዓል መታሰቢያና ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት #ስልሳ_አምስተኛ ለሆነ ለእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #ለአባ_ሱንትዩ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰቡ፦ ከእስክንድርያ ነቢዪት ከሆነች #ከሴቴንዋ_ከቅድስት_አንስጣስያና #ከአባ_ሊባኖስ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
🌹 #የእስክንድር_ሊቀ_ጳጳስ_ቅዱስ_አባት #አባ_ጴጥሮስ ፦ እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃያ ሰባተኛ ነው ይህንንም ቅዱስ እግዚአብሔር ለሊቀ ጵጵስና ሹመት መርጦ በሐዋርያ ቅዱስ ማርቆስ ወንበር ላይ ከአስቀመጠው በኋላ የቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አካክዮስ እንዲህ የሚል መልክትን ጻፈለት "እንደ ቅዱሳን ቄርሎስና ዲዮስቆሮስ ሃይማኖት ልዩ ሦስት በሆነ በአንድ አምላክ እናምናለን እናሳምናለን"። ዳግመኛም በዚች መልክት ውስጥ እንዲህ ብሎ ገለጠ "የተዋሕዶ ጥቅም እንዳይሻር ከተዋሕዶ በኋላ የአካላዊ ቃልን መለኮትን ከትስብእቱ ሊለዩት አይገባም"።
🌹 ይህ አባ ጴጥሮስ እንደ ተቀበላት ገልጦ ስለ ቀናች ሃይማኖት ከራሱም ያለውን ጨምሮ ለመልእክቱ መልስ ጽፎ ከሦስት ምሁራን ኤጲስቆጶሳት ጋር ላካት። አባ አካክዮስም ተቀበላቸው በቅዳሴና በቊርባንም አንድ ሆኑ ያቺንም መልእክት በቃሉ በሚያምኑ ሕዝብ ፊት አነበባት።
🌹 ከዚህም በኋላ ሌላ መልክትን ጻፈ በውስጧም ከቅዱሳን መጻሕፍት ብዙ ቃላትን ተርጒሞ ወደ አባ ጴጥሮስ ላካት። ይህም አባ ጴጥሮስ ኤጲስቆጶሳቱን ሰብስቦ ያቺን መልእክት በፊታቸው አነበባት እነርሱም እጅግ ደስ አላቸው ከቃሏና ከትርጓሜዋም የተነሣ አደነቁ በቀናች ሃይማኖትም ከእርሳቸው ጋር አንድነት ያላቸው መሆኑን ተማመኑ።
🌹 ይህንን አባት አባ ጴጥሮስንም ከሀዲያን ከሆኑ አይሁድ ከአረማውያንም ከመንበረ ሢመቱ እስኪያሳድዱት ድረስ ስለቀናች ሃይማኖት ብዙ መከራ ደረሰበት።
🌹 ከጥቂት ወራትም በኋላ ወደ ሹመቱ ወንበር ተመለሰ መንጋውንም በቀናች ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ አዘውትሮ ያስተምራቸው ነበር ከእነርሱም ርቆ በስደት በነበረበት ጊዜ ከመናፍቃን እንዲጠበቁና በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ መልእክቶችን ጽፎ ይልክ ነበር በሹመቱ ወንበርም ዐሥር ዓመት ኑሮ ኅዳር 2 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ጴጥሮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
🌹 በዚችም ቀን ዳግመኛ ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት #ስልሳ_አምስተኛ_የሆነ_የእስክንድርያ_ሊቀ_ጳጳሳት #አባ_ሱንትዩ_ዐረፈ፦ ይህም አባት መንጋዎቹን እያስተማረ በሹመቱ ወንበር ዐሥራ አምስት ዓመት ኑሮ ኅዳር 2 ቀን በሰላም ዐረፈ። በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 2 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
🌹 "#ሰላም_እብል_ለብፁዕ_ሱንትዩ። #ወለጴጥሮስ ዓዲ ሱታፌ ዕበዩ። ኪያሆሙ ሕዝብ በከመ ሠምሩ ወኀርዩ። ሤሞሙ አብ ጳጳሳተ ቤተ ክርስቲያኑ ይርዐዩ። እንተ አጥረያ በደሙ ወማዩ"። #ሊቁ_አርከ ሥሉስ (አርኬ) #የኅዳር2።
✝️ ✝️ ✝️
🌹 #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ዝክረ ጻድቅ ለዓለም ይሄሉ። ወኢይፈርህ እምነገር እኩይ። ጥቡዕ ልቡ ለተወክሎ በእግዚአብሔር"። መዝ111፥6-7። የሚነበቡት መልዕክታት ቈላ 4፥16-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 1፥1-7 እና የሐዋ ሥራ 20፥18-31። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 10፥1-22። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።
ሰው ፍለጋ እግሩን የሚያደክም ሰው
ልቡ ይወልቃል እንጂ ሰው አያገኝም
የራስን ልብ እራስን ማስተካከል ነው
ሰውን ከማስተካከል እራስን ማስተካከል
ሰውን ለማስተካከል መድከም በፍፁም አይቻልም
እሚቻለው እራስን ማስተካከል ነው
ተስፋ የቆረጡ ሰዎች ይሄን ሁሉ አልፈው
ከተስፋ መድረስ እንደሚቻል የምታሳይ
ብቸኛዋ የቤተክርስቲያን ተስፋ ምልክት
እመብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም ነች።
እግዚአብሔርን ለያዘ ብቸኝነት የለበትም።
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ❤️
This automated cryptocurrency trading system uses intelligent algorithms to buy low and sell high on leading crypto exchanges. Many users have already enjoyed significant profits!
🔴 Sign-Up Bonus: Get 8 USDT for free upon registration!
🔵 Withdrawals: Start withdrawing from just 1 USDT per day.
💰 Investment Plans:
Invest 10 USDT: Earn 0.25 USDT per day, totaling 25 USDT over 30 days.
Invest 100 USDT: Earn 5.25 USDT per day, totaling 262 USDT over 30 days.
Invest 1,000 USDT: Earn 58.85 USDT per day, totaling 2,835 USDT over 30 days.
Invest 5,000 USDT: Earn 330 USDT per day, totaling 12,450 USDT over 30 days.
💰💰You can withdraw your earnings daily!
If you are interested please contact me
If you are interested please contact me
If you are interested please contact me
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ኅዳር 6-በዚህች ዕለት ክብርት እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር ከስደት በሚመለሱበት ጊዜ ደብረ ቁስቋም ገብተው ካገኛቸው ድካም ዐረፉ፡፡
አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ከስደት በተመለሰች ጊዜ እንዲህ ሆነ፡- የብርሃን እናቱ ክብርት እመቤታችን ልጇን ይዛ ከእነ ዮሴፍ ጋር ወደ ምድረ ግብፅ ስትሰደድ ግብፅ ደርሰው በዚያ ቢቀመጡም ነገር ግን ግብፅ አልተመቸቻውም፡፡ ሕዝቡም በሰላም አልተቀበላቸውም፡፡ እንዲያውም በምድረ ግብፅ ብዙ ተሠቃይተዋል፡፡ ከግብፅም ተነሥተው ወደ ኢትዮጵያ በመጡ ጊዜ ግን ኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ በሰላምና በፍቅር ተቀበላቸው፡፡ ከመንገዱና ከርሃብ ጥሙ ጽናት የተነሣ እጅግ ደክማለችና የኢትዮጵያ ሰዎች እመቤታችንን አይተው እጅግ አዘኑላት፡፡ ‹‹ይህችስ የነገሥታት ዘር ትመሥላለች ነገር ግን አንዳች ችግር አጋጥሟት ተሰዳ ወደ ሀገራችን መጥታለች..›› ብለው እንክብካቤን አደረጉላት፡፡ እግራቸውን አጥበው በክብር ማረፊያዎች ላይ አሳረፏቸው፡፡ መልካም መስተንግዶም አደረጉላቸው፡፡ እመቤታችንም ከድካሟ ካረፈች በኋላ ሀገሪቱን በእጅጉ ወደደቻትና የተወደደ ልጇን ‹‹ይህን ሀገርና ሕዝቧን በመላ ወድጃቸዋልሁና በዚህ እስከ መጨረሻው እንኑር›› አለችው፡፡ ጌታችንም ክብርት እናቱን ‹‹ይህች ቅድስት ሀገር ናት፣ በኋለኛው ዘመን የቅዱሳን መነኮሳት ቦታ ትሆናለች፡፡ በውስጧም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ እመሰገንባታለሁ፤ የአንቺም ስም ሳይጠራ አይውልባትም›› አላት፡፡
ከዚህም በኋላ ጌታችን ደመና ጠቅሶ በእርሷ ላይ ተቀመጡ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤልም መጣና እየመራቸው መላ ኢትዮጵያን ጎበኟት፡፡ እመቤታችንም ሀገሪቱንና ሕዝቦቿን ወዳቸዋለች ደስም ተሰኝታባቸዋለችና ጌታችን ለክብርት እናቱ ‹‹ይህችን ቅድስት ሀገር አሥራት አድርጌ ሰጠሁሽ›› አላት፡፡ እመቤታችንም እጅግ ተደስታ ‹‹ልጄ አምላኬ›› ብላ አመሰገነችው፡፡ ከዚህም በኋላ ከአንዱ ቦታ ወደ አንዱ ቦታ እየተዘዋወሩ መላዋ ኢትዮጵያን በኪደተ እግራቸው ባረኳት፡፡ ጌታችንም ‹‹በዚህ ቦታ እንዲህ ዓይነት ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል፤ እከሌ የሚባል እንዲህ ዓይነት ቅዱስ ይነሣል…›› እያለ ብዙ ምሥጢራትን ለክብርት እናቱ ነገራት፡፡ ከዚህም በኋላ የስደቱ ዘመን ሲያልፍ ሄሮድስም በመጨረሻ ክፉ አሟሟትን ሲሞት መልአኩ ወደ ገሊላ አውራጃ እንዲመለሱ ነገራቸው፡፡ እመቤታችንም ‹‹ከዚህች ሀገርስ ባንሄድ እመርጣለሁ›› ስትለው የተወደደ ልጇ ግን ‹‹እናቴ ሆይ ጽድቅንና ፈቃድን ሁሉ ልንፈጽም ይገባናል›› ብሎ አጽናናትና ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ሄዱ፡፡
ተመልሰውም ሊሄዱ ሲነሡ የኢትዮጵያ ሰዎች ልዩ ልዩ አምሐ እጅ መንሻ ሰጧቸው፡፡ ልዩ ልዩ ልብሶች፣ ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ፣ ሽቱ እና ሥንቀቸውን በግመሎች ላይ ጭነው እመቤታችንንና የተወደደ ልጇንም በበቅሎ ላይ አስቀምጠው በክብር ሸኟቸው፡፡ እመቤታችንም ልጇን ታቅፋ በበቅሎ ተቀምጣ በበረሃው በመጓዝ ወደ መጣችበት አገር ሄደች፡፡ ኢትዮጵያንም የሰጧትን ብዙ እጅ መንሻዎች በግመሎች ጭና ይዛ ወደ አገሯ በተመለሰች ጊዜ ከአንድ ባሕር ዳር ደረሰች፡፡ ከዚያም የጀልባውን ባለቤት ‹‹እግዚአብሔርን ስለመውደድ አሻግረኝ›› ብላ ለመነችው፡፡ ባለጀልባውም ‹‹እነሆ ዕቃ የተጫኑ አምስት ግመሎችና ከአንቺ ጋር ከዚህም ሕፃን ጭምር አምስት ሰዎች እመለከታለሁ፣ አንቺ የተቀመጥሽባት በቅሎም አለች፡፡ ጀልባዋም ታናሽ ናት፣ የመቀመጫ ክፍሏም በውስጧ የተሳፈሩት ሰዎችም ተጨናንቀው ነው ያሉት፡፡ ስለዚህ እንዴት ላሻግርሽ እችላለሁ? ነገር ግን እመቤቴ ሆይ! ይቅርታ አድርጊልኝ ይህን በክፋት አላደረግሁትምና›› አላት፡፡
ክብርት እመቤታችንም የጀልባው ባለቤት ሊያሻግራት እንዳልቻለ በተረዳች ጊዜ ‹‹ልጄ ሆይ የእግዚአብሔር ልጅ እንደመሆንህ ይህን ትልቅ ወንዝ ለመሻገር የአምላክነትህን ሥራ ትሠራ ዘንድ እለምንሃለሁ›› ስትል ማለደችው፡፡ ያንጊዜም ጌታችን ክብርት እናቱን ‹‹የወለደሽኝ እናቴ ሆይ! አትዘኝ›› ብሎ አረጋጋት፡፡ ዳግመኛም ‹‹በእኔ ፈቃድ በአባቴ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ካንቺ ሰው ሆኛለሁና ሰው መሆኔንም ከአባቴ በቀር መስተፍሥሒ ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስም በቀር ያወቀ የለም፡፡ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ ለሁሉም እንደየሥራው እከፍለው ዘንድ እመጣለሁ፡፡ ያችንም ሰዓት የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ የአዳም ልጆችም ቢሆኑም ከእኔና ከአባቴ ከመንፈስ ቅዱስም በቀር የሚያውቃት የለም፡፡ ያንጊዜ ‹ዐመፅን የሚናገር አንደበት ሁሉ ይዘጋል› ብሎ አባትሽ ዳዊት እንደተናገረ እከራከራለሁ የሚል አንደበት እንደድዳ ምላሽ ያጣል›› አላት፡፡
ክብርት እመቤታችን ማርያምም ይህንን ሁሉ ምሥጢር የተወደደ ልጇ የነገራትን ታስተውለው በልቧም ትጠብቀው ነበር፡፡ ጌታችንም አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለክብርት እናቱ ይህንን ከነገራት በኋላ ቀኝ እጁን ዘርግቶ ከወንዙ ማዶ ጢር በሚባል ተራራ ያሉትን ድንጋዮች ጠቀሳቸው፡፡ ያንጊዜም እነዚህ ድንጋዮች እየተገለባበጡ መጥተው እንደ ጀልባ ሆነው በወራጁ ወንዝ ላይ ተንሳፈፉ፡፡ ከዚያም እመቤታችንን ከሕፃኑ ጋር ከነቤተሰቧና ከነጓዟ አሻገረሯት፡፡
እነዚህንም ድንጋዮች ያዩ ሰዎች ሁሉ እጅግ አድንቀው ‹‹ብቻውን ድንቅ ተአምራት ያደረገ፣ እስራኤልን የፈጠረ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን የጌትነቱም ስም የተመሰገነ ነው›› እያሉ አመሰገኑ፡፡ እነዚህም የተባረኩ ሰዎች ወንዙን ከተሻገሩ በኋላ በዚህች አገር ለስምንት ቀን ተቀመጡ፡፡ ከዚህም በኋላ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ስለደረገላት መልካም ሥራ ሁሉ እግዚአብሔርን ፈጽማ እያመሰገነች ወደ አባቷ ወደ ዳዊት አገር ተመለሰች፡፡
ዳግመኛም በኋለኛው ዘመን ጌታችን በዚህ በደብረ ቍስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቶቹን ሰበሰባቸውና ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንን አክብሮ የቍርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወገኖቹ ሰጣቸው፡፡ ለዚህም ነገር የእስክንድርያ አገር ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱሳን አባቶቻችን ቄርሎስና ቴዎፍሎስ ምስክሮቹ ሆኑ፡፡
ክብርት እመቤታችን ከስደቷ በረከት ትክፈለን!
+ ዳግመኛም በዚህች ዕለት አባ ፊልክስ ዐረፈ፡፡
አባ ፊልክስ፡- ይኸውም ቅዱስ ምግባር ሃይማኖቱ፣ ትሩፋት ተጋድሎው ያማረ ሆኖ ቢያገኙት በእግዚአብሔር ፈቃድ የሮሜ አገር ሊቀ ጳጳሳት አድርገው ሾሙት፡፡ በዘመኑም ከሃዲው ቴዎስድሮስ ቄሳር ነግሦ ምእመናንን ሲያሠቃያቸውና ሲገድላቸው ሊቀ ጳጳሳት አባ ፊልክስንም ብዙ አሠቃጥቷቸዋል፡፡ አባ ፊልክስም በክርስቲያኖች ላይ እየደረሰ ያለው ጽኑ መከራ እንዲቆም ወደ እግዚአብሔር በጸለየ ጊዜ ይህን ከሃዲ ንጉሥ በነገሠ በ2ኛ ዓመቱ አጠፋው፡፡
ከዚህም በኋላ የክርስያኖችን ደም እንደውኃ ያፈሰሰው ከሃዲው ዲዮቅልጥያኖስ ነገሠና ክርስቲያኖችን በዓለም ላይ እያደነ ማሠቃየትና መግደል በጀመረ ጊዜ ይህ አባት አባ ፊልክስ የክርስቲያኖችን ሥቃይ እንዳያሳየው ወደ እግዚአብሔር በጸለየ ጊዜ ወዲያው በመጀመሪያው ዓመት ዐረፈ፡፡ ይህም አባ ፊልክስ ለክርስቲያን ወገኖች እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ብዙ ድርሳናትንና ትግሣጻትን የጻፈ ነው፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!
ከገድላት አንደበት
✞ ✞ ✞
ዘፈን የምትወዱ እናንተ የወለተ ሄሮድያዳ ወዳጆች ወዮላችሁ
ሱሪ የምትለብሱ ለዝሙት ምክንያት የምትሆኑ ቅርፅ የምታሳዩ አህቶች ወዮላችሁ
በየመሸታ ቤት እየሄዳችሁ በመደነስ የምትስክሩ ወዮላችሁ
በኋላ ትሉ የማያንቀላፋ እሳቱ የማይጠፋ ገሀነም ላይ ትገባላችሁና።
ህዳር 6/2017 #በዐለ_ቁስቋም_ማርያም
👉በሰመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን እኛን ልጆቹን ከእናቱ ጋር ሆኖ ተሰዶ ስለፈለገን እያመሰገነዉ #ከእናታችን_ማርያም ከቅዱስ ዮሴፍ ከቅድስት ሰሎሜ ጋር ከስደት ለተመለሱበት አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
"የህፃኑን ነፍስ የሚፈልጉት ሞተዋልና ተነስ እናቱንና ህፃኑን
ይዘህ ወደ እስራኤል ተመለስ ማቴ.2፥19_20"
👉ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሆይ አስበን በቃችሁ በለን ስደት ይብቃን እኛ ኢትዮጲያዊያን ፍቅር አጥተን አንዱ በአንዱ ላይ እየተነሣ አንዱ ተሳዳጅ አንዱ አሳዳጅ ሆነናልና በቃችሁ ብለህ በምህረት አይንህ ጎብኘን
👉የእመቤታችን ከልጇ ከወዳጇ #ከኢየሱስ_ክርስቶስ ጋር የግብፅ ስደት አልቆ ወደ አገሯ ኢየሩሳሌም የተመለሰችበት ዕለት ናትና ክርስቶስ የአዳምን ከገነት የተሰደደውን ስደት በማሰብ ወደ ግብፅ ተሰደደ
👉የቅዱሳንን በእምነታቸው ምክንያት የሚሰደዱትን ስደት ይባርክ ዘንድ #ጌታ_ተሰደደ በነፍስ በስጋ ከቅድስና የሚሰደዱትን ወገኖች ወደ ህይወት ወደ ክብሩ ይመልስ ዘንድ እርሱ #ተሰደደ አሳዳጁን ጠላት ዲያቢሎስ ያዋርደው ዘንድ እርሱ ተሰደደ
👉ለህዝባችን ለሀገራችን #መመለስ ይሁን ስደት ይብቃ #ክርስቶስን ያሳደደው ሄሮድስ እንደሞተ ሁሉ የአገራችንና የህዝባችን #አሳዳጆችን ልቦና ሰጥቶ ይመልስልን
👉ኢትዮጲያዊያንና የዓለም ህዝቦችን ከመከራና ከስደት እርሱ አምላካችን በቃችሁ ብሎ ይጠብቅልን እናታችን አማላጃችን ወላዲተ ቃል #እመቤታችን_ማርያም በምልጃ ፀሎትሽ ሁላችንንም አስቢን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ምዕረ በዘባንኪ ወምዕረ በገቦኪ፤
ማርያም ብዙኀ በሐዚለ ሕፃን ደከምኪ፤
ሶበኒ የሐውር በእግሩ ከመ ትጹሪዮ ይበኪ፤
አልቦ እንበለ ሰሎሜ ዘያስተባርየኪ ለኪ፤
ወዮሴፍ አረጋዊ ዘይጸውር ስንቀኪ።
🖌 ማርያም! አንድ ጊዜ በጀርባሽ፣
አንድ ጊዜ በጎንሽ ልጅን በማዘል በእጅጉ ደከምሽ
በእግሩ በሚሄድበት ጊዜም ትሸከሚው ዘንድ ያለቅሳል፣
ስንቅሽን ከሚሸከም ከሽማግሌ ዮሴፍና
ከሰሎሜ በቀር አንችን የሚያስተጋግዝሽ የለም፡፡
🌹🌹🌹ሰቆቃወ ድንግል 🌹🌹🌹
#የፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_42ኛ_ዓመት_የምሥረታ_በዓል
#ፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሰንበት_ትምህርት_ቤት
#ፍሬ_ዓምደ_ሃይማኖት_ሚዲያ
Follow us on
👉 /channel/fre_amde_haymanot_media
👉 http://linktr.ee/fre_amde_haymanot_media
ህዳር 5/2017 #ቅዱስ_ጴጥሮስ_እና_ቅዱስ_ጳዉሎስ
#ፃድቁ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በፃድቁ ስም ለሚመሰገንበት ፃድቁ አባታችን #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስን
በምልጃ ፀሎቷቸዉ እንዲያስቡን ለምንማፀንበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉ፃድቁ አባታችን ሐገራቸው ንሂሳ ግብፅ ነው አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል አንድ ቀን አቅሌሲያ #ቤተ_እግዚአብሔር ገብታ ከሥዕለ ሥላሴ ሥር ወድቃ ስትማፀን ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበልጥ ልጅ እንኪ ተቀበይ የሚል ድምጽ ሰማች
👉በዚህ መሠረት አባታችን #ፃድቁ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ መጋቢት 29 ተፀንሰው ታኀሣስ 29 ተወለዱ አባታችን ዓይን በገለፁ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ብለዉ ተነስተው «ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ዘዓውፃእከኒ እምጽልመት ውስተ ብረሃን» ብለው አመስግነዋል
👉በኋላም ምድራዊ መብል መጠጥ ሳይመገቡ ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መላዕክትን መስለዋል አባታችን ፃድቁ #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ በኢትዮጵያ 262 ኖረው በ562 ዓመታቸው በተስፋቸው ያመነውን በኪዳናቸው የተማፀነ ጌታ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሊምርላቸው ተስፋቸውን ተቀብለው በዕለተ እሁድ ዐርፈዋል
👉መላእክት #በአክናፈ_እሳት_ኢየሩሳሌም ወስደው በየማነ ምስዋዕ ቀብረዋቸዋል ፃድቁ አዲሱ የምህረት አመት የሠላም የፍቅር የአንድነት ይሆን ዘንድ በምልጃ ፀሎታቸዉ ያስቡን
👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸዉ የምናስባቸው ቅዱሣን #ብርሃናተ_አለም_ጴጥሮስ_ወ_ጳዉሎስ እንዲሁም ሌሎች ቅዱሣን ምልጃ ፀሎታቸዉ ይጠብቀን ረድኤት በረከታቸዉ አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ህዳር 5/2017 #ቅዱስ_ጴጥሮስ_እና_ቅዱስ_ጳዉሎስ
#ፃድቁ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በፃድቁ ስም ለሚመሰገንበት ፃድቁ አባታችን #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስን
በምልጃ ፀሎቷቸዉ እንዲያስቡን ለምንማፀንበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉ፃድቁ አባታችን ሐገራቸው ንሂሳ ግብፅ ነው አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል አንድ ቀን አቅሌሲያ #ቤተ_እግዚአብሔር ገብታ ከሥዕለ ሥላሴ ሥር ወድቃ ስትማፀን ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበልጥ ልጅ እንኪ ተቀበይ የሚል ድምጽ ሰማች
👉በዚህ መሠረት አባታችን #ፃድቁ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ መጋቢት 29 ተፀንሰው ታኀሣስ 29 ተወለዱ አባታችን ዓይን በገለፁ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ብለዉ ተነስተው «ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ዘዓውፃእከኒ እምጽልመት ውስተ ብረሃን» ብለው አመስግነዋል
👉በኋላም ምድራዊ መብል መጠጥ ሳይመገቡ ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መላዕክትን መስለዋል አባታችን ፃድቁ #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ በኢትዮጵያ 262 ኖረው በ562 ዓመታቸው በተስፋቸው ያመነውን በኪዳናቸው የተማፀነ ጌታ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሊምርላቸው ተስፋቸውን ተቀብለው በዕለተ እሁድ ዐርፈዋል
👉መላእክት #በአክናፈ_እሳት_ኢየሩሳሌም ወስደው በየማነ ምስዋዕ ቀብረዋቸዋል ፃድቁ አዲሱ የምህረት አመት የሠላም የፍቅር የአንድነት ይሆን ዘንድ በምልጃ ፀሎታቸዉ ያስቡን
👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸዉ የምናስባቸው ቅዱሣን #ብርሃናተ_አለም_ጴጥሮስ_ወ_ጳዉሎስ እንዲሁም ሌሎች ቅዱሣን ምልጃ ፀሎታቸዉ ይጠብቀን ረድኤት በረከታቸዉ አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ህዳር 4/2017 #ወንጌላዊዉ_ቅዱስ_ዮሐንስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱስ ዮሐንስ ስም ለምናመሰግንበት ለወንጌላዊዉ ለፍቁረ እግዚእ ቅዱስ #ዮሐንስ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉በመጀመሪያው ቃል ነበረ፣ቃልም #በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፣ቃልም እግዚአብሔር ነበረ፣ቃልም ስጋ ሆነ ዮሐ1፥1-14
👉ወንጌላዊው #ቅዱስ_ዮሐንስ የተለያዩ ስሞች አሉት ከነዚህም ጥቂቶቹ
✝️ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ
✝️ ፍቁረ እግዚእ
✝️ ታኦሎጎስ
✝️ አቡቀለምሲስ
✝️ ቁፅረ ገፅ
✝️ ዮሐንስ ዘንስር
👉 #ቅዱስ_ዮሐንስ እመቤታችንን በአደራ የተቀበለ በአንድ ቤት ልጅ ሆኗት 15 ዓመት የኖረ ቅዱስ አባት ሐዋርያ ነዉ የአለሙን ገዢ ወልዳ ያሳደገች በፀጋ ተሞላታ ተቀድሳ የኖረች እናታችን #ማርያምን በእናትነት የተቀበለ ወንጌላዊው #ቅዱስ_ዮሐንስ በረከት እና ፀሎቱ አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
✝እንኳን አደረሰነ!
✞በዓለ ቅዱሳን አበው፦
✿መድኀኒነ እግዚእ ጻድቅ (ወላዴ አእላፍ)
✿ዓምደ ሚካኤል ሰማዕት (ሊቀ ሠራዊት)
✿ፍሬ ካህን መነኮስ (ገባሬ ተአምር)
✿ቶማስ ገዳማዊ (ዘዘናቁዴ ደብረ ማርያም)
✿ነአኩቶ ለአብ (ንጉሠ ኢትዮጵያ)
✿ኪርያቆስ (ዘቆሮንቶስ)
✿አትናቴዎስ ወኢራኢ (ሰማዕታት)
ኅዳር ፫፦
✝ማርያም ድንግል ዘደብተራ ኦሪት ማዕነቅ፤
ዘካርያስ ዘርእየኪ በአርአያ ተቅዋም ዘወርቅ፤
ፍጽምናኪ ተግህደ በላዕለ ፯ቱ አዕጹቅ፤
አመ ይመጽእ ወልድኪ እንዘ በቅድሜሁ መብረቅ፤
ተማኅጸንኩ በብካይኪ ገብርኪ ዕሩቅ!
✝ዓምደ ሚካኤል ኃያል መልአከ ሥረዊሆሙ ለነገሥት፤
ዘአድምአ ስመ በቅድመ ሰብእ ወመላእክት፤
በእንተ ዘገብረ ሰላመ ለኢትዮጵያ ቅድስት፤
ፈደይዎ እኩየ መኳንንተ ንጉሥ ዐበይት፤
ወዲበ ሥጋሁ ሠረቀ ብርሃነ መለኮት እኩት!
✝መድኃኒነ እግዚእ መምህር ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን፤
ነአኲቶ ለአብ ንጉሥ ወገባሬ መንክር ፍሬ ካህን፤
አትናቴዎስ ሰማዕት ወኪርያቆስ ምዕመን፤
ዓምደ ሚካኤል ጻድቅ ወሰማዕተ ክርስቶስ ብርሃን፤
ዘቀተልዎ ውስተ ኲርጓኔ መኳንንተ ዘመን አብዳን!
(አርኬ - ዝክረ ቅዱሳን ርቱዓነ ሃይማኖት)
✝ተአምረ ኀይልከ አባ፥ መድኀኒነ እግዚእ አቡነ፤
እምኀበ ዜናዊ ሰማዕነ፥ ወበዐይነ ሥጋ ርዒነ፤
መንክርኬ አእላፈ ቤትከ ንኅነ፤
ባሕቱ በዝ ተአምሪከ ርድአነ፤
ለሰይፈ አርዕድ ንጉሥ፥ ዘወሀብኮ ኪዳነ፤
ከመ ረድኤቱ ታፍጥን፥ ጊዜ ጸብእ ኮነ!
(መርገፍ)
ህዳር 3/2017 #እናታችን_ቅድስት_ባዕታ
#ቅዱስ_ፋኑኤል
#ፃድቁ_ዜና_ማርቆስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በእናታችን ስም ለምናመሰግንበት ለእናታችን #ባዕታ_ማርያም ቤተ መቅደስ ለገባችበት ወርሐዊ መታሰቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ መዝ.45፥4
👉 #ባዕታ ማለት ባዕት ከሚለው ግስ የወጣ ሲሆን መግባት ማለት ነው ባዕታ ለማርያም ስንል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ታኅሣሥ 3 ቀን ወደ #ቤተ_መቅደስ የገባችበት እለትን በመሆኑ ወር በገባ በ3ኛው ቀን የምናከብረው ታላቅ ቀን ነው
👉እናታችን #ባዕታ_ማርያም ለሰው ልጆች ድህነት ምክንያት እንድትሆን ከአምላክ የተሰጠች ታላቅ ስጦታ ነች
👉እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የስደት ልጅ በመሆኗ ቅዱስ እያቄምና ቅድስት ሃና #በቤተ_መቅደስ እንድታድግ ብለው በ3 ዓመቷ አምጥተዋት ለሊቀ ካህኑ ለዘካሪያስ አስረከቧት ነገር ግን ካህኑ ምን በልታ ታድጋለች ብሎ ቢጨነቅም መልአኩ ቅዱስ #ፋኑኤል ከሠማይ መናን እያወረደ እየመገበ 12 ዓመት በቤተ መቅደስ ኖራለች
👉እመቤታችንም ቅድስት ድንግል ማርያም #እግዚአብሔርን እያመሰገነች ለመላእክት እያገለገለች ሐርና ወርቅን እያስማማች እየፈተለች በንፅህና በቅድስና #በቤተ_መቅደስ በምስጋና ኖራለች
👉እርሱ ጌታችን #ክርስቶስ መርጧታልና ልክ 15 ዓመት ሲሆናት ከሲዖል የታሰርነውን እኛን ለማዳን ሲል ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ 9 ወር ከ5 ቀን በማህፀኗ አደረ ተወልዶ አደገ
👉በዚህ ምድር ሲኖር አዳኛችን #ክርስቶስ ወንጌልን አስተማረ ምሳሌ ሆነ መከራን ተቀበለ በቀራኒዮ መስቀል ላይ ክቡር ደሙን አፈሰሰ ክቡር ሥጋውን ቆረሰ በእርሱ ሞት እኛን ነፃ አወጣን ክብርና ምስጋና ለስም አጠራሩ ይሁን ምስጋና ለድህነታችን ምክንያት ለሆነችው ለእናታችን #ባዕታ_ማርያም ይሁን
👉የእናታችን #ባዕታ_ማርያም ፍቅር በረከቷ ምልጃና ፀሎቷ ሁላችንንም ይጠብቀን ለሀገራችን ለህዝባችን ሠላሙን አንድነቱን ይስጥልን በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸዉ የምናስባቸዉ የመልአኩ #ቅዱስ_ፋኑኤል ጥበቃዉ የአባታችን የፃድቁ አቡነ #ዜና_ማርቆስ ፀሎታቸዉ አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
🌹 አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባንም አመንኵሰው መርቀው ሲሸኟቸው እንዲያገለግሏቸው አንበሶችን ከጫካ ጠርተው ያዘዙላቸው አባታቸው አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ናቸው፡፡ የዋልድባው አቡነ ሳሙኤል አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ከመነኰሱ በኋላ በደብረ በንኰል 12 ዓመት አባታችንን ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ እሳት እስከማያቃጥላቸው ድረስ ከብቃት ደረጃ ላይ ሲደርሱ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ መርቀው በማሰናበት በዓት እንዲያጸኑ ሲያደርጓቸው አቡነ ሳሙኤል በቅዱስ ሚካኤል መሪነት ጣና ደሴት ገብተው ሱባኤ ያዙ፡፡ በዚያም ሳሉ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ማረፋቸውን በመንፈስ ዐውቀው ሲያለቅሱ ጌታችን የአቡነ መድኃኒነ እግዚእን ነፍስ በእቅፉ አድርጎ ወደ ገነት ሲያሳርጋት አሳያቸው፡፡ ወዲያውም ጌታችን በብርሃን ሰረገላ አድርጎ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባን ደብረ በንኰል አድርሷቸዋል፡፡ በዚያም እስከ 40ኛው ቀን ከቆዩ በኋላ በዚሁ ዕለት ሲቀድሱ ክንድ ከስንዝር ከመሬት ከፍ ብለው ቅዱሳን ሐዋርያት እየተራዱዋቸው ከቀደሱ በኋላ ወደነበሩበት መልሷቸዋል፡፡ የጻዲቁ የአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዕረፍታቸው ኅዳር 3 ቀን 1360 ዓ.ም ሲሆን ጠቅላላ ዕድሙያቸውም 180 ዓመት ነው፡፡
🌹 ዐፄ ፋሲል ጻድቁ የተከሏቸውን የጥድ ዛፎች በሙሉ ተቆርጠው የአክሱም ቤተ ክርስቲያን እንዲሠራበት አዋጅ አወጁና መልእክተኞች መጥተው ዛፎቹን ሲቆርጡ መነኰሳቱ ግን "ጻድቁ አባታችን የተከሏቸው የጥድ ዛፎች መቆረጥ የለባቸውም" ብለው ቢከራከሩም ሰሚ አላገኙም፡፡ መነኰሳቱም ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክቱ ጩኸታቸው ተሰምቶላቸው ወዲያው እየተቆረጡ ያሉት የጥድ ዛፎች በሙሉ በተአምራት ወደ ወይራ ዛፍነት ተለወጡ፡፡ የወይራ ዛፎቹም ለዐፀድ እንጂ ለሕንፃ የማይመቹ ጎባጣ ሆኑ፡፡ የዚህም ምልክቱ ዛሬም ድረስ አለ፡፡ ግንዱ ጥድ ዛፉ ግን ወይራ የሆነ ትልቅ ዛፍ "ወይራ ዘገብረ ተአምር" በሚባል ቦታ አሁንም ድረስ ቆሞ ይታያል፡፡
🌹 ጻድቁ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ በ1312 ዓ.ም የመሠረቱት ገዳማቸው ደብረ በንኰል ከአክሱም በእግር ሦስት ሰዓት ያስኬዳል፡፡ ይኸውም በንግሥተ ሳባ ቤተ መንግሥት አድርጎ የቀዳማዊ ሚኒሊክን መቃነ መቃብር አልፎ በመሄድ ነው፡፡ ወይም በመኪና ለመጓዝ አክሱም ጉበዱራን አቋርጦ ውቅሮ ማራይ ከተማን አልፎ በስተ ሰሜን አቅጣጫ 10 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ በስተ ምዕራብ የአቡነ አላኒቆስ ዘማይበራዝዮን ገዳም፣ በስተ ምሥራቅ የአቡነ ሰላማን ገዳም እየተለመከቱ እንደተጓዙ ጥቅጥቅ ባለ ደን የተሸፈነውን ደብረ በንኰልን ያገኙታል፡፡ ኅዳር 20 ጻድቁ ስለሚነግሱ ገዳሙም ለአክሱም ቅርብ ስለሆነ ይህ ለአክሱም ጽዮን ተጓዦች ተጨማሪ ትልቅ በረከት ነው፡፡
🌹 ደብረ በንኰል ማለት "ሙራደ ቃል" ማለት ነው፡፡ ትርጉሙም የምሥጢር መውረጃ ማለት ነው፡፡ በቦታው ላይ ሱባኤ ለያዘ ሰው እንደ ቅዱስ ያሬድና እንደ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ምሥጢር እንደሚገለጥለት የሚጠቁም ነው፡፡ በ14ኛው መ/ክ/ዘ የነበሩት ደጋግ መነኰሳት ሕይወታቸውን በሙሉ በምንኵስና፣ በጸሎትና በታላቅ ተጋድሎ መኖር ሲፈልጉ ከደብረ ዳሞ፣ ከሐይቅ እስጢፋኖስ፣ ከደብረ ሊባኖስና ከሌሎቹም የሀገራችን ክፍሎች እየተነሡ ወደ ደብረ በንኰል አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ገዳም ነበር የሚሄዱት፡፡
🌹 የአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ቃልኪዳን፡- ጻድቁ ባርከው ያፈለቁት ጸበላቸው ላበደ ሰው መድኃኒት ነው፡፡ ከመቃብራቸው ላይ የሚነሣውን አፈር ጻድቁ ባርከው ባፈለቁት ጸበላቸው ታሽቶ በእጃቸው መስቀል ተባርኮና ታሽቶ የሚዘጋቸውን የአቡነ መድኃኒነ እግዚእን እምነታቸውን በእምነት ሆኖ የያዘን ሰው ንብረቱን ሌባ ቀማኛ ዘራፊ አይሰርቀውም፤ የመኪና አደጋ አይደርስበትም፤ ጥይት አይመታውም፡፡ "በእምነት ሆኖ የያዘን ሰው" መባሉን ልብ ይሏል፡፡ ይኸውም ለጻድቁ የተሰጣቸው ታላቅ ቃልኪዳን ነው፡፡ ከአቡነ መድኃኒነ እግዚእ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤት በረከትን ያሳትፈን፣ በጸሎታቸው ይማረን!።
✝ ✝ ✝
🌹 #አቡነ_ዓምደ_ሚካኤል፡- ትውልዳቸው ወሎ ቦረና ነው፡፡ ወላጆቻቸው ገላውዲዮስና ኤልሳቤጥ ሁለቱም በሃይማኖትና በዓለም ገንዘብ የበለጸጉ ናቸው፡፡ ይህንንም ጻድቅ ልጃቸውን የአርባዕቱ እንስሳ በዓል ዕለት ወለዱትና ስሙን ዓምደ ሚካኤል ብለው ጠሩት፡፡ ለዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ፣ ለዐፄ በእደ ማርያምና ለዐፄ እስክንድር የሠራዊት አለቃ የነበረ ጻድቅ ነው፡፡ በአንድ ዓመቱ ወላጆቹ ወደ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ይዘውት እንደሄዱ ከወላጆቹ ተለይቶ ጠፍቶ ሳይገኝ ቀረ፡፡ መልአክም ከቤተ መቅደስ አግብቶ እየመገበው 3 ቀን አቆይቶታል፡፡ በ3 ኛው ቀን ቄሱ ሊያጥን ሲገባ በከርሰ ሐመሩ ውስጥ ሕፃኑን አገኘውና ወስዶ ለወላጆቹ ሰጣቸው፡፡
🌹 ባደገም ጊዜ በመመጽወትና አብያተ ክርስቲያናትን በማደስ የሚተጋ ሆነ፡፡ ለድኆችም በቅንነት በመፍረድ በታላቅ ተጋድሎ የሚኖር ሆነ፡፡ ለነገሥታም ገዥ ከሆነ በኋላ በጸሎቱና በበረከቱ በሀገራችን ላይ ሁሉ ሰላም ሆነ፡፡ ጠላቶችም ሁሉ ለነገሥታቱ ተገዝተው ይገብሩ ነበር፡፡ በበጎ ምግባሩ የቀኑ ዐመፀኞችም በክፋ ተነሡበት፡፡ ጻድቁ በመንፈስ አድጎ መንኵሶ በታላቅ ተጋድሎ ሲኖር ነገር ሠሪዎች በሐሰት ወንጅለው ከሰሱት፡፡ ንጉሡም እጅግ ስለሚወደው የራራለት ቢሆንም በነገራቸው ባስጨነቁት ጊዜ ወደ ሩቅ አገር አስሮ አጋዘው፡፡ አባታችንም በግፍ ታስረው ሳሉ በእስር ቤቱ ውስጥ ብርሃን ወረደላቸው፣ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልም ሰማያዊ መና እያመጣ ይመግባቸው ነበር፡፡ የጌታችንንም ሥና ደም በሰንበት እያመጣለቸው ያቆርባቸው ነበር፡፡ ነገረ ሠሪዎቹ ይገድሏቸው ዘንድ ንጉሡን ለመኑት፡፡ በዓመፃቸውም ብዛት ወደ ፍርድ ሸንጎ አምጥተው ገደሏቸው፡፡
🌹 አንድ ጻድቅ መነኩሴ የቅዱስ ዓምደ ሚካኤልን ሥጋ ሦስት ቅዱሳን መላእክት ሲያጥኑ አገኛቸውና ያየውን ለሕዝቡ ተናገረ፡፡ በሌላም ጊዜ የብርሃን ፋና ከሰማይ ሲወርድላቸው ብዙ ቀን የተመለከቱ ብዙ ቅዱሳን ምስክርነታቸውን ሰጡ፡፡ ንጉሡም ይህንን ሁሉ ሲሰማ በአሳቾቹ ልበ ደንዳናነትና ክፋት እጅግ ተጸጽቶ በሞት ቀጣቸው፡፡ ቅዱስ ዓምደ ሚካኤልንም በአባቶች መቃብር በክብር አስቀበራቸው፡፡ ስማቸውንም በበጎ እንጂ በክፋ ማንም እንዳያነሳቸው በአዋጅ አስነገረ፡፡ መታሰቢያም አቆመላቸው፡፡
🌹 ከዚህም በኋላ ዐፄ ልብነ ድንግል በነገሠ ጊዜ የአባቱን የበእደ ማርያምን ቃል ኪዳን ሰምቶ ዐፅማቸውን አፍልሶ ወደ አትሮንስ ማርያም ወሰደውና በቅዱሳን ነገሥታት መቃብር በክብር አኖረው፡፡ ሊቀ ብርሃናት መርቆሬዎስ አረጋም ጻድቁ ሲያርፉ በደብረ ሊባኖስ ገዳም የተቀበሩ ቢሆንም ከብዙ ዘመን በኋላ ዐፅማቸውን አፍልሰው በተድባበ ማርያም እንደቀበሯቸው ጽፈዋል፡፡ ከአቡነ ዓምደ ሚካኤል እግዚአብሔር አምላክረድኤት በረከትን ያሳትፈን፣ በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ።
✝ ✝ ✝ 🌹"#ሰላም_ለእርስከ_ዘተከለለ_ቆብዐ። አርአያ አክሊሉ ለክርስቶስ በዲበ መስቀል ሶበ ተመርዐ። #መድኃኒነ_እግዚእ አፋየ አመ ስመከ ጸውዐ። ነዓ ነዓ ምስለ ሳሙኤል ነዓ። ምስሌየ ትግበር ሰላም ወስንዓ። ሊቀ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የኅዳር 3።
🌹 "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌹
🌹 #ኅዳር ፫ (3) ቀን።
🌹 እንኳን #ለኢትዮጵያውያኑ_ጻድቃን አኲሱም አካባቢ የሚነኘውን #ታላቁ_ገዳም_ደብረ_በንኰልን ለመሰረቱት ሰባቱን ከከዋክብት የተባሉት እነ #አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባን_አስተምረው ላመነኰሱትና ውኃ ይቀዳላቸው የነበረውን አህያቸውን አንበሳ ቢበላባቸው በአህያው ምትክ #አንበሳውን_7ዓመት_ለገዳማቸው_ውኃ_ላስቀዱት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_መድኃኒነ_እግዚእ፣ ለጻድቁ የኢትዮጵያዊው ንጉሥ #ለቅዱስ_ነአኵቶ_ለአብ እንደነ #ሄኖክና_ኤልያስ_በሞት_ፈንታ_ለተሰወረው_ዕለት ለመታሰቢያ በዓሉና #ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ሚካኤል ሰማያዊ መና ሲመግባቸውና የጌታችንንም ቅዱስ ሥና ደም በሰንበት እያመጣለቸው ያቆርባቸው ለነበሩት ሰማዕቱ #አቡነ_ዓምደ_ሚካኤል ለዕረፍታቸው በዓል እግዚአብሔር አምላክ ሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
🌹 #ጻድቁ_ንጉሥ_ቅዱስ_ነአኵቶ_ለአብ፦ ከዐሥራ አንዱ ነገሥታተ ዛጕዬ መካከል በዐሥረኛ የሚገኝ ቅዱስ ስመ ጥሩ ንጉሥ ነው። አባቱ ንጉሥ ቅዱስ ገብረ ማርያም ሲሆን እናቱ ደግሞ ቅድስት መርኬዛ ትባላለች። ቅዱሱ ፍጥረት ነአኵቶ ለአብ ከነዚህ ቅዱሳን ሰዎች የተወለደው በብስራተ መልአክ ነው። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤ ወደ ቅዱስ ላሊበላ ወጥቶ ከወንድምህ የሚወለደው ልጅህ ቅዱስና ደግ ነው የአንተም ወራሽ እርሱ ነው አለው። ቅዱስ ላሊበላም ይህን ሰምቶ "ይትባረክ እግዚአብሔር አምላክ እስራኤል ወይትባረክ ስመ ስብሐቲሁ ቅዱስ" እያለ ጸልዮ ሲጨርስ ወደ ነአኵቶ ለአብ እናት "ሰላም ለኪ ወሰላመ እግዚአብሔር የሀሉ ምስሌኪ ኢትፍርሂ ወኢትህዝኒ በከመ ዐወፀ ማሕፀኖን ለሣራ ወለሐና ከማሁ ሀወፀ እግዚአብሔ ማህፀንኪ በፍሬ ሰናይ" ብሎ ላከ እርሷም ይህን ስትሰማ መካን ሆና ትኖር ነበርና በእውነት ፈጣሪ በማህፀኔ ፍሬ ሊያሳድርብኝ ይሆን እያለች ብትጠረጥር ቅዱስ ገብርኤል እራሱ ለቅዱስ ላሊበላ እንደነገረው መልእክተኛው አረጋግጦላት ሲሆድ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤ እንደ ገና ለእናቱ ተገልጦ ልጅ እንደምትወልድ አበሰራት።
🌹 በዚህም መሰረት ቅድስት መርኬዛ ቅዱስ ነአኵቶ ለአብን በብስራተ መልአክ ልክ ጌታችን በተወለደበት ዕለት ታኅሣሥ 29 ቀን ወለደችው። ቅዱስ ነአኵቶ ለአብ አባቱም እናቱም በህፃንነቱ ነበር የሞቱት በሆኑም ቅዱስ ላሊበላና ቅድስት መስቀል ክብራ በቤተ መግሥታቸው በጥበብና በሞገስ እንዲሁም በእንክብካቤ አሳደጉት ዕድሜው ለትምህርት ሲደርስ አባ ይስሐቅ የተባሉ መምህር ተቀጥረውለት ሲማር መንፈስ ቅዱስ ያደረበት በመሆኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ጨርሶ ተማረ። ከዚህም በኋላ ቅዱስ ላሊበላ ሞግዚትም ጓደኛ እንዲሆንና የቤተ መግሥት ሥርዓት እንዲያስተምረው ገብረ ክርስቶስ የሚባል አገልጋይ ሰጠው።
🌹 ነአኵቶ ለአብም በዚህ ሲኖር ዲቁና ተቀብሎ ፈጣሪው እያገለገለ በቅድስና ኖረ ሃያ ዓመት ሲሆነው በፍቃደ እግዚአብሔር ቅዱስ ላሊበላ በሱባኤ ጠይቆ የጥንት ስሟ አምባጌ የዛሬ እምባጽዮን በመባል ከምትታወቀው አካባቢ ቄስ እስጢፋኖስና አቅሌስያ ከሚባሉ ደናግ ሰዎች የምትወለደው ንጽሕት የምትባ ልጅ ለሚስትነት አጩለት፡፡ የሠርጉ ስርዓትና ቁርባን ከተፈጸመ በኋላ ሕገ መርዓዊ ወመርዓት ይፈጽሙ ዘንድ መጋረጃ ጥለውላቸው ሲወጡ "እህቴ ወይ እባክሽ ድንግልናችንን እንደነ ድሜጥሮስ እንጠብቅ ብሎ ለባለቤቱ ነገራት በዚሁም ተስማምተው እሰከ ሃያ አምስት ዓመት ድረስ በድንግልና ኖሩ ቅዱስ ነአኵቶ ለአብም በዘመኑ ሁሉ ከመላእክት ጋር ይነጋገር ነበር። በየቀኑም ብረትና ድንጋይ ተሸክሞ ሺህ ጊዜ ይሰግድ ነበር። በዚህም የቅድስና ተግባሩም የአባቶቹ በረከት አደረበት። በተለይም ቅዱስ ላሊበላ ላይ የነበረው ጸጋና ስጦታ በእርሱም ላይ አደረ። በዚህ መሠረት አባቱን ቅዱስ ላሊበላን አስፈቅዶ እርሱ ጀምሮት የነበረውን የእመቤታችንን ቤተ ክርስቲያንን እንደሰራ በገድሉ ተጽፏል። ያነጻትንም ቤተ ክርስቲያን ደብረ ጽዮን ብሎ ሰይሞ ህዳር 21 ቀን ታቦቷ ገባች።
🌹 ከዕለታት አንድ ቀን እቴጌይቱ ቅድስት መስቀል ክብራም በመንፈስ ቅዱስ ተመርታ ለቅዱስ ላሊበላ እንዲህ አለችው። "እንግዲህ የመግሥትህ ፍፃሜ እየደረሰ ነውና ለነአኵቶ ለአብ ትሰጠው ዘንድ ከወዲሁ አስተዳደር እንዲማር የአንድ አውራጃ ገዥ አድርገህ ሹመው አለችው። ቅዱስ ላሊበላም ነአከኵቶ ለአብን ጠርቶ መርቆ ሥርዓተ ንግሥና ፈጽሞ ሾመው ነአኵቶ ለአብ ግን አይገባኝም በማለት አብዝቶ ከተከራከረ በኋላ በሐዘንና በለቅሶ ተሾመ ቅዱስ ላሊበላ ባርኮ መርቆ ከሠራዊት ጋር ወደ ቆቅህና (ብሔረ ቆቅህና) ሰደደው።
🌹 ከዚህም በኋላ ቅዱስ ላሊበላ ሊያርፍ አቅራብያ ነአከኵቶ ለአብን እንደገና አስጠርቶ ይስሐቅ ያዕቆብን እንደመረቀው መንበረ ዙፋኑን አስቀምጦ በመሉ መንግስቱ በኢትዮጵያ ላይ አነገሠውና ከቅዱስ ላሊበላ ጥቂት ቀይቶ ሞተ፡፡ ነአኵቶ ለአብም እስከዚህ ድረስ እርሱም ሚስቱም በድንግልና ሲኖሩ ቅዱስ ሩፋኤል በራዕይ ተገልጦ ልጅ ተወልዳላችሁ ብሎ አበሰረው ነአከኵቶ ለአብም ድግልናው እንዳይሻርበት እያዘነ እያለቀሰ ሲጸልይ እመቤታችን ተገልጻ በራዕይ ድንግልናው እንደ ማይሻር ገልጣ አጽናናችው። ስለዚህ ለመጀርያ ጊዜ ሚስቱን ንጽሕትን አወቃት እርሷም ወንድ ልጅ ወለደች ስሙም በሀይለ መስቀል ተባለ ይህ ልጅም በደምግባቱና በውበቱ የሚመስለው የሌለ በጣም መልከ መልካም በመሆኑ ነአኵቶ ለአብ ይህ "ልጅ በመልኩ እየተመካ ኃጢያት ሰርቶ የሞት ሞት ከሚሞትብኝ እባክ ፈጣርዬ ዛሬውኑ ውሰድልኝና በአንተ ስም ኄሮድስ ከአስፈጃቸው ሕፃናት ጋር ጨምርልኝ" ሲል በማልቀስ ፈጣሪን ለመነው ጌታም ልመናውን ተቀብሎ የካቲት 16 ቀን በሞት ለይቶ ወሰደው በዚህም ጊዜ ነአከኵቶ ለአብ ደስ ብሎት ታላቅ ግብዣ አደረገ።
🌹 ከዚህም በኋላ ቅዱስ ነአከኵቶ ለአብ ከባለቤቱ ጋር ከአንድ ቀን በስተቀር ከዚያን በፊት ከዚም በኋላ ግኑኙነት አላደረጉም ምግብም ቢሆን ቀዳሚትና እሑድ እንዳይሻሩ የቤተ ማርያምን አፈርና ጥቂት የዘንጋዳ ቂጣ ይቀምስ ነበር እንጂ ዘወትር የሚዘጋጀውን የቤተ መንግሥት ምግብ አይመገብም ነበር።
🌹 ከዚምህ በኋላ ቅዱስ ነአኵቶ ለአብ በተጋድሎው እየጨመረ በመሄዱ 30ሰው የማይችለው ድንጋይ በአንገቱ ላይ በማሰር ክርስቶስ ለቤዛ ዓለም ብሎ የፈጸመውን ፀዋትኦ መከራ እያሰበ ላቡ ከምድር ወርዶ እስኪ ረጋ ድረስ ይሰግድ ነበር። አይሁድም እየተሳለቁበትና እየተዘባበቱበት የነበረውን መከራ በማስታወስ ዘወትር ያለቅስ ነበር። ቀን ከወርቅ ወንበር ሆኖ ሲታይ ህጋዊ ንጉሥ ይምሰል እንጂ በውስጡ ግን ማቅ ታጥቆ የከሸሎ እሾህ ከሰውነቱ በማስገባት ሲዋጋ ይኖር ነበር።
🌹 ቅዱስ ነአኵቶ ለአብ እንደ ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ የጌታን ሕማምና ሞት በማሰብ በፊቱ ሳቅ ቀርቶ ፈገግታ እንደማያውቅ ቅዱስ ገድል ያስረዳል። በዕለተ ዐርብ የችሎቱን ዙፋኑን አይዘረጋም ከ6 እስከ 9ሰዓት እጁን ዘርግቶ በ9 ሰዓት መራራ ነገር ይቀምስ ነበር። በሥግደትም ጊዜ በፊት በኋላ በቀኝ በግራ የሚዋጉ ጦሮችን በማድረግ የጌታ መወጋትን ያስታውስ ነበር።
ተወዳጆች
ተራራ የሚያፈልስ እምነት ቢኖረኝ
ፍቅር ከሌለኛ ከንቱ ነኝ
አየህ ከፀና ሐይማኖት ይልቅ ፍቅር ይበልጣል
ሐይማኖት ኑሮህ ፍቅር ከሌለህ
በሐይማኖቱ አትድንበትም
ፍቅር ከሰማዕትነትም ይበልጣል
ወእመኒ ወሀብኩ ኵሎ ሥጋየ ለዕውየተ እሳት
✅ ተመልከቱ
ሥጋየን እንኳ ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ
ፍቅር ከሌለኝ ምንም የምጠቀመው ነገር የለም
ወእመኒ ወሀብኩ ኵሎ ንዋይየ ለምፅዋት
ገንዘቤን ሁሉ ለምፅዋት ብሰጥ
ፍቅር ከሌለኝ ከንቱ ነኝ
ኮነኩ ከመ ከበሮ ዘይዘበጥ ወከመ ብርት ዘይነቁ
እንደሚንሿሿ ፅናፅል እንደሚመታ ከበሮ
ፍቅር የሌለው ሰው አንገቱ እንደ ቀለበት
እስኪ ቀጥን ድረስ ቢሰግድ እንኳ
ከለፋበት ስግደት የሚያተርፈው የለም
መሥዋዕት ቢያቀርብ
ቤተክርስቲያን በእንቁ በወርቅ ቢሰራ
✅ ለምን ወርቅ
አይኑን ግድግዳ አድርጎ
ለምን ቤተክርስቲያን አይሰራም
ለምን ገዳም አይሰራም
ለምን አብነት ትምህርት ቤት አይሰራም
ልጁን እንኳን ቢገብር
ለምን አንገቱን ቆርቶ አይሰጥም
ፍቅር የሌለው ሰው ሰማእት እንኳን ቢሆን አይፀድቅም
እግዚአብሔር አምላክ ፍቅርን ይስጠን
ቂም በቀል ክፋትን ያርቅልን
የበደሉንን ይቅር እንድንል ይርዳን🙏
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን
ተወዳጆች
እጃችን ላይ ያሉ ብዙ ነገሮች አሉ
እድል እግዚአብሔር ሰጥቶናል
አሁን ላይ የመማር ዕድል አለን
ጆሮ ሳይፈዝ አይን ሳይደነግዝ
የማንበብ ዕድል አለን ነገ አይን ይፈዛል
ሰዉ ሲያረጅ በመጨረሻ ምን እንደሚቀረው ታውቃላችሁ?
ሰዉ ሲያረጅ በመጨረሻ ምን ነው ሚቀረው
የሰራቸውን ተንኮሎች ማስታወስ
ድሮ በልጅነቱ የሰራቸው ተንኮሎች
እንደ መስታወት ሲያረጅ እየመጡ
ብቅ ብቅ ብቅ ብቅ ይላሉ በፊቱ ልክ እንዳውሬ
ሲያረጅ ይመጣበታል ሰዉ ደግሞ ማውራት አይፈልግም
ሰው ማውራት አይፈልግም ሽማግሌው ጋር
አፍላው አፍላው ጋር ነው ሚጫወት
ሰዉ ጋር ተጫወቶ እንዳይቀለው
ሰው ማን ሽማግሌ ጋር መጫወት ይወዳል
መጨረሻ ላይ ምንድን የሚቀረው የድሮ ተንኮሎቹ
እየመጡ መውጋት
በልጅነቱ ግን ቢያነብ ኖሮ እነማን ይመጣሉ
እነዚያ ታሪኮች የመጻፍ ቅዱስ ታሪኮች
እየመጡ ያፅናኑታል ከልቡ ይፈሱሉታል
ደስ ይሰኛል
ስለዚህ አሁን ስንቅ ሸምቁ
አይን እድል ነው የሚፈዝበት ጊዜ አለ
ማንበብ ማንችልበት ጊዜ አለ
መቅረዝህን ነው ካንተ አጠፋታለሁ እንዳለ
አይን እኮ ይፈዛል
መስማት ማንችልበት ጊዜ አለ
ነገ ጀሮአችሁ
ቃለ እግዚአብሔር መስማት እንዳይችል ይደነግዛል
መስገድ ሚቻለው አሁን ነው
ነገ ወገብ ይታሰራል
እጃችን ላይ ያሉ ችግሮች እንድንጠቀም ፈጣሪ ይርዳን🙏
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን
እመቤታችን በጣም በጣም ችግሮቻችንን ትመለከታለች
ድካም ትረዳለች እናታችን ናት
እመቤታችን ጥቃቅን የሰው ችግር አይሰወራትም
ሁሉን ማየት ትችላለች ለዚህ ነው እርግበየ መደምደሚያየ
ለሁሉም የምትበቃ እናት እመቤታቸን ናት
እኔ እናቴ ልታበላኝ ትችላለች ልታድነኝ ግን አትችልም
በነፍሴ ብታሰር ግን ልታስፈታኝ አትችልም
እመቤታችን ለሁሉም ምትብቃ ናት
ርዕሰ ሊቀውንት አባ ገብረ ኪዳን❤️
የአንዲት ጀግና እህታችን ተሞክሮ
ያው ስለ ወደድኩት አቀረብከት
ሱሪን ለመተው እነዚህን ነገሮች አደረገች
1, ንስኃ ገባሁ
2,ፀሎት ማድረግ ጀመርኩ
3,ከነበሩኝ ሱሪዎች ዉጭ አዲስ መግዛት አቆምኩ
4,ቀሚስ እና ጉርድ ገዛሁ
5,በፆም ወቅት እና የማርያም ቀን ሲሆን ሱሪ አለብስም ነበር
6,መንፈሳዊ ትምህርቶችን እና መዝሙር ማዳመጥ ጀመርኩ
7,ምዉልበትን ቦታ አስተካከልኩ
8,ቤተክርስቲያን ማዘዉተር ጀመርኩ
በመጨረሻም ፈጣሪ ያደረገላትን ነገር በመደነቅ
እግዚአብሔር ይመስገን 🙏 ብላ አመሰገናች
ለመተው ያሰባችሁ ፈጣሪ አምላክ ሀሳባችሁን ያሳካላችሁ