#ነገ_ታኅሣሥ 2️⃣ #የእመቤታችን_ወዳጅ_የቅዳሴ_ማርያም ደራሲ #የአባ_ሕርያቆስ_ወርሐዊ መታሰቢያው ነው።
#እንኳን___አደረሳችሁ ❤️🥰🙏
ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ይሰውረን።🙏❤
✝እንኳን አደረሰነ!
✞በዓለ ቅዱሳን፦
✿ኤልያስ ድንግል (ነቢየ ልዑል)
✿ናቡቴ ኢይዝራኤላዊ
✿ቤርሳቤህ ኅሪት (ብእሲተ ዳዊት)
✿ጴጥሮስ ዘጋዛ
✿ዮሐንስ ዘእስክንድርያ
✿አትናቴዎስ በርትርያርክ
✿ጴጥሮስ ወያዕቆብ ወኤልያስ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤
በረከቶሙ ይብጽሐነ፤ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡
💕ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 💕
ተወዳጆች ኾይ
በነፍሱ መከራ የሚቀበል የትኛው ነዉ።
የተሳደበ ሰዉ ወይስ የተሰደበ ሰዉ?
አወ የተሰደበ ሰዉ መሆኑ ግልጽ ነዉ።
✅ ምክንያቱም
አንድን ሰዉ ሐጢአተኛ የሚያሰኙት ከዉስጥ ከሰዉየዉ የሚመነጩ ክፋቶች እንጂ ከአፍአ የሚመጡ አይደሉምና
👉ከድርጊቱ ራሱ የታወቀ ነዉ
ስሜት መባሉም ለዚህ ነዉና።
👉ዳግመኛም በተሳዳቢው ላይ በሚፈጥሩት ነገር የታወቀ ነዉ።
ማለትም
ተሳዳቢው ሲቆጣ
👉አይነ ልቦናው ይታወራልና
👉አንጎሉም ይታወካልና
👉 የጤና መታወክ ሳይቀር ሌሎች ስፍር ቁጥር የሌለው ጉዳት ይደርስበታልና
ስለዚህ
መከራ እየተቀበለ ያለው ተሰዳቢው ሳይኾን ተሳዳቢዉ
መኾኑን በዚህ መረዳት ይቻለናል ።
💕የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ💕 አማላጅነት አይለየን
ህዳር 29/2017 #ፃድቁ_አባታችን_ዮሐንስ_ዘጠገሮ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ #እጨጌ_ዮሐንስ_ዘጠገሮ አመታዊ የልደት በአል ክብረ በአላቸውእንኳን አደረሰን
👉ህዳር ሃያ ዘጠኝ በዚህች ቀን #አቡነ_እጨጌ_ዮሐንስ ዘጠገሮ ልደታቸው ነው ፃድቁ አባታችን የተወለዱት በኢየሩሳሌም አውራጃ ልዩ ስሙ ሳሬራ በሚባል ቦታ ነው የካቲት 28 ቀን ተፀንሰው ህዳር 29 ተወለዱ
👉አባታቸው #ድላሶር እናታቸው #እምነ_ፅዮን ይባላሉ ሲወለዱ በወላጆቻቸው ቤት ውስጥ ብርሃን ወርዷል ወላጆቻቸውም #እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው አባታችን ገና በተወለዱ በ5 ዓመታቸው ወላጆቻቸው ወደ #እግዚአብሔር ቤት ይዘዋቸው የእመቤታችንን ሥዕል ተመልክተው በደስታ ተመልተው ሳቁ
👉አምላክን የወለደች የብርሃን እናቱ #እመቤታችንም ከምሥሉ ወጥታ በምን አውቀኸኝ ነው ብላ አቅፋ ሳመችውና ከእንግዲህ ወዲህ የልጄ አገልጋይ ትሆናለህ ኑሮህም እንደ #መላእክት ይሆናል በአንተ ምክንያት ብዙ ሰዎች ይድናሉ በምድር ላይም 500 አመት ትኖራለህ ብላ ባርካው ተሰወረች
👉ከዚያችም ቀን ጀምሮ አባ ዮሐንስ #ለክርስቶስ ተላልፎ ተሰጠ 50 ዓመትም በበረሃ ሲጋደል ኖሮ ከ50 ዓመት በኋላ በደመና ተጭኖ በመልአኩ #በቅዱስ_ገብርኤል መሪነት ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ መጣ
👉ፃድቁ አባታችን በአቡነ #ተክለሃይማኖት ዘመን መጨረሻ የመጡ ሲሆን ምንኩስና ከደብረ ሊባኖስ ገዳም ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ተቀብለው በዚያው በደብረ ሊባኖስ ገዳም ለ50 ዓመት በፆምና በጸሎት በተጋድሎ ኖረዋል
👉ከዚኽም በኋላ #አባ_ዮሐንስ ወደ ተዘጋቸላቸው ምድር #በቅዱስ_ገብርኤል አሳሳቢነት ወደ ጠገሮ መጡ ይኽም ጠገሮ ያለው ገዳማቸው በሰሜን ሸዋ በመንዝና ይፋት ክልል መዘዞ በሚባል ቦታ ሲደርሱ በእግር አንድ ሰዓት ከተጓዙ በኋላ ይገኛል
👉ሕዝቡ በተለምዶ #እጨጌ_ዮሐንስ እያለ ይጠራቸዋል አቡነ #እጨጌ_ዮሐንስ መስቀል ከሰማይ የወረደላቸው ታላቅ አባት ናቸው መስቀሉም ሁልጊዜ ተአምር ይሠራል
👉በልደታቸው ቀን ህዳር 29 ቀን #መስቀሉ ከመቅደሱ ወጥቶ በካህናቱ ታጅቦ ወደ ፀበሉ ሲወርድ ከየት እንደመጣ ሳይታሰብ ደመና መጥቶ #ከመስቀሉ ላይ ብቻ እረቦና እንደ ጃንጥላ ተዘርግቶ አብሮ ወደ ፀበሉ ይወርዳል
👉እዛው ቆይቶ #መስቀሉ ሲመለስም አብሮ አጅቦ ይመለስና መስቀሉ ቤተ መቅደስ ውስጥ ሲገባ ደመናው ወዴት እንደተበተነ ሳይታወቅ ይጠፋል ይህ በዘመናችንም ጭምር እየታየ ያለ ታላቅ ተአምር ነው
👉የፃድቁ አባታችን ታሪክ ከብዙ በጥቂቱ ይህን ይመስላል
👉የአባታችን የፃድቁ #እጨጌ_ዮሐንስ ፀሎትና ልመና ሀገራችንን ህዝባችንን ከክፉ መከራ ይጠብቅልን የከበረዉ ቃል ኪዳናቸዉ አይለየን የተባረከ የተቀደሠ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ተወዳጆች
ቆይ እግዚአብሔር እንዳንሳሳት አድርጎ ቢፈጠረን አይችልም ነበር ? ብሎ የሚጠይቅ ይኖራል ።
የዚህ ጥያቄ ችግር ልንገራችሁ
አንደኛ
የሚያሳሳት እግዚአብሔር ብቻ ነው
ማንሳሳት ተደርገን ከፈጠርን
ከ እግዚአብሔርጋር እኩል ሆን ማለት ነው
ስህተት የማይስማማው እግዚአብሔር ነው
ከተፍጥሮ በላይ የሆነ ፍጹም ባህሪ
Absalute being የሚባለው እግዚአብሔር ነው
ፍጹም ነውር የሌለበት
እፍ የሚባል የሌለው እግዚአብሔር ነው
ይሄ ቀረህ የማይባል
እግዚአብሔር ኃጢአት ጨምሮ አልፈጠረነም
ኃጢአት እንዲስማማን
በኃጢአት እንድንወድቅ አድርጎ አልፈጠረንም
ልንወድቅም እንድንችል አድርጎ ነው የፈጠረን
እንደዚያ አለመሆን ለፍጡር አይቻለውም
ሁለተኛ
እንደዚህ ብሎ መጠየቅ
ከእግዚአብሔር ባህሪ ጋር መተካከል ነው
Unfair Quation ነው ወይም ፍርደ ገምድልነት ነው
ፍርደ ገምድልነት ማለት ምን ማለት ነው
እግዚአብሔር 3ት ነገሮችን ሰጦናል
ምርጫ
ችሎታ
ዕውቀት
እነዚህን ባይሰጠን ኑሮ
እግዚአብሔርን መጠየቅ እንችል ነበር ።
እሱ ነው እንዲ ያደረገኝ እንዲ አርጎ ፈጥሮኝ እያልን
፩ ምርጫ
እስካለ ድረስ በእግዚአብሔር ማመካኘት አንችልም
መጽሐፍ ቅዱስ ባንማር እንኳ
ክፉ ነገር እንዲሰቀን ተደርገን ተፈጥረናል
፪ ዕውቀት
ወንጀልና ፍትህ የኖረው ለምን ነው ?
ህሊናችን እንዲፈርድ እንዲያውቅ እግዚአብሔር ፈጥሮናል
፫ ችሎታ ወይም ክሂል
ለምሳሌ :- ፆም አልቻለን ስላለ ነው እንላለን
ምኑ ነው ማይቻለን ? ሸክም ነው ፆም ?
ወደን ነው ምንበላው ወደን ስለምንበላ
ስሜታችንን ስለምንከተል እንጂ ስለማንችል አይደለም
ለምን ነው ዘፈን ማትተወው ? ስለማልችል
ለምን ነው ማትችለው ? ስለማት ፈልግ ነው እንጂ ስለማትችል አይደለም ።
ለምን ነው ሱሪ ሴቶች ሱሪ ትታችሁ ቀሚስ ማትለብሱ ?
ስለማልችል ? ስለማትፈልጉ ነው እንጂ ስለማትችል አይደለም ።
ስለማትወስን ስለማትወስኑ ምቾትን መልቀቅ ስለማትፈልግ
ስለማትፈልጉ ነው ። እንጂ ስለማትችል አይደለም
ችሎታ እግዚአብሔር ሰጦናል
ምክንያቱም እንደዚያ መሆንም ችለናልና ።
መራራ ውን ነገር ለምደነዋል
ቀንተን ፈልገን ነው የለመድነው
መራራውን ነገር ከለመድነው
ያ መልመድ ከቻልን ስለመድነው
እንደዚያ ባህሪ አልነበረብንም
ለጌጥ ብለን ለጓደኝነት ብለን ለምደነዋል
ጣፋጩንስ ለእግዚአብሔር ብለን መቼ እንልመደው ?
ፈጣሪ ከክፉ ሀሳብ ይጠብቀን🙏
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❣️
ተወዳጆች
በሽታና ህመም ሲያጋጥመን
ሁሉም ለበጎ ነው ማለት አለብን
ምክንያቱም በህመም ወቅት
የሰው ነፍስ ንጹህ ትሆናለች
ሰውም ወደ እግዚአብሔር ይቀርባል።
ባብዛኛው በበሽታ ምክንያት ወደ ንስኃ የሚመለሱ ሰዎች
በ 1000 ስብከት ከተመለሱ ይሻላሉ
በሸታ
በሁሉም ሰዉ ዘንድ ከጓደኞችና ከሌሎች ሰዎች ጋር
ማህበራዊ የሀዘን መካፈል ስሜትን ይፈጥራል።
ይህም ማኅበራዊ በጎ ምግባር ነው።
መድኃኒት ከሌላቸው በሽታዎች እንኳን በጎ ነገር አለ
ከአባቶች አንዱ❣️
ህዳር 27/2017 #የአለም_መድኃኒት_መድኃኔዓለም
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ አምላክ አሜን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን #መድኃኔአለም ኢየሱስ ክርስቶስ አለምን ለማዳን ዋጋ ለከፈለበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉 #መድኃኔዓለም ማለት ዓለምን ያዳነ የዓለም መድኃኒት ማለት ነው ሰው በመበደሉ ምክንያት ከክብር ተዋርዶ ይኖር ነበር #ኢየሱስ_ክርስቶስ ግን የተዋረደውን ሰው እርሱ በመስቀል ተሰቅሎ ወደ ቀደመ ክብሩ መለሰው ምን ዓይነት ፍቅር ነው ስለኛ የሰዉ ልጆች ሲል በመስቀል ላይ ዋለ
👉ራቁትን መሰቀል አሳፋሪ ነገር እንደሆነ እናውቀዋለን ጌታ ግን እኛን ለማዳን ብሎ #ራቁቱን_ተሰቀለ በፈጠራቸው ፍጥረታት ተናቀ ተተፋበት
👉እኛን ትእግስት ሊያስተምረን እነርሱን ማጥፋት እየቻለ እርሱ ግን በፍቅር እያየ የሚያረጉትን አያውቁምና አባት ሆይ ይቅር በላቸው ይል ነበር #ክርስቶስ እኛን ልጆቹን ለማዳን ሲሰድቡት አልተሳደበም ሲንቁት አልናቃቸውም ሲታበዩበት ሁሉ እርሱ ግን በትሕትና ያያቸው ነበር
👉አይሁድ በ5 ችንካር ነበር የቸነከሩት ጌታችን ሲሰቀል በመሰቀሉ የተገኙት እናታችን #ማርያምና ሐዋርያው አባታችን #ቅዱስ_ዮሐንስ ነበሩ አኛም #በመስቀሉ ስር ለመገኘት ትዕግስትን ፍቅርን ትሕትናን መለማመድ ይኖርብናል
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በፈቃድህ በተሰቀልክ ጊዜ በቀኝህ ለተሰቀለዉ ወንበዴ የገነት መክፈቻን እንደሰጠኸዉ ወደ ገነትም እንዳስገባከዉ በኃጢአት የወደቅን ልጆችህን ነፍስና ስጋችንን አክብረህ ብርሀነ ፀጋህን አብራልን
👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የሚታሠቡት ፃድቁ አቡነ #መብአ_ፅዮን በምልጃ ፀሎታቸዉ ሁላችንንም ይጠብቁን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ተወዳጆች ሆይ
✅ ስድብን በሚመለከት
በፍትሐ ብሔር ሕጋችን ልቡና ግምት ውስጥ የማይገባ ሲኾን
በወንጀል ሕጋችን ደግሞ የተሰዳቢው ልቡና/ ሐሳብ ወሳኝ ነው፡፡
✅ ስድብን መናቅ ማለት
ለምሳሌ አንድ ሰው “አንተ አህያ” ቢለን
“እኔ'ማ አህያ ለመባል አልበቃም።
ምክንያቱም አህያ ታዛዥ ነው፡፡
ባለቤቱን ያገለግላል፡፡
እኔ ግን አምላኬን አልታዘዝም፧ አላገለግልምም"
ብለን ከመለስንለት ስድብ መኾኑ ይቀራል፡፡
✅ “አንተ ውሻ ቢለንም “
እኔ'ማ ውሻን አላክልም፡፡
ውሻ ለጌታው ታማኝ ነውና፡፡
ቢደበድቡትም ቂም ይዞ አያማርርምና'' ካልን
ስድብ ስድብ መኾኑ ይቀራል፡፡
ሌሎች ነገሮችንም እንደዚህ በጥበብ ከያዝናቸው
ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳለን አይጎዱንም፡፡
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በረከት አማላጅነት አይለየን🙏
ህዳር 26/2017 #ፃድቁ_ሐብተ_ማርያም
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ለምናመሰግንበት ለፃድቁ አባታችን #አቡነ_ሐብተ_ማርያም አመታዊ የእረፍት በአል መታሠቢያ እንኳን አደረሰን
👉ኢትዮጲያዊዉ ፃድቅ ትዉልዳቸዉ ሸዋ መንዝ ልዩ ስሙ ራዊ ውስጥ ሲሆን አባታቸው #ፍሬ_ቡሩክ እናታቸው ደግሞ ቅድስት #ዮስቴና ትባላለች በተለይ ቅድስት ዮስቴና እጅግ ደመ ግቡ ምጽዋትን ወዳጅ ቡርክት ሴት ነበረች እንዲያውም ከጻድቁ መወለድ በፊት መንና ጭው ካለ በርሃ ገብታ ነበር
👉ግን የበቃ ግኁስ አግኝቷት ከማሕጸንሽ ደግ #የሥላሴ ባርያ አለና ተመለሽ ብሏት እንደ ገና ተመልሳለች ፃድቁን ወልዳ አሳድጋም እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ 7 #አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች
👉ወደ ፃድቁ ዜና ሕይወት ስንመለስ #አቡነ_ሃብተ_ማርያም ገና ሕጻን እያሉ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ሲባል ይሰማሉ ይሕችን ጸሎት በሕጻን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ "ማረን እባክህን" እያሉ ይሰግዱ ነበር
👉የ5 ዓመት ሕጻን እንዲህ ሲያደርግ ማየቱ በእውነት ይደንቃል ትንሽ ከፍ ብለው #በእረኝነት ሳሉም ፍፁም ተሐራሚና ፀዋሚ ነበሩ ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል የፈጣሪውን ስም ያቃለለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል
👉ፃድቁ አባታችን በዝመታኘንትና በአርምሞ ኑሯቸዉ የታወቁ ናቸዉ በመልአክ መሪነት #አክሱም_ኢየሩሣሌም_ምድረ_ግብፅ በእግራቸዉ በመሔድ ተሣልመዋል
👉ለፃድቁ አባታችን ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ቃል ኪዳን ሰጥቶዋቸዋል ወረርሽኝ በሽታና የአባላዘር በሽታ የያዘዉን ሰዉ ፀበልህን ቢጠመቅ ቢጠጣ በፍጥነት ይድናል ለ15 አይነት መቅሰፍቶች እንዲያድን ቃል ኪዳን ተሰጥቶዋቸዋል
👉ፃድቁ አባታችን #ማእጠንት ሲያጥኑ መንበረ ፀባኦት ይታያቸዉ ነበር ፃድቁ በዚህ እለት የእረፍት በአላቸዉ ሲሆን ራሳቸዉ በገደሙት ገዳም ተቀብረዋል
👉የፃድቁ ምልጃና ፀሎት ሀገራችንን #ህዝባችንን ይጠብቅልን ቃል ኪዳናቸዉም አይለየን "አሜን"
👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የሚዉሉ ቅዱሣን ረድኤትና በረከት የከበረዉ #ቃል_ኪዳናቸዉ ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
ፍጹም ከእውነት የራቀ ውሸት ነው ከፈለጋችሁ ሙሉውን ከስር Show የሚለውን በመንካት ማረጋገጥ ትችላላችሁ
ሙሉ ታሪኩን ለማየት show የሚለውን ንኩት👇
SHOW
ህዳር 24/2017 #ሀያ_አራቱ_ካህናተ_ሰማይ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ኅዳር ሃያ አራት #በእግዚአብሔር ዙፋን ዙሪያ የሚኖሩ የሃያ አራቱ #ካህናተ_ሰማይ አመታዊ የበዓላቸው መታሰቢያ ነው
👉እሊህም ሥጋ የሌላቸው ረቂቃን የእውነት #ካህናት የሆኑ ከቅዱሳን ሁሉ በላይ የሆኑና ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ ከፍ ከፍ ያሉ ናቸው እነርሱም #ለእግዚአብሔር ቀራቢዎች በመሆን ለሰው ወገን የሚማልዱ ከእጃቸው ውስጥ ካለ ማዕጠንት ጋር እንደ ዕጣን የቅዱሳንን ፀሎት የሚያቀርቡ ናቸው ያለ እነርሱም አቅራቢነት ፅድቅና ምፅዋት ወደ #እግዚአብሔር አይቀርብም
👉ወንጌላዊ #ቅዱስ_ዮሐንስ በራእዩ እንዲህ ብሎ እንደተናገረ በዙፋኑ ዙሪያ ሃያ አራት መንበሮች አሉ በእነዚያ መንበሮች ላይም #ሃያ_አራት_አለቆች ተቀምጠዋል ነጭ ልብስ ለብሰዋል በራሳቸውም ላይ የወርቅ አክሊል አለ።
👉ሁለተኛም እንዲህ አለ ሌላም መልአክ መጥቶ በመሠዊያው ፊት ቆሞ የወርቅ ፅንሐሕ ይዟል በመንበሩ ፊት ባለ በወርቁ መሠዊያ ላይም የቅዱሳንን ሁሉ ፀሎት ያሳርግ ዘንድ ብዙ ዕጣንን ሰጡት የዕጣኑም ጢስ #ከቅዱሳኑ ፀሎት ጋር በዚያ መልአክ እጅ ወደ #እግዚአብሔር ፊት ዐረገ ።
👉የነበረ የሚኖር የአማልክት አምላክ #እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ነው እያሉ በመዓልትና በሌሊት ዕረፍት የላቸውም እሊህም እንስሶቹ ለዘላለሙ ሕያው ለሚሆን በዙፋን ላይ ለተቀመጠ ለሱ እንዲህ እያሉ ክብር ምስጋና አቀረቡ
👉እሊህ ሃያ አራቱ አለቆች አክሊላቸውን በዙፋኑ ፊት አውርደው ለዘላለሙ ሕያው ለሚሆኑ በዙፋን ላይ ለተቀመጠ ለእሱ ሰገዱለት አክሊላቸውንም ወደ ዙፋኑ ፊት ወስደው አቤቱ ፈጣሪያችን #ኃይልና_ምስጋና_ክብር ላንተ ይገባል ይሉታል አንተ ሁሉን ፈጥረሃል የተፈጠረውም ሁሉ በአንተ ፈቃድ ይኖራልና
👉እነርሱ #በእግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት እጅግ የቀረቡ መሆናቸውንና ስለሁላችን የአዳም ልጆች ስለሚለምኑና #ስለሚማልዱ ከብሉይና ከሐዲስ የከበሩ መጻሕፍት ምስክር ሁነዋል ስለዚህም የበዓላቸውን መታሰቢያ እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ
👉በጌታ ዙፋን ፊት ለምስጋና የሚተጉ #24ቱ_ሽማግሌዎች #ካህናተ_ሰማይ የከበረዉ ቃል ኪዳናቸዉ ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን"
👉ጊዜዉ ያላችሁ በአሉን ለማክበር የምትፈልጉ የተዋህዶ ልጆች በእንጦጦ ደብረ ኃይል #ቅዱስ_ራጉኤል ወ #ቅዱስ_ኤልያስ ቤተክርስቲያን #የ24ቱ_ካህናተ_ሰማይ የንግስ በአል በታላቅ ድምቀት ይከበራል በቦታዉ ተገኝታችሁ የበረከቱ ተሣታፊ ሁኑ
👉 #24ቱ_ካህናተ_ሰማይ ስማቸዉ እነማን ይባላሉ
1 አካኤል 2 ፋኑኤል 3 ጋኑኤል 4 ታድኤል 5 አፍድኤል
6 ዘራኤል 7 ኤልኤል 8 ተዳኤል 9 ዮካኤል 10 ገርድኤል
11 ልፍድኤል 12 መርዋኤል 13 ኑራኤል 14 ክስልቱኤል
15 ኡራኤል 16 ባቱኤል 17 ሩአኤል 18 ሰላትኤል
19 ጣርኤል 20 እምኑኤል 21ፔላልኤል 22 ታልዲኤል
23 ፐሰልዲኤል 24 አሌቲኤል
እመብርሃን ሆይደስ ብሰኝ ባንቺ ደስ እሰኛለሁ፡፡ ባዝንም ባናንቺ እጽናናለሁ፡፡ መከራና ችግርም ቢያገኘኝ ወዳንቺ እጮሃለሁ፡፡ያመፀኛም ምላስ ቢያስከፋኝ ወዳንቺ ፊት እማለላለሁ፡፡
ሰወነቴም የወደደችው ነገር ቢኖር አንቺን እለምናለሁ፡፡ በመታመን የሻትሁትንና የተመኘሁትንም ባንቺ አገኛለሁ ።
መታመን ያድናል ሃይማኖትም ያስቀናል መታመን ያነጻል፡፡ ሃይማኖትም ያራቅቃል መታመን ተስፋ ያደርጋል ሃይማኖትም ይሰጣል፡፡ መታመን ይጀምራል ሃይማኖት ይፈጽማል፡፡
የ ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን🙏
ተወዳጆች
አለም ሁሉ ተደምሮ
የአንዷን የፀጉሯን ዘላላ ያህል ክብር የለውም
የአንዷን የፀጉሯን ዘላላ
አሁን ስለ እመቤታችን ስለምኗ ትናገራላችሁ ?
ሰው ስለምኗ ይናገራል ?
ስለ እናትነቷ ቢናገር ድንግል ትሆንበታለች
ስለ ድንግልናዋ ቢናገር እናት ትሆንበታለች
እናትነቷን ብቻ ልናገር ቢል አይሆንለትም
አምላክን መውለድ እንደምን ያለ ነገር ነው
ይሄ እስከዛሬ ድረስ አይገባንም
ከገባንማ ነገሩም ቀላል ነው ማለት ነው ።
ታህሳስ 1/2017 #ነብዩ_ቅዱስ_ኤልያስ
ኤልያስ እንደኛ የሆነ ሰው ነበረ ዝናብም እንዳይዘንብ
አጥብቆ ፀለየ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር
አልዘነበም ሁለተኛም ፀለየ ሰማዩም ዝናብን ሰጠ
ምድሪቱም ፍሬዋን አበቀለች ያዕ.5÷17-18
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን በዚህችም በታኅሣሥ አንድ ቀን በእስራኤል ፊት ነቢይ #ኤልያስ የተገለጠበት ነው ይህ ቀናኢ ኤልያስ ከሌዊ ወገን የሆነ የአባቱ ስም #ኢያስኑዩ የእናቱም ስሟ #ቶና ነው ለአመታዊ ክብረ በዐሉ እንኳን አደረሰን
👉ስለርሱም እንዲህ ተነገረ #በተወለደ ጊዜ ብርሃንን የለበሱ አራት ሰዎች ሲሰግዱለትና ሕፃናት በሚጠቀለሉበት ጨርቅ ፈንታ #በእሳት ሲጠቀልሉት አባቱ አየ
👉እርሱም ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ይህን ለካህናቱ ነገራቸው እነርሱም ማደሪያው በብርሃን ውስጥ ይሆን በቃሉም የሚቆርጥ ይሆን ወይም #እስራኤልን_በሰይፍና_በእሳት እየቀጣ ይገዛቸው ይሆን ተባባሉ
👉በእስራኤል ንጉሥ በአክዓብና በሚስቱ በኤልዛቤል በልጁም በአካዝያስም ዘመን ያደረገው የተአምራቱ ዜና በመጽሐፈ #ነገሥት ተፅፎአል ወደ ሰማይ ያረገበት ዜናው ግን በጥር ወር በስድስት ቀን ተፅፎአል
👉በኋላ ጊዜም ስለሚሆነው ሞቱ ራእይን በሕይወቱ ያየ #ዮሐንስ_ከኄኖክ ጋር እንደሚመጣና ሐሳዊ መሲሕን እንደሚቃወሙት ተአምራትንም እንደሚያደርጉ ተናግሮአል ሁለቱ የዘይት ዕንጨቶች በምድር ላይም የተሾሙ #በእግዚአብሔር ፊት የሚያበሩ ሁለት መብራቶች ናቸው አለ
👉ከጠላቶቻቸውም ወገን ሊጣላቸው የወደደውን እሳት ከአፋቸው ወጥታ ታጠፋቸዋለች የሚጠሏቸው እንዲህ ይጠፋሉ #ትንቢት በሚናገሩበት ወራት በምድር ላይ ዝናም እንዳይዘንም ይዘጓት ዘንድ #በሰማይ_ላይ_ሥልጣን አላቸውና ዳግመኛም ደምን ያደርጉት ዘንድ በውኃው ላይ ሥልጣን አላቸው የፈለጉትን ያህል በመቅሠፍቱ ሁሉ ምድርን ያስጨንቋታል
👉ምስክርነታቸውንና #ትንቢታቸውን ከፈፀሙ በኋላ ከባህር የወጣው አውሬ ከእሳቸው ጋር ይጣላል ድል ነስቶም ይገድላቸዋል አስከሬናቸውንም ፍጥሞ በምትባል በታላቂቱ አገር ያስጥለዋል
👉አስከሬናቸውንም ሕዝብና አሕዛብ በሀገርም ያሉ ነገዶች ሦስት ቀን ተኩል ያዩታል አስከሬናቸውንም በመቃብር ይቀብሩት ዘንድ አያሰናብቱም በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች በእነርሱ ሞት ደስ ይላቸዋል እርስ በርሳቸውም በደስታ እጅ መንሻ ይሰጣጣሉ እሊህ #ሁለቱ_ታላላቅ_የጌታ_ነቢያት በምድር በሚኖሩ ሰዎች መከራ አፅንተውባቸዋልና ይላሉ
👉ከሦስት ቀን ተኩል በኋላ #ከእግዚአብሔር ዘንድ የሕይወት መንፈስ መጥታ ታድርባቸዋለች ተነሥተውም በእግራቸው ይቆማሉ በሚያዩዋቸው ላይም ፅኑ ፍርሀት ይሆናል
👉ከወደ ሰማይ ቃል መጥቶ ወደዚህ ውጡ ይላቸዋል ከዚህ በኋላ ጠላቶቻቸው እያዩአቸው #በደመና_ያርጋሉ በዚያችም ሰዓት ፅኑ መነዋወጥ ይሆናል የዚያችም አገር ዐሥረኛ እጅዋ ይጠፋል በዚያም መነዋወጥ ሰባት ሺህ ሰዎች ይሞታሉ የቀሩት ግን ደንግጠው #የሰማይ_አምላክን ፈፅመው ያመሰግናሉ
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከታላቁ ነብይ #ነብዩ_ቅዱስ_ኤልያስ ከልደቱ ረድኤት በረከት ያሣትፈን ፀሎቱ ይጠብቀን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
👉ሰለሞን የገብርኤል
👉ታህሳስ 1/2017
ተወዳጆች
የድንግል ማርያም እራስ ግን እግዚአብሔር ነው
ህሊናዋ ውስጥ ከእግዚአብሔር ውጭ አስባ አታውቅም
ስለዚህ ምን ትባላለች ? የእግዚአብሔር ከተማ ትባላለች
ተወዳጆቹ
እኔ ተስፋዬ ጤና አይደለም
እኔ ተስፋዬ ሀብት አይደለም
እኔ ተስፋዬ የሰው መውደድ አይደለም
እኔ ተስፋዬ ክርስቶስ ነው ።
ክርስቶስን እስካለኝ ድረስ የፀሎቴ ምላሸ
ከጌታየ ጋር እኖራለሁ አለበት
እንጂ ልክ እንደ ኤሳው ሰይጣን ሁልጊዜ ስትተኙ
ውዳሴ ማርያም ስትደግሙ ዳዊት ስትደግሙ
ንስኃ ስትገቡ ንስኃ ገባህ አልገባህ ምን አምጥተሀል ቢላችሁ
ለሰይጣን ይሄን መልሱለት ።
እግዚአብሔር አይለወጥም
እግዚአብሔር በቃኝ አይባልም
እግዚአብሔር አይሰለችም
እግዚአብሔር ሁልጊዜ ደስታ ነው።
የዚህ ዓለም ደስታ ሀዘን ተክቶ ነው የሚሄደው
እግዚአብሔር ግን ሀዘን ተክቶ የማያልፍ ዘላለማዊ ደስታ ነው።
የድንግል ማርያም እራስ ግን እግዚአብሔር ነው
ህሊናዋ ውስጥ ከእግዚአብሔር ውጭ አስባ አታውቅም
ስለዚህ ምን ትባላለች የእግዚአብሔር ከተማ ትባላለች
ርዕሰ ሊቃውንት ቆሞስ አባ ገብረ ኪዳን❣️
ህዳር 29/2017 #ፃድቁ_አባታችን_ዮሐንስ_ዘጠገሮ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ #እጨጌ_ዮሐንስ_ዘጠገሮ አመታዊ የልደት በአል ክብረ በአላቸውእንኳን አደረሰን
👉ህዳር ሃያ ዘጠኝ በዚህች ቀን #አቡነ_እጨጌ_ዮሐንስ ዘጠገሮ ልደታቸው ነው ፃድቁ አባታችን የተወለዱት በኢየሩሳሌም አውራጃ ልዩ ስሙ ሳሬራ በሚባል ቦታ ነው የካቲት 28 ቀን ተፀንሰው ህዳር 29 ተወለዱ
👉አባታቸው #ድላሶር እናታቸው #እምነ_ፅዮን ይባላሉ ሲወለዱ በወላጆቻቸው ቤት ውስጥ ብርሃን ወርዷል ወላጆቻቸውም #እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው አባታችን ገና በተወለዱ በ5 ዓመታቸው ወላጆቻቸው ወደ #እግዚአብሔር ቤት ይዘዋቸው የእመቤታችንን ሥዕል ተመልክተው በደስታ ተመልተው ሳቁ
👉አምላክን የወለደች የብርሃን እናቱ #እመቤታችንም ከምሥሉ ወጥታ በምን አውቀኸኝ ነው ብላ አቅፋ ሳመችውና ከእንግዲህ ወዲህ የልጄ አገልጋይ ትሆናለህ ኑሮህም እንደ #መላእክት ይሆናል በአንተ ምክንያት ብዙ ሰዎች ይድናሉ በምድር ላይም 500 አመት ትኖራለህ ብላ ባርካው ተሰወረች
👉ከዚያችም ቀን ጀምሮ አባ ዮሐንስ #ለክርስቶስ ተላልፎ ተሰጠ 50 ዓመትም በበረሃ ሲጋደል ኖሮ ከ50 ዓመት በኋላ በደመና ተጭኖ በመልአኩ #በቅዱስ_ገብርኤል መሪነት ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ መጣ
👉ፃድቁ አባታችን በአቡነ #ተክለሃይማኖት ዘመን መጨረሻ የመጡ ሲሆን ምንኩስና ከደብረ ሊባኖስ ገዳም ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ተቀብለው በዚያው በደብረ ሊባኖስ ገዳም ለ50 ዓመት በፆምና በጸሎት በተጋድሎ ኖረዋል
👉ከዚኽም በኋላ #አባ_ዮሐንስ ወደ ተዘጋቸላቸው ምድር #በቅዱስ_ገብርኤል አሳሳቢነት ወደ ጠገሮ መጡ ይኽም ጠገሮ ያለው ገዳማቸው በሰሜን ሸዋ በመንዝና ይፋት ክልል መዘዞ በሚባል ቦታ ሲደርሱ በእግር አንድ ሰዓት ከተጓዙ በኋላ ይገኛል
👉ሕዝቡ በተለምዶ #እጨጌ_ዮሐንስ እያለ ይጠራቸዋል አቡነ #እጨጌ_ዮሐንስ መስቀል ከሰማይ የወረደላቸው ታላቅ አባት ናቸው መስቀሉም ሁልጊዜ ተአምር ይሠራል
👉በልደታቸው ቀን ህዳር 29 ቀን #መስቀሉ ከመቅደሱ ወጥቶ በካህናቱ ታጅቦ ወደ ፀበሉ ሲወርድ ከየት እንደመጣ ሳይታሰብ ደመና መጥቶ #ከመስቀሉ ላይ ብቻ እረቦና እንደ ጃንጥላ ተዘርግቶ አብሮ ወደ ፀበሉ ይወርዳል
👉እዛው ቆይቶ #መስቀሉ ሲመለስም አብሮ አጅቦ ይመለስና መስቀሉ ቤተ መቅደስ ውስጥ ሲገባ ደመናው ወዴት እንደተበተነ ሳይታወቅ ይጠፋል ይህ በዘመናችንም ጭምር እየታየ ያለ ታላቅ ተአምር ነው
👉የፃድቁ አባታችን ታሪክ ከብዙ በጥቂቱ ይህን ይመስላል
👉የአባታችን የፃድቁ #እጨጌ_ዮሐንስ ፀሎትና ልመና ሀገራችንን ህዝባችንን ከክፉ መከራ ይጠብቅልን የከበረዉ ቃል ኪዳናቸዉ አይለየን የተባረከ የተቀደሠ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ኅዳር ፳፰ (28) ቀን።
❤ እንኳን #ከዘጠኙ_ቅዱሳን ለአንዱ ለሆኑት በጸሎት ጊዜ የእጆቻቸው ጣቶች እንደ መብራት ያበራ ለነበሩት በአክሱም ከተማ አካባቢ የሚገኘውን ደብረ ቊንጽል ገዳም ለመሰረቱት #ለአባ_ሊቃኖስ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_ሊቃኖስ፦ ቊጥራቸው ከዘጠኙ ቅዱሳን ሲኾን የመጡት ከቊስጥንጥንያ (ሮም) አገር ሲኾን በአክሱም ከተማ አካባቢ ደብረ ቊናጽል የሚል ገዳምን ገድመዋል፤ በዓለ ዕረፍታቸውም ኅዳር 28 ቀን ነው፤ በጸሎት እጃቸውን በዘረጉ ጊዜ ዐሥሩ ጣቶቻቸው እንደ መብራት ይበራ እንደነበር ዜና ገድላቸው ያስረዳል። ምንጭ፦ ተአምኆ ቅዱሳን ንባቡና ትርጓሜው።
ፍጹም ከእውነት የራቀ ውሸት ነው ከፈለጋችሁ ሙሉውን ከስር Show የሚለውን በመንካት ማረጋገጥ ትችላላችሁ
ሙሉ ታሪኩን ለማየት show የሚለውን ንኩት👇
SHOW
ሲሳየነ ዘለለእለትነ
የ ዕለት እንጀራችንን ስጠን ዛሬ እንላለን
የ ዕለት እንጀራ በ 7ት በ 8ት በአንደምታ ይፈታል
✅ አንዱ ትርጉሙ
በየቀኑ ፍትህ አታሳጣን ማለት ነው
እግዚአብሔር የሰጠን ይሄን ነው።
ስለዚህ እግዚአብሔር የሚመሰገነው ምስጋና
ቤተክርስቲያን ምታቀርበው ምስጋና
እኛ ተለይተን ከምንፀልየው ምስጋና ይበልጣልና
ስጣዌ ስጣዌያት እኛ ጠይቀን ከምናገኘው መልስ
ቤተክርስቲያን የምትጠይቅልን ጥያቄ ይበልጣል
አይን ብቻየን ሁኜ አሁን እንደው ቢመካ ማለት ነው
እኔ እኮ አይን ነኝ በአካላት ላይ ቢመካ ቅ.ጳውሎስ ፅፎታል
✅ እኔ አይን
ባላይልህ እኮ እግርም እጅም ጅብ በልቶህ ነበርኮ
ምትሮጠው እኮ እኔ ጅብ መኖሩን አይቸልህ እኮ ነው
✅ ጆሮም ደግሞ
አይ እኔ ሲጮህ ባልሰማው ምን ታውቅ ነበር ቢል ደግሞ
✅ እግር ደግሞ
አይ እኔ ባሮጥ አንተስ ምን ቁም ነገር አለህ ቢል
ሁሉም ተያይዞ መጥፋት
✅ እራስስ ቢሆን
እኔ እኮ ነኝ እግርን ማስተዳድረው እኔ ነኝ
መመርያ ምሰጥ እኔ ነኝ ያለራስ ምንቁም ነገር አላችሁ ቢል
እስቲ ተቆረጥና ህይወት ሲኖርህ እናያለን ቢሉት
ህይወት ይኖረዋል ?
✅ ዝም ብሎ
ከብለል ከብለል ሲል አንድ መርግ ጨፍልቆ ይጥለዋል ማለት ነው
ዱባ ማለት እኮ ነው እራስ ከህዋሳት ከተለየ
አዕምሮ ይጠፋል
አዕምሮ ከነዚህ ተለይቶ ከተቆረጠ ይጠፋል።
አንድ የአንገት ደምስር ቢቆረጥ አዕምሮ ዋጋ የለውም።
✅ ስለዚህ ምንድን ነው ?
ቤተክርስቲያን ህብረታዊት ተዋህዳዊት ናት
✅ ቤተክርስቲያን
በክርስቶስ እራስነት ዓለምን ሰብሰባ የምትይዝ ናት።
ሰላምም ፍቅርም አንድነትም ከቤተክርስቲያንም በላይ ምንጭም የለም በእውነቱ ማለት ነው ።
ሰላም ማለት እኮ የሁከት አለመኖር ነው
ሰላምን ሚሰጥ ደግሞ እግዚአብሔር ነው።
"ይኩን ሰላም በኃይልከ" ይላል ቅዱስ ዳዊት።
ሰላም የሚመጣው በኃይለ እግዚአብሔር ነው
✅ ስለዚህ ከዚች ቤተክርስቲያን
ጠላቶቻችሁን ውደዱ
የሚረግሟችሁን መርቁ ከምትል ቤተክርስቲያን በላይ
ሰላምን የምታስተምር ማን ሊገኝ ይችላል።
ምን አይነት አስተምህሮስ ይገኛል።
✅ እናስ ቤተክርስቲያን
ከኪዳን ከቅዳሴ እየቀረን
ብቻችንን እያነበነብን
በዓመት አንድ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን እየመጣን
ነው ኢትዮጵያ ሰላም ምትሆነው ?
ሰላሙን ፍቅሩን መድኃኔዓለም ያድለን አሜን🙏
ርዕሰ ሊቃውንት ቆሞስ አባ ገብረ ኪዳን❣️
ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
“ድኽነት ትልቅ ሀብት ነው" የሚለው ስንፍናን እያስተማረ አይደለለም፡፡ “በጥበብ ለያዙት ሰዎች" ነው፡፡
ይህንን ከአላዛርና እና ከነዌ ልንረዳው እንችላለን፡፡
✅ አልዓዛር
የተመሰገነውና በአብርሃም ዕቅፍ የተቀመጠው
ነዳይ፣ ሕመምተኛና እጅግ ስቃይ ስለነበረበት ሳይኾን
በእነዚህ ውስጥ ኾኖ እግዚአብሔርን ባለማማረሩና በመታገሡ ነው፡፡
ባለጸግነትም እንዲሁ በደፈና መጥፎ ነው አንለውም ፣
ሊቁም እያለ ያለው እንደዚህ አይደለም ።
✅ እንደ አብርሃም እንደ ኢዮብ
በጥበብ ከተጠቀሙበት ባለፀጋነት አይጎዳም ።
ድኽነትም
✅ እንደ አልዓዛር ከተጠቀሙበት አይጎዳም፡፡
ድኻ መኾን ግን የመንግሥተ ሰማያት ዋስትና አይደለም፡፡
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በረከት አይለየን❣️
በዚህ አለም ላይ
ተወዳጆች ሆይ
የእመቤታችን ፍቅር
እንደውሃ የፈሰሰለት ሰው የታደለ ነው።
አባ ጊዮርጊስ ለዚህ ነው
ፍቅርሽ እንደ ወይን እና እንደ ውሃ በልቤ ውስጥ ተቀላቅሏል
ወይን እና ውሃ ከተቀላቀለ በኋላ
ይሄ ወይን ነው ይሄ ውሃ ነው ማለት አይቻልም
እኔን ከማርያም ፍቅር ለይቶ ማሳየት የሚችል የለም
እንዴት አድርጎ ቢወዳት ነው እናንተ
እንዴት አድርጌ ላመስግንሽ ይሆን አለ
ምን ላድርግ ?
ፀጉሬ እንኳን አፍ አውጥቶ ቢዘምርልሽ አይበቃሽም ይላል
ስለዚህ ዝም ብየ ቡርክት ቡርክት ቡርክት እልሻለሁ ይላል።
አምላክ እናቴ ያላትን እኔ እናቴ ላልላት ነው እንዴ
ፈጣሪ እናቴ ካላት እኔማ ሎሌሽ ነኝ ብላት
ኧረ! እናትም የሆነችን በቸርነቷ ነው
አንደኛ
የእግዚአብሔር ቸርነት ይገርማል
የእሱን እናት እኛም እናታችን ስንል
ለነገሩ ፈጣሪ ቅናት የለበት አይደል
እንጂማ የአምላክን እናት
እናቴ ማለትኮ እራሱ ትዕቢት እኮ ነው
ትዕቢት ነው አዛኘን
ሁለተኛ ደግሞ
የሷም ደግነት
እኔ አንተን ልጄ ባልኩበት
ዘማያውያንን ሁሉ ልጄ አልልም አለማለቷ
የረከሱት ሁሉ እናቴ ማርያም አይሉኝም
እንዳይሉኝ ከልክላቸው አለማለቷ
የምድር ንግስት ብትሆን እኮ
ዞርበል ያንተ እናት አይደለሁም ትለን ነበር።
እሷ ግን
ቸር እናት ስለሆነች
የመሀሪው እናት ፣ እርህርሂት ማርያም
የውሻ ያዘነች ስለሆነች እናታችን ስንላት አናፍርም
እናትነቷ ሲበዛብን እንጂ
የፈጣሪን እናት እናት እንድትሆነን የፈቀደልን እግዚአብሔር
ስሙ የተመሰገነ ይሁን አሜን አሜን አሜን 🙏
ህዳር 26/2017 #ፃድቁ_ሐብተ_ማርያም
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ለምናመሰግንበት ለፃድቁ አባታችን #አቡነ_ሐብተ_ማርያም አመታዊ የእረፍት በአል መታሠቢያ እንኳን አደረሰን
👉ኢትዮጲያዊዉ ፃድቅ ትዉልዳቸዉ ሸዋ መንዝ ልዩ ስሙ ራዊ ውስጥ ሲሆን አባታቸው #ፍሬ_ቡሩክ እናታቸው ደግሞ ቅድስት #ዮስቴና ትባላለች በተለይ ቅድስት ዮስቴና እጅግ ደመ ግቡ ምጽዋትን ወዳጅ ቡርክት ሴት ነበረች እንዲያውም ከጻድቁ መወለድ በፊት መንና ጭው ካለ በርሃ ገብታ ነበር
👉ግን የበቃ ግኁስ አግኝቷት ከማሕጸንሽ ደግ #የሥላሴ ባርያ አለና ተመለሽ ብሏት እንደ ገና ተመልሳለች ፃድቁን ወልዳ አሳድጋም እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ 7 #አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች
👉ወደ ፃድቁ ዜና ሕይወት ስንመለስ #አቡነ_ሃብተ_ማርያም ገና ሕጻን እያሉ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ሲባል ይሰማሉ ይሕችን ጸሎት በሕጻን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ "ማረን እባክህን" እያሉ ይሰግዱ ነበር
👉የ5 ዓመት ሕጻን እንዲህ ሲያደርግ ማየቱ በእውነት ይደንቃል ትንሽ ከፍ ብለው #በእረኝነት ሳሉም ፍፁም ተሐራሚና ፀዋሚ ነበሩ ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል የፈጣሪውን ስም ያቃለለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል
👉ፃድቁ አባታችን በዝመታኘንትና በአርምሞ ኑሯቸዉ የታወቁ ናቸዉ በመልአክ መሪነት #አክሱም_ኢየሩሣሌም_ምድረ_ግብፅ በእግራቸዉ በመሔድ ተሣልመዋል
👉ለፃድቁ አባታችን ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ቃል ኪዳን ሰጥቶዋቸዋል ወረርሽኝ በሽታና የአባላዘር በሽታ የያዘዉን ሰዉ ፀበልህን ቢጠመቅ ቢጠጣ በፍጥነት ይድናል ለ15 አይነት መቅሰፍቶች እንዲያድን ቃል ኪዳን ተሰጥቶዋቸዋል
👉ፃድቁ አባታችን #ማእጠንት ሲያጥኑ መንበረ ፀባኦት ይታያቸዉ ነበር ፃድቁ በዚህ እለት የእረፍት በአላቸዉ ሲሆን ራሳቸዉ በገደሙት ገዳም ተቀብረዋል
👉የፃድቁ ምልጃና ፀሎት ሀገራችንን #ህዝባችንን ይጠብቅልን ቃል ኪዳናቸዉም አይለየን "አሜን"
👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የሚዉሉ ቅዱሣን ረድኤትና በረከት የከበረዉ #ቃል_ኪዳናቸዉ ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ኅዳር 25-የታላቁ ሰማዕት የቅዱስ መርቆሬዎስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ‹‹መርቆሬዎስ›› ማለት የአብ ወዳጅ ማለት ነው፡፡ ዳግመኛም የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ወላጆቹ አስሊጥ ከምትባል ሀገር ቢሆኑም እርሱ ግን ተወልዶ ያደገው በሮሜ ከተማ ነው፡፡ አያቱና አባቱ ሥራቸው አውሬ ማደን ስለነበር አንድ ቀን እንደልማዳቸው አውሬ ሲያድኑ ከገጸ ከለባት ወገን የሆኑ ሁለት ወንዶች አግኝተዋቸው የመርቆሬዎስን አያት በሉት፡፡
አባቱንም ሊበሉት ሲሉ የታዘዘ መልአክ ከለከላቸው፡፡ ዙሪያቸውንም በእሳት አጥሮ ከበባቸው፡፡ እነርሱም በተቸገሩ ጊዜ ለመርቆሬዎስ አባት ሰገዱለት፡፡ በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር ፍጥረታቸውን ወደገራምነት ለወጠውና እንደበጎች የዋሆች ሆነው አብረውት ወደ መንደር ገቡ፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዎስ ተወለደና ስሙ ፒሉፓዴር ተባለ፡፡ የውሻ መልክ ያላቸውም በእርሱ ዘንድ ብዙ ዘመናት ኖሩ፡፡ ከዚህም በኋላ ክርስቲያኖች ሆኑ፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስም ወላጆች አስቀድመው አረማውያን ነበሩና የክርስትና ጥምቀትን በጸጋ ተቀበሉ፡፡ አባቱን ኖህ እናቱንም ታቦት ብለው ሰየሟቸው፡፡
ቀድሞ ፒሉፓዴር የነበረውም ስሙ ተለውጦ መርቆሬዎስ ተባለ፡፡ የውሻ መልክ ያላቸው ግን መልአኩ በተገለጠላቸው ጊዜ እንደነገራቸው ለቅዱስ መርቆሬዎስ አባት የሚታዘዙና የሚያገለግሉ ሆኑ፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባትና የውሻ መልክ ያላቸውን ዜናቸውን ሲሰማ ወታደሮቹን ልኮ በፊቱ አቆማቸው፡፡ እግዚአብሔርም የቀድሞ ፍጥረታቸውን መልሶላቸው አራዊት አደረጋቸውና ንጉሡን እጅግ አስፈሩት፡፡ ንጉሡም የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት የአራዊት ተፈጥሮአቸውን ያርቅለት ዘንድ ለመነው፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስም አባት በለመነ ጊዜ ተፈጥሮአቸውን መልሶላቸው ገራሞች ሆኑ፡፡
ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ገዥና የሠራዊቱ አለቃ አድርጎ ሾመው፡፡ የውሻ ፊት ያላቸውም አብረው ያገለግሉት ስለነበር ሁሉም ይፈራው ነበር፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ወደ ጦርነት ከላከው በኋላ ሳይመለስ ስለቀረ ሚስቱን ሊያገባት አሰበ፡፡ የመርቆሬዎስ አባትም የመርዶሳውያን አገሮች ሁሉ ገዢ በነበረው ንጉሥ ተይዞ ቢማረክም ገዥው ክርስቲያን መሆኑን አይቶ አከበረው፡፡ ቆይቶም በሀገሩ ላይ ሾመው፡፡ ሚስቱም ጠፍታ ከሀገሯ ወጥታ ሄዳ ስለነበር ከባሏ ተገናኝተው በዚያው መኖር ጀመሩ፡፡ መርቆሬዎስም አባቱና እናቱ ከሞቱ በኋላ ንጉሡ በአባቱ ፈንታ በመርዶሳውያን አገር ላይ ሾመው፡፡
መርቆሬዎስ መኰንንነት በተሾመም ጊዜ ገጸ ከለባቱ አብሮት ነበር፡፡ ለመዋጋትም በወጣ ጊዜ የቀድሞው የአራዊት የሆነ ተፈጥሮውን እግዚአብሔር ይመልስለት ስለነበር ማንም አይቋቋመውም ነበር፡፡ ለቅዱስ መርቆሬዎስ ታላቅ የድል አድራጊነት ኃይል ተሰጠውና ዜናው በሁሉም ሀገሮች ተሰማ፡፡ በሮሜ ሀገር ጣዖትን የሚያመልከው ዳኬዎስ የተባለውም ንጉሥ የበርበር ሰዎች ጋር ጦርነት ሊገጥም በወጣ ጊዜ እጅግ ሲበዙበት ፈራ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም በጦሩ መሀል የተሳለ ሰይፍ የያዘ የእግዚአብሔርን መልአክ ስላየ ንጉሡን እግዚአብሔር ያጠፋቸዋልና አትፍራ›› አለው፡፡ መልአኩም ሰይፉን ለቅዱስ መርቆሬዎስ ሰጠውና ‹‹ጦርነቱን ድል ባደረግህ ጊዜ እግዚአብሔርን አስበው›› አለው፡፡ ጦርነቱን ድል አድርጎ ሲጨርስም መልአኩ ድጋሚ ተገልጦለት ‹‹ለምን የፈጣሪህን ስም መጥራት እረሳህ?›› አለው፡፡ ከጦርነቱም በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረግ በዓልን አደረገ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም በዚያ ስላልተገኘ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረጉ እንዳልተባበረ ንጉሡ ሲያውቅ መልእክተኞችን ልኮ አስመጣው፡፡ ንጉሡም ‹‹ከእኔ ጋር ለምን አታጥንም?›› ባለው ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ ትጥቁንና ልብሱን አውልቆ ከወረወረለት በኋላ ‹‹ክብር ይግባውና አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን ፈጽሞ አልክደውም፣ ለረከሱ ጣዖቶችህም አልሰግድም›› አለው፡፡ ንጉሡም ተናዶ ልዩ ልዩ በሆኑ ሥቃዮችም እጅግ አሠቃየው፡፡
ንጉሡም ስለ መርቆሬዎስ ብለው የአገሩ ሰዎች እንዳይነሱበት ፈርቶ በብረት ችንካር ቸንክሮ የቀጵዶቅያና የእስያ ክፍል ወደሆነች ወደ ቂሳርያ ከደብዳቤ ጋር ላከው፡፡ በዚያም እጅግ ካሠቃዩት በኋላ ንጉሡ ዳኬዎስ እንዳዘዘ ኅዳር 25 ቀን አንገቱን በሰይፍ ቆረጡትና የሰማዕትነት ተጋድሎውን ፈጸመ፡፡ የሕይወትንም አክሊል ተቀዳጀ፡፡ በዓለሙ ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ታነጹለት፡፡
እግዚአብሔርም ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን በቅዱስ መርቆሬዎስ ስም አደረገ፡፡ ከብዙ ተአምራቱም አንዱ የቂሳርያውን ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስን እረድቶ ከሃዲውን ዑልያኖስን የገደለበት ነው፡፡ ዑልያኖስ ነግሦ የክብር ባለቤት ጌታችንን ክዶ ጣዖታትን ማምለክና ክርስቲያኖችን ማሠቃየት ጀመረ፡፡ የቂሳርያው ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስም አስተምሮ ሊመልሰው ወደ ንጉሡ ቢመጣ ክብር ይግባውና ዑልያኖስ ጌታችንን ሰድቦ ባስልዮስንም አሰረው፡፡
ባስልዮስም በእሥር ቤት ሳለ በቅዱስ መርቆሬዎስ ሥዕል ፊት ጸለየ፡፡ ሥዕሉም ወዲያው ተሰወረው፡፡ ያንጊዜም ወደ ከሃዲው ንጉሥ ዑልያኖስ ዘንድ ሄዶ በጦር ወግቶ ገደለውና ወዲያው ወደ ቦታው ተመለሰ፡፡ ከጦሩም አንገት ደም ይንጠፋጠፍ ነበር፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ከሃዲውን ንጉሥ እንደገደለው ዐውቆ ‹‹የክርስቶስ ምስክር ጌታዬ ሆይ የእውነት ፀር የሆነ ዑልያኖስን ገደልከውን?›› አለው፡፡ ሥዕሉም ያን ጊዜ አዎን እንደሚል ራሱን ዘንበል አደረገ፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ደስ ብሎት እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡
ሌላው የሰማዕት የቅዱስ መርቆሬዎስ ተአምር ከእስልምና እምነት መልሶ ክርስቲያን ያደረገው አንድ ኢስላም ሰው አለ፡፡ ይኸውም የመሐመድን መቃብር ለመሳለም በሔደው ኢስላም ላይ ያሳየው ታላቅ ተአምር ነው፡፡
ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን!
የታላቁን ሰማዕት የቅዱስ መርቆሬዎስ ረድኤት በረከቱ ይድርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡
ከገድላት ከንደበት
ህዳር 24/2017 #ፃድቁ_ቅዱስ_ተክለሃይማኖት
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት #ለአባታችን_ለአቡነ_ተክለሃይማኖት አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉አባታችን #አቡነ_ተክለሀይማኖት በዳዊት ፀሎት ከነቢያት ምስጋና ሌሊቱን ሙሉ ይተጉ ነበር በያንዳንዱ መዝሙርም አስር 10 ስግደትን ይሰግዱ ነበር፡፡
👉በሕዳር 24 ቀን #ቅዱስ_ሚካኤል ወደ ላይ ነጠቃቸው አወጣቸው #ከሐያ_አራቱ_ካህናተ_ሰማይ ጋር ሐያ አምስተኛ ካህን ሆነው የሥላሴን መንበርን #አሐዱ_አብ_ቅዱስ #አሐዱ_ወልድ_ቅዱስ #አሐዱ_ውእቱ_መንፈስ_ቅዱስ በማለት አጥነዋል
👉በሐይቅ 10 ዓመት በደብረ ዳሞ 12 ዓመት ኖረዋል አባታችን #አቡነ_ተክለሃይማኖት በ1267 ዓ.ም ደብረ ሊባኖስን በአት አድርገው ኖሩ፡፡
👉ለ22 ዓመት ቆመው #በመፀለያቸዉ የአንድ እግራቸው አገዳ ተሠበረ ደቀ መዝሙሮቻቸው በጨርቅ ጠቅልለው ቀበሩት፡፡
👉በአንድ እግራቸው ለ7 ዓመት በፀሎት ቆሙ በጠቅላላው ለ29 ዓመት በፀሎት ከቆሙ በኋላ በ99 ዓመት ከ10 ወር ከ10 ቀን ነሐሴ 24 ቀን አረፉ አባታችን ባረፉ በ54 ዓመታቸው ለአባታችን ለአቡነ ሕዝቅያስ ተገልፀው አፅማቸው #ከደብረ_አስቦ ወደ #ደብረ_ሊባኖስ ግንቦት 12 ቀን እንዲፈልስ አድርገዋል፡፡
👉ለሃይማኖታችን መፅኛ ለሀገራችን አፅር ቅፅር የአባታችን #ፀሎት ኃይል ይሁነን ቃል ኪዳኑ ይጠብቀን "አሜን"
👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ እንኳን በሰላም በያላችሁበት ቦታ ለታላቁ አባታችን #ለአቡነ_ተክለ_ሐይማኖት ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረስን ከሃያ አራቱ ካህናተ ስማይ ጋር አባታችን #የሥላሴን_መንበር ያጠኑበት ያመስገኑበት ቀን የበረከትና የረድኤት ቀን ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️