kedusgebreal | Unsorted

Telegram-канал kedusgebreal - የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

1895

ይህ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ ክፍት የሆነ ለመማማርያ እና መወያያ ታስቦ የተከፈተ ነው። ልቦናችንን እግዚአብሔርን ለመሻት ያነሳሳን ከሚያልፈው ወደማያልፈው ሀሳባችንን ይሰብስብልን።✝️🙏 for any comment or report (le asteyayet) https://t.me/fekerelehulu

Subscribe to a channel

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ወንድምህ ወደ ኃጢአት ሲኼድ ብታየው ምከረው ።
እምቢ ካለህም ጨርቁን ይዘህ ጎትተው ።
ትጠቅሟለህ እንጂ አትጎዳውም ።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❣️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ታህሳስ 16/2017 #እናታችን_ቅድስት_ኪዳነ_ምህረት

"ከመረጥኋቸዉ ጋር #ቃል_ኪዳኔን አደረግኹ"መዝ.88፥3

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በምስጋና ከፍ ለምናደርግበት እናታችን #ኪዳነ_ምህረትን በቃል ኪዳኗ እንድታስበን ለምንማፀንበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአሏ እንኳን አደረሰን

👉 #ኪዳነምህረት ስንል የምህረት ቃል ኪዳን ማለት ነው በዚህ ውስጥም ምህረት አድራጊው ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ምህረት ተቀባይም መላው የአዳም ዘር ነው

👉 #እናታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም በምድራዊ ቆይታዋ ዘውትር ወደ #ክርስቶስ_መካነ_መቃብር_ጎለጎታ እየሔደች ትፀልይ ነበር ልጇ እና ወዳጇ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገችውን ልመናና ፀሎት ተመልክቶና ሰምቶ #የምህረት_ቃል_ኪዳንን ሰጣት

👉እንኳን የእናቱን ፀሎት እና ልመና ቀርቶ ዘውትር በሀጥያት የምንዘፈቀውን እኛን ክፉዎቹን የሚሰማ አምላክ ስለ አንቺ ስለ እናቴ ክብርና ፀጋ ስል ይኸው ቃሌ ብሎ #ቃል_ኪዳን አደረገ

👉ስሟን ለሚጠሩ በእርሷ አማላጅነት ለሚታመኑ በምድር በረከትን በሰማይ የዘለዓለም መንግስትን እንደሚወርሱ የምህረት እና የቸርነት #ቃል_ኪዳን ሰጥቷታል

👉በታላቁም መፅሐፍ ቀስቲቱም በደመና ትሆናለች በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘላለም #ቃል_ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ ኦሪት ዘፍ.9፥16

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ለእናቱ በሠጣት #ቃል_ኪዳን ያስበን ሀገራችንን ህዝባችንን ከክፉ መከራ ይጠብቅልን የአበዉ ነብያት ረድኤት በረከት አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

👉ሰለሞን የገብርኤል
👉ታህሳስ 16/2017

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝እንኳን አደረሰነ!

✞በዓለ አበው ቅዱሳን፦

✿ጎርጎርዮሰ ከሣቴ ብርሃን (ዘአርማንያ)
✿ኤዎስጣቴዎስ ረባን (ዘኢትዮጵያ)
✿ሉቃስ ዘዓምድ (ዘቁስጥንጥንያ)
✿ቆራይ ጻድቅ
✿ይምላሕ ገዳማዊ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤
ኪያነኒ ይምሐረነ በጸሎቶሙ።
ወበረከቶሙ ይብጽሐነ፤ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡

/channel/zikirekdusn

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ጉዞ_ወደ_ወደ_ሀ ዋሳ _ገብርኤል
ታህሳስ_18 እና 19

ቀድመው ይመዝገቡ ለባልና ሚስት ዋጋ 2900 ብር
የ አንድ ሰው 1500 ብር
☎️09-91-11-96-29



መነሻ_ አርብ ታህሳስ 18
መመለሻ_ታህሳስ 19
መነሻ ቦታ
1 አስኮ
2 ፒያሳ

የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል
#ባሉት_ጥቂት_ቦታ_እና_ቀን_ስልኮች_ደውለው_ይመዝገቡ
ጉዞ ለመመዝገብ👇
❤ 2519-91-11-96-29
❤ 2519-25-49-26-34
በአካል መክፈል ለማትችሉ በቴሌብር በ0991119629
እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000490586621 ክፍያ ይፈፅሙ
አዘጋጅ: ቅዱስ ገብርኤል መንፈሳዊ የጉዞ

ለሁሉም ህዝበ ክርስቲያን ይዳረስ ዘንድ ሸር ኮፒሊንክ አድርጉት🙏🙏🙏

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ታህሳስ 15/2017 #ሰማእቷ_ቅድስት_ኢየሉጣ
#ህፃኑ_ቅዱስ_ቂርቆስ
#ሰማእቱ_ቅዱስ_ሚናስ

ስለ አንተ ብለን ሁል ጊዜ ተገድለናል እለት እለት
እንደሚታረዱ በጎች ሆነናል መዝ.43፥22

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሳኑ ስም ለምናመሰግንበት #ለቅዱስ_ቂርቆስ_ለቅድስት_ኢየሉጣ እና #ለቅዱስ_ሚናስ ለወርሐዊ መታሠቢያ በአላቸዉ እንኳን አደረሰን

👉 #ቅዱስ_ቂርቆስ ዕድሜው የሦስት ዓመት ሳለ እናቱ ቅድስት #ኢየሉጣ ከሮሜ ወደ ሌላ ሃገር ሸሽታ ይዛው ሄደች በዚያም የሸሸችውን መኮንኑን አገኘችው የሚያውቋትም ሰዎች ሸሽታ እንደመጣች ስለተረዱ ለመኮንኑ ነገር ሰሩባት

👉መኮንኑም #ቅድስት_አየሉጣን አስጠራትና ስለ አምልኮ ጠየቃት ቅድስት ኢየሉጣም መኮንን ሆይ ዕድሜው ሦስት አመት የሆነው ሕፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እርሱን ጠይቅ አለችው

👉 #ሕፃኑ_ቅዱስ_ቂርቆስም ወደ አለበት ጭፍራውን ልኮ ወደ እርሱ አስመጣው ሕፃኑንም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና “አንተ ደስተኛ ሕፃን ሆይ እንዴት ነህ?” አለው።

👉ሕፃን #ቅዱስ_ቂርቆስም መለሰለት እንዲህም አለው “አዎ እኔ በጣም ደስተኛ ነኝ ደስታዬም ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ሐዘንና ለቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስም ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏልና” አለው።

👉 #እግዚአብሔር አምላክ ኃይልንና ንግግርን ሰጥቶታልና በዚያ ለተሰበሰቡት ሰዎች እስኪደነግጡ ድረስ ብዙ ተናገረ ሕፃኑ #ቅዱስ_ቂርቆስም ንጉሱን መኳንንቱንና ጣዖታቱን ረገማቸው ከብርታቱም የተነሳ አደነቁ።

👉መኮንኑም በአፈረ ጊዜ በየዓይነቱ በሆነ ስቃይ ታላላቆች እንኳ የማይችሉትን ታላቅ አስጨናቂ የሆነ ስቃይን አሰቃየው እናቱ #ቅድስት_ኢየሉጣንም ከእርሱ ጋር እንደ እርሱ በጣሙን አሰቃያት

👉 #እግዚአብሔር ግን ያለ ምንም ጉዳት ያነሳቸው ነበር ብዙዎች አህዛብም ይህን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን በመድሃኒታችን #በኢየሱስ_ክርስቶስ አምላክነት አምነው በሰማእትነት ሞቱ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበሉ።

👉በሕፃኑ #ቅዱስ_ቂርቆስ ላይም የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ አደረበት ታላላቅ ድንቅ ተአምራቶችንም ያደርግ ነበር ብዙዎች በሽተኞችንም ያድናቸው ይፈውሳቸው ነበር

👉ይህንን ያየ መኮንን በታላቅ የናስ ጋን ውስጥ ውሃ ጨምረው በእሳት ያፈሉት ዘንድ አዘዘ የፍላቱም ድምጽ እንደ ክረምት ነጎድጓድ ሆነ ድምጹም በጣም ያስተጋባ ነበር

👉ይህን ያየችና የሰማች እናት #ቅድስት_ኢየሉጣም ፍርሃትና የሃይማኖት ጉድለት ታየባት ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ሁኔታዋን አይቶ ወደ አምላኩ እግዚአብሔር ፀለየ

👉ያን ጊዜ ልዑል #እግዚአብሔር ልቧን ወደ ሰማይ አሳርጎ ለቅዱሳን ሰማዕታት የተዘጋጁ የብርሃን ማደሪያዎችን አሳያት ቅድስት ኢየሉጣም እንደገና በሃይማኖቷ ጸናች እግዚአብሔር አምላኳንም አመሰገነችው ልጇን ሕፃኑን ቅዱስ ቂርቆስንም “ልጄ ሆይ አንተ ከእንግዲህ አባቴ ነህ እኔም ልጅህ ነኝ” አለችው

👉 #ቅድስት_እየሉጣም ለልጇ “ያች የተወለድክባት ዕለት ቀኗ የተባረከችና የተቀደሰች ናት” አለችው የመኳንንቱ ጭፍሮችም እሳት ወደ አለበት ጋኖች ውስጥ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣን በጨመሯቸው ጊዜ የውሃው ፍላት ወድያዉኑ ቀዘቀዘ ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የእሳቱን ኃይል አቀዝቅዞታልና

👉ይህን ያየ መኮንን ሥጋቸው ተቆራርጦ እስከሚወድቅ ድረስ በመቃጥን ውስጥ አድርገው አንዲጎትቷቸው አዘዘ #ከእግዚአብሔርም የታዘዘ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል አዳናቸው

👉መኮንኑም በታላቅ ስቃይ ያሰቃያቸው ዘንድ አስቦ እስኪመክር ድረስ በወህኒ ቤት ዘጋባቸው በዚህን ጊዜ ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ወደ ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስን አረጋጋው አጽናናው ስሙን ጠርተው መታሰቢያ ለሚያደርጉለትም በረከትን እንደሚያገኝና ሌላ ብዙ ቃል ኪዳን ሰጠው

👉ሲነጋ መኮንኑ ከመካነ ምኩናኑ ተቀምጦ ካለበት አስጠርቶ የተመለስከው መመለስ አለን አለው #ቅዱስ_ቂርቆስም አይሆንም አልመለስም አለው ሰይፍ ጃግሬውን ጠርቶ ንሳ ውደቅበት አለው በሰይፍ መታው ጌታም ነፍሱን ከመካነ ዕረፍት ሥጋውንም ነጥቆ #በሰረገላ_ኤልያስ አኑሮለታል እናቱ ቅድስት ኢየሉጣንም በማግስቱ ጥር 16 በሰይፍ አስመትቷት በሰማዕትነት ዓርፋለች

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከሕፃኑ #ቅዱስ_ቂርቆስ እና ከእናቱ #ቅድስት_እየሉጣ እንዲሁም ከሰማእቱ #ቅዱስ_ሚናስ ረድኤት በረከት ያሣትፈን ምልጃ ፀሎታቸዉ አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።


        ታላቅ የንግስ ጉዞ ወደ ሀዋሳ ገብርኤል

ሀዋሳ ገብርኤል


ታህሳስ 18 መነሻ
ታህሳስ 19 መመለሻ

በዕለቱ የሚኖሩን ፕሮግራሞች


-መንፈሳዊ ትምህርቶች
-የተለያዩ ዝማሬሞች
-የንግስ ላይ አገልግሎቶች
-የፀሎት ፕሮግራም
- የበረከት ስራዎች

እንዳያመልጦት 🙏🙏🙏

ዋጋ ከሙሉ መስተንግዶ ጋር

1500 ብር ብቻ

     
ለበለጠ መረጃ




0991119629
0925492634


ይደውሉ 📞📞

አዘጋጅ ቅዱስ ገብርኤል መንፈሳዊ የጉዞ ማህበር

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

አራት ዓይነት ፍቅር አለ፡፡

(1) አጋፔያዊ ፍቅር (Agape Love) ምንም ዓይነት ቅድመ - ኹኔታዎችን ሳያስቀምጡ የሚሰጡት ፍቅር ነው፡፡ በዚህ ውስጥ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሚሰጠው እና ሰው ለእግዚአብሔር ሊያሳየው የሚገባ ፍቅር ያጠቃልላል፡፡ ፍቅረ ቢጽም እዚህ ውስጥ ነው፡፡

(2) ቤተሰባዊ ፍቅር (Storge Love) - ወላጆች ለልጆቻቸው የሚሰጡት ፍቅር፡፡

(3) ጾታዊ ፍቅር (Eros Love) - ለትዳር አጋር የሚሰጥ ፍቅር፡፡

(4) ፊሊያዊ ፍቅር (Philia Love) - ለጓደኛ፣ ለሥራ ባልደረባ የሚሰጡት ፍቅር፡፡

ሦስቱ ዓይነት ፍቅር ግን


ወደ መጀመሪያው ማለትም ወደ አጋፔያዊ ፍቅር በኺደት ሊያድጉ ይገባል፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

የገላን ሰሚ በዕለቱ ቅዱስ ሚካኤል ገዳም

⛪️ ከአዲስ አበባ በ32 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው ይህ ጥንታዊ ገዳም ከተመሠረተ ከመቶ ዓመት በላይ ሆኗል
ይሁንና በዚህ ሰዓት በምስጥ እየተበላ ቤተክርስቲያኑ ከፍተኛ አደጋ ላይ ወድቋል

⛪️ በሀገር ውስጥም በውጭም የምትገኙ ኦርቶዶክሳውያን የአቅማችሁን ድጋፍ በማድረግ ገዳሙ አዲስ የጀመረውን ቤተክርስቲያን ያጠናቅቅ ዘንድ ድጋፋችን አይለየው

⛪️ የገዳሙ የባንክ አካውንት
1000265718063 - ኢ.ን.ባ /CBE/

⛪️ ለበለጠ መረጃ በ +251920612968 ይደውሉ

⛪️ በዚህ ጥሪ ላይ በመሳተፍ የበረከት ተካፋይ እንሁን። የቅዱስ ሚካኤል ጥበቃና በረከት አይለየን።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በዚህችም ቀን ዳግማዊ ቂርቆስ የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ልጅ ብሔረ ብፁዓን የገባበት ነው፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን እንዲህ ሆነ፡- ብፅዕት ቅድስት እናታችን ክርስቶስ ሠምራ ከአገልጋዮቿ መካከል አንዷ ምግባሯ የከፋ ነበርና በጣም ስላበሳጨቻት በዚያች አገልጋይ አፍ ውስጥ የእሳት ትንታግ ጨመረችባት፡፡ ያም የእሳት ትንታግ እስከ ጉሮሮዋ ዘለቀና አገልጋይዋን ገደላት፡፡ በዚህ ጊዜ ብጽዕት ክርስቶስ ሠምራ ደንግጣ ወደ ሌላ ክፍል ገባችና ኃጢአቷን ለእግዚአብሔር እየተናዘዘች እጅግ በጣም አዝና ጥፋቷ እንደ ጸጸታትና እግዚአብሔር አምላክም በእጇ የሞተችውን አገልጋይዋን ከሥጋዋ አዋሕዶ ቢያሥነሳላት ያላትን ገንዘብና ሀብት ትታ ባላት ዘመኗ ሁሉ አገልጋዩ እንደምትሆን ብጽዓት (ስዕለት) አደረገች፡፡ እግዚአብሔርም ጸሎቷን ሰምቶ አገልጋይዋን ከሞት አሥነሳለት፡፡ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ‹‹ልመናዬን ቸል ያላለ ቸርነቱንም ከእኔ ከባሪያው ያላራቀ አምላክ ይክበር ይመስገን›› ብላ በታላቅ ምስጋና እግዚአብሔርን ካመሰገነች በኋላ አስቀድማ የገባችውን ቃል አስባ ልብሰ ምንኩስናዋን አዘጋጀች፡፡ ሕፃን ልጅዋንም ይዛ ወደ ደብረ ሊባኖስ ሄደች፡፡ ስትሄድም በልስላሴና በእንክብካቤ የኖረ እግሯ ከመንገዱ ብዛት ከእንቅፋቱም የተነሳ ፈለግ ሲያወጣ ሥጋውን እየቆረጠች ስትጥለው ደሟ መሬት ለመሬት እየፈሰሰ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ደረሰችና አስቀድማ ያዘጋጀችውን ልብሰ ምንኩስናዋን ለብሳ ከሴቶች ገዳም ገባች፡፡

ቅድስት እናታችን ይዛው የተሰደደችውን የ3 ዓመቱ ሕፃን ግን ወንድ ስለሆነ ከደጅ ላይ አስቀምጣው ስለገባች ሕፃኑ አምርሮ አለቀሰ፡፡ በዚህም ጊዜ ከመነኮሳይያቱ አንዲቷ ‹‹ሕፃኑ ሲያለቅስ ከሚያድር›› ብላ ወደ በአዓቷ ልታስገባው ስትል የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሕፃኑን ነጥቆ ወስዶ በገነት አስቀመጠው፡፡ እርሱም ታኅሣሥ 29 ቀን ተወልዶ በ3 ዓመቱ ታኅሣሥ 12 ቀን ብሔረ ብፁዓን ገብቷል፡፡ እጅግ አሳዛኝ ገድሉ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ይገኛል፡፡

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት አና ጻድቃን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ታህሣሥ እና #ከገድላት_አንደበት)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#ታኅሣሥ_12

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ታኅሣሥ ዐስራ ሁለት #የአቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ ዐረፉ፣ #ቅዱሳን_አንቂጦስ እና #ቅዱስ_ፎጢኖስ በሰማዕትነት ዐረፉ፣ #ዳግማዊ_ቂርቆስ የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ልጅ ብሔረ ብፁዓን የገባበት ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ

ታኅሣሥ ዐስራ ሁለት በዚህች ዕለት ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የሥሉስ ቅዱስን መንበር ያጠኑ አቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ዋሊ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ጻድቁ የተወለዱት በአክሱም ጽዮን ነው፡፡ ነገዳቸው የአክሱም ገበዝ ከነበረው ከጌድዮን ነው፡፡ የአባታቸው እስጢፋኖስና እናታቸው አመተ ማርያም ምግባር ሃይማኖታቸው የቀና ትሩፋት ተጋድሏቸው የሰመረ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ገና በ12 ዓመቱ ማይ ሹም በተባለው ባሕር ገብቶ ሲጸልይ ባሕሩ በብርሃን ተከቦ ይታይ ነበር፡፡ ከባሕሩም ወጥቶ ወደ ቤተክርስቲያን ገብቶ እያለቀሰና እያዘነ ሲጸልይ ካህናቱ ‹‹ይህ ሕፃን የእኛ ኃጢአት እየታየው? ወይስ ምን ኃጢአት ኖሮበት ነው እንዲህ የሚያዝነውና የሚያለቅሰው?›› እያሉ ያደንቁና ይገረሙ ነበር፡፡

አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ እናቱ አመተ ማርያም ቤተሰቧንና ቤት ንብረቷን ትታ ከመነኮሰች በኋላ እርሱም ካልመነኮስኩ በማለት አባቱ እስጢፋኖስን ቢለምነውም እምቢ ስላለው በራሱ ፈቃድ ከአንድ ሽማግሌ ጋር ወደ አባ መድኃኒነ እግዚእ ገዳም ደብረ በንኰል ገብቶ መነኮሰ፡፡ በዚያም ነፍሱን ‹‹ነፍሴ ሆይ! እነሆ ለክርስቶስ ታጨሽ፣ የቅዱሳንን ቀንበር እንሆ ተሸከምሽ፣ የመላእክትን ንጽሕና ትጠብቂ ዘንድ ዛሬ በእግዚአብሔርና በቅዱሳኑ ሁሉ ፊት ቃልኪዳን ገባሽ፣ ቃልኪዳንሽን ብትጠብቂ መላእክት ይደሰቱብሻል፣ ባትጠብቂ ግን አጋንንት ይዘባበቱብሻል…›› እያለ ብዙ መከራን በራሱ ላይ በማብዛት ሰባት ዓመት በዚያች ገዳም ኖረ፡፡ እህልም አይቀምስም ነበር ይልቁንም የሚሰጡትን እንጀራ ለሕጻናትና ለውሾች እየሰጠ አሠር ይመገብ ነበር፡፡

ዳግመኛም በሌላ ጊዜ ቅጠልን እየቀቀለ እስከ አምስት ቀን ከድኖ ያስቀምጠዋል፣ እስከሚተላም ድረስ ይጠብቀውና ያን ይመገባል፡፡ ኩስይ የምትባል ከሣር ሁሉ የምትመርን ሣር ምግቡ አደረገ፡፡ በኋላም አባቱም ልጁን ሳሙኤልን ተከትሎ ወደ እርሱ መጥቶ በአባ እጅ መነኮሰ፡፡ ለአባቱም መምህር ሆኖት እያገለገለው ያስተምረው ነበር፡፡ በሌላም ጊዜ 17 ዓመት ከተቀመጠባት ወይና በምትባል ቦታ ሲኖር ከውኃ በቀር ምንም ሳይቀምስ 12 ዓመት ተቀምጧል፡፡ ለ50 ዓመትም ያህል ሣር፣ ቅጠል፣ የዛፍ ሥርና ፍሬን እነዚህንና የመሳሰሉትን እየበላ ኖረ እንጂ እህል የሚባል አልበላም፡፡

ወጥቶም ወደ ዋሻ እየገባ ብዙ ጊዜ 40 ቀንና 40 ሌሊት በጾም በጸሎት እየኖረ እንቅልፍም እንዳያሸንፈው እስከሚነጋ ድረስ ሳይቆም ሳይተኛ እንደቆመ በጽኑ ተጋድሎ ተቀመጠ፡፡ ትልቅ ጉድጓድ ቆፍሮ በውስጡ እየገባ ሳይቀመጥ ሳይተኛ ሰውነቱ እንደ እንጨት እስኪደርቅ ድረስ በጾም በጸሎት በእጅጉ ይተጋ ነበር፣ በዚህም ወቅት ጌታችን ተገልጦለት ሰውነቱን በሙሉ ምራቁን ስለቀባለትና አውራ ጣቱን ስላጠባው ከዚህ ጊዜ በኋላ ርሀብና ጥሙ ጠፍቶለት ሰውነቱም ታድሶለታል፡፡ ዳግመኛም በአፉም ድንጋይ ጎርሶ፣ እግሩንም ታስሮና ማቅ ለብሶ ወደ ባሕር እየገባ ይጸልይ ነበር፡፡

አባታችን አባ ሳሙኤል በሕይወተ ሥጋ ሳለ እጅግ ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን አድርጓል፡፡ እንደሙሴ ባሕርን የከፈለበት ጊዜ አለ፤ በልዑልም ዙፋን ፊት እየቀረበ ከቅዱሳን መላእክት ጋር የሚያመሰግንበት ጊዜ አለ፣ ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይም ጋር ሆኖ የሚያጥንበት ጊዜ አለ፤ በሰማያዊት ኢየሩሳሌምም ሆኖ ከእነ ቅዱስ ጴጥሮስና ከሁሉ ቅዱሳን ጻድቃን ሰማዕታት ጋር በአንድ ላይ ማዕድ የሚቀርብበት ጊዜ አለ፤ በእጆቹ የያዛቸው መጻሕፍቶቹ ምንም ሳይርሱ ትልቅ ወንዝን በውስጡ እያቋረጠ የሚሻገርበት ጊዜ አለ፤ እመቤታችንንም ሲያመሰግናት ከምድር ወደ ላይ አንድ ክንድ ያህል ከፍ የሚልበት ጊዜ አለ፤ በቤትም ውስጥ ሆኖ ምስጋናዋን ሲጀምር የቤቱ መሠረት እየተናወጠ ዝናብ እንደያዘ ደመና ቤቱ ከምድር ከፍ ብሎ የሚቆምበት ጊዜ አለ፤ መንፈስ ቅዱስም በብርሃን ክንፍ እየወሰደው ወደተለያዩ ገዳማት ያደርሰውና ሥጋ ወደሙን እንዲቀበል ያደርገው ነበር፡፡ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልም የሁልጊዜ ጠባቂው ነውና በሁሉ ነገር ይራዳውና እንደ ጓደኛም ያማክረው ነበር፡፡ በአንዲት ዕለትም በጎዳና ሲጓዝ ወንዝ መልቶበት አገኘው፡፡ አባታችንም መጻሕፍቶቻቸውንና እሳት በእጃቸው እንደያዙ በወንዙ ውስጥ ለውስጥ ውኃውን አቋርጠው ሲሻገሩ መጻሕፍቶቻቸው አልራሱም በእጃቸው የነበረው እሳትም አልጠፋም ነበር፡፡

አባታችን ሊያስቀድሱ ወደ በተ መቅደስ በሚገቡ ጊዜ ሰማያዊ ኅብስትና ጽዋ ይወርድላቸው ነበር፡፡ የእመቤታችንንም ውዳሴዋን ሲደግሙ ክንድ ከስንዝር ያህል ከምድር ከፍ ይሉ ነበር፡፡ እመቤታችንም እየተገለጠች ንጹሕ ዕጣንንና የሚያበራ እንቁን ሰጥታቸዋለች፡፡

ቅዱስ አባታችን ለክቡር ሥጋ ወደሙ እጅግ ትልቅ ክብር አላቸው፡፡ በቤተክርስቲያን አስቀድሰው ሁሉም ሥጋ ወደሙን ተቀብለው ወደ ቤታቸው ሲወጡ ከአራቱ መነኮሳት ውስጥ አንዱ አስታወከ፣ በቤተክርስቲያንም ዳርቻ ተፋው፡፡ ያዩትም ሁሉ ደንግጠው ቆሙ፡፡ የእግዚአብሔር ሰው ብፁዕ ሳሙኤል ግን ሁሉንም በአፉ ተቀበለው፣ በምላሱም መሬቱን ላሰው፡፡ ይህን ጊዜ ከሰማይም ‹ሳሙኤል ሳሙኤል› የሚልን ድምጽ ሰማና ወደላይ ባንጋጠጠ ጊዜ ሰባቱ ሰማያት ተከፍተው አየ፡፡ ከላይ ያለው ያ ቃልም መለሰ፡- ‹በሰው ፊት እንዳመሰገንኸኝና ፈጽሞም እንዳከበርከኝ የባልንጀራህን ትውኪያ ትቀበል ዘንድ እንዳላፈርህ እኔም እንዲሁ አከብርሃለሁ፤ በሰማያት ባለው በአባቴም ፊት በመላእክት ማኅበር አመሰግንሃለሁ› አለው፡፡›› ሌሎቹም ቅዱሳን እነ አቡነ ተክለሐዋርያትም እንዲሁ ለሥጋ ወደሙ ክብር ሲሉ የቆረበ ሰው ሲያስመልሰው የዚያን ሰው ትውኪያ ይጠጡት እንደነበር በቅዱስ ገድላቸው ላይ በሰፊው ተጠቅሷል፡፡ ቅዱሳን አባቶቻችንና እናቶቻችን ለክርስቶስ ያላቸው ክብር እስከዚህ ድረስ ነው፡፡

አንድ ቀን አባታችን በገዳም ውስጥ ሳለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይጎበኘው ዘንድ ወደ እርሱ መጣ፡፡ ከእርሱም ጋር ተቀምጦ ‹ወዳጄ ሆይ! ሰላምታ ይገባሃል፡፡ አንተ ግን ከትንሽነትህ ጀምሮ አገለገልኸኝ፣ ምን አደርግልህ ዘንድ ትወዳለህ?› አለው፡፡ ትሑት ሳሙኤልም ‹የነፍሴ ወዳጅ ጌታዬና አለቃዬ ሆይ! መልካም ሀብት ሁሉ ከአንተ ዘንድ ነውና ምሕረትህንና ብሩህ ፊትህን ታሳየኝ ዘንድ እሻለሁ› አለ፡፡ ጌታችንም ‹አገልጋዬ ወዳጄ ሆይ! የፈለግኸውን እሰጥሃለሁ፣ ዳግመኛም ያልፈለግኸውንም እጨምርልሃለሁ› አለው፡፡ አባ ሳሙኤልም ‹ጌታዬ ሆይ! አንዲት ልመናን እለምንሃለሁ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ኃጢአቴን አይ ዘንድ እወዳለሁ፡፡ የሌላውን ኃጢአት ግን አታሳየኝ› አለው፡፡

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ወዳጄ ሆይ

አንድ ሰው መጥቶ ሰድቦህ ሳለ አንተ ግን ምንም ስሜት አልተሰማችህምን? እንኪያስ አልተጎዳህም፡፡

ጡጫን ከመቀበል ይልቅ ጡጫን አቀብልሃል! [እንዴት ያልከኝ እንደ ኾነም] የተሳደበው ሰው ስድቡ በሚነቅፋቸው ሰዎች ሰውነት እንዳላረፈ ሲገዘነብ ሰንበር የሚወጣበት እርሱ ራሱ [ተሳዳቢው] ነውና፡፡

የተነቀፉት ሰዎች እንዲሁ ዝም ሲሉ የስድብ ቡጢዋ ወደ ኋላ ትመለስና ሌላውን ለመንቀፍ ያሰበውን ሰው ራሱን ትደቀዋለች፡፡

ስለዚህ ተወዳጆች ሆይ!

በኹሉም ነገር ላይ መንፈሳውያን ጠቢባን እንኹን፡፡
ይህን ያደረግን እንደኾነም ድኽነት ምንም ጉዳት አያደርስብንም፤


ይልቁንስ ታላቅ የኾነ በቁዔትንና ክብርን ይሰጠናል፤ ከባለጸጎቹ ይልቅም ባለጸጎች ያደርገናል እንጂ፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❣️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።


        ታላቅ የንግስ ጉዞ ወደ ሀዋሳ ገብርኤል

ሀዋሳ ገብርኤል


ታህሳስ 18 መነሻ
ታህሳስ 19 መመለሻ

በዕለቱ የሚኖሩን ፕሮግራሞች


-መንፈሳዊ ትምህርቶች
-የተለያዩ ዝማሬሞች
-የንግስ ላይ አገልግሎቶች
-የፀሎት ፕሮግራም
- የበረከት ስራዎች

እንዳያመልጦት 🙏🙏🙏

ዋጋ ከሙሉ መስተንግዶ ጋር

1500 ብር ብቻ

     
ለበለጠ መረጃ




0991119629
0925492634


ይደውሉ 📞📞

አዘጋጅ ቅዱስ ገብርኤል መንፈሳዊ የጉዞ ማህበር

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ለአእላት ዝማሬ መርሀ ግብር
ለሰርግ
ለክርስትና
ለተለያዩ መንፈሳዊ መርሀ ግብሮች ለሴት እና የወንዶች ኦርቶዶክሳዊ ይዘታቸውን የጠበቁ መንፈሳዊ የሀገር ልብሶችን የምትፈልጉ እህታችን ጋር ማዘዝ ትችላላችሁ ።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ታህሳስ 10/2017 #መስቀለ_ኢየሱስ_ክርስቶስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን #ለኢየሱስ_ክርስቶስ ቅዱስ እፀ መስቀል ለተገኘበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉እውራንን የሚያበራው ድውያንን የሚፈውሰው ሰላመ #እግዚአብሔርን ያገኘንበት የድህነታችን አርማ ሀይላችን የምንመካበት የምንድንበት ቅዱስ #እፀ_መስቀላችን ነው

👉የድህነታችን አርማ የሆነውን ቅዱስ #እፀ_መስቀል አይሁድ በቅናት ተነሳስተው ቀበሩት ለዘመናት የቆሻሻ ክምር በመጣል መስቀሉ እዲሰወር አደረጉ

👉በ 320 ዓ.ም የንጉስ ቆስጠንጢኖስ እናት #ቅድስት_እሌኒ ልጇ ቆስጠንጢኖስ ከ አረማዊ እምነት ወደ ክርስትና እንዲመለስ ስለት ተሳለች በስለቷ መሰረት ልጇ ወደ ክርስትና አምነት ከተመለሰ #የጌታችን_ኢየሱስን_መስቀል ለማግኘት በተሳለችው ስለት መሰረት መስከረም 16 ደመራ ደምራ እጣን በውስጡ ጨምራ አበራች

👉በዚህም ወቅት ጢሱ ወደ ሰማይ ወጥቶ ተመልሶ ወደ ምድር ሰግዶ በዘመኑ ከነበሩት ብዙ የቆሻሻ ክምር ተራራዎች የጌታችን #ቅዱስ_እፀ_መስቀል ወዳለበት ተራራ አመለከተ

👉 #ቅድስት_አሌኒም መስከረም 17 ቁፋሮውን አስጀምራ መጋቢት 10 ቀን ቅዱስ እፀ መስቀሉ ተገኘ።

👉መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ከመስቀሉ መታሰቢያ ክብረ በአል በረከት ያሣትፈን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

👉ሰለሞን የገብርኤል
👉ታህሳስ 10/2017

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

ውኃ የሚቀዱ ሴቶች ብዙ ጊዜ እንዳይመላለሱና
ድካማቸው ከንቱ እንዳይኾን ወደ ቤታቸው ሲመለሱ እንስራቸውን ከሞሉ በኋላ በጥንቃቄ ያደርሱታል እንጂ በምንጩ ሳሉ የሞሉት እንስራ እየተንቦጫቦጨ
ተደፍቶ ባዶውን እንዲደርስ አያደርጉትም፡፡
እኛም እነዚህን ሴቶች እንምሰላቸው፡፡
ወደ ቤታችን ስንመጣም
የተነገረንን ኹሉ በአግባቡ ` እናስታውሰው፤


እዚህ ሙሉ ኾናችሁ

ወደ ቤታችሁ ስትመለሱ ግን ባዶ ብትኾኑ
ማለትም ልቡናችሁ እዚህ የተነገረውን ነገር ቢረሳው
እዚህ ሙሉ መኾናችሁ ምንም ጥቅም አይሰጣችሁምና፡፡


አርበኛ መኾናችሁን

በውጊያው ሜዳ ላይ እንጂ
በልምምድ ሥፍራ ላይ አታሳዩኝ፤
ሃይማኖታችሁንም በመስማት ጊዜ ሳይኾን
በተግባር ጊዜ አሳዩኝ፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❣️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

እግዚአብሔርን እንደ ማመስገን ምንም በጎ ነገር የለም፡፡

የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ እንደ ማንሣትም (እንደ ማማረርም) ምንም ክፉ ነገር የለም፡፡

✅መንፈሳዊ ነገሮችን ማድረግ ስናበዛ

መከራው ቢበረታብን ምንም ልንደነቅ አይገባንም፡፡

✅ሌቦች

ወርቅና ብር ያለውን እንጂ ድርቆሽና ገለባ እንዲሁም ሰንበሌጥ ያለውን ቤት አይበረብሩምና፡፡

ዲያብሎስም የሚያጠቃው መንፈሳዊ ምግባራትን የሚያበዙትን ሰዎች ነው፡፡
በጎ ምግባር ባለበት ኹሉ ብዙ ወጥመዶች አሉ!
ቸርነት ባለበት ቅንአት አለ!

✅ እነዚህን ኹሉ ከንቱ የሚያደርግ

አንድ ፍቱን የጦር ዕቃ መሣሪያ ግን አለ፤

ስለ ኹሉም ነገር እግዚአብሔርን ማመስገን
!

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❣️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

ባለጸጋ ማለት

ብዙ ሀብት ያለው ሰው ማለት ሳይኾን ብዙ የሚሰጥ [ለሌሎች የሚያካፍል] ሰው ማለት ነው፡፡
አብርሃም ባለጸጋ ነበር፤ ስስታም ግን አልነበረም፡፡
የሰውን ሀብት ላግኝ ብሎ አልተመኘምና፤
ወይም የዚያን ሰው ሀብት ስጠኝ ብሎ አልጸለየምና፡፡
ከዚህ ይልቅ ማረፊያን (እንግዳ ተቀባይን) የሚሻ መንገደኛ ወይም ስለ ድኽነቱ ሊረዳው የሚችል ነዳይ ያለ እንደ ኾነ ለማየት ወደ ውጭ ወጣ እንጂ፡፡

የቤቱን ባጥ በወርቅ አልከደነውም፤
በዋርካ ዛፍ ሥር ድንኳን ተከለ እንጂ፤
በዛፊቱ ቅጠል ጥላ ደስ ተሰኘ እንጂ፡፡
መኖሪያ ቤቱ ግን ይህ ቀረሽ የማይባል ነበር፤

መላእክት እንኳን በቤቱ እንግዳ ኾነው ለማረፍ አላፈሩምና፡፡

ለምን?

የተመለከቱት የነፍሱን በጎነት እንጂ የቤቱን ማማር አይደለምና፡፡

ተወዳጆች ሆይ!

እንኪያስ እኛም ያለንን ለነዳያን በመስጠት አብርሃምን እንምሰለው፡፡

[የአብርሃም] መኖሪያ ቤቱ ደሳሳ ናት፤
ነገር ግን ከነገሥታት አዳራሽ ይልቅ እጅግ የተዋበች ነች፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❣️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ሥርዓተ ዋዜማ ዘቅዱስ ገብርኤል "ታኅሣሥ ፲፱"
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
@esate_yarade
ዋዜማ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ
አብሠራ ገብርኤል ለማርያም ወይቤላ ትወልዲ ወልደ፤ ሚካኤል መልአክ በክነፍ ፆራ፤ መንጦላዕተ ደመና ሠወራ፤ ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና፤ ወልድ፤ ተወልደ እምኔሃ።
@esate_yarade
@esate_yarade
ምልጣን
ሚካኤል መልአክ በክነፍ ፆራ፤ መንጦላዕተ ደመና ሠወራ፤ ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና፤ ወልድ ተወልደ እምኔሃ፤ ወልድ ተወልደ እምኔሃ።
@esate_yarade
@esate_yarade
አመላለስ፦
ወልድ ተወልደ እምኔሃ/2/
ወልድ ተወልደ እምኔሃ/4/
@esate_yarade
በ፭ ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ፦
ገብርኤል አብሠራ ለማርያም፤ ወይቤላ ትወልዲ ወልደ፤ ገብርኤል አብሠራ ለማርያም።
@esate_yarade
እግዚአብሔር ነግሠ፦
ገብርኤል አብሠራ ለማርያም፤ ተፈሥሒ ይቤላ፤ ኢሳይያስ ይቤላ ሐዳስዩ ጣዕዋ፤ ሰሎሞን ይቤላ ደብተራ።

@esate_yarade
ይትባረክ፦
ገብርኤል መልአክ መጽአ፤ ወዜነዋ ለማርያም ጥዩቀ፤ ሠናየ ዜና ከመ ይመጽእ አምላክ ላዕሌሃ።
@esate_yarade
@esate_yarade
ሰላም፦
አመ ፲፱ ለወርሀ ታኅሣሥ አመ ይትጋብዑ መላእክት፤ መልአከ ሰላሞሙ ውእቱ ገብርኤል፤ ገብርኤል ይስእል ምሕረተ፤ ለእንስሳ ሣዕረ ለሰብእ ተግባረ፤ መልአከ ሰላሞሙ ውእቱ ገብርኤል፤ ሚካኤል በየማነ ምሥዋዕ ይቀውም ዓውዶ፤ መልአከ ሰላሞሙ ውእቱ ገብርኤል፤ መልአከ ኪዳኖሙ ውእቱ ገብርኤል ስሙ።
@esate_yarade

አመላለስ፦
መልአከ ሰላሞሙ ውእቱ ገብርኤል/2/
መልአከ ኪዳኖሙ ውእቱ ገብርኤል ስሙ/4/

@esate_yarade
@esate_yarade

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

/channel/orthodox_tewahdo_mezmurs/116

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝እንኳን አደረሰነ!

✝ በዓለ ብርሃን፥ ዘመጽአ ውስተ ዓለም (ዝ ውእቱ መድኀኒነ ክርስቶስ)

✞ወበዓለ ቅዱሳን፦

✿መርህምናም ወሣራ
✿አግብርቲሁ ፵
✿፲ወ፯ቱ ፼ ሰማዕታት (ማኅበሩ)
✿ነሣሒት ዘሮሜ
✿አሞንዮስ ሰማዕት
✿ይስሐቅ ካህን (ዘእስና)
✿ገብረ ክርስቶስ ሊቀ ጳጳሳት
✿አርያኖስ ወአርክሊስ
✿ብሑር ወሚናስ
✿ስምዖን ዘመኑፍ
✿ያዕቆብ ዘአውሲም

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤
ኪያነኒ ይምሐረነ በጸሎቶሙ።
ወበረከቶሙ ይብጽሐነ፤ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡

/channel/zikirekdusn

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ታህሳስ 14/2017 #ፃድቁ_አባታችን_አቡነ_አረጋዊ
#ፃድቁ_ገብረ_ክርስቶስ

" ፃድቅን በፃድቅ ስም የሚቀበል የፃድቁን
ዋጋ ይወስዳል ማቴ.10፥42 "

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሳኑ ስም ለምናመሰግንበት ለቅዱሣን አባቶቻችን #አቡነ_አረጋዊ እና #ፃድቁ_ገብረ_ክርስቶስ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአላቸው እንኳን አደረሰን

👉በሃገራችን ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ እኒህ ፃድቅ ናቸው ፃድቁ የተወለዱት በአምስተኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ ኣካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ንጉሥ #ይስሐቅና ቅድስት #አድና ይባላሉ የተለወለዱበት አካባቢም ሮም ነው

👉ስማቸው ብዙ ዓይነት ነው ወላጆቻቸው #ዘሚካኤል ሲሏቸው በበርሃ #ገብረ_አምላክ ተብለዋል በኢትዮዽያ ደግሞ #አረጋዊ ይባላሉ #አቡነ_አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መፃሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ

👉በዚያም በገዳመ ዳውናስ ግብፅ የታላቁ #ቅዱስ_ዻኩሚስ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል ከመነኮሱ ከዓመታት በኋላም ወደ ሃገራቸው ሮም ተመልሰው በማስተማር ሰባት ያህል የቤተ መንግስት ሰዎችን ወደ ምናኔ ማርከዋል

👉የት ልሒድ ብለው ሲያስቡም #መልአክ_በክንፉ_ጭኖ ወስዶ ኢትዮዽያን አሳያቸው ተመልሰውም ለስምንቱ ባልንጀሮቻቸው ሃገርስ ባሳየሁዋችሁ ሐዋርያ ሳያስተምራት በሕጉ በሥርዓቱ ፀንታ የምትኖር ብለው ከስምንቱ ጋር ወደ ኢትዮዽያ መጡ

👉በዚህ ጊዜም እናታቸው ቅድስት እድናና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ ወደ ሃገራችን የመጡ በ470ዎቹ አካባቢ ሲሆን አልዓሜዳ በክብር ተቀብሏቸዋል በቤተ ቀጢን #አክሱም ተቀምጠውም መጻሕፍትን እየተረጐሙ ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል

👉ለሥራ በተለያዩ ጊዜም #አቡነ_አረጋዊ በዓት ፍለጋ ብዙ ደክመዋል በመጨረሻ ግን ደብረ ዳሞን (ደብረ ሃሌ ሉያን) አይተው ወደዷት የሚወጡበት ቢያጡም ጅራቱ 60 ክንድ የሚያህል ዘንዶ ተሸክሞ ከላይ አድርሷቸዋል

👉እንደ ወጡም #ሃሌ_ሉያ_ለአብ፤#ሃሌ_ሉያ_ለወልድ #ሃሌ_ሉያ_ለመንፈስ_ቅዱስ ብለው ቢያመሰግኑ ከሰማይ ሕብስት ወርዶላቸው ተመግበዋል በዚህም ቦታዋ ደብረ #ሃሌ_ሉያ ተብላለች ፃድቁ ቦታውን ከገደሙ በኋላ ከተለያየ ቦታ መጥተው ስድስት ሺ ያህል ሰዎች በእጃቸው መንኩሰዋል

👉ምናኔን በማስፋፋታቸውና ሥርዓቱን በማስተማራቸውም #የኢትዮዽያ_መነኮሳት_አባት ይባላሉ #አቡነ_አረጋዊ በሕይወታቸው ከተጋድሎ ባሻገር በወንጌል አገልግሎትና መጻሕፍትን በማዘጋጀትም ደክመዋል

👉 #ቅዱስ_ያሬድና አፄ ገብረ መስቀልም ወዳጆቻቸው ነበሩ በተራራው ግርጌ ያለችውን #ኪዳነ_ምሕረትን ለሴቶች ሲገድሟት ቀዳሚዋ መነኮስ እናታቸው ንግስት እድና ሁናለች

👉መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ የቅዱሣኑን ረድኤትና በረከት ለሁላችንም ያድለን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

እግዚአብሔር

ኃጢአት ርኅራኄዉን ከማሳየት እንዳልከለከለው
ወይም አለመታዘዝ ለአዳም ያለውን ፍቅር እንዳላጠፋው
እስከ አሁን ድረስም ለዚያ ለወደቀው መግቦቱንና ጠብቆቱን እንዳላቋረጠበት ሊያሳይ ወድዶ
“አዳም ሆይ ወዴት ነህ?” አለ (ዘፍ.3፡9)፡፡

እንዲህ ብሎ ሲጠራው

አዳም የት እንዳለ ጠፍቶት ሳይኾን

የበደሉ ሰዎች አፋቸው ስለሚዘጋ፣
በደል አንደበታቸውን ስለሚይዘው፣
ሕሊናም እንደዚህ ዓይነት ሰዎች
በአርምሞ ተይዘው እንዲቆዩና
በሰንሰለት እንደታሰሩ ኾነው ዝም እንዲሉ ስለሚያደርጋቸው ነው፡፡

በመኾኑም

በራሱ ስም ሲጠራው
የያዘው ብዙ ጭንቀትንና ፍርሐትን እንዲያስወግድ
የተዘጋው አፉም እንዲከፈትና
ሥርየተ ኃጢአትን እንዲያገኝ ሽቶ
አዳምን በነጻነት ይናገር ዘንድ ሲጠራው፣
መተማመንን ሲሰጠው፣
ስለ በደሎቹም ይቅርታን ይጠይቅ ዘንድ ሲመራው
እርሱ ራሱ ቀድሞ ጠራው፡፡

ስለኾነም፡-

አዳም ሆይ! ወዴት ነህ?
በአንድ ቦታ ላይ አስቀምጬህ ነበር፤
አሁን ግን በሌላ ቦታ አይሃለሁ፡፡
በእምነትና በክብር ትቼህ ነበር፤
አሁን ግን በሐፍረትና በጸጥታ አይሃለሁ!” አለው፡፡

እዚህ ላይ ያለው የእግዚአብሔር ኀዘኔታ ተመልከት!

ሔዋንን አልጠራትም - እባቡን አልጠራዉም -

አስቀድሞ ከኹሉም ይልቅ የበደለውን እርሱን ወደ ፍርድ ወንበር አመጣው እንጂ፤ ይኸውም ጥቂት ይቅርታን ሊያገኝ ከሚችለው ጀምሮ የምሕረት ፍርዱን እጅግ ኃጢአት በሠራችው በሔዋንም እንኳን ለመፍረድ ነበር፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❣️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ታህሳስ 13/2017 #መልአኩ_ቅዱስ_ሩፋኤል

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በመልአኩ ስም ለምናመሰግንበት ለመልአኩ #ለቅዱስ_ሩፋኤል ለቅዳሴ ቤቱና ለተአምር በአሉ አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉ታኅሣሥ ዐስራ ሦስት በዚህች ቀን በዚህች ዕለት ፈታሄ ማህፀን ሊቀ መልአክት #ቅዱስ_ሩፋኤል ቅዳሴ ቤቱና ተአምር ያደረገበት ዕለት ነው

👉ሰማያውያን ከሆኑ ከመላአክት አለቆች ከቅዱስ ሚካኤልና ከቅዱስ ገብርኤል ቀጥሎ 3ተኛ ነው "ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ #እኔ_ሩፋኤል ነኝ” እንዲል ጦቢት.12፥15 ሩፋኤል የሚለው የስሙ ትርጓሜ ደስ የሚያሰኝ ቸር መሐሪ ቅን የዋህ ማለት ነው፡፡

👉 #ቅዱስ_ሩፋኤል መልአክ የሰላምና የጤና መልአክ ይባላል በሰውነታችን ላይ የሚወጣውን ደዌም ሆነ ቁስል ይፈወስ ዘንድ ከልዑል እግዚአብሔር ሥልጣን ተሰጥቶታል “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” መጽሐፈ ሄኖክ.6፥3

👉#ቅዱስ_ሩፋኤል የሰው ልጆች ከተያዙበት የኀጢአት ቁስል ይፈወሱ ዘንድ በአማላጅነቱና በጸሎቱ የማይለይ መልአክ ነው “በበሽታ ሁሉ ላይ በሰው ልጆችም ቁስል ላይ የተሾመው ቅዱስ ሩፋኤል ነው በማለት ሄኖክ #ከእግዚአብሔር መልአክ ያገኘውን የምስክርነት ቃል ፅፏል ሄኖክ.10፥13

👉ለሴቶች ረዳታቸው #ቅዱስ_ሩፋኤል ነው በማኅፀን ላለ ችግርና ሴት በፀነሰችበት ወቅት ቅዱስ ሩፋኤል አይለያትም ሕፃኑ ዐርባ ቀን ሞልቶት በማሕፀን እያለ ማለትም በሥላሴ አርአያ መልኩ መሳል ከጀመረበት ቀን አንሥቶ እስከሚወለድበት ቀን ድረስ #ቅዱስ_ሩፋኤል አይለየውም

👉በመውለጃቸው ቀን ሴቶች ከሚደርስባቸው ጭንቀትና ሕመም ስሙን ጠርተው ይማጸኑታል ፈታሔ ማኅፀን ነውና ቅዱስ ሩፋኤልም ጭንቀታቸውን ያቀላል #ቅዱስ_ሩፋኤል በሰውነት ያለን ረቂቅ ርኩስ መንፈስ ያውቃል

👉አስማንድዮስ የተባለ ጋኔን በወለተ ራጉኤል ጭን ላይ አድሮ ባሎቿን እየገደለ ቢያሠቃያት #ቅዱስ_ሩፋኤል ጋኔኑን አስጨንቆ አስወጥቶላታል ጦቢት.3፥8-17

👉ዳግመኛም #እግዚአብሔር ሩፋኤልን አዛዝኤልን እጁን እግሩን አስረህ በጨለማ ውስጥ ጣለው አለው ሄኖክ3፣5-7 በዚህ መሠረት ለቃየን ልጆች ሰይፍና ሾተል መሥራትን የምንዝር ጌጥ ማጌጥን መቀንደብን ያስተማረ አዛዝኤል የተባለውን ጋኔን በእሳት ሰይፍ እየቀጣ በረቂቅ አስሮ ወደ ጥልቁ የጣለው ይኸው መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ነው ሄኖክ.2፥18 ሰማያዉያን መዛግብት በእጁ የሚጠብቃቸው #እግዚአብሔር እንዳዘዘዉ የሚከፍታቸዉ የሚዘረጋቸዉ ይህ ታላቅ መልአክ ነዉ

👉የምህረትና የረድኤት መልአክ #ቅዱስ_ሩፋኤል ከሥራዎቹ አንፃር በተለያየ ስም ይጠራል #ፈታሔ_ማህጸን ይባላል እናቶች ሲወልዱ ምጥ እንዳይበዛባቸዉ የሚራዳ መልአክ ስለሆነ አያሌ ክርስቲያኖች ማርገዛቸዉን ካወቁ ጀምሮ ድርሳኑን በማንበብ መልኩን በመድገም ጠበሉን በመጠጣት ሰዉነታቸዉን በመቀባት ይለምኑታል እንደ እምነታቸዉ ጽናት ይደረግላቸዋል

👉ዳግመኛም #ዐቃቤ_ኖኀቱ_ለአምላክ ይባላል ሰማያዉያን መዛግብት በእጁ የሚጠበቅ ስለሆነ ነው ዳግመኛም "መራሔ ፍኖት" ይባላል

👉ጦቢትን በቀና መንገድ መርቶታልና ነው እንዲሁም "መላከ ክብካብ" ይባላል ጦቢያና ሣራን ያጋባ ጋብቻቸዉን የባረከ በመሆኑ ነው የመልአኩ #ቅዱስ_ሩፋኤል ስንክሳር ከብዙ በጥቂቱ ለበረከት ይሄን ይመስላል የመልአኩ ጥበቃና ተራዳኢነት አይለየን ሀገራችንን ህዝባችንን ይጠብቅልን የተባረከ የተቀደሰ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

👉ሰለሞን የገብርኤል
👉ታህሳስ 13/2017

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

አባ ሳሙኤልን የዱር አራዊትም ሁሉ ይገዙለት ነበር፡፡ ታላቅ የሆነ ዘንዶ፣ ነብር፣ ጅብ፣ ቶራህ፣ ዝሆን፣ አንበሳና ሌሎችም የዱር አራዊት ሁሉ እየመጡ እግሩን እየላሱት ወደ ቦታቸው ይመለሱ ነበር፡፡ አንበሶቹንም እሾህም በወጋቸውና እግራቸው መግል በያዘ ጊዜ በመርፌ እያነቆረ ያድናቸው ነበር፡፡ ስንጥርም ሲወጋቸው ወደ እርሱ እየመጡ ያሳዩትና ያወጣላቸው ነበር፡፡ አንበሳም አጋዘንን ገድሎ ሲበላ ሲያየው ‹‹አንዴ ዞር በልልኝ ቆዳዋን ለልብሴ እፈልገዋለሁ›› ባለው ጊዜ ይለቅለት ነበር፡፡ እንዲሁም አንበሳው ለአባታችን ምግብም ትሆነው ዘንድ ጅግራን እየያዘ በሕይወት ሳለች ያመጣለት

ነበር፡፡ አባታችንም ከገዳም ወጥቶ መሄድ በፈለገ ጊዜ አንበሶችን እንደ ፈረስና በቅሎ ይጋልባቸዋል፣ መጻሕፍቶቹንም ይጭንባቸዋል፤ መንታ የወለደች አንበሳም ብትኖር ልጆቿን እየታቀፈ በየተራ ያጠባቸው ነበር፡፡

ወደ ደብረ ዋሊም በሄደ ጊዜ ጌታችን ተገልጦለት በዕለቱ የእመቤታችን በዓል ስለነበር እንዲቀድስ ነግሮት ከሰማይ ኅብስትና ጽዋ መጥቶለት ቅዱሳን ሐዋርያት በቀኝ በግራ እየተራዱት ሲቀድስ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ ኅብስቱንና ጽዋውን ጋርዶታል፡፡ ጌታችንም ቦታዋንና በዚያ ያሉትን መነኮሳት ሁሉ ልጆቹ ይሆኑ ዘንድ አስራት አድርጎ ሰጠው፡፡ ዋልድባ የተመሠረተው በቀደምት ጥንታዊያን አበው ቢሆንም አባ ሳሙኤል ሲገቡበት ምድረ በዳ ሆኖ ጠፍቶ ቋያ በቅሎበት የወባ ትንኞች መፈልፈያ ሆኖ ነበር፡፡ አባታችን ግን የተበታተኑትን መነኮሳት ሰብስበው ዋልድባን እንደገና አደራጅተውና አድሰው አቀኑት፡፡ የተባሕትዎ ኑሮንም አጠናከሩበትና ገዳሙን የመናንያን አበው መሰብሰቢያ አደረጉት፡፡ አባታችን ዋልድባን እንደ ሞሰብ አንስተው አስባርከዋታል፡፡

አባ ሳሙኤል ጊዜው ደርሶ ከማረፉ በፊት ቅዱስ ሚካኤል ነሐሴ 16 ቀን ወደ ገነት ነጥቆ ወስዶ ከዕረፍቱ በኋላ ከልጆቹ ጋር የሚኖርበትን ሥፍራ አሳይቶታል፡፡ በገነት ያሉ ቅዱሳንን ሁሉ ካሳየው በኋላ በእግዚአብሔርም ዙፋን ፊት ቀርቦ ምስጋናና ቃልኪዳንን ተቀብሎ ወደ በዓቱ ተመልሶ ታኅሣሥ 12 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፎ ነፍሱን ጌታችን በእጆቹ ተቀብሏታል፡፡

መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ የገባላቸው ልዩ ቃልኪዳን፡- ‹‹መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልም ወደ ገነት ነጥቆ ወስዶ በዚያ ያሉ ቅዱሳንን ሁሉ መኖሪያቸውንና ክብራቸውን አሳየኝ፡፡ ‹እነሆ የተጋድሎህን ሥራ ፈጽመሃልና አንተም ወደተዘጋጀችልህ ትመጣ ዘንድ ጊዜህ ቀርቧል› ብሎ ጌታዬ የሰጠኝን መኖሪያዬን አሳየኝ፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ ልዑል ዙፋን ወደ አርያም አደረሰኝ፡፡ በዚያም በክብሩ ዙፋን በአባቱ ቀኝ ተቀምጦ ተወዳጅ ወልድን አየሁት፡፡ በዚያም እመቤታችን ማርያምን ከተወዳጅ ልጁዋ ቀኝ አየኋት፡፡ የብዙ ብዙ ቅዱሳን መላእክትና ጻድቃን ሰማዕታት ሁሉ በየወገናቸው ‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ፍጹም አሸናፊ እግዚአብሔር የክብር ምስጋና ሰማያትንና ምድርን መላ› እያሉ በፊቱ ይዘምሩ ያመሰግኑ ነበር፡እኔም በአምላኬ ፊት ሰገድኩ፡፡ ተወዳጅ ወልድም ተናገረኝ፣ እንዲህም አለኝ፡- ‹ወዳጄ ሳሙኤል ሆይ! ሰላምታ ይገባሀል፣ ደስ ይበልህ፡፡ በጥቂቱ የታመንህ ባሪያዬ ሆይ በብዙ እሾምሃለሁ፡፡ እኔን በመውደድ ብዙ ደክመሃልና የመስቀሌንም መከራ በመሸከም እኔን መስለሃልና እኔም በመንግሥቴ መልካም የሆነውን የድካምህን ዋጋ እሰጥሃለሁ፡፡ እነሆ ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የተካከለ መቀመጫህንና አክሊልህን አዘጋጀሁልህ፣ ዕድል ዕጣህም ከአሥራ ሁለቱ ቅዱሳን ሐዋርያቶቼ ጋር ነው፡፡ አፅምህ በተቀበረበት፣ የገድልህ መጽሐፍ በተነበበት፣ መታሰቢያህ በተደረገበት፣ ሥፍራ ሁሉ ምሕረትና ድኅነት ይሁን፡፡ በጸሎትህ የሚታመነውን፣ መታሰቢያህን የሚያደርገውን ሁሉ ለአንተ አሥራት ሰጥቼሃለሁ፡፡ ስለ እኔ የተቀበልከውን ድካም ሁሉ ዛሬ ያገኘኸውን የአንዲት ቀን የደስታ ልክ አይሆንም፡፡››

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ሰማዕታቱ_ቅዱስ_አንቂጦስ_እና_ቅዱ_ፎጢኖስ

ዳግመኛም በዚህች ቀን ወንድማማቾቹ ቅዱሳን አንቂጦስ እና ቅዱስ ፎጢኖስ በሰማዕትነት ዐረፉ፡፡ ከሃዲው ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ መእመናንን የሚያሠቃይባቸውን የማሠቃያ መሣሪያዎች ለሕዝቡ እያሳየ ሲያስፈራራ የጸኑንም ሲገድል ቅዱስ አንቂጦስ በሕዝቡ መሐል ቆመና ንጉሡን ስለከንቱ እምነቱ ዘለፈው፡፡ ንጉሡም ይዞ ብዙ ካሠቃየው በኋላ በሕዝቡ ፊት ለተራበ አንበሳ ሰጠው፡፡ ነገር ግን አንበሳው ቅዱስ አንቂጦስን ፊቱን አሻስቶ ሲተወው በማየቱ ንጉሡ ሰይፉን መዞ ሊሰይፈው ሊሄድ ሲል መንቀሳቀስ ተሳነው፡፡ ከዚህም በኋላ ሰውነትን ቆራርጦ ወደሚጥል መንኮራኩር ውስጥ ከተተው ነገር ግን ሰማዕቱን ጌታችን ፍጹም ጤነኛ አድርጎ አስነሣው፡፡

ንጉሡ ዳግመኛ ቅዱስ አንቂጦስ እርሳስ ካፈሉበት ትልቅ ጋን ውስጥ ቢጨምረውም የታዘ መልአክ ከጋኑ ውስጥ ነጥቆ አውጥቶ በንጉሡ ፊት አቆመው፡፡ ይህን ጊዜም ወንድሙ ፎጢኖስን አንጢቆስን አቅፎ ካሳመው በኋላ ንጉሡን ‹‹አንተ ከዳተኛና ጎስቋላ ንጉሥ ወንድሜን ታሸንፈው ዘንድ አይቻልህም አምላኩ ይጠብቀዋልና›› አለው፡፡ ንጉሡም የሚያደርግባቸውን ነገር እስኪያስብ ድረስ ቅዱሳኑን ወንድማማቾቹን እጅና እግራቸውን አሳሥሮ ወህኒ ቤት ጨመራቸው፡፡

በማግሥቱም አውጥቶ ሰውነታቸውን ጥፍር ባለው ብረት ሰነጣጠቃቸው፡፡ ወደ አደባባይም አውጥቶ በድንጋይ አስወገራቸው፡፡ ከብዙ ግርፋትም በኋላ በቁስላቸው ላይ ጨው ጨምሮ ካሠቃያቸው በኋላ እሳት ውስጥ ጨመራቸው፡፡ ነገር ግን አሁንም እሳቱ እንደቀዝቃዛ ጠል ሆነላቸው፡፡ ንጉሡም ይህን ባየ ጊዜ ነበልባሉ ከፍ ብሎ እስኪታይ ድረስ እሳት አስነድዶ ከዚያ ውስጥ ጨመራቸው፡፡ ቅዱሳኑም ከእሳቱ ውስጥ ሆነው በመስቀል ምልክት አማትበው ረጅም ጸሎት ካደረጉ በኋላ ቅድስት ነፍሳቸውን ለእግዘኢብሔር አሳልፈው ሰጡ፡፡ የሥጋቸውም በድን ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሌሊቱ 6 ሰዓት ድረስ ከእሳቱ ፍሕም ላይ ነበር ነገር ግን የራሳቸው ፀጉር እንኳን አልተቃጠለችም ነበር፡፡ ምእመናንም ቅዱስ ሥጋቸውን ወስደው በክብር አስቀመጡት፡፡ ከሥጋቸውም ብዙ አስደናቂ ተአምራት ተፈጽመው ታዩ፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ዳግማዊ_ቂርቆስ (የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ልጅ)

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

✝እንኳን አደረሰነ!

✞በዓለ ቅዱሳን፦

✿ሚካኤል ሊቀ መላእክት
✿ሳሙኤል ጻድቅ (ዘዋልድባ)
✿ዘሩፋኤል ረድኡ
✿ሠለስቱ ደቂቅ
✿ነድራ ጻድቅ (ዘደብረ እስዋን)
✿አልዓዳድ ንጉሠ ሮሜ
✿አንቂጦስ ወፎጢኖስ (ሰማዕታት)
✿ቂርቆስ ዳግማይ (ወልዳ ለሠምራ ክርስቶስ)
✿ዮሐንስ ተአማኒ (ዘኢትዮጵያ)
✿ጉቡአን ጳጳሳት (ዘሮሜ)
✿እንጦንዮስ ወአውሲስ ወመሐር

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤
ኪያነኒ ይምሐረነ በጸሎቶሙ።
ወበረከቶሙ ይብጽሐነ፤ ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡

/channel/zikirekdusn

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ቅዱስ ጳውሎስም እንዲህ ሲል ይጠይቅሃል፡-

ወይስ የእግዚአብሔር ቸርነት ወደ ንስሐ እንዲመራህ ሳታውቅ የቸርነቱንና የመቻሉን የትዕግሥቱንም ባለጠግነት ትንቃለህን?” (ሮሜ.2፡4)፡፡

ስለዚህ እግዚአብሔር የሚታገሥህ በኃጢአት ላይ ኃጢአት እንድትጨምር ሳይኾን ንስሐ እንድትገባ ነው፡፡

አንተ ንስሐ ለመግባት ፈቃደኛ ሳትኾን የምትቀጥል ከኾነ ግን ይህ ትዕግሥት ታላቅ ፍዳ ይኾንብሃል፡፡

ወባሕቱ በአምጣነ ታጸንዕ ልብከ ወኢትነስሕ ትዘግብ ለከ መቅሰፍተ ለእመ ይበጽሐከ ኵነኔሁ ለእግዚአብሔር፡፡
እስመ ውእቱ ይፈድዮ ለኵሉ በከመ ምግባሩ በኵነኔ ጽድቁ


ነገር ግን እንደ ጥንካሬህና ንስሐ እንደማይገባ ልብህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ በሚገለጥበት በቊጣ ቀን
ቊጣን በራስህ ላይ ታከማቻለህ፡፡


እርሱ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ያስረክበዋል” ብሎ ሲል ይህን ሲናገር ነውና (ሮሜ.2፡4-5)፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❣️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ታህሳስ 11/2017 #ማህሌታዊዉ_ቅዱስ_ያሬድ
#እናታችን_ቅድስት_ሐና

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሳኑ ስም ለምናመሰግንበት #ማህሌታዊዉ_ቅዱስ_ያሬድ ዜማዎቹን ለቅድስት ቤተክርስቲያን ላዋለበት አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉ቅዱስ ያሬድ #ከእግዚአብሔር ያገኘነው አባታችን ክብራችን ሞገሳችን ነውና በምን እንመስለዋለን

👉አንደበቱ ጣፋጭ ልቡናው #የቅድስና_ማሕደር ሕሊናው የምሥጢራት ሠረገላ ነው እስከ አርያም ተነጥቆ የማይፈፀም ምሥጢርን የተመገበ ማን እንደርሱ

👉ቅዱስ ያሬድ #ለኢትዮዽያ_ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከራስ ፀጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ ሙሉ አካሏ ነው ቅዱስ ያሬድ የተወለደው በ505 ዓ/ም አክሱም አካባቢ ሲሆን እናቱ ክርስቲና (ታኡክልያ) አባቱ ደግሞ ይስሐቅ (አብድዩ) ይባላሉ

👉 #ቅዱስ_ያሬድ በሕፃንነቱ ምሥጢር (ትምሕርት) አልገባው ብሎ ይቸገር ነበር ትምሕርት እንቢ ያለው ሰነፍ ስለ ነበር አይደለም በጥበበ #እግዚአብሔር እንጂ ምን ትምሕርት ባይገባው ፆምና ጸሎትን ያዘወትር ነበር

👉ልቡናው ደግሞ በእመቤታችንና በልጇ ፍቅር የታሠረ ነበር አንድ ቀን ግን መምሕሩ የነገሩት ቀለም አልያዝሕ አለው ሲፈትኑትም ባለመመለሱ ተገረፈ ዱላው በጣም ስለ ተሰማው ቅዱሱ ከመምሕሩ ኮብልሎ #ማይ_ኪራሕ አካባቢ ሲደርስ ደክሞት አርፎ እግዚአብሔር ትጋትንና ተስፋ አለመቁረጥን ከትል አስተማረው ትሏ ስድስት ጊዜ ወድቃ በሰባተኛው ፍሬዋን ስትበላት ተመልክቷልና

👉ከዚህ በኋላ #ቅዱስ_ያሬድ ወደ መምሕሩ ተመልሶ ይቅርታ ጠይቆ ትምሕርት ጀመረ ሊቁም ትጋትንና ጸሎትን ከሰጊድ ጋር አበዛ እግዚአብሔር ደግሞ በድንግል እናቱ አማካኝነት የምሥጢር ጽዋን አጠጣው

👉 #ካህኑ_ያሬድ እንዲያ አልገባህ ያለው ምስጢር ተገልጦለት በጥቂት ጊዜ ብሉይ ከሐዲስ ወሰነ በምሥጢር ባሕርም ይዋኝ ጀመር ያን ጊዜ ሰማያዊ ዜማ አልተገለጠም ነበርና በጸሎት ላይ ሳለ ተደሞ መጣበት #ሦስት_መላእክት በሦስት ወፎች አምሳል መጥተው አነጋገሩት ድንገትም ነጥቀው ወደ #ሰማያት ወደ ልዑላኑ መላእክት ዘንድ አደረሱት

👉ሊቁ በሰማያት ልዩ ምሥጢር ልዩ #ምስጋናና ልዩ #ዜማን አዳመጠ ይሕንን ምስጋና ብዙ ቅዱሳን ቢሰሙትም ቅዱስ ያሬድ ግን ይዞት እንዲወርድ ተፈቀደለት ሊቁ ወደ ምድር ተመልሶ በታላቅ ተመስጦ አክሱም ጽዮን ውስጥ በሃሌታ አመሰገነ ሕዝቡና ንጉሡም ከጣዕሙ የተነሳ አደነቁ #ቅዱስ_ያሬድ ለተወሰነ ጊዜ በአክሱምና ደብረ ዳሞ ሲያገለግል ቆይቶ ከመሬት ክንድ ከስንዝር ከፍ ብሎ ለእመቤታችን አንቀጸ ብርሃንን ደርሶላታል

👉 #ቅዱስ_ያሬድ በቀሪ የሕይወቱ ዘመናት አምስት ያሕል መጻሕፍትን ፅፏል በጣና ቂርቆስ በዙር አንባና በሌሎችም ቦታዎች ወንበር ዘርግቶ ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርቷል በሰሜን ተራሮች አካባቢ በትጋት እንደ #መላእክት በተባሕትዎ ኑሯል በተወለደ በ71 አመቱ ተሰዉሯል የአባታችን ታሪክ ከብዙ በጥቂቱ ይህን ይመስላል

👉የማህሌታይ #ቅዱስ_ያሬድ የእናታችን #ቅድስት_ሐና እንዲሁም በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የሚዉሉ ቅዱሣን ረድኤትና በረከት ለሁላችንም ይድረሰን "አሜን"

👉ሰለሞን የገብርኤል
👉ታህሳስ 11/2017

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ክፉውን_በክፉ_አለመቃወም

ክፉውን በክፉ አለመቃወም ማለትም

ክፉውን ነገር በክፉ ድል ለመንሣት አለመዘጋጀት ፣
ክፉውን ግብር በክፉ ግብር አለመቃወም
በጠቅላላው አለመበቀል ማለት ነው።


ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ

«ለማንም ስለ ክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤
በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ።
ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።


ተወዳጆች ሆይ

ራሳችሁ አትበቀሉ ፥
ለቁጣው ፈንታ ስጡ እንጂ»በማለት የተናገረው።

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

ተወዳጆች

ባለጸጋው ሰው ስለ ሀብቱ ብዛት የብዙ ሰዎች ባሪያ ነው፡፡
ብዙ ነገሮችን ከመውደዱ የተነሣ ብዙ ሰዎችን ለመሸንገል፣
በአድርባይነትም ሊያገለግላቸው ይገደዳል፡፡


ድኻው ሰው ግን

እንዴት መንፈሳዊ ሊኾን እንደሚገባው ካወቀበት
ሰውስ ይቅርና ዲያብሎስ ራሱም ቢኾን እንደዚህ አያጠቃውም፡፡


እንዲህም ስለ ኾነ

ኢዮብ አስቀድሞ ብርቱ እንደ ነበረው
በኋላም ሀብቱንና ንብረቱን
እንደዚሁም ልጆቹን ኹሉ ሲያጣ
ይበልጥ ኃይለኛ ኾነ፤
ዲያብሎስን ድል በማድረጉ
[ከእግዚአብሔር ዘንድ] ታላቅ የኾነ ውዳሴን አገኘ (ኢዮ.42፡7)!


ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❣️

Читать полностью…

የ ቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች

#አባ_ሳዊሮስ_የሥጋ_ፍልሰት_ከእስክድርያ_ወጪ_ወደሆነች_ደብረ_ዝጋግ_ገዳም፦ እንዲህም ሆነ ይህ ቅዱስ አባት በአገረ ስሓ አምላክን በሚወድ ክርስቲያን ባለጸጋ ስሙ ዱራታዎስ በሚባል ሰው ዘንድ በዐረፈ ጊዜ እርሱም ከምእመናን ሰዎች ጋር በመርከብ አሳፍሮ ላከው በጥልቅ ባሕር ላይ እንጂ በአነስተኛ ሸለቆ እንዳይሔዱ ከዚያም በወደቡ እንዲወጡ አዘዛቸው።

❤ ወደ ደቡባዊ ባሕረ ቅርጣስ በደረሱ ጊዜ የቅዱሱም ሥጋ ከእርሳቸው ጋር ሳለ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ጥቂት እንደተጓዙ መርከቡን የሚሸከም ውኃ አላገኙም መርከቡንም እየጐተቱ ታላቅ ድካምን ደከሙ መርከባቸውንም ወደ ኋላ ይመልሱ ዘንድ አሰቡ ግን አልተቻላቸውም ፈጽሞ አዘኑ ደነገጡም ዕውቀታቸውም ተሠወራቸው ሰውን የሚወድ እግዚአብሔር የእስራኤል ልጆች ከጠላቶቻቸው ፊት ሰውሮ በኤርትራ ባሕር ውስጥ መንገድ ገልጦ ያላለፋቸው እርሱ የቅዱስ ሳዊሮስን ሥጋ መለካውያን ከሆኑ ከከሀድያን ሰዎች ሠወረ እነርሱ በሕይወቱ ሳለ ይጠሉት ነበርና እንዲሁ ከሞተ በኋላ ቃሉ እንደ ሰይፍ የሚቆራርጣቸው ሆነ።

❤ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ከተአምራቱ ገለጠ ያቺን መርከብ ወደሚወጡበት ወደብ እስከምትደርስ በጥቂት ውኃ ላይ ሰባት ምዕራፍ ያህል እንድትጓዝ አደረጋት ገዳም ከዚያም ተሸክመው ወደ ደብረ ዝጋግ ገዳም አድርሰው ያ ባለጸጋ ዱራታዎስ በሠራለት ቦታ ውስጥ አኖሩት በግብጽ አገርም ታላቅ ደስታ ሆነ ይልቁንም በእስክንድርያ ከተማ። እግዚአብሔርም ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራቶችን ገለጠ በሕይወቱ ሳለ ከጥርሶቹ የወደቀች አንዲት ነበረች የደብረ ዝጋግ ገዳም አንድ መነኵሴ አንሥቶ በሐር ጨርቅ ጠቅልሎ አኖራት እርሷም ለታመሙ ሕዝቦች የምትፈውስ ሆነች እነርሱም ወደ እስክንድርያ አገር ያመጧትና በበሽተኞች ላይ ያኖሩዋታል እነርሱም ይድናሉ። እግዚአብሔርም ቅዱስ ሳዊሮስን በሕይወቱ ካለበት ጊዜ ይልቅ ከሞተ በኋላ እጅግ ከፍ ከፍ አደረገው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሳዊሮስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

✝ ✝ ✝
❤ #አባ_ኒቆላዎስ፡- አባቱ ኤጲፋንዮስ እናቱ ዮና ይባላሉ፡፡ እርሱም ሜራ በምትባል አገር እጅግ ባለጸጎች ሆነው የሚኖሩ ደጋግ ሰዎች ናቸው፡፡ እጅግ ባለጸጎች ቢሆኑም ልጅ ስላልነበራቸው እያዘኑ እግዚአብሔርን በመለመን ብዙ ዘመን ኖሩ፡፡ የመውለጃ ጊዜአቸውም ባለፈ ጊዜ ስለ ልጅ መለመናቸውን አቆሙ፡፡ እግዚአብሔር ግን በመጨረሻ ዘመናቸው የተባረከ ይህን ኒቆላዎስን ሰጣቸው፡፡ እግዚአብሔርም በልጃቸው ላይ የጽቅን ሥራ ገለጠ፡፡ ልጁ ገና እንደተወለደ ተነሥቶ በእግሮቹ ቆሞ በሰዎች መካከል ለሁለት ሰዓት ያህል ቆመ፡፡ ይህም ለመንደሳዊ ሥራ የተነሣ ቅዱስ መሆኑን ያጠይቃል፡፡ በሕፃንነቱም የሐዋርያትን ትምህርት ፈጽሞ ረቡንና ዓርብን በመጾም እስከ ዘጠኝ ሰዓት የእናቱን ጡት አይጠባም ነበር፡፡

❤ ከዚህም በኋላ ወላጆቹ ለመምህር ሰጥተውት የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሁሉ ተማረ፡፡ ወደ ገዳምም ገብቶ ማንም እንደ እርሱ ሊሠራው የማይችለውን ጽኑ ገድል ተጋደለ፡፡ ዘጠኝ ዓመትም በሆነው ጊዜ ቅስና ተሾመና ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን ማድረግ ጀመረና ሕመምተኞችን ሁሉ የሚፈውሳቸው ሆነ፡፡ አንድ ባለጸጋ በሀገሩ ነበር፡፡ እርሱም የዕለት እራት ድረስ ፈጽሞ ድኃ ሆነ፡፡ አራት ሴት ልጆችም ነበሩትና እነርሱን ስለድኅነቱ የሚያገባቸው ጠፋ፡፡ ባለጸጋ የነበረውም ሰው የዝሙት ሙት ሠርቶ በዚያ ልጆቹ እያመነዘሩ በዝሙት ዋጋ ይኖሩ ዘንድ ይህንን የረከሰ ሀሳብ ሰይጣን አሳሰበው፡፡

❤ እግዚአብሔር ግን የዚያን ባለጸጋ የነበረ ሰው ክፉ ሀሳብ ለአባ ኒቆላዎስ ገለጠለት፡፡ አባ ኒቆላዎስም ከአባቱ ገንዘብ ላይ መቶ የወርቅ ዲናር ወስዶ በሌሊት ማንም ሳያየው ወደዚያ ባለጸጋ ወደነበረው ሰው ቤት ሄዶ በበሩ ሥር አስቀምጦለት ተመለሰ፡፡ ባለጸጋ የነበረውም ሰው ወርቁን ወስዶ እጅግ ደስ ብሎት ታላቂቱን ልጁን አጋባት፡፡ አሁንም ለ2ኛ ጊዜ አባ ኒቆላዎስ መቶ የወርቅ ዲናር አስቀመጠለትና ሰውየውም ሌላኛዋን ታላቅ ልጁን ዳራት፡፡ አባ ኒቆላዎስም ለ3ኛ ጊዜ እንዲሁ አደረገ፡፡ ባለጸጋውም በስተመጨረሻ "ይህን የሚያደርግልኝ የእግዚአብሔርን ሰው ማየት አለብኝ" ብሎ ቁጭ ብሎ እያደረ በሌሊት የሚመጣውን መጠበቅ ጀመረ፡፡ አባ ኒቆላዎስም ለ4ኛ ጊዜ ወርቁን ሲያኖርለት አገኘውና ወድቆ ሰገደለት፡፡ "ከገንዘብና በኃጢአት ከመውደቅ አድነኸኛልና ዋጋህ ፍጹም ነው" ብሎ አመሰገነው፡፡ አባ ኒቆላዎስ በአካባቢው ባለው ዛፍ ላይ አድረው በሰውየው ላይ መከራ ያመጡበትን አጋንንት አባረራቸው፡፡ በዚያ የነበሩ ሕመምተኞችንም አዳናቸው፡፡ ዳግመኛም ጥቂት እንጀራን አበርክቶ ብዙ ሕዝቦችን አጠገባቸው፡፡ እጅግ የበዛ ትራፊም ተመልሶ ተነሣ፡፡

❤ ከዚህም በኋላ አባ ኒቆላዎስ ኤጲስቆጶስነት ከመሾሙ አስቀድሞ የክህነት ልብስንና ብርሃንን የለበሰ ሰው በዙፋን ላይ ተቀምጦ በራእይ አየና "ይህንን የክህነት ልብስ ለብሰህ በዙፋኑ ተቀመጥ" የሚል ድምጽ ሰማ፡፡ ለሁለተኛ ጊዜም እመቤታችን ተገልጣለት የክህነትን ልብስ ስትሰጠው ጌታችንም የከበረች ወንጌልን ሲሰጠው አየ፡፡ ከዚህም በኋላ የሜራ አገር ኤጲስቆጶስ በሞት ባረፈ ጊዜ የታዘዘ መልአክ ለሮሜው አገር ሊቀ ጳጳስ ተገለጠለትና ስለ አባ ኒቆላዎስ መልኩንና ስሙን በዝርዝር ነገረው፡፡ እርሱም ለሕዝቡ ሁሉ ነገራቸው አባ ኒቆላዎስን ወስደው በሜራ አገር ላይ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት፡፡

❤ ከሃዲው ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ አምለኮ ጣዖትን በግዛቱ ሁሉ ሲያውጅና የክርስቲያኖችን ደም እንደውኃ ሲያፈስ አባ ኒቆላዎስ ደግሞ ክርስቲያኖችን ያስተምራቸውና በሃይማኖት ያጸናቸው ነበር፡፡ ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ አባ ኒቆላዎስን ይዞ እጅግ ብዙ አሠቃየው፡፡ ነገር ግን ጌታችን ከመከራው ሁሉ እያዳነው ከቁስሉም ይፈውሰው ነበር፡፡ ንጉሡም እጅግ ቢያሠቃየውም ቅዱሱ ደግሞ መልሶ ጤነኛ ሆኖ ያገኘዋል፡፡ በዚህም ማሠቃየት ቢሰለቸው ወደ እሥር ቤት ጨመረው፡፡ እግዚአብሔርም ዲየቅልጥያኖስን አጥፍቶት ጻደቁን ቆስጠንጢኖስን እስካነገሰው ድረስ አባ ኒቆላዎስ በእሥር ቤት ብዙ ዓመታት ኖረ፡፡

❤ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስም የታሰሩትን ቅዱሳን ሁሉ በፈታቸው ጊዜ አባ ኒቆላዎስ ከእሥር ወጥቶ ወደ መንበረ ጵጵስናው ተመለሰ፡፡ ሕዝቡንም ስለቀናች ሃይማኖት አስተማራቸው፡፡ ሃይማኖታቸው የቀና እጅግ የከበሩ 318 ቅዱሳን በአርዮስ ጉዳይ በተሰበሰቡ ጊዜ ይህ ቅዱስ አባት አባ ኒቆላዎስ ከእነርሱ ውስጥ አንዱ ነው፡፡ እርሱም ከሌሎቹ ቅዱሳን ጋር ሆኖ አርዮስን አሳዶ የቀናች ሃይማኖትን ደነገገልን፣ ሥርዓትን ሠራልን፡፡ እርሱም ተጋድሎውን ፈጽሞ በዚህች ዕለት ታኅሣሥ10 በሰላም ዐረፈ፡፡ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ኒቆላዎስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ትደርብን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ 10 ስንክሳር።

✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ዘረወ ወወሀበ ለነዳይ። ወጽድቁኒ ይነብር ለዓለም። ወይትሌዓል ቀርኑ በክብር"። መዝ 109፥9። የሚነበቡት መልዕክታት ቲቶ 1፥5-12 ወይም 1ኛ ቆሮ 9፥1-15፣ 1ኛ ዮሐ 2፥20-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 20፥16-22። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 6፥1-5። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የአባ ኒቆላዎስ፣ የአባ ጥዋሽ የቅድስት ሱርስት፣ ቅዱሳን ሰማዕታት ተላስስና አልዓዛር የዕረፍታቸው በዓል፣ አቡነ ሳዊሮስ የሥጋ ፍልሰት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

Читать полностью…
Subscribe to a channel